ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
📖፤ / ሱረቱ መርየም 19፤ 27-28
(2ተኛ እትም 1998 ዓ.ም)
*ሱራህ 19, አያህ 27*
فَأَتَتْ بِهِۦ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُۥ ۖ قَالُوا۟ يَٰمَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْـًۭٔا فَرِيًّۭا
በእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡
*ሱራህ 19, አያህ 28*
يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ ٱمْرَأَ سَوْءٍۢ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّۭا
«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡

የክፍሉ የግርጌ ማብራሪያ ላይ ማሪያም #የሙሴ ወንድም #የአሮን #እህት እንደሆነች ይናገራል።
ይህ ደግሞ #ከክርስቶስ #ልደት በፊት 1500 #ዘመን ዘሎ #የአሮንን ዘመን #ከክርስቶስ እናት #ማርያም ጋር በምን #አይነት ሂሳብ እንዳጠጋጋው እንጃ??

▶️ "የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን" ደግሞ #ሁለት #ተቃራኒ ሀሳቦችን ታስቀምጣለች፦

1ኛ👉 <"የዮሴፍ የወንድም ልጅ ናት">

<<የእስራኤል ሽማግሎችና መምህራንም አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችን #የአባቷን #ወንድም #ዮሴፍን ወደ በአደባባይ . . . አደራ ያስጠበቅንህን #የወንድምህን #ልጅ #እጮኛህ #ማርያምን. . .[3]>>

በመሰረቱ "የዮሴፍ የወንድም ልጅ ናት" የሚለው #መጽሐፍ ቅዱስ ዮሴፍ #የማርያም #እጮኛ እንጅ አጎት(የአባት ወንድም) መሆኑን አይናገርም።
ምናልባት #ወንድሙ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው አባቷ #ኢያቄም ይሆን?? ብለን እንዳንገምት እንኳን። #ኢያቄም ወንድም እንዳልነበረውና #ለእናቱም #ለአባቱም አንድ እንደሆነ በሌሎች #መጽሀፍቶቻቸው ላይ ተጽፏል[4]። <የወንድምህን ልጅ እጮኛህን> ማለት በምን ዓይነት ቋንቋ እንደሆነ እንጃ!!

2ኛ👉 <"ማርያም የሃናና የኢያቄም ልጅ ስትሆን አያቷም #ቅስራ ነው"> ትላለች።

ማርያም " #የሃናና #የኢያቄም ልጅ" መሆኗን ለመጀመሪያ ጊዜ #ያለምንም #መረጃ የጠቀሰው " #በተአምረ #ማርያም" መጽሀፍ < #አጼ #ዘረያቆብ> ነው።/በ 1426-1460/ ዓ.ም።
በመቅድሙ ላይ "ስመ አቡሃ ኢያቄም ወስመ ወላዲታ ሐና -የአባቷም ስም ኢያቄም ነው የእናቷም ስም ሐና ነው" ብሏል[5]።

▶️ የ" #ዘውትር #ፀሎት" ድርሳኑም ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል።
ቡሀላ ግን ከእነዚህ #ኑፋቄ #ትምህርት ከገባባቸው #አዋልድ #መጽሀፍት በስተቀር
<•የሀናና የኢያቄም ልጅ•> ናት ብሎ ያመነ #የቤተክርስቲያን #አባት አንድም እንኳ እንዳልነበረ አንድ መጽሀፍ ሲገልጽ
<<እም ሐና ወኢያቄም ተወለድኪ - ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ>> የሚለው #የሃገራችን #ደራሲያን የሚናገሩት #ቃል ነው እንጅ #ከአገር ውጪ ያሉ #አቢያተ #ክርስቲያናት ጠቅሰውት አያውቁም።
<ሐና ኢያቄም> የሚል ቃል #በሃይማኖተ #አበው መጽሀፍ ላይ ድርሰታቸው የተሰበሰበላቸው #ከ55 በላይ የሆኑ #ሊቃውንቶች ይህንን #ቃል አልጠቀሱም። ከእነዚህም በተለይ #እነቅዱስ #ኤፍሬም#እነዩሐንስ #አፈወርቅ አመሰገኗት የሚባሉት ላይ እንኳን እነዚህ ቃላቶች #አልተጠቀሱም ይላል[6]።
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ ከላይ እንዳየነው አንዳንዶች #የስሙን ሙሉ #ሐረግ ተከትለው ሌሎች ለሁለት ከፍለው #ለመተርጎም ከሞከሩት #ውጪ ሌሎች ደግሞ ከዚህ በተለየ መንገድ #ማርያም የሚለውን ስም #ለማብለጥ ወይም #ከፍ #ለማረግ ሲሉ #ማርያም ስለሚለው #ስም #ትርጉም #የአማርኛውን ወይም #የግእዙን ሆህያት ብቻ ተከትለው #ፊደል #በፊደል እየከፋፈሉ #በግእዝ ቋንቋ #በግጥም መልክ ይተረጉማሉ።👇👇 ✳️👉 ማኅደረ መለኮት…
▶️ 'አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫና አፄ ዘርዓ ያዕቆብ' በመጽሐፋቸው <ማርያም> የሚለውን #ስም ባለመቀበል <ማሪሃም> በሚለው አስተካክለው <<በዕብራይስጥ እመቤታችን ስሟ "ማሪሃም" ነው>> ብለዋል[5]።

▶️ ትርጓሜው ግን በግልጽ ባይቀመጥም "ነገረ ማርያም" #በመጽሐፉ ሲተረጉመው <የሁሉ እናት ማለት ነው> ይላል[6]።

▶️ አጼው ሆነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #በአርጋኖን መጽሐፋቸው ስሟ <ማሪሃም> ነው ማለታቸው 'አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ' በመዝገበ ቃላታቸው መጽሐፍ <ማርያም> የሚለውን <ማሪሃም> ማለትም #ስህተትና #አላዋቂነት ነው ብለዋል[7]።

▶️ እንግዲህ ከላይ ያየናቸው ትርጉሞች ሁሉ #ቅድስት #ድንግል #ማርያምን #ማእከል ያደረገና ስለእሷ ከሰበኩ #አጼዎች ጋር #ለማስማማት #የተፈጠረ #ተራ #መላ #ምት እንደሆነና #ከስሟ #ትርጉም ጀምሮ #ከቃለ #እግዚአብሄር ውጪ እንደሆነ አይተናል።

▶️ አንድ ሰው ደግሞ #ስሙን ሌላ #ማንም ሰው ቢይዘው ወይም አንድ #አይነት ቢሆን ሊኖር የሚችለው #ትርጉም ግን አንድ ብቻ ነው። #አንድ #ስም #ከአንድ በላይ #ትርጉም ሊኖረው አይችልም።
[ለምሳሌ ያክል #በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ " #ዩሐንስ" የሚለውን ስም ብዙዎች #መጠሪያቸው አድርገው ከተጠቀሙት መካከል

✳️ ሐዋሪያው ዩሀንስ {ማቲ 1፤1-4}
✳️ ማርቆስ የሚሉት ዩሐንስ {ሐዋ 12፥12}
✳️ መጥምቁ ዩሐንስ {ማር 1፥1-4} የሚጠቀሱ ናቸው። ይሁን እንጂ #ዩሐንስ የሚለው #የስሙ ትርጉም <<እግዚአብሔር ጸጋ ነው>> ማለት ነው[8]። ስለዚህ #በአንድ #አይነት #ቋንቋ ለተነገረ ለማንኛውም #ስም የተለያየ #የስም #ትርጉም ሊኖረው ፈጽሞ አይችልም። #አንድ #ስም ከአንድ #ትርጉም በላይ ሊወክል አይችልምና።

▶️ በመሆኑም 'በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ' #መዝገበ #ቃላት #ትርጉም መሰረት #ማርያም ማለት <መራራ ዘመን> ማለት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ #ስሙን የተጠቀመችው #የሙሴ #እህት #ማርያም ሆና #የስሙ #መነሻነት 'ዮሴፍ' ያደረገውን ውለታ ያላወቀ 'ፈርኦን' የሚሉት #አዲስ #ንጉስ #በግብጽ ተሹሞ #በሃገሪቱ ውስጥ #እስራኤላውያን #እንደበረቱና #እንደበዙ አይቶ #ከጠላቶቻችን ጋር #አብረው ሆነው #ሊዋጉን ይችላሉ በሚል #ስጋት በከባድ ጭቆና #ሲገዛቸውና የሚወለዱ #ወንዶችን ሁሉ #እንዲገድሉ #ትዕዛዝ በመስጠቱ #የወንድሟ #የሙሴ መወለድ #ቤተሰቧን #በማሳሰቡ #ለ3 ወራት እንዳይሞት #በጭንቅ #ደብቀው #ለማሳደግ ቢሞክሩም #ወሬም እየተሰማ ስለመጣባቸው #በሳጥን አርገው የተወለደውን ልጃቸውን ተገደው #በባህር ላይ #ሰለጣሉት #የወቅቱ #የአገዛዝ ስርአት #ቤተሰቦቻቸው ላይና #ዘመዶቻቸው ላይ #መራራ #ዘመን ስለሆነባቸው #የሙሴ #እናት የሴት ልጇን ስም <ማርያም> ወይም #መራራ #ዘመን ብለው ሰይመዋታል[9]።

️ሙሴንም ቢሆን #የንጉስ #ፈርኦን #ሴት ልጅ #ከባሕር አግኝታ ስላሳደገችው <ሙሴ> ትርጉሙም < #ከባህር #የተገኘ> ብላዋለች።
በተጨማሪም ከዚህ <ከአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ> መዝገበ ቃላት #ትርጉም ጋር በተመሳሳይ <የአለቃ ደስታ ተክለወልድ መዝገበ ቃላት> #መጽሀፍም #የማርያምን #ስም #ትርጉም ያብራራል[10]።

▶️ በመሆኑም #በመጽሀፍ #ቅዱስ ውስጥ #በማርያም #ስም የተጠሩ #ሴቶች ሁሉ በዘመናቸው #የፖለቲካ ወይም #የማህበራዊ ችግር ሲደርስባቸው የነበሩ መሆናቸውና #የስማቸው መጠሪያም <<መራራ ዘመን፣ Bitterness>> ወይም <ማርያም> ይሉት እንደነበር መረዳት አያዳግትም።
🔽 ለምሳሌ፦
<ቅድስት ድንግል ማርያም> ትኖርበት በነበረበት #ዘመን #እስራኤል #በሮም #መንግስት #ቀኝ ግዛት ስር ስትሆን #ሄሮድስ በወቅቱ #የሮም መሪ ከነበረው <ከአንቶኒ[11]> #ድጋፍ አግኝቶ #በሮም ምክር ቤት <የአይሁድ ንጉስ> በሚል ስያሜ #እስራኤልን #ሲገዛ እንደነበር ይታወቃል። በወቅቱ #አይሁዳውያንም ጠልተውትና #በሮም መንግስት ስር መሆናቸውን #በመቃወም እስራኤል ሁከት የሰፈነባት፣ ጭካኔ የሞላባት፣ የእርስ #በእርስ መጠላላት እንኳን ሳይቀር የነገሠበት ጊዜ ነበር። #ንጉሥ #ሄሮድስም እጅግ #ጨካኝ ከመሆኑ የተነሳ #መንግስቴን #ይወርሱኛል ብሎ የጠረጠራቸውን <2 ሚስቶቹንና 2 ወንድሞቹንም> ሳይቀር #የገደለበት ጊዜ ነበር። #በዚህም #ምክንያት <ከ27 ዓ.ዓ እስከ 14 ዓ.ም> #የሮም ንጉሥ የነበረው <አውግስጦስ[12]> <<የሄሮድስ ልጅ ከመሆን አሳማ መሆን ይሻላል!!>> በማለት በግልጽ ተናግሮ ነበር። #ሄሮድስ #ሰብአ ሰገል የተወለደውን መሲህ #ኢየሱስን <የአይሁድ ንጉስ> ብለው #በመጥራታቸው ነገሩን በጥንቃቄ #መርምሮ #ኢየሱስ #ክርስቶስን ለመግደል ባደረገው ጥረት #በቤተልሔም ውስጥ በወቅቱ የተወለዱትን በጣም #ብዙ #ህጻናት #ከእናቶታቻቸው ጉያ በመንጠቅ #በሰይፍ #ቆራርጦአቸዋል። በዚህም #ምክንያት <በነብዩ በኤርምያስ> የተተነብየው [ኤር 31፤15-16] <ድምጽ በራማ ተሰማ ልቅሶና ብዙ ዋይታ ራሔል ስለልጆቿ አለቀሰች የሉምና መጽናናትን ስለልጆቿ እንቢ አለች> የተባለው ተፈጸመ[13] {ማቲ 2፤16}።

️ማርያም በዘመኗ ሁሉ ብርቱ #የመከራ #ዘመን እንደምታሳልፍ ተነግሯት ነበር [ሉቃ 2፤35]። #ሄሮድስ #ህጻናትን ሲያስገድል በወቅቱ #በመልአኩ #ምሪት #ማርያምና #ዮሴፍ ህጻኑን (ኢየሱስ ክርስቶስን) ይዘው ወደ #ግብጽ ተሰደዋል። #ሄሮድስም እንደ #ሞተ ሰምተው ቢመለሱም #ልጇ #ኢየሱስ ክርስቶስ ባሳለፈው #ህይወትና #ሲሰቃይ ማየቷ #በእንጨት ላይም #ሲሰቅሉት #ማየቷ በአጠቃላይ እንደ ስሟ #ዘመኗ <መራራ ዘመን> ሆኖባታል።

️ በመሆኑም #ማርያም የተባሉ ሁሉ በተመሳሳይ #ሁኔታ #ዘመናቸው #መራር የሆነባቸው #ሰዎች ነበሩ እንጂ ከላይ አንዳንዶች እንደተረጎሙት የተለያየና፣ የተሳሳተ #ከእውነትም #የራቀ አልነበረም። እነዚህ መተርጉማን ስለማርያም የሰጡት ሃተታ #ቋንቋውንና #ታሪካዊ ዳራውን ያላገናዘበ፣ ከልዩ #ባእድ #አምልኮ መሻት #የመነጨና #ከእውነት የራቀ ብቻ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4፥6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
______________
[1] 📚፤ የኢትዮጵያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር "የመጽሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት" 8ተኛ እትም 1998 ዓ.ም *ገጽ 51።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ውዳሴ ማርያም ንባቡና ትርጓሜው፤ ዘሠሉስ *ገጽ 45። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1983 ዓ.ም።

📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ <ወንጌል ቅዱስ ንባቡና ትርጓሜው>፤ ዘሉቃስ ፧ *ገጽ 265፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ 1997 ዓ.ም።

📚፤ <ነገረ ማርያም> *ገጽ 28-31። ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ 1991 ዓ.ም።

📚፤ ብርሃኑ ጉበና "አምደ ሃይማኖት" *ገጽ 91። 1985 ዓ.ም።

📚፤ ሚልዮን በለጠ አሰፋ፤ <ቅዱሳት ስዕላት አመጣጥና ታሪክ ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር> ፤ *ገጽ 25-26። 1994 ዓ.ም።

[3] 📚፤ <ነገረ ማርያም>፤ *ገጽ 28-30፤ ተስፋ ገብረ ስላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1991 ዓ.ም።

[4] 📚፤ ሚሊዮን በለጠ አሰፋ
"ቅዱሳን ሥዕላት አመጣጥና ታሪክ ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር" *ገጽ 26። አለም ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ መጋቢት፥ 1994 ዓ.ም።

📚፤ <ነገረ ማርያም> ፤ *ገጽ 29፥ ተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1991 ዓ.ም።

[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም፤ መቅድም ቁ.4 *ገጽ 3፤ 3ተኛ ዕትም፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት አ.አ፤ 1989 ዓ.ም።

📚፤ <አርጋኖን> የእመቤታችን ምስጋና፤ ዘሰኑይ ምዕራፍ 6 ክፍል 4፤ ተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1996 ዓ.ም።

[6] 📚፤ ነገረ ማርያም፤ *ገጽ 34

[7] 📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ <ማርያም>፤ *ገጽ 610፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1948።

📚፤ Dr. Strong፥ "Exhaustive Concordance of the Bible" HEBREW AND CHALDEE DICTIONARY፥ pp 72 no.4805፣ 4813

〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Miriam_(name)

[8] 📚፤ የኢትዮጽያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር፤ <የመጽሀፍቅዱስ መዝገበ ቃላት>፤ 7ኛ እትም፤ <ዩሐንስ> *ገጽ 222። ንግድ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ 1996 ዓ.ም።

📚፤ Douglas & Tenney by International Bible Society Bible Dictionary፤ John pp. 532, 1987።

📚፤ Truesdale, Lyons, Eby clark, A Dictionary of the Bible & Christian Doctrine in every day English, United Bible Societies, 1978፥ pp 155-156.

[9] 📚፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ <ማርያም> የስም ትርጉም። *ገጽ 610፥ 1948 ዓ.ም።

[10] 📚፤ አለቃ ደስታ ተክለወልድ፤ መጽሀፈ ሰዋሰው ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡ <ማርያም>፤ *ገጽ 808 1ኛ ዕትም፥ 1945 ዓ.ም።

[11] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Mark_Antony

[12] 〽️ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Augustus

[13] 📚፤ S I M፤ <የአዲስ ኪዳን ታሪካዊና ባህላዊ መሰረቶች> ፥ *ገጽ 22-23፤ ኤስ አይ ኤም ማተሚያ ቤት፥ አ.አ፤ 1993 ዓ.ም።

(2.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ ማርያም #ስለመሲሁ የመምጣት #ተስፋ ብታውቅም እንዴት #እንደሚፈጸም ግን አታውቅም ነበር። #በሉቃ 1፥34 ላይ #አለማመኗን የሚያሳይ ሳይሆን #እምነቷን የሚገልጽ ነበር። አንዲት #ልጃገረድ እንዴት #ከወንድ ጋር #ሳትገናኝ #ልትወልድ ትችላለች ብላ በማሰቧ #እጮኛዋ ከሆነው #ከዮሴፍ ጋር #ባለመጋባቷና #ግንኙነት ፈጽማ ባለማወቋ #መልአኩን <<ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?>> ብላ ጠየቀችው። #መልአኩም ይህ #በመንፈስቅዱስ የሚፈጸም #ተአምር እንደሆነ ነገራት። ደግሞም #ከአዳም #የውርስ ኃጥያት #በመንፈስቅዱስ መጸለል(መጋረድ) ምክንያት የሚወለደው #ህጻን <ቅዱስ> እንደሚሆን አመለከታት።

▶️ መልአኩ #መልእክቱን የደመደመው ለማርያም #የማጽናኛ #ቃል በመስጠት ነበር። ይኸውም #በዕድሜ የገፋችው ዘመዷ #ኤልሳቤጥ #ወንድ ልጅ #መጸነሷና 6ኛ ወሯ መሆኑን በመግለጽ #ለእግዚአብሄር #የሚሳነው ነገር የለምና አንቺም #መጸነስ ትችያለሽ በማለት #አስረዳት

▶️ ከዚህ ቡኋላ #ማርያም እንደታዛዥ #ባርያ ራሷን #ለእግዚአብሄር #በመስጠት <<እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ>> በማለት #የእምነት #ምላሽ ሰጠች {ሉቃ 1፥38}። መልአኩም ይህን #ውይይት እንደጨረሰ ከእርሷ ተለይቶ #ሄ

▶️ እንግዲህ በዚህ #ውይይት ውስጥ እጅግ #ዝቅተኛ #የኑሮ #ደረጃ ውስጥ ትኖር የነበረች #ልጃገረድ #የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈጸም #ለጌታ ሙሉ በሙሉ ራሷን #መስጠቷን ስናይ እንዴት የሚገርም ነው ያሰኛል። #ማርያም በእርግጥም #ለእግዚአብሄር #የተሰጠች #ሴት ነበረች። ይሁን እንጂ በአሁኑ #ዘመን በዚህ 'በቅድስት ድንግል #ማርያምና በቅዱስ #ገብርኤል' መካከል የተደረገውን #ውይይት ከተጻፈው #ውጪ በርካታ #የሃይማኖት መጽሐፍት በተለይም #አዋልድ መጽሐፍት #ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊ ጽንፈኛ #አስተምህሮቶችን ለብዙ ዓመታት #ሲያንጸባርቁ ቆይተዋል። ከዚህም የተነሳ ማርያምን የሃይማኖታቸው ማዕከል ያደረጉ በርካታ መናፍቃን ስለመነሳታቸው ታሪክ ይዘግባል።

👉 ለምሳሌ #የዘውትር ጸሎት መጽሐፍ የሆነው <<ይወድስዋ መላዕክት - መላዕክት ማርያምን ያመሰግኗታል>> በሚለው አርስቱ <<መልአኩ ገብርኤል ማርያምን •ድንግል ለአንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል• አላት፣ •ወላዲት አምላክ ምስጋና ይገባሻል•፣ •ቅድስት ነሽና ምስጋና ይገባሻል•፣ •የመለኮት ማደሪያ ነሽና ምስጋና ይገባሻል•፣ •የተሸለመች ድንኳን ነሽና ምስጋና ይገባሻል•፣ •የሁሉ እመቤት ማርያም ምስጋና ይገባሻል•፣ •የሁሉ ፍቅረኛ ማርያም ምስጋና ይገባሻል•፣ •ልዑል ማደሪያው ትሆኚ ዘንድ መርጦሻልና ምስጋና ይባገሻል•፣ •በወርቅ የተሸለምሽ የርግብ ክንፍ በብር ያጌጥሽ ምስጋና ይገባሻል•፣ •ጎኖችሽ በወርቅ አመልማሎ የተሸለሙ ለአንቺ ምስጋና ይገባሻል•፣ •ከጸሀይ 7 እጅ የምታበሪ ክብርሽ ከአድባራቱ ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ ለአንቺ ምስጋና ይገባሻል•[3]>> ይላል። ይህ #ጸሎት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ #በቃል አልያም #በንባብ ዘውትር ወደ #ማርያም የሚቀርብ #ምስጋና ነው።

▶️ ይሁን እንጂ #ቆም ብለን በእውኑ ከላይ የተገለጸውን #ንባብ (አንቀጽ) #ቅዱስ ገብርኤል የተናገረው ነውን? #መላእክትስ ማርያምን #ያመሰግኗታልን? እኛስ እንዲህ ያለውን አንቀጽ አስቀምጠን ወደ #ማርያም #እንድንጸልይ (እንድናመሰግን) #ሕግ ተሰጥቶአልና? ብለን ብንጠይቅና ለማየት ብንሞክር ፈጽሞ የሌለና #ያልተባለ ወደፊትም #የማይባል እንደውም #ኃጢአት እንደሆነ #መጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ ይናገራል።

▶️ በመሆኑም #መላእክት #የሚያመሰግኑትንና #ምስጋና #የሚገባውን ጠንቅቀው ስለሚያቁ ሲያመሰግኑ እንዲህ ይላሉ፦

<<በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።. . . በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን. . . በረከትና ክብር ጥበብም ምስጋናም ውዳሴም ኃይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤ አሜን አሉ።>>

የሚል ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ አምልኮና ምስጋና ብቻ ነው {ራዕ 5፤10፣ 12-13;፣ ራዕ 7፥12፣ በተጨማሪም ራዕ 4፥8፣ 11፥15፣ 12፥10፣ 15፥3፣ 19፥1. . .።}

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ ወንጌል ቅዱስ፡ ሉቃስ አንድምታ 1፥47፣ ገጽ 268። ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1997 ዓ.ም።

[2] የእግዚአብሄርም ቃል <<ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥>> {1ኛ ቆሮ 1፤ 27-28} የሚለው ለዚሁ አይደል??

[3] የዘውትር ጸሎት መጽሐፍ <ይወድስዋ መላእክት> ቁ.3።


(4.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
▶️ እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉት #ሀሳቦች በሙሉ #የተፈለሰፉት #ማርያም <<ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች>> እንደሆነች #መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚናገር በማሰብ ሲሆን ከላይ እንደተገለጸው #ከእግዚአብሄር #ቀጥላ #ሁለተኛ #አምልኮት የሚቀርብላት ሆናለች። ነገር ግን #መልአኩ #ገብርኤልም፣ #ኤልሳቤጥም የተናገሩት አንድ አይነት ቃል <<ከሴቶች በላይ፣ ከፍጡራን ሁሉ በላይ>> ሳይሆን <<ከሴቶች #መካከል>>…
▶️ እስቲ እነዚህን ጥቅሶች ይመልከቷቸው።

〽️ ሐዋ 1፤ 9-11፦

<<ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።>>

⁉️ #ኢየሱስ ወደ #ሰማይ ሲያርግ ሁሉም #ደቀመዛሙርትና #ሴቶች #ማርያምም ጭምር #በደብረ ዘይት ተራራ #ዕርገቱን ሲመለከቱ ሁለቱ #መላእክት በአጠገባቸው #ቆመው < #ለማርያም ብቻ> ወይም < #በማርያም #በኩል> ሳይሆን የተናገሩት ለሁሉም #በእኩል አይን <<የገሊላ ሰዎች ሆይ...>> በማለት ነበር።

〽️ ሐዋ 1፤ 12-14፦

<<በዚያን ጊዜ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው። በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፥ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም። እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።>>

⁉️ #ከክርስቶስ #እርገት ቡሀላ ወደ #ኢየሩሳሌም ሲመለሱ #ማርያም #ከሐዋሪያቶቹ ጋር ሌሎችም #በርካታ #ሴቶች ያለምንም #ልዩነት ለአንድነት #ለጸሎት #ይተጉ ነበር። ይህ ደግሞ #ማርያም #ከፍጡራን #የተለየች ወይም #ወጣ ያለች እንዳልነበረች አንብቦ #መረዳት አያቅትም።

〽️ ሐዋ 1፥15፦

<<በዚህም ወራት ጴጥሮስ መቶ ሀያ በሚያህል በሰዎች ማኅበር አብረው በነበሩ በወንድሞቹ መካከል ተነሥቶ አለ።>>

⁉️ የጸሎቱም #መሪ ሐዋሪያው #ጴጥሮስ ነበር እንጂ #ማርያም #ከጉባኤው ጋር #ምእመን ከመሆን ውጪ #የአምልኮው #መሪ እንኳን አልነበረችም። ይህ #ከፍጡራን #የተለየች ናት እንድንል አያደርገንም።

〽️ ሐዋ 1፥16፦

<<ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤>>

⁉️ ማርያም ባለችበት #ጉባኤ ተነስቶ <<ወንድሞች ሆይ>> በማለት #በቀጥታ #ንግግሩን ጀመረ እንጂ #በመካከላቸው ለነበረችው #ማርያም #ስግደት ወይም የተለየ #አክብሮት አላቀረበም። ይህም ከእነሱ #የተለየች እንዳልነበረች ያስረዳል።

〽️ ሐዋ 1፤ 21-22፦

<<ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።>>

⁉️ አሁንም ሐዋሪያው #ጴጥሮስ #ማርያም ባለችበት በዚህ #ጉባዔ #በይሁዳ ምትክ ሌላ #ሐዋሪያ እንዲተካ #ሃሳብ ሲያቀርብ <<ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር #የትንሳኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል>> አለ እንጂ ስለ #ማርያም #ምስክር የሚሆን አለማለቱ በአሁኑ #ዘመን ለእኛ #ምስክርነታችን መሆን የሚገባው #ስለክርስቶስ እንጂ #ስለማርያም #መመስከር #የሐዋሪያት #ትምህርት እንዳልሆነ #የሚያስረዳ ነው።

〽️ ሐዋ 1፥25፦

<<ሲጸልዩም። የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ፥ ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው አሉ።>>

⁉️ ይሄው ጉባዔ #ማርያም ባለችበት <<ሲጸልዩም የሁሉንም ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ>> ብለው #ቀጥታ ወደ #ጌታ ጸለዩ እንጂ እሷ #ከፍጡራን #በላይ ነች ብለው ወደ #ማርያም ወይም #በማርያም #ስም #አልጸለዩም። ይህም በግልጽ #ማርያም #ከሰው #የተለየች እንዳልሆነች ያሳያል።

〽️ ሐዋ 2፤ 1-4፦

<<በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው>>

⁉️ በዓለ #ሀምሳ የተባለውም #ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም #በአንድ #ልብ ሆነው አብረው ሳሉ #መንፈስቅዱስ #በጉባዔው መካከል ከነበረችው #ከማርያም ወይም #በማርያም #በኩል ሳይሆን #ከሰማይ #መምጣቱ አንዳንዶች እንደሚሉት #ማርያም #መለኮታዊ መነሻ ወይም #ምንጭ ወይም #ሰጪ እንዳልሆነችም ያስረዳናል።

〽️ ሐዋ 2፤ 3-4፦

<<እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።>>

⁉️ #መንፈስቅዱስም ሲወርድ ሁሉም ላይ #እኩል ወረደ እንጂ #ለማርያም የተለየ #ጸጋ(መንፈስ) አለመሰጠቱ #በእግዚአብሄር ፊት ያው እንደማንኛውም #ክርስቲያን #እኩል እንደሆነች #እንጂ የተለየች ወይም #ከፍጡራን #የምትበልጥ እንደሆነች አያሳይም።

〽️ ሐዋ 2፤ 5-10፦

<<ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ። እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን?...>>

⁉️ #በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት #አይሁዶች በሁሉም ላይ #ከወረደው #ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ በገዛ #ቋንቋዎቻቸው ሲናገሩ እየሰሙ በሁሉም ተገረሙ እንጂ #ለማርያም የተለየ #አትኩሮት አልሰጡም። ይህም #ማርያም እንደነሱ #እኩል #ማንነትና #ጸጋ እንደነበራት ያሳያል።

〽️ ሐዋ 2፤ 9-12፦

<<የጳርቴና የሜድ የኢላሜጤም ሰዎች፥ በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም፥ በፍርግያም በጵንፍልያም በግብፅም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊቢያ ወረዳዎች የምንኖር፥ በሮሜም የምንቀመጥ፥ አይሁድም ወደ ይሁዲነትም የገባን፥ የቀርጤስና የዓረብ ሰዎች፥ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።...>>

⁉️ እነዚህ #የኢየሩሳሌምና #የአረብ ሰዎች <<የእግዚአብሄርን ታላቅ ስራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን>> አሉ እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት #የማርያምን #ታላቅ #ስራ ሲናገሩ #ሰማን ስላላሉ እንደ ሐዋሪያት #ምስክርነታችን <<የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራ>> እንጂ #ስለማርያም #መስበክ #የሀዋሪያት #ፈለግ እንዳልነበረ ያስተምረናል።
▶️ ይህም #ቤተመቅደስ #ማርያም በነበረችበት #ዘመን የነበረ ሲሆን ሁሉም #ሴቶች #በቁ.4 ላይ በተገለጸው ውስጥ በፍጹም #አይገቡም ነበር። ይሁን እንጂ #በውጭ (በተራ ቁ.7 ላይ) በተገለጸው #አደባባይ ላይ እንደ #የ91 ዓመቷ ዕድሜ #የፋኑኤል ልጅ #ሃና #ነብይት ዓይነቶች {ሉቃ 2፤ 36-38} #መቆም ይችሉ ነበር።

እስከዛሬም ድረስ የትኛዋም #ሴት ብትሆን #ቤተመቅደስ (ቅድስተ ቅዱሳን) ውስጥ #መግባት አልቻለችም። #ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን #ሴቶች ወደ #ቤተ መቅደስ እንዲገቡና #በመቅደስ ውስጥ #እንዲጸልዩ ለአፍታ እንኳ አለመፍቀዷ የራሷ #ስርዓት #ይደነግጋል[1]።
ታድያ #ማርያም በየትኛው #ቦታ በየትኛው #ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ #መኖሪያዋ አድርጋ አደገች? አዎን #ማርያም #ቤተ መቅደስ ነበረች የሚለው #ሃሳብ ከየት መጣ ቢባል #ከቁርዓን ነው {ሱረቱ አልዒምራን 3፥37}። እርሱም #ስለቤተ መቅደሱ ሁኔታ #እውቀት የለውምና አይፈረድበትም።
<<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን የተቀነባበረ <የጸሎት> ክፍል #በኢየሱስ ክርስቶስ #አስተምህሮ #ወቅት ብቻ ሳይሆን ከእሱ ቡሀላም ለብዙ #ዘመናት አልነበረም። ምናልባትም ሌሎች እንደሚሉት #ማርያም ገና #ክርስቶስን ሳትወልድ የነበረ #የገብርኤል #ሰላምታ ነው ተብሎ እንዳይወሰድ እንኳን #መልአኩ መጥቶ ያደረገው #ውይይት እንጂ #ጸሎት አይደለም። #ክርስቶስም #ለደቀመዛሙርቱ #ጸሎት ባስተማረበት #ወቅት #የገብርኤልንም #ሰላምታ ጨምሩበት በማለት ባስተላለፈ ነበር፤ ያንን ደግሞ አላደረገውም [ማቴ 6፤ 1-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]። << #በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ....>> የሚለው #የጸሎት #አስተምህሮቱን #ድንግል ማርያምን በትክክል በሚያውቋት #በደቀመዛሙርቱ ፊት ምናልባትም #በአስተምሮው #ወቅት ብዙ ጊዜ በምትገኝዋም #በድንግል #ማርያምም በራሷ ፊትም ተናግሯል።

▶️ ስለሆነም የተቀነባበረው <<የማርያም የጸሎት>> ምዕራፍ #በክርስቶስ #ወቅት ያልነበረ ከዚያም ቡኋላ #ሐዋሪያቱ #በአገልግሎታቸውና #በጸሎታቸውም ወቅት የማያውቁትና #የጥንት #ቤተ ክርስቲያን #አባቶችም በልዩ ልዩ ምክንያት #ጉባኤ ሲያደርጉ ለምሳሌ፦ #በኒቂያ ጉባኤ #በ325 ዓ.ም 318 የሃይማኖት አባቶች በእነ #እስክንድሮስ አፈጉባዔነት በንጉስ #ቆስጠንጢኖስ ዘመን ተሰብስበው #አርዮስን <<ወልድ #ፍጡር ነው>> ያለበትን #የክህደት ትምህርት #ሲያወግዙና #የሃይማኖት መግለጫ ሲያወጡ #ኢየሱስን ከመውለዷ ውጭ #ስለማርያም ፈጽሞ #መሠረታዊ #ትምህርት እንኳ በወቅቱ እንዳልነበረ መረዳት ይችላል። እንዲሁም #በቁስጥንጥንያ #በ375 ዓ.ም 150 #የሃይማኖት #አባቶች #በጢሞቴዎስ ዘአልቦጥሪት በንጉሥ ዘየዓቢ #ቴዎደስዩስ ወቅት #መቅደንዩስ << #መንፈስ ቅዱስ #ሕጹጽ ወይም #ሀይል ብቻ>> ብሎ በተነሳ ጊዜ ተሰብስበው #አውግዘው ትምህርቱንና እርሱን ሲለዩ #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #የአስተምህሮ #መግለጫ ሲያወጡ ያኔም ቢሆን #ኢየሱስን #ከመውለዷ ውጪ #ስለማርያም ያስተላለፉት ምንም #አዲስ #ትምህርት የለም። #በኤፌሶን ሀገርም #በ435 ዓ.ም 200 #የሃይማኖት #አባቶች #በቄርሎስ አፈጉባዔነት በቴዎደስዩስ ዘይንእስ ንጉሥነት ጊዜ ንስጥሮስ << #ክርስቶስ #ሁለት #አካል #ሁለት #ባህሪይ ነው>> ብሎ ሲነሳ #እርሱንም #ትምህርቱንም #አውግዘው #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #አስተምህሮ በመግለጫ መልክ ሲያስቀምጡ ድንግል #ማርያም #ክርስቶስን እንደወለደች ብቻ እንጂ << #እመቤታችን>> ብለውም ሆነ << #ለምኝልን>> የሚል አስተምህሮ አያውቁም። #ጤናማ #አስተምህሮ አይደለምና።

▶️ ዛሬ ሁሉም #አብያተክርስቲያናት የሚቀበሉት #ሙሉ #የሃይማኖት #መግለጫቸው

<<ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን የተፈጠረ ሳይሆን የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምን ምንም የሆነ የለም በሰማይም ያለ በምድርም ያለ ስለእኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፈጽሞ ሰው ሆኖ በጴንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ ሞተ ተቀበረም በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና ሙታንንም ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም ጌታ ማህየዊ በሚሆን ከአብ በሰረጸ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋሪያት በሰበሰባት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሰረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።>> የሚል ነው።

ይህንንም መግለጫ #በ1530 ዓ.ም #ሉተራውያን << #የአውግስበርግ #መግለጫ>> በሚል አጸደቁ። እንዲሁም #በ1546 ዓ.ም #ካቶሊክ በድጋሜ << #የትሬንት #መግለጫ>> በማለት አጸደቀችው። #በ1571 ዓ.ም ደግሞ #የአንግሊካን #ቸርች መግለጫውን ተቀብላ አጸደቀችው። #በ1646 ዓ.ም #ፕሪስቢቴሪያን << #የዌስት #ሚኒስቴር #መግለጫ>> በሚል አጸደቀችው[1]።

▶️ ኦርቶዶክስ #ቤተክርስቲያን መግለጫውን በድጋሜ << #ጸሎተ #ሃይማኖት>> በማለት #በ1426-1460 ዓ.ም በኢትዮጵያ የነገሰው #አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ ሙሉውን ተቀበሉና ሌላ #በመጨመር << #ለማርያምና #ለእፀ መስቀሉ (ለመስቀሉ እንጨት) #ስግደት ይገባቸዋል>> በማለት እንዲሁም <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን <<ከአባታችን ሆይ>> #ቀጥሎ እንዲባል ብሎ #አዋጅ አወጣ። ከዚህም የተነሳ በርካታ #ካህናት << #አባቶቻችን ካስቀመጡት #ከሃይማኖት #መግለጫው ውጪ ተጨማሪውን #አንቀበልም>> በማለታቸው #በሰይፍ እንደቆራረጣቸውና እንዳሳደዳቸው #ገድለ #እስጢፋኖስ#ገድለ #አበው ወአኀው፣ #ገድለ #አባ አበከረዙል፣ #ገድለ #አባ ዕዝራ፣ #ገድለ #ደቂቀ እስጢፋኖስን ማንበብ #በቂ ነው።

▶️ ነገር ግን #በዘር #ቅብብሎሽ አማካኝነት የነበረው #የንግስና #ሥርአት ለዚህ <<አዳራሻውን ወደ ሳተው ጸሎት>> ሰፊ እድል አግኝቶ #ሰይፍ ያስፈራቸውና በክርስትናው #ትምህርት ብዙም #መሰረታዊ #እውቀት ያልነበራቸው #ህዝብና #ካህናት #የጸሎት #ምዕራፋቸው አድርገው ለቀጣዩ #ትውልድ በማስተላለፋቸው ይሀው አሁን የምናየውን #ከእግዚአብሄር #ቃል ውጪ የሆነ #ትውልድ ፈጥረውልናል። ዛሬ ዛሬ #በየጸሎቱ #መዛግብት ውስጥ እየተጨመረ ተጽፎ #ምዕመናን ሁሉ #በቀን ቢያንስ #አንድ ጊዜ እንዲደግመው በመደረጉ እንግዳው <<ጸሎት>> #የተለመደ ሆኖ ቀረ። እንዲያውም በዚህ #ዘመን አስቀድመን እንዳልነው <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል #ጥቅሶችን ያለቦታቸው እንደ #ስጋ #ዘንጥለውና #በጣጥሰው #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል የሚታገሉ ተነስተዋል። እኛ ግን <<የእግዚአብሔርን ቃል #ቀላቅለው #እንደሚሸቃቅጡት እንደ #ብዙዎቹ አይደለንምና፤ #በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ #ተላክን #በእግዚአብሔር ፊት #በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።>> [2ቆሮ 2፥17]

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን፤ አውግስበርግ ሃይማኖታዊ መግለጫ፤ በአማርኛ የተተረጎመ፤ አ.አ፥ 1993 ዓ.ም።
▶️ የሰውነት #አካላትን እየዘረዘረ #የሚያስመሰግነው ባለ ብዙ #አርኬ ግጥም #መልክእን #አለቃ #ኪዳነ ወልድ ክፍሌ <<መልክእ ከራስ ጸጉር እስከ እግር ጥፍሩ የሚቆጠር መጽሀፍ ነው ብለውታል[1]።>> የሚገርመው #የሰውነት #አካል የሌላቸው እንኳ #መልክዕ ከተጻፈላቸው ውስጥ #መልክዓ #መስቀል(ለእንጨቱ) ፣ #መልክዓ #ሰንበት(ለቀኑ)፣ #መልክዓ #አንቀጸ #ብርሃን(ለመጽሀፍ ስም)፣ #መልክዓ #ስዕል(ለስዕሉ)፣ #መልክዓ #ቁስቋም(ለቦታ) ይጠቀሳሉ። ሌላው ደግሞ #ማንም ሊቀርበው በማይችል #ብርሃን ውስጥ ለሚኖረው #መልክዓ እና #ገጽ የሌለው #መንፈስ ለሆነው #ለእግዚአብሄር እንኳን #በሰው #አካል(ብልቶች) እየቆጠረ ባለ ብዙ #አርኪ #ግጥም #መልክ ተዘጋጅቶለታል። #ለመላእክትም#ቅዱሳን ለተባሉ #ሰዎችም#በኢትዮጵያ ነግሰው ለነበሩ #አጼዎችም ሁሉ "መልክእ" አላቸው። ይህ <መልክእ> የተባለው #የስነ ጽሁፍ #አይነት መጻፍ የተጀመረው #ፕሮፌሰር #ኃይሌ #በ17ኛው ክፍለ ዘመን #ፌሬንክ በተባለ #እንግሊዛዊ እንደሆነ ሲናገሩ #አለማየሁ #ሞገስ የተባሉት ደራሲ ደግሞ #በ14ኛው ክፍለ ዘመን #በአጼ #ዘረዓ ዕቆብ #ዘመነ መንግስት ነው ይላሉ። ሌላው ዜግነቱ ያልታወቀው "ቤደርሰን" የተባለ ጸሀፊ ደግሞ #በ17ኛው ክፍለ ዘመን ባልታወቀ #የዜማ #አቀንቃኝ ነው ይላል። ሁሉም #በጀማሪውና #በጅማሬው #ዘመን ባይስማሙም #የቤተክርስቲያኒቷ ጅማሬ ላይ ያልነበረ #አበው ያላስተማሩት #መጤ እንደሆነ ይስማማሉ።

▶️ መነሻ ሀሳባችን ስለማርያም ነውና በ"መልክእ" ይዘት ድንግል ማርያም የምትመለክበትን ከ"ጸሎት መጽሀፍ" አንዱ የሆነውን < #መልክዓ #ማርያምን> እንመልከት፦
▶️ ምስለ ፍቁር ወልዳ ተብሎ የተሰየመው #ሥዕል "አንዲት ሴት ('ማርያም') ልዩ #ሐምራዊ_መጎናጸፊያ ለብሳ በአንድ #ረዘም ያለ #ወንበር ላይ ተቀምጣና #በግራ እጇ ልጇን ('ኢየሱስን') ታቅፋ በቀኝ ትከሻዋ በኩል #ክንፉን ወደላይ #የዘረጋ #ሰው የሚመስል ('መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል')፣ በግራ ትከሻዋም በኩል እንደዚሁ #ክንፉን ወደላይ #የዘረጋ #ሰው የሚመስል ('መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል') ሆነው እነዚህ 'መላእክት' በአንዳንድ ቦታ ላይ #ሰይፍ አንዳንድ ጊዜም #አበባ አንዳንድ ጊዜም የ "ቸ" ቅርጽ ያለው #በትር አንዳንዴም #ጦር ይዘው የሚሳለው #ሥዕል ነው።

▶️ ይህ #ሥዕል በተለይ #በኢትዮጵያ በብዙ #አዋልድ_መጽሐፍት ውስጥና #በፖስተር #መልክ ተስሎ #በየገዳማቱና #አድባራቱ እንዲሁም በየገበያ ቦታ በተለያየ መጠን ይገኛል። ይህን #ሥዕል ለመጀመሪያ ጊዜ #በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ገዳም /ወሎ -- አንባሰል/ ውስጥ ያለው "ጤፉት" እና "ተአምረ ማርያም" የተባሉት መጽሐፍት <<ወንጌላዊው ሉቃስ ስሏታል[1]>> ብለው ከሚናገሩት በቀር ከእሱ ውጭ ብዙ #መረጃ የለም። ያለው #መረጃ ቢበዛ #ትውፊት ወይም ሰው እርስ በእርሱ የሚያወራው የተለመደ #ወሬ ብቻ ነው።

▶️ እነዚህ #መጻሕፍት የሚናገሩለት #ስዕል #በኢትዮጵያ ዋና #መዲና በሆነችው #በአዲስ_አበባ ከተማ "ብሔራዊ ሙዝየም" ውስጥ በቁፋሮ ተገኘ ተብሎ የሚጎበኘው #ስዕል ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን ይህም #የአሳሳል_ጥበብና ሰዓሊው የተጠቀመባቸው #መሳሪያዎች ሲታዩ #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ገደማ የነበረ #ሰዓሊ እንደሆነ ያታመናል። ይህ ከሆነ ደግሞ #በወንጌላዊው ሉቃስና በዚህ #ስዕል መካከል #የ1,500 ዘመናት #ርቀት ስለሚኖር #ሉቃስ ሳላት የሚባለው #አፈ_ታሪክ ውሃ ይበላዋል። ይልቁንም #በገዳሙ #ታሪክ መሰረት "እፀ መስቀሉን" #በግሸን_ደብረ_ከርቤ_ገዳም አምጥቶ ሲሰጥ "የመጽሐፈ ጤፉት" እና "የተአምረ ማርያም መጽሐፍ" አብሮ በመስጠቱና የመጻሕፍቱ #ጸሐፊ #አጼ_ዘርዓ_ያዕቆብ በመሆኑ በሁለቱም #መጽሐፍት ውስጥ "ሉቃስን ማን መርማሪ ይመጣበታል እኛ ያልነውን የሚቀበል ሰው መች ይታጣል" በሚል በጊዜው #በድፍረት አስገብቶ ጽፎት እንደሚሆን #መገመት ይቻላል።

▶️ የካቶሊኩ #መጽሐፍ ግን የ "እመ አምላክ ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ሳለ የሚነገርለት ቅዱስ ሉቃስ መሆኑን ማረጋገጫና ማስረጃ የለንም" ብሏል[2]።

▶️ የቤተ ክርስቲያን #ታሪክ ፀሐፊ የሆኑት #ሉሌ_መልአኩም "ሉቃስ ስሎታል ብለው ብዙዎች ይተርካሉ" ብለው #በአፈ_ታሪክ ብቻ እንጂ #ምንጭ እንዳጡለት ገልፀዋል[3]።

▶️ በመሰረቱ #ወንጌላዊው_ሉቃስ #የህክምና_ባለሙያ እንጅ #ሰዓሊ እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም {ቆላ 4፥14}። ፈጽሞ #የስዕል ጊዜ እንኳን የነበረው #ሰው አልነበረም።

ሌላው #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በድንግልና #ኢየሱስ ክርስቶስን ከወለደች ቡኋላ እንደ #መቅደስ ስርዓት #ግዝረት ለመፈጸም #በስምንተኛው ቀን (የመንጻት ወራቷ በተፈጸመ ጊዜ) ወደ #ቤተመቅደስ በመሄድ #የሙሴን_ህግ ስትፈጽም #የሙሴ_ህግ እንደሚያዘው አንዲት #ሴት ከወለደች ቡኋላ #የመንጻቷ ጊዜ ሲደርስ #ጠቦት (በግ) ይዛ #ስርዓቱን መፈጸም ነበረባት። በመሆኑም #ጠቦት የሚገዛ #ገንዘብ ስላልነበራት በድህነት አቅሟ #ህጉ የሚፈቅድላትን #ሁለት #የእርግብ_ጫጩቶች #ለመስዋት አቅርባለች [ሉቃ 2፥23፣ ዘሌ 12፥8]።

▶️ ማርያም በኖረችበት #ዘመን #የወፍ_ዝርያዎች ዋጋ 5 ሳንቲም ነበር [ማቴ 10፥29]። እነዚህን 2 #ጫጩቶች ማምጣቷ #ህጉ እንደሚል አንዱን #ስለሀጢአቷ ሌላኛው ደግሞ #ለሚቃጠል_መስዋዕት (እግዚአብሔርን ለማምለክ) ነበር [ዘሌ 12፥8]።

እንግዲህ #ማርያም ፈጽሞ #በድህነት ትኖር ከነበረችና #መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ከተናገረ #በስእሉ ላይ የተገለጸችው እጅግ #የከበረ ቤት ውስጥ #በዘመናዊ #ወንበር ላይ፣ #የከበረ #የወርቅ_ፈርጥ ያለባቸው #የሐር_መጎናፀፊያ (ወርቀ ዘቦ)፣ የሚገርም #ሐረጋማ ያሉት #የወርቅ_አክሊሎች #ዘመናውያን #ወይዛዝርት በሚቀቡት #የከንፈር_ቀለም (ሊፕስቲክ) ያሸበረቀችዋ #ሴት እውን #ማርያም ነች ብሎ ለመቀበል #ድፍረቱስ ይኖረን ይሆን?

ደግሞስ #አዋልድ_መጽሐፍት #ማርያም #ክርስቶስን ስትወልድ #የ16 ዓመት ወጣት ነበረች ካሉ #በስዕሉ ላይ የምትታየዋ ሴት #በግምት #ከ35-38 ዓመት የሆናት #ወይዘሮ እና #ከ12 ዓመት በላይ የሚሆነውን #ታዳጊ ወጣት #ታቅፋ የምትታየዋ #ስዕል #እውን #ማርያምንና_ክርስቶስን ይገልጻልን?

▶️ አንዳንድ ጊዜ #በአንዳንድ ቦታ ተስለው የሚገኙት ደግሞ "የማርያምና" የታቀፈችው #ልጅ መልክና #የጸጉር ቀለም #የሐበሻ #ጥቁር_ፀጉርና #አፍሮ ሁለቱም አንገቶቻቸው #ባለንቅሳት የሆኑ አሁን እነዚህ #እስራኤላዊያን የነበሩትን #ማርያምና #ክርስቶስን ይገልጻሉን?

▶️ ሌላኛው "የማርያም ስዕል" ደግሞ #በእንዝርት #ጥጥ_ስትፈትል የሚያሳየውን ብንመለከት ይህ #የቤት_ተግባር #የኢትዮጵያን እናቶች ተግባር ወይስ #የእስራኤላውያን ባህል?

▶️ በመሆኑም ሁሉንም #የማርያምን_ስዕል ደርድረን ብንመለከተው #ሰዓሊው ደስ ያለውን #ቀለምና_ቅርጽ ያሳረፈበት ለእለት ጉርሱ #ለገበያ ያቀረባቸው #ምስሎች ስለሆኑ #አምልኮና_ስግደቱን ትተን #ስዕሎቻችንን #ለቅርስነትና #ለማስተማርያ ብቻ እናውላቸው!

@gedlatnadersanat
(9.6▶️ጥያቄ) ይቀጥላል. . .
@gedlatnadersanat