ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ሀሳባቸውንም ሲያብራሩ፦
<<የድንግል ማርያም #ወላጆች#አያቶች#ቅድመ አያቶች .. አጽመ ርስታቸውን #አገራቸው ከሆነችው #ከኢትዮጽያ ተነስተው መስራችና አስተዳዳሪዋ በሆነው #በኢትዮጽያዊው #መልከ #ጼደቅ ምክንያት ምድረ - ርስት #ቅድስት #አገር #ከተማቸው ወደሆነችው ወደ #ኢየሩሳሌም ተጓዙ። በዚህ መልክ ከግንዶቹ #አዳምና #ሔዋን #የሰረጸው #የኢትዮጽያዊና #የኢትዮጽያዊነት #የትውልድ #ሀረግ #ከልጅ #ልጅ ተያይዞ እየወረደ #በመጨረሻው #በኢያቄምና #በሃና አማካኝነት #ከድንግል #ማርያም ደርሷል .... እርሷም #ኢትዮጽያዊ ተብላ እኛን #ኢትዮጽያዊ አሰኘችን። #እናታችን #ማርያም ሆይ.... ቀድሞ #በነብያት " #ኢትዮጽያ ታበጽሐ እደዊሃ ኅበ እግዚአብሔር - #ኢትዮጽያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" የተባልሽ እኛም " #አምነ #ጽዮን - #እናታችን #ጽዮን" ስንልሽ የኖርን #በሰማይና #በምድር ንግስታችን ሆይ ደስ ይበልሽ[1]>> ብለዋል።.

▶️ አንዳንድ #ካቶሊኮችም #በመንፈስቅዱስ እንደተሰራችና #አዲስ ፍጡርም (ኃይል አርያማዊት) እንደሆነችና #እናትም #አባትም የሌላት #ከሰማይ ዱብ ያለች #እንደሆነችም የሚናገሩ አልጠፉም[2]።

▶️ ከእስልምናውም #ማርያም #የኢምራ ልጅ ናት ብሎም #የአሮን(የሙሴ ወንድም) #እህት ናት ይላል።
ይህን ያዩ ሌሎች #ሴቶች በዚህ ወራት አምላክ #ከድንግል #ይወለዳል የተባለው ከአንቺ ይሆንን? ብለው ዘበቱባት። ወዲያው #መልአኩ መጥቶ #ትጸንሲ (ትጸንሻለሽ) አላት ዝም ብላ ሄደች። ከቤትም ደርሳ ውሃውን ስታወርድ #ትጸንሲ (ትጸንሻለሽ) አላት ይህ ነገር ደጋገመኝ #ከቤተመቅደስ ሄጄ ልረዳው ብላ #ከደናግለ #እስራኤል ጋር ተካፍላ እያስማማች የምትፈትለው #ሐርና #ወርቅ ነበር። ያንን ይዛ ሄደች #ከቤተ #መቅደስ ተቀምጣ #ሐርና #ወርቁን እያስማማች ስትፈትል #መልአክ መጥቶ #ትጸንሲ (ትጸንሻለሽ) አላት እፎኑ ይከውነኒ ዝንቱ እንዝ ኢያአምር ብእሴ - #ወንድ #ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል? አለች። እኔ ይህን አላደርገውም #እንደምን #ይሆናል ስትለው ነው ከዚህ ቡኋላ መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላእሌኪ - ቅዱስ #የእግዚአብሔር #መንፈስ #በአንቺ ላይ #ይመጣል አላት። ይኮነኒ በከመ ትቤለኒ (እንደ ቃልህ ይሁንልኝ) አለችው። ይህን #ቃሏን ምክንያት አድርጎ #በማህጸኗ ተቀርጾአል[4]>> ብለው ያቀርባሉ።

▶️ የዚህ #ተረት #ፈጣሪ #በመጽሐፍ ቅዱስ #በዮሴፍ ቤት #ናዝሬት #ከተማ ነበረች የሚለውን #የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ #ገለጻ በመተው ሌላ #ያልነበረና የሌለ #ታሪክ ጽፏል። ይህ ደግሞ በቃሉ ላይ #አመጽና #መሸቃቀጥን ያመለክታል። አዎን ቅዱስ #ገብርኤል #ማርያምን ሲያበስራት #በእጮኛዋ #ዮሴፍ ቤት #በናዝሬት ከተማ ነበረች እንጂ #ቤተ መቅደስ ወይም #በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ አልነበረችም #ወቅቱና #ሁኔታውም አይፈቅድም {ሉቃ 1፥26}።

▶️ አንዳንዶችም #በቤተ መቅደስ ነበረች የሚለውን #አባባል #መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ብለው #በመቃወም #ማርያም የነበረችው #በቤተ መቅደስ #ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ሳይሆን #በቤተ መቅደሱ ግቢ #በማህደረ #ደናግል ውስጥ ትኖር ነበር የሚሉ አሉ። ነገር ግን #ሄሮድስ በሰራው #ቤተ መቅደስ #አደባባይ ጊቢ ውስጥ ይኖሩና ቆመው #ለአፍታ ያህል ይጸልዩ የነበሩት #አሮጊቶችና #መበለቶች እንደነ #ሃና #የሳሙኤል እናት {1ኛ ሳሙ 1፥9 እና አሮጊቷ ሃና} ሉቃ 2፤ 36-38} እንጂ #ደናግል ወጣት #ሴቶች በጭራሽ አይገቡምና ይህም #ጥናቱ ያላላቀ #ጅምር #አንካሳ #ሃሳብ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ ፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ 1 ዲድስቅሊያ 44።

📚፤ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ፤ <ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን 3ኛ ዕትም፡ ብራና ማተሚያ ድርጅት፤ አ.አ፥ ገጽ 18፡ 1995 ዓ.ም።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፡ "ፍትሐ ነገስት ንባቡና ትርጓሜ፤ አንቀጽ 1፤ 13፡ ገጽ 23፤ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፡ አ.አ፡ 1990 ዓ.ም።

[2] 📚፤ ኢንተርናሽናል መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ አዲሱ መደበኛ ትርጉም፤ የሉቃስ 2፥4 እና 22 ማብራርያ፡ ገጽ 1531-1532፡ 1993 ዓ.ም።

[3] 📚፤ አባ ቤተማሪያም እና መዘምራን ሞገስ ዕቁባ ጊዮርጊስ፤ "አምስቱ አዕማደ ምሥጢር ምስል ሥነፍጥረት አንድምታ"፤ አክሱም ማተሚያ ቤት፤ አክሱም፡ ገጽ 36፤ 1991 ዓ.ም።

📚፤ አስረዳ ባያብል (ሊቀ ጠበብት)፤ "ማህሌተ ጽጌ ትርጓሜ"፤ አ.አ፡ ገጽ 80፤ 1998 ዓ.ም።

[4] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ "ውዳሴ ማርያም ንባቡና አንድምታው" ዘሰንበተ ክርስቲያን፤ ገጽ 210፥ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1983 ዓ.ም።

(7.4▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat