ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ተአምረ ማርያም እርግማን እንጂ በረከት የሌለው መጽሐፍ ብዙዎች ተአምረ ማርያም ቅዱስ መጽሐፍ እንደሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንደተጻፈ ይናገራሉ። እነርሱ እንደሚሉት ከሆነና የእግዚአብሔር እስትንፋስ ከሆነ እንደ ቅዱሱ መጽሐፍ ፍቅር ፍቅር የሚሸት፣ የእግዚአብሔር ምህረት የሚታይበት መጽሐፍ መሆን አለበት። ነገር ግን መጽሐፉ ከዚህ ተቃራኒ እንደሆነ እስካሁንም ብዙ እያየን መተናል የሚከተሉት ሃሳቦችም…


#ተአምረ ማርያም የተባለው ጉደኛ መጽሐፍ የምንወዳትን ድንግል ማርያምን ያከበረ የሚመስል ነገር ግን #ስድብ እና #ክህደት የሞላበት ስለመሆኑ እርግጥ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ #ከ1400 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ንጉሥ በዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሲሆን በወቅቱ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና ምእመናን ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ #አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ #አንገታቸው በጉድጓድ #ተቀብረው #በጭንቅላታቸው ላይ #የፈረስና #የከብት #መንጋ #እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን #እንደተቆረጡ በሚገርም ሁኔታ ራሱ #ተአምረ ማርያም ይመሰክራል።
( #ታምር 24 እና 25 ገጽ 112- 121።)
*****************************
***

አብዛኛው የቤተክርስቲያናችን የዋህ ምዕመን እምነቱን የመሠረተ የሚመስለው #በታምረ ማርያም ላይ ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ እንኳ #ታምሯን #ሰምተን እንምጣ እንጂ ወንጌል #ተምረን አንምጣ ብለው አያስቡም አይናገሩም። በተለይ እሁድ እሁድ ታምር የሚያነብ እንጂ ወንጌል ለማስተማር የሚያስብ ቄስም የለንም።
#ከ400,000 ካህናት በላይ እንዳላት የሚነገርላት ቤተ ክርስቲያናችን #ታምረ ማርያም አንብቦ ከማሳለም ያላፈ አገልግሎት የሚሰጥበት አይደለም። በጣም በሚገርም ሁኔታ #ታምሯን #ሰምቶ የሄደ #ሥጋውና #ደሙን #እንደተቀበለ #ይቆጠርለታል የሚለው ባዕድ ወንጌል ስለ ጌታ ራት ከተሰጡት የስህተት ትምህርቶች ውስጥ በዋንኛነት ከሚጠቀሱት #አንዱ ነው።
አረ እንደው በፈጠራቹ ህሊና ያለው ሰው አሁን ይሄን ምን ይላል?
ክርስቲያን የሆነ ሰው አላልኩም
እንደው ህሊና ብቻ ያለው ሰው።

#ብዙ ጊዜ ደግሞ ስህተቱን እያወቁ በዝምታ የሚያልፉ አገልጋዮች አጋጥመውኛል ለምን እውነቱን እንደማይናገሩ ስጠይቅ ለዚህ ጊዜዬን አላጠፋም ወንጌል ሲረዱ እውነቱ ይገለጥላቸዋል የሚል ነው። እንደ እውነቱ ካየነው #የወንጌል #ብርሃን የማይፈታው ጨለማ የለም እንዲሁም ወንጌል ላይ ትኩረት ማድረጉም እደግፈዋለው ነገር አንድ የማልስማማበት ነገር አለ ስንቱን ወደ ዘላለማዊ ሞት እየነዳ ያለውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ #የተአምረ ማርያም ዓይነቱ ስጋ ስጋ የሚሸቱ የሰይጣን ሀሳብና ምክሩ የሰፈረበትን በግልፅ መዝለፍ ተገቢ ነው ብዬ አስባለው። ቃሉም እንደዛ ነውና የሚለው
የይሁዳ መልእክት 1:22

አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም #ከእሳት #ነጥቃችሁ አድኑ፥

#ብዙ ሰዎች ይሰድቡኛል ለምን ራስህን አትመለከትም ምናምን እኔ ግን አሁንም ቢሆን በሰው ልብ ውስጥ የነገሰውን በብልሃት የተፈጠረን #ተረትና #መንፈሳዊ #ይዘት ባለው ነገር የሚሰራውን #ክፉ ወገኖቼ ላይ እንዳይሰለጥን የበኩሌን አደርጋለው። የገድላትንም ደባ ባለኝ መረዳትና እግዚአብሔር በሰጠኝ #ፀጋ እጋደላለው በቃ ይሄ ነው የእኔ #አቋም
የገድላትን ደባ በማጋለጥ ሂደት ውስጥ ብዙ ሰዎች መልካም የሆነውን #እውነት ለይተውበታል ለዚህም በውስጥ መስመር የሚደርሰኝ አበረታች ቃላት ወደ ፊት እንድገፋበት ብርታት ሆኖኛል። እናም አጋልጣለው የሚሰማ ባይኖር እንኳ አልተውም። በእርግጥ #ከእውነቱም መሸሽ አይቻልም።

ብቻ ግን ለዛሬ ከላይ በርዕሱ እንደጠቀስኩት #የተአምረ ማርያምን ደባ #ከበለዔ #ሰብ ጋራ ያለውን ታሪክ በተያያዘ የኑሮአችን የመኖሪያ ልክ ወይም ቱንቢ በሆነው በሕያውና በሚሰራው #በቅዱሱ #የእግዚአብሔር #ቃል እንፃር እንመለከታለን መልካም #ንባብ
▶️ በቅዱስ ገብርኤል #ሰላምታ #ሰላም እልሻለሁ የሚለውን #ቃል ራሱ ብናየው #የተሳሳተ #አባባልና #ያልተለመደ #ንግግር ነው። በሌላ አገላለጽ #ዩሐንስ #ለጋይዮስ #ሰላም ለአንተ ይሁን ባለው #ሰላምታ [3ኛ ዩሀ 1፥15] #ጋይዮስ ሆይ #በዩሐንስ ሰላምታ #ሰላም እልሃለው እንደማለት ነው። ነገሩን #ግልጽ ለማድረግ አቶ #አበበ አቶ #ከበደ ቤት ገብቶ <<አቶ #ከበደ በአቶ #አበበ #ሰላምታ #ሰላም #እልሀለው>> ብሎ #ሰላምታ እንደመስጠት ያክል ነው። ይህም በማንኛውም #ህብረተሰብና #ክፍለዘመን ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው #ከጤናማው #የሰላምታ ሥነ-ሥርዓት የወጣ #አባባል ነው።

▶️ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #መልዕክት አድርስ ተብሎ ወደ #ድንግል ማርያም በመምጣት ያደረገውን #ሰላምታ ተንተርሶ #አጼ #ዘረዓ #ያዕቆብ <<ይወድስዋ መላእክት - {መላዕክት ማርያምን ያመሰግኗታል}>> የሚል #ድርሰት ሲያዘጋጅ #የቦረናው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ደግሞ <<ተፈሥሒ ኦ ሙኃዘፍስሐ፤ የተድላና የደስታ መፍሰሻ ሆይ ደስ ይበልሽ መላእክት ብለዋታል[1]>> ብሏል። ነገር ግን ወደ #ማርያም ተልከው የመጡት #መላእክት ሳይሆኑ አንድ #መለአክ ነው። እርሱም ቅዱስ #ገብርኤል ሲሆን ንግግሩም #ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደተላከ ማሳወቅና #ክርስቶስን ያለ #ወንድ #ዘር #በድንግልና እንደምትወልድ የሚገልጽ እንጂ የተለየ #ምስጋና ለመስጠትና #የተድላና #የደስታ #መፍሰሻ እንደነበረች ያሳሰበበት #ክፍል አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን #መልአኩ እርሱ ከመምጣቱ በፊት #ማርያምን #የሚያመሰግንበትም የተለየ #የሰራችው አንዳች ነገር የለም። ያም ሆኖ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት #መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም በነበራቸው የአጭር ጊዜ የመረዳዳት #ውይይትን እንደመደበኛ #የግል #ጸሎታቸው አድርገው #መጽሀፍ አዘጋጅተው የሚደግሙ አሉ። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው መልአኩ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም #ውይይት አደረጉ እንጂ #አንዱ #ለአንዱ ያቀረቡት #ጸሎት የለም። ንግግራቸውም #የዘውትር #ጸሎት እንዲሆንላቸው ያሳሰቡት ነገርም የለም።

▶️ ጌታ #ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ #ሰማይ ሲያርግ #ድንግል #ማርያም ባለችበት #በማርቆስ #እናት ቤት ሐዋሪያት #በአንድነት #በጸሎት ሲተጉ አጠገባቸው ያለችውን #ማርያምን <<በገብርኤል #ሰላምታ ሰላም እንልሻለን #በነፍስሽም #በስጋሽም ድንግል ነሽ ከተወደደው #ልጅሽ #ይቅርታ #ለምኚልን #ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ>> አሏሏትም፤ #የጸሎት #ማዕከላቸውም አልነበረችም። እርሷም እነርሱም በአንድነት << #የሁሉንም #ልብ የምታውቅ #ጌታ ሆይ>> እያሉ #ጌታን እያከበሩ ወደ #ጌታ ሲጸልዩ ነበር። በድንገት #መንፈስ ቅዱስም ለእሷም ለእነሱም #እኩል ያለልዩነት ወረደባቸው። [ሐዋ 1፤ 12-14፣ ሐዋ 2፤ 1-4]።

በተለይ ደግሞ << #ይቅርታን #ለምኚልን>> የሚለው #ቃል ጠቅላላውን #የክርስቶስን #ይቅርታ #ለሰው ልጆች እንዴት እንደተሰጠ አለማወቅና #የክርስቶስን #የደኅንነት #መስዋዕት #ከንቱ የሚያደርግ ነው። በመሆኑም ይህን #ጸሎት ማቅረብ #የጸሎትን #ትርጉም አለማወቅ ብቻ ሳይሆን በግልጽ #የክርስቶስ #ተቃዋሚ መሆን ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ "መጽሐፈ ሰዓታት" ገጽ 29።