ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.84K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram


ሮሜ 8÷34

" #የሞተው÷ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው÷ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው÷ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡"

#ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ ማስተላልፍ የፈለገው ‹‹ #እንግዲህ #በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን #ኵነኔ የለባቸውም›› የሚለውን ነው (ቊጥር 1)፡፡ ሐዋርያው በመቀጠል ‹‹ #በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው #የሕይወት መንፈስ ሕግ #ከኀጢአትና #ከሞት ሕግ ዐርነት›› ያወጣን መሆኑን ያበሥርና (ቊጥር 2) እንደ #ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ #መንፈስ ፈቃድ መመላለስ እንደሚገባን ይመክራል፡፡ ምክንያቱንም ደግሞ ‹‹ስለ #ሥጋ ማሰብ #ሞት ነውና÷ ስለ #መንፈስ ማሰብ ግን #ሕይወትና #ሰላም ነው›› በሚል ያስቀምጣል (ቊጥር 6)፡፡ ስለዚህ እንደ #ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ #መንፈስ ፈቃድ መመላለስ እንደሚገባ ካሰፈረ በኋላ ‹‹ #አባ #አባት ብለን የምንጮኽበትን #የልጅነት #መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና #ለፍርሀት #የባርነትን #መንፈስ አልተቀበላችሁምና›› ይላል (ቊጥር 15)፡፡ በመቀጠል ልጆች ከሆንን ደግሞ ወራሾች ነን ይልና ‹‹ #ዐብረንም ደግሞ እንድንከበር ዐብረን #መከራ ብንቀበል #ከክርስቶስ ጋር አብረን #ወራሾች ነን›› የሚል ሐሳብ ያቀርባል፡፡ ነገር ግን #መከራው #ልንወርሰው ካለው ክብር ጋር ሲመዛዘን ‹‹ምንም እንዳይደለ አስባለሁ››፡፡ ይህ ግን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት በሙሉ በመሆኑ ‹‹ #የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች #መገለጥ›› በመቃተት በተስፋ እየተጠባበቀ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በመቃተት ላይ ያለው ግን #ፍጥረት ብቻ ሳይሆን እኛም ጭምር መሆናችንን ያስቀምጥና ‹‹ #እንዲሁም ደግሞ #መንፈስ #ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት #እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና÷ ነገር ግን #መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት #ይማልድልናል›› ይላል፡፡ ምክንያቱንም ‹‹ #ልብንም የሚመረምረው #የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል÷ እንደ #እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ #ቅዱሳን #ይማልዳልና›› በማለት ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ ቡኋላ ቀደም ሲል ያቀረበውን በዚህ ምድር የሚያገኘንን #መከራ መነሻ በማድረግ ‹‹ #እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ #አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ #ለበጎ #እንዲደረግ እናውቃለን›› በማለት ይጀምርና #እግዚአብሔር #አስቀድሞ እንደ #ወሰነን፣ እንደ #ጠራን#እንዳጸደቀን እና #እንዳከበረን አስፍሮ ‹‹ #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን #ይቃወመናል?›› የሚል ጥያቄ ያነሣል፡፡ እንግዲህ ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው ‹‹ #እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? #የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው÷ #የሚኰንንስ ማን ነው?›› የሚለውን ጥያቄ በማንሣት #የኰናኙን ማንነት ለማሳየት ጥረት የሚያደርገው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት #ኰናኙ
▶️ "የሞተ"
(ሞቱ አንድ ጊዜ ብቻ የሆነ ወደፊት የማይደገም በመሆኑ በኃላፊ ጊዜ ነው የተቀመጠው)፣

▶️ "ከሙታንም የተነሣ"
(ትንሣኤውም ቢሆን ሞትን ድል አድርጎ በተነሣበት ጊዜ ብቻ የሆነ አንድ ክንውን ነውና የተነሣ አለው)፣

▶️ "በእግዚአብሔር ቀኝ ያለ"
(በእግዚአብሔር ቀኝ መሆኑ ስለ ሰው ልጆች ሊታይ ነው(ዕብ 9፥24)፡፡ ይሄውም የምልጃ ሥራው አካል ነውና አሁንም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፡፡ ስለዚህ ነው ሐዋርያው በእግዚአብሔር ቀኝ ነበረ ሳይሆን አለ ያለው)፣

▶️ "ስለ እኛ የሚማልድ" (የክርስቶስ ምልጃ ምንም እንኳ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ በተሠራው ሥራ የተፈጸመ ስለ ሆነ የማይደጋገም ቢሆንም፣ ቀደም ሲል እንደ ተባለው አሁንም ስለ እኛ በመታየት ይቅርታን እንድናገኝ ያደርጋልና ሐዋርያው ስለ እኛ የሚማልድ በማለት አሁንም አማላጃችን መሆኑን ተናገረ።) በማለት ስለ እኛ #የሚማልድ መሆኑን በማሳየት በዚህ ምድር ላይ ያለውን #መከራ #ማሸነፍ የሚቻልበትን #ማበረታቻ ይሰጣል፡፡ ይህ ምንባብ #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #የሚከሳቸው #ማን ነው? ለሚለው #ጥያቄ #ማንም የሚል ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን ማንም #ሊከሳቸው የማይችልበት #ምክንያት ደግሞ ስለ #እነርሱ #ሞቶ የነበረ #ሞትን #ድል አድርጎ #የተነሣው እና #በአብ ቀኝ ሆኖ #የሚያማልድላቸው #ስላለ ነው በሚል ነው የሚያስቀምጠው፡፡ #ሐዋርያው ቀደም ሲል #በክርስቶስ #ኢየሱስ ላሉት #አሁን #ኵነኔ የለባቸውም ማለቱን ማስታወሱም #ጠቃሚ ነው (ቊጥር 1)።
@ ( #ጳውሎስ "ስለ እኛ የሚማልደው" በማለት እርሱም #በክርስቶስ ኢየሱስ #የምልጃ ስራ ተጠቃሚ መሆኑን ይናገራል። አንዳንዶች #ሐዋሪያው #ጳውሎስን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን #በምልጃ ስራ ውስጥ አሰልፈው #የክርስቶስን የምልጃ ስራ ፊት ለፊት በመቃወም ላይ ናቸው። #ሐዋሪያው በዚህ ክፍል ላይ እርሱ #አማላጅ ስለመሆኑ ሳይሆን #ስለ ኢየሱስ #አማላጅነት እና እርሱም #በኢየሱስ #ምልጃ ተጠቃሚ ስለ መሆኑ ነው የሚያስተምረው። #መጽሀፉ እንደሚለው ደግሞ #ኢየሱስ የእኛ ብቻ ሳይሆን #የቅዱስ ጳውሎስም #አማላጅ ነው። ስለ ሌሎች #ያማልዳል የሚባለው #ጳውሎስ #በክርስቶስ ምልጃ ተጠቃሚ እንደሆነ የገለጸውን መመልከት ሁላችንም #አማላጅ #እርሱ ብቻ ወደ ሆነው ወደ #ክርስቶስ እንድንጠጋ ያበረታታል።)

#በመቀጠልም ስለ እኛ #ከሞተው#ሞትን ድል አድርጎ #ከተነሣው#በእግዚአብሔር ቀኝ ካለው እና #ስለ እኛ #ከሚያማልደው ‹‹ #ከክርስቶስ #ፍቅር ማን ይለየናል? #መከራ÷ ወይስ #ጭንቀት÷ ወይስ #ስደት÷ ወይስ #ራብ÷ ወይስ #ራቁትነት÷ ወይስ #ፍርሀት÷ ወይስ #ሰይፍ ነውን?›› ሲል ይጠይቃል፡፡ በእርግጥም ከዚህ #ጌታ ምንም የሚለየን የለም፡፡ ‹‹ #ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ #እንገደላለን÷ #እንደሚታረዱ #በጎች ተቈጠርን ተብሎ›› ተጽፏልና፡፡ ‹‹በዚህ ሁሉ ግን #በወደደን [በአማላጃችን] #በእርሱ #ከአሸናፊዎች እንበልጣለን፡፡ #ሞት ቢሆን÷ #ሕይወትም ቢሆን÷ #መላእክትም ቢሆኑ÷ #ግዛትም ቢሆን÷ #ያለውም ቢሆን÷ #የሚመጣውም ቢሆን÷ #ኀይላትም ቢሆኑ÷ #ከፍታም ቢሆን÷ #ዝቅታም ቢሆን÷ #ልዩ ፍጥረትም ቢሆን #በክርስቶስ ኢየሱስ #በጌታችን ካለ #ከእግዚአብሔር #ፍቅር ሊለየን #እንዳይችል ተረድቼአለሁ›› በማለት #ምዕራፉ ያበቃል፡፡ #በዚህ ምዕራፍ ውስጥ #አሁን #ኵነኔ #የለብንም በማለት የጀመረው #ሐዋርያው #ክርስቲያኖች ስለሚያጋጥማቸው ነገር #እየመከረና #እያበረታታ ሁሉን #በጽናት #ማሸነፍ እንዳለባቸው ሲናገር፣ ‹‹ #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው÷ #የሚኰንንስ ማን ነው?›› ለሚሉት #ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ‹‹ #ስለ እኛ የሚማልደው #ክርስቶስ #ኢየሱስ›› መሆኑን ነገረን፡፡ ለዚህስ ሳይሆን ይቀራል #በአንድምታው ላይ ‹‹ #እሱ #ቢያጸድቅ ማን #ይኰንነናል፡፡ #ኢየሱስ ክርስቶስ #ሞተ #ከሙታንም #ተለይቶ #ተነሣ፡፡ #በአብ #ዕሪና(እኩል፣ መተካከል) #ይኖራል ስለ እኛ #ይከራከራል፡፡ #መከራከርስ የለም #ስለ እኛ #በዕለተ #ዐርብ #ባደረገው #ተልእኮ ፍጹም #ዋጋችንን #የምናገኝ ስለ ሆነ›› እንደ ሆነ የሰፈረው????
📖/፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሀፍ ንባቡና ትርጓሜው (አ.አ፣ ግንቦት 1988) ገጽ 70።
📖/፤ መሐሪ ትርፌ (ሊቀ ሊቃውንት)፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሀፍ ንባቡ ከነትርጓሜው (አ.አ፤ ጥቅምት 23 1948) ገጽ 100።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..(ሮሜ 8፥34)
@gedlatnadersanat @teeod
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ስለዚህም ክፍሉን ስናየው እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? ብሎ ጠየቀ ።ምን ብሎ መለሰ? << #የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው>>ብሎ ነው የመለሰው ።ይህ ማለት ከሳሹ ማነው? #እግዚአብሔር ነው ማለት አይደለም ።ምክንያቱም #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ራሱ #አይከሳቸውምና በተመሳሳይም << #የሚኮንንስ ማነው? >ብሎ ጠየቀ ምን ብሎ መለሰ? የሞተው ይልቁንም #ከሙታን የተነሣው #በእግዚአብሔር…
<< #እግዚአብሔር የመረጣቸውን #የሚከሳቸው ማነው? #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር
ነው>> ሮሜ8:33 አለ።

< #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው>> አለ። #እግዚአብሔር #የሚያጸድቀው #እነማንን
ነው? አግዚአብሔር #የሚያጸድቀው እሱ #የመረጣቸውን ነው።
እሱ < #የጠራቸውን እነዚህን #አጸደቃቸው> ሮሜ8:30 እግዚአብሔር #የመረጣቸውን እሱ ራሱ #የሚያጸድቃቸው ከሆነ እንግዲህ በእነዚህ ምርጦች ላይ ክስ ማንሳት የሚችል
ማነው? #ማንም ሊኖር አይችልም
#እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማንም #ሊከሳቸው አይችልም ለምን? ምክንያቱም #እግዚአብሔር #አምላካችን
#የመረጣቸውን #ምርጦቹን #የሚያጸድቅ አምላክ ነውና።
#እርሱ የመረጣቸውን
#ያጸድቃል ።እርሱ መርጦ #ያጸደቃቸውን ማን #ይከሳቸዋል?
<የጠራቸውን እነዚህን አጸደቃቸው> ተብሎ ተጽፏል። እርሱ እንዲህ አድርጎ ያጸደቀውን ማን
#ሊከስ ይችላል? ማንም #ሊከሳቸው አይችልም ።
---
<< #የሚኮንንስ ማነው? #የሞተው ይልቁን ከሙታን የተነሣው #በእግዚአብሔር ቀኝ
ያለው ደግሞም ስለ እኛ #የሚማልደው #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው >>
ከላይ እንዳየነው #ዮሐንስ አፈወርቅ እንደገለጸው
<< #እግዚአብሔር ዘውዱን
አቀዳጅቶናል ማን #ይኮንነናል? #ክርስቶስ ስለሞተልን ደግሞም ከዚህ በኋላ
#ስለሚማልድልን ማን #ይኮንነናል>> ባለበት አገላለጽ ስንመለከተው
#እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #ያጸድቃቸዋል ፣ታዲያ እርሱ መርጦ #ያጸደቃቸውን
#የሚከሳቸው ማነው? #የሚኮንናቸውስ ማነው? ማንም #ሊኮንናቸው አይችልም።
እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #የሚኮንናቸውስ ማነው? ማንም።
እግዚአብሔር #ምርጦቹን #የመረጣቸው በክርስቶስ ነው ።
<< #ቅዱስና #ነውር የሌለን #በፍቅር እንሆን ዘንድ #በክርስቶስ ኢየሱስ
#መረጠን>>ኤፌ1:4
-
ይላል።
ታዲያ እነዚህ የእግዚአብሔር ምርጦች #በክርስቶስ ናቸው።
#በክርስቶስ #ኢየሱስ ላሉት ደግሞ #ኩነኔ የለባቸዎም << #በክርስቶስ #ኢየሱስ #ላሉት አሁን #ኩነኔ የለባቸውም >>ሮሜ8:1
#በክርስቶስ #ኢየሱስ የሆኑት እነዚህ የእግዚአብሔር ምርጦች አሁን #ኩነኔ #የለባቸውም#ኩነኔ #የሌለባቸውን እነዚህን ምርጦች ማን #ይኮንናቸዋል? ማንም
#ሊኮንናቸው አይችልም።
ለምን? ምክንያቱም ለእነርሱ ሲል #የሞተ አለ ፣ለእነርሱ
ሲል #ከሞት የተነሳ አለ ፣ለእነርሱ ሲል #በእግዚአብሔር ቀኝ #የተቀመጠ አለ
፣ ለእነርሱ ሲል #የሚማልድ #ሊቀ #ካህናት አለ እርሱም #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው።
የእግዚአብሔር ምርጦች #ከኩነኔ #ነጻ የመሆናቸው #ማረጋገጫ በክርስቶስ ሞት
#ትንሣኤ#እርገት እና #ምልጃ ነው ።
#እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይኮንናቸዋል? ማንም #አይኮንናቸውም
ምክንያቱም ለእነርሱ ሲል #የሞተ አለ እርሱም #ክርስቶስ ነው።
#ክርስቶስ #ለምርጦቹ ሲል በደላቸውን ተሸክሞ በእንጨት ላይ #ሞቷል#በበደላቸው
የሚመጣባቸው #ፍርድ እሱ #ተሸክሟል #ፍርዱም #በሞቱ ተፈጽሟል ፣ታዲያ
#ክርስቶስ #ኢየሱስ የሞተላቸውን እነዚህን ምርጦች ማነው #የሚኮንን?
ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ #ሞት #ታርቀዋል /ሮሜ5:8/
ታዲያ ማነው #የሚኮንናቸው? ስለእነርሱ #መሞት ብቻ አይደለም ይልቁንም ስለ እነርሱ #ከሞት #ተነሥቷል ፣ለምን #ከሞት ተነሣ? ።
< #እኛን #ስለማጽደቅ #ከሙታን #ተነሣ> /ሮሜ4:24/
ተብሏል።
#ከሞቱ በበለጠ #ትንሣኤው #ከኩነኔ #ለመዳናቸው ትልቅ ዋስትናቸው ነው። እነርሱን #ለማጽደቅ ከሞት #ተነስቷል #በትንሣኤውም #ጸድቀዋል ፣በክርስቶስ
#ትንሣኤ #የጸደቁትን እነዚህን የእግዚአብሔር ምርጦች #ማን #ይኮንናቸዋል?
እነዚህ ምርጦች #ከእግዚአብሔር ጋር #በልጁ #በክርስቶስ #ሞት #ታርቀዋል
ይልቁንም #ከሞት #ተነስቶ ሕያው ሆኖ በመኖሩ በህይወቱ ደግሞ ይድናሉ ፦
< #ከእግዚአብሔር ጋር #በልጁ ሞት #ከታረቅን #ይልቁንም ከታረቅን በኋላ #በሕይወቱ #እንድናለን> /ሮሜ5:11/
#ክርስቶስ ባይነሳ ኖሮ #ጽድቃቸው አይረጋገጥም
ነበረ ኃጢአተኛ ሆነው ይቀሩ ነበር << #ክርስቶስ #ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት
እስከ አሁን ድረሰ #በኃጢአታችሁ #አላችሁ>> /1ኛቆሮ15:17/ #በክርስቶስ ትንሣኤ
ዘለለማዊ #ጽድቅ አግኝተዋል።
#እግዚአብሔር #በልጁ #ትንሣኤ #ያጸደቃቸውን
ምርጦቹን ማን #ይኮንናቸዋል? ማንም። ስለዚህ #የክርስቶስ #ትንሣኤ #ከኩነኔ #የሚድኑበት ማረጋገጫቸው ሆኗልና የእግዚአብሔርን ምርጦች ማንም
#አይኮንናቸውም
#ይህም ብቻ አይደለም #ክርስቶስ ወደ #ሰማይ አርጎ
#በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡም ታላቅ የደኅንነት #ማረጋገጫቸው ነው።
#ክርስቶስ ወደ ሰማይ የወጣው #የሰዎችን ሥጋ #እንደያዘ ነው።
<< #ወደላይ
#በወጣህ ጊዜ ምርኮን ማረክህ>> /ኤፌ4:7/ እንደተባለ ክርስቶስ #በኃጢአት #በሕግ
#በሞት #በሰይጣን እንዲሁም ከማንኛውም ጠላት ሥር የነበረውን #የሰውን ሥጋ
ከጠላት ማርኮ በድል አድራጊነት ይዞት #በሰማያዊ ሥፍራ #በቀኙ ሥጋችንን #ሲያስቀምጠው በእርሱ #በኩል ከሞት በላይ መሆናችን ማንም ዝቅ ሊያደርገው
#በማይችል ከፍታ ላይ #መሆናችን ሲታወቅ በእርግጥም በእንዲህ አይነት ከፍታ
#ከፍ ያደረጋቸውን የእግዚአብሔር ምርጦች ማንም #ሊኮንናቸው አይችልም።
<< #ከክርስቶስ ጋር አስነሳን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ #ስፍራ ከእርሱ ጋር
#አስቀመጠን >> /ኤፌ2:7/ለው
ያለውም ይህን ነው ።
#ስለ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት #ይታይላቸው ዘንድ
ወደ ሰማይ #ገብቷልና #ማንም #ይኮንናቸው ዘንድ አይችልም
/ዕብ9:24/

እግዚአብሔር መርጦ #ያጸደቀንን ማን #ይከሰናል? #ክርስቶስ #ለኃጢአታችን
#የሞተልንን ማን #ይኮንነናል? #ክርስቶስ እኛን #ለማጽደቅ ከሞት ተነስቷል ታዲያ
ማን #ይኮንነናል? ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት #ይታይ ዘንድ ወደ ሰማይ
ገብቷልና ማን #ይኮንነናል? ክርስቶስ #ስለ እኛ #ይማልዳልና ማን ይኮንነናል?

አሜን ሃሌ ሉያ። ማንም

የክፍሉ ዓብይ ሀሳብ ይህ ነው። ይህንን ከተረዳን። ነገ ደግሞ ስለዚህ ጥቅስ የተነሱትንና የተባሉትን የተለያዩ ኑፋቄዎች እንመለከታለን።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል..(ሮሜ 8፥34)
@gedlatnadersanat @teeod
▶️ መድኃኒት የሚለው ቃል #በመጽሐፍ #ቅዱስ ውስጥ ያለው #ቦታ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ #ዳዊት ስለዚህ ሲናገር <<እግዚአብሔር አምባዬ አለቴ #መድኃኒቴ ነው>>/2 ሳሙ 22፥2/ ብሏል። በኢሳያስ አንደበትም እግዚአብሔር ለእስራኤል ሲናገር <<እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር #መድኃኒትህ ነኝ... እኔ እግዚአብሔር ነኝ #ከእኔ #ሌላ #የሚያድን የለም>> /ኢሳ 43፥3 ፣11/ ብሏል። እንደዚሁም ነብዩ በሌላ ቦታ ሰዎች እግዚአብሔርን <<የእስራኤል አምላክ #መድኃኒት ሆይ...>> ብለው እንደሚጠሩት ይናገርና በዚያው ክፍል ደግሞ #እግዚአብሔርም ስለራሱ በነቢዩ አንደበት <<እናንተ ከአህዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ ተሰብስባችሁ ኑ፤ በአንድነትም ቅረቡ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም። ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ ከጥንት ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም እኔ ጻድቅ አምላክና #መድኃኒት ነኝ ይላል>>/ኢሳ 45፥15 ፣ 20፥21/። በሌሎች ነብያትም <<ከእኔም በቀር ሌላ አምላክና #መድኃኒት የለም>>/ሆሴ 14፥4/ እያለ እግዚአብሔር ያውጅ ነበር። #መድኃኒትነት የእርሱ #ብቻ ነበርና ምንም እንኳን #በብሉይ ኪዳን #ሰንበት#በዓለ ሰዊት፣ #በዓለ መጸለት፣ #በዓለ ፍሥሐ፣ #በዓለ ናእት /የቂጣ በዓል/፣ #ኢዮቤልዩ የሚባሉ ታላላቅ #በዓላት ቢኖሩም ከእነዚህ አንዳቸውም #መድኃኒት አልተባሉም። ከእርሱ #ከእግዚአብሔር ሌላ #መድኃኒት እንደሌለ የተገነዘቡ የዘመኑ ነብያትም <<አንሥእ ኃይለከ ወነዓ አድኅነነ ማለትም ኃይልህን አንሣ መጥተህም #አድነን>>/መዝ 80፥2/ ይሉ ነበር እንጂ ሰንበትን #መድኃኒታችን ነሽ አላሏትም። በአዲስ ኪዳንም #ድንግል #ማርያም ጌታን በጸነሰች ጊዜ <<ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፤ መንፈሴም በአምላኬ #በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች የባርይቱን ውርደት ተመልክቷልና>>/ሉቃ 1፥47/ብላለች። ጊዜው ደርሶ ጌታ #በተወለደ ሰዓትም #መላእክት በለሊት መንጋ ለሚጠብቁ እረኞች << ዛሬ በዳዊት ከተማ #መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ #ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ብለው አበሰሩ>>/ሉቃ 2፥11/። #መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከላቸው ሲመላለስ ሕይወት ሰጪ ትምህርቱን የሰሙት የሰማርያ ሰዎችም ስለእርሱ ሲናገሩ << እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱም በእውነት ክርስቶስ #የዓለም #መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን>> ሲሉ ክርስቶስ መድኃኒት መሆኑን ተናግረዋል/ዩሀ 4፥42/። በእርግጥም #ጌታ እኛን ለማዳን #በመስቀል ላይ #ሞቶ ወደ ከርሠ መቃብር ወርዶ #ሞትን ድል ማድረግ ነበረበትና እንደ #መጻሕፍት ሐሳብ #በኃጢአተኞች እጅ ተሰጥቶ #ሞተ። እንደ እግዚአብሔር አሠራርም #ሞትን #አሸንፎ ተነሣ። ይህንን በዓይናቸው ያዩና የተገነዘቡ #ሐዋርያትም #ጌታ #ካረገ ቡኋላ ስለእርሱ #ለአይሁድ ሸንጎ ሲናገሩ <<እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤ ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ #ራስም #መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው>> ሲሉ ራስና #መድኃኒት ስለመሆኑ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል/ሐዋ 5፥31/። ኢየሱስ ማለት #አዳኝ #መድኃኒት ማለት ነው፤ #ዕለተ #ሰንበት ማዳን ብትችል ኖሮ "ወልደ እግዚአብሔር" #ሰው መሆን ባላስፈለገው ነበር።
#የሐዲስ ኪዳን #ምእመናን #ለመዳን እጆቻቸውን ወደማንም አያነሡም፤ #መዳን #በክርስቶስ ካልሆነ #በቀር በሌላ #በማንም... የለምና/ሐዋ 4፥12/። #እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን የሚያስችለውን #ከክርስቶስ ሌላ አማራጭ ቢፈልግ ኖሮ #ከሰንበት ይልቅ ብዙ ታላላቅ #ፍጥረታት ነበሩት፤ ሆኖም ግን #ከፍጥረት ወገን #ለማዳን የሚበቃ አልነበረምና #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ብቻውን #ለሰው ልጆች #መድኃኒት ሆነ።
እንደዚሁም በዚህ መጽሀፍ #ሰንበት <<ለዘላለም ገዥ>> ተብላለች፤ #በመጽሀፍ #ቅዱስ ስንመለከት ግን #ሰንበት ለሰው #ተፈጠረች እንጂ ሰው #ስለሰንበት #አልተፈጠረም። ሰዎችንም #ልትገዛ ከቶ አትችልም፤ #ለዘላለም የመኖር እድልም የላትም፤ የእርሷ #የጥላነት ጊዜ አብቅቶ #አካሉ #ክርስቶስ ተገልጧልና።

▶️ መድኃኒትነትም ሆነ #ገዥነት ያለው እርሱ #እግዚአብሔር #ብቻ ነው። መጽሀፍ ቅዱስ <<ብቻውን የሆነ ገዢ>> የሚለው እርሱን #ብቻ ነው/1ጢሞ 6፥15/። እንደዚሁም <<እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም፣ ወገበረ #መድኃኒት በማዕከለ ምድር ማለትም #እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው በምድርም መካከል #መድኃኒትን አደረገ>>/መዝ 74፥12/ የተባለለት የዘለዓለም ንጉሥ አንድ ጌታ ነው እንጂ ሰንበት አይደለችም።
እንደዙሁም ይች #ሰንበት <<ለምኝልን>> ተብላለች። አንዲት የማትሰማና #የጊዜ #መለኪያ ብቻ የሆነችው ^ዕለት^ #አፍ አውጥታ #እንድትናገርና በእግዚአብሄር ፊት ቆማ #እንድታማልድ ወደ እርሷ #እጅን #ዘርግቶ #መማጸን ወደ ልቡ ተመልሶ #ላስተዋለው ሰው ምን ያህል #አሳፋሪ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። ቃሉ ግን እኛ ራሳችን #በኢየሱስ #ክርስቶስ #ስም #እግዚአብሔርን እንድለምነው ሲያስተምረን እንደዚህ ይለናል፤ <<ማናቸውንም ነገር #በስሜ #ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ>>/ዩሀ 14፥13/፤ <<የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል>>/ዩሀ 15፥7/፤ <<እውነት እውነት እላቹሀለው #አብ #በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችሀል እስከ አሁን #በስሜ ምንም አለመናችሁም ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ>>/ዩሀ 16፤ 23-24/።
በዚህ መሰረት ወደ ማን #መለመን እንዳለብን ግልጽ ነው፤ በአጠቃላይ #ጸሎታችንና #ልመናችን #በኢየሱስ #በኩል ወደ #አብ እንዲደርስ እንጂ #በሌላ #በኩል ማለትም #በሰንበት ወደ #አብ መግባት እንደማይችል ልንረዳ ይገባል። ጌታም <<በእኔ #በቀር ወደ #አብ የሚመጣ #የለም>> ማለቱ ለዚሁ አይደለምን/ዩሀ 14፥6/?

@gedlatnadersanat
▶️ በቅዱስ ገብርኤል #ሰላምታ #ሰላም እልሻለሁ የሚለውን #ቃል ራሱ ብናየው #የተሳሳተ #አባባልና #ያልተለመደ #ንግግር ነው። በሌላ አገላለጽ #ዩሐንስ #ለጋይዮስ #ሰላም ለአንተ ይሁን ባለው #ሰላምታ [3ኛ ዩሀ 1፥15] #ጋይዮስ ሆይ #በዩሐንስ ሰላምታ #ሰላም እልሃለው እንደማለት ነው። ነገሩን #ግልጽ ለማድረግ አቶ #አበበ አቶ #ከበደ ቤት ገብቶ <<አቶ #ከበደ በአቶ #አበበ #ሰላምታ #ሰላም #እልሀለው>> ብሎ #ሰላምታ እንደመስጠት ያክል ነው። ይህም በማንኛውም #ህብረተሰብና #ክፍለዘመን ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው #ከጤናማው #የሰላምታ ሥነ-ሥርዓት የወጣ #አባባል ነው።

▶️ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #መልዕክት አድርስ ተብሎ ወደ #ድንግል ማርያም በመምጣት ያደረገውን #ሰላምታ ተንተርሶ #አጼ #ዘረዓ #ያዕቆብ <<ይወድስዋ መላእክት - {መላዕክት ማርያምን ያመሰግኗታል}>> የሚል #ድርሰት ሲያዘጋጅ #የቦረናው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ደግሞ <<ተፈሥሒ ኦ ሙኃዘፍስሐ፤ የተድላና የደስታ መፍሰሻ ሆይ ደስ ይበልሽ መላእክት ብለዋታል[1]>> ብሏል። ነገር ግን ወደ #ማርያም ተልከው የመጡት #መላእክት ሳይሆኑ አንድ #መለአክ ነው። እርሱም ቅዱስ #ገብርኤል ሲሆን ንግግሩም #ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደተላከ ማሳወቅና #ክርስቶስን ያለ #ወንድ #ዘር #በድንግልና እንደምትወልድ የሚገልጽ እንጂ የተለየ #ምስጋና ለመስጠትና #የተድላና #የደስታ #መፍሰሻ እንደነበረች ያሳሰበበት #ክፍል አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን #መልአኩ እርሱ ከመምጣቱ በፊት #ማርያምን #የሚያመሰግንበትም የተለየ #የሰራችው አንዳች ነገር የለም። ያም ሆኖ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት #መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም በነበራቸው የአጭር ጊዜ የመረዳዳት #ውይይትን እንደመደበኛ #የግል #ጸሎታቸው አድርገው #መጽሀፍ አዘጋጅተው የሚደግሙ አሉ። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው መልአኩ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም #ውይይት አደረጉ እንጂ #አንዱ #ለአንዱ ያቀረቡት #ጸሎት የለም። ንግግራቸውም #የዘውትር #ጸሎት እንዲሆንላቸው ያሳሰቡት ነገርም የለም።

▶️ ጌታ #ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ #ሰማይ ሲያርግ #ድንግል #ማርያም ባለችበት #በማርቆስ #እናት ቤት ሐዋሪያት #በአንድነት #በጸሎት ሲተጉ አጠገባቸው ያለችውን #ማርያምን <<በገብርኤል #ሰላምታ ሰላም እንልሻለን #በነፍስሽም #በስጋሽም ድንግል ነሽ ከተወደደው #ልጅሽ #ይቅርታ #ለምኚልን #ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ>> አሏሏትም፤ #የጸሎት #ማዕከላቸውም አልነበረችም። እርሷም እነርሱም በአንድነት << #የሁሉንም #ልብ የምታውቅ #ጌታ ሆይ>> እያሉ #ጌታን እያከበሩ ወደ #ጌታ ሲጸልዩ ነበር። በድንገት #መንፈስ ቅዱስም ለእሷም ለእነሱም #እኩል ያለልዩነት ወረደባቸው። [ሐዋ 1፤ 12-14፣ ሐዋ 2፤ 1-4]።

በተለይ ደግሞ << #ይቅርታን #ለምኚልን>> የሚለው #ቃል ጠቅላላውን #የክርስቶስን #ይቅርታ #ለሰው ልጆች እንዴት እንደተሰጠ አለማወቅና #የክርስቶስን #የደኅንነት #መስዋዕት #ከንቱ የሚያደርግ ነው። በመሆኑም ይህን #ጸሎት ማቅረብ #የጸሎትን #ትርጉም አለማወቅ ብቻ ሳይሆን በግልጽ #የክርስቶስ #ተቃዋሚ መሆን ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ "መጽሐፈ ሰዓታት" ገጽ 29።
▶️ በ1962 -1965 እ.ኤ.አ የ2ኛው #የካቶሊክ #የቫቲካን ጉባዔ <<ስለማርያም የሚሰጠው ትምህርት እውቅና እንዲያገኝና የማርያም ምስል ከፍ ተደርጎ እንዲያዝና እንዲሰገድለት ቅዱስ ተብሎም እንዲጠራ የአምልኮም መገልገያ እንዲሆን ወስነናል፤ ይህ የሲኖዶስ ውሳኔ ለቅድስት ማርያም ያለንን አክብሮት ለማሳየት ነው>> አለ[1]።

▶️ ይህን #የቫቲካን #ሲኖዶስን ጨምሮ ብዙ #ሰዎች #ምስልን ለመቀበል የወሰኑት <<ምስልን ማክበር ባለቤቱን ማክበር ነው>> በሚል #የተሳሳተ ሃሳብ ነው። አንዳንድ ጊዜም #ጣዖት ብለው የሚያስቡት #በእግዚአብሔርና #በማርያም አልያም #በመላዕክት #ተመስሎ የተሳለውን ወይም የተቀረጸውን ሳይሆን #በእንስሳት፣ በተለያዩ #ቁሳቁሶች መልክ የተዘጋጀውን #ቅርጽ ብቻ ይመስላቸዋል። በእርግጥ እነርሱም ቢሆኑ #አምልኮና #ስግደት ከቀረበባቸው #ጣኦታት ናቸው። ነገር ግን እንኳንስ #በማርያም #በእግዚአብሔር በራሱ #መልክን ሰርቶ ማስቀመጥ ብሎም ወደ #ምስሉ መስገድ #እግዚአብሔር ከመቃወምም ባለፈ #ይጸየፋል#ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ #ሲያስጠነቅቅ

<<እግዚአብሔርም በእሳት ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ የቃልን ድምፅ ሰማችሁ፥ መልክ ግን አላያችሁም፤ ድምፅን ብቻ ሰማችሁ።. . . እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤ እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥. . . ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።>> [ዘዳ 4፤ 12፣ 15-19]።

▶️ ከዚህ #ከበድ ካለ #ማስጠንቀቂያ እንደምንረዳው #በኮሬብ ለእስራኤል #እግዚአብሔር ራሱን ሲገልጥ #ያለመልክ በመሆኑ ይህን ይመስላል ብሎ #መሳልም #መቅረጽም ብሎም #መስገድ መሳት እንደሆነ እንረዳለን። #እግዚአብሔር እንኳንስ #ለማርያም ለራሱም ቢሆን #በተቀረጸ #ምስል #አምልኮ እንዲቀርብለት ፈጽሞ አይፈልግም።

▶️ በ15ኛው #ክፍለ ዘመን የነበሩት #እስጢፋኖሳውያን የአፄ ዘርዓያዕቆብ #አፍቅሮተ #ጣኦታት የተጠናወታቸው ሰዎች <<ምስለ ፍቁር ወልዳ>> ለሚባለው #ስዕል እንዲሰግዱ ቢያሳዩአቸው #ሥዕሉን አድንቀው <<ለሰው ስራ አትስገዱ>> የሚለውን #አምላካዊ #ትዕዛዝ በማስታወስ <<የሰው ስራ ነውና አንሰግድም>> እንዳሉ ገድላቸው ይተርካል[2]።

▶️ ሌሎችም ለምሳሌ #ዘሚካኤልና #ገማርያ የሚባሉ 2 ሊቃውንት <<አልቦቱ መልክዓ ለእግዚአብሔር ከመ መልክዓ ሰብዕ - እግዚአብሔር የሰው መልክ የሚመስል መልክ የለውም>> በማለታቸው አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ #ተቆጥቶና #ተከራክሮ አስቀጥቷቸዋል[3]።

▶️ ደቂቀ እስጢፋኖስ ይወቁት አይወቁት አይታወቅም እንጂ #ለስዕል #አይሰገድም የሚለው እውነት #በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ሃሳብ አይደለም። እነርሱ ከመነሳታቸው #ከ150 አመት በፊትም እዚያው ትግራይ <<ለስዕል አይሰገድም ጣኦት ነው፣ ሰሌዳ ነው>> ያሉ ታላላቅ #የሃይማኖት #አባቶች ነበሩ። ነገር ግን #አጼ #ያግብአ #ጽዮን[4] [1278-1286] <<በዚህ ጥያቄ እያመነታሁ ሳለው ቀይ ሴት (እመቤታችን) ተገልፃልኝ <<ለሥዕሌ መስገድ ይገባል ብላኛለችና ያልታዘዘ ገመድ ለአንገቱ ያከማቸው ንብረቱ ለሰራዊቴ ቤቱ ከጠመንጃዬ አፎት ለምታወጣ እሳት ይደረጋል>> ሲሉ #ነጋሪት #ጎስመው ስላወጁ ያገሩ ሰዎች ሁሉ #የስዕለ #ማርያም #አምልኮ ትምህርት ተደናግጠው ለጊዜውም ቢሆን ከንጉሱ #ጥይት ለመትረፍ <<ንጉሱ ያዘዘንን ሁሉ እናደርጋለን ለስዕልም እንሰግዳለን>> እንዳሉና በዚህም #እንቅስቃሴው ቀዝቀዝ እንዳለ የታሪክ ጸሀፊዎች ዘግበውታል[5]። <<እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላቹ ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ>> {ኢሳ 40፥18}።

<<እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።>> [ሐዋ 17፥29]።

<<እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።>> [ኢሳ 42፥8]።

<<እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚመለከውም በእውነትና በመንፈስ ነው>> [ዩሐ 4፥24]።

▶️ በመሆኑም #ምስሎች ወደ #ቤተክርስቲያን በገቡበት #ትርጉማቸው #ለማስተማሪያነት ካልሆነ በቀር #ለስርዓተ #አምልኮ መጠቀሚያ ሊውሉ አይገባም። <<ፀልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል-በቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል ፊት ፀልዩ>> ብሎ #ዘርዓያዕቆብ ያወጀው #አዋጅ #የኃጢአት አዋጅ ነውና ዲያቆኑ ቢተወው #ከእግዚአብሔር ጋር #መስማማት ነው።

<<የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ። እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።>> ይላል እግዚአብሔር [ዘዳ 7፤ 25-26]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ "The Docmates of Vatican vol. 2 pp 94,95, Londen 1973.

[2] 📚፤ ገድለ አባ ዕዝራ ገጽ 38።

[3] 📚፤ ጌታቸው ሀይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ" ገጽ 28፣ የህዳግ ማብራሪያ፤ 1996 ዓ.ም።

[4] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Yagbe'u_Seyon

[5] 📚፤ K.contirossini, the act፥ vol 16 (1965)፤ pp. 12-14።

📚፤ ጌታቸው ሀይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ" ገጽ 24፣ 1996 ዓ.ም።

@gedlatnadersanat
(9.5▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat