ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽 #ኢየሱስ #አማላጅ መሆኑን መቀበል የከበዳቸው ሰዎች፤ ክፍሉ(ሮሜ 8፥34) ምን ያህል #እንዳስጨነቃቸው የሚያሳየው ለአንዱ #ጥቅስ የሚሰጡት የመከላከያ #ሐሳብ #ብዛት ነው፡፡ ቀደም ሲል ከቀረቡት #ሐሳቦች #ሌላ ደግሞ፤ መምህር በርሀ ተስፋ መስቀል እንዲህ ይላሉ.. 〽️ 3፦ ‹‹ስለ እኛ #የሚማለደው ተብሎ መጻፍ ሲገባው ‹ #ለ› ን ‹ #ል› በማድረግ ስለ እኛ #የሚማልደው ተብሎ…
🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽

እንደገና ከላይ ከቀረቡት #ሐሳብ የተለየ ደግሞ መሪጌታ ሀየሎም በርሄ እንዲህ በማለት ያስቀምጣሉ...

〽️ 4፦ ‹‹ይህ ሕያው #ሥጋውና #ደሙ ሁል ጊዜ #ሰውን ወደ #እግዚአብሔር #ሲያቀርብ የሚኖር ከእግዚአብሔርም ጋር የመታረቂያው #ብቸኛ #መንገድ በመሆኑ #አማለደን /አስታረቀን/ ሲል ገልጦታል›› የሚል ሐሳብ አቅርበዋል፡፡
📖/፤ ኃየሎም በርሄ (መሪጌታ)፣ ሁለቱ ኪዳናት (ዐዲስ አበባ 2002) ገጽ 219።

▶️ እኚህ ጸሀፊ ደግሞ ከላይ የቀረቡትን ሐሳቦች በሙሉ ተቃርነው፤ ይልቁንም አዎ #ኢየሱስ ይማልዳል! ነገር ግን #የሚያማልደው #በቅዱስ #ቁርባን ነው ይሉናል፡፡ እንግዲህ ማንኛውም #ልባም #አንባቢ ክፍሉን ተመልክቶ #መረዳት #እንደሚችለው በዚህ #ምንባብ ውስጥ #ከክርስቶስ #ሥጋና #ደም (ከቅዱስ ቁርባን) ጋር የተያያዘ #ሐሳብ ማግኘት ፈጽሞ አይችልም፡፡ ይህን #ምንባብ #መሠረት አድርጎ ስለ #ቅዱስ #ቁርባን #ለማስተማር የሚሞክር #ሰው ሆነ ብሎ የሰዎችን #ትኵረት ወደ ሌላ #አቅጣጫ #ለመውሰድ ያሰበ #ሰው እንጂ #ጥቅሱን መሠረት አድርጎ ማብራሪያ #እየሰጠ አለመሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
እነዚህ ሁሉም እንግዲህ #መምህራን ተብለው መድረክ ላይ የሚቆሙና ይህን እና ይህን መሰል #የኑፋቄ ትምህርት #በህዝቡ ላይ የሚረጩ፤ #ከእግዚአብሄር ቃል ይልቅ ለፈቃዳቸውና ላሉበት ባህላዊ እምነት ቅድሚያ የሚሰጡ ሰዎች ናቸው። እንዳያችሁት #አንድ #ጥቅስ ላይ ራሱ እንዲህ ያለ #አለመግባባት ይታይባቸዋል፡፡ እርስ በእርስ ያልተስማሙ ሰዎች ታዲያ እንዴት ነው #ከቅዱሱ #መጽሐፍ ጋር ተስማምተው #ለማስተማር የሚችሉት? ስለዚህም እኛን ለማስተማር ከመሞከራቸው በፊት #እርስ በእርሳቸው #ይስማሙ ዘንድ ይሄው ወንድማዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ይህ ሁሉ ግን ለምን ይሆን? ስንል ምክንያቱም #ቤተ ክርስቲያኒቱ #ከክርስቶስ #የማዳን ሥራ ጋር የተሳሰረውን #የምልጃ ስራውን አልቀበልም በማለቷ ነው፡፡

@gedlatnadersanat @teeod
▶️ የማርያም #መጻሕፍት አብዛኞቹ እንደነ <<ውዳሴ ማርያም>>፣ <<ቅዳሴ ማርያም>> የመሳሰሉት #የእግዚአብሔርን ቃል ወስደው ወደ #ማርያም የማጠጋጋት #ባህሪ አላቸው። በሌላ በኩል ደግሞ #የተጋነኑና #አሳፋሪ #ሐሰት ይገኝባቸዋል። #የእግዚአብሔር ቃል #እውነትን በእጅጉ ይቃረናሉ ለምሳሌ <<መጽሐፈ አርጋኖን[1]>> የተባለው ፦

〽️ <<አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12 ክፍል 8፤ ቁ.6]
〽️ <<ኖህ ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12 ክፍል 8፤ ቁ.9]
〽️ <<አብርሃም ከሳራ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.10]
〽️ <<ይስሐቅ ከርብቃ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.11]
〽️ <<ዕብራዊው ያዕቆብም ከልጁ ከይሁዳ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.14]
〽️ <<ሙሴ ከእስራኤል ልጆች ሁሉ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.20]
〽️ <<ዳዊት ከመዘምራን ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.23]
〽️ <<ማህበረ መላዕክት ያመሰግኑሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.26]
〽️ <<ማህበረ ነብያት ሁሉም ያመሰግኑሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.27]

▶️ እነዚህ የተጠቀሱ #የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሲሆኑ ክፍሎቹን ወደ #መጽሐፍ ቅዱስ ሄደን #በጥሞና ብናነባቸው የሚነግሩን፦ #አዳም #ከልጆቹ ጋር #እግዚአብሔርን እንጂ #ማርያምን አላመሰገነም። ጭራሽ #አይተዋወቁም። በመካከላቸው ያለው #የዘመን ልዩነት #የሰማይና #የምድር ርቀት ያክል ነውና። [ዘፍ 4፥3፣ ዘፍ 5፤ 1-5]። #ኖህ ከልጆቹ ጋር [ዘፍ 6፥9፣ ዘፍ 8፤ 20-22፣ ዕብ 11፥7] #አብርሃም ከሣራ ጋር [ዘፍ 28፥8፣ ዘፍ 21፥1፣ ዕብ 11፥8፣ 19] #ይስሐቅ #ከርብቃ ጋር [ዘፍ 27፥27]፣ #ያዕቆብም [ዘፍ 28፤ 18-22፣ ዕብ 11፥20]፣ #ሙሴ #ከእስራኤላውያን ጋር [ዘጸ 15፤ 1-26፣ ዕብ 11፤ 23-28]፣ #ዳዊትም [2ሳሙ 6፤ 12-33፣ መዝ 8፤ 1-9] #ማህበረ #መላእክትም [ኢሳ 6፥3፣ ራዕ 4፤ 7-11]። #የሐዋርያት ማህበርም [ሐዋ 2፤ 46-47፣ ሐዋ 16፥25]፣ ሁሉም በግልጽ #እግዚአብሔርን ብቻ እንዳከበሩ እንጂ #ማርያምን ያመሰግኑበትም ሆነ #ስሟን እንኳን የጠሩበት አንድም #ቦታ የለም።

▶️ ስለሆነም <<ማርያምን ያመሰግናሉ>> የሚለው #ኢ-መጽሐፍቅዱሳዊና #የነብያትን#የመላእክትን፣ እንዲሁም #የሐዋርያትን ስም ማጥፋትና #ለእግዚአብሔር ያቀረቡትን የተባረከ #ምስጋናቸውን ወደራስ #ሃሳብና #መሻት ለመጠምዘዝ የተደረገ ከንቱ #የባእድ #አምልኮ #ሙከራ ነው።

ሌላው #ውሸት የታጨቀበት #መጽሐፍ ደግሞ <<መጽሐፈ ሰዓታት[2]>> የተባለው #መጽሐፍ ነው። ለምሳሌ ያክል

〽️ <<ለመጸብሐዊ ማቴዎስ እንተ ረሰይኪዩ ወንጌላዊ - ለቀራጩ ማቴዎስ ወንጌላዊ ያደረግሽው አንቺ ነሽ>> ይላል [መጽሐፈ ሰዓታት ርኅርኅተ ህሊና ገጽ 132 - 133]። ነገር ግን #ማቴዎስ ወደ #ወንጌላዊነት እንዴት እንደመጣ #ራሱ #ስለራሱ ሲናገር <<ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።>> [ማቴ 9፥9] ብሏል። ይህንን #መጽሐፍ ቅዱሳዊ #እውነት ክዶ #ማርያም #ማቴዎስን #ወንጌላዊ አደረገችው ማለት ምን ይሉታል?

▶️ ማህሌተ ጽጌ የተባለው #መጽሐፍ ደግሞ <<ቅዱስ ጴጥሮስ በ30 እስታቴር (በ30 ብር) በርተሎሜዎስን ለግብርና ስራ ሸጠው>> ይላል። በመቀጠልም <<የጴጥሮስ ጥላው የጳውሎስም ልብሱ ማርያም አንቺ ነሽ>> ይላል። አንባቢ ሆይ አረ #እናስተውል!!። ሐዋርያው #ጴጥሮስ ሐዋርያው #በርተሎሚዎስን እንደሸጠ ከየት የተገኘ #ወሬ ነው?። #ከታሪክ አንጻር እንኳን ብንመለከተው #ጴጥሮስም #በርተሎሚዎስም #ለወንጌል አገልግሎት ከመጠራታቸው በፊት #በሮማ ግዛት ስር የነበሩ ተራ #አይሁዳውያን ነበሩ እንጂ #ሰውን የሚሸጡ #ገዢዎች እንኳ አልነበሩም። ታድያ ሐዋርያው #ጴጥሮስ የወንጌል ጓደኛውን #በርተሎሜዎስን #ለግብርና ስራ #በ30 ብር ሸጠ ማለትና #የጴጥሮስ ጥላው #የጳውሎስም የልብሱ ዘርፍ #በሽተኞችን ሲፈውስ #ፈዋሹ #እግዚአብሔር ብቻ ሆኖ ተጽፎ እያለ <<ጥላና ልብሱ ማርያም ነበረች>> ማለት አያሳተዛዝብም? [ሐዋ 5፤ 15-16፣ 19፤ 11-12]። አረ ያስተዛዝበናል!

▶️ ይህ በብዙ የሳተ #መጽሐፍ #በግእዝና #በዜማ ለህዝቡ ስለሚቀርብለት አብዛኛው #ቋንቋውን ስለማያውቅ የሚባለውን #ሳይሰማና #ሳያስተውል #አሜን ብሎ ይሄዳል። ምናልባት ጉዳዩን በጥሞና #መረዳት ቢችልና ለማረም ቢሞክር ደግሞ #ተሐድሶ#መናፍቅ ወ.ዘ.ተ ተብሎ #የውግዘት ናዳው ይዘንብበታልና አብዛኛው #ዝም ማለቱን የመረጠ ይመስላል።

<<ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ። ማደሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፥ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።>> [ኤር 9፤ 5-6]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ አርጋኖን የእመቤታችን ምስጋና፤ ተስፋ ገብረስላሴ ማተሚያ ቤት፡ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።

[2] ሰፊ ማብራሪያ
📚፤ GBV <መጽሀፈ ሰአታት በመቅደሱ ሚዛን> 2ተኛ ዕትም ጥቅምት፡ 1995 ዓ.ም፤ BGNLJ፤ አ.አ፥ ኢትዮጵያ።
ይመልከቷል።

@gedlatnadersanat
(8.6.6▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat