ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ሌላው መጽሀፍ ደግሞ <<ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ አንቺን ደግሞ በጠላቶች አንገት #የብረት #ዛንጁር አግቢባቸው የመለከታቸውን ድምጽ #አክብጅው #ደንቆሮም አድርጊው እርሳቸውንም #በቀፎ #በቅርጫት በእግር ብረት #እሰሪያቸው በእግራቸው #ወጥመድ በከንፈራቸውም #ልጓም በአፍንጫቸው #ጉንፋን ላኪባቸው ሊሄዱበትም ወዳልፈቀዱበት መንገድ #መልሻቸው በልቦናቸውም #ፍርሃትን #መንቀጥቀጥን አሳድሪባቸው #መሸበርንና መንቀጥቀጥን ጨምሪባቸው #እንደሴቶች ይሁኑ። ከጽኑ ነፋስ ኃይል የተነሳ ዛፍ ሲንቀሳቀስ ቅጠሉ እንረዲረግፍ እንዲበተን እንዲሁ #ይሁኑ#በርሃብ #በቸነፈር #እህልን #በማጣት ቅሰፊያቸው፣ በሜዳ ሰይፍ ልጆቻቸውን #ያጥፋቸው በቤታቸውም ውስጥ #ፍርሃት ያስጨንቃቸው። #እሳት#በረዶ #ረሀብ፣ ቸነፈር ይፍጃቸው ይህ ሁሉ የእግዚአብሄር #የምጽአቱ #ጽዋ በጠላቶቼ ላይ ይውረድ እድል ፈንታቸው #ጽዋ ትርታቸው ይሁን[1]>>

▶️ እንግዲህ ይህ አይነቱ #ጸሎት #ክርስቶስና #ሐዋሪያቱ #ለገዳዮቻቸው እንኳ <<አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው>> ብለው ከጸለዩት ጋር ይጻረራል። ስለሆነም ይህ አይነት #ጸሎት #የበልዓም ትምህርት {የሰይጣን ትምህርት} እንጂ #የክርስቶስ #ትምህርትና #ጸሎት አይደለም [ዘኃ 22፥17 ፣ ራዕ 2፥14]። አንዳንዶች ለማስተባበል እንደሚሞክሩት <<ይሄ እርግማን ለሰይጣን ነው>> እንዳል እንኳን #አንደኛ <<የሚጠላኝን፣ የሚቃወመኝን ሰው..>> በማለት #ለሰውም ጭምር እንደሆነ ተጽፏል ሁለተኛ #ለሰይጣንም ቢሆን እንኳን እርሱ #መንፈስ ስለሆነ <<የሚለጎም አፍ፣ #ዲዳ የሚሆን #አንደበት፣ የሚዘጋ #ጉሮሮ#የሚደነቁር #ጆሮ፣ የሚቆረጥ #አንገት፣ የሚሰበር #ክንፍ የሉትም። ጌታ ኢየሱስም #አጋንንትን ከሰዎች ሲያስወጣ < #ውጡ!> ብሎ #ከመገሰጽና #ከማስወጣት በስተቀር [ማር 1፤ 25-27] #ዲዳ ሁኑ!፣ #ተቆረጡ!፣ #ተሰበሩ! አላለም። #ደቀመዛሙርቱም ቢሆኑ #አጋንንትን አውጡ ባላቸው መሰረት #በኢየሱስ ስም አስወጡ እንጂ [ማቴ 10፥8] #ቆራርጧቸው#ሰባብሯቸው#አደንቁሯቸው#ሽባ አርጓቸው አላለቸውም። እነርሱም #እርግማንና ሌላ #ቃላትን አልተጠቀሙም። ምክንያቱም ደሞ #አጋንንት #መንፈስ እንጂ #ሥጋዊ #አካላት የላቸውምና [ሐዋ 16፤ 16-18፣ ሉቃ 10፥17፣ ኤፌ 6፥12]። ጌታ በነገር ሁሉ #ማስተዋልን ያድለን [2ጢሞ 2፥7]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
______________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አርጋኖን ፤የእመቤታችን ምስጋና ዘሰኑይ፡ ገጽ 33-37፥ ተስፋ ገብረ ስላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።

@gedlatnadersanat
(8.6.4▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ በ"መጽሀፈ #ባርቶስ" ውስጥ ደግሞ <<ኢያኤል ኢያኤል ኢያኤል ኢያኤል ኢያኤል ኢያኤል ኢያኤል፣ ሄዳኤል ሄዳኤል ሄዳኤል ሄዳኤል ሄዳኤል ሄዳኤል ሄዳኤል፣ ዮዳኤል (7 ጊዜ)፣ ኡርናኤል (7 ጊዜ)፣ ሄርናኤል (7 ጊዜ)፣ አሚስ (7 ጊዜ)፣ ዲህዲክን፣ ኤልጌኩጲ፣ ህዱዲመታሮ፣ ዳዩለሚጢስ፣ ንልዲካአር፣ ሄብሩስ፣ ድዮስ፣ ድልዳ፣ ሆራ፣ ዲ ፣ ኒ ፣ ለውላ፣ ዲ፣ ካባ፣ ኒ፣ ዩዳ፣ ሆሪ፣ ሆሪ፣ ድልዳ፣ ኡሁዲ.... ዮሴ፣ ቅድላድ፣ ቂ፣ ቂ፣ ቢ፣ ጹ፣ ቁ፣ ኤል፣ ቅውንዋኤል፣ ሄኬልል፣ ውድናኤል፣ ውድናኪኢል፣ ቋጓከነስናኤል፣ ጓኩናኤል[3]።>>

▶️ ሰኔ ጎሎጎታ የተባለውም ሌላኛው የማርያም መጽሀፍ ከእነዚህ ህቡዕ አስማቶች ጋር የሚስማማ #ቋንቋዎች አሉት፦ [ሰኔ ጎሎጎታ" ገጽ 11]

▶️ የእነዚህን #ቋንቋዎችና #ፊደላት ትርጉማቸውን #የመጽሀፍት መተርጉማን #አባቶች ሲጠየቁ የሚሰጡት የተለመደው #ምላሽ <<ህቡዕ #አስማቶች(ስሞች) ስለሆኑ አይተረጎሙም፤ ትርጉማቸው አይታወቅም>> ይላሉ። ነገር ግን እነዚህ ከላይ ያየናቸው የማይተረጎሙ ቋንቋዎች <<አውደ ነገስት ወፍካፌ ክዋክብት>> #በ1953 ዓ.ም ታትሞ #በስውር አገልግሎት ላይ ከሚውለው አደገኛ #የጥንቆላ #መጽሀፍ ጋር ይመሳሰላል።

<<ሃሃሃኤል፣ አድናኤል፣ ኤልኤል፣ ላላላኤል፣ አሞላኤል፣ ሞላኤል፣ ሓሓሓኤል፣ ሐራዋኤል፣ ማማማኤል፣ ማሚመ፣ ኑዳኤል፣ ሣሣሣኤል፣ ራራራኤል፡ ራሙኤል፣ ኅዳታኤል፣ ቃቃቃኤል፣ ቅላኤኤል፣ ቀፍኤል ... ፖፖፖኤል፣ ቁቌቌቋቋኤል፣ ኮኩኩኳኳኤል፣ ጎጉጉጓጓኤል፣ ሆሆኁኁኋኋኤል፣ ኋኋራቱኤል፣ ካኤል፣ አጽናኤል[4]>>

ስለዚህ <<የማርያም የጸሎት መጽሀፍት ናቸው>> ብሎ መቀበል በራስ ላይ #እርግማንን ማውረድና #አጋንንትን መጥራት ነው።

<<አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።>> [ዘዳ 18:፥11]

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] ሰፊ ማብራሪያ ለማግኘት <ከመጋረጃው በስተጀርባ> በመሪጌታ ሙሴ መንበሩ፤ 3ተኛ ዕትም፥ ሶላር ማተሚያ ቤት፤ ሐምሌ 2009 ዓ.ም። እንዲሁም <ማሳቀል> ፣ <የዘመናት እንቆቅልች ሲፈታ> ... በመሪጌታ ሠረቀ ብርሃን ዘወንጌል ሌሎችንም ይመልከቷል።

[2] 📚፤ ነገረ ማርያም፥ ገጽ 47 "ተስፋ ገብረ ስላሴ ማተሚያ ቤት" አ.አ፤ 1991 ዓ.ም።

[3] 📚፤ መጽሐፈ ባርቶስ፤ ገጽ 8፣ 36፣ 51።

[4] 📚፤ በጥንታውያን የኢትዮጵያ ጠበብቶች፤ "ዓውደ ነገሥት ወፍካፌ ክዋክብት፤ በእንተ ፍቅረ ሰብእ፤ 58ኛ ምዕራፍ ገጽ 184፤ ተስፋ ገብረ ስላሴ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ፥ 1953 ዓ.ም።