አትሮኖስ
279K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ትልቁ የሮማ ስታዲዬም በተመልካቾች ተጨናንቋል፡፡
መንገዶች ተጣበዋል
ለተሽከርካሪ ዝግ በሆነው መንገድ ላይ ህዝቡ
እንደ ጉንዳን ይርመሰመሳል፡ ሳቅ ጨዋታ, ዳንኪራ ሁሉም እንደየግል ዝንባሌው ያሻውን ይፈፅማል። ከዘመናዊው ስታዲዬም
በጣልያንኛ በእንግሊዝኛ• በፈረንሳይኛ… ስለውድድሩ ታላቅነት ስለ ውድድሩ አጀማመር ተወዳዳሪዎች ምርጥነት ስለ ያሸንፋሉ
ተብለው ስለሚገመቱ አትሌቶች በተለያየ ቋንቋ ይተነበያል።

አኜስ ሎካዬን ወደ ሮማ እንዲሄድና ውድድሩን እንዲያይ ያግባባቸው ከብዘ ልፋትና ድካም በኋላ ነው፡፡

“…ሉካዬ ውድድሩን ማዬት መቻል አለብን!” ስትለው:

"አኜስ አንች ሂጂ እኔ ግን እዚሁ መቆየት እፈልጋለሁ።
ምናልባት አንቺ ከተመለሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ሄጄ ዘመዶቼን ብፈልግ ደስ ይለኛል"

“ሎካዬ አብረኸኝ እንድትሆን እፈልጋለሁ: ጣልያን ውስጥ ጥሩ የመዝናናት እድል ይኖረናል። ወንድሜና ሴት ጓደኛው አብረን እንድንሆን ይፈልጋሉ ልጃችንም ክሪናም ከሁለታችን ጋር መሆኑን
እንደምትመርጥ ነግራኛለች፡፡

“ሊሆን ይችላል አኜስ ከእነሱ ይልቅ አንች እኔን በሚገባ ታውቂኛለሽ፡ ሮማ በመሄድ ደስተኛ ይሆናል ብለሽ እንደማትገምች
ነው የማስበው፡ እዚህ ብሆን ግን ቢያንስ የልጅነት ጊዜዬን እያሰብኩ
በፀጥታው ልዝናና እችላለሁ: ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስም በመሄድ
በማዕበሉ ውሃ እግሮቼን እየነከርሁ ለመደሰት እሞክራለሁ: ሮም ሄጄ ግን ጎንና ጎኔ ጨዋታ ወዳድና ደስተኛ ሰዎች ይቀመጡና
እየጎነታተሉ እንድጫወት ተፅዕኖ ያደርጉብኛል፡፡ እየቆየ ግን ዝምታዬ እየከበዳቸው ሲመጣ ይሸሹኛል። ያኔ ጩኸቱ በሚያስበረግግ
ፀጥታ እዋጥና አዕምሮዬ ይረበሻል። ስለዚህ አኜስ! እባክሽን እኔን እንሂድ ማለትሽን ተይኝና ከሌሉች ጋር ሄደሽ ተዝናንተሽ ተመለሽ አላት ረጋ ብሎ

“ኦ አምላኬ! ለምን ይኸን ቅዠትህን አታቆምም። ስግብግብ አትሁን እሽ! ለሌሎች ደስታ ማሰብ መቻል ኦለብህ፡ ግትርነትህንና
የገነተረ አስተሳሰብህን አለዝበው" አፈጠጠችበት፡፡

…ለሌሎች ደስታ ማሰብ መቻል አለብህ አባባሏ ውስጡን ረበሸው፡ ሉካዩ ራሱን አይወድም ሌሎች ደስ ሲላቸው ማየት
ያረካዋል። እራሱን ግን ለማዝናናት እንዳይችል በልጅነቱ ከወላጆቹና
ከዘመዶቹ ካደገበት ቀዬ ነጥቀው በጭንቀት በሃዘን… እያለቀሰ!
ማንነታቸውን የማያውቃቸው ሰዎች እንደ
አውሬ  ደስታውን
ገነጣጥለው በልተውበታል፡ ተስፋውን  አምክነውበታል፧ ስሜቱን ጭምትርትር አድርገው አኮራምተውበታል፡፡ እድሜው እየጨመረ
በሄደ ቁጥር ከጠባሳው በታች ሊድን የማይችል የቁስሉ ጎሚ እየበረታበት መጣ። ራሱን ሊያክም ሞከረ ውስጡ ግን እያመረቀዘ በሰራ አካላቱ የስቃይ መርዙ ተሰራጨ፡

“አኜስ! ለምን ስቃዬን አትረጅልኝም ሁሌ ለሞን አሸናፊነት ትመርጫለሽ!"

“ሎካዬ! ተው እንዲህ ምርር አትበል ልለይህ አለመፈለጌ
ላንተ ካለማሰብ የመጣ ነው ብለህ ታስባለህ? እንደዚያማ ላለማሰብ
ሞክር" ብላ አንገቷን ሰበር ስታደርግ ሎካዬ ጠጋ ብሎ ፀጉሯን ደባበሰና፡-

“ይቅር በይኝ እሽ አብረን እንሄዳለን" ሲል ቀና ብላ
አይታው እንባዋ ከአይኖችዋ ረገፉ:: ሎካዬ ግን እንባዋን ማየቱ
ከብዶት ፀጉሯን ስሞ ወጣ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በተለያየ ቀለማት ያሸበረቁ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሜዳውን ሞልተው እክሮባት ሲያሳዩ እንደቆዩ እውቁ ጣሊያናዊ አቀንቃኝ
ከሙዚቃው ጋር አጣጥሞ ድምፁ ሲያስረቀርቀው በስቴዲየሙ ውስጥ
ያለው ህዝብ አድናቆቱን በጭብጨባ በፉጨት በጩኸት በጥሩንባ በከበሮ
ሲገልፅ ድምፃዊው አሳ እንደሚውጥ ትልቅ አሳ ፉን
ከፍቶ ሲዘፍን በስታዲየሙ ዙሪያ የተደገኑት ማጉያዎች ድምፁን አስተጋቡት:: አሁንም ጭብጨባ ጩኸት ደስታ ሁካታ ሆነ፤
ጭፈራው ቀለጠ፡ ርችት ተለኮሰ፡፡

ከዚያ ከያገሩ የመጡት ሯጮች ወደ መወዳደሪያው ቦታ ሲወጡ  ተመልካቹ
ቆሞ በጭብጨባ
ተቀበላቸው፡፡ ከያገሩ
ስለተወከሉት ተወዳዳሪዎች ማንነት ጋዜጠኞች በየቋንቋው መዘርዘር
ቀጠሉ፡

አኜስ ሎካዬ ከሪናና የአኜስ ወንድም ከሴት ጓደኛው ጋር
ሮም ስታዲዬም ናቸው: ከሎካዬ በስተቀር ሁሉም ያጨበጭባሉ ብድግ ቁጭ ይላሉ ይለፈልፋሉ… ሎካዬ ግን  በብዙ ሺ ህዝብ መሀል ሆኖ ያልማል የልጅነቱን ህይወት  የወላጆቹን ቀዬ...

ተወዳዳሪዎች ተደረደሩ፤ ችቦው ተለኮሰ፤ ማራቶን  የሮማ ማራቶን ተጀመረ፡

ከዚያ በስቴዲየሙ ውስጥ የጥቂት አትሌቶች ገድልና
በዛኔው ውድድርም ያሸንፉ ይሆናል የሚለው ግምት ተለፈፈ፡፡አውሮፓውያን  አሜሪካውያን ሩቀ ምስራቆች የአሰለፏቸው
አትሌቶች መጠን በ ውድድር አፍሪካውያን ተወዳዳሪዎችም በተወሰኑ አትሌቶች መወከላቸው ተነገረ፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራት መቶ ዘጠና በፔርሽያና አቴና በተፈጠረው ድንገተኛ የጦር ወረራ ትንኮሳ የተደናገጡት
አቴናውያን ፊዲፒደስ የተባለውን ጀግና ስፖርት ላኩት: ፊዲፒደስም
ለሃምሳ ሰዓታት ካለ ምግብና መጠጥ ሩጦ መልዕክቱን አድርሶ
በመመለሱ ውጊያው ተጀመረ፡፡

የአምባገነኑ የፔርሺያ ኃይል
ግን የማታ ማታ ሟሾ የውጊያው ድል ፎክሮ  ጦር አውድማ ከሄደው ከፔርሽያው መሪ
ከዳሪዮስ እጅ ወጥቶ አቴናውያን እጅ ገባ፡፡

የአቴና ፍቅር ያማለለው ጀግናው ሯጭና ተዋጊ
ፌዲፒደስም ያንን ያገሩን ታላቅ ድል ሲያይ ደስታ
ፈንቅሎት አቅጠበጠው ስለዚህ  ያንን ታላቅ ድል ለወገኑ ለማብሰር ቂጤማ
የያዘች እርግቡን ህሊናው ቆጥ ላይ አስፍሮ ሀያ ሁለት ማይልስ ካለ እረፍት የተነሳውን ክቡር ቃል ሊያደርስ ሮጠ፡፡

ፊዲፒደስ ከተማ
ሲደርስ አካሉ ደክሞ ! ሕይወቱ የተንጠለጠለችው ጠንካራ ሞራሉ ላይ ነበርና ወገን ሊያገኝ ያን
እንደ አልማዝ የሚያንፀባርቅ ቃል እያከለከለከ “ቪክትሪ" ብሉ ቃሏን ብቻ አሰምቶ ህዝቡ ሲደሰት እሱ ግን ሕይወቱን ለአገሩ ድል ሰዋ እየሳቀ አንቀላፋ!

መልካም ሥራና እውነት
ግን ውሎ አድሮ ከትቢያ
መነሳታቸው የክብር ሥፍራቸውን መያዛቸው አይቀርምና በአስራ
ስምንት መቶ ዘጠና ስድስት ግሪኮች የፊዲፒደስን ውለታ ለመክፈልተ ተስማሙ፡፡ መልካሙ ስሙን ከመቃብር ውጭ ሊያውለበልቡት
አቀዱ! ስለዚህ ባምላካቸው መሪ በዜውስ ስም ሰይመው የኦለምፒክ
ማራቶን ጀመሩ… ያ የመልካም ስራ ሽቶ መዓዛም አለማችንን
አወዳት፡፡ ከዚያ የማራቶን ሩጫ ውድድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንና በምዕራባውያን አገሮች በተለይ ሩጫን ዘመናዊ
ለማድረግ ሳይንሳዊ አሰለጣጠን ዘዴዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን አትሌቶች ከህፃንነታቸው ጀምሮ እየተመለመሉ ድንቅ
ተወዳዳሪዎችን ማፍራት መቻሉም ተናገረ፡፡

ሚዲያዎች ተወዳዳሪዎች የደረሱበትን ማን እየመራ
እንደሆነ ገለፁ፡፡የሚመራው  አፍሪካዊ' ነው ሲባል ስለ ዘመናዊ የሩጫ አሰለጣጠን ዘዴ የሰማው ተመልካች ግራ የገባው መሰለ፡፡ብዙዎች ግን በማራቶን እሩጫ ትልቁ ዘዴ ትንፋሽን መጠበቅና ሃይልን እየቆጠቡ ቆይቶ የተወስነ ርቀት ሲቀር አፈትልኮ እንደ
ቀስት መወርወር ነው፡፡ ሲጀመር አካባቢ የቀደመ በስተመጨረሻ አትሌቶችን እየተሰናበተ ውራ ይወጣል' እየተባባሉ ተሳለቁ፡፡

ህዝቡን ከሚያዝናና ዝግጅቶች ጣልቃ ላይ  የማራቶን ተወዳዳሪዎች ደረጃ እንደገና ተጠቀሰ:: አሁንም “አፍሪካዊው
👍25🥰2👏21🔥1😁1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታረ


“ሶራ ልታስብበት ይገባል" አለችው በጥሞና እያየችው፡
"ወደ ኢትዮጵያ አብሬሽ ልሂድና የአያትሽን የትውልድ ቦታ ላፈላልግሽ እፈልጋለሁ፡፡ ያሳየሽኝ መቀመጫ ታችኛው የኦሞ ወንዝ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ማህበረሰቦች በሙሉ ይጠቀሙበታል። ኤርቦሬ
ሐመር በና ካሮ መቀመጫው በእርግጥም የኦሞ ህዝቦች ብቻ
እንደሆነ አምናላሁ" አላት።

ጥሩ! እኔ የተዘጋጀሁት ለአንድ ሰው በሚበቃ ባጀት ነው" በግልፅ ችግሯን ገለፀችለት፡

“እኔ ደግሞ የራሴን እችላለሁ በዚያ በኩል አታስቢ"

አመሠግናለሁ ሶራ በእውነት አንተን ማግኘቴ ያላሰብሁት
እድል ነው" ብላ ፈገግ አለችለት::

ሶራና ኮንችት በዚህ መልክ ለአፍሪካ ጉዞዋቸው
መሰናዶአቸውን አብረው ቀጠሉ፡፡

ከሁዌልቫ ሊዝበን በመርከብ የሚፈጀወ ጊዜ ግማሽ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከጅበላርታር ለንደን በሚወስደው የጉዞ መስመር መርከቡ
አቅጣጫውን ካስተካከለ በኋላ ተጓዡ እንደየግል ፍላጎቱ ተሰማራ፡፡

ኮንችትና ሶራ በመርhቡ ግራ ጎን ባለው ማማ ላይ ወጥተው በርቀት የተዘረጋውን የአትላንቲክ ውቅያኖስ እያዩ ተቀምጠዋል፡፡
ኮንችትና ሶራ የለበሱት ነጭ ቲሸርት ነው፡፡ በሁለቱ መካከል የአለባበስ ልዩነቱ ኮንችት ነጭ አጭር ቀሚስ በሰፊ ቀበቶ ሶራ
ደግሞ ቡላ ሲልክ ሱሪ መልበሳቸው ነው፡፡ ሁለቱም ጥቁር የፀሐይ መነፅር አድርገዋል። ቀኑ ሞቃታማና ፀሐያማ ነው፡፡

ወደ ሊዝበን የመሄዱን ሐሳብ ያመጣችው ኮንችት ናት ሶራን የተለያዩ ቦታዎችን ሙዚዬሞችን ታሪካዊ ቦታዎችን መዝናኛዎችን… እንዲያይ ብዙ ጊዜ እየጋበዘች ወስዳዋለች፡፡

ስለ ፖርቹጋሎች ምን ታውቃለህ?" አለችው  አንድ ቀን በማድሪድ ከተማ መናፈሻ ውስጥ እንደተቀመጡ፡፡

“ባህረተኞችና ቅኝ ገዥዎች እንደነበሩ"

“አዎ! ፖርቹጋሎች ማንም እሚያውቃቸው በባህር ላይ
ህይወታቸውና ለቅኝ ገዥነት በብዙው የዓለም ክፍል በተለይም በአፍሪካና በላቲን አሜሪካ ያደርጉት የነበረውን ቅኝት ነው፡ ይህ ጥንት ሌላው ስለእነሱ ያውቅ የነበረው እውቀት ነው በአሁን ሰዓት ግን ፖርቹጋል ብዙ ቱሪስት የሚስተናገድባት አገር ናት።

“ሙዚየሞቻቸው የዓለምን ቅርስ የያዙ ናቸው ይባላል።
ስለ ዓለም ይበልጥ ማወቅ የማፈልገው ይህ ትውልድ ደግሞ ቅርሶች አሉ የተባለበት መጉረፉ የተለመደ ነው፡፡

“አፍሪካ የራሷ ካሏት ቅርሶች ይልቅ በአውሮፓ ያሏት ቅርሶች ይበልጣሉ፡ የሚያሳዝነው ግን አፍሪካ ለቅርሷ የባለቤትነት
መብት የላትም፡፡ በኮለኒያሊስቶች የተዘረፈችው ቅርስ አሁንም የእነሱ ኪስ ማድለቢያ ነው፡፡

“ከኢትዮጵያ የመጡ
ቅርሶች ከዚህ በፊት ፈረንሳይ እንግሊዝ ጣሊያን… ሄጄ አይቻለሁ፡፡ ፖርቹጋልም እንደዚሁ ብዙ
የሃይማኖት መጽሐፍትና የታሪክ ቅርሶች አሉ: አንዳንዴ ሳስበው እንዲያውም ኢትዮጵያውያን
የታሪክ የባህል ተመራማሪዎች ወደ ፊት በአገራቸው ታሪክና ባህል ላይ ምርምር ማድረግ ቢፈልጉ ዋቢ ቅርሶችን ለማየት ወደ አውሮፓ ብቅ ማለታቸው የግድ
ይመስለኛል

“አውሮፖና በሌላው የሰለጠነው ዓለም አንድ ወቅት የቅርስ ዝርፊያ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በስምምነት አንዱ ዘንድ ያለው ወደ ሌላው እየተመለሰ ነው። ባይመለስ እንኳን የዛ ቅርስ ባለቤት
የሚሆነው በመጀመሪያ ባለቤት የነበረው አገር ነው፡፡ ለዚህ ውጤት
ግን ብዙዎች ልሳናቸው እስኪዘጋ እየጮሁ ታግለዋል፡፡ ግዞት ስደት
እስራትም ደርሶባቸዋል: አሁን ግን ቀስ በቀስ ህልማቸው እውን
እየሆነ ነው:

ሶራ አንተም ፖርቹጋል ያሉትን ሙዚየሞች ስታይ
እርግጠኛ ነኝ ብዙ የአገርህን ቅርሶች ታያለህ የኢትዮጵያ ቅርሶች
የሚል ጽሁፍ ግን አይታይባቸውም፡፡ አንድ እውነት ግን በህሊናህ
ይመጣል! ቅርስ ለአንድ ሀገር ህዝብ ማንነት ምን ያህል አስፈላጊ
መሆኑን ትገነዘባለህ፡፡

የአውሮፓውያን ስልጣኔ ባሰባሰቡት ቅርስ ላይ የተመስረተ ነው ለቅርሶች ልዩ ከበሬታ መስጠትም የአንድ ሃገር ስልጣኔያዊ
ብስለት መለኪያ ነው፡
“ሶራ ስለ! ሌላውን ለማወቅ ከሌላው ለመማር ራስሀን
ለማነፃዐር ያጣኸውን ለመፈለግ… ጉብኝት አስፈላጊ ነው" አለችው፡፡

ልክ ነሽ ኮንችት ለምን ለጊዜው ፖርቹጋልን አብረን
አናይም?” አላት፡
“በደስታ! ሶራ" ብላ ሳቋን ለቀቀችው: ኪሊሊ... የሚለውን ሳቋን ሰማው: ናፍቆት ነበር ሣቋ::

“ሳቅሽ ደስ ይለኛል አላት ፈገግ ብሎ፡፡

“አመለግናለሁ” አለችው። ኪሊሊ ብላ እየሳቀች:: እያያት አሰበ: ሌላውን ማወቅ ነው….. የተናገረችውን አስታወሰ፡
አውሮፓውያን ስልጣኔ  ባሰባሰቡት ቅርስ ላይ የተመሰተ ነው ገረመው: በልተህ በልተህ ወደ አገርህ አንጋጥ ተሪቱማ እሱም
አገር አለ፡፡ ተግባሩ ግን ጠፋ፡፡ ሌላው እስኪጀምረው መጠበቅ አንዱ የአፍሪካውያን ችግር ነው። እና የሚጠቅመውን  ሁሉ  ለአገሩ ጆሮ
ለማድረስ ለአገሩ ሕዝብ ለማሳየት የተማረውን ዜጋ ህሊና ለማንኳኪያ ከእንቅልፍ  ለመቀስቀሻ ሊጠቀምበት እንደሚገባ ቃል ገባ: እራሱን ግን ተጠራጠረው “ፍርፋሬ ያዘናጋኝ ይሆን?” አለ።

ኮንችት ያለውን አልሰማችም፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሁለቱ መንገደኞች መርከቡ ጉዞ ከጀመረ በኋላ
ጨዋታቸውን ጀመሩ፡፡

“…ለወላጆቼ የመጀመሪያ ነኝ፡ ከኔ በታች ሁለት ታናናሽ
ወንድሞች አሉኝ፡ በተለይ ከኔ ተከታይ ጋር በሰፊ አልጋ አብረን ነበር የምንተኛው።

አባቴ ፍራንሲስኮ ፔሶ ቤኒ ለወደፊቱ መፃኢ እድላችን
ስለሚያስብ ገንዘብ ለማስቀመጥ ቢጥርም ግማሽ ኢትዮጵያዊቷ እናቱ
ካሪና ግን ለግል ውበቷ ብቻ የምትጪነቅ አባካኝ በመሆኗ አባቴ
እንዳሰበው ገንዘብ የማስቀመጥ ህልሙ አልሳካ ሲለው በእናቴና
በአባቴ መካከል አለመጣጣሙ እየበዛ በመምጣቱ ተለያዩ በዚህ
ሳቢያ አባቴ ወደ ቤታችን የሚመጣው በጣም እየቆዬ ሆነ፡ እኔ ደግሞ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኔ መጠን የአባቴን ፍቅር በምሻበት
ወቅት ላገኘው ባለመቻሌ ከልቤ ጠላሁት ስለዚህ ከአባቴ ይልቅ ለኢትዮያዊው አያቴ ለሎካዬ ሆነ ፍቅሬ” ብላ ክሊሊ… ብላ ሳቀች
እሱም ፈገግ አለ ጉሮሮዋን ለማራስ የቆርቆሮ ቢራዋን ለመክፈት ዘወር ስትል የቢራው ቆርቆሮ ወደቀባት ለማንሳት ጎንበስ ስትል
አየው  ጥቁር ፓንቷን

አፈር አለና ፊቱን ወደ አትላንቲክ ውቂያኖስ አዙሮ
ሲመለከት hርቀት የሆነ ብረት አዬ

ኮንችት ተመልከች ያ ምንድው?” አላት።

መርከብ ነው የመሬት ክብነትን  ስትማር ስለዚህ
አልተማርህም..."

አዎ አሁን ትዝ አለኝ: ሳታይ የተማርሽው ቶሎ
ይዘነጋል እሽ ጨዋታሽን ቀጥይ? አላት አንጋጣ አንዴ ጉንጯን ሞልታ ተጎነጨችና

"ኧህ ብላ ጨዋታዋን ያቆመችበትን አሰብ በማድረግ

ቸበርቻቻ ወዳጅዋን እናቴን ግን እወዳት ነበር በፊት
እንነገርሁህ በቁመናዬ ሳቢያ በትርፍ ጊዜዬ የግል ገቢ ማግኘት የጀመርሁት ገና በህፃንነቴ ቢሆንም እናቴ እናደ ሌሉች ልጆች
አስባ ልብስ ስለማትገልኝና ከሷ የምጠብቀውን አንድም ቀን "ቆንጆ ብላኝ ስለማታውቅ ለእሷ የነበረኝ ፍቅር እየሟሽሽ የጥላቻ
ስሜት ህሊናዬን ይተናነቀው ጀመር አንድ ቀን እንዲያውም አባቴ ጠፍቶ ከርሞ በመጣበት አጋጣሚ
እናቴና አባቴ አንድ ላይ በሚገኙበት ወቅት ጠባቂ በነበረኝ ገንዘብ ላይ ስጦታ ገዝቼ አልጋቸው ላይ አስቀመጥኩላቸ
ንግግሯን ሳትጨርስ ሶራ
አቋረጣትና

ይቅታ ስላቋረጥኩሽ የዚያን ጊዜ የስንት ዓመት ልጅ ነበረሽ።

ምናልባት የአስራ አራት ዓመት ከዚያ አይበልጠኝም
አለችው።

እሽ ቀጥይ አላት ሶራ
👍21
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

“እናቴም አባቴም ስለዚያ የልጅነት ስጦታዬ ትንፍሽ ሳይሉኝ ስጦታውን ግን እየተቀባበሉ ሲያዩት አይቻቸዋለሁ ይህ ደሞ አይወዱኝም ማት ነው የሚል ስሜት ፈጠረብኝና
ያልደነደነችው ልቤ ሐዘን እንደ ደሰቀ ዳቦ ነካከተች ከዚያን ቀን በኋላ ከነሱ የምለይበትን ቀን ማሰላሰል ጀመርሁ

“በየቀኑም ከነሱ ለመራቅና እነሱን ለመርሳት ስል የወንድ ጓደኛ ያዝሁ
የያዝኋቸውን የወንድ ጓደኞቼን እንድርቃቸው ተገደድሁ።

“እናቴ እንደነገርሁ የስነ አዕምሮ ትምህርት እውቀት
አላት ይሄ እከሌ የሚባለው የወንድ ጓደኛዬ ነው ስላት፡-

የጨካኝ ሰው መልክ ነው ያለው፡፡ ወንጀል ለመሥራት ወደ ኋላ አይልም…” ትለዋለች ወይም ደግሞ፡-ዠ

“ይኸ ጅላጅል ነው: የታወረ አዕምሮ ያለው ነው፡፡ እና
እሱን ስትመሪ መኖር ትፈልጊያሽ" ትለኛለች፡፡ ሌላውን ሳስተዋውቃት
ደግሞ፡-

ይኸ ጭልፋ አፍንጫ አንድ ቀን አይንሽን ያወጣዋል: እንደ ጣውላ የተላገ የሚመስል የወንድ ቅርፅ የሌለው... እኔ አንችን
ብሆን ኖሮ ከሱ ጋር በሆንሁ ቁጥር በጥላቻ አስመልስ ነበር….እያለች ስታጥላላብኝ ከያዝኋቸው የወንድ ጓደኞቼ በሙሉ ራቅሁ: በኋላ ግን ወደ ቤታችን አልፎ አልፎ ብቅ ከሚለው የእናቴ ጓደኛ
ልጅ ጋር ግንኙነት ጀመርሁ፡

ፔድሮ ይባላል፡ ሙልቅቅ ያለ ባህሪው መያዣ መጨበጫ የሌለው ነው፡፡ ከፍቅር ይልቅ የጦርነት ታሪክ ማውራት ይወዳል:
ህዝብ ከተጨናነቀበት መዝናኛ መሃል ይወስደኝና ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ እየጮኸ ጩኸትና ሁካታ አልወድም' ይለኛል ማን
ለምኖህ መጣህ? ደሞ ማንስ ጩኸት ይወዳል እንዳንተ ካለው ደደብ
በስተቀር' እልና በሃሳቤ እነቂው እነቂው ያሰኘኛል፡፡ አማራጭ ግን አልነበረኝም፡፡ ወላጆቼን ለመርሳት ስል በሄደበት ሁሉ እንደ ግል
ውሻው ካለሰንሰለት እየተሳብሁ እሄድለታለሁ! ሁኝ ያለኝንም እሆንለት ጀመር፡፡ እናቴም ከእሱ ጋር መሆን ደገፈችልኝ
የማላይበትን ውበት እየደረደረች አይታይሽም፧ እስኪ ተመልከች
እያለች እራሴን አይነ ስውር እንደሆንሁ እስክቆጥር ድረስ ግራ አጋባችኝ፡፡ ስለዚህ ፔድሮን በእናቴ ግፊት ልወደው ሞከርኩ፡
“የግንኙነቴን ጥልቀትና እንደ እንቁላል ተጠንቅቄ
እንደያዝሁት የተገነዘበው
ፔድሮ ግን ልቡ እያበጠ
ለፍቅር የዘረጋሁሉትን ልቤን ይጠብሰው ጀመር! እየቆየም በመጥፎ ባህሪው እየወጋጋ ማድማቱን ቀጠለ፡፡ ከእሱ ከተለየሁ ብቸኝነቱን ስለማልችለውግን
ስቃዬን አምቂ በትዕግስት እየተለማመጥሁ
የሞዴሊስነት ፍላጎቴን ገትቼ ለሶስት ዓመታት የመከራ ጊዜ አሳለፍሁ?።

“ሶራ! የሚገርምህ ደግሞ ያ የጭራቅ ልጅ አንድም ቀን "ቆንጆ ነሽ" ብሎኝ አያውቅም፡፡እንደወላጆቼ እሱም  አሞካሽቶኝ
አለማወቁ ደግሞ ፍርሃት ለቀቀብኝ፡፡ ከውጪ ሰው ይልቅ እነሱ ቆንጆ ነሽ ቢሉኝ ደስተኛ እሆን ነበር፡ ይህን ባለማለታቸው ግን
እራሴን ለማወቅ ወደ ሞዴሊስትነቱ ሞያ ተመለስሁ፡፡ ጅምናዚዬም
መሄድ አዘወተርሁ፡ በቁንጅና ውድድር ከተመረጡት አንዷ ብሆንም
ማሸነፍ ባለመቻሌ በገንሁ፡፡ ፔድሮ ያኔም ይጀነንንብኝ ነበር በመጨረሻ በቁንጅና ውድድሩ ባሽነፍሁበት እለት እናቴ አበባ አበረከተችልኝ፤ እሱ ግን ሳይመጣ ቀረ፡፡

“የሚገርምህ ያን ጭራቅ እንዲያ አንጀቴን እየበጣጠሰ ሲጥለው ልርቀው አልቻልሁም፡፡ ስለዚህ ከስፔን ውጭ ሄዶ ሥራ መስራት ማስታወቂያ ሲወጣ ከቤተሰቦቼ ለመራቅና እፎይታን
ለማግኘት አመች በመሆኑ እሱም እንዲወዳደርና አብረን እንድንሄድ
ጠየኩት፡፡

“ምን እንዳለኝ ታውቃለህ? ማራኪዋን አገሬን ጥዬ የትም አልሄድም አለኝ፡፡ የዚያን ቀን ብቻ ደፍሬ ገሃነም ግባ ብየው
በማስታወቂያው መሰረት ሄጄ አፍሪካ በተለይም አያቴ አገር ኢትዮጵያ እንዲመድቡኝ ጠየኳቸው፡፡ ሆኖም አላሰመረም፡ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች እንጂ ኢትዮጵያ ከዝርዝሩ
ውስጥ እንደሌለችበት ሲነግረኝ እጢዬ ዱብ አለች፡፡ ከዚያ በኋላ ግን
ምርጫዬ አስፈላጊ ስላልነበረ የትም መድቡኝ ስላቸው ቡርኪናፋሶ
መደቡኝ፡፡
ሶራ የሚሳዝንህ ፔድሮ ውጭ አገር እንደማይሄድ
እንዳልነገረኝ ሁሉ ሃሣቤን ቀይሬ ተወዳድሬ ላቲን አሜሪካ ብራዚልን አግኝቻለሁና አብረን እንሃድ' አለኝ፡፡

የዛኑ እለት እኔጋ የነበረውን የአፓርታማችንን ቁልፍ
ወርውሬለት ሁለተኛ አጠገቤ እንዳይደርስ አስጠንቅቄው ሄድሁ፡፡ ከሱ
ከተለየሁ በኋላ ግን አይኔ የፈረጠ እስኪመስለኝ ድረስ ሳለቅስ አደርሁ: ጠዋት ከመኝታዬ ስነሳ ትክክለኛ ውሳኔ መወስኔን በመረዳቴ ትልቅ እፎይታ ተሰማኝ፡፡

“በልጅነቴ የወላጅ.
ከአደግሁ በኋላ ደግሞ የፍቅረኛዬ 'አፈቅርሻለሁ' አለማለት የማልወደድ
ቢያደርገኝም ወደ አፍሪካ ከመሄዴ ሦስት ወራት በፊት
የተዋወኳቸው የተለያዩ ወንዶች ግን ውበቴን እያዩ የተንጠለጠለ ሥጋ እንዳየ ድመት እየተቁለለጩ  ሲያላዝኑ ስሰማና በተለይም
በጓደኝነት የያዝሁት ፎራንችስኮ መላ ሰውነቴን እየላሰ “ቆንጆ ነሽ…
ውሸት  ነው!.." እያለ  ደርቆ የነበረውን ሞራሌን  በፍቅር ዜማ ሲያረሰርሰው ድርቆሹ ሞራሌ እንደገና ለመለመ፤ እንደገና ታነፀ….አፍሪካ ሄጄ ስመለስ ግን የቁንጅናን ትልቁን ትርጉም አወቅሁት‥
አካላዊ ሳይሆን ህሊናዊ መሆኑን….

“ሶራ! ይታይሃል ከፊት ለፊታችን ሊዝበን ናት
የፖርቹጋል ዋና ከተማ፡፡ ወደ ጕብኝት ቦታችን እየደረስን ነው" ብላው ከመርከቡ መቀመጫ ተነሳችና ሄድ ብላ ወገቧን ለማንቀሳቀስ ከወገቧ እጥፍ ብላ ስፖርት ስትሰራ አየው  ጥቁር ፓንቷን…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
"ሔሉ… ሔሉ… ካርለት አልፈርድ ነኝ ከአዲስ አበባ"

"ሃይ ካርለት! ደህና ነሽ? ስፖንሽኛውን ስታቀላጥፈው
ገረመኝ እኮ"

“እውነትሽን አመሰግናለሁ፡፡
አዲሳባ ከመጣሁ
አምስተኛ ቀኔ ነው፡፡ ወደ ሐመር ከአንድ ሣምንት በኋላ እሄዳለሁ፡፡ መቼ ልትመጭ አስሰሻል?"

“አዝናለሁ ላገኝሽ የምችል አይመስለኝም፤ ምክንያቱም እኔ ከማድሪድ ወደ ሮም ከዚያ ወደ አዲሳባ የምበረው የዛሬ አስራ
አምስት ቀን ነው፡፡ ባገኝሽ ደስ ይለኝ ነበር፡፡

“አልችልም ኮንችት ቶሉ መሄድ አለብኝ፡፡ ምናልባት…" ካርለት ፀጥ ብላ አሰበችናi “ምናልባት አዲሳባ ስትመጭ የሚቀበልሽ ሰው ላስተዋውትሽ እችላለሁ፡፡ ሔሎ! …”

“አመሰግናለሁ ካርለት፡፡ አንችን ማግኘት ካልቻልኩ ለጊዜው ችግር የሚያጋጥመኝ አይመስለኝም፧ አብሮኝ የሚመጣ ኢትዮጵያዊ
አለ  ሔሎ!"

“ሔሎ  ኢትዮጵያዊ!” ካርለት አዕምሮዋ ደነሰባት፡፡

“ጥሩI እንግዲያው እዚህ ከመጣሽ በኋላ" ተቀጣጠሩና ካርለት ስልኩን ዘጋችው፡፡ በአይነህሊናዋ ኮንችትን ልታስታውሳት
ሞከረች ረጅም ሸንቀጥ ያለች ውብ ጠይም! ካርለት ከንፈሯን እንደ ጡጦ ጠብታ እራሷን ወዘወዘች፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::
ካርለት ዋና የለመደችበትን
ጊዜ አታስታውሰውም፡
ምናልባት በእናቷ ሆድ ካለበለዚያም ገና ጨቅላ እያለች፡ ቁም ነገር
ብሎ የነገራት የለም፡፡ ጥሩ ዋናተኛ ሆና ነው ራሷን የምታውቀው፡
ግዮን ሆቴል የሄደችውም ለመዋኘት ነው፡፡ ብቅ ጥልቅ, ብቅ ጥልቅ
ውሃው ውስጥ ግልብጥ እያለች የግዮንን ሆቴል መዋኛ በቁመትና በወርዱ እየዋኘች አሳ ሆና ለመቆየት፡፡ ከዚያ ፎጣዋን አንጥፋ ገላዋን
👍20🥰1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሰማዩ ከአድማስ እስከ
አድማስ ዙሪያውን በከዋክብት ተጥለቅልቋል፡፡ አንዳንዶቹ ብርሃናቸው ደመቅ የሌሎቹ ደግሞ ፈዘዝ ቢልም ሁሉም ይብለጨለጫሉ፡ ብልጭ ድርግም፤ ብልጭ ድርግም
እያሉ፡ ጨረቃ የለችም ዳመናም የለም። ሰማዩ ግን ተውቧል፡፡ጨለማው
ለትናንሾቹ ከዋክብት ጠቅሟቸዋል። ውበታቸውን
የምትነፍጋቸው ጨረቃ፤ መኖራቸውን ጭራሽ የምታጠፋው ፀሐይ
የለችም።

“በህይወቴ እንዲህ እልፍ
አዕላፍ ከዋክብት አይቼ
አላውቅም፡፡ ለካ ሰማዩ  ለእግር መቋሚያ የሌለው በከዋክብት የተጠቀጠቀ ነው!” አለና ወደ ሰማዩ አንጋጠጠ፡፡ ከዋክብቱ በድቅድቅ ጨለማው እየፈነደቁ ብርሃናቸውን ቦግ እልም ያደርጋሉ፡

“ድንቅ ነው  ታምር፧ የጨለማ ውበት!” አለች ለምለሙ ሳር ላይበጀርባዋ
እንደተንጋለለች፡፡ ሁለቱም ግን አንዱ ሌላው ያለውን አልሰማም።

የጉደር ፏፏቴ ይንፏፏል፡፡ የጉደር ወንዝ ለሁለት ተከፍሎ አንዱ ከደልዳላው መሬት ላይ ተወርውሮ ድንጋይ ላይ ይፈጠፈጥና
ለሰዎች አይን የሚማርክ ነጭ አረፋ ፈጥሮ ህሊናን አርክቶ ሲፈስ ፧ በስተግራ ያለው ደግሞ አክሮባቱን ሳያሳይ በኩራት ቁልቁል እየፈሰሰ ከፏፏቴው ጋር ተመልሶ ይገናኛል፡፡ ወንዝ ሆኖ ለመፍሰስ… ትዝ
አለው ስዩምን  ወንዙ፡፡

“ድንጋዩ ላይ ተፈጥፍጦ አረፋ የደፈቀው ውሃና በሰላም የተጓዘው ውሃ እንደገና ሲገናኙ ልዩነት አይኖራቸው ይሆን? የቱ
ይሆን እድሉን የሚያማርረው?  ከድንጋይ ላይ ተላትሞ አረፋ
የደፈቀው ወይንስ ጓደኛው ያስቀናው ሰዎችን መማረክ ያልቻለው ውሃ ሆኖ ተፈጥሮ ከጎኑ የተለየው ውሃ እየተንፏፏ አረፋውን
ሲደፍቅ ሰዎች እጅ ወደ እሱ ሳይሆን ወደ ፏፏቴው ተቀስሮ እያዩ ወይ ነዶ እኔም
በውስጤ ያለውን አረፋ ደፍቄ አሳያቸው ነበር፡ ምን ያረጋል ውሃ መሆኔን ያኔ ያውቁ ነበር። እርጉም ጊዜ ግን እሱን ተመልካች
አጎረፈለት፤ እኔን አይቶ አድናቂ አሳጣኝ' ይል ይሆን! ብሎ አሰበ፡፡

ሁለቱም ፀጥታን ወዳጆች ናቸው በዚ ደግሞ
ተግባብተዋል፡ ጸጥታን የሚፈራ የራስ መተማመን የጎደለው ፈሪ
ነው፡፡ አካባቢውን የማያውቅ ጨቅላ አስተሳሰብ ያለው… ፀጥ ካላሉ የቅጠል ሹዋሹዋቴ አይሰማም  የጨለማ ውበት አይታይም! የጽልመት ብርሃን የውበት ሚስጥር አይገለጥም… ፀጥታ የግዑዙ ዓለም ቁልፍ ነው  የሚስጥራት መክፈቻ…

ይህን የተረዱት ጥቁሩና ነጯ ግንኙነታቸው ገና ያልጠበቀ ቢሆንም በፀጥታ ቋንቋ ተግባብተዋል፡፡ ሁለቱም የየራሳቸው ውበት
አላቸው ከቀለማቸው ጀምሮ።

ፏፏቴው ይንፏፏል የሌሊት ወፍ እንደ ንጋት ወፍ
የችሎታዋን እየዘመረች በጨለማው ትበራለች… ሁለቱም በየግላቸው
በፀጥታ የሙከራ መስሪያ  ህሊናቸው ውስጥ እንደየአቅማቸው
ይመራመራሉ፡ ይቀንሳሉ ይደምራሉ አንዱ ሌላውን ያስባል፡፡

የጋዝ ምድጃው ላይ በብረት ድስት የጣዱት ፓስታ ክዳኑን
ሽቅብ እየገፋ ሲንፈቀፈቅ ግን ሁለቱም ከዚያ የፀጥታ ዓለማቸው ተመለሱ፡፡

ስዩም ከተቀመጠበት ተነስቶ ባትሪውን አብርቶ የብረት ድስቱን ክዳን ከፈተና ፓስታው መብሰል አለመብሰሉን አረጋገጠ
በስሏል… ለምግብነት ያመጡትን አቀራረቡ የጉደር ወይኑንም ዷ አድርገው ከፈቱ፡፡

"መልካም ራት!” አለችው፡፡
“ለአንችም” አላትና መብላት ጀመሩ
"ተወርዋሪ ኮከብ! ፈነደቀች፡፡

“ለብዙ ጊዜ ተወርዋሪ ኮከብ ስጠበቅ ነበር አሁን ግን አየሁ ዘግይቶም ቢሆን ያሰብሁት ይሳካል፡፡ አውሮፓ ውስጥ እንዲሁ ዓይነት እምነት አለ" አለችው፡፡ ስዩም ፈገግ ብሎ ራሱን ወዘወዘ ለአባባሏ እንግዳ አይመስልም፡፡
በሰባት ሰዓት ተኩል
ከአዲስ አበባ ተነስተው ገነት አዲሳለም ጊንጭ አምቦን እያዩ ጉደር የደረሱት ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ነው፡፡ አምቦ ኢትዮጵያ ሆቴል ትልቁ ዋርካ ስር
ቁጭ ብለው ማራኪውን አትክልት ቦታ እያዩ ቆዩ፡

"ጥሩ አገር አለቻችሁ፡፡ ከአዲሳባ እዚህ ድረስ ትንፋሽ ቆራጩ ተፈጥሮ በደስታ እንዴት እንዳረካኝ ልገልፅልህ አልችልም”
አለችው።

"ገና ይቀርሻል: ጉደር ስንደርስ የጉደርን ተፈጥሮ ስታይ የማድነቂያ ቃል እንዳታጭ” አላት፡ በፈገግታ ግንባሯን ሰበሰበች፡፡
ከአምቦ አንድ አስር ኪሉ ሜትር እንደተጓዙ ጉደር ከተማ ገቡ፡ በከተማው መሃል አለፉ፡፡ ወደ ግራ ታጥፈው አልባሌ መዝጊያ
ያለው በር ላይ ቆሙ፡፡ ትህትና ያለው ዘበኛ እየሮጠ መጥቶ በሩን ከፈተላቸው፡፡ አናገሩት፡፡

ፏፏቴው ይንፎለፎላል፤ ድምፁን እየሰሙ ቁልቁል ወረዱና ብብቱ ስር ገቡ። ስዩም ካርለትን አያት “ዋው!” ብላ አፏን ከፍታ
አይኖችዋን ወረወረቻቸው  አረፋው ላይ ለምለሙ  ጫካ ላይ የበልግ እፀዋት ላይ… የመጨረሻዋ ማድነቂያ አባባሏ ሁለት ፊደል ሆነ “ዋው! ብቻ፡፡

ሁለቱም በልተው ጨረሱ
የጉደር ፏፏቴ ይሰማል
ካርለት የጉደርን ወይን በሁለት ብርጭቆ ቀድታ አንዱን ለስዩም ሰጠችው። “ለጤናችን ለኢትዮጰያውያን አዲስ ዓመት" አለችው:
በየመንገዱ ያየችው ቢጫ    አበባ ከለምለም ቄጠማ ጋር በየሰዎች እቅፍ ላይ የነበረው አበባ፤ የኢትዮጵያ የአዲስ ዘመን አብሳሪ አደይ
አበባ እንደ ህፃንነቷ ከአረንጓዴው ለምለም መስክ እየቀነጠሰች
ችቦዋን ሞልታ መዓዛውን ባፍንጫዋ የሳበችው የአደይ አበባ ሽታ
መጣባት፡

ፏፏቴው ከብቶቹ ህፃናት… ቃናቸው ተዋህዶ “አደይ
አደይ አበባ…" እያሉ ያዜማሉ፡፡ ስዩም “ችቦው ተለኮሰ' አላት፡፡

“የምኑ” አለችው፡፡

“የአዲሱ ዓመት የአዲስ
ዘመን... የነገ ፈገግ አሉ
አንጋጠው ተጎነጩት ጉደሩን፡፡ ፀጥ አሉ እንደገና አዲሱን ነገ ህልሙን ነገ፤ ሽፍንፍኑን መጭ አመት እያዩ፡፡ ከዚያ  ካርለት
ለመናገር ስትቁነጠነጥ አያት፡፡

“አመሰግናለሁ፡ በዚህ የደስታ ቀንህ አብሬህ እንድሆን ስለመረጥኸኝ" አለቸው:

“ምስጋና አያስፈልገኝም: ሌላ አብሮኝ ሊመጣ የሚችል ባለመኖሩ ነው" አላት፡፡

“ለምን?” አለችው ካርለት፡፡

“በአዲስ ዓመት ዋዜማ የአዲሳባን ሰው ወደ ገጠር ወጣ እንበል ብትይው ፀበል ይወስድሽና በመስቀል እያስደበደበ ሰባት ቀን
ቤት ያዘጋብሻል እብድ ነሽ ብሎ" አላት: በቀልድ አዘል አባባሉ ፈገግ አለችለት፡ ከጥርሷ ይልቅ ቀይ ከንፈሯን በከዋክብት የብርሃን ወጋገን አየው፡

ካርለት፧ እንግዳ ባህሪው
የሚገርማት ኢትዮጵያዊ
ዮትያትሪካል አርት ምሩቅ መሆኑን እንጂ የግል ህይወቱን አልዘረዘረላትም፡፡ የሴት ጓደኛ አለኝ ብሏት የነበረውም ትዝ አላት።

የሴት ጓደኛህስ ፍላጎትህን አትወድልህም?"

“እሷማ ሁሌም አብራኝ ነች፡፡ በውኔ ቀርቶ በህልሜም"

“አልገባኝም?" አለች ካርለት፡፡

"በገሃድ የሚሆነኝን አላገኘሁም !በምናቤ ግን
ፍቅርኛ አለችኝ

“ለምን?''

"የፈጠራ ሰዎች ግላዊ እምነታቸውን በተከተሉ ቁጥር ከህብረተሰቡ ጋር የነበራቸው የመግባባት ቅኝት እንደተበላሽ የሚገምተው ይበዛል። እነሱም የብቸኝነት ጥዑም ዜማው ያረካቸዋል፡፡ ስለዚv
ሌለች የሚወዱት ሙዚቃ ለእነሱ ጩኸት ይሆንባቸዋል፡፡
በምናቤ ግን ፍቅረኛ
“ቁም ነገሩ ግን ግላዊ ዓለማቸውም ውስጥ ሆነው
የህብረተሰቡን ህይወትና ቅላፄ ምንነት ለመረዳት ህሊናቸውን ወደ
ዱ ዓለም እየዶሉ እርቀው ይቀርባሉ፤ ከህዝቡ ጋር ይሆናሱ፤
👍21👎1😁1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከሉ ሆራ ጎይቲ አንተነህን ሐመር ካደረሳት በኋላ አስር ቀን በማይሞላ ጊዜ ተመልሶ እንደሚመጣና እሱ አዲሳባ ለተወሰኑ ቀናት
ሲቆይ ካርለት ደግሞ ወደ ሐመር ለመሄድ እቅድ ነበራቸው፡፡ ከሎ ሆራ ግን የውሃ ሽታ ሆነባት፡፡

“ምን ነካው?” እያለች ብዙ አሰበች ካርለት: ደህንነታቸውንና
ያጋጠመውን ችግር ግን ማወቂያ አንዳችም የመገናኛ እድል
አልነበራትም፡ ስልክ  ደብዳቤ ፋክስ ኢሜል.. አንዳቸውንም የሉም: ሐመር ውስጥ መገናኛ ዘዴው “ላልሰማው አሰማ" የሚለው ዘዴ ነው:: መንገደኛ ሲገናኝ በርኮቶው ላይ ቁጭ ይልና ሰዉ ከብቱ
ቀየው. ሰላም መሆኑን በጥሞና ይነጋገራል: አዲስ ነገር ደስታ ችግር ግጭት ካለ ያየው ላላየው ይነግራል፡፡ ወይንም የሰማው ከሆነ ሰማሁ ብሎ ያወራል፡፡

አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጥ
ማህበረሰቡን የሚጎዳ ችግር ካለ ግን ሁለት እጃቸውን ያቆላልፉና ከትንፋሻቸው የሚወጣውን
አየር የእጅ ጣታቸውን ከፈት ከደን በማድረግ ድምፅ ይፈጥራሉ፡፡ የሰማው ላልሰማው በተመሳሳይ መልኩ እየነፋ ያስተላልፋል፡፡ ያን
ጊዜ ዋናው መንገድ ላይ የሚሄድ ሐመር ሁሉ ጫካ ጫካውን አድፍጦ እየተጓዘ ባለ ጠበንጃው ጠበንጃውን ባለ ጦሩ ጦሩን… ሁሉም ያለውን እየያዘ እየተሰበሰበ መንደሩን የሚጠብቁ እነ እከሌ እከሌ ከብቶች ዘንድ እነ እከሌ እነ እከሌ እየተባለ አሳሾች,ሸማቂዎች
ሰላዮች ይመደቡና የመጣባቸውን ችግር በጋራ
ይጋፈጣሉ፡፡ ሰላም ሲሆንም አንዱ ለሌላው እያሰማ ወደ እለት የኑሮውን ይመለሳል፡፡ በሐመር ይኸ ነው ለዘመናት የቆየው መገናኛ:

“ምናልባት መኪናዋ ተበላሽታ ይሆን? ወይንስ መንገዱ ተበላሽቶ ድልድይ ተሰብሮ…" እያለችም አሰበች ካርለት መልስ ግን
አጣች! መላ ምት ብቻ::  ስለዚ አዲሳባ ተቀምጣ ከምትጨነቅ መሄዱን መረጠች፡፡

በምን እንደምትሄድ ግን ጨነቃት። በትራንስፖርት መኪና መሄዱን አሰበች እንዲያውም እስካሁን በትራንስፖርት መኪና
ከተማ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር ሄዳ አታውቅም፡ ችግሩ ግን ጓዟ
ብዙ ነው፡

እዚሆ ሆኜ በሃሳብ ከመጨነቅ መሄዱ ይሻለኛል ካለስራ አዲሳባ መቀመጡ ደግሞ ራሱን የቻለ ትልቅ ችግር ነው' ብላ
አሰበች: ለጊዜው የሚያስፈልጋትን ብቻ ይዛ ሌላውን ሌላ ጊዜ ከሎ
እንዲወስድላት ብታደርግ እንደሚሻላት አመነች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።፡።
ካርለት ታክሲ ተኮናትራ መርካቶ የክፍለሃገር አውቶብስ መናኸሪያ ስትደርስ የሚተራመሰው ሰው ለጉድ ነው: ሆንኮንግና
ህንድ  አገር ግን እንዲያ ያለውን ትርምስ ስለለመደችው አልተገረመችም፡፡ ባለታክሲው ደንበኛዋ ነው፡ ታክሲዋን ወደ ዜድ ሙዚቃ ቤት አቅራቢያ አቆሞ ጓዟን ተከፋፍለው መንገዱ አቆራርጠው ከሚተራመሰው ህዝብ መካከልም አልፈው በሰፊው በር በኩል ወደ መናኸሪያው ገቡ፡

“ድሬዳዋ ደሴ  ለቀምት በካቻማሊ በዋሊያ" እያሉ
ሰውን የሚጎትቱት እሷንም ጎነታተሏት! ያስፈራሉ። ስነ ስርዓቱ ቅጥ የለውም
ለዝርፊያና ቅሚያ አመች ነው: አለንጋ የያዙት ዘበኞች
ስርዓቱን ለማስጠበቅ ከአቅም በላይ ሆኖባቸዋል፡፡ መንደኛው ግን እራሱን ይጠብቃል። ካርለት ሻንጣዋን በትከሻዋ አንጠልጥላ በሁለት
እጅዋ ከፊት ለፊቷ አጥብቃ ይዛ ገባች፡፡ ታክሲ ነጂው
የሚያዣብቡትን ይክላከላል፡፡ እንደ ሽንት ቤት ዝንብ ግር ብለው
ይመጡና እሱን ሲያዩ ገለል ይሉላታል

“አርባምንጭ አንደኛ አርባምንጭ
ሁለተኛ ከሚለው
አውቶበስ ዘንድ ደረሰ! ለመስቀል የሚጓዘው መንገደኛ ከአውቶብሉ
በስተኋላ አቧል። “ትኬት ይኖራል?” ታክሲ ሾፌሩ ካርኒ ቆራጮችን
በየተራ ጠየቃቸው: “አልቋል ባክህ  ገለል ገለል በሉ ካለበለዚያእቃችሁ አይገመትም• አይጫንም፤ ስለዚህ ማርፈዳችሁን እወቁ…" አለ እንደኛው ካርኒ ቆራጭ በስጨት ብሎ። አንድ ብልጣ ብልጥ
ለእራሱ እየተጠጋ “እስኪ እሽ በሉ ማርፈዱ የሚጎዳን እኛን ነው…"አለ፡፡ መስማማት የለም። ሁሉም እቃውን ጭኖ ፊት አካባቢ
ተቀምጦ ለመጓዝ ጓጉቷል፡፡ ደሞ መስቀል ነው። የዓመቱ መገናኛ ዓውዳመት! ካርኒ ቆራጩ አኩሩፎ “ያውላችሁ"  ብሎ ወጣና ተደናግጣ ከቆመችው ካርለት ጎን ቆመ:: አየችው አያት! ታለትንሽ ጊዜ ተያዩ፡፡

ካኪ ካፖርት ሁለት ጥራዝ ካርኒ ጭንቅላቱ ላይ ደግሞ
ፎጣ ጠምጥሟል፡ ፊቱ ምጥጥ ያለ ጠይም መልከ መልካም ግን ነገረኛ መሳይ ነው። ሲያናግሩት አይናገርም:: ከመሰላቸት ወይም ከኩራት ይሁን እግዜር ይወቀው

"አርባምንጭ ዘላቂ ምንም ትኬት የለም ለሷ ነበር”
አለው ታክሲ ሾፌሩ ጠጋ ብሎ። አላናገረውም! ካርለትን ግን እንደገና አያትና፦

ነገርኩህ አይደለም የኔ ወንድም አልቋል" አለና የሚያስብ መሰለ: እስኪ አንዴ የት ነው እባካችሁ ሁለት ትኬት ገዝቶ አንድ
ወንበር ላይ መቀመጥ እፈልጋለሁ ያለ ሰው ነበር”

“የታል?" አለ ታክሲ ሾፌሩ: ካርለት! ነገሩን ለማጣራት
ፈለገች በእንግሊዘኛ የሚገልፅላት ግን ጠፋ።

ዩ ዌት" አላት ታክሲ ሾፌሩ ለከት ባጣ እንግሊዘኛ::
“ቆይ ግዴለም እኔ አናግረዋለሁ ብሎ እቃውን እየገመተ መጫን ተጀመረ ከዚያም የአትወብሱ
በር ሲከፈት ግፊያው
ያስፈራል፡፡  ሽማግሌዎች, ህፃን የያዙ ሴቶች….. እየተወረወሩ በግፊያው እየተሽቀነጠሩ ጉልበት ያለው እየበረቃቀሰ ገባ ካርለት ገረማት፡፡

“ሁሌም እንዲህ ይሆን ወይንስ ዛሬ ብቻ? ነፍስ እስኪጠፋ ነው የሚጠበቀው? ምናለ  በወንበር ቁጥር ወይንም በሌላ ዘዴ የማንም መብት ሳይነካ መንገደኛው ቢስተናገድ' ብላ አዘነች፡፡

“እስኪ ነይ እቃሽ እላይ ይውጣ ጫንላት” አለ ካርኒ
ቆራጩ በምልክት። ካርለት ተከትላው አውቶቡስ ውስጥ ገባች፡፡መንገደኛው ገና ተረጋግቶ አልተቀመጠም። ሲገባ ከነበረው ትርምስ
ግን ይሻላል፡፡

“የኔ ወንድም አንተ ነህ አይደለም ሁለት ትኬት
የያዝኸው?"

“አዎን! እኔ ነኝ። አንዱ ጎን ካልተቀመጥሁ' ብሎ ለምን
አያፈጥብኝ: እኔ ደልቶኝ መሰለው ሁለት ትኬት መግዛቴ፡ ሰላም ፈልጌ ነው መሳቀቅ ጠልቼ ነው. አሁን ግን ሰላም ነው አስበህ
ልትጠይቀኝ በመምጣትህ አመሰግናለሁ። ለዚህ አይደል እኔስ ቀደም
ብዬ አደራ ማለቴ አለው ፂሙን በቀኝ እጁ ቁልቁል እሞዠቀ፡፡

የለም አመጣጤ ለሌላ ነው። ይህች የሰው አገር ሰው ናት… እባክህ ተባበራት ብዙም አታስቸግርህም። ገንዘቡን ተቀብያት እሰጥሃለሁ።”

ኖ የለም እኔ አፓርታይድ አይደለሁ ጥቁር ነጭ የምል!መሳቀቅ መጨነቅ ስለማልፈልግ ብቻ ነው። ይህንን ደግሞ አስረድቻችሁ ተስማምተናል በጭራሽ አጠገቤ ሰው አይቀመጥም፡"

“…እባክህ ተባበራት መስሪያ  ቤታችን እኮ ይህን ጉዞ ሲያዘጋጅ ገንዘብ ማግኘት ብቻ ሳይሆን ህዝቡንም ለመርዳት ነው"
አለው።

“ይኸ እኮ ነው የጠላሁት። ሰላም ለማግኘት ብዬ ገንዘቤን አውጥቼ ያላሰብሁት አተካራ ገዛሁበት: ጭቅጭቅ አልፈልግም እሽ!
ገንዘቤን! ያው ቦታዋ” አለ: ካርለት  ሰላሣ ሁለት ብር ከአስር ሣንቲም ከፈለችው: ለታክሲ ሾፌሩም ኪራዩን ከጉርሻ ጋር ስትሰጠው በደስታ ፊቱ በርቶ ተሰናብቷት ሄደ፡

አጠገቧ የተቀመጠው ሰው አንድ አነስ ያለች ጀሪካን አንድ በመጠኑ ከትንሽዋ ጀሪካን ከፍ ያለ እንደ ህጻን በእቅፉ ይዟል። ሰፊ
ኮት የወታደር ቦት ጫማ ተጫምቷል! ፀጉሩ ዞማ ነው አበጣጠሩ ግን ለከት የለውም! ፊቱ ከፊሉ በፂሙ ተሸፍኗል! ከንፈሩ
አይታይም…
👍161🔥1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


“እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፡ በሰላም አብረው እንዲኖሩ ከብርሃን ወደ ጨጎጎታሙ ጨጓራዬ ውስጥ አስገብቻቸው እነሱ ተባብረው እኔን አንደማጥቃት እርስ በርሳቸው ካልተስማሙና ከተጣሉ የከፋው ተበደልሁ ባይ በሁለት መንገድ (በጁ ምልክት እያሳያት
ወይም በላይ ወይ በታች መውጣት ይችላል። እኔ ደድግሞ በጠየቁኝ
አቅጣጫ በሬን እከፍታለሁ" ብሎ ፈገገ፤ ካርለት ግን ሳቋን መቆጣጠርን ተሳናት፡ ወርቃማ ፀጉሯ እስኪርገፈገፍ ተሳፋሪው ሁሉ እየዞረ እስኪያያት… ሳቀች እሱ ግን ፀጥ አለ፤ እንቅልፍ እንቅልፍ አለው ተኛ! ካርለት ትከሻ ላይ፤ ወርቃማ ፀጉሯ እንደ በቆሉ ጭራ ፊቱን ሲነካካው የናቱን ጡት እንደሚጠባ ህፃን ፍርክስክስ ብሎ ተኛ
“ኩርር… ኩርርር. እያደረገ፡፡

ዝዋይ ላይ አውቶቡስ ለቁርስ ሲቆም ነቃ። ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ነው: ሰዉ ሁሉ ወረደ: ካርለት ካለፂማሙ ሰው
የምታውቀው የለም:: ስለዚሀ አብረው ወረዱ፡፡

የኢትዮጵያውያን ምግብ ለሷ አዲስ አይደለም። ግን
ለተወሰኑ ወራት እርቃው ቆይታለች፡፡

እሱ ጥሬ ክትፎ እሷ ዳቦና ሻይ አዘው ሲበሉ ቆዩና፡-

“ስለ ከቡ ነገርኩሽ" አለ ፂሞ:

“ማነች ከቡ?"

“ሚስቴi ለጋብቻ ስጠይቃት ፂማም ነህ' ብላ ናቀችኝ፡ ዝም ብዬ ጥረቴን ቀጠልሁ፡፡ ፂሙ አያስጠላሽም፤ምኑን ልትስሚው ነው' ብለው ሲያጥላሉባትም እኔ ጥረቴን እንደቀጠልሁ ነበር፡ አንድ
ቀን ታድያ ተሳካልኝ ለትዳር እንደምፈልጋት የተማርሁ መሆኔን ላዬ ሞኛ ሞኝ ቢሆንም ውስጤ ግን ዘመናዊ እንደሆነ በአለማችን ካሉ በጣት ከሚቆጠሩ ደስተኞች መካከል አንዱ መሆኔን…
እየዘረዘርሁ ሳጫውታት ቆየሁ፡፡ ምኗ ሞኝ መሰለችሽ! ቆቅ ነች:
ከምታየውና ከሰማችው ጋር እኔ ያልኋት ሁሉ ተምታታባት ከቡ!

“ሰርቲፍኬቴን ስቀበል የተነሳሁትን ፎቶ ሳሳያት ግን ውሃ ሆነች፡ ፍንጥር ፍንጥር ማለቷን ቀነሰች፡ ያኔ ጠልፎ እሚጥላትን ምላሴን እያወናጨፍሁ እግሯን አንስቼ እግሬ ላይ አደረግሁና የርግብ
አሳሳም ስሚያት ወጥቼ ስሄድ የጨው መላሾ እንደቀመሰ ከብት
እየተከተለችኝ ለምን አትመጣም መሰለሽ!" ብሎ ሳቁን ለቀቀው፡፡

ካርለት ስለ አንድ ነገር መናገር በጀመረ ቁጥር መጨረሻው አስቂኝ
መሆኑን መጠበቅ ጀምራ ስለነበር እሷም አብራው
ሳቀችና የሆነ ነገር
በህሊናዋ ትዝ አላት  እንግዳ አባባል፡

“ምንድነው የርግብ አሳሳም''

“አታውቂም? ብዙው ኧረ በጠቅላላው ሰው የሚያውቅ አይመስለኝም" አላትና ቀና አለ፡፡ “እኔ ግን የተማርሁት ከርግቦች
ነው፡፡ ቆርቆሮዬ ላይ ሲ
ሲዳሩ አይቼ፡፡
“ታያለሽ ከንፈሬ አካባቢ ያለውን ፂሜን ለመሳም ከፈለግሁ ከሴቷ አፍ ውስጥ ገብቶ ጉሮሮዋን ያንቃታል፡፡ እኔ ደግሞ ችግር
መፍጠር አልወድም፤ ለምን ብዬ! ሰው ሁሉ የሌላው ሳይጨመር የራሱ ችግር መቼ አነሰው… ስለዚህ እኔ እንደ እርግብ አፌን
ስከፍትላት ክቡ ከንፈሯን ውስጥ ትጨምረዋለች ያኔ እጠባታለሁ  ከንፈሯን: ያ ነው የእርግብ አሳሳም! ያ የርግብ አሳሳም ነው ነው
ከቡዬን እንደ ከብት  እያንደረደረ እቤቴ  ያስገባት፡፡ ፂሜ ችግር
ስለማይፈጥርባት ቅቤ እየቀባች ሽሩባ ትሰራኝ ጀመር፡፡ ከዚያ እንዲያውም ልቧ እየራራ እንደ ሰናፍጭ የሚሰነፍጥ ፍቅሯን
እየመገበች ይኸው ያየኝን ሁሉ አጠገብህ ካልተቀመጥን' እያስኘ
የሚያስጎመጅ ሰው ወጣኝ" አላትና ሳቀ ተሳሳቁ…..

አውቶብሱ እንደገና ጉዙውን ሲቀጥል ፂሞ ከያይነቱ
ጎንጨት አድርጎ ተኛ: ካርለት እንግዳ ባህሪው ገርሟታል። አጠገቡ
መቀመጧን እንዳልጠላችው አሁን ግን ከነበረው ሰው
ልትግባባው የምትችለው ከሱ የተሻለ እንዳልነበር ተሰማት።

አውቶብሱ የላንጋኖንና የሻላን ደን እያቆራረጠ ሲጓዝ ሙቀቱ እየጨመረ የዳቦ መጋገሪያ ፍም ላይ የተቀመጡ ያህል
ያተኩስ ጀመር። የአውቶብሱ መስኮትና በር ባጠቃላይ ክርችም ብሎ
ተዘግቶ ህዝቡ በላብ ሻወር ይታጠባል፡ መስኮቱን ለምን
እንደማይከፍቱት ፂሞን ጠይቃው የአውቶብስ መስኮት አትክፈቱ•
ብርድ ይመታችኋል ያለው ዶክተር ባይታወቅም ልጅ አዋቂውን ቃሉን አክብሮ በሙቀት መቀቀል መምረጡን ነግሯታል፡ ስለዚህ የለበሰችውን ጃኬት አውልቃ በነጭ ቲሸርት ሆና የሙቀት ቅጣቷን
እየተቀበለች ለማረፍ ከፊት ለፊቷ ካለው ወንበር የብረት ዘንግ ላይ ራሷን ደገፍ አደረገች፡፡

ሙዚቃው ማንቧረቁ አልቆመም፡፡ አውቶብሱ ማርሹን እየቀያየረ ይጓዛል፡ ካርለት እንደ ቀልድ እንቅልፍ ወስዷት ቆይታ የአውቶብሱ ሹፌር አህያ ድንገት ልትገባበት ስትል ፍሬኑን ያዝ
ሲያደርግ ከወንበሩ ጋር ተጋጨችና ብንን ብላ ደንግጣ ተነሳች፡፡

ፂሞ ያነባል። ብጥስጥስ ያለች መጽሐፉን፡ ትንሽ ቆይቶ ከትልቁ ኪሱ ወረቀቶች ያወጣና ያነብ ጀመር፡ ካርለት
ተደንቃ አየችው፡፡ ልታምን አልቻለችም፡፡ ማንም ሰው ያደርገዋል ብላም አትገምትም፡:

የምን ወረቀቶች ናቸው?”

“ወረቀቶቹ አያቸው ግንባሩን ሽቅብ ሰብሰብ አድርጎ፡፡

"ቁም ነገር ያላቸው ወረቀቶች ናቸው፡፡"

ላያቸው እኮ ቆሻሻ አለባቸው?”

“አዎ አይነምድር አው፡ ግን ደርቋል፡፡ ሳነሳው እንኳን ብዙም አልደረቀም ነበር፡ ይኸ ጃኬት ግን ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለመሃረቤና
ስለሚፈጥር እዚያው ደረቀ፡፡
ለወረቀቶችም ሙቀት
እስክርቢቶ አይበረክትልኝም ሙቀቱ ያገነፍለዋል፡፡"

“ወረቀቶቹን ከየት ነው ያገኘሃቸው?''።

“በየሄድሁበት መፀዳዳትም ባልፈልግ ሽንት ቤት መሄድ
አዘወትራለሁ የተፃፈውን ማንበብ ሱስ ሆኖብኛል፡ አሁን አሁን ደግሞ አንዳንድ ሽንት ቤቶች ውስጥ ያሉ ቅርጫቶች ላይ ሰው
ተፀዳድቶባቸው እማገኛቸው ወረቀቶች ሽንት ቤቶች ከመፀዳጃነት
አልፈው ወደ መፃህፍት ቤትነት እየተቀየሩ ነው
የሚያሰኝ ነው፡፡

“በአማርኛ ሆነ እንጂ ይህን ብታነቢው የወደቅሽበትን
ሳታውቂው ሶስት ቀን ተኝተሽ ትከርሚ ነበር" አላት፡፡

“ቆሻሻ ወረቀቱን አትጠየፍም?"

“እጠየፋለሁ እንጂ! ግን ጠቃሚ ነገር ኣለበት፡፡ ጠቃሚ ነገር ደግሞ ቆሻሻ አለው ተብለቀ አይጣልም፡፡ ቆሻሻ ማለት ጥቅም
የማይሰጥ ተራ ነገር ነው፡፡

“ይገርምሻል ካለ እነዚህ'' ጀሪካኖቹን ጠቁሞ አሳያት
“...ካለ እነዚህና ካለ ከቡ የረባም ጓደኛ የለኝ፡፡ ምናልባት እኔ ወይ እነሱ ቆሻሻ ስለሆን ይሆናል  ከብዙው የሥራ ጓደኞቼ ጋር
የማልግባባው ታዲያልሽ…" የትንሽዋን ጀሪካን ክዳን ከፍቶ ወደ መስታዋቱ ዞሮ አንደቀደቀና

“…ታዲያልሽ ከሽንት ቤት ቅርጫት ቆሻሻ ወረቀት አንስተህ እንዴት እኪስህ ትከታለህ ያሳዝናል! ይህን የሚፈጽም ህሊናው
የተስተካከለ ሰው የለም ካለ እብድ በቀር' ብለው አጥላሉኝ፡፡

“አንድ ቀን ታድያ ሁለት ቀያይ ብሮችን ይዥ ሽንት ቤት ገባሁና በብሩ ተፀዳጅቼ ወጣሁ፡፡ ከኔ የሚቀጥለው አላየኝም ገባ ብሎ ሲወጣ ተመልሼ ብገባ የተፀዳዳሁባቸውን የብር ኖቶች ወስዷቸዋል
ደሞ ሌላ ቦታ ሄጄ በሁለት አምስት አምስት ብሮች ተፀዳዳሁ ... ቀጥሎ የገባው ሲወጣ ብሮቹ የሉም፡፡ hዚያ ደግሞ በአንድ አንድ ብር ሞከርኩ፤ እነሱም ተወሰዱ ታዲያልሽ!ብሮቹ ከእለት ጥቅም
ሌላ ጠቃሚ አይደሉም፤ ማንም ሰው ግን ቆሽሸው ቢያገኛቸውም ወደ ኪሱ ይላቸዋል፡፡

“እና እኔ ለይወት ጠቃሚ ቁም ነገር ያለውን ቆሻሻ ወደ
ኪሴ ብል ያለፋሁበትን ገንዘብን ፈልጌ አይደል? እውቀት ጠምቶኝ
እንጂ፡፡ ስለዚህ ምኑ ያስነውራል" ከት ከት ብሎ ሳቀ፡ ካርለት አንገቷን በአድናቆት ወዘወዘች፤ አልሳቀችም፡፡

“ኢትዮጵያ ውስጥ የፍልስፍና ሰዎችም አሉ፡፡ ማህበረሰቡ ግን እንደ ቆሻሻ ያያቸዋል፧ እነሱ ግን ለአገሪቱ ጠቃሚ እሴቶች
ነበሩ…" የትልቁ ጀሪካን ክዳን እንደገና ተከፈተ፡፡ ደቅ ደቅደቅ…
👍27🥰2😁21
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሲሚንቶና ብረት የጫነው ኤንትሬ ከሌሊቱ አስር ሰዓት
ከእርባምንጭ ተነሳ፡፡ ያጓራል ያቃስታል ይንቶሰቶሳል. ጉራው
እንጂ ጎዞው የኤሊ ነው፡፡ ማዝገም… ከአርባምንጭ ቀይ አፈር ሁለት መቶ ስምንት ኪሎ ሜትር ለመጓዝ አስራ ሁለት ሰዓት ፈጀበት፡፡ሲሚንቶና ብረቱ ላይ ያሉት ተሳፋሪዎች የተሳፈሩት ተለምነው
ሳይሆን ለምነው ነው፡ ወደ ጂንካ የሚሄድ አስተማማኝ
ትራንስፖርት የለም፡፡ ወደዚያ መሄድ የፈለገ አማራጭ እንደሌለው አውቆ በአጋጣሚው መጠቀም አለበት፡፡ ካለበለዚያ ሲቀላና ሴቻ እያለ ሲንገላወድ ይከርማታል፡፡

የሚያንሰፈስፈው ውርጭ እያኮማተረው የማያተኩሰው የፀሐይ ሙቀት እያቃጠለው አይኑ ጆሮው አፍንጫው፦ አፉ አቧራ እየቃመ ከመሬት ርቆ ጭነት ላይ የወጣው ተሳፋሪ ለሁሉም
ሳይሳቀቅ ጭንቅላቱን በጨርቅ ቢጤ ጠቅልሎ በሁለቱ እጁ ካቦውን
ጥርቅም አድርጎ ይዞ እየተናጠ መጓዝ ነው፡፡ ታዲያ አቀበት ቁልቁለቱ  ጫካና ሜዳው አይጠገብም፡፡ እንደ ጥሩ ትርዒት እየተቀያየረ ያዝናናል፧ “ሣይደግስ አይጣላ" እንዲሉ!

ካርለት አልፈርድ አርባ ምንጭ መቆየት አልፈለገችም፡፡በእርግጥ በቦታ አመራረጡ ምሥራቅ አፍሪካ ወደር አይገኝለትም
ተብሎ በውጭ ዜጎች የተመሰከረለት የበቀለ ሞላ ሆቴል ሁለት ቀለማቸው የተለያዩ ሐይቆች (ጫሞና  አባያ) በርካታ የሆኑ ምንጮች በኢትዮጵያ ከሚገኙት ታላላቅ ተራሮች አንዱ ጉጂ ተራራና ከስሩ የኢኳቶሪያል የዝናብ ደን ያለው ተፈጥርው የማይሰለቻት ቢሆንም ችግሩ ሐመሮች ናፍቀዋታል።
የሐመሩን የፍዬል ቆዳዋን የሐመር ጎረምሶች የሽለሟትን የእጅ አንባር በአስሩም እጣቷ የምትጠቀምበትን ቀለበት የአንገቷን ጨሌ ስታይ የሐመር ትዝታዋ አገረሸ፡፡ መከባበሩ መተዛዘኑ አብሮ
መብላት መጠጣቱ ጫካውና መንደሩ ተራራውና ሜዳው
በተለይም የኢቫንጋዲ ጭፈራው ውልብሎ ታያት፡ ወደ ሐመር የምትሄድ ሳይሆን ከሐመር እንደምትመለስ ሁሉ! ልቧ እንደ ፅናፅል በፍርሃት ተንሿሿ፡ ፊቷ ገረጣ የሐመር ተፈጥሮአዊ ህይወት
ራባት፡፡

አጠገቧ ከኤንትሬው ጀርባ መኪናው ቆጥ ላይ ብዙ ሰው ሰፍሯል፡፡ ወታደር ተማሪ ነጋዴ ቄስ ሳይቀር አለ፡፡ ቀልዱ ጨዋታው ያስቀናል፡፡ ሰዎች ሁሌም ችግር ሲበዛባቸው ደጎች
ተዛዛኞች... መሆናቸው ያለ ነው፡ ካርለት ሁሉንም ስታጤን ቄሱ ሌላው ሲጫወት ዝም ብለው ሲያዳምጡ ይቆዩና ፈርጠም ብለው
ማሳረጊያ ሲሰጡ አስተውላቸዋለች፡፡ በእርግጥም የሚጫወቱት
አይገባትም ፤ ሆኖም ግን ይንከባከቧታል፡፡  አይናቸውን ወርወር
ያደርጉና ፈገግ ይሉላታል፡፡ እየደጋገሙ ያዩዋታል፡፡ ብታናግራቸው በወደደች ግን የቋንቋ ችግር አለ በመካከላቸው፡፡ እሳቸው ስለ እሷ እያሰቡ እንደሆን ገምታለች፡፡ ጠይቃ ሃሣባቸውን ማወቅ ባለመቻሏ ግን በተራዋ እሷም ስለ እሳቸው ማሰብ ጀመረች

ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች ያሉባት ሃገር ነች፡ ክርስቲያኑ ሙስሊሙ… ህዝቡ የአንዱ ወይም የሌላው ተከታይ ነው በአመዛኙ፡ የአገሪቱ ታሪክና የባህል መዘክርም የሚገኙ ናቸው፡፡ ካርለት አንዴ ሰሜን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አክሱም ላሊበላ ባህርዳር ጎንደር ሄዳ ብዙ ቤተክርስቲያኖችንና መስጊዶችን ጎብኝታለች፡ በምስራቅም እንዲሁ ማየት የሚገባትን አይታለች፡፡
ግን ደብረብርሃን ስላሴ
ጎንደርን በጎበኘችበት ጊዜ
የሚባለውን ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ካየች በኋላ ከሁለት ወንድ መነኮሳት ጋር ያደረገችው የሣሣብ ልውውጥ አይረሳትም፡፡
ደርቡሾችና ግራኝ  ሞሐመድ ብዙውን የጎንደር ቤተ
መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ሲያፈርሱና ሲያቃጥሉ ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ግን ከመፍረስና ከመቃጠል ተርፏል፡ ሁሉም
አልደረሱበትም፡፡ እና ቤተክርስቲያኑ በወቅቱ
የነበረውን የአገሪቱን
የህንፃ ሥራ ጥበብ ምጥቀት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

አፀደ ግቢው በውስጡ ያሉት ሥነ ስዕላቱ በመፅሐፍ ቅዱስ
ላይ ስሟ ሰባ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰላትን ኢትዮጵያን ሃይማኖታዊ
ጥንካሬና ድንቅ የቤተ ክህነት ሥርዓት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ልጅ እግሩ መነኩሴ ለካርለትና ስአስጎብኚዋ የቤተ ክርስቲያኗን ታሪካዊነት ሲያስረዱዋቸው ከቆዩ በኋላ ከደብሩ
ከመውጣታቸው በፊት አንድ ጠና ያሉ መነኩሴ መግቢያው እድሞ
ካለው ሁለት ክፍል አንደኛው በር ላይ ዳዊታቸውን ሲደግሙ አየችና ከመነኩሴው ጋር ለመነጋገር ፎቁ ላይ ወጣች፡፡

መነኩሴው የተቀመጡት ! እሳቸውና ልጅ እግሩ
ከሚኖሩበት ክፍል
በሩ ላይ ነው፡: ከጎን ያለችው ክፍል ቢሮ ናት፡፡
ካርለትና አስጎብኝዋን ሲያዩ መነኩሴው ከተቀመጡበት
ተነሱና በትህትና ተቀበሏቸው፡፡ ወደ ውስጥ ግቡ እንዳይሉ ካርለት
ሴት ናት፡፡ ሴት ደግሞ ወደ መነኩሴ መኖሪያ ቤት አትገባም! ስለዚህ በረንዳ ላይ ቁጭ አሉ፡፡

አባ ከሰል ላይ በበራድ ውሃ ሞልተው ጣዱና ተመልሰው
ለወግ መጀመሪያ እህሣ እንደምን ናችሁ" አሉ፡ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ትግርኛ መሆኑ ከአነጋገራቸው ይታወቃል፡
“እንዴት መነኩሴ ሆኑ?" ብላ ጠየቀቻቸው ካርለት
በአስተርጋሚዋ፡፡

“በአያልቅበቱ ፈቃድ ነዋ ካለ እሱ ፈቃድ ምን የሚሆን አለ" አምላካቸውን ሽቅብ አዩ፡፡ እግዚአብሔር ከመንበሩ ላይ ተቀምጦ
ታያቸው በአይነ ህሊናቸው: ቶሎ ሰገድ ብለው አይናቸውን መለሱ፡፡

እዚህ ምን አገልግሎት ይሰጣሉ?"

እህ የእግዚአብሔርን ቤት! ቤተ ክርስቲያኒቱን አገለግላለሁ ተደብር ደብር እየሄድሁ እግዚአብሔርን ማገልገል ነው ሥራዬ፡ ሌላ
ዓለማዊውን ህይወትማ ትቸው መጥቻለሁ,," ቀና ብለው ሁለት እጆቻቸውን ዘርግተው አጮልቀው
አዩ ወደ መንበሩ

“ቤተሰብ ልጅ አልነበረዎትም? ካርለት ሌላ ጥያቂ ጠየቀቻቸው፡

“ነበረኝ እንጂ! ግና ከአንድዬ ምን የሚበልጥ አለ!-" አዩ ሽቅብ፡፡ካርለት ከመነኩሴው ጋር ብዙ ሃሣብ ተለዋወጠችና ደስ
አላት፡

መነኩሴው ሻዩን በብርጭቆ ቀዱና በቀለምሻሽ ዳቦ ቆራርሰው ሰጧቸው ለነካርለት፡፡

“አባ… ሻዩ ፈልቷል አይመጡም ወይ" ጠና ያሉት መነኩሴ ልጅ እግሩን መነኩሴ ጠሩአቸው፡፡

“…ከቤተ-ክህነት ሙያ ሌላ ምን ሙያ አላችሁ?"

“ኧረገይ ከዚህ ሌላ ደግሞ ምን ሞያ ይኖረናል! ኧረ
የለንም፡፡"

“የሃይማኖት ተከታዩ ወደ ቤተ-ክርስቲያኗ ሲመጣ ምንድን ነው የምታስተምሩት?”

“መንፈሳዊ ትምህርት  መንፈሳዊ ትምህርት ይማራል! ቅዱሳት መጽሐፍት ይነበበለታል…"

“ቤተ ክርስቲያኗን ስታገለግሉ ለእናንተ የሚያስፈልገው
መሠረታዊ ነገር ይሟላላችኋል?

“ኧረገይ! ኧረ ችግር ነው ችግሩማ እንዲህ በአጭር ጊዜ ተነስቶ አያልቅም ልጅ እግሩ መነኩሴ ተከዝ አሉ፡

"እርስዎ ሃይማኖትዎ ምንድነው? ጠና ያሉት መነኩሴ አንዴ አስተርጓሚዋን ሌላ ጊዜ እሷን እየተመለከቱ ጠየቋት፡፡

“የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ ነኝ፡” ሁለቱም መነኮሳት ቀና ብለው አዩዋትናı “አሃ አሉ ባንድነት እንደ መደንገጥ ብለው፡፡

“በእኛ ሃገር መነኮሳት ከመንፈሳዊ እውቀታቸው ሌላ የሞራል ትምህርትና የሙያ ስልጠና ይሰጣቸዋል፡ ስለዚህ መነኮሳት ምዕመናኑ ወደ ቤተ ክርስትያን ሲመጡ መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን
ሞራላዊ ትምህርትም ያስተምራሉ፡

“የመነኮሳት እርዳታ በመንፈሳዊና ሞራላዊ ትምህርትም ብቻ
ሳይሆን በስልጠና ባገኙት
ሙያ በህክምና. በጓሮ አትክልት በእንጨትና ብረታብረት ሥራ….. ወዘተ ህዝቡን ያገለግሉታል፡፡
ስለዚህ መነኮሳት የራሳቸው ገቢ ያላቸው፤ ህዝቡን የሚረዱ ምፅዋት
የማይጠይቁ ነገር ግን ለህብረተሰቡ መንፈሳዊና ሞራላዊ ትምህርት
እየሰጡ በሙያ ሰልጥነው ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን አገርን ወገንን… መርዳት መቻሉን አርአያን ሆነው የሚያስተምሩ አባቶች ናቸው
👍24🥰2👎1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


የቀይ አፈር መንደር ገና እያዛጋች ነው፡፡ ካርለት ጥቁርና ቡናማ ቀለም ያለው የፍዬል ቆዳዋን ለብሳ አንባሯን ጨሌዋን
አንገቷ ላይ ደርድራ ቀለበቶችዋን በጣቶችዋ ሰክታ ጥልፍልፍ ነጠላ
ጫማዋን ተጫምታ
እቃዋን በጀርባዋ በማዘል ከከተማው ቁልቁል
በሚወስደው መንገድ ትንሽ ሄደችና ሰፊውን የአርባምንጭ መንገድ
ትታ ወደ ግራዋ በመታጠፍ ወደ ዲመካ የሚወስደውን ጎዳና ይዛ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

በሾላ ቆንጥር ዘረማይ ሶውት• ዲሎ ጉርዶ  ሶቆላ… የተሞላውን ጫካ ግራና ቀኝ እያየች የድርጭት ጭልፊት ቁራ
አቲ ሴሌ አርክሻ… አዕዋፍ ዝማሬ እያዳመጠች ልቧ በደስታ እየዘለለ ነጎደች፡፡

የእግር ጉዞ ትወዳለች፡፡ አቀበት ወጥታ ቁልቁለት ወርዳ! ላብ በጀርባዋ ተንቆርቁሮ, ሰውነቷ ዝሎ. ካሰበችበት ስትደርስ
የአሸናፊነት ስሜት  ይሰማታል፡፡ በራሷ ትኮራለች ህይወቷ ይታደሳል፤ ልቧ በደስታ ይዘላል።

በተለያዩ ቦታዎች ተራራ ወጥታለች በበረሃ አሸዋ
ተጉዛለች በበረዶ ተንሸራታለች ስለዚህ አካሏ ብቻ ሳይሆን የህሊናዋ ጡንቻም ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ ነው።

በሰዓት በአማካይ ከአራት እስከ አምስት ኪሎ ሜትር መጓዝ ትችላለች፡፡ ከቀይ አፈር መንደር እስከ ዲመካ ያለው ርቀት ሃምሳ ስምንት ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ሃምሳውን ኪሎ ሜትር ለመጓዝ ከአስር እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ይፈጅባታል፡፡ በየመካከሉ ግን እረፍት
ማድረጓ ስለማይቀር የመድረሻ ሰዓቷ በሁለትና ሶስት ሰዓት ይጨምር ይሆናል፡፡

የለበሰችው የሐመር ባህላዊ ልብስ አምሮባታል፡ ከኋላዋ በኩል የለበሰችው ቆዳ ውን ውን የሚል ሲሆን ከፊት ለፊቷ ግን አጭር ነው፡ ጭኖችዋ ለፀሐይ እንብዛም ተጋልጠው ስላልከረሙ እንደ ፋርኖ ነጭ ሆነው ያስጎመጃሉ፡፡ አንድ ወቅት ፀሐዩ ጠብሷቸው እንሶስላ መስለው ነበር፡፡

በየመንገዱ የሚያገኝዋት መንገደኞች እንግዳነቷን ገምተው ተደንቀው ቆም ብለው ሲያይዋት

ነጋ ያ” ትላቸዋለች፡

ጋ ያኒ" ይሏታል፡፡

“ነኖኖምቤ ቀለሎምቤ
ፈያዎ…" በነጭዋ ሐመር
ይገረማሉ፡ በደስታም ፈገግ ይሉና፡“ፈያኔ! ያ ፈያዎ! ይሏታል፡ ሰላምታዋን አቅርባ ከብቶች… ደህና ብላ ስትጠይቃቸው፡፡ እነሱም የእሷን ደህንነት ሲጠይቋት፡-

“ኢንታ ፊያዋ…” ብላ መንገዷን ትቀጥላለች፡እነሱም በአይናቸው ይሸኝዋታል፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሰላምታ ከተለዋወጡ ደህንነታቸውን ከተነጋገሩ በኋላ፡

“ናቢ ናሞ አይኔ? ይሏታል ስምሽ ማነው ለማለት በሐመርኛ፡፡

“ኢንታው! ፈገግ ትላለች የእኔ  ስም በማለት፡፡ እየሳቁ
እራሳቸውን ሲወዘውዙ፡

ናሞ አይኔ ካርለት ስትላቸው ይከብዳቸዋል፡ እንደገና
እየደጋገመች የእኔ ስም ካርለት ነው፡" ትላቸውና ተጨዋውተው
ደሞ ይለያያሉ፡፡

አንዳንዶቹ እንዲያውም ከደስታቸው ብዛት ሮጠው ሄደው በለሻ ወተት ይዘውላት ይመጣሉ፡ እነሱ ዘንድ እንድትውል
እንድታድርም ይጠይቋታል፡፡ “ምነው እዚች ምድር ያለው ሁሉ እንደእናንተ ቅን በሆነ! ብቻ ግን ሁሉም እንዲህ ቢተዛዘን ምናልባት
የህይወት ጣምናውን መግለጽ ይከብድ ይሆናል" እያለች ታስባለች፡፡

ስለዚህ ደግነታቸው  አቀባበላቸው ሞራል ስለሚሆናት ስትጓዝ ድካም አይሰማትም፡፡ ላብ ብቻ፡፡ የትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ
ማለት ብቻ… ውስጧ ግን ብርቱ ነው፡፡ ብረት ሞራሏም እንደአለት ጥንካሬው እያደገ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ hብቶችን የሚጠብቁ አፍላ ጎረምሶች
ያጋጥሟታል፡፡መፉቂያቸውን አፋቸው ውስጥ ሰክተው
የሚያብለጨልጭ ጭናቸውን ሳንቃ ደረታቸው ላይ ጨሌያቸውን
ያንዠረገጉ ይቀርቧትና ሞቼ ጉምዛ ክሮጃ  መፋቂያ  ጨሌ ይሸልሟትና፡-

“እጮኛ አለ?” ይሏታል፡፡

“አዎ!” ትላቸዋለች፡፡

“ሐመር ነው?”

“ከዎ፡፡

“ማን ይባላል?"

“ደልቲ ጉልዲ…"

“ይእ- አንች ነሽ ነጭዋ ሐመር?"

“አዎ"

ካርለት የምትባይው አንቺ ነሻ?

“አዎ-” ይገረሙና
“አንችንማ በስም የማያውቅ ማን አለ! ይእ!.." ሲሏት ካርለት ደስ ይላታል፡፡

ቀኑ እንኳን መሽቶ ከጨለመ በኋላ ሲያገኝዋት ጠጋ ብለው ያነጋግሯትና ሽኝተዋት ይመለሳሉ፡፡ በዚህ በጉዞው ወቅት ቀበሮ
ጅብ… ሲጮሁ ይሰሟታል፡፡ ግን አልፈራችም፡፡ አውሬዎች የሚያጠቁት ፊሪን ነው፡፡ የዓላማ ዕፅት ያለውን ያከብሩታል፡፡

ካርለት ዲመካ ለመድረስ ወደ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲቀራት ደከመች፡፡ በሐመር ባህል ልጃገረድ በምሽትም ሆነ
በቀን ብትጓዝ የሚደፍራት እንደሌለ ጠንቅቃ ታውቃለች:: ስለዚህ
በጉዞዋ ብትቀጥል የሚያሰጋት ነገር የለም፤ ድካሙ ሲጠነክርባት ግን
አንድ በቆሎ እርሻ ውስጥ ገብታ ለወፍ: መጠበቂያ ከተዘጋጀው ማማ ላይ ወጣች ትንሽ ብስኩትና ቼኮሌት ተመግባ በኮዳ ከያዘችው ውሃ ተጎንጭታ “ስልፒንግ ባጓ" ውስጥ ገብታ ከዋክብትን እያየች,
ተወርዋሪ ኮቦችን እየቆጠረች የእንቁራሪቶችን የኮኮሮችን ዝማሬ
እያዳመጠች እንቅልፍ እያባበለ ይዟት ጭልጥ አለ

ካርለት ከእንቅልፏ ስትነቃ ለጊዜው የት እንዳለች ድንግርግር አለባት፡፡ አይኖችዋን ከድና ስታስብ ከየት ተነስታ ወዴት
እንደምትጓዝ መቼ እንደደከማትና ማማው ላይ እንዴት እንደወጣች
ትዝ አላት፡ ራቅ ብለው ጎረምሶችና ህፃናት ይጫወቱ ነበር፡፡ ከማማው
ለመውረድ ስትሞክር ግን ሁሉም ዘወር ብለው አይዋት፡፡ ሻንጣዋን
ማማው ላይ ይዛ መውጣቱ ስለከበዳት ማማው ስር ነበር ጥላው የወጣችው፡ ማማው ከመንገዱ ብዙም  ስለማይርቅ እሷንም ሆነ
እቃዋን ብዙ ተላላፊዎች እያዩ ነው ያለፉት፡፡ ሐመር ውስጥ ግን የአንዱን ንብረት ሌላው አይነካም ወድቆ እንኳን ቢያገኝ ዛፍ ላይ
አንጠልጥሎት ይሄዳል፡፡ የጠፋው ተመልሶ እንዲያገኘው

ካርለት ልጆችንና ጎረምሶችን ሰላም ስትል አንድ ልጅ እግር ከቡዱኑ ነጠል ብሉሎ ሄደና፡-

“አይቶ!  እረ ኦይቶ" ብሎ ተጣራ፡፡

“ዬ!” የሴት ድምፅ ተሰማ፡፡
“ይዘሽው ነይ እንግዳዋ ልትሄድ ነው" ሲል በሐመርኛ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ካርለት ሰንደል ጫማዋን ቆልፋ ሳትጨርስ
አንዲት ልጃገረድ በዛጎልና ጨሌ የተዋበውን ቆዳዋን እያንሿሿች በቀጭኗ መንገድ እየሮጠች መጣች፡፡ በእጅዋ የወተት መያዣ ዶላ በሾርቃ ደግሞ የማሽላ ጭብጦ ይዛለች፡፡
ካርለት ልጃገረዷ ወደ እሷ ስትመጣ በአድናቆት
ተመለከተቻት፡፡ ኦይቶ ሰላም ብላት የወተቱን ዶላ ሰጠቻት፡፡ በሐመር ባህል የቁጥ ቁጥ ስጦታ የለም ያን የምታውቀው ነጭዋ ሐመር ዶላውንና ሾርቃውን ተቀበለቻት፡ ርቧታል፡፡ የዶላውን ክዳን ደፍታ
በ“ዶንግ" የታጠነውን ትኩስ ወተት በክዳኑ ቀዳቸና አንዱን ለጥሟ ጠጣች፡ ከዚያ ጭብጦውን በወተቱ እያማገች በላችና፡-

“ባይሮ ኢሜ” እግዜር ይስጥልኝ ብላ አመስግና ዶለውንና ሾርቃውን ለልጃገረዷ መልሳ ሁሉንም ተሰናብታ አሁንም “ሁላችንም ምን ነበረ እንደ እናንተ ብንሆን! ብላ እየተመኘች ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

ወፎች ይዘምራሉ እሷም ትዘምራለች ከብቶች ያገሳሉ
ተፈጥሮም እንዲሁ. የሙዚቃው  ህብረ ዜማ ተዋህዶ በሐመር
ቀዬዎች ያስተጋባሉ አይ ሕይወት! ተፈጥሮ የቃኘችው የህይወት
ለዛ.... ሳያቋርጥ እንደ ምንጭ ውሃ ከአድማስ አድማስ ይንቆረቆራል።

ምህረትየለሽ ቴክኖሉጂ አየሩን ከመበከሉ
ስግብግብነትንና ጦርነትን ከማስፋፋቱ ሌላ ተፈጥሮን ሊያዛባ አሁንም ባልተዳረሰበት ሁሉ ሃዲዱን ዘርግቶ ባህላዊ ህይወትን ሊጨፈልቅ ወደ ሐመር ሲምዘገዘግ ታያት፡፡

“አይ አፍሪካ! አለች ካርለት ከግብፅ እስከ ደቡብ አፍሪካ፧.ከኢትዮጵያ እስከ ሞሪታንያ ያሉትን የአፍሪካ አገሮች እያሰበች፡፡
👍26😱2🥰1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የንጋት ፀሐይ ከወደቀችበት ተነስታ ብርሃኗን ሐመር
ላይ ፈንጥቃለች፡ ካርለት ከወሮ መንደር ሆና ቁልቁል የሐመርን ተፈጥሮ ደኑን የልጃገረድ ጡት መስለው በሰማዩ ደረት የተሰካኩትን የአለሌ  ኤሎ ኤዲ ቢታ… ተራራዎች ስታይ
የምትሆነው ጠፋት ልብ ሰራቂው ተፈጥሮ አነሆለላት እና! ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ወደ ተፈጥሮ ሮጠች ተፈጥሮም ወደ እሷ ገሰገሰች ተቃቀፉ.. አንዱ የሌላውን ሽፋን አወለቀ… አየሩን ሳመችው... መሬቷን አቀፈቻት... ቅጠሉን ሰበሰበችው…ከወፎች ጌር
ሽቅብ ጎነች… ዳመናውን እየበረቃቀሰች በረረች የተፈጥሮ ፍቅር

የሐመር ተፈጥሮአዊ ሕይወት እንደ ቅንቡርስ በውስጧ ገብቶ በሰራ
አካላቷ ተንከላወሰባት ! እንደ እንበሶች ቦረቀች….. ፈነደቀች ከማራኪዋ ተፈጥሮ ጋር እየደጋገመች ተወሳሰበች…..

እንዲህ በደስታ ሰክራ በድካም ጥንዝል ዝርግትግት ብላ
ሳሩ ላይ እንደተንጋለለች የሰው ድምፅ ሰማች፡፡ 'ምን ነበረበት ከእንደዚያ ካለው ዓለም የማይመለሱ ቢሆን!'

ካርለት!

“አቤት" አለች ዞር ብላ እያየች ካርለት፡፡ “ጎይቲ ነይ
እስኪ አጠገቤ ቁጭ በይ"

“ይእ! ምነው እስካሁን ሳትጠይቂኝ ቀረሽ?''

“ምን ብዬ ጎይቲ?

"ይእ! አሁን እውን እሱ የሚረሳ ሆኖ ነው፡ ናፍቆትሽን ውስጥሽ ቀብረሽ ደብቀሽኝ እንጂ…" ያ ሐጫ በረዶ መሳዩን ችምችም
ያለ ጥርሷን እያሳየቻት ጠየቀቻት፡፡

“ደልቲን ነው! ምን ብዬ ልጠይቅሽ? ወሮ እንደማይኖር
አውቃለሁ፤ ዛሬ ግን ሄጀ ላየው እፈልጋለሁ  ናፍቆኛል!"

ጎይቲ ናፍቆኛል የሚለው አባባል የእሷንም እሳት
ጫረባት ወዲያው ገለባው ልቧ ቦግ ብሎ ነደደ፡

“ይእ! ካርለቴ አያ ደልቲ እኔንም ናፍቆኛል ግን የት ሄጄ ላግኘው" ብላ እንባዋ እንደ በጋ ዝናብ የመጣበት ሳይታወቅ ዥጉድጉድ ብሎ ወረደ፡፡ የሳግ ብርቅታ የውስጣዊ ስሜት
ነጎድጓድ… ጎይቲን ደፈቃት፡፡ ካርለት ደነገጠች ደስታዋ በኦንድ ጊዜ ሙሽሽ አለባት፡፡

“ጎይቲ ምን ሆነ? ካርለትን ጩሂ ጩሂ ብረሪ ብረሪ
አሰኛት፡፡ ጎይቲ ግን ካርለት የጠቀቻትን አልሰማችም! በአይነ ህሊናዎ ጀግናዋ እየተንጎማለለ ሲጓዝ አየችው፡፡ ስታየው አቅበጠበጣት ልቧ ዳንኪራ ረገጠባት… ሊርቃት ሆነ፤ መጥራት ፈለገች፡፡
ካልጠራችው እየተንጎማለላ ሄዶ ጫካው ውስጥ ገብቶ ይጠፋባታል፡፡

“አያ ደልቲ!” ተጣራች ጎይቲ ጮክ ብላ እንዲሰማት፡፡

ምን ሆነ ደልቲ" ካርለት ጎይቲን እየነቀነቀች ጠየቀቻት ጎይቲ ግን የጠራችው አንበሳዋ ዞር ብሎ የጠራውን ሰው በአይኖቹ ሲፈልግ የጡቶችዋ ጫፎች እየቆሙ ሰውነቷን እየነዘራት ወደ እሱ
ስትጓዝ ድንገት ጀግናው እየተንጎማለለ ጫካ ገባ፡፡ ሮጠች! እንቅፋቱ
መታት እሾሁ በልቧ ተሰገሰገ… ጫካው ደልቲን ሸፈነው ዋጠው
ለለቀጠው... ስለዚህ ድምጿን ከፍ አድርጋ ተጣራች፡

“አያ ደልቲ ጮኸች ጎይቲ፡፡ ካርለት ግን የምትሆነው
ጠፋት፡-

“ጎይቲ- ደልቲ ምን ሆነ?" ካርለት ሰውነቷ ተንቀጠቀጠባት
አቅም አነሳት• ድካሟ አገረሸ፡፡ ጎይቲ ደግማ ደጋግማ አለቀሰች
እውነተኛውን ደም መሳዩን እንባ!

ደልቲ ምን ሆነ ደ-ል-ቲ ካርለት እንባዋ ግድብን ጥሶ ወጣ› ጎይቲና ካርት ተቃቅፈው ልቅሶአቸውን አስነኩት፡፡

“አያ ደልቲ" እያሉ ጮሁ፤ የገደል ማሚቶው ግን
ድምፃቸውንም ደልቲንም ዋጠው…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካርለት ለምን አለቀስሽ?" አላት ከሎ ሆራ፡፡ ቲማቲም
የመለለ ፊቷን እያዬ:

እንዲሁ ጎይተን ምን እንደሆነ ደጋግሜ ስለጠይቃት…"አቋረጣት ከሎ፡-

“ጎይቲ ምን አለችሽ ታዲያ?

“ምንም"

“እንግዲያው ለምን አለቀስሽ?''

“እንጃ ክፉ ነገር የደረሰበት መስሎ ተሰማኝ፡፡ ከማጣራቴ በፊት ግን እንደዚህ መሆን አይገባኝም ነበር ይቅርታ! አለች ካርለት፡

ከዚያ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ፡፡

“ከሎ አንተ ግን ለምን አትነግረኝም?"

“ምኑን?

“ስለ ደልቲና ስለ አጋጠመው ሁሉ፡፡"

ካርለት ምን ብዬ ልንገርሽ? ጎይቲ እንደዚያ መሄጃ
መቀመጫ አሳጥታኝ መኪናዋን አስተኛሃት! እያለች ወትውታኝ
ካለረፍት ተጉዘን እዚህ ስንደርስ ደልቲ አልነበረም

“ቡስካ ሄዷል' አሉንና እዚያ ሄደን ስንጠይቅ ዳራ የምትባል የሳላ መንደር ልጃገረድ አብራው እንደተቃበጠችና ደልቲ
መቀመጫውን ሰርቶ እንደሄደ ወይሳ እየነፋ ያም እንደነበርና በእርግጥ አልፎ አልፎ ትክዝ ይል እንደነበር ሰማን፡፡ ከዚያ የላላም
የሻንቆም የቡስካም ሰው ዳግመኛ አለማየቱን ተረዳን፡፡

“ጎይቲ ይህን ጊዜ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች መጮህና ማልቀስ ጀመረች፡፡ ዳራ በበኩሏ ጎይቲ ስታለቅስ እሷም በተራዋ ትንፈቀፈቅ
ጀመር” ብሎ ከሎ ገጠመኛቸውን ሊቀጥል ሲል፦

“ከዚያስ ተገኘ? ካርለት  ረጅሙን ታሪክ መከታተል
አልቻለችም! ሲቃ ያዛት፡፡

“ከዚያማ ጫማ ጣዮች እንዲተነብዩ ተጠየቀና “ክፉ
አልደረሰበትም፧ ራቅ ብሎ ግን ሄዷል' አሉ፡፡ አንጀት አንባቢዎችም ትንሽ ቆይቶ ይመጣል ብለው የታያቸውን ተናገሩ፡፡ጎረምሶች ጫካውን ደአሰሱት መልዕክት በየአቅጣጫው ተላከ ከዚያ  በካሮ  ማህበረሰብ በኩል ያሉት የደንበላ መንደር ሰዎች አየነው ብለው መናገራቸውን ሰማን፡፡

እኔም የአንችን መኪና ይዤ በየመንደሩ ለፍለጋ ዞርሁ
አሁን ደንበላ አይተነዋል እሚለውን ስንሰማ ግን እሱን ልፈልግ ወይንስ አንቺን አዲሳባ ሄጄ ላምጣ በሚለው ከሽማግሌዎች ጋር ስማካር አንች መጣሽ?

ከወጣ  ማለቴ ከሄደ ስንት ጊዜ ሆነው?

"ሃያ ቀን በላይ ሆኖታል፡"
እሽ ለምን ነው አንዳንዴ ከፍቶታል የተባለው?"

“ጎይቲን ያፍቅራታል፡ የአንድ ቤተሰብ አባል በመሆናቸው
እንጂ አብሯት ቢኖር ደስታውን አይችለውም ነበር፡፡ ስለዚህ ከአይኑ
ስትርቅ ላይከፋው ሳይተክዝ አልቀረም። ስለ አንችም ደጋግሞ ያነሳ እንደነበር ሰምቻለሁ የእሷ መባለግ አንሶ ጎይቲንም ይዛት ሄደች!  እያለ እንደሚቆጭ ኮይታውን ከፍሉ እንደጨረሰ አንችን ሲያገባ ያንን
ለስላሳ ገላዋን እገለብጠዋለሁ' እያለም ሲፎክር እንደነበር ሰምቻለሁ" አላት ከሎ ፈገግ ብሎ።

እውነቱን ነው የሐመር ልጃገረድ ነኝ ብዬ ባህሉን
መቀበሌን አሳውቄ! ካለ ሽማግሌ ፈቃድ ያውም ከሐመር ምድር ርቂ መሄዴ በእርግጥ ሊያበሳጨው ይገባል" አለችና በሃሣብ ተውጣ ቆየች፡፡

እንዲህ ካርለትና ከሎ በሃሣብ ተውጠው እንደተቀመጡ ጎይቲ አንተነህ መጣች

“ይእ ምን ሆናችኁል?"
አለቻቸው ሁለቱንም በፍርሃት አየቻቸው ሆዷ ፈራባት “ጎይቲ ምንም አልሆነም፡፡ አንችን
ጠይቄ ልትነግሪኝ ያልቻልሽውን ስለ ደልቲ ከሎን እየጠየቅሁት ነበር"

“እሁሁ… እኔስ ደሞ ምን ሰማችሁ ብዬ የሆንሁትን
አላውቅም" አለችና ሐጫ በረዶ ጥርሶችዋን አሳይታ

“ይእ! የአያ ደልቲን የኦሞ ዳር ጥንቅሽ የቀመስን እኔና
አንች ሌላው ጣምናውን የት ያውቀዋል" ብላ በሣቅ ተፍለቀለቀችና

ነይ በይ አሁን ቡና ጠጭ እህልም ባፍሽ አድርጊ፡፡
የደንበላ ሰዎች “አይተነዋል ብለዋል እንኳን እስካሁን ደና ሆነ እንጂ ከአሁን በኋላስ ከምስጥ ዋሻ ቢገባም አያመልጠን፡፡ ይእ!

አንተስ ና እንጂ  ይኸውልሽ ከመጣን ጀምሮ አበሳውን እያሳየሁት ነው፡፡ ና በል የኔ ጌታ.." አለችውና ከሎን ሶስቱም ተያይዘው በር ወደሌለው የሐመር ጎጆ ሄዱ!
👍291👏1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ብላንክ ፓሎማ' ይሉታል ስፔኖች! ነጭ እርግብ ማለት ነው፡ የዚህ የስፔኑ ተወላጅ እውቁ ሰዓሊ ፓውሉ ፒካሶ ደግሞ ነጭ
እርግብን የሰላም ምልክት አድርጎ ለአለም ህዝብ አበርከቷል፡

ብላንካ ፓሎማ ሮሲ በተባለ ቦታ በዓመት አንዴ የሚከበር ከኢትዮጵያውያን ጥምቀት ጋር የሚመሳሰል በዓል ነው፡፡ ስፔናውያን
እየደነሱና እየጨፈሩ የአለፈውን ዘመን አመስግነው መጭውን
ደግሞ ሰላም የሰፈነበት የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው አምላክን የሚያመሰግኑበትና የሚለምኑበት ክብረ በዓል ነው ብላንካ ፓሎማ።

በዓሉን ለማክበር ከተለያየ ቦታ ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ  እንዲሉ ሴቶቹ ከወገባቸው ጠቡብ ብሎ  ከታች ቦለል በማለት መሬት
የሚነካውን ቀሚሳቸውን ወደ ላይ በጣታቸው ሰብሰብ ያርጉና
አንቧለሌ እየዘሩ ጣቶቻቸውን እንደ ኮብራ አንገት እያሟለሉ ወንዶች ደግሞ የተተፈተፈ የቆዳ ሱሪና ሰደርያ ነጭ ሸሚዝ ሰፊ ባርኔጣ ይለብሱና ብብቱ ውስጥ ዝንብ እንደገባበት ፈረስ ባለ በሌለ ኃይላቸው መሬቱን እየደለቁ እጆቸውን እየሰበቁ እንደ አውራ ዶሮ በሴቷ ክብ ሲዞሩ ጭብጨባው ዝማሬው ፉጨቱና ጨኸቱ
ይቀልጣል፡፡ አሸነፈችው! አሸንፏታል! እየተባለ አቧራው ይጤሳል።

በብላንክ ፓሎማ በዓል
ዘመናዊ ተሽከርካሪ አይኬድም ዘመናዊ ነገር ፈጽሞ እንዲታይም አይፈለግም ወደ በዓሉ ቦታ
የሚጓዘው ሰው በፈረስና በቅሎ  በሚሳቡ ባህላዊ ጋሪዎች የሚበላ የሚጠጣው  ይጫንና ህፃናትና አዋቂን በባህል ልብሳቸው አሸብርቀው አልፎ አልፎ ወንዶቹ በሚገባ በተቀለበ ጠብደል ፈረሰና በቅሎ ሆነው ሶምሶማ እየረገጡ እንደ አባቶቻቸው ወግና ባህል በዓሉ ወደ ሚከበርበት ሮሲ ሲጓዙ በየከተማው ህዝቡ እየወጣ እያጨበጨበና
አብሮ እየጨፈረ ይሽኛቸዋል፡፡

በግብርና ምርቷ በመላው አውሮፖ በይበልጥ የምትታወቀው
ስፔን ህዝቧ በደስታ ፍንድቅድቅ እያለ የአለፈ  ወግና  ልማዱን በዓመት በዓመት እየተከተሉ አምላኩን ሲያመሰግን ሮሲ ሲሰባሰብ ደስታውን ለመክፈል ፈገግተኛና ደስተኛውን የበዓል አክባሪ አይቶ ለመርካት በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ከፈረንሳይ ከፖርቹጋል ከሌሎችም የአውሮፓ አገሮች ወደ ሮሲ ይጎርፋል፡፡

ብላንክ ፓሉማን ለማክበር የሚሰባሰበው ሁሉ ዓላማው በሰላም  መዝናናት ነው፡፡ በቡድን በቡድን ጨዋታና ጭፈራው
ይቀልጣል ፍቅር እየታጨደ ይወቃል ደስታ እንደ ብርቱካን እየተላጠ ይበላል.. በብላንካ ፓሉማ
ኮንችትና ሶራን ወደ ኢትዮጵያ ከመሄዳቸው በፊት እዚህ ባህላዊ በዓል ላይ እንዲካፈል ጋበዘችው፡፡ ሶራ ሆራ ብላንካ ፓሎማን
ለማክበር የተሰባስበው ህዝብ  ለበዓሉ የሚሰጠው ግምት ሲያይ የባህል የማንነት መለያነት ጥቅሙ የመገናኛ ድልድይ መሆኑ
የፍቅር ማጠናከሪያነቱ… ወለል ብhሎ ታየው።
ስዉ ይጨፍራል ይተቃቀፋል በአንድ ጠርሙስ እየተቀባበለ ይጎነጫል እየተሸማ ይበላል... ደስ አለው ሶራን፡፡
እሱንም እየነካኩ  እያጨዋወቱ የስፓኛን ወይን እያቀማመሱ… በህዝቡ መስመር አሰለፉት፡፡ የችሎታውን አጨበጨበ ጨፈረ “ኢትዮጵያዬ' እያለም ጮኸ፡፡ የጥቁሩም የነጩም ፈጣሪ ወደ ሆነው
አምላኩም ምስጋናውን በማህሌተ ዜማው አሰማ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከጎኑ ጽናጽሉን እያንሿሿ ያዜም ቀሳውስት ሲወርቡ የአማራው የጉራጌው የወላይታው. የሲዳማው የኦሮሞው
የኤርቦሬ..ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ባህላዊ ጭፈራ ታየው፡፡ እና ዘለለ!
ብቻውን ሳይሆን ምናቡ ከአመጣቸው ወገኖች ጋር ከዚያ ውብ አፍሪካዊ ጋር ከብላንካ ፓሎማ በዓል አክባሪ ጋር ዘለለ ነጭ
እርግቦች ሰማዩን ሞልተውታል፡

“ብረሩ ሂዱ አፍሪካንም ሙሏት..." ጠራቸው ነጫጭ
እርግቦችን፡፡ እርግቦቹ ይስሙት አይስሙት ግን አያውቅም፡፡

ኮንችት አረንጋዴ ሆኖ ዳር ዳሩ በቀይ ሪባን የተከፈፈ
ቀሚሷን ለብሳ ዞማ ፀጉሯን ጎንጉና አናቷ ላይ በቀይ ሮዝ የፀጉር ማስያዣ አስይዛ የሙቀት ማራገቢያዋን በቄንጥ በመያዝ እንደ አበባ
ፈክታ ወንዶች እንደ ንብ ዙሪያዋን እየበረሩ፤ መሬቱን እየደለቁ ጣታቸውን እየሰበቁ… በዚያ እንደማግኔት በሚስበው ፈገግታቸው እያሽኮረመሟት ሲያይ ኮንችት ልዩ ፍጥረት ሆነችበት፡፡ ጠይሟ
ለግላጋዋ... ኮንችት ደሙን ተክታ በውስጡ ተሰራጨች፡

ብላንካ ፓሎማ… ብላንካ ፓሎማ… ሶራ በሺ የሚቆጠረው ህዝብ ተረሳው፡፡ ሌሎችን ዘነጋቸው. ኮንችት ብቻ ታየችው ኢትዮጵያዊዋ ውብ የጠይም ቆንጆዋ የቁንጅና ልዕልቷ…

“በብላንካ ፓሎማ ስጦታ አበረክትልሀለሁ" ብላዋለች፡፡

“ምን ይሆን ስጦታዋ! ጎመዠ፡፡ እስካሁን ልትሰጠው ስላሰበችው ስጦታዋ አለማሰቡ  አስገረመው፡ አያት ከርቀት
ትደንሳለች፡፡ ቼኮሌቷ ጠይም እንቁዋ! በአይኑ ነካት  በአይኑ ቀመሳት  ጣፈጠችው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እኩለ ለሊት አካባቢ ሰዉ ተዳከመ፡፡ ሁሉም ወደ
የማደሪያው ተበታተነ… ኮንችት ገላዋን ታጥባ ስስ የሌሊት ገዋኗን ለብሳ ስትወጣ ከድንኳኑ ትይዩ ሶራ ያቀጣጠለውን እሳት አየች፡፡
ከሐር የተሰራ ሰፊ  ስጋጃ ተነጥፏል አንድ ጠርሙስ ወይንና   ሁለት ብርጭቆ ይዛለች

እሳቱ አስቸግሮህ ነደደ" አለችው ስጋጃው ላይ
ቁጭ እያለች።

የት ያመልጣል ብሎ ሲያያት የሆነ ነገር ተመለከተ ነጭ ፓንት ተምታታበት፡ አንዳች ሀይል ከውስጡ አንገጫገጨው

"ብላንካ ፓሉማን ወደድከው?"

ቆንጆ በዓል ነው፡ ስሙ ራሱ ነጭ…" እንደገና ወደ እሷ
ተመለከተ ነጩንም ...አየው

ኮንችት ከላይ ገዋኗን ከታች ነጭ ፓንቷን ትልበስ እንጂ
እንደ ሎሚ ሁለት ቦታ ጉች ጉች ያሉት ጡቶችዋ ሰርጓዳ ወገቧ ለስላሳው ጭኗ ካለመከላከያ ይታየዋል፡

ሶራ ጫን ጫን ተነፈሰ ልቡ ፈራ ስሜቱ ተረበሸ ይባስ ብሎ ተንጫጫ።

ኮንችት በሁለቱ
ብርጭቆዎች ለብላንካ ፓሎማ የሚዘጋጀውን ምርጥ ወይን ቀዳችና  የዚህ ዓይነት ወይን ከዚህ
በፊት እርግጠኛ ነኝ የቀመስህ አይመስልኝም፡፡ ውድ ነው! እኔ ግን
የምወደው በውድነቱ ወይንም በቃናው ሳይሆን በመልኩ ነው፡፡
ፀሐይ ላይ ወይን ጠጀ በጨረቃ ብርሃን ደግሞ ወርቃማ ይሇናል ና አዚህ ጋ ቁጭ በልና ተጎንጨው" አለችው፡፡

ሄዶ ከሷ ፈንጠር ብሎ ቁጭ አለ መዓዛዋ ግን
አልራቀውም ለጤናችን ለስጦታዬ" ብላ አየችው፡ ተጎነጫጨለት፡፡

ለስጦታዬ አሰበ ሶራ
እንዳንጋጠጠ ወይኑ መሆኑ
ነው ስጦታዋ .. ውዱ በጨረቃና በፀሐይ ብርሃን እንደ እስስት ቀለሙን የሚቀያይረው

ጣምናውን  ለማወቅ እንደገና ጎንጭ አድርጎ አጣጣመው ወደ አፍንጫው ጠጋ አድርጎ አሽተተው ቀና አድርጎ በጨረቃ ብርሃን ተመለከተው… ወርቃማ ነው!

“ወደድከው አይደል?" የኮንችት አነጋገር እንደ ከላሲካል ሙዚቃ የጆሮውን ታንቡር እየዳሰሰው በሰራ አካላቱ ሰረገ፡፡

“አዎ ጥሩ ነው" ዝም ተባባሉ እሳቱ ይነዳል፡፡ የእሳቱ ብርሃን እነሱ ላይም ተንፀባርቆ ከርቀት ለሚያያቸው እነሱም የሳት
ላንቃ መስለዋል፡፡ ሶራ በጀርባው ስጋጃው ላይ ተኛ እሷ ደግሞ ወደ እሱ ዙራ በጎኗ ተኛች፡፡ የሆነ ነገር እየወዛወዘ እያት እያት አሰኘው ግን ፈራ፡፡

ዛሬስ ገና ስሜቷን እያዳመጠችው ይሆን? ጠየቀ ራሱን ዞር ብሎ ሊያያት አሰበ፡፡ የሆነው ነገር ወዘወዘው እንደገና ቀስ ብሎ ዞር ብሎ አያት  አይኗ ነው የወዘወዘው ፍዝዝ ብሏል አይኗ ከንፈሯ እንደ እንቡጥ ፅጌሬዳ አሞጥሙጧል አይኑን ፈጠጥ አድርጎ አያት፡፡ አየችው እሷም  በፈዘዙ አይኖችዋ፤ የእሳቱ ብርሃን
ግን በመካከላቸው አለ፡፡ ጡቷ ወገቧ ነጩ ፓንት. ታዩት የገዛ ምራቁ ሊያንቀው
ተቃረበ፡፡ ዘወዲያው ልቡ አይኑን ስልብ ስልምልም… አደረገበት፡፡
👍27👎2
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ብጠጣለት የሚጎዳኝ ይመስልሃል?"

ወራጅ ውሃ እኮ ነው። እፅዋት በልምላሜ ፈክተው ጎንበስ ቀና እያሉ የሚወዛወዙበት አራዊት እየፈነደቁ የሚፈነጥዙበት
ዋኔ ዳክዬዎች ብቅ ጥልቅ እያሉ ተጎንጭተው የሚንሳፈፉበት ወደ
ሰማዬ ሰማያት ጉነው የሚበሩበት... ውሃ የሚጎዳሽ አይመስለኝም፡፡
ስለዚህ ይህን ከብክለት ነፃ የሆነ ውሃ በእጆችሽ መዳፍ እያፈሰሽ ተጎጭው  ማሬ አላት፡፡

ኮንችት እድሜዋ ባጠረ ግርምታ ተመሰከተችውና፡-

“ይገባኛል ገና አልተበከለም ገና አልቆሸሽም… ስልጣኔ
ኩሉን አልጣላበትም ቅርሻቱን አልደፋበትም… በእርግጥ ሳልፈራ መጠጣት ነበረብኝ ብላ በርከክ ብላ ሁለት እጆችዋን እንደ አካፋ አሹላ በእፍኝዋ የቀዳችውን ውሃ እንደ ወፎቹ አንጋጣ ወደ ጉሮሮዋ
አንቀረቆረችው፡ ጎርፍ መሳዩ ንፁህ ውሃ ጉሮሮዋን እያቀዘቀዛት ቁልቁል ወረደ ደስ አላት ጣማት፡፡ ስለዚህ እየደጋገመች ተጎነጨችው፡፡

ቀና ብላ አየች ሰማያዊው ሰማይ ተውቧል ! ወደ ዳርና
ዳር እፅዋትን ተመለከተች  የቆላ ዋንዛ፡ ጥቁር እንጨት እንኮይ ጠዪ. ቃጫ. . . በአረንጓዴ ልምላሜ ተሞልተው ምድሯን
አስውበዋታል፡ ጉጉት ድርጭት ጂግራ ቆቅ… ወፎች ይዘምራሉ ይጯሀሉ ይስቃሉ… አቦ ሽማኔ አንበሳው ቆርኪው ዝንጀሮው ጦጣና ጉሬዛው. በእዕዋት ስር ሲርመሰመሱ፡ በእዕዋት ቅርንጫፎች
ላይ እየተንጨዋለሉ ሲወናጨፉ ይታያሉ፡፡
እባቡ እንሽላሊቱ… በዕፅዋት ግንድ
ይልወሰወሳሉ፡፡ ኦሞ ወንዝ ላይ አዞው ራሱን አውጥቶ ይንሳፈፋል፧አሶች ብቅ እያሉ ጥቡሉቅ ይላሉ….

ተፈጥሮ እንደ ሙሽራ ደምቃለች አምራለች ፈክታለች...እንደ ማራኪው የአዳም ዘመን ገነት ኑሮ! ኮንችት ያን ድንቅ ውበት
በአይኗ  በጆሮዋ ባጠቃላይ በስሜት ሕዋሶችዋ እየኮረሻሽመች በላችው  እንዳያንቃት ከወንዙ ውሃ ተጎነጨለት….

“…ገና ካሁኑ አያቴ ያጣውን ተረዳሁለት" አለች ወደ ሶራ
ዙራ፡

“ድንግል ውበትን ነፃነትን እርጋታን… ነበር አያቴ ያጣው'' እንባዋ በአይኖችዋ ሞላ፡፡ “ሁካታ የሌለበት ዓለም አንዱ ሌላውን
የማይጎዳበት ተፈጥሮ ቅኝቱ የተዋሃደ ቅላፄ ነበር አያቴ ያጣው ለካ" እየሳቀች አለቀሰች፡፡ እንባዋ እየፈሰሰ ጥርሶችዋ ግን ተገለጡ
ሰዎች እውነተኛ ስሜት ሲሰማቸው ስሜታቸው ይደበላለቃል" ይህች
ፕላኔት የሚለቀስባት ካልያም የሚሳቅባት ብቻ አይደለችም፤ ደስታና
ሐዘን ሣቀና ልቅሶ እንደ ሳንቲም ገፅታ አብረው የሚኖሩባት ናት፤እና እውነተኛው የተፈጥሮ ስሜት ኮንችት ላይም ደረሰ
እንደ አያቷ ትናንትን ዛሬ ላይ ቁማ አለመችው፧ እንደ
ልጆችዋ ዛሬ ላይ ቆማ ነገን አሰበችው ተፈጥሮ እንደ ሰው አታረጅ ይሆናል እሚያቆሽሻት ሰው እስካለ ግን እንደ ትናንቱ ዛሬ
አታምርም፡ እንደ ዛሬው የውበት ፀዳሏ ለነገ አይደርስም፡፡ እና
ኮንችት ከመሃል ሆነች ከኢትዮጵያዊው አያቷና ካልወለደችው ልጅዋ መካከል!

ኮንችት የእፎይታ ትንፋሽዋን አንቦለቦለችና ሃዘንና ደስታዋን ሙሉ በሙሉ የተካ ፈገግታ ለውቡ ተፈጥሮ አበርክታ ሶራን ተመለከተችው፡፡

ኮንችት እንደ ከብቶች፥ እንደ አዕዋፍ እንደ እፅዋት ራቁቷን ብትሆን ትመረጣለች በተለይ በእንዲህ ዓይነቱ ተፈጥሮአዊ ተፈጥሮ… መመሳሰል ያረካታል።

ፓንትና ጡት ማሲያዣ ሲቀር
ሁሉንም ልብሷን አወለቀችው ልብስ ገመናን ሃፍረተ ሥጋን መሸፈኛ ነው።
እውነተኛው ተፈጥሮ ግን ገመና ሃፍረተ ስጋ የለም፡፡ ተፈጥሮ ገነት ናት አዳምና ሄዋን ዕፀ በላሷን ከመብላታቸው በፊት
እንደነበሩት።

ቤጫ መስመር በጎንና ጎኗ የተጋደመባት ሰማያዊ ቀለም ያላት የፕላስቲክ ጀልባ እየተጀነነ በኩራት ቁልቁል ይሁን ሽቅብ
መፍስሱ ግራ በሚያጋባው የኦሞ ወንዝ ላይ እንደ ቄብ ዶሮ ቂብ ብላ በአፍንጫዋ ውሃውን ግራና ቀኝ እየከፈለች ትንሳፈፋለች፡

ኮንችት አጠር ያለውንና ቢጫውን መቅዘፊያ ካስቀመጠችበት
አንስታ ከሶራ ጎን ካለው ቦታ ቁጭ ብላ በግራ እጅዋ የመቅዘፊያውን እጀታ ጨብጣ ውሃውን ሶስቴ
ገፋችና ወደ ሶራ ዞራ ፈገግ አለች፡፡ ሶራም በመቅዘፊያው ውሃውን
ወደ ኋላ እየገፋ ፈገግ አለላት፡፡

ኮንችት ከተቀመጠችበት ተነስታ ቆመችና ወደ ወንዙ ዘለለች ወደ ኦሞ ቁልቁል ሰጠመች፤ እግርና እጅዋ በስልት እየተንቀሳቀ
እንደ አሶች ውስጥ ለውስጥ ዋኘች፡፡

ሶራ መቅዘፉን አቁሞ ኮንችት ካለ ህይወት አድን ጃኬት ባዶዋን ወንዝ ውስጥ በመግባቷ ደነገጠ፡፡ ልብሱን ከመቅጽበት አውልቆ አያት ገና ብቅ አላለችም፡፡ ዘሎ ውሃው ውስጥ ገባና
በውሃው ውስጥ ለውስጥ ፈለጋት፡፡ ስማያዊዋ ጀልባ ግራ ቀኝ ተወዛወዘ ቀስ በቀስ ተረጋግታ ተንሳፈፈች፡፡ ሶራ የሆነ ድምፅ ሰማና
ሽቀብ ወደላይ ቀዘፈ:

እህ! እህ. በድካም እያቃሰተች ኮንችት ትስቃለች፡፡እሱም አብሯት ሳቀ፡ ውሃው ውስጥ ተጠጋጉ፡ ሳቀ ሳቀች ፍርስ
እያሉ ተሳሳቁ ውሃ ተራጩ የአፍሪካ ንሥር አየሩ ላይ
ይንሳፈፋል፡፡ ከዳር በኩል ውሃ ሲጠጡ የነበሩት ዝሆኖች በአድናቆት
ተመለከቷቸው
“ዝሆን የአፍሪካ ዝሆን ጆሮ ሰፊው የዝሆን ጉዞ' በሚል
በልዕልት ሚድታውን ታናል' ስርከስ ላይ ከቀረቡት ዝሆኖች ሁሉ እጅግ የገዘፈ' ብላ ኮንችት ዝሆኖችን በአድናቆት ተመሰከተቻቸው፡፡

ሶራና ኮንችት ጀልባዋ ላይ ወጡ፡፡ ሰውነታቸው በውሃ
ነጠብጣብ ተሞልቷል፡ ዝሆኖች ለምለም ጨሌ ሣር ከሚታይበት ሜዳ ወጣ አሉና አንድ ኮርማ ዝሆንና አንዲት ሴት ዝሆን መዳራት
ጀመሩ፡፡ ከጥቂት ማሽኮርመም በኋላ ወንዱ ዝሆን ያን ግዙፍ ሰውነቱን ወደ ላይ አንስቶ በኋላ እግሩ ቆመና የፊት እግሮቹን ሴቷ
ዝሆን ላይ ጭኖ የእንግሊዘኛውን ኤስ' ፊደል ቅርፅ ያለውን ብልቱን
እንደምንም ብሎ ሴቷ ብልት አስገባና ሰረራት፡፡

ኮንችትና ሶራ ያን ተፈጥሮአዊ ትርኢት አፋቸውን ከፍተው
ሲያዩ ላያቸው ላይ የነበረው የውሃ ነጠብጣብ ደረቀላቸው፡፡ የጫካው
የተፈጥሮ ድሪያ ሳባቸው፡፡ ተፈጥሮ ውስጥ የተፈጥሮ ድሪያ ያስጎመዣል ...

ኮንችት ለስላሳና ቀጥ ያሉ ጭኖችዋን አጥፋ የመቅዘፊያውን እጀታ አንስታ ለመቅዘፍ ጠምዘዝ ስትል ሰፋ ያለው ዳሌዋ ሰርጓዳው ወገቧ ጠባቡ ትከሻዋ ሰውነቷ ላይ የተለጠፈው ዞማ ፀጉሯን…
አየው! ተስገበገበ… ኮንችት እንዲህ የውበቷን ሰዲቃ ሲቋደስ ዞር ብላ ፈገግታዋን አከለችለት፡

ከወንዙ ውሃ ግራና ቀኝ ካሉት የውበት ፀዳሎች ጋር
የተጣጣመው ውበቷ እንደ ፍላፃ ሕሊናውን ወጋው፡፡ ዞር አለች እንደገና፤ ሶራ ከንፈሮቹን በቀስታ ግራና ቀኝ እንደ ላስቲክ እየለጠጠ
ዘርዘር ያሉ ጥርሶቹን አሳያት እሷም ፈገግ አለች  ፈገግታዋ በመቀጣጠል ላይ ያለውን ስሜቱን ቤንዚን እንደጨመሩበት እሳት
ባንዴ ቦግ አደረገው፡፡ ሰደዱ እሷ ህሊናም በቅጽበት ደርሶ እሷንም ለበለባት…ሳይታወቃቸው እሳታቸውን ለማብረድ ሁለቱም
ከንፈሮቻቸውን በምላሳቸው አረጠቡ የአይናቸው ቆብ ቁልቁል እየወረደ ተከደነ… ዝሆኑ ሽቅብ ተነሳ. ሴቷ ተጠጋችው፡
የሚመነጭቀው እንዳለ ሁሉ ጥብቅ አድርጎ አቀፋት… ዝሆኑ!
አእዋፍ ያፏጫሉ ጀልባዋ
ትንሳፈፋለች እንቁራሪቶች
ያንቆርራሉ ኮንችት የሶራን
የእጅ ጡንቻዎች ሳም ሳም ስታደርግለት እሱ አካሏን እየላሰ ሎሚውን በእጁ ጣቶች እያሻሽ ከንፈሩና ከንፈሯ ተገናኘ ኮንችት ይበልጥ እየሰረሰረች ተጠጋችው !
ያኔ! ጎርበጥ ያለው ነገር ቆረቆራት የቆረቆራትን የቀኝ እጅዋን ሰዳ ከተደበቀበት ስታወጣው እንደ ህፃን ልጅ ፈነደቀ…

ኦሞ ወንዝ በኵራት ይፈሳል እፅዋት በንፋስ ይወዛወዛሉ
+ፈጥሮ አራዊትና አዕዋፍ ይዳራሉ:: ብርጉዱ እጣኍ ጠጅ ሳሩ ጤናዳሙ ጽጌረዳው የበረሃ እጣነ አካባቢውን አልባብ አልባብ
እሸተ† ድንቅ የተፈጥሮ ህይወት ታምር ይታያል!
👍19
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ኮንችትና ሶራ የሶስተኛ ቀን የኦሞ ወንዝ ላይ ጉዟቸውን
ሲጀምሩ አየሩ ጨፍገግ ያለና ሰማዩ በጥቁር ዳመናዎች የተሸፈነ
ነበር፡፡

“ብንቆይ አይሻልም  ኮንችት"

“አይ! አስቸጋሪውን ጉዞ ብንጋፈጠው ይሻላል፡፡ ምናልባት እየተጓዝን ዝናቡን ልናመልጠው እንችል ይሆናል፡፡ስለዚህ ቶሉ
መንቀሳቀሳችን ይሻላል፡"

“ወንዙ ላይ ዝናቡ ከያዘንስ?''

“ያኔ ከወንዙ ወጥተን ድንኳን ወጥረን እንጠለላለን፤ እዚህ
ሆኖ ሳይሞክሩ ተሸናፊ መሆን ግን አልፈልግም" አለችው፡

“እሽ በኔ በኩል ለጉዞ ዝግጁ ነኝ፡፡"

“ቆየኝ አንዴ” ብላው ለመፀዳዳት ወደ ጫካው ገባች፡፡ ሶራ የወንዝ ላይ ጉዞ አስደሳችም አስፈሪም እንደሆነ እየተረዳ መጥቷል፡፡

በተለይ ከመጀመሪው ቀን ቀጥሎ በነበረው ውድቅት ሌሊት አንበሶች የድሪያ ወቅታቸ በመሆኑ ከድንኳናቸው ብዙም ሳይርቅ እያገሱ ሲታገሉ
ኮንችትና ሶራ ከአሁ አሁን ላያችን ላይ ወጡ ገነጣጥለው ሊቀራመቱን ነው ሲሉ እንቅልፍ በዓይናቸው ሳይዞር ነው ያደሩት።

በሁሉተኛው ቀን ደግሞ ድንገት የጣለው ከባድ ዝናብ ድንኳናቸውን በጎርፍ ውጦ ልብሳቸው በሙሉ ረጥቦ በዚያ ጥርስ
በሚፋጨው ብርድ እንደከበት ዛፍ ስር ጎን ለጎን ኵርም† ብለው
አንዱ በሌላው ትንፋሽ ሙቀት እየተጋሩ ነበር የመከራ ሌሊቱን ያሳለፉት።

ስለዚህ በነጋታው እስከ አጥንታችው ድረስ ዘልቆ የገባው ቆፈን እስኪወጣላቸው ፀይይ ላይ ተሰጥተው አረፈዱ ሰውነታቸውን ማዘዝና ማንቀሳቀስ ሲችሉ በጎርፍ የተዋጠውን ድንኳን ነቅለው
እቃውን አውጥተው… ፀሐይ ላይ አሰጡት ከዚያ ረጅም ሰዓት ቆይተው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ተነስተው ሰላሳ ኪሎ ሜትር ተጉዘው እንቅልፍና ድካም ተጫጭኖአችው ስለነበር ደረቅ ዳቦና ብስኩት ብቻ ተመግበው ተኙ ልክ እንደሞተ ሰው ተኝተው
አድረው ሲነቁ ስማዩ የታቀፈውን ጥላሽት የመሰለ ዳመና እላያችው
ላይ ሊዘረግፈው ተዘጋጅቷል።

የሶራ ምርጫ ዝናቡን ማሳለፍ ይሻላል ነበር ኮንችት ግን ሃሳቡን ልተቀበለችውም።

አሁን መሄድ እንችላለን የህይወት ማዳኛ ጃኬቱን ልበስ ሱሪውን አውልቀውና የዋና ፓንትህን ታጠቅ አለችው ሶራ የተባለውን እየፈፀመ አያት የለበሰችው የዋና ፓንቷን ነው
ጭኖችዋ ከምን ጊዜውም በላይ አምረዋል: ከላይ ቀይ የህይወት ማዳኛ ጃኬቷን ቀይ ሄልሜቷን ደፍታ ዮጉዞ ቦርሳን ከጀርባሞ አዝላለች ሶራም እንደ እሷ ትጥቁን እያስመረ ስማዩን ቀና ብሎ
አየው ጠቁሯል
ጀልባዋን ውሃው ላይ ካሳረፉ በኋላ ድንኳናቸው
ምግባቸውን የማብሰያ እቃቸውን… ከጀልባው መሀል አስቀምጠው
በጣም አስፈላጊ የሆነውን ቁሳቁስ በጀርባ ቦርሳቸው አዘሉት፡፡ ከዚያ “አድሪፍት" የምትለው ጀልባ ላይ ያለውን ረጅም ገመድ ወገባቸው ላይ ካለው ሰፊ ቀበቶ ጋር አያያዙት፡፡

ጀልባዋ ላይ ወጥተው ሚዛናቸውን ለመጠበቅ ከኋላ በኩል ግራና ቀኙ ተቀመጡና መቅዘፊያቸውን አንስተው አውራ ጣታቸውን
በማንሳት ዝግጁ ተባባሉና ወደ ኦሞ ወንዝ መሃል ሄደው ቁልቁል ቀዘፉ

ሰማዩ እንደ ተቆጣ ነብር ማጉረምረም ጀመረ። ድንገት ሰማዩ በቀጫጭን የብርሃን ዝግዛግ እየተሰነጣጠቀ ብልጭታው
ይታይና ብራቁ ድብልቅልቅ ብሎ መጮሁ እየጨመረ ሄደ፡፡

“ኮንችት!” ብሎ  ጠርቶ አያት፡፡ ቶሎ ቶሎ ትቀዝፋለች ለማምለጥ፡፡ ድክም ያላት መሆኑ በዚያ ቆፈን የሚወርደው ላቧ ያስታውቃል፡፡ ሶራ አዘነላት፡፡ ምን ሊያደርግላት እንደሚችል አሰበ፡፡
መላው አጥጋቢ አልመሰለውም፡፡ ይሻል ይሆናል ብሎ ገመተና ጮክ
በማለት ደግሞ ጠራት፡-

“ኮንችት…….” ሲል ሰማዩ ብልጭልጭ አለና የጆሮ
ታንቡራቸው የተነደለ እስኪመስል ብራቁ ጮኸ፡፡ሁለቱም በደመነፍስ ዝቅ አሉ በድንጋጤ፡፡

ኮንቺት አያቷ ትዝ አላት አደራው ተጭኗት ኖሯል፡፡
ማንኛውንም መስዋዕትነት ከፍላ አደራውን መፈፀም መቻል አለበት፡፡ህሊናዋ ከዚህ ግዴታዋ ውልፍት እንድትል አይፈቅድላትም፡፡ የዚያ ምስኪን ኢትዮጵያዊ አያቷን ዘመዶች ከመፈለግ ከአቅሟ በላይ በሆነ
ችግር ሞት ጥፍሩን አሽሎ መጣሁ' እያለ ቢያስፈራራትም እንኳ
ላለመሽሽ ለራሷ ቃል ገብታለች፡፡ ብዙ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ አስባ
ከማያዳግም ውሳኔ ላይ ደርሳለች፡፡

ብራቁ ካለፈ በኋላ ማጉረምረሙ እየበዛ የመጣውን ሰማይ ቀና ብሎ አየና ሶራ ኮንችትን አያት፡፡ ከዝያቡ ሊያድናት ፈለገ
ስለዚህ ጮክ ብሎ ጠራት

ኮንችት ለምን ጉዞውን አቁመን እንጠለልም፡፡ ከዚያ…" ብሎ ሃሣቡን ሳይጨርስ ገሃነም ግባ እሽ ቦቅቧቃ ፈሪ ነህ!  ወደፈለግበት መሄድ
ትችላለህ! እኔን ግን አትጥራኝ  ደደብ!" አለችው፡ ሶራ መብረቁ ጭንቅላቱ ላይ እንደወደቀ ሁሉ ክው አለ። ስላዘነላት ነበር የጠየቃት እሷ ግን አውሬ ሆነችበት ።

ሶራ እንደተወጋ አውሬ ሸቅሽቆት ውስጡ የገባው አነጋገሯ አደነዘዘው አበሸቀው።

ዝናቡ ህፃናት የሚጫወቱበትን ብይ እያካከለ ዥጉድጉድ
ብሎ መውረድ ጀመረ፡፡ ኮንችትና ሶራ ማየት እንኳ ተሳናቸው፡፡የመዋኛ መነፅራቸውን አደረጉ: ጉሙ እየሸፈነ ይበልጥ ማየት
ተሳናቸው፡ ቀስ እያለ ደግሞ አዙሪቱ ሰማያዊ ጀልባዋን ወደ ታች ሳይሆን እንባለሌ ያዞራት ጀመር፡፡

ሁለቱም ባለ ሃይላቸው ቀዘፉ አዙሪቱ ደግሞ  እነሱን
ይበልጥ እያሽከረከረ ቀዘፋቸው፡፡ ቁልቁልና ሽቅቡ ዳሩና መሃሉ እስኪጠፋቸው ድረስ ከላይ ዝናቡ ከታች ዙሪቱ ልባቸውን
አጠፈው፡

ድንገት ደግሞ ዥው ብለው በአየር ላይ ሲንሳፈፉ እነሱ
ከሥር ጀልባዋና ውሃው ከላይ ሆኑ፡፡ ከሁሉም የከፋው አዲስ መከራ
ተጀመረ፡፡ ኮንችትና ሶራ ውሃው ያላጋቸዋል ያሰጥማቸዋል። ዝናቡ
ከላይ ዶፉን ያወርደዋል፡፡ ወገባቸው ላይ ገመዷን ያሰሯት ጀልባም
ወዲህ ወዲያ ትመነጭቃቸዋለች በጀልባዋ ወለል የነበረውን
ጓዛቸውንም ኦሞ ሰለቀጠው፡፡

ሰማዩ  አልበቃውም ያጉረመርማል  ይጮሃል፤
ይወርዳል. ኦሞ ወንዝም እርጋታው ጠፍቶ ይደነፋል ይሽከረከራል እላይ ደርሶ ይፈርጣል አሶች አዞዎችና ጉማሬዎች የሚሉትና
የሆኑት አይታወቅም፡፡ ኮንችትና ሶራ ግን አበሳቸውን ያያሉ። በኒያ
ወጣቶች መሃል ውሃ ገባ በቅጽበት እንደ ተራራ የገዘፈ ችግርና መከራ ላያቸው ላይ ተከመረ ይባስ ብሎ በእንቅርት ላይ  ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አካባቢውን ፅልመት አለበሰው፡፡ ኮንችት መከራው ሲበዛባት ያመለጠች መስሏት የጀልባዋን ገመድ ከጎኗ ፈታችው፡፡ ከዚያ ከሶራና ከጀልባዋ ተጠፋፋች… እሪ ይላል ሰማዩ፡- አካባቢው
በእሮሮ በእግዚኦታ ተዋጠ፡፡

ሶራ ጀልባዋ እየጎተተችው ብዙ ከተጓዘ በኋላ በጭንቅ ወደ ዳር ወጣ፡፡ የይወት ማዳኛ ጃኬቱና ሄልሜቱ ነፍሱን አተረፋት፡ ዝናቡ ቆሟል ቀና ብሉ ሰማዩን አየ፡፡ ሰማዩ ጠርቷልı ጨረቃ ወጥታለች ከዋክብት ብልጭ ድርግም ይላሉ፡፡ ሶራ የሆነውን ሁሉ
ለማሰብ ሞከረ፡፡

ጀልባዋ ከሱ ጋር ነች፡፡ ኮንችት ግን አብራው የለችም፡ ያች መለሎዋ ያች ኢትዮጵያዊት  ደፋርና የፍቅር ልዕልቱ አጠገቡ
የለችም፡፡ ከጀልባዋ ጋር ያያዘችው ገመድ ተበጥሷል፡፡

ሶራ ኦሞን ዞር ብሉ አየው፡፡

“ኦሞ አላማ ያለውን ሰው  እውን ትበላለህ?” ብሎት ማልቀስ ጀመረ ሶራ። ጮኸ “ፍቅሬን ምሳሌዬን… ተነጠቅሁ” ብሎ ቀና
ብሎ ሰማዩን እያዬ ተማፀነ፡፡

እኔንም መብላት አለብህ ኦሞ፡፡ልትነጣጥለን አይገባም ሲሆን እኔን ማስቀደም ነበረብህ…” እየተንቀጠቀጠ አለቀሰ፡፡

“ምነው እግዚአብሔር... ምነው! የኦሞ ወንዝ ዳርን ጭቃ እያፈሰ ፊቱን እየቀባ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ለአምላኩ
👍16
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ሶራ ሲያገኛት በጭቃ ልውስውስ ብላ ሰው አትመስልም። ጦርሷቿ ይፏጫሉ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል አካሏ የማታዝበት በድን ሆኗል። በጀርባው ያዘለውን ፈቶ በፕላስቲክ የተጠቀለለ ስሊፒግ ባግ አውጥቶ የበሰበሰና በጭቃ የተለወሰ ልብሷን አውልቆ ፎጣ አልብሶ ስሊፒግ ባግ ውስጥ እየጎተተ አስገባት።

በውርርድ ደረቅ ቦታ የለም ደለሉ በሙሉ ጨቅይቷል ውሃ ተኝቶበታል ስለዚህ ሶራ በቶሎ ከዚህ አካባቢ መራቅ እንዳለበት አምኖ ጀልባዋን ለማምጣት ሄደ።

ሶራ የፕላስቲክ ጀልባዋን በኦሞ ወንዝ ዳር ለዳር እየቀዘፈ ኮንችት ወዳለችበት ሄደ።ከጀልባዋ ወርዷ ወደኮንቺት ሲጠጋ አትሰማም። እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ወስዷታል።
የጀርባ ቦርሳቸውን ከጫነ በኋላ እሷን ጀርባው ላይ
አስተካክሎ በሰፊ ቀበቶ ከገላው ጋር አሰራትና የጀልባዋን ገመድ ፈቶ
ቀስ ብሎ ጀልባዋ ላይ ወጣ፡ hዚያ ጆልባዋ ወለል ላይ ትራስ አድርጎ
አጋደማትና ከጀልባዋ በስተኋላ እግሩን አንፈራጦ ቁጭ ካለ በኋላ መቅዘፍ ጀመረ"

ቀኑ ፀሐያማና ነፋሻማ ነው፡፡ ኮንችት ወዲያ ወዲህ ሳትል
ተንጋላለች፡ ሶራ ትንሽ ሲቀዝፍ ይቆይና ጆሮ'ውን ልቧ ላይ ይደቅናል። ከዚያ ተመልሶ ደግሞ ይቀዝፋል…
የሞላው የኦሞ ወንዝም ቁልቁል መግፋቱን እየረዳው እስከ ቀኑ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ድረስ ተጓዘ፡፡

ኮንችት በስፓኒሽ “ውኀ" ትለውና አንገቷን ቀና አድርጎ
ሰሰጣት ጎንጨት ታደርግና ትተኛለች፡ ርሃቡ ራሱ ሊጎዳት እንደሚችል ቢያምንም ጀልባዋን ሊያቆምበት የሚችል የተሻለ ቦታ በማጣቱ እግር ጉልበት እየጨመረለት ብዙ እንደተጓዘ ሜዳማ ደረቅ• ጨሌ ሣርና ጥላቸው ዘርፈፍ ያሉ ዛፎች ዘንድ ደረሰ፡፡ ቀስ ብሎ  እየቀዘፈ ጀልባዋን ወደ ዳር አስጠጋና ኮንችትን እንዳይጫናት
ተጠንቅቆ በጀርባው አዘላትና ቀስ ብሎ
ቁጭ አለ፡፡ ጀልባዋ
ስለምትንቀሳቀስ ጀልባዋን እንደገና ወደዳር
ይበልጥ አስጠግቶ
እንደተቀመጠ ተንጠራርቶ ወንዙ ዳር ላይ ያለ የዋርካ ሥር ያዘ ያለው እድል ያ ብቻ ነበር።

መቅዘፊያውን ከጀልባዋ ላይ ፈቶ ወደ ውሃው ውስጥ ከቶ ለካው፡፡ መሬቱን ነክቶ ለመሻገር ኮንችትን አዝሉ እስከ አንገቱ ውሃ
ውስጥ መነከር አለበት፡፡ ምናልባት ከታች ያለው መሬት ድቡሽት
ከሆነ ስለሚሰምጥ እሷን ይዞ ለመዳን ይፍጨረጨር ይሆናል፡፡ እሷን አዝሎ ግን ካልተመቸው እንደተመኘው ሁለቱም እንደተዛዘሉ
አብረው ከአስቸጋሪው ሕይወት ለዘላለም ያርፋሉ፡፡ሶራ አሁን አልፈራም፡፡ ተለያይቶ ከመሞት አብሮ መሞትን ይመረጣል፡፡
በአርግጥ ሞትን ሊያመልጥ ብዙ ተጉዟል፡ ብዙ ሸሽቷል፡፡ ሞትን ግን ሊያመልጠው አልቻለም፡፡ ለሁሉም ወረቀት ፅፎ ሊያስቀምጥ ፈለገ፡ አዎ የሷም ሆኑ የእሱ ዘመዶች ሙት እንደሆናቸው መጠን እንደማንኛውም ሰው  መሞታቸውን አውቀው ልሳቸውን በማውጣት በነሱ ላይ ያላቸው አጉል የተስፋ ህልማቸው ሊቆም ያስፈልጋል የእሱንም
የእሷንም ስም አድራሻ… ፃፈና በላስቲከ አስሮ ወገቡ ላይ ባሰረው ውሃ የማይገባው ላይነን ቀረጢት ከተተው፡፡

ከዚያ ውሃው ሲወስዳቸው እንዳይለያዩ በሌላ የዕቃ ማሰሪያ ቀበቶ በሷና እሱ ትከሻና ጉያ ስር አሰረው፡፡
“እፎይ  ድሮ ሞትን እንዴት እፈራው ነበር፡፡ አሁን ግን
ቢያንስ መሞቴ እንደማይቀርልኝ አመንሁ! ከማንም ሰው  በላይ
የመሞቻ ጊዜዬ መድረሱን ከነደቂቃው አውቄያለሁ, ከፍቅረኛ ጋር ደግሞ ወደ ሞት መሄዴ የሙት ዕድለኛ ያደርገኛል" ብሎ እዕዋቱን
ሰማዩን የማታዋን ጀንበር ከማህደሩ መግደያ ሰይፉን በመምዝ ላይ ያለውን የኦሞን ወንዝ አየና የዋርካ ስሩን ጠበቅ አድርጎ ይዞ
ከጀልባዋ ወደ ውሃው ውስጥ ገባ፡፡

የኢትዮጵያዊውን አያቷን እትብት የተቀበረበትን ለመፈለግ ደክማ ያልተሳካላትን ቆንጆ ውሃው ውስጥ እየገባ አያት፡፡ ከዚያ
ውሃው አሰመጠው? እንደፈራው ከደረቱ አላለፈም፡፡ ስለዚህ በዛፉ
ሥር አማካኝነት እየተጎተተ ወደ ውጭ ወጣ፡፡ መከራና ስቃይን ውጦ እንደጨረሰ ሁሉ ፊቱ በደስታ ፀዳል በራ፡ በቅፅበት ከመከራ
ወደ ደስታ ተመለሰ፡፡

ከዚያ ጫካ ውስጥ ገብቶ የደራረቁ እንጨቶችን ለቅሞ
አመጣና ውኃ የማያበላሸውን ክብሪት ጭሮ እሳት አቀጣጠለ፡፡
ከጀልባዋ ላይ ያለውን የጀርባ ሻንጣ አውርዶ ለኮንችት ፓንት ሣይቀር ቀይሮ እሳቱ ዳር አስተኛትና ለችግር ጊዜ ብለው የያዟትን
ትንሽ ድንኳን ዘረጋ፡፡

ከጀርባ ሻንጣው ተጣጣፊ መጥበሻና ብረት ድስት አውጥቶ ለችግር ጊዜ ካስቀመጡት ምግብ መካከል የሚበላ አዘጋጀና ሻይ  አፈላ ኮንችት ቀስ በቀስ ዓይኖቿን መግለጥ ስትጀምር የአይብና አሳ ሳንዲዊች ወደ አፏ አስጠጋላት ከጭኖቹ ደገፍ እንዳለች ሳንዱቹን ገመጠች ሻየለንም መጠጣት ጀመረች።

ከዚያ የራስ ምታታ መድሃኒት እንደዋጠች ፈሳሽ ቅባት ጀርባዋን ጭኖቿን ክንዷን ፊቷን እያሸላት  እቅልፍ ይዟት ሄደ ቀስ አድርጎ አቀፈና ድንኳን ውስጥ አስተኛት።

የሱ እስሊፒግ ባግ ካንጠለጠለበት ዛፍ ላይ ንፋሱ ሲያወዛውዘው ጠፈፍ እስኪልለት እሳቱ ዳር ጋደም አለና ሽቅብ ወደ ሰማይ አየ። ሰማዩ ጥርት ያለ ደመና አልባ ነው አየሩ በደንብ እንደበዘቀዘ እርጎ የሚገመጥ ነው ተወርዋሪ ኮኮቦች ይወረወራሉ ጨረቃ ትንሳፈፊለች ድንቁ ተፈጥሮ እንደገና የሚያስጓመጅ ሆኗል ቀናት ያልፋሉ ዛሬም አይቀርም ያልፋል ግን በሚያልፍ ጊዜ ስንቱ አዝኖ ስንቱ ይደሰታል?

እኩለ ሌሊት ላይ የትንሿ ድንኳን ዚፕ ጢዝዝዝ ብሎ ተከፈተ ጨለማው በጨረቃ ብርሃን ድል ተነስቷል የእሳቱ ነበልባል ጠፍቷል ፍሙ ግን አለ አጠገቡ ኩርምትምት ብሎ የተኛው ሶራ ነገር አለሙን ዘንግቶ እንቅለሰፉን ይለዋል።

ኮንቺት እጇን ግንባሩ ላይ አስቀመጠች ሶራ አልተንቀሳቀሰም ዝቅ ብላ አየችው። ተመልሳ ደግሞ የሆነውን ሁሉ ለማስታወስ ሞከረች ሰመመናዊ ህልሟ ሳይቀር።

ሶራ ከዚያ መአትና የጫካ አውሬ አፍ አውጥቷታል አሁን ግን ያሉበት ተፈጥሮ እየነፈሰ ስሜትን የሚኮረኩር ነው። እንደገና አየችው ሶራ የለበሰው ስሊፒግ ባግ እርጥብ በጭቃ የተለወሰ ነው።

ዝቅ ብላ ከንፈሩን ሳመችውና ቀና ብላ ላፈቅርህ በመቻሌ ደስታ ይሰማኛል አለችው እንደዚያ እንደ ዘቢብ የጣፈጠ አባባሏን ቢሰማ ኖሮ ምንኛ በደስታ በፈነጠዘ የተቃጠለ አንጀቱ እንዴት በራሰ ግን አልሰማትም መልካም ነገር እንዲህ በቀላሉ መቼ
ይሰማል!

ኮንችት ቀስ ብላ የሞቀ ትኩስ  ትንፋሽዋን በጆሮ ግንዱ እያንቦለቦለች

“ሶራ ሶራ..." አለችውና ጭቃ የተቀባባውን አንገቱን
ግንባሩን ስትስመው አይኖቹን እንደምንም ብሎ ከፈተደ።

“ሶራ" ያ ሙዚቃዊ ጣዕም ያለው ድምፅ ጆሮው ላይ
አዜመ። ለመንቃት ታገለና አያት

ኮንችት! ጥርሱ ሳቀና አይኑ እንባ ሞልቶ ወደ ጎን ወደ
ጆሮ ግንዱ ፈሰሰ፡ ኮንችት እንባውን በምላሷ ቀመሰችው በፍቅር
የተቀመመ ጣፋጭ ነው  እንባው!

“አፈቅርሃለሁ የእኔ ማር!'' አለችው። ሶራ አባባሏ
“አታፍቅሪኝ ኮንችት!  ካፈቀርሽኝ ፍቅሬ ይከብድሻል ከከበደሽ ደግሞ ወርውረሽ ትጥይውና ትጠፊብኛለሽ:: ያኔ መከራ ይውጠኛል: ስለዚህ…" ከንፈሩን በከንፈሯ ከደነችው:: ከንፈሯ
ትንፋሽዋ ምላሷ. ሙቅ ነው።

ፍቅር ይከብደኛል!
ስፈራው ስሸሸው ኖሪያለሁ:
ካለፍቅር መሞት አልፈልግም የሞትን በር ሳንኳኳ+ የሚከፍቱት
ሲንቀራፈፉ አንተ ነጥቀህ መለስኸኝ። እኔ ደግሞ ፍቅሬን ዘንጥፌ
ልሰጥህ ወሰንኩ! ላለማፍቀር ስሸሽ እንደኖርኩት! ለማፍቀር ደግሞ ቅንጣት ታክል ፍርሃት የሌለኝ ደፋር ነኝ!

ሶራ ተምታታበት፤  ሳታፈቅረው እንዳፈቀራት አብሯት ቢዞር መከራም ገፍቶ ቢመጣ ቀድሟት ቢሞት ደስተኛ ነው።
ፍቅሯን እንደተሸከመው ሁሉ አሷም ፍቅሩን ብትሸከመው ሸክሟን ወርውራ ትሸሸው ይሆን?
👍342😱1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


የሐመር ታዋቂ ሽማግሌዎች ጫማ ጣዮች አንጀት አንባቢዎች... ቡስካ ላይ እንደገና ተሰባስበው ሸፈሮ ቡና ተፈልቶ
የጋራ ምርቃቱ ተዥጎደጎደ።

ጫማ ጣዮች ደልቲ ገልዲ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ
ጫማቸውን እያሽከረከሩ እየወረወሩ የጫማውን አወዳደቅ ደጋግመው አዩና “ሰላም ነው፤ ወደ ኦሞ አቅጣጫ ሄዷል" አሉ፡

"አንጀት አንባቢዎች ደግሞ ትንበያቸውን ለመጀመር ሁለት ፍየሎችን አሳረዱና አንጀቱን በጥንቃቄ አነበቡት ! “አደጋ
አልደረሰበትም ሆዱ ውስጥ ግን ነገር አለ! መንገድ አሁንም እየተጓዘ ነው  ወደ ፀሐይ መውደቂያ'' አሉ።

የፍየሎች ሥጋ በሐመር ደንብ መሰረት ወጠሌ ጥብስ ተጠበሰ፡ እሳቱ ከመሐል ነደደ የሥጋው ብልቶች ጫፉ በሾለ
ረጃጅም ችካል ላይ ተሰክቶ ችካሉ  በሳቱ ዙሪያ ተተከለ: እሳቱ ሥጋውን አይነካውም፤ የእሳቱ ወላፈን ግን ሥጋውን ሙክክ አድርጎ አበሰለው።

ሽማግሌዎች የግማሽ ጨረቃ ክብ ሰርተው እንደ
እድሜያቸው ልዩነት ተቀመጡ። ከዚያ በሐመር ደንብ መሰረት የፍየሎቹ ፍሪንባ ለሽማግሌዎች ቀሪው ደግሞ ብልቱ እየተቆራረጠ እንደየ እድሜው ታደለ።

ሽማግሌዎች ሲመገቡ ጎረምሶችና ልጃገረዶች ራቅ ብለው ቁጭ አሉ። ከልጃገረዶች ውስጥ እንግሊዛዊቷ የስነ ሰብዕ ተመራማሪ አለች: ተመራማሪነቷ የሚያውቁት የማንቸስተር ዩንቨርስቲና ከሎ ሆራ ብቻ ናቸው፡ ሐመር ላይ ካርለት አንድ የሐመር ልጃገረድ ናት። የተገረፈችውን የጀርባ ላይ ምልክት ሳትሸፍን የፍየል ቆዳዋን ለብሳ ጭኖችዋን ጡቷን ለጎረምሶች እይታ ገልጣ ፀጉሯን አኖ
ተቀበታ ከሐመር ልጃገረዶች ጋር ወሬዋን እየሰለቀች የአባቷን
የሐመር ቀዩ በሣቋ የምታደምቅ ዝናብ ናት።

ካለ ዝናብ ጨሌ ሳር ካለ ጨሌ ሳር ከብት ካለ ከብት
ደግሞ ሐመሮች መኖር እንደማይችሉት ሁሉ በጨሌ በዛጎልና
በአምባር ያጌጡ ልጃገረዶች በሐመር  ምድር ካልታዩ ሳቃቸጡ ካልተሰማ ዳንኪራቸው ካልታዬ... ሐመሮች የሉም ማለት ነው:

ካርለት አልፈርድ ከልጃገረዶች ጋር ሽማግሌዎች የሚፈፅሙትን ከቅርብ ሆና ታያለች: ጎይቲ መንደር ውስጥ ናት ከሎ ሆራ ግን የሐመር ደን (ያገባ ሙሉ ወንድ) በመሆኑ
ከሽማግሌዎች ግርጌ የተሰጠውን ያላምጣል።

ስነ-ስርዓቱ ካለቀ በኋላ ደልቲን ለመፈለጉ ከሎ ሆራና አንተነ ይመር ተመረጡና ተመርቀው አደራቸውን ከተቀበሉ በኋላ
ወደ ካርለት ሄዱ።

"መሄድ እንችላለን  ካርለት"

"ምን ተባለ?”
"
“ያው እንዳየሽው ባህላዊ ትንበያው ተፈጽሟል። ወንዙን ከመሻገሩ በፊት ድረሱበት… ብለውናል" አላት።

hዚያ ተያይዘው ወደ መንደር ሄዱና ጎይቲን አገኝዋት የተባለውን ካርለት አስረዳቻት

“ጎይቲ ለብቻሽ ላናግርሽ?”

“ይእ!  እሽ ምን አዲስ ነገር ገጠመሽ?"

ይኸውልሽ አሁን እንግዲህ ለፍለጋ መሄዳችን ነው::አንች

“ይእ ካርለቴ እኔ ልቀር ማለት ነው?

"አዎ  አንቺ ቅሪ ከሎም ሊከፋው ይችላል አየሽ
እሱ .. "

“በይ በቃሽ እቴ አንችስ አንደኔ ሴት አደለሽ: የወለድሽው ልጅ አድጎ መልሶ አያገባሽ ግን ለምን ነው የምተወጂው
ለምን ነው ለልጅሽ
የምትሳሽው እኔ በርግጥ አግብችለሁ ግን
ያልወለድሁት ሽል ሆኖ ልቤ ውስጥ  የሚኖር ሰው አለኝ ሆዴ ውስጥ ሲንከላወስ የማየው . ያ ሰው ልቤን በፍቅር መዳፍ መሃል
የያዘው በገዛ ፍላጎቴ ነበር ልቤን ከፍቼለፈት ውስጤ ገባ.. አሁን ያ ሰው ሲጠፋ ከማንም በላይ በሐዘን አንጀቱ የተመተረ ከኔ በላይ
ማንም የለም:: የፍቅር ጀግናዩ ልቤ ውስጥ የታቀፍሁትም ልጄ
ነው  አውጥቼ የማልጥለው

“ይእ! እኔኮ ከንግዲህ ከእሱ ጋር የመቃበጥ እድሌ እንደ
እትብት ተቆርጧል እትብት ከመቼ ወዲህ ተመልሶ ተቀጥሎ ያውቃል ውስጤ የታቀፍኩት ግን ከገላዬ ጋር እንደተጣበቀ ነው ለልጄ  ለፍቅሬ ጌታ እሳሳ እጨነቅለታለሁ ስለዚህ የሱን መጨረሻ ሳላውቅ ጎኔ አያርፍም! ልቤ አይተኛም::

እና የኔ እህት እባክሽ ሴት ሆነሽ የሴትነት ምጥ
ይሰማሽ" ብላ  እንባዋን
ታወርደው ጀመር።

ሰውነቴ አረ ተይ ይብቃሽ አይንሽ ይጠፋል ምን
ይሆናል ብለሽ እንዲህ ቀን ከሌት የምታነቢው?

“ይእ ካርለትም ከሎም ደብቂው ዋሾ ሁኚ አንጀትሽ
እየከሰለ ሳቂ በእዝነ ልቦናሽ እያየሽው በአካል ግን አ
እጥፍጥፍ ብለሽ ተቀመጭ! ፍቅርሽን አውጠሽ ድፊው እያሉ ሲታከኩብኝ አታይም
ስቅ ስቅ ብላ አለቀሰች እንደገና::
"ተዋት የኔ ልጆች
የልጅነት ጨዋታዋን ዘንጊው ማለትማ ደግ አይደለም ማንስ የልጅነት  ዘመኑን ዘንግቶት ያውቃል ምስጥ አለ አንተነህ ይመር: ወደ ልጅነት ዘመኑ
የኋልዮሽ እየተንደረደረ:: አየው የልጅነት ዘመን
ቡርቃውን…

“ሁሉ ነገር ሲለዋወጥ  ካለበት የማይንቀሳቀስ ትዝታ ነው የልጅነት ዘመን! የወጣትነት ዘመን" ብሎ አንተነህ ይመር እንደ
ልጁ እሱም ወደ ልጅነት ትዝታው የኋልዮሽ ሮጠ ሁሉ
የሚጣፍጥበት ዘመን በራስ መተማመን ጢቅ ብሎ ሞልቶ የሚኮፈስበት ዘመን ትዝ አለው:

ተዋት አትፍረድባት አፍኝው ቻይው ምጥሽን አትናገሪ
አትበሏት ብሶቷን ታውጣው: ሐዘኗን ትግለፀው። እንዲህ ሁናስ መቼ ሰላም ይኖራታል አብራን ትሃድ፤ ተነሽ መስታዋቴ ከለ። ካርለት በተናገረችው ተፀፀተች: አንተነህ ሲናገር ህሊናዋን ሐዘን እንደቁርጥማት አኘካት። መኪናዋ አራቱን ፈላጊዎች ይዛ ወደ ኦሞ
ተንቀሳቀሰች።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የወንዝ ላይ ጉዞውን ከጀመሩ ስምንት ቀን ሞላቸው። ወገቧ ላይ ቢጫ መስመር የተሰመረባት ሰማያዊ ጀልባ በኦሞ ወንዝ ላይ እየተንሳፈፈች ኩዱማ እና ማርኩል መንደሮች አደረሰቻቸው

ኮንችት አያቷ ባስጠናት መረጃ መሰረት በየመንደሩ
እየተዘዋወረች ስታስተውል አያቷ የነገራትን ፍንጭ ባለማግኘቷ ጎዞአቸውን ቀጠሉ።

ሙርሲ ማህበረሰብ ሲደርሱ ወንዶች ፀጉር
የማይወዱ የራስ  ፀጉራቸውን የወንድ ብልታቸውን ብብታቸውን
የሚላጩና ፀጉር ማሳደግ እንደ ነውር የሚቆጠርበት
የወንዱን የራሱንም ሆነ የጉያውን ፀጉር መላጨት ያለባት ሴቷ መሆኗንና
ፀጉር ቢያድግ ግን የምትወቀስ ሴቷ እንደምትሆን አዩ።
የሙርሲ ሴቶች ከሸክላ አፈር የተሰራ ክብ ገል ኸንፈራቸው ላይ ጠፍጣፋ እንጨት ጆሮአቸው ላይ ያንጠለጥላሉ: ቁጥሩ
ከአምስት ሺ የማይበልጠው የሙርሲ ማህበረሰብ የተሻለ የግጦሽ ፈና የእርሻ ቦታ በመፈለግ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወር ከበርካታ አጎራባቾቹ ጋር በዚሁ የተሻለ ቦታ ለማግኘት ሲንቀሳቀስ የሚጠቃ ማህበረሰብ በመሆኑ በጥንቱ ዘመን ብዙውን ጊዜ የሙርሲ ሴቶች፡ ከብቶቹ
በግጭቱ ወቅት የሚዘርፍና ከሱዳን የሚመጡ ባርያ ፈንጋዮችም ሴቶቹን ስለሚወስዱባቸው ለዚያ መከላከያ የሙርሲ ሴቶች ከሌሎች ሴቶች የተለዩ እንዲሆኑ ገል ከንፈራቸው ላይ እንዲያስገቡ በማድረግ
የሴቶችን ዝርፊያ ማስቆሙ! ይኸ ጠቃሚ ዘዴ በማህበረሰቡ እንዲ
ለመድም ሰፋ ያለ ገል ከንፈራቸው ላይ የሰኩ ልጃገረዶች አነስ ያለ
ገል ካደረጉት ልጃገረዶች የበለጠ ጥሉሽ እንዲከፈልባቸው መደረጉ!
ያ ድርጊት ሴቶች በከንፈራቸውና ጆሮአቸው ገል እንዲሰኩ የተጀመ
ረው ተቀባይነት አግኝቶ እንዲቀጥል አሁን አሁን እንዲያውም ሰፊ
ገል hንፈር ላይ መሰካት ብዙ ጥሉሽ የሚያስገኝ በመሆኑ የቁንጅና
መለኪያ ተደርጎ በውጩ ማህበረሰብ እንደሚገመትም አወቁ።
👍23🥰1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ኮንችትና ሶራ በኦሞ ወንዝ ሲጓዙ በኡዱማ መርኩል
ጎዋ ኩረምና ሻንጋሮ ያሉትን የቦዲና የሙርሲ መንደሮች ካዩ በኋላ የደቡብ ሱዳንን አቅጣጫ  ይጓዝ የነበረው
አቅጣጫውን ከደቡብ ወደ ምስራቅ ድንገት እጥፍ በማድረግ መጓዝ ጀመረ

በአለምአቀፍ አቅጣጫ ማስተካከየዋ ጂፒ ኤስ'
ከሳተላይቶች ጋር ግንኙነት ፈጥራ ያለችበትን የኬክሮስና ኬንትሮስ
ዲግሪ ካወቀች በኋላ ማፑን ስትመለከት በጣም ከሚጠማዘዘው የኦሞ
ወንዝ ጉዞ በኋላ የካራ የሙሩሌ ዳሰነች ማህበረሰቦችና ዝቅ ብሎ
የሚታየው የቱርካና ሐይቅ ብቻ የሚቀራቸው መሆኑን ተረዳች በዚህ ጊዜ ኮንችት ትልቅ ሃሣብ ላይ ወደቀች የአያቷን ቀዬ ለማግኘት የቀራት እድል በጣም ውስን ነው  የዳሰነች ማህበረሰብ ያለው  ከቱርካና ሐይቅ ጥግ ሲሆን አያቷ ስለሃይቅ ፈፅሞ አንስቶ ስለማያውቅ የሱ ማህበረሰብ ዳሰነች ሊሆን አይችልም ስለዚህ ጥርጣሬዋ ወደ ሁለት ዝቅ አለ ከካራና ከሙረሌ
ከነዚህ አንዱ ካልሆነ ግን የአያቷን ቀዬ ለማግኘት
የምትወስደው አማራጭ
ጭልምልም ያለና  ምናልባት ሌሎች ተጨማሪ አመታትን የሚወስድ ይሆናል ስለዚህ ኮንችት ጭንቀት አንገቷን ሲያስደፋት ሶራ ችግሯ ምን እንደሆነ ገብቶት፡-

አዞይሽ ካሰብሽው ትደርሻለሽ" አላት::

ያ ሃሳብ አንዳች ውስጣዊ ሃይል ፈጠረላት አመሰግናለሁ ብላው ጉዟቸውን ቀጠሉ።

ትንሿ ድንኳናቸው ከኦሞ ወንዝ ራቅ ካለ ጉብታም ቦታ አግራር ዛፍ አቅራቢያ ተተክላለች።

ኮንችት ሁለት እግሯን እጥፍጥፍ አድርጋ ድንቁን
የተፈጥሮ ውበት የማታዋን ጀንበርና ልዩ መስህብ የተጎናፀፈውን የዳመናውን ቀለም እያየች የተፈጥሮን ሙዚቃ የአዕዋፍ ዝማሬ
የንፋሱን ሽውሽውታ... ታዳምጣለች።

ይህች አንደበት ያጣች ሃገር ምንኛ ታሳዝናለች። የሌላ
ውበት በውሸታም ካሜራ ቀርፀው ሌላውን እየኮረኮሩ ለማዬት ሲያራኮቱት ኢትዮጵያ ግን እንዲህ ትንፋሽ ቆራጭ የሆነውን
ውበቷን ቆንጥሮ ለዓለም ህዝብ የሚያሳይላት አጣች

ከጥሩው የተበላሸው  የሚበዛበት አለማችን ሳታወቅ ከተበላሽው ጥሩው የሚበዛባት አፍሪካ ግን ጨለማ ዳፍንታም
አህጉር ተባለች

“የሚዲያ ልሳን ያልተፈጠረባት ምስኪን ኢትዮጵያ ስለ ውበቷ ማን የራሱን ጥሎ የእሷን ያስተዋውቅላት ታውቃለህ ሶራ ስለ አፍሪካ ዜና በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች ስናይ አንበሳ ሲያገሳ ፏፏቴው ሲንፏፏ... አዕዋፍ ሲበሩ አውሬው ሲተራመስ ይታይና
ኢትዮጵያን የሚመለከት ዜና ሲመጣ ግን ሁሌ ከረጂ ድርጅቶች ዳቦ ሲታደል ማየት ብቻ የሰሃራ በርሃ አገሮች ግመላቸውና አሸዋቸው ሲታይ ኢትዮጵያ ዛፍ አይበቅልባት ፏፏቴም የላት አውሬና አዕዋፍም አይገኙባት የሚባባለው ብዙ ነው።

ለካ ኢትዮጵያ ምንም አላጣች: ሰው ግን ያላት
አይመስለኝም እንደ “ኢብንባቱታ እየዞረ እሚያስተዋውቃት
የላትም..." አለችው እያሸጋገረች አድማሱን አያዬች: ሶራ የሚላት
ጠፋው: ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ስላላቸው ነገር ማለት እንኳን አይችሉም። ብዙ ኢትዮጵያውያን በሌላው ዓለም ይኖራሉ ፧ ግን ስለ አገራቸው ትንፍሽ አይሉም በቅኝ ግዛት የማቀቁት ህዝቦች
አንገታቸውን ቀና አድርገው መዘመር ሲጀምሩ ኢትዮጵያውያን ግን
የተውሶ ካባ ከጃማይካ ተበድረው ትዮጵያዊነታቸውን ከውስጥ
ጃማይካነታቸውን ከላይ ደርበው ተደበቁ። hገሃዱ እውነት ማስመሰሉን መረጡ።' ሶራ አዕምሮው ተረበሸ።

“ተፈጥሮን አትወድም? ሶራ
እስኪ እየው ይህን ውበት?
የሰው ኪነታዊ ጥበብ ምን ብሎ ሊገልጸው ይችላል?" አለችው።

“ያምራል ኮንችት... ብቻ ምን ይሆናል እያለን ያጣን
መሆናችን ያሳዝናል። ለቤት ማስዋቢያ በየግድግዳችን የምንለጥፈው የባህር ማዶ ስዕሉችን ነው። የባር ማዶው ህዝብን ደግሞ አንች እንዳልሽው? “ለመሆኑ አገራችሁ ዛፍ ያበቅላል ወይ! ይሉናል።

“ህይወት ሳናይ ገና የናታችንን ጡት ሳንጠግብ በባህር ማዶህይወት ለሃጫችንን እያዝረበረብን እንነሆልላለን።

“ከዚያ ማነህ? ሲሉን  ጸጥ ምን አለህ ሲሉን ቁልጭልጭ በመጨረሻ እነሱም ንቀው እንደ ምራቃቸው ይተፉናል!... የመጣበትን ያላወቀ የደረሰበትን ማን ይጠይቀዋል?.." ብሎ ፀጥ አለ::

ኮንችትና ሶራ እንዲህ በፀጥታ ድባብ ተውጠው ማራኪዋን ተፈጥሮ እየቃኙ የበኩላቸውን ሃሣብ ሲያንሰላስሉ የሆነ ድምፅ
ንፋሱ ይዞ መጣ: እንደገና ድምፁን ጠበቁት  ተመልሶ መጣ የወፍ ዝማሬ የወንዝ ኩሉልታ የእፅዋት ሽዋሽዋቴ
አይደለም።የአራዊት ድምፅ… ከሁሉም የተፈጥሮ ቅላፄዎች የተቀነባበረ የሙዚቃ ቃና ነው: ጥዑም ዜማው ይማርካል!
ይስባል! ከተፈጥሮ ጋር ተዋህዶ ልብ ይሰርቃል። ተያዩ ኮንችትና ሶራ: ድምፁ እንደገና እየተስረቀረቀ መጣ። ተጠቃቅሰው ተነስተው ማራኪውን የሙዚቃ ቃና ወደሰሙበት አቅጣጫ ሄዱ።

“ክላሽንኮቭ” መሳሪያውን ጎኑ ያጋደመ ሰው ወይሳውን'
ይነፋል። አዕዋፍ ነፍሳቱ ፀጥ እረጭ ብለው ያዳምጡታል፤ ሶራና
ኮንችትም ከተደበቁበት ሳይወጡ የዜማው እንቅፋት ሳይሆኑ ያን ጥዑም ዜማ በፀጥታ ማዳመጥ ቀጠሉ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካርለት ካሎ ጎይቲና አንተህ ይመር ከካሮ ማህበረሰቦች
መንደር አንዷ የሆነችው ቆርጮ ዘግይተው ስለተነሱ ከመሸ በኋላ ደረሱ። ከዚያ ወደ መንደሩ ገብተው ሽማግሌዎች ከፀሐይ ቃጠሎ ከሚጠለሉበትና ከሚወያዩበት ኦሞ ወንዝ ዳር ላይ ካለው ዳስ ሄዱ

ቆርጮ ከፍ ብሎ ሜዳማ ከሆነ ቦታ  ላይ ያለች መንደር በመሆኗ ለጥ ያለውን የኦሞን ወንዝ ግርጌው ሌላውን የካሮ መንደር ዱሰን ከቀኝ የሙሩሌን ሚዳ ከግራ ማዶው ደሞ የማሽላ
አዝርዕቱን በስተ ምስራቅ ለጥ ያለውን የማንጎ ፓርክ አረንጓዴን ደን ማየት ስለሚቻል ቆርጮ ቀለል ያለችና የተፈጥሮ ውብት በትርኢት መልክ የሚቀርብባት መንደር ናት።

ከሎና አንተነህ ሽማግሌዎችን መጀመርያ ተጥሎ ጎረምሶችን የሐመሩን ደልቲ ገልዲን አይተው እንደሆን ጠየቋቸው በእርግጥ ከጎረምሶች ጥቂቶቹ እንጂ ብዙዎቹ አያውቁትም  የሚያውቁት አላየነውም አ
ሲሉ ሌሎቹ ግን ብዙ የሐመር ወንዶች ከከብቶቻቸው ጋር ሙርሌ ያሉ መሆናቸውን ነገሯቸው።

በእርግጥ ይህ ለአንተነህ  እንግዳ አልነበረም ዝናብ ሲቀንስና የግጦሽ ሳር ሲጠፋ የሐመር ከብቶች ፍየሎችና በጎች ወደ ኦሞ ወንዝ  ይመጣሉ ኦሞ ወንዝ አካባቢ ሳሩ ጥሩ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ከብቶች የሚጠጡት በቂ ውሃ ከኦሞ ያገኛሉ ስለዚህ የቆርጮ
መንደር ካሮዎች እንደነገራችው ሐመሮች ከብቶታቸው ጋር በሙርሌ ሜዳና በኦሞ ወንዝ ዳር አሉ::

“ታዲያ ምን ይሻላል? አለች ካርለት ከሎንና ጋልተንቤን

የሚሻለውማ ለአንድ ሶስት አራት ቀን እዚሁ አካባቢ
ማጠያየቅ ነው" አላት አንተነህ ይመር ረጋ ብሎ እያንዳንዱን ቃል
እየረጋገጠ፡

ጎይቲ ጆሮዋን በሁለት እጅዋ ይዛ እግሯን አጣጥፋ መሬት ላይ ቁጭ ብላለች:: ደልቲ ቆርጮ መንደር ነኝ ብሎ እንደነገራት ሁሉ ስትመጣ ባለመኖሩና ያለበትም አለመታወቁ ሆዷን አዋለለው ! ሆድ ባሳት...

“እንግዲህ ለዛሬ እዚሁ እንደር ነገና ተነገ ወዲያ ሙርሌ ወርደን እንፈልገውና ተዚያ ወደ ሌሎች የካሮ መንደሮች ዱስና ለቡክ
እንሄድና እንፈልገዋለን!" አለና ጋልታምቤ አያቸው። ሁሉም ተስማሙ፤ ጎይቲ ግን ተነጫነጨች። እሱን ሳታይ ጎኗን ማሳረፍ
አልፈለገችም: ጀግናው እየተንጓለለ እሷ እንቅልፍ እንዴት ያሸልባት? ግን ከአቅሟ በላይ በድምፅ ብልጫ ተሸነፈችና ሁለት
ድንኳናቸውን ዘርግተው ካርለትና ጎይቲ አንዱ ድንኳን ጋልታምቤና ከሎ ደግሞ ሁለተኛው ድንኳን ሊተኙ ተስማሙ።
👍14
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ኮንችትና ሶራ የሰጎን ላባ የተሰካበትን የራስ ጌጥ(ጶሮ) እንደ አቦ ሸማኔ
አይን አሸጋግሮ  እየተንተገተገ የሚመለከተውን አይኑን የተተለተለ ሳንቃ ደረቱን እየተመለከቱ  ከንፈሩን አሞጥሙጦ የሚያሽለከልከው ትንፋሹ ከፍ ዝቅ በሚሉት ጣቶቹ እያንኳለለ የሚያጣው ስሜተ ሰላቢ ዜማውን ሳይንቀሳሱ ሲያዳምጡ  ወይሳ ተጨዋቾቹ ድንገት ዜማውን ቀጥ አደረገና መሳርያውን አንስቶ ሲያቀባብል ሶራና ኮንቺት
ድንግጥ ብለው ሲመለከቱ ድው አድርጎ ሲተኩስ አመዳቸው ቡን ብሎ ነፌሴ አውጪኝ መሬት ላይ ሲንበለበሉ እንደገና ተኮሰ።

ከዚያ ለጥቂጥ ሰአታት ከመሬቷ ጋር ተላትመው ጠበቁና ቀና ብለው ሲመለከቱ   ሰውየው ኦሞ ወንዝ ዳር ሄዶ ተረጋግቶ ወንዝ ዳር ሄዶ ቆሟል ኮንቺት እየተሳበች ወደ ሶራ ተጠግታ

"ለምን ተኮሰ? አለች ሶራን።

"አልገባኝም"

"አይቶን ይሆን?"

አይመስለኝም ቢያየን ወይንም ድምፅ ሰምቶረ ቢሆን ኖሮ በሁኔታው ማወቅ እንችል ነበር።

"እሱስ ልክ ነህ ቢገርመኝ እኮ ነው ተረጋግቶ መቆሙም ለጠየቅሁት ጥያቄ ፍንጭ ሰጪ አይደለም ስትለው ከኦሞ ወንዝ ማዶ ድምፅ ተሰማ ሰባቶ ጎረምሶች ናቸው። ወደ ወንዙ ሲጠጉ

"ፃሊ!” አላቸው በካሮኛ  ሰላም ናችሁ ለማለት:

'ፃሊና..." አሉትና አምስቱ ወንዙ ዳር እንደቆሙ ፤ ሁለቱ ዳር ላይ የቆመች ቀጠን ብላ ረዘም ያለች የእንጨት ታንኳ ላይ
ወጡና በረጅም ዘንግ ውሃውን ቁልቁል ሲገፉት ታንኳዋ እንደ ውሃ
እናት ውሃውን ወደ ጎን እየሰነጠቀች መጣች::

ለካ የተኮሰው እነሱን ለመጥራት ነው:: ጥሪ በተኩስ አይገርምም!” ስትል ሶራ በአድናቆት ራሱን ወዘወዘ።

“እነሱ ግን እነማን ናቸው?"

"አላውቅም ኮንችት  ብናነጋግራቸው ይሻላል?" ሲላት ወዲያው ከተደበቁበት ወጥተው ወደ ሰውዬው ሲጓዙ ፊቱን ዞሮ
የቆመው ሰው የሰው ዳና ሲሰማ ከመቅፅበት መሳሪያውን ከትከሻው
አውርዶ፡-

“ከጠን ማሲዲ" ብሎ መሣሪያውን አቀባብሉ ደገነባቸው።

“ኖት አሱስቴ" አለች ኮንችት በስፓኒሽ እጅዋን እያወዛወዘች ተረጋጋ ለማለት:

ባለመሣሪያው ትኩር ብሎ ሲያያቸው ቆየና “ነጋያ! አለ
ከተቀመጠበት ተነስቶ መሳሪያውን ወደ ትከሻው እየመለሰ: ሶራ ለሰላምታ አፀፋውን መለሰ። “...ሐመር አፎ ዴሲቲኒ"  አለው ባለመሣሪያው ሐመርኛ ትችላለህ ለማለት።

ሶራ ፈገግ ብሎ “ሊካ ሊካ ቂንሲዲ...” (ትንሽ ትንሽ
እችላለሁ) አለው። ባለመሳሪያው ፈገግ አለ: ያኔ ነብርነቱ ተለውጦ
እንደ ድንቡሽዬ ህፃን ፈገግታው የሚማርክ ሆነ

ባለመሳሪያውና ኮንችት ከሁለቱ የታንኳዋ ቀዛፊዎች ጋር ተሻግረው ሲጠብቁ ሶራ ጀልባዋን ይዞ ሄደና በጀርባቸው አዝለው
ጀልባዋን ከአምስቱ ጎረምሶች ሁለቱ እየተሳሳቁ ተሸክመው ጫካው
ውስጥ ገቡና በመስመር ሆነው በትላልቅ የግራር የኮሶ... ዛፍ ውስጥ ለውስጥ ትንሽ እንደተጓዙ ኮንችትና ሶራ ዛፍ ላይ እንደ ጦጣ የሚንጨዋለሉ ልጆች አዩ: ቆይቶ ደግሞ በቋንቋቸው ቶሎ ቶሎ
የሚናገሩ ልጃቸውን በቆዳ ብብታቸው ስር ያዘሉ እናቶችና ሽምገል
ያሉ ወንዶችን አዩ።

ጨቅላ ህፃናት ዛፍ ላይ በቆዳ ተንጠልጥለው አንዳንዶቹ ተኝተው እየተቁለጨለጩ ሲወዛወዙ እያዩ እንደ ሄዱ ከርቀት ላይ
የወፍ ጎጆ የሚመስል የኤሊ ቅርፅ ያለው ጎጆ ቤት ተመለከቱ።

ኮንችትን ሲያዩ ህፃናት  ወላጆቻቸው ጉያ እየገቡ ወደ መንደራቸው እየሮጡ አለቀሱ: ለኩዩጉ ህፃናት አስፈሪው አውሬ ቀላ ያለ ልብስ ለባሽ ሰው ነው። ከፍ ያሉት ግን የመጣው ይምጣ ብለው በቋንቋቸው ሰላም ቢሏትም ፍርሃታቸው ግን ያስታውቃል: ለጊዜው
ሰላምታቸውን ልብ ብላ አልተከታተለችም ነበር ድንገት አንድ ሽማግሌ፡-

“አሹቃ” ሲሏት አያቷ የነገራት ሰላምታ ትዝ አላት:
ኮንችት አያቷ የሚጠቀምባትን መቀመጫ የመሰለች ሁሉም
ሽማግሌዎችና ወንዶች ይዘው አየች:: ሶራን ዘወር አለችና ምን የሚባሉት ማህበረሰቦች ናቸው?" አለችው ማፕ ላይ ያየችውን ስም ለማስታወስ እየሞከረች:: ሶራ መጀመሪያ ያዩትን ባለ ዋሽንት ጠየቀው።

ሙጉጅዎች ናቸው። እነሱ ግን ራሳቸውን ኩዩጉ ነው
የሚሉት አለው ነገራት ሶራ  ለኮንችት። ማፕ ላይ መጉጅም ሆነ ኩዩጉ የሚል እንዳላየች እርግጠኛ ነች: ለማረጋገጥ ግን ወዲያው
ማፕዋን ዘርግታ አየች፤ ሁሉም እሷ ላይ አፈጠጡባት። ማፑ ላይ
የሉም። ካርታው ላይ አየች የሉም፤ ይበልጥ ደነቃት።
ኦኗኗራቸውም ልዩ ነው ፤ የጫካና የወንዝ ዳር ሰዎች: ከመንደሩ እንደደረሱ ሰዉ በአድናቆት ቆሞ አያቸው: ህፃናት ራቅ ብለው ሽሽተው ያያሉ:: አንዱ 'መጡላችሁ' ሲል ሌሎች ህፃናት ደግሞ
እየተሯሯጡ በመላቀስ ይጯጯሃሉ…..

ኮንችት ከጀርባዋ ያዘለችውን ጓዟን አውርዳ ተለቅ ተለቅ ያሉ የአያቷን ፎቶ አወጣች: የዘጠኝ ሰዓት ፀሐይ አሁንም ማቃጠሏ
እንብዛም አልቀነሰም:

ፎቶውን የያዘውን እጅዋን ወደ ህዝቡ ዘረጋችው። ፈሯት፤በምልክት እንኩ' አለቻቸው: ትክ ብለው እያዩ ዝም አሏት ከዚያ ባለዋሽንቱ ውሰዱ' አላቸው በሐመርኛ።

ሶራ ደስ አለው የራሳቸውን የሆነውን ቋንቋ ሲናገሩ
አንድም ቃል ሊገባው አልቻለም ነበር ሐመርኛ ከቻሉ ግን እሱም
ሊያናግራቸው ይችላል። ኩዩጉዎች ግን ሐመርኛን ብቻ አይደለም የሚችሉት። ሙርሲኛ ኒያንጋቶምኛም ይችላሉ።ስለዚህ ሶራ
በሐመርኛ፦

“ውሰዱና እዩ ችግር የለም” አላቸው። አሁንም ዝም ብለው ኮንችትን ሲመለከቷት ቆዩና አንዱ
ሽማግሌ ሌላውን በጆሮው አናገረው ከዚያ ብድግ ብሎ መጣና ተቀበላት።

ፎቶውን ዘቅዝቆ ስለያዘው ኮንችት አስተካክላ ሰጠችው ሽማግሌው ቀረብ እራቅ አድርጎ አየውና በቋንቋው የሆነ ነገር
ተናግሮ ወደ ሀዝቡ ሲጠጋ ለማየት ህዝቡ እንደ ንብ ዙሪያውን ከበበውና ሁካታ ሆነ: ማንም ሌላውን አያዳምጥም።

ከዚያ ሁሉም እነ ኮንችትን ጥለው እንደ ድንጉላ እምም.. እያሉ ወደ አንድ አቅጣጫ ተሯሯጡ: ኮንችትና ሶራ እርስ በርስ
ተያዩ ህዝቡ የሄደበትን ምክንያት ግን ከመካካላቸው ሊመልስ የቻለ አልነበረም።

አንድ ጎጆ ቤት ሲደርሱ ሁሉም ቆሙ። ከውስጥ የሆኑ ሽማግሌ አንጀታቸው ካጥንታቸው ጋር የተጣበቀ አጎንብሰው ወጡ ህዝቡ አሁንም ክብብ አደረጓቸው።
ከዚያ እንደገና ሁካታ ሆነና ጎረምሶች እየተሯሯጡ ርቀው ሄዱ። ፎቶዎችም በልጥ ታስረው ሽማግሌው ከወጡበት ጎጆ ፊት
ለፊት ተንጠለጠሉና ሴቶች ሰማይ ሰማይ እያዩ እልልታውን አቀለጡት ወንዶች እየዘለሉ ጭፈራ ጀመሩ።

ኮንችትና ሶራ እንደገና ተያዩ። ምን እየተሰራ እንደሆነ ማወቅ ተሳናቸው: ባለ ዋሽንቱን ጠየቁት፤ መልስ አጡ። ከዚያ
አራት አምስት መሳሪያ የያዙ ሽቅብ ተኮሱ።

ኮንችትና ሶራ ደነገጡ፡ “ምን እየሰሩ ነው ሶራ?" አለች
የሶራን ትክሻ እየወዘወዘች
በፍርሃት: ሶራ ትከሻው ከፍ ዝቅ አድርጎ አላውቅም አላት በምልክት።  ሰው ከየጫካው ተሰባሰበ !
ጥሩንባው እየተነፋ እልል መባል ጀመረ።

ጫካ የሄዱት ጎረምሶች በሾርቃ የሆነ ነገር ይዘው
እየተሯሯጡ መጡ የደከማቸው አይመስሉም የግንባራቸው ደም
ስር ግን ውሃ እንደሽረሸረው የዋርካ ስር አበጥ አበጥ ብሎ በየአቅጣጫው ተጋድሟል። እንደ ተመለሱ ከህዝቡ መሃል ገቡ
ከሌላ ጎጆ ደግሞ ማር የያዘ ትልቅ ቅልና ውሃ ሌሎች ጎረምሶች አመጡ። ውሃውና ማሩ ተቀላቀለና በእንጨት ተማሰለ።

ከዚያ ጥሩንባው እየተነፋ እልል እየተባለ እየተጨፈረ... ሁሉም የሉካዬን ስም እየጠሩ ሰማይ እያዩ ቆዩና ከሲታ ሽማግሌውን አስቀድመው ሶራ ኮንችትና ባለወይሳው ወደ ቆሙት እያሸበሸቡ
እየዘለሉ ጡሩንባው እየተነፋ መጡ።
👍18😢2👏1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የኩችሩ መንደር እንደደመቀች ናት:: ብዛት ያላቸው አሣዎች በወጣቶች በጦር ተወጉ ማጅራታቸውን በዱላ ተመቱ በመንጠቆ ተያዙ፤ ሣር በል የሆኑ አራዊት የሜዳ ፍየልና ውድንቢት ታድነው ተገደሉ ፤ ከጫካ ብዛት ያለው ማር ተቆረጠ፤ ቦቆሎና ማሸላ ኦሞ ወንዝ ተወስዶ ተወቃ.. ይበላል ይጠጣል
ይጨፈራል ይመረቃል።

ሉካዬ ሰማይ ላይ ሆኖ ምስሉ እየታዬ ቢሆንም ሶስት ቀን ሙሉ አልመጣም:

“ሎካዬ ለመምጣት ያስባል! ነጩ እባብ ግን “አልመጣም ብሎ አስቸግሮታል ደንቡን ሳናጓድል ሥርዓቱን ብናሟላ ግን ሁለቱም ይመጣሉ" ስላሉ ሽማግሌዎች፣ ሴት ወንዱ ይኳትናል ሰማይ ላይ ላሉት  ለሎካዬና ለነጩ እባብ በደስታ ለመፍጠር።

ኮንችት የሎካዬ የልጅ ልጅ መሆኗን ከሰሙም በኋላ
የመንደሩ ሰው ተስብስቦ ከአያቷ ወንድም ቤት ፊት ለፊት ተቀመጡ" የሉካዬ ፎቶ ጎጆው ላይ እንደተንጠለጠለ ነው። ከሥሩሁሌም ግልገል ፍየል ከካሮ እየመጣ ታርዶ ይቀመጥለታል።

ልጃገረዶች ኮንችትን ወደ ጎጆው ቤት ውስጥ ይዘዋት
ገብተው ውስጥ ሱሪዋንና ጡት ማስያዥዋን ሳይቀር አስወለቋት::ከውጭ ይዘፈናል እልል ይባላል. ልጃገረዶች በአኖና የዱር እጣን አላቁጠው ፀጉሯን ሰውነቷን ቀብተው የፍየል ቆዳ አለበሷት: ከዚያ
ይዛው የመጣችውን ልብሷን በእጅዋ እንድታንጠለጥል ሰጧትና ከቤት ወደተሰበሰበው ህዝብ ይዘዋት ወጡ። እሳት ነዷል.
ይጨፈራል... ሁለት ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፍተው እጅና እጅዋን
ይዘው ልብሷን ወደ እሳቱ አስወረወሯትና እልልታቸውን ሲያስነኩት
የተሰበሰበው ህዝብ እንደገና ፈነጠዘ ዘለለ  አቅራራ.. ጡሩንባ
እልልታ ተኩስ ድብልቅልቅ አለ:

ኮንችት የተረጋጋች አትመስልም። ቆዳዋ ግን አማረባት ጡቶችዋ ቀልተው ቆሙ ለስላሳው ጭኗ... ሁለመናዋ አጓጊ ሆኗል:
ድንጋጤው ስላልለቀቃት ግን ካንገቷ በላይ ውበቷ ቀንሷል።

ሴቱም ወንዱም እየመጣ እጅዋን እየሳመ ደስታውን
እየገለፀላት ወደ ጭፈራው ሲገባ እንደቆዬ ሰው ሰላምታ እየሰጣት
ኩዩጉነቷን አንድነታቸውን እያረጋገጠላት ከሄደ በኋላ ሶራ እየሳቀ ወደ ኮንችት ተጠግቶ አቀፋት: ሽጉጥ አለች ወደ ደረቱ እንደ
እንቦቀቅላ  ህፃን፡ አይቷት እንደማያወቅ ሁሉ በሁለት እጆቹ ጡቶችዋን እንደያዘ ፈገግ ብሎ ቁልቁል አያት: ልትስመው ስትል
የሆነች ሴት መጥታ መነጨቀቻት። የኩዩጉ ሴት ወንድን በአደባባይ
አትስምማ!

“እሺ!” አለች ኮንችት
የሴትዮዋ ግሣፄ ስለገባት።

“ለምን ልብሴን አወለቁ?  ለምንስ እንዳቃጥለው አደረጉ?''አለችው እሏና ሶራ ከእቅፎቻቸው ከተላቀቁ በኋላ

“የአያትሽን ባህል ረድኤት ለማካፈል! ተፈጥሮአዊ ፀጋሽን ለመመለስ ጎረምሶች ፍቅራቸውን እንደ ወለላ ማር እንዲያውጡሽ….
ለማድረግም" አላት ሶራ እየሳቀ
ባለወይሳው ኮንችትን ባህላዊ ልብስ ለብሳ ሲያያት ደስ አለው። ስለዚ ፈገግ ብሎ ከሌላው ጊዜ በተለዬ ሁኔታ ቀረባትና

ካርለትን አይተሻታል ወይ? ብለህ ጠይቃት" አለው ሶራን።ሶራ የነገረውን ለኮንችት ሲተረጉምላት ተኩስ ተሰማ ተኩሱ
ተደገመ።

ጎረምሶች እየተሯሯጡ ወደ ኦሞ ወንዝ ሄዱ። ጭፈራው
ግን አልቆመም። ባለወይሳው ከሌላ አካባቢ የመጣች ፀጉረ ረጅም
ልብስ ለባሽ... ሁሉ እሱ የሚያውቃትን ካርለትን ያውቃል ብሎ አምኗል።

“ካርለት! ማነች ካርለት? የአባቷስ ስም? ዜግነቷስ?”
ኮንችት በስም ብቻ አውቃለሁ፤ አላውቅም  ማለት ትክክል
እንዳልሆነ ታውቃለች: በያገሩ ስንት  ካርለት
ዴቪድ... ሊኖር ፥ይችላል። መጀመሪያ ስም  አገር ሥራ የሚኖርበት አድራሻ...
ለማንነት መለያ ይጠቅማል: በተረፈ በደፈናው ይከብዳል።ባለወይሳው ግን “አውቃታለሁ' አለማለቷ አስከፋው:

ምን የማረጋት መሰላት ካርለት ልጃገረድ ናት!
ብታጠፋም አላገባኋት ጥሎሽ መክፈል አልጀመርሁ... እና-
አላዝባት አልቀጣት... ይህን እያወቅች መደበቋ ምን ይሉታል? ብሎ አስቦ አዘነባት በኮንችት:

በኦሞ ወንዝ ዳር ካለው ጫካ የሆኑ ሰዎች ብቅ ሲሉ ህዝቡ ተንጫጫ። ኮንችት ቀና ብላ ታይ የኩዩጉ ጎረምሶች እንግዶችን
እየመሩ ይመጣሉ። ለኩዩጉ መንደር በሩ ኦሞ ወንዝ የበሩ ደወል ተኩስ መሆኑ ኮንችትን እንዳስደነቃት ነው።

እንግዶቹ ሲጠጉ አንዷ ነጭ ናት ሁለት ወንዶችና
አንዲት ሴት አብረዋት አሉ። እነሱ ከነጭዋ አንፃር ጥቁር ናቸው።እንግዶቹ እንደቀረቡ ባለወይሳው ዘወር ብሎ አያቸውና ከመቅፅበት
አይኑን እንደ አውሬ አፍጦ አንገቱን እንደ ሰጎን መዘዘው
ሁለቱ ሴቶች ባለወይሳውን ሲያዩ ፊታቸው በደስታ ፀዳል አበራ ቸኩለው ግን ወደ እሱ አልተጠጉም።
ከዚያ ነጯ እንደቆመች ሌላዋ ሴት ቀረብ አለችና፡-

“አያ ደልቲ!'' አለችው
በሐመርኛ:ጎይ ቲ"

ረጋ ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ ላዩ ላይ ተጠመጠመችበት: እቅፍ አድርጓት ቆየና ለቀቃት:: ነጭዋንም ካርለት" ብሉ አቀፋት፤ እሷም አቀፈችው ...

የኩችሩ መንደር ኗሪ በሁኔታው ተደንቆ ጭፈራውን አቁሞ
ያያል።

ካርለት! አለች ወገቧን ወደኋላ ለጥጣ በአድናቆት አፏን እንደከፈተች ኮንችት።

ኮንችት! ካርለት ኮንችትን ከእግር ጥፍሯ እስከ ፀጉሯ
በአድናቆት እያየቻት ቆየችና

“አገኘሻቸው?" አለቻት

“አዎ ተገናኘን” ብላ ኮንችት ሳቀች ተሳሳቁ ኮንችትና
ካርለት! ህዝቡም አብሯቸው ሳቁ! መንደሯም በሣቅ ሙላት ተጥለቀለቀች

“ኮንችት እንዴት ልታገኛቸው ቻልሽ?''

“..በጀልባ ነበር እኔና ሶራ የምንጓዘው፤ እና ባጋጣሚ እዚህ ደረስን

“ማንም ሳይመራሽ?'

“ባገኘሁት ማፕም ሆነ ካርታ ኩዩጉዎች ለመኖራቸው ፍንጭ የሚሰጥ ምልክት የለም:: አያቴ የስጠኝ የአደራ ምልክቶች ግን እንደ ኮኮብ መርተውኛል ያም ሆኖ ግን ባጋጣሚ ኩዩጉዎችን
የሚፈልገው ሰው ተኩሶ እነሱ ሲመጡ ማየት ባንችልና ተጠራጥረን
አብረን ባንመጣ ልፋቴ መና ሆኖ! ስሜቴ በስለት ቢላዋ ለሁለት ተተርትሮ ወደ መጣሁበት እየቆዘምኩ እመለስ ነበር። አጋጣሚው
ግን ረዳን፤ ተገናኘን:

“እንዴት አገኘሻቸው ታዲያ?

“ደግ ሩህሩህና ተግባቢዎች ናቸው:: ኑሯቸው በኦሞ ደለል ላይ ማሸላ በማብቀል ከጫካ ማር በመቁረጥና አሣ በማጥመድ ነው።
ከብት ፍየል የላቸውም፤ ይህ ደግሞ ከብት በሚያረቡት የአጎራባች
ያስንቃቸዋል:: ቁጥራቸው
ማህበረሰቦች ማነሱ ከብት
ባለማርባታቸው የሚያጠቃቸው ብዙ ነው። ስለዚህ የሚኖሩት
በጠባቂ ሞግዚት ነው"

“በሞግዚት?”

“አዎ ካርለት!  ጥንት ሞግዚታቸው ካሮ ማህበረሰብ ነበር። አሁን
ግን የካሮዎች ኃይል እየደከመ የኒያንጋቶሞች
(ቡሜዎች) ኃይል እየበረታ በመምጣቱ ኩዩጉዎች ወደ ኒያንጋቶሞች በመጠጋት ከአጎራባች ማህበረሰቦች የሚደርስባቸውን ጥቃት
ሞግዚታቸው ኒያንጋቶሞች ይከላከሉላቸዋል።

“ታዲያ ለሃያሉ ሞግዚታቸው ማር እህል  ከሚሰፍሩት ሌላ ልጃገረዶቻቸውን ካለጥሎሽና ካለ አንዳች ክፍያ ኒያንጋቶሞች
በሚስትነት ይሰጣሉ። ኩዩጉዎች ግን ከኒያንጋቶሞች ካሮዎች.. ጋርዐመጋባት አይችሉም ስለሚናቁ።

“ኩዩጉዎች የሌላቸውን የማይመኙ በዚህ ኑሯቸውም ከአቅም በላይ ለሆኑ ነገሮች የማይሰጉና የማይጨነቁ ናቸው። ከሁሉም በላይ ባህላቸውን አክብረው ራሳቸውን ሆነው መኖርን ይመርጣሉ።
የሚገርምሽ በልጅነቱ ከነሱ የተለየው አያቴ እንኳን እንደ
ዘይትና ውሃ ለረጅም ጊዜ ከኖረበት ስልጣኔና ባል ጋር ሳይዋሃድ ነው ወደ መቃብሩ የወረደወ:
👍261👎1🥰1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


“ይህ ክላሲካል ዋሽንት ተጫዋች ማነው?"

ሐመሩ የፍቅር ጓደኛዬ ነው ዋሽንት ግን መጫወት
ይችላል?

“ያውም ልብን በሚሰልብ ቅላፄ ነዋ የአጨዋወት ስልቱ ልብሽን የሚሰውርበት አካልሽን የሚያንሳፍፍበት... አንዳች ኃይል አለው:: ከርቀት የሚቀሰቅስሽ የሚንጥሽ…"

“እንኳን ደስ አለሽ በይኛ!በፍቅር ክንዱ አፍቃሪዎቹን
በተራ ያሰለፈን ጀግና በሙዚቃ አርቱም የምንተኛበትንና
የምንነቃበትን ፕሮግራም ያወጣልናላ ደልቲ ገልዲ…

ምን

የሱ ታሪክ ብዙ ነው ኮንችት: በርቀት ስታይው የፍልፈል
አፈር! እየተጠጋሽ ሄደሽ ውስጡ ስትገቢ ግን እንደ ተራራ እየገዘፈ፤ወደላይ እየተከመረ የሚሄድ የሚስጥር ዓለም ነው።''

“እውነትሽን ነው"

“አዎ  ኮንችት"

ኮንችት ደነቃት ገረማት ፍቅራቸውን ልታየው ሞከረች አንዴ ካርለትን
ተመልሳ ደልቲን… አየችው አጠጋጋቻቸው አሰተቃቀፈቻቸው
አሳሳመቻቸው… በሃሳቧ ምራቋን እየዋጠች፡፡

“ምነው ኮንችት? ካርለት ኮንችትበብ ጭልጥ ስል
እየሳቀች ቀስቅሳ ጠየቀቻት።

“እንጃ! ግን." ኮንችት ሃሣቧን ገደበችው ዋጠችው ካርለት እንደገና ሳቀች። ሳቋ ደልቲን ጎሻሸመው። ዞር ብሎ ፈገግ
ሲል የኮንችት አይኖች ጥርሶቹ ላይ ተሰኩ! እንደ በረዶ ጥርሱ ነጭ ነው።

“ታፈቅሪዋለሽ?” ሞኝ ሆነች ኮንችት

"አዎ የፍቅር እንጥሌን ሌሎቹ ተንጠራርተው ሲያጡት ተቀምጦ የነካው እሱ ብቻ ነው ተሳሳቁ ካርለትና ኮንችት::

'እንጥሌን እምም...” ኮንችት እንደገና ምራቋን ዋጠች።

“እሱም ያፈቅርሻል?”

“እኔ እንጃ... ቢሆንም አይላኝም እኔ ለእሱ ገና
ያልተገራሁ ባዝራ ነኝ: ስለዚህ ከኔ ይልቅ እሷን ይወዳታል:"

ካርለት በአገጯ ጎይቲን ለኮንችት አሳየቻት
ኮንችት ጎይቲን እስከ አሁን ለምን እንዳላስተዋለቻት
ገረማት የጠይም ቆንጀ እግሮችዋና ወገቧ የሚያምር ችምችም
ያሉት የወተት አረፋ ጥርሶችዋ የሚያስጎመጁ ሆነባት።

ኮንችት ጎይቲን ስታያት እንደቆየች ስለ ውበት አሰበች።ስለ ሰው ልጆች የራቁት ውበት ልብስ ስላልሸፈነው ተፈጥሮአዊ ገላ አለመች:: ሰው ሁሉ በተፈጥሮው ማራኪ ነው ያምራል ይስባል...

“አሁን ግን እሷ አግብታለች ስለዚህ የደልቲን ፍቅር እንደ
ማንጎ እየጋጥሁ እረካባታለሁ ስል ጀግናው ሌላ ቆንጆ በፍቅሩ ግዳይ
ጥሎ ቆንጀዋ ልቡን ሰብራ ልትገባ ስትፈልጠው ደረስሁ... ሳቀች

ካርለት: ሳቋ ኮንችትን ስለውበት ከምታልምበት የፍልስፍና ዓለም ቀሰቀሳት።

"እሷ ደግሞ ማን ናት?"

“ዳራ ትባላለች ሐመር ናት: ልቅም ያለች ቆንጆ!...”

ካርለትና ኮንችት እንዲህ ሲጨዋወቱ ጎይቲ አንተነህ
የምታየው የምትሰማው የምትነካው የምታልመው... አንድ ሰው ነው:: ከፊት ለፊቷ የተቀመጠውን የፍቅር ጀግናዋን ትኩር ብላ
ስታስተውለው ቆይታ ወደ እሱ ሄደች።

በእጇዋ ጨሌ
አንጠልጥላለች መለሎ
አንገቱ ላይ አጠለቀችለት! ቀና ብሎ አያት እሷም ዝቅ ብላ አየችው።

አልተቀየረም  እሷም
አልተቀየረችም ትንፋሻቸው ይጥማል። የጫካ ነፃነታቸው ግን የለም ጭኗቿ አይታቀፏትም ደረቱ ላይ አትተኛም፤እሱም ዳሌዋን አያቅፍም
ጡቶችዋ እንደ እንቧይ ደረቱ ላይ አይነጥሩም...

“ይእ! እንኳን ደና ሆነህልኝ እንጂ..." ብላው እንባዋ
በአይኗ ዙሪያ ተኮለኮለ

“ምን ይሆን ብለሽ ነው አንች..." እሱም መናገሩ
አቃተው: ይህን ሲል ጎይቲ የፍቅር ትዝታው ጠቅ አድርጎ ወጋት ስለዚህ ሃዘን የሰራ አካላቷን በጨካኝ ስለቱ አብጠለጠለው። ያኔ ልቧ፣ ሲኮማተር አይኗ ዙሪያ የተኮለኮለው እንባዋ ኩልል ብሎ ወረደ።

“ይእ ባይሆን አልጣህ- አይንህን ልየው ፍቅርህ ልቤ ውስጥ ሲንፈራገጥ አንተ ሳትኖር እንደ ምጥ ያስጮኸኛል ጤና ይነሳኛል። እንኳንም ግን ፍቅርህ ተሆዴ አይወጣ! እንኳንም
አልገላገለው! እሚወለድ ቢሆን ሲያድግ ብቻዬን ጥሎኝ ይሄድ ነበር.." ትክዝ አለች እይታዋን የከለከለውን እንባዋን ጭምቅ አድርጋ
አፍስሳ።

ስሜቷ ጭምትርትር ያለውን ጎይቲን ሲያይ ደልቲም የሆነ
ነገር እሱም ሆድ እንደጉማሬ ሲገላበጥ በዓይነ ህሊናው ታየው።

“ተይው የኔ እህት! ተይው እርሽው ተንግዲህ ተሱ
ምሰይ: የአባት ደንብ ተሁሉም ይቦልጣል  ተፍቅርም!! ስለዚህ
ጉም መቼስ አይዘገን.." ብሎ የባሰ የሐዘን ቦይዋን ከፍቶ ለቀቀባት
የሚያጉረመርም ሳግ ቀጥሎ የህሊና ብራቅ ከዚያ እንባዋ አጨቀያት:
ጎይቲ እንገቷን ደፋች: እሱን ማጣቷ እውነት ነው! እውነትም የሱ የመሆን
እድሏ አክትሟል፤
አክትሟል፤እውነትም
የፍቅር ጥገታቸው
ነጥፋለች...

ጎይቲ እንባዋ ቦዩን ይዞ ፈሰሰ፣ እንባ የጠማት መሬት ደግሞ የፍቅር እንባዋን እያጣጣመች ጭልጥ አድርጋ ጠጣችው::መሬት ሰዎች ሲፋቀሩ የሚተርፋት እርግጫቸው ነው ሲያዝኑ ግን ፀሐይ ያቃጠው ጉሮሮዋን ጨዋማ እንባቸው ጥሟን ያረሰርስላታል ጥሟን ይቆርጥላታል ጣፋጩ የሰው ልጅ እንባ የጎይቲን እንባም መሬቷ አፏን ከፍታ ጠጣችው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

' ...ይእ ተወኝ አንተ ሰው! መች አንተ ለእኔ አነስከኝ።
የአንተ መሆኔን ነጋሪ አልሻም ሰው መቼስ ካሉት በረት ሙሉ ከብቶች የሚቆረቆረውና የሚቆጨው አውሬ የበላበትን ጫካ
ያስቀረበትን ከብት አይደል! እንደማያገኘው ልቦናው ያውቀዋል ቢኖርም ለእሱ እስካላለው ድረስ በሽታ ይገለው ይሆናል: ይህን ግን
አያስብም። ዘወትር ቁጭት ብቻ ወይኔ ብቻ. እሮሮ ብቻ

“አያ ደልቲ የኔ አይደለም:: ከእንግዲህ በሴትነት መላዬ
ጀግናውን እየመራሁ ወስጄ ልቤ ውስጥ አላስተኛውም ሙቀቱን አልጋሪውም... ያች የፍቅር ጨረቃ አሁን የማይወለደውን ጨቅላ
አቅፌ እሽሩሩ….' የምልባት ብርሃን ናት: የፍቅሩን ትዝታ!
የጀግናውን ገድል፤ የማይጎረምስ ፍቅሩን፤ ጠረኑ የማይለውጥ
ፍቅሩን... የማልምባት ናት ጨረቃ!

"በእጅ ያረጉት አንባር ከእንጨት ይቆጤራል' እንዲሉ ለአያ ደልቲ ስንሰፈሰፍ ልብህ ቢከፋው አይደንቀኝም!በድየሃለሁ
"ዘንግቼሃለሁ... ግን ወድጄ አይደለም። ስቆምበት ልብህ እንደ ደረቀ
እንጨት ሲሰባበር ይሰማኛል። ወንድነትህን ብታሳዬኝ ሸንቆጥ
ብታደርገኝ አብያው ልቤ አደብ ገዝቶ ትዝታዬን እያረሰ ገለባብጦ የአንተን የፍትር ቡቃያ ያበቅለው ነበር: አንተ ግን ወኔ ከወንድነቱ
ይልቅ ወደ ሴትነቱ ያደላል፡ እንደ ወንዶች አታገሳም አትፎገራምI አትዋጋም አሯሩጠህ አትጥልም! አትጀነንምI የተከደነውን በሃይል አትከፍትም...

“እና ልቤ ሃይ ባይ አጣ ትዝታዬን የሚሽር ትዝታ
አጣሁ ይእ! አይ ልፋቴ አንተ እቅፍ ውስጥ ሆኜ ከተራራው ማዶ ሰው ፍለጋ ስንጠራራ! 'አሁንም ትወጂዋለሽ... እያልህ ከምትለኝ በወንድነት በልቤ ውስጥ የሚዋኘውን ጀግና አጥምደውና ሃሣቤን
ቆልምመው: ለእኔስ አያ ደልቲ እንዳለኝ ተአባቴ ደንብ ውጭ እሱን ማሰብ 'ጉም መዝገን' አይደል!

“አንተና እኔ ሰውነታችን እንጂ አበቃቀላችን ለየቅል ነው።መስሎህ እንጂ ማንም ትሁን ማን የደረሰ ቡቃያዋን አሽቶ ያቃማትን ሐመር አትረሳም:: ያውም ያያ ደልቲን የፋና ወጊውን የጀግናውን አንበሳ ቀጭኔ... ከገደለው እቅፍ የገባችውን... 'ተይ' ተብላ ፍቅሩን ከልቦናዋ አውጥታ ልትወረውረው ይህ የሚቻላት ሐመር የለችም።

“እኔ የኔ ጌታ በቃልህ ተይ ዘንጊው... አትበለኝ: ቅጣትህ ይሻለኛል! ልመናህ ግን ያብሰኛል.." ጎይቲ አይኖችዋን አድማሱ ላይ
ሰንቅራ ሃሳቧን ሳትጨርሰው ፀጥ አለች።
👍281
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


“አፈርሁኝ በራሴ ከሎ!

“ሃፍረት ልብሳችን ሆኗል፡ በተለይ ከዚች ሃገር ወጣ ብለህ ስትመለስ የት ነን? ማን ይዞ አስቀረን?... ሺ ጥያቄ በህሊናሀ ይደረደራል። መልሱን ግን አታገኘውም! የሚመልስልህም የለም::

“መጽሐፍ ስታነብ ያለፉትን የኪነ ጥበብ ስራዎች ስታይ
በታላላቆቻችንና በኛ መካከል ያለው ግሉህ ልዩነት ያፈጥብሃል
ጠልፎ እሚጥል ! ጉቶ ይመስል እንቅፋት ሆኖ ለመስራት የሚፍጨረጨሩትን የሚያደናቅፍ ምክንያት ይኖራል! ደግሞ አለ!
ነበረም።

“ይህ ግን በእንቅልፍ ለመደበቅ በቂ ምክንያት አይደለም ችግር ሲበዛ መፍትሄውም ከውስጡ ይፈለፈላል። ለመሻሻል ምንጩ ችግር እርካታ ማጣት ነው:

“እኛ ግን ብዙ አጥተን ብዙ ነገር ካላቸው በላይ ቆመን
እናናውዛለን። ብቸኛ ሆነን አጠገባችን ያሉትን እናኮርፋለን እንኮንናለን
ከመሃከላችን ለመውጣትና እኛኑ ለመሳብ
የሚንቀሳቀሰውን ሞራል እየስጠን ከማደፋፈር ይልቅ ተጋግዘን በጠረባ እንዘርረዋለን። የኛ ደስታ የሚታየው በወደቀው ስንስቅ ነው ሌሎቹ ደግሞ በእኛ በወደቅነው ይሳለቁብናል።

“ሰው ሆነን ተፈጥረን ሰው ሆነን ከመከበር ራሳችንን
አራቅን ያለንን አናውቅም! ሌላው ቀርቶ ባለንም አኮራም፡ ከዚያ ይልቅ በተውሶ አልባሳትና ቅራቅንቦ የማስመሰል ተውኔት በባለቤቶቹና በእኛው ህዝብ ፊት እንሰራለን፡ ሁለቱም ግን ረክተው አያጨበጭቡልንም! ከሁለት ያጣ ጎመን' ነን…”
ሶራ በከሎ ሃሳብ መመሰጡና መስማማቱ በሚተናነቀው እልህ ያስታውቃል።

“ሳይጠባበቁ ለስራ መነሳት አስፈላጊ ነው" ብሎ ሶራ ትንሽ አሰብ አደረገና፡-

“ይህችን ሃገር ግን አቅጣጫዋ ወዴት ይሆን የሚለውን ለመመለስ ይከብዳል፤ ወደ ተፈጥሯዊ ሕይወት ወይንስ ወደ ዘመናዊ ኑሮን ሔ? ይህ ሃሳብ በህዝቡ ሲመለስ ህዝቡ ያሰበው ጋ ለመድረስ
መጣጣር ይጀምራል፡ አሁን ግን ያለው ነገር ዝብርቅርቁ የወጣ ነው እስኪ አስበው ጉዟችን እውነት ወዴት ነው? አለና ሃሳቡን ገቶ ከሎን አየው: ሁለቱም ጆሮ ላይ የሚያላዝን ውሻ ጩኸት
የመሰለ ኦምቧረቀ።

“ግን አንድ እውነት አለ፡ አንድ ወቅት የቀደምናቸው
አገሮች አሁን ጥለውን ተፈትልከዋል። እነሱ  ዘንድ ለመድረስ ቀጥሎም ለማለፍ በእልህ የታገዘ ጥረት ያስፈልጋል! ከኋላችን
ተነስተው አሁን ከፊት የሚገኙት ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑን ይገባል::
መላና ዘዴ ሳንቀይስ፤ የምንነሳበትንና የምንደርስበትን... ሳናውቅ ግን በለመድናት ጠባብ ጎዳና እንጓዝ ካልን አንዱ መሄጃችን ላይ ገብቶ
ሲሰነቀር ሌላው እንደተለመደው ቆሞ ይቀራል። ለዚህ ሁሉ ግን
ከየት እንጀምር?'' አለ ሶራ ጥያቄ እያቀረበ መልሱን ራሱ ለመመለስ።

“ከራሳችን ከራሳችን መጀመር አለብን" በስሜት ያቀረበው ሃሳብ እንደ ጦር ጎኑን ወጋው። ባዶ ምኞት ወይንስ በተግባር የሚውል ህልም... ፍቅሯ ልቡን እንደ ክትፎ የበላበት ኮንችትስ?
ከሎና ሶራ አንዱ ሌላውን ይበልጥ ለማወቅ፤ ተረዳድተው የአገራቸው አለኝታ ለመሆን ህሊናቸው ቋምጧል: የውጪ ዓለም
ልምዳቸው በራስ መተማመናቸውን ብትንትኑን ቢያወጣቸውም ማንነታቸውን ግን እንደ መስታዋት ቁልጭ አድርጎ አሳይቷቸዋል።
በዚህ የአድቬንቼር ዘመን በትርኪ ምርኪው የግደለሽነት ሕይወት መኖር እንደ አበቅ አንጓሉ አንጓሉ የሐፍረት ቆሻሻ ላይ
እንደሚጥል ተረድተዋል ከሌላው መማር እንጂ እንደ ተውሳክ ጥገኛ መሆን አይንን ጨፍኖ መለመን... በቁም ከመሞት በሞራል
ከመላሸቅ በቀር የሚያመጣው ህሊናዊ ጥጋብ አለመኖሩን ከሕይወት ገጠመኞቻቸው አንፃር አንስተው ብዙ ጊዜ ተጨዋውተዋል::

በህዳሩ የመኸር ወቅት ጨረቃ እንደ ቡሄ ዳቦ ክብ ሆና ገና የብርሃን ወጋገኗን በኒያንጋቶም ተራሮች ወደ ኩዩጉ መንደር ወደ
ኩችሩ ስትፈነጥቅ ከሎና ሶራ እንደተለመደው ሃሳብ ሲለዋወጡ እንደ ቆዩ በመካከላቸው ዝምታ ሰፈነና በእዝነ ሊናቸው ሰማዩ ላይ ጎላ ብሎ የተፃፈ ነገር ተመለከቱ ያን ፅሑፍ ሁለቱም ቀና ብለው አዩት።

“የህይወት ጀልባ ከማዕበል ጋር እየታገለች በውቅያኖሶች ጉያ
አካሏን ነክራ ትንሳፈፋለች ሞት ችግር መከራ ... ያደፍቋታል፤ ደስታ እርካታ ፍቅር. እንደ እንዝርት እያሾሩ ይፈትሏታል እና ጀልባዋ በሁለቱ እጣ ፈንታ ሚዛኗን ጠብቃı የተኙትን የሚስሩት
እየረጋገጧቸው ትሰሩለች:

“በእርገጥ የጎደለው ይተካል ያጣው ያገኛል! ያፈቀረ ይጠላል! የተለጣለ ያነሳል፤የሄደ ይመጣል... በተቃራኒዎች የተወጠረችው ጀልባ የሚፈራረቁባትን ችላ ትጓዛለች።

“አቅጣጫዋ መነሻ መድረሻዋ አይታወቅም:: ጀልባዋ አልቆላታል ትባል እንጂ ከጉዞዋ ከቶ ተገታ አታውቅም: አንድ ቀን
ግን ሥቃይና ሰቆቃ፤ እብሪትና ግፍ የበዛባት ጀልባ ብልሽት
ይገጥማት ይሆናል ያኔ ተሳፋሪዎችዋን ይዛ ትዘቅጣለች  ቁልቁል!
“እሪታ ሰማዩን ያቀልጠዋል የቀስተ ዳመና ቀለሞች በሺ
ተባዝተው ሰማዩን ያስውቡታል ከዋክብት ከነበሩበት በታች ዝቅ
ብለው ብርሃናቸውን ያንተገትጋሉ ገነትና መንግሥተ ሰማያት
ይጣመራሉ።

“ሟቹ ያን ውብ ሰማይ ርቆት ሲሄድ እማይጠገብ
ይሆንበታል! ጀልባዋ ስትዘቅጥ ተስፋ የቆረጠ ያለቅሳል... ሰሚና
ጯሂ እንዲሆ በአንድ ጀልባ ሆነው ዋይ ዋይ' ሲሉ ስቃይ እንደ ቅርጫት ላያቸው ላይ ሲከደንባቸው ይወርዳል።

“በዚያ ሰዓት ቅድስት ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ ሰማይ ትዘረጋለች አምላኳም ድምጿን ሰምቶ ህዝቧን ስለ ስንፍናው አምርሮ ይገስፀዋል።

“እጆቻችሁ ስለምን ሽባ ሆኑ! ስለምንስ ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅን መረጣችሁ... ሆድ ብቻ. ጥቅምን ማነፍነፍ ብቻ... ብሎ አዝኖ ውቅያኖሱን ሜዳ ያደርገዋል ድህነትም በምድር ይወርዳል….ልብ ያለው ልብ ይበል" ይላል ሶራና ከሎ አይናቸውን ጨፍነው ያነበቡት።

በጥቁር የሰማይ ሰሌዳ የተፃፈውን ታምር 'ሁለቱም
እየደጋገሙ አነበቡት:
እንግዳው አጋጣሚ
አስገረማቸው አስፈራቸው ... ያ አጉራሽ የለመደው ህሊናቸው ግን ትርጉሙን በጊዜው ሊያቀርብላቸው አልቻለም።

“የምን ጽሑፍ ነው?... ማንስ ፃፈው?...በየግል የፍች "ቀመሩን ለማግኘት ዳንኪራ ረጋጭ ህሊናቸውን አስጨፈሩት። አንዱ
ለሌላው ያየውን ሚስጥር ግን አላወጣም።

ችግርን ለመናድ ማነስ የሚያመጣውን የአዕምሮ ሰንካላነት ለማስቀረት በራስ የመተማመንን ተፈጥሯዊ ፀጋ ጠብቆ ልጅ የልጅ
ልጆችን ከሃፍረት ለማዳን ሆዳምነትን አስወግዶ በእጅና አዕምሮ መጠቀም... ጀልባዋ ሳትሰጥም ደካማ ጎንን ማስተካከል እንደሚገባ
ዘግይተውም ቢሆን የተረዱ ይመስላል።

በዚያች ሰዓት ከሎና ሶራ ተያዩ! ኤርቦሬና ሐመሩ
ሁለቱ አፍሪካውያን ሊግባቡ
ሞከሩ! ሃይላቸውን ለማስተባበር ተቃቀፉደ
ፍቅራቸው ስህተታቸው ቁጭታቸው... ያስፈነደቃት ጨረቃም አላማቸውን ለማጠንhር ብርሃኗን እያሰፋች ፍጥነቷን በመጨር ጥቁሩን ሰማይ እየገለጠች ወደ እነሱ ገሠገሠች።

ከዚያ ያ ኩሩው ድፍርሱ ሚሊዮን ነፍሳትን በውስጡ
አጭቆ ቁልቁል ይሁን ሽቅብ መፍሰሱ ሳይታወቅ በፀጥታ የሚጓዘው ኦሞ ወንዝ በቁጭት አፍ አውጥቶ ሲናገር! እንደ ውሻ ሲጮህ ተሰማ።

"ኢትዮጵያ ፈላስፎቿን ተመራማሪዎቿን የንብ ተምሳሌት ታታሪ ምሁሮቿን, ማቀፍ እርስ በርሳቸው በጡንቻ ሳይሆን
👍18👏1🤔1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት 


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ካርለት ከዳንሱ ቦታ ራቅ ብላ ጀግናዋን በአይኖቿ
ስትፈልገው በጆሮዋ ስልምልም የሚያደርግ የሙዚቃ ቃና ሰማች።
እንግዳ ነው ያ ሙዚቃ ለጆሮዋ! ሳባት ሙዚቃው
ተጎተተችለት: ቃናው ጆሮዋን እየላሳት ወደ ውስጧ ዘለቀ የህሊናዋን ጓዳ! የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው። አሻት፤ ዳሰሳት…..እሷም
አንኳኳ የሆሊናዋን ጓዳ የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው አሻት፤ ዳሰሳት
ሁለመናዋን ነካካው
አንሸራተታት ደመቅ
ደመቅመቅ... የሚለው ዜማ ፍል ውኃ ውስጥ እንደገባች ሁሉ ቁልቁል እየፈሰሰ ሰውነቷን አጋላት ደስ አላት ሰውነቷ ሲግል‥. ጡቶችዋ ግን ተቆጥተው ቆሙ፤ ዳሌዋ አኩሩፎ አበጠ ፤ ጭኗ አዝኖ ለሰለሰ… ሙዚቃና ልብ ወለድ ጽሑፍ ካለ እሳት ሰውነቷን ሲያጋግሉት ደስ ይላታል... የረሳችው ስሜት
ፈረሰኛው አረፋ እንደሚያስደፍቀው ወራጅ ወንዝ ሞተሯን አሽከረከረው፤ አቃሰተች ያኔም ስርቅርቁ ዜማ በጆሮዋ መግባቱን
አላቆመም:

እየቀረበች ስትሄድ በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ ወይሳውን እየነፋ ጥዑም ዜማ የሚያወጣውን ጀግና አየችው። የሙዚቃው
ቅላፄ እንደ “ቤቶሆቨን ሞዛርት ሲንፎኒ" ቃናው እየቆዬ ጣማት።እሰይ እሱ ነው ብላ አጉተመተመች..

ከዚያ ዱካዋን አጥፍታ በሙዚቃው ስልት እርምጃዋን አስተካክላ ተጠጋችው፡
ባለወይሳው አይኖቹ ከጨረቃና ከዋክብቱ ጋር ይጫወታሉ ቅላፄው
ወዲያና ወዲህ ይመላለሳል። ሙዚቃው እንኳን ሌላውን ራሱንም
መስጦታል። እውነተኛ የኪነ ጥበብ ሥራ ውጤት ስቃይና ደስታዋ፤ሐዘንና ትካዜዋ. እፍታውን ቀማሹ ጣዕሙን አስተካካዩና ፈጣሪው
ያኔው ነውና ወይሳው ደልቲን መስጦታል! ወጥሮታል...

ካርለት ደልቲን በሚጫወተው የሙዚቃ ቃና ተመስጦ በማየቷ ይበልጥ ወደደችው፡ ደልቲ
ለስሜቱ ታማኝ ነው አይቀጥፍም አያስመስልም...
ስርቅርቁ የሙዚቃ ቃና
የሚንቆረቆረው ለህሊናው እርካታ ነው::

ካርለትን የሙዚቃው ስልት አቅም አሳነሳት: ሁለመናዋ
እንቅስቃሴ ፍጥነቱን ስለጨመረ ደካከመች: ስሜቷን አፋጭቶ
ሃይሏን መልሶ ለመሳል አጋዥ ያስፈልጋታል
ባለወይሳው ያን ሰው አጥታው ከርማለች! አሁን ግን አጠገቧ ነው።

እጆችዋ ትከሻው ላይ አረፉ። ባለወይሳው ስርቅርቅ ዜማውን አቁሞ ቀና ብሎ አያት። ቆዳዋ ተገልቧል፣ ከርቀት ጠቆር
ብለ የታየው አካሏ ቁልቁል ወደሱ ሲመጣ እየጎላ ታየው። የራቀው
ሽለቆ ቀረበው።

ንጥት ያለው ገላዋ  በተለይም ጭኗን ትክ ብሎ እያዬ፡ “ካርለትት አላትና አይኖቹ ሳቁ። ሃይል ያጣችው ካርለት
የተሸበሸበ ርጥብ ከንፈሯን ለጠጥ አርጋ ደካማ ፈግታዋን አሳየችው።

ባለወይሳው አስተውሎ አያት ውስጧንም አየው
የተቀጣጠለውን ስሜቷን ነካው፡

ጭኖቹ ላይ ያለውን ወይሳ አንስቶ ለጨረቃ ሰጣት!
ጨረቃም ወይሳውን ተቀብላ እየነፋች ጥዑም ዜማዋን ማንቆርቆር ጀመረች። በጨረቃ የሙዚቃ ቃና ደልቲ ቀኝ እጁ እየተንከላወሰ ወደ
ነጩ ጭኗ ገባ። ነዘራት
በሽተኛዋን! “በሽታውን የደበቀ..." እንዲሉ እሷም ሃኪሟን ረዳችው የሚያቃጥላትን የሚቆረጥማትን እጁን
በእጅዋ ይዛ አሳየችው።
ጆሮ ግንዱን ፀጉሩን
ማጅራቱን...እየደባበሰች የእርዳኝ ጥሪዋን አሰማችው። ሀኪሟ በስሜቷ እሱም ተሽፈነ። ለጋራ በሽታቸው ግን የሚበጀውን ያውቃል። ስለዚህ ማገገሚያ ቀንዱን አቁሞ ይዞ ከተቀመጠበት ተነሳ።

ሙዚቃው ይስረቀረቃል! ዳንሱ ጦፏል... ጨረቃ
ታዜማለች ! ቅጠሉ እስክስታ ይወርዳል! ነፋሱ አታሞውን
ይደልቃል... ጥቁርና ነጭ ቀለሙ ማራኪ ዜብራም ያናፋል...

ኮንችት ጭፈራውን በጉጉት እያየች እንደቆየች ስለ ነገው
ጉዟቸው ካርለትን ለመጠየቅ ፈልጋ አጣቻት የኩችሩ መንደር ኗሪ
ጥበቃውን አላቆመም። ነጩ እባብና ሎካዬ ግን አልመጡም። ኮንችት
በየዋህነታቸው ብታዝንም ማድረግ የምትችለው ባለመኖሩ በዝምታ
ሁኔታውን ስትከታተል ሰነበተች። የመቆያ ፈቃዷ  እያለቀ ነው:: ስፔን ስትመለስ ብዙ ልትሰራ አስባለች በተለይ ስለ ኢትዮጵያ  ስለ ኩጉዩ፡ ከመሄዷ በፊት ግን ሐመርን ኤርቦሬን ከካርለት ጋር በሷ
መኪና ለማየት ተስማምታለች ጉዞዋን በተመለከተ ግን ከካርለት
ጋር መነጋገር ያለባት ቁም ነገር ነበር።

ኮንቺት ካርለትን ስታጣት ደልቲን በጨረቀዋ ብርሃን  ፈለገችው የለም:

ካርለት የሄደችው እሱ ዘንድ ይሆን?' አብረው ሆነው
ለማየት ጓጓች: ፍቅር ሲለዋወጡ እንዴት ይሆን?' ለማስብ ሞከረች:: መልሳ ደግሞ ሃጢያት እንደሰራች ሁሉ አስበችው አፈረች። ሆኖም ግን አልቻለችም ጉጉቷ ጨመረ።

በዚህ መካከል ድክምክም ያለውን የወይሳውን ድምፅ
ኮንችት ከርቀት ሰማችው። በድፍረት ሄደች  ወደ ጫካው! ድንገት ግን ክው ኦለች ! ባለበት የሚሰግር
ዜብራ አየች ፈራችው
ዜብራውን ይጋልባል ... በስሜት ተውጣ አይኖችዋን ጨፈነች:
"...የፍቅር እንጥሌን ሌሎች ተንጠራርተው ሲያጡት የነካው እሱ ብቻ ነው" ኮንችትን የነገረቻት ትዝ አላት።

“ዋው! ጎመጀች በዜብራው
ግልቢያውን አሰጋገሩን
አደነቀችው። ወደደችው ያን ስሜት ሰላቢ ጥዑም ዜማ... ፈውስ ሰጭ ዳንኪራ… ንፁህ የጫካ ፍቅር... ማራኪ ተፈጥሮ ተጋግዘው እንግዳዋን መልሀቋን አስጥለው በጉጉት ገተሯት!  ተጣራች በሲቃ ሶራ ግን አልሰማትም! ኤጭ! ብላ ከንፈሯን ጣለች። ጎደሎነት
ተሰማት ያማራትን የዜብራ ግልቢያ ግን የሚያቀምሳት አጣች.የጎመጀችለትን ያጣችው ኮንችት አዘነች። ...ዛፉ ቅጠሉም አዘነላት ላልተጠራችው ተመልካች!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

“እ. እ..." አቃሰቱ እምቡዋ እ. እ" ሳግ ተናነቃቸው
ህፃናት ወጣቶች አዛውንቶች ኦሞ ወንዝ ዳር ጫካ ተሰባስበው እንግዶች በእንጨቷ ታንኳ ኦሞን ሲያቋርጡ አያቸው።

ኮንችት እጅዋን አውለበለበችላቸው “ቻው... ባባይ... አለቻቸው። ዝም አሉ ኩዩጉዎች የነሱ የጥልቅ ፍቅር መግለጫቸው ዝምታ ነው። ሳግ ያበት “እ... እ..." እሚያሰኝ ከጥጃዋ በሃይል እንደተነጠለች ላም የሚያንሰፈስፍ ዝምታ! “እ. እ. እምቡዋ.. እያሰኘ የማይፈስ እንባ የሚያስነባ, የማይገልፁት ግን የሚታይ
የሚነካ... የመለየት ጭንቀት የሚታይበት ስሜት..

“እወዳችኋለሁ! ከናንተ በመለየቴ አዝናለሁ. ምንጊዜም አልረሳችሁም..." ኮንችት በስፓኒሽ ለመግለፅ ለፈለፈች¦ ምላሽ ግን
አልነበረም። “ፀጥታ ብቻ! ለኩዩጉዎች የመለየትን መጥፎነት የሚገልፅ ቋንቋ የላቸውም ካለ ዝምታ በቀር።

ኮንችት አነባች::
የካርለትን ትከሻ ተደግፋ አነባች አለቀለች  ሌሎች ግን ዝም ረጭ ብለዋል  እንደ ሌሎች ወንዞች
የማይጮኸው የማይደነፋው.
የኩዩጉዎች ህይወት የመልክ ማያ መስታዋታቸው የሆነው የኦሞ ወንዝም በዝምታ ድባብ እንደ ተዋጠ
ነው: ወፎች ግን ይበራሉ ያዜማሉ! እዕዋት ያሽበሽባሉ...

“እሷ ሄደች በሉ
ሉካዬንና የሰላም አድባራችን
የነበረውን ነጩን እባብ እንጠብቅ ! ተከፍተን ታዩን መምጣቱን እንዳይተዉት እንዝፈን እንጫወት.."
ሽማግሌዎች ለኩችሩ መንደር ህዝባችው ተናገሩ ኮንችት ካርለት ከሎ ሶራ… ኦሞን ከተሻገሩ በኋላ ዞር ብለው አዩ: ኩዩጉዎች የሉም!.ሲደልቁ ግን ይሰማል ለዚህች ተለዋዋጭ ዓለም ለረጅም ጊዜ አልቅሶና አዝኖስ መኖር እንዴት ይቻላል!
👍263👎1🥰1😁1