#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....እሱም ዓለሚቱም ለአገሩ እንግዶች በመሆናቸው ምክንያት ፍላጎቱን በአስቸኳይ ማሳካት አልቻለም፡፡ ይሁን እንጂ እየዋለ እያደረ እሱ የሚፈልጋት ወንጀል እሱ የተጠማት ደም ወዳጅዋን ፍለጋ ዳዴ እያለች እየመጣችለት ነበር።
እንደ ልማዱ የአንበሶቹን ግቢ አጥር አንቆ አንበሶቹን ይመለከታል።
“ሲያዩት ገና ከገጠር የመጣ ነው" አለ ከወዲያ ማዶ ሆኖ ሁኔታውን ሲከታተል የነበረው ጆብሬ፡፡በአዲስ ልብሱ በቦላሌ ሱሪው ውስጥ ደንበኛ ባላገርነቱን አነበበ፡፡ በሃሳቡ ከኮት ኪሱ ውስጥ ከብብቱ ስር ገብቶ ሲሞዠልቀው ታየው።
እጅሬ የእርሻ በሬዋን ወይንም የጎተራ ጥሬዋን ሸጣ በርካታ ብር ሳትይዝ አትቀርም"ብሎ ገመተና "ልዳብሳት!"ሲል ወሰነ፡፡ አስፋልቱን ተሻገረና ወደ አንበሶቹ ግቢ መጣ፡፡ ጠጋ አለ። ወደ ጎንቻ፡ ሽቦውን በሁለት እጆቹ ግጥም አድርጎ ይዞ "ፓ! ወይኔ! ኧረረረ!!…አፉን እንዴት ነው የሚከፍተው በእናታችሁ?!” የጎንቻን የባላገሯን ልብ ሰልቦ ትኩረቷን በአንበሳው
ላይ እንድትጥል ለማድረግና ከዚያም ያለ ሀሳብ ኪሷን ለመዳበስ ነበር።
በጆብሬ አመለካከት ጎንቻ አፏን ከፍታ የቀረችው አንበሳ አይታ ስለማታውቅ ነው፡፡ ያላወቁ አለቁ! አሉ?…ቀስ በቀስ ባላገሯን ተጠጋት። እባቡ ጎንቻ! እንኳንስ ስው ጥላውን የሚጠራጠረው ጎንቻ የጆብሬን እንቅስቃሴ ቀርቶ ሃሳቡን ከነቃበት ቆይቷል። የበግ ለምድ የለበስ የቀበሮ ባህታዊነቱን ያላወቀው ጆብሬ ሲፈርድበት እነዚያ በልምድ የዳበሩ ጣቶቹን
በመቀስ ፎርም ወደ ጎንቻ የኮት ኪስ ሰደዳቸው።
“ሌንጨ ቦሩ!!" አለና ፎከረ እንደ ልማዱ።
ሂድ!ጀጋ! ምን አባክ ሆነሃል?!! ገገማ!!. ጆብሬ ዐይኖቹ እንደፈጠጡ እንደማፈግፈግም እንደማስፈራራትም አደረገው፡፡ ጡንቻውንም እንደማሳየት ቃጣው። ዳሩ ምን ያደርጋል? ያ ባላገር ፤ላጆብሬም እንደ ህልም ሆኖ በሚታወሰው ኃይል ከብረት ምጣዱ ላይ ተሰቅስቆ እንደሚነሳ ቂጣ ሰቅስቆ ወደ ሰማይ አነሳና አስፋልቱ ላይ አነጠፈው። ሲሰርቀው ኪሱ ሊገባ የተመለከቱ ሰዎች ከበቡ። ጆብሬ ሌባ
መሆኑን ከሚመስክረው የተጫጫረ ፊቱ ሌላ የሚያውቁትም ነበሩ፡፡
“ጎሽ! ጎሽ! እሰይ! ወንድ!.. ይበለው! ይበለው ይንጫጩ ጀመር፡፡
“ባላገር መስላ አጅሬ ወንድ ናት!!" ጎንቻን አደነቁ፡፡ ጎንቻም አዲስ አበባ ከገባ ከአንድ ወር በኋላ ደም ካየ ደም ከተጠማ ከአንድ ወር በኋላ ምንም እንኳን ትርፍ የሌለውና ጥቅም የማያስገኝ ቢሆንም ደፍሮ ኪሱ የገባ
ጠላቱን ወደ መሬት ደፍቶ በአፍንጫና በአፉ ደም አስደፈቀው...ጎንቻ ደም አየ። ተደሰተ፡፡ በብዙ ሰው ኃይልና በበርካታ ክንዶች ወደ ላይ በግድ
ተጎትቶ ተነሳ። ቀልጣፋው ጆብሬ፣ አንበሳው ጆብሬ ጣቶቹ አነጣጥረው የማይስቱት ጆብሬ፣ ጉልበቱ የጅብ የነበረው ጆብሬ በጎንቻ ክንድ ውርደት ቀመሰ፡፡ ፍፁም ያልገመተው ነበርና ጎንቻን በአድናቆት ተመለከተው።
ጎንቻን ፈራው፡፡ በፍርሃትና በአድናቆቱ ውስጥም ወደደው። ደሙን ጠራረገና ሄደ። ራቅ ብሎ ከሄደ በኋላ እንደገና ዘወር ብሎ ጎንቻን በጥንቃቄ አስተዋለው፡፡ በአድናቆት ጭንቅላቱን እያከከ ተመልሶ መጣ፡፡
“ወንድ ነህ! ወንድ ጀግና!" እጁን በአድናቆት ዘረጋለት፡፡ ወንድነቱን አምኖ ተሸናፊነቱን ተቀብሎ እጁን የሰጠውን ምርኮኛ ሊያሳፍረው አልፈለገም::ያን ሲመኘው የነበረ፣ ያን ሲያቅበጠብጠው የከረመ ስራ የሚጀምርበትን ቀን ምክንያት አድርጎ ይሆን ጆብሬን የጣለለት? ማን ያውቃል?እጁን ሲዘረጋለት እሱም እየሳቀ ወዘወዘው፡፡ እንደገና ተቃቀፉ፡፡
"አንበሳ ነህ!" ሲል ጆብሬ በድጋሚ አደነቀው። ይሄ ሁሉ እርቀ ሰላም
የወረደው ፀቡ ከበረደና ለወሬ የተሰበሰበው ሰው ከተበተነ በኋላ ሆነ እንጂ ሁኔታቸውን ከመጀመሪያ ጀምሮ ለተከታተለ ሰው ጉድ የሚያሰኝ ነበር፡፡ እንደዚያ ተናንቀው ሲደባደቡ የነበሩት ሰዎች የደም ማግኔት አሳሳባቸውና አንደኛው አድናቂ ሌላው ተደናቂ ሆነው ጨዋታ ጀመሩ።
“ጆብሬ ጫን ያለው እባላለሁ!"
“ጎንቻ ሀጂ ቦሩ" እሰኛለሁ፡፡
"በጣም ወድጄሃለሁ ልጋብዝህ እፈልጋለሁ።"
“ዛሬ አልጋበዝልህም፡፡ ከፈለክ ለነገ እንቀጣጠር” አንድም ቶሎ ብሎ ተጋባዥ ላለመሆን ሁለተኛው ደግሞ የጆብሬን ቁም ነገረኛነት ለማወቅ
እንዲያስችለው በማግስቱ እዚያው አንበሶቹ ግቢ በራፉ ላይ ለመገናኘት ተቀጣጥረው ተለያዩ፡ ጆብሬ ሀቀኛ ስዓት አክባሪነቱንና ጎንቻን ለቁም ነገር የሚፈልገው መሆኑን አረጋገጠ፡፡ ከቀጠሮው ቀድሞ እየጠበቀው ነበር። ተቃቀፉ፡፡
“ቦታ ይዘን እንጫወት" አለውና ጆብሬ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ቁልቁል ይዞት ወረደ። ከዚያም አረቄ ቤት ይዞት ገባና አረቄ እየጠጡ ጨዋታው ደራ። ጆብሬ የህይወት ታሪኩን ይተርክለት ጀመር፡፡
"ወላጆች ነበሩኝ፡፡ መቼም ሰው ያለወላጅ አይፈጠርም! የኔ ወላጆች ግን በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ጥሩ ደመወዝ የሚከፈለው አንደኛው ራስ ወዳድ ሌላው ለኔ አሳቢ ሆኑና በሀሳብ ተለያዩ። አባቴ
ተቀጣሪ ነበር፡፡ እናቴ የቤት እመቤት ነበረች። ገና የሰባት ዓመት ልጅ ሆኜ በቤት ውስጥ ጭቅጭቅና ንትርክ በዛ። አባቴ መጠጥ ይወድ ነበር።
ወላ ሚስቴ የለ ወላ ልጄ የለ! ደመወዙን በአራጣ ለሚበደራቸውና በዱቤ
መጠጥ ለሚሸጡለት ሰዎች ከፋፍሎ ይጨርስና ዐይኑን አፍጥጦ በአል ኮል ነብዞ ይገባል። እናቴ ትንሽ ልትናገረው ከሞከረች አበቃላት። ዛሬን አያድርገው ዛሬን አትውደደኝና በጣም ትወደኝ፣ በጣም ታፈቅረኝ ነበር፡፡ለእኔ ስትል ታገሰችው፡፡ ሲደበድባት ተደብድባ ሲረግጣት መሬት ሆና ብዙ ቻለችው። እንደዚያ የሚያደርገው ቤቱን ጥላለት እንድትጠፋ ሆን
ብሎ ነበር። ጥላው እንዳትሄድ የኔ ነገር ጨነቃት። ከዚያ ቤት ውጭ
የማድግ አልመሰላትም። የአባት ፍቅር እጦት እንዳይጎዳኝ አሰበች፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን ሁሉም ነገር ከአቅሟና ከትዕግስቷ በላይ ሆነባትና እኔን ይዛ ቤቱን ትታለት ጠፋች። ደስ አለው፡፡ ሊፈልጋት አልሞከረም፡፡ወዲያውኑ ሌላ ሚስት አገባ። እኔና እናቴ ከእህቷ ቤት ለኔ አክስት መሆኗ
ነው ከአክስቴ ቤት ገባን። አክስቴ ጠላና አረቄ ትሸጥ ነበር፡፡ እናቴ
እዚያው እሷን እየረዳች መኖር ጀመርን፡፡በዚሁ መሃል እናቴን አንዱ ካላገባሁሽ አላት። አገባችውና እኔን ይዛኝ ቤቱ ገባች፡፡ አዲሱ ባሏ እሷን ይወዳታል።እኔን ግን አይወደኝም፡፡ ዲቃላ! እያለ ይሰድበኝና ያሸማቅቀኝ ነበር።አባዬ ስለው አባት ይንሳህ የለማኝ ልጅ እያለ ያሳቅቀኝ ነበር።
ይሄን የሚያደርገው እናቴ ሳትሰማ ነው። እናቴ በጣም እንደምትወደኝ
ያውቃል። እሷ ፊት ይስመኛል። እሷ ዘወር ስትል ጭንቅላቴ እስከሚበሳ ድረስ በኩርኩም ያጋጨኝና ሳለቅስ እውላለሁ። የእንጀራ አባቴ ቀስ በቀስ ሰው ሳይሆን ጭራቅ እየመሰለኝ ሄደ። ሁል ጊዜ "ዲቃላ! ዲቃላ!
ዲቃላ!” እያለ እየሰደበ እየደበደበ ራሴንም እሱንም እንድጠላ አደረገኝ።
ይሄ ጥላቻዬ ደግሞ ለሱ ጥሩ እንዳልሆን መጥፎ ስራ እንድሰራ ይገፋፋኝ ጀመር፡፡ ቀስ በቀስ ገንዘብ ከኪሱ መስረቅ ጀመርኩ። የሱን ገንዘብ ሰርቄ ብስኩት ገዝቼ ስበላ ይጣፍጠኛል። የጠላት ገንዘብ ይጣፍጣል። እናቴ

❤1👍1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....አሜሪካን ግቢ፣ጌሾ ተራ፣ ዶሮ ማነቂያ፣ ሠራተኛ ሰፈር፣ እሪ በከንቱ በጎንቻ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ የጆብሬና የጎንቻ ጓደኝነት ከሁለትነት ወደ አራትነት ተሸጋገረ። ጎንቻ ጀግንነቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመሰከረው
በፈጣን የአንገት ጥምዘዛ ነበር፡
አንድ ምሽት በሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ ለወሊድ የደረሰች ሚስቱን በሌሊት ሆስፒታል አድርሶ የመመለሻ መኪና አጥቶ ወደ ቤቱ ኩስ ኩስ የሚል ምስኪን አንገት እንደ ዶሮ ጠምዝዞ በመጣል ማንነቱን አሳየው።
ጆብሬ ፍጥነቱንና ቅልጥፍናውን የበለጠ አደነቀው።ከዚያን ግዜ ጀምሮ የበለጠ እያከበረውና እየፈራው መጣ፡፡ገንዘብ በሽበሽ ሆነ፡፡ ጆብሬ ኪስ ይዳብሳል።ጎንቻ ማጅራት ይመታል። ክርክር ከበዛ አንገት እንደ ፎጣ ጠምዝዞ ይጨምቅና ይበረብራል"ለካስ በከንቱ ኖሯል ኛሮ ኛሮ ያሰኘኝ?”
አለ፡፡ ኛሮን በአሜሪካ ግቢ ውስጥ፣ ኛሮን በጌሾ ተራ ውስጥ፣ ኛሮን በዶሮ ማነቂያ ውስጥ፣ ኛሮን በሠራተኛ ሰፈር ውስጥ፣ ኛሮን በእሪ በከንቱ ውስጥ አገኘው
ከኛሮ የቀረ የቀረበት ነገር ቢኖር
ዋሻውና የአውሬ ስጋው ብቻ ነበር፡፡በአዲስ አበባ ውስጥ የወላጆቹን ሃይማኖት ቀይሮ የዓለሚቱ ሃይማኖት ተከታይ ሆኖ አብረው ጮማ ይቆርጣሉ፡፡
አልኮል ይጨልጣሉ። ከዓለሚቱ ጋር በአረግራጊ ሽቦ አልጋ ላይ ያረገርጋሉ። ከዓላሚቱ ጋር እንደዚህ ዓለምን እየቀጩ በአዲስ አበባ ውስጥ መኖርን ቀስ በቀስ እየለመደው፣ እየወደደው መጣ፡፡ አዲስ አበባ ጣመችው፡፡ ጆብሬም
እውነተኛ ታማኝ ጓደኛነቱን አስመሰከረ ጎንቻን ጋሻ መከታው አደረገ፡፡ፀብ ከተነሳ ጎንቻ ገላጋይ መስሎ ተበዳይ ላይ ጉብ ነው፡፡ ጆብሬ የደነዘዘ ሰውነት ካገኘ ሞሽልቆ ያመልጣል። ከተነቃበትም ጎንቻ አለኝታው
ነው። ትርዒቱ ቀጠለ፡፡ አንደኛው የአደጋ ጣይ ቡድን ከሌላው ጋር
ተዋወቀ። በጎንቻ የበላይነት በዓለሚቱ ንብረት ተቀባይነትና አስቀማጭነት ወዳጅነቱ ተጧጧፈ።ሌሎቹ የቡድኑ አባላትም ዓለሚቱን በጥሩ አስተናጋጅነቷ ወደዷት። ፍቅር በፍቅር ሆኑ። መኖሪያ ቤታቸውንም ከእንጦጦ ወደ ዋናው መስሪያ ቤታቸው ወደ እሪ በከንቱ አዛወሩና አንድ ሰፊ ክፍል ቤት ተከራዩ።
በገንዘብ ላይ ገንዘብ ተጨመረ፡፡ እያለቀ፣ እየመነመነ የመጣው ገንዘብ ሲያሳስባት የቆየችው ዓለሚቱ ለመቁጠር እስከሚታክታት ድረስ ተንበሽበሸች፡፡ አራጣ በማበደር ሌላ የገቢ ምንጭ ከፈተች፡፡ በውበቷ ላይ ውበት፣
በጌጣጌጦቿ ላይ ጌጣጌጥ፣ በብር ላይ ብር አከማቸች።
ዛሬም በዓለሚቱ ካዳሚነት ጫት እየተቃመ የተዘረፈው ንብረት የሚቆጠርበት፣ ክፍፍል የሚደረግበት፣ እየተመረቀነ፣ እየተፈረሽ ውይይት የሚካ
ሄድበት፣ ተጨማሪ ዕቅድ የሚወጣበት፣ ስትራቴጂ የሚቀየስበትና ስልት
የሚነደፍበት ዕለት ነው፡፡ በቤቱ ውስጥ ያሉት ከዓለሚቱ ጋር አምስት ሲሆኑ ከጆብሬ ሌላ በቅፅል ስሙ “መቀስ" እየተባለ የሚጠራው አንበሴና
በጫት ምርቃና ላይ የሚንተፋተፈው አበራም ይገኙበታል። ጫት ከመጀመሩ በፊት ዓለሚቱ ሳር ጎዝጉዛ ፍራሽ አንጥፋ፣ ከሰል አያይዛ ሁሉን
ነገር አዘገጃጅታለች፡፡
የሜቱ ሥነ ሥርዓት የሚጠይቀው የቄጤማው ጉዝጓዝ ሰንደሉ ዕጣኑ
ሁሉ የተሟላ ነው፡፡ እውነተኛ ካዳሚነቷን አረጋግጣለች ማለት ይቻላል። የሰላም አምባሳደሮች፣ የሳይንስና ምርምር ፕሮፌሰሮች፣ የዕድገት መሀንዲሶች፣ ጥበበኞች እና ምሁራኖችን የምታስተናግድ ካዳሚ..እግሮቻቸውን አጣጥፈው ቦታ ቦታቸውን እንደያዙ ጎንቻ ግድግዳው ላይ ወዳን
ጠለጠለው ኮት ኪሱ ውስጥ ገባና በርካታ ነገሮችን ማውጣት ጀመረ።
በደም የተለወስ የአንገት ሀብል... ትላልቅ የጆሮ ጉትቻዎች… ከወርቅ
የተሰሩ የሴት የእጅ አምባሮች የተለያዩ የብር ኖቶች ያሉበት ትንሽ
ቦርሳ ያ ሁሉ ንብረት ከጥቂት ሰዓታት በፊት አንቆ የዘረፋት ሴት
ሀብት ነበር፡፡ ጆብሬ ዛሬ የሰራውን ሁለት መቶ ብር ከደረት ኪሱ ላጥ
አድርጎ አወጣና አስቀመጠ፡፡ አበራ አልቀናውም፡፡ አንበሴ ዛሬ እንደ አንበሳነቱ ሳይሆን ውርደት ቀምሶ ቡጢ ልሶ ነው የመጣው። ሁለቱ የሰሩትን ሲያወጡ ሁለቱ አፈጠጡ። ወላ ሀባ ጭቅጭቅ ንትርክ የለም። አንዱ ከቀናው ላልቀናው ያካፍላል ዛሬ ባይቀናው ነገ እንደሚክስ የታወቀ ነው፡፡
ይሁን እንጂ መቀስ በጣም አብዝቶታል። ያንን መልካም ቁመናውን ብቻ ዋቤ አድርጎ ዕይኖቹን ያስለመልምና ድርሻውን ላፍ አድርጎ መሰስ ይላል። የቀናው ዕለት እንኳ የረባ ነገር አበርክቶ አያውቅም። እፍኝ ቆሎ ይዞ ከአሻሮ መጠጋት አብዝቷል፡፡ በማንኪያ ሰጥቶ በአካፋ መዛቁን እየደጋገመ መጥቷል።
የተማመነው በማን ይሆን? ጎንቻ ጆብሬ ያስቀመጠውን አየና ወደ ሁለቱ ፊቱን አዙሮ በምልክት
እጃችሁ ከምን? ሲል በእንቅስቃሴ ጠየቃቸው፡፡ ያገኘው መልስ ግን የፈጠጡ አራት ዐይኖች ሲንከባሉና ሲቁለጨለጩ ከማየት ሊዘል አልቻለም።
“ስማ መቀስ ብዙ ብልጥ መሆን አያስፈልግም! የምታገኘውን ላፍ አድርገህ ትሄዳለህ፡፡ ይዘህ የምትመጣው የሰራኸውን ሳይሆን በብልጠት እየቀነጨብክለት መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን። በመካከላችን ዋናው ቁም ነገር መተማመን ነው! አንተ ግን ሁኔታህን ደጋግሜ ስመለከ
ተው እምነት የጎደለህ ትመስላለህ፡፡ ሁል ጊዜ የሌላውን ድካም ጠባቂ መሆን ብልጥነት ብቻ ሳይሆን ዐይን አውጣነት ነው!” ተቆጣ፡፡ 'የአበራ ጉዳይ እንኳ ምንም አይደለም የታወቀ ነው። ቶሉ ቶሎ ባይቀናውም
አንዴ ከቀናው በሽ በሽ ስለሆነ ግድ የለም። አንተ ግን አበዛኸው። ከዚህ ውስጥ ምንም የሚደርስህ ነገር እንደማይኖር አረጋግጥልሀለሁ! በርጫህን ቅመህ ለጨብሲ የምትሆን አስር ብር በቂህ ስለሆነ ሌላውን እን
ዳትጠብቅ!" ቁርጡን ነገረው፡፡ ከጎንቻ ያላነሰ የአረመኔነት ባህሪ የነበረው መቀስ ለግላጋ ቁመቱና ወንዳወንድነቱ ከውጭ ለሚያየው ሰው የሚስብ ነው። መቀስ በጎንቻ አነጋገር ወሽመጡ ብጥስ አለ። በጉምዥት አፉን የሞላው ምራቅ በድንገት ደረቀ፡፡ ጎንቻ የበላይነቱን በመያዙ እኔስ ከማን አንሼ? በማለት ሊቀናቀነው የሚሞክር ሰው ነው። የቡድኑን የመሪነት ሥልጣን ለመውሰድ ከመመኘት ባለፈ በጎንቻ ላይ ንቀት ነበረው። ይህንን ንቀቱን በተግባር ለማሳየት ደግሞ ዓለሚቱን አጥምዷታል። ጎንቻ ያን የመሰለ አንጀት
የሚበጥስ ንግግር ሲናገረው ቀስ ብሎ ዓለሚቱን በቆረጣ ተመለከታት፡፡ እሷም የጎንቻን ዐይኖችና የሌሎቹንም
እንቅስቃሴ ጠብቃ ማንም ሳያያት ተደብቃ "ጥቅስ" አደረገችው። ፀብ አትፍጠር ማለቷ ነው፡፡ ምን አሳስበህ? ማለቷ ነው። ተረጋጋ....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከሶስት ዓመታት የላምበረት ኑሮ በኋላ ዘይኑን ዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት አስገባት። ከላምበረት ዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት ከምትመላለስ በአቅራቢያው ቤት መከራየት ፈለገና እሪ በከንቱ አካባቢ ሰራተኛ
ስፈር ሁለት ክፍል ያላት ቤት አግኝቶ ተከራየ፡፡ ዘይኑ ለትምህርት ቤቷ ቅርብ የሆነ ቤት አገኘች። ትንሽ ደስ ያላላት ላምበረት የትውልድ መንደሯን ዓይነት ፀጥታ የሰፈነበት ሲሆን እሪ በከንቱ ግን የተጨናነቀና ሁካታ የበዛበት መሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ረጅም መንገድ ከመመላለስ ታድጓታልና ጉዳቱን በጥቅሙ አካክሳ ተቀብላዋለች፡፡ ጌትነት እህቱን በቅርበት እየተከታተለ ለጥሩ ውጤት እንድትበቃ ማድረጉ፣ በትምህርት ቤት ተጀምሮ ለሁለት አመታት የዘለቀውና ውስጥ ውስጡን ሲያሰቃየው የኖረው ፍቅር መቋጫው አምሮ ከሚወዳት ከአማረች ጋር አስደሳች

#ክፍል_አርባ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....በዚህ ላይ ደግሞ አቶ አባይነህ ስራቸው ተጋልጦ ከሥልጣናቸው ዝቅ እንዲሉ ምክንያት በመሆኑ እያቶኮቶኩ ነገር ያቀጣጥላሉ።
እውነትህን ነው ይሄ ጦሰኛ ጦሳችንን ይዞ ካልሄደ በስተቀር ምን ሰላም እናገኛለን?!” በማለት ብሶቱን ያባብሳሉ፡፡ በዚህ ምክንያት የምረቃ በአሉ ለጌትነት ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ ልዩ የደስታ ቀን ሆኖ ሲውል
ለልኡልሰገድ ግን መርዶ ነው የሆነበት። ይህንን መጥፎ ስሜቱን ለማብረድ ደግሞ ሰሞኑን ሲሯሯጥ ሰንብቷል። ትጉህ ሰራተኛነቱ እንኳንስ አብረውት በሚሰሩ የስራ ባልደረቦቹ ቀርቶ በሚጠሉት ሰራተኞች ጭምር
የታወቀ ነው፡፡ ዲግሪውን ይዞ ሲመጣ ያንን እንደቀላዋጭ ውሻ ከንፈሩን እየላሰ ሲጎመዥለት የኖረውን የሂሳብ ዋና ክፍል ሃላፊ ቦታ እንደ ሚወስደው የታወቀ ነው፡፡ በሱ እምነት ያንን እድገት ለማግኘት ጌትነት ከዚያ አካባቢ ገለል ማለት አለበት።እሱ ገለል እስካላለ ድረስ ሊረጋጋ አይችልም፡፡ አንዳንዱ ሰው እድገት ለማግኘት ሲል ከፊት ለፊቱ የቆመው ሰው በሆነ ምክንያት ገለል እንዲልለት ይመኛል። ፀሎት ያደርሳል፡በዚህ የተነሳ ከፊት ለፊቱ በሚታየው የተስፋ ጭላንጭል ላይ የተንጠለጠለ የምኞት እስረኛ ሆኖ ይቀራል።ከጭላንጭሉ በስተጀርባ ዕድል ደማቅ የብርሃን ውጋጋኗን አብርታ እየጠበቀችው መሆኑን በፍጹም አያስብም፡፡ በፈጠራት ጠባብ ዓለም ውስጥ ራሱን ወስኖ በማስቀረት ለትንሹ
ነገር ሲጓጓ የሱ የነበረው ትልቁና መልካሙ ነገር በድቅድቁ ጨለማ
ውስጥ ተውጦ ይቀራል። ልኡልሰገድም ተምሮ ራሱን በመለወጥ ከዚያ የተሻለ ወፍራም እንጀራ መብላት ሲችል የተመኛትን ትንሽ ሹመት እንዳይቀማው በመስጋት የጌትነትን ሞት ተመኘ፡፡ በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይም ሳይገኝ ቀረ። ጌትነት አለቃው በጥሪው ቦታ ሳይገኝ በመቅረቱ ቅር ቢለውም ጥሪውን አክብረው የመጡ ጓደኞቹ እቅፍ አበባ እያበረከቱ ሲስሙት ተፅናና፡፡ እናቱን እቅፍ እያደረገ ከአማረች እና ከቤተሰቦቿ ጋር እንደዚሁም ከትምህርት ቤት ጓደኞቹና ከሽመልስ ጋር በርከት ያሉ ፎቶ
ግራፎችን ተነሱ፡፡ እናቱ እጮኛነቷን ባታውቅም የልጇ ፍቅረኛ መሆን
ዋን ገምታ ከአማረች ጋር በፍቅር እየተቃቀፈች በርከት ያሉ የማስታወሻፎቶግራፎችን ስትነሳ ዋለች::
የፎቶ ግራፍ ስነ ስርአቱ እንዳበቃ ጥሪውን አክብረው በመጡ ጓደኞቹ ታጅቦ ከእናትና ከእህቱ ጋርም ተያይዘው ወደ መኖሪያ ቤቱ ሄዱ። ጌትነት እምብዛም በማይወደው ሰፈር ውስጥ የተከራያት ጎጆውን የወደዳት ገና ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ ከጓደኞቹና ከሚወዳቸው ቤተሰቦቹ ጋር ደማቅ የደስታ ጊዜ እያሳለፈባት ነውና ሰፈሩን ዘንግቶ ጎጆውን ቢወድ የሚደንቅ አይሆንም ጌትነት የተከራያት ቤት መሀሏ በመጋረጃ ተከፍሎ ከመጋረጃው ውስጥ
አንድ ሰፊ የሞዝቮልድ አልጋና ዘይኑ የምትተኛበት አንድ ታጣፊ
አልጋ አለ፡፡ የወዲህኛው ክፍል በሳሎንነት የሚጠቀሙበት ሲሆን አንድ ትልቅ ጠረጴዛና አራት የእንጨት ወንበሮች መሀል ላይ ጉብ ብለዋል።
ከጥግ ላይ አንድ አግዳሚ ወንበር አለ፡፡ ቤቱ ከውጭ እንደሚታየው
አይደለም፡፡ በዘይኑ ከፍተኛ ጥንቃቄና ጥረት ፅዳቱ ተጠብቆ ያምራል።
ዘይኑና እናቷ ላባቸውን ጠብ አድርገው የጠመቁት ጠላ ከውስኪ ያስንቃል።
"በሉ አረፍ በሉ!" አለች የጌትነት እናት ለመስተንግዶው ተፍ ተፍ
እያለች። ጌትነት ግን ልቡ ወደ አማረች በሯል። የሱን ደሳሳ ጎጆ የምታያት ዛሬ ነበር፡፡ከወዳጅ ዘመዱ ጋር በይፋ የሚያስተዋውቃትና በቅርቡ
የሚያገባት እጮኛው መሆንኗ የሚያበስርበት ቆንጆ አጋጣሚ ዛሬ በደስታው ቀን ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል? እሷም ተመራቂ ነችና በወላጆቿ ቤት ከሠርግ መልስ ግብዣ ተደርጎ ዓለም እየታየ በመሆኑ አልተቻለም፡፡
“ሰውዬው በል እንጂ ምሳችንን ቶሎ አስቀርብልን፡፡ አንተ ልብህ ወዴት እንደኮበለለ አውቄዋለሁ"ባልቻ እየሳቀ በነገር ወጋ አደረገው፡፡
"አንተ ቡዳ! ምንድነው የምታውቀው ደግሞ?" እሱም ሳቀና ጎሽመው ባልቻ የአማረችና የጌትነትን ፍቅርን ጠንቅቆ የሚያውቅ የትምህርት ቤት
ጓደኛው ነው።እሱም የሚቀጥለው ዓመት ተመራቂ ነው፡፡
“ዘይንዬ! እባክሽ ገላግይኝ ሰዎቹ ጠላው አናታቸው ላይ እየወጣ ነው መስለኝ ምሳ! ምሳ!! ቶሎ በይ!” አለና ዘይኑን ተጣራ። ዘይኑ ከእናቷ ጋር ተጋግዛ በፍጥነት ምሳ አቀረበችና መመገብ ጀመሩ።
"እንግዲህ እርስዎም እዚሁ ከልጆችዎ ጋር መጠቃለል አለብዎት እማማ በመመላለስ ይጎዳሉ..." አለ ዘበነ፡፡
“አይ የኔ ልጅ እዚህ ከልጆቼ ጋር መቀመጡን ጠልቼው መሰለህ ? ደስታውን አልችለውም ነበር፡፡ እነሱን ተለይቼ የምኖረው ኑሮ አይደለም፡፡
በሬሳ ውስጥ አስሮ ያስቀመጠኝ የሟች አባታቸው ቃል ነው "
“እንዴ?! ለምን?” ባልቻና ዘበነ በአንድ ላይ ጠየቁ፡፡
“መኩሪያ አሁን ያለሁበትን ቤት ተአባቱ የወረሰው ነው። የአባቱ አስክሬን ከወጣበት ቤት ነው የሱም የወጣው፡፡ ታዲያ ሊሞት ሲያጣጥር ከዚች ቀዬ ንቅንቅ እንዳትይ መታመሚያሽ፣ መሞቻሽ መቀበሪያሽ እዚች ጎጆ እዚች መንድር ውስጥ ይሁን አደራ! ብሎ አስሮኝ ነው ያረፈው"
በሬሳን መልቀቅ የማትችልበትን ምክንያት አጫወተቻቸው። ለነገሩ በመኩሪያ ቃል አሳበበች እንጂ ያቺን ጎጆ መልቀቅ የማትፈልግበት እንዲህ ነው ብላ ልትገልፀው የማትችለው የራሷ ምክንያት ነበራት፡፡ጌትነት ሽመልስን ለእናቱ ሲያስተዋውቃት "እማዬ ሽመልስ ማለት እሱ ነው በህይወቴም ሆነ በህይወታችን ውስጥ ታላቅ ለውጥን ያስገኘልን ወንድሜ ነው፡፡
ስለ እውነት ሲል የተሟገተ፡፡ የገባውን ቃል ያከበረ.." ቃላት አጥረውት ስለ ሽመልስ ማንነት ገለፀላት፡፡
“እሰይ! እስይ! እግዚአብሔር የሱንም ኑሮ እንደዚሁ ያሳምርለት። ለሰው ደግ መስራት ከምድር ባይገኝ እሱ ፈጣሪ ውለታውን በሰማይ ይከፍለዋል" ሽመልስን አመሰገነችለት፡፡ በዚህ ሁኔታ በተሰባስቡ ወዳጅ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ የጌትነት ቤት ተጣባ ደስታውን ተደስተው ፅዋቸውን
እያነሱ ሲያጋጩ ሲጫወቱ ሲጨፍሩ ዋሉ.....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የወይዘሮ ባንቺደሩ ጎጆ የሞት ጥላ እያንዣበበባት ነው። ጨካኙ
ሞት ህፃን፣ አዋቂ፣ ሴት፣ ወንድ አይመርጥም፡፡ እንደ ቋያ እሳት ያገ
ኘውን በእጁ የወደቀለትን ሁሉ እየበላ እያኘከ መሄድ ነው። ምህረት የለም፡፡ አሮጊቷ ወይዘሮ ባንቺደሩ በአንድ በኩል የዕድሜ ጫና በሌላ በኩል ደግሞ የሙት ልጆችና እናታቸው ጥላቸው የኮበለለች ሁለት ህፃናትን ለማሳደግ መከራቸውን እያዩ ናቸው፡፡ የአያትነት ግዴታ በላያቸው ወድቆ በስተርጅና የልጃቸውን ልጆች በህይወት ለማቆየት ብዙ ደከሙ፡፡ በበሽታ ክፉኛ የተደቆሰው ምትኬ እናቱንና አባቱን ክፉኛ እየናፈቀ አባቱን በአካል ሲያጣው እየተሳቀቀ እናቱ እንደ ድሮው እንድትሆንለት እየተመኘ እናቱ ስትጨክንበት፣ ሀሳብ አደቀቀውና፣ ተሳቀቀና ለጋ
የህፃንነት አዕምሮው በሀዘን ቆስለ። ቀስ በቀስ እየመነመነ በሽተኛ እየሆነ ሄደ፡፡ አሮጊቷ በአብዛኛው የሚሰጡት ርዳታ እንባቸውን ማፍሰስ ብቻ
ነበር። "አብዬ የኔ ጌታ አይዞህ!...እኔ ልጨነቅ. እኔ ልጠበብ እህ!...”ምትኬ ግን በሳቸው እንባ ሊጠነክርና ሊለመልም አልቻለም፡፡

#ክፍል_አርባ_ሦስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ዛሬም በሱ የቡድን መሪነት ውስጥ በአባልነት በታቀፈው በሸጋው አንበሴ ቁመናና የዐይኖቹ ውበት ተማርካ በመልከ
መልካምነቱ ልቧ ተሸንፎ በፍቅሩ ነዳለት ጎንቻን ደብቃ ፍቅሯን እያስኮመኮመችው አለማቸውን እየቀጩ ነው።
ይሄንን ያላወቀው ጎንቻ ደግሞ ስሞኑን በብዙ አፈላላጊ ከተገናኘው ሰው ላይ ቀብድ ለመቀበል ተፈልጎ ሄዷል መቀስ ያንን ሹልክ እያለ እየመጣ
የሚቀምሰውን ፍቅር ለመቅመስ በዚያውም ተጨማሪ ገንዘብ ለመበደር ነበር የጎንቻን እግር ጠብቆ የገባው፡፡ እንደተገናኙ ተቃቀፉና አልጋው ላይ ወደቁ፡፡ ያንን የስርቆሽ ፍትወት ከፈፀሙ በኋላ በጀርባቸው ተንጋለሉ። ዓለሚቱ ልቧ ድው ድው ማለት ጀመረ።ስርቆሹን ትወደዋለች፡፡
ይጣፍጣታል።የሚያስከትለውን መዘዝ ስታሰላስለው ግን ትሰጋለች። ትርበተበታለች። በዚያ የስሜት እሳት ውስጥ ገብታ ፍሙን፣ ረመጡን እስከምታጣጥመው ድረስ ምንም አይነት የፍርሃት ስሜት አያድርባትም፡፡አደጋው አይታወሳትም፡፡ ሁሉ ነገር ጎልቶ የሚታያት ከዚያ በኋላ ነው፡፡ አሁንም የፍትወት ስሜቷን ካረካች በኋላ ስጋቷ በረታና መተንፈስ ግድ ሆነባት።
"አይታወቅም የሱ ነገር ወይ በመሀል ከተፍ ይላል። ቶሎ ቶሎ ተጨዋውተን በጊዜ ብትሄድ አይሻልም?" አለችው፡፡
"ልክ ነሽ፡፡ እውነትሽን ነው። እኔም ሳስበው ነበር። እሱ እኮ ስላቢ ነው፡፡ በድንገት ከች! ሊል ይችላል ፡ጉሮሮ ለጉሮሮ ሳንያያዝና በእጄ ሰበብ ሳይሆንብኝ ብሄድ ይሻላል” አለና ከአልጋው ላይ ተነስቶ ሱሪውን ማጥለቅ ጀመረ፡፡ እሷም ተነሳች፡፡ዓለምዬ ዛሬ ችስታ ወግሮኛል ሁለት መቶ ብር ትጨምሪልኛለሽ፡፡ አንድ
ላይ ወደ አንድ ሺህ መጠጋቱ ነው" አላት፡፡“ትቀልዳለህ እንዴ አንበሴ?! እንዲያውም ስሞኑን የሌለበትን የገንዘብ
መቆጣጠር ፀባይ እያሳየ ነው፡፡ አሁን በድንገት ውለጂ ቢለኝ ምን እመልስለታለሁ? ዛሬ ሁሉንም ይዘህ ትመጣለህ ብዬ ነበር የገመትኩት። አንተ ግን ጭራሽ በላይ በላዩ ልትጨምር ትፈልጋለህ፡ የበላችው ያስገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታልሆነ አሁንስ!" በስጨት ብላ ተናገረችው።
አንበሴ ያልጠበቀው ነበር፡፡ በሱ ቤት ተደብቆ እየመጣ የሚያቀምሳት ፍቅር ጣፍጧት ስለሚጠይቃት ገንዘብ ደንታ የሌላት መስሎት ነበር።
ተወድጃለሁ የፈለኩትን እንድታደርግልኝ ባዝዛት ትፈፅማለች ባይ ነበር፡፡
ለእንቢታው አንደበቷ የሚፈታ የተጠየቀችውን ገንዘብ ላጥ አድርጎ ለመስጠት እጅዋ የሚያጥር አልመሰለውም ነበር፡፡ በዓለሚቱና በገንዘብ መካከል ግን ቀልድ አልነበረም።
ሲቀር ፍቅሩ ተሽቀንጥሮ ይቀራል እንጂ ብሯን የምትበትን ሆና አልተገኘችም። እንደዚያም ሆኖ ግን ለሱ እጇ ብዙም አይጨክንም ነበር። ከዚያ በፊት ያለውን በደስታ ነው የሰጠችው
ዛሬ በዛባትና ፊት ነሳችው እንጂ፡፡ ባሏ ጎንቻ የቡድኑ ገንዘብ አዛዥ ሆኖ የበለጠውን ድርሻ መውሰዱ ውስጥ ውስጡን በቅናት ቢያቃጥለውም ቁልፉን በእጁ ይዟል። የገንዘቡን ካዝና የዓለሚቱን ልብ ተቆጣጥሯልና
በተዘዋዋሪ መንገድ እየተካስ ይፅናናል።ይሄ በመሆኑ እንጂ እንደ ጎንቻ አያያዝ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ድብልቅልቅ ብለው በተጣሉ ነበር፡፡ ዓለሚቱ ቀስ ትልና ብሩንም ፍቅሩንም እየሰረቀች ትሰጠዋለች። ይቀዘቅዛል፡፡
"ተይ እንጂ ዓለሚቱ! ምን ማለትሽ ነው? ገንዘቡን ለጥብቅ ጉዳይ ስለምፈልገው ነው እኮ!ደግሞ ብዙ ችግር እንደሌለብኝ ታውቂያለሽ፡፡ በሙሉ እምነት ነው ወዳንቺ የመጣሁት። ዓለሚቱ ካንቺ ሌላ ማንንም ብድር
መጠየቅ አልፈልግም!"
“አንበሴ ሙት አትቀልድ! ይልቁንስ የወሰድከውን ቶሎ መልስ እንዳን
ጣላ!"
ትቀልጃለሽ እንዴ ዓለሚቱ?"
አልቀለድኩም አንተ ነህ የምትቀልደው!"
“ኧረ በናትሽ ዓለሚቱ?!"
“አይገባህም እንዴ?!" ቁጣዋ ባሰ...የበለጠ ተደናገጠ፡፡ ፕሮግራሙ ሊከሽፍ ነው፡፡ የበርጫውና የጨብሲው... ከአዲሷ የሴት ጓደኛው ጋር የያዘው ቀጠሮ ዜሮ…ደግሞም ባለሥልጣን ነኝ ብሉ የዋሻት፣ ልቡ የወደዳት ቆንጆ ልጅ....
“በቃ እንጣላ?!"
«አንበሴ ሙት በዚህስ እንጣላ! በዚህስ የፈለከውን አምጣ እንጂ አላደርገውም! ትንሽ አታስብም እንዴ?! ያምነኛል እንጂ ገንዘቡን ያውቀዋል እኮ! ምን ልለው ነው በተለይ እንደዚህ መንገብገቡ ከሴት ጋር ቀጠሮ ቢኖረው ነው ብላ ስለገመተች ጨከነችበት።
“በዚህ ላይ አንተ ጋ ያለው ብቻ አይደለም፡፡ በአራጣ ያበደርኳቸው
ብዙዎቹ መክፈል እያቃታቸው አሮጌ ዕቃ እያግበሰበሱልኝ ነው። አሮጌ እቃ ለኔ ምን ያደርግልኛል? የረቡ ዕቃዎች ያየሃቸው ሀብሎችና ቀለበቶች ብቻ ናቸው። ሌላው ዝባዝንኬ ቅራቅንቦ ነው!”
"ገባኝ!... እኔን እኮ እንደሌላው አራጣ ተበዳሪ ማየት የለብሽም። ማወቅ ያለብሽ ነገር ገንዘቡን በጋራ የሰራነው መሆኑን ጭምር ነው! የንዴት ትኩሳት ማተኮስ ጀመረውና ሳያስበው ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ የወጣ
ንግግር ተናገራት፡፡
"ኧረ? በጋራ?! በል ተወው! የራስህን ድርሻማ እየላፍከው ሄደሃል። ከዚህ ውስጥ ሰባራ ሳንቲም የባለቤትነት መብት የለህም! በጠየከኝ ቁጥር እያ
ወጣሁ ያስታቀፍኩህ እኮ የተግባባን መስሎኝ ነበር! ለካስ የራስህ ገንዘብ አድርገህ ነዋ እስካሁን ያልመለስከው?! አንበሴ ሙት እንደዚህ አይነት የማይረባ አስተሳሰብ ያለህ ሰው አትመስለኝም ነበር፡፡ ወይ የሰው ነገር? ለካ ሰው እያደር ነው የሚታወቀው?! እና የወሰድከውን ለመመለስ ሀሳብ የለህም ማለት ነው?! እንዴት ያለኸው ቀላል ነህ ባክህ?! ይህንን ያዳፈረህ ጎንቻን ደብቄ ቀሚሴን ስለገለብኩልህ ይሆን እንዴ ? እሱ ይሆናል
እንጂ ያናናቀን! ለምነህ የወሰድከውን ከምስጋና ጋር መመለስ ሲገባህ ጭራሽ..." ፊቷ በንዴት ቀላ፡፡
“እና አሁን አትሰጭኝም?!"
“እስቲ ድብን ያደርግህ እንደሆነም ጉድ አያለሁ! ሰባራ ሳንቲም! " አንበሴ የዓለሚቱን ንዴት ሲመለከት አጉል እልህ ምንም ዋጋ እንደሌለው ተረዳ፡፡ ከብዙ ጉልበት ትንሽ ብልሃት የምትበልጥበትን ጊዜ አሰበ፡፡ በዘዴ አባብሎ ብዙ ነገር ማድረግ ሲችል ብጥብጥ ፈጥሮ ቢሄድ ራሱን ይጎዳል እንጂ እሷን አይጎዳትም ይሄን ማመዛዘን ጀመረ፡፡ ቀስ በቀስ ረገበና ልምምጡን ቀጠለ፡፡ ከውስጡ ንዴትና ብሽቀት ቢያቃጥሉትም ከውጭ ሌላ ሆነ፡፡ ፈገግ አለ፡፡
“እሺ ዓለምዬ እንዳልሽው ይሁን። ማወቅ ያለብሽ ግን እኔን ልቤን የነሳሽው ጣፋጭ ፍቅርሽ እንጂ ገንዘብሽ ያለመሆኑን ነው። ገንዘብ ገደል ይግባ! ፍላጎቴ ፍቅር ሳይሆን ገንዘብ ቢሆን ኖሮ በሴት ብር ብቻ ፎቅ ቤት መስራት እችል ነበር፡፡ ያንን ግን አልፈልገውም፡፡ እዚህ የባልሽን ኮቴ እየጠበኩ ስር ስርሽ የሚያስሮጠኝ ፍቅርሽ ብቻ ነው። አሁንም ቢሆን እኔ የምፈልገው ገንዘብሽን ሳይሆን ፍቅርሽን ነውና አለብህ የም
ትይኝን በሙሉ አምጥቼ እወረውርልሻለሁ። አንቺነትሽን እንደዚህ የለወጣው ገንዘብ ከሆነ ካንቺ የሚተርፍ ገንዘብ አስታቅፍሻለሁ። እውነቴን
ነው የምልሽ ሩቅ ቦታ ስላስቀመጥኩት እንጂ እንኳን ለራሴ ለሌላ የምትርፍ ስው ነኝ ጉራውን ቸረቸረላት።
ዓለሚቱ ልቧ ወከክ... አለ፡፡ እውነትም አንበሴ ገንዘብ በገንዘብ ሲያደርጋት ታያት። በአምስቱ ጣቶቹ ላይ የደረደራቸው የወርቅ ቀለበቶቹ በየቀኑ የሚቀያይራቸው ፋሽን ልብሶቹ ሁሉ ነገሩ የገንዘብ ችግር የሌለበት መሆኑን ይመሰክራሉ። ገንዘብ ስጠኝ ብላ ባለመጠየቋ እንጂ ብትጠይቀው ሊያንበሸብሻት እንደሚችል ተስፋ አደረገች፡፡ በአንድ ጊዜ' በደስታ

👍2😱1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ጭንቀት በጭንቀት ሆነች። ብቅ ጥልቅ ወጣ ገባ.አበዛች። ለመጀመሪያ ጊዜ ማምሸቱ ያሳሰባት ዘይኑ የምትሆነውን አጣች። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ጀምሮ ነበር መጠባበቅ የጀመረችው። እንደበፊቱ ትምህርት ቤት እንዳትል ትምህርቱን ጨርሷል። ምን ነክቶት ይሆን? ተርበተበተች፡፡ ስዓቱ እየገፋ እየሄደ ነው። ስጋት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ጌትነት
አደጋ ላይ እስከወደቀበት እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ...
ከዚያም ሙሉውን ለሊት ስታምጥ አነጋች፡፡ ወንድም ጋሻዋ..ድምጡ
ጠፋ፡፡ የውሃ ሽታ ሆነ፡፡ ለሊቱን ተቅማጥ ሲያጣድፋት አደረ። ጎረቤታቸው ወይዘሮ ጤናዳም ደግሞ ሲያፅናኗት አነጉ።
"ምንም አይደለም ወንድ ልጅ አንዳንድ ጊዜ አመሉ ነው። አይዞሽ ጠዋት ይመጣልሻል"እያሉ ሞራል ሲሰጧት አደሩ። መንጋት አይበለው እንደ ምንም ነጋላት። ወንድም ጋሻዋን የበላችባት ወፍ ግን ድምጿን አላሰማ አለች፡፡ እዬዬ... ኡኡታ... ዋይታ…ቁጭ ብድግ.. በዚያች እሷ በጭንቀት በምትሸበርባት ማለዳ አንድ ሰው ወደ ስራ በማምራት ላይ እያለ እሪ በከንቱ ዳገቱ ላይ ወደተፈጠረው ትርምስ ጎራ አለ።
ታደሰ ገብረማሪያም ይባላል። በአሰቃቂ ሁኔታ የተደበደበውን ወጣት ሲመለከት ዐይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡ አደጋውን ለፖሊስ ቀድሞ ሪፖርት ያደረገው እሱ ነበር፡፡ ፖሊስ ከስፍራው ሲደርስ ነፍሱ አልወጣችም እንጂ ያ ወጣት የሞት ያክል ከባድ ጉዳት ደርሶበት ተገኘ፡፡ ወጣቱ በአንቡላንስ ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ታደስ ወደ መስሪያ
ቤቱ ቢያመራም የእለት ተግባሩን በአግባቡ መከወን ተስኖት ነበር። ገና በጠዋቱ ከቤቱ እንደወጣ ባየው አሰቃቂ አደጋ ቀኑን ሙሉ ሲረበሽ ውሎ ሲመሽ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡
ታደሰ የጨለማ ድባብ በዋጣት ጠባብ ክፍሉ ውስጥ ብረቱ የዛገ የሽቦ አልጋውን ተንተርሶ በሃሳቡ ጭልጥ ብሎ ሄደ። የዚያ በደም ተለውሶ የተንጋላለ ወጣት ሁኔታ ከፊቱ እየተመላለሰ ሰላም አየነሳው ነበር።
መንግሥትና ህግ ባሉበት አገር ውስጥ እዚያ ጥግ የደረሰ አስከፊ ወንጀል በአደባባይ መፈፀሙ እያስቀጨነቀው፣ የቀማኞችና የነፍሰ በላዎች መሸሽጊያ ዋሻ እሪ በከንቱ የሚፀዳበት ጊዜ እየናፈቀው እንቅልፍ የሚባል ነገር
በአይኑ ሳይዞር ሰማይና ምድር ተላቀቁ።
ታደሰ በጠዋቱ ተነሳና ወንበር ላይ አጣጥፎ ያስቀመጣቸው ልብሶቹን
ለባብሶ በየማዕዘኑ ሸረሪት ያደራባት ጎጆውን ከውጪ ቆለፈና እንደ ልማዱ ወደ መስሪያ ቤቱ የሚያደርሰውን ሰርቪስ ለመያዝ ወጣ፡፡ያ አሳዛኝ ወጣት ወድቆበት የነበረውን አካባቢ በጥላቻ ወደ ጎን እየተመለከተ ወደ ፊት በር አቀና፡፡
አንገቱን አቀርቅሮ እጆቹን እያወራጨ ሲራመድና ለራሱ ሲያወራ የተመለከተ ሰው ከአዕምሮው ጤነኛ አለመሆኑን ቢጠራጠር የሚፈረድበት
አይሆንም፡፡ ለሰው ልጅ ህይወት ደንታ ሳይኖራቸው እየነጠቁና ደም
እያፈሰሱ በእሪ በከንቱ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው የሚኖሩ ግፈኞች ጉዳይ በእጅጉ እያሳስበውና ነገ ከነገ ወዲያ የዚያ ወጣት እጣ ፈንታ በሱ ላይ
የማይደርስ ስለመሆኑ ዋስትና በማጣት ጭምር እየተጨነቀ ነው። ታደሰ ይሄ ጉዳይ ክፉኛ ስላሳሰበው አቅሙ በፈቀደ መጠን ወንጀልና ወንጀለኞችን ለመፋለም ለራሱ ቃል ገብቷል። "ምነው ታዴ እንደ እብድ ብቻሽን ታወሪ ጀመር እንዴ ?" አለው ጓደኛው አማኑኤል፡፡
"እብደት አልከኝ አማኑኤል? ልክ ነህ አእምሮ ጫና ሲበዛበትና ፊውዙ ሲቃጠል ተከታዩ እብደት ሊሆን ይችላል። የኔ አዕምሮ ፊውዝ ግን የነሱን ሳያቃጥል በቀላሉ አይቃጠልም!!" ፊቱን ቅጭም አደረገ፡፡ አማኑኤል በታደሰ አነጋገር ግራ ተጋባ፡፡
"እነማንን ነው የምትለው ታዴ?"
"እነዚያን የሰውን ልጅ ህይወት በጩቤ ጀልባ እየቀዘፉ በደም ውቅያኖስ ውስጥ የሚዋኙትን፣ እነዚያን የንፁሃንን ጉሮሮ ያለርህራሄ የሚበጥሱትን፣ እነዚያን ሳይሐፉ፣ሳይደክሙ በደም የተለወሰ እንጀራ የሚበሉትን!"
አማኑኤል ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ስራውን ከጀመረ ሁለት ዓመት እንኳን አልሞላውም ነበር፡፡ ከታደስ ጋር በዚህ መስሪያ ቤት ውስጥ ከተዋወቁበት ጊዜ ጀምሮ ተግባብተውና ተሳስቀው ስራቸውን በትጋት ከማከናወን
ባለፈ የዚህ ዓይነቱን የመረረ ሁኔታ አይቶበት አያውቅም ነበር ።
አስቃቂ ድርጊትም አከለለት።
“ባልና ሚስትን ደብድበው ንብረታቸውን ዘርፈው ተሰወሩ፣ እገሌን ማጅራቱን መቱት፣ የለበሰውን ልብስ ገፈው ቱቦ ውስጥ ጥለውት ሄዱ፤
እገሌን ሃንግ አደረጉ..." ሌላም ሌላም፡፡ በዚያ ወጣት ላይ ደርሶ ያየውን አሰቃቂ ድርጊት አከለለት
“ይሄ አረመኔነት የተጠናወተው ሰይጣናዊ ተግባር ነው። ይሄ እኩይ መቆሚያ ካልተበጀለት የእያንዳንዳችን ጉሮሮ ተራ በተራ መታነቁ የማይቀር ነው" አለ በብስጭት።
"አቦ ተወና ታዴ! ያልበላህን እያከክ ነው እንዴ?! እሱ የኛ ችግር አይደለም! ይሄ ለዚሁ ተግባር የተሰማሩ የፖሊሶች ስራ ነው፡፡ የሰው ስራ አትሻማ!” አለው።
“እንደሱ አይደለም አማኑኤል!.….በፍፁም አትሳሳት!…አንዱ ለሌላው ፖሊስ ሊሆን ይገባል፡፡ የኛ ድጋፍ፣ የኛ ትብብር በሌለበት ፖሊስ ብቻውን ተአምር ሊፈጥር አይችልም፡፡ የሌላው ቤት ሲፈተሽ፣ ሲበረበር፣ ሌላው አንገቱ ሲመታ፣ሲታነቅ እንደ ዶሮ ሲጠመዘዝ እያየን እንዳላየ ፊታችንን አዙረን የመሄዱን አስከፊ ልማድ እስካልቀየርነው ድረስ የደህንነት ዋስትናችን አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው፡፡ የሰው ልጅ ጥሮ ግሮ ያፈራው አንጡራ ሀብቱን በገሃድ መነጠቁ አንሶ ህይወቱ መጥፋት የለበትም። በየሜዳውና በየድልድዩ ውስጥ መደፋት የለበትም፡፡ ወንጀለኞቹ
ገንዘብ ብቻ ዘርፈው አይሄዱም እኮ! እሱ ብቻውን አያረካቸውም፡፡የሚያረካቸው ደሙ ሲንዠቀዠቅ፣ እስትንፋሱ ስትቆም ማየት ነው"
እና መፍትሄው ምንድን ነው ታዴ ? ምንስ ማድረግ ትችላለህ?"
ከዚች ደቂቃና ሴኮንድ ጀምሮ ምሽጋቸውን ለመናድ ከተደራጀው ሰራዊት ጎን ቆሜ እኩይ ተግባራቸውን ለማስቆም የበኩሌን ጥረት አደርጋለሁ” አለው በፅናት፡፡
'ተው እንጂ ታደስ? ለምን በአንገትህ ላይ ሸምቀቆ ታስገባለህ? ለምን ራስህን ለአደጋ ተጋልጣለህ?ፖሊስ የሚፋለማቸውኮ በተገቢው ትጥቅ ተደራጅቶ ነው፡፡ አንተ ግን ባዶ እጅህን ነህ በባዶ እጅ ያዋጣል? እንኳን በባዶ እጅ በትጥቅም አልተቻሉም ወዳጄ!.."
ተራህ እስከሚደርስ ቁጭ ብለህ ጠብቃቸው እያልከኝ ነው?"
“ታዴ ብቻህን ተቆርቋሪ በመሆንህ ወይንም ራስህን ለጥቃት በማጋለጥህ ለችግሩ መፍትሄ ትሆናለህ ብዬ ስለማላምን ነው። ጨለምተኛ እንዳትለኝ እንጂ መፍትሄው ያለው በመንግሥት እጅ ብቻ ነው።ማጅራት መቺው፣ ቤት ሰርሳሪው፣ ኪስ አውላቂው ሁሉ የየራሳቸው የሆነ የተለያየ ታሪክ ያላቸውና በተለያዩ ጊዜያት ተይዘው እስር ቤት የገቡ፣ የተገረፉ፣ የተደበደቡ ጭምር ናቸው፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ የስራ መስክ አልተፈጠረልንም፣ ሰርተን የምንኖርበት ሁኔታ አልተመቻቸልንም የሚል ነው።
ዘላቂ መፍትሄ የሚገኘው እነሱን በማጥፋት ብቻ ሳይሆን እነሱን
የሚፈለፍለውን የኋላ ቀርነት ማሽን ከስር መሰረቱ በማጥፋት ነው።
ወንጀልና ወንጀለኛን መከላከል የሚቻለው ስራ አጥነትን፣ የትምህርት እድል እጦትን፣ ረሃብን ፣ በሽታን ፣ ድንቁርናን በአጠቃላይ በድህነት ሰፊ ማህፀን ውስጥ የሚፀነሱ ችግሮችን በመዋጋት ነው። ለዚህ ደግሞ በቂ የስራ እድል በመፍጠር፣ ህብረተሰቡ ለስራ ያለውን ዝቅተኛ አመለካከቱን እንዲለውጥ በማስተማር፣ መሃይምነትን በመታገል እና ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት እንጂ ወንጀለኛን በማሳደድ ብቻ ማስቆም የሚቻል አይሆንም፡፡ ይሄ እጅግ ሰፊ አገራዊ ችግርና አጀንዳ ስለሆነ

👍1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ሰሞኑን ያየችው ህልም ክፉኛ ያስደነገጣት እናት አመዱን ይነሰንስባት ጀምሯል። የወትሮ ህልሟ ተስፋን የሚያበስር መሆኑን ስለምታውቅ ፊቷ እንደ ፀሀይ እያበራ በደስታ መንፈስ ለቡና ማህበረተኞቿ ታወራላቸው ነበር፡፡ ከማህበርተኞቿ ውስጥ ደግሞ በህልም ፈቺነታቸው ወይዘሮ
ተዋበችን የሚደርስባቸው የለም፡፡ ህልም ሲፈቱ እንከን አይወጣላቸውም ተብሎ በአብዛኛው ነዋሪ ስለሚታመንባቸው ህልም ለመፍታት ኩራታቸው አይጣል ነው። ትንሽ ካላስለመኑ ህልም አይፈቱም፡፡ ከልመና በኋላ ግን መተንተን ይጀምራሉ፡፡
ሲሳይ ነው! ዓለም ነው!አቤት ደስታ! ልጅ ልትወልጂ ነው...ስለትሽ ሊደርስ ነው፣ በዚህ ሊገባ በዚህ ሊወጣ ነው፡፡ የተጣላው ሊታረቅ፣ የደለው ሊሞላ.. ብቻ ጥሩ ጥሩውን ሁሉ ልታገኙ ነው እያሉ አላሚውን
ተስፋ በተስፋ ያደርጉታል፡፡ ከሁሉ የበለጠ የህልም ደንበኛቸው ግን
አስካለ ነበረች። ያየችውን ህልም ስትነግራቸው ሁሌም የሚያያይዙት ከልጆቿ ጋር ነው፡፡
አቤት! አቤት! በውነት ህልም አይደለም ያየሽለት ራዕይ ነው፡፡ ጉድ! ደሞዙ ከፍ ሥልጣኑም ከፍ ሊል ነው፡፡ ጥሩ ደረጃ ላይ ሊደርስልሽ ነው! ትንሿም ደስ ብሏታል ያንቺ ናፍቆት አለባት መሰለኝ እዚህ ጋ ትንሽ ቅር
እንዳላት አያለሁ፡፡ ይሁን ግድ የለም ትምህርት ቤት ሲዘጋ ትመጣለች።
ጥሩ ህልም ነው ይሏታል የቡናው አሻራ ያረፈበትን ባዶ ስኒ ዘቅዝቀው እየተመለከቱ፡፡ ከዚያም አስካለ በደስታ መፈንደቅ ነው። በዚህ ሁሉ ቆንጆ ቆንጆ ህልሞቿ ጣልቃ ስሞኑን ያየችው መጥፎ ህልም ግን ክፉኛ አስደንግጧታል
ለማንም ሳትናገር ፍርሃትና ሃሣብ ውስጥ ውስጡን ሲያካት ቆይቶ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ወዛም ነበረ ፊቷ ላይ አመዱን ይነዛበት ገባ።
"ተነሳብሽ ደግሞ አንቺ ሴት! ለመሆኑ ሄደሽ ከመጣሽ ሁለት ወር እንኳ ይሞላዋል እንዴ? ናፈቁኝ ነው ወይስ ምን አዲስ ነገር ተገኘና ነው እንዴዚህ ነጭ እስከምትሆኚ ድረስ ራስሽን መጣል ያመጣሽው?” ለመሽፋፈን ጥረት ብታደርግም ሃሳብ እየወዘወዛት መሆኑ የገባቸው ወይዘሮ ተዋቡ ተቆጡ።አስካለ የመጀመሪያ መጥፎ ህልሟን አይታ መረበሽ ከጀመረች
በኋላ ጭንቀቱ ነው መሰል በላይ በላዩ የሚያስፈራራ ህልም እየደጋገመ አስቸገራት። የአሁኑ ደግሞ ፍፁም የተለየ ሆነባት።
ጌትነት ይመስላታል፡፡ እንደ ልጅነቱ አብሯት እንጨት ለቀማ ይሄዳሉ።
ከአንዱ ዛፍ ወደ ሌላው ዛፍ እየዘለለ ጥሩ ጥሩውን እንጨት እየሰበረ ኢያቀበላት የቆመበት ቅርንጫፍ ተገንጥሎ መሬት ላይ ይወድቃል። ከዚያም
ይንከባለላል. በዚያው እንደ ሙቀጫ ጅው ብሎ ተንከባሎ ቁልቁል ይወርዳል። ለካስ ከስሩ ገደል ነበር፡፡ ከታች ገደል መኖሩን፣ ልጅዋ አደጋ ላይ መውደቁን ያየች እናት ኡኡ! ልጄን! ልጄን!.. ልጄን! እየጮኸች አብራው ልትገባ ወደ እሱ ትሮጣለች። ጌትነት ገደሉ ውስጥ ተወርውሮ ከመግባት ለትንሽ የተረፈው የሆነ ቁጥቋጦ ነገር እጁ ውስጥ ስለገባ ነበር፡፡
ከዚያም እናቱ ጉዳት ላይ እንዳትወድቅበት ውትወታውን ይቀጥላል።
“እማዬ! እማዬ!ደህና ነኝ! ምንም አልሆንኩም! እዚያው ቁሚ! መጣሁ! መጣሁ! መጣሁ!" ወደሱ ስትሮጥ ወድቃ እንዳትሰበር ፈርቶ ይጮሀል። እሷ ደግሞ አሻፈረኝ ብላ ወደ ገደሉ እየሮጠች ትመጣና ገደሉ ጫፍ ላይ
ሆና “ጌትዬ! ተረፍክ የኔ ጌታ?!” ቁልቁል እያየችው ትጠይቀዋለች::
"ተርፌአለሁ! ተርፌአለሁ!አይዞሽ! ምንም አልሆንኩም በቃ እዚያው ጋ ሁኚ!" ይላትና በአንድ ትልቅ ቋጥኝ ላይ ተጋድሞ በተንጠለጠለ ወፍራም
ሀረግ አማካኝነት እየተሳበ ሽቅብ መውጣት ጀመረ። ወጣ ወጣ...
ወጣና አጠገቧ ሊደርስ ትንሽ ቀረው። ደክሞታል። አልቦታል። ..
“አይዞህ ጌትዬ በርታ የኔ ልጅ... ቆይ እጅህን ልያዝልህ" ጐንበስ
ትላለች።
“ተይ !ተይ! እማዬ ተይ! እንዳያንሸራትትሽ !እኔ ቀስ እያልኩ እወጣ ለሁ ተይ!!"
“ግዴለህም ይልቁንስ እጅህን አቀብለኝ" ትለውና ሄዳ ከገደሉ ጫፍ ላይ ተንጠልጥላ የቀኝ እጇን ትልክለታለች። አልደርስብሽ ይላታል። እንደገና ብሃይል ወደሱ ተንጠራርታ እጇን ልትስጠው ጐንበስ ትላለች። በግራ እጅዋ አንድ ትልቅ ጉቶ ይዛ ነበር፡፡ አሁንም አልደርስብሽ ይላታል።
ጭንቅቱ አስጨንቋት ቶሎ ልታወጣው ቸኩላለች። እሱም አወጣዋለሁ ብላ ስትፍጨረጨር ጉዳት ላይ እንዳትወድቅ ፈርቶ እጅዋን ቶሎ ለመያዝ ይንደፋደፋል። ተቃረበ ። ሊይዛት ትንሽ ብቻ ቀረው። በጣም
ተንጠራራ። እጇን ልታስይዘው አብዛኛው ሚዛኗን በገደሉ አፋፍ ላይ ወጥራ በሃይል ተንጠራራች። ጣቶቻቸው ሊነካኩ የስንዝር ያክል ልዩነት ብቻ ነበር የቀራቸው። በዚሁ መሀል ግን ከየት መጣ ሳይባል አንድ ትልቅ ጭልፊት አሞራ ይመጣና ፊቷን በጥፊ ይላታል። ደንግጣ አሞራውን ለማየት ቀና ስትል ጌትነት የተንጠለጠለበት ሀረግ ቷ!! ብሎ ከመስረቱ ተነቀለና ቁልቁል እየተምዘገዘገ ይዞት ሲወርድ አየች።
ገደሉ ርቀት ነበረው። ጌትነት ጥረቱ ሳይሳካለት ቀረና ሄዶ በአናቱ ተደፋ። ጭንቅላቱ ያረፈው አለት ድንጋይ ላይ ነበር፡፡ በጀርባው እንደተዘረረ ደሙ እንደ ምንጭ ውሃ ቡልቅ! ሲል እናቱ ተመለከተች፡፡
“ወይኔ..ልጄን!እኔ ልደፋ!” ባለ በሌለ ሀይሏ ወደ ገደሉ ራሷን ወረወረች... ከእንቅልፏ እየተወራጨች የባነነችው በዚህ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ እያለች ነበር፡፡ በዚህ እጅግ አሰቃቂ በሆነ ህልሟ ምክንያት ሰውነቷ ይንዘፈዘፍ፣ ወባ እንደተነሳበት ስው ይንቀጠቀጥ ጀመር፡፡
እውን... እውን መሰላት። ከአልጋዋ ላይ ተነሳችና መንታ መንታውን
አወረደችው። ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ማልቀስ ካቆመች ረጅም ጊዜ ሆኗት ነበር፡፡ የተጠራቀመ እምባዋን እንደ ጐርፍ ለቀቀችው
"ወይኔ ጉዴ?! ወይኔ ልጆቼ?! ምን ዓይነት ህልም ነው? የኔ ደም
ክንብል ይበል። ዛሬ ፈጣሪዬ ምኑን አሳየኽኝ? ደግሞ የምን ጭልፊት
ነው? ዐይኔን ሊያጠፋው ነበረኮ! እስቲ አንተ ታውቃለህ? " ከዚህ አሰቃቂ ህልሟ በኋላ መንፈሷ በፍፁም አልረጋጋ አላት። ጭንቀቱ እረፍት ነሳትና ዳቦ ቆሎ መቁረጥ ጀመረች። በሌላ ጊዜ ደግሞ ትልቅ እባብ ሲያባርረው አየች። ይሄንን ግን ለወይዘሮ ተዋበች አልደበቀቻቸውም፡፡
“ምቀኛ ነው! ምቀኛ! ለመሆኑ ነደፈው?" ብለው ጠየቋት።
የለም! የለም! አልነደፈውም ብቻ ሲያባርረው ሮጦ አመለጠው'
ባለመነደፉ ነው ህልሟን የተናገረችው እንጂ ነድፎት ቢሆን ኖሮ አትነግራቸውም ነበር፡፡
“ጐሽ!...ጎሽ! እባብ ምቀኛ ነው። ምቀኞቹን ሁሉ ድል አድርጓል ማለት ነው፡፡ ቢነድፈው ኖሮ ጥሩ አልነበረም፡፡ ካመለጠው እንኳ ከጠላት፣ ከምቀኛ ተንኮል አምልጧል ማለት ነው፡፡ ማለፊያ ህልም ነው ያየሽለት!”
ሲሉ አጽናኗት። የወላድ አንጀት፣ የልብ ፍቅር እውነትም አንዳንድ ጊዜ ሹክ የሚለው መንፈስ አለ፡፡ ጌትነት የዚያን አይነት አሳዛኝ አደጋ ሊደርስበት ሳምንት ሲቀረው ጀምሮ በሃሣብና በጭንቀት ተወጥራ እየተብሰለሰላች በሆነ ባልሆነው ልቧ ድንግጥ ድንግጥ እያለባት እንቅልፍ እንቢ እያላት
እያቃዣት ሰውነቷ መጨማደድ ጀመረና በጥቂት ቀናት ውስጥ
ተለወጠች፡፡ ለተመልካች ግራ እስከሚገባው ድረስ በአንድ ጊዜ ቆረቆዘች።ጉዷን ያላወቀች እናት። በሷ ቤት የሳምንት ተጓዥ መንገደኛ ናት።የስንቅ ጣጣዋን ጨርሳ ወደ ልጅዋ ለመሄድ ዝግጅቷን በማጠናቀቅ ላይ

👍2
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
#አዲስ_ዓለም
..የመንገዱ መብራቶች ተበላሽተው ብርሃን አይሰጡም። አካባቢው ፀጥ እረጭ ብሏል። ትናንትና ማታ እስከ ስድስት ሰዓት የነበረው ጩኸት፣ ሁካታ የሰካራሞች ልፍለፋ፣ የሴተኛ አዳሪዎች ስድብ፣ በየቀይ መብራቱ ውስጥ የነበዙ ጠጪዎች ዳንኪራና ጭፈራ ትርምሱ ሁሉ እዚህ ቦታ
የነበረ መሆኑ የሚያጠራጥር ነው፡፡ የሥጋ ቤቶቹ ብርሃን ድምቀት፣ከቡና ቤት ቡና ቤት የሚያማርጠው ጠጪ ብዛት፣ የሙዚቃው ጩኽትና የመኪናው ኳኳታ ጆሮ ሲያደነቁር እንዳላመሽ ሁሉ እንደዚህ እንደ አሁኑ እረጭ ብሎ ሲታይ በግርግርና በፀጥታ መካከል ያለውን ልዩነት
ለማሳየት ደፈጣ የያዘ ይመስል ነበር፡፡
የወዳደቀ አጥንት ለመለቃቀም የሚያነፈንፉ ውሾች ውር ውር
ይላሉ፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ግን ያን ሰው የማይታይበትን አካባቢ ፀጥታ በማደፍረስ የጠዋት ገበያዋን ለመላፍ የተጣደፈች ታክሲ ከእሪ በከንቱ ወደ አራት ኪሎ አቅጣጫ በረረች፡፡ በዚያው ቅጽበት ደግሞ
ቁልቁል ከፒያሳ ወደ እሪ በከንቱ እየዘለለ የሚወርድ ሰው ታዬ። መላ ሰውነቱን ሬንጅና ጥላሸት የተቀባ ፀጉሩ እዚህም እዚያም ተገምዶ እንደ ጭራሮ የቆመ፣ ጎድኖቹ ሥጋ ባልለበሰ አጥንት የገጠጡት እብዱ ምን ሽንሽ! ብቻውን በመንገዱ ግራና ቀኝ ቱር ቱር እያለ እየተሯሯጠ ሽቅብ
ይወጣል ቁልቁል ይወርዳል። ዐይኖቹ እንደ በርበሬ ቀልተው ለተመልካች ያስፈራራሉ። ከወገቡ በታች እዚህም እዚያም የተቦጫጨቀ ሱሪ መልበስ
ከተባለ ለብሷል። ቆም ይልና ድንጋይ ይፈነቅላል ያነሳውን መልሶ ይወረውረዋል። ደግሞ ወደታች ይወርዳል። ከዚያም ጉንበስ ይልና የሲጋራ ቁራጭ ለመልቀም ያነፈንፋል።እንደገና ወደ ላይ ይወጣል። የዚያ አስፈሪ
የጨለማ ንጉሥ ሁሉም በየቤቱ በተከተተበት ሰዓት እሱ እየዘለለና እየቦረቀ ብቻውን በየመንገዱ ላይ ሲሯሯጥ ምሽቱን ለብርሃን ለማስረከብ የተዘጋጀ ባለሥልጣን ይመስል ነበር።
ከለሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት ሆኗል። ወደየጠቅላይ ግዛቱ የሚጓዙ መንገደኞች አውቶቡስ ተራ ለመድረስ በዋናው አስፋልት መንገድ ላይ ብቅ ብቅ ብለዋል። በዚያ ሰዓት በእግር የሚጓዝ መንገደኛ አንድም በራሱ የተማመነ አሊያም ከወሮበላና ከማጅራት መቺው ሰይፍ እግዚአብሔር እንዲጠብቀው በልቡ ፀሎት እያደረስ በፍርሃት የሚራመድበት እንጂ ልቡ
በድፍረት ተሞልቶ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት አልነበረም፡፡ ለሁሉ ነገር ግድ
የለሌው ለማጅራት መቺው ለብርዱ ለፀሀዩ ለሞትም ለህይወትም ደንታ የሌለው እብዱ ምንሽንሽ ብቻ ነበር። የእሪ በከንቱን ድልድይ ተሻግሮ
ወደ አራት ኪሎ ሲያቀና አንድ ዕድሜው ከሰላሳ ስምንት እስከ አርባ አመት የሚገመት ወደ ወሎ ጠቅላይ ግዛት ለመሄድ የሚገስግስ ሰው ብቅ! አለ። ሰውዬው ምንሽንሽን ሲያየው “በስመአብ ወልድ ጌታዬ” አለና
አማተበ፡ የሰይጣን ቤት አጋፋሪ የመሰለውን እብድ ሲመለከት ከመንገዱ ፈንጠር አለና ወደ ዳር ወጣ፡፡ ካደረበት ከዘውዲቱ ሆቴል ቁልቁል ወደ እሪ በከንቱ የሚወስደውን መንገድ ሲጀምረው ዳፍንቱ በብርሃን ባለመተካቱ ልቡ ፈራ ተባ እያለ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
የአራት ልጆች አባት የሆነው ጓንጉል ቢሆነኝ አዲስ አበባ የመጣው ያደለባቸውን ሁለት ሠንጋዎች ወልዲያ ገበያ ሸጦ ባገኘው ገንዘብ ለሚስቱና ለልጆቹ ልብስና ጫማ ለራሱ ደግሞ የፋሲካን በዓል መዋያ ልብስ
አማርጦ በርካሽ ዋጋ ገዝቶ ቀሪውን ገንዘብ ለልዩ ልዩ ችግሮች ማቃለያ ሊያደርግና በኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ የመጀመሪያ አመት ተማሪ የሆነችው የታናሽ እህቱን ልጅ ሊጠይቅ በዚያውም የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባን ሊጎበኛት ነው።
በዚሁ መሠረት ጣጣውን ጨርሶ ለአራቱ ልጆቹ ልብስ ሲያማርጥ ቆይቶ ሻንጣ ገዝቶ ከቆጣጠረና አዳሩን ዘውዲቱ ሆቴል ካደረገ በኋላ ወደ ቤተሰቦቹ ለመገስገስ ከዚያም ቤት ደርሶ ልጆቹና ሚስቱ ከበውት ሲንጫጩ የኔ ያምራል የኔ ይበልጣል እያሉ ህፃናቱ እርስ በርሳቸው ሲሟገቱ፣ሚስቱ ደግሞ የገዛላትን ቀሚስ እየላካች ረዝሞ ከሆነ ሰነፍ ልኬን እንኳን
የማታውቅ? ስትለው፣ ልኳ ከሆነ ደግሞ እሰይ የኔ አንበሳ” ብላ ስታደንቀው፣ ጉንጬን ሳም ስታደርገው በሀሳቡ እየታየው ቶሎ ሊደርስላቸው ነበር ለሊቱ አልነጋልህ ብሎት ዐይኑ ፈጥጦ ያደረውና ከለሊቱ ለአሥራ
አንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ያውም የረፈደበት መስሎት ልብሱን በፍጥነት ለባብሶ የወጣው...
ጓንጉል ምንሽንሽን ሲያየው በድንገጤ እግሩ ተሽመደመደበት እንደዚህ አይነት አጋንንት መሳይ ሰው ሚልኪው ጥሩ አይደለም አለ በልቡ። የሰው ዘር ሳያይ ዐይኑ ያረፈው በእብዱ ላይ ነበር። እብዱ ምንሽንሽ ወደሱ እንደመጠጋት ብሎ ፊት ለፊት ሲመጣበት በድንጋጤ ወደ ግራ
በኩል እሸሻለሁ ሲል አደናቀፈው።
“ወንዱ!” አለና ፎክሮ ተንገዳገደ። እብዱ ጠጋ አለውና እጁን ዘረጋለት።
ፍራንክ እንደሚጠይቀው አወቀ። ወይ ይቺ ፍራንክ? አለ በልቡ።እብዱም፣ጤነኛውም፣አዋቂውም፣ ህፃኑም ሁሉም ይወዷታል ሲል ተገረመ::
የመጨረሻዋ የስድስት ወር ህፃን ልጁ እንኳን ወሪቀት በግራ እጁ ብር በቀኝ እጁ ይዞ ሲያስጠጋላት እጅዋ ወደ ቀኝ እጁ ነበር የሄደው። ይሄን አስታወሰና ትንሽ እንደ መሳቅ ብሎ እጁን ወደ ኪሱ ከተተና ያገኘውን ድፍን ሃያ አምስት ሣንቲም ኣውጥቶ ወረወረለት። ምንሽንሽ ሳንቲሟን
ለማንሳት ጐንበስ ሲል እሱ ደግሞ አውቶቡሱ እንዳያመልጠው በሩጫ ዳገቱን ተያያዘው፡፡
የሆነ ነገር ውልብ አለበት፡፡ የሰው ቁመና መስለው። ከግራ ወደ ቀኝ
የሮጠ ነገር ነበር፡፡
“ጅብ ነው! ጅብ መሆን አለበት። ከወዲህኛው ገደል ዘሎ ወደዚያኛው መግባቱ ነው! ልክ ነው አውሬ መሆን አለበት! አቋረጠኝ እኮ ልክ ነው ደግሞ ጠቆር ያለ ነገር ነው! ወይኔ ዛሬ እግዚአብሔር ከዚህ ጉድ ያውጣኝ እንጂ ያጋጠመኝን ሁሉ ቤት ገብቼ ለሚስቴ ነው የማጫውታት፡፡ ገና በጠዋቱ ቀንዳም ጋኔን የመሰለ እብድ ለከፈኝ እሱን ሳልፍ ደግሞ ይኸውና ጥቁር ጅብ አቋረጠኝ። እግዚአብሔር ያውቃል” እያለ በልቡ እያወራ ወደ ድልድዩ ተጠጋ፡፡ ሰግጠጥ እንደማለት
አደረገው። ድልድዩ ላይ ሲደርስ ከበደው፡፡ ገልመጥ፣ ገልመጥ አለ። ሰላም ይመስላል። ፀጥ ረጭ ብሏል። ብቅ ብቅ ብለው መታየት የጀመ ሩት ሰዎች በተለያየ አቅጣጫ ሄደዋል። በዚያ መንገድ ላይ ተፍ ተፍ የሚለው እሱ ብቻ ነበር፡፡
“ስው ሊሆን አይችልም፡፡ በዚህ ሰዓት ሰው እዚህ ድንጋይ ውስጥ እገደል ስር ምን ይሰራል? ሰው አይደለም አውሬ መሆን አለበት...” ፈራ ተባ እያለ ወደ ድልድዩ ገባ፡፡ እንደፈራው አይደለም፡፡ ምንም ነገር የለም።
ወደ ኋላው ገልመጥ ብሎ አየ፡፡ እብዱ በተሰጠው ሳንቲም ተደስቶ እየዘለለ ወደ አራት ኪሎ ሲያቀና ተመለከተው፡፡ አካባቢው ጭር.እረጭ...ያሉ የሞት ጥላ የሚያንዣብብበት መሰለ፡፡ ሁለቱን ሠንጋዎቹን ሸጦ ሸቀጣ ሸቀጥ ከሽመተበት ሌላ በኪሱ ውስጥ ሁለት መቶ አርባ ብር ቀርታዋለች፡፡
እሷንም ጥሩ ቦታ አስቀምጧታል፡፡ መጀመሪያ ከሱሪው ኪስ ከተታት፡፡ ደስ አላለውም፡፡ ወደ ኮቱ የውስጥ ኪስ ወሰዳት። አላመናትም፡፡ የአንድ ዓመት ሙሉ የልፋቱ ውጤት እነዚያ ቤት ቤት የሚያካክሉ ሠንጋዎቹ የተለወጡባት ትንሽ ነገር ብትጠፋ ሁለት ሠንጋዎች ቀለጡ ማለት ነው። በየኪሱ ሁሉ አዟዟራት። በመጨረሻ ላይ ጥሩ የማስቀመጫ ቦታ አገኘላት። በጥንቃቄ የሚደብቀበት አስተማማኝ ቦታ! ወደ ጫማው ወረደ። እንደገና እጁን መለሰው። አሁንም አሰላስለ። ፊቱ ፈካ አለ፡፡የመጨረሻውን አስተማማኝ ቦታ አገኘላት። በመታጠቂያው ዘልቆ በውስጥ ሱሪው መካከል በደንብ አድርጐ አጣጥፎ ቀረቀራት። የአሁኑ ከፍተኛ ሥጋቱ ይቺኑ እንቅልፍ ያጣባትን

👍3
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...በአረቄና በጠላ ሽያጭ የሚተዳደሩት እማማ ወደር የለሽ ከጐረቤታቸው ከወይዘሮ አረጋሽ ጋር ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን ተሳልመው እየተመለሱ
ነበር፡፡ አሳዛኙ ጓንጉል ጨሌ ያጣች ሚዳቋ መስሎ አፉን ከፍቶ ድልድዩ ላይ ተቀምጧል። አላፊ አግዳሚውን በዐይኖቹ ይማፀናል። ችግሩን ጠይቀው አዝነው አንድ መፍትሄ እንዲሰጡት በአጠገቡ ሰው ካለፈ ዕይኖቹን ክርትት ክርትት ያደርጋቸዋል። ቀርቦ የሚያናግር ችግሩ ምን
እንደሆነ የሚጠይቀው ስው ግን አጣ፡፡ “አይዞህ!” የምትለው ቃል ብቻ ለሱ እንደዚያ ልቡ በሀዘን ተሰበረ ሰው ትልቅ የማፅናኛ የተስፋ ቃል ነበረች፡፡ ሌላው ሁሉ ቀርቶ ያቺ የራቀችበትን “የአይዞህ ወንድሜን” ቃል የሚለግሰውና በሃዘን ከንፈሩን የሚመጥለት አንድ ሰው እንኳን በማጣቱ
እየተንገበገበ የእንባ እጢው እስከሚደርቅ ድረስ አለቀሰ፡፡ ወይዘሮ ወደሬ ግን እንደሌላው ዝም ብለው አላለፉትም፡፡
“ውይ በሞትኩት! ይሄ ሰው ምን ነክቶት ነው እንደ ሴት ልጅ እንባ
ውን የሚያፈስው? ወይ ወንድሜ ምን አጋጥሞት ይሆን በሌሊት እዚህ ተቀምጦ እንባውን የሚረጨው?” አሉና ጠጋ አሉት። ከዚያ ሁሉ ሰው መካከል እማማ ወደሬን ጣለለት። “የኔ ወንድም ችግርህ ምንድነው?”ብሎ አንጀቱ የተቃጠለበትን ምክንያት እንዲተነፍስ ዕድል የሰጠው ሰው
አንድ ወይዘሮ ወደሬን በማግኘቱ ደስ አለው። የደረሰበትን አሳዛኝ አደጋ ተናግሮ ምንም ባያደርጉለት እንኳ ከንፈራቸውን የሚመጡለት ጠያቂ በማግኘቱ ደስ ቢለውም ሆዱ ባባና ፊቱ በሀዘን ተከፋ።
ምን ሆነሃል ወንድሜ? በለሊቱ እዚህ ተቀምጠህ ታለቅሳለህሳ?” ብለው ጠየቁት ፡፡ ወይዘሮ አረጋሽም ፈራ ተባ እያሉ
እየተጠራጠሩ ወይዘሮ ወደሬን ተከትለው ወደ ጓንጉል አመሩ።
“ደህናም አይደለህ እንዴ የኔ ወንድም? ምን ችግር ገጠመህ?” ሲሉ እሳቸውም አክለው ጠየቁት፡፡
ምን ደህንነት አለኝ እናቶች? ምን ደህንነት? ምን አገር? ምን ሰው
አለና ደህና እሆናለሁ?” ቁዝም አለ፡፡ ሁለቱም እርስ በርሳቸው ተያዩ። የስውዬው ሁኔታ አሳዝኗቸዋል።
የምንረዳህ ነገር ካለ የሆንከውን ብትነግረን?” አሉ ወይዘሮ ወደሬ፡፡
የለም የኔ እናቶች አትቸገሩ እሱ ያመጣብኝን ጣጣ እሱ እስኪመልስልኝ ድረስ ጉዴን ለብቻዬ እሸከመዋለሁ። እናንተን የማስቸግርበት ምክንያት
የለም፡፡ ወይኔ ጓንጉል? ወይኔ ልጆቼ? ወይ ሚስቴ?! ” ስሙን ሲናገር ወይዘሮ ወደሬ ተጠራጠሩ።
“ከየት አገር ነው የመጣኸው? የዚሁ የአዲስ አበባ ስው ነህ? ወይስ ከጠቅላይ ግዛት?” የአማርኛ አጣጣል ዘዬው እሳቸው የገመቱት አገር ሰው መሆኑን ይመሰክራል።
“ኸወሉ” አለ ጓንጉል።
“ወይኔ! እኔን አፈር ይብላኝ፡፡ የኔው አገር ስው ነሃ! አፈር ስሆን ምን
ሁነህ ነው?ለመሆኑ ወሎ እምኑ ጋ?”
“ወልዲያ!”
“ኸረገኝና እናንተ ሆዬ የኔው ሰው ነሃ! እነ አያ እገሌን እነ እገሊትን ታውቃለህ?” የቅርብና የሩቅ ዘመዶቻቸውን ስም እየጠሩ ጠየቁት።
ጭውውቱ ቀጠለ፡፡ እሳቸው የሚጠራቸውን ሰዎች በብዛት የሚያውቃቸው ነበሩ፡፡ ወይዘሮ ወደሬ በጣም ደስ አላቸው፡፡
“በል እስቲ የሆንከውን ንገረኝእማ ለካ የኔው ሰው ሁነህ ኑሯል አንጀቴን የበላኸው? በል አሁን አንድም ሳትደብቅ ንገረኝ ሌባ ነጠቀህ? ወይስ ምን ሆንክ?”
“ሌባም አይደለም እናቴ እንደዚህ አይነት ሌብነት አይቼም ሰምቼም አላውቅም፡፡ ጅቦች ናቸው የበሉኝ፡፡ ጅቦች! ህይወቴን እስከምስት ድረስ ማጅራቴን መትተው ከጣሉኝ በኋላ ተቀራምተውኝ ሄዱ። አይ እኔ? ወይ ድካሜ?”
“በል አሁን ተዚህ ተነሳና እቤት አረፍ ብለህ አዋይሃለሁ” እጁን ሳብ አደረጉት። ሳይደግስ አይጣላም፡፡ ከዚያ ሁሉ ህዝብ መካከል የአገሩን ልጅ ወይዘሮ ወደሬን አምጥቶ ለጣለለት አምላክ ምስጋና በልቡ አደረሰና አብሯቸው ማዝገም ጀመረ። ከቤት ሲደርሱ ወይዘሮ ወደሬ ያቀረቡለትን እንጀራ በበርበሬ አፍ አውጥቶ መጮህ ወደ ጀመረው ሆዱ ቁልቁል ይልከው ጀመር፡፡ በደንብ አድርጉ እስከሚጠግብ ድረስ በላ፡፡ በጣሳ የቀረበለትን ጠላ ጠጣ፡፡ “
እፎይ..” አለና የሆነውን ሁሉ ያጫውታቸው ጀመር፡፡
“አይ ልጄ? ወንድሜን! አይ አለማወቅ? በለሊቱ ገስግስህ በተከፈተ አፋቸው ውስጥ ስተት ብለህ ገባህላቸው? ለመሆኑ በስንት ሰዓት ላይዐነው እንደዚህ ጉድ ያደረጉህ?”
“እኔማ ኦቶቡስ እንዳያመልጠኝ መጣደፌ ነበር ለካ ለሊቱን ሙሉ እንቅልፌን አጥቼ ያደርኩት የነሱ ሲሳይ ለመሆን ነበር?”
“አይ የኔ ልጅ ጉድ አደረጉህ አይደለም? ለመሆኑ ምን ያክል ቀሙህ?”አሉ ወይዘሮ ወደሬ ለራሳቸው ጠላ በብርጭቆ ቀድተው በርጩማቸው
ላይ እየተቀመጡ።
“እባክዎት ልፋቴን ድካሜን ሁሉ ውሃ በላው። ሁለት ዓመት ሙሉ የቀለብኳቸው ሠንጋዎች ቀለጡ” አለና ፊቱ በንዴት ጠቆረ።
“በጥሬ ገንዘብ ሁለት መቶ አርባ ብር፡፡ ሌላውን ይተዉት። ለልጆቼ፣
ለሚስቴ፣ለራሴም የገዛኋቸው ልብሶች ከነሙሉ ሻንጣው" የአገራቸው ልጅ ጓንጉል በለሊት ተነስቶ የጩሉሌዎች ሲሳይ መሆኑ በጣም አሳዘናቸው። በተቻላቸው አቅም ሊረዱት ፈለጉ። ጓንጉል ዕድለኛ ሆነና ውሃ የሚያጠጣው ችግሩን የሚካፈልለት ሰው አገኘ፡፡
“ለመሆኑ እማማ? እንዲያው አዲስ አበባ ውስጥ ስው እንደፈለገው መውጣት መግባት አይችልም ማለት ነው? እንኳንስ በንጋቱ በጠዋቱ ይቅርና በውድቀት ጨለማ ሲሄድ ቢያድር መንግሥት ባለበት አገር
እንዴት እንደዚህ ያለው ዓይን ያወጣ ዝርፊያ ይፈፀማል? እንዴ?!
እንዴ?! እንዴ?!” ግርም፣ ድንቅ አለው፡፡
“አይ ልጀ አዲስ አበባ እንደ አገር ቤት መስሎሃል? አዲስ አበባ እኮ
ሁሉም ዓይነት ሰው የተሰበሰበበት አገር ነው። እንደኔ ለፍቶ አዳሪው
እንዳለ ሁሉ ስላቢው፣ ቡዳው፣ ቀማኛው፣ቤት ሰርሳሪው፣ ነፍሰ ገዳዩ ፣ማጅራት መቺው ምኑን ትቼ ምኑን ልንገርህ? ሁሉም አይነት የተጠረቃቀመበት የጉድ አገር ነው። በቀማኛውና በማጅራት መቺው አለመቀደም እንጂ አንዴ ከተቀደሙ ምን ማድረግ ይቻላል? እንኳንም ህይወትህ ተረፈ እንኳንም የልጆችህ አምላክ ከጉድ አወጣህ እንጂ ገድለውህስ ቢሆን ኖሮ? ማን ይይዛቸው ነበር? ገንዘብ ምንአባቱ አንተ እስካለህ
ድረስ ነገ ተነገ ወዲያ ሰርተህ ትተካዋለህ” የአሮጊቷ ምክር ልቡን መለስ አደረገው፡፡ እውነትም ማጅራቱን ብለውት እንደወደቀ በዚያው ቅርት ቢልስ? ልጆቹ ያለ አባት ሊቀሩ ትዳሩ ሊፈርስ ነበር ማለት ነው።
“ሆቸ ጉድ!” ነገ ተነገ ወዲያ እንዳሉት እሱ በህይወት እስካለ ድረስ የሚተካው ገንዘብ ነው። ወይ የፈጣሪ ሥራ ይህም አለ ለካ? በአንዱ ሲያማርሩ ይብስን አታምጣን ማስብ ትልቅ ነገር ነው ሲል ተፅናና፡፡ ዳሩ አንድ ጊዜ ቀልጦ ለቀረ ገንዘብ ሲብከነከን ምን ዋጋ አለው? በፍርድ ቤት
ተሟግቶ ነጣቂውን አስይዞ ለማስመለስ የሌቦቹ ፍንጭና ዱካ አይታወቅም፡፡ ቢያለቅስ ቢዘል ቢፈርጥ ምን ዋጋ አለው? ይህን ሁሉ ቀስ በቀስ ማስብ ማሰላሰል ጀመረ።
“አሁን ለመሳፈሪያ የሚሆን ምንም የለህም አይደል?” በሃሣቡ የሚጉላላ ችግሩን ተረድተው ሲጠይቁት ደስ አለው። የውለታቸው ነገር ከብዶት

#ክፍል_አርባ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....ወይዘሮ ወደሬ ከእሪ በከንቱ ወደ ፊት በር በሚወስደው መንገድ በስተግራ በኩል ከአፋፉ ላይ በመኖሪያና በመሸታ ቤትነት የሚጠቀሙበት ሁለት ክፍል ቤት አላቸው፡፡ አሻሻጫ ቀን ቀን በግርድና ማታ ማታ ደግሞ ልብሷን ቀያይራ፣ ፀጉሯን አበጣጥራ በሴተኛ አዳሪነት ብቅ የምትለው ጽጌ ነበረች፡፡ ጽጌ ከአካባቢዋ ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ጥሩ መግባባት አላት። ኑሯቸውን እየኖረች ቀን ቀን የቤት ስራተኛ ማታ ማታ ደግሞ ሴተኛ አዳሪ እየሆነች ስትገለባበጥ ኖራለች።
ፅጌ ከኩሽና ንግስትነት እስከ አረግራጊው አልጋ ፊታውራሪነት... ሁለቱንም የህይወት ተሞክሮ እኩል እየኖረች ስፊ ልምድ ያዳበረች ሴት ነች።አዲሷ አሻሻጭ ሰላማዊት ወደ እማማ ወደሬ ቤት ከመምጣቷ በፊት ፅጌ ብቸኛዋ የወንዶች አይን ማረፊያ ነበረች። ሰላማዊት በአሻሻጭነት ስራ
ልትጀምር የአሮጊቷ የእማማ ወደሬን ቤት ከአራት አመታት በፊት ከተቀላቀለች በኋላ ግን የተፈላጊነት ደረጃዋ እያሽቆለቆለ ሄዶ ነበር ሰላማዊት የእማማ ወደሬ ጓደኛ የሆኑት የወይዘሮ አረጋሽ ልጅ የቅድስት ጓደኛ ስትሆን “ እማማ ወደሬ ቤት ይሻልሻል” ብላ ይዛት የሄደችው
ቅድስት ነበረች።
የአሻሻጭ ችግር የነበረባቸው እማማ ወደሬ ቀንበጥ የመሰለችው የቆፍጣናው ገበሬ ልጅ እቤታቸው ድረስ ሰተት ብላ የመጣችላቸው እለት ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ። ገበያቸው በሰላማዊት ምክንያት ሲደራ፣ ሲጧጧፍ ደንበኞቻቸው መሸታ ቤቱን ሲያጣብቡት በሷ የአሻሻጭነት ተግባር ውስጥ የዕለት ገቢያቸው በእጥፍ ድርብ ሲጨምር ወለል ብሎ ታያቸው።
ደንበኞቻቸው ቦታ ቦታቸውን ይዘው እየጠጡ ነበር፡፡ በሞቅታ ሃይል
ግማሹ ይዘፍናል ከፊሉ የቤቱን ጣጣ፣ የሚስቱን ጉድ... የመሥሪያ ቤት ችግሩን... የአለቃውን ተንኮል....ሁሉም የየራሱን ወሬ ያወራል። የሰከረው ብዙውን ጊዜ ከማዳመጥ ይልቅ ማውራት ስለሚቀናው መደማመጥ ይጠፋና አውራው የጠፋበት የንብ መንጋ ይመስል አየሩ በጫጫታ
ይሞላል። የተጀመረው የወሬ ርዕስ መቋጫ ሳያገኝ ሌላ የወሬ ርዕስ ይከፈታል። እሱም በወጉ ሳይሰማ አዲስ ርዕስ ይጀመራል። ምን እንደተወራ ርዕሱ በውል ሳይታወቅ እንደገና ሌላ ርዕስ ይቀጥላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተጀመረው አዲስ ርዕስ ምን እንደሆነ እንኳንስ አድማጩ ተናጋሪው ራሱ በውል አያውቀውም፡፡ ዝም ማለት በህግ የተከለከለ ይመስል ማውራት..
ማውራት.. ማውራት... መጮህ... የአንድ ቀን ትውውቅ የሌለው በስካር መንፈስ መጠጥ ቤት ውስጥ ይተዋወቅና ወዲያውኑ መሳሳም ይጀምራል።ሰክሮ እጁ የማይፈታ፣ የማይጋብዝ፣ ሰክሮ ጥሩ ዘፋኝ፣ ጥሩ ስዓሊ...ጥሩ ደራሲ...ጥሩ የእግር ኳስ ተጫዋች የማይሆን ስለአንበሳ ቦክሰኛነቱ የማያወራ ጥቂቱ ነው። በዚያን ዕለትም እንደተለመደው ጠጪው የእማማ ወደሬን ቤት ከአፍ እስከገደፉ ሞልቶ አጨናንቋት ነበር ደላላው፣ ተሸካሚው፣አናፂው፣ግንበኛው፣ አስተማሪው... በያይነቱ...
እማማ ወደሬ የዶሮ ዓይን የመሰለ ጠላቸውና የነጠረ ካቲካላቸው ለመድኃኒትነት ይፈለጋሉ እየተባለ ዝናን ስላተረፉላቸው ቤታቸው ምንጊዜም ቀዝቅዞ አያውቅም ነበር፡፡ እማማ ወደሬ ደስ ያላቸው ቀን ከጠጪው መሃል ይደባለቁና ጨዋታውን ያጧጡፉታል። በዚያን ጊዜ የግብዣው መዓት ይወርድላቸዋል፡፡
እሳቸውም ፈታ ብለው ስለ ትኩስ ዘመን የፍቅር ታሪካቸው፣ ስለ ባልንጀሮቻቻው፣ ስለ ውሽሞቻቸው፣ስለ ጣፋጭነታቸው እያነሳሱ እንደ ዋዛ አለፈ እያሉ ጠጪውን ያዝናናሉ፣ ያፍነክንካሉ በጨዋታ ያሰክራሉ። ሰላማዊትን ለገበያ ባቀረቡበት በዚያን ዕለትም ልባቸው በሀሴት ተሞልቶ
ፊታቸው በፈገግታ በርቶ ነበር፡፡ ለደንበኞቻቸው አዲስ ዜና የሚያስ
ሙበት ቀን በመሆኑ በኩራት ትከሻቸው ሁሉ ሰፍቷል። አንድ ሁለት መለኪያ ወስዱና ሳቅ...ፈገግ.…አሉ፡፡
ከወዲያ ማዶ ከትንሽ በርጩማ ላይ ቁጭ እንዳሉ ነበር፡፡ አፋቸውን በቀኝ እጃቸው እብስ እብስ ካደረጉ በኋላም ማስታወቂያውን አሰሙ።
“ልጃገረድ የምሽልመውና ዋጋውን የሚከፍለኝ?” ጠጪዎቹን እየተዟዟሩ
በዐይኖቻቸው ቃኙና ንቅሳታም ጥርሶቻቸውን እንደ ፋኖስ እያበሩ የምስራቹን አበሰሩ። በዚህ ጊዜ ጠጪው በሙሉ በአንድ ላይ በሳቅ አውካካ.
“ምን ያስቃችኋል? ይልቁንስ አትጃጃሉ! ማርያምን እውነቴን ነው” አሉ ከወዲያ ጥግ ተቀምጦ የነበረ አንድ ግንበኛ “እንዴ?! እትዬ ወደሬ ልጃገረዷ እኔው ነኝ እንዳይሉን ብቻ?! ካ! ካ.ካ..ካ” አለና አስካካ:: ሁሉም የግል ወሬአቸውን አቋረጡና ተከትለውት በሳቅ ፈነዱ፡፡
“ግድየላችሁም እትዬ ወደሬ እንደዚህ ደፍረው የሚናገሩት ያለምክንያት አይመስለኝም የሚያውቁት አንድ ሚስጥር ቢኖር ነው” አለ ከጎኑ የተቀመጠ ጓደኛው።
“ጉሽ አንተ ትሻላለህ እንዲያውም ላንተ ነው የምድራት ማርያምን! ሌሎቻችሁ እንደሴቃችሁ ትቀሯታላችሁ” መጋረጃውን ገለጡ። “ሰላማዊት!..ነይ እስቲ ወደዚህ ብቅ በይ የኔ ልጅ፡፡ እንግዲህ ዐይን አፋርነቱ ይበቃል፡፡ ሳምንት ያክል ተደብቀሽ ከረምሽ፡፡ ደፈር ደፈር ማለት ነው እንጂ እስከመቼ ጓዳ ውስጥ ተወሽቀሽ ትዘልቂዋለሽ ልጄ? የኛ ሥራ
ወጣ ወጣ ማለት ያስፈልገዋል። በይ ተደንበኞቼም ጋር ተዋወቂ፡፡ ሳቅ ሳቅ እያልሽ አስተናግጃቸው” ብድግ ብለው ከፊት አስቀደሟት። ከወዲያ ጥግ ፅጌ በአንድ ሰካራም እየተጋበዘችና ጡቶቿ ወተት እስከሚያመነጩ ድረስ እየታሸች በመስለምለም ላይ ነበረች።
የሁሉም ዐይኖች በሰላማዊት ላይ ተተክለው መቅረታቸውን ስታስተውል የሆነ የቅናት ስሜት ቆነጠጣት።ስራዋን ልትጫረትባት “ሀ” ብላ የአሻሻጭነት ስራ የምትጀምረውን ልጅ በጥላቻ ዐይን ተመለከተቻት።
ወንዶቹ ሰላማዊትን ካዩበት ቅፅበት ጀምሮ የምራቅ ዕጢዎቻቸው በከፍተኛ የምርት ሂደት ተጠምደው ነበር፡፡ ብዙዎቹ ወይዘሮ ወደሬ የሚቀልዱ
መስሏቸው ነበር፡፡በሁለመናዋ የምትስብ ልብ የምትሰርቅ ትንሽ ልጅ! በይብልጥ ዐይኖቻቸው የተሰኩት በዳሌዋ ላይ ነበር፡፡ አቤት ቅርፅ?!...
“እንዴ! እትዬ ወደሬ” አንዱ አረቄ ጠጪ በአድናቆት ጮኸና ጓደኛውን ጐሽመው።
እንዴት አይነት መረቅ የሆነች ልጅ ናት በናትህ?” እርስ በርስ ተጐሻ
ሸሙ:: “እትዬ ወደሬ ይሄ በፍፁም ከኔ ማምለጥ የለበትም” የሁልጊዜም ደንበኛቸው አዳሙ ጮኽ፡፡
“እንግዲህ ያልኩትን ቁጭ ማድረግ ከቻልክ ነዋ!” ወይዘሮ ወደሬ መለኪያቸውን አንስተው ጨለጡና የተወለጋገዱ ጥርሶቻቸውን ብልጭ አደረጉለት።
የፈለገውን እትዬ ወደሬ ምንም ይሁን ምን!”
ኖ...ኖ! እትዬ ወደሬ በቃላችን መሰረት ላንተ ነው ያሉት ለኔ መሆን አለበት፡፡ደግሞ እኔ ሳላዋጣዎ አልቀርም!”ዳንኤል አረቄውን እየጨለጠ ተከራከረ። በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ግን ገበያ እንደወጣ በግ በዋጋ የሚከ
ራከሩባት ልጅ ስለምን እንደሚያወሩ ለሷ ግልጽ አልነበረም፡፡ ሄዳ ከአግዳሚው ወንበር ጫፍ ላይ ከአረቄ ጠርሙስ መደርደሪያው አጠገብ ቁጭ አለችና አንገቷን ድፍት አድርጋ መሬት መሬቱን እያየች ተሽኮረመመች፡፡
አጠገቧ የነበረው ደጀኔ እነሱ ሲከራከሩ አጠገቡ መጥታ ቁጭ ያለችለትን እንኮይ ለቀም አደረጋት፡፡ በዋጋ ከመከራከር በእጅ ይዞ እያሻሹና እያሟ
ሟቁ መቀላጠፉ ሳይሻል አይቀርም ሲል ለራሱ አወራ፡፡

#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገ
...አፍንጫ ጎራዳነቷ ውበቷን አደመቀው እንጂ አላደበዘዘውም፡፡ ስላማዊት ብዙ ሰው ቢረባረብባትም ከሁሉ የበለጠ የምትቀርበውና ወዳጇ
መሆኑ በብዙዎቹ ዘንድ እየታወቀ የመጣው ታደሰ ነው። ታደሰ መልኩ ጥቁር ሆኖ ረዘም ያለ ጉብል ነው፡፡ እሱ ሲመጣ ሰላማዊት ማንንም አታነጋግርም፡፡ ሄዳ እሱ ላይ ጥብቅ ነው። ይሄ ሁኔታ በፅጌ አማካኝነት ለሰፈሩ ሴተኛ አዳሪዎች ሁሉ ስለተወራ ታደሰ ብቅ ማለቱን ሲያዩ ስሟን
እንደማስቲካ ሲያኝኩት ይውላሉ።
“አሳበዳት እንጂ! ነፍሷን አጠፋላት!ታደሰን አታውቂውም እንዴ? ደላላ ነው እኮ! ኸረ በሌላም የሚጠረጠር ሰው ነው አሉ። አንዱ ውሽማዬ ስለሱ ነግሮኛል።ነጭ ለባሽ ነው ተብሎ ይጠረጠራል ብሎ አጫውቶኛል”
“አረ እባክሽ?! ነጭ ለባሽ ?ምን አስነክቷት ይሆን እንደዚህ በፍቅር የከነፈችለት?”
“ትቀልጃለሽ እንዴ? ያቅማታላ! ብር እንደ አሸዋ ይበትንላታላ! እስቲ ይታይሽ? ደላላ ነው። በዚህ ላይ ደግሞ በነጭ ለባሽነቱ መንግሥት ይከፍለዋል! ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ነው
“ምን እያቀመሰቻቸው ይሆን ወንዶቹ ሁሉ እንደዚህ በሷ ላይ የሚረባረቡት በናትሽ?”
“ወረት ነው እባክሽ! ወረት! አዲስ ጀማሪ አይደለችም? በወረት ነው እንደ ንብ የሚከቧት”
የታደሰ ደግሞ ባሰ፡፡ ፍቅር ድብን አድርጎ ገድሎታል እኮ፡፡ ምን ማለትሽ ነው? አሁን አሁንማ ግንባሯን ሳይሳለም አይውልምኮ! እኔም ሳላየው የዋልኩበት ቀን የለም”
“ምን ታደርጊዋለሽ አጅሬ የወረት ፍቅር ነዋ!” ተንሾካሾኩባት። እውነትም ከዚያ ሁሉ የወንድ መንጋ መካከል ለታደስ ልዩ ፍቅር ነበራት። ታደሰ ፍቅሩን በብዙ መልኩ የሚገለፅላትና የሚያስፈልጋትን ሁሉ የሚያሟላላት የስካር ሳይሆን እውነተኛ ጓደኛዋ ነበር።
ዛሬም እንደ ወትሮው ካፖርቱን ከላይ ጣል አድርጉ ባርኔጣውን ደፍቶ አንገቱ ላይ ሻርፕ ጠምጥሞ ተፍተፍ የሚለው ወደሷ ነበር፡፡ ከሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ቀኝ ተገንጥሎ ወደ እሪ በከንቱ የሚወስደውን ቀጭን የአስፋልት መንገድ ተከትሎ ወደ ፍቅረኛው ወደ ሰላማዊት ለመድረስ እየተጣደፈ ነበር፡፡
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሆኗል። በአላፊ አግዳሚ ላይ ዐይኖቻቸውን እያፈጠጡ የሚያስፈራሩ ሴተኛ አዳሪዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል። በዚህ
ሰዓት እብዱ ምንሽንሽ ከአካባቢው አይታጣም ነበር፡፡ አንዴ ወዲህ አንዴ ወዲያ እየዘለለ ድንጋይ እያነሳ ድንጋይ እየጣለ ይሯሯጥ ነበር፡፡ ሣንቲም
ይለምናል። ከሰጡት ይቀበላል፡፡ ዝም ካሉት ደንታም የለው። የሱ ቁም ነገር መዝለል፣ መዝለል፣ ድንጋይ መፈንቀል፣ ድንጋይ ማንሳት ድንጋይ መጣል ብቻ ነው፡፡ ዛሬ ግን በሱ ምትክ ሰካራሙ ታከለ ያንን የማያስከፍል ድራማውን እያሳየ ለሴተኛ አዳሪዎች መሳለቂያና መደበሪያ ሆኖላቸው ነበር፡፡ መጀመሪያ ቀይ አጣብቂኝ ሱሪ ለብሳ ፀጉሯን እንደ ገዳይ ጐፈሬ ወዳቆመችው ሴት ቤት ጥልቅ ብሎ ገባ..
ሰካራሙ ታከለ ትዳሩን በመጠጥ ምክንያት ካፈረሰ በኋላ መቅኖ አጥቶ በደሞዝ ሰሞን ሲጠጣ፣ያገኘውን ሲጋብዝ፣ ሲሸልም፣ ሲበትን ይከርምና
ባዶ ኪሱን ጨረቃ አስመስሎ መውጣት ልማዱ ነው። እንደምንሽንሽ ሲለይለት አንድ ሀሙስ ብቻ ነው የቀረው፡፡ ሴትዮዋ በሯን ዘጋችና...
“እሺ ሂሣብ በቅድሚያ!” አለችው።
“ም. ን. ድ. ነው... ቅርሚያ ቅርሚያ! የምትይው? እኔን አታ..
አታምኝ.. ኝ.. ኝምምም?” አላት ልፍድድ ባለ የስካር ንግግር።
“ኡፋ! ሰውዬ ወሬ አታብዛ ! የምትከፍል ከሆነ በቅድሚያ ክፈልና እሺ። አለበለዚያ ውጣልኝ!ገበያዬን አትዝጋ!” አለችና አንባረቀችበት። ታከለ በጠጅና በአረቄ ብዛት የደነበሹ ዐይኖቹን ብልጥጥ አድርጎ ሲመለከታት ተንኮል የቋጠረ አመፀኛ ዝንጀሮ እንጂ ለጉዳይ የገባ እንግዳ አይመስልም ነበር።
በል ተናገር?! ያለበለዚያ ውጣ!” የዘጋችውን በር መልሳ እየከፈተች ጭኽችበት።
“ቆይ .. እ- ሺ ቆይ! ቆይ!” አለና ወደ ኪሱ ገባ፡፡ ያገኘው ሰላሳ አምስት ሣንቲም ብቻ ነበር።
እሺ ያው..ልሽ!
አትፈልጊምምም.?” እየተንተባተበ፡፡ ብልጭ አለባት።
ከኋላው አሽቀንጥራ ስትወረውረው ከፊት ለፊቱ ካለው ቆሻሻ ውሃ ከሚ ወርድበት ቦይ ውስጥ ሂዶ ተወተፈ፡፡ ከዚያም እየተውተረተረ ተነሳና ሣንቲምቹን መለቃቀም ጀመረ፡፡ እንደምንም ብሎ ሃያ አምስት ሣንቲም አገኘ።
ትርዒቱን እያዩ ወደሚሳሳቁት ግራና ቀኙን ወደተኮለኮሉ ሴተኛ አዳሪዎች እየተመለከተ“ይህቺን... ፈላጊ!.. ይህቺን... ይህቺን.” እያለ ሳንቲ ሞቹን ሽክ... ሽክ... ሽክ ሲያደርጋቸው የበለጠ በሳቅ ፈነዱ።
“አንተ ጠንባራ ሰካራም ድራሽህ ይጥፋ! የቀረችህ እሷ ናት። ሂድና ለሚስትህ ቀሚስ ግዛበት ፉዞ!” የስድብ መአት አወረዱበት። እሱም እየተንገዳገደ ቁልቁል ወረደ። ታደሰ ይህ ትርዒት የሚካሄድበትን አካባቢ
አልፎ ወደ ሰላማዊት ዘንድ ሊደርስ ትንሽ ቀርቶታል። አስፋልቱን ከመሻገሩ በፊት ግን ቆም ብሎ ምን ይዞላት እንደሚሄድ አሰላሰለ። እንደ
ሴተኛ አዳሪነቷ ሳይሆን እንደ ሚስቱ ያስብላት ስለጀመረ ወደ መኖሪያ ቤቱ የሚሄድ አባወራ እንጂ ወደ መሸታ ቤት የሚሄድ ጠጪ አይመስልም ነበር፡፡ ሰላማዊትም ከልቧ ስለምትወደው እሱ ከመጣ ሌላው ጠጪ
ሰው መስሎ አይታያትም፡፡ እንደሚጨነቅላት ስለምታውቅ አፀፋውን ፍቅር እየሰጠችው ነው፡፡ ታደስ ከእማማ ወደሬ ቤት ከፍ ብሎ ወደሚገኘው ሉካንዳ ቤት ገባና ከሽንጥ ሥጋ ላይ ሁለት ኪሎ ግራም አስቆርጦ አስጠቅልሎ ሄደ። ወይዘሮ ወደሬ የታደሰ ውለታ እየከበዳቸው ስለመጣ በሱ ምክንያት ሰላማዊትን ማክበርና መፍራት ጀምረዋል። ታደሰ ወደ ቤት ሊገባ ካለ በኋላ ምናምን እንዳቋረጠው ሰው ወደ ኋላው ሰግጠጥ አለና ቆመ፡፡ቀስ ብሎ በጓሮ በኩል ዞረ። የጓሮውን በር ያለሱ የሚደፍረው የለም።
“ሰላምን ጥሪያት” አላት ላፅጌ። ሰላማዊት ፅጌ ስትነግራት ሮጣ መጣች።
“ውይ ታዴ!”እቅፍ አድርጋ ሳመችውና በእጁ የያዘውን ተቀበለችው።
በጓሮ በኩል ዞሮ የገባው የያዘውን ሊሰጣት መሰላት። ድርጊቱ የበለጠ ገረማት። ማንም እሱ የሚያደርገውን አያደርግላትም። የፈለገውን ያክል ገንዘብ አስታቅፈዋት ቢሄዱ ታደሰ የሚያስበውን ያክል አስበውላት አያውቁም፡፡ በበዓላት ቀን ሹልክ ብሎ ይመጣና ገንዘብ ይሰጣታል። እንዳይደብርሽ እያለ ትያትርና ሙዚቃ ቤት ወስዶ ያዝናናታል፡፡
“አይ ታደሰ?አሁንስ አበዛው ምነው እሱ እንዲህ ተጨነቀ? እኔ ውለታ
ሲበዛብኝ ደስ አይለኝም፡፡ ይከብደኛል። ከሌላው የተለየ ለሱ ምን የተደረገለት ነገር አለ?” ወይዘሮ ወደሬ ስለታደሰ ተጨነቁ፡፡
“ታድዬ እቤት ትገባለህ ወይስ እዚሁ ጠላ ይዤልህ ልምጣ?” ስትል ጠየቀችው።
“እቤት አልገባም እዚችው ጓሮ ቁጭ ብለን ትንሽ አጫውቺኝና ጠላ ጠጥቼ እሄዳለሁ” አሁን አሁን የገባው ጠጪ ሁሉ እንደፈለገው እየጎተተ ሲያሻሻት፣ ሲያቅፋት፣ ሲስማት፣ ሲደባብሳት ማየት እያስጠላው መጥቷል።
“እሺ የኔ ቆንጆ ይዤልህ ልምጣ” አለችና ተመልሳ ገባች።
“ታዴ ወደ ቤት አይገባም እንዴ ሰላም?” አሉ ወይዘሮ ወደሬ።
“ውጭ ይሻለኛል ብሉኝ እኮ ነው”

#ክፍል_ሃምሳ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ከቀኑ አስራ አንድ ሰዓት ሆኗል። እማማ ወደሬ የፀበል ፃዲቅ ተጋባዦቻቸውን ለማስተናገድ ጉድ ጉድ እያሉ ናቸው። ወዳጃቸው ታደሰንም ፀበል ቅመስልኝ ብለው ስለጠሩት በጊዜ ተገኝቷል። ሌሉች ፀበል ፃዲቅ እንዲቀምሱ የተጠሩ እንግዶችም የእማማ ወደሬን ቤት አጨናንቀዋታል።ከፊሉቹ ደጅ አግዳሚ ወንበር ላይ ተኰልኩለው ጠበል ጠዲቁን እየቀማመሱ ይጨዋወታሉ።
ጥሪ ሳይደረግለት ፀበል ፃዲቅ ለመቅመስ በራሱ ፍላጐት የመጣ እንግዳም አለ፡፡ እብዱ ምንሽንሽ፡፡ ከአጥሩ ውጭ ድንጋይ ላይ ተቀምጧል።የሰፈሩ ስዎች ለምደውታል፡፡ እሱም ለማዳ እንስሳ እንጂ እንደ እብደቱና እንደ አስፈሪነቱ ተናካሽ አውሬ አልነበረም፡፡ የአንዳንዱ እብድ ጥሩ ፀባዩ ስው ያለመንካቱ ጉዳት ያላማድረሱ ሲሆን አንዳንዱ እብድ ደግሞ ስው አያሳየኝ በሚል ልክፍት የተለከፈ ይመስል ድንጋይ ተሸክሞ መንገደኛውን ሁሉ ሲያስበረግግ የሚውል ነው። ምንሽንሽ በፍፁም ሰው አይነካም፡፡ ዛሬም እንደ ወትሮው ሰውነቱ በምናምን ተድበስብሶ አመድ ላይ የተንከባለለች እንትን መስሏል፡፡ ወይዘሮ ወደሬ ወደ ደጅ ወጣ ሲሉ ምንሽንሽን አዩት።
“ምንሽንሽ እንደምን ዋልክ?! እንካ!” አሉና ኩባያ አቀበሉት። ምንሽንሽ አንገቱን በአክብሮት አቀርቅሮ ኩባያውን ተቀበለ። የሚያውቁት ምንም ።መስሎ አይታያቸውም። የማያውቁት ግን ድንገት ሲያዩት ይደነግጣሉ።
ምንሽንሽ ዛሬም የለበሳት ያቺኑ ቀንም ሆነ ማታ ከላዩ የማትወልቀውን፣ ጭቅቅት የበላትና የተበጫጨቀች ሱሪውን ነው፡፡ ፀሀይ አያቃጥለው፣
ብርድ አይበርደው፣ ቅማል አያሳክከው ለሁሉ ነገር ደንታ ቢስ ነው።ከላይኛው ከንፈሩ ላይ የበቀለው ጢሙ አድጎ የተዘቀዘቀ የፍየል ቀንድ መስሏል። ፊቱም ደም የማይዘዋወርበት ያልታሸ ቁርበት መስሏል።
በስመአብ ወልድ አለች ከዚህ ቀደሞ ምንሽንሽን አይታ የማታውቅ አንድ ልጅ እግር የጠበል ጠዲቅ ተጋባዥ በግርምት አፏን በእጅዋ እየሽፈነች
አይዞሽ ምነው?አታውቂውም እንዴ ምንሽንሽን?” አጠገቧ የነበሩት አሮጊት በድንጋጤ የተሸማቀቀችውን ልጅ አተኩረው እያዩ።
“አሁን ተነስቶ በድንጋይ ቢጨርስንስ?!” አለች በፍርሀት ተውጣ፡፡
“አይዞሽ የኔ ልጅ አትፍሪ ምንሽንሽ ድንጋይ ይዘሽ ብታሯሩጪው እንኳ
የሚሸሽ እንጂ የሚተናኮል አይደለም፡፡ አህያ ነው” በማለት ሊያረጋጓት ሞከሩ፡፡የአሮጊቷ አነጋገር ልጅቷን ሊያረጋጋት አልቻለም፡፡ እሷ እንደዚያ
ተጨነቀች እንጂ ምንሽንሽ እንደሆነ ዳቦ እየገመጠ በጠላ ከማወራራድ ውጪ የሚያስበው ሌላ ጉዳይ፥ አልነበረውም። ሀሣቡ በሙሉ በጠላውና በዳቦው ላይ ተጠምዷል። ሌሎቹም እንደ ዝንጀሮ ቁጢጥ ብሉ ዳቦውን
ስለሚገምጠው እብድ እያወሩ ነበር።
“ፍቅር ነው ያሳበደው ይባላል!” አለ አንዱ።
“ፍቅር ደግሞ ያሳብዳል እንዴ?” ሌላው።
“እሱን የደረሰበት ነው የሚያውቀው። ምን ማለትህ ነው? እንኳን ማሳበድ ህይወት ያስጠፋ የለም እንዴ? ሮሚዎና ጁልዬትን አላነበብክም መሰለኝ፡፡ኦቴሎ ዴዝዴሞናን የገደላትና በኋላ የሞተላት በፍቅር ምክንያት አይደለም እንዴ? ፍቅር ይዞህ አያውቅ እንደሆነ እንጂ!”
“ምንሽንሽን በጤነኛነቱ ጊዜ እናውቀዋለን የሚሉ ሰዎች ሲናገሩ የሰማሁት አንተ ከምትለው የተለየ ነው ! ብዙ ሰው የገደለ አረመኔ ነበር አሉ፡ የሟቾቹ ዘመዶች ተከታትለው ሊያገኙት ባለመቻላቸው በሴት ካጠመዱት በኋላ መድኃኒት አጠጥተው ጨርቁን ጥሎ እንዲሄድ አደረጉት
ሲባል ነው የሰማሁት”
“አቤት! አቤት! የሰው ወሬ” አለ ከወዲያ ማዶ የተቀመጠው፡፡ እሱ
ስለምንሽንሽ የስማው ሌላ ነበረ። ሰው እየፈጠረ የሚያወራው ወሬ አስደንቆት “በእናታችሁ ስው ዝም ብሎ ሲያወራ አይገርምም? እኔ የሰማሁት እናንተ ከምታወሩት ፍፁም የተለየ ነው። ሰውዬው በጣም የተማረና ፈረንጅ አገር ብዙ ዓመት የኖረ ነው አሉ፡፡ ያበደው ደግሞ በትምህርት ብዛት አንጐሉ ተቃጥሎ ነው አሉ” ሌሎቹ የተናገሩት ሀሰት፣
ሌሎቹ የሰሙት የፈጠራ ወሬ እሱ የሰማው ወሬ ግን እንከን የሌለበት
እውነተኛ ታሪክ መሆኑን ለማስረዳት ቀበጣጠረ፡ታደስ ስለ እብዱ ምንሽንሽ የተለያዩ ወሬዎችን ሰምቷል፡፡ እሱ የሰማውንም ያልሰማውንም እየ
ጨማመሩ ሲያወሩ እያዳመጠና እሱ የሚያውቀውን እውነታ በልቡ እያብሰለስለ አይ መቀስ?አይ አንበሴ? መጨረሻህ እንደዚህ ይሆን? ሲል በልቡ አወራ፡፡ የእብደቱ መንስኤ በትምርት ብዛት አለመሆኑን በሚገባ ያውቃል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን እንደሚባለው ወይ በፍቅር፣ ወይ በጭካኔ፣ወይ በመድኃኒት ወይንም ደግሞ በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች በእብደት ላይ ሌላ እብደት እየጨመረ፣ የእብደትን ሪኮርድ የሰበረ አዲስ ፍጡር ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡ ምናልባት በፍቅር ማበድ
ከዚያም መዳን፡፡ቀጥሎ በመድኃኒት ማበድ ከዚያ መዳን፡፡ ከጭካኔ ብዛት ለእብደት ተዳርጎ ጨርቅ መጣል...ማን ያውቃል ሌላውም እንደዚሁ ስለ ምንሽንሽ ቢጠየቅ ሌላ የእብደት ምክንያት ሊጨምርለት ይችላል።
“ስላምዬ አንቺስ ስለምንሽንሽ እብደት የሰማሽው የለም?” እየሳቀ
ጠየቃት፡፡
ገለል ብለው ሁለቱ ከቤቷ ጥግ ላይ ተቀምጠው ነበር፡፡ ሰላማዊትም እየሳቀች “አይ ታዴ? እንኳንስ ስለምንሽንሽ እብደት ላጠና ይቅርና ስለ ራሴ
ህይወት ስለ ራሴ እብደት የማሰላስልበት ጊዜ የለኝም”
“አንቺ ደግሞ ታሳብጃለሽ እንጂ ታብጃልሽ እንዴ ሰላም?”
“ማንን ነው ደግሞ የማሳብደው?” ጨዋታውን ወዳዋለች። የታደሰን
የፍቅር ጽናት ከአንደበቱ እንደ አዲስ መስማት ያስደስታታል።
“ፍቅር እንደሚያሳብድ እየሰማሽው መሰለኝ?”
“እና?”
“ያው ነዋ! ፍቅርሽ እኔንም እንዳያሳብደኝ ማሰብ አለብሽ”
“ያንተን ፍራልኝ እንጂ የኔ እንደማይነካህ እርግጠኛ ነኝ ታዴ። ስውን የሚያሳብድ ፍቅር የፍቅር ወንጀለኛ ነው፡፡የኔ ፍቅር ወንጀለኛ ሳይሆን ጤናማ ፍቅር ነውና አይዞህ አትፍራ” እብዱ ምንሽንሽን በሃዘኔታ እያስተዋለች ሳም አደረገችው።
ልክ ነሽ ስላም ጤናማ ፍቅር አፍቃሪና ተፈቃሪን የሚያስጨንቅ የሚያሳብድ መሆን የለበትም፡፡ጤናማ ፍቅር መተሳሰብን ኣንቺ ትብሽ አንተ ትብስን የሚፈጥር በጋብቻ አጣምሮ ቤተሰብን ለማፍራት የሚያስችል የህይወት ቅመም ነው”
“በትክክል”
“እና?”
“እናማ ያው እንዳልከው ነዋ ታዴ!”
“ያንቺ ሃሳብ ምንድነው ሰላም? የኔን ዳር ዳር እያልኩ ስገልፅልሽ ኖሬአለሁ። የኔ ብቻውን ደግሞ ውጤት ሊኖረው ስለማይችል በአንድ እጅ ማጨብጨብ እንዳይሆን እሰጋለሁ”
“ታዴ ዛሬ እኮ ፀበል እንድትቀምስ እንጂ ሚስት እንድትለምን አልተጠራህም” የተለመደውን የከንፈር ካሳ ልትሰጠው አንገቷን ቀና ካደረገች በኋላ መቅበጥ መሰላትና እያማራት ተወችው፡፡ ይህንን የሚጨዋወቱት
ሰው እንዳይሰማቸው አፍ ለአፍ ገጥመው ነበር፡፡
“የምጠጣው ጠላ አስካሪ ፈሳሽ ሳይሆን ፈዋሽ ፀበል እንዲሆንልኝ በዛሬዋ ዕለት ሃሳቤን ልትደግፊ ምኞቴ ምኞትሽ ሊሆን በእትዬ ወደሬ የማርያም ፀበል ፍቅራችን እንድትለመልምና አንድ ሆነን እንድንጠመቅ ፍላጐትህ
ፍላጐቴ ነው በይና ቃል ግቢልኝ...”
“ተነስ ወደ ጓዳ እንግባ!” እጁን ሳብ አድርጋ አስነሳችው፡፡ አነጋገሩ ልቧንነካው። የሆነ ስሜት ተሰማት፡፡እንዲህ እንደዋዛ እሱ ደጋግሞ እየጠየቃት እሷ እየሳቀች ስታሳልፈው እውነቱ ሁሉ ቀልድ ይሆንና እምቢ ካለችኝ ሁለተኛ አልጠይቃትም ይልና በእማማ ወደሬ የማርያም ፀበል ስትይ የልብሽን ግለጭልኝ እያለ ሲማጠናት አይሆንም ብትለው በዚያው አኩርፎ እስከ መጨረሻው የሚሄድ መሰላትና ሃሳቧን ልትገልፅለት ምኞቷን ልታስረዳው ማንም ሰው ወደሌለበት ወደ ጓዳዋ ውስጥ ይዛው ገባች።ቀና ብላ

👍5
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ከምሽቱ አምስት ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ከአስፋልቱ መንገድ ፈንጠር ብሎ
ከአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ መርካቶ በሚወስደው መንገድ ላይ በስተቀኝ በኩል እርስ በርሳቸው ተደጋግፈው
ከቆሙት የጭቃ ቤቶች መካከል በአንደኛዋ ዳንኪራው ጦፏል፡፡
ቀን ቀን ቡና ቤት ውስጥ በገንዘብ ተቀባይነት በምትሰራውና ማታ ማታ ደግሞ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ የአልኮል መጠጦች እየሸጠች እንግዶቿን
በምታስተናግደው በማህሌት ቤት እየተደነከረ፣ እየተጨፈረ ነው።
ማህሌት በዚያ አጭር ቁመቷ ላይ የለበሰችው ጮማ ተከምሮ በድንገት ስትታይ የምትገላበጥ እንጂ የምትራመድ መሆኗ የሚያጠራጥር ቀይ አፍንጫ ጎራዳ ሴት ናት። ማህሌት ወደዚያ ስትሄድ ወደዚህ የመጣች እየመሰላቸው ቁጭ ብለው የጠበቋት ጓደኞቿን ብዙ ቀን ጉድ
ያደረገች ጉደኛ ሰው ነች።በዚች ጠባብ ቤቷ ውስጥ የመሽኛ ግብዣ የተደረገላቸው ሰዎች ተሸኝተዋል። በመሥሪያ ቤት እድገት ያገኙ ሠራተኞች ማህሌት ቤት እያሉ እየተቀጣጠሩ ፅዋቸውን አንስተዋል፡፡ ለእንኳን
ደህና መጣችሁ እንግዶች ተጋብዘዋል፡፡ የተለያዩ የግብዣ ሥነ ሥርዓቶች በተለያዩ ጊዜያትና አጋጣሚዎች ተካሂደዋል፡፡ ማለፊያ ገንዘብ እስከተከፈላት ድረስ ማህሌት የሚያምሩ ጥርሶቿን ፍልቅቅ፣ ትሙክ፣
ትሙክ የሚሉ ጉንጮቿን ስርጉድ እያደረገች በጥሩ አስተናጋጅነት እንግዶቿን አስደስታ ሽኝታበታለች። ዛሬ በታደሰ አስተባባሪነት የመሸኛ ይሁን የመዝናኛ ውሉ ያልታወቀ ግብዣ እንድታዘጋጅ ተነግሯት አልኮል በያይነቱ ቀርቦ ጮማ እየተቆረጠ ሊጠጣ... ሊዘለል... ሊጨፈር... የጠየቀችው ሞቅ ያለ ክፍያ ተከፍሏታል። በዚህ የግብዣ ሥነ ሥርዓት ላይ የሚገኙት አምስት ወንዶች ናቸው።
ሙዚቃው ጦፏል!ተጋባዦቹ ከሙቀቱና ከሙዚቃው ጋር እንደ ውሃ የሚጨልጡት አልኮል ተጨምሮበት መስከር ብቻ ሳይሆን እብደት ቀረሽ ዝላይ እየዘለሉ ናቸው። በስካር ላይ ስካር የሚጨምረው የሚያብረከርከው ሙዚቃ ደግሞ በረጅሙ ተለቋል...
አንቺ ከቶ ግድ የለሽም፣
ስለፍቅር አልገባሽም፣
ሁሉን ነገር እረስተሽው፣
ችላ ብለሽ ስለተውሽው፣
ቻልኩት ፍቅርን... ለብቻዬ፣
ስለዚህ ትቼሻለሁ ይቅር፣
ስላልገባሽ የፍቅር ሚስጥር፣
ትቼሻለሁ አትምጪ ይቅር፣
እችክ፣ እችክ፣ እችክ፣ እችክ፣እችክ.....
ወገብ ብጥስ ቅንጥስ ይላል፡፡ አንዳንዱ ደናሽ ሳይሆን ዳንግላሳ የሚመታ ፈረስ ይመስላል፡፡ ማህሌት የወንዶቹ ጭፈራና ዝላይ ፈንቅሏት እዚያ እመሀላቸው ገብታ እንደ ግንድ እየተገላበጠች ነው።መቼም ከጭንቅላት ቀጥሎ ያለው የሰው ልጅ አካል በማህሌት ዘንድ አለ ለማለት የሚያስደፍር አልነበረም፡፡ ያቺኑ አንገት ተብዬ እየወዘወዘች ከትከሻዋ እየ
ተርገፈገፈች እያሳበደቻቸው ነው። በአምስት ወንዶች መካከል የተገኘች ብርቅዬ... ሞናሊዛ ሆናላቸው ደብለል. ደብለል.. ዞር ዞር...ደግሞ ከትከሻዋ መታ መታ ወረድ... ቀና... እያለች ልባቸውን እያጠፋችላቸው ነው፡፡
ከታደሰ በስተቀር ሌሎቹ በደስታ ብዛት የሚሆኑትን አሳጥቷቸዋል።
አራቱም በየልባቸው ማህሌትን ተመኝተዋታል፡፡ ምን ችግር አለ? የራሳቸውን ስሜት የሚያረኩበት ብቻ ሳይሆን የሌላ ሰው ስሜት ጭምር የሚማርኩበት ረብጣ ገንዘብ ተይዟል። በዚሁ መካከል ግን ሰዓቱ እየበረረ ነበር። ማህሌት ወደ ታደሰ ጆሮ ጠጋ አለችና.....
“ታደስ እስከ ስድስት ሰዓት ብቻ አልነበረም እንዴ የተነጋገርነው? ሩብ ጉዳይ ሆነ እኮ! ሁኔታችሁን ስመለከተው ሙሉ ሌሊት የሚበቃችሁ አልመስለኝም” አለችው።ታደሰ እጇን ሳብ አደረገና
ወደ ጓዳዋ ውስጥ ይዟት ገባ።
“ማህሌት ከስድስት ሰዓት አንድ ደቂቃ ቢያልፍ የተነጋገርንበትን ዋጋበእጥፍ እከፍልሻለሁ፡፡ በዚህ በኩል በፍፁም ሃሳብ አይግባሽ፡፡ በኔ ተይው። ሰዓት አልፏል ብለሽ ጨዋታሽን እንዳትቀንሺባቸው ፊት እንዳትነሻቸው፡፡ እንደ ልባቸው ይጨፍሩ ይዝለሉ። ዛሬ የመዝለያ የመጨፈሪያ ቀናቸው ስለሆነ ሌላ ንግግር ተናግረሽ እንዳታስቀይሚያቸው”
ለስለስ ደግሞም ኮስተር ባለ አነጋገር አስጠነቃቃት። ልቧ ተረጋጋና ተያይዘው ወደ ጭፈራው መሃል ገቡ... አንዱ በአንዱ ላይ እየወጣ እየቦረቀ ለጤናችን እያለ መለኪያ ለመለኪያ እያጋጨ ተዝናና። ለሁሉም ነገር
ድፍረትና ወኔ የሚስጠውን አልኮል በብዛት ወስዶ ሰውነቱን በሚገባ
ወደ ሁለተኛዋ ክፍል አሟሟቀ፡፡ ታደሰ ወጣ ገባ እያለ አካባቢውን ያጠናል።
“የሙዚቃ ድምፅ ይቀነስ... ጩኸት ቀንሱ” እያለ የአካባቢው ነዋሪ እንዳይረበሽ ማስጠንቀቂያ እየስጠ ብቅ ጥልቅ ይላል።በዚያ ሀድራው በሚጨስበት፣ሙቀቱ ጨፋሪዎቹን በትኩስ ላብ በሚዘፍቅበት፣ ሙዚቃው
ልብ እየነጠቀ እንደ ጋላቢ ውሃ ሽቅብ በሚያዘልልበት፣ አልኮል እንደ ፏፏቴ በሚፈስበት፣ የሚገኘው የወደፊት ብሩህ ተስፋ የሚቆጠረው የገንዘብ ብዛት በሚያጓጓበት አስደሳች ዓለም ውስጥ እያሉ ልክ ስድስት
ሰዓት አናቱ ላይ ሲሆን “እጅ ወደ ላይ!” የሚል ድምፅ ሲሰማና በሩ ሲበረገድ አንድ ሆነ፡፡
ማህሌት ከድንጋጤዋ የተነሳ ያ ዝሆን የሚያክለው ግዙፍ ሰውነቷ እንደ ባሉን ቀላላትና እንደ ህፃን ልጅ ሮጣ አልጋዋ ስር ገብታ ተደበቀች።ከሁሉ ቀድሞ እጁን ያነሳው ታደሰ ነበር።
አለቃቸው እጅ መስጠቱን ሲያስተውሉ ሁሉም ተስፋ ቆረጡና እጆቻቸውን ወደ ሰማይ ሰቀሉ።በየኪሳቸውና በጉያቸው የደበቋቸውን ሰንጢዎች፣ ስንስለቶች፣ መሰርሰሪያ ለመሽሽግ ወይንም ለመወርወር ፋታ ኣላገኙም ነበር፡፡ ፖሊሶቹ እጅግ ቅልጥፍና በተሞላበት መንገድ ኪሶቻቸውን ፈተሹና መሳሪያዎቹን በቁጥጥር ስር አዋሉ፡፡ ብዛት ያለው ገንዘብና
ከታደሰ ኪስ የተገኘው አንድ ሽጉጥም በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደረገ፡፡በዚህ ሁሉ ትርምስ ውስጥ ግን ያ ሽለምጥማጥ አበራ በጓዳ በር በኩል ተሽሎክሉኮ በር በርግዶ አጥር ጥሶ አጥር ዘሎ ሲያመልጥ ከታደስ ጋር አራቱ ተያዙ።
ፖሊሶቹ ወሮበሎቹን በቁጥጥር ሥር በማዋላቸው ምክንያት ዛሬ በሌሊት ቤቱን ሰብረው በመግባት ህይወቱን ለማጥፋት ቀብድ የተቀበሉበት የቡና ነጋዴው የአደም ሁሴን ህይወት ተረፈች። አስር ሺህ ብር ከአደም ላይ
የተበደረው ኡስማን አብደላ የተበደረውን ገንዘብ ለመመለስ ፈቃደኛ ሆኖ አልተገኘም። ጫማው ላይ ወድቆ ምሎ ተገዘቶ የተበደረውን ገንዘብ ከለከለው።
"ኡስማን ገንዘቡን ስትቀበለኝ የነበረህን ሁኔታ ታስታውሳለህ አይደለም?
ዘመድ አዝማድ ልከህ ደጅ ጠንተህ ከነወለዱ ለመክፈል ተስማምተህ ነበር። የኔ ፍላጎት ወለዱ ቀርቶ ዋናውን ብቻ እንድትመልስልኝ ነው፡፡
ከገባኸው ውለታ ውጪ አራት ወር ከአስራ አምስት ቀን ጠብቄሃለሁ።
እምቢ የምትለኝ ከሆነ ግን በህግ ልጠይቅህ እገደዳለሁ” ሲል አስጠንቅ ቆት ነበር።
ኡስማን የአደምን ማስጠንቀቂያ ከሰማ በኋላ አደም ገንዘቡን ስታበድረኝ የጽሁፍም ሆነ የሰው ማስረጃ እንዳለህ አውቃለሁ። እኔም ገንዘብህን ላለ
መስጠት ሳይሆን ሀጃዬ ስላልሞላልኝ ነው። እባክህ ትንሽ ጊዜ ስጠኝ?"በማለት ዋሽቶት ነበር። ጊዜ ስጠኝ ያለው ዕዳውን ለመክፈል ሳይሆን ነፍሰ ገዳዮችን በሁለት ሺህ ብር ገዝቶ አደምን ለማስገደልና ስምንት ሺህ
ብር ለማትረፍ ነበር፡፡ በዚሁ መሰረት እነኝህ ኡስማን የገዛቸው የወሮበላ ቡድን አባላት ለወንጀል መፈፀሚያ ከያዟቸው መሳሪያዎች በተጨማሪ ወንጀሉን ለመፈፀም የተቀበሉት ቀብድ ታደስ በሰጠው መረጃ መሠረት በቡድኑ አባል በጥጋቡ ኪስ ተገኘ፡፡ ታደስም ከወሮበሎቹ ጋር አብሮ እየተነዳ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደ፡፡

#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ጉለሌ አካባቢ ታደሰ የተከራያት ሁለት ክፍል ቤት ለብዙ ጊዜ ተዘግታ የከረመች ሸረሪት ያደራባትና ግድግዳዋ የተላላጠ ነበር፡፡ አሁን ግን ቀለም ተቀብታ ሲረግጡት ቡን... ይል የነበረ ጣውላዋ በሰም ታሽቶ አብረቅርቃለች፡፡ ጠረጴዛና ወንበሮች ተኮልኩለዋል፡፡ ጠጅና ጠላ በጠርሙስ ተሞልቶ ከላይ በነጭ ወረቀት በቄንጥ ተሸፍኖ በየጠረጴዛው ላይ ተደርድራል። ሸክላ ሳህኖች በየጠርሙሶቹ መሀል መደዳውን ተቀምጠዋል፡፡
የሸረሪቶችና የአይጦች መፈንጫ ሆና የከረመችው ጎጆ ሰርገኞች የሚታደሙባት፣ ዋንጫዎቻቸውን እያጋጩ የሚጨፍሩባት፣ ሙሽሮች ደግሞ የፍቅር አክርማቸውን የሚቀጩባት ጫጉላ ቤት ለመሆን ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡ ልዩ ሆና ደምቃለች፡፡ አዎን ታደሰ ሰላማዊትን የሚያገባበት ቀን፡፡ ዕለተ እሁድ.…የዛሬዎቹ ሙሽሮች በማዘጋጃ ቤት በሽማግሌ
ዎች ፊት በወረቀት ፊርማ ሳይሆን ተፈቃቅደውና ተማምነው ሊቆራኙ
የተዘጋጁበት ቀን ነው፡፡
ዛሬ ሰላማዊት ከእሥር ቤት ወጥታ ወደ ነፃ ህይወት ለመቀላቀል ከዚያ ስቃይ ከበዛበት የሴተኛ አዳሪነት ህይወት ተላቃ ከምትወደው ሰው ጋር አብራ ለመኖር እምነትን ብቻ ውል አድርጋ ፍቅርን ብቻ ሰማንያ አድርጋ አዲስ ህይወት ለመጀመር የተዘጋጀችበት ቀን ነው።
እማማ ወደሬ ዕድለኛ ሆኑ። የወይዘሮ ስመኝን እጅ መድኃኒት አድርጎላቸው ከሞት ተረፉና በልባቸው ስቀው፣ አጨብጭበው መርቀው ያስተሳሰሯቸው ልጆቻቸውን ለመዳር በቁ፡፡ እንደተመኙት በጥርሶቻቸው
እየሳቁ በእጆቻቸው እያጨበጨቡና ልባቸው በደስታ እየጨፈረች በአዲስ ነጭ የአገር ባህል ልብስ አጊጠው በእናትነት ወግ ሙሽሪትን ለሙሽራው ለማስረከብ ጉድ ጉድ ለማለት ታደሉ፡፡ ሰላማዊት አምራለች። ተውባለች፡፡ የውቦች ውብ! የቆንጆዎች ቆንጆ! ሆናለች። ባማረ አለባበስ አጊጣ ፀጉሯን በወጉ ተሰርታ ዐይኖቿ ኩል ተኩለው እንደ ጽጌረዳ አበባ ፈክታላች። ሸርሙጣ ከሚል ወራዳ ስም ተላቃ ሙሽሪት የመባል ወግ ማዕግረ ደርሷታል፡፡ የተለያዩ ወንዶችን በወሲብ እያስተናገደች መኖር ከጀመረች ወዲህ ወደር የሌለው ደስታ ያገኘችበትና እንደ አዲስ የተወለደችበት ቀን
ሆኖ የተሰማት ገና ዛሬ ነው። ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ ከምትወደው ሰው ጋር እስከመጨረሻው በፍቅርና በደስታ ልትኖር የእገሌ ሚስት ባለ ትዳር ተብላ ልትጠራ ነው፡፡
"ሰላም እንግዲህ ጣጣችሁን ቶሎ ቶሎ በሉና ጨርሱ። የመምጫ ሰዓታቸው እየደረሰ ነው” አሉ ወይዘሮ ወደሬ ተፍ ተፍ እያሉና የምትኳኳላውን ልጅ በፍቅር እየተመለከቱ።
ዛሬ ሰላማዊትን በማስዋብና አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ በኩል ሙሉ ሃላፊነቱን የወሰደችው ጽጌ ነች።ያቺ
ገበያዋን የዘጋችባት ልጅ
ያቺ ለሰፈሩ ሴተኛ አዳሪዎች ምላስ አሳልፋ የሰጠቻት ልጅ ሰፈሩን እስከመጨረሻው ጥላላት ልትሄድላት ነውና ከዚያ በፊት የነበረውን ቂም ከዚያ በፊት የነበረውን የጥላቻ ስሜት ፍፁም እርግፍ አድርጋ ረስታ እንደ ታላቅ እህት እየተንከባከበች የውበቷን እንከን እየነቀሰች አሳምራ
እያዘጋጀቻት ነው።
“እሺ እማማ ጨርሰናል እኮ!" አለች ጽጌ እየተጣደፈች፡፡ ወይዘሮ ወደሬ የዛሬ ሁኔታቸው መቼም ለጉድ ነው። ወልደው አሳድገው ለትዳር እንዳበቋት ልጃገረድ ሰላማዊትን አሥር ጊዜ እየተመለከቱ ውበቷን እያደነቁ
ሁለመናቸው በደስታ ስቋል። የፊታቸው ፈገግታ ከእርጅናቸው ውስጥ ደብዝዞ ብቅ ባለው የልጅነት ውበታቸው ምክንያት ለወትሮው መወላገዱ ከሩቁ ይታይ የነበረው ጥርሳቸውን ሁሉ አሳምሮታል። ሰላማዊት
ጣጣዋን ጨራረሰች።ዝግጁ ሙሽሪት! ሽቅርቅር፣ ዝንጥ አለች። የዛሬው የሰላማዊት ሙሽርነት በሚስጥር ቢያዝም አልፎ አልፎ ማፈትለኩ አልቀረም ነበር፡፡ ጽጌ ለጓደኞቿ ሹክ... ብላቸው ውስጥ ውስጡን ወሬው ተዳርሶ ለአንዳንዶቹ የቡና ማጣጫ ሆኖላቸዋል።
በሰላማዊት ጉዳይ የተነጋገሩባት ሴተኛ አዳሪዎቹ ብቻ አልነበሩም፡፡
ከእማማ ወደሬ መሸታ ቤት ፊት ለፊት ባለው ትልቅ የመኖሪያ ግቢ
ውስጥ የሚኖሩት የነጋዴው የአቶ ዘላለም ልጅ ተማሪዋ ምንተስኖትም የዚሁ የሃሜት ሱሰኞች በሽታ ለክፏት የውጪውን በር ከፍታ ጓደኛዋ ሊባኖን ስታስገባት ሰላማዊትን እያማችላት ነበር፡፡
“ኡ. ኡ. ቴ! የሸርሙጣ ሙሽራ አይተንም ሰምተንም አናውቅ!” ከንፈሯን ወደ ጎን እየሽረመመች፡፡
“በቀደም የነገርሽኝን ነው አይደል? እውነት ልታገባ ነው እንዴ?” አለች
ሊባኖስ ወደ ግቢው እየዘለቀች።
"ከየት የመጣ ፋራ ነው በናትሽ ? የጠላ ቤት ሸርሙጣ ሚስቱ ለማድረግ አበሳውን የሚያይ አይገርምም? አ.ሃ..ሃ..ሃ.ሃ." እንጥሏ እስከሚታይ ድረስ አፏን ከፍታ ሳቀች።
"ፍቅር ከያዘው ምን ታደርጊዋለሽ? እንኳን ሴተኛ አዳሪ ሰው ከወደደ
ቆማጣና እውር ማግባቱ ይቀራል ?” አለች ሊባኖስ፡
“ከሽርሙጣ ቆማጣ ይሻላል።ለጊዜው መደበሪያ ልታደርገው ካልሆነ በስተቀር አብራው ትኖራለች የሚል እምነትም የለኝም" “እንደሱ ብለሽ ባትደምድሚ ይሻላል። አብዛኛዎቹ ሴተኛ አዳሪዎች የችግር ማእበል ገፍትሮ ዳር ላይ ሲጥላቸውና ዙሪያው ገደል ሲሆንባቸው እንጂ ፈልገው የገቡበት አይደለም፡፡
አጋጣሚውን ካገኙ ቤተሰብ
መስርተው በታማኝነት ለመኖር ምንም የሚያግዳቸው ነገር ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ ቅድስት እንደነገረችኝ ከሆነ ደግሞ ሰላማዊት በጣም የምታሳዝን ልጅ ናት። ወላጆቿ የሞቱባት፣ምን የመሰለ ወንድሟን ማጅራት
መቺዎች ደብድበው ያለረዳት ያስቀሯትና ትምህርቷን አቋርጣ በዚህ ህይወት ውስጥ ለመግባት የተገደደች አሳዛኝ ልጅ መሆኗን አጫውታኛለች። እንደኔ እሷን ያገኘ ባል የታደለ ነው" ስትል ሊባኖስ ምንተስኖትን ተቃወመቻት።
"ምነው ጠበቃ ሆንሽላት በናትሽ ? እኔ በበኩሌ በየቀኑ አዳዲስ ባሎችን እያገባችና ገላዋን እየቸረቸረች የኖረች ሴት ስፊ ልማዷን እርግፍ አድርጋ
በጠባብ ጐጆ ውስጥ ዲቃላዋን እያጫወተች መኖርን በቀላሉ ትለምደዋ ለች ብዬ አላስብም”
“ምን እያልሽ ነው ምንተስኖት? በአልኮል የተሟሽ የሰካራም አፍ ጠረን እንደ ሰንደል እየታጠኑ የአባለዘር በሽታን በጅምላና በችርቻሮ ከሚያከፋፍሉ ዝሙተኞች ጋር ለግብረ ሥጋ መውደቅና መነሳት ኑሮ መሆኑ
ነው እንዴ? ሰፊ ልማድ የምትይውስ ከፍላጐት ውጪ ስሜት አልባ ገላን እየቸረቸሩ ሳንቲም በመለቃቀም የሚገኝ ነው እንዴ? በየቀኑ መኳኳሉና
አዳዲስ ልብስ መቀያየሩ ትርጉም ያለው መሰለሽ? ውጫዊ መብለጭለጭ እኮ ውስጣዊ መብለጭለጭን አያመጣም፡፡ ቢከፍቱት ተልባ ነው፡፡ የምትወጂውና የሚወድሽ የትዳር ጓደኛ ስታገኚ፣ተስመው የማይጠገቡ ህፃናት እናት ሆነሽ መኖር ስትጀምሪ ብቻ ነው ኑሮ ኑሮ የሚሆነው። ትዳሬን ሚስቴን ልጆቼን የሚል አሳቢ ባል ካገኘሽ ደግሞ ከዚያ በላይ ደስታ ከዚያ
በላይ እርካታ ይኖራል ብዬ አላስብም”
“አንቺ እንደምትይው አይነት ባል እንደዚህ በቀላሉ የሚገኝ ቢሆን እሰየው ነበር፡፡ ትዳሬን፣ ልጆቼን የሚልና ከራሱ በፊት ለትዳሩና ለልጆቹ የሚያስብ ወንድ ደግሞ ሚስት ለማግባት የጠላ ቤት ሽርሙጣን የመጀመሪያ
ምርጫው ያደርጋል የሚል እምነት የለኝም” አለች ምንተስኖት ባለመሸነፍ ስሜት ።

👍2❤1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....አሥር አለቃ ንጉሤ ብድግ
አለ፡፡ በቤቱ ውስጥ ያሉቱ በሙሉ ዐይኖቻቸውን ተከሉበት።
“እህህ..እህ... እናቶቼ ወንድሞቼና እህቶቼ..” ጉሮሮውን አፀዳና ቀጠለ..
“መቼም የዛሬው ደስታ የሁለቱ ሙሽሮቻችን ብቻ ሳይሆን የኛ የሁላችን በዚች ቤት ውስጥ ተሰባስበን ፅዋችንን ያነሳንላቸው ተጋባዦች ጭምር ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም። እንደ ባህላችን ሰፊ ዝግጅት ተደርጎ ጠጁ ተጥሎ ጠላው ተጠምቆ ሻኛ እየተቆረጠ ዘመድ አዝማዱ ያለገደብ እየበላ፣እየጠጣ፣ እየጨፈረ ሃይሎጋ እያለ ጋብቻ ሲፈፀም ለተመልካች ደስ ይላል፡፡ ይህቺ የኛዋ ሠርግ ግን በዚህ በሚቆረጠው ጮማ በሚጣው ጠጅና በወገን ብዛት ደምቆ በሚፈፀመው የጋብቻ ደንብ ውስጥ የምትጣፍና ከቁጥር የምትገባ አይደለችም፡፡ በእውነት ነው የምላችሁ ይቺ በእኛ ሃያ በማንሞላው ሠርገኞች የታደመችው ሠርግ ግን እልፍ
አእላፍ ሠርገኞች የጨፈሩበትን ጋብቻ የምታስንቅበት አንድ ትልቅ ምክንያት አላት። ሁለቱ ልጆቻችን ወይንም ደግሞ ወንድማችን ታደሰና እህታችን ሰላማዊት ያለምንም ፊርማና ያለአንዳች የሃብት ድርድር ፍቅርን ብቻ ዋስትና ጠርተው ፍቅርን ብቻ የጋራ ሃብት አድርገው ትዳር ለመመስረት መወሰናቸው በሁለቱም ልብ ውስጥ ያለው የመተማመንና የመፈቃቀድ ደረጃ ምን ያክል ከፍተኛ እንደሆነ የሚያረጋግጥልን ነው።
በፊርማ የሚፈፀመውን ትዳር ለመቃወም አይደለም። ፊርማ
በትዳር ላይ ሊፈፀም የሚችለውን ወንጀል ለመከላከልም ሆነ በተጋቢዎቹ መካከል በራስ መተማመን እንዲኖር የሚያበረክተው ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ይሁን እንጂ የጋብቻ ውል የእስር ሠንሠለት ሆኖ የሚታያቸው ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ከፍቅር በኋላ ውሎ እያደር በሚመጣ አዲስ ስሜት የተነሳ የጋብቻ ውል መፈፀማቸው ከባድ ስህተት ሆኖ የሚታያቸው፣ ትዳር መመስረታቸው የሚያማርራቸውና
ያንን የሚማረሩበትን የጋብቻ ሠንሠለት በጣጥሰው በመጣል በአስቸኳይ ለመለያየት በየፍርድ ቤቱ የሚጓተቱ በርካቶች ናቸው። ለዘላቂ ትዳር ዋናው ቁም ነገር እውነተኛ ፍቅር እንጂ የጋብቻ ውል አይደለም። በከፍተኛ ወጪ ሠርጉ ተደግሶ በሺህ አጀብ ጋብቻው ከተፈፀመ በኋላ በሁለተኛው እና በሦስተኛው ወር ላይ ለፍቺና ለንብረት ክፍፍል በየፍርድ
ቤቱ መሯሯጥ የተለመደ ነው፡፡ ቁም ነገሩ የተጋባዡ ቁጥርና የግብዣው ብዛት ሳይሆን የተጋቢዎቹ ፅኑ ፍላጐትና እምነት ነው። ለእኔ እንደሚገባኝና እንደማምነውም ከሆነ በሁለቱ የዛሬዎቹ ሙሽሮቻችን መካከል
ያለው ሃብት ንብረት ሲኖር አንድና ብቸኛ የሆነው " ፍቅር" ብቻ ነው።
ፍቅር ሳይኖር የሚፈፀም ጋብቻ ከጥሩ ቪላ ቤት ከጥሩ መኪና በአጠቃላይ ከጥሩ ገንዘብ ጋር የሚደረግ ጋብቻ እንጂ ንብረቱን በሚያፈሩት የትዳር ጓደኛሞች መካከል የሚፈፀም ስላልሆነ አንድ ቀን ያ ገንዘብ እንደ
ጉም በንኖ ሲጠፋ የውሽቱ ፍቅርም አብሮ ሰናኝና ጠፊ ይሆናል። ስለዚህ በታደስና በሰላማዊት መካከል ያለው እውነተኛ ፍቅር አብቦ ከዚህ የበለጠ ሆነው ልጅ ወልደው ለመሳም በቅተው አብረው ጥረው ግረው ንብረት ሲያበጁ ደግሞ እምነት አለኝ አስር ልጆች ወልደውም ቢሆን እንኳ
በዛሬዋ እለት አልተደረገም ብለው ቅር የተሰኙበት ነገር ቢኖር በዚያን
ጊዜ እንደ አዲስ ተጋብተው እንደ አዲስ የሙሽራ ልብስ ለብሰው ሰንጋው ተጥሎ ጮማው እየተቆረጠ በሺህ አጃቢ ታጅበው እልል እየተባለላቸው
ጋብቻቸውን በድጋሜ ሊፈፅሙ እንደሚችሉ አልጠራጠርም፡፡ እኛም ዕድለኞች ከሆንና እድሜም ከሰጠን ያንን ደስታ ያንን አለም ለማየት እንበቃ ይሆናል። በእውነት ነው የምላችሁ ይህንን የምናገረው ስሜታዊ ሆኜ ሳይሆን ከዚህ በፊት ያየሁት እና ያጋጠመኝ ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡ በድህነትና በችግር ላይ ሆነው ትዳር ከመሰረቱ በኋላ ሀብት አግኝተው ወልደው
ከብደው በልጆቻቸው ሚዜነት እየታጀቡ እንደ አዲስ ሰርጋቸውን የሰረጉ ብዙ ሰዎች መኖራቸውን ስለማውቅ ነው። የዛሬዎቹ ሙሽሮቻችን የተገናኙበትና ለጋብቻ የተጫጩበት አጋጣሚ ብዙዎች የማይደፍሩት ሆኖ
ሳለ እነሱ ግን ደፍረው ገብተዋልና ዛሬ የጋብቻቸው ቀን ብቻ ሳይሆን
የህይወታቸው አዲስ ምእራፍ የሚጀመርበት ቀን ጭምር ነው ብዬ አስባለሁ። በዚህ አዲስ የህይወት ምእራፍ ውስጥ አዲስ የኑሮ ትግል ጀምረው በድል በመወጣት ወልደውና ከብደው የምናይበት ጊዜ ሩቅ ይሆናል ብዬ አልገምትም፡፡ የዛሬዋን ጋብቻ እግዚአብሔር የአብርሃምና
የሳራ እንዲያደርግላቸው ቤት ንብረት ይዘው እንዲያስጨፍሩን ምኞቴን እየገለፅኩ መልካም የትዳር ዘመን ይሁንላቸው እላለሁ” አነጋገሩ የብዙዎችን ልብ የነካ በመሆኑ ጭብጨባው ቶሎ አላበቃም ነበር፡፡ በአስር አለቃ
ንግግር አንጀታቸው ቅቤ የጠጣው እማማ ወደሬ ትንሽ ንግግር ለማስማት፣ ልባቸው ላይ የምትንቀለቀል የደስታ ስሜታቸውን በቃላት ለመግለፅ ፈለጉ፡፡ በያዟት አሮጌ መሀረብ ከንፈሮቻቸውን አብስ አብስ አደረጉና የተወለጋገዱ ጥርሶቻቸውን ብልጭ አደረጉ።
እኔም ደስ ብሎኛል! አንጀቴ ቅቤ ጠጥቷል፡፡ ሞት ቀድሞኝ ቢሆን ኖሮ ይህን ዓለም ይህን ሲሳይ አላየውም ነበር፡፡ እመቤቴ ማርያም ጠሎቴን ሰምታ ለዚህ ታበቃችኝ ከእንግዲህ በኋላ ብሞት እንኳ ሞትኩ አይባልም፡፡ ልጅ ወልጄ ለመዳር ማህፀኔ ባይታደልም በስተርጅና በመሞቻ
ጋዜዬ ምስጋና ይግባትና እመቤቴም ሰላማዊትን የመሰለች ልጅ ሰጥታኝ ለዚህ ስትበቃ እንዳይ ስለረዳችኝ ደስታዬን የምገልጥበት ቋንቋ የለኝም።
እንደ ማር እንደ ወተት ያጣፍጣችሁ። ፍቅራችሁ ፍቅር ይሁን። አይለያችሁ። የምታስቀኑ ያድርጋችሁ። በክፉ የሚያያችሁን ዐይኑን ይያዝላችሁ" ብለው መረቁና ተንፈስ አሉ። ሙሽሮቹ እማማ ወደሬ ሲናገሩ
ልባቸው በደስታ ተሸበረ። ዐይኖቻቸው እምባ አቀረሩ... የደስታ እምባ...
እየተበላ እየተጠጣ እስክስታ እየወረዱ ሲደሰቱ ሲጨፍሩ ቆይተው መሸትሸት ሲል ሙሽሪት በአጃቢዎቿ በታደሰና በጓደኞቹ ታጅባ በአንድ ታክሲ ውስጥ ታጭቀው ወደ ታደሰ ቤት በረሩ...
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አዲሷ ሙሽራ ሰላማዊት አዲሱን ህይወት በመላመድ ላይ ነች፡፡ ከታደስ እውነተኛ ፍቅርና መተሳሰብ ጋር ከዚያ አስቃቂ ኑሮ ከእስር ተላቃ የነፃ ህይወት አየር በመተንፈስ ላይ ነች፡፡ ከውስጥም ከውጭም አማረች፡፡ደመቀች። ታደስ በደላላነት ሥራው ከሚያገኘው ገንዘብ በተጨማሪ ነጋዴዎች የቀናቸው እለት በተደሰቱበት ጊዜ የሚስጡት ድጉማ ላሌላ ባይተርፍም ሁለቱን በደስታ ሊያኖራቸው የሚችል ነው፡፡
የፋሲካ በዓል ደርሷል። ህዝቡ በሁሉም መስክ ለዝግጅቱ መሯሯጥ ጀምሯል፡፡ ዓመቱን ሙሉ ሽሮ ያረረበት ለፋሲካ በዓል በቅቤ ያበደችውን ዶሮ ሰርቶ ከጐረቤቱ ከጓደኛው እንዳያንስ ራሱን እየበደለ በቋጠራት ሳንቲም ቢቻል በግ ካልቻለ ደግሞ የቅርጫ ስጋ ተቀራጭቶ ይገባል።
ልጆቹ ሚስቱ የጐረቤት ወጥ እንዳይሽታቸው የሌላ ሰው ቤት እንዳይቀላውጡ የበይ ተመልካች እንዳይሆኑ.. በፋሲካ ሰሞን ሁሉ ነገር ዋጋው እሳት ቢሆንም የአቅሙን ያክል ይዘጋጃል። ለፋሲካ የዶሮ ላባው ይበላ
ይመስል ገብስማ፣ ወሰራ፣ ልበወርቅ፣ ቀይ፣ነጭ.እየተባለ ዋጋው ይሰቀላል። እንደዚያም ሆኖ ግን ሁሉም ጥርሱን ነክሶ ይገዛታል እንጂ አይቀርም፡፡ ምን ዶሮ ብቻ? በበአል ሰሞን ምን የማይወደድ ነገር አለ?

👍4
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ባሏ ታደስ የሰውን የማይመኝ ከሰው የማይጠብቅ በራሱ የሚተማመን ኩሩ ባል መሆኑን ብቻ ነው፡፡ እንደዚህ ዛሬ በአይኗ እንዳየችውና ከአንደበቱ እንደምትሰማው የተበደለውን፣ የቆሰለውንና የደማውን ሰላማዊ
ህዝብ ለመካስ ቆርጦ የተነሳ ስለመሆኑ ምልክቱን ያየችው ገና ዛሬ ነው።
ታደሰ ብዙውን ጊዜ ይህንን ጉዳይ ሊገልጽላት እየፈለገ ህይወትህ አደጋ ላይ ትወድቃለች ይቅርብህ” ትለኛለች በሚል ሥጋት ነው የደበቃት፡፡ዛሬ ግን አጋጣሚው በተወሰነ መልኩ ራሱን እንዲያስተዋውቅ አደረገው።
“ይህ ሰው ምናልባት እኔ ሳላውቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ሰባኪ ይሆን እንዴ?"አለች በልቧ። መደበኛ ስራው ድለላ መሆኑን ተጠራጠረች።
“ታዴ ከድለላ ሌላ የምትሰራው ስራ አለ እንዴ? ድለላ አንዱን እየጎዱ ሌላውን የመጥቀም ነገር የለበትም? ሸፍጥ የለበትም? ለመሆኑ በዚህ ፀባይህ የድለላ ስራን እንዴት ልትመርጠው ቻልክ?” ከሚነግራትና በተግባርም ካየችው ባህሪው የተነሳ የድለላ ስራው የሚያሳድርበትን ተፅእኖ
ለማወቅና ከዚያ ጣፋጭ አንደበቱ የሚወጡ ተጨማሪ ቃላትን ለመስ
ማት ጥያቄ ጫና አደረገችበት።
“ስላምዬ ስራዬ የምታውቂው ድለላ ነው። የድለላ ስራዬ ሻጭና ገዥ በሚያዋጣቸው ዋጋ እንዲገበያዩ በማድረግ ሁለቱንም ወገኖች አስደስቼ ለኔም የሚገባኝን ጥቅም ማግኘት ነውና በሽተኛን የሚፈውሰው ዶክተር፣
የእውቀት ጮራ የሚፈነጥቀው መምህር፣ የአገር ድንበር የሚጠብቀው ወታደር ሥራቸውን የሚወዱትን ያክል እኔም በእኔ የእውቀት ደረጃ የደላላነት ስራዬን እወዳታለሁ፡፡ ያልተገባ የድለላ ስራን በመስራት ሰዎችን መጉዳት ግን ለበጎ ህሊና ተቃራኒ ከመሆን አልፎ ከሰዎች ጋር የሚያጋጭ ነውና እንዳልሽው ጥንቃቄን የሚጠይቅ ስራ ለመሆኑ ጥርጥር
የለውም። ድለላን የመረጥኩት ግን በማንበብና በመፃፍ የትምህርት ደረጃ ዶክተር መሆን ስለማልችል ነው” እየሳቀ መለሰላት። ሰላማዊት ባሏ
ታደስ በማንበብና በመፃፍ የእውቀት ደረጃው የርቱእ አንደበት ባለቤት መሆኑ እያስደነቃት የበለጠ እንዲያወራላት ስሜቱን በመኮርኮር ልትሞግተው ፈለገች፡፡
“ታዴ ገዥና ሻጭ በድለላ ስራህ ሁሌም ደስተኛ ሊሆኑ አይችሉም::
እያየህ ዝም አትልም፡፡ በመሃል ገብተህ በተሻለ ዋጋ አገበያያለሁ ማለት የማይቀር ይሆናል፡፡ ያንን ስታደርግ ደግሞ በውድ ዋጋ ሊገዛ የነበረው ሰው ሲደሰትብህ በውድ ዋጋ ሊሸጥ የነበረው ሻጭ ባንተ ቅር ይሰኝብሃል አይደለም?” አለችው። ታደሰ የሚስቱን የመከራከሪያ ነጥብ ስለወደደው
ለጠየቀችው ጥያቄ መልስ በመስጠት ሊያሳምናት ፈለገ፡፡
“በእርግጥ ሁሉም አይነት ስራ ሁሉንም ወገን እኩል የሚያስደስት ነው ብዬ ልከራከርሽ አልችልም፡፡ በጣም በርካሽ ዋጋ የሚገዛ ሰው ሻጨን ጎድቶ ነው የሚገዛው። በውድ ዋጋ የሚሸጠውም ገዢውን ጎድቶ ነው የሚሽጠው። በዚህ ጊዜ ሚዛን ማስጠበቅና ማካካስ ያስፈልጋል። በጣምም
ሳይወደድ፣ በጣምም ሳይረክስ፡፡ የኔ ስራ ሰዎች ተካክሰው ሳይጎዳዱ እንዲጠቃቀሙ ማድረግ ነው። ስራዬ ሻጭና ገዢ አሸናፊ የሚሆኑበትን መንገድ በማመቻቸት ሚዛኑን ማስጠበቅ ነው። የድለላ ስራ የሚያስጠላው ተዋዋይ ወገኖችን የሚጎዳ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲባል
ሽፍጥ የተቀላቀለበት ሲሆን ነው። አይመስልሽም ?" አላት።
“ታዴ ሁሉንም ወገን እኩል የሚያስደስት ስራ እንደዚህ በቀላሉ የሚገኝ ይመስልሃል? ዳኛው ፍርድ ሲፈርድ እንኳ የተፈረደለት የሚደሰተውን
ያክል የተፈረደበት መከፋቱ የማይቀር ነው። ጠበቃው የሚጣላ፣ የሚደባደብ፣ የሚፋታ፣ የሚፈናከት በአጠቃላይ የሚካሰስ የጠፋ እንደሆነ አዝኖ ገበያዬ ቀዘቀዘ ይላል፡፡ የሬሳ ሳጥን ሻጩም ሰው ሞቶ የሰራው
ሳጥን ቶሎ ቶሎ ካልተሽጠለት ገበያ ጠፋ ብሎ ማዘኑ አይቀርም፡፡ እንዲያውም በነገራችን ላይ ስለ ሬሳ ሳጥን ሻጩ የሰማሁትን የሚያስቅ ነገር ልንገርህ፡፡ ስውዬው ዘመድ ሲሞትበት ሁል ጊዜ የሬሳ ሳጥን የሚገዛው
ከአንድ ቋሚ ደንበኛው ነበር አሉ፡፡ የሬሳ ሳጥን ሻጩ የዚህ የቋሚ ደንበኛው ውለታ ይከብደውና ሊክስው ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሀል እናት ይሞቱበትና ሳጥን ለመግዛት ሲመጣ የሬሳ ሳጥን ሻጩ ውለታውን ለመክፈል አስቦ በትልቁ ሳጥን ላይ አንድ ትንሽ የሬሳ ሳጥን ያስቀምጥለታል።
ሰውዬው ግራ ተጋብቶ ይሄ ደግሞ ምን ያደርግልኛል? ብሎ ቢጠይቀው ግድ የለም ጋሽዬ የዚህን ያክል ዘመን ደንበኛዬ ሆነው አንድ ቀን እንኳ
ክሼዎት አላውቅምና እሷን ደግሞ ለልጅዎ እንዲያደርጓት ምርቃት ነች አለና መለሰለት" ታደሰ በሳቅ ፍርስ አለ። “ሰላምዬ በጣም ያስቃል። ግን ምን ታደርጊዋለሽ የዓለም ነገር ይኸው ነው። ሳጥን ሻጩ ውለታ መክፈሉን እንጂ ልጅህን ይግደልልህ ማለቱን አላሰበውም። እሱ የታየው
በልጁ ሞት ምክንያት ደንበኛው የሚደርስበትን ሀዘን ሳይሆን ቋሚ ደንበኛውን መካሱንና ደንበኛነቱን ማጠናከሩን ብቻ ነው"እንደዚህ እየተጨዋወቱ ከቆዩ በኋላ ተቃቅፈው ወደ ጓዳ ገቡ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ያቺ በናፍቆት የተጠበቀችው የፋሲካ በዓል ደረሰች። ታደሰና ሰላማዊትም በደስታ ሊቀበሏት ሽር ጉድ ሲሉ የከረሙላት፣ በለሊት ተነስተው የሚጐራረሱባት ዕለት ከተፍ አለች።
“ታድዬ...ተነስ...ዶሮ ጮኋል” አለችው። እስከ እኩለ ለሊት ዶሮ
ወጡን ስትስራ ቆይታ እንቅልፍ ሳይወጣላት ነበር የመፈሰኪያው ስዓት የደረሰው።
“ከምንጊዜው ሰላምዬ? ትንሽ እንኳን ሳንተኛ?" እሱም በቂ እንቅልፍ አላገኘም ነበር። በአንዳንድ ነገር ሲያግዛት ነው ያመሸው። ከአልጋቸው ላይ ተነስተው እየተጉራረሱ ፆም ይፈቱ ጀመር።
“ይሄኔ..” አለ ታደሰ።
“ይሄኔ ምን?” ወደ ጐን በፍቅር እያየች ጠየቀችው።
“እንትን...” ሳቅ አለና ሆዷን ተመለከተ።
“ገባኝ” እሱን ተከትላ እየሳቀች።
አንድ አድማቂ የመሀል አጫዋች፣ሌላ ፍቅርን የሚጨምር ፀጋ በመካከላችን ቢኖር ኖሮ ፋሲካው የበለጠ ፋሲካ ደስታው የበለጠ ደስታ ፍቅሩም የበለጠ ፍቅር ይሆን ነበር ማለቱ እንደሆነ ገባት ።
“እሱማ የዛሬ ዓመት ነዋ ታዴ?”
በሚቀጥለው ዓመት በዛሬዋ ቀን ፋሲካን ሲፈስኩ ድንቡሽቡሽ ያለ ልጅ ወልደው መጪዋን ፋሲካ በድምቀት እንደሚቀበሏት በምኞት ተጨዋወቱ፡፡ ሰላማዊት የወር አበባዋ ከቀረ ውሎ አድሯል። ማቅለሽለሽና ማስመለስ እያዘወተራት ነው። ታደሰ ይሄ ሁኔታ እርግዝና መሆኑን ካወቀ
በኋላ ልጅ የማግኘት ጉጉቱ በጣም ከፍተኛ ሆኗል። ዛሬም ይሄኔ...
የሚላት አንድ ልጅ በመካከላችን ቢኖር ደስታው ድርብ በአሉም በእጥፍ ደማቅ ይሆንልን ነበር ማለቱ ነበር፡፡
“ታዴ ወንድ ነው ወይንስ ሴት ብወልድ ደስ የሚልህ?“
“ስላምዬ ማሚቱም ማሙሽም ተወዳጅ የአምላክ ስጦታዎች
ናቸው። ሰው ነንና አንዳንድ ጊዜ ማሙሽን ከማሚቱ ማሚቱን ከማሙሽ የምንመርጥበት ጊዜ ይኖራል። ብዙውን ጊዜ እናት ሴት ልጅ ለመውለድ ትፈልጋለች፡፡ አባት ደግሞ ለወንድ ልጅ ያደላል ለምን እንደሆነ ግን አይገባኝም።
እኔ እንጃ ታዴ እኔ ግን አሁን አንተ እንዳልከው ሴት ልጅ ብወልድ ደስታውን አልችለውም”
እንደሱ ካልሽ እኔ ደግሞ ወንድ ልጅ ብትወልጅልኝ ደስታውን

👍5❤3
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...የፖሊስ አዛዥ ያዘጋጁትን ንግግር ለመጀመር ጉሮሯቸውን አፀዱ “እህ..እህህ..ውድ የእለቱ የክብር እንግዶች ወንድሞቼ እህቶቼና የሥራ ባልደረቦቼ በዛሬው እለት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኛችሁበት
ይህን ፕሮግራም ማዘጋጀት አስፈላጊ የሆነበት ዋነኛ ምክንያት ያለፈው ዓመት አፈፃፀማችንን በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎናችንን ለመለየት ሲሆን ባለፈው ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ አጠናክረን የተሻለ
ውጤት ለማስመዝገብና ድክመቶቻችንን በውል ተገንዝበን በማስወገድ በቀጣይ የስራ ዘመናችን አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ የምንችልበትን
ስትራቴጂ ለመንደፍ ነው፡፡
የተቋማችን ዋነኛ ዓላማ የማህበረሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በየ አካባቢው እያቆጠቆጠ ያለውን የወንጀል ድርጊት በተቻለ መጠን ለመግታትና ለመቆጣጠር እንደመሆኑ መጠን ይህንን ዓላማ እውን ለማድረግ በርካታ ተግባራት ከፊት ለፊታችን ሆነው ይጠብቁናል፡፡ ወንጀል በተለያዩ
መንገዶች የሚገለፅ የማህበረሰቡ ቁስል ነው። ወንጀል አብሮ የመኖር እንቅፋት የመተሳሰብና የመተባበር ነቀርሳ፣ የልማትና የእድገት ፀር ነው። በአጠቃላይ ወንጀል የማህበረሰቡ ክፉ በሽታ ነው። በሽታ ካለ የመንፈስም ሆነ የአካል ጥንካሬ አይገኝም። በሽታን ለማጥፋት ሳይንቲስቶችና
ተመራማሪዎች የእያንዳንዱን በሽታ ባህሪ ለማወቅ የጀርሞች፣ የባክቴሪያና የቫይረሶችን አፈጣጠር በማጥናት መፈወሻ መድኃኒት ለመቀመም ቀን ከለሊት ይማስናሉ። በሽታ ሽባ ያደርጋል፣ በሽታ እብድ ያደርጋል፣
በሽታ የአልጋ ቁራኛ ያደርጋል። በሽታ ይገድላል። ወንጀልና በሽታ አንድ ናቸው፡፡ ወንጀል ከትንሹ ጀምሮ ቀስ በቀስ እያደገና እየሰፋ ሲሄድ ቀሳፊነቱ በዚያው ልክ እያደገ ይሄዳል። በጊዜውና በወቅቱ ያልተቀጨ በሽታ
ህይወት ይዞ እንደሚሄደው ሁሉ በወቅቱና በጊዜው ያልተቀጨ ወንጀል እያደገና እየሰፋ ሲሄድ ማህበራዊ ቀውስን ያስከትላል። አገራዊ ሰላምን አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ ወንጀለኛ ከሌላ ወንጀል አይኖርም፡፡ ወንጀል እንዳይስፋፋ አስፈላጊው ጥረት ከተደረገ ደግሞ ወንጀለኛ አይኖርም፡፡ ወንጀልን
በማስወገድ የህብረተሰቡን አጠቃላይ የደህንነት ዋስትና ማረጋገጥ የሚቻለው ሁሉም የህብረተሰብ አባል ለደህንነቱ መረጋገጥ የግልና የቡድን አስ
ተዋፅኦ ሲያደርግና የቆምንለትን ዓላማ መደገፍ ሲችል ብቻ ነው። እኛም እያንዳንዱ ሰው ይሄንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ ያለመታከት ማስተማር ይጠበቅብናል።
አብዛኛው ነዋሪ ያለስጋት የሚዘዋወረው አምሽቶ የሚገባውና የሚወጣው እኛ የሱን ሰላም የምናስጠብቅ እንቅፋት ቢመታው ፈጥነን የምንደርስ፣ ያላግባብ በደልና ጥቃት ቢደርስበት ጥብቅና የምንቆም ባለአደራዎች በሰው ልጆች የተፈጠረና ሰዎችን በበላይነት እንዲመራ የተደነገገውን ህግ የምናስከብር አካላት መኖራችንን ተስፋ አድርጎ ነው። በመሆኑም ህጉንና ደንቡን ተላልፈው ወንጀል የሚፈፅሙ ህገወጦችን ለፍርድ
በማቅረብ የተረጋጋና አስተማማኝ የሰላም ዋስትናን ማረጋገጥ እስከሚቻል ድረስ አገልግሎታችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል። የህብረተሰቡን ስላም ለማስጠበቅ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሰላም መጠበቅ ይኖርበታል። ይህን ዓላማችንን እውን ለማድረግ ደግሞ ሰፊ የህዝብ ድጋፍና
ትብብር ያስፈልገናል።
የህብረተሰቡ እርዳታ የህብረተሰቡ ድጋፍና ትብብርና በሌለበት ብቻችንን የምናደርገው ሩጫ በአንድ እጅ እንደማጨብ
ጨብ ነው። ወንጀለኞች በህዝቡ ውስጥ ሆነው ወንጀል በህዝቡ ላይ እየፈፀሙ ተመልሰው ህዝቡ ውስጥ ገብተው የሚሸሸጉ ከሆነ የሚጐዳው ህዝቡ ራሱ ነውና የበለጠ የኃላፊነት ስሜት ተሰምቶት ራሱን ከአደጋ
ለመከላከል ወንጀለኞችን የማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅብናል። ህብረተስቡ ወንጀለኛን የሚያቅፍ፣ የሚሽሽግ ከሆነ ደግሜ እናገራለሁ ድካማችን ሁሉ በአንድ እጅ ማጨብጨብ ብቻ ሳይሆን ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ነው የሚሆነው። በንግግሬ መሃል አንድ ከዚህ ነጥብ ጋር አብሮ የሚሄድ ትምህርት ይሰጠናል ብዬ የምገምተውን ቀልድ ልንገራችሁ። ሁለት ወንድማማቾች የታጨደ የእህል ክምር ከሌባ ለመጠበቅ ማሳቸው ላይ ገለባ ለብሰው ይተኛሉ። ለሊት ላይ ጅብ ይመጣና
ያንን ገለባ ገላልጦ የአንደኛውን እግር መቆርጠም ይጀምራል። በስማው ድምፅ ግራ የተጋባው ወንድም “ምንድነው የሚሰማኝ ድምፅ?" ብሎ ወንድሙን ይጠይቀዋል።
“ቀስ በል አትጩህ የኔን እግር እየበላ ነው” ሲል በፍርሃት ተውጦ
ይመልስለታል። በዚህ ጊዜ ፎክሮ ይነሳና “አንተ ፈሪ አንተን በልቶ
ሲያበቃ ወደኔ መምጣቱ ይቀራል እንዴ?” በማለት ቆርጥሞ ሳይጨርሰው እሱንም ሳይጀምረው ጅቡን አባረረው ይባላል” በዚህ ጊዜ ሁሉም
በሳቅ ፈነዱ... የተሰብሳቢው ሳቅ ጋብ እስከሚል ድረስ ጠብቀው ቀጠሉ።
“እና ከዚህ ቀልድ ትልቅ ቁም ነገር እንማራለን፡፡ ዛሬ ወንጀለኛን ያቀፈ
ህዝብ ወንድሙ አጠገቡ ሲመታ ሲቆስል ሲሞት እያየ እኔ እስካልተነካሁ ድረስ ምን ቸገረኝ? በማለት ወንጀለኛውን ከማጋለጥ የሚቆጠብ ከሆነና ወንጀለኛን እንደ ጅቡ በጊዜ ማባረር ካልቻለ ተመልሶ በሱ በራሱ ላይ
የሚዘምትበት መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡በዚህ ረገድ የዛሬው ሁለተኛው የስብሰባችን ዋና አላማም ከህዝቡ መካከል ይህንን ተገንዝበው በቀጥታም
ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከእኛ ጋር እጅና ጓንት ሆነው በመስራት ለከፍተኛ ውጤት ያበቁን ወንድሞቻችንን በመሸለም ለሌሎችም አርአያ እንዲሆኑና ሞራላቸው እንዲጠበቅ ለማድረግ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት እነኝህን
ውድ የህዝብ ልጆች ለማታውቋቸው በማስተዋወቅ ላበረከቱት አስተዋፅኦ
ማበረታቻ ይሆናቸው ዘንድ የተዘጋጀላቸው ሽልማት በእናንተ ፊት ይስጣቸዋል። ሁላችንም እንደምናውቀው ወንጀል ይበዛባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል ዋነኛው እሪ በከንቱ እንደነበር ግልፅ ነው። ከስም አወጣጣቸው ጀምሮ ዶሮ ማነቂያ፣ እሪ በከንቱ በሚባሉት በእነዚህ ሰፈሮች ውስጥ በርካታ ወንጀሎች የሚፈፀሙበት ለእሪ ባይ ረዳት የማይደርስበት የሰው ልጅ እንደ ዶሮ ተቆጥሮ በዶሮ ማነቂያ ስም አንገቱ የሚታነ
ቅባቸው አካባቢዎች ነበሩ፡፡ እነዚያ አካባቢዎች እንደምታውቁት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ሰው በልቡ እምነት አሳድሮ የሚረማመድባቸው አልነበሩም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግን እሪ በከንቱነቱና ዶሮ ማነቂያነቱ ቀርቶ ሰዎች
በፈቀዳቸው ሰዓት የሚመላለሱባቸው አልፎ አልፎ በጣም አልፎ አልፎ ንጥቂያዎች ቢፈፀሙ ለእርዳታ ድምፅ የሚያሰማ ፈጥኖ ደራሽ የሚያገ
ኝባቸው የሰላም ቀጠናዎች እየሆኑ መጥተዋል። ይሄ ውጤት የተገኘው በተአምር ሳይሆን ሌት ተቀን ከእኛ ጋር አብረው በተሰለፉ ወንድሞቻችን ድካምና ጥረት ነው፡፡ ለዚህ ውጤት መገኘት በርካታ ተባባሪዎች ቢኖሩንም የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን ከዚህ ቀጥሎ አስተዋውቃችኋላሁ”
አሉና ዐይኖቻቸውን ወደ ተሰብሳቢዎቹ መካከል ወረወሩ።ፈገግታ የተላበስ ፊታቸውን ወደ ታደስ በእውነቱ አዞሩና ሁለቱን እጆቻቸውን ዘረጉ።
ታደስ ተነስቶ ቆመ:: ጭብጨባው አስተጋባ፡፡ ታደሰ ወደ መድረኩ ሄደ። “አዎን እሱ ወንድማችን ታደሰ በእውነቱ ይባላል! ወንጀለኞችን መስሎ ወንጀለኞችን ተቀላቅሎ ቀን ከሌሊት ብርቱ ትግል ያደረገና ተደጋጋሚ
ውጤቶችን ያስመዘገበ ወንድማችን ነው!”

#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....የህዝቡ ብዛት….በዚህ ላይ ጨለማ...ያ ሽለምጥማጥ አበራ ፍላጐቱን በቀላሉ ፈፅሞ ከአካባቢው ተሰወረ።..
ጓደኞቹ በሙሉ በመሀሌት ቤት እጅ ከፍንጅ ተይዘው ከታሰሩበት በኋላ ታደሰ ብቻውን ሊለቀቅ የቻለበትን ምክንያት ለማወቅ ስውርና ረቂቅ በሆነ መንገድ ሲከታተለው ነበር የሰነበተው፡፡
ባደረገው ክትትል ታደስ የነጣቂው ቡድን ዋነኛ መቅሰፍት መሆኑን እያወቀ መጣ፡፡ መረጃ እየሰበሰበ
ሲያቀብል ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሲወጣ ሲገባ..ራሱን እየለዋወጠ ወንጀልና ወንጀለኛን ለማሳደድ የሚስራውን ሥራ በሙሉ ሲከታተለው ቆይቶ በመጨረሻ ላይ እውነታውን ደረሰበት።
ታደስ ከመረጃ አቀባይነቱ አልፎ ተርፎ እስከ መሸለም መብቃቱን፣
በዚያን እለትም ሌሎቹን ወንጀለኞች በሙሉ ካሳሰረ በኋላ እሱ በነፃ መለቀቁን፣ ለጊዜው የታሰረውም ለሽፋን መሆኑን አረጋገጠ፡፡ በዚሁ መሰረት
ታደሰን ለመበቀል ሲያደባ ቆይቶ ሰላማዊትና ታደሰ ከመኖሪያ ቤታቸው ተነስተው ትያትር ቤት እስከገቡበት ጊዜ ድረስ በጥብቅ ሲከታተላቸው ዋለና ያን አስከፊ ድርጊት ፈጽሞ አመለጠ፡፡
በከፍተኛ የህዝብ ትብብር
ነፍሰ ጡሯ ግራና ቀኝ ተይዛ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ እንክብካቤ ተደርጉላት ከባሏ ጋር ወደ ሆስፒታል ተወስዱ። በመውደቋ ምክንያት መጠነኛ ንቅናቄ ደርሶባት ስለነበረ ወደ ማህፀን ክፍል ተወሰደች። ታደሰ ደግሞ
ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እንዲገባ ተደረገ፡፡ በግራ ጐኑ የገባችው ጥይት ጉበቱን በስታ በቀኝ ጐኑ ወጥታ ነበር፡፡ ሆስፒታል እንደገባም አጣዳፊ
የሆነ የቀዶ ጥገና ህክምና ተደረገለትና ደም ከተሰጠው በኋላ ግሉኮስ በግራ ክንዱ ላይ ተሳካለት፡፡
ሰላማዊት የደረሰባት መጠነኛ ጉዳት በመሆኑ በማግስቱ ድና ተነሳች። ታደሰ ግን ክፉኛ ተጐድቷል፡፡ እማማ ወደሬ በጠዋቱ ጉዳቸውን ሲሰሙ
በድንጋጤ ክው ብለው ቀሩ፡ ያ እንደ እናቱ የሚያያቸው፤ ትንሽ ሲያማቸው የሚጨነቅላቸው፣ የዳሩት ልጃቸው የሆነውን ሰሙ። በተለይ ይህ አደጋ በደረሰበት እለት “እንኳን አደረስዎ” ሊላቸው የሚወዷትን ነጭ አረቄ ይዞላቸው ሄዶ ሊያጫውታቸው፣ ሲያስፈነድቃቸው ነበር የዋለው።
“ታዴን! ታዴን! ልጄን! .እኔ እናትህ ድፍት ልበል! የኔ ደም ክንብል
ይበል! ለካ ለዚህ ነው? ለካ አንጀቴን ሲበላው ነው? ምነው ከኔ በፊት? እኔ አሮጊቷ ቁጭ ብዬ...እኔን ያስቀድመኝ...” ልብሳቸውን ሳይቀሩ እየጮሁ ወደ ሆስፒታል ሮጡ አደጋውን የሰሙ
የቅርብ ጓደኞቹ ሲያስታምሙትና ሲጠይቁት ከረሙ:: ታደሰ ግን በየጊዜው የመሻሻል ምልክት ከማሳየት ይልቅ የድካም ምልክቱ እየጨመረ ሄደ። ጉበቱ ክፉኛ ተጐድቶ ነበር፡፡የመዳን ተስፋው የመነመነ መሆኑን ሆስፒታሉ አስታወቀና ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ከሆስፒታል ወጥቶ ህክምናውን በቤቱ ውስጥ እንዲ
ከታተል ተደረገ፡፡ ወይዘሮ ወደሬ ቤታቸውን ዘግተው ንግዳቸውን ርግፍ አድርገው ትተው በአንድ በኩል ነፍስ ጡር ልጃቸውን በሌላ በኩል በሽተኛ ልጃቸውን ለመርዳት ጉለሌ ተጠቃለው ገቡ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጀርባ በአንድ ትልቅ የባህር ዛፍ ቅርንጫፍ ላይ የሆነ የተንጠለጠለ ነገር በርቀት ይታያል፡፡ በአካባቢው ግርግር እየ
ተፈጠረ ነው፡፡ የሰፈሩ ነዋሪዎች ከህፃናት ጀምሮ ወደ ጫጫታና ግርግሩ ስፍራ እየሮጡ ሲደርሱ ሙሉ ጥቁር ሱፍ የለበሰ፣ ክራቫት ያደረገ መልከ መልካም ወጣት በወፍራም ገመድ ላይ ዘለዓለማዊ የቁም እንቅልፍ አንቀላፍቶ ጠበቃቸው።
ዐይኖቹ ገርበብ ብለው ሲታዩ የሚያዝንለትና የሚያዝንበትን ህዝብ በትዝብት የሚያስተውል ይመስል ነበር፡፡ ቀይ ቀሚስ፣ እጅጌ ጉርድ ሰማያዊ ሹራብ የለበሰች ዕድሜዋ ከአስራ ሰባት ዓመት የማይበልጥ ጠይም መካ
ከለኛ ቁመት ያላት ሴት ልጅ ደግሞ በሟቹ እግር ላይ እየተንከባለለች እዬዬና ዋይታዋን በማሰማት ላይ ነበረች።
“የኔ አለኝታ! የኔ መመኪያ ! ምነው? እኔን ለማን ጥለኸኝ? የቀን ጅብ በላኝ እኮ! ሰማዩ ተደፋብኝ...” በሟቹ ምክንያት ስለሚደርስባት ችግር እያወራች ለራሷ የምታለቅስ ትመስላለች። በዚያን ሰሞን በሰፈሩም ሆነ
በመሥሪያ ቤቱ አካባቢ የሰመረ ሞት የሳምንቱ ዐብይ የመወያያ ርዕስ ሆኖ ሰነበተ። ሰመረ በገዛ ህይወቱ ላይ እንዲፈርድ ያቺን የምታሳሳ ህይወት እንዲንቃት ያስገደደው ምን ይሆን? ምክንያቱን ለማወቅ ሁሉም
ጆሮውን አቁሞ ፍንጩን ለማግኘት አነፈነፈ። ገሚሱ በሰማው ላይ
የራሱን እየጨመረ ወሬውን አራገበ፡፡ ሰመረ ህይወቱን ለማጥፋት ያነሳሳውን ምክንያት ማወቅ አለማወቅ የሚያመጣው ለውጥ ግን አልነበረም።
የሰመረን የልብ ውስጥ ቁስል ከሚያውቁ ጓደኞቹ መካከል የቅርብ ጓደኛው ሳሙኤል ነበር፡፡ ከልጅነት እስከ እውቀት ችግርና ደስታን የተካፈሉ ጓደኛሞች ናቸው፡፡
ሳሙኤል !" ጐረቤቱ ጌዴዎን ነው የጠራው፡፡
“አቤት!” አገር ሰላም ነው ብሎ የጠዋት ፀሀይ ለመሞቅ በረንዳው
ላይ ቁጭ ብሏል፡፡
“አልሰማህም ?”
“ምኑን?”
“የሰመረን?”
“ምን ሆነ?!”
“ሰመረ እኮ . . .”
“መኪና ገጨው እንዳትለኝ ጌዴዎን!!.…” ደንግጦ ተነሳ።
“እ…እ..እኔማ ሰምተህ መስሎኝ፡፡ መኪና አይደለም…ራሱን አጥፍቶ ነው...” ከሳሙኤል የወጣ ትንፋሽ አልነበረም። በድን ሆኗል።
አንጀቱ ድብን ብሏል። ጌዴዎን ሳያውቀው በቀላሉ ሞቱን ያረዳው ሰው ለሳሙኤል የወንድም ያክል ነበር።ቀሳሙኤል ጭንቅላት ውስጥ በርካታ የሰመረ ትዝታዎች ተመላለሱ። ሰመረ በልጅነቱ፣ ስመረ በቄስ ትምህርት ቤት፣ ሰመረ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምሀርት ቤት፣ ሰመረ በዩኒቨርስቲ በይዘታቸው አንድ በዓይነታቸው ግን ብዙ ሰመረዎች በዓይነ ህሊናው ላይ ሄዱበት። ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ይዞ በቤቱ በረንዳ ጠርዝ ላይ በክርኑ ተደግፎ አንገቱን ቁልቁል ደፍቶ ለረጅም ጊዜ ሲተክዝ ቆየ። ትዝታ የጓደኝነት ፍቅር....ከውስጥ እያቃጠሉት እንባ ያቆረዘዙ
ዐይኖቹ ያዘሉትን ውሃ ወደ ታች ለቀቁት...
ጌዴዎን የጓደኝነታቸውን ደረጃ ሳያጣራ በመናገሩ አዘነ። ድርጊቱ አንድ ችኩል መርዶ አርጂ ከፈፀመው ድርጊት ጋር ተመሳሰለበት፡፡ ሰውዬው
እናቱ የሞተች ባልንጀራውን በደንቡና በሥርዓቱ መሰረት በለሊት እንዲያረዳ ሃላፊነት ይሰጠዋል፡፡ ችኩሉ መርዶ አርጂ ግን እዚያው መሥሪያ ቤቱ ድረስ ይሄድና “ስማ እንጂ! ስለ እናትህ ስማህ እንዴ?”በማለት ይጠይቀዋል። አነጋገሩ ያስደነገጠው ልጅም “ምነው አመማት እንዴ?!”
በማለት መልሶ ጠያቂን ይጠይቀዋል፡፡
“ኽረግ ሊያውቅ ነው መሰል!" ይላል ችኩሉ መርዶ አርጂ። ይህ አባባሉ የበለጠ ያስደነግጠው ሰው "ምነው ባሰባት እንዴ?!” ሲል ደግሞ ይጠይቀዋል፡፡ ከዚያም ችኩሉ መርዶ አርጂ..“ጠረጠረ በለው!” ይላል። በዚህ ጊዜ ልጅ ክፉኛ ይደነግጥና...“ምነው?! ሞተች እንዴ?!” ብሎ በድጋሚ ይጮሃል፡፡ ችኩሉ መርዶ አርጂም “አወቀ በለው!ማን አባቱ
አረዳኝ ሊል ነው?!” አለና ፊቱን አዙሮ ሩጫውን ቀጠለ፡፡ ጌዴዎንም የሳሙኤልን ሁኔታ ሲመለከት በችኩል መርዶ አርጂነቱ ደንግጦ ሊሮጥ
ቃጥቶት ነበር፡፡ ትውውቃቸውን እንጂ የቅርብ ባልንጀራሞች መሆናቸውን ቢያውቅ ኖሮ ሞቱን እንዲህ በቀላሉ አያረዳውም ነበር። ሳሙኤል በቀብሩ እለት እዬዬ ብሎ አለቀስ። ያቺ ሰመረ ራሱን በሰቀለ እለት እግሩ

👍6❤1👎1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ትናንትና አስተማሪው የሰጣትን የቤት ሥራ ሊያስረዳት ጀምሮ አቋርጦት ነበር። ቶሎ ብላ መጽሀፏን ደብተሯን ይዛ ከተፍ አለች። የለበሰችው ጉርድ ቀሚስ ነው፡፡ ፀጉሯን በወፍራሙ ጐንጉናዋለች። ታደስ ጥሩ ፀባይ እንዳለው እየተረዳች በመምጣቷ ሰውነቷ መሸማቀቁን ዘንግቶ ዘና ፈታ ማለት ጀምሯል።በአልጋ ላይ በጎኑ ጋደም እንዳለ ማስጠናቱን ቀጠለ... አጥኚና አስጠኚ አለቅጥ ተቀራርበው ነበረና
ልብስ ባልለበሰ ክንዱ ልብስ ያልለበስ ክንዷን ሲተሻሽው ልስላሴዋና ሙቀቷ በክንዱ በኩል ዘልቆ ሁለመናውን አዳረሰው፡ሙቀቱ የፈጠረበት ስሜት ረበሽውና ቀና ብሎ ወደ ጎን አያት፡፡ እሷም እየተሽኮረመመች ወደ ጉን አየችው። ደማቅ የውበት ቀለም የተቀባች መሆኗን አጤነ፡ በቃ! አልቻለም፡፡ያንን ለብዙ ጊዜ ከራሱ ጋር ሲሟገት የቆየበትን ነገር ለማድረግ መገደዱን አመነ፡፡ሳብ አደረገና በክንዶቹ አቀፋት። አልተቃወመችም ሄዳ ልጥፍ አለችበት፡፡ ቀስ ብሎ ከንፈሯን ሳማት። እሷም አፀፋውን
መለሰች። ሲፈላለጉም ሆነ ሲገናኙ የነበረው ሁኔታ ከዚህ በፊት የሚተዋወቁ እንጂ አዲስ ጀማሪዎች አይመስሉም ነበር፡፡ ምግብ አብሳዩ እንጂ አቻው አለመሆኗ እየተሰማት እየተሸማቀቀች ለብዙ ጊዜ የቆየች ቢሆንም አስገዳጁ የጾታ ማግኔት ሳታስበው በስሜት አጋግሉ፣ ሰሜን ጫፍና ደቡብን አሳስቦ በድንገት ሲያስተቃቅፋቸው ምን ታድርግ? ከዚያም እግሮቿን በእግሩ ከታች ወደ ላይ ቢያስፈነጥራቸው ተወርውራ ሄዳ አልጋው ላይ በግራ ጎኑ ወደቀችና ከደረቱ ተጣበቀች፡፡ የአዳም የግራ ጎኑ ሄዋን...ታደሰ ከስድስት ወር የአእምሮ ሙግት በኋላ ዛሬ ዳበሳት... ዙሪያሽ ጨዋነቷን አስመሰከረች. . ልጃገረድ! ...
“ጋሼ ታደስ እኔ እኮ ድሃ የድሃ ልጅ ነኝ ካንተ ጋር እንደዚህ አይነቱን
ነገር መፈፀም አልችልም፡፡ ያለ አቅም መንጠራራት ትርፉ አደጋ ላይ መውደቅ ነው”
“ዙሪያሽ እኔም ድሃ የድሃ ልጅ ነኝ ነገር ግን ወላጆቼ የገንዘብ ድሆች
እንጂ የመንፈስና የሞራል ድሆች አልነበሩም፡፡ ከገንዘብ ድህነት የበለጠ ሰውን የሚጐዳው የመንፈስ ድህነት ነው። ያንቺም ወላጆች የገንዘብ ድሆች ከነበሩ እኔም እንዳንችው የድሃ ገበሬ ልጅ ነኝና ስለአቻነታችን በፍፁም አትጠራጠሪ፡፡ በዚያ በኩል ስላለን ልዩነት አትጨነቂበት” አላት።
“ጋሼ ታደሰ የሞራልና የመንፈስ ድህነት ከአጐቴ ሞት ጋር ተደምረው ጐድተውኛል። አጐቴ... አጐቴ... የሀብታም ልጅ የሆነችውን የትምርት ቤት ጓደኛው እመቤት መስፍንን ወደዳት... እሷም ወደደችው። ፍቅራቸው ግን አቻ አልነበረም፡፡ አጐቴ የድሃ ልጅ በመሆኑ ወላጆቿ አልወደዱትም፡፡ ዘረ ምናምንቴ የድሃ ልጅ እያሉ አንቋሸሹት። ቅስሙን ሰበሩት። ሁለቱ ይፋቀሩ ነበር፡፡ የእሷ ወላጆች ውሻ አደረጉት።ለሀብታም ልጅ ታጭታ ቀለበት እንድታስር አስገደዷት።ጋሼ ሞራሉ ወደቀ፡፡
ብስጩ ሆነ፡፡ እሷ ትወደው ነበር፡፡ እየተዋደዱ ግን ተለያዩ፡፡ጋሼ ጤንነቱ ተቃወሰ፡፡መጨነቅና መጠበብ አበዛ፡፡ ብቸኝነት፣ የሞራል ውድቀት በዚህ ላይ ፍቅር አለ፡፡ እያፈቀሩ ማጣት ሰላም ነሳው። ብስጩነቱ እንዳይታወ
ቅበት ጥረት ቢያደርግም ያስታውቅበት ነበር፡፡ የሃብታም ልጅ ባይወድ ኖሮ ቢጤውን ቢፈልግ ኖሮ ይሄ ሁሉ አይመጣበትም ነበር፡፡ ጋሽ ታደሰ
የኔና ያንተም ተመሳሳይ ነው፡፡ አቻ አይደለንም፡፡ የድሆች ልጆች ብንሆንም በእውቀት እንበላለጣለን፡፡ አንተ የተማርክ ጥሩ ሥራ ጥሩ ደመወዝ ያለህ ሰው ነህ፡፡ እኔ ግን እዚህ ግቢ የማልባል በትምህርት ያልገፋሁ
ገረድህ ነኝ፡፡ ዝቅ ብለህ ከገሪድህ ጋር...እኔ ደግሞ ያለአቅሜ ተንጠራርቼ የሚደረግ ግንኙነት ጥሩ ነው ብለህ ታስባለህ?”
“ዙሪያሽ እንደሱ አታስቢ። በዚች በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በሚገባ ተጠናንተናል።ያየሽብኝ ጉድለት ካለ ደግሞ ግለጪልኝና ላርም፡፡ በእውነት ነው የምልሽ ዙሪያሽ እኔ ከዚህ በፊት ብቸኛ ነበርኩ ጓደኞቼ አይጦችና
ሽረሪቶች ነበሩ። ቤቴ ብቻ ሳይሆን አእምሮዬ ሸረሪት አድርቶበት ነበር፡፡
ብቸኝነትና የመንፈስ ጭንቀት ነበሩብኝ፡፡ መንፈሴን የሚያስጨንቀኝ ነገር ከሞላ ጎደል መፍትሄ እያገኘ ሃሳቤ እየሰመረ በመምጣቱ ደስተኛ ነኝ፡፡
ወንጀሎች እንዲቀንሱ የበኩሌን ጥረት በማድረጌና ውጤቱን እያየሁ በመምጣቴ ደስተኛ ሆኛለሁ። በዚህ ደስተኛ ብሆንም አንድ ነገር እንደሚጐድለኝ ሁሌም ይታወቀኝ ነበር፡፡በተለይ እንደዚህ እንደአሁኑ ከነ ክብርሽ አገኝሻለሁ የሚል ግምት ባይኖረኝም አብረን በቆየንባቸው ወራቶች ውስጥ
ሳጠናሽ ነበር የቆየሁት። ያንን በጭንቅላቴ ውስጥ አድርቶ የነበረውን የብቸኝነት ድር የበጣጠስሽልኝ ከግማሽ ወደ ሙሉነት የምሸጋገርበት ተስፋ
የፈነጠቅሽልኝ አንቺ ነሽ፡፡ ያደረ የሆቴል ቤት ምግብ ትርፉ ቃር ነው።ከዚያ ነፃ ሆኛለሁ። አፈር አፈር የምትሽተው ኦና ቤቴ ዛሬ ሞቅ ደመቅ ብላ ቄጤማ ተጐዝጉዞባት እጣን ጤሶባት ሽታዋ የሚስብ ሆኗል። የቆሽሽ
ልብሴ ታጥቦ ንፁህ ሆኖ አገኘዋለሁ፡፡ በውጭ እስከዚህ ድረስ ለውጠሽኛል። ነገር ግን የውጭ ለውጥ ብቻውን ዋጋ የለውም፡፡ ውስጤ መለወጥ
አለበት፡፡ ባዶነቴን ብቸኝነቴን ለማስወገድ ለኔ ካንቺ የተሻለ እንደማይኖር በተለይ በዛሬዋ ምሽት በይበልጥ አረጋግጫለሁ። ጥንድነት ለአልጋ ብቻ አይደለም፡፡ችግር ሲያጋጥም የምታማክሪው፣ ደስታና ሀዘንሽን የምታካፍይው፣ የኑሮ ብልሃቱ እክል ሲገጥመው ዘዴ የሚቀይስ የሚያፅናና ጓደኛ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከሁሉ የሚበልጠው ጓደኛ ደግሞ የቤተሰብ መሠረት የትዳር ጓደኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሄዋንን ለአዳም አዳምን ለሄዋን የፈጠረላቸው ይህን ችግራቸውን አውቆ ነውና የታደሰ ሄዋን
አንቺ ዙሪያሽ ብትሆኚለት ምን ይመስልሻል ? በዛሬዋ ምሽት በእምነት ክብርሽን እንደሰጠሽኝ ሁሉ እኔም ንፁህ ፍቅሬን ልሰጥሽ ዝግጁ ነኝ፡፡ ከዛሬዋ እለት ጀምሮ በደንቡና በወጉ ተፈራርመን ገሃድ እስከምናወጣው ድረስ በባልና ሚስትነት አብረን እንኖር ዘንድ ምኞቴን የተቀበልሽው ስለ
መሆኑ ማረጋገጫ..” አለና ከንፈሩን አስጠጋላት፡፡
“ጋሽ ታደሰ እኔ እኮ... እኮ...ደሃ ነኝ ቢጤዬን እንጂ” የታችኛው ከንፈ
ሯን ነከሰች።
“ዙሪያሽ ስለድህነትና አቻ ስላለመሆናችን የምታወሪውን ለመርሳት ሞክሪ፡፡ እንደሱ እያልሽ አታስጨንቂኝ፡፡ ድህነት በደማችን ውስጥ የሚዘዋወር አብሮን የተፈጠረ ወይም እንደሚባለው የአርባ ቀን ዕድላችን አይደለም፡፡ ድህነትን በሥራ ልንደቁሰው እንችላለን፡፡ የእመቤት ወላጆች ሌላ እኔና አንቺ ደግሞ ሌላ ነን። የአጐትሽ ሞት ያስከተለብሽ ሥነ ልቦናዊ ጫና ቀላል እንዳልሆነ ይሰማኛል። የእመቤት ወላጆች የገንዘብ ሃብታሞች ቢሆኑ የእውቀት ድሆች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከገንዘብ ድህነት የከፋው
ደግሞ የአእምሮ ድህነት ነው። እኔና እነሱን አታወዳድሪን፡፡ ቢያንስም ቢበዛም ፊደል የቆጠርኩ ነኝና የፍቅርና የገንዘብን አንድነትና ልዩነት ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ሁለቱም ለሰው ልጅ ህልውና አስፈላጊ ናቸው።
ገንዘብ ያለበት ፍቅር አይጠላም፡፡ ማለፊያ ነው። ፍቅር የሌለበት ገንዘብ ግን ገንዘብ አይደለም፡፡ አያረካም፡፡ እመቤትን ወላጆቿ ገንዘብ ላለው ሰው አሳልፈው ቢሰጧት የምትረካ እንዳይመስልሽ፡፡ ዋናውን ግምት

👍15
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
..ባሌ... በሬሳ!
( ከአራት ዓመታት በፊት)
ከቀኑ አስር ሰዓት ተኩል አናቱ ላይ! በፀጥታዋ የምትታወቀው በሬሳ
በኡኡታ ተደበላለቀች። ሰማዩ በነጎድጓድ ድምፅ ታረሰ... በሬሳ ወልዳ አሳድጋ ለከፍተኛ ቁም ነገር ያበቃችው ተወዳጅና ብርቅዬ ልጇን እንደ ክፉ ድመት መልሳ ወደ ማህፀንዋ ልታስገባ አፏን በሰፊው ከፍታ አዛጋች፡፡ መልአከ ሞት አስገምጋሚውን የነጕድጓድ ድምፅ አሰምቶ በመቅስፍት በትሩ የአስካለን ልብ ያለርህራሄ በረቃቀሰው... ልጅዋ ናፍቋት፣
በህልሟ እየተመላለስ ሲያቃዣት ከረመና፣ ናፍቆቱ ዐይኗን ሊያወጣው ደረሰና ዳቦ ቆሎ ቆርጣ አዘጋጅታ ወደ አዲስ አበባ ሄዳ ልጇን እቅፍ
አድርጋ ለመሳም ቸኩላ ዝግጅቷን በማፋጠን ላይ ነበረች። ያ እንደነ
ፍሷ የምትወደው የምትሳሳለት ልጇ ግን መንገዱን ሊያስቀርላት፣ አዲስ አበባ ድረስ ሄዳ እንዳትንከራተት ድካሙን ሊቀንስላት በእንጨት ሳጥን
ተሞሽሮ ወደሷ እየገሰገሰላት ነበር።
ዘይኑን፣ አማረችንና ባልንጀሮቹን የጫነው አውቶቡስ ከቀኑ አስር
ሰዓት ተኩል ላይ በሬሳ ሲደርስ መንደሪቱ በጩኸት ታመሰች። እማዬ! እማምዬ! ጉድ ሆን! ወንድም ጋሼ...ወንድም ጋሼ! ጌትዬ!ጌትሽ!…. የኔ ፍቅር! እናቱ አስካለ አስቀድሞ ምንም ፍንጭ እንዲደርሳት ሳይደረግ ተዘጋጂ! ተጠንቀቂ! ሳትባል ሳይነገራት መአት ወረደባት። ምፅአተ
ቁጣውን ያረገዘው የሰቆቃ ጭጋግ ጥቁር ደመናውን በደሳሳ ጎጆዋ ላይ በድንገት አጥልቶ እንደ ንስር አሞራ ሲያንዣብብ ቆየና በከፍተኛ ጭካኔ መአተ እርግማኑን እንደ በረዶ ያዘንብባት ጀመር።
የመኩሪያ አደራ! ስትል የኖረች እናት ከሷ በፊት ትንሹ ልጇ እሷን ቀድሞ አባቱን ጠያቂ ይሆናል ብላ ለደቂቃ እንኳ አስባ አታውቅም ነበር። እንኳን ሞቱ ረጅም
እንቅልፉ የሚያስጨንቃት ልጅ ጉንፋን ስለመታመሙ ወሬ ሳትሰማ አስከሬኑን እንድትሸከም ሲፈረድባት ምን ይባላል? ያልፍልኛል ብሉ ደፋ ቀና ሲል ከርሞ በማእረግ የተመረቀላት ልጇን ደስታ አጣጥማ ሳትጨርስ ከጎኗ በድንገት ስታጣው የሚስማትን ስሜት ምን ቃላት ሊገልጡት ይችላሉ? ምናልባት በአስካለ ላይ የደረሰባትን ሰቆቃ ምሳ ቋጥሮ እቅፎ ስሞ ትምህርት ቤት የሸኘውን ህፃን ልጁን በመኪና አደጋ የተነጠቀ ወላጅ፣ ለወሊድ ሆስፒታል ይዟት የገባ ጤነኛ ሚስቱን አስከሬን በድንገት የታቀፈ አባወራ፣ በሠርጓ ዋዜማ እጮኛዋ በተኛበት አልጋ ላይ እስትንፋሱ ተቋርጣ ያገኘች ሙሽራ የበለጠ ሊረዷት ይችሉ ይሆናል። በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የተደረገለት ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱ በሶስተኛ ቀኑ በዚያው በሆስፒታሉ ውስጥ እንዳለ ህይወቱ ያለፈው ልጇ አስከሬኑ
ተጭኖ መምጣቱና ከሷ ቀድሞ ከአባቱ መቃብር አጠገብ የቀብር ስርአቱ በህዝብ ፊት በአደባባይ ተፈፅሞ አፈር መልበሱ በገሃድ እየታየ ለደቂቃ እንኳ ሞቱን አምና መቀበል ተስኗት በድን ሆና ቀረች፡፡
በቀብሩ ዕለት የአማረችን አሳዛኝ የለቅሶ ዜማ፣ የእናቱን ሁኔታ፣ የእህቱን እሪታ ሰምቶ አንጀቱ ያልተርገፈገፈ፣በእንባ ያልተራጨ፣ በእዬዬ ጉሮሮው ያልተዘጋ አልነበረም፡፡ ለዚያ ምግባረ ሰናይ ልጅ፣ ላዚያ አመለ ሽጋ ልጅ፣ለዚያ ትህትናው ለተመሰከረለት ልጅ፣ ለዚያ ገና በለጋነቱ የአባቱን አደራ ሊወጣ የቤተሰብ ሃላፊነት ቀንበርን በጫንቃው ተሸክሞ
ሲጎትት ለኖረ ልጅ የማያለቅስ ማን አለ? ከእያንዳንዱ ሰው እንባ እንደ
ውሃ ተቀዳለት፡፡ የሰማይ አእዋፍ ጭምር ተንጫጩለት። አጅሬ ሞት አይረታ የበላውን አይመልስ ሆነ እንጂ....
በዚያን እለት በማህፀኗ የተሸከመችው የአራት ወር ፅንስ ትንሹ ጌትነት ከሆዷ ውስጥ ሆኖ እየረገጣት አማረች የሚከተለውን የሃዘን እንጉርጉሮዋን አሰማች...
ስንዴ ዘርቻለሁ ቡቃያው ያማረ፣
ዛላው ተንዠርጎ ተስፋን ያሳደረ።
ዘሮች ተበትነው በእፍኝ አፈር ላይ፣
ጎልቶ እንዲወጣ ምርጡ እንዲለይ፣
ተመራማሪዎች ተወራረዱና፣
ውጤቱን ለማወቅ አወጡ ፈተና።
እኩል እየበሉ እኩል እየጠጡ፣
አንደኛው ከሌላው ከተበላለጡ፣
ሊመርጡ ፈጣኑን ለልማት ሊያወጡ፣
ተስማሙ ባንድ ድምፅ ሽልማት ሊሰጡ፡፡
አያጠራጥርም ቡቃያዬ አደገ፣
ቀድሞ ለመበላት ለመድረስ ፈለገ፡፡
በከባድ ልዩነት ሁሉንም በለጠ፣
ተፈላጊነቱን በኩራት ገለጠ።
ታዲያ ምን ያደርጋል ሳይታይ ውጤቱ፣
ታጭዶና ተወቅቶ ሳይመዘን ምርቱ፣
አብቦ እንዳሽተ ፍሬ እንዳጋተ፣
ስሩ ተበጠስ ሞተ ተከተተ።
ቡቃያዬ እንጭጩ ቡቃያዬ ሆዴ፣
እጦማለሁ ብዬ ነይ ነይ ከሁዳዴ፣
ተስፋ ያደረግሁት ባንተ አይደለም እንዴ?
ጌትሽ ቡቃያዬ ጌትሽ ቀለበቴ፣
አጊጬ ሳልጠግብህ አድርጌህ ከጣቴ፣
ምነው ሾልከህ ጠፋህ ሆድዬ አንጀቴ?
ቃልህን አታጥፍም ብዬ ስኮራብህ፣
ሚስጥር ጠባቂ ነህ ብዬ ስመካብህ፣
አሳፈርከኝ ዛሬ አመኔታም የለህ፡፡
አይታችሁ ያጣችሁ እናንተ ፍረዱ፣
እምነትን ዘርታችሁ ክህደትን ስታጭዱ።
አበቃ ተስፋዬ ሞተ መነመነ፣
የመኖሬ ትርጉም ባዶ ቀፎ ሆነ፡፡
አልችለውምና ጧት ማታ እዬዬ፣
ክብርና ኩራቴ ጥላ ከለላዬ፣
አልቀርም ጠብቀኝ ጌትሽ እጮኛዬ።
የእናቱ የአስካለ ሁኔታ እንዲህ ነበር ተብሎ በቀላሉ የሚገለፅ አል
ሆነም፡፡ የሚያዩ ዐይኖቿ ታወሩ...
የሚሰሙ ጆሮዎቿ ደነቆሩ... የሚናገረው አንደበቷ ተዘጋ፡፡በዚያ በደካማ ሰውነቷ ላይ የወደቀባትን ክምር የስቃይ ሸክም መቋቋም ተስኗት አቅም አጣችና ራሷን ሳተች። ቀወሰች።
ሁለት ቀን ሙሉ ነፍሷ ሳትወጣ የሞተ በድኗ እየተጠበቀ ሳለ በሶስተኛው ቀን ላይ ማንም ሰው ሳያያት በእኩለ ለሊቱ ሹልክ ብላ ሮጣ ወጣችና በባሏና በልጇ መቃብር መካከል ወዲያና ወዲህ ስትንከላወስ ከቆየች በኋላ
የምትወደው ልጇን ተከትላ ባሏ አዘጋጅቶ ወደሚጠብቃቸው አዲስ ዓለም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አብራ ተቀላቀለች። አይ የሰው ነገር?!
ከደሙ ንፁህ መሆኑን ሳያውቅለት ለዘለዓለም አንደበቱ በመዘጋቱ የሸዋዬ ባል ቶሎሳ እንኳ“ሞት ሲያንሰው ነው” ሲል ነበር የፈረደበት።
#የመጨረሻው_መጨረሻ
#ሳኦልና_ጳውሎስ
ታደሰ በእውነቱ ከሆስፒታል እንዲወጣ ተደርጐ በመኖሪያ ቤቱ
ውስጥ አልጋ ላይ ከዋለ ልክ ሳምንቱ.. ለሰው ጥሩ መስራት ለራስ ነው። ታደሰን ለመጠየቅና ለማፅናናት በየጊዜው የሚመጣው ሰው ቁጥሩ
በርካታ ነው፡፡ በጠያቂ ብዛት መዳን ቢቻል ኖሮ ታደሰ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን በቻለ ነበር። ዛሬ ግን እያቃሰተ ህመሙን የሚያዳምጥበት ቀን አልነበረም፡፡ የምራቅ ዕጢዎቹ ማመንጨት አቁመዋል። ከንፈሮቹ ኩበት መስለው ደርቀዋል። ጥቁር መልኩ የጣፊያ ዓይነት መልክ
እየያዘ ሄደ...ወይዘሮ ወደሬ ማዕድ ቤት ውስጥ ጉድ ጉድ እያሉ ነበር።
ለጊዜው ሁለቱ ብቻ ነበሩ። ሰላማዊት የታደሰን ሁኔታ አጤነች፡፡ በየጊዜው እየሰለለች የመጣች ተስፋዋ ልትበጠስ መቃረቧን ተረዳች፡፡ ውድ ባሏ ሊለያት እንደሆነ ጠርጥራ ፍርሃት አደረባት።
“ታዴ! እየበረታህ ነው?” አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ በግራ
መዳፏ ትኩሳቱን እየለካች ጠየቀችው፡፡
“እህ!.. እህ!.. እህ.! ሰላሜ..” ዐይኖቹን በዐይኖቿ ላይ አንከራተ
ታቸው።ከሆስፒታል የወጣው የመዳን ተስፋው እየመነመነ በመምጣቱ ምክንያት መሆኑን አውቆታል፡፡ሚስቱን እያፈቀረና እየወደዳት ብቸኛ አድርጓት ሊሄድ በአስገዳጁ የሞት ጠንካራ ክንድ ተጨምድዶ መያዙን ተገንዝቦታልና ሙሉ ለሙሉ እጁን ከመስጠቱ በፊት አደራ ሊላትና የልቡን ሊነግራት ወሰነ።

👍10
የለወጥኩትን፣ እውነተኛ ስሜን ዘይኑ መኩሪያነቴን ሳልነግርህ መቅረቴ ነው የኔ ፍቅር፡፡ እስቲ አባዬ ባወጣልኝ እማዬና ወንድም ጋሻዬ ይጠሩኝ በነበረ ስሜ ጥራኝ? ዘይንዬ በለኝ? ኣንድ ጊዜ ብቻ ዘይኑ በለኝ? እንደ አባዬ፣ እንደ እማዬ፣ እንደ ወንድም ጋሻ ታዴ አንተም እንደነሱ ልትከዳኝ ነውና እስከምትለየኝ ድረስ ዘይንዬ እያልክ ጥራኝ?” በደረቱ ላይ
ድፍት ብላ ተንሰቀሰቀሰች። ከመክሳታቸው የተነሳ እንደ ጭራሮ በቆሙ ጣቶቹ ሆዷን እየደባበሰ “ስላምዬ እኔም እስከ ዛሬ ድረስ ያልነገርኩሽ እውነተኛ ስሜን ነበር። አጋጣሚው ግን በጣም ያስደንቃል፡፡ ታደሰ በእውነቱ የቆሸሽ አእምሮዬ የታደሰበት፣ በፈፀምኩት ክፉ ድርጊት የተፀፀትኩበት የቀድሞ ማንነቴን ለመሸሸግ የተጠቀምኩበት የምወደው መጠሪያ ቢሆንም በእውነተኛ ስሜ ላይ የተጀቦነ መከናነቢያ እንጂ እውነተኛውን የልጄን አያት ማንነት የሚገልፅ አይደለም።ታደሰ በእውነቱ በተግባርና
በአስተሳሰብ መታደሴን የሚያሳይ የምወደው መጠሪያዬ ቢሆንም እውነተኛው የልጄ አያት ስም ግን ሌላ ነው። የልጄ ትክክለኛው የአያቱ ስም ሐጂ ቦሩ ነው፡፡ እውነተኛው እኔነቴም ጉንቻ ቦሩነቴ ነው.....
የገደለው ባልሽ፣
የሞተው ወንድምሽ፣
ሃዘንሽ ቅጥ አጣ፣
ከቤትሽ አልወጣ፡
እንበላት ይሆን?......
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አሟሟቱ በበርካታ ጓደኞቹና የሥራ ባልደረቦቹ ልብ ውስጥ ጥልቅ
የሆነ ሀዘንን ተክሎ ላለፈው ተሸላሚ የተበረከተለትን የአበባ ጉንጉን በመካነ መቃብሩ ላይ ያኖረው አብሮ ተሸላሚው ታደሰ ገብረ ማርያም ነበር።
✨ተ ፈ ጸ መ✨
#የተወጋ_ልብ ይሄን ይመስላል ብዙ አስተያየት እንደሚኖራችሁ አምናለው ጥሩም ይሁን መጥፎ አስተያየት ወዲህ በሉ እስቲ እጠብቃለሁ።
ሌላው በቅርቡ #ምንትዋብ የሚል ታሪካዊ ልብ ወለድ የደራሲ ሕይወት ተፈራ ስራን ለማቅረብ አስቢያለሁ እዚም ላይ በቅድሚያ ያላችሁን አስተያየት ልወቅ አድርሱኝ አመሰግናለው
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍6