አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የክሪስቶፈርፍለጋና ውጤቶቹ

ድንገት የሆነ እጅ ትከሻዬን እየወዘወዘ ቀሰቀሰኝ! በድንጋጤና በመርበትበት እናቴ መሆኗን እንኳን መለየት ያልቻልኳት ሴት ላይ በፍርሀት አፈጠጥኩ::
መልሳ አፍጥጣብኝ እጅግ በተቆጣ ድምፅ “ወንድምሽ የት ነው?" ስትል ጠየቀችኝ፡፡

በጣም ከቁጥጥር ውጪ ሆና ስትናገር ስሰማት እንዳትመታኝ እየተሸማቀቅኩ አይኖቼን ክሪስቶፈር ወደሚተኛበት አልጋ ወረወርኩ ባዶ ነበር። አምላኬ
በጣም ብዙ ቆይቷል።

መዋሸት ይገባኝ ይሆን? ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሄዷል ብዬ ልከላከልለት? አይሆንም እቺ እናታችን ናት፤ ትወደናለች… ትረዳናለች… “ክሪስ እዚህ ፎቅ
ላይ ያሉ ክፍሎችን ለማየት ወጥቷል” አልኩ።

ግልፅነት መልካም ነው አይደል? እርስ በርሳችን ተወሻሽተንም ሆነ ለእናታችን ዋሽተን አናውቅም፡ የምንዋሸው ለአያትየው ነው እሱም አስፈላጊ ሲሆን ብቻ።

“የተረገመ! የተረገመ! የተረገመ! ስትል እየጮኸች ወደ እኔ ባተኮረ አዲስ የቁጣ ማዕበል ነደደች ውዱ ትልቁ ልጇ፣ ከሁሉም የምታስበልጠው ልጇ፣ የዲያብሎስ ተፅዕኖ ካላረፈበት በስተቀር በጭራሽ አይከዳትም፡ ትከሻዬን ይዛ ልክ እንደሚራገፍ ጨርቅ አራገፈችኝ፡፡

“በማንኛውም ሁኔታ ሁለተኛ አንቺና ክሪስቶፈር ከዚህ ክፍል እንድትወጡ አልፈቅድላችሁም ሁለታችሁም ቃላችሁን ሰጥታችሁኝ ነበር ግን ቃላችሁን
አጠፋችሁ አሁን ታዲያ እንዴት ላምናችሁ እችላለሁ ላምናችሁ የምችል መስሎኝ ነበር የምትወዱኝና በፍፁም የማትከዱኝ ይመስለኝ ነበር!”

አይኖቼ ፈጠጡ እኛ ነን የከዳናት? እንደዚህ አይነት ሁኔታ ስላሳየችን
ደንግጫለሁ። ለእኔ እሷ የከዳችን ነው የመሰለኝ፡

“እማዬ ምንም መጥፎ ነገር አልሰራንም: የተደበቅንበት ቦታ የቆየነው በፀጥታ ነበር፡ ሰዎች በዙሪያችን ሲመጡና ሲሄዱ ነበር፡ ግን ማንም እዚያ መሆናችንን አላወቀም ማንም እዚህ እንዳለን አያውቅም: ሁለተኛ ከዚህ
አላስወጣችሁም ማለት አትችይም ከዚህ ልታስወጪን ግድ ነው፡ ለዘለዓለም እዚህ ውስጥ ልትደብቂንና ልትቆልፊብን አትችይም:” ምንም መልስ ሳትሰጠኝ በእንግዳና በንቀት አይን ተመለከተችኝ፡፡ በጥፊ የምትመታኝ መስሎኝ ነበር
ግን አላደረገችውም ትከሻዬን ለቀቀችኝና ለመውጣት ፊቷን አዞረች።

ልክ ክፍሉን ለቃ ወጥታ ራሷ ልትፈልገው ስትል በሩ ተከፈተና ወንድሜ ሹክክ ብሎ ወደ ውስጥ ገባ:: በሩን ለቀቀና ዞሮ ወደ እኔ ተመለከተ። ከዚያ ለመናገር ከንፈሩን አላቀቀ: የዚያን ጊዜ እናታችንን ሲመለከት እጅግ እንግዳ የሆነ ስሜት ፊቱ ላይ ታየ።

ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ እንደ ሁልጊዜው እናታችንን ሲያይ አይኖቹ በደስታ አልበሩም።

እናታችን በቅፅበት አጠገቡ ደረሰችና አንዴ በጥፊ አላሰችው: የንዴቷ ብዛት ከድንጋጤው ሳይመለስ ግራ እጇን አነሳችና ሌላኛው ጉንጩ ላይ በጥፊ
መረገችበት።

የክሪስ የገረጣ ፊት ሁለት ትልልቅ ቀያይ ምልክቶች አወጣ።

“ክሪስቶፈር ፎክስወርዝ፣ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ነገር ብታደርግ እኔ ራሴ ነኝ የምገርፍህ! አንተን ብቻ ሳይሆን ካቲንም ጭምር” ክሪስ የተፈጥሮ ቀለሙ ጠፍቶ ፊቱ በጥፊ የተመታበት ምልክቶች የደም አሻራዎች ሆነው
ይታዩ ነበር የራሴ ደም ወደ እግሬ ሲወርድ ከጆሮዎቼ ኋላ የሚያቃጥል ስሜት ተሰማኝ
ጥንካሬዬ እያነሰ መጥቶ እንግዳ እየመሰለች የመጣችው ሴት ላይ አፈጠጥኩ።

ልክ እንደማላውቃትና ለማወቅም ግድ የሌለኝ አይነት ሴት ሆነችብኝ፡ እውነት ይህቺ ሁልጊዜ በደግነትና በፍቅር የምታነጋግረን እናታችን ናት? ረጅም ጊዜ ተዘግቶብን በመቆየታችን የሚሰማንን ስሜት እጅግ ትረዳን የነበረችው
እናታችን ናት? ቤቱ እንደዚህ እንድትሆን የሆነ ነገር አደረጋት ይሆን? ፈጥኖ የመጣልኝ ሀሳብ ይሄ ነው ...ትንንሾቹ ነገሮች ሁሉ ተደምረው እንድትለወጥ አደረጓት
የሚለው፡ በፊት እንደምታደርገው ብዙ ጊዜ አትመጣም: መጀመሪያ አካባቢ እንደምታደርገው በቀን ሁለት ጊዜ ወይም በየቀኑ አትመጣም አሁን የምናምንበትና የምንጠጋበት ነገር ሁሉ ከእግራችን ስር ሾልኮ፣ ሁሉን ነገር አጥተን አሻንጉሊቶች፣ መጫወቻዎችና ስጦታዎች

ብቻ የቀሩን ስለመሰለኝ ፈራሁ።

በክሪስ የደነገጠ ፊት ላይ ንዴቷን የሚያጠፋ የሆነ ነገር አይታ መሆን አለበት በክንዶቿ አቅፋ የጎዳችውን ለመካስ በጥፊ ተመትቶ የቀላውን ፊቱን
በችኮላና በትንንሹ በመሳም ልታፅናናው ሞከረች። ሳመችው፣ ሳመችው፣ሳመችው ፀጉሩን በጣቶቿ አበጠረች ጉንጮቹን አሻሸች: ጭንቅላቱን ወደ ጡቶቿ አስጠግታ አቀፈችው

“ይቅርታ አድርግልኝ ውዴ” አይኖቿና ድምፅዋ ውስጥ እምባ አለ፡ “ይቅር በለኝ… እባክህ ይቅር በለኝ. ስለ መግረፍ ያወራሁት ከልቤ አይደለም:እንዴት እኔን ልትፈራኝ ትችላለህ? እወድሀለሁ እኮ ታውቃለህ አንተንም
ሆነ ካቲን በጭራሽ አልገርፋችሁም: ገርፌያችሁ አውቃለሁ? ራሴን ስላልሆንኩ ነው እንደዚያ የተናገርኩት። ሁሉም ነገር ባሰብኩት መንገድ
እየሄደልን ስለሆነ ያንን ለማበላሸት ምንም ነገር ማድረግ ስለሌለባችሁ ነው በጥፊ የተማታሁበት ብቸኛው ምክንያት ያ ብቻ ነው።” አለችው:

ፊቱን በመዳፎቿ መሀል ጥብቅ አድርጋ ይዛ፣ የተጨማደደ ፊቱን እያየች ጉንጩ ላይ ሳመችው: የሆነ ስሜት እየተሰማኝ ቁጭ ብዬ በመገረም እየተመለከትኩ ነበር… ግራ ከመጋባቴና ልጅ ከመሆኔ ውጪ ምን እየተሰማኝ እንደሆነ አላውቅም በዙሪያችን ያለው አለም ግን በሙሉ ያረጀ በጣም
ያረጀ ነበር።

ይቅርታ አደረገላት በእርግጥም ምን እየተካሄደ እንደሆነ ማወቅ አለብን። “እባክሽ እማዬ፣ ምን እንደሆነ ንገሪን እባክሽ?”

“ሌላ ጊዜ” አለች ወደ ዳንሱ ለመመለስ ጥድፊያ ላይ ነበረች: ሁለታችንንም እንደገና ሳመችን፡ “ሌላ ጊዜ ምናልባት ነገ ሁሉንም ነገር እነግራችኋለሁ"አለችና በችኮላ እየሳመችን የሚያፅናኑ ቃላት ነገረችን: በእኔ ላይ ተንጠራርታ ኬሪን ሳመቻት ከዚያ ወደ ኮሪ ሄዳ ጉንጩን ሳመች።

“ይቅር ብለኸኛል ክሪስቶፈር?”
“አዎ እማዬ፤ ልክ ነሽ እዚሁ ክፍል ነው መቀመጥ ያለብን ለማየት መውጣት አይገባኝም ነበር”
ፈገግ አለችና “መልካም የገና በዓል፣ በቅርቡ አያችኋለሁ:" ከዚያ ወጣችና በሩን ቆልፋ ሄደች።

እዚህ ከመጣን ያሳለፍነው የመጀመሪያው የገና በዓላችን አለቀ: አዳራሹ ውስጥ ያለው ሰዓት ሰባት ሰዓት መሆኑን አመለከተ: በስጦታ የተሞላ
ክፍል፣ ቲቪ፣ የጠየቅነው የቼዝ መጫወቻ፣ የሚሞቁ አዳዲስ ልብሶችና ብዙ የሚበሉ ጣፋጮች ነበሩን፡፡ እኔና ክሪስ ደግሞ አስገራሚ ግብዣ ነበረን
ሆኖም የሆነ አዲስ ነገር ወደ ህይወታችን መጥቷል የማናውቀው አዲሱ
የእናታችን ባህርይ ለአጭር ደቂቃ እናታችን ልክ አያታችንን መስላ ነበር።

በጨለማ አንድ አልጋ ላይ በአንደኛው ጎን ኬሪ፣ በሌላው ጎን ክሪስ ተኝቶ እኔና ክሪስ እጅ ለእጅ ተያይዘናል፡ ጠረኑ ከእኔ የተለየ ነው ጭንቅላቴ ደረቱ ላይ አርፏል። ከሩቅ ወደ ጆሯችን ከሚመጣው በትንሹ ከሚሰማው ሙዚቃ
“ ልቡ ሲመታ ይሰማኛል ፀጉሬን በጣቶቹ እያፍተለተለ ነበር።

ክሪስ ትልቅ ሰው መሆን በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው አይደል?"

“ይመስለኛል”

“ትልቅ ሰው ስትሆን የትኛውንም አይነት ሁኔታ መቋቋም እንደምትችል አስባለሁ መቼም ቢሆን ስህተትና ትክክል ለሆነው ነገር ጥርጣሬ ገብቶህ አያውቅም ትልልቅ ሰዎች እንደኛ ይፍጨረጨራሉ ብዬ አልገምትም
👍33
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...አሁን ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ባለው ሚስጥር ላይ ቆሻሻና የሚሸቱ ጨርቆች በሻንጣዎቹ ውስጥ በመክተት ሌላ ሚስጥር ጨመርንበት.

ስለ ሁኔታው አብዝተን ባለማውራታችን ከነገሩ እጅግ አስፈሪ መሆን አመለጥን:
ጠዋት እንነሳና ፊታችን ላይ ውሀ ረጨት እናደርጋለን። ጥርሶቻችንን በባዶ ውሀ እናፀዳለን፤ ጥቂት ውሀ እንጠጣና ትንሽ ወዲያ ወዲህ እንላለን፡ ከዚያ ጋደም ብለን ቴሌቭዥን እናያለን ወይም እናነባለን፡

መንትዮቹ ምግብ ፈልገው ሲያለቅሱ መስማቴ ህይወቴን ሙሉ ልቤ ላይ የሚኖር ጠባሳ አስቀመጠልኝ፡ አያታችንን እንዴት እንደጠላኋት። ያቺ አሮጊት እና እናታችን ይህንን ስላደረጉብን ጠላኋቸው።

የመመገቢያ ሰአታችን ያለ ምግብ ሲያልፍ እንተኛለን፡ ለሰዓታት እንተኛለን::እንቅልፍ ሲወስደን የርሀብ ወይም የብቸኝነት ወይም የምሬት ስቃይ አይሰማንም በእንቅልፍ በውሸት የደስታ ስሜት ውስጥ እንሰምጣለን ከዚያ
ስንነቃ ስለምንም ነገር ግድ አይኖረንም።

እንደ ፈዘዝኩና እንደደከምኩ ጭንቅላቴን ዞር አድርጌ ክሪስንና ኮሪን እያየሁ ነበር ከዚያ ክሪስ ከኪሱ ሰንጢ አውጥቶ የእጁን አንጓ ሲቆርጥ ያለምም
ስሜት ጋደም ብዬ እየተመለከትኩ ነው። የሚደማ እጁን ወደ ኮሪ አፍ አስጠጋና ኮሪ ቢቃወምም እሱ ግን ደሙን እንዲጠጣ አደረገው: ከዚያ የኬሪ ተራ ሆነ ሁለቱ ምንም ነገር ያልበሉ በመሆናቸው፣ የትልቁ ወንድማቸውን ደም ጠጥተው፣ በደበዘዘ፣ በፈጠጠና በተቀባይነት አይን አተኩረው ተመለከቱት።

ማድረግ ባለበት ነገር የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰምቶኝ ፊቴን አዞርኩ። ያንን በማድረጉ አድናቆት ተሰምቶኛል። ሁልጊዜ ከባባድ ችግሮችን ማቃለል
ይችልበታል።

ከዚያ ክሪስ ወደኔ አልጋ መጣና፣ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ሲመለከተኝ ከቆየ በኋላ አይኖቹ ወደተቆረጠው አንጓው ዝቅ
አሉ አሁን መድማቱን አቁሟል። እኔም ደሙን ጠጥቼ ረሀቤን እንዳስታግስ ሌላኛውን ደም ስሩን ለማድማት ሰንጢውን አወጣ እንዳያደርገው ነግሬ ሰንጢውን ቀምቼ ወረወርኩት። ብርታት ለማግኘት ስል የእሱን ደም
እንደማልጠጣ ምዬ ተገዝቼ ብነግረውም መሀላዬን ከቁም ነገርም ሳይቆጥር ሰንጢውን በአልኮል ማፅዳት ጀመረ።

“ተመልሳ ባትመጣ ምንድነው የምናደርገው ክሪስ?" ስል ጠየቅኩት አያታችንን ለሁለት ሳምንት አላየናትም: አይጥ ለማጥመድ ወጥመዱ
ላይ ያደረግነውን ቺዝ የሚላስ የሚቀመስ ባጣን ጊዜ በልተን ጨርሰነዋል።ምግብ የሚባል ሳንቀምስ ሶስት ቀናችን ሆኗል፡ መንትዮቹ እንዲጠጡት
የተውንላቸው ወተትም ካለቀ አስረኛ ቀን ሆኖታል።

“በረሀብ አትገድለንም” አለ ክሪስ አጠገቤ ተኝቶ በደካማ ክንዱ እያቀፈኝ። “እሷ ያንን እንድታደርግ ከፈቀድንላት ደደቦች ነን ማለት ነው ነገ ምግብ ይዛ ካልመጣች ወይ ደግሞ እናታችንም ብቅ ካላለች አንሶላ ተልትለን መሰላል
እንሰራና ወደ መሬት እንወርዳለን” አለ፡

ጭንቅላቴ በደረቱ ላይ ስለሆነ ልቡ ሲመታ ይሰማኛል። “ምን እንደምታደርግ ታውቃለህ? ስለምትጠላን እንድንሞት ትፈልጋለች። መወለድ የማይገባን
የሰይጣን ልጆች መሆናችንን ስንት ጊዜ ነው የነገረችን?

ካቲ፤ ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ደደብ አይደለችም: እናታችን ካለችበት ከመምጣቷ በፊት ምግብ ይዛ ትመጣለች::”

የተቆረጠ እጁን ላሽግለት ተንቀሳቀስኩ ከሁለት ሳምንት በፊት እኔና ክሪስ ለማምለጥ መሞከር ይገባን ነበር። የዚያን ጊዜ ሁለታችንም ጥንካሬ ነበረን
አሁን ብንሞክር ግን በእርግጠኝነት ወድቀን እንሞታለን፡ መንትዮቹን
በጀርባችን አዝለን ከሆነ ደግሞ የበለጠ ከባድ ይሆንብናል።

በማግስቱ ጠዋት ምንም ምግብ እንዳልመጣ የተመለከተው ክሪስ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል እንድንሄድ አስገደደን፡ እኔና ክሪስ ለመራመድ እጅግ ደክመው
የነበሩትን መንትዮች ተሸከምናቸው የመማሪያ ክፍሉ ጥግ ላይ ስናስቀምጣቸው አቅማቸው ስላልቻለ እንደመተኛት
እያሉ ግድግዳውን ተደግፈው ቁጭ አሉ። ክሪስ መንትዮቹን ጀርባችን ላይ የምናስርበትን ገመድ እያዘጋጀ ነው

“በሌላ መንገድ እናደርገዋለን” አለ ክሪስ እንደገና እያሰበ “በመጀመሪያ እኔ እሄዳለሁ መሬት ስደርስ ኮሪን ታስሪውና ቀስ እያልሽ ወደታች ትለቂዋለሽ
ቀጥሎ ኬሪንም እንደዚያው ታደርጊያለሽ: በመጨረሻ አንቺ ትመጫለሽ ስለ እግዚአብሔር ብለሽ የምትችይውን ጥረት ሁሉ አርጊ! አደጋ በሚደርስበት
ወቅት ከፍተኛ ንዴት ከሰው በላይ የሆነ ጥንካሬ እንደሚፈጥር ሰምቻለሁ።"

“አንተ የበለጠ ጠንካራ ስለሆንክ እኔ መጀመሪያ ልሂድ” አልኩት በድካም ስሜት “አይሆንም! ድንገት ፈጥነው ከመጡ ለመያዝ ታች መሆን አለብኝ ያንቺ ክንዶች የኔን ያሀል ጥንካሬ የላቸውም: ክብደቱ ሁሉ አንቺ ላይ
እንዳይሆን ገመዱን ጭስ መውጫው ላይ አስርልሻለሁ እና ካቲ ይvህ የአደጋ ጊዜ ነው!”

በአይጥ መያዣ ወጥመዱ ላይ አራት የሞቱ አይጦችን በድንጋጤ ተመለከትኩ።“ትንሽ ጥንካሬ እንድናገኝ እነዚህን አይጦች መብላት አለብን፡” አለ ኮስተር ብሎ፡ “ማድረግ ያለብንን ሁሉ ማድረግ አለብን::''

እነዚያን የሞቱ ትንንሽ ወፍራም ነገሮች በመጠየፍ እየተመለከትኩ “ጥሬ ስጋ? ጥሬ አይጥ? አይሆንም!" አልኩ በቀስታ:
በጣም ተናዶና አስገዳጅ በሚመስል አይነት መንትዮቹንም ሆነ ራሴን በህይወት ለማቆየት የሚያስፈልገውን የትኛውንም ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ነገረኝ፡ “ተመልከቺ ካቲ፣ መጀመሪያ እኔ ሁለቱንም እበላለሁ ገመዶቹን
በደንብ ለመቋጠርም የልብስ መስቀያ ስለሚያስፈልገኝ ላምጣ… ታውቂያላሽ ኬቲ እጆቼ አሁን በደንብ አይሰሩም” አለ፡

ሁላችንም በጣም ከመድከማችን የተነሳ የምንንቀሳቀሰው የግዳችንን ነው::

አየት አደረገኝና “በእውነት አይጦቹ በጨውና በበርበሬ በጣም የሚጣፍጡ ይመስለኛል” አለ፡፡

ጭንቅላታቸውን ቆርጦ ቆዳቸውን ገፈፈና አንጀታቸውን አወጣው: ትንንሽ ሆዳቸውን በመሰንጠቅ ረጃጅምና ቀጫጭን አንጀቶቻቸውን እንዲሁም ትንንሽ
ልቦቻቸውንና ሌሎች የውስጥ እቃዎቻቸውን ሲያወጣ እየተመለከትኩት ነበር ሆዴ ባዶ ባይሆን ኖሮ ሊያስመልሰኝ ይችል ነበር።

ክሪስ ጨውና በርበሬ ሊያመጣ ሲሄድ አይኖቼ ቆዳቸው ተገፍፎ ለምግብነት የተዘጋጁት አይጦች ላይ ተተክለው ቀሩ። አይኖቼን ጨፍኜ የመጀመሪያውን
ጉርሻ ለመጉረስ ሞከርኩ እርቦኛል ግን ይህንን ለመብላት የሚያክል አይደለም ረሀቤ።

ወዲያው እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ ግንባራቸውን አጋጥመውና አይናቸውን ጨፍነው ጥጉ ላይ የተኙትን መንትዮች አሰብኩ በእናታችን ማህፀን ውስጥም እንደዚህ ተቃቅፈው የነበሩ ይመስለኛል: ምስኪን ልጆች! በአንድ ወቅት በጣም የሚወዷቸው እናትና አባት ነበሯቸው።

እነሱን በደህና መሬት ለማድረስና ከጎረቤት ምግብ ለማግኘት አይጦቹ ለእኔና ለክሪስ በቂ ጥንካሬ እንደሚሰጡን ተስፋ አድርገናል።

ክሪስ ቀስ እያለ ወደኛ ሲመለስ ሰማሁ። በሩ ላይ ቆም ብሎ አመነታ።ሽራፊ ፈገግታ እያሳየ ነው ሰማያዊ አይኖቹ ወደኔ እየተመለከቱ አንፀባረቁ።
በሁለት እጆቹ በደንብ የምናውቀውን ትልቅ የሽርሽር ቅርጫት ይዟል። ቅርጫቱ መክደን እስከሚያስቸግር ድረስ በምግብ ተሞልቷል ሁለት ትልልቅ
ፔርሙዞች አወጣ አንደኛው ውስጥ የአትክልት ሾርባ፣ ሌላኛው ውስጥ ወተት ነበረበት በማየው ነገር ግራ ተጋባሁ። እናታችን አምጥታልን ነው?
ከሆነ ታዲያ ለምን ወደታች እንድንሄድ አልጠራችንም? ለምንስ ደግሞ እኛን ፍለጋ ወደዚህ አልመጣችም?
👍252👏2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የመንግስተ ሰማያት ጣዕም

ክሪስ በቀስታና በጥንቃቄ እጁን ከእጁ ስር፣ እግሩን ከእግሩ ስር እያደረገ ወደ መሬት ወረደ እኔ ደግሞ ጣሪያው ጠርዝ ላይ በደረቴ ተኝቼ ወደታች ሲወርድ እያየሁ ነው እጁን አንስቶ ሲያውለበልብልኝ ጨረቃዋ ወጥታ ብሩህ ሆና እያበራች ነበር፡ እንድወርድ ምልክት እየሰጠኝ ነበር። ክሪስ
እንዴት እንደወረደ አይቻለሁ: ዥዋዥዌ ከመጫወት የተለየ አይደለም ብዬ
ለራሴ ነገርኩት። ቋጠሮዎቹ ትልልቅና ጠንካሮች ናቸው: በዚያ ላይ በበቂ ሁኔታ አራርቀን ነው የሰራናቸው አንድ ጊዜ ጣሪያውን ከለቀቅኩ በኋላ ወደ
ታች እንዳልመለከት አስጠንቅቆኛል መጀመሪያ አንደኛውን እግር ካሳረፍኩ
በኋላ በሌላኛው እግሬ የታችኛውን ቋጠሮ መፈለግ ላይ እንዳተኩር ነገረኝ።
እንዳለኝ እያደረግኩ ከአስር ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መሬት ላይ ከክሪስ አጠገብ ቆምኩ።

“ዋው!” አለ ወደሱ አስጠግቶ እያቀፈኝ ከእኔ በተሻለ አደረግሽው”

የፎክስወርዝ አዳራሽ የጓሮ አትክልት ቦታ ውስጥ ነን፡ ክፍሎቹ በሙሉ ጨለማ ውጧቸዋል። የሠራተኞቹ መኖሪያ መስኮቶች ሁሉ ደማቅ ቢጫ ናቸው፡ ዝቅ ባለ ድምፅ “በል መንገዱን ካወቅከው ወደ መዋኛው ምራኝ አልኩት:

በእርግጥም መንገዱን ያውቀዋል እናታችን እሷና ወንድሞቿ ከጓደኞቻቸው
ጋር እንዴት ተደብቀው ወደ ዋና እንደሚሄዱ ነግራናለች:
እጄን ይዞ በጣቶቻችን እየተራመድን ከትልቁ ቤት ወጣን በሞቃታማው
የበጋ ምሽት ውጪ መሬት ላይ መሆን ለየት ያለ ስሜት አለው መንትዮቹን ብቻቸውን የተቆለፈ ክፍል ውስጥ ትተናቸዋል፡ ትንሽዬዋን ድልድይ ስናቋርጥ አሁን ከፎክስወርዝ ግዛት ውጪ መሆናችንን ስላወቅን ደስታ ተሰማን:: ነፃ የሆንን መሰለን፡ ቢሆንም ማንም እንዳያየን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ወደ ሜዳውና እናታችን ወደ ነገረችን ሀይቅ ሮጥን።

ጣሪያው ላይ ስንወጣ አራት ሰዓት ነበር: በዛፎች የተከበበውን ትንሽ የውሀ
አካል ስናገኝ አራት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር። ሌሎች ሰዎች እዚያ ኖረው ምሽታችን ይበላሽብናል ብለን ፈርተን ነበር። ነገር ግን የሀይቁ ውሀ ፀጥ ያለና
በንፋስ እንኳን የማይንቀሳቀስና የሚዋኙም ሆኑ በጀልባ የሚቀዝፉ ሰዎች የሌሉበት ነበር።

በጨረቃ ብርሃን በኮከቦች በደመቀ ሰማይ ስር ሆኜ ሀይቁን እየተመለከትኩ እንደዚህ አይነት የሚያምር ውሀ አይቼ እንደማላውቅና እንደዚህ በሀሴት
የሞላኝ ምሽት ኖሮ እንደማያውቅ አሰብኩ።

“እርቃናችንን እንዋኛለን?” ሲል ክሪስ ለየት ባለ ሁኔታ እያየኝ ጠየቀኝ፡

“አይ የውስጥ ሱሪያችንን ለብሰን ነው የምንዋኘው” አልኩት።

ችግሩ አንድም የጡት መያዣ የሌለኝ መሆኑ ነበር። አሁን ግን እዚህ ደርሰናል: አጉል የሆነው የጨዋነት ጥያቄ በዚህ በጨረቃ ብርሀን በደመቀ ውሀ ከመደሰት አያስቆመኝም። ልብሴን አውልቄ የመርከብ ማቆሚያ ወደ
ሆነው ጥልቀት የሌለው ጥግ ጋ ሮጥኩ። ስደርስ ግን ውሀው እንደ በረዶ ይቀዘቅዝ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ በመጀመሪያ እግሬን ነከር አድርጌ አረጋገጥኩ እውነትም በጣም ቀዝቃዛ ነው! ክሪስን ሳየው ሰዓቱን ከእጁ ላይ ፈትቶ ወደጎን
በማስቀመጥ ወደ እኔ እየሮጠ መጣና ደፍሬ ወደ ውሀው ከመግባቴ በፊት ጀርባዬ ጋ ደርሶ ገፈተረኝ: ውሀው ውስጥ በደረቴ ወደቅኩና ሙሉ በሙሉ
ውሀ ውስጥ ጠለቅኩ።

ከውሀው ስወጣ እየተንቀጠቀጥኩ ነበር። ወደ ክሪስ ተመለከትኩ ከፍ ያለ ድንጋይ ላይ ቆሟል ክንዶቹን ወደ ላይ አነሳና ወደ ሀይቁ ተወርውሮ ገባ፡ በድንጋጤ አቃተትኩ። ውሀው በቂ ጥልቀት ያለው ባይሆንስ? መሬቱ
መትቶት አንገቱ ወይም ጀርባው ቢሰበርስ?

ክሪስ ወደ ላይ አልተንሳፈፈም: አምላኬ! ሞቷል ሰምጧል!

“ክሪስ!” እየጠራሁትና እያለቀስኩ ገብቶ ወደተሰወረበት ቦታ መዋኘት ጀመርኩ።

ድንገት የሆነ ነገር እግሬን ያዘኝ! ጮህኩና ወደ ውስጥ ገባሁ የጎተተኝ ክሪስ ነበር፡ በጥንካሬ እግሮቹን እያወራጨ ወደምንስቅበትና ውሀ ወደምንረጫጭበት ወጣን

“እዚያ የተረገመ የሚሞቅ ቤት ውስጥ ከመዘጋት ቅዝቃዜው አይሻልም? ሲል ጠየቀኝ፡ ልክ እንደ እብድ ዙሪያውን እየዞረ ሲጮህ ላየው ይህች ትንሽ ነፃነት እንደ ጠንካራ የወይን ጠጅ አናቱ ላይ ወጥታ ያሰከረችው ይመስል
ነበር። ዙሪያዬን እየዞረ ዋኘና እግሬን ይዞ ወደታች ሊጎትተኝ ሞከረ: አሁን
ግን አልቻለም:

ውሀ እየተረጫጨንና እየዘፈንን፣ ከዚያ ደግሞ አቅፎኝ ስንስቅና ስንጮ ነበር። ልክ እንደገና ልጆች የሆንን ይመስል ታገልን… አበድን ውሀ ውስጥ በጣም ጎበዝ ነው ልክ እንደ ዳንሰኛ: እየዋኘን እያለ በድንገት ደከመኝ::በጣም ከመድከሜ የተነሳ እንደ እርጥብ ፎጣ ሆኜ ነበር። ክሪስ በክንዱ ደግፎ ወደ ዳር እንድወጣ አገዘኝ።

ሁለታችንም ሀይቁ ዳር ላይ ያለው ሳር ላይ በጀርባችን ተጋድመን ማውራት ጀመርን።

“አንድ ጊዜ እንዋኝና ወደ መንትዮቹ እንመለስ” አለ ሁለታችንም
የሚያብረቀርቁና የሚጣቀሱ የሚመስሉት ኮከቦች ላይ አተኩረናል። ደስ የምትል ግማሽ ጨረቃ ደመናው ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያለች ድብብቆሽ
የምትጫወት ትመስላለች፡ “ምናልባት ወደ ጣሪያው መውጣት ባንችልስ?” አልኩ

“እንችላለን፡ ምክንያቱም ማድረግ አለብን” ክሪስቶፈር ሁልጊዜ እንደሚቻል የሚያምን ልጅ ነው: ሰውነቱ በውሀ ረጥቦ፣ ፀጉሩ ግንባሩ ላይ ተጣብቆ አጠገቤ ተጋድሟል። አፍንጫው እንደ አባታችን አፍንጫ ቀጥ ያለ ነው: ከንፈሮቹ የሚያምር ቅርፅ አላቸው:: አገጩ አራት ማዕዘን ሲሆን ደረቱ መስፋት ጀምሯል። እያደገ ያለው ወንድነቱ በጠንካራ ጭኖቹ መሀል ማበጥ ጀምሯል። ስለ ወንዶች ሳስብ አንድ ነገር ይማርከኛል
ያም ጥሩ ቅርፅ ያላቸው ጭኖች ናቸው፡ ጥፋተኝነት ሳይሰማኝና ሳላፍር ቁንጅናውን በአይኖቼ ለመመገብ ባለመቻሌ አዝኜ ጭንቅላቴን አዞርኩ።

ፊቱን አዙሮ አይኖቼን ተመለከተ: እኔም አየሁት። ሌላ ቦታ መመልከት
የማንችል እስኪመስል ድረስ እይታዎቻችን ተቆላለፉ ለስላሳ የደቡብ ነፋስ ፀጉሬ ውስጥ እየተጫወተና ፊቴ ላይ ያለውን ውሀ
እያደረቀው ነው፡ ምሽቱ በጣም ጣፋጭና በጣም ደስ የሚል ቢሆንም ፍቅርን የመራብ ከፍተኛ ስሜት ውስጥ ባለ ዕድሜ ላይ ያለሁ በመሆኔ ብቻ ምንም
ምክንያት ሳይኖረኝ ማልቀስ ፈለግኩ: ከዚህ በፊት እዚህ የነበርኩ አይነት ስሜት ተሰማኝ፡ ከሀይቁ አጠገብ ሳሩ ላይ እንደተጋደምኩ እንግዳ የሆነ
ሀሳብ በመጀመሪያ እንደ ተሳዳጅ ወደዚህ ወደመጣንበትና ከማይፈልገን አለም ወደተሸሸግንበት ወደዚያ ምሽት መለሰኝ።

ክሪስ፣ አሁን አስራሰባት አመት ሊሆንህ ነው፣ አባቴ እናቴን በመጀመሪያ ሲያገኛት የነበረበት እድሜ ማለት ነው”

አንቺ ደግሞ አስራ አራት፤ ልክ በእሷ እድሜ” ድምፁ ጎርነን ብሎ ነበር።

መጀመሪያ እይታ በሚፈጠር ፍቅር ታምናለህ?”

“በዚህ ርዕስ ላይ ጠቢብ አይደለሁም ትምህርት ቤት እያለሁ፣ አመነታ አንዲት የምታምር ልጅ አይቼ ወዲያው ፍቅር ይዞኝ ነበር ስናወራ ግን የሆነች ደነዝ ነገር ሆና ሳገኛት ለሷ የነበረኝ ስሜት ጠፋ፡ ግን ውበቷ በሌሎች
ነገሮች ከተደገፈ በመጀመሪያ እይታም ፍቅር ሊይዘኝ ይችላል ብዬ አስባለሁ ነገር ግን እንደዚያ አይነት ፍቅር አካላዊ መሳሳብ ብቻ እንደሆነ አንብቤያለሁ።

“እኔስ ደነዝ እመስልሀለሁ?”

“በጭራሽ! እንደሆንሽ እንደማታስቢ ተስፋ አለኝ፡፡ ምክንያቱም አይደለሽም።ፈገግ ብሎ ፀጉሬን ሊነካ እጁን እየዘረጋ ችግሩ ካቲ፣ ብዙ ተሰጥኦዎች ስላሉሽ ሁሉንም መሆን ትፈልጊያለሽ ያ ደግሞ የማይቻል ነው:"

“ዘፋኝም ተዋናይም መሆን እንደምፈልግ እንዴት አወቅክ?”
👍332
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

አንድ ዝናባማ ከሰዓት

ሰማዩ ከብዶ ዝናቡ በጣም እየወረደ ነው: ክፍላችን ውስጥ ያሉ መብራቶች
ሁሉ በርተዋል፡ ቲቪውም እንደተለመደው ተከፍቷል። ክሪስ የመስኮቱን ከባባድ መጋረጃዎች በሁለት እጆቹ ከፈት አድርጎ ይዞ በመቆም ከሩቅ ትንሽ የአሻንጉሊት ባቡር መስሎ ሁልጊዜ አስር ሠዓት ገደማ አሳዛኝ ፊሽካውን እያሰማ የሚያልፈውን ባቡር ለማየት እየጠበቀ ነው:

በራሱ ዓለም ውስጥ ነው፧ እኔም በራሴ አለም ውስጥ እግሮቼን አጣምሬ እኔና
ኬሪ የምንጋራው አልጋ ላይ በመቀመጥ እናታችን ለመጨረሻ የመጣች ጊዜ
ካመጣችው መፅሄት ላይ ምስሎች እየመረጥኩ በውስጡ ያሉትን ፎቶግራፎች በጥንቃቄ እየቆረጥኩ የማልመውን አይነት በደስታ የምኖርበት ቤት፣ ሺ ሴቶችን በጎኑ የሚደርግ ሳይሆን እኔን ብቻ የሚወደኝ የምምኘውን አይነት ረጅም፣ ጠንካራ፣ ጥቁር ፀጉር ያለው ባል በማድረግ የቆራረጥኳቸውን የምስል ቁራጮች ሌላ መፅሀፍ ላይ እየለጠፍኩ ህይወቴን እየሳልኩ ነው።

ዳንሰኛ መሆን ሳቆም ባልና ልጆች ይኖሩኛል የማልመው አይነት ቤት ሲኖረኝ ደግሞ ከውድ ድንጋይ የተሰራ የመታጠቢያ ገንዳ ይኖረኛል ከዚያ ለውበት የሚሆኑ ዘይቶች አደርግበትና ማንም በሩን እያንኳኳ ፈጠን በይ
ሳይለኝ ከፈለግኩ ቀኑን ሙሉ ተዘፍዝፌ እውላለሁ። ከዚያ ቆዳዬ በጣም
ለስላሳና ምንም እንከን የሌለበት ጥርት ያለ ይሆንና ደስ የሚል ሽታ ያለው
የሽቶ ጠረን ይኖረኛል። ይሄ የበሰበሰ አሮጌ ደረቅ እንጨት ሽታና ጣሪያው
ስር ያለው ክፍል አቧራ ከነችግሮቹና አሮጌ እቃዎቹ ጋር እኛን ወጣቶቹን ልክ እንደዚህ አሮጌ ቤት ያለ ጠረን እንዲኖረን አድርጎናል

ክሪስ” አልኩት ጀርባው ላይ እያፈጠጥኩ። “አሁን ጠንካሮች ነን፤ ታዲያ
ለምንድነው እናታችን ተመልሳ እስክትመጣና ሽማግሌው እስኪሞት መጠበቅ ያለብን? ለምንድነው የማምለጫ መንገድ የማንፈልገው?” ቃል አልተነፈሰም። ግን እጆቹ የመጋረጃውን ጨርቅ ጨምድደው ሲይዙ ተመለከትኩ::

“ክሪስ...”

“ስለሱ ማውራት አልፈልግም” አለ በንዴት
“ስለመሄድ እያሰብክ ካልሆነ ታዲያ ለምንድነው እዚያ ቆመህ ባቡሩ እስኪያልፍ የምትጠብቀው?”

“ባቡሩን እየጠበቅኩ አይደለም! በቃ ዝም ብዬ ወደ ውጪ እየተመለከትኩ
ነው:”

በግንባሩ የመስኮቱን መስታወት ተደግፏል። ቅርብ ያለ ጎረቤት እንዲያየው የደፈረ ይመስላል

“ክሪስ ከመስኮቱ ዞር በል የሆነ ሰው ሊያይህ ይችላል”

“ማንም ቢያየኝ ግድ የለኝም!”

የመጀመሪያ ስሜቴ ወደሱ ሮጬ በክንዶቼ አቅፌ ከእናታችን ያጣቸውን
እነዚያን መሳሞች ለማካስ ፊቱን በሙሉ በሚሊየን በሚቆጠሩ መሳሞች
ማዳረስ ነበር እሷ እንደምታደርገው ጭንቅላቱን ደረቴ ላይ አስደግፌ ፀጉሩን እያሻሸሁ በፊት ወደነበረበት አይነት ደስተኛ፣ የሚናደድበት ቀን የሌለው፣ መልካም ነገር ብቻ የሚመለከት ሰው ወደመሆኑ ልመልሰው ፈለግኩ። ነገር ግን በፊት እናታችን ታደርግለት የነበረውን ነገር ሁሉ ባደርግለትም ተመሳሳይ
እንደማይሆን አውቅ ነበር፡ እሷን ነው የሚፈልገው: ተስፋዎቹ፣ ህልሞቹና
እምነቱ በሙሉ በአንዲት ሴት ውስጥ ታሽጓል በእናታችን፡፡

አሁን ከመጣች ሁለት ወር አልፏታል! እዚህ ቤት የምናሳልፈው አንድ ቀን በትክክለኛው ህይወት ሲለካ ከወር በላይ እንደሚረዝም አልገባትም
ስለኛ አትጨነቅም? እንዴት እንደምንኖር አታስብም? ያለምንም ማብራሪያ፣
ምክንያት ወይም ሰበብ ስትተወን እያየ ክሪስ ሁልጊዜ የሷ ቀንደኛ ደጋፊ
እንደሚሆን ታምናለች? ፍቅር በጥርጣሬና በፍርሀት በአንድ ጊዜ ሊፈርስ
እንደሚችልና በፍፁም ዳግመኛ ሊገነባ እንደማይችል አታውቅም?

"ካቲ” አለ ክሪስ ድንገት “የሆነ ቦታ የመሄድ ምርጫ ቢኖርሽ የት ትሄጃለሽ?

“ደቡብ” አልኩ “የሚሞቅና ፀሀያማ የባህር ዳርቻ ወዳለው… ሞገዶች ለስላሳ
ወደሆኑበትና ሀይለኛ ነፋስ ወደማይነፍስበት መሄድ እፈልጋለሁ በነጭ አሸዋ ላይ ጋደም ብዬ የፀሀይ ብርሃኔን እየጠጣሁ ለስለስ ያለ ንፋስ ፀጉሬ ውስጥና ጉንጮቼ ላይ ሲንሸራሸር መስማት ነው የምፈልገው”

“ልክ ነው…” ተስማማ፡ “የገለፅሽበት መንገድ አሪፍ ይመስላል እኔ ግን ልክ
እንደ በረዶ ሸርተቴ ሁሉ በሀይለኛ ሞገድ ውስጥ መንሳፈፍም እወዳለሁ።”

ምስሎቹን እየቆራረጥኩ የነበርኩበትን መቀስና መፅሄቱን አስቀምጬ ሙሉ
በሙሉ ክሪስ ላይ ትኩረት አደረግኩ፡ ክሪስ የሚወዳቸውን ብዙ ስፖርቶች አጥቶ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ ታሽጎ፣ ከእድሜው በላይ አርጅቶና አዝኖ ስመለከተው ላፅናናው ብፈልግም እንዴት እንደማፅናናው ግን አላወቅኩም።

ክሪስ እባክህ ከመስኮቱ ጋ ተመለስ?” አልኩት።

“ተይኝ! ይሄ ቦታ እጅግ ሰልችቶኛል ይህንን አታድርግ፣ ያንን አታድርግ፣
ካላናገሩህ እንዳትናገር መባል፤ በየቀኑ እነዚህን በደንብ በደንብ የማይሰሩ ጣዕም አልባ ምግቦች መብላት ታክቶኛል
በምግብም እንኳን እንዳንደሰት ሆነ ብላ ነው እንደዛ የምታደርገው: ስለዛ
ሁሉ ገንዘብ ሳስብ ደግሞ ግማሹ የእናታችንና የእኛ በመሆኑ እንደሚገባን
አስባለሁ። ያ ሽማግሌ መቼም ለዘላለም መኖር አይችልም:"

“በዓለም ላይ ያለ ገንዘብ ሁሉ ቢደመር ያጣናቸውን የመኖሪያ ቀኖች ያህል
ዋጋ የለውም!” በቁጣ መለስኩለት ወደኔ ዞር አለ፤ ፊቱ ቀልቷል። “ምናልባት
አንቺ በተሰጥኦሽ ገንዘብ ታገኚ ይሆናል እኔ ግን ከፊት ለፊቴ የብዙ አመታት
ትምህርት ይጠብቀኛል፡ አባታችን ዶክተር እንድሆን ይጠብቅ እንደነበረ ታውቂያለሽ፡ እንደምንም ብዬ ያንን ማሳካት አለብኝ፡፡ ከዚህ ከኮበለልን ግን
መቼም ዶክተር መሆን አልችልም: አንቺንና መንትዮቹን እንዲሁም ራሴን
ማኖር ይኖርብኛል። እስቲ እኛን ለማኖር ልሰራ የምችላቸውን ስራዎች
ንገሪኝ… ፍጠኚ! ሳህን አጣቢ ወይም ፍራፍሬ ለቃሚ ሌላ ምን መሆን
እችላለሁ? እነዚህ ስራዎችስ የህክምና ትምህርት ቤት ያስገቡኛል?”

የነደደ ቁጣ ሞላኝ፡ እኔ ላደርገው ስለምችለው አስተዋፅኦ ትንሽ እንኳን
ዋጋ አልሰጠውም: “እኔም መስራት እችላለሁ!” አልኩት። “ሁለታችን
ሆነን ማስተዳደር እንችላለን፡ ክሪስ የተራብን ጊዜ አራት የሞቱ አይጦች
ስታመጣልኝ፣ እግዚአብሔር በትልቅ መከራ ጊዜ ለሰዎች ተጨማሪ ጥንካሬና
ችሎታ ይሰጣል ብለኸኝ ነበር፡ እኔም እንደሚሰጥ አምናለሁ: ከዚህ ወጥተን በራሳችን መኖር ስንጀምር በአንድም በሌላም በኩል መንገዳችንን እናስተካክላለን፡ እናም ዶክተር ትሆናለህ! ያንን ዶክተር የሚለውን ማዕረግ
ከስምህ በፊት ለማየት የትኛውንም ነገር አደርጋለሁ፡”

“ምን መስራት ትችያለሽ?" በጥላቻና በመመረር አይነት ጠየቀኝ፡ መልስ መስጠት ከመቻሌ በፊት ከጀርባችን ያለው በር ተhፍቶ አያትየው በሩ ላይ ቆመችና ወደ ክፍሉ ሳትገባ ክሪስ ላይ አፈጠጠች: እሱ ደግሞ እንደበፊቱ ለመታዘዝ ፈቃደኛ ባለመሆን ግትርና እምቢተኛ ሆነና ከመስኮቱ ጋር ሳይንቀሳቀስ ፊቱን መልሶ እንደገና ዝናቡ ላይ ማፍጠጥ ቀጠለ።

“ልጅ!” ተጣራች። “ከመስኮቱ ጋር ዞር በል አሁኑኑ!

“ስሜ ልጅ አይደለም፧ ስሜ ክሪስቶፈር ነው በተሰጠኝ ስም ልትጠሪኝ ትችያለሽ ወይም ጭራሽ አለመጥራት ትችያለሽ ... ግን እንደገና ልጅ ብለሽ እንዳትጠሪኝ፡”
👍38😁2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


በመጨሻ እኖታችን

እኔና ክሪስ በግርፋቱ ቀን በመሀከላችን ስለተፈጠረው ነገር በፍፁም አላወራንም
በአብዛኛው አተኩሮ ሲመለከተኝ እይዘዋለሁ፧ ግን አይኖቼ አይኖቹን ሲመለከቱ አይኖቹን ያሸሻል እኔም ሳየው ከያዘኝ አይኖቼን ወዲያው እመልሳለሁ።

እኔም እሱም በየቀ እያደግን ነው፡ ጡቶቼ ሙሉ ሆነዋል። ዳሌዬ ሰፋ ብሎ ወገቤ ቀጠን ብሏል ግንባሬ አካባቢ የተቆረጠው ፀጉሬ አድጎ ደስ በሚል አይነት ተጠቅልሏል። ክሪስ ደግሞ ትከሻው ሰፍቷል። ደረቱና ክንዶቹ የበለጠ ወንዳወንድ ሆነዋል አንድ ጊዜ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ
ሆኖ የተገረመ በሚመስል አይነት ወንድነቱን ወደታች ሲመለከትና ሲለካው
ይዤዋለሁ። ርዝመቱ ምን ጥቅም እንዳለው ለማወቅ ስለጓጓሁ “ለምን?” ብዬ
ስጠይቀው አንድ ጊዜ አባታችንን እርቃኑን ሆኖ እንዳየውና አሁን ያየው
ነገር መጠኑ በቂ እንደማይመስል ነገረኝና ፊቱን አዞረ። ልክ እኔ እናታችን የምትለብሰው የጡት መያዣ መጠን ስንት እንደሆነ ማወቅ እንደምፈልገው ማለት ነበር። “እንደገና እንደዚያ እንዳታደርግ።" አልኩት። ኮሪ ያለው የወንድ አካል ትንሽ ስለሆነ ክሪስን ተመልክቶ ልክ እንደ ክሪስ መጠኑ ትንሽ ነው
የሚል ስሜት ቢሰማውስ?

ድንገት የመማሪያ ክፍሉን ወንበሮች ማፅዳቴን አቁሜ ወደ ኬሪና ኮሪ ተመለከትኩ፡ አምላኬ! በጣም መቀራረብ እንዴት እይታን እንደሚያደበዝዝ!
ሁለት አመት ከአራት ወር የተቆለፈብን ቢሆንም መንትዮቹ እዚህ የመጣን
ጊዜ ከነበሩት አልተለወጡም ጭንቅላታቸው ተለቅ ብሎ ስለሚታይ የአይኖቻቸው መጠን ያነሰ ይመስላል፡ ሰውነታቸው ጭንቅላታቸውን መሸከም
የሚችል አይመስልም ፍዝዝ ብለው ወደ መስኮቱ ያስጠጋነው አሮጌ ፍራሽ
ላይ ተቀምጠዋል እስኪተኙ ጠበቅኩና ቀስ ብዬ ለክሪስ “ተመልከታቸው ምንም አላደጉም: ጭንቅላታቸው ብቻ ነው ትልቅ የሆነው:” አልኩት።

በከባዱ ተነፈሰ፤ ከዚያ አይኖቹን አጥብቦ ወደ መንትዮቹ ቀረበና የገረጣውን ቆዳቸውን ለመንካት ዝቅ አለ፡ “ውጪ ጣሪያው ላይ ከእኛ ጋር ወጥተው ፀሀይና ንፁህ አየር ቢነካቸው ጥሩ ይሆን ነበር ካቲ፤ ምንም ያህል ቢጮሁና ቢንፈራገጡ ወደ ውጪ እንዲወጡ ማስገደድ አለብን” አለኝ።

እንቅልፍ ላይ እንዳሉ ተሸክመን ወደ ጣሪያው ብንወስዳቸውና ፀሀይ ላይ ሆነው እኛ እንዳቀፍናቸው ቢነቁ ደህንነት ይሰማቸዋል ብለን አሰብንና ክሪ ኮሪን በጥንቃቄ ሲያነሳ፣ እኔም ኬሪን ብድግ አደረግኳት ወደ ተከፈተው የጣሪያው ስር ክፍል መስኮት ቀረብን፡ የጣሪያውን የኋላ ክፍል መጠቀም የተሻለ ነው: ቀኑ ሀሙስ ስለሆነና ሰራተኞቹ ቀኑን ሙሉ ከተማ ስለሚውሉ ጣሪያው ላይ ወጥተን የምንዝናናበት ብቸኛው ቀን ነው።

ክሪስ ቀስ ብሎ ኮሪን እንደያዘ መስኮቱን አልፎ ሲወጣ የበጋ ፀሀይ ኮሪን
ከእንቅልፉ አነቃው ዙሪያውን ሲመለከት እኔም ኬሪን ተሸክሜ ጣሪያው ላይ
ልወጣ መሆኑን ሲመለከት ጮኸ! ኬሪ ከእንቅልፏ ባነነች። ክሪስ ኮሪን ይዞ
ጣሪያው ጫፍ ላይ ሆኖ እኔ ደግሞ የት እየወሰድኳት እንደሆነ ስትመለከት
ጩኸቷን አቀለጠችው።

ክሪስ ጣሪያው ጫፍ ላይ እንዳለ “አምጫት! ለራሳቸው ነው ይህንን ማድረግ አለብን:” አለኝ፡ መጮህ ብቻ አይደለም እየተራገጡና እየመቱን ነበር።ኬሪ ክንዴ ላይ ስትነክሰኝ እኔም ጮህኩ። በጣም ትንንሾች ቢሆኑም አደጋ ላይ እንደሆኑ በማሰባቸው በጣም በጥንካሬ እየታገሉን ነበር። ፊቴን አዙሬ ወደ መማሪያ ክፍሉ መስኮት አቀናሁና እየተንቀጠቀጥኩ ኬሪን በእግሮቿ አቆምኳት እኔም አየር አጥሮኝ እያለከለክኩ ወንበሩን ተደግፌ በሰላም ወደ ውስጥ እንድመልሳት ስላደረገኝ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ። ክሪስም ኮሪን
እህቱ አጠገብ መለሰው፡ ሙከራችን ጥቅም አልነበረውም እነሱን ጣሪያው ላይ እንዲወጡ ማስገደድ የአራታችንንም ህይወት አደጋ ላይ መጣል ነው።

በጣም ስለተናደዱብን በመጀመሪያ ቀን ወደዚህ ክፍል ስንመጣ ቁመታቸውን
ወደ ለካንበት ግድግዳ ምልክት ስንወስዳቸው ሁሉ እየታገሉን ነበር ክሪስ
ሁለቱንም ቦታው ላይ አድርጎ ሲይዝልኝ እኔ ምን ያህል እንዳደጉ ለማንበብ
ሞከርኩ፡

ሊሆን መቻሉን ባለማመን በድንጋጤ አፈጠጥኩ: በዚህ ሁሉ ጊዜ የጨመሩት
ሁለት ኢንች ብቻ ነው? ሁለት ኢንች! እኔና ክሪስ ከአምስት እስከ ሰባት
አመት እድሜያችን መሀከል ብዙ በጣም ብዙ ነበር ያደግነው ሲወለዱም
ክብደታቸው ትንሽ የነበረ ቢሆንም የተሻለ ማደግ ነበረባቸው።

የደነገጠና የፈራ ገፅታዬን ማየት እንዳይችሉ በእጆቼ ፊቴን መሸፈን ነበረብኝ፡፡
ከዚያ ሳግ ጉሮሮዬን ሲይዘኝ ጀርባዬን ሰጥቻቸው ፊቴን አዞርኩ።

“አሁን እንዲሄዱ መልቀቅ ትችላለህ” አልኩት ዞር ብዬ ሳያቸው ልክ እንደ ሁለት አይጦች በደረጃው እየተንደረደሩ ወደ ተወዳጁ ቴሌቪዥን ሮጡ።

ክሪስ hጀርባዬ ቆሞ እየጠበቀ ነው: “ምን ያህል ቁመት ጨምረዋል?” አለኝ:

ፈጠን ብዬ እምባዬን በእጄ ጠራርጌ ወደ እሱ ዞርኩ ከዚያ አይኖቹን እየተመለከትኩ ሁለት ኢንች እንደሆነ ነገርኩት᎓ አይኖቼ ውስጥ ህመም ነበር።
እሱም ያየው ያንን ነበር:

ጠደ እኔ ተጠግቶ አቀፈኝና ጭንቅላቴን ወደ ደረቱ አስጠጋኝ፡ አለቀስኩ በጣም
አለቀስኩ ይህንን በማድረጓ እናታችንን ጠላኋት የእውነት ጠላኋት! ልጆች እንደ አትክልት እንደሆኑና ለማደግ የፀሀይ ብርሃን እንደሚያስፈልጋቸው
ታውቃለች በወንድሜ እቅፍ ውስጥ እንዳለሁ ተንቀጠቀጥኩ። ነፃ ስንሆን
እንደገና ቆንጆ እንደሚሆኑ ራሴን ለማሳመን እየሞከርኩ ነበር። ቆንጆ ይሆናሉ፤ ያጡትን አመታት ያካክሳሉ፡ ልክ የፀሀይ ብርሃን ማግኘት ሲጀምሩ እንደ አትክልት ያድጋሉ። አዎ ያድጋሉ፤ ጎንጮቻቸው በጣም የጎደጎዱት፣አይኖቻቸው ወደ ውስጥ የገቡት ረጅም ጊዜ ቤት ውስጥ ስለሚቀመጡ ነው እና ያ ሁሉ ሊስተካከል ይችላል፤ አይችልም?

ከዚያ በሻካራ ድምፅ “ገንዘብ ነው አለምን የሚያሽከረክራት ወይስ ፍቅር? ለመንትዮቹ በቂ ፍቅር ሰጥተናቸዋል እናም ስድስት፣ ሰባት፣ ምናልባትም ስምንት ኢንች ቁመት መጨመር ነበረባቸው: ሁለት ብቻ አልነበረም" አልኩ፡

እኔና ክሪስ ወደዛ ወደ ደብዛዛው እስር ቤታችን ተመለስንና እንደ ሁልጊዜው
እጆቻቸውን እንዲታጠቡ ላክናቸው የምግብ ጠረጴዛችን ጋ በፀጥታ ተቀምጠን ሳንድዊቻችንን እየበላንና ወተት እየጠጣን ቲቪ ስንመለከት የክፍላችን በር ተከፈተ: መዞር አልፈለኩም ነበር። ግን ዞርኩ:

እናታችን እየሳቀች ወደ ክፍሉ ገባች የሚያምር ልብስ ለብሳለች የለበሰችው
ጃኬት አንገቱና እጆቹ ላይ ፀጉር አለው: “ውዶቼ!” አለች በመጓጓት አይነት
ሰላምታ: ከዚያ አንዳችንም ሰላም ልንላት ባለመነሳታችን እያመነታችና እርግጠኛ ባልሆነ ስሜት “መጥቻለሁ! ስታዩኝ ደስ አላላችሁም? ስላየኋችሁ እንዴት ደስ እንዳለኝ አታውቁም በጣም ስናፍቃችሁ፣ ስለናንተ ሳስብና ሳልም ነበር፡ እና በጣም በጥንቃቄ የመረጥኳቸው የሚያምሩ ስጦታዎች አምጥቼላችኋለሁ: እስክታዩዋቸው ጠብቁ፡፡ ረጅም ጊዜ የጠፋሁበትን ማካካስ እፈልጋለሁ፡ ለምን እንደምሄድ ልነግራችሁ ፈልጌ ነበር፣ እውነቴን ነው፣
ግን በጣም የተወሳሰበ ነው: ለምን ያህል ጊዜ እንደምቆይ አላወቅኩም
ነበር። ናፍቃችሁኛል! በደንብ ተይዛችኋል አይደል? አልተሰቃያችሁም
ተሰቃይታችኋል እንዴ?”

ተሰቃይታችኋል? ናፍቃችሁኛል? እሷ ማናት? አፍጥጬ እያየኋትና አራት
የተደበቁ ልጆች የሌሎችን ህይወት እንዴት አስቸጋሪ እንደሚያደርጉ እየሰማሁ
መጥፎ ሀሳቦች መጡብኝ፡ ሁለተኛ በጭራሽ እንዳትጠጋኝ ላደርጋት ፈለግኩ።ከዚያ አቅማማሁ በተስፋ ተሞልቼ እንደገና ልወዳትና ላምናትም ፈለግኩ
👍42👎2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ



...“ክሪስቶፈር” አልኩ እየጮህኩ፤ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም አንዳንድ ጊዜ እናቴን እጠላታለሁ! ያ ብቻ አይደለም አንዳንዴ አንተንም እጠላሀለሁ አንዳንዴ ሁሉንም ሰው በተለይ ራሴን እጠላዋለሁ! አንዳንዴ በሞትኩ ብዬ እመኛለሁ:
ምክንያቱም እዚህ ቦታ በቁም ከመቀበር መሞት ይሻላል! እኛ የበሰበሰ፣ የሚራመድ፣ የሚያወራ አትክልቶች ነን!...

ሚስጥራዊ ሀሳቦቼ በሙሉ ይፋ ወጡ፤ ልክ እንደ ቆሻሻ ተዘርግፈው ሁለቱንም
ወንድሞቼን አስደነገጣቸው፡ ትንሸዋ እህቴ ደግሞ መንቀጥቀጥ ጀምራ የበለጠ ትንሽ መሰለች እነዚያ ጨካኝ ቃላት ከአፌ እንደወጡ ወዲያውኑ እንዲመለሱ ፈለግኩ በእፍረት ሰመጥኩ፣ ይቅርታ መጠየቅና መመለስ አልቻልኩም።ዞርኩና እየሮጥኩ ወደ ልብስ ማስቀመጫው ከዚያ ወደ ደረጃዎቹ ከዚያ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሄድኩ። ስጎዳ፣ ብዙ ጊዜም እጎዳለሁ ሙዚቃ ፈለግኩ፤ የዳንስ ልብሴን ለበስኩና ችግሮቼን ሁሉ ለመርሳት መደነስ ጀመርኩ።
እስኪደክመኝ ድረስ መደነስ ቀጠልኩ፡ ከዚያ ድንገት ሙዚቃው ሲያልቅ
ቀኝ እግሬ ታጠፈና ወለሉ ላይ ወደቅኩ። ለመነሳት ብታገልም መራመድ
አልቻልኩም: ጉልበቴን በጣም አሞኛል: ሌላ አይነት እምባ ወደ አይኖቼ
መጣ እየተጎተትኩ ወደ መማሪያው ክፍል ሄድኩኝ፡ ጉልበቴ ለዘለዓለም
ባይሰራም ግድ አልነበረኝም መስኮቱን በሰፊው ከፈትኩና ወደ ጥቁሩ ጣራ ወጣሁ። እያመመኝ መታጠፊያው ጫፍ ደረስኩና በውሀ መውረጃው አሸንዳ
ጠርዝ ላይ ስደርስ ቆምኩ። ታች ያለው መሬቱ ነው። ፊቴ ለራሱ የማዘን እምባና ህመም ምልክት አወጣ፣ እምባዬ እይታዬንም ብዥ አደረገው አይኖቼን ጨፍኜ ሚዛኔን ሳልጠብቅ መወዛወዝ ጀመርኩ፡ በደቂቃዎች ውስጥ
ሁሉም ያበቃል። እሾሀማ የፅጌረዳ ተክሎቹ ውስጥ እወድቃለሁ።

አያትየውና እናቴ አንዲት የማትታወቅ ደደብ ልጅ ጣሪያው ላይ ወጥታ
ድንገት ወደቀች ሊሉ ይችላሉ። እናቴ ሞቼና ተሰብሬ የሬሳ ሳጥን ውስጥ
ተጋድሜ ስትመለከት ታለቅስ ይሆናል። ከዚያ ያደረገችውን ታስታውስና
ክሪስንና መንትዮቹን ነፃ ለማድረግ በሩን ከፍታ እንደገና እውነተኛ ኑሮ
እንዲኖሩ ታደርግ ይሆናል።

ያ ራሴን የመግደሌ ወርቃማ ጎን ነበር።

ሌላኛውን ጎን ማየት አለብኝ: ካልሞትኩስ? ብወድቅና አወዳደቄ የሚገል ሳይሆን ቀርቶ ህይወቴን ሙሉ አካለ ጉዳተኛ ወይም ጠባሳ ቢያደርገኝስ? ከዚያ እንደገና ምናልባት ብሞትና እናታችን ባታለቅስ ወይም ባታዝን ወይም ባትፀፀትስ? እንዲያውም እንደኔ አይነቷን ተባይ በማስወገዷ ደስ
ቢላትስ? ክሪስና መንትዮቹ ያለ እኔ እንዴት ይሆናሉ? ማን ይንከባከባቸዋል?
ለመንትዮቹ ማን እናት ይሆናቸዋል?

ክሪስ ምናልባት አይፈልገኝ ይሆናል፤ የሚገዛለት ትልቁ ውዱ መፅሀፍ የኔን
ቦታ ይተካለት ይሆናል ከስሙ በፊት ዶክተር የሚለውን ማዕረግ ሲያገኝ
ህይወቱን ሙሉ ለመርካት በቂ ይሆንለት ይሆናል ግን ዶክተር ቢሆንም በቂ እንደማይሆን፣ እኔ ከሌለሁ በጭራሽ በቂ እንደማይሆን አውቃለሁ።ሁለቱንም ገፅ ለማየት ባለኝ ችሎታ ከሞት ተረፍኩ፡

ህፃንነትና ሞኝነት እየተሰማኝ ከጣሪያው ጠርዝ ስርቅ አሁንም እያለቅስኩ ነበር ጉልበቴ በጣም ስላመመኝ የጭስ መውጫው ጀርባ ጋ እስክደርስ ድረስ ጣሪያው ላይ ዳዴ እያልኩ እየሄድኩ ነበር። ሁለት ጣራዎች ተገናኝተው ምቹ ጥግ የፈጠሩበት ቦታ ነው: በጀርባዬ ተጋድሜ የማይታየውና ግድ
የሌለው ሰማይ ላይ አፈጠጥኩ። እግዚአብሔርም ሆነ መንግስተ ሰማያት
እዚያ መኖራቸውን ተጠራጠርኩ።

እግዚአብሔርና መንግስተ ሰማያት እዚሁ ምድር ላይ በአትክልት ስፍራዎቹ፣
በጫካዎቹ፣ በመናፈሻዎቹ፣ በባህር ዳርቻዎቹ፣ በሀይቆቹና በአውራ ጎዳናዎቹ ውስጥ ናቸው።

ሲኦልም እዚሁ ነው… እኔ ያለሁበት ያለማቋረጥ የከበበኝ ወደ እሱ ሊወስደኝ
የሚሞክርና አያትየው እንደምታስበው የሰይጣን ዘር ሊያደርገኝ የሚጥር
ነው።

ጨለማ እስኪሆን ድረስ እዚያ ጠንካራና ቀዝቃዛ ጣራ ላይ ተጋደምኩ።
ጨረቃ ወጣች፣ ኮከቦቹም ምን እንደሆንኩ እንደሚያውቁ ሁሉ በቁጣ እኔ ላይ አበሩ የለበስኩት የዳንስ ልብስ ብቻ ነበር ከብርዱ የተነሳ ክንዶቼ ላይ ሽፍ አለብኝ አሁንም በቀሌን እያቀድኩ ነው፡ ከመልካም ወደ ክፉ የለወጡኝንና
ከዚህ ቀን ጀምሮ የምሆነውን አይነት ሰው ያደረጉኝን እበቀላለሁ። አያቴና እናቴ በመዳፌ ስር የሚሆኑበት ቀን እንደሚመጣ ራሴን አሳመንኩት አለንጋ
እይዛለሁ፣ ሬንጁንም እይዛለሁ፣ የምግብ አሰጣጥም እቆጣጠራለሁ።

ምን እንደማደርጋቸው ለማሰብ እየሞከርኩ ነው:: ትክክለኛው ቅጣት
ምንድነው? ሁለቱንም ቆልፌባቸው ቁልፉን መወርወር? እኛ እንደተራብነው ማስራብ?

ለስላሳ ድምፅ ምሽቱንና የተጠላለፉ ሀሳቦቼን አቋረጠ። ክሪስ እያመነታ
ስሜን እየጠራ ነው: ምንም አልተናገረም ስሜን ብቻ ይጠራል: መልስ
አልሰጠሁትም አልፈልገውም፣ አሳፍሮኛል ማንንም አልፈልግም ባለ መረዳቱ አልፈልገውም።
የሆነው ሆኖ መጣና አጠገቤ ጋደም አለ። ምንም ቃል ሳይናገር ይዞት
የመጣውን ሞቃት የሱፍ ጃኬት ደረበልኝ፡ ልክ እንደ እኔ ወደ ቀዝቃዛውና
የተከለለው ሰማይ ላይ አፍጥጧል በመከላችን አስፈሪና ረጅም ፀጥታ
ነገሰ። ስለ ክሪስ የምጠላው ወይም የማልወደው ምንም ነገር የለም ወደ እሱ ዞሬ ይህንን ልነግረውና የሚሞቅ ጃኬት ስላመጣልኝ ላመሰግነው በጣም
ፈልጌያለሁ። ነገር ግን አንዲት ቃል መናገር አልቻልኩም: የሚሰማኝን
እሱና መንትዮቹ ላይ ስለተወጣሁት እንደተፀፀትኩ እንዲያውቅ ፈልጌ ነበር።ማንኛችንም ሌላ ጠላት እንደማያስፈልገን እግዚአብሔር ያውቃል በጃኬቱ ውስጥ ሆነው የሚንቀጠቀጡት ክንዶቼ አቅፈው ሊያፅናኑት ናፍቀዋል ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ከቅዠቴ ስባንን የሚያባብለኝ እሱ ነው ነገር ግን ማድረግ የቻልኩት ብቸኛው ነገር፣ እዚያው ጋደም ብዬ በብዙ ነገሮች የተያዝኩ መሆኔን እንዲረዳ ተስፋ ማድረግ ብቻ ነበር።

ሁልጊዜ አስቀድሞ ነጭ ባንዲራ የሚያውለበልበው እሱ ነው፡ ለዚህም
ለዘለአለም አመስጋኝ ነኝ። እንግዳ በሆነ ጎርናና እና ውጥረት በሚሰማበት
ከሩቅ የሚመጣ በሚመስል ድምፅ፤ እሱና መንትዮቹ ራታቸውን እንደበሉና
ለእኔ ድርሻዬን እንዳስቀመጠልኝ ነገረኝ፡ “እና ከረሜላዎቹን ሁሉ በላናቸው ያልነው እያስመሰልን ነው ካቲ ለአንቺ ብዙ ተቀምጦልሻል” አለኝ።

ከረሜላ? ስለ ከረሜላ ያወራል፤ አሁንም ከረሜላ የእምባ ማበሻ በሆነበት
የልጆች አለም ውስጥ ነው? እኔ አድጌ ለልጆች መደሰቻ ጉጉት አጥቼያለሁ።
የምፈልገው ሌሎች በእኔ እድሜ ያሉ ልጆች የሚፈልጉትን ነው፤ የምፈልገው ወደ ሙሉ ሴትነት ማደግ የምችልበትን ነፃነት ነው፤ ህይወቴን በሙሉ የምቆጣጠርበትን ነፃነት ነው፡፡ ይህንን ልነግረው ስሞክር ድምፄ ልክ እንደ እምባዬ ደረቀብኝ
ካቲ ያልሺው ነገር... ሁለተኛ አስቀያሚና እንደዚያ አይነት ተስፋ ቢስ ነገሮች አትናገሪ” አለኝ፡

“ለምን?” ተናነቀኝ “የተናገርኩት እያንዳንዱ ቃል እውነት ነው፡ የተናገርኩት በውስጤ የሚሰማኝን ነው ያወጣሁት አንተ በውስጥህ የቀበርከውን ነው
ከራስህ መደበቅህን ቀጥልበት እነዚያ እውነታዎች ወደ አሲድነት ተቀይረው ውስጥህን ሲበሉት ታገኛቸዋለህ!” “አንድ ጊዜም መሞት ተመኝቼ አላውቅም”
👍46🥰31
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የእናታችን ድንገተኛ ዜና

እናታችን እንደገና ልታየን ከመምጣቷ በፊት ባለፉት በእያንዳንዱ አስር ቀናት
ውስጥ፣ እኔና ክሪስ ለምን አውሮፓ ሄዳ እንደቆየችና ከሁሉም በላይ ደግሞ
ልትነግረን የነበረው ትልቅ ዜና ምን እንደሆነ ለመገመት ለሰአታት እናወራ
ነበር።

አስሩን ቀናት እንደ ሌላ ቅጣት አሰብነው ቅጣትም ነበረ: እዚህ አንድ ቤት
ውስጥ ሆነን ልክ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ያለን አይጦች እንደሆንን ሁሉ
ችላ ልትለንና ልትዘጋን ችላለች:

ስለዚህ ያን ያህል ቆይታ ስትመጣ እኔና ክሪስ በደንብ ስለተቀጣን የጥላቻ
ወይም የመውጣት ጥያቄያችንን ከደገምን ተመልሳ ላትመጣ ትችላለች ብለን በጣም በመፍራት ፀጥ ብለን እጣ ፈንታችንን ተቀበልን፡ ተመልሳ ካልመጣች ምን እናደርጋለን? መንትዮቹ ገና ጣሪያው ላይ ሲደርሱ ብርክ ከያዛቸው ከተተለተለ አንሶላ በሰራነው መሰላል ተጠቅመን ማምለጥ የማይታሰብ ነው።

ስለዚህ ለእናታችን ፈገግ አልንላት አንድም የማማረር ቃል አላሰማንም
ለወራት ጠፍታ ስለምታውቅ አስር ቀናት በመቆየት ለምን እንደቀጣችን
አልጠየቅናትም፡ ልትሰጠን የፈቀደችውን ተቀበልን፡ ከአባቷ ጋር ለመሆን
እንደተማረችው አይነት ታዛዥ የማይቃወሙ ቅን ልጆች ሆንን የሚገርመው እንዲህ መሆናችንን መውደዷ ነው: እንደገና የሷ ጣፋጭ አፍቃሪና ሚስጥራዊ “ውዶች” ሆንን።

አሁን በጣም ጥሩ፣ አስደሳች፣ ለእሷ አድናቆት ያለን፣ አክባሪና በእሷ
የምንተማመን መሆኑን ስታውቅ ጊዜውን ቦምቧን ለመጣል መረጠችው።
“ውዶቼ፣ ለእኔ ደስ ይበላችሁ! በጣም ደስ ብሎኛል!” እየሳቀች እጆቿን ደረቷ ላይ አድርጋ በክብ ተሽከረከረች: “ምን እንደተከሰተ ገምቱ ቀጥሉ… ገምቱ!” አለችን።

እኔና ክሪስ ተያየን “አያታችን ሞተ!” አለ። ልቤ ደስ የሚለውን ዜና ስትነግረን
ለመዝለልና ለመቦረቅ በመዘጋጀት በጣም እየደለቀ ነው።

“አይደለም!” አለች በድንገት ደስታዋ በጥቂቱ የደበዘዘ ይመስላል።

“ወደ ሆስፒታል ተወሰደ?” ብዬ ሁለተኛውን ምርጥ ግምት አቀረብኩ።
“አይደለም: አሁን አልጠላውም፧ ስለዚህ እናንተ ጋ መጥቼ በሞቱ መደሰቴን ልነግራችሁ አልችልም:”

“ታዲያ ለምን መልካም ዜናውን ራስሽ አትነግሪንም? ስለ ህይወትሽ ብዙም
ስለማናውቅም መገመት አልቻልንም” አልኳት።

ማለት የፈለግኩትን ችላ ብላ ቀጠለች፤ “ለረጅም ጊዜ የጠፋሁበትን ለመግለፅ አስቸጋሪ ሆኖብኝ የነበረው ምክንያት ባርት ዊንስሎ የተባለ ሰው ማግባቴ ነው። ጠበቃና በጣም ጥሩ ሰው ነው። ትወዱታላችሁ። እሱም ሁላችሁንም ይወዳችኋል። ጥቁር ፀጉር ያለው፣ በጣም መልከመልካም፣ ረጅምና የሚያምር ሰውነት ያለው ነው። ክሪስቶፈር፣ ልክ እንዳንተ የበረዶ ሸርታቴ ይወዳል፧ ቴኒስ ይጫወታል፤ ልክ እንዳንተ ጎበዝ ነው” ይህንን ስትናገር ወደ ክሪስ
እየተመለከተች ነበር።

በጣም ደስ የሚል ሰው ነው ሁሉም ይወዱታል። አባቴም ሳይቀር ይወደዋል
ወደ አውሮፓ የሄድኩት ለጫጉላ ሽርሽር ነበር። ያመጣሁላችሁ ስጦታዎች
ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ፣ ከስፔንና ከጣልያን የተገዙ ናቸው:” እኔና ክሪስ
በፀጥታ ተቀምጠን፡ ስለ አዲሱ ባሏ የምታወራውን እየሰማን ነበር።

እኔና ክሪስ ከገና በአል ግብዣ ምሽት ጀምሮ ብዙ ጊዜ ጥርጣሬዎቻችንን
አውርተናል: ልጆች ብንሆንም፣ እንደ እናታችን ያለች ወንዶች የምትፈልግ
ቆንጆ ወጣት ሴት ለረጅም ጊዜ ካለ ባል እንደማትቆይ እናውቅ ነበር። ሰርግ
ሳይደረግ ሁለት አመት ሲያልፍ ግን ያ ትልቅ ፂም ያለው መልከመልካም
ባለ ጥቁር ፀጉር ሰው ለእናታችን ብዙም አስፈላጊ ነው ብለን አላሰብንም
ነበር። በየዋሁ ልባችን እናታችን ለሞተው አባታችን አሁንም ታማኝ እንደሆነች ራሳችንን አሳምነን ነበር። ባለወርቃማ ፀጉር፣ ሰማያዊ አይኖች ያሉት አማልክትን የመሰለ የቅርብ ዝምድና እያላቸው እንኳን እሱን ለማግባት ከምክንያት ባሻገር ላፈቀረችው አባታችን ታማኝ ናት ብለን እናስብ ነበር::

የአባታችንን ቦታ ስለሚወስድ ሌላ ሰው ስትነግረን በጥላቻ የተሞላ ድምፅዋን ላለመስማት በመሞhር አይኖቼን ጨፍኜ ነበር: አሁን የሌላ ሰው ሚስት ናት ሙሉ በሙሉ የተለየ ሰው ሚስት ሆናለች: አሁን አልጋዋ ውስጥ
ይገባል፣ ከእሷ ጋር ይተኛል: እንግዲህ ከዚህ በኋላ ከምናገኛት ያነሰ ጊዜ
ነው የምትመጣው ማለት ነው: አምላኬ፣ እዚህ የምንቆየው ለምን ያህል ጊዜ ይሆን? ለምን ያህል?

ዜናዋና ድምፅዋ በደረቴ አጥንቶች ውስጥ የተያዘችና ልውጣ ልውጣ የምትል ትንሽ የፍርሀት ወፍ ፈጠረ።

“እባካችሁ…” ለመነችን፡ ፈገግታዋና ሳቋ ሀሴትና ደስታዋ እኛ ዜናውን
ባስተናገድንበት ቀፋፊና የተበላሽ አየር ላይ ለመቆየት እየታገሉ ነው::
“ለመረዳት ሞክሩና ለእኔ ደስ ይበላችሁ አባታችሁን እወደው እንደነበር
ታውቃላችሁ ግን እሱ ሞቷል። ከሞተ ረጅም ጊዜው ነው እና የምወደውና
የሚወደኝ ሰው ያስፈልገኛል።”

ክሪስ እንደሚወዳት፣ ሁላችንም እንደምንወዳት ለመናገር አፉን ከፈተ። ነገር
ግን ይህ ከልጆቿ የምታገኘው ፍቅር፣ እሷ የምታወራው አይነት ፍቅር
እንዳልሆነ ስለገባው ከንፈሮቹን ገጠመ እኔ ከአሁን በኋላ አልወዳትም።
ከዚህ በኋላ ትንሽ የመውደድ ስሜትም ለእሷ እንደሚኖረኝ እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም: ግን መንትዮቹ በሁኔታዬ እንዳይደነግጡ መሳቅና ማስመሰል እንዲሁም ከአንገት በላይ መሆን እችላለሁ፡ “አዎ እማዬ፣ ለአንቺ ደስ ብሎኛል እንደገና የሚወድሽ ሰው ማግኘትሽ ጥሩ ነው።”

“ለረጅም ጊዜ ይወደኝ ነበር ካቲ፣” ተበረታታችና እንደገና በራስ በመተማመን
ፈገግ እያለች ቀጠለች “ወንደላጤ ሆኖ ለመቆየት ወስኖ ስለነበር ሚስት
እንደሚያስፈልገው ለማሳመን ቀላል አልነበረም: አያታችሁ ደግሞ በፊት
አባታችሁን በማግባት ለሰራሁት ኃጢአት ቅጣት እንዲሆን ሁለተኛ ጊዜ
እንዳገባ አልፈለገም ነበር። ግን ባርትን ይወደዋል፤ ብዙ ስለምነው ቆይቼ
በመጨረሻ እሺ አለኝ ባርትን ማግባትና ሀብቱንም መውረስ እንድችል
ፈቀደ” ንግግሯን ቆም አደረገችና የታችኛውን ከንፈሯን መብላት ጀመረች።
እንደገና ደግሞ በጭንቀት ተዋጠች ቀለበት ያጠለቀችበት ጣቷ ወደ ጉሮሮዋ ሄደና አንገቷ ላይ ያንጠለጠለችውን ጌጥ በጭንቀት ያፍተለትል ጀመር።“በእርግጥ አባታችሁን የምወደውን ያህል ባርትን አልወደውም” አለች።
የበራው ፊቷ አሁን ያላት ፍቅር በፊት ከምታውቀው እጅግ የበለጠ እንደሆነ
እያጋለጣት ነበር በረጅም ተነፈስኩ: ምስኪን አባቴ!

“ያመጣሽልን ስጦታዎች... ሁሉም ከአውሮፓ፣ ወይም ከእንግሊዝ ደሴቶች
አይደሉም: የስኳር ከረሜላው የመጣው ከቬርሞንት ነው: ቬርሞንትም ሄደሽ ነበር? እሱም ከዚያ ነው የመጣው?”

ልክ ቬርሞንት ብዙ ነገር የሰጣት ይመስል በደስታ ሳቀች። “አይ፣ እሱ የመጣው ከቬርሞንት አይደለም ካቲ፤ ግን እዚያ የምትኖር እህት አለችው ከአውሮፓ ከመጣን በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ ልንጠይቃት ሄደን ነበር የስኳር ከረሜላ
ምን ያህል እንደምትወጂ ስለማውቅ ከዛ ነው ያመጣሁልሽ። ደቡብ የሚኖሩ ሌሎች ሁለት እህቶችም አሉት: ደቡብ ካሮላይና ውስጥ ካለች ግሪንግሌና ግሪንግሌና ወይም እንደዚያ አይነት ስም ካላት ከተማ ነው የመጣው: ግን በኒው ኢንግላንድ ብዙ ቆይቷል: የተመረቀው ከሀርቫርድ የህግ ትምህርት
👍393😁2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

....ክንዱን ለመንካት እጄን ዘረጋሁ። “ክሪስ” እምባ እያነቀኝ በሹክሹክታ ጠራሁት
“ወንድ መሆንህ እንዲሰማህ ምን እንደሚያስፈልግህ የማውቅ ይመስለኛል።"
አልኩት።

“ኧረ? ምን ማድረግ ትችያለሽ?”

አሁን ወደ እኔ እየተመለከተ አይደለም:: በዚያ ፋንታ ኮርኒስ ላይ እያፈጠጠ ነው ለእሱ ታመምኩ ምን እንዳስከፋው አውቄያለሁ። ሀብቱን ወረስንም አልወረስንም ህልሙን የተወው እኔን መምሰል እንዲችል ብሎ ነው: እኔን
መምሰል ደግሞ ጎምዛዛ፣ መራራ፣ ሁሉን የሚጠላና የተደበቀ ምክንያታቸውን
የሚጠራጠር መሆን ማለት ነው።

ቀስ እያልኩ ፀጉሩን ነካካሁትና “የሚያስፈልግህ አንድ ነገር ነው ፀጉር
መቆረጥ። ፀጉርህ በጣም ረጅምና የሚያምር ነው፡ ወንድነት እንዲሰማህ አጭር ፀጉር ሊኖርህ ይገባል። አሁን ግን ፀጉርህ የኔን ፀጉር ነው የሚመስለው”

እና ማነው የአንቺ ፀጉር ያምራል ያለው? ምናልባት በአንድ ወቅት ከሬንጁ
በፊት የሚያምር ፀጉር ነበረሽ” አለኝ፡

“የእውነት?” ብዙ ጊዜ አይኖቹ ፀጉሬ ከማማር በላይ እንደሆነ ነግረውኛል።
hፊት ለፊቴ ያለውን ፀጉሬን ሊቆርጥ መቀስ ሲያነሳ እየተመለከተኝ የነበረበትን
መንገድ ነግሮኛል። በጣም ሲያመነታ ላየው ህመም የማይሰማውን ፀጉር
ሳይሆን ጣቶች የሚቆርጥ ነበር የሚመስለው ከዚያ አንድ ቀን ጣሪያው
ስር ያለው ክፍል ውስጥ ፀሀይ ላይ ተቀምጦ የተቆረጠውን ጸጉሬን በእጆቹ ይዞ ሲያሸተው፣ በጉንጮቹ ሲዳስሰውና ወደ ከንፈሮቹ ሲያስጠጋቸው
አይቼዋለሁ ከዚያ ደግሞ ትራሱ ስር ለማስቀመጥ ካርቶን ውስጥ ሲደብቀው
ተመልክቻለሁ፡

ማየቴን እንዳያውቅ ሳቄን መደበቅ ቀላል አልነበረም: “ኦ ክሪስቶፈር… በጣም ውድ ሰማያዊ አይኖች አሉህ፤ ከዚህ ቦታ ነፃ ስንሆንና ወደ አለም
ስንመለስ አንተን ለሚያፈቅሩ ሴቶች ሁሉ በጣም አዝንላቸዋለሁ። በተለይ ደግሞ ከመልከመልካም ባሏ ጋር የፍቅር ግንኙነት የሚፈልጉ
በሽተኞች ያሉት ዶክተር ባል ላላት ሚስትህ አዝናለሁ። እና እኔ ሚስትህ ብሆን ከጋብቻህ ውጪ አንድ የፍቅር ግንኙነት ቢኖርህ እገድልሀለሁ! በጣም ስለማፈቅርህ እቀናለሁ ምናልባት በሰላሳ አምስት አመትህ ከህክምና
እንድትወጣ አደርግሀለሁ” ያልኩትን ሁሉ ችላ ብሎ “አንድ ጊዜም ፀጉርሽ
ያምራል ብዬ ተናግሬ አላውቅም” አለ።

በቀስታ መላጨት የሚያስፈልጋቸው ፀጉሮች ያሉበትን ጉንጩን ዳሰስ
አደረግኩት፡

ከዚያ “ባለህበት ቁጭ በል! ታውቃለህ ለረጅም ጊዜ ፀጉርህን ቆርጬህ
አላውቅም… መቀስ ላምጣ” አልኩት፡ ግን የፀጉራችን ምንም መምሰል
የህይወት ዘይቤያችን ለመለወጥ አስፈላጊ ካልሆነ የክሪስንና የኮሪን ፀጉር
ለመቁረጥ ለምን እቸገራለሁ? ከፊት ያለው ፀጉሬ ብቻ በዚያች ከብረት
የተሰራች የምትመስል ክፉ አሮጊት መሸነፋችንን ለማሳየት ከመቆረጡ
በስተቀር፤ እዚህ ከመጣን እኔና ኬሪ ፀጉራችን ጫፍ ጫፉ እንኳን ተከርክሞ
አያውቅም።

መቀሱን ላመጣ ስሄድ የእኛ ፀጉር በጣም ሲያድግ አንዳቸውም አረንጓዴ
ተክሎቻችን አለማደጋቸው እንግዳ ነገር መሆኑን አሰብኩ።

ክሪስ ወለሉ ላይ ተቀመጠ ከኋላው ተንበረከክኩ ፀጉሩ ከትከሻው በታች
የወረደ ቢሆንም ብዙ እንዲቆረጥ አልፈለገም፡ “ቀስ እያልሽ ቁረጪ" ሲል
አዘዘኝ “በአንዴ ብዙ አታሳጥሪው ድንገት በአንድ ዝናባማ ከሰአት በኋላ
ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ወንድነት ቢሰማኝ አደገኛ ሊሆን ይችላል
ብሎ ቀለደና ፈገግ አለ። ከዚያ ድርድር ያሉ ነጫጭ ጥርሶቹን እያሳየ ሳቀ:
መምሰል የሚገባውን ያህል አሳምረዋለሁ።

ዙሪያውን እየዞርኩ ፀጉሩን ስቆርጥና ስከረክም እንዴት እንደምወደው እያሰብኩ ነበር፡ ያለማቋረጥ ወደኋላ ሄድ እያልኩ ፀጉሩ በትክክል መቆረጡን አረጋግጣለሁ ጭንቅላቱ የተጣመመ እንዲመስል አልፈለግኩም።
ፀጉር አስተካካዮች ሲያደርጉ እንዳየሁት፣ ፀጉሩን በማበጠሪያ ይዤ በጥንቃቄ ቆረጥኩት። ምን መምሰል እንዳለበት እንደምፈልግ አእምሮዬ ውስጥ አሉ
የሆነ የማደንቀውን ሰው

ስጨርስ ትከሻው ላይ የወደቁትን የተቆራረጡ ፀጉሮች አራገፍኩና ወደኋላ
ራቅ ብዬ በማየት ቆንጆ እንዳደረግኩት አረጋገጥኩ።

“ያው!” አልኩ በድል አድራጊነት ከባድ ጥበብ የሚመስለውን ስራ ባልተጠበቀ ጉብዝና በማጠናቀቄ ደስ ብሎኛል። “የተለየህ መልከመልካም ብቻ ሳይሆን በጣም ወንዳወንድ ሆነሀል! ሁልጊዜም ወንዳወንድ ነበርክ። አለማወቅህ
ያሳዝናል” አልኩት።

ብራማ ጀርባ ያለው የስሜ የመጀመሪያ ፊደል የተቀረፀበትን መስተዋት እጁ ላይ አስቀመጥኩለት፡ ይህ መስተዋት እናታችን ለመጨረሻ ልደቴ ከሰጠችኝ
ስጦታዎች አንዱ ነበር። ብሩሽ፣ ማበጠሪያና መስተዋት አያትየው ሶስቱ
ውድና ኩራት የሚያመጡ እቃዎች እንዳሉኝ እንዳታውቅ የሚቀመጡት
ተደብቀው ነው።

ክሪስ በመስተዋቱ ላይ ለረጅም ደቂቃዎች አፈጠጠ ለቅፅበት ደስ ያላለውና ያልወሰነ ሲመስለኝ ልቤ ደነገጠ፡ ከዚያ ቀስ በቀስ ደማቅ ፈገግታ ፊቱን አበራው።

አምላኬ! ልዑል አስመሰልሽኝ! በመጀመሪያ አልወደድኩትም ነበር። አሁን ግን ሳየው የፀጉሬን ሁኔታ ስለቀየርሽው ፊቴን አሳምሮታል። አመሰግናለሁ
ካተሪን ፀጉር መቁረጥ ላይ እንደዚህ አይነት ችሎታ እንዳለሽ አላውቅም ነበር" አለኝ።

አንተ የማታውቃቸው ብዙ ችሎታዎች አሉኝ፡”

"እኔም መጠርጠር ጀምሬያለሁ”

“እና ልዑሉ መልከመልካም፣ ወንዳወንድና ባለወርቃማ ፀጉሩን ወንድሜን በመምሰሉ እድለኛ ነው” ስል ቀለድኩ። የጥበብ ስራዬን አለማድነቅ
አልቻልኩም። ኦ አምላኬ! አንድ ቀን ልብ የሚሰብር ቆንጆ ነው የሚሆነው።

አሁንም መስተዋቱን እንደያዘ ነበር ከዚያ ቀስ ብሎ ወደጎን አስቀመጠውና
ምን ሊያደርግ እንደሆነ ከማወቄ በፊት እንደ ድመት እመር ብሎ ተነሳ ታገለኝ፤ ወደ ወለሉ እያስጎነበሰኝ መቀሱን ያዘ! ከእጄ ላይ መነጨቀኝና ፀጉሬን በእጁ ያዘ አሁን የኔ ቆንጆ እስቲ እኔም እንዳንቺ ማድረግ እችል እንደሆነ እንመልከት:"

በፍርሀት ገፈተርኩት

ስገፈትረው በጀርባው ወደቀ ከዚያ ተነሳ። ማንም የጸጉሬን ጫፉን እንኳን
አይነካም! ምናልባት አሁን በጣም ስስ ሆኖ ይሆናል። ግን ያለኝ ፀጉር ይኸው
ነው! አሁንም ከብዙ ሴቶች ፀጉር በተሻለ የሚያምር ነው እንዳይዘኝ ሮጥኩ።
ከመማሪያው ክፍል ወጥቼ ሻንጣዎቹን እየዘለልኩ በትልልቆቹ ጠረጴዛዎች
ስር እየሾለኩ ሮጥኩ። እሱም እያሯሯጠኝ ነው፡

ምንም ያህል በፍጥነት ብሮጥና በፍጥነት ብሽሎከለክም ላመልጠው
አልቻልኩም፡ በትከሻዬ በኩል ዞር ብዬ ስመለከተው ፊቱን እንኳን መለየት
አልቻልኩም ያ ደግሞ የበለጠ አስፈራኝ፡ ከጀርባዬ የተበተነውን ረጅሙን
8ጉሬን ለመያዝ ጥረት አደረገ። ፀጉሬን ቆርጦ ለመጣል የወሰነ ይመስላል

አሁን ጠልቶኛል ማለት ነው? ፀጉሬን ለማትረፍ አንድ ቀን ሙሉ በትጋት እንዳልለፋ ሁሉ… አሁን ደስ ስላለው ብቻ ሊቆርጠው ነው?

ተመልሼ ወደ መማሪያው ክፍል ሮጥኩ። ከዚያ ውስጥ ገብቼ በሩን እቆልፍና ወደ ራሱ ተመልሶ ሲረጋጋና ስህተት መሆኑ ሲገባው ተመልሼ እወጣለሁ::

ምናልባት ያሰብኩት ገብቶት ሳይሆን አይቀርም ረጃጅም ቅልጥሞቹ ላይ ፍጥነት ጨመረና ደርሶብኝ ረጅሙን ፀጉሬን ሲይዘውና ወደፊት ስወድቅ ጮህኩ!

እኔ ብቻ ሳልሆን እሱም ወደቀ ቀጥታ ላዬ ላይ! ጎኔ ላይ ድንገተኛ ህመም
ሲሰማኝ እንደገና በፍርሀት ሳይሆን በድንጋጤ ጮህኩ።

እላዬ ላይ ነው። በእጆቼ መሬቱን ተደግፎ ፊቴን አተኩሮ ይመለከታል። ፊቱ
ነጭ ሆኖ የፈራ ይመስላል። “ተጎዳሽ? ወይኔ አምላኬ! ካቲ ደህና ነሽ?” አለኝ።
👍401
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

...“ተነሽ ልጆቹ ቲቪ ላይ ብዙ ከማፍጠጣቸው የተነሳ አይናቸው ሳይጠፋ
ወደታች እንሂድ” አለኝ...

ስነሳ ስላመመኝ አገዘኝ በክንዶቹ ውስጥ አስጠግቶ ስለያዘኝ ጉንጬ ደረቱ
ላይ ነበር ከእሱ በፍጥነት ቢያላቅቀኝም እኔ ግን ጥብቅ አድርጌ ይዤው
ነበር። “ክሪስ አሁን ያደረግነው ኃጢአት ነው?
እንደገና ጉሮሮውን አፀዳና

“ነው ብለሽ ካሰብሽ ነው:"

ምን አይነት መልስ ነው? የኃጢአት ሀሳብ ካልገባባቸው እነዚያ ወለሉ ላይ ተኝተን በምትሀታዊ ጣቶቹና ከንፈሮቹ ሲነካካኝ የነበረባቸው ጊዜያት እዚህ
አስጠሊታ ቤት ልንኖር ከመጣንበት ጊዜ ጀምሮ አጋጥመውኝ የማያውቁ
ጣፋጭ ጊዜያት ናቸው ምን እንደሚያስብ ለማየት ቀና ብዬ ሳየው አይኖቹ ውስጥ እንግዳ የሆነ አስተያየት ተመለከትኩ፡ እርስ በእርሱ በሚጋጭ አይነት
ደስተኛ፣ ያዘነ፣ ያረጀ፣ ወጣት የሆነ፣ ብልህ፣ ሞኝ ... ይመስል ነበር። ወይም አሁን እንደ ትልቅ ወንድ እየተሰማው ይሆን? እንደዚያ ከሆነ ኃጢአት
ይሁንም አይሁንም ደስ ብሎኛል።

እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ መንትዮቹ ለመሄድ ደረጃውን መውረድ ጀመርን።ኮሪ የሙዚቃ መሳሪያ እየተጫወተና ኬሪ ደግሞ እየዘፈነች ነው:

ከኮሪ አጠገብ ወለሉ ላይ ተቀመጥኩና ጊታሩን ተቀብዬ ለመጫወት ሞከርኩ።

ሁላችንንም አስተምሮናል በጣም የሚወደውን ዘፈን ዘፈንኩለት፡ ስጨርስ
“የኔን ዘፈን አልወደድሽውም ካቲ?” አለኝ።

“በጣም ወድጄዋለሁ ኮሪ ግን በጣም ያሳዝናል።
ለምን ደስ የሚሉ ግጥሞች
አንጨምርበትም?” አልኩት።

“ታውቂያለሽ ካቲ… እናታችን ስለመጫወቻዬ ምንም አላለችም" አለኝ፡

“አላየችውም እኮ ኮሪ።''

“ለምን አላየችውም?”

እንወዳት የነበረች እንግዳ ሴት ከመሆኗ በስተቀር ከአሁን በኋላ እናታችን
ማንና ምን እንደሆነች ባለማወቄ በከባዱ ተነፈስኩ፡ አንዳንዴ የምንወዳቸውን ሰዎች ከእኛ ነጥሎ የሚወስዳቸው ሞት ብቻ አይደለም: አሁን ይህንን አውቄያለሁ።

“እናታችን አዲስ ባል አግኝታለች:” አለ ክሪስ “እና ሰው ፍቅር ሲይዘው ደግሞ ከራሱ ደስታ በስተቀር የሌሎችን ደስታ አያይም"

ኬሪ ሹራቤን አተኩራ እየተመለከተች፣ ካቲ፣ ሹራብሽ ላይ ያለው ምንድነው?” አለችኝ። “ቀለም” አልኩ ያለምንም ማመንታት። “ክሪስ ስዕል
መሳል ሊያስተምረኝ እየሞከረ ነበር። ከዚያ የኔ ስዕል ከእሱ ስዕል ይበልጥ
እንደሚያምር ሲመለከት ቀይ ቀለም የነበረበትን ዕቃ አንስቶ ወደ እኔ ወረወረው"

ትልቁ ወንድሜ አተኩሮ እያየኝ ነበር። “ክሪስ፣ ካቲ ከአንተ የተሻለ መሳል
ትችላለች?”

“እችላለሁ ካለች መቻል አለባት”

“ስዕሉ የታለ?”

“ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ።”

“ማየት እፈልጋለሁ”
“እኔ ደክሞኛል አንቺ ሂጂና አምጪው ካቲ ራት እስክታዘጋጅ ቲቪ ማየት
እፈልጋለሁ፡" ብሎ አየት አደረገኝ፡፡ “ውድ እህቴ ጨዋ ለመሆን ብለሽ
ተቀምጠን ራት ከመብላታችን በፊት ንፁህ ሹራብ ብትለብሽ ቅር ይልሻል? ስለዛ ቀይ ቀለም ጥፋተኝነት እንዲሰማኝ የሚያደርግ የሆነ ነገር አለ:”

“ደም ይመስላል” አለ ኮሪ። “አጥበሽ ካላስለቀቅሽው እንደ ደም ይሆንብሻል።"
በዚያ ምሽት የማይመች ስሜት ተሰምቶኝ እረፍት የለሽ ሆንኩ ሀሳቤ ክሪስ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ይመለከተኝ ወደነበረበት ሁኔታ
ይመላለሳል።

ለረጅም ጊዜ ስፈልገው የነበረው ሚስጠር ምን እንደሆነ አወቅኩ ያ የሚስጥር ቁልፍ ፍቅርን አካላዊና ወሲባዊ ፍላጎትን የሚገልጥ ነበር። እርቃን
ሰውነቶችን ማየት አይደለም ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ኮሪን ሳጥብ ነበርና።
ክሪስም እርቃኑን ሆኖ አይቼው አውቃለሁ: ነገር ግን እሱና ኮሪ ያላቸው
ነገር እኔና ኬሪ ካለን ነገር የተለየ መሆኑ ምንም አይነት የወሲብ መነሳሳት
ፈጥሮብኝ አያውቅም: እርቃን መሆን አይደለም

አይኖቹ ናቸው: የፍቅር ሚስጥር አይን ውስጥ ነው። አንድ ሰው ሌላኛውን
የሚመለከትበት መንገድ፣ ከንፈሮች ሳይነቃነቁ አይኖች የሚገናኙበትና
የሚያወሩበት መንገድ ነው: የክሪስ አይኖች ከአስር ሺህ ቃላት በላይ ተናግረዋል።

እኔን የነካበት መንገድም አይደለም… ቀስ እያለ በደግነት ማድረጉም አይደለም ሲነካኝ ወደኔ የሚመለከትበት መንገድ ነው እና ለዚያ ነው ማለት ነው አያትየው ሌላኛውን ፆታ መመልከት እንደማይገባ ህግ ያወጣችው:: ያቺ
ጠንቋይ አሮጊት የፍቅርን ሚስጥር ታውቃለች ብሎ ማሰብ ከባድ ነው መቼም ተፈቅራ ልታውቅ አትችልም አይሆንም እሷ ባለ ብረት ልብ፣ ባለ ብረት አጥንት ናት... አይኖቿም ለስላሳ ሆነው አያውቁም:

ከዚያ ርዕሱን በጥልቀት ስመረምር ከአይኖች በላይ ነው: ከአይኖች ኋላ
አእምሮ ውስጥ ነው፧ ሊያስደስትህ የሚፈልግ፣ ደስ የሚያሰኝህ፣ ሀሴት
የሚሰጥህና እንዲረዱህ በምትፈልግበት መንገድ የሚረዳህ፣ ማንም ሳይረዳህ ሲቀር ደግሞ ብቸኝነትህን የሚወስድልህ ነው። ኃጢአት በፍቅር ጉዳይ ምንም አያገባውም

ፊቴን ስመልስ ክሪስም እንደነቃ ተመለከትኩ። በጎኑ ተኝቶ ወደ እኔ
እየተመለከተ ነው። በጣም ደስ የሚል ፈገግታ ነው ያለው።እናታችን በዚያን ቀን ልታየን አልመጣችም: ከዚያ ቀን በፊትም ብቅ አላለችም
እኛ ግን የኮሪን የሙዚቃ መሳሪያ በመጫወትና በመዝፈን ራሳችንን የማስደሰቻ መንገድ አግኝተናል: እናታችን በጣም ግድ የለሽ እየሆነች የመጣች ቢሆንም
በዚያ ምሽት ሁላችንም የተኛነው በተስፋ ተሞልተን ነው፡ ለረጅም ሰዓት የደስታ ዘፈኖች መዝፈናችን፣ ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ የወረሰው ጫካ ውስጥ የነበረን ጉዞ እያለቀ መሆኑንና ፀሀይ፣ ፍቅር፣ ሐሴትና ደስታ መታጠፊያው ላይ እየጠበቁን መሆናቸውን እንድናምን አድርጎናል።

በብሩህ ህልሜ ውስጥ የሆነ ጨለማና የሚያስፈራ ነገር ይመጣብኛል።
በየቀኑ ቅርፁ የጭራቅ አይነት ይሆንብኛል። አይኖቼን ስጨፍን አያትየው ሳትታይ መኝታ ክፍላችን ገብታ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አስባ ፀጉሬን በሙሉ ስትላጨኝ አያለሁ። እጮሀለሁ አትሰማኝም ማንም አይሰማኝም፡ ከዚያ ትልቅ የሚያንፀባርቅ ቢላዋ ታወጣና ሁለቱንም ጡቶቼን ቆርጣ ክሪስ አፍ ውስጥ ትጨምረዋለች: እና ሌላም ሌላም… ከዚያ እወራጫለሁ። ክሪስን የሚያነቃ የጩኸት ድምፅ አሰማለሁ። መንትዮቹ ልክ ሞቶ እንደተቀበሩ ልጆች ተኝተዋል። ክሪስ እንቅልፉ ሳይለቀው አልጋው ላይ ቁጭ ብሎ እጄን
ለመያዝ እየፈለገ “ሌላ ቅዠት ነው?” ሲል ጠየቀኝ።

አይይ! ... ተራ ቅዠት አይደለም ቀድሞ ማወቅና በተፈጥሮ መረዳት መቻል ነው:: የሆነ መጥፎ ነገር እንደሚፈጠር በአጥን መቅኒ ሳይቀር ተሰምቶኛል።
ድክም ብዬና እየተንቀጠቀጥኩ አያትየው ያደረገችኝን ለክሪስ ነገርኩት። “ያ ብቻ አይደለም መጥታ ልቤን ቆርጣ ያወጣችው እናታችን ነበረች: ሁሉ ነገሯ
በአልማዝ ያብረቀርቅ ነበር” አልኩት

ካቲ ህልም እኮ ምንም ትርጉም የለውም::”

“አለው!”

ሌሎች ህልሞችና ሌሎች ቅዠቶች ለወንድሜ እነግረዋለሁ። ያዳምጠኝና ይስቃል ከዚያ ሌሊቱን ልክ ፊልም ቤት እንዳሉ አይነት ሆኖ ማሳለፍ አሪፍ እንደሆነ ያለውን እምነት ይገልፅልኛል። ግን በፍፁም እንደዛ አልነበረም::ፊልም የሆነ ሰው የፃፈው መሆኑን እያወቅህ ቁጭ ብለህ ትልቁን ስክሪን
ትመለከታለህ እኔ ግን በህልሜ ውስጥ ተሳታፊ ነኝ፡ ህልም ውስጥ
እየተሰማኝ… እየተጎዳሁ እየተሰቃየሁና ይህንን ስል እያዘንኩ ነው አልፎ አልፎም በጣም እየተደሰትኩ ነው።

ክሪስ፣ እሱ ከእኔና ከእንግዳ መንገዶቼ ውስጥ የሌለ ሆኖ ሳለ ይህ ህልም ከሌሎች ይልቅ እሱን ይጎዳው ይመስል ለምን ፀጥ ብሎ እንደ ሀውልት ተቀመጠ? እሱም ህልም አይቶ ይሆን?
👍44👏21
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


....ክሪስ ከመልበሻ ጠረጴዛው ፊት ያለ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡ አገጩን በእጁ "ደግፎ ለደቂቃዎች እያሰበ ቆየ: “በአንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። አንቺም ሆንሽ መንትዮቹ ስትቀጡ ማየት አልፈልግም ስለዚህ ወጥቼ የምሰርቀው እኔ
ነኝ። ድንገት ከተያዝኩ ጥፋተኛው እኔ ብቻ እሆናለሁ: ግን አልያዝም።
ከዚያች አሮጊት መስረቅ አደገኛ ነው በጣም ተጠራጣሪ ናት፡ ቦርሳ ውስጥ ያለውን ገንዘብ መጠን ሳንቲሙን ሳይቀር እንደምታውቅ ጥርጥር የለውም እናታችን ግን ገንዘቧን ቆጥራ አታውቅም: አባታችን እንዴት ይወቅሳት
እንደነበረ ታስታውሳለህ?” በማረጋገጥ ፈገግ አለልኝ፡ “ልክ እንደ ሮቢን ሁድ.
ከሀብታሞች እየሰረቅኩ ለተቸገሩ ለእኛ የምስጥ እሆናለሁ! እናታችንና ባሏ
ወጣ እንደሚሉ የምትነግረን ምሽት ላይ ብቻ እሰርቃለሁ”

“በማትመጣባቸው ቀናት በመስኮት ማየት እንችላለን ደፋር ከሆንን የሚመጡትንና የሚሄዱትን የሚያሳይ መታጠፊያ አለ”

ትንሽ ቆይቶ እናታችን ግብዣ እንደምትሄድ ነገረችኝ። “ባርት ስለማህበራዊ
ህይወት ብዙም ግድ የለውምº ቤት ቢቆይ ይሻለዋል: እኔ ግን ይህንን ቤት ጠልቼዋለሁ ከዚያ ለምን ወደራሳችን ቤት አንገባም ብሎ ጠየቀኝ። ምን ማለት እችላለሁ?”

ምን ማለት ትችላለች? ውዴ አንድ የምነግርህ ሚስጥር አለ። ፎቁ ላይ ራቅ
ያለው የሰሜኑ ክፍል ውስጥ የደበቅኳቸው አራት ልጆች አሉኝ።

ለክሪስ ከእናቱ ግዙፍና ያማረ መኝታ ክፍል ውስጥ ገንዘብ መስረቅ ቀላል ነበር::ስለ ገንዘብ ግድ የለሽ ናት፡ እንዲያውም ብዙ ገንዘብ በግዴለሽነት የመልበሻ ጠረጴዛዋ ላይ መበታተኗ አስደንግጦታል በጭንቅላቱ ጥርጣሬ እንዲያኖር አድርጎታል። አሁን ባልም ቢኖራት እንኳ ከዚህ እስር ቤት ለምታስወጣን ቀን ማጠራቀም አልነበረባትም? ክሪስ የባሏ ኪሶች ውስጥ ጥቂት ዝርዝር ሳንቲሞችን ብቻ አገኘ፡፡ እሱ ገንዘብ ላይ የሷን ያህል ግድ የለሽ አይደለም ነገር ግን ክሪስ የወንበሮቹ ትራስ ስር በጣም ብዙ ሳንቲሞች አግኝቷል በእናቱ ክፍል ውስጥ የማይፈለግ ሰርጎ ገብ ሌባ እንደሆነ ተሰማው

በዚያ ክረምት ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደዚያ ክፍል ሲመላለስ፣ መስረቅ በጣም
ቀላል ስለሆነለት ግድ የለሽ እየሆነ መጣ፡ አንዳንዴ ተደስቶ አንዳንዴ አዝኖ
ወደ እኔ ይመለሳል፡ ከቀን ወደቀን የተደበቀው ገንዘባችን እያደገ መጥቷል።ታዲያ ለምንድነው የሚያዝነው? “በሚቀጥለው ቀን አብረሽኝ ትመጫለሽ ራስሽ ታይዋለሽ” ነበር መልሱ።

መንትዮቹ ነቅተው መሄዳችንን እንዳያውቁ አረጋግጬ በንፁህ ህሊና መሄድ እችላለሁ: ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። ጠዋት ለመንቃት እንኳን
አይናቸው እየተጨናበሰ ቀስ ብለው ነው የሚነቁት። አንዳንድ ጊዜ ተኝተው
ሳያቸው ያስፈራኛል። ሁለት ትንንሽ አሻንጉሊቶች፣ የማያድጉ፣ የሚያንቀላፉ
ሳይሆን ትንሽ ሞት ውስጥ የሰመጡ ይመስሉ ነበር።

ሂዱ! አምልጡ! ፀደይ እየመጣ ነው፡ ከመዘግየቱ በፊት ቶሎ መልቀቅ
አለብን በውስጤ ያለ ድምፅ ደመነፍሴ ያለማቋረጥ በውስጤ ይደውላል።ክሪስ ስነግረው ሳቀብኝ፡ “ካቲ አንቺና የአንቺ ደመነፍስን መስማት ብቻ
ሳይሆን ገንዘብ እንደሚያስፈልገንም መረዳት ያስፈልጋል ቢያንስ አምስት መቶ ያስፈልገናል። ለምንድነው የምንቸኩለው? አሁን ምግብ አለን
አልተገረፍንም፣ በግማሽ እርቃናችንን ሆነን ስትይዘን እንኳን ምንም ቃል አልተናገረችም ለምንድነው አሁን አያትየው የማትቀጣን? ስለ ሌሎቹ
ቅጣቶቿ፣ እኛ ላይ ስለሰራችው ኃጢአት ለእናታችን አልተናገርንም ለእኔ እኛ ላይ ያደረገችው ነገር በምንም መንገድ ማስተባበል የማይቻል ኃጢአት የተሞላ ነው ሆኖም ያቺ አሮጊት ሴት እጇ አልተለየንም በየቀኑ በሳንድዊች የተሞላ የሽርሽር ቅርጫት ለብ ካለ ሾርባና ወተት እንዲሁም ከአራት ስኳር ከተነሰነሰባቸው ዶናቶች ጋር ታመጣልናለች።

“ፍጠኚ!” አስቸኮለኝ። ክሪስ ጨለማና ባዶ በሆነው ኮሪደር ላይ እየጎተተኝ
ነው። “አንድ ቦታ ላይ መቆም አደገኛ ነው የሽልማቱን ክፍል በፍጥነት
አየት አድርገን ከዚያ ወደ እናታችን መኝታ ክፍል በፍጥነት እንሄዳለን”
የፈለግኩት የሽልማቱን ክፍል ለአፍታ አየት ማድረግ ነው። በድንጋይ የተሰራው እሳት ማንደጃ ላይ ተቀምጦ ያየሁት በጣም አባታችንን የሚመስል በዘይት ቀለም የተሰራውን ምስል ጠላሁት እንደ ማልኮም ፎክስወርዝ ያለ ጨካኝና ልበ ደንዳና ሰው ወጣት ሆኖም እንኳን መልከመልካም የመሆን
ምንም መብት የለውም: እነዚያ ቀዝቃዛ ሰማያዊ አይኖቹ የቀረውን እሱነቱን
በቁስል መምታት ይገባቸዋል። ወለሉ ላይ ያለውን የድብና የነብር ቆዳ
እንዲሁም የሞቱ እንስሳት ጭንቅላቶች አየሁ እንደዚህ አይነት ክፍል መፈለጉ በራሱ ማንነቱን የሚያሳይ ነው።

ክሪስ ቢፈቅድልኝ ኖሮ ሁሉንም ክፍሎች እመለከት ነበር፡ ነገር ግን የተዘጉትን
በሮች ዝም ብለን እንድናልፍና ጥቂቶቹን ብቻ አየት እንዳደርግ ፈቀደልኝ
ሰርሳሪ አለኝ በሹክሹክታ: በአንደኛቸውም ውስጥ የሚያስደስት ነገር
የለም:" ትክክል ነበር፡ በዚያ ምሽት ክሪስ ያለው ነገር በብዙ መልኩ ትክክል
እንደሆነ አወቅኩ ክሪስ፣ ይሄ ቤት ግዙፍና ቆንጆ እንጂ የሚያምርና የሚመች
አይደለም ብሎኝ ነበር፡ የሆነ ሆኖ፣መገረሜን መግታት አልቻልኩም።በንፅፅር ግላድስተን የነበረው ቤታችን ተራ ቤት ይሆናል፡

ብዙ ረጅምና በሚያስጠላ አይነት ደብዛዛ የሆኑ አዳራሾች አልፈን በመጨረሻ የእናታችን ግዙፍ ክፍል ደረስን፡ ክሪስ ስለ አልጋውና ስለ ሁሉም በዝርዝር ነግሮኛል፡፡ ግን መስማት ማየት አይደለም:: ትንፋሼ ተሰበሰበ ህልሞቼ ክንፍ አወጡ፣ ኦ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን! ይህ ክፍል ሳይሆን የንግስት ወይም የልዕልት መኖሪያን የሚመጥን ነው። ሁሉም ነገር የሚያስደምም ነበር፡
ከዚያ እናታችን አባታችን ካልሆነ ከሌላ ሰው ጋር የምትተኛበትን አልጋ
በመጥላት አፈገፈግኩ፡ ወደ ግዙፉ የልብስ ማስቀመጫ ሳጥኗ ተጠግቼ በህልም ካልሆነ በስተቀር የእኔ ሊሆን ከማይችለው የህልም ሀብት ውስጥ
ገባሁ: ሱቆች ውስጥ ከሚገኙት በላይ ልብሶች አሏት: ያሏትን ልብሶች
ጫማዎችና ጌጣጌጦች ሁሉ አንዳንድ ጊዜ ለመልበስ እንኳን ሺህ አመት መኖር አለባት

አይኖቼን የያዘው ሌላ ነገር ደግሞ ክሪስ ያሳየኝ ወርቃማ የመልበሻ ክፍል
ነው: ዙሪያውን መስታወት ያለበት፣ አረንጓዴ ተክሎችና እውነተኛ አበቦች
ያደጉበት መታጠቢያ ክፍሏን ተመለከትኩ፡ “ሁሉም አዲስ ነው” ክሪስ
አብራራልኝ: በመጀመሪያ የገና ግብዣው ቀን ስመጣ እንደዚህ በጣም.
የሚያምር አልነበረም”

ከበፊት ጀምሮ እንደዚህ እንደነበር ግን ስላልነገረኝ ዞር ብዬ ተመለከትኩት
ስለነዚህ ሁሉ ልብሶች፣ በሚስጥር ሳጥኗ ውስጥ ስለቆለፈቻቸው ጌጣጌጦች
እንዳውቅ ስላልፈለገ ሆነ ብሎ እየሸፈነላት ነበር። አልዋሸኝም። ግን ደግሞ
አልነገረኝምም ነበር። የእኔን ጥያቄዎች ላለመመለስ አይኖቼን የሚሽሹት
አይኖቹንና በእፍረት የቀላ ፊቱን እያየሁ ነው። እኛ ክፍል ውስጥ መተኛት
አለመፈለጓ የሚያስገርም አይደለም የመልበሻ ክፍሏ ውስጥ ሆኜ የእናታችንን ልብሶች እየሞከርኩ ነው፡
በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የናይለን ስቶኪንግ ለበስኩ አቤት… እንዴት
እንደሚያምሩ! ሴቶች እንደዚህ አይነት የእግር ሹራቦች ቢወዱ አያስገርምም! ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የጡት መያዣ ለበስኩ በጣም ትልቅ ነበር። ልክ
የሆኑኝ እንዲመስል ውስጣቸው የመፀዳጃ ወረቀቶች ጠቀጠቅኩ። ቀጥሎ ደግሞ ጫማ ሞከርኩ፡ እሱም ትልቅ ነበር።
👍55
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የእንጀራ አባቴ

በዚያ ፀደይ ክሪስ ታመመ አፉ አካባቢ አረንጓዴ መሰለና በየደቂቃው
ያስመልሰው ጀመር። ከመታጠቢያ ቤት ወጥቶ እየተንገዳገደ አልጋ ላይ ወደቀ። የስነ አካል ጥናት ለማንበብ እየሞከረ ግን በራሱ ተናዶ ወደጎን አሽቀነጠረው። “የሆነ የበላሁት ነገር መሆን አለበት" ሲል ተነጫነጨ።

ክሪስ ብቻህን ልተውህ አልፈልግም” አልኩ ከእንጨት የተሰራውን ቁልፍ
ወደ ቁልፍ ቀዳዳው ለማስገባት እያዘጋጀሁ።

“ተመልከቺ ካቲ!” ሲል ጮኸ “በራስሽ ሁለት እግሮች መቆም የምትማሪበት ጊዜ ነው: በእያንዳንዱ ደቂቃ አጠገብሽ እንድሆን አትፈልጊ! የእናታችን ችግር
ያ ነበር። ሁልጊዜ የምትደገፍበት ሰው አጠገቧ እንዲኖር ታስባለች: በራስሽ ላይ ተደገፊ እሺ ካቲ… ሁልጊዜም!”

ፍርሀት ዘሎ ልቤ ውስጥ ገባና በአይኖቼ ፈሰሰ። አየኝና በእርጋታ “እኔ ደህና
ነኝ። እውነቴን ነው ራሴን መንከባከብ እችላለሁ: ካቲ ገንዘቡ ያስፈልገናል።
ሌላ ዕድል ላይኖረን ስለሚችል ብቻሽንም ቢሆን ሂጂ።

ወደ እሱ አልጋ ሮጩ ተመለስኩና በጉልበቴ ተንበርክኬ ፊቴን ደረቱ ላይ
አደረግኩ። በደግነት ፀጉሬን ዳሰሰኝ፡ “እውነት ካቲ፣ ደህና እሆናለሁ፤ ልታለቅሺበት የሚገባ አይደለም: ግን ሊገባሽ የሚገባው ነገር አንዳችን ላይ ምንም ነገር ቢፈጠር የቀረነው መንትዮቹን ከዚህ ማውጣት አለበት።”

“እንደዚህ አይነት ነገሮች አትናገር!” ጮህኩበት። እንደሚሞት ማሰቡ ውስጤን አሳመመኝ።
"ካቲ… አሁን እንድትሄጂ እፈልጋለሁ: ተነሺ ራስሽን አስገድጂ! እዚያ
ስትደርሺ ደግሞ ባለአንዳንድና ባለ አምስት ኖቶች ብቻ ውሰጂ እንጂ ትልልቆቹን እንዳትነኪ የእንጀራ አባታችን ኪሱ ውስጥ የሚጥላቸውን ሳንቲሞች ግን ሁሉንም ውሰጂ ከልብስ ማስቀመጫው ሳጥን ጀርባ ሳንቲሞች የሞሉበት
አንድ ቆርቆሮ ያስቀምጣሉ፡ ከእነሱ ዝገኚ”።

የገረጣና የደከመው ይመስላል። በዚያ ላይ ከስቷል: ደህና ሳይሆን ትቼው መውጣት እያስጠላኝ በፍጥነት ጉንጩን ሳም አደረግኩት። ወደተኙት መንትዮች አየት አድርጌ ከእንጨት የተሰራውን ቁልፍ ይዤ ወደ በሩ ተጣደፍኩ። “እወድሀለሁ ክሪስቶፈር” አልኩት በሩን ከመክፈቴ በፊት።

“እኔም እወድሻለሁ ካተሪን መልካም አደን” አለኝ፡
በአየር ላይ ሳምኩትና ወጥቼ በሩን ዘጋሁና ቆለፍኩት። እናቴ ክፍል ገብቶ መስረቅ አደጋ የለውም። እናታችን እሷና ባሏ ከመንገዱ በታች ያለ ጓደኛቸው ግብዣ ላይ መገኘት እንዳለባቸው የነገረችን ዛሬ ከሰአት በኋላ ነበር:

ኮሪደሩን አቋርጬ ስሄድ ለራሴ እያሰብኩ የነበረው ቢያንስ አንድ ባለ ሀያና
አንድ ባለ አስር ኖቶች መስረቅ እንዳለብኝ ነበር: የሆነ ሰው እንዳያስተውል
አደርጋለሁ። ምናልባትም ከእናታችን ጌጣጌጦች የተወሰኑ እሰርቃለሁ፡
ጌጣጌጦች አቅም ሊኖራቸው ይችላል ልክ እንደ ገንዘብ፤ ምናልባትም በተሻለ።

ሁሉም ስራ ነው፤ ሁሉም ቆራጥነት። የሽልማት ክፍሉን ለማየት ጊዜ ማባከን አልፈለግኩም ቀጥታ ወደ እናታችን መኝታ ክፍል አመራሁ። አሁን አራት
ሰዓት ነው፡ በጊዜ በሶስት ሰዓት የምትተኛውን አያትየውን እንደማላያት
አውቄያለሁ በጀግና የመተማመን ቆራጥነት ወደ ክፍሎቿ በሚያስገቡት በሮች ገባሁና በፀጥታ ዘጋኋቸው:: አንድ ደብዛዛ መብራት ብቻ በርቷል። በአብዛኛው ክፍሎቿ ውስጥ ያሉትን መብራቶች አብርታ ትተዋቸዋለች: አንዳንዴ ደግሞ
አንዱን ብቻ አብርታ እንደምትተወው ክሪስ ነግሮኛል። አሁን ለእናታችን
ገንዘብ ምኗ ነው?

እያመነታሁና እርግጠኛ ባለመሆን በሩ ጋ እንደቆምኩ ዙሪያውን ስመለከት በፍርሀት ደነዘዝኩ የእናታችን አዲስ ባል ወንበሩ ላይ ረጅም እግሮቹን ዘርግቶና ቁርጭምጭሚቱ
ጋር አጣምሮ ተዘርግቷል: ቀጥታ ፊት ለፊቱ ነኝ፡ አጭር የሚያሳይ የሌሊት ልብስና ከስር ደግሞ ከእሱ ጋር የሚመሳሰል ፓንት ለብሻለሁ፡ ማን እንደሆንኩና ሳልጠራ መኝታ ቤት ውስጥ ምን እያደረግኩ እንደሆነ ለማወቅ እስኪያጓራ ልቤ በአበደ አይነት እየመታ እጠብቃለሁ።

ግን አልተናገረም ጥቁር ቶክሲዶ ጠርዙ ላይ ወደታች ከሚወርድ ጥቁር ጌጥ ያለው ሮዝ ሸሚዝ
ጋር ለብሷል። አልጮኸም. አልጠየቀም ምክንያቱም እያንቀላፋ ነበር። ፊቴን አዙሬ ልመለስ ነበር ግን ይነቃና ያየኛል ብዬ ፈራሁ
መቼም መጓጓት ስራዬ ሆኗል በደንብ ልመለከተው ቀረብ አልኩ፡ ልነካው
እስከምችል ወንበሩ ድረስ ለመጠጋት ደፈርኩ እጄን ኪሱ ገብቼ መስረቅ
የምችልበት ቅርበት ላይ ሆንኩ ግን አላደረግኩትም፡

እንቅልፍ የወሰደው መልከመልካም ፊቱን ስመለከት፣ መስረቅ ጭንቅላቴ ውስጥ የመጣው የመጨረሻ ሀሳብ ነበር፡ አሁን የተገለጠውን በጣም የቀረብኩትን የእናቴን ተወዳጅ ባርትን በማየቴ ተደንቄያለሁ፡ የተወሰኑ ጊዜያት በሩቅ አይቼዋለሁ: በመጀመሪያ የገና ግብዣው ምሽት ሌላው ደግሞ ደረጃው አጠገብ እናታችን እጇን እንድታጠልቅ ኮት ይዞላት ማጅራቷና ጆሮዋ
ስር ሲስማትና ፈገግ እንድትል የሚያደርግ የሆነ ነገር በጆሮዋ ሲያንሾካሹክላት
እና ከበር ከመውጣታቸው በፊት ወደ ራሱ ጎትቶ ደረቱ ላይ ሲያስደግፋት
አይቼዋለሁ።

አዎ አዎ አይቼዋለሁ... እና ደግሞ ስለሱ ብዙ ሰምቼያለሁ፡ እህቶቹ የት
እንደሚኖሩ አውቃለሁ፡ የት እንደተወለደ፣ የት እንደተማረ ሁሉ አውቃለሁ።
አሁን እያየሁት ላለሁት ግን ማንም እንድዘጋጅ አላደረገኝም:

እንዴት እናቴ? ማፈር አለብሽ! ይህ ሰው በእድሜ ካንቺ ያንሳል በብዙ
አመታት ያንሳል! ግን አልነገረችንም ሚስጥር ነበር። እንደዚህ አይነት
አስፈላጊ ሚስጥር እንዴት መደበቅ እንደቻለች! ማንኛዋም ሴት የምትፈልገው አይነት ወንድ ነው፡ እና ብትወደውና ብታመልከው ምንም አይገርምም። የተለየ ግርማ ሞገስ ባለው ሁኔታ ተጋድሞ ስመለከተው ፍቅር ሲሰሩ
ኃይለኛና በስሜት የተሞላ እንደሚሆንላት ገመትኩ፡

ወንበር ላይ ተቀምጦ የሚያንቀላፋውን ይህንን ሰው መጥላት ፈለግኩ
ግን አልቻልኩም: እንቅልፍ ወስዶት እንኳን ቆንጆ ነውና ልቤ በፍጥነት እንዲመታ አደረገው። ባርትሎሚዮ ዊንስሎ ሳያውቀው በእንቅልፍ ልቡ ለእኔ የአድናቆት ምላሽ
በመስጠት አይነት ፈገግ አለ፡ እንደ ዶክተሮችና እንደ ክሪስ ሁሉንም ነገር
ከሚያውቁ ሰዎች አንዱ ነው ጠበቃ: እርግጠኛ ነኝ የሆነ በተለየ ሁኔታ ደስ የሚያሰኝ ነገር አይቶና ሞክሮ ያውቃል፡ በተከደኑ አይኖቹ ስር ያለው
ምን ይሆን? አይኖቹ ሰማያዊ ይሆኑ ወይም ቡናማ ማወቅ ፈለግኩ። ሰውነቱ ቀጭን፣ ጠንካራና ጡንቻማ ነው: ከንፈሮቹ አጠገብ ከላይ ወደታች የተሰመረ የሚመስል በእንቅልፍ ልቡ ፈገግ ሲል እየመጣ የሚመለስ ስርጉደት አለው::

ትልቅ የጋብቻ ቀለበት አጥልቋል። አይነቱን እናቴ ጣት ላይ አይቼዋለሁ:
በቀኝ እጁ አመልካች ጣት ላይ ብዙ ብርሀን በሌለበት እንኳን የሚያንፀባርቅ
የአልማዝ ቀለበት አለው ትንሽዋ ጣቱ ላይ ትምህርት ቤት ለሽልማት የሚሰጥ
የወንድማማችነት ቀለበት አድርጓል። ረጃጅም ጣቶቹ በደንብ የተፀዱና ልክ
እንደኔ ጥፍሮች የሚያንፀባርቁ አራት ማዕዘን ጥፍሮች አሏቸው
ረጅም ነው: ይህንን አስቀድሜ አውቃለሁ፡ ከሁሉ ነገር በጣም ደስ ያለኝ ስሜት የሚቀሰቅሱ ከፂሙ በታች ያሉት ማራኪ hንፈሮቹ ናቸው: በእነዚህ
ቅርፃቸው በሚያምር ማራኪ ከንፈሮቹ እናታችንን ሁሉም ቦታ ይስሟታል። ያ የወሲብ ደስታ ያለበት መፅሀፍ ትልልቅ ሰዎች እርቃናቸውን ሲሆኑ ምን ስሜት እንደሚሰጣቸው በሚገባ አስተምሮኛል።

ድንገት ያ ጥቁር ፂሙ ይኮረኩር እንደሆነ ለማየት እሱን የመሳም ግፊት
አደረብኝ:፡ በዚያውም ምንም አይነት የደም ዝምድና የሌለው እንግዳ መሳም ምን ስሜት እንደሚያሳድር ማወቅ ፈልጌያለሁ:
👍473😁2🔥1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

“ደህና እደሪ ካተሪን፡ በጣም ጥሩ እህትና ለመንትዮቹም እናት ነሽ. ግን በጣም ቀሽምና ጥሩ ያልሆንሽ ሌባ ነሽ" አለኝ።.

እያንዳንዱ የክሪስ የእናታችንን ክፍል መጎብኘት የተደበቀውን ገንዘባችንን መጠን አሳደገው ነገር ግን ግባችን የሆነው አምስት መቶ ዶላር ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ይወስዳል አሁን እንደገና በጋ መጣ: አሁን አስራ አምስት አመት ሆኖኛል። መንትዮቹ በቅርቡ ስምንት አመት ይሆናቸዋል። በቅርቡ ነሀሴ ሲመጣ የታሰርንበት ሶስተኛ አመት ይሆናል። ሌላ ክረምት ከመግባቱ በፊት ማምለጥ አለብን፡ ኬሪን ስመለከተው ፍዝዝ ብሎ አደንጓሬዎች ይለቅማል። ምክንያቱም የመልካም ዕድል ጥራጥሬ ስለሆኑ ነበር በአዲሱ አመት መጀመሪያ ትንንሾቹ ቡናማ አይኖች ውስጡን እንዳያዩት ብሎ አይበላቸውም ነበር አሁን ግን እኔና ክሪስ እያንዳንዱ አደንጓሬ የአንድ ቀን ሙሉ ደስታ ይሰጣል ብለን ስለነገርነው ይበላል እኔና ክሪስ እንደዚህ አይነት ተረቶች እየፈጠርን እንዲበሉ እናደርጋለን፡ ወለሉ ላይ ይቀመጥና ጊታሩን አንስቶ
አይኖቹን የካርቱን ፊልም ላይ ይተክላል። ኬሪ በቻለችው መጠን ወደሱ
ተጠግታ ቲቪውን ሳይሆን የሱን ፊት እየተመለከተች ትቀመጣለች።

"ካቲ" አለች በዚያች እንደ ወፍ በመሰለች ድምፅዋ

“ኮሪ ደህና አይደለም፡”

“እንዴት አወቅሽ?”

“በቃ አወቅኩ”

“አመመኝ ብሎ ነግሮሻል?”

“ማለት የለበትም”

“እና ምን ተሰማሽ?”

“እንደ ሁልጊዜው”

“እንደ ሁልጊዜው እንዴት ነው?”

“አላውቅም”

"አዎ! መውጣት አለብን፣ በፍጥነት!

በኋላ ላይ መንትዮቹን አንድ አልጋ ላይ አደረግኳቸው: ሁለቱም እንቅልፍ
ሲወስዳቸው ኬሪን አንስቼ ወደ አልጋችን እወስዳታለሁ ለአሁን ግን ለኮሪ
እህቱ አጠገቡ ሆና መተኛት በጣም የሚመች ነው: “ሮዝ አንሶላ አልወድም።”
አለች ኬሪ ተኮሳትራ “ሁላችንም ነጭ አንሶላ ነው የምንወደው: ነጩ አንሶላ
የታለ?”

እኔና ክሪስ ነጭ ከሁሉም ቀለማት ይልቅ ተስማሚ ነው ብለን የተናገርንበት
ቀን ፀፀተኝ። ካቲ እናታችን በአብዛኛው ጥቁር ቀለም ያላቸውን ቀሚሶች
የምትወደው ለምንድነው? ጠየቀች ኬሪ ሮዙን አንሶላ አንስቼ በነጭ እስክቀይረው እየጠበቀች።

“እናታችን ፀጉሯ ቢጫና የፊቷ ቀለም ነጣ ያለ ነው፡ እና ጥቁር ቀለም ደግሞ
የበለጠ ቆንጆ ያደርጋታል።

“ጥቁር አትፈራም?”

“ጥቁር ቀለም በትልልቅ ጥርሶቹ የማይባላ መሆኑን ለማወቅ ስንት አመት
መሆን ነው ያለብሽ?”

“እንደዚህ አይነት የሞኝ ጥያቄዎችን ማወቅ የምችልበት በቂ እድሜ ሲኖረኝ::

“ግን ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ያሉት ጥቁር ጥላዎች ሁሉ የሚያበራ፣
ሹል ጥርሶች አሏቸው::” አለ ኮሪ ሮዙ አንሶላ እንዳይነካው እየሸሸ።

“አሁን ተመልከቱ” አልኩ የሆነ ዘዴ እየፈጠርኩ እንደሆነ ጠርጥሮ ክሪስ
በሚስቁ አይኖቹ እያየኝ ነው: “እናንተ ቆዳችሁ አረንጓዴ፣ አይናችሁ
ወይንጠጅ፣ ፀጉራችሁ ቀይ እንዲሁም በሁለት ጆሮዎች ፋንታ ሶስት ጆሮዎች
ከሌሏችሁ በስተቀር ጥቋቁሮቹ ጥላዎች የሚያበራ ሹል ጥርስ አያወጡም::እንደዛ ከሆነ ብቻ ነው ጥቁር የሚያስፈራው:”

ዘና አሉ‥ ከዚያ ነጭ አንሶላቸውንና ነጭ ብርድ ልብሳቸው ውስጥ ገቡና
ወዲያው እንቅልፍ ወሰዳቸው ከዚያ ገላዬንና ፀጉሬን ለመታጠብና ልብሴን ለመቀየር ጊዜ አገኘሁ: ጣራው ስር ወዳለው ክፍል ሮጥኩና መስኮቶቹን ከፋፈትኳቸው፡ ቀዝቃዛ አየር ገብቶ ክፍሉን እንዲያቀዘቅዘውና ጠውልጌ
ከምቀመጥ የመደነስ ፍላጎት እንዲሰማኝ ፈልጌያለሁ ንፋሱ ወደ ክፍሉ መግቢያ የሚያገኘው በክረምት ብቻ የሆነው ለምንድነው? ለምን አሁን በጣም በምንፈልገው ጊዜ አይመጣም?

እኔና ክሪስ ሀሳቦቻችንን፣ ተስፋዎቻችንን፣ ጥርጣሬዎቻችንንና ፍርሀቶቻችንን
አንንነጋገራለን ችግር ሲያጋጥመኝ ዶክተሬ ነው: እንደመታደል ሆኖ
የሚያጋጥሙኝ ችግሮች ከባድ አይደሉም ወር ሲመጣ የሚያጋጥመኝ
ቁርጠትና የወር አበባዬ በፕሮግራሙ መሰረት አለመምጣቱ ብቻ ነበር።
ለዚህም ዶክተሬ የሚጠበቅ እንደሆነ ይነግረኛል። እኔ በረባው ባልረባው ጥንቃቄ የማደርግ አይነት ስለሆንኩ ውስጣዊው ማሽኔም ይህንኑ ይከተላል።

ስለዚህ አሁን በመስከረም አንድ ምሽት እኔ ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ
ሆኜ ክሪስ ሊሰርቅ ሄዶ የሆነውን ነገር ልክ ክሪስ የነበረበት ቦታ እንደሆንኩ
አድርጌ መፃፍ እችላለሁ: ስለዚህ የተለየ ወደ እናታችን ክፍል የተደረገ ጉዞ
በዝርዝር ነግሮኝ ነበር።
እንደነገረኝ መሳቢው ውስጥ ያለው መፅሀፍ ሁልጊዜ ይስበው ነበር ማረከው፣በኋላ ግን አስጥሞታል። ልክ እንደኔ ለምሽቱ የፈለገውን በቂ ገንዘብ ካገኘ በኋላ ልክ በማግኔት እንደተሳበ አይነት ወደዛ ጠረጴዛ ሄደ።

እሱ እያወራልኝ እኔ ግን በአንድ እይታ እያንዳንዱ ፎቶግራፍ ለዘለአለም
ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርፆ እያለ ለምን እሱ ደጋግሞ ይመለከተዋል? እያልኩ
ከራሴ ጋር እያወራሁ ነበር:

“እዚያ ቆሜ በየጊዜው የተወሰኑ ገፆች ላይ የተፃፈውን እያነበብኩ ነበር” አለኝ እና ስለ ትክክልና ስህተት ስለሚባሉ ነገሮች እያሰብኩና ስለ ተፈጥሮ፣ ደስ ስለሚያሰኘው እንግዳ ጥሪዎቹ እየተገረምኩና ስለእኛ ህይወት ሁኔታዎች
እያሰላሰልኩ ነበር ስላንቺና ስለኔ እያሰብኩ ነበር፡ እነዚህ ለእኛ የማበቢያችን
አመታት መሆን ይገባቸው ነበር። በማደጌና በእኔ እድሜ ላይ ያሉ ወንዶች
ፈቃደኛ ከሆኑ ሴቶች ሊያገኟቸው የሚችሉ ነገሮችን ስለማሰብ ጥፋተኝነትና እፍረት ይሰማኛል። እና እዚያው ቆሜ ባላገኝሽ እያልኩ ስመኝ አዳራሹ ውስጥ ወደ ክፍሉ እየቀረበ የሚመጣ ድምፅ ሰማሁ። ማን እንደሆነ ታውቂያለሽ እናታችንና ባሏ እየተመለሱ ነበር። በፍጥነት መጽሀፉን ቦታው ላይ መለስኩና ቀጥሎ ትልቁ አልጋው አጠገብ ያለው የእናታችን ልብስ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ ተደበቅኩ: ከገባች አታየኝም ብዬ አሰብኩ። ግን ልታየኝ እንደምትችልም ተጠራጥሬያለሁ። ነገር ግን ይህንን እያሰላሰልኩ
ድንገት በሩን ሳልዘጋ መርሳቴን አስታወስኩ።

የዚያን ጊዜ ነው የእናታችንን ድምፅ የሰማሁት። “የእውነት ባርት? አለች
ወደ ክፍሉ ገብታ መብራት እያበራች። “ብዙ ጊዜ የኪስ ቦርሳህን መርሳትህ
ግዴለሽነትህን ያሳያል”

“ተመሳሳይ ቦታ ስለማላስቀምጠው ነው የምረሳው:” ሲል መለሰላት።እቃዎችን ሲያንቀሳቅስ መሳቢያዎችን ሲከፍትና ሲዘጋ ይሰማኛል። ከዚያ “እዚህኛው ሱሪ ኪስ ውስጥ እንደተውኩት እርግጠኛ ነኝ ... ካለ መንጃ ፈቃዴ የትም መሄድ አልችልም::” አለ

“በአነዳድህ ላይ ቅሬታ የለኝም፧ ግን በዚህ ምክንያት እንደገና ልንዘገይ ነው ምንም ያህል በፍጥነት ብትነዳ የመጀመሪያው ክፍል ያመልጠናል” አለች
እናታችን

“ሄይ!” አለ ባሏ ድምፁ ውስጥ መደነቅ ይሰማኛል። ምን እንዳደረግኩ አስታውሼ በውስጥ አቃሰትኩ ቦርሳዬ ይኸው ኮመዲኖው ላይ: እዛ ላይ ማስቀመጤን አላስታውስም ሱሪው ውስጥ እንደነበረ መማል እችላለሁ” አለ

“መሳቢያው ውስጥ ደብቆት ነበር” ክሪስ አብራራልኝ፡ “ሸሚዞቹ ስር ተቀምጦ ጰነው ያገኘሁት: የተወሰኑ ገንዘቦች ወስጄ ከዚያ አስቀምጬው ያንን መፅሀፍ እሱ እያወራልኝ እኔ ግን በአንድ እይታ እያንዳንዱ ፎቶግራፍ ለዘለአለም ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርፆ እያለ ለምን እሱ ደጋግሞ ይመለከተዋል? እያልኩ
👍511
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

ውድ አንባብያን #የጣሪያ_ስር_አበቦች የተሰኘው መፅሀፍ #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ድርሰት ነው ስለዚህ እውነተኛ ታሪክ ደሞ የሚቀናነስ ነገር አይኖረውም ከባህላችን ምናምን አትበሉ እኛም በየቤታችን ስንት ጉድ አለ ያልወጣ ያልታተመ...መልካም ንባብ



...ይገባዋል እንዳልል እንኳን አእምሮው ውስጥ ያለውን ሙሉ በሙሉ አልተረዳሁትም። ያለውን ያደርጋል ብዬ ግን አስባለሁ ስሜት ግን ሰውን
የሚቆጣጠርበት መንገድ አለው ሁለታችንም ወለሉ ላይ ወደቅን ልታገለው ሞከርኩ። ታገልን፣ ተገለባበጥን፣
መንፈራገጥና መጨነቅ ያለበት የፀጥታ ትግል የእሱ ጥንካሬ ከእኔ ጋር።ፍልምያ አልነበረም።

እኔ ጠንካራ የዳንሰኛ እግሮች አሉኝ፡᎓ እሱ ትልቅ ክብደትና ቁመት አለው... በዛ ላይ ከእኔ የበለጠ የሆነ የጋለ ያበጠና ጠንካራ ነገር ለመጠቀም ማስተዋሉንና
ጤንነቱን የሰረቀው ቆራጥነት ነበረው
እወደዋለሁ ያንን ያህል የሚፈልገው ከሆነ እሱ የሚፈልገውን እኔም
እፈልገዋለሁ ትክክልም ይሁን ስህተት᎓ የሆነው ሆኖ ከዚህ ምሽት በፊት
ፍቅረኞችን የማያውቀው አሮጌ፣ ቆሻሻና የሚሸት ፍራሽ ላይ አረፍን፡ እዛ
ነው የወሰደኝ እና መርካት ያለበትን ያንን ያበጠ፣ ጠንካራ የወንድ የወሲብ
አካል በግድ ያስገባው: ጥብቅና የተቋቋመውን አካሌን ቀዶትና አድምቶት
ወደ ውስጥ ገባ።

አሁን በጭራሽ አናደርገውም ብለን የማልንበትን ነገር አደረግን።

አሁን ለዘለዓለም ተፈርዶብናል። ለዘለዓለም በእሳት ልንጠበስ ተረግመናል።በማያቋርጠው የገሀነም እሳት ውስጥ እርቃናችንን ተዘቅዝቀን እንሰቀላለን
ልክ አያትየው ከረጅም ጊዜ በፊት እንደተነበየችው ሆንን ኃጢአተኞች!

አሁን መልሶች ሁሉ አሉኝ፡

አሁን ልጅ ሊኖር ይችላል፡ ለእንደኛ አይነቶቹ የተዘጋጀውን ዘለአለማዊ
የገሀነም እሳት ሳይጠብቅ በህይወት ስለኃጢአታችን የሚያስከፍለን ልጅ
ይመጣል። ተራራቅንና እርስ በርስ ተያየን: ፊቶቻችን በድንጋጤ የደነዘዙና
የገረጡ ሆነዋል። ልብሶቻችንን ስናስተካክል መነጋገር እንኳን አልቻልንም

አዝናለሁ ማለት አያስፈልገውም ሁሉ ነገሩ ላይ ይታያል... የሚንቀጠቀጥበት
መንገድ፣ ልብሶቹን ለመቆለፍ ሲሞክር እጆቹ የሚንቀጠቀጡበት መንገድ
መደንገጡን ይናገራሉ፡

ቆይቶ ወደ ጣራው ላይ ወጣን።

ረጃጅም የደመና መስመሮች የድፍኗን ጨረቃ ፊት እያቋረጡ ነው እሷም
ትደበቅና እንደገና ትወጣለች:: ጣራው ላይ ሆነን ለፍቅረኞች በተዘጋጀው ምሽት ተቃቅፈን ተላቀስን ሊያደርገው ፈልጎ አልነበረም፡ እኔም ልፈቅድለት ፈልጌ አልነበረም ከእኔ ጋር ተመሳሳይ ደም ካለው ሰው ጋር አንድ ጊዜ ባደረግነው ነገር ልጅ የመምጣቱ ፍርሀት ወደ ጉሮሮዬ መጥቶ ምላሴ ላይ ቀረ: ከገሀነም ወይም ከእግዚአብሔር ቁጣ በላይ የሆነው ከባዱ ፍርሀቴ ጭራቅ የሚመስል፣ ቅርፁ የተበላሸና ደደብ ልጅ መውለድ አስፈርቶኛል። ግን
እንዴት ስለዚህ ጉዳይ ለክሪስ መናገር እችላለሁ? በበቂ ሁኔታ እየተሰቃየ
ነው: ሆኖም ግን መንገር አለብኝ ምክንያቱም የእሱ ሀሳቦች ከእኔ በተሻለ
በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ናቸው።

“በአንድ ጊዜ መፀነስ አይኖርም:: ምንም ነገር ቢፈጠር ሌላ ጊዜ እንደማይሆን
እምልልሻለሁ፡ ይህ ነገር ከመፈጠሩ በፊት ራሴን አኮላሻለሁ! አለኝ፡ ከዚያ
ወደ እሱ ሳበኝና የጎን አጥንቶቼ የሚሰበሩ እስኪመስለኝ ድረስ አጥብቆ አቀፈኝ። “አትጥይኝ ካቲ… እባክሽ እንዳትጠይኝ፡ ልደፍርሽ ፈልጌ አልነበረም
በእግዚአብሔር እምልልሻለሁ። ብዙ ጊዜ ተፈትኜ አውቃለሁ ግን ብዙ ጊዜ ክፍሉን እለቃለሁ ወይም ወደ መታጠቢያ ቤት እገባለሁ አለዚያም ጣራው
ስር ወዳለው ክፍል እወጣለሁ ወይም እስክረጋጋ ድረስ አፍንጫዬን መፅሀፍ ውስጥ እቀብራለሁ እና ማለፍ ችዬ ነበር:”

በቻልኩት መጠን ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት። “አልጠላህም ክሪስ” ስል አንሾካሾኩ ጭንቅላቴን ደረቱ ላይ አድርጌያለሁ: “አልደፈርከኝም፤ የምሬን ብፈልግ ኖሮ ላስቆምህ እችል ነበር ማድረግ ያለብኝ ጉልበቴን ጥንክር አድርጌ ወደላይ ማድረግ ብቻ ነበር፡ የኔም ጥፋት ነው” አዎ የኔም ጥፋት ነው። የእናቴን
መልከመልካም ወጣት ባል ከመሳም የተሻለ ነገር ማወቅ ነበረብኝ፡ የወንድ
ጥንካሬ አካላዊ ፍላጎቶች ባሉትና ሁልጊዜ በሁሉም ነገርና በሁሉም ሰው
ተስፋ በቆረጠ ሰው ዙሪያ ወንድሜም ቢሆን እንኳን ሰውነትን የሚያሳይ ልብስ
መልበስ አልነበረብኝም: በፍላጎቶቹ እየተጫወትኩ፣ ሴትነቴን እየሞከርኩ፣
የራሴን የሚቃጠል የመርካት ፍላጎት እያየሁ ብቻ ነበር።

ይህ የተለየ አይነት ምሽት ነው፤ ልክ ዕድል ከረጅም ጊዜ በፊት ይህንን ቀን
ያቀደው ይመስላል እና ይህ ምሽት ትክክልም ይሁን ስህተት እጣ ፈንታችን
ነው:

ንፋሱና ቅጠሎቹ ዜማ አልባ ሙዚቃ ያሰማሉ: ሙዚቃው ያው ነው: ሰው የመሰለ አፍቃሪ የሆነ ፍጥረት እንዴት በዚህ ቆንጆ ምሽት አስቀያሚ ሊሆን
ይችላል?

ምናልባት ጣሪያው ላይ ብዙ ቆይተናል፡

የመስከረም መግቢያ በመሆኑ ጣሪያው ቀዝቃዛ፣ ጠንካራና ሻካራ ሆኗል።
ቅጠሎቹ መርገፍ ጀምረዋል ጣራው ስር ያለው ክፍል ልክ እንደ ገሀነም ያቃጥላል ጣራው ላይ ግን በጣም በጣም ይቀዘቅዛል
እኔና ክሪስ ለደህንነትና ለሙቀት ተቃቅፈን ተቀምጠናል። በጣም መጥፎ ወጣቶችና ኃጢአተኞች:: ያለማቋረጥ በመጠጋጋት በጣም ተወጥረው በቀጠኑ
ታሪኮች የራሳችንን ክብር አሽቀንጥረን ጥለነዋል፡ በአንድ ወቅት በራሳችን
ስሜታዊ ተፈጥሮ አብዝተን የተፈተንን ቢሆንም... በዚያ ወቅት እንኳን እሱ እኔም ስሜታዊ መሆኔን አላውቅም ነበር፡ ልቤን የሚሰውርና ሽንጤን
እንድሰብቅ የሚያደርገኝ ቆንጆ ሙዚቃ ብቻ ይመስለኝ ነበር፡ በጣም ተጨባጭ የሆነ ሌላ ነገር እንዳለ አላውቅም ነበር።

ልክ አንድ ልብ እንደምንጋራ ሁሉ በሰራነው ስራ ራስን የመቅጣት አሳዛኝ ቅኝት
እየደለቅን ነበር ቀዝቃዛው ነፋስ የረገፈ ቅጠል ወደ ጣራው አምጥቶ ድንገት
ፀጉሬ ውስጥ እንዲያዝ አደረገው:: ክሪስ ሊያነሳው ሲሞክር ደርቆና ተሰባብሮ
ወደቀ ህይወቱ ቅጠሉ በንፋስ መብረር እንዴት እንደሆነ በሚያውቀው
ሚስጥር ላይ የተመሰረተ ይመስል ክሪስ ቅጠሉን አተኩሮ እየተመለከተ
ነበር: እጆችም ክንፎችም የሉትም... ግን ሞቶም መብረር ይችላል።

“ካቲ” በሚደነቃቀፍ ደረቅ ድምፅ ጠራኝ፡ “አሁን ልክ ሶስት መቶ ዘጠና ስድስት
ዶላር ከአርባ አምስት ሳንቲም አለን በቅርቡ በረዶ መጣል ይጀምራል።
በልካችን የሆነ የክረምት ኮት ወይም ጫማዎች የሉንም፧ መንትዮቹ ደግሞ
ደካማ ስለሆኑ በቀላሉ ብርድ ሊያሳምማቸውና ከዚያ ወደ ኒሞኒያ ሊለወጥባቸው
ይችላል ሌሊት ነቅቼ ስለእነሱ እጨነቃለሁ እና አንቺንም አልጋሽ ላይ
ሆነሽ ኬሪን አተኩረሽ ስትመለከቻት አይሻለሁ፡ አንቺም ተጨንቀሽ መሆን
አለበት። አሁን ከእናታችን ክፍል ውስጥ እንደበፊቱ ገንዘብ የማግኘታችንን
ነገር እጠራጠራለሁ። ሠራተኞች ገንዘብ እየሰረቋቸው እንደሆነ ጠርጥረዋል።አሁን ምናልባት እናታችን አንቺ ልትሆኚ እንደምትችይ ትጠራጠር ይሆናል አላውቅም... እንደማይሆን ተስፋ አለኝ።

“እነሱ ምንም ቢያስቡ በሚቀጥለው ለመስረቅ ስሄድ ጌጣጌጧን ለመስረቅ
እገደዳለሁ። ትልቅ ነገር እወስድና ከዚያ እናመልጣለን ልክ ርቀን እንደሄድን በቂ ገንዘብ ስለሚኖረን መንትዮቹን ወደ ዶክተር እንወስዳቸዋለን፡” አለ፡

“ጌጣጌጦቹን ውሰድ።” እንዲወስድ ብዙ ጊዜ ለምኜው ነበር። በመጨረሻ
ሊያደርገው ነው እናታችን ልታገኘው የታገለችለትን ብዙ ገንዘብ የሚያወጣ
ጌጥ ታጣለች በዚያ ሂደት ውስጥ እኛንም ታጣለች: ግን ግድ ይኖራት
ይሆን?
👍402👏2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


ቀኖቹን ሁላ ሰማያዊ ስትቀባ አንዱን ለጥቁር ተወው።

በማንኛውም ቀን ልንሄድ ነው፡፡ እናታችን በምሽት ወጣ እላለሁ እንዳለች፣
መጓጓዝ የሚችሉ ውድ ንብረቶቿም ከእሷ ይወጣሉ። ወደ ግላድስተን
አንመለስም እዚያ አሁን ክረምት ገብቷል። ገና እስከ ግንቦት ይቆያል።ሰርከስ የሚሰሩ ሰዎች ወደሚኖሩበት ወደ ሳራሶታ እንሄዳለን፡ እዚያ ያሉ
ሰዎች ለየት ያለ የኋላ ታሪክ ላላቸው ሰዎች ደግነት በማሳየት የሚታወቁ
ናቸው ክሪስና እኔ ከፍ ያለ ቦታ ማለትም ጣራ ላይ ስለኖርን ምሰሶዎቹ
ላይ ብዙ ገመዶች የታሰሩበት በመሆኑ ለክሪስ “የዥዋዥዌ ትርኢት የምንሰራ እንሆናለን” አልኩት እየተፍለቀለቅኩ። በመጀመሪያ የሞኝ ሀሳብ እንደሆነ አስቦ ፈገግ አለ፤ ቀጥሎ ግን መንፈስን የሚቀሰቅስ ሀሳብ ብሎ ጠራው።

ኮሪ ጭንቅላቱን ቀና አደረገ፡፡ ሰማያዊ አይኖቹ በፍርሀት ፈጥጠዋል።

“አይሆንም!” አለች ኬሪ “እቅዳችሁን አልወደድነውም እንድትወድቁ አንፈልግም::”

“አንወድቅም” አለ ክሪስ፡ “እኔና ካቲ የማንቻል ቡድን ነን፡" አሻግሬ ወደ እሱ
እየተመለከትኩ መማሪያ ክፍሉ ውስጥ ከዚያም ጣሪያው ላይ ሆነን “ከአንቺ
በስተቀር ማንንም አላፈቅርም፣ ካቲ አውቀዋለሁ... እንደዚያ አይነት ስሜት ነው ያለኝ... ሁልጊዜ እኛ ብቻ:" ያለኝን አስታወስኩና በተለየ ሁኔታ ሳቅኩ። “ሞኝ አትሁን፣ በዚያ መንገድ እንደማትወደኝ ታውቃለህ፡ እና ጥፋተኝነት
ሊሰማህ ወይም ልታፍር አይገባም: የእኔም ጥፋት ነው: እንዳልተፈጠረ
ማስመሰልና በድጋሚ እንዳይፈጠር እርግጠኛ መሆን ነው ያለብን፡"

"ግን ካቲ....."

“አንቺና እኔ ሌሎች ሰዎች ሲኖሩን፣ በፍፁም… በፍፁም እርስ በርሳችን በዚህ መንገድ እንዲሰማን አይሆንም''

“እኔ ግን ስላንተ በዚህ መንገድ እንዲሰማኝ ነው የምፈልገው። እና ለእኔ ሌላ
ሰው ለማመንና ለመውደድ በጣም ዘግይቷል።”

ክሪስን መመልከት… ከዚያ መንትዮቹን. ለሁላችንም እቅድ ሳወጣና እንዴት
እንደምንሄድ ሳወራ ትልቅ የሆንኩ አይነት ስሜት ፈጠረብኝ፡ ለመኖር
የትኛውንም ነገር ለመስራት እንደምንገደድ ባውቅም እንኳን መንትዮቹ ሰላም
እንዲሰማቸው መፅናኛ ነገሮች አወራቸዋለሁ።

መስከረም አልፎ ጥቅምት ተተካ። በቅርቡ በረዶ መጣል ይጀምራል:
“ዛሬ ማታ” አለ ክሪስ፡ እናታችን በሩጋ ቆም ብላ ዞራ እንኳን ሳታየን
በግዴለሽነት ደህና ሁኑ ብላን ሄደች:: አሁን እኛን መመልከት እንኳን
መቋቋም አቅቷታል። አንዱን የትራስ ልብስ ሌላኛው ላይ ደርበን ጠንhር እንዲል አደረግን፡ በዚያ ትራስ ጨርቅ ውስጥ ክሪስ የእናታችንን ውድ
ጌጣጌጦች ሁሉ ከትቶ ያመጣል፡ እኔም ሁለት ሻንጣዎችን አሽጌ እናታችን
አሁን ወደዚያ ስለማትሄድ ጣራው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ደብቄያለሁ።

ቀኑ መምሸት ሲጀምር ኮሪ ማስመለስ ጀመረ። እየደጋገመ ያስመልሰው
ጀመር። በመድኃኒት ማስቀመጫው ውስጥ ለሆድ የሚሆን መድኃኒት ነበረን የገረጣውን፣ የሚያንቀጠቅጠውን፣ የሚያስለቅሰውን አሰቃቂ ማስመለስ ያደረግነው ጥረት ሁሉ ሊያስቆመው አልቻለም ከዚያ ክንዶቹን በአንገቴ ዙሪያ ጠምጥሞ “እማዬ ደህና አይደለሁም::” ሲል አንሾካሾከ።

“እንዲሻልህ ምን ላድርግልህ ኮሪ?” ስል በጣም ልጅ መሆኔና ልምድ የሌለኝ መሆኔ እየተሰማኝ ጠየቅኩ።

“ሚኪ” አለ ያላመደውንና ጓደኛ ያደረገውን አይጥ በደካማ ድምፅ እየተጣራ
“ሚኪ እኔ ጋር እንዲተኛ እፈልጋለሁ”

“ግን ስትገለበጥ ላዩ ላይ ትተኛበትና ይሞትብሀል፡ እንዲሞትብህ አትፈልግም
አይደል?”

“አልፈልግም” አለ ሀሳቡ ራሱ ያስደነገጠው መሰለ፡ ከዚያ ያ አሰቃቂ መጓጠጥ
እንደገና ጀመረውና ክንዶቼ ላይ እንደያዝኩት እየቀዘቀዘ መጣ፡ በላብ የረጠበ
ፀጉሩ ግንባሩ ላይ ተለጥፏል ሰማያዊ አይኖቹ ፊቴ ላይ ተተክለው እየደጋገመ እናቱን ይጣራል። “እማዬ፣ እማዬ፣ አጥንቶቼን አሞኛል” “አይዞህ” አልኩት።
የተበላሸውን ፒጃማውን ለመቀየር ተሸክሜ ወደ አልጋው እየወሰድኩት ነው።
ሆዱ ውስጥ የቀረ ምንም ነገር ሳይኖር እንዴት ሊያስመልሰው ይችላል?
ክሪስ ይረዳሻል አትጨነቂ!” ሲለኝ ከጎኑ ጋደም ብዬ ደካማና የሚንቀጠቀጥ
ሰውነቱን በክንዶቼ አቀፍኩት::

ክሪስ ጠረጴዛው ጋ ተቀምጦ የኮሪ የህመም ምልክቶች የሚያሳየውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያንዳንችንን ሊያጠቃን የሚችለውን ሚስጥራዊ በሽታ ለማወቅ
የሀክምና መፅሀፍ ላይ ተደፍቷል አሁን አስራ ስምንት አመት እየሆነው
ነው እኔንና ኬሪን ትታችሁን አትሂዱ! ሲል ለመነኝ፡ ጮክ ባለ ድምፅ “ክሪስ አትሂድ እዚህ ቆይ!” አለ።

ምን ማለቱ ነው? እንድናመልጥ አይፈልግም? ወይስ ለመስረቅ እንደገና
ወደ እናታችን ክፍል አትሂድ ማለቱ ይሆን? እኔና ክሪስ መንትዮቹ የምናደርጋቸውን ነገሮች በመረዳት ይመለከታሉ ብለን ያመንነው ለምንድነው?
በእርግጠኝነት እሱና ኬሪ ትተናቸው እንደማንሄድ ያውቃሉ ያንን ከማድረግ
ብንሞት ይሻለናል።

ኬሪ ነጭ ልብስ የለበሰች ትንሽ ጥላ መስላ ወደ አልጋው መጣችና በረጠቡት ትላልቅ ሰማያዊ አይኖቿ መንትያ ወንድሟን አተኩራ እየተመለከተች
ቆመች: ትንሽ ናት። በጨለማ ክፍል ውስጥ መንምና በአጭር ቀርታ ያደገች ትንሽዬ ተክል ናት።

“ከኮሪ ጋ መተኛት እችላለሁ? ምንም መጥፎ ወይም ክፉ ወይም ቅዱስ
ያልሆነ ነገር አንሰራም: እሱ አጠገብ መሆን ስለፈለግኩ ብቻ ነው” አለች።

አያትየው ትምጣና መጥፎ የምትለውን ነገር ታድርግ! ኬሪን ከኮሪ ጋር አስተኛኋት። ከዚያ እኔና ክሪስ ከትልቁ አልጋ ግራና ቀኝ ቆመን በሀዘን ተሞልተን ኮሪ ረፍት ባጣ ሁኔታ ሲቅበጠበጥና ለመተንፈስ ሲታገል እንዲሁም በቅዠት ሲጣራ እየተመለከትን ነው
እናቱንና አባቱን፣ ክሪስንና እኔን ይፈልጋል እምባዬ በሌሊት ልብሴ ኮሌታ
ላይ እየወረደ ነው ክሪስንም ስመለከተው ጉንጮቹ በእምባዬ ረጥበዋል። “ኬሪ
ኬሪ... ኬሪ የታለች?" ሲል በመደጋገም ጠየቀ እንቅልፍ ከወሰዳት ትንሽ
ቆይታለች: ፊቶቻቸው ተጠጋግተው ነበር። ቀጥታ ወደ እሷ እየተመለተ
ቢሆንም እያያት አይደለም

ቅጣት እንደሆነ አሰብኩ፡፡ እግዚአብሔር እኔና ክሪስ ስለሰራነው ነገር እየቀጣን
ነው አያትየው አስጠንቅቃን ነበር. እስክተገረፍንበት ቀን ድረስ በየቀኑ
ታስጠነቅቀን ነበር ሌሊቱን ሙሉ እኔ ክፍሉ ውስጥ ስንጎራደድ፣ ክሪስ ደግሞ ከአንዱ የህክምና መፅሀፍ ወደ ሌላው እየሄደ ሲያነብ ነበር።

በመጨረሻ ደም የመሰሉ አይኖቹን ቀና አድርጎ “የምግብ መመረዝ ነው::
ወተቱ ተበላሽቷል ማለት ነው” አለ።

“ስቀምሰውም፣ ሳሸተውም ደህና ነበር” ስል መለስኩለት ሁልጊዜ የትኛውንም ምግብ ለክሪስና ለመንትዮቹ ከማቅረቤ በፊት በጥንቃቄ አሽትቼና ቀምሼ ነበር። በሆነ ምክንያት ሁሉንም ነገር ከሚወደውና ምንም ነገር ከሚበላው
ክሪስ የተሻለ የመቅመስ ችሎታ እንዳለኝ አስባለሁ።

“ሀምበርገሩ ይሆናል፡ ለየት ያለ ጣዕም ነበረው”

“አረ ጣዕሙ ለእኔ ደህና ነበር” አልኩት ለእሱም ደህና የነበረ ይመስለኛል::
ምክንያቱም ቀኑን ሙሉ ኮሪ ምንም መብላት ስላልፈለገ የኬሪን ግማሽ ሀምበርገር ጨምሮ የኮሪንም ፋንታ ነበር የበላው ኮሪ ቀኑን ሙሉ ምንም መብላት አልፈለገም ነበር።

“ካቲ አንቺም ቀኑን ሙሉ ምንም እንዳልበላሽ አስተውያለሁ አንቺም እንደ
መንትዮቹ ያህል ከስተሻል፡ የምታመጣልን ምግብ በቂ ነው ራስሽን መበደል
አይጠበቅብሽም” አለኝ፡
👍342🥰1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

...የእናታችን ባዶ ፍጥጫ ወደ እሱ ዞረ:: ልክ ምን ማለት እንደፈለገ ለመያዝ የምትታገል ይመስል ነበር፡ የተምታታባት ትመስላለች… አይኖቿ ከኔ ወደ ክሪስ ከዚያ ወደ እናቷ ከዚያ ወደ ኬሪ ዘለሉና ተመልሰው ወደ ኮሪ መጡ።

“እማዬ” አለ ክሪስ ጥንክር አድርጎ፡ ካቲ አብራሽ ትሂድ ለኬሪ እኔ አለሁ
ምናልባት ያስጨነቀሽ ያ ከሆነ።"

እንድሄድ አልፈቀዱልኝም።

እናታችን ኮሪን ይዛ ወደ አዳራሹ ወጡ አያትየው ባገኘሁት ድል የጭካኔ
ፈገግታ ሰጥታኝ በሩን ቆለፈችው ኬሪ ወንድሟን በማጣቷ እየጮኸችና እምባዋ እየወረደ ትተዋት ሄዱ። ትንንሽ ደካማ ቡጢዎቿ ጥፋተኛዋ እኔ የሆንኩ ይመስል እኔ ላይ አረፉ፡ ካቲ እኔም
መሄድ እፈልጋለሁ! እንድሄድ እንዲፈቅዱልኝ አድርጊ! ኮሪ እኔ የማልሄድበት ቦታ መሄድ አይፈልግም... ጊታሩን ደግሞ ረስቶታል” አለች።

ከዚያ ቁጣዋ ሁሉ ሲበርድላት፣ ክንዶቼ ላይ ሆና ተንሰቀሰቀች: “ለምን ካቲ? ለምን?”

“ለምን?”

በህይወታችን ትልቁ ጥያቄ ነው።

በህይወታችን ከነበሩት አስቀያሚውና ረጅሙ ቀን ነበር። ኃጢአት ሰርተናል
እና እግዚአብሔር እንዴት በዚህ ፍጥነት ቅጣት ላከብን? ፈጠነም ዘገየም
አያትየው እንዳወቀችው ሁሉ ራሳችን ዋጋ ቢስ መሆናችንን እንደምናረጋግጥ
ያወቀ ይመስል፣ አይኖቹ እኛ ላይ ነበሩ ማለት ነው።

ቲቪ መጥቶ የቀኖቻችንን የተሻለ ክፍል ከመውሰዱ በፊት እንደነበረው እንደ
መጀመሪያው ቀን ቀኑን ሙሉ ቴሌቪዥን እንኳን ሳንከፍት በፀጥታ ቁጭ
ብለን ኮሪ እንዴት እንደሆነ ለመስማት እየጠበቅን ነው።

ክሪስ በሚወዛወዘው ወንበር ላይ ተቀምጦ እኔና ኬሪ ጭኖቹ ላይ ተቀምጠን
በቀስታ ወደፊት ወደኋላ፣ ወደፊት ወደኋላ እየተወዛወዝን ነው።

ለረጅም ጊዜ ጭኖቹ ላይ ስንቀመጥበት የክሪስ እግሮች ለምን እንደማይደነዝዙ
አላውቅም ምግባችንን ለማሰናዳት ተነሳሁ። ጭራሽ አልነካነውም: የቀኑ
የመጨረሻ ምግብ ሲያበቃና ሳህኖቹ ታጥበው ከተቀመጡ በኋላ እኛም ገላችንን ተጣጥበን ለመተኛት ተዘጋጀን፡ ኮሪ አልጋ አጠገብ በመደዳ ተንበርክከን ፀሎታችንን አቀረብን “እባክህ፣ እባክህ ኮሪ እንዲሻለውና ወደ እኛ እንዲመለስ አድርግ አልን ሌላ ነገር ፀልየንም ከነበረ ምን እንደነበረ አላስታውስም ተኛን ወይም ለመተኛት ሞከርን ኬሪን በእኔና በክሪስ መካከል አድርገን ሶስታችንም አንድ አልጋ ላይ ተኛን በሁለታችን መካከል ድጋሚ ምንም
ነገር አይፈጠርም መቼም... መቼም እንደገና አይፈጠርም እግዚአብሔር
እኔና ክሪስን ለመጉዳት ብለህ ኮሪን አትቅጣው አስቀድመን ተጎድተናል
ልናደርገው ፈልገን አልነበረም ጌታ ሆይ አልነበረም በአጋጣሚ ነው
የሆነው ለዚያውም አንድ ጊዜ ብቻ በዚያ ላይ ምንም ደስታ አልነበረበትም።

እግዚአብሔር ሆይ በእውነት በእውነት ደስታ አልነበረበትም
አዲስ ቀን ነጋ ከመጋረጃዎቹ ጀርባ ውጪ ለሚኖሩት በእኛ ለማይታዩት
ህይወት ተጀመረ። ራሳችንን ዘና ለማድረግ፣ ሰዓታችንን ለመሙላትና ለመብላት ሞከርን ክሪስ እየረዳኝ የፍራሹን ልብስ ቀየርኩ ምክንያቱም በጣም ከባባድ በመሆናቸው ብቻዬን ላገባቸው አልችልም፡ በዚያ ላይ ኮሪ በአብዛኛው ሽንቱን ስለሚሸና በየጊዜው መቀየር ነበረበት፡ ክሪስና እኔ አልጋውን አንጥፈን ክፍሉን አፀዳድተን ጨርሰን ኬሪ የሚወዛወዘው ወንበር
ላይ ብቻዋን ተቀምጣ ባዶ አየር ላይ አፍጥጣለች።

አራት ስዓት ገደማ የምንሰራውን ሁሉ ጨርሰን ወደ አዳራሹ ቀረብ ወደሚለው አልጋ ላይ ተቀምጠን በሩ እጀታ ላይ አይኖቻችንን ተክለን ዜናውን ይዛልን የምትመጣልንን እናታችንን እንዲያስገባ እየጠበቅን ነው።

ጥቂት ቆይቶ እናታችን ከማልቀስ ብዛት አይኖቿ ቀልተው መጣች። ከእሷ
ጋር ባለብረት አይኗ አያታችን ረጅም፣ ድርቅ ያለችና እምባ የሌላት ሆና ተከትላታለች።

እናታችን እግሮቿ መቆም አቅቷቸው ወለሉ ላይ እንዳይጥሏት የፈራች
ይመስል በሩን ተደገፈች እኔና ክሪስ ከተቀመጥንበት ዘለን ተነስተን ቆምን፡
ኬሪ ግን እናታችን ባዶ አይን ላይ እንዳፈጠጠች ነው: “ኮሪን በመኪና ወደ
ሆስፒታል እየወሰድኩት ነበር ቅርብ ወዳለው ሆስፒታል ነበር በእውነት"
አለች እናታችን ውጥረት በተሞላበት ሻካራና አሁንም አሁንም እንቅ እንቅ
በሚል ድምፅ፡ “እና የወንድሜ ልጅ ነው ብዬ በውሸት አስመዘገብኩት"

“ውሸት! እማዬ ሁልጊዜ ውሸት እንዴት ነው?” ትዕግስት ባጣ ሁኔታ ጠየቅኳት። ሰማያዊ አይኖቿ ወደ እኛ ዞሩ፡፡ ባዶ ነገር ላይ ያፈጠጡ፣ የጠፋ፣የሆነ ለዘለአለም የጠፋ ነገር የሚፈልጉ አይኖች ሰብአዊነቷ እየፈለጉ
እንደሆነ ገምቻለሁ። “ኮሪ የያዘው የሳምባ ምች ነበር። ዶክተሮቹ የቻሉትን ሁሉ
አድርገው ነበር . . .ግን በጣም በጣም . . . በጣም ዘግይቶ ነበር”

“የሳምባ ምች ነበር?"

“የሚችሉትን አድርገው ነበር?”

“ዘግይቶ ነበር?”

“ነበር… ነበር!

ኮሪ ሞቷል እንደገና አናየውም!

ዜናው ክሪስን ልክ ወንድነቱ ላይ የተመታ አይነት ስሜት ነበር የፈጠረበት
እንደተረገጠ አይነት፡ ወደ ኋላ ተንጋሎና ፊቱን ለመደበቅ ዞሮ ትከሻዎቹ
እየተርገፈገፉ ሲንሰቀሰቅ አይቼዋለሁ።

በመጀመሪያ አላመንኳትም ነበር። ቆምኩ፣ አፈጠጥኩ፣ ተጠራጠርኩ፣ ፊቷ አሳመነኝ እና ልቤ ውስጥ የሆነ ትልቅና ባዶ ቦታ ሲሰፋ ተሰማኝ። ደንዝዤና
ሽባ ሆኜ አልጋው ላይ ወደቅኩ። ልብሶቼ ረጥበው እስክመለከት ድረስ
እያለቀስኩ እንደነበረ አላወቅኩም ነበር
ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ ቢሆንም ኮሪ ከህይወታችን ወጥቶ መሄዱን ማመን
አልፈለግኩም ደግሞ ኬሪ፣ ምስኪን ኬሪ ጭንቅላቷን ቀና አደረገች። ወደ
ኋላ ወረወረችና አፏን ከፍታ እሪ... አለች።

ድምፅዋ ተዘግቶ መጮህ እስከማትችል ድረስ ጮኸች: ኮሪ ጊታሩን
ወደሚያስቀምጥበትና ትንንሽ ያለቁ የቴኒስ ጫማዎቹን ወደደረደረችበት
ጥግ ሄደች። መቀመጥ የፈለገችው እዚያ ከጫማዎቹና ከሙዚቃ መሳሪያው ጋር ነበር እና ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ አንዲት ቃል እንኳን ከከንፈሮቿ አልወጣም::

“ወደቀብሩ እንሄዳለን?” ክሪስ ጀርባውን እንዳዞረ ጠየቀ።

“ተቀብሯል” አለች እናታችን፡ “በመቃብሩ ላይ የውሸት ስም አፅፌያለሁ"አለችና ከጥያቄዎቻችንና ከክፍሉ ለማምለጥ በጣም በፍጥነት ወጣች
አያትየውም ተከተለቻት፡

በፈሩት አይኖቻችን ፊት ኬሪ በእያንዳንዱ ቀን የበለጠ እየጠወለገች ነው
እግዚአብሔር ኬሪንም ሊወስዳት እንደሚችል እና ሩቅ ቦታ ባለ የመቃብር
ስፍራ በሀሰት ስም ከኮሪ አጠገብ በቅርብ ርቀት የተቀበረ አባት እንኳን
በሌለበት እንደምትቀበር ተሰማኝ።

ማንኛችንም ብዙ መብላት አልቻልንም:: ፈዛዛና የደከመን ሁልጊዜ የደከመን
ሆነናል፡ ምንም ነገር ፍላጎታችንን አያነሳሳውም: ዕንባ ብቻ። ክሪስና እኔ
ውቅያኖስ የሚሞላ ያህል አለቀስን ወቀሳውን ሁሉ የእኛ አደረግነው: ከብዙ
ጊዜያት በፊት ማምለጥ ይገባን ነበር፡ ያንን የእንጨት ቁልፍ ተጠቅመን
ወጥተን እርዳታ መፈለግ እንችል ነበር። ኮሪ እንዲሞት አድርገናል: የእኛ
ሀላፊነት ነበር! ትንሹ ባለ ብዙ ተሰጥኦውና ፀጥተኛው ውድ ልጃችን እንዲሞት አደረግን አሁን ደግሞ ጥግ ላይ ተኮራምታ የምትቀመጥ በየቀኑ እየደከመች የምትሄድ ታናሽ እህት አለችን፡

ክሪስ ኬሪ እንዳትሰማ
ቀስ ባለ ድምፅ “ማምለጥ አለብን ካቲ! በፍጥነት።
አለዚያ ሁላችንም እንደ ኮሪ እንሞታለን፡ ሁላችንም የሆነ ነገር ሆነናል።ለረጅም ጊዜ ተዘግቶብናል፡ የምንኖረው ትክክለኛ ያልሆነ ህይወት ነው፡ ልክ ጀርሞች በሌሉበት አየር አልባ ቦታ እንደመኖር ነው።
👍45😢63👎1🥰1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አርባ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

ማምለጥ

ህዳር አስር… እዚህ እስር ቤት ውስጥ የምንቆይበት የመጨረሻ ቀናችን ነው
እግዚአብሔር አላዳነንም: ራሳችንን ማዳን አለብን።

ክሪስ ዛሬ ማታ ልክ አራት ሰዓት ሲያልፍ የመጨረሻውን ዝርፊያ ያከናውናል።እናታችን ለጥቂት ደቂቃዎች ለመቆየት መጥታ ነበር። አሁን ከእኛ ጋ መሆን
ብዙም እንደማይመቻት በግልፅ ይታያል። “ባርትና እኔ ዛሬ ማታ ወጣ እንላለን፡ እኔ አልፈለግኩም እሱ ግን ድርቅ አለ፡ አያችሁ፣ ለምን እንዳዘንኩ አይገባውም” ብላን ነበር።

እንደማይገባው እርግጠኛ ነኝ። ክሪስ ከበድ ያሉ ጌጣጌጦችን ይዞ ለመመለስ ሁለት የትራስ ልብሶችን ትከሻው ላይ አንጠለጠለ፡ የተከፈተው በር ጋ ቆመና ወጥቶ በሩን ከመቆለፉ በፊት ረዘም ላለ ጊዜ ቆም ብሎ ተመለከተን
በሩን ክፍት መተው አይችልም: ምክንያቱም አያትየው ድንገት ከመጣች
መጠንቀቅ ስለሚያስፈልግ ነው ክሪስ ጨለማ በዋጠው በሰሜን አቅጣጫ
ካለው ኮሪደር ሲሰርቅ ልንሰማው አንችልም።
ምክንያቱም ግድግዳዎቹ በጣም ወፍራም ሲሆኑ አዳራሹ ውስጥ የተነጠፉት ምንጣፎች ደግሞ ወፍራምና ድምፅ የማያሳልፉ ናቸው።

ኬሪና እኔ ጎን ለጎን ተኝተን በክንዶቼ አቅፌያታለሁ።

ያ ህልም ኮሪ ደህና መሆኑን ባይነግረኝ ኖሮ፣ ቅርብ መሆኑ ስለማይሰማኝ
አሁንም አለቅስ ነበር። ታላቅ ወንድሙ እንደማይሰማን ባረጋገጠ ቁጥር
እማዬ ብሎ ይጠራኝ ለነበረው ትንሽ ልጅ መታመሙን ልረዳው አልቻልኩም ሁልጊዜ ክሪስ ምን ያህል እናቱን እንደናፈቀና እንደፈለገ ካወቀበት ሴታ ሴት
ብሎ ሊጠራው እንደሚችል ስለሚፈራ የሚነግረኝ ለእኔ ነበር እኔም ክሪስ

ራሱ እናቱን ስለሚፈልግ በጭራሽ እንደማይስቅበትና እንደማያሾፍበት
እነግረው ነበር በአንድ ወቅት ኮሪ በእሱ፣ በእኔና በኬሪ መካከል ሚስጥር
አድርጎት ነበር ወንዳወንድ ለመሆን እናትም አባትም ባይኖረው ምንም
እንዳልሆነ ራሱን ያሳመነ ይመስላል

ኬሪን ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳትና ልጅ ወይም ልጆች ሲኖሩኝ የማይሰማኝ
ወይም ለእነሱ ምላሽ የማልሰጥበት እኔን የመፈለግ ስሜት እንደማይኖራቸው
ማልኩ ምርጥ እናት እሆናለሁ ሰዓታት ልክ አመታት መሰሉ። ክሪስ
እስካሁን የእናታችንን ክፍል ለመጨረሻ ጊዜ ሊጎበኝ ከሄደበት አልተመለሰም
ዛሬ ለምን ይህን ያህል ጊዜ ፈጀ? ንቅት ብዬና ተከፍቼ በፍርሀት ተሞላሁና
ሊያቆየው የሚችለውን ሁሉንም መሰናክሎች ማሰብ ጀመርኩ።

ባርት ዊንስሎ ... ተጠራጣሪው ባል ... ክሪስን ሊይዘው ይችላል! ከዚያ ፖሊስ ይጠራና እስር ቤት ይወስዱታል። እናታችን ድንጋጤዋን እየገለፀችና
የሆነ ሰው ሊሰርቃቸው በመድፈሩ እየተገረመች በእርጋታ ትቆማለች። እሷ
በፍፁም ልጅ የላትም

ሁሉም ሰው የሚያውቀው ልጅ እንደሌላት ነው በእግዚአብሔር! ከልጅ ጋር
ታይታ ታውቃለች? ያ ባለወርቃማ ፀጉርና ባለ ሰማያዊ አይን ልጅ በጣም የሷ ልጅ እንደሚመስል አታውቅም በዚያ ላይ ብዙ የተራራቁ የአክስትና የአጎት
ልጆች አሏት። እና የስጋ ዘመድም ቢሆን የሆነ አምስተኛ ወይም ስድስተኛ
ሩቅ የሆነ ዘመድ ያው ሌባ ነው።

ፀ እና ያቺ አያት ተብዬ ከያዘችው እጅግ መጥፎ የተባለው ቅጣት ያገኘዋል።
በዶሮ ጩኸት ንጋት እየመጣ መሆኑ ይሰማል።

ፀሀዩዋ በአድማስ ላይ እየመጣች ነው:: ትንሽ ከቆየ ለመሄድ በጣም የዘገየን እንሆናለን፡ የጠዋት ባቡር በጣቢያው በኩል ያልፋል፡ እና አያትየው በሩን
ከፍታ መሄዳችንን እስክታውቅ ድረስ ብዙ ሰዓታት ያስፈልጉናል። የሚፈልጉን ሰዎች ትልክብንም ይሆናል፡ ለፖሊስ ታስታውቃለች? ወይስ በመጨረሻ
ልታስወግደን ስለቻለች በመሄዳችን ትደሰታለች?

ተስፋ በመቁረጥ ውጪውን ለማየት በደረጃው ጣሪያው ስር ወዳለ ክፍል ወጣሁ: ጭጋጋማና ቀዝቃዛ ነው: ያለፈው ሳምንት የጣለው በረዶ ጣራው ላይ እዚህም እዚያም ይታያል፡ ደስታና ነፃነት ሊያመጣልን የማይችል ፈዛዛና
ክሪስ የትም ይሁን የት ወይም ምንም እየሰራ ይሁን እሱም እንደሚሰማውና
ሚስጥራዊ ቀን ነው እንደገና ዶሮ ሲጮህ ሰማሁ: በጣም ሩቅ ይመስላል።ክሪስ የትም ይሁን የት ወይም ምንም እየሰራ ይሁን እሱም እንደሚሰማውና እንዲፈጥን እንዲያደርገው ፀለይኩ ክሪስ ቀስ ብሎ ወደ ክፍላችን የሚገባበትን ያቺን ማለዳ አስታውሳታለሁ ኬሪ አጠገቤ ተኝታ እኔ ደግሞ የክፍላችን በር እንደተከፈተ ቶሎ እንድነቃ በሰመመን እንቅልፍ ላይ እሆናለሁ: ልብሶቼን ለባብሼ ለመሄድ ተዘጋጅቻለሁ። ክሪስ ተመልሶ መጥቶ እስኪያድነን ድረስ እጠብቃለሁ ድንገት ክሪስ እያመነታ ክፍሉ ውስጥ ገባ የፈዘዙ አይኖቹ ወደ እኔ እየተመለከቱ ነው፡ ከዚያ
ወደ እኔ አቅጣጫ መጣ: መፍጠን የሚገባውን ያህል እየቸኮለ አይደለም።
ወዲያው ይዞት ሄዶ የነበረውን የትራስ ልብስ ተመለከትኩ ባዶ ይመስላል።
“ጣጌጦቹ የታሉ?” ስል ጠየቅኩት። “ለምንድነው የቆየኸው!? በመስኮት
ተመልከት፣ ፀሀዩዋ እየወጣች ነው: ወደ ባቡር ጣቢያው በሰዓቱ አንደርስም”ድምፄ ጠንካራ፣ ከሳሽና የንዴት ነበር “እንደገና አዛኝ ሆንክ አይደል? ለዚያ
ነው የእናታችንን ጌጣጌጦች ሳትይዝ የመጣኸው!” አልኩት።

በዚህ ጊዜ አልጋው ጋ ደርሶ ባዶውን የትራስ ጨርቅ በእጁ እንዳንጠለጠለ
ቆሞ ነበር።

“የሉም… ሁሉም ጌጣጌጦች የሉም” አለ።

“የሉም?” አልኩት በቁጣ እየዋሸ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ። እየሸፈነላት
ነው እናታችን በጣም የምትወዳቸውን ነገሮች ሊወስድባት አልፈለገም።
ከዚያ አይኖቹን ተመለከትኩ፡ “የሉም? ክሪስ ጌጣጌጦቹ እኮ ሁሌም እዚያው ነው የሚሆኑት ግን ምን ሆነሀል? ለምንድነው እንግዳ ፀባይ ያሳየኸው?
አልጋው አጠገብ በጉልበቱ ተንበረከከ አጥንት የሌለው ይመስል ተልፈስፍሶ
ፊቱን ደረቴ ውስጥ ቀበረ፡ ከዚያ ይንሰቀሰቅ ጀመር: አምላኬ! ምንድነው
ነገሩ? ለምንድነው የሚያለቅሰው? ወንድ ልጅ ሲያለቅስ መስማት ይከብዳል።

በክንዶቼ ያዝኩት: በእጆቼ ፀጉሩን፣ ጉንጩን፣ ክንዶቹንና ጀርባውን
እየዳበስኩና እየሳምኩት ላባብለው ጥረት አደረግኩ የሆነ ከባድ ነገር
እንደተፈጠረ አውቄያለሁ: ሲከፋው እናታችን ስታደርግለት እመለከት
የነበረውን ነገሮች እያደረግኩለት ነው: እና ስሜቱ ተቀስቅሶ ልሰጠው
ከምፈቅደው በላይ እንደማይፈልግ ስለማውቅ አልፈራሁም እንዲናገር
እንዲያብራራልኝ ማስገደድ ነበረብኝ፡

ሳጉ እየተናነቀው መዋጥ ነበረበት እምባውን ጠረገና ፊቱን በአንሶላው ጠርዝ
አደረቀ ከዚያ አይኖቹን ዞር አድርጎ ገሀነምና ቅጣቱን
ወደሚያሳየው አስፈሪ
ስዕል ተመለከተ። ንግግሩ በአብዛኛው እየተቆራረጠና ለቅሶውን ለመመለስ ሲሞክር እየቆመ ነበር።

በጉልበቱ አልጋው አጠገብ እንደተንበረከከ፣ የሚንቀጠቀጡ እጆቹን እንደያዝኩ አስጠንቅቆኝ መናገር ጀመረ: አስቀድሜ እንድጠነቀቅ የነገረኝ ቢሆንም ሰውነቱ እየራደና ሰማያዊ አይኖቹ ጠቁረው ሊያስደነግጠኝ እንደሚችል
ለሰማሁት ነገር ግን በጭራሽ አልተዘጋጀሁም ነበር።

በከባዱ ተነፈሰና ጀመረ። “ልክ ወደ ክፍሏ እንደገባሁ የሆነ የተለየ ነገር እንዳለ
አውቄያለሁ: የክፍሉን መብራት ሳላበራ የያዝኩትን ባትሪ ብቻ በመጠቀም
ዙሪያውን ስመለከት ማመን አልቻልኩም! መሄዳችንን የሚያዘገይ፣ የሚያጠፋ
👍30🤔1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

...“እናታችንን መዝረፍ አለመቻሌ ሲገባኝ አያትየው ክፍል ሄጄ ለመስረቅ ወሰንኩ” አለኝ።

አምላኬ አይሆንም... ማድረግ አይችልም ግን ደግሞ በጣም ጥሩ በቀል ነው! ስል አሰብኩ። “ታውቂያለሽ… ጌጣጌጦች አሏት: ጣቶቿ ላይ ብዙ ቀለበቶች እና በዚያ ላይ የደንብ ልብሷ አንድ ክፍል እንደሆነ ሁሉ እድሜዋን
በሙሉ የምታደርገው የአልማዝ ጌጥ አላት እንደገናም በገና ግብዣው ላይ አድርጋቸው ያየናት እነዚያ አልማዞችም አሉ። እሷ የሚሰረቅ ብዙ ነገር እንዳላት አውቄያለሁ: በጨለማው መተላለፊያ አቋርጬ በጣቶቼ
እየተራመድኩ የአያትየው የተዘጋ ቢሮ ጋ ደረስኩ።”

ያንን ለማድረግ መድፈሩ እኔ መቼም በፍፁም . . .

“በበሩ ስር የሚታየው ቀጭን ቢጫ የብርሀን መስመር አሁንም እንቅልፍ
እንዳልተኛች እያስጠነቀቀኝ ነበር፡ ምርር አለኝ፡ መተኛት ነበረባት። ሁኔታዎቹ ያ ብርሀን እዛው እንድቆይና አሁን ካደረግኩት የባሰ አጉል ነገር እንዳላደርግ
አደረገኝ ወይም አሁን አንቺ የድርጊት ሰው ከሆንሽ በኋላ አንድ ቀን የቃልሽ ሰው ለመሆን እቅድ ስላለሽ “ድፍረት” ብለሽ ልትጠሪው ትችይ ይሆናል:"

“ክሪስ ከርዕሱ አትሽሽ! ቀጥል! ምን አይነት የእብደት ስራ እንደሰራህ ንገረኝ! አንተን ብሆን ኖሮ ፊቴን አዙሬ ቀጥታ ወደዚህ እመለስ ነበር!”

“እኔ አንቺን አይደለሁማ ካተሪን፣ እኔ እኔ ነኝ... ትንሽ ጥንቃቄ ተጠቅሜ
በቀስታ በሩን በትንሹ ከፈትኩ… በእያንዳንዷ ሰኮንድ ሲከፈት ድምፅ ያሰማል ብዬ ፈርቼ ነበር። ነገር ግን የሆነ ሰው መታጠፊያውን ዘይት አጥግቦታል:: እና እሷ ታየኛለች ብዬ ሳልፈራ በተከፈተው በር ወደ ውስጥ ተመለከትኩና ወደ ውስጥ ገባሁ:"

“እርቃኗን ሆና አየሀት?!” አቋረጥኩት።

“አይ!” ትዕግስት ባጣና በተናደደ አይነት መለሰልኝ፡ “እርቃኗን ሆና አላየኋትም እና በዚያም ደስ ብሎኛል፡ አልጋ ውስጥ ብርድ ልብሱ ስር ነበረች: እጅጌው ረጅም የምሽት ገዋን ለብሳ ተቀምጣ ነበር በትንሹ እርቃኗን ሆና አይቻታለሁ። ታውቂዋለሽ ያ የምንጠላው ብረት የሚመስለው ፀጉሯ
ጭንቅላቷ ላይ አልነበረም ሌሊት ድንገት አስቸኳይ ነገር ቢያጋጥም
አጠገቧ መሆኑን እርግጠኛ ለመሆን የፈለገች ይመስል ቅርብ ኮመዲኖ ላይ
ተቀምጧል"

“ዊግ ነው የምታደርገው?” ብዬ በመገረም ጠየቅኩት ግን ማወቅ ነበረብኝ

“አዎ ዊግ ታደርጋለች የክሪስማስ ግብዣው ዕለት ያደረገችውም ፀጉር ሳይሆን ዊግ ነበር። ጭንቅላቷ ላይ የቀረው ፀጉር የሳሳና ወደ ቢጫ የሚያደላ ነጭ ነው፡ እና ጭንቅላቷ ፀጉር የሌለባቸው ሰፋፊ ሮዝ ቦታዎች አሉት ረጅሙ አፍንጫዋ ጫፍ ላይ ጠርዝ የሌለው መነፅር ሰክታ ትልቅ ጥቁር መፅሀፍ ቅዱስ ታነባለች አሁን ከእሷ መስረቅ እንደማልችል ሳውቅ እየተመለከትኳት
መፅሀፍ ቅዱሱ ውስጥ ያቋረጠችበትን ቦታ በፖስት ካርድ ምልክት አድርጋ ኮመዲኖው ላይ አስቀመጠችና ከአልጋዋ ወርዳ ተንበረከከች ከዚያ አንገቷን አቀርቅራ እኛ እንደምናደርገው እጆቿን አገጯ ስር አደራርባ ረጅም ፀሎት ፀለየች:: ከዚያ ጮክ ብላ “ጌታ ሆይ ስለ ኃጢአቴ ይቅር በለኝ፡ ሁልጊዜ የምሰራው ጥሩ ነው ብዬ የማስበውን ነው እና ስህተቶች ከሰራሁ እባክህ ትክክል ለመስራት አስቤ እንደሆነ እመንልኝ በአንተ አይኖች ለዘለዓለም ፀጋ
ላግኝ አሜን ከተንበረከከችበት ተነስታ አልጋዋ ውስጥ ገባችና መብራቱን አጠፋች አዳራሽ ውስጥ ቆሜ ምን እንደማደርግ አሰብኩ ባዶ እጄን ወዳንቺ ተመልሼ መምጣት አልቻልኩም:: ምክንያቱም አባታችን ለእናታችን የሰጣትን ቀለበቶች እንደማንሽጣቸው ተስፋ አድርጌያለሁ "

ቀጠለ. አሁን እጆቹ ፀጉሬ ላይ ናቸው፡ ጭንቅላቴን እየዳበሱኝ ነው። “ ወደ ዋናው ክፍል ሄድኩና የወንድ አያታችንን ክፍል አገኘሁት፡ በሩን ከፍቼ ያንን እዚያ ተጋድሞ ከአመት አመት ሞቱን የሚጠብቀውን ሰው
የመጋፈጥ ድፍረት እንዳለኝ አላውቅም ነበር።

“ግን ይህ ብቸኛው እድሌ ነው: እጠቀምበታለሁ። የመጣው ይምጣ ብዬ

ልክ እንደ እውነተኛ ሌባ ድምፅ ሳላሰማ በደረጃው ወደ ታች ወረድኩ።ትልልቆቹን ውድ ክፍሎች አየሁ። በጣም ግዙፍና የሚያምሩ ነበሩ ልክ አንቺ እንደምታስቢው እኔም እንደዚህ አይነት ቤት ውስጥ ስለማደግ አሰብኩ
በብዙ ሰራተኞች ተከቦ ሁሉ ነገር በሰው ሲቀርብ ያለውን ስሜት አሰብኩ።
ኦ ካቲ፣ በጣም ቆንጆ ቤት ነው እቃዎቹ ከቤተመንግስት የመጡ መሆን አለባቸው: እናታችን ብዙ ጥያቄዎች ትጠይቂያት ስለነበር ወደ ቤተ መፃህፍት
የሚወስደውን መንገድ አውቄዋለሁ እና ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ካቲ?
ብዙ ጥያቄዎች በመጠየቅሽ በጣም ደስ ብሎኛል ባይሆን ኖሮ ከመሀሉ ተነስተው ወደ ግራና ወደቀኝ የሚታጠፉ ብዙ አዳራሾች ስለነበሩ ይጠፉብኝ ነበር:

“ግን ወደ ቤተመፃህፍቱ መሄድ በጣም ቀላል ነበር። ረጅም፣ ጨለማማ፣ በጣም ግዙፍ ክፍል ሆኖ ልክ እንደመቃብር ስፍራ ፀጥ ያለ ነው::"

ለመስማት የምናፍቀው የነበረውን ነገር እየነገረኝ ነው: በረጅሙ ተነፈስኩ።
መሳቢያዎቹ ውስጥ ገንዘብ እንደሚደበቅ ገምቻለሁ። ስለዚህ ባትሪዬን እያበራሁ
እያንዳንዱን መሳቢያ መፈተሽ ጀመርኩ አንዳቸውም አልተቆለፉም: እና ሁሉም ባዶ፣ ሙሉ በሙሉ ባዶ በመሆናቸው አለመቆለፋቸው አይገርምም እነዚያ ሁሉ ባዶ መሳቢያዎች፣ የወረቀት መያዣዎች፣ እርሳሶች፣
እስኪሪብቶዎች፣ ማስታወሻ ደብተሮች የመሳሰሉት ነገሮችን ለማስቀመጥ
ካልተጠቀሙባቸው መሳቢያው ለምን ይጠቅማል? ወደ ሀሳቤ የመጡት ጥርጣሬዎች ምን እንደሆነ አታውቂም: የዚያን ጊዜ ነው ከቤተመፃህፍቱ
ባሻገር ያለው የወንድ አያቴ ክፍል ለመግባት የወሰንኩት በመጨረሻ ላገኘው ነው... ከምጠላው አያቴ… እንዲሁም አጎቴ ጋር ፊት ለፊት ልገናኝ ነው:
“ግንኙነታችንን በሀሳቤ ሳልኩት እሱ አልጋ ላይ ነው ታሟል። ግን አሁንም
መብራቱን አበራዋለሁ: ከዚያ ያየኛል ትንፋሽ ያጥረዋል። ይለየኛል... ማን እንደሆንኩ ማወቅ አለበት: አንድ ጊዜ ሲያየኝ ወዲያውኑ ያውቃል፡ ከዚያ
እኔ “አያቴ… እንዲወለድ ያልፈለከው የልጅ ልጅህ እኔ ነኝ. እለዋለሁ:: ፎቁ ላይ በሰሜን በኩል ባለው የመኝታ ክፍል ውስጥ የተቆለፈባቸው ሁለት እህቶች አሉኝ በአንድ ወቅት ታናሽ ወንድምም ነበረኝ፡ አሁን ግን ሟቷል እንዲገድሉት ረድተሀቸዋል” ይሄ ሁሉ አእምሮዬ ውስጥ ነበር።ግን አንዳቸውንም ስለማለቴ ተጠራጥሬያለሁ። አንቺ ብትሆኚ ግን ጮኸሽ እንደምታወጪው ጥርጣሬ የለኝም:: ልክ ኬሪ ራሷን የምትገልፅበት ቃላት
ሲኖራት እንደምታደርው አይነት ማለቴ ነው አንቺ ግን ቃላቶቹ አሉሽ ምናልባት እናገረዋለሁ፣ ሲሸማቀቅ አይቼ እደሰት ይሆናል ወይም ምናልባት ሀዘኔታ ያሳይ ይሆናል ወይም በህይወት በመኖራችን የጋለ ብስጭት ያድርበት ይሆናል፡ ይህንን አውቃለሁ ከአሁን በኋላ ግን ለተጨማሪ አንድ ደቂቃ
እንኳን እስረኛ ሆኜ ኬሪም እንደ ኮሪ ስትሞት ማየትን መቋቋም አልችልም::

ትንፋሼን ዋጥኩ። አሁንም ሞቱን በሚጠብቅበት አልጋ ላይ ተጋድሞ፣ ያ ጠንካራ የመዳብ የሬሳ ሳጥን እስኪገባበት እየጠበቀው ቢሆንም የምንጠላውን
👍502
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...“እኔስ ማሬ? እኔን አግኝተሻል። ቢያንስ የምትቀጥለዋ ቆንጆ እስክትመጣ ድረስ አለሁልሽ”

“እና እኔ ከሶፋው ጀርባ ሆኜ ይህንን ስሰማ በድንጋጤ ፈዘዝኩ። ሊያስመልሰኝ የተዘጋጀሁ መሰለኝ ግን ፀጥ ብዬ ተጋድሜ ጥንዶቹ ሶፋ ላይ ሆነው ሲያወሩ እያዳመጥኩ ነበር። ብድግ ብዬ በፍጥነት ወዳንቺና ወደኬሪ ሮጬ መምጣትና
ከመዘግየቱ በፊት ከዚህ ላስወጣችሁ ፈለግኩ።

“ግን ተይዣለሁ ብንቀሳቀስ ያዩኛል። በዛ ላይ ጆን ከሴት አያትየው ጋር
ዝምድና አለው፡ ጆን የአያትየው መተማመኛ ሳይሆን አይቀርም አለበለዚያ መኪናዎቿን እንዲጠቀም ያን ያህል ነፃነት አትሰጠውም ነበር። ካቲ፣
አይተሽው ታውቂያለሽ እኮ… የክሪስማስ ግብዣው ቀን የአገልጋዮች ልብስ ለብሶ የነበረው ?መላጣ ሰውዬ ነው” ማንን ማለቱ እንደሆነ አውቄያለሁ ግን የራሴ የመደንገጥ ድንዛዜ ተሰምቶኝ መናገር ስላቃተኝ፣ ማድረግ የቻልኩት ዝም ብዬ መጋደም ብቻ ነበር።

ክሪስ ቀጠለ። “ሶፋው ጀርባ እንደተደበቅኩ ጆንና ሰራተኛዋ መላፋት ጀመሩ። ልብሶቿን ማውለቅ ሲጀምርና እሷም የእሱን ልታወልቅ ስትጀምር እንቅስቃሴዎቻቸው ይሰማኛል።" “አንዳቸው የሌላኛቸውን ልብስ አወለቁ?” ስል ጠየቅኩት። “ልብሱን እንዲያወልቅ የምር አገዘችው?”
“እንደዛ ነው የተሰማኝ አለኝ በግድየለሽነት:

“አልጮኸችም፣ አልተቃወመችውም?”

“አልተቃወመችውም፡ እሷም ፈልጋ ነበር! አምላኬ ሆይ እና በጣም ረጅም ጊዜ ወሰደባቸው! ካቲ
የሚያወጡትን ድምፅ አታምኚም! ታቃስታለች፣ትጮሀለች አየር ያጠራት ትመስላለች፣ ታለከልካለች እና እሱ ደግሞ እንደ አሳማ ያጓራል ግን እዛ ላይ በጣም ጥሩ ሳይሆን እንደማይቀር እገምታለሁ::
ምክንያቱም በመጨረሻ ሠራተኛዋ እንዳበደ ሰው ነበር የጮኸችው። ከዚያ ሲያልቅ ጋደም ብለው ሲጋራ እያጨሱ እዚህ ቤት ስለሚደረገው ነገር እያወሩ ነበር። እመኚኝ የማያውቁት በጣም ጥቂት ነገሮችን ብቻ ነው። ከዚያ ለሁለተኛ
ጊዜ ፍቅር ሰሩ:"

“በአንድ ምሽት ሁለት ጊዜ?”

“ይቻላል።”

“ክሪስ ለምንድነው አነጋገርህ የተቀየረው?”

አመነታ፤ ትንሽ ራቅ አለና ፊቴን አጠና። “ካቲ እያዳመጥሽኝ አይደለም? ሁሉንም ነገር ልክ እንደሆነው አድርጌ ለአንቺ ለመንገር ትልቅ ህመም ውስጥ
ነኝ። አልሰማሽኝም?”

መስማት? አዎ ሰምቼያለሁ ሁሉንም:

የእናታችንን ጌጣጌጦች ለመዝረፍ ብዙ ጊዜ ጠበቀ።

እናታችንና ባሏ ሌላ ሽርሽር ሄዱ። ይሄ ምን አይነት ዜና ነው? ሁልጊዜ
ይመጣሉ… ይሄዳሉ፤ ከዚህ ቤት ለመውጣት ምንም ነገር ያደርጋሉ። እና እወቅሳቸዋለሁ ማለት አልችልም: እኛስ ተመሳሳይ ነገር ልናደርግ ተዘጋጅተን
የለ? ቅንድቦቼን ወደ ላይ ሰቅዬ ክሪስን በጥያቄ አስተያየት ተመለከትኩት ያልነገረኝ
የሆነ የሚያውቀው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው: አሁንም እየተከላከለላት ነው። አሁንም ይወዳታል

ካቲ” ሲል ጀመረ፡ ድምፁ እየተቆራረጠ ነው

“ምንም አይደል ክሪስ፣ እየወቀስኩህ አይደለም ውዷ፣ ጣፋጯ፣ ደጓና አፍቃሪዋ እናታችን ከመልከመልካም ወጣት ባሏ ጋር ጌጣጌጣቸውን ሁሉ ይዘው ሌላ ሽርሽር ሄዳለች፡ በውጪው አለም ያለውን ጥበቃ ደህና ሁን
በለው: ግን አሁንም እሄዳለሁ! እንሰራለን ራሳችንን የምንደግፍበት መንገድ እንፈልጋለን፡ ከዚያ ኬሪ እንደገና ደህና እንድትሆን ለዶክተር እንከፍላለን፡ዠ ስለጌጣጌጦች አትጨነቅ፤ ስለ እናታችን ርህራሄ የለሽ ድርጊት አትጨነቅ።
የት እንደምትሄድ፣ መቼ እንደምትመለስ እንኳን አልነገረችንም: አሁን አስቀያሚ መጥፎ የማናስብ ቸልተኞች እንድንሆን ተትተናል፡ ታዲያ ይሄ
ሁሉ ዕንባ ለማን? ለምን?

"ካቲ!” ተቆጣ በእምባ የረጠበ ፊቱን ወደ እኔ መልሶ አይኖቼ ላይ አተኮረ:
“ለምንድነው የማታዳምጪውና የሆነ ነገር የማትይው? ጆሮሽ የት ነው? ያልኩትን ሰምተሽኛል? ወንድ አያታችን ሞቷል! ከሞተ አንድ አመት ገደማ ሆኖታል!”

ምናልባት በደንብ አልሰማሁትም፤ በጥንቃቄ አላዳመጥኩትም ማለት ነው ሀዘኑ ምንም ነገር እንዳልሰማ አድርጎኛል ማለት ነው አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ መታኝ አያትየው በእውነት ከሞተ እጅግ መልካም ዜና ነው አሁን እናታችን ውርስ ታገኛለች… ሀብታም እንሆናለን…በሩን ትከፍትልናለች… ነፃ ታደርገናለች:: አሁን ለማምለጥ መሞከር የለብንም:

ሌሎች ሀሳቦች ጎረፉ አስደንጋጭ የጥያቄ ጎርፍ መጣብኝ። እናታችን አባቷ መሞቱን አልነገረችንም:: እነዚህ አመታት ለእኛ እንዴት ረጃጅም እንደሆኑ እያወቀች፣ ለምን በጨለማ ሁልጊዜ በመጠበቅ ውስጥ አስቀመጠችን? ለምን?
ግራ ተጋባሁ። ተደናገረብኝ፤ የትኛው ስሜት እንደሚሰማኝ አላውቅኩም። ደስታ ይሁን ሀዘን ሀሳቤን አለመቁረጤን ሽባ የሚያደርግ እንግዳ ፍርሀት
አስቆመኝ።

“ካቲ…” አለኝ ክሪስ በሹክሹክታ። ለምን ማንሾካሾክ እንዳለበት አላወቅኩም ኬሪ እንደሆነች አትሰማም: የእሷ አለም ከእኛ በእጅጉ ተለይቷል ኬሪ
በህይወትና በሞት መካከል ተንጠልጥላለች: በእያንዳንዱ ቅፅበት ወደ ኮሪ እየተጠጋች ነው: ራሷን በማስራብ ያለ ግማሽ አካሏ ለመኖር መፈለጓን ትታዋለች። “እናታችን ሆን ብላ አታላናለች: ካቲ አባቷ ሞቶ ከወራት በኋላ
ኑዛዜው ተነቧል። እና ሳትነግረን ፀጥ ብላ ሞታችንን እንድንጠብቅ እዚህ ተወችን፡ ከዘጠኝ ወራት በፊት ሁላችንም በዘጠኝ ወራት ጤናማ ነበርን! አባቷ የሞተ ጊዜ ከዚህ አስወጥታን ቢሆን ወይም ኑዛዜው የተነበበ ጊዜ እንኳን ወጥተን ቢሆን ኮሪ አሁን በህይወት ይኖር ነበር፡"

ስሜቴ ተጎድቶ እናታችን ልታሰምጠን የቆፈረችው ጥልቅ የክህደት ጉድጓድ ውስጥ ወደቅኩ። ማልቀስ ጀመርኩ።

“ዕንባሽን ለበኋላ አቆይው" አለ ክሪስ ራሱም እያለቀሰ ነው። “ሁሉንም ነገር አልሰማሽም ሌላም አለ። ብዙና የከፋ”

“ብዙ?” ሌላ ምን ብዙ ነገር ሊነገረኝ ይችላል? እናታችን ከእንግዲህ
ከማትወዳቸውና ከማትፈልጋቸው ልጆቿ ጋር መካፈል የማትፈልገውን
ንብረት በማካበት ሂደት ውስጥ ኮሪን የገደለች፣ውሽታም፣ አታላይና
ወጣትነታችንን የሰረቀች ሌባ መሆኗ ተረጋግጧል። በዚያ ምሽት ደስተኛ ባለመሆናችን ትንሽዋን ንስሀችንን ስትሰጠን ምን መጠበቅ እንዳለብን እንዴት አሳምራ እንዳብራራችልን! የዚያን ጊዜ አያታችን የሰራት አይነት
ሴት እንደምትሆን ታውቅ ወይስ ትገምት ነበር ይሆን? ክሪስ ክንዶች ላይ ወደቅኩና ደረቱን ተደገፍኩ “ከዚህ በላይ አትንገረኝ! የሰማሁት ይበቃኛል ከዚህ በላይ እንድጠላት አታድርገኝ! አልኩት።

“መጥላት. ጥላቻ ምን እንደሆነ ገና ማወቅ አልጀመርሽም ግን የቀረውን
ከመናገሬ በፊት ምንም ቢሆን ይህንን ቦታ ለቀን እንደምንሄድ አስቢ።እንዳቀድነው ወደ ፍሎሪዳ እንሄዳለን በፀሀይ ብርሀን ውስጥ እንኖራለን::እና ህይወታችንን በቻልነው ሁሉ በጣም ጥሩ እናደርገዋለን። ማን በመሆናችን ወይም በስራነው ለአንዲት ሰኮንድ እንኳን ሳናፍር እንኖራለን።
በመሀከላችን የተፈጠረው ነገር እናታችን ካደረገችው ጋር ሲነፀር ምንም ማለት አይደለም ከእኔ በፊት ብትሞቺም እንኳን፣ እዚህ ጣሪያ ስር ያለው ክፍል የነበረንን ህይወት ሁልጊዜ አስታውሰዋለሁ: በወረቀት አበባዎቹ ስር ስንደንስ አንቺ በጣም ግርማ ያለሽ እኔ ደግሞ ገልጃጃ ሆኜ የአቧራውንና የበሰበሰ እንጨቱን ሽታ ልክ እንደ ጣፋጭ ሽቶ አስታውሰዋለሁ ምክንያቱም
ህይወቴ ያላንቺ በጣም ቀፋፊና ባዶ ነው የሚሆነው። ፍቅር ምን ሊሆን
እንደሚችል የመጀመሪያውን ጣዕም ሰጥተሽኛል።
👍403🥰3👎2😢2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አርባ_ሶስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የጨሻው መጀመርያ

“ምን እንደነገረቻቸው ገምቺ…” ክሪስ ቀጠለ “ክፍሉ በወሩ መጨረሻ
በሚመጣው አርብ እንዳይፀዳ የፈለገችበትን ምክንያት ገምቺ።

“እንዴት መገመት እችላለሁ? እኔ የእሷ አይነት አእምሮ የለኝም:" ጭንቅላቴን ነቀነቅኩ። ሠራተኞቹ ወደዚህ መምጣት ካቆሙ ብዙ ጊዜያቸው ነው እነዚያን
አስፈሪ የመጀመሪያ ሳምንታት ረስቻቸው ነበር፡

“አይጦች ካቲ...” አለ ክሪስ ሰማያዊ አይኖቹ ቀዝቃዛና ጠንካራ ሆነዋል
“አይጦች አያትየው የፈጠረቻቸው ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ የሚገኙ በመቶ የሚቆጠሩ አይጦች ከሁለተኛ ፎቅ በደረጃ ወደታች የሚወርዱ
ትናንሽ ብልጥ አይጦች፣ አርሰኒክ የተደረገበት ምግብ ትታላቸው በሩን
ቆልፋባቸው ልትሄድ የምትገደድባቸው ትንንሽ ጨካኝ አይጦች”

ሠራተኞቹ እዚህ አካባቢ እንዳይደርሱ ግሩምና ድንቅ ታሪክ እንደሆነ አሰብኩ ጣራው ስር ያለው ክፍል በአይጥ ተሞልቷል። አይጦቹ በደረጃውም
ይወርዳሉ።

“አርስኒክ ነጭ ነው ካቲ፣ ከተፈጨ ስኳር ጋር ሲቀላቀል ምሬቱ አያስታውቅም

ጭንቅላቴ ተሽከረከረ! በየቀኑ በሚመጣልን አራት ዶናት ላይ ያለው የተፈጨ
ስኳር! ለእያንዳንዳችን አንድ አንድ: አሁን ግን ቅርጫቱ ውስጥ ሶስት ብቻ ነው: “ግን ክሪስ ታሪክህ ምንም ስሜት አይሰጥም አያትየው በአንድ ጊዜ ብዙ መርዝ ሰጥታ ልትገድለን ስትችል ለምን ቀስ በቀስ ትመርዘናለች? ለምን
በአንዴ አትገላግለንም?”

ጭንቅላቴ በመዳፎቹ መሀከል ሆኖ በረጃጅም ጣቶቹ ፀጉሬን እየዳበሰኝ ነበር።ቀስ ባለ ድምፅ ተናገረ “በቲቪ ያየነው የሆነ ያረጀ ፊልም አስታውሺ
አስታውሺ ለሽማግሌው ለሀብታሙ ሰውዬ ቤት የምትጠብቅለትን ያቺን ትንሽ ሴት ካመኗት፣ ከወደዷትና ኑዛዜያቸው ውስጥ ካስገቧት በኋላ
በየቀኑ ትንሽ ትንሽ አርሰኒክ ትመግባቸው አልነበር? በየቀኑ ትንሽ ትንሽ
አርሰኒክ ሲወሰድ ቀስ በቀስ ወደ ሰውነታችን ይሰርግና በየቀኑ ተጠቂው ትንሽ ትንሽ እያመመው ይመጣል፤ በጣም ብዙ ግን አይታመምም ትንንሽ
የራስ ምታቶች የአንጀት መቆጣት እና የመሳሰሉት በቀላሉ መገለፅ የሚችሉ
ህመሞች ያጋጥሙታል ተጠቂው ሲሞት፣ ለምሳሌ ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን
መጀመሪያውኑ ከስቶ፣ ደም ማነስ ይዞትና ረጅም የህመም ታሪክ፣ የጉንፋን
አይነት ትኩሳት፣ ብርድና የመሳሰሉት ይታዩበታል እና ተጠቂው የሳምባ ምች ምልክቶችን ሁሉ ቢያሳይም ልክ እዛ ፊልም ላይ እንዳየነው ዶክተሮቹ
መመረዝ መሆኑን አይጠራጠሩም:”

ኮሪ!” ትንፋሽ አጠረኝ: “ኮሪ የሞተው በአርሰኒክ ተመርዞ ነው? እናታችን የገደለው የሳምባ ምች ነው ብላን ነበር”

“የምትፈልገውን ልትነግረን አትችልም? እውነቱ መናገሯን በምን
እናውቃለን? ምናልባት ሆስፒታል ወስዳውም ላይሆን ይችላል። ወስዳውም ከሆነ ዶክተሮቹ ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ሞት መሆኑን አልጠረጠሩም ማለት ነው። እንደዛ ባይሆን ኖሮ አሁን እስር ቤት ትሆን ነበር”

“ግን ክሪስ” ተቃወምኩ። “እናታችን አያትየው መርዝ እንድታበላን አትፈቅድም! ያንን ገንዘብ እንደምትፈልገው አውቃለሁ፤ በፊት የምትወደንን ያህል እንደማትወደንም ይገባኛል፤ ግን አሁንም ልትገለን አትፈልግም”

ክሪስ ጭንቅላቱን ወደጎን ዘምበል አደረገ፡ “እሺ አንድ ሙከራ እናድርግ፤ ለኮሪ ጓደኛ አይጥ ትንሽ የተፈጨ ስኳር ያለበት ዶናት እንስጠው”

“አይሆንም! በሚወደንና በሚያምነን ላይ እንደዚህ ማድረግ አንችልም ኮሪ
ያንን ግራጫ አይጥ ይወደው ነበር። ክሪስ፣ ሌላ አይጥ እንይዛለን” ካቲ አይጡ አርጅቷል፡ በዚያ ላይ እግሩ ሽባ ነው፡፡ አይጥን ከነህይወቱ መያዝ ደግሞ ከባድ እንደሆነ ታውቂያለሽ፡ ከዚህ ስንሄድ ነፃ ስንለቀው አሁን የቤት እንስሳ ስለሆነ መኖር አይችልም በእኛ ላይ ጥገኛ ሆኗል።"

ከእኛ ጋር ይዘነው እንድንሄድ አስቤ ነበር

“በዚህ መንገድ ተመልከቺው ካቲ። ኮሪ ሞቷል፣ ገና መኖር እንኳን አልጀመረም ነበር። ዶናቶቹ መርዝ ከሌለባቸው አይጡ በህይወት ይቆያል፡ ከዚያ ይዘነው መሄድ እንችላለን፡ የግድ ካልሽ ማለቴ ነው: አንድ ነገር እርግጥ ነው፣ማወቅ አለብን፡ ለኬሪ ስንል እርግጠኛ መሆን አለብን: ተመልከቻት፡ እሷም
"እየሞተች እንደሆነ አይታይሽም? ከቀን ቀን ጤና እያጣች ነው። እኛም እንደዚያው

ተጠግቶ እኛን፣ ያ ትንሽ ፍጥረት በሶስቱ ጤናማ እግሮቹ እያነከስ ወደ እኛ መጣ። ወደ ክሪስ ጣቶች ተጠግቶ እኛን፣ ጌቶቹን፣ ወላጆቹን፣ ጓደኞቹን አምኖ ቁንጥር አድርጎ በላ፡፡ ያንን ማየቱ ራሱ ያሳምማል።

አልሞተም! ወዲያውኑ አልሞተም፡ ቀርፋፋ፣ ፈዛዛ፣ ፍላጎት ያጣ ሆነ። በኋላ እንዲያቃስት ያደረገው ትንሽ ህመም ተሰማው፡ በጥቂት ስዓታት ውስጥ ድርቅ ብሎና ቀዝቅዞ በጀርባው ተጋደመ: ሮዝ ጣቶቹ ተቆለመሙ፤ ትናንሽ ጥቁር አይኖቹ ጎደጎዱ። አሁን አወቅን... በእርግጠኝነት ኮሪን የወሰደው
እግዚአብሔር አይደለም!

“አይጡንና የቀሩትን ሁለት ዶናቶች በኪስ ወረቀት ውስጥ አድርገን ወደ
ፖሊስ እንወስደዋለን" አለ ክሪስ በሚያስተማምን አይነት አይኖቹን ከእኔ ዞር እያደረገ፡“አያትየውን እስር ቤት ያስገቧታል” አልኩት
“አዎ” አለና ጀርባውን አዞረ:
“ክሪስ፣ የሆነ ነገር ደብቀኸኛል፡ ምንድነው?”

“በኋላ... ከሄድን በኋላ፡ አሁን ማለት የምችለውን ሁሉ ሳያስመልሰኝ
ተናግሬያለሁ። ነገ በማለዳ ከዚህ እንሄዳለን፡” አለ ምንም አልተናገርኩም እጆቼን በሁለት እጆቹ ይዞ ጭምቅ አደረጋቸውና “በተቻለ ፍጥነት ኬሪን ወደ
ዶክተር መውሰድ አለብን ራሳችንንም ጭምር” አለ ቀኑ በጣም ረጅም ሆነብን፡ ሁሉንም ነገር አዘጋጅተን ስለጨረስን ለመጨረሻ ጊዜ ቲቪው ላይ ከማፍጠጥ በስተቀር ምንም የምንሰራው አልነበረንም ኬሪ
ጥጉ ላይ እንደተቀመጠች ሁለታችን ደግሞ በተለያየ አልጋ ላይ ጋደም ብለን የምንወደውን ተከታታይ የቴሌቭዥን ፊልም እያየን ነው: ሲያልቅ ክሪስ እዚህ ፊልም ውስጥ ያሉት ሰዎች ልክ እንደኛ ናቸው: እምብዛም ወደ ውጪ
አይወጡም ሊወጡም መውጣታቸውን እንሰማለን እንጂ አናይም ሳሎንና መኝታ ቤት ውስጥ ሲንጎራደዱ፣ ወጥ ቤት ቁጭ ብለው ቡና ሲጠጡ ወይም
ቆመው ብራንዲያቸውን ሲጠጡ ነው የምናያቸው: ግን በፍፁም ውጪ ወጥተው አይተናቸው አናውቅም፡ የሆነ ጥሩ ነገር ተፈጥሮ በመጨረሻ ደስተኛ እንደሚሆን ባሰቡ ቁጥር የሆነ መቅሰፍት ይመጣና ተስፋቸውን ሁሉ ያጠፋዋል” አልኩት ድንገት የሆነ ሰው ክፍሉ ውስጥ እንዳለ ተሰማኝ፡ ትንፋሽ አጥሮኝ ዞር ስል
አያትየው ቆማለች: አቋቋሟና ከጨካኝና ንቀት የሚያሳዩ አይኖቿ ለሆነ ጊዜ ያህል እዚያው እንደነበረች ነገሩኝ።

በቀዝቃዛው ድምጽዋ ተናገረች “ከአለም ተነጥላችሁም እያላችሁ ሁለታችሁም እንዴት ሰልጥናችኋል! ህይወት እንዴት እንደሆነ በቀልድ መልክ እያጋነናችሁ ነበር በትክክል ነው የገመታችሁት ምንም ነገር እናንተ በምታስቡት መንገድ
አይሰራም: በመጨረሻ ሁልጊዜም ታዝናላችሁ” አለች:

እኔና ክሪስ አተኩረን ተመለከትናት: ሁለታችንም ፈርተናል። ፀሀዩዋ
አፍንጫዋን ወደ ምሽቱ ውስጥ እየደበቀች ነው:: የምትፈልገውን ተናግራለች: ስለዚህ ወጣችና በሩን ቆለፈች: አልጋዎቻችን ላይ ተቀመጥን፡ ኬሪም ጥጉ
ላይ ተቀምጣለች።

ካቲ፣ የተሸነፍሽ አትምሰይ! እንደገና ተስፋ ልታስቆርጠን እየሞከረች ብቻ
ነው። ምናልባት ምንም ነገር በትክክል አልሄደላት ይሆናል። ያ ማለት ግን እኛ እንሞታለን ማለት አይደለም ምንም ፍፁም የሆነ ነገር እናገኛለን ብለን ሳንጠብቅ እንሂድ። ትንሽ ደስታ እንደሚኖረን ብቻ እንጠብቅ። ተስፋ አንቆርጥም:”
👍47🥰5👏1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

“ቆንጅዬ ልጅ ይዘሻል” አለ ረጅሙ ፖስተኛ በፍርሀት ቀሚሴን ጥብቅ አድርጋ የያዘችውን ኬሪን በአሳዛኝ አይን እየተመለከተ። “ይህንን ስናገር ቅር
ካላላችሁ ትንሽ ያመማት ትመስላለች።”

“አሟት ነበር” ክሪስ አረጋገጠለት፡ “ግን አሁን ይሻላታል” አለው። ፖስተኛው ጭንቅላቱን ነቀነቀ፤ የነገርነውን ያመነ ይመስላል።

“ትኬት ይዛችኋል?”


“ገንዘብ ይዘናል፤ ለትኬቱ ክፍያ የሚበቃ ገንዘብ ይዘናል” አለ

“ስጠኝ ልጄ፤ የአስራ አንድ ሰአት ከአርባ አምስት ደቂቃው ባቡር መጥቷል”
አለው በዚያ ማለዳ ወደ ቻርለትስቪል በሚወስደው ባቡር ስንጓዝ የፎክስወርዝ ግዙፍ ቤት በኮረብቶቹ ላይ ከፍ ብሎ እያየነው ነበር። እኔና ክሪስ አይኖቻችንን
ከእሱ ላይ መንቀል አልቻልንም: እስር ቤታችን ከአይናችን እስኪሰወር ድረስ ውጪ እየተመለከትነው ነበር በተለይ በጥቁር መጋረጃ የተዘጉትን የጣሪያ
ስር ክፍል መስኮቶች እያየናቸው ነበር

ከዚያ ትኩረቴ በሰሜን አቅጣጫ ባለው የሁለተኛው ፎቅ የመጨረሻ ክፍል ሄደ ከባዱ መጋረጃ ተከፍቶና ጥላ የሚመስል ከሩቅ የሚታይ የግዙፍ
አሮጊት ሴት ምስል ወጥቶ ሲፈልገንና… ከዚያ ሲጠፋ ታይቶኝ ክሪስን ጎነተልኩት።

እርግጥ ነው ባቡሩን ማየት ትችላለች: ግን እዚያ ሆነን መንገዶቹን ማየት
እንደማንችለው ሁሉ እሷም እንደማታየን አውቀናል። ቢሆንም ግን እኔና
ክሪስ መቀመጫችን ላይ እንዳለን ወደ ታች ሸርተት አልን፡

“በዚህ ጠዋት ምን ትሰራ ይሆን?” ስል ክሪስን በሹክሹክታ ጠየቅኩት።
“በተለምዶ እስከ አስራ ሁለት ሰአት ተኩል ድረስ ምግባችንን ይዛ አትመጣም”

ሳቀ። የምሬት ሳቅ ይመስላል። “ምናልባት የሆነ ኃጢአት ወይም የተhለከለ ነገር ስንሰራ ለመያዝ ጥረት እያደረገች ይሆናል” አለ። ይሆን ይሆናል። ግን እዚያ ክፍል ውስጥ ገብታ ባዶ ሆኖ ስታገኘውና ልብሶቻችንም ማስቀመጫው ውስጥ ያለመኖሩን ስታይ፣ ከዚያ ስትጣራ፣ ምንም አይነት ድምፅም ሆነ ሮጦ
የሚመጣ የእግር ኮቴ ሳትሰማ ስትቀር የምታስበውንና የሚሰማትን ባውቅ ደስ ይለኝ ነበር።

ቻርለትስቪል ስንደርስ ወደ ሳሪሶታ የሚያደርሰንን የአውቶቢስ ቲኬት ስንገዛ
ወደ ደቡብ የሚሄደውን አውቶቢስ ለመያዝ ሁለት ሰአት መጠበቅ እንዳለብን
ተነገረን።

በሁለት ሰአት ውስጥ ጆን ጥቁሩን ሊሞዝን ይዞ ቀርፋፋውን ባቡር
ይቀድመዋል!” አልኩ
“አታስቢ” አለ ክሪስ፡ “ስለ እኛ ለእሱ የምትነግረው ሞኝ አይደለችም ምናልባት
በራሱ መንገድ ካላወቀ በስተቀር" እንዲከተለን ከተላከም እንዳያገኘን ምርጡ መንገድ አለመቆም እንደሆነ አሰብን ዕቃ ማስቀመጫ ተከራይተን ሁለቱን ሻንጣዎቻችንንና ጊታሩን አስቀመጥን ኬሪን መሀከል አድርገን እጅ ለእጅ ተያይዘን ዋና ዋና መንገዶች
ተከትለን የፎክስወርዝ ሰራተኞች በእረፍት ቀናቸው ዘመድ ለመጠየቅ ዕቃ ለመግዛትና ሲኒማ ለመግባት ወይም በሌሎች መንገዶች ራሳቸውን ለማስደሰት የሚመርጡትን ከተማ በደንብ አየነው። ሀሙስ ቢሆን ኖሮ በጣም
ያስፈራ ነበር። ግን እሁድ ነው።

በልካችን ያልሆኑ ልብሶቻችን፣ ጫማዎቻችን፣ ያልተስተካከለው የፀጉር
ቁርጣችንና የገረጣው ፊታችን ከሌላ አለም የመጡ ጎብኚዎች መስሎኝ ነበር። ግን እንደፈራሁት ማንም አላፈጠጠብንም ልክ የሰው ዘር እንደሆንን ነው የተቀበሉን እንግዳ ፍጡር አልመሰልናቸውም ብዙ ሰዎች ወዳሉበት ቦታ መመለሳችን በጣም ጥሩ ነበር: የተለያዩ ፊቶች ያሉበት ቦታ መሆን።

“ሁሉም እየፈጠነ ወዴት እንደሚሄድ አይገርምም?” ስል ክሪስን ጠየቅኩት:
መወሰን አቅቶን ጥግ ላይ ቆምን፡ ኮሪ የተቀበረው ከዚህ ብዙም ሳይርቅ
እንደሆነ ገመትኩ። መቃብሩን ፈልጌ አበባ ማስቀመጥ በጣም ፈለግኩ።በሌላ ቀን ቢጫ አበቦች ይዘን ተመልሰን እንመጣና ይጥቀምም አይጥቀም ተንበርክከን ፀሎት እናደርስለታለን፡ ለአሁኑ ግን ኬሪን ከአደጋ ለመጠበቅ ወደ ዶክተር ከመውሰዳችን በፊት . . . ከቨርጂኒያ ርቀን በጣም ርቀን መሄድ አለብን

የዚያን ጊዜ ነው ክሪስ በኪስ ወረቀት የያዘውን የአይጥ ሬሳና ስኳር
የተነሰነሰባቸውን ዶናቶች ከጃኬት ኪሱ ያወጣው ኮስታራ አይኖቹ ከአይኖቼ
ጋር ተገናኙ ኪስ ወረቀቱን ፊት ለፊቴ ይዞ ፊቴን እያጠና በአይኖቹ “አይን ላጠፋ አይን?” እያለ ጠየቀኝ፡

“ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደን ታሪካችንን መናገር እንችላለን" አለ ክሪስቶፈር
አይኖቹን ከእኔ እያሸሸ፡ “መንግስት ለአንቺና ለኬሪ ማደጎ ቤት ይፈልግላችኋል።
ስለዚህ መኮብለል አይጠበቅባችሁም: ለእኔ ደግሞ አላውቅም . . .
ክሪስ የሆነ ነገር ካልደበቀኝ በስተቀር አይኖቼን ሳያይ አያወራም: ያ የተለየ ነገር ከፎክስወርዝ አዳራሽ እስክንወጣ መቆየት የነበረበት ነገር መሆን አለበት።“እሺ ክሪስ አሁን አምልጠናል ምንድነው የደበቅከኝ ተናገር!

ኬሪ ብዙ መኪናዎች ወዲያ ወዲህ ሲሉና አንዳንድ ሰዎች ፈገግ እያሉላት
እየፈጠኑ ሲያልፉ አይኖቿ በአድናቆት ፈጥጠው ወደ እኔ ተጠግታ ቀሚሴን
ስትይዝ ክሪስ አንገቱን ደፋ አደረገ።

እናታችን ናት” አለ ዝቅ ባለ ድምፅ:: ከአባቷ ለመውረስ እንድትችል እሽታውን ለማግኘት ምንም ነገር እንደምታደርግ ስትናገር ታስታውሻለሽ? ምን ቃል እንዳስገባት አላውቅም ካቲ፣ ግን ሠራተኞቹ ሲያወሩ ሰምቻለሁ።
ወንድ አያታችን ከመሞቱ ጥቂት ቀናት በፊት፣ ኑዛዜው ውስጥ ተጨማሪ ቃል ገብቷል። ያስገባው ቃል የሚለው እናታችን ከመጀመሪያው ባሏ ልጆች እንዳሏት ከተረጋገጠ የወረሰችውን ንብረት በሙሉ በቅጣት መልክ ትመልሳለች
በገንዘቡ የገዛቻቸውን ነገሮች ሁሉ፣ ልብሶቿን ጌጣጌጦቿንና ዋጋ የሚያወጡ ነገሮችን በሙሉ ትመልሳለች። ያ ብቻ አይደለም: ያፃፈው
ኑዛዜ ውስጥ ከሁለተኛ ትዳሯ ከወለደችም ሁሉንም ነገር ታጣለች: እና
እናታችን ይቅር እንዳላት ታስባለች። ይቅር አላላትም፣ አልረሳምም፣ መቃብር
ውስጥ ሆኖ እንኳን እየቀጣት ነው::”

ነገሮችን ሳገጣጥም አይኖቼ በድንጋጤ ፈጠጡ። “ማለት እናታችን . . . ?
እናታችን ናት አያትየው አልነበረችም?”

ሊሰማው እንደሚችል ባውቅም ግን ልክ ግድ እንደሌለው ሁሉ ትከሻውን
ሰበቀ: “ያቺ አሮጊት አልጋዋ አጠገብ ሆና ስትፀልይ ሰምቻታለሁ። ክፉ ናት፣ ግን ዶናቶቹ ላይ መርዝ መጨመሯን እጠራጠራለሁ።ወደ እኛ
ይዛቸው ትመጣለች... እንደምንበላቸውም ታውቃለች ግን እንዳንበላቸው ታስጠነቅቀን ነበር።"

“ግን ክሪስ፣ እናታችን ልትሆን አትችልም ዶናቶቹ በየቀኑ መምጣት ሲጀምሩ
እሷ የጫጉላ ሽርሽር ላይ ነበረች”

ፈገግታው የመምረርና የመጠየፍ ነበር “አዎ ግን ከዘጠኝ ወር በፊት ኑዛዜው
ተነቦ ነበር፤ ከዘጠነኛ ወር በፊት እናታችን ተመልሳ ነበር። ከወንድ አያታችን
ኑዛዜ የምትጠቀመው እናታችን ብቻ ናት ሴት አያታችን አይደለችም እሷ
የራሷ ገንዘብ አላት፡ የእሷ ስራ በየቀኑ ቅርጫቱን ማምጣት ብቻ ነበር።"

መጠየቅ የምፈልጋቸው ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ፡ ግን ኬሪ ነበረች: ቀሚሴን
ይዛ አተኩራ እያየችኝ ነበር ኬሪ በተፈጥሮ ሞት መሞቱን እንጂ ሌላ ምንም
ነገር እንድታውቅ አልፈለግኩም: የዚያን ጊዜ ነው ክሪስ ማስረጃ የሆነውን
👍50👎1🔥1