ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
🔽 ለምሳሌ፦
<ቅድስት ድንግል ማርያም> ትኖርበት በነበረበት #ዘመን #እስራኤል #በሮም #መንግስት #ቀኝ ግዛት ስር ስትሆን #ሄሮድስ በወቅቱ #የሮም መሪ ከነበረው <ከአንቶኒ[11]> #ድጋፍ አግኝቶ #በሮም ምክር ቤት <የአይሁድ ንጉስ> በሚል ስያሜ #እስራኤልን #ሲገዛ እንደነበር ይታወቃል። በወቅቱ #አይሁዳውያንም ጠልተውትና #በሮም መንግስት ስር መሆናቸውን #በመቃወም እስራኤል ሁከት የሰፈነባት፣ ጭካኔ የሞላባት፣ የእርስ #በእርስ መጠላላት እንኳን ሳይቀር የነገሠበት ጊዜ ነበር። #ንጉሥ #ሄሮድስም እጅግ #ጨካኝ ከመሆኑ የተነሳ #መንግስቴን #ይወርሱኛል ብሎ የጠረጠራቸውን <2 ሚስቶቹንና 2 ወንድሞቹንም> ሳይቀር #የገደለበት ጊዜ ነበር። #በዚህም #ምክንያት <ከ27 ዓ.ዓ እስከ 14 ዓ.ም> #የሮም ንጉሥ የነበረው <አውግስጦስ[12]> <<የሄሮድስ ልጅ ከመሆን አሳማ መሆን ይሻላል!!>> በማለት በግልጽ ተናግሮ ነበር። #ሄሮድስ #ሰብአ ሰገል የተወለደውን መሲህ #ኢየሱስን <የአይሁድ ንጉስ> ብለው #በመጥራታቸው ነገሩን በጥንቃቄ #መርምሮ #ኢየሱስ #ክርስቶስን ለመግደል ባደረገው ጥረት #በቤተልሔም ውስጥ በወቅቱ የተወለዱትን በጣም #ብዙ #ህጻናት #ከእናቶታቻቸው ጉያ በመንጠቅ #በሰይፍ #ቆራርጦአቸዋል። በዚህም #ምክንያት <በነብዩ በኤርምያስ> የተተነብየው [ኤር 31፤15-16] <ድምጽ በራማ ተሰማ ልቅሶና ብዙ ዋይታ ራሔል ስለልጆቿ አለቀሰች የሉምና መጽናናትን ስለልጆቿ እንቢ አለች> የተባለው ተፈጸመ[13] {ማቲ 2፤16}።

️ማርያም በዘመኗ ሁሉ ብርቱ #የመከራ #ዘመን እንደምታሳልፍ ተነግሯት ነበር [ሉቃ 2፤35]። #ሄሮድስ #ህጻናትን ሲያስገድል በወቅቱ #በመልአኩ #ምሪት #ማርያምና #ዮሴፍ ህጻኑን (ኢየሱስ ክርስቶስን) ይዘው ወደ #ግብጽ ተሰደዋል። #ሄሮድስም እንደ #ሞተ ሰምተው ቢመለሱም #ልጇ #ኢየሱስ ክርስቶስ ባሳለፈው #ህይወትና #ሲሰቃይ ማየቷ #በእንጨት ላይም #ሲሰቅሉት #ማየቷ በአጠቃላይ እንደ ስሟ #ዘመኗ <መራራ ዘመን> ሆኖባታል።

️ በመሆኑም #ማርያም የተባሉ ሁሉ በተመሳሳይ #ሁኔታ #ዘመናቸው #መራር የሆነባቸው #ሰዎች ነበሩ እንጂ ከላይ አንዳንዶች እንደተረጎሙት የተለያየና፣ የተሳሳተ #ከእውነትም #የራቀ አልነበረም። እነዚህ መተርጉማን ስለማርያም የሰጡት ሃተታ #ቋንቋውንና #ታሪካዊ ዳራውን ያላገናዘበ፣ ከልዩ #ባእድ #አምልኮ መሻት #የመነጨና #ከእውነት የራቀ ብቻ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4፥6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
______________
[1] 📚፤ የኢትዮጵያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር "የመጽሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት" 8ተኛ እትም 1998 ዓ.ም *ገጽ 51።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ውዳሴ ማርያም ንባቡና ትርጓሜው፤ ዘሠሉስ *ገጽ 45። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1983 ዓ.ም።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ <ወንጌል ቅዱስ ንባቡና ትርጓሜው>፤ ዘሉቃስ ፧ *ገጽ 265፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ 1997 ዓ.ም።

📚፤ <ነገረ ማርያም> *ገጽ 28-31። ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ 1991 ዓ.ም።

📚፤ ብርሃኑ ጉበና "አምደ ሃይማኖት" *ገጽ 91። 1985 ዓ.ም።

📚፤ ሚልዮን በለጠ አሰፋ፤ <ቅዱሳት ስዕላት አመጣጥና ታሪክ ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር> ፤ *ገጽ 25-26። 1994 ዓ.ም።

[3] 📚፤ <ነገረ ማርያም>፤ *ገጽ 28-30፤ ተስፋ ገብረ ስላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1991 ዓ.ም።

[4] 📚፤ ሚሊዮን በለጠ አሰፋ
"ቅዱሳን ሥዕላት አመጣጥና ታሪክ ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር" *ገጽ 26። አለም ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ መጋቢት፥ 1994 ዓ.ም።

📚፤ <ነገረ ማርያም> ፤ *ገጽ 29፥ ተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1991 ዓ.ም።

[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም፤ መቅድም ቁ.4 *ገጽ 3፤ 3ተኛ ዕትም፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት አ.አ፤ 1989 ዓ.ም።

📚፤ <አርጋኖን> የእመቤታችን ምስጋና፤ ዘሰኑይ ምዕራፍ 6 ክፍል 4፤ ተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1996 ዓ.ም።

[6] 📚፤ ነገረ ማርያም፤ *ገጽ 34

[7] 📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ <ማርያም>፤ *ገጽ 610፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1948።

📚፤ Dr. Strong፥ "Exhaustive Concordance of the Bible" HEBREW AND CHALDEE DICTIONARY፥ pp 72 no.4805፣ 4813

〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Miriam_(name)

[8] 📚፤ የኢትዮጽያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር፤ <የመጽሀፍቅዱስ መዝገበ ቃላት>፤ 7ኛ እትም፤ <ዩሐንስ> *ገጽ 222። ንግድ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ 1996 ዓ.ም።

📚፤ Douglas & Tenney by International Bible Society Bible Dictionary፤ John pp. 532, 1987።

📚፤ Truesdale, Lyons, Eby clark, A Dictionary of the Bible & Christian Doctrine in every day English, United Bible Societies, 1978፥ pp 155-156.

[9] 📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ <ማርያም> የስም ትርጉም። *ገጽ 610፥ 1948 ዓ.ም።

[10] 📚፤ አለቃ ደስታ ተክለወልድ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡ <ማርያም>፤ *ገጽ 808 1ኛ ዕትም፥ 1945 ዓ.ም።

[11] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Mark_Antony

[12] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Augustus

[13] 📚፤ S I M፤ <የአዲስ ኪዳን ታሪካዊና ባህላዊ መሰረቶች> ፥ *ገጽ 22-23፤ ኤስ አይ ኤም ማተሚያ ቤት፥ አ.አ፤ 1993 ዓ.ም።

(2.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ ኤልሳቤጥ በጸነሰች #በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል #ልጅ #የመውለድ #መልእክት ይዞ ወደ እሷ መጣ። በዚህ ጊዜ #መልእክቱ የመጣው #በገሊላ አውራጃ ከምትገኝ #በናዝሬት ከተማ ለምትኖርና ስሟ #ማርያም ለምትባል #ድንግል ልጃገረድ ነበር። #ማርያም #ከይሁዳ ነገድ #ከዳዊት ትውልድ የሆነች #አይሁዳዊት #ድንግል ነበረች (ኢሳ 7፥14)። #በናዝሬት ከተማ #በአናጺነት ሙያ ለሚተዳደር #ዮሴፍ ለተባለ #ሰው የታጨች ስትሆን (ማቴ 13፥55) ሁለቱም ድሆች ነበሩ (ሉቃ 2፥24 ፣ ዘሌ 12፥8)።

▶️ ከሉቃስ ወንጌል #ምዕራፍ 1፤ 26-33 #የቅዱስ ገብርኤልን #ሰላምታ በደንብ ስንመለከተው #ማርያም ለጊዜው #እንደፈራችና #ግራ እንደተጋባች ያስረዳል። <<ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው>> አላት። #መልአኩ #ሠላምታ ሊሥጣት የመጣው ለምንድን ነው?? #ጸጋ የሞላባትስ በምን #መንገድ ነው? #እግዚአብሔር #ከእሷ ጋር የሆነውስ #እንዴት ነው??..

▶️ የማርያም #ምላሽ #በእግዚአብሄር ፊት #ትሁትና #እውነተኛ እንደነበረ ያሳያል። ከቶውንም #ከመልአክ ጋር እንደምትነጋገርና #ከሰማይ ልዩ #ጸጋዎችን እንደምታገኝ አልጠበቀችም። #የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ #የሉቃስ ወንጌል #አንድምታው እንደሚለው <<ማርያም #የኢሳያስን #ትንቢት የሆነውን ኢሳ 7፥14 ስታነብ ያቺን #ሴት ምነው እኔ #በሆንኩ አላለችም። እንደውም ምነው #ከጊዜዋ ደርሼ #ወጥቼ #ወርጄ አገልግያት በማለት #ታስብ እንደነበር ይገልጻል[1]። እንዲህ አይነት #ሁኔታዎች እንዲፈጸምላት የሚያደርግ #ምንም የተለየ ነገር አልነበራትም። አንዳንድ የስነ መለኮት #አስተማሪዎችም እንደሚናገሩት <<ማርያም #ከሌሎች አይሁዳውያን #ሴቶችና #ልጃገረዶች #የተለየች ብትሆን ኖሮ <<መልካም እንግዲህ #ጊዜው #ደርሷል! እስከአሁንም #ስጠብቀው ቆይቻለሁ! ትል ነበር። ነገር ግን #በፍጹም አላለችም[2]!!! ሁሉ ነገር ለእሷ #አዲስና #አስደናቂ #ዱብእዳ ስለነበረ ግራ #ተጋብታለች#ፈርታለች#ደንግጣለችም <<ይህ እንዴት ያለ #ሰላምታ ነው?>> በማለትም አስባለች። #ቅዱስ ገብርኤልም #አትፍሪ በማለት #የማረጋጋት ተግባር ሲያከናውን ይታያል።

▶️ ከዚያም #መልአኩ ገብርኤል #መልካሙን #ዜና ያበሰራት #ኢየሱስን (አዳኝ፣ መድኃኒት) ማቲ 1፥21 ብላ የምትሰይመውን #መሲህ እንደምትወልድ ነበር። በመቀጠልም #መልአኩ የኢየሱስን #አምላክነትና #ሰብአዊነት አስረግጦ በመንገር #የምትወልደው #ልጅ ታላቅ እንደሆነና እንደሚሆን እንጂ በእርሷ ታላቅነት ላይ አላተኮረም {ሉቃ 1፥31}።

▶️ የሚወለደው ህጻን(ኢየሱስ) #ንጉስ ሆኖ #የዳዊትን #ዙፋን በመውረስ #ለዘላለም በእስራኤል ላይ #ይነግሳል#እግዚአብሔር #ከዳዊት ጋር የገባውን #ቃል #ኪዳን (2ኛሳሙ 7) እና ለእስራኤል #ህዝብ የሰጠውን #የመንግስት የተስፋ #ቃሎች #እያመለከተ ነበር {ኢሳ 9፤1-7፣ 11-12 ፣ 61 ፣ 66፣ ኤር 33}።
▶️ ዘካርያስ #በቤተ መቅደስ #ምድብ ተራ (ሰሞን) ደርሶት #በእግዚአብሄር ፊት #በክህነት #በቤተ መቅደስ ውስጥ በሚያገለግልበት ጊዜ #ዩሐንስም እንደሚወለድ #መልአክ ተገልጦ ሲያነጋግረው #የአሮንን #ቡራኬ እንዲያሰማቸው ህዝቡ #በውጭ #በአደባባይ ይጠባበቅ ነበር እንጂ ከእነርሱ ጋር #አንድም #ሰው እንዳልነበረ #መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል {ሉቃ 1፥21፣ ዘሁ 6፤ 24-26}። እንዲሁም #መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል #በ6ኛው ወር #ማርያም ወደ ነበረችበት #በገሊላ አውራጃ ወደነበረችው #ናዝሬት #ከተማ ቤቷ ድረስ ሄዶ #አበሰራት እንጂ #በቤተ መቅደስ እንዳልነበረ #ቃሉ ይናገራል {ሉቃ 1፥26}።

▶️ ናዝሬት #ከተማ ደግሞ #ከገሊላ ባህር በስተ #ምዕራብ 25 ኪ.ሜ ርቃ #በዛብሎን ነገድ ድርሻ ውስጥ #የተመሰረተች የሃገሩ #ጠረፍ ከተማና #ዝቅተኛ #ግምት ይሰጣት የነበረች #ከተማ ስትሆን {ዩሐ 1፥47} #ቤተመቅደሱ የነበረው ደግሞ #በኢየሩሳሌም ሆኖ #በይሁዳ አውራጃ #በዮርዳኖስ ወንዝ #ወደጨው #ባህር ከሚገባበት #በምዕራብ 30 ኪ.ሜ #ከታላቁ #የሜድትራኒያን #ባህር 50 ኪ.ሜ ርቃ #በተራራ ላይ የምትገኝ #ከተማ ነች። በመሆኑም #ገብርኤል ሲያበስራት #ማርያም የነበረችው #በኢየሩሳሌም #ቤተ መቅደስ ሳይሆን #በቤቷ በተናቀችው #ከተማ #በናዝሬት ውስጥ ነበረች። ጌታ #ኢየሱስም በዚህ #ስፍራ #አደገ {ሉቃ 2፤ 39-40 ፣ 51}።

▶️ ከናዝሬት እስከ #ቤተልሔም #በእግር ቢያንስ 3 ቀን ያክል ያስኬዳል። #ከቤተልሔም እስከ #ኢየሩሳሌም ድረስ ያለው #ርቀት ደግሞ 8 ኪ.ሜ ነው። ስለዚህ #ማርያምና #ዮሴፍ ለቆጠራ ወደ #ኢየሩሳሌም በመሄድ እስከ #ቤተልሔም 3 ቀናት ያክል ተጉዘው #በመንገድ ላይ #ማርያም #የመውለጃዋ ሰዓት ቢደርስባት በዚያው በአንድ #ከብቶች #በረት ውስጥ #ክርስቶስን ወልዳዋለች። በተወለደ #በ8 ቀኑ እንደ #መልአኩ አጠራር <ኢየሱስ> ተብሎ ሲጠራ #ለ40 ቀናት ያክል #የመንጻት #ወራታቸውን በዚያው ፈጽመው {ዘሌ 12፤ 2-8፣ ዘሌ 5፥11} #ከ8.ኪሜ ጉዞ ቡኋላ ወደ #ኢየሩሳሌም #ቤተመቅደስ አደባባይ ደርሰዋል። #በጌታ #ህግ የታዘዘውን ሁሉ ከፈጸሙ ቡኋላ #በገሊላ አውራጃ ወዳለች #ናዝሬት #ከተማቸው ተመልሰዋል {ሉቃ 2፥39}[2]።

▶️ በገሊላ #አውራጃ #በቃና #መንደር #ሠርግ በነበረበት ሰዓት #ማርያም ለሰርግ ቤቱ #ዘመድ እንደመሆኗ መጠን #በአስተናጋጅነት ስታገለግልና #የጓዳው #ወይን በማለቁ #ኢየሱስን ጠርታ የመጀመርያውን #ተአምር ሲያደርግ የምናነበው #ዘመዶቻቸው #ለናዝሬት ከተማ በቅርብ እንደነበሩ ያሳያል። #ኢየሱስም የራሱና የቤተሰቦቹ #አገር #ናዝሬት መሆኑን ጠቅሷል {ሉቃ 4፤ 16-30}። #ናዝራዊ መባሉም ለዚሁ ነው {ማቴ 2፥23፣ 1፥47}። #የይሁዳ ሰዎች #በገሊላ #አውራጃ የሚኖሩ አይሁዶች #ከአህዛብ ጋር ካላቸው #ግንኙነት ሳቢያ #የአይሁድ #ህግ የሚጠበቅባቸውን እንደማያሟሉ በመግለጽ በተለይም #የናዝሬት ነዋሪዎችን ይጠሏቸው ነበር {ማቴ 4፥15፣ ዩሐ 1፤ 45-46}። ይህም ሆኖ #ከማርያም ማንነት ሳይሆን #እግዚአብሔር #በጸጋው በዚህ በተናቀው #በገሊላው #ናዝሬት ትኖር የነበረችውን #ልጃገረድ #ተስፋ የተሰጠው #የመሲሁ #እናት እንድትሆን መረጠ!።

▶️ ወደ ዋናው #ሃሳብ ስንመለስ #በኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ #ማርያም ትኖርበት ስለነበረችበት #ስፍራ #ሁኔታ በዋናነት 2 አመለካከት አለ።
አንደኛው #በናዝሬት #በዮሴፍ ቤት ነበረች የሚሉና ሌሎች ደግሞ #ከቤተ መቅደስ ዘንድ ነበረች የሚሉ ሲኖሩ ሁለቱን #አስታራቂ #ሃሳብ አለን ያሉ ደግሞ ሌላ 3ኛ ሃሳብ የሚያቀርቡ አሉ[3]። ሃሳባቸውም፦

<<አንዳንዶች #ከዮሴፍ ቤት አንዳንዶች #ከቤተ መቅደስ ይላሉ ግን #አይጣላም ሁሉም ተደርጓል #ከድናግለ እስራኤል ጋር #ውሃ ልትቀዳ ሄዳ #ውሃ #ቀድታ ስትመለስ #የተጠማ #ውሻ አገኘችና #በጫማዋ ቀድታ #አጠጣችው
<<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን የተቀነባበረ <የጸሎት> ክፍል #በኢየሱስ ክርስቶስ #አስተምህሮ #ወቅት ብቻ ሳይሆን ከእሱ ቡሀላም ለብዙ #ዘመናት አልነበረም። ምናልባትም ሌሎች እንደሚሉት #ማርያም ገና #ክርስቶስን ሳትወልድ የነበረ #የገብርኤል #ሰላምታ ነው ተብሎ እንዳይወሰድ እንኳን #መልአኩ መጥቶ ያደረገው #ውይይት እንጂ #ጸሎት አይደለም። #ክርስቶስም #ለደቀመዛሙርቱ #ጸሎት ባስተማረበት #ወቅት #የገብርኤልንም #ሰላምታ ጨምሩበት በማለት ባስተላለፈ ነበር፤ ያንን ደግሞ አላደረገውም [ማቴ 6፤ 1-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]። << #በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ....>> የሚለው #የጸሎት #አስተምህሮቱን #ድንግል ማርያምን በትክክል በሚያውቋት #በደቀመዛሙርቱ ፊት ምናልባትም #በአስተምሮው #ወቅት ብዙ ጊዜ በምትገኝዋም #በድንግል #ማርያምም በራሷ ፊትም ተናግሯል።

▶️ ስለሆነም የተቀነባበረው <<የማርያም የጸሎት>> ምዕራፍ #በክርስቶስ #ወቅት ያልነበረ ከዚያም ቡኋላ #ሐዋሪያቱ #በአገልግሎታቸውና #በጸሎታቸውም ወቅት የማያውቁትና #የጥንት #ቤተ ክርስቲያን #አባቶችም በልዩ ልዩ ምክንያት #ጉባኤ ሲያደርጉ ለምሳሌ፦ #በኒቂያ ጉባኤ #በ325 ዓ.ም 318 የሃይማኖት አባቶች በእነ #እስክንድሮስ አፈጉባዔነት በንጉስ #ቆስጠንጢኖስ ዘመን ተሰብስበው #አርዮስን <<ወልድ #ፍጡር ነው>> ያለበትን #የክህደት ትምህርት #ሲያወግዙና #የሃይማኖት መግለጫ ሲያወጡ #ኢየሱስን ከመውለዷ ውጭ #ስለማርያም ፈጽሞ #መሠረታዊ #ትምህርት እንኳ በወቅቱ እንዳልነበረ መረዳት ይችላል። እንዲሁም #በቁስጥንጥንያ #በ375 ዓ.ም 150 #የሃይማኖት #አባቶች #በጢሞቴዎስ ዘአልቦጥሪት በንጉሥ ዘየዓቢ #ቴዎደስዩስ ወቅት #መቅደንዩስ << #መንፈስ ቅዱስ #ሕጹጽ ወይም #ሀይል ብቻ>> ብሎ በተነሳ ጊዜ ተሰብስበው #አውግዘው ትምህርቱንና እርሱን ሲለዩ #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #የአስተምህሮ #መግለጫ ሲያወጡ ያኔም ቢሆን #ኢየሱስን #ከመውለዷ ውጪ #ስለማርያም ያስተላለፉት ምንም #አዲስ #ትምህርት የለም። #በኤፌሶን ሀገርም #በ435 ዓ.ም 200 #የሃይማኖት #አባቶች #በቄርሎስ አፈጉባዔነት በቴዎደስዩስ ዘይንእስ ንጉሥነት ጊዜ ንስጥሮስ << #ክርስቶስ #ሁለት #አካል #ሁለት #ባህሪይ ነው>> ብሎ ሲነሳ #እርሱንም #ትምህርቱንም #አውግዘው #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #አስተምህሮ በመግለጫ መልክ ሲያስቀምጡ ድንግል #ማርያም #ክርስቶስን እንደወለደች ብቻ እንጂ << #እመቤታችን>> ብለውም ሆነ << #ለምኝልን>> የሚል አስተምህሮ አያውቁም። #ጤናማ #አስተምህሮ አይደለምና።

▶️ ዛሬ ሁሉም #አብያተክርስቲያናት የሚቀበሉት #ሙሉ #የሃይማኖት #መግለጫቸው

<<ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን የተፈጠረ ሳይሆን የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምን ምንም የሆነ የለም በሰማይም ያለ በምድርም ያለ ስለእኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፈጽሞ ሰው ሆኖ በጴንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ ሞተ ተቀበረም በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና ሙታንንም ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም ጌታ ማህየዊ በሚሆን ከአብ በሰረጸ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋሪያት በሰበሰባት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሰረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።>> የሚል ነው።

ይህንንም መግለጫ #በ1530 ዓ.ም #ሉተራውያን << #የአውግስበርግ #መግለጫ>> በሚል አጸደቁ። እንዲሁም #በ1546 ዓ.ም #ካቶሊክ በድጋሜ << #የትሬንት #መግለጫ>> በማለት አጸደቀችው። #በ1571 ዓ.ም ደግሞ #የአንግሊካን #ቸርች መግለጫውን ተቀብላ አጸደቀችው። #በ1646 ዓ.ም #ፕሪስቢቴሪያን << #የዌስት #ሚኒስቴር #መግለጫ>> በሚል አጸደቀችው[1]።

▶️ ኦርቶዶክስ #ቤተክርስቲያን መግለጫውን በድጋሜ << #ጸሎተ #ሃይማኖት>> በማለት #በ1426-1460 ዓ.ም በኢትዮጵያ የነገሰው #አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ ሙሉውን ተቀበሉና ሌላ #በመጨመር << #ለማርያምና #ለእፀ መስቀሉ (ለመስቀሉ እንጨት) #ስግደት ይገባቸዋል>> በማለት እንዲሁም <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን <<ከአባታችን ሆይ>> #ቀጥሎ እንዲባል ብሎ #አዋጅ አወጣ። ከዚህም የተነሳ በርካታ #ካህናት << #አባቶቻችን ካስቀመጡት #ከሃይማኖት #መግለጫው ውጪ ተጨማሪውን #አንቀበልም>> በማለታቸው #በሰይፍ እንደቆራረጣቸውና እንዳሳደዳቸው #ገድለ #እስጢፋኖስ#ገድለ #አበው ወአኀው፣ #ገድለ #አባ አበከረዙል፣ #ገድለ #አባ ዕዝራ፣ #ገድለ #ደቂቀ እስጢፋኖስን ማንበብ #በቂ ነው።

▶️ ነገር ግን #በዘር #ቅብብሎሽ አማካኝነት የነበረው #የንግስና #ሥርአት ለዚህ <<አዳራሻውን ወደ ሳተው ጸሎት>> ሰፊ እድል አግኝቶ #ሰይፍ ያስፈራቸውና በክርስትናው #ትምህርት ብዙም #መሰረታዊ #እውቀት ያልነበራቸው #ህዝብና #ካህናት #የጸሎት #ምዕራፋቸው አድርገው ለቀጣዩ #ትውልድ በማስተላለፋቸው ይሀው አሁን የምናየውን #ከእግዚአብሄር #ቃል ውጪ የሆነ #ትውልድ ፈጥረውልናል። ዛሬ ዛሬ #በየጸሎቱ #መዛግብት ውስጥ እየተጨመረ ተጽፎ #ምዕመናን ሁሉ #በቀን ቢያንስ #አንድ ጊዜ እንዲደግመው በመደረጉ እንግዳው <<ጸሎት>> #የተለመደ ሆኖ ቀረ። እንዲያውም በዚህ #ዘመን አስቀድመን እንዳልነው <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል #ጥቅሶችን ያለቦታቸው እንደ #ስጋ #ዘንጥለውና #በጣጥሰው #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል የሚታገሉ ተነስተዋል። እኛ ግን <<የእግዚአብሔርን ቃል #ቀላቅለው #እንደሚሸቃቅጡት እንደ #ብዙዎቹ አይደለንምና፤ #በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ #ተላክን #በእግዚአብሔር ፊት #በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።>> [2ቆሮ 2፥17]

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን፤ አውግስበርግ ሃይማኖታዊ መግለጫ፤ በአማርኛ የተተረጎመ፤ አ.አ፥ 1993 ዓ.ም።
Forwarded from እውነት አርነት ያወጣል (ቴዎድሮስ)
ኢየሱስን በስንት ብር ብንቀይረው ያዋጣል?

ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚረዳው ወደ ኢየሱስ መጀመሪያ ለምን መጣህ? የሚለው ሲመለስ ነው፡፡ ወደኢየሱስ የመጣኸው በቀጥታ ገንዘብን ወይም በመጀመሪያ ዝናን ከዛም ገንዘብን አስልተህ ከሆነ አሁን ወደ ድርድሩ መግባት ይቻላል፡፡

ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የነበረው ይሁዳ ከአሥራ አንዱ ይልቅ ለሰይጣን የተመቸ ልብ ነበረው፡፡ ስለዚህም በጥቂት ሊያውም መልሶ ሊበትነው ለጨከነበት ብር ሲል ጌታውን አሳልፎ የሰጠ "ደቀ መዝሙር" ነበር፡፡ ከዛ በፊት ግን ኢየሱስን ብሰጣቹ ስንት ትሰጡኛላቹ? የሚል የዋጋ ድርድር ውስጥ ገብቷል፡፡ ምናልባትም አይ በእሱማ አያዋጣኝም ጨምሩልኝ ብሎም ይሆናል፡፡ የተከፈለው ገንዘብ ግን አልጠቀመውም፡፡ ወደተሸመቀቀ ገመድ መራው እንጂ፡፡

አሁንም ጌታቸውን ለገንዘብ ሲሉ የሚለውጡ "የተሻለ የከፈለ" በሜዳው የሚያጫውታቸው "የቀድሞ ደቀ መዛሙርት" ወይም የዘመናችን ይሁዳዎች ለሆዳቸውና ለልጃቸው የትምህርት ቤት ክፍያ አቅጣጫ የሚያስቀይራቸው ሰዎች አሉ፡፡

የዛሬዎቹ ከዘመኑ ጋር የዘመኑ በመሆናቸው እንደ ይሁዳ የገንዘብ ፍቅር ብቻ ሳይሆን የልብ ክፋትም አለባቸው፡፡ ስለዚህ ኢየሱስን በገንዘብ ለመለወጥ (ለመቀየር) የሚጠቅሱት ጥቅስ አላቸው፡፡ ነገራቸውን መንፈሳዊ ለማስመሰልና አሁንም ከኢየሱስ፡ጋር ነን፡ለማለት አቅፈው፡ሲስሙትና ሲያስመስሉ ታያቸዋለህ፡፡

የሚገርመው እነዚህ የዘመናችን ይሁዳዎች ሚዲያው የእነርሱ ናቸው፤ ድሮም የሰይጣን ልጆች ናቸውና ሰይጣን በክብር ከፍ ከፍ አድርጎ እድሉን አመቻችቶላቸዋል፡፡ እሱ በሰጣቸው እድልም የኢየሱስ፡ወዳጅ እንደሆኑ በማስመሰል የገንዘብ አምሮታቸውን ይወጣሉ፡፡

ወዳጄ ኢየሱስን የምትሸጥብት፣ ጌታህን፡የምትለውጥበት ምንም የሚመጥን፡ክፍያ፡አታገኝም፡፡ ምንም ቢከፈልህ አያዋጣም!!! የአባቴ ልጅ ስማኝ የተብለጨለጨ በለበሱ፣ ወዛቸው ባንጸባረቀ የዘመኑ አርዮሳውያን አጓጉል ሽንገላ አትታለል፡፡ እነርሱ ሆዳቸው አምላካቸው የተባሉቱ ናቸው፡፡ ድሮም ከእኛ ጋር የነበሩት ለሚላስ ለሚቀመስ እንጂ እውነቱን ተቀብለው አልነበረም፡፡ ይሄን ደግሞ ራሳቸው በሚዲያ የተናገሩት መሆኑን፡ማረጋገጥ ትችላለህ፡፡

ስለዚህ ወንድሜ ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል የሚለውን፡የቅዱሱን መጽሐፍ ምክር አትርሳ!!!

#ኢየሱስን_በምንም_እና_በምንም_አያዋጣም!!!


https://tttttt.me/tewoderosdemelash/914