ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
📖፤ / ሱረቱ መርየም 19፤ 27-28
(2ተኛ እትም 1998 ዓ.ም)
*ሱራህ 19, አያህ 27*
فَأَتَتْ بِهِۦ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُۥ ۖ قَالُوا۟ يَٰمَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْـًۭٔا فَرِيًّۭا
በእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡
*ሱራህ 19, አያህ 28*
يَٰٓأُخْتَ هَٰرُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ ٱمْرَأَ سَوْءٍۢ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّۭا
«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡

የክፍሉ የግርጌ ማብራሪያ ላይ ማሪያም #የሙሴ ወንድም #የአሮን #እህት እንደሆነች ይናገራል።
ይህ ደግሞ #ከክርስቶስ #ልደት በፊት 1500 #ዘመን ዘሎ #የአሮንን ዘመን #ከክርስቶስ እናት #ማርያም ጋር በምን #አይነት ሂሳብ እንዳጠጋጋው እንጃ??

▶️ "የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን" ደግሞ #ሁለት #ተቃራኒ ሀሳቦችን ታስቀምጣለች፦

1ኛ👉 <"የዮሴፍ የወንድም ልጅ ናት">

<<የእስራኤል ሽማግሎችና መምህራንም አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችን #የአባቷን #ወንድም #ዮሴፍን ወደ በአደባባይ . . . አደራ ያስጠበቅንህን #የወንድምህን #ልጅ #እጮኛህ #ማርያምን. . .[3]>>

በመሰረቱ "የዮሴፍ የወንድም ልጅ ናት" የሚለው #መጽሐፍ ቅዱስ ዮሴፍ #የማርያም #እጮኛ እንጅ አጎት(የአባት ወንድም) መሆኑን አይናገርም።
ምናልባት #ወንድሙ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው አባቷ #ኢያቄም ይሆን?? ብለን እንዳንገምት እንኳን። #ኢያቄም ወንድም እንዳልነበረውና #ለእናቱም #ለአባቱም አንድ እንደሆነ በሌሎች #መጽሀፍቶቻቸው ላይ ተጽፏል[4]። <የወንድምህን ልጅ እጮኛህን> ማለት በምን ዓይነት ቋንቋ እንደሆነ እንጃ!!

2ኛ👉 <"ማርያም የሃናና የኢያቄም ልጅ ስትሆን አያቷም #ቅስራ ነው"> ትላለች።

ማርያም " #የሃናና #የኢያቄም ልጅ" መሆኗን ለመጀመሪያ ጊዜ #ያለምንም #መረጃ የጠቀሰው " #በተአምረ #ማርያም" መጽሀፍ < #አጼ #ዘረያቆብ> ነው።/በ 1426-1460/ ዓ.ም።
በመቅድሙ ላይ "ስመ አቡሃ ኢያቄም ወስመ ወላዲታ ሐና -የአባቷም ስም ኢያቄም ነው የእናቷም ስም ሐና ነው" ብሏል[5]።

▶️ የ" #ዘውትር #ፀሎት" ድርሳኑም ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል።
ቡሀላ ግን ከእነዚህ #ኑፋቄ #ትምህርት ከገባባቸው #አዋልድ #መጽሀፍት በስተቀር
<•የሀናና የኢያቄም ልጅ•> ናት ብሎ ያመነ #የቤተክርስቲያን #አባት አንድም እንኳ እንዳልነበረ አንድ መጽሀፍ ሲገልጽ
<<እም ሐና ወኢያቄም ተወለድኪ - ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ>> የሚለው #የሃገራችን #ደራሲያን የሚናገሩት #ቃል ነው እንጅ #ከአገር ውጪ ያሉ #አቢያተ #ክርስቲያናት ጠቅሰውት አያውቁም።
<ሐና ኢያቄም> የሚል ቃል #በሃይማኖተ #አበው መጽሀፍ ላይ ድርሰታቸው የተሰበሰበላቸው #ከ55 በላይ የሆኑ #ሊቃውንቶች ይህንን #ቃል አልጠቀሱም። ከእነዚህም በተለይ #እነቅዱስ #ኤፍሬም#እነዩሐንስ #አፈወርቅ አመሰገኗት የሚባሉት ላይ እንኳን እነዚህ ቃላቶች #አልተጠቀሱም ይላል[6]።
▶️ ማርያም #ስለመሲሁ የመምጣት #ተስፋ ብታውቅም እንዴት #እንደሚፈጸም ግን አታውቅም ነበር። #በሉቃ 1፥34 ላይ #አለማመኗን የሚያሳይ ሳይሆን #እምነቷን የሚገልጽ ነበር። አንዲት #ልጃገረድ እንዴት #ከወንድ ጋር #ሳትገናኝ #ልትወልድ ትችላለች ብላ በማሰቧ #እጮኛዋ ከሆነው #ከዮሴፍ ጋር #ባለመጋባቷና #ግንኙነት ፈጽማ ባለማወቋ #መልአኩን <<ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?>> ብላ ጠየቀችው። #መልአኩም ይህ #በመንፈስቅዱስ የሚፈጸም #ተአምር እንደሆነ ነገራት። ደግሞም #ከአዳም #የውርስ ኃጥያት #በመንፈስቅዱስ መጸለል(መጋረድ) ምክንያት የሚወለደው #ህጻን <ቅዱስ> እንደሚሆን አመለከታት።

▶️ መልአኩ #መልእክቱን የደመደመው ለማርያም #የማጽናኛ #ቃል በመስጠት ነበር። ይኸውም #በዕድሜ የገፋችው ዘመዷ #ኤልሳቤጥ #ወንድ ልጅ #መጸነሷና 6ኛ ወሯ መሆኑን በመግለጽ #ለእግዚአብሄር #የሚሳነው ነገር የለምና አንቺም #መጸነስ ትችያለሽ በማለት #አስረዳት

▶️ ከዚህ ቡኋላ #ማርያም እንደታዛዥ #ባርያ ራሷን #ለእግዚአብሄር #በመስጠት <<እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ>> በማለት #የእምነት #ምላሽ ሰጠች {ሉቃ 1፥38}። መልአኩም ይህን #ውይይት እንደጨረሰ ከእርሷ ተለይቶ #ሄ

▶️ እንግዲህ በዚህ #ውይይት ውስጥ እጅግ #ዝቅተኛ #የኑሮ #ደረጃ ውስጥ ትኖር የነበረች #ልጃገረድ #የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈጸም #ለጌታ ሙሉ በሙሉ ራሷን #መስጠቷን ስናይ እንዴት የሚገርም ነው ያሰኛል። #ማርያም በእርግጥም #ለእግዚአብሄር #የተሰጠች #ሴት ነበረች። ይሁን እንጂ በአሁኑ #ዘመን በዚህ 'በቅድስት ድንግል #ማርያምና በቅዱስ #ገብርኤል' መካከል የተደረገውን #ውይይት ከተጻፈው #ውጪ በርካታ #የሃይማኖት መጽሐፍት በተለይም #አዋልድ መጽሐፍት #ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊ ጽንፈኛ #አስተምህሮቶችን ለብዙ ዓመታት #ሲያንጸባርቁ ቆይተዋል። ከዚህም የተነሳ ማርያምን የሃይማኖታቸው ማዕከል ያደረጉ በርካታ መናፍቃን ስለመነሳታቸው ታሪክ ይዘግባል።

👉 ለምሳሌ #የዘውትር ጸሎት መጽሐፍ የሆነው <<ይወድስዋ መላዕክት - መላዕክት ማርያምን ያመሰግኗታል>> በሚለው አርስቱ <<መልአኩ ገብርኤል ማርያምን •ድንግል ለአንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል• አላት፣ •ወላዲት አምላክ ምስጋና ይገባሻል•፣ •ቅድስት ነሽና ምስጋና ይገባሻል•፣ •የመለኮት ማደሪያ ነሽና ምስጋና ይገባሻል•፣ •የተሸለመች ድንኳን ነሽና ምስጋና ይገባሻል•፣ •የሁሉ እመቤት ማርያም ምስጋና ይገባሻል•፣ •የሁሉ ፍቅረኛ ማርያም ምስጋና ይገባሻል•፣ •ልዑል ማደሪያው ትሆኚ ዘንድ መርጦሻልና ምስጋና ይባገሻል•፣ •በወርቅ የተሸለምሽ የርግብ ክንፍ በብር ያጌጥሽ ምስጋና ይገባሻል•፣ •ጎኖችሽ በወርቅ አመልማሎ የተሸለሙ ለአንቺ ምስጋና ይገባሻል•፣ •ከጸሀይ 7 እጅ የምታበሪ ክብርሽ ከአድባራቱ ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ ለአንቺ ምስጋና ይገባሻል•[3]>> ይላል። ይህ #ጸሎት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ #በቃል አልያም #በንባብ ዘውትር ወደ #ማርያም የሚቀርብ #ምስጋና ነው።

▶️ ይሁን እንጂ #ቆም ብለን በእውኑ ከላይ የተገለጸውን #ንባብ (አንቀጽ) #ቅዱስ ገብርኤል የተናገረው ነውን? #መላእክትስ ማርያምን #ያመሰግኗታልን? እኛስ እንዲህ ያለውን አንቀጽ አስቀምጠን ወደ #ማርያም #እንድንጸልይ (እንድናመሰግን) #ሕግ ተሰጥቶአልና? ብለን ብንጠይቅና ለማየት ብንሞክር ፈጽሞ የሌለና #ያልተባለ ወደፊትም #የማይባል እንደውም #ኃጢአት እንደሆነ #መጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ ይናገራል።

▶️ በመሆኑም #መላእክት #የሚያመሰግኑትንና #ምስጋና #የሚገባውን ጠንቅቀው ስለሚያቁ ሲያመሰግኑ እንዲህ ይላሉ፦

<<በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።. . . በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን. . . በረከትና ክብር ጥበብም ምስጋናም ውዳሴም ኃይልም ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤ አሜን አሉ።>>

የሚል ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ አምልኮና ምስጋና ብቻ ነው {ራዕ 5፤10፣ 12-13;፣ ራዕ 7፥12፣ በተጨማሪም ራዕ 4፥8፣ 11፥15፣ 12፥10፣ 15፥3፣ 19፥1. . .።}

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ፤ ወንጌል ቅዱስ፡ ሉቃስ አንድምታ 1፥47፣ ገጽ 268። ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፤ 1997 ዓ.ም።

[2] የእግዚአብሄርም ቃል <<ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥>> {1ኛ ቆሮ 1፤ 27-28} የሚለው ለዚሁ አይደል??

[3] የዘውትር ጸሎት መጽሐፍ <ይወድስዋ መላእክት> ቁ.3።


(4.1▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ ማርያም #በቤተመቅደስ ውስጥ ኖራለች የሚለውን #አባባል ከማየታችን በፊት መልአኩ #ፋኑኤል ማን ነው? የሚለውን ማየቱ #ተገቢ ነው።

▶️ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በርካታ #መላእክት እንዳሉ ቢገለጽም #ስማቸው ግን የተጠቀሱ #ቅዱሳን #መላዕክት #ገብርኤል#ሚካኤል#ሱራፌል#ኪሩቤል ብቻ ናቸው። ሌሎቹ #ስሞቻቸው #በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጠቀሰው በአጋጣሚ ወይም ተረስተው ሳይሆን #የመላእክትን አምልኮ #ሰዎች እንዳይከተሉ #እግዚአብሔር የወሰደው ጥንቃቄ ነበር {ዘዳ 4፤ 19-24}። በስም የተጠቀሱት #ኃያላን መላእክት በየትኛውም #መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክፍል ብናነብ የአገልግሎታቸው #ማእከል #የክርስቶስ #ጌትነት ነበር። #መላእክት በተጠቀሱበት አንቀጽ ሁሉ ሄደን ብናነብ #የኢየሱስ ክርስቶስ #ክብርና #አዳኝነት ለህዝብ ሁሉ ጥቅም እንዲሆንና ለእርሱ #እንደሚሰግዱ #እንደሚዘምሩ #እንደሚያመልኩትም ክብሩን #እንደሚጠብቁ ለማሳየት የተጠቀሱ ናቸው {ሉቃ 1፤ 26-38፣ 2፤ 10-14፣ ማቴ 2፤13፣ 4፥11፣ ራዕ 4፤ 7-11፣ ራዕ 12፤ 7-12}።

▶️ መልአኩ #ፋኑኤል ግን #በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ #ስሙ ባለመጠቀሱ እንዲህ የሚባል #መልአክ አለ ለማለት #መረጃ የለም። ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን #መልአክ መኖሩን በስም የጠቀሰው አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ #በተአምረ ማርያም መጽሐፍና #በ18ኛው ክፍለ ዘመን ያልታወቀ ጸሐፊ ምናልባት #ደብተራ የጻፈው <<ድርሳነ ፋኑኤል>> ከተባለው #አዋልድ #መጽሐፍት ውጪ አይታወቅም።

▶️ በቁሙ የመልአኩ #ፋኑኤል #ተግባር ነበር ተብሎ የተጠቀሰውን #የማርያምን #ሰማያዊ #ህብስት (ምግብ) እና #ሰማያዊ #መጠጥ #ማርያም #ቤተመቅደስ ውስጥ ነበረች እስከተባለችበት 12 ዓመት ሙሉ #በየሰዓቱ #በታማኝነት ማመላለሱን እያንዳንዱ #የቤተመቅደሱን #ታሪክ #በመጽሐፍ ቅዱስ ሲዘገብ #የፋኑኤል ድካም አለመጻፉ ታሪኩን #ተራ ያሰኘዋል። ይልቁንም #እግዚአብሔር አምላክ የፍጥረት ሁሉ #ምግብ #በምድር ላይ አደረገ የሚለው #ለአእምሮ የሚመች ነው {ዘፍ 1፤ 29-31}።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

(7.3▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
<<ሁሉም ወደ #አምላኩ ወደ #እግዚአብሔር አንጋጦ #ሲለምን በአየን ጊዜ #መንፈሳዊ #ቅንዓትን ቀንቶ #ገሰጻቸው። በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች #አምላክን ወደ ወለደች ወደ ክብርት #እመቤታችን #ማርያም ለምን #እርዳታ አትሹም እርሱዋ #ከቅዱሳን ሁሉ #ድንቅ ድንቅ #ተአምራትን የምታደርግ፣ #ፈጥና #የምታደርስ #ልመናን የምትሰማ ናትና አላቸው። በዚያችም ጊዜ #ተአምራትን ወደ ምታደርግ #በድንጋሌ #ስጋ #በድንጋሌ #ነፍስ ወደ ጸናች ወደ ክብርት እመቤታችን #ማርያም ለመኑ .... የሃገሩም ሰዎች #እመቤታችንን አመሰገኑ[1]።>>

<<እግዚአብሔር #ሲመሰገን #ግሣጼ መጣ #ስለማርያም ግን #ምስጋና ሽልማት ይሆናል #ቀሲስ #እንድርያስም #የማርያምን #ቅዳሴ #ዘወትር ይቀድሳል #ከእርሷም #በቀር ሌላ #ቅዳሴ አያውቅም ነበር ... #ኤጲስቆጶሱ ጠርቶ ሁልጊዜ #ከአንድ #ቅዳሴ በቀር ለምን #ለእግዚአብሄር #አትቀድስም ብሎ ተቆጥቶ #እንዳይቀድስ ቢከለክለው #ማርያም ተገልጣ #የእኔን #ቅዳሴ ሲቀደስ አገልጋዩን #ያወገዝከው ለምንድን ነው? ... #በክፉ #አሟሟት እንድትሞት #በእውነት እነግርሃለው አለችው #ኤጲስቆጶሱም ከዛሬ ጀምሮ #ከእመቤታችን #ቅዳሴ በቀር ሌላ #ቅዳሴ #አትቀድስ አለው[2]።>>

▶️ ከላይ ያየነው ሁሉ #ስለማርያም የሚናገሩት #አዋልድ #መጽሀፍት #ከእግዚአብሄር ይልቅ #ማርያምን የሚያስበልጡና እርሷን #ስለማምለክ የሚያሳዩ የጠቀስናቸው #ጥቂት #አጸያፊ #ክፍሎች ሲሆኑ ከዚህ በታች ደግሞ #ከእግዚአብሄር ጋር ባልተናነሰ መልኩ #ስትመለክና #ስትመሰገን የሚያሳዩ #ጥቂት #ክፍሎችን ደግሞ #በመገረም እንመልከት፦

<< #ለአብ #ምስጋና ይገባል፣ #ለወልድ #ምስጋና ይገባል፣ #ለመንፈስ ቅዱስም #ምስጋና ይገባል፣ #አምላክን #ለወለደች #ለእመቤታችን #ድንግል #ማርያም #ምስጋና ይገባል[3]>>

ይህም ማለት #ከአብ #ከወልድና #ከመንፈስቅዱስ ጋር #እኩል #ምስጋና የምትቀበል #የስላሴ 4ተኛ #አካል ሆነች ማለት ነው። በሌላ መጽሐፍም
<<ወላዲተ አምላክ ማርያም ሆይ፥ ጧት ስነሳ #እግዚአብሔርንና #አንቺን እመቤቴን #በጸሎት #እንዳመሰግን የሚያነቃቃ መንፈስ ኅሊና አሳድሪብኝ፤[4]>> ይላል።

▶️ ከዚህም የከፋ #ማርያም እንደ #አምላክ #እግዚአብሔር ደግሞ ከእርሷ #ዝቅ ብሎ #እንደመማለጃዋ ሆኖም የቀረበበትን #መጽሀፍ ደግሞ እስኪ እንታዘብ ፦

<< #ዘጠኝ ወር #የተሸከምሽው ከሃሊ በሚሆን #ከጡትሽ #ወተቱን ባጠባሽውም #ልጅሽም #በሰው ልጅ ላይ #ቸርነቱና #ይቅርታው በበዛ #በአባቱ... #በእግዚአብሄርም #እማጸንሻለው #እማልድሻለሁ #እለምንሻለሁ[5]>> ይላል።

▶️ ስለዚህ እነዚህን የመሳሰሉ #ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊና #አጸያፊ የሆኑ #አዋልድ መጽሀፍት ይዞ እግዚአብሔርን #አመልካለሁ ማለት ራስን #ማታለል ነው። እግዚአብሔር ግን <<እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ ይላል ቅዱሱ>> |ኢሳ 40፥25] ደግሞም <<እንደ እኔ ያለ ማን ነው ይነሳና ይጣራ ይናገርም>> ይላል እግዚአብሔር [ኢሳ 44፥7]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
___________
[1] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ "መጽሀፈ ግብረ ህማማት፤ ዘረቡዕ በ1 ሰአት በነግህ የሚነበብ፤ ገጽ 394፤ ቁጥር 1-13፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ፥ 1996 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ "መጽሀፈ ግብረ ሕማማት" ዘሐሙስ በመዓልት በ11 ሠዐት የሚነበብ፤ ገጽ 587 - 588 ቁጥር 1፤ 10 ፤ 1996 ዓ.ም።

[3] 📚፤ ተስፋ ገብረስላሴ፤ "ውዳሴ ማርያም ምስለ መልክዓ ማርያም በአማርኛ"፤ የዘውትር ጸሎት፤ ገጽ 6 ፥1986 ዓ.ም።

[4] እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት አርኬ 15።

[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም ግእዝና አማርኛ 3ተኛ ዕትም፥ ምዕ 102፥7፤ ገጽ 170፤ ትንሳዔ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።
▶️ ምስለ ፍቁር ወልዳ ተብሎ የተሰየመው #ሥዕል "አንዲት ሴት ('ማርያም') ልዩ #ሐምራዊ_መጎናጸፊያ ለብሳ በአንድ #ረዘም ያለ #ወንበር ላይ ተቀምጣና #በግራ እጇ ልጇን ('ኢየሱስን') ታቅፋ በቀኝ ትከሻዋ በኩል #ክንፉን ወደላይ #የዘረጋ #ሰው የሚመስል ('መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል')፣ በግራ ትከሻዋም በኩል እንደዚሁ #ክንፉን ወደላይ #የዘረጋ #ሰው የሚመስል ('መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል') ሆነው እነዚህ 'መላእክት' በአንዳንድ ቦታ ላይ #ሰይፍ አንዳንድ ጊዜም #አበባ አንዳንድ ጊዜም የ "ቸ" ቅርጽ ያለው #በትር አንዳንዴም #ጦር ይዘው የሚሳለው #ሥዕል ነው።

▶️ ይህ #ሥዕል በተለይ #በኢትዮጵያ በብዙ #አዋልድ_መጽሐፍት ውስጥና #በፖስተር #መልክ ተስሎ #በየገዳማቱና #አድባራቱ እንዲሁም በየገበያ ቦታ በተለያየ መጠን ይገኛል። ይህን #ሥዕል ለመጀመሪያ ጊዜ #በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ገዳም /ወሎ -- አንባሰል/ ውስጥ ያለው "ጤፉት" እና "ተአምረ ማርያም" የተባሉት መጽሐፍት <<ወንጌላዊው ሉቃስ ስሏታል[1]>> ብለው ከሚናገሩት በቀር ከእሱ ውጭ ብዙ #መረጃ የለም። ያለው #መረጃ ቢበዛ #ትውፊት ወይም ሰው እርስ በእርሱ የሚያወራው የተለመደ #ወሬ ብቻ ነው።

▶️ እነዚህ #መጻሕፍት የሚናገሩለት #ስዕል #በኢትዮጵያ ዋና #መዲና በሆነችው #በአዲስ_አበባ ከተማ "ብሔራዊ ሙዝየም" ውስጥ በቁፋሮ ተገኘ ተብሎ የሚጎበኘው #ስዕል ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን ይህም #የአሳሳል_ጥበብና ሰዓሊው የተጠቀመባቸው #መሳሪያዎች ሲታዩ #በ15ኛው ክፍለ ዘመን ገደማ የነበረ #ሰዓሊ እንደሆነ ያታመናል። ይህ ከሆነ ደግሞ #በወንጌላዊው ሉቃስና በዚህ #ስዕል መካከል #የ1,500 ዘመናት #ርቀት ስለሚኖር #ሉቃስ ሳላት የሚባለው #አፈ_ታሪክ ውሃ ይበላዋል። ይልቁንም #በገዳሙ #ታሪክ መሰረት "እፀ መስቀሉን" #በግሸን_ደብረ_ከርቤ_ገዳም አምጥቶ ሲሰጥ "የመጽሐፈ ጤፉት" እና "የተአምረ ማርያም መጽሐፍ" አብሮ በመስጠቱና የመጻሕፍቱ #ጸሐፊ #አጼ_ዘርዓ_ያዕቆብ በመሆኑ በሁለቱም #መጽሐፍት ውስጥ "ሉቃስን ማን መርማሪ ይመጣበታል እኛ ያልነውን የሚቀበል ሰው መች ይታጣል" በሚል በጊዜው #በድፍረት አስገብቶ ጽፎት እንደሚሆን #መገመት ይቻላል።

▶️ የካቶሊኩ #መጽሐፍ ግን የ "እመ አምላክ ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ሳለ የሚነገርለት ቅዱስ ሉቃስ መሆኑን ማረጋገጫና ማስረጃ የለንም" ብሏል[2]።

▶️ የቤተ ክርስቲያን #ታሪክ ፀሐፊ የሆኑት #ሉሌ_መልአኩም "ሉቃስ ስሎታል ብለው ብዙዎች ይተርካሉ" ብለው #በአፈ_ታሪክ ብቻ እንጂ #ምንጭ እንዳጡለት ገልፀዋል[3]።

▶️ በመሰረቱ #ወንጌላዊው_ሉቃስ #የህክምና_ባለሙያ እንጅ #ሰዓሊ እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም {ቆላ 4፥14}። ፈጽሞ #የስዕል ጊዜ እንኳን የነበረው #ሰው አልነበረም።

ሌላው #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በድንግልና #ኢየሱስ ክርስቶስን ከወለደች ቡኋላ እንደ #መቅደስ ስርዓት #ግዝረት ለመፈጸም #በስምንተኛው ቀን (የመንጻት ወራቷ በተፈጸመ ጊዜ) ወደ #ቤተመቅደስ በመሄድ #የሙሴን_ህግ ስትፈጽም #የሙሴ_ህግ እንደሚያዘው አንዲት #ሴት ከወለደች ቡኋላ #የመንጻቷ ጊዜ ሲደርስ #ጠቦት (በግ) ይዛ #ስርዓቱን መፈጸም ነበረባት። በመሆኑም #ጠቦት የሚገዛ #ገንዘብ ስላልነበራት በድህነት አቅሟ #ህጉ የሚፈቅድላትን #ሁለት #የእርግብ_ጫጩቶች #ለመስዋት አቅርባለች [ሉቃ 2፥23፣ ዘሌ 12፥8]።

▶️ ማርያም በኖረችበት #ዘመን #የወፍ_ዝርያዎች ዋጋ 5 ሳንቲም ነበር [ማቴ 10፥29]። እነዚህን 2 #ጫጩቶች ማምጣቷ #ህጉ እንደሚል አንዱን #ስለሀጢአቷ ሌላኛው ደግሞ #ለሚቃጠል_መስዋዕት (እግዚአብሔርን ለማምለክ) ነበር [ዘሌ 12፥8]።

እንግዲህ #ማርያም ፈጽሞ #በድህነት ትኖር ከነበረችና #መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ከተናገረ #በስእሉ ላይ የተገለጸችው እጅግ #የከበረ ቤት ውስጥ #በዘመናዊ #ወንበር ላይ፣ #የከበረ #የወርቅ_ፈርጥ ያለባቸው #የሐር_መጎናፀፊያ (ወርቀ ዘቦ)፣ የሚገርም #ሐረጋማ ያሉት #የወርቅ_አክሊሎች #ዘመናውያን #ወይዛዝርት በሚቀቡት #የከንፈር_ቀለም (ሊፕስቲክ) ያሸበረቀችዋ #ሴት እውን #ማርያም ነች ብሎ ለመቀበል #ድፍረቱስ ይኖረን ይሆን?

ደግሞስ #አዋልድ_መጽሐፍት #ማርያም #ክርስቶስን ስትወልድ #የ16 ዓመት ወጣት ነበረች ካሉ #በስዕሉ ላይ የምትታየዋ ሴት #በግምት #ከ35-38 ዓመት የሆናት #ወይዘሮ እና #ከ12 ዓመት በላይ የሚሆነውን #ታዳጊ ወጣት #ታቅፋ የምትታየዋ #ስዕል #እውን #ማርያምንና_ክርስቶስን ይገልጻልን?

▶️ አንዳንድ ጊዜ #በአንዳንድ ቦታ ተስለው የሚገኙት ደግሞ "የማርያምና" የታቀፈችው #ልጅ መልክና #የጸጉር ቀለም #የሐበሻ #ጥቁር_ፀጉርና #አፍሮ ሁለቱም አንገቶቻቸው #ባለንቅሳት የሆኑ አሁን እነዚህ #እስራኤላዊያን የነበሩትን #ማርያምና #ክርስቶስን ይገልጻሉን?

▶️ ሌላኛው "የማርያም ስዕል" ደግሞ #በእንዝርት #ጥጥ_ስትፈትል የሚያሳየውን ብንመለከት ይህ #የቤት_ተግባር #የኢትዮጵያን እናቶች ተግባር ወይስ #የእስራኤላውያን ባህል?

▶️ በመሆኑም ሁሉንም #የማርያምን_ስዕል ደርድረን ብንመለከተው #ሰዓሊው ደስ ያለውን #ቀለምና_ቅርጽ ያሳረፈበት ለእለት ጉርሱ #ለገበያ ያቀረባቸው #ምስሎች ስለሆኑ #አምልኮና_ስግደቱን ትተን #ስዕሎቻችንን #ለቅርስነትና #ለማስተማርያ ብቻ እናውላቸው!

@gedlatnadersanat
(9.6▶️ጥያቄ) ይቀጥላል. . .
@gedlatnadersanat