አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሰባት

...በሙዚቃው ደነስኩ.. ውልቅልቅ እስክል ውስኪውን አንጠፍጥፌ ጠጣሁ"..አዎ አውቃኛለች... ፈፅሞ አልረሳችኝም...ከሁሉም ያስደሰተኝ ደግሞ ‹‹ቀናህ!!!›› የምትለዋ ቃል ነች...ምክንያቱም ቅናት እነጠቃለሁ ብሎ ከመፍራት ጋር ወይም ከመሠሠት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ስሜት ነው።ፍርሀትም ስስትም ምንጫቸው ፍቅር ነው...እርግጠኝነት ከጎደለው ፍቅር።እና ታፈቅረኛለህ እያለችኝ ነው?ግን እንዳዛ ስላሰበች ለምንድነው እንደዚህ የፈነጠዝኩት? የእውነት እያፈቀርኳት ይሆን እንዴ ? እንዴ ከነጠላ ስሞ ሌላ ስለእሷ ምንም የማላውቃትን ሴት እንዴት ላፈቅራት እችላለሁ? ግን እኮ ፍቅር የኋላ ታሪክን አጥንቶ የወደፊት መድረሻን ገምቶ አሁን የቋሙበትን ድልዳል በሚዛን መዝኖ የሚገባበት  የምክንያትና ውጤት ቁርኝት ማሳያ አይደለም..?ፍቅር ጨርቁን እንደጣለ ዕብድ ነገረ ስራው ቅፅበታዊና ተአምራዊ ነው።ስለዚህ ሳላቃትም በፍቅሯ ብወድቅ የሚደንቅ አይደለም!ግን ዕድሜዋ ጉዳይስ? ቢያንስ 10 አመት ትበልጠኛለች? እርግጥ በዕድሜ ሰላሳም ሀምሳም የምትበልጠውን እንስት ማፍቀር የተለመደ ነው?ቢሆንም ግን ቢገለበጥ ነበር የሚያምረው ..እኔ 10 አመት ብበልጣት።

ወየጉድ አሁንኮ ነገረ ስራዬን ላየ የመጀመሪያ የፍቅር አይነጥላዬን ገና እየገለጥኩ ያለው  ጀማሪ አፍቃሪ ነው የምመስለው ፤ግን እኔ ቢያንስ አምስት አጫጭር ጣፍጭ ለወግ የሚበቁ እና አንድ ረጅም የተወሳሰበ  ልቤንም ቅስሜንም  አብሮ እንቅሽቅሽ አድርጎ የሠበረ.. በአለንጋ ተደጋግሞ በመገረፍ የተነሳ ትላልቅ ተጠላላፊ ሰንበር እንደተጋደመበት ጀርባ የእኔም ልብ በዛ ፍቅር ምክንያት ዙሪያ ጥምጥም የዞረበት ጠባሳ የተጋደመበት ሆኗል...
"ያ ፍቅር ህይወትን አስተምሮኛል ?ያ ፍቅር  ደስታን አሳይቶኛል...?ያ ፍቅር ዘመዶቼን አሳጥቶ የከተማ ስደተኛና ምፅተኛ  አድርጎኛል...ያ ፍቅር በራስ መታመኔን እንቅሽቅሽ አድርጎ  የህይወት መስመሬን ከላይ ወደታች ገለባብጦታል…ያ ፍቅር ዛሬ ቢቋረጥም ግን ትዝታ ብቻ ሆኖ የቀረ እንደይመስላችሁ፡፡ ዛሬም ጣጣው እያደነኝ ነው...፡፡

እስከህይወቴ ፍፃሜ እንደተጣባኝ የሚዘልቅ ይመስለኛል። ...ይሄው ስድስት አመት ሞላኝ ባዶ ሆኜ መኖር ከጀመርኩ ...እና አሁን የማፍቀር ስሜት ሲሰማኝ የተገረምኩት ለዛ ነው።እውነት እርቃን ገላዋን ስላሳየችኝ ...ተዳፍኖ የኖረው የወሲብ ስሜቴ ስለተወጣጠረ ነው የተምታታብኝ። ግን አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከለል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል፤ ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን  ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ...የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር  እስከ እርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች ስለሆን ይሆናል።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል..ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር ከቃላት ልውውጥ እና ከአይን መሠራረቅ  ላያልፍ ይችላል፤ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቋረጥ ይችላል..እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ አለ?።

ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ ስላለቀ ነው ብለን መደምደም አንችልም... አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው  ጉዞቸውን  በተለያየ ጎዳና  ሊቀጥሉ የሚገደዱባቸው አያሌ አጋጣሚዎች አሉ። ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።

ወይ ጉድ ..በዚህች እንግዳ ሴት የተነሳ የፍቅር ኤክሰፐርት መሆን ዳዳኝ እኮ….ጠርሙሶ ውስጥ ያለችውን መጠጥ እያወዛወዝኩ ከሆቴል ወጣሁና በእኩለ ለሊት ወደቤቴ ገባሁ፡፡በፀጥታ አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ….፡፡ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰደኝ፡፡
ጥዋት
..ከእንቅልፌ ባንኜ አይኖቼን ብገልጥም ቀልጠፍ ብዬ ከአልጋዬ መውረድ አልቻልኩም። ብነሳም ምን አልባት ምሳዬን ሰርቼ ከመብላት ውጭ ሌላ የምሄድበት ቦታ የለም ።ምሳ ደግሞ አላሰኘኝም፡፡ ምን አልባት ቁርሴን ከጋሽ ሙሉአለም የተሠጠኝን ቋንጣ ፈርፍር በደንብ ስለበላሁ ይሆናል። ተንጠራራሁና ከኮመዲኖዬ ላይ rich Dad poor Dad የሚለውን መፅሀፍ አነሳሁና ማንበብ ጀመርኩ .. አንድንም አባት የሌለው ሰው ሁለት አባቶች ያሉት ሰው የፃፈውን መፅሀፍ ለማንበብ መቋመጡ የሚገርም ነው። ብቻ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሁለት ገፅ ሳላነብ ስልኬ ጠራ አነሳሁና አየሁት..፡፡

የማላውቀው ቁጥር ነው ፡፡ላንሳው ልተወው ተወዛገብኩ።በስተመጨረሻ አነሳሁት

‹‹ሄሎ»

"ሄ...ሎ"ጥፍጥ ያለ የህፃን ድምፅ...ደነገጥኩ፡፡

‹‹ሄሎ..ሄሎ ..ማን ልበል?"

«ተአምል...ነኝ»

"ተአምር"የተኛሁበት የእንጨት አልጋ ከስር እርብራብ ተቀንጥሶ ይዞኝ ወደታች እየሰመጠ መሠለኝ...፡፡ስልክ ባልያዘው ቀኝ እጄ ፍራሹን ጨምድጄ ያዝኩ....፡፡እለተ መፅአት የፊታችን እሁድ መሆኑን ተረጋገጠ የሚል አዎጅን አስከትሎ የነጋሪት ጉሰማ ብሰማ ራሱ እንዲህ ሰማይ ምድሩ አይዞርብኝ፡፡

ልጅቷ ኩልትፍትፍ ባለ ድምፅ ንግግሯን ቀጠለች
"አዎ ተአምል...ል..ጅህ"
ይሄ መቼስ ተአምር ነው....፡፡ ተአምር አሁን ስምንት አመቷ ነው።በአካል ከተያየን 6 አመት አልፎናል።ማለቴ ቀጥታ በአካል ያየዋት አቅፌ የሳምኮት :ለጥቂት ቀናትም ቢሆን ስታለቅስ ያባበልኮት የዛሬ ስድስት አመት ገና ክፉና ደጉን በቅጡ መለየት ባልቻለችበት ጊዜ ነው። ለዛውም እንደአባትና እንደልጅ እኮ አይደለም እንደ እህቴ ልጅ...እንደአጎቷ ሆኜ..፡፡ለምን እንደዛ ሆነ የእውነትም አጎቷ ስለሆንኩ፤ እንደዛም ስለመሰለኝ...፡፡ከዛ ወላጆቾ የውጭ ፕሮሰስ ጀምረው ስለነበር  ተአምር ዲ.ኤን. ኤ ምርመራ ማድረግ ግዴታ ሆነ …ተመረመረች...ውጤቱ  ለቤተሠብ በሀይለኛ መብረቅ የመመታት ያህል ድብ እዳና አስደንጋጭ ነበር... ልጅቱ የእህቴ ባል አይደለችም?
‹‹እንዴት ሆኗ...?"የህግ ሚስቱ እኮ ነች…፡፡››
"በተክሊል ነው እኮ የተጋብት"ብዙ ብዙ ተባለ... እኔ የምገባበት ጠፋኝ..ጠጋ አልኩና
በወቅቱ"ምስር ይሄ ነገር እንዴት እንደዚህ ሆነ ?››ብዬ ጠየቅኳት።
"አንተም እንደሌላው እንዴት ሆነ ብለህ ትጠይቀኛለህ?"
‹‹ምን ማለት ነው ?እንዴት አልጠይቅሽም?"
‹‹ያደረከውን ታውቃለህ ብዬ ነዋ ?››
👍56😁2😱1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
#ክፍል_ስምንት
////

"ሠላም ነሽ ታአምር?"

"ሠላም ነኝ"

" አባዬ...ድምፅህን ስለሠማው ደስ ብሎኛል"

"እኔም ደስ ብሎኛል የእኔ ጣፋጭ...ግን ስልኬን እንዴት አገኘሽ?"

"የጓደኛዬ የቢጡ አባት ነው አባቴን ባገኝ ደስ ይለኛል እያልኩ ሳለቅስ አሳዘንኩትና ..ከፌስብክ ላይ ፈልጎ ባንተ ስም የሚመሳሰል ሶስት ቁጥር ሰጠኝና …ሞክሬ …ሞክሬ..  ከዛ አገኘውህ...እናም ደስ አለኝ"

"ውዴ..እስከዛሬ ፈልጌ ስላላገኘውሽ በጣም ይቅርታ...እቴቴን ስላስቀየምኳት ፈርቼ እኮ ነው"

ዕድሜ ልኬን ከብዙ ሰዎች ጋር በክፉም በደጉም ብዙ ንግግር ተነጋግሬያለሁ... እንደዛሬው ግን የምይዘው የምጨብጠው ጠፍቶኝ አያውቅም...ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፊት ብቀርብ እራሱ እንዲህ አልርበተበትም።

"አባዬ"
አልተቀየምኩህም..እቴቴም ደግሞ ሰው ሳያያት ክፍሏ ውስጥ ትደበቅና ያንተን ፎቶ እና የእናትህን ፎቶ እያየች "የእህቴን አደራ በላሁ›› እያለች ታለቅሳለች ..፡፡

"እውነትሽን ነው..?"

"አዎ አባዬ እውነቴን ነው"

""ታአምሬ"

"ወዬ አባዬ"

"ስልኩ..ማለት የደወልሽልኝ በማን ስልክ ነው?"

"ስልኩ የራሴ ነው...እማዬ ከአሜሪካ ስትደውል በራሴ ስልክ እንዳናግራት ልካልኝ ነው"

"እና በዚህ ብደውል አገኝሻለሁ?"

"አዎ ግን..ማለቴ አንተን እንዳገኘሁህ እቴቴ ስለማታውቅ ፈርቼ ነው"

"ችግር የለም"

ሲመችሽ..እንዳወራሽ ስትፈልጊ ሚስኮል አድርጊልኝ"

"እሺ አባዬ"

"ቻው...እወድሀለሁ"

"እኔም በጣም ወድሻለሁ..ቻው"ስልኩ ተዘጋ፡፡

ስልኩን ከዘጋሁ በኃላ እንኳን እንባዬንም ስሜቴንም መቆጣጠር አልቻልኩም.፡፡ አልጋውን ለቅቄ በመውረድ ቤት ውስጥ ከላይ ወደ ታች እየተመላለስኩ   ወለሉ ላይ የተዝረከረከኩትን ዕቃዎች  እየረገጥኩ ዘለልኩ ..፡፡በቃ እብድ ነው የሆንኩት ። የማልረባ ነኝ...፡፡እኔ ሰው አይደለሁም፡፡መኖር ፈፅሞ አይገባኝም…

ከብዙ ቆይታና  መታገስ በኋላ ጋሽ ሙሉአለም ድምፅ አውጥተው ተናገሩ ...፡፡ ውስጤ መተራመሱ  ብሶ ቤቱን በማተራመሴ እሳቸውንም እየረበሸኩ መሆኑን እስከአሁን ልብ አላልኩም ነበር።

"ልጄ ምን ገጠመህ?"

‹‹አያቴ ጉድ ሆኜሎታለሁ? ..እኔ እኮ ሰው አይደለሁም?

‹‹ሠው አይደለሁም ስትል?

"በስህተት እና  ሀጥያት የተጨማለቅኩ እርኩስ ነኝ።

"እንደዛማ ከሆነማ እንደውም ኦርጅናሌ ሰው ነህ...››

‹‹አያቴ ትክክል ኖት ..ግን ይሄን ታሪክ ብነግሮት  ቀጥታ ይጠሉኛል...ዛሬውኑ ነው ቤቱን ለቀህ ውጣልኝ የሚሉኝ "

"ይበልጥ አጓጓኸኝ..‹.ምን ሰራው ቢለኝ ነው ይሄንን ልጅ የምጠላው?›እያልኩ ውስጤን እየጠየቅኩ ነው?...እስቲ ንገረኝና የትዕግስቴንና ይቅር የማለት ችሎታዬን  ልክ ልፈትሽበት።››

"ልጄ ደወለችልኝ"

"ልጄ ..?.›

‹‹አዩ አያቴ ገና ከመጀመሪያው ደነገጡ አይደል?"

"ሂድ ከዚህ…. ቀላማጅ፡፡ እኔ አልደነገጥኩም...ይልቅ ቅድምአያት ስላደረከኝ ተደስቼ ነው"

‹‹ይሁን እሺ….ልጅቷን የወለድኩት ካሳደገችኝ ከአክስቴ ልጅ መሆኑን ስነግሮትስ ምን ይሰማዎታል....? 40 ለሚሆን ደቂቃ ከመጀመሪያው አንስቼ አወራሁላቸው...በፅሞና አዳመጡኝ።

"የማልረባ ሰው ነኝ አይደል?"እንዲጮሁብኝ …እንዲረግሙኝ ፈልጌለሁ፡፡

.እሳቸው ግን ለስለስ ብለው ሀዘኔታ ባጠቃው አነጋገር"የማትረባም ብትሆንም ልጄ ያው ሰው ነህ… ዋናው እሱ ነው።ሰው ደግሞ በማንኛውም ጊዜና አጋጣሚ አውቆም ሆነ ሳያውቅ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ስህተት ይሰራል!ምክንያቱም ሰው እንደዛ ስለሆነ?ልዩነቱ አንዳንድ የሰራውን ስህተት ለመሸፈን ሌላ ስህተት ሲጨምር አጠቃላይ ሁኔታውን ጭምልቅልቅ አድርጎ እስከወዲያኛው ያበላሸዋል..፡፡ሌላው ደግሞ ስህተቱን በማረምና ያስከፋቸውን ሰዎች በመካስ ቀሪ ህይወቱን ያስተካክላል..፡፡.ደግሞ ያንተ የሚገርም ነው..፡፡ልጅ አለችህ..ልጅቷ ደግሞ ስህተት ልትሆን አትችልም..፡፡.እሷ ንፁህ እውነት ነች...፡፡ስህተቱ እሷ የተገኘችበት መንገድ ነው...፡፡እሱም ቢሆን አንዴ የተዘረጋ መንገድ ነው... በመንገድ ዙሪያ ያለውን ገደል ማስተካከል  ነው የምትችለው፡፡ መንገድን ለሁለት በመክፈል የለያዩት ገደሎች ድልድይ መስራት ነው የምትችለው፤ድልድዩ ደግሞ በይቅርታ ብረትና በፍቅር አርማታ ነው የሚገነባው... ፡፡

‹‹እንደሚሉት ቀላል አይደለም››

‹‹አትሞኝ ልጄ ፤የሰው ልጅ ከባባድ ነገሮችን ለመስራት ብዙም አይቸግረውም …ብዙ ጊዜ እንዝላል የሚሆነው ጥቃቅን ነገሮችን ለመስራት ነው፡፡ያው ዞሮ ዞሮ ጥቃቅን ነገሮች ተደምረው ነው ከባድ ችግሮችን የሚፈጥሩት ፡፡አሁን የነገርከኝን ታሪክ ስትሰራ በአንድ ቅፅበትና በአንድ ቀን አይደለም..ቀስ በቀስ፣አንድን በአንዱ ላይ እየደረብክ….በአመታት ውስጥ ነው የሆነው፡፡ለማጥፋት እንደዛ ከሆነ ያንን የጠፋውንም ለማደስ እንደዛው ቀስ በቀስ ምን አልባት የአራት እና በአምስት አመታት ጥረትና ልፋት ይጠይቅ ይሆናል..ግን በየእለቱ የምትችለውን ስራ.››

‹‹እንዴት አድርጌ አያቴ?››

‹‹ይው እኮ አስበህበትም ባይሆን ዛሬ ጀመርክ፡፡››

‹‹አልገባኝም፡፡››

‹‹ያው ከልጅህ ጋር አወራህ፣ድምፆን ሰማህ፤ምን ያህል አንተን እየናፈቀች እንደሆነ እና በአንተም ምንም ቅሬታ እንደሌላት ከአንደበቷ አረጋገጥክ፡፡››

‹‹አዎ አያቴ እሱን እንኳን እውነቶትን ነው፡፡››

‹‹አዎ እውነቴን ነው፤ አሁን ማድረግ ያለብህ ከጭንቀትና ትካዜ እራስህን ሙሉ በሙሉ አላቅና ከልጅህ ጋር ያለህን ግንኙነት በጥበብ በጣም ሳታግለበልበው ፤በጣም ሳታደፋነው በሚገባው ልክ  ይዘህ አስቀጥለው››

‹‹ማግለብለብ ማለት?››

‹‹ለምሳሌ የሚቀጥለው እሁድ ብር ብለህ ደብረብርሀን ሄደህ ላግኝሽ ብትላት ቤተሰቦቾ ሳይዛጁበት ይሰሙና ልጃችንን ይዞብን ሊጠፋ ነው ብለው ፈፅሞ እንዳታያትና እንዳታናግራት በሊያደርጉ ይችላሉ.. ወይም እናቷ ጋ አሜሪክ ሊልኳት ይችላሉ….ስለዚህ መጀመሪያ በስልክ ግንኙነትህን በደንብ አጠንክር..ስለቤተሰቦችህ አሁናዊ ሁኔታ ቀስ በቀስ ከልጅህ እየጠየቅክ ተረዳ..፡፡ታዲያ ስትጠይቃት በጥበብ ማለቴ ድንገት በወሬ በወሬ ትዝ ብሎህ እንዳነሳህ እያስመሰልክ መሆን አለበት..፡፡የዛሬ ልጆች ቀላሎች አይደሉም…..እሷን ስለዘመዶችህ መረጃ ለማግኘት እየተጠቀምክባት እንደሆነ ከተሰማት ልትቀየምህ ትችላለች፡፡ከዛ አጠቃላይ ሁኔታውን ከተረዳ በኃላ ምን አይነት እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብህ ትወስናለህ…፡፡ችግሮችሀን በደረጃ ከፋፍላቸው…ከዛ እያንዳንዱን በተናጠል ስታየው  መፍትሄ ለማበጀት ያን ያህል ከባድ አይደለም…..፡፡

ለምሳሌ የልጅህን በአካል ማግኘት፤ከልጅህ እናት መታረቅ፤የአክስትህን ልጆች ይቅርታ መጠየቅ፤ የአክስትህን ባል ይቅር እንዲልህ መማፀን፤ የእራስህን ህይወት ለልጅህ በሚመጥን መልኩ ማስተካከል፡ እነዚህን ሁሉ ኮተት ችግሮች በአንድ ኩንታል ውስጥ ጠቅጥቀህ ካየሀቸው  ዘላለም በጫንቃህ ተሸክመህ ስታላዝን ትኖራለህ እንጂ መቼም አትፈታቸውም፤ግን እያንዳንዱን በፔስታል ለየብቻ አድርገህ ያዛቸው ቅደም ተከተል ስትሰጣቸው በአንድ ጊዜ አንዱ ፔስታል ብቻ ተሸክመህ መዞር ቀላል ስለሆነ ሳትጨናነቅ በተወሰነ ጥረትና መስዋዕትነት ትፈታዋለህ፡፡ እሱን መፍታትህ ለሁለተኛው ፔስታል ውስጥ ላለው ችግርህ መፍቻ መንደርደሪያ ይሆናል.እንደዛ ነው ልጄ››
👍711
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ዘጠኝ

ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው፡፡የምሰራበት ሆቴል ቤርጎ ይዛለች፡፡ስራ እንደጨረስክ ና ብላኝ ስለነበረ ስራዬን ጨርሼ ወደእሷ ለመሄድ እየተዘጋጀው ነው፡፡ስደርስ በረንዳ ላይ ባለ ወንበር ላይ ኩርምት ብላ ቁጭ ብላለች አይኖቾን ሰማይ ላይ ሰክታ ፈዛለች፡፡ከጎኗ ቁጭ አልኩና‹‹ጨረቃን እያየኋት ነው እንዳትይኝ?››አልኳት፡፡

‹‹አልኩህ››

‹‹እራስሽን ምን አሳየሽ?››

‹‹ማለት? ››

‹‹ያው እንቺም ጨረቃ ነሽ ብዬ ነዋ...››

‹‹ጨረቃ ነሽ ስትል በቀጥታ ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››

"ከዚህ ንግግሬ ምን የማይገባ ነገር አገኘሽበት... ጨረቃ ነሽ ስል አደንዛዥ የሆነ ውበት ባለቤት ነሽ ማለቴ ነዋ።"

‹‹ጨረቃ እውነትም እንደምትለው አደንዛዥ ውበት አላት ?››

" የላትም እንዴ?"

‹‹እኔ ምን አውቄ እንደዛ ስላልከኝ ነው..ይህቺን አባባል ሁሉም ሰው ይጠቀማታል …ግን በትክክል በምሽት ስራዬ ብሎ የቤቱን በራፍ ከፍቶ በረንዳ ላይ ወጥቶ አንገቱን ወደ ሰማይ አንጋጦ፤ አይኖቹን ጨረቃ ላይ ተክሎ፤ ውበቷን ያስተዋለ ድምቀቷን ያጣጣመ..  ከመቶ ሺ አንድ ሠው ይገኝ ይመስልኸል...ግን ዝም ብሎ ስለሚባል ብቻ ትክክል ይሁን አይሁን ሳያውቅ ሁሉም ይደሰኩራል....

"እና ማጠቃለያሽ ጨረቃ ቆንጆ አይደለችም ነው?›

"አይ ነችምም አይደለችምም..ለምሳሌ እኔ ቆንጆ ነኝ?"

"ግጥም አድርጎ ...በጣም ውብ ነሽ"

"ከዚህ በፊት ሁለት ሰዎች ቀጥታ አሁን አንተ እንደቆምከው ፊቴ ቆመው ምንሽም የማያምር አስቀያሚ ሴት ነሽ ብለውኝ ያውቃሉ።እንደውም እንደዛ አይደለም.አስቀያሚ ወንዳወንድ ነገር ነሽ ነው ያሉኝ፡፡››

"እና ማንኛችንን አመንሽ?"

"ሁለታችሁኑም"

"ሁለታችንንማ ልታምኚ አትችይም ..አንቺ ወይ ቆንጆ ወይ አስቀያማሚ ነሽ.."

"አይ እንደየሁኔታው ቆንጆም አስቀያሚም ልሆን እችላለሁ...ውበት እንደየተመልካቹ ነው በሚለው ንግግር አምናለሁ...ለዚህ ነው ቆንጇ ነሽ ሲሉኝ ብዙ የማልፈነጥዘው አሰቀያሚም ሲሉኝ አንገቴን የማልደፋው።"

‹‹እና ማየቴን ላቁም?››

‹‹እንዳሰኘህ…ግን ጨረቃ በትከክልም  ምን ግዜ ውብ እንደምትሆን ታውቃለህ?››
‹‹አላውቅም ንገሪኝ ››
ጦር ሜዳ ፊት ለፊት ግምባር ላይ እያለህ የሆነ ግዳጅ  ተሰጥቶህ ከጓደኞችህ ጋር ድቅድቅ ባለ ጨለማ እየተጓዝክ መንገድ ጠፍቶህ ከጠላት ምሽግ ሰተት ብዬ ገባሁ ወይስ የጠላት ደጋፊ ከሆኑ ህብረተሰብ እጅ ወደቅኩ እያልክ አቅጣጫህን እንዴት እደምታስተካክል ግራ ገብቶህ እያለ ድንገት ብልጭ ብላ ስትወጣ…ከዛ እየደመቀች ስትሄድ….በቃ ውብ መሆኗ የሚገባህ የዛን ጊዜ ነው፡፡ምክንያም ህይወትህ የምታድንበት ጭላንጭል እድል ሰጥታሀለችና፡፡
‹‹ወይም ደግሞ›› ብዬ እኔ ቀጠልኩላት
‹‹ወይ ደግሞ.. በጣም የምትወጃትን ማለቴ የምታፈቅሪያት ልጅ  አባትዬው ከእቅፍሽ ነጥቀው ለሌላ ሊድሩብሽ መሆኑን ስትሰሚ እሷን በጠፍ ጨረቃ ከቤት አስኮብልለሻት በየጫካው ይዘሻት ስትጠፊ በዛን አስደሳችና ጭንቀት በተቀላቀለበት ወሳኝ ሰዓት ለመንገድሽ ብርሀን ሆና ከፊት ለፊትሽ ቦግ ስትል .. በዛን በክፉና በደስታ ቀን የመንገድሽ አጃቢና መሪ ብሎም  ለፍቅርሽም ድምቀት ስትሆን…አዎ የዛን ቀን ነው ጨረቃ ከውብም ውብ መሆኗን በደንብ የሚገባሽ››
‹‹አየህ ጨረቃን እንደየልምዳችን ነው ለውበቷ ትርጉም የሰጠነው..››
‹‹እንደልምዳችን  ማለት?አንቺ ወታደር ነሽ እንዴ?››ግራ ገብቶኝ ጠየቅኳት፡፡
‹‹አይ ማለቴ ጓደኛዬ ወታደር ነው….ታውቃለህ አይደል?››
‹‹አዎ የበቀደምለታው ጄኔራል አይደል?››
‹‹አዎ ..እሱ ነው››
‹‹ግን…እንዲህ ከሌላ ሰው ጋር በምትሆኚበት ጊዜ ችግር አይፈጥርብሽም?››
አይኖቾ በንዴት ግልብጥብጥ አሉ….‹‹እንደዚህ ከማን ጋር ስሆን አይተኸኛል?›አፋጠጠችኝ፡፡
‹‹አረ አረጋጊው…ከእኔ ጋ ለማለት ፈልጌ ነው›
‹‹ካንተ ጋርስ ምን አድረግናል?››
‹የባሰ አለ ሀገርህን አትልቀቅ› ይላል የሀገሬ ሰው..ድንብርብሬ ወጣ…ምን ብዬ በንዴት ወደላይ የተመነጠቀ ስሜቷን  ልመልሰው?‹‹ምንም አለማድረጋችንን እኮ የምናውቀው እኔና አንቺ ብቻ ነን…ቢያንስ ሁለት ቀን አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ አድረናል…››
‹እ..እሱስ እውነትን ነው….ግን ያ ምንም ችግር የለውም..እሱም አመቱን ሙሉ ከሚስቱ ጋ ሲተኛ እኔ ምንም ብዬው አላውቅም፡፡››
‹‹ሚስቱ?›
‹‹አዎ ሚስቱ….ሚስትና ሶስት ልጆች አሉት››
‹‹ከባድ ነው››
‹‹አዎ ፍቅር ምን ጊዜም ቀላል ሆኖ አያውቅም››
‹‹ግን ምንድነው ስራሽ..?››
‹‹እሱን ማፍቀር?››
‹‹አይ ስራ መትተዳደሪበትን  ነው የጠየቅኩሽ..?››
‹‹ነገርኩህ ስራዬ እሱን ማፍቀር ነው….ገንዘብ ማገኝበትን ከሆነ የጠየቅከኝ ሌላ ጊዜ ነግሀለሁ…ግን ለራሴ የሚበቃ በቂ ገቢ አለኝ፡፡››
‹‹አይ ጥሩ ነው‹‹
‹‹ጥሩ ባይሆንስ ምን ምርጫ አለኝ....በል አሁን ይብቃን ገብተን እንተኛ››
‹‹አዎ ተነሽ.. ግን እኔ ወደቤቴ ልሂድ››
ፈገግ አለች‹‹ምነው ምን አሳቀሽ?››
‹‹አይ ወደቤት ልሂድ አባባልህ እራሱ ያስቃል..ምነው የጄኔራሉ ሽጉጥ ፊትህ ላይ ሲደቀንብህ በምናብህ አየህ እንዴ ››
‹‹ቀላል…ትቀልጂያለሽ እንዴ…?ገና በቅጡ እንኳን ያላየኋት እና ያላሰደኳት ልጅ አለችኝ..ድፍት ቢያደርገኝ ምን እላለሁ፡?፡››
ከተቀመጠችበት ተነስታ እጄን ይዛ ወደክፍሏ እያመረን ነው.. በራፍ አካባቢ ስንደርስ ነው ስለልጄ የነገርኳትን …ስትሰማ በድንጋጤ እጄን ለቀቀችና ባለችበት በመቆም አፍጥጣ አየችኝ፡፡
‹‹አንተ የእውነትን እንዳይሆን?››
‹‹ግራ ገባኝ ..ስለፍቅረኛዬ እያወራኋት ቢሆን ልሸመጥጣት እችል ነበር ..የልጅ ነገር ግን እንዴት አድርጌ…?መጀመሪያ አዳልጦኝ የተናገርኩ ቢሆን ወደኃላ ልመልሰው ግን እልፈለኩም …ቀጠልኩበት፡፡
‹‹አዎ ልጅ..አለቺኝ..የ7 አመት ልጅ..ተአምር ትባላለች››
‹‹ከዚህ በፊት ግን ፍቅረኛም ሚስትም እንደሌለህ የነገርከኝ መሰለኝ››
ይሄን ደግሞ መች ይሆን የቀባጠርኩላት…ማስታወስ አልቻልኩም፡፡አሁን ወደፊት ተንቀሳቅሰን በራፍ ጋር ደርሰናል….በእጇ ያንጠለጠለችውን ቁልፍ በማስተካከል በራፉን እየከፈተች ነው‹‹አዎ አሁንም  ሚስትም ፍቅረኛም የለኝም ….እውነቴን ነው››
ወደውስጥ ገባች…ሄዳለሁ ያልኩት ሰውዬ ተከትያት ወደውስጥ ገባሁ ..መልሳ በራፉን ከውስጥ ቆለፈችው፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡ከጎኗ ተቀመጥኩና ወሬዬን ቀጠልኩ፡፡
‹‹ነገሩ ውስብስብ እና የድሮ ታሪክ ነው… ሀይስኩል ተማሪ እያለው ነው የልጅ አባት የሆንኩት››
‹‹ታድለህ….ምን አለ እኔም ከእናቴ ቤት ሳልወጣ አንድ ዲቃላም ቢሆን ወልጄ በሆነ››
‹‹እውነትሽን ነው?፡፡››
‹አዎ..እውነቴን ነው…..የህይወቴ አንዱ ህመም የልጅ እናት ካለመሆኔ ጋ የተያያዘ ነው…››አይኖቾ በእንባ ተሞሉ…አረ ዘረገፈችው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ አሁንም  ይቻላል.. ገናነው አልረፈደም…ሶስትም አራትም ልጅ መውለድ ትችያለሽ››
ኩስትርትር ብላ‹‹መቻሌን በምን አወቅክ?››በሚል ጥያቄ አስበረገገችኝ፡፡
👍53😢21🤔1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_አስር


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

እራሴን አመም ስላደረገኝ አስፈቅጄ ወደቤት ስገባ ሶስት ሰዓትም አልሆነም።..ሹክክ ብዬ ገብቼ አልጋዬ ላይ "በመውጣት አረፍ እንዳልኩ ስልኬ ጠራ...አሁን ማንንም ቢሆን አንስቶ የማናገር ፍላጎት የለኝም የዜና ወርቅም ብትሆን እንኳን፡፡ስልኩ መጥራቱን ቀጥሏል ማንም ቢሆን ላለማንሳት ድምዳሜ ላይ ከደረስኩ ማንነቱንም ማየት አስፈላጊ አልነበረም ..እኔ ግን እጄን ሰድጄ ስልኬን አነሳሁ፡፡ እስክሪኑን ወደአይኔ አስጠጋሁ..ተፈናጥሬ ከመኝታዬ ተነሳሁና ቁጭ አልኩ..እንዳይዘጋብኝ እየተስገበገብኩ አነሳሁት..

‹‹ሄሎ የእኔ ውድ..?

"ሄሎ አባዬ እንዴት ነህ?

"አለሁልሽ ..በጣም ሰላም ነኝ..አልተኛሽም እንዴ?"

"አይ ገና ልተኛ እየተዘጋጀሁ ነው...አባዬ የእኔ ክላስ የትኛው እንደሆነ ታውቃለህ አይደል?"

በምናብ ወደ አደኩበት ቤት ፈረጠጥኩ..ሁሉንም ክፍሎች በሀሳቤ ቃኘሁ ከእነቴቴ መኝታ ቤት ቀጥሎ ያለችው ክፍል ነች አይደል?"ግምቴ መቼስ የቤቱ ትንሽዬ ህፃን ስለሆነች ለቁጥጥርም ለሊት ተነስቶ ደህንነቷን ለማየትም ቅርብ ያለው ክፍል ነው የሚመረጠው ብዬ ነው...፡፡

"አይደለም..እዛ ህፃን ሆኜ ነበር አሁን ትልቅ ስሆን የአንተና የእማዬ  የነበረውን ክፍል ወሰድኩት

ደነገጥኩ"በእውነት እሱ ክፍል መኖሩ ትዝ አላለኝም ነበር፡፡ እንደዛ ያልኩት ከዛ ሁሉ ዝብርቅርቅ ክስተት በኃላ እቴቴ ክፍሉን ምንቅርቅር አድርጋ የአንድን ሳይድ ግድግዳ በመደርመስ ከሌላው ጋር በመቀላቀል ክፍሉ ለታሪክነትም  እንዳይታወስ የምታደርገው ነበር የሚመስለኝ ..ለዛ ነው ያንን አይነት ጥያቄ የጠየቅኳት"

"ልጄ ሳይገኝ ያ ክፍል አይከፈትም ብላ ከእነዕቃው አሽጋበት ነበር...ከዛ እኔ አክስቴ ትልቋን ለመንኩና እሷ በሌለችበት አስከፈቼ ገባሁበት፡፡"

"ታዲያ አልተቆጣችሽም?"

"አይ  ምንም አላለቺኝም ግን አለቀሰች፡፡"

እኔም አሁን አለቀስኩ የሚቆጠቁጥ እምባ በቀኝ ጉንጬ ረገፈ"የእኔ ማር እናትሽ ለእቴቴ ትደውልላታለች አይደል?"ድንገት በእምሮዬ ብልጭ ያልኝን ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡

"ትደውልላታለች...እቴቴ ግን ትሰማታለች እንጂ አታናግራትም፡፡"

"ለምን?"

‹‹"እኔ እንጃ አባዬ...የሙት እህቴን ቃል እንድበላ አደረጋኛለች..ልጄን ወይ በህይወት አልያም ሞቶ ከሆነ ሬሳውን አግኝቼ እርሜን ሳላወጣ ከእሷ  ጋር ባወራ እግዜር ይቀየመኛል ትላለች...ግን አባዬ እርም ማውጣት ማለት ምን ማለት ነው?።››

"ቁርጥ ማወቅ ማለት ነው የእኔ ልጅ"ቀላል ነው ብዬ ባልኩት ቃል ገለፅኩላት።

"አባዬ"

"ወዬ የእኔ ልጅ"

"እቃችሁን ስጎለጉል የእማዬ  ማስታወሻ ደብተር አገኘሁት..ሁል ጊዜ አነበዋለሁ.. ደስ ይላል..።"

"እናትሽ ማስታወሻ ደብተር ነበራት እንዴ? እኔ አላውቅም..."

"አዎ አላት ..ትልቅ ሰማያዊ ደብተር....እና ደግሞ ስላንተ ብቻ ነው የፃፈችው...ትንሽ ትንሽ አንብቤው ስላልገባኝ ተውኩት.. ››

የእውነትም በጣም ተገርሜ "በእውነት ይገርማል .!"አልኩ ፡፡

በድንገት ማስታወሻው ላይ ያለውን ሀሳብ ለማወቅ የሚቀስፍ አይነት የጉጉት  ስሜት ተሰማኝ..ልጄ የውስጤን እንዴት ማንበብ እንደቻለች አላውቅም"አባዬ ከፈለክ ትንሽ ትንሽ ፎቶ እያነሳው ልልክልህ እችላለሁ"ደ

ተነቃቃሁ"እንዴት  አድርገሽ?"

"ቴሌግላም መጠቀም እኮ በጣም እችላለሁ...ለእማዬ ፎቶዬንና የፈተና ውጤቴን እያነሳሁ ሁሌ ነው የምልክላት"

"በጣም ደስ ይለኛል የእኔ ማር...በይ አሁን ተኚ"
"እሺ አባቢ ..ደህና እደር...እወድሀለሁ"

"እኔም እወድሻለሁ"

ስልኩ ተዘጋ...እራስ ምታት የሚባል ነገር ከጭንቅላቴ ተጠራርጎ ወዴት ጥርግ እንዳለ እኔ እንጃ።ልጅ መድሀኒት ነው የሚባለው ለካ ዝም ብሎ አባባል አይደለም፡፡

ስልኬ ተንጣጣ...ሚሴጅ ነው..ከልጄ ነው ከፈትኩት

‹‹ልኬያለሁ›› ይላል ወዲያው ዳታ አበራሁና ቴሌግራም ከፈትኩ .ተአምር እዬብ  ሁለት ፋይል ልካልኛለች...የእኔ ቅመም ልጅ...፡፡ዳውን ሎድ አደረኩትና ከፈትኩት ፡፡ እውነትም ልምድ አላት ፡፡ፍይሉ በጥራት የሚነበብ በጥንቃቄ ተነስቶ የተላከ ነው።የእናቷን የእጅ ፅሁፍ ሳየው ሰውነቴን ነዘረኝ ፅሁፍና ምስሏ በአእምሮዬ እየተፈራረቀ  ትዝታ ውስጥ ጨመረኝ...ምን አለ እህቴ ባትሆኚ።ትራሴን አስተካክዬ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩና ማንበብ ጀመርኩ።

ግንቦት 5/2008 ከምሽቱ 5 ሰዓት

እቤታችን ሲመጣ 9 አመቱ ነበር ።የመጣበትን ቀን በደንብ ነው የማስታውሰው እማዬና አባዬ ለቅሷ ብለው ወደ አዲስአባ ከሄዱ ከሳምንት በሀላ ነው ጥቁር በጥቁር ለብሰው  ፊታቸው ጨልሞና ከፍቶቸው ሌላ የከፋው ፤ለንቦጩን የጣለና ግራ የገባው ልጅ ይዘው የመጡት፡፡ልጁን ቀድሞውንም አውቀዋለሁ፤ ያውቀኛል፡፡ አዲስአባ ያለችው የአክስቴ ልጅ ነው።የአሁኑ አመጣጡ ግን እንደከዚህ ቀደሙ ቦርቆና ፈንድቆ ከእኔና ከእህቶቼ ጋር ለአራት ለአምስት ቀን እቃ እቃ ተጫውቶ ለመመለስ እንዳልሆነ ገብቶኛል።

ትላልቅ ሰዎች አክስቴም ባሏም በድንገተኛ አደጋ ዘእንደሞቱ ሲያወሩ ሰምቼያለሁ ..ግን ይሄ ድንገተኛ አደጋ   የተባለው ሰውን የሚገድል አውሬ ምን አይነት ነው?ስል በወቅቱ በነበረኝ የልጅነት አዕምሮዬ  አሰብኩና በጣም ተበሳጨሁ። አክስቴን በተመለከተ ጣፋጭና የማይሳሳ አይነት ትዝታ ነው ያለኝ።በሶስት  ወር ሆነ በስድስት ወር ልትጠይቀን ስትመጣ ..ኬክ፤ቸኮሌት፤ እና ልብስ ቀሚስ፤ ቲሸርት ጫማ ብቻ አንድ ነገር ይዛልን ትመጣ ነበር።

ትምህርት ቤት ሲዘጋ ደግሞ አዲስአባ እንሄዳለን...ያንን ቢሄድ ማለቂያ የሌለውን ከተማ በፈንጠዝያ ስንዝናናበት ቆይተን ሽክ ብለን በአዳዲስ ልብስ አሸብርቀን እንመለሳለን..አመቱን ሙሉ ከደብረብርሀን ወጥተው ለማያውቁ ጓደኞቻችን ስለአዲስአባ ተረት መሰል ታሪኮችን እየተረክን ስንጎርርባቸው እንከርማለን ለእኔ የአክስቴ ሞት ትርጉም በዛ የጨቅላነት ዕድሜዬ እንኳን  በደንብ ነበር የገባኝ...ከአሁን በሀላ ከአዲስ አበባ የሚመጣልኝ ምንም ኬክ ሆነ ቸኮሌት እንደማይኖር ገባኝ..ዘናጭና ፍሽን ቀሚሶችም ከአክስቴ እንደማይበረከቱልኝ ከሁሉም በላይ ግን ክረምት መጥቶ ት/ቤት በተዘጋ ቁጥር አዲስአበባ ሄዶ መዝናናት የማይቻል መሆኑን ምን አልባትም ትልቅ ሰው እስክሆን አዲስአበባን እንደማላያት ተረዳሁ..
እና እዬቤን እማዬ ከሌሎች ሀዘንተኞች ጋር ይዛው ስትመጣ እላዩ ላይ ተጠምጥሜ አንገቱን አቅፌ አለቀስኩ..ቢያባብሉኝ እራሱ ላቆም አልቻልኩም... በወቅቱ እንደዛ ማለቀሴ  አክስቴን አስታውሼ ነበር. የምታመጣልኝ ኬክና ቸኮሌትም ስላማራኝ ነበር...እናም አዲስአባም መሄድ ስለፈለኩ ግን ደግሞ እንደማልችል ስለገባኝ ነበር.፡
.ታላላቆቼ በድርጊቴ ግራ ቢጋቡም እኔ ግን በጣም አዝኜ ነበር..እና ለእዬቤ የራሱ አልጋ ከአዲስአባ እስኪመጣለት አልጋዬን አጋራሁት..እርግጥ አብዛኛውን ጊዜ እማዬ እያለ ሲቃዠና ሲንፈራገጥ እማዬ እየመጣች ወደራሷ መኝታ ቤት ትወስደውና ከማዬና አባዬ መሀል ይተኛ ነበር...እንደዛ ሲያደርግ እኔም ምን አለ አብሬው ሄጄ መሀከላቸው በተኛሁ እላለሁ፡፡እኛ ልጆቻቸው እንደው ፍርጥ እንላታለን እንጂ ከእነሱ ጋር የመተኛት እድል አናገኝም።እና በዚህ አይነት ሁኔታ እዬቤ ወንድማችን ሆነ፡፡ እቃቸው ከአዲስአባ መጣና ከእኛ ቤት እቃ ጋር ተቀላቀለ..ቤታቸውም እንደተከራየ  እማዬ ስታወራ ሰምቼያለሁ። አልጋውም መጣለትና ከእኔ አልጋ ጎን ቦታ ተመቻቸለት።ግን ስንላፋና ስንጫወት ቆይተን ሳናስበው ወይ እሱ አልጋ ላይ ጥቅልል ብለን ተቃቅፈን
👍672👎1🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ቀኑ ጭፍግግ ያለው ነው።እቤት ተቀምጬ ከግድግዳዬ ባሻገር ካሉት ጋሽ  ሙሉአለም ጋር  የተለመደውን የአያትና የልጅ ወሬ  ማውራት በጣም ፈልጌ ነበር ...ግን   ዛሬ ዝም እንዳሉ ነው...አንዳንዴ  እንዲህ ያደርጋቸዋል፡፡

ዝምታቸው ሶስት አራት ቀን ባስ ሲልም እስከ ሳምንት ይዘልቃል።እናም በዚህ ሁለት ቀን እየሆነ ያለው እንደዛ ነው።ያ ደግሞ ለእኔ ድብርት ይለቅብኛል። እና አሁን ለዚህ ነው እቤቴን ለቅቄ የወጣሁት። የስራ ሰዓት እስኪደርስ ሁለት ትርፍ ሰዓት አለኝ፡፡
.አይገርምም በዚህ ድህነቴ ይሄ ሁሉ ትርፍ ሰዓት ..
ኑሮዬ የሚያሻሽል መአት ነገር ልሰራበት እችል ነበር...ለምሳሌ ጀብሎ ሆኜ ሲጋራና መስቲካ ባዞር የተወሰኑ ብሮች በእርግጠኝነት አገኝ ነበር....ሊስትሮም ሆኜ ጫማ ብጠርግም እንደዛው...ግን ሰነፍ ነኝ ወይም ግብዝ ነኝ ..ዲግሪ ተመርቄ እንዴት ሊስትሮ? እንዴት ጀብሎ ?ግን ባለዲግሪ ሆኜ አስተናጋጅ መሆን ከቻልኩ ጀብሎስ መሆን ምኑ ይከብዳል? ዛሬ ደገሞ ምን አይነት ሀሳቦች ናቸው በአዕምሮዬ የሚራወጡት ?
ምንአልባት እንዲህ ምነጫነጨው ልጄ ናፍቃኝ ይሆናል..ድምፆን ከሰማው ሶስት ቀን አለፈኝ..ወይ ጉድ ለአመታት ረስቼት እንዳልነበር አሁን  እንዲህ ታሪክ ይቀየር..?.በሀሳብ ስናውዝ አንድን መኪና እንዳልገጨው ስለፈራሁ ፊት ለፊቴ ካገኘሁት ካፌ ዘው ብዬ ገባሁ እና በቅርብ ያገኘውት ጠረጰዛ ላይ ወንበር ስቤ ተቀመጥኩ።

ማኪያቶ አዝዤ ለመጠጣት እያማሰልኩ ፊት ለፊቴ ያለው ቴሌቪዥን የሚያሰራጨውን ፕሮግራም  እያየሁ ነው.፡፡:ፕሮግራሙ የተደገመ ይላል፡፡ምንአልባት ከሶስት ወይም ከአራት ቀን በፊት የተከናወነ ክንውን መሰለኝ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ለመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ሰጡ .››ይላል፡ከዚህ በፊት በቴሌቭዝን የማውቃቸውም ፤በጦርነቱ ምክንያት በየፌስቡኩ ምስላቸውና የጀግንነት ስራቸው ያነበብኩላቸው ጉምቱ የሀገሪቱ የጦር ጄኔራሎች አሉበት.፡፡እኔም እንደወትሮው የቴሌቭዝን ፕሮግረሞች በተሰላቸ መንፈስ  ሳይሆን በተነቃቃ ስሜት ነበር ስከታተል የነበረው..
የማዕረግ እድገቱ ኮረኔሮችን እና ጀኔራሎችን ያከተተ ነው..የፈረጠሙና የገዘፍ የጦር ሹሞቹን ብርጋዴር ጄኔራል፤ሜጄር ጀኔራል.፤ሌፍተራን ጄኔራል እያሉ ትከሻቸወ ላይ ማዕረጉን የሚያሳይ ኮኮብ ሲያስሩላቸው ደስ ይላል፤ይነሽጣልም፡፡፡ምን አለበት እኔም ባለፈው ምልመላ ብመዘገብና ወታደር ብሆን በዚህ ህይወት ከመርመጥመጥ አይሻልም ነበር? ብዬ እራሴን ጠየቅኩ ፡፡ጥያቄዬ አግባብ ነው ወይስ አልፎ ሂያጅ ግልብ ስሜት የፈጠረው..?መልስ ከማግኘቴ በፊት በመሀከል ነጎድጎድ ተንጓጓ፤ ፍንጥቅጣቂና ዝብርቅርቅ ቀለማት በአካባቢዬ ተረጩ፤  መብረቅ  በድንገት ወደቀ…ከመቀመጫዬ ተነሳሁ ወደእስክሪኑ አፈጠጥኩ አዎ እራሷ ነች..፡፡
ኮረኔል ዜናወርቅ ይግዛው  ወደ ብርጋድር ጀኔራልነት ተሸጋግረዋል፡፡በዛ በእውቅ ቀራፂ በአመታት ጥረትና  ልፋት የተቀረፀ የሚመስለው የታነፀና የተገናባ ሰውነቷ ላይ ያንን ባለግርማ ሞገሱ የመከላከያ ልብስ ስትለብስበት ዋው…ጠቅላይ ሚስቴሩ ፊት ቆማ ቆፍጣና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠች…ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደጆሮዋ ጠጋ ብለው የሆነ ነገር እያንሾካሾኩላት ማዕረጉን በትከሻዋ አጠለቁላት.
እንደ አጀማማሯ ሰላምታ  ሰጥታ  ከመድረኩ ስትወርድ ጋዜጠኛ ተቀበላት፡
‹‹ብርጋዴር ጀኔራል እንኳን ደስ ያሎት››
‹‹እንኳን አብሮ ደስ ያለን?››
‹‹ሴት ሆኖ እዚህ ትልቅ ክብር ያለው ወታደራዊ ማዕረግ ላይ በመድረሶት ምን ተሰማዎት?››
‹‹ያው ይሄ ማዕረግ በደም እና በላብ ነው የሚገኘው…ደምና ላብ ደግሞ የወንድም ሆነ የሴት ጠረኑም ቀለሙም አንድ ነው…በአጠቃላይ ሴት ስለሆንኩ ሳይሆን ስለሚገባኝ ያገኘሁት ማዕረግ ስለሆነ ደስ ብሎኛል፡፡››

ጋዜጠኛው ያልጠበቀውን መልስ ማግኘቱ በሁኔታው ያስታውቃል፡፡
‹‹ምስጋና የሚያቀርብለት ሰው ወይም አካል ካለ እድሉን ልስጦት›የሚል የተለመደ የመዝጊያ ሀሳብ አቀረበ
‹‹የእውነት  ወታደር እንድሆን እና ህልሜን እንድኖር የረዳኝን ተቋሜን አመሰግናለሁ….ሀገሬንም እንደዛው…በደሜ ቁስሏን አጥባለሁ.. በአጥንቴ በጀርባዋ የተሸከመችውን ችግሯን አክላታለሁ የሚል አላማ ነበረኝ ያንንም ያደረኩ ይመስለኛል….ወደፊትም በተለየ መልኩ ተመሳሳዩን ማድረጌን ኦቀጥላለሁ…አመሰግናለሁ፡፡›› ብላ ከእስክሪኑ ወጣች…እኔም ኪሴ ገብቼ የጣጣሁበትን የማኪያቶ ሂሳብ ጠረጳዛ ላይ አስቀመጥኩና ለብቻዬን እየለፈለፍኩ ወደቤት ተመለስኩ ተንቆራጠጥኩ ..ጨጓራዬን ለበለበኝ..ምን አስዋሻት?.የጄኔራሉ ውሽማ እንደሆነች ነበር የነገረቸኝ…?ታዲያ አሁንስ ስለአለመሆኗ ምን መረጃ አለኝ ?ብዬ እራሴን ጠየቅኩ.፡፡ውሸቷን ነዋ ውሸቷን…..ቅምጡ እንደሆነች እኮ ነበር የነገረችኝ….ስራ እንደሌላትም ነግራኝ ነበር…፡፡እንደእብድ በግትልትል ሀሳቦች ሰክሬ ቀባጠርኩ፡፡

ዘንድሮ ምን ውስጥ ነው የገባሁት…?የጄኔራል ቅመጥ አፈቀርኩ ብዬ ስሰጋና ስሸማቅ ጭራሽ እራሷ ጀኔራል…ለመሆኑ ስንት አመቷ ነው…?ስትታይ እኮ ሰላሳም የሞላት አትመስልም..መቼስ በሰላሳ አመት እዚህ ደረጃ ደርሳ እኔን አታሳቅቀኝም..እኔም እኮ ሰላሳ ሊሟለኝ ሁሉት አመት ያልሞላ ጊዜ ነው የቀረኝ…ይሄው ታዲያ እኔ ያለሁበትን እና እሷ ያለችበትን እዩት..
ግን ግላዊ ህይወቷ እንዴት ነው….?ለምን እንደዛ ታደርጋለች..?እንዴት እኔን መረጠችኝ…?ንቃኝ ነው አምናኝ…?
ግን እኮ እስከዛሬ ሶስት ለሚሆኑ ቀናቶች አብረን ተጫወትን አብረን አንድ አልጋ ላይ ተኛን እንጄ ምንም በመሀላችን የተፈጠረ አካላዊ ንክኪ ሆነ ፍቅራዊ ድርድር የለም፡፡..ዝም ብዬ ነወ የምቀባጥረው...እሷ እኔን የምትፈልገኝ ለመደበሪያ ነው..ካላባት ትልቅ ሀላፊነት እና የስራ ጫና ዘና ለማለት እና የህወትን ሌለኛውን ጀርባ ለማየት ስትፈልግ ይሆናል እንደዛ የምታደርገው….ኡኡ ላብደ ነው..፡፡ልብሴን ቀየርኩና ከቤት ወጣሁ ፡፡ሰዓቱ ስለደረሰ ወደስራ ነው የገባሁት..ከአንገት በላይ የግድ ስለሆነብኝ ብቻ ስራዬን መሰራት ጀመርኩ፡፡

ማታ አራት ሰዓት አካበቢ የደንበኞችን ትዕዛዝ ለመተግበር ከአንዱ ጠረጴዛ ወደሌላው ጠረጴዛ ስመላለስ አይኔ አንድ ነገር አየ..ጄኔራሏ እንደተራ ሰው ጅንስ ሱሪ ለብሳ ኮፍያ ያለው ቢጃማ ጃኬት አድርጋ ኮፊያውን ጭነቅላቷ ላይ ደፍታ  በአይኖቿ ጥቁር መነፅሯን ሰክታ ልክ የሰፈር ማጅረት መቺ መስላ ሚሪንዳ ቶኒኳን  ትጠጣለች፡ ፡ተንደርድሬ ስሯ ደረስኩና ጠረጴዛውን ተደገፍኩ…. አይኖቾ ላይ አፈጠጥኩባት ….ተረጋግታ ቀስ ብላ መነፅሯን አወለቀችና በፈግታ አየችኝ...ምለው ነገር ስለጠፋኝ ካጎነበስኩበት ቀና አልኩና ፊቴን ዞሬ ከመቀመጫዋ ራቅኩ…ተመልሼ ወደእዛ አልሄድኩም… .በጣም ተበሳጭቼባተለሁ፡፡
እንዲያ በተወጠረ ስሜት ላይ ሆኜ ሰዓቱ እንደምንም ገፋ፡፡ ተስተናጋጆችም አንደ በአንድ እያሉ ወጥተው አለቁ… ፡፡እሷም ምን ጊዜ እንደወጣች፤ወደየት እንደወጣች  ባላያሁበት የጊዜ ቀፅበት ከእይታዬ ተሰወረች …ሂሳብ አሰረክቤና  አንገቴን አቀርቅሬ በተከፋ ስሜት ወደቤት ሄድኩ..በራፍን ከፍቼ ገባሁ፡፡

‹‹አንተ ቀልማዳ መጣህ?››አያቴ ናቸው፡፡

ውይ ተመስጌን አያቴ መናገር ጀመሩ…

‹‹አዎ አያቴ..ግን ቢያዩ ድክም ብሎኛል››መናገር በመጀመራቸው በጣም ደስ ቢለኝም እኔ ደግሞ በተቃራኒዊ በዚህ ወቅት ምንም አይነት የመናገር አፒታይት የለኝም.፡፡ጥልቅ ምስጠት ውስጥ ገብቼ በሀሳብ መንቦራጨቅ ነው ያማረኝ፡፡
👍527🔥1🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹እኔ እዬብ እኮ ነኝ.›› ብዬ ቃላት ከአንደበቴ ለማውጣት አፌን ስከፍት ከንፈሯ ከንፈሬን ጎረሰው…ተአምር ነው በዚህ ሀገር ስንት ሴት ጄኔራሎች አሉ…?ከእነዚህ ውስጥ ከ ጄኔራሎች ጋር ፍቅር ለመጋራት ስንት የአዳም ልጅ እድል አግኝቷል.?.ልቤ በትዕቢት ስታብጥ ታወቀኝ…፡፡እጄን በወገቧ ዙረያ ጠምጥሜ ይበልጥ ወደሰውነቴ አጣበቅኳት..ብስጭቴ ሁሉ ከጭንቅላቴ እየተነነ አየሩን ሲሞላ ታየኝ…ውስጤ ተንፈቅፍቆ መሳቅ ጀምሯል…
ከከንፈሯን አላቃ በአንድ እጇ ብቻ ወገቤን ይዛ ወደላይ አንጠለጠለችኝና አልጋው ላይ ወረወረችኝ…፡፡ወይኔ ዛሬ በቃ እስከመጨረሻው ነው…ቆይ ልብሴን ላውልቅ ብዬ ልነሳ ቀና ስል ግንባሬ ላይ ሽጉጥ ደቅናለች..መልሼ በድንጋጤ  በመደንዝ አልጋው ላይ ተዘረርኩ፡
‹‹ሽጉጥ እንኳን ሊደቀንብኝ በህይወቴ በፊት ለፊቴ አይቼው አላውቅም በፊልም እና በፎቶ ብቻ ነው የማውቀው..እና የጋለው ሰውነቴ ቀዘቀዘ…››

‹‹እንዴ ምን አጠፋሁ..?››

‹‹ሌባ ነህ..››

‹‹እኔ እዬብ እኮ
ነኝ››ለስንተኛ ጊዜ ይሆን ስሜን የነገርኳት?፡፡

‹‹አዎ ልቤንም የሰረቅከው እዬብ የተባልከው አስተናጋጅ አንተ አይደለህ?››

‹‹ይቅርታ የእኔም ልብ እኮ የለም ›አልኳት በአሳዛኝ ድምፅ ሽጉጡን ከግንባሬ አንስታ ትራሷ ስር ሸጎጠችና ከጎኔ ተኛች

‹‹በፈጣሪ ምነው ምን አድርጌሽ ነው እንዲህ ምታስደነግጪኝ.?››

‹‹ይቅርታ››

‹‹እስከአሁን እንዴት ሳትተኚ››

‹‹አየጠበቅኩህ ነበር››
‹‹እንዴት …ወደቤት ሁሉ ሄጄ ተኝቼ ነበር.

‹‹እናስ?››

.እናማ እንቅልፍ አልወስድም ሲለኝ ተመልሼ መጣዋ››

‹‹መጀመሪያ ለምን ሄድክ? አኩርፈሀኝ ነበር አይደል?››

‹‹አዎ በጣም ነበር የተበሳጨሁብሽ ..ደግሞ ዛሬ ነው ያየሁት..ወታደር መሆንሽን ብትነግሪኝ ምን አለበት ?ለዘውም ጄኔራል.››

‹‹ምን ይጠቅምሀል… እኔ ከአንተ ጋ እየተገናኘሁ ያለሁት ጄኔራል ሆኜ ሳይሆን ዜና-ወርቅን ብቻ ሆኜ ነው..››

‹‹ኸረ ተይ በናትሽ..ከቀድሞ አውቄ ቢሆን ልቤን መች እንዲህ አዝረከርካት ነበር…››

‹‹ምን  ወታደር አይመችህም እንዴ?.››

‹‹አረ እንደዛ ማለቴ
አይደለም ግን ይከብዳል…በተለይ ለአንቺ የሚከብድ ይመስለኛል..አለ አይደለ እኔ እንጃ ብቻ.››

‹‹ለማለት የፈለከው ገብቶኛል.ግን አታስብ በቅረብ ጡረታ ልወጣ ነው..››

‹ጡረታ ምነው በዚህ ዕድሜሽ.?ለዛውም የማአረግ እድገት ባገኘሽበት ማግስት ››
‹ ምክንቱን ሌላ ጊዜ እንግርሀለሁ …ግን ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ከሰራዊቱ እሰናበትና ሌላ የሲብል ስራ ላይ የምመደብ ይመስለኛል…››

‹‹አሁን ትንሽ ቀለል አለኝ…መቼስ ጡረታ ከወጣሽ በኃላ ችላ አትይኚም አይደል?››

‹‹አይ አልልህም….ግን አንድ ልደብቅህ ማልፈልገው ነገር አለ››

ስለጄኔራሉ ፍቅረኛዋ የሆነ ነገር ልትለኝ ነው ብዬ በታፈነ ስሜት‹‹ ምን?›› ስል ጠየቅኳት

‹‹አንተን በተመለከተ በጣም የተወዛገበ ስሜት ነው የሚሰማኝ…የሆነ ድሮ የማውቀው የጠፋ ዘመዴ ወይም ወንድሜ ነው ምትመስለኝ››ብላኝ እርፍ፡፡

‹‹ባክሽ አትቀልጂ …ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?፡፡››

‹‹እኔ እንጃ …ሁል ጊዜ ላገኝህና ላቅፍህ እፈልጋለው..አግኝቼ ሳቅፍህ ደግሞ ታናሽ ወንድምሽ እኮ ነው የሚል ስሜት ይተናነቀኛል፡፡››

‹‹ምነው የጠፋ ወንድም ነበረሽ እንዴ?››

‹‹ኸረ ፍፅም.. እኔ ምንም የጠፋም ያልጠፋም ወንድም ኖሮኝ አያውቅም››
ኮስተር ብዬ‹‹ተይው በቃ ይህ የእህት ነገር እጣ-
ክፍሌ  አይደለም..ለጊዜው ጓደኞች ከሆን ይበቃል›› አልኳት …ውስጤ ግን ምንም አይነት ከእሷ ጋር ጓደኛ የመሆን ጉጉት የለውም…
በተረጋጋ አንደበት‹‹እንደዛ ከሆነ  እንተኛ››አለችኝ፡፡
‹‹ደስ ይለኛል›አልኳት፡፡
እሺ ብላ አልጋው ላይ ቆመች…የለበሰችውን ቢጃማ አወላለቀችና በሰማያዊ ፓንት ቆመች.እኔ በተኛሁበት ከስር ወደላይ እያየኋት ነው..ይገርማል በቴቪ በዛ ግርማ ሞገስ ያያት ሰው አሁን እንዲህ እርቃኗን ቆማ ከነሙሉ ውበቷና ደምግባቷ  ቢያያት ደግሞ ምን ይል ይሆን?፡እኔም በተኛሁበት ልብሴን አወላልቄ ወደጠረጳዛው ወረወርኩና ከውስጥ ገባሁ ..ቀድማኝ ገብታ ነበር፡፡ መብራቱን አጠፈሁና ከሰውነቷ ተጣበቅኩ፡፡እና ከየት እየተንቀዠቀዠች እንደመጣች ሳላውቅ የተአምር እናት በምናቤ ተሰነቀረች…የሴት ልጅን ገላ ሳቅፍ እንዲህ አይነት የሚነዝርና የሚያሾር አይንት ስሜት ሚሰማኝ ከእሷ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ዳሩ ነገሮች ባለምኳቸው መጠን እድገት አላሳዩም.. ሊቱን በሙሉ በመተቃቀፍ ገደብ ባይኖረውም ከዛ እልፎ ወደ  ጭን መፈላለቅ ሊያድግ አልቻለም፡፡ ‹‹በፈጣሪ አሁን እኔ ምኔነው የእሷ ወንድም የሚመስለው?››ይሁን እስቲ  ….ማምሻም ዕድሜ ነው ይባል የለ፡፡

…በማግስቱ ማታ
//
ከምሽቱም አምስት ሰዓት ከስራ መልስ ነው፡፡አልጋዬ ላይ ወጥቼ  ከብርድልብሴ ስር ገብቼ ስለነበር ስልኬን ካስቀመጥኩበት አነሳሁና  ተነጠራርቼ መብራቱን አጠፋሁ፡፡ብርድልብሱን ተከናነብኩና ሞባይሌን ከፈትኩ ፡፡ቅድም ልጄ ተአምር ልካልኝ የነበረው ቴሌግራም ከፈትኩ….እናቷ  ስለእኔ የፃፈችው ቀጣይ ፀሁፍ ነው….የእሷን ፅሁፍ ማንበብ የቡና ሱስ  ነው የሆነብኝ፡፡ ተመቻችቼ ማንበብ ቀጠልኩ፡፡

ግንቦታ 16/2008 ዓ.ም

እዬቤ ከእህቶቼ በላይ ነው ማቀርበው…ከእህቶቼም በላይ ነው የምወደው..እሱ ለእኔ የሚስጥር ተጋሪዬ ነው..እሱ ለእኔ የትምህርት ቤትም ጓደኛዬ ነው።እርቃኔን እህቶቼ ፊት ስቆም ሰውነቴን ይበላኛል...እዬቤ ፊት ሲሆን ግን የራሴን ሰውነት በራሴ አይን እያየሁ ነው የሚመስለኝ።ለምን እንደዛ ሆነ ?ለእኔም ለራሴ ግራ ይገባኛል። ለምሳሌ ልብስ ለእህቶቼ ተገዝቶ ለእኔ ባይገዛ ችግር የለውም..ለእኔ ተገዝቶ ለእሱ ላይገዛ ግን አይችልም።በቃ ያንን ልብስ በምንም አይነት አለብሰውም።እሱም እንደዛው ነው።አንዳንዴ ያው የሙት ልጅ ነው በሚል ስሌትም ከቤተሠቦቹ ቤት ኪራይ የሚገኝ ገንዘብ ስላለ በሚል  ስሌትም ብቻ ምክንያን አላውቅም ለእሱ ለብቻው ልብስ ይገዛለታል..እሺ ብሎ ይቀበልና አጣጥፎ ያስቀምጣታል"ለእኔ እስኪገዛልኝ ስድስት ወርም ቢፈጅ አይለብሳትም ።ከዛ በቤተሠብ ሁሉ ተለመደና ለሁለታችንም መግዛት እስኪችሉ ነጥለው መግዛት አቆሙ..
ከእዬቤ ጋር እድሜያችንም ተቀራራቢ በመሆኑ ክፍላችንም አንድ ነው። የምንቀመጠውም አንድ መቀመጫ ላይ ነው።ያው ግን ለትምህርት የምንሰጠው ትኩረት በጣም የተለያየ ነው።እዬቤ ከአንደኛ ክፍል አንስቶ እስከመጨረሻው አንደኛ ወይም ሁለተኛ ነው የሚወጣው..ተሳስቶ እንኳን 3 ተኛ መውጣቱን አላስታውስም ።ብዙ አያጠናም ..ክፍል ውስጥ አስተማሪ የሚያስተምረውን በፅሞና ያዳምጣል..የቤት ስራ ሳይረሳ ይሰራል፤ ፈተና ሲቃረበ ያጠናል በቃ...እኔ ግን ተውኝ "አንድ ቤት እየኖራችሁ አንድ ክፍል እየተማራችሁ አንድ አስተማሪ እያስተማራችሁ ይሄ ሁሉ  ልዩነት ምንድነው?"የአባቴ የዘወትር ጥያቄ ነበር

"ቆይ አንድ ክፍል አይደል እንዴ የምትኖሩት? ለምን አብራችሁ አታጠኑም?" አባቴ ይጠይቀዋል

‹‹ጋሼ አብረን ነው የምናጠናው..ግን እሺ አትለኝም..እያጠናን ትተኛለች..ወይም ትረብሻለች"
👍60👏1🤔1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አስራ_ሶስት

///
እንደተለመደው ከሳምንት በኃላ ወደሆቴል መጥታ እኔም ስራዬን ስሰራ አሷም ስትዝናን አምሽተን እኩለ ለሊት ላይ ተያይዘን ወደተከራየችው ሆቴል በመግባት ተቃቅፈን ተኝተን እያወራን ነው፡፡እንዴት እንደሆነ አለወቅም ወሬው ደግሞ እንደወትሮው  ፍቅር ፍቅር ሚሸት ሳይሆን ኮምጠጥ ያለ ሀገራዊ ጉዳይ ነው..፡፡ዛሬ እንኳን እሷን የሚመጥናትን ጫወታ ልጫወት ብዬ መሰለኝ በገዛ ጥያቄዬ ውስብስብ ወሬ ውስጥ እነንድንገባ መንገዱን የከፈትኩት

‹‹መቼስ ወታደር ነሽ…ለዛውም ባለትልቅ ማአረግ….የሀገሪቱን ችግር  ለማከምና ከመከራዋ እንድትወጣ ለማገዝ በደምና በላብ ዋጋ ከፍለሻል…ግን አሁን ስታስቢው መስዋዕትነቴ ባክኗል….ደሜም ያለውጤት ፈሷል ብለሽ ታስቢያለሽ፡፡?››ስል ጠየቅኳት፡፡

እስኪ ምን ሚሉት ጥያቄ ነወ….ይሄንን ጥያቄ አንድን የተከበረች ጄኔራል ስጠይቅ የሀገሪቱ ደህንንት ቢሮ ጆሮ ቢገባ የትኛው ተቃዋሚ አካል ነው አስርጎ ያስገባህ ብሎ  ቢያፍነኝ  ይፈረድበታል?
እሷ ግን ተረጋግታ መመለስ ጀመረች‹‹ፈፅሞ አላስብም…አርግጥ እኔ እንዲሆን እያሰብኩና እያለምኩ እንደነበረው የተከወነ ነገር ላይኖር ይችላል፡፡ውጤቱ ከግምቴ በጣም ዝቅ ያለ ወይንም ሙሉ በሙሉ ተቃራኒ ሊሆን ይችላል…እንደዛም ነው የሆነው፡፡ግን እኔ ነገሮችን ለማስተካከል በተሰጠኝ  ኃላፊነትና ሪሶርስ በአግባቡ በመጠቀም በቀናነት እናም በሙሉ ችሎታዬ ተንቀሳቅሼለሁ ወይ ?ብዬ ነው የምጠይቀው…መልሱ አዎ ከሆነ በቂ ነው፡

ነገሮችን ሁሉ በውጤታቸው ብቻ ከለካህ መጨረሻው ጥሩ አይሆንም… ወደፊትም አያስኬድህም፡፡
‹‹እስቲ አብራሪልኝ››
‹‹ስራዎችን ከመከወንህ በፊት ስለስራው ሞያዊ ጥናት   ታርጋለህ፡ ውጤታማ የሚደርግህን እቅድ ትነድፋለህ ፡ከዛ ወደተግባር ትገባለህ…. .በእኔ አረዳድ እቅድ በወረቀት በሰፈረው መሰረት ተግባራዊ የሚሆነው ከ50 ፐርሰንት በታች ነው..ማንኛውም እቅድ ማለቴ ነው..የጦርነት እቅድ ሲሆን ደግሞ የተለየ ይሆናል….ግን ደግሞ  እቅድ አስፈላጊና በጥንቃቄ መሰራት የሚገባው ጉዳይ ነው..ቢያንስ ነገሮችን ለመጀመር መነሻ ይሆንሀል፡: በሂደት ለሚያጋጥሙህ እዲስ ክስተቶች የሚሆን የሚሳራ ቅፅበታዊ እቅደም ለማቀድ  መነሻ  ፍንጭ ይሰጥሀል…በአጠቃላይ ለማለት የፈለኩት እንኳን እንደኛ የተወሳሰበና የተጨመላለቀ የችግር ትብታብ ያለባት ሀገር ይቅርና ባደጉት ሀገሮች የማስፈፀም ብቃት እንኳን ነገሮች እንደሀሳብ አይሄዱም..ምሳሌ አሜሪካ ኢራቅን ሰትወር  የስንት ቀን ኦፕሬሽን ብላ ገባች? ስንት አመትስ ፈጀባት…?ራሺያ ዩክሬንን ላይ ለሳምንት ብላ የጀመረችው ጦርነት  ምን ያህል ጊዜ ፈጀባት ?
ይሄ የወታደራዊ ፤ አመራሩ ችግር፤የፖለቲካኛው ችግር ፤የቦታው ነባራዊ ሁኔታ..የተፋላሚህ አቅድህን ለማበላሸት  የሚነድፈው ሌላ እቅድ…የተፋላሚህ ወዳጆች ተፅዕኖ፤የአንተ ጠላቶች በሁኔታው ለመጠቀም የሚያደርጉት ጥረት፤ ጠላትም ወዳጅም ሳይሉ ከነገሩ ገቢያቸውን ለማደለብ የሚዳክሩ ሚዲያዎች፤ነጋዴዎች፤ ደላላዎች….ምኑ ቅጡ…የአንተ ዕቅድ በእግዚያሄር ካልተዘጋጀ በስተቀር የእንዚህን ሁሉ ተዋናይ ትርምስ ከግምት አስገብቶና   በትክክል ተንብዮ የሚሰራ እቅድ ሊያዘጋጅልህ አይችልም…..እና መጀመሪያ        ይሆናል ተብሎ ተነገሮህ አንተም ያንን አምነህ ወደጦርነት ትገባለህ..እንዳልከው ላብህም ይንጠባጠባል ፤ ደምህም ይረጫል  …አካልህም እየተቦደደሰ ይበራል…..ነፍስህም ልትሰናበት ችላለች…. ውጤቱ ደግሞ ከታሰበው ተቃራኒ ወይንም በጎን የልታሰበ ሽንቁር ከፍተት እየተስገመገመ ወዳልታወቀ መዳረሻ የሚያደርስ ሊሆን ይችላል፡፡

፤የዛን ጊዜ  ልትደነግጥ ትችላለህ…ሊከፋህ ይችላል…ግን በምንም አይነት ተስፋ አትቆርጥም…ተስፋ መቆረጥ ከሁሉም ጠባሳዎችህ እንዳታገግም እና ሁለተኛ እድል እንዳሞክር እስከወዲያኛው ነው የሚያደቅህ….ሀገር ደግሞ ቢያንስ ህልውናዋ ማስጠበቅ የምትችለው ሁል ጊዜ ተስፋ በማድረግና ከነመዝረክረኩም ቢሆን ወደፊት በመጎዝ ነው፡፡በምንም አይነት ሁኔታ በሀገርህ ላይ ያለህ ተስፋ በውስጥህ እንዲፈርስ ልትፈቅድ አይገባም፡፡በተለይ በዚህ የኢንፎርሜሽን ዘመን ጦርነት በጣም የማይተነበይ እና የሸረሪት ድር አይነት የተወሳሰበ ሆኗል፡፡

ከሌላ አካል ተልኮ ተሰጥቶት እንደሚጠይቅ እንደ ችኮ ጋዜጠኛ ሙግቴን ቀጠልኩ‹‹ግን የእኛ ሀገር ዋና ችግር ምን ይመስልሻል…?ድህነታችን መሆኑን አውቃለሁ…. ቢሆንም እንደወታደር በሀገሪቱ ፍፅም ሰለም እንዳትሆን ዋናው እንቅፋት ምንድነው?፡፡

‹‹ትክክል ነህ እኮ.. በግራም ዞርክ በቀኝ ለእኛ ሀገር ዋነው ችግራችን ድህነታችን ነው፡፡፡ሚያናጥቀንም ሚያላትመንም እሱ ነው፡፡ግን ከድህታችን በመለስ ዋናው ችግር ምንድነው ካልከኝ ፅንፈኝነት ነው…ፅንፈኝነት ማለት አይነ ልቦናል ጨፍኖ በደመነፍስ ማሰብ ነው፡፡ያ ማለት በውድቅት ለሊት የቤቱን መብራት ሁሉ አጥፍቶ የጠፋብንን መርፌ ለማግኘት የመዳከር ያህል ነው፡፡ቀንቶህ መርፌውን በዳበሳ መጨበጥ ብትችል እንኳን መወጋትህና መድማትህ አይቀርም፡፡
ፅንፈኝነት የራስን ፍላጎት ጥቅምና ስሜት ብቻ  መሰረት አድርጎ ብይን መስጠት ለዛም ብይን  ደምሳሽና ጨፍላቂ ውሳኔን መውሰድ ማለት ነው፡፡

አክራሪነት በብዙ    ዘርፍ አለ....የብሄር አክራሪነት፤ የሀይማኖት አክራሪነት ፤የፆታ አክራሪነት ፤የፖለቲካ አክራሪነት…የሀገር አክራሪነት ወዘተ፡፡ፅንፈኝነት ነገሮችን ከአንድ የተቸነከረ ፖይንት ኦፍ ቪው ብቻ መመልከትና ፍርድ መስጠት ማለት ነው፡፡ወደአንዱ ፅንፍ በጣም ተለጥፈን ስንቆም ከሌላኛው ፅንፍ ያለን ርቀት በጣም ሰፊ ይሆናል…ከእይታችንም ይጠፋል፡፡
ፅንፈኞች መቼም የእኛ ነገር የመጀመሪያው ይሁን…የእኛ ነገር ይሰማ …የእኛ ነገር ይቀመስ ፤ የእኛ ነገር ይበላ….ባይ ናቸው፡፡ማመቻመች የሚባል ነገር ፈፅሞ አልፈጠረባቸውም…. የጋራ በሆነ ነገር ላይ ደግሞ የእኔ ብቻ አይሰራም…፡፡
እና እንደአንድ ወታደር የትኛውንም ሀይማኖት ተከታይ ብትሆን ችግር የለብኝም.፤የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ብትሆን እኔን አይመለከተኝም…አህዳዊ ብትሆንም ፌዴራሊስት ብትሆንም ግድ አይሰጠኝም….ግን ሁሉም ውስጥ ሆነህ ፅንፈኛ ከሆንክ የዛን ጊዜ ችግር አለ..አንዳንድ ሰው አክራሪነት ላይ የተሳሳተ የትርጉም ስህተት ሲፈፅም አያለሁ….አንድ ሰው የራሱን ሀይማኖት ይዞ የሀይማቱን ዶግማዊና ቅኖናዊ ህግጋን ሳያፋለስ በፍፅም መሰጠትና ትኩረት ተግባራዊ በማድረጉ አክራሪ ሀይማተኛ ነው ልንለው እንችላለን…አክራሪነቱ ግን የሌላው ሀይማኖት አማኝ ላይ ድንጋይ እስካልወረወረ እና የሌላውን አማኝ ማምለኪ ቦታ ላጥቃና ላውድም እስካላለ ድረሰ በክፍትም በስህተትም ሊወሰድ አይገባም….፡፡በብሄርም ስትመጣ እንደዛው…አንድ የኦሮሞ ብሄር ተከታይ በኦሮሚኛ ቋንቋ ማውራቱ..በእየእለቱ የኦሮሞ ባላዊ ልብስ መልበሱና ገንፎና፤አንጮቴ እና ወተት የእየለት ምግቡ ማድረጉ በፍፅም ችግር የለውም…..ችግሩ በአካባቢዬ ያለው ስው ሁሉ ከአንጮቴ ውጭ ሌላ ምግብ እንዳይቀምስ ካለና በጆሮዬ ከኦሮምኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ አንዳይሰማ በማለት  ከሌላው ብሄር ጋር ባለው መስተጋብር ችግር መፍጠር ከጀመረ ነው፡፡
👍336🔥2🥰2👏2😁1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
#ክፍል_አስራ_አራት

/////

እለተ እሁድ ነው፡፡ረፋድ ላይ ቁርሴን ከበላሁ በኃላ ወደአልገዬ ተመልሼ ልጄ የላከችልኝን የእናቷን ማስታወሻ በተመስጦ እያነበብኩ ነው፡፡ይሄ ታሪክ የአፈላነት ጊዜ ታሪካችን ነው፡፡ትኩስ ወጣት ሆነን የኖርነው፡፡ወጣትነት ውስጥ የሚንፎለፎል ኃይል አለ።"ልክ የኒዩክሌር ኃይል አይነት።ወደማብራት ኃይል ተቀይሮ ልማትን ሚያሳልጥ...ወደአውዳሚ ቦንብ ተቀይሮ   ለጦርነት ውሎ ከተማን የሚያፈርስ  ወጣትነት ከተራራ የሚገዝፍ ነገሮችን የማድረግ ጉጉት እና   ሳይታክቱ የመሞከር ትጋት ..ቢወድቁ በፍጥነት ተነስቶ የመቆም ፅናት፡፡ አዎ  ከሰው ልጅ የዕድሜ እርከኖች ጎልደን ኤጅ የሚባለው ነው ወጣትነት፡፡ ህፃንነትና ታዳጊነት ከኃላው ትቶ ጎልማሳነትና አዛውንትነትን ከፊቱ አስቀምጦ  ከህይወት ዘንግ የመሀል አንጓ ላይ ያለ በዕንቁ  ያሸበረበቀ ጌጥ ነው።

ወጣትነት ውበት በመጨረሻው እንጥፍጣፊ አቅሙ የሚጎመራበት ስሜት ክላይማክሱን ገጭቶ የሚንፎለልበት የአበባነት እድሜ ነው።የፍቅር  ኮንሰርት ቢዘጋጅ የዳንሱን መድረክ የሚሞላው ወጣት ነው...የጦርነት ነጋሪት ቢመታ ለመስዋዕትነት ግር ብሎ የጦር ካንፑን የሚያጨናንቀው ወጣት ነው።አብዬት አንስቶ ከተማውን በድንጋይ አጥሮ አስፓልቱን በጎማ ጭስ የሚያጥነው ወጣት ነው....ለድጋፍ ሰልፍ ቲሸርትና ኬፕ ገድግዶ ጎዳናውን በመፈክርና  በባንዲራ የሚያጣብበውም ያው ወጣት ነው። በቀደድለት ቦይ የሚፈስ ፤ባሳዩት መንገድ የሚነጉድ ወጣት ነው።ቤተ እምነቱ የሚሻማው ቤተመንግስቱም የሚፈራው ያው ወጣት ነው...፡፡ ወጣት ሆነህ ጥበብ  ቀድሞ ከበራልህ ቤተእምነትም ሆነ ቤተመንግስት  አያታልሉህም....፡፡ፓለቲከኛው በስሜትህ ጢባጢብ አይጫወትብህም ...፡፡አዎ የነቃህ ወጣት ከሆንክ  ለእሱ ወደስልጣን ማማ መስፈንጠሪያ እስፕሪንጉ ለመሆን በምንም አይነት ሁኔታ ፍቃደኛ ልትሆን አትችልም" ግን ወጣትነት በብዙ ችኮላ ፤ፋታ በማይሰጥ ጉጉት፤ ስር ባልሰደደ ዕውቀትና ልምድ የሚጓዝ በመሆኑ ከስህተት ሊፀዳ አይችልም፡፡እርግጥ ሙሉ የሰው ልጅ ከስህተት ጋር የእድሜ ልክ ትስስር አለው…ወጣትነት ላይ ግን  ይለያል..እኔም እንደአብዛኛው ሰው ህይወቴን ያጨመላለቅኩት በዚህ የወጣትነት ዕድሜዬ በሰራሁት ስህተት ነው፡፡ውይ እስቲ መዘበራረቁን

ገታ አድርጌ እጄ ላይ አንከርፍፌ የያዝኩትን ከሪች ማስታወሻ ፎቶ ተንስቶ በልጄ አማካይነት በቴሌግራም የተላከልኝን ቀጣይ ታሪክ ላንብብላችሁ፡፡

ሰኔ 5 2008 ዓ.ም
11 ኛ ክፍል ሆነን ነው፡፡ማታ 11 ሰዓት ሆኖ ከትምህርት ቤት ከገባን በኃላ በምን ሰዓት በየት እንደሄደ ሳላውቅ እዬብ ከቤት ወጥቶ ጠፋ..ሰፈር ዞር ዞር ብዬ ብፈልገው ላገኘው አልቻልኩም.ግራ ገባኝ…ማታ እራት ሰአት ላይም ተመልሶ አልመጣም.. እነእማዬ ሲጠይቁኝ ጓዳኛዬ ጋ አብረን እናጠናለን ሲል ሰምቼለሁ ብዬ ዋሸሁ…የቤቱ ሰው ሁሉ ከተኛ በኃላ አምስት ሰዓት አካባቢ የክፍላችን መስኮት ከፈትኩለት.ዘሎ ገባ፡፡

‹‹እስከአሁን አልተኛሽም እንዴ?››

‹አፈር ብላ…ዝም ብለህ ከቤት ወጥተህ እስከእዚህን ሰዓት ድረስ ትቆያለህ?››

‹‹የእኔ ውድ እህት …አሳስብኩሽ እንዴ ..?

ድንገተኛ በረከት አጋጥሞኝ ነው፡፡››

‹‹የምን በረከት ነው?››

‹‹ባክሽ ሶፊያ ጋር ነበርኩ››
አቤት የደነገጥኩት
ድንጋጤ‹‹ሶፊያ የት? .ለምን?.ከእሷ ጋር ምን አባህ ትሰራለህ?››

ተንሰረዘረኩበት ፤አዎ ሶፊያን በደንብ አውቃታለሁ...አረ እንደውም. የክፍላችን ልጅና ለእኔም ጓደኛዬ ነች..የተበሳጨሁበት ጉዳይ ግን ወደጎን ነው፡፡ሶፊያ እዬብዬን በጣም እንደምትወደው አውቃለሁ፡፡.ማለት እንደምታፈቅረው አውቃለሁ….ብዙ ጊዜ ደጋግማ ‹ወንድምሽን አፈቅረዋለሁ› …ብላ ነግራኝ ፊት ነስቻታለሁ፡፡እንደዛ ስትለኝ የማቀርብላት ምክንያት ‹ወንድሜ ጎበዝ ተማሪ ነው..ያለጊዜው ፍቅር ምናምን እያልሽ እንድታዘናጊው አልፈልግም› የሚል ነበር››ዋናው ምክንያቴ ግን ያ አልነበረም…እዬብን ፍቅረኛም ሆነ ጓደኛ በሚል የብእር ስም አንድ ሴት መሀከላችን ገብታ እንድትሻማኝ አልፈልግም፡፡

‹‹እረጋ በይ እቤቷ ነበርን››አለኝ.በሚያበሳጭ የድምፅ ቃና..

‹ለመሆኑ እስከዚህን ሰአት እቤቷ ጎረምሳ ስታቆይ እቤተሰቦቾ ምንም አይሏትም?››

‹‹አታስቢ የእኔ እህት… ብቻዋን ነበረች››

‹‹ብቻዋን?››

‹‹አዎ ምነው ደነገጥሽ…ገጠር ሄደዋል… ብቻዋን ስለምታድር ነው የጠራቺኝ››
‹‹እና ምነው ብቻዋን ጥለኸት መጣህ ..የሆነ ነገር ቢያስደነግጣትስ…?አብረሀት አታድርም ነበር?››
‹‹እንኳን አድሬ ላመሸሁትም ሞቼልሻለሁ…አንቺ ጓደኛሽ እንዳንቺ መሰለችሽ.. አስጮኸችኝ እኮ››

‹እስጮኸችኝ ማለት…?መታህ ነው
አስደንግጣህ?››

‹‹አይ አንቺ ልጅ በቀላሉ አይገባሽም…ወሲብ ፈፀምን ….ወሲብ እንደዚህ እንደሚጥም ዛሬ በእሷ አወቅኩ፡፡››

‹ወሲብ .ወይኔ እቴትዬ…ወይ እግዚያብሄር ድረስ..ከተቀመጥኩበት አልጋ ተነሳሁ .እንባዬ አራት መስመር ሰርቶ በጉንጮቼ ላይ መፍሰስ ጀመረ…ወለሉ ላይ ተዘርፍጬ መሬቱን አሰስኩት..እዬቤ ያላሰበው ዱብ እዳ ነው የገጠመው...በጣም ግራ ገባውም በጣምም ደነገጠ.

‹‹አንዴ ምን ሆነሻል.?አረ ደምፅሽን ቀንሺ.እነቴቴ አንዲሰሙ ተፈልጊያለሽ እንዴ?›

‹‹አንተ እንዴት እንዲህ ትሰራለህ…?ምን ነክቶህ ነው?››

‹‹ምን ችግር አለው ?ይሄ እኮ ማንም ወጣት የሚሰራው ኖርማል ነገር ነው›

‹አይደለም እኔስ ወጣት አይደለሁ ለምን ሳልሰራሁም…?ለምን ቆይ?
‹‹እሱን እግዲህ እራስሽን መጠየቅ ነው››

‹‹አይደለም..በሽታውስ እንዴት እንዲህ እንዝላል ትሆናለህ.?.በዛ ላይ ብታረግዝብህስ…?ምን አባህ ልታደርግ ነው…ደግሞ ቤተክረስቲያን ይሄን ሁሉ ዘመን የተመላለስከው ለዚህ ነው፡፡ይሄ እኮ ዝሙት ነው..››

‹‹አረ በፈጠረሽ..እኔ ፀፀት እንዲሰማኝ ለማድረግ የሚያስቸልሽን አንድም ምክንያት እኮ አልቀረሽም..እኔ እኮ አስቤበት አልነበረም አሷ ጋር የሄድኩት..ድንገት ነው ሳናስበው ወደወሲብ የገባነው….ጥሩነቱ ግን እሷ ሁሉንም አዘጋጅታ ነበር የጠበቀችኝ.››

‹‹ሁሉንም ማለት?››

‹ኮንደም ነበራት..ልታረግዝ አትችልም አትፍሪ... በሽታውም እንደዛው…››

‹‹እሷማ አዎ እንደዛ ታደርጋለች …ልምድ ያላት ሸርሙጣ ነች፡፡እሺ የእግዚያብሄር ቃልን መጣሱስ? ዝሙቱስ?›
‹እሱን አንግዲህ አንዴ ተሳሳትኩ ወደኃላ መልሼ አልውጠው…ማድረግ የምችለው ንሰሀ መግባት ነው…እሱን አስብበታለሁ…አሁን እንተኛ ደክሞኛል አለኝና ልብሱን ፊቴ አወላልቆ ከውስጥ ገባና ከጭቅጭቄ ለማምለጥም ጭምር መሰለኝ ጥቅልል ብሎ ተኛ፡፡
‹‹እኔማ ከሻርሙጣ ጋር አብሬ አልተኛም›› አልኩና አልጋ ልብሱን ከላዩ ገፍፌው ትራሴን ወሰድኩና ምንጣፍን ወለሉ ላይ ዘርግቼ ተኛሁ…ተነስቶ እንዲለምነኝ ፤ጉንጬን፤ ግንባሬን እየሳመ ይቅርታ እንዲጠየቀኝ…እቅፍ አድርጎ ፀጉሬን እያሻሸ ሁለተኛ አልመለስበትም ብሎ በስሜ እየማለ ቃል እንዲገባልኝ ፈልጌ ነበር….እሱ እቴ ዝም አለኝ….ደረቅ ወለል ላይ ብገላበጥ..እህህ ብል ምንም ጭራሽ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገብቶ ማንኮራፋት ጀመረ..
👍37
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አስራ_አምስት
///
ከጄኔራሏ ጋር የነበረን የጋለ የፍቅር መሳሳብ ቀስ  በቀስ እየተዳፈነ የጓደኝነት ቁርኝታችን እየጠነከረ መጥቶል፡፡ይሄን አይነት የስሜት  ለወጥ በመከሰቱ ልደሰት ወይስ ይክፋኝ እስከአሁን መለየት አልቻልኩም፡፡ ነግቶ ከእንቅልፌ ስባንን እሷ ከጎኔ ተኝታለች..እስክትነቃ ጠበቅኩና
"ደህና አደርሽ?" በሚል በአክብሮት በታሸ ለስላሳ ንግግር ተቀበልኳት፡፡
"አዎ ..ደህና አድሬያለሁ..ነጋ እንዴ?"
አዎ ነግቷል.. አታይውም እንዴ? በክፍላችን ብርሀን ተጥለቅልቆ ደሰ ሲል፡›
‹‹ብርሀን ብቻ ነው እንዴ ደስ ሚለው?››.
‹‹ጨለማማ ያው ጨለማ ነው ምኑ  ደስ ይላል?››
ጨለማ ያን ያህል አስፈሪ አይደለም።በድፍረት ላጣጣመው ጨለማ የራሱ ውበት አለው።ጨለማ ደግሞ ከብርሀን በላይ ፈጣን ነው።ሁል ጊዜ ብርሀን በጨለማ ቀድሞ የተያዘውን ግዛት አስለቅቆ ነው  አለሁ እዚህ ነኝ የሚለው።እኛም ወረተኛና ፍርደ ገምድል ስለሆን ኃላ ስላየነው አንፀባራቂና ደማቁ ብርሀን አጋነን እናወራለን እንጂ ቀድሞ ቦታው ላይ  የነበረውን ጨለማ ትዝ አይለንም፡፡
ከእሱ ማምለጥ ባንችልም  መሞከራችን አይቀርም።ደግሞ እኮ የብርሀኑ ውበትና ድምቀት ሙሉ ሆኖ የሚታየው በድቅድቁ ጨለማ ሰንጥቀን ማለፍ ሲችል ነው።ደግሞ ወታደር ብትሆን ለጨለማ ያለህ እይታ ይቀየር ነበር፡፡
‹‹እንዴት?››
‹‹ጨለማ ወሳኝ ወዳጅህ የሚሆንበት ብዙ አጋጣሚዎች ይኖራሉ...ከጠላት አይታ ከልሎ ህይወትህን ያተርፍልሀል….ከብርሀን በተሻለ መረጋጋተትና ትንፋሽ መውሰጃ ሰላማዊ እረፍት ዕድሎችን ያመቻችልሀል…ኦ እኔ ጨለማ ወዳለሁ…በተለይ ድቅድቅ ጨለማ፡፡
‹‹በስመአብ በይ››
‹‹አልኩ.. አሁን ስንት ሰዓት ሆነ?››
"ሁለት ሰዓት ሆኗል"
"ስራ ትገባለህ እንዴ?"
"ማታ አስራሁለት ሰዓት ነዎ..አንችስ?"
"እኔኮ ስራ የለኝም.?."
"አንድ ጄኔራል ለዛውም በዚህ ጊዜ..."

እጄን ያዘችና  ወደ ሆዷ ወሰደችኝ፡፡ ያሳረፈችኝን ቦታ ዳበስኩት፡፡  የታረሰ ቦይ መስሎ ያስታውቃል፡፡ ...ብርድልብስን ከነአንሶላው ገለጥኩና አየሁት እንብርቷን ከፍ ብሎ ወደታች በመውረድ ፓንቷ ውስጥ ድረስ የሚዘልቅ አስፈሪና ሰፊ ጠባሳ አለ፡፡
.‹‹..እስከዛሬ እንዴት ሳላየው?"
"አይኖችህ  መቀመጫዬ ላይ ነበር የሚንከባለሉት..ለዛነው ያላየኸው"
"እውነቴን ነው ..ማታ እንኳን እርቃንሽን ሆነሽ  ከስሬ ቆመሽ ነበር"
"ባክህ እንዳታየው በዘዴ ስለጋረድኩት ነው"
"ምን ሆነሽ ነው?"
"ቆስዬ ፡፡በጦርነቱ ላይ ቅስዬ ላለፍት ሶስት ወራት በከፍተኛ የህክምና ክትትል ጦርሀይሎች ተኝቼ ነበር...፡፡ገና ከወጣሁ አንድ ወር  አይሆነኝም..፡፡.አሁንም ከሆስፒታል ወጣው እንጂ ህክምናውን  ሙሉ በሙሉ አላጠናቀቅኩም ...በሳምንት አንድ ቀን ቼክአኘ አለኝ፡፡..እና በአጠቃላይ ከስራ ውጭ ነኝ፡፡
‹‹ስትድኚ ትመለሺያለሽ አይደል?››
‹‹ከዚህ በፊት እኮ ነግሬህ ነበር..መመለስ እንደማልችል ሀኪሞቹ ተስማምተው ፅፈውልኛል...መጀመሪያ ከፍቶኝ ነበር...ቆይቼ ሳስበው ግን ውሳኔውን በፀጋ ተቀብዬዋለሁ።››
"ይገርማል.. ታዲያ እንደዚህ ከፍተኛ ህክምና ላይ እያለሽ ነው እንደዛ አልኮል ስትጠቀሚ የነበረው ።››
‹‹አንድ ቀን ነው የጠጣሁት.. እሡኑም ቦርድ መውጣቴን የሠማው ቀን ..››..
"አረ ተይ...ከሰውዬሽ ጋር የመጣሽ ቀንስ..?"
"እ በቃ..የወታደር ነገር አንዳንዴ እንዲህ ነው...አየህ ከተወረወረ ቦንብ መሀል አምልጠህ የሚንጣጣ መትረየስ ሸውደህ፤ ታንክና ድሽቃ ሳይገልህ በህይወት ተርፈህ አሁን አልኮል በብርጭቆ ስለጠጣሁ ይገለኛል ብለህ ለማመን ይከብድሀል...እና መጠጣት እንደሌለብህ ብታምን እንኳን ትንሽ ከተበሳጨህ ወይም ድብርት ውስጥ ከገባህ እኔ እንዳደረኩት ታደርጋለህ...፡፡
"አሁን ቁርስ ልጋብዝሽ"
"የት እቤትህ ወስደህ"
"አረ እዚሁ ሆቴል"
"እቤትህ ስልህ ምነው ደነገጥክ...ሴትየዋ አለች እንዴ?"
‹‹አይ የለችም"ብዬ ስለጋሽ ሙሉአለም ታሪክ ስነግራት ማመን ነው ያቃታት።
"እሺ እኔ ቤት ሄደን እንዋላ"
"እኔ ቤት ...እዚህ አዲስ አባ ቤት አለሽ"
"አዎ ብዙም ባልጠቀምበትም ቤት አለኝ››
‹‹ታዲያ ቁርስ በልተን እንሂድ?..›
‹‹ምነው ቁርስ መስራት እትችልም አሉህ እንዴ?››
‹‹እስከዛ ይርብሻል ብዬ ነዋ;››
‹‹ለራስህ አስብ ..አንተ ወታደር እኮ ነኝ..አስርና ሀያ ቀን ያለምግብ ያሳለፍኩባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ...በል ተነስ ››አለችና …አልጋዋን ለቃ በመውረድ ልብሷን መለባበስ ጀመረች፡፡.
‹‹አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ››
‹‹ጠይቀኝ››
‹‹ስንት አመትሽ ነው?››
‹‹ምን?››ደንግጣ
‹‹አይ ለሌላ እኮ አይደለም….በዚህ ዕድሜሽ እንዴት ይሄ ሁሉ ብዬ ነው፡፡››
‹‹እስኪ ገምት ስንት እሆናለሁ?››
‹‹35››
‹‹ብዙም አልተሳሳትክም…10 ብቻ ጨምርበት፡፡››
‹‹የእውነትሽን ብቻ እንዳይሆን?››
‹‹ምነው አረጀሁብህ?››
‹‹አረ አቋምሽና ጠቀሽወ እድሜ ፈፅሞ አይመሳሰልም››አልኳት የእውነትም ተገርሜ፡፡
ትራስ አስቀምጣ የነበረውን ሽጉጥ አነሳችና የጃኬቷን የውስጠኛ ኪስ ውስጥ አስቀመጠች፡፡..እኔም ለብሼ ጨርሼ ስለነበረ .ተያይዘን ወጣን….ወደሆቴሉ የመኪና ማቆሚያ ፓርክ ነው የወሰደችኝ፡፡
.አንድ አይጣማ ቪታራ ጋር ስትደርስ ቁልፉን ከኪሷ አወጣችና ከፈተች.፡፡መኪና ይዛለች ብዬ ስላላሰብኩ ታክሲ ለመጥራት ስልኬን አውጥቼ ስልክ ቁጥር  እየፈለኩ ነበር…ፈገግ አልኩና ገቢና ገብቼ ቁጭ አልኩ፡፡ከመንቀሳቀሳችን በፊት ግን ስልኬ ጠራ…ጋሼ ሰለሞን ነው የደወልኝ፡፡ አነሳሁት፡፡
‹‹ሄሎ ጋሼ››
‹‹እዬብ የት ነህ?››ኮስተር ያለ ጥያቄ  ነው፡፡
‹‹ሆቴል ነኝ››
‹‹ቶሎ እቤት ና.. ፈልግሀለሁ›
‹‹እቤት ማለት.?››.ግራ ገብቶኝ ጠየቅኩ፡፡
‹‹.አንተ ቤት.. አባዬ አሞታል መሰለኝ››
‹‹መጣጣሁ መጣሁ›ስልኩን ዘጋሁት
‹‹ምነው ችግር አለ?…››
‹‹አያቴ ማለት  ጋሽ ሙሉአለም አሞቸዋል መሰለኝ .›መሄድ አለብኝ ይቅርታ››
‹‹…ላድርስህ?››
‹‹ምን ታደርሺኛለሽ…..ከዚህ ገቢ ቀጥሎ እኮ ነው ቤታችን..ደውልልሻለሁ›ተንጠራርቼ ጉንጯን ሳምኳት፡፡
‹‹በቃ ቸው›
ገቢናውን በር ከፍቼ ወጣሁ‹‹..ቁርሱ ደግሞ ለሌላ ቀን ይዘዋወርልኝ.››
‹‹በተመቸህ ጊዜ ደስ ይለኛል.. ነገም ተነገ ወዲያም.. ደውልልኝ…መጥቼ ወስድሀለሁ…፡፡››
እየሮጥኩ ወደቤት ሄድኩ፡፡
//
አያት መድሀኒት ከወሰደና ቀኑን ሙሉ ስንከባከበው ከዋልኩ በኃላ አሁን ከመሸ  ተሸሎታል፡፡በአካል ስሩ ባልሆንም ከግድግዳ ማዶ ሆኜ ደህንነቱን እንድከታተል በሀለቃዬ በአቶ ሰለሞን ተነግሮኝ የስራ ፍቃድም ተሰጥቶኝ ስራ አልገባሁም፡፡አሁን ከፍሌ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ከእንቅልፌ ጋር እየታገልኩ አያቴም በክፍሉ ውስጥ በተኛበት የልጅና የአባት ወሬ እያወራን ነው፡፡
‹‹አያቴ እርሶ እኮ ፃድቅ ኖት››ድንገት ነው ይሄ አረፍተነገር ከአፌ ሾልኮ የወጣው..ግን ደግሞ ለሽርደዳ ወይም ለማስመሰል አይደለም..የእውነትም ከልቤ እንደዛ ነው የማምነው፡፡
👍42👏21
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹አያቴ ዛሬ በጣም አዝኛለሁ…››

‹አይ አንተ ልጅ ..መቼ ነው ዛሬ ተደስቼያለሁ የምትለው….ደግሞ ምን ሆንክ?››

‹‹ስለልጅቷ ነግሬዎታለሁ አይደል?›

‹‹ሥለየቷ… ስለልጅህ እናት››

‹‹እማይደል… እኛ ሆቴል ስለምትመጣው››

‹‹እ. ጄኔራል ውሽማ አላት ያልከኝ››

‹‹አዎ…›

‹‹ምነው? ተተናኮላት እንዴ?››

‹‹አይ ነገሩ ወዲህ ነው…›

‹‹እንዴት..››

‹‹በቀደም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዕረግ እድገት ከሰጣቸው ጀኔራሎች መካከል አንዷ እሷ ነበረች››

‹‹ምን?››

‹‹አዎ ወታደር መሆኗን ሳላውቅ ..ጄኔራል ሆና አገኘኋት››

‹‹እርግጠኛ ነህ..በመልክ መመሳሰል ወይም መንታ እህት ኖሯት ይሆናል››

‹‹አይ አያቴ እንደዛ አይደለም..ማታ እቤት ከገባኁ ቡኃላ ሳይሰሙኝ ቀስ ብዬ ወጥቼ ወደሆቴል ሂጄ ነበር›

‹‹አንተ ቀልማዳ ምን ለመፍጠር…›

‹‹ቤርጎ ይዛ ስለነበረ አግኝቼ ልጠይቃት..እና እውነት መሆኑን አረጋጣልኛለች፡፡››

‹‹ታዲያ ይሄ ይደንቃል እንጂ ምኑ ያሳዝናል….እርግጥ ይገባኛል…አንተ የምታስበው ፍቅር እውን የመሆን እድል የለውም ብለህ ልታስብ ትችላለህ..እንደዘ ብታስብ አይገርምም፡፡ ማንም ባንተ ቦታ ቢሆን በተለየ መልኩ ሊያስብ አይችልም..ግን ማወቅ ያለብህ መቼም ቢሆን ፍቅር ምክንያታዊ ሆኖ አለማወቁን ነው፡፡እና በፍቅርና በጦርነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው›› የሚባለው ለምን ይመስልሀል፡፡ምንም ያልተገመተ እና ያልታቀደ ነገር መከሰት በፍቅርና በጦርነት ውስጥ ተደጋሞ የሚስተዋል እውነት ስለሆነ ነው፡፡

‹‹አያቴ ትክክል ኗት፤ እሱ እንዳለ ሆኖ እኔ ያዘንኩት ግን በአሁኑ ጦርነት ክፉኛ ተጎድታ ለሶስት ወር ሆስፒታል እንደነበረች ነገረችኝ…..››

‹‹ያሳዝናል….ድሮስ ከጦርነት ምን መልካም ዜና ይሰማል.››

‹‹አዎ እንደነገረችን ከሆነ ለአንድ ወር ሙሉ እራሷን አታውቅም ነበር..ከተንቤን በረሀ ተጭና አዲስ አበባ እስክትመጣ ..ኦፕራሲዬን ሲሰራላት ሁሉንም አታስተውስም…ጓደኞቾ እንደነገሯት አንጃቷ ሙሉ በሙሉ ተዘርገፎ ከተዝረከረከበት ተፋሶ ወደውስጥ ተመልሶ ነው ልትተርፍ የቻለችው  …

ጠባሳዋ ከእንብርቷ ከፍ ብሎ ወደታች  ከ20 ሴ.ሜትር በላይ ይረዝማል…እንደተነገራት ከሆነ ማህፀኗም ተቆርጦ ስለወጣ ከአሁን ወዲህ መውለድ አትችለም….. ለሀገሯ ደሞን ማፍስ ብቻ ሳይሆን …..››

‹‹በቃ በቃ ልጄ…በህይወት መትረፎም አንድ ተአምር ነው….ሌላው በሂደት የሚታይ ነው፡፡››

‹‹አያቴ እንዲህ መስዋዕት የሚከፈልላት ሀገር የምትባለው ጣኦት ግን ማን ናት?;›

ይህቺን ጥያቄ ለእሷ ብታቀርብላት እርግጠና ነኝ በእንባ ባቀረሩ አይነቾ በሞቀና በደመቀ ስሜት የሚያንሳፍፍ አይነት መልስ ልትሰጥህ ትችል ነበር፡፡እኔ ግን የተለመደው አይነት ቀና መልስ ልሰጥህ አልችልም ፡፡፡ልጄ እንደእኔ ሀገር ሀሳብ ወለድ ፅንሰ ሀሳብ ነው።ቋሚ እውነት አይደለም..ይጠባል ይሰፋል...ይለማል ፤ይፈርሳል ። ቢሆንም ከስነልቧናችን ጋር  ስር የሰደደ ትስስር አለው፤ምክንያቱም ዘሬ ምንለውን መንጋ ህዝብ አዝሎ የሚያኖርልን .. ሀይማኖቴ የምንለውን መንፈሳዊ ተቋም የሚያቅፍልን ...መከታዬ ብለን የምንመካበትን ወታደርና ፓሊስ    የሚያስገኝልን ….ተወልደን ያደግንበት ስፍራ ብቻ ሳይሆን ወልደንም የምናሳድግበት. .ዘርተን የምናጭድበት…ሞተንም የምንቀበርበት፤መታወቂያ እንጂ ፓስፖርት የማንጠየቅበት ስፍራ ነው፡፡
ሀገር በህይወት ጉዞችን በኑሮ ውጣ ውረዳችን ቀላል ትርጉም የለውም።ከሀገር በላይ ለእውነት የቀረበው  እቤታችን ነው..፡፡ .አዎ ሚስታችን የምታስተዳድረው...ልጇቻችን የሚያደምቁት .. የልባችን የመጨረሻ ማረፊያ የአካላችን የየእለት መገኛ ..አዎ ሀገርን እንደ እንቁላል ውሰዷት ...ቅርፊቱ የአገር የመጨረሻው ድንበር ማለት ነው ...፡፡ጠላት በቀላሉ የሚበረቅሰው የመጀመሪያው ከለላ...ከዛ የመሀሉ ነጭ ክፍል የመሀል ሀገር ..ወይም ዋና ከተማ በለው...አስኳሉ ግን እቤትህ ነው ...ሚስትና ልጇችህ ወይም እናትና አባትህ እናም ቤተሠብህ የሚኖርበት ቢላ ቤትም ሆነ ደሳሳ ጎጇ።ግን አጥቂ ጠላት ሲመጣ ገና ከሩቅ ቅርፊቱን እንዳይሸነቁር ነፍስህን አሲዘህ ትፋለማለህ...ደምህን ታፈሳለህ ከዛም ከጨከነ ህይወትህንም ትሰጣለህ...ምክንያቱም ከቅርፊት መሸንቆር በኃላ እንቁላሉ ነጭ ክፍል መዝረክረኩ አስኳሉም መፍረሱ አይቀሬ ነውና...እና ለሀገሬ ብለን ስንፍለም አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የምንለፋበት ዋናው ምክንያት ለገዛ  ቤታችን ደህንነት ነው...ለሚስታችንና ልጆቻችንን ለመታደግ ነው።
እስቲ የሀግርህን ሰው ተመልከት ቤት የሚሰራበት መሬት ሲመራ ቀድሞ አጥር ነው የሚያጥረው፡፡ ይህን የሚያደርገው  በቀላሉ ሰው ያለእሱ ፍቃድ አልፎ የማይገባበትን..እንስሳ ሳይቀሩ የማይደፍሩትን የግል ይዞታን ለመፍጠር ነው፡፡እቤቱ ቀስ ብሎ ይደርሳል ዋናው ግን ግዛትን ማስከበር ነው የሚል ሳያውቀው በውርስ ያዳበረው እውነት አለው፡፡
ተረታችን እንኳን ባለቤቱን ካናቁ አጥሩን አይነቀንቁ፡፡››የአንድን ኢትዬጵያዊ ግለሰብ አጥር ሄደህ መነቅነቅ ቀጥታ ሰውዬውን በዱላ ከመዠለጥ የተለየ ትርጉም አይሰጠውም…ህግ የመጣስ ሳይሆን  የክብር ጉዳይ ነው፡፡እና የሀገር ስሜት እንዲህ ከማንነታችን የተጋመደና የተወሳሰበ እሳቤ ነው፡፡እውነት ሆነ ሀሰባ ወለድ እሱ ብዙም ትርጉም የለውም፡፡ምክንያቱም አብዛኛው የሰው ልጅ የህይወት ፍልስፍና የተቃኘው በእውነት ላይ ሳይሆን በሚያማልሉ አፈታሪኮች ላይ ነው፡፡
‹‹ጋሼ…እሷም ከዚህ በላይ አታስረዳኝም…ግን ዋናው አሁን ምን ላድርግ ?አሳዝናኛለች››
‹‹አይ ልጄ…..ፍታ ያልኩህን ችግሮች ሳትፈታ ሌላ የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ተጎትተህ እየገባህ ነው፡፡ቢሆንም ይቅርብህ አደጋ ስላለው ሸሽተህ አምልጥ አልልህም….ህይወትን በመጋፈጠ እንጂ ሸሽቶ በማምለጥ ምንም የምታተርፈው ነገር የለም…ግን አንድ ነገር ልመክርህ እችላለሁ፡፡
‹‹ምን አያቴ …?››
‹‹ስራህ ቀይር››
‹‹ምን አያቴ?››
‹‹አዎ ከዚህ በላይ አስተኛጋጅ ሆነህ መቀጠልህ ህይወትህን ማባከን ነው የሚሆነው..ደግሞም አስተናጋጅ ሆነህ በቀጣይ እየመጣብህ  ያለውን የህይወት ፈተና ተታግለህ ለማሸነፍ ትቸገራለህ፡፡›
‹‹ትክክል ነህ አያቴ..ግን?››
‹‹ግን ምን?››
‹‹ሁለት ችግር አለብኝ..አንድ የሂሳብ ደብተሬ ውስጥ ያለው 70 ሺ ብር ብቻ ነው..በዛ ብር ደግሞ እራሴን ችዬ ምን አይነት ስራ መጀመር እንደምችል አላውቅም…?››.
‹‹ሁለተኛውስ?››
‹‹ሁለተኛውም..ጋሼ ነው….ጋሼ ለእኔ በጣም ባለውለታዬ ነው….እሱ ጎትቶ ባያወጣኝ ዛሬም እዛ ጎዳና ትኬት መኪና ላይ እየለጠፍኩ ነበር ምገኘው…በዛ ላይ አያቴ ከእርሶ መለየትም ዝግጁ አይደለሁም…››
‹‹እኔም ካንተ ለመለየት ዝግጁ አይደለሁም…ለዛውስ ስራ ቀይር አልኩህ እንጂ እቤቱን ለቀህ ወጥተህ ተንዘላዘል ወጣኝ….?.››
‹‹አይ ማለቴ?››
ይሄውልህ ስማኝ..ጋሼ ውለታ ምናምን የምትለውን እርሳው እኔ ነገረዋለሁ…ማለቴ ካለፍላጎትህ እንድትለቅ የፈለኩት እኔ እንደሆንኩ እነግረዋለው…ይሄውልህ ስማኝ እኔ እንደምታየኝ ሽማግሌ ነኝ…ለዛውም የከተማ ባህታዊ ሆኜ ባህት  የዘጋሁ…ምን ለማለት ነው ምንም ስራ የመስራት ፍላጎት የለኝም…ግን የተወሰነ ብር ደብተሬ ውስጥ አለ…እና አንተ ደስ የሚልህን ቢዝነስ አጥናና አምጣ እኔ ገንዘብ እሰጥሀለሁ…የጋራ ቢዝነስ እንመስርታለን ማለት ነው፡፡›
👍65👏3😁3🔥1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እንደተለመደው እቤቴ አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተዘርሬ በመተኛት ጣፋጮና ተወዳጇ ልጄ በቴሌግራም የላከችልኝን የእናቷን ዲያሪ በከፍተኛ ተመስጦና ውስጥን በሚሸረካክት የልብ ድማት ያለፈ ታሪኬን እያነበብኩ ነው፡፡
////
ማትሪክ በተቀበልን  በአንድ ወር ውስጥ  ለሰርግ ሽር ጉድ ተጀመረ..፡፡ለሠርጉ 15 ቀን ሲቀረው ጨነቀኝ..፡፡በረሽ ጥፊ ጥፊ..ወይም እራስሽን አጥፊ የሚል ስሜት ይተናነቀኝ ጀመር...፡፡እስቲ በፈረሰኛው በግድ  ካላገባሽ  እቆራርጥሻለሁ ብሎ ያስፈራራኝ ሰው የለ... ሁሉንም ያደረኩት በራሴ ፍቃድና ምርጫ ነው። እንደውም ቤተሠቦቼ በዚህ ሀሳብ እንዲስማሙ ለማሳመን ብዙ ነገር ቀባጥሬ ነበር...እና ታዲያ  ?የቁርጡ ቀን ሲመጣ ምነውሳ...?ዋናው ጉዳይ ከእዬቤ እንዴት አድርጌ የምር እለያለሁ ?የሚለው ሀሳብ ነው እረፍት የነሳኝ....፡፡ እርግጥ አውቃለሁ ወደ ጋብቻው የገባሁበት ዋና አላማ ከእዬብ ለመራቅ ከአምላክ የተላከ ልዩና ረቂቅ ዘዴ አድርጌ በደፈናው ተቀብዬው ነበር እንጂ ዝርዝር ጉዳዬች ላይ በደንብ  ያሰብኩባቸው አልነበረም። ይታያችሁ ባል ካገባው እኮ አብሮ ማደር ከዛም ያለፈ ነገር ማድረግ የግድ ነው ፡፡ በህልሜም ሆነ በእውኔ ከእዬብ ገላ ውጭ የወንድ ገላ  ታስቦኝ በፍፁም አያውቅም።የሚገርመው እናትና አባቴን ጨምሮ የቤቱ ሰው ሁሉ በደስታ ሰክሮ ለድግሱ መሳካት ጠብ እርግፍ ሲል እዬቤ ግን ልክ  እንደእኔ በተመሳሳይ ሁኔታ ድባቴ ውስጥ ገብቶ ነበር።አሳዘነኝ።እሱም እንደ እኔ ያፈቅረኝ ይሆን እንዴ?ለመጀመሪያ ጊዜ በአእምሮዬ የተሠነቀረ አስደሳች ጥርጣሬ ነበር ፡፡

ለማንኛውም የሰርጉ ቀን ደረሰ በተክሊል ስለምንጋባ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ለሊት ስምንት ሰዓት ነው ቤተክርስቲያን የሄድነው። ግን በተክሊል እንዴት ልንጋባ ወሰንን? እርግጥ ሀሳብን ቀድሞ ያቀረበው መስፋን ነው።ግን እኔም ያለምንም ማቅማማት ነበር እሺ ያልኩት ፡፡ለዚህም ምክንያቴ በዋናነት ሁለት ነው። አንደኛው በተክሊል መጋባት ጋብቻውን ጥብቅ ስለሚያደርገው ወለም ዘለም የሚለውን ልቤን ያቃናልኛል ወይም መስመር ያስገባልኛል ብዬ ስላመንኩ ነው።ሁለተኛው ብዙ የሠንበት ት/ቤት ጓደኞቼ በተክሊል ሲያገቡ ሚዜም ሆነ አጃቢ ሆኚ አይቼ ስለነበረ እኔም አንድ ቀን እንደዚህ አገባ ይሆን የሚል የተደበቀ ምኞት በውስጤ ስለነበረ ያንን ምኞቴን ለማሳካት ያገኘሁትን እድል ለመጠቀም ነበር።

ስርዓቱም ከቅዳሴው ጥዋት ሶስት ሰዓት ተጠናቀቀ።በሰንበት ት/ቤት መዘምራን የሠርግ መዝሙር በመታጀብ ወደ የቤታችን ሄድን።እንግዲህ  ምሳ ሰዓት ላይ ሙሽራው ከሚዜዎቹና አጃቢዎቹ ጋር መጥተው እስኪወስድን የተወሰነ ለማረፍና ለመዘገጃጀት የሚሆን ጊዜ ይኖረናል ብዬ ነው።እቤት ከገባን በኃላ ትንሽ ለማረፍ ሞከርኩ እንቅልፍ ሊወስደኝ ግን አልቻለም፡፡ ተነሳሁና እየተኳኳሉና እየተቆነጃጅ ካሉት ሚዜዎቼ ጋር ተቀላቀልኩ።እኔም መዘገጃጀት ስላለብኝ ያሳምሩኝ ጀመር...፡፡ሁሉም ደስተኛ ይመስላል... የተከፈተ ጥርስ..የፈገገ ፊት...በማይክራፎን የተለቀቀ መዝሙር እኔ ግን ቅር እንዳለኝ ነው ።ከቤተ ክርስቲያን መልስ ጀምሮ እዬቤን አላየሁትም።የት ገባ?ከአሁኑ በጣም ነው የናፈቀኝ።እህቴን ጠራኋትና ጠየቅኳት..እንዳላየችው ነገረችኝ።ሌላ የምትሰራውን ስራ ሁሉ ትታ እሱን ፈልጋ እንድትጠራልኝ ጠየቅኳት...ሌላ ቀን ቢሆን የራስሽ ጉዳይ ነበር የምትለኝ።በእለቱ ግን ያው የቤቱ ንግስት ነኝና  ጥያቄዬን በእሺታ ተቀብላ ልትፈልገው ወጣች።

15 ከሚሆኑ ደቂቃዎች በኃላ ይመስለኛል እየተጎተተ በግድ የፈገገ ግን ደግሞ የዳመነ ፊቱን ይዞ መጣ..ሴቶች የሞሉበትን ክፍል በራፍ ላይ ቆሞ አንገቱን ወደውስጥ አስግጎ  ‹‹ሪች ፈለግሺኝ" ሲል ጠየቀ….ገና ድምፁ ጆሮዬ ከመድረሱ ሰውነቴ በጠቅላላ ነዘረኝ፡፡

‹‹አዎ ግባ››

‹‹ወዴት ልግባ..?››

‹‹ጥፋሬን ቀለም እየተቀባሁ ስለሆነ እኮ ነው..ግባ የማታውቀው ሰው የለም "ብዬ አደፋፈርኩት፡፡ገባና ወደእኔ ቀረበ..እንዲቀመጥ ኩርሲ ከጎኔ አስቀመጥኩለት እያቅማማ ተቀመጠ።እዛች ክፍል ውስጥ የተጠቀጠቁት ሴቶች ጆሮና አይን በጠቅላላ እኛ ላይ እንደሰፈረ አውቃለሁ። ቢሆንም ምርጫ የለኝም።ድምፄን ቀነስ አድርጌ በሹክሹክታ መጠን

"የት ጠፍተህ ነው? ናፈቅከኝ እኮ"አልኩት

"ደክሞኝ ተኝቼ ነበር"

"የት?"ይህንን ጥያቄ የጠየቅኩት የእኔና የእሱን የጋራ ክፍል አሁን እያተረማመሰነው ስለሆነ ብዬ ነው፡፡

"እቴቴ ክፍል"

"አይንህ ግን ምንም የተኛ ሰው አይን አይመስልም"
እንደዛ ያልኩት አይኑ በርበሬ ይመስላል እንደሚባለው ቀይ ሆኖ ስለደፈራረሰ ነው።

"ተኝቼ ነበር እኮ አልኩሽ...አሁን ለምን ፈለግሺኝ?"ቆጣ አለ፡፡

"አትቆጣኛ"

"አልተቆጣሁሽም"

"አብረኸን ትሄዳለህ አይደል?"

ደንግጦ"የት?"

ለእሱ መልስ ከመመለሴ በፊት ‹‹ተነሡ ተነሱ ሰርገኛው ደረሰ ተዘጋጅ ..››የሚል የማንቂያ ድምፅ ከውጭ ተሰማ…ትርምስምስ ተፈጠረ... የእሱን አደነጋገጥ እስከዛሬም በፊቴ ላይ አለ።በርግጎ ተነስቶ ፊቴ ተገተረ...እኔም ተነስቼ ቆምኩ።ተጠመጠምኩበት..ጭምቅ አድርጎ አቀፈኝ።እንባዬን ዘረገፍኩት እሱም ተንሰቅስቆ ማልቀስ ጀመረ።ሊያላቅቁን መሀላችን ገቡ።

‹‹አረ ቆርበሽ እንዴት ታለቅሺያለሽ?››

"አገባች እንጂ አልሞተች… የምን ሟርት ነው?።››

"አረ ተው ነውር ነው።››
ሁሉም የመሰለውን ተንጣጣ...አላቀቁን ።እዬቤ ተስፈንጥሮ ክፍሉን ለቆ ተፈተለከ።ከፋኝ ።በጣም ከፋኝ።ፈፅሞ ጥሎኝ እንዲሄድ አልፈለኩም ነበር።እጥፍጥፍ አድርጌ ጡቶቼ መሀከል ከትቼ በየሄድኩበት ይዤው ብሄድ  ደስተኛ ነበርኩ።..የምሳ ፕሮግራሙ ሲካሄድም ሆነ እኛ ቤት የነበረው  ዝግጅት ተጠናቆ ከእኛ ቤት ወጥተን ስንሄድ አይኔ ቢንከራተትም እዬቤን ዳግመኛ ሳላየው ነበር የእናትና አባቴን ቤት ለዘላለም በሚመስል  መንገድ ለቅቄ  በቅርብ ከተዋወቅኩት እና በቅጡ እንኳን ያለመድኩትን ሰው ተከትዬ የሄድኩት።

ሙሽራው ሙሽሪት..እንኳን ደስ ያላችሁ
የአብርሀም የሳራ-ይሁን ጋብቻችሁ።

እንደዛ እንደዛ እያለ ሰርጉ ተጠናቀቀ ..መሸ ጫጉላ ቤት ገባን ..እግዚያብሄር ይመስገን ፡፡ በተክሊል ስለተጋባንና በእለቱም ስለቆረብኩ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድም ነበርና አንድ አልጋ ላይ ብንተኛም ሰውነታችንን እንኳን ሳናነካካ ተራርቀን ተኛን ፡፡የሁለት ቀን የተጠራቀመ እንቅልፍ ስለነበረብኝ የት እንዳደርኩ አላውቅም ነበረ ።የሚገርመው ጥዋት እንደነቃሁ በእጆቼ የሞጨሞጩ አይኖቼን እያሻሸው"እዬብ ነጋ እንዴ?"ብዬ ነበር ጠየቅኩት ።ደግነቱ ክፍል ውስጥ ማንም ስላልነበረ የሰማኝ ሰው አልነበረም። እንደምንም አልጋዬን ለቅቄ በመውረድ ልብሴን እየለበሰኩ ሳለ በሩ ተከፈተና መስፍኔ ገባ፡

"እንዴ ተነሳሽ እንዴ?"ዝም አልኩት።

"ምነው አመመሽ እንዴ?"አለኝ ወደእኔ እየተጠጋ።

ጭራሽ እየታገልኩት የነበረውን ስሜቴን ነቅንቆ አደፈራረሠው...እንባዬን ዘረገፍኩት።

"እንዴ ምነው?ምን ተፈጠረ?"

"እዬቤ"

"እዬቤ ምን ሆነ?››
👍767🥰1😢1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////

ከጋሽ ሙሉ አለም ጋር ከተነጋገርን በኃላ አዎጪ ስራ ለመምረጥ ያልበረበርኩት ዌብ ሳይት ያላማከርኩት የቢዝነስ ሰው...በሰበብ አስባብ ያልጎበኘሁት የንግድ ተቋም የለም።ምንም ግን ልቤን እርግጥ አድርጎ ሞልቶ በቃ ይሄንን ነው ብዬ እንድወስን የሚያደርገኝ ስራ በቀላሉ ማግኘት አልቻልኩም። ሰው ደግሞ አላውቅም የሚለው ነገር የለውም፡፡ ትንሽ መንገድ ካሳዪት በማንኛውም ነገር ከኤክስፐርት በልጦ ይቦተረፈዋል።

"እኔነኝ ያለ አሪፍ ቡቲክ ብትከፍት በጣም ትርፋማ ነው የምትሆነው...በተለይ የሴቶች ካረከው ትርፍህ ባለሁለት ስለት ነው የሚሆነው..እነዚህ የሀብታም ቺኮችን ገንዘባቸውንም ውበታቸውንም እጥብ ነው የምታደርገው...››እንደዚህ የመከረኝ ጎረምሳ  ነጋዴ እንዳይመስላቹሁ  የአምስት ልጆች አባትና ባለሁለት ቀለም ፀጉር ባለቤት የሆነ አዛውንት ነው።
"ለምን ማሳጅ ቤት አትከፍትም›› ያለኝ ሰውም አለ...
"በአሁኑ ጊዜ አዎጪው ስራ ድለላ ነው፡፡ ፍቃድ አውጣና የውጭ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ብትሆን አሪፍ ትሸቅላለህ..በጎንም ቤት መደለል ፤:መኪና መደለል ፤ሴት መደለል አይነት አዋጪ ስራዎችን ትሰራለህ

የሪል እስቴትና የባንክ ቤት ኤጀንቶችም "ከሰርኩ አልከሰርኩ እያልክ ምን አጨናነቀህ፡፡ በገንዘብህ አክሲዬን ግዛበት.፡፡ አንተ ዘና ብለህ በየአመቱ በምትዝቀው የትርፍ ድርሻ ብቻ  ዘና ብለህ መኖሮ ነው››ብለውኛል
"በአጠቃላይ በሰሞኑ ውጣ ውረዴ የተረዳሁት አንድ ነገር ቢኖር ከዚህ በፊት ስራ ለመጀመር ትልቁ መስፈርት መነሻ ካፒታል ማግኘት ብቻ ነበር የሚመስለኝ፤ለካ መጀመሪያ አውጥተን አውርደን ይሄንን ስራ በዚህ አይነት ሁኔታ  እንሰራለን የሚል ቢያንስ መነሻ የሚሆን ሀሳብ በውስጣችን ከሌለን  ገንዘቡ ቢኖር እንኳን  ትልቅ እራስ ምታት ውስጥ ነው የምንወድቀው ?
ስዞር ውዬ ደክሞኝ ወደቤት ገባሁና አልጋዬ ላይ በቁሜ ወደቅኩበት ...ተንሳጠጠ፡፡

"ጎረምሳው ቀስ..."

"አያቴ...ደክሞኛል"

""የትኛውን ተራራ ወጥተህ ነው ይሄ ሁሉ ማለክለክ?"

"አረ ተራራ መውጣት ይሻላል...ሰው የሚሰራበት ገንዘብ ለማግኘት ይባክናል እኔ የምሰራው ስራ ማሰብ ና መወሰን ያቅተኝ።አረ ምን አይነት ቀሺም ነኝ?››

"እንኳንም አቃተህ"

"እንዴት አያቴ?"

"አየህ ተጨንቀህ ተጠበህ ያፈለቅከው ሀሳብ ጥልቀትም ውጤትም ይኖረዋል።"

"አይ አያቴ እስከአሁን ምንሞ የረባ ሀሳብ ላይ አልደረስኩም እኮ...የማማክረው ሰው ሁሉ ሺ ሀሳብ ነው የሚሰጠኝ...አንድ አሪፍ ነው ይሄን ስራ ጀምር ብሎኝ አሳምኖኝ ዞር ስል ሌላው ደግሞ ያንን ስራ ተሳስተህም ቢሆን እንዳትጀምረው አገርምድሩ የከሰረበት ስራ ነው ብሎ ኩም ያደርገኛል።

"እንደዛ ከሆነ ከማንም ምክር መጠየቅ አቁም.."

"ማለት?"

"ስለቢዝነስ መሠረታዊ ግንዛቤ ለማግኘት ይሄው በዚህ 15 ቀን ውስጥ የጠየቅካቸውና ያማከሩህ ሰዎች ከዩቲዩቨ እያወረድክ ያየሀቸው ቨዲዬዎች በቂ ናቸው"

"እና ምን ላድርግ?"

"እየሠማሀኝ አይደለም እንዴ ..?ምክር መጠየቅ አቁም እያልኩህ እኮ ነው"
"አያቴ ደግሞ… እርሷ እኮ ሌላ ሰው አይደሉም የቢዝነስ  ፓርትነሬ ኗት"

"ቢሆንም ስራአስኪያጅና  ፈላጭ ቆራጩ አንተ ነህ"

"አያቴ ደግሞ..እሺ የመጨረሻ ምክር ከእርሶ ልወሰድና ከዛ ያሉኝን አደርጋለሁ።››

"እንደዛ ከሆነ ሶስት ምክር ልስጥህ "

‹‹ደስ ይለኛል"

"1 አንተ የተሻለ ግንዛቤ ወይም እውቀት ባለህ የስራ ዘርፍ ብትሰማራ ተመራጭ ነው።ቀጥረህ የምታሠራው ስራ ቢሆን እንኳን ለመቆጣጠር የተወሰነ ግንዛቤና እውቀት ሲኖርህ  ውጤታማ ይሆናል፡፡

2/የምትወደውና የምትደሰትበት...ትርጉም የሚሰጥህ ስራ ቢሆን የግድ ባይሆንም የተሻለ ነው"..ኢንጂነር ኮንትራክተር እንደሚሆነው...የህክምና ዶክተር ክሊኒክ እንደሚከፍተው ማለት ነው

3/ኪሳራ የሚባል ነገር  ከአዕምሮህ አውጣ...ፍፅም ኪሳራ የሚባል ነገር በህይወት የለም ..ይህ የመጀመሪያ የቢዝነስ ስራህ ነው፤ አሁን የምትጀምረውን ስራ ለሁለት አመት ከሰራህ በኃላ  ከስረህ ብትዘጋው ያጣሀው ገንዘብ ነው ግን ከፍተኛ ልምድ ታካብትበታለህ… ቀጣይ ስራ ሀ ብለህ ለመጀመር እንደአሁኑ ድንብርብርህ አይወጣም...በል አሁን ተኝተህ አስብ››

"እሺ አያቴ አመሰግናለሁ "

ይሄንን ከተነጋገርን ከአራት ቀን በኋላ የሚገርም አጋጣሚ ተከሰተ፡፡ አንድ አለማያ አብረን የተማርን የቢሾፍቱ ልጅ ነበር..ከዛ እንደወጣ ወላጆቹ የችግኝ ስራ ይሰሩ ስለነበር እሱም ተቀላቀላቸውና መስራት ጀመረ..ሞያው ስለሆነ በሁለት አመት የሚገርም ለውጥ አመጣ ፡በሶስተኛው  አመት 2 ሺ ካሬ  መሬት ተከራይቶ ...የተለያዩ የአበባ አይነቶች ፤ለግቢ ውበት ማስጌጫ ተክሎች፤ ለምግብ የሚሆኑ አትክልቶች  መንጎ፤ፓፓያ ፤አቡካዶ በስፋት አምርቶ ማቅረብ ጀመረ…

የዘንድሮውን ምርትም ለገበያ ለማቅረብ ሁለት ወር ሲቀረው  የውጭ እድል አገኘና  ጠቅላላ ልማቱን ባለበት ለመሸጥ ገዢ በማፈላለግ ላይ እንደሆነ ሰማሁና ደወለኩለት ..፡፡እርግጥ ከአንድ ሰው ጋር ተነጋግሬና ተስማምቼ ነበር፤ ቢሆንም.እኔ ስራውን ለሚያውቅና ለማውቀው ሰው መሸጤ ነው በጣም የሚያስደስተኝ…የአትክልት የማልማት ስራ ልጅ ከማሳደግ ጋር የሚያመሳስል ነገር አለው…ዝም ብሎ ብር የማግኛ ስራ ብቻ አይደለም…የተቀዳደደ እና የተቦተራረፈውን  የተፈጥሮ ልብስ በጥንቃቄ የመስፋትና የማደስ ፤ እፍረቷንም የመሸፈን ስራ ነው፡፡ ..ግን ትንሽ ተወደደብኝ ካላልክ.. እርግጥ ከሁለት ወር በኃላ ብሸጥ አገኘዎለሁ ካልኩት ብር  ከግማሽ በላይ ቀንሼ ነው የምሸጠው አለኝ
"መጀመሪያ ልየው አልኩት፡፡በፈለከው ሰአት ቢሾፍቱ ናና ደውልልኝ አለኝ..ጊዜ ሳልፈጅ እየበረርኩ ሄድኩና  አየሁት  ..ከገመትኩት በላይ በጣም ማራኪና አስደማሚ ሆኖ አገኘሁት ...እሱም በቦታው ላይ ስራ ከሁለት አመት በፊት  ሰራ ሲጀምር እንደዚህ አይስፋ እንጂ የተወሰነውን ባለበት ከሰው ገዝቶ እንዳስፍፍው አስረዳኝ ..በተቻለኝ መጠን ፎቶም ቪዲዬም አነሳሁ።አንዳንድ  ብቻውን በመኪና ተጭኖ ሄዶ ሲተከል መለስተኛ ዛፍ የሚሆንና ከ10 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ በርከት ያሉ ዛፎች ያሉበት ነው። ዎጋውን የአምስት ወር ከተከፈለበት የመሬት ኪራይ ጋር 350 ሺ ብር አለኝ።  ከሸሪኬ ጋር ተማክሬ በአንድ ቀን ውስጥ አሳውቅሀለሁ ብየው   ወደአዲሳባዬ ተመለስኩ።

እቤት እንደደረስኩ .."አያቴ"
"አቤት መጣህ..የት ጠፍተህ ነበር?"
"የሆነ ቦታ ሄጄ ነበር፡፡ ቀላል እቃዎችን በምንቀባበልበት  ስንጥቅ እጄን አሸልኬ""እንኩ ይቀበሉኝ"
"ምንድነው...?ሞባይልህን ምን ላድርገው?።››
"አሁን ትክክለኛ የምንሰራውን ስራ ያገኘው ይመስለኛል...እስኪ ቪዲዬውንም ፎቶዎችንም ይዩት"
"ከተቀበሉኝ በኃላ..ለ15 ደቂቃ ንግግር አልነበረም... ዝም ማለታቸው ያልጣማቸው ነገር ስለአለ ነው ብዬ ደነገጥኩ .. ፈራሁም።ምክንያቱም ስራውን በጣም ከልቤ ነው የፈለኩት.ደግሞም በሙሉ የራስ መተማመንና በዕውቀት የምሰራው ስራ ነው….ይሄ ግን ለእሷቸው ካልተገለፀላቸው የእኔ መሻት ብቻ ዋጋ የለውም፡

"ለዚህ እኮ ነው የምወድህ?"

"ምን አሉኝ አያቴ?"

"ውብ የሆነ  ስራ መርጠሀል"

"ወደዱት..ልጁ ጓደኛዬ ነው ማለት አለማያ አብረን ነው የተማርነው ..አሜሪካ የመሄድ እድል ስላገኘ ባለበት ሊሸጠው ነው የፈለገው። ሌላ ሰው ሊገዛው ጠይቆታል እሱ ግን ሰውዬው የሰጠኝን ምትከፍለኝ ከሆነ ላንተነው መሸጥ የምፈልገው ብሎኛል››
👍734👏1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ልጄ ስልክ ደውላልኝ  እያወራኋት ነው፡፡

‹‹አባዬ እንዴት ነህ?››

"አለው የእኔ ማር ትምህርት እንዴት ነው?።››

"ትምርት ጨርሰናል አላልኩህም..እሁድ የወላጆች በአል ነው..ካርድ ይሰጠናል።››

‹‹በእውነት ደስ ሲል.."

"አዎ !!ቲቸር ደግሞ ተሸላሚ ስለሆንሽ ወላጆችሽ  እንዳይቀሩ አለችኝ...ለእቴቴ ስነግራት ‹ጎበዝ ልክ እንደአባትሽ ብሩህ ጭንቅላት ነው ያለሽ› አለችኝና አለቀሰች።"

እንባዬን መቆጣጠር ተሳነኝ...ያለፍቃዴ  እየተንጠባጠበ ነው።

"አባዬ ምነው ዝም አልከኝ ?"

"ልጄ ደስ ብለኸኝ እኮ ነው ... እና ማነው አብሮሽ የሚሄደው...?››

"እቴቴና አክስቴ ትልቆ አብረንሽ እንሄዳለን ብለውኛል...ደግሞ እቴቴ ቆንጆ ቀሚስና ጫማ ገዝታልኛለች ..."

"አሪፍ ነው ...እናትሽ  ጀግና ልጅ እንዳላት ሰምታለች?"

"አዎ ….በቀደም በእስካይ ፒ  ስናወራ ነገርኳትና ..ከሀይስኩል በኃላ እዚህ አሜሪካ ነው ምትማሪው አለችኝ"

"እና ምን አልሻት ..?.ደስ አለሽ?"

"አይ አላለኝም..እኔ አባቴን ፈልጌ ሳላገኘው  አንቺ ጋር መምጣት አልፈልግም .. ከፈለግሽ አንቺ ነይ  አልኳት..."

ደንግጬ"እና ምን አለችሽ?"
"ከየት አባሽ ነው ፈልገሽ የምታገኚው...?በህይወት መኖሩን እራሱ እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚችል ሰው  የለም ።"አለችኝ

እኔ ደግሞ‹‹ እኔ ልጅ ስለሆንኩ ይታወቀኛል በቅርቤ አለ...በጣም እንደሚወደኝም አውቃለሁ›› ስላት ተበሳጨችና ዘጋችብኝ።››

"አትቀየሚያት …እኔ ዝም ብያት ስለጠፋሁ እስከአሁን እንደተናደደችብኝ ነው።››

"አይ አውቃለሁ.. ከዛ እኮ ቆይታ ደውላ ይቅርታ ጠይቃኛለች ..ወደፊት እመጣና አብረን እንፈልገዋለን አለችኝ"

"የእውነትሽን ነው ..አራሷ እንደዛ አለቺሽ?"

"አዎ …ቃል ገብታልኛለች...ሁኔታዎችን አመቻችቼ  ረጅም ፍቃድ ወስጄ እመጣና እንፈልገዋለን …በህይወት ካለ እናገኘዋለን..››አለችኝ፡፡

‹‹አና አንቺ ምን አልሻት?››
"እማዬ አንቺ ብቻ ነይ እንጂ ፈልገን አናገኘዎለን...በልቤ ይታወቀኛል።"አልኳት፡፡

‹‹ልጄ በጣም ነው የምኮራብሽ...እና ለሚመጣው አመት እንደአሁኑ ተሸላሚ ከሆንሽ እንደምንም ብዬ ከጎንሽ እገኛለሁ!››

"አባዬ ›

ወዬ ልጄ..?

‹‹ቻው እማዬ የላከችልኝን ፎቶዋን በቴሌግራም ልኬልሀለሁ.. ከናፈቀችህ  ብዬ ነው"

‹‹እሺ የእኔ ልጅ አመሠግናለሁ..ሰሞኑን ደውይልኝ።››

"እም ጶ… የእኔ ውድ አባት እወድሀለሁ።"ስልኩ ተዘጋ፡፡ የእኔም አንደበት ተዘጋ..

."የፈጣሪ  ያለህ!!እኔ ምን አይነት እድለኛ ሰው ነኝ...፡፡ምን አይነት እንደስሟ ተአምር የሆነች ልጅ ነው የሠጠኝ?።እሷ በመወለዷ ምክንያት ህይወቴ ተሠነካከለ ብዬ ለረጅም ጊዜ በማሰብ ሳማርር ቆይቼ ነበር ..፡፡ግን አሁን ለዚህች በረከት ለሆነች ልጅ ከዚህ በላይ መከራና ስቃይ ቢቀበሉላት የማታስቆጭ ልጅ ሆና በማግኘቴ ደስተኛ ሰው ሆኜያለሁ።

ይቀጥላል..
👍8117🥰11👏2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


ስበሳጭ ጀርባዬን ይበላኛል...የበላኝን ቦታ ለማከክ እጄን በወገቤ አዙሬ አሽከረክራለሁ፤ ግን ደግሞ አልደርስበትም.. በትከሻዬ በኩል  አጠማዝዤ ሞክራለሁ፤ ትርፉ ድካም ነው። ከእከኬ ስቃይ እራሴን ለማስታገስ እገዛ መፈለጌ ያበሳጨኛል ደካማነቴንና ማድረግ የማልችላቸው ነገሮች ብዛት ያስጨንቀኛል...ጀርባዬን በላኝ እከኩልኝ ብዬ የሰው እገዛ ላለመጠየቅ ልብሴን አወልቅና ከሻካራ ግድግዳ ጋር እራሴን አፋትጋለሁ... ቢያቆስለኝም ያስተነፋሰኛል። ቢያንስ ገበናዬ ጠብቄያለሁ፡፡
አለመቻሌንም በሚስጥር በውስጤ አፍኜ ይዘዋለሁ፡፡አዎ አንዳንዴ ህይወት በዛ መጠን ትጨክንብኛለች በዛ መጠንም ታሰቃየኛለች፡፡
ዛሬ እርግጥ አልተበሳጨሁም ፤ግን ደግሞ በጣም ተጨንቄያለሁ፡፡ ጊዜው ጨለምለም ብሎል...አንድ ሰአት ከሩብ አካባቢ ነው›፡፡ ጀማሪ ማፊያ ይመስል ተጀባብኜ ወደሰፈር ተጠጋሁ...፡፡

እየተንቀጠቀጥኩ ነው ፡፡መቼስ ብርድ ብቻ አይመስለኝም እንደዚህ ውስጤ ገብቶ እያንቀጠቀጠኝ ያለው ።ኳስ እንጫወትበት የነበረው ሜዳ ባለአራት ፎቅ ህንፃ ተገማሽሮ ቆሞበታል። መቼስ ደፍረው ጠጠርና አሸዋ አምጥተው የሠፈሩ ሰው እያየ ሲሚንቶ አውርደው ፤ቀስበቀስ የገነቡት ሳይሆን ድንገት ከእለታት በአንድ ቀን ሁሉም የሰፈር ጎረምሳ ሆነ አሮጊት መተኛታቸውን አረጋግጠው ከሆነ ቦታ ጭነው መተው የተከተሉት ነው የሚመስለው። ወደቤታችን አየተቃረብኩ ስመጣ እግሬ እየተሳሰረ አስቸገረኝ፤ መራመድ ሁሉ አቃተኝ።
የውጩ ፍሬንች ዶር በአዲስ ከመቀየሩ ውጭ ቤታችን  ከውጭ ያለው እይታ በፊት እንዳነበረ ነው።አለፍ ብዬ ሄድኩና ኮርነር ጋር ስደርስ ጨለማን   ተገን አድርጌ ቆምኩ፡፡ ፊቴን ወደ በራፋችን አነጣጠርኩ

፡፡ ...ምንድነው የምጠብቀው..?.ማን እንዲወጣ ወይ ማን እንዲገባ ነው  ? ልጄን አሁን የማየት እድል አለኝ ይሆን?በዚህ ጨለማ ምን ልትሰራ ትወጣለች...?ምን አልባት አክስቴ...አዎ ምንአልባት እሷን ነው ላይ የምችለው...፡፡ባላናግራትም ላያት ምኞቴ ነው፡፡ ሶስት ሰአት ድረስ እዛው በቆምኩበት ደንዝዤለሁ… የጨው ሀውልት እንደሆነችው ልክ እንደ ሎጥ ሚስት  እኔም የበረዶ ሀውልት ከመሆኔ በፊት ወደ ሆቴሌ  ልመለስ ወስኜ እግሬን ሳንቀሳቅስ ስልኬ ተንጫረረ ።በደነዘዘ እጄ አወጣሁና አየሁት ..የደዋዪን ማንነት ሳይ ከሰውነቴ ላይ በረዶ የሠራው ቅዝቃዜ  በቅፅበት የረገፈ ይመስል ሙቀት ተሠማኝ ።ልጄ ነች።እንዴ አይታኝ ይሆን እንዴ? ዙሪያ ገባዬን ተገላምጬ  ተመለከትኩ።ምንም የለም፡፡ስልኩን አነሳሁት

"ሄሎ የእኔ ልዕልት"

"አባዬ እንዴት ነህ..?ምን እየሠራህ ነው?"

"ስለአንቺ እያሰብኩ"

"ታድዬ" ታድዬ አባባሏ  ልቤን ስንጥቅ አድርጎ  ቃላቱ በስንጥቁ እየተንጠባጠበ ወደውስጤ ሲዘልቅ ተሠማኝ።

"ምን  እየሠራሽ ነው...?ነገ ዝግጅት ስላለብሽ በጊዜ አትተኚም እንዴ?

"እነቴቴ እንደዛ ብለው አጠፋፍተው በጊዜ ተኙ።እኔ ግን ክፍሌ ከገባሁ ብኃላ ከመተኛቴ በፊት  መስኮቴን ከፍቼ ጨረቃን ሳያት አንተ ትዝ አልከኝ...እና ደወልኩልህ"

ቀና ብዬ ምትላትን ጨረቃ አያየኋት… ግማሽ ቅርፅ፤ግማሽ ውበት፡፡
"ልጄ እውነትሽን ነው ..ታምራለች"
"ማን ነች የምታምረው አባዬ"

"ያልሻት ጨረቃ ነቻ..አይኖቼን አንጋጥጬ እያየኋት ነው… ግማሽ ብትሆንም ልክ እንደአንቺ ታምራለች"

"አባዬ ዛሬ ከጎኔ ሆነህ እቅፍ አድርጌህ ብተኛ ደስ ይለኝ ነበር"

"እንግዲያው መስኮቱን ክፍት አድርጊና ለጥ በይ ..እኔ በርሬ እመጣና በመስኮት ክፍልሽ ገብቼ  እቅፍ አደርግሻለሁ..ግን ከተኛሽ በኃላ ነው የምመጣው"

"አባዬ ደስ የሚል ጫወታ ነው ...በቃ ሳልዘጋው ነው የምተኛው..ነገ ከዝግጅቱ በኃላ ደውልልሀለሁ.ወድሀለሁ።››

"እኔም ወድሻለሁ "ስልኩ ተዘጋ..

የእኔም ወደሆቴሌ የመመለስ አፒታይቴም አብሮ ተዘጋ፤

"ምን ላድርግ?"ከሀያ ደቂቃ በላይ ባለሁበት ቦታ ተገትሬ ማሰብ እንኳን አቅቶኝ ደንዝዤ ቆየሁ።ወደጓሮ ሄድኩ  ..፡፡.ካልተቀየረች አንድ ወደጊቢ  ዘሎ መግቢያ ምቹ  ቦታ ነበረች..አዎ አገኘኋት።ዙሪያ ገባውን ዞር ዞር ብዬ ሰው አለመኖሩ  አረጋገጥኩና እንደምንም ተንጠላጥዬ ዘልዬ ግቢውስጥ ገባሁ። ድሮ የሀይእስኩል ተማሪ እያለሁ በተለያየ ምክንያት ውጭ ሳመሽና በራፍ ሲዘጋብኝ በዚህ ዘዴ ነበር  ወደ ውስጥ የምገባው..፡፡ይሄው የዛን ጊዜው ልምድ ለዛሬ ረዳኝ።

የውጭ መብራት ስለጠፍ ግቢው በፀጥታና በጭለማ  ተውጧል።ኮቴዬን ሳላሰማ ቀስ ብዬ ወደልጄ ክፍል ማለት ወደእኔ የድሮ ክፍል አመራሁ...፡፡ወይ የእኔ ማር እንዳልኳት  መስኮቱን ከፍታ ነው የተኛችው። እንደምንም ተንጠላጠልኩና  መስኮቱ ላይ ወጣሁ ..ደግነቱ መስኮቱ አጠር ስለሚል በተለይ ከእኔ ቁመት አንፃር  አልተቸገርኩም፡፡  በቀላሉ ወደላይ ወጣሁና እግሬን አሽከርክሬ ወደውስጥ ገባሁ፡፡ ልጄን እንዳላስደነግጣት ተጠንቅቄ ወደማብሪያ ማጥፊያው አመራሁ..፡፡አብዛኛውን ዕድሜዬን የኖርኩበት ቤት መሆኑ ነገሮች የት የት እንደሆኑ በቀላሉ ለመለየት ረድቶኛል ።  መብራቱን አበራሁ።ልጄ እንዴት አድጋለች..ደግሞ አተኛኞ ልክ እንደናቷ ዝርግትግት ብላ ነው።በቅርቤ ያገኘኋት ኩርሲ መቀመጫ ወደአልጋዎ   አስጠጋሁና  ቁጭ አልኩ ...፡፡ጭንቅላቴን ሸፍኜበት የነበረውን  ኮፍያ ከላዬ ላይ ገፍፌ  ጣልኩት።አይኔ ላይ ሰክቼ የነበረውን መነፅር አወለቅኩና በአቅራቢዬ ያለ ትንሽ ጠረጰዛ ላይ አስቀመጥኩ። ሙሉ ትኩረቴን  ወደልጄ ሰበሰብኩ።እጆቼን በእርጋታ   ወደጭንቅላቷ ሰደድኩ .."ቀስ ብዬ ስዳብሳት  አይኖቾን ገለጠች...፡፡ደነገጥኩና እጄን ሰበሰብኩ...እሪ ብላ የምትጮህ መሠሎኝ ፈራሁ። ምን ላድርግ...?ፈጠን ብዬ  ዘልዬ   እንደአመጣጤ ልውጣ እንዴ?ብዙ ነገር አስቤ አንድንም ሳላደርግ

"አባዬ....ህልም አይደለም አይደል..?"አለችኝ፡፡

"አይደለም የእኔ ማር ...››በተኛችበት ጉንጮቾን ሞጨሞጭኳት...እሷም እጇቾን በአንገቴ ዙሪያ ጠመጠመችና ግንባሬን፤ጉንጬን ፤አገጬን ምንም የቀራት ቦታ የለም...ሙሉ በሙሉ ንቁ ሆና አልጋዎ መካከል ቁጭ አለች።

"አባዬ እኔ እኮ እመጣለሁ  ስትለኝ በህልሜ መስሎኝ ነው ቶሎ የተኛሁት።

"በጣም ስለናፈቅሺኝና ..ነገ  የደረጃ ተማሪ ሆነሽ ልትሸለሚ ስለሆነ እኔ  አባትሽ በጣም ኩራት ስለተሰማኝ  እንዴ ተደብቄም ቢሆን በዚህ ቀን ልጄን ካላየኋት  እኔ ምን አይነት አባት ነኝ ?ብዬ ነው በዚህ ለሊት ሹልክ ብዬ ክፍልሽ የተገኘሁት።

"አባቴ ውድድድ ነው የማደርግህ...አሁን አቅፍቅፍ ብለን እንተኛ"
"ግን አቴቴ ለሊት ልታይሽ ብትመጣስ?"

"አትመጣም ..ደግሞ እኮ ከውስጥ ተቀርቅሯል ..ብትመጣም ገና ስታንኳኳ ቶሎ ብለህ በመስኮት ትሄዳለህ"

"ምን አይነት ብልጥ ልጅ ነው ያለኝ"አልኩና ከላይ የለበስኩትን ጃኬት በማውለቅ ጠረጳዛ ላይ አኑሬ አልጋ ላይ ወጣሁ..ይሄ አልጋ የእኔና የእናትሽ እንደነበር ታውቂያለሽ?"

"አዎ …ለዛ እኮነው ክፍሌንም አልጋዬንም የምወደው"
👍564
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

"አባዬ ምንድነው?


"በሹክሹክታ ጠየቀችኝ

"እኔ እንጃ ..የውጭ በራፍ እየተንኳኳ ነው" ብዬ የተኛሁበትን አልጋ ለቅቄ ወረድኩ፡

‹‹ምነው ልትሄድ ነው እንዴ?"

"አይ ልነሳና ሁኔታውን እንይ"
"ምንድነው?
ማነው?"የእቴቴ ድምፅ ይሰማል
"ቀስ በይ.. ጫማ አላደረግሺም"እህቴ ነች
በዚህ ጊዜ ልጄ"አባዬ" አለችኝ በሹክሹክታ

"ወዬ ማሬ "በተመሳሳይ ቶን
"የውጩን በራፍ ሊከፍቱ ሲወጡ መስኮቱን ክፍት ሆኖ ያዩታል...ለምን ተከፈተ ብለው ወደእዚህ እንዳይመጡ ፈራሁ"
በበሳል አዕምሮዋ ተደምሜ ወደራሴ ሳብኩና ግንባሯን በመሳም ፈጠን ብዬ ወደ
መስኮቱ በመሄድ  ዘጋሁት.፡፡አውልቄ ጠረጰዛ ላይ አስቀምጬ የነበረውን ጃኬቴን ለበስኩ ፡፡ጫማዬን አጠለቅኩ..፡፡መነፅሬን ግንባሬ ላይ ሰካሁና ዝግጅ ሆኜ ወንበሩ ላይ በተጠንቀቅ ቁጭ አልኩ።
እቴቴና እህቴ በራፍ ከፍተው ሲወጡ ሰማን ...ልጄ ከመኝታዋ ወረደችና ወደእኔ መጣች፡፡ ስሬ ቆመች ፡፡በቀልጣፍ የአስተሳስብ ብቃቷ ታላቄ ብትሆንም ያው በእድሜ ልጄ ነችና አነሳሁና  ታፍዬ ላይ አስቀምጬ ወደ ውስጤ ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት ፡አንገቴ ስር ሽጉጥ አለች

..."ማን ነው?"
"እኔ ነኝ ክፈቱ"የሚል  የደበዘዘ አይነት  የቃላት ልውውጥ  ይሰማል"አሁን በዚህ ድንገተኛ ግርግር ምክንያት ሲኦል ከመግባት በላይ በምፈራት በአክስቴ ፊት እቆም ይሆን..?.አረ ፈጣሪ ምንም ሀጢያተኛና ዳተኛ ሰው ብሆንም ይሄን ያህልማ ጨክነህ አሳልፈህ አትሰጠኝም" ስል ፀለይኩ...ፀሎቴን ተከትሎ ‹‹ጉድ ጉድ …››እያለች አክስቴ ወደቤት ስትመለስ ሰማሁ
..‹‹.በቃ መርዶ ነው›››ስል አሰብኩ ..የታላቅ እህቴ ልጅ ምን ሆነው ይሆን?"ከአሁን አሁን ቤቱ በለቅሶ ይደበላለቃል ብዬ  መጠበቅ ጀመርኩ...አሁን ደግሞ ከእኔ  መጋለጥ በላይ ለቀናት ስታስበውና ስትዘጋጅበት የከረመችው የልጄ   ፕሮግራም መሰነካከሉን ሳስብ ልቤ ላይ ህመም ፈጠረብኝ።
"አባዬ ምንድነው? ጨነቀኝ?"
"አይዞሽ ልጄ.. አይዞሽ"እኔ እራሴም  ውስጤ በፍራቻ እየራደ ቢሆንም እሷን ግን ላበረታት ሞከርኩ፡፡
"በጊዜ አንድ ወይም ሁለት ሰዓት እኮ ነበር የምንገባው.. ሸኖን እንዳለፍን መኪናዋ ተበላሸችብን....መከራ አይተን ከሸኖ መካኒክ መቶ ነው ያስነሳት....››
በስመአብ እየቃዠሁ ነው እንዴ? ይሄንን ድምፅ አውቀዋለሁ፡፡
"እንደምትመጪ እኮ አልነገርሺንም...አዲስ አበባ ከገባሽ በኃላ እንኳን አትደውይም እንዴ..?›.
"በእኔ ቤትማ ሰርፐራይዝ ላደርጋችሁ ነበር....ግባ ….አዎ ሻንጣው እዛው ጋ ይሁን..ሌላው  መኪናው ላይ ይደር …ነገ ይወርዳል..ተቀመጥ ..አዎ ሶፋው ላይ ተቀመጥ››
"አባዬ. …እማዬ መጣች መሰለኝ"ልጄ ነች ጥርጣሬዋን በጆሮዬ ሹክ ያለችኝ
"አዎ መሰለኝ"
እቅፍ አድርጋ ሳም አደረገችኝ   ...እሷ ደስ ስላላት ደስ አለኝ...አረ በራሴም ደስ ብሎኛል ልቤ በውስጤ ስትንፈራፈር ሁሉ ይታወቀኛል።
አሁንም ጆሮዬ እዛኛው ክፍል ነው፡፡..."እማዬ ዛሬ እንኳን አታናግረኝም?"
"ተያት ... ደንግጣ ነው…እንኳን እሷ እኔ  እራሱ  በድንጋጤ ደርቄልሻለሁ"
"ታዲያ አሁን የት ሄደች ...?"
"ክፍሏ ገብታለች መሠለኝ"
"እሺ ልጄስ....?"
‹‹ተኝታለቻ..."
"ንፍቅ ብላኛለች ..በናትሽ ልቀስቅሳት"
"አይ ..ነገ ዝግጅቷ  ላይ ከምትንገላጀጅ ይቅርብሽ..እንደውም በጥዋት ስትነሳ ሰርፐራይዝ ታደርጊያታለሽ"
"ጥሩ ነው… እንደውም እንደዛ ይሻላል።"
ተንፈስ አልኩ...ወደእኛ አይመጡም ማለት ነው፡
"እማ አሁን እናትሽን ልታገኚያት ትፈልጊያለሽ?››ፈራ ተባ እያልኩ ታፋዬ ላይ የተቀመጠችውን ልጄን  ጠየቅኳት፡፡
"አይ አሁን ምፈልገው ከአንተ ጋር ተመልሶ መተኛት ነው..ከእሷ ጋር ነገ እተኛለሁ"
እቅፍ አደረኩና ወደአልጋው ይዤት ሄድኩ፤ ጫማዬን አወለቅኩና እቅፍ እንዳደረኳት ተኛሁ...ጆሮዬ ግን እዛው ሳሎን ነው ያለው፡፡
"የሚበላ ነገር ትፈልጋላችሁ ላሙቅ"እህቴ ነች እንግዶቹን የጠየቀችው
"አረ መንገድ ላይ ጂውስና ብስኩት ተጠቅመናል...አሁን መተኛት ነው የምንፈልገው...ለሀሰኖ የእንግዳ ክፍሉን ታሳይዋለሽ ..?እኔ ያው ካንቺ ጋር ነው ምተኛው?
"ምን ጥያቄ አለው...ወንድም ተነስ መኝታህን ላሳይህ››
‹እሺ›
የእግር ኮቴ .ከዛ ረዘም ያለ ዝምታ..ቀጥሎ ማንኳኳት ተሰማኝ
‹‹እቴቴ..እማ.እማዬ››
‹‹አረ አናግሪኝ..ውቅያኖስ አቆርጩ የመጣሁት እኮ አንድም አንቺ ስለናፈቅሺኝ ነው..በአመታት ርዝመት  እንኳን ይቅር አትይኝም››
‹‹እማ እንዳልተኛሽ አውቃለሁ›
‹‹እንዴ ምን እየሰራሽ ነው.››እህቴ ነች እንግዳውን አስተኝታ ስትመጣ ያየችው ነገር በመቃወም የተናገረችው፡
‹‹ብታናግረኘ እኮ ብዬ ነው››
‹‹ታገሺ….ነው ወይስ ዛሬውኑ ተመልሰሽ ሀጄ ነሽ››
‹‹ከገዛ እናት ጋር መዘጋጋት እንዴት እንደሚጨንቅ  እኮ ስለማታውቂ ነው..›
‹በይ በይ አሁን ወደመኝታችን እንሂድ››
ፀጥታ ሰፈነ…
…….በነጋታው

ከትምህርት ቤቱ ቅፅር ግቢ የፊት ለፊት  በራፍ ራቅ ብዬ በአንደኛው መንገድ ቆሜያለሁ።በተቻለኝ መጠን አለባበሴ በቀላሉ ማንነቴን ለመለየት የማያስችል እንዲሆን የተቻለኝን ጥንቃቄ አድርጌያለሁ።በአንድ እጄ ከጄኔራሏ የተዋስኩትን ካሜራ ይዣለሁ ሌላ እጄ ዝም ብሎ ከወዲህ ወዲያ እየተወናጨፈ ግራ መጋባቴን ለተመልካቹ እያሳበቀብኝ ነው። ተማሪዎች ለብቻቸውም ከወላጆቻቸው ጋርም በመሆን ወደውስጥ መግባት ከጀመሩ ደቂቃዎች አልፈዋል። እዛው ከቆምኩበት ሳልንቀሳቀስ ከፊት ለፊቴ ካለው መንገድ ሙሉ ቤተሠቤ ሲመጡ ተመለከትኩ።ፈጠን ብዬ ከመሀል መንገድ በመውጣት ደር ላይ የሚገኝ የት/ቤቱ ቢልቦርድን ተከልዬ እይታዬን ወደእነሱ አስተካከልኩ።

ቀድሞ በእይታዬ የገባችው  ደርባባዎ እመቤት አክስቴ ነች።ቅሬታ ያረበበት  የደግነት ተምሳሌት መሆኑ የሚያስታውቅ  የእናት ፊት ...ሮጠህ ሄደህ እግሯ ስር እዛ አቧራው ላይ በመንከባለል ይቅርታ ጠይቃት የሚል ስሜት ከጀርባዬ ወደ ፊት ሲገፈትረኝ ይታወቀኛል።እራሴን በመቆጣጠር ችሎታዬ ላይ ጥርጣሬ  ስለገባኝ የተከለልኩበትን የቢልባርድ ብረት ጨምድጄ ያዝኩ።ከመዋረዴ በፊት ትኩረቴን እንደምንም ከእቴቴ አንስቼ ወደ ልጄ አሸጋገርኩት።ልጄ ትንሽ ልዕልት መስላለች..ቦፍ ብሎ ሜዳውን የሞላ ነጭ ቀሚስ ከነጭ ጫማ ጋር ለብሳለች...ያ ክብ ፊቷ የደስታ ብርሀን እየረጨ ነው።በአጠቃላይ ድምቀትና ውበት የተዋሀደባት ሙሉ ጨረቃ መስላለች።አዎ ከአመታት የናፍቆት መቃተት በኃላ በአንድ ቀን እናትንና አባትን ማግኘት ከዚህ በላይም ቢያስፈነድቅ የሚገርም አይሆንም።የእኔ ልጅ የእኔ መላአክ እንኳንም ፈካሽልኝ።

ቀጥሎ እናትዬውን ነው ያየሁት፤ሩቾ ፍፅም ተቀይራ ሌላ ሰው መስላላለች ።በሳቋ ነው የለየኋት።ሙሉ ቆዳዋን አስገፍፋ በሌላ እንደተካች አይነት ነው የተሠማኝ።ደግሞ እንዲህ እረጅም ነበረች እንዴ?እርግጠኛ ነኝ ይሄንን እጄን እንደጥንቱ ፊቷ ላይ አሳርፌ ፊቷን ብዳብስ ይሸረካክታታል...ጉንጮቻ እኮ ተንጠልጥለዋል"ተአምርን በቀኝ እጆ ሌላ አነስ ያለ ወንድ ልጅ በግራ እጇ ይዛ ጠብ እርግፍ ትላለ…ወንድ ልጅ የማነው ልጅ?"

"ውይ ለካ ሁለት ልጆቾ ነው  ያሏት….አሁን እቺ ምኗ ነው የሁለት ልጅ እናት የሚመስለው፤  . .ይልቅስ እኔ  ነኝ በመጎሳቆሌ የተነሳ ግርጅፍጅፍ ብዬ የአራት ልጆች አባት የምመስለው።
👍60🤔21
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////

መቼስ የሀገራችን የሚካሄድ ትንሽም ሆነ ትላልቅ ዝግጅቶች ተሳስተው እንኳን ከመዝረክረክ አያመልጡም።እና ይጀመራል ከተባለበት ሰዓት 40 ደቂቃ አርፈደው  ጀመሩ...ዝግጅቱ ከተጀመረ ከአንድ ሰአት በኃላ  የሽልማቱ ፕሮግራም ተጀመረ ። እንደአጋጣሚ ሽልማቱ ከታችኛው ክፍል ነው የተጀመረው...

‹‹ አማካይ ውጤት 97.5 በማምጣት ከሁለተኛ-ለ ክፍል እንዲሁም ከአጠቃላዩ  ሶስቱም  የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት ልዩ ተሸላሚያችን ተአምር እዬብ  ..››አካባቢው በጭብጨባ ተነጋ.. ቤተሰቦቼ  ሁሉም ከተቀመጡበት ተነስተው  አካባቢውን ቀወጡት..፡፡በስሜት ካሜራዬን ደቅኜ ወደፊት ተጠጋሁ .በተቻለኝ መጠን ልጄን በካሜራዬ ለማደን ሙከራዬን  ቀጠልኩ...፡፡የእኔ ልዕልት እየተንሳፈፈች ወደመድረክ
እየቀረበች ነው...፡፡

እናትዬውና አክስቶቾ ሰፌድ የሚያካክል  አይፓዳቸውን ቀስረው ከኃላ ተከተሏት...፡፡መድረክ  ላይ ወጥታ ከክብር እንግዳው ሽልማቷን ስትቀበል ስመለከት እንባዬን ከመርገፍ ላግደው አልቻልኩም...የራስ ልጅ  እንዲህ በክብር አደባባይ ላይ ብዙዎችን በአድናቆት ሲያስጨበጭብ ማየት ለአንድ ወላጅ ምን አይነት ልብን በደስታ የሚያጥለቀልቅ  መባረክ እንደሆነ እድሉ የገጠመው ወላጅ ብቻ ነው የሚያውቀው።

እኔም በጊዜው እዚህ መድረክ ላይ እስኪሰለቸኝ ድረስ በተደጋጋሚ በመውጣት ተሸልሜበታለሁ...በዛን ወቅት ግን  እቤተሠቧቼ አሁን እኔ የተሠማኝን አይነት ልዩ ስሜት እንደሚሰማቸው ገምቼ አላውቅም ነበር...፡፡ልጄ ሽልማቷን  በአየር ላይ እያወዛወዘች ህዝብን  አስጨበጨበች።ከዛ በእኔ አቅጣጫ ስትደርስ ሽልማቱን ባለበት አቆመችና ትኩር ብላ ወደእኔ ተመለከተች፤ እኔም በደስታ  እጄን እስኪያመኝ በአየር ላይ አወናጨፍኩት..ከዛ ለሌላ ተሸላሚ መድረኩን ለቃ ስትወርድ እኔም ፈጠን ብዬ በፊት ወደነበኩበት ቦታ ተመለስኩ…፡፡

ዘመዶቾ ከበዋት ያውካካሉ እያንዳንዱ በየተራ አብረዋት ፎቶ ይነሳሉ…፡፡ቀናሁ… በጣም ቀናሁ…..እኔም ከመሀከላቸው መገኘት ነበረብኝ፡፡.ቁጭ አልኩና በሀሳብ ሰመጥኩ፡፡.አይኖቼ እንባ አግተዋል….፡፡ትንሽ ፊት ሚያሳየኝ ወይ ሚነካካኝ ነገር ባገኝ እዘረግፈዋለሁ….፡፡

አንድ ነገር ተከሻዬን ከኃላዬ ነካኝ…..ከሀሳብ ባነንኩና ዞር ስል ልጄ ነች…፡፡

‹‹አባዬ ተከተለኝ›› ብላ ብን ብላ ወደኃላ ሄደችና ከእኔ ጀርባ ባለ የመማሪያ  ክፍል ግድግዳ ኮርነር ተጠመዘዘች፡፡ፊቴን ወደ ፊትለፊት ላኩ ፡፡ወደዘመዶቼ፡፡ በራሳቸው ነገር ተጠምደው ያውካካሉ.፡፡ፈጠን አልኩና ተንቀሳቀስኩ፡፡ ልጄ ወደሄደችበት በፍጥት ሄድኩ ፡፡እንደተጠመዝኩ አገኘኋት፡፡ እጄን ያዘችና በፈጣን እርምጃ ወደፊት መጓዝ ጀመረች.፡፡ዝምብዬ ተጎተትኩላት…፡፡ምን ልታደርግ እንደሆነ አልገባኝም…፡፡ክፍሉን አለፈችና ሌላ ጠባብ መንገድ ውስጥ  ይዛኝ ገባች፡፡ጥቂት ተራመድንና  በፅድና በአትክልት የደመቀ የት/ቤቱ መናፈሻ ውስጥ ገባን፡፡ ምትፈልግበት ቦታ ከደረሰች በኃላ አዲስ እንዳገኘችኝ ነገር ተጠመጠመችብኝ፡፡

‹‹እንዳያዩን ብዬ እኮ ነው እዚህ ይዤህ የመጣሁት››

‹‹አይፈልጉሽም?››

‹‹ቶሎ እመለሳለሁ… ሽንት ቤት ብያቸው ነው የመጣሁት››

‹‹የእኔ ብልጥ በጣም ነው የኮራሁብሽ….፡፡.በጣም ነው ያስደሰሽኝ ….፡፡እንቺ ይህቺ ያዘጋጀውልሽ ትንሽ ስጦታ ነች›አልኩና  በሚያብረቀርቅ የስጦታ ወረቀት አምሮ የተጠቀለ እና በፔስታል ያለ ስጦታዬን ሰጣኋት..

‹‹አባዬ ምንድነው? ልክፈተው?››

‹አይ እቤት ብቻሽን ስትሆኚ ተከፍቺዋለሽ›

‹‹እሺ አበባዬ አመሰግናለሁ…በጣም አስደስተህኛል›ብላ ወደታች አስጎንብሳ ጉንጬን ሳመቺኝና

‹አባዬ ፎቶ እንነሳና ልሂዳ..›

‹‹እሺ …እሺ›› አልኩና የያዝኩትን ካሜራ በራሱ እንዲያነሳ አጀስት በማድረግ አንድ አምስት የሚሆኑ ፎቶዎች ተነሳን፡፡

‹‹አሁን ልሂድ አባዬ››

‹የእኔ ማር ሂጀ …አሁን እኔም ወደአዲስአባ ልመለስ…ማታ ብቻሽን ስትሆኚ ደውይልኝ››

‹‹እሺ አባዬ…ሌላ ጊዜም መጥተህ ታየኛለህ አይደል.?››

‹‹የእኔ ማር ከአሁን ወዲህ አንቺን ሳላይ ብዙ ጊዜ መቆየት ስለማልችል .አዎ መጥቼ አይሻለሁ›

አገላብጬ ሳምኳት.እሷም ሳመችኝና እንዳመጣጧ እየተሹለከለክች ብን ብላ ሄደች.፡፡እኔ እዛ መናፈሻ ውስጥ ለታሪክ ድምቀት የታነፀ በድን ሀውልት መስዬ ለረጅም ደቂቃዎች ቆምኩ፡፡ አሁን እንደቅድሙ የተንጠለጠለውን እንባዬን ገድቤ ማቆየት አልቻልኩም….ዝርግፍ ብሎ ሲንጠባጠብ እኔም ልክ እንደሌላ ሰው በትዝብት እያየሁት ነው፡፡ከዛ በኃላማ ወደዝግጅቱም አልተመለስኩም፡፡ ምን ላደርግ…?ሹልክ ብዬ ግቢውን ለቅቄ ወጣሁና ወደመናኸሪያ ነው ያመራሁት.፡፡ከዛ ቀጥታ ወደ አዲስአባዬ ፡፡

ይቀጥላል
👍998🥰6😁5🔥2👏2👎1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ_አራት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ከደብረብርሀን ከተመለስኩ በአራተኛው ቀን ይመስለኛል ማታ ከስራ ተመልሼ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ለመተኛት እየተገላበጥኩ ሳለ ልጄ ደወለች..አነሳሁና ስለእናቷ ስለቤተሰቡ ብዙ ብዙ ነገር ካወራን በኃላ

‹‹እናት…እናትሽ ከመጣች በኃላ እኮ ያቺን ነገር መላክ አቆምሽ››ስል ወቀስኳት

‹‹ምንድነው አባዬ?››

‹‹የእናትሽን ደብዳቤ ነዋ….ነው ወይስ ነጠቀችሽ?››

‹‹አይ አልነጠቀቺኝም እኔው ጋር ነው. ያለው...ግን እኮ አንድ ገፅ ብቻ ነች የቀረቺው..እሷን አሁን እልክልሀለሁ››

‹‹እሺ የእኔ ማር …እጠብቃለሁ..ደህና አደሪልኝ››

ከተሰናበትኳት ከ10 ደቂቃ በኃላ ቃሏን አክብራ የመጨረሻ ያለችውን ቅጠል በተለመደው መንገድ ላከችልኝ..እስኪ ከመተኛቴ በፊት የሪቾን የመጨረሻ ኑዛዜ አብረን እናንብባት፡፡
 
ሀምሌ 20/2008 ዓ.ም
ተስፋ መቁረጥ ብቻም ሳይሆን እግዚያብሄርን በጣም ነው የተቀየምኩት…. ወደ እዚህ ጉድ ከመግባት  እንዲታደገኝ እቤቱ ተመላልሼ አቧራ ላይ እየተንከባለልኩ ብዙ ቀን ተማፅኜዋለሁ…. በመሰናክሉም ተሰናክሎ ላለመውደቅ ያቅሜን ያህል ሞክሬያለሁ፡፡

የማላፈቅረውን ሰው በተክሊል እስከማግባት ድረስ ሄጄለሁ፣እኔ ይሄንን ሁሉ ስጥር እግዚያብሄር ምን ረዳኝ…..?እንደውም በተቃራኒው ላልተገባ ሀጥያት አሳልፎ ሰጠኝ……..ምንአልባት ጥንቱን ሲፈጥረኝ ለሲኦል አጭቶኝ ስለሆነ ይሆናል….ስለዚህ እጅ ሰጥቼያለሁ……በመንፈሳዊም ሆነ በስጋዊ ህይወቴ ያለኝ ተስፋ ፈርሶል፡፡አሁን ነፍሴ ሴይጣን ይንገስባት….. በተሰነካከለ ተስፋዬም  ዳቢሎስ ይደሰትበት ብዬ እራሴን ረገምኩ……
ከዛ በሃላ ብቸኛው ያስጨነቀኝ ጉዳይ የቤተሰቦቼ ሀዘን ነው…የእናቴ ቅስም መሰበር ነው…..እና እንደፈራሁትም በክስተቱ ቤተሰቦቼ የመጨረሻውን  ሀዘን አዘኑ ..እናትና አባቴ የ30 አመት ትዳራቸውን በተኑ……በወቅቱ ሁሉን  ነገር ጣጥዬ እራሴን ለማጥፍት  ወስኜ ነበር……ግን  ደግሞ ፈራሁ ..የፍራቻዬ ምክንያት ደግሞ የሚያስቅ ነው…‹‹ከሞትኩ በኃላ   እዬቤ ቢናፍቀኝስ…..?እውነት ይሄ ልክፍት ነው…፡፡አንድ የሁለት ልጆች እናት የሆነች  ባለ ጤነኛ አዕምሮ ሴት በሆነ ችግር እራሷን ለማጥፋት ስትነሳ ሊያሳስባት የሚገባው የመጀመሪያው ነገር ‹‹እኔ ከሞትኩ በኃላ ልጆቼ እንዴት ይሆናሉ?›› የሚለው ስጋት መሆን ነበረበት፡፡እኔ ግን ፈፅሞ እንደዛ አይት ሀሳብ አላስጨንቀኝም
…….ስላማያስጨንቀኝ ግን አፍራለሁ….እውነትም በጣም አፍራለሁ፡፡
በዛ መወዛገብ ውስጥ እያለሁ እዬብ የተአምር አባት እንደሆነ ሲያውቅ ማቄን ጨርቄን ሳይል እብስ ብሎ ጠፋ …ለአንድ ወር ፈለኩት እስከሀለማያ ሄጄ ፈለኩት…አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም አይደል የሚባለው…ሊገኝ አልቻለም፡፡
በቃ ሁሉን ነገር ጣጥዬ በደስታ ሳይሆነ በሀዘን ተቆራምጄ..በተስፋ ሳይሆን  በተሰባበረ ልብ ወደአሜሪካ ለመጓዝ ወሰንኩ፡፡   ……አዎ እራሴን ማጥፋት ካልቻልኩ እራሴን መርሳት አለብኝ …እራስ ለመርሳት ደግሞ አሜሪካ ምቹ ቦታ ትመስለኛለች፡፡አዎ እዛ ሄጄ እራሴን በስራ እጠምዳለሁ ……ልክ ከአሜሪካ ሮቦቶች ማካከል እንደአንዱ እሆናለሁ ……በቃ ከሶስት ቀን በኃላ ሁሉን ነገር ጣጥዬ የፈረሰ ተስፋዬን እና የቆሰለ ልቤን ይዤ ወደአሜሪካ… እዛ እንደረስኩ ከምፈታው ባሌ ጋር እበራለሁ..

እዚህ ላይ ሪች ብዙ ነገር ሸፋፍና እና በጥቅሉ ጠቃቅሳ  አልፋቸዋለች…. ለዛውም ዋናውን አስኳል  ነገር ..እርግጠኛ ነኝ ሰለዛ ስታስብ  እእምሮዋ ከተገቢው በላይ እየተጨናነቀባት አስቸግሯት በምልሰት እያስታወሰች መፃፍ ከብዶት መሰለኝ እንደዛ ያደረገቺው፡፡
እኔና ሪች ለመጀመሪያ ጊዜ  ወደ ጻታዊ ግንኙነት ሰተት ብለን የገባናው ካገባች ከ10 ኛው ቀን በኃላ ነው፡:፡ሰርጉ አልፎ እኛ ቤትም መልስ ተጠርተው  ከተመለሱ በኃላ  እና ቤታቸው  ገብተው ኑሮን አህድ ብለው እንደጀመሩ መስፍኔ  አንድ ጎጃም ፍኖተሰላም ሚኖሩ አጎቱ ሞተው መርዶ ተነገረው፡፡
ከመሄዱ በፊት እኔን በአካል አግኝቶኝ በከፍተኛ አደራ ሪችን እንዳስተዳድራትና ቀንም ቢሆን ብቻዋን እንዳልተዋት በልመና ተማፀነኝ‹‹በሬ ከአራጁ ይውላል ይሎችኋል እንዲህ አይነቱን ነው››

…ለአስራአምስት ምናምን አመት  አንድ አልጋ ላይ አብረን ተኝተን ምንም ያላደረግን ሰዎች..ይሄው ከሰርጎ በኃላ አብረን በተኛን በመጀመሪያው ቀን እንዲህ  የሰማይ መስኮት ተከፍቶ የጥፋት ዘንዶ በላያችን ተጠመጠመ… ከሲኦል ድንገት የተረጨ ሚመስል የመርገምት እሳት ሁለታችንንም ለብልቦ አቃለጠን፡፡
.በመጀመሪያ ቀን ወሲብ ፈፅመን ነግቶ በማግስቱ ስንነሳ  ከመተፋፈራችን የተነሳ አይን ለአይን መተያየትም ሆነ ቃል አውጥተን ምንም  ነገር ማውራት አልቻልንም ነበር…፡፡ሁለታችንም ቀኑን ሙሉ በፀፀት ስንብሰለሰልና  እና ግራ በመጋባት  ደንዝዘን  ነበር የዋልነው…፡፡

የሚገርመው ግን መሽቶ መልሰን ስንተኛ መልሰን ተመሳሳዩን ከመፈፀም እራሳችንን መግታት አልቻልንም…፡፡በአጠቃላይ ጥቅምት ላይ የዩኒቨርሲቲ ትመህርት ተከፍቶ  ተመልሼ ወደ አለማይ እስከምሄድ ድረስ ከሰባት ወይም  ስምንት ቀን በላይ ፍቅር ሰርተናል፤እና ደግሞ በስድስተኛው ወር ሊጠይቁኝ ሀለማያ ድረስ ከመስፍኔ ጋር  መጥተው እራሱ እሱን   ለሆነ ሰዓት ሸውደን ለብቻችን የመንሆንበትን ሁኔታ በማመቻቸት  ፍቅር ሰርተናል፡፡ስሜቱ አስቀያሚ  ግን ደግሞ በጣም ጣፋጭ ነበር..በተለይ መስፍኔን ፊት ለፊት ማየት ልብን ይሰብራል.፡፡
የሚገርመው ደግሞ በጣም ብዙ ብዙ ቀናት እሷ መሀል ሆና ሶስታችንም በአንድ አልጋ ላይ አንዳችንን በግራ እጇ ሌላችንን በቀኝ እጇ  እያቀፈች ብዙ በጣም ብዙ የመሳቀቅ ለሊቶችን እንድናሳልፍ አድርጋናለች…አይ ወንዶች በፍቅር አይናችን ከተጋረደ እኮ በቃ በጣም የዋህና ገራሞች ነን፡፡ከዛ ያው እሷ  እንደነገረቻችሁ የአሜሪካው ጉዳይ መጣና ዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ምናምን ተባለ ሁሉን ነገር አደፈራረሰው..ሀጥያታችንን ፀሀይ ላይ ተሰጣ…..ሁሉ ነገር እንደምታውቁት ሆነ፡፡

ይቀጥላል
👍82🥰53
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
ከጄኔራሏ ጋር ከአስራ አምስት ቀን በኃላ መገናኘታችን ነው፡፡ በጣም ናቃኛለች፡፡እኔም ሰሞኑን በጣም በተወጣጠረ እና በተጨናነቀ ሁኔታ ላይ ስለነበርኩ ላገኛት አልቻልኩም ነበር…እሷም ለምን እንደሆነ አላውቅም ላግኝህ ብላኝ አታውቅም ፡፡

‹‹እንዴት ነች ልጅህ?››

‹‹ደህና ነች…በጣም ደህና ነች››

‹‹ደህና ነች ስትል ፊትህ ላይ ብርሀን ይረጫል …ታድለሀል፡፡››

‹‹አዎ ..ትክክል ነሽ ታድያለሁ….በተለይ በአካል ካገኘዋት በኃላ ነው በጣም መታደሌን ያወቅኩት፡፡››

‹‹እናትዬውስ…?›

‹‹አናትዬው ምን….?››

‹‹ማለቴ ካየሀት በኃላ አላገረሸብህም?››

‹‹አይ እንዴት ያገረሽብኛል…በሩቅ አየኋት እንጂ በቅርብ አለላወራኋት..በዛ ላይ እህቴ እኮ ነች..››

‹‹መጀመሪያም እኮ እህትህ  ነበረች››

‹‹መጀመሪያማ አለመብሰልና ልጅነት ነው…››

‹‹ብለህ ነው…?››

‹‹አዎ….››

‹‹ይሁንልህ…ለማንኛውም ልሄድ ነው››

‹አልገባኝም….ገና አሁን መምጣትሽ እኮ ነው›

ፈገግ አለችና‹‹ማለቴ ሰሞኑን  መንገድ ልሄድ ነው..››

ይበልጥ ደንግጬ

‹‹ወደየት…?››

‹‹ግብፅ››

‹‹ግብፅ..ለምን …..?››

‹‹አባይን ተከትዬ…››

‹‹አትቀልጂ››

‹‹እሺ ለስራ …››

‹‹የምን ስራ…እዚህ  ስራ ጀምራለው ብለሺኝ አልነበረ እንዴ…?አንተንም አግዝሀለው አላልሺኝም ነበር?››

‹‹አዎ ብዬህ ነበር..ግን…››

‹‹ግን ምን…;?

ያው እንደዛ ከተባባልን በኃላ አንተ ጋር ሆነ እኔ ጋ ብዙ የተቀያየሩ ነገሮች ተፈፅመዋል…..ደግሞ አሁን ያገኘሁትን የስራ እድል በቀላሉ ገሸሽ ላደርው አልፈልግም፡፡››

‹‹ለመሆኑ ምንድነው ስራው…?››

‹‹አንባሳደር ሆኜ ነው የተመደብኩት…››

‹‹ወታደር አምባሳደር……;››
‹‹አዎ፡፡ ምን ችግር አለው…?ብዙ ሰዎች ምታበሽቁኝ ወታደር ተኩሶ ከመግደል ውጭ ሌላ ዕውቀት ያለው አይመስላችሁም….ወታደር እኮ እንደሌላው ሰው ከሙሉ ጭንቅላት ጋር የተፈጠረ ነው፡፡ማንኛውንም ትምህርት ተምሮ የየትኛውም እውቀት ባለቤት የመሆን ብቃትም አቅሙም አለው..እኔም ወታደር ከመሆኔ በተጨማሪ ላይ በውጭ ግንኑነትና ፖለቲካል ሳይንስ ዲግሪ እንዳለኝ አትርሳ…፡፡››

‹‹አረ አታምርሪ እኔ እንደዛ ማለቴ አይደለም…››

‹‹ባክህ ነው…የንግግር ቃናህ እራሱ ይሻክራል፡፡››

‹‹እሺ እንደዛ እንዲሰማሽ ስላደረኩ ይቅርታ ,.እኔ ግን ባትርቂኝ ደስ ይለኝ ነበር..››

‹‹አይ የምን መራራቅ አመጣህ፡ ከአሁን በኃላ እኮ ልንለያይ የማንችል ዘመዳማቾች ሆነናል፡፡አንተ እኮ የጋሽ አያና ልጅ ነህ..ወንደሜ ማለት ነህ;››
የእውነት ተደንቄም ተበሳጭቼም‹‹ግን የእኔ  እጣ ፋንታ  ምን አይነት ነው?››አልኳት ‹‹ምነው ምን ሆነ? ››

‹‹እንዴት ምን ሆነ ትያለሽ..?ዘላለሜን የማፈቅረው እህቶቼን መሆኑ አይገርምም?››

‹‹የማፈቅረው….ከእኔ ፍቅር ይዞሀል እንዴ?››

‹‹እየቀለድሽ ነው….?ካገኘውሽ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ አንቺን ከማፈቀር ውጭ ሌላ ምን ስራ አለኝ ብለሽ ነው››

ዝም አለች……..አንገቷን አቀረቀረችና ለደቂቃዎች በዝምታ ተውጣ አሰበች…እና እንደምንም ፈገግ ለማለት እየጣረች

‹‹ለማንኛውም ይሄንን ርዕስ ለጊዜው እንርሳው››አለችኝ፡፡

‹‹ለጊዜው ማለት?››

‹‹ለጊዜው ማለትማ …ጊዜ የራሱን መልስ አዘጋጅቶ በየልባችን ሹክ እስኪለን በነበረበት ተከድኖ ይቀመጥ ማለቴ ነው፡፡››

‹‹ይሻላል?›››

‹‹አዎ ይሻላል…ሳረሳው የፊታችን እሁድ እቤቴ ሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅቼያለሁ.. ልክ 7 ሰዓት እንድትገኝ››

‹‹እኔ?››

‹‹አዎ አንተ..ዋናው የክብር እንግዳዬ ነህ››

‹‹አረ በፈጣሪ እኔ ፓለቲከኞችና ባለስልጣናት ያሉበት ቦታ መገኘት ይጨንቀኛል፡፡››

‹‹አይዞህ አታስብ…ግብዣው ላይ ሚገኙት ጓዶኞቼ እና ጥቂት ዘመዶቼ ናቸው፡፡ ተጋባዦቹ ከአሰር አይበልጡም፡፡››

‹‹እንደዛ ከሆነ እሺ…››
እጇን ወደ ቦርሳዋ ከተተችና ፖስታ ይዛ ወጣች…ከዛ ሰጠችኝ

‹‹ምንድነው?››

‹‹የጥሪ ካርድ››

‹‹በቃል ነገርሺኝ አይደል…አይበቃም፡፡››

‹‹አይ ለአንተ አይደለም››

‹‹እናስ?››

‹‹ ለአያትህ››

በጣም ደነገጥኩ..እስኪ ምን ሚያስደነግጥ ነገር አለ‹‹እየቀለድሽ ነው…?››

‹‹አንተ ምን  አስጨነቀህ..ብቻ የታሸገውን ፖስታ ሳትነካካ ወስደህ ስጣቸው…. መምጣትና አለመምጣቱን እሳቸው ይወስኑ››

‹‹ቀልደኛ ነሽ…እኔማ ምን
ቸገረኝ እሰጠቸዋለሁ…ውሳኔያቸውን ግን እኔው ልንገርሽ  አይመጡም… አታስቢው፡፡››

‹‹እሺ አንተ ብቻ ስጣቸው፡፡››
ተቀብዬ ኪሴ ከተትኩ
////
በተባለው እሁድ ቀን የልቤ ሰው የሆነችውን የጄኔራሏን የሽኝት በአል ላይ ለመታደም…ለዝግጅቱ የሚመጥን ሽክ ያለ አለባበስ ለብሼ አምሬና ተሸቀርቅሬ በእጄ ደግሞ ይመጥናታል ያልኩትን የማስታወሻ ስጦታና አንድ ጠርሙስ ውስኪ አንጠልጥዬ ልክ ከቀኑ ሰባት ሰዓት መኖሪያ ቤቷ በራፍ ላይ ተገኘሁ፡፡ወደውስጥ ለመግባት ግን ትንሽ አመነታሁ፡፡ውስጥ የማገኛቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ጋር እንዴት ብዬ እንደምግባባቸውና እንዴት አይነት ጊዜ አብሬያቸው ላሳልፍ እንደምችል ሳስበው ጨነቀኝ…በተለይ እኛ ጄኔራል የቀድሞ ወዳጇ ተጠርተው ከሆነ ሙዴ ሁሉ ነው የሚከነተው…ለማንኛውም ምርጫ ስለሌለኝ እራሴን አበረታትቼ ወደግቢው ዘልቄ ገባሁ….በሩቅ በረንዳ ላይ አንድ ታዳጊ ልጅ ትታየኛለች…እየቀረብኩ ስመጣ የማየውን ማመን ነው ያቃተኝ ፡፡ልጅተቷ እኔን ሳታይ ተመልሳ ወደውስጥ ሮጣ ገባች ፡፡
በዛች ቅፅበት ምንም ነገር ማሰብ አልቻልኩም።ልክ ልጅቷ እንደወፍ በራ የምታመልጠኝ ይመስል በሩጫ ተከተልኳት……ታአምር ታምሬ እያልኩ ተንደርድሬ ወደቤት ገባሁ።አንድ እግሬን እቤት ውስጥ አንድ እግሬን በረንዳ ላይ አድርጌ ከነሀስ እንደተሠራ ሀውልት ተገትሬ ቆምኩ።ውስጥ ሳሎኑ ሙሉ ነው። የሚገርመው ደግሞ ሁሉንም ሰዎች አውቃቸዋለሁ… በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንዲህ ግራ ገብቶኝ አያውቅም።ወደኃላ ተመልሼ ሮጬ ማምለጥ ወደፊት ሄጄ ሁኔታዎችን መጋፈጥ.."ሁለቱንም ለማድረግ አእምሮዬን መጠቀም ሰውነቴንም ማዘዝ አልቻልኩም።

ጄኔራሏ  ከሌላኛው ክፍል ወጣችና ቀጥታ ወደእኔ መጣች "እንዴ ግባ እንጂ"
ስሬ ደርሳ ክንዴን ቀጨም አድርጋ ያዘቺኝ እና ጎትታ ከተቸነከርኩበት አነቃነቀችኝ።ከውስጥ አፍጥጠው ከሚያዩኝ ሰዎች መካከል አንድ አዛውንት ወደእኔ መንቀሳቀስ ጀመሩ..ማን እንደሆኑ መገመት አትችሉም፤አያቴ ናቸው።ከሶስት አመት በኃላ እንዴት ክፍላቸውን ለቀው እዚህ ሊገኙ ቻሉ?የጥሪውን ካርድ በሰጠዋቸሁ ቀን ፈፅሞ እንዳላስበው በማያሻማ ቋንቋ ነግረውኝ እኔም አምኜያቸው ነበር….እና ታዲያ እንዴት ሀሳባቸውን ቀየሩ?ይሄ ነገር ህልም  ይሆን እንዴ ?
‹‹ና በል አክስትህን ይቅርታ ጠይቅ።›አያቴ ናቸው የተናገሩት፡

ካለሁበት ድንዛዜ ድንገት ባንኜ በአየር ላይ እንደመንሳፈፍ ተንደርድሬ አክስቴ እግር ስር ድፍት አልኩ… እሷም ፈጥና ልታነሳኝ ትከሻዬን ለመያዝ ብትሞክርም እንደምንም አመለጥኳትና እግሯ ስር ተደፍቼ በእንባ እየታጠብኩ ‹‹እቴትዬ በፈጣሪ ይቅር በይኝ..አሳፍሬሻለሁ.››የመጣልኝን ቀባጠርኩ፡፡

ይቀጥላል
👍1067👏1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

እኔ ይቅርታዬን ሳልጨርስ ምስርም ካለችበት ተንደርድራ መጥታ ልክ እኔ እንዳደረኩት እቴቴ እግር ስር ድፍት አለች።አንዳንድ እግር ተከፍፋልን ።እቤቱ ለቅሶ በለቅሶ ተደበላለቀ።ተረባርበው ሁለታችንንም ከተደፋንበት አነሱን ..እንደተነሳን በግራና ቀኝ ትከሻዋን ተከፋፍለን ተጠመጠምንባት፡፡ ተአምርን ጨምሮ ሌሎቹም እየመጡ ተቀላቀሉን። መላቀሱና መሳሳሙ አልቆ ስርአት ይዘን ለመቀመጥ ምን አልባት ከ20 ደቂቃ በላይ ሳይፈጅ አልቀረም።የዛ ሁሉ አመት ስቃይ….የዛ ሁሉ ጊዜ ቁጭትና ፀፀት ….የዛ ሁሉ ለሊትና ቀን የልብ ድማትና የጨጓራ ቁስለት እንዲህ በአስር ደቂቃ የይቅርታ ቃላቶች እና መላቀሶች መሻሩእና መጠገኑ የሚገርም ነው፡፡ይቅርታ የሚባል ነገር ባይኖር የሰው ልጅ ጠቅላላ ህይወቱ ምን መልከ ይኖረው ነበር ?ብዬ አሰበብኩና ዝግንን አለኝ ፡፡ብቻ ቀስ በቀስ መረጋጋቱ ሲመጣ ወደ ጫወታና መሳሳቅ ገባን።

"አያቴ ግን እንዴት..?"እኔ ነኝ ለመጀመሪያ ጊዜ አያቴን ፊት ለፊት በአካል ከእነአዛውንት ውበቱና ግርማ ሞገሱ በማየቴ እየተደመምኩ የጠየቅኩት፡፡

"እንዴት ምን..?"

"ዛሬ እንዴት ወጡ..አታስበው አልመጣም ብለውኝ ነበርኮ"

‹ሀሳቤን ቀየርኮ…ይሄ ተአምራዊ ቀን እንዲያመልጠኝ ፈፅሞ አልፈለኩም..ስለልጅህ ስለአክስትህ በአጠቃላይ ስለመላው ቤተሠብ ለሁለት አመት በእየለቱ ስታወራልኝ ስለከረምክ ለእኔም ልክ እንደቤተሠቤ ነበር የሚናፍቁኝ.ጄኔራል ሁኔታውንና የተቀደሰ ሀሳቧን አብራርታ ስትነግረኝ በእንቢታዬ መግፋት አልቻለልኩም።"

‹‹እሱሰ እውነቷትን ነው አያቴ. ግን ይሄ በጣም የሚገደርም ውሳኔ ነው ?መቼስ ጋሼ ይሄንን ቢያይ ተገርሞም አያባራም…››

ከዛ ብዙ ብዙ ጫወታ ተጫወትን..ምሳ ቀረበ የሚጣጡ መጠጦች እንደየምራጫችን ታደሉን …በሳቅና ጫወታ ያወራረድን በደስታ ተመገብን፡፡
እስከ10 ሰዓት ስንጫወት ቆየንና ከሳምንት በኃላ ወይ እኔ ሄጄ ልጠይቃቸው ወይ ደግሞ ሁሉም ተሰብስበው እኔ ቤት ሊመጡ ተነጋገርንና እንዳመጣጣቸው ሸኘናቸው….በመጨረሻ እኔና ጄኔራሎ ብቻ ቀረን፡፡ከዛ የተደመምኩባቸውን ጥያቄዎች ተራ በተራ አቀርብላት ጀመር፡፡

"ግን እንዴት?"
"እንዴት ማለት?"
"እነ አክስቴን እንዴት አገኘሽ ?እንዴት አሳመንሻቸው?"

"ቀላል ነበር..የአንተን ማንነት ካወቅኩ በኃላ የወላጆችህን ቤት የተከራዪት ሰዎች ጋር ሄድኩና ያክስትህን ስልክ ተቀበልኩ …ከዛ ወደ ደብረብርሀን ሄድኩ።"
"ደብረ ብርሀን ድረስ?"
"ደብረብርሀን እኮ እዚሁ አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ነች።"
"እሺ ይሁን .ከዛስ..?"
"ከዛማ ደረስኩና ደወልኩላት… የሞች እህቷ የድሮ ወዳጅ እንደሆንኩ ነግሬ የቤቷን አድራሻ ጠየቅኩ ።በቀላሉ ነገረችኝ፡፡ቀጥታ እቤት ሄጄ አዋዝቼ ስላንተ ነገርኳት።"

"በፈጣሪ ምን አለች ..?አልተበሳጨችም?"በከፍተኛ ጉጉት ጠየቅኳት

"ወይ መበሳጨት ..እዬብ በህይወት አለ ስላት እህተሽ ከመቃብር ወጣች ያልኳት ነው የመሠላት ..ለአንድ ሰዓት ስታለቅስ፤ ስትስመኘ፤ስትመርቀኝ ምኑን ልንገርህ..እውነት መሆኑን አላመነችም እህትቶችህ..በተለይ በተለይ እማ!!ያው ይገባሀል..አሁንም የፍቅር ስቃይ ፊቷ ላይ አለ…አሁንም በናፍቆት እየቃተተች ነው..አሁንም በማይድነው አጉል በሽታ ተለክፋ ትንፍሽ እንዳጠራት መሆኑን ሁኔታዎን ለደቂቃ አይቶ መረዳት ይቻላል።››

"ልጅህ ደግሞ።"
"ልጄ ምን?"
"አደገኛ አክተር ይወጣታል ..ልክ ስለአንተ ለመጀመሪያ ቀን እንደሰማ ሰው አብራ ስታዳንቅ ሳይ እኔ እራሴ ይሄ ልጅ ዋሽቶኛል እንዴ?በእርግጥስ የእውነት አግኝቶት ያውቃል? ብዬ እራሴን ለመጠየቅ ተገደድኩ"
"አዎ ቆቅ የሆነች ልጅ ነች ያለቺኝ"
"እስማማለሁ"
"እሺ አያቴንስ እንዴት አሳምነሽ አመጣሻቸው?"
ቀላል አልነበረም፣የጥሪ ካርዱን ባንተ በኩል ል እንዳልተስማሙ ከነገርከኝ ቡኃላ ያንተን አለመኖር እየጠበቅኩ ከሶስት ቀን በላይ መመላለስ ነበረብኝ..ቢያለፋኝም ተሳክቶልኛል።በዚህ አጋጣሚ ልንገርህ ..መቼም መቼም አያትህን እንዳታስቀይማቸው።የእውነትም እንደልጃቸው ነው የሚያዪህ።በጣም ነው የሚወድህ"
"አውቃለሁ..እኔም አያቴ ስላቸው ለማስመሰል አይደለም...የእውነት ከልቤ እንደዛ ስለሚሰማኝ ነው።
"ታድለህ"
እንዴት ታድለህ ልትይ ቻልሽ?"
"ብዙ ሰዎች ብዙ ደክመው ብዙ ጥረው የማይሳካላቸውን የሠው መውደድ አንተ በቀላሉ አለህ..አክስትህ..እህቶችህ.ልጅህ..አያትህ ..እኔ..ሁላችንም አምርረን እንወድሀለን "
"የእውነት ..?አንቺም አምርረሽ ትወጂኛለሽ?"
"ከዝርዝሩ ውስጥ የእኔ ነው አጠራጣሪው?"
"አይ እንደዛ ማለቴ አይደለም ..እንዲሁ አለ አይደል ..ለማረጋገጥ ነው የጠየቅኩት"
‹‹አይዞህ አትጠራጠር ..አንተ በጣም ውድድድ የማደርግህ ፤ታናሽ ወንድሜ ነህ?"
"በለው....አየሽ እድሌን?"
"እንዴት?"
"አሁን እኔ እህት የናፈቀኝ ይመስልሻል..?"
"አሁን እኳ ምርጫ የለህም ..የልጅህ እናት አሁንም እንደተራበችህ ነው..እርግጠኛ ነኝ አንተን ሳትይዝ ወደአሜሪካዋ አትመለስም።"
"ይዛኝ ሄዳስ?"
"እሱን እንግዲህ ጊዜ የሚመልሰው አስቸጋሪ ጥያቄ ይሆናል።››

"እሺ እንዳልሽ አሁን ትንሽ ጉዳይ ስላለችብኝ ልሂድ… ነገ እመጣና እዚሁ አድሬ እሸኝሻለሁ..ይቻላል አይደል?"
"በጣም ደስ ይለኛል።ጉንጯን ስሜ ተሠናብቼ ወጣሁ።››

ይቀጥላል
👍808😢2🔥1🤔1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ+ነበረ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ትንፋሽ ወሰድኩና ከመተኛቴ በፊት  ከአያቴ ጋር ለማውራት አፌን ከፈትኩ…አያቴ እንዳልተኙ በመብራቱ አለመጥፋት እና በዕቃ መንኳኳት ማወቅ ችያለሁ፡፡

‹‹አያቴ ጉዴን እየሰሙ ነው አይደል?››
መልስ የለም

‹‹አያቴ ይሰሙኛል?››
መልስ የለም

‹‹እንዴ..ያን የተለመደ ዝምታቸውን ጀመሩ ማለት ነው..?አሁን በዚህ ከእሳቸው ጋር ማውራት በፈለኩ ቀን ዝም ይላሉ..››ብዬ ተሰፋ በመቁረጥ ልተኛ ልብሴን ማውለቅ ስጀምር በጆሮዬ ደምፅ ሰማሁ፣፣

‹ምንድነው… አያቴ ሙዚቃ…?››ወደግድግዳው ተጠጋሁና ጆሮዬን ቀስሬ አዳመጥኩ….ውይ እለተ ምፅአት ደርሶል መሰለኝ…ከአያቴ ቤት የሲሊንዲዮን ዘፈን እየተሰማ ነው…፡፡

‹‹አያቴ እኔ አላምንም…ሰሞኑን በጣም እያስደመሙኝ ነው..ከቤት ለመውጣት መወሰኖት ሳያንስ ጭራሽ የፈረንጅ ሙዚቃ….በአንዴ ግን እንዲህ አይነት ለውጥ አይከብድም.?

አሁንም ፀጥታ ነው….

‹‹አያቴ ምንም የማያናግሩኝ ከሆነ በፊት ለፊት በራፍ ዞሬ መምጣቴ ነው..››

‹‹በፊት ለፊት በራፍ… ተው ይቅርብህ..አታድርገው››

‹‹ምን ?››የባሰ አለ ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም

‹‹ሰምተሀል››
አዎ በደንብ ሰምቼያለሁ… አያቴ ቤት ሴት….አረ አይደረግም…እያናገረችኝ ያለችው ሴት ነች..ወጣት ሴት፡፡

‹‹አያቴ የሉም እንዴ?››
‹‹አያትህ የለም››ለስላሳ ለጋ የሴት ድምፅ መልስ ሰጠኝ፡፡
‹‹ይቅርታ ማን ልበል….?››ግራ በመጋባት ተሞልቼ ጠየቅኩ፡፡

‹በዚህ ውድቅት ለሊት ከአዲስ ሰው ጋር መተዋወቅ አይክብድም..?ይቅርታ ጥዋት እንተዋወቃለን… ባይሆን አሁን የአያትህን መልዕክት ተቀበለኝ..››

ከአያቴ ጋር እቃ ወደምንቀባበልበት ስንጥቅ አመራሁ...ለግላጋ ጠይም የእጅ እጣት ብጣሽ ወረቀት አቀበለኝ.. .ተቀበልኳት እና ወደአልጋው ተመለስኩ… ገለጥኩና ማንበብ ጀመርኩ፡፡

ልጄ ሳልነግርህ ይህን በማድረጌ ይቅርታ..ለአንድ ወር ወደገዳም ሄጄያለሁ…ትንሽ በፅሞና ከእግዚያብሄር ጋር ማውራት አምሮኛል…ልክ የዛሬ ወር ተመልሼ እመጣለሁ...እስከዛ የምወዳት የልጅ ልጄ ማራናታ ካንተ ጋር  እንድትቆይልኝ እፈልጋለሁ፡፡ያው ከሰሎሞን ሚስት ማለት ከእንጀራ እናቷ  ጋር አምርራ ስለማትስማማ እነሱ ጋር መቀመጥ አትችልም…እኔ ወደገዳም መሄዱን ቀድሜ የያዝኩት ቀጠሮ ነው…  ከእግዚያሄር ጋር የያዝኩትን ቀጠሮ ማስተጓጎል አልችልኩም…እሷ ደግሞ ድንገት መጣችብኝ….ግን ያው አንተ ልጄን ከእራሴ በላይ ስለማምንህ ልክ እንደእኔ አረገህ  ከእኔም በላይ እንደምትጠብቃትና እንደምትንከበከባት ቅንጣት ጥርጣሬ አይገባኝም…ቀንም ስራም ሆነ ሌላ ቦታ ስትሄድ ይዘሀት ሂድ…ማታም ጥለሀት ውጭ እንዳታድር..ነግሬሀለው አንተ ወሽካታ..ደግሞ ለእሷም እንዳታስቸግርህ ነግሬያታለሁ...አደራ አንተ ቀልማዳ እናንተ ሁለታችሁ በአለም ላይ እጅግ የምወዳችሁ የልጅ ልጆቼ ናችሁና ተመልሼ እስክመጣ በመደጋገፉ ጊዜችሁን በጥሩ ሁኔታ አሳልፉ.፡፡

ያንተው አያት ሙሉአለም ነኝ፡፡

‹‹እህት ይቅርታ ማራናታ ይሄ ምንድነው..?አያቴ ምንድነው የሰሩት?››

‹‹ያው አያትህ የሰራው እንዳነበብከው ነው›

‹‹እያሾፍሽ ነው እንዴ?››
‹አንተ እንዴት ነው የምታናግረኝ እንግዳህ እኮ ነኝ…ከደበረህ ነገ ጥዋት ተነስቼ ወደ ሀገሬ እበራለሁ..››

‹‹አረ በፈጣሪ ..ነገሩ ዱብ እዳ ሆኖብኝ እንጂ እንደዛ ማለቴ አይደለም...አሁን እራት በልተሻል..?››

‹‹አዎ በልቼያለሁ››
‹‹ሌላ የምትፈልጊው ነገር አለ….?››

‹‹አዎ አንድ ጠርሙስ ቢራ ባገኝ ደስ ይለኝ ነበር..››

‹‹እሺ አሁን አመጣልሻለሁ.››.ከአልጋዬ ተነሳሁና ጫማዬን ማድረግ ጀመርኩ

‹‹ምነው አለህ እንዴ?››ጠየቀችኘ
‹‹አይ የለኝም ግን አታስቢ አሁን ገዝቼ መጠለሁ. ምንድነው ሚመችሽ ማለት ጊርጊስ፤ በደሌ፤ሀረር ..››
‹‹አራት ሰዓት  እኮ አልፏል..የእውነት አሁን በዚህ ሰዓት ሄደህ ልትገዛልኝ ነው?›

‹‹አራት ሰዓት አይደለም ስድስት ሰዓትስ ቢሆን ምን ችግር አለው…የአያቴ አደራ እኮ  ነሽ…››

‹‹በል ስቀልድ ነው..አሁን አልፈልግም ነገ ትጋብዘኛለህ››

‹‹እውነተሽን ነው…?››
‹‹.አዎ አሁን ስለደከመኝ እንቅልፌ መጥቷል …ቻው ደህና እደር..››

‹‹ደህና እደሪ …ለሊት በማንኛውም ሰዓት የምትፈልጊው ምንም ነገር ቢኖር ንገሪኝ..››

‹‹ለሊት ምንም ነገር ብፈልግ?››ሳቅ ባፈነው ድምፅ

‹‹አዎ ምንም ነገር ብትፈልጊ..››

‹‹እሺ ነግርሀለሁ.. .አሁን ደህና እደር››

‹‹ደህና እደሪ›› ብዬ ሳደርግ የነበረውን ጫማ መልሼ አወለቅኩና ወደ አልጋዬ  ወጣሁ...ከልጅቷ ጋር በግድግዳ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ ሆነን የተነጋገርናቸውን ነገሮች መልሼ ሳስብ...ልጅቷ ልክ እንደ አያቴ ተንኮለኛ ቢጤ ነች መሰለኝ ስል አሰብኩና ፈገግ አልኩ…

ስለእዚህች ልጅ አያቴ ለብዙ ቀን አውርተውኛል..በየ15 ቀኑም ደብደቤ እየጻፉ እየሰጡኝ ለረጂም ጊዜ ፖሰታ ቤት ወስጄ የማስገባላቸው አኔ ስለሆንኩ ስለእሷ በመጠኑ አውቃለሁ..…ለምሳሌ የድሬደዋ ልጅ መሆኗን..ከእናቷ ጋር እንደምትኖርና… ጋሽ ሰለሞን የአሁኗን ሚስቱን ከማግባቱ በፊት እናትዬውን አግብቶ እሷን ከወለደ በኃላ እንደተፋቱ ከዛ እናትዬው ልጆን ይዛ ቤተሰቦቾ ጋር ድሬደዋ እንደገባች አውቃለሁ…አያቴም ከቤት አልወጣም ብለው እራሳቸውን ኳራንቲን ከማስገባቸው በፊት ቢያንስ በስድስት ወር አንዴ እየሄዱ እንደሚጠይቋት እሷም አልፎ አልፎ እየመጣች ትጠይቃቸው እንደነበረ መረጃው አለኝ ….ከልጃቸው ከጋሽ ሰለሞን በላይ ከእሷ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸውም አውቃለሁ....ሌላው በ1987 ዓ.ምህረት እንደተወለደች ነግረውኛል…ያ ማለት ይህቺ የሚቀጥለው ክፍል ውስጥ ያለች ወጣት አሁን 25 ዓመቷ ነው፡ በትምህርቷ በአካውንቲንግ ዲግሪ አላት…የእናቷ ቤተሰቦች ሀብታም ነጋዴዎች ስለሆኑ የራሷ ቡቲክ ከፍተውላት እየሰራች እንደሆነም አውቃለሁ...በቃ ስለእሷ የማውቀው ይሄንን ያህል ብቻ ነው ፡፡በተረፈ ቀጭን ትሁን ወፍራም..ቀይ ትሁን ጥቁር..ረጀም ትሁን አጭር ….ትሁት ትሁን መሰሪ ምንም አላውቅም….ምንም ፡፡ ግን ምንም ትሁን ምንም ለአንድ ወር የእኔ ኃላፊት ነች.. ፡፡ ያንን ኃላፊነት ደግሞ ያለምንም ማቅማማት በፍጽም ትዕግስት እና ብቃት እወጣለሁ...ምክንያቱም ያዘዙኝ አያቴ ናቸው..አሁን ልተኛ….ነገ ምን አልባት ረጅም ቀን ሊሆን ይችላል፡፡

ይቀጥላል
👍5944🔥4😁3👎1