ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.82K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
መዝሙር


ዝማሬ ለፈጣሪ ወይስ ለፍጡር???

እናንተየ በመጽሃፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ግዜ ዝማሬን ለእግዚአብሄር ያቀረበችው ማን እንደሆነች ታውቃላችሁ??? የሙሴ እህት ማሪያም ነች. ሙሴ እጁን ዘርግቱ ባህሩን በከፈለና 600፣000 እስራኤልን አስመልጦ ግብጽን በዋጠ ግዜ ከበሮዋን አንስታ በለው አለች. መቼስ ሰው ሁሉ የጠበቀው እንዲህ ትዘምራለች ብሎ ነበር…
ጻድቁ ሙሴ ጻድቁ ሙሴ
ባንተ ዳነች ነፍሴ
ሙሴ ጻድቁ ሰው - ሙሴ ጻድቁ ሰው
የግብጽን ሰራዊት ባህር ገለበጠው
እሷ ግን ለማን እንደሚዘመር ታውቃለች.ሙሴ ባህሩን ቢከፍልም የሚዘመረው ለሙሴ አምላክ እንጂ ለሙሴ እንዳልሆነ ታውቃለች. ታላቅ ወንድሜ ሙሴ ቢቀየመኝስ-ቢከፋውስ አላለችም. #ዘጸ15 “በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሄር ዘምሩ“ ብላው እርፍ .

ዝማሬ በባህሪው አምላክ ለሆነ ብቻና ብቻ የሚሰጥ የአምልኮ ክፍል ነው. መጽሃፍ ቅዱሳችንን 1000 ገጽ ብናገለባብጥ ለሰው የተዘመረበት ስፍራ አናገኝም. አንድም ቦታ. የመጽሃፍ ቅዱሶች ቅዱሳን አባቶቻችንም ያስተማሩንና ያሳዩን ይህንን ነው. ሁሉም ዝማሬ ለእግዚአብሄር ብቻ እንደሆነ በሚከተሉት ክፍሎች አሳይተውናል

#ሙሴ - ዘጸ 15-2 “ጉልበቴና ዝማሬዬ እግዚአበሄር ነው“

#ዳዊት - መዝ 9-11 “በጽዮን ለሚኖር #ለእግዚአብሄር ዘምሩ “ @ መዝ 108-3 “በወገኖቼ መካከል ለእግዚአብሄር እዘምራለሁ“
@ መዝ 69፥30 #የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመስግኑ
@ መዝ 71፥6 " ....... ሁልጊዜ ዝማሬዬ #ለአንተ ነው"
@ መዝ 118፥14 "ኃይሌም ዝማሬዬም #እግዚአብሔር ነው እርሱ መድሃኒት ሆነልኝ
@ መዝ 30፥4 "ቅዱሳን ሆይ #ለእግዚአብሔር ዘምሩ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ
@ መዝ 59፥17 ረዳቴ ሆይ #ለአንተ ለአምላኬ እዘምራለሁ"
@ መዝ 66፥2 #ለስሙም ዘምሩ ለምስጋናውም ክብርን ስጡ።
@ መዝ 66፥4 #በምድር #ያሉ #ሁሉ #ለአንተ #ይሰግዳሉ #ለአንተም #ይዘምራሉ #ለስምህም #ይዘምራሉ
@ መዝ 146፥2 "....... በምኖርበት ዘመን ሁሉ #ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ
...
#ኢሳያስ -
ኢሳ12-2 “#እግዚአብሄር ሃይሌና ዝማሬየ ነው“

#ኤርሚያስ-
ኤር20-13 “#ለእግዚአብሄር ዘምሩ እግዚአብሄርንም አመስግኑ “
#ጳውሎስ -
ቆላ3-16 “#ለእግዚአብሄር ዘምሩ
ኤፌ 5-19 “#ለጌታ በልባችሁ ተቀኙ ዘምሩ“

ወገኖቼ ቅዱሳን አባቶች ዝማሬአቸው ለጌታ ብቻ ሆኖ ሳለ ዳዊት ራሱ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ለአንተ ይዘምራሉ እያለ እኛ “ማሪያም ማሪያም ብዩ ስምሽን ልጥራሁ... “ -
“ድንቁ ታምራቱ እጅግ ብዙ ነው -አባ ተክለ ሃይማኖት “ -
"ሚካኤል አዳነኝ...ሚካኤል ደረሰልኝ....
"ያሳደገኝ መልአክ “……እያሉ ለፍጡራን መዘመር ከማን ተማርነው ???
ይህ ሃጢአት መሆኑን እንዴት ማወቅ ተሳነን ??? የእግዚአብሄር ክብርና ዝማሬ ለማንም አይሰጥም ባልን ተሃድሶ መናፍቅ ተኩላ …ወዘተ ይሉናል.
ቢሉንም ግን ያወቅነውን ከመናገር ዝም አንልም. እህቶቼና ወንድሞቼ የኦርቶዶክስ ዘማሪን የእግዚአብሄርን ዝማሬ ለፍጡር መስጠት ጣኦት አምልኮ እንደሆነ አታውቁምን ???በእርግጥ ብዙዎቻችሁ ይህንን አውቃችሁዋል. ለፍጡር ዝማሬ አታስቀምሱም. የእግዚአብሄር ዝማሬ ምድራችንን ያጥለቅልቅ።
👇
@Literature_For_God
@Literature_For_God
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
@gedlatnadersanat


ለዚህም ነው ቤተ ክርስቲያኗ ራሷ በግርጌ ማስታወሻ " #በግሪኩ #የሚማልደው #ነው #የሚለው" ብላ የጻፈችው። ይህ ከሆነ ደግሞ #የአዲስ ኪዳን በኩረ ጽሁፍ(እናት ቋንቋ) #ግእዙ ሳይሆን #ግሪኩ መሆኑ ግልጽ ነው። #ግእዙን ጨምሮ ሁሉም #የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት #የትርጉም ሥራቸው የተሰራው #ከግሪኩ በመሆኑ የትኛውም የትርጉም ስራ ሲሰራ #ግሪኩ የሚለውን በማለት ግሪኩ የተወውን በመተው መስራቱ #ለእግዚአብሄር ቃል ያለንን ታማኝነት የምናሳይበት ትልቁ መንገድ ነው። #ግሪኩ እንዲህ #አይልም እያሉ ሌላ ነገር መጻፍ #ታማኝ መሆንን አያሳይም።

▶️ ይህ እንዳለ ሆኖ #ጸሀፊው #ከጠቀሱት #መጻሕፍት በፊት " #በዐጼ ሚኒልክ" ጊዜ የታተመው #የ1887 ዕትም #መጽሀፍ ቅዱስ ይህን ጥቅስ እንዴት #አስፍሮት እንዳለ #መመልከቱ መልካም ነው።
" #ማን ነው የሚኮንን? ክርስቶስ የሱስ የሞተ ነውን? ከሙታን እንኳ የተነሣ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠ እርሱም #ያስምረናል"

አንባቢው ልብ እንዲል የሚገባው ነገር #ሰዎቹ እያሉ ያሉት " #ከጊዜ ቡሀላ #የታተሙት ናቸው እንጂ #ቀደምት ዕትሞች " #ክርስቶስ ያማልዳል" አይሉም የሚል ሲሆን እነርሱ #የቀደሙ ናቸው ከሚሏቸው #ቀድሞ #ለንባብ የበቃው #መጽሀፍ ግን እነርሱ እንዲልላቸው የሚፈልጉትን ሳይሆን #እውነታውን #አስፍሮት ይገኛል።
#ወንድሞቻችን መፈናፈኛ ሲያጡ " #እናንተ የቀየራቹትን ሳይሆን #አባቶቻችን ቀደም ሲል #በግእዝ ጽፈው ያስቀመጡልንን ነው የምንቀበለው" ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ለዚሁ ደግሞ #በግእዝና #በአማርኛ ተዘጋጅቶ #በትንሣኤ #ማተሚያ ቤት የታተመውን #መጽሀፍ በዋናነት የሚጠቅሱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ #ግእዙን መሠረት አድርጎ ነው #የታተመው #የሚባለውንና #በ2000 ዓ.ም ለንባብ የበቃውን 80 አሀዱ #መጽሀፍ ቅዱስ ያነሳሉ።
#በግእዝና በአማርኛ የተዘጋጀው መጽሀፍ ምንም እንኳን በአማርኛው
" #የሚፈርድ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም #ከሙታን ተለይቶ የተነሳው፥ በእግዚአብሄር ቀኝ የተቀመጠው፥ ደግሞም " #ስለእኛ #የሚፈርደው" በማለት ቢያስቀምጡትም ግእዙ ራሱ ግን
" #ወመኑ፡ ውእቱ፡ እንከ፡ ዘይትዋቀሦሙ ለኅሩያነ እግዚአብሔር ለእመ ለሊሁ ያጸድቅ፤ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ኢየሱስ ዘሞተ፡ ወተንሥአ እምውታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር #ወይትዋቀሥ #በእንቲአነ" በሚል ነው የሰፈረው።(ሮሜ 8፤ 33-34)
📖/፤ ትንሳኤ ማሳተሚያ ድርጅት ዐዲስ ኪዳን በግእዝና በዓማርኛ (ዐዲስ አበባ፤ 1994) ገጽ 644።

ሰዎቹ " #ይፈርዳል" እንዲልላቸው የሚጠብቁት ቃል " #ወይትዋቀሥ" የሚለውን ነው።
ሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
🔽 " #ተዋቀሠ" የሚለውን ቃል ትርጉም " #ተሟገተ#ተከራከረ" እንደሆነ በግልጽ አስቀምጠውታል።
ይህ እንዲህ ሳለ ግን #ሰዎቹ ከመሰረተ ሀሳቡ #ውጭ በሆነ ሁኔታ #ለመተርጎም የተነሳሱበት ምክንያት #ከእግዚአብሄር ቃል ይልቅ #ለፈቃዳቸው ቅድሚያ የሚሰጡ #ሰዎች በመሆናቸው መሆኑ ግልጽ ነው።
📖/፤ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(አለቃ)፣ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ዐዲስ፣(1948) ገጽ 401።

" #ይከራከል" የሚለው እንዲያውም " #ይማልዳል" ከሚለው በላይ #ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የሚቆም #መካከለኛ መሆኑን #አጠንክሮ ይገልጣል እንጂ #ይፈርዳል ማለትን አያመለክትም፤ #ግእዙን እንኳን የተጠቀምነው #በአገራችን የተለመደ #ጥንታዊ ትርጓሜ ነው በማለት እንጂ #የአዲስ ኪዳን #መጻህፍት ሁሉ በመጀመሪያ በተጻፉበትና ለሁሉም #ትርጓሜዎች መሰረት በሆነው #የግሪክ ቋንቋ በግልጽ #የሚማልደው ተብሎ ተቀምጧል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው #በግሪክ ቋንቋ እንደሆነ የታወቀ ቢሆንም። ይህንን ስለ እኛ #የሚማልደው የሚለውን ቃል « #የሚፈርደው» ብለው የቀየሩ ሰዎች ራሱ በግሪኩ #የሚያማልደው እንደሚል ራሳቸው ይስማማሉ።(ፎቶው ላይ የግርጌ ማስታወሻውን ይመልከቱ)

@gedlatnadersanat
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ብዙ ሴቶች #ማርያም በሚል ስም ይጠራሉ[1]። [ለምሳሌ]👇 〽️ 1፦ "የሙሴ እህት ማርያም" /ዘጸ 2፥4-8/ ▶️ የዚችን #ማርያም ታሪክ #በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ ስናይ #ወንድሟ #ሙሴ በወንዝ #ዳር #በተጣለ ጊዜ በእርሱ ላይ የሚሆነውን #ለማወቅ ስትመለከት ወደ ወንዙ የመጣችውን #የፈርኦንን #ልጅ #በጥበብ አነጋግራና #እንድታጠባው የገዛ #እናታቸውን #በሞግዚትነት ስም አገናኝታ…
▶️ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ለ"ማርያም" ለሚለው ስም የተሰጡ #ትርጉሞች #የቤተስክርስቲያን #አባቶችም ሆኑ #ወጣት #ሰባኪያንና #ህዝቡም በብዛት የሚያውቁት #የተለመደ #ትርጉም ነው። የሚገርመው ደሞ #የስሙ #ትርጉሞች ብዙ #ማርያም የተባሉ #ሴቶች እያሉ ማእከል ያደረገው ግን #የጌታችን #እናት #ድንግል #ማርያምን ብቻ ይመስላል። እነዚን #ትርጉሞች ይዘን ለሌሎች < #ማርያም> ለተባሉ #ሴቶች ትርጉሙን ብንሰጣቸው #የትርጉሙ #ባለቤቶች ራሱ #ይሸማቀቁበታል። [ለምሳሌ]፦
#በስም #ደረጃ ከክርስቶስ እናት ጋር #ምንም #ልዩነት ላልነበራት #ለመግደላዊት #ማርያም ትርጓሜውን ብንሰጣት
< #ማርያም> ማለት < #ፍጽምት ማለት ነው>። #መልክ #ከደም #ግባት አስተባብራ ተገኝታለችና ፍጻሜው ግን #ንጽሐ ሥጋ #ንጽሐ ነፍስ #በድንጋሌ ሥጋ #በድንጋሌ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችንና ብንል #በወንጌል እንደተገለጸው #መግደላዊት #ማርያም #ድንግል አልነበረችም።

▶️ ሌላውንም #ትርጉም ብናይ (ጸጋ ወሀብት) ለሰው ሁሉ #ጸጋ ሆና #ተሰታለችና#የመንግስተ #ሰማይም #መሪ ናት፤ " #ከፈጣሪ በታች #ከፍጡራን በላይም ነች"፤ #ለሰውና #ለእግዚአብሄር #ተላኪ ናት ብንል፤ ምኗ #ለሰው #ሁሉ #ጸጋ ሆኖ #እንደተሰጠ፣ ማንንስ #መንግስተ #ሰማይ #መርታ እንዳስገባች፣ #ከፍጡራን በላይ ያደረጋትስ ምንድነው ብንል #ሊቃውንት ነን የሚሉ ሰዎች #የተምታታና #የተጋጨ ወይም #የእፍረት መልስ ካልሆነ በቀር #መልስና #ማስረጃ የሌለው ነገር ነው። በመሆኑም ከላይ እንደተጠቀሰውም " #ማርያም" የሚለውን #የስም ትርጉም ለሌሎች " #ማርያም" ለተባሉ ሴቶች #ትርጉሙን ብንሰጠው #የማያስኬድና #ስህተት ሆኖ እናገኘዋለን።

️የስም #ለውጥ ባይኖረውም ብቻ #ትርጉሙ የሚሰራው ለጌታችን እናት #ለድንግል #ማርያም ብቻ ነው #ብንል #እንኳን
" ማርያም << #ፍጽምት በስጋም በነፍስም ነች>> ማለት #ጻድቅ #የለም አንድስኳ {ሮሜ 3፥11} ከተባለው እና ከሌሎች #የመጽሀፍቅዱስ ክፍሎች ጋር የሚቃረን ይሆናል።
በምድር ላይ #ኃጢአትን አላደረኩም፤ #የውርስ #ኃጢአት የለብኝም የሚል #ፍጹም ወይም #ፍጽምት ቢገኝ ኖሮ #ክርስቶስ ራሱ #መምጣት ባላስፈለገው ነበር።

▶️ ሁለተኛውን ትርጉም ደሞ ብናይ #ጸጋና #ሀብት ሆኖ #ለምድር የተሰጠው፤ የተዘጋውንም #የገነትን #ደጅ #በከበረ ሞቱ ከፍቶ #ከተሰቀለው #ወንበዴ አንዱን እንኳ #እየመራ #መንግስተ #ሰማያት ያስገባ፤ #በእግዚአብሄርና #በሰው መካከል ሆኖ #የመካከለኛ አገልግሎት #የሰጠውና #የሚሰጠው ጌታችን መድሃኒታችን #ኢየሱስ እንጅ ሌላ #ማንም አይደለም። ለዚህም እባክዎትን #መጽሀፍ #ቅዱስዎትን ገልጠው እነዚህን #የተጠቀሱ ጥቅሶችን ያንብቡ። {ቲቶ 2፥11-14፣ ኤፌ 2፥8፣ ሮሜ 5፥17፣ ዩሐ 3፥16፣ ሉቃ 23፤ 42-43፣ 1ጢሞ 2፥5፣ ዕብ 7፥24}።

▶️ ሌሎች #ሊቃውንትና #ተርጓሚዎችም << ማርያም ማለት በዚህ ዓለም #ከሚመገቡት ሁሉ #ምግብ #ለአፍ የሚጥም #ለልብ የሚመጥን < #ማር> ነው፤ #በገነትም #በህይወት ለተዘጋጁ #ጻድቃንና #ቅዱሳን < #ያም> የሚባል #ምግብ አላቸው፤ ስለዚህ ሁለቱን < #ማር" እና #ያም> የተባሉትን #ሁለት ፊደላት ስናገጣጥማቸው #ማርያም የሚል ስም #ተገኝቷል ምክንያቱም #እናትና #አባቷ አንቺ ከዚህም ኩሉ #የበለጥሽ #ጣፋጭ #የከበርሽ ነሽ ሲሉ #ማርያም ብለዋታል>> ይላሉ።

▶️ አሁንም ሌላ #ትርጉማቸውን ይቀጥሉና " #ማርያም ማለት #ሠረገላ #ፀሐይ ማለት ነው፤ #መንግስተ #ሰማያት ታገባለችና ፤ አንድም #ማርያም ማለት #ውኅብት #ወስጥወት (የተሰጠች) ማለት ነው፤ እመቤታችን እግዚእትነ ማርያም የተወለደች ዕለት በአባት እናቷ ቤት ውኅብት ወስጥወት ሆና ተገኝታለች፤ ኋላም በዓለሙ ሁሉ #አማላጅ ሆና #ሞታለችና ስለዚህ ውኅብት ወስጥወት (የተሰጠች) ናት" ይላሉ[3]።

️አሁንም እነዚህ #ሁለት #ትርጉሞች የአንድ ሰውን #የጌታችን የመድሃኒታችን #የኢየሱስ #ክርስቶስን #እናት #ድንግል #ማርያምን #ማእከል ያደረገ እንጅ ሌሎቹን #የማርያምን #ስም የያዙትን #ሴቶች ያገናዘበ አይደለም። ሆኖም ግን #የአማርኛውን ፊደል ወይም #ሐረግ ብቻ ተከትሎ < #ማር> እና < #ያም> በሚል የተከፋፈለ #ትርጉም መስጠት #አዋጭነት የለውም። ምክንያቱም ስያሜው #የእብራይስጥ #ቋንቋ እንጅ #የአማርኛ ወይም #የግእዝ አይደለም። እንደዛም እንኳን ቢሆንና ብንወስደው < #ያም> የሚባል #ቅዱሳኑ የሚበሉት #ምግብ አለ" ስለተባለው ሁኔታ #መጽሀፍ #ቅዱስም ሆነ ሌሎች መጽሀፍት #በሰማይ #ምግብ እንዳለ አይናገሩም። እንደውም #መጽሀፍ ቅዱስ #እግዚአብሔር #ምግቦችን ሁሉ #በምድር እንዳደረገ ነው የሚናገረው። {ዘፍ 1፤29-31} በተጨማሪም #የእግዚአብሔር ቃል << #መብል #ለሆድ ነው #ሆድም #ለመብል ነው እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንንም #ያጠፋቸዋል>> ይላል {1ቆሮ 6-13}።
በመሆኑም #መብል የእግዚአብሔር ዘላለማዊ #እቅዱ ስላልሆነ #በመንግስተ #ሰማያት አስቤዛ መግዛት መለዋወጥ ምግብ ማብሰል ... የለም፤ #አይኖርምም#አልተጻፈምም። በመሆኑም < #ማር" እና " #ያም> ብሎ ከፋፍሎ #የስም #ትርጉም መስጠቱ #ትርጉም የለሽ ይሆናል።

▶️ ሌላው << #ለዓለሙ ሁሉ #አማላጅ ሆና #ሞታለችና #ማርያም ማለት #ስጦታ ማለት ነው>> ብሎ መናገርና መጻፍ #ስለበደላችንና #ስለሐጢአታችን #በቀራኒዮ #መስቀል አደባባይ ላይ #የሞተውን ለይቶ #አለማወቅ ወይም #ክህደት ነው። #ለዓለም ሁሉ #ኃጢአት #አስታራቂ እንዲሆን የተሰጠንና ከአባቱም ጋር #ያስታረቀን ስለበደላችን #የሞተልን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ብቻና ደግሜ እላለሁ #ብቻ ነው። {1ጢሞ 1፥15፣ ሮሜ 3፥23፣ ሮሜ 5፥8፣ ሮሜ 8፥34፣ ዕብ 7፥24}።
▶️ ማርያም #ስለመሲሁ የመምጣት #ተስፋ ብታውቅም እንዴት #እንደሚፈጸም ግን አታውቅም ነበር። #በሉቃ 1፥34 ላይ #አለማመኗን የሚያሳይ ሳይሆን #እምነቷን የሚገልጽ ነበር። አንዲት #ልጃገረድ እንዴት #ከወንድ ጋር #ሳትገናኝ #ልትወልድ ትችላለች ብላ በማሰቧ #እጮኛዋ ከሆነው #ከዮሴፍ ጋር #ባለመጋባቷና #ግንኙነት ፈጽማ ባለማወቋ #መልአኩን <<ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?>> ብላ ጠየቀችው። #መልአኩም ይህ #በመንፈስቅዱስ የሚፈጸም #ተአምር እንደሆነ ነገራት። ደግሞም #ከአዳም #የውርስ ኃጥያት #በመንፈስቅዱስ መጸለል(መጋረድ) ምክንያት የሚወለደው #ህጻን <ቅዱስ> እንደሚሆን አመለከታት።

▶️ መልአኩ #መልእክቱን የደመደመው ለማርያም #የማጽናኛ #ቃል በመስጠት ነበር። ይኸውም #በዕድሜ የገፋችው ዘመዷ #ኤልሳቤጥ #ወንድ ልጅ #መጸነሷና 6ኛ ወሯ መሆኑን በመግለጽ #ለእግዚአብሄር #የሚሳነው ነገር የለምና አንቺም #መጸነስ ትችያለሽ በማለት #አስረዳት

▶️ ከዚህ ቡኋላ #ማርያም እንደታዛዥ #ባርያ ራሷን #ለእግዚአብሄር #በመስጠት <<እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ>> በማለት #የእምነት #ምላሽ ሰጠች {ሉቃ 1፥38}። መልአኩም ይህን #ውይይት እንደጨረሰ ከእርሷ ተለይቶ #ሄ

▶️ እንግዲህ በዚህ #ውይይት ውስጥ እጅግ #ዝቅተኛ #የኑሮ #ደረጃ ውስጥ ትኖር የነበረች #ልጃገረድ #የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈጸም #ለጌታ ሙሉ በሙሉ ራሷን #መስጠቷን ስናይ እንዴት የሚገርም ነው ያሰኛል። #ማርያም በእርግጥም #ለእግዚአብሄር #የተሰጠች #ሴት ነበረች። ይሁን እንጂ በአሁኑ #ዘመን በዚህ 'በቅድስት ድንግል #ማርያምና በቅዱስ #ገብርኤል' መካከል የተደረገውን #ውይይት ከተጻፈው #ውጪ በርካታ #የሃይማኖት መጽሐፍት በተለይም #አዋልድ መጽሐፍት #ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊ ጽንፈኛ #አስተምህሮቶችን ለብዙ ዓመታት #ሲያንጸባርቁ ቆይተዋል። ከዚህም የተነሳ ማርያምን የሃይማኖታቸው ማዕከል ያደረጉ በርካታ መናፍቃን ስለመነሳታቸው ታሪክ ይዘግባል።

👉 ለምሳሌ #የዘውትር ጸሎት መጽሐፍ የሆነው <<ይወድስዋ መላዕክት - መላዕክት ማርያምን ያመሰግኗታል>> በሚለው አርስቱ <<መልአኩ ገብርኤል ማርያምን •ድንግል ለአንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል• አላት፣ •ወላዲት አምላክ ምስጋና ይገባሻል•፣ •ቅድስት ነሽና ምስጋና ይገባሻል•፣ •የመለኮት ማደሪያ ነሽና ምስጋና ይገባሻል•፣ •የተሸለመች ድንኳን ነሽና ምስጋና ይገባሻል•፣ •የሁሉ እመቤት ማርያም ምስጋና ይገባሻል•፣ •የሁሉ ፍቅረኛ ማርያም ምስጋና ይገባሻል•፣ •ልዑል ማደሪያው ትሆኚ ዘንድ መርጦሻልና ምስጋና ይባገሻል•፣ •በወርቅ የተሸለምሽ የርግብ ክንፍ በብር ያጌጥሽ ምስጋና ይገባሻል•፣ •ጎኖችሽ በወርቅ አመልማሎ የተሸለሙ ለአንቺ ምስጋና ይገባሻል•፣ •ከጸሀይ 7 እጅ የምታበሪ ክብርሽ ከአድባራቱ ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ ለአንቺ ምስጋና ይገባሻል•[3]>> ይላል። ይህ #ጸሎት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ #በቃል አልያም #በንባብ ዘውትር ወደ #ማርያም የሚቀርብ #ምስጋና ነው።

▶️ ይሁን እንጂ #ቆም ብለን በእውኑ ከላይ የተገለጸውን #ንባብ (አንቀጽ) #ቅዱስ ገብርኤል የተናገረው ነውን? #መላእክትስ ማርያምን #ያመሰግኗታልን? እኛስ እንዲህ ያለውን አንቀጽ አስቀምጠን ወደ #ማርያም #እንድንጸልይ (እንድናመሰግን) #ሕግ ተሰጥቶአልና? ብለን ብንጠይቅና ለማየት ብንሞክር ፈጽሞ የሌለና #ያልተባለ ወደፊትም #የማይባል እንደውም #ኃጢአት እንደሆነ #መጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ ይናገራል።

▶️ በመሆኑም #መላእክት #የሚያመሰግኑትንና #ምስጋና #የሚገባውን ጠንቅቀው ስለሚያቁ ሲያመሰግኑ እንዲህ ይላሉ፦

<<በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።. . . በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን. . . በረከትና ክብር ጥበብም ምስጋናም ውዳሴም ኃይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤ አሜን አሉ።>>

የሚል ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ አምልኮና ምስጋና ብቻ ነው {ራዕ 5፤10፣ 12-13;፣ ራዕ 7፥12፣ በተጨማሪም ራዕ 4፥8፣ 11፥15፣ 12፥10፣ 15፥3፣ 19፥1. . .።}

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ ወንጌል ቅዱስ፡ ሉቃስ አንድምታ 1፥47፣ ገጽ 268። ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1997 ዓ.ም።

[2] የእግዚአብሄርም ቃል <<ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥>> {1ኛ ቆሮ 1፤ 27-28} የሚለው ለዚሁ አይደል??

[3] የዘውትር ጸሎት መጽሐፍ <ይወድስዋ መላእክት> ቁ.3።


(4.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
<<ሁሉም ወደ #አምላኩ ወደ #እግዚአብሔር አንጋጦ #ሲለምን በአየን ጊዜ #መንፈሳዊ #ቅንዓትን ቀንቶ #ገሰጻቸው። በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች #አምላክን ወደ ወለደች ወደ ክብርት #እመቤታችን #ማርያም ለምን #እርዳታ አትሹም እርሱዋ #ከቅዱሳን ሁሉ #ድንቅ ድንቅ #ተአምራትን የምታደርግ፣ #ፈጥና #የምታደርስ #ልመናን የምትሰማ ናትና አላቸው። በዚያችም ጊዜ #ተአምራትን ወደ ምታደርግ #በድንጋሌ #ስጋ #በድንጋሌ #ነፍስ ወደ ጸናች ወደ ክብርት እመቤታችን #ማርያም ለመኑ .... የሃገሩም ሰዎች #እመቤታችንን አመሰገኑ[1]።>>

<<እግዚአብሔር #ሲመሰገን #ግሣጼ መጣ #ስለማርያም ግን #ምስጋና ሽልማት ይሆናል #ቀሲስ #እንድርያስም #የማርያምን #ቅዳሴ #ዘወትር ይቀድሳል #ከእርሷም #በቀር ሌላ #ቅዳሴ አያውቅም ነበር ... #ኤጲስቆጶሱ ጠርቶ ሁልጊዜ #ከአንድ #ቅዳሴ በቀር ለምን #ለእግዚአብሄር #አትቀድስም ብሎ ተቆጥቶ #እንዳይቀድስ ቢከለክለው #ማርያም ተገልጣ #የእኔን #ቅዳሴ ሲቀደስ አገልጋዩን #ያወገዝከው ለምንድን ነው? ... #በክፉ #አሟሟት እንድትሞት #በእውነት እነግርሃለው አለችው #ኤጲስቆጶሱም ከዛሬ ጀምሮ #ከእመቤታችን #ቅዳሴ በቀር ሌላ #ቅዳሴ #አትቀድስ አለው[2]።>>

▶️ ከላይ ያየነው ሁሉ #ስለማርያም የሚናገሩት #አዋልድ #መጽሀፍት #ከእግዚአብሄር ይልቅ #ማርያምን የሚያስበልጡና እርሷን #ስለማምለክ የሚያሳዩ የጠቀስናቸው #ጥቂት #አጸያፊ #ክፍሎች ሲሆኑ ከዚህ በታች ደግሞ #ከእግዚአብሄር ጋር ባልተናነሰ መልኩ #ስትመለክና #ስትመሰገን የሚያሳዩ #ጥቂት #ክፍሎችን ደግሞ #በመገረም እንመልከት፦

<< #ለአብ #ምስጋና ይገባል፣ #ለወልድ #ምስጋና ይገባል፣ #ለመንፈስ ቅዱስም #ምስጋና ይገባል፣ #አምላክን #ለወለደች #ለእመቤታችን #ድንግል #ማርያም #ምስጋና ይገባል[3]>>

ይህም ማለት #ከአብ #ከወልድና #ከመንፈስቅዱስ ጋር #እኩል #ምስጋና የምትቀበል #የስላሴ 4ተኛ #አካል ሆነች ማለት ነው። በሌላ መጽሐፍም
<<ወላዲተ አምላክ ማርያም ሆይ፥ ጧት ስነሳ #እግዚአብሔርንና #አንቺን እመቤቴን #በጸሎት #እንዳመሰግን የሚያነቃቃ መንፈስ ኅሊና አሳድሪብኝ፤[4]>> ይላል።

▶️ ከዚህም የከፋ #ማርያም እንደ #አምላክ #እግዚአብሔር ደግሞ ከእርሷ #ዝቅ ብሎ #እንደመማለጃዋ ሆኖም የቀረበበትን #መጽሀፍ ደግሞ እስኪ እንታዘብ ፦

<< #ዘጠኝ ወር #የተሸከምሽው ከሃሊ በሚሆን #ከጡትሽ #ወተቱን ባጠባሽውም #ልጅሽም #በሰው ልጅ ላይ #ቸርነቱና #ይቅርታው በበዛ #በአባቱ... #በእግዚአብሄርም #እማጸንሻለው #እማልድሻለሁ #እለምንሻለሁ[5]>> ይላል።

▶️ ስለዚህ እነዚህን የመሳሰሉ #ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊና #አጸያፊ የሆኑ #አዋልድ መጽሀፍት ይዞ እግዚአብሔርን #አመልካለሁ ማለት ራስን #ማታለል ነው። እግዚአብሔር ግን <<እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ ይላል ቅዱሱ>> |ኢሳ 40፥25] ደግሞም <<እንደ እኔ ያለ ማን ነው ይነሳና ይጣራ ይናገርም>> ይላል እግዚአብሔር [ኢሳ 44፥7]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
___________
[1] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ "መጽሀፈ ግብረ ህማማት፤ ዘረቡዕ በ1 ሰአት በነግህ የሚነበብ፤ ገጽ 394፤ ቁጥር 1-13፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ፥ 1996 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ "መጽሀፈ ግብረ ሕማማት" ዘሐሙስ በመዓልት በ11 ሠዐት የሚነበብ፤ ገጽ 587 - 588 ቁጥር 1፤ 10 ፤ 1996 ዓ.ም።

[3] 📚፤ ተስፋ ገብረስላሴ፤ "ውዳሴ ማርያም ምስለ መልክዓ ማርያም በአማርኛ"፤ የዘውትር ጸሎት፤ ገጽ 6 ፥1986 ዓ.ም።

[4] እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት አርኬ 15።

[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም ግእዝና አማርኛ 3ተኛ ዕትም፥ ምዕ 102፥7፤ ገጽ 170፤ ትንሳዔ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።
▶️ የሰውነት #አካላትን እየዘረዘረ #የሚያስመሰግነው ባለ ብዙ #አርኬ ግጥም #መልክእን #አለቃ #ኪዳነ ወልድ ክፍሌ <<መልክእ ከራስ ጸጉር እስከ እግር ጥፍሩ የሚቆጠር መጽሀፍ ነው ብለውታል[1]።>> የሚገርመው #የሰውነት #አካል የሌላቸው እንኳ #መልክዕ ከተጻፈላቸው ውስጥ #መልክዓ #መስቀል(ለእንጨቱ) ፣ #መልክዓ #ሰንበት(ለቀኑ)፣ #መልክዓ #አንቀጸ #ብርሃን(ለመጽሀፍ ስም)፣ #መልክዓ #ስዕል(ለስዕሉ)፣ #መልክዓ #ቁስቋም(ለቦታ) ይጠቀሳሉ። ሌላው ደግሞ #ማንም ሊቀርበው በማይችል #ብርሃን ውስጥ ለሚኖረው #መልክዓ እና #ገጽ የሌለው #መንፈስ ለሆነው #ለእግዚአብሄር እንኳን #በሰው #አካል(ብልቶች) እየቆጠረ ባለ ብዙ #አርኪ #ግጥም #መልክ ተዘጋጅቶለታል። #ለመላእክትም#ቅዱሳን ለተባሉ #ሰዎችም#በኢትዮጵያ ነግሰው ለነበሩ #አጼዎችም ሁሉ "መልክእ" አላቸው። ይህ <መልክእ> የተባለው #የስነ ጽሁፍ #አይነት መጻፍ የተጀመረው #ፕሮፌሰር #ኃይሌ #በ17ኛው ክፍለ ዘመን #ፌሬንክ በተባለ #እንግሊዛዊ እንደሆነ ሲናገሩ #አለማየሁ #ሞገስ የተባሉት ደራሲ ደግሞ #በ14ኛው ክፍለ ዘመን #በአጼ #ዘረዓ ዕቆብ #ዘመነ መንግስት ነው ይላሉ። ሌላው ዜግነቱ ያልታወቀው "ቤደርሰን" የተባለ ጸሀፊ ደግሞ #በ17ኛው ክፍለ ዘመን ባልታወቀ #የዜማ #አቀንቃኝ ነው ይላል። ሁሉም #በጀማሪውና #በጅማሬው #ዘመን ባይስማሙም #የቤተክርስቲያኒቷ ጅማሬ ላይ ያልነበረ #አበው ያላስተማሩት #መጤ እንደሆነ ይስማማሉ።

▶️ መነሻ ሀሳባችን ስለማርያም ነውና በ"መልክእ" ይዘት ድንግል ማርያም የምትመለክበትን ከ"ጸሎት መጽሀፍ" አንዱ የሆነውን < #መልክዓ #ማርያምን> እንመልከት፦