#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
ጦርነቱ የፈነዳው በአንዱ ፀሐያማ እሁድ ቀን ነበር፡
አይሮፕላኑ እስካሁን ከተሰሩት ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ጦርነቱ የታወጀ ቀን ስድስት ሰዓት ከሰላሳ ላይ አይሮፕላኑ ብቅ ይል ይሆን እያለ ቶም ሉተር ልቡ ተሰቅሎ ወደ ሰማይ አንጋጦ እየጠበቀ ነው።
ቶም ወሬ ለማየት ባሰፈሰፉ ሰዎች ተከቧል፡ የፓን አሜሪካን ኩባንያ ንብረት የሆነው ባህር ላይ ማረፍና መነሳት የሚችለው አይሮፕላን ሳውዝ ሃምፕተን ወደብ ላይ ሲያርፍ ይህ ዘጠነኛው ጊዜ ቢሆንም አሁንም ማራኪነቱ አልደበዘዘም፡፡ ይህ አይሮፕላን አስደናቂ በመሆኑ አገሪቱ ጦርነት
ባወጀችበት ቀን እንኳን ሰዎች እሱን ለማየት ወደሚያርፍበት ቦታ
እየተንጋጉ ነው፡፡ በዚሁ ወደብ ዳርቻ አንዳች የሚያካክሉ ሁለት መርከቦች መልህቃቸውን ጥለው ቢቆሙም እነሱን ነገሬ ያለ የለም፡፡
ታዲያ አይሮፕላኑን እየጠበቁም ቢሆን ሰዎች የሚያወሩት ስለጦርነቱ
ነው ወንዶቹ ስለታንክና መድፎች ሲያወሩ ሴቶቹ በአርምሞ ይመለከታሉ፤
ከፍቷቸዋል። ሉተር አሜሪካዊ እንደመሆኑ ፍላጎቱ ሀገሩ በጦርነቱ እጇን እንዳታስገባ ነው፡፡ ጦርነቱ የእሷ ጉዳይ አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ ናዚዎች በኮሚኒስቶች መጨከናቸው ተገቢ ነው፡፡
ሉተር በንግድ ሥራ የሚተዳደር ሲሆን የልብስ ስፌት ፋብሪው ውስጥ የሚሰሩት ኮሚኒስቶች አንድ ወቅት ላይ ችግር ፈጥረውበት ሊያጠፉት ሁሉ ምንም አልቀራቸውም ነበር፡፡ ትዝ ሲለው በንዴት
ይንቀጠቀጣል፡፡ የአባቱ የልብስ መሸጫ መደብር በይሁዳውያን ተቀናቃኞች
አፈር ድሜ ሊበላ ነበር፡፡ ሉተር ሬይ ፓትሪያርካን በጡት አባትነት ሲይዝ
ግን ህይወቱ ባንድ ጊዜ ተለወጠ የፓትሪያርካ ሰዎች እዚህም እዚያም
አደጋ በመፍጠር ኮሚኒስቶችን ልክ ማስገባት ያውቃሉ አንዱ ከውካዋ
ኮሚኒስት እጁ በማዳወሪያ ማሽን ውስጥ ተወትፎ እንዲቀር ተደረገ፡፡ የሰራተኛ ማህበር ቀስቃሽ አባል በመኪና ተገጭቶ ህይወቱ አለፈ፡ በፋብሪካ ውስጥ ስላለው የደህንነት ደምብ መጣስ ቅሬታ ያቀረቡ ሁለት ሰዎች ቡና ቤት ውስጥ በተፈጠረ ጠብ ቆስለው የአልጋ ቁራኛ ሆኑ፡ አንዷ ችግር ፈጣሪ ቤቷ በእሳት እንዲጋይ በመደረጉ በኩባንያው ላይ ያቀረበችውን ክስ ለማንሳት
ተገደደች፡፡ ከዚህ በኋላ ሰላም ሰፈነ፡፡ ፓትሪያርካ ሂትለር የሚያውቀውን
ያውቃል፡፡ ኮሚኒስቶችን ልክ ለማስገባት እንደ በረሮ መንጋ መደምሰስ ነው::
ሉተር ይህን እያሰላሰለ እግሩን ወለሉ ላይ ይጠበጥባል፡፡ አንዲት ጀልባ
አይሮፕላኑ የሚያርፍበት የባህር ክፍል አካባቢ ለማረፍ ችግር የሚፈጥርበት
አንዳች የተንሳፈፈ ነገር እንዳለ ለማየት ወደ ቦታው በረረች፡፡ የተሰበሰበው
ሰው ይህን ሲያይ በጉጉት አጉተመተመ አይሮፕላኑ እየመጣ ነው ማለት
ነው፡፡
አይሮፕላኑን ቀድሞ ያየው አንድ ትንሽ ልጅ ነው፡፡ አጉልቶ የሚያሳይ
መነጽር ባይዝም ‹‹ያውላችሁ!›› ሲል ጮኸ፡፡ ‹‹ባህር ላይ የሚያርፈው
አይሮፕላን መጣ!›› በማለት ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሲያመለክት ሁሉም
ዓይኑን ወደዚያው ወረወረ፡፡ ሉተር በመጀመሪያ አሞራ የመሰለ ነገር ደብዘዝ
ብሎ ታየው፡፡ በኋላ እየጎላ መጣ ‹‹ልጁ እውነቱን ነው! እውነቱን ነው!››በማለት የተሰበሰበው ህዝብ አውካካ፡፡
ፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰዎችን በምቾት አሳፍሮ አትላንቲክ ውቅያኖስን ማቋረጥ የሚችል ቦይንግ B 134 የተሰኘ አይሮፕላን በቦይንግ ኩባንያ አሰርቷል፤ ግዙፍ፣ ማራኪና ጉልበቱ ከፍተኛ የሆነ የአየር ላይ ቤተ መንግስት፡፡ አየር መንገዱ ስድስት አይሮፕላኖችን ያስመጣ ሲሆን ሌሎች ስድስት ደግሞ እንዲሰሩለት አዟል። በምቾትና በማራኪነት በወደቡ ላይ ከቆሙት የመንገደኛ መርከቦቹ አይተናነሱም፡፡ ነገር ግን መርከቦቹ አትላንቲክን ለማቋረጥ አራት ወይም አምስት ቀን ሲወስድባቸው ይህ ባህር ላይ ማረፍና ከባህር ላይ መነሳት የሚችል አይሮፕላን ግን ይህን ጉዞ በሃያ አራት ወይም በሰላሳ ሰዓት ያጠናቅቀዋል፡፡
ልክ ክንፍ ያለው ዓሳ ነባሪ ይመስላል› አለ ሉተር በሆዱ አይሮፕላኑ እየቀረበ ሲመጣ፡፡ ከወደ ፊቱ ሾል ያለ ግዙፍ ነው፡፡ ክንፎቹ ውስጥ ኃይለኛ
ሞተሮች ተሰክተዋል፡ አይሮፕላኑ ውሃ ላይ ሲያርፍ ሚዛኑን እንዲጠብቅ
የሚያስችሉት ከክንፎቹ በታች አጠር ወፈር ያሉ ትናንሽ ክንፎች
ተገጥመውለታል፡፡ የአይሮፕላኑ የታችኛው ክፍል እንደ ፈጣን ጀልባ
ውሃውን መሰንጠቅ እንዲያስችለው ጫፉ እንደ ቢላ የሰላ ነው፡፡
አይሮፕላኑ ፎቅና ምድር አለው፡ ሉተር ባለፈው ሳምንት ስለመጣበት
የአይሮፕላኑን ውስጣዊና ውጫዊ ገጽታ በሚገባ ያውቀዋል፡ የላይኛው ፎቅ
ፓይለቶቹንና የዕቃ ማስቀመጫ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን የታችኛው ክፍል
ተሳፋሪዎች የሚቀመጡበት ነው፡፡ ተሳፋሪዎች የሚቀመጡባቸው ክፍሎች
በመደዳ በተደረደሩ የእንግዳ ማረፊያ ሶፋዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ በመብል ጊዜ እነዚህ ክፍሎች ወደ መብል ቤትነት የሚለወጡ ሲሆን በመኝታ ጊዜ ደግሞ
ሶፋዎቹ እንደ አልጋ ይዘረጋሉ፡
ተሳፋሪዎቹን ከሙቀትና ከብርድ ለመጠበቅ አይሮፕላኑ ውስጡ
ተለብጧል፡ ወለሉ ወፋፍራም ምንጣፍ የተነጠፈበት ሲሆን ክፍሉ ዓይን የማይወጉ መብራቶች ተገጥመውለታል፡፡ በሃር ጨርቅ የተሸፈኑ ሶፋዎቹ
ድሎታቸው ልክ የለውም፡ የአይሮፕላኑ ግድግዳ ላይ የተገጠመው ድምጽ
ማፈኛ የሞተሮቹን ድምጽ ይውጣል፡ የአይሮፕላኑ ካፒቴን የአዛዥነት ባህሪ
የተላበሰ ሲሆን ባልደረቦቹ ደግሞ ጸዳ ያለና ማራኪ የፓን አሜሪካን አየር
መንገድ ዩኒፎርም ለብሰዋል፡፡ አስተናጋጆቹ የተሳፋሪዎቹን ፍላጎት ለማርካት ተፍ ተፍ ይላሉ፡ ምግብና መጠጥ ያለማቋረጥ ይጋዛል፡፡ ተሳፋሪዎች የጠየቁት ነገር በሙሉ ልክ በአስማት የሚመጣ እንደሆነ ሁሉ እፊታቸው ዱብ ይላል፡ እንዲህ አይነት ድሎት በቀላል ዋጋ አይገኝም፡ ተሳፋሪዎቹ አብዛኛውን ጊዜ የንጉሣውያን ቤተሰቦች፣ የፊልም ተዋናዮች፣ የትላልቅ ኮርፖሬሽኖች ኃላፊዎች እና የአገር መሪዎች ናቸው፡፡ ቶም ሉተር ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች ጋር የሚመደብ አይደለም፡ ሀብታም ቢሆንም እዚህ ደረጃ ለመድረስ ብዙ የለፋ በመሆኑ ለድሎት ሲል ብቻ ገንዘቡን አይረጭም: ቢሆንም ራሱን ከአይሮፕላኑ ጋራ ለማለማመድ ፈልጓል፡፡
አንድ ኃያል ሰው በጣም ኃያል የሆነ አንድ አደገኛ ተግባር እንዲፈጽምለት
ውለታ ጠይቆታል፤ ለዚህ ስራው ሉተር የሚከፈለው ነገር የለም፡ ነገር ግን
ለዚህ ሰው ውለታ መዋል ከገንዘብ ይልቃል፡
ይሄ ዕቅድ ምናልባት ይሰረዝ ይሆናል፡ ሉተር ‹‹ስራውን ቀጥል››
የሚለውን የመጨረሻውን ትዕዛዝ እየጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን አዕምሮው
ዕቅዱን ቶሎ ለመፈጸም በመጓጓትና ምነው ባልሰራሁት! ብሎ በመመኘት መካከል ይዋልልበታል፡
አይሮፕላኑ ከአፍንጫው ከፍ ከጭራው ዝቅ እያለ ወደ መሬት እየወረደ
ነው፡፡ አሁን ለማረፍ ተቃርቧል፡ ሉተር በአይሮፕላኑ እንደአዲስ ተደንቋል፡፡
ለአፍታ ያህል አይሮፕላኑ እየተንሳፈፈ ይሆን እየወደቀ ሳይለይ አንዳንዴ ደግሞ ወደ ላይ ከፍ እያለ በመጨረሻም ባህር ላይ እንደተወረወረ ዝይ እዚህም እዚያም እየነጠረና ውሃውን ሁለት ቦታ እየከፈለ ፍጥነቱን በመቀነስ ውሃው ላይ አረፈና እንደ ጀልባ ይሄድ ጀመር፡
ሉተር ትንፋሹን ውጦ ቆይቶ ስለነበር በእፎይታ ለቀቀው፡ አይሮፕላኑ ወደ መቆሚያው ተጠግቶ ቆመ፡ ሉተር ከሳምንት በፊት እዚህ ቦታ ላይ ነው ከአይሮፕላኑ የወረደው:፡ ከአፍታ በኋላ አይሮፕላኑ ከፊትና ከኋላ
በገመድ ከወደቡ ምሰሶ ጋር ይታሰራል፡

👍59❤3👎1🔥1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
ጦርነቱ የታወጀው የበጋው ወቅት ማብቂያ አካባቢ በአንድ ፀሃያማና ቀለል ያለ እሁድ ነበር፡፡
የጦርነቱ ዜና ሲታወጅ ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ ቤት ውስጥ ነበረች፡፡ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ተዘጋጂ በመባሏ ጨሳለች፡፡ ከርቀት ያለማቋረጥ
የሚሰማት የቤተክርስቲያን ደወል አሰልቺ ሆኖባታል፡ የ19 ዓመት ልጅ በመሆኗ ስለሃይማኖት የራሷን ውሳኔ መወሰን ብትችልም አባቷ ከቤተክርስቲያን እንድትቀር አይፈቅዱላትም፡፡ ከዓመት በፊት ቤተክርስቲያን መሄድ
እንደማትፈልግ ነግራቸው ነበር፡፡ እሳቸው ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል።
‹‹በእግዚአብሔር የማላምን መሆኔን እያወቅሁ ቤተክርስቲያን መሄድ
ማስመሰል አይመስልም ወይ?›› አለቻቸው አንድ ቀን፡፡
‹‹ጅል አትሁኚ›› አሏት አባቷ ሎርድ ኦክሰንፎርድ፡
ትልቅ ስትሆን እንደማትሄድ ለእናቷ ነገረቻቸው፡፡
‹‹ባልሽ ይጨነቅበት የኔ ማር›› አሏት እናቷ፡፡ ከዚያ ቀን በኋላ ስለዚሁ ጉዳይ ተነጋግረው ባያውቁም እሁድ በመጣ ቁጥር ማርጋሬት ጥላቻዋ
ይጠነክራል፡
እህቷና ወንድሟ ከቤት ሲወጡ ሰማች። ኤልሳቤት 21 ዓመቷ ነው፡፡ ቁመቷ የብቅል አውራጅ ሲሆን መልክ አልፈጠረባትም፡፡ በልጅነታቸው እህትማማቾቹ ምስጢረኞች ስለነበሩ አይለያዩም፡፡ ካደጉ በኋላ ግን ተራራቁ፡፡
ትምህርት የተማሩት እንደሌሎች እኩዮቻቸው ትምህርት ቤት ሄደው
ሳይሆን አስተማሪ ተቀጥሮላቸው ቤት ውስጥ ነው፡ ኤልሳቤት በጉርምስና
ጊዜ የምታራምደው የወላጆቿን ግትር ልማዳዊ አስተሳሰብ ነበር፡፡
አመለካከቷ አክራሪ ሲሆን ከመኳንንት ዘር በመገኘቷ በእጅጉ ትመካለች፡
አዳዲስ ሃሳቦችና ለውጥ ጠላቶቿ ናቸው፡፡ በአንጻሩ ማርጋሬት የእሷ ተቃራኒ ናት፡ የሴቶች መብት ተሟጋችና የሶሻሊስት ፖለቲካ አቀንቃኝ
ስትሆን ጃዝ ሙዚቃ ትወዳለች፡ ኤልሳቤት ማርጋሬት ተራማጅ አስተሳሰብ በማፍቀሯ ለወላጆቿ ታማኝ አይደለችም ብላ ታምናለች፡፡ ማርጋሬት ደግሞ በእህቷ ጅልነት ትናደዳለች፡፡ በዚህ ምክንያት የልብ ወዳጆች ባለመሆናቸው ታዝናለች፡፡ የልብ ጓደኞች ደግሞ የሏትም፡፡
የእሷ ተከታይ ፔርሲ 14 ዓመቱ ነው፡፡ ተራማጅ ሃሳቦችን ወይ አይወድ ወይ አይቃወም፡፡ በተፈጥሮው ሸረኛ ነው፡፡ የማርጋሬት አመጸኝነት ባህሪ ግን ደስ ይለዋል፡፡ በአባታቸው አምባገነንነት ሁለቱም ተጎጂዎች በመሆናቸው ይተዛዘናሉ፣ ይደጋገፋሉ፡ ማርጋሬትም ለእሱ ልዩ ፍቅር አላት፡
ሎርድና ሌዲ ኦክሰንፎርድ ቀድመው ከቤት ወጥተዋል፡፡ ሎርድ
ዥንጉርጉር ክራቫት አስረዋል፡፡ እመቤቲቱ ጸጉራቸው ቀይ፣ ዓይኖቻቸው አረንጓዴ ሲሆን ፊታቸው የገረጣ ነው፡፡ ጌቶች ጥቁር ጸጉራቸው ላይ ሽበት ጣል ጣል አድርጎባቸዋል፡ ፊታቸው ደግሞ እንደ ቲማቲም የቀላ ነው።
ኤልሳቤት የአባቷን ጥቁር ጸጉርና ቅርጸ ቢስ መልክ የያዘች ስትሆን ማርጋሬት ደግሞ የእናቷን ግርጣት ወርሳለች፡ ፔርሲ መልኩ በየጊዜው ስለሚለዋወጥ የማንን መልክ እንደሚይዝ በውል አይታወቅም:
መላው ቤተሰቡ ከግቢው ወጣና በእግር ጉዞ ጀመረ፡፡ ከቤታቸው በአንድ
ኪሎ ሜትር ርቀት ከሚገኙት አብዛኛዎቹ ቤቶችና መሬቱ በሙሉ
የአባትየው ሀብት ሲሆን ይህንን ሀብት ያገኙት ያለምንም ድካም ነው፡
በአገሪቱ ያሉት ባለመሬት ቤተሰቦች በጋብቻ በመተሳሰራቸው የፈጠሩት
ርስት ይኸው ከዘር ወደ ዘር ተላልፎ በአባትየው እጅ ገብቷል፡
በመንደሩ ውስጥ ለውስጥ ተጉዘው ከድንጋይ ጥርብ የተሰራው ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ደረሱ።
ከዚያም አባትና እናት ከፊት፣ማርጋሬትና ኤልሳቤት በመከተል ፔርሲ ደግሞ ከእነሱ ኋላ ተከታትለው
ገቡ፡ የኦክሰንፎርድን መሬት የተከራዩ ገበሬዎች በአክብሮት እጅ ነሷቸው፡
ማርጋሬት ይሄ ኋላቀር ልማድ ሲፈጸም ስታይ በእፍረት ትሽማቀቃለች፡
‹‹ሁሉም ሰው በእግዜር ፊት እኩል ነው! በይ በይ ይላታል፡፡ አንድ ቀን
ድፍረቱ ይኖራትና እዚያ ሁሉ ሰው ፊት ትናገር ይሆናል፡፡ ነገር ግን አባቷ
የሚያደርሱትን ነገር ስታስብ አስፈራት፡፡
የሰው ሁሉ አይን እየተከተላቸው ቤተክርስቲያኑ ውስጥ የቤተሰቡ መቀመጫ ጋ እንደደረሱ ፔርሲ አባቱን ‹‹ክራቫትህ ታምራለች አ
አላቸው፡፡ ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ሳቅ አፈናት፡፡ እሷና ፔርሲ ቶሎ ቁጭ አሉና ሳቃቸው እስኪጠፋ የሚጸልዩ ለመምሰል ራሳቸውን አጎነበሱ፡
ሰባኪ ወንጌሉ ገንዘቡን በዋዛ ፈዛዛ ስላባከነውና በመጨረሻም ወደ
ቤተሰቡ ስለተመለሰው ልጅ ታሪክ አስተማሩ፡፡ ማርጋሬት ጨርጫሳው ቄስ!
በእያንዳንዱ ሰው ጭንቅላት ውስጥ ስለሚጉላላው ጦርነት ቢሰብኩ ምናለ
ስትል አሰበች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሂትለር ማስጠንቀቂያ ቢልኩለትም
ሂትለር ማስጠንቀቂያውን ከምንም ባለመቁጠሩ የጦርነቱ እወጃ የማይቀር
ሆነ፡
ማርጋሬት እንደ ጦርነት የምትፈራው ነገር የለም፡፡ የእስፓኒሽ እር በእርስ ጦርነት ፍቅረኛዋን ነጥቋታል ዓመት ያለፈው ቢሆንም ትዝ ሲላት
ትሳቀቃለች፡፡ ጦርነት ለሷ አስጨናቂ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ጦርነትን ትሻለች፡፡ ለብዙ ዓመታት በእስፓኒሽ
ጦርነት እንግሊዝ ያሳየችው ቦቅቧቃነት ያሳፍራታል
በሂትለርና በሙሶሊኒ
የታጠቁ ወሮበሎች የተመረጠውን ሶሻሊስት መንግስት ሲገለብጡ አገሯ ዳር ቆማ ተመልክታለች፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ሶሻሊስት ወጣቶች ከመላው አውሮፓ
ዲሞክራሲን ለመታገል ወደ ስፔን ዘምተዋል፡፡ ነገር ግን በቂ መሳሪያ አልነበራቸውም፡፡ በመላው ዓለም ያሉ ዲሞክራቲክ መንግሥታት ፊታቸውን ቢያዞሩባቸውም ወጣቶቹ ግን ህይወታቸውን ሰዉ፡፡ እንደማርጋሬት ያሉ ሴቶችም
አንገታቸውን በሃዘን ደፉ፤ እፍረትንም ተከናነቡ፡፡ ብሪታንያ ፋሺስቶችን
ተቃውማ ብትነሳ ማርጋሬት በአገሯ እንደገና እንደምትኮራ ተማመነች፡፡
የጦርነቱ አይቀሬነት ልቧ ውስጥ ሌላም ደስታ አጫረባት፡፡ የዚህ ነፃነት
የሌለውና የተጨናነቀው የቤተሰብ ህይወቷ ማብቂያ ይሆናል ስትል አሰበች፡
ይሄ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ የማይታይበት ልማዳዊና ትርጉም የለሽ አኗኗሯ
አንገቷ ጋ ደርሷል፡ ከዚህ አሰልቺና ተስፋ አስቆራጭ ማህበራዊ ሕይወት
አምልጣ ወጥታ የራሷን ህይወት ለመኖር ፈልጋለች። ነገር ግን የሚሆን
የሚሆን አልመስልሽ ብሏታል፡፡ ዕድሜዋ ገና ነው ቤተሰቧን ለቃ ለመውጣት አይፈቀደላትም፡፡ ገንዘብም የላትም፡፡ ለየትኛውም የስራ ዓይነት ደግሞ ብቁ አይደለችም፡፡ ነገር ግን በጦርነት ጊዜ ሁሉ ነገር የተለየ ይሆናል ስትል አሰበች፡፡
ባለፈው ጦርነት ወቅት ሴቶች ሱሪ ታጥቀው ፋብሪካ ውስጥ እንዴት
ይሰሩ እንደነበር በአድናቆት አንብባለች፡፡ ባሁኑ ጊዜ ምድር ጦር፣ ባህር ኃይልና አየር ኃይል የሴቶች ቅርንጫፍ አላቸው፡ ማርጋሬት ምድር ጦርን
መቀላቀል ፈልጋለች፡ አንድ የምታውቀው ስራ መኪና መንዳት ብቻ ነው፡
የአባቷ ሾፌር መኪና መንዳት አስተምሯታል፡ የሞተው ፍቅረኛዋ ሞተር
ሳይክል አስነድቷታል፡ የሞተር ጀልባ መንዳት አያቅታትም፡ የምድር ጦር
መምሪያ የአምቡላንስ ሾፌሮችንና ፖስታ አመላላሽ ሞተር ሳይክል ነጂዎችን
ይፈልጋሉ፡ ዩኒፎርም ለብሳ ብረት ቆብ አድርጋ በሞተር ሳይክል ከጦር ሜዳ ወደ ጦር ሜዳ እየበረረች አገልግሎት መስጠት እንደምትችል እርግጠኛ ሆናለች፡

👍24👎1🔥1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
...ማርጋሬት እንባ አነቃት፡ ኢያን ሮችዴል በህይወቷ ውስጥ ታላቁ ክስተት ነበር ሞቱ አሁንም ስቃይ ሆኖባታል፡፡ ለአመታት ዶሮ ጭንቅላት ከሆኑ የባላባት ልጆች ጋር ፓርቲ ደንሳለች እነዚህ ልጆች ከመጠጥና
ከአደን በስተቀር አእምሮአቸው ምንም አያስብም፡፡ የእሷን አስተሳሰብ የሚጋራ የእድሜ አቻዋ የሆነ ሰው በእጅጉ ትመኝ ነበር፡፡ አንድ ቀን ኢያን በድንገትና በህይወቷ ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል፧ እሱ ከሞተ
ወዲህ እንደገና ህይወቷን ጨለማ ወርሶታል
ኢያን በኦክሰንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ አመት ተማሪ ነበር፡
ማርጋሬትም ዩኒቨርሲቲ መግባት ምኞቷ ቢሆንም መስፈርቱን አላሟላችም፡፡አንብባለች፡ ሌላ ትምህርት ቤት ሄዳም አታውቅም ሆኖም ብዙ የምታደርገው ነገር አልነበረም:: በሀሳብ መፋጨት የምትወድ መሆኗ
ይገርማታል፡ ሀሳቡን በፍጹም ትህትና የሚገልፅላትና እስካሁን ከገጠሟት ሰዎች ሁሉ ነፃ አስተሳሰብ ያለው ሆኖ ያገኘችው ኢያንን ብቻ ነበር፡፡በውይይት ወቅት ታላቅ ትዕግስት ያሳያል፤ ባለው አቅም አይኮራም፣ያልገባውን ገብቶኛል አይልም፤ ካየችው ጊዜ አንስቶ ነበር የወደደችው፡
ለረጅም ጊዜ በመሀከላቸው የነበረው ስሜት ፍቅር ነው ብላ አታስብም ነበር፡ አንድ ቀን በማፈር እየተንተባተበ ‹‹ካንቺ ፍቅር ይዞኛል፧
ጓደኝነታችንን ያበላሽብን ይሆን?›› በማለት ተናዘዘላት፡ ያኔም እሷ በፍቅሩ መነደፏን ተረዳች፡
በዚህም ህይወቷን ለወጠው፤ ልክ ሁሉም ነገር ልዩ ወደሆነበት ሌላ
አገር የሄደች መሰላት፤ ሁሉም ነገር የሚያስደስት መሆን ጀመረ፤ ከቤተሰቦቿ ጋር የምትኖረው አጣብቂኝ የበዛበት ህይወትና ብስጭቱ ሁሉ ተረሳት፡ የዓለም አቀፉን ብርጌድ ተቀላቅሎ ህዝብ የመረጠውን ሶሻሊስት መንግሥት ለመታደግ ወደ ስፔን ሄዶም እንኳን ለህይወቷ ብርሀን ይፈነጥቅበት ነበር፡ ላመነበት ዓላማ ህይወቱን ለመስጠት በመዘጋጀቱ
ኮርታበታለች: አንዳንድ ጊዜ ደብዳቤው ይደርሳት ነበር፡ አንድ ጊዜ ግጥም ልኮላታል፡ በኋላ የመጣው ደብዳቤ ግን አስደንጋጭ ነበር፡፡ ከጠላት በተተኮሰ
ላውንቸር ሰውነቱ ተበጣጥሶ መሞቱን አረዷት፡ ማርጋሬት ከእንግዲህ አበቃልኝ! ስትል ደመደመች፡፡
‹‹መጥፎ ተፅዕኖ አሳድሮብኛል›› ስትል አስተጋባች የእናቷን አባባል
በመድገም፡፡ ‹‹ቀኖናን እንዳልቀበል፣ ሐሰትን እንድፀየፍ፣ ድንቁርናን
እንዳወግዝና ማስመሰልን እንድጠላ አስተምሮኛል፡
በመሆኑም በሚባለው ህብረተሰብ ውስጥ ቦታ የለኝም፡››
አባት፣ እናትና ኤልሳቤት በአንድ ላይ መናገር ጀመሩና ሁሉም ሰሚ
አለመኖሩን አውቀው ድንገት ዝም አሉ፡ ፔርሲ ድንገተኛውን ዝምታ
በመጠቀም ‹‹ይሁዳውያንን በተመለከተ›› አለ ‹‹ከስታንፎርድ ከመጡት ሻንጣዎች ውስጥ አንድ የሚገርም ፎቶግራፍ አገኘሁ፡፡››
ስታንፎርድ በአሜሪካ ኮኔክቲከት ክፍለ ሀገር የእናትዬው አገር ነው፡፡ ከደረት ኪሱ ውስጥ አንድ የተጨማደደና ቀለሙ የፈዘዘ ፎቶግራፍ አወጣና ‹‹ሩዝግሌንኬር
የሚባሉ ቅድመ አያት ነበሩኝ አይደለም?›› አለ።
እናትም ‹‹አዎ የእናቴ እናት ነች ታዲያ ምን አገኘህ የኔ ማር
አሉ።
ፔርሲ ፎቶውን ለአባቱ ሰጣቸው: ሁሉም ለማየት ተሰበሰቡ
ፎቶግራፉ ላይ በግምት ከሰባ አመት በፊት በአሜሪካ ውስጥ ምናልባት ኒውዮርክ ውስጥ አንድ አዳፋ የስራ ልብስ የለበሰና ኮፍያ ያደረገ ዕድሜው በግምት ሰላሳ ዓመት የሚሆነው ጢማም ሰው መንገድ ላይ ቆሞ ይታያል
ሰውየው የሞረድና ቢላ መስሪያ ጋሪ ይገፋል ጋሪው ላይ በግልፅ ሩቤንራሽቤን ብረት ቀጥቃጭ›› ይላል። አጠገቡ አስር አመት የሚሆናት ቀሚስና ቦት ጫማ ያደረገች ልጅ ቆማለች፡፡
‹‹ምንድነው ይሄ ፔርሲ? እነዚህ ድሆች እነማን ናቸው?›› ሲሉ አባት ጠየቁ።
‹‹ጀርባው ላይ የተጻፈውን እየው፣ አባባ›› አለ ፔርሲ።
አባት ፎቶውን ገለበጡ፤ ፎቶው ጀርባ ላይ ‹‹ሩዝግሌንኬር ራሽቤ
ዕድሜ 10›› የሚል ተፅፏል።
ማርጋሬት አባቷን ተመለከተች በጣም ተናደዋል፡
‹‹የእናታችን ቅድም አያት በየመንገዱ እየዞረ ቢላ የሚሰራ ሰው ልጅ ማግባቱ የሚገርም ነው፤ አሜሪካ ደግሞ እንደዚህ ናት ይላሉ›› አለ ፔርሲ
‹‹ይሄ የማይሆን ነው!›› አሉ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ድምፃቸው ሻክሮ
ማርጋሬት ግን አባቷ ሊሆን ይችላል ብለው እንደሚያስቡ ገመተች፡
ፔርሲም በግድ የለሽነት ‹‹የሆነ ሆኖ ይሁዳነት የሚተላለፈው በእናት
በኩል ነው ስለዚህ የእናቴ ቅድም አያት ይሁዳዊ ናት፤ ይህም እኔን
ይሁዳዊ ያደርገኛል›› አለ፡፡
አባት ፊታቸው በንዴት አመድ መሰለ፡፡ እናት ፊታቸው ላይ ጥርጣሬ ተነበበበት ግምባራቸውን በመጠኑ አኮማተሩ፡፡
ፔርሲም ‹‹ጀርመኖች ይህን ጦርነት ያሸንፋሉ፡፡ ማርጋሬት ሲኒማ ቤት
መሄድ አይፈቀድልሽም፤ እማማም በዳንስ ልብሶቿ ላይ በሙሉ ቢጫ ኮከብ ትሰፋለች›› አለ፡፡
ማርጋሬት ፎቶው ጀርባ ላይ የተፃፈውን ጽሁፍ በአትኩሮት ስታይ
እውነቱ ተገለፀላት፤ ‹‹ፔርሲ!›› አለች በመደሰት ‹‹ይሄ ያንተ ጽህፈት ነው!››
‹‹አይደለም›› አለ ፔርሲ፡
ጽሁፉ የእሱ መሆኑን አውቃ ማርጋሬት በሳቅ ተንከተከተች፡፡ ፔርሲ አባቱን ለማሞኘት መሬት ላይ ወድቆ ያገኘው ፎቶ ጀርባ ላይ ፃፈበት ፧አባትም አመኑት፡ ዘረኛ ሁሉ የእኔም ዘር የተደባለቀ ይሆን እያለ ሲባንን ይኖራል፤ ይገባዋልም ስትል ማርጋሬት አሰበች።
አባት ፎቶውን ጠረጴዛ ላይ ወረወሩት፡፡
የቤት አሽከራቸው ‹‹ምሳ ቀርቧል ጌቶች›› አለ፡፡ ቤተሰቡ ተያይዞ ወደ
መብል ቤት ሄደ፡ ሲጠበስ ፕሮቲኑ ይጠፋል በሚል የተጠበሰ ምግብ
አይበሉም፡፡ እሁድ እሁድ የሚበሉት የተቀቀለ ስጋ ነው።
አባት ‹‹ፀሎት እናድርስ›› አሉ፡፡
‹‹አንድ ነገር ማድረግ ይቀረናል›› አሉ እናት ሳይታሰብ ለንግግራቸው
ትኩረት እንዲሰጥ በማሰብ ‹‹ሁላችንም ይሄ የሞኛሞኞች ጦርነት እስኪያበቃ አሜሪካ እንሄዳለን››
ለአፍታ ሁሉም በድንጋጤ ዝም አሉ፡፡
ማርጋሬት በንዴት ‹‹አይሆንም!›› ስትል ጮኸች፡፡
እናትም ‹‹ለዛሬ የሚበቃንን ያህል ተጨቃጭቀናል፤ አሁን ምሳችንን
በሰላም እንብላ›› አሉ
‹‹አይሆንም›› አለች ማርጋሬት እንደገና በንዴት አፏ መናገር
አቃተው፡ ‹‹ይህን ማድረግ አትችሉም! ይሄ . .›› ልትወርድባቸው ፈለገች።
በአገር ክዳት ብትወነጅላቸው ተመኘች፡፡ ነገር ግን ከአፏ አውጥታ መናገር አቃታት፧ ማለት የቻለችው ‹‹ይህ ጥሩ አይደለም›› ብቻ ነበር፡
‹‹አፍሽን ካልያዝሽ ውጪ ከቤት!››
አሉ አባት።
ማርጋሬት በመሐረብ አፏን ጠርጋ ከወንበሯ ተነሳችና እያለቀሰች ከመብል ቤቱ ወጥታ ሄደች፡
የአሜሪካውን ጉዞ ያቀዱት ከወራት በፊት ነው፡፡
ፔርሲ ወደ ማርጋሬት ክፍል መጣና ዝርዝሩን ነገራት ‹‹ቤቱ ተዘግቶ
የሚቆይ ሲሆን የቤት ዕቃዎች በሙሉ በአቧራ መከላከያ ጨርቅ ይሸፈናሉ ሰራተኞቹ ይሰናበቱና ርስቱ ለሰው በአደራ ይተዋል፡ ገንዘቡ ባንክ ይቀመጣል፡፡ በመንግሥት በተላለፈው የውጭ ምንዛሬ ቁጥጥር ምክንያት
ገንዘብ ወደ አሜሪካ መላክ አይቻልም፡፡ ፈረሶቹ በሙሉ ይሸጣሉ፤ ጌጣጌጦቹ
ይቆለፍባቸዋል፡››
ኤልሳቤት፣ ማርጋሬትና ፔርሲ አንዳንድ ሻንጣ ውስጥ ዕቃዎቻቸውን ከተዋል፡፡ የቀረው ዕቃ በዕቃ ወሳጅ ኩባንያ ይላክላቸዋል፡ አባት ለሁሉም
በፓን አሜሪካ አውሮፕላን የሚጓዙበትን የአውሮፕላን ቲኬት ገዝተዋል የጉዟቸው ቀን ረቡዕ ዕለት ነው።

👍28🤔3👎1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
...ለሁለት ቀን ቤርጎ ትከራይና በሚቀጥለው ቀን ትወጣለች ምድር ጦር
መምሪያ ተመዝግባ ለሆቱሉ በመደወል የሆቴል ኪራዩን ደረሰኝ ለአባቷ ጠበቃ እንዲላክ ታደርጋለች፡
በረጅሙ ተነፈሰችና በሩን ከፍታ ገባች፡፡
ማርጋሬት በቀጥታ ወደ እንግዳ ተቀባዩ አመራች ከፍተኛ እረፍት ተሰማት። ፍርሃትና ቅዠቱ አብቅቷል።
አንድ ወጣት እንግዳ ተቀባይ ባንኮኒ ተደግፎ ያንጎላጃል። ማርጋሬት
‹‹እህምም›› ብላ ጉሮሮዋን ስትጠራርግ ወጣቱ ነቃ ድንጋጤ እና መደናገር
ፊቱ ላይ ይታያል።
‹‹ቤርጎ አላችሁ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹በዚህ ሰዓት?›› ሲል መለሰ።
‹‹ጨለማው አላስኬድ አለኝና እቤት መሄድ አልቻልኩም››
ወጣቱ ራሱን ገዛና ‹‹ሻንጣሽ የታለ?›› ሲል ጠየቃት።
<<የለኝም›› አለች ማርጋሬት በማፈር፧ ከዚያም አሰብ አደረገችና
‹‹የለኝም ጨለማው አያስኬደኝም ብዬ አላሰብኩም ነበር›› አለች
ወጣቱ ሁለመናዋን አስተዋለ። ፊቱን ደባበሰና መዝገቡን የሚያይ
መሰለ። ሰውዬው ምን ነካው? ስትል አሰበች።
‹‹ቦታ የለንም›› አላት።
‹‹አላችሁ››
‹‹ከአባትሽ ጋር ተጣልተሽ ነው አይደለም?›› አላት እየጠቀሳት።
‹‹አይደለም፣ እቤት መሄድ ስላልቻልኩ ነው›› ስትል ደገመች።
‹‹ታዲያ ምን ላድርግ ሂትለርን ጠይቂ››
ልጅነቱን አየችና ‹‹አለቃህ የት ነው?›› አለችው፡
የተሰደበ መሰለው ‹‹እስከ ጧቱ 12፡00 ሰዓት እኔ ነኝ ኃላፊው›› አላት
ማርጋሬት ዙሪያውን አየችና ‹‹እስኪነጋ እዚሁ እቀመጣለሁ›› አለች
በመሰላቸት፡
‹‹አይቻልም!›› አለ ወጣቱ ፈርቶ ሻንጣ ያልያዘች ኮረዳ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ልታድር?› ሲል አሰበና ‹ቀዚህ ምክንያት ከስራ እባረራለሁ›› አላት።
‹‹እኔ ኮረዳ አይደለሁም›› አለች ብልጭ ብሎባት፤‹‹እኔ እመቤት ኦክሰንፎርድ ነኝ›› ማዕረጓን መጠቀም አልፈለገችም ነበር፤ ምን ታድርግ፡
ይህን ብትልም ምንም አልጠቀማትም፡ እንግዳ ተቀባዩ ገላመጣትና
‹‹ትቀልጃለሽ!›› አላት በማሽሟጠጥ።ማርጋሬትም ልትጮህበት አሰበችና መልኳን በመስታወት ስታይ ዓይኗ እንደጠቆረ ተገነዘበች ከዚያም በላይ እጇ ቆሽሿል፤ ቀሚሷም ተቀዳል፡
እንግዳ ተቀባዩ ቦታ የለንም ማለቱ አያስደንቅም: በተስፋ መቁረጥ ‹‹መቼም
ጨለማ ውስጥ ሂጂ አትለኝም!›› አለችው:
‹‹ከዚህ ሌላ የምልሽ የለም›› አላት።
ማርጋሬት ዝም ብዬ ብቀመጥና ከዚህ አልነቃነቅም ብል እንግዴ
ተቀባዩ ምን ይለኝ ይሆን? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ይኸው ነው ማለት የፈለገችው ምክንያቱም በጣም ደክሟታል፤ ሰውነቷም ዝሏል ለጠብ
የሚሆን ጉልበት የላትም፡፡ ከዚህም በላይ ውድቅት በመሆኑ ወጣቱ ምን
እንደሚያደርጋት አይታወቅም፡፡
ሰውነቷ እንደዛለ ጀርባዋን ሰጥታው እንደከፋት ወጥታ ጨለማ ውስጥ ገባች፡፡ እየሄደችም ከእንግዳ ተቀባዩ ጋር ልጣላ ይሆን?› ስትል ነገር ስታስብ ይበልጥ ኃይል ያላት የሚመስላት? አሁን እጅ ከሰጠች በኋላ
አሰበች፡፡ ግን ለምንድ ነው ከምታደርገው ይልቅ ማድረግ የምትፈልገው
ይበልጥ መናደዷ ገረማት፡፡ እንደ ንዴቷ ከሆነ ከእንግዳ ተቀባዩ ጋር ትጣላ ነበር፡፡ ተመልሳ ለመሄድ ፈለገች፡ ሆኖም ወደፊት መራመዷን ቀጠለች:: አዎን መሄዱ ነው የሚሻለው፡፡
ዳሩ ምንም መሄጃ የላትም፡፡ ከእንግዲህ የካትሪንን ቤት ማግኘት አትችልም፡፡ የአክስቷ ቤት ጠፍቶባታል፡ ሌሎች ዘመዶቿን አታምናቸውም ሰውነቷ ስለቆሸሽም ቤርጎ ማግኘት አልቻለችም፡
እስኪነጋ መዞር ትችላለች፡፡ አየሩ ጥሩ ነው፡፡ ዝናብ ስለሌለም ብዙም
አይበርድም፡፡ ያለማቋረጥ ከተራመደችም አይበርዳትም አሁን ያለችበት መንገድ ላይ ብዙ የትራፊክ መብራት ስላለ የምትሄድበትን መንገድ ማየት ትችላለች በየደቂቃው መኪና ይተላለፋል፡፡ ከየምሽት ክበቡ ሙዚቃና ሁካታ ይሰማታል፡፡ በየመንገዱ ሽክ ያሉ ሴቶችና በየፓርቲው ያመሹ ሱፍ ግጥም አድርገው የለበሱ ወንዶች በሾፌር በሚነዱ መኪኖች ሲሄዱ ታያለች፡፡ አለፍ እንዳለች ሶስት ብቸኛ ሴቶች አየች፣ አንዷ በር ላይ ሌላዋ ደግሞ ስልክ እንጨት ተደግፋ ቆማለች፣ ሶስተኛዋ መኪና ውስጥ ቁጭ ብላለች፡፡ በአንድ ወቅት እናቷ ኑሮ የጨለመባቸው ሴቶች ያሏት እነዚህን ሳይሆን አይቀርም፡
ድካም ተሰማት ጫማዋ ከቤት እንደወጣች ያደረገችው ነጠላ ጫማ
ነው: ያገኘችው ደጃፍ ላይ ቁጭ አለችና ጫማዋን አውልቃ እግሯን
አከከች።
ቀና ስትል ከመንገዱ ባሻገር ያለው ህንፃ ቅርፅ በመጠኑ ታያት፡፡ እየነጋ ይሆን? በጧት የሚከፈት ሻይ ቤት ታገኝ ይሆናል። ለቁርስ የምድር ጦር መምሪያው የምግብ ክፍል እስኪከፈት ትቆያለች፡፡ ምግብ ከበላች ረጅም ጊዜ በመቆጠሩ የአሳማ ስጋና እንቁላል ትዝ ሲላት በአፏ ምራቋ ሞላ፡፡
ድንገት ቁልቁል የሚያያት አመድ የመሰለ ፊት ድቅን አለባት በድንጋጤ ጮኸች፡፡ ሰውዬው ወጣት ነው፡ ታዲያስ ቆንጂት›› አላት፡
እመር ብላ ተነሳች፡፡ ሰካራም አትወድም፡፡ እነሱ ክብራቸውን የሸጡ ናቸው፡፡ ‹‹ሂድ ጥፋ ከዚህ!›› አለች ቆጣ ብላ፤ ድምጿ ግን ይንቀጠቀጣል፡ቀስ እያለ ተጠጋት ‹‹ታዲያ ሳሚኛ›› አላት፡፡
‹‹አላደርገውም!›› አለች በንዴት ከእሱ ለመሸሽ ወደኋላዋ ስትሄድ ጫማዋ ወለቀባት፡፡ ዞር ብላ ጫማዋን ፍለጋ ስታጎነብስ ወጣቱ አስካካና እጁን ጭኖቿ መሀል ሰዶ ጎነታተላት፡፡ ጫማዋን ይዛ በፍጥነት ቀጥ ብላ
ቆመችና ‹‹ሂድ ከአጠገቤ›› ብላ ጮኸች፡፡
እንደገና ሳቀባትና ‹‹ልክ ነሽ፤ ሴቶች እምቢ ሲሉኝ ደስ ይለኛል›› አለና
የጠጣውን አልኮል ሲተነፍስባት አቅለሸለሻት፡፡ አንቆ አፏን ግጥም አድርጎ
ሳማት፡፡
ሁኔታው ሁሉ የሚያስጠላ ነው፤ ሆዷ ታወከ፡፡ አጥብቆ ስለያዛት ለመታገል ቀርቶ ለመተንፈስ አቃታት፡፡ ለማምለጥ ሙከራ ብታደርግም ለሀጩን እያዝረበረበ ይስማታል፡፡ ከዚያም አንድ እጁን ወደ ጡቷ ሰደደና በእጁ ሲጨመድደው ላንቃዋ እስኪላቀቅ ጩኸቷን ለቀቀችው፡፡
‹‹ደህና፧ ልጎዳሽ አይደለም፧ አታምርሪ›› አላት፡፡ እሷ ግን ጩኸቷን ቀጠለች፡ ሰዎች ከየቦታው ብቅ ብቅ አሉ፡ ሰካራሙ ሰው መምጣቱን ሲያይ ጨለማው ውስጥ ገብቶ ተሰወረ፡ ማርጋሬትም ጩኸቷን አቁማ ለቅሶዋን
ተያያዘችው፡:
አንድ ፖሊስ ባትሪውን እያበራ መጣና ፊቷ ላይ አበራባት፡፡ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀል አንዲት ሴተኛ አዳሪ ‹‹እቺ ልጅ ሽሌ አይደለችም›› አለችው ፖሊሱን፡፡
ፖሊሱ ‹‹ስምሽ ማነው ልጅት?›› አላት
‹‹ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ››
‹‹እመቤት ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ ነሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
ማርጋሬት ንፍጧን ወደ ውስጥ ሳበችና ራሷን ነቀነቀች በአዎንታ
‹‹ነግሬሃለሁ አይደል! ሸሌ አይደለችም›› አለችው ሴተኛ አዳሪዋ፡፡
‹‹ነይ እንሂድ የኔ እመቤት፣ አይዞሽ›› አላት በማጽናናት፡፡
ማርጋሬት በእጅጌዋ ፊቷን ጠርጋ ተነሳች፡:
ፖሊሱ ባትሪውን እያበራ አብረው ሄዱ፡በፍርሃት እየተርገፈገፈች ‹‹ሰውዬው እንዴት ያስፈራል!›› አለች፡፡
‹‹ሀዘኔታ የጎደለው ነው እሱ ምን ይፈረድበታል›› አለ ፖሊሱ ሳቅ እያለ፡፡ ‹‹ይህ ቦታ ከለንደን መንገዶች ሁሉ አደገኛው ነው፡፡ በዚህ ሰዓት
የምትጓዝ ሴት የምሽቱ እመቤት የሆነች ሴት ብቻ ናት፡››
ማርጋሬት ፖሊሱ ያለው ትክክል ነው አለች በሆዷ፡
‹‹ትኩስ ሻይ እንሰጥሽና ብርዱ ለቀቅ ያደርግሻል›› አላት ወደ ጣቢያው ገቡ፡፡ ከባንኮኒው ኋላ ሁለት ፖሊሶች ይታያሉ፡ አንዱ
ጎልማሳና ወደል ሲሆን ሌላው ደግሞ ወጣትና ከሲታ ነው፡፡ ክፍሉ ከጥግ
እስከ ጥግ በእንጨት ባንኮኒ ተገጥግጧል፡፡ ጣቢያው ውስጥ አንዲተ ሴት ትታያለች፡፡
‹‹እዚህ ቁጭ በይ›› አላት ፖሊሱ፡፡ማርጋሬት ተቀመጠች

👍28👎2
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
እንደ ሄሪ ማርክስ አይነት እድለኛ ሰው የለም፡፡
እና ሁል ጊዜ እድለኛ እንደሆነ ይነግሩት ነበር፡ ምንም እንኳን አባቱን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ያጣ ቢሆንም ደከመኝ ሰለቸኝ በማይሉ ብርቱ እናቱ እጅ በማደጉ እድለኛ ነው፡፡ እናቱ የፅዳት ሰራተኛ ናቸው አገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በገባችበት በዚያ ቀውጢ ወቅት እንኳን ስራቸውን አላጡም ነበር፡፡ የሚኖሩት እዚህ ግባ በማይባል ኮንዶሚኒየም
ውስጥ ቢሆንም በችግር ጊዜ የሚረዳዱ ጥሩ ጎረቤቶች አሏቸው: ሄሪ ከችግር የማምለጥ እድልና ክህሎት ነበረው፡፡ እሱና የትምህርት ቤት ጓደኞቹ
ረብሸው ሲገረፉ የአስተማሪው አርጩሜ እሱጋ ሲደርስ ይሰበር ነበር፡ ሄሪ ከፈረስ ወይም ከጋሪ ላይ ሲወድቅ ፈረሶቹ ሳይረግጡት በስልት ያሳልፋቸዋል፡፡
ለውድ ጌጣጌጥ ፍቅር ስላለው ነው ሌባ የሆነው፡፡
በጉርምስናው ወቅት በየወርቅ ቤቱ እየተዘዋወረ ዕንቁዎችን መመልከት
ይወድ ነበር፡ እነዚህ እንቁዎች የሚመስጡት ስለሚያምሩ ብቻ ሳይሆን በመጻሕፍት ላይ እንደሚያነበው የሀብታም ምልክት ስለሆኑም ጭምር ነው፡
አንድ ቦታ ረግቶ መስራት ስለማይወድ አንድ ወርቅ ሰሪ ጋ በተቀጠረ በስድስት ወሩ ስራውን ለቀቀ፡፡ ሰዓት መጠገንና የጋብቻ ቀለበቶች ማስፋት ስራም እንዲሁ አስጠላው፡ ነገር ግን የተለያዩ የከበሩ ድንጋዮችን ለይቶ
የማወቅ ችሎታ አዳብሯል፡፡
ሬቤካ ሞግሃም ፍሊንትን የተዋወቃት በፈረስ እሽቅድድም ቦታ ላይ ሲሆን የአንዱ ተወዳዳሪ ደጋፊ ነው ብላ አስባለች ሬቤካ ቀውላላ፣አፍንጫዋ አለቅጥ የረዘመ መልከ ጥፉ ሴት ናት፡ ራሷ ላይ በደፋችው ቆብ ላይ ላባ ሰክታለች፡፡ አጠገቧ ያሉት ወጣት ወንዶች ከምንም ሳይቆጥሯት ሄሪ
ስላናገራት በጣም ነው በሆዷ ያመሰገነችው::
እሷን ለመተዋወቅ የጓጓ እንዳይመስል መግባባቱን በዚያው ቀን ማድረግ አልፈለገም፡፡ በሌላ ቀን ስዕል አዳራሽ ስታገኘው ደስ ብሏት ከዚህ ቀደም በደምብ እንደምታውቀው ሁሉ ሰላምታ ሰጠችውና ወስዳ ከእናቷ ጋር
አስተዋወቀችው፡፡
እንደ ሬቤካ ያሉ እመቤቶች ሲኒማ ወይም ምግብ ቤት ያለ አጃቢ
አይሄዱም፡፡ ብቻቸውን የሚሄዱ የደሃ ልጆች ናቸው፡፡ የሬቤካ እናትና አባት የሄሪን የቤተሰብ ሁኔታ ማጣራት አልደፈሩም፡፡ ቤተሰቦቹ ዮርክሻየር ውስጥ የገጠር ቤት፣ ስኮትላንድ ውስጥ የትግል ትምህርት ቤት እንዳላቸው፣ አካል
ጉዳተኛ እናቱ ደቡብ ፈረንሳይ ውስጥ እንደሚኖሩና በንጉሠ ነገሥቱ አየር ኃይል ውስጥ ለሹመት መታጨቱን ሲነግራቸው እውነት ነው ብለው ተቀብለውታል።
ሄሪ በከፍተኛው መደብ ህብረተሰብ ዘንድ ውሸት ማውራት እንደሚብስ አውቋል።
በዚህ አይነት ሄሪ ከሬቤካ ጋር ጓደኝነት ከመሰረተ ሶስት ሳምንት
ሞላው፡፡ አንድ ቀን አንድ ፓርቲ ይዛው ሄደች፡፡ እዚያም ክሪኬት ሲጫወት ዋለና ከተጋበዘበት ቤት ገንዘብ ሰረቀ፡ ጋባዦቹም እንግዶቻቸውን ማሳጣት
ስላልፈለጉ ለፖሊስ ሳያሳውቁ ቀሩ፡፡ በሌላ ቀን ደግሞ አንድ ዳንስ ምሽት ላይ ወስዳው ኪስ ሲያወልቅና የሴቶችን ቦርሳ እየከፈተ ሲበረብር አመሸ፡፡ ሬቤካ
ቤተሰቦቿን ልታስተዋውቀው የወሰደችው ጊዜ እንኳን ገንዘብ፣ ከብር የተሰሩ ቢላዎችንና ከወርቅ የተሰሩ የቀሚስ ማያያዣዎችን መንትፏል፡
በሱ አመለካከት ከሀብታሞች መስረቅ እንደ ጥፋት አይቆጠርም፡
እነዚህ ሃብታሞች የሰበሰቡት ሃብት አይገባቸውም ባይ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ህይወታቸውን በሙሉ የአንድ ቀን ስራ እንኳን ሰርተው አያውቁም፡፡ ከነዚ ሰዎች ገንዘብ መስረቅ ናዚዎችን እንደመግደል ይቆጠራል እንደወንጀል
ሳይሆን ለህዝብ እንደሚሰጥ አገልግሎት።
ይህን የስርቆት ተግባር ከጀመረ ሁለት አመት ያህል ሆኖታል፡ ነገር
ግን በዚህ ከቀጠለ አንድ ቀን መያዙ እንደማይቀር ተገንዝቦ ሌላ ስራ
መፈለግ ሲያስብ ጦርነቱ ከተፍ አለለት፡
ምንም ቢሆን በመደበኛ ወታደርነት መቀጠር አይፈልግም፡፡ አሸር ባሽር
ምግብ፣ ዩኒፎርምና ወታደራዊ ስነ-ስርዓት የእሱ ዕጣ ክፍሎች አይደሉም ሆኖም የአየር ኃይል ዩኒፎርም ይማርከዋል፡፡ አይሮፕላን አብራሪ መሆን ይፈልጋል፡፡ እንዴት እንደሚፈፅመው ባያውቅም ያደርገዋል፡፡ እሱ እንደሆነ
እድለኛ ነው፡፡
ሬቤካን ርግፍ አድርጎ ከመተዉ በፊት እሷን ተጠቅሞ አንድ ሁለት
የሀብታም ቤት መዝረፍ ፈልጓል፡፡
ሰር ሲሞን ሞንክፎርድ የተባሉ ሀብታም የመጽሐፍ አሳታሚ ቤት
ለግብዣ ተጠርተው ሄዱ፡ ሄሪ ክብርት ሊዲያ ሞስ ከተባለች እመቤት ጋር ወሬ ጀመረ፡፡ እመቤቲቷ ብቻዋን ስለነበረች ለአንድ ሃያ ደቂቃ ያህል
አጫወታትና ወደ ሬቤካ ዞረ፡ ከዚያም ጊዜው አሁን ነው ብሎ በመገመት ተንቀሳቀሰ፡፡
ሁለቱን ወይዛዝርት ይቅርታ ጠየቀና ከዳንሱ አዳራሽ ወጣ
የሚቀጥለው ፎቅ ላይ ወጣና ኮሪደሩን ይዞ ሄደ፡፡ ኮሪደሩ መጨረሻ አንድ ትልቅ መኝታ ክፍል አገኘ፡፡ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል አንድ ሰው ‹‹ምን ነበር?›› አለው፡፡
‹‹እዚህ ነው?›› ብሎ ጠየቀው
‹‹ምኑ?››
‹‹መፀዳጃ ቤቱ?››
ወጣቱ ሰው ከቁጣው መለስ አለና ‹‹አሃ ገባኝ፤ መፀዳጃ ቤቱ ኮሪደሩ
ጥግ ነው የሚገኘው›› አለው፡፡
‹‹በጣም አመሰግናለሁ፡››
‹‹ምንም አይደል››
ሄሪ ወደ መፀዳጃ ቤቱ እየሄደ ‹‹በጣም የሚያምር ቤት ነው›› አለው ወጣቱን፡፡
‹‹አዎ›› አለና በደረጃው ወርዶ ሄደ ወጣቱ፡
ሄሪ በእፎይታ ፈገግ አለ፡፡ ወጣቱ ሰው መሄዱን አረጋገጠና ወደ
መኝታ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፡
መኝታ ቤቱ የእመቤት ሞንክፎርድ ሲሆን የመልበሻ ክፍልም እንዳለው
ሄሪ ተመለከተ፡ ቀጥሎ ደግሞ የወንድ መልበሻ ክፍል አለ፡፡ ሀብታም ባልና ሚስቶች የየራሳቸው መኝታ ክፍል አላቸው፡፡ ይህም የሆነው ከሰራተኛው
መደብ ያነሰ ወሲባዊ ፍላጎት ስላላቸው ይሆን?› ሲል አሰበ፡፡
ሄሪ የሰር ሲሞን መልበሻ ክፍል ገባና የኮሞዲኖውን መሳቢያ ከፈተው፡፡መሳቢያው ውስጥ በተለያዩ ጌጣጌጦችና አምባሮች የተሞላ ከቆዳ የተሰራ
የጌጣጌጥ ማስቀመጫ ሳጥን አገኘ፡፡ ብዙዎቹ ጌጣጌጦች ተራ ቢሆኑም ከነዚያ ውስጥ ግን ከወርቅ የተሰሩ የእጅ አምባሮች ላይ አይኑ አረፈ፡ አምባሮቹን
ኪሱ ጨመራቸው፡፡ ከጌጣጌጥ ሳጥኑ ቀጥሎ ውስጡ ሃምሳ ፓውንድ የያዘ የቆዳ የኪስ ቦርሳ አገኘ፡፡ ከቦርሳው ውስጥ ሃምሳ ፓውንድ ወሰደ፡፡ ብዙ ሰዎች ሃያ ፓውንድ ለማግኘት ከሁለት ወር ያላነሰ ከባድ የፋብሪካ ስራ
መስራት ያስፈልጋቸዋል፡፡
በየሄደበት ያገኘውን ሁሉ አይሰርቅም፡፡ የተወሰነ ዕቃ ብቻ መስረቅ ጥርጣሬ ይፈጥራል። ሰዎች ዕቃ ጎድሎ ሲያዩ ጌጣጌጡን ሌላ ቦታ እንዳስቀ
መጡት ወይም ቦርሳ ውስጥ ምን ያህል ገንዘብ እንደነበራቸው ማስታወስ ስለሚያቅታቸው ስርቆት ተፈፅሟል ብለው ለፖሊስ ሪፖርት አያደርጉም፡፡
መሳቢያውን ዘጋና እመቤት ሞንክፎርድ መኝታ ክፍል ዘው አለ፡፡
የያዘውን ይዞ ለመውጣት ቢመኝም ትንሽ ደቂቃዎች እመቤቲቱ ክፍል
ቢያጠፋ ወደደ፡፡ ሴቶች ከባሎቻቸው የተሻለ ጌጣጌጥ ይኖራቸዋል፡፡ እመቤት
ሞንክፎርድ ደግሞ ዕንቁ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ ሄሪ ደግሞ ዕንቁ ነፍሱ ነው፡፡
የምሽቱ አየር ምቹ በመሆኑ መስኮቶቹ በሙሉ ተከፍተዋል፡ በቀጥታ መልበሻ ክፍል ውስጥ ገባና ጌጣጌጡ ያለበት ኮሞዲኖጋ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ሁሉንም መሳቢያዎች ሲከፋፍት የተለያዩ የጌጣጌጥ ሳጥኖች እና ትሪ ሙሉ
ጌጣጌጥ አገኘ፡፡ የበር መከፈት ድምፅ ለመስማት ጆሮውን ቀስሮ እያንዳንዱን የጌጣጌጥ ሳጥን ፈተሸ፡፡

👍19👎2❤1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
የጀርመንን ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ለማሳሳት በርካታ ትላልቅ ብርማ
ቀለም ፊኛዎች ሰማዩ ላይ ያንዣብባሉ፡ ሱቆችና የመንግስት ህንፃዎች
ከቦምብ ናዳ ለመጠበቅ በአሸዋ በተሞሉ ጆንያዎች ዙሪያቸውን ተከበዋል፡
በየመናፈሻው የቦምብ
መከላከያ የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉም ሰው በእጁ የጋዝ
ጭስ መከላከያ ጭምብል አንጠልጥሏል ሰዎች በማንኛውም ደቂቃ በቦምብ
ናዳ እንደሚያልቁ ያስባሉ፡፡
ሄሪ ስለ አንደኛው የአለም ጦርነት ምንም ትዝታ የለውም፡ ጦርነቱ
ሲያልቅ የሁለት አመት እምቦቃቅላ ነበር፡፡ ነፍስ እያወቀ ሲመጣ ጦርነት
ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ አወቀ፡፡ በኋላም ፋሺስቶች በለንደን መንገዶች
ያደረጉትን ወታደራዊ ሰልፍ አዛውንት ይሁዳውያን በፍርሃት ሲመለከቱ
ሲያይ የጦርነትን አስፈላጊነት ተረዳ፡ሆኖም ሂትለር ሶቭየት ህብረትን
ይደመስስልኛል ብሎ የአንግሊዝ መንግስት የሆነውን ሁሉ እንዳላየ ሲያልፍ ጥላቻው ነገሰ፡፡
ሄሪ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ቤቱ መሄድ እንደሌለበት ወስኗል።
ፖሊሶች በዋስ በመለቀቁ ስለተበሳጩ በማንኛውም አጋጣሚ ሊያስሩት
አቆብቁበዋል፡፡ ለትንሽ ጊዜ መደበቅ ያዋጣዋል፡፡ ተመልሶ እስር ቤት መግባት
አይፈልግም፡፡ ታዲያ ስንት ጊዜ ፖሊስ መጣ እያለ ሲበረግግ ሊኖር ነው?
ሁልጊዜስ ፖሊስን መሽወድ ይቻላል? ካልሆነስ ምን ማድረግ ይኖርበታል?
እናቱ በሃዘን ፊታቸው ጠቁሯል፡ ገንዘብ እንዴት እንደሚያገኝ ቢያውቁም አንስተውበት አያውቁም፡፡ ‹‹በእናትነቴ ምንም አድርጌልህ አላውቅም›› አሉት ‹‹እማማ ያለሽን አድርገሽልኛል›› ሲል መለሰላቸው፡፡
‹ሃሰት፤ ምንም አላደረኩልህም፤ ለዚህ አይደለም መስረቅህ››
ሄሪ ለዚህ መልስ አጣ፡፡
ከአውቶብስ እንደወረዱ ጋዜጣ ሻጩ በርኒን እናቱን በስልክ ስለጠራለት
እንደውለታ ቆጥሮት ጋዜጣ ገዛው፡፡ የጋዜጣው የፊት ሽፋን ጀርመን ፖላንድን በቦምብ ደበደበች ይላል፡ ወዲያውም አንድ ፖሊስ በብስክሌት ሲመጣ ተመልክቶ በደመነፍስ ተርበተበተ፡፡ እግሬ አውጪኝ ሊል ሲያስብ ሰው ለማሰር ሁለት ሆነው የሚመጡ መሆኑን ሲያውቅ አደብ ገዛ፡፡
እንደዚህ እየሰጋሁማ እንዴት እኖራለሁ› ሲል አስበ፡፡
እቤት ሲገባ እናቱ ሻይ ጥደው ‹‹ሰማያዊ ሱፍ ልብስህን ተኩሼልሃለሁ፤ መለወጥ ትችላለህ›› አሉት
እስካሁንም ልብሱን የሚያጥቡለትና የሚያዘገጃጁለት ካልሲውንም የሚሰፉለት እናቱ ናቸው፡፡ ሄሪ መኝታ ቤት ገባና ከአልጋው ስር ሻንጣውንዐአውጥቶ ገንዘቡን ቆጠረ፡፡ ሁለት ዓመት በስርቆት ተሰማርቶ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ፓውንድ አጠራቅሟል፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት እጁ ገብቷል በሃሳብ ተውጦ ፓስፖርቱን እያገላበጠ ተመለከተው፡፡ ከአንድ አሜሪካዊ ላይ እንደመነተፈው አስታወሰ፡ የሰውየው ስም ሃሮልድ መሆኑን ሰውየውም
እሱን እንደሚመስል ተገነዘበና ኪሱ ከተተው፡
የአሜሪካውያንን የአነጋገር
ቅላጼ ይችላል፡፡ በአሜሪካ ውስጥ የእንግሊዛውያን የአነጋገር ቅላጼ ካለህ የከበርቴ መደብ አባል እንደሆንክ ተደርጎ ይቆጠራል፡ አሜሪካ ውስጥ በርካታ በፍቅር ልታሳብዳቸው የምትችላቸው ኮረዶች አሉ፡፡
እንግሊዝ ውስጥ የሚቀርበት እስር ቤትና ውትድርና ብቻ ነው፡፡
አሁን ፓስፖርትና ኪሱ ሙሉ ገንዘብ አለው፡ እናቱ ቁም ሳጥን ውስጥ ንፁህ ሱፍ ልብስ ያለው ሲሆን አንድ ሁለት ሸሚዝ መግዛት ይችላል።
ከሳውዝ ሃምፕተን 75 ማይል ነው የሚርቀው
ዛሬውኑ መሄድ ይችላል።
ሁሉም ነገር እንደ ህልም መሰስ ይላል።
እናቱ ‹‹ሄሪ ሳንድዊች ትፈልጋለህ?›› ሲሉ ጠየቁት
‹‹እሺ እማ››
ኩሽና ሄዶ ተቀመጠ፤ እናቱ ሳንድዊቹን ፊቱ ቢያደርጉለትም ንክች
አላደረገውም፡፡‹‹እማ አሜሪካ እንሂድ›› አላቸው
እናቱ በሳቅ ፈነዱ ‹‹እኔ አሜሪካ?!››
‹‹እውነቴን ነው፡ እኔ ልሄድ ነው፡››
አሁን ፈገግታቸው ጠፋ ‹‹ለኔ አይሆንም ልጄ፡፡ በዚህ እድሜዬ ስደት
ለኔ አይሆንም››
‹‹እዚህ እኮ ጦርነት ሊጀመር ነው፡፡››
‹‹አንድ ጦርነት፣ የስራ ማቆም አድማና የኢኮኖሚ መዳሸቅ አሳልፌያለሁ፡››
ጠባብዋን ማድቤት አማተሩና ‹‹የኔ ዓለም ይሄ ነው›› አሉ።
ሄሪ እናቱ በዚህ እንደማይስማሙ ቢያውቅም ቁርጡን ሲነግሩት ተስፋው ተሟጠጠ፡፡
በዚህ አለም ላይ ያሉት እናቱ ብቻ ናቸው፡፡
‹‹እዚያስ ምን ልትሰራ አስበሃል?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹የሌብነት ስራዬ ያሳስብሻል?››
‹‹ሌብነት የትም አያደርስም፡ በሌብነት ያለፈለት ሰው አላውቅም›› አሉት፡፡
‹‹እዚያ አየር ኃይል ገብቼ አብራሪ መሆን እፈልጋለሁ፡ አሜሪካ ውስጥ ጭንቅላት ካለሽ የሰራተኛው መደብ ብትሆኝም ግድ የላቸውም።››
እናቱ በመጠኑ ፈገግ አሉ፡ እሳቸው ሻይ ሲጠጡ እሱ ሳንድዊቹን ይገምጣል።
በልቶ እንደጨረሰ ገንዘቡን ከኪሱ አወጣና ሃምሳ ፓውንድ ቆጥሮ ለየ
‹‹ይሄ ለምንድን ነው?›› ሲሉ ጠየቁ፡፡ ይህ ገንዘብ ሁለት አመት ልብስ አጥበው የሚከፈላቸውን ገንዘብ ያክላል
‹‹ይጠቅምሻል እማ ውሰጂው›› አለ፡፡
እናቱ ገንዘቡን ተቀበሉና
‹‹እውነት ልትሄድ ነው?›› ሲሉ ጠየቁት።
‹‹ወደ ሳውዝ ሃምፕተን በሞተር ሳይክል እሄድና መርከብ ላይ እሳፈራለሁ»
እጃቸውን ሰደዱና የልጃቸውን እጅ ለቀም አደረጉ፡፡ ‹‹ልጄ መልካም
ዕድል ይግጠምህ፡››
እሱም የእናቱን እጅ ጨበጥ አደረገና ‹‹ከአሜሪካ ገንዘብ እልክልሻለሁ አለ።
‹‹አያስፈልግም፡፡ ከዚያ ደብዳቤ ቶሎ ቶሎ ስደድልኝና ጤንነትህን
ልወቅ፡፡››
‹‹እሺ እፅፍልሻለሁ፡››
አይናቸው በእንባ ተቆረዘዘ ‹‹አንድ ቀን ናና አሮጊት እናትህን እያት››
እጃቸውን ጨበጥ አደረገ፡፡ ‹‹እመጣለሁ እንጂ እማ፡፡ እመለሳለሁ፡››
ሄሪ በመስታወት ከላይ እስከ ታች ራሱን አየ፡፡
ሰማያዊው ሱፍ ልብስ ያማረበት ሲሆን ከሰማያዊው የአይኑ ቀለም ጋ ሄዷል፡፡
ሸሚዙ የአሜሪካ ሽሚዝ ይመስላል፡ ፁጉር አስተካካዩ የባለ ሁለት
ደረት ኪስ ኮቱን ትከሻ በቡሩሽ ሲጠርግለት ሄሪ ጉርሻ ሰጠውና ወጣ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሳውዝ ሃምፕተን ወደብ በሰው ተጥለቅልቋል። ከዚህ ቦታ ነው የአትላንቲክ አቋራጭ ጉዞ የሚነሳው፡፡ በመሆኑም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች
ከእንግሊዝ ለመውጣት ይተራመሳሉ፡፡
ሄሪ መርከብ ለማግኘት ሲጠያይቅ የሁሉም መርከቦች ቦታ ለመጪዎቹ
ሳምንታት ጉዞ አስቀድመው እንደተያዙ አወቀ፡ አንዳንዶቹ የመርከብ ትራንስፖርት ድርጅቶች ባዶ ቢሮ ታቅፈው ለሰራተኛ ደመወዝ ከመክፈል በራቸውን ዘግተዋል፡ ለተወሰነ ጊዜ ምንም ቦታ የማይገኝ መሰለው።
በመርከብ መሄዱን ትቶ ሌላ አማራጭ መጓጓዣ ሲያፈላልግ አንድ የጉዞ ወኪል ባህር ላይ የሚያርፍና ከባህር ላይ የሚነሳ የፓን አሜሪካን
አውሮፕላንን እንዳለ
አበሰረው፡፡ ስለዚህ አይሮፕላን በየጋዜጣው ላይ
አንብቧል፡ መርከብ ወደ ኒውዮርክ ከተማ ለመሄድ አራትና አምስት ቀን
የሚፈጅበት ሲሆን አይሮፕላኑ ከ30 ሰዓት ባነሰ ይደርሳል፡ ታዲያ የአንድ
ጊዜ ጉዞ ትኬት ዋጋ 90 ፓውንድ አዲስ መኪና ይገዛል።
ሄሪ በርካታ ገንዘብ አባክኗል፡፡ እብደት ነው፡፡ ታዲያ ከአገር ለመውጣት
ሲል የፈለገውን ያህል ዋጋም ቢሆን ለመክፈል ወስኗል፡፡ አይሮፕላኑ ምቾቱ
ያጓጓል፡ ኒውዮርክ እስክትደርስ ድረስ ሻምፓኝ መጨለጥ ነው፡፡ እንዲህ
አይነት ቅንጦት ደግሞ ለሄሪ ነፍሱ ነው፡፡
ፖሊስ ባየ ቁጥር መደንበሩ ሊቀር ነው፡፡ ሳውዝ ሃምፕተን ውስጥ
ደግሞ ስለ እሱ ሌብነት የሚያውቅ ፖሊስ የለም፡፡ ከዚህ ቀደም በአይሮፕላን
በርሮ ስለማያውቅ ግን አዕምሮው ተረብሿል፡፡
ሰዓቱን አየ፤ከቤተመንግሥት አንጋች ላይ የመነተፈው ነው፡፡

👍30
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
ከሳውዝ ሃምፕተን ወደ ፎየንስ (አየርላንድ)
ባቡሩ ጫካውን እየሰነጠቀ ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ሲያመሩ የማርጋሬት
ኦክሰንፎርድ እህት ኤልሳቤት አንድ አስደንጋጭ ነገር ለእህቷ ነገረቻት
የኦክስንፎርድ ቤተሰቦች በአየር በራሪው በተያዘላቸው ልዩ ፉርጎ ውስጥ ተቀምጠዋል፡ ማርጋሬት ፉርጎው መጨረሻ ላይ ተቀምጣ በመስኮት ውጭ ውጩን ታያለች፡፡ አገሯን በችግሯ ጊዜ ጥላት መሄዷ ክፉኛ ቢያበሳጫትም አሜሪካ የመሄዷ ነገር ደግሞ በሌላ በኩል ደስታ አጭሮባታል፡
እህቷ ኤልሳቤት ከቤተሰቡ ነጠል ብላ ወደ ማርጋሬት መጣችና
‹‹እወድሻለሁ ማጊ›› አለቻት።
ማርጋሬት በእህቷ አባባል ልቧ ተነካ፡ በዓለም ላይ የሚካሄደውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነትና ጦርነት መረዳት ከጀመሩ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተቃራኒ አቋም በመያዝ በነገር መጠዛጠዛቸው አራርቋቸው ነበር።ማርጋሬት ይህ የአስተሳሰብ ልዩነት ከእህቷ ስለነጠላት ታዝን ነበር
እንደገና ጓደኛ ቢሆኑ በወደደች፡፡ ‹‹እኔም እወድሻለሁ እታለም›› አለቻትና እቅፍ አደረገቻት፡፡
ትንሽ ቆየችና ‹‹አሜሪካ ከእናንተ ጋር አልሄድም›› አለች ኤልሳቤት ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ደነገጠች ‹‹እንዴት እባክሽ?››
‹‹ለእማማና አባባ እንደማልሄድ በቀጥታ ልነግራቸው ነው፤ ሃያ አንድ
ዓመት ስለሆነኝ ሊያስገድዱኝ አይችሉም››
ማርጋሬት የእህቷ ውሳኔ ትክክል ይሁን አይሁን አላወቀችም ‹‹የት ነው የምትሄጂው?››
‹‹ወደ ጀርመን››
‹‹ሊሆን አይችልም ኤልሲ›› አለች ማርጋሬት በፍርሃት፡፡ ‹‹ትሞቻለሽ››
‹ሶሻሊስቶች ብቻ አይደሉም ላመኑበት ዓላማ የሚሰዉት››
‹‹ግን ለፋሺዝም ብለሽ?››
‹‹ለፋሺዝም ብዬ አይደለም›› አለች
ኤልሳቤት፡፡ ዓይኗ ላይ እንግዳ አመለካከት ይነበባል፡፡ ‹‹በጥቁሮችና በክልሶች የመዋጥ አደጋ ላንዣበበበት ንፁህ ነጭ ዘር ብዬ ነው፡፡››
ማርጋሬትን ያበሳጫት እህቷን ማጣቷ ብቻ አይደለም፡፡ በዚህ ሰይጣናዊ ዓላማ ከእህቷ መለየቷ ነው ያሳዘናት፡ ሆኖም የቀድሞውን ጊዜ የፖለቲካ ጭቅጭቃቸውን አሁን ማንሳት አልፈለገችም፡ አሁን ያስጨነቃት ጉዳይ
የእህቷ ደህንነት ነው፡፡
‹‹እንዴት ትኖሪያለሽ ጀርመን ውስጥ?›› ስትል ጠየቀቻት
‹‹ገንዘብ አለኝ››
ማርጋሬት አያታቸው ሲሞቱ ያወረሷቸውን ገንዘብ አስታወስች፡፡ ገንዘቡ
ብዙ ባይሆንም ያኖራል፡
ማርጋሬት አንድ ነገር በሃሳቧ መጣ፡፡ ‹‹ሻንጣሽ ወደ ኒውዮርክ ተልኳል እኮ››
‹‹ኒውዮርክ የተላኩት ሻንጣዎች የተሞሉት በጠረጴዛ ልብስ ነው::
ልብሴን በሌላ ሻንጣ ሞልቼ ሰኞ ዕለት ልኬያለሁ።››
ማርጋሬት በእህቷ ብልህነት በእጅጉ ተደነቀች፡፡ ኤልሳቤት ሁሉንም
ነገር አቅዳ በትክክልና በምስጢር አከናውናለች፡፡ እሷ ከዚህ ቀደም ያደረገችው የማምለጥ ሙከራ እህቷ ካደረገችው ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል የተውሸለሸለና በሚገባ ያልታቀደ እንደሆነ ተረዳች፡፡ እኔ ምግብ አልበላም እያልኩ ስተክዝ እሷ ግን ለጉዞዋ ቦታ ለመያዝና ዕቃ ለመላክ ትሯሯጥ ነበር፡
እህቷ የያዘችው የፖለቲካ አስተሳሰብ የተሳሳተ ቢሆንም ከእሷ በተሻለ
ሁኔታ መንቀሳቀስ መቻሏ የዝቅተኝነት ስሜት ፈጠረባት፡፡ ወዲያው ደግሞ ከእህቷ ጋር እስከ ወዲያኛው መለያየቷ ገባት፡፡ ምንም እንኳን ብዙም ባይቀራረቡም አብረው አድገዋል፡ ብዙ ጊዜ በሃሳብ ሲከራከሩና አንዷ ያንዷን አስተሳሰብ ስታጣምም ቢኖሩም ማርጋሬት ይሄም ሊቀርባት ነው: በችግር ጊዜ ይረዳዱ ነበር፡፡ ኤልሳቤት የወር አበባዋ በመጣ ቁጥር ህመም ሲሰማት ማርጋሬት አልጋ ላይ አስተኝታት የሚጠጣ ትኩስ ነገርና የሚነበብ መጽሔት ታመጣላታለች፡ የማርጋሬት ፍቅረኛ ኢያን ሲሞት መሪር ሀዘን ላይ ወድቃ የነበረ ጊዜ ምንም እንኳን ኢያንን ባትወደውም ታጽናናት ነበር
ማርጋሬት ዓይኗ በእምባ ተሞልቶ ‹‹ትተሽኝ ልትሄጂ ነው?›› አለቻት እህቷን፡፡
‹‹ግርግር አታብዢ›› አለች ኤልሳቤት ‹‹ገና አልነገርኳቸውም››
ማርጋሬት መነፋረቋን አቆመችና ‹‹መቼ ልትነግሪያቸው ነው?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹ መጨረሻው ደቂቃ ላይ፤ አንቺም እስከዚያው አታስነቂ››
‹‹እሺ እታለም›› ብላ የግድ ፈገግታ አሳየቻት፡
«አይ ማርጊ›› አለች ኤልሳቤት እምባ እየተናነቃት፡፡ ሳጓን ዋጥ
አደረገችና ‹‹እኔ እስከምረጋጋ ድረስ ሂጂና አዋሪያቸው::››
ማርጋሬት የእህቷን እጅ ጨበጥ አደረገችና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች
እናት የፋሽን መጽሔት ያገላብጡና የሚነገር ነገር ሲያገኙ ለአባት ያነባሉ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ ለማዳመጥ ፍላጎት የላቸውም፡፡ እናት
ግን ተስፋ ሳይቆርጡ ያነባሉ፡፡ ሎርዱ የንቀት ፊት ይነበብባቸዋል፡ ትልቋ
ልጃቸው የደገሰችላቸውን አያውቁም፡
ለማርጋሬት መንገር አንድ ነገር ነው፤ ለአባቷ መንገር ግን ሌላ ነገር.ነው፡፡ ኤልሳቤት በመጨረሻ ደቂቃ ለመንገር ድፍረት ታጣ ይሆናል፡፡
ማርጋሬትም ከዚህ ቀደም ከአባቷ ጋር እሰጥ አገባ ልትገጥም ነበር በኋላ
እጇን ሰጠች እንጂ፡
ኤልሳቤት ወንድ ወጥቷት ለአባቷ ከነገረች ወደ ጀርመን መሄዷ
የተረጋገጠ ላይሆን ይችላል፡ ሃያ አንድ አመት የሞላትና ገንዘብ ያላት
ብትሆንም እሳቸው ግን አቋመ ፅኑና ያሻቸውን ከማድረግ የማይመለሱ ሰው ናቸው፡ ኤልሳቤት ከፈቃዳቸው እንዳትወጣ ማቆም የሚችሉ ከሆነ
እንደሚያደርጉት ማርጋሬት አትጠራጠርም: በመርህ ደረጃ ኤልሳቤት
የፋሺስት ፓርቲን ብትቀላቀል አይጠሉም፤ ነገር ግን ትዕዛዛቸውን ጥሳና ቤተሰቡን ትታ ብትሄድ ግሥላ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡
ማርጋሬት ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ከአባቷ ጋር ተጣልታለች። ያለሳቸው
ፈቃድ መኪና መንዳት በተማረች ጊዜ ተቆጥተዋታል፡ የእርግዝና መከላከያ ፈር ቀዳጅ የሆነችው የሜሪ ስቶፕስን ንግግር ለመስማት መሄዷን ያወቁ ጊዜ.ፊታቸው በንዴት በርበሬ መስሎ ነበር፡ አባቷ ሳያውቁ ካላደረገች በስተቀር ፊት ለፊት ተጋፍጣ እንደማይሆንላት ታውቃለች፡፡ የአስራ ስድስት ዓመት ኮረዳ ሳለች ከአጎቷ ልጅ ጓደኞች ጋር ትምህርት ቤት ሲዘጋ ሽርሽር ልሂድ
ብላ ስትጠይቃቸው አልፈቀዱላትም፡፡ ያልፈቀዱላት ከሴቶችም ከወንዶችም.እንዳትቀላቀል ነው: ትልቁ ጦርነት የነበረው ትምህርት ቤት ልሂድ ያለች
ጊዜ ነበር፡ ትምህርት ቤት ለመግባት እንዲፈቀድላት ብትለምንም፣ ብታለቅስም ወይም ብታኮርፍም አባት ጆሮ ዳባ ልበስ አሉ፡ ‹‹ትምህርት ለሴቶች ምንም አያደርግላቸውም ሴቶች ቤት ውስጥ አድገው ባል
አግብተው መቀመጥ ነው ያለባቸው›› ነበር ያሏት፡፡
ማርጋሬት እረፍት አጣች፡ አንድ ነገር አገኝ ብላ ተነሳችና ፉርጎው
ውስጥ ተንጎራደደች፡ የሰማይ በራሪው ጀልባ ተሳፋሪዎች ሲታዩ ገሚሶቹ
የተከፉ ከፊሎቹ የተደሰቱ ይመስላሉ፡፡
ከተሳፋሪዎቹ መካከል አንዲት በዓለም የታወቀች አሜሪካዊት ኮከብ የፊልም ተዋናይ ስላለች ሁሉም ስለእሷ በሹክሹክታ ያወራል፡ ሉሉ ቤል ትባላለች፡ ፔርሲ ከሷ ጋር ቁጭ ብሎ ልክ ረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቁ ሁሉ
ያወራታል፡ ማርጋሬት ከተዋናይዋ ጋር ማውራት በወደደች፤ ነገር ግን
ዓይኗን በጨው አጥባ ሄዳ ልታወራት አልደፈረችም፡፡ ፔርሊ ዓይን ቀቅሎ
የበላ ነው፡፡
ሉሉ ቤል በፊልም ስትታይ ወጣት ብትመስልም በአካል ሲያይዋት ግን ያረጀች ትመስላለች፡ አንድ አርባ ዓመት ሳይሆናት አይቀርም ስትል ማርጋሬት አሰበች ምንም እንኳን ፊልሞቿ ላይ ወጣቶችንና በቅርብ ያገቡ
ሴቶች ገጸ ባህሪ ወክላ ብትጫወትም፡፡ ምንም ሆነ ምን አሁንም ውብ
ሽንቃጣና ተግባቢ ናት፡፡
ማርጋሬት ሉሉን ስታይ ፈገግ አለች፡፡ ሉሉም ‹‹ታናሽ ወንድምሽ ያጫውተኛል›› አለች፡፡

👍17🥰2
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
‹‹አይሮፕላኑን ባህሩ ላይ እንድጥለው ትፈልጋለህ?››
‹‹እንደዚያማ ማድረግ አትችልምº እኔ አይሮፕላኑ ውስጥ አለሁ
ፓይለቱ እዚያ ቦታ ላይ በድንገት እንዲያርፍ የሚያስገድደው አንድ ችግር ፍጠር›› አለው በሚገባ በተከረከመ ጥፍሩ ፖስት ካርዱ ላይ ያለውን ቦታ እያመለከተው፡፡
የበረራ መሃንዲሱ ፓይለቱ በድንገት አይሮፕላኑን ለማሳረፍ የሚያስገድደው ችግር መፍጠር አያቅተውም፡፡ ነገር ግን አይሮፕላኑን የሚያሳርፍ ችግር መፍጠር ለጊዜው ኤዲ አልከሰትልህ አለው፡፡
‹‹ቀላል እንዳልሆነ ይገባኛል፤ ነገር ግን የማይሆን ነገር ግን አይደለም
እኔም ይህን ማድረግ እንደሚቻል አረጋግጫለሁ››
‹‹ማነው ይህን የነገረህ? እናንተስ እነማን ናችሁ? አለ ኤዲ ንዴቱ ተቀስቅሶ፡
‹‹ትዕዛዝ መፈጸም እንጂ መጠየቅ አትችልም›› አለው ሉተር::
ኤዲ መጀመሪያ ሉተርን ሊያስፈራራው ሞከረ፣ አሁን ግን አቅመ ቢስ ሆኗል፡ አሁን በፍርሃት መሸበብ የእሱ ተራ ሆኗል፡ ሉተር ይህን ጉዳይ በሚገባ ያቀደ የወሮበላ ቡድን አባል ነው፡፡ ኤዲን ለእኩይ ተግባራቸው
በመሳሪያነት ሊጠቀሙበት ነው የመረጡት፡ ውጥናቸውን ዳር ለማድረስ
ደግሞ ካሮል አንን እመዳፋቸው ስር አውለዋታል፡
ኤዲ ፖስት ካርዱን ኪሱ ከተተና ትተባበራለህ ወይስ አትተባበርም?›› ሲል ሉተር በጉጉት ጠየቀ፡፡
ኤዲ ዞር አለና አፈጠጠበት፡ ከዚያም መልስ ሳይሰጥ መንገዱን ቀጠለ፡
ኤዲ በጠላቶቹ ፊት ፈርጠም ያለ ባህሪ ለማሳየት ቢሞክርም እውነታው ግን እንዳንበረከኩት ነው የሚያሳየው እነዚህ ወሮበሎች ለምንድነው ይህን ማድረግ የፈለጉት? ባንድ ወቅት ጀርመኖች ቦይንግ 314 አይሮፕላንን
ሰርቀው ዲዛይኑን ኮፒ ለማድረግ ፈልገው እንደነበር ያውቃል፡ አሁን ይህን ማድረግ ቢፈልጉ አይሮፕላኑን ሜይን ስቴት ውስጥ ሳይሆን አውሮፓ
ውስጥም ሰርቀው መውሰድ የሚያግዳቸው ነገር የለም፡፡
አይሮፕላኑን በሚፈልጉበት ቦታ ላይ እንዲወርድ ለማድረግ ማሰባቸው
ቦታው ላይ የሚጠብቅ ጀልባ እንዳላቸው ይጠቁማል፡ ‹ግን ለምን?› ሉተር ሻንጣ ሙሉ ሃሺሽ፣ ባዙቃ፣ ኮሚኒስት አብዮተኛ ወይስ የናዚ ሰላይ ነው
ወደ አሜሪካ ማስገባት የፈለገው? እነ ሉተር እዚህ ችግር ውስጥ ለመግባት
የወሰኑት መቼም ሊያስገቡት ያሰቡት ሰው ወይም ነገር በጣም ጠቃሚ
ስለሆነ ነው፡፡
ኤዲ ከሌሎቹ የስራ ባልደረቦቹ ይልቅ እሱን የመረጡበት ምክንያት
አሁን ገብቶታል፡አይሮፕላኑን አንድ ቦታ በድንገት እንዲያርፍ ከተፈለገ
ይህን ማድረግ የሚችለው የበረራ መሀንዲሱ ነው፡፡ ናቪጌተሩ ምንም ማድረግ አይችልም የሬዲዮ ኦፕሬተሩም እንዲሁ፤ ፓይለቱ ደግሞ የረዳት
ፓይለቱ ድጋፍ ያስፈልገዋል፡ የበረራ መሀንዲሱ ግን ብቻውን
የአይሮፕላኑን ሞተር ቀጥ ሊያደርገው ይችላል፡፡
ሉተር የፓን አሜሪካንን አየር መንገድ መሀንዲሶች ስም ዝርዝር ሳያገኝ አልቀረም፡ ስም ዝርዝሩንም ማግኘት ከባድ አይደለም:፡ የአየር መንገዱን መረጃ ለማየት አንድ ምሽት ላይ አንዱ የሉተር ጓደኛ የአየር መንገዱን ቢሮ ሰብሮም ቢሆን ሊያገኘው ይችላል ወይም አንዷን ጸሐፊ በጉቦ መደለል ነው፡፡ ለምን ግን ኤዲን መረጡ? ሉተር በዚህ ቀን የሚበረው የበረራ
መሃንዲስ ስም እጁ ገብቷል ከዚያም ኤዲ ለዚህ ሰይጣናዊ ተግባር
እንዲሆን ለማድረግ ሲያስብ አንድ መላ ያገኛል፤ ሚስቱን ማገት፡፡
እነዚህን ወንበዴዎች መርዳት ለኤዲ ልብ የሚሰብር ጉዳይ ሆኖበታል፡
ወንበዴዎች እጣ ክፍሎቹ አይደሉም፡ ሰርተው ከማግኘት ይልቅ ሌት ተቀን
ከሚለፉ ሰዎች አፍ እየነጠቁና እያጭበረበሩ ተንደላቀው ይኖራሉ፡ ህግ
አክባሪ ሰዎች የዕለት እንጀራ ለማግኘት ጀርባቸው ሲጎብጥ ይውላል፡ እነዚህ
ማፊያዎች ግን ለፍቶ አዳሪዎች ላይ ሽጉጥ እየደገኑ፣ ለፍተው ያገኙትን
ተሽከርካሪዎች ያሽከረክራሉ፡፡ እነዚህን ወንጀለኞች በኤሌክትሪክ ወንበር ላይ ጠፍሮ በኮረንቲ እያንጨረጨሩ መግደል ነው የሚያዋጣው፡፡
ቶም ሉተርን ማሞኘት ቀላል አይደለም፡፡ ሚስቱን ካሮል አንን አግቷታል። ሉተር ያቀደውን ትልም ኤዲ ለማደናቀፍ ሞከረ ማለት በሚስቱ አንገት ላይ የታሰረውን ገመድ ሸምቀቆ አጠበቀ ማለት ነው፡፡ ሊያታልላቸው
ወይም ሊታገላቸው አይችልም፤ ያሉትን ከመፈጸም ውጭ፡
ሆዱን እንደጨነቀው ከወደቡ ወጥቶ በመንደሩ ያለችውን ብቸኛ መንገድ አቋርጦ ወደ አንድ ሆቴል ሄደ፡ ሆቴሉ እንዳለ የተያዘው በፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኞች ነው ማለት ይቻላል፡፡ እዚያም ካፒቴን ቤከርና ረዳቱ ጆኒ ዶት ከፓን አሜሪካ የፎየንስ ጣቢያ ኃላፊ ጋር የራዲዮ
መልእክቶችን እየገመገሙ የአትላንቲክ አቋራጭን በረራ ስለማድረግና አለማድረግ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ጉባኤ በተቀመጡበት ክፍል ኤዲ ገብቶ ተሰየመ፡
በአይሮፕላን በረራ ሳይንስ ቁልፍ ጉዳይ የነፋሱ ጥንካሬ ነው፡፡ ወደ ምዕራብ ሲጓዙ ከጠንካራው ነፋስ ጋር እየታገሉ ነው በረራው የሚካሄደው፡ ከፊት ለፊት የሚመጣውን የንፋስ ግፊት ለመሸሽ ሲሉ ፓይለቶች
በተደጋጋሚ ከፍታቸውን ለመለዋወጥ ይገደዳሉ፡ ይህም ቴክኒክ በበረራው
ሳይንስ ‹ነፋሱን ማሳደድ›› ይባላል፡ ዝቅተኛ ቦታ ላይ ያለ ነፋስ ግፊቱ ያነሰ
ቢሆንም አይሮፕላኑ ዝቅ እያለ በበረረ ቁጥር ከመርከብ ወይም ባህር ላይ ከሚዋልል የበረዶ ቋጥኝ ጋር ሊላተም ይችላል፡፡ ከፊት ለፊት የሚመጣን ንፋስ ግፊት ለመቋቋም በርካታ ነዳጅ ማቃጠል ይጠይቃል፡ ኃይለኛ የንፋስ ግፊት ካለ ከአይርላንድ እስከ ኒውፋውንድ ላንድ (ካናዳ) ከሁለት ሺህ ማይል
በላይ ለመብረር የሚበቃ ነዳጅ አይሮፕላኑ መያዝ ስለማይችል የነዳጅ
እጥረት ሊያጋጥም ይችላል፡ በዚህም ምክንያት በረራው ለሌላ ቀን ሊተላለፍ
ስለሚችል የአየሩ ጠባይ እስከሚሻሻል ተጓዦች በሆቴል ሊቆዩ የሚችሉበት
አጋጣሚ ይፈጠራል፡
የዚህ ዓይነት የአየር መዛባት ቢከሰት ካሮል አንን ምን ይውጣት ይሆን?
የአየር ጠባይ ሪፖርቱ ነፋሱ ከባድ መሆኑን፣ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ደግሞ ከባድ ማዕበል እንዳለ ያመለክታል፡፡ አይሮፕላኑ ሙሉ ሰው ጭኗል፡
ስለዚህ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ሁሉ ነገር በጥንቃቄ መሰላት አለበት፡፡ የአየሩ
ጠባይ መጥፎ መሆን የኤዲን ጭንቀት አባባሰው፡፡ ሚስቱ ካሮል አን በወዲያኛው የውቅያኖስ ጥግ በጨካኝ ወንበዴዎች እጅ ወድቃ እሱ እዚህ አየርላንድ ውስጥ ተጣብቆ መቅረቱን
ሊቋቋመው የሚችለው ነገር
አይደለም፡፡ ለመሆኑ ምግብ ይሰጧት ይሆን? የምትተኛበት ቦታስ አላት
ይሆን? ብርድስ ይመታት ይሆን?› እያለ ያስባል።
የአትላንቲክ ውቅያኖስን አካባቢ የሚያሳየው ማፕ ጋ ሄደና ቶም ሉተር የሰጠውን አይሮፕላኑ እንዲያርፍበት የሚፈለግበትን ቦታ ተመለከተ፡፡ ቦታው
ተጠንቶ የተመረጠ ነው ከካናዳ ጠረፍ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቆ ቤይ አፍ
ፈንዲ› የሚባል በጠረፉና በአንድ ትንሽ ደሴት መካከል የሚገኝ ቦታ ነው:
ምንም እንኳን ባህር ላይ ለሚያርፉ አይሮፕላኖች ማረፊያነቱ ብዙም
ተመራጭ ባይሆንም ከገላጣው የባህር ክፍል የተሻለ ነው፡፡ ይህን ሲያውቅ ኤዲ ተስፋው ለመለመ፡ ቢያንስ የማረፉ ነገር ብዙ ችግር የለውም፡፡ ሉተር ሚስቱን በእጁ እንዲያስገባለትና እቅዱ እንዲሳካ አቅሙን በሙሉ አሟጧዐየተጣለበትን ግዴታ መወጣት አለበት፡
አሁንም ግን አይሮፕላኑን እዚያ ቦታ እንዴት ሊያሳርፍ እንደሚችልዐመጨነቁ አልቀረም፡ በዚህ ቦታ እንዲያርፍ ያደረኩት አንዱ የአይሮፕላኑ ሞተር ስለተበላሽ ነው ቢል በሶስት ሞተር ሊሄድ እንደሚችል ረዳት የበረራ መሀንዲሱ ሚኪ ፊን ስለሚያውቅ ይህ ምክንያት ብዙም አያስኬድም የአዕምሮውን ጓዳ ቢያስስም ተጨባጭ መፍትሄ አልመጣለት አለ፡፡

👍16
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
በተቃራኒው ጦርነት
ወደ ተዘፈቀች አገር መመለሱ ራሱ አንድ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው፡.... እዚህ ነገር ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ለምን ገባሁ? አለች ልቧ
እየተሰበረ ሁን ለመጸጸት ጊዜ የለም፡ አንዴ ስለወሰንኩ ወደ ኋላ
የምልበት ነገር የለም፡፡ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥም አለች መልሳ
በሆዷ ሀሳቧ አንድ ቦታ አልረጋ ብሏት፡
ማርክ እጇን ለቀም አድርጎ ሲይዝ እንዳይለቃት ፈራች፡፡ ‹አንድ ጊዜ ሃሳብሽን ለውጠሻል። አሁንም ደግመሽ መለወጥ ትችያለሽ›› አለ ለማሳመን፡፡
ከኔ ጋር አሜሪካ እንሂድና ላግባሽ፡፡ ልጆቻችንን ይዘን ባህር ዳር እንጫወታለን የምንወልዳቸው ልጆች ቴኒስ እየተጫወቱ፣ እየዋኙ ብስክሌት እየነዱ ያድጋሉ፡ ስንት ልጅ ነው መውለድ የምትፈልጊው?››
አሁን መወላወሉን አቁማለች፡፡ ‹‹ማርክ እያደረኩት ያለሁት ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ ተመልሼ ወዳገሬ እሄዳለሁ›› አለች፡፡
ያለችውን የተቀበለ መሆኑን ተረዳች፡፡ ሁለቱም ሀዘን ገብቷቸውና የሚሰሩትን አጥተው ዓይን ላይን ይተያያሉ፡፡ የሚናገሩት ጠፍቷቸው ዝም
ዝም ብለዋል፡
ከዚያም መርቪን ቡና ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፡፡
ዳያና ባሏ ፊቷ መጥቶ ድቅን ሲልባት ዓይኗን ማመን አቃታት፡ ልክ
አንድ የሆነ መንፈስ ፊት የቆመ ይመስል አፈጠጠችበት፡ እንዴት እዚህ ሊመጣ ቻለ? ሊሆን አይችልም
‹‹እዚህ ተገኘሽ አይደል!›› አለ መርቪን በተለመደው አስገምጋሚ ድምጹ
ዳያና ግራ ተጋባች፡፡ መርቪን እዚህ መገኘቱ አስደንቋታል፣ አስፈርቷታል፣ እፎይታ ሆኗታል፣ ቅሌት ውስጥም ከቷታል፡፡ ከሌላ ወንድ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ ባሏ ሲደርስባት በደመነፍስ እጇን ከማርክ እጅ መንጭቃ አላቀቀች
ማርክም ‹‹ምንድነው እሱ?›› ሲል ጠየቃት ነገሩ ስላልገባው፡
መርቪን ሁለት እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ ፊታቸው ተገትሯል፡
‹‹ማነው ይሄ ፊታችን የተገተረው?›› ሲል ጠየቀ ማርክ፡፡
‹‹ባሌ መርቪን ነው›› አለች በደከመ ድምጽ፡
‹‹ወይ አምላኬ!›› አለ ማርክ፡
‹‹እንዴት እዚህ ልትመጣ ቻልክ መርቪን?›› ስትል ጠየቀች ዳያና የምንተ እፍረቷን፡፡
‹‹ብራሴ አይሮፕላን በርሬ መጣሁ›› አለ ቁርጥ ባለ የአነጋገር ባህሪው:
ቆዳ ጃኬት የለበሰ ሲሆን በእጁ የሞተር ሳይክል ነጂ ቆብ አንጠልጥሏል፡፡
‹‹ኧረ ለመሆኑ እዚህ መሆናችንን እንዴት አወቅህ?›› ስትል ጥያቄዋን
ደገመች፡፡
‹በጻፍሽልኝ ደብዳቤ አሜሪካ እንደምትሄጂ ገልጸሻል፡ ወደ አሜሪካ
የሚኬደው ደግሞ በሰማይ በራሪ ጀልባ ብቻ መሆኑ ይታወቃል›› አለ በድል
አድራጊነት፡፡
የሷን ዱካ ተከታትሎ የምትሄድበትን መንገድ ገምቶ እሷ ጋ በመድረሱ ደስ እንዳለው ከገጽታው ይነበባል፡ በራሱ አይሮፕላን በርሮ ሊደርስባቸው
እንደሚችል ፈጽሞ አልጠረጠረችም፡፡ በዚህ መንገድ ተከታትሎ ስለደረሰባት ደካማ ነኝ ስትል አሰበች፡፡
ከእነሱ ትይዩ ባለው
ወንበር ላይ ተቀመጠና
‹‹እስቲ ዊስኪ አምጪልኝ›› ሲል አዘዘ አስተናጋጇን፡፡
ማርክ ብርጭቆውን አንስቶ ባንዴ ሲጨልጥ ዳያና ታየዋለች::በመጀመሪያ መርቪንን ሲያየው ተርበትብቶ ነበር፡፡ በኋላ ግን መርቪን አምባጓሮ እንደማያነሳ ሲገነዘብ ተረጋጋ ሆኖም ወምበሩን ገፋ አደረገና ከዳያና ፈንጠር ብሎ ተቀመጠ፡፡ የሰው ሚስት እጅ እንደያዝ ባሏ ከተፍ ሲልበት ሳያፍር አልቀረም፡
ዳያና ድፍረት እንዲሰጣት ብላ ከአልኮሉ ተጎነጨች፡ መርቪን በጭንቀት ያያታል። ግራ መጋባቱንና መጎዳቱን ከፊቱ ስታይ ደረቱ ውስጥ
ተወሸቂ! ተወሸቂ! አላት፡፡ ከፊቱ ምን እንደሚጠብቀው ሳያውቅ እሷን ፍለጋ
አገር አቋርጦ መጥቷል፡፡ እጇን ሰዳ በማጽናናት ሁኔታ ክንዱን ያዝ አደረገችው፡፡
ሚስቱ በውሽማዋ ፊት ያዝ ስታደርገው መርቪን ማርክን በእፍረት አየት አደረገው፡፡ ዊስኪው ሲመጣለት አንስቶ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠው::
ማርክ በበኩሉ ዳያናን የሚያጣ መስሎት ወምበሩን ወደ እሷ አስጠጋ
ዳያና በሁኔታው ግራ ተጋባች፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ከዚህ በፊት
ገጥሟት አያውቅም:: ሁለቱም ሰዎች ይወዱዋታል ከሁለቱም ጋር ተኝታለች፡ ሁለቱም ይህን ያውቃሉ፡፡ በጣም አሳፋሪ፡፡ ሁለቱንም ማጽናናት ፈለገች፧ ሆኖም ፈራች፡፡ አሁን ወደ መከላከሉ አዘምብላለች። ከሁለቱም ራቅ ብላ ተቀመጠችና ‹‹መርቪን አንተን ልጎዳ ብዬ አይደለም እዚህ መዘዝ ውስጥ የገባሁት›› አለች
መርቪን ፊቱን ቅጭም አድርጎ ‹‹አምንሻለሁ›› አለ
‹‹ታምነኛለህ? የሆነውን ሁሉ ትቀበለዋለህ?›› አለች ዳያና፡፡
መርቪን ማርክ ላይ አፍጥጦ ነገር ለመፈለግ በሚመስል ሁኔታ
ተጠጋውና ውሽማሽ አሜሪካዊ ይመስላል፤ከአፍ የወደቀ ጥሬ!
የተመኘሺውን አግኘተሻል›› አለ፡፡
ማርክ አፈገፈገ፤ ምንም ቃል ሳይተነፍስ መርቪንን አፍጥጦ ያየዋል ማርክ ጠብ ፈላጊ አይነት ሰው አይደለም፡፡ ሁኔታው ግራ አጋብቶታል፡ ከዚህ በፊት ተገናኝተው ባያውቁም መርቪን ዋና ባላንጣው ነው፡፡ ማታ ማታ ዳያና አቅፋው የምትተኛው ሰው ማን ይሆን?› ሲል ራሱን ሲጠይቅ ከርሟል፡፡ አሁን ማን እንደሆነ አውቆታል። ከማርክ ጋር ሲተያይ መርቪን ስለማርክ ምንም የተጨነቀ አይመስልም፡፡
ዳያና ሁለቱን ባላንጣዎች ተመለከተቻቸው፡ ምንም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም መርቪን ዘንካታ፣ ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚል፣ ኮስታራና ነርቨስ ነው ማርክ
ደግሞ አጭር፣ ሽክ ያለ፣ ነቃ ያለና ስው ሲናገር ጆሮ የሚሰጥ ሰው ነው ማርክ
አንድ ቀን ይህን ታሪክ በኮመዲ ስራው ውስጥ አካቶ ሳያቀርበው አይቀርም ስትል ዳያና አሰበች፡
አይኖቿ እምባ አንቆርዝዘዋል፡ መሃረብ አውጥታ ንፍጧን ተናፈጠች
«ልክስክስ መሆኔን አውቄዋለሁ›› አለች፡
‹‹ልክስክስ!›› ሲል አሾፈ መርቪን ቃሉ አንሶበት፡፡ ‹‹በጣም የጅል ስራ
ዳያና ባሏ በተናገረው ተሸማቀቀች፡ ብዙ ጊዜ ስድቡ አፏን እንዳዘጋት
ነው፡፡ ዛሬ ግን ከስድብም በላይ ይገባታል፡፡
አስተናጋጇና ጥግ ተቀምጠው መጠጣቸውን የሚኮመኩሙት ሁለት
ሰዎች ሁሉን ነገር ጣጥለው ትእይንቱን በጉጉት ይመለከታሉ፤ ‹‹ምን ይከተል ይሆን?› እያሉ።
መርቪን አስተናጋጇን ጠራና ‹የኔ ቆንጆ ሳንድዊች ብታመጪልኝ›› ሲል አዘዛት እሷም ‹‹እሺ የኔ ጌታ›› አለችው በፍጹም ትህትና፡፡
አስተናጋጆች መርቪንን ይወዱታል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሮ እያስጠላኝ መጥቷል ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው አሜሪካ ለመሄድ የወሰንኩት›› አለች ዳያና፡፡
"ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው ያልሽው! አሜሪካ ጓደኛ የለሽ፣ ዘመድ የለሽ፣ ቤት የለሽ. . .አዕምሮሽ ማሰብ አቆመ እንዴ!›› አለ መርቪን፡፡
ዳያና መርቪን ስለደረሰላት አምላኳን ብታመሰግንም እንዳይጨክንባት
ፈርታለች ማርክ በእጁ ትከሻዋን ነካ አደረገና ‹‹ለምንድነው አሜሪካ ደስታ
የማታገኚው፧ እዚያ ለመሄድ ማሰብሽ ስህተት አይደለም›› አላት ድምጹን
ዝቅ አድርጎ፡፡
መርቪንን ከዚህ በላይ ማናደዱ አስፈርቷታል፡፡ ምናልባትም ትቷት
ተመልሶ ይሄድ ይሆናል፡ በማርክና በሉሉ ቤል ፊት ‹‹አልፈልግሽም›› ብሎ
ቢላት እንዴት እንደሚያበሳጫት መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ አያደርግም
አይባልም፡፡ መርቪን ተከትሏት ባይመጣ ጥሩ ነበር፡፡ ይህ ማለት ደግሞ
እዚሁ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ ይኖርበታል፡፡ ከዚያም ብርጭቆዋን አነሳችና ከንፈሯን አስነክታ ‹‹ይህን መጠጥ አልፈልግም›› ብላ መልሳ አስቀመጠችው
በዚህ ጊዜ ማርክ ‹‹ሻይ ላምጣልሽ?›› አላት፡፡

👍20❤4🥰1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
...‹‹ሪሌይ ለኔ ታማኝ ነው›› አለችው ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ
ፒተር አልለቀቃትም ‹‹ማበረታቻ ካገኘስ?››
ይሄ ነው ለካ የፒተርን ልብ እንዲህ ያሳበጠው አለች ናንሲ በሃሳቧ ዳኒ ሪሌይ ጉቦ በልቷል፡፡ አሁን የምር ጭንቅ ጭንቅ አላት፡ ራሊይ እልም ያለ ሙሰኛ ስለሆነ ጉቦ ከመብላት እንደማይመልስ ታውቃለች፡፡ ፒተር ምን ቢሰጠው ነው ሪሌይ እንደዚህ የተንበረከከለት?› ይህን ማወቅ አለባት፡ ይህን"
ጉቦ ሳይበላው ከአፉ ትነጥቀዋለች ወይም ፒተር ከሰጠው የበለጠ ጉቦ
ታቀርብለታለች፡
‹‹ዕቅድህ ዳኒ ሪሌይ ላይ ላንተ ባለው ታማኝነት ላይ የተንጠለጠለ
ከሆነ እኔን አያስጨንቀኝም›› አለችና በንቀት ሳቀችበት፡
‹‹አዎ ዕቅዴ ዳኒ ሪሌይ በሚሰጠኝ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ዳኒ
ምን ያህል ገንዘብ እንደሚወድ ታውቂ የለም›› አለ በድል አድራጊነት
መንፈስ፡፡
ናንሲ ወደ ናት ፊቷን አዞረችና ‹‹እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ይሄን እውነት ነው ብሎ መቀበል ይከብደኝ ነበር›› አለችው፡፡
‹‹ናት በዚህ በኩል ምንም ጥርጥር የለበትም›› አለ ፒተር ፈርጠም ብሎ፡፡
ናት በወንድምና እህቱ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባት ተቆጥቧል፡
ፒተር ቀጠለና ‹‹ናት ለሪሌይ ከጄኔራል ቴክስታይል ኩባንያው ጠቀም
ያለ የአክሲዮን ድርሻ ሊሰጠው ነው፡፡››
ፒተር በመጨረሻ የተናገረው ለናንሲ አቅል እንደሚያስት ምት ነበር፡
ናንሲ በንዴት ጉሮሮዋ ተዘግቶ መተንፈስ አቃታት፡፡ ለዳኒ ሪሌይ ጄኔራል
ቴክስታይልስን በመሰለ ግዙፍ ኩባንያ ውስጥ እግሩን ከመትከል በላይ
የሚያጓጓ ነገር አይኖርም፡፡ ኒውዮርክ ውስጥ ከሚገኝ ትንሽ የህግ ጥብቅና
ተቋም ጋር ሲነጻጸር ይሄ በሳህን የቀረበለት ስጦታ የዕድሜ ልክ ገቢ
የሚያስገኝ በመሆኑ ሪሌይ ይህን ስጦታ ላለመቀበል ወደ ኋላ አይልም፡፡
ሪሌይ እንደዚህ አይነት እጅ መንሻ ከቀረበለት እናቱን ከመሸጥ አይመለስም፡፡
የፒተር 40 በመቶና የሪሌይ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በድምሩ 50 በመቶ ነው፡፡ የናንሲ 40 በመቶ ከአክስታቸው 10 በመቶ ጋር ሲደመር እንደዚሁ ሃምሳ በመቶ ነው፡፡ ሆኖም የቦርድ አባላት ድምጽ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ አሸናፊውን ለመለየት የኩባንያው ኃላፊ (ሊቀመንበሩ)
የሚሰጠው ድምጽ ወሳኝነት አለው፡፡ የኩባንያው ኃላፊ ደግሞ ፒተር ነው፡
ፒተር ናንሲን መደፍጠጥ በመቻሉ በኩራት ፈገግ አለ፡፡
ናንሲ ገና እጇን አልሰጠችም፡ አጠገባቸው ያለውን ወንበር ሳበችና
ቁጭ አለች፡ ፊቷንም ወደ ናት አዞረች፡ ከወንድሟ ጋር ይህን ያህል ስትከራከር የእሷን አባባል እንዳልወደደ አውቃለች፡፡ ፒተር በድብቅ ነገር ሲጎነጉን ናት ያውቅ ነበር ስትል አሰበች፡፡ ስለዚህ ነገር ናትን ልትጠይቀው ወደደች፡
‹‹ፒተር የሚለው እውነት ይመስልሃል?››
በአንድ ወቅት ፍቅረኛው የነበረችው ሴት ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ እሷም በጸጥታ ምንም ሳትናገር ምላሹን ጠበቀች፡፡ በመጨረሻም የዓይኗን ፍጥጫ መቋቋም አቅቶት ‹‹እኔ አልጠየቅሁትም፡፡ ደግሞ በቤተሰባችሁ ጠብ ውስጥ
እኔን ምን ያገባኛል? እዚያው በጠበላችሁ፡ እኔ የንግድ ሰው እንጂ የእርዳታ
ድርጅት ሰራተኛ አይደለሁ›› አላት፡
‹‹ናት አንተ እውነተኛ የንግድ ሰው ነህ?
‹‹እንደሆንኩ ታውቂያለሽ›› አላት ፈርጠም ብሎ፡፡
‹‹ከሆንክ አንተ
እንደዚህ ያለ ሸፍጥ ቢፈጸምብህ ዝም ብለህ
ታልፋለህ?››
ናት ትንሽ አሰብ አደረገና ይሄ የአንድን ኩባንያ ባለቤትነት ለሌላ
የማዛወር ሂደት እንጂ የሻይ ግብዣ አይደለም›› አለ፡፡
ናት ብዙ ሊል ፈልጎ አቋረጠችውና በወንድሜ እምነተ ቢስነት
እጠቀማለሁ ብለህ አስበህ ከሆነ አንተም እምነተ ቢስ ነህ ማለት ነው የአባታችን ምክትል ሆነህ በመስራትህ
ነው ዛሬ እዚህ ደረጃ የደረስከው››አለችና ናት መልስ ከመስጠቱ በፊት ወደ ፒተር ዞረችና ‹‹ለሁለት ዓመት ያህል የኔ ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ብትረዳኝ አሁን
በመሸጥ ከምታገኘው እጥፍ እንደምታገኝ አታውቅም?›› አለችው::
‹‹ይሄን እቅድሽን አልቀበለውም፡፡››
‹‹ኩባንያው የአወቃቀር ለውጥ እንኳን ባይደረግበት በጦርነቱ ምክንያት
የአክሲዮን ዋጋው ሰማይ ሊነካ ይችላል፡ የወታደር ጫማ በማቅረብ በኩል
የሚስተካከለን የለም፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ብትገባ ደግሞ የምናገኘው ገቢ የትየሌለ ነው›› አለች፡፡
‹‹አሜሪካንን ደግሞ ጦርነቱ ውስጥ ምን ይጨምራታል?››
‹‹ባይሆንስ? አሁን አውሮፓ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት ብቻ እንኳን ለእኛ ንግድ ጥሩ ገቢ ያስገኝልናል›› አለችና ወደ ናት ዞር ብላ ‹‹ይሄን ታውቃለህ አይደለም? ለዚህ አይደል የእኛን ኩባንያ መግዛት
የምትፈልገው?›› ስትል አፋጠጠችው፡፡
ናት ምንም አልተነፈሰም፡፡
ቀጥሎ ወደ ወንድሟ ዞር ብላ ‹‹ትንሽ ብትቆይ ትልቅ ቢዝነስ ፊታችን ይጠብቀናል፡፡ አድምጠኝ ወንድምዬ፧ የምለው ሁሉ ስህተት ነው? የኔን
ምክር በመከተልህ የከሰርክበት ጊዜ አለ? የኔን ምክር ገሸሽ በማድረግህ
ደግሞ ገቢ ያገኘህበት ጊዜ አለ?›› ስትል በጥያቄ አጣደፈችው፡፡
‹‹አንቺ ምንም አይገባሽም›› አለ ፒተር፡፡
አሁን ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ አታውቅም፡፡
‹‹ምንድነው የማይገባኝ?››
“ለምን ኩባንያው ከናት ሪጅዌይ ኩባንያ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ጋር እንዲዋሃድ እንደፈለኩ? ለምን እንደዚህ እንደማደርግ አይገባሽም፡፡››
‹‹እሺ ለምንድነው?››
ፒተር አንድ ነገር ሳይተነፍስ ትክ ብሎ ተመለከታት፡፡ እሷም መልሱን
ከዓይኑ አይታ አገኘች::
ለእሷ ከፍተኛ ጥላቻ አለው፡:
በጣም ደነገጠች፡፡ ልክ ከማይታይ ግድግዳ ጋር የተጋጨች መሰላት፡
ይህን ሃቅ በእጅጉ ማመን አልፈለገችም:: ሆኖም ይህን በፊቱ ላይ ያየችውን
እንግዳ የሆነ የጭካኔ ገጽታ እንደሌለ አድርጋ መቀበል አስቸገራት፡፡ በታላቅና
በታናሽ መካከል ያለው ተፈጥሮአዊ ባላንጣነት ድሮም አለ፡፡ ይሄኛው ግን
ከዚያ ይለያል። ይሄ አስፈሪ፣ ለመግለጽ አስቸጋሪና እንግዳ የሆነ የጥላቻ
ገጽታ ነው፡፡ ይህን ከዚህ ቀደም ጠርጥራ አታውቅም፡፡ ታናሽ ወንድሟ
በጣም ይጠላታል፡ ልክ ከሆነ ነገር ጋር የተጋጨች ይመስል ደነዘዛት፡ ይን
እውነታ አምኖ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ይፈጃል።
ፒተር ጅል ወይም ስስታም ወይም ንፉግ ስለሆነ አይደለም ይህን
የሚያደርገው፡፡ እህቱን ለማጥፋት ሲል ራሱን ከመጉዳት አይመለስም፡ ይሄ ደግሞ የለየለት ጥላቻ ነው፡፡ ወንድሟ ትንሽ አዕምሮው ሳይነካ አይቀርም፡
ትንሽ ማሰብ ፈለገች፡ ንጹህ አየር ለማግኘት ብላ በጭስ ከታፈነው ቡና ቤት ወጣች፡ ከቡና ቤቱ እንደወጣች ቀለል አላት፡፡ ከባህር የሚወጣው ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበላት፡፡ መንገዱን አቋረጠችና ወደ ወደቡ ሄደች፡
የሰማይ በራሪው ጀልባ ወደቡ ጥግ ተኮፍሷል፡ አይሮፕላኑ ከጠበቀችው
በላይ ግዙፍ ነው፡፡ የአይሮፕላኑን ነዳጅ የሚሞሉት ሰዎች ከሩቅ ሲታዩ ጉንዳን ያካክላሉ፡፡ ግዙፎቹ ሞተሮች በአይሮፕላኑ ላይ እምነት እንድትጥል አድርገዋታል፡፡ በዚህ አይሮፕላን ላይ ፍርሃት አይሰማኝም› ስትል አሰበች፡ በዚያች ሚጢጢ አይሮፕላን እንኳን ህይወቷን ሸጣ መጥታ የለም፡፡
አገሯ ስትደርስ ምንድነው የምታደርገው? ፒተር ይህን እቅዱን እንዲለውጥ ማሳመን አይቻልም: አሁን ካሳየው ባህሪ በስተጀርባ ለረጅም ዓመት አምቆ የያዘው ድብቅ ጥላቻ እንዳለ አውቃለች፡፡ ለወንድሟ አዘነችለት፡፡ ይህን ያህል ዓመት ከቅናት የተነሳ ጥላቻ በሆዱ ሲያስታምም ቆይቷል፡፡ እጇን ልትሰጥ አልፈለገችም፡፡ የተወላጅነት መብቷን ለማስከበር
‹ሌላ መንገድ ይኖር ይሆን?› ብላ አሰበች፡፡

#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
‹‹አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ግድ የለኝም፡፡ ጦርነት አውድማ ውስጥ ገብቼ ፋሺዝምን ከሀገሬ ለማባረር እዋጋለሁ›› አለች በልበ ሙሉነት፡ ፊቷ ላይ
የሚነበበው ገፅታ ለህይወት ግድ እንደሌላት ያሳያል፡ ሄሪ ይህን ሲያይ ጎበዝ ናት› አለ በሆዱ፡፡
‹‹የቆረጥሽ ትመስያለሽ››
‹‹በዚህ እምነቱ የተነሳ የስፔን ፋሺስቶችን ሊዋጋ ሄዶ አፈር በልቶ የቀረ ፍቅረኛ ነበረኝ፡፡ የእሱን አርማ አንስቼ አላማውን ዳር ለማድረስ እታገላለሁ››ደ አለች በወኔና በሀዘን፡
‹‹ትወጂው ነበር?»
በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች፡፡
አይኗ እንባ እንዳቀረረ ተመለከተና በሀዘኔታ ክንዷን ያዝ አደረጋት
‹‹አሁንም ትወጂዋለሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ምን ጊዜም ከልቤ አይጠፋም›› አለች የሹክሹክታ ያህል ‹‹ስሙ ኢያን ይባላል፡››
ሄሪ አሳዘነችው፡፡ ማርጋሬትን ደረቱ ውስጥ ወሽቆ ሊያፅናናት
ቢፈልግም በየት በኩል። ውስኪያቸውን እየጨለጡ ጋዜጣ የሚያነቡ በርበሬ
ፊት አባቷ ፊት ለፊት ተቀምጠዋል፡ እንደ ምንም እጁን ሰደደና አጇን ጨመቅ አደረገው፡፡ እሷም ለማፅናናት መሆኑ ገብቷት
ፈገግ አለች።
‹‹እራት ደርሷል ሚስተር ቫንዴርፖስት›› አለ አስተናጋጁ፡ ሄሪ አስራ
ሁለት ሰዓት ከምኔው እንደደረሰ ገርሞታል፡ ከማርጋሬት ጋር የጀመረውን
ጭውውት ማቋረጡ አሳዝኖታል፡፡ እሷም የእሱ ጭንቀት ገባትና ‹ብዙ
የምንጫወተው ነገር አለ›› አለች ‹‹ለሚቀጥሉት ሃያ አራት ሰዓታት አብረን
እንሆናለን››
‹‹ልክ ነሽ›› አለና ፈገግ አለ፡፡ እንደገና እጇን ዳበስ አደረገና ‹‹በኋላ
እንገናኝ›› አላት፡፡
ምስጢሩን በሙሉ የነገራት አጋሩ ሊያደርጋት ነው፡፡
ወደሚቀጥለው ክፍል ሲገባ ክፍሉ ከሳሎን ቤት ወደ መብል ቤትነት ተለውጦ ሲያይ ተገረመ እያንዳንዳቸው አራት ሰዎች የሚቀመጡባቸው
ሶስት ጠረጴዛዎች የተዘረጉ ሲሆን ሌሎች ሁለት ትንንሽ ጠረጴዛዎችም ይታያሉ፡፡ የእቃው አደራደር እንደ ምግብ ቤት ሲሆን ጠረጴዛዎቹ ጨርቅ
ለብሰዋል፡፡ በላያቸው ላይ የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ስምና ምልክት ያለባቸው ብርጭቆዎች፣ ሰሃኖችና ናፕኪኖች ተቀምጠዋል። የመብል ክፍሉ ግርግዳ የአለም ካርታ ተለጥፎበታል አስተናጋጁ ሄሪን አንድ ሱፍ የለበሰ አጠርና ደልደል ካለ ሰው አጠገብ ወስዶ አስቀመጠው: ሄሪ የሰውዬው አለባበስ አስቀናው፡ ሰውዬው ክራቫት ያደረገ ሲሆን ውድ በሆነ ማያያዣ ጌጥ ከሸሚዙ ጋር አያይዞታል፡ ሄሪ እራሱን አስተዋወቀ፡ ሰውዬውም እጁን ለሰላምታ ዘረጋና ‹ቶም ሉተር እባላለሁ›› አለ፡፡ እጁ ላይ ያለው የወርቅ አምባር ከክራቫት ማያያዣው ጋር ይሄዳል፡፡ ለውድ ጌጣጌጥ ገንዘቡን
መበተን የሚወድ ሰው ማለት ይሄ ነው፡፡
ሄሪ የታጠፈውን ናፕኪን ዘረጋ፡፡ ሉተር አነጋገሩ የአሜሪካዊ ነው።
‹‹ከየት ሀገር ነው የመጣኸው?›› ሲል ሄሪ ጠየቀው ሰውዬውን
‹‹ፕሮቪደንስ ሮድ አይላንድ፧ አንተስ?››
‹‹ፊላደልፊያ›› አለ ሄሪ፡ ፊላደልፊያ የት እንዳለ እንኳን አያውቅም፡፡
አሜሪካ ውስጥ ያልኖርኩበት ቦታ የለም፡፡ አባቴ የኢንሹራንስ ሰራተኛ
ነበር፡››
ሉተር አንገቱን ነቀነቀ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገም የሰውዬው ዝምተኛነት ለሄሪ ተስማምቶታል፡ ስለአኗኗሩ ሰው እንዲጠይቀው
አይፈልግም: በዝምታ ማለፍ ጥሩ ነው፡
ሁለት የአይሮፕላኑ ሰራተኞች በመጡና ራሳቸውን አስተዋወቁ፡ የበረራዐመሀንዲሱ ኤዲ ዲኪን ትከሻው የሰፋ፣ የደስ ደስ ያለው ፀጉረ ነጭ ሰው
ነው፡ ሁለተኛው ጃክ አሽፎርድ የሚባል ናቪጌተር ነው ፀጉረ ጥቁር ሲሆን
የለበሰው ዩኒፎርም ሄዶበታል።
ሰዎቹ እንደተቀመጡ በሉተርና በመሃንዲሱ መካከል የሆነ ጠብ እንዳለ
ሄሪ አስተዋለ።እራት ቀረበ፤ ሁለቱ የአይሮፕላን ሰራተኞች ኮካ ኮላ ሲመጣላቸው ሄሪ
ነጭ ቪኖ ቀረበለት፡ ቶምሉተር ማርቲኒ አዘዘ
ሄሪ እራት እየበላ ሳ
በአይሮፕላኑ መስኮት እያየ ስለማርጋሬትና ስፔን
ሄዶ ስለቀረው ቦይ ፍሬንዷ ያስባል፡፡ ስለእሱ አሁን ምን ያህል እንደምታስብ ማወቅ ፈለገ፡፡ ከእሷ እድሜ አንጻር አንድ አመት ትንሽ ጊዜ አይደለም፡፡
ጃክ አሽፎርድ ሄሪ በመስኮት እያየ መሆኑን ተገነዘበና ‹‹እስካሁን አየሩ
ጥሩ ስለሆነ እድለኞች ነን›› አለ፡
‹‹ሁልጊዜ እንዴት ነው አየሩ?›› ሲል ጠየቀ ሄሪ
‹‹አንዳንድ ጊዜ ከአየርላንድ እስከ ካናዳ በዝናብ የምንሄድበት ጊዜ አለ፡፡
‹‹አንዳንዴ ደግሞ በረዶና መብረቅ ያጋጥማል፡››
ሄሪ አንድ ጊዜ ያነበበውን አስታወሰና ‹‹በረዶ ከዘነበ ለአይሮፕላኑ አደገኛ አይደለም?›› ሲል ጠየቀ፡
‹‹በተቻለን መጠን ቀዝቃዛው የአየር ንብረት እንዳያገኘን እንጥራለን፡፡ለማንኛውም ተብሎ ግን አይሮፕላኑ ክንፎች ላይ የበረዶ ማቅለጫ ሸራ
ተደርጎለታል፡››
የመጪው የአየር ትንበያ ምን ያመለክታል?››
ጃክ ይህን መልስ ለመስጠት ሲጠራጠር አየና ስለአየሩ ባልጠየቅ ይሻል
ነበር›› ሲል አሰበ፡፡ ‹‹አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል››
አለ፡፡
‹‹ይህን ያህል መጥፎ ነው?›› ጠየቀ ሄሪ፡
‹‹ዶፍ ዝናቡ መሃል ከገባን መጥፎ ነው፡ ሆኖም እኛ ከዶፍ ዝናቡ ራቅ ብለን እንበራለን›› አለ በሰጠው መልስ ብዙም ባለመተማመን፡፡
ቶም ሉተርም ቀጠለና ‹በዶፍ ዝናብ ውስጥ መጓዝ ምን ችግር አለው ሲል ጠየቀ።
ጃክ በዝርዝር አልተናገረም፤ ነገር ግን የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ፣ ቶም ሉተርን ለማስፈራራት ሲል ወደ እሱ እያየ ‹‹ልክ ባልተገራ ፈረስ የሚጋልቡ ይመስል ያነጥራል›› አለ፡
ሉተር ኤዲ ያለውን ሲሰማ በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ኤዲ በተሳፋሪው
ፊት አፉ እንዳመጣ በመናገሩ ጃክ ገላመጠው:
ተሳፋሪዎቹ ሁለተኛ ዙር የእንቁራሪት መረቅ መጣላቸው:🤮
አሁን የሚያስተናግዱት ሁለቱ አስተናጋጆች ኒኪና ዴቪ ናቸው፡ ኒኪ ድብልብል ሲሆን ዴቪ ደግሞ ከአፍ የወደቀች ጥሬ ነው የሚያክለው፡፡
ሄሪ ሁለቱም ወንዳገረዶች ሳይሆኑ አይቀሩም› ሲል ገመተ፡ ታዲያ ቅልጥፍናው አስደስቶታል፡፡
ሄሪ በድብቅ እንደተከታተለው የበረራ መሀንዲሱ አዕምሮው በአንድ ነገር የተጠመደ ይመስላል፡፡
‹ሄሪ መሀንዲሱ ባህሪው አኩራፊ አይመስልም፡፡ ሲያዩት ተጫዋችና
ግልፅ ይመስላል› ሲል አሰበና እንዲናገር ለማበረታት ‹‹አንተ ምግብ በምትበላበት ጊዜ የበረራ ምህንድስናውን ስራ ማን ይሰራል?›› ሲል ጠየቀው
‹‹ረዳት የበረራ መሀንዲሱ ሚኪ ፊን ነው›› አለ፡ ‹‹በፈረቃ ነው የምንሰራው፡፡ ጃክና እኔ ከሳውዝ ሃምፕተን በረራ ከጀመርንበት ከቀኑ
ስምንት ሰዓት ጀምሮ ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ስለዚህ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት
ላይ እረፍት እናደርጋለን፡፡››
‹‹ካፒቴኑስ?›› ሲል ጠየቀ ቶም ሉተር ሀሳብ ገብቶት።
‹‹እንቅልፍ እንዳይዘው መድሃኒት ይውጣል፡ ከቻለ በተቀመጠበት ትንሽ ያንቀላፋል›› አለ ኤዲ፡ ‹‹ወደኋላ የማንመለስበት ሁኔታ ላይ ስንደርስ
ፓይለቱ ምን አልባት ረጅም እረፍት ያደርጋል፡››
‹‹ስለዚህ በሰማይ በምንበርበት ጊዜ ፓይለቱ ይተኛል ማለት ነው?››
ሲል ጠየቀ ሉተር ሳያስበው ጮክ ብሎ፡
‹‹አዎ›› አለ ኤዲ በፈገግታ:፡ ሉተር ፍርሃት ፍርሃት እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ ሄሪ ጨዋታው ሰላማዊ እንደሆነ በማሰብ ‹‹ወደኋላ
የማንመለስበት ሁኔታ ማለት ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀ፡፡

👍19
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
ማርጋሬት ደስ ደስ ብሏታል፡ ከእውነተኛ ሌባ ጋር መወዳጀቷን ማመን
እያቃታት ነው፡ አንድ ሰው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት አታምነውም፡ ነገር ግን
ሄሪ አንድ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ተከሶ ስላየችው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት እውነቱን መሆኑን አወቀች።
ከስርዓት ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ማለትም ወንጀለኞች ለህግና ለመንግስት የማይገዙ ሰዎች፣ ሴተኛ አዳሪዎችና በረንዳ አዳሪዎች ሁልጊዜ
ያስደንቋታል፡ እነሱ ነጻ ሰዎች ናቸው፡፡ በእርግጥ በህብረተሰቡ የተተፋ ሰው
ጥሩ ነው የሚል አመለካከት የላትም፡፡ ነገር ግን እንደ ሄሪ ያሉ ሰዎች አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ለማድረግ አይፈቅዱም፡ይህ ነጻነታቸው ነው ማርጋሬትን የሚያስቀናት፡፡ አንዳንዴ የወታደር ልብስ ለብሶ ጠመንጃውን ታጥቆ በየመንደሩ እየዞረ ህዝብ የሚዘርፍ ሽፍታ መሆን ያምራታል እንደዚህ አይነት ሰዎች ገጥመዋት አያውቁም: አንድ ጊዜ በለንደን ጎዳናዎች
ላይ ሴተኛ አዳሪ መስላቸው ሊደፍሯት የመጡትን ሰዎች ባታይ የምታውቅበት ሁኔታ አልነበረም፡፡
ሄሪ እሷ የምትመኘውን ነገር ሁሉ ያሟላ ሆኖ ነው ያገኘችው የፈለገውን ማድረግ የሚችል ሰው! ዛሬ ጧት አሜሪካ ለመሄድ ወሰነና ዛሬ ከሰዓት በኋላ አይሮፕላኑ ላይ ተገኘ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ መደነስና ቀኑን በሙሉ መጋደም ከፈለገ ያደርገዋል፡ ከልካይ የለበትም፡፡ መብላት የፈለገውን ይበላል፧ መጠጣት የፈለገውን ይጠጣል፡ ገንዘብ ከፈለገ ገንዘባቸውን መጣያ
ካጡ ባለጸጎች ይሰርቃል፡ እሱ ነጻ የሆነ ሰው ነው፡
ስለሄሪ በይበልጥ ማወቅ ፈለገች፡ ከእሱ ጋር ራት ሳትበላ ያሳለፈቻቸው
ቀናት ቁጭት ውስጥ ጣሏት፡፡
ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ከኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ቀጥሎ ተቀምጠዋል እነዚህ ሰዎች ይሁዲ ስለሆኑ ነው ገና ወደ መብል ክፍሉ እንደገቡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ክፉኛ የገላመጧቸው፡አብረዋቸው
የተቀመጡት ኦሊስ ፊልድና ፍራንክ ጎርደን ናቸው፡፡ ፍራንክ ጎርደን በዕድሜ
hሄሪ ብዙም የማይበልጥ መልከ መልካም ወጣት ነው፡፡ ኦሊስ ፊልድ ደግሞ
ኑሮ የጠመመበት የመሰለ በዕድሜ ገፋ ያለ ራሰ በራ ሰው ነው፡፡
ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ሁሉም ሰው ከአይሮፕላኑ ወጥቶ
በየፊናው ሲበታተን እነዚህ ሁለት ሰዎች አይሮፕላኑ ውስጥ በመቅረታቸው
የለው ሁሉ መነጋገሪያ ሆነው ነበር፡፡
ሶስተኛው የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ሉሉ ቤልና ሾርባው ጨው የበዛበት ነው እያሉ ሲያማርሩ የዋሉት ልዕልት ላቪኒያ ተቀምጠዋል ከነሱ ጋር ፎየንስ ላይ የተሳፈሩት ሚስተር ላቭሴይና ሚስስ ሌኔሃን ተቀምጠዋል። ወሬ መለቃቀም የሚወደው ፔርሲ እነዚህ ሰዎች ባልና ሚስት ባይሆኑም የሙሽሮቹን ክፍል እንደሚጋሩ ወሬ ለጠማቸው አውርቷል
ባልና ሚስት ያልሆኑ ሰዎች ይህን ክፍል እንዲይዙ ፓን አሜሪካን አየር
መንገድ እንዴት እንደፈቀደላቸው ማርጋሬት ገርሟታል። አየር መንገዱ ብዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ መሄድ ስለፈለጉ ህጉን መጋፋት የግድ ሆኖበታል፡
ፔርሲ ጥቁር የይሁዲዎች ኮፊያ አናቱ ላይ ደፍቷል፡ ማርጋሬት ይህን ስታይ በሳቅ ተንፈቀፈቀች፡፡ ከየት ነው ያመጣው! አባቱ ግን ‹‹ጅል!›› ብለው ተሳድበው ኮፍያውን መንጭቀው ወረወሩት፡፡
ሌዲ ኦክሰንፎርድ ኤልሳቤት ተለይታቸው ከሄደች ወዲህ ለመጀመሪያ
ጊዜ ፊታቸው በመጠኑ ፈካ ብሏል፡፡
ሌዲ ኦክሰንፎርድ ‹‹የራት ሰዓታችን ገና ነው›› አሉ፡፡
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ ‹‹አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል እኮ›› አሉ፡፡
‹‹ለምንድነው ታዲያ ያልጨለመው?››
‹‹እንግሊዝ አገር አሁን ጨለማ ነው፡ አሁን ግን ከአየርላንድ ባህር
ጠረፍ ሶስት መቶ ማይል ርቀት ላይ ነው የምንገኘው ጸሃይዋን እያሳደድን
ነው›› አለ ፔርሲ፡፡
‹‹መቼም መጨለሙ አይቀርም››
‹‹ምናልባት ሶስት ሰዓት ላይ የሚጨልም ይመስለኛል›› አለ ፔርሲ
‹‹ጥሩ›› አሉ እናት፡፡
እንደማይጨልም
‹‹ጸሃይዋን ተከትለን በፍጥነት ብንጓዝ
እንደማይጨልም ታውቃላችሁ? አለ ፔርሲ፡፡
‹‹እንደዚህ አይነት ፍጥነት ያለው አይሮፕላን የሰው ልጅ ይሰራል ብዬ አልገምትም›› አሉ አባት ከኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል ግብዝነት፡
ቦትውድ ካናዳ ለመድረስ አስራ ስድስት ሰዓት ተኩል ይፈጃል›› አለ ፔርሲ ‹‹እዚያ በግሪንዊች ሰዓት አቆጣጠር ከጧቱ ሶስት ሰአት እንደርሳለን››
‹‹ካናዳ ስንት ሰዓት ይሆናል ማለት ነው?,,
‹‹የኒውፋንድላንድ ካናዳ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች የሰዓት አቆጣጠር ሶስት ሰዓት ወደ ኋላ ነው›› አለ ፔርሲ፡፡
እናት የፔርሲን ችሎታ አጤኑና ‹‹ወንዶች የቴክኒክ እውቀት ላይ ጎበዞች ናቸው›› አሉ፡፡
ማርጋሬት በእናቷ አነጋገር ተናደደች፡፡ እናት የቴክኒክ ነገሮች ሴቶች አይገባቸውም ብለው ያምናሉ፡፡ ‹‹ወንዶች ሴቶች ጎበዝ ሲሆኑ አይወዱም››
ብለዋታል ብዙ ጊዜ፡ በዚህ ጉዳይ ማርጋሬት ከእናቷ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት ባትፈልግም እሷ ግን አታምንበትም፡ ይህን የሚቀበሉ ወንዶች ደደቦች ናቸው ብላ ነው የምትገምተው ጎበዝ ወንድ ጎበዝ ሴት ይወዳል፡
አጠገባቸው ካለው ጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጡት ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ክርክር ገጥመዋል አጠገባቸው ያሉት የጠረጴዛ ተጋሪዎች
ባይገባቸውም በጸጥታ ያዳምጣሉ: ሁለቱ ሰዎች አይሮፕላኑ ላይ ከወጡ
ጀምሮ ጥልቅ ውይይት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ በዓለም ከታወቀ ሳይንቲስት
ጋር እንደዚህ ያለውን ውይይት የምታደርጉ ከሆነ ውይይቱ ጥብቅ መሆኑ
አያስደንቅም፡፡ በክርክራቸው ውስጥ ፍልስጤምንና እስራኤልን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡ ማርጋሬት የውይይት ርዕሳቸውን ስትሰማ
‹‹አባባ ምን ይል
ይሆን?›› እያለች አስሬ ታያቸዋለች፡፡ እሳቸውም የሁለቱ ሰዎች ውይይት
አልጥም ብሏቸው አኩርፈዋል፡፡ አባቷ ነገር እንዳይጭሩ ርዕስ ለማስለወጥ
‹‹አይሮፕላኑ የሚጓዘው ኃይለኛ ነፋስ በቀላቀለ ዝናብ ውስጥ ነው›› አለች
‹‹እንዴት አወቅሽ?›› አለ ፔርሲ አነጋገሩ ቅናት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በበረራ መረጃ ከማርጋሬት ይልቅ እሱ ነው ኤክስፐርቱ።
‹‹ሄሪ ነገረኝ››
‹‹እሱ እንዴት ያውቃል?››
‹‹እሱ ዛሬ ራት የበላው ከበረራ መሃንዲሱና ከናቪጌተሩ ጋር ነው፡››
ማርጋሬት ዝናቡ ችግር ይፈጥራል ብላ አልገመተችም፡፡ በእርግጥ
በዝናብ ውስጥ መጓዝ ምቾት ቢነሳም ለክፉ አይሰጥም፡፡
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ብርጭቋቸው ውስጥ የቀረውን ቪኖ አጋቡና ሌላ
እንዲጨመርላቸው ቆጣ ብለው ጠየቁ፡፡ ዝናቡ ችግር ያመጣል ብለው ፈሩ
እንዴ? ከተለመደው በላይ እየጠጡ መሆናቸውን ማርጋሬት ተገንዝባለች።
ፊታቸው ከመጠጥ ብዛት ፍም መስሏል: ዓይናቸው ፈጧል፡ ምናልባትም
ነርቭ ሆነዋል፡፡በኤልሳቤት መኮብለል ክፉኛ ተበሳጭተዋል
እናትም ማርጋሬትን ‹‹ሚስተር መምበሪን አጫውቺው›› አሏት፡
ማርጋሬት የእናቷ አባባል ገርሟት ‹‹ለምን?›› ስትል ጠየቀች፡ ሲያዩት
ሰው እንዲያናግረው የሚፈልግ አይመስልም፡
‹‹ምናልባትም አይናፋር ሳይሆን አይቀርም›› አሉ እናት፡፡
እማማ ከመቼ ወዲህ ነው ለአይናፋሮች መቆርቆር የጀመረችው?የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ‹‹ግን ምን ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀች ማርጋሬት።

👍13🔥1