አትሮኖስ
#ወንድ ጀግንነት ድፍረት እውቀት ፥ የታደለው ትዕግስት ፣ ማስተዋል ከአምላክ የተቸረው፤ ወንድነት ጀግንነት ወንድነት ፥ ክብር ነው ውሳኔው ቆራጥ የበላይ ፥ በቤቱ ለልጆቹ አባት ፤ አዛኝ ነው ለሚስቱ። ለእንስቱ ደስታ ፥ የሳቅ ምንጭ የሆነው፡፡ ተባዕት ሚስጥር፤ ተባዕት ቅኔ ነው፡፡
#ሴት
ከ ጨ ረቃ ፣ የ ምት በ ልጥ
ከ ፀ ሐ ይ ፡ የላቀች ፤
ለወንድ ፡ ልጅ ፡ ድምቀት፤
ብ ር ሐ ን ፡ የሆነች ፤
ሴት፡ ማለት፡ ሚ ስ ጥ ር ፤
ሴት፡ ማለት፡ ቅኔ ፡ ነች ።
የፈጣ ሪ ፡ ስ ጦታ፤
የ ተ ባ ዕት ፡ ጌጡ ፤
ሴት ፡ማለት፡ እንቁ ፡ ነች ፤
በሷ፡ ለሚያጌጡ።
ከ ጨ ረቃ ፣ የ ምት በ ልጥ
ከ ፀ ሐ ይ ፡ የላቀች ፤
ለወንድ ፡ ልጅ ፡ ድምቀት፤
ብ ር ሐ ን ፡ የሆነች ፤
ሴት፡ ማለት፡ ሚ ስ ጥ ር ፤
ሴት፡ ማለት፡ ቅኔ ፡ ነች ።
የፈጣ ሪ ፡ ስ ጦታ፤
የ ተ ባ ዕት ፡ ጌጡ ፤
ሴት ፡ማለት፡ እንቁ ፡ ነች ፤
በሷ፡ ለሚያጌጡ።
❤21👏3👍2
በጠየቁህ ቁጥር ደህና ነኝ በል በጣም
አይደለሁም ብትል ምንም አታመጣም
ደህና ነኝ በል በርታ………....ቢከፋም ቢደላ
ሁሉም ህመም አለው ማይገልፀው ለሌላ
🔘በረከት ዘውዱ🔘
አይደለሁም ብትል ምንም አታመጣም
ደህና ነኝ በል በርታ………....ቢከፋም ቢደላ
ሁሉም ህመም አለው ማይገልፀው ለሌላ
🔘በረከት ዘውዱ🔘
❤16👍6
#አለቀለት_ያሉት
ከጅረት አጠገብ ፥ቆሞ የኖረ ዛፍ
መብረቅ ገነደሰው
አሁን ድልድይ ሁኖ፥ ያሸጋግራል ሰው።
“አለቀለት” ያሉት፤ ተልኮው መች አልቆ
ቆሞ የጠቀመ፥ መላ አያጣም ወድቆ፤
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
ከጅረት አጠገብ ፥ቆሞ የኖረ ዛፍ
መብረቅ ገነደሰው
አሁን ድልድይ ሁኖ፥ ያሸጋግራል ሰው።
“አለቀለት” ያሉት፤ ተልኮው መች አልቆ
ቆሞ የጠቀመ፥ መላ አያጣም ወድቆ፤
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
👍20❤9👏2
#መስታወት
1
አባቴ ኃይለኛ ነው። እናቴ ስታናደው በር ዘግቶ በቀበቶ ነበርየሚገርፋት። እንፈራዋለን። ይጮህብናል። ዝም የሚል ነበር፤ ሲስቅ እንኳን አይቼው አላውቅም። እናቴ በጣም ታሳዝነኝ ነበር። እኔን እንኳን እንደሚወደኝ ለማሳየት ቃል ሳያወጣ ጸጉሬን ነበር የሚያሻሸው፤ በቃ እቺ የፍቅሩ ማሳያ አጽናፍ ነበረች።
ከቁጣ በስተቀር ገርፎኝ አያውቅም። ግን እናቴ ሳበሳጫት ለአባትሽ ነው የምናገረው ስትለኝ ሽንቴ እስኪያመልጠኝ ነበር የምደነግጠው፤ ብርገጋዬን ስለምታውቅ በቀላሉ በአባቴ አታስፈራራኝም።
አንድ ቀን ለሥራ ክፍለሀገር በሄደ በአራተኛ ቀን መኪና ተገልብጦ የአባቴ በድን በሳጥን ተጀቡኖ መጣ። ሐዘን ሆነ።
እናቴ በጣም ስታዝን ገረመኝ፤ ይመታት፣ ይቆጣት፣ ትፈራው አልነበር እንዴ ለምንድን ነው እንዲህ የምታዝነው አልኩ።
ጊዜ ሄደ። እናቴ ኑሮ በጣም ከበዳት። አበራ የሚባል ሴት ወሲብ ብቻ የምትመስለው ሸፋዳ አገባች። ኑሮ ቀለል አለን፤ አበራ ቸር ነው፣ ገንዘብ አይሰስትም ነገር ግን ባዳው መሆኔን እይታው ይነግረኛል። እናቴ ከሌለች ይጎነትለኛል፣ ይተሻሸኛል፣ ወደ ራሱ ይስበኛል። እናቴ ተሳቀቀች፤ እኔም ቤታችን እናቴ ከሌለች ያልለመደኝ ተናካሽ ውሻ ያለበት ግቢ ነው የሚመስለኝ። ከአቅሜ በላይ ሲሆን፣ የጭቅጭቃቸው ምክንያት ስሆን፣ ትምህርቴን አቋርጬ መስተንግዶ ገባሁ፤ ጥንጥ ቤትም ብቻዬን ተከራየሁ።
ለካ ሁሉም አበራ ነው።
ትንሽ ያወራኸው፣ ፈገግ ያልክለት ወንድ ሁላ እራት ልጋብዝሽ፣ ሌላ ቦታ እንገናኝ፣ እንቀምቅም፣ ልሳምሽ፣ እንዋሰብ፣ እንመቻች፤ ወሬው ከዚህ አይዘልም።
የወንዶች መስገብገብ ይመሰለኛል ወሲብን ወንድ ብቻውን የተለየ ደስታ የሚያገኝበት ያስመሰለው።
ከ'ከስተመሮቼ ቃለዓብ ደስ ይላል። ረጋ ያለ፣ ትንሽ ፈገግታ፣ ከትንሽ ቲፕ ጋ የሚሰጥ ነው። በጣም ከብዙ ጊዜ በኋላ ተግባባን። መደዋወል፣ መገናኘት አበዛን። በአባቴ ፍርሀት እና በአበራ ሴሰኝነት፣ በ'ከስተመሮቼ ሴት አውልነት ተጽዕኖ የተበጃጀሁት ትምኒት በቃለዓብ ምክንያት አንድ አንድ ወንድ አለ ማለት ጀመርኩ።
ትንሿ ቤቴ ይመጣል። ተስፋ፣ ገንዘብ፣ ክብር፣ ፍቅር ትርጉም ሰጠኝ። ወደድኩት። ያቺ የወንድ ገላ የሚሸክካት ትምኒት ተቀየረች፡፡ ገላዬ ከገላው ሲነካካ፣ ሰውነቴ ይለዋወጣል፣ ይቅበዘበዛል፣ ይከፋፈታል። እቅፍቅፍ አደርገዋለሁ፣ ጉያው ውስጥ እገባለሁ፣ አንገቴን ሲስመኝ ደስታ መላ አካሌ ላይ ሲርመሰመስ ይሰማኛል። ስንራከብ እና ውስጤ ሲጨርስ ሐሴት ሲያጥለቀልቀኝ ከጸጉሬ እስከ ጥፍሬ እርካታ ይመዘምዘኛል።
ቃለዓብን ወደድኩት። እንደዚህ ከሆንን አምስት ወር ከሰባት ቀን በኋላ ቃለዓብ ድንገት ጠፋብኝ፤ ፈለግኩት የለም። በሕልሜ አየሁት፣ ቃዠው፣ ለፈለፍኩ፣ በአይነ ስጋ ዳግም ማግኘት ግን አልተቻለኝም፡፡
እጦት፣ ናፍቆት፣ ፍቅር፣ ስጋት ተባብረው ከደቆሱኝ ከትንሽ ዕለታት በኋላ አንድ ጓደኛው ሚስቱ እና ልጁ ጋ አሜሪካ መሄዱን በማያጠራጥር መልኩ ነገረኝ።
ማርያም ደጅ ሄድኩኝ እና ለምን አልኳት፤ እንዴት አንቺ እያለሽልኝ ከክፉ ነገር አልጋረድሽኝም። እንዴት አላጋለጥሽውም፤ ነገሩ እንደሆነብኝ ቢሆንበት፣ የዘራውን ቢያጭድ፣ እሱ ይጎዳል እንጂ እኔ ስብራቴ አይድን!
ምነው ማርያም? ምነው? ምነው ብርሃኔ? ከስንት አፈ ጮሌ፣ ከስንት መደለያ ቁስ አስመልጠሽኝ፣ ምነው ዛሬ ተውሽኝ? ምነው ማርያሜ?!
እንዴት አንቺ እያለሽ ያመንኩት፣ ራሴን የሰጠሁት ሲያጠፋኝ ዝም አልሽኝ እያልኩ አነባሁ፣ አዘንኩ፣ ተደበትኩ። አሁንም ጠባሳው ልቤ ውስጥ ተሰንዷል።
አፈጮሌ ወንድ ጠላሁ። በሰዎች ጥሩ ነው የሚባል ትሁት፣ ደግ፣ አዝንልሻለሁ ባይ አስጠላኝ፡፡ ከብዙ ዓመታት የብቸኝነት ሕይወት በኋላ ክንፈን አወቅኩት። ነገረ ሥራው ከሰው አይገጥምም።
ከክንፈ ጋር የጋራ ነገር ኖረን መሰለኝ ደስ አለኝ። ለማንም ግድ የለውም፣ ለማንም ምንም የልብ ወዳጅ አለኝ ሲል ሰምቼው አላውቅም። ሕይወቱ ወሰብሰብ ያለ ነው፣ ያሳዝነኛል። የማንንም አቴንሽን ለመሳብ አይሞክርም። ሥራ ቦታም መኖርያ ቦታውም መዋጮ፣ ድጋፍ፣ እርዳታ ደፍሮ የሚጠይቀው የለም፤ ከጠየቁት ደረቅ ብሎ አላዋጣም ነው የሚለው፣ ያሳቅቀኛል። የሰው ልጅ የማስመሰሉን ጭምብል ሲያወልቅ ክንፈን ነው የሚመስለኝ።
አይሸነግልም፣ የሚሆነው እና የሚያወራው ተመሳሳይ ነው። ከማንም ጋ ስለማይቀራረብ አይተወኝም አይወሰልትብኝም ስሜት ምቾት ሰጠኝ።
በሂደት የፍቅር ግንኙት ጀመርን። ወሲባዊ ግንኙነታችን ግን ጤናማ ሊሆን አልቻለም። ክንፈ ሴክስ ላይ ካልተማታ አይረካም።
ክንፈ ብዙ ነገሩ የተሸሸገ ነው።
አልጋው ጎን የተቀመጠው የመጽሐፍ መደርደሪያ ውስጥ የተወሸቁ ጥራዞች በሙሉ ስለላ፣ በቀል እና ሴራ የተሞላበት መሆኑ አልጎረበጠኝም። ለየት ማለቱ፣ ውስብስብነቱ ሳበኝ፣ ግራ አጋቢነቱ፣ ልጨብጠው አለመቻሌ፣ ትኩረት፣ ከጊዜ እና ፍቅር ጋ እንድሰጠው አደረገኝ።
ክንፈ ሁሉ ነገሩ እንግዳ ነው፤ ፊቱ ሲጨፈግግ ድምጼን አለስልሼ ምን ደብሮኻል እንዴ? ስለው "How do you know?" ይላል የሆነ ጎረምሳ ሸሚዙን ከአንገቱ ጋ አጣብቆ የያዘው ይመስል የጨፈገገ ፊቱን ይበልጥ አጨፍግጎ። እንዲህ ዓይነት ሰው ለማጽናናትም ለማበርታትም አይመችም፤ ይገርመኛል።
ሌላ ሰው ስለማይቀርብ፣ ስሜቱን ለሰዎች መናገር ስለማይሆንለት አሞት እንኳን እያቃሰተ አመመኝ የሚል ስላልሆነ ያሳዝነኛል።
በዙሪያው ያለነውን ሰዎች የፊት ገጽታ እንደዋዛ አይመለከትም፤ ይተነትነዋል፡፡ እይታው ደግሞ ያስደምማል፣ በዙሪያው ያለነው ራሳችን አስተውለነው የማናውቀውን እንቅስቃሴ ሳይቀር ያስተውላል።
ሥራ ላይ ቀልድ አያቅም!!
ምንም እንደዋዛ የሚቆጥረው ነገር የለም፤ ጥንቁቅ ነው። አመንኩበት የሚለውን ለማንም በቀላሉ አያጋራም፤ አስር ጊዜ የግራ ቅንድቡን በሌባ ጣቱ ልብስ ማድረግ ለምዶበታል።
የበለጠ በቀረብኩት ቁጥር የበለጠ ስጉነቱ ታወቀኝ። በዙሪያችን ያሉትን ሰዎች እንከን ያሳየኛል፤ እኔ ደግሞ አይአይመስለኝም እለዋለሁ፤ በሌላ ቀን በዙሪያዬ ያሉትን ሰዎች እንከን በነገረኝ መሠረት ማስተዋል ስጀምር ትክክለኝነቱ ያስደምመኛል።
ነገር ግን በተጣላን ቁጥር ጥጋችን ላይ ይንደረደራል። ጥሩ ትላንት የነበረው አይመስለኝም። ቢሆንስ ግን መጥፎ ትናንቱን እንዴት ፍቅራችን አልሸረሸረውም እያልኩ አስባለሁ?
እኔ ተጣልተን እንኳን በሰላሙ ጊዜ እንደምጠራው ነው የምጠራው። ለእሱ ያለኝ ፍቅር ይሉኝታ ቢስ እንዳያደርገኝ ይከልለኛል። ተጣልተን መልዕክት በስልኩ ስልክለት እንኳ መልዕክቴ ድ'ርቅ እንዳይል እጠነቀቃለሁ። ፍቅራችን ለምናፈቅራቸው እንድንጠነቀቅ ካላደረገን ፍቅራችን የእውነት ላለመሆኑ ምስክር ነው።
ክንፈ እብድ ብቻ ነው የሚወደው። ለእብድ ብቻ ነው የሚያዝነው፤ እውነት ያለው እብድ ጋ ብቻ ይመስለዋል። ለእብድ ጥብቅና እንዲቆም ሹመት ያለው እስኪመስል ይቆረቆራል።
አፈጣጠሩ ሁሉ ነገሩ ከሰው አይገጥምም። “ይሄ ባለጌ ሕዝብ እብድ የሚለውን ስሜት አልባ ይመስለዋል። ይሄ ሲቸር እያስጨበጨበ፣ እያሰገደ ቸር ነኝ ፉከራ ሳያሳይመስጠት የማይወድ ሕዝብ አእምሮ ለታመመ መስጠት አያረካውም። ይሄ ድንጋይ ሕዝብ ሆድ በሚያባባ ቃል መሞቴ ነው፣ ተሰቃየሁ ድምጽ እና አኳኋን ምልክት ካላየ
ስላማይቸር ለእነሱ የሚሰጥ አንድም የለም" ይላል። ቁም ነገር እያወራን እብድ ካየ ቀልቡ ይነጠቃል። ልስልስ ብሎ የሚያወራው ስለ አበደ ሰው ሲወራ ብቻ ነው። አንድ ቀን ማታ እየጣጣን እኔ እምልህ ክንፉ
"አቤት"
ነገር እና ተቆርቋሪነትህ እኮ አብደህ የምታውቅ ነው የምትመስለው አልኩት።

❤29👍5🔥1
ፊቱ ተቀያየረ። በክፉ አይቶኝ ያወራል ስል ዝም ብሎ ፊቱ የነበረውን አልኮል ጨለጠው። የዛ ምሽት ከወትሮ በተለየ እየቀጠቀጠ ወሰበኝ። በእርግጥ በእርካታ ሳይመታኝ የወሰበኝ ቀን አላስታውስም። ሳለቅስ ነፍሱ በሐሴት ሲሞላ ምንም እንዳልመሰለው እየመሰለ ደስስ ሲለው ይታወቅበታል።
ድል አድራጊነት ውስጡ የሚንቦለቦል ይመስለኛል። ተናደድኩኝ ብሎ እየደበደበ ሲወስበኝ ፊቱ ላይ የሚታየው ድል አድራጊነት እና ደሰታ ምንም ላይ ምንም ሲያገኝ አይቼበት አላውቅም። በሂደት ቀስ እያለ ባሻው መንገድ አበጃጀኝ።
የማጣው ሁሉ እኩይ ማንነቱን የሚያየብኝ እንስት መሆኔ እንዳልጠራጠርሆኘ፣ የተበጃጀው ፍጡር ነኝ። የተመሰከረብኝ ለመቀለጃነት
በሂደት ዱላ የተቀላቀለበት ወሲብ ለመድኩ። ልምድ ደግሞ ሱስ ነው፤ ሱስ ደግሞ ባርነት ነው።
አሆናለሁ ብዬ አስቤ የማላውቀው የሕይወት መንገድ ላይነኝ፣ ሰው በዕድሜ ብዛት ማስተዋል ከቻለ የሚማረው ነገር አለመፍረድን ነው!
አስተዳደጌ የተመረዘ ነው ሲለኝ ከማዘን ውጪ መመረዙን ላየው አልፈቀድኩም። ለማኅበረሰቤ ያለኝ ቦታ የተበላሸ ነው ሲለኝ ራሴን የማኅበረሰቡ አካል አድርጌ አልቆጠርኩትም። ስሜቱን ሲያወራኝ ከእሱ ጋ እንደተሰማኝ ሆኜ ሳልሞግተው አሸበሸብኩ። ወሲብ ላይ የሚያደርገው ጀብደኛ አወሳሰብ ከጥላቻ እንጂ ከፍቅር እንዳልተወለደ መገመት ነበረብኝ፡፡ ዝም ያለ ስፍራ መውደዱ ከዚህ ሕዝብ ጋ ላለመጋፋት እንደሆነ አልገመትኩም።
2
ምድር ላይ ከተሰሩ ደግነት ብቸኛው ነገር የልባችን እውነት ግንባራችን እና አንደበታችን ላይ አለመታየቱ እንጂ፤ እኔ ነበርኩ እንደመቅደላዊት ማርያም ይወገር ይወገር የሚለው ይሄ መንጋ የሚወግረኝ። ጥላቻዬ ግንባሬ ላይ ቢነበብ የሚቀርበኝ አልነበረም። ጥላቻዬ አቅም ሲያገኝ ከሚያዘንበው በቀል ማን ይተርፋል? ጥላቻዬንስ ማን ችሎ ያለዝበዋል?
ምቹ ጊዜ ነው የምጠብቀው። በእናቴ ሞት ምክንያት የቀዠበው አባቴን፣ ካለ እናት ያሳደገኝን አባቴን ኮቴ እየተከተሉ ናላውን ያዞሩትን የሰፈሩ ነዋሪዎችን አቂሜባቸዋለሁ። በልጅነቴ አባቴ የሚደበቅበት ሲያጣ ተመልክቼዋለሁ፤ ሳድግ አንደማስጥለው እየተኮላተፍኩ ቃል ገብቼለታለሁ።
እብድ የሚከፋው አይመስላቸውም፤ እብድ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ የሚቀዥብ ይመስላቸዋል፡፡ ምን በድሏቸው ነው እንዲህ እግር በእግር አየተከተሉ የሚያበሽቁት? እያልኩ በልጅነቴ መልሱን ፍለጋ አስሻለሁ።
በአይኔ አባቴን የሚቆጣለት ፈልጌ አጥቻለሁ። ውለታ ለማይከፍሉ ጥብቅና የሚቆም ጻዲቅ አላገኘሁም። ሲናደድ፣ ሲሳደብ፣ ሲጮህ ካጠገቡ ራቅ ብለው በሁኔታው ይዝናናሉ። በሰው እንባ የሚስቁት ጤነኛ ተብለው አባቴ እንዴት እብድ ተባለ?
ስምምነት ብቻ እንዴት ሚዛን ደፋ?
ጓደኛ ስለሌለው ይሆን፣ መንገድ ላይ ከሚተነኩሱት እንዳድነው ይሆን፤ ስለሚወደኝ ይሆን፤ ብቻ ካ'ጠገቤ አይለየኝም። ያወራኛል፣ ስለእናቴ ይነግረኛል። እንዴት እንደተገናኙ፣ እንደናፈቀችው፣ ይገዛላት የነበረውን ውድ የስጦታ ዓይነት ይተርክልኛል።
ለእናቴ ያለውን ፍቅር፣ ሕልሙን የሚያጫውተኝን ሁሉ ብናገር ማን ያምነኛል??
ከጓደኞቼ ጋር ጨዋታ ላይ ስንጣላ የእብድ ልጅ ብለው ሰድበውኝ ሦስት ልጅ ከፈነከትኩ በኋላ ድሮስ የእብድ ልጅ ብለው ቤተሰቦቻቸው ከእኔ ጋ እንዳይጫወቱ ከለከሏቸው። ሁሉም ፊት ነሱኝ።
የበዳይን ምክንያት ሳንጠይቅ በደልን ከምንጩ ማድረቅ እንዴት ይቻላል
ሂደቱን ሳንመረምር በውጤቱ ብቻ እንዴት እንዳኛለን?
በቃ አባቴን ጓደኛዬ አደረግሁት። ሕመሙን፣ መገፋቱን እያየሁ አደግሁ። አድጌ ጎረቤቶቻችንን፣ የሰፈራችንን ሰዎች፣ የከተማችንን ሰዎች እንዴት እንደምበቀላቸው እያቀድኩ ደረቴ ሰፋ። በአባቴ የቀለዱትን ሰዎች እንዴት ጉንጮቼን ሳውጠነጥን እንደምቀልድባቸው ወረራቸው። አባቴን ከለካፊዎች ልከላከልለት ትንሽ ዓመት ሲቀረኝ ሞተብኝ።
ሥልጣን፣ ገንዘብ ለማግኘት የምጓጓው ያቄምኩባቸውን በግላጭ ለማግኘት ነው። ክፉ ባለሥልጣን፣ ግፈኛ ሀብታም የሆነ ሰው ሲያጋጥመኝ አባቱን ወይ እናቱን አሳብደውበት እየተበቀላቸው ይመስለኛል። ሊበቀላቸው ስለተቻለው ደግሞ እቀናበታለሁ።
ሁሉም የሚቀናበት ነገር የተድቦለቦለው በልጅነቱ በተዋቀረው ሕልሙ መነሻነት ነው። የቀን ጉዳይ ነው፤ በጅምላ አገኛቸዋለሁ።
ስሜት አልባ ነው ይሉኛል፣ ደግሞ ስሜቴን ገድለው፡፡ የተሰባሰበ መንጋ ሳይ የሚያለቅስ አባቴ ነው የሚታየኝ፡፡ ትምህርቴን ጠንክሬ የተማርኩት ብቻዬን ለመቆም ነው፡፡ ከማንም እርዳታ ላለመቀበል። ጥገኝነትን ፈርቼ ነው የበረታሁት። ለማኝ ጥላቻውን እና አቋሙን ማንጸባረቅ የሚቻለው ስለማይመስለኝ ነው ጠንክሬ የተማርኩት፡፡ ሳያዩ የበደሉኝን እያየሁ፣ እየሳቅሁ የምቀጣበት ጊዜ ሩቅ አደለም ማነህ ሲሉኝ መስታወት ነኝ እላቸዋለሁ፡፡ ክፉ ነህ ሲሉኝ ክፉነቴ የራሳቸው ክፋት ነጸብራቅ እንደሆነ እነግራቸዋለሁ። መስታወት መች ዋሽቶ ያውቃል!
🔘አድኀኖም ምትኩ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

❤35👍15
#እውነት_እንደ_ገጹ
#በአድኀኖም_ምትኩ
ገጽ ፩
የተሸነፈ ሰው ምንም ታሪክ ያለው አይመስላቸውም። የሚሰማ ታሪክ ያለው ድል ላይ ብቻ ይመስላቸዋል!! ጣፋጭ የፍቅር ሕይወት ያለው ሰልካካ፣ አይነግቡ ፊት ብቻ ነው የሚመስላቸው። ስንት ፉንጋ አይን ውስጥ የማትገባ ጣፋጭ ትዝታ እንዳላት መጠርጠር ለምንድን ነው
የሚሳናቸው?
ካደኝ ስላቸው በውስጣቸው 'ድሮም እኮ' የሚል መልእክት ፊታቸው ላይ አያለሁ። በተለይ ቁመናውን፣ ሰፊ ደረቱን፣ ፈገግታውን በአካል ወይም በፎቶ የሚያውቁት ሰዎች የሚለኩን በቁመና እና በፊታችን ቅርፅ ነው። ፊት፣ ቁመና እና ደምግባት ለመተዋወቅ ብቻ የሚረዳ አይመስላቸውም። ከተዋወቅን በኋላ የጤነኛ ሰው መመዘኛው ማንነት እንደሆነ አይገባቸውም፡፡
ለምኖኝ ነው የተወዳጀነው!
ልበ ሙሉነትን እኔ እንዳስተማርኩት ብነግረው ማን ያምናል? ወዳጆቻችን ሲቀላቀሉን ደቂቃዎች ሳይቆጥሩ ነው የእኔን ይሁንታ እየተማጸኑ የሚለፍፉት። ጭንቅላቱን ገንቢ ነገር በየቀኑ እየመገብኩ፣ ሥራውን፣ ውሎውን እና የትምህርት ደረጃውን እኔ ነኝ አሰበጣጥሬ ወደ ስኬት ያንደረደርኩት። ምን ያደርጋል? እኔው ላይ ተንጠልጥሎ ባለ ሕልም ካደረግኩት በኋላ ረገጠኝ፤ ሕልምን እውን አድርጎ መኖርያ ትርጉም ከመስጠት በላይ ምን አለ?
ድሮ የሚያውቁት ሰዎች እስኪጠፋባቸው ነው ሞገሳም ያደረግኩት። ውሸት አይደለም፤ እሱም ከስሜ በቀር ማንነቴን አድቦልቡለሽ ነው ያበጃጀሽኝ ይላል።
ያልቀረቡን፣ ከሩቅ የሚያቁን እንዴት አድርጋ ብትሰጠው ነው እንደዚህ ዓይነት መልከመልካም እና ስኬታማ ሰው እዚች አስቀያሚ ጋ የተለጠፈው ይሉት ነበር። ጫጫታው ሲደጋገም ሰማቸው፡፡ ሳያማክረኝ የማይራመደው፣ ሳልሰማ የሚያጸድቀው ነገር አልነበረም፤ እሱ ለእኔ ኃላፊነቴ ነው።
እሱ ግን ካደኝ።
ዓለም ከጀርባ ላለው እውነት ትኩረት አትሰጥም፤ የእሱ መብራት ምንጩ እኔ እንደነበርኩ ማን ያውቃል!?
እሱ ራሱ ብርሃኑ ሲያሸበሸብለት እንዲያበራ የሆንኩለትን ዘነጋው፤ አድናቆት አወከው፣ የገዘፈ ሲመስለው አነስኩበት።
ጭብጨባ አስተውሎቱን የማይነጥቅበት የተባረከ ነው! አስተውሎት የሌለበት ከፍታ ይዋል ይደር እንጂ ውደቀት መጠናቀቅያው እንደሆነ ነግሬው ነበር። ትምክሕቱ ሲጎላ . አታስፈልጊኝም፣ ብቻዬን ሙሉ ነኝ ዓይነት እንቅስቃሴ ላይ እንደነበረ አስተውያለሁ። አንድ ቀን ከወዳጆቹ ጋ ቢዝነስ ለመሥራት ሲንቀሳቀስ 'ውል አብጁ' አልኩት።
“ማርያማዊት ሕግ ላይ ሙጭጭ አትበይ፤ ዓለም በሎጂክ አትመራም፤ በፍቅር፣ በመግባባት እንጂ" አለኝ። «
እንኳን ቢዝነስ ወዳጅነትም ራሱ ያልተጻፈ ሕግ አለው። ሁሉም ግንኙነት እኮ ሳታወራ የምትግባባበት መርሕ አለው፤ በአምነዋለሁ፣ በወንድሜ ነው፣ እሱ ማለት ተብሎ ውል አልባ ቢዝነስ መጨረሻ ካተረፍነው የበለጠ ነው የሚያከስረን።
ትኩር ብሎ አይቶኝ “አልገባሽም! አልገባሽም! አሁን ራሱ ያወራሽው ሎጂክ ነው! እግዜር ስላለመኖሩ ኢ-አማኝ በጸበል ለዳነ ሰው ቢዘበዝብለት የሚያምነው ይመስልሻል? ጸበልተኛው መርቻ አንደበት ባይኖረው እንኳን“
ዘበዘብሽ እያልከኝ ነው? ደግሞስ ምኑን ከምኑ ለውሰኸው ነው ሰማያዊ ሕይወትን ከዓለማዊ የሥራ ግንኙነት ጋ የዶልከው?
“እንደሱ አላልኩም!"
በሂደት መለሳለሱን እየተወ ከእኔ መቃረንን እውቀት አረገው። ለእሱ ስል እንደምሞግተው ትዕቢቱ ሸፈነበት። ሰው የሚመዘነው በአድራጎቱ ውስጣዊ ፍላጎቱን በመመርመርእና በመረዳት አይደለምን?
የምናደርገው እና የምንናገረው በደረቁ ከተተረጎመ ማን ከማን ጋ ይኖራል!?
ፈርጠም እያለ መጣ።
የሆንኩለትን ዘነጋ፤ ለስኬቱ የከፈልኩለትን ዋጋ አደበዘዘው፤ እንቅስቃሴውን ይደብቀኝ ጀመር፤ ውጤቱን ያውም ያሳካውን ነው የሚነግረኝ፤ ያቀደውን ሳይሆን የወሰነውን ነው የሚያሳውቀኝ።
አንድ ቅዳሜ ዕለት ቤቱ ሄጄ ተጨዋውተን እየተመካከርን ሳለ ድንገት አንገቴን እየሳመ፤ እያቻኮለ የለበስኩትን ከላዬ ገፈፈው። ቤብ 'what's wrong' ከማለት ውጪ መናገርአልቻልኩም፤ ከሌላ ቀኑ በተለየ ተዋሰብን። ሴቶች አዲስ ነገር ስለምንወድ ይሁን፣ በተለየ መንገድ እርካታ ስለተሰማኝ ይሁን፤ እንደሚወደኝ ስለነገረኝ፤ ባልጠበቅኩበት መንገድ ስለተኛኝ ይሁን ብቻ ደስስ ቢለኝም ውስጤ ትንሽ ጥርጣሬ ተወለደች። የተሰማኝን ደስታ ከጥርጣርዬ ጋ ተደበላልቆ ምንም ሳልነግረው ግርታ ፊቴ ላይ እየታየ ተለያየን፡፡
በሂደት... ማግኘት፣ ናፈቅሽኝ ማለት፣ ሴት ልጅ ከወንድ ልጅ መስማት የምትፈልገውን መስጠት ነሳኝ። ይጠፋብኛል፣ አያገኘኝም፣ ሲያገኘኝ ያጣጥለኛል፤ ድክመት፣ እንከኔን ያስሳል።
ትናንትን መርሳት፣ የተዋለለትን መዘንጋት የደካማ ባሕሪ ነው!! ደካማነት ምቹ ስፍራ ሲያገኝ እና ጊዜ ሲደላደልለት የሚያብብ ደዌ ነው፤ ከአንደበቱ ቃል ሳያወጣ በሁኔታው ብቻ አባረረኝ፤ ሁኔታ የድርጊት ዋዜማ ነውና ሂጂ ሳይለኝ ሁኔታውን ሰማሁት። ትዝታው ይበቃኛል ሄድኩለት...
✨ነገ እንጨርሰው✨

❤28🔥1😁1

ገጽ ፪
ማርያማዊትን እወዳት ነበር፤ ሕይወቴ ላይ አሻራዋ ጉልህ ነው። ምን ያላደረገችልኝ ነገር አለ? የከፋኝ ዕለት፣ ኪሴ ውስጥ ሳንቲም ያልነበረ ዕለት፣ አላዋቂነት የመሰከረብኝ ዕለት፣ ልብሴ እንደቸሰትኩ ያቃጠረብኝ ዕለት፣ የተንሻፈፈ ጫማ የተጫማሁ ዕለት አብራኝ ነበረች፣ የደመነብኝ ዕለት ሁሌ ከጎኔ አትለይም፡፡
ሳንቲም ከኪሴ ሞልቶ፣ ባንኬ ላይ የጠቀጠቅኩኝ ወቅት፣ አለቃ የሆንኩ ዕለት፣ በእይታዬ አልያም በዕውቀቴ የተጨበጨበልኝ ቀን አብራኝ ነበረች። መጽሐፌ ሲታተም ምስጋናዬን ለእሷ ብቻ ሰጥቻለሁ፤ መመረቂያ ጽሁፌ ላይ
በጉልህ የእሷ ስም ነው ያለው፤ እወዳታለሁ ስል ፍቅሬ የሚዳሰስ ነው።
ካደኝ ትላለች።
ስታገኘኝ ሱሴ እየበላኝ፣ እያደቀቀኝም ነበር። ለራሴ ያለኝ ስፍራ እዚህ ግባ የማይባል ነበር፤ ባንክ ቤት ስሄድ ወረፋ መያዣ መቀመጫ ወንበሩን የማቆሽሸው ያህል ለመቀመጥም የማልመጥን ነበር . የሚመስለኝ። ሱሴ ልምጥምጥ አድርጎኝ ነበር፤ ተስፋ ያልቆረጠብኝ አንድም አልነበረም። ስለ ደቂቃ እና ሰዓታት እንጂ ስለ ነገ የማላስብ · ነበርኩ። ማርያማዊት ነች ቁልቁል አይታ ያነሳችኝ።
ግን ካድኳት።
ታውቃለች እንደምወዳት፣ ታውቃለች እንደማከብራትም። ታውቃለች ላገኘሁት ሰው ሁሉ እንደማጣቅሳት። ያኔ ገና በንፁሕ ወዳጅነት እያለን አንስቶ ስትባትልልኝ ነው ውለታዋ ደምስሬ ውስጥ የሰረጸው። ከሁሉ ሰው በተለየ ስለምታየኝ፣ ስለምታዝንልኝ፣ የወዳጅነት ፍቅሯ፣ መላመዳችን ሲጨማመር በፍቅሯ ወደቅኩ።
አንድ ጊዜ አባቴ ታመመብኝ። ለአባቴ ከእኔ በቀር ማንም አልነበረውም። ሥራ ፍቃድ አላገኝ ስል የዓመት ፍቃድ ወስዳ ቀን ከሌሊት አባቴን አስታመመችልኝ። ለአባቴ መድኃኒት ለመግዛት ሲወደድባት እሱም የለውም ብላ የአንገት ጌጧን ሸጣ መድኃኒት መግዛቷን ያወቅኩት ወርቅሽ የት ሄደ ብዬ ስጠይቃት "ለአባባ መድኃኒት መግዣ ሳንቲም አልነበረኝም፤ አንተ ደግሞ ወጪ ላይ ስለነበርክ ከማስጨንቅህ ብዬ ነበር የሽጥኩት” በሚል መልሷ ነበር።
ፍቅርን ሳያንኮሻኩሽ የሚኖር የተባረከ ነው። ስጦታ ነፍስ ከማዳን በላይ ምን ያደርጋል ብላ ነው የሚሆነው፡፡

❤19👍3
ሌላ ቀን ሰብሰብ ብለን እየጠጣን፣ እራት በልተን እንዳበቃን ጃኬት ኪሴ ውስጥ ገብታ ወጣች፤ ትንሽ ቆይታ “ስልክህ ቴክስት ገባልህ" አለችኝ ሳየው ራሷ ናት የላከችው። “ጀለሴ ኪስህ ውስጥ እኮ ብር አለ ክፈል እንጂ” ይላል። ቢል ሲመጣ ተሻምቼ ከፈልኩ። መክፈል ውስጥ ያለውን ሥነ-ልቦና ታውቀዋለች። ያለመክፈል ውስጣዊ ስሜት ቢገባት ነው። እንድተልቅላት ነው፤ እኔ ከምከፍል አንተ ክፈል፣ አንተ ስትተልቅ እኔ እተልቃለሁ ብላ ነው።
በስንት ጣር እንቅስቃሴዬን አይታብኝ ስትጠይቀኝ ነው ፍቅሬን የገለጥኩላት። ተንጠራርቶ ማፍቀር ይቻል ይሆናል፤. ተንጠራርቶ ፍቅር መንገር ግን ቀላል አይደለም። በጣር ተቅለስልሼ ፍቅሬን ገለጽኩ፤ በቀን ብዛት እሺም እምቢም ሳትለኝ ራሳችንን ፍቅረኛሞች ሆነን አገኘነው። ጥንካሬዋን አጋባችብኝ፤ ድክመቴን ተጠግታ አተነነችው፤ አብረን የማንውልበት ጊዜ ጠፋ።
እኔ ግን በመጨረሻ ካድኳት። ግን ለምን ካድኳት?!
ማርያማዊት ሱሰኛው ቶማስን፣ በራሱ የማይተማመነው ቶማስን ልምጥምጡ ቶማስን ሱሱን አስትታ ልበ ሙሉ አድርጋው ቆፍጥኖ እንኳን የትናንቱን ቶማስ ልትረሳው አልቻለችም። የተቀየርኩ ይመስላታል እንጂ እንደተቀየርኩ አልተቀበለችኝም።
ፈርጠም፣ ኮራ ብዬ ሳወራ ትገረማለች። እኔ ላይ ፈርጠም የሚል ፊት መሰስ እያለ ራሱን ይገልጣል። የዋለውን ውለታ ለዋሉለት በየሰበብ አስባቡ ማጣቀስ ውለታውን የማኮስመን አቅሙ ግዙፍ ነው። መልካም አድራጎት የሚገዝፈው መልካም አድራጊው በየሰበቡ ካልፎከረበት ነው። ትናንት ያ ኮስማና ቶማስ ማርያማዊት ላይ ተንጠልጥሎ ገዝፏል እና ሁሌ ተንጠልጥሎ ይኖራል?!
ማርያማዊት አታከተችኝ።
ከእሷ ውጪ መቆም እንደምችል በርካታ ጊዜ አሳየኋት፤ ማርያማዊት ተማሪዋ ነው የምመስላት። ስታየኝ፣ ሳወራት፣ ስንጨዋወት ማረም ነው የሚታያት። ከእሷ ውጪ ተረማምጄ ማሳካት እንደሚቻለኝ በተደጋጋሚ አሳይቻታለሁ። አጥፍታ፣ ተሳስታ ላሳያት ስሞክር እና አልሰማ' ስትለኝ ፈርጠም ስል ማርያማዊት እኮ ነኝ ስማር እንኳን B የለኝም ዓይነት ሽለላ ትሸልላለች። የሰው ልጅ ስለሆነለት እና ስላገኘው ሁሌ የሚመሰጥ ፍጡር አለመሆኑ አልገባትም።
በየጊዜው "Never outshine the master" ዓይነት መልዕክት ታስተላልፋለች። አንድ ቀንም ስለ ጉብዝናዋ፣ ስለ ጥንቃቄዋ ተጠራጥሬ አላውቅም። ግን ጎበዝ መሆን ማለት ስሕተት አልባነት ነው እንዴ? ዘወትር አለቃህ ነኝ፣ የሕይወትህ መሥመር ቀያሽ እና አዳሽ ነኝ ከሚል ሰው ጋር መሆን ከበደኝ። ለማስተካከል ንግግር ስጀምር ትናንትህን ረስተሃል፤ ትናንትን ዞር ብለው ያላዩ ሰዎች ወሬ ልብህን አጠገበህ ትለኛለች።
አታከተኝ!!!
ሳገኛት ለፈተና የተዘጋጀ፣ ኤክስ እንዳይገባበት የሚጠነቀቅ ተማሪ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል። የተሰማኝን ነገር ላለማስተያየት ሞከርኩ፣ ግን አልቻልኩም። በተለያየ ጊዜ ስሜቴን፣ ፍቅርንም፣ ጭቅጭቅንም ተገን አድርጌ አብራራሁ፤ ላስረዳትም ሞከርኩ። የበላይነት ስሜቷ ውስጥ የተወሸቀ የበታችነት ስሜት አቆጥቁጦባታል። ወይ እንደ እሷ ሰው መቀየር አልችልም፤ አልያም እሷ እንደ እኔ ለመቀየር ዝግጁ አይደለችም፤ ብቻ አብሪያት መሆን ሲያታክተኝ መታከቴ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ተውኳት!
እሷ ክሕደት አለችው፡፡
ገጽ ፫
ድሮስ በዳይ የሚለው ያጣል? ላገኘው ሰው ሁሉ ፍሬከርስኪ እንደሚዘበዘብ ነግረውኛል።
ልቡ የሸፈተን ሰውን ልብ ማሸነፍ ግዙፍ ድንጋይ ዳገት ላይ ይዞ ለመውጣት መሞከርን ያክላል። ቶማስ ሳጠፋ፣ ሳስቀይመው ወይም ሳናድደው ስለ ማስተካከል እያሰበ አይደለም የሚሞግተኝ፤ እንዴት ልለያት እያለ መለያያ መንገድ እያነፈነፈ ነበር። ጭንቅላቱ ከሃዲ፣ ውለታ ቢስ እንዳይለው ጣፋጭ መለያያ ምክንያት እያከማቸ ነው ከእኔ ጋር የነበረው።
ከበደሉ በጣም እንደው በጣም ያመመኝ እንደሚያዝንልኝ መዘብዘቡ ነው። ያደረገውን እያወቅን በዳይ፣ አዛኝ መስሎ ሲጎዘጎዝ ሳይሰቀጥጠው መስማት የሚቻለው ምን ዓይነት
ጀሮ ነው!?
ዓለማችንን ያጎደፉት እየበደሉን ደግመው መጥተው ለበደላቸው ከአራምባ እና ቆቦ ምክንያት እየደረቱ የሚደረድሩ፤ ተጠቅመው ሳለ እንደተጎዱ ሙሾ የሚያወርዱ ተርመስማሽ ነፍሶች ናቸው።
ደግሞ የበደሉትን ስለሚያብለሰለስሏት በደላቸውን ማፍዘዣ አሳማኝ የምትመስል ነገር አያጡም፡፡ ትናንት እኮ ሰዎች አብሮኝ ሲሆን ለሱሱ ሳንቲም እየለመነኝ እንጂ የልብ ወዳጄ አይመስላቸውም ነበር። ትናንት ከእሱ ጋር ስሆን የሚያየኝ ስንት ሰው አዝኖ አይመጥንሽም እያለ መክሮኛል። ሐሳባቸውን የጫጫታ ያህል እንኳን ቦታ አልሰጠሁትም
እሱ ግን ካደኝ!
አጣጥለው ሲያዋሩት፣ ሲቀልዱበት እና ሲያሳንሱት ከስንቱ ጋ ተሟገትኩ? ከስንቱ ተጣላሁ? ጭሎ አድርገውት እኩዮቹ ሲልኩት፤ ታናናሾቹ ሲያሳንሱት ስንት ቀን ቀና እንዲል ባተልኩ። ወደ በጎ መለወጥ ብዙ ጠመዝማዛ መንገድ አለው። እንደ መበላሸት ቀላል አይደለም። እሱን ለመለወጥ ስንት መጽሐፍ አነበብኩ? ስንት ስልጠና አስገባሁት? እሱን ለመቀየር ሰንት ቀፋፊ ስፍራዎች ዋልኩ?
ከማይረባ ሰው ጋር ሆንሽ በሚል ቤተሰቦቼ መከሩኝ፣ ጨቀጨቁኝ፣ ተጣሉኝ። እኔ ግን ተጋፈጥኩ።
እሱ ካደኝ እንጂ!!
ሱስ አሸንፎት ምን ያልሸጠብኝ ነገር ነበር? ከቤተሰቦቼ የተቀበልኳቸው ስጦታዎች እጄ ላይ መቼ አሉና? መቀየሩ ስጦታዬ ይሆናል ብዬ ነበር የታገስኩት። ለምንፈልገው ነገርዋጋ ካልከፈልን የምንፈልገውን ነገር መቼ እናገኛለን!
እሱ ግን ካደኝ!
ተነጫናጭ፣ ግትር ነሽ ይለኛል። ነገር ግን ያኔ ንፁሕ ወዳጆች ሳለን ጭምር አስቸጋሪነትሽ ለታገሰሽ ደቂቃዎች እንኳን አይከርምም ይለኝ አልነበር? ትናንት አሜን ያለውን ማንነቴን ዛሬ ጎረበጠኝ አለ። ይሄን ማንነቴን እያወቀ እና እያየ እኮ ነው ከመጠንኩሽ ፍቀረኛ ካልሆንን ያለኝ።
ዛሬ ከሱሱ ሲላቀቅ፣ ሲያምርበት፣ ጥሩ ደመወዝ ሲያገኝ፣ አለቃ ሲሆን ትናንት በደከመበት ወራት የተቀበለው ማንነቴ
ሕሊናው ሲጠይቀው፣ ሲሞግተው ያሳለፍናቸውን ጥልፍልፍ መንገዶች ለማያውቁ፣ ለማይሞግቱ ሰዎች ጥሩ ሰው ነች ግን ካድኳት ብሎ ጆሮ ሲሰጡት ኃጥያቴን አግዝፎ እና አለስልሶ ያትታል። የውስጥ እውነት በጭብጨባ ሆነ በእርግማን ብዛት የሚዛነፍ መስሎት። ኢየሱስን የከሰሱት እና የሰቀሉት እኮ ያልደረሰባቸው እና የፈወሳቸው ናቸው፤ ሰቃይ እና ከሳሾቹ ሲጠየቁ የሚሉት መች አጡ?
እሱ ግን ትዝታችን ይበቃኛል ያልኩትን አላመነኝም! ...

❤27👍9👎1😱1
#ለነጻነት_አንድ_ወደፊት
ሽፋሽፍቷ በእንባ ርሶ ደረስኩ፤ እንዳላየሁ መሆን በማልችልበት መልኩ ነበር ያየኋት። እኔ ደግሞ የሰው ሐዘን ምንጭ ለማወቅ ከማይጓጉ የሰው ልጆች መካካል ነኝ። ሽፋሽፍቷ ላይ ወፍራም እንባ እንደተጣበቀባት አፍጥጣ አየችኝ። ተጠፋፋን እኮ ብዬ አቀፍኳት፤ እናቷ ጠፍታ ውላባት እንዳገኘቻት ትንሽ ልጅ ተጠመጠመችብኝ። አሪፍ ማኪያቶ ልጋብዝሽ ብዬ ይዣት ወጣሁ።
ጭንቅላቷን በሌላ ወሬ ወጠርኩት፣ ተላፋኋት፣ ካፌ ጋ ወዳለው የሚያንደረድረው መንገድ ገፍቼ አንደረደርኳት፤ እየተሳደበች፣ እየተራገመች እና እየሳቀች ተንደረደረች። አንተ እብድ ነህ ምናምን እያለች እንድርድሮሹ እንዳበቃ ተነጫነጨች።
ካፌ እንደተቀመጥን ሁለት ቡና አዘዝን። እንድታወራልኝ አፍጥጬ አየኋት።
“ይልማ ሕይወቴን አወሳሰበብኝ፤ አብሬው መሆን ከጀመርኩ ዘጠኝ ወራት ቢቆጠሩም አልጨበጥ አለኝ፤ እንደ ወደድኩት ስለገባው ችላ አለኝ፤ ለመድኩትና ይናፍቀኛል፤ እንዳልተናፈቅክ እያወቅክ መደወል እና መፈለግ ደስ አይልም። አኩርፈህ ዝም ስትባል ደውሎ አኩርፌሃለሁ ማለት አለመፈለግህን በትልቁ ይመሰክርብሃል።
ስልኩ ሲጠራ ሴት የደወለች እየመሰለኝ በመሳቀቅ፣ በቅናት መንፈስ የደዋይን ማንነት በአይኔ ስልኩ ስክሪን ላይ አጣራለሁ፣ ስልኩ እንዲጠራ አልፈልግም። ሰቀለኝ እኮ! አሸነፈኝ፣ ከእሱ ጋ መሆን አልፈልግም ብዬ ፎክሬ፣ ምዬ ሲጠራኝ ያለኝ ቦታ ካለኝ ሰዓት ቀድሜ እገኛለሁ፣ ተሰቃየሁ። በተከታታይ ከተገናኘን እሰለቸዋለሁ መሰለኝ ይጠፋል። ስልኩን ያጠፋል። አስሰዋለሁ፣ እጨነቃለሁ፣ ይደብተኛል።የምበላው ሳይቀር ጣዕም አልባ ይሆንብኛል። ጸጉሬን መሠራት፣ አዲስ ሰው የማግኘት ፍላጎት አጣለሁ፣ እነጫነጫለሁ::
ራሱ በፈለገ ቀንና ሰዓት አውቆ ከጠፋበት ብቅ ይልና የማያሳምን ምክንያት ይደረድራል። ይስመኛል፣ ይላፋኛል፣ ቀፋፍሎ፣ ፎግሮ ባዶ ክላስ ውስጥ ከእሱ ጋ ብቻ ራሴን አገኘዋለሁ። የማይስምኝ ቦታ የለም፣ ይገለባብጠኛል፣ እንደናፈቀኝ ይሆናል ሰውነቴ። ሁለመናዬ ይከፋፈታል፣ እጦቴ ይሞላል፣ ድብርቴ ይበራል፣ በጀርባዬ አንጋሎ፣ እላዬ ላይ ተጋድሞ በእጆቹ ጸጉሬን ይዞ በጆሮዬ በለሆሳስ ቁንጅናዬን፣ ጥፍጥናዬን ሹክ ይለኛል፤ ያኔ ዓለም ትጠበኛለች፣ ሐሴት ሰውነቴን ሲያጥለቀልቅ ይታወቀኛል። ምንሽ ነኝ ሲለኝ፤ ነፍሴ ነህ እለዋለሁ።
ተቃቅፈን፣ ተሳስመን፣ ተዋሕደን ስናበቃ ተቆላልፈን ስለ ነገ እያወራን በጎዳናዎቹ እንነጉዳለን። ፊቴ ይደምቃል፣ የሚያደርገኝን ያሳጣኛል። ይሄ ስሜት እና ፍቅራችን ከሦስት ቀን በላይ አይዘልቅም። ያበሳጨኛል፣ ስልኩ ረጅም ሰዓት መያዝ ይጀምራል። ወይ ስልክ አያነሳም፣ አልያም ስናወራ ወሬ አጠር አጠር ያደርጋል። ሕልሙ ውሰጥ እንደሌለሁ መለየት እንደሚፈልግ ምልክት ይሰጠኛል ከዛም ድብርት፣ ብሶት፣ ንጭንጭ ይታገለኛል። አጥፍቶ ስናገረው ይጮሃል። ጨቀጨቅሽኝ ብሎ ስለመጨቅጨቄ እንድናወራ እንጂ ስለጭቅጭቄ ምንጭ መወያየት አይፈልግም፤ ከዛ ይጠፋብኛል። ካለበት እሄዳለሁ፣ እለማመጠዋለሁ፣ እንደፈለግክ ሁን እለዋለሁ፣ አልጨቀጭቅህም የኔ ጥፋት
ነው ብዬ ራሴን ጉያው ውስጥ አገኘዋለሁ። ተሰቃየሁ" አለችኝ።
አይዞሽ ትግልሽ እና አልሸነፍ ባይነትሽ ነው ስቃይሽን ያበዛው፤ ራስሽን አረጋጊ፣ ስለግንኙነታችሁ ስሜታዊ ሳትሆኚ ራስሽን ጠይቂ?
ይወድሻል?
ለምን ካንቺ ጋ ሆነ?
ለምንድን ነው የምትወጂው?
ግንኙነታችሁ ፍሬ ያፈራል ወይ?
ባል መሆን ይችላል?
ኃላፊነት መሸከም ይችላል?
ተረጋጊ! እልህ አትጋቢ፣ ራስሽን ሁኚ፣ ረጋ በይ፣ ያለሽበት ደረጃ እውነታን ከነባራዊ ሁኔታ ጋ ማግባባት የምትችይበት ነው። በአንድ ጀምበር ለመቆጨት አትታገይ፣ በአንድ ጀምበር ያልተጀመረ ነገር እንደዋዛ በአንዴ አይፈርስም። አትከታተይው፤ ጊዜሽን፣ ትኩረትሽን በቀስታ ሌላ ነገር ላይማዋል ጀምሪ።
የያዘሽ ፍቅር አይደለም ሱስ እንጂ። ቁጭት፣ መብከንከን፣ እልህ ይሉት ነገር ሱስን የማባባስ ኃይሉ ከባድ ነው። ወደ ራስሽ ማተኮር ስትጀምሪ፣ አይንሽን ስትገልጪ፣ ሱስሽ አቅም ያጣል።
ተረጋጊ አዳዲስ ሰዎች ተዋወቂ ራስሽን ተንከባከቢ ተረጂው አትማረሪ ከሰዎች ጋር ያለውን መስተጋብር መርምሪ ምን አይነት ሰው ነው ? ከቤተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል ? ሕልሙ ምንድን ነው ? ጊዜውን የት ያሳልፋል?ስለራሱ ያለው ምልከታ ምንድን ነው ? ከዚ በፊት ፍቅረኛ አለችው ወይ? በምን ተለያት ?
እንደዚህ የከበደሽ ሰው ምን አልባት ቀላል ይሆናል አንዴ ስለተሸነፍሽለት ይሆናል የተወሳሰበብሽ በደንብ ስታውቂው ምናልባት ማስተካከል ይቻልሻል ምን አልባት የማትፈልጊው ሰው ይሆናል ምን አልባት ባሕሪው ይሆናል ያኔ በምክንያት ትለይዋለሽ ወይ በምክንያት አብረሺው ትሆኛለሽ አትማረሪ ጥቃቅን ነገሮች ላይ ብቻ አትመሰጪ የገጠመሽን ችግር ወጣ ብለሽ ችግሩን ለማሰላሰል ይጠቅምሻል።
ብዬ እንደጨረስኩ ከመቅፅበት ከተቀመጠችበት ብላ እቅፍ አድርጋ አመሰገነችኝ።
"እንዳልከኝ አደርጋለሁ የችግሬ ግማሽ የተፈታ ዓይነት ተሰምቶኛል።
በለመለመው ተስፋዋ ላይ አንዲት ቃል ሰነዘርኩላት...
ከችግሩ ወጥተን ችግራችንን ካስተዋልን ችግራችንን እንበልጠዋለን።
የኔን አልነገርኳትም ቃል እየተፈታተነችኝ ነው።

❤22👏4
#ፍቅር_ለሠዓሊው
==
እኔ የያዝኩት ፍቅር አይበረክትም ይቅርታ ፍቅሩ እንኳን አይደለም ተፈቃሪዎቹ ናቸው ማይበረክቱልኝ..መቼ እጄ እንደሚገቡ መቼ ደግሞ ሾልከው እንደሚጠፉ አይደለም ለተመልካች ለእኔም እራሱ ይገርመኛል፡፡ደግነቱ ኮከቤ ነው መሰለኝ ብርና ፍቅረኛ እንዲሁ እንደቀልድ ምንም ሳልጥር እና ሳለፋ ነው ወደእኔ ሚሳቡት..እንደዛውም የሚበተኑት…፡፡.የአሁኗ ፍቅረኛዬን ግን ላለማጣት ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጥረት እያደረግኩ ነው፡፡ አረ ለሰው አፍ ስል እራሱ ከእሷ ጋር ወደ ትዳር አለም መዝለቅ አለብኝ ብዬ ወስኜያለው፡፡ይሄንንም ውሳኔዬን ዛሬ ልነግራት ቅድመ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለው፡፡ግን ይሄንን የመሰለ ወሳኝ የህይወት ክስተት በዚህች ዝብርቅርቋ በወጣ የአዲስአባ ኳኳታ ውስጥ ብነግራት ቀልቧን ሰብስባ በጽሞና ልትሰማኝ አትችልም ብዬ በመፍራት ወደ ወንዶገነት ይዤት እየሄድኩ ነው፡፡
ይሄንን ፕሮግራሜን ለአንድ ጓደኛዬ ትናንት ስነግረው ያው እንደተለመደው ‹‹ልፋ ቢልህ ነው…› ነበር ያለኝ፡፡ለርብቃ ደግሞ እንዲህ ነበር የነገርኳት
‹‹ርብቅዬ››
‹‹ወይዬ ማሬ››
‹‹እሁድ ከከተማ ወጣ እንድንል ፈልጌ ነበር››
‹‹የመቼው እሁድ? ››
‹‹የፊታችን እሁድ ››
‹‹ምን ችግር አለ …እንወጣለን ቢሾፍቱ ነው ወይስ…?››
‹‹አይ ተለቅ ያለ ሰርፕራይዝ ስላለኝ.. ራቅ ያለ ቦታ እንድንሄድ ነው የምፈልገው... ሁለታችንም ከዚህ በፊት ሄደን የማናውቀበት ቦታ››
‹‹ወይኔ ታድዬ የእኔ ማር..ዱባይ እንሄድ ብቻ እንዳትለኝ….››
‹‹ኸረ ምን በወጣኝ..ፈጽሞ እንደዛ አልልሽም፡፡ ነፍስ አባቴ የኢትዮጵያን ድንበር አልፈህ እንዳትወጣ ብለው እንደገዘቱኝ ከዚህ በፊት አልነገርኩሽም››
‹‹አልነገርከኝም..ደግሞ ነፍስ አባትህ ማን ናቸው? ነፍስ አባት አለህ እንዴ? ››
ለሚያበሳጭ ጥያቄዋ የሚያበሳጭ መልስ ከመስጠት ታቅቤ ቀጥታ ወደ ነጥቤ አመራው፡፡
‹‹ወንዶ ገነትን ታውቂያታለሽ?››
‹‹አዎ አውቃታለው መሰለኝ.. ጐንደር አካባቢ ነው አይደል የምትገኘው?››ይሄንን ወሬ የምናወራው ካፌ ውስጥ ቁጭ ብለን ስለነበረ የእሷን መልስ ሰው ሰምቶት ይሆን? ብዬ በመሸመቀቅ ግራና ቀኝ ተገለማመጥኩ፡፡ ተመስገን ነው በአቅራቢያችን የሰው ጆሮ አልነበረም፡፡
‹‹ወንዶ ገነት ደብብ ክልል ውስጥ ከሻሸመኔ ወይም ከሀዋሳ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ ትንሽ እና ለምለም ከተማ ነች ፤ ለማንኛውም ስለማታውቂያት እንሄዳለን ተዘጋጂ ›››አልኳት ፡፡ይሄው ዛሬ ለመምጣት በቃን፡፡ ዝዋይ አካባቢ እንደደረስን
‹‹ለምን ወደ ወንዶ ይዘኸኝ እንደመጣህ እኮ አውቃለው ››ስትለኝ በድንጋጤ የመኪናዬን ፍሬን ሲጢጢጢ አድርጌ አቆምኩት
‹‹ማን ነገረሽ?››
‹‹እንዴ ማን ይነግረኛል.. ያን ያህል ጅል አደረግከኝ እንዴ?›› ብላኝ እርፍ፡፡
‹‹እንዴት ጅል አደረግከኝ ?››
‹‹በቃ ለማንኛውም በጣም ፍቅርረቅር አደርግሀለው …የልደቴን በዓል አስታውሰህ ለየት ባለ ሁኔታ ልታከብርልኝ ስለወሰንክ አመሰግናለው›› ብላ ተንጠራርታ ሳመቺኝ..ምኔን ነው የሳመችኝ..? አልነግራችሁም…..ብቻ ተንፈሰፈስ አልኩ፡፡
‹‹ግን በጣም የደነቀኝ ….የልደት በዓል ቀኔን እንዴት ልታውቅ እንደቻልክ ነው?››
‹‹ካሰቡበት የሚከብድ ነገር አለ ብለሽ ነው?ፍቅረኛዬ እኮ ነሽ››ብዬ አቅራራው
‹‹ባክህ አትጐርር እርግጠኛ ነኝ ከፌስቡክ ላይ ነው ያየኸው፡፡››
ዝም አልኳት …በውስጤ እድለኛ ልጅ መሆኗን እያሰብኩ ወደፊት የቀለበት በአልሽን እና ልደትሽን በአንድ ላይ ደርበሽ ልታከብሪ ነው ስል ስለአጋጣሚው መደራረብ አብሰለሰልኩ፡፡
።።።
ለማንኛውም አሁን ከርብቃ ጋር ወንዶ ገነት ደርሰናል ፡፡ የእኔ ማር በደስታ እና በመፍለቅለቅ ነፍሷን አስደስታ ነፍሴን በማስደሰት ላይ ትገኛለች፡፡ርብቃ እስከዛሬ ካጋጠሙኝ ሴቷች ትለያለች፡፡ አይ የእኔ ነገር እንዲሁ ለወሬ ማድመቂያ ብዬ እንጂ አንደኛዋ ሴት ከሌለኛዋ ሴት መለየቷ የት ይቀራል? ግን ክፋቱ ወንዶ እንደደረስን ሳላስበው ትኩረቴ በአንዴ ከርብቃ ወደ ወንዶ አዘዋወርኩት፡፡ ለወንዶ መሳቅ ፤ለወንዶ ማውጋት ፤ለወንዶ ማንሾካሾክ ጀመርኩ፡፡ወንዶ ገነት ምን አልባት በሄዋን ስህተት ምክንያት የፈረሰችው እውነተኛዋ ገነት ትሆን እንዴ?ከተማዋን ሲያስተውሏት ሁለት አይነት ገጽታ አላት::የመጀመሪያው ገፅታዋ ኑዋሪዎቾ የገነቧቸው ወይም የሚኖሩባቸው ቤቶች እንደማንኛውም ጐስቋላ የኢትዬጵያ ትናንሽ ከተሞች የደከሙ ፤ የፈራረሱ እና የተንሻፈፉ ቤት መሰል መጠለያዎች የሚበዙባቸው ናቸው፡፡የተፈጥሮ ደኑም ከሌሎች በደን የተሸፈኑ የኢትዬጵያ አካባቢዎች እንደ ጅማ፤ኢልባቦር፤ባሌ ከመሳሰሉት ጋር ብዙም የተለየ አይደለም ልዩ የሆነው ሌላዋ ገጽታዋ ማለት የእኔን ቀልብ ከርብቃ የነጠለው እና በጣም የመሰጠኝ ነገር አንደኛው የምንጮቾ ብዛት እና አይነት ነው፡፡ በእዚህም እዛም በሚንቋረሩ የምንጭ ውሃዎች የተሞላች ከተማ ነች፡፡በየተወሰኑ ሜትር ልዩነት ምንጮች ይንፎለፎሉባታል ፡፡አንዱ ምንጭ ቀዝቃዛ ይሆናል፡፡ሌላው ደግሞ የሚንተከተክ ሙቅ…
ሌላው እውነተኛ ገነት የሚያስብላት ነገር ደግሞ ሚበቅሉባት የፍራፍሬ ዓይነቶች ናቸው፡፡በአካባቢው ከበቀለው አረንጓዴ ዕፅዋት መካከል ከማይበላው ይልቅ የሚበላው በቁጥር ይበልጣል ሸንኮራ፤ ሙዝ፤ ፓፓዬ፤ ዘይቱና፤ አቡካዶ፤ መንደሪን፤ ሎሚ፤ መንጎ፤አናናስ ፤እንሰት፤ጫት ፤ቡና…ወዘተ በአካባቢ ውበት በተትረፈረፈ ሁኔታ የሚበቅሉ አዳምና ሄዋን ይበሉት ዘንድ ያልተፈቀደላቸው የበለስ ፍሬ ብቻ ነው ያላየውት….ታዲያ እንዲህ የሚያስጐመዥ ጣዕምና ባላቸው ፍራፍሬዎች የተሞላች ሀገር የድሮዋ ገነት የአሁኗ ወንዶ ገነት ትሆን እንዴ ብዬ ብጠረጥር ጅል ያሰኘኝ ይሆን..?
ደግሞ እንዲው ዙሪያዋን የከበቧት የተጠላለፉ ተራሮችን ስመለከት የአዳም ልጅ የሆነው ቃኤል ወንድሙ አቤልን ከገደለ ቡኃላ በመቅበዝበዝ እና በመባከን ቀሪ ህይወቱን በፀፀት ያሳለፈባቸው የውጣ ውረዱ መገለጫ ኮረብቶች ይመስሉኛል፡፡
ከርብቃ ጋር በሀሳብ አለመስማማት የጀመርነው ገና ወንዶ እንደደረስን ነው..እሷ እዛ ከተማው ውስጥ የአፄ ሀይለ ስላሴን ቤተመንግስት ጐብኝተን በፍል ውሃው ሰውነታችንን አስመትተን ከዛ መዋኛ ገንዳው ውስጥ ገብተን ስንዋኝ እንድንውል ፈለገች፡፡እኔ ደግሞ ከሁሉም በፊት ይሄንን አስደማሚውን ተፈጥሮ ተከትለን ወደላይ ወደተራራው እንድንወጣ ፈለኩ፡፡ሳይመስላት ተስማማች፡፡ማደሪያ ቤርጐ ተከራየንና ጓዛችንን አስቀመጥን እንቅስቃሴ ጀመርን፡፡
====
ወደ ታራራው ከፍታ ብቻችንን አይደለም ያቀናነው፤ ለማንኛውም በሚል መንገዱን የሚያሳየን እና እንደጋይድ የሚያገለግለን አንድ ወጣት ተከራየን ..ግን ሰው ይከራያል እንዴ ?ብላችሁ እንዳትጠይቁኝ፡፡ብቻ ጉዞችንን ጀምረናል …መንገዱ ከባድ ነው…. ከባድነቱ ግን ለእኔ ለድንዝዙ ሳይሆን ለብልጧ ፍቅረኛዬ ለርብቃ ነው፡፡እኔማ በመደመም ነው የምጓዘው፡፡ ቀድሞ አዕምሮ ካልደከመ አካል አይደክምም፡፡ ወደ ላይ ከፍ እያልን ስንሄድ በጉዞችን የሚያጋጥሙን ምንጮች ሞቃት ናቸው፤ ይፋጃሉ ፡፡አንዳንድ ሰዎች እንደውም ድፍን ጥሬ እንቁላል ውስጡ በመጨመር ለጥቂት ደቂቃ በማቆየት እየቀቀሉ ሲመገቡ ታዝቤያለው፡፡ መሄድ የቻልነው እስከ ተራራው ወገብ ድረስ ነው፡፡በብርድና በተለያየ በሽታ ሲሰቃዩ የከረሙ ሰዎች መተው ፈውስ ሚያገኙበት ቦታ ደረስን ፡፡የተለየው ነገር ሰውነትን በአሸዋ ቀብሮ በሚያቃጥለው ምንጭ መጠመቅ ነው፡፡ እኛ በቦታው ስንደርስ ከአምስት በላይ ሰዎች አንገታቸው ሲቀር ሌላውን ጠቅላላ የሰውነታቸውን ክፍል በአሸዋው ቀብረው እንፋሎታማውን ምንጭ

❤1
ለሳዕታት አካላቸውን እንዲለበልባቸው በማድረግ ከሚያሰቃይ በሽታቸው ለመፈወስ ሲጥሩ አገጥመውናል.. ከዛ መቼስ የመልስ ጉዞችንን አልተርክላችሁም፡፡ በርብቃ ንጭንጭ እና ኩርፊያ ተማርሬ ስለነበረ የመልስ ጉዞው ደስ የማይል ነበር፡፡
====
ርብቃ ፍቅሬ ወደ ከተማ ከተመለስን ቡኃላ እንኳን ወደ ቀደመ ቦታዋ ለመመለስ እና ፈገግ ለማለት ሰዓታት ፈጅቷባታል፡፡ዛሬ ደግሞ ታውቃላችሁ በምንም አይነት ሁኔታ የእሷ ሙድ እንዲበላሽ አልፈልግም፡፡ እራት ሰዓት ላይ ልደቷን ላከብርላት ቀለበትም ላስርላት እፈልጋው፡፡ የከሰዓት ፕሮግራማችን ያው የመዋኛ ገንዳው አካባቢ ማሳለፍ እና መዋኘት እንዲሁም የሚዋኙትን የሀገር ውስጥና የሀገር የውጭ ቱሪስቶችን ዕንቅስቃሴ እና ሁኔታ እያዩ መዝናናት ነው፡፡አሁን እያረግን ያለነውም እንዳዛው ነው ፡፡አንድ ዛፍ ስር ሁሉንም ለማየት የሚያስችል ቦታ ጎን ለጎን ተቀምጠን በቱቦው ከተራራው ላይ ተስቦ እየተወረወሩ በሚመጣው ፍል ውሃ ሰውነታቸውን የሚያስቀጠቅጡትን ሰዎችና በመዋኛ ገንዳው ውስጥ በመዋኘት የሚዝናኑ ሰዎችን በማየት እየተዝናናን ነው፡፡
…..ግን መዝናናት ማለት ምን ማለት ነው?ይመስለኛል አንድ ሰው ተዝናና የሚባለው የህይወት ችግሩን ፤የቤተሰብ ጣጣውን፤የስራ ውጣ ውረዱን፤ያለፈ ፀፀቱን፤የወደፊት ተስፋውን ረስቶ ወይም ከአዕምሮው ጓዲያ ደብቆ ፊት ለፊት ያለውን የአዕምሮ ክፍል የነጻ እና የጠራ አድርጐ ልክ እንደ ህጻን ከይሉኝታ ውጭ ሆኖ ፤ከማንነት ኬላ ተሸግሮ….. ሲጨፍር፤ ሲቧርቅ፤ሲደንስ ስናይ ተዝናና ይባላል፡፡ ክርስቶስስ ‹እንደ ህጻናት ካልሆናችሁ ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት አይቻላችሁም› ብሏል እኔ ደግሞ እላለው ‹እንደ ህጻናት ካልሆናችሁ መዝናናትን ውስጥ ያለችውን ጣፋጯን የደስታ ፍሬ አትቀምሷትም ››፡፡
ሰው ቅዱስ የሚሆነው እራሱን በረሳበት፤ የማንነት ኩራቱን አሽቀንጥሮ ጥሎ ከእከሌ እበልጣለው ብሎ ሳይኩራራ እከሌ ይበልጠኛል ብሎም ሳይፈራ…የእንትና ዘር ነኝ…እሱ ደግሞ የምጠላው የእንትን ዘር ነው ሳይል…በገንዳው ውስጥ በአንድነት ሲንቦጫረቅ..በቢቹ ዳር እየተሯሯጠ ኳስ ሲጣልዝ….አዎ የዛኔ ለእኔ እነዛ ሰዎች በሰማያዊ የደስታ እቅፍ ውስጥ ያሉ ቅዱሳን ይሆናሉ፡፡
እኔ ስለ እዚህ ጉዳይ ሳሰላስል እና ሳጠነጥን ቆይቼ ‹‹አይገርምሽም የእኔ ማር …››ብዬ ስለጉዳይ ላወራት ዞር ስል ርብቃ ከጐኔ የለችም .. ጥላኝ ከሄደች ምን ያህል ደቂቆች እንዳለፉ ማወቅም፤ መገመትም አልቻልኩም፡፡ አይኔን ከግራ ወደቀኝ እሷኑ ፍለጋ አንከራተትኩ፡፡ ብዙም ሳለፋ አየዋት፡፡ መዋኛ ገንዳ ውስጥ ከወገብ በታች አካሏ በውሃ ተሸፍኖ ከወገብ በላይ ለአደባባይ ዕይታ ተጋልጣ ተመለከትኳት፡፡ ስትታይ እንዴት ደስ ትላለች…አሁን የስዕል መሳያ ዕቃዎቼን ብይዝ ኖሮ እንዴት አድርጌ ነበር የምስላት? ብዬ አሰብኩ..ባልይዝም ግድ የለም…. በምናቤም ቢሆን ልሳለው ብዬ ወስኜ ወደ ተመስጦ ውስጥ ገብቼ ከፊቷ ጀምሬ መላ አካላቷን በቄንጠኝ ሁኔታ በሀሳብ እያሳልኳት ሳለ አንድ የፈረንጅ ነጭ… ኸረ ነጭም አይባል ሽሮ መልክ እጅ ሰውነቷ ላይ አርፎ ተመለከትኩ ፡፡ይሄንንማ አልስለውም ፡፡ ብቀደው ይሻለኛል አልኩና ቀልቤን ወደ እውኑ ነባራዊ ሁኔታ ስመልስ ያንኑ ፈረንጅ ለዛውም ከእነሙሉ አካሉ የኔዋን ርብቃን… በዛሬው ቀን የትዳር ጥያቄ ላቀርብላት ወደ 300 ኪሎ ሜትር ጉዞ ተጉዤ እዚህ ድርስ ያመጣዋትን ፍቅረኛዬን ፈረንጁ እጅ ላይ… ፈሰስ ብላ ተኝታ በገንዳው ውሃ ስትንቧጫረቅ አየዋት..በቃ የእውነት አየው…..እንግዲህ ዋና እያለማመዳት መሆኑ ነው፡፡ ሳቋ ና መፍለቅለቋ ደግሞ ልክ አውሮፕላን ማብረር የሚያለማምዳት ነው የስመሰለቺው..፡፡በየመሀሉ ደግሞ የፈራችና የደነገጠች በማስመሳል ዛላ አንገቱን አቅፋ ትጠመጠምበታለች ፡፡
ከዛ በላይ መታገስ አልቻልኩም፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነሳውና የሸሚዜን እጅጌ ሰበሰብኩ…ለካ ያሰብኩትን ነገር ለማድረግ መዋኛ ገንዳ ውስጥ መግባት አለብኝ… ለዚያ ድግሞ ሸሚዜን መሰብሰብ ሳይሆን ማውለቅ ነው የሚጠበቅብኝ አልኩና አወለቅኩት… ጫማዬን እና ሱሬዬንም ጨምሬ አወለቅኩና ወደ ገንዳው መጓዝ ጀመርኩ፡፡ የአንድ ወር ፍቅረኛዬን እና የወደፊት ሚስቴን ከወራሪ ፈረንጅ እጅ ነጥቄ እሱ የሚያደርግላትን ነገር በራሴ ላደርግላት …..ግን መሀል መንገድ ላይ ጉዞዬ ተገታ፡፡
የምታማልል ሌላ ሴት አይቼ እና ደንዝዤ እንዳይመስላችሁ.. ልወስድ ያሰብኩትን ሀሳቤን ቀይሬ ነው እርምጃዬን የገታውት ፡፡እንዴት የነገሮችን ተፈጥሮዊ አካሄድ እቀይራለው… እስቲ የዚህ ፈረንጅ እና የእኔ ፍቅረኛ በድንገት የተጀመረ ግንኙነት እስከየት ይቀጥላል? ምን ያህል ዕድሜስ ይኖረዋል? አስር ደቂቃ …ሰላሳ ደቂቃ..ሶስት ቀን ሶስት ሳምንት… አዎ መታዘብ አላብኝ እልኩና ወሰንኩ ፡፡ወስኜም ቀኝ ኃላ ዞሬ ወደ ቦታዬ ተመለስኩ፡፡ያወለቅኩትን ልብስ አንድ በአንድ መልሼ ለበስኩና እዛው ሳር የለበሰ መሬት ላይ ቁጭ ብዬ መታዘቤን ቀጠልኩ ፡፡ለአንድ ሠዓት አልተላቀቁም፡፡
እርግጠኛ ነኝ ማንም ሰው ሲመለከታቸው የሚገምተው ባልና ሚስት ሆነው አንድ ሁለት አመት የቆዩ እና አሁን ሀገሯን እያስጐበኘችው እንደሆነ ነው..እኔ እራሴ አዕምሮዬ ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዛ አስቦብኛል…አብሬያት የመጣዋት ፍቅረኛዬ አይደለች ይሆን እንዴ….?ዝም ብዬ በምናቤ የፈጠርኮት የእኔ ያልነበረች ሴት ትሆን እንዴ? እያልኩ ውዝግብ ውስጥ ገብቼ ነበር፡፡ ለማንኛውም አሁን ከመዋኛ ገንዳው እየወጡ እንዳለ ይታየኛል…አዎ እሱም ልብሱን አውልቆ ወደአስቀመጠበት ሄዶ መልበስ ጀመረ እሷም ልብሷን ወደ አስቀመጠችበት ሄደችና መልበስ ጀመረች ፡፡የሚገርመው ሁለቱም እየለበሱ አይናቸው አንዱ ያንደኛውን አካል እየሰረቀ ይመለከት ነበር..በአይናቸው ሲሸረሙጡ እንዴት ያስቃሉ….ለማንኛውም ለብሳ እየጨረሰች ስለሆነ ወደ እኔ ልትመጣ ነው….ስለፈረንጁ ምን እንደተሰማት በዘዴ እጠይቃታለው ..፡፡መቼስ በግልፅ የውስጧን ስሜት ሙሉ በሙሉ ባትተነፍስልኝም በገደምዳሜው ቢሆን የሆነ ነገር ማለቷ አይቀርም..፡፡የጎደለውን እኔ በምናቤ ሞላዋለው፡፡
……እንዴ ይሄ ፈረንጅ ልብሱን ለብሶ እንዳጠናቀቀ ወደ እሷ እየተሳበ ሄደ..ቢሄድስ በቃ ሊሰናበታት ነው ብዬ አስቤ እንኳን ሳልጨርስ እጇን ይዞ ወደ ካፌው ወሰዳት…እውነት ይህቺ ልጅ ከማን ጋር ነው የመጣችው…?ከእኔ ጋ ነው ወይስ ከእሱ ጋር? ዓይኔን እነሱ ላይ እንዳጣበቅኩ ነው… ጁስ አዘው እየተሳሳቁ መምጠጥ ሲጀምሩ የሆነ የሚቦረቡር …ሳል ሳል የሚል ስሜት ወረረኝ፡፡ አቀማመጣቸው ፤የጁሱን ብርጭቆ አያያዛቸው፤ በመሀከላቸው ያለው መሳሳብ ልዩ ነበር
ስለዚህ ደውዬ ልረብሻት ስላልፈለኩ ሞባይሌን አነሳውና መልዕክት ጻፍኩላት
‹‹ወደክፍል ሄጃለው ስትጨርሺ እዛ እንገናኝ ››አልኩና ወደያዝነው የቤርጐ ክፍል አመራው፡፡ ለማንኛውም ብዬ ይዤ የነበረውን የተወሰነ የስዕል መሳያ ቁሳቁስ አወጣውና በምናቤ ያለውን የፍቅራኛዬን እና የፈረንጁን የአብሮነት ምስል መሳል ጀመርኩ፡፡ ጨርሼ ሰዓቴን ስመለከት መሽቶ አንድ ሰዓት ሊሆን አስር ደቂቃ ብቻ ነበር የቀረው…፡፡አይገርማችሁም እስከ አሁን ርብቃ ምትባለው ፍቅረኛ ተብዬ አልመጣችም፡፡ወይንም እኔ ሳላስተውላት መጥታ ተመልሳ ሄዳ ይሆናል፡፡ለማንኛውም አሁን ተመልሳ ከመምጣቷ በፊት ለማታው ዝግጅት መሰናዶ ማድረግ አለብኝ፡፡

‹‹ሀኒ የልደትሽን ኬክ ለማምጣት ወጥቼያለው››ብዬ መልዕክት ላኩላትና ሄድኩ፡፡ ጥዋት የታዘዘ ትዕዛዝ ስለነበር ይዤ ለመምጣት ከአስር ደቂቃ በላይ አልወሰደብኝ…ኬክ ብቻ አይደለም.. ከረሜላ፤ ፍራፍሬ፤ ሻማ ፤ቸኮሌት ምንም አልቀረኝም፡፡ክፍላችን ውስጥ ያለችውን አነስተኛ ጠረጳዛ በፍራፍሬ ሞላዋት ፡፡ሻማውን ግን ስገዛ በከፍተኛ መጠራጠር ውስጥ ሆኜ ነው፡፡ ዕድሜዋን በግምት ከ22-25 የሚሆን መስሎ ስለተሰማኝ ሁለት ቁጥር ሻማ ገዛውና ከዛ ሌላ 2 ቁጥር ፤3 ቁጥር ፤4ቁጥር እና 5 ቁጥር ገዛው፡፡ ምክንያቱም 23 ዓመቴ ነው ካለች ከ2 ቁጥር ጋር 3ትን ማዛመድ ነው፤ 24 ዓመቴ ነው ካለችም እንደዛው ችግሩ ከእነዚህ ሁሉ ውጭ እንደይሆን ነው
እንደምንም ሁለት ሰዓት ላይ መጣች‹‹እንኳን ሰለም መጣሽ ማሬ››ስላት በድንጋጤ ፈዛ አየችኝ
‹‹ምነው ምንሆንሽ?››
‹‹እብድ ነህ እዴ?›››አለችኝ፡፡ ዘመዶቼ ቢሆኑ ‹ጅል ነህ እንዴ?› ነበር የሚሉኝ እሷ ግን አሻሻለችልኝ… ጅልነትን በዕብድነት በመተካት፡፡
‹‹ምን አጠፋው .ይ.ልቅ ሀፒ በርዝ ደይ..መልካም ልደት..በሚቀጥለው አመት ደግሞ 24 ዓመት ሲሞላሽ ጐንደር ላይ ነው የማከብርልሽ››
‹‹ባክህ አትቀባዥር ዘንድሮ ነው 24 ዓመቴ ››ብላ ብትጮህብኝም እኔ የምፈልገውን መረጃ ስላገኘው አልተከፋውም….
‹‹ውይ ሻማውን እረሳውት አልኩና ኮመዲኖውን በስሱ ከፍቼ ሁለት እና አራት ቁጥር ሻማዎችን አወጣውና ከኬኩ ግራና ቀኝ አስተካክዬ አስቀምጬ ቀና ስል ርብቃ ስሬ የለችም፡፡ ስስል የቆየውት ስዕል ላይ ሄዳ አፍጥጣ እየተመለከተችው ነው፡፡ ቨውይ የእኔ ነገር ያነሳውት መስሎኝ ነበር …ለካ እዛው መሳያው ላይ እንደተንጠለጠለ ነው፡፡
‹‹ግሩም ስዕል ነው››አለች
‹‹ወደድሽው?››
‹‹ለምን አልወደውም… ግን እንብርቴ አካባቢ ያሳረፈውን እጁን ትንሽ ወደታች ዝቅ ብታደርገው ይበልጥ እወደው ነበር…ማንም ግን እስከዛሬ እንዲ ሰድቦኝ አያውቅም››
‹‹ስዕልና ስድብን ምን አገናኛቸው?››
‹‹ምትገርም ጅላጅል ፍጡር ነህ …ፍቅረኛዬ ምትላትን ሴት አስረክበህ ወደ ቤትህ ገብተ የቅዠት ስዕልህን ትሞነጫጭራለህ..እኔ እንደውም ከአሁን አሁን መጥተህ ከፈረንጁ መንጭቀህ ትወስደኛለህ…ተናደህ መጥተህ በጥፊ ታጮለኛለህ …ቢያንስ ስልክ ደውለህ ትዝትብኛለህ ..የታባሽ ምናባሽ እየሰራሽ ነው? ትለኛለህ ብዬ ስጠብቅ ጭራሽ አንተ………..ምንም አይነት እንጥፍጣፊ ኢትዬጵያዊ ሙቅ ደም የሌለብህ አልጫ ነገር ነህ››አለችና ስልኳን በማንሳት ደወለች… አወራች ለፈለፈች ..ምን እንደተባባለች ግን አልገባኝም ምክንያቱም አዕምሮዬ ቀኑን ሙሉ ሲጠቀም የነበረው በአማርኛ ሶፍት ዌር ስለነበረ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ በፍጥነት ለመቀየር እና የምታወራውን ለመረዳት አልቻልኩም፡፡ ብቻ እንደጨረሰች
‹‹ በል ደህና እደር››ብላ ከክፍሉ ለመውጣት ጉዞ ጀመረች
እንዴ ልትሄጂ ነው እንዴ? ቢያንስ ኬኩን ቆርሰሽ ሂጂ እንጂ..ልፋቴ አያሳዝንሽም? ››
‹‹ልፋትህ ሳይሆን የሚያሳዝነኝ..የእኔ ከማያፍቅረኝ ሰው ጋር ወር ሙሉ ስንከራተት መክረሜ ነው ››
‹‹አረ ማሬ በጣም እኮ ነው የማፈቅርሽ ….እንደውም ሰርፕራይሰዝድ አለኝ እኮ ያልኩሽ…..› አላስጨረሰችኝም
‹‹ሰርፕራይዝህን እዛው ቀቅለህ ብላው ….አንተ እንደውም ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሀ..ሁ… ብለህ መማር አለብህ ….አሁን ሄዳለው ደህና እደር እንኳን ስልህ ከመቅናት እና ማን ጋር ነው የምትሄጂው? ምን ልትሰሪ ነው የምትሄጂው? ብለህ መበሳጨት ሲገባህ አንተ ስለኬክ መቁረስ እና መበላሸት ታስባለህ…የጅል ፍቅር ድሮም ከዚህ አያልፍም››ብላኝ በራፍን ከፍታ በላዬ ላይ በሀይለኛው በሚያስበረግግ ጩኸት ደርግማብኝ እብስ አለች … እኔም በኪሴ ውስጥ ያሉትን ቀለበቶች እየዳበስኩ ስለቅናት እና ፍቅር ግንኙነት እየተመራመርኩ…ይሄ ስሜት በስዕል እንዴት በጥልቀት ሊገለጽ እንደሚችል ወደማሰላሰሉ ገባው…. ሌላ ሸራ ወጥሮ ሌላ ስዕል ወደመሳሉ…..፡፡
✨አለቀ✨

❤1👎1
Forwarded from ONLY BETTING
ሃናንን በጣም እወዳት ነበር እሷም እንደዛው ለዛ ነው ትምህርት ላይ እያለን ኒካህ ያሰርነው።ከኔ ይበልጥ የሷ ፍቅር ከፍ ይል ስለነበር ነፃነቴን አሳጣቺኝ በ ቀን ከ 10ጊዜ በላይ ትደውላለች ምሳ ፣ ቁርስ ፣ እራት ፣ መክሰስ ጭምር መብላቴን ታረጋግጣለች። ሰለቸኝ!!
አንድ ቀን እንቅልፌን ልተኛ እየተዘጋጀው እያለ ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ ሃናን ነበረች ቀን ስላወራን መልዕክቱን ሳልከፍተው ተኛው።
ጠዋት ስነሳ እናቴ እያለቀሰች ትቀሰቅሰኛለች ምን እንደሆነች ስጠይቃት የ ሃናን እናት ደውላ እንደነበር እና ማታ . ...read more 📍ሙሉ ለማንበብ 📥 ይጫኑ