ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
✍✍ ⚜ ሮሜ 8÷34 " #የሞተው÷ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው÷ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው÷ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡" #ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ ማስተላልፍ የፈለገው ‹‹ #እንግዲህ #በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን #ኵነኔ የለባቸውም›› የሚለውን ነው (ቊጥር 1)፡፡ ሐዋርያው በመቀጠል ‹‹ #በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው #የሕይወት መንፈስ ሕግ #ከኀጢአትና…
✍✍
⚜ 1ኛ ጢሞቲዎስ 2፥5
"አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም #መካከል ያለው #መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው #የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው፤"
#የክርስቶስ ሰው የመሆን ምክንያት በዚህ መልእክት በሚገባ ሰፍሯል። በአዳም #በደል ምክንያት #ከእግዚአብሄር ፊት የራቀው #የአዳም ዘር ዳግመኛ #የእግዚአብሄርን #ፊት ለማየት የሚያስችል #ንጽህና ያልነበረው በመሆኑ፣ በእርሱ እና በአምላኩ #መካከል ያለውን #ክፍተት የሚሞላ ስላላገኘ፣ "አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን #አድን፤ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን፥ #አቅና"፣ እጅህን፥ ከአርያም ላክ #አድነኝም" (መዝ 118፥25 ፣ 144፤ 7-8) በሚል በብዙ #ጩኸት ውስጥ ነበር። ክብር ለእርሱ ይሁንና ፍጹም #ሰው ፍጹም #አምላክ በሆነው #በክርስቶስ <<.... #በደሙ የተደረገ #ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም #የበደላችን #ስርየት>> ነው (ኤፌሶን 1፥7)።
" #መካከለኛ እንዲሆን እግዚአብሔር #አንድያ #ልጁን ላከው... [ምክንያቱም ደግሞ <<ወንድም ወንድሙን #አያድንም ሰውም #አያድንም>> እንደሚል(መዝ 49፥7) መጽሀፍ፥ #ሰው(ፍጡርና የአዳም ልጅ) #መካከለኛ ሊሆን... እና #ሊያድን የማይችል ደካማ #ፍጡር ነውና። የሰው ልጅ ብቻም ሳይሆን <<ከሰማይ #መላእክት እንኳ ቢሆን ከምድርም ሰው መካከል አንድስ እንኳ #ለመካከለኝነቱ ብቁ ሆኖ #ሰውና #እግዚአብሔርን #ማስታረቅ የተቻለው አልተገኘም አይገኝምም። "ደም ሳይፈስም ስርየት የለም"(ዕብ9፥22)። #በሰውና #በእግዚአብሄር #መካከል የነበረውን #የጥል #ግድግዳ ለማፍረስ በመካከል የገባ፣ ሁለቱን #ያስታረቀ፣ ሰውን ከሰማያዊ ርስት የቀላቀለ #ጌታ #ኢየሱስ #ብቻ ነው>>።
📖/፤ ብርሃኑ አበጋዝ፤
^ክርስቶስ^ (2007) ገጽ 38።
#ክርስቶስ #የመካከለኛነት ሥራውን የሰራው በመከራ ሞቱ በመሆኑ ሁላችን #በእርሱ #በኩል ወደ #እግዚአብሔር #የመቅረብ መብት እንድናገኝ አስችሎናል ለዚህ ነው መጽሀፍ ቅዱስ "እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን #በዐዲስና #በሕያው #መንገድ ወደ ቅድስት #በኢየሱስ #ደም በመጋረጃው ማለት #በሥጋው #በኩል እንድንገባ ድፍረት..." እንዳለን የሚያስተምረው (ዕብ 10፤ 19-20)።
#የክርስቶስን #የመካከለኝነት ሥራ ለመቀበል የከበዳቸው ሰዎች ለዚህ ጥቅስ የሚሰጡት መከላከያ #ሐሳብ ቢያጡ ከምንባቡ ውስጥ <<ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ>> የሚለውን መዘው በማውጣት በእርግጥ #ክርስቶስ በዚህ ምድር ሳለ #የመካከለኝነት #ሥራ ሰርቶ ነበር አሁን ግን እንዲህ ያለ ነገር #በእርሱ ዘንድ #የለም የሚል #ሐሳብ ያቀርባሉ። ወገኖቻችን በዚህ ስፍራ ላይ #ሐዋሪያው #ጳውሎስ #ክርስቶስን ^ #ሰው^ ማለቱን አላስተዋሉም ይሆን?? አሁን በሰማያት የእኛን ሥጋ ሥጋው ያደረገ መካከለኛ (ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ) አለን። ለዛም እኮ ነው መጽሀፍቅዱስ፤
""ስለእኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ ሰማይ ገባ"(ዕብ 9፥24 ፣ 28)""
""ስለእኛ የሚማልደው(ሮሜ 8፥34)፤""
""ዘውትር ሊያማልድ...ብሎም በእርሱ በኩል የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል(ዕብ 7፥25)፤""
""እንዲሁም በሰማይ ባለችው መቅደስ አገልጋይ"(ዕብ 8፥2)""
""የአዲስ ኪዳን መካከለኛ(ዕብ 9፥15፣ 12፥24)፤""
""በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ #መካከለኛ #እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል።""(ዕብ 8፥6)
""ዘላለማዊ ሊቀካህን""(ዕብ 2፥17፣ 3፥1፣ 4፥14፣ 6፥20፣ 7፥26፣ 8፥1)....ወ.ዘ.ተ የሚለው።
#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/
ይቀጥላል..
@gedlatnadersanat @teeod

▶️ ቅዱስ ገብርኤል #ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ #ለማርያም #ለማስረዳት የተጠቀመው #ምሳሌ #መካን የነበረችውና #ያረጀችው ዘመዷ #ኤልሳቤጥ #ወንድ ልጅ እንደጸነሰች በመግለጽ ነበር። #ልጅ አለመውለድ #የወላጆችን #የግል #ደስታ የሚያሳጣ ብቻ ሳይሆን #እግዚአብሔር እንደማይወዳቸውም የሚያመለክት ነው ተብሎ #በህብረተሰቡ ዘንድ ስለሚታመን {ዘፍ 16፥2 ፣ ዘፍ 25፥21 ፣ ዘፍ 30፥23 ፣ 1ኛሳሙ 1፤ 1-18 ፣ ዘሌ 20፤ 20-21 ፣ መዝ (128)፥3 ፣ ኤር 22፥30}። <<ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ ተመለከተኝ>> ብላ #እግዚአብሔር #የመካንነትን #ህይወቷን ስለቀየረላት ምስጋና አቅርባለች {ሉቃ 1፥24}። #በደስታ፣ #በጥሞና፣ #በምስጋና... የነበረችውን #ኤልሳቤጥን ማርያም #ከገብርኤል መልእክት(ብስራት) ቡኋላ ወደ እሷ መጥታ #ሰላምታ ስታሰማት #ኤልሳቤጥ #በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ከማርያም አፍ ሳትሰማው ማርያም #የጌታ #እናት እንደምትሆን አወቀች። በዚህ ጊዜ #ኤልሳቤጥ አፏን የሞላው #ቃል <<አንቺ ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?>> የሚል ነበር። አንዳንዶች እንደሚሉት ሳይሆን ኤልሳቤጥ ማርያምን <<ከሴቶች #በላይ የተባረክሽ>> እንዳላለቻትና ዳሩ ግን <<ከሴቶች #መካከል የተባረክሽ>> እንዳለቻት ልብ ማለት ያስፈልጋል። #ማርያም #በእግዚአብሄር #እቅድ ውስጥ ያላትን #ስፍራ ባናሳንስም(ልናሳንስም አንችልም) #እግዚአብሔር #ብቻ ሊቀበል የሚገባውን #የአምልኮት #ክብርና #ልእልና መስጠት ግን አይገባንም።
▶️ ስለማርያም ኤልሳቤጥ #ያገነነችው ነገር ቢኖር <<ያመነች ብጽኢት[1] ናት>> በሚል የማርያምን #እምነት ነበር {ሉቃ 1-45}። #ማርያም #የእግዚአብሔርን #ቃል ስላመነች የእግዚአብሔርን #ኃይልና #አንድያ #ልጅ ተቀበለች።
▶️ በኤልሳቤጥ #ጽንስ ውስጥ ያለው #ዩሀንስም በጊዜው #ደስ #ተሰኝቷል {ሉቃ 1፤ 41-44}። ዩሀንስ #በምድራዊ #አገልግሎቱ እንዳደረገው ሁሉ #ሳይወለድም በፊት #በኢየሱስ ክርስቶስ #ብቻ ደስ ተሰኝቷል {ዩሀ 3፤ 29-30}። #ካደገ ቡሀላም #መጥምቁ #ዩሀንስ ተብሎ ሲታወቅ #መሲሁን #ኢየሱስ ክርስቶስን ለአይሁድ ህዝብ የማስተዋወቅና የመግለጥ ታላቅ #እድል አግኝቷል። ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ <<ዩሀንስ በእናቱ ማህጸን ውስጥ የማርያምን ድምጽ በመስማቱ #ለማርያም #ሰገደላት>> የሚሉ #መናፍቃን አልታጡም። ይሁን እንጂ #የጽንስ #መዝለል #ሁኔታን #ጸንሰው የሚያቁ #እናቶች የሚረዱት ነገር ቢሆንም •ስግደት• ብሎ መቀየር ግን. . . •ለማርያም ሰገደ• ያሉትም #መጽሀፍ ቅዱስ ሳይሆን #ሲኖዶስ ተብለው የተጠሩ ተስብሳቢዎች እንደሆኑ #ራሱ #ኦርቶዶክስ ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን ያሳተመችው #የሉቃስ ወንጌል አንድምታው ይገልጻል።
<<. . . ከዘካርያስ ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን እንዴት ነሽ አለቻት፥ ወሶበ ስምዓት ኤልሳቤጥ ቃላ ለማርያም እንዝ ትትኣምኃ ኦንፈርዓፀ እጓል በውስተ ከርሣ እመቤታችን እንዴት ነሽ ስትላት ኤልሳቤጥ በሰማች ጊዜ በማኅፀኑዋ ያለ ብላቴና ሰገደ። ሐተታ፡ ሐዋርያት #በሲኖዶስ ሰገደ ብለውታል። #ያሬድም ሰገደ ብሎታል።[2]>>
▶️ ከዚሁ #ከማርያምና #ከኤልሳቤጥ #ውይይት በመነሳት <<ቅድስት ኤልሳቤጥ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ ነሽ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እያማለድሽ የምትሰጪ መዝገበ በረከት ነሽ>> ብላ #አመስግናታለች #ዘምራላታለች የሚሉ አሉ[3]።
▶️ እንግዲህ እንዲህ አይነት #ቃል #በመጽሀፍ ቅዱስ ፈጽሞ ሳይኖር #ኤልሳቤጥ እንዲህ አይነት #ቃል ተጠቅማለች ብሎ #መጻፍና #ማስተማር #መጽሀፍ ቅዱስ እኛ ጋር #ብቻ ይገኛል ሌላው #ማንበብ አይችልም ብሎ ከማሰብና #የመጽሐፍ ቅዱስን #የበላይነት ካለመቀበል የሚመነጭ #ከንቱነት ነው። #ኤልሳቤጥ የተናገረችው <<አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።>> {ሉቃ 1፥47} የሚል ብቻ ነው።
▶️ በአንጻሩ ደግሞ <<መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የለብሽም>> ማለት በግልጽ #መጽሀፍ ቅዱስን መካድና #ማርያም የሰው ዘር መሆኗን #መዘንጋት ነው። እንዲያውም ማርያም ራሷ ክርስቶስን <<መድኃኒቴ>> ብላዋለች። #መድኃኒት ደግሞ #ለበሽተኞች (ለኃጢአተኞች) እንጂ #ለጤነኞች (ለጻድቃን) የሚያስፈልግ እንዳልሆነ #ቃሉ #በግልጽ ይናገራል{ማቴ 9፥12}።
▶️ በመሆኑም <<መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለብሽ. . . እያማለድሽ የምትሰጪ>> እያለ #የዘመረ #አካል #በመጽሀፍ ቅዱስ ባለመኖሩ የሌለ ነገር ላይ ተንተርሶ #ዶክትሪን ማስቀመጥ በቃሉ #መልእክት ላይ የተፈጸመ ተራ #አመጽ ነው።
✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
"ማጣቀሻዎች - References"
_______________
[1] ብፁዕ፤፦
<<በቁሙ የታመነ፣ የተመሰገነ፣ ሥራውና ልቡ የቀና፣ ... ምስጉን፣ ብሩክ...>>
📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ *ገጽ 2081። አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ 1948 ዓ.ም።
<<የተባረከ፣ ደስተኛ>>
📚፤ የኢትዮጽያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር፤ <የመጽሀፍቅዱስ መዝገበ ቃላት>፤ 6ኛ እትም፤ *ገጽ 112። ባናዊ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ 1992 ዓ.ም።
[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፡ ወንጌል ቅዱስ፡ የሉቃስ ወንጌል ንባቡና አንድምታው 1፤ 36-40፤ ገጽ 268። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1997 ዓ.ም።
[3] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ ቤ/ክ፤ <መርሐ ጽድቅ ባህለ ሃይማኖት>፡ ገጽ. 24-25፡ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት። አ.አ፥ 1988 ዓ.ም።
📚፤ አንዱዓለም ዳግማዊ (መምህር) <ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት> ገጽ 290። ብራና ማተሚያ ድርጅት፥ ሚያዚያ፥ 1998 ዓ.ም።
(5.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat