▶️ መድኃኒት የሚለው ቃል #በመጽሐፍ #ቅዱስ ውስጥ ያለው #ቦታ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ #ዳዊት ስለዚህ ሲናገር <<እግዚአብሔር አምባዬ አለቴ #መድኃኒቴ ነው>>/2 ሳሙ 22፥2/ ብሏል። በኢሳያስ አንደበትም እግዚአብሔር ለእስራኤል ሲናገር <<እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር #መድኃኒትህ ነኝ... እኔ እግዚአብሔር ነኝ #ከእኔ #ሌላ #የሚያድን የለም>> /ኢሳ 43፥3 ፣11/ ብሏል። እንደዚሁም ነብዩ በሌላ ቦታ ሰዎች እግዚአብሔርን <<የእስራኤል አምላክ #መድኃኒት ሆይ...>> ብለው እንደሚጠሩት ይናገርና በዚያው ክፍል ደግሞ #እግዚአብሔርም ስለራሱ በነቢዩ አንደበት <<እናንተ ከአህዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ ተሰብስባችሁ ኑ፤ በአንድነትም ቅረቡ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም። ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ ከጥንት ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም እኔ ጻድቅ አምላክና #መድኃኒት ነኝ ይላል>>/ኢሳ 45፥15 ፣ 20፥21/። በሌሎች ነብያትም <<ከእኔም በቀር ሌላ አምላክና #መድኃኒት የለም>>/ሆሴ 14፥4/ እያለ እግዚአብሔር ያውጅ ነበር። #መድኃኒትነት የእርሱ #ብቻ ነበርና ምንም እንኳን #በብሉይ ኪዳን #ሰንበት፣ #በዓለ ሰዊት፣ #በዓለ መጸለት፣ #በዓለ ፍሥሐ፣ #በዓለ ናእት /የቂጣ በዓል/፣ #ኢዮቤልዩ የሚባሉ ታላላቅ #በዓላት ቢኖሩም ከእነዚህ አንዳቸውም #መድኃኒት አልተባሉም። ከእርሱ #ከእግዚአብሔር ሌላ #መድኃኒት እንደሌለ የተገነዘቡ የዘመኑ ነብያትም <<አንሥእ ኃይለከ ወነዓ አድኅነነ ማለትም ኃይልህን አንሣ መጥተህም #አድነን>>/መዝ 80፥2/ ይሉ ነበር እንጂ ሰንበትን #መድኃኒታችን ነሽ አላሏትም። በአዲስ ኪዳንም #ድንግል #ማርያም ጌታን በጸነሰች ጊዜ <<ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፤ መንፈሴም በአምላኬ #በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች የባርይቱን ውርደት ተመልክቷልና>>/ሉቃ 1፥47/ብላለች። ጊዜው ደርሶ ጌታ #በተወለደ ሰዓትም #መላእክት በለሊት መንጋ ለሚጠብቁ እረኞች << ዛሬ በዳዊት ከተማ #መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ #ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ብለው አበሰሩ>>/ሉቃ 2፥11/። #መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከላቸው ሲመላለስ ሕይወት ሰጪ ትምህርቱን የሰሙት የሰማርያ ሰዎችም ስለእርሱ ሲናገሩ << እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱም በእውነት ክርስቶስ #የዓለም #መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን>> ሲሉ ክርስቶስ መድኃኒት መሆኑን ተናግረዋል/ዩሀ 4፥42/። በእርግጥም #ጌታ እኛን ለማዳን #በመስቀል ላይ #ሞቶ ወደ ከርሠ መቃብር ወርዶ #ሞትን ድል ማድረግ ነበረበትና እንደ #መጻሕፍት ሐሳብ #በኃጢአተኞች እጅ ተሰጥቶ #ሞተ። እንደ እግዚአብሔር አሠራርም #ሞትን #አሸንፎ ተነሣ። ይህንን በዓይናቸው ያዩና የተገነዘቡ #ሐዋርያትም #ጌታ #ካረገ ቡኋላ ስለእርሱ #ለአይሁድ ሸንጎ ሲናገሩ <<እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤ ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ #ራስም #መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው>> ሲሉ ራስና #መድኃኒት ስለመሆኑ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል/ሐዋ 5፥31/። ኢየሱስ ማለት #አዳኝ #መድኃኒት ማለት ነው፤ #ዕለተ #ሰንበት ማዳን ብትችል ኖሮ "ወልደ እግዚአብሔር" #ሰው መሆን ባላስፈለገው ነበር።
#የሐዲስ ኪዳን #ምእመናን #ለመዳን እጆቻቸውን ወደማንም አያነሡም፤ #መዳን #በክርስቶስ ካልሆነ #በቀር በሌላ #በማንም... የለምና/ሐዋ 4፥12/። #እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን የሚያስችለውን #ከክርስቶስ ሌላ አማራጭ ቢፈልግ ኖሮ #ከሰንበት ይልቅ ብዙ ታላላቅ #ፍጥረታት ነበሩት፤ ሆኖም ግን #ከፍጥረት ወገን #ለማዳን የሚበቃ አልነበረምና #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ብቻውን #ለሰው ልጆች #መድኃኒት ሆነ።
እንደዚሁም በዚህ መጽሀፍ #ሰንበት <<ለዘላለም ገዥ>> ተብላለች፤ #በመጽሀፍ #ቅዱስ ስንመለከት ግን #ሰንበት ለሰው #ተፈጠረች እንጂ ሰው #ስለሰንበት #አልተፈጠረም። ሰዎችንም #ልትገዛ ከቶ አትችልም፤ #ለዘላለም የመኖር እድልም የላትም፤ የእርሷ #የጥላነት ጊዜ አብቅቶ #አካሉ #ክርስቶስ ተገልጧልና።
▶️ መድኃኒትነትም ሆነ #ገዥነት ያለው እርሱ #እግዚአብሔር #ብቻ ነው። መጽሀፍ ቅዱስ <<ብቻውን የሆነ ገዢ>> የሚለው እርሱን #ብቻ ነው/1ጢሞ 6፥15/። እንደዚሁም <<እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም፣ ወገበረ #መድኃኒት በማዕከለ ምድር ማለትም #እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው በምድርም መካከል #መድኃኒትን አደረገ>>/መዝ 74፥12/ የተባለለት የዘለዓለም ንጉሥ አንድ ጌታ ነው እንጂ ሰንበት አይደለችም።
እንደዙሁም ይች #ሰንበት <<ለምኝልን>> ተብላለች። አንዲት የማትሰማና #የጊዜ #መለኪያ ብቻ የሆነችው ^ዕለት^ #አፍ አውጥታ #እንድትናገርና በእግዚአብሄር ፊት ቆማ #እንድታማልድ ወደ እርሷ #እጅን #ዘርግቶ #መማጸን ወደ ልቡ ተመልሶ #ላስተዋለው ሰው ምን ያህል #አሳፋሪ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። ቃሉ ግን እኛ ራሳችን #በኢየሱስ #ክርስቶስ #ስም #እግዚአብሔርን እንድለምነው ሲያስተምረን እንደዚህ ይለናል፤ <<ማናቸውንም ነገር #በስሜ #ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ>>/ዩሀ 14፥13/፤ <<የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል>>/ዩሀ 15፥7/፤ <<እውነት እውነት እላቹሀለው #አብ #በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችሀል እስከ አሁን #በስሜ ምንም አለመናችሁም ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ>>/ዩሀ 16፤ 23-24/።
በዚህ መሰረት ወደ ማን #መለመን እንዳለብን ግልጽ ነው፤ በአጠቃላይ #ጸሎታችንና #ልመናችን #በኢየሱስ #በኩል ወደ #አብ እንዲደርስ እንጂ #በሌላ #በኩል ማለትም #በሰንበት ወደ #አብ መግባት እንደማይችል ልንረዳ ይገባል። ጌታም <<በእኔ #በቀር ወደ #አብ የሚመጣ #የለም>> ማለቱ ለዚሁ አይደለምን/ዩሀ 14፥6/?
@gedlatnadersanat

ተሻሽሎ የቀረበ
መጽሀፈ ሰአታት
💠 "ኪሩቤል አፍራሰ ፌማ፣ ወሱራፌል ዘራማ፣ ክሉላነ ሞገስ ወግርማ፣ ይሴብሑኪ ማርያም በሐዋዝ ዜማ"
💠 " ግርማንና ሞገስን የተቀዳጁ የፌማ ፈረሶች ኪሩቤልና ራማዊው ሱራፌልም ባማረ ዜማ ማርያም ሆይ አንቺን ያመሰግኑሻል"
/ኲሎሙ ዘኪዳነ ምህረት -- ገጽ 109/
▶️ በዚህ ክፍል ላይ ደራሲው #ኪሩቤልና #ሱራፌል ባማረ ዜማ #ማርያምን #እንደሚያመሰግኗት ይናገራል። በእርግጥ እነዚህ #ቅዱሳን #ፍጥረታት #ተጨማሪ አድርገው ወይም #እግዚአብሔርን #ትተው #የሚያመሰግኑት #ሌላ ተመስጋኝ #ፍጡር #እንደተመደበላቸው የሚያሳይ #መፅሀፍቅዱሳዊ መረጃ የለንም። ደግሞም #በሰማይ #ፍጡር #አይመሰገንም፤ ወደዚያች #ከተማ #የገባ ሁሉ #የከተማዋን #ባለቤት #ያመሰግናል፤ <እኔ ልመስገን> የሚል #ፍጡርም የለም።
<ድንግል ማርያምም> በሰማይ #ከአእላፋት #መላእክትና #ከቅዱሳን ጋር ሆና ስለተደረገላት ነገር #ፈጣሪዎን ታመሰግናለች።
ከዚህ ውጪ ግን በዚያ #በሰማይ #ከኪሩቤልና #ከሱራፌል #ውዳሴን #ትቀበላለች ብሎ ማሰብ #በምድር እንኳን #የተወገዘውን #ፍጡራንን #ማምለክ ወደ #ሰማይ ለማውጣትና #በሰማይም #ተቀባይነት ያለው #ለማስመሰል የተደረገ ^ጥረት እንደሆነ #አስተዋዮች አያጡትም።
▶️ የሰማይ አምልኮ በተገለጠበት #በራእይ #መፅሀፍም #ቅዱሳን #መላእክት #በአንዱም አጋጣሚ #ፍጡራንን #ሲያመልኩ #አለመታየታቸው #ትምህርት ሊሆነን ይገባል።
<የጌታን እናት> የሕይወት #ታሪክ በሚገባ የሚያውቁ #ሐዋሪያት እንኳ ምንም #የጌታቸው #እናት ብትሆንም እርሷ #ምስጋናና፣ ውዳሴ #ልትቀበል #እንደሚገባት ለማመልከት #አንድ #ጥቅስ እንኳን አልፃፉልንም።
<< እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ #ብፅኢት ይሉኛል>>/ሉቃ 1-48/። ብላ ራሷ #ድንግል #ማርያም የተናገረችው #ቃልም ቢሆን እንደ #ኤልሳቤጥ <ከጌታ የተነገረላት ይፈጸማልና ያመነች ብጽኢት ናት>/ሉቃ 1-45/። ብሎ #ስለጌታ #እናት #በሦስተኛ መደብ #ምሥክርነት #መስጠት ማለት ነው እንጅ #እርሷ #ከሞተች ቡሀላ #በጸሎትና #በውዳሴ #በሁለተኛ #መደብ
<< #ማርያም ሆይ #ብጽኢት ነሽ>> ማለትን የሚያመለክት አይደለም።
( <ለድንግል ማርያም የሚጠቀሱ የተለመዱ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው> በሚለው ስር ሰፊ ማብራሪያ ያገኙበታል።)
#ሐዋርያትም ለእርሷ የሚሆን #ውዳሴ አላቀረቡም፤ ይህንም አለማዳረጋቸው #በንቀት ሳይሆን #ማድረግ የሚገባቸውን #በውስጣቸው የሚኖር #መንፈስ #ቅዱስ ስለሚያሳያቸው ነው። #በሰማይ ያሉ #መላእክትም ባመሰገኑ ጊዜ ሁሉ #እሷን አለመጨመራቸው ይህን ማድረግ #ስህተት ስለሆነ ነው። በመሆኑም #የሰማይ #ቅዱሳን #ፍጥረታት #የሚያመሰግኑትንና፣ #ምስጋና #የሚገባውን #ጠንቅቀው ስለሚያቁ #ሲያመሰግኑ እንዲህ ይላሉ፤ ፦
<<መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ #ይገባሃል፥ #ታርደሃልና፥ #በደምህም ለእግዚአብሔር #ከነገድ ሁሉ #ከቋንቋም ሁሉ #ከወገንም ሁሉ #ከሕዝብም ሁሉ #ሰዎችን #ዋጅተህ #ለአምላካችን #መንግሥትና #ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ #ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።>>
<<አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥ በታላቅም ድምፅ። #የታረደው #በግ #ኃይልና #ባለ #ጠግነት #ጥበብም #ብርታትም #ክብርም #ምስጋናም #በረከትም #ሊቀበል #ይገባዋል አሉ።>> /ራእይ 5፤ 9-12/።
በዚህ ክፍል ላይ #ሲመሰገን የምናየው #ክርስቶስ ነው እንጅ #ድንግል ማርያም አይደለችም።
በአካባቢው መኖሯንም የሚገልጽ ምንም #የመጽሀፍ #ቅዱስ ክፍል የለም። በተጨማሪም እስቲ የሚከተሉትን ጥቅሶች እንመልከታቸው፤ ፦
✅ ራእይ 4-8 , 7-9 , 11-15 , 12-10 , 15-3 , 19፥1።
በእነዚህም #ጥቅሶች #በሙሉ #ከጌታ #በስተቀር #በሰማይ #ማንም #አልተመሰገነም። #በመንፈስ #ቅዱስ #ተመርተው #የጌታ #ሰዎች የጻፉት #መጽሀፍ #ቅዱስ በሰማይ #የሚመሰገነውንና ያለውን #የአምልኮ #ስርዓት በዚህ ዓይነት አስቀምጦልናል። ስለሆነም #ያላየነውንና #ያልሰማነውን #በመጽሀፍ #ቅዱስም የሌለውን በሚያስተምሩ #ሰዎች ላይ #በእውነትና #በመንፈስ የሚመለከው #አምላክ ይፈርድባቸዋል። #ከቅዱስ #መጽሐፍ #ሐሳብና #እውነታ በተለየ መንገድ <<በሰማይ ማርያም ትመሰገናለች፤ እነ ሱራፌል ያመሰግኗታል>> ማለቱ ራስን #ሀሰተኛ #ምስክር ማድረግ ነው። ይህም #በእግዚአብሄር ፊት ተጠያቂ ያደርጋል። ምክንያቱም #በእውነተኛው #ቅዱስ #መጽሀፍ #ባለመመዝገቡና #እውነት ባለመሆኑ ነው። ስለሆነም #ኪሩቤልና #ሱራፌል እንዲህ ያለውን #ስህተት ይፈጽማሉ ብሎ #መመስከሩ #የሀሰት #ምስክር #ያሰኛል እንጂ #ማርያምንም ሆነ #ኪሩቤልን ደስ ማሰኘት እንዳልሆነ #መገንዘብ ይገባል። ዩሐንስ #በራእይ ያን ሁሉ #ምስጋና ሲያይ አንዴ እንኳ <ድንግል ማርያም> #ስትመሰገን አልሰማም። በመሆኑም #ኪሩቤልና #ሱራፌል <<የታረደውን በግ>> ብቻ #እንደሚያመሰግኑ #መመስከሩ በቂ ነውና እንዲህ የሚያደርጉትን <<ከተጻፈው አትለፍ>> /1ቆሮ 4፥6/ የሚለውን #የተቀደሰ #መመሪያ ተማሩ እንላቸዋለን።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝