ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
<<ምስጋና ለእናትና ልጁ???>>

መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ›› በማለት ምስጋና የሚገባው ለማን እንደሆነ በግልጽ አስፍሯል (2ኛ ሳሙ. 22፡4)፡፡ ይህንንም ደግሞ ‹‹ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ፤ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ›› (1ኛ ዜና. 16፡29) በሚልም ጭምር በተደጋጋሚ ይናገራል (መዝሙር 18፡3፤ 96፡8፡፡ ራእይ 4፡10)፡፡

#ማርያም ናት ተብሎ ምስጋና ለሚቀርብላት #አካል #ምስጋና ማቅረብ እንደሚኖርብኝ የሚያሳይ #የመጽሐፍ ቅዱስ #ምንባብ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ በተቻለኝ አቅም #መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባደረጉት ፍለጋ #ምስጋና ማቅረብ የሚገባኝ #ምስጋና ለሚገባው #ለእግዚአብሔር #ብቻ መሆኑን ነው የተማርኩት፡፡
አንዳንድ #መናፍቃን ምስጋና #በደረጃ አለ ይሉና ግና ምስጋና #ለእናትና #ልጁ በሚል አንዱን ምስጋና #ለሁለት #አካላት በማጋራት #ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድርጊት ውስጥ ገብተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች #ጣዖት #አምልኮ ውስጥ ያሉ ቢሆንም ይህን #ድርጊታቸውን ግን #መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስማሰል ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን ለዚህ #የተሳሳተ ድርጊታቸው የሚረዳቸው አንዳች እንኳ #ጥቅስ ማግኘት አልቻሉምና #የባሕርይና #የጸጋ በሚል #የቃላት #ጨዋታ ውስጥ ገብተው ሲዳክሩ ይታያሉ፡፡
በእኔ #እምነት #ምስጋና ለእናትና #ልጁ በሚል እየቀረበ ያለው #ሐሳብ #ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ብቻ ሳይሆን #ጣዖት አምልኮትን #በክርስትና ካባ ውስጥ ማቅረብ ነው፡፡ ተሳስተሀል የሚለኝ ሰው ካለ #መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ካለው ማቅረብ ይቻላል፡፡ ልብ ያድርጉ #ለማርያም #ምስጋና ማቅረብ እንዳለብኝ የሚናገር #የመጽሐፍ ቅዱስ #ምንባብ ያለው #ሰው ካለ ነው ያልኩት፡፡


ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል ራእይ 4፡10፡፡

@gedlatnadersanat
@gedlatnadersanat
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ለ"ማርያም" ለሚለው ስም የተሰጡ #ትርጉሞች #የቤተስክርስቲያን #አባቶችም ሆኑ #ወጣት #ሰባኪያንና #ህዝቡም በብዛት የሚያውቁት #የተለመደ #ትርጉም ነው። የሚገርመው ደሞ #የስሙ #ትርጉሞች ብዙ #ማርያም የተባሉ #ሴቶች እያሉ ማእከል ያደረገው ግን #የጌታችን #እናት #ድንግል #ማርያምን ብቻ ይመስላል። እነዚን #ትርጉሞች ይዘን ለሌሎች < #ማርያም> ለተባሉ #ሴቶች ትርጉሙን…
▶️ ከላይ እንዳየነው አንዳንዶች #የስሙን ሙሉ #ሐረግ ተከትለው ሌሎች ለሁለት ከፍለው #ለመተርጎም ከሞከሩት #ውጪ ሌሎች ደግሞ ከዚህ በተለየ መንገድ #ማርያም የሚለውን ስም #ለማብለጥ ወይም #ከፍ #ለማረግ ሲሉ #ማርያም ስለሚለው #ስም #ትርጉም #የአማርኛውን ወይም #የግእዙን ሆህያት ብቻ ተከትለው #ፊደል #በፊደል እየከፋፈሉ #በግእዝ ቋንቋ #በግጥም መልክ ይተረጉማሉ።👇👇

✳️👉 ማኅደረ መለኮት [የመለኮት ማደሪያ]።
✳️👉 ርግብየ ይቤላ [ንጉስ ሰለሞን ርግቤ ያላት፥ መኃ 6፥9]።
✳️👉 ያንቀዓዱ ኅቤኪ ኩሉ ፍጥረት [ሁሉም ፍጥረት ወደ አንቺ ያንጋጥጣል(ያቀናል)]።
✳️👉 ምስአል ወምስጋድ [ወምስትሥራየ ኃጢአት፣ የምንለምናት፣ የምንሰግድላት[4]]።

️ይህም #ትርጉም ከላይ እንዳልነው #የአማርኛ #ፊደላትን #በግዕዝና #በግጥም #የመተርጎም ሙከራ ሲሆን ይህም እንደሌሎቹ #ትርጎሞች ለሌሎች " #ማርያም" የሚለው #ስም ላላቸው የሚያገለግል አይመስልም። እንዲህ አይነቱ #ትርጉም የመስጠት አካሄድ ደግሞ #ከዓውደ #መሠረቱ ያስወጣል።

️በዚህ #ትርጉም መሠረት " #ማርያም ማለት #የመለኮት #ማደሪያ የሆነች፤ ንጉስ ሠሎሞን #በመኃልይ #መኃልይ መጽሐፉ #ርግቤ ያላት፤ ፍጥረት ሁሉ ወደ እርሷ #የሚያቀኑ#የሚሰግዱ#የሚለምኑ እና እርሷም #ለምላሹ #ኃጢአትን #የምታስተሰርይ ናት" ማለት በግልጽ #ማርያምን #ማምለክ ማለት ነው። #አምልኮ ከዚህ ውጪ #ካለ ንገሩን!!

▶️ መቼም #ሰይጣን በተለይም #በኢትዮጵያ #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ጊዜና ባለስልጣናት ገጥሞት በብዙ #ሠይፍ < #የማርያምን #ምልጃ> ትምህርት ወደ #ቤተክርስቲያን አስገብቶ #ማርያም ባትሰማቸውም ወደ እርሷ #የሚያንጋጥጡ#የሚሰግዱ#የሚለምኑ#ኃጢአታቸውን #የሚናዘዙ ይብዙ እንጅ #በመጽሀፍቅዱስ ታሪክ እንኳን #ወደእሷ ወደየትኛውም #ፍጡር #የጸለየ አናገኝም።

▶️ ደግሞ #ሰሎሞን #በመኃልየ #መኃልይ መጽሐፉ ሱናማይት{ሱናማጢሳዊት} የሆነችውን አንዲት ልጃገረድ #ውዴ#ርግቤ#መደምደሚያየ እያለ በፍቅር እንዴት #አሸንፎ ወደ ቤቱ እንዳመጣትና #ባሸበረቀ አልጋው ላይ አጋድሞ #ጡቶቿ እንዴት እንዳረኩት እርሷም በእርሱ እንዴት #እንደረካች የሚናገረውን #የፍቅር #ኃይልና ግለት #የተንጸባረቀበትን መጽሐፍ ወስዶና #በጥሶ <ሰሎሞን #ርግቤ #መደምደሚያዬ ያላት #ማርያምን ነው> ማለት ምናልባት መጽሐፉንና #ዓላማውን #ካለማንበብና #ካለማወቅ የመነጨ፣ አሳፋሪም ጭምር መሆኑን #የሱናማይቷ ሴት #ለፍቅር ስሜት የመጦዝ ባህሪ ታላቅ አድርገው ለሚገምቷት "ለቅድስት ድንግል ማርያም" ባልተስማማ ነበር።

▶️ መኃልየ #መኃልየ መጽሀፍም #የብሉይኪዳን ክፍል እንደመሆኑ #በሰለሞንና #በማርያም መካከል ያለውን "የዘመን ልዩነት" መገመት ራሱ አይከብድም። #ማርያም #በሰለሞን ዘመን ፈጽማ ያልነበረችውን፤ #ሰለሞን እንዴት በወቅቱ ከነበሩት < #ስልሳ ንግሥታት #ሰማኒያም ቁባቶች(ውሹሞች) #ቁጥር የሌላቸው ቆነጃጅቶች> ጋር #በውሽምነት መልኩ ሊቆጥራት ይችላል? {መኅልየ 6፥8}

▶️ ደግሞ < #የዓለምን #ኃጢአት ሊያስወግድ የተገለጠ #የእግዚአብሄር #በግ> {ዩሐ 1፥29 , ራዕ 5፤5-10} #ኃጢአትን #የማስተሰረይ ስልጣንም #የኢየሱስ #ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ እያወቅን {ማር 2፤10} ማርያምን "ወምስትሥራየ ኃጢአት" {ኃጢአትን የምታስተሰርይ} እንዴት ልንል እንችላለን?? #በኃጢአት ላይ የወጣውን #የእግዚአብሄርን #ቁጣ #ፍርዱን #ሊያቃልለው ወይም #ሊያስተወው የሚችልስ ጉልበተኛ ማነው? #ሙሴ እንኳ በምድር ህይወቱ #የእስራኤልን #ኃጢአት ተከራክሮ #ለማስቀረት ቢሞክርም #እግዚአብሔር #ፍርዱን መለወጥ ባለመቻሉ በርካቶች #ሞተዋል። {ዘዳ 32፤30-35}። #ኃጢአተኛው እራሱ #ካልተመለሰና #ንስሐ ካልገባ በቀር #እግዚአብሔር ኃጢአትን ይጠላል #ይቀጣልምም {ዩሐ 8-24}።
🔽 ለምሳሌ፦
<ቅድስት ድንግል ማርያም> ትኖርበት በነበረበት #ዘመን #እስራኤል #በሮም #መንግስት #ቀኝ ግዛት ስር ስትሆን #ሄሮድስ በወቅቱ #የሮም መሪ ከነበረው <ከአንቶኒ[11]> #ድጋፍ አግኝቶ #በሮም ምክር ቤት <የአይሁድ ንጉስ> በሚል ስያሜ #እስራኤልን #ሲገዛ እንደነበር ይታወቃል። በወቅቱ #አይሁዳውያንም ጠልተውትና #በሮም መንግስት ስር መሆናቸውን #በመቃወም እስራኤል ሁከት የሰፈነባት፣ ጭካኔ የሞላባት፣ የእርስ #በእርስ መጠላላት እንኳን ሳይቀር የነገሠበት ጊዜ ነበር። #ንጉሥ #ሄሮድስም እጅግ #ጨካኝ ከመሆኑ የተነሳ #መንግስቴን #ይወርሱኛል ብሎ የጠረጠራቸውን <2 ሚስቶቹንና 2 ወንድሞቹንም> ሳይቀር #የገደለበት ጊዜ ነበር። #በዚህም #ምክንያት <ከ27 ዓ.ዓ እስከ 14 ዓ.ም> #የሮም ንጉሥ የነበረው <አውግስጦስ[12]> <<የሄሮድስ ልጅ ከመሆን አሳማ መሆን ይሻላል!!>> በማለት በግልጽ ተናግሮ ነበር። #ሄሮድስ #ሰብአ ሰገል የተወለደውን መሲህ #ኢየሱስን <የአይሁድ ንጉስ> ብለው #በመጥራታቸው ነገሩን በጥንቃቄ #መርምሮ #ኢየሱስ #ክርስቶስን ለመግደል ባደረገው ጥረት #በቤተልሔም ውስጥ በወቅቱ የተወለዱትን በጣም #ብዙ #ህጻናት #ከእናቶታቻቸው ጉያ በመንጠቅ #በሰይፍ #ቆራርጦአቸዋል። በዚህም #ምክንያት <በነብዩ በኤርምያስ> የተተነብየው [ኤር 31፤15-16] <ድምጽ በራማ ተሰማ ልቅሶና ብዙ ዋይታ ራሔል ስለልጆቿ አለቀሰች የሉምና መጽናናትን ስለልጆቿ እንቢ አለች> የተባለው ተፈጸመ[13] {ማቲ 2፤16}።

️ማርያም በዘመኗ ሁሉ ብርቱ #የመከራ #ዘመን እንደምታሳልፍ ተነግሯት ነበር [ሉቃ 2፤35]። #ሄሮድስ #ህጻናትን ሲያስገድል በወቅቱ #በመልአኩ #ምሪት #ማርያምና #ዮሴፍ ህጻኑን (ኢየሱስ ክርስቶስን) ይዘው ወደ #ግብጽ ተሰደዋል። #ሄሮድስም እንደ #ሞተ ሰምተው ቢመለሱም #ልጇ #ኢየሱስ ክርስቶስ ባሳለፈው #ህይወትና #ሲሰቃይ ማየቷ #በእንጨት ላይም #ሲሰቅሉት #ማየቷ በአጠቃላይ እንደ ስሟ #ዘመኗ <መራራ ዘመን> ሆኖባታል።

️ በመሆኑም #ማርያም የተባሉ ሁሉ በተመሳሳይ #ሁኔታ #ዘመናቸው #መራር የሆነባቸው #ሰዎች ነበሩ እንጂ ከላይ አንዳንዶች እንደተረጎሙት የተለያየና፣ የተሳሳተ #ከእውነትም #የራቀ አልነበረም። እነዚህ መተርጉማን ስለማርያም የሰጡት ሃተታ #ቋንቋውንና #ታሪካዊ ዳራውን ያላገናዘበ፣ ከልዩ #ባእድ #አምልኮ መሻት #የመነጨና #ከእውነት የራቀ ብቻ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4፥6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
______________
[1] 📚፤ የኢትዮጵያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር "የመጽሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት" 8ተኛ እትም 1998 ዓ.ም *ገጽ 51።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ውዳሴ ማርያም ንባቡና ትርጓሜው፤ ዘሠሉስ *ገጽ 45። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1983 ዓ.ም።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ <ወንጌል ቅዱስ ንባቡና ትርጓሜው>፤ ዘሉቃስ ፧ *ገጽ 265፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ 1997 ዓ.ም።

📚፤ <ነገረ ማርያም> *ገጽ 28-31። ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ 1991 ዓ.ም።

📚፤ ብርሃኑ ጉበና "አምደ ሃይማኖት" *ገጽ 91። 1985 ዓ.ም።

📚፤ ሚልዮን በለጠ አሰፋ፤ <ቅዱሳት ስዕላት አመጣጥና ታሪክ ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር> ፤ *ገጽ 25-26። 1994 ዓ.ም።

[3] 📚፤ <ነገረ ማርያም>፤ *ገጽ 28-30፤ ተስፋ ገብረ ስላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1991 ዓ.ም።

[4] 📚፤ ሚሊዮን በለጠ አሰፋ
"ቅዱሳን ሥዕላት አመጣጥና ታሪክ ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር" *ገጽ 26። አለም ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ መጋቢት፥ 1994 ዓ.ም።

📚፤ <ነገረ ማርያም> ፤ *ገጽ 29፥ ተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1991 ዓ.ም።

[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም፤ መቅድም ቁ.4 *ገጽ 3፤ 3ተኛ ዕትም፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት አ.አ፤ 1989 ዓ.ም።

📚፤ <አርጋኖን> የእመቤታችን ምስጋና፤ ዘሰኑይ ምዕራፍ 6 ክፍል 4፤ ተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1996 ዓ.ም።

[6] 📚፤ ነገረ ማርያም፤ *ገጽ 34

[7] 📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ <ማርያም>፤ *ገጽ 610፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1948።

📚፤ Dr. Strong፥ "Exhaustive Concordance of the Bible" HEBREW AND CHALDEE DICTIONARY፥ pp 72 no.4805፣ 4813

〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Miriam_(name)

[8] 📚፤ የኢትዮጽያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር፤ <የመጽሀፍቅዱስ መዝገበ ቃላት>፤ 7ኛ እትም፤ <ዩሐንስ> *ገጽ 222። ንግድ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ 1996 ዓ.ም።

📚፤ Douglas & Tenney by International Bible Society Bible Dictionary፤ John pp. 532, 1987።

📚፤ Truesdale, Lyons, Eby clark, A Dictionary of the Bible & Christian Doctrine in every day English, United Bible Societies, 1978፥ pp 155-156.

[9] 📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ <ማርያም> የስም ትርጉም። *ገጽ 610፥ 1948 ዓ.ም።

[10] 📚፤ አለቃ ደስታ ተክለወልድ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡ <ማርያም>፤ *ገጽ 808 1ኛ ዕትም፥ 1945 ዓ.ም።

[11] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Mark_Antony

[12] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Augustus

[13] 📚፤ S I M፤ <የአዲስ ኪዳን ታሪካዊና ባህላዊ መሰረቶች> ፥ *ገጽ 22-23፤ ኤስ አይ ኤም ማተሚያ ቤት፥ አ.አ፤ 1993 ዓ.ም።

(2.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ #ሴቶች ሰፊ ስፍራ #ከወንዶች #እኩል ተሰጥቷአቸው #እግዚአብሔር ሲጠቀምባቸው እናነባለን። በተለይ #በአዲስ ኪዳን #የእግዚአብሄር ቃል በግልጽ <<አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።>> {ገላ 3፥28} ይላል። እንዲሁም <<እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።>> {ሮሜ 2፥11}፣ <<በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤>> {ሮሜ 10፥12} ይላል።

▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ከወንዶች ባልተናነሰ አንዳንዴም #በሚበልጥ ሁኔታ #እግዚአብሔር በተለያየ መልኩ የተጠቀመባቸው #ከ87 የሚበልጡ #ሴቶች #ከነታሪካቸው ተጽፏል። ከእነዚህም ውስጥ #ልጅ ባለመውለዳቸው #ሲነቀፉ የነበሩት #እንደነሳራና #ሐና የመሳሰሉ #እግዚአብሔር #ቃል ኪዳን ያለውን #ልጅ በመስጠት #አስደናቂና #ታዋቂ #እናቶች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

▶️ የተጠቀሱት ሁሉም #ሴቶች #አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር #መሲሁን (ኢየሱስ ክርስቶስን) ማገልገላቸውና ለእርሱም #መንገድ ማዘጋጀታቸው ነው። ለምሳሌ፦


1፦ ሔዋን፦ #ከሴቲቱ #ዘር የሚመጣው (ኢየሱስ ክርስቶስ) #የእባቡን (የዲያብሎስንና የኃጢአትን) #ራስ #እንደሚቀጠቅጥ የተናገረላትና ይህንንም #ትንቢት በመጠበቅ ለዚህ #ዘር #ሐረግ በመጀመሪያ #አቤልን ከዚያም #ሴትን የወለደች።

2፦ ሩት፦ #ከሞዓባውያን ወገን የነበረች #በእምነት #ከወገኖቿ ተለይታ #ከእግዚአብሄር ህዝብ ጋር በመቀላቀል #እስራኤላዊውን #ቦኤዝን አግብታ #የእሴይን አባት #እዮቤድን በመውለድ ወደ #ክርስቶስ #የዘር #ግንድ ውስጥ ገብታለች።

3፦ አስቴር፦ #ዝርያው እንዲጠፋ የተፈረደበት #የአይሁድ #ህዝብ ወደ #ንጉሡ #በድፍረት በመግባት #ህዝቤን #በመሻቴ #ህይወቴም #በልመናየ ይሰጠኝ በማለት #በህዝቧ ላይ #የታወጀውን #የሞት #ፍርድ በመቀልበስ #ከአይሁድ ወገን ሊመጣ ያለውን #የኢየሱስ ክርስቶስን #ዘር በመጠበቅ የበኩሏን #አስተዋጽኦ አድርጋለች።

▶️ እነ #አቢግያ#ኢያኤል#ኤልሳቤጥ#ቤርሳቤህ#ራሔል#ሊዲያ#ፌበን#ሰሎሜ፣ . . .ወዘተ ሁሉም #እግዚአብሔር የሰጣቸውን #ተግባር ሁሉ #በድል ያከናወኑ አንቱ የሚባሉ #ሴቶች ናቸው።

▶️ ጌታ ኢየሱስ #በአገልግሎቱ #ወቅት #ከፍተኛ #እገዛ ሲያደርጉ የነበሩ በዚያ #አስፈሪ #ሰዓት በሆነው #በስቀለቱም ወቅት #ከመስቀሉ #ግርጌ ስር በስፋት #ሃዘናቸውን የገለጹ #በመቃብሩም ሄደው እንደተናገረው #መነሳቱን #ከቅዱሳን #መላእክት ሰምተው #ለህዝቡ ሁሉ በመጀመሪያ #ትንሳኤውን ያወጁና የእርሱን #መሞትና #መነሳት ... ወዘተ የሚያበስረውን #ወንጌል ይዘው ወጥተው #የግል #ቤታቸውን እንኳ #የወንጌል አደባባይና #ቤተክርስቲያን አድርገው #የእግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምሩ የነበሩ #ሴቶች ነበሩ።

▶️ ይህን #ማንሳታችን ያለ ምክንያት ሳይሆን <<ማርያም #ከሴቶች ሁሉ እንዲያውም #ከፍጡራን ሁሉ የበላይ የሆነች #ፍጡር>> የሚል #የተዛባና #መጽሀፍቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምህሮ ስላለ ነው። ለዚህም #ትምህርት መነሻው #በሉቃስ 1፥28 እና 1፥42 <<አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ>> ተብሎ የተገለጸው #ቃል ሲሆን <<ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ማርያምን ብሩክት አንቲ እምአንስት - አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተለየሽ ሲል ከሴቶች ሁሉ የተለየች መሆኗን በምስጋና ቃል ገልጦ ተናግሯል፤ የዚህን መልአክ ቃል በመደገፍ በማጽናትም ኤልሳቤጥ አንቺ ከሴቶች የተባረክሽ ነሽ ብላ ጮሀና አሰምታ ተናግራለች። ይህም ቃል ቅድስት ማርያምን በነፍስ በሥጋ ቅድስት መሆኗን መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን (ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ) መሆኗን ያጠቃልላል>> ብለው የተረጎሙት ስላሉ ነው[1]። በመሰረቱ ይህ #ትርጉም ሳይሆን #የመጻሐፉን ግልጽ #ቃል በመቀየርና ወደሚፈልጉት የማርያም #አምልኮ በማዞር የተቀመጠ #አስተምህሮ ነው።

▶️ ማርያምን <<ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች>> የሚለውን ቃል #ለመጀመሪያ ጊዜ የገለጸው #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረው #የደቡብ ወሎ ቦረናው #ሰው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ነው[2]።

▶️ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው #ምክንያታቸው ከላይ የተገለጸው #የቅዱስ ገብርኤልና #የኤልሳቤጥ #ንግግር ሲሆን ሌላው እንደ #ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ #ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን #መውለዷ ነው።

▶️ ከዚህ የተነሳ #ከእግዚአብሄር #ምስጋና #ቀጥሎና #አያይዞ #ማርያምን #ማመስገን እንደሚገባ #ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቡኋላ #የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን መጠቀም ጀምራለች። ለምሳሌ፦

〽️ 1፦ <አቡነ ዘበሰማያት(አባታችን ሆይ)> ከሚለው #ጸሎት ቀጥሎ <እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ.... ሰላም እንልሻለን> ማለትን

〽️ 2፦ <ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ (ምስጋና ይሁን ለአብ፣ ምስጋና ለወልድ፣ ምስጋና ለመንፈስቅዱስ ይገባል)" ከሚለው #ቀጥሎ <ስብሐት #ለእግዝትነ #ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ (አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይሁን)> ማለትን

〽️ 3፦ <ለልዑል እግዚአብሔር ፍጹም #ምስጋና ይገባል> ይባልና ቀጥሎ <ለወለደችው ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይገባል> ማለትን

〽️ 4፦ <የእግዚአብሄር ስሙ ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱ በየሰአቱ #ምስጋና ይገባል> ካለ ቡሀላም <እናታችን ማርያም ሆይ ሰላምታ ለአንቺ ይሁን እያልን #እንሰግድልሻለን #እንማልድሻለን> ይላል[3]።
▶️ የማርያም #መጻሕፍት አብዛኞቹ እንደነ <<ውዳሴ ማርያም>>፣ <<ቅዳሴ ማርያም>> የመሳሰሉት #የእግዚአብሔርን ቃል ወስደው ወደ #ማርያም የማጠጋጋት #ባህሪ አላቸው። በሌላ በኩል ደግሞ #የተጋነኑና #አሳፋሪ #ሐሰት ይገኝባቸዋል። #የእግዚአብሔር ቃል #እውነትን በእጅጉ ይቃረናሉ ለምሳሌ <<መጽሐፈ አርጋኖን[1]>> የተባለው ፦

〽️ <<አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12 ክፍል 8፤ ቁ.6]
〽️ <<ኖህ ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12 ክፍል 8፤ ቁ.9]
〽️ <<አብርሃም ከሳራ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.10]
〽️ <<ይስሐቅ ከርብቃ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.11]
〽️ <<ዕብራዊው ያዕቆብም ከልጁ ከይሁዳ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.14]
〽️ <<ሙሴ ከእስራኤል ልጆች ሁሉ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.20]
〽️ <<ዳዊት ከመዘምራን ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.23]
〽️ <<ማህበረ መላዕክት ያመሰግኑሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.26]
〽️ <<ማህበረ ነብያት ሁሉም ያመሰግኑሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.27]

▶️ እነዚህ የተጠቀሱ #የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሲሆኑ ክፍሎቹን ወደ #መጽሐፍ ቅዱስ ሄደን #በጥሞና ብናነባቸው የሚነግሩን፦ #አዳም #ከልጆቹ ጋር #እግዚአብሔርን እንጂ #ማርያምን አላመሰገነም። ጭራሽ #አይተዋወቁም። በመካከላቸው ያለው #የዘመን ልዩነት #የሰማይና #የምድር ርቀት ያክል ነውና። [ዘፍ 4፥3፣ ዘፍ 5፤ 1-5]። #ኖህ ከልጆቹ ጋር [ዘፍ 6፥9፣ ዘፍ 8፤ 20-22፣ ዕብ 11፥7] #አብርሃም ከሣራ ጋር [ዘፍ 28፥8፣ ዘፍ 21፥1፣ ዕብ 11፥8፣ 19] #ይስሐቅ #ከርብቃ ጋር [ዘፍ 27፥27]፣ #ያዕቆብም [ዘፍ 28፤ 18-22፣ ዕብ 11፥20]፣ #ሙሴ #ከእስራኤላውያን ጋር [ዘጸ 15፤ 1-26፣ ዕብ 11፤ 23-28]፣ #ዳዊትም [2ሳሙ 6፤ 12-33፣ መዝ 8፤ 1-9] #ማህበረ #መላእክትም [ኢሳ 6፥3፣ ራዕ 4፤ 7-11]። #የሐዋርያት ማህበርም [ሐዋ 2፤ 46-47፣ ሐዋ 16፥25]፣ ሁሉም በግልጽ #እግዚአብሔርን ብቻ እንዳከበሩ እንጂ #ማርያምን ያመሰግኑበትም ሆነ #ስሟን እንኳን የጠሩበት አንድም #ቦታ የለም።

▶️ ስለሆነም <<ማርያምን ያመሰግናሉ>> የሚለው #ኢ-መጽሐፍቅዱሳዊና #የነብያትን#የመላእክትን፣ እንዲሁም #የሐዋርያትን ስም ማጥፋትና #ለእግዚአብሔር ያቀረቡትን የተባረከ #ምስጋናቸውን ወደራስ #ሃሳብና #መሻት ለመጠምዘዝ የተደረገ ከንቱ #የባእድ #አምልኮ #ሙከራ ነው።

ሌላው #ውሸት የታጨቀበት #መጽሐፍ ደግሞ <<መጽሐፈ ሰዓታት[2]>> የተባለው #መጽሐፍ ነው። ለምሳሌ ያክል

〽️ <<ለመጸብሐዊ ማቴዎስ እንተ ረሰይኪዩ ወንጌላዊ - ለቀራጩ ማቴዎስ ወንጌላዊ ያደረግሽው አንቺ ነሽ>> ይላል [መጽሐፈ ሰዓታት ርኅርኅተ ህሊና ገጽ 132 - 133]። ነገር ግን #ማቴዎስ ወደ #ወንጌላዊነት እንዴት እንደመጣ #ራሱ #ስለራሱ ሲናገር <<ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።>> [ማቴ 9፥9] ብሏል። ይህንን #መጽሐፍ ቅዱሳዊ #እውነት ክዶ #ማርያም #ማቴዎስን #ወንጌላዊ አደረገችው ማለት ምን ይሉታል?

▶️ ማህሌተ ጽጌ የተባለው #መጽሐፍ ደግሞ <<ቅዱስ ጴጥሮስ በ30 እስታቴር (በ30 ብር) በርተሎሜዎስን ለግብርና ስራ ሸጠው>> ይላል። በመቀጠልም <<የጴጥሮስ ጥላው የጳውሎስም ልብሱ ማርያም አንቺ ነሽ>> ይላል። አንባቢ ሆይ አረ #እናስተውል!!። ሐዋርያው #ጴጥሮስ ሐዋርያው #በርተሎሚዎስን እንደሸጠ ከየት የተገኘ #ወሬ ነው?። #ከታሪክ አንጻር እንኳን ብንመለከተው #ጴጥሮስም #በርተሎሚዎስም #ለወንጌል አገልግሎት ከመጠራታቸው በፊት #በሮማ ግዛት ስር የነበሩ ተራ #አይሁዳውያን ነበሩ እንጂ #ሰውን የሚሸጡ #ገዢዎች እንኳ አልነበሩም። ታድያ ሐዋርያው #ጴጥሮስ የወንጌል ጓደኛውን #በርተሎሜዎስን #ለግብርና ስራ #በ30 ብር ሸጠ ማለትና #የጴጥሮስ ጥላው #የጳውሎስም የልብሱ ዘርፍ #በሽተኞችን ሲፈውስ #ፈዋሹ #እግዚአብሔር ብቻ ሆኖ ተጽፎ እያለ <<ጥላና ልብሱ ማርያም ነበረች>> ማለት አያሳተዛዝብም? [ሐዋ 5፤ 15-16፣ 19፤ 11-12]። አረ ያስተዛዝበናል!

▶️ ይህ በብዙ የሳተ #መጽሐፍ #በግእዝና #በዜማ ለህዝቡ ስለሚቀርብለት አብዛኛው #ቋንቋውን ስለማያውቅ የሚባለውን #ሳይሰማና #ሳያስተውል #አሜን ብሎ ይሄዳል። ምናልባት ጉዳዩን በጥሞና #መረዳት ቢችልና ለማረም ቢሞክር ደግሞ #ተሐድሶ#መናፍቅ ወ.ዘ.ተ ተብሎ #የውግዘት ናዳው ይዘንብበታልና አብዛኛው #ዝም ማለቱን የመረጠ ይመስላል።

<<ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ። ማደሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፥ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።>> [ኤር 9፤ 5-6]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ አርጋኖን የእመቤታችን ምስጋና፤ ተስፋ ገብረስላሴ ማተሚያ ቤት፡ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።

[2] ሰፊ ማብራሪያ
📚፤ GBV <መጽሀፈ ሰአታት በመቅደሱ ሚዛን> 2ተኛ ዕትም ጥቅምት፡ 1995 ዓ.ም፤ BGNLJ፤ አ.አ፥ ኢትዮጵያ።
ይመልከቷል።

@gedlatnadersanat
(8.6.6▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ አባ ጊዮርጊስ #የሸዋ #ሊቀ #ጳጳስ የነበሩት "የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ" በሚለው #መጽሀፋቸው #ስለምስል #አመጣጥና የነበራቸው #ጠቀሜታ ሲገልጹ <<ስእል በቤተክርስቲያን የተጀመረበት ምክንያት የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ትምህርታቸውን ያስፋፉት ዋሻ ፈልፍለው ጉድጓድ ቆፍረው በዋሻ በፍርከታ ውስጥ ነው። ካታኮምብ {ግበበ ምድር} ይሉታል። በዚህ ዋሻ ውስጥ የሰማዕታት አጽም እየሰበሰቡ ትምህርት ያስተምሩ ነበር። በዚህ ውስጥ ብዙ አማኞች እየመጡ የማህበራቸው አባል መሆን ጀመሩ። በዚህ ጊዜ የክርስትናውን ትምህርት አስፋፍቶ ለመስጠት በቂ መጽሀፍት አልነበሩም። እንደልብ ወጥቶ ለመፈለግና ለማዘጋጀት ነጻነት ስላልነበራቸው ከመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንድ ምሳሌዎችን በስዕል እያሰፈሩ ማስተማር ጀመሩ። በዚህ ሁኔታ ስእል ማስተማሪያ ሆነው ቆይተዋል። ሥዕሎችም የሚሳሉት በምሳሌነት {ሲምቦሊክ} ሲሆን የሚሳሉትም በአመድና በከሰል በዋሻ ዙሪያ ነው። በዋሻ ፊት ለፊት ላይ የሚስሉት እረኛው በጉን እንደተሸከመ አድርገው ነው። ይህም ክርስቶስ ያመኑበትን ሁሉና በእርሱም አምነው የሞቱትን ሁሉ የሚያጸናቸው ቸርና ታማኝ ጠባቂ መሆኑን ለማስረዳት ነው>> ብለዋል[5]። @gedlatnadersanat

▶️ ነገር ግን ይህን #የማስተማርያ መንገድ በመጠቀም #ሰዎች ዝም ብለው #በአንቃእዶተ ህሊና {ህሊናን በማንሳት} #ከመጸለይ ይልቅ በፊታቸው #ሥዕሎችን በማየት #መጸለይ ብሎም #ስግደትና #መሳም #እየበዛ መጣ። በወቅቱ ነገሩ #ወደጣኦት #አምልኮ ሄዷል ያሉ ታዋቂ #የክርስትና #ምሁራን #ሥዕሎችን እያወረዱ #መሰባበር ጀመሩ። በተለይም #ከአሕዛብ #ሥዕልን የማክበር #ልማድ የነበራቸውና #ሥዕል #በመሳል ኑሮአቸውን #ይደጉሙ የነበሩ #ሰዓሊዎች #ጥቅማቸውና #ሙያቸው ስለተነካ #ከፍተኛ #ተቃውሞ ከፈቱ። በዚህ ምክንያት #የክርስትና #መከፋፈልና #ስደት ከ815 - 843 ዓ.ም ድረስ ቀጠለ። ይሁን እንጂ ግለሰቦች #በየጉድጓዱ #ሥዕልን በመሳልና #በግል #መኖሪያ ቤታቸው #በመስቀል ብሎም #ለምስሎቹ #ስግደት በማቅረባቸው ምክንያት ነገሩ #እየተስፋፋ መቶ ዛሬ #በቤተክርስቲያን #በረቀቀና #ስእል#በሃውልት መልክ ጭምር #የአምልኮ #ማስፈጸሚያ እስከመሆን ደርሷል።
▶️ በ1962 -1965 እ.ኤ.አ የ2ኛው #የካቶሊክ #የቫቲካን ጉባዔ <<ስለማርያም የሚሰጠው ትምህርት እውቅና እንዲያገኝና የማርያም ምስል ከፍ ተደርጎ እንዲያዝና እንዲሰገድለት ቅዱስ ተብሎም እንዲጠራ የአምልኮም መገልገያ እንዲሆን ወስነናል፤ ይህ የሲኖዶስ ውሳኔ ለቅድስት ማርያም ያለንን አክብሮት ለማሳየት ነው>> አለ[1]።

▶️ ይህን #የቫቲካን #ሲኖዶስን ጨምሮ ብዙ #ሰዎች #ምስልን ለመቀበል የወሰኑት <<ምስልን ማክበር ባለቤቱን ማክበር ነው>> በሚል #የተሳሳተ ሃሳብ ነው። አንዳንድ ጊዜም #ጣዖት ብለው የሚያስቡት #በእግዚአብሔርና #በማርያም አልያም #በመላዕክት #ተመስሎ የተሳለውን ወይም የተቀረጸውን ሳይሆን #በእንስሳት፣ በተለያዩ #ቁሳቁሶች መልክ የተዘጋጀውን #ቅርጽ ብቻ ይመስላቸዋል። በእርግጥ እነርሱም ቢሆኑ #አምልኮና #ስግደት ከቀረበባቸው #ጣኦታት ናቸው። ነገር ግን እንኳንስ #በማርያም #በእግዚአብሔር በራሱ #መልክን ሰርቶ ማስቀመጥ ብሎም ወደ #ምስሉ መስገድ #እግዚአብሔር ከመቃወምም ባለፈ #ይጸየፋል#ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ #ሲያስጠነቅቅ

<<እግዚአብሔርም በእሳት ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ የቃልን ድምፅ ሰማችሁ፥ መልክ ግን አላያችሁም፤ ድምፅን ብቻ ሰማችሁ።. . . እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤ እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥. . . ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።>> [ዘዳ 4፤ 12፣ 15-19]።

▶️ ከዚህ #ከበድ ካለ #ማስጠንቀቂያ እንደምንረዳው #በኮሬብ ለእስራኤል #እግዚአብሔር ራሱን ሲገልጥ #ያለመልክ በመሆኑ ይህን ይመስላል ብሎ #መሳልም #መቅረጽም ብሎም #መስገድ መሳት እንደሆነ እንረዳለን። #እግዚአብሔር እንኳንስ #ለማርያም ለራሱም ቢሆን #በተቀረጸ #ምስል #አምልኮ እንዲቀርብለት ፈጽሞ አይፈልግም።

▶️ በ15ኛው #ክፍለ ዘመን የነበሩት #እስጢፋኖሳውያን የአፄ ዘርዓያዕቆብ #አፍቅሮተ #ጣኦታት የተጠናወታቸው ሰዎች <<ምስለ ፍቁር ወልዳ>> ለሚባለው #ስዕል እንዲሰግዱ ቢያሳዩአቸው #ሥዕሉን አድንቀው <<ለሰው ስራ አትስገዱ>> የሚለውን #አምላካዊ #ትዕዛዝ በማስታወስ <<የሰው ስራ ነውና አንሰግድም>> እንዳሉ ገድላቸው ይተርካል[2]።

▶️ ሌሎችም ለምሳሌ #ዘሚካኤልና #ገማርያ የሚባሉ 2 ሊቃውንት <<አልቦቱ መልክዓ ለእግዚአብሔር ከመ መልክዓ ሰብዕ - እግዚአብሔር የሰው መልክ የሚመስል መልክ የለውም>> በማለታቸው አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ #ተቆጥቶና #ተከራክሮ አስቀጥቷቸዋል[3]።

▶️ ደቂቀ እስጢፋኖስ ይወቁት አይወቁት አይታወቅም እንጂ #ለስዕል #አይሰገድም የሚለው እውነት #በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ሃሳብ አይደለም። እነርሱ ከመነሳታቸው #ከ150 አመት በፊትም እዚያው ትግራይ <<ለስዕል አይሰገድም ጣኦት ነው፣ ሰሌዳ ነው>> ያሉ ታላላቅ #የሃይማኖት #አባቶች ነበሩ። ነገር ግን #አጼ #ያግብአ #ጽዮን[4] [1278-1286] <<በዚህ ጥያቄ እያመነታሁ ሳለው ቀይ ሴት (እመቤታችን) ተገልፃልኝ <<ለሥዕሌ መስገድ ይገባል ብላኛለችና ያልታዘዘ ገመድ ለአንገቱ ያከማቸው ንብረቱ ለሰራዊቴ ቤቱ ከጠመንጃዬ አፎት ለምታወጣ እሳት ይደረጋል>> ሲሉ #ነጋሪት #ጎስመው ስላወጁ ያገሩ ሰዎች ሁሉ #የስዕለ #ማርያም #አምልኮ ትምህርት ተደናግጠው ለጊዜውም ቢሆን ከንጉሱ #ጥይት ለመትረፍ <<ንጉሱ ያዘዘንን ሁሉ እናደርጋለን ለስዕልም እንሰግዳለን>> እንዳሉና በዚህም #እንቅስቃሴው ቀዝቀዝ እንዳለ የታሪክ ጸሀፊዎች ዘግበውታል[5]። <<እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላቹ ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ>> {ኢሳ 40፥18}።

<<እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።>> [ሐዋ 17፥29]።

<<እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።>> [ኢሳ 42፥8]።

<<እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚመለከውም በእውነትና በመንፈስ ነው>> [ዩሐ 4፥24]።

▶️ በመሆኑም #ምስሎች ወደ #ቤተክርስቲያን በገቡበት #ትርጉማቸው #ለማስተማሪያነት ካልሆነ በቀር #ለስርዓተ #አምልኮ መጠቀሚያ ሊውሉ አይገባም። <<ፀልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል-በቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል ፊት ፀልዩ>> ብሎ #ዘርዓያዕቆብ ያወጀው #አዋጅ #የኃጢአት አዋጅ ነውና ዲያቆኑ ቢተወው #ከእግዚአብሔር ጋር #መስማማት ነው።

<<የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ። እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።>> ይላል እግዚአብሔር [ዘዳ 7፤ 25-26]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ "The Docmates of Vatican vol. 2 pp 94,95, Londen 1973.

[2] 📚፤ ገድለ አባ ዕዝራ ገጽ 38።

[3] 📚፤ ጌታቸው ሀይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ" ገጽ 28፣ የህዳግ ማብራሪያ፤ 1996 ዓ.ም።

[4] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Yagbe'u_Seyon

[5] 📚፤ K.contirossini, the act፥ vol 16 (1965)፤ pp. 12-14።

📚፤ ጌታቸው ሀይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ" ገጽ 24፣ 1996 ዓ.ም።

@gedlatnadersanat
(9.5▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat