አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

...ከሩቅ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በርሜሎች ሲመለከት ክንዷን ይዞ ወደዚያው ጎተታት፡፡አካባቢውን ባለበሰው የቆሻሻ ክምር ላይ ተሻግረሁ ከበርሜሎቹ ጀርባ ዞረው ሸብረክ ሸብረክ አሉ፡፡በስተግሪ ራቅ ብሎ መደዳውን ከተኮለኮሉት የመሸታ ቤቶች የሚወጣው ደብዛዛ ብርሃን አካባቢውን በድቅድቁ ጨለማ ከመዋጥ አድኖታል ወዲያ ማዶ አንድ የጭነት መኪና ቆሟል፡፡ በስተቀኝ የውሾች ጥል በጨለማ ውስጥ አስተጋባ፡፡ድምፃቸውን አጥፍተው ተጠባበቁ፡፡

ናትናኤል ቀና ሲል በጨለማው ውስጥ አንድ ነገር ውልብ ሲል ተመለከተ፡፡ ዓይኖቹን በሰፊው ከፍቶ በጨለማው ላይ አፈጠጠ፡፡ ድምፅ ተሰማው... እየቀረበች ስትመጣ ሲለያት በእፎይታ ትንፋሽን ለቀቀ።ሰካራም ሴት ነበረች:: እንደመንገዳገድ ትልና ወደፊት ትራመዳለች፡፡ ትንሽ ታንጎራጉርና ደግሞ ወደፊት ተራመዳለች፡፡ ብዙም ሳይቆይ ከሰካራሟ ጀርባ የሌሎች ሰዎች ሩጫ ተሰማ፡፡ ናትናኤል ከበርሜሎቹ ጀርባ ሳይወጣ ጭንቅላቱን ብቻ አቅንቶ ተመለከተ::

ሦስት ሰዎች እየተሯሯጡ በኮረኮንቹ መንገድ መጡ፡፡ በኮረኮንቾ
መንገድ ላይ እየተወለካከፉ ሲሮጡ ናትናኤል አዳኞቹ እንደሆኑ ገባው::
ሰካራሟ ሴትጋ እንደደረሱ ከሦስቱ አንደኛው የያዘውን ባትሪ መለስ አድርጎ
ፊቷ ላይ ቦግ እደረገባት፡፡
“ትዝታ እ.. እባላለሁ፡፡” አለች ሰካራሟ ኣይኖቿን ባትሪው ብርሃን በክንዷ ከልላ “ሀ! ሀ! ሀ! ከፈለግህ ደሞ እቤት እንሂድና::ባትሪውን ያበራባት ሰው ትቷት ከጓደኞቹ ጋር ወደፊት ቀጠለ።
ሦስቱ ሰዎች ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎቹ ሲደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው ቆም አሉና ተነጋገሩ፡፡ ወዲያው ሁለቱ በስተቀኝ ታጥፈው በጨለማው ውስጥ ሲሰወሩ ባትሪ የያዘው ሰው በበርሜሎቹ ኣቅጣጫ አመራ፡፡
ናትናኤል አብራው የተደበቀችውን የካልቨርትን ወዳጅ ጠረጠራት፡፡
ብትጮህስ? ብትጣራና ብታሲዘውስ? እዚሁ ቆሻሻ መጣያ በርሜል : ስር
ደፍተውት ሊሄዱ አይደል? ፈጠን ብሎ ቀኝ እጁን በትከሻዋ አሳልፎ አፏን
አፈናትና በግራ እጁ የያዘውን የቢላ ጫፍ አንገቷ ስር ሽጎጠው፡፡

“ትንፍሽ እንዳትይ… ፊቱን ከማዞሩ በፊት ይሄ ቢላ ማጅራትሽ ነው የሚደርሰው፡፡” አላት ዓይኖቹን በበርሜሎቹ አቅጣጫ ቀሮጠው ሰው ላይ ተክሎ፡፡

ሳትነቃነቅ አይኖቿን ብቻ ኣቅንታ በጭንቀት ተመለከተችው::እንገቷ ስር የተሸጎጠው የቢላ : ስሎት ለስላሳ ቆዳዋን እንደ ምላጭ ሲሰነጥቀው ተሰማት::
ሰውየው ወደ በርሜሎቹ እየተጠጋ በመጣ ቁጥር በደመነፍስ ያወቀና የተረዳ ይመስል ፍጥነቱን ቀንሶ የባትሪውን ብርሃን እንደ ነብር ጅራት ከወዲያ ወዲህ እያላጋ ዙሪያውን እየፈትሽ በዝግታ ይራመድ ጀመር፡፡ እየቀረባቸው ሲመጣ ናትናኤል በበርሜሎቹ አናት ላይ ተመለከተው።በግራው ባትሪውን እንደጨበጠ በስተቀኝ የኮት ኪሱ ውስጥ የጨመረውን እጁን ሲመለከት ስውየው መሣሪያ እንደያዘ ናትናኤል ተረዳ፡፡ በየምሥራች አፍ ላይ የጫነውን የቀኝ እጁን ጠበቅ አደረገና በግራው የያዘውን ቢላ ከአንገቷ ስር አውጥቶ ይዞ ተዘጋጀ፡፡ ተጠባበቀ፡፡ ከበርሜሎቹ ዙሪያ
የፈሰሰው ቆሻሻ ላይ ሲረግጥ የአዳኙ ኮቴ ኮሽታ ተሰማው። ሲጠጋውና
ሲቀርበው ሲደርስበት ተወርውሮ ቢላውን ሊሰካበት ተዘጋጀ፡፡ ሰውየው
ድንገት ቆም አለ፡፡ ያመነታ መስለ ባትሪውን ዞር አድርጎ በበርሜሎቹ ላይ
እበራ፡፡ የባትሪውን ብርሃን በዙሪያው አወናጨፈው፡፡ ወዲያው ፊቱን መልሶ
በኮረኮንቹ መንገድ ወደፊት ቀጠለ፡፡

ሰውየው ከራቀ ወዲያ ነበር ናትናኤል ለመተንፈስ የደፈረው።የምሥራችን አፍ ለቀቀና ቀና አደረጋት፡፡

“አይዞሽ አትፍሪ፤ ልጎዳሽ አልፈልግም:: እመኚኝ፡፡ ከዚህ በላይ ምን ማረጋገጫ ነው የምትፈልጊው?” አለ ትከሻዋን በሁለት እጆቹ ይዞ እየነቀነቀ፡፡ “በይ ተነሺ… ሳንቻኮል በእርጋታ እየተራመድን ወደ ዋናው መንገድ እንውጣለን፡፡ ለመሮጥ ወይ ለመጮህ ብትሞክሪ ግን ምርጫ አይኖረኝም::”

“አልሮጥም::” አለች ፊቷን መልሳ በፍርሃት እየተመለከተችው::

ናትናኤል የምሥራችን ክንድ እንደያዘ ቁጢጥ ካለበት ብድግ ሲል እንቅስቃሴ ታየው፡፡ ተመልሶ ሸብረክ አለና እንዳጎነበሰ አሻግሮ ተመለከተ፡፡
እየተንገዳገደች ቆም ራመድ እንደገና ቆም እያለች በኮረኮንቹ መንገድ
ተመልሳ ትመጣለች ሰካራሟ፡፡

“ተነሽ…” አለ ናትናኤል የምሥራችን ክንድ እየጎተተ፡፡ “ሰካሪሟ ከተደበቁበት የቆሻሻ ማጠራቀሚያ በርሜሎች ስር ወጥተው ፈጠን ብለው በዋናው መንገድ አቅጣጫ አመሩ፡፡

“ታዲያስ!” አለቻቸው ከፊት ለፊታቸው እየተወለካከፈች፣ እየተንገዳገደች የምትመጣው ሰካራም::“እስቲ ወንድም ብር ግፋ፡፡” አለችው ናትናኤልን ስትመለከት እጇን ወደፊት ዘርግታ፡፡

“ዞር በይ!” አላ ናትናኤል አልፏት ለመሄድ እየሞከረ:: ድንገት በዘረጋችው መዳፏ ውስጥ የጨበጠችውን ሲመለከት ግን መላ አካላቱን ደነዘዘው፡፡ : የምሥራች ከፊቷ የተደቀነውን ስታይ እንዳትጮህ የፈራች ይመስል የገባ አፏን በገዛ መዳፏ ግጥም አድርጋ ዘጋችው፡፡

“የማይሆን ነገር አትሞክር፡፡” ኣለች ሰካራሟ የያዘችውን ሽጉጥ ወደ
ሆዱ ገፋ አድርጋ፡፡ “ተነቃነቅ..ዘረግፍሃለሁ፡፡” ድንገት ፊቷን ወደ የምሥራች መለሰችው፡፡ “አንድ ዕድል እሰጥሻለሁ፤ ካልቨርት የት ነው?”
የሽጉጧን አፈሙዝ መለስ አድርጋ የምሥራች ላይ ደቀነችው፡ “ንገሪኝ ጊዜ
አትውሰጂ!”

“እኔ ኣላውቅም፡፡”
በእጁ የጨበጠው የምሥራች ክንድ ሲንቀጠቀጥ ተሰማው:: “ተኩሼ ሳልቀረድድሽ ንገሪኝ:: ካልቨርት የት ነው?' ሴትየዋ አፏን ሳትከፍት በጥርሶቿ መሃል ተናገረች፡፡

“አላውቅምኮ፡፡” የምሥራች ድምፅ እንደ ወፍ ትንፋሽ ሳሳ፡፡ፍርሃት ያንቀጠቅጣት ጀመር፡፡

ሴትየዋ አላመነቻም፡፡ ወደኋላ ጥቂት እርምጃዎች አፈገፈገች፡፡ ናትናኤል ያልጠበቀው ድምፅ ቡፍ አለ፡፡ የምሥራች እጁ ላይ ተልፈሰፈሰችበት... ለቀቃት። ዝልፍልፍ ብላ በስተቀኙ ተዘረጋች፡፡ ከፊት
ለፊቱ ሽጉጧን ደግናበት ከቆመችው ሴት ጋር ተፋጠጠ፡፡ ትንፋሹን ይዞ ጠበቃት፡፡ አእምሮው እርስበርሱ ተጣላበት፡፡ ሊፈነዳ ያሰበ ይመስል ማጅራቱ ሲወጠር ተሰማው:: ዘሎ ይነቃት? ወይስ መጨረሻውን በቆመበት ይቀበል?
ድንገት ፈገግ ያለች መሰለው.. ፈገግ አለች ሴትየዋ፡፡ ከኋላው የሩጫ ድምፅ
ተሰማው፡፡ ከፊት ለፊቱ ቆማ የነበረችው ሴት በፍጥነት የሽጉጧን አፈሙ
ወደ መሬት መለሰችና ከትከሻው ላይ አሻግራ በጨለማው ላይ አፈጠጠች

“ሩጥ!” አለችው በሹክሹክታ ወደጎን ትታው የሩጫው ድምፅ ወደመጣበት እየተራመደች፡፡ “ተዋትና ሩጥ፤” አለችው ድጋሚ ፊቷን መልሳ፡፡ የምሥራችን እየጎተተ ወደ ጥግ ሲሸሸግ ስታየው፡፡ “እሷን ተውና ሩጥ!”

ናትናኤል ሳይመልስላት የምሥራችን ብብቶቿ ውስጥ ገብቶ እየጎተታት ወደ ጥግ ሽሽግ አለ፡፡ መሬቱ ላይ ተንበርክኮ የምሥራችን ጭንቅላት ቀና አደረገና ትንፋሿን አዳመጠ፡፡ አለች፡፡ የምሥራች... የምሥራች...” ድምፁን ቀንሶ ተጣራ፡፡
እያኖቿን በትግል ፡ ገልጣ ተመለከተችው.. እየሞተች ነው...
እየቀዘቀዘች ነው… እያበቃች ነው... ሊያድናት እንደማይችል ተረዳ፡፡
“የምስራች ንገሪኝ ካልቨርት የት ነው ንገሪኝ! ሁላችንን ሳይጨርሱን በፊት ንገሪኝ?”
“ካልቨርት ዮ....ሴፍ” ከጉሮሮዋ የሚወጣው ድምፅ ሻከረበት፡፡
“አዎ ዮሴፍ ዮሴፍ፡ ካልቨርት የት ነው ያለው?”
ከወዲያ የሚሰማው የሩጫ ድምፅ እየቀረበው መጣ አንድ ሴት
ስታንጎራጉር ይሰማል.. በጨለማው ውስጥ..
ዮ....ሴፍ...” የምሥራች ድምፅ በጭንቀት እየተበጣጠሰ ተንጠባጠበ፡፡
“አዎ.... አዎ የት ነው?”

የሩጫው ድምፅ ቀረበ፡፡ ናትናኤል ጭንቅላቱን መልሶ ከጀርባው ተመለከተ፡፡ ሰካራሟ መሀል
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ



#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....በጥፊ ጆሮ ግንዷን እናጋው፡፡
ለጥቂት ደቂቃዎች ያለችበት ጠፋት፤ዘሪያዋ ጨለማ ለበሰ፡፡ እዛው
አፓርትመንት ክፍሏ ውስጥ እጆቿንና እግርቿን ከአልጋዋ ጋር በአንሶላ
ጨርቅ ጥፍር አድርገው አስረው እንዳትጮህ አፏ ውስጥ ጨርቅ ጎስጉሰው ለጉመው አጋድመዋታል፡፡

“ንገሪኝ!” አለ ድጋሚ ሊያጣፋት እየተንጠራራ “የት ነው ያለው?
ትነግሪኛለሽ አትነግሪኝም?”
ጭንቅላቷን በጭንቀት አርገፈገፈችው:: ከተለጎመው አፏ ጀርባ ጉሮሮዋ . “የት እንዳለ አላውቅም:: እውነቴን ነው!” አለች:: ድምፅ ግን አላወጣችም፡፡

ውልብ አለባት ድጋሚ፡፡ ጆሮዋ ላይ ሌላ ጥፊ ደወለ፡፡
“ንገሪኝ!”

ዱላው እየጨመረ በመጣ ቁጥር እልኋና ቁጣዋ እንዴት ተደፈርኩ ባያነቷ እንደጨው እየሟመ ለማይታክተው እንባዋ እስረከበዋታል፡፡ ፀጉሯ
ሲጨመደድ ተሰማት::

“ንገሪኝ! የት ነው ያለው?”
ድጋሚ በጥፊ አይኖቿን ከደናቸው፡፡
“ንገሪኝ!”

ተከትሎ ምን እንደተናገረ አልሰማችውም:: ጆሮዋ ላይ የሚደውለውን ስቃይ ተከትሎ ዙሪያዋ ፅልመት ተከናነበ፡፡ አይኖቿን ድጋሚ ስትገልጣቸው ሰውነቷን ክፉኛ ቀዘቀዛት፡፡ለሶስተኛ ጊዜ ውሃ አፍስሰውባታል፡፡
አልጋዋ በየደቂቃው ህሊናዋን በሳተች ቁጥር በሚቸለስባት ቀዝቃዛ ውሃ
ረስርሳል:: የለበሰችው ስስ ቀሚስ እላይዋ ላይ ተጣብቋል፡፡

ዓይኖቿን ግርብብ አድርጋ ተመሰከተቻቸው፡፡ ሶስቱም በአልጋዋ
ዙሪያ ቆመው ቁልቁል ይመለከቷታል፡፡ ሁለቱን አታቃቸውም፡፡ ሶስተኛው
ግን ያው የህዋሷ መሪ ማርቆስ ነበር፡፡ በጠባሳ የተገመሰ ፊቱን ቁልቁል
አንዘርቦ ይመለከታታል፡፡ ደጉን የተወያየችው የገዛ ጓደኛዋ አልመስልሽ
አላት፡፡ አይኖቿን ጭምቅ አድርጋ ጨፈነቻቸው፡፡ በተንጋለለችበት እንባዋ
የገዛ አይኖቿን እንደጨው እየለበለበ ፈሰሰ፡፡

“ከሃዲ!” አለ ሰስተግራዋ የቆመ ሌሊቱን ሲጠፈጥፋት ያደረው ሰው ድንገት ፊቱን መልሶ የመኝታ ክፍሏን በር ከፍቶ እየወጣ፡፡

በክፍሉ ውስጥ የቀሩት ሁለት ሰዎች ለጥቂት ደቂቃዎች ያለ እንቅስቃሴ ቁልቁል ሲመለከቷት ቆዩ፡፡ ወዲያው ማርቆስ ጠጋ ብሎ አፏ የተለጎመበትን ጨርቅ መፍታት ጀመረ፡፡ ሽቅብ ፊቱን ስትመለከተው ከዓመት በላይ የምታውቀው አብራው የቀለደችና የሳቀች ያው የድሮው የህዋሷ መሪ ማርቆስ መሆኑን ማመን አቃታት፡፡

“ምን ማድረግህ ነው?” አለ ከበስተግርጌ የቆመው ጺማም ሰውዬ ማርቆስ አፏ የተለጎመበትን ጨርቅ ሲፈታላት ሲያይ እየተቁነጠነጠ።

ማርቆስ ለሰውየው መልስ ሳይሰጠው አፏን ሞልቶ ተርፎ የነበረውን ቡትቶ ጨርቅ ጎትቶ አወጣላት፡፡ ተበርግዶ የቆየ መንጋጋዋ የራሷ መንጋጋ እንዳልሆነ ሁሉ አልገጥምልሽ አላት፡፡ ደርቆ የቆየ ጉርሮዋ የገዛ ምራቋን አልውጥልሽ አላት፡፡ እንባዋ ብቻ ጉንጮቿን እየተለተለ መውረዱን
ቀጠለ፡፡

“ርብቃ …ለምን ለእኛም ለራስሽም አስቸጋሪ ትሆኛለሽ?” ማርቆስ
ቁልቁል እየተመላከተ ተማፀናት፡፡ “ርብቃ ልለምንሽ የት እንዳለ ንገሪንና
ይህ ሁሉ ያብቃ፡፡” ተለማመጣት፡፡

ለምን አይገባቸውም?! ናትናኤል የት እንደለ ኣላውቅም ስትላቸው ለምን አያምኗትም?! እንዴት አድርጋ ነው እውነቱን እውነት ነው የምትላቸው?

“የት እንዳለ አላውቅም፡፡” ልትል ፈለገችና ጉሮዋ አልታዘዝሽ አላት፡፡ በጀርባዋ በተንጋለለችበት ጭንቅላቷን ነቀነቀች፡፡
“ርብቃ ጊዜ በወሰድሽ ቁጥር ሁኔታው ለራስሽ እየከፋ ነው የሚሄደው፡፡ የምትጋፈጫቸው ሰዎች ትዕግሥታቸው ያለቀና ቁጣቸው ወደ ዕልህ የተቀየረ ራሳቸውን መቆጣጠር የማይችሉ ናቸው:: ርብቃ እነዚህ ሰዎች ሊያደርጉት የሚገፋፉትን ደግሞ ማንም አይወደውም፡፡ አንቺ ሴት ነሽ፡፡ እነዚህን ሰዎች የሚቋቋም የመንፈስ ጠንካራነት የለሽም:: በቀላሉ እንደቀርከሃ ሊሰባብሩሽ ይችላሉ፡፡ በቀላሉ! እባክሽን ንገሪኝ፡፡፡ ናትናኤል የት ነው?” የሌሊት ሁኔታዋን መቋቋም አቅቶት ሲቁነጠነጥ ያደረው
ማርቆስ የባሰ ከመምጣቱ በፊት ሊያሳምናት ታገለ፡፡

አ....አላውቅም፡፡” አለችው እንባዋን እያስተናገደች::
“ጥሩ፡፡ መስሪያ ቤትሽ ደውሉ ሲያጣሽና ስራ ከገባሽ ውሰሽ ማደርሽን ሲረዳ እንዴት እዚህ አልደወለም?”
“ፈርቶ ይሆናል... እኔ ምን አውቃለሁ፡፡” እውነተኛነቷን ይገልፅላት ይመስል ድምጿን አለሰለሰችው::

“ምን? ማንን ነው የሚፈራው?”
“እናንተን፡፡” አለች በለቅሶ መሃል፡፡

“አየሽ ይህ ማለት አንቺ ከእኛ ጋር ግንኙነት እንዳለሽ አውቋል ወይም በፊትም ያውቅ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህን ሊያውቅ የሚችለው ደግሞ አንቺ....”

አልነገርኩትም!” አለች አቅጣጫውን ስትረዳ አቋርጣው፡፡ “እኔ አልነገርኩትም፡፡እኔ በእርሱ ላይ መረጃ ስስበስብ መቆየቴንም ጭራሽ አያውቅም፡፡ ግን እዚህ ሲመጣ ልታገኙት እንደምትችሉ ጠርጥሮ ይሆናል፡፡”
ለምን ድጋሚ መሥሪያ ቤትሽ ስልክ አልደወለም? ባለፈው ጊዜ ሲደውል ጓደኛሽ ቢሮ ከገባሽ ዉስሽ ማደርሽን እንድትነግረው አድርገናል፡፡እዚህ መደወል ወይ መምጣት ነበረበት፡፡ አልመጣም፧ አልደወለም:: መሥሪያ
ቤትሽም መልሶ አልደወለም:: ለምን?”

“አላውቅም::” እለች በማስተዛዘን፡፡

“ውሽት አውቋል… ሁሉንም ተረድቶታል:: ለዚህ ነው ሊገናኝሽ ያልሞከረ፡፡ ባያውቅ ኖር..”

“ውሸቴን አይደለም!” አቋረጠችው “እመኑኝ ናትናኤል ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ናት…”

“ያውቃል! ያውቃል! ምንም የማያውቅ ሰው በጭካኔ የሁለት ሰው ነፍስ አጥፍቶ አይሰወርም፡፡ ትሰሚኛለሽ? የፈጸመው ወንጀል ምንም የማያውቅ ሰው የሚፈጽመው አይደለም!” ትከሻዋን በሁለት እጆቹ ይዞ ነቅነቃት፡፡

“ናትናኤል ሰው ፡ አይገድልም...ውሸት
ነው፡፡” ለራሷ ፡ ነበር የተናገረችው፡፡

“ርብቃ…. ሰዎቻችን ያውቁታል፡፡ ለይተው ስላወቁትም ነው የተከታሉት፡፡ ይገባሻል? የካልቨርትን አድራሻ ከሴትየዋ ማግኘት ስላልቻለ ምናልባትም አድራሻውን አስገድዶ ካውጣጣት በኋላ ነው ደረቷን በጥይት የበሳው፤ ገድሏት የሄደው፡፡
አስታውሽ እሷን ብቻ አይደለም ያጠፋው!
የኛንም ሰው ነው:: ርብቃ… እባብ ነው ሰውዬሽ፡፡ ሁላችንንም አታሎናል፡፡
ምንም የማያውቅ የዋህ መስሎ አታሎናል፡፡ አንቺንም አታሎሻል፡፡ አብረን
ልናቆመው ይገባናል፡፡ ንገሪኝ፤ የት ነው የተሸሸገው?”

“አላውቀውም አልኩህ፡፡”
ገፁ በንዴት ተኮማተረ፡፡

“ርብቃ” አይኖቹን አጥብቦ ተመለከታት፡፡ “በአንድ ወቅት ከጎናችን መቆምሽን አንዘነጋውም፤ ያ የሩቅ ትዝታ አይደለም፤ ግን ደግሞ መረባችን በከዳተኞች ምላጭ ሲበጣጠስና ውጥናችን በባንዳዎች ራስ ወዳድነት እርቃኑን ወጥቶ እያንዳንዳችን ለስደትና ለሞት ስንዳረግ በዝምታ መመልከት አንችልም፡፡ ይህ እንዳይሆን ደግሞ የምንጠላውንም ነገር ቢሆን ለማድረግ እንገደዳለን፡፡ ርብቃ ትሰሚኛለሽ? መንፈስሽ መኮሳሽት ካለበት እናኮላሽዋለን፤ሰውነትሽ መዋረድ ካለበት እናዋርደዋለን! ህሊናሽ መጨቅየት ካለበት እናጨቅየዋለን… የማታ ማታ የጠየቅንሽን ሁሉ ታወጪዋለሽ፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት አስተውይ፡፡ ናትናኤል አታሎሻል! የስጋ ፍላጎትሽን ተጠቅሞ
ምስጢራችንን ከቀዳ በኋላ አጋልጦሽ ተሰውሯል፡፡ የት ነው ያለው?
ናትናኤል የት ነው?”

“አላውቅም'ኮ” እንባዋ ገና ድሮ በቀደደው ቦይ ያንቆረቆር ጀመር፡፡

የመኝታ ቤቷ በር ተከፍቶ ሦስት ሰዎች ተከታትለው ገቡ፡፡ ሁለቱን አይታቸው አታወቅም አንደኛው ግን ከትላንት ጀምሮ ሲቀጠቅጣት የቆየ ነው ከፊት ቀደም ያለው ሰው በእድሜ ጠና ያለ ይመስላል፡፡ ወደፊት ራመድ ብሎ ወደ አልጋዋ ግርጌ ከተጠጋ በኋላ በክፍሉ ውስጥ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንዲፈቷት ምልክት ሰጣቸውና ከማርቆስ ጋር በሹክሹክታ ይነጋገር ጀመር
1👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


.....ናትናኤል ጊዜ ሳያጠፋ ታክሲ ተሣፍሮ ወደ ለገሃር ሄደ፡፡ ደጋግሞ ደውሎ ነበር ስልኩ የተነሳለት፡፡ቀደም ብሎ የመሥሪያ ቤቷ ጓደኛዋ ምህረትጋ ደወሎ ርብቃን አቅርቢልኝ ሲላት: እሁንም ወደ ስራ
ገበታዋ አለመመሰሏን ስትነግረው አለቅጥ ተጨነቀ፤ከራሱ ጋር ክርክር
ገጠመ፡፡ እንደታመመችና ቤቷ ደውሎ ከቻለም ሄዶ ቢያያት እንደሚሻል
ምህረት ስትነግረው መንፈሱ ሸፈተበት፡፡ ልቡ ላይ እንደጦር የተሸነቀረበት
ግን ሌላ ነበር

“በጣም አሟታል እንዴ?” አላት ምህረትን ቅንድቦቹን አጠጋግቶ፡፡ “ምንድነው በሽታዋ ማለቴ…”
“እንዴት ነው ነገሩ..ኣላወቅህም ማለት ነው? ወይስ…ናትናኤል ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች፡፡”
ድንገት እንደመሽ ሁሉ ጭልምልም አለበት ፤ ጭንቅላቱ እንደ ድንጋይ ከበደው፤ ማጅራቱን ጨምድዶ ያዘው፡፡ አንድ ቃል ብቻ ይደጋግም ጀመር “ፈጣሪዬ! . ፈጣሪዬ! ፈጣሪዬ! ስልኩን ከዘጋ በኋላ በቆመበት ተገትሮ ቀረ፡፡ እንደህፃን ልጅ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ፈለገ፡፡ “ርብቃ ... ርብቃ!” ራሱን መቆጣጠር ተሳነው “ገደል ይግባ!” ሁሉ ነገር ገደል ይግባ!” የሚንቀጠቀጥ እጁን ኪሱ ከቶ ከአንድ ቡና ቤት ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ለሰዓታት ከራሱ ጋር ተወራጨ፡፡ በመጨረሻ ከቡና ቤቱ ወጥቶ የህዝብ ስልክ ይፈልግ ጀመር፡፡

ስልኩ ቢጠራም የሚያነሳው ሰው አልነበረም፡፡ በሚንቀጠቀጥ ቀኝ
እጁ የስልኩን እጀታ ጨምድዶ ይዞ ተጠባበቀ:: ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች ስልኩ
ይጠራል፤ የማያነሳ የለም፡፡ ቀጥታ እቤቷ ድረስ ብሄድስ? አሰበ፡፡ መሄድ የለብኝም:: እሷንም ቢሆን ለባሱ አደጋ ማጋለጥ ነው የሚሆነው፡፡ ደጋግሞ ደውሎ ነበር ስልኩ የተነሳለት

“ሀሎ” አለ ስልኩ እንደተነሳ ቀድሞ፡፡ ድምፅ ተጠባበቀ፡፡ ግን ምንም
አልነበረም:: መልሶ “ሃሎ አለ የሚንቀጠቀጥ ድምፁን ማረጋጋት
እየታገለ፡፡

“ናቲ..ናናቲ” ድምጿን ከመቅጽፅት ለየው፡፡ ቢሆንም በጣም የደከመ ድምጽ ነበር፡፡
“ርብቃ! ደህና ነሽ…?”
“ናቲ...ናቲ አቃጠሉኝ..ና…” .
“ናትናኤል ነኝ ርብቃ… ጮክ በይ አይሰማኝም፡: ርብቃ መሥሪያ
ቤትሽ ደውዬ ነበር፡፡ ርብቃ… እ?… አይሰማም፡፡” ድምጿ እየደከመበት ሄደ፡፡
ሌላ ሰው ስልኩን እንደተቀበላት ተረዳ፡፡
“ሀሎ፡፡” አለ ለስለስ ያለ የወንድ ድምፅ፡፡
“ሃሎ.… እባኮት ርብቃን ነበር፡፡”
“ማን ልበል? ” .
“ሀሎ..እባኮት ርብቃን ያቅርቡልኝ::” ናትናኤል ረጋ ብሎ ጠየቀ፡፡
“ይቅርታ፡፡ትንሽ አሟታል፡፡ በስልክ መቅረብ አትችልም::
የምነግርልዎት መልዕክት ካለ.….”
"እሷኑ ለማነጋገር ስለምፈልግ ነበር፡፡” ናትናኤል ጠንከር አለ፡፡
“ይቅርታ… ስትነጋገር ስለሚደክማት ነው፡፡ መልዕክት ካሎት ልንገርሎት፡፡ ታናሽ ወንድሟ ነኝ ብስራት ነኝ፡፡”
ናትናኤል ለማስታወስ ሞከረ፡፡ ቤተሰቦቿን ብዙም አልቀረባቸውም፤ ቢሆንም ከብስራት ጋር ከአንድ ሁለት ሦስት ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡ ብስራት ገና ሃያ ዓመት ያልሞላው ወጣት ወንድሟ ነው::

“እንደምንዋልክ ብስራት፡፡ ናትናኤል ነኝ፤
ታስታውሰኛለህ? የርብቃ..እ… ”

“እዎ እዎ አስታውስሃለሁ፡፡ እንደምንድነህ? ደህና ነህ? ምነው
ጠፋህ? ርብቃ በጣም አስባለች፡፡ ለምን ብቅ አትልም? ”

“እ..” ናትናኤል አመነታ፡፡ “ምን መሰለህ ብስራት መምጣት እንኳን አልችልም፡፡ ግን እሷ እንዴት ነች?”

“አሟታል…በጣም ነው የታመመችው ሐኪም ቤት እያመላለስናት ነው::”

“ምን አሉ ሐኪሞቹ? ማለቴ ምንድነው?” ናትናኤል በልቡ የሚንቀዋለለውን ለመጠየቅ ጭንቅ አለው::

“አላወቁላትም፡፡ ግን ምግብ አይበላላትም፤ ስትበላም አይረጋላትም፡፡
ሰውነቷ ላይ ግን ችግር የለባትም፡፡ 'ጭንቀት ነው' ነው የሚሉት ሐኪሞች፡፡
ምን እንደሚያስጨንቃት ግን ሊገባን ኣልቻለም፡፡ በጣም ደክማለች::
ናትናኤል መጥተህ ብታያት ጥሩ ነበር:: በእንቅልፍ ልቧ ሁሉ ስምህን
ትጠራላች፤ ከቀን ወደቀን እየባሰባት ነው፡፡” ናትናኤል በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ እጁን ግንባሩ ላይ ጫነ፡፡ ከራሱ ጋር ክርክር ገጠመ:: የፈለገው ይምጣ ሄዶ ያያታል፡፡ መቼም በቤቷ አካባቢ ሊያንዣብቡ ይችሉ ይሆናል፡፡ ግን ምርጫ የለውም:: ሹልክ ብሎ ገብቶ ሹልክ ብሎ ይወጣል ወሰነ::

“ብስራት መደወሌን ለማንም አትናገር ዛሬ ማታ መጥቼ አያታለሁ እሺ? ልክ ከምሽቱ አስራ ሁለት ተኩል ሲሆን ውጭ በሩጋ ጠብቀኝ” ናትናኤል ስልኩን ከዘጋ በኋላ በግራው ያንጠለጠለውን ትንሽ የሽራ
ሻንጣ ይዞ እዚያው ለገሃር ኣቅራቢያ ወዳለ አነስተኛ ቡና ቤት ተመልሶ ገባ፡፡
ጥግ ወዳለ ወንበር ሄዶ ሰውነቱን ለማርገብ፣ ለማረጋጋት በዝምታ
ተቀመጠ፡፡ በግራሶና ዘይት የተጨማለቀ ሰማያዊ ቱታ ለብሷል። ጭንቅላቱ
ላይ ያጠለቀው ዙሪያው እንደጠወለገ ቅጠል የተልፈሰፈሰው ባርኔጣ በግንባሩ
ላይ ኣዝምሞ ፊቱን ሸፍኖታል፡፡ ከደረት ኪሱ ሲጋራ አውጥቶ ከሚንቀጠቀጥ እጁ ጋር እየታገለ ከለኮሳት በኋላ ክብሪቱን እያጠፋ ሲጋራዋን ምጥጥ አደረጋት፡: “ርብቃ... ርብቃ.… ምነው አጠገብሽ መሆን ብችል!”

“ምን ልታዘዝ::” አለችው ሰማያዊ ሽርጥ ወገቧ ላይ ሸብ ያደረጎች አስተናጋጅ የለበሰውን ቆሻሻ ቱታ ስታይ ድምጿን ቆጥብን አድርጋ::

“ቡና፡፡” አላት ቀና ብሎ አያቷት የዋጠውን የሲጋራ ጭስ ቀረጁሙ እየለቀቀ፡፡

“ሂሣብ በቅድሚያ ነው የሚከፈለው፡፡” አለች ሁለት እጆቿን በጎንና ጎን የሽርጥ ክሶች ውስጥ እየወሸቀች፡፡

ከቀኝ ኪሱ ውስጥ ሣንቲሞች አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ በተን እደረገላት፡፡ ሃሳቡ ግን ሌላ ቦታ ነበር፡፡ ርብቃ ለምን ደበቀችው? «ወይስ ወሯ ገና ነው ማለት ነው ሊሆን አይችልም:: ደብቃው ነው፡፡ ግን ለምን.… ለምን?

የሚወደው ገጿ መጥቶ ፊቱ ላይ ድቅን አለበት፡፡ ርብቃ'ኮ እርጉዝ ነች የምህረት ድምፅ እቃጨለበት፤ አሟታል ምግብ አይበላላትም ብትበላም አይረጋላትም “ጭንቀት ነው" ነው የሚሉት ሐኪሞቹ….
የብስራት ድምፅ ደወለበት...

“አምላከኔ ምን ዓይነት ጉድ ወስጥ ነው የከተትከኝ ኣለ እምላከ ከፊት ለፊቱ ባለ ወንበር ላይ የተቀመጠ ይመስል ፊት ለፊት አፍጥጦ፡፡

ምንድነው ሊያደርግ የሚችለው? ቀጥ ብሎ ፖሊስጋ ሄዶ እጁን መስጠት፡፡ ቢገሉትስ? ይግደሉት፡፡ ከዚህ በላይ ስቃይ መሸከም አይችልም ግን ለፖሊሶችስ ምን ሆንኩ ብሎ እጁን ይሰጣል? ሁሉን ነዋ!.. የሆነውን
ሁሉ ዘርዝሮ ማውጣት ነዋ! ግን ማን ያዳምጠዋል? ማን ያምነዋል? ፍጹም!
ፖሊስ ወጥመድ ነው! እጁን መስጠት ማለት ሞቱን ማፋጠን ማለት ነው፡፡
ለማን ይበጃል መሞቱ? ለርብቃ? ስልጁ? የአብርሃም መሞት ማንን ጠቀመ?
መረጋጋት ነው ያለበት፡፡ ካሁን ወዲያ ወደኋላ ማለት አይችልም፤ መረጋጋት
ነው ያለበት፡፡

ከቁጥጥር ውጭ በሚንቀጠቀጥ ቀኝ እጁ የያዛትን ያለቀች ሲጋራ ለመጨረሻ ጊዜ መጠጣትና ከፊት ለፊቱ ጠረጴዛ ላደ በተቀመጠው የሲጋራ መተርኮሻ ውስጥ ደፈጠጣት፡፡ መረጋጋት…. መረጋጋት ነው ያለበት...

የቡና ቤቱ አስተናጋጅ ያዘዛትን ቡና አምጥታ እፊቱ ደነቀረችለት::
አንስቶ ፉት ኣላው፡፡ ስኳር አልነበረውም:: ክፉኛ መረረው፡፡ ቢሆንም ስኳር
አልጠየቃትም፡፡ ድጋሚ ፉት ኣለው፡፡ ትኩስ ቡና በጉሮሮው አልፎ በሆዱ
ሲተራመስ ስንዝር በስንዝር ተከታትለው:: ሆዱ ጩርርርር ሲል ተሰማው:: ትላንት ምሳ የበላ ነው፡፡ ቢሆንም ምግብ አላሰኘውም:: ከቡናው ድጋሚ ፉት አለለት፡፡ ሰውነቱን ማዝናናት አለበት፤ ማረጋጋት አለበት፡፡በተቀመጠበት ወንበር ላይ በደኋላ ጋለል ብሎ ዓያኖቹን ጨፈናቸው፡፡ ቀኝ እጁ ከደረት ኪሱ ገብቶ ሲጋራና ክብሪት ይዞ ተመለሰ፡፡ ርብቃ ለምን ደበቀችው? በቃ በቃ... ስለርብቃ
👍2
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....ናትናኤል ለጥያቄው መልስ ሲያገኝ ይበልጥ ተበሳጨ፡፡ ለዚህ ቀላል ጥያቄ፣ ለዚህ ቀላል መልስ ይህን ያህል ከተቸገረ እንግዲያው ማስተዋል ቀንሷል ማለት ነው ከሚገባው በላይ ተወናብዷል ማለት ነው፡፡ ፈርቷል ማለት ነው፡፡

እራሱን ገሰጸወ፡፡

ረጋ ማለት አለበት፡፡ አለበለዚያ በማይረባ ስህተት እራሱን አጋልጦ ይሰጣል፡፡

ስሟን እስካወቀ፤ የስልክ ቁጥሯን እስካወቀ፤ የአባቷንና የአያቷን ስም ከማንኛውም የስልክ ደብተር ላይ በቀላሉ ያገኘዋል፡፡

ሌሊቱን በሙሉ በሃሳብ ሲታመስ ሳያሸልበው ፀሐይ ሥፍራዋን
ተረከበች::

ናትናኤል ከአልጋው ተነስቶ ማታ አለቅልቆና በእርጥብ መሃረቡ
ጠራርጎ ከግርጌ ካለ ወንበር ላይ ያሰጣቸውን ሸሚዙንና ኮቱን አንስቶ
ለባበሰና ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ፡፡ በተቻለው መጠን ረጋ ብሎ ተጣጥቦ
ያለፈውን ሌሊት አሻራ ሙልጭ አድርጎ ካፀዳ በኋላ ወደ ሆቴሉ አዳራሽ ብቅ
አለ፡፡

ጥግ ላይ ተቀምጦ ሁለት ስኒ ቡና ጠጣና ፈጠን ብሎ ከሆቴሉ ወጣ፡፡ ሌላቱን ያለእንቅልፍ ቢያሳልፈውም የድካም ስሜት አልተሰማውም፡፡ምናልባት ድንጋጤው ይሆናል፧ ምናልባት ፍርሃት፣ ምናልባት ሥጋት፡፡

ደሙ በሰውነቱ ውስጥ ሲሽቀዳደምና ሲራወጥ ለራሱ ይሰማዋል፡፡ መፍጠኝና
መሮጥ አለበት!

ታክሲ ተሳፈረና ወደ መርካቶ ሸሸ፡፡

መርካቶ ባህር ነው ውቅያኖስ፤ መርካቶ ጫካ ነው ደን፡፡መርካቶ ቤቱ ነው የዘውድዬ፡፡


መሀል መርካቶ ከታክሲ እንደወረደ ወደ አንድ ቡና ቤት ገባ፡፡ገንዘብ ተቀባይዋን ተጠግቶ ሠላምታ ከሰጣት በኋሳ የስልክ ማውጫ ጠየቃት፡፡

“ጩኒ ቁልፍ፡፡” አለች ረጅም ወንበር ላይ የተቀመጠችው ወጣት ሴት ወደኋላ ዞራ፡፡
“ በእድሜ የሚመጣጠናት ወንድ ልጅ በቀጭን ሰንሰለት ውስጥ የተሰገሰጉ አስር የሚሆን ቁልፎች አቀበላት፡፡ ከቁልፎቹ ውስጥ አንዷን መርጣ አወጣችና አጠገቧ ያለ መሳቢያ ስባ የስልኩን ደብተር አውጥታ
አቀበለችው::

"እግዜር ይስጥልኝ” አላት ማውጫውን ተቀብሏት እየከፈተው፡፡

'የምሥራች ይልማ መጀመሪያ የምሥራችን ስም ፈለገ፡፡ በርካታ የምሥራች ይልማዎች የተደረደሩትን ገፅ እንዳገኘ የስልክ ቁጥሯን ፈለገው:: ቁጥሩን እንዳገኘ ወደኋላ ተመልሶ በትይዩ የተፃፈውን የምሥራችን ስም እስከ አያቷ ስም አነበበው የምሥራች ይልማ ገዛኽኝ::
“እቶ ይልማ ገዛኸኝ ድጋሚ የስልክ ማውጫውን እያገለባበጠ
ይፈልግ ጀመር አቶ ያልማ ገዛኸኝ... ይ.… ይ. ይ.. ያልማ አዳሙ... ይልማ መብራቱ
ይልማ ገብረማርያም…ያልማ ገዛኽኝ
የስልክ ቁጥሩን በወረቀት ላይ ገለበጠና የቡና ቤቱን ገንዘብ ተቀባይ አመስግኖ ወጣ፡፡ እዚያው አካባቢ የሕዝብ ስልክ ፈልጎ ኣቶ ይልማ ገዛኸኝ መኖሪያ ቤት ደወለ፡፡“

ከቤት” አለው ቀጠን ያለ የሴት ድምፅ፡፡
“እባኮት አቶ ይልማን ነበር”
“ሥራ ናቸው” አለች ሴትየዋ በተሰላቸ ድምዕ::
“እባኮት ችግር ገጥሞኝ ነው የሥራ ቦታቸውን ስልክ ቢሰጡኝ፡፡

“የሱቁን ነው?”
“አዎ ላገኛቸው የምችልበትን ቦታ፡፡”

ነገረችው:: ቀልጠፍ ብሎ ቁጥሩን ጻፍ ጻፍ አደረገና አመስግኗት ስልኩን ዘጋ:: ወዲያው የሰጠችውን ቁጥር ደወለ፡፡

ሃሎ” አለ ውፍረት የደፈነወ፣ ስጋ የዘጋው፣ እርስ በእርስ የሚተሻሽ ድምፅ::

“እባኮት አቶ ያልማ ይኖራሉ?”
“ነኝ:: ማን ልበል?”
“እንደምን ዋላ፡፡ የምሥራች ነበረች የላከችኝ..." ናትናኤል የሰውየውን ስሜት ለማጥናት ለአንድ አፍታ ዝም አለ፡፡

“ማን አሉኝ?” አለ ሰውየው መልሰው፡፡
“የምሥራች… የምሥራች ይልማ፡፡”
“ከየት ነው? ማንን ነው የሚፈልጉት?” ሰውየው ግራ የተጋቡ መሰሉ፡፡
“የምሥራች... የምሥራች የእርሶ ልጅ::”
“የማን ልጅ? ” ሰውየው ያበልጥ ተደነጋገራቸው፡፡
““ካዛንቺስ ሆቴል ያላት የእርሶ ልጅ::የምሥራች ይልማ ባለሆቴሏ...

“የምን ሆቴል ነው የሚሉኝ?”
ይቐርታ ጠይቋቸው ስልኩን ዘጋ፡፡

ሌላ ይልማ ገዛኽኝ በአዲስ አበባ ስልክ ማውጫ ደብተር ውስጥ የተመዘገበ የለም፡፡ ያለው አማራጭ ወደ ድሬዳዋ መንጎድ ብቻ ነው፡፡ድሬዳዋን አያውቃትም:: እዚያም ሄዶ መቸገሩ የማይቀር ነው፡፡ ግን የተሻለ
ምርጫ የለም::

መፍጠን አለበት፡፡ ምንም ጠባብ ቢሆን በተከፈተለት በር ሁሉ መሮጥ አለበት፡፡

ወደ ካልቨርት መጠጋት አለበት::
ዝግጅቱን ለማጠናቀቅ ወደ ባቡር ጣቢያ ሄዶ በማግስቱ ምሽት ላይ ወደ ድሬዳዋ በሚሄድ ባቡር ላይ የሁለተኛ ማዕረግ ትኬት ከቆረጠ በኋላ አውቶቡስ ተራ ወደ ዘውዲቱ ቤት ወደ ጎሬው በረረ፡፡

ምሳውን ከዘውዲቱ ጋር ከበላ በኋላ አሰዓት ወደ ገበያ ወጣ፡፡መርካቶ የዘመን መለወጫ በዓልን መስከረም አንድን ለመቀበል በሚዘገጃጅ ገብያተኛ ተጣባለች፡፡

ወደ ድሬዳዋ ሲሄድ ሊለብስ ያሰበውን ጀለቢያና ሽርጥ ነጠላ ጫማ እንዲሁም አንድ አነስተኛ የሸራ ሻንጣ ገዛ፡፡ አዲስ አበባ እስካለ ድረስ ደግሞ አጥልቆት የሚዘዋወረውን ወራጅ የጋራዥ ቱታና ፊቱን ጥሩ እድርጋ የምትሸፍንለት አንድ የተልፈሰፈሰች ባርኔጣ ጨመረ፡፡መንገድ ላይ ከኣንድ ጋራዥ ገባ ብሎ ለዘበኛወ ሁለት ብር ሰጠና በትንሽ ቆርቆሮ የተቃጠለ ዘያት ይዞ ወደ ጎሬው ሲመለስ ከእንድ ሱቅ ጎብቶ አንድ ጥሩ ሽቶና የሴት
ነጠላ ጫማ ሾመተ:: ከዘውዲቱ ቤት ሲደርስ ባይመሽም ቀኑ ገፍቶ ነበር።
ልብሱን አወላልቆ ዘወዲቱ እልጋ ወስጥ ገብቶ ጥቅልል አለ፡፡ የዘውዲቱን ቤት ተከራይቶ ከገባ ጀምር ለመጀመሪያ ጊዜ ዘውዲቱ፡ አብሯት የሚያድር ደንበኛ አጥታ እንድትመጣ ተመኘ፡፡

ያን ሌሊት በውዲቱ ቀንቷት ደንበኛ አገኘች አልተመለሰችም፡፡አልጋዊ ላይ ብቻዉን ሲገላበጥ ሲያቃዠው አደረ፡፡አንዱን ቅዠት ሳያገባድድ ሌላ ቅዠት እያቋረጠው ያባረረው ውሻ ሳያዘው ጭልጥ ካለ ገደል እየገባ ከገደሉ ወለል ደርሶ አናቱ እንደ እንቁላል ሳይፈርጥ አየር ላይ ጭልፊቶች
ገላውን እየገመጡ አይኖቹን እየጓጎጡት ሲወራጭ አደረ፡፡

ጠዋት በሩ ሲከፈት በርግጎ ሲነሳ ጭንቅላቱን በፋስ ሲወቅረው ተሰማው እራስ ምታት ነፍስ ዘርቶ፡፡

“እንደምን አደርክ?” አለችው ዘውዲቱ ወደ ውስጥ ገብታ በሩን እየዘጋች፡፡ እስካሁን አልተነሳህም? ሁለት ሰዓት አልፏልኮ::” የያዘችውን የላስቲክ ከረጢት ወንበር ላይ ጣል ኣድርጋ ኣልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለችና ኩንታል ስትሸከም እንዳደረች “
ኡፍ.....ፍ፡!” አለች፡፡ “እንዴ ለምን እራትህን ሳትበላ አደርክ?” አለች ሳይከፈት ያደረውን የምግብ ሳህን ከራስጌ ስታይ ዞራ እየተመለከተችው::

“አላየሁትም ነበር፡፡” አላት ናትናኤል እራቁት ደረቱን እያከከ ዞር ከራስጌ የተቀመጠውን ሳህን እየተመለከተ::

“እና ጾምን አደርክ ማለት ነው? ደግሞ ከትላንት ወዲያ የት ነበር ያደርከው?” ጥያቄ አከታተለችበት፡፡

ሳይመልስላት ከአልጋው ተነስቶ ከወገቡ በላይ ለመለቃለቅ በሩን ከፍቶ ወጣ፡፡ ሰወነቱን ተለቃልቆ ሲመለስ ዘውዲቱ ከራስጌ ያደረውን ሳህን ከፍታ በግራ እጇ ይዛ እየተንጎራደደች በላይ በላዩ ስትጎርስ አገኛት::

“ቡዳ የሆነ ሰውዬ ራቴን ሳያበላኝ ቤቱ ወስዶ እንደቅሪላ ሲያለፋኝ አደረ::” አለች እየሳቀች፡፡ “ላጉርስህ? ”
ራሱን ነቀነቀ፡፡ ናትናኤል ምግብ አላሰኘውም፡፡
“ምን ሆነሃል? ቤት ደህና አይደሉም እንዴ? ”
“ደህና ናቸው እነሱስ...” የጀመረውን አንጠልጥሎ ተወው፡፡
“ታዲያ ምን ሆነሃል? "
“ሰውየው ተያዘ::”

የቱ ሰውዬ?” መንጎራደዷን አቁማ በተቀመጠበት ቁልቁል ተመለከተችው፡፡

“አለቃዬ። የመሥሪያ ቤታችንን ገንዘህ ያጠፋው፡፡”

“አትለኝም!” የያዘችውን የምግብ ሳህን ከራስጌ አስቀምጣ በወጥ የተጨማለቀ እጇን አንከርፋ ኣልጋው ላይ ከጎኑ
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....እንደ ድንጋይ ከተጫናት ሰመመን ውስጥ ቀስ በቀስ እየወጣች ስትመጣ… እላይዋ ላይ ተጭኖ የያዛት ድቅድቅ ጨለማ እንደ ጭስ እየሳሳ እየበነነ ለቋት ሲጠፋ በመጀመሪያ የተቀበላት በእግሮቿ መሃል የሚነዝራት የደነዘዘ ስቃይ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ጭንቅላቷ እየጠራ ሲመጣም አይኖቿን ለመክፈት አልደፈረችም፡፡ ሌላ ዱላ፣ ሌላ ስቃይ ሌላ የጋለ ሽቦ የሚችል
አካል አልነበራትም። በክፍሉ ውስጥ ብቻዋን ትሁን አትሁን እርግጠኛ
አልነበረችም፡፡ አይኖቿን ለመክፈት ግን አልደፈረችም፡፡

እጆቿ ግራና ቀኝ ተወጥረው ከታሰሩሰት ተፈተው በድን እንደሆኑ ሁሉ በግራና በቀኝ ተዘርረዋል፡፡ በተኛችበት ልብስ ደርበውላታል፡፡ እግሮቿ ግን አሁንም ግራና ቀኝ ሁለት ቦታ ተወጥረው እንደታሰሩ ናቸው፡፡ ቁስሏን ለማዳመጥ ሞከረች፡፡ በጭኖቿ መሃል የሚሰማትን ስቃይ ለማዳመጥ ዝም አለች የተዳፈነ... የደነዘ… የደበዘዘ ስቃይ፡፡ ግራ ክንዷ ላይ ህመም ተሰማት:: ለመነቃነቅ ግን አልደፈረችም፡፡ በአይነ ህሊናዋ ሁኔታውን
ለመቅረፅ ሞከረች። መቼ ነበር በጋለ ሽቦ ጭኖቿ መሃል ሰውነቷን ያቃጠሏት? ዛሬ? ትላንት? ዛሬ ምንድነው? ቀን ነው ሌሊት? ሰዓታትና ቀናት ትርጉም ካጡባት ቆይተዋል፡፡

ድምፅ የሰማች መስላት። ዓይኖቿን እንደከደነች ጆሮዎቿን ኣስልታ ተጠባበቀች፡፡ የበር ድምፅ ተሰማት… የሚከፈት የበር የሚያሰማው ድምፅ..

“አልተነሳችም፡፡” አለ አንድ ድምፅ በሹክሹክታ፡፡

“ኮለኔል” አለ አንድ ድምፅ በሹክሹክታ “ዙርያውን አጥረነዋል።በርም ላይ አንድ ሰው አቁመን እየተጠባበቅን ነው::”

“መጣሁ” ሲል ተሰማት ማርቆስ፡፡

ሁለት የእግር ኮቴዎች በግራና በቀኟ ተስሟት…በስተቀኝ ኣንድ መዳፍ ግንባሯ ላይ አረፈ::

“ከነቃች የመርፌ ማደንዘዣውን ስጣትስቃይ ሊኖርባት ይችላል።” የማርቆስ ድምፅ ነበር።

“ካስቸገረችኝስ ልምታት?” አለ በስተግራዋ የቆመ ሌላ ሰው፡፡

“ረጋ ብለህ አባብለህ ውጋት። ለምን ትመታታለህ? ደግሞ አታስቸግርህም.. ከተወራጨችብህ ግን ግሉኮሱን ንቀልላት፡፡” አለ እጁን ግንባሯ ላይ የጫነው ማርቆስ በጣቶቹ ፀጉሯን ወደኋላ እያበጠረ፡፡ “ጠዋት እቀየርልሃለሁ፡፡”

ኮቴ ተሰማት፡፡ ተከታትለው ሲወጡ ሰማች። በሩ ሲዘጋ በክፍሉ ውስጥ ፀጥታ ሲነግስ ስትፈራ ስትቸር አይኖቿን ገለጠቻቸው::መኝታ ክፍሏ ውስጥ ብቻዋን አስተኝተዋታል፡፡ በቢጫው የብርድ ልብሷ ከአንገቷ እስከ
እግሯ ጫፍ ድረስ ሸፍነዋታል፡፡ በተንጋለለችበት ዙሪያዋን ተመለከተች፡፡
ግራ ክንዷ ላይ የሚሰማት ህመም ከራስጌዋ ከተንጠለጠለው የግሉኮስ
ከረጢት ጋር የተያያዘው መርፌ ክንዷን ጠልቆ የገባበት ላይ መሆኑን ተረዳች። የክፍሉ መጋረጃ ተዘግቷል፡፡ በጥግና ጥግ የታየው ሰማይ ጨልሟል... መሽቷል፡፡ ሰመነቃነቅ ስትሞክር ግራና ቀኝ የታሰሩት እግሮቿ መሃል የተዳፈነው ስቃይ እንደ ጦር ወጋት፡፡ ከስሱ የብርድ ልብስ በታች ያለው እራቁት ሰውነቷ ተንሰፈሰፈ፡፡

ድምፅ ተሰማት የመኝታ ቤቷ በር ተከፈተ፡፡ ቶሎ ዓይኖቿን ጨፈነቻቸው፡፡ : እንደነቃች ማወቅ የለባቸውም፡፡ ዝም ብላ መተኛት ነው ያለባት፡፡ መረበሽ የለባትም! አለበለዚያ ይመቷታል፡፡ ዝም ብላ መተኛት። በሩ ሲዘጋ ተሰማት: የእግር ኮቴ እየቀረባት መጣ. አንድ በላብ የረጠበ እጅ
እራቁት ትከሻዋ ላይ ሲያርፍ ተሰማት… ትንፋሼ እላይ እታች የሚል ትንፋሽ እላይዋ ላይ የነበረው ስስ የብርድልብስ ፡ ተገፈፈ፡ መረበሽ የለባትም… መንቃቷን ማወቅ የለባቸውም... አለበለዚያ ድጋሚ
ያስቃይዋታል. , ትከሻዋ ላይ ያረፈው በላብ የራሰ መዳፍ ወደታች ወደ
ደረቷ ተንሸራተት…. እልተንቀሳቀሰችም ጡቶቿ ሲዳስሱ ተሰማት እላይ እታች የሚል ትንፋሽ… ፍርሃት ወረራ ግራ ክንዷ ላይ የተሰካውን መርፌ አስሮ የያዘው ፕላስተር ተላጠ.. ክንዷ ላይ የተሰካው መርፌ ተነቀለ መንቃቷን ማወቅ የለባቸውም… አለበለዚያ ይመቷታል... እላይ እታች የሚለው ትንፋሽ ቀረባት፡፡ ብርድ ልብሷ ወደታች ተጎተተ ፍርሃቷ
እየጨመረ መጣ እላይ እታች የሚለው ትንፋሽ ወደ አንገቷ ስር ሲጠጋ ተሰማት.. ብርድ ልብሱ ከላይዋ ላይ ተንሸራቶ ወደ መሬት ወደቀ፡፡ ራሷን መቆጣጠር አቃታት… አይኖቿን ገለጠቻቸው፡፡

ጺማሙ ሰውዬ ነበር፡፡ እላይዋ ላይ እንዳንገርበበ ድንገት አይኖቿን ስትገልጥ ደንገጥ አለ፡፡ ወዲያው ፈገግ አለላት... የሸሚዙን ቁልፎች መፍታት ጀመረ… ፈገግ አለላት ድጋሚ… ሸሚዙን ከላዩ ላይ ወርውሮ ተጠጋት… እጆቹን ጡቶቿ ላይ ጫናቅው ድንገት ተወራጨች፡፡ ሙቅ
እርጥብ እጆቹን ከላይዋ ላይ ገፍትራ ተሸማቀቀች ፈገግ አለላት፡፡ አልጋዋ
ላይ የተንጋለለውን እራቁት ገላዋን ከላይ እስከታች በተራሱ ኣይኖቹ ዳሰሰው፡፡ ምራቁን ሲውጥ ትልቅ ማንቁርቱ እላይ እታች ሲመላለስ በፍርሃት ተንቀጠቀጠች፡፡ ድንገት ዘሉ አፏን በመዳፉ ኣፈናት… ታገለችው…
እጆቿን እያፈራረቀች እንደብረት የደደሩ ሁለት ክንዶቹን ደበደበቻቸው
ቧጠጠቻቸው... ያለብዙ ችግር እፏ ውስጥ ጨርቅ ጎስጉሶ ለጎማት

ትንፍስ ትንፍስ እያለ ቁልቁል ተመለከታት፡፡ አይኖቹ የሚያርፉበት
ቦታ ያጠ ይመስላል፡፡ መላ ሰውነቷ ላይ ተንቀዠቀዡ።

ሱሪውን ማውለቅ ጀመሬ በተንጋለለችበት በምሬት… ጭንቅላቷን አወራጨችው… እንባዋ ደረሰላት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ቢሮው ትዕግስቱ አልቋል፡፡” አለ ከቴልአቪቭ የገባው ይሁዳ አሚ
የብርቱካን ጭማቂውን ተጎንጭቶ ብርጭቆውን ካስቀመጠ ሰኋላ ረጅም
ጺሙን እየዳሰሰ፡፡

የአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴልኝ የመዋኛ ስፍራ በስተቀኛቸው አድርገው ተቀምጠዋል፡፡ በርካታ እንግዶች በመዋኛ ልብሶቻቸው ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡ የተቀሩት በደረትና በጀርባቸው እየተገላበጡ ጭል ጭል የምትለውን ለስላሳ የጳጉሜ ፀሐይ ይሻማሉ፡፡

ይሁዳ አሚ በሆቴሉ ውስጥ ከያዘው የመኝታ ክፍል ወጥቶ ከቀጠሮኣቸው ስፍራ የደረሰው ልክ በሰዓቱ ነበር። ከቀጠሮው ሰዓት ቀደም ብሎ የደረሰው አሃሮን የእንግዳውን ፀባይ ስለሚያውቅ የብርቱካን ጭማቂ አዝዞ ከፊት ለፊቱ አስቀምጦ ይጠባበቅ ጀመር፡፡ አሚ የሌሊት ልብሱን ሳይቀይር በላዩ ላይ ወፍራም የጠዋት ልብሱን ደርቦ ወገቡ ላይ ቀበቶውን ሽብ አድርጎ ከጥጥ የተሰራ ወፍራም የእግር ሹራብና የቤት ነጠላ ጫማዐእንዳደረገ ወደ መዋኛው ስፍራ የሚወስደውን ደረጃ በእርጋታ ወርዶ ወደዐአሃሮን አመራ፡፡

“እንኳን ደህና መጣህ፡፡” አለ አሃሮን ተነስቶ እንደቆመ የአሚን እጅ
ጠበቅ አድርጎ እየጨበጠ፡፡

“እንኳን ደህና ጠበቅኸኝ።” አለ አሚ ነጫጭ ውብ ጥርሶቹን ለአንድ አፍታ ብልጭ አድርጎ የጓደኛውን እጅ እየወዘወዘ፡፡

አሚ “ ኪዶን” በሚል ስያሜ በሚታወቀው የሞሳድ ገዳይና አፋኝ
ክፍል ውስጥ ለአስራ ሰባት ዓመታት የሰራና አትግደል እና አትዋሽ
ከሚሉት ከሙሴ ትዕዛዛት በስተቀር በተቅሩት በስምንቱ ትዕዛዛት ላይ ፌዝ
የማያውቅ ጥብቅ ሃይማኖተኛ አይሁዳዊ ነው። በሌሊት ልብሱ ላይ የደረበው
ወፍራም የጠዋት ልብስና ቡፍ ካለ ጥጥ መሳይ የቤት ጫማው ጋር ሲያዩት
ጺማሙ ሰው በቤት ውስጥ ተቀምጦ የሳጠራ ዘንቢሉችን ሲሰራ የሚውል
የዋህ በሬ ይመስላል፡፡

“የብርቱካን ጭማቂ፡፡” አለ አሚ ፈገግ ብሉ ከጎኑ የቆመውን የሆቴሉን አስተናጋጅ እየተመለከተ፡፡

የአልኮል መጠጥ ፍጹም የማይቀምስና የአሳማ ስጋ አፉ የማይገባ ጥብቅ ሃይማኖተኛ የሆነው አሚ በመስከረም 5 1972 በሙኒክ ሃያኛው ኦሎምፒክ ዝግጅት ላይ የብላክ ሴፕቴምበር ቡድን የእሥራኤል ስፖርተኞችን ሰፈር በመውረር አስራ አንድ ተጨዋቾችን ከገደለ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ጎልዳሜይርን የብቀላ ትዕዛዝ
👍2
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....አፓርትመንቷ ጋ ከመድረሱ በፊት ወደ ግራ እጥፍ ብሎ ከአንድ ትንሽ ሻይ ቤት ገባና በሩ አጠገብ ካለ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሻይ አዘዘ፡፡ ጥንቃቄ ያስፈልጋል እርጋታ፡፡ ባሻገር የሚታየው የአፓርትመንቱ ቅጥር ግቢ አለቅጥ ጭር ብሏል፡፡ የወትሮው ግርግር ወጪና ገቢ አይታይም፡፡ ከአፓርትመንቱ ስር መኪናዎች በስርኣት ተደርድረው ቆመዋል፡፡ ለወትሮው ሲሯሯጠ የሚታዩ ሲጫወቱ የሚገኙ የአፓርትመንቱ ነዋሪዎች ልጆች በግቢው አይታዩም፡፡በር ላይ ብቻ እኛው የድሮው ሽማግሌ ዘበኛ አፈርማ ካፖርታቸውን ደርበው ከዘበኛዋ ቤት ደጃፍ ላይ ቁጭ ብለው ያንጎላጃሉ፡፡

ይህ ነው ብሎ ምክንያት ሳይሰጠውም ፍርሃት ገባው፡፡ ፀጥታ ተራ ነገር አይደለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሙሉ ፀጥታ አደጋ ከመድረሱ በፊት የሚያንዣብብ ማዘናጊያና አደጋው ከደረሰ በኋላ ድንጋጤን ደርቦ የሚንጠለጠል ግግርት ነው፡፡ ጥፍሩን መቆረጣጠም ጀመረ። ጭንቅላቱ ግራና ቀኝ ቆሞ ይሟገት ጀመር፡፡

ሰዓቱን ተመለከተ አሥራ ሁለት ከሃያ፡፡

ዝም ብዬ ነውኮ ይልቅ ብሎ ገብቼ እይቻት ብወጣ ይሻላል...ግን በአካባቢው የአውሬው አይን ቢኖርስ ስገባ ቢያየኝስ?ወዲያው ቢከቡኝስ ታዲያ እስከመቼ እዚህ ተቀምጨ እቆያለሁ?! ስልክ ደውዩ
ወንድሟን «ውጣ» ብለውስ ከአፓርትመንቱ እራቅ እንዲል ነግሬው
ባነጋግረውስ ምን ዋጋ አለው? ገብቼ ካላየኋትማ ለምንስ መጣሁ? ብገባ
ይሻላል... አዎ አይቻት ቶሉ እወጣለሁ… በአካባቢው ካሉ ግን ያለጥርጥር
እንደ ጅግራ ነው ክንፌን ብለው የሚጥሉኝ…ምን ዘዴ መፍጠር ይሻላል?

ጭንቅላቱን አፋጨው፡፡ አካባቢው እየጨለመ መጣ፡፡ የመንገድ
መብራቶች ቦግ ቦግ ቢሉም ደቂቃዎች በሄዱ ቁጥር ይበልጥ የሚደምቀውን
ጨለማ መታገል ማሸነፍ መግፈፍ እያቃታቸው መጠ፡፡ ናትናኤል ያለበትን
ክፍል ቃኘው፡፡ ትንሿ የሻይ ቤት ንጽህና የሌላት ናት፡፡ . በውስጧ የተሰበሰቡትም ሰዎች እሱው?እንዳጠለቀው በህይት የተጨማለቀ የጋራዥ ቱታ ቆሻሻ ልብስ የለበሱ ቀዝቅተኛ ኑሮ የሚገፉ፤ የሚጎትቱ እንደሆነ “ ያስታውቃሉ፡፡ ሰዓቱን ድጋሚ ተመለከተ፡፡ አስራ ሁለት ተኩል፡፡
በተቀመጠበት እንዳለ አሻግሮ የአፓርትመቱን መግቢያ በር ቃኘው፡፡ በሩቅ በድንግዝግዝ አንድ ሰው ይታየዋል፡፡ የበሩን አንድ ወገን መቃን ተደግፎ ቆሟል ሰውየወ:: ናትናኤል አትካር ተመለከተው፤ ካፖርት ለብሶ
አንገተዬውን ቀልብሶ የቆመውን ሰው ግን ሊለየው አልቻለም፡፡

'ብስራት ይሆን? መሆን አለበት። አሰበ፡፡
ተነስቶ ወደ አፓርትመንቱ መሄድ ግን ፈራ፡፡ ድጋሚ ዞር አለና እሱ ከተቀመጠበት ስፍራ ፈንጠር ብሎ ሁለት ክንዶቹን ጠረጴዛ ላይ ተክሎ
ጉንጭጮቹን በሁለት መዳፎቹ ደግፎ የተቀመጠ ጎረምሳ ላይ አተኮረ፡፡ አንድ
ዘዴ መጣለት:: ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ ወጣቱ ተጠጋ፡፡

“ሰላም...ልቀመጥ?” አለ ከወጣቱ ጠረጴዛ ዙሪያ ከተደረደሩት ሦስት
ወንበሮች አንዱን ያዝ ኣድርጎ፡፡

ወጣቱ ጉንጮቹን ዘሁለት መዳፎቹ ውስጥ ሳያወጣ አይኑን ብቻ
አቅንቶ ተመለከተው::

“ተቀመጥ:: አለ ወጣቱ ግድ እንደሌለው ለማሳየት ትከሻውን ከፍ ዝቅ አድርጎ፡፡

“እንድ የምትሰራልኝ ስራ ነበር፡፡ በቂ ገንዘብ እከፍልሃለሁ፡፡” አለ ናትናኤል ከኪሱ ቦርሳወን አውጥቶ ሁለት የአስር ብር ኖቶች እየመዘዘ፡፡

ከፊት ለፊቱ የተቀመጠው ወጣት ቀያዮቹን ኖቶች ሲመለከት ጉንጮቹን ለቀቅ አደረገና ቀና አለ፡፡ የደረበው ረጅም አሮጌ ኮት አንገትዬው ነትቧል፤ ከውስጥ ሸሚዞ በሽቅጧል፡፡

“ትስማማለህ?”
“ምንድነው የምሰራልህ? የሚደበደብ ሰው ከሆነ እርሳው፡፡” አለ ወጣቱ አገጩ ላይ ችፍርግ ብሎ የበቀለውን የቆሽሽ ጺም እያከከ፡፡

“አይደለም፡፡” አለ ናትናኤል ወደፊት ጠጋ ብሎ “እየው ያ ፎቅ ይታይሃል? በሩ ላይ የቆመው ሰውዬ ይታይሃል?”
ወጣቱ በ'አዎንታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ፡፡

“…ቀጥ ብለህ ወደ ሰውየው ትሄድና አጠገቡ ልትደርስ ጥቂት
እርምጃዎች ሲቀርህ ናትናኤል ይፈልግሃል። ተከተለኝ በለውና ድንገት
ፊትህን መልሰህ እየሮጥክ ከግቢው ወጥተህ ትመጣለህ፡፡”

“እናስ.. ከዛ በኋላስ?”
“በቃ::”
“እንዴት በቃ? እለ ወጣቱ ፊቱ ጥርጣሬ ለብሶ:: “እዛች ደርሼ ስለተመለስኩ ነው ይህን የምትሰጠኝ?” ወጣቱ፡፡ ዓይኖቹን በሁለቱ፡ የአስር ብር ኖቶች ላይ አነጣጠራቸው፡፡

“አዎ::"
“ምንም ሳልሰራ?”
“አዎ፡፡”
“አትቀልድ፡፡ ነገር አለው፡፡” አለ ጎረምሳው ወደ አንድ ወገን እየሳቀ፡፡

“ምንም ነገር የለውም፡፡”

ወጣቱ ኣይኖቸን አጥብቦ ናትናኤልን ሊያጠናው ሞከረ::
“ለምን እራስህ አትሄድም?"
“ትፈልጋለህ አትፈልግም?” አለ ናትናኤል ሁለቱን የአስር ብር ኖቶች ወደፊት እየገፋ::

ወጣቱ፡ ከራሱ ጋር ክርክር የገጠመ መሰለ፡፡ ናትናኤል ድንገት ትቶት ሲነሳ ፈጠን ብሎ አብሮት ተነሳ፡፡

“እሺ አምጣ፡፡ ፀጥ ብዬ ገብቼ ናትናኤል ያጠራሃል ብዬው ፀጥ ብዬ መወጣት ነው… እይደል?”

“እየሮጥክ ነው የምትወጣው፤ ፀጥ ብለህ አያደለም:: ልክ ከሰውየው እንደምትሸሽ ዓይነት እየሮጥክ፡፡” ናትናኤል ቆፍጠን አለ ሃያ ብር
የያዘውን ቀኝ እጁን ወደኋላ ሰብስቦ፡፡

“እሺ ኣምጣ…. እሮጣለሁ፡፡” አለ ወጣቱ እጁን ወደ ብሩ ዘርግቶ፡፡
“ደርስህ ስትመለስ…. መሮጥሀን ካየሁ በኋላ፡፡” ናትናኤል ፈርጠም አላ::

“እሺ ግማሹን ስጠኝ::”
“ደርሰህ ስትመለስ መሉው ያንተ ነው፡፡”
ወጣቱ ከሻይ ቤቷ ወጥቶ ወደ አፓርትመንቱ ሲያመራ ናትናኤል
ተከትሎት ወጣና የመኪና መንገዱን ተሻግሮ ከለላ ይዞ የሚሆነውን
ይከታተል ጀመር፡፡

የሚጠባበቁት ሰዎች ካሉ ወደ አፓርትመንቱ ሲገባ ሊይዘት ወጥመድ ያጠመዱ ካሉ። ወጥመዳቸው በወጣቱ ላይ እንደሚወነጨፍ እርግጠኛ ነበር፡፡

ወጣቱ የአፓርትመንቱን የአጥር ግቢ በር አልፎ ሲገባ ሽማግሌው ዘበኛ ከእንቅልፋቸው አልነቁም:: ወጣቱ እጆቹን የኮት ከሶቹ ውስጥ ከትቶ በእርጋታ አፓርትመንቱ በር ላይ ወደቆመው ሰው አመራ፡፡ ሰውዬውጋ ለመድረስ በግምት አአስር እርምጃዎች ሲቀሩት ድንገት ቆም አለና ናትናኤል እንዳዘዘው መልዕክቱን ተንፍሶ ፊቱን መልሶ ሮጥ ከማለቱ፡ ግራና ቀኝ ቆመው የነበሩ መኪናዎች በሮች እየተበረገዱ አራት ሰዎች ዱብ ዱብ አሉ፡፡
ናትናኤል አይኖቹን አፍጥጦ ቀረ፡፡ በሁኔታው የተደናገጠው ወጣት
ለማምለጥ ቢሞክርም ከአጥር ግቢው በር ከመድረሱ በፊት ይዘው እፍስፍጥ
አድርገው ከአንደኛዋ መኪና ውስጥ ከተቱት፡፡

ለደቂቃዎች ናትናኤል ካለበት ሳይንቀሳቀስ ተጠባበቀ፡፡ ወዲያው
የመኪናዋ በር ተከፈተና በሁለት በኩል የወጣቱን ክንዶች የልጨመደዱ ሁለት
ሰዎችና ሌሎች ተጨጨማሪ ሶስት ሰዎች ወደ አፓርትመንቱ፡ ግቢ በር ያጣደፉ ጀመር፡፡ ከአፓርትመንቱ፡ ግቢ ሲወጡ ናትናኤል ወደ ኋላ አፈገፈገና ጥሩ ከለላ ይዞ በሩቁ በአይኑ ያስተውላቸው ጀመር::

አምስቱ ሰዎች ወጣቱን ከበው ወደ ሻይ ቤቷ ተጣደፉ፡፡ ከሻይ ቤቷ ደጃፍ፡ እንደደረሱ ሀለቱ ልጁን አስቀድመን ከተል ብለው ሲገቡ ሁለቱ፡፡ በሻይ ቤቷ ጓሮ ዞሩ፡፡ የተቀረው አምስተኛው እፊት ለፊት ጀርባውን ግድግዳው ላያ ለጥፎ ቀኝ እጁን ከኮቱ፡ ስር ብብቱ ስር ከቶ ቆመ::

ናትናኤል ሰውየው ከኮቱ ስር የጨበጠው ምን እንደሆነ ሲረዳ አብርሃም ታወሰው፡፡ ሻይ ቤቷ ውስጥ የቡት ሰዎች ከውስጥ ሲያጡት ወጥተው አካበቢውን ሊያስሱ እንደሚችሉ ሲረዳ ፈጠን ብሎ ከተደበቀበት ወጣና ሽቅብ በሩጫ ተፈተለኩ ታክሲ ተራ ደርሶ ለገሃር ብሎ ታክሲው ወንበር ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሁሉ ሁለት ሦስቴ እየተገላመጠ ተመለከተ፡፡ ከጀርባው የተከተለው ሰው ግን አልነበረም፡፡ ወደኋላ መመለስ
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....በለሃጩ አጨማለቃት፡፡ራቁት ገላውን እራቁት ገላዋ ላይ እንደቁንቡርስ አንደባለለው፤ መላ ፊቷን በሚርገበገብ ከንፈሩና በምላሱ አልኮሰኮሰው፤ እጆቿንና እግሮቿን ከአልጋው ጠርዞች ጋር እንደተጠፈሩ አፍዋ በቡትቶ ታጭቆ እንደተጎስጎስ በተንጋለለችበት ጥያፌዋን፣ ምሬቷን ሰውነቷን እያወራጨች አሳየችው፡፡

ግድ አልነበረውም...

በከርዳዳ ጺም የተሸፈነ ፊቱን ከፊቷ ላይ አንስቶ እስረኛው ምርኮኛው በሆነው ከስሩ በተንጋለለላት ገላዋ ላይ አንቀዋለሰው፣ አይን አዋጅ ሆነበት:: ..በደመነፍስ ያዳብሳት ጀመር፡፡ በል..በል የሚለውን ግፊት፤

ሂድ..ሂድ የሚለውን ስካር ሩጥ..ሩጥ የሚለውን እብደት ጥድፊያ አምቆ
መቆየቱ ጣፋጭ የስቃይ ስሜት ፈጠረለት፡፡ ከረሜላውን ከአፉ ከትቶ
ኮረሻሽሞ ጎረዳድሞ ከመዋጡ በፊት፣ የጎረሰውን ከረሜላ እየመላለሰ በመዳፉ
ላያ እየተፋ በስስት በስቃይ ስሜት እያየ ቀስቃዩ በሰቀቀኑ እንደሚደሰት ህፃን
የጓጓለትን የተንቀዋለለለትን ገላዋን ከስሩ አጋድሞ ተሰቃየ ለራቁት ገላዋ
ሳሳለት፡፡

ፂማም ፊቱን ወደ ደረቷ አስጠግቶ በጡቶቿ መሃል ወደቀ፡፡ሳያጎረድማት መጠጣት፤ ሳይኮረሽማት ላሳት፤ መልሶ ከአፉ አውጥቶ ተመለከታት::አውሬ ሆነች፡፡ ጥላቻዋ እየጨመረ. ምሬታ እየኮረረ. እልኋ እየጋመ በመጣ ቁጥር የልቡ ምት እየጨመረና ትንፋሹ እየተፋጀ መጣ ሰውነቱ በላብ አሙለጨለጨ ፊቱን ከጡቶቿ መሃል አውጥቶ ቁልቁል
አዘገመ...

ወገቧን ሰብቃ ሰደበችው ፧ ሽንጧን እያላጋች ረገመችው፧ ጭኖቿን
እያማታች ተፋችው

ደስታው ወሰን አጣ…

ጎንበስ ብሎ የሚወራጭ . አካሏን በለሀጩ በራሱ ከንፈሮቹ ተረከበው:: እንደ እንፋሎት የሚጋረፍ፡ ትንፋሹ ለስላሳ ቆዳዋን ፈጃት ፡ ለበለባት:: ህሊናቸውን መሳት የጀመሩ ደዳራ ጣቶቹ የሴት አካልዋን በጭካኔ አፍረጠረጡት፡፡

በሩ ተበረገደ፡፡

በጉልበቶቿ መሃል እንደተንበረከከ በድንጋጤ ፊቱን ወደጀርባው መነጨቀው የተመለከተውን አልወደደውም፡፡ በር ላይ በድን ይመስል የተገተረው ሰው የሚያየውን ትርዒት ለመረዳት ጊዜ ፈጀበት:: የሚመለከተው እየተገለጸለት ሲሄድ በእልህ ይንቀጠቀጥ ጀመር፡፡

“ጠርጥሬሃለሁ! አንት ውሻ ጠርጥሬሃለሁ!” አለ ማርቆስ በሩን
ለቅቆ ወደ ክፍሉ ከመግባቱ በፊት ከኮቱ ስር ሽጉጡን ላጥ አድርጎ አቀባብሎ
እላይዋ ላይ በተከመረባት ሰው ላይ እየደገነ። “እንዳትነቃነቅ... ከዚያ አልጋ
ላይ ለመውረድ ሞክርና እንደ ውሻ እገድልሃለሁ!” አለ ማርቆስ ሽጉጠን
እንደደገነ ወደ ስልኩ እያመራ፡፡ “ትንሽ ተነቃነቅና ምክንያት ስጠኝ ግንድህን አጋድምሃለሁ!” በቀኝ የያዘውን ሬድዮ ወደ አፉ ኣስጠግቶ ተናገረ።
“ሃሎ… ቆንጆዎቹ ቡድን ለ... አስቸኳይ ነው... ዜሮ አራት” ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም አለ፡፡ “ቁጥር አንድ ጋር አገናኝኝ፡፡” የሬዲዮ መገናኛውን በግራው እንደጨበጠ በቀኙ የያዘውን ሽጉጥ እላይዋ ላይ በተከመረው ሰው
ላይ ደግኖ ተጠባበቀ፡፡ “ሃሎ …ዜሮ አራት በፍጥነት እፈልግሃለሁ… እዚሁ
ድረስ… ሌላ ሰው አይደለም አንተ ራስህ ተገኝታህ መመልከት አለብህ።”
አነጋግሮ ሊያበቃ ስልኩን ዘግቶ ሽጉጡን ወደፊት ኣስቀድሞ ወደ አልጋው
ተጠጋ፡፡

“ጉድህን እናየዋለን” አለ ማርቆስ ጺማሙን ሰውዬ በጥላቻ
እየተመለከተ፡፡

“ይቅርታ አድርግልኝ ማርቆስ፡፡ ሌላው ይቅር ልብሴን ልልበስ፡፡” አለ ሰውየው በጭኖቿ መሃል እራቁቱን እንደተንበረከከ በልምምጥ ፊት ማርቆስን እየተመለከተው፡፡

“ከማነው ሃጢያታችንን የምንሸሽገው? ለዓመታት አንዳችን የአንዳችንን ሃጢያት እንዳናይ የገዛ ሃጢያታችን እንዳይታይ ፊታችንን ስንመላለስ ቆይተናል፡፡ ከአሁን ወዲያ ግን ገበናችን መገለጥ አለበት፡፡
ከኃጢያታችን እራቁታችንን መተያየት አለብን። : እውነት ተሽፋፍና ተጀቧቡና አትኖርም፡፡ እራቁቷን ነው የምታምር፡፡” በዕልህ ተንቀጠቀጠ፡፡
“እራቁቷን!”

“ማርቆስ ልብህ ይራራ… ሁላችን እንሳሳታለን… ማረኝ፡”

"ማነው አውሬ… ለተናካሽ እውሬ የሚራራ? ቀሚሷን ገልበው እርቃኗን አንጋለው ለሚያረክሷት፣ ጭኖቿን በርግደው ሴትነቷን አጋልጠው ለባእድ
ለሚሽጧት አፍሪካ ርህራሄ አይኖራትም፡፡ ምህረት ምንድነው? በየዋህነት ለቸረቸራችሁ፣ በልበ ገርነቷ ለሽረሞጣችሁ፣ በድንግልናዋ ላቃጠራችሁ ምህረት ምንድነው? አፍሪካ መቼ ነው ቀሚሷን ዝቅ የምታደርግ፣ ጭኖቿን የምትሰበስብ፣ እፍረቷን የምትሸፍን? እናንተ ስትጠረጉ ብቻ ነው! ምህረት አያሻም! ራቁታችንን መተያየት አለብን!”

የክፍሉ በር ከጀርባው ሲበረገድ የተንበረከከው ጺማም ሰው ዓይኖቹን ጨፈነ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የቢሮውን በር በርግዶ ሲገባ ብርጋድየር ጀኔራሉ ከጠረጴዛው ጀርባ እንደተቀመጠ አፍጥጦ ተመለከተው፡፡
“ያዝነው!” አለ ማርቆስ ትንፍስ ትንፍስ እያል፡፡
“ናትናኤልን?” አለ ጀኔራሉ የሰማውን ለማረጋገጥ፡፡
“አዎ፡፡” አለ ማርቆስ ጭንቅላቱን ነቅንቆ ፀጉሩን እየደባበሰ፡፡
“ብታምነኝም ባታምነኝም እራሴን እስከምጠላ ተስፋ ቆርጬ ነበር፡፡”

“እንዴት ያዝስከው? ማለቴ የት?” አለ ጀኔራሉ ማርቆስን ተቀመጥ ሳይለው በቆመበት እንዳፈጠጠበት፡፡

“ባቡር ላይ፡፡” አለ ማርቆስ ወደፊት ተራምዶ ወንበር ላይ እየተቀመጠ፡፡ “ዛሬ ማታ ወደ ድሬዳዋ ለመሄድ ባቡር ላይ ሲሳፈር እዛ የመደብኳቸው ሁለት ሠራተኞቼ አይተውት አብረውት ተሳፍረዋል፡፡”

“ወደ ድሬዳዋ ተሳፍራል ነው የምትለኝ? ያዝኩት ያልከኝ መስሎኝ ነበር'ኮ፡፡” አለ ጀኔሪሉ ፊቱን አኮሳትሮ “መከታተሉ ምንድነው ትርጉሙ ለምን ቀጥታ አላስወገድከውም? "

“አታስብ... ከአዲስ አበባ እስከ ድሬዳዋ ያሉትን ጣቢያዎች በሙሉ በሰዎቻችን ሸኛቸዋለሁ፡፡”

“ባበሩ ሳያነሳ ለምን አልያዝከውም
“ጀኔራል ሰውየው ትኬት ሲቆርጥ ሰዎቻችን አላዩትም፡፡ ምናልባት
በሌላ ሰው እስቆርጦም ሊሆን ይችላል:: ድንገት ባቡር ላይ ሲሳፈር ያዩ ሠራተኞቼ ምርጫ ስላልነበራቸt ስልክ ደውለው ሲያስታወቀኝ ባበር ጣቢያ ውስጥ አስወጋጅ ሃያል ስላልነበረ ተከትለውት እንዲሳፈሩ አዘዝኳቸው።

ታዲያ ምኑን ነው ያዝኩት የምትለኝ?”

“ከዚህ ወድያ ሊያመልጥ አይችልም:: በየትኛውም ጣበያ ቢወርድ
ከማንም ጋር ከመገናኘቱ በፊት እንዲያስወግዱት ትዕዛዝ አስተላልፌአለሁ::”አለ ማርቆስ በፍጹም እርጋታ:: “በየጣብያው የሚጠባበቁት ሰዎች አሉ።

“አንተ ራስህ ለምን ድሬዳዋ በረህ አትጠብቀውም? የምልህ ይህን
ሰው አደገኛ ነው ጀኔራሉ ተረበሸ… “አንተ ራስህ ቀድመህ ብትጠበቀው
እመርጣለሁ:::”
“አንድ ሄሊኮፕተር እዛጋጅቼ እየተጠባበቅሁ ነው… ቀጥታ ወደ
ድሬዳዋ እንዳልበር ምናልባት በመሃል ሊወርድ ስለሚችል ባቡሩ እያንዳንዱን
ጣቢያ ሲያልፍ፡-የጣቢያው ያሉ ሰዎች የሬድዮ መልዕክት እያስተላለፉልኝ
እየጠበቅሁ ነው::”

“የት ነው ያለው ኣሁን?” አላ ጀኔራሉ በጉጉት፡፡
“ባቡሩ ናዝሬትን ማለፉን :: እንዳረጋገጥኩ ነው ወዳንተ የመጣሁት:: አላ ማርቆስ፡፡

ማርቆስ!” አለ ጀኔራሉ ፊቱ በጭንቀት ተወሮ፡፡ “ይህ አካሄድህ አላማረኝም እንበልና ይህ ሰው በሁለት ጣቢያዎች መሃል ከባቡሩ ቢዘል ምን ልታደርግ ነው? ከቦታው ላይ ምን ያህል ዘግይተህ እንደምትደርስ አታውቅም?”

“አብረውት የተሳፈሩት ሰዎች የነፍስ ወከፍ መሳሪያ የታወቁ ናቸው፡፡”

“የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ይታጠቁ እንጂ ለዚህ ሥራ የሰለጠነና የተዘጋጁ አይመስሉኝም። ተራ የክትትል አባላት ናቸው… አይደለም?” አለ ጀኔራሉ ጠረጴዛውን ቡጢ ደልቆ፡፡

“እርግጥ የክትትል ሠራተኞች ናቸው ግን”

ማርቆስ! ማርቆስ! ምን እየሰራህ ነው?
👍3
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

..... የረር ጎታ ሲቃረቡ ነበር ሲቲና ከእንቅልፏ የተነሳችው፡፡

“ለምን አትተኛም ነበር? ቀንኮ ይደክምሃል» አለችው:: እንቅልፍ
ያሳቀጣቸውን ጉንጮቿን እያሻሸች::

“ተመችቶሽ ተኛሽ? ” አላት ፈገግ ብሎ፡፡
“አመሰግናለህ፡፡ የሚመች ትከሻ አላህ፡፡” አለች እየሳቀች፡፡ ጎንበስ ብላ ከሻንጣዋ ውስጥ ሎሚ አወጣችና አንድ ለእሱ አንድ ለራሷ ወሰደች::
“ሎማ ያነቃቃል፤ ታውቃለሁ? " አለች የያዘችውን ሎሚ እየመጠጠች፡፡

ድሬዳዋ ለገሃሬ ደርሰው ከባቡሩ ሲወርዱ ናትናኤል ተደነጋገረው:: የባቡር ጣቢያው በሰው ተጨናንቋል፡፡ አንድ እርምጃ ለመራመድ ሁለት ሦስት ሰዎች መገፍተር አለባቸው:: ሰው የት ወደየት እንደሚሄድ መለየት ያስቸግራል፡፡ ብቻ ባለበት ይተራመሳል፧ ይገፋፋል ፧ ይታሻሽል። ከኋላው ተቀምጣ የነበረችው ሴት አብሯት ከተቀመጠው ተሳፋሪ ጋር እያወራች ስትወርድ ዞሮ ተመሰክታት:: አብሯትት ካለው ሰው ጋር ታውራ እንጂ
አይኖቿ ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ እርግጠኛ ነው... ከዚህ ቀደም አያቷታል፡፡

“የት ነው የምታርፈው አለችው
ሲቲና ቀደማ ከባበሩ እየወረደች::

“እ… አልወሰንኩም።” አላት ከጀርባው ተቀምጣ የነበረችውን ሴት ማንነት ለማስታወስ እየጣረ:: እርግጠኛ ነው.. መልኳን ያውቀዋል ግን ራቀበት፡፡
“ማለቴ ዘመድ ጋ ነው... ወይስ ሆቴል?” አለችው ሲቲና::ድንገት ብልጭ ሲልለት ድጋሚ ፊቱን ወደ ሴትየዋ አዙሮ ተመለከታት፡፡ የአብርሃም ሠራተኛ! ዞሮ ተመስከታት:: ሳያውቀው ዓይን ለዓይን ተጋጩ፡፡ ቀድማው ፊቷን መለሰች:: ሴትየዋ ቀድሞ ካላያቸው ሁለት ሰዎች ጋር ስታወራ ተመለከተ፡፡

“እ..ምን አልሺኝ? አይ…. ሆቴል ነው የማርፈው ለጊዜው፡፡” አለ ፊቱን ወደ ስቲና መልሶ፡፡

“ከፈለግህ እኔጋ ማረፍ ትችላለህ፡ባዶ ቤት ነው ያለሁት፡፡”
“እ... አለ አሁንም ፊቱን መልሶ የአብርሃምን ሠራተኛ ባየበት አቅጣጫ ተመለከተ፡፡ ዓይኑን የምትሸሽ መሰለው፡፡ አብረዋት የነበሩት ሦስት ሰዎች በአጠገቧ የሉም፡፡ ሴትየዋ ብቻዋን ጥግ ይዛ ቆማለች፡፡

«ማለቴ ለሁለት ለሦስት ቀን ችግር የለም ማለቴ ነው፡» ከጎኑ ከጎኑ እየሄደች አንገቷን አቀርቅራ ተናገረችው ሲቲና፡፡

ከሰው ግፊያ ወጣ ብለው ወደዳር ላይ የያዟቸውን ሻንጣዎች ከመሬት ላይ አሳርፎ ቀና ሲል ባሻገር ተመለከታት፡፡ ሴትየዋ አሁንም ታየዋለች:: ምናልባት የት እንያምታውቀኝ ጠፍቷት ይሆናል።" ብሎ አሰበ፡፡

“አስቸግርሽ እንደሆነ…” አለ ፊቱን ወደ ሲቲና መልሶ፡፡
“በፍጹም፡፡” አለች ፊቷ በሃፍረት እየቀላ፡፡
“እ... ” ናትናኤል አመነታ፡፡ ሆቴል አለመያዙ ከዓይን የሚያድነው ብቻ ሳይሆን ገንዘብም የሚቆጥብለት ነው፡፡ ግን ይቺን ልጅ ተከትሎ ከቤቷ ሄዶ ምን እንደሚከተል ለማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ መቼም ምሳና እራት ሊያባላት ወይ ለነፍሷ ብላ እንዳላስጠጋችው ግልጽ ነው፡፡ ግን ቢሆንስ እንዴት ድንገት ልታቀርበው ፈለገች? “ምን መሰለሽ…” አለ ግብዣዋን
እምቢ የሚልበት ዘዴ ጠፍቶት ኣቧራ ያበላሸውን ነጭ ጀለቢያውን
እያራገፈ፡፡

“አስቸግራታለሁ ብለህ አስበህ ከሆነ ምንም ችግር የለም፡፡ ባዶ ቤት ነው ከፍቼ የምገባው:: ወላሂ አልኩህ፡፡”

“እስቲ እየሄድን እናውራ፡፡” አለ ናትናኤል - የሰው ትፍግፍግ ማለትና የአየሩ ሙቀት ትንፋሽ ቢያሳጥረው።

ጎንበስ ብሎ ሻንጣውን ሲያነሳ ከጎኑ ቆማ የነበረችው ሲቲና ገፍትራ ከመሬት ደባለቀችው፡፡ መሬት ላይ ሁለቴ ተንኮበሉ ቀና ሲል ነበር ነገሩ ጭንቅላቱን የመታው ከጀርባወ ቆመው የነበሩ አንድ አዛውንት በደም የተጨማለቀ ሆዳቸውን ይዘው ወደ ሠሬት ሲያዘቅጡ አያኖቹን አፍጥጦ
ተመለከታቸው!” እሪ አለች ከጎናቸው የነበረች ወጣት ሴት፡፡ ከወደቀበት
ለመነሳት ሲጣደፍ ሲቲና ሸብረክ ብላ ከተከናነበችው ድሪያ ስር ሽጉጥ
መዥረጥ ስታደርግ አያት:: ተቀደመች:: የያዘችው ሽጉጥ እጇ ወስጥ ተፈናጥሮ ሲወረወር እሷ ደረቷን አፍና ወደ ኋላዋ ወደቀች.. ዙሪያውን ረብሻ ሆነ... ጩኸት... ሩጫ.. ኡኡታ... ቶክስ እሪታ ዙሪያወን አደባለቀው..ናትናኤል ከአንገቷ ቀና አደረጋት...

«ሩ...ጥ! ተክትለውሃል... ሩጥ!» አለችው በግራ እጇ በደም የተዘፈቀውን ደረቷን አፍና እንደያዘች ሲር ሲር ከሚለው ትንፋሿ እየቆነጠበች ‹‹ ሩጥ!»

ቀና ሲል አየው:: የጨበጠውን ሽጉጥ ከትከሻው በላይ ይዞ ከፊቱ የሚጋረጡትን ሰዎች አንዴ ወዲህ አንዴ ወዲያ እየገፋ እየገፈታተረ ወደ እሱ እየቀረበ ሲመጣ በሚተራመሰው ሕዝብ መሃል በሩቁ አየሁ
ከአብርሃም ሠራተኛ ጋር የነበረውን አንድ ሰውዬ! እንደ ጥንቸል ተፈናጥሮ ከሚደነባበረው ከሚራበሸው ሕዝብ መሃል እየተሹለከለከ በትርምሱ ውስጥ
ሰመጠ... የአብርሃም ሠራተኛ! የፈጣሪ ያለህ! የአብርሃም ሠራተኛ! ከራሱ ጋር እያነበነበ ሮጠ፡፡ ከጀርባው የተኩስ እሩምታ አጀበው::

ወዴት እንደሚሮጥ.. የት እንደሚደርስ ግድ አልነበረውም:: ብቻ ሮጠ፡፡ እራቅ እንዳለ በሩቁ እንዳይለዩት ጭንቅላቱ ላይ የጠመጠመውን ሽርጡን አውልቆ በእጁ ያዘው:: ትንሽ ከራቀ በኋላ ደግሞ ወደ ጥግ ዞር አለና ጀለቢያውን አውልቆ ወርውሮ ከወገቡ በታች ሽርጡን አጥልቆ ከላይ ነጭ ሸሚዙን እንዳደረገ ከራሱ ጋር እያጉተመተመ ሮጠ፡፡ የአብርሃም
ሠሪተኛ! እንዴት ሊከተሉት ቻሉ? ወደ ድሬዳዋ መምጣቱንስ እንደት አወቁ? ሲቲና ባትገፈትረው'ኮ ወደፊቱ ሲወድቅ ባይስቱት'ኮ.. ' በደም የተጨማለቀ ሆዳቸውን ይዘው ያዘቀጡት ሽማግሌ ታዩት:: የፈጣሪ ያለህ! ገለውት ነበር'ኮ የአብርሃም ሠራተኛ! ወያኔ አብርሃም! ለካ ሳያውቀው!

ሲቲና ማነች? ሩጥ…ተከትለውሃል ሩጥ የምስራችን የገደለቻት ሴት ምንድን ነበር ያለችው? ሩጥ!' ሲቲና ማነች? የፈጣሪ ያለህ! ሁሉ ነገር ተወሳሰበበት:: ማሰቡን አቁሞ ሩጫውን ቀጠለ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ያለበት ቦታ የት እንደሆነ ለመረዳት አልቻለም፡፡ በስተግራው መደዳ የተሰሩ ቤቶች ማስታወቂያዎቻቸውን በየቢሮዎቻቸው ላይ እንዳንጠለጠሉ ተደርድረዋል:: ፈቶግራፍ ቤት..የልብስ ሰፊ...ስዓት ማደሻ..በስተቀኙ ደግሞ በረንዳው ላይ የሳጠራ ወንበሮች የተደረደሩበት በሐረግ የተሸፈነ በረንዳ ያለው ቤት ይታያል ድሪዳዋ፡፡

ወደ ቡና ቤቱ፡ ተጠጋና አካባቢያን ለማጥናት ሞክረ፡፡ የፊተኛው ክፍል ሰፊ ቢሆንም ጨለምለም ያለ ነው፡፡ ፈጠን አለና ወደ ውስጥ ገባ፡፡በትናንሽ ጠረጴዛዎች ዙሪያ የተኮለኮሉ ትናንሽ የብረት ወንበሮች ፈንጠር ፈንጠር ብለው ክብ ክብ ሰርተዋል፡፡ በጋዝ የተወለወለው የሲሚንቶ ወለል ቢያብለጨልጭም ሽታው ይከብዳል:: ቁርስ የሚያቂርጉ የቡና ቤቱ ደንበኞች በየወንበሮቻቸው ተቀምጠሁ ያዘዙትን ይስተናግዳሉ፡፡

ባዶ ወረጴዛ ፈለገና ወንበር ስቦ ተቀመጠ፡፡

“ምን ልታዘዝም ! በስተቀኝ የተንዘላዘለ ፀጉሯን ጣቷ ላይ እየጠመጠመች እየፈታች ጠየቀችው::

ሻይ አላት ቶሎ ለመገላገል፡፡ ፊቷን መልሳ ሄደች፡፡ ናትናኤል ከራሱ ጋር ምክክር ቀጠለ።

ጊዜ የለውም:: መፍጠን አለበት:: አለበለዚያ ያገኙታል በማያውቀው ከተማ ውስጥ ተደብቆ መቆየት ዘበት ነው ግን እንዴት ተከተሉት? ከርብቃ ቤት አምልጦ ሲሮጥ ተከትለውት ነበር ማለት ነው?
መሆን አለበት፡፡ የአብርሃምስ የቤት ሰራተኛ እዚህ ምን አመጣት? ወይኔ!
አብርሃምን ትከታተለው ነበር ማለት ነው! አሁን ደግሞ

የቡና ቤቱ አስተናጋጅ ያዘዘውን ሻይ አምጥታ ፊቱ አስቀመጠችለት::

እባክሽ የእኔ እመቤት የስልክ ቁጥር ማውጫ ደብተር ይኖራችኋል? “ አላት

“ይቅርታ የለንም ለምን ማዞሪያ አይጠይቁም
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

"ከየት ነው ?" አለች ሴትየዋ በመገረም ቃና።

“ከዚሁ ነው ከድሬዳዋ እባኳት አንዴ ቢያገናኙኝ፡፡” ልቡ ተንጠለጠለ፡፡

“ይቅርታ ተሳስተዋል::” አለች ሴትየዋ ለመናገር ያልፈለገችው ነገር እንዳለ ሁሉ እያቅማማች፡፡
“ቆይ፤ ቆይ!” አለ ስልኩን እንዳትዘጋበት ተሽቀዳድሞ፡፡ የስልክ ቁጥሩን በእርጋታ እየጠራ ትክክል መሆኑን ጠየቃት፡፡

“ቁጥሩ ትክክል ነው:: ግን…” አቅማማችበት፡፡
“አቶ ይልማ የሉም? ” ጭንቅላቱ በጭንቀት ተወጠረ፡፡
“እንደዛ የሚባል ሰው የለም::” ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጋችበት፡፡

ሊሆን አይችልም! ነገሩ ሁሉ ተደበላለቀበት፡፡ የስልኩን መነጋገሪያ
ከቦታው መልሶ ወደ ወንበሩ ተመለሰ፡፡ አለቀ፡፡ ካልቨርትን ለማግኘት የነበረው ተስፋ : ከእጅ ያመለጠ እንቁላል ሆነበት፡፡ ህ!… አስራ ሶስት ብር ይዞ ሽሽት ታየው:: አስራ ሶስት ብር ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ እንኳን በቂ አይደለም፡፡ ምንም ምርጫ የለውም! መስረቅ ካለበት ይስቃል! ማጅራት መምታት ካለበት ይመታል ግን አዲስ አበባ አይመለስም! ካልቨርት ያለው እዚህ ነው፡፡ የምሥራች ነግራዋለች፡፡ ካልቨርት ድሬዳዋ ነው! ካልቨርት አፍንጫው ስር ነው!” ጠረጴዛውን በቡጢ ደወለው፡፡

በቡና ቤቱ አዳራሽ የተቀመጡ ሰዎች ጠረጴዛውን ሲጠልዘው ሲሰሙ ቀና ቀና አያሉ እየተገላመጡ ያዩት ጀመር፡፡በዛ ድርጊቱ ተደናገጠ፡፡
ጥንቃቄ!…. መረጋጋት! መረጋጋት! ሻዩን አንስቶ ፉት አለው፡፡ ቀዝቅዟል፡፡ አልተወውም፡: በእርጋታ ደጋግም ፉት እያለ ጨረሰው፡፡ ቢደግም አይጠላም
ነበር፡፡ ኪሱ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ሲያስታውሰው ተወው፡፡

በተቀመጠበት ዓይኖቹን ባዘዝ አድርጎ አእምሮውን ለማስራት ሞከረ
…ካልቨርት የት ነው?- «እማዪጋ ድሬዳዋ…እማዬ…የአቶ ይልማ ገዛኸኝ
ባለቤት… ኣቶ ይልማ ገዛኸኝ .. ይልማ ይልማ ምንድን ነበር ያለችው ስልኩን ያነሳችው ሴት ይልማ ምን? …ይልማ ጋራዥ… ጋራዥ…

የቡና ቤቱን አስተናጋጅ ጠቀሳት፡፡መጣች።

“እባክሽ የኔ ቆንጆ ይልማ ጋራዥ የሚባል ታውቂያለሽ ድሬዳዋ ውስጥ? ” የአንድ ጋራዥ ስም ጠርቶ ውለዱ ሲል እራሱን አስገረመው፡፡

“ይልማ…ይልማ…እንትንጋ ነው… ማነው? ...በቃ ከአሸዋ ሜዳ ከድልድዩ ሳይደርሱ ወዲህ ከባንኩ ትንሽ አለፍ እንዳሉ…” የማያውቀውን ከተማ ትተርክለት ጀመር፡፡

“እይው...” አለ ድምፁን አለዝቦ አቋረጣት፡ “ለድሬዳዋ አዲስ
ስለሆንኩ ነው::”

“የሚያሳይዎት ልጅ ልጥራሉት? ቅርብ ነው::” አለች፡፡
“ጥሩ ጥሩ፡፡” ጭንቅላቱን እየወዘወዘ መስማማቱን ገለፀላት፡፡

ጋራዡን ከሚያሳየው ልጅ ጋር ካገኘችው በኋላ በደረቅ ምሥጋና ተሰናብቷት ከልጁ ጋር ተፈተለከ፡፡ ጉርሻ ቢሰጣት ደስ ባለው ነበር… ግን...፡፡

“ይልማ ጋራዥ ነው አይደል? ኑ” ይለዋል ከፊት ለፊቱ ቱስ ቱስ የሚለው ህፃን ልጅ፡፡ ዕድሜው ከአስር አመት አይበልጥም፡፡ ያደረጋት የላስቲክ ነጠላ ጫማ ተበጣጥሳለች፡፡ በተራመደ ቁጥር ወደ ኋላ ልትቀር ታስባለች፡፡ ልጁ ግን ትቷት ሊሄድ ፈቃደኛ አይመስልም፡፡ በእግሮቹ ጣቶች ቆንጠጥ አድርጎ ይዞ ወደፊት ይጎትታታል፡፡ ትንሽ ይሄድና “…ይልማ
ጋራዥ ነው አይደል? ኑ” ይለዋል፡፡

ናትናኤል ላቡ በጆርባው እየተንቆረቆረ ከልጁ ኋላኋላ ይጣደፋል፡፡

“ያው! ይሄ ነው ይልማ ጋራዥ:: ሜካኒኮቹን ልጥራሎት?” አለ ልጁ ተስፋ ያደረገውን ጉርሻ በሆዱ ይዞ መስተንግዶውን እያጧጧፈ፡፡

“አይ ተወው፡፡” አለ ናትናኤል ከኪሱ አስር ሳንቲም አውጥቶ ለልጁ
እየዘረጋለት::

አቦ ይጨምሩ! ከለገሃሬ ድረስ አምጥተውኝ” አለ ልጁ አስር
ሳንቲሟን ሲያይ ፊቱ በቅያሜ ተንጠልጥሎ፡፡

“ሌላ ጊዜ እሰጥሃለሁ፡፡” ኣለ ናትናኤል አስር ሳንቲሟን ገፋ አድርጎ፡፡

“እስር አልወስድም!” አለ ልጁ በብስጭት::

ናትናኤል አልተግደረደረም ሳንቲሟን ኪሱ ከቶ ወደ ጋራዡ በር ተጣደፈ፡፡ልጁ ከጀርባው እናቱን ተሳድቦ ሲሮጥ ሰማው። ግድ አልበረውም፡፡ የጋራዡ ግቢ ስፋት ያለው ቢሆንም ከውስጥ የተሰገሰጉት በርካታ መኪናዎች ጠባብ አስመስለውታል፡፡ ደማቅ ሰማያዊ ቱታ የለበሱ የጋራዥ ሠራተኞች ኮፈናቸው በተበረገዱ መኪናዎች ዙሪያ ተፍ ተፍ ይላሉ።

· “የት ነው?” አሉት ከበሩ ጥግ በተደራረቡ ድንጋዮች ላይ የተቀመ
ጡት ሽበት ያሸፈናቸው ዘበኛ ከተቀመጡበት ወገባቸውን ይዘው እየተነሱ፡፡የከንፈሮቻቸውን ጥግና ጥግ በጎረሱት ጫት አረንጓዴ ሆኗል፡፡

“እንደምን ዋሉ.…አቶ ይልማን ነበር፡፡” አላቸወ ጠጋ ብሎ::

ሰውየው ግራ በመጋባት መልክ ትክ ብለው ተመለከቱት፡፡ መልስ አልሰጡም ብቻ እብድ እንደሆነ ሁሉ አፍጥጠው አዩት::

“እ..ቀጠለ“ልጃቸው ከአዲስ አበባ ልካኝ ነው፡፡ ይኖሩ ይሆን?”

“አቶ አደፍርስ ማለትህ ነው?” አሉ ሽማግሌው የፀሃይዋን ጨረር
በመዳፋቸው ከልለው::

“አይ አቶ ይልማን ነው::”
ሰውየው ጤነኛ እንዳልሆነ ጭንቅላታቸውን ነቀነቁበት፡፡

“የአቶ ይልማ ጋራዥ አይደል እንዶ ይሄ?” አለ ናትናኤል ተስፋው እየተሟጠጠ፡፡

“ክፉው ሞት ሳይወስዳቸው በፊት አዎ፡፡" አሉት ሰውየው ተመልሰው በተደራረቡት ድንጋዮች ላይ እየተቀመጡ፡፡

“ምን አሉኝ?” አለ ደንገጥ ብሎ፡፡
“የኔ ወንድም አቶ ይልማ ከሞቱ መጪው ህዳር ሁለተኛ ዓመታቸዉ ነው::” አሉት ሽማግሌው ከጎናቸው በኮካኮላ ጠርሙስ ካስቀመጡት ውሃ እየተጎነጩ፡፡

ናትናኤል ለጥቂት ደቂቃዎች ፈዞ ቆየ፡፡

“እባኮት ባለቤታቸው የሚኖሩበትን ያውቁ ይሆን?”

ሽማግሌው ችላ ብለውት በዝምታ ጭንቅላታቸውን ነቀነቁበት፡፡
ወሬው የጣማቸው አይመስልም፡፡

“እባኮት ስለባለቤታቸው የሚያውቅ ሰው ካለ ላስቸግርዎት...”ናትናኤል የሽማግሌውን ፊት ሲመለከት ቶሎ ኪሱ ገባና ሁለት ብር መዞ ተመለሰ፡፡

“እስቲ ግባና ባለቤትየውን አነጋግር፡፡ ወንድም ናቸው::” አሉት ሽማግሌው ዘበኛ ሁለት ብራቸውን ኪሳቸው እየጨመሩ።

“የማን ወንድም? ”
“የአቶ ይልማ ወንድም::አቶ ኣደፍርስ ብለህ ጠይቅ::
ናትናኤል ሹማግሌውን አመስግኖ ወደ ውስጥ ገባ፡፡
“ይቅርታ ወንድም አቶ አደፍርስን ፈልጌ ነበር፡፡” አንዱን የጋራዥ ሰራተኛ አስቁሞ ጠየቀው::

“እኛውልህ፡፡” አለው በዘይት የተጨማለቀ እጁን ዘርግቶ እያመለከተው::

ናትናኤል ወደ ሰውየው አመራ ተጠግቶ በአክብሮት ሠላምታ ሰጣቸው፡፡ በጣም አጭርና ሆዳቸው ወደፊት የገፋ ናቸው፡፡ ሙልጭ ካለው መላጣቸው ጎንና ጎን ከጆሮዎቻቸው በላይ ቡፍ ቡፍ ያሉ ጥቂት የማቆጠሩ የፀጉር ብናኞች ይታያሉ፡፡ የጋራዥ ባለቤት ሳይሆን የሆቴል ወጥቤት ኃላፊ ነው የሚመስሉት::

“እንደምን ዋሉ፡፡ እባኮት ላስቸግርዎት፡፡ ከአዲስ አበባ ነው የመጣሁት።”

“አላህ ይስጥህ አላህ ይስጥህ!” በሚያስገመግም ድምፅ ጮሁና
እጃቸውን እያወናጨፉ ፊታቸውን አዞሩበት፡፡

“አይደለም ጌታዬ፡፡ ለእርዳታ አይደለም፡፡ መልዕክት ይዤ ነው የመጣሁት፡፡”

“የምን መልዕክት?” በዚያው ሃይለኛ ድምፃቸው ጠየቁት ፊታቸውን
ከስክሰው::

“የምሥራች ነበረች የላከችኝ እናቷጋ፡፡ጽፋ የሰጠችኝ ኣድራሻ ጠፋብኝና የአባቷን ስም አውቀው ስለነበረ ማዞሪያ ስጠይቅ የእርስዎን አድራሻ ሰጡኝ፡፡”

“አንተ ግም፣ ያችን መኪና ፍታት አላልኩም? ጥሩ አውደልድል
ሳምንት ይድረስና ከጎንህ ታገኘዋለህ! ” ሰውየው ተቆጥተው ሲጮሁ የጋራዥ
ሠራተኞች ሁሉ ጭልፊት እንዳዩ ጫጩቶች በየስርቻው አንገታቸውን
ይቀብራሉ፡፡ “የማነች የምሥራች?” አሉት ድንገት በቁጣ የተለዋወጠ ፊታቸው ወደ ናትናኤል መልሰው፡፡

“የአቶ ይልማ ልጅየምሥራች ይልማ፡፡”
ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውየው ረጋ ብለው አትኩረው
2👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

#ቆንጆዎቹ

“ማርቆስ” አለ ጀኔራሉ ጥፋትህ ፍጹም ከይቅርታ በላይ ነው::"

ማርቆስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዘመናት ሚያውቀው አስተማሪው አለቃውና ጓደኛው ፊት ላይ ጽያፍ የተሞላ ቅዝቃዜ የተመለከተ መሰለው፡፡

“በአጭሩ የውጭ ጉዳዩ ሰው ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል።”አለ ጀኔራሉ በንዴት የቀሉ ዓይኖቹን ከማርቆስ ላይ አንስቶ በስተግራ በተቀመጠው ምክትሉ በሆነው በአንድሬ አማሪ ላይ እየተከለ፡፡

“እኔ መጀመሪያውኑ…” ዣክ ዊልያም ፊቱ ላይ ጎልቶ የሚታየውን ንቀትና ጥላቻ ሳይደብቅ፡፡ ዓይኖቹን በኮሎኔል ማርቆስ ላይ ተክሎ ጀመረ።

በቃ! አለ ጀኔራሉ አቋርጦት “እሁን ባለፈና በሞተ ነገር ላይ ጊዜዬን ማጥፋት
አልፈልግም፡፡ ያለን ጊዜ በደቂቃዎች የሚቆጠር ነው፡፡ ይህ ሰው ወደ ድሬዳዋ የሄደው እንደምፈራው የካልቨርትን መሸሸጊያ አግኝቶ ከሆነና ምስጢሩንም አስገድዶ እጁ ካገባ ምን እንደሚከተል ልትገምቱ ትችላላችሁ፡፡”

ለአንድ አፍታ የፀጥታው ቡድን ሃላፊ ንግግሩን አቁሞ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ በአፍንጫው ላይ ሽፍ ያለው ላብ በክፍሉ ውስጥ ካለው ቀዝቀዝ ካለው አየር ጋር ሲያገናዝቡት ሰውየው በንዳድ የሚሰቃይ ይመስላል፡፡

“ለማንኛውም እናንተን ቢሮዬ ድረስ ከመጥራቴ በፊት ከዚህ ወዲያ ምን ማድረግ እንዳለብን ዝርዝር ዕቅድ አውጥቻለሁ፡፡” አለ ጀኔራሉ ቀጥሎ
“ጉዳዩን ከአሁን በኋላ አንድሬ በቀጥታ እየተከታትልክ በየአንድ አንድ ሰዓቱ
ሪፖርት ታደርግልኛለህ፡፡” አለ ወደምክትሉ ፊቱን መልሶ

የፀጥታው ክፍል ምክትል አዛዥ ጭንቅላቱን በስምምነት ነቀነቀ፡፡

“በቅድሚያ ኣለ ጀኔራሉ ፊቱን የአጥቂ ስለላ ሃላፊ ወደሆነው ወደ ዣክ ዊልያም መልሶ በቅድሚያ ዣክ ድሬዳዋ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች….
በገበያ ቦታዎች…. እ... የውጭ ዜጎች በሚኖሩበት ክልል.… ተከታታይ የፈንጂ
አደጋዎችን ትጥላለህ፡፡ ይህ በሚቀጥለው አንድ ሰዓት ውስጥ እንዲጠናቀቅ እፈልጋለሁ፡፡” አለ ጀኔራሉ በጣቱ ጠረጴዛውን እየተመተመ፡፡ “እንድሪ” ፊቱን ወደ ምክትሉ መለሰ፡፡ “የፈንጂ አደጋዎቹ፡፡ እንደደረሱ ወድያውኑ
ድሬዳዋ ገብተህ እያንዳንዱን በር ትዘጋለሁ፡፡ ለጊዜው በማንኛውም የቴሌኮ
ሙኒኬሽንና የፖስታ አገልግሎቶች ጥብቅ ክትትል አደርጋለሁ፡፡ ከዛም ውጪ አራት የኮማንዶ ሃይል ወደዚያው ልኬልሃለሁ ማንኛውም የመጓጓዣ መስመር ከአንድ ሰዓት በኋላ ይዘጋል፡፡ አንድሬ አሁኑኑ ቀጥታ ወደ ድሬዳዋ በረህ ከተማዋን ትመነጥራለህ፡፡ ቤት ማፍረስ ካለብህ አፍርስ፤ ጉድጓድ መማስ ካለብህ ማስ፤ ያንን ሠይጣን ቀኑ ሳይመሽ በፊት እጅህ ማስገባት አለብህ:: ለምናደርገው ሁሉ ያፈንጂዎቹን “ፍንዳታ የአሸባሪዎች ጥቃት
መሆኑን በማጉላት ዣክ በቂ አሳሳች ፕሮፖጋንዲ እያዘጋጀ ለመገናኛ
ብዙሃን ያቀርባል።” ፊቱን ወደ ዣክ ዊልያም መልሶ ተናገረ፡፡

“እዚህ ላይ ይቅርታ፡፡” አለ ሩዋንዳዊው አንድሬ አማሪ፡፡ “ድሬዳዋ የአሸባሪዎቹ ጥቃት እንደደረሰ እዛ ያሉ የመንግሥት ሃይሎችና ፖሊስም ጣልቃ ሊገቡብን ይችላሉ፡፡”

“ለዚያ አታስብ” አለ ጀኔራሉ እጁን ወደጎን አወናጭፎ “ያ የኔ ስራ ነው፡፡ ማንኛውም የመንግሥት ሃይል ጣልቃ አይገባም፡፡ፈንጂዎቹን የምናፈነዳውና አሳሳች ፕሮፖጋንዳ የምንነዛው የሕዝቡን ስነልቦና ለመጠበቅና የጠላትን ጥርጣሬ ላለማነሳሳትና ሽፋን ለመፍጠር ነው፡፡በመንግሥት በኩል ችግር አይኖርም:: ድሬዳዋ በእጅህ ናት::”

“እዛ ከተላከው ሃይል ጋር እንዴት ነው የምገናኘው?” አለ ኣንድሬ ኦማሪ፡፡

“ወደዛው ትበራለህ። እንዳልኩህ እራት የኮማንዶ ሃይል ከነሙሉ ትጥቁ ወደዛው በሮ ከአውሮፕላኑ ሳይወርድ- በተጠንቀቅ ይጠብቅሃል፡፡በተረፈ ከዚህ ከተላከው ሃይል ጋር የሚኖርህ ግንኙነት ቀጥታ በሃይሉ አዛዥ አማካኝነት ይሆናል፡፡”

ጀኔራሉ ተክታታይ ትዕዛዞችን ሲያስተላልፍ ከቆየ በኋላ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲቆም በክፍሉ ውስጥ ያሉት ሁሉ ተነስተው በተጠንቀቅ ቆሙ::

“አሁን” አለ ጀኔራሉ ሰዓቱን እየተመለከተ፡፡ “ከጠዋቱ አስራ ሁለት ከሩብ ነው፡፡ ዣክ አንድ ሰዓት ተኩል ከመሆኑበፊት ፈንጂዎች እንዲፈነዱ፡፡አንድሬ ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ሁለት ድሬዳዋ ታርፋለህ፡፡ ከሁለት እስከ ሦስት ባለው ሰዓት ሃይልህን አቀናጅተህ ስራህን ትጀምራህ” ጀኔራሉ በረጅሙ ተነፈሰና ያመነታ መስለ። “ከአሁን ወዲያ ይህን ጉዳይ እዚሁ ልናቆየው አንችልም:: ዝርዝር ሁኔታውን ለበላዮቹ ማስታወቅ ይኖርብኛል፡፡ምን ያህል አደገኛ ሁኔታ ላይ እንዳለን አስተውሉ፡፡ ለምትሰሩት ማንኛውም ስህተት በቀጥታተ ጠያቂ አድርጌ አቀርባችኋለሁ፡፡” አለ ጀኔራሉ የዣክ ዊልያምን ፊት እየሸሸ፡፡ “መሄድ ትችላላችሁ::”

ሁለቱ ባለስልጣናት ከወጡ በኋላ ጀኔራሉ በወንበሩ ላይ ተቀመጠና ፊቱን በተጠንቀቅ በቆመው ኮሎኔል ማርቆስ ላይ መለሰ፡፡

ጋዜጠኛዋጋ ሄደህ ጥበቃውን ተከታተል፡፡” አለው ከፊቱ ዘወር
እንዲልለት በመፈለግ፡፡ ኮሎኔል ማርቆስ በተጠንቀቅ ሠላምታ ሰጥቶ ፊቱን
መልሶ ወደበሩ ሲያመራ “ኮሎኔል” አለ አለቅየው ፊቱ ላይ ንዴት የተቀላቀለበት ጽያፌ እየተነበበ …እሷ ደግሞ እንዳታመልጥህ፡፡”

ኮሎኔል ማርቆስ በድጋሚ ወታደራዊ ሠላምታ ኣቅርቦ በፀጥታ ከክፍሉ ወጣ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በተከታታይ የፈንጂ ድምጾች ድሬዳዋ ስትናወጥ ናትናኤል ከተኛበት ስስ ፍራሽ ላይ በርግጎ ተነሳ፡፡

ተከታትለው ሌሎች ሁላት ፍንዳታዎች ጠባቧን ከተማ ሲንጣት፤ ያለበትን ክፍል በርና መስኮት ሲያርገፈግፉት ናትናኤል ተነስቶ ቆመና ዙሪያውን ቃኘ፡፡ በፍንዳታው ውስጥ አጉረምርሞ ተገላብጦ መልሶ የተኛው ካልቨርት አሁንም ከገባበት የስካር ባህር ብቅ ያለ አይመስልም፡፡
ናትናኤል ካልቨርትን በጭንቀት ተመለክተው፡፡ ከአንድ ቀን በፊት
ሲያገኘው ብስጭት ተስፋ መቁረጥና ስካር የተሻሙት ግማሽ እሬሳ ነበር፡፡
በዛን ሰዓት ናትናኤል ከካልቨርት ጋር ቁጭ ብሎ ለማውራት መሞከር
ፍሬቢስ መሆኑን ለመረዳት አልተቸገረም። ይልቁንም በቅድሚያ የካልቨርትን አመኔታ ሊያገኝበትና ሊያረጋጋውም የሚችልበትን መንገድ መረጠ ከጎኑ ፍራሽ ላይ ቁጭ ብሎ አረቄ ሲጠጣ ቆየ፡፡

አለፍ አለፍ እያለ ግራ የተጋባው ካልቨርት
“ማነህ? ለምን አትገለኝም?… ምንድነው የምትጠብቀው?” እያለ በስካር መንፈስ ሲወተውተውም ናትናኤል መልስ አልሰጠውም።

ከሰዓት በኋላ ናትናኤል ካልቨርት ከተሸሸገበት ጠባብ ክፍል ውጥ
የምሥራችን እናት አነጋገራቸው፡፡

“ድንገት በመምጣቴ ይቅርታ…የላከችኝ የምሥራች ነበረች፡፡ ግን በዚህን ዓይነት ሁኔታ ላያ ይሆናል ብለን አልገመትንም ነበር፡፡" እላቸው የካልቨርት ስካር ያስደነገጠው መስሎ፡፡

“ምን አባቴ ላድርገው? በጠዋት ተነስቶ አረቂ ነው ማታ ተኝቶ አረቂ ነው…ምግብ ሲሉት በሩቁ እጁን ያውለበልባል አረቄ የከለከልኩት ጊዜ ሲያቃስት ማደር ነው..ተው አይሉት ነገር አፉ እንግዳ…እኔ'ኮ ጨነቀኝ፡፡

አንድ ነገር አድርጊ አልላት ነገር ድምጿ ጠፋ፡፡ሰወ አልክባት..ማንም ማወቅ
የለበትም ብላኝ እንዴት አድርጌ ለሰው ልናገር?” ሴትየዋ የተማረሩ መሰሉ፡፡

“ግድ የለም:: ዋናው ነገር በህይወት መቆየቱ፡ ነው:: ብቻ እርሶ ትንሽ ተቸገሩ፡፡ የምሥራችን አይሆንም አታስቸግሪያቸው ብያት ነበር፡፡ እምቢ አለች እንጂ፡፡” በተቻለው የልጃቸው የምሥራች የቅርብ ወዳጅ ለመምሰል ጣረ፡፡

“እኔማ ምን ችግር አለብኝ..ቢበዛ የገዛ ገዝቡን፤ ቢጠጣ የገዛ ብሩን ከኔ ሳንቲም
አላወጣ.…ግን ቢሆንም... ሰው እንዲህ ራሱን በመጠጥ በመርዝ ልበለው እንጂ ሲገድል ሲያዩ ህሊናም አያርፍ፡፡”

“እውነት አለዎት፡፡”
👍4
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

...“ውሸቴን አይደለም ካልቨርት። እርግጥ ጥፋቱ የኔው የራሴ ነው::ወደ እርሷ ባልሄድ ምናልባት ያች ሴትዮ አግኝታ አታጠፋትም ነበር፡፡”

ካልቨርት በቆመበት ቁልቁል ናትናኤልን ተመለከተው፡፡ ወዲያው የሰማው ቀስ በቀስ እየሰረገ ወደ ሰውነቱ ሲገባ በፍራሿ ላይ ተቀምጦ ፊቱን ጉልበቶቹ መሃል ቀብሮ በፀጥታ ያለቅስ ጀመር፡፡ እልህና ንዴት ትከሻውን ሲሰብቁተ ናትናኤል ለጥቂት ደቂቃዎች በትዕግሥት ጠበቀውና ቀጠለ፡፡

“ከመሞቷ በፊት እናቷጋ ድሬዳዋ መሆንህን ብቻ ተነፈሰችልኝ፡፡”
ናትናኤል ታሪኩን በሙሉ አንድም ሳያስቀር እውርቶ ሲያበቃ ወደኋላ ፈቀቅ አለና ከፍራሹ ኋላ ያለውን ግድግዳ ተደግፎ ተቀመጠ።ለተከተሉት በርካታ ደቂቃዎች በክፍሉ ውስጥ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ እልፎ አልፎ
ብቻ ካልቨርት መሃረቡን እያወጣ አፍንጫውን ሲያፀዳዳና ሳግ ሲተናነቀው
ከሚሰማው ድምፅ በስተቀር ዝምታ ሽፈናቸው፡፡

“ሲገድሏት እዛው ነበርክ ማለት ነው?” አለ ካልቨርት ጉንጮቹን ያረሰረሰውን እንባ እንኳን ለመጥረግ ሳይሞክር ካቀረቀረበት ከጉልበቶቹ መሃል ቀና ብሎ ናትናኤልን እየተመለከተው፡፡

ናትናኤል በዝምታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ 'አዎ'

ካልቨርት በእንባ የደፈረሱ አይኖቹን ከጣሪያው ላይ ሰቅሎ የሚተናነቀውን እንባ ታገለው፡፡

“እና ምንድን እንድነግርህ ነው የምትፈልገው?” አለ በተሰበረ ድምፅ ጭንቅላቱን ወደፊት ጉልበቶቹ ላይ ጣል አድርጎ፡፡

“ሁሉን፤ እነማናቸው? . ምንድነው የሚሰሩት? አንተስ ለምን ተሰወርክ? ሁሉን ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡”

“ዋጋ የለውም።” አለ ካልቨርት ዓይኖቹን ቦዘዝ አድርጎ፡፡ “እንዴት ዋጋ የለውም? ምስጢሩን ስረዳ ብቻ ነው ራሴንም ሆነ
አንተን ልረዳ የምችለው፤ እነዚህን ነፍሰ ገዳዮች ላቆማቸው የምችለው፡፡”

“ነፍሰ ገዳዮች አይደሉም::”

“ታዲያ ምንድናቸው? ከዚህ በላይ ምን ትፈልጋለህ?”
ነገርኩህ ነፍሰ ገዳዮች አይደሉም!” በስጨት አለ ካልቨርት፡፡
ድጋሚ መሃረብ አውጥቶ አፍንጫውን እያጸዳዳ፡፡

“የምሥራችን የገደሏት እነርሱ ፡ መሆናቸው እንዳልተዘነጋህ
እርግጠኛ ነኝ”
“እነሱ አይደሉም፡፡ አስታውስ… የገደለቻት ሴት…”
“ያው ነው!” አቋረጠው ናትናኤል።
“ያው እይደለም!” ካልቨርት በስጨት አለ። “ማነው ስምህ.…
ናትናኤል ነው ያልከኝ? ብዙ የማታውቀው ነገር አለ፡፡ ምንም አታውቅም ማለት ይቀላል፡፡ ነፍሰ ገዳዮች አይደሉም።አዎ ጓደኛህን ገድለውብህ ይሆናል!አንተንም ሊያሳድዱ ይችላሉ ግን አንተ እንደምትለው አይደሉም፡፡”

“የፈለጉትን ይሁኑ፡፡ ብቻ ልናቆማቸው ይገባል፡፡ ትሰማኛለህ?”
“ልናቆማቸው አይገባም፡፡ ተስፋችን እነርሱ ብቻ ናቸው። የቀረን ጭላንጭል ብርሃን ቢኖር የእነርሱ ዓላማ ብቻ ነው፡፡ ዳር መድረስ አለባቸው።”

ናትናኤል የሚያዳምጠው ሁሉ እንቆቅልሽ ሆነበት፡፡

“ምንድነው የምታወራው የሚስሩትን ትደግፋለህ ማለት ነው?
ወይስ…”

ካልቨርት በመስማማት ጭንቅላቱን ነቀነቀ፡፡

“ታዲያ ለምን ተሰወርክ…እነሱስ ለምን ያሳድዱሃል ለምን ለሌሎች ህይወት መጥፋቱ ምክንያት ሆንክ?" ናትናኤል መጥፎ ስሜት ጉሮሮውን ሲተናነቀው ተሰማው፡፡ “ጓደኛዬ የሞተው ለምን ይመስልሃል? ቤቴን ትቼ ጠፍቼ የቀረሁ ለምን ይመስልሃል? አንተ እዚህ አረቄ በምትጋትበት ሰዓት ሌሉች የአንተን ዱካ ሲያፈላልጉ በጥይት እየታደኑ ነበር፡፡ ይገባሃል የምልህ?” በንዴት ተንቀጠቀጠ ናትናኤል።

ካልቨርት ቀና ብሎ በቁጣ የተጨማተረውን የናትናኤልን ፊት
ተመለከተና ድጋሚ አቀረቀረ፡፡

የተቀመጡበት ክፍል በር ተከፍቶ የምሥራች እናት በትሪ ላይ ሁለት ሳህኖች ይዘው ገቡ፡፡ በቅመም የሚሰራው ምግብ ሽታ ከጓዳ ተነስቶ በተከፈተው በር አልፎ የተቀመጠበት ድረስ አወዳቸው፡፡ ከተዘጋው መስኮት ጀርባ ከጓሮ ሴቶች ምግብ ሲያሰናዱ ዕቃ ሲያጣጥቡ የሳህን ኳኳታ ሳቅ ጨዋታ ልጆች ሲጨፍሩ... ልጃገረዶች 'አበባዬ ሆያ… ለምለም…. ' እያሉ ሲዘፍኑ ይሰማል፡፡ ዘመን መለወጫ... መስከረም እንድ... አዲስ እመት፡፡

“ሰሉ ቁርሳችሁን አድርጉ፡፡” አሉ ሴትዬዋ ትሬውን ፍራሹ ጥግ እያስቀመጡ፡፡ ወዲያው በእንባ ያባበጠውን የካልቨርትን ፊት ሲያዩ ደንገጥ ብለው ቆሙ፡፡

“እግዜር ይስጥልንመቼም አስቸገርንዎት።” አለ ናትናኤል የተፈ
ጠረውን ድንጋጤ ለማርገብ፡፡

የምሥራች እናት ቶሎ ፊታቸውን መለሱና ከክፍሉ ወጡ፡፡ ሴትየዋ ቢወጡም ሁለቱ ሰዎች ምግቡን ለመብላት እጃቸውን አላነሱም፡፡

“ናትናኤል በእኔ ምክንያት ስለተፈጸመው ሁሉ እጅግ አዝናለሁ፡፡ግን ልነግርህ የምችለው ነገር የለም፡፡” አለ ካልቨርት ሴትየዋ ዘግተውት የሄዱት በር ላይ አፍጥጦ::

“በጣም ጥሩ!” : ናትናኤል ከተቀመጠበት ትፈናጥሮ ተነሳ ምሥጢሩን አወጣዋለሁ፡የማውቀውን ሁሉ በአገርና በውጭ ለሚገኙ ጋዜጠኞች እበትነዋለሁ፡፡ እርግጠኛ ነኝ… የማወጣው ፍንጭ ምንም ትንሽ ቢሆን ያንተን አድራሻ ይጨምራል፡፡ያ ደግሞ ከትክክለኛው ጆሮ እንደሚደርስ አልጠራጠርም!” ናትናኤል ያለማወላወል ወደ በሩ አመራ፡፡

“ረጋ በል ናትናኤል… ረጋ በል… ምን እያደረግህ እንደሆነ አታውቅም!” አለ ካልቨርት ከተቀመጠበት በርግጎ እየተነሳ፡፡ “ለህይወቴ ፈርቼ ወይ አድራሻዬን እንዳታወጣ ሰግቼ አይምሰልህ ግን አንተ የማትረዳው የከፋ ጥፋት እንዳትፈጽም ስለምፈራ ነው::”

የካልቨርት መደናገጥ ናትናኤልን የልብ ልብ ሰጠው፡፡

“ጊዜዬን አታጥፋ! ለጓደኛዬ ሞት ምክንያት ሆነሃል፡፡ ከአሁን ወዲያ
ግን ለእንዳንተ አይነቱ ጅል ህይወቴን አደጋ ላይ አልጥልም::” ናትናኤል
የክፍሉን በር ከፍቶ ቆመ፡፡ “ትነግረኛለህ አትነግረኝም?”

ካልቨርት በተስፋ መቁረጥ ራሱን አወዛወዘና ተመልሶ ከፍራሹ ላይ
ዘፍ አለ፡፡

“ቀጥል… እውነቱን ነው የምፈልገው፡፡” አለ ናትናኤለ በሩን ዘግቶ ካልቨርት ጎን ፍራሹ ላይ እየተቀመጠ፡፡

“ከየት እንደምጀምር አላውቅም፡፡” ካልቨርት በባዶው አየር ላይ አፈጠጠ፡፡

“ከኔ ልጀምር ከእነርሱ?” አለ በለሆሳስ ናትናኤልን ሳይሆን እራሱን የሚጠይቅ ይመስል።

“ከሚቀድመው ጀምርልኝ::” ናትናኤል እያበረታታው::

“በወታደራቂ አታሺነት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የአገሬ ኤምባሲ ውስጥ እንድሰራ ከመመደቤም በፊት በአገሬ የአየር ወለድ ኮማንዶ ሠራዊት ውስጥ በኋላም በተለያዩ አገሮች በወታደራዊ አታሼ የሥራ መደብ ሰርቻለሁ፡፡ በዚሁ የስራ መደብ ሉሳካ በሚገኘው ኤምባሲያችን ውስጥ እየስራሁ በነበርኩበት ጊዜ ነው... ደቡብ አፍሪካ በነጮች ስር በነበረች ጊዜ.. የደቡብ አፍሪካ የነጮች የስለላ ድርጅት ተደራሲ ወኪል አድርጎ የመለመለኝ፡፡ ወድጂ አልነበረም፡፡ ያኔ ባለትዳር ነበርኩ፡፡ ባለቤቴ ከመሞቷ በፊት ነው የማይሆን ነገር ሳደርግ ያዘኝ:: የሚፈልጉትን ካላቀበልኳቸወ ያደረኩት ሁሉ በፎቶግራፍ ከተደገፈ ማስረጃ ጋር ለባለቤቴ እንደሚደርሳት አስጠነቀቁኝ:: እወዳት ነበር፡፡ አሁን ይቆጨኛል...ያኔ ግን ከባለቤቴ ጋር መለያየቱ ሞት መስሎ ታየኝ፡፡ ወጥመዳቸው ውስጥ ገባሁላቸው፡፡”

“ምንድን ነበር ካንተ የሚፈልጉት፡፡”

“ያን ጊዜ ናሚቢያ ነፃነቷን ገና አልተቀዳጀችም ነበር፡፡ የስዋፖ
ሽምቅ ተዋጊዎች ከአንጎላና ከዛምቢያ ከፍተኛ ድጋፍ ይሰጣቸው ነበር፡፡
የጦር ሠፈሮችም ነበሯቸው፡፡ በተለይ ከዛምቢያ የሚነሱ የስዋፖ አደጋ ጣይ
ቡድኖች በካኘሪቪ ሰርጥ ውስጥ በተደጋጋሚ በነጮቹ ላይ ጥቃት ያደርሱ ነበር፡፡ ያንን ነበር ከእኔ ለማግኘት የሚሹት ስዋፖ በዛምቢያ ውስጥ ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ፡፡ ለነገሩ እዛ የቆየሁት በጣም ለአጭር ጊዜ ነዉ ሁለት ዓመት አይሞላም፡፡ ቢሆንም በጊዜው
👍3
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....“ዝግጅቱ በተጀመረ በሦስተኛው ወር ምሥጢሩ አፈትልኮ ተገኘ፡፡ ማን አወጣው? እንዴት አወጣው? የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ብቻ በእንግሊዞቹ
ኦብዘርሸርና በፈረንሳዮቹ አፍሪካን ዲፌንስ ላይ ያዕቅዱ ፍንጭ ታትሞ
ወጣ፡፡ እውነቱን ንገረኝ ካልካ ምሥጢሩን ያወጣው የዕቅዱ ጠንሳሽ እራሱ
ነበር፡፡”

“እንዴት? የዛ ምሥጢሩን ሰምን?”

“ቆይ… ዝም ብለህ ተከተለኝ.… እርግጥ ይህ የእኔ መላምት ነው… ግን ዳር ስንደርስ አንተ እራስህ ተመሳሳይ መላምት ላይ እንደምትደርስ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እንዳልኩህ ምሥጢሩ አፈተለከ፡፡ ይህ እንደተሰማ የተለያዩ የአፍሪካ ባለሥልጣናት ከወዲያ ወዲህ ሲሯሯጡ ሰነበቱ፡፡ ውጤት ወታደራዊ ዝግጅቱ እራሱን በቻለ ምስጢራዊ መልክ እንዲካሄድና በማንኛውም አገር የሚገኝ ቅርንጫፍ ክፍል በቀጥታ ከዋናው ማዘዣ ካልሆነ በስተቀር በሚገኝበት አገር የመከላከያ ሚኒስቴርም ሆነ ሌላ መንግሥታዊ አካል ጣልቃ ገብ ቁጥጥርም ሆነ ተፅዕኖ እንዳይደረግበት ስምምነት ላይ ተደረሱ፡፡

“ዓላማው ዝግጅቱን አንድ ወጥ
በሆነ መልኩ ለማፋጠንና ምሥጢሩም እንዳይባክን ለመጠበቅ ተብሎ የተቀየሰ ነበር፡፡ በሌላ መልኩ ለተመለከተው ደግሞ ስምምነቱ አገሮች በተናጠል በክልላቸው ውስጥ በሚደረገው ወታደራቂ ዝግጅት ላይ መረጃ እንዳያገኙ የሚያግዳቸው ሆነ፡፡ ይህንን ስምምነት ተቃውሞ የሚቆም አገር ደግሞ ቀደም ሲል የተከሰተው አደነት የምሥጢር መዝረክረክ እንደማይፈጠር ማረጋገጫ ማቅረብ ሊኖርበት ሆነ፡፡ የዚህን ዓይነት ዋስትና መስጠት ደግሞ ለማንኛውም አገርዐአዳጋች ነው፡፡ ያም ሆነ ደሀ ምሥጢሩ በጨቅላ ደረጃው በማፈትለኩ ከዛ በኋላ የወታደራዊ አካሉ እቅሰቃሴ ሁሉ ከኣገሮች ቁጥጥር ውጭ በምስጢር
ለመሆን በቃ፡፡ ይሀን ነበር የፈለገው የዕቅዱ ባለቤት-እንቅስቃሴውን ያላታዛቢ
በቀጥታና በምስጢር መምሪት፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላ የአፍሪካ መሪዎች
የሚያጊንት መረጃ ሁሉ ከዋናው ማበዣ በሚተላለፉ በገባዎች ላይ ብቻ
የተወሰነ ሆነ፡፡

በሌላ ቋንቋ የአፍሪካ መሪዎች የሚያውቁት የእንቅስቃሴው መሪ እንዲያውቁ የሚፈቅድላቸውን ብቻ ሆነ:: ይህም እያንዳንዱ አገር አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ ኤምባሲው ባስቀመጠው የወታደራዊ አታሼው
በኩል ብቻ የሚፈጸም ነበር፡፡

“የወታደራዊ አካሉ መረብ እየሰፋና እየተጠላለፈ በመጣ ቁጥር
በየአገሩ የሚገኙ እውቀት ችሎታና ተሰሚነት ያላቸወ የጦር ባለሙያዎች
በጥንቃቄ እየተጠኑና አየተመዘኑ በዚሁ አካል ይዋጡ ጀመር፡፡ ብቻ ምን
ልበልህ..በሁለት ዓመታት ውስጥ እጅግ ጠንካራ፤ እጅግ ሰፊ፧ እጅግ ምስጢራዊ ወታደራዊ አካል አፍሪካ ውስጥ በስውር ተገንብቶ አበቃ:: አልፎ ኣልፎ አንዳንድ ባለስልጣኖች የወታደራዊ ኣካለን አለቅጥ ምስጢራዊ መሆንና መግዘፍ፡ የመቃወም ፍንጭ ሲያሳዩም ያለምንም ምህረት በተናጠል እየተለቀሙ ተወገዱ፡፡ ከዚህ ወዲያ ማንኛውም ምስጢሩን የሚያውቅ ባለሥልጣን ድምፁን ዝቅ እድርጎ መናገርን መረጠ፡፡”

ይህን 'አካል የምትለውን ማነው የሚመራው?” ናትናኤል ጠየቀው፡፡

“በትክክል እነማን እንደሆኑ አላውቅም...ግን ከአፍሪካ አገሮች ሁሉ
የተውጣጡ የጦር አዛዦች እንደሆነ አውቃለሁ፡፡”

“እሺ ቀጥል።”

“ሁኔታው በዚህ ላይ እንዳለ ከሁለት ወር በፊት ወደ አገሬ ተጠራሁ፡፡ አገሬ ውስጥ የቆየሁት ግን ለእራት ሰዓታት ብቻ ነበር፡፡
ሞንሮቪያ እንደደረስኩ ወደ መከላከያ ሚኒስቴር ተወስጀ ስለዚሁ ኣካል
መጠነኛ ገለፃ ከተደረገልኝ በኋላ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ግልጋሎቴን
ለዚሁ አካል እንደምሰጥና ተጨማሪ መመሪያዎችንም ለመቀብል ወደ ሌላ
ስፍራ የምወሰድ መሆኑ ተነገረኝ፡፡

“እንዳልኩህ ሞንሮቪያ ከደረስክ ከአራት ሰዓታት በኋላ በሌላ አነስተኛ አውሮፕላን የሁለት ሰዓታት ጉዞ እድርጌ ከአንድ በረሃማ ቦታ አረፍን፡፡ ቦታው የቶ እንደሆነ ለመናገር ያስቸግራል። እርግጥ ባንዲራ
ተሰቅሉ ይውለበለባል ግን ባንዲራው አንድ ነው፤ የአፍሪካ አንድነት
ድርጅት ባንዲራ “ከአውሮፕላኑ እንደወረድኩ ማረፊያ ቦታ ተሰጠኝ፡፡ ከእኔ ቀደም ብለው የደረሱ ነበሩ፤ እኔ ከገባሁ በኋላም ሌሎች በተከታታይ ከተለያዩ
እገሮች በሄሊኮኘተሮችና በአነስተኛ አውሮፕላኖች እየተጫኑ ገቡ፡፡ በማግስቱ
ፕሮግራሙ ተጀመረ፡፡ በአጠቃላይ አስራ እንድ ነበርን፡፡ በኋላ እንደተረዳሁት
ሁላችንም በአዲስ አበባ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ኤምባሲዎች ውስጥ
እንድንሰራ የተመረጥን ነበርን፡፡ እንደውም አንድ ሁለቱን ኤአዲስ ኣበባ ውስጥ ቀደም ብዬ አውቃቸው ስለነበር እዛ በረሃማ ቦታ በቆየሁባቸው ጥቂት
ቀናቶች ልቀርባቸው ችዬ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ የሞሮኮ ወታደራዊ አታሼ የነበረው መሃመድ ባስሪ እኔ በነበርኩባቸው ቀናቶች እዛው ነበር፡፡ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በወሩ ከጊነው ሰው ጋር ተገድሎ ተገኘ፡፡”

“ምን ላይ ነበር የኘሮግራሙ አትኩሮት?» ናትናኤል ወደፊት አዝምሞ ጠየቀው፡፡

“ዝርዝር ነጥቦች ውስጥ አልገባም፡፡ በአጠቃላይ የቆየነው ለሁለት ሳምንታት ነበር፡፡ በመጀመሪያው ሳምንት በአፍሪካ ወቅታዊ ችግር ላይ ነበር ያተኮርነው፡፡ በሁለተኛው ሳምንት ግን ስለ 'ቆንጆዎቹናሰ ስለዓላማው! ስለእን ቅስቃሴው ነበር በጥቅሉ፡፡ በአጭሩ ከመጪው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ
በኋላ የአፍሪካ መንግሥታት እንደማይኖሩ ነበር የተገለጸልን፡፡››

“ምን ማለት ነው ይሄ?” ናትናኤል ግራ ገባው::
“ነገርኩህ'ኮ ከጥቂት ቀናት በኋላ የምትኖረው አፍሪካ አንድ አፍሪካ
ብቻ ትሆናለች::”

“እንዴት? አልገባኝም፡፡”ናትናኤል የሚያዳምጠው ቅዥት መሰለው፡፡

“የስብሰባው ጊዜ ሲደርስ ጠቅላላ የአፍሪካ መሪዎች ተጠቃለው
አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ይህ ከተገባደደ በኋላ በመላው አፍሪካ በየአገሩ ያሉ
የአካሉ ቅርጫፍ ክፍሎች በያሉበት አገር ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት
አድርገው ሥልጣን ይጨብጣሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ማንኛውም መመሪያ ከአፍሪካ
አንድነት ድርጅት ይወጣል፡፡ በአዲስ አበባ በየአገሮች ኤምባሲዎች ውስጥ
በሚገኙ ወታደራዊ አታሼዎች አማካኝነት መመሪያዎች እንደአስፈላጊነቱ ለየአገሮች ይተላለፋሉ፡፡ አበቃ::”

“እንዴ! ስንት መፈንቅለ መንግሥት ማለት ነው?” ናትናኤል ካልቨርቶን አተኩሮ ተመለከተው፡፡ ሰውየው ድጋሚ የሰከረ መሰለው፡፡

“ሃምሳ ሦስት፡፡”
“የፈጣሪ ያለህ! ይህ'ኮ እልቂት ነው፤ ሃምሳ ሦስት አገሮች ውስጥ ጦርነት መፍጠር እኮ ማለት ነው::መቼም ሁሉም አሜን ብሎ አይቀበልም:: ጦርነት ይኖራል፡፡”

“እልቂት አይደለም፡፡ ይኽው አካል ተብትቦ ያልያዘው ወገን በዝብዞ
ያላወቀው ምስጢር በየትኛውም አገር አታገኝም፡፡ ውስጥ ውስጡን በየአገሩ
ጠንካራና ተሰሚ ደጋፊዎች አሉት፤ ውስጥ ውስጡን የየአገሩን ደካማ ጎን
አብጠርጥሮ ያውቃል፤እነማን መያዝ መታሰር.መወገድ አለባቸው? እነማን
ሊታመኑ ይገባል? እነማን ባንዳዎች ናቸው? እነማን ዲቃላዎች ናቸው?
እነማን ንፁህ አፍሪካውያን ናቸው? ሁሉ ይታወቃል።”

“አሁጉራዊ መከላከያ የተባለውስ? ማለቴ" ናትናኤል ግራ ገባው::

“ሽፋን ነው:: አየህ... ወታደራዊ አካሉ የአፍሪካ መንግሥታት እያወቁና ሙሉ ድጋፍ እየሰጡት በምስጢር ለመነቃነቅና የዚህን ዓይነት ስፋት ያለው ወታደራዊ ዝግጅት ለማድረግ በየአገሩ የሚገኙትን ከፍተኛ መኮንኖችን በስሩ ለማሰባሰብ አንድ ተቀባይነት ያለው ሽፋን ያስፈልገው
ነበር፡፡ አህጉራዊ የመከላከያ ሃይል ተስማሚ ሽፋን ነበረ፡፡”

“እና የአፍሪካ መንግሥታት ሁሉ ስለእንቅስቃሴው ምንም
አያውቁም ማለት ነው?''

“ያውቃሉ፡፡ዝግጅቱ ሁሉ: ተቀነባብሮ በየአገሩ ያሉ ቅርንጫፍ ኣካላት
👍3
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


...የሠራሁትን ጥፋት ለአገሬ መንግሥት እንደሚያሳውቁ እስጠነቀቁኝ፡፡ በዚህ
ላይ እንዳለን የጊኒና የሞሮኮ አታሼዎች ተገደሉ፡፡

“አየህ... እኔ ምስጢሩን ላወጣ አልፈለግሁም:: እርግጥ በአንድ
ወቅት በገዛ አገሬ ላይ ሰልያለሁ፡፡ በመላው አፍሪካ ላይ ይህን በደል
ልፈጽም አልቻልኩም፡፡ የምከዳው አንዲትን አገር ሳይሆን መላውን አፍሪካ
ነበር፡፡ እንዳስፈራሩኝ ከዚህ ቀደም የሰራሁትን ወንጀል ቢያወጡ: ደግሞ
ያለጥርጥር እንደጊኒና ሞሮኮ ወታደራዊ አታሼዎች መሰበሬ ሆነ:: ተሰወርኩ፡፡” ካልቨርት የያዘውን ግማሽ መለኪያ አረቄ ጨልጠው::

“የጊኒና የሞሮኮ አታሼዎች ምስጢር አውጥተው ነው ማለት ነው ለሞት የበቁት?” አለ ናትናኤል ፊቱን አኮማትሮ።

“በእርግጥ አላውቅም.… ግን ሊሆን ይችላል፡፡ አየህ.. ይኸው አካል
የተጠናከረ የመረጃ መረብ አለው:: ከፍተኛ ቁጥጥርም ያደርግብናል፡፡
ምንም እንኳን ቀደም ብሎ ስለ እያንዳንዳችን ጥልቅ ጥናት የተደረገ ቢሆንም አንዳንድ ያልታሰቡ ሁኔታዎች ለመቋቋም ሲባል ይከታተሉናል፡፡ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ በሁለቱ ኣታሼዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከፍተኛ የአፍሪካ ባላሥልጣናት ላይም የተፈጸመውን ግድያ ከመፈጸም ወደኋላ የሚል ኃይል አይደለም፡፡ብቻ ሁለቱ አታሼዎች ምሲጥር፡ አውጥተዋል ብዬ ስመናገር ያዳግተኛል አውጥተውት ቢሆን እስካሁን ብዙ መፍረክረኮች ይከተሉ ነበር፡፡ቢሆንም አመኔታ እስከታጣብን ድረስና የአንተ መኖር ለአፍሪካ ስጋት
እስከሆነ ድረስ ያለማመንታት ትወገዳለህ፡፡ ብዙዎቹ ተወግደዋል፡፡ ለዚህ ነው ከሁሉ የተሰርኩ፤ ከምደግፋቸውም ከምፀየፋቸውም የተሰወርኩ፡፡እኔም እንደሌላው አፍሪካዊ አፍሪካ አንድ ሆና ማየት እፈልጋለሁ፡፡”

"በመጀመሪያ ለሌላ ባዕድ ድርጅት መስራትህን እንዴት ሳይደርሱበት ቀሩ?”

“ስህተት ነው፡፡ ስህተት ነው የፈፀሙት፡፡ እርግጥ ጠንቃቃ ነበርኩ፤ ቢሆንም መሳሳታቸው በጊዜው እኔንም ያስደነገጠኝ ጉዳይ ነበር።”

“ከጠፋህስ ሰኋላ እንዴት ሊያገኙ አልቻሉም? ማለቴ መንግሥት የሚደግፋቸው እስከሆነ ድረስ አንተን ማደን ያን ያህል አስቸጋሪ አይሆንም...
ሌላውን ብንተወው እንኳን አድራሻህን እንድትነግራቸው የምሥራችን
ሊያስገድዷት ይችሉ ነበር፡፡ እኔ'ኮ ግራ የሆነብኝ ይህን ያህል በመላው አፍሪካ
እየተርመሰመስ ያለ ኃይል አድኖ ሊያገኘው ያልቻለውን ሰው እንዴት እኔ
ላገኝህ ቻልኩ?”

“ሊያገኙኝ ያልቻሉት ስላልሞከሩ ብቻ ነው፡፡ለመሰወር እንደቆረጥኩ
ከዚህ በፊት ያጠፋሁትን ጥፋት በገዛ አገሬ ላይ የሰራሁትን ወንጀል በሙሉ
ዘርዝሬ በጽሁፍ አስተላዕፍኩላቸው፡፡ይህንንም ያለፈ ጥፋቴን እንደማስፈ
ራሪያ በመጠቀም የባዕድ የስለላ ድርጅቶች ምስጢሩን ከእኔ ለማግኘት
በመጣር ላይ መሆናቸውንና ምስጢሩን አውጥቼ ከዳተኛ ከመሆን አለበለዚያም ነጮቹ ያለፈ ስራዬን ይፋ አውጥተው ለጥፋት ሳይዱርጉኝ በፊት ለመጥፋት መወሰኔን ገለጽኩላቸው፡፡ ሆኖም እኔን አድነው ለማግኘት ቢጥሩ ወይም የምሥራችን ለማስገደድ ቢሞክሩ ደብቄ የያዝኩት ምሥጢር የጋዜጦች ቆሎ እንደሚሆኝ እስፈራራኋቸው፡፡” ካልቨርት በቀኙ የጨበጠ ውን ባዶ መለኪያ አተኩሮ ተመለከተው፡፡ “ለዚህ ነው ሳይተናኮሉኝ ባለሁበት ሊተውኝ የመረጡት። ድምጼን አጥፍቼ ጭንቅላቴን ቀብሬ ሰዓቷ እስክትደርስ ከታገለኩ ከዚያ ወዲያ ሊበቀሉኝ እንደማይሞክሩ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ምክንያት አይኖራቸውማ፡፡ ለምስጢራቸው ደህንነት ስል ነዋ የተሰወርኩት፡፡”

“ታዲያ የምሥራችን ለምን ገደሏት?”
“እመነኝ እነሱ አይደሉም የገደሏት… ነጮቹ ናቸው፡፡”
“እነማን ናቸው ነጮቹ?”
“እንግሊዞቹ አስራኤላውያኑ… አላውቅም”
“እንዴት ለምን?”
“አየህ እንዳልኩህ ከመጥፋቱ በፊት በምሥራች ላይ አደጋ ሲደርስ
ምሥጢሩን እንደማመጣ ዝቼ ስለነበር ጥበቃ ይደረግላት ነበር በስውር፡፡”

“በማን?”
“በቆንጆዎቹ።”
“ማን እንዳይጎዳት?”
“በብስጭት ምሥጢሩን ይፋ እንዳደርገው ሲሉ ነኞቹ የምሥራችን
ሊያፍኗት ወይ ሊገሏት ይችላሉ ብለው በመፍራት ይመስለኛል። አንተም
ከሆቴሏ ድረስ ሄደህ አንድ ክፍል ውስጥ አስገብተሃት ስትዘጋ የነጮቹ
ቅጥረኛ መስለሃቸው አንድ ነገር እንዳታደርጋት በመፍራት ይሆናል
ቆንጆዎቹ ሊያቆሙህ የሞከሩት፡፡”

“ግን እንዴት ነው ነገሩ?” ናትናኤል ግራ ተጋባ፡፡ “ያ የባዕድ የሆነ የስለላ ድርጅት ኢትዮያውያንን መልምሎ አሰማርቷል ማለት ነው? የገደለቻት ሴት'ኮ ያለ ጥርጥር ኢትዮጵያዊት ነች::” አለ ናትናኤል ሲቲና ፊቱ ላይ ግጥም ስትልበት::

“አይደለም አይደለም::” አለ ካልቨርት የናትናኤል ውሱን እውቀት ነገሩን ሁሉእንዳዘበራረቀበት ሲረዳ፡፡ “ለነጮቹ የስለላ ድርጅት በአዲስ አበባ
ውስጥ የመስክ ስራ እየሠራላት ያለ ሞሳድ ነው፡፡ እሥራኤል ቀደም ሲል
ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የኢትዮጵያ አይሁዳውያንን
መልሳ ወደ አዲስ አበባ በብዛት አስገብታ የመረጃ ስራ እያሰራቻቸው ነው::”

“ለምን?” ናትናኤል አቋረጠው፡፡ “እሥራኤል ለምን ብላ ለነጮቹ
ትሠራለች? ከኢትጵያ ጋር ያላት ግንኙነት መጥፎ አይደለም!እንደውም ግንኙነታችን ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ነው::”

“የስለላ መረብ የምትዘረጋው በጠላትህ ላይ ብቻ አይደለም። ስለላ በአጭሩ መረጃዎችን መሰብሰቢያ መንገድ እንጂ የግድ አንዱ አንዱ ካለው
ጥላቻ የሚመነጭ አይደለም፡፡
አስታውስ እሥራኤል በ1980ዎቹ መጨረሻ በዋንኛ ደጋፊዋ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ሳይቅር ስለላ ስታካሂድ ተደርሶባታል፡፡ አይደለም፡፡ እሥራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ካላት ግንኙነት ጋር የተያያዘ አይደለም::”

“ታዲያ ለምን?” ናትናኤል አፈጠጠ፡፡

“በመጀመሪያ ነገሩ የተለመደ ነው::የተለያዩ የመረጃ ቤቶች አንዱ
ለአንዱ ውለታ መፈጻጸሙና መረጃ መለዋለጠ የተለመደ ነው፡፡ ግን
እሥራኤል እዚህ ውስጥ አጇን የከተተችው ለራሷ ስትል ነው፡፡ አየህ
አፍሪካ ተባብራ ለመንቀሳቀስ ከቻለች ምናልባት በግብጽና በጥቂት የሰሜን
አፍሪካ አገሮች ገፋፊነት አጥፊ እርምጃ በእርሷ ላይ እንዳይፈጸም የሰጋች
ይመስለኛል ለዚህ ነው ሁኔታውን ከወዲሁ ለመከታተል የመረጠችው::”

“እና…. የምሥራችን የገደሏት…”
ቆንጆዎቹ አይደሉም፡፡ የነጭ ጠላቶቻችን ናቸው::” አለ ካልቨርት አቋርጦ::

“ታዲያ እሁን ምን ልታደርግ ነው? ምሥጢሩን ልታወጣ ነው
ወይስ…?”

ካልቨርት ጭንቅላቱን ነቀነቀ፡፡

“ስታየኝ ጅል እመስላለሁ? በፍጹም! ሊያታልሉኝ ሲሞክሩ...
እንዳችንን በአንዳችን ላይ ሊያነሳሱ ሲሞክሩ እያየሁ እንዴት እጃጃላለሁ?”

“ጥሩ፡፡ አሁን ምንድነው ማድረግ ያለብን?” ናትናኤል ዙሪያው
ድቅድቅ ጨለማ ሆነበት፡፡
“መጠበቅ፡፡”
“ምኑን?”
“ቀኑን፡፡”
“የቱን ቀን?”
“የስብሰባውን ቀን፤ አፍሪካ አንድ የምትሆንበትን.…”
“አንችልም!” ናትናኤል ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳ።
“ለምንድነው የማንችለው.…የቀሩን ሦስት ቀናት ብቻ ናቸው፡፡ ከዚያ በኋላ ነፃ ነን፡፡”

“ይይዙናል!” አለ ናትናኤል በጭንቀት ተወጥሮ፡፡
“አያገኙንም፡፡”

“ያገኙናል፡፡ ባቡር ጣቢያው ድረስ ተከታትለውኛል ! አይቼዋለሁ፡፡
ሽጉጡኝ ከትከሻው በላይ ይዞ ሊቀጥፈኝ ሲንደረደር እነዛን አይኖቹን አይቻቸዋለሁ! ትሰማኛለህ? ! ድጋሚ ካገኘኝ ስሜን እንኳን አይጠራም፡፡ በጆሮ ግንዴ ነው የሚለቅብኝ! ትሰማኛለህ? ! መሞት አልፈልግም፡፡ በጤና ከቤቴ መመለስ ነው የምፈልገው!” ናትናኤል ሰውነቱ ሳይታወቀው ከቁጥጥሩ ውጭ ሲሆንበት ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ግጥም አድርጎ ይዞ መሃል ወለሉ ላይ ቆመ፡፡

“ቁጭ በል…” አለ ካልቨርት
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


“ይሰማኛል ይሰማኛል ቀጥል፡፡” አለ ጀነራሉ በሬድዮው መቀበያ
ላይ አጎንብሶ::

በሬድዮው ክፍል ውስጥ የክፍሉ ሠራተኞች ያልሆኑ ባለሥልጣናት
ከጀኔራሉ ጀርባ ቆመው ይጠባበቃሉ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ያለው አየር ለክፍሉ
ሠራተኞችና ከውጭ ተግተልትለው ለገቡት ለሁሉም የማይበቃ ይመስል
እያንዳንዱ ሰው ትንፋሹን ይዞ በጭንቀት ተወጥሯል፡፡

“ጀኔራል” አለ ከድሬዳዋ.. የቃል ሪፖርት የሚያደርገው አንድሬ ኦማሪ በሚንኮሻኮሻው የሬዲዮ መልዕክት ማስተላለፊያ ውስጥ “ኦኘሬሽኑ
ያለምንም ችግር እየተካሄደ ነው፡፡ መውጫ በሮች ተዘግተዋል፤ ቃል
የገባህልኝ የስልክ ግንኙነት ግን ገና አልተቋረጠም፤ ሰውየውን በተመለከተ
እንዳንድ ፍንጮችን አግኝተናል፡፡ ከባቡር ጣቢያ ከሸሽ በኋላ የገባበትን
መጠጥ ቤት አግኝተን ወደ እንድ ጋራዥ እንደመሩትና ከጋራዥም ባለቤት
ጋር ተገናኝቶ እንደነበር ደርሰንበታል፡፡ ጊዜው የዓመት በዓል ስለሆነ
የጋራቹን ባለቤት ለማግኘት እቤታቸው ድረስ ልጆቼን ልኬአለሁ፡፡ በተረፈ
በተቻለኝ መጠን አትኩሮት ሳልስብ ፎቶግራፉን የያዙ ሰዎች በከተማው
አሰማርቼ እያሰስኩ ነው፡፡”

ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ የሚለው አንድሬ የደረሰበትን ደረጃ አንድነትና በአንድ በሬድዮው ውስጥ ሲያስተላልፍ አዲስ : አበባ በሬድዮ መቀበያው ክፍል ያሉት ሁሉ በፀጥታ ሲያዳምጡ ቆዩ::

“አንድሬ” አለ ጀኔራሉ “ስልኩን ያላቋረጥኩበት ምክንያት እያንዳንዱን የውጭ ጥሪ እየተከታተልን ስለሆነ መረጃ ለማስተላለፍ ሲሞክር ግንኙነቱን አቋርጠን ስልኩ አድራሻ እንድናጠምደው ስል ነው፡፡ የቤት ለቤት ፍተሻ ለምን እንዳልጀመርክ ግን…”

“አስፈላጊ አይደለም::” አለ አንድሬ ጀኔራሉ መጨረሱን እንዳሳወቀው “በቀላሉ እጄ ላስገባው እችላለሁ:: ከጋራዥ ከገባ በኋላ በተናጠል
የአንድ ሰው አድራሻ ጠይቆ የጋራዥ ባለቤት እንዳመላከቱት ደርሼበታለሁ::
የጋራዥን ባለቤት አግኝቼ አድራሻውን እስካገኘሁ ድረስ ምንም አስጊ ሁኔታ
ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡”

የሬድዮው መልዕክት ተላልፎ እንዳለቀ ከአንድ ሰዓት በኋላ በድጋሚ
የሚቀርበው ሌላ የሬድዮ ሪፖ'ርት እስኪደርስ ድረስ ከሬድዮው ክፍል ውስጥ ተስብስበው የነበሩ ሁሉ ጀኔራሉን ተከትለው ወጡ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ናትናኤልና የየምሥራች እናት ከቤት ወጥተው በጠባቧ የከረኮንች መንገድ በዋናው መንገድ አቅጣጫ ራቅ ብለው ሄዱ፡፡ ከአንድ አነስተኛ ቤትዐእንደደረሱ የየምሥራች እናት ከባለቤቶቹ ጋር በኦሮምኛ ቋንቋ እያወሩ አስክትለወት ገቡ፡፡ ከቤት ከገቡ በኋላ የቤቱ ባለቤት ደርባባ ወፍራም ሴትዮ ከፊት ለፊቱ ድክ ድክ እያሉ ስልክ ወዳለበት ክፍል አስገቡት፡፡

ናትናኤል የስልኩን እጀታ አንስቶ አዲስ አበባ ርብቃጋ ደወለ፡፡ የደወለበት ስልክ ሲነሳ ሁለት ጊዜ ቃቃ… ሲል ተሰማው፡፡

ሃሎው… ” አለው ወፈር ያለ የወንድ ድምጽ፡፡
“እባኮት ርብቃን ነበር፡፡”
“ናትናኤል ስልኩን እንዳትዘጋው። ልናነጋግርህ እንፈልጋለን፡፡» አለ
ያው ወፈር ያለ ድምጽ።
“ማነህ?”
“ማን እንደምሆን መገመት ትችላለህ፡፡ አብርሃምን አስታውስ..
ሌሎቹንም አስታውስ ርብቃ በእጃችን ነች::” ለአንድ አፍታ ሰውየው ዝም
አለ፡፡ “የት ነው ያለኸው? ንገረኝ።” .
“ጫፏን ብትኳት ምስጢራችሁን እንደምነዛው እወቁ! ታዳምጠኛለህ?!” አለ ናትናኤል ድንጋጤውን በቁጣ ለመሽፈን እየታገላ፡፡

ናትናኤል አትችልም::ምንም መንገድ የለህም፡፡ ከድሬዳዋ የሚወጣ :
ማንኛውም የስልክ ጥሪና ፖስታ ሁሉም በቁጥጥራችን ውስጥ ነው፡፡
በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በእጃችን ትገባለህ፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት በፈቃድህ
ያለህበትን ቦታ ንገረኝ..ስማ… ”

“ኮሎኔል ትንሽ ድምጽ እንፈልጋለን” አለ ሰውየው በሌላ ስልክ ውስጥ ለሚያዳምጠውና በርብቃ ኣልጋ ጎን ለቆመው ኮሎኔል ማርቆስ፡፡

ናትናኤል የስቃይ ድምጽ ጆሮው ላይ ኣንጫረረበት …እሪታ. የሴት
ልጅ... የስቃይ እዬዬ
“ሰማህ? ርብቃ ነች፡፡ ምን እያደረግናት እንደሆነ ልነግርህ አልሞክርም:: እመነኝ እራስህን ትጠላለህ፡፡ ናትናኤል እመነኝ መፈጠርህን ትጠየፋለህ፡፡ምስጢሩኝ ካልቨርት እንዳገኘኸው እገምታለሁ! . ዓላማችን ለጋራ ጥቅም ነው፡፡ እጅህን ስጠን፡፡ ምንም ጉዳት አይደርስብህም፡፡”

“ርብቃ ምንም አታውቅም!” ናትናኤል ስልኩ ውስጥ አምባረቀ

አዎ ስለማታውቅ ነው ያለማቋረጥ የምናሰቃያት...በአንተ ኃጢያትአበሳዋን የምናሳያት፡፡ የምታውቀው ነገር ቢኖር በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ማንኛውንም ምስጢር ደብቃ መያዝ አትችልም ነበር…ግን አሁንም እጅህን እስካልሰጠኸን ድረስ የጀመርነውን ኣናቋርጥም፡፡ አስታውስ.በማህፀኗ የያዘችውኝ፡፡”

ናትናኤል በስልኩ ውስጥ ድጋሚ የስቃይና የጣር እሪታ ተሰማው፡፡
“ናትናኤል ” ያው ድምጽ ቀጠለ፡፡ “ጊዜ የለንም፡፡ ያለህበትን ቦታ ንገረን፡፡ እዚህ እሷጋ እናመጣሃለን እመነኝ፡፡” “ለሶስተኛ ጊዜ ያው የስቃይ ድምጽ በሩቁ በረጅሙ አንቋረረ፡፡

ናትናኤል ጉሮሮውን ተናነቀው ጭንቅላቱን ነዘረው፡፡ ዓይነ ተጭበረበረበት

“ተዋት! ተዋት! በቃ .. ድሬዳዋ ነኝ”
“አውቃለሁ ድሬዳዋ መሆንህን፡፡ ግን ድሬዳዋ የት?”
“ሰፈሩን አላውቀውም፡፡ ትንንሽ ቤቶች ያሉበት ኣካባቢ ነው፡፡”
ናትናኤል ጭንቅላቱ ውስጥ የሚነዝረውን ስቃይ መቋቋም አቃተው፡፡
“በአካባቢህ ምን የሚታይሀ ነገር አለ? ሆቴል.…ህንፃ ማንኛውም
ምልክት:”
“ቤት ውስጥ ነው ያለሁት፡፡ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው፡፡”
“ስልክ ቁጥሩን ንገረኝ፡፡”
ናትናኤል የስልክ ቁጥሩን አነበበለት፡፡
“ጥሩ፡፡ የትም ሳትነቃነቅ እዛው ባለህበት ጠብቀን፡፡ ካልቨርት አብሮህ ነው ያለው?”
“አይደለም:: ግን ቅርብ ነው፡፡ ላመጣው እችላለሁ፡፡” አለ ናትናኤል
በጭንቀት እየተውተረተረ፡፡

“ጥሩ፡፡ በፍጥነት ፈጽመው፡፡ : ተጠንቀቅ፡፡ ካልቨርት ሳይነግርህ
እንዳልቀረ እርግጠኛ ነኝ፥ እኛ ብቻ አይደለንም ከተማውን እያሰስን ያለነው፡፡
ናትናኤል በእነሱ እጅ መውደቅ የለብህም፡፡ ነጮቹ:: ተግባባን?”

“አዎ… አዎ አያገኙኝም… በጥንቃቄ አመጣዋለሁ… ብቻ ርብቃን አታሰቃይዋት፡፡ ምንም አታውቅም፡፡”

“ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ማንም የቀሚሷን ጫፍ አይነካም! እመነኝ ናትናኤል፡: ቅሪት የሆነችን ሴት ቀሚስ ገልቦ ማሰቃየት ምን ያህል አስጠሊታና ሰቅጣጭ እንደሆን ብታውቅ ችግሬን ትረዳልኝ ነበር፡፡ በእጄ
ያለችው ሴት ርብቃ እርጉዝ ነች! ለማድረግ የምጠየፈውን እያደረግሁ ነው፡፡ አንተ ብቻ ነህ ልታቆመኝ የምትችል፡፡”

ናትናኤል ስልኩን ዘግቶ ለጥቂት ደቂቃዎች ባለበት ፈዝዞ ቆመ፡፡ በደም የተጨማለቀ፣ ያበጠና የዘጓጎነ ፊት ታየው:: የእርጉዝ ሴት ፊት… የርብቃ:: ሁለት እጆቹን ዓይኖቹ ላይ ጭኖ ፊቱ ላይ የተደቀነውን አስፈሪ ምስል ሊያጠፋው ታገለ። የዘጎነና የበለዘው ምስል ግን ይበልጡን እየደመቀ ደም እየጎረሰ እየደፈረሰ… እየረሰረሰ መጣበት፡፡ ምንም የማታውቀው የእሱ ርብቃ በሱ ኃጢያት ቀሚሷ ይዋ ትቦጫጭቆ ጀርባዋ ተገልቦ ራቁቷን በጅራፍ ስትተለተል ታየችው... ሰውነቱን ኣንቀጠቀጠው፡፡

ፈጠን ብሎ ስልኩ ካለበት ክፍል ወጣና የየምስራችን እናት አስከትሎ በጥድፊያ እየተራመደ ወደ ካልቨርት አመራ፡፡

“ደህና ነች?” አሉት የየምሥራች እናት መንገድ ላይ ከጎን ከጎኑ ሱክ ሱክ እያሉ፡፡

"እ..."

“ደህና ነች ወይ አልኩ… ምስርዬ.… " አሉት ፈገግ ብለው::
“ታገናኘኛለህ ብዬ ስጠብቅህ'ኮ ስልኩን ዘጋህብኝ፤ ምነው?»

“እ…እ… አዎ… አ… ደህና ነች” አላቸው፡፡ ኮረኮንቹ መንገድ እየተወለካከፈ እየተጣደፈ ወደ ካልቨርት፡፡
🥰1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_አራት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ

....ናትናኤል ባለበት እንደቆመ በእልህ የሚርገበውን ካልቨርትን ሲመለከት የፈጸመው ስህተት ወለል ብሎ ታየው፡፡

“እጇን እየጠመዘዙ ሲያስጮኋት መፈረካከስ ጀመርክ.. እዬዬዋን
ስትሰማ ስለሰጡህ ቃልኪዳን መስበክ አማረህ… ናትናኤል የሚወዱት ሰው
አደጋ ላይ ሲወድቅ ምን እንደሚሰማ አውቀዋለሁ፡፡ እንዳንተ ለደቂቃዎች
ሳይሆን ለቀናት ለሳምንታት አብሮኝ ከርሟል። ይህ ብቻ አይደለም፤
የሚወዱትን ማጣት ምን ምን እንደሚልም ቀምሼዋለሁ። አሁን ድንገት
ወጣ ብለህ የፍቅረኛህን ለቅሶ አዳምጠህ ስለመጣህ ካንተ ጋር በአንድ ሲባጎ ተሸብቤ ወደ መቃብራ እንድነዳ ትጠይቀኛለህ? !ኦ ! ኢየሱስ!”

ናትናኤል ድምፅ ሳያሰማ ባለበት እንደቆመ ቆየ።

“ኣብረኸኝ ትጠፋለህ ወይስ እጅህን ትሰጣለህ? ” አለ ካልቨርት የሴት
ነጠላ ጫማውን ኣጥልቆ ሰፊ የሴት ቦርሳውን ዚፕ ከመዝጋቱ በፊት ድንገት
ቀና ብሎ እየተመለከተው፡፡

አብሬህ እጠፋለሁ፡፡” አለ ናትናኤል ጥርሱን ነክሶ እንባውን እየታገለ፡፡

“ትረፍ ሲልህ ጥሩ መንገድ መርጠሃል” አለ ካልቨርት ከስፊው ቦርሳው ውስጥ አንድ ትንሽ ሽጉጥ አውጥቶ እየፈተሽ፡፡ “እጅህን ልትሰጥ ብትወስን ኖሮ እዚሁ ጨርሼህ ልሄድ ነበር የወሰንኩት፡፡ መቼም አይኔ እያየ እየመራህ እንድታሲዘኝ ልተውህ አልችልም፡፡ በል ቶሎ እንውጣ፡፡” አለ ካልቨርት ሽጉጡን ፈትሾ አቀባብሎ መጠበቂያውን ብቻ ባለበት ትቶ መልሶ
ቦርሳው ውስጥ እየከተተው፡፡

ካልቨርት የሴት ልብስ ለብሶ በላዩ ላይ ድሪያውን ተከናንቦ ናትናኤል ደግሞ ከወገቡ በታች ሽርጡን እንዳሸረጠ በነጭ ሸሚዝ ከትንሿ ክፍል ተከታትለው ወጡ፡፡

“ወዴት ልትሄዱ ነው?” አሉ የየምሥራች እናት ድምፅ ሰምተው ከጓዳ ብቅ እያሉ፡፡
“ሰላም ነው፡፡ወደ አዲስ አበባ ነው የምንሄደው በላቸው፡፡” አለ
ካልቨርት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈጠን ብሎ፡፡ “እና ስላደረጉልኝ ሁሉ በደንብ
አመስግንልኝ፡፡”

ናትናኤል ካልቨርት ያለውን በአማርኛ ተርጉሞ ለሴትየዋ ተናገረ፡፡

“ውዴታዲያ ብትሄዱስ በዓመት በዓል ነው እንዴ! ምነው ዋል አደር ብትሉ፡፡” አሉ የተከፉ የሚመስሉት ሴትዮ ካልቨርት ለብሶት የመጣውን የሴት ልብስ ድጋሚ ለብሶ ሲያዩ ምስጢሩ እያጓጓቸው፡፡

“ብንሄድ ይሻላል፡፡ የምሥራች ትጠብቀናላች:: ዛሬ ከሰዓት መግባት
አለብን፡፡”

“በአውሮፕላን ነው የምትሄዱ?” አሉ ሴትየዋ፡፡
“አዎ፡፡” አላቸው ናትናኤል፡፡
“ውይ አፈር በበላሁ! ደብዳቤ እንኳን ሳልጥፍ!” ኣሉ ሴትየዋ
እጃቸውን ሽርጣቸው ሳይ እየጠራረጉ “ማነሽ እመ… እመቤት ወረቀት
ወዲህ በይ ...ቶሎ...”
“አይ… ” አቋረጣቸው ናትናኤል እንዳያዘገይዋቸው ሰግቶ፡፡ “ሰሞኑን
ከቻልኩ ተመልሼ እመጣለሁ ከምሥራች ጋር፡፡ መልዕክት ግን እነግሮለታለሁ፡፡ አሁን ቶሎ መሄድ አለብን፡፡”

ሊወጡ ሲሉ ካልቨርት ከቦርሳው ውስጥ በርካታ ገንዘብ አውጥቶ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ምሥጋና እየደረደረ ለሴትየዋ ዘረጋላቸው፡፡

“በቁልቢው! ኧረ እኔ'ቴ! እዚህም ሆኖ የተቀበልኩት'ኮ ሁሉን ላሟላበት አቅም ስለሌለኝ እንጂ. ደግሞ የምን ክፍያ አመጣችሁብኝ? የልጄ ባልንጀሮች ልጆቼም አይደላችሁ? ግድ የለም 'እግዜር ይስጥህ የኔ ልጅ በልልኝ በኣ
አፉ በቋንቋው፡፡” አሉ ሴትየዋ ፊታቸውን ወደ ናትናኤል መልሰው፡፡

የምሥራች እናት ቤት ወጥተው ብዙም ሳይርቁ ከአንድ አነስተኛ ቡና ቤት ገቡና ጥግ ላይ ጨለምለም ያለ ቦታ መርጠው ተቀመጡ፡፡

“አዲስ አበባ ነው ለመሄድ ያሰብኩት::” አለ ካልቨርት ቦታ ይዘው እንደተቀመጡ፡፡ “በዚህ ሰዓት ተመልሰው እመህላችን ይገባሉ ብለው አይጠረጥሩንም:: ወደዚያው ማምራታችንን በትክክል እስካልደረሱበት ደግሞ ሠላም ልናገኝ የምንችለው አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ነው፡፡”

“ታዲያ ለምን ለየምሥራች እናት እውነቱን እንድነግራቸው ነገርከኝ?” አለ ናትናኤል፡፡

“አውቄ ነው:: ተባራሪ የሚሄድበትን፤ የሚሽሽበትን በትክክል አይናገርም። ሴትየዋ ቢያወሩም ዋጋ የሚሰጠው የለም፡፡ ይልቅ እንዴት አድርገን ወደ አዲስ አበባ መሄድ እንደምንችል ነው ያልተገለፀልኝ፡፡”

“ሦስት አማራጭ ነው ያለን አውሮፕላን- ባቡር መኪና፡፡”

“አውሮፕላኑን እርሳው:: ባቡር አንድ አማራጭ ነው:: ቢሆንም በጣቢያዎች ላይ ሰዎች ሊኖሩአቸው ይችላል፡፡ አውቶቡስ ጣቢያዎችም ተመሳሳይ ናቸው”

“እያቆራረጥን መጓዝ እንችላለን፡፡” አለ ናትናኤል ዝም ብለው ተቀምጠው ያዘዙትን ሻይ ሲጠጡ ከቆዩ በኋላ፡፡

“እንዴት?”
“ለጊዜው ክድሬዳዋ ብእግርም ቢሆን መውጣት.… ከዛ በኋላ የጭነት
መኪናዎችና የቤት መኪናዎች እየተከራየን እያቆራረጥን መጓዝ
እንችላለን፡፡”

“በእግር እስከየት ድረስ እንሄዳለን?” አለ ካልቨርት ትክሻው ላይ ካነገበው ከሰፊው የሴት ባርሳው ውስጥ አነስተኛ የአገር ጎብኚ ካርታ አውጥቶ እመሃል ካለው ጠረጴዛ ላይ እየዘረጋ፡፡ «እዚህ ነው ያለነው፡፡ አለ ካልቨርት የሌባ ጣቱን ድሬዳዋ ላይ ተክሎ፡፡ «እዚህ ነው መድረስ ያለብን፡፡ጣቱን ከድሬዳዋ አንስቶ አዲስ አበባ ላይ ጫነው፡፡

“እዎ..ይኽውልህ አንደኛው መንገድ በሐረር አቅጣጫ አድርጎ አለማያ ከመድረሱ በፊት ወደ ግራ ታጥፎ አሰበ ተፈሪ ይገባና ከዚያ ወዲያ በሚኤሶ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ይደርሳል፡፡ የተለመደው መንገድ ይህ ይመስለኛል፡፡”

“ይመስለኛል? አታውቀውም እንዴ?” አለ ካልቨርት ደንገጥ ብሎ፡፡

“እውነቱን ለመናገር አላውቀውም.. የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው ድሬዳዋ ስመጣ፡፡”

“በእየሱስ! ከኔ አትሻልማ!” አለ ካልቨርት ወደኋላ ወንበሩ ላይ ተደግፎ፡፡

“አታስብ አማርኛ እስከተናገርኩ ድረስ የትም ይዤህ መሄድ እችላለሁ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ፡፡ ይኸውልህ... ሌላው አማራጭ ደግሞ ከሞላ ጎደል ከባበር ሃዲዱ ጋር ጎን ለጎን የሚሄደው የየረር ጎታ መስመር ነው፡፡ ይታይሃል በዚህ እድርጎ.” . ናትናኤል ወደ አዲስ አበባ ሊያመሩ
የሚችሉባቸውን ሁለት የመኪና መንገዶች አንድ በአንድ ለካልቨርት አሳየው፡፡

እኔ ሁለተኛውን እመርጣለሁ፡፡ እንዴልከው ብዙም የማይዘወትር ከሆነ አለ ካልቨርት፡፡

“ጥሩ፡፡ ግን ከዚያ በፊት ልብሶቻችንን መቀየር አለብን። ቤት ስንመጣ የምሥራች እናት እይተውናል፡፡አዳኞቻችን ከጠነከሩባቸው ፈርተው
ሊናገሩ ይችላሉ፡፡”

መዝድ ከመጀመራቸው በፊት ናትናኤል ከአንድ የልብስና የጫማ ሱቅ ገብቶ ለካልቨርት የሚሆን ሽርጥናጫማ፣ ለሁለቱም ደግሞ የእስላም ቆቦች ገዝቶ ተመለሰ፡፡ ከአንድ ቡና ቤት መጸዳጃ ቤት ውሰጥ ካልቨርት የለበሰውን የሴት ልብስ በአዲሱ ሼርጥ ከቀየረ በኋላ የወንድ ጫማውን ተጫምቶ መኪና ፍለጋ ወጡ።

“ጎን ለጎን ባንሄድ ጥሩ ነው። የሚፈልጉት ሁለት ሰዎችን ስለሆነ ዓይናቸው ጥንድ መንገደኞች ላይ ይበልጥ ጠንቃቃ ይሆናል፡፡አንተ ከፊት ከፊቴ ሂድ፡ እኔ በቅርብ ርቀት እከተልሃለሁ።” አለ ካልቨርት፡፡

"እንጠፋፋለና።”

“አንጠፋፋም፡፡ ብቻ አተ ከጀርባህ መኖሬን ለማረጋገጥ አትገላመጥ፡፡ ኣማርኛ የምትናገር አንተ ስለሆንክ በተቻለ መኪናውን ቶሉ ለማግኘት ብቻ ሞክር፡፡ እኔ እከተልሃለሁ። አታስብ፡፡ ለአት እዲስ ነው እንጂ እኔ የኖርኩበት ዓለም ነው ድብብቆሽ፡፡” አላ ካልቨርት፡፡
«እ..ናትናኤል ሊይዙን ቢችሉም ቀድመው የሚይዙት አንዳችንን ነው…አንተን ከያዙህ ዕሩቅ ስለማይህ ችግር የለውም! አመልጣለሁ፡፡ እኔን ከያዙኝ ግን የጥይት ድምፅ ስትሰማ ሳትገላመጥ ሳትደናገጥ ለማምለጥ ሞክር፡፡አንተንም ከያዙህ የምመክርህ የገዛ ሕይወትህን እንድታጠፋ ነው፡፡ አለበለዚያ
የሚከተለውን ለመሸከም መምረጥህ ነው፡፡”

“መሣሪያ እኮ
👍2
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....ደውዬ አነጋግራቸዋለሁ። እስካልለቀቋትና በሰላም እስካልተዋት
ድረስ ዕቅዳቸውን እንደማወጣ አስጠነቅቃቸዋለሁ፡፡”

“እንበልና ሊለቋት ባይስማሙስ?”
“አዝረከርከዋለኋ ጉዳዩን! እየተለቀመ ይጎባታል፡፡” ናትናኤል ንዴት ወረረው::

“አየህ... እዚህ ላይ ነው የማንስማማው:: ልንገርህ... ይህን ምስጢር ልታወጣ ብትሞክር ቀድሜ የምቀነጥስህ እኔ ነኝ፡፡” አለ ካልቨርት ሽጉጥ የከተተበትን ኪሱን በቀኝ እጁ መታ መታ እያደረገ፡፡

“ምን ለማለት ነው?” አለ ናትናኤል ዓይኖቹን አጥብቦ፡፡

“ሰምተኸኛል፡፡ ባጭሩ ምስጢሩን ለማውጣት ብትሞክር ቀድሜ
እገድልሃለሁ፡፡ ናትናኤል ኣንድ ተስፋ ቢኖረን... አንድ ጭላንጭል ቢታየን
እሱንም ልታጨልመው ስትሞክር ዝም ብዬ አልመለከትህም::” ቆፍጠን አለ
ካልቨርት፡፡

“ተስፋ… ተስፋ አትበልብኝ ሰባቴ…” ናትናኤል የተሰማውን ንዴት መደበቅ አልቻለም የነፍሰ ገዳዮች ጥርቅም...““ የወንበዴዎች ሆያሆዬ አይደለም ተስፋ
የሚፈነጥቅብኝ ተስፋ አይደለም፡፡ የሚታየኝ..እልቂት ነው ጥፋት ውድቀት፡፡”

“ታዲያ ለምኑ ፈራህ? ለአፍሪካዊ እልቂትና ፍጅት፣ ጥፋትና ዉድቀት ከመቼ ወዲህ ባዳ ሆነበት? በዘርና በጎሳ፣ በፖለቲካና በሃያማኖት ሰበብ የገዛ ወንድሙን በየጫካው በጥይት እየጠዘጠዘ እየቆላ ላለ አዳኝ ታዳኝ ሕዝብ እልቂትና ፍጅት እዲስ ናቸው? የገዛ መንጋጋው ሊያላምጠው የሌለው የገዛ ጨጓራው ሊሰለቅጠው የሌለው ነጋ ጠባ ከኣውሮፓ ኣራጣ አበዳሪዎች ጓዳ ለማይጠፋ ድሀ ህዝብ ወድቀት ብርቅ ሆነ? ለምነ ፈራህ ..ምን እንዳይመጣ ሰጋህ? ከዜሮ በታች ቁጥር አለ? ከአፍሪካ በታች ገሃነም አለ? ብንሻውም እንኳን ከዚህ በታች የምንወርድበት የምናዘቅጥበት ስፍራ የለም አትስጋ፡፡”

“አንዱ የተፋጀ ዝንተ ዓለም ቢፋጅ… አንዴ የወደቀ ዘለአለም ቢወድቅ ምን ገዶኝ ማለትህ ነው?" አለ ናትናኤል በሃሳሱ የመጣችበት ግን ዘውዲቱ ነበረች… ተጎድቸ ያላቀልኝ ሸርሙጣ… ምኔ ይጎዳል?

“አላልኩም፡፡ ለደዌአቸው መድሃኒቱ እዚያው እመህላቸው አፍሪካ ውስጥ መሆኑን መቀበል ተስኗቸወ ከባዕድ ጋር እየተመሳጠሩ ከመጤ ጋር እየተሻረኩ የገዛ ወንድሞቻቸውን ዕልቂት የሚያራቡ አፍሪካውያን ናቸው፡፡ አፍሪካ አንድ መሆን አለባት።”

“እንድነት'ኮ በዘፈቀደ በአየር ላይ አይመስረትም፡፡” አለ ናትናኤል
ስሜቱን ለማስረዳት ተቸግሮ። “እኔ'ኮ ውህደትን አልተቃወምኩም፡፡ ግን
ፖለቲካዊ አንድነት የኤኮኖሚያዊና የማህበራዊ ዕድገት ጥንቅር ውጤት
ነው፡፡ ከዚያ ውጭኮ ውህደት ጭፍን ውህደት ዲሞክራሲን ችላ ማለት ብቻ
ሳይሆን ኢሳይንሳዊ ነው፡፡”

“ፐ! ኢሳይንሳዊ ሳይንሳዊ ቅራቅንቦ! በአፍሪካ ውስጥ ከነፃነት ወዲህ ስንት ሳይንሳዊ ፖሊሲዎችና ሳይንሳዊ ዕቅዶች በወረቀት እንደሰፈሩ አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቅ፡፡ የየትኛው አፍሪካዊ አገር ኤኮኖሚ ሲያብብ ሲፈካ… የየትኛው አፍሪካዊ አገር ማህበራዊ ኑሮ ሲለመልምና ሲምነሸነሽ ታየ? በላ ንገረኝ!”

“ታዲያ እኮ የዚህ ምክንያቱ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ስለሌለ ነው፡፡
ዲሞክራሲና ሠላም በሌለበት ዕድገት የለም…” አለ ናትናኤል፡፡

“ውህደት ነው መልሱ!” ዕልህ ያጨናነቀው የካልቨርት ድምፅ
አቋረጠው:: “ልክ እንዳንተ በርካታ አፍሪካውያን ከፖለቲካ ውህደት በፊት
ኤኮኖሚያዊ ግንባታ ሊቀድም እንደሚገባና የፖለቲካን ውህደት ወደፊት
ልንቀዳጀው የምንችል ግብ አድርገው ያቀርቡታል፡፡ ነገር ግን ማስተዋል
የሚገባን የምንጓጓለት ኤኮኖሚያዊ ጥንካሬ ሊፈጠር የሚችለው ሙሉ
ፈቃደኝነት የተሞላበት መደጋገፍና መረዳዳት በአፍሪካ አገሮች መሃከል
ሲሰፍን ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ መደጋገፍና መረዳዳት በቅድሚያ
የሚጠይቀው ነገር አለ የጋራ ፖለቲካዊ መድረክ፡፡”

“አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ…” አለ ናትናኤል አቋርጦት፡፡ “አፍሪካውያንን፤ ምንድነው ሊያስተሳስረን የሚችል? የአፍሪካ አንድነትና በሥነ ስርዓቱ የተደከመበት ዓላማ ነው፡፡ አልሆነም እንጂ፡፡”

“ከባድ ጥያቄ!” ካልቨርት ጭንቅላቱን ወደኋላ ጥሎ የማሾፍ ሳቅ ሳቀ። “ምንድነው የውህደታችን መሠረት? በእየሱስ ምን እንድልህ ትፈልጋለህ? የሴንጎር ኒግሪትዩድ? የሴኩትሬ አፍሪካዊ ብሄረተኝነት?የንክሩማን የቅኝ ግዛት እስክ ቁስል ጠባሳ? አይደለም፡፡ ለእኔ ባዶ ሆዳችን ነው አንድ የሚያደርገን! የመሰንበትና ያለመሰንበት ጥያቄ ነው
የሚያስተባብረን፡፡ ተነጣጥለን ልንሞላው ያልቻልነውን ከርሳችንን .. ለየብቻ
ቆመን ልናረጋግጠው ያቃተንን ሰላምና ደህንነታችንን እጅ ለእጅ ተያይዘን
ልንጋፈጠው ይገባል! በእኔና በአንተ እግር ላይ የወደቀን ቋጥኝ ለማንሳት የእኔና ያንተን የዝምድና ግንድ መቁጠርና መመርመር አያሻንም።

በመጀመሪያ እግሮቻችን ከመጨፍለቃቸው ፡ በፊት ተረዳድተን ቋጥኙን ከላያችን ማንሳት አለብን፡፡ አለቀ፡፡ የአፍሪካ ውህደት የተደከመበት ነው ላልከው... እርሳው:: ለእኔ አይዋጥልኝም:: በቆንጆ ቆንጆ ከተሞች ቆንጆ ቆንጆ ህንፃዎች እየገነቡ የአፍሪካ ድርጅት'፤ 'የአፍሪካ… ኮሚሽን የአፍሪካ...
ኢንስቲትዩት እያሉ ስም ማውጣት ትንሽ ትንሽ እየሰሩ ብዙ ብዙ የሚከፈላቸውና በሽንጠ ረጃጅም ቆንጆ ቆንጆ የአውሮፓ መኪናዎቻቸው ቆንጆ . ቆንጆ ኮረዶችን እየጫነ መዞር ሥራቸው የሆነ : ውድ ውድ
ኤክስፐርቶችን ማሰባሰብ አፍሪካን አንድ አያደርጋትም::”

“እኔኮ ሊገባኝ ያልቻለው…" ናትናኤል የጀመረውን ሳይጨርስ ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም አሉ፡፡ “እሺ ሆነ እንበል፡፡ እንዲያው ድንገት አፍሪካ አንድ ሆናለች ብለህ በመገናኛ መስመሮች ስትለፈልፍ፡ ሌላውን ተወው አፍሪካውያን እራሳቸው ምን ይላሉ? ፍጹም ያላሰበበትና በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህብረት ያላለፉብት ወንድማማችነታቸውን አጠናክረው በሚገባ ያልተዋወቁበት… ድንገተኛ ዱብ ዕዳ ሲመጣባቸው ምን ይላሉ?

“ምን ይላሉ?” ካልቨርት መልሶ ጠየቀ፡፡ “አየህ… ኣንተ በተላያዩ የአፍሪካ አገሮች ያለውን ህዝብ የፖለቲካ አመለካከት አልተረዳህም:: አፍሪካ ውስጥ ፖለቲካ ግለሰብአዊ ነው፡፡ ግለሰቦች ፖለቲካን ይፈጥሩታል እንጂ የፖለቲካ አመለካከት ግለሰቦችን አይቀርጽም ምክንያቱም ፖለቲካ ራስን መጠበቂያ መሣሪያ ነው
አፍሪካ ውስጥ ጥያቄው የትኛው የፖለቲካ መስመር ለእድገት ይበጃል
አይደለም:: ጥያቄው የትኛው የፖለቲካ መስመር ሥልጣን ላይ ያሰነብተኛል ነው ለዚህ ነው ፖለቲካ ግለሰብአዊ ነው
የምልህ፡ ነፃ አፍሪካ አንድ ብትሆን አፍሪካውያን የሚሉት 'አፍሪካ አንድ
ሆነች ነው:: በቃ::”

ያሉባት መኪና ድንገት ፍጥነቷን አብርዳ ከኋላዋ የአቧራ ቁልል አንስታ፡፡ ወደ ቀኝ ስትታጠፍ፡ ቤኬ መገንጠያ ላይ ደርሰናል ብለው አሰቡ፡፡ ለአንድ አፍታ ተያዩ፡፡ ወዲያው ካልቨርት ወደጎን አዝምሞ ከሹፌሩ ጀርባ ያለችውን ትንሽ መስኮት እየደበደበ ሹፌሩ መኪናዋን እንዲያቆም በምልክት ይወተውተው ጀመር፡፡

“ምንድነው? ምንድነው የምታደርገው?” አለ ናትናኤል የካልቨርት ፈሊጥ አልገባህ ሲለው፡፡

“አቁም በለው፡፡ እቃ ጥለሃል በለው::” አለ ካልሸርት ፊቱን ወደ ናትናኤል መልሶ፡፡

ናትናኤል ወደ መስኮቱ ተጠግቶ ለሹፌሩ ዕቃ መጣሉን በምልክት ሲያስረዳው ሹፌሩ መኪናውን አብርዶ ጥግ አስያዛት፡፡

“ምን ሆናችኋል?” ጮኸ ሹፌሩ ጭንቅላቱን ጠምዝዞ፡፡
“ምንድነው የፈለከው? አለ ናትናኤል በተራው ፊቱን ወደ ካልቨርት መልሶ::

"መጣሁ፡፡” አለ ካልቨርት:: ከጭነት መኪናዋ ጀርባ ዘሎ ወረደና ወደ ሹፌሩ ሄደ፡፡ የሽፌሩን በር ከፍቶ ያለሃተታ የሹፌሩን ክንድ ጨመደደና ጎትቶ አወረደው፡፡ የሚነጫነጨው
👍2
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....“ጥሩ እንዳትነቃነቅ::" አለ አራተኛው ሰው መሣሪያውን ደግኖ እንደያዘ ወደ ጭነት መኪናው እየተጠጋ፡፡ በእርጋታ ወደፊት እየተራመደ በዓይነ ጭነቱን ያዳብስ ጀመር፡

እራቅ ብለው ሁኔታውን በዝምታ ይከታተሉ የነበሩት ሦስት ሰዎች የመሃሉ ድንገት ተጣራና ጭንቅላቱን ወደኋላ መታ አደረገ፡፡ ወዲያው ወደ ጭነት መኪናው የተጠጋው አራተኛው ሰው ፊቱን መልሶ ወደ ጓደኞቹ ሮጥ ብሎ ተመለስና ሰብሰብ ብለው ይነጋገሩ ጀመር፡፡
“ጠዋት ምንያህል መኪናዎች ቀድመዋችሁ ወደ አዲስ አበባ
ተነስተዋል?” አለ አራተኛው ሰው ፊቱን ወደ ጭነት መኪናው ሹፌር
መልሶ ድምፁን ከፍ አድርጎ፡፡

“አንድ ሶስት አራት ይሆናሉ፡፡” አለ ከጭነት መኪናው ወርዶ የቆመው ሹፌር፡፡

ወዲያው አራቱ ሰዎች ሮጥ ሮጥ እያሉ ሬንጅሮቨራቸው ውስጥ ገቡና በአዲስ አበባ አቅጣጫ በረሩ፡፡
“ኡፍ .…ፍ!!” አለ ካልቨርት ጭንቅላቱን በተኛበት ጆንያ ላይ ጥሎ፡፡
“ሄዱ? ” አሉ ናትናኤል ሽራውን እንደተከናነበ በሹክሹክታ፡፡
“አዎ፡፡ ያለቀልን መስሎኝ ነበር::”

የጭነት መኪናው ሹፌር መኪናው ውስጥ ገብቶ ሲንቀሳቀሱ በተቻላቸው መጠን መንፈሳቸውን አረጋግተው መመካከር ያዙ፡፡

“ያላጥርጥር በየከተሞቹ ኬላዎች ላይ ይጠብቁናል፡፡ በተለይ ወደ አዲስ አበባ እየቀረብን ስንመጣ አስቸጋሪ ነው የሚሆንብን፡፡” እለ ናትናኤል፡፡
“አዎ፡፡ : ካአሁን ወዲያ ወደየትኛውም ከተማ መግባት የለብንም፡፡ ወደ ከተሞች ስንቀርብ እየወረድን ከጀርባ በግማሽ ክብ ቅርፅ በእግር ማለፍ ነው ያለን አማራጭ፡፡”

“ከናዝሬት ወዲያ ያለውን አካባቢ አውቀዋለሁ! መንገዱን በሩቅ
እይታ እስከተከተልን ድረስ ችግር አይገጥመንም::አለ ናትናኤል፡፡
ናዝሬት ከተማ ሲደርሱ እንድ አምስት ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው ከተደበቁበት ሸራ ውስጥ ብቅ ብቅ እያሉ ከኋላና ከፊት ሌላ ተሽከርካሪ አለመኖሩን ካረጋገጡ በኋላ በጭነት፡ ላይ እየዳሁ ወደ መኪናወ ኋላ ተጠጉ፡፡
ሸራው የተጠፈረባቸውን ወፋፍራሃም ገመዶች የሙጢኝ ጨምድደው ይዘው
ቁልቁል ተንጠለጠሉ፡፡

“ተጠንቀቅ፡፡ አስፋልቱ ላይ ኣንዳታርፍ፡፡ በሁለት እግሮችህ ለማረፍና ለመቆም አትሞክር፤ ከዘለልክ በኋላ ጭንቅላትህን ቀብረህ ተንከባለል፡፡ እኔ ስዘል ተመልከት፡፡” አለ ካልቨርት በወጣትነት ዘመኑ በአገሩ ውስጥ ያሳለፋቸውን የኮማንዶ ህይቱን እያስታወሰ፡፡ "

በሰላሳ ሜትር ርቀት ልዩነት ሁለቱም የተንጠላጠሉባቸውን ገመዶች እየለቀቁ ከጭነት መኪናው ላይ ተፈናጠሩ፡፡ ካልቨርት አልተጎዳም፤ ናትናኤል ግን ግራ ክንዱ ክፉኛ ተገሸለጠ፡፡

“አስፋልቱ ላይ አትረፍ፡ እያልኩህ እንዲያውም ተርፈሃል፡፡ወደጎን
ባትንከባለል ኖሮ ይሄ አስፋልት ጭንቅላትህን ነበር የሚፈረክስልሀ፡፡” አለ
ካልቨርት እየሮጠ መጥቶ ናትናኤልን ደግፎ እያነሳው፡፡

አውራ መንገዱን እየራቁ፤ እየሸሹ የናዝሬትን ከተማ በስተቀኝ
ጀርባዋ ዞሯት::

"መንገዱ ወደቀኝ የሚታጠፍ፡ ስለሆነ ከዚህ በኋላ በቀጥታ መስመር ብንሄድ ወይም በሃያ አምስት ኪሎ ሜትር ላይ በዱከምና በሞጆ መሃል መንገድ ላይ ብቅ እንላለን፡፡ አለ ካልቨርት ካርታውን አውጥተው ሲያጠኑት ከቆዩ በኋላ፡፡

እንዳለው ከሦስት ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ በሞጆ ከተማ አልፈው ከአውራ ጎዳናው ጋር ተገናኙ:: ብዙም ሳይቆዩ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ የገጠር አውቶቡስ አስቁመው ተሳፈሩ፡፡

“አዲስ ፈለጥ!“ ይላሉ አውቶብሱ ውስጥ ከሹፌሩ ጀርባ የተቀመጡ አዛውንት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፡፡ “ከአውቶብሱ ገብቶ
መፈተሽ የአባት... “ቆብህን አውልቅ፤ ክንብንብህን አውርድ ብሎ ነገር
ምንድነው? ወቸጉድ!”

“የሚፈልጉት ሰው አለ መሰለኝ::” አለ ባሻገር የተቀመጠ ልጅ እግር፡፡

ታድያ ቢኖርስ ባለፍንበት ከተማ ሁሉ እየቆምን ቆብና ክንብንባችንን መገፈፍ የአባት ነው?ልማድ ነው? ወይ ፈጣሪ?” ሽማግሌው ተቆጠ፡፡

“ምንድነው?” አላቸው ናትናኤል ከጎኑ የተቀመጡትን ሴትዮ::

“እንጃ! ባለፍንበት ከተማ ሁሉ መሣሪያ ደግነው እንደ ሽፍታ ሲበረብሩን ቆዩ፡፡” አሉት ሴትየዋ መደነቃቸውን፣ መገረማቸውን ለማሳየት እጃቸውን አፋቸው ላይ ጣል አድርገው፡፡

“እነማን ናቸው?” ናትናኤል ግራ የተጋባ መስሎ ጠየቃቸው፡፡

“ምኑን አወቄው ብቻ ከወለንጭቲ የጀመሩ ሰባቴ እያስቆሙ ሁለት
ሁለት፥ሦስት ሦስት እየሆኑ እንዲህ እንዲህ እያደረጋቸው ሲበረብሩን ዋሉ፡፡
ሆ! እንደ አነሳሳችንኮ ገና ቅድም ታዲስ አበባ ደርስን ነበር ጊዮርጊስ ይይላቸው”

ናትናኤል ዞር ብሎ ካልቨርትን ሹክ አለው::

ደብረዞይት ሊደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው ተጠቃቀሱና መጀመሪያ ካልቨርት እራቅ ብሎ ደግሞ ናትናኤል ተከታትላው ወረዱ፡፡

“ምንድነው?” አለ ካልቨርት አውቶቡሱ ውስጥ የተባለውን ሁሉ አጣርቶ ለመረዳት ጓጉቶ፡፡

ናትናኤል አውቶቡሱ ውስጥ የሰማውን ሁሉ ዘርዝሮ ነገረው፡፡

“ከአሁን ወዲያ መኪና ላይ መውጣት የለብንም::” አለ ካልቨርት፡፡
“ታዲያ እንዴት አናደርጋለን?”
“አሁን ሁለታችንም የተዳከምን ይመስለኛል፡፡ ለጊዜው ከመንገድ
ፈቀቅ ብለን እንረፍና ከጨለመ ወዲያ ሌሊቱን መንገዱን ተከትለን በእግራችን እንቀጥላለን፡፡ ከበረታንና ሰሰዓት አምስት ኪሎ ሜትር ብንጓዝ እንኳን ከምሽቱ አንድ እስከ ጠዋቱ አንድ ሰዓት ስልሳ ኪሎ ሜትር ሽፈንን ማለት ነው:: ፀሐይ ስለማይበረታብን የምንሸነፍ፡ አይመስለኝም፡፡”
ከመንገዱ በስተቀኝ እርቀው ገብተው
ለብቻዋ በቆመች የግራር ዛፍ ስር በደረታቸው ተደፍተው ለማረፍ
ሞከሩ::እየጠለቀች ያለችው ፀሐይ እንደጌጥ ብታብረቀርቅም ሙቀቷ እየከዳት መጣ፡፡ አውላላ ሜዳ ላይ ብቻውን እየተመላለሰ የሚጋልበው ቀዝቃዛ ነፋስ ሰውነታቸውን ጠዘጠዘው፤ ምግብ ሳያገኝ ሁለተኛ ቀኑን የያዘው
ሰውነታቸውም ከፊት የተደቀነውን መንገድ ቁጭ አድርጎ ተዳከመ፡፡ ቢሆንም ፀሐይ ልትሸሽግ ሲዳዳት ከተኙበት ተነስተው የመንገዱን ጥግ ይዘው በአዲስ አበባ አቅጣጫ ጉዞአቸውን በእግር ተያያዙት፡፡

“እርምጃህን አትቀያይር በአንድ ዓይነት ፍጥነት አንድ አይነት ስፋት ተራመድ አለበለዚያ ይደክምሃል፡፡” አለ ካልቨርት እጆቹን እያወናጨፈ፤ “ከጎን ከጎኑ የሚንቶሰቶሰውን ናትናኤልን ዞር ብሎ
ተመልክቶ፡፡

አልፎ አልፎ በሩቁ የመኪና መብራት ሲታያቸው ፈጠን ብለህ ከአውራ መንገዱ እራቅ እያሉ መሬቱ ላይ በደረታቸው አየተኙ እያሳለፉ መንገዳቸውን ያለንግግር ቀጠሉ፡፡ ሁለት ጊዜ ጅቦች ሲያጋጥሟቸውም ሁለቱንም ጌዜ የካልቨርት ሽጉጥ የጥይት ጩኹት አተረፋቸው፡፡

እንዳሰሱት እስከጠዋቱ አንድ ሰዓት ድረስ አልተጓዘም፡፡ ከጠዋቱ አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ አቃቂ ከተማ እንደደረስ ያለዕረፍት መቀጠል እንደማይችሉ ስለተረዱ ከመንገዱ ወጥቶ እራቅ ካለ ጫካ ውስጥ ገብተው ካልቨርት እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡ናትናኤል እስካሁን ያሳለፋውን ሁኔታዎች አንድ በአንድ በህሊናው እየመላለሰ ይቃኝ ጀመር፡፡ ርብቃ…
አብርሃም… የቢሮ አለቃው.… ወታደራዊ አታሼዎቹ… ነጭዋ ሲትሮይን
የምሥራች ዘውዲቱ… አዲስ አበባ ድሬዳዋ…ካልቨርት ይህ ሁሉ ውጣ
ውረድ ከርብቃ ስቃይና ከእርግዝናዋ ጋር እየተሰባጠረ ይታየው ጀመር፡፡
ርብቃን ለማዳን ምን ማድረግ አለበት? አወሬዎቹን መጋፈጥ? ከአውሬዎቹ
ጋር መደራደር? ካልቨርት ምስጢሬን ይዤ ልሙት ባይ ነው፡፡ ካልቨርትን እንደገና ማግባባትና ማሳመን ይቻላል? ወይስ የሞተ ፡ ነገር ነው? ለማናቸውም ለካልቨርት ምንም ፍንጭ ማሳየት የለበትም… ማናቸውንም ጉዳይ ከካልቨርት መደበቅ ይኖርበታል፡፡

የተጫናቸው ድካም በዙሪያቸው ከነበረው የማለዳ ውርጭ የከበደ
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


...“አሁን ገና ሰው መሰልክ?” አለ ካልቨርት ፊቱ ፈገግታ ለብሶ፡፡
“አይዞህ አንተም ውሃ ሲገላምጥህ ሰው ትመስላለህ::” ናትናኤል ፀጉሩን በፎጣ እያደራረቅ ወደተከራዩት የሆቴል ክፍል ገብቶ ከኋላው በሩን ዘጋው፡፡
“ህ! ! ህ ለሁሉም ጊዜ አለው::”አለ ካልቨርት ከተቀመጠበት ተነስቶ የሚቀይረውን አዲስ ልብስ ተሸክሞ ወደ መታጠቢያ ቤት እየሄደ፡፡

ካልቨርት ከክፍሉ ወጣ እንዳለ ናትናኤል ፈጠን ብሎ ካልቨርት ከጥግ ያስቀመጠውን ቦርሳ ይፈትሽ ጀመር፡፡ እንደተመኘውና እንዳሰበው፣
እንዳቀደው የካልቨርትን ሽጉጥ ቦርሳው ውስጥ አገኘሁ፡፡ ሽጉጡን ቶሎ ብሎ
ከቦርሳው ውስጥ አወጣና ካርታን አውጥቶ ጥይቱን ቆጠረ፡፡ ሰባት ጥይት
በቂ ነው፡፡ ካርታውን በቦታው መለሰና ሽጉጠን አቀባብሎ መጠበቂያውን
ለቆ በሩን እያየ ካልቨርትን ይጠባበቅ ጀመር፡፡ ምርጫ የለውም... ሌላ
ምንም ምርጫ የለውም!

ባያስማማስ ጭራሽ ባይስማማስ ፍንክች አልል ቢልስ? የራሱ ጉዳደ:: እዚሁ ይጨርሰዋል፡፡ አለዛም ትቶት ይሄዳል፤ ብቻውን ይጋፈጣቸዋል:: የሚላቸውን ካልሰሙትም ጉዳቸውን ያዝረክርክዋል፡፡ ጊዜ የለውም:: ነገ ሳይመሽ ርብቃን እጁ ማድረግ አለበት አለበለዚያ የሚመጣው አይታወቅም...
ናትናኤል ከአልጋው ግርጌ እንደቆመ የርብቃን መጨረሻ ሲያስብ ሊደርስባት የሚችለውን አደጋ ሲያሰላስል ትንፋሽ አጠረው፡፡

የነገዋ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ርብቃን እጁ ማግባት አለበት፡፡አለበለዚያ በግርግርታ አንድ ነገር ሲያደርጓት…. - በማታወቀው ምስጢር የመስዋዕት በግ ቢያደርጓት...እርሱ ነፍሰን ስለወደደ የገዛ ደህንነቱን ስለፈለገ ብቻ ቢያጠፏት ከዚያ ወዲያ ምን ሊሆን ህይወቱ?' ናትናኤል ሽጉጡን ጨምድዶ እንደያዘ በተከራዩት ክፍል ውስጥ ካሉት አልጋዎች በአንደኛው ጫፍ ላይ ቁጭ አለና ካልቨርትን ይጠባበቅ : ጀመር፡፡ የራሱ ጉዳይ! ካልተስማማ ትቶት ይሄዳል፡፡ ሊቃወመው ወይ ሊያቆመው ከሞከረ ግን…. የራሱ ጉዳይ! ሞት ነው የሚጠብቀው፡፡ . ናትናኤል የጨመደደውን ሽጉጥ ወደግራ እጁ አዙሮ በላብ የተጠመቀውን የቀኝ እጁን ሱሪው ላይ ሞዥቀና ሽጉጡን ጨሰጠ፡፡

ብዙም ሳይቆይ ካልቨርት ፎጣውን ትከሻው ላይ ጥሎ መንገድ ላይ
ለብሶት የቆየውን በአቧራና በላብ የተበከለ ሽርጥና ሸሚዝ በጥያፌ በሁለት
ጣቶቹ አንጠልጥሎ የተከራዩትን ክፍል በር ከፍቶ ሲገባ የገጠመውን ትርዒት ማመን አቃተው፡፡

“ካልቨርት ምርጫ የለኝም...
የማይሆን ነገር እንዳደርግ
አታስገድደኝ::'' አለ ናትናኤል ከተቀመጠበት¨ ሳይንቀሳቀስ የያዘውን ሽጉጥ ቀና እያደረገ፡፡

“ምንድነው የምትሰራው? ምን ልትሆን ነው?” አለ ካልቨርት የተሸከመውን ቆሻሻ ልብስ ወለሉ ላይ እየዘረገፈ፡፡

“ከአንተ ምንም እርዳታ አልፈልግም፡፡ ርብቃ ያለችበትን ሁኔታ እያወቅሁ በዝምታ መጠበቅ ግን አልችልም:: አዝናለሁ ካልቨርት… ሽጉጥሀን ስለሰረቅሁ፡፡ ግን ምርጫ ያለኝም:: ይሀንን ካላደረግሁ እስረኛሀ እንደምታደርገኝ ግልጽ ነው፡፡”

“ስማ!” አለ ካልቨርት በንዴት መንፈስ ወደፊት አንድ እርምጃ እየተራመደ።

“አ! አ" ናትናኤል የሽጉጠን አፈሙዝ ካልቨርት ላይ ደግኖ ተነስቶ ቆመ፡፡ “እንዳትጠጋኝ፡፡ ሞኝ ነገር አትፈጽም:: ክፉ ነገር መፈጸም አልፈልግም፡፡ ግን ምርጫ የለኝም... ካስገደድከኝ ደፍቼህ ነው የምወጣው፡፡”

ካልቨርት ተስፋ በመቁረጥ አልጋው ላይ ቁጭ አለና ፊቱን ሁለት መዳፎቹ ውስጥ ቀበረ፡፡

ናትናኤል የምትሰራው ጥፋት ነው... ከአሁን ወዲያ ምንም ልትረዳት አትችልም፡፡ እጃቸው ውስጥ ነች፡፡”

“አስፈራራቸዋለሁ! አንተ የምስራችን እንዳይነኩ እንዳስፈራራሃቸው
አስፈራራቸዋለሁ፡፡”

“እናስ ከዛስ?”
“ይለቋታላ! ”
“ሞኝ አትሁን፡፡ እርግጥ ይለቋት ይሆናል… ግን ከለቀቋት ወዲያ እንደ ወጥመድ ነው የሚጠቀሙባት ምክንያቱም ወይ ሰስልክ ወይ በአካል ልትገናኛት መሞከርህ አይቀርም፡፡ እትጠራጠር ይይዙሃል።”

“ከያዙኝ ይያዙኝ ዝም ብዬ ግን አልቀመጥም”
“ባይስማሙስ? ባይለቋትስ?”
“አወጣዋለሁ ምሥጢራቸውን፡፡”

ካልቨርት ቀና ብሎ በቁጣ ፊት ናትናኤልን ገላመጠው፡፡

“እታደርገውም… የምትጎዳው እነሱን አይደለም አፍሪካን ነው፡፡ ነገሮችን አስፍቶ የሚያይ ጭንቅላት ካለህ የምልህ ይገባሃል፡፡ የዚህን ዓይነት ጥፋት ስታጠፋ ደግሞ በዝምታ አልመለከትህም፡፡”

“ሽጉጡ ያለው በእኔ እጅ ነው፡፡”

“ተኩስ! ፈሪ!” ካልቨርት ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳ፡፡

“ተጠንቀቅ ካልቨርት ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይመለሳል ብለህ አታስብ እንደዛፍ ነው በቁምህ የምጥልህ፡፡” ናትናኤል ጥርሱን ነክሶ አፈጠጠ፡፡

የናትናኤልን አዝማሚያ ሲመለከት ካልቨርት ራሱን ነቀነቀና ተመልሶ አልጋው ላይ ተቀመጠ፡፡

“እና አሁን ምን ልታደርግ አሰብክ?” አለ ካልቨርት፡፡
“ጠዋት ስልክ ደውዬ እነግራቸዋለሁ፤ አስጠነቅቃቸዋለሁ፡፡ ከዚያ
ወዲያ የራሳቸው ምርጫ ነው፡፡”
“ናትናኤል እስቲ አስበው በቀላሉ ድምፃችንን ብናጠፋ ሁሉ ነገር
ጊዜውን ጠብቆ መድኃኒት ያገኛል እመነኝ ይለቋታል፡፡”

“ባይሳካስ ዕቅዱ ቢከሽፍስ? ጉዳቸውን ልመሰክር ለመደበቅ እንደሚገድሏት አታውቅም። ካልቨርት መፍጠን አለብኝ! አንድ ነገር ብትሆን ለራሴ ይቅርታ አላደርግለትም::"

“ናትናኤል ስሜትህ ያገባኛል… ምናልባት እኔም በአንተ ቦታ ብሆን ተመሳሳይ ስህተት ለመፈጸም እገፋፋ ይሆናል፡፡ ለምን እንዲህ አናደርግም..ጥፋት ማጥፋታችን ካልቀረ አንስተኛ ጥፋት ይሻላል፡፡” ካልቨርት ያሰበውን እቅድ ለናትናኤል በእርጋታ ተነተነለት፡፡

“አይሆንም! ይይዙናል፡፡”

“ይገባናል ሊይዙን ይችላሉ
እንዳልከው በስልክ ልታስፈራራቸው ብትሞክርም መያዝሀ አይቀርም፡፡ የእኔ መንገድ ይሻላል፡፡ሁልጊዜ የተሻለው አስተማማኙ መንገድ ይበልጥ አደገኛና ይበልጥ አስፈሪ! ይበልጥ አስደንጋጭ የሆነው ጤነኛ ሰው በጤነኛ አእምሮ
የማይመርጠው መንገድ ነው አትጠራጠር፡፡”

“ግን ቢይዙንስ?”
“አለቀልና! ምነው ፈራህ እንዴ?” ካልቨርት ፈገግ አለ፡፡ ««ቢያዙኝም ይያዙኝ አላልክም ዋናው ነገር ፍቅረኛህን ከመዳፋቸው ማውጣታችን የእነሱንም ዕቅድ እለማደናቅፋችን ነው... ለዚህ ደግሞ የተሻለው መንገድ የእኔ ነው:: ትስማማለህ?

ናትናኤል በዝምታ ማውጣትና ማውረድ ያዘ፡፡

“እትፍራ፡፡” አለ ካልቨርት ፈገግ ብሎ፡፡
“አልፈራሁም!” በስጨት አለ ናትናኤል፡፡
“እንግዲያው እንስማማ…” ካልቨርት ቀኝ እጁን ዘረጋለት
“እንተማመን ናትናኤል ደግሞ እሱን ሽጉጥ ዞር አድርገው:: ቢባርቅ
ሆዴን ነው የምትዘረግፈው::”
“ካልቨርት ልታታልለኝ ብትሞክር…” አለ ናትናኤል በጥርጣሬ ፊት ካልቨርት የዘረጋለትን እጁን እየተመለከተ፡፡ “ከአሁን በኋላ ሁለቴ ለማሰብ ጊዜ የለኝም:: አንዲት አጉል እንቅስቃሴ ካደረክ አጓጉል ነው የምትሆነው፡፡”

“ቃል እገባልሃለሁ፡፡”አለ ካልቨርት እጁን ወደፊት እንደዘረጋ፡፡

ናትናኤል ሽጉጡን ወደግራው አሻግሮ የተዘረጋውን የካልቨርትን እጅ በቀኙ ጨበጠው፡፡

“ጥሩ አሁን እቅዳችንን አንድ በአንድ ተንትነን እንነጋገርበት ካጠፋን አይቀር፡፡” አለ ካልቨርት ሁለት ወንበሮች አምጥቶ አንዱን ለናትናኤል አቀብሎት በሁለተኛው ላይ እየተፈናጠጠ፡፡

ፊት ለፊት ቁጭ ብለው በማግስቱ ስለሚፈፅሙት ተግባር አንድ በአንድ ተነጋገሩ ተመካከሩ ፤ ተከራከሩ፤ ተስማሙ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰማዩ ጥርት ብሏል፡፡ ለጋዋ ፀሐይ ከእንቅልፏ እንደነቃች ሁሉ ከረጅሙ የክረምት ጨለማ በኋላ በሰማዩ ላይ ብቻዋን ትምነሸነሽበታለች:: አለፍ አለፍ እያሉ እንደ
👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....ከዋናው መንገድ ብዙም ሳይርቁ የመኖሪያ ቤቶች ከተደረደሩበት
የሠፈር ውስጥ መንገድ ዳር አንድ ጥግ ላይ መኪናቸውን አቆሙ፡፡

መኪናዋ ጥግ ይዛ እንደቆመች ፡ ናትናኤል የመኪናዋን ሬድዮ ከፈተው፡፡ ጎርናና የጋዜጠኛ ድምፅ መኪናዋ ውስጥ አስተጋባ፡፡

እንዲሁም የአንጎላና የሞሮኮ የሴኔጋልና የቡሩንዲ መሪዎች ከሰዓት በኋላ አቀባበል ሲደረግላቸው እስካሁን ወደ አፍሪካዋ ያልገቡት ሦስት የአፍሪካ መሪዎች ማለትም የሴራሊዮን የጋቦንና
የቡርኪናፋሶ መሪዎች ምሽቱን ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በወጣው ኘሮግራም መሠረት ዛሬ ሰኞ መስከረም አራት ምሽት በሁለት ሰዓት ተኩል ያልገቡት ሦስት የአፍሪካ መሪዎች ማለትም የሴራሊዮን የጋቦንና የቡርኪናፋሶ መሪዎች ምሽቱን ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በወጣው
ፕሮግራም መሠረት ዛሬ ሰኞ መስከረም አራት ምሽት በሁለት ሰዓት ተኩል
ላይ ጠቅላላ ፡ የአፍሪካ መሪዎች የሚገኙበት ስብሰባ ሲከፈት ይቅርታ
አድማጮቻችን አሁን ዘግይቶ የደረሰን ዜና አለ የሴራሊዮኑን መሪ
የያዘችው አውሮኘላን አዲስ አበባ ኢንተርናሽናል አውሮኘላን ማረፊያ
አርፋለች ኘሬዚዳንቱ፡ የክብር ሰላምታ ላቀረበላቸው.. አፀፋውን..…”

ናትናኤል ሬዲዮኑን ዘጋው፡፡
“ሁለት ቀሩ::” አለ ናትናኤል አይኖቹን አቦዝዞ ለራሱ እንደሚናገር ሁል፡፡

ጊዜው እየሄደ . ሰዓቱ እየቀረበ ሲመጣ ተራርቀው የዋሉት ደመናዎች እየተጠራሩ እጅ ለእጅ መያያዝ ጀመሩ:: ቀኑን ሙሉ ማን አለብኝ ብላ ያለርህራሄ ምድሪቷን ስትወቃት የዋለችው ፀሃይ የተባበሩትን
ደመናዎች ማለፍ ሲያቅታት ዙሪያው ቀዝቅዝ ተንፈስ አለ፡፡ ንፋሱ ብቻ
እንደ ወሬ ነጋሪ ከወዲያ ወዲህ ይመላለስ ጀመር፡፡

ሁለት ሰዎች የጫነች የቴሌኮሙኒኬሽን የጥገና መኪና ከአስመራ መንገድ ተነስታ በላይኛው ቤተመንግስት አድርጋ ፒያሳን ለሁላት ከፍላ ሲኒማ ኢትዮጵያ አጠገብ ስትደርስ ሊመሻሽ ተቃርቦ ነበር፡፡ መኪናዋ
አደባባዩን ዞረችና ቁልቁል ወረደች፡፡ ብዙም ሳትርቅ ከአንድ አፓርትመንት
ህንፃ የአጥር በር ፊት ለፊት ቆመች፡፡

“አቤት::” አለ አፈርማ ካፖርት የደረቡ የአፖርትመንቱ የማታ ዘበኛ የብረቱን በር ከፈት አድርገው ብቅ አሉና፡፡

“አንዴ ይክፈቱልን እባክዎት፡፡” አለ ከሾፌሩ ጎን የተቀመጠው ሰው ጭንቅላቱን በመስኮት ብቅ አድርጎ። “ስልከኞች ነን.… የተበላሸ ስልክ
ለመጠገን ነው፡፡”

ሽማግሌው እያቅማሙ የብረቱን በር ወለል አድርገው ከፈቱት፡፡
የቴሌኮሙኒኬሽኗ መኪና ወደ አፖርታማው ግቢ ገብታ ጥግ ይዛ ቆመች፡፡ወዲያው ካኪ ቱታ የለበሱ ሠራተኞች ፈጠን ብለው ከመኪናዋ ወርደው የጥገና መሣሪያዎቻቸውን የያዙባቸውን ቦርሳዎቻቸውንና ሌሎችንም
ዕቃዎቻቸውን አንግበው ወደ አፖርትመንቱ በር ተጣደፉ፡፡

ከመጀመሪያው ደርብ እንደደረሱ ወደግራ ብለው በጠባቡ መተላለፊያ ፊትና ኋላ ራመድ ራመድ እያሉ ቀጠሉ፡፡ 21 የተላጠፈበት በር አጠገብ እንደደረሱ ተያዩ:: ወዲያው በሩን አልፈው 22 የሚል ቁጥር የተለጠፈበትን የሚቀጥለውን በር አንኳኩ፡፡
“አቤት"አለች በሩን የከፈተችው ልጅ እግር ሴት ህፃን ልጅ እንደታቀፈች፡፡

“ከቴሌኮሙኒኬሽን ነው፡፡ በአካባቢው የተበሳሹ ስልኮች አሉ፡፡ የናንተንም ለማየት ነበር፡፡አላት ቀጠን ቀላ ያለው፡፡

“ደህና ነው የኔ ስልክ፡፡” አለች ሴትየዋ በተራ እያየቻቸው፡፡
“ገብተን እንየው?” አላት የመጀመሪያው ሰው፡፡
“ግቡ ግቡ፡፡“ አለች ሴትያዊ የታቀፈቻትን ህፃን ከመሬት አውርዳ በሩን በሰፊው እየከፈታችላቸው::

ካኪ ቱታ የለበሱት ሁለት ሰዎች ተከታትለው ገቡ፡፡
“ቅድም ስንደውል ያነጋገሩን እርሶ ኖት?” አላት ቀጠን ያለው፡፡
“አይ እዚህ አልደወላችሁም::”
“ምናልባት ሌላ ሰው አንስቶት እንዳይሆን…”
“እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት በቤቱ፤ ከሷ በስተቀር፡፡” አለች ሴትየዋ ፈገግ
ብሳ የህፃን ልጇን ጭንቅላት እየደባበሰች፡፡ “እዚህ አልደወላችሁም፡፡”
ሰውየው የፈለገውን ያገኘ ይመስል ጊዜ ሳይወስድ ከቱታው ከስ ውስጥ ሽጉጥ አውጥቶ ሴትየዋ ላይ ደገነባት፡፡ ከጎኑ ቆሞ የነበረው ጥቁር ስው ያንጠለጠለውን የሸራ ቦርሳ ወደጎን ጥሎ በሚያስደንቅ ፍጥነት አፏን አፍኖ ወንበር ላይ አስቀመጣት፡፡ ሽጉጥ የያዘው ሰው ማልቀስ የዳዳትን ህፃን ልጅ ከመሬት አንስቶ ታቀፋት።

“ኣይዞሽ አንቺንም ሆነ ልጅሽን የመጉዳት ሃሳብ የለንም:: ነገር ግን ለመጮህ ወይ ለመሮጥ ብትሞክሪ ጥሩ አይሆንም ውጤቱ፡፡” አለ መሣሪያ የያዘው ሰው የሽጉጡን አፈሙዝ ህፃኗ ለስላሳ አንገት ውስጥ እያፍተለተለ፡፡

ሽጉጡን የያዘው ሰው ምልክት ሲሰጠው ኣፍዋን አፍኖ የያዛት ሰው ለቀቃት::

“ምንድነው የምትፈልጉት? የምትፈልጉትን ያዙና ውጡልኝ፡፡” አለች ልጇ አንጎት ስር የተሸጎጠውን ሽጉጥ የተመለከተችው እናት እየተርበተበተች::

“ሌቦችና ቀማኞች እይደለንም፡፡ ጉዳት ልናደርስብሽም አይደለም የመጣነው፡፡ እርዳታሽን ብቻ ነው የምንፈልገው፡፡” አላት ቀጠን ያለው ሰው ህፃኗን እንደታቀፈ ከተቀመጠችበት ወንበር አጠገብ በርከክ ብሎ፡፡
ምንድነው የምትፈልጉት?” አለች ሴትየዋ ኣይኖቿን በሁለቱ አፋኞች ላይ ተራ እያንከራተተች፡፡

እዚህ ጎረቤትሽ 21 ቁጥር ውስጥ ያለችውን ሴት ታውቂያታለሽ?"
አለ ልጇን የታቀፈው ሰውዬ ማልቀስ የጀመረችውን ህፃን በማባበል እየጣረ

“አዎ… ርብቃ ትባላለች… ልጄን ልቀቅልኝ፡፡”

ሀዋኗን የታቀፈው ሰው እየተቁነጠነጠች ያስቸገረችውን ህፃን ለእናቷ ካቅበለ በኋላ ወንበር ስቦ አጠገቧ ተቀመጠ፡፡

“ይህን ሰሞን አይተሻታል?” “ አለ የያዘውን መሣሪያ ከቱታው ኪስ
ውስጥ እየጨመረ::

“ኣሳየኋትም፡፡ ረጅም ጊዜ ነው ካየኋት.. ግን ሌሎች ሰዎች ወደ ክፍሏ ሲገቡና ሲወጠ አይቻለሁ፡፡ ምንድነው የምትፈልጉት ከኔ?” ሴትየዋ ልጇን እቅፍ አድርጋ ይዛ እየደባበሰች አፈጠሰችበት፡፡
“ምን ያህል ይሆናሉ ሰዎቹ?" ጠየቃት፡፡
“የቶቹ ሰዎች?” መልሳ ጠየቀችኑ፡፡
“ክፍሏ ውስጥ ያሉት ሰዎች፡፡"
“እኔ እንጁ ሲገቡና ሲወጡ ነው ያየኋቸው.. ውስጥ ይኑሩ አይኖሩ አላውቅም።

ቀጠን ያለው ሰው በርከክ ካለበት ተነስቶ በፀጥታ ከቆመው ጓደኛው ጋር በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሹክሸከታ ያወራ ጀመር፡፡ ወዲያው ፊቱን ወደ
ሴትየዋ መለሰ፡፡

“እንዳልኩሽ እርዳታሽን እንፈልጋለን፡፡ ጉዳት ላይ እንድትወድቂ አንፈልግም። የምልሽን ያለማወላወል መፈጸም አለብሽ፡፡ አለበለዚያ ግን ያልጠበቅነው አደጋ ሊደርስ ይችላል፡፡”

“ምንድነው የምትፈልጉት?” አለች ሴትየዋ ግራ ተጋብታ፡፡ ተራ ሌቦችና ቀማኞች አለመሆናቸውን ስታረጋግጥ ድፍረቷ ተሰባስበላት፡፡ ኮስተር ብላ ተመለከተችው።

“አብረሽን ወደሚቀጥለው ክፍል ትሄጅና በሩን ታንኳኪያለሽ፡፡”
“እኔ የማላውቀው ሰው ቤት ሄጄ ኣላንኳኳም::” አለች ነገሩ ያልጣማት ሴትዮ የልጇን ጭንቅላት ጡቶቿ መሃል ቀብራ፡፡
“ምርጫ የለም፡፡ እምቢ ካልሽን እኛም የማንወደውን እንድንፈጽም እንገደዳለን፡፡” አለ ሽጉጡን የያዘው ሰው ጎንበስ ብሉ የህፃን ልጇን ጭንቅላት እየደባበሰ፡፡ “ተነሽ የፍርሃት መልክ አታሳዬ፡ በሯን
ካንኳኳሽ በኋላ ትጠባበቂያለሽ፡፡ በሩ ሲከፈት…” ማድረግ የሚገባትን ሁሉ
አንድ በአንድ እያስረዳ ክንዷን ይዞ ከተቀመጠችበት አስነሳት፡፡

ሴትየዋ ህፃን ልጇን እንደታቀፈች ከሁለቱ አፋኞቿ ጋር ክክፍሏ ወጥታ ጭር ባለው መተላለፊያ ወደሚቀጥለው ክፍል አመራች፡፡ ከጎረቤቷ ክፍል መዝጊያ እንደደረሱ ሁለቱ ሰዎች በበሩ ግራና ቀኝ ጀርባቸውን ለጥፈው ቆሙ:: ቀጠን ያለው ሰው ሽጉጡን አውጥቶ ደረቱ ላይ ለጥፎ
ያዘው በስተግራዋ ያለው ሰው ደግሞ ከሽራ
👍2
​​ወዳለችበት ክፍል እንድትገባና ድምፃቸውን እንዲያጠፉ ነገራት፡፡ ሴትየዋ
ወደ መኝታ ክፍሏ ስታመራ ካልቨርት በፍጥነት ወደ ዋናው በር ሄዶ
መዝጊያው መቆለፉን ኣረጋገጠ፡፡ ወዲያው መብራቱን አጥፍቶ በስሷ
የጨረቃ ብርሃን እየተመራ ወደ ናትናኤል ተጠጋ፡፡

“እነሱ ናቸው::” አለ ካልቨርት ስማቸውን መጥራት እንደፈራ ሁሉ በሹክሹክታ፡፡
በጨለማው ውስጥ ኣንዳቸው የአንዳቸውን ትንፋሽ እያዳመጡ
ተጠባበቁ፡፡ ከተቆላፈው በር ጀርባ በመተላለፊያው ላይ የእግር ኮቴዎች
ተሰማቸው፡፡ተከትሎም ከጎን ያለው ክፍል ሰር ተበርግዶ ሰዎች ተከታትለው
ሲገቡ ኣዳመጡ፡፡ ካልቨርትና ናትናኤል በጨለማው ውስጥ በፍርሃት
ተያዩ፡፡

የርብቃ ጩኽት ድንገት አስተጋባ፡፡

ናትናኤልና ካልቨርት በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ፡፡ መተላለፊያው የእግር ኮቴ ተሰማቸው፡፡ ተጠባበቁ፡፡ የመኪና ድምፅ ሲጥጥ! አለ። ካልቨርት በቀስታ ወደ መስኮቱ ተጠጋ፡፡ ቀደም ብለው ከአፓርትመንቱ አጥር ግቢ በር ላይ ከቆሙት ሁለት ተደርበው ከቆሙ ሌሎች ሁለት መኪናዎች የወረዱ ስምንት ስዎች የያዙትን የጦር መሣሪያ ለመሸሸግ እንኳን ሳይሞክሩ ወደፊት እንደደገኑ የአፓርትመንቱን የአጥር በር አልፈው ተከታትለው ገቡ:: ከግቢው መሃል እንደደረሱ ከአፓርትመንቱ ከወጣ አንድ ሰው ጋር ሰብሰብ ብለው ተነጋገሩ፡፡ ወዲያው ሁለቱ ሰዎች ወደ መጡባቸው
መኪናዎች ሲመለሱ የተቀሩት ወደ አፓርትመንቱ ተጣደፉ፡፡ ካልቨርት ወደ
ናትናኤል ተመልሶ ያየውን ሁሉ ለናትናኤል አንሾካሾከለት፡፡

“አፓርትመንቱን የሚፈትሹ ይመስልሃል?”አለ ናትናኤል ጨለማው
ላይ አፍጥጦ፡፡

“ፈጣሪ አያድርገው::”
“ስንት ሰዓት ነው?” ናትናኤል ጠየቀ፡፡
“ሁለት ከሰላሳ፡፡” አለ ካልቨርት ሰዓቱን ወደ አይኑ አስጠግቶ፡፡

የመኝታ ቤቱ በር ተከፈተ:: ከውስጥ የሚወጣው ደብዛዛ ብርሃን የሳሎኑን ጨለማ ወገግ አደረገው የሆፃኗ እናት አንድ ነገር ታቅፋ ተጠጋቻቸው፡፡

“ተገላገለች፡፡” አለች በሚንቀጠቀጥ ድምፅ፡፡

"ባለ ግሮሰሪዋም አርጊት ቀረብ ብለው የህፃኑን ፊት ትኩር ብለው ተመለከቱት
ካልቨርትና ናትናኤል የሚመልሱት ግራ ገብቷቸው በጨርቅ በተጠቀለለው
አዲስ ህይወት ላይ አፈጠጡ፡፡

ወንድ ልጅ ተገላገለች:፡” አለች የህፃኗ እናት ድጋሚ ወንዶቹ ያልሰሟት ይመስል ዝም ሲሏት አሁንም ከወንዶቹ መልስ አላገኘችም። ሁለቱም ቡዝዝ ብለው እሩቅ ሄዱበት።


ቆንጆ ልጅ እይደለም?” አለች ከተደናገጡት ወንዶች መልስ ያጣችው ሴት ፊቷን ወደ አሮጊቷ መልሳ በአማርኛ::

“የዛሬ ልጆች ቆንጆዎች ናቸው::” አሉ አሮጊቷ አይኖቻቸውን ከህፃኑ ፊት
ላይ ሳያነቅሉ፡፡

ሴቶቹ፡፡ በአማርኛ ቋንቋ የተመላለሱት ያልገባው ካልቨርት ወደ ናትናኤል ፊቱን መልሶ ጠየቀው::

“ምንድነው ያሉት?

"የዛሬ ልጆች ቆንጆዎች ናቸው ነው ያሉት” አለው ናትናኤል የሚታገለውንና የሚተናነቀውን የደስታ እንባ እየታገለ፡፡

💫 ተፈፀመ 💫

#ቆንጆዎቹ ይህን ይመስላል በደራሲ ሠርቅ-ዳ በ 1988 የተዘጋጀው ቆንጆዎቹ ተወዳጅ መጽሐፍ ከዚህ በፊት ያነበባችሁት ለትውስታ ያላነበባችሁት ደግሞ በክፍል በክፍል ተዘጋጅቶ እንድታነቡት ቀርቦ ዛሬ ተጠናቀቀ ሁሌችሁም አስተያየታችሁን ብታደርሱኝ ደስ ይለኛል።

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍31