ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.82K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ቅዱስ ገብርኤል #ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ #ለማርያም #ለማስረዳት የተጠቀመው #ምሳሌ #መካን የነበረችውና #ያረጀችው ዘመዷ #ኤልሳቤጥ #ወንድ ልጅ እንደጸነሰች በመግለጽ ነበር። #ልጅ አለመውለድ #የወላጆችን #የግል #ደስታ የሚያሳጣ ብቻ ሳይሆን #እግዚአብሔር እንደማይወዳቸውም የሚያመለክት ነው ተብሎ #በህብረተሰቡ ዘንድ ስለሚታመን {ዘፍ 16፥2 ፣ ዘፍ 25፥21 ፣ ዘፍ 30፥23 ፣ 1ኛሳሙ 1፤ 1-18 ፣ ዘሌ 20፤ 20-21 ፣ መዝ (128)፥3 ፣ ኤር 22፥30}። <<ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ ተመለከተኝ>> ብላ #እግዚአብሔር #የመካንነትን #ህይወቷን ስለቀየረላት ምስጋና አቅርባለች {ሉቃ 1፥24}። #በደስታ#በጥሞና#በምስጋና... የነበረችውን #ኤልሳቤጥን ማርያም #ከገብርኤል መልእክት(ብስራት) ቡኋላ ወደ እሷ መጥታ #ሰላምታ ስታሰማት #ኤልሳቤጥ #በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ከማርያም አፍ ሳትሰማው ማርያም #የጌታ #እናት እንደምትሆን አወቀች። በዚህ ጊዜ #ኤልሳቤጥ አፏን የሞላው #ቃል <<አንቺ ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?>> የሚል ነበር። አንዳንዶች እንደሚሉት ሳይሆን ኤልሳቤጥ ማርያምን <<ከሴቶች #በላይ የተባረክሽ>> እንዳላለቻትና ዳሩ ግን <<ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ>> እንዳለቻት ልብ ማለት ያስፈልጋል። #ማርያም #በእግዚአብሄር #እቅድ ውስጥ ያላትን #ስፍራ ባናሳንስም(ልናሳንስም አንችልም) #እግዚአብሔር #ብቻ ሊቀበል የሚገባውን #የአምልኮት #ክብርና #ልእልና መስጠት ግን አይገባንም።

▶️ ስለማርያም ኤልሳቤጥ #ያገነነችው ነገር ቢኖር <<ያመነች ብጽኢት[1] ናት>> በሚል የማርያምን #እምነት ነበር {ሉቃ 1-45}። #ማርያም #የእግዚአብሔርን #ቃል ስላመነች የእግዚአብሔርን #ኃይልና #አንድያ #ልጅ ተቀበለች።

▶️ በኤልሳቤጥ #ጽንስ ውስጥ ያለው #ዩሀንስም በጊዜው #ደስ #ተሰኝቷል {ሉቃ 1፤ 41-44}። ዩሀንስ #በምድራዊ #አገልግሎቱ እንዳደረገው ሁሉ #ሳይወለድም በፊት #በኢየሱስ ክርስቶስ #ብቻ ደስ ተሰኝቷል {ዩሀ 3፤ 29-30}። #ካደገ ቡሀላም #መጥምቁ #ዩሀንስ ተብሎ ሲታወቅ #መሲሁን #ኢየሱስ ክርስቶስን ለአይሁድ ህዝብ የማስተዋወቅና የመግለጥ ታላቅ #እድል አግኝቷል። ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ <<ዩሀንስ በእናቱ ማህጸን ውስጥ የማርያምን ድምጽ በመስማቱ #ለማርያም #ሰገደላት>> የሚሉ #መናፍቃን አልታጡም። ይሁን እንጂ #የጽንስ #መዝለል #ሁኔታን #ጸንሰው የሚያቁ #እናቶች የሚረዱት ነገር ቢሆንም •ስግደት• ብሎ መቀየር ግን. . . •ለማርያም ሰገደ• ያሉትም #መጽሀፍ ቅዱስ ሳይሆን #ሲኖዶስ ተብለው የተጠሩ ተስብሳቢዎች እንደሆኑ #ራሱ #ኦርቶዶክስ ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን ያሳተመችው #የሉቃስ ወንጌል አንድምታው ይገልጻል።

<<. . . ከዘካርያስ ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን እንዴት ነሽ አለቻት፥ ወሶበ ስምዓት ኤልሳቤጥ ቃላ ለማርያም እንዝ ትትኣምኃ ኦንፈርዓፀ እጓል በውስተ ከርሣ እመቤታችን እንዴት ነሽ ስትላት ኤልሳቤጥ በሰማች ጊዜ በማኅፀኑዋ ያለ ብላቴና ሰገደ። ሐተታ፡ ሐዋርያት #በሲኖዶስ ሰገደ ብለውታል። #ያሬድም ሰገደ ብሎታል።[2]>>

▶️ ከዚሁ #ከማርያምና #ከኤልሳቤጥ #ውይይት በመነሳት <<ቅድስት ኤልሳቤጥ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ ነሽ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እያማለድሽ የምትሰጪ መዝገበ በረከት ነሽ>> ብላ #አመስግናታለች #ዘምራላታለች የሚሉ አሉ[3]።

▶️ እንግዲህ እንዲህ አይነት #ቃል #በመጽሀፍ ቅዱስ ፈጽሞ ሳይኖር #ኤልሳቤጥ እንዲህ አይነት #ቃል ተጠቅማለች ብሎ #መጻፍና #ማስተማር #መጽሀፍ ቅዱስ እኛ ጋር #ብቻ ይገኛል ሌላው #ማንበብ አይችልም ብሎ ከማሰብና #የመጽሐፍ ቅዱስን #የበላይነት ካለመቀበል የሚመነጭ #ከንቱነት ነው። #ኤልሳቤጥ የተናገረችው <<አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።>> {ሉቃ 1፥47} የሚል ብቻ ነው።

▶️ በአንጻሩ ደግሞ <<መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የለብሽም>> ማለት በግልጽ #መጽሀፍ ቅዱስን መካድና #ማርያም የሰው ዘር መሆኗን #መዘንጋት ነው። እንዲያውም ማርያም ራሷ ክርስቶስን <<መድኃኒቴ>> ብላዋለች። #መድኃኒት ደግሞ #ለበሽተኞች (ለኃጢአተኞች) እንጂ #ለጤነኞች (ለጻድቃን) የሚያስፈልግ እንዳልሆነ #ቃሉ #በግልጽ ይናገራል{ማቴ 9፥12}።

▶️ በመሆኑም <<መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ. . . እያማለድሽ የምትሰጪ>> እያለ #የዘመረ #አካል #በመጽሀፍ ቅዱስ ባለመኖሩ የሌለ ነገር ላይ ተንተርሶ #ዶክትሪን ማስቀመጥ በቃሉ #መልእክት ላይ የተፈጸመ ተራ #አመጽ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_______________
[1] ብፁዕ፤፦
<<በቁሙ የታመነ፣ የተመሰገነ፣ ሥራውና ልቡ የቀና፣ ... ምስጉን፣ ብሩክ...>>
📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ *ገጽ 2081። አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ 1948 ዓ.ም።

<<የተባረከ፣ ደስተኛ>>
📚፤ የኢትዮጽያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር፤ <የመጽሀፍቅዱስ መዝገበ ቃላት>፤ 6ኛ እትም፤ *ገጽ 112። ባናዊ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ 1992 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፡ ወንጌል ቅዱስ፡ የሉቃስ ወንጌል ንባቡና አንድምታው 1፤ 36-40፤ ገጽ 268። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1997 ዓ.ም።

[3] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ ቤ/ክ፤ <መርሐ ጽድቅ ባህለ ሃይማኖት>፡ ገጽ. 24-25፡ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት። አ.አ፥ 1988 ዓ.ም።

📚፤ አንዱዓለም ዳግማዊ (መምህር) <ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት> ገጽ 290። ብራና ማተሚያ ድርጅት፥ ሚያዚያ፥ 1998 ዓ.ም።


(5.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ የማርያም #መጻሕፍት አብዛኞቹ እንደነ <<ውዳሴ ማርያም>>፣ <<ቅዳሴ ማርያም>> የመሳሰሉት #የእግዚአብሔርን ቃል ወስደው ወደ #ማርያም የማጠጋጋት #ባህሪ አላቸው። በሌላ በኩል ደግሞ #የተጋነኑና #አሳፋሪ #ሐሰት ይገኝባቸዋል። #የእግዚአብሔር ቃል #እውነትን በእጅጉ ይቃረናሉ ለምሳሌ <<መጽሐፈ አርጋኖን[1]>> የተባለው ፦

〽️ <<አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12 ክፍል 8፤ ቁ.6]
〽️ <<ኖህ ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12 ክፍል 8፤ ቁ.9]
〽️ <<አብርሃም ከሳራ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.10]
〽️ <<ይስሐቅ ከርብቃ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.11]
〽️ <<ዕብራዊው ያዕቆብም ከልጁ ከይሁዳ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.14]
〽️ <<ሙሴ ከእስራኤል ልጆች ሁሉ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.20]
〽️ <<ዳዊት ከመዘምራን ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.23]
〽️ <<ማህበረ መላዕክት ያመሰግኑሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.26]
〽️ <<ማህበረ ነብያት ሁሉም ያመሰግኑሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.27]

▶️ እነዚህ የተጠቀሱ #የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሲሆኑ ክፍሎቹን ወደ #መጽሐፍ ቅዱስ ሄደን #በጥሞና ብናነባቸው የሚነግሩን፦ #አዳም #ከልጆቹ ጋር #እግዚአብሔርን እንጂ #ማርያምን አላመሰገነም። ጭራሽ #አይተዋወቁም። በመካከላቸው ያለው #የዘመን ልዩነት #የሰማይና #የምድር ርቀት ያክል ነውና። [ዘፍ 4፥3፣ ዘፍ 5፤ 1-5]። #ኖህ ከልጆቹ ጋር [ዘፍ 6፥9፣ ዘፍ 8፤ 20-22፣ ዕብ 11፥7] #አብርሃም ከሣራ ጋር [ዘፍ 28፥8፣ ዘፍ 21፥1፣ ዕብ 11፥8፣ 19] #ይስሐቅ #ከርብቃ ጋር [ዘፍ 27፥27]፣ #ያዕቆብም [ዘፍ 28፤ 18-22፣ ዕብ 11፥20]፣ #ሙሴ #ከእስራኤላውያን ጋር [ዘጸ 15፤ 1-26፣ ዕብ 11፤ 23-28]፣ #ዳዊትም [2ሳሙ 6፤ 12-33፣ መዝ 8፤ 1-9] #ማህበረ #መላእክትም [ኢሳ 6፥3፣ ራዕ 4፤ 7-11]። #የሐዋርያት ማህበርም [ሐዋ 2፤ 46-47፣ ሐዋ 16፥25]፣ ሁሉም በግልጽ #እግዚአብሔርን ብቻ እንዳከበሩ እንጂ #ማርያምን ያመሰግኑበትም ሆነ #ስሟን እንኳን የጠሩበት አንድም #ቦታ የለም።

▶️ ስለሆነም <<ማርያምን ያመሰግናሉ>> የሚለው #ኢ-መጽሐፍቅዱሳዊና #የነብያትን#የመላእክትን፣ እንዲሁም #የሐዋርያትን ስም ማጥፋትና #ለእግዚአብሔር ያቀረቡትን የተባረከ #ምስጋናቸውን ወደራስ #ሃሳብና #መሻት ለመጠምዘዝ የተደረገ ከንቱ #የባእድ #አምልኮ #ሙከራ ነው።

ሌላው #ውሸት የታጨቀበት #መጽሐፍ ደግሞ <<መጽሐፈ ሰዓታት[2]>> የተባለው #መጽሐፍ ነው። ለምሳሌ ያክል

〽️ <<ለመጸብሐዊ ማቴዎስ እንተ ረሰይኪዩ ወንጌላዊ - ለቀራጩ ማቴዎስ ወንጌላዊ ያደረግሽው አንቺ ነሽ>> ይላል [መጽሐፈ ሰዓታት ርኅርኅተ ህሊና ገጽ 132 - 133]። ነገር ግን #ማቴዎስ ወደ #ወንጌላዊነት እንዴት እንደመጣ #ራሱ #ስለራሱ ሲናገር <<ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።>> [ማቴ 9፥9] ብሏል። ይህንን #መጽሐፍ ቅዱሳዊ #እውነት ክዶ #ማርያም #ማቴዎስን #ወንጌላዊ አደረገችው ማለት ምን ይሉታል?

▶️ ማህሌተ ጽጌ የተባለው #መጽሐፍ ደግሞ <<ቅዱስ ጴጥሮስ በ30 እስታቴር (በ30 ብር) በርተሎሜዎስን ለግብርና ስራ ሸጠው>> ይላል። በመቀጠልም <<የጴጥሮስ ጥላው የጳውሎስም ልብሱ ማርያም አንቺ ነሽ>> ይላል። አንባቢ ሆይ አረ #እናስተውል!!። ሐዋርያው #ጴጥሮስ ሐዋርያው #በርተሎሚዎስን እንደሸጠ ከየት የተገኘ #ወሬ ነው?። #ከታሪክ አንጻር እንኳን ብንመለከተው #ጴጥሮስም #በርተሎሚዎስም #ለወንጌል አገልግሎት ከመጠራታቸው በፊት #በሮማ ግዛት ስር የነበሩ ተራ #አይሁዳውያን ነበሩ እንጂ #ሰውን የሚሸጡ #ገዢዎች እንኳ አልነበሩም። ታድያ ሐዋርያው #ጴጥሮስ የወንጌል ጓደኛውን #በርተሎሜዎስን #ለግብርና ስራ #በ30 ብር ሸጠ ማለትና #የጴጥሮስ ጥላው #የጳውሎስም የልብሱ ዘርፍ #በሽተኞችን ሲፈውስ #ፈዋሹ #እግዚአብሔር ብቻ ሆኖ ተጽፎ እያለ <<ጥላና ልብሱ ማርያም ነበረች>> ማለት አያሳተዛዝብም? [ሐዋ 5፤ 15-16፣ 19፤ 11-12]። አረ ያስተዛዝበናል!

▶️ ይህ በብዙ የሳተ #መጽሐፍ #በግእዝና #በዜማ ለህዝቡ ስለሚቀርብለት አብዛኛው #ቋንቋውን ስለማያውቅ የሚባለውን #ሳይሰማና #ሳያስተውል #አሜን ብሎ ይሄዳል። ምናልባት ጉዳዩን በጥሞና #መረዳት ቢችልና ለማረም ቢሞክር ደግሞ #ተሐድሶ#መናፍቅ ወ.ዘ.ተ ተብሎ #የውግዘት ናዳው ይዘንብበታልና አብዛኛው #ዝም ማለቱን የመረጠ ይመስላል።

<<ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ። ማደሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፥ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።>> [ኤር 9፤ 5-6]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ አርጋኖን የእመቤታችን ምስጋና፤ ተስፋ ገብረስላሴ ማተሚያ ቤት፡ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።

[2] ሰፊ ማብራሪያ
📚፤ GBV <መጽሀፈ ሰአታት በመቅደሱ ሚዛን> 2ተኛ ዕትም ጥቅምት፡ 1995 ዓ.ም፤ BGNLJ፤ አ.አ፥ ኢትዮጵያ።
ይመልከቷል።

@gedlatnadersanat
(8.6.6▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat