ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ #ሴቶች ሰፊ ስፍራ #ከወንዶች #እኩል ተሰጥቷአቸው #እግዚአብሔር ሲጠቀምባቸው እናነባለን። በተለይ #በአዲስ ኪዳን #የእግዚአብሄር ቃል በግልጽ <<አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።>> {ገላ 3፥28} ይላል። እንዲሁም <<እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።>> {ሮሜ 2፥11}፣ <<በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤>> {ሮሜ 10፥12} ይላል።

▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ከወንዶች ባልተናነሰ አንዳንዴም #በሚበልጥ ሁኔታ #እግዚአብሔር በተለያየ መልኩ የተጠቀመባቸው #ከ87 የሚበልጡ #ሴቶች #ከነታሪካቸው ተጽፏል። ከእነዚህም ውስጥ #ልጅ ባለመውለዳቸው #ሲነቀፉ የነበሩት #እንደነሳራና #ሐና የመሳሰሉ #እግዚአብሔር #ቃል ኪዳን ያለውን #ልጅ በመስጠት #አስደናቂና #ታዋቂ #እናቶች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

▶️ የተጠቀሱት ሁሉም #ሴቶች #አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር #መሲሁን (ኢየሱስ ክርስቶስን) ማገልገላቸውና ለእርሱም #መንገድ ማዘጋጀታቸው ነው። ለምሳሌ፦


1፦ ሔዋን፦ #ከሴቲቱ #ዘር የሚመጣው (ኢየሱስ ክርስቶስ) #የእባቡን (የዲያብሎስንና የኃጢአትን) #ራስ #እንደሚቀጠቅጥ የተናገረላትና ይህንንም #ትንቢት በመጠበቅ ለዚህ #ዘር #ሐረግ በመጀመሪያ #አቤልን ከዚያም #ሴትን የወለደች።

2፦ ሩት፦ #ከሞዓባውያን ወገን የነበረች #በእምነት #ከወገኖቿ ተለይታ #ከእግዚአብሄር ህዝብ ጋር በመቀላቀል #እስራኤላዊውን #ቦኤዝን አግብታ #የእሴይን አባት #እዮቤድን በመውለድ ወደ #ክርስቶስ #የዘር #ግንድ ውስጥ ገብታለች።

3፦ አስቴር፦ #ዝርያው እንዲጠፋ የተፈረደበት #የአይሁድ #ህዝብ ወደ #ንጉሡ #በድፍረት በመግባት #ህዝቤን #በመሻቴ #ህይወቴም #በልመናየ ይሰጠኝ በማለት #በህዝቧ ላይ #የታወጀውን #የሞት #ፍርድ በመቀልበስ #ከአይሁድ ወገን ሊመጣ ያለውን #የኢየሱስ ክርስቶስን #ዘር በመጠበቅ የበኩሏን #አስተዋጽኦ አድርጋለች።

▶️ እነ #አቢግያ#ኢያኤል#ኤልሳቤጥ#ቤርሳቤህ#ራሔል#ሊዲያ#ፌበን#ሰሎሜ፣ . . .ወዘተ ሁሉም #እግዚአብሔር የሰጣቸውን #ተግባር ሁሉ #በድል ያከናወኑ አንቱ የሚባሉ #ሴቶች ናቸው።

▶️ ጌታ ኢየሱስ #በአገልግሎቱ #ወቅት #ከፍተኛ #እገዛ ሲያደርጉ የነበሩ በዚያ #አስፈሪ #ሰዓት በሆነው #በስቀለቱም ወቅት #ከመስቀሉ #ግርጌ ስር በስፋት #ሃዘናቸውን የገለጹ #በመቃብሩም ሄደው እንደተናገረው #መነሳቱን #ከቅዱሳን #መላእክት ሰምተው #ለህዝቡ ሁሉ በመጀመሪያ #ትንሳኤውን ያወጁና የእርሱን #መሞትና #መነሳት ... ወዘተ የሚያበስረውን #ወንጌል ይዘው ወጥተው #የግል #ቤታቸውን እንኳ #የወንጌል አደባባይና #ቤተክርስቲያን አድርገው #የእግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምሩ የነበሩ #ሴቶች ነበሩ።

▶️ ይህን #ማንሳታችን ያለ ምክንያት ሳይሆን <<ማርያም #ከሴቶች ሁሉ እንዲያውም #ከፍጡራን ሁሉ የበላይ የሆነች #ፍጡር>> የሚል #የተዛባና #መጽሀፍቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምህሮ ስላለ ነው። ለዚህም #ትምህርት መነሻው #በሉቃስ 1፥28 እና 1፥42 <<አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ>> ተብሎ የተገለጸው #ቃል ሲሆን <<ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ማርያምን ብሩክት አንቲ እምአንስት - አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተለየሽ ሲል ከሴቶች ሁሉ የተለየች መሆኗን በምስጋና ቃል ገልጦ ተናግሯል፤ የዚህን መልአክ ቃል በመደገፍ በማጽናትም ኤልሳቤጥ አንቺ ከሴቶች የተባረክሽ ነሽ ብላ ጮሀና አሰምታ ተናግራለች። ይህም ቃል ቅድስት ማርያምን በነፍስ በሥጋ ቅድስት መሆኗን መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን (ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ) መሆኗን ያጠቃልላል>> ብለው የተረጎሙት ስላሉ ነው[1]። በመሰረቱ ይህ #ትርጉም ሳይሆን #የመጻሐፉን ግልጽ #ቃል በመቀየርና ወደሚፈልጉት የማርያም #አምልኮ በማዞር የተቀመጠ #አስተምህሮ ነው።

▶️ ማርያምን <<ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች>> የሚለውን ቃል #ለመጀመሪያ ጊዜ የገለጸው #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረው #የደቡብ ወሎ ቦረናው #ሰው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ነው[2]።

▶️ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው #ምክንያታቸው ከላይ የተገለጸው #የቅዱስ ገብርኤልና #የኤልሳቤጥ #ንግግር ሲሆን ሌላው እንደ #ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ #ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን #መውለዷ ነው።

▶️ ከዚህ የተነሳ #ከእግዚአብሄር #ምስጋና #ቀጥሎና #አያይዞ #ማርያምን #ማመስገን እንደሚገባ #ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቡኋላ #የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን መጠቀም ጀምራለች። ለምሳሌ፦

〽️ 1፦ <አቡነ ዘበሰማያት(አባታችን ሆይ)> ከሚለው #ጸሎት ቀጥሎ <እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ.... ሰላም እንልሻለን> ማለትን

〽️ 2፦ <ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ (ምስጋና ይሁን ለአብ፣ ምስጋና ለወልድ፣ ምስጋና ለመንፈስቅዱስ ይገባል)" ከሚለው #ቀጥሎ <ስብሐት #ለእግዝትነ #ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ (አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይሁን)> ማለትን

〽️ 3፦ <ለልዑል እግዚአብሔር ፍጹም #ምስጋና ይገባል> ይባልና ቀጥሎ <ለወለደችው ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይገባል> ማለትን

〽️ 4፦ <የእግዚአብሄር ስሙ ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱ በየሰአቱ #ምስጋና ይገባል> ካለ ቡሀላም <እናታችን ማርያም ሆይ ሰላምታ ለአንቺ ይሁን እያልን #እንሰግድልሻለን #እንማልድሻለን> ይላል[3]።
▶️ በቅዱስ ገብርኤል #ሰላምታ #ሰላም እልሻለሁ የሚለውን #ቃል ራሱ ብናየው #የተሳሳተ #አባባልና #ያልተለመደ #ንግግር ነው። በሌላ አገላለጽ #ዩሐንስ #ለጋይዮስ #ሰላም ለአንተ ይሁን ባለው #ሰላምታ [3ኛ ዩሀ 1፥15] #ጋይዮስ ሆይ #በዩሐንስ ሰላምታ #ሰላም እልሃለው እንደማለት ነው። ነገሩን #ግልጽ ለማድረግ አቶ #አበበ አቶ #ከበደ ቤት ገብቶ <<አቶ #ከበደ በአቶ #አበበ #ሰላምታ #ሰላም #እልሀለው>> ብሎ #ሰላምታ እንደመስጠት ያክል ነው። ይህም በማንኛውም #ህብረተሰብና #ክፍለዘመን ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው #ከጤናማው #የሰላምታ ሥነ-ሥርዓት የወጣ #አባባል ነው።

▶️ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #መልዕክት አድርስ ተብሎ ወደ #ድንግል ማርያም በመምጣት ያደረገውን #ሰላምታ ተንተርሶ #አጼ #ዘረዓ #ያዕቆብ <<ይወድስዋ መላእክት - {መላዕክት ማርያምን ያመሰግኗታል}>> የሚል #ድርሰት ሲያዘጋጅ #የቦረናው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ደግሞ <<ተፈሥሒ ኦ ሙኃዘፍስሐ፤ የተድላና የደስታ መፍሰሻ ሆይ ደስ ይበልሽ መላእክት ብለዋታል[1]>> ብሏል። ነገር ግን ወደ #ማርያም ተልከው የመጡት #መላእክት ሳይሆኑ አንድ #መለአክ ነው። እርሱም ቅዱስ #ገብርኤል ሲሆን ንግግሩም #ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደተላከ ማሳወቅና #ክርስቶስን ያለ #ወንድ #ዘር #በድንግልና እንደምትወልድ የሚገልጽ እንጂ የተለየ #ምስጋና ለመስጠትና #የተድላና #የደስታ #መፍሰሻ እንደነበረች ያሳሰበበት #ክፍል አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን #መልአኩ እርሱ ከመምጣቱ በፊት #ማርያምን #የሚያመሰግንበትም የተለየ #የሰራችው አንዳች ነገር የለም። ያም ሆኖ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት #መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም በነበራቸው የአጭር ጊዜ የመረዳዳት #ውይይትን እንደመደበኛ #የግል #ጸሎታቸው አድርገው #መጽሀፍ አዘጋጅተው የሚደግሙ አሉ። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው መልአኩ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም #ውይይት አደረጉ እንጂ #አንዱ #ለአንዱ ያቀረቡት #ጸሎት የለም። ንግግራቸውም #የዘውትር #ጸሎት እንዲሆንላቸው ያሳሰቡት ነገርም የለም።

▶️ ጌታ #ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ #ሰማይ ሲያርግ #ድንግል #ማርያም ባለችበት #በማርቆስ #እናት ቤት ሐዋሪያት #በአንድነት #በጸሎት ሲተጉ አጠገባቸው ያለችውን #ማርያምን <<በገብርኤል #ሰላምታ ሰላም እንልሻለን #በነፍስሽም #በስጋሽም ድንግል ነሽ ከተወደደው #ልጅሽ #ይቅርታ #ለምኚልን #ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ>> አሏሏትም፤ #የጸሎት #ማዕከላቸውም አልነበረችም። እርሷም እነርሱም በአንድነት << #የሁሉንም #ልብ የምታውቅ #ጌታ ሆይ>> እያሉ #ጌታን እያከበሩ ወደ #ጌታ ሲጸልዩ ነበር። በድንገት #መንፈስ ቅዱስም ለእሷም ለእነሱም #እኩል ያለልዩነት ወረደባቸው። [ሐዋ 1፤ 12-14፣ ሐዋ 2፤ 1-4]።

በተለይ ደግሞ << #ይቅርታን #ለምኚልን>> የሚለው #ቃል ጠቅላላውን #የክርስቶስን #ይቅርታ #ለሰው ልጆች እንዴት እንደተሰጠ አለማወቅና #የክርስቶስን #የደኅንነት #መስዋዕት #ከንቱ የሚያደርግ ነው። በመሆኑም ይህን #ጸሎት ማቅረብ #የጸሎትን #ትርጉም አለማወቅ ብቻ ሳይሆን በግልጽ #የክርስቶስ #ተቃዋሚ መሆን ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ "መጽሐፈ ሰዓታት" ገጽ 29።