▶️ ኤልሳቤጥ በጸነሰች #በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል #ልጅ #የመውለድ #መልእክት ይዞ ወደ እሷ መጣ። በዚህ ጊዜ #መልእክቱ የመጣው #በገሊላ አውራጃ ከምትገኝ #በናዝሬት ከተማ ለምትኖርና ስሟ #ማርያም ለምትባል #ድንግል ልጃገረድ ነበር። #ማርያም #ከይሁዳ ነገድ #ከዳዊት ትውልድ የሆነች #አይሁዳዊት #ድንግል ነበረች (ኢሳ 7፥14)። #በናዝሬት ከተማ #በአናጺነት ሙያ ለሚተዳደር #ዮሴፍ ለተባለ #ሰው የታጨች ስትሆን (ማቴ 13፥55) ሁለቱም ድሆች ነበሩ (ሉቃ 2፥24 ፣ ዘሌ 12፥8)።
▶️ ከሉቃስ ወንጌል #ምዕራፍ 1፤ 26-33 #የቅዱስ ገብርኤልን #ሰላምታ በደንብ ስንመለከተው #ማርያም ለጊዜው #እንደፈራችና #ግራ እንደተጋባች ያስረዳል። <<ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው>> አላት። #መልአኩ #ሠላምታ ሊሥጣት የመጣው ለምንድን ነው?? #ጸጋ የሞላባትስ በምን #መንገድ ነው? #እግዚአብሔር #ከእሷ ጋር የሆነውስ #እንዴት ነው??..
▶️ የማርያም #ምላሽ #በእግዚአብሄር ፊት #ትሁትና #እውነተኛ እንደነበረ ያሳያል። ከቶውንም #ከመልአክ ጋር እንደምትነጋገርና #ከሰማይ ልዩ #ጸጋዎችን እንደምታገኝ አልጠበቀችም። #የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ #የሉቃስ ወንጌል #አንድምታው እንደሚለው <<ማርያም #የኢሳያስን #ትንቢት የሆነውን ኢሳ 7፥14 ስታነብ ያቺን #ሴት ምነው እኔ #በሆንኩ አላለችም። እንደውም ምነው #ከጊዜዋ ደርሼ #ወጥቼ #ወርጄ አገልግያት በማለት #ታስብ እንደነበር ይገልጻል[1]። እንዲህ አይነት #ሁኔታዎች እንዲፈጸምላት የሚያደርግ #ምንም የተለየ ነገር አልነበራትም። አንዳንድ የስነ መለኮት #አስተማሪዎችም እንደሚናገሩት <<ማርያም #ከሌሎች አይሁዳውያን #ሴቶችና #ልጃገረዶች #የተለየች ብትሆን ኖሮ <<መልካም እንግዲህ #ጊዜው #ደርሷል! እስከአሁንም #ስጠብቀው ቆይቻለሁ! ትል ነበር። ነገር ግን #በፍጹም አላለችም[2]!!! ሁሉ ነገር ለእሷ #አዲስና #አስደናቂ #ዱብእዳ ስለነበረ ግራ #ተጋብታለች፣ #ፈርታለች፣ #ደንግጣለችም <<ይህ እንዴት ያለ #ሰላምታ ነው?>> በማለትም አስባለች። #ቅዱስ ገብርኤልም #አትፍሪ በማለት #የማረጋጋት ተግባር ሲያከናውን ይታያል።
▶️ ከዚያም #መልአኩ ገብርኤል #መልካሙን #ዜና ያበሰራት #ኢየሱስን (አዳኝ፣ መድኃኒት) ማቲ 1፥21 ብላ የምትሰይመውን #መሲህ እንደምትወልድ ነበር። በመቀጠልም #መልአኩ የኢየሱስን #አምላክነትና #ሰብአዊነት አስረግጦ በመንገር #የምትወልደው #ልጅ ታላቅ እንደሆነና እንደሚሆን እንጂ በእርሷ ታላቅነት ላይ አላተኮረም {ሉቃ 1፥31}።
▶️ የሚወለደው ህጻን(ኢየሱስ) #ንጉስ ሆኖ #የዳዊትን #ዙፋን በመውረስ #ለዘላለም በእስራኤል ላይ #ይነግሳል። #እግዚአብሔር #ከዳዊት ጋር የገባውን #ቃል #ኪዳን (2ኛሳሙ 7) እና ለእስራኤል #ህዝብ የሰጠውን #የመንግስት የተስፋ #ቃሎች #እያመለከተ ነበር {ኢሳ 9፤1-7፣ 11-12 ፣ 61 ፣ 66፣ ኤር 33}።

▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ #ሴቶች ሰፊ ስፍራ #ከወንዶች #እኩል ተሰጥቷአቸው #እግዚአብሔር ሲጠቀምባቸው እናነባለን። በተለይ #በአዲስ ኪዳን #የእግዚአብሄር ቃል በግልጽ <<አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።>> {ገላ 3፥28} ይላል። እንዲሁም <<እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።>> {ሮሜ 2፥11}፣ <<በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤>> {ሮሜ 10፥12} ይላል።
▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ከወንዶች ባልተናነሰ አንዳንዴም #በሚበልጥ ሁኔታ #እግዚአብሔር በተለያየ መልኩ የተጠቀመባቸው #ከ87 የሚበልጡ #ሴቶች #ከነታሪካቸው ተጽፏል። ከእነዚህም ውስጥ #ልጅ ባለመውለዳቸው #ሲነቀፉ የነበሩት #እንደነሳራና #ሐና የመሳሰሉ #እግዚአብሔር #ቃል ኪዳን ያለውን #ልጅ በመስጠት #አስደናቂና #ታዋቂ #እናቶች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
▶️ የተጠቀሱት ሁሉም #ሴቶች #አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር #መሲሁን (ኢየሱስ ክርስቶስን) ማገልገላቸውና ለእርሱም #መንገድ ማዘጋጀታቸው ነው። ለምሳሌ፦
✅ 1፦ ሔዋን፦ #ከሴቲቱ #ዘር የሚመጣው (ኢየሱስ ክርስቶስ) #የእባቡን (የዲያብሎስንና የኃጢአትን) #ራስ #እንደሚቀጠቅጥ የተናገረላትና ይህንንም #ትንቢት በመጠበቅ ለዚህ #ዘር #ሐረግ በመጀመሪያ #አቤልን ከዚያም #ሴትን የወለደች።
✅ 2፦ ሩት፦ #ከሞዓባውያን ወገን የነበረች #በእምነት #ከወገኖቿ ተለይታ #ከእግዚአብሄር ህዝብ ጋር በመቀላቀል #እስራኤላዊውን #ቦኤዝን አግብታ #የእሴይን አባት #እዮቤድን በመውለድ ወደ #ክርስቶስ #የዘር #ግንድ ውስጥ ገብታለች።
✅ 3፦ አስቴር፦ #ዝርያው እንዲጠፋ የተፈረደበት #የአይሁድ #ህዝብ ወደ #ንጉሡ #በድፍረት በመግባት #ህዝቤን #በመሻቴ #ህይወቴም #በልመናየ ይሰጠኝ በማለት #በህዝቧ ላይ #የታወጀውን #የሞት #ፍርድ በመቀልበስ #ከአይሁድ ወገን ሊመጣ ያለውን #የኢየሱስ ክርስቶስን #ዘር በመጠበቅ የበኩሏን #አስተዋጽኦ አድርጋለች።
▶️ እነ #አቢግያ፣ #ኢያኤል፣ #ኤልሳቤጥ፣ #ቤርሳቤህ፣ #ራሔል፣ #ሊዲያ፣ #ፌበን፣ #ሰሎሜ፣ . . .ወዘተ ሁሉም #እግዚአብሔር የሰጣቸውን #ተግባር ሁሉ #በድል ያከናወኑ አንቱ የሚባሉ #ሴቶች ናቸው።
▶️ ጌታ ኢየሱስ #በአገልግሎቱ #ወቅት #ከፍተኛ #እገዛ ሲያደርጉ የነበሩ በዚያ #አስፈሪ #ሰዓት በሆነው #በስቀለቱም ወቅት #ከመስቀሉ #ግርጌ ስር በስፋት #ሃዘናቸውን የገለጹ #በመቃብሩም ሄደው እንደተናገረው #መነሳቱን #ከቅዱሳን #መላእክት ሰምተው #ለህዝቡ ሁሉ በመጀመሪያ #ትንሳኤውን ያወጁና የእርሱን #መሞትና #መነሳት ... ወዘተ የሚያበስረውን #ወንጌል ይዘው ወጥተው #የግል #ቤታቸውን እንኳ #የወንጌል አደባባይና #ቤተክርስቲያን አድርገው #የእግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምሩ የነበሩ #ሴቶች ነበሩ።
▶️ ይህን #ማንሳታችን ያለ ምክንያት ሳይሆን <<ማርያም #ከሴቶች ሁሉ እንዲያውም #ከፍጡራን ሁሉ የበላይ የሆነች #ፍጡር>> የሚል #የተዛባና #መጽሀፍቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምህሮ ስላለ ነው። ለዚህም #ትምህርት መነሻው #በሉቃስ 1፥28 እና 1፥42 <<አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ>> ተብሎ የተገለጸው #ቃል ሲሆን <<ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ማርያምን ብሩክት አንቲ እምአንስት - አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተለየሽ ሲል ከሴቶች ሁሉ የተለየች መሆኗን በምስጋና ቃል ገልጦ ተናግሯል፤ የዚህን መልአክ ቃል በመደገፍ በማጽናትም ኤልሳቤጥ አንቺ ከሴቶች የተባረክሽ ነሽ ብላ ጮሀና አሰምታ ተናግራለች። ይህም ቃል ቅድስት ማርያምን በነፍስ በሥጋ ቅድስት መሆኗን መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን (ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ) መሆኗን ያጠቃልላል>> ብለው የተረጎሙት ስላሉ ነው[1]። በመሰረቱ ይህ #ትርጉም ሳይሆን #የመጻሐፉን ግልጽ #ቃል በመቀየርና ወደሚፈልጉት የማርያም #አምልኮ በማዞር የተቀመጠ #አስተምህሮ ነው።
▶️ ማርያምን <<ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች>> የሚለውን ቃል #ለመጀመሪያ ጊዜ የገለጸው #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረው #የደቡብ ወሎ ቦረናው #ሰው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ነው[2]።
▶️ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው #ምክንያታቸው ከላይ የተገለጸው #የቅዱስ ገብርኤልና #የኤልሳቤጥ #ንግግር ሲሆን ሌላው እንደ #ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ #ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን #መውለዷ ነው።
▶️ ከዚህ የተነሳ #ከእግዚአብሄር #ምስጋና #ቀጥሎና #አያይዞ #ማርያምን #ማመስገን እንደሚገባ #ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቡኋላ #የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን መጠቀም ጀምራለች። ለምሳሌ፦
〽️ 1፦ <አቡነ ዘበሰማያት(አባታችን ሆይ)> ከሚለው #ጸሎት ቀጥሎ <እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ.... ሰላም እንልሻለን> ማለትን
〽️ 2፦ <ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ (ምስጋና ይሁን ለአብ፣ ምስጋና ለወልድ፣ ምስጋና ለመንፈስቅዱስ ይገባል)" ከሚለው #ቀጥሎ <ስብሐት #ለእግዝትነ #ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ (አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይሁን)> ማለትን
〽️ 3፦ <ለልዑል እግዚአብሔር ፍጹም #ምስጋና ይገባል> ይባልና ቀጥሎ <ለወለደችው ለድንግል ማርያም #ምስጋና ይገባል> ማለትን
〽️ 4፦ <የእግዚአብሄር ስሙ ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱ በየሰአቱ #ምስጋና ይገባል> ካለ ቡሀላም <እናታችን ማርያም ሆይ ሰላምታ ለአንቺ ይሁን እያልን #እንሰግድልሻለን #እንማልድሻለን> ይላል[3]።

ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ እስቲ እነዚህን ጥቅሶች ይመልከቷቸው። 〽️ ሐዋ 1፤ 9-11፦ <<ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ…
〽️ ሐዋ 2፤ 14-18፣ 17-20፦
<<ነገር ግን ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ፥ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው። አይሁድ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፥ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ቃሎቼንም አድምጡ። ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም፥ ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤ ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለው ነው። እግዚአብሔር ይላል። በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ. . .>>
⁉️ መንፈስቅዱስም የመጣው #ማርያም ስላለች ሳይሆን በነብዩ #በኢዩኤል #የተተነበየው #ይፈጸም ዘንድ ነበር። ስለዚህ #የማርያም #በአካል መኖር የተለየ ነገር አልነበረውም። #ማርያምም እዛ #ትንቢት ውስጥ መካተቷ <<ስጋ በለበሰ ሁሉ ላይ>> እንደተባለው #ማርያምን ጨምሮ ሳያበላልጥ #እኩል #በወንዶችና #በሴቶች ላይ ማደሩ፤ እሷም #ስጋ ከለበሱት ጋር #እኩል #መቆጠሯ ፈጽሞ ከሌላው #የተለየች እንዳልሆነች ያሳያል።
〽️ ሐዋ 2፤ 22-35፦
<<የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤ እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት። እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና። . . . ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤. .>>
⁉️ #ሐዋርያት #በመንፈስ ቅዱስ ሆነው #በመካከላቸው #ማርያም ብትኖርም <<የናዝሬቱን ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሄር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበር>> በሚል ቃል #ክርስቶስን ብቻ #ማዕከል ያደረገ #ስብከት #ሰጡ እንጂ #ስለማርያም ያሉት ነገር አልነበረም።
〽️ ሐዋ 2፤ 37-38፦
<<ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ፥ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት። ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉአቸው። ጴጥሮስም። ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።>>
⁉️ #የሐዋርያትን #ስብከት የሰሙት ህዝቦች #ሐዋርያትን ምን እናድርግ ብለው #ሲጠይቋቸው በመካከላችን እናቱ #ማርያም ስላለች #በእርሷ #አማላጅነት #እመኑ ወደ እርሷ ወይም #በእርሷ በኩል ቅረቡ ሳይሆን ያሉት #ንስሃ ገብታችሁ #በኢየሱስ ስም ተጠመቁ #የመንፈስ ቅዱስ #ስጦታ #ትቀበላላችሁ የሚል #ክርስቶስን #ብቻ የገለጸ #መልስ ነበር የሰጡት።
〽️ ሐዋ 2፥47፦
<<እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።>>
⁉️ ሁሉም #በአንድነት #እግዚአብሔርን #በቀጥታ #ያመሰግኑ ነበር እንጂ ወደ #ማርያምም ሲጸልዩም ሆነ #ምስጋና ሲያቀርቡ አላየንም። በዚህም #ምክንያት የማርያም #በመካከላቸው #መኖርና #አለመኖር የተለየ ምንም #ጥቅም እንደሌለው የተረዱ ሲሆን #ጌታም #አብሮአቸው በመስራት #ዕለት #ዕለት #ቁጥራቸው ይጨምር ነበር።
▶️ ደግሞም #በብሉይም ይሁን #በአዲስ ኪዳን #እጹብ ድንቅ #በእግዚአብሄር ኃይል #ተአምራትን ካደረጉ #ሴቶች ይልቅ #ማርያም ከፍ ብላ የምትታይበት #አንድም #ተአምር #በመጽሀፍ ቅዱስ እንዳደረገች እንኳ #አልተጻፈም። #በወንዶችም ቢሆን የተደረገው #ተአምር #ምድርን ሁሉ ቢያስገርምም ማንም <ከፍጡራን በላይ> የተባለ ግን የለም። ምክንያቱም #የተአምራቱ ባለቤት #እግዚአብሔር እንጂ #ሰዎች አይደሉምና። ስለዚህም እዚህ ላይ ልንገነዘበው የሚገባን #እውነት ቢኖር #ማርያም ከተባረኩ #በርካታ #ሴቶች #መካከል #የተባረከች #አንዷ #ሴት መሆኗን ነው {ሉቃ 1፥28 ፣ ሉቃ 1፥42}። #ቃሉም እንደ እርሱ ነው የሚለውና #ቃሉን #ብቻ እንመን።
✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
"ማጣቀሻዎች - References"
_______________
[1] 📚፤ አባ መልከ ጻድቅ (ሊቀ ጳጳስ) <ኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ እምነትና ትምህርት> ገጽ 217፥ ንግድ ማተሚያ ድርጅት፡ አ.አ 1994 ዓ.ም።
📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤
<መጽሐፈ ሚስጥር> ገጽ 97፤
<መጽሀፈ ደጓ> ገጽ 380 እና 386።
📚፤ አባ ጎርጎሪዮስ (የሸዋ ሊቀ ጳጳስ)፡ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ታሪክ፡ ገጽ 133፤ አ.አ ፡1994 ዓ.ም።
[2] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
<መጽሀፈ ሚስጥር> ገጽ 97፥
"አርጋኖን ዘዓርብ" ገጽ 296፥ 3፤ 3-4። ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ 1989 ዓ.ም።
[3] 📚፤ የዘውትር ጸሎት፡ ውዳሴ ማርያም በአማርኛ፤ ገጽ 5-8፡ ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1986 ዓ.ም።
📚፤ አንዱ ዓለም ዳግማዊ (መምህር)፤ <ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት> ገጽ 257፤ ብራና ማተሚያ ድርጅት፤ አ.አ፥ ሚያዚያ 1998 ዓ.ም።
(6.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat