አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
456 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ራሄል ሰዓቷን ለማየት በድብቅ የሸሚዟን እጅጌ ወደላይ ሰብሰብ አደረገችና ተመለከተች። ለመሰናበት ካሰበችው ጊዜ በላይ እየወሰደባት ነው፡፡በቀራት ደቂቃ ቀጠሮው ቦታ  ለመድረስ  የመኪናዋን ፍጥነት ከተገቢው በላይ ለመልቅ ልትገደድ እንደምትችል አሰበች፡፡የተጨናነቀ ትራፊክ እንዳያጋጥማት እየተመኘች  ሸሚዞን ወደ ቦታው መለሰች፡፡ድንገት ዶ/ሩ  በግማሽ ፈገግታ በትኩረት ሲመለከታት ያዘችው። ራሄል ይህን አልለመደችም። አብዛኞቹ ወንዶች ከእሷ ጋር እንዲህ አይነት የዓይን ጫወታ መጫወት አይደፍሩም፡፡

አባቷ ፀጋን በእቅፋቸው ይዘው እያጫወታት ነው‹‹አይዞሽ ልጄ ..ትደርሺያለሽ. .አትጨናነቂ…ሁሉነገር እግዚያብሄር ከፈቀደ ይሆናል…ካልፈቀደ ደግሞ ምንም ብትለፊ የቱንም ያህል ብትጥሪ  አይሆንም››የሚል ምክር አከሉበት፡፡

የአባቷን  ስብከት ውጦ ለመቀበል  ትዕግሥት አጣች፡፡ ወዲያው ደግሞ እሳቸው እንደሚያምኑት ማመን ባለመቻሏ እፍረት ተሰማት። አባቷ በእምነታቸው ቅን ሰው ናቸው። እሳቸው በዚያ መጠን በእግዚያብሄር እያመኑ መቀጠላቸው እሷን ሊያበሳጫት አይገባም ነበር፡፡  እንዲያውም እሷም እንደእሳቸው በአምላክ ላይ ያላትን እምነት ለመጋራት የምትመኝበት ጊዜ አልፎ አልፎ ነበር። ግን ማድረግ አልቻለችም፡፡

ለአባቷ መልስ መስጠቱን ተወችውና እይታዋን ወደ ዶ/ሩ  አዞረች፡፡እጆቹን ቁልቁል እያየ ነበር፣ የአንዱን እጁን ጣቶች  ወደ ደረቱ ወሰደ ፤ከዛ በኋላ ነበር ከክርኑ አንጓ እስከ አውራ ጣት ግርጌ ድረስ የሚሄድ ረዣዥም የተሰነጠቀ ጠባሳ እንዳለበት ያስተዋለችው። በደንብ ያልተሰፋ ይመስል  ነጭ እና የተቦጫጨቀ ሆኖ ይታይ ነበር። ሞተር ሳይክሉን ሲያበር  ያገኘው አደጋ ይሆናል ስትል አሰበች ፡፡በዚያን ጊዜ ቀና ብሎ አያት።

‹‹ኬክሽ ይኸውልሽ ውዴ።››ወ.ሮ ትርሀስ አንድ መለስተኛ  የታሸገ ካርቶን በሰማያዊ ፔስታል ውስጥ አድርገው  አቀበሏት፡፡  ራሄል  ፔስታሉን ተቀበለችና በእጇ እየመዘነች ‹‹ይህ ግማሹ ነው››አለች ።

‹‹ቀሪውን ደግሞ  እኔና አባትሽ አንበላዋለን - ››

‹‹ለሚቀጥሉት ጥቂት  ቀናት ምግቦቼ  የቸኮሌት ኬክ እንደሆነ በምናቤ ሳስብ ደስታ ተሰማኝ ።››

‹‹ማር, እንዳታደርጊው››ወ.ሮ ትርሀስ ፊታቸውን  በማኮሳተር ኬኩን መልሰው  ሊወስድባት ሞከሩ፡፡

‹‹አይ, አታደርጊውም››ራሄል እናቷ እቃውን እንዳይነጥቋት እየተከላከለች ‹አትጨነቂ እኔ እየቀለድኩ ነው. ዛሬ ማታ አንድ ቁራጭ ከላዩ ላይ በላለትና  የቀረውን ወደ ሥራ ቦታ  እወስደዋለው፡፡እርግጠኛ ነኝ ሮቤል እና ሎዛ በዚህ ኬክ  ላይ ይጣሉበታል.››

‹‹አዎ እንደዛ ነው ማድረግ ያለብሽ››

‹‹አሁን ሳሙኝ እና ብሄድ ይሻላል።››

ራሄል እናቷን በፍጥነት አቅፋ ሳመች እና ከአባቷ እና ከፀጋ ጋር ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ ጎንበስ ብላ ሳመቻቸው።ከመሄዷ በፊት በዔሊያስ  ላይ ዓይኗን ጣለች። እሱ በሁለት ሜትር ርቀት ላይ ነበር፣ ነገር ግን በዚያ ርቀት ላይ ቢሆንም ሰውነቷን የዳሰሳት አይነት ስሜት ነው የተሰማት።ወደ መኪናዋ ስትሄድ ስሜቷን ተናወጠ።

ስትመለስ ለወላጆቿ ሁሉን ነገር ግልጽ የምታደርግላቸው መስሏት ነበር። አስፈላጊው የእናት እና የሴት ልጅ ውይይት ጊዜ እንደደረሰ አውቃለች። በተቃራኒው ራሄል በአጀንዳው ላይ የሚቀጥለውን ንጥል ፋይል ስትከፍት ማዛጋት ጀመረች።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
36👍7
‹‹ደህና፣ በቃ ቻው፣ ከአንድ ፊዚዬቴራፒስት ጋር ቀጠሮ አለኝ እና ከዚያ በኋላ ዶ/ር ኤሊያስን  አገኘዋለው። ሰላም እንዳልሽው  ልንገረው?››እናቷ የማይበገሩ  ነበሩ።

‹‹እናቴ የፈለግሽውን አድርጊ…. እወድሻለሁ።››

የእናቷ ድርጊት አንዳንድ ጊዜ  እብድ ሲያደርጋት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንድታፍር ያደርጋታል… እንደዛም ሆኖ ራሄል ወላጆቿን በጣም ትወዳለች።‹‹አንቺንም እወድሃሸለው ውዴ።››

ራሄል ስልኩን ዘግታ በሀሳብ ተዋጠች። ራሄል እናቷ ፀጋን በማደጎ ወደቤቷ ስያመጣት ውስጣዊ ስሜቷን እንደምታረካላቸው እና እሷ ላይ የሚያደርጉትን  ትኩረት ይቀንሳሉ  ብላ ገምታ ነበር ግን አሁን እንደምታየው ምንም የተቀየረ  ነገር የለም፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronoseቀ
👍3011
የራሄል ሆዷ ሲገለባበጥ ይታወቃታል እንደገና የማዞር ስሜት ተሰማት።ራሄል ፀጋ ከእጇ   ሾልካ ከመውደቋ በፊት  ‹‹እባክህ ልትወሰዳት ትችላለህ?››በማለት  ወደ ዔሊያስ ገፋቻት፣ ዶ/ር ኤልያስ ግራ አጋቢ እይታ ካያት በኃላ ፀጋን  ወሰዳት እና በቀላሉ ወደ እቅፍ አስገባት።ራሄል ወደ ዶ/ር ምንያህል ትኩረቷን ሰበሰበችና  ‹‹ይቅርታ ስለ እናቴ እየነገርከን ነበር …ሙሉ በሙሉ የማገገም እድሏ ምን ያህል ነው?"ስትል ጠየቀችው፡፡መልሱን ለመስማት ግን ብርታቱ አልነበራትም፡፡

‹‹በጣም ጥሩ  የሚባል ነው:፡፡እርግጥ እንደእሷቸው ብርታትና ጥረት ይወሰናል…ቢሆንም ጊዜ ይወሳዳል እንጂ መዳናቸው አይቀርም፡፡››

‹‹ምን ያህል ጊዜ በሆስፒታል የምትቆይ ይመስልሀል?››አቶ ቸርነት ጠየቁት፡፡

‹‹ከሦስት እስከ አራት ሳምንታት ገደማ ምን አልባትም ከወር በላይ የግድ በሆስፒታል መቆየት አለባቸው…ከዛ በኃላ ያለውን ህክምና ምን አልባት እቤታቸው ሆነው የሚከታተሉበት መንገድ እናመቻች ይሆናል፡፡››

አቶ ቸርነት በቆሙበት አገጫቸውን በእጇቸው እያሻሹ፣ የቦዙ ዓይኖቻቸውን ግድግዳው ላይ ሰክተው በሀሳብ ጠፋ።ወደ ራሔል ተመለከቱ ‹‹ከእናትሽ ጋር ያን ያህል ረጅም ጊዜ መለየት አልችልም..አብሬት እዚህ ምቆየው እኔ ነኝ›› አሉ፡፡

‹‹አውቃለሁ አባዬ›› እጇቸውን ያዘችና  ጨመቀቻቸው።

‹‹እና ስለ ፀጋስ?››አባቷ በጭንቀት እና ግራ በመጋባት ጠየቁ።

ዶ/ር ምንያህል  ዔሊያስን ተመለከተ። ‹‹ዶክተር ዓሊ የቀሩትን ጥያቄዎችችሁን ሊመልስላችሁ ይችላል ብዬ አስባለሁ. አሁን ወደ ባለቤቶት ሄጄ አንዳንድ ምርመራዎችን ማድረግ አለብኝ፡፡››ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡

‹‹አስደሳች ዜና ስለሌለኝ አዝናለሁ፣ ግን ደግሞ ከዚህም  የከፋ ጉዳት ስላልደረሰባቸው ልናመሰግነው ይገባል።››ኤልያስ ነው ተናጋሪው፡፡

አቶ ቸርነት በኤልያስ ሀሳብ በመስማማት ‹‹ለቸሩ ጌታ ምስጋና ይድረሰው ››ሲሉ ተናገረሩ፡፡

‹‹ፀጋን ከእኛ ጋር እዚህ መሆን   ትችላለች?›› አቶ ቸርነት ዶ/ር ኤሊያስን ጠየቁት፡፡

ኤልያስ ራሱን  በአሉታ  ነቀነቀ። ‹‹አይ እሷ እቤት መሆን ነው ያለባት … ።›› አለና ወደ ራሔል ተመለከተ፣ ከዚያም ወደ አቶ ቸርነት ተመለሰ። ‹‹እናትሽን ለመርዳት አባትሽ ሙሉ ትኩረታቸውን  እሷቸው  ላይ ማድረግ አለባቸው…  እና ለፀጋ  ጤና ደግሞ በዚህ ሁኔታ ውስጥ መገኘት  ጥሩ ውጤት አያመጣም።››

‹‹ደህና, ስለ ትንሹ ልጃችን የሆነ ውሳኔ መወሰን  እንዳለብኝ ይሰማኛል.››እጇቸውን ራሰ በራ ጭንቅላታቸው ላይ አሳርፈው ወደ ራሄል ዞሩና ፈገግ አሉ‹‹ራሄል፣ ማሬ፣ ፀጋን መንከባከብ ትችያለሽ?››ሲሉ ጠየቁ፡፡

‹‹እኔ? ፀጋን  መንከባከብ?››የራሄል ድንጋጤ አስፈሪ ነበር፡፡

እጆቿን እርስ በርሳቸው አቆላለፈች….‹‹ግን ብዙ ስራ መስራት አለብኝ … ማለቴ ፀጋ  የምትፈልገውን ያህል ጊዜ አብሬያት ለማሳለፍ እንደምችል እርግጠኛ አይደለሁም›› ራሄል ተርበተበተች፡፡ አቶ ቸርነት  ተነፈሱ።

‹‹ሞግዚት እቀጥርላት ነበር፣ ግን እንደምታውቂው እሷ ከአዲስ ሰው ጋር በቶሎ መልመድ አትችልም…በዛ ላይ ትእግስት ኖሮት እሷን በስርዓቱ የሚንከባከብ ሰው ለማግኘት ይከብዳል….ቤት ካሉት ሰራኞች ጋር እንኳን ያላትን ግንኙነት የምታውቂው ነው››በማለት ያሳሰባቸውን ነገር በዝርዝር አስረዷት፡፡

ውይይታቸውን እና በአባትና ልጅ መሀከል የተፈጠረውን ውጥረት በትኩረት ሲከታተል የነበረው ዶ/ር ኤልያስ ሌላ  አማራጭ ፕሮፖዛል ሊያቀርብ ሲዘጋጅ ድንገት ራሄል እጇን በአባቷ ትከሻ ላይ አድርጋ ፈገግ በማለት‹‹ ያልኩት የስራ ጫና እንዳለ ቢሆንም ..ነገር ግን ፀጋ እህቴ ነች። ለእሷ ቅድሚያ መስጠት እንዳለብኝ እገነዘባለው…እና አባዬ አንተ ምንም አታስብ ለእሷ  አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደማደርግላት  አረጋግጥልሀለው።››ስትል ሁለቱም ባልጠበቁት ወኔና ቁርጠኝነት ቃል በመግባት አስደመመቻቸው፡፡

አቶ ቸርነትም ትልቋን  ሴት ልጇቸውን በፍቅር  ትከሻዋን መታ መታ እያደረጉ ‹‹እናመሰግናለን ውዴ››ሲሉ አመሰገኗት ። ወደ ፀጋ ዞረው  አቀፏትና‹‹ ከእህቷ ጋር ከመሄዷ በፊት እናቷን  እንድታይ ማድረግ  እችላለሁ?›› ሲል ደ/ር  ዔሊያስን ጠየቁት።

ዔሊ መጋረጃውን ወደ ጎን ያዘና ‹‹ምን አልባት የመድሀኒቱ ተፅዕኖ ማንንም እንዳይለዩ  ሊያደርጋቸው ይችላል  ግን መሞከር እንችላለን።››

አቶ ቸርነት ፀጋን ይዘው ወደባለቤታቸው ክፍል ገቡ ፣ ራሄል ተከትላቸው ልትሄድ ስትል ዔሊ ትከሻዋን ያዘና አስቆማት። ወደ ኋላ ተመለሰች። ኮስተርተር አለችበት፡፡

‹‹ለአንድ አፍታ ላናግርሽ ፈልጌ ነበር››አለ ። ራሄል ወደ አባቷ ተመለከተች፣ ከዚያም ወደኃላ ቀረችና ‹‹ እሺ ይቻላል፡፡›› አለችው፡፡

‹‹ፀጋን  መንከባከብ የሚከብድሽ ከሆነ  ለአንቺ  አማራጭ እንደማገኝልሽ እርግጠኛ ነኝ።››አላት፡፡

ራሄል አይኗ ጠበበ። ‹‹አማራጭ አያስፈልገኝም… እህቴ ነች። እሷን በጥንቃቄ መንከባከብና መጠበቅ  እችላለሁ።››በንግግሯ ውስጥ ያለውን እርግጠኝነት አስገረመው።

በአስተያየቱ በእሷ እርግጠኛ እንዳልሆነ ተረዳች‹‹አውቃለው…ከዚህ በፊት ልጅ ተንከባክቤ አላውቅም፣ ግን...››በራስ የመተማመን አቅሟ ለአፍታ ቢሆን ሲወርድ ታወቃት።  ‹‹ይህን አደርጋለሁ››

‹‹ጥሩ እንደምታደርጊው እርግጠኛ ነኝ ..ወደ ቢሮዬ ለመምጣት ፈቃደኛ ከሆንሽ የሚያስፈልጉሽን  መረጃ ልሰጥሽ እችላለሁ›› አላት፡፡

‹‹እሺ››አለችው።

ዔሊያስ የትንሿ ልጅ  ጤንነትን በቅርበት የመከታተል ሞያዊም ሆነ ሞራላዊ ግዴታ እንዳለበት ያውቃል። ለዚች  ሴት ኩራት ሲባል ያቺ ሚስኪን ልጅ እንድትሰቃይ አይፈቅድም።

‹ከሃያ ደቂቃ በኋላ ቢሮዬ እንገናኝ።››

በእሺታ ራሷን ነቀነቀች፣ ከዚያም አልፋው ጥላው ሄደች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
50👍16
‹‹ለጊዜህ አመሰግናለሁ፣ ዶ/ር ኤሊያስ  እንደምንገናኝ እርግጠኛ ነኝ።››አለችው፡፡

ዔሊያስም በሩን ሊከፍትላት በጠረጴዛው ዙሪያ ዞሮ ተራመደ..

ራሄል ስለጸጋ የጤና ችግር የሰማችው ነገር አእምሮዋ ሊሸከም ከሚችለው በላይ ነው የሆነባት፡፡እንዴት እንደምትወጣውም መገመት አልቻለችም፡፡

ዓሊ ከዚህ በፊት በግዴለሽነት የፍቅር ግንኙነት  ቢጀምርም፣ ዘላቂነት ላለው ግንኙነት ግን ዝግጁ ሀኖ አያውቅም ነበር ። አሁንም  እንደ ራሄል  ካለች ሴት ጋር ተመሳሳዩን ማድረግ እንደማይችል ያውቃል፡፡ እሷ ሌሎች ምታስቀድማቸው ጉዳዮች እንዳሏት ተረድቷል, እርግጥ ቤተሰቦቿ ከእሱ ጋር እንዳትገናኝ ተስፋ እንዳደረጉ ያውቃል፡፡ በዋነኛነት የእሱን  ጀርባ ምን እንደሆነ ባለማወቃቸው ነው። ወላጆቹን ማንነት ቢያውቁ እንደዛ እንደማያስብ እርግጠኛ ነው፡፡ ኮፍያውን ይዞ ቢሮውን ለቆ ወደ ቤቱ አመራ።

ወደ ቤቱ ሲገባ ስልኩ እየጮኸ ነበር እና የጥሪ ማሳያውን በጨረፍታ ተመለከተ ፈገግ አለና አነሳው።‹‹ሄይ እናቴ እንዴት ነሽ?›› ስልኩን በትከሻውና በጆሮው መካከል አድርጎ ጠየቀ። እናቱ የቤቱን ሁኔታ ማየት እንደማትችል ቢያውቅም የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶታል።

‹‹ደህና ነኝ።  ጧት የት ነበርክ?›› አሳዳጊ እናቱ ጠየቀችው፡፡ ‹‹ሁለት ጊዜ ሞክሬልህ ነበር.›› በድምጿ ውስጥ የስጋት ስሜት ይነበባል ፣ ይህም ዔሊን የበለጠ የጥፋተኝነት ስሜት›› እንዲሰማው አድርጎታል።

‹‹ የእረፍት ቀኔ ነበር ..ግን ሆስፒታል ድንገተኛ ተደወለልኝና ስራ ገባው…ገና በር ከፍቼ ስገባ ነው የደወልሺልኝ.››

‹‹አንተም ሆንክ ቢኒ ቤተክርስቲያን ትመጣላችሁ ብዬ ጠብቄ ነበር..አንተስ እሺ ስራ ላይ ነኝ አልክ… የእሱስ ሰበብ ምንድነው?››

ሰበቡን ያውቃል..እሱ ብቻ ሳይሆን አሳዳጊ እናቱም ጭምር ለምን በቤተክርስቲያን መሄድ እንዳቆመ በደንብ ያውቃሉ..እሱ እንኳን ድሮም  ለቤተክርስቲያን እስከዚህም ነበር ወንድሙ ግን ባለቤቱ በአንድሳምንት በሽታ ታማ  ሳይታሰብ እስክትሞትበት ድረስ በጣም አካራሪ የሚባል ሀይማኖተኛ  ሰው ነበር…ከዛ በኋላ ግን ቀስ በቀስ እግሩን ከቤተክርስቲያን ልቡን ደግሞ ከእግዚያብሄር ሰበሰበ…..በዚህ ጉዳይ ከራሄል ጋር ተመሳሳይ ታሪክ እንዳላቸው ያውቃል…አሁን ግን ይህንን የወንድሙን ጉዳይ ከእናቱ ጋር አንስቶ መጨቃጨቅ ስላልፈለገ በዝምታ ዘለለው

እሱ  ከአሳዳጊ ወላጆቹ ጋር የነበረው ዝምድና ሁል ጊዜ ወጣ ገባ ያለው ነበር ።  አሳዳጊዎቹ  ከእሱ ይልቅ ከቢኒያም  ጋር ንፁህ በፍቅር የተሞላ የወላጅ እና የልጅ ግንኙነት ነው ያላቸው፡፡  እሱ ግን  ስለ ስጋ ወላጆቹ ማወቅ ይፈልግ ስለነበር ብዙ ጊዜ ባየተዋርነት ይሰማው ነበርና እቤት ውስጥ በራሱ ችግር ይፈጥራ ል… ስለወላጆቹ የሚያውቁትን እንዲነግሩት ያስቸግራቸው ነበር ..እነሱ ግን  ምንም ሊነግሩት አልቻሉም።

ባለፈው ዓመት እሱ እና ቢንያም የወላጆቻቸውን ቤት እያፀዱ ሳለ በሰገነት ላይ የፎቶ ሳጥን አገኘ. እነዛን ፎቶዎች ከዚህ በፊት አይቷቸው አያውቅም ነበር ፡ የእሱ የስጋ ወላጆቹ ነበሩ።  አሳዳጊዎቹ እሱን ከማደጎ ቤት  በተረከቡት ጊዜ  ፎቶውንም አብረው ነበር የተረከቡት… ከዛ ግን  አርቀው አስቀመጡና ረሱት ፡፡

‹‹ወደ ሆስፒታል እንደተጠራህ ተናግረሃል›› ስትል እናቱ  ተናገረች። ‹‹በጣም ከባድ ነገር እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ.››ዔሊ ራሔልን እና ጸጋን  አሰበ እና ግንባሩን በጣቱ አሻሸ።

‹‹ከታካሚዬ አንዷ ወደቀች፣ ግን ደህና ነች፣ አንቺ እና አባ እንዴት ናችሁ?››

‹‹ደህና ነን ፡ ግን አንዳንድ ጊዜ መጥተን አንተን እና ቢኒን ቤቱን እንደትጨረሱት ልንረዳችሁ እንፈልግ ነበር።››

‹‹እሺ እማማ፣ አንቺና አባባ በዚህ ጉዳይ ላይ እንድትጨናነቁ  አልፈልግም። ››
የእናቱ ዝምታ ሌላ የጥፋተኝነት ስሜት ፈጠረ።

ተሰናበታቸውና እና ስልኩን ዘጋው፡፡

በዚህ ቤት ጉዳይ ወላጆቹንም ሆነ  ወንድሙ ቢኒያምን ብዙ ማስቸገር አይፈልግም፡፡
- ይህንን ቤት መስራት መጀመሩ ለእሱ ትልቅ ስኬት ነው ፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ የራሱን ቦታ ይፈልግ ነበር ፡፡  እራሱን የሚገነባበት ቦታ። ይህንን ለአሳዳጊ ወላጆቹ በቀላሉ ማስረዳት የሚችለው ነገር አልነበረም፣ ። ገና ወንደላጤነቱን ሳያጣጥም ብድር  ውስጥ ገብቶ እቤት ወደመገንባት ውስጥ የገባበትን  ምክንያት ቢኒያም እንኳን አልተረዳውም።ምክንያቱም ወንድሙ  እንደ እሱ ስለ ስጋ ወላጅቹ   ምንም አይነት ትዝታ አልነበረውም። ለእሱ አሳዳጊ ወላጆቹ የስጋ ወላጆቹ እንደሆኑ ነው የሚሰማውም…የሚያምነውም፡፡

እርግጥ ኤልያስም አሳዳጊ ወላጆቹን ይወዳል ፡፡  ለመጀመሪያ ጊዜ ከእነሱ ጋር ለመኖር ወደቤታቸው ሲወስዱት የስጋ ወላጆቹን  ትዝታዎች በጀርባው አዝሎ ስለነበረ  በተለየ ሁኔታ በጣም ያስቸግራቸው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ስለ ወላጆቹ በጭራሽ ማውራት አቆሙ፡፡ ኤሊ የዛሬ አመት ፎቶዎቹን እስኪያገኝ ድረስ ይህን ተቀብሎ ነበር።አሁን  .የፎቶ ሣጥኑን ወደቤቱ አምጥቶታል  እነኚያ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ሙከራ ላይ ነው፡፡ ህይወት የሰጡት ወደዚህ ምድር ጎትተው ያመጡት፤እነዛን   የመጀመሪያዎቹን ጥቂት የህፃንነት አመታትን ይንከባከቡት የነበሩትን ሰዎች ማነነት የማወቅ ጉጉት እያሰቃየው ነው።

ሳያውቅ እጁን አዞረና  ጀርባ ላይ ያለውን ጠባሳ አሻሸው፣ከአደጋውን ያተረፈው ቅሪት ነው ።ስለ ፀጋ  አሰበ። ገና ህፃን ስለሆነች ወደፊት ስለ እናቷ ምንም ትዝታ እንዳማይኖራት ተስፋ አደረገ ። ግን ቢያንስ ለእሷ እሱ አለላት..እናቷ ምን አይነት ሰው እንደሆነች….ስለደግነቷ..ስለውበቷ እና ስለአስቂኝ ጫወታዋ …በዝርዝር ሊነግራት ይችላል፡፡ከፈለገችም…አሁን በህይወት ስለሌሉት አያቶቹም ጭምር ሊነግራት ይችላል…ምክንያቱም  የእናቷ የፅጌረዳን እናትና አባት ከልጅነቱ ጀምሮ በደንብ ያውቃቸዋል…ፅጌረዳ ተከትሎ ብዙ ጊዜ እቤታቸው የመመላለስ እድል ነበረው..ደሆች ቢሆኑም ልበ ቀና መልካም ሰዎች ነበሩ…ይሄንን ሁሉ ሊያስረዳት ይችላል..ለእሱ ግን እንደዚህ አይነት ስለዋላጆቹ ጥቂት እንኳን አውቃለው የሚል ሰው የማግኘት እድል የለውም፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
69👍12
የራሄል ልብ በእፎይታ ተነፈሰ።አብሮት እየተራመደ ያለውን ተለማማጅ ዶ/ር ወደ ጎን ተመለከተው፣ እያወሩ ነበር ። ድንገት ዞር ሲል ከራሄል ጋር አይን ለአይን ተገጣጠሙ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ  የተሰማትን አይነት  ተመሳሳይ ምላሽ ተሰማት። ተንደርድሮ ወደእሷ መጣ፡፡

ከዚያም  የፀጋን  የህክምና  ቻርት ላይ የሆነ ምልክት እያደረገች ወዳለችው ነርስ ተጠጋና  ተመለከተ። ‹ታዲያ ችግሩ ምን ይመስላሻል ?›› ብሎ ጠየቀ ከራሄል ወደ ፀጋ   ከዚያም ወደ ነርሷ ተመለከተ። ራሄል ‹‹ከፍኛ ትኩሳት አላት›› አለችው.

ነርሷ ‹‹አሁን የሙቀት መጠንዋን ወስጃለሁ….ትንሽ ከፍ ያለ ነው፣ ግን ምንም የሚያሳስብ ነገር የለም።››

ራሔል  ነርሷ ላይ አፈጠጠች ፣ግራ ተጋባች፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለከተች። ‹‹ በጣም እኮ ነበር የምትሞቀው.››

ዔሊ ሰንጠረዡን ከነርሷ ተቀብሎ ተመለከተ እና እጁን በህፃኗ ግንባሩ ላይ አደረገ። ፀጋ  በድንገት ሁሉም ነገር ደህና የሆነ ይመስል ፈገግ አለችለት‹‹አሁንም አንቲ ባዮቲኮችን እየሰጠሻት ነው?›››

‹‹አዎ ››

‹‹ደህና፣ እየሰሩ ያሉ ይመስላሉ፣ ግን ፈገግታዋ ጠፍቷል፣ የድምፁ ቃናዋም ተለውጣል፣ እሷን መናደድ የለባትም››

‹‹የምን መናደድ …ከሰአት በኋላ  ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ለመንከባከብ የተመሰከረለትን የመዋለ ሕጻናት  አገኘሁ።እና እዛ ወሰድኳት..ከስራ ተመልሼ ልወስዳት ስሄድ ታማ አገኘኋት… እና አሁን የሚያስፈልገኝ በእሷ ላይ ያለውን ችግር እንድትነግሩኝ ነው።››

ዔሊያስ በትንሹ ተነፈሰ… ነገር ግን ዓይኖቿን ራሄል ላይ እያንከራተተች ወዳለችው ታዳጊ ልጅ ተመለከተ። የታችኛው ከንፈሯ ያብለጨልጭ ጀመር እና እንደገና ልታለቅስ ያሰበች ይመስላል ። ራሄል ጀርባዋን እየደባበሰች አባበለቻት፡፡

በወረቀት ላይ ማስታወሻዎችን እየጻፈ። ‹‹ደህና ነች..አዎ፣ የሙቀት መጠኑ በትንሹ ከፍ ብሏል፣ ግን ያ ስለተበሳጨች ሊሆን ይችላል። አንድ ጆሮዋ ትንሽ ቀላ ያለ ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ በፀረ-ባዮቲክስ መድሀኒት  ይወርዳል። መበሳጨት ከጀመረች ስጧት። የሙቀት መጠኗን መቆጣጠሪያ በእጅሽ ላይ ሊኖርሽ ይገባል.. የሚያስፈልጉሽን ነገሮች ዝርዝር ነገ እሰጥሻለሁ፤››አለና ወረቀቱን ከፓድ ላይ ቀዶ  ዘረጋላት።ራሄል በድንገት ሞኝነት ተሰማት፣ነገር ግን ፀጋ ደህና መሆኗን በማወቋ እፎይታ አግኝታለች።

ወረቀቱን ወደ ቦርሳዋ እያስገባች‹‹ለምክርህ አመሰግናለሁ››አለችው

‹‹በዚህ ኢንፌክሽን ደረጃ ለማረጋገጥ ከነገ ወዲያ እሷን ማየት እፈልጋለሁ። ለአንቺ ስንት ሰዓት ይምችሻል?››በጥያቄው ስለተበሳጨች እኩለ ሌሊት ልትለው አሰበች. ፡፡

‹‹ለምን አንተ ቀጠሮ አትይዝልኝም እኔ ፕሮግራሜን ማሸጋሸግ እችላለው፡፡ ››አለችው፡፡

‹‹ቤት ላገኝሽ ካልቻልኩ… የት ላገኝሽ እችላለሁ?››

የቢሮ ቁጥሯን እና የሞባይል ስልኳን ሰጠችው።በስራ ቦታ ልታገኘኝ  ካልቻልክ ለሎዛ መልእክት ተውልኝ።  ሞባይል ስልኬ በአብዛኛው ክፍት ነው። በተጨማሪም የወላጆቼ ቁጥር አለህ። ››

የንዴት  ፈገግታ አሳያት።‹‹እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች አያስፈልጉኝም?››

በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከወ.ሮ ላምሮት ጋር መገናኘት ነበረባት እና አሁን ለፀጋ የምትገዛቸው መድሀኒቶች አሉ..በዛ ላይ ምግቧንም መመገብ አለባት….በዚህ ሁኔታ ላይም እያለች ጥላት መሄድ አትችልም ፡፡ያላት ምርጫ ሴትዬዋን ይቅርታ ጠይቃ ሌላ ቀጠሮ ማስያዝ ነው፡፡

‹‹መሄድ አለብኝ››አለች.

‹‹ትሁትን  ስላየህልኝ አመሰግናለሁ፣››አለችው በድጋሜ
‹‹ ከሁለት ቀናት በኋላ እንገናኝ።››አለና  የድንገተኛ ክፍልን ለቅ ወጣ።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
26🤔13👏6
የራሄል ልብ በእፎይታ ተነፈሰ።አብሮት እየተራመደ ያለውን ተለማማጅ ዶ/ር ወደ ጎን ተመለከተው፣ እያወሩ ነበር ። ድንገት ዞር ሲል ከራሄል ጋር አይን ለአይን ተገጣጠሙ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ  የተሰማትን አይነት  ተመሳሳይ ምላሽ ተሰማት። ተንደርድሮ ወደእሷ መጣ፡፡

ከዚያም  የፀጋን  የህክምና  ቻርት ላይ የሆነ ምልክት እያደረገች ወዳለችው ነርስ ተጠጋና  ተመለከተ። ‹ታዲያ ችግሩ ምን ይመስላሻል ?›› ብሎ ጠየቀ ከራሄል ወደ ፀጋ   ከዚያም ወደ ነርሷ ተመለከተ። ራሄል ‹‹ከፍኛ ትኩሳት አላት›› አለችው.

ነርሷ ‹‹አሁን የሙቀት መጠንዋን ወስጃለሁ….ትንሽ ከፍ ያለ ነው፣ ግን ምንም የሚያሳስብ ነገር የለም።››

ራሔል  ነርሷ ላይ አፈጠጠች ፣ግራ ተጋባች፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለከተች። ‹‹ በጣም እኮ ነበር የምትሞቀው.››

ዔሊ ሰንጠረዡን ከነርሷ ተቀብሎ ተመለከተ እና እጁን በህፃኗ ግንባሩ ላይ አደረገ። ፀጋ  በድንገት ሁሉም ነገር ደህና የሆነ ይመስል ፈገግ አለችለት‹‹አሁንም አንቲ ባዮቲኮችን እየሰጠሻት ነው?›››

‹‹አዎ ››

‹‹ደህና፣ እየሰሩ ያሉ ይመስላሉ፣ ግን ፈገግታዋ ጠፍቷል፣ የድምፁ ቃናዋም ተለውጣል፣ እሷን መናደድ የለባትም››

‹‹የምን መናደድ …ከሰአት በኋላ  ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ለመንከባከብ የተመሰከረለትን የመዋለ ሕጻናት  አገኘሁ።እና እዛ ወሰድኳት..ከስራ ተመልሼ ልወስዳት ስሄድ ታማ አገኘኋት… እና አሁን የሚያስፈልገኝ በእሷ ላይ ያለውን ችግር እንድትነግሩኝ ነው።››

ዔሊያስ በትንሹ ተነፈሰ… ነገር ግን ዓይኖቿን ራሄል ላይ እያንከራተተች ወዳለችው ታዳጊ ልጅ ተመለከተ። የታችኛው ከንፈሯ ያብለጨልጭ ጀመር እና እንደገና ልታለቅስ ያሰበች ይመስላል ። ራሄል ጀርባዋን እየደባበሰች አባበለቻት፡፡

በወረቀት ላይ ማስታወሻዎችን እየጻፈ። ‹‹ደህና ነች..አዎ፣ የሙቀት መጠኑ በትንሹ ከፍ ብሏል፣ ግን ያ ስለተበሳጨች ሊሆን ይችላል። አንድ ጆሮዋ ትንሽ ቀላ ያለ ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ በፀረ-ባዮቲክስ መድሀኒት  ይወርዳል። መበሳጨት ከጀመረች ስጧት። የሙቀት መጠኗን መቆጣጠሪያ በእጅሽ ላይ ሊኖርሽ ይገባል.. የሚያስፈልጉሽን ነገሮች ዝርዝር ነገ እሰጥሻለሁ፤››አለና ወረቀቱን ከፓድ ላይ ቀዶ  ዘረጋላት።ራሄል በድንገት ሞኝነት ተሰማት፣ነገር ግን ፀጋ ደህና መሆኗን በማወቋ እፎይታ አግኝታለች።

ወረቀቱን ወደ ቦርሳዋ እያስገባች‹‹ለምክርህ አመሰግናለሁ››አለችው

‹‹በዚህ ኢንፌክሽን ደረጃ ለማረጋገጥ ከነገ ወዲያ እሷን ማየት እፈልጋለሁ። ለአንቺ ስንት ሰዓት ይምችሻል?››በጥያቄው ስለተበሳጨች እኩለ ሌሊት ልትለው አሰበች. ፡፡

‹‹ለምን አንተ ቀጠሮ አትይዝልኝም እኔ ፕሮግራሜን ማሸጋሸግ እችላለው፡፡ ››አለችው፡፡

‹‹ቤት ላገኝሽ ካልቻልኩ… የት ላገኝሽ እችላለሁ?››

የቢሮ ቁጥሯን እና የሞባይል ስልኳን ሰጠችው።በስራ ቦታ ልታገኘኝ  ካልቻልክ ለሎዛ መልእክት ተውልኝ።  ሞባይል ስልኬ በአብዛኛው ክፍት ነው። በተጨማሪም የወላጆቼ ቁጥር አለህ። ››

የንዴት  ፈገግታ አሳያት።‹‹እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች አያስፈልጉኝም?››

በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከወ.ሮ ላምሮት ጋር መገናኘት ነበረባት እና አሁን ለፀጋ የምትገዛቸው መድሀኒቶች አሉ..በዛ ላይ ምግቧንም መመገብ አለባት….በዚህ ሁኔታ ላይም እያለች ጥላት መሄድ አትችልም ፡፡ያላት ምርጫ ሴትዬዋን ይቅርታ ጠይቃ ሌላ ቀጠሮ ማስያዝ ነው፡፡

‹‹መሄድ አለብኝ››አለች.

‹‹ትሁትን  ስላየህልኝ አመሰግናለሁ፣››አለችው በድጋሜ
‹‹ ከሁለት ቀናት በኋላ እንገናኝ።››አለና  የድንገተኛ ክፍልን ለቅ ወጣ።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
26👍7🔥1
‹‹እሷን ለማገዝ በአቅራቢያዋ ስለነበርክ ደስ ብሎኛል.››አለችው

‹‹ምንም አይደል…ሁሌ ከእሷ ጎን ለመገኘት ለራሴ ቃል ገብቻለው..እሷ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አላት››

‹‹በጣም ጥሩ ››አለች፡፡

ውይይቱ ወደ ስንብት ወይም ለቡና ግብዣ እየቀረበ ነበር። ራሄል ትንሽ እንዲቆይ ልትጠይቀው አስባ  ከንፈሯን ነከሰች። የወንድ ጓደኛ  ረጅም ጊዜ አልነበራትም። እጮኛዋ ኪሩቤል በአደጋ  ከሞተ በኋላ  የፍቅር ጓደኛ ለመያዝ የተወሰነ ሙከራ ሞክራ ነበር ፣ ነገር ግን ሁሉም ወንድ ከእሷ ሚዛን ቀሊል እየሆኑ ተቸገረችና እርግፍ አድርጋ ተወችው ፡፡ አሁን ምንም እንኳን የእጮኛዋ  ትውስታዎች ቢደበዝዙም ፣ እምቅ ህመሟ በህይወቷ ውስጥ የተደበቀ ቁስል ነበር ።እንደገና ልቧን  ለመክፈት አልፈለገችም፡፡

ኤሊያስ ከተቀመጠበት ተነሳ ፡፡የሞተር ብስክሌቱን ሄልሜት ከአንድ እጁ ወደ ሌላው አዘዋወረ ፡፡ ራሄል ከእሱ ለመራቅ ባደረገችው ውሳኔ ፀናች።

‹‹መልካም፣ የሆነ ነገር ከተቀየረ አሳውቂኝ››በማለት ሌላ ፈገግታ ፈገግ አለላትና ሄደ።በሩ ከኋላዋ ሲዘጋ፣ ራሄል በረጅሙ ተነፈሰች። እሱን እንዲቆይ አለመጠየቋ ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነ  አሰበች። እንኳን ፍቅር ተጨምሮበት ህይወቷ   አሁንም  በጣም የተወሳሰበ ነው፡፡  ታዲያ ለምን ድንገት ብቸኝነት ተሰማት? ለምን ታዲያ  በአንድ ወቅት አስደሳችና  ውብ የሆነው አፓርታማዋ   አሁን  በቅፅበት በጣም ቀዝቃዛ  እና ባዶ መሰላት?የጭንቀት ስሜት ወረራት…  ከተቀመጠበት ተነሳችና  ወደ ፀጋ  ክፍል ተመልሳ ሄደች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
36👍8
ከዛ መዝሙር መዘመር ጀመረ…መዝሙሩ ለእሷ አዲስ ነበር ፣ዜማው ግን ደስ ስለሚል
በተመስጦ ነበር ስታዳምጥ የነበረው…ሁለተኛውን መዝሙር ግን ከልቧ ነበር  ስትዘምር የነበር …
ልጅ እያለች ጀምሮ ሁልጊዜም በመዝሙሩ ትደሰት ነበር፣
ሰባኪው ስብከቱን ሲጀምር ሁሉም በፀጥታ ማዳመጥ ጀመሩ
///
…. እግዚአብሔር በህይወታችን ስለሚያደርገው ነገር  እንበሳጫለን። እኛን ሊያስተምረን  እየሞከረ እንደሆነ አይገባንም። እግዚአብሔርን ችላ ለማለት ልንሞክር እንችላለን፣ነገር ግን ያንን ማድረግ በግድግዳው ላይ‹‹ጨለማ››የሚለውን ቃል በመጻፍ ብርሃንን ለማስወገድ እንደመሞከር ነው። በችግር  እና በስቃይ ውስጥ ልንሆን እንችላለን፣ ነገር ግን ‹‹እግዚአብሔር በሹክሹክታ በሕሊናችን ይናገራል .. በሥቃያችን ምክንያት የሚያሰማው ጩኻት መስማት የተሳነውን ዓለም ለመቀስቀስ የሚጠቀምበት የእሱ ሜጋፎን ነው። ህመማችን እና ሀዘናችን የእኛን የፈዘዘ ትኩረት የሚስብበት መንገድ ይሆናል ብዬ አምናለሁ።  ራሳችንን የቻልን ፍጥረታት ነን ብለን ስለምናስብ… ሁሉንም ነገር በራሳችን ማድረግ እንደምንችል እናስባለን. ከእግዚአብሔር ተለይተን መኖር የምንችል ይመስለናል ይህም የአበባው ሽታ ከአበባው ለመለየት እንደመሞከር ነው። እግዚአብሔር ሁል ጊዜ አለ እና የህይወታችንን ቁጥጥር ለእርሱ አሳልፈን  እንድንሰጥ እየጠበቀን ነው።
ራሄል ስብከቱ ለእሷ ታቅዶ የተዘጋጀ መስሎ ተሰማት…ኪሩቤል ከሞተ በኃላ እግዚአብሔር የሚናገራትን ነገር ሁሉ ላለመስማት  ጆሮዋን ዘጋች። የህይወቷ የበላይ ለመሆን እና ለመቆጣጠር ጣረች።ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ፣ በህይወቷ ውስጥ የተከሰቱት ክስተቶች ይህ ምን ያህል ከንቱ እንደሆነ አሳይቷታል።ግን ሌላ ምን ማድረግ ነበረባት? እሷ ፋውንዴሽን ውስጥ መልካም ነገር እየሰራች ነበር. ሰዎችን ከችግራቸው ለማላቀቅ  የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በስራዋ ላይ ይደገፋሉ.
ሰባኪው ስብከቱን ቀጥሏል  ….
..እኛ በሕይወታችን ውስጥ ኃላፊ እንደሆንን በማሰብ፣እንዴት ራሳችንን እንዲህ እናቆስላለን?  በእውነቱ እኛ የራሳችን ህይወት ሀለቆች አይደለንም…አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር የራሳችንን መንገድ ለማወቅ እንድንችል በራሳችን መንገድ እንድንሄድ ይፈቅድልናል። ነፍሶች ወደርሱ እስኪጠጉ ድረስ ዕረፍት የላቸውም። ስለዚህ አሁን በመዝሙራዊው ዳዊት መዝሙረ  139፡6 ላይ ባለው የእግዚያብሄር ቃል የእለቱን ትምህርታችንን እንዘጋለን፡፡

‹‹በሰማይእና በምድር በባሕር እና በጥልቆች ሁሉ፣እግዚያብሄር የወደደውን ሁሉ አደረገ ..

….››ቃላቱ በህንፃው ውስጥ ተስተጋብተው በራሔል ልብ ውስጥ አረፉ። ለእግዚአብሔር ጀርባዋን ሰጥታው ነበር። አላመነችበትም ነበር። እና ይህ ሁሉ ቢሆንም ፣ በእሷ ውስጥ ግልፅ የሆነ እረፍት አልነበረም…. ያለ ምንም ጥርጣሬ፣ እግዚአብሔር የለም ማለት አልቻለችም።አዎ ለአመታት በኪሩቤል  ሞት አዝናለች… አዎ…እሱን እንዴት እንዳጣችው በማሰብ አሁንም ለብስጭት እና ተስፋ ለመቁረጥ ተጋላጭ እንድትሆን አድርጓታል። አሁንም አምላክ ለምን ጸሎቷን እንዳልመለሰላት ግራ ተጋብታለች። ለዚያ መልሱን አላወቀችም። ነገር ግን በሕይወቷ ውስጥ የእግዚአብሔርን መገኘት እንዲህ በቀላሉ መካድ እንደማትችል ታውቃለች። ዛሬ የእሱ የተለመደ መነካካት ተሰምቷታል። የመጨረሻው መዝሙር ሲዘመር  ፀጋን አቀፈቻትና ከማንም ሰው በመራቅ ከምዕመናኑ መሀከል  ሾልካ ወጣች።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
57👍6
እርግጠኛ ያልሆነውን ስሜት ወደ ጎን ገሸሽ አድርጎ በአዘኔታ ስሜት እጇን ያዛት።የሚገርመው  ጣቶቿን  ዘርግታለት እንደፈለገው እንዲያፍተለትላት ፈቀደችለት… ፣ እና  ቀስ በቀስ በልቡ ውስጥ ለእሷ ሚሆን  ቦታ ሲከፈት ታወቀው።

ኤልያስ ቀና ብሎ ተመለከታት …አንድ የእንባ ዘለላ  በጉንጯ ላይ ሲንሸራተት በማየቱ ተገረመ። ወደራሱ አስጠጋትና   ቀስ ብሎ ጠረገላት።

‹‹ይቅርታ››አለች በሹክሹክታ። ወደ ኋላ ዞራ ተመለከተች። እጇን ከእጁ አውጥታ ወደ ፀጋ አመራች።በእነዚህ ጥቂት ጊዜያት ጥቂት ሰዎች እንዳዩ የጠረጠረውን የራሷን ክፍል እንዳሳየችው ተረዳ።

ራሄል ኩኪሶችን በሰሀን አድርጋ ስታቀራርብ  ዔሊ ቡናውን ቀዳ ፡፡የተለያዩ ስሜቶች በእሱ ውስጥ እየተሽከረከሩ ነበር። ስለ ኪሩቤል የበለጠ ለማወቅ ፈልጎ ነበር። ስለ ራሄል የበለጠ ለማወቅ ፈልጎ ነበር። ቢሆንም ግን የእርሷን መመሪያ መከተል እንዳለበት ያውቅ ነበር….ለዚህ ነው የበለጠ እንድታወራ ሊጎተጉታት ያልፈቀደው፡፡

‹‹ቡናው ጥሩ መዓዛ አለው››አላት፡፡

‹‹አመሰግናለው››አለችና .. ለፀጋ ኩኪስ ሰጥታ ብርጭቆዋን  ወሰደች።በሻይ እየነከረች ታጎርሳት ጀመር፡፡

ሁኔታዋን በትኩረት ሲከታተል ከቆየ በኃላ‹‹ጥሩ እናት ይወጣሻል ››አላት

‹‹..ቢያንስ እየተማርኩ ነው››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹አዎ…የሚገርመው እኮ እናትነት ቀድመሽ ተምረሽ ካወቅሽ በኃላ አይደለም እናት የምትሆኚው….በድንገት እናት ትሆኚያለሽ ከዛ የግድሽን ትማሪያለሽ…ይሄ አንቺን ብቻ ሳይሆን ሁሉም እናቶች የሚያጋጥማቸው ነው፡፡አይደለም ለመጀመሪያ ጊዜ ልጅ ስትወልጂ ይቅርና….የመጀመሪያ ልጅ ከሁለተኛ ልጅ..ሁለተኛው ልጅ ከሶስተኛው ልጅ በፀባይ ..በሚወዳቸውና በሚጠላቸው ነገሮች በብዙ  ብዙ ነገር ስለሚለያይ  በእያንዳንዱ ልጅ በማሳደግ ሄደት ውስጥ የተለየ አይነት ልምድ ነው የምታገኚው… ››

‹‹አረ ከባድ ነው…..አይደለም ሁለት ሶስት አንዱም ከባድ ነው›››አለችው፡፡

ጥቂት ተጨማሪ ጥያቄዎችን ጠየቃት እና ንግግራቸው በቀላሉ ከስራ ወደ ቤተሰብ ተዛወረ።

እሱም ልክ እንደ  እሷ ያደገው በክርስቲያን ቤት ውስጥ እንደሆነ ነገራት።  እንደ እሱ፣ እሷም ምንም አይነት የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች አልነበራትም።ስለ ወላጆቹ ጠየቀችው።ስለ አሳዳጊዎቹ ነገራት። እና ስለስጋ  ወላጆቹም አወራት፡፡ .

‹‹አሁንም ታስታውሳቸዋለህ?››ራሄል ጠየቀች፣ የፀጋን እጆች እርጥብ በሆነ ፎጣ ለመጥረግ ጎንበስ አለች።

‹‹በመኪና አደጋ ሲሞቱ ስድስት አመቴ ነበር:: ዔሊ በእጁ ጀርባ ላይ የተጋደመውን ጠባሳ ተመለከተ።‹‹እኔ ብቸኛ ልጅ ነበርኩ እና  በሕይወት የተረፈኩት እኔ ብቻ ነኝ.››

‹‹ስለዚህ አንተም ሀዘንን ታውቃታለህ ማለትነው.››

‹‹ከረጅም ጊዜ በፊት ነበር››

‹‹አዎ። ግን እነሱ የስጋ  ወላጆችህ ስለሆኑ ትዝታቸው እና ሀዘኑ ከውስጥህ መቼም አይጠፋም  ።››

‹‹እሱስ ትክክል ነሽ››

‹‹እናቴና አባቴ ይህችን ትንሽ ልጅ በጣም እንደሚወዷት አውቃለሁ፣ ነገር ግን እሷ አሁንም አንዳንድ ታሪክ ያላት ሰው ሆና  ነው ወደ እነርሱ የመጣቸው…ይታይህ  የስድስት አመት ልጅ ሆና ቢሆን ኖሮ በጣም ጠንካራ ትዝታ ይኖራት  ነበር ብዬ አስባለሁ። ››

‹‹እኔ ግን ወላጆቼ ሞተዋል. ትዝታዎች ብቻ ናቸው  የቀሩኝ…. ለማንኛውም ስለግንኙነት ብዙ ነገር አላውቅም ትያለሽ ግን ሌላ የማስበውን ነገር ሰጥተሺኛል፡፡: ትርጉም ያለው ነገር ነው የተናገርሽው:››

ፈገግ አለችለት…ፈገግታዋ ሳበው። የሆነ ነገር ልትለው አፏን ስትከፍት የእሱ ስልክ ጠራ….

‹‹ይቅርታ ይህ ሆስፒታል ስልክ  ነው…ማንሳት አለብኝ። ››

አነሳና አናገረ..ዘጋውና ወደእሷ ዞረ፡፡

‹‹አዝናለው ጥያችሁ ልሄድ ነው…..ችግር አጋጥሞት መግባት ያልቻለ ዶክተር አለ…የእሱን ተራ መሸፈን አለብኝ…እንዲህ ከእናንተ ጋር እደምገናኝ ስላላወቅኩ ቀድሜ  ነው ቃል የገባሁለት››

‹‹አረ ችግር  የለውም ..እስከአሁን አብረኸን ስለቆየህ በጣም ደስ ብሎናል››አለችው

ሁለቱንም ተሰናበተ እና ሄደ…ራሄል ከእይታዋ እስኪሰወር በትኩረት እያየችው ነበር፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
64👍4👏1
ራሄል በትህትና ፈገግ ብላ የዘረጋችውን እጅ ጨበጠችና ወደኃላዋ ዞር ብላ‹‹ ዶ/ር ዔሊያስ ይባላል…እሷ ደግሞ እህቴ ነች››በማለት አስተዋወቀቻቸው፡፡ቀጠለችናም‹‹ከሁለት ሳምንት  በፊት  እናታችን ወድቃ እግሯን ተሰብሮ ህክምና ላይ ስላለች እህቴን ፀጋን እየተንከባከብኳት  ነው…ዶ/ር ደግሞ የእሷ ሀኪም ነው …።››

ፀጋ ለታላቅዋ ሴት ብሩህ ፈገግታ ሰጠቻት ‹‹እንዴት የምታምር ልጅ ነች… ወላጆችሽ ትንሽ ልጅ እያሳደጉ እንደሆነ  ሰምቻለሁ። ሴሬብራል ፓልሲ አለባት አይደል?››

‹‹አዎ ››ስትል መለሰች ራሄል።
‹‹ልዩ ፍላጎት ያለው ህፃን በማደጎ ለመውሰድ መወሰናቸውን ስሰማ አእምሮአቸውን የሳቱ መስሎኝ ነበር፣ነገር ግን አሁን ሳያት  ጠንካራ የጤና እክል ቢኖርባትም ለምን እርሷን ለማሳደግ እንደወሰኑ አሁን ገባኝ.. ።ተቀመጡ.. ምን ይምጣ ቡና? ጣፋጭ ሻይ? ለትንሿ ሴት ጭማቂ?››
ሁሉም ወንበር ይዘው እየተቀመጡ‹‹እኔ  ሻይ እጠጣለሁ እና ለፀጋ የአፕል ወይም የብርቱካን ጭማቂ ብታገኝ ትደሰታለች››አለች ፡፡ኤሊያስ ሁለቱንም አልተቀበለም።ወይዘሮዋ ትዕዛዙን ለሰራተኞቾ አስተላለፈች፡፡
ያዘዙት መጠጥ መጣላቸው…ኤልያስ ጭማቂውን ወስዶ ፀጋን ያጠጣት ጀመር፡፡
ራሄል  ከኤሊያስ ጸጋን ልትቀበለው ስትለ‹‹ችግር የለውም እኔ አጠጣታለው…እንደውም ግቢውን ዞር ዞር እያልን እያየን ጭማቂያችንን ብንጠጣ ጥሩ ይመስለኛል…ችግር የለውም አይደል ወ.ሮ ላምሮት?፡፡››

‹‹አረ ችግር የለውም …እንደፈለጋችሁ ዘና በሉ››
ተነሳና በአንድ እጁ ጭማቂውን በሌላ እጁ ፀጋን ይዞ ከእነሱ እራቅ ብሎ ወደ አትክልት ስፍራው በጥልቀት ገባ…

ወ.ሮ ላምሮት ከፀጋ ጋር አይኗቾ ተንከራተቱ ..ከዛ ድንገት መናገር ጀመረች‹‹እኛ ..ማለቴ እኔና ባሌ  ልጆች አልነበረንም። ››በማለት ትካዜ ውስጥ ገባች፡፡
ራሄል እንደመደነጋገር አላትና  ‹‹አንድ ጊዜ ልጅ ነበረሽ አይደል?›› ስትል ድንገት ከአፏ አመለጣትና ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዎ ነበረኝ…ገና የሶስት አመት ልጅ ነበር። ከዚህች ከአንቺ እህት ትንሽ ይበልጣል››አለች

‹‹ምን ሆነ?›› ራሄል ጠየቀች፣ 
‹‹ከረጅም ጊዜ በፊት ነበር. ረጅም ጊዜ.… ሊገለጽ የማይችል በሽታ ነበረበት..ድንገት ታመመና ሞተብኝ…ምንም ልረዳው አልቻልኩም ››

ራሄልን በሀዘን ፈገግታ ተመለከተቻት።

‹‹ ይገባኛል›› አለች ራሄል ። የራሷን ህመም  በወ.ሮዋ አይን ውስጥ ማየት ቻለች። ፡፡

ወ.ሮ ላምሮት   በጣቷ ላይ ያለውን ቀለበት ማዞር በመቀጠል. ‹‹እንደገና ሞክረን ነበር… ግን አልተሳካልንም..አንድን ሰው መውደድ ሁልጊዜ እድል ነው. ግን ደግሞ ህመም ሊያመጣ እንደሚችልም ቀድመን አውቀን መዘጋጀት አለብን››

‹‹ለማንኛውም፣ ያ ያለፈው ታሪክ ነው››አለች ወይዘሮዋ፣  እጆቿን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች፣ ቀለበቷ መስታወቱ ላይ አስተጋባ። ‹‹ስለዚህ ጉዳይ ለመወያየት ወደዚህ እንዳልመጣሽ እርግጠኛ ነኝ። ››ወደ ራሄል መለስ ብላ ተመለከተች፣
ቀጠለች‹‹ፋውንዴሽኑ በዚህ አመት ከእኔ የሚያገኘውን ገንዘብ ምን አይነት ቁምነገር ላይ ለማዋል እንዳሰበ ወይንም ለየትኞቹ የበጓ አድራጎት ድርጅቶች ለማከፋፈል እቅድ እንዳወጣና ….ብሩን ካከፋፈለ ብኃላ አፈፃፀማቸውን እንዴት መከታተል እንዳሰብ እንድታብራሪልኝ ነው የምፈልገው››አለቻት፡፡
ራሄል‹‹ጥሩ›› ብላ የተዘጋጀችበትን ወረቀት አውጥታ አንድ በአንድ እየተነተነች ለ30ደቂቃ ያህል አብራራችላት፡፡

‹‹ጥሩ ነው..ማለቴ ስራችሁ በደንብ የታቀደበት ይመስላል..ግን የበጎ አድራጎት ድርጅቷችን ዝርዝር ስትገልጪልን በቀደም ያንቺ ሰራተኛ እዚህ መታ ካስረዳችኝ ጋር ልዩነት ያለው መሰለን፡፡እሷ በዚህ አመት ስለተመሰረተው  ጎህ የህፃናት ማሳደጊያ ድርጅት አስረድታኝ ነበር..አብዛኛውን ብር ለዛ ድርጅት ልትሰጡ እንዳሰባችው ነበር የተነገረኝ፡፡››

‹‹ጎህ!!››ራሄል ድንግርግሯ ወጣ…እደዚህ አይነት በጎ አድራጎት ድርጅት መኖሩንም ዛሬ መስማቷ ነው፡፡

‹‹ሮቤል ነው አይደል…ምን ነገረሽ?››ፊቷን አኳሳትራ ጠየቀች፡፡
‹‹አይ.. ንግግሩን ሁሉ ያደረገችው ወጣቷ ሴት ነበረች። እዚህ በየቦታው  የተጣሉ ህጻናትን የሚሰበሰቡ እና  እነሱን በእንክብካቤ የሚያሳድጉ ድርጅት በመሆናቸው   ሀሳብን ወድጄዋለሁ።››

ራሄል  ‹‹ይህ ቡድን በእኔ ተመርምሮ አያውቅም››ንዴቷ እየጨመረ ሄደ።

‹‹ምን ማለትሽ ነው?››ወ.ሮ ላምሮት  አሁን ግራ የተጋባች ይመስላል።

‹‹የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ወይም ገንዘባቸውን ለማሰባሰብ የሚያመለክቱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በትክክለኛው መንገድ ስራቸውን እንደሚሰሩ  እና ከፍተኛ የአስተዳደር ወጪዎችን እንደማይከፍሉ ቀድመን  እናረጋግጣለን። አንዳንድ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች አሉ እስከ ሰማንያ በመቶ የአስተዳደር ወጪዎችን የሚከፍሉ በመሆናቸው ለተረጂዎች የሚደርሰው እርዳታ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ፡፡ለማንኛውም ይሁንታ አልሰጧሻትም አይደል?››

‹‹አላደረግኩትም።ከንቺ ጋር ቀድሜ ልነጋገር ብዬ እንጂ  ላደርገው ፈልጌ ነበር።››

ራሄል በእፎይታ ተነፈሰች..በገዛ ረዳቷ ተጭበርብራ የአገር መሳቂያ ሆና ነበር፡፡

‹‹ስላላደረግሽው ደስ ብሎኛል፡ እኔ በግሌ ያልመረመርኩትን ማንኛውንም ድርጅት በፍጹም እንደማልመክርሽ እንድታውቂ እፈልጋለሁ። እና ይሄ ትልቅ የገንዘብ ጉድጓድ ነው፤ብሩን ካንቺ ስንረከብ ኃላፊነትን ነው አብረን የምንረከበው..ለእያንዷንዷ ሳንቲም ተጠያቂዋ እኔ ነኝ። ››

‹‹ልጅቷ ለአንቺ ነው የምትሰራው አይደል?››

‹‹አዎ ረዳቴ ነች ወይም ነበርች››ራሄል ረጅም ትንፋሽ ወስዳ የጣቶቿን ጫፍ እርስ በርሳቸው አሻሸች። ከቀናት በፊት አንድ ሰው ኮምፒተሯን ሰብሮ ሊገባ ሲመሞከር እንደነበር አስተውላለች  ፡፡ በዛን ቀን  በአካባቢው ያለችው ብቸኛዋ ሰው ሎዛ ነበረች።አሁን ነው ያሳታወሰችው፡፡

‹‹ይህን እንዴት ማድረግ ቻለች? ራሔል በሮቤል ተጠራጥራው ነበር..ሎዛን ግን በፍፅም እንዲህ ታደርጋለች ብላ ግምቱ አልነበራትም ። በሎዛ የክህደት ሀሳብ ትንሽ የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰማት… ወንበሯ ተደገፈች።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
52👍10😱3
አእምሮዋ እንደምንም ከኤልያስ ትዝታ ተላቀቀና  ወደ እሁድ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተመለሰ። ሰባኪው እግዚአብሔር ሕይወታቸሁን  እንዲቆጣጠር እንዲፈቅዱ  እንዴት እንዳበረታታቸው ትዝ አላት።ከተኛችበት ተስፈንጥራ ተነሳች ፤አልጋዋ አጠገብ ያለውን የራስጌ  መብራቷን አበራች ፣ ጋወኗን አንስታ ደረበችና   ወደ አባቷ ቢሮ ወረደች። ጠረጴዛው በሙሉ  በወረቀቶች ተሞልቶ ነበር ፡፡ችላ ብላ አባቷ የሃይማኖት መጽሃፎቹን እንደያዘ ወደምታውቀው መደርደሪያ ሄደች እና መጽሐፍ ቅዱስ አገኘች፡፡ ከመፅሀፍቶቹ መሀከል መዝዛ አወጣች። ወላጆቿ በአልጋቸው አጠገብ የራሳቸው መጽሐፍ ቅዱስ ነበራቸው። ይህ አሁን በእጇ የያዘችው በሠርጋቸው ቀን የተሰጣቸው ጠንካራና በልዩ ቆዳ የተለበጠ ልዩ አይነት ሽፋን ያለው መፅሀፍ ቅዱስ ነው ፡፡ወደ አልጋዋ ተመልሳ ብርድብሱን ገልጣ ገብታ ትራሱን ደገፍ አለችና  በግምት ከፈተችና ማንባብ ጀመረች…ማኃልዬ..ማኃልዬ ዘሰለሞን ምዕራፍ-ዠ 2/10

ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ
ወዳጄ ሆይ ተነሺ
ውበቴ ሆይ ነይ
እንሆ ክረምቱ አለፈ
ዝናቡም አልፎ ሄደ
አበቦችም በምድር ላይ ተገለጡ
የዜማም ጊዜ ደረሰ
የቁርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ
በለሱ ጎመራ ወይኖቹም አበቡ
መዓዛቸውንም ሰጡ
ወዳጄ ሆይ ተነሺ
ውበቴ ሆይ ነይ
ደስ የሚል ስሜት ተሰማት…..መፃፍ ቅዱስን ከድና አስቀመጠችና ተከናንባ ተኛች…ጭልጥ ያለ ሰላማዊ እንቅልፍ  ወሰዳት፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
47👍12
ራሄል ከንፈሯን ነከሰች። ከእሱ ጋር እያወራች ቢሆንም በተመሳሳይ ጊዜ ኮምፒውተሯ ላይ ባለው ፎርም እያስገባች ያለችውን መረጃ ከማስተር ፋይሉ ጋር እያመሳከረች ነው። በየዓመቱ የምታደርገው ዝግጅቱ ምን እንደሚፈልግ በትክክል ታውቃለች ፡፡እናም በየዓመቱ  በተለያዩ ቦታዎች  የሚደረገው አመታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት  በብዙ ሚዲያዎች ሽፋን የሚያገኝ ..ትላልቅ የሀገሪቱ ሀብታሞችና የጥበብ ሰዎች፤የሀይማኖት ሰዎች እና ባለስልጣናት ከልባቸው አምነውበትም ሆነ ለታይታ ብለው በመጋፋት የሚሳተፉበት፤ ለድርጅቱ አብዛኛው ባጀት የሚሰበሰብበት ትልቅ ዝግጅት  ነው. እና እስከዛሬ በነበሩት ዝግጅቶች እያንዳንዱ ጥቃቅን ነገሮች ሳይቀር በእሷ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትና ክትትል የሚከወኑ ነበሩ…ዘንድሮም ምንም እንኳን ፀጋን ከመንከባከብ ጋር እንዴት አንድ ላይ እንደምታስኬደው ባታውቅም…ነገሮች ግን በተመሳሳይ መንገድ እንደሚቀጥሉ እርግጠኛ ነች..ለዛም ብላ ነው የዘንድሮ አመታዊ ዝግጅት ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኘው በወላጆቾ ግዙፍ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ እንዲከናወን ውሳኔ ያስተላለፈችው፡፡  እንደዛ ከሆነ ፀጋን መንከባከብ ሆነ ዝግጅቱን ማቀናጀትን ትወጣዋለች፡፡
ሮቤልን ከእስክሪብቶ ጋር እያደረገ ያለው ጫወታ   ጨመረ ..ድፍረቱን አሰባስቦ‹‹ራሄል አሁን መነጋገር ያለብን ይመስለኛል ››አላት….ቃላቶቹ ትኩረቷን ሳቧት።
‹‹አንድ ሰው መነጋገር አለብን ካለ ..ጉዳዩ በጣም ውጥረት ያለበትና ወሳኝ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡

‹‹እየተነጋገርን አይደል…?መናገር የምትፈልገው ነገር ካለ..እያዳመጥኩህ ነው››አለችው፡፡

እጁን ወደጭንቅላቱ ላከና ፀጉሩን አከክ..አከክ እደረገ … ከመቀመጫው ተነሳ..ከዛ ወደእሷ በትኩረት እየተመለከተ‹‹ስራ ስጀምር ቀስ በቀስ   የበለጠ ሀላፊነት የሚሰጠኝና ለድርጅቱ ጠቅሜ እራሴንም እያሻሻልኩ የምሄድ መስሎኝ ነበር ። አውቃለው  በፋውንዴሽኑ ውስጥ የቆየውት ለስድስት ወራት ብቻ ነው።ቢሆንም ግን በእነዚያ ስድስት ወራት ውስጥ የስራ አካሄዱን እና እኔ ያለኝን ቦታና ተፈላጊነት ብዙም እንዳልተረዳሁ መናዘዝ አለብኝ። ሁሉንም ስራዎች በራስሽ ነው የምትሰሪያቸው። የበለጠ ኃላፊነት ለመረከብ የበለጠ መልፋትና እራሴን ማሳየት እንዳለብኝ አውቃለው….ግን ቢያንስ ወደየት እንደምጓዝ መንገዶቹን ከአሁኑ ማወቅ አለብኝ… እንደዛ ሲሆን ነው ተስፋ ማድረግና መበርታት የምችለው.. ፡፡ እኔ ወጣት ነኝ፣ እድገት በማያሰይ  ስራ ላይ  ጊዜዬን ማጥፋት የለብኝም ።ነገሩን በስህተት አትይብኝና ..በእውርድንብር ነው እተጓዝኩ ያለሁት፡፡››› አላት፡፡
ራሄል ብልጭ አለባት። ቃላቶቹ ከእሱ በፊት የነበረችው ሰራተኛ ስራ  ስታቆም ከተናገረችው ጋር ቀጥተኛ ኮፒ ነው። ሎዛን በክህደቷ ባባረረችበትና የአመታዊ ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሚደረግበት በዚህ ጊዜ  ሮቤልን የማጣት አቅም የላትም።ሮቤልን ተመለከተች፣ ትክክለኛውን  ነገር መናገር እንድትችል ተመኘች።
ትናንት ከመፅሀፍ ቅዱስ ያነበበችው ‹‹ እኔ ስደክም ያን ጊዜ ብርቱ ነኝና።››የሚለው ቃል ወደ ህሊናዋ መጣ፣ ወደ ልቧ ብርሃን ገባ፣ትኩረቷን ሳበሰበች።
ሮቤል በጣም ተጨንቆ ነበር።ቀና ብላ ተመለከተችው እና ቃላቱ በአእምሮዋ ውስጥ ሲያስተጋባ፣የተናገረው ሁሉ ትክክል እንደሆነ ተገነዘበች፡፡ በረጅሙ ተነፈሰች እና መናገር ጀመረች፡፡

‹‹እሺ ለአንተ ጠቃሚ ስራ አለኝ። ሎዛን የሚተካ ሰራተኛ ፈልግና ቅጠር..ከዛ በኃላ   ለአመታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ  ዝግጅት አቀናጅ አድርጌ እሾምሃለሁ..ይሄ ለፋውንዴሽኑ የጀርባ አጥንት የሆነ ትልቅ ዝግጅት ሙሉ ኃላፊነት በአንተ ትከሻ ላይ ያርፋል ማለት ነው…ቀጣይ ምን ማድረግ እንደምንችል ደግሞ የዝግጅቱን አፈፃፀም ገምግመን እንወስናለን..››አለችውና ወዲያው የዝግጅቱን እቅዶችን የያዙ ወረቀቶችን ቀጥታ  ከኮምፒውተሩ ፕሪንት አድርጋ   ተመለከተቻቸው እና ሃሳቧን ከመቀየር በፊት ሰጠችው።

‹‹ይህ እኔ የምጠቀመው ዝርዝር እቅድ ነው ።እንደጋይድ ተጠቅመህ የራስህን ማሻሻያና ፈጠራ ልትጨምርበት ትችላለህ… ጥያቄ ካለህ በማንኛውም ሰዓት አለው››

. ሮቤል በጥልቅ  ፈገግታ ወረቀቶቹን ተቀበላትና   ገለበጠባቸው።‹‹እሺ ከቀላል እንጀምራለን.፣በጣም አመሰግናለው››አላት፡፡የሀሳብ ልዩነታቸው ካሰበው በተቃራኒው በሰላማዊ መንገድ ስለተፈታ በጣም ደስ አለው፡፡

ከአንድ ሰአት ቆይታ  በኋላ ሮቤል እያፏጨ ከቤት ወጣ። ራሄል የቤታቸውን ደረጃ   ወርዶና ግቢውን አቆርጦ  ወደ መኪናው ሲገባ ተመለከተችው።በፊቱ ላይ ያለው ፈገግታ በሩቅ ይታያል።‹‹ትክክለኛውን ነገር ነው ያደረኩት ?››እራሷን ጠየቀች፡‹‹አዎ ሮቤል ጎበዝ ሰራተኛ ነው… በችሎታው ከመጠን በላይ ይተማመናል፤በመጠኑ
ነበር የሳሎኑ ደውል ያቃጨለው….‹‹ወይ ሳለባብስ ዓሊ መጣ››አለችና ወረቀቱና በለበት በታትና ወደመኝታ ክፍሏ ሮጠች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3924
ኤልያስ እጆቹን ዝቅ አደረገ…ተወጣትሮ የነበረው ስሜቱ ተኮመታተረ፡፡የብቸኝነት ማዕበል ሲያናውፀው ተሰማው ። ምን አድርጋው እንደሄደች አላወቀም…ብቻ የሆነ የአካሉን ክፍል ቦጭቃ ከራሷ ጋር ይዛ እንደሄደች ነው የተሰማው ፡፡ደግሞ በተመሳሳይ ከተሰቀለበት ማማ ገፍትራ ወደገደል ውስጥ ጨምራው ነው የሄደችው፡፡ ቀስ አለና ማንም ሳያየው ሹክክ ብሎ ወጣ…ቀጥ ብሎ ወደቤቱ ነው የሄደው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
43👍6
ኤሊያስ ለአፍታ ተስፋ መቁረጥ ተሰማው። ከዚህ በፊት የወላጆቹን ፎቶዎችን ካገኘ በኋላ ከእሱ የተደበቁ ብዙ መረጃዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተስፋ አድርጓል ። ልክ እንደሌሎች  ልጆች፣ወላጆቹ  ሲሞቱ ከፊል የህይወቱ  ክፍል እንደተወሰደበት ሆኖ ተሰምቶት ነበር። ስለእነሱ ተጨማሪ መረጃ ማወቁ..  ትዝታቸውን ለእርሱ የበለጠ እውን ያደርጋለታል።
ወ.ሪት ሜሮን ፋይሉን ይዛ መጣችና እንዲመለከታቸው ከሰጠችው በኋላ ወደ መቀመጫዋ ሄዳ ተቀመጠች፡፡

‹‹ወደ ቤት ልወስደው እችላለሁ?››ሲል ጠየቃት

‹‹ፋይልህ ባይታሸግም ከቢሮው እንዲወጡ አንፈቅድም ፣ ግን ኮፒውን ላዘጋጅልህ እችላለው››አለችውና ፋይሉን ከእጁ ተቀብላ መልሳ ወጥታ ሄደች፡፡

ኤሊያስ ፊት ለፊት  ግድግዳው ላይ  በተርታ የተሰቀለ የሕጻናት እና የትንሽ ልጆች ምስሎች ተመለከተ። አንዳንዶቹ ደብዝዘው ነበር፣ ግልፅ የሆነለት እሷ ስልጣን ከመውሰዷ በፊት ከነበረው ጊዜ ጀምሮ በበጎአድራጎት ድርጅቱ ውስጥ ያለፉትን ህፃናትን ብቻ የሚያካትት ነበር። በዚህ ግድግዳ ላይ የእሱ እና የቢንያም  ምስል ታይቶ ይታውቅ እንደሆነ አሰበ፡፡ከአምስት ደቂቃ በኋላ ፋይሉን በካኪ  ፖስታ ይዛ ተመለሰች። ‹‹ሁሉንም መረጃ እዚያ ውስጥ ጨምሬልሀለው. ሁሉንም ነገር እንዳገኘህ ለማረጋገጥ  ከፈለክ ዳግመኛ  ከመጀመሪያው የፋይል ይዘቶች ጋር ልናወዳድረው እንችላለን.››

ኤሊያስ ኤንቨሎፑን ተቀበለና ‹‹ግድ የለም…ቤት ወስጄ ብመለከተው እመርጣለሁ‹›› አላት ፡፡በእጁ የያዘው ፋይል በጣም ቀላል ሆኖ ተሰማው፤የህይወቱ የመጀመሪያዎቹ  ስድስት ዓመታት ታሪክን እንደማይመጥን ተሰማው፡፡ ‹‹ለዚህ አመሰግናለሁ, ብድር መላሽ ያድርገኝ.››ብሎ ቢሮዋን ለቆ ወጣ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍2715🔥1🥰1
‹‹እሳት››ኤሊ ወንበሩ ላይ ተመልሶ ተቀመጠ። ‹‹እንዴት አስቂኝ ነው?።››አለ በመገረም፡፡ ትንሽ ቢጠብቅ ኖሮ ከብዙ ችግር እና የልብ ህመም መዳን ይችል ነበር። አንድ ቀን ቢጠብቅ ኖሮ የወላጆቹ ፋይል ተቃጥሎ አሁን ያወቀውን ነገር መቼም አያውቅም ነበር ፡፡

‹‹የሙሉውን ፋይል ቅጂ ትናንትና  ከወይዘሪት ሜላት አግኝቻለሁ። አሁን ግን ምነው  ባላገኘሁትና ከቤቱ ጋር ተቃጥሎ አመድ ቢሆን ይሻለኝ ነበር የሚል ምኞት ነው ያለኝ ።››

‹‹ለመሆኑ ምን ብታገኝ ነው እንዲህ የሆንከው?››

ዔሊ በረጅሙ ተነፈሰ፣ ከዚያም ‹‹እኔ ለዘመናት ወላጆቼ ናቸው ብዬ ሳስባቸው የነበሩ ወላጆቼ በጣም ጥሩ  የሆኑ ሰዎች አልነበሩም… ህይወታቸውን ለማሻሻል እና ኑሮአቸውን ለማሸነፍ  መኪና እየነዱ ከባህር ዳር ወደአዲስ አበባ የመጡ ሚስኪን ሰዎች አልነበሩም ፣ እውነታው ከዛ በጣም የራቀ ነበር ..እነሱ ከህግ ለመሸሽ ነበር ወደ አዲስአባ የመጡት ። በትዝታዬ ውስጥ ሳሽሞነሙናቸው እንደነበረ አይነት የተዋጣላቸው ድንቅ ሰዎች እንዳልሆኑ ተረዳሁ። በቀላሉ ምንም ክብር የሌላቸው  ተራ አጭበርባሪዎች ነበሩ።እኔ የሌባ እና የአጭበርባሪ ልጅ ነበርኩ…››

‹‹ምን?››ቢንያም መደነቁን ሊደብቅ አልቻለም፡፡

‹‹አንዳንድ መረጃዎችን ተከታትያለሁ, ቆፍሬያለሁ. ስሜ ኤሊያስ ሉቃስ  አልነበረም, ኤሊያስ አለሙ ነበር. ወላጆቼ የመኪና አደጋ በደረሰባቸው ጊዜ, በአማራ ክልል  ውስጥ ከፖሊስ ይሸሹ ነበር. በገንዘብ ማጭበርበር ይፈለጉ  ነበር. ዝርፊያ እና ሌሎች ያልተጠቀሱ  ወንጀሎችን በመስራት የሚተዳደሩ ወረበሎች ነበሩ። ››ዔሊያስ ራሱን ነቀነቀና የቀረውን የቀዘቀዘውን ሻይ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠው።

‹‹ራሄል ታውቃለች?››ቢንያም ጠየቀው፡፡

‹‹ልነግራት አልቻልኩም እና ለምን ብዬስ ነግራታለሁ?››

‹‹ምክንያቱም ስለሷ ስታወራ  ፊትህ ላይ ደስታ ነው የሚታየው ። እና እሷን ስትመለከት..." ኤልያስ እጁን አነሳ እና ንግሩን ሊያቋርጠው ሞከረ ፣ ቢንያም ግን ንግግሩን ቀጠለ‹‹ምን ለማለት እንደፈለግሁ ታውቃለህ…የምትወዳት ይመስለኛል››

‹‹አዎ አፈቅራታለው…ግን ምን ይሁን ?እንደምታየው ይህ ቤት ገና ዝግጁ አይደለም. …አሁንም እዳዎች አሉብኝ. እሷ በጣም ሀብታም ቤተሰብ ነው ያላት, እኔ ግን የዘራፊና የአጭበርባሪዎች ልጅ ነኝ  ..በምንም አንመጣጠንም፡፡ስለዚህ የእኛ ፍቅር ቅዠት ነው፡፡››

‹‹እንዲህ በነገሮች  ሁሉ ጭፍን የሆነ አመለካከት አይኑርህ …አሁን ያልካቸው ሁሉ  ለሷ ምንም ትርጉም የሚኖራቸው  አይመስለኝም።››

ዔሊያስ ሳቀ ….ከዛ ቀና ብሎ ወንድሙን ተመለከተ።

‹‹ምንም አልክ ምንም አሁን  በህይወቴ ዙሪያ ከማንም ጋር ግንኙነት መፍጠር አልፈልግም።›› አለውና ኪችኑን ለቆለት ወጣ…የመታፈን ስሜት ስለተሰማው ጃኬቱን ለብሶ ሄሌሜቱን አንጠለጠለና ከቤት ወጣ..ንፁህ አየር ካላገኘ ታፍኖ የሚሞት ነው የመሰለው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3518😁1
የራሄል  አይኖች ግን ፀጋ ላይ ብቻ ነበር የተሰኩት። ከአንድ ትከሻዋ ላይ የወረደ የሆስፒታል ጋዋን ለብሳ አልጋው ላይ እንዳለች ትንሽ አሻንጉሊት ትመስላለች። ሌላ ነገር ማየት አልቻለችም። በፀጋ አፍ ውስጥ የገባውን ቱቦ ያስፈራል፣ የምትተነፍስበት የመተንፈሻ አካል ጩኸት ሰቅጣጭ ነው፣ ህይወቷን ህልውና የሚቆጣጠሩ የተለያዩ ማሽኖች የሚያሰሙት ድምፅ ለራሄል በጣም ቀፋፊ የሚባል ነው  ፡፡ ከደረቷ እና ክንዷ በሌሎች ማሽኖች አማካኝነት በአልጋዋ ላይ ተንጠልጥለው ከከረጢት ፈሳሽ እየመጠጡ ወደሰውነቷ ያስገባሉ...ከጥቂት ሰዓታት በፊት ይህቺ ምስኪን  በራሄል እቅፍ ውስጥ ነበረች፡፡፡አሁን ግን ህይወቷ በበርካታ  መሳሪያዎች ተደግፎ ይገኛል ...አንድ የታወቀ ድንጋጤ ደረቷን ሲሰነጣጥቃት  ታወቃት። ‹‹እዚህ መሆን አልቻለችም። በዚህ የተደራጁ የቧንቧ እና የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች የታጠረችውን  ተወዳጇን ይህችን  ትንሽ  አቅመቢስ ህጻን  ማየት አልቻለችም። የዚችን ትንሽ ልጅ ነፍስ ከደካማ አካሏ ስትለይ ማየት አልቻለችም።››…ኪሩቤል ልክ እንደእሷ በማሽን ቁጥጥር ስር ሆኖ  ሲያጣጥር  ‹‹በቂ አየር እያገኘሁ አይደለም…መተንፈስ እያቃተኝ ነው።››እንዳላት ታስታውሳለች….ይህቺ ትንሽ ፍጡርም አንደበቷን አላቃ መናገር ባትችልም…ምን አልባት መተንፈስ በጣም ከብዷት ሊሆን ይችላል ስትል አሰበች፡፡

ራሄል ከእይታዋ እየጨለመባት መጣ ..ቀስ ብላ  በእጇ የወንበሩን ጀርባ ያዘች እና እራሷን ዝቅ አደረገች።ቀስ ብላ ተንበረከከች…እጇን በዝግታ ዘረጋች ፣የፀጋን እጅ ስታገኝ አቆመች፣ ከፀጋ አውራ ጣት ጋር የተጣበቀውን የኦክስጂን መቆጣጠሪያ እንዳትነቅል እየተጠነቀቀች  ጣቶቿን በዙሪያው አንሸራተተች።ከእጇ ጋር ያለው ቅጽበታዊ ግንኙነት በልቧ ውስጥ የተስፋ ጭላንጭል ፈነጠቀባት።

‹‹ኃይሌ በድካም ፍጹም ነው›› የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ወደ አእምሮዋ ገባ እና ራሄል ደጋግማ ደጋግማ አነበነበችው፣ የቀረውን ክፍል ብታስታውስ ደስ ይላት ነበር፣ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ረገድ  እሷ በጣም ከልምምድ ውጪ ሆና ቆይታለች ፣ ቢሆንም ግን አሁን ማድረግ የምትችለው ብቸኛው ነገር  መፀለይ ነው።ለዛ ነው ሰራተኛዋ አለምን ከቤት መፅሀፍ ቅዱስ እንድታመጣላት ያደረገችው፡፡ምን አልባት የምታደርገው ፀሎት ያቺን ሚስኪን ህፃን ሊጠቅም ይችላል?የሚል ከፊል እምነት በውስጧ በቅሏል… የምትወደው ሰው አልጋ አጠገብ ተቀምጣ በሀዘን በተሰበረ ድምፅ  ስትፀልይ ይሄ የመጀመሪያ ጊዜዋ አልነበረም ።ነገር ግን ሀሳቡ በአእምሮዋ ውስጥ ሲንሸራሸር ውስጧ ሙሉ በሙሉ አልተቀበለውም. ፀጋን ወደቤተክርስቲያን ይዛት ከሄደች ቀን ጀምሮ እግዚአብሔርን ዳግመኛ በልቧ ውስጥ የማግኘት ስሜት ተሰምቷት ነበር። ሕልውናውን መካድ አልቻለችም። የምትኖርበት የሱ አለም እንደሆነ  ታውቀዋለች።

ጭንቅላቷን በአልጋው ሀዲድ ላይ ባለው ቀዝቃዛ ብረት ላይ አስደገፈች፣ ዓይኖቿ ፀጥታ ባለው የታናሽ እህቷ አካል ላይ እንደተተከሉ ነው ፣ ፍፁም እርዳታ የለሽ፣ ድካም እና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ስሜት እየተሰማት ነው።መፅሀፍ ቅዱስን ከፍታ እያነበበች መጸለይ ጀመረች።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
54👍8
‹‹ቆንጆ ትመስያለሽ.››አላት… ቃላቶቹ ከሱ አምልጠው ነው የወጡት… ሊያቆማቸው አልቻለም።ራሄል ጭንቅላቷን ቀና አደረገች…፣  በግንባሯ ላይ  ብስጭት ይታያል። አልወቀሳትም። ከሁለት ቀን በፊት ወደ እሱ መጥታ የልቧን ልትገልፅለት ፈልጋ ነበር…በምላሹም እሷን ከቤቱ አስወጥቶ ነው ያባረራት ፡፡

ግን ሌላ ምን ማድረግ ይችል ነበር?በወቅቱ የራሱ ህይወት ተዘበራርቆበት ነበር፣ ትዝታው ከእሱ ተሰርቋል፣ ባወቀው ነገር ተበሳጭቷል ፡፡እሱ ተራ ሆኖ ሳለ እንዴት እንደ ራሄል ያለችን ሴት እንዴት ሊጠይቅ ይችላል?

ራሄል እሱ እያሰበ ካለው ሀሳብ ፍፅም ተቃራኒ  የሆነ ጥያቄ ድንገት ጠየቀችው፡፡

‹‹ግልፅ ሆነህ…ምንም ሳትደብቀኝ…ፀጋ ምን ችግር እንዳለባት ልትነግረኝ ትችላለህ?›› የንግግሩን ርዕሰ ጉዳይ ወደ ጋራ ጉዳያቸው ቀየረችው…።

ዔሊያስ እጁን ዘርግቶ ጣቱን ከንፈሯ ላይ በማሳራፍ ከአፏ የሚወጣውን የጥፋተኝነት ፍሰት አቆመ።

‹‹ አሁን ማድረግ የምንችለው መጠበቅ ብቻ   ነው….ከዛ ውጭ ምንም የሚጠቅምሽን  ነገር ልነግርሽ አልችልም ››

አላት….ዝም አለች…በሀሳብ ርቃ እንደሄደች ከሁኔታዋ ማወቅ ችሏል…ሊያቋርጣት አልፈለገም…ከዚህ በፊት እላፊ ቀርቧት በሁለቱ  መካከል የሆነ ነገር እንዳለ እንድታስብ አደረጋት።እና አሁን? ምን እንደሚያስብ እርግጠኛ አልነበረም። በአንድ ወቅት በደንብ ይቆጣጠረው የነበረ   ህይወቱ አሁን  ተገለባብጦበታል ።ነገሮችን ወደቦታቸው ለመመለስ ጊዜ ያስፈልገዋል። ቢሆንም ግን አሁን ከፊት ለፊቱ የተቀመጠችውን ሴት በጣም እንደሚፈልጋት እርግጠኛ ነው፡፡

ድንገት መናገር ጀመረች‹‹ለአመታት በፀሎት ማመን አቁሜ ነበር ።››

‹‹ታዲያ አሁን  ምን ተለወጠ?››

‹‹ህይወቴ.›› በጥንቃቄ ፈገግታ ሰጠችው። ‹‹ሁሉንም ነገር የምቆጣጠር መስሎኝ ነበር፣ እና ለተወሰነ ጊዜ  ነገሮች እኔ በምፈልገው መንገድ እያስኬድኳቸው መስሎኝ ነበር። የምፈልገው አይነት  ስራ እና የምወደው አይነት የመኖሪያ ቦታ እና ትክክለኛ ህይወት ነበረኝ። የኪሩቤልን ሞት ለመርሳት ለማደርገው ጥረት መሸሸጊያ አግኝቼ ነበር። አሁን ግን ፀጋ  ታማለች።›› ራሄል ተነፈሰች። ‹‹አዎ. እና ፈራሁ. እና አዝኛለሁ. ወደ ህይወቴ ባትገባ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ እና አጣብቂኝ ውስጥ ገብቼያለው… በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኜ በራሴ ኩራት የምኮፈስበት ምንም አይነት አቅም የለኝም….እና እግዚያብሄር እጅ ላይ ወድቄለው….ይህንንም በግልፅ ማወጅ የምችለው ቀጥታ ከእሱ ጋር በመነጋገር ነው….በፀሎት››

የሚላት ሌላ ነገር ስለጠፋው‹‹ ጥሩ ነገር  ያደረግሽ ይመስለኛል…ግን ዳግመኛ እንድትጎጂ አልፈልግም?››አላት፡፡

‹‹አንዳንዴ መጎዳት ጥሩ ነው… ስጎዳ በህይወት መኖሬን አውቃለሁ። ኪሩቤል ከሞተ በኋላ ስብርብር ስል ሁሉም ሰው ነገሮችን እያጋነንኩ እንደሆነ ነበር የሚያስቡት ። አውቃለው እንደዛ ልጎዳ አይገባም ነበር ። አየህ  ችግሩ ለኪሩቤል ሞት እራሴን ነበር ተጠያቂ ያደረኩት… የዛን ቀን  ባንጣላ ኖሮ በብስጭት ጥሎኝ አይሄድም ነበር …ባይበሳጭ ኖር ደግሞ በተሻለ ትኩረት ያደርግ ነበር፣ እናም በዛ ሰካራም ሹፌር አይመታም ነበር፣ ….አይገርምም .. ከእኔ አንደበት የሰማቸው የመጨረሻ ቃላቶች  ስለዛ ሞተር ሳይክል የተሰነዘረ  ትችት እና ቁጣ ነበር…. ‹‹ሞተር እየነዳህ ሁለተኛ ወደእኔ እንዳትመጣ ››ነበር ያልኩት….፡፡

‹‹ራሄል እንደዚያ አታስቢ። ጥፋቱ ያንቺ አልነበረም።››

‹‹ አሁንማ አውቃለሁ,… ግን ለዓመታት, እንደዛ ነበር የማስበው … እሱን አፈር ውስጥ እንዲገባ አድርጌ እኔ ግንኙነት የመጀመር መብት የለኝም   ብዬ እራሴን ስቀጣ ነበር የኖርኩት … ከዚያም ባላሰብኩት አጋጣሚ ድንገት  ፀጋ ወደ ህይወቴ ገባች….ተስፋዬን አደሰችው …ጨለማ ጎኔን ሸንቁራ ብርሀን እንዲፈስበት አደረገች …ከእንደገና በጣም እንዳፈቅር አበረታታችኝ…ነገን እንድናፍቅና  ከስራ ውጭ ስላለ ህይወቴ እንዳሰላስል አደረገቺኝ…እንደገና እየወለደችኝ እንዳለ ነው የሚሰማኝ…አንድ ነገር ከሆነችብኝ እንዚህን ሁሉ በጎ ስሜቶች መልሼ እንዳላጣቸው ፈራለሁ…ስጋቴ ዳግመኛ እንዳልሞት ነው ››በእንባ እየታጠበች ቢሆንም   ፈገግ አለች፣ የእፎይታ ትንፋሽ ወሰደች።‹‹ እናም ለዛም ነበር ከአንተ የራቅኩት እና ስለፈራሁ ይቅርታ።››

‹‹ ራሄል እባክሽ ለዚህ ይቅርታ አትጠይቂ››በነገረችው ነገር ልቡ አዘነ። የሆነ ነገር ለመናገር አስባ ..ተወችው…ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠ ነው። ዔሊያስ ከዚህ በላይ ሊቋቋመው አልቻለም። ጠጋ ብሎ ወደ እቅፉ አስገባት።ደረቱ ላይ ለጠፋት፣ እንባዋ በገላው ላይ ሲንጠባጠብ  ሙቀት ተሰማው።

‹‹ ፈራሁ ኤሊ። በጣም ፈርቻለሁ። እና እንደዚህ አይነት ስሜት እንደገና እንዲሰማኝ አልፈልግም ነበር። ›› ድምጿ ተሰባበረ እና ወደ እሱ ተጣበቀች።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
59👍14
ዔሊያስ ‹‹ፀጋ አሁን ደህና ናት…ወላጆችሽ አሁን አሉ እና ነርሶች ሁል ጊዜ አጠገቧ ናቸው.››

‹‹አውቃለሁ።››አጠገቧ ያለውን መቀመጫ እየደበደበች ቀና ብላ ተመለከተችው።

‹‹እባክህ መጥተህ እዚህ ተቀመጥ …አንድ ነገር ልነግርህ እፈልጋለሁ ››አለችው፡፡
በጣቷ ላይ ያለውን ቀለበት እያሽከረከረች  በጎን  ተመለከተችው። በወቅቱ ያጠለቀችው  ብቸኛው ጌጣጌጥ እንደሆነ ተገነዘበ።የሚገርመው እጁን በራሷ ያዘች።

ፈራ ተባ እያለ ወደእሷ ተጠጋና ግማሽ ሜትር ያህል ክፍተት ትቶ ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ጥቂት የፅሞና ጊዜ ወሰደችና  መናገር ጀመረች‹‹ዛሬ ጥዋት አንተ ባልነበርክበት ጊዜ  አንድ ሰው  ጎብኝቶኝ  ነበረ - ወንድምህ ቢንያም። ስለ ወላጇችህ  ነገረኝ። በቅርብ ስለእነሱ ያወቅከው ነገር እንደጎዳህ አስረዳኝ።››
በኤልያስ ፊት  ላይ ብስጭት ታየ።‹‹ወንድሜ ሚስጥር መጠበቅ የማይችል ወንፊት  መሆኑን አላውቅም ነበር.››

‹‹አንተን ፈልጎ  ነበር የመጣው…እድሉን ሳገኝ ላናግረው ፈለኩ..እኔ ነኝ የወተወትኩት።››ራሄል ፣እጇን ወደእሱ   ዘረጋችና በእጁ ላይ ያለውን ጠባሳ በትንሹ ተጫነችው። ያለፈውን ጊዜ የሚያስታውሰው ምልክት ነው፡፡
‹‹ስለ አንተ ልጠይቀው ፈልጌ ነበር።››

‹‹ለምን?››

‹‹ያን ቀን ልጠይቅህ የመጣሁት  በዝግጅቱ ቀን  ስለእኛ  ስህተት እንደሰራሁ ልነግርህ ነበር ። እንዳልኩት በህይወቴ ውስጥ ሌላ ሰው ላለመፍቀድ በጣም ፈርቼ ነበር። ኪሩቤልን ማጣት ከባድ ነገር ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀናት ከአንተ የሰማሁት ነገር የበለጠ ከባድ ነበር፣ እናም ከዚህ በኋላ መጎዳት አልፈልግም - ምናልባት ወንድምህ ሊያውቅ ይችላል ብዬ አስቤ ነበር።

‹‹ለሕይወቴ እቅድ ነበረኝ›› አለ ኤሊያስ። ጣቶቹን ከጣቶቾ አቆላለፈ። ሊለቃት አልፈለገም።

‹‹ቤት ለመስራት  ብድር መበደር ነበረብኝ  ፡፡እዳዬን አስክከፍል ድረስ ቢያንስ ለአንድ ወይም ለሁለት አመት የምጨነቅለትን ሰው  ወደህይወቴ ማስገባት አልፈልግም ነበር ።›› በለሆሳስ ሳቀ፣ ‹‹ከዚያም አየሁሽ፤ ቀድመሽ መጣሽ።››የራሄል የጨለማ አይኖች እየፈኩ ቢሄዱም  ዞር ብላ አላየችም።‹‹ኤሊ ምን እያልክ ነው?››

‹‹ራሄል ላንቺ አስባለሁ:: ከማንም በላይ ህይወቴን ቀይረሽዋል:: ግን ስለ ወላጆቼ ካወቅኩ በኃላ ነገሮች ተገለባበጡብኝ… ምን ማሰብና ምን ማድረግ እንዳለብኝ  አላውቅም. ››

‹‹ወላጆችህ ከእኛ ጉዳይ ጋር ምን አገናኛቸው?››

‹‹... ሌሎች ወላጆች እንዳሉኝ እያወቅኩ ነው ያደግኩት እድሜዬን ሙሉ ወላጆቼ ድንቅ ሰዎች ናቸው ብዬ ነበር የማስበው ›› አለና የተገናኙትን እጆቻቸውን እያየ።
‹‹እርግጥ ያደኩት በሚያስደንቅና እንክብካቤ እና  በፍቅር በተሞላ ቤት ውስጥ ነው፣ነገር ግን ሁልጊዜ የማስታምማቸው ሌሎች ትዝታዎች ስለነበሩኝ፣ለአሳዳጊ ቤተሰቦቼ  በቀላሉ ሊረዱት የሚከብድ አስቸጋሪ  ልጅ ሆንባቸው ነበር።ቢንያም በማደጎ የተወሰደው በጣም ህፃን ሆኖ ስነበር  ወደኋላ ሚጎትተው የስጋ ወላጆቹ ምንም ትዝታ ስላልነበረው ለእነሱ መልካም ልጅ ሆኖ ማደግ ችሏል፡፡እና አሁን ድንገት ስጓጓለት ስለኖርኩት ስለስጋ  ወላጆቼ ታሪክ ካወቅኩ በኃላ በጣም ተናደድኩ  …የተከዳው አይነት ስሜት ነው ተሰማኝ ።"

‹‹ለዛ ነው የዛን ቀን ፎቶዎቹን የጣልካቸው፡፡››

‹‹አዎ…››

‹‹አሳዳጊ ወላጆችህ   ስለስጋ ወላጆችህ ታሪክ ያውቁ ነበር ብለህ ታስባለህ?››

‹‹አይ. አሁን አንኳን እንደዛ  ለማሰብ ይከብደኛል ..ምናልባት እነሱ ለእኔ ውለታ እየሰሩኝ እንደሆነ አድርገው እያስቡ ይሆናል. ነገር ግን እኔ ወላጆቼ ዙሪያ  ህልም  ፈጠርኩ. እኔ ከእውነተኛ ወላጆቼ ጋር ብሆን ኖሮ የተሻለ ህይወት እንደምኖርና የተሻለ ፍቅር እንደማገኝ አስብ ነበር ስለዚህ ፎቶዎቹን ድንገት ሳገኝ  በጣም አስፈላጊ ከሆነው የሕይወቴ ክፍል ጋር የተገናኘሁ ያህል ተሰማኝ። ፍለጋዬ ግን በቀላሉ እራሴን ጎትቼ ማውጣት ወደማልችልበት ቅርቃር ውስጥ ነው ያስገባኝ -በወላጆቼ ላይ ባለኝ ንዴት አሳዳጊዎቼ ላይ  በማመፅ ስጎዳቸው እንደኖርኩ መገንዘቤ ሌላ ፀፀት ላይ ነው የጣለኝ…››
‹‹ከአሳዳጊዎችህ ጋር ያለህን ግንኑኙነት ለማሻሻልና እንሱን ይቅርታ ለመጠየው እኮ አሁንም ጊዜው አረፈደም… እነሱ ድንቅ ወላጆች ናቸው፣አንተን አሳድገው ለዚህ ደረጃ አብቅተውሀል..ስለዚህ መመስገንና የሚገባቸውን የአንተን ፍቅር ማግኘት ይገባቸዋል፡፡ ›› አለችኝ ቀና አድርጋ ጉንጩን እየዳሰሰች።

‹‹ትክክል ነሽ…እንደዛ ነው የማደርገው…››አላት

‹‹ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እግዚአብሔር ከእኔ የሚፈልገውን ለማወቅ በመጸለይ ብዙ ጊዜ አሳልፌአለሁ፣ እና አላውቅም። ፀጋን ሊራራላት ወይም ሊወስዳት እንደሆነ አላውቅም። ታገልኩት። በቃ ጠንክሬ ከጸለይኩ፣ ነገሮች በፈለኩት መንገድ ይከሰታሉ ብዬ በማሰብ የምችለውን ሁሉ እያደረኩ ነው…እኛ የሰው ልጆች በወቅቱና በሰዓቱ ማድረግ የምንችለውን ነገር ሁሉ ማድረግነው የሚጠበቅብን …ፀፀትና ቁጭት  ነፍሳችንን የሚያከሳ በሽታ ነው….እንደዛ ይመስለኛል፡፡››

‹‹‹ሙሉ በሙሉ ትክክል ትመስይኛለሽ.››አላትና አቅፎ ጉንጮን ሳማት፡፡ፊቷ ቀላ፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዝም ተባባሉ፡፡ከዛ እንደምንም አማጠና‹‹ታዲያ ይህን እንዴት እናደርጋለን ራሄል?ማለቴ የእኔና የአንቺ ጉዳይ …በፀጋ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው ?››ሲል ስጋቱን ጠየቃት፡፡
በጥንቃቄ ፈገግ  አለችና ‹‹አሁንም በእሷ ላይ ስለሚደርስባት  ነገር እፈራለሁ፣ ምንም እንድትሆንብኝ አልፈልግም… ነገር ግን በዝግታም ቢሆን መልቀቅን እና በእግዚአብሔር እጅ ማስቀመጥን እየተማርኩ ነው። እናቴ ቅድም የተናገረችው ነገር ልቤ ላይ አርፏል፡፡ ፀጋ  ለእኔ ለአንተ ፤ለአባቴ እና ለእናቴ ለሁላችንም  ከእግዜር የተሰጠችን አደራችን ነች፣ከእኛ የሚጠበቀው አብራን እስካለች ድረስ እሷን መንከባከብ፤መጠበቅና ምቾት እንዳይጓደልባት ማድረግ ነው…ሌላውን ለእሱ ለባለቤቱ መተው አለብን…አዎ እንደዛ ማድረግ የሚገባን ይመስለኛል…ወደጥያቄህ ስመለስ የእኔ እና የአንተ ጉዳይ ላይ ምንም ችግር እንደማያመጣ ነው የማስበው፡፡  ››ዔሊያስ በዚህች አስደናቂ ሴት እየተደመመ ፊቷን በጣቶቹ ዳሰሰ። ከዚያም ሳያስበው፣ ጠጋ ብሎ ሳማት። ተጣበቀችበት።

‹‹እዚህ ስላመጣሀኝ ደስ ብሎኛል››አለች ..ወዲያው መልሷ ይስማት ጀመር…ድንገት በሩ ተከፍተ …በድንጋጤ ተለያዩ::
አንድ  ነርስ ነበረች ‹‹ይቅርታ ደ/ር  ፀጋ በጭንቀት ላይ ነች።››ሁለቱም በምን ፍጥነት ተፈትልከው ፀጋ ወደተኛችበት ክፍል  ደደረሱ እነሱም አያውቁትም፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
85👍15
‹‹እየወጣህ ነው?››ዔሊ በትከሻው አሻግሮ ወደ ኋላ ተመለከተ። ሊፍቱ ቆሞ ነበር እና በሮቹ ክፍት ነበሩ። አንድ ትልቅ ወንድ እና ሴት በዋናው ፎቅ ኮሪደሩ ላይ ቆመው በፈገግታ እየተመለከቷቸው ነበር። ራሄል እራሷን አላቀቀችና   ‹‹ይቅርታ›› ስትል አጉተመተመች።

‹‹ይህ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ነገር አይደለም›› አለ ሰውዬው… ሚስቱን መስማማቷን በፈገግታዋ ገለፀች፡፡

ራሄል ሳቀች፣ ከዛ ዔሊን እጁን ይዛ ከአሳንሰሩ አወጣችው። በዝግታ ጎን ለጎን መራመድ ጀመሩ፡፡ግራ መጋባቱን አየችና ‹‹ምን ፈልገህ ነው?›› ብላ  ጠየቀችው።

‹‹ለብቻችን ሆነን በአግባቡ የምንነጋገርበት ቦታ ››

ራሄል እግሩ ላይ ቆማ በፍጥነት እና ጠንክር ያለ ስሞሽ  ሳመችው። ‹‹ኤሊ እወድሃለሁ። እና ማንም ቢያውቅ ወይም ቢያየን  ግድ የለኝም። ለትክክለኛው ነገር ግድ የለኝም እና  ከየት እንደመጣህ ግድ የለኝም። ወዴት እንደምንሄድ ግድ የለኝም ከአንተ ጋር መሆን ብቻ ነው የምፍልገው።››ዔሊ ራሱን በአግራሞት  ነቀነቀ እና እጁን በወገቧ ዙሪያ ጠመዘዘ እና አቀፋት።

‹‹እኔም እንዲሁ። ግን ያለ ተመልካቾች አንዳንድ ተራ ውይይት ማድረግ እመርጣለሁ።››ራሄል ወደ እሱ ተጠግታ ቃተተች።‹‹ የዚያህን  ቃል ድምፅ ወድጄዋለሁ።ታዲያ ወዴት እንሂድ?››

‹‹የወላጆችሽ ቦታስ? ያን ያህል ሩቅ አይደለም››

‹‹ይህ የግል ጉዳያችን አይመስልህም..ለእኛ የሚሆን ድብቅ ቦታ እዛ የምናገኝ ይመስልሀል? ›› አለች ራሄል ፡፡

‹‹እየቀለድሽ ነው? በዚያ ቦታ ቢያንስ 20 ክፍሎች አሉ…።››

‹‹ሀያ አይደለም  …አስራስምንት  ብቻ ነው››ስትል አረመችው፡፡  ‹‹ከእነዚያም አንዳንዶቹ የአገልጋዮች መኖሪያ ናቸው።››ስትል አከለችበት

‹‹ይቅርታ አድርጊልኝ››አለ ኤሊ እየሳቀ። ‹‹ግን  ለመነጋገር  ልንጠቀምበት የምንችለው ጸጥ ያለ ቦታ ከአስራስምንቶቹ  ክፍሎች በአንዱ ውስጥ እንደምናገኝ እርግጠኛ ነኝ።››

‹‹እንደምንችል እገምታለሁ..የራሴ መኝታ ቤት እስከአሁንም ባለበት እንዳለ አትርሳ" አለችው እና እጇን ከእጁ ጋር አቆላልፋ ወደእሷ መኪና ገብታው  ከሆስፒታሉ ወጡ።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍4011
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

//
ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡

ፀጋ   ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡

ራሄል ከተቀመጠችበት ተነሳችና   የፀሐይ መነፅሯን ወደ ጭንቅላቷ ገፋ በማድረግ   እህቷ የፈለገችውን  አበባ ቀነጠሰችና በትናንሽ እጆቾ ውስጥ አስቀመጠችላት…ፀጋ በደስታ ፈነጠዘች፡፡
ሮቤል እና አዲሷ ረዳት የፋውንዴሽኑን ስራ ከአሰበችው በላይ  በጥሩ ብቃት እየመሩላት እንደሆነ ለሁለት ቀን ወደቢሮ ተመልሳ ባደረገችው የስራ ግምገማ መረዳት ችላለች፡፡
…እህቷን ለማስታመም በሆስፒታል ባሳለፈቻቸው አስር ቀናት ውስጥ ምንም የጎደለ እና ሳይሰራ የተወዘፈ ስራ አልነበረም…እና አሁንም ለሌላ አንድ ሰምንት ታናሽ እህቷ በደንብ እስክታገግም አብራት እንድትሆንና ቀለል ያሉ  ስራዎችን እዛው እቤት ሆና እንድትሰራ ፈቅደውላት እሷም ተስማምታ  ወላጇቾ ቤት ነው ያለችው፡፡

‹‹ኤሊ እመጣለሁ ያለው መቼ ነው?››ወ.ሮ ትርሀስ  መጽሃፏቸውን  ከጎኗቸው  ባለ የመስታወት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ራሄልን  ጠየቋት።

‹‹ከሶስት እስከ  አራት ሰዓት እመጣለሁ ነበር ያለው ፡፡ ››መለሰች…ጸጋ  ራሷ ቀጥፋ የሰጠቻትን አበባ  ፀጉሯ መካከል ሻጠችላት…ራሄል  በፈገግታ እህቷን ወደራሷ ሳበችና ጉንጮን በመሳም‹‹ትንሿ እህቴ ..እንዲህ ስላሳመርሺኝ አመሰግናለው››አለቻት፡፡
በዛው ቅፅበት ወደግዙፉ ግቢ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ተሰማ ፡፡

‹‹የምትጠብቂው ጓደኛሽ  አለ እንዴ?››አቶ ቸርነት ጠየቁ፡፡

‹‹ አይ አይመስለኝም?››ራሄል እርግጠኛ ባለመሆን ጠየቀች፡፡

‹‹እንግዲያው አለም መጥታ ማንነቱን እስክታሳውቀን እንጠብቅ  ?››በማለት እናቷ ሳቁ።

አለም ወዲያው እየተፍለቀለቀች መጣች…‹‹ራሄል  ነይ እንግዳሽን ተቀበይ››

‹‹ማን ነው?››

‹‹አትንገሪያት ተብያለው…እራስሽ መጥተሸ እይው››አለችና ወደኪችኗ ተመለሰች፡፡

ራሄል.‹‹ማነው በወላጆቼ ቤት ከእኔ ጋር እንዲህ አይነት ጫወታ ለመጫወት የደፈረው?››በማለት ተነስታ ፀጋን ይዛ   ሄደች።ራሄል እና ፀጋ  ወደ ግቢው የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ሲሄዴ ኤሊ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት  ።ራሄል እንዳየችው  በውስጧ የደስታ ማዕበል አጥለቀለቃት።

ባለመኪና ስትጠብቅ ባለሞተር ሰው በማየቷ ተደንቃ ‹‹ሄይ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ? የሞተር ሳይክልህን ድምፅ አልሰማሁም።››አለችው…

ዔሊ ጎንበስ ብሎ በቀስታ ሳማት እና ፀጋን አንስቶ ካቀፋት በኃላ‹‹ሌላ አይነት  የመጓጓዣ ዘዴ ነው የተጠቀምኩት.››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ሞተርህ ተበላሸች እንዴ ?›› አለችና አይኖቾን ወደመኪና ማቆሚያ አዞረች  ከእሷ   ቀይ መኪና  አጠገብ የቆመ ባለ ሰማያዊ ቀለም  መኪና እያየች ግራ ተገባች።

‹‹ ያን መኪና  ከማን ነው የተዋሰከው? ወንድምህ እንደዚህ አይነት መኪና የለውም።››

ዔሊ ተነፈሰ። ‹‹እነሆ፣ ወ.ሮ ራሄል  ሞተሬን ሸጥኩት።››

ራሄል መኪናዋን በድጋሜ  ተመለከተች፣ ‹‹ሞተር ሳይክልህን አስወገድከው !አየህ እኔ ስለ አንተ የምወደው ያን  ነው ። ቆንጆ እና ፈጣን ተማሪ ነህ….ግን ለምን?››

…‹‹ደህና፣ በአንድ ወቅት አንድ ሰው እንዴት አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ለዛውም የህፃናት ሀኪም የሆነ ሰው ሞተር ሳይክል ይነዳል ? የሚል  ጥያቄ ጠየቀኝ። እና ለእሱ መልስ ለመስጠት ብዬ ነው መኪና የገዛሁት፡፡››

ራሄል ወደ መኪናው ሄዳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ  ትንሽ ነካችው፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለሰች፣ ››

‹‹አስደንቀኸኛል ››አለችው

‹‹ስለሞተር ሳይክሎች ያለሽን ስሜት ስለማውቅ  እናም የፍራቻሽም ምክንያት በከፊል ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት  ነው...››

እዛው የሳሎኑ በረንዳ ላይ ካሉ ወንበሮች አንዱን እንዲቀመጥ ሳበችለት ፀጋን በክንዱ እንዳቀፈ ተቀመጠ….ከጎኑ ሌላ ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

ከዛ ሳታስበውና ምንም ሳትዘጋጅበት ትልቅ  ቁም ነገር ከአንደበቱ አፈትልኮ ወጣ  ‹‹ይህን ሁሉ  በትክክለኛው መንገድ ይፋ   ማድረግ ፈልጌ ነው …ራሄል፣ ላገባሽ እፈልጋለሁ።››አላት፡፡

ጆሮዎቾን ማመን አልቻለችም…ልቧን  ደረቷን ሰንጥቆ እንዳይወጣ የፈራች ይመስል ደግፋ ያዘችው ። በውስጧ የሚንተከተከው ደስታ እና ፍቅር እና ምስጋና መውጫ ለማግኘት እየሞከሩ በአንደበቷ ላይ ተንገዋለሉ….ማልቀስ ብቻ ነው የቻለችው፡፡

‹‹ሄይ እኔ ያን ያህል መጥፎ ነገር አልተናገርኩም….ለምን ታለቅሻለሽ?››

‹‹በጣም ደስ ብሎኝ ነው…..››ስትል በለሆሳሳ መለሰችለት፡፡‹‹እወድሀለሁ ኤሊ›› ወደ እሱ ተሳበችና ጉንጩን ሳመችው..ታፋው  ላይ የተቀመጠችው ፀጋ  በደስታ እጆቿን እያጨበጨበች በሳቅ ተንከተከተች። የእሷ ሳቅና ደስታ ወደ እነሱም ተጋባ፡፡

‹‹መጀመሪያ ዝም ብዬ ለአንቺ ምንም ሳልነገርሽ ወደቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ለመላክ አቅጄነበር …››

‹‹እንዴ የእኔን ሀሳብ ሳታውቅ ሽማግሌ ልከህ እምቢ ብልህስ?››

‹‹ያው ምን አደርጋለው የተሰበረ ልቤን  ይዤ  የብቸኝነት ኑሮዬን ቀጥላለዋ !!››ብሎ ትከሻውን ነቀነቀ።ራሄል ጣቷን ከንፈሩ ላይ አድርጋ ሳቀች።

‹‹ ስለነርከኝ ደስ ብሎኛል፣ደግሞ ስትነግረኝ  ፀጋ በመሀከላችን መገኘት በመቻሏ  ደስታዋ ድርብ  ሆኗል … ለነገሩ እኛን አንድ ያደረገች እሷ ነበረች.››

‹‹እሺ ስላልሽኝ ደስ ብሎኛል…:በዚህ ምክንያት በህይወቴ ለሆነው ነገር እግዚአብሔርን በየቀኑ አመሰግነዋለሁ:: በአንቺ ምክንያት ህይወቴ መሉ ሆኗል››

‹‹አንተ ስጦታዬ ነህ ኤሊ ›› አለችና አቀፈችው።

‹‹አሁን እናትና አባትሽን እንፈልግ።››

ተስማሙና …ተያይዘው በአረንጓዴ ተክሎች ወደተሸፈነው ግዙፉ ጊቢ  ተያይዘው እየተሳሰቁ ሄዱ፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
41👍12