አትሮኖስ
273K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
435 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#
#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በክፍለማርያም

...ፍፁም ለማምለጥ እየሞከረ ነዉ
ቤዛዊት በተቀመጠችበት ቦታ በሀሳብ እሩቅ ተጉዛ ስለ ፍፁም መቅረት ትብከነከናለች

"ምን ሆኖ ቀረ?"

በአይምሮዋ የሚመላለስ ጥያቄ ነዉ።
ሀሳቧ ሁለት ፅንፍ ይዞ ይጋጫል
"ይመጣል አይቀርም"
የሚል የመፅናኛ እና የጤነኝነት ሀስብ በተቃራኒዉ
"አይመጣም ቀርቷል"
የሚል በህመም የገነነ ዉጥረት ባላቸዉ ጥያቄወች ተዉጣ በቀኝ እጇ አገጯን ደገፍ አርጋ
አይኖቿን አሁንም ፊት ለፊቷ አሻግራ ተስፋ ባለነቁረጥ የፍፁምን መምጣት በጉጉት ስትጠባበቅ
ቆይታ አሉታዊዉ ሀሳቧ የፍፁምን መቅረት አሳምኗት ከተቀመጠችበት በፍጥነት ዘላ ተነስታ እንደወታደራዊ አቋቋም በተጠንቀቅ ከቆመች በኋላ ለመራመድ መንቀሳቀስ ስትጀምር
በርቀት ሁኔታዋን ሲታዘቡት የነበሩት እማማ ስንቅነሽ ፈጠን እያሉ ተራምደዉ አስቆሟት

"የት ልትሄጂ ነዉ ልጄ?"

በእድሜ ብዛት የደከመ በሚመስል አሳዛኝ የእናትነት ድምፅ
የቤዛዊትን እጆች ለመያዝ እጃቸዉን እየሰደዱ
"ቀረ በቃ አይመጣም"
ቆጣ ብላ እጆቿን እያወናጨፈች ሊይዟት የቀረቡትን የእማማ ስንቅነሽን እጅ እየገፋች
"ማን ..."
ካሉ በኋላ እማማ ስቅነሽ ይመጣል እየጠበኩት ነው ያለቻቸዉን አስታዉሰዉ
"ፍፁምን ነዉ ምን አለ ትንሽ ብትጠብቂዉ ታድያ ልጄ ወዴት ልትሄጂ ነው የተነሳሽዉ.."
ከጎናቸዉ እንዳትርቅ እየፈለጉ ቤዛዊትን ማባበል ጀመሩ
የት እንደምትሄድ ያላረጋገጠችዉ ቤዛዊት ግን የእማማን ተማፅኖ ከቁብ ሳትቆጥር
ሂጂ ሂጂ የሚላትን ስሜት እየተከተለች እማማን
"እመለሳለሁ እመለሳለሁ እሺ"
እያለች በእርጅናና በህይወት የጎበጠ ትከሻቸዉን በእጇ ዳበስ አርጋ
እማማ ስንቅነሽን ወደ ኋላ ትታ እስዋ ወደ ፊት መራመድ ጀመረች።
ፍፁም ፍቃዱን አመልጣለሁ ብሎ ዘዉ ብሎ የገባበት ቤት መኖርያ ቤት መስሎት እየተሳቀቀ የያዝኩትን ክራንች ማነከሴንም አይተዉ ያዝኑልኛል ብሎ ሰተት እንዳለ
ቤቱ ዉስጥ በቁጥር የሚቆጠሩ ሰወች ሰብሰብ ብለዉ ስላየ በፍርሀት እና ተመልሼ ልዉጣ አልዉጣ እያለ በቆመበት
ሲያስብ አንዲት ደርባባ ሴትዮ ከቤቱ ዉስጠኛ ክፍል መጋረጃ ገልጣ ስትወጣ ፊት ለፊት ሲገጣጠሙ ፍፁም እንደምንም ብሎ
"ሰላም ዋልሽ"
አንገቱን ለሰላምታ ያክል ዝቅ እያረገ
ሴትየዋ ፊት ለፊቷ አይታዉ የማታዉቀዉ ሰዉ በማየቷ ጥቂት ተገርማ ክራንቹን አቋቋሙን ፊቱን በገረፍታ አይታዉ ፊቷ ላይ ፈገግታ እየተነበበ
"እንዴ ምን አስቆመህ አረፍ በል እነጂ..."
በአይኖቿ ሰወቹ ከተቀመጡበት አግዳሚ ወንበር ክፍት ቦታ እያሳየችዉ መቀመጡን ስታይ ተመልሳ ወደ ጓዳዋ ፈጠን እያለች ገባች
ፍፁም የተቀመጡትን ሰወች ቃኛቸዉ የራሳቸዉ ጨዋታ ላይ ናቸዉ ሁሉም እግራቸዉ ስር ንኬል ተቀምጧል መሀል ላይ ጆግ ሙሉ ጠላ መኖሩን አስተዋለ ወድያዉ ሴትየዋ በጣሳ ዉሉ ጠላ ይዛ መጥታ ፊት ለፊቱ አስቀመጠች
ጠላ ቤት መግባቱ ስለገባዉ ፈገግ እያለ አመስግኖ ተቀብሎ መጠጣት ጀመረ።
ቤዛዊት የመንገዱን ጠርዝ ይዛ በለሆሳስ እያወራች ከንፈሮቿ እየተንቀሳቀሱ አንዴ ቆም
ብላ እያሰበች ሲላት ፈጠን ፈጠን እያለች እየተራመደች ነዉ
"ቀረ !!"
አንገቷን ከግራ ወደ ቀኝ እያንቀሳቀሰች
"ቤቱ ለምን አልሄድም እንደዉም እሄዳለሁ"
እጇን ከንፈሯ ላይ ጣል አርጋ ትንፋሽ እየሳበች አሰበች
"ይሄኔ ከእህቴ ጋር ይሆናል"
ንዴቷ እየጨመረ ሄዶ እጆቿን ለቡጢ በሚመስል አኩዋሀን ጨበጠቻቸዉ
ወደ ፍፁም ቤት ሄዳ ፍፁም እና እህቷን አብረዉ ሆነዉ ስታገኛቸዉ ምን ልታረግ እንደምትችል እያሰበች
"ኪኪኪኪኪ ኪኪኪኪ ኪኪኪኪኪ"
እየተንከተከተች ስትስቅ መንገደኛ ሰዉ አይቷት እጆቹን ለማማተብ አንዴ ግንባሩን ቀጥሎ ወደ ሆዱ በስተመጨረሻ ሁለቱን ትከሻወቹን አስነክቶ እየዞረ እያያት ሲያልፍ ሳቋን አቁማ ኮስተር ለማለት እየሞከረች ወደ ፍፁም ቤት አመራች።

ፍቃዱ በንዴት ብዛት ተበሳጭቷ ባዶ ሜዳ ላይ ቆሞ ይዉረገረጋል
"እንዴት ይሄ ያመልጠኛል የት ሊገባ ይችላል"
እያለ በቆመጠት ዙርያዉን ይቃኛል ነገር ግን ፍፁምን ማየት ስላልቻለ እና ፀሀይዋም አቅም አሳጥታዉ ስለደከመዉ ለመመለስ እያሰበ ጥቂት ወደ ኋላ ሲራመድ
አንድ ጎልማሳ ሰዉዬ የጣሳ ምልክት ከተሰቀለበት ቤት በመጠኑ ገድገድ እያለ ሲወጣ ተመልክቶ ቆመ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

...የከተማው ዋና ዋና መንገዶች በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መወረር ጀምረዋል ። የአራት ኪሎና እካባቢዋ ቡና
ቤት አሳላፊዎች፥ ለተማሪ ሻይ ቡና በማቅረብ ተዋክበዋል ። የተማሪዉ አንሶላዎች'ልብሶች በየሥርቻው ተወርውረው የከረሙ የእግር ሹራቦች ከውሃ በመታረቅ ላይ ናቸው ሕሜት ፥ ውረፋ ፡ ዘለፋና ቀልድ ጊዚአቸውን
ጠብቀው ተመልሰዋል በሴሚስተሩ ውስጥ በዩኒቨርስቲው የተደረገች አንዳች ነገር ሳትቀር እየተነሳች መብጠልጠያዋ ጊዜ ነው።

ይህ ሁሉ ፈተና ማለቁን የሚያበሥር ነው የፈተና ውጤት ቀርቦ ማዕበሉ ማንን ጠርጎ ማንን እንደ ተወ እስኪታወቅ ድረስ ለሁለት ሳምንቱ የዕረፍት ቀናት አብዛኛው ተማሪ ከዚህ ክልል አይወጣም ።

እቤልና እስክንድርም የመጨረሻውን ፈተና እንደ ተፈተኑ ግቢውን ለቀው ወጥተዋል ። የተዝረከረኩ ዕቃዎች
ለማስተካከል እንኳ፥ ወደ መኝታ ክፍላቸው አልተመለሱም።ተያይዘው በቀጥታ ወደ እስክንድር እናት ቤት ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ሔዱ። አቤል ለአውደ አመትና አልፎ አልፎም ለዕረፍት እነ እስክንድር ቤት መሔድ የጀመረው ገና የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሳለ ከእስክንድር ጋር እንደተዋወቁ ነው።አንዳንዴ አብረው ይሔዱና የተገኘውን ቀማምሰው ተጫውተው ይመለሳሉ ። ዘንድሮ ግን አቤል ቤታቸው ሳይሔድ ቆይቷል ።

የጠፋው ሰው እንደ ምን አላችሁ ልጆቼ ?
እሁና እናትየዋ ፥ ሁለቱን አቅፈው ሳሙዋቸው ።

“ አቤል ፣ ምነው እንዲህ ጠፋህ ልጄ ?”
ምን እባክዎን ፥ ጥናት በዝቶ ነው
“ ቢሆንስ ታዲያ ፥ አንዳንዴ መቼስ እናት ቤት ብቁ ተብሎ የተገኘውን ቀማምሶ ይኬዳል ። አሀን ፈተና ጨረሳችሁ አይደለም ? ”
“ አዎ መቼስ"

“ እንግዲህ አንድ ፈተና ነዋ የቀራችሁ ? የፊታችን ሰኔ መመረቂያችሁ አይደለም ?

አቤል ዝም አለ ። እስክንድር ስሜቱ ስለ ገባው ቶሎ ብሎ ጣልቃ ገባ ።

“ አዎ ! አይዞሽ ደርሰናል ” አላቸው « እጁ ላይ ሲጋራ መኖሩን ያዩት ይሄኔ ነበር ።

« ይኼንን ሲጋራህን ምናለ ብትተወው እስክንድር ? አቤል ጓደኛህን አትመክረውም ? ! ”

ብዙ ዓመት የተናገሩት ነገር ነው ። ሆኖም ዐይናቸው ባየ ቁጥር ዝም ማለት አይችልም ። አቤል ከመቅለስለስ ልላ
ምንም አልመለሰም።

“አይዞሽ ፡ በቅርቡ አቆማለሁ” አላቸው እስክንድር ራሱ ። እሳቸው ሣቁ ሁሌም
የሚላቸው ነገር ስለሆነ።

ማዘር ሙች አቆማለሁ ። አራት ወር ያህል
ብቻ ታገሽኝ ብቻ አላቸው።

ከልቡ ለማቆም ቆርጦ ነበር እናትየው ግን ጊዜው ደርሶ እስካሳዩ ድረስ ሊያምኑት አይችሉም ።

“ምግብ አቀረቡላቸው ከበላሉ በኋላ ሲጫወቱ ቆይተው ሲመሻሽ እስክንድርና አቤል ሊሔዱ ሲሉ፡-

ዛሬ ለምን ከዚሁ ስትጫወቱ አታድሩም ” እሉ እናትየዋ ።

“ አአይ እንሔዳለን ። እዚያው ካምፓችን ይሻለናል አለ እስክንድር እሳቸው በሚናገሩት አይነት ፣

እስክንድር በዕረፍቱ ሰሞን አቤልን ጥሎ ቤት መክረም አልፈለገም። አብረው እንዳይሆኑ ደግሞ ቤቱ አይበቃም።
ሁለት መኝታ ብቻ ነው ያለው “ አንዱ የናትየዋ ነው " በአንዱ መኝታ ላይ ከታናሽ ወንድሙ ጋር ሦስት ሆነው ተጨናንቀው መክረሙን ኣልፈለገም ። በዚያ ላይ እናትየዋ ለእነሱ የሚያቀርቡትን ምግብ ጣፈጠ አልጣፈጠልኝ ብለው ሲጨነቁ እንዲከርሙ አይፈልግም " ከአሁን በፊትም ቢሆን ትልቁ የክረምት ዕረፍት ላይ ካልሆነ የገናወን ዕረፍት ቤቱ አሳልፎ አያውቅም ። እዚያው ዩኒቨርስቲ
ውስጥ የሚከርመው ። እናትየውም ይህንኑ ስለሚያውቁ ብዙም አላግደረደሩት "

ተሰናብተዋቸው ከውጭው በር እንደ ደረሱ። እናትየው እስክንድርን ወደ ኋላ አስቀሩትና አንድ ነገር እጁ ውስጥ
ሽጉጥ አደረጉለት።

“ ምንድነው እሱ ? ” አላቸው ፡ ምን እንደሆን ልቡ እያወቀ።

“ ያዘው ለዚያ ለምናምንቴ ለሱስህ ይሆንሃል አሉት ። የዐሥር ብር ኖት ነበር ።
እኔ ከሌላ ቦታ አላጣም እባክሽ ። ይሄ ለራስሽ ይሁንሽ ” አላቸው ።ለመግደርደር ያህል ሳይሆን ከልቡ ነበር ።
ምን ጊዜም ከእናቱ ገንዘብ ሲወስድ ልቡ ያዝናል ። እንደ ሲጋራ ሱሰኝነቱ አይቅበዘበዝም ።

ያዘው ግድ የለህም” ። እኔ አለኝ ። አንድ አረርባ ብር የመንደር ዕቁብ ነበረችኝ ፤እሷ ወጥታልኝ ነው ” አሉት ።

አመስግኖ ብሯን ኪሱ ከተተ ወዲያው ማርታ በሀሳቡ መጣችበት ግን በዐሥር ብር ምን ሊኮን ?

“ አቤል ፡ በል እንግዲህ ብቅ እያላችሁ ጠይቁኝ ። አሁን ዕረፍት ናችሁ ” አሉት እናትየዋ « አቤልን ቅር እንዳይለው

ከእናቱ ተለይተው ከሔዱ በኋላ እስክንድር ስለ ድህነትና የእናት አንጀት ተቃራኒ ሁኔታ እያብሰለሰለ ነበር
ድህነት እጅዋን ሊያስራት ይሞክራል ፤ እናት እጅን ለልጅዋ ለመዘርጋት ትፍጨረጨራለች ፡፡ ምኞቷና አድራጎቷ እኩል አይሆንም “ በፍቅር ወደ ልጅዋ ስትንጠራራ
ድህንት ጨምድዶ ይይዛታል ግን ያም ሆኖ እትረታም አትሽንፍም እንደ ምንም ተፍጨርጭራ የልጅዋን እጅ
ትነካለች።

“ አሁን ወዴት ነን ?” አለ አቤል " ትንሽ እንደተጓዙ

“ አንድ ቤት ጎራ ብለን ደርቆ የከረመ ጉሮሮአችንን እናርጥብ እንጂ ! ” አለ እስክንድር ።

አቤል ገንዘብ መቆጠብ የማይችለው የእስክንድር እጅ አስግርምት ሳቀ ። ከእናቱ የተቀበላትን ገንዘብ ለማጥፋት
እንደ ቸኮለ ገባው።

“ ይልቅ ቦታ ምረጥ የት ይሻለናል ? ” አለው እስክንድር

“ ወደ ሠፈራችን አቅራቢያ አይሻልም ? ” አለ አቤል ።መቼም ከዩኒቨርስቲው አካባቢ ርቆ መቆየት አይሆንለትምና።

“ ስድስት ኪሎ ደኅና ቡና ቤት የለማ ! ከጠጣን አይቅር ትንሽ ትርምስ ብጤ ያለበት ይሻለናል ። የጠርሙስ ካካታ ! ”

" አራት ኪሎ እንሒዳ! በዚያው ወደ ካምፓስ ለመግባት ይቀርበናል ”

በዚሁ ተስማምተው ወዶ አራት ኪሎ እመሩ ።

እዚያ ሲደርሱ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ገደማ ሆኖ ነበር እስክንድር ቻቻታ ያለበትን ቦታ መምረጥ ስለፈለገ ከቡና ቤት ቡና ቤት ሲዘዋወሩ በብዛት የሚያገጥማቸው የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበር ። ተማሪው ታስሮ እንደተፋታ ሆኖአል ንኮኒ ትተደግፎ የሚጠጣው የሴት አሳላፊዎችን ዳሌ የሚዳብሰው በቡድን ተቀምጦ እየጠባ የሚንቻቻው ተሜ ነው። ከወላጅ ከዘመድ የተላከ ከወዲያ ወዲህ ተጠራቅሞ ተቀብሮ የቆየ ገንዘብ መውጫው ዕለት ነዉ። በፈተና ማግሥት ሰክሮ መጥቶ ግቢው ውስጥ መደንፋት ፡ የማይጠጡ ተማሪዎችን መረበሽ ። ወይም ሰክሮ በየበረንዳው አድሮ
ጠዋት “ ጀብድ ” አርጎ ማውራት በዩኒቨርስቲ ውስጥ እየተለመደ የመጣ ይመስላል በተለይ ይህ ሁኔታ አይሎ
የሚታየው ከገጠር በወጡ ተማሪዎች ላይ ነው ። የአዲስ አበባው ተማሪ የቡና ቤቱን ትርምስ ከማዘውተር “ የኖርንበት ነው ” በማለት ዐይነት ቆጠብ ይላል ። ገንዘቡንም ቢሆን ከገጠረ እንደ መጡት አጠራቅሞ ማቆየት አይችልም ። አንዳንዱ እንደ ቱሪስት አስጐብኝ ገጠሬዎቹን ይዞ የከተማውን
ምርጥ ቡና ቤቶች በማስተዋወቅ የጋራ “ ጀብድ ” ይፈጽማል

እስክንድር አንድ ሞቅ ያለ ቡና ቤት አግኝተዉ ገቡ አንድ አንድ ቢራ ይዘው ቁጭ ከማለታቸው ፡ ሳምሶን ጉልቤው ዝንጥ ብሎ መጣ ሁሉም አራት ኪሎ መጠጣት የመረጡት ማታ ወደ መኝታ ቤታቸው ለመግባት እንዲቀርባቸው ይመስላል ።

ሳምሶን እስክንድርና አቤልን ሲያገኛቸው ደስ አለው ።በተለይ አቤልን መጋበዝ፤ ይፈልግ ነበር ።ጠዋት የለበሰውን
ቀያይሮ አፍላ ጉልበቱን ወጣጥሮ በሚያሳይ መሉ ጅንስ ሽክ ብሎአል ።

"ከመቼው ተሠየማችሁ ? አላቸው ፡ አጠግባቸው ለመቀመጥ መንበር እየሳበ

“ አንተም ደህና ጊዜ ደርሰሃል ፤ ቁጭ በል አለው እስክንድር።

ሳምሶንም ቢራ አዝዞ
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

#ክፍል_ሁለት
#ቬንዴታ
#ብቀላ

...በፈጸመባት ተደጋጋሚ ወንጀል ምክንያት ህሊናዋ ሊሸከመው
ከሚችለው በላይ በደል ያደረሰባት፤ እንደሻውን አጥፍታ፤ እራሷን ለማጥፋት የገባችውን ቃል ተግባራዊ የምታደርግበት የመጨረሻዋ ሰዓት
ከአክስቷ ጀምሮ የቅርብ የሆኑ ሰዎችን በሙሉ ተዘዋውራ ጠየቀች፡ስንብት መሆኑን አላወቁም፡፡

ውሣኔዋን ተግባራዊ የምታደርገው እንደ ነገ ሆኖ፤ ዛሬ ግን አሉኝ የምትላቸውን እናቷን፣ ወንድሟን፣ ጓደኛዋን፣ በደንብ አጫውታ መለየት አለባትና፤ የልቧን በልቧ ይዛ፤ እንደታላቅ እህቷ የምታየት፣ ደስታዋንም ሆነ ከሁሉም በላይ ችግሯን ስትጋራት የኖረች ጓደኛዋን በፍቅር ልትሰናበታት ሄደች፡፡
እንዳገኘቻት ሄዳ እላይዋ ላይ ጥምጥም ብላ አለቀሰች፡፡ አዜብም እንደሷው አቀፈቻትና ተላቀሱ፡፡
“በፍጹም እንደዚህ ያለ አደጋ ይደርስበታል ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ ትሁቲና እኔ ባንቺ ምንም ዕድለኛ አልሆንኩም፡፡ የኔ ድርጊትና ምክር ሁል ጊዜ ሲጉዳሽ እንጂ ሲጠቅምሽ ባለማየቴ፤ በጣም ነው
የተሰማኝ፡፡ ከዚህ ሁሉ ለምን ትንሽ ራቅ አልልላትም የሚል ስሜት ተሰምቶኝ ነው እንጂ፣አንቺን ለማሳዘን አይደለም፡፡ ይቅርታ አድርጊልኝ” በማለት እየሳመች፤ እያባበለች፤ ይቅርታ ለመነቻት፡፡
“አዜቢና ቁጭት ተሰምቶሽ ነገርሽው እንጂ፤ እንደዚህ ጭካኔ የተሞላበት የከፋ ጉዳት ያደርስበታል ብለሽ እንዳላሰብሽ ይገባኛል። በዚህ ምንም ልትፀፀቺ አይገባም፡፡ እግዚአብሔር ገና ስፈጠር ይህንን ሁሉ መከራ እንድሸከም ፈርዶብኝ ያሸከመኝ እዳ ስለሆነ እችለዋለሁ :: አንቺ
ግን ሁሌም ስቸገር ከጉኔ ከመገኘት ሌላ ምንም ያደረግሽኝ ነገር ስለሌለ
መጥፎ ስሜት በፍጹም ሊሰማሽ አይገባም፡፡ እንኳንም ብቻ ከሞት
ተረፈ፡፡ ምንም ቅሬታ አላደረብኝም፡፡ አትጨነቂ የኔ ቆንጆ፡፡ ብላ እቅፍ አድርጋ አፅናናቻትና፤ እንደ ዱሮአቸው በፍቅር ሲጨዋወቱ አረፈዱ፡፡ለሻምበል ብሩክ ስልክ ደውላ አንዱአለም ስለደረሰበት አደጋ የነገረችው መሆኑን፤ እሱም ደንግጦ "አይዞሽ እንደሻውን ገርፈን እናውጣጣዋለን" በማለት ቃል የገባላት መሆኑን፤ እውነት አስመስላ ስትነግራት አዜብ ተደሰተች፡፡ እንደሻው የእጁን እንዲያገኝ ቸኮለች፡፡

“በጣም ቆንጆ ነው ያደረግሽው ትሁትዬ የውስጥ እግሩ ወደ ውጭ እስኪገለበጥ ድረስ እንዲያስገርፈው አድርጊ፡፡ ይሄ ግፈኛ! ለሱ ምንም ምህረት አያስፈልገውም!” ስትል በቁጭት መከረቻት፡፡ ነገ ጠዋት በፓሊስ እንደሚያስወስድላትና! የሚሰራበትን ሱቅ
ለመጠቆም፡ ዛሬ ቦታውን ማየት እንደሚያስፈልጋት ስትነግራት፤ አዜብ
ልብሷን ቶሎ ለባብሳ ተነሳች፡፡መርካቶ ሄደው የእንደሻውን ሱቅ በሩቁ አሳየቻት፡፡ ሱቁን በስንት ሰዓት እንደሚከፍት ሁሉ በቂ መረጃ አገኘች፡፡ ዋናው
የእንደሻውን ሱቅ ማየቱ ነበር፡፡

ዓላማዋ እንደሻው ውስጡ ይንጐራደዳል፡፡ ለነገው ብቀላ እንድ እርምጃ ተጠናቀቀ፡፡ እዚያ ሱቅ ውስጥ ነገ... ነገ... ጠዋት ጠላቷ ገላው፣
በጥይት ወንፊት ሆኖ የወንድሟን ደም እንዳንዠቀዠቀው፣ ደሙ ይንዠቀዠቃል....

ይህንን የነገውን ትርዒት በአእምሮዋ እያውጠነጠነች፤ ተያይዘው ወደ እነ አዜብ ቤት ተመለሱ፡፡
በመሰነባበቻቸው ሰዓት ላይ ግን የትህትና ሁኔታ ትንሽ ከወትሮው ለየት አለ፡፡ ጥብቅ አድርጋ አቀፈቻት፡፡ እያገላበጠች ሳመቻት፡፡ እንደገና ... እንደገና ... እንደገና ይህ ለአዜብ እንግዳ ነበር፡፡ ትህትና
ግን የስንብት ስለሆነ አልታወቃትም፡፡

ዐይኖቿ ፍዝዝ ብለው፤ እላይዋ ላይ ተተክለው ይቀሩ ነበር፡፡ እነዚያ ውብ ዐይኖቿ፣ ለየት ያለ መልዕክት ያስተላልፉ ነበር፡፡ ስንብት! ደህና ሁኝልኝ ውዷ ጓደኛዬ.... ዐይነት፡፡ አሁን ደግሞ ትንፋሽ
እስከሚያጥራት ድረስ አቅፋ እየተሰናበተቻት ነው፡፡ይህ የትህትና ሁኔታ
አዜብን ረበሻት፡፡
“ስላስቀየምኳት ይሆን ወይስ?...” መልስ የሌለው ጥያቄ፡፡ በመጨረሻም አገላብጣ ሳመቻትና፤ ታክሲ ውስጥ ገባች። ዞር ብላ
እጆቿን አውለበለበችላት፡፡ የምሣ ሰዓት ደርሶ ነበር፡፡ ምሣ በሁለት ሣህን
አዘጋጅታ፣ ሠራተኛዋ የካቲት አሥራ ሁለት ሆስፒታል እናቷ ጋ እንድትሄድ ስታደርግ፤ እሷ ደግሞ ወደ ወንድሟ ሄደች፡፡ ሆስፒታል ውስጥ ወንድሟን ስታጨዋውተው ዋለች፡፡ አዳሯን ደግሞ እናቷ ጋ አስባለች፡፡
የቀኑን ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ ለአንዱዓለም ሰጠችው፡፡ወንድሟን ለመሰናበት ስሜቷን በእንባ ለመግለጽ አልፈለገችም፡፡ ሆዷ እንዳይባባ፤ ራሷን አጠነከረች፡፡ በእርግጥም ተሳካላት፡፡ ከምንጊዜውም የበለጠ ሳቂታና ደስተኛ መስላ ታየች፡፡

እዚያ አጠገቡ ቁጭ ብላ እንዲሁ ስትደባብሰው፣ ስታሻሽው፣ ስትስመው፣ ስታሳስቀው፤ ዋለች፡፡ ሰዓቱ እየሄደ ነው፡፡ የምታዘጋጀው ደብዳቤ አለ፡፡ እናቷ ዘንድ አዳሪ ነች፡፡ ልትለየው ባትፈልግም ፤ ጣጣዋ ብዙ ነውና፤ ልትሰናበተው ተዘጋጀች፡፡

በዚያን ሰዓት ግን ቆራጥ የነበረችው ልጅ ተረታች፡፡ ሳታስበው እላዩ ላይ ድፍት እንዳለች ቀረች፡፡ ሆዷ ቡጭ ቡጭ አለ፡፡ መተንፈስ አስከሚያቅተው ደረስ እላዩ ላይ ተጣበቀች፡፡
በሽተኛ መሆኑን ዘንግታ፤ አየር አሳጠረችው፡፡ እንዱዓለም ቶሎ
ቶሎ መተንፈስ ሲጀምር፤ ደንግጣ ቀና አለችለት፡፡ በዚያን ጊዜ ግን ዕይኖቿ በእንባ ተሞልተው ነበረና፤ እንባዋ እየወረደ ፊቱን አረጠበው፡፡
“ተሽሎኛል እኮ እታለምዬ ለምን ታለቅሻለሽ?” ለመጨረሻ ጊዜ እንደምትሰናበተው ያላወቀው ወንድሟ፡፡ እየደጋገመች ሳመችው፡፡ “ደህና
ሁንልኝ አንዱዓለሜ” ከሳግ ጋር እየተናነቀች ተነሣች፡፡
“ደህና እደሪ እታለም” በአለቃቀሷ ሆዱን ባር ባር እያለው፡፡ ከዚያም ወደ ኋላ ገልመጥ አለችና ባይ ባይ " በማለት እጆቿን አወዛወዘችለት፡፡ የመጨረሻ ስንብት፡፡ ከዚያም በሚንከራተቱት ዐይኖቿ
በስስት ተሰናበተችውና፤ ፈጠን ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣች፡፡

እቤት እንደደረሰች ለሻምበል ብሩክ ደብዳቤ ትጽፍ ጀመር፡፡
“ይድረስ ለማፈቅርህ ውድ ወንድሜ ለሻምበል ብሩክ በላይ ለጤናህ እንደምን አለህልኝ፡፡ እኔ እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ፡፡ ብሩኬ በጣም ናፍቀኸኛል፡፡ ግን ምን ያደርጋል? አልታደልኩምና ናፍቆቴን መወጣት አልችልም፡፡ይህ የመጨረሻው ቃሌ ስለሆነ አንድ ነገር ልጠይቅህ? ይህንን ደብዳቤ አንብበህ ከመጨረስህ በፊት እንዳታቋርጠው እሺ? ዛሬ የምንግርህ በሙሉ ቁም ነገር ነው እሺ? ብሩኬ መጀመሪያ ያየሁህ ዕለት የደነገጥኩብህ እኮ አባዬን ስለመሰልከኝ ነበር፡፡ አባዬ ልክ እንዳንተው እንዴት መሰለህ የሚያምረው? በተለይ የምትለብሱት
ዩኒፎርም እንዴት መሰለህ የሚያምርባችሁ። በቁመታችሁ፣ በግርማ
ሞገሳችሁ፣ በቃ ምን ልበልህ አንድ ዐይነት ናችሁ፡፡ ያኔኮ ጣቢያ መጥቼ
ቢሮህ ስገባ ደንግጬ የቀረሁት ለዚያ ነበረ፡፡ ምናልባትም የዚያን ዕለት
የተሰማኝ ስሜት በህይወቴ ውስጥ የመጀመሪያው ነበረ ብልህ ውሸታም
አድርገህ ስለቆጠርከኝ አታምነኝ ይሆናል፡፡ እንደዚያ ለወንድ ልጅ
ደንግጬ አላውቅም ነበረ፡፡ ባንተ ግን ደነገጥኩ፡፡ ከዚያም ቀስ በቀስ ወደድኩህ፡፡ ቀንም ሆነ ሌሊት አስብህ ጀመር፡፡ ስላንት ማውራት ደስ ይለኛል፡፡ እንደዚያ የሚያደርገኝ አዲስ ነገር ፍቅር መሆኑን ከኔ በፊት ያወቀችው አዜብ ነች ብልህ ይገርምህ ይሆናል፡፡ ብሩኬ ሙት አሁንም እወድሀለሁ፡፡ በእውነት እኔ እኮ ባለጌ ልጅ አልነበርኩም፡፡ የሆነውን ሁሉ
ልንገርህ? ዶክተር ባይከዳኝ ምኔም አይደለም፡፡ ምንም አላደረገኝም፡፡ ከሱ
ጋር የነበረኝ ግንኙነት እናቴን አክሞ እንዲያድንልኝ እንጂ ባንተ ላይ
ደርቤ ያፈቀረኩት ሰው ሆኖ አልነበረም አንተ ከዶክተር ባይከዳኝ
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....እንደ ድንጋይ ከተጫናት ሰመመን ውስጥ ቀስ በቀስ እየወጣች ስትመጣ… እላይዋ ላይ ተጭኖ የያዛት ድቅድቅ ጨለማ እንደ ጭስ እየሳሳ እየበነነ ለቋት ሲጠፋ በመጀመሪያ የተቀበላት በእግሮቿ መሃል የሚነዝራት የደነዘዘ ስቃይ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ጭንቅላቷ እየጠራ ሲመጣም አይኖቿን ለመክፈት አልደፈረችም፡፡ ሌላ ዱላ፣ ሌላ ስቃይ ሌላ የጋለ ሽቦ የሚችል
አካል አልነበራትም። በክፍሉ ውስጥ ብቻዋን ትሁን አትሁን እርግጠኛ
አልነበረችም፡፡ አይኖቿን ለመክፈት ግን አልደፈረችም፡፡

እጆቿ ግራና ቀኝ ተወጥረው ከታሰሩሰት ተፈተው በድን እንደሆኑ ሁሉ በግራና በቀኝ ተዘርረዋል፡፡ በተኛችበት ልብስ ደርበውላታል፡፡ እግሮቿ ግን አሁንም ግራና ቀኝ ሁለት ቦታ ተወጥረው እንደታሰሩ ናቸው፡፡ ቁስሏን ለማዳመጥ ሞከረች፡፡ በጭኖቿ መሃል የሚሰማትን ስቃይ ለማዳመጥ ዝም አለች የተዳፈነ... የደነዘ… የደበዘዘ ስቃይ፡፡ ግራ ክንዷ ላይ ህመም ተሰማት:: ለመነቃነቅ ግን አልደፈረችም፡፡ በአይነ ህሊናዋ ሁኔታውን
ለመቅረፅ ሞከረች። መቼ ነበር በጋለ ሽቦ ጭኖቿ መሃል ሰውነቷን ያቃጠሏት? ዛሬ? ትላንት? ዛሬ ምንድነው? ቀን ነው ሌሊት? ሰዓታትና ቀናት ትርጉም ካጡባት ቆይተዋል፡፡

ድምፅ የሰማች መስላት። ዓይኖቿን እንደከደነች ጆሮዎቿን ኣስልታ ተጠባበቀች፡፡ የበር ድምፅ ተሰማት… የሚከፈት የበር የሚያሰማው ድምፅ..

“አልተነሳችም፡፡” አለ አንድ ድምፅ በሹክሹክታ፡፡

“ኮለኔል” አለ አንድ ድምፅ በሹክሹክታ “ዙርያውን አጥረነዋል።በርም ላይ አንድ ሰው አቁመን እየተጠባበቅን ነው::”

“መጣሁ” ሲል ተሰማት ማርቆስ፡፡

ሁለት የእግር ኮቴዎች በግራና በቀኟ ተስሟት…በስተቀኝ ኣንድ መዳፍ ግንባሯ ላይ አረፈ::

“ከነቃች የመርፌ ማደንዘዣውን ስጣትስቃይ ሊኖርባት ይችላል።” የማርቆስ ድምፅ ነበር።

“ካስቸገረችኝስ ልምታት?” አለ በስተግራዋ የቆመ ሌላ ሰው፡፡

“ረጋ ብለህ አባብለህ ውጋት። ለምን ትመታታለህ? ደግሞ አታስቸግርህም.. ከተወራጨችብህ ግን ግሉኮሱን ንቀልላት፡፡” አለ እጁን ግንባሯ ላይ የጫነው ማርቆስ በጣቶቹ ፀጉሯን ወደኋላ እያበጠረ፡፡ “ጠዋት እቀየርልሃለሁ፡፡”

ኮቴ ተሰማት፡፡ ተከታትለው ሲወጡ ሰማች። በሩ ሲዘጋ በክፍሉ ውስጥ ፀጥታ ሲነግስ ስትፈራ ስትቸር አይኖቿን ገለጠቻቸው::መኝታ ክፍሏ ውስጥ ብቻዋን አስተኝተዋታል፡፡ በቢጫው የብርድ ልብሷ ከአንገቷ እስከ
እግሯ ጫፍ ድረስ ሸፍነዋታል፡፡ በተንጋለለችበት ዙሪያዋን ተመለከተች፡፡
ግራ ክንዷ ላይ የሚሰማት ህመም ከራስጌዋ ከተንጠለጠለው የግሉኮስ
ከረጢት ጋር የተያያዘው መርፌ ክንዷን ጠልቆ የገባበት ላይ መሆኑን ተረዳች። የክፍሉ መጋረጃ ተዘግቷል፡፡ በጥግና ጥግ የታየው ሰማይ ጨልሟል... መሽቷል፡፡ ሰመነቃነቅ ስትሞክር ግራና ቀኝ የታሰሩት እግሮቿ መሃል የተዳፈነው ስቃይ እንደ ጦር ወጋት፡፡ ከስሱ የብርድ ልብስ በታች ያለው እራቁት ሰውነቷ ተንሰፈሰፈ፡፡

ድምፅ ተሰማት የመኝታ ቤቷ በር ተከፈተ፡፡ ቶሎ ዓይኖቿን ጨፈነቻቸው፡፡ : እንደነቃች ማወቅ የለባቸውም፡፡ ዝም ብላ መተኛት ነው ያለባት፡፡ መረበሽ የለባትም! አለበለዚያ ይመቷታል፡፡ ዝም ብላ መተኛት። በሩ ሲዘጋ ተሰማት: የእግር ኮቴ እየቀረባት መጣ. አንድ በላብ የረጠበ እጅ
እራቁት ትከሻዋ ላይ ሲያርፍ ተሰማት… ትንፋሼ እላይ እታች የሚል ትንፋሽ እላይዋ ላይ የነበረው ስስ የብርድልብስ ፡ ተገፈፈ፡ መረበሽ የለባትም… መንቃቷን ማወቅ የለባቸውም... አለበለዚያ ድጋሚ
ያስቃይዋታል. , ትከሻዋ ላይ ያረፈው በላብ የራሰ መዳፍ ወደታች ወደ
ደረቷ ተንሸራተት…. እልተንቀሳቀሰችም ጡቶቿ ሲዳስሱ ተሰማት እላይ እታች የሚል ትንፋሽ… ፍርሃት ወረራ ግራ ክንዷ ላይ የተሰካውን መርፌ አስሮ የያዘው ፕላስተር ተላጠ.. ክንዷ ላይ የተሰካው መርፌ ተነቀለ መንቃቷን ማወቅ የለባቸውም… አለበለዚያ ይመቷታል... እላይ እታች የሚለው ትንፋሽ ቀረባት፡፡ ብርድ ልብሷ ወደታች ተጎተተ ፍርሃቷ
እየጨመረ መጣ እላይ እታች የሚለው ትንፋሽ ወደ አንገቷ ስር ሲጠጋ ተሰማት.. ብርድ ልብሱ ከላይዋ ላይ ተንሸራቶ ወደ መሬት ወደቀ፡፡ ራሷን መቆጣጠር አቃታት… አይኖቿን ገለጠቻቸው፡፡

ጺማሙ ሰውዬ ነበር፡፡ እላይዋ ላይ እንዳንገርበበ ድንገት አይኖቿን ስትገልጥ ደንገጥ አለ፡፡ ወዲያው ፈገግ አለላት... የሸሚዙን ቁልፎች መፍታት ጀመረ… ፈገግ አለላት ድጋሚ… ሸሚዙን ከላዩ ላይ ወርውሮ ተጠጋት… እጆቹን ጡቶቿ ላይ ጫናቅው ድንገት ተወራጨች፡፡ ሙቅ
እርጥብ እጆቹን ከላይዋ ላይ ገፍትራ ተሸማቀቀች ፈገግ አለላት፡፡ አልጋዋ
ላይ የተንጋለለውን እራቁት ገላዋን ከላይ እስከታች በተራሱ ኣይኖቹ ዳሰሰው፡፡ ምራቁን ሲውጥ ትልቅ ማንቁርቱ እላይ እታች ሲመላለስ በፍርሃት ተንቀጠቀጠች፡፡ ድንገት ዘሉ አፏን በመዳፉ ኣፈናት… ታገለችው…
እጆቿን እያፈራረቀች እንደብረት የደደሩ ሁለት ክንዶቹን ደበደበቻቸው
ቧጠጠቻቸው... ያለብዙ ችግር እፏ ውስጥ ጨርቅ ጎስጉሶ ለጎማት

ትንፍስ ትንፍስ እያለ ቁልቁል ተመለከታት፡፡ አይኖቹ የሚያርፉበት
ቦታ ያጠ ይመስላል፡፡ መላ ሰውነቷ ላይ ተንቀዠቀዡ።

ሱሪውን ማውለቅ ጀመሬ በተንጋለለችበት በምሬት… ጭንቅላቷን አወራጨችው… እንባዋ ደረሰላት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ቢሮው ትዕግስቱ አልቋል፡፡” አለ ከቴልአቪቭ የገባው ይሁዳ አሚ
የብርቱካን ጭማቂውን ተጎንጭቶ ብርጭቆውን ካስቀመጠ ሰኋላ ረጅም
ጺሙን እየዳሰሰ፡፡

የአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴልኝ የመዋኛ ስፍራ በስተቀኛቸው አድርገው ተቀምጠዋል፡፡ በርካታ እንግዶች በመዋኛ ልብሶቻቸው ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡ የተቀሩት በደረትና በጀርባቸው እየተገላበጡ ጭል ጭል የምትለውን ለስላሳ የጳጉሜ ፀሐይ ይሻማሉ፡፡

ይሁዳ አሚ በሆቴሉ ውስጥ ከያዘው የመኝታ ክፍል ወጥቶ ከቀጠሮኣቸው ስፍራ የደረሰው ልክ በሰዓቱ ነበር። ከቀጠሮው ሰዓት ቀደም ብሎ የደረሰው አሃሮን የእንግዳውን ፀባይ ስለሚያውቅ የብርቱካን ጭማቂ አዝዞ ከፊት ለፊቱ አስቀምጦ ይጠባበቅ ጀመር፡፡ አሚ የሌሊት ልብሱን ሳይቀይር በላዩ ላይ ወፍራም የጠዋት ልብሱን ደርቦ ወገቡ ላይ ቀበቶውን ሽብ አድርጎ ከጥጥ የተሰራ ወፍራም የእግር ሹራብና የቤት ነጠላ ጫማዐእንዳደረገ ወደ መዋኛው ስፍራ የሚወስደውን ደረጃ በእርጋታ ወርዶ ወደዐአሃሮን አመራ፡፡

“እንኳን ደህና መጣህ፡፡” አለ አሃሮን ተነስቶ እንደቆመ የአሚን እጅ
ጠበቅ አድርጎ እየጨበጠ፡፡

“እንኳን ደህና ጠበቅኸኝ።” አለ አሚ ነጫጭ ውብ ጥርሶቹን ለአንድ አፍታ ብልጭ አድርጎ የጓደኛውን እጅ እየወዘወዘ፡፡

አሚ “ ኪዶን” በሚል ስያሜ በሚታወቀው የሞሳድ ገዳይና አፋኝ
ክፍል ውስጥ ለአስራ ሰባት ዓመታት የሰራና አትግደል እና አትዋሽ
ከሚሉት ከሙሴ ትዕዛዛት በስተቀር በተቅሩት በስምንቱ ትዕዛዛት ላይ ፌዝ
የማያውቅ ጥብቅ ሃይማኖተኛ አይሁዳዊ ነው። በሌሊት ልብሱ ላይ የደረበው
ወፍራም የጠዋት ልብስና ቡፍ ካለ ጥጥ መሳይ የቤት ጫማው ጋር ሲያዩት
ጺማሙ ሰው በቤት ውስጥ ተቀምጦ የሳጠራ ዘንቢሉችን ሲሰራ የሚውል
የዋህ በሬ ይመስላል፡፡

“የብርቱካን ጭማቂ፡፡” አለ አሚ ፈገግ ብሉ ከጎኑ የቆመውን የሆቴሉን አስተናጋጅ እየተመለከተ፡፡

የአልኮል መጠጥ ፍጹም የማይቀምስና የአሳማ ስጋ አፉ የማይገባ ጥብቅ ሃይማኖተኛ የሆነው አሚ በመስከረም 5 1972 በሙኒክ ሃያኛው ኦሎምፒክ ዝግጅት ላይ የብላክ ሴፕቴምበር ቡድን የእሥራኤል ስፖርተኞችን ሰፈር በመውረር አስራ አንድ ተጨዋቾችን ከገደለ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ጎልዳሜይርን የብቀላ ትዕዛዝ
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


....ከግንባሯ እና ከብብቷ ስር ላቧን እየጠረገች አኔ ቤታማን ከሶል ሳይክል
የዳንስ ትምህርቷ ወደ ብሬንት ውድ ፀሃያማ ቀን በጥሩ ስሜት ውስጥ ሆና
ወጣች፡፡

የስትራንቨስኪ ኮንሰርት ላይ ባሳየችው ብቃቷ የተነሳ በሁሉም ቦታዎች ላይ ቫዮሊን እንድትጫወት ግብዣዎች እየቀረቡላት ይገኛሉ። በዚህም የተነሳ
ምንም የገንዘብ ችግር እንደማይገጥማትና ቀጣይ ሥራ አላገኝ ይሆን ከሚል ሃሳብ ወጥታለች፡፡

በግላዊ ህይወቷም ቢሆን ሁሉም ነገር ሰላም የሆነ ይመስላል።ምክንያቱም ባሏ በስልክ መልዕክቶች፣ በስልክ ጥሪዎች እና ስጦታ አበባዎች እሷን ማስጨነቁን ትቶታል፡፡ በዚህም የሃዘኔታ ስሜት ቢሰማትም በመጨረሻ ግን ልቧ እረፍት ሊያገኝ ችሏል፡፡ አሁንም ቢሆን የሆነ የልቧ ክፍል እሱን ያፈቅረዋል፡፡ ግን ደግሞ ኒኪ ትክክል ናት፤ የሁለቱ መፋቀር
ብቻ በቂ አይደለም፡፡

አሁን ጥሩ ስሜት እንዲስማት ያደረገው ሌላ ነገር ከኒኪ ጋር መስማማት መቻላቸው ነው፡፡ ኮንሰርቱን ባቀረበችበት አዳራሽ የመልበሻ ክፍል ውስጥ እያሉ ባሏ በላከላት ብዙ አበቦች የተነሳ የማይገባ ነገር ከተነጋገሩ በኋላ አኔ መልሳ ኒኪን ማየት አፍራለች፡፡ ስለሆነም ከኒኪ ጋር ያላትን የህክምና ቀጠሮ ደውላ ሳታሳውቅ ሰረዘችው፡፡ ቀጣዩንም የህክምና ቀጠሮ ሳትሄድ ቀረች፡፡ ቀጠሮውን ሳታሳውቅ በመሰረዟ ከኒኪ የስልክ ጥሪ ወይም ደግሞ በኢ-ሜይል ቀጠሮውን ሳታሳውቅ በመሰረዟ የቀጠሮዎችን ክፍያዎች እንደምትከፍል የሚያስጠነቅቅ መልዕክትም አልተላከላትም፡፡ኩራቷን ውጣ ለኒኪ ልትደውልላት እና ባለፈው ምሽት ስላሳየቻት ያልተገባ ባህሪ ይቅርታ ልትጠይቃትም ነበር። በዚያ ላይ ደግሞ በጣት የሚቆጠሩ ጓደኞችን እያጣች ነው፡፡ እና ብቸኝነት እየተሰማት ነው በዚህ ስሜት ውስጥ እያለች በነበረችበት ወቅት ነበር እንግዲህ የኒኪ በወረቀት ላይ የተፃፈ ይቅርታን ያዘለ መልዕክት አፓርትመንቱ ድረስ የመጣው፡፡
ሌላ አዲስ ቴራፒስት ጋ ብትሄጅ እረዳሻለሁ፡፡ ምንም ዓይነት መጥፎ
ስሜትም አይሰጠኝም፡፡ ነገር ግን ሌላ ቲራፒስት ጋር እንዳልሄድሽ ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም አብረን ስንሠራቸው የነበሩ ነገሮች እየረዱሽ እንደሆነም አስባለሁ፡፡ አንቺም በውስጥሽ ይሄ እንደሚሰማሽ እርግጠኛ ነኝ ይላል መልእክቱ፡፡ አኔ ምን እንደሚሰማት እርግጠኛ አይደለችም፡፡ ማለትም ኒኪ ወደ እሷ ስለተመለሰች ደስ ብሏታል፡፡

የሆነ ያልተለመደ ነገር እየተሰማት እንደሆነ ይገባታል፡፡ ለዚህ ደግሞ
ዋነኛዋ ተጠያቂ እሷ ኒኪ ናት፤ ምክንያቱም የአካሚና የታካሚ የግንኙነት
መስመርን አልፋ እሷም እንድታልፍ ያደረገቻት እራሷ ናት፡፡

ከፊት ለፊቷ ከሚገኘው ካፌ ገብታ ውድ የፍራፍሬ ጭማቂ ጠጣች፡፡ እና መኪናዋ ውስጥ ዘልላ ገባች እና ወደ ኒኪ ቢሮ በሚወስዳት መንገድ ላይ መኪናዋን ማሽከርከር ጀመረች፡፡ የተለመደው የህክምና ቀጠሮዋ ከሰዓት ላይ ቢሆንም አኔ የኒኪን ፊት ለማየት ስለጓጓች ነው በአሁኑ ሰዓት ወደዚያ ለመሄድ የፈለገችው፡፡ ምናልባትም ቢሮዋ ውስጥ ታካሚ ከሌለ ወጣ ብለው ወይንም እዚያው ቢሮ ውስጥ ለጥቂት ጊዜ ያህል እያወሩ ሻይ ቡና ማለት ይችላሉ፡፡

የመኪናዋን ጣሪያ ከፈተችና ንፋሱ ሰውነቷ ላይ ያለውን ላብ እንዲያደርቅላት አደረገች፡፡ የጠራው ሰማያዊ ሰማይንም ቀና ብላ ስትመለከት ሰማዩ የእሷን ደስታ የተጋራት መሰላት፡፡ የኒኪ ቢሮ ከሚገኝበት ህንፃ ስትደርስ ከመኪናዋ ወርዳ ቁልፏን መኪናዋን በተገቢው ቦታ ለሚያቆምላት
ሰው ልትሰጠው ስትል የምታውቀው ድምፅ ከኋላዋ ሲያወራት ሰማች እና
በድንጋጤ ደርቃ ቀረች፡፡

“ሆላ የኔ መልአክ” የሚለው የባለቤቷን ድምፅ ስትሰማ ልቧ በአፏ የሚወጣ እስኪመስላት ድረስ ደነገጠች፡፡ ጥላው ከመጣች ጀምሮ ይሄ ነገር ሊከሰት እንደሚችል ስታስብ ነበር፡፡ በቃ እሷ ያለችበት ቦታ ድረስ በድንገትመጥቶ እንደሚያገኛት ስታስብ ነበር፡፡ በመጀመሪያ ላይ እነዚህ ሃሳቦች
በህልሟ እየመጡ ቅዠት ይሆኑባት ነበር፡፡ በህልሟ ትታው ወደመጣችው ባሏም ተገድዳ ስትመለስ ለብዙ ጊዚያት ስታልም ነበር፡፡ ከጊዜ ብዛት ግን ይሄ ስሜቷ እየጠፋ መጥቶ ነበር፡፡ አንዳንድ ቀን ስለእሱ ስታስብ እንዲህ ባለ ድንገተኛ ሁኔታ እንዳያገኛት የቀን ህልሟን ስታልም ነበር፡፡

ይኼው አሁን ግን እሱ አጠገቧ ይገኛል፡፡ እሷን ሊያገኝም እሷ ያለችበት
ቦታ ድረስ ለመምጣት ችሏል፡፡

ለጥቂት ጊዜ ትቷት የነበረው ሽብርም ከባሏ ጋር ተመልሶ መጣ ማለት
ነው፡፡ “ተወኝ ብዬሃለሁ! ከአጠገቤ ዞር በል!” ብላ የመኪናውን ቁልፍ
ለፓርኪንግ ሠራተኛው ለመስጠት ስብስብ ወዳሉት ጥቂት ሰዎች ተጠጋች::

“እኔ” ብሎ ሉዊስ ሮድሪጌዝ ተወዳጅ ሚስቱን በፍቅሯ በተጎዳው ዓይኑ ተመለከታት፡፡ “ምን ሆነሻል ውዴ፤ ሉዊስ ነኝ እኮ ለምንድነው የፈራሽኝም
አላት፡፡

ድምፁ ውስጥ ንዴት አይሰማም፡፡ ከዚያ በላይ ግን የሃዘኔታ ድምፀት
ይነበብበታል፡፡ ይህንን ስታይ በሃይል ይመታ የነበረው ልቧ እየተረጋጋ
መምታት ጀመረ፡፡

እንደሁልጊዜውም ዝንጥ ብሎ ለብሷል። ምርጥ የሳቪሌ ሙሉ ልብስ፣ የሐር ከረቫትና የጉቺ አፍተር ሼቭ የተቀባው አዲስ የተላጨው ፂሙ እንኳን ሳታስበው ከእግሮቿ መሃል ንዝረትን ፈጠረባት፡፡ በግራ እጇ በደንብ ተደርገው የተሠሩ የእሷ ምርጫ የሆኑ አበቦችን ይዟል፡፡

“እዚህ ምን ትሠራለህ ሉዊስ?” ብላ ጥርጣሬ በማይነበብበት ለስላሳ
ድምፅ ጠየቀችው፡፡

“ኤል ኤ ውስጥ የሆነ ቢዝነስ አለኝ፡፡ እዚህ ለጥቂት ቀናት እቆያለሁ”
አላት፡፡

አኔም ዓይኗን አጥብባ “ወደ አሜሪካ መቼም ተመልሰህ እንደማትመጣ
ነግረኸኝ ነበር፡፡”

“ልክ ነሽ በጣም ሞክሬ ነበር... ግን ይሄ ነገር በጣም አስፈላጊዬ ነገር ነው፡፡”

ሉዊስ ቢዝነስ ሲል እሷን ይሁን ወይንስ የእውነት ለቢዝነስ ነው ወደ እዚህ የመጣው ብላ አስላሰለች እና ለቢዝነሱ ብሎ ወደ ኤል ኤ በመጣ ብላ ተመኘች፡፡ ፊቱንም ትክ ብላ እያየችው እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ስሜቶችን
ማስተናገድ ጀመረች፡፡ ለቢዝነስ ነው እዚህ የመጣሁት ያለው እውነቱን
ነው? ደስ ሊለኝ ይገባል ወይስ ልፈራ?”
“አኔ በጣም እንደናፈቅኩሽ ታውቂያለሽ አይደል?” አላት በተሰበረ የፍቅር
ድምፅ፡፡

“እኔም ናፍቄሃለሁ” ብላ እውነቱን ተናገረች፣ እና በመቀጠልም “
ግን እንደዚህ በድንገት ልታገኘኝ አይገባም... ልትደውልልኝ ይገባ ነበር።
“ስልክሽ እኮ የለኝም”
“እኔ የምሠራበት ኦርኬስትራ ቢሮ በመሄድ መልዕክት ልታስቀምጥልኝ
ትችል ነበር፡፡ ደግሞ እኔን ማግኘት ያን ያህል አይከብድም፡፡ እንደዚህ

በድንገት መጥተህ መንገድ ላይ ከምታገኘኝ ይልቅ አስቀድመህ ብታስጠነቅቀኝ መልካም ነበር” አለችው፡፡

“አስቀድሜ ባሳውቅሽ ኖሮ እኔን ለማግኘት አትስማሚልኝም ነበር” አላት።

“ቢሆንስ እሱ የእኔ ውሳኔ አይደል?” ብላ አኔ ጠየቀችው፡፡

“በእርግጥ ባሳውቅሽ ችግር የለውም ነበር፡፡” አላት እና ፈገግ ብሎ “ይኼ
ደግሞ የእኔ ውሳኔ ነው፡፡ በዚህ
ውስጥ አንቺን ማግኘቴ ደግሞ
ተስማምቶኛል።”

አኔ ምንም ማድረግ ስላልቻለች ፈገግ አለችለት፡፡ ይኼ የሉዊስ አካሄድ
ነው። የለየለት ጥጋበኛነቱን ከጥሩ ስሜት ጋር ቀላቅሎ ስለሚያቀርበው ነገሮች ይሆኑለታል፡፡ እንደርሱ ያለ ወንድ ገጥሟት አያውቅም፡፡ በእርግጥ
ደግሞ ኒኪ እሱን ዳግመኛ እንዳታገኘው ማስጠንቀቂያ ልካ ነበር፡፡

“ምሳ አብረን እንብላ” አላት እድሉን ለመጠቀም በማሰብም አበባውን
እያቀበላት፡፡

አኔ አበባውን ስትቀበለው ጣቶቻቸው ሲነካኩም በጣም ነዘራት፡፡ ያን ምሽት በእሱ ላይ ከጮኸችበት በኋላ በአካል
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


...«አባባ ትላንት ከሰዓት በኋላ ሔደ፡፡ ከሳምንት በላይ ይቆያል፡፡ሲያተራምስ ነው የሚሰነብተው:: ያሰብነው ጉዳይ እንደፈለግነው ሊፈጸም ይችላል ማለት ነው» አለች የውብነሽ ቅዳሜ ማለዳ በቁርስ ሰዓት የምሥራች ነው
የምትለውን ወሬ እያወራች፡፡

ለግብግቤ አንድ ተጨማሪ ርምጃ እንደሚሆን በማመኔ ደስ አለኝ።
ጠረጴዛውን ተደግፋ ወደ ቆመችው ባለቤቴ ዞር አልኩና ዛሬ ጋሻዬነህ አብሮኝ
ለቁርቁስ የሚሔድበት ቀን በመሆኑ አደይ አበባ እስመስለሽው ቆይኝ፣ የሚያምርበትን ልብስ አንቺ ታውቂዋለሽ፡፡ ወዴት እንደሚሄድና ጉዳዩ ምን እንደሆነ ነግሬሻለሁ» ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ፡፡ ልክ እንደ እዲስ ወፈፌ ያቅበዝብዝ
ያዘኝ፡፡ “ጭንቅላት በደስታ ሲሰክር! ለብሼ ስመለስ እኅቴና ባለቤቴ ወሬያቸውን
ተያይዘውታል፡፡ አልተጋራኋቸውም፡፡ መኪናይቱን እስከማሟሙቅ ድረስ ደረሱብኝ፡፡መንገድ ስንጀምር የወዲያነሽ ተመለሰች። «የውብነሽ፣ ሰባት ሰዓት ሲሆን እዚሁ ጠብቂኝ» ብያት ከመሥሪያ ቤቷ በር ላይ ተመለስኩ፡፡ የሥራ መግቢያ ሰዓት ሞልቶ ስለ ነበር ሠራተኛው በሙሉ ነጠላና ጥንድ ሆኖ እያውካካ ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ ገና ቁጭ ከማለቴ ቅናት እንደሚያንዘፈዝፈው ሰው መላ አካላቴ እየተንቀጠቀጠ አወከኝ፡፡ በአካባቢዬ ያለው ዕቃ ሁለ ጥያቄ የሚያቀርብልኝ እየመሰለኝ ”እስቲ አባክ! አንድ ቃል ይውጣህ! እንደሚል ሰው እጉርጩ አየሁት።

በጦርነት ዋዜማ እንደምትሸበር የፈሪ ልብ የልቤ ትርታ ከገደቡ በላይ ናረ፡፡ ለቆላ ቁስል የሆድ ቁርጠት መድኃነት መዋጥ ሆነብኝ፡፡ ብናኝ የምታህል የመንፈስ ጸጥታ ሳላገኝ ቀረሁ። የሰዓቴን ጠቋሚ ዘንግ ወደፊት በማስኬድ የጊዜን
ሥርዓታዊ ጉዞ ለመለወጥ ያስችለኝ ይመስል ሦስት ከኻያ የነበረውን አራት ከኻያ አደረግሁት፡፡ራሴን በማጭበርበሬና ሕሊናዬን በታለሌ ረቂቅ ኃፍረት ተሰማኝና
መልሼ አስተካከልኳት። እርሳሱ፣ ወረቀቱ፣ ብዕሩ፣ ወንበርና ጠረጴዛዉ ደመኛዩ
መሰሉኝ፡፡ ሒድ ሒድ ውጣ ውጣ የሚል ነገር ያዘኝ። በቀጥታ አለቃዬ ቢሮ ገባሁ፡፡
አእምሮው ተቃውሶ ሁኔታዎችን እንደ ዘነጋ ሰው ከፊታቸው ተገተርኩ፡፡ ቀና
ብለው ሲያዩኝ «ዛሬ በጣም አሞኛል ምናልባት ቢሻለኝ ብዬ ነበር የመጣሁት።
እያመመኝ ከመቀመጥ ብሄድ ይሻላል» አልኩና በዙሪያዬ የውሸት ገረገራ አጠርኩ።አለቃዩ ዘለው ለመግባት አልቻሉም። ካመመሕማ ሂድ፣ በጎ ካልሆንክ ደግሞ ሰኞ ሰው ላክ» አለና ያስደስተዋል ብለው ያሰቡትን በሞኝ ሰው ፊት ላይ የሚታይ የፈገግታ ዐይነት አቀረቡልኝ፡፡ ልቤ በደስታ ከመነረቱ የተነሣ ሣቄ ፈንድቶ አጉል እንዳያደርገኝ ነገር ሳላበዛ አመስግኜ ሹልክ አልኩ፡፡

ጭንቀትና ሥጋት ተንጠርዞ እንደ ከበደኝ በመኪናዩ ገሠገሥኩ። በራሴ
ለመተማመን ያልቻልኩበትን ምክንያት ፈልፍዬ ማውጣት ባለመቻሌ በውስጡ
ትልቅ ችግር ተፈጠረ። ከመኪናዬ ወርጄ ወደ ቤት ስራመድ ምንና የት
እንደምረግጥ የማውቅ አልመስልም። ማንም ሳያየኝ ሰተት ብዬ እንግዳ መቀበያ
ክፍላችንም ገባሁ፡፡ በቀስታ ሄጄ ከመስተዋቱ ፊት ለፊት ቆምኩ። አኳኋኔ
ስላላስደሰተኝ ምናልባት በፈገግታ ቢለወጥልኝ ብዬ ፈገግ አልኩ። ከውስጥ
ያልመነው ፈገግታ በመሆኑ ወዲያው ከሰመ፡፡ እንዲያውም ስካሩ ያልበረደለት
ሰው መሰልኩ እንጂ ጤነኛውን ጌታነህን ለመሆን አልቻልኩም፡፡ ከወደ መኝታ
ቤት እየኮረኮሩ የሚያሥት የልጅ ሣቅ አሁንም አሁንም ይሰማል። ወዲያው
ከሚከታተሉትና ሊይዙት ከተዘረጉት እጆች ለማምለጥ ግማሽ ኃይሉን ለሣቅ ያዋለ
ልጅ ከወደጓዳ እየሮጠ መጣ። ከእኔ ራቅ ብሉ ድካም የዋጣት ሣቅ እየሣቀ ቆመ፡፡
አላየኝም። የወዲያነሽ ጥቂት ዘግየት ብላ ጫጩቷን ተከትላ እንደምትሄድ ዶሮ
እሱን ለመያዝ እየሮጠች መጣች።
በልፊያ የተበታተነው ጸጉሯ እንደ ጋሽበ አዝመራ የራሱን ግላዊ ውበት ፈጥሯል። በዚያች ሰዓት ወደ ቤት ይመለሳል ብለው ስለማይጠረጥሩ እናትና ልጅ አላዩኝም፡፡ ፊቷ እንደ በጋ ወራት ሙሉ ጨረቃ ደምቆ «መጣሁብህ! ያዝኩህ!» ብላ ወደ እርሱ ተራመደች፡፡

በመሮጥ ፈንታ ሆዱን ወደ ውስጥ እጥፍ ሣቁን ለቀቀው። አፈፍ አደረገችው:: ከቡችላዋ ጋር እንደምትላፋ እናቲት ወሻ ጎበስ ብላ ወገቡን ያዘችውና ትግል ገጠሙ:: ከወዲያ ወዲህ አባተለችው፡፡ የጋሻዬነህ ሣቅ ገነነች፡፡ ትርዒቱ እንዲቀጥል እንጂ እንዲቋረጥ ባለመፈለጌ እንደ ምሰሶ ጸጥ ብዩ
ተገተርኩ፡፡ ወደ ላይ እንሥታ አንጋጣ ስትመለከተው ውብ ጥርሶቿ ተፈለቀቁ፡፡
ስለ ከበዳት አወረደችው:: ወለሉ ላይ ስታቆመው ጸጉሯን በጣቶቹ በተነባት፡፡
ሲናከሱና ሲናጩ ውለው እንደ ደከሙ አውራ ዶሮዎች እናትና ልጅ ፊት ለፊት
ቆመው ተያዩ። ጋሻዬነህ በአጋጣሚ እኔ ወዳለሁበት ዐይኑን መለስ ሲያደርግ
ድንገት አየኝና «አባብዬ! » ብሉ በሩጫ መጥቶ እግሬ ላይ ተጠመጠመ፡፡
አንሥቼ ታቀፍኩት፡፡ የወጂያነሽ ባደረገችው ልፊያ ፍቅራዊ ኃፍረት ስለ ተሰማት ከበስተጀርባዬ ቆማ አንገቴ ላይ ተጠመጠመች፡፡ በአፍንጫዋ በኩል የሚወጣው ትንፋሽ እየተናጠች እንደምትስቅ ያስታውቃል። ወደ መስታወቱ ላይ የፊተኛው ጨምዳዳ ገጽታዩ ጠፍቶ በአዲስ ፈገግታ ተተክቷል። ከግራናከቀኝ አማከለውኝ ተቀመጡ፡፡ ያ ሲያዋክበኝ የነበረው ጭንቀት ለጊዜው ገለል ስላለልኝ ጥቂት ተዝናናሁ፡፡ . የጋሻዩነህ ወለላ አንደበትና የየወዲያነሽ ለዛሚ ቃላት አያረኩኝ አምስት ተኩል ሆነ። ከዚያ በኋላ ግን እሷ ወደ ማድ ቤት፣ ልጃችን ከቤት ውጪ ወጣ፡፡ ወጣ ከማለታቸው ሥጋትና ጭንቀት ተቃረጡኝ:: እንቅልፍ የሥጋትን
እድፍ አጥቦ ይወስድልኝ ይመስል ገብቼ ጋደም አልኩ፡፡ ዳሩ ግን አስጨናቂ
ሐሳብ ከጣራው ላይ የተንጠባጠበ ያህል ልዩ ልዩ ሐሳብ እንደ ጉንዳን ወረረኝ።
ታገልኩት፡፡ በመጨረሻ ግን «ዛሬ ድል ማድረግ አለብኝ የሕሊናዩ ትክክለኛ ወኔ
መገንፈል አለበት። ምንም እንኳ ከንትርክ ይልቅ መግባባት ለመቀራረቢያ የተሻለ
ቢሆንም ዛሬ ደግሞ አንድ ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ሰፊ የኑሮ ምዕራፍ
የምደመድምበት ቀን ነው» አልኩ፡፡ አእምሮዬ ጥቂት ሰከን በማለቱ ለዐርባ
ደቂቃ ያህል ደህና እንቅልፍ ወሰደኝ። ከሩቅ የሚሰማው የኤሌትሪክ እምቢልታ
በወፍራሙ ጀምሮ በቀጭኑ በመዉረስ ሰባት ሰዓት መሙላቱን አሰማ፡፡ የጋለ ሽቦ
እንዳ ነካው ሰው ደንግጬ ተነሳሁ። እመር ብዬ ወርጄ ጫማዬን አደረግሁና ወደ እንግዳ መቀበያ ክፍል ገባሁ፡፡ ለካስ የውብነሽ ቀደም ብላ ገብታ ኖሮ የውጪ
አገር መጽሔት እያገላበጠች ተዝናንታ ትጠብቀኛለች፡፡ አንዳችም ሐሳብና ሥጋት
ያለባት አትመስልም፡፡

ከምሳ በኋላ የአለባበስ ችሎታዬን ሁሉ አጠቃልዩ በዕለቱ አለባበሴ ላይ
አዋልኩት፡፡ ሙሽራ ሆኜ ባላውቅም ሙሽራ መሰልኩ። አንጎሌ የኑሮ ፈተናውን
ውጤት ለማየት አሰፈሰፈ። የወዲያነሽ የመሄጃችን ጊዜ መዳረሱን በማወቋ
ጋሻዬነህን ይዛ ወደ መኝታ ቤት ገባች፡፡ አሥር ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ
አጥቢያ ኮከብ አስመስላው መጣች። በእኔና በየውብነሽ ዝምታ ጭር ብሎ
የነበረው ክፍል በጋሻነህ የልብስ ውበት እንደገና ነፍስ ዘራ፡፡

«በሉ እንግዲህ በርቱ ይኸውላችሁ! ይቅናችሁ! አድባር ትቀበላችሁ ነው
የሚባለው» ብላ አስረከበችን፡፡ «ጨክነሽ?» አልኳት የምትለውን ለመስማት። ከዚህ አልፈ ምን ለማለት እችላለሁ በሚል አስተያየት አየችኝ። የውብነሽ ጋሻዩነህን ይዛ ፊት ለፊቴ ቆመች፡፡ ልማደኛው ሐሳቤ ተመሳቀለ፡፡ እኔንና ልጄን ወደ ሰው አለባ ምድረበዳ የምትገፈትረን መሰለኝ፡፡

«ተነሥ እንጂ ምን ትጠብቃለህ» ተባልኩ፡፡ በድካም እንደ ተጠቃ ሰው
በዝግታ ተነሣሁ።

የመጨረሻው ግብ ግብ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተከፈተ፡፡
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


....በባላባት ቱሬ ሰፈር ሰርግና ምላሽ ሆነ፡፡ድብልቅልቁ ትርምስምሱ ወጣ፡፡ ባላባቱ ስሙ የተዋረደበትን ያክል ተካሰ፡፡ እሱ በሌለበት እንደ ዕቃ ተስርቃ እንደ ከብት ተነድታ የተወሰደች ሚስቱ ሌባዋ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ተመልሳ ከእጁ ገባች፡፡ ጎንቻ በለሊት ጨለማ ለብሶ ሌቱናን
ከሰንጋ ፈረሱ ላይ ከኋላው እንደ ዕቃ ጭኖ ሲገባ ፎከሪ! አቅራራ! ቱሪ በጣም ተደስተ። ጎንቻን ወደደው። አመለከው:: ብዙዎቹ እንፈፅምልሀለን እያሉ ገንዘቡን በልተው ጠፍተዋል፡፡ ጎንቻ ግን ካሰው፡፡ አስቦረቀው አስፈነደቀው እሱም ጎንቻን ሊክስው ሊያስፈነድቀው ፈለገና ከውላቸው
ውጪ አምስት መቶ ብር ጨምሮ ከነቀሪው ሶስት ሺ ብር ጀባ ብሎ
ጎንቻ ብሩ በእጁ እንደገባ ያንን ምኞቱን በቶሉ ሊፈፅም አሰበ፡፡ አዎን ገንዘቡን በሙሉ ለብቻው ካደረገ ጀሌዎቹ እንደማይለቁት ያውቃል።ታዲያ መላው ምንድን ነው? ጎንቻ ጥቅምና ጉዳቱን በጥሞና አሰላሰለ፡፡አለሚቱ ካልጠፋን ብለዋለች ወደደም ጠላም ከአለሚቱ ተነጥሎ መኖር
አይታሰብምና አብሯት መጥፋቱ ቁርጥ ነው። መጥፋቱ ካልቀረ ደግሞ ከጃኖ ቤት ያገኘውንና ከባላባት ቱሬ የተቀበለውን ገንዘብ የብቻው አድርጎ ማስቀረት አማራጭ የሌለው ነው። ጎንቻ ከመጨረሻ ውሳኔ ላይ ደረስ፡፡
ያንን የሚወደውን ጫካ ትቶ ከዓለሚቱ ጋር እሷ ወደምትፈልገው አገር
ቢሄዱ በእጃቸው በቂ ገንዘብ አለና ችግር እንደማይገጥማቸው ተማመነ፡፡እሷ ዘንድ ካስቀመጠው ጋር ሲደማመር ጥሩ አድርጎ ሊያቋቁማቸው እንደሚችል ገመተና ይህንኑ ሂዶ ሊያሳውቃት ተጣደፈ።

እነ ጊርቦ ደግሞ ከአሁን አሁን ያካፍለናል በሚል እምነት በጉጉት እየጠበቁት ነው። ያቀምሰናል ድርሻችንን ይጥልልናል ብለው እንደ ቀላዋጭ ውሻ ከንፈራቸውን እየላሱ ዓይን ዓይኑን እየተመለከቱት ነው። ጎንቻ
ግን ዝም አላቸው:: ለወትሮው እምብዛም የሚያረካቸው ባይሆንም ለአፍ መዝጊያ ያክል ከፀበሉ ረጨት ያደርግባቸው ነበር፡፡ የአሁኑ የአለቃቸው
ማድፈጥ ታዲያ ለምን ይሆን? ነገሩ ሆድ ሆዳቸውን ሲበላቸው ከረመ::ውሎ ሲያድር ጊርቦ እንደምንም ብሎ ወኔውን አሰባስቦ ትንፋሹን ውጦ
ጥያቄ አቀረበለት፡፡

“የምትደርሰንን አስበህ ወርውርልን እንጂ ምነው ዝም አልከን ጌታዬ?" ጭንቅላቱን እያከከ በአክብሮት ጠየቀው። ጎንቻ ጣቱን ከምንሽሯ ቃታ
ላይ እንዳደረገ በየድንጋዩ ውስጥ የሚሽሎኮለከውን እባብ ውር፣ ውር የሚሉ ሽኮኮዎችን እያስተዋለ ከአንድ ትልቅ ድንጋይ ላይ ደገፍ ብሎ ፀሃይ እየሞቀ ነበር፡፡ እንዳልሰማ ሆነ፡፡ ዐይኑ ሁሉ ቦታ ያያል። ቆቅ ወዲያ ማዶ የሚያይ ይምሰል እንጂ የጀሌዎቹን እንቅስቃሴ በንቃት ነበር የሚከታተላቸው፡፡ ሶስት መቶ ስልሳ ዲግሪ የምታይ እንስሳ
አህያ ነች ይባላል እንጂ ጎንቻም ቢሆን በዚህ ረገድ የሚታማ አይደለም፡፡ዐይኖቹ ፈጣንና ቀዥቃዦች ስለነበሩ አካባቢያቸውን በደንብ ይቆጣጠራሉ። ወዲያ ማዶ የሚያይ መስሎ...

"ምነው አሳሰባችሁ እንዴ? አውቄ ነው እኮ ችላ ያልኩት፡፡ ምን የሚያ
ጣድፍ ነገር አለ? አብረን አይደለም እንዴ ያለነው? ኢተያ ሄደን የልማዳችንን እየቀማመስን እንከፋፈላታለን እንጂ ብቻዬን አልበላው?! ምነው ሰጋችሁ?” በፌዝ መልክ ጥርሶቹን ፈልቀቅ አደረጋቸው፡፡ መቼም የጥርሶቹ ነገር አይነሳ! ሲበዛ ነጫጮች በመሆናቸው ከጥቁረቱ ውስጥ እንደ ወተት ፍልቅ እያሉ ለየት ያለ ውበትን ይፈጥሩለታል፡፡ ጊርቦ ይህንን የተስፋ ቃል ከአለቃው አንደበት ሲስማ ልቡ መለስ የሱም ጥርሶች የአለቃውን ተከትለው ብልጭ አሉ፡፡ ጥርሶቹን ብርድ ማስመታቱን አላወቀም
ነበር፡፡ ጎንቻ ብቻውን ዋጥ ስልቅጥ ሊያደርጋት ማሰቡን በፍፁም አልጠረጠረም ነበር፡፡ ሁለቱ ይህን ሲነጋገሩ ቱሲ ራቅ ብሎ ከአንድ ትልቅ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ ይመለከታቸው ነበር፡፡

“ዘራፍ የጎንቻ አሽከር!" አለና አፈሙዙን አዞረ፡፡ በጣም ትልቅ ርዝመቱ ከአስር ሜትር የሚበልጥ ዘንዶ በጎንቻ አናት በኩል ተምዘገዘገ...
“እረፍ!" አለና ጎንቻ ተቆጣ፡፡ ዘንዶው ከሰሰሰስ እያደረገ በጢሻው ውስጥ እየተሹለከለከ ሄደ። አሁን አሁን ጀሌዎቹ ሲፎክሩ በአለቃቸው ስም ሆኗል። የአለቃቸው ድፍረት፣ የአለቃቸው ወደር የማይገኝለት ጭካኔ፣ የአለቃቸው ተጠራጣሪነትና ጠንቃቃነት እነዚህ ሁሉ ተፅዕኖ አሳድረውባቸው የሚፎክሩት በራሳቸው ጀግንነት ሳይሆን በሱ አሽከርነት ሆኗል፡፡

በጃኖ ላይ አደጋ ጥለው ከተመለሱ በኋላ ለአንድ ሳምንት ያክል በኛሮ ጫካ ውስጥ የአውሬ ስጋ ብቻ እየበሉ ሰነበቱ፡፡ ጎንቻ የዓለሚቱ ጠረን መዓዛዋ በናፍቆት አውዶታል። በተለይ አሁን አሁን የምትቀባው ሽቱ አቤት ጠረኗን ማጣፈጡ! ድሮም ለሱ ማር የነበረችው ዓለሚቱ በውበቷ
ውስጥ ሌላ ውበት በጣፋጭነቷ ውስጥ ሌላ ጣፋጭነት በመአዛዋ ውስጥ ሌላ መአዛ እያመነጨች ነፍስና ስጋውን በፍቅር እያነደደቻቸው ነው።ዛሬ ግን የአንድ ሳምንት ናፍቆቱን በተለይም ደግሞ የመጥፋቱን ነገር ካብሰለሰለ በኋላ ውሳኔውን ሊነግራት ሳምንቱ እንደ ዓመት ረዝሞበት ከምንግዜውም የበለጠ በናፍቆቷ እየተሰቃየ ነው፡፡ይሄንኑ ናፍቆቱን ሊወጣ፣ ሚስጢር ሊያጫውታት፣ ውሳኔውን ሊገልፅላትና ረብጣ ገንዘብ ሊያስታቅፋት የሚሄድበት ዕለት ስለሆነ መንገዱ ሁሉ አላልቅልህ አለው፡፡ ሶስቱም በጥድፊያ እየተዋከቡ ገና ከምሽቱ
አራት ሰዓት ሳይሆን ኢተያ ከተማ ገቡ፡፡ ጮማው ተቆረጠ፡፡ አረቄው
ተጨለጠ፡፡ ተሰከረ። ተፈነደቀ። ለጀሌዎቹም ሴቶች መጡላቸውና ለብዙ ጊዜ የዘነጉትን ወንድነታቸውን ፈተሹ፡፡ በደስታ አበዱ፡፡
"እንዲህ ነው እንጂ! ይሄ ነው አለቃ ማለት!" አለ ጊርቦ ባለፈው ጊዜ ብቻውን መደብ ላይ ተኮራምቶ ያደረበትን ደረቅ ምሽት አስታውሶ።ጎንቻና ዓለሚቱ ለሚስጢር ጨዋታ እንዲያመቻቸው ለብቻቸው ሆነና
ጨዋታቸውን ቀጠሉ...

"ስሞኑን ሳወጣ ሳወርድ ከረምኩ፡፡ ወደ ሻሽመኔ፣ወደ አሰላ፣ ወደ ናዝሬት፣ደብረ ዘይት ሁሉ ተመኘሁ እነኝህ ሁሉ አልተዋጠልኝም፡፡ ትንሽ ከተማ መግባት ትርፉ ለሰው ዐይን መጋለጥ ነው፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ከደጅ ወደ ጓሮ ነው፡፡ አሁን መጨረሻ ላይ ግን የት አስብኩ መሰለህ?"
እየሳቀች። በመጨረሻ ላይ የት ለመሄድ እንደወሰነች ጎንቻ መገመት እንዳለበት በማሰብ ጠየቀችው። እሱ ግን የአውሬ ኮቴ የማያይበት፣ የአራዊት ጩኸት የማይሰማበት ጠረናቸውን የማያሽትበት ዳገት ቁልቁለት
የሌለበት፣ ጫካ ዋሻ የሌለበት የከተማ ኑሮው የት ሊሆን እንደሚችል በፍፁም መገመት አልቻለም ነበር።

"ሸገር! ሸገር! አዲስ አበባ! አዲስ አበባ!" ተፍነከነከች።
“አዲስ አበባ?ሸገር? " ስሙን በአዕምሮው ደጋገመው። "ልክ ነው" አለ፡፡ ዝናውን የሚያውቀው ሸገር፣ በጣም ሰፊ የሆነው ሸገር ጥሩ ዋሻ መሸሸጊያ ሊሆናቸው እንደሚችል እሱም ርግጠኛ ሆነ፡፡
"በቃ ይሁን!" አለና አቀፋት። በሸገር ተስማሙ:: በከንፈር ማህተም የሸገር ኮብላዮች መሆናቸውን ተፈራረሙ:: እሷ ገንዘቡን ጠቅልላ ልታስቀምጥ እሱ ደግሞ በማግስቱ በለሊት ሊመጣ ወሰኑና ተለያዩ።

ወደ ኛሮ ሲመለሱ ገንዘቡን እነቱሲ ጠይቀውት ነበር፡፡ ሞቅታ ስላለብን ነገ ማታ እንከፋፈላን አላቸው፡፡ነገ ገንዘቡን እንደሚከፋፈሉ ተስፋ ሰንቀው አስደሳች እንቅልፍ ወስዷቸው አደረ።
ጠዋት ፀሃይዋ በኛሮ አናት ላይ ብቅ አለችና አካባቢውን በብርሃኗ ወለል አደረገችው።አራዊት ከጎሬአቸው ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል። ደስ የሚል ቀን ነበር፡፡ ያለወትሮው ብቅ ያላለው ያልነቃው ጎንቻ ነበር። ጊርቦና ቱሲ
እየተንጠራሩና እያዛጉ ተገናኙ ጌታው ሚስቱ አድክማ ነው የላከችው መስለኝ አልነቃም" አለ ጊርቦ፡፡
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...ኑሮ በክበረ መንግስት ለሔዋን አልተመቸም፡፡ በእናት በአባቷ ቤት ደባል ብቸኛ ሆናለች፡፡ ተወልዳ ባደገችበት አገር ባይተዋር ሆናለች ዙርያዋን ብዙ ሰው እያለ ብቸኛ ሆናለች በሃሳብ እና በጭንቀት
ብዛት ራሷን ረስታለች፡፡ ብትበላ ብትጠጣ ሆዷ ይጥገብ እንደሆን እንጂ መንፈሷ ግን ረሀብተኛ ሆኗል።
ባህሪዋም ተለውጧል። ደስተኛ የነበረች ሔዋን ብስጩ ሆናለች። ፍልቅልቋ ሔዋን አኩራፊ ሆናለች፡፡ ታዛዥና ትሁት የነበረች ሔዋን ነጭናጫ ሆናለች።ተጨዋቿ ሔዋን በትካዜ ተውጣ በጭንቀት ተወርሳለች፡፡ ጤንነቷም ተጓደለ፡፡
ዘወትር 'ልቤን' ማለት አበዛች፡፡ ከመቆም ይልቅ መቀመጥን፣ ከመቀመጥም መተኛትን አዘወተረች።የምግብ ፍላጎት አጣች። ከምትብላው ምግብ ይልቅ የምትጠጣው ውሃ ያማራት ጀመር። ከቶም 'ብይ' ባትባል ደስታዋ ሆነ፡፡ - የግድ ብትበላም ብዙ አይስማማትም። እሷ ተቸግራ ቤተሰቦቿንም አስቸገረች፡፡ የህመሟ ጉዳይ
ቤተሰቦቿ በተለይ በአባትና እናቷ ዘንድ ሌላ ስጋት ፈጠረ፡፡ 'ያ የልጅነት ህመሟ ሊነሳባት እያሉ ይጨነቁ ጀመር።

ስጋታቸው መነሻ አለው፡፡ ሔዋን በህጻንነቷ እስከ ሁለት ዓምቷ ድረስ ፍፍት፣ ድንቡሽቡሽ ያለችና ፍልቅልቅ ነበረች። ከዚያ በኋላ ግን ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ሁለመናዋ ተለዋወጠ፡፡ ሰውነቷ እየከሳ ቆዳዋ እስከ መሸብሸብና እየጠቆረ መልኳ እስከ መቀየር ደረስ፡፡ በእግሯ መሄድ ከጀመረች በኋላ ወደ መዳህ! ቀጥሎም
ቁጭ ብላ ቀረች፡፡ ለቅሶ የማታውቀው ሔዋን መብሰክሰክ አብዝታ አልቃሻ ሆነች።
ወላጅ አባትና እናቷ ትሞትብናለች እያሉም መስጋት ጀመሩ።
የእሷን ህይወት ለማትረፍ ያልተደረገ ጥረት አልነበረም፡፡ በተለይ እናቷ ያልተሳለባት ቤተክርስቲያን ያልሄዱበት ጠበልና ያልጠየቁት ጠንቋይ አልነበረም።
ዘመናዊ ህክምናም እንዲሁ፡፡ የሔዋን ጤንነት ግን አንዳችም መሻሻል ሳያሳይ ድፍን ስድስት ዓመት ሞላት፡፡ እናቷ ሲፈጩም ሲጋግሩም፣ ሲያነፍሱም ሲቀቅሉም ገብያ ሲሄዱም እንኳ ልጃቸውን አቅፈው ወይ አዝለው መንከራተት ግድ ሆነባቸው።

የሔዋን እናት በዚሁ ሁኔታ በመልፋት ላይ ሳሉ ረንድ ቀን ያልታሰበ ሁኔታ ገጠማቸው:: ቤታቸው ከክብረ መንግስት ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ከከተማው
ወጣ ብሎ በሚገኝ ገጠራማ ሥፍራ ስለሆነ የሱቅ ዕቃ ሊገዙ ሔዋንን ታቅፈው መደ ከተማ ሄዱ፡፡ ከአንድ ሱቅ ደርሰው የግዢ ወረፋ ሲጠብቁ ሔዋንን በሱቁ
ባንኮኒ ላይ አስቀመጧት:: ሔዋን ምንም እንኳ በህመም ምክንያት ሰውነቷ ቢጥመለመልም ነፍስ እያወቀችና አፏን እየፈታች በመሄዷ በሱቁ መደርደሪያ ላይ
የሚታዩ የሸቀጥ ዓይነቶችን ለእናቷ እየጠቆመች “ያ ምንድነው እማ? ያስ? ያኛውስ?… እያለች ትጠይቃቸዋለች፡፡ እሳቸውም ያወቁትን ያህል ያስረዷታል።
በሰቁ ውስጥ ዕቃ ሊገዙ የገቡ አንዲት ዕድሜያቸው ወደ ስልሳ የሚጠጋ ሴት አዛውንት ሔዋንና እናቷ የሚመላለሱትን እያዳመጡ በተለይ ሔዋንን አየት ያደርጓት ኖሯል፡፡ ጤነኛ እንዳልሆነች ከሁኔታዋ እየተረዱ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ሲያዝኑላት ቆይተው የገዙትን ዕቃ በመቀነታቸው ላይ ከቆጣጠሩ በኋላ «ይቺ ልጅ ስንት ዓመቷ ነው የኔ እህት? ሲሉ የሔዋንን አናት ጠየቋቸው።
«እድሜዋ እንኳ ስድስት ዓመት ሞላት፡፡»
«ጤና የላትም?»
«የላትም የኔ እናት! በጣም ተቸግሪሃለው። ከሁለት ዓመቷ ጀምሮ ይኸው ተንገላታባኛለች።
ይኸው አራት ዓወት በሙሉ እሷን አዝዬ እኖራለሁ።
«እምም...ም» አሉና ሴትየዋ ቤትዎ የት ነው?» ሲሉ ጠየቋቸው
የሔዋን እናት በምልክት ሲነገራቸው። «እስቲ አንድ ቀን ብቅ ብዬ እጠይቆታለሁ ምናልባት መዳኒት ያገኘሁላት እንደሆን።» አሏዋቸው።
«ሆኖ ነው የኔ እናት!» ብለው፧ የሔዋን እናት ፍንድቅድቅ እያሉ «አገርዎ የት ነው?»ሲሉ ጠየቋቸው።
«ቅርብ ነው:: ተሲያት ላይ ብነሳ እርስዎ ቤት መድረስ እችላለሁ፡፡»
«አደራ የኔ እናት! እንደው አደራ እንደው አደሪ» በማለት የሔዋን እናት ሴትዮዋን አጥብቀው ተማፀኗቸው::»
«አላህ ከፈቀድ ሳምንት እመጣለሁ::"»
«እሺ የኔ እናት፤ እጠብቅዎታለሁ::»
እዛውንቷ ሴት ቀጠሮአቸውን አክብረው ከሔዋን ወላጆች ቤት መጡና የባህል ህክምናቸውን ጀመሩ ሔዋን አካላቷን እንድትታጠብ ከአደረጉ በኋላ
ራሳቸው ታቅፈው ቅባት መሰል በሆነ ነገር መላ አካላቷን እየቀሱ ያሿት ጀመር፡፡ ያን ሲጨርሱ ሌላ መድሃኒት በማር እየበጠበጡ ያጠጧታል። እምቢ ስትላቸው
የግድ ይግቷታል። በዚህ ዓይነት ለሰባት ቀናት እራሳቸው ከአከሟት በኋላ ለሚቀጥሉት ሰባት ቀናትም እናቷ እንዲያደርጉላት መክረዋቸው ወደ አገራቸው ተመለሱ።የሔዋን እናትም በተመከሩት መሰረትም ፈፀሙ።

ዘመናዊ የህክምና ጠበብቶች እንዴት ሆኖ? ምኑ ከምን ተገናኝቶ? ለሜን ዓይነት በሽታ ያ
ምን ዓይነት መድሃኒት? አወሳሰዱስ? መጠኑስ? ወዘተ እያሉ አመክኒየአቸውን እንደ ስጋ እየዘለዘሉ ሊጠያየቁ ይችሉ ይሆናል፤ የሔዋን ጤንነት
ግን ከዕለት ወደ ዕለት እየተሻሻለ ሄደ። የተሸበሸበ ቆዳዋ ወጠር፣ ፊቷ ፈካ፣ እያለ ከመምጣቱም በላይ መዳህ ጀመረች። ህክምና በተደረገላት በሁለተኛው ወር ቆማ
መሄድ ቻለች፡፡ ሦስት ወር ሲሞላት ሙሉ ጤነኛ ሆነች::
የሔዋን እናትና አባት የተሰማቸው ደስታ ወሰን አልነበረውም። ሔዋን
እንደገና እንደ ተፈጠረች ቆጠሯት፡፡ እየተመላለሱ የሚጠይቋትን ሀኪሟን ሴት
የሚያደርጉላቸውን አጡት ሰጥተዋቸው አልረካ አሉ፡፡ አመስግነዋቸው አልጠግብ
አሉ። ሁሉም ነገር ሳያረካቸው ቢቀር ቅድስት የነበረውን የሔዋን ስም 'ሀዋ" ብለው በአዛውንቷ ስም ቀየሩት። ነገር ግን በዘር ማንዘራቸው ክርስቲያን ስለሆኑ ከዚያው ሳይርቁ «ሔዋን» በሚል ተኩት፡፡ እነሆ ቋሚ ስሟ ሔዋን ሆኖ ቀረ::
ዛሬ ታዲያ 'ልቤን' እያለች ስትሰቃይባቸው፣ ድካም እየተሰማት ድፍት ብላ
ስትውልባቸው፣ ምግብ በአግባቡ መመገብ አቅቷት ሲያዩ፣ ፍዝዝ ትከዝ ስትል እየተመለከቱ እጅጉን ይሰጉ ጀመር፡፡ ወደ እመት ሐዋ አይሮጡ ነገር እመት ሐዋ
መሞታቸውን ከሰሙ ቆይተዋል። ወደ ዘመናዊ ሀኪም ቤት ወስደው
ሊያስመረምሯት ሀኪሞቹ የልብ ችግር እንዳለባት አረጋግጠው ክኒን ብቻ ሰጥተው የራሷ ሃኪም ራሷ ናት፡፡ ሃሳብና ጭንቀት ካለባት ያንን ትታ መንፈሷን ማረጋጋት እረፍት ማድረግ ይኖርባታል አሏቸው። ይሄ ደሞዝ በሔዋን በኩል የሚሞከር አልሆነም፡፡ ከሀሳብ " ከትካዜና ከጭንቀት ማን ጎትቶ ያውጣት?
ከህመሟ በተጨማሪ ያለባትን የውስጥ ችግር የሚያውቁላት እናቷ ግን ተስፋ አልቆረጡም' ሔዋንን የማረጋጋት ጥረታቸውን ቀጠሉ፡፡ መጀመሪያ ፍላጎቷን አጠኑ። ሔዋን ቤት ውስጥ ከሆነች መደብ ላይ ጋደም ማለት ነው ቤቱ ሲጨንቃት ወደ ጓሮ ሄዳ ከዛፍ ስር መቀመጥ ነው
ጓሮአቸወ ደግሞ ሰፊና በትላልቅ ዛፎች የተሞላ ነው። ሔዋን ከዛያ ውስጥ በአንዷ ዛፍ ስር መቀመጥ ታዘወትራለች ያንንም አጠኑ።
አቀማመጧ ይመቻት ዘንድ የዛችን ዛፍ ዙርያ በአፈር ደለደሉ፡፡ በፀሃይ ጊዜ አቧራ በዝናብ ጊዜ ጭቃ እንዳይሆንባት ሳር ተክለው ውሃ እያጠጡ አለመለሙላት ይበልጥ
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....የሕዳር ቁስቋም ዕለት ነው። ምንትዋብ ትልቅ ግብር ጥላለች። ምግቡም፣ወይን ጠጁም፣ ጠጁም፣ አረቄውም በገፍ ተዘጋጅቷል። አስቀድማ፣
ዛሬ ሊቃውንቱና ካህናቱ ከገቡ ወዲያ ዋናውን ሆነ የስርቆሹን በር
እንድትዘጉ። የወይን ጠጅም እየደጋገማችሁ እንድትሰጧቸው” ብላ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።

“ይኸ ሁሉ ስለምንድርነው?” ሲል ጠየቃት፣ ኢያሱ።

“ዛሬ ካህናቱንና ሊቃውንቱን ጉድ ሠራለሁ።”

“እንዴት አርገሽ... ደሞስ ስለምን?”

“እነሱ ሁልግዝየ በቅኔው፣ በተረትና ምሳሌውና በመጠጥ ያቸንፉኛል።
ዛሬ ግን እኔ አቸንፋቸዋለሁ ብዬ ተነስቻለሁ።”

ሳቀ ኢያሱ ።
ከቅዳሴ በኋላ፣ ከየደብሩ የተጋበዙት ካህናትና ሊቃውንት ወደ ቤተመንግሥት ተመሙ። ሠዓሊዎችና ሙዚቀኞችም ጎረፉ። የግብር ሥርዐት ተጠብቆ ምግብ ተበላ። የወይን ጠጅ ተቀዳ ። የካህናቱና የሊቃውንቱ ዋንጫ ሲጎድል አጋፋሪዎች በታዘዙት መሠረት እየተመላለሱ ሞሉ።

እንግዶቹ ፊኛቸው አስቸገራቸው። ሊወጡ ፈልገው ቢነሱ ከፊት
ከኋላ በሩ ዝግ ነው። የሚከፍት የለም። ተጨነቁ፤ ተጠበቡ። እየተያዩ መቅበጥበጥ ብቻ ሆነ። በመጨረሻ መለኛው ሊቅ አለቃ ኢሳያስ ተነሥተው እናትና ልጁን እጅ ነሱና፣ “እቴጌ አንድ ነገር እንድጠይቅ ይፈቀድልኝ” አሏት።

“ይበሉ ይጠይቁ።”

“እቴጌ አምስት መቶና አምስት መቶ ስንት ነው?”

ያልጠርጠረችው ምንትዋብ፣ “ምን ያለ ጥያቄ ነው? ይኸ ሊያቅተኝ? ሽ ነዋ!” አለች።

አለቃ ኢሳያስ፣ “እቴጌ “ሽናዋ' ብለዋል” ሲሉ ያ ፊኛው አስጨንቆት የነበረ ሊቅና ካህን ሁሉ የተቀመጠበትን ከህንድ ሃገር የመጣ ስጋጃ አረሰረሰ።

ምንትዋብ በመሸነፏ ሳቀች፣ ተንኮሏ እንዳልሠራ ተገነዘበች።
በእርግጥም ሊቃውንቱን ማሸነፍ እንደማትችል ተገነዘበች። አለቃ
ኢሳያስን ለብልሐታቸው ሽለመቻችው። አዲሱ የግብር ኣዳራሽም በሕዝብ ዘንድ “ሽናዋ” የሚል ስያሜ አተረፈ።

ከሽናዋ በኋላ፣ የሴቶች ሙያ ትምህርት ቤቱ ግንባታ ተጀመረ።
ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ሴቶች ተመርጠው እንደ
ፈትል ያሉ ልዩ ልዩ የእጅ ጥበባትና ዶሮ መገነጣጠል እንዲማሩ ሆነ።
ተማሪዎቹ ዶሮ አስራ ሁለት ብልት እንዳላት አወቁ። ፊደልና የቁም
ጽሕፈት እንዲከታተሉ ተደረገ። ምንትዋብ ልትጎበኛቸው በሄደች
ቁጥር በሙያና በትምህርት በርትተው እንዲማሩ አስጠነቀቀች።ከዓመታት በፊት አያቷ የነገሥታት ዝርያዎች ወህኒ ይላካሉ እዛው አርጅተው ይሞታሉ፣ ብለው ሲነግሯት፣ “ክፉ ነገር። እኼማ መሆን የለበትም” እንዳለችው ከጸሎት ቤቷ በስተቀኝ በኩል የአፄ በካፋ ዘመዶች ሆኑ የሌላ ነገሥታት ዝርያዎች ወይንም የራሷ ዘመዶች መኖሪያና መማርያ የሚሆን ህንፃ አሠርታ፣ ልጆቹ ወህኒ አምባ በእግር
ብረት ታስረው ከመማቀቅ ይልቅ ፊደል፣ የቁም ጽሕፈትና ፍትሖ
ነገሥት እንዲማሩ ሆነ።

ምንትዋብና ኢያሱ ስማቸው ከአጥናፍ አጥናፍ ገነነ።

ምንትዋብና ዳግማዊ ኢያሱ ስማቸው ቢገንም፣ አልፎ ኣልፎም ቢሆን በመኳንንቱ ዘንድ “ቋረኞች” ላይ ጥርጣሬ ስላለ፣ ምንትዋብም ብትሆን ያለነሱ ድጋፍ ርቃ እንደማትሄድ ስለምታውቅ በጉዳዩ ከኢያሱ ጋር መምከር ፈለገች።

“ኢያሱ እንዳው አንድ ነገር ላጫውትህ ብየ” አለችው፣ አንድ ቀን እንቁላል ግንብ ውስጥ ተቀምጠው እየተጫወቱ ሳለ።

“ምን ነገር?”

“እንደምታውቀው “ቋረኞች” ሚሉ ዘይቤ እንደ ዱካ ይከተለናል።
ሥልጣኑን ሁሉ ቋረኞች ይዘውታል ይላሉ። ይሰንብት እንጂ ቀን
ጠብቀው በኛ ላይ መነሳታቸው አይቀርም። የጎዣም፣ የትግሬ፣
የቤገምድርና የስሜን መኳንንት ዋዛ ማዶሉ። ይመስገነው እስታሁን ሰላም ነን። ወደ ፊት ግን እንጃ ሰላማችን ሊደፈርስ ይችላል ብየ ሰጋለሁ።ሰላም ማጣት ብቻ ሳይሆን አልጋውን ሊፈታተኑ ይችላሉ። የወህኒዎቹ
እንደሆኑ ዐይናቸው መቸም ግዝየ ኻልጋው ላይ ተነስቶ አያውቅም።
ተዘጋጅቶ መቀመጡ አይከፋም። ሥልጣን አይበቃቸው፣ ጉልት፣
ርስትና ርስተ ጉልት ለስንቱ መኳንንት ሰጠን። አይጠቅማቸውም።ኢያሱ ጥቂቱ እኮ ነው ላገሬ ሚለው። ኻለነሱ ድጋፍ ደሞ አይሆን።እነሱን ለማስታገስ ስንቱን ድሬ ጨረስሁ። አሁንም ቢሆን አርቀን ማሰብ አለብን። ነገ አንዱ ቢነሳ አጋዥ ያስፈልገናል። እና አሳቤ ምን
መሰለህ ይኸ የስሜን፣ የጎዣም፣ የቤገምድርና የትግሬ ባላባት ሁሉ
ቀልቡን ሰብስብ እንዲያረግ ወሎዎች ጠንካራ ጦር አላቸውና ኸነሱ ጋር በጋብቻ ብንተሳሰር ምን ይመስልሀል?”

“ኣሳብሽ መልካም ነው። ማነን ልታጋቢ አሰብሽ?”

“አንተን።”

“እኔን?” ከት ብሎ ሳቀ።

“አዎ አንተን:: ብዙ አስቤበት ነው። አሁን ኸወሎች ጋር መጋባት
ያስፈልጋል። የልገሮችህ እናት...” ዕቁባት ሆና ትቀመጣለች ማለት
ፈልጋ ዝም አለች።?
“እና እኔን ኸማን ልታጋቢ ነው?” አላት፣ ዝም ስትል ።

“ውቢት ምትባል የወሎ ባላባት ልዥ አለች። አጠያይቄ አለላ ናት
አሉ። ብቻ የወሎ ልዥ ስለሆነች በድብቅ መሆን አለበት።”

ኢያሱ ስለመኳንንቱ ያለችው አሳስቦት ነበርና ዝም አለ። ምንትዋብ ዝምታውን እንደ እሺታ ቆጠረች።

ብዙም ሳይቆይ ምንትዋብ የወሎ ባላባት ልጅ የሆነችውን ውቢትን
ከኢያሱ ጋር አጋባች። ውቢትን ክርስትና አስነስተው ወለተቤርሳቤሕ አሰኝተው፣ የመኳንንቱን ጉምጉምታ ለማቀዝቀዝ በድብቅ ኣስቀመጡ።
ውቢት ኢዮአስ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደች።

ምንትዋብና ኢያሱ ምንም እንኳን ራስ ቢትወደድ ወልደልዑል
መንግሥታቸውን ከዘመዶቹ ጋር አስከብሮና አጠናክሮ ቢይዝላቸውም፣ባላባቶች ከወሎ በማምጣት ሥልጣን ላይ አስቀመጡ። ሲያንገራግር
የነበረውን የጎጃሙን ባላባት ዮሴድቅን ደግሞ፣ ደጃዝማች ብለው፣ይዞታውን ጨምረው፣ በኋላ ሞጣ ጊዮርጊስን የደበረችውን ወለተእስራኤልን ድረውለት አረጋጉት።

እናትና ልጅ ያሰቡትን ሥራ ላይ ከማዋል አልቆጠብ አሉ። በተለይም ኢያሱ ለአትክልት ቦታ ልዩ ፍቅር ስለነበረው፣ ጐንደርን አፀድ በአፀድ አደረጋት። ሎሚና ሌሎች ፍሬዎች ጐንደርን የመዓዛ ባለፀጋ አደረጓት።

አብያተ ክርስቲያናትን በጭልጋ፣ አለፋ ጣቁሳና ጐንደር በኖራ
አሠሩ። ሌሎችን አሳደሱ። ጣና ሐይቅ በታንኳ እየተመላለሱ ኢያሱ
ክብራን ገብርኤልን ሲያሳድስ፣ እሷ ደቅ ውስጥ “ስሞት እቀበርበታለሁ” ያለችውን ናርጋ የኛ - ሥላሤን በጡብና በጐንደርኛ ይዘት አሠራች። ናርጋ ሥላሤን ስታሠራ፣ ሥሙር የተባለውን የራሷን ምስል የላከላትን ሠዓሊ አስታወሰች። እንዴት ሊገኝ እንደሚችል አሰበች።ሌሎች ሠዓሊዎች በሥዕል ሥራው ተሳተፉ። ናርጋ ሥላሤ በሥዕል
አሸበረቀች። ምንትዋብ አክብሮቷን ለመግለፅ ከማርያምና ከክርስቶስ
እግር ሥር የራሷን ምስሎች አሠራች። አብያተ ክርስቲያናቱ የሥዕል ባለቤት ሆኑ።

ብርሃን ሰገድ ኢያሱ “ብዙው መጻሕፍት ወደ ክብራን ገብርኤል
እንዲሄዱ ፈቃዴ ነው” ባለው መሠረት ከተለያዩ የሃገሪቱ ከፍሎች የተሰበሰቡ በሺህ የሚቆጠሩ መጻሕፍት ክብራን ገብርኤል ገብተው
ተቀመጡ።

“አንተ ደሞ ሁሉ ነገር ወደዛ እንዲኸድ ትፈልጋለህ” ብላ ፈገግ
አለች፣ ምንትዋብ አንድ ቀን። ቀጠል አድርጋ፣ “ለየደብሩ እኩል
ማከፋፈል ነው እንጂ” አለችው።
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ደረጃውን እያንኳኳ ቶሎ ቶሎ ሲሄድ ማሪየስ ኮቴውን ሰማ። በዚህም ወደ ውጭ መውጣቱን አረጋገጠ፡፡ ወዲያው በአካባቢው የሚገኝ ቤተክርስቲያን የስዓት ደወል ደውሎ ሰባት ሰዓት መሆኑን አበሰረ::

ማሪየስ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ተረኛ መኰንን እንዳለ ጠየቀ
መኮንኑ አለመግባታቸው ተገለጸለት:: ሆኖም አስቸኳይ ከሆነ ዋናውን አዛዥ ማነጋገር እንደሚችል ተነገረው፡፡

«አስቸኳይ ነው» አለ ማሪየስ፡፡

የቀኑ ዘበኛ ወደ ዋናው አዛዥ ቢሮ አመላከተው፡፡ ዋናው ኃላፊ
ከቁመቱ ዘለግ ያለ ጢማምና ቁጡ ሰው ነው: ሲያዩት ከሞት
ይበልጥ ያስፈራል ወፍራምና ረጅም ካፖርት ለብሷል ፊቱ ክብ ሆኖ ሪዙ ላይ ሽበት ጣል ጣል አድርጎበታል አፍጥጦ ሲያይ ወደ ውስጥ የገባውን ኪስ የሚገለብጥ ይመስላል:: ጠቅላላ ሁኔታው ከዦንድሬ የተለየ አልነበረም ሆኖም የሕግ ስው በመሆኑ ብቻ ከተኩላ ውሻን ማየት እንደሚሻል ዓይነት ትርኢት ነበር ለማሪየስ፡፡
«ጉዳይህ ምንድነው?» ሲል አክብሮት በተለየው አነጋገር ጠየቀው:
«እኔ እንኳን የፈለገሁት የእለቱን ተረኛ መኰንን ነበር፡፡»
«አልመጣም እሱ ፤በእርሱ ምትክ ጉዳይህን እኔ ልፈጽምልህ
እችላለሁ፡፡»
«ጌታዬ ትልቅ ምሥጢር ነው፡፡
«ተናገራ ታዲያ፡፡»
«እና ደግሞ በጣም አስቸኳይ ነው፡፡»
«ይሁና አሳብህን ቶሉ ልስማው፡፡»
ዋናው አዛዥ ይህን ተናግሮ ዝም አለ፡፡ ከጥቂት ጊዜ ጨዋታ በኋላ
ከማሪየስ ሳይሆን ከአሰረው ከረባት ጋር ይነጋገር ይመስል አዛዡ እንዳቀረቀ
«መቼስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል» ብሎ ከተናገረ በኋላ መልሶ ዝም አለ:
«ቁጥር 50 52 ፤ ሰፈሩን አውቀዋለሁ፡፡»
‹‹ምን ማድረግ ይቻላል?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ፡፡
«ያልካቸው ሰዎች ትልቁን በር የሚከፍቱበት ቁልፍ አላቸው! አንተስ አለህ?»
«እነሱም አላቸው፤ እኔም አለኝ፡:››
‹‹ቁልፉን አሁን ይዘኸዋል?»
«ይዤዋለሁ:፡»
«ስጠኝ» አለ ዋናው አዛዥ::
ማሪየስ ቁልፉን ከኪሱ አውጥቶ ሰጠው፡፡
«የነገርክዎት ነገር ካመኑበት ኃይል ይዘው ቢመጡ መልካም ነው፡፡
ዋናው አዛዥ እንደ መናደድ፧ እንደ መብሸቅ ብሎ ማሪየስን ቀና ብሎ
አየው፡፡ ‹‹ልጅ ለእናትዋ ምጥ አስተማረች» ዓይነት ሆነበት፡፡ ቢሆንም ነገሩ?
ናቅ አድርጎ በመተው ከካፖርቱ ግራና ቀኝ ኪስ ሁለት ሽጉጥ አወጣ:
ሁለቱንም በችኮላ ለማሪየስ ሰጠው።

«ያዛቸውና ወደ ቤትህ ተመለስ፡፡ ክፍልህ ውስጥ ተደበቅ፡፡ ስትገባ
ባያዩህ ጥሩ ነው ወደ ወጭ ወጥቷል ብለው እንዲያስቡ ድምፅህን አታሰማ፡፡ ሽጉጦቹ ጥይት አለባቸው:፡ እንደነከረከኝ ከሆነ የሁለታችሁን ክፍል የሚያገናኘው ግድግዳ ቀዳዳ አለው፡፡ ሰዎቹ መጥተው ከክፍሉ
ውስጥ ከገቡና ነገሩ አንተ ባልከው ዓይነት ሲጀመር አንድ ጊዜ ተኩስ ግን እንዳትፈጥን ወይም እንዳትዘገይ:: ጥሩ ሰዓት ነው በምትልበት ጊዜ ነው
የምትተኩሰው:: ከዚያ በኋላ የእኔ ጉዳይ ይሆናል፡፡»

ማሪየስ ሽጉጦቹን ይዞ ለመውጣት እጁን ከበሩ እጄታ ላይ እንዳሳረፈ ዋናው አዛዥ ያናግረዋል፡፡

«በነገራችን ላይ፣ ከአሁን ጀምሮ እስከ ማታ ብትፈልገኝ እኔ ከዚሁ
ስለምሆን ራስህ ልትመጣ ወይም ሰው ልትልክብኝ ትችላለህ፡፡ ከመጣህ ዣቬር ብለህ ጠይቅ::»

ማሪየስ እጅ ነስቶ ወጣ፡፡

የማይደርስ የለም ፤ ሰዓቱ ደረሰ፡፡ ደመና ስለነበረ ገና በአሥራ ሁለት
ለዓይን ያዝ ማድረግ ጀምሮአል፡፡ ማሪየስ ወደ 50 52 ተመለሰ፡፡ ትልቁ በር ክፍት ነበር፡፡ ቀስ ብሎ ድምፅ ሳያሰማና ማንም ሳያየው ከክፍሉ ገባ፡፡ካልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ፡፡ ልቡ በኃይል ይመታ ጀመር፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ምን ሊሆን እንደሚችል ታወሰው፡፡ በአንድ በኩል የወንጀል
ሙከራ ሲደረግ በሌላ በኩል ፍትሕ ሲሰፍን ታየው:: ልቡ አልፈራም፡፡ የሕይወት አጋጣሚን መጋፈጥ ደስ እንደሚለው እንደማንኛውም ሰው እርሱም ደስ አለው:: የተወጠነው ነገር ሕልም እንጂ እውነት አልመሰለውም::

ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ ማሪየስ በር ሲከፈት ሰማ፡፡ ሁለት ልጆች
በር ከፍተው ሲገቡና አባታቸው ሲጮህባቸው አዳመጠ፡፡ ቀጥሎ የብዙ ሰዎች ድምፅ በሩቁ ተሰማ፡፡
«ስሙ ልጆች፤ አንዳችሁ በላይኛው አንዳችሁ በታችኛው በር በኩል ሆናችሁ የሚመጣ ሰው ካለ ተጠባበቁ፡፡»

«በዚህ ብርድ በባዶ እግራችን ከውጭ ልንቆም» በማለት ትልቅዋ
ልጅ አጉረመረመች::

«ነገ ምን የመሰለ ጫማ ትገዢያለሽ» ሲል አባትዋ መለሰላት፡፡

ማሪየስ ከለመደበት ሥፍራ ወጥቶ መጠባበቅ እንዳለበት ገመተ፡፡

ቀዳዳው ከነበረበት አካባቢ ወጥቶ ቁጭ አለ፡፡ ወደ እነሚስተር ዦንድሬ ክፍል ተመለከተ፡፡

ከክፍሉ ውስጥ ከሰል ተቀጣጠለ እንጂ ሌላ ብርሃን አልነበረም:: ከበሩ አጠገብ ረጅም ገመድና ሁለት ወፍራም የብረት ዱላዎች ተቀምጠዋል፡፡በኋላ ሻማ አያያዙ፡፡

ሚስተር ዦንድሬ ፒፓውን አያይዞ ከወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ባለቤቱ ዝግ ባለ ድምፅ ታናግረዋለች:: በድንገት ዦንድሬ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ::

«በነገራችን ላይ በዚህ ብርድ ሰዎቹ በጋሪ እንጂ በእግራቸው
አይመጡም፡፡ ታዲያ አንቺ ምን ማድረግ ያለብሽ ይመስልሻል? ወዲያው የፈረስ ኮቴ እንደሰማሽ ቶሎ ብለሽ ትወጪና ለሰዎቹ ሰላምታ ሰጥተን በፍጥነት እቤት ይዘሻቸው ትመጫለሽ፡፡ ከዚያም «ቤት ለእንግዳ» በማለት
ካስገባሻቸው በኋላ ቶሎ ብለሽ ወደ ጋሪው በመመለስ ሂሣቡን ከፍለሽ ታሰናብቺዋለሽ:: እሺ?»
«የሚከፈለው ገንዘብ የት አለ?» ስትል ሴትዮዋ ጠየቀችው::
ዠንድሬ ኪሱን ዳበስ ፤ ዳበስ በማድረግ አምስት ፍራንክ ሰጣት::
«ምንድነው እርሱ?» ስትል ጠየቀች፡፡
ዛሬ ጠዋት ጎረቤታችን የሰጠን ገንዘብ ነዋ! አሁን እንግዲህ ቶሎ
ብለሽ ወደ በሩ ሄደሽ ብትጠባበቂ ይሻላል፡፡ የለም፤ አሁኑኑ ቶሎ ሂጂ፡፡»
ትእዛዙን ተቀብላ ቶሎ ወጥታ ሄደች:: ዦንድሬ ብቻውን ቀረ፡፡
የእሳት ማንደጃው፤ ጠረጴዛውና የቤቱ ሁለት ወንበሮች ማሪየስ
ከሚያይበት ቀዳዳ ትይዩ ነበሩ፡፡ አካባቢው በጣም ጭር ስላለ ማንኛውም ድምፅ በቀላሉ ከሩቅ ይሰማል፡፡

ዦንድሬ በአሳብ በመዋጡ ፒፓውን መማግ እንዳለበት ረስቶ እሳቱ ይጠፋል፡፡ እጁን ዘርግቶ የጠረጴዛውን ኪስ ሳበ፡፡ ከኪሱ ውስጥ የነበረውን ጩቤ አነሳ፡፡ ስለት እንዳለው በአውራጣቱ ሞከረው:: በኋላ መልሶ ከጠረጴዛው ኪስ ውስጥ አስቀመጠውና መሳቢያውን መልሶ ዘጋው::

ማሪየስ ደግሞ ከቀኝ ኪሱ ውስጥ የነበረውን ሽጉጥ አውጥቶ ቃታውን ስቦ ያዘው:: ቃታውን ሲስብ ሽጉጡ ድምፅ አሰማ፡፡
ዦንድሬ ደንግጦ ከተቀመጠበት ብድግ አለ፡፡

‹‹ማነህ?» ሲል ጮኸ፡፡

ማሪየስ ትንፋሹን ያዝ አደረገ፡፡ ዦንድሬ ጆሮውን አቅንቶ አዳመጠ፡፡ ከዚያም ብቻውን ይስቅ ጀመር፡፡
«ምን ጅል ነኝ! የኮርኒሱ እንጨት ድምፅ መሆኑን ማወቅ እንዴት
ተሳነኝ!» ሲል ዦንድሬ ራሱን ነቀፈ::

ማሪየስ ሽጉጡን እንደያዘ ቀረ

ልክ አሥራ ሁለት ሰዓት ስለሆነ በአካባቢው የሚገኘው ቤተክርስቲያን ደወል ተደወለ፡፡ ሚስተር ዦንድሬ የሚጠብቃቸው ሰዎች ከመጡ ብሎ የቤቱን በርና መስኮቶች ዘጋጋ፡፡ ይበራ የነበረውን ሻማ እየተመለከተ ከቤት ውስጥ ይንቆራጠጥ ጀመር፡፡ መንቆራጠጥ ሰልችቶት ከወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ወንበር ላይ እንደተቀመጠ የቤቱ በር ተከፈቱ:: የመጣችው ባለቤቱ
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...“የገዛ ልጁን ለሞት አሳልፎ ለመስጠት አገር ላገር የሚያሳድደው ከሆነ አረመኔ ነው የምለው " አለች እንባዋ በሽፋሽፍቷ እየተንቆረዘዘ " ከዚያ ዐይኗን ተጠንቅቃ አደራረቀችና ወደ ቁርስ ቤት ገባች።

የሔር ቤተሰብ እንግዳ በማይኖራቸው ጊዜ ራት የሚበሉት በዐሥር ሰዓት
ነበር " የራት ሰዓት ደረስና ሁሉም ከበታው ተቀመጡ ሚስዝ ሔርም ተሽሏት
ነበር ብራው ቀንና የውሎው ሽርጉድ የሕልሙን ሐሳብ አውርደውላት ልቧ ዕርፍ
ብሎላት ዋለ " ሚስተር
ሔር የጆይስን ወድቃ መሰበር ነገራቸው
ጠያቂም ሳይመጣ እነሱም ሳይወጡ ስለ ዋሎ አልሰሙም ነበር " ጆይስ ሁሉም ይወዳት ስለ ነበር ሚስዝ ሔር አዘነች።

የጠረጴዛው ልብስ ተነሥቶ ሚስተር ሔር ወይኑን እስኪጨርስ ጥቂት ተቀመጠና ተነሣ !ምክንያቱም የሥራ ጓደኛው ከነበረው ከጀስቲስ ሔርበርት ጋር ከራት
በኋላ ትምባሆ ለማጤስ ቀጠሮ ነበረው ።

“ ለሻይ ትመለሳለህ አባባ ? ” አለችው ባርባራ

“ አንቺ ደግሞ ብመጣ ባልመጣ ምን ጥልቅ አደረገሽ የኛ እመቤት ?

“አይ ምናልባት የምትመጣ ከሆነ እንድንጠብቅህ ብዬ ነው የጠየቅሁሀ እንጂ ነገሩስ ምንም አያገባኝም

“ ከሚስተር ሔርበርት ጋር አመሻለሁ ያልክ መስሎኝ ነበር ? ” አለች ሚስዝ
ሔር።

“ አዎን አመሻለሁና ! ብቻ ባርባራ የገዛ ምላሷ ሲንቀለቀል መስማት ደስ ይላታል ” አለ አባቷ
የጆይስ ነገር አሳዘነኝ" ወደ ኢስት ሊን በግሬ ተሻግሬ ልጠይቃት እፈልጋለሁ " " የባርባራ ልብ ቶሎ ቶሎ መታ መቸም እሷ ጊዜና ለውጥ የማይሽረው
እውነተኛና የማይጠፋ ፍቅር ይዟታል " ምናልባትም ከውስጧ ተቀብሮና ተዳፍኖ
ስለ ተቀመጠ ይሆናል ኃይልና ጥልቀት እየጨመረባት ሔደ።

“ በእግሬ ሔጄ አልሽ እማማ ? ” አለች ባርባራ "
“ አዎን አሁን አሁን ብዙ የእግር ጉዞ ልምምድ ስለ አደረግሁ የምችል ይመስለኛል » ደግሞም ዛሬ ምንም አልወጣንም " ግን በስንት ሰዓት እንሒድ ?”

"በአንድ ሰዓት ብንደርስ ራት በልተው የምናገኛቸው ይመስለኛል

"አዎን!” አለች ሁልጊዜ ሌላ ሰው ሲወስንላት ደስ የሚላት ሚስዝ ሔር !
ግን ከመነሣታችን በፊት ሻይ ባገኝ ደስ ይለኛል ”

ባርባራ እናቷን ሻይ አጠጥታ ስታበቃ ወደ ኢስት ሊን ጉዞ ጀመሩ ደስ የሚል ሞቃት ምሽት ነበር በራሪ ነፍሳት እየተቅበዘበዙ ሲያነበንቡ በመዋገድ ላይ የነበረውን በጋና ሞቃት አየሩን የሚሻሙ ይመስላል " ሚስዝ ሔር በመጀመሪያ
በጣም ደስ አላት ወደ መጨረሻው ስትቃረብ ግን ከአቅሟ በላይ መጓዟ ታወቃት" ከኢስት ሊን መኖፈሻ በር ስትደርስ የመዝጊያውን ብረት ይዛ ቀጥ አለች ".

በመምጣቴ ተሳስቼ ኑሯል ' ባርባራ ?”

ግድ የለም እማማ
በጣም ሙቀት ስለሆነ ጭምር ነው የደከመሽ ።
አሁን ከመናፈሻው አግዳሚ ወንበሮች ስንደርስ ትቀመጭና ከመግባታችን በፊት ዐረፍ ትያለሽ ።

ከጥላማ ዛፎች ሥር ከነበሩት መቀመጫዎች ደረሱና ሚስዝ ሔር ተቀመጠች።ሚስተር ካርላይል ሚስቱና እኅቱ ከእንግዳቸው ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር ሆነው ራት
እንደበሉ በመናፈሻው አበቦች መኻል ሲንሸራሸሩ ከሩቅ ለዩዋቸውና ወዲያው
ሒደው ከበቡቸው ልጆቹም ከመጠረሻሙ በቀር አብረው ነበሩ እመቤት ሳቤላ ሚስዝ ሔርን በደስታ ተቀበለቻት » ከዚያች ረቂቅና ሥቃይተኛ ሴትዮ ጋር በጣም ከፍተኛ መፈቃቀር ነበሪት "

ይኽውልህ አርኪባልድ እኔው በሽተኛ ሁኜ በሽተኛ ልጠይቅ ስመጣ ደከምኩና ከመንገድ ቆምኩ " የጆይስን ነገር ስምቸ በጣም አሳዘነችኝና መጣሁ
አለችው ሚስዝ ሔር "

አሁን ከመጡ እንግዲህ እዚህ 0ረፍ ብለው ያመሻሉ ሻይ ሲጠጡ ደግሞ
ያበረታዎታል ” አለች እመቤት ሳቤላ ።

ተባረኪ ልጄ ሻይ እንኳን ጠትተናል ”

ታዲያ ሁለተኛ የማትጠጡበት ምክንያት አለ ? እንዲያውም በጣም ስለደከሙ ለሁለት ሰዓት ያህል እኛ ዘንድ እስረኛ ሆነው መቆየትዎ አይቀርም ” አለች ሳቤላ

"እሱንስ እኔም እንዳልሺው ፈርቻለሁ "

“እነማን ናቸው ? ሲል ካፒቴን ሌቪሰን አሰበ ለራሱ እንግዶቹን ገና ከሩቅ
ሲያያቸው ። “ እንዴት የምታምር ልጅ ናት ! እስኪ ቀርቤ ልያቸው " '

ቀረበና ትውውቅ ተደረገ ካፒቴን ሌቪሰን ሚስዝ ሔርና ሚስ ሔር ትንሽ ከተነጋገሩ በኋላ ካፒቴን ሌቪሰን ከትንሹ ዊልያም ካርላይል ጋር አየተሯሯጠ
ይጫወት ጀመር ።

“ እናትሽ በጣም የታመሙ ይመስላሉ " አለ ሚስተር ካርላይል ለባርባራ ሁለቱም ከወይዘሮ ሳቤላና ከሚስዝ ኮርኒሊያ ካርላይል ጋር ስትነጋገር ከነበረችው
ከሚስዝ ሔር ጆሮ ርቀው ነበር '' በቅርቡ በጎ መሆን ጀምረው ነበር።"

“አየህ ሚስተር ካርላይል
እሷ ብዙውን ጊዜ በሽተኛ የምትመስለው እነዚያ አስጨናቂ ሕልሞች ሲታይዋት መሆኑን ታስታውሳለህ ” ዛሬ ጠዋትም በመጀመሪያ የነገረችኝ እነዚያን ሕልሞች ማየቷን ነበር ።

ሚስተር ካርላይል፡ ስለሕልሙ ምንም ሳይናገር “እንዲያው የሪቻርድ ወሬ
መጥፋት አይገርምሽም ?”

“ በጣም አሳስቦኛል " እናቴም በነገሩ ተጨንቃበታለች ዛሬ ጧትም ስለሱ ስትናገር ስትለፈልፍ ነበር ። እኔ ለራሴ በሕልምም አላምንም ። እናቴ መላልሳ ስላአየቻቸው ሕልሞች ግን ልዩ ስሜት እንዳሳደረብኝ ለመካድ አልችልም በተለይ ደግሞ ትናንት ሌሊት ያየችውን ሕልም በቀላሉ ላየው አልችልም ሚስተር
ካርላይል

"የትናንቱ ምን ነበር ? አለ ሚስተር ካርላይል "

እውነተኛዉ ወንጀለኛ ዌስት ሊን መጥቶ ታያት በሕልሟ ሰውየው ከኛ ቤት የገባ ይመሰላታል " እሷ እንደምትለው አንድ እንግዳ በጧት ከኛ ቤት ይመጣና
እኔና እሷ ሆነን ስለ ግድያው ስናነጋግረው እሱ ያልፈጸመ መሆኑን ክዶ በሪቻርድ
ሊያላክክበት ፈለገ " ወዲያው ደግሞ እሱ ተቀምጦበት ከነበረው ወንበር በስተኋላ ቁም ለነበረው ለኦትዌ ቤቴል አንድ ነር በጆሮው ሹክ አለ ይኸ ደግሞ ሌላ እንግዳ ነገር ነው አለችው ባርባራ ዐይኖቿን ወደ ሚስተር ካርላይል ፊት ቀና አድርጋ”

“በእንቆቅልሽ ነው የምትናገሪው ... ባርባራ ምኑ ነው እንግዳ ነገር ?

“ኦትዌይ ቤተል፡ሁልጊዜ በሕልሟ መታየቱ ራሱ አይገርምህም ? ሪቻርድ
በመጣ ጊዜ እስኪነግረን ድረስ ቤተል በግድያው አካባቢ መኖሩንም አናቅም
ነበር እሷ ግን ከዚያ በፊትም ታየው ነበር በእርግጥ ሪቻርድ ቤተል በነገሩ እንዳልነበረ ባት ተናግሯል እማማ ግን ይህ ሰው ከወንጀሉ ጋር አንዳች ግንኙነት እንዳለው ታምናለች "

ግን እናትሽ ገዳዩ ማነው ይላሉ ?

“ልታስታውሰው አልቻለችም ብቻ አየህ ... እኛ ስለ ካፒቴን ቶርን ያነሣንላት ነገር የለም ሰውየው በሁኔታው የትልቅ ስው ልጅ ይመስላል ትላለች "

“አንቺም ራስሽ በሕልም እያመንሽ መሰለኝ ከልብሽ ተከታትለሽዋል አላት

“ እኔን የሚያሳስበኝ የሕልሙ ጉዳይ ሳይሆን የወንድሜ ነገር ነው " ይኽን
ምስጢር መግለጥ ቢቻለኝ ድካምንና መከራን ሳልፈራ በባዶ እግሬ እስከ ዓለም
ዳርቻ በተጓዝኩ ቶርንን ወደ ዌስት ሊን ተመልሶ ለመምጣት ቢያበቃው እንደ
ባለፈው በዋዛ አልለቀውም እስከ መጨረሻ እተናነቀዋለሁ " አለችው "

“ ቶርን እንኳን ዳግመኛ ወደ ዌስት ሊን ለመምጣት የሚጓጓ አይመስልም"
ምንያቱም ባርባራ ክንዱን ቶሎ ያዝ አድርጋ ምልክት ስትሰጠው ዝም አለ ሁለቱ ስለዚህ ጉዳይ እየተነጋገሩ መናፈሻውን አቋርጠው በልዩ ልዩ ቅርጽ ወደ ተጌጠው አካባቢ ሲሔዱ ዙሪያውን በትልልቅ ቋጥኞች ከተከበበ ጠባብ የእግር መንገድ ደረሱ
ልክ ሚስተር ካርላይልና ባርባራ ከቆሙበት ቦታ ላይ ከነበረው ትልቅ ድንጋይ ላይ
ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጀርባውን ለነሱ ሰጥቶ ተቀምጦ ነበር
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


....ክሪስ ከመልበሻ ጠረጴዛው ፊት ያለ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡ አገጩን በእጁ "ደግፎ ለደቂቃዎች እያሰበ ቆየ: “በአንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። አንቺም ሆንሽ መንትዮቹ ስትቀጡ ማየት አልፈልግም ስለዚህ ወጥቼ የምሰርቀው እኔ
ነኝ። ድንገት ከተያዝኩ ጥፋተኛው እኔ ብቻ እሆናለሁ: ግን አልያዝም።
ከዚያች አሮጊት መስረቅ አደገኛ ነው በጣም ተጠራጣሪ ናት፡ ቦርሳ ውስጥ ያለውን ገንዘብ መጠን ሳንቲሙን ሳይቀር እንደምታውቅ ጥርጥር የለውም እናታችን ግን ገንዘቧን ቆጥራ አታውቅም: አባታችን እንዴት ይወቅሳት
እንደነበረ ታስታውሳለህ?” በማረጋገጥ ፈገግ አለልኝ፡ “ልክ እንደ ሮቢን ሁድ.
ከሀብታሞች እየሰረቅኩ ለተቸገሩ ለእኛ የምስጥ እሆናለሁ! እናታችንና ባሏ
ወጣ እንደሚሉ የምትነግረን ምሽት ላይ ብቻ እሰርቃለሁ”

“በማትመጣባቸው ቀናት በመስኮት ማየት እንችላለን ደፋር ከሆንን የሚመጡትንና የሚሄዱትን የሚያሳይ መታጠፊያ አለ”

ትንሽ ቆይቶ እናታችን ግብዣ እንደምትሄድ ነገረችኝ። “ባርት ስለማህበራዊ
ህይወት ብዙም ግድ የለውምº ቤት ቢቆይ ይሻለዋል: እኔ ግን ይህንን ቤት ጠልቼዋለሁ ከዚያ ለምን ወደራሳችን ቤት አንገባም ብሎ ጠየቀኝ። ምን ማለት እችላለሁ?”

ምን ማለት ትችላለች? ውዴ አንድ የምነግርህ ሚስጥር አለ። ፎቁ ላይ ራቅ
ያለው የሰሜኑ ክፍል ውስጥ የደበቅኳቸው አራት ልጆች አሉኝ።

ለክሪስ ከእናቱ ግዙፍና ያማረ መኝታ ክፍል ውስጥ ገንዘብ መስረቅ ቀላል ነበር::ስለ ገንዘብ ግድ የለሽ ናት፡ እንዲያውም ብዙ ገንዘብ በግዴለሽነት የመልበሻ ጠረጴዛዋ ላይ መበታተኗ አስደንግጦታል በጭንቅላቱ ጥርጣሬ እንዲያኖር አድርጎታል። አሁን ባልም ቢኖራት እንኳ ከዚህ እስር ቤት ለምታስወጣን ቀን ማጠራቀም አልነበረባትም? ክሪስ የባሏ ኪሶች ውስጥ ጥቂት ዝርዝር ሳንቲሞችን ብቻ አገኘ፡፡ እሱ ገንዘብ ላይ የሷን ያህል ግድ የለሽ አይደለም ነገር ግን ክሪስ የወንበሮቹ ትራስ ስር በጣም ብዙ ሳንቲሞች አግኝቷል በእናቱ ክፍል ውስጥ የማይፈለግ ሰርጎ ገብ ሌባ እንደሆነ ተሰማው

በዚያ ክረምት ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደዚያ ክፍል ሲመላለስ፣ መስረቅ በጣም
ቀላል ስለሆነለት ግድ የለሽ እየሆነ መጣ፡ አንዳንዴ ተደስቶ አንዳንዴ አዝኖ
ወደ እኔ ይመለሳል፡ ከቀን ወደቀን የተደበቀው ገንዘባችን እያደገ መጥቷል።ታዲያ ለምንድነው የሚያዝነው? “በሚቀጥለው ቀን አብረሽኝ ትመጫለሽ ራስሽ ታይዋለሽ” ነበር መልሱ።

መንትዮቹ ነቅተው መሄዳችንን እንዳያውቁ አረጋግጬ በንፁህ ህሊና መሄድ እችላለሁ: ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። ጠዋት ለመንቃት እንኳን
አይናቸው እየተጨናበሰ ቀስ ብለው ነው የሚነቁት። አንዳንድ ጊዜ ተኝተው
ሳያቸው ያስፈራኛል። ሁለት ትንንሽ አሻንጉሊቶች፣ የማያድጉ፣ የሚያንቀላፉ
ሳይሆን ትንሽ ሞት ውስጥ የሰመጡ ይመስሉ ነበር።

ሂዱ! አምልጡ! ፀደይ እየመጣ ነው፡ ከመዘግየቱ በፊት ቶሎ መልቀቅ
አለብን በውስጤ ያለ ድምፅ ደመነፍሴ ያለማቋረጥ በውስጤ ይደውላል።ክሪስ ስነግረው ሳቀብኝ፡ “ካቲ አንቺና የአንቺ ደመነፍስን መስማት ብቻ
ሳይሆን ገንዘብ እንደሚያስፈልገንም መረዳት ያስፈልጋል ቢያንስ አምስት መቶ ያስፈልገናል። ለምንድነው የምንቸኩለው? አሁን ምግብ አለን
አልተገረፍንም፣ በግማሽ እርቃናችንን ሆነን ስትይዘን እንኳን ምንም ቃል አልተናገረችም ለምንድነው አሁን አያትየው የማትቀጣን? ስለ ሌሎቹ
ቅጣቶቿ፣ እኛ ላይ ስለሰራችው ኃጢአት ለእናታችን አልተናገርንም ለእኔ እኛ ላይ ያደረገችው ነገር በምንም መንገድ ማስተባበል የማይቻል ኃጢአት የተሞላ ነው ሆኖም ያቺ አሮጊት ሴት እጇ አልተለየንም በየቀኑ በሳንድዊች የተሞላ የሽርሽር ቅርጫት ለብ ካለ ሾርባና ወተት እንዲሁም ከአራት ስኳር ከተነሰነሰባቸው ዶናቶች ጋር ታመጣልናለች።

“ፍጠኚ!” አስቸኮለኝ። ክሪስ ጨለማና ባዶ በሆነው ኮሪደር ላይ እየጎተተኝ
ነው። “አንድ ቦታ ላይ መቆም አደገኛ ነው የሽልማቱን ክፍል በፍጥነት
አየት አድርገን ከዚያ ወደ እናታችን መኝታ ክፍል በፍጥነት እንሄዳለን”
የፈለግኩት የሽልማቱን ክፍል ለአፍታ አየት ማድረግ ነው። በድንጋይ የተሰራው እሳት ማንደጃ ላይ ተቀምጦ ያየሁት በጣም አባታችንን የሚመስል በዘይት ቀለም የተሰራውን ምስል ጠላሁት እንደ ማልኮም ፎክስወርዝ ያለ ጨካኝና ልበ ደንዳና ሰው ወጣት ሆኖም እንኳን መልከመልካም የመሆን
ምንም መብት የለውም: እነዚያ ቀዝቃዛ ሰማያዊ አይኖቹ የቀረውን እሱነቱን
በቁስል መምታት ይገባቸዋል። ወለሉ ላይ ያለውን የድብና የነብር ቆዳ
እንዲሁም የሞቱ እንስሳት ጭንቅላቶች አየሁ እንደዚህ አይነት ክፍል መፈለጉ በራሱ ማንነቱን የሚያሳይ ነው።

ክሪስ ቢፈቅድልኝ ኖሮ ሁሉንም ክፍሎች እመለከት ነበር፡ ነገር ግን የተዘጉትን
በሮች ዝም ብለን እንድናልፍና ጥቂቶቹን ብቻ አየት እንዳደርግ ፈቀደልኝ
ሰርሳሪ አለኝ በሹክሹክታ: በአንደኛቸውም ውስጥ የሚያስደስት ነገር
የለም:" ትክክል ነበር፡ በዚያ ምሽት ክሪስ ያለው ነገር በብዙ መልኩ ትክክል
እንደሆነ አወቅኩ ክሪስ፣ ይሄ ቤት ግዙፍና ቆንጆ እንጂ የሚያምርና የሚመች
አይደለም ብሎኝ ነበር፡ የሆነ ሆኖ፣መገረሜን መግታት አልቻልኩም።በንፅፅር ግላድስተን የነበረው ቤታችን ተራ ቤት ይሆናል፡

ብዙ ረጅምና በሚያስጠላ አይነት ደብዛዛ የሆኑ አዳራሾች አልፈን በመጨረሻ የእናታችን ግዙፍ ክፍል ደረስን፡ ክሪስ ስለ አልጋውና ስለ ሁሉም በዝርዝር ነግሮኛል፡፡ ግን መስማት ማየት አይደለም:: ትንፋሼ ተሰበሰበ ህልሞቼ ክንፍ አወጡ፣ ኦ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን! ይህ ክፍል ሳይሆን የንግስት ወይም የልዕልት መኖሪያን የሚመጥን ነው። ሁሉም ነገር የሚያስደምም ነበር፡
ከዚያ እናታችን አባታችን ካልሆነ ከሌላ ሰው ጋር የምትተኛበትን አልጋ
በመጥላት አፈገፈግኩ፡ ወደ ግዙፉ የልብስ ማስቀመጫ ሳጥኗ ተጠግቼ በህልም ካልሆነ በስተቀር የእኔ ሊሆን ከማይችለው የህልም ሀብት ውስጥ
ገባሁ: ሱቆች ውስጥ ከሚገኙት በላይ ልብሶች አሏት: ያሏትን ልብሶች
ጫማዎችና ጌጣጌጦች ሁሉ አንዳንድ ጊዜ ለመልበስ እንኳን ሺህ አመት መኖር አለባት

አይኖቼን የያዘው ሌላ ነገር ደግሞ ክሪስ ያሳየኝ ወርቃማ የመልበሻ ክፍል
ነው: ዙሪያውን መስታወት ያለበት፣ አረንጓዴ ተክሎችና እውነተኛ አበቦች
ያደጉበት መታጠቢያ ክፍሏን ተመለከትኩ፡ “ሁሉም አዲስ ነው” ክሪስ
አብራራልኝ: በመጀመሪያ የገና ግብዣው ቀን ስመጣ እንደዚህ በጣም.
የሚያምር አልነበረም”

ከበፊት ጀምሮ እንደዚህ እንደነበር ግን ስላልነገረኝ ዞር ብዬ ተመለከትኩት
ስለነዚህ ሁሉ ልብሶች፣ በሚስጥር ሳጥኗ ውስጥ ስለቆለፈቻቸው ጌጣጌጦች
እንዳውቅ ስላልፈለገ ሆነ ብሎ እየሸፈነላት ነበር። አልዋሸኝም። ግን ደግሞ
አልነገረኝምም ነበር። የእኔን ጥያቄዎች ላለመመለስ አይኖቼን የሚሽሹት
አይኖቹንና በእፍረት የቀላ ፊቱን እያየሁ ነው። እኛ ክፍል ውስጥ መተኛት
አለመፈለጓ የሚያስገርም አይደለም የመልበሻ ክፍሏ ውስጥ ሆኜ የእናታችንን ልብሶች እየሞከርኩ ነው፡
በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የናይለን ስቶኪንግ ለበስኩ አቤት… እንዴት
እንደሚያምሩ! ሴቶች እንደዚህ አይነት የእግር ሹራቦች ቢወዱ አያስገርምም! ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የጡት መያዣ ለበስኩ በጣም ትልቅ ነበር። ልክ
የሆኑኝ እንዲመስል ውስጣቸው የመፀዳጃ ወረቀቶች ጠቀጠቅኩ። ቀጥሎ ደግሞ ጫማ ሞከርኩ፡ እሱም ትልቅ ነበር።
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት በሰማችው ተንገሸገሸች ‹‹በጣም የሚያስፈራ ነገር ነው
የነገርከኝ፡፡ ለዚህ ነው እንደ ፍራንኪ ጎርዲኖ ያሉ ወሮበሎች የእጃቸውን
ማግኘት አለባቸው የሚባለው

ትንሽ ዝም ብለው ቆዩና ‹‹ኧረ ለመሆኑ በፍራንኪ ጎርዲኖ እና በክላይቭ መምበሪ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?,,

‹‹እንጃ እኔ አላውቅም›› አላት፡፡

‹‹ፔርሲ መምበሪ ሽጉጥ ይዟል ብሎ ነግሮኛል፡ ፖሊስ ሳይሆን አይቀርም››

‹‹እውነት! እንዴት?››

‹‹እንደዚህ አይነት ልብስ የለበሰው እንዳይታወቅበት ነው››

‹‹ፍራንክ ጎርዲኖን የሚጠብቅ ፖሊስ ይሆናል››

‹‹ለምን? ጎርዲኖ እንግሊዝ አገር ውስጥ ታድኖ የተያዘ አሜሪካን አገር እስር ቤት የሚወስድ ወንጀለኛ ነው፤ ከአይሮፕላኑ ዋጋ ውድነት አንጻር የእንግሊዝ ፖሊስ ኮሚሽን ገንዘቡን ገፍግፎ እስረኛ እንዲያጅብ ፖሊስ
የሚልከው ለምንድነው?››

‹‹አንተን ይሆን የሚከታተለው?›› አለች በጆሮው

‹‹አሜሪካን አገር ድረስ›› አለ ሄሪ ጥርጣሬ ገብቶት ‹‹ለሁለት የወርቅ
አምባሮች ሲል?››

‹‹ታዲያ እዚህ ለምን መጣ?››

‹‹አላውቅም››

‹‹የሆነ ሆነና የጎርዲኖ ጉዳይ ራት ላይ አባቴ ያሳየውን መጥፎ ባህሪ
የሚያረሳሳ ይመስለኛል፡››

‹‹ለምንድን ነው እንደዚያ የሆኑት አባትሽ?›› ሲል ጠየቀ ሄሪ፡

‹‹እኔ እንጃ ከዚህ በፊት እንደዚህ ሆኖ አያውቅም››
‹‹ከዚህ ቀደም የፋሺስት አስተሳሰብ አራማጆች አጋጥመውኛል አለ
ሄሪ ‹‹እነዚህ ሰዎች ፍርሃት አለባቸው››

‹‹እንደዚያ ነው?›› ማርጋሬት አባባሉ ያስደነቃት ከመሆኑም በላይ ሊሆን የማይችል ሆነባት፡፡ ‹‹ፋሺስቶች ሲያይዋቸው ሞገደኛ ይመስላሉ
ውስጣቸው የተረጋጋ አይደለም፡፡ ለዚህ ነው ዩኒፎርም ለብሰው ላይ ታች
የሚሉት፡፡ በቡድን ሲሆኑ ነው ደህንነት የሚሰማቸው ዲሞክራሲ የሚጠሉት ለዚህ ነው፡፡ አየሽ ዲሞክራሲ የተለያየ አስተሳሰብ እንዲንፀባረቅ
ይፈቅዳል ገደብ አይጥልም
አምባገነንነትን ለምን እንደሚወዱ ታውቂያለሽ? ወደፊት የሚሆነው የታወቀ ስለሆነና የፋሺስት መንግስት በቀላሉ ለውጥ ስለማይደረግበት ነው››

‹‹አባቴ ኮሚኒስቶችን ወይም ጽዮናዊያንን ወይም የሰራተኛ ማህበራትን
ያለ ምክንያት አይደለም የሚጠላው እነዚህ ሐይሎች
ያንበረክኳታል ብሎ ይሰጋል፡››

‹‹ፋሺስቶች ሁልጊዜ ብስጩ ናቸው›› አለ ሄሪ፡፡

‹‹አባቴም እንዲሁ ነው  አያቴ ሲሞቱ ዕዳ ያለበት ርስት ነው ያወረሱት፧ እናቴን እስኪያገባ ድረስ ተቸግሮ ነበር የኖረው፤ከዚያም
ለፓርላማ አባልነት ተወዳድሮ ቢያሸንፍም በሩን አልረገጠም፤ አሁን ደግሞ
ካገሩ ተነቅሎ ተባረረ›› አለች፡፡

ማርጋሬት ‹ሄሪ ማርክስ ከቤተሰብ ጠፍቼ እንድሄድ ይረዳኝ ይሆን?› ስትል አሰበች አሜሪካ ከገቡ በኋላም እንዳሁኑ ይቀርባት እንደሆነ እርግጠኛ
አይደለችም፡፡ ‹‹አሜሪካ የት ነው ልትኖር ያሰብከው?›› ስትል ጠየቀችው።

‹‹ኒውዮርክ ቤት ተከራይቼ እኖራለሁ፤ አሁን እጄ ላይ ጥቂት ገንዘብ አለኝ፤ ሌላም ገንዘብ የሚገኝ ይመስለኛል፡››

ሄሪ ሁሉን ነገር አቅልሎ ነው የሚናገረው ‹‹ምናልባትም ለወንዶች ቀላል ይሆናል፡፡ ሴት ልጅ ግን ረዳት ያስፈልጋታል››

‹‹ናንሲ ሌኔሃን ስራ ልትቀጥረኝ እንደምትችል ነግራኛለች›› አለች፡
‹‹ሆኖም ወንድሟ ኩባንያውን ከወሰደባት የገባችልኝን ቃል ላትጠብቅ
ትችላለች››

‹‹ከፈለግሽ እኔ አግዝሻለሁ›› አላት፡፡

እሷ እንዲህ አይነት ድጋፍ ነው የፈለገችው

‹‹ትረዳኛለህ?›› ስትል
ጠየቀችው፡፡

ሄሪ ምን ሊያደርግላት እንደሚችል ግልፅ ባይሆንለትም ‹‹ቤርጎ ፈልጌ
አሳይሻለሁ›› አላት፡፡

ይህን ቃል ስትሰማ የተሰማት እረፍት ቀላል አይደለም፡፡

‹‹እግዜር ይስጥህ፡፡ እኔ በህይወቴ ቤርጎ ፈልጌ ይዤ አላውቅም፡፡››
‹የቤት ኪራይ ማስታወቂያ እናያለን››

በታይምስ ጋዜጣ ላይ እንዲህ አይነት ማስታወቂያ አይቼ አላውቅም››አለች አባቷ የሚያነቡት ይህን ጋዜጣ ብቻ መሆኑን አስታውሳ፡፡

‹‹ማታ ማታ የሚወጡ ጋዜጦች ላይ ነው ማስታወቂያዎች የሚወጡት››

እንዲህ አይነት ቀላል ነገር እንኳን ባለማወቋ አፈረች፡፡
‹‹እኔ የሚረዳኝ ሰው ያስፈልገኛል››
‹‹አይዞሽ አትፍሪ እኔ የምችለውን ያህል እረዳሻለሁ››
‹‹በእውነት የሚያስደስት ነው›› አለች ማርጋሬት ‹‹ሚስስ ሌኔሃንና አሁን ደግሞ አንተን ካገኘሁ ኑሮውን እቋቋመዋለሁ፡ ውለታ ከፋይ ያድርገኝ፡፡ ምን እንደምል እንጃ፡:››

ዴቪ ወዳሉበት መጣና ‹‹በመስኮት ተመልከቱ አንድ ነገር ታያላችሁ›› አለ።

ማርጋሬት አይሮፕላኑ ለአስራ አምስት  ደቂቃ ያህል ሳይወዛወዝ
እንደተጓዘ ተገነዘበች፡

ማርጋሬት በመስኮት አሻግራ ተመለከተች፡፡ ሄሪ የመቀመጫ ቀበቶውን
ፈታና በማርጋሬት ጀርባ በኩል አሻግሮ አየ፡፡

‹‹ለእኛ ብለው ይሆናል መብራቱን ሁሉ ያበሩት›› አለ አንዱ፡፡

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የአየር ጥቃቱን በመፍራት በጨለማ ነው የሚጓዙት፡ ማርጋሬት ሄሪ በጣም ወደሷ መጠጋቱን አልጠላችውም:
የአይሮፕላኑ የመገናኛ ሰራተኛ ከመርከቡ የመገናኛ ሰራተኛ ጋር በሬዲዮ
ሳይነጋገር አልቀረም፡፡ የመርከቡ ተሳፋሪዎች ወደ መርከቡ በረንዳ ላይ
ወጡና እጃቸውን አውለበለቡ፡፡ አይሮፕላኑ ከመርከቡ በቅርብ ርቀት የሚበር በመሆኑ ወንዶቹ ነጫጭ የራት ልብስ፤ ሴቶቹ ደግሞ ቅልጥም የሚታከክ
ልብስ መልበሳቸውን በግልጽ ይታያል፡፡

መርከቡ ማዕበሉን በሹል አፍንጫው እየሰነጠቀ ሲጓዝ አይሮፕላኑ አልፎት በረረ፡፡ ማርጋሬት ሁኔታው አስደስቷታል፡ ሄሪን ስታየው እሱም አያትና ተሳሳቁ፡፡ ሰዎች እንዳያዩት በሰውነቱ ከልሏት እጁን ወገቧ ላይ ጣል አድርጓል፡፡ በእጁ ገላዋን ነካ ያደረጋት ቢሆንም በመላ ሰውነቷ ላይ
የኤሌክትሪክ ሞገድ ያህል ሙቀት ለቆባታል፡ ይህ ሁኔታ በመጠኑ ድንግርግር እንዲላት ቢያደርግም እጁን እንዲያነሳ ግን አልፈለገችም ከትንሽ ጊዜ በኋላ ቁልቁል የሚያዩትን መርከብ አልፈው ሲሄዱ ከመርከቡ የሚፈነጥቀው መብራትም እየራቃቸው ሄደ፡፡ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ወደ
ቦታቸው ሲመለሱ ሄሪም ወደ ቦታው ሄደ፡፡

ዋናው ሳሎን ውስጥ ካርታ ከሚጫወቱት ጋር ማርጋሬትና ሄሪ ብቻ
ሲቀሩ ሌሎቹ ተሳፋሪዎች ወደ መኝታቸው ሄዱ፡ ማርጋሬት ከሄሪ ብቻዋን ተቀምጣ እፍረት ተሰማትና ‹‹መሽቷል ብንተኛ ይሻላል›› አለች ወዲያው ለምን እንዲህ አልኩ? አለች ለራሷ መተኛት አልፈለገችም: ሄሪ
ከእሷ መለየቱ ደስ ስላላለው ‹‹እኔም ትንሽ ቆይቼ እሄዳለሁ›› አለ
ማርጋሬት ከመቀመጫዋ ተነሳች ‹‹ወደፊት አሜሪካ ውስጥ እረዳሻለሁ
ስላልከኝ አመሰግናለሁ›› አለች፡፡
" ምንም አይደል"
"መልካም ምሽት"
"ለአንቺም እንዲሁ" አለ ሄሪ
ከመሄዷ በፊት ዞር አለችና እረዳሻለሁ ያልከኝ ከአንጀትክ ነው አይደል?

"አይዞሽ አታስቢ›› አላት፡፡

ማርጋሬት ለሄሪ ያላት ፍቅር እየጨመረ መጥቷል፡፡  ከዚያም  በደመነፍስ እዚያው ቁጭ ባለበት ከንፈሩን ሳም አደረገችው፡፡ ይህም ደስ የሚል ስሜት አጭሮባታል፡፡ ግን ደግሞ ወዲያውኑ ባደረገችው ነገር ክው አለች ያጫረባት ደስታ ጉልበቷን አብረክርኳታል፡፡ ዙሪያ ገባውን
ስትመለከት ሚስተር መምበሪ የላይኛውን አልጋ ሲይዝ የታችኛውን ሄሪ
ይዟል፧ ፔርሲም የላይኛው አልጋ ላይ ተኝቷል፡፡ መጋረጃውን ጋረደች፡፡

መብራቱን አጠፋችና ብርድ ልብስ ውስጥ ገብታ ተኛች። መኝታው ይሞቃል፡፡ በመስኮት ስታይ ከጨለማና ከዝናብ በስተቀር ምንም የሚታይ ነገር የለም፡፡ እሷና ኤልሳቤት ትንንሽ ልጆች ሆነው በበጋ ውስጥ እውጭ ድንኳን ተክለው የሚተኙት ትዝ አላት፡፡

ኤልሳቤት የት ትሆን ያለችው?
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


“ይህ ክላሲካል ዋሽንት ተጫዋች ማነው?"

ሐመሩ የፍቅር ጓደኛዬ ነው ዋሽንት ግን መጫወት
ይችላል?

“ያውም ልብን በሚሰልብ ቅላፄ ነዋ የአጨዋወት ስልቱ ልብሽን የሚሰውርበት አካልሽን የሚያንሳፍፍበት... አንዳች ኃይል አለው:: ከርቀት የሚቀሰቅስሽ የሚንጥሽ…"

“እንኳን ደስ አለሽ በይኛ!በፍቅር ክንዱ አፍቃሪዎቹን
በተራ ያሰለፈን ጀግና በሙዚቃ አርቱም የምንተኛበትንና
የምንነቃበትን ፕሮግራም ያወጣልናላ ደልቲ ገልዲ…

ምን

የሱ ታሪክ ብዙ ነው ኮንችት: በርቀት ስታይው የፍልፈል
አፈር! እየተጠጋሽ ሄደሽ ውስጡ ስትገቢ ግን እንደ ተራራ እየገዘፈ፤ወደላይ እየተከመረ የሚሄድ የሚስጥር ዓለም ነው።''

“እውነትሽን ነው"

“አዎ  ኮንችት"

ኮንችት ደነቃት ገረማት ፍቅራቸውን ልታየው ሞከረች አንዴ ካርለትን
ተመልሳ ደልቲን… አየችው አጠጋጋቻቸው አሰተቃቀፈቻቸው
አሳሳመቻቸው… በሃሳቧ ምራቋን እየዋጠች፡፡

“ምነው ኮንችት? ካርለት ኮንችትበብ ጭልጥ ስል
እየሳቀች ቀስቅሳ ጠየቀቻት።

“እንጃ! ግን." ኮንችት ሃሣቧን ገደበችው ዋጠችው ካርለት እንደገና ሳቀች። ሳቋ ደልቲን ጎሻሸመው። ዞር ብሎ ፈገግ
ሲል የኮንችት አይኖች ጥርሶቹ ላይ ተሰኩ! እንደ በረዶ ጥርሱ ነጭ ነው።

“ታፈቅሪዋለሽ?” ሞኝ ሆነች ኮንችት

"አዎ የፍቅር እንጥሌን ሌሎቹ ተንጠራርተው ሲያጡት ተቀምጦ የነካው እሱ ብቻ ነው ተሳሳቁ ካርለትና ኮንችት::

'እንጥሌን እምም...” ኮንችት እንደገና ምራቋን ዋጠች።

“እሱም ያፈቅርሻል?”

“እኔ እንጃ... ቢሆንም አይላኝም እኔ ለእሱ ገና
ያልተገራሁ ባዝራ ነኝ: ስለዚህ ከኔ ይልቅ እሷን ይወዳታል:"

ካርለት በአገጯ ጎይቲን ለኮንችት አሳየቻት
ኮንችት ጎይቲን እስከ አሁን ለምን እንዳላስተዋለቻት
ገረማት የጠይም ቆንጀ እግሮችዋና ወገቧ የሚያምር ችምችም
ያሉት የወተት አረፋ ጥርሶችዋ የሚያስጎመጁ ሆነባት።

ኮንችት ጎይቲን ስታያት እንደቆየች ስለ ውበት አሰበች።ስለ ሰው ልጆች የራቁት ውበት ልብስ ስላልሸፈነው ተፈጥሮአዊ ገላ አለመች:: ሰው ሁሉ በተፈጥሮው ማራኪ ነው ያምራል ይስባል...

“አሁን ግን እሷ አግብታለች ስለዚህ የደልቲን ፍቅር እንደ
ማንጎ እየጋጥሁ እረካባታለሁ ስል ጀግናው ሌላ ቆንጆ በፍቅሩ ግዳይ
ጥሎ ቆንጀዋ ልቡን ሰብራ ልትገባ ስትፈልጠው ደረስሁ... ሳቀች

ካርለት: ሳቋ ኮንችትን ስለውበት ከምታልምበት የፍልስፍና ዓለም ቀሰቀሳት።

"እሷ ደግሞ ማን ናት?"

“ዳራ ትባላለች ሐመር ናት: ልቅም ያለች ቆንጆ!...”

ካርለትና ኮንችት እንዲህ ሲጨዋወቱ ጎይቲ አንተነህ
የምታየው የምትሰማው የምትነካው የምታልመው... አንድ ሰው ነው:: ከፊት ለፊቷ የተቀመጠውን የፍቅር ጀግናዋን ትኩር ብላ
ስታስተውለው ቆይታ ወደ እሱ ሄደች።

በእጇዋ ጨሌ
አንጠልጥላለች መለሎ
አንገቱ ላይ አጠለቀችለት! ቀና ብሎ አያት እሷም ዝቅ ብላ አየችው።

አልተቀየረም  እሷም
አልተቀየረችም ትንፋሻቸው ይጥማል። የጫካ ነፃነታቸው ግን የለም ጭኗቿ አይታቀፏትም ደረቱ ላይ አትተኛም፤እሱም ዳሌዋን አያቅፍም
ጡቶችዋ እንደ እንቧይ ደረቱ ላይ አይነጥሩም...

“ይእ! እንኳን ደና ሆነህልኝ እንጂ..." ብላው እንባዋ
በአይኗ ዙሪያ ተኮለኮለ

“ምን ይሆን ብለሽ ነው አንች..." እሱም መናገሩ
አቃተው: ይህን ሲል ጎይቲ የፍቅር ትዝታው ጠቅ አድርጎ ወጋት ስለዚህ ሃዘን የሰራ አካላቷን በጨካኝ ስለቱ አብጠለጠለው። ያኔ ልቧ፣ ሲኮማተር አይኗ ዙሪያ የተኮለኮለው እንባዋ ኩልል ብሎ ወረደ።

“ይእ ባይሆን አልጣህ- አይንህን ልየው ፍቅርህ ልቤ ውስጥ ሲንፈራገጥ አንተ ሳትኖር እንደ ምጥ ያስጮኸኛል ጤና ይነሳኛል። እንኳንም ግን ፍቅርህ ተሆዴ አይወጣ! እንኳንም
አልገላገለው! እሚወለድ ቢሆን ሲያድግ ብቻዬን ጥሎኝ ይሄድ ነበር.." ትክዝ አለች እይታዋን የከለከለውን እንባዋን ጭምቅ አድርጋ
አፍስሳ።

ስሜቷ ጭምትርትር ያለውን ጎይቲን ሲያይ ደልቲም የሆነ
ነገር እሱም ሆድ እንደጉማሬ ሲገላበጥ በዓይነ ህሊናው ታየው።

“ተይው የኔ እህት! ተይው እርሽው ተንግዲህ ተሱ
ምሰይ: የአባት ደንብ ተሁሉም ይቦልጣል  ተፍቅርም!! ስለዚህ
ጉም መቼስ አይዘገን.." ብሎ የባሰ የሐዘን ቦይዋን ከፍቶ ለቀቀባት
የሚያጉረመርም ሳግ ቀጥሎ የህሊና ብራቅ ከዚያ እንባዋ አጨቀያት:
ጎይቲ እንገቷን ደፋች: እሱን ማጣቷ እውነት ነው! እውነትም የሱ የመሆን
እድሏ አክትሟል፤
አክትሟል፤እውነትም
የፍቅር ጥገታቸው
ነጥፋለች...

ጎይቲ እንባዋ ቦዩን ይዞ ፈሰሰ፣ እንባ የጠማት መሬት ደግሞ የፍቅር እንባዋን እያጣጣመች ጭልጥ አድርጋ ጠጣችው::መሬት ሰዎች ሲፋቀሩ የሚተርፋት እርግጫቸው ነው ሲያዝኑ ግን ፀሐይ ያቃጠው ጉሮሮዋን ጨዋማ እንባቸው ጥሟን ያረሰርስላታል ጥሟን ይቆርጥላታል ጣፋጩ የሰው ልጅ እንባ የጎይቲን እንባም መሬቷ አፏን ከፍታ ጠጣችው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

' ...ይእ ተወኝ አንተ ሰው! መች አንተ ለእኔ አነስከኝ።
የአንተ መሆኔን ነጋሪ አልሻም ሰው መቼስ ካሉት በረት ሙሉ ከብቶች የሚቆረቆረውና የሚቆጨው አውሬ የበላበትን ጫካ
ያስቀረበትን ከብት አይደል! እንደማያገኘው ልቦናው ያውቀዋል ቢኖርም ለእሱ እስካላለው ድረስ በሽታ ይገለው ይሆናል: ይህን ግን
አያስብም። ዘወትር ቁጭት ብቻ ወይኔ ብቻ. እሮሮ ብቻ

“አያ ደልቲ የኔ አይደለም:: ከእንግዲህ በሴትነት መላዬ
ጀግናውን እየመራሁ ወስጄ ልቤ ውስጥ አላስተኛውም ሙቀቱን አልጋሪውም... ያች የፍቅር ጨረቃ አሁን የማይወለደውን ጨቅላ
አቅፌ እሽሩሩ….' የምልባት ብርሃን ናት: የፍቅሩን ትዝታ!
የጀግናውን ገድል፤ የማይጎረምስ ፍቅሩን፤ ጠረኑ የማይለውጥ
ፍቅሩን... የማልምባት ናት ጨረቃ!

"በእጅ ያረጉት አንባር ከእንጨት ይቆጤራል' እንዲሉ ለአያ ደልቲ ስንሰፈሰፍ ልብህ ቢከፋው አይደንቀኝም!በድየሃለሁ
"ዘንግቼሃለሁ... ግን ወድጄ አይደለም። ስቆምበት ልብህ እንደ ደረቀ
እንጨት ሲሰባበር ይሰማኛል። ወንድነትህን ብታሳዬኝ ሸንቆጥ
ብታደርገኝ አብያው ልቤ አደብ ገዝቶ ትዝታዬን እያረሰ ገለባብጦ የአንተን የፍትር ቡቃያ ያበቅለው ነበር: አንተ ግን ወኔ ከወንድነቱ
ይልቅ ወደ ሴትነቱ ያደላል፡ እንደ ወንዶች አታገሳም አትፎገራምI አትዋጋም አሯሩጠህ አትጥልም! አትጀነንምI የተከደነውን በሃይል አትከፍትም...

“እና ልቤ ሃይ ባይ አጣ ትዝታዬን የሚሽር ትዝታ
አጣሁ ይእ! አይ ልፋቴ አንተ እቅፍ ውስጥ ሆኜ ከተራራው ማዶ ሰው ፍለጋ ስንጠራራ! 'አሁንም ትወጂዋለሽ... እያልህ ከምትለኝ በወንድነት በልቤ ውስጥ የሚዋኘውን ጀግና አጥምደውና ሃሣቤን
ቆልምመው: ለእኔስ አያ ደልቲ እንዳለኝ ተአባቴ ደንብ ውጭ እሱን ማሰብ 'ጉም መዝገን' አይደል!

“አንተና እኔ ሰውነታችን እንጂ አበቃቀላችን ለየቅል ነው።መስሎህ እንጂ ማንም ትሁን ማን የደረሰ ቡቃያዋን አሽቶ ያቃማትን ሐመር አትረሳም:: ያውም ያያ ደልቲን የፋና ወጊውን የጀግናውን አንበሳ ቀጭኔ... ከገደለው እቅፍ የገባችውን... 'ተይ' ተብላ ፍቅሩን ከልቦናዋ አውጥታ ልትወረውረው ይህ የሚቻላት ሐመር የለችም።

“እኔ የኔ ጌታ በቃልህ ተይ ዘንጊው... አትበለኝ: ቅጣትህ ይሻለኛል! ልመናህ ግን ያብሰኛል.." ጎይቲ አይኖችዋን አድማሱ ላይ
ሰንቅራ ሃሳቧን ሳትጨርሰው ፀጥ አለች።
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

እቤት እንደገባች መኝታ ቤቷን ዘጋችና ትንሽ እረፍት ልትወስድ ፈልጋ ጋደም አለች፡፡ነገ ቃልን እንደምታፈቅረው ልትነግረው በመወሰኗ በውስጧ የተፈጠረባት መረበሽን ተከትሎ ኃይለኛ እራስ ምታት እያንገላታት ነው..እራሷን ለሁለት ከፍሎ ይፈልጣት ጀመር .ከመኝታዋ እንደምንም እየተንገዳደገደች ተነስታ ኮመዲኖዋን ከፈተችና የህመም መስታገሻ መድሀኒት አወጣች ሁለት ፍሬ ወስዳ ወጠች.እንዲሁ መድሀኒቱ የህመም ማስታገሻ ይባላል እንጂ ድንዛዜ ውስጥ የሚከትና የሚያንሳፍፍ  ሀሺሽነት ባህሪ ያለው መድሀኒት ነው..ለአሷ ግን ይመቻታል፡፡መኝታዋ ላይ ተመቻችታ ተኛች፡፡ቀስ በቀስ ደስ የሚል ስሜት እየተሰማት መጣ..ደስ የሚሉ ሀሳቦች የአምሮዋን የፊተኛ ስፍረ መቆጣጠር ጀመሩ…እሷም በደስታ ፈቀደችላቸው..ድንገት የሆነ ቅፅበታዊ መገለጥ አይነት ነገር ሲከሰተ እየታወቃተ ነው...በአእምሮዋ የፊተኛው ሰሌዳ ላይ ብልጭ ድርግም...ብልጭ ድሮግም  ማለት የጀመረው ...አባቷን በአይኖቾ ያየችበት የመጨረሻ ቀን   ጓሮ ከትክልቶች መካለል ገብታ ተደብቃ ነበር..እንደዛ ያደረገችው የሚያማምር ቀለም ያላቸው አበቧች ቀልቧን ስለሳቧት ነበር...አበባ ትወዳለች...ማንም ሳያያት ሹክክ ብላ ገብታ ከየአይነቱ አንዳአንድ አበባ በመቀንጠስ ወደ ክፍሏ ይዛ በመሄድ በዛ እየተጫወቱ መደሰት ተደጋጋሚ ተግባሯ ነበር...የጊቢያቸውን አትክልተኛ የነበሩት አዛውንት ግን በስራዋ አይደሰቱም.. ሁሌ እንደተነጫነጩና ለእናቷ ስሞታ እንዳሰሙ ነበር...እናቷም ልታስቀይማቸው ስለማትፈልግ ፊታቸው ይቆጧትና ዞር ሲሉ ደግሞ የፍላጎቷን እንድታደርግ ያበረታቶት  ነበር...ይህ  የአበባ ፍቅሯ ዛሬም ድረስ ህያው ነው...ከመጨረሻ ጠላቷም ቢሆን የአበባ ስጦታ ከመቀበል ወደኃላ አትልም።

አዎ የመጨረሻዋ ቀን አሁን ጥርት ብሎ እየታያት ነው።ግን ውስጧ ከነበረ ለምንድነው እስከዛሬ ትዝ ሳይላት የቆየው ...?በየትኛው የአእምሮዋ ጎዳ ውስጥ ደብቃው ብትቆይ ነው?በጣም ያስገረማት ጉዳይ ነበር..በእለቱ ልክ እንደወትሯዋ እዛ የጓሮ  አበባ ውስጥ ተወሽቃ አባተዋና አያቷ ከውጭ  እየተጨቃጨቁ  መጡና እሷ ያለችበት አካባቢ ሲደርሱ ...ቆሙ።

"ከልጄ እንድትርቅ እፈልጋለሁ…. ሁሉን ነገር ጥለህ ይሄን ሀገር እንድትለቅና ዳግመኛም ተመልሰህ እንዳትመጣ አስጠነቅቅሀለሁ"አያተዋ ናቸው በቁጣ አበቷ ላይ የሚጮሁበት፡፡

"ምን እያሉ ነው ...ልጅ አለቺኝ ኦኮ...እንዲህ እንዲያደርጉኝ አልፈቅድም››አባቷ ነው ተቃውሞውን የሚያሰማው፡፡

"እሱን ከመስረቅህ በፊት ማሰብ ነበረብህ..."

‹ስርቆት› ምትለው ቃል በደማቅ ቀለም ነበር በእምሮዋ ላይ የፃፈችው፡፡

""በቃ አንዴ ተሳስቼያለሁ...ሁለተኛ አልደግምም...ከልጄ መለየት አልፈልግም"

"የልጅ ልጄ  በሌባ እጅ እንድታድግ አልፈልግም...ከአንተ ጋር አንድ ጊቢ ውስጥ ሆና በአንድ ከተማ አብሬህ መኖር አልፈልግም..አንድ ቀን ሰጥቼሀለሁ...ካለበለዚያ በማደርገው ነገር ታዝናለህ .."ብለውት ከዘራቸውን እየወዘወዙ ወደ ትልቁ ቤት ሲገብ ትዝ ይላታል።

አባቷ እዛው እቆመበት አካባቢ ያለ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ልክ እሷ አሻንጉሊቶቾ ሲጠፍባት እንደምታደርገው እንባውን ሲያንጠባብ አይታለች...ከዛ ከተደበቀችበት ሹክክ ብላ ወጥታ ወደአባቷ ነበር ያመራችው...ተደብቃ የቀነጠሰችውን አበቦች ምንሞ ሳትሰስት እንዳለ ለአባቷ መስጠቷ ትዝ ይላታል። እሱም ጉያው ውስጥ ሸጉጦ በማቀፍ ጉንጮቾን  አንገቷን ትናንሽ እጆቾን እየቀያየረ እና እየደጋገመ ለሳዕታት ደክሞት እዛው ክንድ ላይ እስክተኛ ሲስማት እንደነበረ ትዝ ይላታል...ስለአባቷ  የተገለፀላት ትዝታ ይሄ ነው።ከእዛን ቀን በኃላ አላየችውም ...ከእንቅልፏ ስትነቃ እራሷን ያገኘችው መኝታ ቤቷ  ውስጥ በስርዓት ተኝታ  ነበር።ተነሳችና ‹ አባዬ› ብትል ለስራ ወጥቶል አሏት...በማግስቱ ብትጠይቅ ሩቅ መንገድ ሄዷል ተባለች...ጥያቄዋን ለወራት ብትደጋግምም ታገኝ የነበረው መልስ ግን በጣም አሰልቺ እና ተደጋጋሚ ነበር...ከዛ በህፃን አእምሮዋ አያቷ ላይ ቂም ያዘችበት...‹ሌባ ሌባ› የሚለው ከአያቷ አንደበት ወደ አባቷ የተሰነዘረው ቃል  በጨቅላ አእምሮዋ እየተመላለሰ  አስቸገራት ተሰቃየች? አዎ አሁን የዘመናት ችግሯ መነሻ ምክንያት ተገልፃላታል...በዛ የአባት ናፍቆት ያንገላታት በነበረበት ጨቅላ ዕድሜዋ እንደአባቷ መሆን በጣም መፈለጓ  ትዝ ይላታል፤ ...እንደ አባቷ ‹‹ሌባ..››ይሄንን ደግሞ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው አባቷን ለመጀመሪያ ጊዜ ሌባ እያለ ሲያወግዘው የሰማችውን አያቷ በመስረቅና ለአባቷ በመበቀል ነው።

"የነገሮች እንዲህ መገጣጠምና መቆላለፍ በጣም  አስገራሚ ነው የሆነባት።ለዚህ ቃል ትልቅ ምስጋና ይገባዋል ፡፡መዳን ከፈለገች ወደ ልጅነት ጊዜዋ ተመልሳ ትዝታዎቾን እንድትቆፍር ባያሳስባት ..ምን አልባትም እኚ ነገሮች በውስጧ እንደተዳፈኑ እዛው ከስመው ይቀሩ ነበር...ግን አሁንም ያልገባት አባቷ ምን ቢሰርቅ ነው አያቷ እንደዛ ሊያስፈራሩት  የቻሉት..?ደግሞስ እንደ እሷ ልክፍት  ይዟት ካልሆነ የገንዘብ   ችግር እንደማይኖርበት እርግጠኛ ነች?ታዲያ ለምን?የእዚህ መልስ እናቷ ጋር ነው ያለው...ግን አሁን እሷ ያልገባት እሺ ለችግሯ መነሻ የሆነ ሰበበ ምክንያቱን አወቀች፡ ግን እንዴት ነው  ፈውስ እንዲሆናት ሊያግዛት የሚችለው?አልገባትም።ቢሆንም ደስ ብሏታል። ነገ ተነገ ወዲያ ደግሞ የሚገለፁላት  ከፈውሷ ጋር የተገናኙ ተጨማሪ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። አዎ እናቷንና ቃልን  ማናገር እንዳለባት ወሰነች፡፡ ከዛ የሚሆነውን ለማየትድምዳሜ ላይ ደረሰች።
አይገርምም ግን የአንድ ቀን  ብጣቂ ገጠመኝ  የረጂሙ  የህይወታችንን  ጉዞ ላይ ጠንካራ ተፅእኖ ማሳረፍ ይችላል።አሁን ይሄን ታሪክ እንዲ አቆላልፍና አዋስቧ ሌላ ሰው ቢነግራት ስቃ ከማለፍ ውጭ እንደቁም ነገር ወስዳ ቦታ አትሰጠውም ነበር...አሁን ግን ዋጋ የከፈለችበት የራሷ ታሪክ ስለሆነ  ችላ ልትለው ፈፅሞ አትችልም። እናቷ ክፍል ገባች...ቁምሳጥናቸው አጠገብ ቁጭ ብለው በመስታወት እራሷቸውን እያዩ ፀጉሯቸውን እያበጠሩ ነበር፡፡በራፋን ከውስጥ ቆለፍችና ወንበር ይዛ ወደእሷቸው በመጠጋት  ከጎነናቸው ቁጭ አለች፡፡
"እማዬ አያቴና አባቴ በምን ጉዳይ ነበር የተጣሉት?"
እናቷ ጠያቄዋን እንደሰሙ ማበጠራቸውን አቁመው ፊታቸውን የሸፈነውን ፀጉሯቸውን ሰብስበው ወደኃላዋ ወረወሩና
‹‹  ምን አልሺኝ ?››አሏት በመኮሳተር
‹‹ ...አያቴ አባቴን ሌባ ነህ ብሎነው ከዚህ ቤት ያባረረው ...አባቴ ምን ሰርቆ ነው?››
"በሰማዕቱ ጊዬርጊስ ይሄን ጉድ ደግሞ ማነው የነገረሽ?
"ማንም አልነገረኝ እማዬ አስታውሼ ነው"
"አስታውሼ ማለት?"አይኖቾን አፍጥጣ፡፡
"አባዬ ከመጥፋቱ በፊት ከአያቴ ጋር ሲጨቃጨቁት ፊት ለፊት አበባ ውስጥ ተደብቄ ሰምቼያቸዋለሁ...አባቴ ከልጄ አይነጥሉኝ እያለ አባትሽን እያለቀሰ ሲለምን  ነበር..አያቴ ግን ከሌባ ጋር አንድ ቤትም አንድ ከተማም አብሬ አልኖርም..ሀገር ጥለህ ጥፋልኝ ሲለው በጆሮዬ ሰምቼለሁ?እና አባቴን ያባረራችሁት ብር ስለሠረቃችሁ ነው ወይስ ወርቅ?"
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
ብርጭቆውን አንስታ ተጎነጨችለትና መልሳ በማስቀመጥ መልስ ለመሰጠት  ተዘጋጀች….
ኬድሮን በምታየው ነገር  በጣም ደንዝዛለች …አላማዋንም ዘንግታ ….የሚበላትንም ነገር ችላ ብላ በምስጠት እየተከታተለችው ነው..በሌላ እይታ…. በሌላ መነጽር
ቀጠለች ልጅቷ‹‹የእኔ ፍቅር በጣም እኮ ነው የምትገርመኝ…. ዛሬም ተስፋ አትቆርጥም፡፡ በቃ እኔን እኮ ከዚህ በሽታዬ ለማዳን ለአመታት ለፋህ..ያለህን ንብረት ጨረስክ ..እስራኤል፤ህንድ፤አሜሪካም ጭምር ወስደህ በአለምአቀፍ ደራጃ አሉ በተባሉ የህክምና ተቋምና ምርጥ ጠቢቦች እድታከም አድርገሀል…በቃ አልተሳካም …እንደውም በአንተ ጥረት ነው የአንድ እና የሁለት አመት ቀሪ እድሜ ማግኘት የቻልኩት..ስለዚህ ይህቺን ባንተ ጥረት ያገኘኋትን ቀሪ ዕድሜዬን እንዳልከው በፍቅር እናጣጥምና ከዛ በሰላም ሸኘኝ …ባይሆን እዛ ጎጆ ቀይሼ መኖሪያ ቦታ  አመቻችታ እጠብቅሀላሁ..››አለችና ጉንጩን በመሳም ስሩ ውሽቅ አለችበት..እሱም አጥብቆ አቀፋትና በአንድ እጁን  ከአይኖቹ ሚንጠባጠበውን  እንባ ማበስ ጀመረ ..

ከዚህ በላይ መቆየትም ሆነ  በአላማዋ መግፋት አልቻለችም ….መኪናዋን አስነሳችና ወደቤቷ ነዳችው..ተቀጣጥሎ የነበረው የወሲብ ስሜቷ አሁን ከስሟል.‹‹.በዚህ አይነት ፍቅር ውስጥ እንዴት መግባት እችላለሁ?››..ይህቺንስ ሞት ፊት ለፊቷ የቆመባትን ሴት እንዴት መፎካከር ይቻላል… ?ከእሷ መንጠቅ ወይም መስረቅ በየትኛው ሞራል….?
እንደውም ከዚህ በላይ ታሪካቸውን ማወቅ ፈለገች..ልታግዛቸው ፡፡ከቻለች ለመሞከር….ግን ዛሬ አይደለም… ሌላ ቀን …በዚህን ሰዓት በዚህ የጨፈገገ ስሜቷ ውስጥ ሆና ምንም ማድረግ አልቻለችም..አሁን እቤቷ ገብታ ጥቅልል ብላ መተኛት ብቻ ነው የምትፈልገው…መኪናዋን እያከነፈች ነው… ንስሯ ክንፉን እያርገፈገፈ ጨለማውን በመሰንጠቅ ከፊቷ ይከንፋል..ሁኔታው የደስታ ነው….መጀመሪያም አካሄዷ ደስ አላሰኘውም ነበር….ሀሳቧን ቀይራ በቁዘማም ቢሆን ወደቤቷ መመለሷ እሱን እያስፈነጠዘው ነው…፡፡
""""

ምቾት የሌላው ምሽት ነበር ያሳለፈችው….ደግሞ ርዝመቱ እንደተለመደው 11 ሰዓት ከእንቅልፏ ተነሳችና እቤቷ ውሰጥ የተወሰነ የሰውነት እንቅስቃሴ ከሰራች  በኃላ ወደበረንዳዋ ወጣች…ንሰሯ አብሯት ነበር የወጣው…..ለተወሰነ ደቂቃ ሀሳቧን ከራሷ ጋር ነበር ያደረገችው.. ኤርፎኗን ጆሮዋ ላይ ሰክታ ከሞባይሏ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ከፍተችና  እያዳመጠች ንጽህ የጥዋት  አየር ወደ ሳንባዋ  እየማገች ነው፡፡

ግን በመረጋጋት ውስጥ ሆና በጽሞና ሙዚቃውን ብቻ ማዳመጡን  ቡዙም ልትዘልቀበት አልቻለችም..ሀሳቧ አሁንም ትናንት ላይ እንደተጣበቀ  ነው…የብልቷ መብላት ቢተዋትም አዕምሮዋ ግን አሁንም ድረስ እያሳከከት ነው….እሷ እኮ ወንድ ልጅን ለዚህን ያህል ጊዜ ርዝመት በልቧ አዝላ አታውቅም… ፎክራ ስላላሳካችው ዝታ  ስላልፈፀመች የመሸነፍ ቁጭት የፈጠረባት መብሰልሰል  ይሆናል……….?
አዎ ከንስር ጋር እየኖሩ ሽንፈትን አሜን ብሎ በመቀበል አንገትን መድፋት የማይታሰብ ነው…በምክንያቱም ለንስር መታገል.. ታግሎም ማሸነፍ ተፈጥሮ ያደለው የብቻ  ፀጋቸው ነው…ንስር የሞተ እንስሳ ንክች አያደርግም…የሚገድለውን ለማጥመድ ወይም ኢላማውን ለማግኘት መቶ ኪሎ ሜትር ሊያስስ ይችላል ..አስሶ አንዴ ራዳር ውስጥ ካስገባ ግን ንቅንቅ አይልም..ምንም ተአምር አያዘናጋውም…ግዳዩን ሳይጥል ውልፍች የለም…አዎ አድኖ አሳዶና ታግሎ በመጣል የገደለውን ብቻ ነው የሚበላው….፡፡እይታው ጠሊቅና እሩቅ ነው፡ካአለበት ቆሞ በአምስት ኪሎ ሜተር እርቀት ያለ ነገር ላይ ማነጣጠር ይችላል፡፡ልፋቱ የሌለበትን… አሸናፊነቱ የማይዘመርበትን ንክች አያደርግም… …ይህ የሰው ልጅም የህይወት መስመሩን ለማግኘት የተፈጠረበትን አለማ ለመገንዘብ የእድሜውን እሩብ ሊያባክን ይችላል…. ማባከኑም አግባብ ነው..መስመሩን ከያዘ በኃላ ግን አይኑም ቀልቡም መቶ ፐርሰንት መስመሩ ላይ መሆን አለበት፡፡ ትኩረቱም ጥረቱም ወደዛ ወደህይወት ግብ መዳረሻው የሚያደርሰው ሊሆን ይገባል…. የንስር ህይወት ይሄንን ነው የሚያስተምረው…
እሷም የሰለጠንችው  በንስራ ስለሆነ ኢላማ ያደረገችበትን  ነገር ከግብ ካላደረሰች ያማታል….አሁን እየተሰማት ያለው ስሜት ግን የተለየ ይመስላታል … ምክንያቱም  ከባሪያው ልጅ  ባልተናነሰ ቀዮ እጮኛውንም ከምናቧ ልታስወግዳት አልተቻለትም፡፡
‹‹አዎ መሞት የለባትም….በዚህ ዕድሜዋ መሞት አይገባትም››…ብላ በውስጧ ደመደመች…መልሳ ደግሞ እራሷን ሞገተች፡፡

‹‹ …በዚህ ዕድሜዋ መሞት የለባትም ስል ምን ማለቴ ነው..
…….?ሰው በስንት አመቱ ነው መሞት ያለበት……….?››ስትል አሰበች፡፡

ወጣት ሆኖ የሞተ ሰው ለምን በዛ ዕድሜዬ ሞትኩ ብሎ ይቆጫል ወይም ፈጣሪውን ይወቅሳል….? አይመስለኝም፡፡.ምን አልባት ይሄኛው አለም እና ከሞት ወዲያ ያለው ያኛው አለም ተብሎ ሚከፈል ዓለም ያለ ቢሆን እንኳን   ያኛው አለም  በእግዜር ሙሉ ቁጥጥር እና ፍቃድ የሚተዳደር ነው ሚሆነው..እንደዛ ከሆነ ደግሞ  ከዚህኛው  ዓለም ፍጽም የተሻለ ነው የሚሆነው..ያ ማለት ደግሞ ሞቶ ወደዛኛው አለም የተሸጋገረ ሰው በህፃንነቱም ሆነ በወጣትነቱ ቢሄድ ተገላገልኩ በምድር ከመሰቃየት፤ከመራብ፤ከመጠማት፤ከመጋዝና ከመታሰር እንኳንም በጊዜ ወደዚህ መጣሁ የሚል ይመስለኛል፡፡ሞት ማለት ሙሉ በሙሉ በስጋ መበስበስ እና በነፍስ መክሰም ወይም  ወደ ምንምነትም መቀየር ከሆነ  ደግሞ ለመፀፀት እና  ለምን ቶሎ ሞትኩ …….?ብሎ ለማሰብም የሚያስችል ዕድልም አይኖርም  ….ሞች በቋሚው አዕምሮ  ሲመዘን ነው በልጅነቱ ተቀጨ..በወጣትነቱ ተቀጠፈ የሚባለው….እና አሁንም እሷ የልጅቷ እሞታለሁ ማለት ለምን ይሄን ያህል እንዳሳሰባት አልገባትም .. …….?ነው ወይስ ለተመኘችው ልጅ ስትል ይሆናል..…….?
‹‹እሱ እንዲያዝንብኝ  ስላልፈለኩ ይሆን….?››ስትል እራሷን ትጠይቃለች ..ለጠየቀችው መልስ ከመፈለግ ይልቅ ግን  ሌላ ጥያቄ እየጨመረችበት ነው….
እሷ እንደሆነ በመግደልም ሆነ በማዳን አታምንም…እንደእሷ እምነት  ሰው የኖረበትን ጊዜ አጭርም ሆነ ረጅም ዋናው የኖረውን ያህል ተደስቶ መኖሩ ነው…..እርግጥ መግደል   የእግዜያብሄር  የአታድርግ ክልከላ ውስጥ ከሚካተቱ ትዕዛዞች መካከል አንዱ እንደሆነ ታውቃለች፡፡ቢሆንም ህይወት ከመግደልና ከመገደል ውጭ ህልውናዋ ፀንቶ እንደማይቆምም በተግባር አይታለች….ብዙ መግደል የቻለ ብዙ ይኖራል….ለመግደል የሰነፈ በጠንካራው ተገድሎ በሞቱ ለሌላው መኖር ምክንያት  ሆኖ ያልፋል፡፡ይሄንን ከህይወት ተምራለች፡፡

ግን እግዚያብሄር  አትግደል ሲል ለሰው ብቻ ነው እንዴ  የሚሰራው..…….?ሰውን መግደል ብቻ ነው በኃጥያት የሚያስጠይቀው….? ለምን ….?ሰው በእግዜያብሄር ሀምሳል  ስለተፈጠረ ልዩ መብት ስላለው….?፡፡ነው ወይስ ሰው የእግዜያብሄር ቤተ መቅደስ ነው የእግዜያብሄርን ቤተ መቅደስ ማፍረስ ደግሞ ያው ቀጥታ እሱን መዳፈር ነው…..ከእሱ ጋር መላተም ነው……ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ  ተብሎ ስለሚታሰብ…..?  …አትግደል የተባለው ነፍስ ያለውን ሁሉ ከሆነስ ……….?ያማ የማይቻል ከባድ ትዕዛዝ ይሆናል…፡፡ምክንያቱም እንስሳት ነፍስ አላቸው… ተክሎች ነፍስ አላቸው…ለመኖር ደግሞ ህይወት ያለው ነገር ሁሉ መመገብ  አለበት..ለመመገብ ደግሞ አንዱ ዝርያ ሌላውን እየበላ ነው ነፍሱን የሚያቆየው…ለመብላት ደግሞ የግድ መግደል
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ትንግርት ፖሊስ ጣቢያ ተወስዳ ከታሰረች ከአንድ ሰዓት በኃላ የዕለቱ ተረኛ መርማሪው ፖሊስ ዘንድ እንድትቀርብ ተደረገ፡፡

‹‹ሙሉ ስምሽን ብትነግሪኝ?››መርማሪው ብዕሩን መዝገቡ ላይ ቀስሮ ጠየቃት፤ነገረችው፡፡

‹‹በምን ምክንያት በቁጥጥር ስር እንደዋልሽ ታውቂያለሽ?››

‹‹አዎ አውቃለሁ፡፡››

‹‹እስቲ የተፈጠረውን በዝርዝር አስረጂኝ?››

ዝም አለች፡፡ትንግርት ዶ/ር ሶፊያ ጋር ባላሰበችው ቦታ ባልታሰበ አጋጣሚ ስትገናኝ እራሷን የመሳት ያህል ስሜቷ ጡዞ አቅሏን ስታ ነበር፡፡ በወቅቱ ምን እንደተከሰተ ምን እንዳደረገች በትክክል አታስታውስም፡፡.

‹‹ምንም የማስታውሰው ነገር የለም?››

‹‹የሰራሽውን ወንጀልማ ማስታወስ አለብሽ ፡፡››

‹‹ምንም ወንጀል አልሰራሁም አላልኩም፤እያንዳንዱን ድርጊት አስታውሼ ግን ልዘረዝርልህ አልችልም፡፡››

‹‹ግድ የለም የምታስታውሺውን ያህል ንገሪኝ፡፡ ዶ/ር ሶፊያ በምትባል ግለሰብ ላይ ከባድ ድብደባ አድርሰሺባታል ፡፡ግለሰቧ አሁን በህያወት እና በሞት መካከል ትገኛላች፡፡››

‹‹እኔም እሷ ከዓመታት በፊት ባደረሰችብኝ ጥቃት ለሦስት ጨለማ ዓመታት በህይወት እና በሞት መሀከል ተንጠልጥዬ ስቃትት ነበር፡፡ ስለዚህ ብትሞት እንኳን በእኔ ላይ የፈፀመችብኝን በደል በማካካስ ስርየት
አያስገኝላትም፡፡>>

‹‹እስቲ በደለችኝ የምትያቸውን ነገሮች ንገሪኝ?››

‹‹አልችልም::››

‹‹የምርመራ ስራዬን አስቸጋሪ እያደረግሺብኝ ነው፡፡››

‹‹ይገባኛል ...ግን አሁን ምንም ልነግርህ አልችልም ፤ጊዜ እፈልጋለሁ፡፡››

መርማሪው ፖሊስ ለተወሰነ ደቂቃዎች በዝምታ አሰላሰለና ‹‹እንግዲህ የተጠቂዋ ሁኔታ እስኪለይለት ማረፊያ ቤት ትቆያለሽ ፡፡ ዛሬ ቅዳሜ ነው ሰኞ ፍርድ ቤት እንድትቀርቢ እናደርጋለን፡፡ፍርድ ቤቱ ምን አልባት ዋስ ሊፈቅድልሽ ይችላል፡፡››በማለት ወደ ማረፊያ ቤቱ እንድትመለስ አደረገ፡፡

ኤልያስ የዶክተር ሶፊያን የህክምና ሁኔታ ሲከታተል ከቆየ በኃላ ትንግርትን ሊያያት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደ፡፡ፖሊሶቹን አስፈቅዶ ወደ እሷ ተጠጋ፤ከአጥሩ ወደዚያና ወደዚህ ሆነው መስኰት በመሰለች ክፍተት መነጋገር ጀመሩ፡፡

‹‹ሀይ ትንግርት ...እንዴት ነሽ?››

‹‹ሠላም ነኝ፡፡››

‹‹ፖሊሶቹ አናገሩሽ?››

‹‹አዎ ..…ማናገር አናግረውኛል፤አልተጋባባንም እንጂ፡፡››

‹‹አይዞሽ ..አንድ መቶ ሃለቃ ወዳጅ አለኝ፤ሁኔታውን ለእሱ አስረድቼዋለሁ፡፡ እንዲያናግራቸው አድርገን በዋስ ምትወጪበትን ሁኔታ እናመቻቻለን፡፡››

‹‹አይዞህ አትጨነቅ ምንም አልሆንም፡፡››

‹‹ቆይ ያልገባኝ... ምንድነው የተፈጠረው? ከልጅቷስ ጋር የት ነው ምትተዋወቁት?››

‹‹ኤልያስ ስለዚህ ጉዳይ አሁን ማውራት አልፈልግምም…አልችልምም፡፡››

‹‹ተይ እነጂ ትንግርት፤ችግር ውስጥ እኮ ገብተሻል፤ ሁኔታውን ካላወቅን እንዴት ልንረዳሽ እንችላለን?››

‹‹ምንም ዓይነት እርዳታ አልፈልግም፡፡ እሷ ሞታ እኔ እዚሁ እስር ቤት ለዘላለም ብበሰብስ እንኳን ደስተኛ ነኝ፡፡››አለችው እየተንዘረዘረች፡፡

‹‹ያን ያህል?››

‹‹ከዚያም በላይ፡፡አሁን ከዚህ በዋስ ብታስፈተኝ እንኳን ቀጥታ ወዳለችበት ሆስፒታል ሄጄ እስትንፋሷን እስከመጨረሻው ማቋረጥ ነው ምፈልገው፤አዎ እንደዛ ነው የማደርገው፡፡››

‹‹ኤልያስ ግራ ገባው ፡፡ትንግርትን በእንዲህ ዓይነት የቂመኝነትና የክፋት ባህሪ ውስጥ ወድቃ አጋጥሞት አያውቅም፡፡እሷን በአዛኝነቷ፤በትእግስተኝነቷ፤ ለሰው ባላት ሀሳቢነት : የሰውን ልጅ ቀርቶ እቤቷ የገባች አይጥ በወጥመድ ተይዛ ብታገኛት በሀዘኔታ ከወጥመዱ አላቃ ከነ ህይወቷ ወደ ጐሬዋ እንድትመለስ የምትፈቅድላት ሰው እንደሆነች ነው የሚያውቀው፡፡ታዲያ እንዴት እንዲህ ልትቀየር ቻለች? ፡፡የዚህን ዓይነት የገዘፈ አውሬነት እንዴት በውስጧ ተሸሽጐ ሊኖር ቻለ? ያቺ ልጅስ ምን ያህል ብትበድላት ነው ይሄን ያህል ልታስቆጣት የቻለችው?››

‹‹እሺ ፎዚያን ምን ልበላት ...በስልክ እያጨናነቀቺኝ ነው?..

‹‹እንዴ!!! ነገርካት እንዴ?››

‹‹አዎ ነግሬያታለሁ... ስታጨናንቀኝ ምን ላድርግ?››

‹‹ሰላም ነች በላት፡፡››

‹‹እሱማ ብያታለሁ..ግን ካልመጣሁ እያለቺኝ ነው፡፡››

‹‹በቃ ከመጣች ከእኔ መኝታ ቤት ካለው ኮመዲኖ ታችኛው መሳቢያ ውስጥ ሁለት ጥቁር ልባስ ያላቸው ዲያሪዎች አሉ..እነሱን ይዛልኝ ትምጣ፡፡››

‹‹እሺ ነግራታለሁ፡፡››አላት፡፡

ብዙ ማውራት ቢፈልጉም ተረኛ ፖሊስቹ ከዛ በላይ ሊፈቅዱላቸው ስላልቻሉ እሷ ወደ ማረፊያዋ እሱ ደግሞ አንዳንድ ነገሮችን ለመመካከር መቶ ሃለቃ ጓደኛው ወዳለበት ቦጋ አመራ፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ 5 ሰው #subscribe ካደረገ ቀጣዩ ክፍል ማታ 3 ሰአት ላይ ይለቀቃል

#Share and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


  ተገለበጣና   ፊቱን ወደእሷ አዞረ…‹ከደፈረኝ በኃላ እዚሁ ሲጥ አድርጎ በጨረሰኝ››ስትል ተመኘች…

እሱ ግን ማውራት ጀመረ‹‹ስሜ አይያዝልሽም አይደል…እረስተሸው ከሆነ ዛሬም መልሼ ላስታውሽ፣፣ ቀናው ይመር እባላለሁ፡፡ይገርምሻል ብዙውን ጊዜ ስምህን እረሳሁት ብለሽ ደጋግመሽ ስትጠይቂኝ በደስታ ነው የምነግርሽ..እና ሁሌ ባገኘሁሽ ቁጥር ስሜ ጠፍቶባት ብትጠይቀኝ እያልኩ አመኛለሁ…ያው ምን አልባት ካንቺ ጋ ማውራት የተለየ ስሜት ይፈጥርብኛል መሰለኝ…..ሰባ አሁን ያለሽበትን ሁኔታ በጣም እረዳዋለሁ፡፡ እንዴት አድርጌ እንደማግዝሽ ግን ስለማላውቅ ነው ዝም ብዬ ማይሽ...ምክንያቱም እኔም እንደአንቺ ቁስለኛ..እኔም እንደአንቺ በሽተኛ ነኝ፡፡እኔ የወሎ ልጅ ነኝ…ቤተሰቦቼ  ገጠር  ኑዋሪ  ገበሬዎች  ናቸው፡፡ሀይስኩል  ደሴ  ወ.ሮ ሰህን ነበር የተማርኩት፡፡ ከ9 ዓመት በፊት ነው ማትርክ  የወሰድኩት  ፡፡በወቅቱ እንደ ኢትዬጵያ ትልቁ ውጤት  የእኔ  ነበር….ወዲያው  እስኮላር  አገኘሁና ወደአሜሪካ ወጣሁ፡፡በቃ በዛን ጊዜ የነበረኝ ደስታ…በውስጤ  የተፈጠረው ፈንጠዝያ አለምን በእጄ የጨበጥኩ  ነበር  የመሰኝ..ከአንዲት  መንደር  ተነስቼ የልዕለ    ሀያሎ    አሜሪካ     ሜትሮፖሊቲያን     ዩኒቨርሲቲ     ኦፍ     ዴንቨር ተማሪ ስሆን…ይህቺን ደሀ  ሀገር  ተመልሼ  እንደምመራና  ልዕለኃያል  ኃያል ላደርጋት ባልችል እንኳን ኃያል  እንደማደርጋት  እየፎከርኩ  ወጣሁ…እዚህ  ላይ አንድ አዛውንት የተናገሩትን ልጥቀስልሽ.. ወጣት ሳለሁ እኔ አስብና

እግዚያብሄርን በፀሎት ጠይቅ የነበረው ..እግዚያብሄር ሆይ አለምን ጠቅላላ የምቀይርበትና    ምስቅልቅሏን    የማስተካክልበት    ኃይል     ስጠኝ     "ብዬ ነበር።ትንሽ በሰል ስል ደግሞ "ጌታ ሆይ አለምን መቀየር በጣም ከባድና ለእኔ አቅም የሚሰፋ ዕቅድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።እስከአሁን አንድ ነጠላ ሰው እንኳን ሳልቀይር   ዕድሜዬ   እየነጎደ   ነው።ቤተሰቤ  ለእኔ በቂ ነው።ቤተሰቤን የምቀይርበት ኃይልና ጥበብ ስጠኝ"ብዬ ወደመፀለይ ተሸጋገርኩ አሁን ሳረጅ ደግሞ እቤተሰቦቼ ራሱ በጣም እንደሚበዙ ተረዳው"..እራሴን መቀየርና ማስተካከል ከቻልኩ በቂ ነው...አሁን ወደትክክለኛው መስመር ተመልሼያለሁ ..ስለዚህ ይሄንን እንዳደርግ የሚያግዘኝ ኃይልና ጥበብ ስጠኝ "ብዬ የመጨረሻ ፀሎቴን ፀለይኩ።አምላክም መለሰልኝ"አሁን የቀረህ ምንም አይነት እንጥፍጣፊ ጊዜ የለህም።ይሄንን መጠየቅ የነበረብህ ከአመታት በፊት በጉልምስና ወራትህ ላይ ነበር..አሁን  ግን  ረፍዶብሀል"አለኝ።እና  ልጄ  የእኔ  እጣ እንዳያጋጥምህ ዛሬውኑ ንቃ...ፀሎትህን አስተካክል...ምኞትህን አርቅ...ብለው የመጨረሻ ምክራቸውን ለገሱ…
ሽማግሌው እንዳሉት አለም ምስቅልቅል ያለች የሚመስለን ምስቅልቅሎን የሚያስተካክል ሰው ስለጠፋ ሳይሆን እራሱን ለማስተካከል የሚጥር ሰው ጥቂት ስለሆነ እንደሆነ ለመረዳት እኔም ረጅም ጊዜ ወስዶብኛል፡፡ለማንኛውም ወደ ታሪኩ ልመለስልሽ፡፡
እዛ እንደደረስኩ ሁሉ  ነገር  አሪፍ  ነበር…ልጅ  ስለነበርኩ  ሁሉን  ነገር  በፍጥነት ነበር  አዳብት  የደረኩት…ትምህርቴን  እንደጨረስኩ.  ወደ  ሚኒሶታ  ሙቭ አደረኩና ፍላይንግ ክላውድ አየር ማረፊያ አካባቢ ዋና ቢሮውን ያደረገ ኬ.ቢ ኢንተርናሽናል ኮስሞቲክ ካምፓኒ ውስጥ ስራ ያዝኩ፡፡ ወዲያው ከአንዲት አሜሪካዊት    የካምፓኒ    ሰራተኛ  ጋር ወዲያው ፍቅር ያዘኝ…ትዝ ይለኛል…የተያየነው ሰኞ ቀን ነው…ማክሰኞ ፍቅር እንደያዘኝ ገባኝና ከስራ

መውጫችን ላይ ከስሯ ኩስ ኩስ እያልኩ  ተከትዬ  አዋራኋት…በሁለተኛው  ቀን እራት አብረን በላን…ይሄንን ያዩ አብረውኝ ሚሰሩ ወንዶች  በአድነቆት  ፈዘው ሲያዩኝ ግራ ገባኝ…‹‹ምንድነው ቆንጆ ስለሆነች እሺ አትለውም  ብለው  እስበው ነበር ማለት ነው?››ስል ማሰላሰል ጀመርኩና በጥረቴ ገፋሁበት..ከሁለት ሳምንት በኃላ እፍ ያለ ፍቅር ውስጥ ያሉ ፍቅረኛሞች ሆን…ከአንድ ወር በኃላ የሚገርም ዜና ሰማሁ..ለካ በድፍረት የጠበስኩት የስራ ባለደረባዬን ብቻ ሳይሆን የተቀጠርኩበት ካምፓኒ ብቸኛ ልጅ እና የወደፊት ወራሽ የሆነችውን ልጅ ነው…ወንዶቹ ሁሉ በድፍረቴ ለምን እንደተደመሙ ቆይቶ  ነው  የገባኝ..እኔም ቀድሜ ባውቅ ያንን አይነት ድፍረት አይኖረኝም ነበር፡፡
ሳባ ከትንፋሹ ጋ ተደባልቆ የሚወጣው ሙቅ አየር ጉንጮቾ ላይ ሲያርፍ እየተሰማት በፀጥታና በተመስጦ እያዳመጠችው ነው፡፡
ካትሪና  በጣም  ቆንጆ፤ንፅህ  ደፋር  ቀጥተኛን  ፤ልታይ  ልታይ  ማትል፤የተለየ  ስብዕና ያላት ልጅ ነበረች..እኔ ግን ይሄንን ሁሉ አይቼና መዝኜ ሳይሆን ዝም ብዬ ድንገት ሳያት ድንገጥ ስላልኩባት ነው ያፈቀርኳት፡፡ የመጀመሪያ   እይታ   ስንተያይ ከአይኖቾ የተረጩ ብርሀን ልቤን ሰንጥቆት ስለነበረነው፡፡ከስድስት ወር በኃላ ተጋባን፡፡በሁለት አመት ውስጥ የተደራጀ ቤትና ኑሮ ኖረን..ሁሉነገር እስደሳችና የገነት ኑሮ መሰለ…ከትሪን ሌላ ካትሪንን አረገዘች፣፣በቃ በደስታ አቅሌን ልስት ደረስኩ፡፡ ወደኢትዬጵያ ተመልሶ ለዚህ ህዝብ መሲ የመሆን   እቅዴ   እየደበዘዘ ሙሉ በሙሉ በአሜሪካ ኑሮ እየተሰባኩ በአሜሪካኖች   ስነልቦና   እየተዋጥኩ ሄድኩ፡፡
ከኢትዬጵያ ጋር የሚያገናኙን ወላጆቼ ነበሩ፡፡ ለእነሱ በሶስት ወርም ሆነ በስድስት ወር ለእኔ ትንሽ  የሚባል  ለእነሱ  ግን  ህይወታቸውን  ሊቀይር  የሚችል  አይነት ብር እልክላቸዋለሁ…በቃ

ከዛ ሱዛና ተወለደች…የእኔ ሱዛና ትንሽዬ መልአክ ነበር የምትመስለው፤እጆቾ ድንብሽብሽ ያሉ አይኖቾ የተቁለጨለጩ…አቤት ሁሉ ነገር እንዴት ፐርፌክት እንደነበረ….ሱዛና ተወልዳ ስድስት ወር ሳይሞላት የካትሪና እናት ሞተችና ወደ 5 መቶ ሚሊዬን ዶላር ሀብት ያለውን ያን ካማፓኒ  ወረሰች  በዛን  ጊዜ  ካትሪን ስራዋን ሙሉ በሙሉ ለቃ የቤት እመቤት ሆና ነበር ፡፡እዛው እቤት ሆና የእድሜ ልክ ታለንቶ የሆነው ሙዚቃ ላይ ትሰራ ስለነበረ ወደስራ ተመልሶ ካምፓኒውን የማስተዳደሩ ፍላጎት ምንም አልነበራም..በዛ ምክንያት እኔ የካማፓኒው ዋና ሰው ሆንኩ…ከዛ  ካትሬን  ሌላ  ልጅ  አረገዘችልኝ…ታዲያ  የዛ  ሁሉ  የተትረፈረፈ የቤተሰብ ደስታ፤ የዛ ሁሉ  የተትረፈረፈ ሀብት ባለቤት የሆንኩት ያ ሸራ ጫማ መግዣ ይቸግረው የነበረው?ያ በሶ እየበጠበጠ በመጠጣት ረሀቡን በማስታገስ የተማረው ቀናው ነኝ...ብዬ በመደመም ሰው ከለፋና ከጣረ.. የት ድረስ መድርስ እንደሚችል እና እድልም ለእሱ አጎብድዳ እንደምታገለግለው ላገኘሁት  ሰው ሁሉ ልክ እንደሞቲቬሽናል  እስፒከር  በመጎረር  ስተርክ  የምውል  በራስ  መተማመኔ ጣራ የነካ ሰው ሆንኩ…..፡፡

ታዲያ ምን ሆነ ዳቢሎስ ቁጣውን በምድር ላይ አዘነበ….እግዚያብሄርም ተባባሪው ነበር…ወይንም መጀመሪያውኑ ዋናው እቅድ  የራሱ  የእግዚያብሄር  ይሆናል፡፡ ጃንዋሪ 2020 አካባቢ ከካምፓኒው ጋር ለተያያዘ ስራ ቻይና ለአንድ ወር ቆይቼ ነበር…በወቅቱ ቻይና አዲስ ቨይረስ መከሰቱን እየተወራ ነበር.ወደአሜሪካ በተመለስኩ በቀናት ውስጥ ቨይረሱ  በቻይና  ምድር  እየተስፋፋ  መሆኑን መንግስት ግን የደበቀ መሆኑን ሀኪሞች መረጃውን እያሾለኩ ማውጣት ጀመሩ የቻይና መንግስትም አመነ፣ብዙ ሰዎች እየሞቱበት እነደሆነ ተናገረ..ከዛ ሌሎች ሀገሮችም ተዛመተ አሜሪካ ገባ ተብሎ ሶስት ቀን ሳይሞላው ካትሪን ያተኩሳት ጀመር፤ወዲያው ትንፋሽ አጠራት …ጉሮሮዋ ቆሰለ..… ዶክተራችን መጥቶ አያትና
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

ኩማንደር ሆስፒታል በረንዳ ላይ ከወዲህ ወዲያ ሲንገዋለል አንዴ እናቷን እቴቴን ሲያፅናና..ቆይቶ ደግሞ ያለመደበትን ፀሎት ለመፀለይ ሲሞክር…ሰለሰሎሜ መጥፎም ሆነ ጥሩ ዜና ሳይሰማ ነጋ፡፡አንድ ሰዓት ነበር ከዶክተሩ አሰቃቂውን መርዶ የሰማው…፡፡‹‹ሰሎሜ የደም ካንሰር በሽተኛ ነች፡፡ለጊዜው ኬሞትራፒ እንዲደረግላት የተወሰነ ሲሆን በቅርብ የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ ማድረግ ስለሚያስፈልጋት ዘመዶቾ በአፋጣኝ መጠራት አለባቸው››…ተባለ፡፡
ህመሟ ከፍተኛ ደረጃ ስለደረሰ በቅርብ ቀናቶች ውስጥ  ቀዶ ጥገናው ካልተደረገ ህይወቷን ልናጣት እንችላለን የሚል ዜና ነገረው፡፡
‹‹ዶክተር እስኪ የመቅኔ ንቅለ ተከላ  ማለት ምን ማለት ነው? እስኪ ትንሽ አስረዳኝ?››ሲል ከፍራቻ ቆፈን ራሱን ሳያላቅቅ ጠየቀው፡፡
‹‹መቅኔ ማለት የደም ህዋሳትን ለማምረት የሚጠቅም በአጥንቶች መሃከል የሚገኝ ዘለግላጋ የሰውነት ክፍል ሲሆን ነጭ የደም ሴሎችን፤ቀይ የደም ሴሎችን እንዲሁም ለደም መርጋት የሚያገለግሉትን የፕላትሌት ንጥረ ነገሮች ለማምረት ይረዳል፡፡እነዚህ ንጥረ ነገሮች አንዴ ከተመረቱ በኋላ ከሰውነት ውጪ ለረጅም ጊዜ የማይቆዩ ሲሆን ይህንንም ለማገዝ እና ሰውነታችን ጤነኛ እድገት እንዲኖረው በመቅኔ አማካኝነት ቶሎ ቶሎ ይመረታሉ ፡፡ከሰውነት በሽታን የመከላከል ስርዓት መታወክ ጋር የተያያዙ ችግሮች የሚመጡት መቅኔ ከሚያመርተው ግድፈት ያለባቸው የደም ህዋሳት ወይም ያልበለጸጉ የደም ህዋሳት ወይም ደግሞ አነስተኛ የደም ህዋሳት መመረት የተነሳ ነው:: ይህም የአዳዲስ የደም ህዋሳት ከቁጥጥር ውጪ ተመርተው በደም ስር ውስጥ እንዲከማቹ በማድረግ ሌሎች ህዋሳትንም ያውካሉ ፡፡ ይህንን ጤነኛ ያልሆነ ሁኔታ ለማከም ልክ አሁን ለሰሎሜ እያደረግን እንዳለነው የኬሞቴራፒ እንዲሁም የጨረር ህክምና ይደረጋል ፡፡በዚህ ህክምና ወቅት ግን ሌሎች በመቅኔ ውስጥ የሚገኙ ጤነኛ የሆኑ የሰውነት ህዋሶችም ሊጎዱ ይችላሉ፡፡የመቅኔ ንቅለ ህክምና ግን  ግድፈት ያለባቸው የደም ህዋሳት እና መቅኔ እንዲወገዱ በማድረግና በጤነኛ መቅኔ በመተካት ሀኪሙ የመፈወስ አቅሙ ጠንከር ያለ የኬሞቴራፒ እና የጨረር ህክምናን መጠቀም እንዲችል ያስችለዋል፡፡ ምንም እንኳን የመቅኔ ንቅለ ተከላ ህክምና በሽታው ተመልሶ ላለመምጣቱ ማረጋገጫ ባይሆንም ታካሚው የመዳን እድሉን ከፍ በማድረግ እንዲሁም ከህመም ነጻ ሆኖ የሚቆይበትን ጊዜ ከፍ ያደርገዋል ፡፡ይህ ህክምና ከሌላ ሰው (ለጋሽ ) ወይም  ደግሞ ከራሱ ከታማሚው ሊከናወን ይችላል፡፡አለማየሁ የዶክተሩን ማብራሪያ በፅሞና ሲያዳምጥ ከቆየ በኃላ‹‹መቅኔውን ማንኛውም ሰው መለገስ ይችላል?››ሲል ሌላ ጥያቄ ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ ማንኛውም ሰው መለገስ ይችላል…ግን ደግሞ ቀላል አይደለም ….የሚወሰደው መቅኔ ውጤታማ እንዲሆን ከታካሚዋ ጋር ቢያንስ ከ50 ፐርሰንት በላይ የሚመሳሰል መሆን አለበት፡፡ይሄንን ማግኘት ብዙውን ጊዜ አስቸጋሪ ነው፡፡ለዛም ነው ወላጆች ወይ እህትና ወንድም የተሻለ የመለገስ እድል አላቸው የሚባለው፡፡እንደዛም ሆኖ ግን አንዳንድ ጊዜ ከአራትና አምስት ወንድሞች አንደኛውም ለመለገስ ብቁ ላይሆን ይችላል፡፡››
የዶክተሩ ገለፃ አለማየሁን የበለጠ ስጋት ውስጥ ጣለው፡፡‹‹አንዴ!! እቴቴ  መለገስ ካልቻለች ምንድነው የሚውጥን?››ሲል እራሱን ጠየቀና ሰውነቱ በስጋት ሽምቅቅ አለ፡፡
‹‹ዶክተር..ምንአልባት የሚለግሳት ሰው ከጠፋ ከራሷ መውሰድ ይቻላል ብለሀል፡፡››
‹‹አዎ ብያለው ..አጠቃላይ ሁኔታው እንደዛ ነው፡፡ያ ግን አሁን ሰሎሜ ባለችበት ሁኔታ ለመተግበር ቀላል አይመስለኝም ..እርግጥ ተጨማሪ ዲቴል ምርመራዎች ማድረግ ይገባናል…ቢሆንም ግን ምን አልባትም የማይቻል ሊሆን ይችላል፡፡ስለዚህ አሁን ተሯሩጣችሁ ለጋሽ መፈለጉ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባችኋል››ሲል ምክር ሰጠው፡፡አለማየሁ ቀስ ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳና ዶክተሩን ተሰናብቶ ወጣ፡፡ቀጥታ ወደሰሎሜ እናት ነው የሄደው፡፡አንገቱን ደፍቶ እየተቅለሰለሰ ዜናውን ነገራት..እንደእብድ እየጮኸች የሆስፒታል ግቢ አመሰችው፡፡
ከሁሴን ጋር በመሆን እንደምንም አረጋጓትና ምረመራውን እንድታደርግ ተደረገ፡፡ቢሆንም ግን ካለባት የጤና ችግር አንፃር ከእሷ መውሰድ እንደማይችሉ ተነገራት..ሌላ ዘመድ አባት ወንድም ወይም እህት ይፈለግ ተባለ፡፡፡፡
አለማየሁ ሆነ ሁሴን ይሄንን ዜና ሲሰሙ ሁሉ ነገር ነው ጭልም ያለባቸው…‹‹ሰሎሜ ወንድምም ሆነ እህት እንደሌላት ያውቃሉ..አባቷንም ቢሆን ለዘመናት መኖር አለመኖሩ የማይታወቅ አባት በሰዓታት ውስጥ ከየት ተፈልጎ ሊገኝ ይችላል?፡፡
አለማየሁ ሁሴንን ከሰሎሜ ጎን እንዲሆን አዘዘውና ምርጫ ስለሌለው ጉዳዩን ለእቴቴ ነግሯት እሷን ይዞ ወደካፌ ወሰደና   ከጎኗ ተቀመጠ፡፡
‹‹ልጄ እንዴት ነች…ንቅለ ተከላው መቼ ነው የሚደረግላት?››ስትል በስጋት ጠየቀችው፡
‹‹እቴቴ እንጃ ..አንቺ ካለብሽ በሽታ የተነሳ ለእሷ መለገስ አትችይም ብለዋል…››
በድንጋጤ አይኖቾን አፍጥጣ ‹‹እንዴት ታዲያ ምን ይሻላል?››
‹‹እኔም ግራ ገብቷኛል››ስል ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ መለሰ፡፡
‹‹የሆነ መፍትሄማ መኖር  አለበት?››
‹‹ወላጆች ወይም ወንድምና እህቶች ካሏት በአስቸኳይ አምጡ ነው ያሉን፡፡››ከዶክተሩ የተነገረውን ነገር ቀጥታ ተናገረ፡፡
እቴቴ በድንገት ንቁ ሆና‹‹ወንድምና እህት ነው ያልከው?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ እቴቴ ወንድምና እህት››ደገመላት፡፡
‹‹ሂድና ወንድሟ ነኝ በላቸውና ..ይመርምሩህ››አለችው፡፡
‹‹እንዴ እቴቴ…ምን ማለትሽ ነው?፡፡››
‹‹ታምነኛለህ አይደል?››
‹‹በደንብ ነው ማምንሽን  እቴቴ…በደንብ አምንሻለሁ››
‹‹እንግዲያው አሁኑኑ ተነሳና ወንድሟ ነኝ በላቸው፡፡››
መከራከርም እሺ ለማለትም ግራ ተጋባ..ትኩር ብሎ ሲያየት ኩስትርትር እንዳለች ነው…‹‹ሴትዮዋ ከድንጋጤ የተነሳ እያበደች ይሆን እንዴ? ››ሲል እራሱን ጠየቀና ቀስ ብሎ ተነሳና እሷን እዛው ካፌ ትቶ ወደ ዶክተሩ ቢሮ እግሩን እየጎተተ ሄደ ..፡፡ያለችውን ከማድረግ ውጭ ምንም ሌላ የመጣለት መፍትሄ የለም…እንዳለችው ወንድሟ ነኝ ብሎ ነገራችው…ወዲያው አፈጥነው ሙሉ ምርመራ አደረጉለት…ውጤቷቹ ሁሉ ተሰብስበው ስኪመጡ ከስምንት ሰዓት በላይ ፈጅቷ ነበር…እሱ ጊዜ ማባከን አድርጎ ነው የወሰደው…እቴቴ ፊት ላይ ግን ትልቅ ተስፋ ይነበብ ነበር..ውጤት ደርሶ ወደ ዶክተሩ ቢሮ ተጠሩ…የተነገራቸው ዜና እናትዬውን በእልልታ ያሰከረ ኩማንደሩን እንዴት በሚለው ጥያቄ ያደነዘዘ ነበር፡፡እርግጥ አንዳንዴ ዘመድ ያልሆነ ሰውም ተመሳሳይ አይነት መቅኔ ሊኖረው እንደሚችል ዶክተሩ በደንብ አስረድቶታል፡፡፡ያ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚሳካ  አይደለም፡፡አልተዋጠለትም፡፡
‹‹በሉ ነገ ጥዋት ተዘጋጅ…..ኦፕራሲዬኑን ጥዋት እናካሂዳለን››ተባለ..እቴቴ አለማየሁን እጁን እየጎተተች ወጣችና ‹‹የሆነ ቦታ ደርሰን እንምጣ ››አለችው፡፡
‹‹የት እቴቴ?››
‹‹ምን ቸገረህ …ተከተለኝ››አለችው ቆፈጠን ብላ፡፡
‹‹ሰሎሜን ትተን?››
‹‹ምንም .. እነሁሴን አሉ አይደል…እነሱ ያዮታል..ደግሞም አንቆይም››