✍✍
⚜ ሮሜ 8÷34
" #የሞተው÷ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው÷ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው÷ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡"
#ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ ማስተላልፍ የፈለገው ‹‹ #እንግዲህ #በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን #ኵነኔ የለባቸውም›› የሚለውን ነው (ቊጥር 1)፡፡ ሐዋርያው በመቀጠል ‹‹ #በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው #የሕይወት መንፈስ ሕግ #ከኀጢአትና #ከሞት ሕግ ዐርነት›› ያወጣን መሆኑን ያበሥርና (ቊጥር 2) እንደ #ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ #መንፈስ ፈቃድ መመላለስ እንደሚገባን ይመክራል፡፡ ምክንያቱንም ደግሞ ‹‹ስለ #ሥጋ ማሰብ #ሞት ነውና÷ ስለ #መንፈስ ማሰብ ግን #ሕይወትና #ሰላም ነው›› በሚል ያስቀምጣል (ቊጥር 6)፡፡ ስለዚህ እንደ #ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ #መንፈስ ፈቃድ መመላለስ እንደሚገባ ካሰፈረ በኋላ ‹‹ #አባ #አባት ብለን የምንጮኽበትን #የልጅነት #መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና #ለፍርሀት #የባርነትን #መንፈስ አልተቀበላችሁምና›› ይላል (ቊጥር 15)፡፡ በመቀጠል ልጆች ከሆንን ደግሞ ወራሾች ነን ይልና ‹‹ #ዐብረንም ደግሞ እንድንከበር ዐብረን #መከራ ብንቀበል #ከክርስቶስ ጋር አብረን #ወራሾች ነን›› የሚል ሐሳብ ያቀርባል፡፡ ነገር ግን #መከራው #ልንወርሰው ካለው ክብር ጋር ሲመዛዘን ‹‹ምንም እንዳይደለ አስባለሁ››፡፡ ይህ ግን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት በሙሉ በመሆኑ ‹‹ #የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች #መገለጥ›› በመቃተት በተስፋ እየተጠባበቀ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በመቃተት ላይ ያለው ግን #ፍጥረት ብቻ ሳይሆን እኛም ጭምር መሆናችንን ያስቀምጥና ‹‹ #እንዲሁም ደግሞ #መንፈስ #ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት #እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና÷ ነገር ግን #መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት #ይማልድልናል›› ይላል፡፡ ምክንያቱንም ‹‹ #ልብንም የሚመረምረው #የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል÷ እንደ #እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ #ቅዱሳን #ይማልዳልና›› በማለት ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ ቡኋላ ቀደም ሲል ያቀረበውን በዚህ ምድር የሚያገኘንን #መከራ መነሻ በማድረግ ‹‹ #እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ #አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ #ለበጎ #እንዲደረግ እናውቃለን›› በማለት ይጀምርና #እግዚአብሔር #አስቀድሞ እንደ #ወሰነን፣ እንደ #ጠራን፣ #እንዳጸደቀን እና #እንዳከበረን አስፍሮ ‹‹ #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን #ይቃወመናል?›› የሚል ጥያቄ ያነሣል፡፡ እንግዲህ ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው ‹‹ #እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? #የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው÷ #የሚኰንንስ ማን ነው?›› የሚለውን ጥያቄ በማንሣት #የኰናኙን ማንነት ለማሳየት ጥረት የሚያደርገው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት #ኰናኙ፤
▶️ "የሞተ"
(ሞቱ አንድ ጊዜ ብቻ የሆነ ወደፊት የማይደገም በመሆኑ በኃላፊ ጊዜ ነው የተቀመጠው)፣
▶️ "ከሙታንም የተነሣ"
(ትንሣኤውም ቢሆን ሞትን ድል አድርጎ በተነሣበት ጊዜ ብቻ የሆነ አንድ ክንውን ነውና የተነሣ አለው)፣
▶️ "በእግዚአብሔር ቀኝ ያለ"
(በእግዚአብሔር ቀኝ መሆኑ ስለ ሰው ልጆች ሊታይ ነው(ዕብ 9፥24)፡፡ ይሄውም የምልጃ ሥራው አካል ነውና አሁንም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፡፡ ስለዚህ ነው ሐዋርያው በእግዚአብሔር ቀኝ ነበረ ሳይሆን አለ ያለው)፣
▶️ "ስለ እኛ የሚማልድ" (የክርስቶስ ምልጃ ምንም እንኳ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ በተሠራው ሥራ የተፈጸመ ስለ ሆነ የማይደጋገም ቢሆንም፣ ቀደም ሲል እንደ ተባለው አሁንም ስለ እኛ በመታየት ይቅርታን እንድናገኝ ያደርጋልና ሐዋርያው ስለ እኛ የሚማልድ በማለት አሁንም አማላጃችን መሆኑን ተናገረ።) በማለት ስለ እኛ #የሚማልድ መሆኑን በማሳየት በዚህ ምድር ላይ ያለውን #መከራ #ማሸነፍ የሚቻልበትን #ማበረታቻ ይሰጣል፡፡ ይህ ምንባብ #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #የሚከሳቸው #ማን ነው? ለሚለው #ጥያቄ #ማንም የሚል ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን ማንም #ሊከሳቸው የማይችልበት #ምክንያት ደግሞ ስለ #እነርሱ #ሞቶ የነበረ #ሞትን #ድል አድርጎ #የተነሣው እና #በአብ ቀኝ ሆኖ #የሚያማልድላቸው #ስላለ ነው በሚል ነው የሚያስቀምጠው፡፡ #ሐዋርያው ቀደም ሲል #በክርስቶስ #ኢየሱስ ላሉት #አሁን #ኵነኔ የለባቸውም ማለቱን ማስታወሱም #ጠቃሚ ነው (ቊጥር 1)።
@ ( #ጳውሎስ "ስለ እኛ የሚማልደው" በማለት እርሱም #በክርስቶስ ኢየሱስ #የምልጃ ስራ ተጠቃሚ መሆኑን ይናገራል። አንዳንዶች #ሐዋሪያው #ጳውሎስን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን #በምልጃ ስራ ውስጥ አሰልፈው #የክርስቶስን የምልጃ ስራ ፊት ለፊት በመቃወም ላይ ናቸው። #ሐዋሪያው በዚህ ክፍል ላይ እርሱ #አማላጅ ስለመሆኑ ሳይሆን #ስለ ኢየሱስ #አማላጅነት እና እርሱም #በኢየሱስ #ምልጃ ተጠቃሚ ስለ መሆኑ ነው የሚያስተምረው። #መጽሀፉ እንደሚለው ደግሞ #ኢየሱስ የእኛ ብቻ ሳይሆን #የቅዱስ ጳውሎስም #አማላጅ ነው። ስለ ሌሎች #ያማልዳል የሚባለው #ጳውሎስ #በክርስቶስ ምልጃ ተጠቃሚ እንደሆነ የገለጸውን መመልከት ሁላችንም #አማላጅ #እርሱ ብቻ ወደ ሆነው ወደ #ክርስቶስ እንድንጠጋ ያበረታታል።)
#በመቀጠልም ስለ እኛ #ከሞተው፣ #ሞትን ድል አድርጎ #ከተነሣው፣ #በእግዚአብሔር ቀኝ ካለው እና #ስለ እኛ #ከሚያማልደው ‹‹ #ከክርስቶስ #ፍቅር ማን ይለየናል? #መከራ÷ ወይስ #ጭንቀት÷ ወይስ #ስደት÷ ወይስ #ራብ÷ ወይስ #ራቁትነት÷ ወይስ #ፍርሀት÷ ወይስ #ሰይፍ ነውን?›› ሲል ይጠይቃል፡፡ በእርግጥም ከዚህ #ጌታ ምንም የሚለየን የለም፡፡ ‹‹ #ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ #እንገደላለን÷ #እንደሚታረዱ #በጎች ተቈጠርን ተብሎ›› ተጽፏልና፡፡ ‹‹በዚህ ሁሉ ግን #በወደደን [በአማላጃችን] #በእርሱ #ከአሸናፊዎች እንበልጣለን፡፡ #ሞት ቢሆን÷ #ሕይወትም ቢሆን÷ #መላእክትም ቢሆኑ÷ #ግዛትም ቢሆን÷ #ያለውም ቢሆን÷ #የሚመጣውም ቢሆን÷ #ኀይላትም ቢሆኑ÷ #ከፍታም ቢሆን÷ #ዝቅታም ቢሆን÷ #ልዩ ፍጥረትም ቢሆን #በክርስቶስ ኢየሱስ #በጌታችን ካለ #ከእግዚአብሔር #ፍቅር ሊለየን #እንዳይችል ተረድቼአለሁ›› በማለት #ምዕራፉ ያበቃል፡፡ #በዚህ ምዕራፍ ውስጥ #አሁን #ኵነኔ #የለብንም በማለት የጀመረው #ሐዋርያው #ክርስቲያኖች ስለሚያጋጥማቸው ነገር #እየመከረና #እያበረታታ ሁሉን #በጽናት #ማሸነፍ እንዳለባቸው ሲናገር፣ ‹‹ #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው÷ #የሚኰንንስ ማን ነው?›› ለሚሉት #ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ‹‹ #ስለ እኛ የሚማልደው #ክርስቶስ #ኢየሱስ›› መሆኑን ነገረን፡፡ ለዚህስ ሳይሆን ይቀራል #በአንድምታው ላይ ‹‹ #እሱ #ቢያጸድቅ ማን #ይኰንነናል፡፡ #ኢየሱስ ክርስቶስ #ሞተ #ከሙታንም #ተለይቶ #ተነሣ፡፡ #በአብ #ዕሪና(እኩል፣ መተካከል) #ይኖራል ስለ እኛ #ይከራከራል፡፡ #መከራከርስ የለም #ስለ እኛ #በዕለተ #ዐርብ #ባደረገው #ተልእኮ ፍጹም #ዋጋችንን #የምናገኝ ስለ ሆነ›› እንደ ሆነ የሰፈረው????
📖/፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሀፍ ንባቡና ትርጓሜው (አ.አ፣ ግንቦት 1988) ገጽ 70።
📖/፤ መሐሪ ትርፌ (ሊቀ ሊቃውንት)፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሀፍ ንባቡ ከነትርጓሜው (አ.አ፤ ጥቅምት 23 1948) ገጽ 100።
#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/
ይቀጥላል..(ሮሜ 8፥34)
@gedlatnadersanat @teeod

📖፤ / ሱረቱ መርየም 19፤ 27-28
(2ተኛ እትም 1998 ዓ.ም)
*ሱራህ 19, አያህ 27*
فَأَتَتْ بِهِۦ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُۥ ۖ قَالُوا۟ يَٰمَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْـًۭٔا فَرِيًّۭا
በእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡
*ሱራህ 19, አያህ 28*
يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ ٱمْرَأَ سَوْءٍۢ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّۭا
«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡
❓ የክፍሉ የግርጌ ማብራሪያ ላይ ማሪያም #የሙሴ ወንድም #የአሮን #እህት እንደሆነች ይናገራል።
ይህ ደግሞ #ከክርስቶስ #ልደት በፊት 1500 #ዘመን ዘሎ #የአሮንን ዘመን #ከክርስቶስ እናት #ማርያም ጋር በምን #አይነት ሂሳብ እንዳጠጋጋው እንጃ??
▶️ "የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን" ደግሞ #ሁለት #ተቃራኒ ሀሳቦችን ታስቀምጣለች፦
1ኛ👉 <"የዮሴፍ የወንድም ልጅ ናት">
<<የእስራኤል ሽማግሎችና መምህራንም አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችን #የአባቷን #ወንድም #ዮሴፍን ወደ በአደባባይ . . . አደራ ያስጠበቅንህን #የወንድምህን #ልጅ #እጮኛህ #ማርያምን. . .[3]>>
✍ በመሰረቱ "የዮሴፍ የወንድም ልጅ ናት" የሚለው #መጽሐፍ ቅዱስ ዮሴፍ #የማርያም #እጮኛ እንጅ አጎት(የአባት ወንድም) መሆኑን አይናገርም።
ምናልባት #ወንድሙ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው አባቷ #ኢያቄም ይሆን?? ብለን እንዳንገምት እንኳን። #ኢያቄም ወንድም እንዳልነበረውና #ለእናቱም #ለአባቱም አንድ እንደሆነ በሌሎች #መጽሀፍቶቻቸው ላይ ተጽፏል[4]። <የወንድምህን ልጅ እጮኛህን> ማለት በምን ዓይነት ቋንቋ እንደሆነ እንጃ!!
2ኛ👉 <"ማርያም የሃናና የኢያቄም ልጅ ስትሆን አያቷም #ቅስራ ነው"> ትላለች።
✍ ማርያም " #የሃናና #የኢያቄም ልጅ" መሆኗን ለመጀመሪያ ጊዜ #ያለምንም #መረጃ የጠቀሰው " #በተአምረ #ማርያም" መጽሀፍ < #አጼ #ዘረያቆብ> ነው።/በ 1426-1460/ ዓ.ም።
በመቅድሙ ላይ "ስመ አቡሃ ኢያቄም ወስመ ወላዲታ ሐና -የአባቷም ስም ኢያቄም ነው የእናቷም ስም ሐና ነው" ብሏል[5]።
▶️ የ" #ዘውትር #ፀሎት" ድርሳኑም ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል።
ቡሀላ ግን ከእነዚህ #ኑፋቄ #ትምህርት ከገባባቸው #አዋልድ #መጽሀፍት በስተቀር
<•የሀናና የኢያቄም ልጅ•> ናት ብሎ ያመነ #የቤተክርስቲያን #አባት አንድም እንኳ እንዳልነበረ አንድ መጽሀፍ ሲገልጽ
<<እም ሐና ወኢያቄም ተወለድኪ - ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ>> የሚለው #የሃገራችን #ደራሲያን የሚናገሩት #ቃል ነው እንጅ #ከአገር ውጪ ያሉ #አቢያተ #ክርስቲያናት ጠቅሰውት አያውቁም።
<ሐና ኢያቄም> የሚል ቃል #በሃይማኖተ #አበው መጽሀፍ ላይ ድርሰታቸው የተሰበሰበላቸው #ከ55 በላይ የሆኑ #ሊቃውንቶች ይህንን #ቃል አልጠቀሱም። ከእነዚህም በተለይ #እነቅዱስ #ኤፍሬም፣ #እነዩሐንስ #አፈወርቅ አመሰገኗት የሚባሉት ላይ እንኳን እነዚህ ቃላቶች #አልተጠቀሱም ይላል[6]።

ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
📖፤ / ሱረቱ መርየም 19፤ 27-28 (2ተኛ እትም 1998 ዓ.ም) *ሱራህ 19, አያህ 27* فَأَتَتْ بِهِۦ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُۥ ۖ قَالُوا۟ يَٰمَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْـًۭٔا فَرِيًّۭا በእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡ *ሱራህ 19, አያህ 28* يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ…
▶️ ሌሎች #በኦርቶዶክስ ያሉ #መጽሀፍቶች ደግሞ የተለያዩ #የዘር ግንድ ቆጠራዎችን ይጠቅሳሉ።
" #ድርሳነ #ጽዮን" የተባለው መጽሀፍ #የማርያም የዘር ሃረግን ሲገልጽ👇
ሜሊኪ። "የሐና(የእናቷ)
/ \ |
ሴም ሌዊ። ኤሊ
| |
ሆናሲን። ሜሊኪን
| |
ቀለምዮስን። ማቴን
| |
ኢያቄምን። ሐና
\ /
ማ ር ያ ም ን
ወለዱ ይላል[7]።
▶️ የማቲዎስ ወንጌል እንድምታ ደግሞ ከዚህ የተለየ ይገልጻል።
አኪም
|
ኤልዩድ
|
አልዓዛር
|
ቅዕራ
|
ኢያቄም ይላል[8]።
እንግዲህ እነዚህ #መጽሀፍት ደግሞ #በማርያም #አባት ቢስማሙም #በአያቶቻቸው ግን ፈጽሞ #አይስማሙም።
▶️ የአንዳንድ ካቶሊካውያን አመለካከትም። << #ማርያም #ሰማያዊ #ፍጡር>> እንደሆነች ሲገልጹ ይህንንም ሀሳብ #የሰዓታት ጸሐፊና #የተአምረ #ማርያም ጸሐፊም በከፊል የሚቀበሉት ቢሆንም #ሃይማኖተ #አበው ግን በግልጽ ይህን ሃሳብ ያወግዘዋል። << እመቤታችን ከሰው የተለየች #ፍጥረት #ምድራዊት ያልሆነች ቀድሞ #በሰማይ #የነበረች #ሃይል(ፍጡር) ናት የሚል ቢኖር #ውግዝ ይሁን። በቅድስት መጽሀፍት እንደተጻፈው #ቅድስት ድንግል ማርያም #ከዳዊት፣ #ከይሁዳ #ከአብርሃም ዘር እንደሆነች #በእውነት የሚያምን ግን #ከግዝት የተፈታ ይሁን>> ይላል[9]።
▶️ ማርያም ዘመዷ #ኤልሳቤጥ፣ እጮኛዋም #ዮሴፍ የነበረ ሴት እንደሆነች ሃገሯም #ናዝሬት #ገሊላ ሆኖ #ከዳዊት #ዘር እንደነበረች #መጽሀፍቅዱስ እየተናገረ #ሰማያዊ #ፍጡር #ናት ማለት " ህዝቤ #እውቀት #ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል/ሆሴ 4-6/። እንደሚለው #የእውቀት #ማጣት ይመስላል።
መጽሀፍቅዱስ የማርያም #አባት #ኢያቄም ሳይሆን < #ኤሊ> የተባለ #ሰው እንደነበር የሚገልጸው ፍንጭ አለ።
(በሉቃስ 3፥23)
ደግሞ #የማርያም #ገድሎች እንደሚሉት #ለእናት #ለአባቷ #አንዲት #ልጅ ሳትሆን #እህትም እንዳላት #መጽሀፍቅዱስ ይናገራል። 👇
<< ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ #የእናቱም #እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።>> {ዮሐ19፥25}።
<<ለዮሴፍ አባቱም #የማታን ልጅ #የያዕቆብ ልጅ (የማታን የልጅ ልጅ) ነው ብሎ #ማቲዎስ (በማቲ 1-16) #የዘር #ሐረጉን ሲቆጥር ወንጌላዊው #ሉቃስ ደግሞ #የማርያምን #የዘር ሃረግ ተከትሎ #በመቁጠር #የማርያም #አባቷ < #ኤሊ> እንደሆነ አስቀምጧል {ሉቃ 3-23}።
🔆 የዮሴፍ የዘር ሀረግ 🔆
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
1፤ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።
2፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ........
............................................
6፤ " እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።"...............................

15፤ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም #ማታንን ወለደ፤ ማታንም #ያዕቆብን ወለደ፤
16፤ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ #ዮሴፍን ወለደ።

🔆 የማርያም የዘር ሃረግ 🔆
(የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ- 3:)
...............
23፤ " ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር እንደመሰላቸው #የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ #የኤሊ ልጅ፥".......
.........................................
32፤ " የዳዊት ልጅ፥ የእሴይ ልጅ፥ የኢዮቤድ ልጅ፥ የቦዔዝ ልጅ፥ የሰልሞን ልጅ፥"....................
...........................................
36፤ የቃይንም ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜህ ልጅ፥
37፤ የማቱሳላ ልጅ፥ የሄኖክ ልጅ፥ የያሬድ ልጅ፥
38፤ የመላልኤል ልጅ፥ የቃይናን ልጅ፥ የሄኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ[10]።
▶️ የማቲዎስ የዘር ሃረግ ገለጻ
" #ከአብርሃም በመነሳት ወደ ፊት ወደ #ኢየሱስ ሲቀጥል " #የሉቃስ ግን #ከኢየሱስ ጀምሮ ወደ ኋላ ወደ #አዳም ይጓዛል።
#ማቲዎስ #የኢየሱስ ህጋዊ አሳዳጊ #አባት የነበረውን #የዮሴፍን #የዘር ሀረግ ሲሰጠን #ሉቃስ #የእናቱን #የማርያምን #የዘር #ሐረግ ይሰጠናል።
✅ በሉቃስ 3-23
"ኢየሱስ አገልግሎቱን በጀመረበት ወቅት ዕድሜው 30 ዓመት ያክል ነበረ ይህም ኢየሱስ #የዮሴፍ ልጅ መሰላቸው እንጂ #የኤሊ...(የማርያም ዘር ማንዘር) ልጅ ነበር" ተብሎ ተገልጾአል።
ምንም እንኳ #ማቴዎስ 4 #ሴቶችን በዘር ሀረግ ዝርዝር ቢጠቅስም/ማቲ 1-3 ፣ 5 ፣ 16/ #ሴቶች #በህጋዊ #የዘር #ሐረግ ውስጥ ስለማይገቡ #ማርያም ራሷ ሳትጠቀስ #ከአባቷ #ከኤሊ ጀምሮ እስከ #ዘር #ማንዘሮቿ #አዳም ድረስ ተገልጾአል[11]።
ይህም #ኤሊ #የዮሴፍ #አባት መሆኑን እንደ ሉቃስ አጻጻፍ #ከተወሰደ ዮሴፍ #የያዕቆብ ልጅ እንደሆነ #ማቴዎስም በግልጽ #አስቀምጧልና #ዮሴፍ #የኤሊም #የያዕቆብም ልጅ ወይም #የሁለቱ #ውህድ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም 1 ሰው 2 #አባት የለውምና።
ይህ ከሆነ ደግሞ #በአዋልድ #መጽሀፍት
<< ጰጥሪቃና ቴክታ የማርያም ስምንተኛ ቅድመ አያት ዝርያዎች፤ ነጭ ጥጃ ከማህጸን ስትወጣ ያች ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲህ እያለ እስከ 7ኛ ትውልድ ድረስ 7ኛይቱም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃም ፀሐይን ስትወልድ አይቻለሁ ብትል ቴክታ ህልም ፈችዎችን ጠርቶ ጨረቃይቱ ማርያም ናት ፅሐይ ግን አልተገለጠልኝም ቢላቸውና ቴክታ ሄኤሜን፤ ሄሜን ዴርዴም ፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ #ሃናን፤ #ሃናም #ማርያምን ወለደች፡ #ሃና በባሏ #በኢያቄም እጅ በትር እንደተያዘች ያች በትር አብባና አፍርታ እንዳየቻት #ኢያቄምም #በሀና እጅ ከፍሬው ሁሉ የሚመስለው የሌላ የሚጣፍጥ መልካም ፍሬ ተይዛ እንዳየች እርሷም ልጃቸው #ማርያም እንደነበረች የሚገልጸው አፈ ታሪክ #ከቁርዓን ተኮርጆ #በነገረ #ማርያም የተጻፈ #ተረት ሆኖ #ይቀራል ማለት ነው[12]።>>
ስለዚህም እንዲህ የሚያደርጉትን #ከተጻፈው #አትለፍ የሚለውን #መመሪያ #እንዲያነቡና #እንዲተገብሩ እናሳስባለን።
✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
"ማጣቀሻዎች - References"
____________
[1] 📚፤ ንቡር ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ፤ <ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት> (3ተኛ መጽሀፍ፥ ቼምበር ማተሚያ ቤት አ.አ፤ *ገጽ 264-267፤ 1998 ዓም።
📚፤ አማረ አፈለ ብሻው፤
<ኢትዮጽያ የሰው ዘር የተገኘባት የእምነትና የስልጣኔ ምንጭ ናት>
*ገጽ 116-122፥ አ.አ ጥር 1996 ዓ.ም
📚፤ አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ <ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው የተዋህዶ አንበሣም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው> (2ተኛ እትም ግንቦት 2001 ዓ.ም)
[2] 📚፤ በርሰ ሊቃነጳጳሳት ዩሐንስ ዳግማዊ ይፋ ካደረጉት ከዋናው የላቲን መጽሀፍ የተተረጎመ <የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ> *ገጽ 145፥ 1997 ዓ.ም።
[3] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ተአምረ ኢየሱስ፤ ምዕራፍ 3(፫)፤ 10(፲) ፤ *ገጽ 16(፲፮)፥ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1994 ዓ.ም።
[4] 📚፤ ድርሳነ ኪዳን ለማርያም ሳልስ፤ *ገጽ 48 1978 ዓ.ም።
[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም፤ የዘውትር መቅድም (*ገጽ 4(፬)፤ 16(፲፮) 1989 ዓ.ም።
[6] 📚፤ ደቀመዝሙር መልአኩ ዘድሜጥሮስ። <ስንዴውን ለመስዋት እንክርዳዱን ለእሳት> አ.አ. ሰኔ 1998፤ *ገጽ 21።
[7] 📚፤ <ድርሳነ ጽዮን ዘሐሙስ> 44-13 *ገጽ 158። አ.አ. ኅዳር 1998 ዓ.ም።
[8] 📚፤ ወንጌል ቅዱስ፤ ዘማቲዎስ ወንጌል፤ ንባቡና ትርጓሜው በግእዝና በአማርኛ፤ 1፡ 16። *ገጽ 52። 1997 ዓ.ም።
[9] 📚፤ ሃይማኖተ አበው፤ ቃል ግዝት ኤጲስቆጶስ፤ ክፍል 6 ፤ *ገጽ 577 1986 ዓ.ም።
[10] 📚፤ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ፤ <ለጌታ የተገዛህ ሁን> ፧ የማቴዎስ ወንጌል; ትርጉም ግርማዌ፤ *ገጽ 9፤ S.A.M፥ ኤስ ኤይ ኤም ማተሚያ ቤት አ.አ፤ 1995 ዓ.ም
[11] 📚፤ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ፤ <ሩህሩህ ሁን፥ የሉቃስ ወንጌል ትርጉም ፤ *ገጽ 31-32፤ S.A.M፥ ኤስ ኤይ ኤም ማተሚያ ቤት አ.አ፤ 1996 ዓ.ም
📚፤ ቄስ ኮሊን ማንሰል፤ <ትምህርተ እግዚአብሔር> ፩ኛ መጽሐፍ፤ *ገጽ 80፥ ንግድ ማተሚያ ድርጅት አ.አ፥ 1995።
[12] 📚፤ ተአምረ ማርያም 2፤ 8-9 3ተኛ እትም *ገጽ 17፥ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት። አ.አ 1989 ዓ.ም
📚፤ ያዕቆብ ሰንደቁ <እናታችን ጽዮን> 3ተኛ እትም *ገጽ 7-12። አ.አ፥ 1997 ዓ.ም።
📚፤ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ 5፥38። *ገጽ 111። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ 1983 ዓ.ም።
📚፤ ቅዱስ ቁርአን ሱረቱ አል-ኢምራ 3፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።
(1.2▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat

▶️ ሰው #በእግዚአብሄር #መልክና #አምሳል ስለተፈጠረ #ከእግዚአብሄር ጋር ለመገናኘት ሲፈልግ #መገናኛ መንገዱ #ጸሎት ነው። #ጸሎት #ከእግዚአብሄር ጋር ያለን የመገናኛ #ምልክትና የግንኙነታችን #ማጽኛ ነው። #ጸሎት #ህብረትን፣ #ምስጋናን፣ #ስግደትን፣ #ንስሀን፣ #ልመናን፣ #ምልጃን ሁሉ ያጠቃልላል። ይህንንም #ሰዎች በራሳቸው #ቋንቋ፣ #ቦታና #ጊዜ ሊያከናውኑት ይችላሉ። ዋናው ነገር #የልብ #መሰበር ነው [ዩሀ 4፤ 20-24]።
▶️ የሁሉም ሰዎች #ጸሎት አድራሻው ሁሉን #ለእርሱ #በራሱ #ለራሱ ወደ ፈጠረው ወደ #እግዚአብሔር #ብቻ እንደሆነና ወደ እሱ #ብቻ ሊሆን እንደሚገባው #መጽሀፍ ቅዱስ ይመሰክራል [ኢዮ 38፥41 ፣ ሉቃ 12፥24]። ለዛ ነው ዳዊት <<ሥጋ ለባሽ ሁሉ ጸሎትን ወደ ምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል>> በማለት የተናገረው። [መዝ 65፥2 ]። ሌላ #ጸሎትን #መስማት የሚችል አካል የለም ማለት ነው[1]።
▶️ ጸሎት #ለክርስቲያኖች ሁሉ የተሰጠ #መለኮታዊ #ትእዛዝ ነው [1ተሰ 5፥17 ፣ ማር 14፥38]። አንዳንድ ጊዜ #እግዚአብሔር የሁሉም #አባት እንደመሆኑ መጠን ምንም እንኳን #መብታቸው ባይሆንም #መጋቤ #ዓለማት የሆነው ጌታ #በቸርነቱ #ለማያምኑና #ላልጸለዩም ሰዎችና ፍጥረታት ሁሉ #ይመግባቸዋል [ሐዋ 10፤ 1-6፣ ማቴ 6፥8]። ይሁን እንጂ አንድ #ሰው #ለመጸለይ ሲያስብ ግን መጀመሪያ #እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም #ዋጋ #እንደሚሰጥ በእርግጠኝነት #ማመን ያስፈልገዋል [ዕብ 11፥6]። ከዚህ #አንጻር በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ያልሆኑ ነገር ግን ወደ #ማርያም የሆኑ #ጸሎቶችን #ክርስቲያን ሊቀበላቸው የማያስፈልጉበት #ዋና #ዋና #ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
"ማጣቀሻዎች - References"
____________
[1] ወደፊት <ጸሎት> በሚል ርእስ በሰፊው የምናየው ይሆናል።