አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
456 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...አስራ ስድስት ወራትን በክብረ መንግስት አሳልፋ ወዴ ዲላ የተመስሰችው ሔዋን ብዙ አካባቢያዊ ለውጥ ሊገጥማት እንደሚችል ገምታ ነበር፡፡ነገር ግን ከሽዋዬ ቤት በዘመናዊ የቤት እቃዎች መሞላትና ወንድ ወንድ ከመሽተት በቀር ሁሉም ነገር ያው ነው።በሸዋዬ ቤት የወንድ ኮትና ጃኬት ግድግዳ ላይ ተሰቅለው የወንድ ጫማ በአልጋ ሥር ተቀምጦና ትልቅ የወንድ ፎቶ ግራፍ ብፌ ላይ ስታይ ሸዋዬ ባል ያገባች መስሎ ተሰማት። በእርግጥም “ማንዴፍሮን ገና የገባች እለት ተዋወቀችው።
ማንደፍሮ መልኩ ጥቁር ፊቱ ጉሩድረድ ያለና አካሉ ግዙፍ
ከመሆኑ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጨብጣት የእጁ አከባበድ የሚያስፈራ ሆኖባት ቢሆንም እያደር ስትግባባው ግን ባህሪው ቀላል የሆነ ሰው ነው። ይስቃል
ይጫወታል። ቀልዶቹ ይጥማሉ፡፡ እየሰነበተች ስታየው እንዲያውም በእሱ መኖር ቤቱ ድምቅ ሲል መንፈሷም ዘና እያለ መጣ፡፡ «የኔ ፍልቅልቅ» በማለት እያጫወተም ይበልጥ ያፍለቀልቃት ጀመር።
ዲላ እንደገባች በአፍንጫዋ የገባው አየር በአስቻለው የሰቀቀን ትዝታ የተለወሰው ነበር፡፡ ሆዷን ባር ባር እያለው እንባዋም ያለ ገደብ ፈስሷል። ያም ሆኖም
በተለይ ታፈሡን፣ በልሁን መርዕድንና ትርፌን አግኝታቸው በጋራ አልቅሰውና አንብተው እፎይ ካሉ ወዲህ ከፊል የመንፈስ መረጋጋትም እያደረባት ሄደ። ሸዋዬም ለአባትና ለእናቷ የገባችውን ቃል ያከበረች መሰለች! ሔዋን በማንኛውም ሰዓት ወደ
ታፈሡ ቤት ሄዳ የቱንም ያህል ጊዜ ቆይታ ብትመለስ የት ነበርሽ ምን አስቆየሽ?” አትላትም፡፡ ለሔዋን ከምንም በላይ የተመቻት ይህ የሸዋዬ ቃል ማከበር ነው።

ለአንድ አስራ አምስት ቀናት ያህል በዚህ አይነት እንፃራዊ የመንፈስ
መራጋጋት ውስጥ የሰነበተችው ሔዋን ሦስተኛው ሳምንት ሲጀመር ግን ያ በሸዋዬ ቤት የመኖር ሥጋቷ የልቧን ግድግዳ ማንኳኳት ጀመረ፣ በድሉ አሸናፊ ማንደፍሮን እየተከተለ በዚያ ቤት ውስጥ ገባ ወጣ ማለት ጀመረ፡፡ ማንደፍሮ ስለ ሔዋን ብዙ ነገር ሲነገረው ከርሟል። ከአስቻለው ጋር የነበራት ግንኙነት፣ በድሉ ሔዋንን ለመቅረብ ያደረገዉ ጥረትና የሰጠችው ምላሽ፣ በአሁኑ ወቅት አስቻለው ስለሚገኝበት ሁኔታና ሌሎችም ሁኔታዎች በዝርዝር ተገልፀውለታል፡፡ ወደፈት
የበድሉንና የሔዋንን ጉዳይ እንዲጨርስም አደራ ተጥሎበታል፡፡
ምንም እንኳ በአስቻለውና በሔዋን መካከል የነበረው ግንኙነት በተዛባ ሁኔታ የተነገረው የተሳሳተ መንገድ እንዲከተል የተገፋፋ ቢሆንም ማንደፍሮ ግን
ሆዱን ፍርሃት ፍርሃት ይለው ነበር። ሁኔታው ምንም ይሁን ምን አንድ ነገር ተገንዝቧል። ሔዋን የምታፈቅረው ሰው አላት። ያ ሰው ለጊዜው በአካባቢው ባይኖረም በተስፋ እየጠበቀችው እንደሆነ ልብ ብሏል። የተጣለበት አደራ ደግሞ ይህን ተስፋ በጥሶ ሌላ እንዲቀጥል ነው። እናም ለህሊናው እየከበደው ውስጥ ውስጡን ይጨነቃል።
በሌላ በኩል ደግሞ ጉዳዩ የበድሉ ነው፣ የሥራ ዋስትናው። እንዲሁም የሸዋዬም ጭምር ነው፤ የአፍላ ፍቅረኛው፡፡ በዚህና በመሳሰሉት ሁኔታዎች እየተገፋፋ የተጣለበትን አደራ መወጣት የሚያስችሉ መላዎችን ሲፈጥር ሰንብቷል።አንድ ቀን በተለመደው
ሁኔታ በድሉና ማንደፍሮ በሽዋዬ ቤት ጫት ለመቃም አቅደው ከሸዋዬ ጋር በተደረገ ምክክር ቤቱ በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል። ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ከቤቷ ሲደርሱ ማንደፍሮ ከቤቱ ወለል ላይ ቆሞ ለየት ያለ ሀሳብ አቀረበ
«ዛሬ ከምንም ነገር በፊት አንድን ነገር መፈፀም አለበት።» አለ በዚያ ሰዓት ጓዳ ውስጥ ለነበረችው ሔዋን በሚሰማ ሁኔታ ድምፁን ከፍ በማድረግ።
«ምን?» አለች ሽዋዩ እንደማታውቅ ሆና፡፡
«ሔዋን የለችም እንዴ?» ሲል ማንደፍሮ እንደገና ጠየቃት፡፡
«አለች። ጓዳ ውስጥ ናት፡፡»
«ኑ ሁላችንም ወደ እሷ እንሂድ፡፡» አለና ማንደፍሮ ቀድሞ ወደ ጓዳ
ተራመደ። በድሉና ሸዋዬም ተከተሉት::
«የኔ ፍልቅልቅ» ሲል ጠራት ማንደፍሮ ሔዋንን፡፡
«አቤት» አለች ሔዋን ድንግጥ እያለች፡፡ የዚያን ዕለት ደግሞ የልብ
ህመሟ ዘወር ብሎባት ፍራሽ ላይ ጋደም ብላለች፡፡
«አንድ ጊዜ ብድግ ብትይ!»
ሔዋን በድንጋጤ ዓይኗ ፍጥጥ እንዳለ ተነስታ በዚያው ፍራሻ ላይ
ቆመችና ከፊት ለፊቷ የተኮለኮሉትን ሁሉ ተራ በተራ ታያቸው ጀመር፡፡
«ዛሬ ዛሬ ሁሉም ነገር ገብቶኛል፡፡» አለ ማንደፍሮ ሳቅ ብሎ። “ይህ ሰውዬ!» ሲል ቀጠለ ወደ በድሉ እያመለከተ ወደዚህ ቤት በመጣ ቁጥር ስሜትሽ ለምን እንደሚቀያየር ተረድቻለሁ። ያለ ፍላጎትሽ እየጎነተለ ሲያስቀይምሽ እንደቆየ ገብቶኛል።አሁን አሁን ጥፋት መሆኑን አምኖ ተቀብሏል፡፡ ይቅርታም ሊጠይቅሽ ተዘጋጅቷል።ይቅርታውን ተቀብለሽ እንድትታረቁና ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ እየተያየን እንድንኖር ፈልጌለሁ።» አላት።
ሔዋን ያላሰበችውና ያልጠበቀችው አቀራረብ ነበር። ለጊዜው ግን ድንግጥ ተብላ ወደ መሬት ከማቀርቀር በቀር ያለችው ነገር አልነበረም። ማንደፍር ወደ በድሉ ዞር አለና ቆጣ ባለ አነጋገር «በል እግሯ ላይ ውደቅ!» ሲል አዘዘው፡፡ በድሉ ኮቱን ወደ ኋላ መለስ አድርጎ በሔዋን እግር ላይ ወደቀ፡፡
«እልልልል» አለች ሽዋዬ። ማንደፍሮም ብቻውን አጨበጨበ። ለሔዋን ግን ትልቅ የእረብሻና የግርግር ጩኸት ወስጥ የገባች መሰላት፡፡ በድሉ በእግሯ ላይ ወድቆ ለአፍታ ሲቆይ ለመግደርደር ያህል እንኳ በቃ ተነስ አላለችውም። ሲበቃው ራሱ ተነሳ::
«ቀጥል!» አለ ማንደፍሮ ነገሩን በማሟሟቅ ዓይነት ፈንደቅ እያለ፡፡
በድሉ ቀኝ እጁን በኮቱ ኪስ አስገብቶ አንዲት በብልጭልጭ ወረቀት የተጠቀለለች ነገር አወጣ፡፡ ወረቀቱን ቀዶ ጣለ፡፡ ከማይካ የተስራች ነጭ ሙዳይ
ብቅ አለች፡፡ እሷንም ከፈታት። በቅድሚያ ጥጥ መሳይ ነገር ታየ። ቀጠለና በግምት አሥራ አራት ግራም የሚሆን የክርስቶስ የስቅለት ተምሳሌት ማጫዎች
የተንጠለጠለበት የወርቅ ሀብል አወጣና በአንገት ውስጥ ለማስገባት የተዘጋጀ በሚመስል ሁኔታ ከያዘ በኋላ ፈገግ እያለ ማንደፍርን አየት አደረገው::
«ቀጥላ! ምን ታየኛለህ?» አለ ማንደፍሮ፡፡ በድሉ እነዚያን አራት ገጣጣ ጥርሶቹን ገልፈጥ አድርጎ ወደ ሔዋን ጠጋ ሲል ሔዋን ግን ድንገት ጮኸች::
«አልፈልግም!»
«ተይ እንጂ የኔ ፍልቅልቅ አለ ማንደፍሮ እሱም ደንግጥ አያለ፡፡
«እምቢ! አልፈልግም» ሔዋን አሁንም፡፡ ፊቷን ክስክስ አድርጋ በድሉን በጥላቻ ዓይን ታየው ጀመር።
«አይ እንግዲህ!" አለና ማንደፍሮ ሔዋንን ወደ ራሱ ጎተት አደረገና ሁለት እጆቿን ያዝ በማድረግ «አጥልቅላት » አለው በድሉን።
በድሉ የሔዋን እጆቿ እንደተያዙለት ሀብሉን በአንገቷ ላይ የመጣል ያህል አስገብቶ ወደ ኋላው ፈግፈግ አለ።ማንደፍሮና ሸዋዬ አጨበጨቡ፡፡ ማንደፍሮ በሔዋን አንገት ላይ ያረፊቱን ሀብል በእጁ ያዝ አድርጎ ወርቁንም ሔዋንንም
ተራ በተራ እየተመለከተ«አንቺን ለመሰለች ቆንጆ የሚገባ ልዩ ስጦታ!» አላት።
ሔዋን ግን ዓይኖቿ በእንባ ሞሉ፡፡ ግንባሯን በከንዷ ጋርዳ ወደ መሬት
በማቀርቀር ታለቅስ ጀመር።
«ሔዋን እንዳንቀያየም» አላት ማንደፍሮ። ሔዋን መልስ አልሰጠችውም፡፡አሁንም አጎንብሳ ታለቅስ ጀመር፡፡
👍8😱1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....ጥቂት ቀናት አለፉ። አንድ ቀን ምሽት ላይ በልሁና መርዕድ በምህጻረ ቃል አምሆ ተብሎ በሚጠራው ሆቴል ውስጥ ከውጭ ወደ ቡና ቤቱ ሲገቡ በስተቀኝ በኩል በምትገኝ ብቸኛ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብለው ከአንዲት የቡና ቤቱ እስተናጋጅ
ጋር እየተቃለዱ ይጠጣሉ። ከጠረጴዛው ፊትለፊት ያለው ባንኮኒና የቡና ማሽን ብቻ
ስለሆነ ቦታው እንደ ልብ ለመጫወት አመቺ ነው። የቀልዳቸውና የጭውውታቸው
ማዕከልም የመርዕድ ዓይን አፋርነት ነው:: አስተናጋጇ ባህሪውን ቀደም ብላ ስለምታውቅ በነገር እየነካካች ታሳፍረው ይዛለች፡፡መቼም የአንተን ድንግል የምወስደው እኔ ነኝ፡፡» ትለዋለች ጉልበቱንና ጭኖቹን እያሻሸች።
«እስቲ እንደ ምንም ብለሽ ገላግይው::» በልሁ እየሳቀ፡፡
«አቦ ተይኝና ሌላ ወሬ አምጪ!» ይላል መርዕድ የአስተናጋጇን እጅ ከላዩ ላይ ለማንሳት እየሞከረ።
አይዞህ! ቦታውን እንደሆነ እኔው ራሴ አሳይሃለሁ፡፡» አስተናጋጇ አሁንም።
«እንዲህ ከመባል ሞት ይሻላል መርዕድ!» እያለ በልሁ ይስቃል::
እንዲህና እንዲያ እያሉ በመጫወት ላይ ሳሉ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ሁለት ሰዎች ተከታትለው ወደ ቡና ቤቱ ገቡና ግራ ቀኝ ተመለከቱ፡፡ ከበሩ
በስተግራ በኩል ያለው ዋናው ሳሎን በሰው ተሞልቷል። በቀኝ በኩል ያለችው ጠረጴዛ ደግሞ በእነበልሁ ተይዛለች። በቀጥታ ወደ ባንኮኒው በመጠጋት ጀርባቸውን ለእነበልሁ ሰጥተው ቆሙ:: ወዲያው ደግሞ በድሉ አሸናፊ ከውጭ መጥቶ
ተቀላቀላቸው:: እሱ ከመሀል ሌሎቹ ግራና ቀኝ በመሆን ፈንጠር ፈጠር ብለው ተደረደሩና የሚጠጡትን አዘዙ፡፡ ለሁሉም አረቄ ቀረበላቸው ::
በልሁ ግን ቅፍፍ ይለው ጀመር፡፡ እሱና በድሉ ቀድሞም ተዳፍጠው ነበር የኖሩት. ዜሬ ደግሞ ገና ሲገባ ገልመጥ አድርጎት ነበርና
እንዲሁም ከተማ ውስጥ አይቷቸው ከማያውቃቸው ሰዎች ጋር ገጥሟልና ጥርጣሬ ገባው መጠጥ አወሳሰዳቸውም አላምር አለው ግልብጥ ግልብጥ ያደርጉታል። በሹክሹክታም ሲወያዩ ያያቸዋል። ወደ ኋላቸው ዞር እያሉ ሲገላምጡት ያይ ጀመር
መርዕድና አስተናጋጇ የሚያወሩትን ትቶ እነ በድለን መከታተል ቀጠለ፡፡
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከምሽቱ ሁለት ሰአት አለፈ። የመደመጥ እድሉን እዚያው የተፈጠረበት አገር ረስቶ የመጣው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቡና ቤቱ ውስጥ ተከፍቶ ያለ ምንም አድማጭ ለራሱ ይጮሀል። ዜና እወጃውን ጨርሶ የግብርና ፕሮግራም ማስተላለፍ ጀምሯል።የመስኖ ስራ እንቅስቃሴ እያሳየ ገበሬዎች ያገኙትን ጠቀሜታ ይዘረዝራል።
በድለና ጓደኞቹ ከቴሌቪዥኑ ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ወሬ ማውራት ጀመሩ። ያም ቢሆን ከበልሁ ጀሮ ደረሰና እሱም በጥንቃቄ ያዳምጥ ጀመር፡፡ከበድሉ በስተቀኝ በኩል ከቡና ማሽኑ አጠገብ ቆሞ የሚጠጣው የበድሎ ጓደኛ "ስሚ አንቺ"
ሲል ጨራት ከባንኮኒ ውስጥ ቆማ የነበረችውን አስተናጋጅ።
«አቤት» አለችው።
የኢትዮጵያ ገበሬዎች ቴሌቪዥን ገዙ ወይስ እኔና አንቺን ገበሬ ለማድረግ ተፈልጎ ነው ይኸ ፕሮግራም የሚተላለፈው ? ሲል ጮክ ባለ ድምፅ ጠየቃት።
«እኔ ምን አወቄ?» አልች አስተናጋጇ።
«የከተማ ገበሬ ሞልቷሌ አትይውም!» አላት ሌላው የበድሉ ጓደኛ ከግራ በኩል ሆኖ ወደ ኋላ
ዞር ብሎ በልሁንም አየት አደረገው፡፡
«ይኽ ከየጓሮው ወፍ ዘራሽ ቡና የሚለቅመው?» ሲል የመጀመሪያው ተናጋሪ ጠየቀ።
«ሞፈርና ቀንበራቸውን ሰቅለው ወደ ከተማ የገቡ ገበሬዎች ስላሉ
ጎምዥተው እንዲመለሱ ይሆናል፡፡ አለና በድሉ ወደ ኋላው ዞር ብሎ በልሁን ገልመጥ ሲያደርገው ዓይን ለዓይን ግጥምጥም አሉ፡፡

«አሃ» አለ በልሁ፡፡ ነገሮች ሁሉ ይበልጥ እየገቡት ሄዱ። ሁኔታው የበለጠ ጆሮውን ጥሎ እንዲያዳምጥ አደረገው።
ከተማ ውስጥ ገብቶ ማውደልደል የጀመለ ገበሬ ምንም ቢሉት ምን
ቢያደርጉት ተመልሶ ገጠር አይገባም፡፡» አለ የመጀመሪያው ተናጋሪ የበድሉ ጓደኛ፡፡
እሱም በልሁን ዞር ብሎ ሲያየው አሁንም ከበልሁ ጋር ተገጣጠሙ::
«ወዶ ነው! ተጎዶ ይመለሳል፡፡» በማለት በድሉ ሲጨምር በልሁ
ሁለመናውን ይነዝረው ጀመር፡፡ በልሁ ጠብ ጠብ ሲሸተው ትንፋሽ ያጥረዋል፡፡እስኪጀምር ድረስ መላ ሰውነቱ ይንዘፈዘፋል። ዓይኑ ይፈጣል፡፡ ያ በሽታው ተነሳበት:: በዚያው ስሜት ውስጥ ሆኖ ምልልሳቸውን ማዳመጡን ቀጠለ፡፡
«ስሚ አንቺ!» ሲል ተጣራ በድሉ አሁንም እስተናጋጇን፡፡
«አቤት»
«ይህን ቴሌቪዥን ዝጊና «ቆይ ብቻ» የሚለውን ካሴት ክፈች፡፡ ይኸ ሴት አውል ሁሉ ልብ ቢገዘ» አለና አሁንም ዞር ብሎ በልሁን ገላመጠው ።
በዚህ ጊዜ በልሁ ለየለት፡፡ ተዘጋጅተው እንደመጡብትም በትክክል ተረዳ፡፡
ወዲያው በግራ ጣቱ ላይ ያጠለቃትን ባለ ፈርጥ ቀለበት ወደ ቀኝ ጣቱ አዛወራት፡፡
ጡንቻውን ማጠባበቅ ጀመረ። አንዲት የትንኮሳ ቃልና ግልምጫ ብቻ ቀረችው። ይጠባበቃትም ጀመር።
በድሉ አሁንም ቀጠለ፡፡ እንኳን የግብርና ወሬ መስማት የግብርና ባለሙያ ነኝ ባይ በከተማው ውስጥ ማየት አስጠልቶናል። አለና ብርጭቆዉን ብድግ አድርጎ
አረቄውን ጨለጠና ከመጠን በላይ ባንኮኒ እያንኳኳ «ቶሎ በይ ነዳጅ ጨምሪ ዛሬ የማነደው አለኝ» አለና አሁንም ወደ በልሁ ዞር አለ።
«ስማ አንተ» አለው በልሁ መርእድን
«ወይ» አለ መርእድ። መሰከረ እየሆነ ያለውን ነገርም ይከታተል ነበርና ደንግጦ መግቢያ ቀዳዳ አቷል
«ከተቀመጥክበት ንቅንቅ እንዳትል እሺ»
«ለምን ወጥተን አንሄድም?» አለ መርዕድ፡፡
«ጉዳዩን እስከምፈፅም" ጠብቀኝ» አለና በልሁ ከወንበሩ ላይ ተነስቶ
በቀጥታ ወደ ባንኒው አመራ፡፡ በበድሉ እና በቀኙ በኩል ባለው ጓድኛው መካከል ባንኮኒ ተደግፎ ቆመና «ጎበዝ» አላቸው ሦስቱንም ተራ በተራ እየተመለከተ፡፡
«የጨዋታችሁ ደስ አለኝና መጣሁ።» እያጋበዛችሁኝ ወይ እየጋበዝኳችሁ እንጫወት
ብዬ ነው::» አላቸው ዓይኑን ፈጠጥ ያለ ቢሆንም ነገር ግን ፈገግ ብሎ
«ታውቀናለህ?» አለው በድሉ በቁመት የሚበልጠውን በልሁን አንጋጦ እየተመለከተ፡፡
«ይመስለኝ ነበር፡፡ አሁን ግን እንደማንተዋወቅ ገባኝ፡፡ ግን ደግሞ ሳንተዋወቅ እንለያይም።» ሲል መለሰለት በልሁ ረጋ ብሎ። «ተገድጄ ወደ አገሬ ልመለስ ነውና የወጪ ልበልህ፤ ጠጣ!» አለው አሁንም እያፌዘ።እስከዚህ ወቅት
ድረስ የበድሉ ጓደኞች ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፡፡ ግን በልሁን በግርምት ዓይን ይመለከቱታል።
«ነገር ፈልገሃል እንዴ?» አለ በድሉ አሁንም በልሁን እየተመለከተ::»
«ራሱ ፈልጎኝ ነው የመጣሁት።
አሁን ጠጣ! ካልጠጣህ ግን
እመታሀለሁ፡፡»
«ኣ?» ብሎ በድሉ ቀስቀስ ሊል ሲል በልሁ ድንገት አንገቱን አነቀወ። ገበሬ አይደለሁ ፊትህን ላርሰው ነው» አለና በመሀል ፊቱ ላይ ሀይለኛ ቡጢ አሳረፈበት፡፡ በፍጥነት ደገመው ከቀኙ በኩል ያለውን የበድለን ጓደኛ እንቅስቃሴ
ይከታተል ነበርና እውነትም ሲንቀሳቀስ አይቶት ኖሮ በቃሪያ ጥፊ ዓይነት በሀይል ሲሰነዝርበት ጆሮ ግንዱን አገኘው። ሰውየው ባላሰበው ሁኔታና ሀይል ስለተመታ
ከመርዕድ እግር ስር ወድቆ ጥቅልል አለ። መርዕድ በዚያው ጀመረው። በወደቀበት
👍12
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

..ሔዋን የልብ ህመሟ ከመቼውም ጊዜ ብሶባት ፍራሽ ላይ ድፍት ብላ
መዋል አዘውትራለች።በበልሁ በጢ ፊቱ የተጠረማመሰው በድሉ አሸናፊ አልጋ ላይ ከዋለ አስራ አንድ ቀን ሆኖታል፡፡ እዚሁ ቀን ላይ ሆኖ ሲቆጠር “ማንደፍሮ በአንድ ሳምንት ያህል ተረኛ ሆኖ በተመደበበት ከአዋሳ ይርጋለም መስመር ላይ ለመስራት ከቤቱ ከወጣ ሶስት ቀናት አልፎታል።
እለቱ እሁድ ነው፣ ከሰአት በኋላ፡፡ ሸዋዬ ቤትዋ ውስጥ ለብቻዋ ቁጭ ብላ ጫት ትቅማለች።
ነገር ግን የጎረሰችውን ጫት ማላመጥ እስከምትረሳ ድረስ
በሃሳብ ተውጣ ፍዝዝ ትክዝ ትላለች። በበድሉ ላይ የደረሰው ውርደት ከእሱ ይበልጥ እሷን አሳፍሯታል። ዛሬ በማውጠንጠን ላይ ያለችው ሃሳብም ይህንኑ
ሀፍረትና ውርደት ስለምታካክስበት መንገድና ሁኔታ ነው።
መነሻ ያደረገችው ከራሱ ከበድሉ የመነጨ ሀሳብ ነው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በተኛበት አልጋ አጠገብ ቁጭ ብላ ስታፅናናው በነበረችብት ወቅት በድሉ
አንድ ነገር ተናግሯታል ሸዋዬ! በእህትሽ ምክንያት ደሜ ፈስሷል፡፡ ቅሌት ደርሶብኛል። መካሻዬም እሷው ናት:: የመጣው ይመጣል እንጂ አልተዋትም። ወይ
እንደኔ ትዋረዳለች። አለያም እስከ መጨረሻው በእጄ ትገባለች። ለዚህ ደግሞ የአንቺን የአላሰለሰ ጥረት እጠብቃለሁ የሚል፡፡ የዛሬው ህሳብና ትካዜዋም በዚሁ
ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡ ከበድሉ የዛቻ ቃሎች በተግባር ተፈጽሞ ማየት የምትፈልገው ሔዋን ጥቅልል ብላ በእሱ እጅ መግባቷን ብቻ ነው::
ሸዋዬ ያለማወላወል በአንድ ሀሳብ ፀንታለች። ሔዋን ከበድሉ እጅ እስከ ወዲያኛው ትገባ ዘንድ አንድ አጋጣሚ ተፈጥሮ ከእሱ መፀነስ ይኖርባታል። ይህ ከሆነ መንገዶች ሁሉ ያጥራሉ፡፡ ሔዋን አስቻለውን በተስፋ የመጠበቅ ሀሳቧ ይቀየራል ቢመጣ እንኳን መሸሹን ትመርጣለች። አስቻለው ራሱም ዘወር ብሎ ሊያያት አይሞክርም አንዴ ከወለደች የልጅ አባት ያስፈልጋታልና በድሉን መራቅ አትፈልግም ምርጫዋም እሱና ብቻ ይሆናል። ማርገዟ ያሳፍራትና ከነታፈሡና ከነበልሁም ትርቃለች እንዲያውም ጭራሽ እንዳያውቁባት ወደ ቤተሰቦቿ ወደ ክብረ መንግስት ልሂድ ከሰል ትችላለች ያኔ በድሉም ወደዛው መመላለስ ይጀምራል በዚያው ከቤተሰቦቿ ይተዋወቅና እጁንም መዘርጋት ይጀምራል። ይሄ ደግሞ ለሸዋዬ ድርብ ድል ይሆናል "እኔም ለዚህ ብዬ ነበር" ለማለት ያበቃታል ይህንም ወርቃማው መላ ብላ ሰይመዋለች።

ይህን ወርቃማ መላ ለፍሬ ለማብቃት ግን በድሉ ከሔዋን ጋር
የሚፈፅመው የወሲብ ግኑኝነት
በተጠና ወቅትና ሰዓት መሆን እንዳለበት ታምናለች ለዚህ መሰረት የሆናት ደግሞ በወር አበባ አቆጣጠር የሚታወቅ
የእርግዝና ወቅት ነው። እንደ ሔዋን ለመውለድ ሳይሆን ላለመውለድ ስትል ራሷ
ስትጠቀምበት ኖራለችና እውቀቱ አይቸግራትም የሚያስፈልጋት የሔዋንን የወር አበባ ዙር ማወቅ ብቻ ነው በየስንት ቀን እንደማታየት ካወቅች በየትኛው ቀን ግኑኝነት ብትፈፅም መፀነስ እንደምትችል ታውቀዋለች።በዚህ ሰአት ሔዋን ይፈፀምባት ዘንድ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ወስናለች። ሔዋን ጩኸት ብታሰማ
እንኳ በተያያዥ ሊነሳባት የሚችለውን ውግወት ጆሮ ዳባ ልበስ ልትለው ቆርጣለች።
የሔዋንን የወር አበባ ዙር ለማወቅ ግን ተቸግራለች፡፡ እሷን እራሷን
አትጠይቃት ነገር ሰሞኑን ተኳርፈዋል። በሌላ በኩል በትክክል ላትነግራት ትችልና
ጥረቷ ሊመክን ይችላል። አስተማማኝ እንዲሆንላት ሐኪም ማማከር እንደሚሻል ታይቷታል። ለዚህ ስኬት ደግሞ የሔዋንን የልብ ህመም መነሻ ማድረግ ፈለገች ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባርናባስ ወይሶ ታወሳት። እሱ ደግሞ የውጭ ሀገር ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ሥራው ከተመለሰ
ሰምብቷል። ከመጣም ተገናኝተዋል፡፡ ባል ማግባቷን ሰምቶ ተነጋግረውበታል፡፡ ባርኔ አልተከፋም እንዲያውም እንኳን ደስ ያለሽ ብሏታል በተገናኙ ቁጥር መቃለዳቸውን አልተውም። እናም የሔዋንን የልብ ህመም በማስመርመር ሂደት ምናልባት የወር አበባሽ ጋር ግንኙነት ካለው በሚል ሰበብ በሚቀርበው ሀኪም በኩል የወር አበባ ቀን መምጫ ዙር ሊያስጠናላት እንደሚችል ገመተች። ይህን ዘዴ ለራሱ ለበድሉ ብታካፍለው ከእሷ በተሻለ
ከባርናባስ ጋር ተመካክሮ ሲያሳካው እንደሚችል አሰበች፡፡ የዚያን ዕለት ልትነግረው ወሰነች።
ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ከቤቷ ወጣች፡፡ በቀበሌ ዜሮ ሦስት የመጨረሻ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው የበድሉ መኖሪያ ቤት ማምራት ጀመረት:
ቀኑ መሽት ብሎ ለዓይን መያዝ ጀምሯል፡፡ ወደ በድሉ ቤት በመሄድ ላይ ሳለች ልክ አስፋልቱ ላይ ስትደርስ ድንገት ሳታስበው ባርናባስን ከሩቅ አየችው
አስፋልቱን ይዞ ከታች ወደ ላይ ከሁለት ሰዎች ጋር በመሆን እሷ ወደነበረችበት አቅጣጫ ይመጣል:: ከበድሉ በፊት ለእሱ ስለ ውስጥ አሳቧ በዚያ አጋጣሚ ትንሽ ፍንጭ ልትሰጠው ወደደች፡፡ መንገድ ዳር ቆማ ጠበቀችው። ባርናባስ ልክ አጠገቧ ሲደርስ ከሰዎቹ ነጠል ብሎ ወደ እሷ እንዲመጣ በእጇ ጠቀሰችው፡፡ ባርናባስም ጥሪዋን ተቀበሎ ወደ እሷ ጠጋ እያለ
«የሽዋ፣ በጨለማ መንገድ ዳር ምን አቆመሽ?» ሲል ጠየቃት እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ።
ቸግሮኝ::» አለችው እንደመሽኮርመም እያለች።
«ምነው? ምን ገጠመሽ? አላት ባርናባስ። ሞቅ ስላለው አፉ ተያይዟል።
«ከቸገረኝ እንኳ ቆይቷል፡፡ ድንገት በሩቅ ሳይህ ግን ላማክርህ ፈልጌ ነው፡፡
«ምንድነው ችግሩ?።»
«ባክህ ያቺን እህቴን ልቧን እያመማት ተቸግሬአለሁ።» ምናልባት በደንብ ሊከታተላት የሚችል አንተ በተለይ የምትቀርበው ሀኪም ካለ አደራ ትልልኝ እንደሆነ ብዬ ነው።»
«እሱ ምን ይቸግራል ይዘሻት ነያ»
«ቢሮህ ውስጥ ምን ጊዜም ትኖራላህ እያደል?»
«የት እሄዳለሁ፡፡» ካለ በኋላ
ባርናባስ እጇን ያዝ አድርጎ «ድሮ እንኳ ወደ ዜሮ አምስት ቀበሌ ጎራ እል ነበር! ዛሬ ግን ማንዴ አስለቀቀኝ» በማለት ሳቅ ብሎ ሸዋዬንም አሳቃት።
«ሁሉም በጊዜው ሆኗል በቃ!» አለች ሸዋዬ እንደ መሽኮርመም እያለች።
«በቃ ! በቃ? አላት ባርናባስ አሁንም ወልገድገድ እያለ፡፡
«አብቅቶ»
«ታዲያ ያቺን ቆንጆ እህትሽን እንዴት አድርጌ ልጠይቃት?»
«እንዴ እሷን መጠየቅ ማን ይከለክልሀል?»
«አሁን እችላለሁ? ወይስ ስውየሽ ይኖር እንደሆን ብሎ ነገሩን ተወት
ሲያደርግ ሸዋዬ ቀጠለች።
«አሁን መሸ ጓደኞችህም ጥለውህ ሂዱ»
«እነሱን ተያቸው እባክሽ!» አለና እውነት ሰውየሽ ከሌለ ልጠይቃት
በጣም በጣም ናፍቃኛለች፡፡» ሸዋዬ የበርናባስሀሳብ አልከበዳትም ማንደፍሮ የለምና ዓይን ለዓይን አይጋጩባትም። በሌላ በኩል እግረ መንገዷን
ሔዋን ወደ ሐኪም ቤት እንድትሄድ ሊገፋፋት እንደሚችል ታያት፡፡
«ከበረታህ እንሂድ፡፡ እንደውም ቀኑን ሙሉ እንደተኛች ነው የዋለችው»
«ሰውየው ግን አይኖርም? አየሽ ምናልባት» ብሎ አፍ አፏን ሲጠባበቅ ሸዋዬ ቀጠለች፡፡ ለነገሩ ሰሞኑን አይኖርም የስራ ተራው ይርጋለም አዋሳ መስመር ሳይ ነው።» አለችና ግን ቢኖርም የኔና የአንተን ጉዳይ የት ያውቃልና
ይጠራጠራል ብለህ ሰጋህ?»
«አለመኖሩ ጥሩ!»
👍13
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_አንድ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....የእልሁን ያህል ወለል ላይ የተጋደመ ፊቷን በጫማው ረግጦ ድፍጥጥ ካደረጋት በኋላ እዚያው እንደተዘረረች ትቷት ወደ በር አመራ።.
«ዘወር በል!» አለ ማንደፍሮ በር ላይ ተኮልኩሎ ሁኔታውን ይመለከት የነበረው ሰው ሁሉ።
ሳሎን ውስጥ መግባት የጀመሩትም በር ላይ የተኮለኮሉትም ሰዎች ግርር ብለው ወደ ውጭ ወጡ፡፡
ማንደፍሮ ግቢ ውስጥ እየተጯጯህ ይርመሰመስ የነበረው ህዝብ መሀል
እየተራመደ «ማንደፍሮ ገና ዛሬ ተደፈረ ተደፈረ ተደፈረ!» ካለ በኋላ “ዋይ ዋይ ዋይ" እያለ
ከግቢ ወጣ። ግራ ቀኝ ሳይመለከት ቀጥታ ወደ ከተማ ሄዴ፡፡ያ በወያዘሮ ዘነቡ ግቢ ውስጥ ይተረማመስ የነበረ ሕዝብ ሁሉ እየተጋፋ ወደ ሸዋዬ ቤት ገባ፡፡ ርቃነ ሥጋዋን ወለል ላይ ተጋድማ ስታለከልክ ላያት ሁሉ
የምትተርፍ አትመስልም ነበር። የወሳንሳ ተሸክመው አልጋዋ ላይ አጋደሟት፡፡ወይዘሮ ዘነቡ እፈቷ ቆመው «ኧረ እስቲ ውሃ! ኧረ እስቲ ውሃ!» እያሉ ጮሁ፡፡ ውሃ
በፍጥነት ቀረበላቸውና በአፍና በአፍንጫዋ ይወርድ የነበረ ደሟን ሲያጥቡ በነበረበት ወቅት ድንገት ሳታስብ ሔዋን ከተፍ አለች:: በትርምስምሱ ደንግጣ እንዳልነበረ ሁሉ ጭራሽ ወደ ቤት ገብታ የሸዋዬን ሁኔታ ስታይ የባሰ በመረበሽ «ወይኔ ጉዴ! እት አበባ ምንድነው?» እያለች በድንጋጤ ትርገበገብ ጀመር።
በዚህ ሰዓት ሸዋዬ በሌባ ጣቷ ወደ ሔዋን እያመለከተች ድክምክም ባለ ድምፆ «ያዙል...ኝ! ይቺን ሰው ያዙልኝ! ጎረምሳዋን ቤቴ ውስጥ ደብቃ ያስገደለችኝ እሷ ናት! ያዙልኝ!» እያለች ጥሪ ታስተላልፍ ጀመር፡፡
ሔዋን ክው ብላ ደነገጠች። በአካባቢው የነበሩትን ሰዎች አየት አየት እያረገች ወደኋላ ታፈገፍግ ጀመር። ከሔዋን የበለጠ
በውሃ ያጥቧት የነበሩት ወይዘሮ ዘነቡ ከመደንገጥ በተጨማሪ ንድድ አላቸውና፡
«ኣ! ምን እያልሽ ነው አንቺ?» አሏት በቁጣ።
ሸዋዬ ግን አሁንም «ያዙልኝ! እሷ ናት ያስገደለችኝ! ያዙል..ኝ»
ማለቷን ቀጠለች።
ሔዋን ጉዳዩ ስላልገባት ይበልጥ እየደነገጠች ሄደች። ከቤት ወጣችና ግቢ ውስጥ ቆም ብላ ስታዳምጥ ሸዋዬ አሁንም ያዘልኝ እያለች ስትናገር ስትሰማ ጭራሽ ከግቢው ወደ ውጭ ወጣች። ደግነቱ ማንም ሊይዛት አልቃጥም እሷ ግን ደንግጣና ፈርታ ገልመጥ ገልመጥ እያለች በቀጥታ ወደ ታፈሡ ቤት ገሰገሰች፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ንዴታቸው ባሰ፡፡ ያጥቧት የነበረቱን ትውት አደረጉና ወደ ውጭ እያተራመዱ በዙሪያቸው ለተሰበሰበው ሕዝብ በሚሰማ ድምፅ።
ጎረቤቶቹ የሆናችሁ ወገኖቼ የሆናችሁ ሁሉ፣ ይቺን መዘዘኛ ሴት ዛሬውኑ ከቤቴ አውጡልኝ ቶሎ በሉ ዕቃዋን አውጡልኝ ቶሎ በሉ ለእናቷ ልጅ እህቷ ያላዘነች ነገ ለኔም አትመለስ ቀጣፊ ናት ወልወልዳ ናት የተረገመች» አሉ
በማከታተል፡፡ ለዚያች ዕለት እንኳ ቢለመኑ እሻፈረኝ አሉ፡፡ በአካባቢው የተከበሩ ናቸውና ልመናቸው ተከበረ።
በቦታው በርካታ ወጣቶች ስለነበሩ የሸዋዬን ዕቃ አንድ ባንድ እየለቀሙ ወደ ውጭ ማውጣት ጀመሩ። ተባባሪው በርካታ ስለነበር
የሸዋዬን የማውጣት ስራ አፍታ
አላቆየም፡፡ ሁሉም ከአጥር ውጪ ወጣ:: ወይዘሮ እልፍነሽ ዕቃዋን
ደረደሩላት በመፍቀዳቸው ከእሳቸው ግቢ ውስጥ እየገባ ተቆለለ፡፡ ራሷ ሽዋዬም በሰዎች
እቅፍ ተይዛ ወደ እሳቸው ቤት ተወሰደች።
ዝቅዝቅ የዶሮ ሸክም እንዲሉ የሔዋንና የአስቻለውን ፍቅር አፍርሳ የራሷን ቤተ ልትገነባ ደፋ ቀና ስትል የነበረች ሸዋዬ ህልሟ ሁሉ ከንቱ ሆነ።
ድሮም የውሸት ቤት ነበርና እነሆ በአንድ ቀን ፈረሰ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ከሶስተ ወር በኋላ ነው ፤ የጥር እና የካቲት ወራት መጋጠምያ
ሳምንት። በደንባራ በቅሎ እንዲሉ ወትሮም ግርግር የማይለያት ዲላ ከተማ ሰሞኑን ደግሞ በባስ ግርግር ውስጥ ሰንብታለች፣ የክፍለ ሀገሩ ስፖርት ሻምፒዮና ሲካሄድባት ሰንብቷል ። ከመላ የሲዳሞ ክፍለ ሀገር በርካታ ስፖርቱኞች መጥተው
ይርመሰመሱባታል፡፡ በተለይ በፈስቲቫሉ ማጠናቀቂያ ቀናት ስፖርተኞች በቡድን በቡድን እየሆኑ የመደባደብ አዝሚያሚያ ስለጀመሩ የፀጥታ ጥበቃውም በዚያው ልክ ተጠናክሯል በከተማዋ ውስጥ ያሉ ፖሊሶችና ሌሎች አጋር የፀጥታ ሐይሎች
በተጠንቀቅ ሆነው የከተማዋን ፀጥታ ይጠብቃሉ፡፡
ልከ ሻምፒዎናው በተጠናቀቃበት ቀን ፡ምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ
የተፈራው ሁከት የተነሳ መሰለ።
ከአንደኛ መንገድ በላይ ወደ አውራጃው አስተዳደር ፅህፈት ቤት መሄጃ አካባቢ ድንገት የእሪታና ኡኡታ ድምፅ ተሰማ። ወዲያው ደግሞ አንድ ጥይት ተተኮሰ። በርካታ የፀጥታ ሀይሎች ወደ አካባቢው መሮጥ ጀመሩ:: ስፖርተኞች የተጣሉ የመሰለው ህዝብና ሌሎች ስፖርተኞችም ወደዚያው ይጎርፍ ጀመር። ለዚያውምበሩጫና በጫጫታ ታጅቦ።
በርካታ ሰው እቦታው ሲደርስ ግን የጠቡ ዓይነትና መነሻው የተለየ ሆኖ ተገኘ የተጣሉቶ ስፖርተኞች ያልሆኑ ሁለት ሰዎች ናቸው መነሻው በአንዲት ሴት ምክንያት መሆኑ ይወራል ሰዎቹ ለድብድብ መጋበዛቸውን እንደ ቀጠሉ
ናቸው። አንዲት በዕድሜ ጠና ያሉ ሴት ደግሞ ከአንድ ቤት በር ላይ ቆመው ይለፈልፋሉ፡፡ «ያቺ ነውረኛ እኔ ደግሞ ደህና ሰው መስላኝ አንገት ደፊ አገር አጥፊ አሉ! ሆሆይ! የድሀ ቤቱን ልታስፈርሰው!» ይላሉ። ከሴትዮዋ አነጋገር በመነሳት አንድ ፖሊስ ጠጋ አላቸውና ‹‹ምንድነው ችግሩ የኔ እናት?» ሲል ጠየቃቸው።
አሪ በገዛ እጄ ጎትቼ ያመጣሁት ችግር ነው ልጄ ከሁለት ወር በፊት
ሳይሆን አይቀርም፤ አንዲት ሴትዮ መጥታ ቤት አከራይኝ ብላ መጣች፡፡ እኔ ደሞ ጨዋ መስላኝ አክራየኋት። ለካ ጋለሞታ ኖራ ይኸው ሁለት ወንዶችን በአንድ ጊዜ ቀጥራ ሰው ታፋጃለች::» አሉና እንደ እንዝርት በሚሾር ምላሳቸው እየተንጣጡ፡፡
«ጋለሞታዋ የታለች? » ሲል ጠየቃቸው ፖሊሱ::
ሴትዮዋ ከቆሙበት ቤት በታች ቀጥሎ ያለውን ክፍል በእጃቸው እየጠቆመው «እዚህ ቤት ውስጥ ናት ስራዋ አሳፍሯት ሳይሆን አይቀርም ቤት ዘግታ
ትነፋረቅልሀለች::» አሉት:: ፖሊሱ ወደ ተጠቆመው ቤት በር ጠጋ አለና እያንኳኳ
«ክፈች አንቺ! አለ።
«እምቢ! አንክፍትም!» የሚል ምላሽ ሰውስጥ ተሰጠው::
«ነገርኩሽ ብቻ! ፖሊስ ነኝ ክፈች!»
በሩ ተከፈተ፡ ሁለት ሴቶች ቆመው ያለቅሳሉ፡፡ ፖሊሱ በር ላይ ቆሞ ወደ ውስጥ እያየ ማንኛሽ ነሽ ጋለሞታዋ?» ሲል ጠየቀ::
«እዚህ ጋለሞታ የለም» አለች ከሁለቱ አንዷ፡፡ ሌላዋ አሁንም አጎንብሳ ታለቅሳለች እኒያ ላፍላፊዋ ሴትዮ ፖሊሱን ተከትለው ወደ በሩ ጠጋ ብለው ያዩ ነበርና
ነበርና ለፖሊሱ በእጃቸው እየጠቆሙ፡ «ይቺ አጎንብሳ የምትነፋረቀዋ ናት የማትረባ የቆንጆ በለል!» ካሉ በኋላ ወደ ኋላ መለስ እያሉ፡ «ይቺን ሁለት እጆቸን የፊጥኝ አስሮ አርባ መግረፍ ነበር እንጂ..»እያሉ ወደ መጡበት አቅጣጫ ተመለሱ።
ሕዝቡ ከዚያም ከዚህም እየጎረፈ አካባቢው በመደበላለቅ ላይ ነው፡፡
ፖሊሱ የተጠቆመችውን ጋለሞታ በቁጣ
«ነይ ውጪ” አላት በር ላይ እንደ ቆመ
«ለምን?» አለኝው በፍርሀት እየተንቀጠቀጠች፡፡
ፖሊሱ እንደ መናደድ አለና ገባ ብሉ በበይለኛ ጥፊ አንዴ አጮላት፡፡እንድና ከኋላ ዞሮ ወደ በሩ ይገፈትራት ጀመር፡ የቤቱን በር ወጣ እንዳለች ፖሊሱ አሁንም በሀይለኛ እርግጫ መቀመጨዋ ላይ ሲያሳርፍባት ወጀ ላይ ነጥራ.
👍18👎1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


.....የምትለቀቀውማ እንደ ነገሩ ሁኔታ ዋስ ጠርተህ ነው» አለው መርማሪው ፖሊስ፣ ነገሩ የዕለት ግጭት በመሆኑ ብዙም ርቀት በማይሄድ ምርመራ እንደሚጠናቀቅ መርማሪው
ያስባል። የጠረጴዛ ደወል
አቃጨለና ረዳቱ ፖሊስ ሲቀርብለት ዓለሙን ወስዶ መብራቴ ባዩ የተባለ ሌላ
እስረኛ እንዲያቀርብለት አዘዘው።
ረዳቱም የተባለውን ፈፀመ፡
መብራቴ ባዩም በዕድሜው ብዙ አልገፋም ፣ ከሠላሳ ብዙ አያልፈውም፡፡ቀጠን ያለ ቀይ ዳማ ቢጤ ነው። መካከለኛ ቁመት አለው፡፡ ፀጉሩ አጠር፣ ከወደ አፉ
ሞጥሞጥ፣ ዓይኖቹ አነስ እነስ ያሉ ናቸው። እሱም በተመርማሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ መርማሪውን በፍርሀት ይመለከተው ጀመር።
መርማሪው ፖሊስ ልክ በዓለሙ ላይ እንዳደረገው ሁሉ መብራቴን
መሠረታዊ መረጃዎችን እየጠየቀ ከመዘገበ በኋላ፡ «ከዓለሙ መርጋ ጋር ከአሁን በፊት ትተዋወቃላችሁ?» ሲል በቅድሚያ ጠየቀው።
«አይቸውም አላውቅ::»
«ምን አጣላችሁ ታዲያ?»
«እኔ ቀድሜ ገብቼ ባለሁበት ቤት መጥቶ ካልወጣህ ብሎ ሊያሳገድደኝ ሞከረ። አልወጣም ስለው በተቀመጥኩብት በጥፊ አቃጠለኝ ከዚያ በኋላ ነው
በደመነፍስ እጆቹን ይዤ ድረሱልኝ ብዬ የጮኩት።» አለው አይኖቹን እያቁለጨለጨ።
«በተጣላችሁበት ቤት ውስጥ ለምን ነበር ቀድመህ የገባኸው?»
«ቤቴ ነዋ!»
«ቤቴ ስትል? ሴትዮዋ ሚስትህ ናት?»
«ያው እንደ ሚሲቴ ናተ።»
«ለምን ያህል ጊዜ አብራችሁ ቆይታችኋል?»
«አረ ብዙ ነው።»
«እኮ በግምት?»
«ከአስራ አምስት ቀን በላይ አብረን አድረናል። ግን በተከታታይ
አደለም አልፎ አልፎ ነው፡፡ ከተዋወቅን ግን ቆይተናል፡፡»
«ወዳጅህ ስሟ ማን ይባላል?»
እየተገረመ ጠየቀው።
«ስሟ?»አለና መብራቴ ወደ ጣሪያ አንጋጠጠ፡፡ ግን ጠፋበት፡ ለማሰላሰል ሞከረና ሲያቅተው «ረሳሁት።» አለ የድንጋጤ ስሜት እየተነበበበት፡፡
«አሥራ አምስት ቀን ሙሉ የአቀፍካት ወዳጅህን» በማለት መርማሪው እየተገረመ ጠየቀው።
«በድንገት ስለሆነ የተገናኘነው ስሟ ይረሳኛል።»
መርማሪው ፖሊስ ጥርጣሬ ገባውና መብራቱን ትኩር ብሎ ተመለክተው።
መብራቴ የበለጠ የእፍረትና የድንጋጤ ስሜት ይነበብበት ጀመር።
«ዋሽተሃል አይደል?» አለው መርማሪው በትኩረት እየተመለከተው፡፡
«አጥፍቻለሁ ጌታዬ» አለ መብራቱ ሽቁጥቁጥ እያለ»
የመርማሪው ፖሊስ ልብ አሁንም እየተከረጢረ ሄደ ሆኖም ቃል
በያዘበት ወረቀት ላይ ከአስፈረመው በኋላ «የአንተንና የዓለሙን ጉዳይ በቀላሉ
ላለፈው አስቤ ነበር፡፡ ነገር ግን ተጠራጥሬአለሁ፡፡ የሁለታችሁንም ጉዳይ እንደገና
ኑነየው አልቀርም:: እለና ወደ እስር ቤት እንዲሄድ አሰናበተው፡፡
የመርማሪው ፖሊስ ጥርጣሬ ቀላል አልነበረም። ዓለሙን በሚጠይቅበት ወቅት ያያቸው ነነበሩ ሁኔታዎች እንደገና ትዝ አሉት። በስካር መንፈስ በአንዲት
ሴተኛ አዳሪ የተጣሉ መስለውት በእርግጥም ዋስ እያስጠራ በቀላሉ ሊሸኛቸው ነበር
አሳቡ:: አሁን ግን በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ምርመራ ሊያደርግ ወሰነ። ለማንኛውም አለ በሆዱ
እስቲ ጋለሞታ የተባለችው ሴት ሌላ አጠራጣሪ ፍንጭ የምታወጣ
ከሆነ በቅድሚያ እሷን ላናጋግራት፡፡” አለና በረዳቱ ፖሲስ እንድትጠራ አደረገ።
ጋለሞታዋ ተጠርታ ወደ መርማሪው ፖሊስ ቢሮ በር ላይ ስትደርስ ሁለመናዋ በፍርሀት ይንቀጠቀጣል፡፡ እንባዋ ከዓይኗ ላይ እንደ በረዶ ይረግፋል።
መልኳ ደግሞ ይህ ቀረሽ የማትባል ወብ ናት። ዓይኖቿ እንደ ንጋት ኮከብ ያበራል። በዕድሜዋ ገና ወጣት ልጃገረድ ትመስላለች። “ጋለሞታ በሚለፈው የሴትነት መገለጫ አንዳች አመልካች ነገር አይታይባትም። ከንፈሮቿ እምቦጦች ይመስላሉ፡፡ የአፍንጫዋ አቀማመጥ ለቄንጥ የተሰራ ይመስላል። የቀይና ነጭ
ቡራቡራ ድሪያ ለብሳ በጡቶቿ ተገትሮ የአንጀቷን ድራሽ አጥፍቶታል።የመርማሪው ቢሮ በር ላይ ደርሳ ምን እንደምትባል ትዕዛዝ እየጠበቀች ሳለች
መርማሪው ፖሊስ ግን ይህንን ገፅታዋን ሲያይ ድንገት ተዘናግቶ ኖሮ ፐ! ይችስ ታደብድባለች አለ በሆዱ። ወዲያው ደግሞ «ምን ያስለቅስሻል?» ሲል ፈገግ ብሎ ጠየቃት ሁኔታዋ ሁሉ እያስገረመው። ግቢ ቁጭ በይ ማለቱን እንኳ እረሳው፡፡
«ፈርቼ» አለችው እንዳቀረቀረች::
«የሰራሽው ስራ አሳፈረሽ!»
«አረ እኔ ምንም አልሰራሁም!»
«እስቲ ግቢና ቁጭ በይ አላት» በእጁ አገጩን ያዝ አድርጎ አሁንም በትኩረት እየተመለከታት። ጋለሞታዋ ቁጭ አለችና አሁንም በፍርሃት ስሜት አቀርቅራ መሬት መሬት ታይ ጀመር።
«ምን አድርገሽ ነው የታሰርሽው?» ሲል ጠየቃት መርማሪው ፖላስ ቀስ እያለ ሊያግባባት ፈልጎ።
«ምንም» አለችና ለቅፅበት ያህል ቀና ብላ አየችው፡፡
«ዓለሙንና መብራቱን የት ነው የምታውቂያቸው?»
«እነማናቸው እነሱ?» አለች አሁንም፡፡ ለቅፅበት ያህል ቀና ብላ አይታው እንደገና እንጋቷን ደፋች::
«ጭራሽ አታወቂያቸውም?»
«አረ እኔ እንደዚህ የሚባሉ ሰዎች አላውቅም።»
«ሁለቱም ወዳጃችን ናት እያሉ እኮ ነው፡፡» አለና መርማሪው ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ለምላሿ ጓጉቶ ይጠባበቃት ጀመር፡፡
"ኣ"አለችና እሁንዎ ቀና ብላ አየት አረገችው፡፡
«ከማናቸውም ጋር አብረሽ አድረሽ አታውቂም?»
«እኔ ከወንድ ጋር ተኝቼ አላውቅም፡፡»
«አንድም ቀን?»
«አንድ ቀን ብቻ ከምወደው ሰው ጋር አድሬ አውቃለሁ፡፡ ግን ከንፈሬን ስሞታል እንጂ ሌላ ምንም አላደረገኝም::»
«ማነው እሱ ደግሞ?» ሲል ጠየቃት መርማሬው።
«እሱ እዚህ አገር የለም፣ ኤርትራ እሚባል አገር ከሄደ ቆይቷል፡፡»
«ኦ!» አለ መርማሪው ፖሊስ አንዳች የማያውቀው ስሜት መላ ሰውነቱን ድንገት ወርር እያረገው፡፡ «ማን ይባላል?» ሲል እንደገና ጠየቃት::
«አስቻለው ፍስሀ»
«አስቻለው ፍስህ ?» ሲል ደግሞ ጠየቃት፡፡
«አዎ፡፡» አለችውና እሷም ድንግጥ ብላ ቀና ብላ ታየው ጀመር፡፡
«እንዴ!» አለና «መርማሪው እንደገና አትኩሮ ያያት ጀመር። ስሜቱ እያደር ተለዋወጠ፡፡ አንቺ ስምሽ ማን ይባላል?» ሲል ጠየቃት የምትሰጠው መልስ ቀድሞ እያስፈራው።
«ሔዋን ተስፋዬ::»
«ምን?» ሰምቶ እንዳልሰማ፡፡
«ሔዋን ተስፋዬ እባላለሁ።»
መርማሪው ፖሊስ ፍዝዝ ብሎ ቀረ፡፡ የያዘው እስኪርቢቶ ከእጁ ላይ ሾልኮ ሲወድቅ ፈጽሞ አልታወቀውም፡፡ ዲላ ከተማ እየኖረ ስለመሆኑ እንደ አዲስ
ታወቀው፡፡ በሀሳብ ጥቅልል ብሎ አስመራ ከተማ ገባ፡፡
መርማሪው ፖሊስ የሀምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ይባላል። በሲዳሞ ክፍለ ሀገር በሀገረ ማሪያም ከተማ ተወልዶ ያደገ ነው። እዚያው በፖሊስነት ተቀጥሮ
እስከ ምክትል አሥር አለቅነት የደረሰና እሱም እንደ አስቻለው ፍሰሀ የዘመቻ ግዳጅ ተወስኖበት
ወደ ግንባር ዘምቶ በኤርትራ ምራባዊ የጦር ግንባሮች ለተከታታይ አምስት ዓመታት ሲዋጋ የቆየ ነው:: በጦር ግንባር የፈጸመው ጀብዱ የሀምሳ አለቅነት ማዕረግ ካገኘ በኋላ በቀጣይ የውጊያ ወቅት በደረሰበት ቁሰለት የተዋጊነት
ብቃቱ ቀንሶ ወደነበረበት የፖሊስ ሰራዊት አባልነቱ እንዲመለስ ተወስኖለት ወደ ሲዳም የተመለሰና ጊዜያዊ ምደባ ዲላ ውስጥ በመርማሪነት እየሰራ ያለ ፖሊስ ነው።
👍2
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....ወደ ሲዳሞ በስተርጅና ዕድሜዬ ብቅ ማለት አስባለሁ፡፡» ካለ በኋላ ወደ ሃምሳ አለቃው ቀና በማለት ፈገግ እያለ
«ግን ደግሞ ከሀገሬ በፊትእኔ ቀድሜ ካረጀሁ » አለው
«አልገባኝም::»
«የሀገር እርጅና፡፡»
አስቻለው ወደ መሬት አቀረቀረና ራሱን ወዘወዘ አውቆም ይሁን ሳያውቅ ከንፈሩን ነከሰ፡፡ ስሮቹ በግንባሩ ላይ ተገተሩ። ፊቱ ተከፋ፡፡
«አስረዳኛ የኔ ወንድም አለው»
የሃምሳ አለቃ ክንዶቹን አቆላልፎ
ጠረጴዛውን በመደገፍ አስቻለውን እየተመለከተ።
«ሀገር በገዳዮቿ መዳፍ ወስጥ እስከ ገባኝ ድረስ ምናልባት እንደ ሰው አትቀበር እንደሆነ እንጂ ማርጀት ቀርቶ ልትሞትም ትችላለች» አለ አስቻለው ፊቱ ክፍት እያለውና ጣሪያ ጣሪያ እያየ፡፡
«ስትል?» ሲል ጠየቀው የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ፡ የአስቻለው አነጋገር ሚስጥሩ ለጊዜው ባይገባውም ግን ደግሞ በውስጡ ብዙ ነገር ስለመሆኑ ከወዲሁ ገምቷል።
«አየህ ሃምሳ አለቃ!» ሲል ቀጠለ እስቻለው፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ ያሉ የህዝብና መንግስት ከተኮራረፈ ምድርና ሰማያዋም ይቀያየማሉ። ያኔ ከዜጎቿ ልብ
ውስጥ ተስፋ ይጠፋል፡፡ ተስፋ የሌለበው ሕዝብ ጭካኔ ይወልዳል።በተለይ ደሃ ከጨከነ
ጠላት የሚያደርገው የገዛ ሀገሩን ነው፡፡ አምባገነኖች የቱንም ያክል
ጡንቻቸው ቢፈረጥም ድሀን ማስተዳደርና መቆጣጠር አይችሉም፡፡ እንዲያውም
በቁጣው እነሱንም ያጠፋቸዋል፡፡ ያኔ ገዢና ተጎዢ አይኖርምና 'ጥፋት ይነግሳል::በዚህ ጊዜ ሀገር መታመም ትጀምራለች። ታዲያ ይህ ከሆነ ሀገር አልሞተችም፣?
የሃምሣ አለቃ ሲል ጠየቀው።
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ባላሰበውና አስቦትም በማያውቅ የተለየ እሳቤ ወስጥ ገባ፡፡ አንዳች አስፈሪ ስሜት ውስጥ ገባ። አንዳች አስፈሪ ስሜት መጣበት እስከዛሬም እንደ ሰው ስለመኖሩ ተጠራጠረ። ፍርሀትና ጭንቀትም አደረበት። በረጅሙ ተነፈሰና
«አስደነገጥከኝ አስቻለው» አለው፡፡
«ሊያስፈራም ሊያስደነግጥም ይችላል ሃምሣ አለቃ። በአሁኑ ሠዓት ሀገራችን ታማለች። ህመም ደግሞ በቶሉ ያስረጃል፡፡ ከሐገሬ በፊት እኔ ካረጀሁ ያልኩህም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ አለና አስቻለው የሃምሳ አለቃን ትኩር ብሎ
ተመለከተው።
«ይህ ገባኝ አስቻለው አለና የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ እንቆቅልሽ የሆነብኝ ግን ለምን ከዚያ ወዲህ ወደ ዲላ ላለመሄድ እንደነሰንክ ነው፡፡ ምናልባት
ይህም ምስጢር ይኖረው?» ሲል ፈራ ተባ እያለ ጠየቀው።
«ምስጢር የለውም፡፡ እኔ ግን መሄድ አልፈልግም::»
«አይመስለኝም አስቻለው፣ ይህ ውሳኔህ ምስጢር ሳይኖረው አይቀርም፡፡አይዞህ ምስጢር ቢኖረውም በበኩሌ እጠብቅልሃለሁና ንገረኝ፡፡» አለው።
«ወታደር አይደለህ! ለምስጢርማ ማን ብሎህ» አለና አስቻለው ፈገግ አለ፡፡
«ሙያዬ ስለሆነ ሳይሆን ባአንተ በመታመን።»
አስቻለው ጭንቅ አለው። የሃምሳ አለቃው ጥያቄ ከልቧ የመነጨ መሆኑ ይገባዋል ግን ደግሞ የሆዱን ምስጢር ለማንም ላለመናገር ወስኗል የሃምሳ አለቃው ልመና ግን መንፈሱን ወጥሮ ያዘው።ወደ ጣርያ ወደ መሬት ጎንበስ ቀና ካለ በኋላ
በቅድምያ በረጅሙ ተነፈሰ።
የሀምሳ አለቃውንም አየት ሲያደርገው በፊቱ ላይ የጭንቅ ስሜት አነበበበት። መጨነቁም ስለ እሱ መሆኑ ገባው። ከዚያ በኋላ ፍንጭ ሊሰጠው ፈለገ።
«አየህ ሃምሳ አለቃ! እኔ በአሁኑ ሰዓት ወደ ዲላ ብሄድ ያለ ጊዜዋ
የምትረግፍ አበባ አለች፡፡» አለና እንባው ከዓይኑ ላይ ዝርግፍ አለ፡፡
«እንዴት»
«አበባ የምልህ በእርግጥ ተክል አደለችም። ሔዋን ተስፋዬ የምትባል የሰው ልጅ ናት:: የምወዳት የምትወደኝ፣ የምሳሳላት የምትሳሳልኝን የመጀመርያ ፍቅረኛዩና እጮኛዬ ነበረች፡ ልንጋባ ሁለት ወር ሲቀረን ነበር እኔ ድንገት ወደዚህ ወደ አስመራ የመጣሁት።አሁን ግን ይህው እንደምታየኝ ግማሽ አካሌ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ያለ ጊዜዋ ትረግፋለች የምልህም ያቺ አበባ እንዲህ ሁኜ ብታየኝ
የሚፈጠርባት፣ የስሜት ስቃይ ስለማውቅ ነው፡፡ እንደኔ እግሯ ባይቆረጥ እንኔ ፊቷ ባይጠበስ! እንደኔ ጆሮዋ ባይበላሽ፣ እንደኔ ዓይኗ ባይጠፋ እኔን በዚህ ሁኔታ
ካየች ግን በንዴት በቁጭት በብስጭትና በፀፀት የአእምሮ ህመምተኛ ትሆንብኛለች ብዬ እሰጋለሁ። ታዲያ ይህን እያወኩ ሄጄ የዚያችን አበባ ህይወት ላበላሸው ሃምሳ አለቃ?» አለውና በጉንጩ ላይ ይንቆረቆር የነበረ እንባውን በእጁ መዳፍ ሙሉ ሙዥቅ አድርጎ ጠረገው።
«አታልቅስ የኔ ወንድም!» አለው ሃምሣ አለቃ እሱም ዓይኑ በእንባ
እየሞላ።
«እኔማ ገና ብዙ ብዙ አለቅሳለሁ ሀምሳ አስቃ! እኔ ዕድለ ቢሱ ያቺን እድለ ቢስ አድርጊያት ቀርቻለሁ:: ስለ ሔዋን ተስፋዩ ገና ብዙ አለቅሳለሁ::በህይወት እስካለሁ ልረሳት አልችልምና ሳለቅስ እኖራለሁ፡፡» አለና አስቻለው
አሁንም እህህህህ …! በማለት መላ ሰውነቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ በለቅሶ ሲቃ ተርገፈገፈ።
“ምናልባት ትጠየፈኛለች ብለህ ሰግተህ ይሆን የኔ ወንድም?» ሲል ሃምሣ አሐቃ የራሱንም አይን እየጠረገ ጠየቀው።
«ፍጹም ሀምሳ አለቃ! የኔዋ ሔዋን መልኳ አበባ እንደሚመስል ሁሉ
ትጠየፈኛለች ብዬ አይደለም፡፡ የኔዋ ሔዋን እንዲህ ያለ ተፈጥሮ የላትም። በራሴ በኩል ግን ከእንግዲህ እኔ ለእሷ አልገባም ብዬ ወስኛለሁ።» አለ እያለቀሰ።
“ታዲያ እሷ እየጠበቀችህ ቢሆንስ?»
«ተስፋ እንድትቆርጥ ብዩ የበኩሌን አንድ ርምጃ ወስጃለሁ። የምትኖረው በኔ ደመወዝ ስለነበር እንዲቋረጥባት ብዬ የመንግስት ስራ ለቅቄ በአንድ የፈረንጆች
ግብረ ሰናይ ድርጅት ክሊኒክ ውስጥ በአስተርጓሚነት ተቀጥሬአለሁ::»
«ምናልባት ርሀብ ላያሽንፋት ቢችልስ?»
«ይህ እኔንም ያሰጋኛል። ግን ልጅ ናትና ከመቆየት ሀሳቧን ብትቀይር
እያልኩ እጓጓለሁ:: በዚያ ላይ ደግሞ ገና እኔ እዚያው እያለሁ ሊድሯትና ሊያገቧትም እያሰቡ የሚያንዣብበ ሰዎች ነበሩና በእነሱ ጫና ተሸንፋ አዲስ
ህይወት ብትጀምር እያልኩም እፀልያለሁ::»
የሃምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ የአስቻለውን ምኞትና ሃሳብ ሲሰማ ቆይቶ ወደ ዲላ ላለመሄድ የወሰኑበት ምክንያት ሲገባው በራሱ ውስጥ ያለው የመንፈስ ቁስል አመመውና ለአስቻለው ይገልፅለት ዘንድ ስሜቱ ገፋፋው።
«ስማ እስቻለው፡፡» አለው ፍዝዝ ትክዝ ብሎ እየተመለከተው እኔም እንዳተው ተገድጄ ወደዚህ ሀሄገር የመጣሁ ነኝ መጥቼ የፈፀምኩት ነገር ቢኖር ሰው መግደል ነው።እላዬ ላይ የምታየው የሃምሣ አለቅነት መአረግ የተሰጠኝም ሰው በመግደሌ ነው። የገደልኩት ደሞ የሀገሬን ልጆች ወንድሞቼን ነው ሶስት አራት ገድዬ ከሆነ በዛው መጠን በርካታ ዘመድ አዝማዶቻቸውን አስለቅሻለሁ አሳዝኛለሁ በዚህ ስራዬ ደግም ተሸልሜበታለሁ። ታድያ እኔ ይሄን ያህል የህሊና እዳ ተሸክሜ ወደ ሃገሬ ልገባ ስቸኩል አንተ ልታክም መተህ ራስክ ከቆሰልክ ልትረዳ
መጥተህ ራስህ በተጎዳህ ልትጠግን መጥተህ ራስክ ከተሰበርክ ምን የህሊና የፀፀት አለብህና ምን የሚያሳፍር ነገር ሰርተሃልና ከዚህ አይነት አሳዛኝ ውሳኔ ላይ ልትደርስ ቻልክ?» ሲል ጠየቀው።
«ሀሳብህን አደንቃለሁ ሃምሳ አለቃ!» ሲል ጀመረ አስቻለው «ልዩነቱ ግን አንተ የገደልካቸው ኢትዮጵያውያን ሞተው አርፈዋል። ቤተሰቦቻቸውም እርማቸውን አውተው ተገላግለዋል።ፀፀቴ ያለው በአንተ ልብ ብቻ ነው።
👍10
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...እንደ ሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ከትዝታ ጋር የተቀላቀለ አይሁን እንጂ መርዕድ እሽቴም በደረቅ ጭንቀት ተወጥሮ ነው ያረፈደው የጀመረው ደግሞ ጠዋት ሁለት ሰዓት በፊት፡፡ መኖሪያው በዜሮ ሁለት ቀበሌ የታችኛው ጥግ ሲሆን የሚያስተምረው ደግሞ የዲላ ከተማ የላይኛው ጫፍ
በሆነ ቀበሌውስጥ በማገኘው
የአፄ ዳዊት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ሔዋንና ትርፊ የተከራዬት መንገዱ ላይ በመሆኑ ሲወጣም ሲወርድም ጎራ እያለ ይጠይቃቸው ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋት ግን ወደ ሥራው ሲሄድ ያ ቤት በጠዋት ከውጭ ተዘግቶ አየው ወዴት እንደሄዱ የጎረቤት ስዎችን ሲጠይቅ ማታ ሲሆንና ሲባል ያመሸው ሁሉ ሁሉ የዝርዝር ተነገረው።
በሰማው ወሬ የተሰማው ድንጋጤ ጭራሽ ራስ ምታት ለቀቀበት። ዛሬ
ቢቸግረው ወደ በልሁ ቢሮ ሮጠ፡፡ ነገር ግን ዘንግቶ ነበር እንጂ በልሁ
ለመስክ ስራ ወጥቷል መስሪያ ቤት ደርሶ ይኸው ሲነግረው ያለ ውጤት ተመለሰ።
እንደገና ወደ ታፈሠ ቤት ላሮጥ አሰበ፡፡ ግን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ክፍለ ጊዜ አስተምሮ ሌሎቹን ክፍለ ጊዜያት ነፃ እንደሆነ አስታወሰና በአንድ ፊት ስራውን
አጠናቆ ለመሄድ ወስኖ እየተጨነቀም ቢሆን ወደ ትምህርት ቤት አመራ፡
ልክ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ሥራውን ጨርሶ ወደ ታፈሡ ቤት
በመገስገስ ላይ ሳለ አስፋልቱን አቋርጦ ሊያልፍ ሲል ከይርጋ ጨፌ አቅጣጫ ትመጣ የነበረች ቶዮታ መኪና ደጋግማ ክላክስ ስታደርግ ሰማ። ዞር ብሎ ሲመለከት የበልሁ የመስክ መኪና ናት:: በክላክስ ያስጠራውም ራሱ በልሁ ኖሯል፡፡ በአለበት ላይ ቆሞ መኪናዋን ጠበቀ።
«ዛሬ ስራ የለም እንዴ?» ሲል ጠየቀው በልሁ አጠገቡ ሲደርስ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ መርዕድን እየተመለከተ፡፡
«እስቲ ና ውረድ!» አለ መርዕድ ፊቱ በድንጋጤ ጭምትርትር እንዳለ።በልሁም የመርዕድ ሁኔታ ገና ሲያየው እስደንግጦታል። «ምነው? ምን ሆነካል?
«ችግር አለ፡፡»
በልሁ ከመኪናዋ ላይ ዱብ ብሎ ወደ መርዕድ በመጠጋት ምንድን ነው ችግሩ? ሲል ጠየቀው።
«ሔዋን ታስራለች!»
«ምን አድርጋ?»
መርዕድ ከሰው የሰማውን በሙሉ ነገረው::
«ያምሀል እንዴ አንተ ሰው?»
«የነገሩኝን ነው እኔ የምነግርህ?»
“ከታሰረች ጠይቀሃታል?»
« አሁን ወዚያው እየሄድኩ ነበር፡፡»
ለነበሩበት ቦታ ፖሊስ ጣቢያው ቅርብ ነው፡፡ በልሁ ሾፈሩን ወደ ቤቱ እንዲሄድ አሰናበተውና ከመርዕድ ጋር ወደ ፖሊስ ጣቢያው ገሰገሱ፡፡ እርምጃቸው
ፈጣን ስለነበር ከአምስት ደቂቃ በላይ አልወሰደባቸውም።
ትርፌ ገና በጠዋት ለሔዋን ቁርስ ይዛ እንደሄደች አልተመለሰችም ኖሯል፡እንዲያውም በእስረኞች ግቢ እንድትገባ ተፈቅዶላት ኖሮ ፊት ለፊት ሔዋን ጋር አብረው ተቀምጠው በልሁና መርዕድን ከሩቅ ሲያዩአቸው ተንጫጬ «በልሁ! መርዕድ! በልሁ! መርዕድ!» በማለት።
በልሁና መርዕድ ጣቢያው በር ላይ እንደ ደረሱ አንድ ፖሊስ ጠጋ
አላቸውና ««ከእናንተ ወስጥ በልሁ ተገኒ የሚባል ማነው?» ሲል ጠየቃቸው፡፡
«እኔ!» አለው በልሁ በሌባ ጣቱ ወደ ራሱ እያመለከተ፡፡
«ሃምሳ አለቃ ይፈልጉሃል።»
«በሰላም?»
«አላወቅሁም አለና ፖሊስ ወደ እነ ሔዋን ዞር ብሎ አየት አደረገና ፊቱን ወደ በልሁ በመመለስ ከልጅቷ ጋር ሳይገናኝ ወደኔ አምጡት ነው ያሉት» አለው።
«ቢሮው የት ነው?» አለ በልሁ ቁና ቁና እየተነፈሰ፡፡
«ተከተለኝ! አለና ፖሊስ በልሁን ከፊት ከፊት እየመራ ወስዶ ካሃምሳ አለቃው ቢሮ አስገባው፡፡
የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ጆሮግንዶቹን በእጆቹ ይዞ
ጠረጴዛው ላይ በማቀርተር ሀሳብ ውስጥ ገብቶ ሳለ ፖሊስ በልሁን ይዞ በመድረስ «አቶ በልሁ
እኒህ ናቸው አለው፡፡ ሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ለካ በልሁን ከተማ ውስጥ በዓይን ያወቀው ኖሯል:: እንዲያውም በአለባበስ፣ በተክለ ሰውነቱና አጠቃላይ አቋሙ
ያደንቀው የነበረ ሰው ሆኖ ሲያገኘው ‹‹በልሁ ተገኒ ማለት አንተ ኖረሀል እንዴ?
እያለ ብድግ ብሎ ጨበጠው::
«አዎ ነኝ» አለ በልሁ ቁና ቁና እየተነፈሰ፡፡
«ቁጭ በል እስቲ! ሁለቱም ፊት ለፊት ተቀመጡና ተፋጠጡ፡፡
«የተበሳጨህ ትመስላለህ!» አለው የሃምሣ አለቃ፡፡
«አዎ እጅግ በጣም ተናድጃለሁ፡፡
«ምነው?»
«የማትታሰር ሰው አስራችኋላ» አለው በልሁ ቁጭ እንዳለ በቀኝ
ሽንጡን በመያዝ ሃምሳ አለቃውን እየተመለከተ።
«ወንጀል ፈጽማ እንሆነስ» አለ ሃምሳ አለቃው ፈገግ እያለ።
«የተባለው ከሆነ አላምንም።» አለና በልሁ የሃምሳ አለቃውን ጠረጴዛ መታ መታ እያደረገ «ቀድሞ ነገር የተሰራ ሁሉ ወንጀለኛ የአሰረ ሁሉ ዳኛ ነው ብዬ ማመን ከተውኩ ቆይቼአለሁ።» አለው።
«አይፈረድብህም»
«አሁን ለምን ፈለከኝ።» ሲል በልሁ ዓይኑን ፈጠጥ አድርጎ ጠየቀው።
«ለብርቱ ጉዳይ !» አለና ሃምሳ አለቃ በረጅሙ ተንፍሶ "ግን አቶ በልሁ አሁን የምነግርህ ጉዳይ ሔዋን ለምትባል ልጅ ፈፅሞ መነገር የለበትም ባይሆን
ለአንተና ለቅርብ ጓደኞችህ ከነገርኳችሁ በኋላ አስባችሁበት የሚሆን ነገር ነው።"
«ምንድነው እሱ?»
«አስቻለው ፍስሀ የሚባል ጓደኛ እንደነበረህ ሰማው።»
«አሁንም አለኝ::»
«አብራችሁ ያላችሁ አይመስለኝም።»
«ከልቤ አይወጣምና ምንጊዜም አብረን የምንኖር ይመስለኛል»
«በአካል ማለቴ ነው፡፡»
«ክፉዎች አለያይተውናል፡፡ አሁን የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ
አላውቅም።» ካለ በኋላ በልሁ «ለአንተ ማን ነገረህ? ሲል ጠየቀን
«በህይወት አለ ብልህ ታምናለህ?
«የት አገር?»
«እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ፡፡»
«ኦ?» አፉ ተከፍቶ ቀረ ዓይኖቹ በሃምሳ አለቃው ላይ ተተከሉ
«እስቲ ከሚቀርበህ ሰዎች ጋር በመሆን ተሰባሰቡልኝና ስለ እሱ ሁኔታ በጋራ ላናጋገራችሁ፡፡ እኔ የማውቀው ነገር አለኝ፡፡
«ዛሬ ማታ ቢሆንስ?»
«ይቻላል»
«ቦታና ሰአት ወስነው ተለያዩ፡፡»
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ፖሊስ ሆኖ ከተቀጠረ ጀምሮ አሁን
ያጋጠመውን ዓይነት አስደሳች ሥራ እግኝቶ አያውቅም። የሔዋንና በእሷ ምክንያት ተጣላን ያሉ ሰዎችን ጉዳይ እንደ የመንግስት ተቀጣሪነቱ ሳይሆን ልክ እንደ ራሱ
ገዳይ በተለየ ስሜትና ትኩረት ሊከታተለው ወሰነ።
የስራው የመጀመሪያ ዕቅድ የሔዋንን ድንግልና በሐኪም ማረጋገጥ ነበር።በእርግጥም ፈፀመው ሔዋን ያልተሟሸ ገላ ባለቤት ሆና አገኛት። የምስክር
ወረቀቱንም በእጁ ያዘ፡፡ ለምርመራው የሚያወመቹ በርካታ ፍንጮችን ከእነበልሁ አግኝቷል፡፡ የምርመራው ሂደት በዚያው አቅጣጫ እንዲጓዝ አድርጎ እቅድና
ስልቱንም ቀይሶታል፡፡ ስለ አስቻለው ሁኔታ ታፈሡን በልዑንና መርዕድን ሲያነጋግር ባመሽበት ሶስተኛ ቀን ላይ ዓለሙ መርጋንና መብራቴ ባዩን ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ከቢሮው አስቀረባቸውና «ልብ ብላችሁ አድምጡኝ» ሲል ሀምሳ አለቃ አስጠነቀቃቸው፥ ዓለሙና መብራቴ ከፊቱ ተቀምጠው የሚሆኑት ሁኔታ በራሱ ውስጣቸውን ያስነብበዋል።
«ሔዋን ተስፋዬ የምትባል ሴት ወዳጃችሁ እንደሆነች ቃል በሰጣችሁበት ወረቀት ላይ ፊርማችሁን አኑራችኋል ነው ወይስ እይደለም?» ሲል ጠየቃቸው።
👍12🔥1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....በድሉ ከመደንገጡ የተነሳ በዓይኑ መግቢያ ቀዳዳ የሚፈልግ ይመስል ወደ ላይ ወደ ታች፣ ወደ ቀኝ ወደ ግራ ዓይኑን እያማተረ ይቁነጥነጥ ጀመር።
«በምን ተገናኝታችሁ ነው ያስደበደበችህ?
«እወዳታለሁ!»
«ለምን ወደድከኝ ብላ አስደበደበችህ?»
«መሰለኝ::»
«ስለዚህ ልትበቀላት ፈለክ?»
«የራሷ እህት ናት የገፋፋችኝና መላውን የፈጠረችልኝ::»
«ስሟን ጥራታ!»
«ሸዋዬ::» አለና በድሉ እነዚያን ገጣጣ ጥርሶቹን የባስ ግጥጥ አደረጋቸው፡፡
ላብ ላብ ብሎት ጭንቀቱ ይታወቅበታል።.
“ 'ተደበደበ ሰው ቢደበድብ ወይም ቢያስደበድብ ድርጊቱ ወንጀል ቢሆንም ነገር ግን ስም አለው:: «ግን ወንድ አደባደበች» ብሎ ማስወራቱ ምንድንነው
ዓላማው? ሲል ጠየቀው፡፡
«ስሟን ለማጥፋት::»
«ማለት?»
«ልጅቷ አስመራ ሄዶ የቀረ እጮኛ' አላት፡፡»
«እሺ»
«እዚህ ያሉት ጓደኞቿ ግን ከማንም ጋር እንዳትገናኝ ይጠብቋታል፡፡
እሷም ትፈራቸዋለች። ወንድ አደባደበች ተብሎ ከተወራባት ግን እነሱ ያርቋታል፡፡እሷም ተስፋ ትቆርጥና የኔን ጥያቄ ትቀበላለች ብዬ በማሰብ ነው፡፡» አለና በድሉ
በተቀመጠበት ላይ ተቁነጠነጠ፡፡
«ስማ » አለው የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ቁጣ በተቀላቀለበት አነጋገር።
«አቤት»
«እዚሁ እንዳለህ የሴራ መሀንዲስህን አስጠራታለሁ፡፡ እጥር ምጥን ባለ ቃል
ሁሉን ነገር እንደተናገርንክ ትነግራታለህ። ነገር አደፋፍናለሁ ካልክ ጠብክ ከመንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ከእኔም ጋር በግል እንደሚሆን እወቅ!!»
«ኧረ እነግራታለሁ!»።
ሃምሳ አለቃ ረዳቱን በደውል ጠራና እንደቀረበለት ሽዋዬን እንዲያመጣ አዘዘው። ረዳቱ ሸዋዬን ወዲያው አቀረባት። በበድሉ ፊትለፊት
እንድትቀመጥ ታዝዛ አለፍ ብላ ተቀመጠች፡፡ ከመርማሪው ፖሊስ ይልቅ በድሉን በፍርሀት ዓይን ታየው ጀመር።
«ቀጥላ!» አለ ሃምሣ አለቃው በድሉ ላይ በማፍጠጥ::
በድሉ ከተቀመጠበት ብድግ አለና ወደ ሽዋዬ ጣቱን ቀስሮ «የቀይ ሽብሩን ጉዳይ ሙልጭ አድርጌ ተናግሬያለሁ፡፡ ብትዋሽ ውርድ ከራሴ!» አላትና ተመልሶ ቁጭ አለ። የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ቀይ ሽብር የሚለውን ቃል ሲሰማ መላ ሰውነቱን አንቀጠቀጠው፡፡ አጠገቡ ያሉት ሰዎች ነፍሰ ገዳዮች መስለው ታዩት። ልክ በቀይ ሽብር ጊዜ እንደተፈጸመው ሁሉ እሱም እነዚህን ሰዎች ዘቅዝቆ ቢለበልባቸው ደስ ባለው ነበር። ግን ደሞ ጨካኞች የፈፀሙትን የጭካኔ ተግባር መድገም የባስ አረመኔነት መሆኑን ይገነዘባልና በቁጭት ራሱን ወዝውዞ ተወው።
ወድያው ረዳቱን በደውል ጠራ። በድሉን ወደ እስር ቤት አስወሰደና ሸዋዬን ብቻዋን አገኛት።
ሽዋዬ በዕለቱ አጠር ያለ ሰማያዊ ጉርድ ቀሚስና ቡናማ ሹራብ ለብሳለች፡፡
ቀላ ያለች ስካርፍ አንገቷ ላይ ጣል አድርጋለች:: ሳታስበው ታስራ በማደሯ ፀጉሯ አላበጠረቾም፣ አልተቀባባችም:: አመዷ ወጥቷል፡፡ ማንደፍሮ ሜዳ ላይ የደፈጠጠው ፊቷ ጠባሳው አልጠፋም፡፡ ተዥጎርጉራለች። ያ አጭር ፀጉሯ ተንጨፍሯል፡፡
ቀጫጭን እግርቿን ስታክካቸው አድራ መስመር ሰርተዋል። በድንጋጤ ዓይኗ ፍጥጥ ብሎ የሴትነት ጥላዋ ተገፏል። ታስጠላለች::
«መምሀርት ሸዋዬ!» ሲል ጠራት የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ሁለት እጆቹ ላይ አገጩን አስደግፎ ዘንበል ብሎ እየተመለከታት፡፡
«አቤት!»
«ሙያሽን ምን ያህል ትወጅዋለሽ?»
«በጣም እወደዋለሁ፣ አከብረዋለሁ፣ ተማሪዎቼም በጣም ይወዱኛል::»
«ምን እያስተማርሻቸው እንደሆነ ስለሚገባቸው ይሆናላ!» አላት በምፀት።
«ትንትን ብትንትን አድርጌ ነው የማስተምራቸው»
የሃምሳ አለቃው በረጅሙ ተነፈሰና ወደ ጠረጴዛው ጎንበስ አለ።
ራሱን ወዝወዝ አድርጎ ብዕርና ወረቀቱን ከአመቻቸ በኋላ «እስቲ እኔም እንደተማሪዎችሽ እንድወድሽ ስለ ቀይ ሽብሩ ጉዳይ ትንትን ብትንትን አድርጎአል ንገሪኝ፡፡» አላት።
ሽዋዬ የደረቀ ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች ወደ ላይ ወደ ታች በማየት ከተቅበጠበጠች በኋላ «ቀይ ሽብሩኮ» ብላ ልትጀምር ስትል እንደገና ወደ ሃምሳ አለቃው
ዞር ብላ «በድሉ ነግሮህ የለ?»
አለችው።
ሀምሳ አለቃው በሸዋዩ አስተሳሰብ እንደ መገረም ብሎ ድንገት ፈገግ እንደ ማለት አለና እሱ ብቻ ሳይሆን ዓለሙም መብራቴም በሰፊው ዘርዝረውታል ግን መጀመርያ ሀሳቡን ያፈለቅሽው አንቺ ስለሆንሽ ከባለቤቷ መስማት ፈልጌ ነው::
እግረ መንገዴን ምን ያህል እውነተኛ እንደሆነሽ ለማወቅ ፈልጌ ነው፡፡» ብሎ አየት ሲያደርጋት ሸዋዬ ቀጠለች።
«እኔ እኮ ውሽት አላቅም!» አለችው ቀበጥበጥ እያለች
«እኔስ መች ወጣኝ? በይ እውነቱን ንገሪኝ።»
«ቀይ ሽብር ማለት ያው ቀይ ሽብር ማለት ነው አለችው አይኖቿን በዓይኖቹ ላይ እያንከባለለች።
«ነገርኩሽ አንቺ ሴትዮ አላት ተናዶ፡፡ ምኗ ደነዝ ናት በሆዱ።
«ምን ልበል ታዲያ?» ሽዋዬ ድንግጥ አለች። ተጨነቀችም።
«ዝርዝር ሂደቱን ንገሪኝ ነው ያልኩሽ አለና «ቀይ ሽብርስ ምን አስፈለ»
«ሔዋን አስቸገረችኝ::»
«ምን አድርጊኝ ብላ?
«በቃ! እሷ እያለች ባልም ትዳርም ሌኖረኝ አልቻሉም፡፡»
«ነጠቀችሽ ወይስ አፋታችሽ?»
«ሁለቱንም።»
«እንዴት እያረገች?»
«መጀመሪያ በልቤ የወደድኩትን ሰው ውስጥ ለውስጥ ሄዳ በጎን
ጠለፈችብኝ፡፡» እንደገና ብላ ልትቀጥል ስትል ሃምሣ አለቃ ቀደማት።
«የነጠቀችሽ ሰው ማን ይባላል?»
«አስቻለው ፍሰህ ይባል ነበር፡፡»
«እንዴ!» አለ ሃምሣ አለቃ በመገረምም በመደነቅም ዓይነት ትኩር ብሎ ሸዋዬን ሲመለከታት ከቆየ በኋሳ አስቻለውን ትወጂው ነበር?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ነፍሴ እስክትወጣ!»
ሃምሣ አለቃ ግራ ገባው፡፡ ልክ ሔዋንን ያነጋገረ ዕለት እንደሆነው ሁሉ እስኪርብቶውን ወረቀት ላይ ጣል አደረገና ጉንጮቹን ደግፎ ወደ ጠረጴዛው አቀረቀረ፡፡ በዚያው ሀሳብ ውስጥ እንዳለ ሸዋዬ በልቤ የወደድኩትን… ያለችውን አስታወሰና ቅናት ከአጎመነበሰበ ቀና በማለት
«እሺ፣ ደግሞ ከማን አፋታችሽ?» ሲል ጠየቃት።
««ያን እንኳ ባናወራው ይሻላል::»
«ለምን?»
«ደስ አይልማ!»
«ሀምሣ አለቃ የሸዋዬ ባዶነት አስገረመውና አሁንም ጎንበስ ብሎ እንደ መሳቅ አለና። እንደገና ቀና ብሎ “ታዲያ ለኔ የሚያስደስተኝ ደስ የማይለውን ነገር ማወቅ መሆኑን አጣሽው? ወይስ ፖለስ ጣቢያ ውስጥ መሆንሽን ረሳሽው አለና ወረቀቶች ብድግ አድርጎ «ታሪክሽ ሁሉ እኮ እዚህ ላይ ተዘርዝሯል መደበቁ ያዋጣሽ መሰለሽ?» አላት። በእርግጥ ስለ ፍቺ ነገር የተጠቀሰ ነገር አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሸዋዬን ለማስፈራራትና ለማስወትወት ተጠቀመበት፡፡
«ሰዎቹ ያንንም አውታዋል? »አለች ሽዋዬ ደንግጣ ብላ፡፡
«በእነሱ ላይ ጨምሮ ቀድሉ አጋልጦሻል::»
«ቅሌታም ነው።»
የሀሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ ድንገት ቂቂቂቂቂ...» ብሎ ሳቀ፡፡ ሸዋዬ ፊደል ከመቁጠሯ በቀር
ምንም እንዳልተማረች ታስበው፡፡፦ እውቀት" ሥርዓትም አጣባት።
በዚያ ምትክ የክፋትና የተንኮል ሰው መሆኗን በውል ተገነዘበና
«ጊዜዬን እትግደያ መምህርት ሸዋዬ!» ሲል ቆጣ ብሎ ተናገራት፡፡ በዚያኑ ልክ
👍15🥰1😁1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

...'መወለድ ቋንቋ ነው' ይላሉ አበው ሲተርቱ፡፡ የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ተደጋግሞ እንደታየው ሰዎች አብረው እስካልበሉና እስካልጠጡ ክፉ ደጉን በጋራ
እስካልተካፈሉ እንዲሁም እስካልተረዳዱ እስካልተደጋገፉ ድረስ የዘር ግንድና የደም ትስስርን ብቻ መሰረት በማድረግ እህቴ! ወንድሜ! አክስቴ! እቴቴ... ወዘተ መባባል ብቻ ከሆነ በርግጥም 'መወለድ' የሚለው ቃል ከቋቋነት ያለፈ ፋይዳ ሲኖረው አይታይም።
በተቃራኒው እንኳንስ መወለድ
የአንድ ወንዝ ውሃ እንኳ አብረው ሳይጠጡ ነገር ግን በአንድ ከተማ ወይም በአንድ አካባቢ አብረው በመኖራቸው ብቻ ስሜት ፍላጎታቸውና አመለካከታቸው ተገጣጥሞ ጥብቅ ቤተሰባዊ ትስስርን ሲፈጥሩ ይታያሉ ለዚህ
ደግሞ የከስቻለው፣ የበልሁ የታፈሡ የመርእድ ከልብ የመነጨ ፍቅር አይነተኛ ምስክር ነው።
ለእነዚህ የፍቅር ቤተሰቦች ትውውቅ መሰረት የሆነው የታፈሡኔ የባለቤቷ ጋብቻ ነበር፡፡ ታፈሡ በወሎ ከፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ውስጥ
ከካቤ እስከ ጃማ ድረስ በተዘረጋው ወይናደጋማ ቦታ ላይ ከትመሰረተ ሰፊ ቤተሰብ ትወለዳለች፡፡ ባለቤቷ ደግሞ በጎጃም ክፍለ ሀገር ደጀን አካባቢ
የተወሰደ ቢሆንም አባቱ መምህር ስለነበሩ በስራ ምክንያት ብዙ በቆዩባት በመሀል ሜዳ ከተማ
ለብዙ አመታት የቆየ ነው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን
በዚያው ከተማ አጠናቆ በኋላም በተግባረእድ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት በምህንድስና ሙያ ሰልጥኖ ትምህርቱን ሲጨርስ ለስራ ተመድቦ ወደ ደሴ ነበር የሄደው።
በዚሁ ጊዜ ተይዩ ታፈሡ እንግዳሰው የአንደኛና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በወረኢሉ ልዕልት የሺመቤት ትምህርት ቤት አጠናቃ ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደሴ በሚዋኘው ዝነኛው የወይዘሮ ስህን ትምህርት ቤት ለመማር ትሄዳለች፡፡ ሁለቱ በአንድ ሰፈር ያኖሩ ነበርና በዚያው ሰበብ ያተያያሉ፡ : በሃደት ይተዋወቃሉ፡፡ ቀስ በቀስ ይቀራረባሉ።የኋላ ኋላ ይዋደዱና በመጨረሻም ይጋባሉ።
ታፈሡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ጨርሳ አዲስ አበባ በሚገኘው የኮተቤ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ትገባለች፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ደግሞ ባለቤቷ በዝውውር ወደ ዲላ ይሄዳል፡፡ ታፈሡም የኮሌጅ ትምህርቷን ስታጠናቅት በጋብቻ ሰበብ ወደ ባለቤቷ እንድትሄድ ተደርጎ እሷም በዲላ
አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ትመደባለች፡፡
አስቻለው ተወልዶ ያደገው በመሀል ሜዳ ከተማ እንደ መሆኑ
የተማረውም እዚያው ነው፡፡ እሱ ልጅ በነበረበት ወቅት የታፈሡ ባለቤት በዚያ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሲከታተል ያውቀው ነበር፡፡ እሱ ራሱም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በነርስነት ሙያ ሰልጥኖ ሲመረቅ ለስራ ተመድቦ ወደ ዲላ ሆስፒታል ይሄዳል፡፡ ገና ዲላ ከተማ የገባ ዕለት የታፈሡን ባለቤት መንገድ ላይ ያየዋል፡፡ ፈራ ተባ እያለ ያነጋግረዋል፡፡ የትና እንዴት እንደሚያውቀው ያስረደዋል። የታፈሱ ባለቤት የአስቻለውን ለአገሩ እንግዳ መሆን በመረዳቱ ወቸ ቤቱ ይወስደዋል። ከታፈሡ ጋር ያስተዋውቀዋል ታፈሡ ለአስቻለው ትመቸዋለች። አዘውትሮ ወደ ቤቷ እንዲመጣ ታደርገዋለች። እሱም እየተመላለሰ መጠየቁን ይቀጥላል።በዚያው እየተግባቡና እየተዋደዱ ይሄዳሉ። ታፈሡ የመጀመሪያ ልጇን ስትወልድ ክርስትናውን ለአስቻለው ትሰጠዋለች፡: አበ ልጆችም ይሆናሉ፡፡
በሌላ መንገድ ደግሞ በልሁና መርዕድ ትውውቅ እየፈጠሩ ነብር
መርዕድ ወደ እጼ ዳዊት ትምህርት ቤት ከመዛወሩ በፊት ከዲላ በስተደቡ በሚገኘው በጩጩ ገብርኤል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ያስተምር
ነበር፡፡ በልሁ ደግሞ አዘውትሮ ወደ መስክ ስራ የሚሄደው በዚያ መስመር ስለነበር፣ በልሁ መርዕድ መምህር መሆኑን ስለሚያውቅ በአጋጠመው ጊዜ ሁሌ
ስለነበርና መርዕድም ብዙ ጊዜ ከዲላ ከተማ ወደ ስራው የሚሄደው በእግሩ ስለነበር
በልሁ መርእድ መምህር መሆኑን ስለሚያውቅ በአጋጠመዉ ጊዜ ሁሉ ለመስክ ስራ በሚጠቀምባት መኪና ላይ ያሳፍረዋል፡፡ በዚያው እየተግባቡ ይሄዳለ፡: መርዕድ በተፈጥሮው ተጫዋች በመሆኑ ለበልሁ በጣም እየተመችው
ይሄዳል ጫትም አብረው መቃም ይጀምራሉ።
በልሁና አስቻለው በከተማ ውስጥ በዓይን ይተዋወቁ ነበር፡፡ አንድ ቀን ደግሞ አስቻለው ከአንድ የዲላ ከተማ ነዋሪ ጋር ሆኖ በአንድ ቡና ቤት ውስጥ
ሻይ እየጠጡ ሳለ በልሁ ድንገት ይደርሳል፡፡ ያ ካአስቻለው ጋር የነበረ ሰው በልሁን በደንብ ያውቀው ኖሮ ቁጭ ብሎ" ሻይ እንዲጠጣ ይጋብዘዋል፡፡
በልሁም ቁጭ ይላል፡፡ ከአስቻለው ጋር የነበረው ሰው ለመሆኑ ሁለታችሁ ትተዋወቃላችሁ? ሲል ሁለቱንም ተራ በተራ እያየ ይጠይቃቸዋል፡፡ በዓይን ይሉታል። ሰውየው አስቻለውና በልሁን በቅደም ተከተል እየጠራ አንተ መንዜ፣ አንተ ቡልጌ፣ በትውልድ ስፍራ እኮ ጎረቤቶች ናችሁ ይላቸዋል፡፡
በልሁና አስቻለው ፈገግ ፈገግ በማለት እንደገና እየተጨባበጡ እንደ አዲስ የስም ትውውቅ ያደርጋሉ፡፡ ከዚያ በኋላ፤ መንገድ ላይ በተገናኙ ቁጥር ጠበቅ ያለ ሰላምታ መለዋወጥ ይቀጥላሉ፡፡
አንዳንዴም ሻይ ቡና መገባበዝ ይጀምራሉ::

ከወራት በኋላ ሁለቱን የበለጠ የሚያቀራርብ አጋጣሚ ተፈጠረ አንድ ምሽት ላይ በልሁ በአንድ ቡና ቤት ውስጥ በተለምዶ ባለጌ ወንበር ተብላ በምትጠራ መቀመጫ ላይ ቁጭ ብሎ ይጠጣል አንዳት የቡና ቤቱ አስተናጋጅ አጠገቡ ቆም እያለች ታጫውተዋለች። በቡና ቤቱ ውስጥ ቁጭ ብለው ይጠጡ የነበሩ አራት ጎረምሶች ልጅቷን እየፈለጉ በልሁን መተናኮል ይጀምራሉ በልሁ ግን ንቋቸው ዝም ብሎ ልጅቷን ያጫውታል ቆየት ብለው ከጎረምሶቹ መሀል መስከር የጀመረው አንዱ ልጅቷን በሀይል ጎትቶ ሊወስድ ወደ ልጅቷና በልሁ መራመድ ሲጀምር ድንገት አስቻለው ይደርሳል።
በልሁ ከተቀመጠበት ባለጌ ወንበር ላይ ወርዶ ጎረምሳውን ሊመታ ሲል አስቻለው ይይዘውና ወደ ጎረምሳው ዞሮ ብሎ 'አንተ እረፍ እንጂ' ይለዋል። ጎረመሳው ግን 'ምን አገባህ' ብሎ በአስቻለው ላይ ያፈጣል። አስቻለው ደግሞ ሲያስጠነቅቀው ያ ጎረምሳ ጭራሽ ይጠገዋል።በዚህ ጊዜ ጎረምሳው የተማመነባቸው ጓደኞቹ አስቻለውንና በልሁን ሊመቱ ግር ብለው ወደ እነሱ ይመጣሉ።ድብድብ ይጀመራል አስቻለውና በልሁ ከወንበር ወደ ወንበር ከጠረጴዛ ወደ ጠረጴዛ እየዘለሉ እነዚያን ጎረምሶች አመድ ያደርጓቸዋል ሁሉንም ይዘርሯቸዋል በድብድቡ ምክንያት የቡና ቤቱ ብርጭቆዎች እንዳሉ ይሾቃሉ ወንበሮች ይሰባበራሉ ይጮሀል ፖሊስ ይደርሳል በልሁና አስቻለው ታስረው ያድራሉ በፖሊስ። በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ሲያድሩ እንቅልፍ አልወሰዳቸውም ነበር።ሲያወሩና ሲጫወቱ ይነጋል።
ጠዋት በዋስ ሲለቀቁ ወደ አስቻሴው ቤት ነበር የሄዱት ለእንቅልፍ አረፍ ሊሉ በልሁ አስቻለው ቤት ሲገባ በቅድምያ አይኑ ያረፈው በአስቻለው አልጋ ፊት ለፊት ለጫት መቃምያ የተነጠፈች በምትመስል ፍራሽ ላይ ነበር።
ጫት ትቅማለህ እንዴ?» ሲል እስቻለውን ይጠይቀዋል፡፡
«እንደውም»
«ፍራሿ ታድያ»
«ባልቅምም ሲቃም ደስ ስለሚለኝ አንዳንዴ የስራ ባልደረቦቼ እየመጡ ይቅሙበታል።
👍8
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....በልሁ ቅስሙ ስብር አለ ከሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ የተሰጠው ምልክትና አድራሻ ያ መናፈሻ ብቻ ነበር።ሃምሳ አለቃ እራሱ በአስመራ ከተማ ውስጥ ከዚያ መናፈሻ በስተቀር ሌላ አካባቢ ብዙም አያውቅም። የአስመራ ቆይታው አጭር ስለ ነበርጰተዘዋውሮ አላየውም።
“ምን ይሻለኛል ታዲያ የኔ ወንድም" ሲል በልሁ ጭንቅ እያለው ሹፌሩን ጠየቀው።
«እኔ እንጃ!» አለና ሾፌሩ ለአፍታ ያህል ቆየት ብሎ ወዴ በልሁ ዞር በማለት «እዚያ የሚሰራ ሰው ነበር የሚፈልጉት?» ሲል ጠየቀው
«እዚያ አዘውትሮ የሚገባ ወንድሜን ነበር፡፡»
«ታዲያ አንዱ ጋ አረፍ ብለው ያፈላልጉታ»
በልሁ ለአፍታ ያህል ፀጥ ብሎ ሲያሰላስል ቆየና እስቲ ጥሩ ማረፍያ ወደምትለው ሆቴል ውሰደኝ።አለው የበልሁ ተክለ ሰውነታዊ ገፅታና በራሱ
አንደበት 'ጥሩ ማረፊያ' በማለት በተናገረው ቃል መሰረት ጥሩ ኗሪ
እንደሆነ የገመተው ሾፈር «ወደ ኮምፒሽታቶ ያሻልዎታል» አለው፡፡
«ኮምፒሽታቶ ምንድነው?ሲል በልሁ ጠየቀው በልሁ ቃሉ የተለየ ትርጉም ካለው ብሎ በማሰብ።
መሀል ከተማ ላይ የሚገኝ ቦታ ነው ጥሩ ጥሩ ሆቴሎችም የሚገኙት በዚያው አካባቢ ነው።» አለ ሹፌሩ።
«እሺ እንሂድ!»
በእርግጥ በልሁም የገንዘብ ችግር የለበትም፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከጥቂት ወራት በፊት ወላጅ አባቱ እስቲ ብትኖርበትም ብትሽጠውም ቦታ መያዝ ደግ ነውና ቤት ለመስራት ሞክር በማለት ከሰጡት በርካታ ገንዘብ ላይ ግማሽ ያህሉን በመንገድ ሻንጣው ውስጥ አድርጐ ይዞት ሄዷል።አስቻለውን በመፈለግ ሂደት ታሪካዊቷን የአሥመራ ከተማ ለማየት ይጓጓ የነበረው በልሁ ገና ከጅምሩ መንፈሱ በስጋት በመወጠሩ በሚጓዝበት
ጎዳና ግራና ቀኙ ያሉትን የከተማዋን ቦታዎች እንኳ ልብ ብሎ ሳያይ ያ ባለ ታክሲ ተጉዞ ተጉዞ ከአንድ ኣካባቢ ሲደርስ ዳር ይዞ በመቆምም «ኮምፒሽታቶ
ማለት ይህ ነው!» አለው፡፡
«ወደ አንዱ ሆቴል ጠጋ ብታደርገኝ
«ይቻላል» አለና ሾፌሩ ከመንታ መንገዱ ወደ ቀኝ ታጠፈና ኒያላ
ሆቴል» ከተባለ ሆቴል በር ላይ አደረሰው፡፡
በልሁ የታክሲ አገልግሎት ክፍያውን ከምስጋና ጋር ከፈልና የልብስ ሻንጣውን ትከሻው ላይ አንግቶ ወደ ሆቴሉ የእንግዳ መቀበያ ክፍል አመራ፡፡አልጋ ሲጠይቅ መኖሩ ተነገረው፡፡ አንድ አስተናጋጅ ከፊት ከፊት እየመራ
ወሰደውና ክፍሉን አሳየው፡፡ ከፍሉ ንፁህና ግሩም የሚባል አልጋ አለው በልሁ የክፍሉን በር ዘግቶ አልጋው ላይ አረፍ በማለት ስለገጠመኑ ችግር ያሰላስል ጀመር፡፡ ማሰቡ ግን መላ አላስገኘሰትም፡፡ ይልቁንም የባሰ ጭንቅ ጭንቅ ይለው ጀመር፡፡
በምሀል አንድ ነገር ትዝ አለውና ከዚያው ጋር በተያዘ ሌላም ነገር ቆጨው በመሠረቱ አስቻለው አካል ጉዳተኛ ነው፡፡ ብዙ መጓዝ ስለማይችል ቤት የሚከራየው በሚሰራበት አካባቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ስራዬ መናፈሻ ውስጥ
የሚያዘወትር ከሆነም ቤቱም ሆነ መሥሪያ ቤቱ በዚያው አካባቢ ከመሆን እንደማያልፍ ገመተና ያንን ባለ ታክሲ በመናፈሻው አካባቢ ማረፊያ ወደዚያ አድርሰኝ ሳይለው በመቅረቱ ነበር ቁጭቱ፡፡ ሆኖም አሁንም ሳይዘገይ ጥሩ ሀሳብ እንደ መጣላት አስቦ ጭንቀቱ ከፈል ሲልለት ሀሳቡን ሰብሰብ አደረገና ወደ መታጠቢያ ክፍል ሊገባ ፈለገ፡፡ የሚለብሰውን ፒጃማ አዘጋጀና ሊታጠብ ገባ።
ታጥቦ አበጥሮ ሲያበቃ ምግብ አሰኘው፡! ወደ ሆቴሉ ሬስቶራንት ሄዶ ከበላ በኋላ በቀጥታ ከሆቴሉ ቅጥር ግቢ ወጣ፡፡ ሰዓቱ ከአስራ ሁለት እለፍ ብሏል፡፡ የመንገድ መብራቶች በርተዋል፡፡ ከሆቴሉ በስተግራ አቅጣጫ ተራመደና መንታውን መንገድ አቋርጦ ወደ ምዕራብ አቅጣፍ ደራመድ
ጀመር፡፡ የምሽት የአስመራ ውበት ማራኪ ነው፡፡ አየሩም ሞቅ ያለ፡፡
መብራቶቸ የደመቁ፡፡ የከተማዋ ከቀማመጥ ማራኪ፡፡ መንገዶች ንፁህና የተስተካከሉ፡: በልሁ በሁሉም የአስመራ ገፅታ እየተደሰተ በግምት እስከ ሶስት
መቶ ሜትር ከተጓዘ በኋላ በስተቀኙ በኩል አንድ በበረንዳው ላይ በርካታ ወንበሮች የተደረደሩበት፣ በሰው ብዛት ሞቅ ደመቅ ያለ ሆቴል አየና ጎራ
አለበት፡፡ ሰው አልባ የነበረች ጠረጴዛ አግኝቶ ቁጭ እንዳለ አንዲት ወፈር ያለች ጠይም ጎፈሬ አስተናጋጅ ቀረብ ኣለችውና፡-
«እንታይ ክዕዘዝ» አለችው፡፡
«ትግሪኛ አልችልም፡፡» አላት በልሁ ቀና ብሎ በፈገግታ እያያት
«ዋይ! ይቅርታ የኔ ወንድም!» ብላ አስተናጋጇ በፈገግታ ኣየት
ካደረገችው በኋላ «ምን ልታዘዝ ማለቴ እኮ ነው፡፡» አለችው::
በልሁ በልጅቷ ትህትናና ፈገግታ ደስ ብሎት እሱም ፈገግ በማለት
«ቢራ አምጪልኝ» አላት፡፡
አስተናጋጇ ቢራውን ይዛ መጥታ በብርጭቆ ሞላችለትና ከአጠገቡ ራቅ ብላ የግድግዳ ጥግ ደገፍ ብላ ቆመች፡፡ በልሁ ልጅቷ ያሳየችውን ትህትና አስታውሶ ሁኔታዋ ደስ ስላለው በልቡ ስላለው ጉዳይም ሊያወያያት ፈልገና ሊጠራት አሰበ፡፡ ነገር ግን በዚያች ቅጽበት ማጣደፉ ለሌላ ነገር ይመስላል በማለት ለጊዜው ተወት አረገው፡፡ የመጀመሪያውን ቢራ ጨርሶ ሁለተኛውን
ስታቀርብለት ግን እንደ ምንም ጨከነና፡-
«የኔ እህት ላነጋግርሽ እፈልግ ነበር!» ሲል ጠየቃት፡፡
«ምን?» አለችው አስተናጋጇ ጠጋ ብላ፡፡
«ቁጭ ማለት አትችይም?»
«እችላለሁ፡፡ብላው ቁጭ ልትል ወንበር ሳብ ስታደርግ በልሁ
ቀደማት:: እየጠጣሽ ነዋ»
አስተናጋጅዋ ሳቅ እያለች ወደ ውስጥ ገባችና ለራሷም ቢራ ይዛ
በመምጣት ከፊትለፊቱ ቁጭ አለች፡፡
«አስመራ፡ ከተማዋም ሰዎቹም በጣም ደስ ትላላችሁ» አላት በልሁ ፈገግ ብሎ እየተመለከታት፡፡
«አይደል?" አለች አስተናጋጇም እንደ መሽኮርመም እያደረጋት።
«በእውነት ታምራላችሁ፡፡»
«እናመሰግናለን::»
በልሁ አስተናጋጇን እያጫወተ ትንሽ ሳያሳስቃት ከቆየ በኋላ ወደ ዋና ጉዳዩ ተመለሰ፡፡ «አንድ ነገር ብጠይቅሽ ታውቂ ይሆን?» ሲል ጠረጴዛውን ደገፍ ብሎ ዓይን ዓይኗን እያየ ጠየቃት፡፡
«ምን?»
«እዚህ አስመራ ወስጥ 'ሰሪዬ መናፈሻ' የሚባል ሆቴል እንዳለ ሰምቻለ። የት አካባቢ ይሆን?»
«ያ የተዘጋው»
«ሲሉ ሰማሁ፤ ግን ለምን እንደተዘጋ ታውቂያለሽ?»
«ኧረ እኔም አላውቅም!» አለችና አስተናጋጇ በልሁን ለየት ባለ
እስተያየት ታየው ጀመር፡፡ በእርግጥ በልሁም የአስተያየቷ መለወጥ ገብቶታል።
«ምነው? መጠየቄ ቅር አለሽ እንዴ? ሲል ጠየቃት፡፡
«አይ እሱ እንኳ ብላ ንግግሯን ቆረጥ ስታደርገው በልሁ ጣልቃ ገባ።
«ቅር ካለሽ ጥያቄዬን አነሳለሁ፡፡» አለና ብርጭቆውን ብድግ አድርጎ ቢራውን ተጎነጨ
«የሸዋ ሰዎች እኮ አትታመኑም፡፡» ብላ አስተናጋጁ የቅንድቧ ስር
አሾልካ በልሁን አየት አደረገችው፡፡
«የሽዋ ሰው መሆኔን በምን አወቅሽ?» አላት በልሁ እንደመገረም ብሎ ለነገሩ አልተግባቡም፡ በልሁ የሸዋ ሰው ሰትለው የደብረ ብርሃን ተወላጅ
መሆኑን ያወቀች መስሎት ነው፡፡ እሷ ግን ቀደም ሲል ትግሪኛ አልችልም ስላላትና ለበርካታ የአስመራ ሰው ትግሪኛ የማይችል ሁሉ የሸዋ ሰው እንደያነ ተደርጎ ስለሚገመት ነው።
«ትግሪኛ አልችልም አላልከኝም?አለችው ፈገግ እያለች፡፡
«ትግሪኛ የማይችል ሁሉ የሸዋ ሰው ነው እንዴ» ሲል ጠየቃት
👍103👎1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....በልሁ አስር ብር ሰጣትና በተረፈው አንቺ ጠጪ እኔ ግን መንገድ ላይ ደክሞኛልና ወደ ማረፊያዪ ልሂድ አላት።
በጥሩ ስሜትና ፈገግታ ተሰነባበቱ
የበልሁ የማግስቱ የመጀመሪያ ስራ አስተናጋጇ በጠቆመችው
አቅጣጫ ሄዶ ያቺን መናፈሻ ማግኘት ነበር።ብዙ ሳይቸገር
አጎኛት፡፡ ሲያዩዋት ደስ የምትል መናፈሻ የነበረች ትመስላለች፡፡ ግቢዋ በልዩ ልዩ ተክል ያሸበረቀ ነው፡፡ ዋናው ቡና ቤት መሀል ላይ ይገኛሉ፡፡ በአራት ማእዘን ቅርፅ ጥርብ ድንጋይ የተሰራ ነው:: በየአትከልቱ መሀል አልፎ አልፎ
የፈራረሱ መዝናኛ ጎጆዎች ይታያሉ። ከአንዱ ወደ ሌላው መተላለፍያ መንገድ በሲሚንቶ የተሰራ ነው፡፡ አሁን ግን የዛፎቹ ቅርንጫፍ ስለማይከረከም እየተዘጉ ያሉ ይመስላሉ፡፡ በዚያ ላይ የወፎች ኩስ ተንጠባጥቦባቸው
ተዥጎርጉረዋል፡፡
የግቢው ዙሪያ አጥር ከታች አንድ ሚትር ያህል በግንብ፡ ከላይ ደግሞ የዚያኑ ያህል በብረት
ፍርግርግ የታጠረ ነው፡፡ ዋና መግቢያው በር በብረት መዝጊያ ተከርችሟል፡፡ አንድ ሰው ብቻ ይጠብቀዋል፡፡
በልሁ የዚያች መናፈሻ የቀድሞ ገፅታ በአይነ ልቦናው ታየውና እንባ እንባ አለው፡፡ አስቻለውን በዚያ ውስጥ አስታወሰው፡፡ አስቻለው አሁን እዚያ ውስጥ እያለ ነገር ግን ቢጠራው አልሰማ፣ እጁን ቢዘረጋ አልደርስበት ያለው
ይመስል ሆዱ ባባ፡፡ እንባውም ፈሰሰ፡፡ መሀረቡን አውጥቶ አይኑን ጠረግ ሲያደርግ ድንገት ድምፅ ሰማ፡፡ ከመናፈሻዋ በር ጠባቂ በኩል ነበር፡፡
“ምን አሉኝ ጌታዬ?» ሲል በልሁ ወደ ሰውየው እያየ ጠየቀው፡፡
ሰውየው አሁንም ተናገሩ።ነገር ግን በትግርኛ ስለነበር ለበልሁ አልገባውም።
ሰውየው ከስልሳ አለፍ የሚላቸው ይመስላሉ የሰማያዊ ካኪ ቱታ ለብሰው ራሳቸው ላይ የዘበኛ ቆብ
አድርገዋል። እሳቸውም አማርኛ በደንብ አይችሉ ኖሮ በእጃቸው እያመለከቱ « ወዲያ ወዲያ..»
አሉት በልሁም ከዚህ አካባቢ ሂድ ማለታቸው እንደሆነ ገብቶት ከቦታው መራቅ ጀመረ፡፡
ከአባ ሻውል በስተደቡብ አቅጣጫ በሚወስደው አቧራማ መንገድ ላይ ዝም ብሎ ይራመድ ጀመር፡፡ ያ አካባቢ ከሌላው የአስመራ አካል ጋር ሲነጻጸር
ደከም ያሉ ናቸው:: ሞቅ ደመቅ ያሉ ቡና ቤቶች አይታዩበትም ትንንሽ ግሮሰሪዎች ጠላና እንዲሁም አረቄ ቤቶች ይበዙበታል።
በልሁ ድንገት በል በል አለውና ከከንድ ጠላ ቤት ውስጥ ገባ ሰዓቱ ገና ከአራት ብዙም አላለፈም፡፡ ነገር ግን በርካታ ጠጪዎች ቤቱ ውስጥ አሉ፡፡ ባለ ጠላ ቤቷ ሳይሆኑ የማይቀሩ
ወደ ሃምሳ የሚጠጋቸው ቀይ ረጅም ዘንካታ የሆኑ ሴት ወይዘሮ ወንበር ላይ ጉብ ብለው በየመደቡ ላይ ተቀምጠው ከሚጠጡ ሰዎች ጋር ይጫወታሉ። ቋንቋቸው ትግረኛ ነው።
በልሁ ገብቶ ሲቀመጥ ምን ልታዘዝ የሚል አስተናጋጅ ከፊቱ
አልቀረበም፡፡ ጠላ ቤት ነውና መስተንግዶው የታወቀ ነው፡፡ አንዲት በኑሮዋ ጎስቆል ያለች ልጅ እግር ሴት በጣሳ ጠላ ይዛለት ቀረበች፡፡ በእጁ ሰጠችው፡፡በልሁ ጠላውን ቀመስ ሳያደርግ ወለሉ ላይ ቁጭ አደረገው።
እኒያ ነጫጭ የሀገር ልብስ ለብሰው ወንበር ላይ ቁጭ ያሉት ቀይ መልከ መልካም ሴት በልሁን
አየት አደረጉና «ብርጭቆ ክህቦም» አሉት በትግርኛ። «ምናሉኝ እማማ!» አለና በልሁ «ትግርኛ አልችልም» አላቸው
«ዋይ!» አሉና ሴትዮዋ «ብርጭቆ ይሰጥህ ወይ ማለቴ እኮ ነው፡፡» አሉት «አያስፈልግም እማማ! አመሰግናለሁ!» አለና ጣሳውን አንስቶ ፉት አለ።
«የሸዋ ሰው ነህ?» ሲሉ ጠየቁት ሴትየዋ ፈገግ እያሉ፡፡
«አዎ» አላቸው፡፡ በልሁ ያቺን የማታዋን አስተናጋጅ አስታወሳት፡፡
«አይዞህ የኔ ልጅ! በል ጠጣ!» አሉትና ሴትዮዋ ወደ ሌለች ጠጪዎች ዞር በማለት ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡
በልሁ አልፎ አልፎ ጠላውን ፉት እያለ የሚያወሩት ነገር ባይገባውም የጠጪዎችን ወሬ ሲያዳምጥ ብዙ ቆየ፡፡ በየመሀሉ ግን ልቡን ዳዳ የሚያረገው
ነገር አለ፡፡ ሊናገር አሁን አሁን ሲል ድንገት ሴትዮዋ ቀድመው አናገሩት:
«ተጫወት የኔ ልጅ!፡፡» አሉት በልሁን ፈገግ ብለው እያዩ፡፡ በልሁ
ጣሳውን እያነሳ ሳለ ሴትዮዋ ቀጠሉ፡፡ «ቋንቋችንን አታውቀው፣ እንዴት እናርግህ?» አሉት እጆቻቸውን በጡቶቻቸው ስር አጣምረው ፊት ለፊት
እየተመለከቱት፡፡
«አረ ይሁን ምንም አይደል» ብሎ በልሁ ወዲያው ደግሞ በዚህ
አካባቢ የሚያውቁት የሚሲዮኖች ሀኪም ቤት ይኖር ይሆን እማማ?» ሲል ጠነቃቸው።
ሴትዮዋ ትንሽ አሰብ አደረጉና «እነዚያ ጥልያኖቹ?» ሲሉ ጠየቁት፡፡ «ይሆናሉ በእርግጥ ፈረንጆች ናቸው»
«ከዚህ ወደታች በኩል ነበሩ፡፡ ነገር ግን አሁን እኮ ከዚያ ቦታ «ለቀዋል?» በልሁ አሁንም ደንገጥ እያለ
«ምን ያህል ጊዜ ሆናቸው?
«ቆዩ እኮ!»
«ምን ያህል ጊዜ ሆናቸው?»
ሴትዮዋ በቀጥታ ለበልሁ ምላሽ ሳይሰጡ ወደ ጠጪዎቹ ዞር በማለት በትግሪኛ ያነጋግሯቸው ጀመር፡፡ ደግመው ደጋግመው ከተመላለሱ በኋላ ሴትዮዋ ፈታቸውን ወደ በልሁ መለስ አድርገው «ከዓመት በላይ ይሆናቸዋል ነው የሚሉኝ» አሉት።
በልሁ እንደገና ወሽመጡ ቁርጥ አለ ፡፡ አጋጣሚዎች ለምን
እንደሚደጋገሙበት ግራ ገባው፡፡ እዝን ባለ ፊት ትክዝ ባለ አነጋገር «በቃ ይተውት እማማ!» እላቸውና ጣሳውን አንስቶ ፉት ካለለት በኋላ መልሶ አስቀመጠው፡፡ ወደ መሬት እጎንብሶ ራሱን ደጋግሞ ወዘወዘው፡፡
«ልትታከም ኖሯል?» ሲሉ ሲትዮዋ ጠየቁት፡፡
«አይደለም፡፡ እነሱ ጋር ይሰራ የነበረ ሰው እፈልግ ነበር፡፡» አላቸውና አሁንም ጎንበስ አለ።
«አየየ... ለቀዋላ!» ብለውት ሲትዮዋ ወደ ጨዋታቸው ተመለሱ፡፡
በልሁ ከዚያ በኋላ ብዙ መቆየት አልፈለገም፡፡ ውስጡም ተናደደ፡፡
እስከ አሁን ባገኘው መረጃ የአስቻለው ዱካ በቀላሉ እንደማይገኝ፡ ምናልባትም
ጭራሽ ላይገኝም እንደሚችል ፈራ፡፡ ተስፋው እየጨለመ ሄደ፡፡
ወዲያው አንድ ነገር ታየው፡፡ ወደ አረፈበት ሆቴል መብረር፡፡ አዎ
ሄደ፡፡ በጠራራ ፀሐይ በአንሶላና ብርድ ልብስ ጥቅልል ብሎ ተኛ አስቻለውን እንዳያገኝ ከጋረደው የጭንቅ ጉም ያመለጠ መስሎት፡፡
የሰው ልጅ የቱንም ያህል ቢያሰብ፡ ቢጨነቅ ወይም ቢናደድ፡ ቢበሳጭ አልያም ቢፈራ በአጠቃላይ በየትኛውም ስሜት ውስጥ ቢሆን በህይወት
ለመሰንበት የግድ የሚያስፈልገው አንድ ነገር አለ፡ ምግብ፡፡ በልሁ በአንሶላና በብርድ ልብስ ውስጥ ቢደበቅም አላመለጠውም፡ አጅሬ ርሀብ ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ የሚነሳ እሳት ነውና አንጀቱን ይሞረሙረው ጀመር፡፡ ከአንድ ጣሳ ጠላ ሌላ የቀመሰው ነገር ባለመኖሩ ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት አካባቢ ከተኛበት ሰቅስቆ
አስነሳው:: ምግ አይሉት ራት አደባልቆ ሊበላው ወደ ሆቴሉ ራስቶራንት ወረደ፡፡ ሚሲዮኖቹ ሀኪሞች ይሰሩ ከነበሩበት አካባቢ በመልቀቅ ዜና ተበሳጭቶ
ሳይበላ ሳይጠጣ በመዋሉ መንፈሱ ድክምክም ብሎበት የነበረው በልሁ ምሳ በልቶ ቀዝቀዝ ያለ ለስላሳ ከውሃ ጋር እየቀላቀለ ሲጠጣ በዚያው ልክ ተነቃቃ፡፡
ረጋ ብሎ ማሰብ ጀመረ።
አንድ ነገር ታየው ሚሲዮኖቹ
ሀኪሞች እንደ መሆናቸው መጠን
ከክፍለ ሀገሩ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ጋር በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል ታሰበው ምናልባትም የስራ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል " ያ ከሆነ ደግሞ ወቅታዊ ሪፖርቶች ይጠበቅባቸው ይሆናል፡፡ በዚያው መጠን በሁለቱ አካላት መካከል መቀራረብና የአድራሻ ልውውጥ ሊኖር ይችላል “ሚሲዬኖቹ እዚያው አስመራ ካሉም እዚያው
👍131
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....«ይቅርታ የኔ ወንድም» ብሎ ጉዳዩን አጠር እድርጎ እስረዳው፡፡
ወጣቱ ርምጃውን ቀጠለ፡፡ በልሁ ግን እዚያው ባለበት አቀርቅሮ
ቆመ ወጣቱ አስቻለውን በዓይን እንደሚያውቀው ተረድቷል ፡፡ ነገር ግን የሰራተኞች በመኪና መግባትና መውጣት ጉዳይ መኖሪያቸው የግድ በዚያ
አካባቢ ላይሆን እንደሚችል አመሰከተው፡፡ በዚያው ልክ በልሁ ተስፋ ቆረጠ፡፡በነገው ዕቅዱ ላይ ብቻ አተኮረ፡፡ ሲያስብበት ውሉ ሲያስብበትም አደረ፡፡

ሰኞ ዕለት ጠዋት ከረፋፍዶ ከመኝታው ተነሳ፡፡ አለባበሱንም ለየት አደረገው፡፡ ዲላ ውስጥ ለሰርግ ወይም ለየት ባለ ድግስ ካልሆነ በቀር አዘውትሮ
የማይለብሰውን ደብዘዝ ያለ ሰማያዊ ሙሉ ልብስ ለብሶ የጥቁርና የነጭ ቡራቡሬ ክራባት አሰረ፡፡ ጥሩ ቁርስ በላ፡፡ ትናንት ቦታውን አጥንቶት ወደነበረው የክፍለ ሀገሩ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አመራ ከጠዋቱ ሶስት
ሰዓት አካባቢ ከቅጥር ግቢው ውስጥ ገባ፡፡ የአስተዳደር ምክትል ሰራ አስኪያጅ የሚል ጽሁፍ ወዳለበት ቢሮ ልቡ አደላ፣ በፀሐፊዋ በኩል ከመራና በር ላይ ቆሞ
«ጤና ይስጥልኝ» አላት፡፡
«አብሮ ይስጠን» አለችና ፀሃፊዋ ከመቀመጫዋ ብድግ አለች፡፡ አጠር ብላ ወፈር የምትል፡ የቀይ መልከ መልካም የሆነች ዕድሜዋ ወደ አርባ የሚጠጋት ሴት ወይዘሮ ናት፡፡ አጠር ያለ ፀጉሯን ጆንትራ አበጥራለች፡፡
«ሃላፊውን ማነጋገር እችላለሁ?»
«ስለምን ጉዳይ?»
በልሁ የልቡን መዘርዘር አልፈለገም ያን ጉዳይ ካነሳ ይህ አይመለከታቸውም ልትለው እንደምትችል አሰባና «የግል ጉዳይ ነው፡» አላት።
በኋላ፡ የምታዝንለት መስሎት «የመጣሁትም ከሲዳሞ ነው» ሲል ገለጸላት፡፡
ፀሐፊዋ ወንበር እያሳየችው ይቀመጡ» ብላ ወደ አለቃዋ ቢሮ
ገባች፡፡ ብዙ ፡ ሳትቆይ ወዲያው ተመለሰችና "ይግቡ አለችው "
የሃላፊው ቢሮ ለየት ያለ ነው፡፡ መጠነ ሰፊ ወለሉ በአረንጓዴ ቀለም ምንጣፍ የተሸፈነ መስኮቱ በነጭ ስስ እና ቀይ ወፍራም መጋረጃ የተከለለ ከስድስት የማያንሱ ወንበሮች ያሉት ትልቅ የእንግዳ ጠረጴዛ የተንጣለለበት
ግድግዳው ሹሯማ ቀለም የተቀባና ደስ የሚያሰኝ ገፅታ ያለው ነው፡፡
ሃላፊው አቶ ካህሳይ ገብሩም መልካ መልካም ነው፡፡ ድምቅ ብሎ ቀይ ጥቁር ሰማያዊ ሙሉ ልብስ በነጭ ሸሚዝና ጥቁሩ በዛ ያለበት ቡራቡሬ ካራባት ያደረገ፣ አፍንጫው ሰልከክ ዓይኖቹ ጎላ ያሉና ዕድሜው ከአርባ አምስት
ዓመት የማያንሰው ጎልማሳ ነው።
«ጤና ይስጥልኝ አለ በልሁ ወደ ውስጥ ገብቶ ሃላፊውን እጅ እየነሳ
«አብሮ ይስጠን» ብሎ ካህሳይ ከወንበሩ ብድግ ብሎ ተቀበለው፡፡
ስማቸውን በመለዋወጥ እጅ ለእጅ ተጨባበጡና በካህሳይ ግብዣ በልሁ ከእንግዳ መቀበያ ወንበር ላይ ተቀመጠ።
«ምን ልርዳዎት አቶ በልሁ?» ሲል ካህሳይ በልሁን ጠየቀው፡፡
«ችግር ገጥሞኝ ነው አቶ ካህሳይ»
«ምን ዓይነት ችግር?
በልሁ የመጣበትን አገርና ለምን ወደ አስመራ እንደመጣ በአጭሩ
ከአስረዳ በኋላ «ወንድሜ በሚሲዮኖች ክሊኒክ ውስጥ ይሰራ እንደነበር ተጠቁሜ ነበር ።
የሚሰኒዮቹን የስራ ቦታ አጠያይቄ ባገኘውም ነገር ግን ከአንድ ዓመት በፊት ከዛ ቦታ እንደለቀቁ ሰማሁ፡፡ ምናልባት ከሙያ አንጻርና
የምታውቸው ከሆነና አሁን የሚገኙበትን ቦታ ትጠቁሙኝ ከሆነ ብዩ ነበር፡፡» አለና በልሁ ካህሳይን ቀና ብሎ ተመለከተው፡፡
«የት አካባቢ የነበሩት ናቸው?» ሲል ካህሳይ በልሁን ጠየቀው::
«ቀበሌውን በትክክል አላወኩትም፡፡ ነገር ግን አባ ሻውል ከሚባለው ቦታ ወረድ ብሎ በምዕራባዊ የከተማዋ ዳርቻ የሚገኝ ክሊኒክ እንደ ነበር ማወቅ ችያለሁ።
ካህሳይ ሚሲዮኖቹን ያወቃቸው ይመስላል፡፡ አንገቱን ነቅነቅ ነቅነቅ ካደረገ በኋላ «ታዲያ እኮ እነሱ አስመራ ውስጥ አይደሉም ቦታ የቀየሩት ጠቅላላ ከሀገር ተባርረዋል አለውደ
«ተባርረዋል?» ሲል ጠየቀ በልሁ፡፡ ዓይኖቹ ፍጥጥ ብለው
በካህሳይ ላይ ተተከሉ፡፡
«ከዓመት በላይ ሆናቸው»
«በምን ምክንንያት ተባረሩ አቶ ካህሳይ? ምናልባት ወንድሜም አብሮ ተባሮ ይሆን?» ሲል በስጋት ስሜት ውስጥ ሆና ጠየቀው፡፡
ወንድምክ እንኳ ከብሮ ሊባረር የሚችልበት ሁኔታ የለም፡፡ እነሱ የተባረሩት በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገቡ ተብሎ ነው፡፡»
«በፖለቲካ?»
«በመሆኑ ነዋ ለነገሩ እነርሱም አያርፉ ነገሮች ሁሉ እንደራሳቸው
ሀገር እየመሰላቸው የኛ መንግስት አካሄድ ሳይጥማቸው ሲቀር በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ወጋ ማድረግ ይወዳሉ፡፡ አለ ካህሳይ ፈገግ ብሎ የበላሁን ምላሽ እየጠበቀ።
በልሁ ፈጥኖ ለካህሳይ መልስ መስጠት አልፈለገም ወይም አልቻለም ዓይኑን ብቻ ትክል አድርጎ ካህሳይን ያየው ጀመር፡፡ እንዲያውም ቀስ በቀስ ዓይኖቹ በእንባ ይሞሉ ጀመር፡፡
«ምነው አቶ በልሁ?» ሲል ካህሳይ የበልሁ ስሜት መለዋወጥ አስገርሞት ጠየቀው፡፡
በልሁ አሁንም መልስ ከመስጠት ይልቅ ፊቱን በካህሳይ ላይ መልሶ
ወደ ጠረጴዛው በማጎንበስ በእንባ የሞላውን ዓይኑን በመሀረብ ይጠርግ ጀመር፡፡
«አቶ በልሁ» አለ ካህሳይ ይበልጥ እየደነገጠ፡፡
«ሆዴ አዘነ አቶ ካህሳይ!»
«ምነው? ወንድምህ አብሮ የተባረረ መሰሎህ?
«አይደለም አቶ ካህሳይ የዕድሉ ነገር እሳዝኖኝ ነው ፡፡" አለና ንግግሩን በማራዘም «አዩ አቶ ካህሳያ፣ ወንድሜ የጤና ባለሙያ እንጂ ፖለቲከኛ አልነበረም፡፡ ነገር ግን በሄደበት ቦታ ሁሉ የፖለቲካ መዘዝ አልለቀው አለው
አሁንም የዓይኖቹን እንባ እየጠራረገ፡፡
«ማለት?»
«ወንድሜ ገና ልጅ ሳለ የሚረዳው ወንድሙ በፖለቲከኞች ተገደለበት
በችግር ተማረ፡፡ በስንት ስቃይ ትምህርቱን ጨርሶ ስራ ከያዘም በኋላ አሁንም ፖለቲከኞች ሰላም ነስተው ሲያዋከቡት ኖሩ፡፡ የኋላ ኋላም በግፍና በተፀዕኖ ወደዚህ ክፍለ ሀገር በ እናት ሀገር ጥሪ ሽፋን እስገድደው ላኩት፡፡ በእነሱ ጦስ አካሉን አጣ፡፡ እዚሁ ከተማ ውስጥ እየተውትሮ ያርፍባት የነበረችው ሰራዩ መናፈሻ ደግሞ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ መዘጋቷን ሰማሁ፡፡ እነሆ አሁን ደግሞ
እርስዎም አሰሪዎቹ በፖለቲካ ጉዳይ ከሀገር መባረራቸውን እየነገሩኝ ነው፡፡ ይህ የፖለቲካ ጉዳይ እኔም እንዳላገኘው ምክንያት ሊሆን ነው፡፡ ታዲያ ይሄ
አያሳዝንም እቶ ካህሳይ?» ሲል በልሁ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ለካህሳይ ገለፀለት::
ካህሳይ ገብሩ በሰማው ታሪክ፣ በበልሁ አለቃቀስና የነገሮች አገላለፅ የእሱም ልብ ነካ፡፡ በልሁን ያህል ግርማ ሞገሱ ግጥም ያለ የወጣት ጠንበለል ከፊቱ ቁጭ ብሎ እንባውን እያፈሰሰ ብሶቱን ሲገልጽላት የእሱም አንጀት
ተላወሰ፡፡ ወንድ ልጅ ሲከፋው እንባው ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሲረዳ ሆዱ ተንቦጫቦጨ በሀዘን ሰሜት ራሱን ደጋግሞ ወዘወዘና በልሁን ትኩር ብሎም ተመለከተው። በልሁ አሁንም ንግግሩን ቀጠለ
«በቃ እኮ አቶ ካህሳይ ከእንግዲህ ወንድሜን ላላገኘው ነው።አለው እንባው በአይኖቹ ላይ ተቋጥሮ ሰማይ እየመሰለ።
ካህሳይ ገብሩ አሁንም ላፍታ ያህል በሀዘን ዓይን ከተመለከተው በኋላ ራሱን ለረጅም ግዜ ወዝውዞ በረጅሙ ተነፈሰና «ለመሆኑ የወንድምህ ስም ማን ይባላል?» ሲል ጠየቀው።
👍9
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


.....«አመሰግናለሁ አቶ ካህሳይ!» አለ በልሁ በአክብሮትና በትህትና እጅ እየነሳ።
«የት ነው ያረፍከው?» ሲል ጠየቀው ካህሳይ፡፡
«ኒያላ ሆቴል ሃያ አራት ቁጥር፡፡»
ጥሩ አቶ በልሁ በተረፈ እግዚኣብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡» ብሎ በልሁን በሰላምታ ለመሸኘት ከወንበሩ ላይ ብድግ አለ፡፡ በልሁም ብድግ አለና ለሁለተኛ ጊዜ የከበረ ምስጋናውን አቅርቦ ተጨባብጠው ተሰነባበቱ፡፡

ስድስት ቀናት አለፉ፡ አንዲያውም በልሁ አስመራ ከገባበት ቀን ጀምሮ ሲቆጠር አሥረኛ ቀን፡፡ የአስቻለው ዱካ ግን አልተገኘም፡ ጭራሽ እየራቀ ሄደ፡፡ የካህሳይ ገብሩ ጥረትም አልተሳካ፡ የአስቻለው ስም በየትኛውም
ኤን ጂ ኦ የሰው ሀይል ሪፖርት ውስጥ ተካትቶ አልተገኘም፡፡ በልሁ በቀጠሮው ቀን ወደ
ካህሳይ ቢሮ ብቅ ባለበት ወቅት የተነገረው ይኸው መጥፎ ዜና ነበር፡፡
በልሁ ከዚያ በኋላ ማድረግ የፈለገው አንድ ነገር ብቻ ነበር፡፡ ሳይታክት ሴይሰለች በአስመራ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ቡና ቤቶች ሁሉ እየተዘዋወረ ሰለ
እስቻለው ወሬ መጠየቅ፡፡ የበልሁ ሀሳብ በየቡና ቤቱ እየተዘዋወረ
አስተናጋጆችን በማነጋገር ምናልባት አስቻለው ያዘወትርባት በነበረችው ስራዬ መናፈሻ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ የሆቴል ሰራተኞችን ከአገኘሁ የሚል ነበር፡፡
በእርግጥም አነስተኛ ሻይ ቤቶችና ኬክ ቤቶች ሳይቀሩ በአስመራ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የተኮለኮሉትን ቡና ቤቶች ሁሉ ጎበኛቸው፡፡ ከቀትር በፊት ሲሆን ሻይ ቡና፣ ወደ አመሻሹ ላይ ደግሞ ቢራ ወይም ሌላ ዓይነት መጠጥ እየያዘ በመቀመጥ ብዙዎቹን አነጋገረ፡፡ ሆኖም ፍንጭ እንኳ ሊያገኝ አልቻለም።እንዳያውም
ከሚጠጣው ሻይና ቡና ብዛት የተነሳ ከንጀቴ ተቃጠለ፡፡ ቢራና የአልኮል መጠጡም በተለይ ሌሊት ሌሊት እንቅልፍ እየነሳው ተቸገረ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሰንብቶ ልፋቱ ሁሉ መና ሲቀርበት ሌላ ሙከራ
ሊያደርግ አሰበ በቀጥታ ወደ ዲላ ስልክ መደወልና ታፈሙን ማግኘት በእሷ በኩል የሀምሳ አለቃ መንጋ ዳርጌን ለማግኘት መሞከር፡፡ ሀሳቡም ምናልባት የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ያን ከአስቻለው ጋር ለመገናኘት ምክንያት የሆነውን የአስመራ ኗሪ ጓደኛውን አድራሻ የሚያቀው ከሆነ ሊጠይቀውና በእሱ እየታገዘ ወደ አስቻለው ለማምራት ነበር በልሁ ይህን ያሳሰጡ አስመራ በገባ በአሥራ አንደኛው ቀን በዕለተ ዕሁድ ላይ ሆኖ ነው፡፡ ታፈሡንም ሆነ የሀምሳ
አለቃ መኮኮንን ዳርጌ ያን ከአስቻለው ጋር ለመገናኘት ምክንያት አለቃ መኮንን ዳርጌን በቀላሉ በስልክ ሊያገኝ የሚችለው በመስሪያ ቤት በኩል
ስለሆነ ስልክ የመደወል ሙከራውን በማግስቱ ሰኞ ሊያደርግ ወሰነ፡፡
ይህን ሀሳብ ያሰሳሰለው በኒያላ ሆቴል ውስጥ አልጋ ላይ ጋደም ብሎ ነው፡፡ ከውሳኔ ላይ የደረሰውም በዕለቱ ወደ አስር ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ በዚያ አልጋ ላይ ለብዙ ጊዜ ቆይቶ ስለነበር ከውሳኔ በኋላ በአስመራ መንገዶች ላይ ጥቂት ሊዘዋወር ፈለገ፡፡ ለባብሶ ወጣ፡፡ ጥቂት ሲዘዋወር ከቆየ በኋላ ሳያስበው
ከዚያ አስመራ የገባ ዕለት ጎራ ባለበትና ስለ አስቻለው ለመጀመሪያ ጊዜ ያወያያት የቡና ቤት አስተናጋጅ በምትሰራበት ሆቴል እግሮቹ አደረሱት፡፡
ጥቂት ለማረፍና ከልጅቷም ጋር ጥቂት ሊጨዋወት ከስቦ ጎራ አለ፡፡ ቁጭ አለና ቢራ አዘዘ፡፡ ልጅቷን ግን በዓይኑ ቢፈልጋትም ሊያያት አልቻለም ወይ
የጠዋት ተረኛ ሆና አሊያም በሌላ ምክንያት በእለቱ በሆቴሉ ውስጥ የለችም እሱ ግን ብቻውን ቁጭ ብሎ ሲጠጣ አመሽ፡፡ ከምሽቱ ሁለት ሠዓት አካባቢ ሂሳቡን ከፈለና ወደ ማረፍያው ኒያላ ሆቴል አመራ።
ልክ እንደደረሰ የአልቤርጎውን በር ከፍቶ ወደ አልጋው ሊራመድ ሲል
እንዲት ለሁለት የታጠፈች ወረቀት ወለሉ ላይ ታየችው፣ በበሩ ስር ወደ ውስጥ የተወረወረች ትመስላለች፡፡ ልቡ ደንገጥ አለና ትኩር ብሎ ተመለከታት፡፡ወዲያው ብድግ አድርጎ ሲያያት አጭር መልእክት ይዛለች።
«አቶ በልሁ፣ ከዚህ በታች በተገለጸው ስልክ ቁጥር ስዩም ብለው ይደውሉ።» ይላል የያዘችው መልእክት።
«እ» አለ በልሁ ሁለመናውን ነዘር አደረገው፡፡ «ማነው ስዩም ማለት?» አለ ብቻውን እየተነጋገረ።
ጉዳዩ ከእስቻለው ጋር የተያያዘ መልዕክት ካለው ብሎም ጓጓ፡፡ ቀስ እያለ ሲያስበው ግምቱ ይበልጥ ጠነከረ፡፡ ጭራሽ ስልክ ለመደወል ቸኮለ፡፡ ያቺ ወረቀት ከእጁ ሾልካ የምትጠፋበት መስሎት በመዳፉ ውስጥ ጭብጥ አደረጋትና በችኮላ የአልቤርጎውን በር ዘግቶ ወደ ውጭ በረረ፡: ኒያላ ሆቴል አጥር ግቢ ወጥቶ መንገዱ ላይ እንደ ደረሰ በመንገድ ላይ በቡድን ሆነው እየሄዱ የነበሩ
ሰዎችን በጅምላ ጠየቃቸው፡፡
«ስልክ፡ በቅርብ የት አገኛለሁ ወንድሞቼ?»
«በዚያም በዚህም ሞልቷል!» አለው ከመንገደኞች አንዱ፡፡ በልሁ
በየት አቅጣጫ መሮጥ እንዳለባት ሲያስብ አሁንም ከመንገደኞች አንዱ ወደ ቀኝ አቅጣጫ እያመለከተ «በዚህ በኩል በቅርብ ታገኛለህ» አለው።
በልሁ በዚያው አቅጣጫ ሮጠ፡፡ አንድ ሁለት ሱቆች ውስጥ ሲጠይቅ አንዱ ጋር ስልክ አያስደውሉም፣ ሌላኛው ደግሞ ለጊዜው ስልኩ ተበላሽቶ ኖሮ
«አይሰራም» አለችው ሱቅ ጠባቂዋ፡፡ በጠየቀበት በአምስተኛው ሱቅ ውስጥ አገኘና ደወለ።
«ሄሎ» አለችው አንዲት ሴት
«አቶ ስዩምን ፈልጌ ነበር የኔ እመቤት»
«ይጠብቁ!» ብላው ሴትየዋ የስልኩን እጀታ በሆነ ነገር ላይ
ስታስቀምጥና በርቀት እጠራር ስልክ ይፈልግሀል ስዩም" ስትል በስልኩ ውስጥ ተሰማው፡፡ በልሁ ከስዩም ድምጽ በፊት ወደ ስልኩ እየቀረበ ስለመሆኑ ለማወቅ
ኮቴውን በጥንቃቄ ያዳምጥ ጀመር፡፡ በእርግጥም ተሰማው::
«ሄሎ!» አለ አንድ ሰው።
«አቶ ስዩም ነዎት ጌታዬ?»
«አዎ ነኝ»
«በልሁ እባላለሁ፡፡ አልቤርጎ ውስጥ መልዕክትዎን አግኝቼ ነው፡፡»
«እ ነዎት? አስቻለው ፍሰሀ የሚባል ሰው በመፈለግ ላይ ያሉት?»
«አዎ ጌታዬ!» አለ በልሁ፡፡ ልቡ በድንጋጤ ትርትር ሊል የደረሰ
መሰለው::
«ታዲያ ለምን አመሹ? በጊዜ አይደውሉም ነበር? እኔ እኮ አስር ሠዓት አካባቢ ነበር መልዕክቱን ያስቀመጥኩልዎት፡፡» አለ ስዩም፡፡
እኔም እኮ በዚያው አካባቢ ነው ከክፍሉ የወጣሁት፣ ለጥቂት ተላልፈን እንደሆነ አንጂ!» አለና በልሁ አጋጣሚው እንዳያመልጠው በመስጋት “ወይ እኔ ወደ እርሶ ልምጣ?” ሲል ጠየቀው፡፡
«መቼ? አሁን?»
«ምንም ችግር የለብኝም ጌታዬ
«ቸኩለዋል ማለት ነው?»
(በጣም አቶ ስዩም፡ እጅግ በጣም
«በቃ እኔ እመጣለሁ፡፡ ባይሆን እንዳንጠፋፋ ከክፍልዎ ይጠብቁኝ፡፡»
«ንቅንቅ አልልም ጌታዬ!»
«እሺ መጣሁ፡፡»
ለበልሁና ለስዩም መተዋወቂያ አስቻለውን የመፈለግ ስራ እንደ
ምልክትነት የመውሰዱ ጉዳይ ነገሩ ከአስቻለው ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የበለጠ ተስፋ አደረበት፡፡ ግን አስቻለውን የሚያስገኝ ይሆን ወይስ ሌላ ሁኔታውን የሚያውቅበት አጋጣሚ? የበልሁ የዚያች ቅፅበት ሀሳብና ስጋት ሆነ፡፡ ግን የሆነው ይሁን፣ በልሁ ዛሬ ስዩምን ማግኘት አለበት፡፡ ስዩም ደግሞ 'መጣሁ አለው እንጂ በምን ያህል ደቂቃ እኒያላ ሆቴል ሊደርስ እንድሚችል
አልገፀለትም። በስልክ ያነጋገረው ሩቅ ይሁን ከቅርብ ቦታ ሆኖ ይሁን አይሁን አያውቅም ለማንኛውም ከቀጠሮ ቦታ ቀድሞ መድረስ ነበረበትና ስልክ ከደወለበት ሱቅ ጀምሮ እስከ ኒያላ ሆቴል የመኝታ ቤት ቁጥር ሃያ አራት ድረስ ያለውን መንገድ በሩጫ ጨረሰው የፎቁን ደረጃዎች እንኳ በሩጫ ነው የረመረማቸው:: ክፍሎ ደርሶ በሩ ላይ ሰው ያለመቆሙን ሲያረጋግጥ ብቻ እፎይ አለ፡፡ ወደ ክፍሉ ከመግባቱ በፊት ሽንጥና ሽንጡን ይዞ በመቆም የሩጫ ትንፋሹን ጨረሰና በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ
👍91
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...«እታች ቡና ቤት ውስጥ ሻይ እየጠባሁ እጠብቅሀለሁ፡» ተረጋግተህ ለባብስና ና
በዚሁ ተስማምተው ስዩም ከፎቁ ላይ ወደ ታች ወደ ቡና ቤቴ ወረደ.
በልሁ ግን ከመደናገጡና ከመቸኮሉ የተነሳ የአለባበስ ቅደም ተከተሉ ሁሉ ጠፋበት። ሳይፀዳዳና ሳይተጣጠብ ልብሱን ለባባሰ ሲያስታውስ የሚቀሩት ነገሮች አሉ።እንደገና መፀዳጃ፡ ከዚያም ወደ ፀጉር ማበጠር ግን ሁሉም ነገር በችኮላና በጥድፍያ ነው።
ሁሉንም ነገር እንደምንም ጨራርሶ ወደ ሆቴሌ ተንደርድሮ ሲወርድ ስዩም ያዘዘውን ሻይ ጠጥቶ ጨርሷል ፡፡ በልሁም” እንዲጠጣ ጋበዘው በልሁ ግን እሺ አላለም"፡ ይልቁንም የስዩምን የሻይ ሂሳብ ለመክፈል ተሽቀዳደመና ከፈለ፡፡ ከቡና ቤቱ ወጡና በስተግራ በኩል ወደ አባ ሻውል በሚወስደው ሰፊ
የአስፋልት መንገድ ላይ ወደ አስቻለው ቤት ጉዞ ተጀመረ፡፡ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሆኗል፥
በልሁ ከስዩም ጋር አብሮ እየተራመደ ሳለ እግሮቹ በፍርሀት
ይንቀጠቀጣሉ፡፡ ከንፈሮቹ እየደረቁ ደጋግሞ በምላሱ ያርሳቸዋል፡፡ ጭራሽ ከስዩም እኩል ከጎኑ ሆኖ ለመራመድ እየፈራ ወደ ኋላ ቀረት ቀረት ይላል፡፡ብዙ ከተጓዙ በኋላ አንዲት የሀገር ልብስ የለበሱ ሴት ወይዘሮ አንዲት ልጅ እግር ቢጤ ሴት ዘንቢል አስይዘው ከፊትለፊት ሲመጡ አዩአቸው:: ከጥቂት ርምጃዎች በኋላ ይበልጥ ተቀራረቡ፡፡በኋላም ተገናኙ
«በጠዋት ወዴት እማማ አብረኸት?» ሲል ስዩም ቀድሞ ጠየቃቸው፡፡
«ለገበያ ወደ ኣባ ሻውል፡፡» አሉት ወይዘሮ አብረኸት በእጃቸው
ስዩምን ሰላም እያሉ በአይናቸው ደግሞ በልሁን እየተመለከቱ።
የት እንደሚያውቁት የሚያሰላስሉ ይመስላሉ፡፡
«የተዋወቁት፣ የአገር ወዳድ ወንድም ነው::»አላቸው ስዩም ፈገግ ብሎ ሁለቱንም ተራ በተራ እየተመለከታቸው፡፡
«አገር ወዳድ የኛ?» አሉ ወይዘሮ አብረኸት አሁንም በልሁን ትኩር
ብለው እያዩት::
«አዎ»
«ከአሁን ቀደም አላየሁህም እንዴ የኔ ልጅ?» ሲሉ ጠየቁት በልሁን::
«አይተውኛል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ከቤትዎ ጠላ ጠጥቻለሁ፡፡
«እኮ የሚሲዮኖችን ሀኪም ቤት የጠየከኝ?»
«አዎ»
«ዋይ የአገር ወዳድ ወንድም ኖረሀል እንደ? ታዲያ ገልፀህ አትነግረኝም" ኖሯል እንዴ ልጄ ቤቱን እኮ አሳይህ ነበር። ከኔም ጋር ብዙም አንራራቅ፣ ያው የጎረቤት ያህል ነው።
«አላወቅሁን የኔ እናት»
ወይዘሮ አብረኸት ወደ ስዩም ፊታቸውን መለስ አድርገው «ግን አገር ወዳድ ከኔ ቤት እልም ብሎ
መጥፋቱ ምን ሆና ይሆን ስዩሜ»? ለወትሮው እንኳ እኔ ጋር
ብቅ ሳይል አይውል አያድርም ነበር፡፡ ወይስ ያ ያመኛል የሚለው ነገር እየጠናበት ሄደ? ይኸው ዓይኑን ከአየሁት ሶስት ወይም አራት ወር ሊሞላኝ ነው።»አሉት
«እያመመው ነው እማማ አብረኸት»
«በቃ ደከመው?»
«መሰለኝ፡፡» አለ ስዩም በዓይኑ ሰረቅ አድርጎ በልሁን እያየ፡፡
የወይዘሮ አብረኸትና የስዩም ቃለ ምልልስ ለበልሁ የመርዶ ያህል
አስደንጋጭ ነበር፡፡ ብቻ ጣልቃ መግባት አልፈልግም፡፡ የሆዱን በሆዱ እምቅ አድርጎ የመጨረሻውን ለማየት በፍርሀት ይጠብቃል፡፡
ወይዘሮ አብረኸት ደረታቸውን በቡጢ መታ መታ እያደረጉ «ልጄን!ልጄን! ልጄን » ካሉ በኋላ «እስኪ ከተመቸኝ ዛሬ ከሠዓት በኋላ ብቅ እላለሁ፡አሊያም ነገ መጥቼ አየዋለሁ፡፡» ብለው ተሰናብተዋቸው ወደ ግቢያቸው አመሩና ስዩምና በልሁም መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
በልሁና ስዩም የያዙትን የኮረንኮች መንገድ በመቀጠል ወደ ታች
ሲወርዱ ከወይዘሮ አብረኸት ቤት መድረሳቸውን በልሁ ልብ አለ፡፡ በዚያው ልክ ወደ አስቻለው ቤት መቃረባቸውን ተረዳና ልቡ የድንጋጤና የፍርሃት ከበሮ ይመታ ጀመር፡፡ የወይዘሮ አብረኸትን ቤት አልፈው ጥቂት ከተጓዙ በኋላ
ስዩም በግራ በኩል የሚገኝ አንድ አቋራጭ መንገድ ይዞ ታጠፈ፡፡ በልሁም ተከተለ፡፡ ጥቂት ከተራመዱ በኋላ ስዩም አሁንም በሌላ የግራ ኣቅጣጫ በሚወስድ መንገድ ይዞ ወደ ላይ ታጠፈ፡፡ በልሁ አሁንም ተከተለ፡፡ በፕላን
የተሰሩ አምስት ቤቶችን አልፈው ስዩም የስድስተኛውን ቤት የውጭ በር አንኳኳ፡፡
በዚህ ጊዜ በልሁ ሁለመናውን ላብ አጠለቀው፡፡ ትንፋሹ በረከተ፡፡
ደረቱ ወጣ ገባ ሆዱ ሞላ ሞሽሽ ይል ጀመር፡፡ በሩ እስኪከፈት ድረስ ሽንጥና ሽንጡን ይዞ በመቆም አንዴ ወደ መሬት ሌላ ጊዜ ወደ ሰማይ እያየ ተቅበጠበጠ፡፡ የአስቻለው መገኘት ነገር እንደ ህልም እልም ብሎ ይጠፋ
እየመሰለው ልቡ ቷ ቷ ቷ ይል ጀመር፡፡
የውጪው በር ተከፈተ፡፡ ፊትለፊት ከጥርብ ድንጋይ የተሰራ ዘመናዊ
ቪላ ቤት ለዓይናቸው ገጭ አለ፡፡ በረንዳው በብረት ፍርግርግ ተሰርቶ ነጭ ቀለም የተቀባ፡ የበርና መስኮቶቹ መስታወት ነጣ ባለ መጋረጃ አሸብርቀው የጥሩ
ኗሪዎች መኖሪያ የሚመሰል ነው:: ግቢው ተስተካክሎ የተደለደለ፡ በየአጥሩ አጠገብ የአበባ ተክሎች
የሚታዩበት እምር ድምቅ ያለ ነው።
ስዩም ወደ ዢላው አላመራም። በስተግራ በኩል ወደ ጓሮ በሚወስድ ቀጭን የእግር መንገድ ይዞ ተራመደ። በልሁም ተከተለው። በጓሮ በኩል አራት ክፍሎች ያሉት ረጅም የስነርቪስ ቤት አለ፡፡ የተሰራው ከጥርብ
ድንጋይ ቢሆንም ነገር ግን ሲሚንቶ የሌለው ደረቅ ካብ ነው፡፡ የአራቱም ሰርቪስ ክፍሎች በር መዝጊያቸው የቆርቆሮ ነው ስዩም መካከል ላይ ከሚገኙት ክፍሎች
ወደ አንዷ ተራመደና ገና በሩ ላይ እንደደረሰ «እንዴት አደርክ አገር
ወዳድ? ሲል ወደ ውስጥ ተናገረ፡፡ ቤቱ ገርበብ ብሎ" ተከፍቷል።
ከውስጥ በኩል ለስዩም ሰላምታ የተሰጠው የምላሽ ድምጽ ግን በተለይ ለበልሁ እጅጉን አስደንጋጭ ነበር እጅግ የደከመ እጅግ የሰለለና የአስቻለው ሊሆን ይችላል ብሎ ለማመን በጣም የሚያስቸግር ነበር፡፡ «ይመስገነው፡፡ ደህና ነኝ ስዩሜ!» የሚል ድምፅ ወጣ ከውስጥ በኩል፡ ግን ደግሞ ድምጽ እንደሚወጣ ላልጠበቀ ሰው ፍፁም ሊሰማ የማይችል ሁኔታ። የበልሁ ጆሮ ቀድሞ ባይ ኖሮ ሰው የተናገረ ሰለመሆኑ ባልታወቀው ነበር።
«እንዴት ነው ሻል አላለህ?» እያለ ስዩም ወደ ውስጥ ገባ በልሁ
ምንም አልተሻለኝም ስዩሜ፣ አሁንማ ከመኝታዬም ለመነሳት ሰው ሊያስፈልገኝ ነው፡፡ እየደከመኝና እያቃተኝ ሄደ፡፡ » የሚል ድምጽ ከውስጥ
ተሰማ፡፡ በዚህ ሰዓት በልሁ በር ላይ ቆሞ በፍርሀት ዓይን ወደ ውስጥ አየት ያደርግ ጀመር፡፡ ከራስጌው በኩል ክራንች ግድግዳ ተደግፎ አየ፡፡ በራስጌ ኮመዲኖ ላይ የምግብ ሳሀኖች ይታያሉ፡፡ ቀጥታ ወደ ታማሚው ሲያይ በግራ ፊቱ ላይ ጠባሳ ታየው፡፡ ነገር ግን ትራስ ላይ ካረፈው የታማሚው ጭንቅላት
በቀር ወደ ታች ያለተ ሰውነቱ ፍጹም ያለ አይመስልም፡፡ ከድምጹ መድከምና መሰለል በተጨማሪ የታማሚው ሰውነት ኣልቆ ከእልጋው ላይ የመጥፋቱ ነገር
ያ ሰው በእርግጥ አስቻለው ስለመሆኑ የበልሁ ልብ ሊያምን አልቻለም፡፡
«ስማ አገር ወዳድ! ዛሬ ደግሞ ዘመድ ዘዳድ ይዤልህ መጥቻለሁ፣ እስቲ እንደ ምንም ብለሀ ቀና በል፡ : " አለ ስዩም አልጋው ስር ቆሞ ታማሚውን
በተኛበት ቁልቁል እያየ::
«የኔ ዘመዶች እዚህ ድረስ አይመጡም፡፡» አለ ታማሚው ከውስጥ፡፡
👍8
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....አስቻለውም እያለቀሰ በሀሳብ ደግሞ ወደ ዲላ ነጎደ፡፡ የሔዋንን አኳኋን
በእዝነ-ልቦናው ይመለከትው ጀመር፡፡ ከዓይኗ የሚፈሰው እንባዋ በስሜት ቆጠቆጠው:: የታሰረችበት እግር ብረት የእሱን እጅና እግር ሲከረክረው
ተሰማው፡፡ በዚህ ጊዜ አንዳች እንግዳ ስሜት ተፈጠረበትና ተነስ! ሂድ! ብረር ወደ ሲዳሞ!! » አለው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ታፈሡ እንግዳሰው ከተፈጠረች ጀምሮ እንደ ሰሞኑ በሀሳብና በጭንቀት መንፈሷ ተናውጦ አያውቅም፡፡ ችግሩ የጀመራት የሀምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌ
ስለ አስቻለው አጠቃላይ ሁኔታ በዝርዝር ከገለፀላቸው ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ በልሁ አስቻለውን ፍለጋ ወደ አስመራ ከሄደ በኋላ ደግሞ ብሶባት ሰንብታለች፡፡ስጋቷም
በልሁ አስቻለውን ያገኘው ይሆን ወይስ ያጣው ይሆን? ቢያገኘው
እሺ ብሎ ይመጣላት ይሆን? ቢመጣስ የሔዋን ስሜታዊ ምላሽ ምን ሊሆን ይችል ይሆን? ከሚል ስጋትና ፍርሀት የሚመነጭ ነው፡፡
በእነዚህ አሳሳቢ ጉዳዮች በቂ ምላሽ ሳታገኝላቸው ውስጥ ውስጡን ሲበሏት፤ ሲያስጨንቋትና ሲያሳስቧት ድፍን አሥራ ሰባት ቀናት አልፉ፡፡ ዛሬ ግን ከሁሉም ነገር መቋጫ ቀን ላይ ደርሳለች፡ በልሁ አስቻለውን ፍለጋ ወደ
አስመራ ከሄደበት ቀን ጀምሮ ሲቆጠር አሥራ ስምንተኛ ቀን በእለተ ቅዳሜ፡፡
በተለይ ሔዋን በማታውቀው ሁኔታ ታፈሡ እንግዶች አሉብኝ
በማለት ማለዳ ተነስታ የድግስ ስራ ጀምራለች፡፡ ስጋና የመጠጥ ዓይነቶችን ጨምሮ በርካታ የምግብ ሸቀጦችን ገዝታ ሔዋንና ትርፌን በስራ ወጥራቸዋለች፡፡ ከአንድም ሁለትና ሦስት ምድጃዎችን በመጠቀም ይከትፋሉ፣ ያቁላላሉ፣ ይቀቅላሉ፡፡
የታፈሡ እጆች በስራ ይጠመዱ አንጂ ቀልቧ በቤት ውስጥ ወይም
በስራው ላይ አልነበረም፡፡ ሀሳቧ ሁሉ ይበታተናል፡፡ ከሔዋንና ከትርፈ ጋር የምትለዋወጠውን ጭውውት ከልቧ አታዳምጠውም፡፡ ብትስቅ እንኳ ሳቋ ለዛ የለውም፡፡ ለጭውውቱ የምትሰጠው ምላሽ ከርእሰ ጉዳዩ ጋር ብዙም አይጣጣምም፡፡ አልፎ አልፎ ከሀሳቧ ብንን ስትል ብቻ •ጭውውቱን እንደ አዲስ
ትጀምረዋለች፡፡
በግምት ከቀኑ አምስት ሠዓት አካባቢ ሳይሆን አይቀርም ታፈሡ ሌላ አስፈሪና አስደንጋጭ ክስተት ተፈጠረባት፡፡ ነገሩ የመነጨው ከወደ ሔዋን አካባቢ ነው፡፡
ሔዋን በልሁ አስቻለውን ፍለጋ ወደ አስመራ ስለመሄዱ አታውቅም፡፡ምናልባት አስቻለው ወደ ዲላ ባለመመለስ አቋሙ የፀና እንደሆነ፡ ወይም ጭራሽ ያልተገኘ እንደሆነ ደስታ በሽታ ሆኖ እንዳያሳቅቃት ሁኔታው ለእሷ
ድብቅ ነበር፡፡ በልሁ ቤተሰብ ሊጠይቅ ወደ ደብረ ብርሃን እንደ ሄደ ነው የተነገራት፡፡ እናም የበልሁን መምጣት የምትጠብቀው ከደብረ ብርሃን
እንደሚሆን አድርጋ ነው፡፡ ታፈሡን አናግራ ያስደነገጠቻትም ከዚሁ ጋር በተያያዘ ነው፡፡
ታፈሠዬ!ስትል ጠራቻት ሔዋን ትርክክ ባለ የከሰል ፍም ላይ
የተጣደ ድስት በረጅም ማማሳያ እያማሰለች፡፡
«ወዬ የኔ ወርቅ አለቻት ታፈሡ ወደ ሔዋን ዞር በማለት በዚያች
ሰዓት የሶፋ ጌጦች እያስተካከለች ነበር፡፡
«ዛሬ ሕልም አየሁ»
«ምን ዓይነት ሕልም ሔዩ?»
«በልሁ ከደብረ ብርሃን የመጣ ይመስለኛል፡፡ መንገድ ላይ ከረሜላ ገዝቶ ሲያላምጥ ቆይቶ ኖሮ ልክ እዚህ ሲደርስ የከረሜላዋን እላቂ ከአፉ
አውጥቶ ይሰጠኝ ይመስለኛል፡፡ ግን እጄ ላይ ሊያስቀምጣት ሲል ድንገት አምልጣኝ መሬት ላይ ትወድቅበታለች ብፈልጋትም አጣታለሁ፡፡ ወዲያው ደግሞ እኔም ያለሁበት ቦታ ይጠፋኛል፡፡» አለችና «ፍችው ምን ይሆን
ታፈሡዬ”? ስትል ጠየቀቻት፡፡
ኣ? አለች ታፈሡ ድንገት ሳታስበው፡፡ በሁለት እጆቿ ሽንጥና
ሽንጧን በመያዝ ቆማ ሔዋንን አተኩራ ታያት ጀመር፡፡
«መጥፎ ህልም ነው እንዴ ታፈሠዬ»
ለነገሩ የህልም ጥሩና መጥፎ የለውም፡ ህልም እንደ ፈቺው ነው ይባል የለ አለችና አሁንም ስሜቷን እፍን እድርጋ ወደ ሶፋ ማስጌጥ ስራዋ ተመለሰች፡፡
ግን ደግሞ ሃሳባ ሁለ ጥቅልል ብሎ ወደ ትናንት ምሽት ሁኔታዋ ነጎደ፡፡

የታፈሡ እንግዳሰው የትናንት ምሽት ሁኔታ የተለየ ነበር፡፡ ሰበቡ
በልሁ አስቻለውን ይዞ ዲላ ከተማ መግባቱ ነው:: በልሁ እስቻለውን ይዞ ከቀኑ ስምንት ሠዓት አካባቢ ዲላ እንደገባ በቀጥታ ወደ ታፈሡ ቤት ይዞት መሂድ አልፈለገም:: አማሆ ተብሎ በሚጠራው ሆቴል ውስጥ አሳረፈው፡፡ ለዚህ
ምክንያቱ አስቻለው አሁን በሚገኝበት ሁኔታ ላይ ሔዋን ብታየው ሊደርስባት
የሚችለውን የመንፈስ ስብራት በምን መልኩ መቀነስ እንደሚቻል ከታፈሡም ሆነ ከሌሎች ጋር መመካከር የሚያስችል ጊዜ ለመግዛት ነበር፡፡
በዚሁ መሠረት በዕለቱ ከአመሻሸ አስር ሰዓት አካባቢ ታፈሡ ወደ
ሆቴሉ ጎራ እንድትል በሚስጥር ላካባት፡፡ እሷም ጥሪውን ስትሰማ ከመደንገጧ የተነሳ ምን እንዳደረገች ሳይታወቃት የቤት ልብሷን እንደለበሰች፣ ነጠላ
ጫማዋን እንዳደረገች ብፌ ላይ ጣል አድርጋት የነበረች የአንገት ልብሷን ብድግ አድርጋ ነበር ወደ ሆቴሉ የበረረችው፡፡ 'ሰዎች ተጣልተው ድረሽልኝ ብለውኝ ነው' ብላ ባትናገር ኖሮ ያበደች መስሏቸው ሔዋንና ትርፌም
በተከተሏት ነበር፡፡ ብቻ ወደተነገራት ሆቴል ሮጣ ስትደርስ ወደ አልቤርጎው ማለፊያ አቅጣጫ እንኳ ጠፍቷት ነበር፡፡ በአመላካች እርዳታ እንደ ምንም
ገባች:: ፊትለፊት ወደ አልጋ ክፍሎች ስትመለከት በልሁ፣ መርዕድና የሃምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ከአንድ የአልቤርጎ ክፍል በር አጠገብ በረንዳ ላይ ቆመው አየች። እጅግ በሚያስገርም ጩኽት በልሁዪ !» ስትል ከርቀት ተጣራች።
ረጋ በይ ታፈሥ፡፡» አላት በልሁ ከአሯሯጧ በተጨማሪ የጥሪዋ
ድምፀት ውስጣዊ ስሜቷን አስረድቶት፡፡
ታፈሡ የበልሁን ማሳሰቢያ ከቁብ አልቆጠረችውም፡፡ ጆላላ የቤት ውስጥ ቀሚሷን ወደ ጉያዋ ሰብሰብ አድርጋ በመሮጥ ከመሀላቸው ጥልቅ አለች።
ወዲያው በበልሁ አንገት ወስጥ ተሸጉጣ ገና የአስቻለውን ሁኔታ ሳታውቀው በመባባት ስሜት ስቅስቅ ብላ ታለቅስ ጀመር።
«አይዞሽ ታፈሥ» አላት በልሁ እሱም ፊቱን በትከሻዋ ላይ እስደግፎ በእጁ ጀርባዋን እያሻሽ፡፡
«እናስ በልሁ?» አላችው ታፈሡ፡፡ የአስቻለውን ሁኔታ በድፍኑ
መጠየቋ ነው:: አሰቻለውን እገኘኸው? ይዘኸው መጣህ? ብሳ በዝርዝር ብትጠይቀው ምናልባት ምላሽ አሉታዊ ቢሆን ብላ ሰጋች፡፡
«እስቲ ነይ ወደ ውስጥ ግቢ፡፡ አለና በልሁ ወዳ አልቤርጎው ክፍል ፊቱን መልሶ ወደ ውስጥ ተራመደ፡፡ ታፈሡ ከፍርሀቷ የተነሳ በጥንቃቄ እርምጃ ከኋላው ተከተለችው፡፡ የሀምሣ አለቃ መኮንን ዳርጌና መርዕድም ወደ ክፍሉ ገቡ።
ታፈሡ ከክፍሉ ውስጥ ገብታ ወደ አልጋው ስትመለከት አንድ ሰው
ተኝቶ አየች፡፡ ከአንገቱ በታች ያለው ሰውነቱ አልጋው ላይ የሚታይ
አይመስልም፡፡ የድዱ ስጋ አልቆ ጥርሶቹ ገጥጠዋል፡፡ የፊቱ ላይ አጥንቶችም እንደዚሁ፡፡ ዓይኖቹ እንባ አቅረው ሲያዩዋት አየች፡፡ የግራ ፊቱ ጠባሳ ያ የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ የገለጸውን መልክ ያንፀባርቃል፡፡ ታፈሡ ያ ሰው
አስቻለው ስለመሆኑ ማመን ቢያዳግታትም በተለይ የፊቱ ጠባሳ፣ የግራ ዓይኑ
ልትጠፋ የደረሰች መሆኗ፣ የግራ ጆሮው ልጣፊ ስጋ መስሳ መታየቷና ከራስጌው በኩል ግድግዳ ተደግፎ የቆመ ክራንች መታየቱ የግዷን እንድትቀበለው አደረጋት፡፡ ብቻ አሁንም ጨርሳ ላለማመኗ ምስክር የሚሆን
👍8
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_ሦስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....አስቻለውን የማገናኛውም ቀን ተወሰነ በማግስቱ ሰዓቱ ደግሞ ምግብ ተሰራርቶ ካለቀ በኋላ ወደ ሰባት ወይም ስምንት አካባቢ፡፡ በሚገናኙም ጊዜ የሔዋንን ልቦና ማደነጋገሪያ ዘዴ ተፈጠረ ከዚህ በኋላ ነበር ታፈሡ ወደ አስራ ሁለት ሰአት አካባቢ ወደ ቤቷ የተመለሰችው.

የዛሬው የድግስ ሽርጉድም የዚሁ ዕቅድና ፕሮግራም እንዱ አካል
መሆኑ ነው የሔዋን ህልም ግን የታፈሡን ልብ የባሰ አሸበረውና በባሰ ስጋት ውስጥ ገባች ይቺ ልጅ የዋህ ናትና አምላኳ ምን እየነገራት ይሆን? በማለት፡፡
ያም ሆኖ የድግሱ ስራ ቀጠለ፡፡ በያይነቱ ተካፋፍለው ይሰሯቸው የነበሩ የወጥ ዓይነቶች ሁሉ ደረሰ ቤት ተወለወለ፡፡ ተስተካከለ፡፡ ጊዜውም ደረሰ፡፡ ልክ ከቀኑ ሰባት ሠዓት ተኩል፡፡
የሚመጡትን እንግዶች በውል የምታውቅ ታፈሡ ብቻ ናት፡፡ ትርፌም ዋናው እንግዳ አስቻለው መሆኑን ታውቃለች፡ ታፈሠ ትናንት ማታ በሆነ ሰበብ ወደ ውጭ ጠርታ ለሔዋን ፍንጭ እንዳትሰጥ አስጠንቅቃ የአስቻለውን መምጣት በጆሮዋ ሽክ ብላታለችና፡፡ ሔዋን ግን ምንም ዓይነት ፍንጭ አልነበራትም፡፡ እሷ የምትጠብቀው የማታውቃቸውን የታፈሡን እንግዶች ብቻ ነው። ነገር ግን በዚያ ሠዓት ይመጣል ብላ ያላሰበችው ነው፡፡ ነገር ግን
ድንገት ከሁሉም ቀድማ ዓይኗን ወደ ውጭ በር ጣል ስታደርግ
የምታውቀውና የምትናፍቀው
ነገር ግን በዛ ሰዓት ይመጣል ብላ ያላሰበችው እንግዳ ብቅ ሲል አየችው።በልሁ ቡላማ ሱሪ በነጭና ሰማያዊ ቡራቡሬ
ሽሚዝ ለብሶ ነጣ ያለ ጃኬቱን ትከሻው ላይ አንጠልጥሎ
በፍጥነት ርምጃ እየገሰገሰ ወደ ታፈሡ ቤት መጣ፡፡
«እንዴ! ታፈሠዬ! ባልሁዩ መጣ!» አለች ሔዋን በልሁን ፍልቅቀቅ ብላ
እያየችና ጆርዋን እነታፈሡ ለሚሰጧት መልስ አቁማ::
«መጣ?» ብላ ታፈሡ ቶሎ ብላ ወደ በሩ በመራመድ ላይ ሳለች በልሁ ወዲያው ከች አለ።
«ታዲያስ! እንደምናችሁ?» እያለ እንደ አዲስ ሊስማት ወደ ታፈሡ
ተጠጋ::
«እንኳን ደህና መጣህ በልሁዬ?» አለች ታፈሡም አንገቱን እቅፍ
አድርጋ እየሳመችው፡፡
«ሔዩ?» አለ በልሁ ወደ ሔዋን እየተመለሰ::
«አቤት በልሀዬ!»
ደጋግመው ተሳሳሙ:: በልሁ ልክ እንደ ታፈሡና ሔዋን ትርፌንም
ከሳማት በኋላ ወዲያው ንግግር ጀመረ፡፡ የሮጠና የቸኮለም ይመስል እንደ ማለክለክ ይቃጣዋል፡፡ «እንዴት ነው፣ አዲስ ስሜት አይነበብብኝም?»
«ይመስላል፡፡ ግን ምንድነው?» አለችው ታፈሡ ዓይኖቿ በፍርሀት
እየተርገበገቡና ልቧ ከወትሮው እጥፍ እየመታ»
«አስመራ ደርሼ መጣሁ፡፡»
«እ» አለች ታፈሡ የደነገጠች መስላ ለመታየት እየሞከረች፡፡
«አስቻለውን እግኝቼ ይዤው መጣሁ፡፡»
በልሁና ታፈሡ እርስ በርስ የሚተያዩ ይምሰሉ እንጂ በዓይናቸው ሰረቅ እያረጉ በማየት የሚሰልሉት የሔዋንን ስሜት ነው::
ሔዋን የበልሁን
አስቻለውን እግኝቼ ያዤው መጣሁ የሚል ቃል ስትሰማ ልከ ሳያስብ
ሳይጠረጥር በኃይለኛ ጥፊ ድንገት ጆሮውን እንደተመታ ሰው ሰማይና ምድሩ ተቀላቀለባት፡፡ ዓይኗ ፈጠጠ፡፡ ጥርሷ ገጠጠ፡፡ አፏም ያለ ፍላጎቷ ቧ ብሎ
ተከፈተ፡፡ በአጠቃላይ የአንጎሏ የማሰብ ሥርዓት ተዛባ፡፡ በድን ሆነች፡፡
በልሁ ለጥያቄ ፋታ በማይሰጥ ፍጥነት ቶሎ ቶሎ ይናገር ጀመር ግን አንድ ነገር ልንገራችሁ
አስቻለው በድንገተኛ አደጋ ምክንያት አንዳንድ የአካል ጉዳቶች ደርሰውበታል፡፡ በእጅና በእግሩ ላይ የፕላስቲክ ልጣፎች
ይታያሉ፡፡ ለጊዜው የሚሄደውም በክራንች ነው፡፡ ፊቱም ላይ ትንሽ
ተጎድቷል:: ነገር ግን የፕላስቲክ ቆዶ ጥገና በተባለ የህክምና ጥበብ በአጭር ጊዜና በአስተማማኝ ሁኔታ ሁሉም ነገር ወደነበረበት ሁኔታ እንደሚመለስ
ሀኪሞች አረጋግጠውልናል፡፡ አለና አሁንም ፈጥኖ በመቀጠል «ልብ በሉ! በዚሁ የህክምና ጥበብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ህክምናውን በተሟላ የሰውነት ስጋ ላይ ማድረግ ስለማይቻል አስቻለው በጣም በጣም እንዲከሳ ተደርጓል፡ለህይወት ማቆያ ብቻ እንጂ በቂ ምግብ አይወስድም፡፡ የመክሳቱም ምክንያት ይኸው ብቻ ነው፡፡ ከስቶ ስታዩት ሌላ ነገር መስሏችሁ እንዳትደነግጡ፡፡ እሺ!»
ፊቱን ወደ ውጭ በር መለስ ሲያደርግ አስቻለውና አጃቢዎቹ
ተከታትለው ብቅ ሲሉ አያቸው፡፡ ወዲያው ደግሞ «ያው አስቻለው እየመጣ ነው፡፡ ወጣ በሉና በእልልታ ተቀበሉት፡ : » አላቸው፡፡
በእርግጥም ሰዎች አስቻለውን አጅበው ከውጭ በር ላይ ደርሰዋል፡፡
ታፈሡና ትርፌ እልልታውን እያቀለጡ ወደ እንግዶቹ ሮጡ፡፡ ሔዋን ግን ከቆመችበት ንቅንቅ አላለችም፡፡ እንደ እንጨት ደርቃ ቀረች፡፡ በልሁ ከተናገረው ቃል እንዱንም አልተረዳችም፡፡ ቀድሞ ነገር ጆሮዋ እንኳ ስለመስማቱ ማንም እርግጠኛ አይደለም፡፡
«ሔዩ» ሲል ጠራት በልሁ ሁኔታዋን ተጠራጥሮት ለመሰለል ያህል፡፡ሔዋን ልክ እንደ አእምሮ ዘገምተኛ ሰው የቴለና የጀለ በሚመስል ድምጽ «እ» አለችው በደመ ነፍስ፡፡
ብቅ ብለሽ አስቻለውን አትቀበይውም እንዴ?»
ሔዋን ግን አሁንም ዝም፡፡ በልሁ ራሱ ክንዷን ያዝ አድርጎ የመጎተት
ያሀል ወስዶ በር ላይ ቢያደርሳትም ከዚያ ማለፍ አልቻለችም፡፡ እንዲያውም
የቤቱን በር የግራ በኩል መቃን ሙጥኝ አለች፡፡ ዓይኗ ከውጭ ከሚመጡት ሰዎች ላይ አልተነቀለም፡፡ ታፈሡና ትርፌ አስቻለውን በመሳም ላይ ናቸው፡፡
ነገር ግን ምን እየተደረገ እንዳለ ለሔዋን አይታዉቃትም፡፡ የአስቻለው አጃቢዎች ካሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌና መርዕድ ሌላ ሦስት የቀድሞ የስራ
ባልደረቦቹ ናቸው ከአስቻለው ጋር
ስድስት ታፈሡና ትርፌ ሴጨመሩ
ስምንት ሆነዋል፡፡ ለሔዋን ግን የሰዎቹ ብዛት አንድ ከተማ ነዋሪ
በሙሉ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣ
መስሎ ነው የሚታያት ሰዎች ስለመሆናቸው እንኳን በውል አይታወቃትም በሰመመን ውስጥ
የሚታይ የአንዳች ፍጡራን
ትርምስምር መሰለዠሎ እንጂ፡፡ በህልም ይሁን በእውን ባለየላት ሁኔታ ሰው ሊመስላት ያልቻለ አንድ ፍጡር በክራንች የሚጎተት መስሎ ይታያታል ጤነኛው እግሩ እንኳ በውል እግር አይመስልም፡ ሱሪው ብቻ ይወዛወዛል፡፡
የፈቱም አጠቃላይ ገፅታ አስፈሪ ጭምብል ያጠለቀ መሰላት ሰው ስለመሆኑ እንኳ እርግጠኛ ሳትሆን
አስቻለው አጠገቧ ደረሰ።
«ሔዩ» አላት አስቻለው ከጤነኛውም ከጉዳተኛውም ዓይኖቹ እንባውን እያፈሰሰ፡፡ ለሔዋን ግን ድምጹ እንኳ የሰው አልመሰላትም፡፡ ስልል ያለና
በጣም የደከመ ነው፡፡ መልስ ሳትሰጠው ፍጥጥ ብላ ብቻ ትመለከተው ጀመር፡፡
«አላወቅሽኝም ሔዩ?»
«ሔዋን አሁንም ዝም፡፡»
«ሳሚው እንጂ ሔዩ!» አለች ታፈሡ አስቻለውን ደገፍ አድርጋ ከጎኑ በመቆም በአሁን ሠአት ከታፈሡ በኩል ለቅሶ የለም። በሔዋን አኳሀን ደንግጣ ሁለመናዋ ደርቋል፡፡ በልሁም ሆነ ሌሎቹ በትኩረት የሚከታተሉት
የሔዋንን ስሜት ነው፡፡ ያሰጋቸውም የልብ ህመምተኛ መሆኗ ነው፡፡
ሔዋን አሁንም በዚያ በተረበሽ ስሜት ውስጥ ሆኗ ልትገደል የተከበበች አውሬ ይመስል ዓይኗን በሁሉም ላይ ከማንከራተት በስተቀር ምላሽ መስጠት አልቻለችም አስቻለው ራሱ «ቀድም የፈራሁት ይሄን ነበር
ዘመዶቼ! አለና እያለቀሰ ፈቱን በሔዋን ትክሻ ላይ አሳረፈው፡፡ እዚያው ላይ ተደፍቶ ይንሰቀሰቅ ጀመር፡፡
👍7
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....በቀድሞው የዲላ ከተማ አውቶብስ መናኸሪያ ፊትለፊት በግምት በሀምሳ ሜትሮች ርቆ ከታች በስተምዕራብ በኩል የሚገኘው «አባይ ፏፏቴ ሆቴል በዕለተ እሁድ ምሽት ለዘወትር ደንበኞች ዝግ ሆኖ ለየት ያሉ እንግዶች ሊስተናገዱበት ተዘጋጅቷል፡፡ ለክብር እንግዶች የተዘጋጀው መድረክ የተለያዩ
ቀለማት ባሏችው መብራቶች አጊጧል፡፡የድግሱ ታዳሚዎች ከመድረኩ ፊትለፊት በተዘጋጀላቸው ወንበርና ጠረጴዛ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ከታዳሚዎቹ
መሀል የሚበዙት የፖሊስ ሰራዊት አባላት ናቸው። መለዮ የለበሱት
ይበልጣሉ፡፡ ጠረጴዛዎቻቸው በነጭ ጨርቅና በላስቲክ ተሸፍነው ያልተከፈቱ
የቢራ ጠርሙሶች ተደርድረውባቸዋል አስተናጋጆች የመስተንግዶ ስራቸውን
ለማከናወን ጥግ ጥግ ይዘዋል:: በትላልቅ ድምጽ ማጉያዎች የሚለቀቀው ሙዚቃ አዳራሹን ያነቃንቀዋል፡፡ የድግሱ ታዳሚዎች ፊትለፊት በመድረኩ
ላይ የተዘረጋውን ልዩ ሶፋ እየተመለከቱ የክብር እንግዶችን ይጠባበቃሉ፡፡ልክ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሠዓት ተኩል ላይ
ሙዚቃው ድንገት ቆመ:: በሙዚቃው ጩኸት ውስጥ እየተጨዋወቱ ይሳሳቁ የነበሩ እንግዶች ዝም ዝም አሉ፡፡ ቤቱ ፀጥ ረጭ አለ፡፡ ወዲያው አንድ የዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሳይሆን የማይቀር ጠየም ያለ ልጅ እግር ሰው ከሆቴሉ ጓዳ በኩል ወጥቶ ወደ መድረኩ ወጣ።
«እንዴት ዋላችሁ እንግዶቻችን?» አለ ፈገግ ባለ ሁኔታ እጆቹን
እያፍተለተለና በሆቴሉ ውስጥ የታደሙ እንግዶችን በሙሉ በዓይኑ እየቃኘ፡፡
«እግዚአብሔር ይመስገን!» የሚል ምላሽ ተሰጠው ከታዳሚዎቹ፡፡
«በቅድሚያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ጊዜያችሁን መስዋት አድርጋችሁ በዚች ሰዓትና ቦታ ስለተገኛችሁልን በዕለቱ የክብር እንግዳና በዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ ስም ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡»
ከታዳሚዎቹ በኩል ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተቀበለው::
«አመሰግናለሁ፡፡» አለና «ዛሬ በዚች ሠዓትና ቦታ የመገናኘታችን
ዓላማ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሰዎች በአንድ ወይም በሌላ አጋጣሚ ይተዋወቃሉ:: የትውውቁ መሰረት በአንድ አካባቢ መኖር፡ የስራ
ባህሪና ቦታ፣ ወይም ሌላ ሌላም ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን መተዋወቅና መግባባት ወይም መዋደድ እንዳለ ሁሉ በሆነ አጋጣሚ መለያየትም ይኖራል፡፡
የመለያያው መንገድና ዓይነትም እንደዚሁ ብዙ ነው፡፡ በጠብና በጥላቻ፣ በሞት በስራ ዝውውር... ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ በአጠቃላይ በደስታም በሀዘንም
የተዋወቁና የተዋደዱ ሰዎች ሊለያዩ ይችላሉ::
«ዛሬ ልናከብረው የተዘጋጀነው የመለያየት በዓል ግን የሰላምና የደስታ ነው፡፡ አንድ የስራ ባልደረባችን ዕድገትና ሹመት አግኝቶ ከመካከላችን
በመለየት ወደ ሌላ አካባቢ ሊሄድ ስለመሆኑ ሁላችንም እናውቃለንና እስቲ ስለወንድማችን ደስታ መግለጫ ይሆን ዘንድ ሁላችንም እንዴ እናጨብጭብ»
ሲል በፈገግታ ዓይን እያየ ታዳሚዎቹን ጠየቃቸው።
አሁንም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተቀበለው::
“አመሰግናለሁ፡፡ ከዚህ ቀጥሉ የክብር እንግዳችን ከቅርብ ዘመድ
ወዳጆች ጋር በመሆን እየመጣ ስለሆነ ወደ መድረኩ በሚያልፍበት ሰዓት ሁላችንም ከተቀመጥንበት ብድግ በማለት በጭብጨባ እንድንቀበለው እያሳሰብኩ በኔ በኩል የመክፈቻ ንግግሬን እዚህ ላይ አበቃለሁ፡፡አመሰግናለሁ፡፡» በማለት እጅ ነስቶ ወደ መጣበት አቅጣጫ ተመለሰ፡፡
የድግሱ ታዳሚዎች የክብር እንግዳውን በዓይናቸው የሚጠብቁት ከውጭ በር በኩል ነበር፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በዚያ የመክፈቻ
ንግግር ባደረገው ሰው እየተመራ ከወደ ጓዳ በኩል ድንገት ብቅ አለ፡፡ የክብር እንግዳው የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ነው፡፡ የምክትል መቶ አለቅነትና
የወላይታ አውራጃ ፖሊስ አዛዥነት ሹመት እግኝቶ ሊሄድ ነው፡፡ ድግሱም እሱኑ ለመሸኘት ነው።
የቀድሞው የሀምሳ አለቃ፡ ዛሬ ግን የምክትል መቶ አለቅነት ማዕረጉን
መለዮ ለብሶ ከአስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢው ኋላ ተከትሎ ብቅ ሲል ታዳሚዎች በሙሉ ከተቀመጡበት ብድግ በማለት በማያቋርጥ ጭብጨባ ተቀበሉት፡፡
ከእሱ ኋላ ነጫጭ የሀገር ልብሷን ለብሳ እንቁጣጣሽ የመሰለችው ታፈሡ እንግዳሰው! ቀጥላ ሔዋን: ከእሷ ኋላ ደግሞ መርዕድ እሽቱ በመሆን ተከታተሉ፡፡ ሁሉም ለታዳሚዎች የጭብጨባ አቀባበል እጅ እየነሱ ወደ
መድረኩ አመሩ፡፡ ምክትል የመቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ እና ታፈሡ ጎን ለጎን እንዲሁም ሔዋን ከታፈሡ ቀኝ በኩል፣ መርዕድ ደግሞ ከምክትል መቶ አለቃ
መኮንን ዳርጌ ግራ ጎን በመቆም ታዳሚዎች እንዲቀመጡ ጋበዙ፡፡ ታዳሚዎች ጭብጨባቸውን አቁመው ሲቀመጡ የክብር እንግዶችም በየቆሙበት አቅጣጫ ተቀመጡ፡፡ ሙዚቃው ተለቀቀ፡፡ አስተናጋጆችና የድግሱ አስተባባሪዎች በታዳሚዎች ፊት ተቀምጠው የነበሩ ጠርሙሶችን መክፈት ጀመሩ፡፡ መስተንግዶው ጦፈ፡፡
በርካታ የድግሱ ታዳሚዎች ታፈሡንና መርዕድን በከተማ ውስጥ ያውቋቸዋል፡፡ ሔዋንን ግን እንኳንስ በውል የሚያውቃት በዓይኑም ዓይቷት የሚያውቅ ስለመሆኑ ኣንድም ታዳሚ እርግጠኛ አልነበረም፡፡ ከሁሉም በላይ ታዳሚዎቹን ያስደነቃቸው በምን ምክንያትና ሰበብ ታፈሡና መርዕድ የምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ የቅርብ ዘመድ ወዳጆች ሊሆኑ እንደቻሉ
ነው፡፡ ያም ሆኖ ሁሉም በየሆዳቸው 'ወይ ጉድ! የሰው ዘሩና የግንኙነት መስመሩ እኮ አይታወቅም በማለት በግርምት አለፉት፡፡
የግብዣው ሥነ-ሥርዓት ቀጠለና በምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ ቀዳሚነት፡ በእነታፈሡ ቀጣይነት የብፌ ምግብ መነሳት ጀመረ፡፡ ታዳሚዎችም
በየአቀማመጥ ቅደም ተከተላቸው ተከታትለው ምግብ አነሱ፡፡ እራት መበላት ተጀመረ፡፡ የመጠጡ ግብዣም ተከታተለ፡፡ ምግብ ተበልቶ አብቅቶ፡ ሳህኖች
ከየጠረጴዛው ላይ ተነስተው: ጠረጴዛዎች በአስተናጋጆች ተወልውለው ካበቁ በኋላ መጠጡ ጭውውቱና የመዚቃው ጩኸት በቀጠለበት ሰዓት አሁንም
ለሁለተኛ ጊዜ ሙዚቃው ድንገት ቆመ፡፡ የታዳሚዎችም ወሬና ጫጫታ ወድያው ቆመና አዳራሹ ፀጥ ረጭ አለ ሰዓቱ በግምት ከምሽቱ ሁለት ተኩል አካባቢ ይሆናል፡፡ አሁንም ያ የመክፈቻ ንግግር ያደረገው ሰው ወደ መድረኩ ሲራመድ ታየ፡፡ ቀድሞ እንዳደረገው ሁለ ከታዳሚዎች ፊትለፊት በመቆም ታዴሚዎችን በፈገግታ እያየ።
«የተከበራችሁ እንግዶቻችን» ሲል ጀመረ፡፡ «ቀደም ሲል በመክፈቻ
ንግግሬ ላይ እንደጠቀስኩት የዛሬው ጉዳያችን የስራ ባልደረባችን የሆነው የቀድሞው የሃምሳ አለቃ ዛሬ ደግሞ...» እያለ ንግግሩን ጎተት በማድረግ ወደ
ኋላው ዞሮ ምክትል መቶ አለቃን ሳቅ እያለ ሲያይ ታዳሚውም ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌና እነታፈሡም ሳቁ።
«አፍሬም ፈርቼም ነው እኮ» አለ በመቀለድ ዓይነት::
ሳቅና ጭብጨባ ከታዳሚዎች ተቸረው፡፡
«አመስግናለሁ።» ብሎ እጅ ከነሳ በኋላ «በቀጣይ ሁለት ፕሮግራሞች አሉን፡፡ በመጀመሪያ የምንወደውና የምናከብረው ጓደኛችንና የስራ ባልደረባችን
ከመካከላችን ተለይቶ ሲሄድ ማስታወሻችን ያደርጋት ዘንድ ያዘጋጀንለትን ስጦታ ማበርከትና ከዚያ ቀጥሎም ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ ስለ አግኘው
የማዕረግ ዕድገትና ሹመት እንዲሁም ከእኛ ከወዳጆቹ በመለየቱ ያደረበትን ስሜት አጠር ባለ ሁኔታ የሚገለጽበት ፕሮግራሞች ናቸው። በዚሁ ቅደም ተከተል ማከናወን እንዲቻል የአውራጃችን ፖሊስ አዛዥ የሆኑት መቶ አለቃ ብዙአየሁ አስራት ስጦታዋን እንዲያበረክቱልንና ምክትል መቶ አለቃም ወደ መድረኩ ጫፍ ቀረብ ብሎ እንዲቀበልልን ሁለቱንም እጋብዛለሁ። አመሰግናለሁ፡፡» ብሎ ከመድረኩ ወረደ።
👍113🔥1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....«ታፈሡና ሔዋን የሚባሉ ካሉ በአስቸኳይ ቤት ድረስ ይምጡ። የሚል መልዕክተኛ መጥቶ ነው።» አለው፡፡
ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ መልዕክቱን እንደሰማ ወደነታፈሡ ዞር ብሎ ሲያይ ለካ የተነገረውን መልዕክት እነሱም ሰምተውት ኖሮ አቆብቁበው እያዩት ኖሯል። «ምንድነው ሃምሳ አለቃ?» በማለት ታፈሡ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነሳች፡፡ ከመደንገጧ ብዛት የቀድሞውን ሃምሳ አለቃ በቀድሞ ማዕረጉ ጠራችው።
«በአስቸኳይ ቤት ድረስ ኑ ተብለዋል ይላል።» አላት ራሱም የድንጋጤ ስሜት እየተነበበበት፡፡
«ኧረ ፍጠኑ ብለዋችኋል!» አለ መልዕክተኛው።
ታፈሡ፣ሔዋንና መርዕድ የምክትል መቶ አለቃውንም ሆነ የድግሱ
ታዳሚዎችን ፈቃድ መጠየቅ የሚያስችል ፋታ እና ጊዜ እላገኙም። በታፈሡ መሪነት የእሽቅድምድም ያህል ተከታትለው ከአዳራሹም ወጡና ወደ ታፈሡ ቤት ሮጡ።
በዚህ ጊዜ የደግሱ ድባብ ፍፁም ተለወጠ፡፡ ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ ራሱ ግራ ገብቶት በአለበት ቆሞ ቀረ። ታዳሚዎችም አንዴ በር በሩን ሌላ ጊዜ ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌን በመመልከት ዓይናቸው ይንከራተት ጀመር፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን ጥቂት ፖሊሶች ወደ ታፈሠ ቢት ሄደዉ
የሆነውን ነገር እንዲያጣሩ ታዘዙና የእነታፈሡን ዱካ ተከትለው ገሰገሱ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በዕሰተ ረቡዕ ከማለዳ ጀምር የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ቀውጢ ሆኗል። ሰበቡ የመኪና አደጋ ነው። አንዲት በተለምዶ ውይይት በመባል የምትታወቅ ታክሲ በርካታ
የመድሐኒዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አሳፍራ ከትምህርት ቤቱ በር ላይ በመድረስ ቁማ በማራገፍ ላይ ሳለች አንድ የፍሬን ችግር የነበረበት የከተማ አውቶብስ ከታክሲዋ ላይ በመውረድ ላይ የነበሩ ተማሪዎችን ጨፍልቃቸው ነው። በርካታ ሞተዋል፡፡ ሌሎች ፣ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአደጋ ተረፉ የሚባሉ ተሳፋሪዎች
ብዙ አልነበሩም ከተማሪዎቹ በተጨማሪ ሌሎች መንገደኞችም የሞትና የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የሞቱትም ሆኑ የቆሰሉት ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ነው የተወሰዱት። ይህ አደጋ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት አካባቢ ደርሶ እረፈድ እያለ ሲሄድ ደግሞ የአደጋ ሰለባዎች ዘመድ አዝማድ ከቦታው እየደረሱ የሆስፒታሉን ቅጥር ግቢ በለቅሶ በእሪታና በጩኸት እያደበላለቁ የጨበጣ ውጊያ የሚካሄድበት ጦር ሜዳ አስመስለውት አርፍደዋል። ሕይወታቸው ያላለፈ የአደጋው ሰለባዎች የስቃይ ጩህት ከቤተሰቦቻቸው ኡኡታ ጋር ተላምዶ ያ ግቢ ግባተመሬት የሚፈፀምበት የመቃብር ቦታ መስሏል፡፡ የሆስፒታሉ ሐኪሞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ስራ በዝቶባቸው የሚይዙትን የሚጨብጡትን አተው ተዋክበዋል። ቀደም ሲል አልጋ ይዘው ይታከሙ ህሙማን ጨርሶ ተረስተዋል ችግሩ ለአስታማሚዎች ተርፎ እነሱም በጭንቀት ወለሌ ይላሉ።
ከዚህ ችግር ተካፋይ አንዱ በልሁ ተገኔ ነው አስቻለው ደሞ ከሰሞኑ ጀምሮ ህመሙ ፀንቶበት ሰንብቷል በዚያው ልክ በልሁ አጠገቡ በመቆም የሚንከራተቱ የአስቻለውን አይኖች አከታትሎ ማየት የዘወትር ስራው ሆኗል። ሀኪም አይቶት በወጣ ቁጥር ለውጥ ያመጣለት እየመሰለው ቢጓጓም ነገር ግን የአስቻለው ሁኔታ ከዕለት ወደ እለት እያስፈራው ሄዷል።
አደጋው በደረሰበት እለትም የአስቻለው ነፍስና የበልሁ ዓይኖች ተፋጠው አረፈዱ ወትሮም እንደሚያርገው ሁሉ አሰሰቻለው በተኛበት አልጋ አጠገብ ቆሞ ቁልቁል እየተመለከተው ሳለ ከኮሪደር አካባቢ ድንገተኛ ጩህት ተሰማ ቀአደጋው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት የነበረች ልጅ ብዙም ሳትቆይ ህይወቷ አልፎ ኖሯል።ህልፈቷ የተነገራቸው ዘመዶቿ በዚያው አስቻለው በተኛበት ክፍል በር አካባቢ ጩህታቸውን ይለቃሉ የሟች ስም 'ሔለን' ኗሯል አልቃሹም " ሔለን ሔለንዬ ሔሉ" እያሉ ይጯጯሁ ጀመር።
ይህን የለቅሶ ጩኸትና የማቿን ስም እስቻለው በሰመመን ውስጥ ሆኖ ሰምቶት ኖሯል። በልሁ ጠጋ ብሎ እጁን እንዲያዘው ጠቀስው፡፡ በልሁ ጠጋ እንዳለት አስቻለው እጁን ያዝ አደረገና፡-
ሔዋን ምን ሆና ሞተች በልሁ?» ሲል ዓይኑን እያንከራተተ ጠየቀው።
«ምን?» አለ በልሁ ድንግጥ በማለት፡ ስለየትኛዋ ሔዋን ነው
የምታወራው አስቻለው?» ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡
አስቻለው ልክ እንደ ጃጀ ሽማግሌ የበልሁን እጀ ጥብቅ አድርጎ በመያዝ ዓይኖቹን እያንከራተተ አትዋሸኝ በልሁ ሔዋን ሞታለች።» አለው።
በልሁ የባስ ተረበሸ፡፡ እሱ በጤናማ ስሜቱ የማቿ ስም ሔለን ስሰመሆኑ እርግጠኛ ቢሆንም ለእስቻለው ግን «ሔዋን የተባለ እንደሚመስለው ሲረዳ ስለ
አስቻለው የእሱ መንፈስ ተሰቃየ። ግን ብቻ ያስተማመንኩ መስሎት
«ሔዋን እኮ በአሁኑ ሠዓት ያለችው ዲላ ነው። ለሃምሳ አለቃ መኮንን
ዳርጌ ሽኝት እንደ ሄደች ገና አልመጣችም። ምናልባት ዛሬ ወደ ማታ ላይ ትመጣና ታያታለህ። አሁን የሚያለቅሱት ሰዎች ሔለን የምትባል ልጅ ሞታባቸው ነው።
ሔዋን አይደለም የሚሉት፡፡ አለው በማከታተልና ሽብር በተቀላቀለበት አነጋገር።

አስቻለው የበልሁን ንግግር ከቁብ አልቆጠረውም። ምናልባትም በትክክል እየሰማው ላይሆን ይችላል። የራሱን ንግግር ብቻ ቀጠለ።
«እኔንም እሷ በተቀበረችበት ቤተክርስቲያንና መቃብር ውስጥ ቅበሩኝ፡»
«ቀድሞ እሷ መች ሞተች?»
አስቻለው አሁንም የራሱን ቀጠለ። «በመቃብራችን ላይ እኛ በከንቱ
ሞተናል፥ እናንተ ግን አደራ ብለህ ፃፍበት፡»አለው የበልሁን እጅ ጭምድድ አድርጎ እንደያዘ፡፡
የበልሁ ጭንቀት ከመጨረሻው ጫፍ ላይ ደረሰ፡፡ ከአስቻለው ጋር መነጋገሩ ዋጋ እንደሌለው አመነ፡፡ ቢሆንም ባይሆን ሐኪም መጥራት እንዳለብት ታየው፡፡
እጁን ከአስቻለው እጅ ውስጥ እንደምንም ፈልቅቶ አላቀቀና በፍጥነት በሩን ከፍቶ ወጣ።
ከነርሶቹ ክፍል በር ላይ እንደደረሰ አስቻለውና በአካባቢው የተኙ
ህሙማንን የምትከታተለዋ ነርስ ከውስጥ ወደ ውጭ ስትወጣ አገኛት። የተለያዩ መድሐኒቶችን ይዛ ወደ ድንገተኛ ክፍል በመሄድ ላይ ነበረች።
«እመቤት ልጁ እኮ ደከመብኝ» አላት በልሁ ትንፋሹ በርክቶ እያለከለከ።
ነርሷን ሲስተር ብሎ መጥራት ሲገባው እመቤት ማለቱ መለማመጡና በአክብሮት
ማሳየቱ ነበር።
«ከወትሮው የተለየ ምን ለውጥ አየህበት» ስትል ነርሶም ከእርምጃዋ ቆም ብላ ጠየቀችው። የበልሁ ሁኔታ ትኩረቷን ስቦታል።
«ይቃዥ ጀመር»
«ምን እያለ?»
«ዝም ብሎ የሆነ ያልሆነውን»
«እስቲ ቆይ! ይህን መድሀኒት ድንገተኛ ክፍል ላድርስና መጥቼ አየዋለሁ።» ብላው ወደ ድንገተኛ ክፍል ለመሄድ ከፎቅ ወደ ምድር ቤት ወረደች።
በልሁ ከስጋቱና ከፍርሀቱ የተነሳ ነርሷን ሊያምናት አልቻለም። እድራሻዋ እንዳይጠፋበት ለመከታተል ተከትሏት ወረደ። የገባችበትን ክፍል አረጋግጦ
እስከምትመለስ ድረስ እዚያው በገባችበት ክፍል በር ላይ ቆሞ ይጠብቃት ጀመር፡፡
ነርሷ በዚያ በድንተኛ ክፍል ውስጥ ብዙ አልቆየችም፡፡ መድኒቶችን አድርሳ ከክፍሉ ወጣች። በሩ ላይ በልሁን ስታገኘው ስሜቱ ገብቷት ፈገግ
አለችና «የምቀር መስሎህ ነው አይደል» አለችው
👍7
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....የኑዛዜውን ምስጢር እንዳገኘው ሁሉ የልብ እይታ
ተሰማው በረጅሞ ተንፍሶ ራሱን ወዘወዘ።
ወዲያው የሰው ኮቴ ተሰማው፡፡ ወደ አስቻለው ክፍል ዞር ብሎ ሲመለከት ሁለቱ ዶክተሮች ተከታትለው ሲወጡ አየ፡፡ ምን ሊሉት እንደሚችሉ በመጓጓት ትኩር ብሎ ሲመለከታቸው ያ የአስቸለው ዶክተር በእጁ ጠቀስ አደረገውና በልሁም ጠጋ ብሎ- ጆርውን ሲሰጠው «አይዞህ ደህና ነው፡፡» በተረፈ ነርሷ የምትሰጥህን ትዕዛዝ ተቀበል፡፡ ብሎት ወደ ቢሮው አመራ። በልሁ ከነርሷ የሚሰጠውን ትዕዛዝ
ለመስማት ጓጉቶ ከክፍሉ የምትወጣበትን ጊዜ በመጠባበቅ ላይ ሳለ ነርሷ ወዲያው ወጣች፡፡ በሩን መልሳ ዘጋችና እንዲያውም ቆለፈችው፡፡ በልሁ ወደ እሷ ሊራመድ ማሰቡን አውቃ “እዚያው ጠብቀኝ፡፡ አለችው፡፡
በልሁ ቀጥ ብላ ቆመ። ዓይኖቹ ግን በነርሷ ላይ ትክል አሉ። ልቡ
ደንገጥ አለና ከንፈሮቹን በምላሱ ያርስ ጀመር፡፡ ነርሷ ግን ወደ በልሁ ስትጠጋ ፈገግ ብላ ነው፡፡ በዚያው ፈገግታ በተላበሰ ሁኔታዋ የበለጠ ጠጋ አለችውና፡
«ደነገጥክ እንዴ?» ስትል ጠየቀችው።
«ፈራሁ»
«አይዞህ! ምንም አይለው። አሁን አንድ ለየት ያለ መድሐኒት
ሰጥተነዋል። መድሐኒቱ ግን የህመምተኛውን እንቅስቃሴና የትኩረት መለዋወጥ
አይፈልግም። ቢያንስ ለግማሽ ሰዓት ዕረፍትና የሀሳብ መረጋጋትን ይጠይቃል።ስለዚህ እንተም እንዳትገባ ብዬ በሩን ቆልፈዋለሁ፡፡ እኔ እስከምጠራህ ድረስ ዘወር
ዘወር እያልክ ራስህን አዝናና። እንዲያውም እታች ወርደህ ወደ ክበብ አረፍ ብትል ጥሩ ነው፡፡ እኔም ስፈልግህ በቀላሉ አገኝሀለሁ፡፡» አለችው ረጋ ባለ መንፈስ::
በልሁ አሁንም በረጅሙ ተነፈሰ፡ ምራቁንም ዋጥ አደረገ። የነርሷን
ትዕዛዝ መቀበል እንዳለበት ከዶክተሩም ተነግሮታል። የነርሷም አነጋገር ለዛ የተላበሰ ነው፡፡ ነርሷ ወደ ቢሮዋ ስታመራ እሱም ሶስተኛ ፎቅ ምድር ላይ ወደሚገኘው የሻይ ክበብ አመራ፡፡
ግማሽ ሰዓት ለበልሁ የግማሽ ዓመት ያህል ረዘመባት፡፡ ነገሩ ከጠዋቱ ጀምሮ ምንም ነገር በአፉ አልገባምና ርሀብም ተሰማው። ሰዓቱ ደግሞ ወደ ስድስት
ተኩል ተጠግቷል፡፡ ሻይና ኬክ አዘዘ። ፉት ፉት፣ ጎረስ ጎረስ አደረገ፡፡ ቡናም አዘዘ። ሲቀርብለት አሁንም ፉት ፉት እለ። ግን የሁሉም ነገር ጣዕም እህል ውሃ
አይለውም፡፡ ማጣፈጫው ስኳር ይሁን ጨው አይለይለትም፡፡ ትኩስ ይሁን ቀዝቃዛ
አይሰማውም፡፡ ስሜቱ ሁሉ በአስቻለውና በሁኔታው ዙሪያ ብቻ ሆነ፡፡ በመሀል የሔዋንና የመርዕድ ጉዳይ ትዝ አለው፡፡ «ዛሬም ላይመጡ?» አለ ለብቻው
አየተነጋገረ። «ትንሽ ልጠብቃቸውና ስልክ ደወዩ ችግራቸውን ማወቅ አለብኝ፡፡ ብቻ ነርሷ ስለ አስቻለው የምትነግረኝ ነገር ሰላም ይሁን!» እያለ በማሰብ በማሰላሰል ላይ ሳለ ሠዓቷ ደርሶ ደርሶ ኖሮ ያቺ ነርስ ድንገት ከፋቱ፡ ከች አለች፡፡
«ሻይ ቡና አልክ?» አለችውና ወንበር ሳብ አድርጋ ከአጠገቡ ቁጭ አለች።
«ሁሉንም አደረጉ።» አላት በልሁ በፍርሀት ዓይኑ እየተመለከታት፡፡
ነርሷ ቡና አዘዘች። እስከሚተርብላትም ድረስ ከበልሁ ጋር ጭውውት ጀመረች። ተነጋገሩ። በእርግጥም ብዙ ተወያዩ፡፡ ተግባቡም፡፡ ከዚያች ሠዓት ጀምሮ በልሁ ወደ ዲላ ስልክ ለመደወል ቁርጥ ሀሳብ ላይ ደረስ፡፡ ከነርሷ ጋር ተሰነባበቱና
እሷ ወደ ስራዋ ስትመለስ በልሁ ደግሞ ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ወጥቶ ስልክ ፍለጋ ኪዎስኮችን ይፈልግ ጀመር ።
ስልክ እንዳገኘ በቀጥታ መርዕድን ለማግኘት ወደ የአፄ ዳዊት ትምህርት ቤት ደወለ፡፡ ለጊዜው መርዕድን አላገኘውም፡፡ ስልኩን ያነሳው ሰው ግን መርዕድን
ከእሥር ደቂቃ በኃላ ሊያቀርብላት እንደሚችል ነገረው። ለካ ዛሬም ወደ እዲስ አበባ ጉዞ አልጀመሩም፡» አላ በልሁ፡፡ ዲላ ውስጥ እንድ ችግር እንዳለ ገመተ።የሆዱን በሆዱ አድርጎ ወደ አውራጃው ግብርና ጽህፈት ቤት ደወለ። በጓደኞቹ አማካኝነት ለታፈሡ ሊደርስለት የሚፈልገውን መልዕክት አስተላለፈ። ይህ ሁሉ
እስከሚሆንበት ድረስ መርዕድን የቀጠረበትም ሰዓት ደረሰና እንደገና ወደ አፃ ዳዊት
ትምህርት ቤት ደወለ፡፡ መርዕድን አገኘው፡፡

«ሀሎ መርዕድ!»
«እቤት!»
«አንተና ሔዋን እንመጣለን ያላችሁት ባለፈው ሰኞ አልነበረም እንዴ?
ነገር ግን ይኸው እስከዛሬ አልተነሳችሁም፡ ችግሩ ምንድነው?» ሲል ጠየቀው፡፡
መርዕድ ለበልሁ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የተቸገረ በሚመስል አኳኋን ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለና እንደ መርበትበትም እያደረገው
«እ..እ...ካለ በኋላ «ግን እኮ ነገ ልንመጣ ተነስተናል» አለው፡፡

«ሔዋን ግን ደህና ናት?»
«ደህና ናት፡፡»
«በእርግጥ ነገ ወደዚህ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ትጀምራላችሁ?»
«እዎ፡ ወስነናል፡፡ »
«ጥሩ እሺ! እንዳትቀሩ፣ እጠብቃችኋለሁ፡፡»
ስልኩ ከሁለቱም በኩል ተዘጋ፡፡
የዕረቡ ቀትር ተጠናቀቀ፡፡ ፀሐይ ወደ ምዕራብ አዘቀዘቀች፡፡ አድማሱን አቅልታ ጨረሯን ወደ ላይ በመዘርጋት እሷ ግን ቁልቁል ሸሸች፡፡ ብላ ብላም ጠለቀች፡፡ ለዓይን መያዝም ጀመረ፡፡ የመንገድ መብራቶች ሁሉ በሩ፡፡
ከዋክብትና ጨረቃ የሰማይ ቦታቸውን ተረከቡ፡፡ ሌሊቱም ተጀመረ፡፡
ለበልሁ ግን ሁሉም ነገር ያው የቀን ያህል ነው፡፡ እንቅልፍ
እላስፈለገውም፡ በንቃት ያስባል፡፡ ዕረፍትም አላገኘም፡ የዘመኑን የሰዓት እላፊ ገደብ በራሱ ጥሶ በአዲስ አበባ አውራ መንገዶች ላይ ከወዲያ ወዲህ ይሯሯጣል፡፡ በሀሳቡ ሔዋንና መርዕድ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ስንቅና
ልብሳቸውን ሲያዘጋጁ እየታየ እሱ ደግሞ ማለዳ ተነስቶ ወደ ዲላ ለመብረር የኮንትራት መኪና ለማግኘት ይለፋል ወደ እኩለ ሌሊት ላይ የሚፈልገውን የመኪና ዓይነት አገኘ፡ ፈጣንና ጠንካራዋን
ባለ እንድ ጋቢና ቶዮታ መኪና በእርግጥም ገና ጎህ ሳይቀድ
ተሳፈረባት ከጨለማው ቅልቅል ጉዞ ወደ ዲላ ጀመረ፡፡
ከአፍንጫው መገተር የተነሳ "መጥረቢያ ፊት ሊባል በሚችል ብቄ ባለሙያ ሾፌር በምትነዳው
ቶዮታ መኪና ማልዳ በመነሳት የአዲስ አበባ መንገዶችን በግላጭ አግኝታ እንደ ንስር ትወረወርባቸው ጀመር ከአዲስ
አበባ ወጥታ አቃቂን፡ ዱከም፣ ደብረዘይትንና ሞጆን አቆራርጣ ወደ ሲዳሞ መስመር መታጠፊያውን መንገድ ስትይዝ ገና ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እንኳ
በወጉ አልሞላም፡፡ከፍጥነቷ የተነሳ ከገመድ የተረፈው የሸራ ሽፋኗ
እየተርገበገብ ሳጮህ የእውቅ ዜመኛ ፉክራ ይመስላል፡፡ ጋቢናዋ በዝምታ ተሞልቶ ከኋላ በኩል ግን ድንቅ የተፈጥሮ ሙዚቃ እየተሰማባት ቶዮታዋ ወደ
ቆጋ ተጠጋች የአዋሽ ወንዝንም ገና በጠዋቱ ተሻገራቸው ከዚያም አልፎ ወደ አለም ጤና፡፡ ሾፌሩና በልሁ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነጋገሩት ዝዋይ ከተማ ሊደርሱ ሲሉ ነው፡፡
«ስማ ሾፌር ቁርስ ያስፈልግህ ከሆነ ዝዋይ ከተማ ላይ አረፍ ብንል፡፡እሱን ካለፋን ዲላ ሳንደርስ የረባ ነገር አይገኝም፡፡» አለው በልሁ፡፡
«ለኔ ሳንይሆን ለአንተ ያስፈልግሃል፡፡ እኔ በጠዋት መብላት ብዙም አልወድም" : አንተ ቁርስ የምታደርግ ከሆን ልቁም» አለው ልክ እንደ
እንደ አፍንጫው ቅንድቡም ወጣ ወጣ ብሎ አስፈሪ ግርማ ሞገስ የተላበሰ ሾፈር፡፡
👍10🔥1
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....ሔዋን በልሁን ስለ አስቻለው ሁኔታ ለመጠየቅ ፈራች። በአንድ በኩል ምላሹን ስትፈራ በሌላ በኩል ትክክለኛውን ሁኔታ ላይነግረኝ ይችላል የሚል ስጋት ያዛት። ነገር ግን ነገሩን ለማንሳት አንድ መላ መጣላትና ወዲያው ተጠቀመችበት።...
«አሁን ነገ ወደ አዲስ አበባ ስንሄድ የትርፌን መሞት ለአስቻለው እንነግረዋለን ወይስ....»ብላ ነገሯን በእንጥልጥል ተወችው።
በልሁ በፍጥነት መለሰላት «ይዋደዱ አልነበር እስካሁን ሆዱ ነግሮት ይሆናል።»አለና ዝም ብሎ በመስታወት ውስጥ ውጭ ውጭ ያይ ጀመር።
«ምናልባት ይደነግጥና አንድ ነገር ይሆናል ብዬ ፈርቼ እኮ ነው።» አለችው ሔዋን ስለ አስቻለው ሁኔታ ምርመራዋን ለመቀጠል።
«እስቲ እዚያው ስንደርስ እንደ ሁኔታው እናደርገዋለን።» እንደገና ፀጥታ። መኪናዋ ግን ሄደች፣ ነጎደች። ጩኮን አልፋ የዲላ ከተማ መዳረሻ ታየ።አንዳንድ ቤቶችም ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። አንዳንድ ልቦች የፍርሃት ከበሮ ይመቱ ጀመር።መኪናዋ ግን ያለ ሀሳብ ናፍጣዋን እየጠጣች በረረች።የመጨረሻውን የለገዳራ ወንዝ ድልድይ ተሻግራ ከዲላ መውጫ የመጀመርያ ኬላ ፍተሻ ላይ ደረሰች።ደግነቱ ከአዲስ አበባ ወደ ዲላ ሲሄዱ ፍተሻ የለም። ያም የፍተሻ ኬላ ታለፈ። ዲላ ከተማን በሰሜንና በደቡብ ለሁለት የሚከፍለው ዳገተማ የአስፋልት መንገድ ተጀመረ ያም ቢሆን ከደቂቃዎች የበለጠ ጊዜ አልወሰደም። ልክ ሰባተኛ መንገድ ተብሎ በሚጠራው የጠጠር መንገድ ላይ ሲደርሱ በበልሁ አመልካችነት ቶዮታዋ ወደ ቀኝ ታጠፈች።ያ መንገድ በለቀስተኛ ተሞልቷል። ነጠላቸውን ያሸረጡ ሴቶችና ጋቢ የለበሱ ወንዶች አጥለቅልቀውታል። አንዳንዶቹ ወደ ታፈሡ ቤት አቅጣጫ ይሄዳሉ
አንዳንዶቹ ደርሰው የሚመለሱ ይመስላሉ። ሹፌሩ የገባው ነገር ነበርና የመኪናዋን ጡሩንባ ደጋግም ሲያንጧጧው ደርሰው ተመላሽ የነበሩ ለቀስተኞች ፊታቸውን ወደ ታፈሡ ቤት አቅጣጫ ይመለሱ ጀመር።
መኪናዋ ከታፈሡ ቤት የማያደርሰውን የመጨረሻ መንገድ ስትጀምር የታፈሡ ቤት አካባቢ ከነጉድጓዱ ብቅ አለ። ሁለት ድንኳን ተተክሎበታል። የሰው ነጭ ይርመሰመሳል። መኪናዋ ወደ ድንኮኑ ስትጠጋ ትልቅ ፎቶ ግራፍ ይዛ እንደ እብደት እንደ ስካር በሚያደርጋት ሴት እየተመራ ያ ሁሉ ሰው ወደ መኪናዋ ተንቀሳቀሰ። ህዝቡና መኪናዋ ሲገናኙ ሴትየዋ የታፈሡ እንግዳ ሰው፣ የያዘችው ፎቶ ግራፍ ደግሞ የአስቻለው ፍስሃ። ነገሮች ሁሉ ግልፅ ሆኑ፣ መርእድ ድንግጥ ሲል ሔዋን ደሞ ሁለመነዋ ደነዘዘ።መኪናዋ ከህዝቡ አጠገብ ስትደርስ ቀጥ ብላ ቆመች።ታፈሡ ወደ መኪናዋ የዕቃ መጫኛ ስትዞር በልሁ የጋቢናውን በር ከፈተና ዱብ አለ። በሩ ላይ ቆሞ ፈዝዞ ደንገዛ መንቀሳቀስ ያቃታትን ሔዋን እየተመለከተ«ሔዋን ፅኒ እንግዲህ! አስቻለው ሞቷል!» አላት።
ሔዋን ግን የሰማችው አትመስልም፣ ፍጥጥ ብላ ቀረች። በልሁ ትላንት መርዕድን በስልክ ባነጋገረበት ሰአት «ነገ ልንመጣ ተነስተናል»ሲለው 'እሺ ኑ' ብሎ
የመለሰለት በእርግጥም እንዲመጡና ልብ በሽተኛዋ ሄዋን መርዷዋን ከመስማቷ በፊት በእጁ እንድትገባለትና ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በእሱ እገዛ ለማስቀረት አስቦ ነበር። አሁን ግን ከዚያ አደጋ የሚያመልጥ አልመስል አለውና ደነገጠ
የሔዋን ፈዝዞ መቅረት አስፈራው። ብቻ የተቻለውን ያህል ለመሞከር በማሰብ መርእድ ገፋ እንዲያደርግለት ጠየቀውና ይበልጡኑ ግን እሱ እራሱ ስቅስቅ አድርጎ አቀፈና ወደ መሬት አወረዳት።
«ሔዩ» ሲል ጠራት ወደ ታች አዘቅዝቆ እያያት። ሔዋን ግን ዝም። ይልቁንም አይኖቿ ስልምልም እያሉ ከእቅፉ ውስጥ
ወደ ታች ወደ ታች ትንሸራተተበት ጀመር፡፡ በልሁ ፈራና በጩህት«ታፈሥ! ድረሽ ታፈሥ ድረሽ!»እያለ ይጣራ ጀመር። በቃል ታፈሱን እየተጣራ በእጁ ደግሞ ሔዋንን ለማቃናት ይጥራል ታፈሡ አልሰማችውም ። እሷ ራሷ በአስቻለው አስከሬን ሳጥን ላይ
ትንፈራፈራለች። ሔዋንን የሰው መዓት ከበባት። እየሆነች ያለችውን ነገር ለማየት አንዱ በሌላው ትከሻ ሳይ ሲንጠራራ አንዳንዱ ደግሞ «ዘወር በሉ! ገለል በሉ! አየር
ስጧት! አየር.…አየር እያለ ይጮሀል። ነገር ግን ሁሉም ነገር ምንም አልፈየደም፡፡ ሔዋን ላትመለስ እየሄደች ስለመሆኑ ምልክቶች ታዩ፡፡ እንቅስቃሴዋ ሁሉ ቆመ።

መርዕድ ለታፈሡ መልዕክት አድርሶ ኖሯል። ታፈሡ ያንን ሰው ሁሉ እየገፈታተረች ከመሀል ስትገባ በልሁ ቁጭ ብሎ በሁለት እጆቹ መሬት እየመታ ሲጮህ ሔዋን ደግሞ ዝርግትግት ብላ አገአቻቸው::
«ኣ» አለች አፏ ጉድጓድ መስሎ እስኪከፈት ድረስ። «እኮ ምንድን ነው!?» ካለች በኋላ ሜዳ ላይ ዝርር ያለችውን ሔዋንን ልክ እንደ ልጆች ቼ ፈረሴ ጨዋታ ጋለበችና የሔዋንን አገጭ ወዲያ ወዲህ እያገላበጠች አንቺ ሒዩ! አንቺ የኔ! አንቺ ሔዩ! ሐዩ ሔዩ!» ትላት ጀምር። ጀሮዋን በአፍና በአፍንጫ ላይ ብትለትምም ምንም ትንፋሽ አጣች፡፡ ጭራሽ እየቀዘቀዘች ሄደችባት፡፡
ታፈታሡ እንደዚያው ቼ ፈረሴ እንደጋለበቻት በሁለት እጆቿ ግራና ቀኝ መሬት እየመታች ዋይ! ዋይ! ዋይ! ዋይ አሁንም ደግማ «ዋይ! ዋይ! ዋይ! ዋይ!» ለሶስተኛ ጊዜ “ዋይ! ዋይ! ዋይ! ዋይ!» በዙሪያው ያለው ሕዝብ ሁሉ
በለቅሶ ተንጫጫ።
የሆነው ሁሉ ሆኗልና ቀጥሎ መሆን ያለበት መሆን ጀመረ፡፡ የሔዋን አስክሪን ከበልሁና ከታፈሡ እጅ ወጣ፡ የመጨረሻ ዝግጅት ለሚያደርላት
ለገናዦቿ ተላልፎ ተሰጠ። በታፈሡ ቤት በር ፊትለፊት በሚገኘው ሰፊ መንገድ ላይ የሚደረገው ረግዶ ግን ነዳጅ እንደተጨመረበት እሳት ይበልጥ ተቀጣጠለ፡፡
ከቀኑ ወደ ስድስት ሰዓት አካባቢ ሌላ አዲስ ከስተት ታየ፡፡ ትናንት በልሁ በመስሪያ ቤት ጓደኞች በኩል የእስቻለውን ሕይወት ማለፍ ለታፈሡ እንዲነገራት አድርጎ ነበርና ታፈሡም በተሰማት መሪር የሀዘን ስሜት መሀል የሔዋን አባትና እናት ትዝ ብለዋት ልጃቸውን ያላቅሷት ዘንድ በሔዋን በኩል ታውቀው በነበረ
የስልክ አድራሻ መልዕክቱ እንዲደርሳቸው አድርጋ ኖሯል። የሔዋን እናትና አባት መርዶውን እንደሰሙ ይበልጥ ያዘኑት ለልጃቸው ነበር፣ ሀዘኑን እንዴት
ትችለዋለች በማለት፡፡ መርዶውን ማታ እንደ ሰሙ ወደ ዲላ ለመብረር ሲዘጋጁ አድረው ክብረ መንግስት ወደ አለታ ወንዶ፡ ከዚያም ወደ ዲላ በመጓዝ ስድስት
ሰዓት አካባቢ በታፈሡ ደጅ እሚወርደው ሙሾ መሀል ገቡ፡፡ የሔዋን እናት ክንፋቸውን ዘርግተው እየሮጡ ወደ ሕዝቡ ሊቀላቀሉ የሚያሰሙት ጨኸት
«ልጄ! ልጄስ...! ልጄን አሳዩኝ! እሙዬን አገናኙኝ..» እያሉ ነው::
ምን እያሉ እንደሆነና ለጊዜሉ የራሳቸውን ማንነት ሕዝቡ ያልተረዳላቸው ቢሆንም ነገር ግን ቆየት እያለ ምስጢሩ ሲታወቅ የታፈሡ ጎረቤቶች ጠጋ ጠጋ
አሏቸው። ክንዳቸውን ከወዲያና እወዲሀ በመያዝ ቀስ ይበሉ! ረጋ ይበሉ ይሏትው ጀመር። እሳቸው ግን አሁንም «ልጄ የታለች? እሙዩ የታለች።ማለታቸውን ቀጠሉ። ባለቤታቸው አቶ ተስፋዬም ከኋላ ከኋላቸው እየተከተሉ ልክ እንደ ሔዋን እናት ይጮሀሉ፡፡ ያለቅሳሉ።
የታፈሡ ጎረቤቶች ሰብሰብ አሉና የሔዋንን እናት ወደ አንድ ገለጥ ወዳለ ቦታ ወስደው ትንሽ ለማረጋጋት እየሞከሩ በኋላ ስለሆነው ነገር ፍንጭ ሰጧቸው፡፡
👍13