አትሮኖስ
270K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
435 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

..ፊሬንዜ ውብ ከተማ ናት፤ የነጻንቴ የነሚኪኤል አንጀሎ ከተማ!

አንዲት ትንሽ ሬስቶራንት ውስጥ እራት ስንበላ ነበር፡፡ ሲልቪ
ምግቧን ረስታ ወደ ኋላዬ በኩል ትኩር ብላ ማየት ጀመረች።
ሳይታወቃት በግራ እጂ ፀጉሯን አስተካከለች ብቻ መስተካከል
አያስፈልገውም ነበር። ገባኝ። የምትጎመጀው ወንድ አይታ መሆን አለበት። ሹካና ቢላዋን ቁጭ አድርጋ ወይን አንስታ ፉት አለችና፣ ብርጭቆውን መልሳ እንደማስቀመጥ፣ በእጆቿ ውስጥ በዝግታ እያሽከረከረችው ወደዚያው ወደ ኋላዬ ማየቷን ቀጠለች። ቀይ ከንፈሮቿ ገርበብ፣ በወይን ረጠብ ብለው ያስጎመጃሉ

እሷ ወደዚያ ስታይ እኔ እሷን ስመለከት፣ ቆንጆ ፊቷ ቀስ ብሎ
ፈገግ አለ፤ ሰማያዊ ኣይኖቿ ስልምልም ማለት ጀመሩ። ምኞቱ
ውስጤ ሲያድግ ተሰማኝ፡፡ አይኖቿ ከአይኖቼ ጋር ተጋጠሙ፣ ፊቷ መቅላት ጀመረ፡ አይኖቿ ተርገበገቡ። ሰውየው ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለግኩ፡ ግን ወደኋላ ከተገላመጥኩ ነገሩ ይበላሻል፣ ስለዚህ ተውኩት

«ፍሬ ይምጣልሽ?» አልኳት
«የለም በቃኝ። አንተ ብላ »
«እኔም በቅቶኛል»
«እንግዲያው እንሂድ?» አለችኝ፣ ወደ ቅድሙ በኩል እያየች
ስንወጣ እሷ ታተኩርበት ወደነበረው በኩል ተመለከትኩ፡፡
በየጠረጴዛው የተበታተኑ አንድ አምስት ወንዶች አሉ፡ የትኛው
ፍላጎቷን እንደ ቀሰቀሰ ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ ግን ፍላጐቷ በሀይል ተቀስቅሷል። አልጋ ውስጥ ስንገባ መብራቱን አጠፋችው፣ እየተንገበገበች አቀፈችኝ፤ በመጨረሻ ላይ በእንግሊዝኛ ቃዥች

«Please, my lord! Please, have mercy!

ሌላ ሰው ሆኜ፣ ግን ማን እንደሆንኩ ሳላውቅ፣ በቅንዝርና
በቅናት እየተቃጠልኩ፣ ጥልቅ የሆነ ስጋዊ ደስታን ተደሰትኩ።
በነጋታው ቀኝ ጡቷን እያመማት ዋለ። ሳይታወቀኝ ጨፍልቄው
ኖሯል በሌላ ቀን፣ «ማን ሆኜ ነበር?» አልኳት። ስንበላ በስተኋላዬ አንድ ሰውዬ እይታ ኖሯል። «ልክ ስመ ጥሩውን ባለቅኔ ሎርድ ሳይረንን ይመስል ነበር አለችኝ እንደዚሀ ስንል፣ እሷ ደስ የሚላትን ወንድ ስታይ፤ እኔ በጭለማ እሱን እየሆንኩ ሳቅፋት እሷ ስትቃዥ፣ እኔ ስነክሳት ስጨፈልቃት፣ እንደዚህ ስንል፣ በሰማያዊ, አይኖቿ ብርሀንና በሰፊ አፏ ሳቅ እያሞቀችኝ፣ በውብ ወጣት ገላዋ እያቃጠለችኝ፡የጣልያንን ከተማዎች እያዞረችኝ «Je men fous» አያለች አያሳቀችኝ፣ እንደዚህ ስንል የበጋው እረፍት ወደ ማለቂያው ተቃረበ፡፡ ከፊሬንዜ ሮማ
ከሮማ ናፖሊ፤ ከናፖሊ ኒስ (ፈረንሳይ) ከኒስ ማርሰይ ተጓዝን።

ከማርሰይ እሷ ቤቶቿን ጥየቃ ፓሪስ ሄደች፡፡ ባቡር ጣቢያው
ሄጄ ስሸኛት ልክ የዛሬ ዘጠኝ ቀን ማክሰኞ ኤክስ እገባለሁ፤ ማታ
ቤቴ እጠብቅሀለሁ» አለችኝ
የሲልቪ ናፍቆት የሚገድለኝ መስሎኝ፤ ዘጠኝ ቀን ሙሉ
እንዴት ሊያልፍልኝ ነው? እያልኩ ስሰጋ ነበር፡፡ ግን ባቡሩ ይዟት
እንደሄደ፣ በሀዘን ፈንታ እፎይታ ተሰማኝ፡፡ ማታ አልጋ ውስጥ
ገብቼ ብቻዬን እንደ ልቤ ስገላበጥ፣ ብቸኝነት ሳይሆን ምቾት ተሰማኝ፡፡ ምቾቴ በደምብ እንዲታወቀኝ ስል በብዙ ተገላበጠኩ።ጧት ስነቃ ሲልቪ የለችም፡ ብቻዬን ነኝ፡፡ በናፍቆት ፈንታ ደስታ ተሰማኝ፡፡ ሲልቪ ሰልችታኝ ኖሯል? ወይስ ከሰው ጋር ለመኖር አልተፈጠርኩም? ሊገባኝ አልቻለም

ኤክስ ሄጄ ሲቴ (ዩኒቨርሲቲ) ውስጥ አንድ የመኝታ ክፍል
ተቀበልኩ፡ ሁለተኛው አመት ወደ መጀመሩ ነበር ጧት ስነሳ በመስኮቱ ደማቅ ሰማያዊ የሆነ ንፁህ ሰማይ ታየኝ።ደስ አለኝ። ሳይታወቀኝ የኤክስ ውብ ሰማይ ናፍቆኝ ኖሯል
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ባህራም ከቅርብ

ኤክስ እንደተመለስኩ መጀመሪያ ያገኘሁት ተካን ነበር፡፡ ያው
እንደ ልማዱ ጥፍሩን እየነከሰ፣ የት ነበርክ? ከማን ጋር ነበርክ? ምን
አደረግክ? ምን አየህ? እያለ በጥያቄ አጣደፈኝ፡፡ ግን ሳየው የጥርሱ መበለዝ የቀነሰ መሰለኝ፡፡ አፉም አልገማኝም፡፡ ጊዜው ከእራት በኋላ ነበር፤ ና ቡና ላጠጣህ ብሎ ወደ ክፍሉ ወሰደኝ፡፡ ቤቱ በጭራሽ
አይገማም!

እንግዲህ፣ የዩኒቨርሲቲው መኝታ ቤቶች ባለ ሶስት ፎቅ
ሲሆኑ፣ እያንዳንዱ ፎቅ ላይ ለሚገኙት ሰላሳ ያህል ክፍሎች የጋራ የሆኑ አንድ የገላ መታጠቢያ ክፍልና፣ አጠገቡ ደግሞ (ልክ ደረጃው መጨረሻ ላይ) አንድ የቡና ማፍያ ምድጃ ያለው ክፍል አላቸው።ተካ ቡናውን ሊጥድ ወደ ማፍያው ክፍል ሲሄድ እኔ የሱን መኝታ ክፍል ተመለከትኩ፡፡ ንፁህ ነው። ፊት መታጠቢያው ዘንድ፡ ግማሹ ያለቀ ኮልጌት የጥርስ ሳሙናና አንድ የጥርስ ብሩሽ አለ። ተካ ጥርሱን ይቦርሻል! ምን ነካው?. ምን ይነካዋል? ያው
የተለመደው መሆን አለበታ! አንድን ጎረምሳ ጥርሱን ሊያስቦርሸው የሚችል ምንድነው? ሴት አይደለችም? ግምቴ ልክ ይሆን? ልክ
መሆን አለበት። አለዚያ ምኑን ደራሲ ሆንኩት?

አንገቴን በበሩ ብቅ አድርጌ አየሁ። ጨለም ያለው ረዥም
መተላለፊያ ኮሪዶር ባዶውን ነው፡፡ ኮሪዶሩ መጨረሻ ላይ ያለው
የቡና ማፍያ ክፍል ተዘግቷል። ተካ ገና ቡናውን በመጣድ ላይ ነው
ማለት ነው። ጊዜ አለኝ፡፡ በሩን ዘጋሁ፡፡ ቶሎ ወደ አልጋው ራመድ
አልኩ፡፡ አንሶላውን ላመሉ ገለጥ ከደረግኩት። ጎምበስ ብዬ ትራሱን
አሸተተኩት፡፡ የሴት ጠረን። ያለጥርጥር። እንዴት ያለች ትሆን?
ቶሎ አልጋውን አስተካከልኩና፣ ቁጭ ብዬ ጋዜጣ እያነበብኩ
ቆየሁት ቡና ከጠጣን በኋላ ሊሎቹን ሀበሾች ፍለጋ ወጣን
ተካ «ተመስገንን ግን አታገኘውም» አለኝ «ወደ ፓሪስ
ተዛውሯል። ለምን እንደተዛወረ ታውቃለህ?»
«ለምንድነው?» አልኩት
«ነጭ ሴት ሰለቸኝ አለ።»
«ምን?
«ጥቁር ሴት ካላገኘሁ ልማር አልችልም አለ፡፡ እዚህ ኤክስ
ውስጥ ሁለት ጥቁር ሴት ብቻ ነው ያለው፡ ሁለቱም አስቀያሚ
ናቸው። ስለዚህ ፓሪስ መሄዴ ነው:: ቢሆን እግዜር ብሎ አንዲት
ሀበሻ ልጅ ታጋጥመኝ ይሆናል፡፡ ባይሆን ደሞ ሌላ ጥቁር ሴት
አላጣም፣ ብሎ ሄዴ»
ተመስገን እውነቱን ነው። ኤክስ ውስጥ ጥቁር ሴት አይገኝም
ሀበሻ ሴት ይናፍቃል። ያገራችን ሴቶች ትዝ ይሉናል፤
አነጋገራቸው፣ አሳሳቃቸው፣ መሽኮርመማቸው ይናፍቀናል፡ ጥቁር ቆዳቸው፣ ነጭ ጥርሳቸው እንቅልፍ ይነሳናል፡ በሀሳባችን
አረ ንሺ» ሲሉ ይሰማናል።

አንዳንድ ጊዜ ተሰብስበን ስለነሱ እናወራለን፡፡ ናፍቆት ሲበዛብን
እየሳቅን እየጮህን እንዘፍናለን
«አንቺ ጥቁር ድንጋይ ፍቅር አይገባሽ በሰው አገር ሆኜ ተቃጠልኩልሽ»
ሉልሰገድማ “ልጆችዬ፣ አብረን አንዲት እምስ የተቀረፀባት ሻማ ለቁልቢው እናብራለትና » አለን እምስ በፖስታ ላክልን፣
መጋረጃ እናስገባልሀለን፣ እንበለው፡፡ እውነቴን'ኮ ነው! ያገሩ ልጆች ነን፡ ይሰማናል። ኧረ እናታችሁን! ይሄ ምኑ ያስቃል?»

እኔና ተካ ሀበሾቹን ሉልሰገድ ቤት እገኘናቸው:: ባህራምና
አንድ ሌላ ኢራናዊ አብረዋቸው አሉ፡፡ ይህ ሌላ ኢራናዊ ጀምሺድ
ይባላል። ረዥም መልከ ቀና ወጣት። ጥቁር ሱፍና ነጭ ሸሚዝ
ከቢራቢሮ ክራቫት ጋር ለብሷል። ግብዣ ለመሄድ የተዘጋጀ
ይመስሳል። ረዘም ያላ ፈት፡ ቀጥ ያለ ረዥም አፍንጫ። ከሀር
መሳይ ውብ ቅንድቦቹ በታች ሰማያዊ ትንንሽ አይኖች ሁልጊዜ
ይጨፍራሉ፡፡ ብርሀን ሳቅ፣ ብልጠት የሚፈራረቅባቸው፣ ህይወት የሞላባቸው አይኖች ናቸው፡፡ በኋላ እንደተረዳሁት፣ ጀምስድ ፈረንሳይ አገር ከመጣ አመት አልፎታል። ታድያ ቢበዛ ስምንት መቶ የፈረንሳይኛ ቃላት ቢያውቅ ነው (የቋንቋ ስጦታ የለውም) ግን እነዚህ ስምንት መቶ ቃላት ለንግግር ኮርተው ይበቁታል። ምክንያቱም ቀጭን ኮሚክ ድምፁና ትንንሽ ብልጮ አይኖቹ፣ ያለ ቃላትም ቢሆን የፈለገውን ይገልፁለታል
#ምንዱባን


#ክፍል_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ፋንቲን ወደ ትውልድ አገርዋ ስትመለስ ከተማው ይህን መስሎ ነው የቆያት፡፡ ማን እንደሆነች ግን ማንም አላስታወሳትም:: ደግነቱ የመሴይ ማንደላይን ፋብሪካ በር ለእርስዋም ተከፍቶ በፈገግታ ተቀበልዋት:: ሴቶች ከሚቀጠሩበት ክፍል ሥራ አግኝታ ሥራ ጀመረች:: ነገር ግን ሥራው
ለእርስዋ ጨርሶ እንግዳ ነበር፡፡ የማታውቀው ዓይነት ሥራ ስለነበር ግራ ተጋባች፡፡ ስለዚህ የሚከፈላት ገንዘብ ዝቅተኛ ሆነ፡: ግን ትንሽም ቢሆን ለእርስዋ በቂ ነበር፡፡ ሠርታ ለመኖር በመቻልዋ ችግርዋ ተቃለለላት፡፡

ፋንቲን ራስዋን ለማስተዳደር በመቻልዋ በጣም ደስ አላት:: ሰውን ሳያስቸግሩ ራስን ችሎ በሁለት እግር ቆሞ ማደር በጣም ደስ ይላል።የጉልበትዋን ዋጋ አገኘች፡፡ በመጀመሪያ ወር ደመወዝዋ መስታወት ገዛች፡፡
ውብ የሆነ ፀጉርዋን፣ ከወተት የነጡ ጥርሶችዋን፣ የልጅነት መልክዋን ጠዋት ማታ ለማየት በመቻልዋ ደስታዋ እጥፍ ሆነ፡፡ የሰው ልጅ ራሱን ከማየት የበለጠ የሚያስደስተው ነገር የለም:: ከልጅዋ ከኮዜት በስተቀር
ብዙ ነገሮችን ረሳች:: የጠዋት ማታ ሕልምዋ ልጅዋ ነበረች:: ወደፊት ምን ሊሆን እንደሚችል በአሳብ በታያት ጊዜ በደስታ ፈነደቀች:: አንዲት ትንሽ ክፍል ተከራይታ ደሞዟል በቅድሚያ በብድር መልክ ወስዳ ክፍሏን አስጌጠቻት።

«ባል አግብቼ ነበር» ብላ ለመናገር ስለማትችል ስለልጅዋ ሰው ፊት እንዳታነሳ ዘወትር ጥንቃቄ አደረገች::ሰዎች ይህን ካወቁ «ጋለሞታ» እያሉ
ስምዋን ሊያጠፉ እንደሚችሉ ታውቃለች::

ቀደም ሲል እንደተመለከተው ልጅዋን ለወሰዱላት ሰዎች ቃል
የገባችበትን ገንዘብ በወር በወር ሳታጓድል ትልካለች:: ስምዋን ከመፈረም በስተቀር መጻፍ ስለማትችል ለልጅዋ ደብዳቤ ስትጽፍ በሰው ነበር የምታጸፈው::

አዘውትራ ደብዳቤ ትጽፍ እንደነበር ተገንዝበናል:: በመሥሪያ ቤትዋ አካባቢ «ፋንቲን ብዙ ደብዳቤ ትጽፋለች፤ የሚጽፍላትና የምትፅፍለት ሰው አለ ማለት ነው» ተብሎ ብዙ ተወራ:: ስለዚህ ተከታታይዋ በዛ፡፡ ከዚህም
በላይ መልክዋ በተለይ ፀጉርዋና ጥርስዋ በጣም ቆንጆ ስለነበር የሚቀነባትም አልጠፉም::

በአማካይ በወር ሁለት ጊዜ ደብዳቤ እንደምትጽፍና ደብዳቤውንም ለተመሳሳይ ሰው እንደምትልክ የሥራ ባልደረቦችዋ ደረሱበት፡፡ ትክክለኛ
አድራሻውንም አወቁ፡፡ ደብዳቤ የሚጽፍላት ሽማግሌ መጠጥ ቤት ሲለፈልፍ አግኝተውት በሞቅታ ሁሉንም ነገራቸው:: ፋንቲን ልጅ እንዳላት ተሰማ::

«አንዳንድ ሴቶች አሉ፤ የትም ሲዘሉ ልጅ የሚቀፈቅፉ፤ የእዚያ
ዓይነት ሰው ናት ማለት ነው» እያሉ አሟት፡፡

ፋንቲን ፋብሪካው ውስጥ ሥራ ከጀመረች ወደ ዓመት ገደማ
ሆኖአታል፡፡ ኣንድ ቀን ጠዋት እርስዋ ትሠራበት የነበረው ክፍል ተቆጣጣሪ አምሳ ፍራንክ በከንቲባው ስም ትሰጣታለች:: «ምንድነው?» ብላ ስትጠይቃት
ከዚያን እለት ጀምሮ ከሥራ የተሰናበተች መሆኑንና ገንዘቡም ለመሣፈሪያ እንዲረዳት ብሎ ከንቲባው በሀዘኔታ የሰጣት መሆኑን ትገልጽላታለች.
ክንፉ እንደተመታ ዶሮ ክው ብላ ቀረች፡፡ ከተማውን ለቅቃ ልትሄድ
አትችልም:: የቤት ኪራይ እዳ አለባት:: አንዳንድ የቤት እቃ በዱቤ ገዝታለች፡፡ ስለዚህ እዳው መከፈል አለበት:: አምሳ ፍራንክ ደግሞ ለዚህ ሁሉ አይበቃም:: ምን እንዳለች ሳታውቅ እንደመጣላት ተናገረች::
ተቆጣጣሪዋ ወደ ቤትዋ እንድትሄድ ምልክት ሰጠቻት፡፡ አፍራና ተከዛ ከሥራዋ ቦታ ወጥታ ወደ ቤትዋ ሄደች። ጥፋትዋ ምን እንደሆነ በሁሉም ዘንድ ታወቀ፡፡ ለሌሎች ሴቶች አርአያ ልትሆን የምትችል ጋለሞታ! በዚህ
ላይ ቅናትም አለ፡፡

መልስ ለመስጠት ኃይል አጣች፡፡ ከንቲባውን እንድታነጋግር ሰዎች
መከርዋት:: ከንቲባው አምሳ ፍራንክ ሰጥቶ አባርሯታል፡፡ ያውም ደግና አዛኝ ሰው ቢሆን ነው እንጂ በገዛ ፋብሪካው ማን ያዝዘዋል:: ያለ ዳረጎት ዝም ብሎ ሊያባርራትም ይችል ነበር፡፡ «ከዚህ በኋላ ምን ማነጋገር ያስፈልጋል። በማለት ወደ ከንቲባው ሳትሄድ ቀረች::

መሴይ ማንደላይን ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቀው ነገር አልነበረም::
ብዙ ጊዜ አዋቂዎች ሥልጣንን ለሚመለከተው ማስተላለፍ እንደ ግዴታ ይቆጥሩታል:: ይህን የመሰለ የሥልጣን ውክልናን መከታ በማድረግ ነበር
ተቆጣጣሪዋ ራስዋን ከሳሽ፣ ዳኛና ፍርድ አስፈጻሚ በማድረግ በፋንቲን ላይ የፈረደችውና ከሥራ ያባረረቻት::

ፋንቲን በነበረችበት አካባቢ በግርድና ለመሥራት ሰዎች ይቀጥራት እንደሆነ ከቤት ቤት እየዞረች ጠየቀች:: ማንም ሊቀጥራት አልፈለገም፡፡

ከተማውንም ለቅቃ ለመውጣት ኣልቻለችም፡፡ የቤት እቃዋን በዱቤ የገዛችው ውራጅ እቃ ከሚሽጡ ባለሱቅ ስለነበር «እዳሽን ሳትከፍዪ ከአገር ብትጠፊ
ለፖሊስ ነግሬ ካለሽበት አሲዝሻለሁ» እያሉ ይዝቱባታል፡፡ የምትኖርበት ቤት ባለቤት ግን «ወጣት ነሽ፤ ከዚህም በላይ ቆንጆ ስለሆንሽ ያለብሽን የቤት
ኪራይ እዳ መክፈል አያቅትሽም» እያሉ ያበረታትዋታል፡፡ አምሳውን ፍራንክ ከፊሉን ቤት ላከራይዋት ስትሰጥ ከፊሉን ለውራጅ እቃ ሻጭ ከፈለች፡፡የእቃው እዳ ብዙ ስለነበር ለጊዜው በጣም የሚያስፈልጓትን እቃዎች
አስቀርታ ቀሪውን ማለት ሦስት አራተኛ የሚሆነውን ለባለቤቱ መለሰች፡፡ የሚቀርባት እዳ ወደ አንድ መቶ ፍራንክ ገደማ ነበር፡፡

ጎረቤትዋ የሆነ ወታደሮች ልብስ ያሳጥቧት ስለነበር ከዚህ የምታገኘው ገቢ ቆሞ ለመሄድ የሚያስችል ስንቅ መግዣ አደረገችው:: ለልጅዋ
የምትልከው የወር ኪራይ ግን መክፈል አቃታት::

ወደ ትውልድ አገርዋ የተመለሰችለት ያሳደረቻት አሮጊት ተቸግሮ መኖር እንዴት እንደሚቻል የሰጠቻት ትምህርት ለአሁን ኑሮዋ የጨለማ መብራት ሆናት:: ትንሽ ዋሽቶና ትንሽ ገቢ አብቃቅቶ መኖር መቻል የችግር ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን አስረድታት ነበር፡፡ የመጀመሪያው ስውር
ሲሆን ሁለተኛው እንደ ጨለማ ድብቅ ነው» ስትል መክራትም ነበር፡፡

ፋንቲን በጨለማ ያለ መብራት መኖር ለመደችው:: የምትቀምሰውን እራት ለመብላት ከጎረቤት መስኮት በሚመጣ የብርሃን ውጋገን እየተጠቀመች
ትጎርሳለች:: እራት ከሌለም ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ጥቅልል ብላ መደፋት ነው::

ትምህርት የለገሰቻት አሮጊት ሩህሩህ ሴት ነበረች:: ስምዋ ማርጋሬት ይባላል፡፡ ድሃ ብትሆንም ለተቸገረ አዛኝ ፣ ቤተክርስቲያንን መሳም
የምታዘወትር ጽኑ አማኝ፣ ምፅዋት መስጠት የሚያስደስታትና ስምዋን ከመፈረም በስተቀር ማንበብና መጻፍ የማትችል ሴት ነበረች::

የሚገርመው፤ ብዙውን ጊዜ እንዲህ ያለው ደግነት፧ እንዲህ ያለው እምነት የኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ ከሆነ ሰዎች ዘንድ አይጠፋም:: ኣንዴ ሲከፋቸው፣ አንዴም ደስ ሲላቸው ይኖራሉ:: በነገ በጣም ያምናሉ::በመጀመሪያ ፋንቲን በጣም አፍራ ለጥቂት ቀናት ከክፍልዋ ሳትወጣ ከቤትዋ
ውስጥ ቁጭ አለች:: ከቤት ከወጣች ሰዎች ኋላ ኋላዋ እየተከተሉ ጣት በመቀሰር የሚጠነቁሉባት መሰላት:: እውነትም ከቤት በወጣች ቁጥር ሰው ሁሉ ያያታል፤ ሰላምታ ግን አይሰጥዋትም:: መንገደኛ ሁሉ ደግሞ በክፉ ዓይን ሲያያት መጥፎ ስሜት አሳደረባት:: ይህም ስሜት እንደ ጥቅምት
#ገረገራ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በታደለ_አያሌው


...ባለ ዲጂኖዉ ትንፋሹ ሳይቀር የሚሰማበት ቅርበት ላይ ከአጠገቤ ደርሷል። ምኔን ቢወጋኝ አንድ ምት እንደሚበቃኝ እያማረጠ ይመስለኛል ትንሽ ፋታ ስጠኝ። ዓይኔን ጨፍኜ ብቻ ስንቱን እንዳሰብሁት በዚች ቅጽበት! ሞት እንዲህ አብሮኝ ኖሯል ለካ። “ቁልቁል ወደ ምድር
ለመዉረድ የፈጀነዉን ያህል፣ የሩብ ሩቡን እንኳን ሽቅብ ወደ ሰማይ ለመዉጣት አንፈጀዉም” ትላለች እመዋ። እዉነቷን አይደል? እንዲያዉ ማርያም ብላዉ የምጡ ጭንቅ ቀለል ያለ ቢሆን እንኳን፣ ለመወለድ ቢያንስ ቢያንስ ለዘጠኝ ወራት በማሕጸን ዉስጥ መክረም የግድ ነዉ።ለመሞት ግን ይኸዉ አንዲት ቅጽበት እና ዲጂኖ ያለዉ ገዳይ በቂ የሚሆኑበት ጊዜ አለ።

ግንባሬን ይለኛል ጸጥ እላለሁ። አበቃልኝ።

እንደ ዛሬ ሞትን ቀርቤ፣ ትንፋሽ ለትንፋሽ ተሻትቼዉ አላዉቅም: በዓይነ ኅሊናዬ የመጡልኝን ሁሉ በልቤ ተሰናብቼ ራሴን ለሞት አደላደልሁ።እመዋ፣ ባልቻ እና እሸቴ ነበሩ ቀድመዉ ትዝ ያሉኝ፡ በእርግጥ በየመሀሉ
የመጡልኝን ሌሎች ማኅበርተኞቼን እና ጓደኞቼን ሁሉ አዳርሻለሁ።በመጨረሻም፣ በሆዴ ወደ ተሸከምሁት ፅንስ እጆቼን ሰድጄ ደባበስሁት፡ እህ? ለካንስ ሐኪሟ ፅንሱ የሴት ነዉ ብላኛለች፡ ሴት ከሆነች ደግሞ እመዋ ስም አዉጥታላታለች: ማን ብላ? ቱናት። ቱናትን በዳሰሳ ተሰናበትኋት፡ ፀእንዲያዉ ነዉ የተሰናበትኂት እንጂ፣ መቼስ እኔ ሞቼ
ቱናት አትተርፍ፡ አብረን ወደ ሞት ተጓዦች ነን

“ዉብርስት?” የሚል ቃል ድንገት አጠገቤ ሰማሁ ገዳዬ አይደል? እንደ ምንም የአንድ ዓይኔን ሽፋሽፍት ፈልቅቄ ስገልጥ፣ ገዳዬ ቆሞበት በነበረ ሥፍራ ቢራራ ቆሞበታል እንደገና ጨፈንሁና ብገልጥም፣ ከቢራራ በቀር ማንም በፊቴ የለም፡፡

“የት ገባ?”

“ማ ?”

“ባለ ዲጂኖዉ?”

ፍርስ ብሎ የንቀት ሳቁን ለቀቀብኝ፡ “ለካ ስ እንዲህ ፈሪ ነሽና” እያለ
እንደ መሽኮርመም እያደረገዉም ጭምር አሁንም አሁንም አሽካካብኝ::እዉነትም ገና ድንጋጤዬ አለቀቀኝም: ድንገት እርም እርም የሚል የብዙ
ሰዉ ሆታ ሰማሁና፣ ዞር ስል ሰዎች ወደ ቤተልሔሙ እና ወደ ግምጃ
ቤቱ ይሯሯጣሉ፡ አንዳንዱ አፈር፣ አንዳንዱ ዉሃ፣ አንዳንዱ ደግሞ
ቅጠል እየያዘ ይራወጣል ያ ይባስ ያ ይቅደም ያን ተወዉ. እዚህ
ጋ አምጣዉ የሚል የተለያየ ሰዉ ድምፅ ተሰማኝ፡

እሳቱ! አሁን ገና ወደ ልቡናዬ ተመለስሁ፡

“እሳቱ! ወይኔ ወይኔ! ቤተልሔሙን ፈጀዉ” ስል ጮኹኩ፣ በሚርገበገብ ድምፅ ብሞትስ ቆይ!? ደግሞ እኮ ለሰማዕትነት ዝግጁ ነኝ እያልሁ ስመጻደቅ ነበር እንደ ደህና ሰዉ በቤተ ክርስቲያን ከመጡብኝ እንኳንስ
ሌላ፣ ሞትንም አልፈራ ባይ ነበርሁ ሐሰት ይኼዋ ልኬን አወቅሁት መስዋእትነቱም ይቅርና፣ ከራሴ ቀድሜ የማተርፈዉ ምንም ነገር
አለመኖሩን ነዉ ያየሁት ቢሆንም ግን ቀደም ብዬ የደወልሁት ደወል
የጠራቸዉ ምዕመናን እንደ ደራሽ ጎርፈዉ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እሳቱን በአጭር አስቀረተዉታል። ቢራራም አጠገቤ ቆሞ በእኔ የሚስቀዉ፣ የእሳቱን መጥፋት ካረጋገጠ በኋላ እንደሆነ ገባኝ፡
ሰአሊ ለነ!

“ቆይ ግን ገዳዬ የት ተሰለበ? አሁን እኮ እንዲህ ብሎ ቆሞ ነበር''
አልሁት ቢራራን፣ እጄን ጦር እንደሚወረዉር አዳኝ አድርጌ እያሳየሁት እሺ እሳቱስ ከምኔዉ ጠፋ? ይኼ ሁሉ ሲሆን እንዴት እንደሆነ የማስታዉሰዉ ምንም ነገር የለኝም:: የሚደንቀዉ ደግሞ አሁንም ገና ድንጋጤዉ ጨርሶ አልለቀቀኝም: ቆመች ቆመች እንደሚባልላት ጨቅላ
የሚያደርገዉን የጉልበቴን መንቀጥቀጥ ማንም እንዳያይብኝ ተሳቀቅሁ፡ቢራራ ከፊቴ እስከሚሄድልኝ ድረስ በዝምታ ብጠባበቀዉም አልሄድልሽ
አለኝ፡ ባለሁበት ቁጢጥ አልሁና ወደ ልቡናዬ ለመመለስ፣ መድኃኒቴ የሆነችዋን ጸሎቴን በለሆሳስ አደረስሁ: ከቅድሙ አንጻር ልቤም የሚመታበት ፍጥነቱ በረድ ቢልም፣ ጨርሶ ግን ልክ ሊሆንልኝ አልቻለም

"እና ፈርቼ ነዉ?” አልሁት ቢራራን፣ ፈቀቅ ብሎ ወዳለዉ የእንጨት
መቀመጫ እየጎተትሁት።

“እንክት!” አለኝ፣ በእርግጠኝነት

“በእርግጥ ፈተና ባይኖር ሁሉ ተማሪ፣ ጠያቂ ባይኖር ሁሉ አስተማሪ መባሉን አዉቃለሁ: ግን እንደዚያ ነበርሁ ወይ እኔ? ተሞክሬ ባላዉቅ ነዉ
እዉነት? በጅቦች መካከል፣ በጨለማ አካፋይ ሞትን ተፋጥጬዉ አላዉቅም? ሌላዉ ሌላዉ ቢቀር፣ ሲራክን ከተቀላቀልሁ እንኳ ን
ይኼዉ ኹለተኛ ዓመቴን ጨልጫለሁ: እስከ አሁንም ድረስ ሐሞቴን የሚፈትኑ ስትና ስጓት ተልእኮዎች በየዕለቱ ከማዕከሉ እቀበላለሁ:: እንዲያዉ ምን ብረሳ ብረሳ በታላቁ ቤተ መንግሥት የገጠመኝን እረሳዋለሁ? እዉነት አተስ ያን ጀብዱ ሳትሰማ ቀርተህ ነዉ?” አልሁት፣ ቤተ መንግሥቱን መጥቀሴ ክፋት እንደ ሌላዉ በማስተዋል እኔ አሁን ጀብዱ ስለምለዉ ነገሬ ላይሰማ ቢችልም፣ ማዕከላችን ሲራክ ፯ በቤተ መንግሥት ምስጢር እንዳለዉ ያወቅነዉ ግን አብረን ነበር

“ሳትሰማ ቀርተህ ነዉ እዉነት ቢራራ?” አልሁት፣ ባለማመን። ይኼ ታሪክ ከተፈጸመ በኋላ፣ እንደኔ ላሉ የሲራክ ፯ መረጃ ሰብሳቢዎች በነበረዉ ወቅታዊ ስልጠና ጭምር ለምሳሌነት ተጠቅሶ እንደ ነበር
በማስታወስ፡
“በታላቁ ቤተ መ ግሥት?”
“ታዲያስ!”
“እንደምታዉቀዉ፣መአከላችን ሲራክ ዋና ዋና በሚባል
የመንግሥት…ብዬ ጀመርሁለት። እዉነትም አልሰማም ኖሯል
እየተቁነጠነጠ አዳመጠኝ።
እንደምታዉቀዉ፣ ማዕከላች ሲራክ ዋና ዋና በሚባሉ የመንግሥት እና ዓለም አቀፍ ዋና በሚባሉ የመንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ዉስጥም እጅግ ቁልፍ ሥራ ያላቸዉን ዳሳሾች (Sensors) እና ካሜራዎች በሥዉር አስቀምጧል: አንዳንዶቹ ድምፅ፣ አንዳንዶቹ ምስል፣ አንዳዶቹ ደግሞ እንቅስቃሴ በድብቅ እየዳሰሱ እና እየቀዱ ወደ ማዕከላችን የመረጃ ቋት
በቀጥታ የሚልኩ ናቸዉ:: ስለሆነም እነዚህ መሣሪያዎች በተሸሸጉበት አካባቢ ሁሉ የተፈሳችም ሆነ የተተነፈሰች ነገር ሲራክን አምልጣ ?
አታዉቅም: ምንም እንኳን መተዳደሪያ ሥነ ሥርዓቱ ስለማይፈቅድልኝ በየትኛዉ ቦታ ስንት ዳሳሽ መሣሪያ እንደ ተተከለ የማዉቅበት ደረጃ ላይ ባልሆንም፣ ከዐሥር ሺ ያላነሱ ዘመናዊ ዳሳሾች በተለያዩ ቦታዎች
እንደሚኖሩ እገምታለሁ: ለግምቴ ደግሞ በቂ ምክንያት አለኝ” አልሁት፣ የማዳመጥ ጉጉቱን ቀና ብዬ እያስተዋልሁበት ቋምጧል።

“ሰኞ ይሁን ማክሰኞ ቀኑን ዘነጋሁት እንጂ…”

ሰኞ ይሁን ማክሰኞ ቀኑን ዘነጋሁት እንጂ፣ የዛሬ ሰባት ወር ገደማ
ለአንድ ተልእኮ እንድዘጋጅ በራሱ በቀድሞዉ የሲራክ ፯ ኃላፊ ታዘዝሁ። “ ስለ ምንነቱ በዝርዝር ከመንገሩ በፊት፣ ስለ አደገኛነቱ አጥብቆ ሊያስረዳኝ ከሞከረ፡ እኔም ተልእኮዉ ምን ይሁን የት ይሁን ገና ሳላዉቀዉ፤ ምንም
ሥጋት እንዳይገባዉ በልበ ሙሉነት ገለጽሁለት።

“የለም የለም፣ የገባሽ አልመሰለኝም” አለኝ እንደገና፣ ጉዳዩን ማቃለሌ ገርሞት ባላስተዋልኋቸዉ ነገሮችም ሳይታዘበኝ የቀረ አይመስለኝም።
እንዲሁ ላይ ላዩን ፍርጥም አለብኝ፡ እዉነትም ከእሱ ጋር ቃል እየተመላለስሁ መሆኑን ራሱ ያስተዋልሁት ዘግይቼ ነበር
“ለወትሮዉ ማንኛዉንም ተልእኮ የምቀበለዉም ሆነ ተልዕኮዬን በተመለከተ የምነጋገረዉ ከቅርብ ኃላፊዬ ጋር ብቻ ነዉ። ሲጀመር የቀድሞዉን ዋና “ ኃላፊ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅርበት ያየሁት ራሱ፣ በዚሁ ዕለት ባልቻ
#ሳቤላ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


... ሎርድ ማውንት አስቨርን ኢስትሊን ለመሰንበት ያሰበው የሁለት ሳምንት ጊዜ ከማለፉ በፊት የእግሩ በሽታ ክፉኛ ስለ ተቀስቀሰበት ወቶ ሊሔድ አልቻለም ሚስቸር ካርይልን ግን
ሁኔታውን በማየት አስከ ፈለገበት ጊዜ ድረስ ሳይሰቀቅ ቢቆይ እንደማይከፋው ገለጸለት ኧርሎም ቶሎ ሽሎት በእግፋ እንደሚቆም ተስፋ በማድረግ ሚስተር ካርላይልን አመሰግነው።

ቢሆንም እንዳሰበው አልተሻለውም " በሽታው ሙሉ በሙሉ ባያስተኛውም ከቤት መውጣት ሳይችል እስከ ጥቅምት ቆየና ትንሽ ምልስ አለለት »

በአጥቢያው የታወቁ ሰዎችም በሽኛውን ተመላልስው ከመጠየቃቸውም ሌላ ሳቤላንም ከቤታቸው እየጠሩ በማነጋገርና በማስተናድ መልካም ጉርብትናቸውን አሳዩዋት " ከሁሉ የበለጠ የርሱ ዋና ጠያቂ ግን ሚስተር ካርላይል ነበር "
ከኧርሎና ከሳቤላ ጋር በጣም ተቀራረቡ " ኧርሎ ከመጠን በላይ ስላላመደወና ስለ ወደደው አንዳንድ ቀን ብቅ ሳይል የቀረ እንዴሆነ በጣም ቅር ይለው ነበር

« እኔ ከኅብረተሰብ የቶለየሁ ብቸኛ ነኝ » አላት ለልጁ " « ሚስትር ካርላይል ይህን ችግሬን ዐውቆ እዚህ ድረስ እየተመለሰ የብቸኝነት በሺታዬን ሲያቀልልኝ ደግነቱና ለሰው አሳቢነቱ በጣም ይሰማኛል።

« በጣም ደግ ሰው ነው እኔማ በጣም ነው የምወደው..አባባ » አለችው

« እኔ ልጄ . . . የሱን ያህል የምወደው ሰው የለኝም » ሚስተር ካርላይል እንደ
ልማዱ በሽተኛውን ለማነጋገር መጥቶ ሳለ አባቷ ሳቤላን እንድትዘምርላቸው
ጠየቃት።

«ካልክ እሺ ... አባባ " ግን የፒያኖው ቅኝት በጣም ስለ ተበላሸ ምቱ ከድምፄ ጋር አይስማማም ደስ አይልም ዌስትሊን ውስጥ እዚህ ድረስ መጥቶ ፒያኖ የሚያይልኝ ሰው አይገኝም ... ሚስተር ካርላይል ?

« ኧረ አለ ሚስተር ኬን ሊያስተካክለው ይችላል » ነገ ልላከው ? »
« የማያስቸግርህ ከሆነ በጣም ደስ ይለኛል " ዕቃው እንኳ ስለ አረጀ ለጊዜው እንጂ ቅኝቱ እምብዛም አይረዳውም " ኢስት ሊን ውስጥ ብዙ የምንሰነብት ከሆነ በአዲስ እንዲተካው አባባን እጠይቀዋለሁ»

ምስኪኗ ሳቤላ ' ፒያኖው የሚስተር ካርላይል እንጂ የሷ አለመሆኑን አላወቀችም » ኧርሎ እንደ መሳል አለና ከሚስተር ካርላይል ጋር በፊት ፈገግታና በዐይን ጥቅሻ ተነጋገሩ ።

ሚስተር ኬን የቤተ ክርስቲያን ኦርጋኖን ተጫዋችና ተማሪ ነበር በበነጋው ወደ ኢስት ሊን ሲመጣ ሳቤላ እንዳጋጣሚ ፒያኖ ስትጫወት አገኛት " በትሕትና
በፈገግታ ተቀበለችው ለማንም ቢሆን ትሑትና ማራኪ ጠባይ ነበራት አታስፈራም " አትከብድም " ሙዚቀኛዋ በፈገግታዋ በመበራታት ድፍረት ተሰማውና
የራሱን የኑሮ ስንክሳር ይተርክላት ጀመር " ምንም ያልነበረው ድሃ መሆኑን ብዙ እየተጨነቀ ነገራት " ከችግሩ ጥናት የተነሣም ትንሽ ገንዘብ ቢያገኝ ብሎ በተከታይ ሳምንት አንድ የሙዚቃ ትርዒት ለማሳየት ተዘጋጅቶ ነበር " ስለዚህ ሳቤላና አባቷ ቢገኙለት ' የነሱን አርዓያ በመከተል ብዙ ሕዝብ እንደሚገባለትና ደኅና ገንዘብም ማግኘት እንደሚችል ገልጾ ለመናት " የሙዚቃው ትርዒት የተሳካ እንደሆነ ኑሮውን በደኅና ለመቀጠል እንደሚችል ካልተሳካ ግን ካለበት ቤት እንኳን ከነቤተሰቡ እንደሚባረር የቤት ዕቃውም ለተቀመጠበት የሁለት ዓመት ውዝፍ ኪራይ በሐራጅ እንደሚሸጥ እያስተዛዘነ አወጋት ሚስተር ኬን የሰባት ልጆች አባት ነበር" ሳቤላ የሰውየውን ታሪክ ስትሰማና ሁኔታውን ስትረዳ አንጀቷ ተንሰፈሰፈና
አባቷን ለመነችው "

« አባባ . . . አንድ ትልቅ ነገር እንድታደርግልኝ ብለምንህ እሺ ትለኛለህ ? »

« ምናለ ልጄ ... ብዙ ጊዜ ጠይቀሽኝ አታውቂም ምንድነው እሱ ? »

« ዌስት ሊን ውስጥ በቅርቡ ከሚታይ አንድ የሙዚቃ ትርዒት እንድትወሰደኝ እፈልግ ነበር " »
ኧርሎ በመገረም ሳቤላን ዐይኑን አፍጥጦ ተመለከታት

«ዌስት ሊን ላይ የሚታይ የሙዚቃ ትርዒት? » አለና ሳቀ « ባላገር ጅማት ሲከረክር ለመስማት ? ላቤላ ልጄ ምን ነካሽ ? »

ሳቤላ የሰማችውን የዚያን ሰው ታሪክና የራሷንም እያከለች አብራርታ ተረከችለት "

« ሰባት ልጆች . . . አባባ ! የሙዚቃው ትርዒት ካልተዋጣለት ያለበትን ቤት ለቆ እነዚያን ልጆች ሁሉ እንደያዘ ከአውራ መንገድ መፍሰሱ ነው ለሱ የሞትና
የሕይወት ጉዳይ ነው #ምናምኒት የሌለው ድሃ ነው»

« እኔም ድሃ ነኝ » አላት አባቷ "

«ሲናገር ብትሰማው አባባ ... ፊቱ ዐሥር ጊዜ ሲለዋወጥ ፡ የችግሩን ጥናት ስለገለጸ ኃፍረት እያስጨነቅው ትንፋሹን ያዝ ለቀቅ ሲያዶርግ ንግግሩ ቁርጥ
ቁርጥ ሲል አንጀት ይበላል እርግጠኛ ነኝ ሰውየው ቀን የጣለው የሀብታም ወገን
ነው »

« አዬ ጉድ የመንዶር ሙዚቃ ! በይ ደግ ነው የአንድ ፓውንድ ቲኬቶች ገዝተሽ ለትልልቆቹ አሽከሮች መስጠት ትችያለሽ »

« እንደሱ አይዶለም እኮ አባባ ( አንተና እኔ እንደምንገኝለት ቃል ከገባንለት በዌስት ሊን አካባቢ ያሉ ታላላቅ ሰዎች ስለሚመጡ አዳራሹ ሊሞላ ይችላል " አሽከሮቻችንን ልከን እኛ እንደምንቀር ከሰሙ ግን ለመገኘት ያሰቡት ሁሉ ይቀራሉ ።እስኪ አንተም አስበው . . . አባባ " አሁን ይኸን ቤትህን ከነዕቃው እንዳለ ቢወስዱብህ ምን ይሰማሃል ? ሰው አዳራሹ እስኪሞላ ከገባለት ግን ከዚህ ጉድ ሊድን ይችላል " አባባ ...እንደ ምንም ብለህ ለአንድ ሰዓት ቢሆንም ተገኝለት እኔ የታምቡር ጓጓታና የክራር ክርከራ ብቻ ቢሆንም ያስደስተኛል

« መንቻካ ለማኝ ነሽ ! በይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ተገኝተን እናይለታለን ንገሪው»

ወደ ሚስተር ኬን እየሮጠች ሔደችና« ሚስተር ኬን... አባቴ ጥያቄህን ተቀብሎታል እሱ አራት ቲኬቶች ይገዛል " አባባና እኔ እንገኛለን » አለችው።

የሚስተር ኬን ዐይኖች የደስታ እንባ አቀረሩ ። ሳቤላም የሰውየውን ደስታ ስታይ የእሷም ዐይኖች እንባ ማቅረር አማራቸው።

« ብዙ ሰው እንዲባልህ የሚረዳህ ከሆነ ለምታገኘው ሁሉ ንገር « እኔም ለሰው ሁሉ እንደምንግባ እየነገርኩ እነሱም እንዲገኙ እጠይቅልሀለው አለችው።

ማታ ሚስተር ካርላይል ሎርድ ዊልያም ቬንን ለመጠየቅ መጣ ኧርሎ ለጊዜው ከክፍሉ አልነበረም ሳቤላ ስለ ሚስተር ኬን ትርዒት አነሣችለት "

« ሚስተር ኬን ከባድ ድፍረት ነው ያደረገው» አለ ሚስተር ካርላይል"
« ይልቅ የበለጠ ገንዘብ እንዳያወጣና በችግሩ ላይ ችግር እንዳይጨምር እፈራለታለሁ

« ለምንድነው ይኸ ሥጋት የተሰማህ ? »

« እሱ ዌስት ሊን ውስጥ ሙዚቃ ለማሳየት ቢሞክር ሰው አያደንቅለትም ሕዝቡ የሱን ችግር ደጋግሞ የሰማውና የሚያውቀው ስለሆነ አንድም ሰው ዞሮ አያየውም አንድ ያልታወቀ እንግዳ ተጫዋች ከውጭ ቢመጣ ግን የዌስት ሊን ሕዝብ ይጐርፍለት ነበር»

«ግን ድህነቱ እሱ እንደሚናገረው እውነት ነው ? » አለችው ሳቤላ "

«በጣም በርግጥ እንጀራ ሊኖረው ይችላል ግን የተሟላ ምግብ አያገኝም በኦርጋኖ ተጨዋችነቱ ባመት ሠላላ ፖውንድ ያገኛል ! ዐልፎ ዐልፎ በማስተማር
ይደጎማል ሚስቱና ልጆቹ የሚኖሩት በዚህ ገቢ ነው " ቤተሰቡ ሥጋ የሚባል ነገር ቀምሰው የሚያውቁ አይመስለኝም»

« ሰውዬውን ሳየው ሚስተር ካርላይል የትልቅ ሰው ልጅ ይመስላል»

« እውነትሽን ነው " የትልቅ ሰው ልጅ ነበር " አባቱ ካህን ነበሩ " እሱ ሙዚቃ በመውደዱ ነው ኑሮው የተበላሸው ደኅና ክፍያ ከሚገኝበት ሥፍራ እንዳይረጋ
አደረገው " ሌላው የውድቀቱ ምክንያት ደግሞ ገና በልጅነቱ በማግባቱ ነው . .
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ዘጠኝ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...ወንበር ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠና እግሩን ወፍራሙና ክብ የሆነው የወንበሩ መደገፊያ ላይ አድርጎ የሚያነበው መፅሀፍ ከፈተ፡ እኔም ብቸኛው ባዶ አልጋ ላይ ጋደም ብዬ ስለ ንጉስ አርተር ማንበብ ጀመርኩ። አመናችሁም
አላመናችሁ ከዚህ በፊት መኖሩን የማላውቀው በር ተከፈተልኝ እጅግ ውብ አለም ጀብደኝነት ያለበት፣ ፆታዊ ፍቅር ያለበትና ስርዓት ያላቸው ሴቶች እንደምሰሶ ቆመው ከሩቅ የሚመለኩባት ናት። ለእኔ የመካከለኛው ዘመን የፍቅር ግንኙነት የተጀመረው የዚያን ቀን ነው። ከሁሉም በላይ ብዙ
የባሌት ዳንሰኞች መሰረታቸው ተረት ነው፣ አይደል? ሁሉም ተረቶች ደግሞ በመካከለኛው ዘመን ካሉ ተረትና ምሳሌዎች አይደል የመጡት።

እኔ ሁልጊዜ ተረት ላይ ያሉ አስማተኛ ፍጡራን ሳር ላይ ሲደንሱ ማየት የምፈልግ ልጅ ነኝ፡ በጠንቋዮች፣ በድግምት፣ በአስማት፣ በጭራቅ ማመን
እፈልግ ነበር፡ አስማቶች ሁሉ በሳይንሳዊ ማብራሪያ ከአለም ላይ እንዲጠፉ አልፈልግም: የዚያን ጊዜ ግን በጠንቋይና በጭራቅ በሚተዳደር ጠንካራና
ጨለማ ቤተመንግስት ውስጥ ለመኖር እንደምመጣ አላውቅም ነበር አንዳንድ የሰለጠነው ዘመን ጠንቋዮች ድግምት ለመስራት ገንዘብ ይጠቀማሉ ብዬ ገምቼም አላውቅም።

የቀኑ ብርሃን ከከባድ መጋረጃዎቹ ጀርባ ሲሸሽ ትንሽዋ ጠረጴዛችን ላይ ለእራት ተቀመጥን፡፡ እኔና ክሪስ ቀዘቀዘም አልቀዘቀዘም ምግባችንን እንበላለን። መንትዮቹ ግን ገና ምግባቸውን ሲያዩት ሁልጊዜ አይጣፍጥም
ብለው ይነጫነጫሉ ኬሪ የምትነጫነጭ ባይሆን ኖሮ ኮሪ የተሻለ ይመገብ እንደነበር ይሰማኛል።

“ብርቱካኖቹ የሚያስቅ መልክ ነው ያላቸው" አለ ክሪስ ብርቱካን እንድልጥ እየሰጠኝ፡ “ፈሳሽ የፀሀይ ብርሀን ናቸው":: አሁን ትክክለኛ ነገር ተናገረ።
መንትዮቹ በደስታ ሊበሉት የሚችሉት ነገር አገኙ: “ፈሳሽ የፀሀይ ብርሀን”።

አሁን መሽቷል። ክፍሉ ግን ቀን ከነበረው የተለየ አልሆነም አራቱንም መብራቶች አበራናቸው፡፡ እናታችን ይዛት የመጣችውን ትንሽዬ የራስጌ
መብራት ደግሞ ጨለማ ለማይወዱት መንትዮች አደረግንላቸው:ከእንቅልፋቸው ሲነቁ እንደገና ንፁህ ልብስ አልብሰን ፀጉራቸውን አበጥረንና
ፊታቸውን አጥበን እንቆቅልሽ እንዲጫወቱ ወለሉ ላይ አስቀመጥናቸው በጣም ቆንጆ ሆነው ነበር። ምስል የመገጣጠሙን እንቆቅልሽ ለእነሱ አዲስ ስላልነበር የትኛው የቱጋ እንደሚገጠም ማወቅ ቀላል ሆኖላቸው ነበር በውድድር መልክ እንዲያደርጉት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰላቹ ከዚያ አልጋ
ላይ አስቀመጥናቸውና ራሳችን የፈጠርናቸውን ታሪኮች እንነግራቸው ጀመር
ያም አሰለቻቸው እኔና ወንድሜ ምን ማድረግ እንዳለብን አላወቅንም: ቀጥሎ ክሪስ ከሻንጣ ውስጥ የመጫወቻ መኪናዎች አወጣና እየገፉ እንዲጫወቱ ነገራቸው።
በጠረጴዛው ስር በአልጋው ስር እየገቡ እንደገና እስኪቆሽሹ ድረስ መጫወት ጀመሩ።

ሲደክመን ክሪስ ቼከርስ እንድንጫወት ሀሳብ አቀረበና መንትዮቹ የብርቱካን
ልጣጮቹን በመኪናቸው ጭነው ወስደው ፍሎሪዳ ላይ እየደፉ ነበር። ያም ጥግ ላይ የተቀመጠው የቆሻሻ ቅርጫት ነበር።

“በቀያዮቹ መጠቀም ትችያለሽ እኔ እንዳንቺ ጥቁር ተሸናፊ ቀለም ነው ብዬ አላምንም” አለ ግንባሬን አጨፈገግኩት በቀንና በማታው መካከል ዘለአለም የሚመስል
ጊዜ አልፏል፤ ይህም እንደገና እንዳልመለስ አድርጎ ለውጦኛል። “ቼከርስ መጫወት አልፈልግም” አልኩት።

ሊመጣ ካለ ነገር ፍራቻና ውስጤን ከሚያሰቃዩኝ ጥርጣሬዎች ለመገላገል
እናታችን ሁሉንም እውነት ብትነግረን ኖሮ የሚለውን ማለቂያ የሌለውን ፀሀሳቤን ተውኩት ነገር ግን አራታችንም እናታችን እንድትመጣ እየጠበቅን
ሳለ ሀሳቦቼ ያልዳሰሱት ቦታ አልነበረም: አብዛኛው ፍራቻዬ እሳት፣ ጣዕረሞትና ሌሎች ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ውስጥ ያሉ አስፈሪ ነገሮች ነበሩ። ከሁሉም በላይ ትልቁ ፍራቻዬ በተቆለፈ ክፍል ውስጥ ሊነሳ የሚችል እሳት ነበር።

ጊዜው በዝግታ አለፈ ክሪስ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ እያነበበ አልፎ አልፎ ሰዓቱን ይመለከታል፡ መንትዮቹ የብርቱካን ልጣጮቻቸውን እያመላለሱ
መጫወት ሰለቻቸው:
ሲኦልንና በሲኦል ያሉ ቅጣቶችን የሚያመለክተውን ስዕል ስመለከት አያታችን ምን ያህል ብልጥና ጨካኝ እንደሆነች እያሰብኩ ነበር ለምንድነው ስለ ሁሉ ነገር ማሰብ ያለባት? እግዚአብሔርም ራሱ ውጪ ስንትና ስንት መጥፎ
ነገሮች የሚሰሩ እያሉ ተቆጣጣሪ አይኖቹን በአራት ትንንሽ ልጆች ላይ ማድረጉ ፍትሀዊ አይደለም እኔ በእግዚአብሔር ቦታ ብሆን ኖሮ ሁሉንም ነገር ማየት የምችል ከመሆኔ አንፃር፣ የተቆለፈባቸውን አባት የሌላቸውን አራት ህፃናት በመቆጣጠር ጊዜዬን ከማጠፋ ሌላ በጣም የሚያዝናና ነገር ላይ
ትኩረት አደርግ ነበር በዛ ላይ አባታችን ያለው እዛው ከእግዚአብሔር ጋር ስለሆነ፣ እግዚአብሔር በደንብ እንዲንከባከበንና አንዳንድ ስህተቶቻችንን አይቶ እንዲያልፍ ሊነግረው ያስፈልጋል።

ክሪስ አኩራፊና ተቃዋሚነቴን ችላ ብሎ መፅሀፉን አስቀመጠና የመጫወቻውን ሳጥን አነሳ፡

“ምን ሆነሻል?” ሲል ጠየቀኝና የመጫዎቻውን ሠሌዳ ዘርግቶ ጥቁሩን በጥቁሩ፣ ቀዩን በቀዩ መደርደር ጀመረ፡ “ለምንድነው ፀጥ ብለሽ የተቀመጥሽው?
ለምንድነው የፈራሽ የመሰልሽው? እንደገና እንዳላሸንፍሽ ነው?”

ስለ እሳት ያሰብኩትን ለክሪስ ነገርኩት ከዚያ ልክ የድሮ ፊልም ላይ እንዳየሁት ከእሳቱ ለማምለጥ መሬት ላይ እንዲያደርሰን አንሶላውን ተልትለንና ቋጥረን
እንደመሰላል መስራት እንደምንችል አወራሁት “ምናልባትም ዛሬ ማታ እሳት ከተነሳ መስኮቱን ከስበርን በኋላ መሬት የምንደርስበት መንገድ ይኖረናል ማለት ነው እና እያንዳንዳችን መንትዮቹን አንድ አንድ ተካፍለን ጀርባችን ላይ
እናስራቸዋለን” አልኩት።

ሰማያዊ አይኖቹ በአድናቆት በሩ እንደዚህ አይነት አክብሮት ሲያሳዩኝ አይቼ አላውቅም፡ “ዋው ካቲ እንዴት የሚገርም ሀሳብ ነው! አስደናቂ ነው! ልክ ነሽ እሳት ቢነሳ ማድረግ ያለብን አሁን እንዳልሽው ነው ግን አይነሳም ከአሁን
በኋላ አልቃሻ ህፃን አለመሆንሽን ማወቄ በጣም ጥሩ ነው ስለ ወደፊት አስብሽ ሳይጠበቅ ለሚመጣ ነገር እቅድ ካወጣሽ አድገሻል ማለት ነው እናም
ወድጄዋለሁ” አለኝ።

ከአስራ ሁለት አመታት ከባድ ሙከራ በኋላ፣ ማግኘት ይቻላል ብዬ የማላምነውን የክሪስን አድናቆትና ማረጋገጫ የማግኘት ግቤን በመጨረሻ አሳካሁ በዚያች ደቂቃ በተለዋወጥናቸው ፈገግታዎች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ አብረን መዝለቅ እንደምንችል ቃል ገባን።

እናታችን እንግዳ ገፅታ ተላብሳ በሚያስቅ ሁኔታ እየተራመደች ወደ ክፍሉ መጣች መምጣቷን ለረጅም ሠዓታት እየጠበቅን የነበረ ቢሆንም፣ እንደገና
ከእሷ ጋር መሆናችን ግን የገመትነውን ያህል ደስታ አልሰጠንም ምናልባት
አብራት ተከትላ የመጣችው አያታችን በክፉ ግራጫ አይኖቿ ስትመለከተን ጉጉታችንን ገድላው ይሆናል።

አንድ ልክ ያልሆነ ነገር ተፈጥሯል፡ ምን ይሆን? ክሪስና እኔ አልጋ ላይ
ተቀምጠን ቼከርስ ስንጫወት የአልጋ ልብሱን በማጨማደድ የሰራነው ጥፋት የአያትየውን እይታ ስቧል።

አንድ ህግ ተጥሷል አይ ሁለት... መተያየትም የአልጋ ልብሱን እንደማጨማደድ ሁሉ የተከለከለ ነው።

መንትዮቹ ደግሞ ሲጫወቱ የነበረው የመገጣጠም እንቆቅልሽ እዚህና እዚያ
ተበታትኗል፡ የመጫወቻ መኪናዎቻቸውም በየቦታው ተዝረክርከዋል ክፍሉ ንፁህ አልነበረም

ሶስት ህጎች ተጥሰዋል።
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


የጀርመንን ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ለማሳሳት በርካታ ትላልቅ ብርማ
ቀለም ፊኛዎች ሰማዩ ላይ ያንዣብባሉ፡ ሱቆችና የመንግስት ህንፃዎች
ከቦምብ ናዳ ለመጠበቅ በአሸዋ በተሞሉ ጆንያዎች ዙሪያቸውን ተከበዋል፡
በየመናፈሻው የቦምብ
መከላከያ የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉም ሰው በእጁ የጋዝ
ጭስ መከላከያ ጭምብል አንጠልጥሏል ሰዎች በማንኛውም ደቂቃ በቦምብ
ናዳ እንደሚያልቁ ያስባሉ፡፡

ሄሪ ስለ አንደኛው የአለም ጦርነት ምንም ትዝታ የለውም፡ ጦርነቱ
ሲያልቅ የሁለት አመት እምቦቃቅላ ነበር፡፡ ነፍስ እያወቀ ሲመጣ ጦርነት
ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ አወቀ፡፡ በኋላም ፋሺስቶች በለንደን መንገዶች
ያደረጉትን ወታደራዊ ሰልፍ አዛውንት ይሁዳውያን በፍርሃት ሲመለከቱ
ሲያይ የጦርነትን አስፈላጊነት ተረዳ፡ሆኖም ሂትለር ሶቭየት ህብረትን
ይደመስስልኛል ብሎ የአንግሊዝ መንግስት የሆነውን ሁሉ እንዳላየ ሲያልፍ ጥላቻው ነገሰ፡፡

ሄሪ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ቤቱ መሄድ እንደሌለበት ወስኗል።
ፖሊሶች በዋስ በመለቀቁ ስለተበሳጩ በማንኛውም አጋጣሚ ሊያስሩት
አቆብቁበዋል፡፡ ለትንሽ ጊዜ መደበቅ ያዋጣዋል፡፡ ተመልሶ እስር ቤት መግባት
አይፈልግም፡፡ ታዲያ ስንት ጊዜ ፖሊስ መጣ እያለ ሲበረግግ ሊኖር ነው?
ሁልጊዜስ ፖሊስን መሽወድ ይቻላል? ካልሆነስ ምን ማድረግ ይኖርበታል?

እናቱ በሃዘን ፊታቸው ጠቁሯል፡ ገንዘብ እንዴት እንደሚያገኝ ቢያውቁም አንስተውበት አያውቁም፡፡ ‹‹በእናትነቴ ምንም አድርጌልህ አላውቅም›› አሉት ‹‹እማማ ያለሽን አድርገሽልኛል›› ሲል መለሰላቸው፡፡

‹ሃሰት፤ ምንም አላደረኩልህም፤ ለዚህ አይደለም መስረቅህ››
ሄሪ ለዚህ መልስ አጣ፡፡

ከአውቶብስ እንደወረዱ ጋዜጣ ሻጩ በርኒን እናቱን በስልክ ስለጠራለት
እንደውለታ ቆጥሮት ጋዜጣ ገዛው፡፡ የጋዜጣው የፊት ሽፋን ጀርመን ፖላንድን በቦምብ ደበደበች ይላል፡ ወዲያውም አንድ ፖሊስ በብስክሌት ሲመጣ ተመልክቶ በደመነፍስ ተርበተበተ፡፡ እግሬ አውጪኝ ሊል ሲያስብ ሰው ለማሰር ሁለት ሆነው የሚመጡ መሆኑን ሲያውቅ አደብ ገዛ፡፡

እንደዚህ እየሰጋሁማ እንዴት እኖራለሁ› ሲል አስበ፡፡

እቤት ሲገባ እናቱ ሻይ ጥደው ‹‹ሰማያዊ ሱፍ ልብስህን ተኩሼልሃለሁ፤ መለወጥ ትችላለህ›› አሉት

እስካሁንም ልብሱን የሚያጥቡለትና የሚያዘገጃጁለት ካልሲውንም የሚሰፉለት እናቱ ናቸው፡፡ ሄሪ መኝታ ቤት ገባና ከአልጋው ስር ሻንጣውንዐአውጥቶ ገንዘቡን ቆጠረ፡፡ ሁለት ዓመት በስርቆት ተሰማርቶ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ፓውንድ አጠራቅሟል፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት እጁ ገብቷል በሃሳብ ተውጦ ፓስፖርቱን እያገላበጠ ተመለከተው፡፡ ከአንድ አሜሪካዊ ላይ እንደመነተፈው አስታወሰ፡ የሰውየው ስም ሃሮልድ መሆኑን ሰውየውም
እሱን እንደሚመስል ተገነዘበና ኪሱ ከተተው፡

የአሜሪካውያንን የአነጋገር
ቅላጼ ይችላል፡፡ በአሜሪካ ውስጥ የእንግሊዛውያን የአነጋገር ቅላጼ ካለህ የከበርቴ መደብ አባል እንደሆንክ ተደርጎ ይቆጠራል፡ አሜሪካ ውስጥ በርካታ በፍቅር ልታሳብዳቸው የምትችላቸው ኮረዶች አሉ፡፡

እንግሊዝ ውስጥ የሚቀርበት እስር ቤትና ውትድርና ብቻ ነው፡፡
አሁን ፓስፖርትና ኪሱ ሙሉ ገንዘብ አለው፡ እናቱ ቁም ሳጥን ውስጥ ንፁህ ሱፍ ልብስ ያለው ሲሆን አንድ ሁለት ሸሚዝ መግዛት ይችላል።

ከሳውዝ ሃምፕተን 75 ማይል ነው የሚርቀው

ዛሬውኑ መሄድ ይችላል።

ሁሉም ነገር እንደ ህልም መሰስ ይላል።

እናቱ ‹‹ሄሪ ሳንድዊች ትፈልጋለህ?›› ሲሉ ጠየቁት

‹‹እሺ እማ››

ኩሽና ሄዶ ተቀመጠ፤ እናቱ ሳንድዊቹን ፊቱ ቢያደርጉለትም ንክች
አላደረገውም፡፡‹‹እማ አሜሪካ እንሂድ›› አላቸው
እናቱ በሳቅ ፈነዱ ‹‹እኔ አሜሪካ?!››
‹‹እውነቴን ነው፡ እኔ ልሄድ ነው፡››
አሁን ፈገግታቸው ጠፋ ‹‹ለኔ አይሆንም ልጄ፡፡ በዚህ እድሜዬ ስደት
ለኔ አይሆንም››

‹‹እዚህ እኮ ጦርነት ሊጀመር ነው፡፡››

‹‹አንድ ጦርነት፣ የስራ ማቆም አድማና የኢኮኖሚ መዳሸቅ አሳልፌያለሁ፡››

ጠባብዋን ማድቤት አማተሩና ‹‹የኔ ዓለም ይሄ ነው›› አሉ።

ሄሪ እናቱ በዚህ እንደማይስማሙ ቢያውቅም ቁርጡን ሲነግሩት ተስፋው ተሟጠጠ፡፡

በዚህ አለም ላይ ያሉት እናቱ ብቻ ናቸው፡፡

‹‹እዚያስ ምን ልትሰራ አስበሃል?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡

‹‹የሌብነት ስራዬ ያሳስብሻል?››

‹‹ሌብነት የትም አያደርስም፡ በሌብነት ያለፈለት ሰው አላውቅም›› አሉት፡፡

‹‹እዚያ አየር ኃይል ገብቼ አብራሪ መሆን እፈልጋለሁ፡ አሜሪካ ውስጥ ጭንቅላት ካለሽ የሰራተኛው መደብ ብትሆኝም ግድ የላቸውም።››

እናቱ በመጠኑ ፈገግ አሉ፡ እሳቸው ሻይ ሲጠጡ እሱ ሳንድዊቹን ይገምጣል።

በልቶ እንደጨረሰ ገንዘቡን ከኪሱ አወጣና ሃምሳ ፓውንድ ቆጥሮ ለየ
‹‹ይሄ ለምንድን ነው?›› ሲሉ ጠየቁ፡፡ ይህ ገንዘብ ሁለት አመት ልብስ አጥበው የሚከፈላቸውን ገንዘብ ያክላል

‹‹ይጠቅምሻል እማ ውሰጂው›› አለ፡፡

እናቱ ገንዘቡን ተቀበሉና

‹‹እውነት ልትሄድ ነው?›› ሲሉ ጠየቁት።

‹‹ወደ ሳውዝ ሃምፕተን በሞተር ሳይክል እሄድና መርከብ ላይ እሳፈራለሁ»
እጃቸውን ሰደዱና የልጃቸውን እጅ ለቀም አደረጉ፡፡ ‹‹ልጄ መልካም
ዕድል ይግጠምህ፡››

እሱም የእናቱን እጅ ጨበጥ አደረገና ‹‹ከአሜሪካ ገንዘብ እልክልሻለሁ አለ።

‹‹አያስፈልግም፡፡ ከዚያ ደብዳቤ ቶሎ ቶሎ ስደድልኝና ጤንነትህን
ልወቅ፡፡››

‹‹እሺ እፅፍልሻለሁ፡››

አይናቸው በእንባ ተቆረዘዘ ‹‹አንድ ቀን ናና አሮጊት እናትህን እያት››

እጃቸውን ጨበጥ አደረገ፡፡ ‹‹እመጣለሁ እንጂ እማ፡፡ እመለሳለሁ፡››
ሄሪ በመስታወት ከላይ እስከ ታች ራሱን አየ፡፡

ሰማያዊው ሱፍ ልብስ ያማረበት ሲሆን ከሰማያዊው የአይኑ ቀለም ጋ ሄዷል፡፡

ሸሚዙ የአሜሪካ ሽሚዝ ይመስላል፡ ፁጉር አስተካካዩ የባለ ሁለት
ደረት ኪስ ኮቱን ትከሻ በቡሩሽ ሲጠርግለት ሄሪ ጉርሻ ሰጠውና ወጣ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሳውዝ ሃምፕተን ወደብ በሰው ተጥለቅልቋል። ከዚህ ቦታ ነው የአትላንቲክ አቋራጭ ጉዞ የሚነሳው፡፡ በመሆኑም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች
ከእንግሊዝ ለመውጣት ይተራመሳሉ፡፡

ሄሪ መርከብ ለማግኘት ሲጠያይቅ የሁሉም መርከቦች ቦታ ለመጪዎቹ
ሳምንታት ጉዞ አስቀድመው እንደተያዙ አወቀ፡ አንዳንዶቹ የመርከብ ትራንስፖርት ድርጅቶች ባዶ ቢሮ ታቅፈው ለሰራተኛ ደመወዝ ከመክፈል በራቸውን ዘግተዋል፡ ለተወሰነ ጊዜ ምንም ቦታ የማይገኝ መሰለው።

በመርከብ መሄዱን ትቶ ሌላ አማራጭ መጓጓዣ ሲያፈላልግ አንድ የጉዞ ወኪል ባህር ላይ የሚያርፍና ከባህር ላይ የሚነሳ የፓን አሜሪካን
አውሮፕላንን እንዳለ
አበሰረው፡፡ ስለዚህ አይሮፕላን በየጋዜጣው ላይ
አንብቧል፡ መርከብ ወደ ኒውዮርክ ከተማ ለመሄድ አራትና አምስት ቀን
የሚፈጅበት ሲሆን አይሮፕላኑ ከ30 ሰዓት ባነሰ ይደርሳል፡ ታዲያ የአንድ
ጊዜ ጉዞ ትኬት ዋጋ 90 ፓውንድ አዲስ መኪና ይገዛል።

ሄሪ በርካታ ገንዘብ አባክኗል፡፡ እብደት ነው፡፡ ታዲያ ከአገር ለመውጣት
ሲል የፈለገውን ያህል ዋጋም ቢሆን ለመክፈል ወስኗል፡፡ አይሮፕላኑ ምቾቱ
ያጓጓል፡ ኒውዮርክ እስክትደርስ ድረስ ሻምፓኝ መጨለጥ ነው፡፡ እንዲህ
አይነት ቅንጦት ደግሞ ለሄሪ ነፍሱ ነው፡፡

ፖሊስ ባየ ቁጥር መደንበሩ ሊቀር ነው፡፡ ሳውዝ ሃምፕተን ውስጥ
ደግሞ ስለ እሱ ሌብነት የሚያውቅ ፖሊስ የለም፡፡ ከዚህ ቀደም በአይሮፕላን
በርሮ ስለማያውቅ ግን አዕምሮው ተረብሿል፡፡

ሰዓቱን አየ፤ከቤተመንግሥት አንጋች ላይ የመነተፈው ነው፡፡
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የሐመር ዕጽዋት ለምልመው፣ ንቦች ከአበባ ወደ አበባ እየተዘዋወሩና እየዘመሩ ሲቀስሙ፣ ከብቶች ጨሌ ሳራቸውን እያመነዠኩ ሲያገሱ፣ እንቦሶች ቃጭላቸውን እያቅጨለጨሉ ሲቦርቁ፣
ልጃገረዶችም ማሳውን እያረሱ ሲያዜሙ፣ ልጆች እራቁታቸውን ሆነው በቀስት ጫካ ለጫካ ተሪ ለመግደል ሲሯሯጡ በሚውሉበት፣
ጎረምሶች ሹልሹላ፣ ሹርባ...ጸጕራቸውን እየተሠሩ «አኖ» በተባለው አፈር ሰውነታቸውን በማዥጐርጐር ለማታው ጭፈራና ድሪያ ሲዘጋጁ፣ የብልታቸውን ጸጕር እየተላጩ በመኸር ጊዜ የሚዘፍኑትን ዘፈን ሲያዜሙ በሚውሉበትና ሐመር የክቱን የተፈጥሮ ሕይወት
ለብሳ ኗሪዎቿን በምታስፈነጥዝበት ወቅት ድንገተኛ ሁኔታ ታየ።

ካርለት አልፈርድ ሰቀላ ቤት አሠርታ መኖር ከጀመረች ዘጠኝ ወር አለፋት። ከሷ በስተግራ ከሃያ ሜትር ላይ የከሎ ክብ ጎጆ አለ።
በግቢያቸው የዱር አበባ፣ ቦዬ፣ ጉደሬ በቅሏል። ከነሱ ግቢ ራቅ ብሎ አለፍ አለፍ በማለት የሐመሮች መኖሪያ ይታያል። ካርለት ቤቷ ሆና
ፀሐይ ስትወጣ ከፊት ለፊት፣ ስትገባ ደግሞ ከበስተኋላ ሆና ልታያት
ትችላለች"

በእርግጥ በፖስት ካርድ ፀሐይ ስትወጣና ስትገባ አስደናቂ ፎቶዎችን ተመልክታለች። ሕይወት ያላት የሐመሯ ፀሐይ ግን ምሽት ላይ በተለያዩ ቀለማት ተውባ እንደ ዕንቁ እያንፀባረቀች አካባቢውን
ቀይ፣ ቢጫ ሐምራዊ ድብልቅልቅ ቀለማትን ስትለዋውጥ ስታያት
ግን በሕይወቷ ካየችው ውብ ነገር ይልቅ፣ በሐሳቧ የቀረፀችው የገነት
ውበት ይታያታል።

ታዲያ፣ በጣም ተመስጣ የአካባቢውን ውበት ስትመለከት ውበትን በትክክል ለማስቀመጥ፣ መጨመር የምትፈልገውንም
ጨምራ ለመርካት፣ ከአንትሮፖሎጂስትነቷ ይልቅ ባለቅኔ ወይንም
ሠዓሊ መሆን ያምራታል
ካርለት ያጣችው ነገር የለም አይባል" የዋና ቦታ አላገኘችም ኑሮዋ ዘመናዊ አይደለም" ያም ሆኖ ግን በሚያውዳት የተፈጥሮ
መዓዛ፣በስሜት በምትውረገረገው የምሽት ጭፈራ፣ ባየችውና
በቀረበችው ቍጥር ጥልቅ እሳቤን የሚጠይቃት የተፈጥሮ ምሥጢር፣ በንጹሕ ሕሊና የምታነባቸው መጻሕፍት የደስታ ሚዛኗን
ይጠብቁላታል።

አሸጋግራ የምታየው የሐመር ሰንሰለታማ ተራራ፣ መሸት ሲል ከየዋሉበት ብቅ ብቅ የሚሉት ሰዎችና እንስሳት፣ ስታንቀላፋ
የዋለችው መንደር፣ ሞቅ ሞቅ ደመቅ ስትል፣ ሁሉም ከፀሐይ ውበት ጋር ውሕደት፣ ቅንብር ሲፈጥሩ ስሜቷ ይረካል» እንዲያውም ከዚህ
ለየት ላለ ያልተበረዘ ተፈጥሮ ያላት ፍቅር «ምነው እናቴ፣ ወንድሜ፣ እኅቴና ስቲቭ ይህን ባዩ» ብላ፣ ቅን ሐሳብ እንድታልም
ያደርጋታል"

አንድ ቀን ግን፣ የተለመደ ትርዒቷን ስትመለከት፣ በግምት የአሥራ አምስት ዓመት ልጃገረድ፣ ከጥቁር ፍየል ለፍቶ የተሠራውን
ቆዳ ዙሪያዋን በነሐስና ጨሊ አስጊጣ ለብሳ፣ አንገቷ ላይ በደረደረችው ጨሌ ራሷን አሰማምራ፣ ዳሌዋንና ቀጥ ብለው ግጥም ያሉ ማራኪ የእግር ቅርፅዋን ስታይ ካርለት አፏን በአድናቆት ከፈተች
«በእርግጥ በጣም ቆንጆና ለየት ያለች ነች መቼም አይቻት እንደማላውቅ እርግጠኛ ነኝ» እያለች በባለ ሌንሱ ካሜራዋ ደጋግማ
ከርቀት አነሣቻት" ልጃገረዷ ካለምንም ሥጋት ወደ ካርለት ሰቀላ ቀርባ ሰላም ብላ ካርለትን ቆም ብላ ካየቻት በኋላ ጸጕሯን በጣቶቿ እሷም በተራዋ እየነካካች አድናቆቷን በሣቋ ገልጣ ልትሄድ ስትል
ካርለት «ወይ አምላኪ፣ አምላኬ! ኧረ ጥርሶቿስ እንዴት ያምራሉ!» አለችና እንድትቀመጥ ጋበዘቻት" ልጃገረዷ ግን፣ ካርለትን የቤት ውስጥ ሁኔታ አንገቷን አስገብታ ቃኝታ በድጋሜ
ፈገግ ብላ፣ «ደህና ሁኝልኝ» ብላ ሄደች"

ከሎ ሆራ የሐመሯን ውብ ቀደም አድርጎ ይመለከታት ነበርና ውበቷ ደንቆታል" በተለይ ወደ እሱ ቤት አቅጣጫ ስትመጣ ልቡ
መዝለል፣ ሐሳቡ መተረማመሱን ጨመረ። ከሎ ሆራ እስh ዛሬ
ታይቶበት የማያውቅ መርበትበትና ድንጋጤ ታየበት"

ልጃገረዷ፣ «ደህና ዋልህ» ብላው፣ ከተከፈተው የጎጆ ቤት መስኮት ላይ ተንጠልጥላ ስታይ እግሮቿ፣ ጭኗ፣ ዳሌዋና የሚሳበው
| ወገቧ ከሎን በሲቃ አፈኑት። ልጃገረዷ፣ የሚተኛበትን መኝታና
ዕቃዎቹን ተመልhታ ስትወጣ የሱም ልብ አብሮ ተከተላት እሷ እንደምታውቀው በማንኛውም የሐመር ቤት የሚገኝ ለመተኛ ቁርበት፣ ለመመገቢያና ለመጠጫ ሾርቃ (ከቅል የተሠራ)
እንስራ (ለሸፈሮ ቡና ማፍያ) ነው" ከነጯ ቤትና እንደ ሐመሮች መልክ ያለውና ጨርቅ ለባሹ ቤት ግን አይታው የማታውቀው ዕቃ
አለ" በኮተቱ ብዛት ትገረም እንጂ አልተደነቀችም“ እንዲያውም ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑት ቁርበት፣ ሾርቃ፣ እንስራ ቤታቸው
ውስጥ ባለመኖሩ ተደንቃለች።

ከሎ ቤቱ በር ፊት ለፊት ሆኖ ጠበቃት በሐመር ባህል ደንብ ልጃገረድ ከቡር ናት ካለፍላጎቷና ሳያግባባ መታገል የውርደት
ውርደትና ነውር ነው" ልጃገረድ እንደሚሰበር ዕቃ የሚጠነቀቁላት፣ እንደ ሕፃን ልጅ ፍላጎቷን የሚያከብሩላት መሆን ይገባል"ልጃገረድ የምትፈልገውን ወንድ ቀጠሮ ትሰጠዋለች" ያውም
ከተመቻት ነው" ካለበለዚያ፣ ካለ እሷ ትብብር አፈቀርኩ፣ ወደድኩ፣ በዚህ ወጥቶ በዚያ ወርዶ፣ ምን ሲባል ያን አይተሽ፣ እያሉ መሟዘዝ በባህሉ አይታወቅም
በሐመር ማኅበረሰብ ልጃገረድ ቀሳሚ ንብ፣ ወንዶች አበባ ናቸው" ባል ካገባች በኋላ ግን ሴት የባል ዕቃና ንብረት ናት።

ስለዚህ ልጃገረዷ ካለፍላጎቷ የሚደርስባት ችግር እንደሌለ
ስለምታውቅ ከሎን አልፈራችውም ከሎ ሆራ ግን ድንገት «እጅ ወደ ላይ» እንደተባለ ሰው ደንዝዟል" ካርለት የሁለቱን ሁኔታ
ከርቀት በጕጕት ትመለከታለች" ልጃገረዷ ሰላምታ አቅርባለት
መንገዷን ሰትቀጥል፣ ከሎ በባህሉ ኰራ ብሎ መታየት ሲገባው ተርበተበተ"

ሰንበት ብሎ ሲያስበው ራሱን ቢታዘብም በሕይወቱ በጣም አደገኛ ወጥመድ ላይ የወደቀበት ጊዜ ያ መሆኑን ራሱ ለራሱ አመነ"
ልጃገረዷ ግን ዳግመኛ ወደ መንደሩ አልተመለሰችም።

ሆኖም ከሎ፣ «ከየትኛው መንደር ይሆን የመጣችው? እጮኛ አላት ይሆን?» እያለ፣ በሐሳቡ መዋለሉ አልቀረም።

«...የሐመር ወንዶች ቢያፈቅሩም ፍቅራቸውን በግልጽ ማሳየት
ነውር ነው። ቢሆንም ልጃገረድን መዳራት ነውርነት የለውም» ብሎ፣
ከሎ የነገራትን ካረለት አስታወሰች"

ከሎ ሲቆዝምና ሐሳብ ሲያበዛ፣ ካርለት በፍቅር ሰመመን መዋጡን በመረዳቷ፥ «ከሎ ያችን ልጃገረድ እውን አፍቅሮ ይሆን? ፍቅሩንስ በምን መልክ ይገልጽ ይሆን? ባህላዊውን ወይስ ዘመን
አመጣሹን ይሆን የሚጠቀመው? ኧረ ኅብረተሰቡስ ምን ይሰማው
ይሆን?» በማለት፣ ካርለት በጥንቃቄና በተመስጦ ማሰቧን ቀጠለች።

«ምን ዓይነት ድንቅ ነገር ነው!» ሁሉም ነገር ምሥጢር ሆኖባት
ተገረመች። ስሜት ረቂቅ ነው፤ አይጨበጥም። ስሜት በአካባቢ ላይ
ተፅዕኖ ቢኖረውም፣ አካባቢም በስሜት ላይ ጫናው ከባድ ነው"
ማፍቀርና መፈቀር ተፈጥሯዊ ነውና ማንም ከዚህ ስበት ሊያመልጥ
አይችልም" ችግሩ ከፍቅር ቀጥሉ ግንኙነቱ በምን መልክ መሆን ይኖርበታል ነው። እኒህ ሁለት ሥረ ግንዳቸው አንድ የሆኑ፣ አካባቢያቸው ግን ለውጥ ያለው ሰዎች እውነት እንዳሰቡት ቢፋቀሩስ?»

አዲሱን ምርምሯን በተለያዩ መንገዶች ተጠቅማ ማወቅ
ይኖርባታል" «ከሎ ከልጃገረዷ ጋር ፍቅር ቢይዘው ልብስ በመልበሱ
ትንቀው ትችል ይሆን? አውሬ ወይንም የጎሳው ጠላት የሆነውን ሰው አልገደለም ከብት የለውም ስለዚህ ዘመናዊዋም ሆነች ቆዳ ለባሿ ሴት ክብርና ዝናን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈላጊ ስለሆነች
ላትቀርበው ትችላለች"»

«ከሎም ቢሆን ልጃገረዷን ለማግባት ኡክሊ ሆኖ በየዘመዶቹ መዞር፣ ከብት መዝለልና ለኮይታ (ጥሎሽ) የሚሰጠው ከብት፣
ፍየል፣ በግና ማር ማግኘት አለበት"
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ጊዜው የበጋ ወቅት እንደመሆኑ መጠን የሁዌልቫ አየር እጅግ ማራኪ ነበር።

ሁዌልቫ ሶራ ከወር በፊት ብርዳማው የክረምት ወቅት
ከመውጣቱ አስቀድሞ ካፖርቱን ከጥጥ የተሰራ የአንገት መጎናፀፊያውንና የሱፍ ቆቡን እያደረገ ወደ “ኢስላእ ክርስቲናእ"
ወደብ በመሄድ የአሳ ማጥመጃ ጀልባዎች በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ
ሲንሳፈፉ ዲካ አልባውንም የአትላንቲክ ውቅያኖስ አድማስ... ማየት
የመኪናውን ሙቀት መስጫ እንደከፈተም ከኮሎምበስ ሐውልት ስር ከተደረደሩትና የፍቅር አላማቸውን ከሚቀጩት ስፔናውያን ጎን
አቁሞ እያሸጋገረ የጠፋው ነገር እንዳለ ሁሉ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ማፍጠጥ ያዘወትር ነበር።

የአገሩን አፈር የአገሩን ባንዲራ ከኮለምበስ ሐውልት ሙዚየም ውስጥ አይቷል። ያ ጠንካራው የውሀ ጀግና ከዘመናት
በፊት ዘግኖ ያመጣውን የአገሩን አፈር ከግዙፉ ሐውልት ስር ካለው
ሙዚየም መስታዋት ውስጥ ተመልክቷል: አፈሩ ከወርቅና እንቁ
በላይ እንደሆነ ሁሉ አፍሶ ቢያሸተው ዘግኖ ቢጨብጠው እንደስኳር
ቢቅመው ተመኝቷል: ግን አልቻለም:: በመካከላቸው ጠንካራ መስታዋት አለ: የአፈሩን ጠረን ባፍንጫው ማሽተት እንኳን
ተመኝቶ አልተሳካለትም።

የአገሩ ባንዲራ የአቢሲኒያ ባንዲራ" ይላል አንጂ ቀለሙ ለቋል: ትክ ብሎ ሲመለከተው ግን ያ የቀስተ ዳመና ቀለም ያ ከህፃንነቱ ጀምሮ “የማሪያም መቀነት ለኔ..." እያለ ጮቤ የረገጠለት
ትምህርት ሲማር እንደገባ በጮርቃ አስተሳሰቡ በእንቦቀቅላነቱ.
አንጋጦ እያየ ያዜመለት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ባንዲራው ታየው ያኔ እጆቹን ዘርግቶ እንባው ከአይኖቹ እየፈሰሰ መስታዋቱ
ላይ ተደፋ።

“መለያዬ መታወቂያዬ...
የጥቁርነቴ አርማ... የነፃነቴ
ምልክት” ብሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለው ባንዲራ ንፋሱ “ጧ" እያደረገው "ሰማዩ ላይ ሲውለበለብ
ታየውና ሆድ ባሰው ባይተዋርነት ተሰማው ማንነቱን ያጣ ሆነ
ብቸኝነት ስለት ጥፍሩን አሹሎ መላ አካሉን ቧጠጠው: ውስጡ
ደማ በብሶቱ ህሊናው ደረቀ ስሩ እንደተቆረጠ እፅዋት ሲጠወልግ ሲወይብ እራሱን ተመለከተው: ስለዚህ ብሶቱን በእንባው ለውሶ
ወፍራሙ እንባው እንደጎርፍ የተሰበረ ልቡን እየሸረሸረው ወደ ውጭ ተደፋ። ማንነቱን ከአጣ ቆይቷል። ከርሱ ቢሞላም ህሊናው ግን
በፍርፋሪ ማንነት ሊጠግብ አልቻለም: እየሄደ ይቆማል እየሰራ ይቃዣል ሲስቅ እንባው ከየት መጣ ሳይባል በአይኖቹ ይሞላል...
“ማነህ?” ሲሉት እውነት ማን ነኝ! የማንነቴስ መለያ ምንድን ነው?  ለምንስ ዓላማ እኖራለሁ? ቅዠቴስ ለምን በረከተ? እውን የምበላውን የሚያፈራ አፈር የለኝም? የሚለበስ በታሪኩ
የሚያኮራ ባንዲራስ የለኝም..." ይልና በሃዘን ይንዘፈዘፋል።

ከወር በፊትም ያጋጠመው ይኸው ነው: የማንነት ረሃቡ
አይሎ ብቸኝነት በዚያ ስለታም አካፋው ህሊናውን እየሰቀሰቀ አንጎሉን ሲያቦካበት ህመሙ እየለበለበ ሲያቃጥለው ልቡ ሲደማ መስታዋቱ ላይ ተደፍቶ ኮሎምበስ ከዘመናት በፊት ያመጣውን
የአገሩን አፈርና ባንዲራ ተማፀነ።

“ምነው አምላኬ መግባባትንና መቻቻሉን ነፈግኸን። ምነው
የርሃብተኞች ምሳሌ አደረግኸን...” ሳግ ተናነቀው እንባው እንደ
ዶፍ ዝናብ ወረደ ንፍጡ ተዝረከረከ፡ በዚህ አጋጣሚ የሆነ ሰው ከተደፋበት ቀስ አድርጎ ቀና አደረገው: ሶራ ከሙዚየሙ ክፍል
ወጥቶ የአትላንቲክ ውቅያኖስ የማዕበል ነፋስ አካሉን ሲዳስሰው
የተለያየ ሃሳብ ተፈራረቀበት።
ከተደፋበት ያቃናው ግን ማን እንደሆነ ለምንስ ከሐዘኑ  እንዳናጠበው ለምን አብሮት
እንደሚራመድ አሰበ
ነፋሱ እየበረታበት ሀሊናው እየተስተካከለ ማሰብ ሲጀምር የያዘውን ሰው
ማንነት ለማየት ሞከረ።

ወፍራም ሰማያዊ ሹራብ
የፈረንሳዮችን ቡትስ ጫማ
የተጫማች ካፖርት ለብሳ ፀጉሯን በሱፍ ኮፍያ ብትሸፍንም በእንቢታ  ያፈነገጡ ፀጉሮችዋ ፊቷ ላይ ብን ብን እያሉ በሚያምረው ጠይም የፊት ቅርጿ ላይ የሚራወጡ፣ በግራ ትከሻው በኩል ወገቡን በእጆችዋ አቅፋው ተመለከተ።

ጡቷ ብብቱን ሊነካካው
ተገርሞ ትክ ብሉ አያት: ፈገግ አለችና አይኗን ሰበር አደረገች። በእርግጥ እርዳታዋ ራሱን መቆጣር እስከሚችልበት ድረስ በመሆኑ እስኪረጋጋ ጠበቀችው። ከዚያ

“ግራሊያስ” አላት በስፓንሽ አመሰግናለሁ ለማለት።

“ዴናዳ...” አለች ምንም አይደል ለማለት። ለቀቅ አድርጋው! አሁን የተረጋጋህ ይመስለኛል። ስለዚህ ብሄድ ይከፋሃል?" አለችው።
በዚህ ግላዊ ህይወት ጥልቅ መሰረት ያለው ፎቅ እየሰራ ባለበት ዓለም አፓርታማው ውስጥ የሚኖረውን ኗሪ በግል ህይወቱ ገብተው
“ለምን  ሳቅህ?... እያሉ መጠየቅ የግል ነፃነቱን እንደመዳፈር ስለሚቆጠር መርዳትና መተባበር የሚችሉትን ፈፅሞ ሌላውን ጣጣ ለባለቤቱ ትቶ ዘወር ማለት ተገቢ በመሆኑ ልጅቷ ካለምንም ጥያቄ፡-

“ደህና ሁን” ብላው ስትሄድ ከወገቡ በፊት እጥፍ ብሎ
አጆቹን ዘርግቶ እጅዋን ያዛት: በግርምታ ዘወር ብላ አየችው አያት እሱም: ወዲያው ሃፍረት ተሰማው ወንጀለኝነት ስሜት አደረበት።የያዛት እጁ እጅዋን አለቀቀም። እሷም ለማስለቀቅ አልሞከረችም።
እጁ ግን ሲንቀጠቀጥ ይሰማታል። ስሜቱም ሲለዋወጥ ተመልክታዋለች። ስለዚህ ልታፈጥበት ልትገስፀው አልፈለገችም:

“አዝናለሁ" አላት ፈገግ
ለማለት ቢሞክርም ቅንድቡ
እየተንቀጠቀጠ እያሳጣው።

“ለምን?” አለችው በፅሞና።

“ትንሽ እንድትቆይ መጠየቅ በመፈልጌ..." አላት ቀስ ብሎ እየተጠጋ።

“ማዘን አያስፈልግህም! ቶሎ መሄድ ስላሰብኝ ግን አሁኑኑ መሄድ አለብኝ።" እጆቹን ኪሱ ከተተና አድራሻውን የያዘውን ካርድ
እየሰጣት “ብትችይ ደውይልኝ አላት በትህትና።

“አዝናለሁ” ትከሻዋን ሽቅብ ሰበቅ አድርጋ “ወደ አፍሪካ
መሄድ ስለምፈልግ ጊዜ የለኝም።''

“አፍሪካ...” ከነበረበት ቅዠት ሙሉ ለሙሉ ነቃ።

“አፍሪካ የት?" አላት ፊቱ ላይ ደስታ እየታዩ፡

“አያቴ አገር... ኢትዮጲያ”  ስትለው  አለከለከ: ድንጋጤ
አይሉት ደስታ ላብ እስኪያሰምጠው ድረስ ተሸበረ:

“ኢትዮጵያ!... ኢትዮጵያ... ኦ! አምላኬ እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ። የሃዘኔም ጦስ ናፍቆት ነው..." ሲል ልጅቷ አይኖችዋን አጥብ
ተመለከተችውና

“ኮንችት”

“ምን?”

“ፔሶ ቤኒ ኮንቺት እባላለሁ። ነገ በአስር ሰዓት እዚሁ እንገናኝ አለችውና ሄደች።
በግርምታ ከአይኑ እስክትጠፋ ተመለከታት።

“…አያቴ አገር ኢትዮጲያ... ያለችው እንደገና ጆሮው
ላይ አቃጨለበት ደስ አለው። ስለ ኢትዮጵያ አብሮት የሚያወራ
አግኝቷል፡ ከጉጉቱ የተነሳ ግን ነገ ራቀበት: ያን ሩቁን ነገ እንግዳውን ነገ. መጠበቅ ግን ግዴታው ነበር።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሶራ መኪናው ውስጥ ሆኖ በሃሣብ ፈረስ ከርቀት ደረቱን እንደ ጎረምሳ ገልብጦ ከሚመጣው የአትላንቲክ ውቅያኖስ ማዕበል ይገባና አብሮ ብቅ ጥልቅ እያለ እየሰጠመ እየተንሳፈፈ ወደ ዳር
ይመጣና ካለው የሲሚንቶ ግንብ ጋር እየተጋጨ እንደ ጥይት ጮሆ.አረፋ ሲደፍቅ... እራሱን እያዬ መሪው ላይ ተደፍቶ ሲጨነቅ ተመልሶ ደግሞ አይኖቹን ውቅያኖሱ ላይ ተክሎ በሃሣብ ለረጅም ጊዜ ሲንቦራጨቅ በምናቡ አለም መግቢያ ጠፍቶት ሲዛክር ቆዬ:

ቶዮታ ኮሮላ መኪና ቀስ እያለች አልፋ ክፍቱ የመኪና
ማቆሚያ ላይ ተስተካክላ ቆመችና ሞተሯ ጠፋ: ለተወሰነ ጊዜ ፀጥታው እንደገና ሰፈነ። ከዚያ የአስር ሰዓት ደወል ተሰማ።
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ዘጠኝ

ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው፡፡የምሰራበት ሆቴል ቤርጎ ይዛለች፡፡ስራ እንደጨረስክ ና ብላኝ ስለነበረ ስራዬን ጨርሼ ወደእሷ ለመሄድ እየተዘጋጀው ነው፡፡ስደርስ በረንዳ ላይ ባለ ወንበር ላይ ኩርምት ብላ ቁጭ ብላለች አይኖቾን ሰማይ ላይ ሰክታ ፈዛለች፡፡ከጎኗ ቁጭ አልኩና‹‹ጨረቃን እያየኋት ነው እንዳትይኝ?››አልኳት፡፡

‹‹አልኩህ››

‹‹እራስሽን ምን አሳየሽ?››

‹‹ማለት? ››

‹‹ያው እንቺም ጨረቃ ነሽ ብዬ ነዋ...››

‹‹ጨረቃ ነሽ ስትል በቀጥታ ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››

"ከዚህ ንግግሬ ምን የማይገባ ነገር አገኘሽበት... ጨረቃ ነሽ ስል አደንዛዥ የሆነ ውበት ባለቤት ነሽ ማለቴ ነዋ።"

‹‹ጨረቃ እውነትም እንደምትለው አደንዛዥ ውበት አላት ?››

" የላትም እንዴ?"

‹‹እኔ ምን አውቄ እንደዛ ስላልከኝ ነው..ይህቺን አባባል ሁሉም ሰው ይጠቀማታል …ግን በትክክል በምሽት ስራዬ ብሎ የቤቱን በራፍ ከፍቶ በረንዳ ላይ ወጥቶ አንገቱን ወደ ሰማይ አንጋጦ፤ አይኖቹን ጨረቃ ላይ ተክሎ፤ ውበቷን ያስተዋለ ድምቀቷን ያጣጣመ..  ከመቶ ሺ አንድ ሠው ይገኝ ይመስልኸል...ግን ዝም ብሎ ስለሚባል ብቻ ትክክል ይሁን አይሁን ሳያውቅ ሁሉም ይደሰኩራል....

"እና ማጠቃለያሽ ጨረቃ ቆንጆ አይደለችም ነው?›

"አይ ነችምም አይደለችምም..ለምሳሌ እኔ ቆንጆ ነኝ?"

"ግጥም አድርጎ ...በጣም ውብ ነሽ"

"ከዚህ በፊት ሁለት ሰዎች ቀጥታ አሁን አንተ እንደቆምከው ፊቴ ቆመው ምንሽም የማያምር አስቀያሚ ሴት ነሽ ብለውኝ ያውቃሉ።እንደውም እንደዛ አይደለም.አስቀያሚ ወንዳወንድ ነገር ነሽ ነው ያሉኝ፡፡››

"እና ማንኛችንን አመንሽ?"

"ሁለታችሁኑም"

"ሁለታችንንማ ልታምኚ አትችይም ..አንቺ ወይ ቆንጆ ወይ አስቀያማሚ ነሽ.."

"አይ እንደየሁኔታው ቆንጆም አስቀያሚም ልሆን እችላለሁ...ውበት እንደየተመልካቹ ነው በሚለው ንግግር አምናለሁ...ለዚህ ነው ቆንጇ ነሽ ሲሉኝ ብዙ የማልፈነጥዘው አሰቀያሚም ሲሉኝ አንገቴን የማልደፋው።"

‹‹እና ማየቴን ላቁም?››

‹‹እንዳሰኘህ…ግን ጨረቃ በትከክልም  ምን ግዜ ውብ እንደምትሆን ታውቃለህ?››
‹‹አላውቅም ንገሪኝ ››
ጦር ሜዳ ፊት ለፊት ግምባር ላይ እያለህ የሆነ ግዳጅ  ተሰጥቶህ ከጓደኞችህ ጋር ድቅድቅ ባለ ጨለማ እየተጓዝክ መንገድ ጠፍቶህ ከጠላት ምሽግ ሰተት ብዬ ገባሁ ወይስ የጠላት ደጋፊ ከሆኑ ህብረተሰብ እጅ ወደቅኩ እያልክ አቅጣጫህን እንዴት እደምታስተካክል ግራ ገብቶህ እያለ ድንገት ብልጭ ብላ ስትወጣ…ከዛ እየደመቀች ስትሄድ….በቃ ውብ መሆኗ የሚገባህ የዛን ጊዜ ነው፡፡ምክንያም ህይወትህ የምታድንበት ጭላንጭል እድል ሰጥታሀለችና፡፡
‹‹ወይም ደግሞ›› ብዬ እኔ ቀጠልኩላት
‹‹ወይ ደግሞ.. በጣም የምትወጃትን ማለቴ የምታፈቅሪያት ልጅ  አባትዬው ከእቅፍሽ ነጥቀው ለሌላ ሊድሩብሽ መሆኑን ስትሰሚ እሷን በጠፍ ጨረቃ ከቤት አስኮብልለሻት በየጫካው ይዘሻት ስትጠፊ በዛን አስደሳችና ጭንቀት በተቀላቀለበት ወሳኝ ሰዓት ለመንገድሽ ብርሀን ሆና ከፊት ለፊትሽ ቦግ ስትል .. በዛን በክፉና በደስታ ቀን የመንገድሽ አጃቢና መሪ ብሎም  ለፍቅርሽም ድምቀት ስትሆን…አዎ የዛን ቀን ነው ጨረቃ ከውብም ውብ መሆኗን በደንብ የሚገባሽ››
‹‹አየህ ጨረቃን እንደየልምዳችን ነው ለውበቷ ትርጉም የሰጠነው..››
‹‹እንደልምዳችን  ማለት?አንቺ ወታደር ነሽ እንዴ?››ግራ ገብቶኝ ጠየቅኳት፡፡
‹‹አይ ማለቴ ጓደኛዬ ወታደር ነው….ታውቃለህ አይደል?››
‹‹አዎ የበቀደምለታው ጄኔራል አይደል?››
‹‹አዎ ..እሱ ነው››
‹‹ግን…እንዲህ ከሌላ ሰው ጋር በምትሆኚበት ጊዜ ችግር አይፈጥርብሽም?››
አይኖቾ በንዴት ግልብጥብጥ አሉ….‹‹እንደዚህ ከማን ጋር ስሆን አይተኸኛል?›አፋጠጠችኝ፡፡
‹‹አረ አረጋጊው…ከእኔ ጋ ለማለት ፈልጌ ነው›
‹‹ካንተ ጋርስ ምን አድረግናል?››
‹የባሰ አለ ሀገርህን አትልቀቅ› ይላል የሀገሬ ሰው..ድንብርብሬ ወጣ…ምን ብዬ በንዴት ወደላይ የተመነጠቀ ስሜቷን  ልመልሰው?‹‹ምንም አለማድረጋችንን እኮ የምናውቀው እኔና አንቺ ብቻ ነን…ቢያንስ ሁለት ቀን አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ አድረናል…››
‹እ..እሱስ እውነትን ነው….ግን ያ ምንም ችግር የለውም..እሱም አመቱን ሙሉ ከሚስቱ ጋ ሲተኛ እኔ ምንም ብዬው አላውቅም፡፡››
‹‹ሚስቱ?›
‹‹አዎ ሚስቱ….ሚስትና ሶስት ልጆች አሉት››
‹‹ከባድ ነው››
‹‹አዎ ፍቅር ምን ጊዜም ቀላል ሆኖ አያውቅም››
‹‹ግን ምንድነው ስራሽ..?››
‹‹እሱን ማፍቀር?››
‹‹አይ ስራ መትተዳደሪበትን  ነው የጠየቅኩሽ..?››
‹‹ነገርኩህ ስራዬ እሱን ማፍቀር ነው….ገንዘብ ማገኝበትን ከሆነ የጠየቅከኝ ሌላ ጊዜ ነግሀለሁ…ግን ለራሴ የሚበቃ በቂ ገቢ አለኝ፡፡››
‹‹አይ ጥሩ ነው‹‹
‹‹ጥሩ ባይሆንስ ምን ምርጫ አለኝ....በል አሁን ይብቃን ገብተን እንተኛ››
‹‹አዎ ተነሽ.. ግን እኔ ወደቤቴ ልሂድ››
ፈገግ አለች‹‹ምነው ምን አሳቀሽ?››
‹‹አይ ወደቤት ልሂድ አባባልህ እራሱ ያስቃል..ምነው የጄኔራሉ ሽጉጥ ፊትህ ላይ ሲደቀንብህ በምናብህ አየህ እንዴ ››
‹‹ቀላል…ትቀልጂያለሽ እንዴ…?ገና በቅጡ እንኳን ያላየኋት እና ያላሰደኳት ልጅ አለችኝ..ድፍት ቢያደርገኝ ምን እላለሁ፡?፡››
ከተቀመጠችበት ተነስታ እጄን ይዛ ወደክፍሏ እያመረን ነው.. በራፍ አካባቢ ስንደርስ ነው ስለልጄ የነገርኳትን …ስትሰማ በድንጋጤ እጄን ለቀቀችና ባለችበት በመቆም አፍጥጣ አየችኝ፡፡
‹‹አንተ የእውነትን እንዳይሆን?››
‹‹ግራ ገባኝ ..ስለፍቅረኛዬ እያወራኋት ቢሆን ልሸመጥጣት እችል ነበር ..የልጅ ነገር ግን እንዴት አድርጌ…?መጀመሪያ አዳልጦኝ የተናገርኩ ቢሆን ወደኃላ ልመልሰው ግን እልፈለኩም …ቀጠልኩበት፡፡
‹‹አዎ ልጅ..አለቺኝ..የ7 አመት ልጅ..ተአምር ትባላለች››
‹‹ከዚህ በፊት ግን ፍቅረኛም ሚስትም እንደሌለህ የነገርከኝ መሰለኝ››
ይሄን ደግሞ መች ይሆን የቀባጠርኩላት…ማስታወስ አልቻልኩም፡፡አሁን ወደፊት ተንቀሳቅሰን በራፍ ጋር ደርሰናል….በእጇ ያንጠለጠለችውን ቁልፍ በማስተካከል በራፉን እየከፈተች ነው‹‹አዎ አሁንም  ሚስትም ፍቅረኛም የለኝም ….እውነቴን ነው››
ወደውስጥ ገባች…ሄዳለሁ ያልኩት ሰውዬ ተከትያት ወደውስጥ ገባሁ ..መልሳ በራፉን ከውስጥ ቆለፈችው፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡ከጎኗ ተቀመጥኩና ወሬዬን ቀጠልኩ፡፡
‹‹ነገሩ ውስብስብ እና የድሮ ታሪክ ነው… ሀይስኩል ተማሪ እያለው ነው የልጅ አባት የሆንኩት››
‹‹ታድለህ….ምን አለ እኔም ከእናቴ ቤት ሳልወጣ አንድ ዲቃላም ቢሆን ወልጄ በሆነ››
‹‹እውነትሽን ነው?፡፡››
‹አዎ..እውነቴን ነው…..የህይወቴ አንዱ ህመም የልጅ እናት ካለመሆኔ ጋ የተያያዘ ነው…››አይኖቾ በእንባ ተሞሉ…አረ ዘረገፈችው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ አሁንም  ይቻላል.. ገናነው አልረፈደም…ሶስትም አራትም ልጅ መውለድ ትችያለሽ››
ኩስትርትር ብላ‹‹መቻሌን በምን አወቅክ?››በሚል ጥያቄ አስበረገገችኝ፡፡
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ዘጠኝ

"ይእ!ጥሩ ነው እንጂ ካርለቴ  ባልሽ በመታሽ ቁጥር የፍቅር ጥገትሽ ይጨምራል ለባልሽ የሚያስገሳውን ፍቅር ትሰጭዋለሽ እሱም እንደ ክረምት ዝናብ በፍቅሩ ያርስሻል ያን ጊዜ ይበልጥ
ትቀራረባላችሁ
በሐመር ሴት ሁለት ሶስት እስት ትወልድ ድረስ ባሏ
እንዲመታት ሰበብ ትፈጥራለች ልጃገረድ እያለሽ በኢቫንጋዲ
ላይ ዘመድሽ አብረሽኝ አልደነስሽም ብሎ ወይ ሌላ ምክንያት ፈጥሮ ይገርፍሻል" ዝምድናውን ለማጥበቅና አንድትግባቡ መፈለጉን ስለምታውቂ አትቀየሚውም ዘመድሽ ካልገረፈሽ ጠልቶሻል ወይንም ተቀይሞሻል ማለት ነው" ችግር ቢመጣ አይደርስልሽም

"ዘመድሽ ከብት ሲዘል እየፎከርሽ የምትገረፊውም የእሱን ዝምድና ለመግለፅ ሲሆን ያን አይቶ መከታሽ ይሆናል" ባልሽ ዘንድ
ስትሄጂም እንዲቀርብሽ:
ዘመድ እንዲሆንሽ
እንዲመታሽ ታደርጊያለሽ ያኔ ይመታሽ ይመታሽና

የኔ ሸጋ ... የኔ ወለላ
አርጊ ያልኸኝን ከአሁን ጀምሮ አንተን
አደርጋለሁ ስጭኝ ያልኸኝን እሰጥሃለሁ ማስደሰትና ልጅ መውለድ ይሆናል ስራዬ ስትይው እንደ ማሽላ
ዱቄት አፍሶ ደረቱ ላይ ነስንሶሽ ጫካ ውስጥ ይገባል አንች ደግሞ
እንደ አለቅት ደረቱን እየበሳሽ ሙቅ ልቡ ወስጥ ትገቢና ጎዝጉዘሽ
ትተኛለሽ ልቡ ውስጥ ሆነሽ ጡትሽን ሲዳስሰው ሁለመናሽን ሲያሸው
ለሴት ልጅ ከዚህ የበለጠ ምን ደስታና ጣእም ያለው ህይወት ይኖራታል!" አለች ጎይቲ ያቆመችውን ፀጉር መስራት ለመጀመር ካርለትን ወደ ጉያዋ ሳብ እያደረገቻት።

"ጎይቲ ታዲያ ዱላ ለሐመር ሴት የፍቅር መግለጫ ነው?"

"ይእ! ልጃገረድ ሆነሽ ዳንስ ቦታ የለመድሽው ፍቅር ባልሽ ዘንድ ስትሄጂም የሚጠብቅሽ ፍቅር  ዱላ ነው"

"እናንተ አገር የፍቅር መግለጫችሁ ምንድን ነው?"

"መተሳሰብ: መሳሳም …"

"ይእ! ታለ ግርፊያ መተሳሰብ የተኮመታተረው ስሜትሽ ተመታቶ ሳይፍታታ መሳሳም በአፍንጫዬ ይውጣ! ምን ኑሮ ነው
እቴ!"

"ስላለመድሽው እንጂ …"

"ይእ! በይ ዝምበይ
እኔ የሌሎችን ነገርሁሽ እንጂ እኔማ ልምዴን ተገፍፌ እንደ ምትታለብ ላም ዳሌየንና ጡት ስሬን
የሚያሽ ባል አግብቻለሁ" እንዲያው ግን ካርለቴ  ከሎ የልምዴን ሰጥቶኝ እንዲህ ማህፀኔ ቢደርቅ እኮ አይከፋኝም  ነበር, ከዛሬ ነገ
ወንድ ወንድ ይሸተኛል ስል ከዛሬ ነገ የወንዶችን ለበቅ ያነሳል ስል ዕጣ ፋንታዬ እንዲህ ይክፋ  ካርለቴ!" ብላ ምርር ብላ አዘነች

"አዝናለሁ ጎይቲ
ግርፊያ ለሐመር ልጃገረድ እንዲህ እንደ ውቅያኖስ ወለል የጠለቀ ትርጉም ያለው አይመስለኝም  ነበር!
ስትላት ጎይቲ ውቅያኖስ ያለችው ባይገባትም

"ይእ! የአባት ደንብ አይደል ካርለቴ እናትሽ ባልሽ ዘንድ
ከመሄድሽ በፊት ባልሽ ሲመታሽ አታልቅሽ የባልሽ ጓደኞች ወደ ቤትሽ ሲመጡ ከጎሽ ቆዳ የተሰራ ጫማቸውን ጠመንጃቸውን ተቀብለሽ ተቀብለሽ ቤት አስገቢ ቀጥለሽ ከውጭ ቁርበት አንጥፈሽ ሸፈሮ ቡና አፍይላቸው" የባልሽን የአደን ጓደኛ ሚሶ'
የዝላይ ወቅት ጓደኛውን ባርግያ በይ በባራዛ አርጩሜ ገርፈው
ምን ተሰማሽ?  ሲሉሽ ፈገግ ብለሽ ምንም በያቸው ያን ጊዜ በማርና ወተት ያደገች ተጨዋች ናት ብለው ይግባቡሻል" ለባልሽም
አንችን አሞጋግሰው ስለሚነግሩት ይቀርብሻል"

"ሲመቱሽ ካለቀስሽና አንገትሽን ከደፋሽ ግን ከብትና ፍየል አልጠበቀችም ቀፎ አልሰቀለችም ድሀ አደግ ጨዋታ የማታውቅ
እንደ አነር ቁጡና ክፉ ናት ብለው ይጠሉሻል" ያን ሲሰማ ደግሞ ባልሽም ይጠላሻል ይርቅሻል ውሎው ከሌላ ሴት ጋር ይሆናል እያሉ ዘመዶችሽ መክረውሽ አለት ድንጋይ ልብሽ ውስጥ ጨምረሽ
ጠንካራ እሆናለሁ ብለሽ ባልሽ ዘንድ ሄደሽ  የጠበቅሽውን  ሁሉ
ስታጭው ምነው አትራቢ ምነው አታዝኝ!" ብላ ጎይቲ እንባዋን ፀጥ ብሎ እንዲፈስ ከፈተችው

ካርለትም ዐይኖችዋ በእንባ እንዳቀረዘዙ ጎይቲን እያባበለች አንድ ቃል በህሊናዋ ብልጭ ብሎ ድርግም አለ ፈለገችው
ያን ቃል ፈረንሳዮች ፍላጀላሲዬን ይሉታል እንግሊዞች ደሞ
ፍላጄሌሽን  ደስ አላት ህሊናዋ ከትውስታው ክፍል ጀባ ያላትን ቃል ወደ ኖረበት ተመልሶ ሳይገባ አፈፍ አድርጋ ስለያዘችው

ፍላጀላሲዬን ስርዓት ባለው ወይንም ሃይል በተሞላበት
መንገድ በሃይማኖት ተከታዮች የሚፈፀም ግርፊያ ነው" በብዙ
የሃይማኖት ተቋማት ፍላጀላሲዬን በመባል የሚታወቀው ግርፊያ
የርኩስ መንፈስ የማስወጫ ስልትና መፈወሻ ዘዴ ተደርጎ ይቆጠራል"በጥንት "ዘመን የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በግርፊያ መሰቃየትን እንደ
አምልኮዋዊ ፀጋ ይቆጥሩት ነበር በነዚህ ህዝቦች እምነት መገረፍ ወይን በአካላዊ ጉዳት መሰቃየት ከሃጢያታቸው መንፃታቸውን፥ከመቅሰፍት
መዳናቸውን የሚያረጋግጡበት
ሆኖ ሲታመንበት ቆይቷል

በሰሜን አሜሪካ ህንዶች: በስፖርታዎችና በሮማውያን
ግርፊያ የአማልክትን ወይንም የቅድመ አያቶችን
ምስል ጭንብል
ባጠለቀ ገራፊ የሚፈፀም ነበር" ይህ ድርጊት በአስራ ሶስተኛው ክፍለ
ዘመን አጋማሽና በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመንም ቀጥሎ እንደ ጀርመን: ሆላንድ በመሣሰሉት አገሮችም ተስፋፍቶ ቆይቷል በብዙ አገሮች በበዓላት ቀን ወንዶች ጀርባቸውንና ደረታቸውን በአለንጋ
ይገረፋሉ።

ይህ አምልኮዋዊ እምነት እ.ኤ.አ. በ1349 ዓ.ም እንደነበሩት ፓትሪያርክ ክሌመንት በመሳሰሉ  የሃይማኖት አባቶች ከረር ያለ ተቃውሞ ግርፊያ እየቀነሰ ቢመጣም በአሁኑ ዘመንም በደቡብ
የአውሮፓ ሀገሮች በላቲን አሜሪካውያንና በመካከለኛውና ሩቅ
ምስራቅ አገሮች የተለመደ ነው ለምሳሌ በታይዋን የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በየአመቱ በስቅለት ቀን እንደ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መገረፍ: መሰቃየት: እጅና እግርን በሚስማር መቸንከር
የእየሱስ ክርስቶስን ፍቅር እንደ ማግኘት ምድራዊ ሃጢያትን እንደ መቀነስና ለሰማያዊው ህይወት በክብር መዝገብ እንደመመዝገብ
ይቆጠራል

ከዚህ ውጭ ግን ዘመንሁ በሚለው ህብረተሰብ በሁለቱም ፆታ ግርፊያ በብዙ ግለሰቦች የወሲብ ስሜት መቀስቀሻ ወይንም የወሲብ ስሜት ማርኪያ ስልት እንደሆነና የገራፊ ልብሶችና የመግረፊያ
አለንጋዎች የሚሸጡባቸው የወሲብ ሱቆች
በርካታ እየሆኑ
መጥተዋል እኒህ ግርፊያን እንደ ወሲባዊ የችግር መፍትሔ የሚቆጥሩ
ሰዎችን የስነ አዕምሮ ጠቢባን የስነ-አዕምሮ
ችግር ያለባቸው እንደሆኑ በመቁጠር ብዙ መላ ምቶችን እየደረደሩ ቢሆንም
የመገረፍ ፍላጎት ወይንም ሱስ ግን አንድም የተፈጥሮ ባህሪ ውጤት ወይንም እምነት የፈጠረው ፍላጎት ስለመሆኑ አያጠራጥርም ብላ አሰበችና የሐመሩ ግርፊያም ባህላዊ እምነት የፈጠረው የህሊናና
የአካል ዝግጁነት ውጤት ነው ብላ ደመደመች።

እየጨለመ ሲመጣ የእሳቱ ወጋገን ይበልጥ እየጎላ  እየጎላ መጣ ወጣቶች ለስነ-ስርዓቱ ከሰበሰቡት እንጨት በተጨማሪ ከጫካ
ግንዲላውን: ጭራሮውን እየተሸከሙ እያመጡ ይከምራሉ ጥቂት ጎረምሶች ደግሞ ለወጠሌ ጥብስ የሚሆነውን ችካል በጩቤያቸው ይጠርባሉ  ሌሎች የእድሜ ጓደኛ ጎረምሶች ደግሞ ከሳቱ ርቀው ተሰብስበው ያወጋሉ፤ አንዳንዴም
በተቀቡት ዥንጉርጉር የአኖ ቀለም ከሹልሹላቸው
ለዳንሱ ዝግጅት
የሰጎን ላባ ሰክተው
ጨሌያቸውን አንገታቸው
ላይ ደርድረው ግንባራቸው ላይ የጨሌ ገመድ
ቋጥረው ዳንሱንና ድሪያውን ናፍቀው ውስጥ ለውስጥ ይቋምጣሉ አልደርስ ብሏቸው"

"ሚሶ!" አለ አንዱ
አለ አንዱ ከመሀላቸው የአደን ጓደኞቹን የሰአት ማሳለፍያ ጨዋታ ሊያወጋቸው።
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ስትባንን በመስኮቱ ሾልካ የገባችው ፀሀይ ልክ አልመው የለቀቋት ይመስል ደረቷ ላይ በጡቶቾ መካከል የአካፋዩ መጀመሪያ ላይ አርፋለች.. ከተኛችበት ቦታ ንቅንቅ ሳትል ነው የነቃችው…አንገቷን ጠምዝዛ ወደጀርባዋ ስትመለከት አልጋው ባዶ ነው…
‹‹እንዴ የት ሔደ…?››ብላ ዞር ስትል
‹‹አለሁ እዚህ ነኝ››አላት… ወደ እዛኛው ክፍል በሚወስደው በራፍ ዳፍ ላይ ፊቱን ወደእሷ ዞሮ በትኩረት እየተመለከታት ነበር፡፡
‹‹ውይ ስንት ሰዓት ሆነ?››ጠየቀችው፡፡

‹‹3፡10፡፡››

‹‹እየቀለድክ ነው?››

‹‹በፍፅም..ምነው የምትሄጅበት ቦታ ከሌለሽ ዛሬ እኮ እሁድ ነው..የእረፍት ቀን ነው?››

‹‹አይ እኔ እንኳን ስራ ፈት ነኝ ..አንተን ስራ ካስፈታሁህ ብዬ ሰግቼ ነው፡፡››

‹‹አይ በፍፁም እኔን ስራ አታስፈቺኝም…ጉዳይ ቢኖርብኝ  እኮ መልዕክት ጥዬልሽ ሄድ ነበር፡፡››

‹‹ዳግመኛማ እንደዛ አታደርግም…፡፡››

‹‹ለምን?›› አለ ግራ በገባው ፊት፡፡

‹‹እንደዛ አድርገህ እኮ በቀደም ላፕቶፕህን ይዤብህ ሄድኩ …ዛሬ ብትደግመው ጠቅላላ ቤትህን አስጭኚ ልወስደው እችላለሁ፡፡››

‹‹እሱ አያሳስበኝም..ይልቅ አሁን ታጠቢና ወደሳሎን ነይ.. የሰራሁትን ቁርስ እንዲቀዘቅዝ አታድርጊ..፡፡››አላት..ለመመፃደቅ ሳይሆን እውነቱን ነው የነገራት…

አሁን እሱ ለቁሳቁስ የሚጨነቅበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው….በቅርብ በዙርያው የኮለኮላቸውን መገልገያ ዕቃዎቹን በጠቅላላ እርግፍ አድርጎ ትቶቸው እንደሚሄድ ያውቃል..ምን አልባት እሷ እንዳለችው  ዛሬውኑ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉ ጫጭና ብትወስድ መሄጃ ቀኑን ከማፍጠኗ ውጭ ሌላ የምታደርስበት ጉዳት ወይም የኑሮ መፋለስ የለም፡፡አሁን እዚህ ቦታ እዚህ ከተማ ውስጥ አስሮ ያቆየው አንድ ጉዳይ ብቻ ነው…የፍቅረኛው ጉዳይ…የእሷን የወደፊት ህይወት መሰረት ካስያዘ በቃ ሌላ የሚቀረው ነገር የለም፡፡

  ልዩ ስለምግብ ሲያወራት በቀደም የበላችውን ምግብ አይኖቾ ላይ  ድቅን  አለ…  እናም በዛው ቅፅበት እስከአሁን ልብ ያላለችው የሚያውድ የምግብ ሽታ አፍንጫዋን ቆጠቆጣት…ቶሎ ብላ ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች…5 ደቂቃ ያህል    ነው የወሰደባት፡፡፡ሳሎን ስትገባ ቀለል ያለ ቆንጆ ቁርስ ተሰናድቶ ጠበቃት…ልክ አስደሳች ጀብዱ እንደሰራ ማራኪ ፍቅረኛ እየተፍለቀለቀች ለቁርስ ቀረበች፡፡ከፊት ለፊቷ ሆኖ እጁን ወደምግቡ ይዘረጋል ስትል  ሁለቱንም እጆቹን አንድ ላይ በማጣመር ወደግንባሩ ወሰደና ወደላይ አንጋጠጠ..፡፡ሊፀልይ መሆኑ ገባትና አብራው መፀለይ ባትችልም በዝምታ መከታተል ጀመርች‹‹….ጴንጤ ይሆን እንዴ ይሄ ልጅ;?›› በውስጧ እራሷን ጠየቀች እሱ ከንፈሩን በማነቃነቅ ሚሰሙ ቃላቶችን ከአንደበቱ እያወጣ ፀሎቱን ቀጠለ…
‹‹ለውስጣችን  የሚስፈልገንን ኃይል በትክክለኛው መንገድ እድናገኝ እርዳን….ይሄ ምግብ የተቀደሰ ይሁን…ይህ ምግብ ያለውን ኃይል አሞጦ ለእኛ እንዲሰጥ በፍቅርና በትህትና እጠይቃለሁ…ኃይሉም ለውስጣችን ጉልበት፤ ለአካላታችን ጤና እና ለመንፈሳችን ብርታትን ለአእምሮአችን ደግሞ  በጎ በጎውን  የማስብ ብቃትን እዲያጎናፅፈን ይሁን፡፡
አሜን
ጨረሰና‹‹..ብይ››አላት
ከመደነቋ ሳትወጣ‹‹..እሺ›› ብላ ለመብላት እጇን ዘረጋች..እንዲህ አይነት ፀሎት የትም በማንም ሲፀለይ ሰምታ አታውቅም‹‹….ከምን አይነቱ ተአበኛ ሰው ጋ ነው ፈጣሪ ያገናኘኝ፡፡››ስትል በውስጧ አብሰለሰለች፡፡
ማሰቧን ለሰከንድም ሳትገታ ቁርሷን ግን ጥብስቅ አድርጋ  በላች…የእሱ አበላል በጣም የተለየ ሆኖ ነው ያገኘችው ….በጣም ስርአት ያለው በፅሞና የታጀበ .ረዘም ያለ ማላመጥ ያለበት ነው፡፡
‹‹…የዚህ ልጅ ፍቅረኛ እንዴት ታድላለች?››

‹‹ምን አልሺኝ?››
ለካ ድምጻን ከፍ አድርጋ ነበር ያጉረመረመችው
በእፍረት አይኖቾን ከወዲህ ወዲያ እያቁለጨለጨች፡ ‹‹ማለት… ያው ለማድነቅ ፈልጌ ነው፡፡››አለችው..
‹‹አይ ምንም የሚደነቅ ነገር የለውም..እኔ በተቻለኝ መጠን የሚጣፍጥ ምግብ መመገብ እፈልጋለሁ…ምን አልባት መጠኑ ካልሆነ በስተቀር አንቺም ባትኖሪ ማበስለው እንደዚሁ ነው..እና ሌላ እንግዳም ቢሆን…››
‹‹እና ላንቺ ብዬ ያደረኩት ምንም የተለየ ነገር የለም ለማለት ነው?››
‹‹በትክክል፡፡››
‹‹እና እስከአሁን እኔን በተመለከተ ያደረካቸው በጎነቶችና ትእግስቶች …ለሌላም ታደርገዋለህ ማለት ነው፡፡››ስትገረምበት የሰነበተችውን ጥያቄ አጋጣሚውን ስታገኝ ጠየቀችው፡፡

ለዚህ ጥያቄ በተወሰነ መጠንም ቢሆን የተሳሳተ ወይም የተጋነነ መልስ ሊሰጣት ወሰነ.. ‹በተቻለኝ መጠን አዎ…ግን አስቤበት ለእከሌ እንዲህ ላድርግ ብዬ አይደለም…በእየእለት ገጠመኜ ፊት ለፊቴ የሚደነቀሩትን ማንኛውንም አጋጣሚዎች አእምሮዬና ልቤ ተጋግዘው በሚወስኑት ውሳኔ በመገዛት ላልፋቸው እሞክራለሁ..በዛ ሂደት ውስጥ እንግዲህ ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር በሌላው ሰው ላይ  ልሰራ እችላለሁ…..በእኔ ምክንያት ግን ሰው  ፊቱን ባያጨማድድ ደስ ይለኛል፡፡››አላት…ያለው ሁሉ እውነትነት ያለው ቢሆንም እሷ ላይ ግን የተለየ አቀራረብና ልዩ የሆነ ትኩረት አደርጓል…ይሄንን ግን ሊነግራት አልፈለገም…ለመዋሸት ፈልጎ ሳይሆን ለምን ብትለው ሚመልስላት የተዘጋጀ መልስ በውስጡ ስለሌለ ነው፡፡
‹‹አእምሮዬና ልቤ የተስማሙበትን ነው ያልከው..እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው..እስኪ ትንሽ አብራራልኝና   ከረዳኝ እኔም ልጠቀምበት፡፡››
‹‹አእምሮሽን ብቻ ስተጠቀሚ እኔነት ያጠቃሻል ….እኔነትን መሰረት አድርገሽ ምትወስኚው ውሳኔ ደግሞ ወደ ራስ ማዳላቱና ከሌላው መብት ላይ የተወሰነ ድርሻ  መስረቁ አይቀሬ ነው..ልብሽን ስትጠቀሚ ደግሞ ስሜት ያጠቃሻል ፡፡በወቅቱ በሚሰማሽ ስሜት ብቻ ሙሉ በሙሉ ተስበሽ ውሳኔ  ላይ ትደርሻለሽ….ብዙን ጊዜ ደግሞ በመጀመሪያው እይታ አይተው የሆነ ስሜት የሚቀሰቅሱ ነገሮች ጠለቅ ብለሽ ሰታጠኛቸው ሌላ ታሪክ በጀርባቸው አዝለው ይገኛሉ….ሁለቱንም ማለቴ ልብሽንና አእምሮሽን በጥምረት መጠቀም ግን ወደእውነታው የበለጠ መቅረቢያ የተሻለው መንገድ ነው፡፡ልብህ ወደሚመራህ ቦታ ተጓዝ እምሮህንም ግን ይዘህ ሂድ ያለው ማን ነበር ››አላት
‹‹ሰው ግን በምኑ ነው የሚያስበው?››ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ ሰው በአእምሮው እንደሚያስብ ነው የሚታወቀው..እኔ ግን በአእምሮችን ብቻ ሳይሆን በልባችንም እናስባለን ብዬ አምናለሁ… በኩላሊትም እንደሚያስቡ የሚያምኑ ማህበረሰቦች አሉ፡፡››
‹‹እንዴ ምን ነካህ ልብ እኮ በደም የተሞሉ የተለያዩ የደም ቱቦሆች ቅጥልጥል ነው … እንዴት ማሰብ ይችላል?››
‹‹አእምሮም ደግሞ እሱንም የለውም….አእምሮ ጭንቅላት ውስጥ ሚካሄድ የሀሳብ ስርአት ነው….ጭንቅላትም ደግሞ በቢሊዬን የሚቆጠሩ የተለያዩ ኒውሮኖች ቅጥልጥል ነው፡፡ እንዴት አድርጎ ነው የሚያስበው..ስታስቢስ በአእምሮሽ ታስብ በኩላሊትሽ፣በልብሽ ታስቢ በጉልበትሽ በርግጥ መለየት ትቺያለሽ?›› መልሶ ጠየቃት፡፡  
  
‹‹አልችልም፡፡››

ከእሱ ጋር ረዘም ያለ ጊዜ ማሳለፍ ስለፈለገች‹‹አሁን የሆነ ቦታ እንሂድ››አለችው፡፡

‹‹ደስ ይለኛል …ግን የት?››

‹‹የፈለክበት ቦታ..ሲኒማ ቤት…ትያትር ቤት.. መጠጥ ቤት…››
‹‹ካልደበረሽ እኔ አንድ ቦታ ልውሰድሽ፡፡›› አላት…
#ህያብ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በኤርሚ

የሆነ እንደመልዓክ የቆጠራችሁት ሰው ከሆነ ጊዜ በኋላ ውስጡ ያለውን የሚያስፋራ አውሬ አውጥቶት ሊበላችሁ እየገሰገሰ ሲመጣ ምን ይሰማችኋል። ትሸሻላችሁ ወይስ ቆማችሁ ትበላላችሁ። እኔ ግን ብዙ ነገሬ እስከሚያልቅ ቆሜ ነበር የተበላሁት

የልቤ ንጉስ  ብዬ የፍቅር ማማ ላይ የሰቀልኩት ሰው ልክ የዛን ቀን ትክክለኛ ማንነቱን አየሁት። ማንኛውም ሰው ሲናደድ ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል የሱ ግን ከዛ የተለየ ነበር። ነገሮችን ለመስማትም ለመረዳትም ፈቃደኛ አልነበረም ያነበበው ደብዳቤ ሳይቀር ቢኒ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅሩን እንደገለፀልኝ እየነገረው እሱ ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ ፍቅረኛሞች ነበራችሁ ብሎ ደመደመ።

"ጯ ጯ" ይህ በማፈቅረው ሰው የተመታሁት የጥፊ ድምፅ ነው። የቦክስን ድምፅ ደግሞ በቃል መግለፅ ይከብዳል እንጂ እኔን እንደመታኝ ቢኒ ዘሎ ተነስቶ ያቀመሰውን ቦክስ ከዛም አንዴ ቢኒ አንዲ ዮኒ ገላጋይ እስኪመጣ የተደባደቡትን በቃል እገልፅላችሁ ነበር።

ከድብድቡ በኋላ ሁለቱንም ሰው ይዟቸው

"አንተ ውሻ አላፈቅራትም ብለህ ያጣበስከኝ ፍቅረኛህን ነበር አይደል?(ደም ያዘለ ምራቅ ከአፉ እየተፋ) አትረባም ወንድ አይደለህም እሺ... ቀሚስ ልበስ"

ቢኒ ደግሞ ሌላ ትዕይንት ነው ከድብድቡ በኋላ እሱንም ሰዎች ቢይዙትም ለመወራጨትም ሆነ ለመሳደብ አልሞከረም የንዴት ትንፋሽ እየተነፈሰ ዝምም ብሎ ዳር ላይ ቆሜ አንዴ እሱን አንዴ ዮኒን እያፈራረቅሁ የማየውን እኔን ያየኛል

"እባካችሁ ልቀቁኝ ምንም አይፈጠርም እሷን ግን ሊጎዳት ይችላል። ሚስቱ ናት ግን እባካችሁ እንዳይጎዳት አድርጉ" አወራሩ ያሳዝን ነበር። ለቀቁትና ወደኔ መጣ

"ይሄ ውሻ ሚስቴ አጠገብ እንዳይደርስ እንዳትነካት አትጠጋት"
ብዙም ሳይቀርበኝ ቆመ

"ከሳምንት በኋላ እበራለሁ እስከዛ ግን ችግር ካለ ደውይልኝ እዛ ስሄድ ደግሞ እኔ እደውልልሻለሁ" አለኝና መልሴን ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ ከመናፈሻው ወጣ

።።።። ።።።።። ።።።። ።።   ።።። 
ሳሎን ሶፋ ላይ ኩርምት ብዬ ተቀምጫለሁ። ዮኒ ደግሞ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ ያለማቋረጥ እየተመላለሰ ይለፈልፋል

"ንገሪኝ እስኪ ስንት ጊዜ ሆናችሁ?" መልሴን ሳይጠብቅ ደግሞ

"የትናዬት ልክ ነበረች አይደል" ለመናገር አፌን እንደከፈትኩ

"ዝምምም በይ ምንም አትናገሪ ባትነግሪኝም አውቄዋለሁ። ግን ከመች ጀምሮ ነው ፍቅረኛ የሆናችሁት አንደኛ አመት እያለሽ"

"ኧረ እኔ ከቢኒ ጋር"
" ዝምም በይ አትንገሪኝ መገመት አይከብደኝም" ለመናገር መሞከሬን አቆምኩና ንዴቱ ሲበርድለት እነግረዋለሁ ብዬ አሰብኩ ግን በፍፁም ያሰብኩት አልሆነም። በውስጡ ያመነበትን የመከዳት፣ የመቀደምና የመሸወድ ስሜት ከውስጡ እንዳስወግድለት እድል ሊሰጠኝ አልቻለም። በራሱ ጭንቃላት ታሪክ ፈጠረና በፈጠረው ታሪክ ደግሞ አመነበት። ህያብ ከቢኒያም ጋር የአንደኛ አመት ተማሪ እያሉ ነው ፍቅር የጀመረችው። እኔ ላይ ተመካክረው ነው የተጫወቱብኝ ይህን እና ሌሎች ነገሮችን በጭንቅላቱ ውስጥ ሞላቸው የሚያውቀውን እውነት ሳይቀር ካደ። ከዛ በኋላማ ያሳለፍኩትን እንዴት ልገልፀው እችላለሁ በአጠቃላይ ህይወቴ ሲኦል ሆነ።

ተመስገን ይህን ሰሞን በፍቅር የተሞላ ጊዜ አሳለፍን ብዬ አመስግኜ ሳልጨርስ ሌላ ታሪክ ይፈጠራል። በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ግን ለሱ ያለኝ ፍቅር እንደድሮው ነበር። ትቼው እንኳን ለመሄድ አቅም አልነበረኝም። በእርግጥ ትቼው ብሄድ ከሱ የተሻለ ደሞዝ ያለኝ ራሴንም ሆነ ልጄን እና እናቴን ቀጥ አድርጌ ማስተዳደር የምችል ሰው ነበርኩ። ግን አፈቅረዋለሁ አንድ ቀን እውነቱን ለመረዳት እንደሚሞክርም አምናለሁ። እምነቴ ከምንም በላይ ለሱ ያለኝ ፍቅር በደልን ችዬ እንድኖር አደረገኝ

ይህ ከተፈጠረ ከአመት በኋላ እናቴ በፀና ታማ ሆስፒታል ገባች። እኔ የምሰራበት ሆስፒታል ነበር።  እንደማትተርፍ እያወቅሁ ብዙ ጣርኩ ግን ልመልሳት አልቻልኩም።

እናቴ ጥላኝ ሄደች እንደሚሰበር እንቁላል የምትጠነቀቅልኝ እናቴ እንደ አይኗ ብሌን የምትጠብቀኝ እናቴ ለኔ እንደኖረች ተምሬ ደርሸላት ትንሽ እንዳሳረፍኳት ገና ውለታዋን ሳልመልስ በደንብ እፎይይይ ብላ መኖር ሳትጀምር ሞት ነጠቀኝ። አመመኝ.... እጅግ በጣም አመመኝ። ከኔ የበለጠ እንቁን ማፅናናት ከባድ ነበር። እማዬ ሁሉ ነገሯ ነበረች።

ለአንድ ቀን መዓድ የተጋራሀውን ሰው እንኳን በሞት ማጣት ከባድ ነው። እማ ከዛም በላይ አለሜ ነበረች፤ የራሴን ውብ አለም ፈጥራ ከፍራቻዬ የሸሸገችኝ፣ ጓደኛዬ፣ ስታመም ሀኪሜ፣ ስጨነቅ አማካሪዬ፣ ተቆጪ መካሪዬ፣ ዘጠኝ ወር በሆዷ ተሸክማ ሶስት አመት ጡቷን አጥብታ ያሳደገችኝ እናቴ ለሰው አንድ ለኔ ግን ብዙዬ ነበረች።
ይገርማል አይደል ነው ከመባል ነበር ወደመባል የምንሸጋገርባት የሽርፍራፊ ሰከንዶች ሞት....

አስፈላጊ ያልናቸውን እቃዎች ሰብስበን ወደኔ ቤት ካመጣን በኋላ ቤቱን አፅድተን ለአከራይዋ ቁልፉን አስረከብን።

አከራይዋን ቻው ብለናቸው ልንወጣ ስንል እንቁ
"ማሚ እዚሁ ነው መኖር የምፈልገው እማዬን ትቼ የትም አልሄድም" እየተንሰቀሰቀች የተቆለፈው በር ስር ሄዳ ቁጭ አለች። አጠገቧ ሄጄ ቁጭ አልኩና አቀፍኳት.... ለረጅም ደቂቃ አብረን ተላቀስን።

አከራይዋ ወ/ሮ ትርንጎ ከቤት ሲወጡ ተቃቅፈን ስንላቀስ አዩንና  ወደኛ መጡ

" ምነው ልጆቼ ተነጋግረን አውርተን... ተው እንጂ እኔንም ሆድ አታስብሱኝ እናታችሁንም አትረብሿት ነብሷ በሰላም ትረፍ። በእናንተ እንደዚህ መሆን ደስተኛ የምትሆን ይመስላችኋል በሉ ልጆቼ ኑ ተነሱ" እጇችንን ይዘው ካነሱን በኋላ እንባችንን ጠራረጉልንና መክረውንና አፅናንተውን በር ድረስ ሸኙን።

"በቃ ቻው እማማ ትርንጎ እየመጣን እንጠይቆታለን ብዬ ቃል አልገባልዎትም ግን ቤተ ክርስቲያንም ቢሆን መገናኘታችን አይቀርም። የምሰራበትንም ሆስፒታል ያውቁታል አይደል ለጤናዎትም ብቅ ማለት ይችላሉ። ቤትም ይምጡ አይጥፉ። በሉ ቻው... ከዚህ በላይ አይቸገሩ" ተሳስመን መኪና ውስጥ ገባንና ወደ ቤት ሄድን።

እንቁ ሙሉ ለሙሉ እኛ ቤት መኖር ከጀመረች በኋላ የዮኒ ፀባይ ተስተካክሏል። ቶሎ ወደ ቤት ይገባል ትምህርት ቤት ያደርሳታል እልፎ አልፎ አብረው ይዝናናሉ። እኔ ብዙውን ጊዜ በስራ ስለማሳልፍ ባልቀላቀላቸውም የልጄ የአባትነት ክፍተት ሲሞላ በማየቴ ደስተኛ ነበርኩ። ሁልጊዜ አባቴ ማነው የሚለው ጥያቄዋ ሊያሳብደኝ ነበር የሚደርሰው.... ለጊዜውም ቢሆን ጥያቄዋን ትታ ዮኒን እንደ አባት ስታየው ማየቴ እፎይታን ሰጥቶኛል።

ትልቅ ልጅ እየሆነች ነው። አንዳንዴ እማዬ እየሳቀች "መልኳ እኮ አንቺን አስደግፈው የሳሏት ነው የምትመስለው። አንቺም ልጅ ሆነሽ እንደሷ እኮ ነው መልክሽ ካላመንሽ  ያንን አልበም አምጪና ፎቶሽን እና እሷን አስተያይ" ትለኝ ነበር።

ልጅ ሆና ብቻ ሳይሆን እያደገች ስትመጣም የኔኑ መልክ ያዘች።

ከዮኒጋ አልፎ አልፎ ጭቅጭቅ እንደ ቅመም ጣል ጣል ያለበት ራት በልተን እንገባለን። ቢሆንም ግን ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር ተመስገን ያስብላል። ትንሽም ቢሆን ቤቴ ትዳሬ ማለት ጀምሯል ያ ለኔ ትልቅ ነገር ነበር።

ቢኒ ከሄደ ጀምሮ ሶስቴ ነው የደወለልኝ። አንደኛው ከእናቴ ሞት በኋላ እግዜር ያፅናሽ ለማለት ነበር። ከዛ በፊት ሁለቴ ደውሎ ቢያውቅም ያን ያክል ግን አላወራንም ነበር ሌላው ቢቀር ስለመጫረሻው ቀናችን ደፍሮ የጠየቀ እንኳን አልነበረም።
ቻው ከማለቱ በፊት
" ግን ደስተኛ ነሽ" ይለኛል።
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
‹‹እና ታዲያ አሁን ምንድነው የሚሆነው.?›› 

‹‹አንቺን ከዚህ ማውጣት እና ወደመሬት ማለቴ ወደቤትሽ መመለስ አለብኝ፡፡››

‹‹አንተስ...?››

‹‹እኔን እርሺኝ፡፡››አለና ሰውነቱን ወጣጠረ …ጭራው ወደላይ ወደወገቡ ሄደና ሰውነቱን እየሰረሰረና ቅርፅን እየቀየረ መጣና በደቂቃ ውስጥ አብረቅራቂ ክንፍ ሆነ..የሰውነቱ ጠቅላላ ገፀ-መልኩ ተቀየረ …የሚያበራና የሚንፏለለ አንጸባራቂ ብርሀን ከውስጡ ይፈስ ጀመር.. እጁን ወደ አንገቷ ስር ሰዶ  ጥፍር በመሰለ ነገር ወጋት..የሆነ የመርፌ ውግ አይነት ስሜት ነው የተሰማት …ወዲያው ድንዝዝ ነው ያላት …ከዛ በኃላ የሆነውን ነገር አላወቀችም….

ስትነቃ…. ያዶት ወንዝ ዳር እራሷን ስታ እርቃኗን ጥቅልል ብላ ተኝታ ነው  ሰዎች ያገኟት….አፋፍሰው ወስደው ለቤተሰቦቾ አስረከቧት…ከዛ በቤታቸውና በጠቅላላ መንደሩ አስፈሪ ትርምስ ተፈጠረ…ሁኔታዋ ሲታይ ተደፍራለች… ነፍስ እንደዛራች ያለችበትን እና የሆነውን ነገር ማመን ነው ያቃታት…ምን እንደሆነች በቤተሰቦቾም ብትጠየቅም የሚጨበጥ ነገር መናገር አልቻለችም‹‹ሴይጣን ደፍሯት ነው›› ተባለ..ተከራክራ ልታሳምናቸው አልቻለችም …እሷ ‹‹ተደፍሬ ሳይሆን በፍቃዴ  ነው›› ብትልም ሰሚ አልነበረም… ያንን የሰይጣን እና መላአክ ድብልቅ የሆነ ፍጡር ለማግኘት ከቤተሰቧ እየተደበቀች  ለወራት ያዶት ወንዝ ላይ በለሊት በመሄድ ወንዙን ብታስስም በለቅሶ እየታጠበች በልመና ብትጣራ.. ብትፈልግ ብትጠብቅ ከየት ታምጣው .?
‹‹ወገኖቹ ምን አድርገውት ይሆን...?ምን አለ ለአንድ ሰከንድ እንኳን ተመልሶ ቢመጣና  ቢገለፃልኝ .?እና ሰላም መሆኑን ባውቅና ብረጋጋ..!!!› የዘወትር ምኞቷ ነበር..ግን ምንም መፍትሄ አልነበረውም፤ዳግመኛ ልታገኘው አልቻለችም..ግን ልትረሳውም አልቻለችም..ምክንያቱም አርግዛለታለች.. ስላረገዘችለትም ደስ ነበር ያላት ..ማንም ምንም ቢላት ግድ አልነበራትም ነበር…ቢያንስ በልጁ ውስጥ  እሱን በማየት ነው ለዓመታት የተፅናናችውና..የተረጋጋችው፡፡ ..እርግዝናዋ ከባድ ነበር ፤በአመት ከስድስት ወሯ ነበር መውለድ የቻለችው..የሰውነቷ አወቃቀር እና መላ ተፈጥሮዋ ልክ እንደ እሷ የሆነ እና ከአንገቷ በላይ ያላት መልክ እና  ነገረ ስራዋ የእሱን የምትመስል ልጅ ወለደች…፡፡ከተአምረኛው ፍጡር ተአምረኛ ልጅ ወለደች..ሰው ሁሉ ግን  የገዛ ዘመዶቾንም ጨምሮ  ከዳቢሎስ  ወለደች ነበር ያሏት .‹‹. ይሁን እንኳንም ወለድኩለት   ፡፡›አለች፡፡ስሟንም ኬድሮን  አለቻት፡፡ ይሄም አባቷ የሚኖርበትን ስውር ፕላኔት ለማስታወስ አስባ ነው፡፡የበሬዱ ታናሽ ወንድሞ ደግሞ ሰውን ግራ አታጋቢ አለና ‹‹ሶፊያ›› አላት፡፡በዚህ የተነሳ ‹ኬድሮን› እና ‹ሶፊያ› የተባለ ሁለት ስም ኖራት፡፡
የበሬዱ ዲንቃ ፍቅር….ምናባዊ አይነት ነው ቢባልም…..ግን ደግሞ ምናባዊ ብቻ ነው ተብሎም ድምዳሜ የሚሰጠው አይደለም… ታሪኩ በአጠቃላይ ተአማኒነት የሚጎድለው ልብ አንጠልጣይ ልብ ወለድ ከሚመስል ታሪክ ውስጥ እውነተኛ የምትጨበጥና የምትታቀፈ ልጅ ተገኝታለች፡፡

….ህልም እና ቅዣት ከሚመስለው የፍቅር ግንኙነት ተጨባጭ ኬድሮን አሁን አለች … መቼስ ልጅቷም እራሷ ከተአምራዊ ነገር የታጠረ የወደፊት ታሪክ እንደሚኖራት እንዲሁ የልጅነት ገፅታዋን ብቻ አይቶ መተንበይ ከባድ  አይደለም፡፡
የፍጥረት ምንጩ ከማይታወቅ አባትና ሰው ከሆነች እናት የተወለደችው ኬድሮን ከውልደቷ ጀምሮ  ልዩ ክስተት ሆና ነው በዚህ ምድር የተከሰተችው፡ሁሉ ነገሯ ከሰው የማይገጥም እና ተለየ የሆነው ገና ከውልደቷ  ጀምሮ ነው፡፡የተወለደችው  እንደማንም የሰው ልጅ በዘጠኝ ወሯ አይደለም..አንድ አመት ከስድስት ወር በእናቷ ማሀፀን ውስጥ ዘና ብላ ኖራለች…ምን አልባት በሰው ልጅ የህይወት ታሪክ በእናቱ ማህጻን  ከበቂ በላይ ለሆነ ጊዜ በመንደላቀቅ እና በምቾት በመኖር ሪከርዱ በእጇ  ሳይሆን አይቀርም…
እርግጥ ብዙዎቹ ይሄንን ታሪክ ሲሰሙ ባለማመንና በመጠራጠር ክርክር ውስጥ ይገባሉ‹..እናቷ እሷን የፀነሰችበትን ቀን ተሳስታ ነው፡፡ ›የአብዛኞቹ መላምት ነው..ግን ይሄ እንዳልሆነ ከመጀመሪያ ሳምንት የጽንሰቷ ጊዜ አንስቶ እስክትገላገል ድረስ የሀኪም ክትትል ውስጥ ስለነበረች ትርክቷ በሳይንስ መረጃ የተደገፋ ነው…ይሄም በተወለደችበት ሳምንት በኢትዬጴያ ሬዲዬ የቀትር ዜና ላይ‹‹በባሌ ክፍለሀገር በደሎ መና ከተማ ኑዋሪ የሆነች በሬዱ ዲንቃ የምትባል ወጣት ሴት በአንድ አመት ከስድስት ወር ጤነኛ የሆነች ሴት ልጅ መገለገሏን ከከተማው ጤና ጣቢያ በደረሰን ዜና ማወቅ ተችሏል፡፡…››የሚል ዜና ተነግሮ ስለነበረ ከመወለዷ የከተማዋ ዝነኛ እና ታወቂ እንድትሆን ተገዳለች፡፡

የኬድሮን ተአምራዊነት በዚህ ብቻ አልተገታም ፤እራሷን ችላ መቀመጥ የጀመረችው በሶስት ወሯ ነው…በስድስተኛ ወሯ መራመድ ጀመረች፤ በአንድ አመቷ በእቤታቸው ውስጥ በኩል ደረጃ ይነገሩ የነበሩትን አማርኛ እና ኦሮሚኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፋ ማውራት ቻለች፡፡
ይሄ ሁኔታዋ  ሰው ሁሉ እንዲፈራትና እንደሌላ ፍጡር እንዲቆጥራት አደረገ፡፡አንዳንዴ እሷ ራሷ ስለራሷ ስታስብ  ያው በአንድ አመት ከስድስት ወር እናቷ ማህፀን ስትቆይ ብዙ ነገር ተምራ ብዙውን ነገር እዛው ጨርሳ የወጣች ይመስላታል…እሷ ምትለው እውነት ከሆነ ደግሞ በዘጠኝ ወራቸው የሚወለዱ የሰው ልጆች እድገታቸውን ሳይጨርሱና ማወቅ ሚገባቸውን ጠንቅቀው ሳያውቁ ፤እራሳቸውን የመርዳት አቅሙ ሳያዳብሩ ቸኩለው እንደሚወለዱ ፍንጭ የሚሰጥ ክስተት ነው ማለት ይቻላል፡፡ለምሳሌ ከሰው ልጅ ውጭ ያለ ሌላ እንስሳት ተመልከቱ…ገና ከመወለዳቸው በራሳቸው ለመቆም ይፍጨረጨራሉ..በቀናት ውስጥ የራሳቸውን ምግብ በራሳቸው ቃርመው መመገብ ይጀምራሉ፡፡ከእናታቸው የሚፈልጉት የተወሰነ የደህንነት ጥበቃ እንድታደርግላቸውና መንገድ እንድታሳያቸው ብቻ ነው  ..የሰው ልጅ ግን ልፍስፍስ ነው…በእናቱ ማህፀን ዘጠኝ ወር አሳልፎ ከተወለደ በኃላ ሌላ ዘጠኝ አመት እናቱ ጉያ ውስጥ ተወትፎ በመነፍረቅ ሲልወሰወስ ይገኛል..በሀያ አመቱ  እንኳን እራሱን ችሎ ከቆመ ጠንካራ ና ጀግና ተብሎ  ይሞገሳል..ሰው እራሱን ለመቻል ለሃያ ረጅም አመታት ማደግ… መማር… መሰልጠን ..መጠንከር ይጠበቅበታል፡፡እሷ ግን እንዲ እንዳልሆነች ገና በጥዋቱ ነው የምታውቀው …፡፡
የእሷ ልዩ መሆነ ከውልደቷ ነው የሚጀመረው ቢባልም እውነታው ግን ከዛም ሳብ ይላል ..ከጽንሰቷ ነው የሚጀምራው…ከአባቷ  ማንነት….

ይቀጥላል
#ትንግርት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


...‹‹ስሚ አሁኑኑ ጨርቅሽን ይዘሽ ከቤቴ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ልጆቼን ላሳድግበት፡፡ ከፈለግሽ ሽርሙጥና ቤት ግቢና እንደፈለግሽ ሁኚ፤አልፈልግሽም፡፡>> በማለት ጨርቄንና ደብተሮቼን ሠብስባ አስታቅፋኝ እየገፈተረችኝ ከቤቷ አውጥታ አባረረችኝ፡፡

በእንደዚህ ሁኔታ ነበርሰ ታሪኳን ያስረዳችው፡፡ ከዛም እንደ እህቱ አድርጎ ተቀበላት፡፡."

ትምህርቷንም እንድትቀጥል አደረጋት፡፡ በወቅቱ እሱ ጋር ስትመጣ የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ አሁን በዲፕሎማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሦስተኛ አመት ተማሪ ነች፡፡

....ሁሴን የሀሳብ ውቅያኖስ ተንፈራግጦ ሲወጣ እቤቱ ሞቆና ተጫጭሷ ነበር፡፡ ፎዚያ ቅድም የለበሠችውን ልብስ አውልቃ ድርያ ለብሳለች፡፡ ብዙውን ጊዜ የምትሸፍነውን ፀጉሯን በነፃነት ለቃዋለች፡፡ አጭር ቢሆንም ሉጫ ስለሆነ ለውበቷ ልዩ ድምቀት ለግሷታል፡፡

‹‹እሺ ፎዚያ ትምህርት እንዴት ነው?›› አላት፡፡

‹‹አሪፍ ነው፡፡አሁንማ ልጨርስ አራት ወር ብቻ ቀረኝ እኮ!››

‹‹በጊዜ ስራ ፈልጉ ማለትሽ ነው?››

‹‹ለስራው እንኳን ብዙም ጉጉት የለኝም፡፡ ዋናው ተምሬ እዚህ ደረጃ መድረሴ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ዕቅዴ አንተን በተሻለ መንገድ መንከባከብ ነው፡፡››

‹‹እንዴት ባክሽ? እኔን ለመንከባከብ እኮ ሦስት ዓመት ሙሉ ኮሌጅ ገብቶ መማር አያስፈልግሽም ነበር

‹‹...እንዲህ ብለህ አታሳምነኝም...አንተ ለእኔ ምርጥ ወንድሜ ብቻ ሳትሆን አባቴም ጭምር ነህ ፡፡ብዙ ነገር አድርገህልኛል፡፡አላህ አንተን ባይጥልልኝ ኖሮ ዛሬ ዕጣ ክፍሌ የሰው ቤት ግርድና ካልሆነም ሽርሙጥና ነበር፡፡ስለዚህ የእኔ አንተን ለመንከባከብ መወሰን ያንስብሀል እንጂ አይበዛብህም፡፡››

‹‹...ፎዚ ለእኔም እኮ ምርጥ እህት ሆነሽኛል፡፡ ይሁን እንጂ እህትም አንድ ቀን የታለቅ ወንድሟን ቤት ጥላ የራሷን ቤት ትገነባለች፡፡ የወንድም ኃላፊነት ደግሞ እህቱ እዚህ ደረጃ እንድትደርስለት ማበረታታትና መደገፍ ነው፡፡ እርግጥ ነገሮች ቀላል አይደሉም፡፡ እኔም እኮ አንድ ቀን ስራ ይዘሽ ፣የፍቅር ጓደኛ አበጅተሸና ትዳር መስርተሸ ጥለሺኝ እንደምትሄጂ ሳስብ በጣም ይጨንቀኛል፤ ቢሆንም ግን የግድ መቀበል እንዳለብኝ አምናለሁ፡፡

የፈላውን ቡና በመቅዳት ስኳር ጨምራ በማማሰል አቀበለችውና ለራሷም ቀድታ ንግግሯን ቀጠለች፡፡

‹‹እንግዲህ ውሳኔዬ የማይቀየር ነው፡፡ ምን አልባት አግብተህ ባለቤትህ ቤቱን ከተረከበችኝና ከልብ እንደምትንከባከብህ እርግጠኛ ከሆንኩ.. ያኔ ያልከውን አደርግ ይሆናል፡፡›

‹‹ዝም ብለን በባዶ ሜዳ እኮ ነው የምንጨቃጨቀው፡፡>>

‹‹እንዴት ማለት?›› ሁሴን ሊላት የፈለገው ምን እንደሆነ ስላልገባት ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔ አሁን በቅርብ የማገባ ይመስልሻል? >>

‹‹ለምንድነው የማታገባው?››

‹‹ማን ነች ፍቃደኛ ሆና እኔን ልታገባኝ የምትችለው?››

‹‹በጣም ዕድለኛዋ ሴት ነቻ፡፡›› ፎዚያ ከምሯ ነው እውነተኛ ስሜቷን የምታወራው፡፡

‹‹አይምሰልሽ .. በዙሪያዬ ያሉ ሴቶች ሁሉ በፍቅር እንጂ ትዳርን ለሚያህል ቁም ነገር ብቁ እንዳልሆንኩ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡››

‹‹ይሄ አንተን በተመለከተ ትክክለኛ ምልከታ ነው ብዬ አላስብም፡፡›› አለች ቅሬታን በዛለ ድምፅ፡፡

‹‹እንዴት ... ? ሌላው ይቅር በአንቺ አመለካከት እኔ ለትዳር የምሆን ግለሠብ እመስልሻለሁ?›› ሲል ጠየቃት ፡፡

‹‹እውነቱን ልንገርህ?›› በታፈነ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹አዋ!.. ንገሪኝ ... ትክክለኛ ስሜትሽን ንገሪኝ፡፡››
‹‹እንግዲያው እኔ ሙሉ በሙሉ ያንተ አይነት ወንድ እስከማገኝ ትዳር ሚሉት ነገር አልሞክርም፡፡››
ደነገጠ፡፡ እንደምትወደው ያውቃል፡፡ ይሄን ያህል ተፅዕኖ ውስጥ እንደከተታት ግን ልብ ብሎ አስተውሎት አያውቅም፤ ውይይታቸው ከወትሮው በመጠኑም ቢሆን ጠንከር እያለ ስለመጣበት ርዕስ ለመቀየር ተገደደ፡፡

‹‹ኦ! ይሄ ቡናሽ ልዩ ነው፤ ከደባሪው እራስ ምታቴ ገላገለኝ›› አላት፡፡

‹‹ስለተሻለህ ደስ ብሎኛል፤በነገራችን ላይ ቀን ትንግርት መጥታ ነበር፡፡››

‹‹እንዴት ሳትደውልልኝ መጣች ..…?››

‹‹እኔ እንጃ፡፡ ሁኔታዋ ግን ከወትሮው የተለየ ሆነብኝ፡፡ ሁሉ ነገሯ ወደ ኖርማል ተመልሷል... አገባች እንዴ?›› የገረማትን ነገር ጠየቀችው፡፡

‹‹አይመስለኝም.. ስራ ግን ቀይራለች›› መለሠላት፡፡

<<ለማንኛውም የሆነ ዕቃ አምጥታልሃለች፡፡ >>

‹‹ምን አይነት ዕቃ? >> ለማወቅ በተጣደፈ ስሜት ጠየቃት፡፡

‹‹እኔ እንጃ ሥዕል መሠለኝ፤ታሽጓል፡፡ መኝታ ቤት አስቀምጬልሀለሁ፡፡››

ተስፈንጥሮ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ፡፡ በግምት ሠማንያ በስልሳ የሚሆን በፍሬም የተወጠረ፤ በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ ሸራ አገኘ፡፡ በጥድፊያ ልባሱን አነሳው፡፡የሚያፈዝ ስዕል ነው፡፡ የጥንት ንግስቶች የሚለብሱትን አይነት አብረቅራቂ ወርቀዘቦ ልብስ የለበሠች እንስት ትታያለች፡፡ እግሮቿ መሬት አይረገጡም፡፡ በአየር ላይ የምትራመድ ትመስላለች፡፡ ፀጉሯን ንፋሱ እያንሳፈፈው በአየር ላይ ተበታትኖ ሲታይ ሰማይ ጠቀስ ማማ ላይ የተሰቀለ የታላቅ ሀገር የተከበረ ባንዲራ ይመስላል የእጆቿ ጣቶች ውበታቸው የገነት ደናግሎችን አይነት ነው፡፡ በቀኝ እጇ ዓይነ ሥውሮች የሚጠቀሙበትን አቅጣጫ መጠቆሚያ ነጭ ዘንግ ይዛለች፡፡ ፊቷ የተለየ ነው፡፡ እንደ ሠው ዓይን፣ አፍንጫ፤ ከንፈር ሳይሆን በቦታው የሙሉ ጨረቃ ቅርፅ ይታያል፡፡ በጨረቃዋ ዙሪያም በህብረ ቀለም የደመቀ የብርሃን አምድ ያንፀባርቃል፡፡የሥዕሉ ጥልቀትና ምጥቀት... ውስጡ የተዳፈነውን የፍቅር እቶን ቀሠቀሠበት፡፡ የናፍቆት እሳት መላ ሰውነቱን ሲለበልበው ተሠማው፡፡

ትንግርት መጽናኛ የሚሆነውን ውድ ስጦታ ስላበረከተችለት ከልብ አመሠገናት፡፡ ፊት አልባ ሥዕል የተሳለላት ድብቋ ደራሲ ግን በምን ተአምር በአካል ሊያገኛት እንደሚችል ከመቼውም ጊዜ በላይ ግራ ገባው፡፡ ስዕሉን እንደታቀፈ ወደ አልጋው ሄደና በጥንቃቄ ተኛ፡፡ የቀለሙ ሽታ ከደራሲዋ ሰውነት የሚመነጭ መግደላዊት ማሪያም የክርስቶስን እግር ያጠበችበትን የአልባስጥሮስ ሽቶ አይነት እንደሆነ ሁሉ በረጅሙ ስቦ ወደ ውስጡ ማገው.. የስሜቱ ጥጋ.. ጥግ ድረስ ገብቶ ለውስጡ ሀሴት እንዲሰጠው በመመኘት ፡፡ በስዕሏ ፋንታ ዋናዋንም አንድ ቀን በአካል አግኝቷት እዚሁ አልጋው ላይ እንዲህ አቅፎት በእጆቹ እየዳበሳት..በከንፈሮቹ እየመጠጣት. በትንፋሹ እያጋላት... በሙቀቱ እያቀለጣት... በፍቅሩ እያሰከራት አብሯት እንደሚተኛ ተስፋ በማድረግ…፡፡...

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች  በባለፈው #ፖስት 10 ሰው ብዬ 2 ሰው ብቻ ነው #ሰብስክራይብ ያደረገው 10 ሰው #ሰብስክራይብ አድርጉና ቀን በቀን እንልቀቅ

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳባ እሷን ላለመረበሽ ስትል የተኛች መስላ አደፈጠች..እናም.ቅድም ወዳቋረጠችው ትዝታ ተመልሳ ገባች፡፡

ከ11 አመት በፊት ጥቅምት- 2004

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተምራ ለመመረቅ ቸኩላ ነበር፡የቸኮለችው ግን ለግል ደስታዋና እራሷን ለመቻል ካላት ጉጉትና ፍላጎት ብቻ አልነበረም፡፡ዋናው ለአባቷ ስትል ነበር፡፡ለአባቷ ምቹ  ሁኔታ መፍጠር እንዳለባት ፅኑ እምነት  ስላላት ነበር፡፡ቀና ብሎ እንዲኖር፤ቢያንስ ከጓደኞቹ ጋር ውጭ ውሎ እንዲገባ..ከጓደኞቹ ጋር ቀብር ሲሄድ፤ሰርግ ቤት ወዳጆቹ ሲጠሩት ብድግ ብሎ ሄዶ ከሚያውቃቸው ሰዎች ጋር ውሎ ስቆና ተደስቶ አንዲመጣ፡፡አዎ ለእሱ ለሁለት እግሮቹ የሚሆኑ ዘመናዊ አርቴፊሻል እግሮች እና እሱ ሊነዳት የሚችል አንድ መኪና ልትገዛለት፡፡ይሄ የህይወቷ ትልቁ ምኞቷ ነበር፡፡ግን ማይታሰብ ነው የሆነባት፤በወቅቱ ጭራሽ እራሷንም ማኖር እየከበዳት ነበር ፡፡ይባስ ብሎ በዛው ወር   አባቷን ልታየው ወደ ትውልድ ከተማዋ አሰላ ሄዳ ነበር፡፡አባቷም ትንሹ  ወንድሟም ስለናፈቋት ተነሳችና ሄደች፡፡ስትደርስ  አባቷ  ሳሎን በእጅ የሚገፋ ማንዋል ዊልቸሩ ላይ ቁጭ ብሎ ነጭ ጋቢ ተከናንቦ ፊት ለፊቱ ያለ ቴሌቪዥን ላይ አይኖቹን ተክሎ እያየ ነበር፡፡ የበራፉ መንገጫገጭ  ድምፅ አነቃውና ፊቱን ወደበራፉ ዞር አደረገ..ፊቱ በአንዴ እንደ ጠዋት ፀሀይ ብርሀን ረጨ…ቦርሳዋን እዛው በራፍ ላይ ጥላ ተንደርድራ በመሄድ ሶፋው ላይ ሙሉ በሙሉ ዘላ ወጣችና አባቷ አንገት ላይ  ተጠመጠመችበት…እጁን  ዘረጋና ግራና ቀኝ ፊቷን እያገላበጠ ጉንጮቿን ሳማት፡፡
‹‹የእኔ እንቁ..በሰላም ነው…?እንዴት መጣሽ?››

‹‹ምን ማለት ነው?አልናፈቅኩህም እንዴ…?እንደዛ ከሆነ ተመልሼ መሄድ እችላለሁ››አለች የውሸት እንደማኩረፍ ብላ..፡፡
‹‹አንቺ እኮ ፀሀዬ ነሽ..ማነው ፀሀይ ጥዋት ስለወጣችለትና ስለነጋለት የሚከፋው…እንዲሁ ሳትደውይ ድንገት ብርት በማለትሽ ምን ገጥሟት ይሆን ብዬ ነው?››

‹‹አይ ደህና ነኝ…ሰርፐራይዝ ላድርጋችሁ ብዬ ነው፡፡››ስትል እንጀራ እናቷ ከኋለኛው ክፍል ውስጥ ተወዳጁን ታናሽ ወንድሟን እጁን እየጎተተች  መጣች፡፡‹‹እንዴ አባትና ልጅ በምስጢር ተጠራርታችሁ ትገናኙ ጀመር?››አለቻት  የእንጀራ እናቷ ስንዱ፡፡
‹‹ምነው ቀናሽ እንዴ?››

‹‹ብቀናስ…መብት የለኝም?›እያለች ወደ እሷ ተጠጋችና ጉንጭ ለጉንጭ  በመሳሳም የሞቀና የደመቀ ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡

አዎ የዛን ጊዜ አባትዬውን ልትጠይቅ አሰላ በሄደች ጊዜ በማግስቱ  አባትዬውን ልታዝናና ወደከተማ ይዛ ለመውጣት ፈልጋ ልብስ እየቀየረችለት ነበር…
‹‹አባዬ ይሄኛው ጃኬት ይሻልሀል?››

‹‹ልጄ አሁን ቤታችን ብናሰልፍስ..?ይሄ እኮ የተወለድሽበትና ያደገሽበት ሀገር ነው፤ብዙ የምታውቂያቸው ሰዎች ብዙ ጓደኞች አሉሽ.››.

‹‹እና? ››

‹‹እናማ እኔን እያንጓተቱ በአስፓልት ላይ መሄድ …››

‹‹አይ አባዬ..ትቀልዳለህ እንዴ.?አንተ እኮ ሁለ ነገሬ ነህ..አይቻልም እንጂ ቢቻል አንገቴ ላይ አንጠልጥዬ በየሄድኩበት ይዤህ ብዞር  በደረስኩበት  ሁሉ  ከጎኔ ብትኖር ደስ ይለኝ ነበር፡፡ አባዬ አንተ እኮ ጌጤ ነህ…አለሜ፡፡››

‹‹ይሁንልሽ ልጄ …››ሲል ተሸነፈላት፡፡

ቤተክርስቲያን ይዛው ሄደች..ከዛ ሆቴል ይዛው ገባች፡፡ አዝናናችው..፡፡ ወደማታ ሲሆን ወደቤት ይዛው ገባች፡፡ ከቤተሰብ ጋር ስትስቅና ስትደሰት አመሸች፡፡ በበፊት መኝታ ክፍሏ ትንሹ ወንድሟን አቅፋ ተኛች፡፡

ለሊት በመነሳት ባልና ሚስቱን ቀሰቀሰችና አባቷን ወደ ቤተክርስቲያን ይዛው ሄደች፡፡ ሶስት ሰዓት ሲመለሱ ቁርስ ተዘጋጅቶ በልተው እስከ  ስድስት  ሰዓት  ቆየችና በማግስቱ ስራ ለመግባት ወደአዲስ አበባ ለመሄድ ተነሳች፡፡ በዚህ  ጊዜ ስንዱ በኩርቱ ፌስታል ሙሉ እቃ ይዛ ከጓዳ ወጣችና ወለሉ መሀከል ከሻንጣዋ ጎን አስቀመጠችው፡፡

‹‹ምንድነው ይሄ ደግሞ? አንቺ መቼስ ዘላለምሽን ኮተት አታጪም..ተማሪ  ሆኜ እሺ፤አሁንም አታቆሚም?››ነበር ያለቻት፡፡
‹‹አንቺ የእናት እጅ ለዘላለም እምቢ አይባልም››

ተከራክራ እንደማታሸንፋት ስለምታውቅ ወደአባቷ ሄደችና..አገላብጣ ስማ ተሰናበተችው፡፡ በቀጣይ እንጀራ እናቷን ተሰናብታ 500 መቶ ብር እጇ ላይ አስቀመጠችና ወንድሟን ወደላይ አንስታ አገላብጣ ስማው ለመሄድ ተዘጋጀች፡፡
የእንጀራ እናቷ ስንዱ ብሩን ለመመለስ ጣረች ‹‹ኸረ አይሆንም .አንቺ ከየት ታመጪዋለሽ?፡››ብላ ብትከራከራትም አልሰማቻትም፡፡ ብሩን የምትመልሺ ከሆነ እኔም የቋጠርሽልኝን ነገር ጥዬ ነው የምሄደው ብላ ስታስፈራራት ነበር በሃሳቧ የተስማማችው፡፡

አባትዬው መሀል ሳይገባ በትዝብት ሁለቱንም ይመለከት ነበር.እውነት ሳባ ከልቧ ለቤተሰቡ ብዙ ነገር ለማድረግ ፍላጎትም ምኞትም ነበራት…ግን  በወቅቱ ሁሉ ነገር ከአቅሟ በላይ ነበር፡በአራት ሺ ብር የወር ደሞዝ እራሷንም ማኖር በጣም እየከበዳት ነበር፡፡እነሱን ለመጠየቅ ለምትመጣበት እና ያንን ብር እንጀራ እናቷ እጅ ላይ ለማስቀመጥ አንኳን ብዙ ፍላጎቶቿን መግደልና ምቾቶቿን መስዋእት ማድረግ ነበረባት..አንባዋ እንዳቀረረ አባቷን በድጋሚ ስማ ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ ከበራፍ ላይ ባጃጅ አስቆመችና መናኸሪያ ድረስ አደረሳት፡፡

ወደአዲስ አበባዋ ተመለሰች…ማታ ከመተኛቷ በፊት ስንዱ የቋጠረችላትን ፌስታል ከፈተች፡፡ ውስጥ ያሉትን ቋጠሮዎች ዘረገፈችና…ተራ በተራ ማየት ጀመረች ሽሮ፤በርበሬ፤ምስር ክክ፤አተር ክክ የቀረ ነገር የለም፡፡
‹‹ይህቺ እኮ ከእናትም በላይ ነች››አለችና በጉንጮቿ ያለፍቃዷ   የሚንኳለለውን ዕንባ አበሰችና ፒጃማ ፈልጋ ቦርሳዋን ከፈተች፡፡ የተጣጠፈ ካኪ ወረቀት አገኘች፡፡

ግራ ገብቷት አነሳችውና ውስጡን ስትከፍት የተጠቀለለ በዛ ያለ ብር አገኘች. ወረቀቱን ዳግመኛ አነሳች፤ውስጡን ገለጠችው፤የአባቷ የእጅ ፅሁፍ ነበር፡፡

‹‹ለታክሲ ትሆንሻለች ብዬ ነው፡፡እንደሚቸግርሽ  አውቃለሁ  ግን ታውቂያለሽ እንደልቤ መሻት ላግዝሸ አልቻልኩም፡፡ አይዞሽ  ትንሽ  ወር  ነው  ነገሮች ይስተካከላሉ እስከዛው እንደምንም በርቺልኝ...ደግሞ አንቺ የእኔ ልጅ ነሽ፤ ሁሉን ነገር ማድረግ ትችያለሽ››ይላል፡፡

ደብዳቤውን ጨምድዳ ወለሉ ላይ ወረወረች…በእንጀራ እናቷ ገደብ  በሌለው ደግነት ተነክታ የጀመረችውን ለቅሶ በሰፊው ለቀቀችው..ብሩን አነሳችና ቆጠረችው…ሶስት ሺ ብር ነው፡፡
‹‹አሁን እኔ ሰው ነኝ....ተማሪም ሆኜ የቤተሰቦቼ ሸክም….አሁንም  ስራ  ይዤ ለዛውም አባቴ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እያለ ከእነሱ ብር መቀበል…››በዛን ቀን ሁሉ ነገር ነበር ያስጠላት …ህይወት እራሱ አስጠላቻት…የሆነ ነገር መቀየር እንዳለባት ተሰማት…አዎ የህይወቷን መስመር ማስተካከል እንዳለባት ወሰነች፡፡ አዎ እንደዛ ነው የተሰማት…‹‹ወይ እንደምንም ቀልጠፍጠፍ ብዬ የተሻለ ደሞዝ የሚያስገኝ የተሻለ ሰራ ማግኘት አለብኝ፡፡ አልያም ደግሞ ረከስ ያለ ኑሮ የሚገኝበት ክፍለሀገር ሄጄ መኖር.›ስትል ነበር የወሰነችው፡፡
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ናኦል የእህቱን ድምፅ ከሰማ አራት ቀናት አልፎታል፡፡ይሄ ያልተለመደና ሊታሰብ የማይችል ነገር ነው፡፡እህቱ ቢዚ ብትሆን እንኳን አራት ቀን ሙሉ ቢያንስ ሚሴጅ ትልክለታለች ወይም ኢሜል ትልክለታለች እንጂ እንዲሁ ዝም ልትለው አትችልም፡፡እንዲህ አይነት ነገር አላስለመደችውም፡፡በተለይ የመጨረሻ ጊዜ ስትደውልለት በመጥፎ አየር ፀባይ ወደብራዚል መድረስ አቅቷቸው ያልሆነ ከተማ አርፋ አልጋ ክፍል ሆና ነበር የደወለችለት፡፡የአየር ፀባዩ ከተስተካከለ በማግስቱ ወደብራዚል በረራውን እንደምትቀጥልም ነግራው እሱም አምኗት ነበር፡፡በማግስቱ ትደውልልኛለች ብሎ ጠብቆ ነበር፡፡ማህበራዊ ሚዲያ ላይም ደጋግሞ ሊያገኛት ሞክሯል ፡፡፡ግን ምንም አይነት እንቀስቃሴ የለም፡፡ሚሲጅም ላከላት.. ኢሚልም ደጋግሞ ፃፈላት፡፡መልስ የለም፡፡መስራቤቷ ሄዶ አመለከተ..የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተፈጥሮ ጥበቃ መስሪያ ቤት ጋር ተፃፅፈው የሚያገኙትን አዲስ መረጃ ከለ ወዲያውኑ እንደሚያሳውቁት ነገረው ሸኑት፡፡የሄደችበትን ድርጅት ድህረ-ገፅ ፈልጎ መረጃ ማሰስ ጀመረ…በአራተኛው ቀን ማታ እቤቱ ቁጭ ብሎ በትካዜ ላይ ሳለ ሰውነት የሚያርድ ልብ የሚያቆም ዜና ከድህረ ገፅ ላይ አነበበ፡፡
‹‹ለተግባራዊ ስልጠና ከፔሩ ወደብራዚል ስትሄድ በአየር ፀባይ መበላሸት ምክንያት ፔሩ ኢኩዩቶስ ከተማ አርፋ የነበረችው ኢትዬጴያዊቷ የተፈጥሮ ጥበቃ ባለሞያ ኑሀሚ በቀለ የገባችበት ጠፋ፡፡ወጣቷ የተፈጥሮ ጥበቃ ኢኬስፐርት አንድ ሆቴል ውስጥ ከአንድ ግለሰብ ጋር አብራ ያደረችና ጥዋትም በታክሲ ተሳፍራ ወደኤርፖርት ጉዞ እንደጀመረች ከሆቴሉ ሰራተኞች ማጣራት ቢቻልም ከዛ በኃላ ግን ኤርፖርት እንዳልደረሰች ታውቋል፡፡ምን አልባትም ወደሀገሯ መመለስ ስላልፈገች እራሷን ሰውራ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ፖሊሶች ግምታቸውን የተናገሩ ሲሆን ፍለጋው ግን መቀጠሉን ታውቋል›› ይላል፡፡
ጮኸ…ኡ..ኡ ብሎ ጨኸ፡፡ግድግዳው ላይ የተንጠለጠለውን መስታወት በቦክስ ነረተው፡፡መስታወቱ ተፈረካክሶ ወለሉን ሞላው፡፡እጁን ሁለት ቦታ ሸረከተውና በደም ታጠበ…ሰራተኛዋ በርግጋ በውስጥ ልብሷ ብቻ መኝታዋን ለቃ መጥታ ፊቱ እስክትቆም ድርስ እራሱን እንደመሳት አድረጎት ነበር…በሶስት መቶ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቤታቸው የተኙ ጎሮቤቶች ከእንቅልፋቸው ባነው ግራ እስኪጋቡ ድረስ ነው የጮኸው፡፡
‹‹እህቴ የደሀዋ ኢትዬጵያ ዜጋ ልትሆን ትችላለች..ግን ደግሞ የእኔ እህት ነች…..እኔን ትታ ገነትም ቢሆን መቅረት አትፈልግም…እህቴ አንድ ነገር ሆናለች፡፡እህቴ ታፋናለች፡፡››
‹‹ምንድነው …..ምን ሆነህ ነው…..?ኑሀሚ ምን ሆነች?››ሰራተኛዋ ነች የምትጠይቀው፡፡
‹‹በሄደችበት ሀገር ጠፋች ነው የሚሉት..ሰው እንዴት ዝም ብሎ ይጠፋል….?እህቴን ወንጀለኞች አፍነዋት ነው፡፡››
ከእጁ እየተንጠባጠበ ያለውን ደም በጨርቅ እያሰረችለት‹‹ተረጋጋ እስኪ…የሰው ሀገር አይደለች ያለችው ..ምን አልባት መንገድ ጠፍቷት ያልሆነ ስፍራ ገብታ ያልሆኑ ሰዎች እጅ ወድቃ ሊሆን ይችላል ፡፡››ስትል
…ልታፅናናው ሞከረች፡፡
‹‹አንቺ ደግሞ ከፊቴ ጥፊ …መንገድ የሚጠፋት እንደአንቺ ደንባራ ነገር አደረግሻት እንዴ?፡፡›› አበሳጨችው፡፡
‹‹ያው ማንኛውም ሰው በሰው ሀገር ሲሆን መደናበሩ ይቀራል?››
ከተቀመጠበት ተነሳና ጀኬቱን ከሶፋው ላይ አነሳ …ወደመኝታ ቤቱ ሄደና የመሳቢያውን ኪስ ከፍቶ የሆነ ያህል ብር በማውጣት በኪሱ ጨመረ …ከሌለኛው መሳቢያ ሽጉጥ አወጣና በጀርባው ሽጦ ወጣ ፡፡ሰራተኛዋ ሳሎኑ መሀከል ተገትራ ግራ በመጋባት እየጠበቀችው ነበር፡፡ቀጥታ ወደሳሎኑ በራፍ ሄዶ መክፈት ጀመረ፡፡
‹‹እንዴ ብቻህን በውድቅት ለሊት ወዴት ነው…?በዛ ላይ ቆስለሀል…ልብስ ልልበስና አብሬህ ልምጣ›››አለችው፡፡
‹‹ወዴት ነው የምትመጪው?››
‹‹ወዴት ማለት ምን ማለት ነው…?ለእኔም እኮ እህቴ ነች …ልፈልጋት ነዋ፡፡››
‹‹አሀ ልትፈልጌት ..ደቡብ አሜሪካ?››
‹‹የትስ ቢሆን እንኳን ሰው ከብትም ጠፍቶ ዝም ተብሎ መቀመጥ ይቻላል እንዴ?፡፡››
እንግዲያው ደቡብ አሜሪካ ትንሽ እራቅ ስለሚል ወፈር ያለ ልብስ ልበሺ ደግሞም የእግር መንገድ ስላለው ደህና ጫማ አድርጊ››አላት፡፡
‹‹ደግ…መጣሁ ቆየኝ ››አለችና ተንደርድራ ወደመኝታ ቤቷ ሄደች፡፡ይንን ንግግር በሰላሙ ጊዜ ሰምቶት ቢሆን ኖሮ ሆዱን ይዞ እስኪያመው ይስቅ ነበር፡፡ዛሬ ግን አይችልም፡፡
‹‹አለማወቅ ደጉ ››አለና ሳሎኑን ከፍቶ ወጣና ዘግቶ ቀጥታ ወደውጨኛው የአጥር በራፍ ሔደ..ወለል አድርጎ ከፈተውና ፒካፕ መኪናውን አስነስቶ ግቢውንም አካባቢውን ለቆ ወጣ፡፡
አስራአምስት ደቂቃ ከነዳ በኃላ ስልኩን አንስቶ አንድ አእምሮ ውስጥ በስውር የተቀመጠ ቁጥር አስታወሰና‹‹አስቸኳይ›› ብሎ ፃፈበትና ላከው፡፡እዚህ ቁጥር ላይ ሲፅፍ ከሶስት አመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡የሞትና የሽረት ጉዳይ ካልሆነ እንዳይደውል ተነግሮታል፡፡እና ሁል ጊዜ መደወል ወይም መልዕክት መላክ ይፈልግና ግን ደግሞ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ እንደቀልድ ችላ ማለት ስለማይችል ውጦ ስሜቱን ያዳፍነዋል፡፡ያም ቢሆን ግን ስለጤንነቷና ስለለችበት ሁኔታ በተዘዋዋሪም ቢሆን በየጊዜው ያረጋግጣል፡፡ ግን አሁን ጊዜው ደርሷል…ለእሱ ከእህቱ መጥፋት በበለጠ የህይወት እና የሞት ሽረት ጉዳይ የለም...ለዛ ነው ይሄን መልዕክት በድፍረት የላከላት፡፡
መልዕክቱ የተላከው ምስራቅ የምትባል በእሱም ሆነ በእህቱ ህይወት ላይ ከፍተኛ ድርሻ እና ተፅዕኖ ያላት የደህንነት ሰው ስልክ ላይ ነው፡፡አሁን ካጋጠመው ችግር መፍትሄ ልታስገኝለት የምትችል በምድር ላይ አንድ ትክክለኛ ሰው ብትኖር እሷ ነች፡፡እሷ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከአለም አቀፍ የዲፕሎማሲው ማህብረሰብ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ስላላት የሆነ ነገር ልታደርግለት እንደምትችል እርግጠኛ ነው፡፡
ቀጥታ ወደ እስታዲዬም ነው የነዳው፡፡መስቀል አደባባይ ሲደርስ መኪናውን አቆመና ወደ መቀመጫወቹ በመሄድ ኩርምት ብሎ ተቀመጠ፡፡በዛ በውድቅት ለሊት በሰባት ሰዓት አልፎ አልፎ ውር ውር ከሚሉ መኪኖች ውጭ አካባቢው ጭር እንዳለ ነው፡፡ብርዱ ግን ያንሰፈስፋል፡፡የጃኬቱን ዚፕ አንሸራተተና ወደላይ ቆለፈው፡፡ይሄንን ብርድ እና ስቃይ ያውቀዋል ፡፡ሰውነቱ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ ውስጥም ጭምር ነው ያለው፡፡ በርካታ አመታት በዛ በጮርቃ እድሜው ከአንዲቷና ከተወዳጅ እህቱ ጋር በረንዳ ኖሮ ያውቀዋል፡፡አሁን መልዕክት ልኮላት እስክትመልስለት ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ በብርድ እየተጠበሰ የሚጠብቃት ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት እንዳገኘቻቸው በትዝታ አመታትን ወደኃላ ተመልሷ ማመንዠግ ጀመረ ፡፡የ12 አመት ጮርቃ ታዳጊ እያሉ እንደተለመደው 22 በሚገኝ በረንዳቸው ላይ በተለመደው መልኩ ተኝተው ነበር፡፡ሰዓቱ ልክ አሁን ባለበት ተመሳሳይ ሰዓት ላይ ነው ፡፡ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ፡፡እሱና እህቱ እርስ በርስ ተቃቅፈው አሮጌ ብርድልብስና ከላይ ጆንያ ደርበውበት ጋደም ብለው ወጪ ወራጁን በማየት ላይ ነበሩ፡፡
‹‹ምነው ወንድሜ እንቅልፍ እምቢ አለህ እንዴ?››ስትል ኑሀሚ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ እህቴ…ያቺን ሴትዬ አየሻት?››
‹‹የቷን?››
‹‹ያቺ ከስልክ ፖሉ አጠገብ ያለችው ልጅ፡፡››
ከትከሻዋ ቀና አለችና አየቻት‹‹አዲሷን ልጅ እያልከኝ ነው?››
‹‹አዎ…አዲሷን ልጅ…፡፡››
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

አቶ ኃይለ መለኮት እቤታቸው ባለ የገዛ ቢሯቸው ውስጥ ተሸከርካሪ ወንበራቸው ላይ ተቀምጠዋል…በቀኝ እጃቸው የሚያብረቀርቅ ማካሮብ ሽጉጣቸውን ይዘው ፊታለፊታቸው ያሉት ሶስት ግለሰቦች ላይ በየተራ እያነጣጠሩ ምላጩን በስሱ እየዳበሱ ይናገራሉ

‹‹በመጀመሪያ ማንን ልግደል?››

‹‹ጌታዬ ይቅር ይበሉን…አጥፍተናል….››

‹‹አጥፍተናል….ጥፋት እኮ በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ስህተት የሆነ ድርጊት ስታደርግ ነው፡፡ለምሳሌ እዚህ መኖሪያ ቤቴ ላይ ጋዝ አርከፍክፈህ ክብሪት በመለኮስ ግማሹን ህንፃ ብታወድመው ጥፋት አጥፍተሀል ብዬ የጠየቅከውን ይቅርታ ልቀበልህ እችላለው፡፡ ምክንያቱም እቤቱን አሁን ካለበት ይዘት ይበልጥ አስውቤ ከእንደገና ላስገነባው እችላለሁ…ወይም ከፋብሪካዎቼ ትልቁን መርጠህ ሙሉ በሙሉ ብታወድመው እንደጥፋት ቆጥሬ ይቅርታህን ልቀበል እችላለው…ወይንም ሽጉጥህ ባርቆብህ ቀኝ እጄን ብትመታኝና በዛ የተነሳ እጄ ቢቆረጥ አዎ ይቅርታህን ልቀበል እችላለው፡፡ግን አሁን ምንም አላስቀረህልኝም፡፡ልጄ ሁለ ነገሬ ነች…ምንም መተኪያ ምንም ማካካሻ የላትም…ያ ማለት ይቅርታ ላደርግላችሁ ፈፅሞ አልችልም.››

‹‹ጌታዬ ይገባናል፣ አንተ ትክክል ነህ..ግን ቢያንስ በፍለጋው ላይ ጠንክረን እየሰራን ነው….የሆነ ትንሽ ቀን ጨምርልንና አቅማችንን አሟጠን እንፈልጋት… የሆነ ያህል ጊዜ ስጠን… ካልተሳካልን ያሰብከኸውን ታደርጋለህ፡፡››

‹‹አዎ እሱማ አደርጋለው….ዋጋማ ትከፍላላችሁ….አሁን የምናደርገው…..››ንግግራቸውን ሳያጠናቅቁ ስልካቸው ጠራ…የደቀኑትን ሽጉጥ ሳያወርድ ስልኩን አንስተው ማውራት ጀመሩ፡፡

‹‹እሺ…ጥሩ …ሶስቱም ነው እይደል… በጥንቃቄ ጠብቋቸው››
ስልኩን ከዘጉ በኃላ ንግግራቸውን ቀጠሉ‹‹ስልኩ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ…?የእናንተ የሁለታችሁን አንዳንድ ልጃችሁን ያንተን ደግሞ ምትወዳትን ሚስትህን አሳግቼቸዋለው…ልጄ በሚቀጥሉት ሶስት ቀን ውስጥ ተገኝታ ወደቤቷ ካልተመለሰች ያው የምወዳትን ልጄን ስላሳጣችሁኝ ለዛ ክፍያ የምትወዱትን ሰው ታጣላችሁ ማለት ነው፡፡››ሲል ሰቅጣጭ መርዶ አረዷቸው፡፡

ሶስቱም ሰዎች ላይ የታየው ድንጋጤ ሲእላዊ ነበር፡፡፡አቶ ኃይለልኡል ሰዎቹን ከቢሮቸው አሰናብተው ሽጉጡን ወደመሳቢያው ውስጥ መልሰው በማስቀመጥ ቆለፉበትና ወጥታው ወደ ባለቤታቸው ወ.ሮ ስንዱ መኝታ ቤት ሄዱ
….ሚስታቸው አልጋው ላይ ተሰትረው ጉልኮስ ክንዳቸው ላይ ተሰክቶ እህህ እያሉ ነው..ለዘመናት ወደዋቸው የማያውቁት ባላቸውን ድምፅ ሲሰሙ የከደኑትን አይን ገለጡ እና በመከራም ቢሆን ከንፈራቸውን አነቃነቀው ማውራት ጀመሩ

‹‹ኃይሌ…ልጃችን አልተገኘችም?››

‹‹አይዞሽ አታስቢ ..ትገኛለች….አንቺ ምንም አትጨነቂ››ሊያፅናኗቸው ሞከሩ፡፡

‹‹እንዴት አልጨነቅ…?በዚህ አለም ላይ ያለቺኝ እሷ ብቻ ነች..በህይወቴ ሙሉ የበደልከኝን በደል እንድረሳልህ…የሰራህብኝን ስራ ይቅር እንድልህ ከፈለክ ልጄን አግኝልኝ….ልጄን ካገኘህልኝ ያልከኸውን ሁሉ አደርግልሀለው….እንደውም ምንም ሀብት ሳልካፈልህ እፈታሀለው…እፈታህና ገዳም እገባለው..አዎ ልጄ ሰላም መሆኗን ካረጋገጥኩ ከህይወትህ ዞር እልልሀለው›

‹‹አረ ተይ …ለእኔም ልጄ እኮ ነች…እሷን ለማግኘትና ወደቤቷ ለመመለስ ከአንቺ ጋር ይሄንን አድርጊልኝ እያልኩ የምደራደር ጭራቅ ነገር እመስልሻለው….?ተይ እንጂ..አሁን ወጣ ብዬ ፖሊሶቹ ምን ላይ እንደደረሱ መጠየቅ አለብኝ..ሀኪሞቹ ሚሉሽን ስሚና ጤናሽን ተነክባከቢ..ልጃችን ስትመጣ እንደዚህ ሆነሽ እንደታገኚሽ አልፈልግም…እናቴ በእኔ ምክንያት ሽባ ሆነች ብለ መፀፀት የለባትም››ብሎ ወጥቶ ሄደ…..
///
በፀሎት ከእንቅልፏ የባነነችው በቤቱ ውስጥ ግርግር እና የብዙ ሰው ድምፅ ስትሰማ ነበር..አይኖቾን ስትገልጥ ግን ያሰበችውን ያህል ብዙ ሰው አልነበረም ነበር…ወ.ሮ እልፌ
፤አቶ ለሜቻና አንድ ሙሉ ሱፍ የለበሰ ጎልማሳ ሰው ነበር በቤቱ ያሉት….ግን ያ ጎልማሳ ሰው ሲያወራ ድምጹ መመጠኛው እንደተበላሸበት ማይክራፎን ከጣሪያ በላይ ይጮኸ ስለነበረ የብዙ ሰው ድምጽ ይመስላል….
አይኗን ስትገልጥ አየና ወደእሷ ተጠጋ.‹‹ልጄ ተነሳሽ..?ጥሩ …ይሄ ዶክተር ታፈሰ ይባላል..የጓደኛዬ ልጅ ነው….አንቺን እንዲያይልኝ አስቸግሬው ነው፡፡›››አቶ ለሜቻ ናቸው ተናጋሪው፡፡

‹‹አባቴ ዝም ብለህ ነው እኮ የተቸገርከው..ደህና ነኝ እኮ››
ከወ.ሮ እልፍነሽ ጋር በተስማማችው መሰረት ቢሻክራትም አንቱታውን በአንተ ቀይራ ማውራት ጀመረች…

‹‹ደህና መሆንሽና አለመሆንሽን እኔ ሀኪሙ አይቼ ብወስን አይሻልም›› ዝም አለችው….
ወደእሷ ተጠጋና  አያት…ግንባሯና ከፊል ፊቷ በስነስርአት መታሸጉን አረጋገጠና  ..አንድ መርፌ በክንዷ ወግቷት መድሀኒት አዘዘላት…
‹‹በቃ ጋሼ..የወንድሞት ልጅ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች..ቁስሉ ጊዜውን ጠብቆ ፋሻው ተነስቶ በደንብ ፀድቶ ከእንደገና መታሸግ አለበት…›››

‹‹ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም እያልከኝ ነው?››

‹‹አይ የለም ሰላም ትሆናለች..ግን ምን አልባት ፊቷ ላይ ጠባሳ ሊሆንባት ይችላል፡፡››

‹‹ያንን ማስቀረት አይቻልም?››አቶ ለሜቻ ጠየቁ፡፡

‹‹ያው የቆዳ ስፔሻሊስቶች ያስተካከሉታል..በአሁኑ ጊዜ ብር ካለ የማይስተካከል ነገር የለም..ዋናው በህይወት መትረፏና አካለ ጎዶሎ አለመሆኗ ነው…የጠባሳው ነገር የገንዘብ ጉዳይ ነው… ይስተካከላል፡፡››

‹‹ይሁን እንግዲህ…….አንተንም አስቸገርኩህ››

‹‹አረ ጋሼ…ለርሶ ባልታዘዝ አባቴ አያናግረኝም….በማንኛውም ሰዓት ካመማት ደውሉልኝ..አሁን ልሂድ….፡፡እግዜር ይማርሽ እህቴ››

‹‹አመሰግናለው ዶ/ር፡፡››

‹‹ዶ/ር አቶ ለሜቻን አስከትሎ ቤቱን ለቆ ወጣ ..ክፍል ውስጥ ወ.ሮ.እልፍነሽና በፀሎት ብቻ ቀሩ፡፡

‹‹ጋሼ ዝም ብሎ እኮ ነው የሚጨነቀው?››

‹‹እሱ..እንዲሁ ነው….ታያለሽ ነገ ደግሞ ሌላ ዶክተር ለምኖ ይዞ ይመጣል..እስክትድኚ እረፍት አይኖረውም››

አቶ ለሜቻ ተመልሰው ከመምጣታቸው በፊት ለሊሴ ከሄደችበት ተመልሳ መጣች፡፡ ይዛ የመጣችው ዕቃ ግን የሳሎኑን ግማሽ የሸፈነ ነበር….ከአምስት በላይ ፔስታል ከባለታክሲው
ጋር እየተጋገዙ ወደውስጥ አስገቡ….ከገዛችው ዕቃዎች ውስጥ ለበፀሎት አዲስ አንሶላዎች
…ምቾት ያለው ብርድልብስ ፣ቢጃማ ..ሸበጥ ጫማ..ቅባት…ፓንቶች..ብቻ ያስፈልጋታል ያለችውን እና በእይታዋ የገባላትን ዕቃ ሁሉ ገዝታ ነበር..ከዛ የቤት አስቤዛ አትክልቱን..ፍራፍሬውን..ፓስታ ..መኮሮኒ..ስጋና የመሳሰሉትን እልክ የታጋባች ይመስል ቤቱን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በቁሳቁስ ሞላችው…፡፡
አቶ  ለሜቻ  ዶክተሩን  ሸኝተው  ሲመለሱ  ትተው  የሄዱት  ሳሎን  ሌላ  መልክ  ይዞ ሲጠብቃቸው ከመደንገጣችው ብዛት ባሉበት ደርቀው ቆሙ….

‹‹ሊሊሴ ምንድነው ይሄ ሁሉ?››
‹‹አየህ አባዬ አንሶላው አያምርም…

ብርድ.ልብሱስ….?.እሄው ቢጃማም ገዛሁላት…››

‹‹ጥሩ አደረግሽ…ብሩን ከየት አመጣሽው?››

‹‹እኔማ ከየት አመጣለው….እራሶ ሰጥታኝ ነው፡››አለች ወደበፀሎት እየጠቆመች፡፡

‹‹ይሄንን ካሮት፤ ቆስጣ ፤ስጋ ፤መኮሮን ይሄን ሁሉ በእሷብር ነው የጋዛሽው ››

‹‹አዎ አባዬ››

‹‹እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ ለሊሴ…?ችግር ላይ ካለች ልጅ እንዴት? ››
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

ቀነ ጎደሎ

ጨለማ በተቀላቀለበት ሌሊት ተነሱ፡፡ ወደ አዳማ ለመሄድ ተቻኩለዋል፡፡ ከቡቲካቸው አልባሳት እና ሌሎች እቃዎችንም ጫኑ፡፡ እንዳይረፍድባቸው ሹፌሩን ፍጥነት ጨምሮ እንዲነዳ አዘዙት፡፡ ከወትሮው በተለየ መልኩ ደብሯቸዋል፡፡ ሰውነታቸውን ከብዷቸዋል፡፡ ፊታቸውን ጨፍጓቸዋል፡፡ አፋቸውን እሬት እሬት ብሏቸዋል፡፡ ደጋግመው አፋቸውን በባዶው አላመጡት፡፡ ለውጥ ግን  አላመጣላቸውም

ለሹፌሩ "ዛሬ ደግሞ ምን እንደሆንኩ እንጃ አፌን እሬት እሬት እያለኝ ነው" አሉት፡፡

"ምነው ቁርስ አልበሉም እንዴ?" ደግሞ ደስተኛ አይመስሉም፡፡ ደህና አይደሉም"? አለ፡፡ ሹፌራቸው ሰለሞን፡፡
"ኧረ ! ደህናነኝ፡፡ ብቻ ውስጤ እርብሽብሽ ብሏል፡፡ ሌሊትም ደግሞ ሲያቃዥኝ ነው ያደረው፡፡ ጥዋትም ቁርስ ወደ አፌ ስል አልዋጥ አለኝ፡፡ ምን እንደሆንኩ ለራሴም ሊገባኝ አልቻለም አሉ ፤ አቶ ላንቻ፡፡

"አስበውት ያላሳኩት ነገር አለ እንዴ"?

"አስቤ ያላሳካሁት ነገር እንኳን ያለ አይመስለኝም፡፡ ምንአልባት ዛሬ ማርፈዴ ብቻ ነው ትንሽ ያበሳጨኝ፡፡ ለምን እንደረፈደብኝም ሳላውቅ ከሩቅ የሚመጣ ደንበኛ ነበረኝ ያሬድ የሚባል፡፡ እንዴው ጠብቆኝ ሲያጣኝ ባልተመለሰ ብቻ እንጅ ቢያድግልኝ እንኳን ከሱቅ የትም ስለማይሄድ አምሽተንም ብንደርስ እናገኘዋለን፡፡ ለማንኛውም ነዳጅ ሰጠት አድርገህ ቶሎ ቶሎ ንዳው ፡፡

"እሽ አሁንም እኮ ፈጥነናል፡፡ ግን እኔም እኮ እጄ ሁሉ ተሳሰረብኝ" አለ ሰለሞን፡፡

"ምነው አንተ ደግሞ ምን ሆነህ ነው ? ስትጨፍር እና ስትጠጣ አድረህ ፤ ምን አልባት እንቅልፍ መጥቶብህ እንዳይሆን"?

"እንኳን ስጠጣ ፣ ስጨፍር ላድር ፤ የጨብስም አጥቼ የዘጠኝ ብር አህያ መስየ ነው፡፡ ያደርኩት ፡፡

.አቶ ላንቻ የሰለሞን ፈሊጣዊ ንግግር አሳቃቸው፡፡ የዘጠኝ ብር አህያ ማለት ደግሞ ምን ማለት ነው? መቼም የዛሬ ልጆች የማታመጡት ጉድ የለም ፡፡

በመስኮት አይናቸውን ወርወር አደረጉ፡፡ ከበስተቀኝ በኩል የጋኔል ቁራጭ የሚመስል ጥቁር ውሻ ሊያቋርጣቸው ይሮጣል፡፡ ሰለሞን አፍጥነው ፣ አፍጥነው መኪናውን ፤ ይሔ ውሻ ሳያቋርጠን ፤ እንቅደመው አሉ፡፡ ሆዳቸው ተርፏ ተርፏ እያለ፡፡

ማርሽ ቀየረም ፤ ነዳጅ እረገጠም ፤ ውሻውን ግን ሊቀድመው አልቻለም፡፡ ውሻው አቋርጧቸው አለፈ፡፡

"ጭራሽ መንዳትም አቃተህ ፤ ውሻ መቅደም ያቅትህ አሉ፡፡ በፊታቸው ላይ የደም ስራቸው በንዴት እየተወጣጠረ፡፡

"መኪናው ሰርቪስ ከገባ ቆይቷል፡፡ ፍጥነት ጨምሬ ስነዳ እንዳይቆም ስለፈራሁ ነው፡፡ እንጅ ውሻ መቅደም አቅቶኝ አይደለም" ፡፡

የባሰ በጭንቀት ላይ ጭንቀት ሆነባቸው፡፡ መኪናው ከመንገድ ላይ እንዳይቆም ስጋቻ አደረባቸው፡፡ብቻ እንዳያዋርደን የባሰ ለማርፈዱ ሲቆጨን ከመንገድ ላይ ቆሞ፡፡ "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" እንደ ሚባለው ከሁለት አጉል እንዳንሆን፡፡ እያሉ ከአፋቸው ተናግረው ሳይጨርሱ መኪናው ማዞሪያ ላይ መሪው አልዞር አለ፡፡ መስመር ሳተ፡፡ ሰለሞን ላብ በላብ ሆነ፡፡ ጎትቶ የማስገባት ያህል መልሶ ወደ መስመር አሰገባው፡፡

አቶ ላንቻ ከአሁን አሁን ተገለበጠ እያሉ ሰለሞን መሪው ሲያዞር ያገዙት ይመስል አንገታቸውን አብረው ያዞሩ ነበር፡፡

ከመስመር ሲገባ ትንሽ ትንፏሻቸው መለስ አለ፡፡ በል አሁን ቀስ ብለህ ንዳ የትም ጫካ እንዳታስቀረኝ አሉ ፤ እየፈሩም ቢሆን፡፡

"አሁን እግዚአብሔር ነው ያተረፈን ፡፡ ተገልብጦብኝ ነበር፡፡ እንጃ ብቻ ዛሬ በሰላም የምንገባ አልመስለኝም፡፡ ሆዴ ሁሉ በጣም ፈርቷል ፡፡

በስ መዓብ በል፡፡ ደግሞ ታሟርታለህ እንዴ ? አንዳንዴ ማሟረት ጥሩ አደለም፡፡ አፍ ሊከተል ይችላል አሉ ፤ አቶ ላንቻ፡፡

"አሁን ደግሞ ጭሱ መሽተት ጀምሯል፡፡

"እስኪ አቁመህ ውረድና እየው፡፡ የጭስ መውጫው ታፍኖ ይሆናል፡፡

ሰለሞን ወርዶ አየው፡፡ መኪናው ከመሽተት ውጭ የሚታይ ነገር አላገኘም፡፡ ተመልሶ ከሁለተኛ ማርሽ ወደ ሶስተኛ ማርሽ ቀይሮ ነዳ፡፡

የባሰ የመኪናው ድምፅ ተቀይሮ የመኪና ድምፅ መሆኑ ቀርቶ እንደ ወፍጮ መንኮራኮር ጀመረ፡፡ በስጋቻ አይኖቹ ተርገበገቡ፡፡ ቀኑ ወደ ጨለማ ተቀየረበት፡፡ አንዳንዴ የመኪና መብራት ያበራል፡፡

የመኪና መብራት የምታበራው መንገዱ አልታይ አለህ"? እንዴ አሉ ፤ አቶ ላንቻ፡፡

አንዳንዴ ጨለማ እየመሰለኝ ነው እኮ፡፡ አሁንማ እጄ ሁሉ እየተንቀጠቀጠብኝ ነው፡፡ እስኪ ከእኔ ይሻሉ እንደሆን ይሞክሩት ፡፡

"እኔ ከአንተ እሻላለሁ ብለህ ነው፡፡ ምን አይነት ቀነ ጎደሎ ነው ፤ የገጠመን ዛሬ፡፡ እያሉ የሰለሞን ቦታ ቀይረው መኪናውን ለመንዳት መሪውን ጨበጡ፡፡ የባሰ እጃቸው ተሳሰረ፡፡ ግራና ቀኝ ዋዥቁ፡፡

"ፍሬን ይያዙ ፣ ፍሬን ይያዙ ፣ መስመር ስቷል፡፡ እያለ ጮኸ ሰለሞን፡፡ መኪናው ግን አልቆመም፡፡ እስከ አሁን ታግሸ አገለገልኳችሁ፡፡ የዚህ አለም ኑሮ ይበቃኛል፡፡ ብሎ አራት እግሩን ወደ ላይ ሰቅሎ ከመስመር በታች ወርዶ ተከረበተ፡፡

የፈሩት አልቀረም፡፡ ሰለሞን በደረሰው አደጋ ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ አቶ ላንቻ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ህይወታቸው ቢተርፍም ወደ ህክምና ሲሄዱ ጭንቅላታቸው በጣም ተጎድቶ ስለነበር ህክምናም ሳይደርሱ ህይወታቸው በመንገድ ላይ አለፈ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 19 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ
================

ወንጀሉ በተፈፀመ በ15ተኛው ቀን ለአለማየሁ ደውሎለት ነበር፡፡

‹‹ሄሎ አሌክስ..እንዴት ነህ?››

‹‹ሰላም ነኝ..አንተስ..?ሰፍር ?እነሰሎሜ ደህና ናቸው?››

‹‹ሁሉም ሰላም ነው….አንተ ጋርስ? ስልጠናው እንዴት ነው?››

‹‹ከባድ ነው.. ግን ያው ስፖርት ስለምወድ…ለእኔ ብዙም አልከበደኝም፡፡››

‹‹ጥሩ…..››

‹‹ምነው የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ ?ድምፅህ እኮ ጥሩ አይደለም…ሰሎሜ ምን ሆነች?››

‹‹አይ እሷ ደህና ነች..አባቴ ነው፡፡››

‹‹አባትህ ምን ሆኑ?
አመማቸው?››

‹‹አልታመመም..ግን የሆነ ወንጀል ሰርቷል..ያንን ወንጀል መስራቱን እኔ ብቻ ነኝ ማውቀው..አሳልፌ ለፖሊስ ልስጠው ወይስ ዝም ብዬ ልቀመጥ? ግራ ገብቷኛል…ምክር እንድትሰጠኝ ነው የደወልኩት..በዚህ ጉዳይ ላይ አንተን ብቻ ነው የማምነው፡፡››

‹‹ምን አይነት ወንጀል ?ከባድ ነው?››

‹‹በጣም ከባድ….እጅግ በጣም ከባድ…በእድሜ ልክ ወይም በሞት የሚያስቃጣ ወንጀል፡፡››

‹‹ግን እኮ አላዛር..አባትህ ትልቅ ሰው ናቸው..በዚህ እድሜቸው የእስር ቤትን ህይወት አይችሉም ..ወዲያው ነው የሚሞቱት…ለመሆኑ ወንጀሉ ምንድነው?››

‹‹የእንጀራ እናቴን ታስታውሳታለህ?››

አላዛር ስለእንጀራ እናቱ ሲያነሳ አለማየሁ ጠቅላላ ሰውነት ጆሮ ነው የሆነው፡፡ፈራ ተባ እያለ‹‹አዎ አስታውሳታለው..ምን ሆነች?››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹አርግዛ ነበር››
የሚያውቀው ነገር ቢሆንም በተሳሰረና በተወለካከፈ ድምፅ   ‹‹በእውነት….?እሱን አላውቅም ነበር››አለው፡፡

‹‹አዎ እኔም አላውቅም ነበር…እና ያረገዘችው ከሌላ ሰው ነው፡፡››

‹‹ከሌላ ሰው ?ከማን …?›

‹‹እሱን እኔ አላውቅም ..አባቴም የሚያውቅ አይመስለኝም….››

በሚርገበገብ ድምፁ በፍራቻ ‹‹እና ምን ተፈጠረ…?››ሲል ጠየቀው፡

‹‹አባቴ ልጁ የእሱ እንዳልሆነ በምን መንገድ እንደሆነ አላውቅም አወቀና ..እርጉዟን ሚስቱን ገደላት››

‹‹ምን ?ገደላት….››

‹‹አዎ ገድሎ የማላውቀው ቦታ ቀብሮታል….አሁን እሱም ሀገር ጥሎ ጠፍቶል..እና ምን እንዳደርግ ትመክረኛለህ?፡፡››

አለማየሁ በሰማው መርዶ የደነገጠው ድንጋጤ መጠን የሌለው ነው..እናትና አባቱ የሞቱ ሰሞን እንኳን እንደዛ አይነት ፍፅም ቀዝቃዛ ሀዘን አልተሰማውም ነበር ‹‹እሳቸው ሳይሆኑ እኔ ነኝ የገደልኩሽ፡፡››ሲል አሰበ፡፡

ድምፅ የጠፋበት አላዛር‹‹አሌክስ እየሰማሀኝ ነው?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አላዛር ይቅርታ ይሄ ጉዳይ ከባድ ስለሆነ ላስብበትና ነገ ልደውልልህ?››አለው፡፡ከንግግሩ ድምፀት  የስሜቱን  መሰባበርን መረዳት ይቻላል፡፡

‹‹እሺ በቃ በደንብ አስብበት..ወንድሜ በጣም ተጨንቄልሀለው፡፡››

‹‹እሺ ጠንከር በል አይዞህ…ቸው፡፡››

አለማየሁ ስልኩን እንደዛጋ ወዲያው ያደረገው ነገር ሲሙ ላይ ያሉትን አድራሻ ወደቀፎው በማስተላለፍ  ስልኩን ከፍቶ  ሲሙን አውጥቶ መሰባበር ነው፡፡
ይሄ የእሱ ጥፋትና መዘዝ ስለሆነ ማንም ላይ ለመፍረድ ሆነ ለማንም ምክር ለመስጠት መብትም ሆነ ብቃት እደሌለው አምኗል፡፡በህይወት ውስጥ ያለውን እድል አሰበና ምርር ብሎ ነበር ያለቀሰው ፡፡መቼም ቢሆን ከማንም ሴት ጋር ፍቅር ፍቅር ላለመጫወትና ረዘም ያለ ግንኙነት ውስጥ ላለመግባት ወሰነ፡፡ከአላዛርም ሆነ ከሰሎሜ ከዛም አልፎ  ከአደገበት አካባቢ ከሚያውቃቸው ሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ አቋረጠ…በብቸኝነት በሶስት ወርም ሆነ በስድስት ወር አንዴ ደውሎ እንዴት ነሽ? ሚለው አሳዳጊ እናቱን  እቴቴን ብቻ ነበር፡፡

አላዛር  ግን ከአለማየሁ ምንም አይነት መልስም ሆነ ምክር ባያገኝም ከፀፀቱ ጋር ህይወቱን ቀጠለ….አባትዬውም በሄዱበት የት እንደገቡ ሳይታወቅ ጠፉ፡፡አላዛር አንገቱን ደፍቶ ትኩረቱን ስራው ላይ አደረገ፡፡በንግዱ ጠንካራ ሰራተኛ ሆነ..፡፡

ከማትሪክ በኃላ  ወደተግባረ እድ የሞያ ማሰልጠኛ ተቋም  ገብቶ የጀመረውን ኮንስትራክሽን ትምህርት አጥብቆ ገፋበት  ..ከሰሎሜ ጋር የነበራቸውም ጓደኝነት ልክ እንደወትሮ ግለቱን እንደጠበቀ ቀጠለ፡፡ እንደውም ከአራት ጓደኛሞች ሁለት ብቻ ስለቀሩ በተሻለ መተሳሰብና በመረዳዳት   ትምህርታቸውን  መማር ብቻ ሳይሆን በህይወትም መተጋገዝና መረዳዳት  ቀጠሉ፡፡እሷ ብቸኛ ስራዋ የጀመረችን የአካውንቲንግ ትምህርት መማር ብቻ ሲሆን እሱ ግን ልክ እንደተለመደው ሁለት ኃላፊነት ነበረበት፤  እየተማረ   ንግዱንም በጎን ማስኬድ ፡፡ ሱቁ እየሰራ..በጎንም ሌሎች ተባራሪ ስራዎች እየሰራ ቀጠለ፡፡እንዲህ እንዲህ እያለ ጊዜ መብረር ጀመረ ፡፡
በዚህ ጊዜ ሁሉ ሁሴን በአመት አንድ ጊዜ እየመጣ በክረምቱ የዩኒቨርሲቲ ዝግ ወቅት  ለአንድ ወር አብሮቸው ያሳልፍ ነበር፡፡በዛን ጊዜ ታዲያ ነገሮች ሁሉ የተለየ ገፅታ ይኖራቸዋል፡፡ከበፊቱ በተለየ አብረው ማሳለፍ..ብዙ መዝናኛ ቦታዎች አብረው  መሄድ ..ሌሎች ለወደፊት ትዝታ የሚሆኑ ኩነቶችን መፍጠር በአጠቃላይ አሪፍ በሚባል  ጣፋጭ ጊዜ ያሳልፈና መልሰው ወደዩኒቨርሲቲ ይልኩታል፡፡

የሆነ የህይወት ጉዞ መጀመር ነው እንጂ ሚከብደው አንዴ ቆራጥ ውሳኔ ወስነው መንገድ ውስጥ ገብተው እግር ማንቀሳቀስ ከጀመሩ  እንቅፋትና ኮረኮንች ከመሀከል ቢያስቸግርም መንገዱ ማለቁና ካሰቡት መዳረሻ መደረሱ አይቀርም ፡፡በተለይ በዚህ ዘመን ሳዕታት እንዴት እንደሚስፈነጠረሩ… ቀናቶች እንዴት እንደሚከንፉ ወርና አመታት እንዴት እንደሚበሩ አይታወቅም፡፡መስከረም፤ጥቅምት….ብለን ሀምሌና ነሀሴ ላይ እንዴት እንደምንደርስ ያስገርማል፡፡ እናም አላዛርና ሰሎሜም የጀመሩትን የኮሌጅ ትምህርት ብዙም ሳይሰላቹና መቼ ባለቀ ሳይሉ ለምረቃት በቁ፡፡ …ሁሴንም እረፍቱን አስታኮ ለምርቃታቸው አዲስአበባ ነው የሚገኘው፡በዛም ምክንያት ምርቃታቸው በጣም ደማቅና በማይረሳ ትዝታ የታጨቀበት ሆኖ እንዲያልፍ ሆኗል…ሶስቱም በየልባቸው አለማየሁም በሆነ ምክንየት ስለምርቃታቸው ሰምቶ ሰርፕራይዝ ሊያደርጋቸው ሶስት አመት ከተደበቀበት ድንገት ብቅ ብሎ ያስደምመናል ብለው ይጠብቁ ነበር፡፡ያ ምኞታቸው ግን እውነት ሊሆን አልቻለም፡፡በተለይ ሰሎሜ አለማየሁን በተመለከተ  ሙሉ በሙሉ  ተስፋ የቆረጠችበት ወቅት ነበር፡፡‹‹በቃ በዚህ ጊዜ ሊያየን ካልመጣ መቼም ወደህይወታችን ተመልሶ ላለመምጣት ወስኗል ማለት ነው፡››ስትል ደመደመች፡፡…በዛም ምክንያት እሷም እስከወዲያኛው ስለእሱ  ረስታ ህይወቷን ወደፊት መቀጠል እንዳለባት ወሰነች፡፡፡ሁሴን ምርቃታቸውን በደስታና በፈንጠዝያ አብሮቸው አክብሮ ወደዩኒርሲቲው ሊመለስ ቀናቶች ነው ቀሩት፡፡ ከመሄዱ በፊት ግን  ብዙ ጊዜውን ሁለት ጓደኞቹ ጋር ነው የሚያሳልፈው፡፡አሁን በምሽት ከአላዛር ጋር ሆቴል ተቀምጠው እየተዝናኑ ነው፡፡ሰሎሜ አብራቸው የለችም፡፡

‹‹ሁሴኖ በእውነት ምርቃታችንን በጣም ነው ያደመቅክልን….› አለው አላዛር፡፡የተናገረው ከልቡ ነው፡፡እስከአሁን ምርቃታቸውን በተመለከተ ያደረገላቸውን ነገር አንስቶ የማመስገኑን እድል አላገኘም ነበር፡፡

‹‹ምን ነካህ ወንድሜ..አንተም አንተ ነህ..ሰሎሜም ያው የምታውቃት ነች…ቢቻል ለእናንተ…››

‹‹አይዞኝ በሚቀጥለው አመት በዚህን ጊዜ  ያንተን ምርቃት  ደረጃውን በጠበቀና በሚመጥንህ መልኩ ነው የምናከብረው፡፡››

‹‹አይ ..እኔ ተመርቄ የደካማ እናቴ ህይወት ለማስተካከል እንጂ ለምርቃቱ ጋጋታ ምንም አይነት ኢንተረስት የለኝም››ሲል ትክክለኛ ፍላጎቱን ሳይደብቅ ነገረው፡፡
#አላገባህም


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///

‹‹በቃ አትንዘላዘልብኝ ..ልበስ››ኮስተር አለችበት፡፡

ይህ ምሽት ከዘሚካኤል ጋር በፍቅር ከመውደቅ  ጋር ወይም ከእሱ ጋር የወደፊት  ከህልም ከማለም ጋር  ምንም ግንኙነት አልነበረውም። እና ሁሉም ነገር የሚከናወነው ለአካላዊ ደስታ ብቻ ተብሎ ነው። የልጅነት ፍቅረኛዋ ለዚህ  ሁሉ አመታት  የሆነ ነገሯን  ሰርቆባታል እና አሁን ሊመልስላት ይገባል ። እና ጉዳዩ ያ ብቻ ነበር።

ጠረጴዛ ላይ ያለው ብርጭቆ አነሳና ከተጎነጨለት በኋላ  እጁን ትከሻዋ ላይ ጫነባት ፡፡
፤ዝም አለች…እጁን በአንገቷ ዙሪያ አሻግሮ በቲሸርቱ ስር አሾለከና ወደጡቷ  መጓዝ ጀመረ..ሽምቅቅ አለች፡፡

‹‹ዘና በይ እንጂ። ይህ ለሁለታችንም ጥሩ ይሆናል፣ ቃል እገባልሻለው።›› መልሶ እጁን አወጣና ወደአልጋው ላይ ቀድሟት በመውጣት እጇን ይዞ ወደ አልጋው እየሳበ ።

‹‹ተነሽ በቃ  እንተኛ። ››አላት፡፡

ዝም ብላ ተጎተተችለትና ሙሉ በሙሉ ወደ አልጋው ላይ ወጣች ።መናገር አልቻለችም፣ የልቧ ፈጣን ምቶች በጉሮሮዋ ላይ ተስፈንጥረው ሚወጡ ይመስላሉ።ወደራሱ ሳበና ደረቱ ላይ አስተኛት፡፡እና እጆቹን ፀጉሯ ውስጥ አስገባና ይልግላት ጀመር…ከመደንዘዞ የተነሳ አይኖቾን ጨፈነች፡፡ከዛ አንገቷን ..ጆሮዋን መሳም ጀመረ …ቃተተች.፡፡ወደታች ዝቅ አለና ቲሸርቷን ገለጠና ከእንብርቷ ጀምሮ እየላሰ ወደላይ ወጣ…ጡቶቾ ጋር ደረሰ የቀኝ ጡቷን ጫፍ በምላሱ እየላሰ የግራውን ጡቷን በእጆቹ እየጨመቀ ያፍተለትላት ጀመር…በፈጣሪ… እንዲህ አይነት ነገር መኖሩን በፍፁም አታውቅም….ጡት ለተሳማ እንዴት ነው መላ ሰውነት እንዲህ ቀልጦ የሚንሳፈፈው…?.በጣም ያስገረማት ጉዳይ ነው፡፡

‹‹ እሺ በቃ አሁን….››ተንተባተበችና እንደምንም ጨክና  ከጡቷ አላቀቀችው

‹‹እስከ ሞት ድረስ የፈራሽ ትመስያለሽ። ምንድነው ችግሩ?፧››ሲላት እንደምንም እያጎለበተችው የነበረው ትንሹ ድፍረት ጥሏት ሄደ…ይሄንን ደግሞ እሱም በግልፅ ማየት ይችላል…፡፡

‹‹መብራቶቹን ማጥፋት እንችላለን?››ብላ በሹክሹክታ ጠየቀችው።

‹‹አላደርገውም።…ውብ እርቃኗን ለማያት ለቀናት ስለእሷ ሳሰላስል የሰነበትኩላትን ልጅ  ሳገኛት …በጭለማ….አይ አይሆንም ..አንቺን ለማግኘት ያን ሁሉ ጥረት የጣርኩት በጨለማ ውስጥ ፍቅር ለመስራት አይደለም።››ተቃወማት፡፡

ጡቶቿ ትንሽ ነበሩ፣ ዳሌዋ ጠባብ እና የልጅ ነበር። ጉንጯን ነካ፣ በዓይኑ ያልጠበቀችው ልስላሴ  እና ፈገግታ ተመለከተች። ' ለመቃወም አፏን ከፈተች እሱ ግን ጣቱን  ከንፈሯ ላይ አሳረፈ።‘

‹‹አትልፊ አልስማማም››አለና የዋናውን መብራት ማብሪያ / ማጥፊያ ለማጥፋት አልጋውን ለቅቆ ወረደ , ደማቁን ብርሀን ቢወገድም አረንጓዴና ደብዛዛ ብርሀን ግን  አሁንም  ቤቱን እንደሞላው ነው፡፡  ከላይ የለበሰውን ካኔቴራ አወለቀና እርቃኑን ወደአላጋው ላይ ወጣ…..እና ቆመ….‹‹ምነው ቁጭ በል እንጂ››

የለበሰውን ቁምጣ ከነፓንቱ አንድ ላይ መዥርጦ አወለቀውና ወደወለሉ ወረወረው….እንደሀውልት የተገተረው እንትኑ አይኗቾን ተቆጣጠረ…..የበለጠ በፍርሀት ተንዘረዘረች፡፡

‹‹ምን እየሰራህ ነው?››

‹‹እንዴ ምን ሰራለሁ.. ልንተኛ አይደል ….?ብርድልብሱን እና አንሶላውን ገለጠና ከውስጥ ገባ…

.‹‹አውልቀሽ ወደእኔ ትመጪያለሽ ወይስ…..?››

ምንም መናገር አልቻለችም….ዝም አለች፡፡‹‹ምንም ልምድ የለሽም አይደል?››ሲል ጠየቃት፡፡፡

‹‹ልክ ነህ። በዚህ ረገድ ብዙ ልምድ የለኝም። እንደውም እውነቱ ለመናገር  እኔ ምንም አይነት ልምድ  የለኝም ›› አለችው ። ማስመሰል ምን ፋይዳ አልነበረው? ከአመታት በፊት ካጋጠማት ከዛ አስጸያፊ ምሽት ገጠመኞ በኋላ በእድሜ ጨምራ እና  በስሜት ጎልምሳ ሊሆን ይችላል… ግን ያ በቂ አይሆንም። ለዛውም እንደ ዘሚካኤል አይነት ከሴት ጋር ባለው ልምድ የበለፀገ አይነት ሰውን ለመቋቋም ፈጽሞ እንደማትችል እርግጠኛ ነች፡፡

‹‹ከብዙ ልምድ ያላቸው ሴቶች ጋር ተኝተሀል ..እና ከእኔ ጋር  በምታደርገው ነገር  ቅር መሰኘትህ  አይቀርም ፣ ››ብላ ጨረሰች ።ሙሉ በሙሉ ተሸነፈች።

‹‹ ውዴ ፣ ስለ እንደዛ አይነት ነገር ፈፅሞ  መጨነቅ አያስፈልግሽም -ሁሉን ነገር አብረን በዝግታና በትግስት እናደርገዋለን….እኔ አንቺን ከማንም ጋር ላወዳድርሽ ሀሳብ የለኝም….››  የእሱ አጽናኝና አበረታች ቃላት  ጉዳቷን እና ውርደቷን ትንሽ አጠበላት።ንግግሩን ቀጠለ‹‹ይህ ፈተና አይደለም.›› ጎተተና ወደውስጥ ስቦ አስገባት፡፡ከዛ ቀስ አለና ቲሸርቷን ወደላይ ስቦ አወለቀውና ወደወለሉ ወረወረው….ከዛ ወደኋላ አጋዳማትና ደረቱ ላይ አስተኛት፡፡

‹‹እንግዲህ እጅ ሰጥቻለው…ችግር የለውም ካልክ….እንደፈለክ አድርገኝ››በማለት ሙሉ በሙሉ እጅ መስጠቷን በይፋ አወጀች፡፡

‹‹ ውዴ አፈጻጸም ላይ  ጭንቀት ካለብሽ ለምንድነው ለተወሰነ ጊዜ  ሂደቱን የማትመሪው?››የሚል አስገራሚ ሀሳብ አቀረበላት፡፡

በድንገት መተንፈስ አቃታት።

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ..?ጭራሽ መምራት…‹‹በል የምታደርገውን እንደፈለግክ  አድርግ፡፡››አለችው፡፡

‹‹ደግሞ እኔም አንቺ የምታስቢውን ያህል  ጎበዝ ላልሆን እችላለው ›› ብሎ ቀጠለ፣ በብልህ ጣቶቹን ጡቷቿን እያፍተለተለ ነው፡ ፡ቃተተች፡፡እሱ ሹክሹክታ በመሰለ ድምፅ መናገሩን ቀጠለ፡፡

ተንቀጠቀጠች፡፡ከአንገቷ ጀምሮ ወደታች ይልሳት ጀመር …ሳታስበው ሰውነቱ ላይ ተጣበቀችበት….ከታች እንትኑ ክፉኛ ቆረቆራት..ደስ የሚል መቆርቆር….የሚበላ እና ሚያሳክክ አይነት መቆርቆር …እሱም እንደተመቻት ስለገባው ይሰመስላል… በጠንካራ ጡንቻው  ሰቅስቆ ወደራሱ አጥብቆ መሳሙን ቀጠለ….እያንዳንዷ የሚስማት ቦታ ልዩ አይነት የተለያየ ጣእም ያለው መስሎ ተሰማት…..ለዘመናት እንደዛ እየሳማት እንዲቆይ ተመኘች….እየቀለጠች ነው….ሆዷና ጀርባዋ በላብ እየታጠበ ነው፡፡እጁን ወደታች ሰደደና በለበሰችው ቁምጣዋንና ፓንቷን ሰቅስቆ ገባ……..‹‹ወይኔ ጉዴ ምን ሊያደርግ ነው?››አሰበች …የእጁን መዳፍ ብልቷ ላይ አሳረፈ……ድምፅ አውጥታ ማቃሰት ጀመረች….ከላዮ ላይ ተነሳና ቀና ብሎ የለበሰችውን ቁምጣን ፓንቷን አንድ ላይ ይዞ ወደታች ጎትቷ ማውለቅ ጀመረ…እግሯን ወደላይ ከፍ በማድረግ ተባበረችው፡፡ወደ ሰውነቱ አጥብቆ አቀፋትና  ከጆሮዋ አንስቶ አንገቷን መሳም ጀመረ….ተቁነጠነጠች፡፡ቀስ እያለ መሳሙንም መዳበሱንም ሳያቋርጥ ወደታች ሄደ… ከዛ አንገቱን እግሯቾ መካከል ደፈቀ….ለፈለፈች….በመላ ሰውነቷ ቤንዚል ተርከፍክፎ ክብሪት የተጫራባት ነው የመሰላት…እጆቾን ፀጉሩ ላይ አድርጋ ታሻሸው ጀመር…ቀስ አለና እየሳማት ወደላይ መጓዝ ጀመረ…  ከንፈሯ ጋር ሲደርስ ቀድማ ተጣበቀችበት….ሙሉ በሙሉ እግሮቾን መካከል ገብቷ ተዋሀዳት….ልዩ ጣፋጭነት ያለው ስቃይ ተሰማት…ስቃዩ እንዲያቆም ግን ፈፅሞ አትፈልግም…ይበልጥ  መቃተት ይበልጥ መሰቃየት ፈልጋለች፡፡ሁለቱም እኩል ከፍተኛ ፍንዳታ ላይ ደረሱ አደኛው ሌለኛውን ወደራሳቸው ጨምቀው አቀፉ..ተርገፈገፉ…..በመከራ ተላቀቁና ጎን ለጎን ተዘረሩ፡፡

ከተወሰኑ ደቂቃዎች እረፍት በኃላ ወደእሷ ዞረና‹‹እንዴት ነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አረ…እንዲህ አይነት ጉብዝና መኖሩን እራሱ የት አውቃለው?››አለችው፡፡

ግንባሩን ወደ እርስዋ አስጠጋ ፣በረጅሙ  ተነፈሰች።‹‹የእኔ ቆንጆ ሁለነገርሽ እንደሚያምር ታውቂያለሽ አይደል?...አይዞሽ ሁሉ ነገር ልዩ ይሆናል…ወደፊት ብዙ የምትማሪው ነገር ሊኖር ይችላል›› አላት፡፡