ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
⛪️ @AMBASSADORLIFE

#የዘርፌ_መንገድ

#መንፈስ_ቅዱስ ሲያግዝ
እነ #ምርትነሽ አቅቷቸው ከጎዳናው የወጡበት
ብዙዎች የሚያውቁት ግን ፍርሀት ቆፍድዷቸው የማያነሱት እውነት!!!

እህታችን ዘርፌ ከበደ ቁጥር አራት የመዝሙር አልበሟን እንደ ምትለቅ ካስተዋወቀች በሀላ የፌስቡክ ዋና አጀንዳ ሁናለች ከተለያዩ ወገኖች የስድብ ናዳ ወርዶባታል ።
ዘርፌ ከበደ ለተቃውሞ አዲስ አይደለችም ለእኔ ዘርፌ ላመነችበት እውነት ለመሞት የተዘጋጀች የጌታ ባርያ ናት ኢየሱስ በሚለው ስም ማትደራደር አርበኛ!

ዘርፌ ሩሀማ የሚለውን የመጀመሪያ መዝሙርዋን ስትለቅ ተኝቶ የነበረው የኦርቶዶክስ ዝማሬ አብዬት ተቀሰቀሰ በየታክሲው በየካፌው የዘርፌ መዝሙር ዘፈንን አሸንፎ ተከፈተ(በአሁን ሰአት አሳዳጆችዋ የሆኑት ሳይቀሩ የዘርፌን መዝሙር በስልካቸው ጭነው ይሰሙ ነበር ለዚህ ምስክሬ ያሁኑ አሳዳጅዋ #ዘመድኩን_በቀለ ነው በፔጁ ላይ "እንባን አልሰፍርም በመዳፌ የሚለው መዝሙሯን ሰምቼ አልጠግብም አንድ ግዜ እንዲያውም መንገድ ላይ ሁሉ አስቁሜያት አንዴ ዘምሪልኝ ብዬ አዘምሬያታለው "ብሎ ፅፏል) ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ የፕሮቴስታንት አማኞችን ልብ አሸንፎ እቤታቸው ገባ ዘርፌ የሀይማኖትን ድንበር ሰበረች ።
ጠላት ዲያብሎስ ይህን ግዜ በትሩን ይዞ በማህበሩ በኩል ተነሳ ዘርፌን ከህዝብ ልብ ውስጥ የማውጣት ተልእኮ ሀ ብሎ መዝሙሯ ያሬዳዊ ዜማን የተከተለ አይደለም ብሎ ማስወራቱ ቀጠለ......
....ሲቀጥል መናፍቅ ናት ብሎ መፈረጁን ተያያዘው ዱላው ውርጅብኙ ስድቡ ከመድረክ መገፍተሩ እህታችን ላይ ተፈራረቁ ለሴት ልጅ የማይገቡ ስድቦችን ተሰደበች መምህራን ተብዬዎች አፋቸውን አላቀቁባት ውርጅብኞቹ ናዳዎቹ ጎርፎቹ ዘርፌን ከፍ አደረግዋት በትንሹ ተቃውሞ እነ ምርትነሽ በሚያሳፍር ሁኔታ ሲብረከረኩ ኢየሱስ ማለታችን ስህተት ነው ይቅርታ አድርጉልን ብለው ከእውነት ፈቀቅ ሲሉ..
ዘርፌ መንፈስ ቅዱስ አግዘኝ እያለች ይሄው አለች ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ!!

#ስለእኔ_የሚማልደው"በኢትዮጵያ አየር ላይ ይለቀቃል። እውነተኛ ኦርቶዶክሶችና ፕሮቴስታንቶች በጉጉት ይጠብቋታል እናንተንም ስለእኔ የሚማልደው ለማለት ከፍርሀት ቆፈን እንድትላቀቁ መንፈስ ቅዱስ ያግዛችሁ... የሌሎች ወንድሞች እንዲሁም የእኔ የወንድማቹ በረከት ምኞት እና ፀሎት ነው ተባረኩልኝ
join as 👇
@ambassadorlife
@ambassadorlife


ሮሜ 8÷34

" #የሞተው÷ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው÷ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው÷ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡"

#ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ ማስተላልፍ የፈለገው ‹‹ #እንግዲህ #በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን #ኵነኔ የለባቸውም›› የሚለውን ነው (ቊጥር 1)፡፡ ሐዋርያው በመቀጠል ‹‹ #በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው #የሕይወት መንፈስ ሕግ #ከኀጢአትና #ከሞት ሕግ ዐርነት›› ያወጣን መሆኑን ያበሥርና (ቊጥር 2) እንደ #ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ #መንፈስ ፈቃድ መመላለስ እንደሚገባን ይመክራል፡፡ ምክንያቱንም ደግሞ ‹‹ስለ #ሥጋ ማሰብ #ሞት ነውና÷ ስለ #መንፈስ ማሰብ ግን #ሕይወትና #ሰላም ነው›› በሚል ያስቀምጣል (ቊጥር 6)፡፡ ስለዚህ እንደ #ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ #መንፈስ ፈቃድ መመላለስ እንደሚገባ ካሰፈረ በኋላ ‹‹ #አባ #አባት ብለን የምንጮኽበትን #የልጅነት #መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና #ለፍርሀት #የባርነትን #መንፈስ አልተቀበላችሁምና›› ይላል (ቊጥር 15)፡፡ በመቀጠል ልጆች ከሆንን ደግሞ ወራሾች ነን ይልና ‹‹ #ዐብረንም ደግሞ እንድንከበር ዐብረን #መከራ ብንቀበል #ከክርስቶስ ጋር አብረን #ወራሾች ነን›› የሚል ሐሳብ ያቀርባል፡፡ ነገር ግን #መከራው #ልንወርሰው ካለው ክብር ጋር ሲመዛዘን ‹‹ምንም እንዳይደለ አስባለሁ››፡፡ ይህ ግን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት በሙሉ በመሆኑ ‹‹ #የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች #መገለጥ›› በመቃተት በተስፋ እየተጠባበቀ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በመቃተት ላይ ያለው ግን #ፍጥረት ብቻ ሳይሆን እኛም ጭምር መሆናችንን ያስቀምጥና ‹‹ #እንዲሁም ደግሞ #መንፈስ #ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት #እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና÷ ነገር ግን #መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት #ይማልድልናል›› ይላል፡፡ ምክንያቱንም ‹‹ #ልብንም የሚመረምረው #የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል÷ እንደ #እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ #ቅዱሳን #ይማልዳልና›› በማለት ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ ቡኋላ ቀደም ሲል ያቀረበውን በዚህ ምድር የሚያገኘንን #መከራ መነሻ በማድረግ ‹‹ #እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ #አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ #ለበጎ #እንዲደረግ እናውቃለን›› በማለት ይጀምርና #እግዚአብሔር #አስቀድሞ እንደ #ወሰነን፣ እንደ #ጠራን#እንዳጸደቀን እና #እንዳከበረን አስፍሮ ‹‹ #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን #ይቃወመናል?›› የሚል ጥያቄ ያነሣል፡፡ እንግዲህ ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው ‹‹ #እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? #የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው÷ #የሚኰንንስ ማን ነው?›› የሚለውን ጥያቄ በማንሣት #የኰናኙን ማንነት ለማሳየት ጥረት የሚያደርገው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት #ኰናኙ
▶️ "የሞተ"
(ሞቱ አንድ ጊዜ ብቻ የሆነ ወደፊት የማይደገም በመሆኑ በኃላፊ ጊዜ ነው የተቀመጠው)፣

▶️ "ከሙታንም የተነሣ"
(ትንሣኤውም ቢሆን ሞትን ድል አድርጎ በተነሣበት ጊዜ ብቻ የሆነ አንድ ክንውን ነውና የተነሣ አለው)፣

▶️ "በእግዚአብሔር ቀኝ ያለ"
(በእግዚአብሔር ቀኝ መሆኑ ስለ ሰው ልጆች ሊታይ ነው(ዕብ 9፥24)፡፡ ይሄውም የምልጃ ሥራው አካል ነውና አሁንም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፡፡ ስለዚህ ነው ሐዋርያው በእግዚአብሔር ቀኝ ነበረ ሳይሆን አለ ያለው)፣

▶️ "ስለ እኛ የሚማልድ" (የክርስቶስ ምልጃ ምንም እንኳ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ በተሠራው ሥራ የተፈጸመ ስለ ሆነ የማይደጋገም ቢሆንም፣ ቀደም ሲል እንደ ተባለው አሁንም ስለ እኛ በመታየት ይቅርታን እንድናገኝ ያደርጋልና ሐዋርያው ስለ እኛ የሚማልድ በማለት አሁንም አማላጃችን መሆኑን ተናገረ።) በማለት ስለ እኛ #የሚማልድ መሆኑን በማሳየት በዚህ ምድር ላይ ያለውን #መከራ #ማሸነፍ የሚቻልበትን #ማበረታቻ ይሰጣል፡፡ ይህ ምንባብ #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #የሚከሳቸው #ማን ነው? ለሚለው #ጥያቄ #ማንም የሚል ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን ማንም #ሊከሳቸው የማይችልበት #ምክንያት ደግሞ ስለ #እነርሱ #ሞቶ የነበረ #ሞትን #ድል አድርጎ #የተነሣው እና #በአብ ቀኝ ሆኖ #የሚያማልድላቸው #ስላለ ነው በሚል ነው የሚያስቀምጠው፡፡ #ሐዋርያው ቀደም ሲል #በክርስቶስ #ኢየሱስ ላሉት #አሁን #ኵነኔ የለባቸውም ማለቱን ማስታወሱም #ጠቃሚ ነው (ቊጥር 1)።
@ ( #ጳውሎስ "ስለ እኛ የሚማልደው" በማለት እርሱም #በክርስቶስ ኢየሱስ #የምልጃ ስራ ተጠቃሚ መሆኑን ይናገራል። አንዳንዶች #ሐዋሪያው #ጳውሎስን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን #በምልጃ ስራ ውስጥ አሰልፈው #የክርስቶስን የምልጃ ስራ ፊት ለፊት በመቃወም ላይ ናቸው። #ሐዋሪያው በዚህ ክፍል ላይ እርሱ #አማላጅ ስለመሆኑ ሳይሆን #ስለ ኢየሱስ #አማላጅነት እና እርሱም #በኢየሱስ #ምልጃ ተጠቃሚ ስለ መሆኑ ነው የሚያስተምረው። #መጽሀፉ እንደሚለው ደግሞ #ኢየሱስ የእኛ ብቻ ሳይሆን #የቅዱስ ጳውሎስም #አማላጅ ነው። ስለ ሌሎች #ያማልዳል የሚባለው #ጳውሎስ #በክርስቶስ ምልጃ ተጠቃሚ እንደሆነ የገለጸውን መመልከት ሁላችንም #አማላጅ #እርሱ ብቻ ወደ ሆነው ወደ #ክርስቶስ እንድንጠጋ ያበረታታል።)

#በመቀጠልም ስለ እኛ #ከሞተው#ሞትን ድል አድርጎ #ከተነሣው#በእግዚአብሔር ቀኝ ካለው እና #ስለ እኛ #ከሚያማልደው ‹‹ #ከክርስቶስ #ፍቅር ማን ይለየናል? #መከራ÷ ወይስ #ጭንቀት÷ ወይስ #ስደት÷ ወይስ #ራብ÷ ወይስ #ራቁትነት÷ ወይስ #ፍርሀት÷ ወይስ #ሰይፍ ነውን?›› ሲል ይጠይቃል፡፡ በእርግጥም ከዚህ #ጌታ ምንም የሚለየን የለም፡፡ ‹‹ #ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ #እንገደላለን÷ #እንደሚታረዱ #በጎች ተቈጠርን ተብሎ›› ተጽፏልና፡፡ ‹‹በዚህ ሁሉ ግን #በወደደን [በአማላጃችን] #በእርሱ #ከአሸናፊዎች እንበልጣለን፡፡ #ሞት ቢሆን÷ #ሕይወትም ቢሆን÷ #መላእክትም ቢሆኑ÷ #ግዛትም ቢሆን÷ #ያለውም ቢሆን÷ #የሚመጣውም ቢሆን÷ #ኀይላትም ቢሆኑ÷ #ከፍታም ቢሆን÷ #ዝቅታም ቢሆን÷ #ልዩ ፍጥረትም ቢሆን #በክርስቶስ ኢየሱስ #በጌታችን ካለ #ከእግዚአብሔር #ፍቅር ሊለየን #እንዳይችል ተረድቼአለሁ›› በማለት #ምዕራፉ ያበቃል፡፡ #በዚህ ምዕራፍ ውስጥ #አሁን #ኵነኔ #የለብንም በማለት የጀመረው #ሐዋርያው #ክርስቲያኖች ስለሚያጋጥማቸው ነገር #እየመከረና #እያበረታታ ሁሉን #በጽናት #ማሸነፍ እንዳለባቸው ሲናገር፣ ‹‹ #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው÷ #የሚኰንንስ ማን ነው?›› ለሚሉት #ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ‹‹ #ስለ እኛ የሚማልደው #ክርስቶስ #ኢየሱስ›› መሆኑን ነገረን፡፡ ለዚህስ ሳይሆን ይቀራል #በአንድምታው ላይ ‹‹ #እሱ #ቢያጸድቅ ማን #ይኰንነናል፡፡ #ኢየሱስ ክርስቶስ #ሞተ #ከሙታንም #ተለይቶ #ተነሣ፡፡ #በአብ #ዕሪና(እኩል፣ መተካከል) #ይኖራል ስለ እኛ #ይከራከራል፡፡ #መከራከርስ የለም #ስለ እኛ #በዕለተ #ዐርብ #ባደረገው #ተልእኮ ፍጹም #ዋጋችንን #የምናገኝ ስለ ሆነ›› እንደ ሆነ የሰፈረው????
📖/፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሀፍ ንባቡና ትርጓሜው (አ.አ፣ ግንቦት 1988) ገጽ 70።
📖/፤ መሐሪ ትርፌ (ሊቀ ሊቃውንት)፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሀፍ ንባቡ ከነትርጓሜው (አ.አ፤ ጥቅምት 23 1948) ገጽ 100።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..(ሮሜ 8፥34)
@gedlatnadersanat @teeod
ተሻሽሎ የቀረበ

መጽሀፈ ሰአታት
💠 "ኪሩቤል አፍራሰ ፌማ፣ ወሱራፌል ዘራማ፣ ክሉላነ ሞገስ ወግርማ፣ ይሴብሑኪ ማርያም በሐዋዝ ዜማ"
💠 " ግርማንና ሞገስን የተቀዳጁ የፌማ ፈረሶች ኪሩቤልና ራማዊው ሱራፌልም ባማረ ዜማ ማርያም ሆይ አንቺን ያመሰግኑሻል"
/ኲሎሙ ዘኪዳነ ምህረት -- ገጽ 109/


▶️ በዚህ ክፍል ላይ ደራሲው #ኪሩቤልና #ሱራፌል ባማረ ዜማ #ማርያምን #እንደሚያመሰግኗት ይናገራል። በእርግጥ እነዚህ #ቅዱሳን #ፍጥረታት #ተጨማሪ አድርገው ወይም #እግዚአብሔርን #ትተው #የሚያመሰግኑት #ሌላ ተመስጋኝ #ፍጡር #እንደተመደበላቸው የሚያሳይ #መፅሀፍቅዱሳዊ መረጃ የለንም። ደግሞም #በሰማይ #ፍጡር #አይመሰገንም፤ ወደዚያች #ከተማ #የገባ ሁሉ #የከተማዋን #ባለቤት #ያመሰግናል፤ <እኔ ልመስገን> የሚል #ፍጡርም የለም።
<ድንግል ማርያምም> በሰማይ #ከአእላፋት #መላእክትና #ከቅዱሳን ጋር ሆና ስለተደረገላት ነገር #ፈጣሪዎን ታመሰግናለች።
ከዚህ ውጪ ግን በዚያ #በሰማይ #ከኪሩቤልና #ከሱራፌል #ውዳሴን #ትቀበላለች ብሎ ማሰብ #በምድር እንኳን #የተወገዘውን #ፍጡራንን #ማምለክ ወደ #ሰማይ ለማውጣትና #በሰማይም #ተቀባይነት ያለው #ለማስመሰል የተደረገ ^ጥረት እንደሆነ #አስተዋዮች አያጡትም።
▶️ የሰማይ አምልኮ በተገለጠበት #በራእይ #መፅሀፍም #ቅዱሳን #መላእክት #በአንዱም አጋጣሚ #ፍጡራንን #ሲያመልኩ #አለመታየታቸው #ትምህርት ሊሆነን ይገባል።
<የጌታን እናት> የሕይወት #ታሪክ በሚገባ የሚያውቁ #ሐዋሪያት እንኳ ምንም #የጌታቸው #እናት ብትሆንም እርሷ #ምስጋናና፣ ውዳሴ #ልትቀበል #እንደሚገባት ለማመልከት #አንድ #ጥቅስ እንኳን አልፃፉልንም።
<< እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ #ብፅኢት ይሉኛል>>/ሉቃ 1-48/። ብላ ራሷ #ድንግል #ማርያም የተናገረችው #ቃልም ቢሆን እንደ #ኤልሳቤጥ <ከጌታ የተነገረላት ይፈጸማልና ያመነች ብጽኢት ናት>/ሉቃ 1-45/። ብሎ #ስለጌታ #እናት #በሦስተኛ መደብ #ምሥክርነት #መስጠት ማለት ነው እንጅ #እርሷ #ከሞተች ቡሀላ #በጸሎትና #በውዳሴ #በሁለተኛ #መደብ
<< #ማርያም ሆይ #ብጽኢት ነሽ>> ማለትን የሚያመለክት አይደለም።
( <ለድንግል ማርያም የሚጠቀሱ የተለመዱ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው> በሚለው ስር ሰፊ ማብራሪያ ያገኙበታል።)

#ሐዋርያትም ለእርሷ የሚሆን #ውዳሴ አላቀረቡም፤ ይህንም አለማዳረጋቸው #በንቀት ሳይሆን #ማድረግ የሚገባቸውን #በውስጣቸው የሚኖር #መንፈስ #ቅዱስ ስለሚያሳያቸው ነው። #በሰማይ ያሉ #መላእክትም ባመሰገኑ ጊዜ ሁሉ #እሷን አለመጨመራቸው ይህን ማድረግ #ስህተት ስለሆነ ነው። በመሆኑም #የሰማይ #ቅዱሳን #ፍጥረታት #የሚያመሰግኑትንና#ምስጋና #የሚገባውን #ጠንቅቀው ስለሚያቁ #ሲያመሰግኑ እንዲህ ይላሉ፤ ፦

<<መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ #ይገባሃል#ታርደሃልና#በደምህም ለእግዚአብሔር #ከነገድ ሁሉ #ከቋንቋም ሁሉ #ከወገንም ሁሉ #ከሕዝብም ሁሉ #ሰዎችን #ዋጅተህ #ለአምላካችን #መንግሥትና #ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ #ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።>>
<<አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥ በታላቅም ድምፅ። #የታረደው #በግ #ኃይልና #ባለ #ጠግነት #ጥበብም #ብርታትም #ክብርም #ምስጋናም #በረከትም #ሊቀበል #ይገባዋል አሉ።>> /ራእይ 5፤ 9-12/።
በዚህ ክፍል ላይ #ሲመሰገን የምናየው #ክርስቶስ ነው እንጅ #ድንግል ማርያም አይደለችም።
በአካባቢው መኖሯንም የሚገልጽ ምንም #የመጽሀፍ #ቅዱስ ክፍል የለም። በተጨማሪም እስቲ የሚከተሉትን ጥቅሶች እንመልከታቸው፤ ፦
ራእይ 4-8 , 7-9 , 11-15 , 12-10 , 15-3 , 19፥1።
በእነዚህም #ጥቅሶች #በሙሉ #ከጌታ #በስተቀር #በሰማይ #ማንም #አልተመሰገነም#በመንፈስ #ቅዱስ #ተመርተው #የጌታ #ሰዎች የጻፉት #መጽሀፍ #ቅዱስ በሰማይ #የሚመሰገነውንና ያለውን #የአምልኮ #ስርዓት በዚህ ዓይነት አስቀምጦልናል። ስለሆነም #ያላየነውንና #ያልሰማነውን #በመጽሀፍ #ቅዱስም የሌለውን በሚያስተምሩ #ሰዎች ላይ #በእውነትና #በመንፈስ የሚመለከው #አምላክ ይፈርድባቸዋል። #ከቅዱስ #መጽሐፍ #ሐሳብና #እውነታ በተለየ መንገድ <<በሰማይ ማርያም ትመሰገናለች፤ እነ ሱራፌል ያመሰግኗታል>> ማለቱ ራስን #ሀሰተኛ #ምስክር ማድረግ ነው። ይህም #በእግዚአብሄር ፊት ተጠያቂ ያደርጋል። ምክንያቱም #በእውነተኛው #ቅዱስ #መጽሀፍ #ባለመመዝገቡና #እውነት ባለመሆኑ ነው። ስለሆነም #ኪሩቤልና #ሱራፌል እንዲህ ያለውን #ስህተት ይፈጽማሉ ብሎ #መመስከሩ #የሀሰት #ምስክር #ያሰኛል እንጂ #ማርያምንም ሆነ #ኪሩቤልን ደስ ማሰኘት እንዳልሆነ #መገንዘብ ይገባል። ዩሐንስ #በራእይ ያን ሁሉ #ምስጋና ሲያይ አንዴ እንኳ <ድንግል ማርያም> #ስትመሰገን አልሰማም። በመሆኑም #ኪሩቤልና #ሱራፌል <<የታረደውን በግ>> ብቻ #እንደሚያመሰግኑ #መመስከሩ በቂ ነውና እንዲህ የሚያደርጉትን <<ከተጻፈው አትለፍ>> /1ቆሮ 4፥6/ የሚለውን #የተቀደሰ #መመሪያ ተማሩ እንላቸዋለን።


@gedlatnadersanat
ይህን ያዩ ሌሎች #ሴቶች በዚህ ወራት አምላክ #ከድንግል #ይወለዳል የተባለው ከአንቺ ይሆንን? ብለው ዘበቱባት። ወዲያው #መልአኩ መጥቶ #ትጸንሲ (ትጸንሻለሽ) አላት ዝም ብላ ሄደች። ከቤትም ደርሳ ውሃውን ስታወርድ #ትጸንሲ (ትጸንሻለሽ) አላት ይህ ነገር ደጋገመኝ #ከቤተመቅደስ ሄጄ ልረዳው ብላ #ከደናግለ #እስራኤል ጋር ተካፍላ እያስማማች የምትፈትለው #ሐርና #ወርቅ ነበር። ያንን ይዛ ሄደች #ከቤተ #መቅደስ ተቀምጣ #ሐርና #ወርቁን እያስማማች ስትፈትል #መልአክ መጥቶ #ትጸንሲ (ትጸንሻለሽ) አላት እፎኑ ይከውነኒ ዝንቱ እንዝ ኢያአምር ብእሴ - #ወንድ #ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል? አለች። እኔ ይህን አላደርገውም #እንደምን #ይሆናል ስትለው ነው ከዚህ ቡኋላ መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላእሌኪ - ቅዱስ #የእግዚአብሔር #መንፈስ #በአንቺ ላይ #ይመጣል አላት። ይኮነኒ በከመ ትቤለኒ (እንደ ቃልህ ይሁንልኝ) አለችው። ይህን #ቃሏን ምክንያት አድርጎ #በማህጸኗ ተቀርጾአል[4]>> ብለው ያቀርባሉ።

▶️ የዚህ #ተረት #ፈጣሪ #በመጽሐፍ ቅዱስ #በዮሴፍ ቤት #ናዝሬት #ከተማ ነበረች የሚለውን #የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ #ገለጻ በመተው ሌላ #ያልነበረና የሌለ #ታሪክ ጽፏል። ይህ ደግሞ በቃሉ ላይ #አመጽና #መሸቃቀጥን ያመለክታል። አዎን ቅዱስ #ገብርኤል #ማርያምን ሲያበስራት #በእጮኛዋ #ዮሴፍ ቤት #በናዝሬት ከተማ ነበረች እንጂ #ቤተ መቅደስ ወይም #በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ አልነበረችም #ወቅቱና #ሁኔታውም አይፈቅድም {ሉቃ 1፥26}።

▶️ አንዳንዶችም #በቤተ መቅደስ ነበረች የሚለውን #አባባል #መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ብለው #በመቃወም #ማርያም የነበረችው #በቤተ መቅደስ #ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ሳይሆን #በቤተ መቅደሱ ግቢ #በማህደረ #ደናግል ውስጥ ትኖር ነበር የሚሉ አሉ። ነገር ግን #ሄሮድስ በሰራው #ቤተ መቅደስ #አደባባይ ጊቢ ውስጥ ይኖሩና ቆመው #ለአፍታ ያህል ይጸልዩ የነበሩት #አሮጊቶችና #መበለቶች እንደነ #ሃና #የሳሙኤል እናት {1ኛ ሳሙ 1፥9 እና አሮጊቷ ሃና} ሉቃ 2፤ 36-38} እንጂ #ደናግል ወጣት #ሴቶች በጭራሽ አይገቡምና ይህም #ጥናቱ ያላላቀ #ጅምር #አንካሳ #ሃሳብ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ ፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ 1 ዲድስቅሊያ 44።

📚፤ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ፤ <ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን 3ኛ ዕትም፡ ብራና ማተሚያ ድርጅት፤ አ.አ፥ ገጽ 18፡ 1995 ዓ.ም።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፡ "ፍትሐ ነገስት ንባቡና ትርጓሜ፤ አንቀጽ 1፤ 13፡ ገጽ 23፤ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፡ አ.አ፡ 1990 ዓ.ም።

[2] 📚፤ ኢንተርናሽናል መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ አዲሱ መደበኛ ትርጉም፤ የሉቃስ 2፥4 እና 22 ማብራርያ፡ ገጽ 1531-1532፡ 1993 ዓ.ም።

[3] 📚፤ አባ ቤተማሪያም እና መዘምራን ሞገስ ዕቁባ ጊዮርጊስ፤ "አምስቱ አዕማደ ምሥጢር ምስል ሥነፍጥረት አንድምታ"፤ አክሱም ማተሚያ ቤት፤ አክሱም፡ ገጽ 36፤ 1991 ዓ.ም።

📚፤ አስረዳ ባያብል (ሊቀ ጠበብት)፤ "ማህሌተ ጽጌ ትርጓሜ"፤ አ.አ፡ ገጽ 80፤ 1998 ዓ.ም።

[4] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ "ውዳሴ ማርያም ንባቡና አንድምታው" ዘሰንበተ ክርስቲያን፤ ገጽ 210፥ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1983 ዓ.ም።

(7.4▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ ክርስቶስ <<በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ>> ብለን እንድንጸልይ እንጂ ያስተማረን << #እመቤታችን ሆይ>> ብለን እንድንጸልይ አላስተማረንም። የተሰጠንም #መንፈስ #አባ #አባ ብለን የምንጮህበት #መንፈስ #ብቻ ነው እንጂ #እማ #እማ ብለን የምንጮህበት አይደለም [ሮሜ 8፥15]። <<ስምህ ይቀደስ>> እንድንል እንጂ << #ሰላምታ #ይገባሻል>> እንድንል <<በደላችንን ይቅር በለን>> እንጂ << #ይቅርታን #ለምኚልን ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ>> እንድንል አላስተማረንም። የሁለቱም #ጸሎቶች #አድራሻና #ፍሬ ነገራቸው #የሰማይና #የምድር #ርቀት ያክል ልዩነት ያላቸውና #የሚጣረሱ ናቸው።

▶️ ከክርስቶስ #ትምህርት ጋር ሌሎችንም <<የጸሎት መጻህፍት>> የተባሉትን ብናስተያያቸው
እንደ <<አንቀጸ ብርሃን መጽሀፍ>> << #ስምሽ #የተመሰገነ ነው>> እንድንል ሳይሆን <<ስምህ ይቀደስ>> እንድንል፤ እንደ <<ተአምረ ማርያም መጽሀፍ>> << #ድንግል ሆይ #ፈጥነሽ እንድትመጪ>> [43፥26] እንድንል ሳይሆን <<መንግስት ትምጣ>> ብለን የክርስቶስን #መንግስትህ መምጣት #በናፍቆት እንድንጠባበቅ፤ <<ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን>> በማለት የእርሱ #ሰማያዊ #ፍቃድ ብቻ በምድራችን እንዲሆን እንጂ እንደ ተአምረ ማርያም ጸሀፊ << #ፈቃድሽ #ይሁንልን ይደረግልን>> እንድንል አላስተማረንም [100 ፤ 29-32]። <<የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን>> በማለት #የዕለት #ኑሮአችንንም እንዲያቀናልን እንድንጸልይ እንጂ። እንደ <<መልክዓ ማርያም መጽሀፍ>> << #መጻህፍትሽ #የማዳን #እንጀራንና የተፈተነ #መድሀኒት መጠጥን ስለሚሰጡ #ሰላምታ ይገባል[ለእራኃትኪ]>> እንድንል አላስተማረንም። <<ኃጢአታችንን ይቅር በለን>> እንድንል እንጂ እንደ <<መልክዓ ማርያም>> ደራሲ << #ኃጢአታችንን #ይቅር #በይን[ለመዛርዕኪ]>> እንድንል አላስተማረንም። <<ከክፉ አድነን>> በማለት #ከክፉ እንዲያድነን ወደ #እግዚአብሔር እንድንጸልይ እንጂ << #ከአዳኝ #አውሬ #አድኝኝ>> [የዘውትር ጸሎት ሰላምለኪ] እንድንል አላስተማረንም። <<ኃይል ክብርም ምስጋናም ለዘላለም ድረስ ላንተ ይሁን>> እንድንል እንጂ እንደ <<ተአምረ ማርያምና እንደ ቅዳሴ ማርያም>> <<ድንግል ሆይ #ክብርና #ምስጋና #ለዘላለም ይገባሻል>> እንድንል አላስተማረንም። ስለሆነም ይህን #ከክርስቶስ #ትምህርት ጋር የሚጣረስ ትልቅ #ኑፋቄ ወደ #ቤተክርስቲያን ማስገባትና ማስተማር ታላቅ #በደልና #ኃጢአት ነው።

▶️ አንዳንድ #ሰዎች ደግሞ ይህን #ኑፋቄ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል #ከሉቃስ ወንጌል 1፤ 28- ጀምሮ ያለውን ክፍል ይጠቅሳሉ።

በክፍሉ እንደሚነበበው ግን #መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል #ከእግዚአብሄር ዘንድ ተልኮ ወደ #ድንግል #ማርያም በመጣ ጊዜ በሚያስደንቅ #ሰላምታ ከተገናኘ ቡኃላ የተላከበትን ጉዳይ <<እግዚአብሔር #ከአንቺ ጋር ነው>> በማለት ስለሚወለደው ቅዱስ #የእግዚአብሄር #ልጅና #ስልጣን ላይ አተኩሮና #ሰፊ ጊዜ ወስዶ ሲያበስራት ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ #አንድ #ቤት ወይም #ከጓደኛው ጋር ሲገናኝ #አይነቱ ይለያል እንጂ #ሰላምታ መለዋወጥ በየትኛውም #ሀገር ያለና የተለመደ #ባህላዊ #ስርአት ስለሆነና በተለይም #በመንፈሳዊ ሰዎች ዘንድ ሲገናኙ #ሰላምታ መለዋወጥ #ልማድ ከመሆኑም ጭምር እንዲሁም #መጽሀፍ ቅዱሳዊ በመሆኑ [ማቴ 10፤ 12-13]። መለአኩ #ቅዱስ #ገብርኤልም ያደረገው ይኸንን ነው #ጸሎት እያቀረበ አለመሆኑን ማንም #ሰው አንብቦ #መረዳት የሚችለው ነገር ነው። #ማርያምም ለቀረበላት ሰላምታ <<ይህ #እንዴት ያለ #ሰላምታ ነው>> ብላ አሰበች እንጂ እንደ #ጸሎት #ተቀባይ ወይ እንደ #ጸሎት #ሰሚ ሆና አልቀረበችም [ሉቃ 1፥29]። ነገር ግን አንዳንዶች ይህን ክፍል በመጥቀስ #ማርያምን <<በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ #ሰላም #እልሻለው>> እንዲባል #አስተምረዋል ጽፈው አልፈዋልም ዛሬም #የሚያስተምሩ አልጠፉም።
▶️ በቅዱስ ገብርኤል #ሰላምታ #ሰላም እልሻለሁ የሚለውን #ቃል ራሱ ብናየው #የተሳሳተ #አባባልና #ያልተለመደ #ንግግር ነው። በሌላ አገላለጽ #ዩሐንስ #ለጋይዮስ #ሰላም ለአንተ ይሁን ባለው #ሰላምታ [3ኛ ዩሀ 1፥15] #ጋይዮስ ሆይ #በዩሐንስ ሰላምታ #ሰላም እልሃለው እንደማለት ነው። ነገሩን #ግልጽ ለማድረግ አቶ #አበበ አቶ #ከበደ ቤት ገብቶ <<አቶ #ከበደ በአቶ #አበበ #ሰላምታ #ሰላም #እልሀለው>> ብሎ #ሰላምታ እንደመስጠት ያክል ነው። ይህም በማንኛውም #ህብረተሰብና #ክፍለዘመን ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው #ከጤናማው #የሰላምታ ሥነ-ሥርዓት የወጣ #አባባል ነው።

▶️ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #መልዕክት አድርስ ተብሎ ወደ #ድንግል ማርያም በመምጣት ያደረገውን #ሰላምታ ተንተርሶ #አጼ #ዘረዓ #ያዕቆብ <<ይወድስዋ መላእክት - {መላዕክት ማርያምን ያመሰግኗታል}>> የሚል #ድርሰት ሲያዘጋጅ #የቦረናው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ደግሞ <<ተፈሥሒ ኦ ሙኃዘፍስሐ፤ የተድላና የደስታ መፍሰሻ ሆይ ደስ ይበልሽ መላእክት ብለዋታል[1]>> ብሏል። ነገር ግን ወደ #ማርያም ተልከው የመጡት #መላእክት ሳይሆኑ አንድ #መለአክ ነው። እርሱም ቅዱስ #ገብርኤል ሲሆን ንግግሩም #ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደተላከ ማሳወቅና #ክርስቶስን ያለ #ወንድ #ዘር #በድንግልና እንደምትወልድ የሚገልጽ እንጂ የተለየ #ምስጋና ለመስጠትና #የተድላና #የደስታ #መፍሰሻ እንደነበረች ያሳሰበበት #ክፍል አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን #መልአኩ እርሱ ከመምጣቱ በፊት #ማርያምን #የሚያመሰግንበትም የተለየ #የሰራችው አንዳች ነገር የለም። ያም ሆኖ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት #መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም በነበራቸው የአጭር ጊዜ የመረዳዳት #ውይይትን እንደመደበኛ #የግል #ጸሎታቸው አድርገው #መጽሀፍ አዘጋጅተው የሚደግሙ አሉ። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው መልአኩ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም #ውይይት አደረጉ እንጂ #አንዱ #ለአንዱ ያቀረቡት #ጸሎት የለም። ንግግራቸውም #የዘውትር #ጸሎት እንዲሆንላቸው ያሳሰቡት ነገርም የለም።

▶️ ጌታ #ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ #ሰማይ ሲያርግ #ድንግል #ማርያም ባለችበት #በማርቆስ #እናት ቤት ሐዋሪያት #በአንድነት #በጸሎት ሲተጉ አጠገባቸው ያለችውን #ማርያምን <<በገብርኤል #ሰላምታ ሰላም እንልሻለን #በነፍስሽም #በስጋሽም ድንግል ነሽ ከተወደደው #ልጅሽ #ይቅርታ #ለምኚልን #ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ>> አሏሏትም፤ #የጸሎት #ማዕከላቸውም አልነበረችም። እርሷም እነርሱም በአንድነት << #የሁሉንም #ልብ የምታውቅ #ጌታ ሆይ>> እያሉ #ጌታን እያከበሩ ወደ #ጌታ ሲጸልዩ ነበር። በድንገት #መንፈስ ቅዱስም ለእሷም ለእነሱም #እኩል ያለልዩነት ወረደባቸው። [ሐዋ 1፤ 12-14፣ ሐዋ 2፤ 1-4]።

በተለይ ደግሞ << #ይቅርታን #ለምኚልን>> የሚለው #ቃል ጠቅላላውን #የክርስቶስን #ይቅርታ #ለሰው ልጆች እንዴት እንደተሰጠ አለማወቅና #የክርስቶስን #የደኅንነት #መስዋዕት #ከንቱ የሚያደርግ ነው። በመሆኑም ይህን #ጸሎት ማቅረብ #የጸሎትን #ትርጉም አለማወቅ ብቻ ሳይሆን በግልጽ #የክርስቶስ #ተቃዋሚ መሆን ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ "መጽሐፈ ሰዓታት" ገጽ 29።
<<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን የተቀነባበረ <የጸሎት> ክፍል #በኢየሱስ ክርስቶስ #አስተምህሮ #ወቅት ብቻ ሳይሆን ከእሱ ቡሀላም ለብዙ #ዘመናት አልነበረም። ምናልባትም ሌሎች እንደሚሉት #ማርያም ገና #ክርስቶስን ሳትወልድ የነበረ #የገብርኤል #ሰላምታ ነው ተብሎ እንዳይወሰድ እንኳን #መልአኩ መጥቶ ያደረገው #ውይይት እንጂ #ጸሎት አይደለም። #ክርስቶስም #ለደቀመዛሙርቱ #ጸሎት ባስተማረበት #ወቅት #የገብርኤልንም #ሰላምታ ጨምሩበት በማለት ባስተላለፈ ነበር፤ ያንን ደግሞ አላደረገውም [ማቴ 6፤ 1-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]። << #በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ....>> የሚለው #የጸሎት #አስተምህሮቱን #ድንግል ማርያምን በትክክል በሚያውቋት #በደቀመዛሙርቱ ፊት ምናልባትም #በአስተምሮው #ወቅት ብዙ ጊዜ በምትገኝዋም #በድንግል #ማርያምም በራሷ ፊትም ተናግሯል።

▶️ ስለሆነም የተቀነባበረው <<የማርያም የጸሎት>> ምዕራፍ #በክርስቶስ #ወቅት ያልነበረ ከዚያም ቡኋላ #ሐዋሪያቱ #በአገልግሎታቸውና #በጸሎታቸውም ወቅት የማያውቁትና #የጥንት #ቤተ ክርስቲያን #አባቶችም በልዩ ልዩ ምክንያት #ጉባኤ ሲያደርጉ ለምሳሌ፦ #በኒቂያ ጉባኤ #በ325 ዓ.ም 318 የሃይማኖት አባቶች በእነ #እስክንድሮስ አፈጉባዔነት በንጉስ #ቆስጠንጢኖስ ዘመን ተሰብስበው #አርዮስን <<ወልድ #ፍጡር ነው>> ያለበትን #የክህደት ትምህርት #ሲያወግዙና #የሃይማኖት መግለጫ ሲያወጡ #ኢየሱስን ከመውለዷ ውጭ #ስለማርያም ፈጽሞ #መሠረታዊ #ትምህርት እንኳ በወቅቱ እንዳልነበረ መረዳት ይችላል። እንዲሁም #በቁስጥንጥንያ #በ375 ዓ.ም 150 #የሃይማኖት #አባቶች #በጢሞቴዎስ ዘአልቦጥሪት በንጉሥ ዘየዓቢ #ቴዎደስዩስ ወቅት #መቅደንዩስ << #መንፈስ ቅዱስ #ሕጹጽ ወይም #ሀይል ብቻ>> ብሎ በተነሳ ጊዜ ተሰብስበው #አውግዘው ትምህርቱንና እርሱን ሲለዩ #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #የአስተምህሮ #መግለጫ ሲያወጡ ያኔም ቢሆን #ኢየሱስን #ከመውለዷ ውጪ #ስለማርያም ያስተላለፉት ምንም #አዲስ #ትምህርት የለም። #በኤፌሶን ሀገርም #በ435 ዓ.ም 200 #የሃይማኖት #አባቶች #በቄርሎስ አፈጉባዔነት በቴዎደስዩስ ዘይንእስ ንጉሥነት ጊዜ ንስጥሮስ << #ክርስቶስ #ሁለት #አካል #ሁለት #ባህሪይ ነው>> ብሎ ሲነሳ #እርሱንም #ትምህርቱንም #አውግዘው #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #አስተምህሮ በመግለጫ መልክ ሲያስቀምጡ ድንግል #ማርያም #ክርስቶስን እንደወለደች ብቻ እንጂ << #እመቤታችን>> ብለውም ሆነ << #ለምኝልን>> የሚል አስተምህሮ አያውቁም። #ጤናማ #አስተምህሮ አይደለምና።

▶️ ዛሬ ሁሉም #አብያተክርስቲያናት የሚቀበሉት #ሙሉ #የሃይማኖት #መግለጫቸው

<<ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን የተፈጠረ ሳይሆን የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምን ምንም የሆነ የለም በሰማይም ያለ በምድርም ያለ ስለእኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፈጽሞ ሰው ሆኖ በጴንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ ሞተ ተቀበረም በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና ሙታንንም ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም ጌታ ማህየዊ በሚሆን ከአብ በሰረጸ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋሪያት በሰበሰባት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሰረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።>> የሚል ነው።

ይህንንም መግለጫ #በ1530 ዓ.ም #ሉተራውያን << #የአውግስበርግ #መግለጫ>> በሚል አጸደቁ። እንዲሁም #በ1546 ዓ.ም #ካቶሊክ በድጋሜ << #የትሬንት #መግለጫ>> በማለት አጸደቀችው። #በ1571 ዓ.ም ደግሞ #የአንግሊካን #ቸርች መግለጫውን ተቀብላ አጸደቀችው። #በ1646 ዓ.ም #ፕሪስቢቴሪያን << #የዌስት #ሚኒስቴር #መግለጫ>> በሚል አጸደቀችው[1]።

▶️ ኦርቶዶክስ #ቤተክርስቲያን መግለጫውን በድጋሜ << #ጸሎተ #ሃይማኖት>> በማለት #በ1426-1460 ዓ.ም በኢትዮጵያ የነገሰው #አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ ሙሉውን ተቀበሉና ሌላ #በመጨመር << #ለማርያምና #ለእፀ መስቀሉ (ለመስቀሉ እንጨት) #ስግደት ይገባቸዋል>> በማለት እንዲሁም <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን <<ከአባታችን ሆይ>> #ቀጥሎ እንዲባል ብሎ #አዋጅ አወጣ። ከዚህም የተነሳ በርካታ #ካህናት << #አባቶቻችን ካስቀመጡት #ከሃይማኖት #መግለጫው ውጪ ተጨማሪውን #አንቀበልም>> በማለታቸው #በሰይፍ እንደቆራረጣቸውና እንዳሳደዳቸው #ገድለ #እስጢፋኖስ#ገድለ #አበው ወአኀው፣ #ገድለ #አባ አበከረዙል፣ #ገድለ #አባ ዕዝራ፣ #ገድለ #ደቂቀ እስጢፋኖስን ማንበብ #በቂ ነው።

▶️ ነገር ግን #በዘር #ቅብብሎሽ አማካኝነት የነበረው #የንግስና #ሥርአት ለዚህ <<አዳራሻውን ወደ ሳተው ጸሎት>> ሰፊ እድል አግኝቶ #ሰይፍ ያስፈራቸውና በክርስትናው #ትምህርት ብዙም #መሰረታዊ #እውቀት ያልነበራቸው #ህዝብና #ካህናት #የጸሎት #ምዕራፋቸው አድርገው ለቀጣዩ #ትውልድ በማስተላለፋቸው ይሀው አሁን የምናየውን #ከእግዚአብሄር #ቃል ውጪ የሆነ #ትውልድ ፈጥረውልናል። ዛሬ ዛሬ #በየጸሎቱ #መዛግብት ውስጥ እየተጨመረ ተጽፎ #ምዕመናን ሁሉ #በቀን ቢያንስ #አንድ ጊዜ እንዲደግመው በመደረጉ እንግዳው <<ጸሎት>> #የተለመደ ሆኖ ቀረ። እንዲያውም በዚህ #ዘመን አስቀድመን እንዳልነው <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል #ጥቅሶችን ያለቦታቸው እንደ #ስጋ #ዘንጥለውና #በጣጥሰው #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል የሚታገሉ ተነስተዋል። እኛ ግን <<የእግዚአብሔርን ቃል #ቀላቅለው #እንደሚሸቃቅጡት እንደ #ብዙዎቹ አይደለንምና፤ #በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ #ተላክን #በእግዚአብሔር ፊት #በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።>> [2ቆሮ 2፥17]

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን፤ አውግስበርግ ሃይማኖታዊ መግለጫ፤ በአማርኛ የተተረጎመ፤ አ.አ፥ 1993 ዓ.ም።
▶️ የሰውነት #አካላትን እየዘረዘረ #የሚያስመሰግነው ባለ ብዙ #አርኬ ግጥም #መልክእን #አለቃ #ኪዳነ ወልድ ክፍሌ <<መልክእ ከራስ ጸጉር እስከ እግር ጥፍሩ የሚቆጠር መጽሀፍ ነው ብለውታል[1]።>> የሚገርመው #የሰውነት #አካል የሌላቸው እንኳ #መልክዕ ከተጻፈላቸው ውስጥ #መልክዓ #መስቀል(ለእንጨቱ) ፣ #መልክዓ #ሰንበት(ለቀኑ)፣ #መልክዓ #አንቀጸ #ብርሃን(ለመጽሀፍ ስም)፣ #መልክዓ #ስዕል(ለስዕሉ)፣ #መልክዓ #ቁስቋም(ለቦታ) ይጠቀሳሉ። ሌላው ደግሞ #ማንም ሊቀርበው በማይችል #ብርሃን ውስጥ ለሚኖረው #መልክዓ እና #ገጽ የሌለው #መንፈስ ለሆነው #ለእግዚአብሄር እንኳን #በሰው #አካል(ብልቶች) እየቆጠረ ባለ ብዙ #አርኪ #ግጥም #መልክ ተዘጋጅቶለታል። #ለመላእክትም#ቅዱሳን ለተባሉ #ሰዎችም#በኢትዮጵያ ነግሰው ለነበሩ #አጼዎችም ሁሉ "መልክእ" አላቸው። ይህ <መልክእ> የተባለው #የስነ ጽሁፍ #አይነት መጻፍ የተጀመረው #ፕሮፌሰር #ኃይሌ #በ17ኛው ክፍለ ዘመን #ፌሬንክ በተባለ #እንግሊዛዊ እንደሆነ ሲናገሩ #አለማየሁ #ሞገስ የተባሉት ደራሲ ደግሞ #በ14ኛው ክፍለ ዘመን #በአጼ #ዘረዓ ዕቆብ #ዘመነ መንግስት ነው ይላሉ። ሌላው ዜግነቱ ያልታወቀው "ቤደርሰን" የተባለ ጸሀፊ ደግሞ #በ17ኛው ክፍለ ዘመን ባልታወቀ #የዜማ #አቀንቃኝ ነው ይላል። ሁሉም #በጀማሪውና #በጅማሬው #ዘመን ባይስማሙም #የቤተክርስቲያኒቷ ጅማሬ ላይ ያልነበረ #አበው ያላስተማሩት #መጤ እንደሆነ ይስማማሉ።

▶️ መነሻ ሀሳባችን ስለማርያም ነውና በ"መልክእ" ይዘት ድንግል ማርያም የምትመለክበትን ከ"ጸሎት መጽሀፍ" አንዱ የሆነውን < #መልክዓ #ማርያምን> እንመልከት፦
▶️ ሌላው መጽሀፍ ደግሞ <<ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ አንቺን ደግሞ በጠላቶች አንገት #የብረት #ዛንጁር አግቢባቸው የመለከታቸውን ድምጽ #አክብጅው #ደንቆሮም አድርጊው እርሳቸውንም #በቀፎ #በቅርጫት በእግር ብረት #እሰሪያቸው በእግራቸው #ወጥመድ በከንፈራቸውም #ልጓም በአፍንጫቸው #ጉንፋን ላኪባቸው ሊሄዱበትም ወዳልፈቀዱበት መንገድ #መልሻቸው በልቦናቸውም #ፍርሃትን #መንቀጥቀጥን አሳድሪባቸው #መሸበርንና መንቀጥቀጥን ጨምሪባቸው #እንደሴቶች ይሁኑ። ከጽኑ ነፋስ ኃይል የተነሳ ዛፍ ሲንቀሳቀስ ቅጠሉ እንረዲረግፍ እንዲበተን እንዲሁ #ይሁኑ#በርሃብ #በቸነፈር #እህልን #በማጣት ቅሰፊያቸው፣ በሜዳ ሰይፍ ልጆቻቸውን #ያጥፋቸው በቤታቸውም ውስጥ #ፍርሃት ያስጨንቃቸው። #እሳት#በረዶ #ረሀብ፣ ቸነፈር ይፍጃቸው ይህ ሁሉ የእግዚአብሄር #የምጽአቱ #ጽዋ በጠላቶቼ ላይ ይውረድ እድል ፈንታቸው #ጽዋ ትርታቸው ይሁን[1]>>

▶️ እንግዲህ ይህ አይነቱ #ጸሎት #ክርስቶስና #ሐዋሪያቱ #ለገዳዮቻቸው እንኳ <<አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው>> ብለው ከጸለዩት ጋር ይጻረራል። ስለሆነም ይህ አይነት #ጸሎት #የበልዓም ትምህርት {የሰይጣን ትምህርት} እንጂ #የክርስቶስ #ትምህርትና #ጸሎት አይደለም [ዘኃ 22፥17 ፣ ራዕ 2፥14]። አንዳንዶች ለማስተባበል እንደሚሞክሩት <<ይሄ እርግማን ለሰይጣን ነው>> እንዳል እንኳን #አንደኛ <<የሚጠላኝን፣ የሚቃወመኝን ሰው..>> በማለት #ለሰውም ጭምር እንደሆነ ተጽፏል ሁለተኛ #ለሰይጣንም ቢሆን እንኳን እርሱ #መንፈስ ስለሆነ <<የሚለጎም አፍ፣ #ዲዳ የሚሆን #አንደበት፣ የሚዘጋ #ጉሮሮ#የሚደነቁር #ጆሮ፣ የሚቆረጥ #አንገት፣ የሚሰበር #ክንፍ የሉትም። ጌታ ኢየሱስም #አጋንንትን ከሰዎች ሲያስወጣ < #ውጡ!> ብሎ #ከመገሰጽና #ከማስወጣት በስተቀር [ማር 1፤ 25-27] #ዲዳ ሁኑ!፣ #ተቆረጡ!፣ #ተሰበሩ! አላለም። #ደቀመዛሙርቱም ቢሆኑ #አጋንንትን አውጡ ባላቸው መሰረት #በኢየሱስ ስም አስወጡ እንጂ [ማቴ 10፥8] #ቆራርጧቸው#ሰባብሯቸው#አደንቁሯቸው#ሽባ አርጓቸው አላለቸውም። እነርሱም #እርግማንና ሌላ #ቃላትን አልተጠቀሙም። ምክንያቱም ደሞ #አጋንንት #መንፈስ እንጂ #ሥጋዊ #አካላት የላቸውምና [ሐዋ 16፤ 16-18፣ ሉቃ 10፥17፣ ኤፌ 6፥12]። ጌታ በነገር ሁሉ #ማስተዋልን ያድለን [2ጢሞ 2፥7]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
______________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አርጋኖን ፤የእመቤታችን ምስጋና ዘሰኑይ፡ ገጽ 33-37፥ ተስፋ ገብረ ስላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።

@gedlatnadersanat
(8.6.4▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat