ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን #ደቀመዛሙርቶቹ ተሰብስበው #ስለጸሎት እንዲያስተምራቸው በጠየቁት ጊዜ እንግዲህ እናንተ እንዲህ #ጸልዩ፦ <<በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ፥ #ስምህ #ይቀደስ#መንግሥትህ #ትምጣ፤ ፈቃድህ #በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ #በምድር ትሁን፤ የዕለት #እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን #ይቅር እንደምንል በደላችንን #ይቅር በለን፤ ከክፉም #አድነን እንጂ ወደ #ፈተና አታግባን፤ #መንግሥት ያንተ ናትና #ኃይልም #ክብርም #ለዘለዓለሙ፤ አሜን።>> በሉ በማለት አስተምሯል። [ማቴ 6፤ 9-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]።

▶️ ከዚህ ጌታ #ኢየሱስ ከሰጠው #የጸሎት #መመሪያ ላይ በመቀጠል #አድራሻው ወደ #ማርያም የሆነ፦ <<እመቤታችን ቅድስት #ድንግል #ማርያም ሆይ በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ....>> ምናምን የሚለው #ጸሎት ቢኖሮ ኖሮ ወይም መኖር ቢኖርበት ኖሮ ደቀመዛሙርቱ #ጸሎት #አስተምረን ባሉት ጊዜ ባገኘው ምርጥ #አጋጣሚ ወደ #ማርያም #መጸለይ #ትክክል ወይም #ተገቢ መሆኑን ባሳየ ነበር። #ዝንጋኤ የሌለበት በማስተዋልም #ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ <<መንግስት ያንተ ነውና ኃይልና ክብርም ለዘላለሙ አሜን>> ብሎ #የመዝጊያ #ቃል አስቀምጦ ባልደመደመውም ነበር።

▶️ መምህራችንና #ሊቃችን አንድ እርሱም #ክርስቶስ የሆነው #ጌታ [ማቴ 23፤ 8-11] ያላስተማረውን #ትምህርት ከእርሱ ይልቅ #ሊቅ ለመሆን #በመሞከርና #በመጨመር ሌላ ድርሰት ማምጣት #ከንቱ #ድካምና #ፍሬ #ቢስ ከመሆኑም በላይ የሚያመጣው #ፋይዳ (ጥቅም) አይኖርምና <<እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን #በቃሉ አንዳች #አትጨምር።>> [ምሳ 30፥6]።

▶️ በመሰረቱ <<አባታችን ሆይ>> በሚለው #የማህበር #ጸሎት ላይ <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን ብቻ ሳይሆን <<ሊቃውንቶች>> የጨማመሩት #ሠላም #ለኪን#ውዳሴ #ማርያምን#አንቀጸ #ብርሃንን#ይወድስዋ #መላዕክትን#መልክዓ #ማርያምን....ወ.ዘ.ተ ደራርበውበታል።

▶️ የካቶሊክ #ቤተክርስቲያንና ሌሎች #እህትማማች ተብለው የሚጠሩት #አብያተ #ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ካለው የ<<እመቤታችን.... ሆይ>> ጸሎት #የቃላትና #የይዘት #ልዩነት አለው። የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትለው፦ <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል ነሽ የአሸናፊ የልዑል እግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ይገባሻል እንዲሁም ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታውን ለምኝልን ኃጢታትችንን ያስተሰርይልን ዘንድ አሜን[1]።>> የሚል ሲሆን #የካቶሊክና#የእህትማማች #አብያተ ክርስቲያናት (የግሪክ፣ የህንድ፣ የአርመን የግብጽ. . .ኦርቶዶክስ) ደግሞ <<ድንግል ወላዲት ሆይ! ማርያም ሆይ፣ ጸጋ የሞላሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው፤ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የነፍሳችንን አዳኝ ተሸክመሻልና ደስ ይበልሽ[2]>> #ብቻ ነው የሚለው። ይህ ግን #መጽሀፍ ቅዱስ የማይቀበለውና #መጽሀፍ ቅዱሳዊ #ማስረጃ የሌለው ከንቱ #ፈጠራ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ ጌታቸው አየነው (መምህር)፤ "የዘውትር ጸሎት በአማርኛ"፥ ገጽ 5 ፥አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጽ/ጠ/ጽ/ቤት ሐዋርያዊ ስራ መምሪያ ፤ "ሕያው እግዚአብሔር" ፤አማርኛ ትርጉም ገጽ 316፤ በገላውዲዎስ ተቋም በአባ ጳውሎስ ጻድዋ ካርዲናል ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እንዲታተም የተፈቀደ፤ ማስተር ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።
▶️ ክርስቶስ <<በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ>> ብለን እንድንጸልይ እንጂ ያስተማረን << #እመቤታችን ሆይ>> ብለን እንድንጸልይ አላስተማረንም። የተሰጠንም #መንፈስ #አባ #አባ ብለን የምንጮህበት #መንፈስ #ብቻ ነው እንጂ #እማ #እማ ብለን የምንጮህበት አይደለም [ሮሜ 8፥15]። <<ስምህ ይቀደስ>> እንድንል እንጂ << #ሰላምታ #ይገባሻል>> እንድንል <<በደላችንን ይቅር በለን>> እንጂ << #ይቅርታን #ለምኚልን ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ>> እንድንል አላስተማረንም። የሁለቱም #ጸሎቶች #አድራሻና #ፍሬ ነገራቸው #የሰማይና #የምድር #ርቀት ያክል ልዩነት ያላቸውና #የሚጣረሱ ናቸው።

▶️ ከክርስቶስ #ትምህርት ጋር ሌሎችንም <<የጸሎት መጻህፍት>> የተባሉትን ብናስተያያቸው
እንደ <<አንቀጸ ብርሃን መጽሀፍ>> << #ስምሽ #የተመሰገነ ነው>> እንድንል ሳይሆን <<ስምህ ይቀደስ>> እንድንል፤ እንደ <<ተአምረ ማርያም መጽሀፍ>> << #ድንግል ሆይ #ፈጥነሽ እንድትመጪ>> [43፥26] እንድንል ሳይሆን <<መንግስት ትምጣ>> ብለን የክርስቶስን #መንግስትህ መምጣት #በናፍቆት እንድንጠባበቅ፤ <<ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን>> በማለት የእርሱ #ሰማያዊ #ፍቃድ ብቻ በምድራችን እንዲሆን እንጂ እንደ ተአምረ ማርያም ጸሀፊ << #ፈቃድሽ #ይሁንልን ይደረግልን>> እንድንል አላስተማረንም [100 ፤ 29-32]። <<የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን>> በማለት #የዕለት #ኑሮአችንንም እንዲያቀናልን እንድንጸልይ እንጂ። እንደ <<መልክዓ ማርያም መጽሀፍ>> << #መጻህፍትሽ #የማዳን #እንጀራንና የተፈተነ #መድሀኒት መጠጥን ስለሚሰጡ #ሰላምታ ይገባል[ለእራኃትኪ]>> እንድንል አላስተማረንም። <<ኃጢአታችንን ይቅር በለን>> እንድንል እንጂ እንደ <<መልክዓ ማርያም>> ደራሲ << #ኃጢአታችንን #ይቅር #በይን[ለመዛርዕኪ]>> እንድንል አላስተማረንም። <<ከክፉ አድነን>> በማለት #ከክፉ እንዲያድነን ወደ #እግዚአብሔር እንድንጸልይ እንጂ << #ከአዳኝ #አውሬ #አድኝኝ>> [የዘውትር ጸሎት ሰላምለኪ] እንድንል አላስተማረንም። <<ኃይል ክብርም ምስጋናም ለዘላለም ድረስ ላንተ ይሁን>> እንድንል እንጂ እንደ <<ተአምረ ማርያምና እንደ ቅዳሴ ማርያም>> <<ድንግል ሆይ #ክብርና #ምስጋና #ለዘላለም ይገባሻል>> እንድንል አላስተማረንም። ስለሆነም ይህን #ከክርስቶስ #ትምህርት ጋር የሚጣረስ ትልቅ #ኑፋቄ ወደ #ቤተክርስቲያን ማስገባትና ማስተማር ታላቅ #በደልና #ኃጢአት ነው።

▶️ አንዳንድ #ሰዎች ደግሞ ይህን #ኑፋቄ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል #ከሉቃስ ወንጌል 1፤ 28- ጀምሮ ያለውን ክፍል ይጠቅሳሉ።

በክፍሉ እንደሚነበበው ግን #መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል #ከእግዚአብሄር ዘንድ ተልኮ ወደ #ድንግል #ማርያም በመጣ ጊዜ በሚያስደንቅ #ሰላምታ ከተገናኘ ቡኃላ የተላከበትን ጉዳይ <<እግዚአብሔር #ከአንቺ ጋር ነው>> በማለት ስለሚወለደው ቅዱስ #የእግዚአብሄር #ልጅና #ስልጣን ላይ አተኩሮና #ሰፊ ጊዜ ወስዶ ሲያበስራት ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ #አንድ #ቤት ወይም #ከጓደኛው ጋር ሲገናኝ #አይነቱ ይለያል እንጂ #ሰላምታ መለዋወጥ በየትኛውም #ሀገር ያለና የተለመደ #ባህላዊ #ስርአት ስለሆነና በተለይም #በመንፈሳዊ ሰዎች ዘንድ ሲገናኙ #ሰላምታ መለዋወጥ #ልማድ ከመሆኑም ጭምር እንዲሁም #መጽሀፍ ቅዱሳዊ በመሆኑ [ማቴ 10፤ 12-13]። መለአኩ #ቅዱስ #ገብርኤልም ያደረገው ይኸንን ነው #ጸሎት እያቀረበ አለመሆኑን ማንም #ሰው አንብቦ #መረዳት የሚችለው ነገር ነው። #ማርያምም ለቀረበላት ሰላምታ <<ይህ #እንዴት ያለ #ሰላምታ ነው>> ብላ አሰበች እንጂ እንደ #ጸሎት #ተቀባይ ወይ እንደ #ጸሎት #ሰሚ ሆና አልቀረበችም [ሉቃ 1፥29]። ነገር ግን አንዳንዶች ይህን ክፍል በመጥቀስ #ማርያምን <<በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ #ሰላም #እልሻለው>> እንዲባል #አስተምረዋል ጽፈው አልፈዋልም ዛሬም #የሚያስተምሩ አልጠፉም።
Forwarded from እውነት አርነት ያወጣል (ቴዎድሮስ)
ካነበብኩት

ትኩረት እንዲደርግበት ከፈለኩት ክፍል በቀር ሳልጨምር ሳልቀንስ

(ከቴሌግራም መንደር)

ኃጢአቷን የምትጽፈዉ ሴት

አንዲት ሴት ነበረች ኃጢአቷን የምትጽፍ
ልቧ በኃጢአት የሰከረ ለኃጢአትም ተገዥ የሆነች ይች ሴት የተለያየ ኃጢያት የምትሰራ ናት ትዘሙታለች፣ ትዋሻለች፣ ታማለች፣ ተሰርቃለች፣ ትገድላለች፣ በአል ትሽራለች፣ በትእቢት የተሞላች ሴት ናት ልቧ ኃጢአት ነበር። ነገር ግን የምትሰራዉን ኃጢአቷን ሁሉ እየጻፈች ታስቀምጥ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀን የጻፈችዉን ኃጢአቷን ብታየዉ ስንክሳር አክሎ ተመለከተችዉ ስንክሳር ማለት በ365 ቀኖች የሚለዉ የቅዱሳን ታሪክ ሰብስቦ የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነዉ። የዚች ሴትም ኃጢአትም ይህን አክሎ ነበር እንዳየችዉ ደነገጠችና ኃጢአቷን ተሸክማ አባት ወደ አለበት ወደ አንጾኪያ ሄደች አባ ባስልዮስን አገኘችዉ አባቴ በዚህ ያለዉ ኃጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችዉ።

አባ ባስልዮስም ይፋቅልሽ አላት ገልጣ ብታሳየዉ ሁሉ ተፍቆ አንዲት ኃጢአት ብቻ ቀርታ አየቻት። በጣም ከባድ ኃጢአት ነበረች ሊፈሩዋት የምትከብድ ሊነግሯት የምታሳፍር ነበረች አባቴ ይችሳ አለችዉ አባ ባስልዮስም ይችን ኃጢአትሽንስ #ማስተሰረይ የሚችል ልጄ ቅዱስ ኤፍሬም ነዉ ሂደሽ ለእርሱ ንገሪዉ አላት።
አባ ባስልዮስ ይሄን ያላት ኃጢአቷን #መፋቅ #አቅቶት #አይደለም የራሱ ክብር ከሚገልጥ የቅዱስ ኤፍሬም ክብር እንዲገለጥ ፈልጎ ነዉ። ደግሞም ስትመላለስ ንስሐ እንዲሆናት ጭምር ነዉ።
እሷም አባ ባሰስልዮስ እንዳላት ቅዱስ ኤፍሬም ወዳለበት ወደ ሶሪያ ሄደች በባዶ እግሯ እንቅፋቱ እየመታት እሾሁ እየወጋት እግሯ ሲደማ ልብሷን ቀዳ እየጠመጠመች ተጉዛ ከቅዱስ ኤፍርም ደረሰች።

አባቴ በዚህ ያለዉ ኃጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችዉ ቅዱስ ኤፍሬም ግን ይሄ ለኔ አይቻለኝም ለአባቴ ለአባ ባስለዮስ እንጂ አላት ቅዱስ ኤፍሬም ግን ኃጢአቷን #መደምሰስ #አቅቶት #አይደለም በፈሊጥ ቀኖና ሲሰጣት እንጂ ስትመላለስ ኃጢአቷ እንዲቀልላትም ነዉ። ሂደሽ ለአባ ባስለዮስ ንገሪዉ ይደመስስልሻል አላት እሷም አግኝቸዉ እኮ አይሆንልኝም ብሎ ወደ አንተ ልኮኛል ሳትል እሽ ብላ መንገድ ስትጀምር እንደ ቀድሞዉ በህይወት አታገኝዉም ሙቶ ካህናት ሊቀብሩት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘዉት ሲሄዱ ታገኝዋለሽ ሳትጠራሪ የተጻፈዉ ኃጢአትሽን ከአስክሬኑ ላይ ጣይዉ አላት እሷም እሽ ብላ ሄደች የቀኑ ሙቀት የሌሊቱ ብርድ እያሰቃያት ደረሰች ሙቶ ካህናት ፍትሀት እየፈቱት አየች።

የእግዚአብሔር አገልጋይ ባስልዮስ ሆይ የባሪያህን ኃጢአት ደምስስልኝ ብላ ከአስክሬኑ ላይ ጣለችዉ አስክሬኑም ድምጽ ወጥቶ ኃጢአትሽ ተደምስሶልሻል አላት ገልጣ ብታይ ተደምስሶላታል። አምላኳን አመሰገነች በደስታ ዘመረች በዚህ በኋላ ዓለምን ንቃ ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች።

እንደዚች ሴት ኃጢአቱን የሚያስታዉስ ማነዉ?
ወደ ካህን ሂዶ ንስሐ የገባስ ስንቱ ነዉ?
ስለ ኃጢአቱ በረሃ የተከራተተ ማን ይሆን?

የዚችን ሴት መጨረሻ ያሳመረ የሁላችንም መጨረሻ ያሳምርልን ኃጢአቷን የደመሠሠ የሁላችንም ኃጢአት ይደምስስልን!!! አሜን ፫

#ለንስሐ #የሚሆን #ፍሬ #አድርጉ!
የዉዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ


////////////////////////////////


https://tttttt.me/tewoderosdemelash/640