ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
69 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ #ሴቶች ሰፊ ስፍራ #ከወንዶች #እኩል ተሰጥቷአቸው #እግዚአብሔር ሲጠቀምባቸው እናነባለን። በተለይ #በአዲስ ኪዳን #የእግዚአብሄር ቃል በግልጽ <<አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።>> {ገላ 3፥28} ይላል። እንዲሁም <<እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።>> {ሮሜ 2፥11}፣ <<በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤>> {ሮሜ 10፥12} ይላል።

▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ከወንዶች ባልተናነሰ አንዳንዴም #በሚበልጥ ሁኔታ #እግዚአብሔር በተለያየ መልኩ የተጠቀመባቸው #ከ87 የሚበልጡ #ሴቶች #ከነታሪካቸው ተጽፏል። ከእነዚህም ውስጥ #ልጅ ባለመውለዳቸው #ሲነቀፉ የነበሩት #እንደነሳራና #ሐና የመሳሰሉ #እግዚአብሔር #ቃል ኪዳን ያለውን #ልጅ በመስጠት #አስደናቂና #ታዋቂ #እናቶች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

▶️ የተጠቀሱት ሁሉም #ሴቶች #አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር #መሲሁን (ኢየሱስ ክርስቶስን) ማገልገላቸውና ለእርሱም #መንገድ ማዘጋጀታቸው ነው። ለምሳሌ፦


1፦ ሔዋን፦ #ከሴቲቱ #ዘር የሚመጣው (ኢየሱስ ክርስቶስ) #የእባቡን (የዲያብሎስንና የኃጢአትን) #ራስ #እንደሚቀጠቅጥ የተናገረላትና ይህንንም #ትንቢት በመጠበቅ ለዚህ #ዘር #ሐረግ በመጀመሪያ #አቤልን ከዚያም #ሴትን የወለደች።

2፦ ሩት፦ #ከሞዓባውያን ወገን የነበረች #በእምነት #ከወገኖቿ ተለይታ #ከእግዚአብሄር ህዝብ ጋር በመቀላቀል #እስራኤላዊውን #ቦኤዝን አግብታ #የእሴይን አባት #እዮቤድን በመውለድ ወደ #ክርስቶስ #የዘር #ግንድ ውስጥ ገብታለች።

3፦ አስቴር፦ #ዝርያው እንዲጠፋ የተፈረደበት #የአይሁድ #ህዝብ ወደ #ንጉሡ #በድፍረት በመግባት #ህዝቤን #በመሻቴ #ህይወቴም #በልመናየ ይሰጠኝ በማለት #በህዝቧ ላይ #የታወጀውን #የሞት #ፍርድ በመቀልበስ #ከአይሁድ ወገን ሊመጣ ያለውን #የኢየሱስ ክርስቶስን #ዘር በመጠበቅ የበኩሏን #አስተዋጽኦ አድርጋለች።

▶️ እነ #አቢግያ#ኢያኤል#ኤልሳቤጥ#ቤርሳቤህ#ራሔል#ሊዲያ#ፌበን#ሰሎሜ፣ . . .ወዘተ ሁሉም #እግዚአብሔር የሰጣቸውን #ተግባር ሁሉ #በድል ያከናወኑ አንቱ የሚባሉ #ሴቶች ናቸው።

▶️ ጌታ ኢየሱስ #በአገልግሎቱ #ወቅት #ከፍተኛ #እገዛ ሲያደርጉ የነበሩ በዚያ #አስፈሪ #ሰዓት በሆነው #በስቀለቱም ወቅት #ከመስቀሉ #ግርጌ ስር በስፋት #ሃዘናቸውን የገለጹ #በመቃብሩም ሄደው እንደተናገረው #መነሳቱን #ከቅዱሳን #መላእክት ሰምተው #ለህዝቡ ሁሉ በመጀመሪያ #ትንሳኤውን ያወጁና የእርሱን #መሞትና #መነሳት ... ወዘተ የሚያበስረውን #ወንጌል ይዘው ወጥተው #የግል #ቤታቸውን እንኳ #የወንጌል አደባባይና #ቤተክርስቲያን አድርገው #የእግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምሩ የነበሩ #ሴቶች ነበሩ።

▶️ ይህን #ማንሳታችን ያለ ምክንያት ሳይሆን <<ማርያም #ከሴቶች ሁሉ እንዲያውም #ከፍጡራን ሁሉ የበላይ የሆነች #ፍጡር>> የሚል #የተዛባና #መጽሀፍቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምህሮ ስላለ ነው። ለዚህም #ትምህርት መነሻው #በሉቃስ 1፥28 እና 1፥42 <<አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ>> ተብሎ የተገለጸው #ቃል ሲሆን <<ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ማርያምን ብሩክት አንቲ እምአንስት - አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተለየሽ ሲል ከሴቶች ሁሉ የተለየች መሆኗን በምስጋና ቃል ገልጦ ተናግሯል፤ የዚህን መልአክ ቃል በመደገፍ በማጽናትም ኤልሳቤጥ አንቺ ከሴቶች የተባረክሽ ነሽ ብላ ጮሀና አሰምታ ተናግራለች። ይህም ቃል ቅድስት ማርያምን በነፍስ በሥጋ ቅድስት መሆኗን መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን (ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ) መሆኗን ያጠቃልላል>> ብለው የተረጎሙት ስላሉ ነው[1]። በመሰረቱ ይህ #ትርጉም ሳይሆን #የመጻሐፉን ግልጽ #ቃል በመቀየርና ወደሚፈልጉት የማርያም #አምልኮ በማዞር የተቀመጠ #አስተምህሮ ነው።

▶️ ማርያምን <<ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች>> የሚለውን ቃል #ለመጀመሪያ ጊዜ የገለጸው #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረው #የደቡብ ወሎ ቦረናው #ሰው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ነው[2]።

▶️ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው #ምክንያታቸው ከላይ የተገለጸው #የቅዱስ ገብርኤልና #የኤልሳቤጥ #ንግግር ሲሆን ሌላው እንደ #ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ #ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን #መውለዷ ነው።

▶️ ከዚህ የተነሳ #ከእግዚአብሄር #ምስጋና #ቀጥሎና #አያይዞ #ማርያምን #ማመስገን እንደሚገባ #ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቡኋላ #የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን መጠቀም ጀምራለች። ለምሳሌ፦

〽️ 1፦ <አቡነ ዘበሰማያት(አባታችን ሆይ)> ከሚለው #ጸሎት ቀጥሎ <እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ.... ሰላም እንልሻለን> ማለትን

〽️ 2፦ <ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ (ምስጋና ይሁን ለአብ፣ ምስጋና ለወልድ፣ ምስጋና ለመንፈስቅዱስ ይገባል)" ከሚለው #ቀጥሎ <ስብሐት #ለእግዝትነ #ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ (አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይሁን)> ማለትን

〽️ 3፦ <ለልዑል እግዚአብሔር ፍጹም #ምስጋና ይገባል> ይባልና ቀጥሎ <ለወለደችው ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይገባል> ማለትን

〽️ 4፦ <የእግዚአብሄር ስሙ ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱ በየሰአቱ #ምስጋና ይገባል> ካለ ቡሀላም <እናታችን ማርያም ሆይ ሰላምታ ለአንቺ ይሁን እያልን #እንሰግድልሻለን #እንማልድሻለን> ይላል[3]።
▶️ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን #ደቀመዛሙርቶቹ ተሰብስበው #ስለጸሎት እንዲያስተምራቸው በጠየቁት ጊዜ እንግዲህ እናንተ እንዲህ #ጸልዩ፦ <<በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ፥ #ስምህ #ይቀደስ#መንግሥትህ #ትምጣ፤ ፈቃድህ #በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ #በምድር ትሁን፤ የዕለት #እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን #ይቅር እንደምንል በደላችንን #ይቅር በለን፤ ከክፉም #አድነን እንጂ ወደ #ፈተና አታግባን፤ #መንግሥት ያንተ ናትና #ኃይልም #ክብርም #ለዘለዓለሙ፤ አሜን።>> በሉ በማለት አስተምሯል። [ማቴ 6፤ 9-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]።

▶️ ከዚህ ጌታ #ኢየሱስ ከሰጠው #የጸሎት #መመሪያ ላይ በመቀጠል #አድራሻው ወደ #ማርያም የሆነ፦ <<እመቤታችን ቅድስት #ድንግል #ማርያም ሆይ በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ....>> ምናምን የሚለው #ጸሎት ቢኖሮ ኖሮ ወይም መኖር ቢኖርበት ኖሮ ደቀመዛሙርቱ #ጸሎት #አስተምረን ባሉት ጊዜ ባገኘው ምርጥ #አጋጣሚ ወደ #ማርያም #መጸለይ #ትክክል ወይም #ተገቢ መሆኑን ባሳየ ነበር። #ዝንጋኤ የሌለበት በማስተዋልም #ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ <<መንግስት ያንተ ነውና ኃይልና ክብርም ለዘላለሙ አሜን>> ብሎ #የመዝጊያ #ቃል አስቀምጦ ባልደመደመውም ነበር።

▶️ መምህራችንና #ሊቃችን አንድ እርሱም #ክርስቶስ የሆነው #ጌታ [ማቴ 23፤ 8-11] ያላስተማረውን #ትምህርት ከእርሱ ይልቅ #ሊቅ ለመሆን #በመሞከርና #በመጨመር ሌላ ድርሰት ማምጣት #ከንቱ #ድካምና #ፍሬ #ቢስ ከመሆኑም በላይ የሚያመጣው #ፋይዳ (ጥቅም) አይኖርምና <<እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን #በቃሉ አንዳች #አትጨምር።>> [ምሳ 30፥6]።

▶️ በመሰረቱ <<አባታችን ሆይ>> በሚለው #የማህበር #ጸሎት ላይ <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን ብቻ ሳይሆን <<ሊቃውንቶች>> የጨማመሩት #ሠላም #ለኪን#ውዳሴ #ማርያምን#አንቀጸ #ብርሃንን#ይወድስዋ #መላዕክትን#መልክዓ #ማርያምን....ወ.ዘ.ተ ደራርበውበታል።

▶️ የካቶሊክ #ቤተክርስቲያንና ሌሎች #እህትማማች ተብለው የሚጠሩት #አብያተ #ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ካለው የ<<እመቤታችን.... ሆይ>> ጸሎት #የቃላትና #የይዘት #ልዩነት አለው። የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትለው፦ <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል ነሽ የአሸናፊ የልዑል እግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ይገባሻል እንዲሁም ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታውን ለምኝልን ኃጢታትችንን ያስተሰርይልን ዘንድ አሜን[1]።>> የሚል ሲሆን #የካቶሊክና#የእህትማማች #አብያተ ክርስቲያናት (የግሪክ፣ የህንድ፣ የአርመን የግብጽ. . .ኦርቶዶክስ) ደግሞ <<ድንግል ወላዲት ሆይ! ማርያም ሆይ፣ ጸጋ የሞላሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው፤ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የነፍሳችንን አዳኝ ተሸክመሻልና ደስ ይበልሽ[2]>> #ብቻ ነው የሚለው። ይህ ግን #መጽሀፍ ቅዱስ የማይቀበለውና #መጽሀፍ ቅዱሳዊ #ማስረጃ የሌለው ከንቱ #ፈጠራ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ ጌታቸው አየነው (መምህር)፤ "የዘውትር ጸሎት በአማርኛ"፥ ገጽ 5 ፥አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጽ/ጠ/ጽ/ቤት ሐዋርያዊ ስራ መምሪያ ፤ "ሕያው እግዚአብሔር" ፤አማርኛ ትርጉም ገጽ 316፤ በገላውዲዎስ ተቋም በአባ ጳውሎስ ጻድዋ ካርዲናል ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እንዲታተም የተፈቀደ፤ ማስተር ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።