ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ እስቲ እነዚህን ጥቅሶች ይመልከቷቸው። 〽️ ሐዋ 1፤ 9-11፦ <<ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ…
〽️ ሐዋ 2፤ 14-18፣ 17-20፦

<<ነገር ግን ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ፥ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው። አይሁድ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፥ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ቃሎቼንም አድምጡ። ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም፥ ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤ ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለው ነው። እግዚአብሔር ይላል። በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ. . .>>

⁉️ መንፈስቅዱስም የመጣው #ማርያም ስላለች ሳይሆን በነብዩ #በኢዩኤል #የተተነበየው #ይፈጸም ዘንድ ነበር። ስለዚህ #የማርያም #በአካል መኖር የተለየ ነገር አልነበረውም። #ማርያምም እዛ #ትንቢት ውስጥ መካተቷ <<ስጋ በለበሰ ሁሉ ላይ>> እንደተባለው #ማርያምን ጨምሮ ሳያበላልጥ #እኩል #በወንዶችና #በሴቶች ላይ ማደሩ፤ እሷም #ስጋ ከለበሱት ጋር #እኩል #መቆጠሯ ፈጽሞ ከሌላው #የተለየች እንዳልሆነች ያሳያል።

〽️ ሐዋ 2፤ 22-35፦

<<የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤ እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት። እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና። . . . ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤. .>>

⁉️ #ሐዋርያት #በመንፈስ ቅዱስ ሆነው #በመካከላቸው #ማርያም ብትኖርም <<የናዝሬቱን ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሄር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበር>> በሚል ቃል #ክርስቶስን ብቻ #ማዕከል ያደረገ #ስብከት #ሰጡ እንጂ #ስለማርያም ያሉት ነገር አልነበረም።

〽️ ሐዋ 2፤ 37-38፦

<<ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ፥ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት። ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉአቸው። ጴጥሮስም። ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።>>

⁉️ #የሐዋርያትን #ስብከት የሰሙት ህዝቦች #ሐዋርያትን ምን እናድርግ ብለው #ሲጠይቋቸው በመካከላችን እናቱ #ማርያም ስላለች #በእርሷ #አማላጅነት #እመኑ ወደ እርሷ ወይም #በእርሷ በኩል ቅረቡ ሳይሆን ያሉት #ንስሃ ገብታችሁ #በኢየሱስ ስም ተጠመቁ #የመንፈስ ቅዱስ #ስጦታ #ትቀበላላችሁ የሚል #ክርስቶስን #ብቻ የገለጸ #መልስ ነበር የሰጡት።

〽️ ሐዋ 2፥47፦

<<እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።>>

⁉️ ሁሉም #በአንድነት #እግዚአብሔርን #በቀጥታ #ያመሰግኑ ነበር እንጂ ወደ #ማርያምም ሲጸልዩም ሆነ #ምስጋና ሲያቀርቡ አላየንም። በዚህም #ምክንያት የማርያም #በመካከላቸው #መኖርና #አለመኖር የተለየ ምንም #ጥቅም እንደሌለው የተረዱ ሲሆን #ጌታም #አብሮአቸው በመስራት #ዕለት #ዕለት #ቁጥራቸው ይጨምር ነበር።

▶️ ደግሞም #በብሉይም ይሁን #በአዲስ ኪዳን #እጹብ ድንቅ #በእግዚአብሄር ኃይል #ተአምራትን ካደረጉ #ሴቶች ይልቅ #ማርያም ከፍ ብላ የምትታይበት #አንድም #ተአምር #በመጽሀፍ ቅዱስ እንዳደረገች እንኳ #አልተጻፈም#በወንዶችም ቢሆን የተደረገው #ተአምር #ምድርን ሁሉ ቢያስገርምም ማንም <ከፍጡራን በላይ> የተባለ ግን የለም። ምክንያቱም #የተአምራቱ ባለቤት #እግዚአብሔር እንጂ #ሰዎች አይደሉምና። ስለዚህም እዚህ ላይ ልንገነዘበው የሚገባን #እውነት ቢኖር #ማርያም ከተባረኩ #በርካታ #ሴቶች #መካከል #የተባረከች #አንዷ #ሴት መሆኗን ነው {ሉቃ 1፥28 ፣ ሉቃ 1፥42}። #ቃሉም እንደ እርሱ ነው የሚለውና #ቃሉን #ብቻ እንመን።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_______________
[1] 📚፤ አባ መልከ ጻድቅ (ሊቀ ጳጳስ) <ኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ እምነትና ትምህርት> ገጽ 217፥ ንግድ ማተሚያ ድርጅት፡ አ.አ 1994 ዓ.ም።

📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤
<መጽሐፈ ሚስጥር> ገጽ 97፤
<መጽሀፈ ደጓ> ገጽ 380 እና 386።

📚፤ አባ ጎርጎሪዮስ (የሸዋ ሊቀ ጳጳስ)፡ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ታሪክ፡ ገጽ 133፤ አ.አ ፡1994 ዓ.ም።

[2] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
<መጽሀፈ ሚስጥር> ገጽ 97፥
"አርጋኖን ዘዓርብ" ገጽ 296፥ 3፤ 3-4። ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ 1989 ዓ.ም።

[3] 📚፤ የዘውትር ጸሎት፡ ውዳሴ ማርያም በአማርኛ፤ ገጽ 5-8፡ ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1986 ዓ.ም።

📚፤ አንዱ ዓለም ዳግማዊ (መምህር)፤ <ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት> ገጽ 257፤ ብራና ማተሚያ ድርጅት፤ አ.አ፥ ሚያዚያ 1998 ዓ.ም።


(6.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ በቅዱስ ገብርኤል #ሰላምታ #ሰላም እልሻለሁ የሚለውን #ቃል ራሱ ብናየው #የተሳሳተ #አባባልና #ያልተለመደ #ንግግር ነው። በሌላ አገላለጽ #ዩሐንስ #ለጋይዮስ #ሰላም ለአንተ ይሁን ባለው #ሰላምታ [3ኛ ዩሀ 1፥15] #ጋይዮስ ሆይ #በዩሐንስ ሰላምታ #ሰላም እልሃለው እንደማለት ነው። ነገሩን #ግልጽ ለማድረግ አቶ #አበበ አቶ #ከበደ ቤት ገብቶ <<አቶ #ከበደ በአቶ #አበበ #ሰላምታ #ሰላም #እልሀለው>> ብሎ #ሰላምታ እንደመስጠት ያክል ነው። ይህም በማንኛውም #ህብረተሰብና #ክፍለዘመን ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው #ከጤናማው #የሰላምታ ሥነ-ሥርዓት የወጣ #አባባል ነው።

▶️ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #መልዕክት አድርስ ተብሎ ወደ #ድንግል ማርያም በመምጣት ያደረገውን #ሰላምታ ተንተርሶ #አጼ #ዘረዓ #ያዕቆብ <<ይወድስዋ መላእክት - {መላዕክት ማርያምን ያመሰግኗታል}>> የሚል #ድርሰት ሲያዘጋጅ #የቦረናው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ደግሞ <<ተፈሥሒ ኦ ሙኃዘፍስሐ፤ የተድላና የደስታ መፍሰሻ ሆይ ደስ ይበልሽ መላእክት ብለዋታል[1]>> ብሏል። ነገር ግን ወደ #ማርያም ተልከው የመጡት #መላእክት ሳይሆኑ አንድ #መለአክ ነው። እርሱም ቅዱስ #ገብርኤል ሲሆን ንግግሩም #ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደተላከ ማሳወቅና #ክርስቶስን ያለ #ወንድ #ዘር #በድንግልና እንደምትወልድ የሚገልጽ እንጂ የተለየ #ምስጋና ለመስጠትና #የተድላና #የደስታ #መፍሰሻ እንደነበረች ያሳሰበበት #ክፍል አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን #መልአኩ እርሱ ከመምጣቱ በፊት #ማርያምን #የሚያመሰግንበትም የተለየ #የሰራችው አንዳች ነገር የለም። ያም ሆኖ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት #መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም በነበራቸው የአጭር ጊዜ የመረዳዳት #ውይይትን እንደመደበኛ #የግል #ጸሎታቸው አድርገው #መጽሀፍ አዘጋጅተው የሚደግሙ አሉ። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው መልአኩ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም #ውይይት አደረጉ እንጂ #አንዱ #ለአንዱ ያቀረቡት #ጸሎት የለም። ንግግራቸውም #የዘውትር #ጸሎት እንዲሆንላቸው ያሳሰቡት ነገርም የለም።

▶️ ጌታ #ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ #ሰማይ ሲያርግ #ድንግል #ማርያም ባለችበት #በማርቆስ #እናት ቤት ሐዋሪያት #በአንድነት #በጸሎት ሲተጉ አጠገባቸው ያለችውን #ማርያምን <<በገብርኤል #ሰላምታ ሰላም እንልሻለን #በነፍስሽም #በስጋሽም ድንግል ነሽ ከተወደደው #ልጅሽ #ይቅርታ #ለምኚልን #ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ>> አሏሏትም፤ #የጸሎት #ማዕከላቸውም አልነበረችም። እርሷም እነርሱም በአንድነት << #የሁሉንም #ልብ የምታውቅ #ጌታ ሆይ>> እያሉ #ጌታን እያከበሩ ወደ #ጌታ ሲጸልዩ ነበር። በድንገት #መንፈስ ቅዱስም ለእሷም ለእነሱም #እኩል ያለልዩነት ወረደባቸው። [ሐዋ 1፤ 12-14፣ ሐዋ 2፤ 1-4]።

በተለይ ደግሞ << #ይቅርታን #ለምኚልን>> የሚለው #ቃል ጠቅላላውን #የክርስቶስን #ይቅርታ #ለሰው ልጆች እንዴት እንደተሰጠ አለማወቅና #የክርስቶስን #የደኅንነት #መስዋዕት #ከንቱ የሚያደርግ ነው። በመሆኑም ይህን #ጸሎት ማቅረብ #የጸሎትን #ትርጉም አለማወቅ ብቻ ሳይሆን በግልጽ #የክርስቶስ #ተቃዋሚ መሆን ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ "መጽሐፈ ሰዓታት" ገጽ 29።
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ነብያት#ካህናት#ሐዋሪያት #ሁሉም ማለት ይቻላል ጸልየዋል። #ጸሎታቸውም በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር እንጂ እንኳን ወደ #ፍጡራን፣ ወደ #መላእክት የጸለየ አንድም #ሰው አናገኘም። #ድንግል #ማርያም እንኳን #በሉቃስ 1፤46-55 እንደተገለጸው <<ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፤ መንፈሴም በአምላኬ በመድሃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች.....>> በማለት እንዲሁም #በሐዋ 1፥25 #ከ120 #ሰዎች ጋር አብራ <<የሁሉንም ልብ የምታውቅ ጌታ ሆይ>> እያለች በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ነው የጸለየችው። #ኢየሱስ ክርስቶስም #በሥጋው ወራት #በርካታ ጊዜ ያለማቋረጥ ወደ #አባቱ <<አባት ሆይ...>> በማለት #ጸሎት አድርጓል [ዩሀ 17፥1]። #ክርስቶስ አገልግሎቱን #በጸሎት ጀምሮ [ማቴ 4፥1] በመስቀል ላይ #ነፍሱን ሲሰጥና #አገልግሎቱን ሲደመድም #በጸሎት ውስጥ ነበር። እርሱ እንዳደረገውም #እንዳስተማረን <<አባታችን ሆይ>> ብለን እንድንጸልይ እንጂ <<እመቤታችን ሆይ>> ብለንም ሆነ #ወደሌላ #እንድንጸልይ አላስተማረንም።

▶️ ክርስቶስ ስለ #ጸሎት ሁኔታ ከሰጠን #መመሪያዎች ውስጥ <<አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሀል>> [ማቴ 6፥6] ብሎ ነው ያዘዘን። #ሐዋሪያትም ቢሆኑ #ከክርስቶስ የተማሩትን #ትምህርት #አብነት (ምሳሌ) አድርገው <<የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ...">> [ #ሐዋ 1፥25]፣ <<ጌታ ሆይ አንተ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በእርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠረህ...>> [ #ሐዋ 4፥24] ፣<<ጌታ ኢየሱስ ሆይ...>> [ #ሐዋ 7፥59]..ወ.ዘ.ተ በማለት #ቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ብቻ ነው የጸለዩት። ስለሆነም እንደ እነርሱ #መጽሀፍቅዱስ <<በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ>> በሚለው መመሪያ መሰረት [ #ፊል 4፥6] ወደ #እግዚአብሔር #ቀጥታ እንድንጸልይ ያሳስበናል።

▶️ ጸሎት በራሱ #የቃሉ #ትርጉም #ከእግዚአብሄር ጋር #መነጋገር ማለት እግዚአብሔርን #ማክበር [ራዕ 4፤ 10-11] እግዚአብሔርን #ማመስገን [መዝ 106(107) ፤1-2] እግዚአብሔርን #መለመን [ያዕ 1፤5] እግዚአብሔር የሚናገረውን #ማዳመጥ [መዝ 84(85) ፤8] ማለት ነው። ለዛም ነው ዳዊትም በመዝሙሩ እንዲህ ያለው <<ሥጋ ለባሽ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል።>> ያለው [ #መዝ 65፥2]። በዚህም መሰረት በብሉይ ኪዳን #አዳም#ኖህ#አብርሃም#ይስሐቅ#ያዕቆብ#ዮሴፍ#ሙሴ#ኢያሱ#የሳሙኤል እናት #ሐና#ሳሙኤል#ጌድዮን#ባርቅ#ሳምሶን#ዮፍታሔ#ዳዊት#ሰለሞን#ኤልያስ#ኤልሳዕ#ኢዮስያስ#ሕዝቅያስ#ኢሳይያስ#ኤርምያስ#ኢዮብ#ዕዝራ#ነህምያ#አስቴር#ዳንኤል#ሕዝቅኤል#ዮናስ . . .ወዘተ በሐዲስ ኪዳንም 12ቱ #ደቀመዛሙርት#ድንግል ማርያም፣ #ዘካርያስ#ስምዖን#ጳውሎስ#ጴጥሮስ፣ በህብረት ደግሞ #ጳውሎስና #ሲላስ#ሐዋርያት #በአንድነት፣ ራሱም #ኢየሱስ ክርስቶስ #በሥጋዌ ማንነቱ፣ እጅግ #ኃጢአተኞች ተብለው የሚቆጠሩት #በክርስቶስ ቀኝ የተሰቀለው #ወንበዴና ከሰፈር ውጭ ተጥለው የነበሩት #ለምጻሞች ሁሉ #ጸልየዋል። የጸለዩትም #ጸሎት #በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ሆኖ የከበረ #መልስ ማግኘታቸውም ሁሉ ለትምህርታችን #ተጽፏል። ስለዚህ ወደ #ማርያምም ሆነ ወደ ማንኛውም #ፍጡር መጸለይ #ኢ #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ዘመን አመጣሽ #ተግባር ነው። ደግሞም ዛሬ በአንዳንድ #ምእመናን እንደሚታየው ከላይ የጠቀስናቸው ሁሉ #ለመጸለይ #የልባቸውን #ጩኸት አቀረቡ እንጂ #ለጸሎት ብለው የተጠቀሙበት #የጸሎት #መጽሐፍ <<የሰኞ የማክሰኞ>> ወ.ዘ.ተ እያሉ የሚደግሙት #መጽሐፍ አልነበራቸውም። #በብሉይ ኪዳን ተጽፎ የነበረው #የመዝሙረ ዳዊት #መጽሐፍ #ኢየሱስ ክርስቶስና #ሐዋርያት ለትምህርቶቻቸው ይጠቅሱት ነበር እንጂ #ለጸሎቶቻቸው #ድጋፍ አድርገው አልተጠቀሙበትም። ስለዚህ #ጸሎት #ከልብ የሚመነጭ ስለሆነ በየቀኑ በብዙ #ገጾች የሚቆጠሩ የተለያዩ #ርዝመት ያላቸውን የተጻፉ #መጽሀፍትን #ማዘጋጀትና#መደጋገም እንዲሁም #ህመም ሲሰማቸው #መጽሀፍቶቹን #መተሻሽት#በራስጌ ላይ #ማንጠልጠል#በአንገት ላይ #ማነገት አይደለም።

▶️ ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን #የፈሪሳውያን (የአህዛብ) #ጸሎት #ስነ - ሥርዓት <<አህዛብም በመናገራቸው #ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና #ስትጸልዩ እንደ እነርሱ #በከንቱ አትድገሙ ስለዚህ አትምሰሏቸው>> በማለት ተቃውሟል [ማቴ 6፤ 7-8]። ስለዚህ #ጸሎት ሰዎች በደረሱልን የ"ጸሎት" #ድርሰት #መጽሀፍ ወይም የሌሎችን #ጸሎት በመድገም #መጸለይ ሳይሆን እንደ ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ #እግዚአብሔር በመቅረብ የልባችንን #ጸሎት #በእውነትና #በመንፈስ #ከአክብሮት ጋር በማቅረብ ነው [ማቴ 26፤ 39-44 ፣ ዩሀ 17፤ 1-26]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆