ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ለ"ማርያም" ለሚለው ስም የተሰጡ #ትርጉሞች #የቤተስክርስቲያን #አባቶችም ሆኑ #ወጣት #ሰባኪያንና #ህዝቡም በብዛት የሚያውቁት #የተለመደ #ትርጉም ነው። የሚገርመው ደሞ #የስሙ #ትርጉሞች ብዙ #ማርያም የተባሉ #ሴቶች እያሉ ማእከል ያደረገው ግን #የጌታችን #እናት #ድንግል #ማርያምን ብቻ ይመስላል። እነዚን #ትርጉሞች ይዘን ለሌሎች < #ማርያም> ለተባሉ #ሴቶች ትርጉሙን…
▶️ ከላይ እንዳየነው አንዳንዶች #የስሙን ሙሉ #ሐረግ ተከትለው ሌሎች ለሁለት ከፍለው #ለመተርጎም ከሞከሩት #ውጪ ሌሎች ደግሞ ከዚህ በተለየ መንገድ #ማርያም የሚለውን ስም #ለማብለጥ ወይም #ከፍ #ለማረግ ሲሉ #ማርያም ስለሚለው #ስም #ትርጉም #የአማርኛውን ወይም #የግእዙን ሆህያት ብቻ ተከትለው #ፊደል #በፊደል እየከፋፈሉ #በግእዝ ቋንቋ #በግጥም መልክ ይተረጉማሉ።👇👇

✳️👉 ማኅደረ መለኮት [የመለኮት ማደሪያ]።
✳️👉 ርግብየ ይቤላ [ንጉስ ሰለሞን ርግቤ ያላት፥ መኃ 6፥9]።
✳️👉 ያንቀዓዱ ኅቤኪ ኩሉ ፍጥረት [ሁሉም ፍጥረት ወደ አንቺ ያንጋጥጣል(ያቀናል)]።
✳️👉 ምስአል ወምስጋድ [ወምስትሥራየ ኃጢአት፣ የምንለምናት፣ የምንሰግድላት[4]]።

️ይህም #ትርጉም ከላይ እንዳልነው #የአማርኛ #ፊደላትን #በግዕዝና #በግጥም #የመተርጎም ሙከራ ሲሆን ይህም እንደሌሎቹ #ትርጎሞች ለሌሎች " #ማርያም" የሚለው #ስም ላላቸው የሚያገለግል አይመስልም። እንዲህ አይነቱ #ትርጉም የመስጠት አካሄድ ደግሞ #ከዓውደ #መሠረቱ ያስወጣል።

️በዚህ #ትርጉም መሠረት " #ማርያም ማለት #የመለኮት #ማደሪያ የሆነች፤ ንጉስ ሠሎሞን #በመኃልይ #መኃልይ መጽሐፉ #ርግቤ ያላት፤ ፍጥረት ሁሉ ወደ እርሷ #የሚያቀኑ#የሚሰግዱ#የሚለምኑ እና እርሷም #ለምላሹ #ኃጢአትን #የምታስተሰርይ ናት" ማለት በግልጽ #ማርያምን #ማምለክ ማለት ነው። #አምልኮ ከዚህ ውጪ #ካለ ንገሩን!!

▶️ መቼም #ሰይጣን በተለይም #በኢትዮጵያ #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ጊዜና ባለስልጣናት ገጥሞት በብዙ #ሠይፍ < #የማርያምን #ምልጃ> ትምህርት ወደ #ቤተክርስቲያን አስገብቶ #ማርያም ባትሰማቸውም ወደ እርሷ #የሚያንጋጥጡ#የሚሰግዱ#የሚለምኑ#ኃጢአታቸውን #የሚናዘዙ ይብዙ እንጅ #በመጽሀፍቅዱስ ታሪክ እንኳን #ወደእሷ ወደየትኛውም #ፍጡር #የጸለየ አናገኝም።

▶️ ደግሞ #ሰሎሞን #በመኃልየ #መኃልይ መጽሐፉ ሱናማይት{ሱናማጢሳዊት} የሆነችውን አንዲት ልጃገረድ #ውዴ#ርግቤ#መደምደሚያየ እያለ በፍቅር እንዴት #አሸንፎ ወደ ቤቱ እንዳመጣትና #ባሸበረቀ አልጋው ላይ አጋድሞ #ጡቶቿ እንዴት እንዳረኩት እርሷም በእርሱ እንዴት #እንደረካች የሚናገረውን #የፍቅር #ኃይልና ግለት #የተንጸባረቀበትን መጽሐፍ ወስዶና #በጥሶ <ሰሎሞን #ርግቤ #መደምደሚያዬ ያላት #ማርያምን ነው> ማለት ምናልባት መጽሐፉንና #ዓላማውን #ካለማንበብና #ካለማወቅ የመነጨ፣ አሳፋሪም ጭምር መሆኑን #የሱናማይቷ ሴት #ለፍቅር ስሜት የመጦዝ ባህሪ ታላቅ አድርገው ለሚገምቷት "ለቅድስት ድንግል ማርያም" ባልተስማማ ነበር።

▶️ መኃልየ #መኃልየ መጽሀፍም #የብሉይኪዳን ክፍል እንደመሆኑ #በሰለሞንና #በማርያም መካከል ያለውን "የዘመን ልዩነት" መገመት ራሱ አይከብድም። #ማርያም #በሰለሞን ዘመን ፈጽማ ያልነበረችውን፤ #ሰለሞን እንዴት በወቅቱ ከነበሩት < #ስልሳ ንግሥታት #ሰማኒያም ቁባቶች(ውሹሞች) #ቁጥር የሌላቸው ቆነጃጅቶች> ጋር #በውሽምነት መልኩ ሊቆጥራት ይችላል? {መኅልየ 6፥8}

▶️ ደግሞ < #የዓለምን #ኃጢአት ሊያስወግድ የተገለጠ #የእግዚአብሄር #በግ> {ዩሐ 1፥29 , ራዕ 5፤5-10} #ኃጢአትን #የማስተሰረይ ስልጣንም #የኢየሱስ #ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ እያወቅን {ማር 2፤10} ማርያምን "ወምስትሥራየ ኃጢአት" {ኃጢአትን የምታስተሰርይ} እንዴት ልንል እንችላለን?? #በኃጢአት ላይ የወጣውን #የእግዚአብሄርን #ቁጣ #ፍርዱን #ሊያቃልለው ወይም #ሊያስተወው የሚችልስ ጉልበተኛ ማነው? #ሙሴ እንኳ በምድር ህይወቱ #የእስራኤልን #ኃጢአት ተከራክሮ #ለማስቀረት ቢሞክርም #እግዚአብሔር #ፍርዱን መለወጥ ባለመቻሉ በርካቶች #ሞተዋል። {ዘዳ 32፤30-35}። #ኃጢአተኛው እራሱ #ካልተመለሰና #ንስሐ ካልገባ በቀር #እግዚአብሔር ኃጢአትን ይጠላል #ይቀጣልምም {ዩሐ 8-24}።
▶️ ቅዱስ ገብርኤል #ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ #ለማርያም #ለማስረዳት የተጠቀመው #ምሳሌ #መካን የነበረችውና #ያረጀችው ዘመዷ #ኤልሳቤጥ #ወንድ ልጅ እንደጸነሰች በመግለጽ ነበር። #ልጅ አለመውለድ #የወላጆችን #የግል #ደስታ የሚያሳጣ ብቻ ሳይሆን #እግዚአብሔር እንደማይወዳቸውም የሚያመለክት ነው ተብሎ #በህብረተሰቡ ዘንድ ስለሚታመን {ዘፍ 16፥2 ፣ ዘፍ 25፥21 ፣ ዘፍ 30፥23 ፣ 1ኛሳሙ 1፤ 1-18 ፣ ዘሌ 20፤ 20-21 ፣ መዝ (128)፥3 ፣ ኤር 22፥30}። <<ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ ተመለከተኝ>> ብላ #እግዚአብሔር #የመካንነትን #ህይወቷን ስለቀየረላት ምስጋና አቅርባለች {ሉቃ 1፥24}። #በደስታ#በጥሞና#በምስጋና... የነበረችውን #ኤልሳቤጥን ማርያም #ከገብርኤል መልእክት(ብስራት) ቡኋላ ወደ እሷ መጥታ #ሰላምታ ስታሰማት #ኤልሳቤጥ #በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ከማርያም አፍ ሳትሰማው ማርያም #የጌታ #እናት እንደምትሆን አወቀች። በዚህ ጊዜ #ኤልሳቤጥ አፏን የሞላው #ቃል <<አንቺ ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?>> የሚል ነበር። አንዳንዶች እንደሚሉት ሳይሆን ኤልሳቤጥ ማርያምን <<ከሴቶች #በላይ የተባረክሽ>> እንዳላለቻትና ዳሩ ግን <<ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ>> እንዳለቻት ልብ ማለት ያስፈልጋል። #ማርያም #በእግዚአብሄር #እቅድ ውስጥ ያላትን #ስፍራ ባናሳንስም(ልናሳንስም አንችልም) #እግዚአብሔር #ብቻ ሊቀበል የሚገባውን #የአምልኮት #ክብርና #ልእልና መስጠት ግን አይገባንም።

▶️ ስለማርያም ኤልሳቤጥ #ያገነነችው ነገር ቢኖር <<ያመነች ብጽኢት[1] ናት>> በሚል የማርያምን #እምነት ነበር {ሉቃ 1-45}። #ማርያም #የእግዚአብሔርን #ቃል ስላመነች የእግዚአብሔርን #ኃይልና #አንድያ #ልጅ ተቀበለች።

▶️ በኤልሳቤጥ #ጽንስ ውስጥ ያለው #ዩሀንስም በጊዜው #ደስ #ተሰኝቷል {ሉቃ 1፤ 41-44}። ዩሀንስ #በምድራዊ #አገልግሎቱ እንዳደረገው ሁሉ #ሳይወለድም በፊት #በኢየሱስ ክርስቶስ #ብቻ ደስ ተሰኝቷል {ዩሀ 3፤ 29-30}። #ካደገ ቡሀላም #መጥምቁ #ዩሀንስ ተብሎ ሲታወቅ #መሲሁን #ኢየሱስ ክርስቶስን ለአይሁድ ህዝብ የማስተዋወቅና የመግለጥ ታላቅ #እድል አግኝቷል። ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ <<ዩሀንስ በእናቱ ማህጸን ውስጥ የማርያምን ድምጽ በመስማቱ #ለማርያም #ሰገደላት>> የሚሉ #መናፍቃን አልታጡም። ይሁን እንጂ #የጽንስ #መዝለል #ሁኔታን #ጸንሰው የሚያቁ #እናቶች የሚረዱት ነገር ቢሆንም •ስግደት• ብሎ መቀየር ግን. . . •ለማርያም ሰገደ• ያሉትም #መጽሀፍ ቅዱስ ሳይሆን #ሲኖዶስ ተብለው የተጠሩ ተስብሳቢዎች እንደሆኑ #ራሱ #ኦርቶዶክስ ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን ያሳተመችው #የሉቃስ ወንጌል አንድምታው ይገልጻል።

<<. . . ከዘካርያስ ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን እንዴት ነሽ አለቻት፥ ወሶበ ስምዓት ኤልሳቤጥ ቃላ ለማርያም እንዝ ትትኣምኃ ኦንፈርዓፀ እጓል በውስተ ከርሣ እመቤታችን እንዴት ነሽ ስትላት ኤልሳቤጥ በሰማች ጊዜ በማኅፀኑዋ ያለ ብላቴና ሰገደ። ሐተታ፡ ሐዋርያት #በሲኖዶስ ሰገደ ብለውታል። #ያሬድም ሰገደ ብሎታል።[2]>>

▶️ ከዚሁ #ከማርያምና #ከኤልሳቤጥ #ውይይት በመነሳት <<ቅድስት ኤልሳቤጥ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ ነሽ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እያማለድሽ የምትሰጪ መዝገበ በረከት ነሽ>> ብላ #አመስግናታለች #ዘምራላታለች የሚሉ አሉ[3]።

▶️ እንግዲህ እንዲህ አይነት #ቃል #በመጽሀፍ ቅዱስ ፈጽሞ ሳይኖር #ኤልሳቤጥ እንዲህ አይነት #ቃል ተጠቅማለች ብሎ #መጻፍና #ማስተማር #መጽሀፍ ቅዱስ እኛ ጋር #ብቻ ይገኛል ሌላው #ማንበብ አይችልም ብሎ ከማሰብና #የመጽሐፍ ቅዱስን #የበላይነት ካለመቀበል የሚመነጭ #ከንቱነት ነው። #ኤልሳቤጥ የተናገረችው <<አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።>> {ሉቃ 1፥47} የሚል ብቻ ነው።

▶️ በአንጻሩ ደግሞ <<መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የለብሽም>> ማለት በግልጽ #መጽሀፍ ቅዱስን መካድና #ማርያም የሰው ዘር መሆኗን #መዘንጋት ነው። እንዲያውም ማርያም ራሷ ክርስቶስን <<መድኃኒቴ>> ብላዋለች። #መድኃኒት ደግሞ #ለበሽተኞች (ለኃጢአተኞች) እንጂ #ለጤነኞች (ለጻድቃን) የሚያስፈልግ እንዳልሆነ #ቃሉ #በግልጽ ይናገራል{ማቴ 9፥12}።

▶️ በመሆኑም <<መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ. . . እያማለድሽ የምትሰጪ>> እያለ #የዘመረ #አካል #በመጽሀፍ ቅዱስ ባለመኖሩ የሌለ ነገር ላይ ተንተርሶ #ዶክትሪን ማስቀመጥ በቃሉ #መልእክት ላይ የተፈጸመ ተራ #አመጽ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_______________
[1] ብፁዕ፤፦
<<በቁሙ የታመነ፣ የተመሰገነ፣ ሥራውና ልቡ የቀና፣ ... ምስጉን፣ ብሩክ...>>
📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ *ገጽ 2081። አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ 1948 ዓ.ም።

<<የተባረከ፣ ደስተኛ>>
📚፤ የኢትዮጽያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር፤ <የመጽሀፍቅዱስ መዝገበ ቃላት>፤ 6ኛ እትም፤ *ገጽ 112። ባናዊ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ 1992 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፡ ወንጌል ቅዱስ፡ የሉቃስ ወንጌል ንባቡና አንድምታው 1፤ 36-40፤ ገጽ 268። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1997 ዓ.ም።

[3] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ ቤ/ክ፤ <መርሐ ጽድቅ ባህለ ሃይማኖት>፡ ገጽ. 24-25፡ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት። አ.አ፥ 1988 ዓ.ም።

📚፤ አንዱዓለም ዳግማዊ (መምህር) <ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት> ገጽ 290። ብራና ማተሚያ ድርጅት፥ ሚያዚያ፥ 1998 ዓ.ም።


(5.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ #ሴቶች ሰፊ ስፍራ #ከወንዶች #እኩል ተሰጥቷአቸው #እግዚአብሔር ሲጠቀምባቸው እናነባለን። በተለይ #በአዲስ ኪዳን #የእግዚአብሄር ቃል በግልጽ <<አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።>> {ገላ 3፥28} ይላል። እንዲሁም <<እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።>> {ሮሜ 2፥11}፣ <<በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤>> {ሮሜ 10፥12} ይላል።

▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ከወንዶች ባልተናነሰ አንዳንዴም #በሚበልጥ ሁኔታ #እግዚአብሔር በተለያየ መልኩ የተጠቀመባቸው #ከ87 የሚበልጡ #ሴቶች #ከነታሪካቸው ተጽፏል። ከእነዚህም ውስጥ #ልጅ ባለመውለዳቸው #ሲነቀፉ የነበሩት #እንደነሳራና #ሐና የመሳሰሉ #እግዚአብሔር #ቃል ኪዳን ያለውን #ልጅ በመስጠት #አስደናቂና #ታዋቂ #እናቶች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

▶️ የተጠቀሱት ሁሉም #ሴቶች #አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር #መሲሁን (ኢየሱስ ክርስቶስን) ማገልገላቸውና ለእርሱም #መንገድ ማዘጋጀታቸው ነው። ለምሳሌ፦


1፦ ሔዋን፦ #ከሴቲቱ #ዘር የሚመጣው (ኢየሱስ ክርስቶስ) #የእባቡን (የዲያብሎስንና የኃጢአትን) #ራስ #እንደሚቀጠቅጥ የተናገረላትና ይህንንም #ትንቢት በመጠበቅ ለዚህ #ዘር #ሐረግ በመጀመሪያ #አቤልን ከዚያም #ሴትን የወለደች።

2፦ ሩት፦ #ከሞዓባውያን ወገን የነበረች #በእምነት #ከወገኖቿ ተለይታ #ከእግዚአብሄር ህዝብ ጋር በመቀላቀል #እስራኤላዊውን #ቦኤዝን አግብታ #የእሴይን አባት #እዮቤድን በመውለድ ወደ #ክርስቶስ #የዘር #ግንድ ውስጥ ገብታለች።

3፦ አስቴር፦ #ዝርያው እንዲጠፋ የተፈረደበት #የአይሁድ #ህዝብ ወደ #ንጉሡ #በድፍረት በመግባት #ህዝቤን #በመሻቴ #ህይወቴም #በልመናየ ይሰጠኝ በማለት #በህዝቧ ላይ #የታወጀውን #የሞት #ፍርድ በመቀልበስ #ከአይሁድ ወገን ሊመጣ ያለውን #የኢየሱስ ክርስቶስን #ዘር በመጠበቅ የበኩሏን #አስተዋጽኦ አድርጋለች።

▶️ እነ #አቢግያ#ኢያኤል#ኤልሳቤጥ#ቤርሳቤህ#ራሔል#ሊዲያ#ፌበን#ሰሎሜ፣ . . .ወዘተ ሁሉም #እግዚአብሔር የሰጣቸውን #ተግባር ሁሉ #በድል ያከናወኑ አንቱ የሚባሉ #ሴቶች ናቸው።

▶️ ጌታ ኢየሱስ #በአገልግሎቱ #ወቅት #ከፍተኛ #እገዛ ሲያደርጉ የነበሩ በዚያ #አስፈሪ #ሰዓት በሆነው #በስቀለቱም ወቅት #ከመስቀሉ #ግርጌ ስር በስፋት #ሃዘናቸውን የገለጹ #በመቃብሩም ሄደው እንደተናገረው #መነሳቱን #ከቅዱሳን #መላእክት ሰምተው #ለህዝቡ ሁሉ በመጀመሪያ #ትንሳኤውን ያወጁና የእርሱን #መሞትና #መነሳት ... ወዘተ የሚያበስረውን #ወንጌል ይዘው ወጥተው #የግል #ቤታቸውን እንኳ #የወንጌል አደባባይና #ቤተክርስቲያን አድርገው #የእግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምሩ የነበሩ #ሴቶች ነበሩ።

▶️ ይህን #ማንሳታችን ያለ ምክንያት ሳይሆን <<ማርያም #ከሴቶች ሁሉ እንዲያውም #ከፍጡራን ሁሉ የበላይ የሆነች #ፍጡር>> የሚል #የተዛባና #መጽሀፍቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምህሮ ስላለ ነው። ለዚህም #ትምህርት መነሻው #በሉቃስ 1፥28 እና 1፥42 <<አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ>> ተብሎ የተገለጸው #ቃል ሲሆን <<ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ማርያምን ብሩክት አንቲ እምአንስት - አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተለየሽ ሲል ከሴቶች ሁሉ የተለየች መሆኗን በምስጋና ቃል ገልጦ ተናግሯል፤ የዚህን መልአክ ቃል በመደገፍ በማጽናትም ኤልሳቤጥ አንቺ ከሴቶች የተባረክሽ ነሽ ብላ ጮሀና አሰምታ ተናግራለች። ይህም ቃል ቅድስት ማርያምን በነፍስ በሥጋ ቅድስት መሆኗን መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን (ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ) መሆኗን ያጠቃልላል>> ብለው የተረጎሙት ስላሉ ነው[1]። በመሰረቱ ይህ #ትርጉም ሳይሆን #የመጻሐፉን ግልጽ #ቃል በመቀየርና ወደሚፈልጉት የማርያም #አምልኮ በማዞር የተቀመጠ #አስተምህሮ ነው።

▶️ ማርያምን <<ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች>> የሚለውን ቃል #ለመጀመሪያ ጊዜ የገለጸው #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረው #የደቡብ ወሎ ቦረናው #ሰው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ነው[2]።

▶️ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው #ምክንያታቸው ከላይ የተገለጸው #የቅዱስ ገብርኤልና #የኤልሳቤጥ #ንግግር ሲሆን ሌላው እንደ #ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ #ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን #መውለዷ ነው።

▶️ ከዚህ የተነሳ #ከእግዚአብሄር #ምስጋና #ቀጥሎና #አያይዞ #ማርያምን #ማመስገን እንደሚገባ #ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቡኋላ #የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን መጠቀም ጀምራለች። ለምሳሌ፦

〽️ 1፦ <አቡነ ዘበሰማያት(አባታችን ሆይ)> ከሚለው #ጸሎት ቀጥሎ <እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ.... ሰላም እንልሻለን> ማለትን

〽️ 2፦ <ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ (ምስጋና ይሁን ለአብ፣ ምስጋና ለወልድ፣ ምስጋና ለመንፈስቅዱስ ይገባል)" ከሚለው #ቀጥሎ <ስብሐት #ለእግዝትነ #ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ (አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይሁን)> ማለትን

〽️ 3፦ <ለልዑል እግዚአብሔር ፍጹም #ምስጋና ይገባል> ይባልና ቀጥሎ <ለወለደችው ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይገባል> ማለትን

〽️ 4፦ <የእግዚአብሄር ስሙ ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱ በየሰአቱ #ምስጋና ይገባል> ካለ ቡሀላም <እናታችን ማርያም ሆይ ሰላምታ ለአንቺ ይሁን እያልን #እንሰግድልሻለን #እንማልድሻለን> ይላል[3]።
▶️ ክርስቶስ <<በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ>> ብለን እንድንጸልይ እንጂ ያስተማረን << #እመቤታችን ሆይ>> ብለን እንድንጸልይ አላስተማረንም። የተሰጠንም #መንፈስ #አባ #አባ ብለን የምንጮህበት #መንፈስ #ብቻ ነው እንጂ #እማ #እማ ብለን የምንጮህበት አይደለም [ሮሜ 8፥15]። <<ስምህ ይቀደስ>> እንድንል እንጂ << #ሰላምታ #ይገባሻል>> እንድንል <<በደላችንን ይቅር በለን>> እንጂ << #ይቅርታን #ለምኚልን ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ>> እንድንል አላስተማረንም። የሁለቱም #ጸሎቶች #አድራሻና #ፍሬ ነገራቸው #የሰማይና #የምድር #ርቀት ያክል ልዩነት ያላቸውና #የሚጣረሱ ናቸው።

▶️ ከክርስቶስ #ትምህርት ጋር ሌሎችንም <<የጸሎት መጻህፍት>> የተባሉትን ብናስተያያቸው
እንደ <<አንቀጸ ብርሃን መጽሀፍ>> << #ስምሽ #የተመሰገነ ነው>> እንድንል ሳይሆን <<ስምህ ይቀደስ>> እንድንል፤ እንደ <<ተአምረ ማርያም መጽሀፍ>> << #ድንግል ሆይ #ፈጥነሽ እንድትመጪ>> [43፥26] እንድንል ሳይሆን <<መንግስት ትምጣ>> ብለን የክርስቶስን #መንግስትህ መምጣት #በናፍቆት እንድንጠባበቅ፤ <<ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን>> በማለት የእርሱ #ሰማያዊ #ፍቃድ ብቻ በምድራችን እንዲሆን እንጂ እንደ ተአምረ ማርያም ጸሀፊ << #ፈቃድሽ #ይሁንልን ይደረግልን>> እንድንል አላስተማረንም [100 ፤ 29-32]። <<የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን>> በማለት #የዕለት #ኑሮአችንንም እንዲያቀናልን እንድንጸልይ እንጂ። እንደ <<መልክዓ ማርያም መጽሀፍ>> << #መጻህፍትሽ #የማዳን #እንጀራንና የተፈተነ #መድሀኒት መጠጥን ስለሚሰጡ #ሰላምታ ይገባል[ለእራኃትኪ]>> እንድንል አላስተማረንም። <<ኃጢአታችንን ይቅር በለን>> እንድንል እንጂ እንደ <<መልክዓ ማርያም>> ደራሲ << #ኃጢአታችንን #ይቅር #በይን[ለመዛርዕኪ]>> እንድንል አላስተማረንም። <<ከክፉ አድነን>> በማለት #ከክፉ እንዲያድነን ወደ #እግዚአብሔር እንድንጸልይ እንጂ << #ከአዳኝ #አውሬ #አድኝኝ>> [የዘውትር ጸሎት ሰላምለኪ] እንድንል አላስተማረንም። <<ኃይል ክብርም ምስጋናም ለዘላለም ድረስ ላንተ ይሁን>> እንድንል እንጂ እንደ <<ተአምረ ማርያምና እንደ ቅዳሴ ማርያም>> <<ድንግል ሆይ #ክብርና #ምስጋና #ለዘላለም ይገባሻል>> እንድንል አላስተማረንም። ስለሆነም ይህን #ከክርስቶስ #ትምህርት ጋር የሚጣረስ ትልቅ #ኑፋቄ ወደ #ቤተክርስቲያን ማስገባትና ማስተማር ታላቅ #በደልና #ኃጢአት ነው።

▶️ አንዳንድ #ሰዎች ደግሞ ይህን #ኑፋቄ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል #ከሉቃስ ወንጌል 1፤ 28- ጀምሮ ያለውን ክፍል ይጠቅሳሉ።

በክፍሉ እንደሚነበበው ግን #መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል #ከእግዚአብሄር ዘንድ ተልኮ ወደ #ድንግል #ማርያም በመጣ ጊዜ በሚያስደንቅ #ሰላምታ ከተገናኘ ቡኃላ የተላከበትን ጉዳይ <<እግዚአብሔር #ከአንቺ ጋር ነው>> በማለት ስለሚወለደው ቅዱስ #የእግዚአብሄር #ልጅና #ስልጣን ላይ አተኩሮና #ሰፊ ጊዜ ወስዶ ሲያበስራት ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ #አንድ #ቤት ወይም #ከጓደኛው ጋር ሲገናኝ #አይነቱ ይለያል እንጂ #ሰላምታ መለዋወጥ በየትኛውም #ሀገር ያለና የተለመደ #ባህላዊ #ስርአት ስለሆነና በተለይም #በመንፈሳዊ ሰዎች ዘንድ ሲገናኙ #ሰላምታ መለዋወጥ #ልማድ ከመሆኑም ጭምር እንዲሁም #መጽሀፍ ቅዱሳዊ በመሆኑ [ማቴ 10፤ 12-13]። መለአኩ #ቅዱስ #ገብርኤልም ያደረገው ይኸንን ነው #ጸሎት እያቀረበ አለመሆኑን ማንም #ሰው አንብቦ #መረዳት የሚችለው ነገር ነው። #ማርያምም ለቀረበላት ሰላምታ <<ይህ #እንዴት ያለ #ሰላምታ ነው>> ብላ አሰበች እንጂ እንደ #ጸሎት #ተቀባይ ወይ እንደ #ጸሎት #ሰሚ ሆና አልቀረበችም [ሉቃ 1፥29]። ነገር ግን አንዳንዶች ይህን ክፍል በመጥቀስ #ማርያምን <<በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ #ሰላም #እልሻለው>> እንዲባል #አስተምረዋል ጽፈው አልፈዋልም ዛሬም #የሚያስተምሩ አልጠፉም።
<<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን የተቀነባበረ <የጸሎት> ክፍል #በኢየሱስ ክርስቶስ #አስተምህሮ #ወቅት ብቻ ሳይሆን ከእሱ ቡሀላም ለብዙ #ዘመናት አልነበረም። ምናልባትም ሌሎች እንደሚሉት #ማርያም ገና #ክርስቶስን ሳትወልድ የነበረ #የገብርኤል #ሰላምታ ነው ተብሎ እንዳይወሰድ እንኳን #መልአኩ መጥቶ ያደረገው #ውይይት እንጂ #ጸሎት አይደለም። #ክርስቶስም #ለደቀመዛሙርቱ #ጸሎት ባስተማረበት #ወቅት #የገብርኤልንም #ሰላምታ ጨምሩበት በማለት ባስተላለፈ ነበር፤ ያንን ደግሞ አላደረገውም [ማቴ 6፤ 1-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]። << #በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ....>> የሚለው #የጸሎት #አስተምህሮቱን #ድንግል ማርያምን በትክክል በሚያውቋት #በደቀመዛሙርቱ ፊት ምናልባትም #በአስተምሮው #ወቅት ብዙ ጊዜ በምትገኝዋም #በድንግል #ማርያምም በራሷ ፊትም ተናግሯል።

▶️ ስለሆነም የተቀነባበረው <<የማርያም የጸሎት>> ምዕራፍ #በክርስቶስ #ወቅት ያልነበረ ከዚያም ቡኋላ #ሐዋሪያቱ #በአገልግሎታቸውና #በጸሎታቸውም ወቅት የማያውቁትና #የጥንት #ቤተ ክርስቲያን #አባቶችም በልዩ ልዩ ምክንያት #ጉባኤ ሲያደርጉ ለምሳሌ፦ #በኒቂያ ጉባኤ #በ325 ዓ.ም 318 የሃይማኖት አባቶች በእነ #እስክንድሮስ አፈጉባዔነት በንጉስ #ቆስጠንጢኖስ ዘመን ተሰብስበው #አርዮስን <<ወልድ #ፍጡር ነው>> ያለበትን #የክህደት ትምህርት #ሲያወግዙና #የሃይማኖት መግለጫ ሲያወጡ #ኢየሱስን ከመውለዷ ውጭ #ስለማርያም ፈጽሞ #መሠረታዊ #ትምህርት እንኳ በወቅቱ እንዳልነበረ መረዳት ይችላል። እንዲሁም #በቁስጥንጥንያ #በ375 ዓ.ም 150 #የሃይማኖት #አባቶች #በጢሞቴዎስ ዘአልቦጥሪት በንጉሥ ዘየዓቢ #ቴዎደስዩስ ወቅት #መቅደንዩስ << #መንፈስ ቅዱስ #ሕጹጽ ወይም #ሀይል ብቻ>> ብሎ በተነሳ ጊዜ ተሰብስበው #አውግዘው ትምህርቱንና እርሱን ሲለዩ #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #የአስተምህሮ #መግለጫ ሲያወጡ ያኔም ቢሆን #ኢየሱስን #ከመውለዷ ውጪ #ስለማርያም ያስተላለፉት ምንም #አዲስ #ትምህርት የለም። #በኤፌሶን ሀገርም #በ435 ዓ.ም 200 #የሃይማኖት #አባቶች #በቄርሎስ አፈጉባዔነት በቴዎደስዩስ ዘይንእስ ንጉሥነት ጊዜ ንስጥሮስ << #ክርስቶስ #ሁለት #አካል #ሁለት #ባህሪይ ነው>> ብሎ ሲነሳ #እርሱንም #ትምህርቱንም #አውግዘው #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #አስተምህሮ በመግለጫ መልክ ሲያስቀምጡ ድንግል #ማርያም #ክርስቶስን እንደወለደች ብቻ እንጂ << #እመቤታችን>> ብለውም ሆነ << #ለምኝልን>> የሚል አስተምህሮ አያውቁም። #ጤናማ #አስተምህሮ አይደለምና።

▶️ ዛሬ ሁሉም #አብያተክርስቲያናት የሚቀበሉት #ሙሉ #የሃይማኖት #መግለጫቸው

<<ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን የተፈጠረ ሳይሆን የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምን ምንም የሆነ የለም በሰማይም ያለ በምድርም ያለ ስለእኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፈጽሞ ሰው ሆኖ በጴንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ ሞተ ተቀበረም በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና ሙታንንም ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም ጌታ ማህየዊ በሚሆን ከአብ በሰረጸ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋሪያት በሰበሰባት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሰረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።>> የሚል ነው።

ይህንንም መግለጫ #በ1530 ዓ.ም #ሉተራውያን << #የአውግስበርግ #መግለጫ>> በሚል አጸደቁ። እንዲሁም #በ1546 ዓ.ም #ካቶሊክ በድጋሜ << #የትሬንት #መግለጫ>> በማለት አጸደቀችው። #በ1571 ዓ.ም ደግሞ #የአንግሊካን #ቸርች መግለጫውን ተቀብላ አጸደቀችው። #በ1646 ዓ.ም #ፕሪስቢቴሪያን << #የዌስት #ሚኒስቴር #መግለጫ>> በሚል አጸደቀችው[1]።

▶️ ኦርቶዶክስ #ቤተክርስቲያን መግለጫውን በድጋሜ << #ጸሎተ #ሃይማኖት>> በማለት #በ1426-1460 ዓ.ም በኢትዮጵያ የነገሰው #አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ ሙሉውን ተቀበሉና ሌላ #በመጨመር << #ለማርያምና #ለእፀ መስቀሉ (ለመስቀሉ እንጨት) #ስግደት ይገባቸዋል>> በማለት እንዲሁም <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን <<ከአባታችን ሆይ>> #ቀጥሎ እንዲባል ብሎ #አዋጅ አወጣ። ከዚህም የተነሳ በርካታ #ካህናት << #አባቶቻችን ካስቀመጡት #ከሃይማኖት #መግለጫው ውጪ ተጨማሪውን #አንቀበልም>> በማለታቸው #በሰይፍ እንደቆራረጣቸውና እንዳሳደዳቸው #ገድለ #እስጢፋኖስ#ገድለ #አበው ወአኀው፣ #ገድለ #አባ አበከረዙል፣ #ገድለ #አባ ዕዝራ፣ #ገድለ #ደቂቀ እስጢፋኖስን ማንበብ #በቂ ነው።

▶️ ነገር ግን #በዘር #ቅብብሎሽ አማካኝነት የነበረው #የንግስና #ሥርአት ለዚህ <<አዳራሻውን ወደ ሳተው ጸሎት>> ሰፊ እድል አግኝቶ #ሰይፍ ያስፈራቸውና በክርስትናው #ትምህርት ብዙም #መሰረታዊ #እውቀት ያልነበራቸው #ህዝብና #ካህናት #የጸሎት #ምዕራፋቸው አድርገው ለቀጣዩ #ትውልድ በማስተላለፋቸው ይሀው አሁን የምናየውን #ከእግዚአብሄር #ቃል ውጪ የሆነ #ትውልድ ፈጥረውልናል። ዛሬ ዛሬ #በየጸሎቱ #መዛግብት ውስጥ እየተጨመረ ተጽፎ #ምዕመናን ሁሉ #በቀን ቢያንስ #አንድ ጊዜ እንዲደግመው በመደረጉ እንግዳው <<ጸሎት>> #የተለመደ ሆኖ ቀረ። እንዲያውም በዚህ #ዘመን አስቀድመን እንዳልነው <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል #ጥቅሶችን ያለቦታቸው እንደ #ስጋ #ዘንጥለውና #በጣጥሰው #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል የሚታገሉ ተነስተዋል። እኛ ግን <<የእግዚአብሔርን ቃል #ቀላቅለው #እንደሚሸቃቅጡት እንደ #ብዙዎቹ አይደለንምና፤ #በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ #ተላክን #በእግዚአብሔር ፊት #በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።>> [2ቆሮ 2፥17]

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን፤ አውግስበርግ ሃይማኖታዊ መግለጫ፤ በአማርኛ የተተረጎመ፤ አ.አ፥ 1993 ዓ.ም።
▶️ የሰው ልጅ #ሃሳቡን ከሚገልጽባቸው አያሌ ነገሮች አንዱ #ሥዕል ነው። #ሥዕላት #የሰውን ልጅና #የተፈጥሮን #የኑሮ #መልክና #ጸባይ በማንጸባረቅ መልሰው ለሰው ልጅ #የሚያስተምሩ#ታሪክን #መዝግበው የመያዝ #አቅማቸው ብርቱ የሆነና #በስልጣኔውም መስክ የበኩላቸውን #መረጃ ዘግበው በመያዝ ከፍተኛ #አስተዋጽኦ ያደረጉ ናቸው። #ሥዕላት ወደ #ቤተክርስቲያን ከመግባታቸው በፊት #በአህዛብና #በአይሁድ ዘንድ #ከአምልኮት ጋር በተያያዘ መልኩ በስፋት #ይገለገሉባቸው ነበር።

በተለይ #እስራኤላውያንና ቀደምት #የሀይማኖት #አባቶች #ሥዕላትን #ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ሲያውሉ ማንኛውም #ጽሁፍን ማንበብ ለማይችል #ሰው #የክርስቶስን #ህማማቱን#መሰቀሉን#መሞቱን#መቀበሩን#መነሳቱንና #ማረጉን ደግሞም ተመልሶ እንደሚመጣ #ለመስበክ እንዲጠቅሙ በማድረግ ነበር።

▶️ ሥዕሎቹን #በተራራ ገመገም፣ #በሰሌዳ ላይ፣ #ድንጋይ #በመጥረብና #በመፈልፈል#በዛፍ #ቅጠልና #ቅርፊት ላይ፤ ቡኋላ ቡኋላም እየቆየ ሲሄድ #ከፍየልና #ከበግ ቆዳ ላይ ሁሉ #እጽዋትን #በቀለምነት በመጠቀም ለማስተማሪያነት ይጠቀሙበት ነበር። እንደውም አስተምረው ከጨረሱ ቡሀላ አንዳንዶቹን #ስዕሎች በቋሚነት #የማስተማሪያ #መሳሪያቸው አርገው እስከ ረጅም #የህይወት #ዘመናቸው በመጠቀም #ለተማሪዎቻቸው ከሚያወርሷቸው #ሃይማኖታዊ ንብረቶች ውስጥ ዋነኛውን #ስፍራ የያዙት #ሥዕላት ነበሩ።

▶️ ቀስ በቀስ #ሥዕሎችና #ቅርጻቅርጾች (ምስሎች) እየበዙ በመምጣታቸው በተለይም #በቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ #በግድግዳ ላይ በብዛት #በመንጠልጠላቸውና ልዩ #ትኩረት እየሳቡ በመምጣታቸው ምክንያት #በ8ኛው መቶ ክፈለ ዘመን #በክርስቲያኖች መካከል <<አምልኮ ባእድ እየሆኑ መተዋል>> በማለት #ከፍተኛ #ክፍፍልና #ጭቅጭቅን ፈጥሩ።

▶️ በ726 ዓ.ም #የቢዛንታይን መሪ የነበረው " #አጼ #ሊያ #ሳልሳዊ[1]" ምስሎችን #ማመን አጥብቆ #ተቃወመ። በዚህ ምክንያት #ፀረ ምስል ተናጋሪዎችና #ምስል ደጋፊዎች ወደ #ከረረ #ግጭት ውስጥ ገቡ። ይሄው ንጉስ #በ730 ዓ.ም ውሳኔውን #አጽንቶ #በግዛቱ #ምስሎችን ጥቅም ላይ መዋላቸውን #አገደ#በምስል #አፍቃሪያን ላይም ከፍትኛ #ስደትን አስከተለ።

▶️ ከዚህም የተነሳ በተለይ #ሊዎንን ተክቶ የነገሰው " #አፄ #ቆስጠንጢኖስ 5ኛ[2]" <<ክርስትናውን ለማጽዳት>> በሚል በርካታ #ምስል #አፍቃሪያን የነበሩትን #የሃይማኖት #መሪዎች እንዲገደሉ አደረገ። ብዙም ሳይቆይ #አፄ #ቆስጠንጢኖስ 5ኛ በመሞቱ ምክንያት ብዙ #መንፈሳዊ #እውቀት ያልነበራት የነገሩን #አሳሳቢነት የተመለከተች #የንጉስ አፄ #ቆስጠንጢኖስ #ባለቤት (ሚስት) የሆነችው #ኢፌኔ ከሁሉም #ክርስቲያን ሃገሮች የተዉጣጡ #የሃይማኖት #አባቶችን #በ784 ዓ.ም #በኒቂያ ጉባዔ ጠራች። ጉባዔውም #ሁለተኛው #የኒቂያ #ጉባኤ በመባል ተሰየመ[3]።

▶️ በዚህ #ጉባዔ በርካታ #አጀንዳዎች ቢኖሩም በተለይ #የሰንበት ቀን [እሁድ] ልዩ #ከበሬታ እንዲኖረው ፣ #ምስሎች ደግሞ #በአስተማሪነታቸውና ምስሉ የሚወክለውን #አካል #ማክበር ስለሆነ #በቤተክርስቲያን #ግድግዳ ላይ #በክብር #እንዲሰቀሉና ልዩ #ክብር እንዲሰጣቸው ብሎም #እንዲሰገድላቸው ጉባዔው ወስኗል።

▶️ ይህን ውሳኔ #ኦርቶዶክስ #ቤተክርስቲያን {ምስራቃውያን} እና #ካቶሊካውያን {ምዕራባውያን} ተቀብለው #ምስሎችን #ማክበር ጀመሩ። በተለይ #የግሪክ #ኦርቶዶክስና #የሊባኖስ #ማሮናይት #ቤተክርስቲያን የማርያምንና #የክርስቶስን #ስቅለት የሚያሳይ #ስዕል በመሳል በአጥቢያዎቻቸው #ግድግዳ ላይ ሲሰቅሉ በጊዜው #በምዕመኖቻቸው ዘንድ ከፍተኛ #ተቃውሞ ስለገጠማቸው <<ይህችን ስዕል የሳለው ወንጌላዊው ሉቃስ ነው ፤ የጌታችንንም ስቅለት የሳለው ዩሀንስ ነው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣልን መመሪያ ነው>> በማለት #እንግዳ #ትምህርት ማስተማር ጀመሩ[4]።
▶️ በ1962 -1965 እ.ኤ.አ የ2ኛው #የካቶሊክ #የቫቲካን ጉባዔ <<ስለማርያም የሚሰጠው ትምህርት እውቅና እንዲያገኝና የማርያም ምስል ከፍ ተደርጎ እንዲያዝና እንዲሰገድለት ቅዱስ ተብሎም እንዲጠራ የአምልኮም መገልገያ እንዲሆን ወስነናል፤ ይህ የሲኖዶስ ውሳኔ ለቅድስት ማርያም ያለንን አክብሮት ለማሳየት ነው>> አለ[1]።

▶️ ይህን #የቫቲካን #ሲኖዶስን ጨምሮ ብዙ #ሰዎች #ምስልን ለመቀበል የወሰኑት <<ምስልን ማክበር ባለቤቱን ማክበር ነው>> በሚል #የተሳሳተ ሃሳብ ነው። አንዳንድ ጊዜም #ጣዖት ብለው የሚያስቡት #በእግዚአብሔርና #በማርያም አልያም #በመላዕክት #ተመስሎ የተሳለውን ወይም የተቀረጸውን ሳይሆን #በእንስሳት፣ በተለያዩ #ቁሳቁሶች መልክ የተዘጋጀውን #ቅርጽ ብቻ ይመስላቸዋል። በእርግጥ እነርሱም ቢሆኑ #አምልኮና #ስግደት ከቀረበባቸው #ጣኦታት ናቸው። ነገር ግን እንኳንስ #በማርያም #በእግዚአብሔር በራሱ #መልክን ሰርቶ ማስቀመጥ ብሎም ወደ #ምስሉ መስገድ #እግዚአብሔር ከመቃወምም ባለፈ #ይጸየፋል#ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ #ሲያስጠነቅቅ

<<እግዚአብሔርም በእሳት ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ የቃልን ድምፅ ሰማችሁ፥ መልክ ግን አላያችሁም፤ ድምፅን ብቻ ሰማችሁ።. . . እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤ እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥. . . ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።>> [ዘዳ 4፤ 12፣ 15-19]።

▶️ ከዚህ #ከበድ ካለ #ማስጠንቀቂያ እንደምንረዳው #በኮሬብ ለእስራኤል #እግዚአብሔር ራሱን ሲገልጥ #ያለመልክ በመሆኑ ይህን ይመስላል ብሎ #መሳልም #መቅረጽም ብሎም #መስገድ መሳት እንደሆነ እንረዳለን። #እግዚአብሔር እንኳንስ #ለማርያም ለራሱም ቢሆን #በተቀረጸ #ምስል #አምልኮ እንዲቀርብለት ፈጽሞ አይፈልግም።

▶️ በ15ኛው #ክፍለ ዘመን የነበሩት #እስጢፋኖሳውያን የአፄ ዘርዓያዕቆብ #አፍቅሮተ #ጣኦታት የተጠናወታቸው ሰዎች <<ምስለ ፍቁር ወልዳ>> ለሚባለው #ስዕል እንዲሰግዱ ቢያሳዩአቸው #ሥዕሉን አድንቀው <<ለሰው ስራ አትስገዱ>> የሚለውን #አምላካዊ #ትዕዛዝ በማስታወስ <<የሰው ስራ ነውና አንሰግድም>> እንዳሉ ገድላቸው ይተርካል[2]።

▶️ ሌሎችም ለምሳሌ #ዘሚካኤልና #ገማርያ የሚባሉ 2 ሊቃውንት <<አልቦቱ መልክዓ ለእግዚአብሔር ከመ መልክዓ ሰብዕ - እግዚአብሔር የሰው መልክ የሚመስል መልክ የለውም>> በማለታቸው አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ #ተቆጥቶና #ተከራክሮ አስቀጥቷቸዋል[3]።

▶️ ደቂቀ እስጢፋኖስ ይወቁት አይወቁት አይታወቅም እንጂ #ለስዕል #አይሰገድም የሚለው እውነት #በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ሃሳብ አይደለም። እነርሱ ከመነሳታቸው #ከ150 አመት በፊትም እዚያው ትግራይ <<ለስዕል አይሰገድም ጣኦት ነው፣ ሰሌዳ ነው>> ያሉ ታላላቅ #የሃይማኖት #አባቶች ነበሩ። ነገር ግን #አጼ #ያግብአ #ጽዮን[4] [1278-1286] <<በዚህ ጥያቄ እያመነታሁ ሳለው ቀይ ሴት (እመቤታችን) ተገልፃልኝ <<ለሥዕሌ መስገድ ይገባል ብላኛለችና ያልታዘዘ ገመድ ለአንገቱ ያከማቸው ንብረቱ ለሰራዊቴ ቤቱ ከጠመንጃዬ አፎት ለምታወጣ እሳት ይደረጋል>> ሲሉ #ነጋሪት #ጎስመው ስላወጁ ያገሩ ሰዎች ሁሉ #የስዕለ #ማርያም #አምልኮ ትምህርት ተደናግጠው ለጊዜውም ቢሆን ከንጉሱ #ጥይት ለመትረፍ <<ንጉሱ ያዘዘንን ሁሉ እናደርጋለን ለስዕልም እንሰግዳለን>> እንዳሉና በዚህም #እንቅስቃሴው ቀዝቀዝ እንዳለ የታሪክ ጸሀፊዎች ዘግበውታል[5]። <<እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላቹ ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ>> {ኢሳ 40፥18}።

<<እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።>> [ሐዋ 17፥29]።

<<እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።>> [ኢሳ 42፥8]።

<<እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚመለከውም በእውነትና በመንፈስ ነው>> [ዩሐ 4፥24]።

▶️ በመሆኑም #ምስሎች ወደ #ቤተክርስቲያን በገቡበት #ትርጉማቸው #ለማስተማሪያነት ካልሆነ በቀር #ለስርዓተ #አምልኮ መጠቀሚያ ሊውሉ አይገባም። <<ፀልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል-በቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል ፊት ፀልዩ>> ብሎ #ዘርዓያዕቆብ ያወጀው #አዋጅ #የኃጢአት አዋጅ ነውና ዲያቆኑ ቢተወው #ከእግዚአብሔር ጋር #መስማማት ነው።

<<የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ። እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።>> ይላል እግዚአብሔር [ዘዳ 7፤ 25-26]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ "The Docmates of Vatican vol. 2 pp 94,95, Londen 1973.

[2] 📚፤ ገድለ አባ ዕዝራ ገጽ 38።

[3] 📚፤ ጌታቸው ሀይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ" ገጽ 28፣ የህዳግ ማብራሪያ፤ 1996 ዓ.ም።

[4] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Yagbe'u_Seyon

[5] 📚፤ K.contirossini, the act፥ vol 16 (1965)፤ pp. 12-14።

📚፤ ጌታቸው ሀይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ" ገጽ 24፣ 1996 ዓ.ም።

@gedlatnadersanat
(9.5▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat