አትሮኖስ
283K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
502 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ በዛሬው ዕለት ከመሰል የሥራ ባልደረቦቹ ጋር ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ሕክምና አጋጥሞት ነበር የዋለው፡፡ የቀዶ ጥገናው የተደረገላት ሴት በማኅፀን ዕጢ
በሽታ የምትሰቃይ ነበረች፡፡የሆድ ዕቃዋ ተከፍቶ ተከፈፍቶ የተገመተውና፤ በተግባር የታየው የሰማይና ምድር ያህል
ልዩነት ነቀረው።

በማህፀኗ ላይ ለአራት ሰአት የተደረገው የቀዶ ሕክምና ከሁለት ኪሎ ግራም በላይ ዕጢ እንዲወጣላት አስቻለ፡፡ ዶክተር ሰውነቱ በሥራ ደክሞ ስለዛለ በቂ ዕረፍት ለመውሰድ በጊዜ ወደ ቤቱ ገብቶ አልጋው ላይ ጋደም ለማለት ፈልጓል፡፡
ከድካሙ ቀለል እንዲለው ፤ በቀዝቃዛ ውሃ ገላውን ሙልጭ አድርጉ ከታጠበ በኋላ፤ የጥጥ ፒጃማውን እንደለበሰ ነበረ የተኛው፡፡በዚሁ መሀል ትህትና ገርበብ ያለውን የመኝታ ክፍሉን በር ከፍታ ገባች::
በዛሬው ዕለት ያለወትሮዋ የተርከፈከፈችው ሽቶ ቀድሟት ገባና
ክፍሉን በመዓዛው አወደው:: የዱር ጽጌረዳ፣ ጣፋጭ መዓዛ፤ እሷም
የጽጌረዳ አበባ መስላለች። ወትሮ ከሚያውቃት ትህትና በእጥፍ አምራ
ተውባለች፡፡ ኮቴዋን ሳታሰማ ወደሱ ትመጣለች፡፡
ቁልቁል ትመለከተዋለች፡፡ ገርበብ ባሉት ዐይኖቹ ሰረቅ አድርጎ አያት፡፡ በልቡ ውበቷን አደነቀ። ቀጭን ሳቋ ጆሮውን ሰረሰረው፡፡ ዐይኖቹን ገለጥ አድርጉ በሚያየው ነገር ተደንቆ፤ ሽቅብ ተመለከታት፡፡ እሷም በፈገግታ ተሞልታ እየተፍለቀለች ጐንበስ ብላ ጉንጬን ሳመችው፡፡
ከበላዩ ቆሞ፤ ውብ ፈገግታን የሚለግስ፤ በኋላም በአካል የሚዳስስ፤ መልአክ መስላ ታየችው፡፡
የዛሬው አመጣጧ ድንገተኛ ሆኖበታል። የተቀጣጠሩት ለዛሬ አልነበረም፡፡ እንዴት ቀድማ መጣች? ገረመው። ከቀጠሮ በፊት መምጣቷ ምናልባትም በፍቅሩ ወጥመድ እየወደቀችለት ለመሆኗ ፍንጭ ስለሰጠው የደስታ ስሜት የሠራ አካላቱን አዳረሰው፡፡
“የደብረዘይቱ የሽርሽር ውጤት እየታየ ነው” አለ በልቡ፡፡ የሚገርመው ደግሞ አንጀቱን ለመብላት ያላደረገችው ጥረት የለም፡፡ የለበሰችው ስስ ተካፋች ጃኬት እኒያ ገና ከሩቅ ሲያያቸው ውሃ
የሚሆንላቸው! ጡቶቿን፤ አጋልጦ ያሳያል። በዚህ ላይ እኒያን ውብ ባትና ጭኖቿን፣ በግልጽ የሚያሳይ አጭር ቀሚስ ነው የለበሰችው፡፡

“በቃ በፍቅር ወድቃልኛለች ማለት ነው”
በስሜት እንደሰከረ ፍዝዝ ባሉት ዐይኖቹ ይመለከታት ጀመር። ጭውው አለበት፡፡ ሽውው የሚል ነፋስ ሲነፍስ፣ የፍቅር አማልክት በያሬዳዊ የሙዚቃ ቅኝት
ስለፍቅር ሲያዜሙ ፧ ተሰማው፡፡ ድብት የሚያደርግ የድካም ስሜት..ድቅቅ
ያለ ሰውነት በደስታ የሰከረ ቀልብና ልብ፡፡
አሁንም ከት ብላ ሳቀች። አሳሳቋ እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋባ፡፡ ሁኔታዋ ሁሉ ግርም ብሉት፤ አፉን ከፍቶ ይመለከታት ጀመር፡፡ ዐይን አፋራ፣ ቅልስልሷ ፤ ትህትና መሆኗን ተጠራጠረ፡፡ ፍቅር ያንን ሁሉ
የእፍረት ማቅ አሽቀንጥራ እንድትጥል አድርጓታል ማለት ነው? ፍቅር እውር ነው ወይስ እውር ያደርጋል? በትክክል እውር እንደሚያደርግ ከሷ እንደዚህ የውቦች ቁንጮ ሆናለት፤ ከቀጠሮአቸው በፊት ሹልክ ብላ ስትመጣለት ምን ይባላል? ማመን አልቻለም፡፡
ዐይኖቹን አሸት አሸት አድርጉ ሁለት እጆቹን ወደላይ ዘረጋና
“ትሁትዬ” አላት በደከመ ድምጽ።
ቀስ በቀስ ያ ሰውነቱ እየጋለ መሄድ ጀምሮ ነበር፡፡ በተለይ የዘረጋላት እጆቹን ወደዚያ ውርውር አድርጋ..
“ከቀጠሮ በፊት ስለመጣሁ መዘነጥህ ነው?” ብላ ከተሰቀለው መስታወት
ውስጥ ፊቷን ለማየት ዘወር ስትል፤ አጭሩ ቀሚስ እላይ ድረስ ዘልቆ እኒያ የሚያማምሩ ጭንና ባቶቿን ወለል አድርጉ ሲያሳየው አልቻለም፡፡ቀስ በቀስ እንደ ካውያ እየጋለ በመሄድ ላይ የነበረው ሰውነቱ የሚያደርገውን ያሳጣው ጀመር፡፡
በተለይ የምትሽኮረመም ሴት ይወዳል። እንዲያ ግፍትር አድርጋው ስትሽኮረመም፧ እልህ ያዘው። በዚህ ላይ ባቶቿ ኑ ብሉኝ! ኑ ብሉኝ! እያሉ ይጋብዛሉ። በዚያ ባዶ ቤት ውስጥ፤ በዚያ ሰፊ የሞዝቦልድ አልጋ ላይ እየተንከባበሉ፤ ያንን ባለፈው ጊዜ ተልፈስፍሶ ያመለጠውን ሲሳይ ዳግም እንዳያመልጠው ሊሞክር ቸኩሎ ተነሳና...
“ከቀጠሮ በፊት መምጣትሽ ምን ያህል ልቤን እንዳስደሰተው ከፍተሽ ባየሽው የኔ ቆንጆ?” በጀርባዋ በኩል ሄዶ፤ በሁለት እጆቹ እቅፍ አድርጓት፤ አንገቱን በአንገቷ ውስጥ ቀበረና! ጡቶቿን ያሻሻቸው
ጀመር..
ቀስ በቀስ እየሞቀች ስትሄድ ግለቷ ተሰማው። ከዚያም አፏ እንደተከፈተ ዘወር ስትልለት፤ በተከፈተው አፉ ቀለባት፡፡ ከዚያም እጆቹ ወገቧ ላይ ሲጠመጠሙ፤ እጆቿ ደግሞ በአንገቱ ዙሪያ እንደ ድር
ተጠንጥነው፤ ሰስሜት ተዋህደው ነጐዱ.....
እኒያ ውብ አይኖቿ ስልምልም ብለው ጠፉ፡፡ ከዚያም ቀስ ብለው እየተደነቃቀፉ፤ እየተደጋገፉ፤ ወደ አልጋው ሄዱና ወደቁ፡፡ ዛሬ ትህትና እንደዚያን ዕለቱ ዐይኖቿ በእንባ አልተሞሉም፡፡ ይልቁንም በደስታ እየተፍለቀለቀች፤ በፍቅር፤ ለፍቅር፤ ስትል ሁለመናዋን በግልጽ እየሰጠችው ነው፡፡
ዶክተር በዛሬው ዕለት ብር አምባር ለመስበር በእርግጠኝነት መንፈስ ተሞልቷል፡፡ በደብረ ዘይቱን የሽርሽር ወቅት በተለይም በሆራ ራስ መኝታ ክፍል ውስጥ ሲልፈሰፈስ ያመለጠው
እንዳያመልጠው በመስጋት፤ ኃይሉን የአንበሳ፤ አድርጎ ትግሉን ቀጠለ፡፡
የታጠቀችው የውስጥ ሱሪ ከዚህ በፊት የሚያውቀው ነጩ ባለወንፊቱ ነበር፡፡ በስሜት ደርተው ሲታገሉ፣ በፍቅር ስሜት ተውጣ የሆነ ነገር እያቃሰተች በጆሮው ሹክ አለችው፡፡ “አስገ...ው...ባ..ው..ው."

በዚህ ጊዜ ዶክተር በሲቃ ስሜት ተውጦ ካሰበበት ለመድረስ ጥድፊያውን ቀጠለ፡፡
እሷ ለሚሆነው ነገር ሙሉ ለሙሉ እራሷን ዝግጁ አድርጋ ሲመለከት፤ ደስታው እጥፍ ድርብ ሆነ፡፡ ዶክተር ላብ በላብ ሆኗል።ትህትናም በላብ ተነክራለች። ከረጅም ጊዜ ትግል በኋላ ...
“ዋ!!.......ይ!! !” ብላ ጮኸችና የዶክተር ባይከዳኝን ሰውነት በጥፍሮቿ ግጥም አድርጋ ይዛ አለቀሰች፡፡ ዶክተር ስለተቧጠጠ ገላው ደንታም ሳይሰጠው በድል አድራጊነት እርካታ ተውጦ ግዳዩን ለማየት ተጣደፈ፡፡
በእርግጥም ድል አድርጓል፡፡ በዚያው ስሜቱ እስከሚረካ ድረስ ቆየ። ከዚያም ተዘርራ ተመለከታት፡፡ ይህ ውስጥ ለውስጥ ያደርገው የነበረው ስሜታዊ ትግል፤ ቀስ በቀስ በውስጡ ሲሯሯጥ ከቆየ በኋላ፤ አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ፤ ወደ ገሀዳዊው ዓለም ተለወጠ፡፡
በዚህ ለውጥ ሰዓት ከእግር ጥፍሩ፤ እስከራስ ጠጉሩ ድረስ የነዘረው ንዝረት አባነነውና፤ በላብ እንደተዘፈቀ ከገባበት የቅዠት ዓለም ወጣ! እግዜኦ! ዶክተር በዚያን ሰዓት የተሰማውን የስሜት ስብራት በቃላት ማስቀመጥ ይከብዳል።
ያ ሁሉ ዓለም፣ ያ ሁሉ ደስታ፤ እንዲህ እንደዋዛ እንደጉም በንኖ ጠፋና፤ የሱን ስሜት እንዳይሽር አድርጎ አቁስሎት በፀፀት ጉድቶት አለፈ፡፡ ያ ሁሉ የድል አድራጊነት ስሜት በቅጽበት ቦታውን ለሽንፈት ለቀቀና፤ በዶክተር ባይከዳኝ ልብ ውስጥ ሀዘን ጥቁር ደመናውን አጥልቶበት ሄደ...
“ቡል ሺት! ” አለና ትራሱን በቡጢ ጠልዞ የሆነውን ነገር እንደ አዲስ አስተዋለ፡፡ በቅዝቃዜው ስሜት ተጠራጥሮ ሲዳብስ፤ ፒጃማውን ረጥቦ አገኘው፡፡ ከዚህ በኋላ ሁኔታዎችን ቀስ ብሎ ይመረምር ጀመር።
በቀላሉ የሚልፈሰፈሰው አካሉ አሳድሮበት የነበረው ሥነ ልቡናዊ ተጽዕኖ
ለጥቂት ጊዜ እራሱ በፈጠረው ትንሽ የቅዠት ደሴት ውስጥ ጠፍቶ፤ነበር
ጊዜያዊ የተስፋ ጮራ በልቡ ውስጥ እንደፈነጥቅበት፤ እሱም ጓደኞቹ
ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ እንደሚችል፤ አረጋግጦለት ነበር።.....

ድንግልናን መግሰስ በማይችል አካላዊ ብቃቱ ለዘመናት አዝኖ እንዳልኖረ ሁሉ፤ በዚህች ቅጽበት፤
2👍2🔥1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

ቀናት ገሠገሡ። ሳምንታት አለፉ። አሮጌው ሄደ፡፡ አዲሱ መጣ፡፡ የጊዜ
ዑደት ሕግ ሥርዓቱን ጠብቆ በአንድ አቅጣጫ ወደፊት ያመራል።
ህይወት ግን በዝብርቅርቅና በውጣ ውረድ ቀለበት ውስጥ እየተዟዟረች
ትህትና ድንበሩና ሻምበል ብሩክ በላይ በከንፈር ማህተም ያፀደቁትን ቃል
ኪዳን ጠብቀዋው ስለወደፊቱ የትዳር ህይወታቸው በሰፊው መወያየቱን
ከጊዜ ጋር ትራመዳለች::
ቀጥለዋል።
ሻምበል ብሩክ በቤተሰቡ ልብ ውስጥ ዘልቆ ከገባና ዝምድናውን ካጠናከረ በኋላ ያ ቤት ድሮ የትህትና አባት መቶ አለቃ ድንበሩ እያለ የነበረውን የህይወት ሙቀት ቀስ በቀስ መላበስ ጀምሯል፡፡
ይህ አባት አከል የወደፊት የትዳር ጓደኛዋ፤ ወድቆባት የነበረውን የህይወት ሸክም አቀለለላት፤ “አለሁልሽ” እያላት ነው፡፡ ለእናቷ የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍሎ ሆስፒታል ተመልሳ እንድትገባ ያደረገ
ዕለት...
“ ለምን ሌላ ሆስፒታል አናስተኛትም ብሩኬ?” ስትለው፡፡
“የመጀመሪያው ሆስፒታል ምን አለን ትሁት?” አላት፡፡
“እሱማ ምንም አላለን፤ አማራጭ እስካለን ድረስ ለምን ሆስፒታል አንቀይርም ለማለት ፈልጌ ነው እንጂ” አለችው መልሳ።
“እንደኔ፤ እንደኔ፤ መጀመሪያ ሲከታተላቸው የቆየው ዶክተር
ቢያክማቸው ውጤቱ ያማረ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡ አዲስ ዶክተር ማለት አዲስ ህክምናን ሀ ብሎ እንደመጀመር ነው የሚሆነው፡፡ ይሁን ካልሽም እሺ” አላት ዐይን ዐይኖቿን በፍቅር እያየ።
ከዶክተር ባይከዳኝ ሙሉ ለሙሉ ለመራቅ እንጂ፤ በህክምናው በኩል ተደናቂ ሀኪም መሆኑን ዘንግታው አልነበረም፡፡ ሻምበል ብሩክም ልክ አዜብ እንዳለቻት ሁሉ ህክምናውን የመጀመሪያው ሀኪም
እንዲቀጥል ሀሳብ ሲያቀርብላት ጥያቄዋን አነሳች፡፡
በዚህ ሰዓት ሆስፒታል በመቀየር ከምታገኘው ጥቅም ይልቅ የእናቷን ጤንነት ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲከታተል በቆየው ዶክተር ህክምናውን መቀጠሉ የሚያስገኘው ጥቅም አመዝኖ ታያትና...
“እንግዲያውስ ይሁን” በማለት ተስማማች። ዕድሜ ለሱ። ዛሬ የሰላምና የንፁህ አየር እየተነፈሰች የወደፊት የትዳር ህይወቷን ትልም በመንደፍ ላይ ነች ፤ እናቷ ተገቢውን ህክምና እንድታገኝ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው። በሻምበል ብሩክ ከፍተኛ ምክርና ጥረት አንዱአለም
ችላ ብሎት የነበረው ትምህርቱን በሚገባ መከታተል ጀምሯል።
ይህ ውጣ ውረድ የበዛበት ህይወቷን ለማስተካከል እንድትችል ማካካሻ ያገኘችበት መልካም እድል
ሊሆንላት፤ የዶክተር ባይከዳኝና
የእንደሻው ጥላ ደግሞ በሄደችበት እየተከተላት፤ ሀሳቧን ጠቅለል አድርጋ
እንዳትተኛ እንቅፋት ከመሆን አልቀረላትም፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ በፍቅሯ እንደተቃጠለ ነው። እንዲያውም እስከመጨረሻው የሱ ሆና እድትቀር የነበረው ምኞቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ልዩ ልዩ ስጦታዎች ያበረክትላት ጀምሯል። የዶክተር ባይከዳኝ ጥርስ የሌለው አንበሳነት፤ በህይወቷ ላይ ችግር የማያስከትል በመሆኑ እናቷ ሙሉ ለሙሉ ከበሽታዋ ድና እስከምትወጣ የተለመደውን ከልብ ያልመነጨ ፍቅር እያቀመሰችው ለመቆየት ወስናለች።
ይህንን የወሰነችው ደግሞ ብቻዋን አልነበረም፡፡ ከአዜብ ጋር በደንብ አድርገው ከተወያዩበትና ከተማመኑ በኋላ ነው።
“አዜቢና ለምን ቁርጡን አልነግረውም?” በማለት ስሜቷን ለጓደኛዋ ስትገልጽላት።
“ምን ብለሽ ትሁት?” ስትል ጠየቀቻት።
“በቃ እጮኛ እንዳለኝና እንዲተወኝ ብጠይቀውስ?”
“ሞኝ ሆንሽ እንዴ ትሁት? እንደሱ ብለሽ ብትነግሪው የሚያምንሽ ይመስልሻል? ጠልተሽው የደረብሽበት ነው የሚመስለው፡፡
በዚህ ላይ ይሄ ሁሉ የስጦታ ግርግር ፍቅር መሆኑን አትርሺ!!
ምን ቸገረሽ ለትንሽ ጊዜ ብትታገሺ? ፍቅር የያዘው ሰው ፍቅሩን ለሌላ አሳልፎ መስጠት ስለማይፈልግ ሌላ አፈቀርኩ ብለሽ ብትነግሪው ጥሩ አይመጣም፡፡ ያፈቀረ ብዙ ነገር ከማድረግም ወደኋላ አይልም፡፡ አቅሙን እንደሆነ የምታውቂው ነው፡፡ ጉዳት እስካላስከተለብሽ ድረስ ማሚ ድነው እስከሚወጡ እየሸወድሽው ብትቆዪ ምናለበት? በዚህ ላይ ታዋቂ ሀኪም ነው” ስትል አማከረቻት።
እሱን በአሁኑ ሰዓት ማጣት ጉዳት እንጂ ጥቅም ስለሌለው ከሻምበል ብሩክ ጋር ጋብቻቸውን እስከሚፈጽሙ ድረስ ግንኙነታቸው እንደነበረ እንዲቀጥል ተስማሙ።
በተቻላት መጠን ግን ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማርገብ ጥረት እንድታደርግ፤ ቀስ በቀስ የግንኙነት ገመዱን ለማላላት እየቀጠሩ መጥፋት፤ ሲገናኙ መለማመጥና ምክንያት እየሰጡ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ላለመገናኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ በዚህ
ውስጥ እንዲጠቃለሉ በስፋት ተማከሩበት። በዚሁ መሠረት ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ለረጅም ጊዜ ሳይገናኙ
ቀሩ። ለረጅም ጊዜ ያለመገናኘታቸው ደግሞ እንደግምታቸው ተስፋ የመቁረጥና የመረሳሳትን አዝማሚያ ከማሳየት ይልቅ ' ዶክተር በናፍቆት
ተጠብሶና፤ በፍቅር ተቃጥሎ፤ እንዲጠብቃት አደረገው፡፡ሻምበል ብሩክ አስፈላጊውን ክፍያ ሁሉ ፈጽሞ እናቷን
ሆስፒታል ባስገባችበት ዕለት ተገናኙ። እናቷ በገንዘብ እጥረት ምክንያት
ከሆስፒታል እንድትወጣ ሲደረግ! ስለገንዘብ ከሆነ አለሁልሽ ብሏት
ነበር፡፡ በክፍያ ችግር ምክንያት መሆኑን ልትገልጽለትና በሽንፈት እጇን
ስላልፈለገች... “ለገንዘቡ አይደለም ዶክተር፤ እናቴ ከሆስፒታል ወጥታ በቤት ውስጥ ለመታከም ስለፈለገች ነው
” በማለት ነበር መልስ የሰጠችው::
አሁን እናቷን ሆስፒታል መልሳ ማስተኛቷን ሲያውቅ ቶሎ ቶሎ ለመገናኘት እድል ይፈጥርለታልና በጣም ተደሰተ፡፡ እሷ ግን ይህንን አልወደደችውም።ሻምበል ብሩክ ግንኙነታቸውን እንዳይደርስበት ሰጋች።
ሆኖም እሱን ከማንኛውም ጥርጣሬ ነፃ የምታደርግበት የራሷ ማረጋገጫ
አላትና፧ ተጽናናች። ሁሌም ለእሷ ንፁህ የመሆን ማህተሙ አብሯት እስካለ ድረስ ዶክተር ባይከዳኝ የእናቷ ሀኪም ከመሆኑ ባሻገር ሌላ ጉዳይ ይኖራቸዋል ብሎ እንደማይገምት ተማምና፤ ከዶክተር ጋር ያላትን ቀዝቃዛ ግንኙነት ቀጠለች።
ይህ ሁኔታ በዚሁ ቀጥሎ ሳለ፤ አንድ ቀን ሻምበል ብሩክ በፖሊስ መምሪያ የተካሄደውን ስብሰባ ተካፍሎ፤ ምሳውን ከበላ በኋላ፤ ወደ ቢሮው ለመመለስ የያዛትን የመንግስት መኪና በሚያሽከረክርበት ወቅት አዲስ ነገር ተፈጠረ።
ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል።
ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ነው። የትራፊክ መብራት ይዞትእንደቆመ፤ በስተቀኝ በኩል ከፊት ለፊቱ ቀደም ብላ የቆመችውን ነጭ
ኦፔል መኪና እንደዋዛ በዐይኖቹ ገረፍ አደረጋት።
በዚያች መኪና ውስጥ እንደዋዛ ያየው ነገር የትኩረት ስሜቱን ሳበውና፤ መኪናውን ቀስ ብሎ ትንሽ ወደፊት በማንቀሳቀስ ተጠጋ፡፡ፍጹም ሊሆን የማይችል ነገር ነው። አእምሮው ሊጠረጥረው የማይችለውን
ነገር በማየቱ፤ አይኖቹን ተጠራጠረ። የሚያየውን እውነታ ህሊናው በቀላሉ ሊቀበልለት ስላልቻለ፤ ቀይ መብራት በርቶ
መኪኖች ሲለቀቀቁ እንኳ አልታወቀውም ነበር። የሚያየው ነገር እውነት መሆኑን፤ አይኖቹ የሚያሳዩት የሌለ ነገር ሳይሆን፤ ያለውን ሀቅ መሆኑን፤ ሲረዳ ግን፤ ጭንቅላቱ በከባድ ነገር እንደተመታ ሁሉ፤ ክው ብሎ ደርቆ ቀረ።
በሚያየው ነገር ምክንያት ሰውነቱን ማተኮስ ስለጀመረው! የመኪናውን የበር መስታወት ወደታች ዝቅ አድርጎ ንፋስ አስገባ፡፡ በዚያች መኪና ውስጥ ያለቸው ትህትና ድንበሩ መሆኗን
ሲያረጋግጥ፤
መኪናውን የሚያሽከረክረውን ሰው ማንነት ለመለየት ፈለገና አተኩሮ
ተመለከተው፡፡ ያውቀዋል። ዶክተር ባይከዳኝ ነው።ጉድ ፈላ! ስራውን ትቶ የዚህን ተአምር ማብቂያ ሊከታተል
ወሰነ። መብራቱ አረንጓዴ በርቶ ሲለቀቁ ነጫን ኦፔል መኪና ተከትሎ ያሽከረክር ጀመር ክትትሉ እንዳይታወቅበት
🔥2👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

#አውጉስታ

ቅዱስ ገብርኤል የሚከበርበት የዓመቱ በአል ደረሰ፡፡ ይህንን በዓል የእንደሻው ወላጆች የሚያከብሩት ሐረርጌ ቁልቢ ገብርኤል በመሄድ ነው። ለዓመቱ ገብርኤል የተሳሉትን ስለት ይዘው፣ ትንሹ ልጃቸው ሲሳይን አስከትለው፤ ለመሄድ የባቡር ትኬት ቀደም ብሎ ተቆርጧል።
ገብርኤል የሚከበርበት ቀን እንደ ነገ ሆኖ፤ ትህትና ሥራዋን በምታከናውንበት ወቅት ደግሞ አንድ ደስ የሚል ዜና ሰማች፡፡ ትናንትና ሻምበል ብሩክን በስልክ ስታነጋግረው የድሮው ሻምበል ብሩክ ሳይሆን ትንሽ የመቀዝቀዝና፤ የመለወጥ ስሜት ስላየችበት ብስጭትጭት ብላ
ነበር የዋለችው። ይህንን ብስጭቷን ሲያካክስላት ነው መሰል የደስደስ
ያለው ወሬ ከአበራ ሰማች፡፡
የምስራች!” አላት አበራ እየፈነደቀ።
“ምስር ብላ” አለችው የምሥራቹ ናፍቋት፡፡
“ጋሼን ምን እንዳስነካሻቸው አላውቅም፡፡ለማንም ያላደረጉትን ነው ላንቺ እያደረጉ ያሉት፡፡የገቡልሽን ቃላቸውን ጠብቀዋል፡፡ ከነገ ጀምሮ ደመወዝሽ አንድ መቶ ብር ሆኖ በገንዘብ ያዥነት እንድትሰሪ ተወስኗል”
በደስታ ብዛት ሄዳ አበራን እቅፍ አደረገችው። እሱም እቅፍ አደረጋት።

“ዛሬ እቤት ይዘሀት ትምጣና አዲስ ውል ትፈርም ብለውኝ ነበር። ዛሬ ሥራ ስለሚበዛ ለነገ ይሻላል ብያቸዋለሁ” አላት ድምጹን ዝቅ አድርጎ፡፡
ትህትና በእርግጥም በሥራዋ ቀልጣፋና ደከመኝን የማታውቅ ልጅ መሆኗን ማንም ይመሰክርላታል።
“ለማንም እንዳትናገሪ ታዲያ! በተለይ ይህቺ አሮጊት ከሰማች ታብዳለች” :: ይህቺ አሮጊት የሚለው ወ/ሮ አረጋሽን ነው። በእርግጥም ወይዘሮ አረጋሽ በዚህ የጫማ መሸጫ አዳራሽ ውስጥ ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ሰርታ ደመወዟ አሁንም ዘጠና ብር ብቻ ነበር፡፡
“ጋሼ አበራ ሙት ለማንም አልናገርም” ቃል ገባችለት፡፡ በዚሁ መሠረት ተደስታ ውላ፤ ተደስታ አደረች፡፡ ትንሽ ቅር ያላት ሻምበል ብሩክ በስልክ ስታነጋግረው ከወትሮው የቀዘቀዘበት ምክንያት ግራ
ስላጋባት ነበር።ምክንያቱን ለማወቅ
ሄዳ እስከምታገኘውና የሳምንቱ
"መጨረሻ እስከሚደርስ ድረስ ከመቸኮሏ በስተቀር ሁሉም ነገር ሰላም ነው፡፡ እናቷ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው። አንዱዓለም ጠንካራ ተማሪ ሆኗል። ይኸውና እሷ ደግሞ ዛሬ ዕድገት የማግኘቷን ዜና ሰማች፡፡ ይህንን የዕድገት ውሏን ለመፈረም አቶ በቀለ ከመኖሪያ
ቤታቸው ድረስ እንድትመጣ በሥራ አስኪያጁ በአበራ በኩል የላኩባትን
መልዕክት ተቀብላ ለመሄድ ተዘጋጀች፡፡
በማግሥቱ ሥራ እንደገቡ አበራ ወደ
ወ/ሮ አረጋሽ ጠጋ ብሎ ከትህትና ጋር አንድ ግዜ ወደ ፋብሪካ ደርሰን እንመጣለን” አለና ምክንያቱን አሳውቆ ትህትናን ጠራትና መኪና ውስጥ አስገባት፡፡ ሞቅ ባለ ፍጥነት ከአውጉስታ ፋብሪካ በስተጀርባ ወደሚገኘው ወደ አቶ በቀላ መኖርያ ቤት በረሩ።
ከዚያ ደርሰው የመኪና ጥሩንባ ሲያሰሙ፤ አንዲት ጠቆር ያለች ልጅ እግር የቤት ሠራተኛ የአጥሩን ብረት በር ወለል አድርጋ ከፈተችው፡፡
ቤቱ በዚያ ሰፊ ቦታ ላይ በግርማ ሞገስ ጉብ ብሎ ሲታይ ይማርካል። በልዩ ልዩ አበቦችና ዛፎች አጊጧል። ከትልቁ ቪላ ፊት ለፊት በሰፊው ተንጣሎ የሚታየው የወይን ዛፍ ቀዝቃዛ ጥላን አጐናጽፎት
ምድረ ገነት አስመስሎታል።
በግቢው ውስጥ የማይታይ የአበባ ዓይነት የለም፡፡ ትህትና በአጠቃላይ የቤቱ ውበት ተማርካለች፡፡ ከዚያም ተያይዘው ከመኪናው ወረዱ።
የወጣ ሰው የለም፡፡ አበራ “ቆይ ጠብቂኝ” አለና በጓሮ በኩል ዞረ።እሷ በፊት ለፊቱ በር ቆማ እየጠበቀችው ነበር፡፡
የቤት ሠራተኛዋ አንድ ጊዜ ብቅ ብላ ትህትናን ሰረቅ አድርጋ አየቻትና ተመልሳ ገባች።
“ነይ ትህትና በዚህ በኩል”፡፡ በፊት ለፊቱ ሳይሆን በጓሮው በር አስገባት፡፡
እዚያ ፈቅ ብሎ በተሠራ የውሻ ቤት ውስጥ የታሰረው ትንሽ የፈረንጅ ውሻ ቡፍ ቡፍ አለ። ትህትና ውሻውን ስታየው ግንባሩ ፍጥጥ ብሎ ወደ ውጭ የወጣ ከመሆኑም በላይ ፤ የሆነ የምታውቀው ሰው መልክ አስታወሳትና፤ ትንሽ ሳቅ ብላ አበራን ተከተለችው::

ቁጭ በይ ወንበር ጋበዛት፡፡ ሄዳ ወንበሩ ላይ ተቀመጠች።
“እስከዚያው ምን ይምጣልሽ?” ፊቱ ጥርስ በጥርስ እንደሆነ።
“ጋሽአበራ ምንም አያስፈልግኝም” እሷም በፈገግታ እንደተዋጠች፡፡
ዕድገትን ለመሰለ ፀጋ መጥቶ ባይበላ፤ ባይጠጣስ? ልቧ ያለው በውሉ ሁኔታ ላይ ነበር። በዚህ ላይ የቤቱ ውበት አስደንቋት ዙሪያ ገባውን እየቃኘች ነበር፡፡
“እንደሱ አይባልም፡፡ ምንም ቢሆን እኮ ለቤቱ እንግዳ ነሽ፡፡
እንዳይለምድብሽ፡፡ ለስላሳ ይምጣልሽ?”
“ይሁን እሺ ጋሽ አበራ፡፡”
ትህትና እዛ ክፍል ውስጥ ሆና በዚያች የምታምር ክፍል ውስጥ የተሰቀለውንም፤ የተንጠለጠለውንም፤ በዐይኖቿ እየቃኘች አቶ በቀላ ብቅ ብለው ውሉን እስከሚያስፈርሟት ድረስ በናፍቆት ስትጠባበቅ፤ በግራ በኩል ውስጥ ለውስጥ የተሠራው ባለመስታወት በር ንቅናቄ አሳየ።
እስከዚያን ጊዜ ድረስ አንዳችም ጥርጣሬ ያልተሰማት ልጅ ልቧ እንደመዝለል አለባትና ዐይኖቿ በበሩ ላይ ተተክለው እንደቀሩ፤ ፒጃማ የለበሰ ወጣት ብቅ!!..... አለ፡፡
ያንን ሰው ስትመለከት፤ እጅግ ከመደንገጧ የተነሳ አፏ ተከፍቶ ቀረ። ከዚያም ነፍሷን ስትገዛ “ዋይ!” ብላ እሪታዋን ልታቀልጠው ስትል፡-
“ፀጥ በይ!! ያለበለዚያ!!” አለና ደብቆ የያዘውን እህል ውሃ የማያሰኝ ጩቤ መዘዘው። ዐይኖቿ ተጎልጉለው ወጡ
በድንጋጤ ደምስሮቿ በግንባሯ ላይ ተገታተሩ፡፡ ትንፋሽ ሳታወጣ ፀጥ አለች፡፡
ከዚያም ሁኔታዎች በእንደሻው ፍላጐት መስመር ያለችግር ይቀላጠፉ ጀመር።
ጠጋ አላትና በግራ በኩል በቃሪያ ጥፊ ቢያላጋት ዐይኖቿ በእጥፉ ተጎልጉለው ከመውጣታቸውና ፊቷ ሳምባ ከመምሰሉ በስተቀር ቃል አልተነፈሰችም።የሚያርዳት ነው የመሰላት፡፡
“የምትታዘዥውን የማታደርጊ ከሆነ ይሄ!” አለና በጡቶቿ ሥር ጩቤውን አሳርፎ “ወደ ውስጥ እንዲዘልቅልሽ ይደረጋል!” አላት በጭካኔ ስሜት።
“ተነሽ!!” አለና አንቧረቀባት።
ሹክክ ብላ ተነሳች። ከኋላ በኩል ዞሮ ያንን ዞማ ፀጉሯን ጨመደደና፤ የገባበትን በር በእርግጫ በረገደው፡፡ ከዚያም ወደ ውስጥ ሲገፈትራት፤ ተንገዳግዳ የገባችበት ክፍል ጨለማ ዋጣት...
እዚያ ጨለማ ውስጥ ሆና የገባችበትን ሲኦል ለማየት ዐይኖቿን ስትገልጥ፧ ሄዶ ማብሪያና ማጥፊያውን ቢጫነው፤ እዚያ ክፍል ውስጥ ከዳር እስከዳር የተንጣለለ ሞዝቮልድ አልጋ ተነጥፎ አየች። ይህንን
የምታተኩርበት ስሜትም፤ ጊዜም፤ አልነበራትም፡፡ ማንስ ጊዜ ሰጥቷት?
እንደዚያ ሲለምናት፤ ሲያስለምናት ከርሞ፤ እንቢ ስለአለችው፤ በቀየሰው ዘዴ የገባችለትን ወጣት ሊሰቀላት ቆርጦ ተነስቷል።
“አውልቂ!! አለና ጮኸባት፡፡
ጩቤውን እንደያዘው ነው፡፡ እየተንፈቀፈቀች ዝም ብላ ቆማ
ዐይን ፤ ዐይኑን፤ ታየው ጀመር፡፡ እንባዋን አይቶ የሚያዝንላት መሰላት፡፡
እንባዋ እንደጎርፍ ፈሰሰ፡፡ አቤት በዚያን ሰዓት የተሰማት ስሜት!? ሻምበል ብሩክ መጣባት፡፡
“እውነት ልታደርጊው ትሁትዬ?” የሚላት መሰላት፡፡
“ተይ! ተይ! ትሁት!” በአካል የቀረባት መሰላት። ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
“አውልቂ!” አለና እንደገና አንቧረቀባት። በዚህ ጊዜ በእልህና ተውጣ፤ : እንደቆሰለ
አውሬ እየጓጎረች፤ ልታንቀው በሲቃ
ተንደረደረችበት፡፡
እንደሻው አመጣጧን አይቶ ካፈገፈገ በኋላ እዚያ ከመንጋጋዋ በታች የሆነ ደም ስሯ ላይ ክፉኛ ቢመታት፤ ሄዳ በአፍ ጢሟ ተደፋች፡፡
ከዚያም ያንን ሲቋምጥለት የነበረው ገላዋን እርቃኑን ለማየት ተጣድፎ
ልብሶቿን በፍጥነት አወላለቃቸው፡፡ እራሷን ስታ ነበር፡፡ ሙሉ በሙሉ
ልብሷን ካወለቀ በኋላ ወስዶ አልጋው ላይ ዘረራት.... ከዚያም ያንን
👍3
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....መንፈሷ ላይድን ቆስሎ፧ ሃሣቧ እዚህም እዚያም እየባከነ፤በተኛችበት ሆና በእንባ እየታጠበች ሁለት ቀን በጓደኛዋ ቤት ካሳለፈች በኋላ፤ ተነሣች፡፡
አካሏ ጠንካራ ቢመስልም፤ መንፈሷ ግን ደካማና የተረበሽ ነበር።በዚህች በሁለት ቀን ውስጥ ከዚህ ዓለም የተገለለች ዓይነት ሰሜት ይስማታል፡፡
የእናቷ፡ የወንድሟና፤ የሻምበል ብሩክ ሁኔታ ከፊቷ ድቅን ይልባታል፡፡
እናቷን ለሁለት ቀን ሳታያት በመቅረቷ ሁለት ዓመት የተለያቻት ያህል በናፍቆት ተቃጥላለች፡፡
“እንዴት ሆና ይሆን?” እያለች ሌሊቱን ስትጨነቅ ነው ያደረችው፡፡እናቷን በህልሟ አይታታለች፡፡ በዚያው ጐን ለጐን የሻምበል ብሩክ ጉዳይ አለ፡፡ ዛሬ እሁድ ስለሆነ ሻምበል ብሩክ እየጠበቃት ነው፡፡ ስለዚህ እሱን ማግኘት አለባት፡፡ ካላየችው ጤነኛ የምትሆን አልመሰላትም፡፡ልቧ ከውስጥ ደም ቢያለቅስም፤ ጥርሶቿ ግን እውነተኛ ስሜቷን በመደበቃቸው፤አዜብ ተጽናናች፡፡
“በቃ እንሂድ”አለቻት ለአዜብ ልብሷን ለባብሳ እንደጨረሰች፡፡
እሺ ትሁት፡፡ መጣሁ ጠብቂኝ” አለችና ሄዳ የታክሲ ገንዘብ ይዛ መጣች፡፡ ከቤት ሲወጡ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ ዕለቱ እሁድ ነው :: ተያይዘው በታክሲ ወደ የካቲት አስራ ሁለት ሆስፒታል በረሩ...
በዚህ ቀን ሻምበል ብሩክ ከአሁን አሁን ትመጣለች በማለት በጉጉት እየተጠባበቃት ነበር፡፡ ትዕግስት መራራ ነች ፍሬዋ ግን ጣፋጭ ነው የሚለውን ብሂል በሃሣቡ እያውጠነጠነ ፣ትዕግስት አልባ በመሆን ስህተት እንዳይፈጽም ከራሱ ጋር እየተሟገተ ይገኛል፡፡
ከዚህ በፊት ከትዕግስት ውጭ በመሆን ከሱ የማይጠበቅ ድርጊት በመፈጸሙ ተፀፅቶ፤ ለራሱ የገባውን ቃል ዘነጋና፤ ባለፈው ስልክ የደወለችለት ዕለት፤ በድጋሚ ስህተት ፈጸመ፡፡በዚያን ሰዓት ትህትና በሁኔታው ተደናግጣ...
ምን ሆነሃል ብሩኬ?“ ነበር ያለችው፡፡ በአነጋገሩ የድሮው ሻምበል ብሩክ መሆኑ ፍጹም አጠራጥሯት፡፡
ሻምበል ብሩክ እንደበረዶ ቀዝቅዞ ነበር ያነጋገራት :: ይህንን ስህተት መፈጸሙን ያወቀው ግን ስልኩን ከዘጋ በኋላ ነው፡፡
ስልኩን አንስቶ ሲያነጋግራትና፤ሲሰናበታት በነበረው ሁኔታ ተደናግጣ ተደናግጣ “ምን ሆነብኝ?“ በማለት ተጨንቃ፤ ምን እንዳጋጠመው ለማወቅ ፤ እሁድ
አልደርስልሽ አላት፡፡ ሻምበል ብሩክም ስልኩን ከዘጋ በኋላ ምን ያደርግ እንደነበር ሲረዳ ተደናገጠና፤ የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፋው፡፡
“ ምን ዐይነት እራሴን መቆጣጠር የማልችል ደደብ ነኝ?” ሲል በራሱ አማረረ
"እሺ አሁን ምን ይሻላል?“ በሚል ጭንቀት ተውጦ ለፈፀመው ስህተት ምክንያት ሲፈልግ አንድ ሃሣብ መጣለት፡፡
ሻምበል ስሜቱ በሁለት ተቃራኒዎች መካከል መዋዠቅ ጀምሯል፡፡ወደር የሌለው ፍቅር በአንድ በኩል፤ የጥላቻ ስሜት በሌላ በኩልእንደከበሮ ወጥረው ይሞግቱታል፡፡
በቃላት ሊገልጸው በማይችለው ሁኔታ ያፈቅራታል፡፡ የዚያን ዕለቱ ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር እጅ ለእጅ ተቆላልፋ ወደ ቤቱ ይዟት ሲገባ የነበረው ሁኔታዋ
ከፊቱ ላይ ድቅን ሲልበት ደግሞ፤ ከአንጀቱ ይጠላታል፡፡
ለማንኛውም ይህ ፍቅሩ ጥላቻውን የሚያጠፋበት፣አሊያም ጥላቻው
ፍቅሩን ከውስጡ ጠራርጉ የሚያስወግድበት፤ እውነተኛው ሰዓት
እስከሚደርስ ድረስ በትዕግስት ለመቆየትና የዚያ የውሽት ልጃገረድነት
ጭምብል ወልቆ እውነተኛው ማንነቷ የሚረጋገጥበትን ጊዜ በጉጉት
መጠባበቁን መረጠ፡፡
በሱ እምነትና ግምት ያ ቀን እሁድ እለት እንዲሆን ወስኗል፡፡ሻምበል እሁድ ዕለት ደርሶለት ይሄ ጥርጣሬና ጥላቻው አንድም የሚወገድበት፤አሊያም ከትህትና ጋር የሚቆራረጥበት ዕለት በመሆኑ የአሁኑ እሁድ ከምንግዜውም የበለጠ ናፈቀው፡፡
ትህትና ደግሞ በበኩሏ ሻምበል ብሩክ እንደዚያ ቅዝቅዝ ብሎና ተለውጦ በስልክ ሲያነጋግራት ተረብሻ፣የመገናኛቸው ዕለት ደርሶላት ሄዳ ምን እንደሆነ እስከምትጠይቀው ድረስ ቸኩላ፤ እሁድን እየተጠባበቀች ነበር፡፡
ሁለት ልቦች በየግል ምክንያቶቻቸውን አምቀው፤ ሰዓቱን በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም፤ ሰዎች በፈለጉት መንገድ ሳይሆን፤ ጊዜ በራሱ ህግና ስርዓት የሚመራ ነውና፤ እሁድ የራሱን አዲስ ክስተት ይዞ ብቅ አለ፡፡
ሰው በጊዜ ቢያቅድም ጊዜ የሰው ተጐታች አይደለምና የታቀደ ሁሉ
አይሳካም :: በተገላቢጦሽ ደግሞ ሰው የጊዜ ተጉታች ነውና፤ አንዳንድ የሰዎች ዕቅድ ጊዜው ካልፈቀደ በዕቅድነቱ ይቀርና ጊዜ የራሱን አዲስ ክስተት ይዞ ይመጣል፡፡
ትህትና ድንበሩ በአበራና በአለሌው እንደሻው አማካይነት በተቀነባበረ ሴራ፤ በአካሏ ላይ ጉዳት ስለደረሰባትና ፤በቀሪ ህይወቷ ላይ ጥቁር ነጥብ የሚጥል ወንጀል ስለተለፈፀመባት፤ በናፍቆት የተጠባበቀችው እሁድ ቢመጣም ያ ቀን ከደረሰባት ዱላና አስገዳጅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጉዳት ያገገመችበት ቀን ሆኖ ዋለ፡፡
እንደዚያ የምታፈቅረው ጓደኛዋ ናፍቋት፤ እናቷን ለሁለት ቀናት ያህል ስትለያት የምታደርገው ጠፍቷት፤ በእንባ እየታጠበች በዚያች በሁለት ቀን ውስጥ ወዟ ምጥጥ ብሎ፤ አካሏ ጠውልጉና ውበቷ ተገፍፎ ስትታይ፤ ትህትና ነች ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነበር፡፡ውበት የስሜት
ነጸብራቅ የመሆኑ እውነታ ከፊቷ ይነበብ ነበር፡፡
ለዚያውም አዜብ ከአጠገቧ ሳትለይ በማንኛውም ረገድ ባታፅናናትና
ባትንከባከባት ኖሮ፤ ጉዳቷ ከዚህም የከፋ ይሆን ነበር፡፡ከዚህ ሁሉ በኋላ በሁለተኛው ቀን ላይ ሰውነቷን ተጣጥባ፤ በቅባት ፊቷን አባብሳ፤ የአዜብን ምርጥ ቀሚስ ለብሳ ፤ ሰው መስላ ተነሣች፡፡
ሞራሏ እንዳይነካና ያለፈውን እንድትረሣ አዜብ ያላደረገችላት ጥረት አልነበረም፡፡ ትህትናም ጓደኛዋን ለማስደሰት ያህል ብቻ ልቧ ከውስጥ ደም እያለቀስ፤ ከላይ ከላይ ፈገግታ እያሳየቻት ተነሳች፡፡
በተለይም በዚያን ዕለት ጨረቃዋ በመኝታ ክፍላቸው ውስጥ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ፤ ከሻምበል ብሩክ ጋር ባሳለፈችው አስደሳች ምሽት የተናገረችው ትዝ ይላትና እረፍት ይነሳታል፡፡ ያንን የሚያሰቃይ ስሜቷን ውጣ በፍጹም ጤነኛና ደሰተኛ መስላ ልብሷን ለባብሳ እንደጨረሰች...
"እንሂድ አዜቢና” አለቻት፡፡
እናቷ ይህችን ሁለት ቀን ልጇ ሳትመጣ በመቅረቷ እዚያ ሆስፒታል ውስጥ በእንባ እየታጠበች አንዱአለምን ካልወለድካት እያለች ስታስጨንቀው፤ በሁለተኛው ቀን ላይ የት እንዳለች ቁርጡን ነገራት፡፡
አንዱዓለም እህቱ የት እንዳለች የሰማው ከአዜብ ነው፡፡
• ትሁት ሻምበል ጋ ነች፡፡ ሁለት ቀን እዚያ ስለምትቆይ አንተ ከእናትህ እንዳትለይ አደራህን” ብላ በሚስጥር ስለነገረችው፤ አንዱአለም ዜናውን በደስታ ተቀብሎ ለደቂቃ ከእናቱ እንደማይለይ በገባላት ቃል መሠረት ከዚያ አካባቢ ውልፍት ሳይል ነው የቆየው፡፡
ትህትና በዚህች በሁለት ቀን ውስጥ ሁለት ዓመት እንደተለያቻች ሁሉ ናፍቃት፤ ሆስፒታል ስትደርስ እየሮጠች ሄዳ እናቷ ላይ ድፍት ብላ አለቀሰች፡፡ አዜብ የጓደኛዋን ሁኔታ ስትመለከት አንጀቷ ተላወሰ፡፡አልቻለችም፡፡ አብራት አለቀሰች፡፡
እናቷም ልጇ ላይ ጥምጥም ብላ በስስት እያገላበጠች ሣመቻትና..
በጤናሽ ነው ትሁቴ? አለሽልኝ የኔ እናት? ” ዐይን ዐይኖቿን በጉጉት እያየች፡፡
“ደህና ነኝ እማይዬ አንቺስ እንዴት ነሽ?” እናቷን እያሻሸች በዐይኗ አንዱአለምን ስትፈልግ እሱም የሆነ ነገር ሊነግራት ፈልጐ ምልክት ሲሰጣት አየችና ልትስመው ሄደች.....
“ሻምበል ጋ እንደነበርሽ ነግሬአታለሁ” አላት ድምፁን ዝቅ አድርጉ፡፡
ትንሽ ሣቅ ብላ......
“እሺ" አለችው::
ከዚያም በኋላ ከእናቷ አጠገብ የተኙትን በሽተኛ አዛውንት ጤንነታቸውን ጠይቀው፣ እናቷን ከበው ተቀመጡ፡፡ እናቷ የልጇን
ዐይን፤ዐይን፤በስስት ስትመለከት ሆዷ ቡጭ ቡጭ
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

.....ሻምበል ብሩክ ይመስላታል፡፡
የሆነ ደስ የሚል መናፈሻ ውስጥ እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ ሲንሸራሸሩ ከቆዩ በኋላ፤ ወደ ኣንድ ጥላው ቀዝቀዝ ያለ፣ ንፁህ አየር ወደሚነፍስበት የወይን ዛፍ ሥር
ይመጡና ከሥሩ ካለው ለምለም ሣር ላይ ጋደም ይላሉ::

በዚህ ጊዜ እሷ እሱን ትራስ አድርጋ፣ ፀጥ ያለውን ኣካባቢ እየቃኙ የተፈጥሮ ውበትን ሲያደንቁ፤ የሁለቱም ዐይኖች ከፊት
ለፊታቸው በሚያዩዋት የጽጌዳ ቅርንጫፍ ላይ ባለችው እንቡጥ ጽጌረዳ አበባ ተማርኮ፤ ጽጌረዳዋን ሲመለከቱ ከቆዩ በኋላ፤ ስለዚያች ጽጌረዳ ለመናገር በአንድ ጊዜ “ እንዴ ” ብለው ይጀምራሉ፡፡

"ምን ልትል ነበር?” ትለዋለች እየሣቀች::
“አንቺስ ምን ልትይ ነበር?” ይላታል እሱም እየሳቀ::

“እንዴት ታምራለች ልል ነበር” ስትለው..
“እኔም እንደሱ ልል ነበር:: ከማማሯም በላይ ደግሞ ልክ የሁለታችንን ፍቅር ትመስላለች ልልሽ ነበር” ይልና ቁልቁል ወርዶ ከንፈሯን ይስማታል፡፡

“ማማሯስ እሺ የሁለታችንን ፍቅር እንዴት ነው የምትመስለው?” ትለዋለች:: ስለፍቅራቸው የበለጠ እንዲያወራላት
ጓጉታ::

“ያልፈነዳ እንቡጥ ጽጌረዳ በአበባነት ደረጃ ላይ ካለው ፍቅራችን ጋር ይመሳሰላል” ይላታል፡፡

“አበባው ፍሬ የሚሆነው መቼ ነው ብሩኬ?” አይን፤ ዐይኑን ሽቅብ እያየች ትጠይቀዋለች::
ወፎች የሚዘምሩ ይመስላታል፡፡ ንፋሱ ሽውው ይላል፡፡ዛፎች ይደንሣሉ፡፡ሰማዩ የጠራ ነው፡፡ሌላ ዓለም፡: ልዩ ዓለም.....
“የሠርጋችን ዕለት በዚያ በጫጉላ ቤት ውስጥ አሀዱ ብለን ትዳርን ስንቀድሰው፡፡ አይመስልሽም ትሁቲና? ቆይ እንዲያውም ይህችን ጽጌረዳ ስለፍቅራችን ገፀበረከት ላቅርብልሽ” ይልና ብድግ ብሎ ያቺን የምታምር እንቡጥ ጽጌረዳ አበባ ቀጥፎ ያመጣና
ይሰጣታል::

“በሠርጋችን ዕለት? .... በጫጉላ ቤት? .... አሀዱ ብለን?... ስንቀድሰው?
ምን ዐይነት ጣጣ ነው? የሆነውን ሁሉ
ብነግረውስ? የጫጉላ ቤቱ ዕቅዳችን መፍረሱን፣ እንደሻው አስገድዶ ክብረ ንፅህናዬን መድፈሩን፤ ብገልጽለትስ?
አያምነኝ ይሆን?
በቃሽኝ አታላይ ነሽ ይለኝ ይሆን? ልንገረው? እያለቀስኩ ልግለጽለት
ወይንስ ልተወው? ወይኔ አምላኬ ምን ጣጣ ውስጥ ከተትከኝ? ወይኔ
ብሩኬ በዚህ ምክንያት እንለያይ ይሆን?...” በስጋት ተዋጠች፡፡
ይህንን ፍርሃቷን በልቧ አምቃ በጭንቀት እንደተዋጠች፤
ሻምበል ብሩክ ቀጥፎ የሰጣትን ጽጌረዳ እንባ በጋረዳቸው ዐይኖቿ ትኩር ብላ መመልከቷን ቀጠለች::
ያቺ የምታምር ጽጌረዳ፣ ያንን የመሰለ ማራኪ ውበት የተላበሰች ለምለም እንቡጥ አባባ፣ ቀስ በቀስ እየጠወለገች፣
እየጠወለገች፣እየደረቀች ሄደችና፣ በእጇ ላይ እንዳለች እርር ብላ ተንኮሻኩሻ ደቀቀች::
በዚህ ጊዜ ትህትና በድንጋጤ ተወራጭታ ከገባችበት አስደንጋጭ የህልም ዓለም ስትወጣ፤ ሰውነቷ ሁሉ በላብ ተዘፍቆ
መንቀጥቀጥ ጀመረች::
ቀስ ብላ ያየችውን ህልም ስትመረምር ፍርሃት ነገሰባትና፤ ሆድ ብሷት “በቃ ልክ ነው:: ህልሜ ትክክል ነው:: ብሩኬን አጣሁት ማለት ነው፡፡ ወይኔ ወይኔ” እያለች ስቅስቅ ብላ ዐይኖቿ
እስከሚያብጡ ድረስ አለቀሰች፡፡
ሻምበል ብሩክ ልጃገረድ ያለመህኗን ሲያውቅ፤ ውሸታም ባለጌ አድርጐ እንደሚገምታት፤ በቃሽኝ እንደሚላት፤ ጠርጥራ ልቧ በሀዘን ተሰበረ::
በዚህ መጥፎ ስሜት ውስጥ ገብታ በሃሣብ ስትዋዥቅ ከቆየች በኋላ፤ ሻምበል ብሩክን የራሷ አድርጋ ለማስቀረት የሚያስችላትን ዘዴ ማውጠንጠን ጀመረች፡፡ በመጨረሻም የሆነ ሃሣብ መጣላት::
“ማን ያውቃል? ዛሬም እንደበፊቱ ሁሉ ልጃገረድ የመሆኔ ምልክቱ ሙሉ ለሙሉ ላይጠፋ ይችላልና የማያስታውቅ ከሆነ ለምን አንድ ሙከራ አላደርግም?” ስትል አሰበች። በመጨረሻም ከሻምበል
ብሩክ ጋር ከመገናኘቷ በፊት ራሷን በዶክተር ልትፈትሽ ወሰነች::
አንዴ ላይታፈስ የፈሰሰ ውሃ፤ በድጋሚ የሚገኝ መስሏት ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ቀጠሮ ያዘች::
ከመቸኮሏ የተነሳ አርብ ዕለት ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር በያዘችው ቀጠሮ መሠረት
ወደ ቤት እንደደረሱ ተያይዘው ወደ ቤት እንደደረሱ ሠራተኛዋን አገላብጣ ሣመቻት::
ምነው ፍቅርሽ በዛ?” አለቻት ሠራተኛዋ በልቧ፡፡ ትህትና ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ካሳለፈችው ጊዜ ሁሉ ለየት ያለው የዛሬው ነው:: ለዛሬው ግንኙነታቸው የራሷ ምክንያት ስለአላት፤ የሚሆነውን ቶሎ ለማወቅ፤ ቶሎ ወደ አልጋ ለመሄድ
ቸኮለች፡፡
ቢሆንም ግን ይህንን መቸኮሏን
ዶክተር እንዲያውቅባት አላደረገችም::
እንደተለመደው ሁሉ ዶክተር እራሱን ሊፈትሽ፤ እሷም የልጃገረድነት ሚስጥሯን ልትፈትሽ፤ ተፈላልገውና፤ ተግባብተው፤
ተያይዘው፤ ወደ መኝታ ክፍል ገቡ::
ዶክተር በዚያ ረገድ በራሱ ላይ እምነት እያጣ ስለሄደ በውስጡ የነበረው ጉጉት ቀዝቅዟል፡፡ ሆኖም እንደተለመደው የማይጠገብ ውብ የልጅነት ገላዋ የሚያመነጨውን ሙቀት ለመቋደስ ያህል ብቻ መፍጨርጨሩን ቀጠለ፡፡
......
እሷ ደግሞ በሥጋት እንደተዋጠች ከአሁን አሁን
“ምን ዐይነት ሁኔታ ይፈጠር ይሆን? ልጃገረድ በመሆንና ባለመሆን መካከል ያለው ልዩነት ምን ይመስል ይሆን? በማለት ቁርጧን ለማወቅ ልቧ ትር፤
ትር፤ እያለች የሚያደርገውን
እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በንቃት ትከታተላለች፡፡

ቀስ በቀስ አካሉ ከአካሏ ጋር እየተሟሟቀ ፤እየተዋሀደ፣ እየተግባባ፤ መጣና የሷ ገላ እሾህ አመኬላውን አስወግዶ ሊያስተናግደው ዝግጁ መሆኑን ሳያውቅ፣ በሀይል ሲታገላት፤ባልጠበቀው መንገድ ተቀብሎ ያስተናግደው ጀመር፡፡
ትህትና ያንን ሁኔታ ስትመለከት ቅስሟ ስብር ብሎ፤ በሃሣብ ጭልጥ ብላ ሄዳ ሌላ ዓለም ውስጥ ገባች፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ ደግሞ በዚያ ባጋጠመው አዲስ ሁኔታ ተደንቆ ጉድ ነው!” አለና ለጊዜው ከገባበት ስሜታዊ ረመጥ ወጥቶ እፎይታ ለማግኘት ያህል ጉልበቱን
እንደድሮው እንደአፍላ የጉርምስና ዘመኑ አድርጐ መጫወቱን ቀጠለ፡፡
በቀላሉ ሊበርድ አልቻለም፡፡ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስዶ ተጫወተ፡፡
ይህቺ ሰው ጨው አላት መሰለኝ” እያለ በሚያደርገው ነገር ሁሉ እየተደነቀ ነበር፡፡
ነበር፡፡
እሱ እንደዚያ በደስታ ሲቃ ተውጦ ሲቦርቅ ፣እሷ ግን በድን አካሏን ከሥሩ አጋድማ ዐይኖቿ በከፈቱት ቧንቧዎች እየታጠበች
ዶክተር የልቡ ሲደርስ ቀስ በቀስ ከዚያ ከሚናጥበት የስሜት ማዕበል ወጥቶ የሆነውን ነገር እንደ አዲስ ያስበው ጀመር፡፡
በዚህ ጊዜ የሆነ የቅናት ስሜት ተለኮሰበትና ገላው በንዴት እየተቃጠለ ይጨስ ጀመር፡፡በወሲብ በኩል እርካታን ቢያገኝም፣ ልቡ በዚያው ልክ የምሬት
ደም ሲረጭ ተሰማው::
የልቡ ከደረሰ በኋላ ንጽህናዋን የወሰደው እሱ ባለመሆኑ፤የሆነ የቅናትና የዝቅተኝነት ስሜት አእምሮውን ሰርስሮት ገባ፡፡
መጀመሪያ ካገኛት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያደረገው ድካሙ ሁሉ ከንቱ መቅረቱን ሲያስታውሰው፤ ያንን ውብ ገላዋን ለሌላ ሰው አሳልፋ መስጠቷን ሲያሰላስለው፣ በንዴት እያረረ፣ ጨጓራው ተቀቅሎ እንደገነተረ ሥጋ ሲገነትር ተሰማው:: የተናቀ የተተፋ መሰለው፡፡
የዚያን ጊዜ የልቡን በልቡ አድርጐ.....
“ትህትና እንደዚህ የማደርገው እኮ ስለምጠብቅሽ ነው” ያላት ቀን
“ይገባኛል ዶክተር” ነበር ያለችው:: ግን ዋሸችው:: እሱ ሲጠብቃት እሷ ከዳችው።

እሱ ተንከባክቦ ያቆየውን ውድ ነገር ለሌላ አስረክባቸው መጣች:: ዶክተር ሁሉም ነገር እንደሰንሰለት ተያይዞ በሃሣቡ
መጣበት:: ደካማነቱ የራሱ ሆኖ ሳለ ራሷን አሳልፋ የሰጠችውን ልጅ ሞራሏን
ሊነካው ፈለገ፡፡የሱ ሞራል ተነክቷል፤ ቅስሙ ተሰብሯልና፤ አጥንት በሌለው ምላሱ አጥንት የሚሰብር ንግግር ሊናገራት ፈልጎ ... ጠጋ አላትና
👍2
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

....የመከራ ቋት መሆኗ እያማረራት መፈጠሯን እስከመጥላትና ሞቷን እስከመመኘት ብትደርስም፤ ምሬቷን በልቧ አምቃ፣ መጨረሻውን እሱ የፈጠራት አምላኳ እንዲያሳምረው መፀለይዋን አላቋረጠችም፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ እግዚአብሔር አይደለም፡፡ በፈጠራት ነፍስ ላይ
የሚወስነው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ መቼ እንደሚወስዳት የሚያውቀው እሱ ብቻ ስለሆነ ፤ ዶክተር ባይከዳኝ እንደማትድን ገልጾ ተስፋ ቢያስቆረጣትም፤ ማን ያውቃል? ፈጣሪ በተአምር ሕይወቷን አትርፎላት፣ ሊተዛዘቡ ይበቁ ይሆናል፡፡ ይህንን ስታስብ፤ ሞቱ ተብለው ደረት የተመታላቸው፤ አበቃላቸው ተብለው ሳጥን የተዘጋጀላቸው፣
በአምላክ ረቂቅ ሥራ ህይወት ዘርተው፤ ለረጅም ዕድሜ ባለፀጋነት የበቁ እንዳሉ ሲታወሳት፣ እንኳንስ ተስፋ ያላት እናቷን፤ ከፈለገ ሬሣ የሚቀሰቅሰው አምላክ፤ በህይወት ሊያቆይላት እንደሚችል በመተማመን፤ የዶክተርን ድንፋታ እየናቀችው፤ እናቷን አሳክማ ለማዳን ትግሏን በጠንካራ መንፈስ ለመቀጠል ወሰነች፡፡

ከዚህ ከእናቷ ህመም በተጨማሪ ደግሞ በተፈጠረው ችግር ምክንያት የሷና የሻምበል ፍቅር ገና በለጋነቱ እንዳይጨናገፍ ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏታል፡፡
በተለይ የዚያን ዕለት ያየችው ህልም ፍርሃት፤ ፍርሃት፣እንዲላት ዋነኛ ምክንያት ሆኖባታል፡፡
ነገ እሁድ ነው፡፡ ዕሁድ ዕለት እሷና ሻምበል ብሩክ የሚገናኙበት፣ ፍቅር የሚጨዋወቱበት፣ የወደፊት የትዳር ህይወታቸውን እየቀየሱ የሚወያዩበት፤ በአጠቃላይ ሁለቱም በናፍቆት የሚጠብቁትና በሻምበል ብሩክ ቤት በደስታ ውለው የሚያድሩበት ቀን ነው፡፡
ቅዳሜ በጠዋት ተነስታ፤ ለእናቷ አጥሚት አዘጋጅታ፧ ምሣ በሣህን ይዛ፤ ወደ ሆስፒታል ሄደች፡፡ እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ድረስ ከቆየች በኋላ አንዱዓለምን እናቱ ዘንድ እንዲቆይ አደረገችና፤ ወደዚያች
ችግሯንም ሆነ ደስታዋን እኩል ወደምትካፈልላት ጓደኛዋ ወደ አዜብ
ሄደች፡፡

ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ትናንትና መገናኘታቸውን፣ ከዚያም ቤቱ ይዟት መሄዱን፣ ከዚያም ራሷን ለመፈተሽ ያደረገችውን ሙከራ፣ ከዚያም ዶክተር ባይከዳኝ ሙልጭ አድርጐ ስድቦ ያባረራት መሆኑን አወራችላትና፤ በመጨረሻም ላይ ዐይኖቿ በእንባ ተሞልተው እናቷ መጨረሻ ደረጃ ላይ በደረሰ.... የካንሰር በሽታ መታመሟንና፤
እንደማትድን የገለፀላት መሆኑን፤ አስረዳቻት፡፡
አዜብ እቅፍ አድርጋ አጽናናቻት፡፡ አቤት እንደዛ እቅፍ አድርጋ ስታጽናናት የተሰማት ስሜት! መዋለድ ብቻውን ምን ዋጋ አለው?አንዳንዱ ተዋልዶም ተመልሶ እንደጠላት ይፈላለጋል፡፡ እንደዚህ ያለው
ጓደኝነት ግን ከመዋለድም በላይ ዋጋ ያለው ነው፡፡ መዋለድ ሳይሆን መዋደድ ነው ተብሉ የለ ወትሮውኑ? ፡፡

ዶክተር ባይከዳኝ ሀኪም እንጂ እግዚአብሔር አይደለም፡፡ ስለማሚ ህይወት የሚያውቀው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ደግሞ ታያለሽ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድነው ከዚያ ሆስፒታል ባይወጡ አዜብ ምን አለች ትይኛለሽ ?” እሷን ለማጽናናት ስትል .
ከእግዜሩ መልዕክት ደርሶኛል ለማለት ትንሽ ነበር የቀራት። ትህትናም ትህትናም
ያለችው ይሄንኑ ነበር፡፡ ድሮውንም የእናቷን ነገር ለፈጣሪ ነበር የሰጠችው፡፡ ልቧ ተጽናና፡፡ ወደ ሌላው ዋና ርእሰ ጉዳይ ተሸጋገሩ፡፡
“የተፈጠረውን ሁሉ ፍርጥርጥ አድርጐ እውነቱን መናገር ይሻላል ወይስ ሌላ መንገድ አለው?” ስትል አዜብን አማከረቻት፡፡
“እውነቱን መናገር ባልከፋ ነበር፡፡ ምን ያህል አምኖሽ ይቀበለዋል የሚለው ነው ችግሩ። አላየሽም ዶክተር እንኳን የሆነውን? እሱስ ልጃገረድ ነኝ ስትይው ከከረምሽ በኋላ ያለመሆንሽን ሲያውቅ ምን ይሰማዋል?ስትዘል የኖረች አይልሽም?” መልሳ ጠየቀቻት፡፡ ትህትና
የዶክተር ሁኔታ መጣባት፡፡ አውሬ ነበር የሆነው፡፡ የሻምበልም ከዚህ ሊለይ እንደማይችል ገመተችና ፈራች ::
"እሱስ እውነትሽን ነው አዜቢና፤ ታዲያ ምን አባቴ ማድረግ ይሻለኛል? ጨነቀኝኮ! እንደነገርኩሽ ህልሜም ጥሩ አልነበረም፡፡ ወይኔ ብሩኬ.... የልቤን እንዴት አድርጌ ባሳየሁት?” ተከዘች፡፡
አዜብ ጉዳዩን ከብዙ አቅጣጫ ተመለከተችው፤ መረመረችው፡፡የሆነውን ሁሉ መናገር፤ ወይንም ሌላ ዘዴ መፈለግ.... በመጨረሻ ላይ የመጣላትን ዘዴ ልትነግራት ካለች በኋላ በቅድሚያ ልታሳምናት ፈለገች፡፡
“ ትሁት የእድልሽን ሳትሞክሪ ከወዲሁ ቶሎ ብሎ እጅ መስጠቱ የሚያዋጣ አልመሰለኝም፡፡ ቀድመሽ እንደዚህ ሆንኩ ብለሽ ተናግረሽ፤አልፈልግሽም ካለ እንዳይቆጭሽ ፡፡ አሪፍ ከሆንሽ በአንድ ጊዜ ልታሳኪው ትችያለሽ፡፡ ካልተሳካልሽ ደግሞ ሁለተኛውን እድል ትጠቀሚያለሽ፡፡
የተፈጠረውን ሁሉ በዝርዝር ታስረጂዋለሽ እርግጠኛ ስለሚያፈቅርሽ ችግርሽ ይገባዋል :: ስለዚህ በቅድሚያ አማራጩን ብትጠቀሚ” አለቻት፡፡ ትህትና አማራጩን ለመስማት ጓጓች፡፡
“ፔሬድሽ መጥቷል?”
“አልመጣም”
ጥያቄውን ለምን እንዳቀረበችላት ለማወቅ
ቸኩላለች፡፡
“መቼ ነው የሚመጣው?”
"እሮብ ወይም ሀሙስ ብዬ እገምታለሁ”
“በቃ እሁድ ዕለት አትሂጂ፡፡ ለእሮብ ወይም ለሀሙስ ቅጠሪው። የዚያን ዕለት አብረሽው እደሪና፤ እሪ ብለሽ አልቅሽ”
ትህትና በጥፊ እንደተመታ ሰው ክው ብላ ደነገጠች፡፡
“ውይ አዜቢና ይሄስ የማይሆን ነው” ተቃወመች፡፡
“ወደድሽም፤ ጠላሽም፤ ያለው አማራጭ እሱ ብቻ ነው ትሁት”
“እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዳታለልኩት ካወቀ ደግሞ የባሰ ነው የሚሆነው” በትካዜ ተውጣ፡፡
“ሊያውቅ አይችልም፡፡ ስንቶቹ ናቸው እንደዚህ የሚሽውዱት ዋናው ያንቺ ቅልጥፍና ነው”
በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው ከተነጋገሩ በኋላ፤ ያለው አማራጭ ይሄና ይሄ ብቻ መሆኑን አሳመነቻት፡፡
ሳምንቱን ሙሉ ከሻምበል ብሩክ ጋር ስልክ ሲደዋወሉ ነበር ያሳለፉት፡፡ ይሁን እንጂ እሷ በእውነተኛ ፍቅር ...
“ብሩኬ " ስትለው፤ እሱ ደግሞ በአንደበቱ “ሀይ ትሁት”ቢላትም፧ በልቡ “አስመሳይ!” ሲላት ነው የከረመው ::
ይሄንን አስመሳይነቷን፤ ሌብነቷን፤ ደርሶበት ቁርጡን እስከሚያውቀው ድረስ በተቻለው መጠን የድሮውን ሻምበል ብሩክን ለመምሰል ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ልቡ ቢሻክርም፤ እንደበቱን ለማለሳለስ
እየታገለ ነው የከረመው ::
ቅዳሜ ዕለት ስልክ ደወለችለትና ከአዜብ ጋር በተመካከሩት መሠረት የእሁድ ፕሮግራማቸውን ወደ እሮብና ወደ ሀሙስ እንዲሸጋገር አሳወቀችው፡፡
“ምነው ምን ተፈጠረ ትሁት?” አላት በመገረም፡፡
“ማዘር ብሶባታል እሁድ እለት ሆስፒታል ነው የማድረው”
“ይሄኔ ከዚያ ጅል ዶክተርሽ ጋር ለማደር ነው” የሚል ስሜት ተሰማውና ቅናት ቅጥል ቢያደርገውም፤ ቻል አድርጐ
“ልምጣ እንዴ?ችግር አለ እንዴ ?” አላት ለማግደርደር ያህል፡፡
“አትድከም ብሩኬ ከቻልክ እሁድ ብቅ በል” አለችው፡፡
ሻምበል ከሶስት ቀናት በፊት ሆስፒታል
ሄዶ ጠይቋታል፡፡ አሁን ብሶባታል ብላ የምትነግረውን ዓይነት አልነበረባትም፡፡ እንዲያውም እየተሳሳቁ፤ እየተጨዋወቱ! ነው የዋሉት፡፡
እሮብ ወይም ሀሙስ ደግሞ ያልተለመደ ቀጠሮ ነው፡፡
“ይሁን እስቲ!” አለና ንዴቱን በልቡ አምቆ፡፡
“ምንም ችግር የለውም ትሁት፡፡ ዋናው የማዘር ጤንነት ነው፡፡ግን እሮብ ወይ ሀሙስ ከምትይኝ ወይ እሮብን፤ ወይ ሀሙስን፤ ለምን አልመረጥሽም? ማለቴ እንድጠብቅሽ?”
“ችግር የለውም ብሩኬ፡፡ ትክክለኛውን ቀን ደውዬ እነግርሃለሁ”
“ይሁን እንዳልሽ” በሃሣቧ የተስማማ በመምሰል አንጀቱ እያረረ እሁድ አልደርስልህ ብሎት በተስፋ ሲጠባበቅ፤ አሁን ደግሞ ይኸውና እሁድ ሲደርስ ተጨማሪ ሶስት ወይም አራት ቀን ጨምራበት ቁጭ አለች፡፡ ይህንን ሁሉ ችሎ፣ እሁድ እለት እዚያው ሆስፒታል ሄዶ፤እናቷን ጠይቆ፤ ልክ
👍2
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....መጨረሻውን ለማየት፤ እንደድሮው በስስት ሳይሆን፤ በውስጡ የነበረውን
ጥርጣሬ ለማስወገድ፤ በተቻኮለ ስሜት ወደ አካሏ በኃይል ዘለቀ.....
በዚያን ጊዜ ከድንጋጤው ብዛት የተነሣ መብረቅ እንደመታውአው ክው ብሎ ቀረ፡፡ ውስጡ የነበረው ጥቃት ደም በስሪንጅ ተመጦ! በምትኩ በረዶ የጨመሩበትን
ያህል ደሙ ቀዝቅዞ፤ ወደ በረዶነት
አብጦ የተነረተው ስሜቱ ሙሽሽ ብሎ ሲወርድ ፤ እሷ ደግሞ እንድ ስህተት መፈጸሟን ተረድታ በነቃችበት ያበቃለት ምዕራፍ ላይ “እሪ!” ብላ ጩኸቷን ስታቀልጠው፤ አንድ ሆነ፡፡ነገሩ ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ሆኖ ነበር፡፡ ሻምበል ብሩክ በሃሣብ ጭልጥ ብሎ ከገባበት ሰመመን እሪታዋ አስደነገጠውና...
“ምን ሆነሻል?” በማለት በተሰበረ አንደበቱ ጠየቃት፡፡
“ወይኔ ብሩኬ! ጉድ አደረከኝ አይደል?!” ፍራሹ ላይ በደረቷ ድፍት ብላ አለቀሰች፡፡
ሻምበል ብሩክ እንደዚያ ሆና ሲያያት አቤት የተሰማው ስሜት!
አቤት የተቃጠለው መቃጠል!! በአንድ ጥይት ቢያስቀራት ምንኛ ልቡ በወደደ...?
“ምን አደረኩሽ?” አላት፡፡ አእምሮው ከዘመተበት ሳይመለስ ጣራ፤ ጣራውን፤ በድን ሆኖ እየተመለከተ፡፡
“ደግሞ ምን አደረኩሽ ትላለህ?” እዬዬ ብላ አለቀሰች፡፡ ያንን የአዞ እንባዋን ስታወርደው፤ ተገርሞ ፍዝዝ ብሎ እንደትንግርት ያስተውላት ጀመር.... እንደዚያ የሚወዳትና የሚያፈቅራት ልጅ ገላ አባጨጓሬ መስሎ እስከሚታየው ድረስ ኮሰኮሰችው፡፡በደረቱ የሚሳብ እባብ
ሆና ታየችው፡፡ ጠላት፡፡ ከጥላቻ ሁሉ በላይ የሆነ ጥላቻ በልቡ ነግሶ....
“ምን ነበርኩ ለማለት ነው?” አላት ንቀትና ምሬት በሚንፀባረቅበት አንደበት፡፡
“አታየውም እንዴ ያደረከኝን?” በዚህ ጊዜ ሻምበል ሣቁን መቆጣጠር አልቻልም፡፡ በሳቅ ፈነዳ!!፡፡ እሱ እንደዚያ በሣቅ ሲፈነዳ ደንግጣ፣ ........
“ምን ያስቅሃል?” አለችው፡፡
የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ፤ ሁኔታዋን ሲመለከተው ፤ የእስከዛሬው ፍቅር ሁሉ የውሸት መሆኑን፣ የለየላት አስመሳይ ትያትረኛ መሆኗን፣ የዚያን ዕለት እንደዚያ ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ እየቦረቀች የገባችው፣ እኔ እኮ ልጃገረድ ነኝ እያለች ያታለለችው፡፡
ለመጀመሪያ ቀን የተገናኙ ዕለት እዚያ እነሱ መኖሪያ ቤት እጥሩ ጥግ
በአየር ላይ እየተንሳፈፈች እንደጥሩ ተዋናይ ፀጉሯን አየር ላይ እየነሰነሰች ትስመው የነበረው፤ በተለይ ለዚያን እለቱ ብለህ ነው የማርከው አይደል? ብላ ያፌዘችበት፡፡ይሄ ሁሉ ሲታሰበው፤ የማስመሰል ችሎታዋ ከከፍተኛ ልምድ የመነጨ መሆኑን ተገነዘበ ። የመጠጥ
ልምዷም ከዚሁ ጩሉሌነቷ የመነጨ መሆኑን ሲያውቅ፤ የእስከዛሬው
የዋህነቱ፣ በቀላሉ መታለሉ፤ ይሄ ሁሉ ታስቦት ጥላቻው ከልክ አለፈና ቋቅ እስከምትለው ድረስ አስጠላችው፡፡ከዚያም ከአልጋው ላይ ብድግ ብሎ፤ የምሽት ልብሱን ለባብሶ፤ የመኝታ ክፍሉን ከውጭ ቆለፈና፤ ወደ ሳሎን ሄዶ ሶፋው ላይ ጋደም አለ፡፡

ሻምበል ብሩክ እዚያ ሶፋ ላይ ተኝቶ በሃሣብ ወደኋላ ጭልጥ. ብሎ ሄዶ በዕድሏን እያሰባት እንባው ኮለል እያለ በጉንጮቹ ላይ ወረደ::
እግዚአብሔር ለምን እያሳየ እንደሚነሳው ግራ ገብቶት
“መጨረሻዬ ምን ይሆን?” በሚል ጭንቀት ተዋጠ፡፡የሰው ልጅ ውስጣዊ ገመናውና፤ውጫዊ ባህሪው ያለመጣጣሙ ሚስጥር ገረመው፡፡
ትህትና ካያት ዕለት ጀምሮ ከልቡ የወደዳት ልጅ ነበረች፡፡በኋላም ዐይኑ ጉድ እስካየበት ቀን ድረስ ሙሉ እምነት ነበረ የጣለባት፡፡
“አይ ሰው? ሰውን ለማመን እንዴት ይቻላል? እራስንም ማመን አይቻልም፡፡ ቀበሮ ለሰው ሞት አነሰው ነበር ያለችው?" ከዚህ በፊት በአንድ ግድግዳ ላይ ተጽፎ ያነበበውን ጥቅስ አስታወሰ፡፡
“ሰው እኮ......"
ይላል፡፡ የማይሞላ የክፋት ጉድጓድ ነው
ማለቱ ይሆን? ሲል አሰበ፡፡ በዚህ ስሜት ተውጦ እንቅልፍ የሚባል ነገር በዐይኑ አልዞር ብሉት እንዲችው ሲገላበጥ ነጋለት ::
ትህትና ደግሞ እዚያ መኝታ ክፍል ውስጥ ስካሯ ሁሉ ጠፍቶ በእንባ እየተንፈቀፈች የቡኮ እቃ መስላለች፡፡
“ለምን ተፈጠርኩ? ለምን እግዚአብሔር በዚህ ሁሉ ቅጣት ይቀጣኛል? ምን አደረኩት?” እያለች አምርራ እያለቀሰች፤ ስትጨነቅ፤የሆነ ሰይጣናዊ መንፈስ ተጠጋትና በጀሮዋ መጥቶ የሆነ ነገር ሹክ
አላት፡፡
ትህትና... ትህትና.... ምን እያደረግሽ ነው? ምን ትጠብቂያለሽ? ለምን ከዚህ ሁሉ ስቃይ አትገላገይም? የወዲያኛውን
የሰላም ዓለም ለምን ፈራሽው? አባትሽ የሄደበት ዓለም አይደለም እንዴ?
ይህንን የመሰለ አእምሮሽ ሊሸከም የማይችለውን ስቃይ አስወግደሽ፤
ለምን እስከወዲያኛው በእፎይታ አትተኝም? ተስፋሽ ምኑ ላይ ነው?
እናትሽ እንደማትድን ዶክተር ቁርጡን ነግሮሻል እኮ!
ሻምበልንም ይኸውና አጥተሽዋል፡፡ ለምን ወደ አባትሽ ዘንድ አትሄጅም?
ሂጅ ወደሱ...ሂጂ. ሂጂ ሂጂ . ሂጅ” አላት፡፡
ከዚያም በቀጭን ገመድ ላይ በድን አካሏ ተንጠልጥሎ በንፋሱ ሃይል ወዲያና፤ ወዲህ፤ ሲወዛወዝ ታያት ...የዚህችን አለም ጣጣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተገላግላ እፎይ.... ስትል ታያት፡፡ ከዚያም አላፊ አግዳሚው የተንጠለጠለ በድን አካሏን ከቦ አዬ ጉድ! ሲባባልባት፤ ምነው ገና በልጅነቷ ምን አግጥሟት ይሆን እየተባለ ሲነጋገርባት ታያት፡ የፈለገው ይምጣ !! በመሞቷ ቆረጠች፡፡ ከዚህ በላይ መከራን የምትቋቋምበት አቅም ፈጽሞ የላትም አሁን ለሷ የሚያስፈልጋት
እረፍት ብቻ ነው፡፡ ቆማም ቢሆን ሞታለች፡፡የትኛው አለም ከእንግዲህ
ያጓጓታል? እናትዋ፤ ሻምበል ብሩክ፤ አባትዋ ፤ የሌሉበት ባዶ አለም?
መፍትሄው መገላገል ብቻ ነው! ስትል ደመደመች፡፡ በዚህ ውሳኔዋ መካከል ግን ሌላ ሃሰብ መጥቶ ድንቅር አለባት፡፡ ለምን ትህትና? ለምን? እናትሽ እኮ ተስፋዋ ገና አላበቃም፡፡ ሞትሽን ስትሰማ አንድ ቀን
እንደማታድር አታውቂም? ወንድምሽ አንዱአለም ገና ታዳጊ ልጅ እኮ ነው ። ለምን ለሱሰ አታስቢለትም? ካላንቺ ማን አለው? እየተሰቃየሽም የምትከፍይው የመስዋእትነት ዋጋ ስለሆነ ቻል ብታደርጊውስ ? እያለ ይሟገታት ጀመር፡፡ እናቷና የምታፈቅረው ወንድሟ መጡባት፡፡ይህ ድርጊት ሲፈጸም ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ታሰባት። በሞቷ ልትቀጣቸው ቀፈፋት፡፡ ሰውነቷን ውርር አደረጋት፡፡
ይሄንን ሹክ ያላትን እርኩስ መንፈስ ሸሸችው፡፡ ፈራች፡፡
“ምነው ከአዜብ ጋር እንደዚህ ያለውን ምክር ባልተማከርኩ ኖሮ? ምነው እውነቱን በነገርኩት ኖሮ? ” እያለች ስትፀፀት፤ ስታለቅስ መንጋቱ አይቀርምና ለሁለቱም ያ ሌሊት በስቃይ ነጋላቸው፡፡
ሻምበል በማለዳ ተነሣና ልብሱን ለባብሶ፤ የመኝታ ቤቱን በር ከፍቶ፤ ቀስ ብሎ ገባ፡፡ በእንባ ምክንያት ተበላሽቶ ያደረው ፊቷን
ሲመለከት ከልቡ አዘነላት፡፡ ቀስ ብሉ ሄዶ ኣልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠና...
“ግን ለምን እንደዚህ ትሁት ?” አላት ልቡ አሁንም በሃዘን እንደተነካ፡፡
እንደዚያ ቅስሙ ስብር ብሎ ስትመለከተው አልቻለችም፡፡ እንጀቷ ተላወሰና፧ ሄዳ እላዩ ላይ ተጠምጥማ፤ እንደ አዲስ ጧ! ብላ ትንሰቀሰቅ ጀመር፡፡ ሻምበል በረጅሙ ተንፍሶ፤ አተኩሮ አያት፡፡ አለቃቀሷ በብሶት የታፈነና ሳግ የተቀላቀለበት ነበረ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ሻምበል ብሩክ በሁኔታዋ እጅግ አዝኖላት ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ ብድግ አለችና
እያለቀሰች የሆነውን ሁሉ ትነግረው ጀመር፡፡ የምትነግረውን ታሪክ
አዳምጦ ካበቃ በሁዋላ፡፡
“ተይው በቃ ትሁት! ቁርጡን ለማወቅ እንጂ የሆነውን ሁሉ በዐይኔ በብረቱ አይቼዋለሁ፡፡ ተይው አትጨነቂ” አላት፡፡
ምን እንዳየ ገርሟት እስከሚነግራት ድረስ አይን አይኑን እያየች በጉጉት ጠበቀችው፡፡
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ድሮ የሰማችው የንፁሁ የአቢላዛር ታሪክ ትዝ አላት፡፡ኤቢላዛር በሀሰት ውንጀላ በአባቱ ዘንድ እምነት ያጣና፤ባልሰራው ወንጀል፡ ከባድ ስቃይና ቅጣት የደረሰበት እናቱ በህጻንነቱ የሞተችበት ወጣት ነበር፡፡አቢላዛር በቁንጅናው ምክንያት በሕይወቱ ላይ ታላቅ ስቃይና
መከራ ደርሶበታል፡፡የአቢላዛር አባት ባትሮሊዮ ሕጻን ልጁን እናትም አባትም ሆኖ አሳደገው፡፡ አቢላዛር ዕድሜው ለአቅመ አዳም ሲደርስ አባቱ ባትሮሊዮ
ሚስት ለማግባት ፈለገ፡፡ሚስት ቢያገባ ለእሱም፤ ለልጁም፤ ረዳት - እንደምትሆን
በመገመት በዕድሜዋ ወጣት የሆነችውን ውቧ ጉቲኤራን አገባት፡፡ጉቲኤራ በቁንጅናዋ እዚህ ጉደለሽ የማትባል ብትሆንም፤ በራሷ ቁንጅና ላይ የነበራት ኩራት ወደታች የወረደው ፤ የባሏን ልጅ አቢላዛርን ያየችው ዕለት ነበር፡፡ በዚያን ዕለት በፍቅር የተነደፈ ልቧን ሐኪምም፤
ፀበልም፤ ማንም እንደማያድነው አወቀች፡፡ መድሃኒቱ አንድ ነው፡፡ እሱም
አቢላዘር ብቻ! ስሜቷን አምቃ እየተሰቃየች፣ በአንድ ወገን የእንጀራ ልጂ
የመሆኑ ጉዳይ ቢያስጨንቃትም፤ ፍቅሯን መቋቋም አልቻለችምና፤የእንጀራ ልጅነቱን ጉዳይ ችላ በማለት፤በፍቅር ልታጠምደው ቆርጣ ተነሳች፡፡
ጉቲኤራ በፍቅር የተረታችለት መሆኑን እንዴት አድርጋ እንደምትገልጽለት ጨንቋት ውስጥ ውስጡን ስትሰቃይ ኖረች።ቀስ በቀስ ውስጥ ውስጡን የሚያብሰለስላት፣ የሚያብከነክናት፤
የፍቅር መጋዝ፤ በአካሏም ላይ ለውጥ እያስከተለ ሄደ፡፡
አፏን ከፍታ ፍዝዝ፣ ድንዘዝ፣ ብላ የምትቀርበት ጊዜ ጥቂት አልነበረም፡፡ ይህ ሁኔታ ለአቢላዛር በፍፁም አልተገለጠለትም ነበር፡፡በእርግጥ አቢላዛር ማንም በቀላሉ አይቶት የሚያልፈው ልጅ አይደለም፡፡ ያጓጓል፡፡ በዚሁ መሀል ለጉቲኤራ አንድ አጋጣሚ ተፈጠረላት። በጣም አስደሳች አጋጣሚ፡፡
ባሏ ባትሪሊዮ ግመሎቹን በሙሉ እየነዳ
የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለማምጣት ድንበር ጥሶ የሚሄድበት ቀን ደረሰ፡፡
ባትሮሊዮ ቢያንስ ከሁለት ወራት በፊት አይመጣም፡፡ በቃ በዚህ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የሚያለቅሰው ልቧ ፈውስ ሊያገኝ ነው፡፡ እሺ አለም እንቢ፤ በውድም ይሁን በግድ፤ አቢላዛርን ማግኘት አለባት፡፡ እንቢ ቢል ልታስገድደው ወሰነች፡፡
አቢላዛር እናትም አባትም ሆኖ ላሳደገው ለአባቱ ያለው ፍቅር የተለየና በአለም ላይ ከሚያፈቅራቸው ነገሮች ሁሉ በላይ ነው፡፡
የአባቱ የጉዞው ቀን ደረሰ፡፡ አቢላዛር አባቱን በፍቅር ተሰነባበተው፡፡ ጉቲኤራ ደግሞ በቶሎ አይመልስህ ብላ ሸኘችው፡፡ ከዚያም ባትሮሊዮ በሄደ በሳምንቱ ጉቲኤራ ተቅበጠበጠች፡፡ ከዚህ በላይ ብትቆይ የምትፈነዳ መሰላት፡፡ከዚህ በላይ መቆየት መታገስ አቃታት፡፡ አቢላዛር
ደግሞ እስከአሁን ድረስ ቅንጣት ታክል ችግሯን አልተረዳላትም፡፡
በሣምንቱ መጨረሻ፤ ያ ምሽት፤ እንደወትሮው ሁሉ፤ አቢላዛር የመኝታ ክፍሉን በር ቀርቅሮ የተኛበት ምሽት ነበር፡፡ ጉቲኤራ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ ሲሆን የውስጥ ሱሪዋን ብቻ እንደለበሰች ወደ መኝታ ክፍሉ መጣች፡፡
“አቢላዛር! አቢላዛር ድረስልኝ! እባክህ በሩን ቶሎ ክፈትልኝ!”
እያለቀሰች በሩን በሃይል መታቸው፡፡
አቢላዛር በዚያን ሰዓት በሆነ ቅዠት ላይ ነበረ፡፡ በሩ በሃይል ተንኳኳ፡፡ ተንጓጓ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእንቅልፉ ባኖ ቢያዳምጥ፤ የእንጀራ እናቱ በእንባ ሲቃ በታፈነ ድምጽ ስትጣራ ሰማ፡፡ በሁኔታው በጣም
ተደናገጠና በሩን ከፈተው፡፡
የሚያየውን ነገር ማመን አቅቶት፤ አሁንም በህልሙ እንዳይሆን ተጠራጠራና፧ አይኖቹን አሻሽ፡፡ በርግጥም በህልሙ አልነበረም፡፡ በውኑ ነው፡፡

የጉቲኤራ ራቁት ገላ፣ ያገጠገጡ ጡቶቿ፤ ባለጥንድ አፈሙዝ ድግን መትረየስ መስለው፤ ከፊት ለፊቱ ተወድረዋል፡፡
ዓይኖቿ በማያቋርጥ የእንባ ምንጭ ይዋኛሉ፡፡
“ምን ሆንሽ ጐቲኤራ?” ደንግጦ ጠየቃት፡፡
“አነቁኝ፡፡ መጡብኝ ሊበሉኝ ነው” ወተወተች፡፡
“እነማናቸው? ማን አባቱ ነው ሊበላሽ የመጣው?”
በእንጀራ እናቱ ላይ እጁን የሰነዘረውን ጠላቱን ሊተናነቀው አይኖቹ በንዴት ቀልተው ጠየቃት፡፡
“ግዴለም ቆይ ቁጭ በል፡፡ አሁን ሄደዋል፡፡”
“ጅል፤ ነገር የማይገባህ ደደብ” አለችው በልቧ፡፡ እኒያ የቆሙ ጡቶቿ ያ ውብና ማራኪ ራቁት ሰውነቷ የማይታየው እውር አናደዳት፡፡
“ሰይጣኖች ናቸው፡፡ ሰዎች አይደሉም፡፡ ይኸውልህ እዚህ ላይ ነው በጣም የትጫኑኝ፡፡ ተመልከት እዚህ ጋ” የቀኝ እጁን ይዛ ጡቶቿ መካከል አስቀመጠችው፡፡
አቢላዛር በየዋህነት እዚያ ጡቶቿ ሥር የሚሰማትን ህመም እንዲወገድላት አሻሻት፡፡
በዚያን ሰዓት ጉቲኤራ ጦፋ በሃሣቧ ከዚያ በኋላ በሚፈጠረው
ትርኢትና፤ በትርኢቱ ውስጥ የሚስማትን የእርካታ ስሜት እያጣጣመችው ነበር፡፡
“በቃ እዚሁ እሆናለሁ ከአሁን በኋላ እዚያ ዳፍንታም ክፍል አልመለስም” አለችውና ሄዳ እሱ አልጋ ላይ ቁጭ አለች፡፡
“ብርድ ይመታሻል ልብስ ልበስ” ብሎ የራሱን ሸሚዝ እላይዋ ላይ ጣል ቢያደርገው ፤ ወደዚያ ውርውር አድርጋ...
“ይልቁን እሱን በደንብ አድርገህ እሽልኝ፡፡ ያለበለዚያ ያመኛል
በታዘዘው መሠረት እዚያ ጡቶቿ
ሥር፧ሰይጣኖቹ ያሳመሟትን ቦታ፤ ለማዳን ማሻሸት ቀጠለ፡፡ጉቲኤራ ደግሞ እንደዚያ
ጡቶቿን ሲያሻሽላት የምትሆነውን አጣች፡፡ እንደሰም ቀልጣ መፍሰስ ጀመረች።
ሙሉውን ሌሊት በእንባ እየታጠበች ብትለምነው ንዴቱ እየባሰበት እንጂ ሃሣቡን የመለወጥ አዝማሚያ ሳያሳይ ቀረ። በዚህ ሁኔታ በተደጋጋሚ ፈተነችው፡፡ አቢላዘር ግን ወይ ንቅንቅ! አለ፡፡
በመጨረሻም እንዳልተሳካላት ቁርጧን ስታውቅ፤ ልትበቀለው ቆርጣ ተነሳች፡፡
ሴራዋን ስትጎነጉን ሰነበተች፡፡ ባሏ ከሁለት ወር በኋላ ሲመጣ፣በናፍቆት ከመቀበል ይልቅ፤ እሳት ጎርሳ፤ እሳት ለብሳ፤ ተቀበለችው:: የሁለት ወር ሙሉ ናፍቆት አቃጥሎት ሲስማት አመናጨቀችው፡፡
“የጋብቻ ውላችንን አፍርስልኝ” ስትል ጮኽችበት ባትሮሊዮ በነገሩ ተደናግጦ ምክንያቱን ቢጠይቃት...
“ምንም እንኳን ባልወልደው፤ ልጅህ ፤ ልጄ ይሆናል ብዬ ነበር እዚህ ጣጣ ውስጥ የገባሁት፡፡ እሱ ግን ለሚስትነት ፈለገኝ” ብላ ከፍላጐቷ ውጭ አስገድዶ በግብረ ሥጋ የተገናኛት መሆኑን እያለቀሰች ነገረችው፡፡
ባትሮሊዮ እንደ አይኑ ብሌን የሚያየው አንድዬ ልጁ፣ እናትም አባትም ሆኖ ተሰቃይቶ፣ በሽንት ተጨማልቆ ያሳደገው የሚወደው ልጁ ተመልሶ እጁን ስለነከሰው ፤ ሀዘኑ ጣራውን አለፈና፤ ለዚህ ወደር ለሌለው ጥፋቱ ቅጣቱን ሲያውጠነጥንለት ዋለ፡፡በመጨረሻ የመጣላት ሃሣብ መግደል ቢሆንም፧ መግደል ብቻውን አላረካህ አለው፡፡ ከዚያ በላይ በቁሙ እያለ እንዲቀጣ ፈለገ፡፡
እንደዚያ በጥጋብ እንዲያነጠንጥ፤ እንደዚያ ያለውን አፀያፊ ሥራ እንዲሠራ፤ የገፋፋውን ችግሩን ከላዩ ላይ ሊያስወግድለት ወሰነና፤ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ የመኝታ ቤቱን በር አስከፍቶት ገባ፡፡
አቢላዘር ከእንቅልፉ ባንኖና፤ በሁኔታው ተደናግጦ፡
“ምነው አባባ?” ሲል ጠየቀው፡፡
“ዝም በል!! የምትታዘዘውን ብቻ ትፈጽማለህ!!” ሲል ጠንካራ ትዕዛዝ ሰጠው፡፡አባቱ እሳት ለብሶ፤ እሳት ጉርሶ፤ ሲያይ ልጁ በአባቱ አዲስ ፀባይ ተደናግጦና፤ ግራ ተጋብቶ፤ የታዘዘውን ሁሉ በአክብሮት ይፈጽም ጀመር፡፡ራቁቱን አስቁሞ እጁንም እግሩንም አሰረው፡፡ ያለተቃውሞ
በአባቱ ትዕዛዝ መሠረት እጁንም፤ እግሩንም፤ ለገመድ ሰጠ፡፡
“በሽንትህ ተጨማልቄ፤ ያለ እናት ያሳደግኩህ አባትህ መሆኔን አውቀህ ፤ ቤቴን ትዳሬን አክብረህ ስለቆየኸኝ ፤የረጅም ዘመን ድካሜን ዋጋ ለመክፈል እንቅልፍ አጥተህ ስለጠበቅከኝ፤ ይህንን የዋልክልኝን ከፍተኛ የልጅነት ውለታህን ተቀብዬ፤ እኔም የአባትነት ውለታዬን
🔥21👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


እቅዳቸው በአሳዛኝ ሁኔታ መክሸፉን፤ መክሸፍ ብቻም ሳይሆን የሷና የሻምበል ብሩክ ፍቅር እስከ ወዲያኛው ዳግም ላይጠገን እንክትክት ብሎ መሰባበሩን ስትሰማ አዜብ ክፉኛ ደነገጠች፡፡ ምን
የማይሆን ምክር መክሬ ጉድ ያደረኳት፤ በሚል ጸጸት ተቃጠለች፡፡ ለዚህ
ችግር መንስኤው እሷ እንደሆነች
ሁሉ “እኔ ነኝ ጉድ ያደረኩሽ ትሁትዬ፡፡ እኔ ነኝ ጥፋተኛዋ፡፡ ድሮውንም ቢሆን አንቺ አይሆንም ብላሽ ነበር። አጉል የማይሆን ምክር መክሬ እዚህ ጣጣ ውስጥ የከተትኩሽ እኔ ነኝ፡፡በደሉ የኔ ነው፡፡ ወይኔ ጓደኛዬ... እዬዬ እያለች አብራት
ስታለቅስ ዋለች፡፡

እየዋለ እያደረ ግን ለትህትና ህይወት መበላሽት ዋናው ምክንያት እሷ ያለመሆንዋን፤ ትህትና ለተደጋጋሚ ፈተና የተጋለጠችው በሷ ምክንያት ሳይሆን በሌላ ሰው ጦስ መሆኑን፤እያመነች መጣች፡፡የወንጀል ድርጊቱ እንደተፈፀመባት ወዲያውኑ ህጋዊ እርምጃ ማስወሰድ ሲችሉ፤ እንደሻው የአዜብ ወላጆች የክርስትና ልጅ ነው፤ አባቱም ለትህትና ባለውለታ ናቸው፤ በሚል ሰበብ ጉዳዩን አዳፍነው፤ አለባብሰው ማለፋቸው ተገቢ ያለመሆኑ እየተገለጠላት መጣ፡፡ በዚያን ሰአት በደም ተጨማልቃ የጠበቀቻት ትህትና ታየቻት፡፡ ከዚያም ከዶክተር ባይከዳኝና
አሁን ደግሞ ከሻምበል ብሩክ ጋር ለነበራት ግንኙነት ዋናው የጸቡ
መንስኤ የእንደሻው ጦስ መሆኑ ያለጥርጥር ታወቃት፡፡ እንደሻው በሰላም
እንቅልፉን ይለጥጣል፡፡ ትህትና ግን በየቀኑ ታነባለች፡፡ በዚህ ላይ አንድም
ቀን እንኳን የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶት ይቅርታ ጠይቆ አያውቅም፡፡ስለዚህ የእጁን ማግኘት አለበት ብላ ወሰነች፡፡ በእንደሻው ምክንያት ትህትና ክብረ ንጽህናዋን፣ ሥራዋን፤ እጮኛዋን፤ አጥታለች። ግዴለም! ስትል በልቧ ዛተች፡፡

አንዱ አለም በሁኔታው ግራ ተጋብቶ.. “እታለም ሥራውን ተውሽው እንዴ?” ብሎ የጠየቃት እለት “ትንሽ ዕረፍት ወስጄ ነው
አልተውኩትም” ብላ ዋሽታው ነበር፡፡ በኋላ ግን በውሸቷ መቀጠል አልቻለችም፡፡ ሥራው ያልተስማማት በመሆኑ ያቋረጠችው መሆኑን
ገለፀችለት፡፡
“አይዞሽ ቆንጆ የቢሮ ሥራ ነው የምትይዥው፡፡ የምን ጫማ
መሸጥ ነው”? ሲል ሞራል ሰጣት፡፡
ከሥራው የበለጠ እንዱዓለምን ያሳሰበው እህቱ ይሄንን ሰሞን ሙሉ ለሙሉ መለወጧን፣ በሆነ ባልሆነ ማልቀስ ማብዛቷን፣ ሲጠሯት ቶሎ ያለመስማቷን፣ ፍዝዝ ማለቷን፣ እህል እምብዛም ያለመድፈሯን፣ እንዳትሞት ያህል ብቻ አፏ ላይ ጣል , አድርጋ በቃኝ ማለትን
ማዘውተሯን፣ ሰውነቷ እየጠወለገ መሄዱን፣ በአጠቃላይ ሻምበል ብሩክን
ካገኘች በኋላ ደስተኛ መሆን የጀመረችው ልጅ ሰሞኑን በሚገርም ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ተለውጣ በማስተዋሉ ነው፡፡

በዚህ ላይ ደግሞ እንደታላቅ ወንድሙ የሚያየው “አንዱዓለም እስቲ እንካ ይህችን ለደብተር መግዣ፣ ለፀጉርህ መስተካከያ አይዞህ በርትተህ ተማር” እያለ የሚንከባከበው የእህቱ እኛ የሻምበል ብሩክ ድምፁ እየጠፋ ነው፡፡ ነገሩ አሳሰበው፡፡ አጠራጠረው፡፡
ይሄ ሁኔታ ከሳምንት በላይ አስቆጠረ፡፡ አንዱዓለም ጥርጣሬው እየጨመረ መጣ፡፡ እህቱ ምንም ነገር ልትነግረው ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡ መላው ቢጠፋው አዜብን ሊያማክራት ፈለገ፡፡
አዜብ አንጀቷ እየተቃጠለ፤ የዚህ ሁሉ በደል ምንጭ የሆነው እንደሻው የሚቀጣበት መንገድ ጨንቋት ውስጥ ውስጡን በንዴት ስትንጨረጨር ነው የከረመችው፡፡
አንዱዓለም ስለእህቱ ሁኔታ ሲጠይቃት፤ ተደስታ አንድም ሳታስቀር እንደሻው የፈፀመባትን ወንጀል ዘከዘከችለት፡፡ በእህቱ ላይ የተፈፀመውን ወንጀል ሲሰማ አንዱአለም በንዴት ተንዘፈዘፈ። ከዚያም
በላይ እንደ እብድ አድርጎት ነበር፡፡ ከዚያም ያንን ግፈኛ ሊበቀለው
የሚገኝበትን ቦታ ጠየቃት፡፡
አዜብ አላመነታችም፡፡ “አሳይሀለሁ” አለችው፡፡ ለዚሁ ጉዳይ ተቀጣጠሩና፤ እንደሻው የሚገኝበትን ሱቅ ልታሳየው ይዛው ሄደች፡፡
ትህትና ይህንን ሁሉ አታውቅም፡፡ ወንድሟ ከሰው ጋር ተጣልቶ አደጋ እንዳይደርስበት ስለምትሰጋ፤ በፍፁም እንዳይሰማ አዜብን አደራ ብላት ነበር፡፡ አዜብ ግን እሺ አልነግረውም ብትላትም፤ እሱ ቀድሞ ባይጠይቃት ኖሮ ቀድማ ልትነግረው ተዘጋጅታ ነበር፡፡
በሷ እምነት እንደሻው ለፈፀመው ግፍ ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡ ለወንጀሉ በቂ ቅጣቱን ማግኘት አለበት፡፡ አለበለዚያም በአፏ አላወጣችውም እንጂ ፤ በሱ ምክንያት ከባድ ችግር ላይ የወደቀች ልጅ
በመሆኗና ክብረ ንጽህናዋን የደፈረው እሱ በመሆኑ ወደደም ጠላም
ሊያገባት ይገባል ነው እምነቷ፡፡
የዚያን ዕለት አንዱዓለም እንቅልፍ በዐይኑ ሳይዞርለት ነጋ:: አንጅቱ እያረረ አደረና፤ በማግስቱ ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሲሆን ብቻውን ወደዚያ ሱቅ ሄደ፡፡
ከሱቁ ሲደርስ እንደሻው ሲጃራውን እያቦነነ አገኘው፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ሲጃራውን ምጉ ቁራጩን በእግሩ ደፈጠጠና የመጣለትን ቁርስ ሊበላ
ሻይ በመቅዳት ላይ እንዳለ፤ ዐይኖቹ እንደ በርበሬ ቀልተው፤ ፊቱ ሳምባ እንደመሰለ፤ በንዴት መላ ሰውነቱ የሚንቀጠቀጥ ወጣት በሩ ላይ ገጭ አለበት፡፡
አንዱአለም የሰራ አካላቱን እንደ ኤሌክትሪክ የሚነዝር የጥላቻ
ስሜት ወሮት ተንደርድሮ ሄደና ያንን የሻይ ማንቆርቆሪያ አንስቶ ፊቱ ላይ ቸለሰበት፡፡ እንደሻው በዚያ ትኩሳ ሻይ ተቀቀለ፡፡ በድንጋጤ ከባንኮኒው ላይ ዘሎ ወጣና ግብ ግብ ተያያዙ፡፡

አንዱዓለም በእህልና፤ በቁጭት፤ ሰይጣናዊ ጉልበት ተላብሷል፡፡
እንደሻው ግን በብርክ ስለተዋጠ ሊቋቋመው አልቻለም፡፡ እየደጋገመ ፊቱን
እንደተርብ ጠዘጠዘው፡፡ ከዚያም ትንሽ በትንሹ ከድንጋጤው ተመልሶ
አንዱዓለምን ሊያንቀው ሲዘጋጅ ጐረቤትም መንገደኛም መሀል ገባና
ገላገላቸው፡፡
አንዱዓለም እየጮኸ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ይሳደብ ጀመር፡፡
“አንተ የውሻ ልጅ!! በዚህ ብቻ የምለቅህ እንዳይመስልህ...!”
አለው፡፡ እንደሻው እየተርበተበተና በድንጋጤ ዐይኖቹ እንደተበለጠው
ይህንን ሰይጣን ማን ላከብኝ በሚል ስሜት ግራ ተጋብቶ ይመለከተዋል፡፡
አበራ በሃሣቡ ድቅን አለ፡፡ “በቃ አበራ የላከው ሰው መሆን አለበት” አለ በልቡ፡፡

መቼም አንዳንድ ግዜ ፍቅር እንደ አጀማመሩ አያልቅም፡፡
በተለይ በጥቅም ላይ የተመሰረተ ፍቅር ዕድሜው አጭር ነው፡፡ ከአበራ ጋር ንግዱን የጀመሩ ሰሞን ፍቅራቸው ሌላ ነበር። እየዋለ እያደር ሱቃቸው ሲደረጅ፣ ጠቀም ያለ ገንዘብ መምጣት ሲጀምር፣ እንደሻው ተስገበገበና፤ ሞቅ ባለው የሽርክና ፍቅራቸው ላይ ቀዝቃዛ
ውሃ ቸለሰበት፡፡
የዚያን ዕለት አበራን የተናገረው ንግግር ትዝ አለው፡፡ “አበራ እስከዛሬ ድረስ የወሰድከው ሳይታሰብ፤ ያዋጣኸውን ገንዘብ በጥሬው እመልስልሃለሁ፡፡ ግድ የለም እኔ ልጐዳ” በማለት ነበር በድንጋጤ ያስበረገገው፡፡
“እና ሱቁን የግልህ ብቻ ልታደርገው?” አበራ በንዴት እየተንቀጠቀጠ፡፡
“የንግድ ፈቃዱ የግሌ መሰለኝ፡፡እዚህ የምፍጨረጨረውም በግሌ
አንተም ከዚህ በላይ ልትጐዳኝ የምትፈልግ መሆኑን እያየኽው
አይመስለኝም” ቁርጡን ነገረው፡፡
“እሺ እንደሻው እግዚአብሔር ለሁላችንም የሥራችንን ይስጠን፡፡ አንተ ግን ሰው አይደለህም! እባብ ነህ! ያንተ ነገር በቃኝ!ሥጋዬም አይደለህ፡፡ በቃኝ! በቃኝ!” እያለ እየተማረረ እየተንቀጠቀጠ
ከሱቁ ወጥቶ የሄደው ትዝ አለው፡፡ በዚሁ ሀሳብ መሀል ግን...
የትህትና ወንድም መሆኔን እወቅ!” ለሠራኸው ሥራ በዚህ ብቻ የምንላቀቅ እንዳይመስልህ! እስከመጨረሻው እፋረድሃለሁ!!” በማለት ፎከረበት፡፡

በዚህ ጊዜ እንደሻው አመዱ ቡን አለ፡፡ እሱ እንደሆነ ትህትናን ከነመፈጠሯ ነበር የረሳት፡፡ አሁን ግን ጉድ ሊፈላ ነው፡፡ የሚበቀል ወንድም አላት ለካ !!
👍3
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

..“ይሸጣል እንዴ?” ከመካከላቸው አንዱ፡፡
“አሉልህ እኮ አሁን ወጣ ብለን ብንፈልግ ደማቸውን እንደ ጭማቂ ለመሸጥ የሚንጐራደዱ አይታጡም" ”ሌላው፡፡ ይሄ ደግሞ የገንዘብ መስዋዕትነትን ጠየቀ፡፡ አሁንም ተፋጠጡ፡፡
“አቦ ትጠራ ምን ትሆናለች” ባዩ በዛና ትህትና ይሄንን መርዶ በጠዋቱ እንድትረዳ ፈረዱባት፡፡ ከዚያም ልጁ ሊጠራት እየበረረ ከሆስፒታሉ ወጣ፡፡
እሷ በዚያን ሰዓት አገር ሠላም ነው ብላ ለእናቷ የምትወስደውን ምግብ እያዘጋጀች ነበር፡፡ ወንድሟ ለሷ ለሚወዳት እህቱ ብሎ በዚህች
ስዓት በሕይወትና በሞት መካከል ይገኛል፡፡
በጠዋቱ የተንኳኳውን በር ሄዳ ከፈተች፡፡ ለምን እንደሆነ አላወቀችም ልቧ ሽብር ሽብር አለባት፡፡
“አንዱአለም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገብቷል” አላት ጭክን ብሎ።
“ኡ ይ!” ምን ሆኖ!” ጮኸች።
“ሰው ደብድቦት፡፡ አሁን በአስቸኳይ ደም ተጠይቋል” ቁርጡን ነገራት። ከዚያ በኋላ ያደረገችውን አታውቅም፡፡ የሞተ ነው የመሰላት፡፡
የውጭውን በር በርግዳ....
“ኡኡ.... አንዱዬ ...! አንዱዬ....! ወንድሜን!... ወንድሜን!”
ሩጫዋን ቀጠለች። ልጁም ከኋላ ከኋላዋ እየተከተለ ተያይዘው ቁልቁል ይሮጡ ጀመር፡፡ እንደዚያ ራሷን ስታ እየጮኸች ስትሮጥ የሚያያት ሰው በጣም ነበር ያዘነላት፡፡ እንባዋ እንደጉድ ይፈሳል፡፡
ከጥቁር አንበሳ ት/ቤት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለመሻገር ከላይም ከታችም መኪና ማየት ሲገባት፤ እንደዚሁ ግብኗን እየበረረች ግማሹን አስፋልት ተሻግራ ደሴቱን አቋረጠችና ወደ ሁለተኛው አስፋልት ጥልቅ ብላ ገባች፡፡
ከዚያ ከላይ ከቴዎድሮስ አደባባይ ቁልቁል እየበረረች የምትመጣው ውይይት ታክሲ በድንገት ጥልቅ ብላ የገባችውን ልጅ ለማዳን ሹፌሩ ፍሬኑን በሃይል ሲረግጠው፤ መኪናዋ ወደጐን ዞረችና ደሴቱ መሐል ገብታ ተቀረቀረች፡፡
እዚያ ታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች በድንጋጤ ውሃ ሆነዋል፡፡ ትህትና የዚህ ሁሉ መንስኤ እሷ መሆኗን አታውቅም፡፡
ሩጫዋን አላቆመችም፡፡ ልጁ በተፈጠረው አደጋ ተደናግጦ ጭንቅላቱን
በሁለት እጆቹ ይዞ ቀረ፡፡ ከዚያም ሮጦ ደረሰባትና! እጇን ይዞ ይማፀናት
ጀመር፡፡ አልሰማ አለችው፡፡ ያለው አማራጭ ከኋላ ከኋላዋ መሮጥ ብቻ
ነበር፡፡ ተያይዘው ሆስፒታል እንደ ደረሱ፤ እነዚያ የሆያ ሆዬ ጓደኞቹ ተሰባስበው! ተቀበሏት፡፡
“የት ነው ያለው? ወንድሜ የት ነው? አንዱዬ የታለ? ሞቶ እንደሆን ንገሩኝ” ትለፈልፋለች፡፡ ከስንት ልመና በኋላ እንደምንም ብለው ሊያረጋጓት ሞከሩ፡፡ ከዚያም ሀኪሞች “አይዞሽ ደህና ነው” ብለው ካጽናኗት በኋላ ደም እንድትሰጥ ተደረገ፡፡
“ወንድሜን ዐይኑን ልየው እባካችሁ?” እያለች ፤ እያለቀሰች ብትለምንም “ሪከቨሪ” ስለሆነ መግባት አይቻልም ተባለች፡፡
ቀስ በቀስ ነፍሷን መግዛት ስትጀምር፤
ለአዜብ ስልክ አስደወለችላትና አዜብ መጣች፡፡ አዜብ ሁኔታውን እንዳረጋገጠች...
“ምን መዘዘኛ ነኝ?” የሚል መጥፎ ስሜት ተሰማት፡፡ ሚስጥሩን ስትነግረው በፍፁም የዚህ አይነቱ አደጋ ይደርስበታል ብላ አልገመተችም ነበር። ትንሽ እዚያ አካባቢ ዞር፤ ዞር፤ እያለች ከቆየች በኋላ፤ ሹልክ ብላ ሳትነግራት ወደ ቤቷ ሄደች፡፡
ትህትና ጨንቋት፤ አጽናኝ በምትፈልግበት ሰዓት ላይ ጓደኛዋን ብትፈልግ አጣቻት፡፡ ወዲያና ወዲህ ተዘዋወረች፡፡ ተዟዟረች፡፡ አዜብ ግን የለችም፡፡ በመጨረሻ ላይ እቤት ስልክ ደወለች፡፡ “የለችም” አስባለች፡፡ እየመሸ መጣ፡፡ እንደገና ስልክ ደወለች፡፡ አሁንም የለችም ተባለች፡፡
ክው ብላ ደነገጠች፡፡ “ምነው? ምን አደረኳት አዜቢናን?” ሽምቅቅ ብላ፤ ስልኩን አስቀምጣ፤ ብቻዋን ጭር ያለ ቦታ ፈልጋ ተቀመጠችና፤ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ እናቷ የካቲት አስራ ሁለት
ሆስፒታል፣ ወንድሟ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ምን ዓይነት ስቃይ
ነው? እንደተመኘችው ሳታየው መሸ፡፡ በማግስቱ እናቷን ጠይቃ፤ ወደ
ወንድሟ መጣች፡፡ ልታየው አልቻለችም፡፡ ፀጉሯን እንኳን ማበጠር አቁማለች፡፡ እንደዚያ የምታምረው ልጅ ነገሮች ተደራርበውባት፧ ማስፈራሪያ እየመሰለች ነው፡፡ እንደዚህ ሆና መከራዋን ካየች በኋላ ወንድሟን ያገኘችው፤ በሶስተኛው ቀኑ ነው፡፡
አንዱአለም ድንበሩ ከሞት ድንበር ደርሶ ተመለሰ፡፡ በሶስተኛው ቀን፤ በሶስተኛ ማዕረግ ከቀዶ ጥገና በሽተኞች ጋር ተቀላቀለ፡፡ እንደዚያ ፊቱ አብጦና፤ ጠቁሮ፤ ስታየው የምትሆነውን ነበር ያጣችው፡፡
“አንዱዬ ምንድነው የሆንከው?” ቀስ ብላ ጠየቀችው። ከትንፋሹ
ጋር እየታገለ....
“እንደሻው... አስደበደበኝ” ብሉ ነገራት፡፡ በዚህ ጊዜ የተሰማትን ስሜት መግለጽ ያስቸግራል፡፡ አዜብ የሸሸችበት ሚስጥር አሁን ገና ወለል ብሎ ታያት፡፡ ሰውነቷን የሆነ ነገር ውርር አደረጋት :: እንደሻው
በግንባሩ ላይ ብዙ ጠመዝማዛ ቀንዶች አብቅሎ፣ ጥርሶቹ ተስለውና፤
አንደመጋዝ ሾለው፣ ጥፍሮቹ እንደ ጃርት እሾህ ተንጨፍርረው፣ ታይዋት፡፡ .
እንደሻው ... እንደሻው ... እንደሻው ... አእምሮዋን እንድትስት አድርጉ ከመታት በኋላ ሊከመርባት፤ በሀሳብዋ መጣባት፡፡ ሰውነቷ እንደሻው ምን ያላደረጋት ነገር አለ? የምትወደው ሻምበል ብሩክን ያጣችው በእንደሻው ምክንያት ነው፡፡ ዶክተር ባይከዳኝ እንደዚያ ውሻ አድርጐ የሰደባት፤ በኋላም ስለእናቷ ክፉ ንግግር የተናገራት፤ እንደሻው በፈጸመባት ወንጀል ምክንያት ነው፡፡ ስራዋንም ያጣችው በሱ
ድርጊት የተነሳ ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ግፍ ምንም የበቀል እርምጃ አልወሰደችም፡፡ እሷ ብትተወውም ግን እሱ ሊተዋት አልፈለገም፡፡
ይሄውና አሁን ደግሞ እንደ ዐይኗ ብሌን የምትሳሳለት፤ አንድና ብቸኛ ወንድሟን እንዳይሞት እንዳይድን፣ አድርጉ! አስደበደበው፡፡ ግን ለምን ይሄን ያክል ጨከነባት?
“የሰው ልጅ አይደለሁም እንዴ? ምነው ምን አደረኩት?” በሚል ጭንቀት ተውጣ ራሷን ጠየቀች፡፡ በሷ እምነት ምንም
አላደረገችውም።የፈጸመችበት በደል አልነበረም፡፡ የማፈቅረው ሰው ስላለኝ
ይቅርታ አድርግልኝ ብላ ለምና ተለማምጣ ልታግባባው ሞከረች እንጂ
አንዳችም ክፉ ነገር አልወጣትም፡፡እሱ ግን ያንን እንደ ጥቃት ቆጥሮ፤ በጭካኔ ደብድቦ፧ ክብረ ንጽህናዋን መድፈሩ ሳያንሰው አሁን ደግሞ እንደገና ,በወንድሟ ላይ የጭካኔ በትሩን አሳረፈ፡፡ግን ለምን?... ለምን?...ለምን?... ለዚህ ጥያቄዋ መልሱ ብዙም ሳይቆይ ወደ አእምሮዋ መጣላት፡፡ አላንገራገረችም፡፡ ይሄ የመጨረሻው ምዕራፍ ነው ስትል ወሰነች፡፡ የሆነውን ሁሉ በተቆራረጠ ድምጽ ነገራት፡፡
አሁን ሁሉንም ነገር ሰምታ ከጨረሰች በኋላ አዜብ አሳዘነቻት፡፡ እሷን ጠልታ ሳይሆን፤ በሷ ላይ በተደጋጋሚ ለሚደርሰው አስጠሊታ አጋጣሚ ሁሉ እጂ ስላለበት፤ መጥፎ ስሜት ተሰምቷት እንደሆነ ስታውቅ፤ “ጓደኛዬን አስጨነኳት፡፡ ጭንቀቴ እንጂ አንድም ቀን ደስታዬ
ተርፏት አያውቅም፡፡ በዚያው ለሷም ግልግል ነው፡፡” የሚል ስሜት
አደረባት፡፡

ታሪኩን በሙሉ አንድ በአንድ ሰምታ ስታበቃም፤ አሞቷ ኮስተር አለ፡፡ ለሁሉም ገደብ አለው፡፡ ትዕግሥትም ልክ አለው፡፡ እንኳንስ በደል፤ ማርም ሲበዛ ይመራል። በደል ሲደጋገም ደግሞ ከምሬት በላይ ነው፡፡ በቃ! እንደሻውን ልትበቀለው ስመ እግዚአብሔርን ጠርታ በልቧ መሀላ
ፈጸመች፡፡

አንዱዓለም የምትወደው ታናሽ ወንድሟ፤ የተፈጸመባት ግፍ አንገብግቦት ሊበቀልላት ሄዶ ጉድ ሆኗል፡፡ እሷ ደግሞ በታናሽ ወንድሟ ላይ ለተፈጸመው ወንጀል ምላሽ መስጠት አያቅታትም፡የመጨረሻው የአባቷ ቅርስ ታያት፡፡ በክብር ተሸፍኖ በሣጥን ውስጥ በድብቅ
የተቀመጠውን፣ እሷና እናቷ ብቻ የሚያውቁትን፣ መቶ አለቃ
👍2
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

#ክፍል_ሁለት
#ቬንዴታ
#ብቀላ

...በፈጸመባት ተደጋጋሚ ወንጀል ምክንያት ህሊናዋ ሊሸከመው
ከሚችለው በላይ በደል ያደረሰባት፤ እንደሻውን አጥፍታ፤ እራሷን ለማጥፋት የገባችውን ቃል ተግባራዊ የምታደርግበት የመጨረሻዋ ሰዓት
ከአክስቷ ጀምሮ የቅርብ የሆኑ ሰዎችን በሙሉ ተዘዋውራ ጠየቀች፡ስንብት መሆኑን አላወቁም፡፡

ውሣኔዋን ተግባራዊ የምታደርገው እንደ ነገ ሆኖ፤ ዛሬ ግን አሉኝ የምትላቸውን እናቷን፣ ወንድሟን፣ ጓደኛዋን፣ በደንብ አጫውታ መለየት አለባትና፤ የልቧን በልቧ ይዛ፤ እንደታላቅ እህቷ የምታየት፣ ደስታዋንም ሆነ ከሁሉም በላይ ችግሯን ስትጋራት የኖረች ጓደኛዋን በፍቅር ልትሰናበታት ሄደች፡፡
እንዳገኘቻት ሄዳ እላይዋ ላይ ጥምጥም ብላ አለቀሰች፡፡ አዜብም እንደሷው አቀፈቻትና ተላቀሱ፡፡
“በፍጹም እንደዚህ ያለ አደጋ ይደርስበታል ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ ትሁቲና እኔ ባንቺ ምንም ዕድለኛ አልሆንኩም፡፡ የኔ ድርጊትና ምክር ሁል ጊዜ ሲጉዳሽ እንጂ ሲጠቅምሽ ባለማየቴ፤ በጣም ነው
የተሰማኝ፡፡ ከዚህ ሁሉ ለምን ትንሽ ራቅ አልልላትም የሚል ስሜት ተሰምቶኝ ነው እንጂ፣አንቺን ለማሳዘን አይደለም፡፡ ይቅርታ አድርጊልኝ” በማለት እየሳመች፤ እያባበለች፤ ይቅርታ ለመነቻት፡፡
“አዜቢና ቁጭት ተሰምቶሽ ነገርሽው እንጂ፤ እንደዚህ ጭካኔ የተሞላበት የከፋ ጉዳት ያደርስበታል ብለሽ እንዳላሰብሽ ይገባኛል። በዚህ ምንም ልትፀፀቺ አይገባም፡፡ እግዚአብሔር ገና ስፈጠር ይህንን ሁሉ መከራ እንድሸከም ፈርዶብኝ ያሸከመኝ እዳ ስለሆነ እችለዋለሁ :: አንቺ
ግን ሁሌም ስቸገር ከጉኔ ከመገኘት ሌላ ምንም ያደረግሽኝ ነገር ስለሌለ
መጥፎ ስሜት በፍጹም ሊሰማሽ አይገባም፡፡ እንኳንም ብቻ ከሞት
ተረፈ፡፡ ምንም ቅሬታ አላደረብኝም፡፡ አትጨነቂ የኔ ቆንጆ፡፡ ብላ እቅፍ አድርጋ አፅናናቻትና፤ እንደ ዱሮአቸው በፍቅር ሲጨዋወቱ አረፈዱ፡፡ለሻምበል ብሩክ ስልክ ደውላ አንዱአለም ስለደረሰበት አደጋ የነገረችው መሆኑን፤ እሱም ደንግጦ "አይዞሽ እንደሻውን ገርፈን እናውጣጣዋለን" በማለት ቃል የገባላት መሆኑን፤ እውነት አስመስላ ስትነግራት አዜብ ተደሰተች፡፡ እንደሻው የእጁን እንዲያገኝ ቸኮለች፡፡

“በጣም ቆንጆ ነው ያደረግሽው ትሁትዬ የውስጥ እግሩ ወደ ውጭ እስኪገለበጥ ድረስ እንዲያስገርፈው አድርጊ፡፡ ይሄ ግፈኛ! ለሱ ምንም ምህረት አያስፈልገውም!” ስትል በቁጭት መከረቻት፡፡ ነገ ጠዋት በፓሊስ እንደሚያስወስድላትና! የሚሰራበትን ሱቅ
ለመጠቆም፡ ዛሬ ቦታውን ማየት እንደሚያስፈልጋት ስትነግራት፤ አዜብ
ልብሷን ቶሎ ለባብሳ ተነሳች፡፡መርካቶ ሄደው የእንደሻውን ሱቅ በሩቁ አሳየቻት፡፡ ሱቁን በስንት ሰዓት እንደሚከፍት ሁሉ በቂ መረጃ አገኘች፡፡ ዋናው
የእንደሻውን ሱቅ ማየቱ ነበር፡፡

ዓላማዋ እንደሻው ውስጡ ይንጐራደዳል፡፡ ለነገው ብቀላ እንድ እርምጃ ተጠናቀቀ፡፡ እዚያ ሱቅ ውስጥ ነገ... ነገ... ጠዋት ጠላቷ ገላው፣
በጥይት ወንፊት ሆኖ የወንድሟን ደም እንዳንዠቀዠቀው፣ ደሙ ይንዠቀዠቃል....

ይህንን የነገውን ትርዒት በአእምሮዋ እያውጠነጠነች፤ ተያይዘው ወደ እነ አዜብ ቤት ተመለሱ፡፡
በመሰነባበቻቸው ሰዓት ላይ ግን የትህትና ሁኔታ ትንሽ ከወትሮው ለየት አለ፡፡ ጥብቅ አድርጋ አቀፈቻት፡፡ እያገላበጠች ሳመቻት፡፡ እንደገና ... እንደገና ... እንደገና ይህ ለአዜብ እንግዳ ነበር፡፡ ትህትና
ግን የስንብት ስለሆነ አልታወቃትም፡፡

ዐይኖቿ ፍዝዝ ብለው፤ እላይዋ ላይ ተተክለው ይቀሩ ነበር፡፡ እነዚያ ውብ ዐይኖቿ፣ ለየት ያለ መልዕክት ያስተላልፉ ነበር፡፡ ስንብት! ደህና ሁኝልኝ ውዷ ጓደኛዬ.... ዐይነት፡፡ አሁን ደግሞ ትንፋሽ
እስከሚያጥራት ድረስ አቅፋ እየተሰናበተቻት ነው፡፡ይህ የትህትና ሁኔታ
አዜብን ረበሻት፡፡
“ስላስቀየምኳት ይሆን ወይስ?...” መልስ የሌለው ጥያቄ፡፡ በመጨረሻም አገላብጣ ሳመቻትና፤ ታክሲ ውስጥ ገባች። ዞር ብላ
እጆቿን አውለበለበችላት፡፡ የምሣ ሰዓት ደርሶ ነበር፡፡ ምሣ በሁለት ሣህን
አዘጋጅታ፣ ሠራተኛዋ የካቲት አሥራ ሁለት ሆስፒታል እናቷ ጋ እንድትሄድ ስታደርግ፤ እሷ ደግሞ ወደ ወንድሟ ሄደች፡፡ ሆስፒታል ውስጥ ወንድሟን ስታጨዋውተው ዋለች፡፡ አዳሯን ደግሞ እናቷ ጋ አስባለች፡፡
የቀኑን ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ ለአንዱዓለም ሰጠችው፡፡ወንድሟን ለመሰናበት ስሜቷን በእንባ ለመግለጽ አልፈለገችም፡፡ ሆዷ እንዳይባባ፤ ራሷን አጠነከረች፡፡ በእርግጥም ተሳካላት፡፡ ከምንጊዜውም የበለጠ ሳቂታና ደስተኛ መስላ ታየች፡፡

እዚያ አጠገቡ ቁጭ ብላ እንዲሁ ስትደባብሰው፣ ስታሻሽው፣ ስትስመው፣ ስታሳስቀው፤ ዋለች፡፡ ሰዓቱ እየሄደ ነው፡፡ የምታዘጋጀው ደብዳቤ አለ፡፡ እናቷ ዘንድ አዳሪ ነች፡፡ ልትለየው ባትፈልግም ፤ ጣጣዋ ብዙ ነውና፤ ልትሰናበተው ተዘጋጀች፡፡

በዚያን ሰዓት ግን ቆራጥ የነበረችው ልጅ ተረታች፡፡ ሳታስበው እላዩ ላይ ድፍት እንዳለች ቀረች፡፡ ሆዷ ቡጭ ቡጭ አለ፡፡ መተንፈስ አስከሚያቅተው ደረስ እላዩ ላይ ተጣበቀች፡፡
በሽተኛ መሆኑን ዘንግታ፤ አየር አሳጠረችው፡፡ እንዱዓለም ቶሎ
ቶሎ መተንፈስ ሲጀምር፤ ደንግጣ ቀና አለችለት፡፡ በዚያን ጊዜ ግን ዕይኖቿ በእንባ ተሞልተው ነበረና፤ እንባዋ እየወረደ ፊቱን አረጠበው፡፡
“ተሽሎኛል እኮ እታለምዬ ለምን ታለቅሻለሽ?” ለመጨረሻ ጊዜ እንደምትሰናበተው ያላወቀው ወንድሟ፡፡ እየደጋገመች ሳመችው፡፡ “ደህና
ሁንልኝ አንዱዓለሜ” ከሳግ ጋር እየተናነቀች ተነሣች፡፡
“ደህና እደሪ እታለም” በአለቃቀሷ ሆዱን ባር ባር እያለው፡፡ ከዚያም ወደ ኋላ ገልመጥ አለችና ባይ ባይ " በማለት እጆቿን አወዛወዘችለት፡፡ የመጨረሻ ስንብት፡፡ ከዚያም በሚንከራተቱት ዐይኖቿ
በስስት ተሰናበተችውና፤ ፈጠን ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣች፡፡

እቤት እንደደረሰች ለሻምበል ብሩክ ደብዳቤ ትጽፍ ጀመር፡፡
“ይድረስ ለማፈቅርህ ውድ ወንድሜ ለሻምበል ብሩክ በላይ ለጤናህ እንደምን አለህልኝ፡፡ እኔ እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደህና ነኝ፡፡ ብሩኬ በጣም ናፍቀኸኛል፡፡ ግን ምን ያደርጋል? አልታደልኩምና ናፍቆቴን መወጣት አልችልም፡፡ይህ የመጨረሻው ቃሌ ስለሆነ አንድ ነገር ልጠይቅህ? ይህንን ደብዳቤ አንብበህ ከመጨረስህ በፊት እንዳታቋርጠው እሺ? ዛሬ የምንግርህ በሙሉ ቁም ነገር ነው እሺ? ብሩኬ መጀመሪያ ያየሁህ ዕለት የደነገጥኩብህ እኮ አባዬን ስለመሰልከኝ ነበር፡፡ አባዬ ልክ እንዳንተው እንዴት መሰለህ የሚያምረው? በተለይ የምትለብሱት
ዩኒፎርም እንዴት መሰለህ የሚያምርባችሁ። በቁመታችሁ፣ በግርማ
ሞገሳችሁ፣ በቃ ምን ልበልህ አንድ ዐይነት ናችሁ፡፡ ያኔኮ ጣቢያ መጥቼ
ቢሮህ ስገባ ደንግጬ የቀረሁት ለዚያ ነበረ፡፡ ምናልባትም የዚያን ዕለት
የተሰማኝ ስሜት በህይወቴ ውስጥ የመጀመሪያው ነበረ ብልህ ውሸታም
አድርገህ ስለቆጠርከኝ አታምነኝ ይሆናል፡፡ እንደዚያ ለወንድ ልጅ
ደንግጬ አላውቅም ነበረ፡፡ ባንተ ግን ደነገጥኩ፡፡ ከዚያም ቀስ በቀስ ወደድኩህ፡፡ ቀንም ሆነ ሌሊት አስብህ ጀመር፡፡ ስላንት ማውራት ደስ ይለኛል፡፡ እንደዚያ የሚያደርገኝ አዲስ ነገር ፍቅር መሆኑን ከኔ በፊት ያወቀችው አዜብ ነች ብልህ ይገርምህ ይሆናል፡፡ ብሩኬ ሙት አሁንም እወድሀለሁ፡፡ በእውነት እኔ እኮ ባለጌ ልጅ አልነበርኩም፡፡ የሆነውን ሁሉ
ልንገርህ? ዶክተር ባይከዳኝ ምኔም አይደለም፡፡ ምንም አላደረገኝም፡፡ ከሱ
ጋር የነበረኝ ግንኙነት እናቴን አክሞ እንዲያድንልኝ እንጂ ባንተ ላይ
ደርቤ ያፈቀረኩት ሰው ሆኖ አልነበረም አንተ ከዶክተር ባይከዳኝ
👍3
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ትህትና ዛሬ ትንሽ ደሟ መለስ ብሎ ስትመለከት እናቷ ደስ አላት፡፡ ሰሞኑን ጥውልግልግ ብላ አስደንግጣት ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሰውነቷን ተጣጥባ፣ ፊቷን ተቀባብታ፣ ምርጥ ለብሳ፣ ትህትናን መስላ ስታያት፤“ተመስገን” አለች በልቧ።
ያንን ምሽት እንደ አስታማሚ ልጅ ሳይሆን፤ እንደ ጥሩ አፍቃሪ ባል ፡ እቅፍ አድርጋት አደረች። ናፍቆቷን ሙሉውን ሌሊት አቅፋት በመተኛት ተወጣች፡፡
አሁን ሁሉንም ጣጣዋን ጨርሳለች፡፡ ዕቅዷን ልትፈጽም ሰዓቱ እየደረሰ ነው፡፡ በሌሊት ተነስታ ልብሷን ለባብሳ ጨረሰችና፣ ከፔርሙስ ትንሽ አጥሚት ቀድታ ካጠጣቻት በኋላ፤ “ወደ ቤት ልሂድ እማ!” ብላ ለመሄደ ተነሳች፡፡
ደግማ፤ ደጋግማ፤ ጉንጮቿን አገላብጣ ሳመቻትና፤ ወጣች፡፡ስትወጣ መንፈሷ ሁሉ ጠንካራ ነበር፡፡ ፍርሀት ጓዙን ጠቅልሎ ነው የሄደው፡፡ ቤት ደርሳ ያንን ትናንትና በፍቅር ስታሽሞነሙነው የዋለችውን የአባቷን ቅርስ ሸፋፍና፤ በቦርሳዋ ይዛ፤ ወደ መርካቶ ገሰገሰች፡፡
እዚያ እፍልሚያው ቦታ ስትደርስ ከታክሲ ወረደችና ራቅ ብላ ዓይኖቿን በሱቁ ላይ ተክላ ትጠባበቅ ጀመር፡፡
ልቧ ድው! ድው፤ ይላል፡፡ እልህና ሲቃ ይተናነቋታል፡፡ እንዷ ደቂቃ አቤት ርዝመቷ! አውሬው ወጥመዱ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ በንቃት መጠባበቋን ቀጠለች፡፡
አንዳንድ ሱቆች መከፈት ጀምረዋል፡፡ እምብዛም ሰው አይታይም፡፡ መርካቶ ትንሽ ሞቅ ሲል እንደዚያ እንደማይተራመስ ሁሉ አሁን ያለው ሁኔታ የሚያስገርም ነው፡፡
ነጠላዋን ተሸፋፍና፣ መንገደኛ መስላ፧ አንድ ጥግ ላይ ተቀመጠችና፤ ግዳይዋን መጠባበቁን ተያያዘችው፡፡ በእርግጥም ስለቸኮለች ነው መሰል በጣም ቀድማ ነበር የመጣችው፡፡
ገንዘብ በገፍ እየገባለት የመጣው ጎረምሳ በንግዱ ላይ ትኩረቱን እየጣለ ሄዶ ነበር፡፡ አበራን ወደዚያ ካባረረ በኋላ ትርፉን ለግሉ ማግበስበስ ጀምሯል።
ገንዘብ ሲቀምሱት ይጣፍጣል፡፡ በላይ በላዩ ያስመኛል። እህል ሲጠግቡት ያስገሳል፡፡ሲበዛም ያስጠላል፡፡ ገንዘብ የሚጠግብ ሆድ ግን የለም፡፡ ግሳትም የለው፡፡ በላይ በላዩ ጨምሩልኝ፣ ጨምሩልኝ፣ የሚያሰኝ፣ እየበሉት የሚርብ ነገር ቢኖር ገንዘብ ነው፡፡
እንደሻው የራሱ የሆነውን፤ እንደፈለገው የሚያዝበትን ገንዘብ ሲያገኝ፤ እንደጠላት ገንዘብ ማውደም ሳይሆን፣ ቀስ በቀስ ሱቁን በማደራጀት ሀብታም መሆን ስለፈለገ፣ ቆጣቢና ትጉህ ሠራተኛ ሆኗል።
ዛሬ ከሌሎቹ ሁሉ ቀደም ብሎ ገበያ ሊሻማ መጣና የሱቁን በር ከፈተ፡፡ ሙሉ ጂንስ ለብሷል፡፡ ከላይ ጥቁር ክብ ባርኔጣ አድርጓል፡፡
አንገቱ ላይ አጠር ያለች ወፍራም ሻርፕ ጠምጥሞ ነበር፡፡
የሱቁን በር ከፍቶ ወደ ውስጥ መዝለቁን ስታይ ትህትና ተዘጋጀች፡፡ እሷም ጂንስ ሱሪ ነው የለበሰችው፡፡
ቀስ ብላ ቀኝ እጇን ወደ ቦርሳዋ ሰደደችና፣ ማጥበቂያውን አላላች፡፡ ሽጉጡ ላግዳጁ ዝግጁ ሆነ፡፡ አሁንም ቀስ ብላ ጨበጠቸው፡፡ እጇ የተንቀጠቀጠ መሰላት፡፡
“አይዞሽ ትህትና ጠንከር በይ” አለች ለራሷ፡፡ “የመጨረሻው ሰዓት የድል ሰዓት ደርሷል፡፡ የመጨረሻውን የድል ሰዓት ባትወጪው አበቃልሽ!” አለችና ራሷን አደፋፈረች፡፡
ይህ የመጨረሻው መክሸፍ የሌለበት እርምጃ ነው፡፡ በእውነትም ጠንከር አለች፡፡ ልቧ በትክክል መምታት ጀመረ፡፡ ሰውነቷ መራራ ደም ሲረጭ ተሰማት፡፡ የቀድሞ ባህሪዋ ከውስጧ ጥርግርግ ብሎ ወጣና፤ አዲስ የቆራጥነት፣ የደፋርነትና፤ የጭካኔ ባህሪይ ተላበሰች፡፡
“አምላኬ በደሌን አንተ ይቅር በለኝ፡፡ ነፍሴን ተቀበላት!” አለችና የሽጉጡን ምላጭ እንደያዘች እየተንደረደረች ወደ ሱቁ ሩጫዋን ቀጠለች፡፡
ሱቁ በር ላይ ስትደርስ እንደሻው በሚያየው ነገር ተደናግጦ፣ ዐይኖቹ ተበልጥጠው፣ አፉ ተከፍቶ እንደቀረ ትንፋሽ ከማውጣቱ በፊት
ሽጉጡን ላጥ አድርጋ አወጣችው፡፡
ንግግር የለ፣ ግርግር የለ፣ ፋታ ሳትሰጠው በቀጥታ እርምጃውን ወሰደች፡፡
ዷ! ዷ! ዷ! ዷ! አምስት የቆጠረች መሰላት፡፡ አራንቱን ጥይቶች ካንጣጣችበት በኋላ፣ ተንገዳግዶ መውደቁን ስታረጋግጥ፧ ሽጉጡን
ወደራሷ አዙራ አፍዋ ውስጥ አስገባቸው፡፡
ሰው መሯሯጥ ጀመረ፡፡ ለሚተራመሰው ሰው ቦታ ሳትሰጥ፤
እርምጃዋን በራሷ ላይ ወሰደች፡፡ ምላጩን ሳበቸው፡፡ ዷ! ዷ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰማዩ የተባዘተ ጥጥ በመሰለው ደመና ተዥጐርጉሯል።
ጨረሯን የፈነጠቀችው ፀሐይ ያንን የደመና ቁልል እየናደችው ስትመጣ፤
ሰዓሊው በሸራ ላይ በብሩሹ የፈነጠቀው ንድፍ እየመሰለ ሄደ፡፡ ከዚያም ሙሉ ለሙሉ ደመናው ተገፈፈና፤ ጥርት ያለ ሰማይ ታየ፡፡
የሰው ልጅ የውስጥ ስሜቱ ሲጐዳ፣ ሲከፋው፣ ሲጨንቀው፤ ልክ ሰማዩ በደመና እንደሚያኮርፈው ሁሉ፤ ይህንን መጥፎ የውስጥ ስሜቱን በጨፈገገ ገጽታው ይገልጸዋል፡፡ በሆነ ባልሆነው ሆደ ባሻነት ያጠቃዋል፡፡
እነሆ ልቡ ከአምስት ዓመታት በላይ ከፍቅር ተገልሎ የቆየው ሻምበል ብሩክ ትህትናን ካገኘበት እለት ጀምሮ መንፈሱ ታድሶ!
የወደፊት የትዳር ህይወቱን በቅርብ ርቀት አሻግሮ መመልከት ሲጀምር፤ በእንጭጩ ተቀጨ፡፡
ትህትና ፍቅሯን ብቻ ሳይሆን፤ ያንን ደስተኛነቱን ጭምር በልቡ ውስጥ ገድላበት ነው የሄደችው፡፡
ድምጿን ለመስማት ይፈልጋል፣ ወዲያውኑ ደግሞ ከነመፈጠሯ እንዲረሳት ይመኛል፡፡ ትናፍቀዋለች፤ የሠራችው በደል ፊቱ ላይ ድቅን
ይልበታል፡፡ በቅናት ይቃጠላል፡፡ ወዲያውኑ ደግሞ ብሩኬ.... ብሩኬ....
ብሩኬ.... የሚለው ያ ለስላሳ ድምጿ፣ ያ ለስላሳ ሰውነቷ ያ ለስላሳ ባህሪዋ፤ ይታወሰዋል፡፡
በፊት የነበረችው ትህትና እንዴት የምትወደድ ልጅ ነበረች? ለምን ፈጣሪ አሳይቶ ነሳው? ምነው እሱ ለፍቅር አልታደለ? ሁል ጊዜ መጨነቅ?
“ምነው የዚያን ዕለት ባልተገናኘን ኖሮ” የሚል ሃሣብ መጣበት፡፡ ሆኖም በመገናኘታቸው አንድ መልካም ሥራ መስራቱ ያስደስተዋል፡፡
አጋር ያልነበራት እናቷን መርዳት መቻሉ እርካታን ይሰጠዋል።
ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም፡፡ እንዲሉ፣ እሷ ትበድለው እንጂ፤ እሱ ከበደል ይልቅ መልካም ሥራን የሠራ ተበዳይ መሆኑ ሲታወሰው፤ “ይሁን እስቲ ሁሉ ነገር ከፈጣሪ ይገኛል” ይልና
ይጽናናል፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ የሰሞኑ ሁኔታው የተለየ ነበር፡፡ ናፍቆቷ ነፍሱን ሊያወጣው ደርሷል፡፡
በውስጡ ፍቅርና ጥላቻ ነግሰውበታል፡፡ እንዳይጠላት ይወዳታል፣ እንዳይወዳት ደግሞ የሠራችው ሥራ...እንዳንድ ጊዜ ያ አለቃቀሷ፤ እዚያ እላዩ ላይ ተጠምጥማ እየተንሰቀሰቀች የተናገረችው ንግግር፣ ትዝ ይለውና፤ “ምን ነበረበት ይቅር ብላት ኖሮ? ግብዝ ነኝ” በማለት እራሱን
ይኮንናል፡፡ ወዲያው ደግሞ የሻክረና ጥርጣሬ የገባው ልብ ተመልሶ ልብ
ላይሆን፡፡ የነቃ ብርሌ ተመልሶ ዕቃ ላይሆን፣ አጉል ሙጥኝ አለማለቱን
ይወደውና..
እንኳንም በጊዜ አቋረጥን” የሚል ስሜት ይሰማዋል፡፡በጠዋቱ መ/ቤቱ እንደደረሰ ወደ ቢሮ ከመግባቱ በፊት ጫማውን
ሊያስጠርግ ሄደ፡፡ሰማዩን አየው፡፡ ከቤት ሲወጣ በደመና የተሸፈነ ነበር፡፡ አሁን
ግን ጥርት ብሏል፡፡ የሱ ስሜት ግን እንደሰማዩ አልጠራም፡፡ ፊቱ ጨፍግጓል፡፡ ጫማውን አስጠርጐ ወደ መሥሪያ ቤቱ ግቢ ሲዘልቅ......
“እንደምን አደርክ ሻምበል መልዕክት አለህ” አዳሪው ፖሊስ ከኪሱ ውስጥ ያስቀመጠውን ፖስታ አቀበለው፡፡
ሻምበል ፖስታውን ተቀብሎ ተመለከተው፡፡ የላኪው ሥም
የለበትም፡፡
የአደራ ደብዳቤነቱን እንጂ ከማን እንደተላከ አይገልጽም፡፡
“ማን ነው የሰጠህ?” ሲል ፖሊሱን ጠየቀው፡፡ ስሟን እንዳልነገረችው ገለፀለት፡፡ በቀጥታ ወደ ቢሮው ሄደ፡፡
የቢሮውን መስኮት ከፈተው፡፡ ንፁህ አየር ገባ፡፡ ከዚያም
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


በድንገት የተከሰተው አደጋ ክፉኛ ስላስደነገጠው ሻምበል ብሩክ ቀን እረፍት፤ ሌት እንቅልፍ፤ የሚባል ነገር አጥቶ እንደዚሁ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ከረመ፡፡ ለዚሁ ጉዳይ ሲልም ከመስሪያ ቤቱ የአስራ አምስት ቀን ፈቃድ ወሰደ፡፡ በዚህ ፈቃድ በወሰደበት ጊዜው
ውስጥ ደግሞ ብዙ መሯሯጥ ይጠበቅበታል፡፡መጀመሪያ ሆስፒታል የተኛች እናቷን ማረጋጋት አለበት :: ከዚያም ለወንድሟ በቂና አሳማኝ ምክንያት መስጠት ይጠበቅበታል ይህንን ሁሉ ሲያደርግ በሀሳብ የምትረዳውና ! አብራው የምትሯሯጠው! አዜብ ብቻ ነች፡፡ አዜብ ስለደረሰው አደጋ የትህትና አክስት እንዲያውቁት ፈልጋ ነበር፡፡

"አይሆንም ትርፉ ማስደንገጥ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ እነሱ ካወቁ ወሬው መዛመቱና፤ እናትዋ ጆሮ መድረሱ የማይቀር ስለሚሆን፤ በሚስጥር ቢያዝ ይሻላል” በማለት የተከራከረው ሻምበል
ነው፡፡ሻምበል ለእናቷ የሚሰጠው ምክንያት አሳማኝ እንዲሆን ሀሳብ
ሲያወጣና፧ ሲያወርድ፤ አዜብም እንደዚሁ ያሳምናታል ብላ ያሰበችውን ምክንያት ስትደረድር፤ ቆዩና ሁለቱም ይሆናል ባሉት ሃሳብ ላይ በጋራ ከተስማሙ በኋላ፤ ይህንኑ ሊያስረዳ ወደ የካቲት አስራ
ሁለት ሆስፒታል አቀና፡፡ ትህትና ከእናትዋ ጋር በአይነ ስጋ ከተገናኙ ሶስት ቀን ሆኗቸዋል፡፡ አንዱአለምም ድምጹ ከጠፋ ሳምንት አልፎታል፡፡በነገሩ እናት ግራ ተጋብታለች፡፡
"ልጆቼን ምን ነካብኝ?" በሚል ጭንቀት ተውጣለች፡፡ትናንትና ሆስፒታል መጥታ ያስተዳደረቻት ሰራተኛዋ ነበረች፡፡ ትህትና ከቤት ያለማደሯን ብቻ ነው የነገረቻት፡፡ በሽታዋን ማዳመጡን ትታ ልጆችዋን
እያብሰለሰለች፤ በሀሳብ እንደተዋጠች ነበር ሻምበል ብሩክ የደረሰው፡፡ብሩክን ስታየው በደስታ ልቧ ቀጥ አለች ::
"ትህትናዬስ ብሩኬ?" ከኪሱ አውጥቶ ይሰጣት ይመስል በጉጉት አይን አይኑን እያየች ጠየቀቸው፡፡ ሻምበል ብሩክ እንደማፈር ብሎ ሳቅ አለና፤ ተቅለሰለሰ፡፡ ለዘዴው...
“ምነው ብሩኬ በደህና ነው?" ከሁኔታው የከፋ ችግር እንደሌለ ተረድታለች፡፡
“ምንም ችግር የለም እማማ፡፡ ምን የኛ የወጣቶች ነገር...
የሚያሰጋ ነገር ያለመኖሩን ከሁኔታው ብትገነዘብም ምክንያቱን ለማወቅ
ቸኮለች፡፡
"ምንድነው እሱ ታዲያ?
ትህትና ምንም እንኳ እጮኛዬ ብትሆንም፤ ከትዳር በፊት እርግዝና ማለት፤ ትንሽ ያልተለመደ ስለሆነ... አንጠልጥሎ ተወው። ነገሩ ገባት
ከዚያ በላይ ልታስጨንቀው አልፈለገችም እሱ ግን ቀጠለ "ከጋብቻ በፊት ልጅ መውለድ የቤተሰብን ክብር መንካት ነው የሚል እምነት አላት፡፡ ተመካከርንና ማህጸኗ እንዲጠረግላት አደረግን፡፡ አሁን
ራስ ደስታ ሆስፒታል ትንሸ እረፍት ትውለድ ስላሉኝ አስተኝቻታለሁ።"አለና አጭር ድራማውን አጠናቀቀ፡፡ እናት የልጇን አቋም በእርግጥ ታውቀዋለች፡፡
አባቷ ያሳደጋትም በዚያ እምነት ጸንታ
እንድትኖር ነውና፤ በወሰደችው እርምጃ የተቃወሞ ድምጽ አላሰማችም፡፡
ነገሩን ውስጥ ውስጡን ስታብላላ ቆየችና......
“ሻምበል አደራህን! ትሁቴ ህጻን ልጅ ናት።እንደታላቅ ወንድም ተንከባከባት፡፡ እሷ ምኑንም የማታውቅ አንድ ፍሬ
ልጅ ናት፡፡ ለመጠንቀቁም ቢሆን አንተ ትሻላለህ፡፡ እሷ ምኑን ታውቀዋለች ብለህ
ነው?" የአሁኑ ስህተት እንዳይደገምና፤ በሌላ ጊዜ ተጨማሪ ጉዳት
እንዳይደርስባት፤ ሻምበል ሃላፊነቱን እንዲወጣ በማሳሰብ፤ አደራዋን
አጠበቀች፡፡ እሱም ትህትና ከሆስፒታል እንደወጣች ይዟት እንደሚመጣ
ቃል ገባላት፡፡ በመጠኑም ቢሆን ልቧ ትንሽ እረፍት አገኘ፡፡
“የአንዱአለሜ ወሬስ ? ምነው ጭልጥ ብሎ ጠፋ?" አከታትላ ጠየቀችው፡፡
“እኔ ራሴ ካገኘሁት ሳምንት ሆኖኛል እማማ፡፡ ለፈተናው ዝግጅት ሸፍቷል፡፡ ዘንድሮ አንደኛ ካልወጣሁ ሰው አይደለሁም ሲል የፎከረውን ለመፈፀም ቆርጦ መነሳቱን ትህትና ነግራኛለች። ምንም አያስቡ፤ ፈተናውን እንደጨረሰ እንዲመጣ እነግረዋለሁ።” ምክንያቱ
ብዙ ባይዋጥላትም የሻምበልን የማፅናኛ ቃል ከማዳመጥ በስተቀር አማራጭ አልነበራትም፡፡ዝም አለች፡፡ ከዚያም ሻምበል በግማሽ ልቡ ሆኖ፤ የሆነ ያልሆነውን፤ ሲያወራት ከቆየ በኋላ፤ ተሰናብቷት ወደ ትህትና ሩጫውን ቀጠለ....
ትህትና የቀዶ ህክምና ከተደረገላት በኋላ በአንደኛ ማእረግ እንድትተኛ ያደረገው ሻምበል ብሩክ ነው፡፡ ሻምበል አስፈላጊውን ክፍያ በመፈጸም ንጽህናው በተጠበቀና፤ ተጨማሪ በሽተኛ በሌለበት
አንደኛ ማእረግ ውስጥ እንድትተኛ የፈለገበት ዋናው ምክንያት፤
በሚተኙ በሽተኞች ስቃይ ተጨማሪ የአእምሮ መረበሽ ሊደርስባት ይችላል በሚል ፍራቻ ነው፡፡
ለቀዶ ጥገናው የተወጋችው ማደንዘዣ ስራውን በማጠናቀቁ ለአስቸኳይ ህክምናው በተሰጣት በሀያ አራት ሰአት ውስጥ ከሰመመናዊ እንቅልፉ ነቃችና አይኗን ገለጥ አደረገችው፡፡ ጣሪያውን ተመለከተች፡፡ ዙሪያዋን ቃኘች
የት እንዳለች፤ ምን እንደሆነች፤ በፍጹም
አታውቀውም፡፡ የተወጋችው የእንቅልፍ
መርፌ ፤ በጥይት የቆሰለው ሰውነቷና
እንደ ጉድ የፈሰሰው ደሟ መላ
አካሏን ድቅቅ አድርጐታል፡፡ከግራ ጆሮዋ ጀምሮ ፊቷ በአጠቃላይ በፋሻ ተሸፍኗል፡፡በክንዷ ላይ የተሰካውን ግሉኮስ ተመለከተችው፡፡ ጠብ ጠብ... እያለ
ይወርዳል። እንደገና አይኗን ጨፈነች፡፡ትንሽ ቆየችና መልሳ ገለጠችው::
እንደገና በሀሳብ ባህር ውስጥ ገባች፡፡ ምን ነበር የሆነው ? የት ነው ያለችው? እዚህ ለምን መጣች? እሷ ማን ነች? ቆይ .. ቆ ይ.. ምን ነበር የሆነው ? የሆነ
ነገር ብዥ ፧ ብዥ አለባት እንዴ ?..
መርካቶ ውስጥ እንደሻውን... ከዚያ በኋላ እራሷን... እንዴ?
ምንድነው ነገሩ? እሷ ሞታለች አይደለም እንዴ? በሰማይ ቤት ነው ወይንስ በምድር ላይ ያለችው? በዚያች በተሰናበተቻት ምድር ላይ? በፍጹም ሊሆን አይችልም! እንቆቅልሹም ሊገባት አልቻለም፡፡ ከዚያም ፊት ለፊትዋ የተቀመጡትን ሰዎች ትኩር ብላ ተመለከተቻቸው፡፡
ብዥ ፤ ብ ዥ ፤አሉባት አላወቀቻቸውም :: እነሱ በሀዘን ተውጠው አይን አይኗን ይመለከቷታል፡፡ እንደገና ትኩር ብላ ከመታሸግ በተረፈው በቀኝ አይኗ አየቻቸው፡፡ አሁንም አላወቀቻቸውም፡፡ እንቅስቃሴ የላትም፡፡እዚያ ከፊት ለፊቷ ሆነው በሀዘን ኩርምት ጭብጥ ብለው የተቀመጡትን ሰዎች በድጋሜ በጥንቃቄ ተመለከተቻቸው፡፡ የሆነ ምስል መጣላት፡፡
የምታውቀው ምስል በርቀት የምታውቀው ምስል.. አዎን
ታውቃቸዋለች እንጂ !! እንዴ..? በሚገባ ታውቃቸዋለች :: ቀስ ብላ በለሆሳስ ተጣራች "ብ..ሩ. ኬ..... አ . ዜ. ቢ . ና
እህህህ....." በዚህ ጊዜ አዜብ ቀስ ብላ ተነሳችና ሄዳ አጠገቧ ቆመች፡፡ ብሩክም አዜብን ተከትሎ ወደ አልጋው ተጠጋ፡፡ሻምበል እንደዚያ ሆና ሊያያት አልቻለም :: እንባው አመለጠውና ቀስ ብሎ ጉንጮቹን
እያቋረጠ ፈሰሰ፡፡
“እ ማ ዬ...ደ ህ...ና. ነች? ..አ.ን.ዱ.ዬስ..?"
"ሁለቱም በጣም ደህና ናቸው፡፡ ስለ እነሱ ምንም አታስቢ፡፡ እኛ አለን፡፡ አሁን ዋናው ማሰብ ያለብሽ ስለራስሽ ጤንነት ብቻ ነው እሺ?” አዜብ ነበረች፡፡
“እ..ሺ በደከመ ድምጽ፡፡
“ትሁት አዜብ የምትልሽን ስሚያት፡፡ስለ እማማ ምንም የሚያስጨንቅሽ ነገር የለም፡፡እሳቸው አንቺ ስለጠፋሽባቸው ነው ትንሽ ያሰቡት እንጂ በጣም ደህና ናቸው፡፡ ቶሎ ድነሽ ሄደሽ እንዲያዩሽ
በሃሳብና በጭንቀት ራስሽን መጉዳት የለብሽም፡፡ እሺ? አንዱ አለምም ድኗል ማለት ይቻላል፡፡ሰሞኑን መጥቶ ይጠይቅሻል እሺ?” ጉንጮቿን
እየዳበሰ፡፡
እሺ” አለች በድጋሜ፡፡ በዚያው ድክምክም ባለ ድምጿ። አሉኝ የምትላቸውና የምትተማመንባቸው ሁለቱ ጓደኞቿ፤ ደራሾቿ ፤ በዚህ በክፉ ቀን እንኳ ከጐኗ
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

እነሱ ለትህትና ሕይወት እንደዚያ ሲሯሯጡ ደግሞ የእንደሻው ወላጆች ደግሞ የልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ከላይ ከተች እየተሯሯጡም ብቻ ሳይሆን እየተራወጡ ናቸው። የእንደሻው ጉዳት ከባድ ነበር። በተለይ አንዷ ጥይት የራስ ቅሉን በስታው ስላለፈች፤ የአእምሮ ቀውስ
እንዳያስከትልበት፤ ከፍተኛ ስጋት አለ፡፡
በተፈጠረው አደጋ ምክንያት የእንደሻው ወላጆችና የአዜብ ወላጆችም ግንኙነት አቋርጠዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ...
"ያቺን የተረገመች ልጅ አምጥታ ልጃችንን ልታስገድለው የነበረችው አዜብ ነች በሚል ሲሆን፤ ፀቡን ከአዜብ ጋር ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቿ ጭምር አድርገውታል :: እነሱ እንደዚያ ብለው ይናገሩ እንጂ ፤ የአዜብ ወላጆች ሁኔታው ሊፈጠር የቻለው አለሌው ልጃቸው
በፈፀመው ተደጋጋሚ አስነዋሪ ድርጊት ሳቢያ መሆኑን ሲያውቁ የክርስትና ልጃችን ነው በሚል ምክንያት ብቻ ፤ በትህትና ላይ ሊፈርዱባት
አልደፈሩም....
"ሁሉንም ስራው ያውጣው በማለት መጨረሻውን ለማየት እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ ትህትና ጤናዋ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም፤ ጐን ለጐን በነፍስ ማጥፋት ሙከራ ወንጀል በአቃቤ ህግ ክስ ተመሰረተባት፡፡ አዜብና ብሩክ ይህንን እንዳወቁ ቀጣዩ ትኩረታቸው
በምን ላይ መሆን እንዳለበት በስፋት ተመካከሩ፡፡ ከዚያም አንዳንድ
በመከላከያነት ይጠቅማሉ ያሏቸውን ማስረጃዎች ለማሰባሰብ ፤ ሁለቱም
በየፊናቸው ሩጫ ጀመሩ፡፡ ለዚህ ጉዳይ አበራ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገመቱ :: ምክንያቱም አበራ በእንደሻው ክህደት የደረሰበትና፤ በትህትና ላይ ስለተፈፀመው ወንጀል በሚገባ የሚያውቅ የአይን ምስክር ስለነበረ ነው፡፡ አበራ በእንደሻው ስለተፈፀመበት ክህደት ለአገሩ ሁሉ ሲያወራ ለአዜብም አጫውቷት ነበር ፡፡
ከዝምድና ይልቅ ገንዘብን አስበልጦ አስር
አመት ሙሉ ያጠራቀምኩትን ገንዘቤን ወስዶ ከከበረበት በኋላ ከዳኝ፡፡ በጋራ
እናድግበታለን ብሎ የገባውን ቃሉን አፍርሶ አባረረኝ " በማለት በምሬት ነበር የገለፀላት፡፡ ታዲያ ያ ሁሉ በደል የተፈፀመበት ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ እውነቱንና የሚያውቀውን ከመናገር ወደኋላ ሊል ይችላል? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ በፍፁም ወደኋላ አይልም ስትል ተማመነች፡፡ምክንያቱም እሱ እንደዚያ በንዴት እየተንቀጠቀጠ
ሲነግራት...

“አይዞህ አበራ ተወው፡፡ አንተ ጤና ሁን እንጂ ፤ገንዘብ አላፊ ጠፊ ነው፡፡ በክህደት የተገኘ ገንዘብ ደግሞ የትም አያደርስም፡፡
ከሰራህ ከካደህ ሰው በላይ መሆን ትችላለህ :: አይዞህ! እግዚአብሄር ላንተ ያለውን ምንግዜም አታጣውም " በማለት ትልቅ የማፅነኛ ቃል ለግሳው ነበር፡፡ ያንን
የሰጠችውን የተስፋ ቃል እንኳ አስታውሶ እሺ ይላት ይሆን? ወይንስ እሱም እንደወላጆቹ ተደርቦ ከእውነት ጀርባ ይቆም ይሆን? ልቧ ተጠራጠረ፡፡ ለማንኛውም አለችና ስልክ ደወለችለት :: ስልኩን አነሳና እሷ መሆንዋን ሲያውቅ የሞቀ ሰላምታ አቀረበላት፡፡ ትንሽ እፎይ አለች በልቧ፡፡ለጉዳይ እንደምትፈልገው
ስትገልፅለት፤ በደስታ ተቀብሎ የሚገናኙበትን ቦታ ተቀጣጥረው
ተሰነባበቱ፡፡ በማግስቱ በቀጠሮው ቦታ ቀድሞ የደረሰው እሱ ነበር።
የተፈለገበትን ጉዳይ ስትነግረው...
"ተይ እንጂ አዜብ እቤት ድረስ የወሰድኳት እኮ እኔ ነኝ፡፡በወንጀለኛነት አያስጠይቅህም ነው የምትይኝ?" ሲል በጥርጣሬ ጠየቃት።
"ስለሱ ከሻምበል ጋር በደንብ ተነጋግረንበታል፡፡ አንተን በወንጀል
ተባባሪነት እንዳያስጠይቅህ በቂ ምክንያት ማቅረብ ይቻላል፡፡”
"ለምሳሌ ምን?"
"አበራ ሙት ምንም አትፍራ! በዚህ ጉዳይ አንተ በጥፋተኛነት እንድትጠየቅ የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ፧ አንተ ይዘሃት የሄድከው ወደ ቀጣሪዋ ቤት እንጂ፤ ወንጀል
ወደሚፈጸምበት ጫካ ውስጥ አይደለም፡ቀጣሪዋ ቤት አደረስካት ማለት፤ እንደሻው ደብድቦና፤ አስገድዶ፧ ክብረ ንፅህናዋን እንዲደፍራት አደረክ ማለት አይደለም :: የቀጣሪዋን ቤት የወንጀል መፈፀሚያ ዋሻ ያደረገው ወንጀለኛ ብቻ ነው ለዚህ ተጠያቂ የሚሆነው፡፡ አይዞህ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለውም፡ አበራን ለማሳመን ብሎ ብሩክ ያስጠናትን ደሰኮረችለት፡፡ አበራ ልቡ ትንሽ ተለሳለሰ፡፡
"በሌላ በኩል ብታየው ደግሞ የቀጣሪዋ ባለቤት ልጅ የቅጥር ውል እንድትፈርም ይዘሃት ና ብሎ አዘዘህ :: አንተም ይህን ነገርካት። እሷም እሺ ብላ ሳታስገድዳት በፈቃደኝነት አብራህ ሄደች። ከዚያም አንተ በሌለህበት እንደሻው ወንጀል ፈፅሞባት ደረስክ፡፡ በቃ፡፡ ይህ አይደለም
ታሪኩ? አንተን የሚያስጠይቅህ ምኑ ነው ታዲያ?" ስትል የማደፋፈሪያ
ሀሳብ አዥጐደጐደችለት፡፡

በልቡ ያሳደረው ጥርጣሬ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋለትም፤ በአዜብ አቀራረብ ተስማማ፡፡ እንዳለችውም እሱን በቀጥታ ተጠያቂ ሊያደርገው የሚችል ጭብጥ እንደሌለ ተሰማው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ
ያቺ ምስኪን እንጀራ ፈላጊ ልጅ ፤ በደም ተጨማልቃ ወድቃ ያያት እለት የተሰማው ስሜት ፊቱ ላይ ድቅን አለበት፡፡ በተፈፀመባት ወንጀል ከልቡ አዝኖ ነበር፡፡ በዚህ ላይ ያ ግፈኛ ከሃዲ ከሱቁ ካባረረው በኋላ አሁን አሁን በርካታ ካፒታል በማንቀሳቀስ በቅናት እያቃጠለው
ነው፡፡ በጥይት መቃጠሉን የሰማ እለት " እሰይ የእጁን ነው ያገኘው"ነበር ያለው፡፡ አሁን ደግሞ እሱ ተጠያቂ በማይሆንበት ሁኔታ ለምን ያየውን ከመመስከር ወደ ኋላ ማለት እንደሌለበት ተገነዘበ ፡፡ያየኽውን እውነት መሰከርክ ብሎ የሚፈርድበት ዘመድ እንደማይኖርና፤ ቢኖርም መፅሀፍ ቅዱስ ይዞ በሚፈፅመው መሃላ በውሸት መስክሮ ነፍሱን ማስኮነን እንደሌለበት ተሰማው። እንደሻውን ሊበቀል
የሚችልበትን ይህንን መልካም አጋጣሚ ሊጠቀምበት ወሰነ : እንቢ ቢልስ የት ሊደርስ ? በተለይ አዜብ እየነገረችው
ያለው ፣ ባለስልጣን ፖሊስ ከአዜብ በስተጀርባ መኖሩን ነው፡፡ በተለይ "ሻምበል ጋር በደንብ ተነጋግረንበታል"
ስትለው ምን እያለች እንደሆነ
ገብቶታል፡፡አልመሰክርም ቢል በተባባሪ ወንጀለኛነት ተፈርጆ፣ ለፍርድ እንደሚቀርብ እየነገረችው ነው፡፡ ይሄንን ጭምር አስቦ፤ ልቡ ስለፈራ፤ ያየውን ሁሉ በዝርዝር ሊያስረዳና፤ ለትህትና ድንበሩ የመከላከያ ምስክር ሊሆን ቃል ገባላት፡፡ ቃል መግባት ብቻም ሳይሆን ተጨማሪ ማስረጃ ጠቆማት..

"እኔ ብቻ ሳልሆን በዚያን እለት ሁኔታውን የተመለከተችው የቤት ሰራተኛዋ ወርቅ ያንጥፉም ያየችውን ሁሉ እውነቱን ሳትደብቅ እንድትመሰክር እናደርጋለን :: ደግሞም ትመሰክራለች፡፡ አትጠራጠሪ!
በትህትና ሁኔታ በጣም ነው ያዘነችው፡፡እሷም ስመ እግዚአብሄርን ጠርታ
ያየችውን ሁሉ ትመሰክራለች፡፡ አይዞሽ ! " አላት፡፡ አዜብ ከጠበቀችው በላይ ተባባሪ ሆኖ ስለኣገኘችው፤ በደስታ እቅፍ አደረገችው፡፡ በዚሁ መሰረት አበራና ወርቅ ያንጥፉ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው፤ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደረገ፡፡ ቀኑን፡ ሰአቱን፡ የድርጊቱን አፈፃፀም፡ ዝርዝር ሁኔታውን፤ በሙሉ በአንድ አይነትና ፤ ተመሳሳይ በሆነ ቃል
መሰከሩ። ያም ብቻ ሳይሆን አንዱአለምን ጋርጠው በሚል ቅፅል ስሙ በሚታወቀው ወሮበላ እንዳይሞት፤ እንዳይድን፤ አደርጐ ያስደበደበው
መሆኑን፤ ራሱ እንደሻው በኩራት ሲናገር መስማቱን፧ ጭምር ገለፀ፡፡
በእርግጥም እንደሻው ያንን ለአበራ የተናገረው፤ ይሄ ይመጣብኛል ብሎ ሳይሆን፤ አንተም አርፈህ የማትቀመጥና ወሬ አበዛለሁ የምትል ከሆነ፤ አስወቅጥሀለሁ፤ የሚል ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ አጋጣሚ እንደሻውን የደበደበው ጉልበተኛ
ስለታወቀ፤ ወዲያውኑ ታድኖ እንዲያዝ ሲደረግ ፤ አበራ ማንነቱን በማሳየትና የሚገኝበትን
👍21
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


#ከሁለት_ወራት_በኋላ

እንደሻው በቀለንና ራሷን በጥይት አቁስላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናዋን ስትከታተል ከቆየች በኋላ በሁለተኛው ወሯ ሙሉ ለሙሉ ዳነች፡፡
በዚያ ጥይት ምክንያት ከላይኛው መንጋጋ ጥርሶቿ ላይ ሁለቱን አጥታለች፡፡ የግራ ጆሮዋ በመስማት በኩል ትንሽ ቅር ቢለውም ሙሉ ለሙሉ አልደነቆረም፡፡
ጥይቶቹ በተከታታይ ሾልከው የወጡበት ቀዳዳ መጠነኛ ጠባሳን ጥሉባት አለፈ እንጂ፤ ውበቷን እምብዛም የሚፈታተነው አልነበረም፡፡
ከዚህ ሁሉ ሥቃይ በኋላ ግን እቤቷ ገብታ አላረፈችም፡፡ ወንጀለኛ ናትና በቀጥታ በማረፊያ ቤት እንድትቆይ ተደረገ፡፡
የወንጀል ክሱ በዐቃቤ ህግ ከሳሽነት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡
ከሳሽ ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ ወይዘሪት ትህትና ድንበሩ የክሱ ምክንያት ሰው የመግደል ሙከራ ወንጀል ዐቃቤ ህጉ ተከሳሽ ሆን ብላ ተዘጋጅታ ወጣት እንደሻው በቀለ ከሚሰራበት የንግድ ሱቅ ድረስ በመሄድ በአራት ጥይቶች ያቆሰለችው መሆኑንና እራሷንም ለመግደል ሙከራ ማድረጓን ከገለፀ በኋላ፤ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና አንቀጽ ጠቅሶ አስፈላጊው ቅጣት እንዲወሰንባት
የተመሰረተ ክስ መሆኑን በማተት አቀረበ፡፡
ትህትና ድንበሩ ተከሳሽ ሆና ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበችበት ዕለት፤ ታናሽ ወንድሟ በችሎቱ ላይ በመገኘት ክሱን
አብሯት አዳመጠ፡፡
ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበላት፡፡
ስምሽ?”
“ትህትና ድንበሩ”
“ዕድሜሽ?”
"አሥራ ሰባት ዓመት”
“አድራሻ?”
“አዲስ አበባ
“ሥራሽ?”
“ሥራ ፈላጊ”
“ወላጆችሽ በህይወት አሉ?”
“አባቴ ሞቷል እናቴም የአልጋ ቁራኛ ነች”
ይህንንና መሰል ጥያቄዎችን ከተጠየቀች በኋላ “የክሱ ቻርጅ ደርሶሻል?” የሚል ጥያቄ ቀረበላት፡፡
“አዎን ደርሶኛል”
ከዚያም የመሐል ዳኛው መነጽራቸውን ዝቅ አድርገው በግንባራቸው ዐይዋትና........
“ወይዘሪት ትህትና ለተመስረተብሽ ክስ እራስሽ ትከራከሪያለሽ ወይስ?
ጠበቃ ታቆሚያለሽ?” የሚል ጥያቄ አቀረቡላት፡፡
ቀስ ብላ ሻምበል ብሩክን አየችው፡፡ የመከራትን አስታወሰች፡፡
“ድሃ ስለሆንኩ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ?” የሚል መልስ ሰጠች፡፡
ይህንን መልስ ስትሰጥ በተቻላት መጠን ድምጿ እንዲሰማ ጮክ ብላ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱ በጥብቅና ሙያው የታወቀው አቶ ምንውዬለት ተዘራ ለተከሳሽ ጠበቃ እንዲሆንላት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ አቶ ምንውዬለትም ትእዛዙን በደስታ ተቀበለ፡፡
ይህ ከሆነ በኋላ ተከሳሽ የተከሰሰችበት ወንጀል በንባብ እንዲሰማ ተደረገ፡፡
“በተመሰረተብሽ ወንጀል ጥፋተኛ ነሽ አይደለሽም?” ተብላ ተጠየቀች፡፡
በዚህ ጊዜ ጠበቃው አቶ ምንውዬለት ጥቁር ካባውን እንደለበሰ
ብድግ ብሎ ቆመ፡፡
“ጥፋተኛ አይደለችም ክቡር ፍርድ ቤቱ” ሲል መልስ ሰጠ፡፡ ዳኛው መልሱን ከመዘገቡ በኋላ፤ ጠበቃው “ክቡር ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የዋስ መብቷ ተጠብቆ እንድትከራከር ይፍቀድልኝ” ሲል ጥያቄ አቀረበ፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ፤ ተከሳሽ በማረፊያ
ቤት ቆይታ እንድትከራከር በመወሰንና፤ ዐቃቤ ህጉ አሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች እንዲያቀርብ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ አበቃ፡፡
ትህትና እዚያ የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ
ቆማ ስትቁለጨለጭ፣እንዳንድ ጊዜ በፍርሃት ተውጣ ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥ፣
ድምጿ ሲርገበገብ፣ ሲያልባት፡ እያየች አዜብ እንባ እየተናነቃት ነበር፡፡ ሆኖም አልቅሳ ልትረብሻት አልፈለገችም፡፡ ይልቁንም ሳቅ ፈገግ እያለች ሞራል ልትሰጣት ሞከረች፡፡
እውነትም እንደዚያ ሰውነቷ በፍርሃት ሲሸበርባት፣ ልቧ ድው ድው ሲል፣ ሻምበል ብሩክን፣ ወንድሟንና አዜብን ቀስ ብላ ታያቸዋለች፡፡ እነሱ ፈገግ ይሉና በ“አይዞሽ” ምልክት ሲያበረታቷት “አይዞኝ” በሚል ስሜት እራሷን ስታጠናክር ከቆየች በኋላ ችሎቱ ሲያበቃ በአጃቢ ፓላስ ታጅባ ወጣች፡፡
ከዚያም በአንዱአለም ጠያቂነት አብረው ምሣ ይበሉ ዘንድ ሻምበል ብሩክ አጃቢ ፓሊሱን አነጋገረውና አብረው ምሣ ለመብላት ፈቃድ ስለ አገኙ ፤ እዚያው አካባቢ በሚገኝ ወደ አንድ ሆቴል ገቡ፡፡
አንዱአለም የዛሬውን ምሣ ለመጋበዝ የፈለገበት ምክንያት ነበረው፡፡ የሚፈለገው ምግብና መጠጥ ታዘዘ፡፡
ከባህር ኃይሉ የተሰጠው የኪስ ገንዘብ ስለነበረው ምሣ የጋበዘው እሱ ነበር፡፡ አንዱአለምን ብሎ ጋባዥ በመገኘቱ እየተሳሳቁ፣እየተጨዋወቱ፣ ግብዣውን በደስታ ተቀበሉት፡፡ አጃቢ ፓሊሱ በሻምበል ብሩክ ላይ እምነት ስለጣላ እስረኛዋ ታመልጣላች የሚል ሥጋት አላደረበትም፡፡ እንደዚሁ እየተጨዋወቱ ከቆዩ በኋላ.......
“አንድ ጊዜ” አለና አንዱአለም ትንፋሹን ሰብሰብ፣ ምራቁን ዋጥ አደረገ፡፡
አራቱም በፀጥታ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ከወትሮው ለየት ያለ ስሜት ይታይበታል፡፡ እነሱ ከተቀመጡበት አካባቢ ትንሽ ራቅ ብለው በርከት ያሉ እየተጨዋወቱ የሚሳሳቁ ሰዎች ድምጽ ብቻ ይሰማል፡፡
“ይህቺ የምሣ ግብዣ በአንድ በኩል እታለም ለመጀመሪያ ጊዜ
ፍርድ ቤት በቀረበችበት ቀን ተገኝቼ እውነተኛ ፍትህን አግኝታ በነፃ
እንድትለቀቅ መልካም ምኞቴን የምገልጽበት ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ
ለራሴ መሸኛ በማድረግ በግል ውሣኔዬ መሠረት ለነገው ጉዞዬ መቃናት
እንድትመርቁኝና፤ የወጪ እንድላችሁ በማሰብ የተደረገች ግብዣ ነች”
አለ፡፡ ስለምን እንደሚያወራ ቶሎ ማወቅ አልቻሉም :: “የምን ጉዞ? የምን መሸኛ?. “ምንድነው የምትለው አንዱዬ?” በድንጋጤና በጥርጣሬ ተውጣ አዜብ ጠየቀችው፡፡ “ ሁሉንም ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቄአለሁ፡፡
ከአንድ ሣምንት በፊት በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ውስጥ ተቀጥሬ ለስልጠና
መሄዱ ነው” ሲል ቁርጡን ነገራቸው፡፡ በዚያ ጨዋታ መካከል ይህንን መርዶ አምጥቶ ሲጥልባቸው ልባቸው ክፉኛ አዘነ፡፡ በተለይ ትህትና የተሰማትን ስሜት መግለጽ ያስቸግራል፡፡ ጭውው አለባት፡፡ ግማሽ አካሏ፣ የምትወደው ታናሽ ወንድሟ ምንም እንኳን እስረኛ ብትሆንም በየጊዜው እየመጣላት ዐይኖቹን ስታየው
የምትጽናናበት አለኝታዋ ነበር፤ በሁኔታው መሪር ሀዘን ተሰምቷት አለቀሰች፡፡
አዜብም እንደዚያው፡ ሻምበል ብሩክም ክፉኛ ነበር የደነገጠው፡፡
ይህ ትንሽ ልጅ የዚህ ዐይነት ከባድ ውሣኔ ላይ ይደርሳል ብሎ ጭራሽ አልገመተም ነበር፡፡ የሱ ፍላጐት አንዱአለም በትምህርቱ ጠንክሮ ዩኒቨርስቲ
እንዲገባ እንጂ እንደዚህ በመሀሉ አቋርጦ ወደ ጦር ሜዳ እንዲሄድ አልነበረም፡፡ ከረጅም ፀጥታ በኋላ......
“እንደሱ ይሻላል አልክ አንዱአለም?” አለው ሻምበል በትካዜ አንደበት።
ትህትና እና አዜብ በእንባ ይንፈቀፈቃሉ፡፡ አጃቢ ፓሊሱ ግራ ተጋብቶ ሁሉንም በዐይኑ ይቃኛል፡፡
“በቃ ብንሄድስ” የሚል ፍላጉት አድሮበታል፡፡ ሞትም ቢሆን በተሰማበት ቅጽበት በድንጋጤ ያደርቃል እንጂ፤ ቀስ በቀስ መለመዱ አይቀርምና፤
ውስጥ ውስጡን እየተቃጠሉ፤ እንባቸውን እየጠራረጉ፤ዐይን፤ ዐይኑን፧ ይመለከቱት ጀመር፡፡ ውሣኔው የፀና፣ ጉዳዩ ያበቃለት መሆኑን ቁርጥ አድርጉ ነገራቸው፡፡
እስከዛሬ ድረስ የቆየው እህቱ ፍርድ ቤት ስትቆምና የተከሰሰችበት ወንጀል ሲሰማ አብሯት ለመገኘት ፍቃድ በመውሰድ መሆኑን፣ ነገ በጠዋት በዋናው መሥሪያ ቤት ተገኝቶ ወደ ማሰልጠኛው ጉዞ የሚጀምርከ መሆኑን፣ለሻምበል ሲያስረዳው ለትህትና እና ለአዜብ ደግሞ የመርዶ ያህል ካረዳቸው በኋላ በአጃቢ ፓሊሱ አሳሳቢነት ተነስተው ወጡ፡፡
“እሺ አሥር አለቃ ስለተባበርከኝ በጣም ነው የማመሰግንህ አለው ሻምበል የአጃቢ ፓሊሱን ትከሻ ቸብ ቸብ እያደረገ፡፡
“እሺ ጌታዬ አኔም የርስዎ ነገር ሆኖብኝ እንጂ፤ ህግ መጋፋቴን አልዘነጋሁትም” አሥር አለቃ ጥላዬ እግረ መንገዱን ውለታውን
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....ቀጠሮው ደረሰ፡፡ ትህትና ድንበሩ ለተመሠረተባት ክስ መልስ የምትሰጥበት ቀን... ጠበቃዋ አቶ ምንውየለት ተዘራ በመልሱ ላይ ተከሳሽ ሆን ብላ ተሰናድታ ሳይሆንእንደሻው በቀለ በእሷና በወንድሟ
ላይ በፈጸመውና ባስፈጸመው ተደጋጋሚ ወንጀል ምክንያት ህሊናዋ ስለቆሰለ፤ ንብረትነቱ የወላጅ አባቷ የነበረውን ከቤት የተቀመጠ መሣሪያ በድንገት ይዛ በመውጣት፤ በደም ፍላት ተነሳስታ፤ ድርጊቱን መፈጸሟን፣ ወጣት እንደሻው በቀለ በፈጸመባት አስገዳጅ የግብረ ሥጋ
ግንኙነት ምክንያት፤ ክብረ ንጽህናዋ በመደፈሩ፤ ለትዳር ከወጠነችው እጮኛዋ ጋር ከመጣላቷም በላይ፤ ታናሽ ወንድሟ አንዱዓለም ድንበሩ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ምክንያት፤ በእንደሻው በቀለ አማካይነት በገንዘብ በተገዛ ወሮበላ ተደብድቦ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን፤ እነዚህ
ተደራራቢ ጥቃቶች፤ ወንጀሉን እንድትፈጽም ያነሳሷት ድርጊቶች
ከመሆናቸው በተጨማሪ፤ ወጣቷ በዕለቱ ወጣት እንደሻውን ለማጥቃት ብቻ ሳይሆን በራሷ ህይወት ላይ የወሰደችው ቅጽበታዊ ሙከራ ሁሉ፤ የነበረባትን የአእምሮ ጭንቀት ደረጃ በግልጽ የሚያሳይ በመሆኑ፧ ክቡር ፍርድ ቤቱ የዕድሜዋን ሁኔታ፤ የደረሰባትን የሞራል መገደድ፣ የቤተሰብ ኃላፊነት ደረጃዋንና ከዚህ በፊት የነበራትን መልካም ስነ ምግባር፧ ከግምት ውስጥ በማስገባት በነፃ እንዲያሰናብታት ሲል በመጠየቅ መልስ ሰጠ፡፡

ለዚህም መልስ የመልስ መልስ እሰጣለሁ በማለት ዐቃቤ ህጉ ስለጠየቀ፤
የመልስ መልሱን እንዲሰጥ ተደረገ፡፡
ከዚህ በኋላ በፓሊስ የቀረበው የምርመራ መዝገብ፣ የሀኪም ማስረጃና፤ በእግዚቢትነት የተያዘው ኮልት ሽጉጥ ለፍርድ ቤቱ ቀረቡ፡፡ ዐቃቤ ህጉ በሰጠው የመልስ መልስ ላይ ተከሳሽም ሆነች
ወንድሟ ተፈጽሞብናል የሚሉት ወንጀል ቢኖር፤ በወቅቱ ጉዳዩን ለህግ አቅርበው ፍትህን መጠየቅ ሲችሉ፤ ይህንን ሳያደርጉ ቀርተው፤ ተከሳሽ ከተመሰረተባት የክስ ጭብጥ፤ ምክንያትና ውጤት ጋር፤ግንኙነት የሌለውን ሀተታ በመልስ ውስጥ በመዘርዘር፤ በነፃ እንድትለቀቅ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤ ወንጀልን ማካካስ የማይቻል
በመሆኑም በመልሱ ላይ የቀረበው የወንጀል ማካካሻ ጥያቄ ውድቅ
እንዲደረግ ጥያቄ በማቅረብና ፤ ተከሳሽ እራሷን ለማጥፋት ያደረገችው ሙከራም ህጋዊ ድጋፍ የሌለው ህገውጥ ድርጊት ከመሆን አልፎ ከጥፋትዋ ነፃ እንድትወጣ በቂና አሳማኝ ምክንያት ሊሆን የማይችል
ስለሆነ፤ ክቡር ፍርድ ቤቱ በተከሳሽዋ ላይ የጥፋተኛነት ውሳኔ

በዚህም መሰረት
ቃለ መሀላ
እንዲሰጥልኝ በማለት ስለተከራከረ ፤ ለተፈጸመው ወንጀል ያውቁልኛል
የሚላቸውን ምስክሮች እንዲያቀርብ ተደረገ በምስክርነት ያቀረባቸው ሶስት ምስክሮች ፍ/ቤት ቀርበው እንዲፈጽሙ ከተደረገ በኋላ ፤ ወንጀሉ የተፈጸመበትን ቦታ፣ ቀንና ሰዓት ጠቅሰው ተከሳሽ እንደሻው በቀለን በአራት ጥይቶች ደጋግማ ማቁሰሏን በማረጋገጥ፤ ተመሳሳይነት ባለው ቃል መሰከሩ፡፡
የዐቃቤ ህጉ ምስክሮች ተሰምተው እንዳበቁ በተከሳሽ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ከበድ ያሉ ሆነው በመገኘታቸው፤ ፍ/ቤቱ ተከሳሽን
እንድትከላከል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡በዚህ ጊዜ የተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮች ሆነው የቀረቡት

1ኛ ወ/ት አዜብ ተሾመ
2ኛ ወ/ት ወርቅ ያንጥፉ አደራ
3ኛ. አቶ አበራ ፈይሳ

አስፈላጊውን ቃለ መሀላ ከፈጸሙ በኋላ፤ ተከሳሽ በአስተዳደግ፤ በተማረችበት ትምህርት ቤት፤ በሥራ ቦታዋ ላይም ሆነ በመኖሪያዋ አካባቢ የነበራትን ሥነ ምግባር፣ ከዚህ በፊት ተከሳ ያልተቀጣች ጨዋ ወጣት መሆኗንና፤ ወጣት እንደሻው በቀለ ድምጽ በሌለው መሣሪያ አስገድዶ ክብረ ንጽህናዋን ለመድፈሩ፤ እያንዳንዳቸው የሚያውቁትንና
ያዩትን ዘርዝረው መሰከሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እራሱ ሻምበል ብሩክ ፍርድ ቤት ቀርቦ ከእጮኛው ከትህትና ድንበሩ ጋር ወጥነውት የነበረው የትዳር ዕቅድ፤
ከተፈጸመባት አስገዳጅ የክብረ ንጽህና መደፈር ጋር ተያይዞ በተፈጠረ
ያለመግባባት ምክንያት መበላሸቱን አስረዳ፡፡
ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክርና የቀረቡትን ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ
“ተከሳሽ በማያጠራጥር ሁኔታ ድርጊቱን የፈጸመች ሆና ስለአገኘናት በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 27/524.ለ/ መሠረት ጥፋተኛ ነች ብለናል”
ሲል የጥፋተኛነት ውሣኔውን ሰጠ፡፡

ጥፋተኛነትዋ ተረጋግጦ ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ፤ ቀሪው በቅጣት ውሣኔው ላይ የሚካሄድ ክርክር ነው፡፡በዚህ መሠረት ተከሳሽዋ ለፈፀመችው ወንጀል የቅጣት ውሣኔውን ለመስጠት እንዲያስችል ዐቃቤ ህጉ የቅጣት ማቅለያ ወይንም የማክበጃ ሃሣብ ካለው እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ስለጠየቀ፤ ተከሳሽ ትህትና ድንበሩ በቀልን በልቧ በማሳደር፤ በቂ ዝግጅት በማድረግና፤ የጦር መሣሪያ በመያዝ፤ ከሥራ ቦታው ድረስ ሄዳ ወጣት እንደሻው በቀለን በአራት ጥይቶች ደጋግማ ህይወቱን ለማጥፋት ሙከራ ማድረጓ በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠባት በመሆኑ፡ ለዚህ ለፈጸመችው ወንጀል ተመጣጣኝ ቅጣት እንድታገኝ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና አንቀጽ ጠቅሶ ጠየቀ፡፡
የተከሳሽ ጠበቃም እንደዚሁ ስለህጉና፤ ስለጉዳዩ፤ በማብራራት ቅጣቱ እንዲቀልላት አስተያየቱን አቀረበ፡፡
በዚህ የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ላይ በወጣት እንደሻው በቀላ ወላጆች ቤት ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉት በተለይ የወጣት እንደሻው የሥጋ ዘመድ የሆነው አቶ አበራ ፈይሣ የዝምድና ደረጃው ሳያግደው በሃቅ እንደመሰከረውና፤ በቤት ሠራተኛነት ተቀጥራ የምታገለግለው ወይዘሪት ወርቅ ያንጥፉ አደራ በዐይኗ ባየችው ድርጊት ላይ በሰጠችው የምስክርነት ቃል በተረጋገጠው መሠረት፤ እንደሻው በቀለ ሃይል ተጠቅሞ፤ በተከሳሿ ላይ የሞራል ተቃራኒ የሆነ፤ የወደፊት የትዳር ህይወቷን ያበላሸና፤ ከምትኖርበት ማህበረሰብ ባህልና እምነት አንፃር ዝቅተኛ ግምት የሚያሰጣትን ወንጀል የፈጸመባት በመሆኑ፤ ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘም ጋርጠው መራን በገንዘብ በመግዛት በወንድሟ ላይ የድብደባ ወንጀል በማስፈጸም ያደረሰባት ድርብ፤ ድርብርብ ጥቃት ለጋ አእምሮዋን የነካና፤ ለወንጀል ያነሳሳት ድርጊት መሆኑን :: ወጣቷ
በምትኖርበትም ሆነ በተማረችበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፍጹም ጨዋና
ዕላማዊ ዜጋ መሆኗ የተመሰከረላት ከመሆኑ በተጨማሪ፧ ወላጅ አባቷ
ለግዳጅ ተጠርቶ በጦር ሜዳ ላይ በመሞቱ ምክንያት፧ በለጋ እድሜዋ
ከራሷ ጭምር ሶስት ቤተሰብ የማስተዳደር ሃላፊነት የተሸከመች ወጣት
በመሆንዋ ክቡር ፍርድ ቤቱ.....

ሀ. ተከሳሽ ወንጀሉን ለመፈጸም የተነሳሳችበትን ሁኔታ
ለ. የተከሳሽን የዕድሜ ሁኔታ
ሐ. ተከሳሽ ወንጀሉን ስትፈጽም የነበረችበትን ሁኔታ
መ. የተከሳሽን የቤተሰብ ኃላፊነት ደረጃ
ሠ. ተከሳሽ ከዚህ በፊት በማናቸውም ወንጀል ተከሳ ቅጣት ያልተፈፀመባትና፤ ለወደፊቱ ያላትን የሥነ ምግባር ታራሚነት ከግምት ውስጥ በማስገባት እስከዛሬ ድረስ በማረሚያ ቤት የቆየችበት ጊዜ በቂ
ሆኖ ቅጣቱ እንዲቀልላት በማለት አስተያየቱን ሰጠ፡፡
ከዚህ በኋላ የሚቀረው ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ የቅጣት ውሣኔ የሚሰጥበትን ዕለት በጉጉትና በናፍቆት መጠባበቅ ብቻ ሆነ
አንዱአለም በአሁኑ ሰዓት ምጽዋ በባህር ኃይል ውስጥ በስልጠና ላይ ይገኛል፡፡ ለኪስ የሚሰጠውን አነስተኛ ገንዘብ የሚልከው ለእህቱ ነው፡፡ እህቱ በማንኛውም ረገድ እንድትበረታ፣ መታሰር ማለት በህይወት ውስጥ ከሚገጥሙ የኑሮ ውጣ ውረዶች አንዱ እንጂ ከህብረተሰቡ መገለል ማለት ያለመሆኑን እየገለጸ “አይዞሽ” እያለ በማጽናናትና፤ ስለሱ እንዳታስብ በቀይ ባህር ዳርቻ፣ በመርከብ ላይ፣ ብቻውንና ከጓደኞቹ ጋር
ሆኖ የተነሣቸውን ፎቶ ግራፎች ለሷና
👍4
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

በዚያን ታሪካዊ ቀን አንዱአለም ብቻ ሳይሆን ያንን የመሰለ ክፉ ንግግር ተናግሮ አእምሮዋን ያቆሰለው ዶክተር ባይከዳኝም የፍርድ ውሳኔው በሚሰጥበት ዕለት እንዲገኝ ስለፈለገች ... አዜብ ልትጠይቃት
ወህኒ ቤት ሄዳ በተገናኙበት እለት.....
“አዜቢና እግዚአብሔር ከሞት ካተረፈኝና፤
ለዚህ ካበቃኝ፤ ዶክተር ባይከዳኝም በዚያን እለት ፍ/ቤት ተገኝቶ ሸርሙጣ ያለመሆኔን ቢያውቀው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ አለቻት፡፡ ይህንን ስትናገር አዜብ ትኩር
ብላ ስታያት ቆየችና ፈገግ አለች :: የአዜብ የፈገግታ ምንጭ ለጊዜው ባይታወቃትም እሷን ተከትላ እሷም ፈገግ አለች፡፡
እንዲገኝ አደርገዋለሁ” አለቻት፡፡ በእርግጠኛነት፡፡ አዜብ እንደዚያ ፈገግ ያለችውና እንደሚገኝም እርግጠኛ የሆነችው ልትሰራው ያሰበችው ተንኮል ፍጻሜው መድረሱን በማወቋ ነበር፡፡ ሁል ጊዜም የሚከነክናት ነገር በዶክተርና በሻምበል መካከል የነበረው ልዩነት ነበር።
ትህትና ልጃገረድ ያለመሆንዋን ሲያውቅ ፤ ሻምበል ፍቅሩን ያቋረጠበት ሁኔታና፤ የዶክተር ሁኔታ፤ ፍጹም የተለያየ ነበር፡፡ሻምበል አባብሎና አጽናንቶ፤ነው የሸኛት፡፡ ዶክተር ግን አዋርዶ፡ ሞራሏን ነክቶና፡ የጭካኔ ንግግር ተናግሮ ነው ያባረራት፡፡ ለዚህ ድርጊቱ ደግሞ መቀጣት አለበት
ብላ ታስብ ስለነበረ ፤ በዚያን እሷና ብሩክ ብቻ በሚያውቁት እለት ተገኝቶ እንዲቀጣ ፈለገች፡፡
በማግስቱ የካቲት አሥራ ሁለት ሆስፒታል የደረሰችው ከቀኑ አምስት ሰዓት ሲሆን ነበር፡፡ ምሽቱን ስትቀምም ያደረችውን መልእክት ይዛ፡፡ እዚያ እንደደረሰች፤ የዶክተር ባይከዳኝን የምርመራ ክፍል ጠይቃ የሚያሳያት ሰው አገኘችና ወደዚያው አመራች፡፡
ዶክተር የመጨረሻውን በሽተኛ እየመረመረ ነበር፡፡ ቀስ ብላ በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ ተመለከተች፡፡ አጠገቡ የነበረችው ነርስ ፈጠን ብላ መጣችና.....
“ምን ፈለግሽ?” አለቻት አንገቷን ወጣ አድርጋ፡፡
“ለግል ጉዳይ ዶክተር ባይከዳኝ ዘንድ ነው የመጣሁት፡፡” ስትላት ሲስተሯ ከላይ እስከታች ተመለከተቻትና “በሽተኛ እየመረመረ ስለሆነ ጠብቂ” ብላ በሩን መልሳ ዘጋችውና ሰው የሚፈልገው መሆኑን ነገረችው ::
ዶክተር ምርመራውን ከጨረሰ በኋላ፤ እንድታስገባት ለሲስተሯ ነገራትና፤ በሩን ከፍታ እንድትገባ በምልክት ጠራቻት ከዚያም አዜብ በሳቅ እየተፍለቀለቀች ፤ እራሷን አስተዋወቀችው፡፡ ዶክተርም
እንድትቀመጥ ጋበዛት፡፡ ሁኔታዋ ግር አሰኝቶታል።
“ለትንሽ ደቂቃ ብቻህን ላነጋግርህ ፈልጌ ነበር ዶክተር” አለችው፡፡
በዚህ ጊዜ ሲስተሯ የዶክተርን የስንብት ቃል ሳትጠብቅ ሹልክ ብላ ወጣች፡፡

“የትህትና ጓደኛ ነኝ” አለችው፡፡ ለምን እንደሆነ ባያውቀውም የትህትናን ስም ሲሰማ ልቡ ዘለለች፡፡ ከዚያም አንዲት የተጣጠፈችና የተቀደደች ፖስታ ከኪሷ አውጥታ፤ አቀበለችው፡፡ በፖስታው ላይ
ያለውን አድራሻ ተመለከተ፡፡ ለዶክተር ባይከዳኝ ሙሉሰው የካቲት አስራ
ሁለት ሆስፒታል ይላል ፡፡ዶክተር ነገሩ ግራ አጋብቶት፤ አይን አይኗን እያየ፤ ደብዳቤውን ተቀበላትና በልቡ የምን መልእክት ይሆን የይቅርታ ወይንስ የስድብ? ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡ ከወዲሁ መገመት አልቻለም፡፡
መልሱን የሚያገኘው ከደብዳቤው ብቻ ነው፡፡ በጉጉት ተውጦ ደብዳቤውን
ገልጦ ማንበቡን ቀጠለ፡፡ እያንዳንዷ ቃላት ተመርጣ የተጻፈች ስለነበረ፡፡ ወደ ውስጥ በዘለቀ ቁጥር የልብ ምቱ እየጨመረ ሄደ፡፡ አዜብ ራሷ ያዘጋጀችው ቀኑ ያልተጻፈበት ደብዳቤ ነው፡፡ ደብዳቤው ልክ ትህትና ለሻምበል ብሩክ የጻፈችለትን አይነት ይዘት ነበረው፡፡ እጅግ የምታፈቅረው የምትወደውና፤ የምታከብረው፤ ባለውለታዋ መሆኑን ይገልጻል ፡፡በፍቅር ስላሳለፉት ጊዜያት ጣፋጭነትም ያወራል፡፡ የመለያየታቸው ምክንያት በመቃቃር ወይንም ደግሞ በመጠላላት ሳይሆን፤ በድንገት በተፈጠረ
ችግር ምክንያት መሆኑን ያስረዳል፡፡ የጸባቸው መንሰኤ በሆነውና የምትወደውን ሰው እንድታጣ ክብረ ንጽህናዋን በደፈረው ወንጀለኛ ላይ
እርምጃ ወስዳ ለመሞት መወሰኗን ካወራ በኋላ፤ እስከ ወዲያኛው አፍቃሪ እህትህ ትህትና ድንበሩ በሚል ይደመድማል፡፡ ምንድነው
ተአምሩ? ዶክተር ግራ ተጋብቶና፤ ፊቱ ላይ ቸፍ ያለውን ላቡን እየጠራረገ፤ በአዜብ ላይ አይኖቹን አፈጠጠ...
“አይዞህ ህይወቷ ተርፏል” ስትል አረጋጋችው፡፡ ዶክተር ከድንጋጤ ሳይመለስ ቡዝዝ ባሉት አይኖቹ ሲመለከታት ከቆየ በኋላ ስለሆነው ነገር እንደ አዲስ ጠየቃት፡፡ ከደብዳቤው የተረፈውን በቃሏ ተረከችለት፡፡ ትህትና ደብዳቤውን አሽጋ በጐረቤት በኩል የላከችላት መሆኑን፡ ደብዳቤው ተቀዶ ከተነበበና፧ እጅግ ከዘገየ በኋላ፤ እንደቀላል ነገር እንዲደርሳት መደረጉን፡አሁን ትህትና ለፍርድ ቀርባ ፍርዷን
እየተጠባበቀች መሆኑንና፤ ድርጊቱ የተፈጸመበትንም ጊዜ በግማሽ
አሳጥራ በቁጭት ስትነግረው ፤ አመናት፡፡አሁን ለዶክተር ቁም ነገሩ የጊዜው ጉዳይ አይደለም፡፡ ለሱ ዋናው ቁም ነገር እውነቱን ማወቁ ብቻ ነው፡፡
ዶክተር ለመጨረሻ ጊዜ ከትህትና ጋር የተለዋወጡት መራራ ቃላት ታወሱት፡፡
ካንተ በኋላ የተዋወቅሁት ፍቅረኛዬ በክብር የወሰደው ነው” የሚለው አጥንት የሚሰብረው ንግግሯ ታሰበው፡፡አሁን ደግሞ አዜብ የምትነግረውና የላከችለት ደብዳቤ የሚያወራው ታሪክ ከዚህ የተለየ
ነው፡፡ የትኛው ይሆን እውነቱ? በእርግጥም ትህትና በግድ የተፈጸመባት
ወንጀል ነበር ወይንስ የታሰረችበት ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን?

በአጠቃላይ እውነቱን ለማወቅ፣ የክሱን መንስኤ፣ የወንጀሉን አፈጻጸምና ድርጊት ለማረጋገጥና፤ ትህትና ለፍርድ ቀርባ ውሣኔ በሚሰጥበት እለት እዚያ አጠገቧ ተገኝቶ እውነታውን ለማየት፤ ልቡ ተንጠለጠለች፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ምንም እንኳን ከተለያዩ አንድ አመት ቢሞላቸውም ሙሉ ለሙሉ ከልቡ አልጠፋችም ነበረና፤ ሄዶ ዐይኖቿን በማየት፤ የአንድ ዓመት ናፍቆቱን ለመወጣት ቸኮለ፡፡
“አልቀርም እመጣለሁ” በማለት ፍርዱ የሚሰጥበትን ቀን በማስታወሻ ደብተሩ ላይ መዝግቦ ከያዘው በኋላ ስለእናቷ ጤንነት ጠየቃት። በዘውዲቱ ሆስፒታል በተመላላሽነት በመታከምና በተሻለ
የጤንነት ደረጃ ላይ የምትገኘ መሆኗን ነገረችው፡፡አዜብ ተሰናብታው
ከወጣች በሁዋላ፤ ዶክተር በሃሰብ ፈረሱ ላይ ተጭኖ ሽምጥ ይጋልብ ጀመር፡፡ ምንድነው ይሄ ተአምር? እውነት ትህትና ድንግልናዋን ያጣችው ተደፍራ ነበር ማለት ነው? አላታለለችኝም ነበር ማለት ነው? ይሄ ሆኖ ከተገኘ በቀላሉ ሊወጣው ከማይችለው የህሊና ጸጸት ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ሲያስበው፤ ዘገነነው፡፡ ነገሩ እውነት እንዳይሆን ተመኘ፡፡ ያሳለፉት ጊዜ ትዝታው እንደ አዲስ ተቀሰቀሰበት፡፡ የዚያ
የደብረዘይቱ የማይረሳ ትዝታ መጣበት፡፡ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ እየተላፉ
እሱ በፈለገው መንገድ አንድም ቀን ተቃውሞ ሳታሰማ፤ እሱን ደስ እንዲለው ታደርግ የነበረው ጥረት፤ ጠጥታ የማታውቀውን መጠጥ እንኳ ለሱ ስትል ታደርገው እንደነበረ፡ ድንግልናዋንም በፍቅር አሳልፋ ስትሰጠው የነበረው ሁኔታዋ : ድቅን አለበት፡፡ ከራሱ ደካማነት እንጂ ከእሷ ምንም የጐደለበት ነገር አልነበረም፡፡ ያቺ ለስላሳ :ያቺ ቅልስልስ፡
ያች ስትስቅ ስትናገር፤ አፍ የምታስከፍት ትንሽ ልጅ፡ ለሱ ሁሉንም ነገር ሆናለት ነበር፡፡ እሱ ግን እንደዚያ አልሆነላትም፡፡ ቅስሟን ሰብሮ፤ ሞራሏን ነክቶ ነበር፤ እንደውሻ ከቤቱ ያባረራት፡፡ ያውም እንደዚያ የምትንሰፈሰፍላት እናቷን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትሞት የቁም መርዶ አርድቶ ነው ያባረራት፡፡ እሷ ግን ይሄውና ለሱ ስትል ህይወቷን
እስከማጥፋት የሚደርስ እርምጃ ወስዳ፤ ፍቅሯን እየገለጸችለት ነው ነገሩ እውነት
👍3
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

....አዜብና አንዱአለም አጠገቡ ናቸው፡፡ ከኪሱ ውስጥ የሆነ ነገር አወጣ፡፡ በትንሽ የፕላስቲክ ሳጥን ውስጥ የተቀመጠች..ውድ ነገር:: በመጠን በጣም ትንሽ፤ በቁም ነገር ግን እዚያ እላይ!! ቀለበት. የቃል ኪዳን ቀለበት ... ስለ እውነተኛ ፍቅር የተዘጋጀች ፤ የትዳር መጠንሰሻ:
የቃል መተሳሰሪያ፤ ቀለበት... በምህጻረ ቃል የሱና የሷ ስም የተጻፈበትን
ቀለበት አወጣና......

“በመንፈሰ ጠንካራነትሽ ለሰጠሽኝ ትልቅ ትምህርት፡ ለእውነተኛ ፍቅር ስትይ ለከፈልሽው መስዋዕትነት፣ በታማኝነት ፀንተሽ ኣብረን ለቆየንባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ማስታወሻ እንድትሆን፡ ይህቺ ሁለት ዓመት ለቀሪ ህይወትሽ ትምህርት የምታገኝበት፣ እኔ ደግሞ ለሠርጋችንም ሆነ ከሠርጋችን በኋላ የትዳር ህይወታችንን በሰላም ለመምራት እንዲያስችለን የምዘጋጅበት እንዲሆንና፤ የማረፊያ ቤት ቆይታሽ፤ መጪውን ብሩህ
ተስፋ አሻግረሽ የምትመለከችበት የዕረፍት ጊዜ እንዲሆንልሽ በመመኘት፤
ያዘጋጀኋትን ገፀ በረከት፤ ይህችን የቃል ኪዳን ቀለበት፣ እንድትቀበይኝ” አለና ከጉልበቱ በርከክ ብሎ ሽቅብ ተመለከታት፡፡ ከዚያም ፍዝዝ ባለችበት
እንባዋ ጉንጮቿን እያቋረጠ፤ ቁልቁል መውረድ ሲጀምር፤ ቀልጠፍ ብሎ
የግራ እጇንና ቀለበቷን ወደ ላይ ከፍ አደረጋቸው፡፡

ከዚያ የከበበው ሰው በሙሉ በደስታና በሆታ አጨበጨበላቸው፡፡ ዕልልታውን አቀለጠላቸው፡፡ አንዱዓለምና አዜብ ተቃቀፉ፡ ሚስጥሩን የምታውቀው አዜብ ብቻ ነበረች፡፡ ቀለበቱንም የመረጠችለት እሷ ናት።
ለአንዱአለም ግን ሁኔታው ድንገተኛ ነበር፡፡ በፍርድ ቤቱ ቅጽር ግቢ ውስጥ ሌላ ተዓምር፡፡ ቃል ኪዳን ......ከዚያም
ቀለበቷን በጣቷ ውስጥ ሲያጠልቅ፤ አዜብና አንዱአለም በደስታ ሲቃ ተውጠው፤ እልልታቸውን፤ አቀለጡት፡፡
ያቺን ቀለበት በዚህ በዛሬው ዕለት ሊያደርግላት የወሰነበት ምክንያት ነበረው፡፡ ይህቺ የውሣኔ ዕለት፣ ይህቺ የፍርድ ቀን፡ በነፃ የምትለቀቅበት ሳይሆን፡ የህግ እስረኛ ሆና በማረፊያ ቤት እንድትቆይ የሚወሰንበት ዕለት መሆኗን አስቀድሞ ስለሚያውቅ፣ በዚህች ቀን የህግ እስረኛ በመሆንዋ፤ የመገለል ስሜት እንዳይሰማትና፤ የሞራል ውድቀት
እንዳይደርስባት፣ መታሰር ማለት፤ ከዚህ ዓለም መገለል ማለት ያለመሆኑን ተረድታ፤ በጥንካሬና በጽናት የእስር ዘመኗን እንድትጨርስ ለማድረግ፣ በዚያች የውሣኔ ዕለት፤ እስረኛ ብቻ ሳትሆን፤ የታጨች ሙሽራ መሆኗን ጭምር እንድታውቅ፣ የህይወት አጋር ፤የትዳር
ጓደኛው ! ከሷ ሌላ ማንም እንደሌለው ሊያረጋግጥላት፡፡ ሊያበረታታት፡፡
ስለወሰነ፤ የቀለበት ስነ ሥርዓቱን ባልጠበቀችው በዚያ ሁኔታ ሲፈጽምና
ቀለበቷን በጣቷ ላይ ሲያኖርላት፣ በደስታ ሲቃ ተውጣ፣ እስረኛ መሆኗን ፍጹም ረስታ፤ በሳቅ እየተፍለቀለቀች፣ ሻምበልን አንገቱ ላይ ተጠመጠመችበት፡፡ ሻምበል አደራውን ተወጣ! የፈራረሰ በድን አካሏ በወደቀበት ስፍራ በመቃብሯ ላይ ሳይሆን፤ ያቺን ውብ የፍቅር ጽጌረዳ
አበባ፤ አለንጋ በሚመስለው የቀለበት ጣቷ ላይ እና፤ በፍቅሩ ምክንያት ታላቅ ጉዳትና ስብራት በደረሰበት ልቧ ውስጥ በክብር አስቀመጠላት ::
ዶክተር ባይከዳኝ በዚያ በሚያየው ነገር ተደናግጦ እና ተገርሞ አፉን በሰፊው ከፍቶ በመቅረቱ ምክንያት፤ እጆቹን ማራገብ እንኳ ተስኖት!በተከፈተው አፉ
ውስጥ ይመላለሱ የነበሩ ዝንቦች ፤ ያለከልካይ ተዝናኑበት፡፡ ከዚያም እንደምንም ብሎ ከሰመመኑ ሲመለስ፤ የሆነ የቅናት መንፈስ ሰውነቱን ውርር አደረገው :: ያንን ያልጠበቀውን
ትእንግርት እያየ፤ አፉን ከፍቶ በቀረበት ቅጽበት ሌላ ነገር ተደገመ
“እኛ ደግሞ ለዛሬ የወርቅ ቀለበት ያላዘጋጀን ቢሆንም፧ ልክ አንቺ ከማረፊያ ቤት ወጥተሽ፤ የጋብቻ ስነ ስርዓታችሁን ስትፈጽሙ ፤
እኔና አዜቢና ደግሞ፧ የቃል ኪዳን ቀለበታችንን የምናስርበት ዕለት
ለመሆኑ ማረጋገጫው፤ የቃል ኪዳን ማህተሙ፤ ይኸው!” አለና ወንድሟ
አዜብን፡ የምታፈቅራት ጓደኛዋን፡ ወደ ደረቱ ሳብ፤ እቅፍ፤ አድርጉ አንገቷን ቀና በማድረግ፤ ከንፈሯን ግጥም አድርጎ ሲስማት፡ ይህ ሁሉ ተአምር በፍጹም ያልጠበቀችው ነበርና፤ ትህትና ከደስታዋ ብዛት የምትሆነውን አጣች፡፡ ያቺ ከልጅነት እስከ እውቀት፤ በሀዘንና፤ በችግሯ
አንድም ጊዜ ተለይታት የማታውቅ፤ እንደነፍሷ የምትወዳት ጓደኛዋ፤
ይሄውና የወንድሟ ሚስት ልትሆን፡ የሚወልዱዋቸው ልጆች የአክስቴ ፡
የአጎቴ፡ ልጅ ሊባባሉ ነው፡፡ የጓደኝነት ፍቅራቸው ወደ ስጋ ዝምድና ሊሸጋገር ነውና፤ አልቻለችም፡፡እንባዋ በድጋሜ ኮለል ብሎ ሲወርድ አሁንም ህዝቡ
ጭብጨባውን አቀለጠላቸው......

በሚያየው ተደጋጋሚ ትርኢት ተደንቆ፤ በሳቅ እያውካካ ዶክተር ባይከዳኝ ከህዝቡ ፈንጠር ብሎ ቆሞ ነበር፡፡ ያንን ሁሉ ትርኢት ተመልክቶ ካበቃ በኋላ ግን፤ የቅናት ስሜቱ እየተገፈፈ ሄዶ፤በምትኩ የደስታ ስሜት ይሰማው ጀመር፡፡ ምንም እንኳ የዛሬው የሻምበል እድል የሱ እንደነበረ ቢሰማውም፤ በራሱ ጥፋት እድሉን አበላሽቷልና፤ ይህቺ ለሱ ፍቅር ስትል ትልቅ ዋጋ የከፈለች ቆንጆ ልጅ
ከዚያ ሁሉ ችግር በኋላ ከጐኗ ቆሞ አይዞሽ የሚላት አጋር በማግኘቷ
ተደሰተ :: ትህትና ምንም በደል ያላደረሰችበት ልጅ መሆኗን ህሊናው
ደጋግሞ ስለጨቀጨቀው ይቅርታ ሊጠይቃትና እንኳን ደስ አለሽ ሊላት
ፈለገ፡፡ ከዚያም ጠጋ አለና.....
“ለተፈጸመው ስህተት ሁሉ አዝናለሁ፡፡ ላደረስኩብሽ በደልም ከልብሽ ይቅርታ እንድታደርጊልኝ እለምናለሁ :: በሰላም የእስር ዘመንሽን እንድትጨርሺና! መልካም የቀለበት ስነ ስርአት እንዲሆንልሽም ከልብ እመኝልሻለሁ
አላት፡፡
አንተም ፈቃደኛ ሆነህ እዚህ በመገኘትህና እውነቱን በማወቅህ
እኔም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ አመሰግንሃለሁ፡፡ ያለፈውን ሁሉ
እረስቼዋለሁ፡፡ላንተም መልካሙ
ሁለ እንዲገጥምህ እመኝልሃለሁ፡፡ አዲስ ቀን ይመጣል : አዲስ ህይወት ይቀጥላል.በማለት አጸፋውን መለሰችለትና፣ ሻምበልን አየችው፡፡ ሻምበልም አያት::ከዚያም ሶስቱም እርስ በርሳቸው ተያይተው ፈገግ ሲሉ፤ አዜብም
ዶክተር ባይከዳኝን እያየች ፈገግ አለች፡፡ ሰራሁልህ ማለቷ ይሆን?

ለጊዜው ቢደብቋትም፤ ውሎ እያደር ለቅሶዋ ቢበዛና ውትወታዋ ቢያስጨንቃቸው፤ እውነቱን ነገሯት፡፡ እንደፈራችውም ልጇ በጤናዋ
እንዳልጠፋች ካወቀች ዕለት ጀምሮ፤ በበሽታዋ ላይ ሌላ በሽታ ተጨመረባት፡፡ ትህትና ከሆስፒታል ድና ብትወጣም እስር ቤት መግባቷን ሰማች፡፡ መርዶ... ትንሹ ልጇ አንዱአለም ደግሞ በእንጭጭነቱ ተለይቷት ለመሄድ መዘጋጀቱን ሰማች፡፡ ሌላ የልብ ስብራት... ያንን የምትወደው ባለቤቷን የነጠቀባት ጦርነት፤ አሁን ደግሞ ሮጦ ያልጠገበ አንድ ፍሬ ልጇን እንዳይነጥቅባት በሥጋት ተውጣ፤
ጠዋትና ማታ እዬዬ ብቻ ሆነ፡፡ሁለቱንም አለኝታዎቿን ከጐኗ ስታጣቸው፤ የወላድ መካን የሆነች መሰላት፡፡ ትህትና ከሆስፒታል ከወጣች በኋላም እቤቷ እንድትገባ ሳይሆን፤ ፍርድ ቤቱ በማረሚያ ቤት እንድትቆይ መወሰኑን ስትሰማ
ከዛሬ ነገ በነፃ ትለቀቅልኛለች ብላ በጉጉት እየተጠባበቀች ጭል፤ ጭል፤ትል የነበረች ተስፋዋ ድርግም ብላ ጠፋች፡፡
ይህ የጨለማ ህይወት ፍጹም ልትወጣው የማትችለው ሆነባት።የቤት ሰራተኛዋ እታፈራሁ የልጅ ያክል ብትንከባከባትና፤ ሻምበል ብሩክና አዜብም ልጆቿን ሊተኩላት ከጐኗ ሳይለዩ
ደፋ ቀና ቢሉም፤ሳይሆንላቸው ቀረ፡፡
ከዚህ በኋላ በሽታው በአንድ ወገን፤ የልጆቿ ናፍቆት በሌላው ወገን ሆነው፤ እየተጋገዙ፤ ስጋዋን እኝከው በመጨረስ፤ የሞት ድግሷን ያፋጥኑት ጀመር..
ትህትና ማረሚያ ቤት በቆየችበት ጊዜ ብቸኝነት፣ መታከት ተስፋ መቁረጥና
👍1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

#ክፍል_ሶስት

#ትንሣኤ
በሁለቱ መንግስታት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት የምርኮኞች ልውውጥ የሚጀመርበት የመጀመሪያው ምዕራፍ......
የድሬዳዋ ከተማ አሸብርቃለች፡፡ ገንደቆሬ፣ ገንደገራዳ፣ መጋላ፣ ከዚራ፣ ለገሀሬ፣ ..... መንደሮች በሙሉ በደስታ ስቀዋል፡፡
በየመንገዱ ግራና ቀኝ ተተክለው ቀዝቃዛና፤ ነፋሻማ አየርን የሚረጩት ዛፎች በደስታ ተውጠው የሚደንሱ ይመስላሉ፡፡ በዚያች ምድር ላይ የተካሄደው ቀውጢ ጦርነት አልፎ፤ ያንን የመሰለ የሰላም አየር መተንፈስ መቻል ዳግማዊ ልደት ነው፡፡
በሐረርጌ ምድር፡፡ በደገሀቡር፣ ቀብሪደሀር፣ መራራሌ፣ በሺላቦ፣
ደቦይን፣ በቆራሄ አሸዋማ ሜዳ፣ በኦጋዴን በረሃ፣ በካራማራ ተራሮችና በሌሎችም ሺህ ሌሊት ሺህ መአልት የፈሰሰው ደም፣ የተከሰከሰው አጥንት፣ያስገኘው ውጤት፡፡
በዚያን ቀውጢ ሰዓት ላይ ለዳር ድንበር ሲሉ ከጠላት ጋር እየተናነቁ አኩሪ ገድል የፈጸሙት፤ በደማቸው ማህተም፤ በአጥንታቸው ክስካሽ፤ ምድሪቱን ያቀሉት...የመስዋዕትነት ፈርጦች! የሚጠበቁበት ዕለት......

ሰማዩ በዚያን ቀውጢ የጦርነት ወቅት በኢትዮጵያ አየር ሃይል የተሠራውን አስደናቂ ትርኢትና ተአምር አፍ አውጥቶ ሊናገር፣ የታሪክ ምስክርነቱን ሊሰጥ፣ የተዘጋጀ ይመስል አጉረመረመ፡፡ ለሚወዷት እናት አገራቸው ዳር ድንበር ሲሉ የተፋለሙና ልዩ ልዩ ጀብድ ከፈጸሙ በኋላ በጠላት እጅ ወድቀው በባእድ ሀገር በምርኮኝነትና፤ በእስረኝነት ለበርካታ
አመታት ከቆዩ በኋላ በሁለቱ መንግስታት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ዛሬ ወደሚያፈቅሯትና፤ ወደሚወዷት፤ እናት አገራቸው የሚመለሱበት እለት ስለሆነ፤ እነዚህን ውድ የሀገር አለኝታዎችና፤ ጀግኖች፤በልዩና፤ በደማቅ አቀባበል ፤ ሊቀበል ህዝቡ የአውሮፕላን
ማረፊያውን አካባቢ አጥለቅልቆታል....
ማርሽ የሚያሰማው ሠራዊት በተጠንቀቅ ቆሞ ይጠባበቃል።ባንዲራዎች ይውለበለባሉ፡፡ ህዝቡ ይሯሯጣል፡፡ ይራወጣል። ሰማይ ሰማዩን እያንጋጠጠ ይመለከታል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ትላልቅ አሞራዎች ያሳስታሉ፡፡ የሁሉም ልብ ተንጠልጥሏል፡፡ እነማን ይሆኑ?! ሞቱ ተብለው ደረት
የተመታላቸው፣ ተዝካር የተበላላቸው፣ ማን ያውቃል? በህይወት ሊገኙ
ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህ ጦርነት በተካሄደባቸው ብዙ አገሮች በተደጋጋሚ
የታየ ክስተት ነው፡፡
ሰዓቱ ደረሰ፡፡ ሰማዩ እንደገና በከፍተኛ ድምፅ አጉረመረመ፡፡አውሮፕላኗ በርቀት ታየች፡፡ ከዚያም እየጐላች ፤እየጐላች፤ መጣችና፤በማረፊያው ላይ እየዞረች፤ ማንዣባብ ጀመረች።
የሰው ጩኸት ሁካታ... ግርግር... ትርምሱ...ሌላ ሆኗል፡፡ማርሽ በረጅሙ ይሰማል፡፡ አውሮፕላኗ አዘቀዘቀች..... ከዚያም አኮበኮበችና አረፈች፡፡
ጀግኖች የታደሙባት አውሮፕላን! ለዳር ድንበሯ ሱሉ ደማቸውን ያፈሰሱላትን፣ በእስር የማቀቁላትን፣ ጥለው የወደቁላትን፣ ታስረው የተገረፉላትን፣ የጦር ምርኮኞችን ይዛ ይሄውና አውሮፕላኗ መሬት ላይ አረፈች....
የአውሮፕላኗ በር ተከፍቶ አንድ ረጅም፧ ቀጭን፤ መነጽር ያደረገና በአየር ኃይሉ ውስጥ በጦር ጄት የጠላትን ሃይል ድባቅ
በመምታት በደማቅ ቀለም ታሪክ ያስመዘገበ ምርኮኛ ብቅ አለ፡፡ማርሹ ይሰማል፡፡ እልልታው ቀለጠ!! ግማሹ በሲቃ ያለቅሳል፣ይፈነድቃል፡፡ ምርኮኞቹን ለማየት ሰው በሰው ላይ ይንጠላጠላል፣
ትዕይንቱ ብዙ ነው፡፡ ከዚያም የተዘጋጀውን እቅፍ አበባ ምርኮኛው ተቀበለ፡፡
ምርኮኞቹ ከአውሮፕላኗ እንደወረዱ መሬቷን ይስማሉ። አፈሯን ይልሳሉ፡፡ ያለቅሳሉ፣ ይንከባለላሉ፡፡ የደስታ እንባ... የናፍቆት እንባ... የትዝታ እንባ...
ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት ከአገር፤ ከወገን፣ ከቤተሰብ ጋር ተለያይተው ፤ የብቸኝነትንና የመከራ ኑሮን ሲገፉ ከቆዩ በኋላ፤የሚወዱትንና፤ የሚያፈቅሩትን፤ ህዝብና አገር መቀላቀል ዳግም መወለድ
ነውና፤ ምርኮኞች ዳግም የተወለዱ ያህል በደስታ ሰከሩ። እንደዚያ ዳር ድንበርዋን ሊያስከብሩላት፤ ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው፡ ሳንጃ ለሳንጃ ተሞዣልቀው፡ ጥለው የወደቁላት፡ የውድ ሀገራቸውን ለም አፈር ለማሽተት በመቻላቸው በደስታ የሚሆኑትን አጡ ...ህዝቡም በእልልታና በሆታ የጀግና አቀባበል አደረገላቸው፡፡ ደስ የሚል ከህሊና የማይጠፋ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት......
ለተወሰኑ ቀናቶች በድሬዳዋ ከተማ እረፍት አድርገው ከቆዩና መንፈሳቸው ከተረጋጋ በኋላ፣ በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ ዘመዶቻቸውን ሊቀላቀሉ የቸኮሉት ቀድመው ተንቀሳቀሱ፡፡


እለተ ቅዳሜ! አዲስ አበባ!! የኢትዮጵያ ዋና ከተማ! ቀዝቃዛ ንፋስ ይነፍስባታል ። በተለይ የባህር ማዶው ዛፍ ለቅዝቃዜው የራሱን ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል፡፡
ባቡሩ መንገደኞቹን ጣቢያው አራገፈ፡፡ ግፊያው ለጉድ ነው፡፡ግማሹ ሲመጣ ግማሹ ሲሄድ... የገቢና ወጪ መንገደኞች ምልልስ የማያቋርጥበት አምባ......
ጊዜው ለዐይን ያዝ ማድረግ የጀመረበት ሰዓት ነው፡፡
አንድ ቁመቱ ረዘም ያለ፣ ሰውነቱ በበረሃ ግርፋትና በእስር ስቃይ ምክንያት የተለበለበ ግንድ ቢመስልም፤ በሰላሙ ጊዜ ማራኪ መልክና ቁመና እንደነበረው አሁንም በግልጽ የሚታየው ትክለ ሰውነቱ
ዐቢይ ምስክርነቱን የሚሰጥለት፤ ከሲታ ሰው ከባቡሩ ወረደ፡፡
ደረቱ ሰፋ ያለ፣ ፀጉረ ዞማና ዐይኖቹ ጐላ ጐላ ብለው የሚታዩ ረጅም ሰው ነው፡፡ ሻንጣ አንጠልጥሏል፡፡ ከተሰጠው የኪስ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛውን ያዋለው ለሁለት ሴቶችና፤ ለአንድ ወንድ የሚሆኑ ልብሶችን በመግዛት ነው፡፡ ከባቡሩ ወርዶ፤ በአምባሳደር ቲያትር በኩል መጥቶ ፤ ወደ ኦርማ ጋራዥ አቀና፡፡ የሚራመደው በደመነፍስ ዐይነት ነው፡፡
በህልም ዓለም የሚራመድ ይመስላል፡፡
እሱ እራሱ የሚያየው ነገር እውነት መሆኑን ተጠራጥሯል።ግራና ቀኙን በዓይኑ ያማትራል፡፡ ሰዎችን ይቃኛል፡፡ ምናልባት የማውቀው ሰው ካገኘሁ በሚል ግምት ነው፡፡ ግን ማንም የሚያውቀው ሰው አላገኘም፡፡ ድሮ የሚያውቁት ሲያዩት እንኳን፤ በቀላሉ ሊለዩት አይችሉም፡፡ ተለውጧል፡፡ ተጉሳቁሏል፡፡
መንገዶቹ የጠበቡ፣ ቤቶቹም ከምዕተ ዓመት በፊት የነበሩ መስለው ታዩት፡፡ በየመንገዱ ላይ ከሚያያቸው ሰዎች ውስጥ ሶስት ሰዎችን ለማግኘት በናፍቆትና በጉጉት ደጋግሞ ይቃኛል፡፡
የሱ ብርቅዬ፤ ድንቅዬዎች፡፡ ልዩ የህይወቱ ቅመሞች፡፡ የተዳፈነ የናፍቆቱ እምቅ ሊፈነዳ ተቃረበ፡፡ ልቡ ተሸበረ... እየተቃረበ ሲመጣ ልቡ ድው ድው የሚል ድምጽ ሰጠ፡፡ ትንፋሽ አጠረው፡፡
እጅግ አስገራሚ ነው! አስደናቂ
የማይጠበቀው ሰው ፤ እንደዚህ ባልተጠበቀ ሰዓት ከች! ሲል፤ እነሱ
ከአንጀቱ የሚያፈቅራቸው፣ የሚወዳቸው፣ የሚሞትላቸው ቤተሰቦቹ እንዴት ሆነው ይሆን? የሚወዳት ሚስቱ፣ የሚወዳቸው ልጆቹ እንዴት ሆነው ይሆን? ሲለያቸው በነበራቸው ዕድሜ ላይ አስራ አንድ ዓመት ሲጨመርበት የትየለሌ ነው፡፡ ምን መስለው ይሆን?
አቤቱ ፈጣሪ ያንተ ተአምር እንዴት ተወርቶ ያልቅ ይሆን? አደራህን ሁሉንም ለአንድ ቀን እንኳን ቢሆን ዐይናቸውን አይቼው
እንድሞት እርዳኝ፡፡ አንተ ታውቃለህ፡፡
ወባ እንደያዘው ሰው እየተቃረበ መጣ፡፡ ቤቱ ጋ ሲደርስ ሰውነቱ ተንዘፈዘፈበት :: ልቡ በፍጥነት ይመታ ጀመር፡፡
ግቢው ...ያ ...ግቢ የሚወደው ግቢ...እዚያ ውስጥ ያሉት እነ.. መራመድ አልቻለም፡፡ ቆመ፡፡ እንደሀውልት ተገትሮ ቀረ፡፡ ከዚያም ለዘመናት በወስጡ ሲንተከተክ የነበረው እንባ በድንገት ገንፍሉ ወጣ፡፡
ከደስታ ብዛት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ ቤቱን አየው፡፡ ልጆቹን አቅፎ የሳመበትን፣ ከሚያፈቅራት ባለቤቱ ጋር ደስታን ያሳለፈበትን፣ በመጨረሻም ወደ ጦርነት ሲሄድ ከቤተሰቦቹ ጋር ተላቅሶ
👍2🔥1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_አርባ_ሶስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


....ሲንተከተክ የቆየው፤ የብሶት ቋያ የቀቀለው ፤ትኩስ እንባና እልህ እንዴ
እሳተ ገሞራ ገነፈለ፡፡ ከዚያም ኡኡ!! ብሎ እየጮኽ ዋይታውን ማስማት ሲጀምር፤ ከደጅ ተኮልኩሎ ሲጠባበቀው የነበረው ዘመድ አዝማድ በሙሉ ተከታትሎ ወደቤት መግባት ጀመረ፡፡ ስዎች እየተንጋጉ ገቡ፡፡ እሱም ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር መቀላቀሉን ሲያውቅ፤ እጅግ ሆድ ብሶት ማንባቱን
ቀጠለ...

“አመልማል ፍቅሬ፡፡ ትዳሬ፡፡ አመልማልዬ ምነው ጨከንሽ? ምነው ደስታዬን ገፈፍሽው? እንግዳ መቀበሉን ስታውቂ ምነው በኔ ልብሽ ጨከነ? አመልማል አስራ አንድ ዓመት ሙሉ የናፈቀሽ ልቤን
ምነው በሀዘን ጉዳሽው እናቴ? ቤቷ ተጨናነቀች፡፡ እዚያ የገቡት በሙሉ እየመጡ እላዩ ላይ እየተጠመጠሙ ይላቀሱ ጀመር፡፡ የሚያለቅሱት ለሱ ይሁን ለሟቿ አይታወቅም ነበር፡፡ ደስታም ከልክ በላይ ሲሆን ያስለቅሳልና የሚወዱት
መቶ አለቃ ድንበሩ ሞትን ድል ነስቶ ሲያገኙት ቢያለቅሱ ምን ይፈረዳል? የሱ በህይወት መገኘት በአንድ በኩል ታላቅ ደስታን ሲፈጥር፧ እሱ አለችልኝ ብሎ፤ በጉጉት ተውጦ፧ ሊያገኛት የመጣ
ሚስቱን በሞት ተነጥቆ፣ እንደዚያ አንጀቱ እየተርገፈገፈ አንጀት በሚበላ
አለቃቀስ ልቡ ተሰብሮ ሲያዩት፤ የሚፈጥረው የሀዘን ስሜት ከባድ ነው፡፡
ክፍሏ በመርዶና በትንሳኤ መካከል ዋዠቀች፡፡ ለቅሶው ቀለጠ፡፡ እየሄዱ
እላዩ ላይ እየተጠመጠሙ፤ እዬዬ ሆነ፡፡ ደስታው ሙሉ ደስታ ባለመሆኑ
መቶ አለቃ ድንበሩ አለቃቀሱ እጅግ የሚያሳዝን፤ ብዙዎችን በእንባ
ያራጨ ነበር፡፡

አትጨክንም ነበር አመልማል በእንግዳ
ጀርባዋን ሰጠችኝ አረገችኝ ባዳ፡፡
ሞትን አሸንፌ ስመጣ በናፍቆት
ሸሸችኝ፤ ራቀችኝ፤ ኧረ ምን በደልኳት?
አመልማል ትዳሬ አመልማል ህይወቴ
እባክሽ ወይ በይኝ፤ አትጨክኝ እናቴ፡፡
አለሽልኝ ብዬ በጉጉት ስመጣ
ምነው ጉድ አረግሽኝ ደስታዬ ቅጥ አጣ፡፡
ፋናዬን ትንሿን አንዱዬ አካሌን
የአጥንታችን ፍላጭ ሁለት ልጆቻችን፡፡
ኧረ የትደረሱ እባክሽ ንገሪኝ
አንዴ በሹክሹክታ ድምፅሽን አሰሚኝ፡፡
ፈጣሪዬ ስማኝ ልንገርህ ብሶቴን
ዐይኖቿን አይቼ የምወዳት ሚስቴን፡፡
ፍቀድልኝ ባክህ ናፍቆቴን ልወጣ
ተከትያት በአካል ጠቅልዬ እስክመጣ፡፡
አመልመል አመልማል
የትዳሬ ዋልታ፡፡
እኔ ድፍት ልበል፤ እኔ ልንገላታ፡፡
መከራና ስቃይ ደቁሰው ገደሉሽ?
አይዞሽ እመጣለሁ፡፡
የህይወትን ሽክም
በምድር ባልረዳሽም፡፡
እዚያ አግዝሻለሁ፡፡
ናፍቆቴን ልወጣ
አልቀርም እመጣለሁ፡፡

የሀዘን እንጉርጉሮ አንጐራጐረላት፡፡
በዚያን ሰዓት በሻምበል ብሩክና በትህትና ሰርግ ላይ ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው፤ እንደ ወላጅ ሆነው፤ የዳሯቸው የረጅም ጊዜ ጐረቤታቸው አዛውንቱ አቶ ብራቱ በተፈጠረው ሁኔታ በደስታ ሰክረው፤
ከአንድ ሌላ ሰው ጋር ሆነው፤ ወደ መገናኛ ወደ ትህትና ቤት በታክሲ
እየገሰገሱ ነበር፡፡
አዲሱን፣ አስደናቂውን፣ ለማመን አስቸጋሪ የሆነውን፣ ታላቅ የምሥራች ይዘው
ትህትና ድንበሩ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በፀሐፊነት ተቀጥራ በማገልገል ላይ የምትገኝ ባለትዳር ስትሆን፤ የአንድ ወንድና፤ የአንዲት ሴት ልጆች እናትም ለመሆን በቅታለች።
በባህር ኃይል ውስጥ ተቀጥሮ በማገልገል ላይ የሚገኘው ዘንካታው ወጣት አንዱዓለም ድንበሩም፤ አንድና ብቸኛ የሆነቸውን፤ እንደ ዓይኑ ብሌን የሚያያት፣ ህይወቷን አሳልፋ የሰጠችለት፤ ታላቅ እህቱን፣ የሚወደውና በቅርቡ የሻለቅነት ማእረግ ያገኘው አማቹ ሻለቃ
ብሩክና፤ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊያገባት የተዘጋጀው እጮኛው አዜብ ተሾመን፤ ሊጠይቅ፤ የአሥራ አምስት ቀን የዓመት ዕረፍት ፈቃዱን ወስዶ ከአሰብ ከመጣ አንድ ሣምንት ሆኖት ነበር፡፡
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ የሻለቃ ብሩክ አጥር በር ተንኳኳ፡፡
ሠራተኛዋ በሩን ከፈተች፡፡ ሁለት ሰዎች ቆመዋል፡፡አታውቃቸውም፡፡
“ሻለቃ አለ?” ሲሉ ጠየቋት ሽማግሌው።
በዚያን ሰዓት አንዱዓለም፣ ትህትና፣ ሻለቃ ብሩክና ወንድሞቹ ስብስብ ብለው እየተሳሳቁ እየተጨዋወቱ፤ እራት እየበሉ ነበር፡፡
“አሉ” ስትል መልስ ሰጠቻቸው፡፡
“አንድ ጊዜ ጥሪልኝ” አሏት ረጋ ብለው፡፡
ሄዳ ብሩክን ጠርታ መጣች፡፡
“እንዴ አባባ ብራቱ ዛሬ ከየት ተገኙ? ይዝለቁ እንጂ!”
ትከሻቸውን እቅፍ እድርጐ እየሳማቸው፡፡
“እሱን አደርሳለሁ ሻለቃ፡፡ አመጣጤ ለብርቱ ጉዳይ.
ነበር። ሥራ ይዘሃል?”
“ሥራስ ብይዝ ምን ችግር አለው ? ደግሞ ለርስዎ? አሁን ግን
ምንም ሥራ አልያዝኩም፡፡ ይግቡዋ ታዲያ” በእጁ ወደ ቤቱ እንዲገቡ
እየጋበዛቸው፡፡
“ባለቤትህስ አለች?”
“ባለቤቴም ፤ወንድሟም፤ ሁላችንም አለን፡፡ ምነው በደህና?”
“እንግዲያውስ አንድ ጊዜ መጣሁ በላቸውና ተመለስ፡፡ በጣም
ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ እኔ መሆኔን እንዳትነግራቸው፡፡ አይዞህ በደህና
ነው” አሉት፡፡
ሄዶ የሆነ ምክንያት ሰጥቷቸው ወደ ሽማግሌው ተመለሰ፡፡
ከዚያም ሽማግሌው እጁን ያዝ አደረጉት :: ብሩክ ልቡ በኃይል መታ፡፡
“ምን ሊነግሩኝ ይሆን?” በሚል ጭንቀት ተዋጠ፡፡
ደግነቱ መርዶ በምሽት አይነገርም፡፡
“የውልህ ሻለቃ” አሉና የሆነውን፣ የተፈጠረውን ተአምር ይተርኩለት ጀመር።
የትህትና አባት መቶ አለቃ ድንበሩ፣ ሞቷል ተብሎ ተዝካሩ የተበላለት ሰው በህይወት መግባቱን፣ አሁንም ከድሮው ቤቱ የባለቤቱን መርዶ ተረድቶ መቀመጡን፡ እድርተኛው በሙሉ እንዲሰማ መደረጉን ፡
በሹክሹክታ ሲነግሩት፤ ሻለቃ ብሩክ በህልም ዓለም ያለ ዓይነት ስሜት
ተሰምቶት፤ በአድናቆትና በድንጋጤ ተውጦ አፉ እንደተከፈተ ቀረ፡፡
ተአምር! እውነትም ትንግርት! ይህን ምን ይሉታል?!
ከዚያም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ከሽማግሌው ጋር በእርጋታ ተመካከሩ፡፡ በመጨረሻም ሲነጋ በሌሊቱ ሁለቱን ልጆቹን ወደ ድሮ መኖሪያ ቤታቸው በመውሰድ ከአባታቸው ጋር ለማገናኘት በፈጠሩት ምክንያት ተስማምተው ተሰነባበቱ፡፡ ሻለቃ ብሩክ ከሽማግሌው ጋር ባደረጉት ስምምነት መሠረት
በጠዋቱ ትህትና ከሁለቱ ልጆቿ ጋር አንዱዓለምንም እንደዚሁ ልብሳቸውን እንዲለባብሱ አደረገ፡፡
“አባባ ብራቱ ጠበል እንድንቀምስላቸው በጠዋት ድረሱ ስለአሉን
እንዳይቀየሙን ቶሎ ቶሎ ልበሱ” በማለት አጣድፎ አለባበሳቸውና፤ይዟቸው በታክሲ ወደ ድሮ ሠፈራቸው ጉዞ ጀመሩ፡፡ አባባ ብራቱ ደግሞ በቀጠሮአቸው መሰረት ቤታቸው ሆነው መምጫቸውን እየተጠባበቁ ነው፡፡ ዛሬ የደስታ ቀን ብቻ እንዳልሆነ ሻለቃ በሚገባ አውቆታል፡፡ ዛሬ
ሞቷል ተብሎ የተለቀሰለት አባታቸው አፈሩን አራግፎ የመጣበት ቀን ነው፡፡ አፈር ለብሳ፤ አፈር ሆና፤ የቀረችው እናታቸው ግን ዳግም ላትነሳ ነው የሄደችው፡፡ ሶስቱ ሲገናኙ በዚያን በሚያስገርም ወደር በሌለው
ደሰታቸው መካከል፤ የተለየቻቸው የእናታቸው ናፍቆት እንደ አዲስ
ተቀስቅሶ፤ በእንባ እንደሚራጩላት አውቋል፡፡
ከልክ በላይ ሲሆን፤ ከሀዘን
ደስታም የበለጠ በእንባ ያንፈቀፍቃል። በተለይ ደግሞ እንደ መቶ አለቃ ድንበሩ ያለ የሚወደድ፤ የሚናፈቅ ፤አባት ሞትን አሽንፎ ሲመጣ ድንጋጤው ብቻ በሽታ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው፡፡ዛሬ ትንሳኤና መርዶ እዚያች ግቢ ውስጥ መንገሳቸው የማይቀር ነው፡፡ ሻለቃ ብሩክ ካሜራውን አዘጋጅቶ ይዟል፡፡ ትህትና እና ወንድሟ
የሚሄዱት ወደ ድግስ እንጂ ወደ አባታቸው ዘንድ መሆኑን እንዴት
ጠርጥረውት? የሞተ ሰው ከመቃብር ተነስቶ አቀባበል ሊያደርግላቸው
እየተጠባበቃቸው መሆኑን እንዴት ገምተውት? ጭቃ እያቦኩ፤ ውሃ
እየተራጩ ባደጉባት፡ በፍቅርና በመተሳሰብ የደስታ ጊአዜአቸውን
ባሳለፉባት፤ አልቅሰው የእናታቸውን ተዝካር ባወጡባት፤ በዚያች የድሮ
ቤታቸው ውስጥ በአካል ተገኝቶ በናፍቆት
👍1