ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ በ1962 -1965 እ.ኤ.አ የ2ኛው #የካቶሊክ #የቫቲካን ጉባዔ <<ስለማርያም የሚሰጠው ትምህርት እውቅና እንዲያገኝና የማርያም ምስል ከፍ ተደርጎ እንዲያዝና እንዲሰገድለት ቅዱስ ተብሎም እንዲጠራ የአምልኮም መገልገያ እንዲሆን ወስነናል፤ ይህ የሲኖዶስ ውሳኔ ለቅድስት ማርያም ያለንን አክብሮት ለማሳየት ነው>> አለ[1]።

▶️ ይህን #የቫቲካን #ሲኖዶስን ጨምሮ ብዙ #ሰዎች #ምስልን ለመቀበል የወሰኑት <<ምስልን ማክበር ባለቤቱን ማክበር ነው>> በሚል #የተሳሳተ ሃሳብ ነው። አንዳንድ ጊዜም #ጣዖት ብለው የሚያስቡት #በእግዚአብሔርና #በማርያም አልያም #በመላዕክት #ተመስሎ የተሳለውን ወይም የተቀረጸውን ሳይሆን #በእንስሳት፣ በተለያዩ #ቁሳቁሶች መልክ የተዘጋጀውን #ቅርጽ ብቻ ይመስላቸዋል። በእርግጥ እነርሱም ቢሆኑ #አምልኮና #ስግደት ከቀረበባቸው #ጣኦታት ናቸው። ነገር ግን እንኳንስ #በማርያም #በእግዚአብሔር በራሱ #መልክን ሰርቶ ማስቀመጥ ብሎም ወደ #ምስሉ መስገድ #እግዚአብሔር ከመቃወምም ባለፈ #ይጸየፋል#ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ #ሲያስጠነቅቅ

<<እግዚአብሔርም በእሳት ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ የቃልን ድምፅ ሰማችሁ፥ መልክ ግን አላያችሁም፤ ድምፅን ብቻ ሰማችሁ።. . . እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤ እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥. . . ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።>> [ዘዳ 4፤ 12፣ 15-19]።

▶️ ከዚህ #ከበድ ካለ #ማስጠንቀቂያ እንደምንረዳው #በኮሬብ ለእስራኤል #እግዚአብሔር ራሱን ሲገልጥ #ያለመልክ በመሆኑ ይህን ይመስላል ብሎ #መሳልም #መቅረጽም ብሎም #መስገድ መሳት እንደሆነ እንረዳለን። #እግዚአብሔር እንኳንስ #ለማርያም ለራሱም ቢሆን #በተቀረጸ #ምስል #አምልኮ እንዲቀርብለት ፈጽሞ አይፈልግም።

▶️ በ15ኛው #ክፍለ ዘመን የነበሩት #እስጢፋኖሳውያን የአፄ ዘርዓያዕቆብ #አፍቅሮተ #ጣኦታት የተጠናወታቸው ሰዎች <<ምስለ ፍቁር ወልዳ>> ለሚባለው #ስዕል እንዲሰግዱ ቢያሳዩአቸው #ሥዕሉን አድንቀው <<ለሰው ስራ አትስገዱ>> የሚለውን #አምላካዊ #ትዕዛዝ በማስታወስ <<የሰው ስራ ነውና አንሰግድም>> እንዳሉ ገድላቸው ይተርካል[2]።

▶️ ሌሎችም ለምሳሌ #ዘሚካኤልና #ገማርያ የሚባሉ 2 ሊቃውንት <<አልቦቱ መልክዓ ለእግዚአብሔር ከመ መልክዓ ሰብዕ - እግዚአብሔር የሰው መልክ የሚመስል መልክ የለውም>> በማለታቸው አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ #ተቆጥቶና #ተከራክሮ አስቀጥቷቸዋል[3]።

▶️ ደቂቀ እስጢፋኖስ ይወቁት አይወቁት አይታወቅም እንጂ #ለስዕል #አይሰገድም የሚለው እውነት #በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ሃሳብ አይደለም። እነርሱ ከመነሳታቸው #ከ150 አመት በፊትም እዚያው ትግራይ <<ለስዕል አይሰገድም ጣኦት ነው፣ ሰሌዳ ነው>> ያሉ ታላላቅ #የሃይማኖት #አባቶች ነበሩ። ነገር ግን #አጼ #ያግብአ #ጽዮን[4] [1278-1286] <<በዚህ ጥያቄ እያመነታሁ ሳለው ቀይ ሴት (እመቤታችን) ተገልፃልኝ <<ለሥዕሌ መስገድ ይገባል ብላኛለችና ያልታዘዘ ገመድ ለአንገቱ ያከማቸው ንብረቱ ለሰራዊቴ ቤቱ ከጠመንጃዬ አፎት ለምታወጣ እሳት ይደረጋል>> ሲሉ #ነጋሪት #ጎስመው ስላወጁ ያገሩ ሰዎች ሁሉ #የስዕለ #ማርያም #አምልኮ ትምህርት ተደናግጠው ለጊዜውም ቢሆን ከንጉሱ #ጥይት ለመትረፍ <<ንጉሱ ያዘዘንን ሁሉ እናደርጋለን ለስዕልም እንሰግዳለን>> እንዳሉና በዚህም #እንቅስቃሴው ቀዝቀዝ እንዳለ የታሪክ ጸሀፊዎች ዘግበውታል[5]። <<እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላቹ ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ>> {ኢሳ 40፥18}።

<<እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።>> [ሐዋ 17፥29]።

<<እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።>> [ኢሳ 42፥8]።

<<እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚመለከውም በእውነትና በመንፈስ ነው>> [ዩሐ 4፥24]።

▶️ በመሆኑም #ምስሎች ወደ #ቤተክርስቲያን በገቡበት #ትርጉማቸው #ለማስተማሪያነት ካልሆነ በቀር #ለስርዓተ #አምልኮ መጠቀሚያ ሊውሉ አይገባም። <<ፀልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል-በቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል ፊት ፀልዩ>> ብሎ #ዘርዓያዕቆብ ያወጀው #አዋጅ #የኃጢአት አዋጅ ነውና ዲያቆኑ ቢተወው #ከእግዚአብሔር ጋር #መስማማት ነው።

<<የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ። እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።>> ይላል እግዚአብሔር [ዘዳ 7፤ 25-26]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ "The Docmates of Vatican vol. 2 pp 94,95, Londen 1973.

[2] 📚፤ ገድለ አባ ዕዝራ ገጽ 38።

[3] 📚፤ ጌታቸው ሀይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ" ገጽ 28፣ የህዳግ ማብራሪያ፤ 1996 ዓ.ም።

[4] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Yagbe'u_Seyon

[5] 📚፤ K.contirossini, the act፥ vol 16 (1965)፤ pp. 12-14።

📚፤ ጌታቸው ሀይሌ፤ "ደቂቀ እስጢፋኖስ በህገ አምላክ" ገጽ 24፣ 1996 ዓ.ም።

@gedlatnadersanat
(9.5▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat