✍✍
⚜ ሮሜ 8÷34
" #የሞተው÷ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው÷ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው÷ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡"
#ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ ማስተላልፍ የፈለገው ‹‹ #እንግዲህ #በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን #ኵነኔ የለባቸውም›› የሚለውን ነው (ቊጥር 1)፡፡ ሐዋርያው በመቀጠል ‹‹ #በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው #የሕይወት መንፈስ ሕግ #ከኀጢአትና #ከሞት ሕግ ዐርነት›› ያወጣን መሆኑን ያበሥርና (ቊጥር 2) እንደ #ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ #መንፈስ ፈቃድ መመላለስ እንደሚገባን ይመክራል፡፡ ምክንያቱንም ደግሞ ‹‹ስለ #ሥጋ ማሰብ #ሞት ነውና÷ ስለ #መንፈስ ማሰብ ግን #ሕይወትና #ሰላም ነው›› በሚል ያስቀምጣል (ቊጥር 6)፡፡ ስለዚህ እንደ #ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ #መንፈስ ፈቃድ መመላለስ እንደሚገባ ካሰፈረ በኋላ ‹‹ #አባ #አባት ብለን የምንጮኽበትን #የልጅነት #መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና #ለፍርሀት #የባርነትን #መንፈስ አልተቀበላችሁምና›› ይላል (ቊጥር 15)፡፡ በመቀጠል ልጆች ከሆንን ደግሞ ወራሾች ነን ይልና ‹‹ #ዐብረንም ደግሞ እንድንከበር ዐብረን #መከራ ብንቀበል #ከክርስቶስ ጋር አብረን #ወራሾች ነን›› የሚል ሐሳብ ያቀርባል፡፡ ነገር ግን #መከራው #ልንወርሰው ካለው ክብር ጋር ሲመዛዘን ‹‹ምንም እንዳይደለ አስባለሁ››፡፡ ይህ ግን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት በሙሉ በመሆኑ ‹‹ #የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች #መገለጥ›› በመቃተት በተስፋ እየተጠባበቀ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በመቃተት ላይ ያለው ግን #ፍጥረት ብቻ ሳይሆን እኛም ጭምር መሆናችንን ያስቀምጥና ‹‹ #እንዲሁም ደግሞ #መንፈስ #ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት #እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና÷ ነገር ግን #መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት #ይማልድልናል›› ይላል፡፡ ምክንያቱንም ‹‹ #ልብንም የሚመረምረው #የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል÷ እንደ #እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ #ቅዱሳን #ይማልዳልና›› በማለት ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ ቡኋላ ቀደም ሲል ያቀረበውን በዚህ ምድር የሚያገኘንን #መከራ መነሻ በማድረግ ‹‹ #እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ #አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ #ለበጎ #እንዲደረግ እናውቃለን›› በማለት ይጀምርና #እግዚአብሔር #አስቀድሞ እንደ #ወሰነን፣ እንደ #ጠራን፣ #እንዳጸደቀን እና #እንዳከበረን አስፍሮ ‹‹ #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን #ይቃወመናል?›› የሚል ጥያቄ ያነሣል፡፡ እንግዲህ ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው ‹‹ #እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? #የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው÷ #የሚኰንንስ ማን ነው?›› የሚለውን ጥያቄ በማንሣት #የኰናኙን ማንነት ለማሳየት ጥረት የሚያደርገው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት #ኰናኙ፤
▶️ "የሞተ"
(ሞቱ አንድ ጊዜ ብቻ የሆነ ወደፊት የማይደገም በመሆኑ በኃላፊ ጊዜ ነው የተቀመጠው)፣
▶️ "ከሙታንም የተነሣ"
(ትንሣኤውም ቢሆን ሞትን ድል አድርጎ በተነሣበት ጊዜ ብቻ የሆነ አንድ ክንውን ነውና የተነሣ አለው)፣
▶️ "በእግዚአብሔር ቀኝ ያለ"
(በእግዚአብሔር ቀኝ መሆኑ ስለ ሰው ልጆች ሊታይ ነው(ዕብ 9፥24)፡፡ ይሄውም የምልጃ ሥራው አካል ነውና አሁንም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፡፡ ስለዚህ ነው ሐዋርያው በእግዚአብሔር ቀኝ ነበረ ሳይሆን አለ ያለው)፣
▶️ "ስለ እኛ የሚማልድ" (የክርስቶስ ምልጃ ምንም እንኳ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ በተሠራው ሥራ የተፈጸመ ስለ ሆነ የማይደጋገም ቢሆንም፣ ቀደም ሲል እንደ ተባለው አሁንም ስለ እኛ በመታየት ይቅርታን እንድናገኝ ያደርጋልና ሐዋርያው ስለ እኛ የሚማልድ በማለት አሁንም አማላጃችን መሆኑን ተናገረ።) በማለት ስለ እኛ #የሚማልድ መሆኑን በማሳየት በዚህ ምድር ላይ ያለውን #መከራ #ማሸነፍ የሚቻልበትን #ማበረታቻ ይሰጣል፡፡ ይህ ምንባብ #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን #የሚከሳቸው #ማን ነው? ለሚለው #ጥያቄ #ማንም የሚል ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን ማንም #ሊከሳቸው የማይችልበት #ምክንያት ደግሞ ስለ #እነርሱ #ሞቶ የነበረ #ሞትን #ድል አድርጎ #የተነሣው እና #በአብ ቀኝ ሆኖ #የሚያማልድላቸው #ስላለ ነው በሚል ነው የሚያስቀምጠው፡፡ #ሐዋርያው ቀደም ሲል #በክርስቶስ #ኢየሱስ ላሉት #አሁን #ኵነኔ የለባቸውም ማለቱን ማስታወሱም #ጠቃሚ ነው (ቊጥር 1)።
@ ( #ጳውሎስ "ስለ እኛ የሚማልደው" በማለት እርሱም #በክርስቶስ ኢየሱስ #የምልጃ ስራ ተጠቃሚ መሆኑን ይናገራል። አንዳንዶች #ሐዋሪያው #ጳውሎስን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን #በምልጃ ስራ ውስጥ አሰልፈው #የክርስቶስን የምልጃ ስራ ፊት ለፊት በመቃወም ላይ ናቸው። #ሐዋሪያው በዚህ ክፍል ላይ እርሱ #አማላጅ ስለመሆኑ ሳይሆን #ስለ ኢየሱስ #አማላጅነት እና እርሱም #በኢየሱስ #ምልጃ ተጠቃሚ ስለ መሆኑ ነው የሚያስተምረው። #መጽሀፉ እንደሚለው ደግሞ #ኢየሱስ የእኛ ብቻ ሳይሆን #የቅዱስ ጳውሎስም #አማላጅ ነው። ስለ ሌሎች #ያማልዳል የሚባለው #ጳውሎስ #በክርስቶስ ምልጃ ተጠቃሚ እንደሆነ የገለጸውን መመልከት ሁላችንም #አማላጅ #እርሱ ብቻ ወደ ሆነው ወደ #ክርስቶስ እንድንጠጋ ያበረታታል።)
#በመቀጠልም ስለ እኛ #ከሞተው፣ #ሞትን ድል አድርጎ #ከተነሣው፣ #በእግዚአብሔር ቀኝ ካለው እና #ስለ እኛ #ከሚያማልደው ‹‹ #ከክርስቶስ #ፍቅር ማን ይለየናል? #መከራ÷ ወይስ #ጭንቀት÷ ወይስ #ስደት÷ ወይስ #ራብ÷ ወይስ #ራቁትነት÷ ወይስ #ፍርሀት÷ ወይስ #ሰይፍ ነውን?›› ሲል ይጠይቃል፡፡ በእርግጥም ከዚህ #ጌታ ምንም የሚለየን የለም፡፡ ‹‹ #ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ #እንገደላለን÷ #እንደሚታረዱ #በጎች ተቈጠርን ተብሎ›› ተጽፏልና፡፡ ‹‹በዚህ ሁሉ ግን #በወደደን [በአማላጃችን] #በእርሱ #ከአሸናፊዎች እንበልጣለን፡፡ #ሞት ቢሆን÷ #ሕይወትም ቢሆን÷ #መላእክትም ቢሆኑ÷ #ግዛትም ቢሆን÷ #ያለውም ቢሆን÷ #የሚመጣውም ቢሆን÷ #ኀይላትም ቢሆኑ÷ #ከፍታም ቢሆን÷ #ዝቅታም ቢሆን÷ #ልዩ ፍጥረትም ቢሆን #በክርስቶስ ኢየሱስ #በጌታችን ካለ #ከእግዚአብሔር #ፍቅር ሊለየን #እንዳይችል ተረድቼአለሁ›› በማለት #ምዕራፉ ያበቃል፡፡ #በዚህ ምዕራፍ ውስጥ #አሁን #ኵነኔ #የለብንም በማለት የጀመረው #ሐዋርያው #ክርስቲያኖች ስለሚያጋጥማቸው ነገር #እየመከረና #እያበረታታ ሁሉን #በጽናት #ማሸነፍ እንዳለባቸው ሲናገር፣ ‹‹ #እግዚአብሔር #የመረጣቸውን ማን #ይከሳቸዋል? #የሚያጸድቅ #እግዚአብሔር ነው÷ #የሚኰንንስ ማን ነው?›› ለሚሉት #ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ‹‹ #ስለ እኛ የሚማልደው #ክርስቶስ #ኢየሱስ›› መሆኑን ነገረን፡፡ ለዚህስ ሳይሆን ይቀራል #በአንድምታው ላይ ‹‹ #እሱ #ቢያጸድቅ ማን #ይኰንነናል፡፡ #ኢየሱስ ክርስቶስ #ሞተ #ከሙታንም #ተለይቶ #ተነሣ፡፡ #በአብ #ዕሪና(እኩል፣ መተካከል) #ይኖራል ስለ እኛ #ይከራከራል፡፡ #መከራከርስ የለም #ስለ እኛ #በዕለተ #ዐርብ #ባደረገው #ተልእኮ ፍጹም #ዋጋችንን #የምናገኝ ስለ ሆነ›› እንደ ሆነ የሰፈረው????
📖/፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሀፍ ንባቡና ትርጓሜው (አ.አ፣ ግንቦት 1988) ገጽ 70።
📖/፤ መሐሪ ትርፌ (ሊቀ ሊቃውንት)፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሀፍ ንባቡ ከነትርጓሜው (አ.አ፤ ጥቅምት 23 1948) ገጽ 100።
#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/
ይቀጥላል..(ሮሜ 8፥34)
@gedlatnadersanat @teeod

ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
✍🔽✍▶️✍ *⃣ #ሮሜ 8፥34 እና #የመናፍቃኑ እርስ በእርስ አለመግባባት፦ ‹‹ #የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ #በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው›› (ሮሜ 8፡34)፡፡ ⚜ #በልማድ ለያዙት #የተሳሳተ ትምህርት አልመች ያለውና #በምንፍቅና #ጎዳና ላይ ሆነው #የአዳኛችንን #የኢየሱስ ክርስቶስ #የማዳን ግብር የሆነው #የምልጃ ሥራውን ሽምጥጥ አድርገው…
🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽
#ቀደም ሲል ከቀረበው "ምንባቡ #ይማልዳል ሳይሆን #ይፈርዳል ነው ማለት የነበረበት" በሚል ከተቀመጠው "ከመጋቤ ዐዲስ ሮዳስ ታደሰ" #ሐሳብ የተለየ #ሐሳብ ያላቸው "መምህር ደምሰው ዘውዴ" ደግሞ #ይማልዳል የሚለውን ይቀበሉና እንዲህ ይላሉ..
〽️ 2፦ ‹‹[መናፍቃን] ለማታለል ሲሉ #በግእዝ #ይማልዳል ብለው ጽፈውታል፤ ቃሉ #ግእዝ ነው #ግእዝና #ፍቺውን የማያውቅ #ሊታለል ይችላል፡፡ እነርሱ ግን ግእዝን ይቃወማሉ፤ #ለማወናበጃ ግን #ሊጠቀሙበት ይሞክራሉ፡፡ #ቅዱስ ዳዊት ግን የቃልህ ፍቺ ያበራል… እንዳለ #ፍቺው ይመሰክርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም
/ #ይማልዳል/ የሚለው #የግእዝ #ቃል ሲሆን #ፍቺው / #ይፈርዳል/ ነው፡፡ አማላጅ ቢሆን ኖሮ ቅዱስ ጳውሎስ በግልጽ ዐማርኛ ‹ #ያማልዳል› ብሎ በጻፈ ነበር፡፡… እስኪ ፍረዱኝ››
📖/፤ (ደምሰው ዘውዴ (መምህር)፣ " ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ" (2001) ገጽ 30)፡፡
▶️ ጸሀፊው መጽሐፍ ቅዱስ በዐማርኛ የተጻፈ መስሏቸው ይሆን? ወይስ ምናልባት #አብርሃም ኢትዮጵያዊ ነው፣ #መልከ #ጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው፣ #ማርያም ኢትዮጵያዊት ናት፣… እንደሚባለው #ሐዋርያው ቅዱስ #ጳውሎስም ኢትዮጵያዊ ነው እያለ ይሆን? እነርሱ እንደ መሰላቸው መጽሐፍ ቅዱስ #በዐማርኛ #ቋንቋ የተጻፈ አይደለም፡፡ ይህን ማንም የሚያውቀው እውነት ነው። #ብሉይ ኪዳን #በዕብራይስጥ #ዐዲስ ኪዳን ደግሞ #በግሪክ ቋንቋ የተጻፉ ሲሆን መላው #ዓለም (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ከእነዚህ #ቋንቋዎች ነው ወደ #የሀገራቸው #ቋንቋ የተረጐሙት፡፡ #የእኛ ሀገር ሰዎች (በተለይ ቤተ ክርስቲያናችን) ግን መጽሐፉን ወደ #ዐማርኛ ሲተረጉሙት #የግሪኩ የማይለውን #በማስፈር #እንግዳ ትምህርት ለማስተማር #ምክንያት ሆኑ እንጂ፡፡ ግሪኩስ የሚለው "ኢየሱስ ይማልዳል" ነው። ይህን ለማረጋገጥ ከፈለጉ #በ2000 ዓ.ም #የታተመውን 80 አሀዱ #በሮሜ 8፥34 የግርጌ ማስታወሻ ላይ "ግሪኩ <የሚማልደው> ይላል" የሚለውን ፎቶው ላይ ይመልከቱ።
ሌላው የኚህ ጸሀፊ አስጋራሚ ነገር ከላይ ከቀበረው የተለየ ሐሳብ ካላቸው "ከመጋቤ ዐዲስ ሮዳስ ታደሰ" ጋር #አለመስማማታቸው ነው፡፡ ቀደም ሲል ያየነው " #የሚማልደው ሳይሆን #የሚፈርደው ነው መሆን ያለበት #የሚማልደው የሚለው የተቀየረ ነው። #መናፍቃን የጨመሩት ነው ሲል" ከዚህ የተለየ ሀሳብ ያላቸው "መምህር ደምሰው ዘውዴ" ደግሞ " #የሚማልደው ነው መሆን ያለበት ምክንያቱም #የግእዝ ቃል ነውና፡፡ በግእዙ #የሚማልደው ማለት #የሚፈርደው ማለት ነው" በማለት ሀሳባቸውን ያስቀምጣሉ፡፡
▶️ በክፍል 2(የኢየሱስ አማላጅነት) ላይ #የምልጃ ትርጉም መቅረቡ ይታወሳል። በዛ #ትርጉም መሰረት #ይማልዳል የሚለው ቃል #ይፈርዳል ተብሎ ሊተረጎም የሚችልበት ምንም ዓይነት አግባብ እንደ ሌለ መመልከት ይቻላል። በመሆኑም ጸሀፊው የሌለ #ትርጉም በመስጠት ሰውን #ለማሳሳት እየሞከሩ ነው ከማለት ያለፈ ሊባል የሚችል ምንም ነገር የለም።
ይቀጥላል...(ሮሜ 8፥34)