አትሮኖስ
277K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
448 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ገረገራ


#ክፍል_ስምንት


#በታደለ_አያሌው

...ክፉ ያሳሰበኝን መንፈስ እከድከ ሰይጣን እያልሁ በልቤ ደጋግሜ ጸልዬ አስታገስሁት። ቀጥዬም ሰላም ለኪን ደገምሁበት እና ከሆስፒታል ወጣሁ። እንደ ወጣሁ የሆነብኝን ሁሉ የምነግረዉ ስፈልግ ከሁሉ ቀድሞ
ሐሳቤ ላይ የገባልኝ ሰዉ ባልቻ ነበር፡ እመዋን አቆይቼ ማለቴ ነዉ።ለእሷስ ያለፈዉ ይበቃታል፡ የሆስፒታሉንም ነግሬ ዳግመኛ ቅስሟን ልሰብረዉ አልፈልግም።

በእርግጥ እህትና ወንድሞቼም ነበሩልኝ። ጓደኞቼ ሁሉ አሉ። እሽቴም ቢሆን እኮ አለ የኖረዉ ቢኖርም፣ በተለይ አሁን ስላንጨዋለለኝ ፈታኝ ጉዳይ ለማማከር ግን፣ ከምድር ማንም እንደ ባልቻ የሚሆንልኝ ሰዉ
አይታየኝም: እሱ ብቻ ነዉ የጭንቄን መጠን ልክ እንደ ነገርሁት፣ እንዲያዉም ከነገርሁት አልፎ የሚገነዘብልኝ። ለማባበል
አይሸነግለኝም። ማባበል ከፈለገም እንደ'ሱ የሚያዉቅበት የለም። ጆሮዉ የተለየ ነዉ። ጭጭ ብሎ ሲያዳምጥ ብቻ ከጭንቅ ይፈዉሳል። እኔ ራሴ
እንኳን ስለ ራሴ የማላዉቀዉን ከእመዋ ቀጥሎ የሚያውቅልኝ ሌላ ሰዉ አላዉቅም: ባልቻ ብቻ:: እንዲያ ቢሆንም ግን፣ እሸቴም መስማት ስላለበት ኹለቱንም ወደማላጣበት ወደ ሲራክ-፯ ማዕከል ሄድሁ።

“አባትዮ” አልሁት፣ ወደ ትልቁ የማኅበሩ ሕንጻ እየተቃረብሁ ሳለ ወደ ባልቻ ስልክ ደዉዬለት።

“አቤት ልጅየዋ”

“ለአንድ አፍታ ፈልጌህ ነበር”

“መቼ”

“አሁን”

“ዉይ፣ አሁን እንኳ አንዲት የጀመርኋት ሥራ አለችብኝ: ባይሆን ይቺን እንደ ጨረስሁ ልደዉልልሽ?”

“በማርያም! አሁኑኑ ነዉ የምፈልግህ፤ ይልቅ ቶሎ ናና ጉዴን ስማልኝ'

“እህ፤ እየነገርሁሽ?”

“ስሞትልህ! ከእሸቴ ጋር እዚሁ አንደኛ ፎቅ ባለዉ ምግብ ቤት
ብትመጡልኝ፣ የምጋብዛችሁ አታዉቁትም: አንተስ ምናለ ለአንዳንዴስ እንኳን ንፋስ ቢያገኝህ? ሁልጊዜ እዚያ ዉስጥ ተቀብረህ” አልሁት፣ ለግብዣዬ ያለዉን ከበሬታ ዘንግቶ ላለመምጣት ሲያቅማማ በዚያም ላይ ሰዓቱ የምሳ ስለሆነ ሦስታችን አብረን የምንበላበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ይሆንልናል። እንዳሰብሁት፣ ብዙም ሳያስጠብቁኝ ከእሸቴ ጋር ፊት እና
ኋላ ሆነዉ መጡልኝ፡

“አንቺ፤ ብለሽ ብለሽ ደግሞ እንዴት እንዴት ነዉ ያናገርሽኝ? እንደ ልጅ ና ከረሜላ ልግዛልህ ማለት እኮ ነዉ የቀረሽ አሁንማ አሁንማ” አለኝ በጨዋታ፣ ወንበር ስቦ ከአጠገቤ እየተቀመጠ፡ መልስ ከለከልሁት

“አንቺ? ምንድነዉ ደግሞ ለንቦጭሽ የታላቁን ንጉሥ አወዳደቅ ወድቋልሳ: ገና ለገና እርምሽን ልትጋብዥን ብትይ፣ ከአሁኑ ማኩረፍሽ ነዉ? አየህልኝ እሽቴ? ገና ከአሁኑ እንዲህ ከሆነች፣ ሂሳቡን ስትከፍልማ
እንደ ጨዉ ሟሙታ ወደ መሬት መስረጓ ነዉ በለኛ”

ወድጄ አይደለም ዝም ያልኋቸዉ ሆስፒታል የጀመሩኝ ክፉ ክፉ የሚባሉ ሐሳቦች ሁሉ አሁንም አሁንም ወደ ልቡናዬ እየመጡ ግብግብ ገጥመዉኛል፡ እንደ ምንም ጥርሴን ለመፈልቀቅ ሞከርሁ። የዉጤቱን ወሬ ከምሳ በኋላ መንገሩን ስለመረጥሁ፣ በግድ ፈገግ ለማለት እየታገልሁ
ነዉ፡ ብቻ የሆነ ያልሆነዉን እየቀላቀልሁ የጨዋታ ወሬ ለማምጣት ተዉሸለሸልሁ

“ምንድነዉ ልጄ?” አለ ባልቻ አዉቆብኝ ያልፈሰሰ እንባዬን እያበሰልኝ “ አሃ፤ ዛሬ ከነጋ አላየሁሽም ለካ? የት ዋልሽ?”

አስተናጋጁ እየተሸቆጠቆጠ መጥቶ የምንፈልገዉን ሊታዘዘን አጎበደደ፡ እሰይ! ገላገለኝ። በባዶ ሆዳቸዉ ሐቲታቸዉን ከምበላዉ፣
ምሳችንን በሰላም ብንበላ ለእነሱም ይሻላቸዋል። የቤቱን
የአገልግል ምግብ ከተጨማሪ ሱፍ ፍትፍት ጋር እንዲያመጣልን አዘዝን ሱፍ ፍትፍት የባልቻ የምንጊዜም ምርጫ መሆኑን
ከእሱ ጋር ለአንዴም
ቢሆን ማዕድ የተጋሩ ሁሉ ያዉቁለታል። የሚበላም የሚጣጠም ሲጠየቅ
ቀድሞ የሚመጣለት ነገር ሱፍ ነዉ። በሀገር ዉስጥ ምግብ ቤቶች ብቻም ሳይሆን፣ አንዴ ሩስያ አብረን የሄድን ጊዜ ሁሉ ቀዝቀዝ ያለ ሱፍ ፍትፍት ይኖራችኋል? ብሎ ሩስያዊቷን አስተናጋጅ ሲጠይቃት
ሰምቼዉ፣ የሳቅሁትን ሳቅ ሞቼም መርሳቴን እንጃልኝ! እስከ አሁን ትዝ ባለኝ ቁጥር ስቄ አይወጣልኝም: ሱፍ አዝዞ የለም ከተባለ፣ ለሆቴሉ የሚኖረዉ ግምት ሁሉ ወርዶ እንዴት እንደሚያደርገዉ አያድርስ ነዉ።
ይኼ ደግሞ ሆቴል ነዉ? ሱፍ ፍትፍት እንኳን የሌለበት ቤት! ብሎ
ሲያጣጥል ብዙ ጊዜ ሰምቼዋለሁ። ለእኔ ግን የሚበላ ይሁን እንጂ ምንም ቢሆን ያን ያህል አላማርጥም: በተለይ አሁን በኃይል ሞርሙሮኛል። ለወትሮዉ እንዲህ ድባቴ ዉስጥ ስሆን እንኳንስ ሊርበኝ ይቅርና የምግብ
ሽታ ሁሉ አይደርስብኝም ነበር አሁን ግን ምራቄ ኩችር ብሎ፣
ትንፋሼም ሳይቀር ሽታዉ እንደ ተለወጠ ለእኔም ታዉቆኛል።

“ችግር አለ እንዴ ዉቤ?” አለ እሸቴ፣ ከበላን በኋላ ከሁላችን በኋላ እጁን ታጥቦ ከመመለሱ፡
“ፊትሽ በፍጹም ልክ አይደለም” አለ፣ ባልቻም ተደርቦ፡
“ሆስፒታል ሄጄ ነበር''
“እ?” አሉ ኹለቱም፣ እኩል። የሆነዉን እና በሐኪሟ የተባልሁትን ሁሉ አንድም ሳላስቀር ነገርኋቸዉ። በየመሀሉ በድንጋጤ ከአሁን አሁን
ራሳቸዉን ይስታሉ ብዬ ስጠባበቅ፣ እነሱ ከመጤፍ ሳይቆጥሩት ቀሩብኝ ጭራሽ ባልቻማ ሊስቅብኝ ምንም አልቀረዉ፡ እሸቴም ቢሆን የምጠብቅበትን ያህል ጸጸት ቀርቶ ሐዘኔታ እንኳን አላሳየኝም፡

“ለዚህ ነዉ እንዴ ፊትሽን እንዲህ የክረምት ሰማይ ያስመሰልሽዉ?
“ከዚህ በላይ ምን አለና አባታለም?”
“ኧረ ዝም በይ! ደም አርግቶ የፈጠረንን አምላክ ለምናመልክ ለኛ፤ ይኼንን ጉዳይ ብለሽ … ምን እና ምኑ ተገናኝቶ፣ ሰዉ ሆነን እንደ
ተፈጠርን ጠፍቶሽ ነዉ? ልጄ ሙች! ካንቺ ይኼን አልጠብቅም”

ድንገት የእጅ ስልኩ ጮኸ፡ ወዲያዉ ፈገግታዉንም ተግሳጹንም አቋርጦ ስልኩን አነሳና፣ ለቅጽበት ያህል ከወዲያ በኩል አዳመጠ። ወዲያዉም
የምግቡን ሂሳብ ለመክፈል ኪሱን መፈታተሽ ሲጀምር አስቸኳይ ሁኔታ እንደ ተፈጠረ ገባኝ። ቀድሜዉ ሦስት ድፍን ድፍን መቶ ብሮች ጠረጴዛዉ ላይ አስቀመጥሁ።

“ምን ተፈጠረ?” አለ እሸቴ፣ እሱም እንደኔ ጥድፊያዉን በጥሞና እየተከታተለዉ ቆይቶ።
“ዕረፍት ያስፈልግሽ ነበር እዴ ዉቤ? አንድ መጥፎ ወሬ ደርሶኛል”

“ምነዉ ምን ተፈጠረ? ከየት ነዉ?”
“መስጊድ ላይ እሳት ተነስቷል ነዉ የሚሉኝ”
“የ..ት?” አለ እሸቴ፣ ልለዉ የነበረዉን ከአፌ ነጥቆኝ።
“ተከተሉኝ” ብሎ ከምግብ ቤቱ የመሮጥ ያህል ተራምዶ ወጣ፡ በእሱ ፍጥነት እግር በእግር ተከትለነዉ አሳንሠሩ ዉስጥ ገባንና ቁልፉን ተጭነን ወደ ላይኛዉ ፎቅ ጋለብን፡ በጠመዝማዛዉ መንገድ ገብተን
የለመድናቸዉን የደኅንነት ኬላዎች ሁሉ አልፈን በዚሁ ሕንጻ ወደ
ተሠወረዉ የሲራክ ፯ ማዕከል ስንደርስ፣ ሁሉም በየጥፍራቸዉ ቆመዉ አገኘናቸዉ እንኳንስ የጭንቅ ወሬ ተሰምቶበት፣ እንዲያዉም የዕረፍት
አልባዎች ቤት ነዉ ማዕከሉ
“እስኪ የታለ?” አለ ባልቻ፣ ከወገብ በላይ በግድግዳዉ ዙሪያ ወደ ተንጣለለዉ ዝርግ መከሰቻ ዓይኑን እያነጣጠረ፡
ደዉሎ የጠራዉ ልጅ የባልቻ ጥያቄ ስለገባዉ፣ የሚነካዉን ነካክቶ በርከት ያሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በሰፊዉ መከሰቻ ከዳር እስከ ዳር ደረደረልን እስከ ሚናራዉ ድረስ በኃይለኛ እሳት ሲንቀለቀል የሚያሳዩ
የመስጊድ ምስሎች ናቸዉ። ወላፈኑ እዚህ ያለንበት ድረስ በሚለበልብ እሳት ሲነድ ይታያል። ብዙ ሰዎችም እሳቱን ለማጥፋት ዙሪያዉን ሲዋደቁ ይታያሉ እንደ እሳቱ አያያዝ ግን መስጊዱን ማትረፍ የሚቻል አይመስለኝም:: ባይሆን ዙሪያዉን ባልተዛመተ እና በአካባቢዉ ተጨማሪ ዉድመት ባልደረሰ ስል በልቤ ጸለይሁ
#ገረገራ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በታደለ_አያሌው


...ባለ ዲጂኖዉ ትንፋሹ ሳይቀር የሚሰማበት ቅርበት ላይ ከአጠገቤ ደርሷል። ምኔን ቢወጋኝ አንድ ምት እንደሚበቃኝ እያማረጠ ይመስለኛል ትንሽ ፋታ ስጠኝ። ዓይኔን ጨፍኜ ብቻ ስንቱን እንዳሰብሁት በዚች ቅጽበት! ሞት እንዲህ አብሮኝ ኖሯል ለካ። “ቁልቁል ወደ ምድር
ለመዉረድ የፈጀነዉን ያህል፣ የሩብ ሩቡን እንኳን ሽቅብ ወደ ሰማይ ለመዉጣት አንፈጀዉም” ትላለች እመዋ። እዉነቷን አይደል? እንዲያዉ ማርያም ብላዉ የምጡ ጭንቅ ቀለል ያለ ቢሆን እንኳን፣ ለመወለድ ቢያንስ ቢያንስ ለዘጠኝ ወራት በማሕጸን ዉስጥ መክረም የግድ ነዉ።ለመሞት ግን ይኸዉ አንዲት ቅጽበት እና ዲጂኖ ያለዉ ገዳይ በቂ የሚሆኑበት ጊዜ አለ።

ግንባሬን ይለኛል ጸጥ እላለሁ። አበቃልኝ።

እንደ ዛሬ ሞትን ቀርቤ፣ ትንፋሽ ለትንፋሽ ተሻትቼዉ አላዉቅም: በዓይነ ኅሊናዬ የመጡልኝን ሁሉ በልቤ ተሰናብቼ ራሴን ለሞት አደላደልሁ።እመዋ፣ ባልቻ እና እሸቴ ነበሩ ቀድመዉ ትዝ ያሉኝ፡ በእርግጥ በየመሀሉ
የመጡልኝን ሌሎች ማኅበርተኞቼን እና ጓደኞቼን ሁሉ አዳርሻለሁ።በመጨረሻም፣ በሆዴ ወደ ተሸከምሁት ፅንስ እጆቼን ሰድጄ ደባበስሁት፡ እህ? ለካንስ ሐኪሟ ፅንሱ የሴት ነዉ ብላኛለች፡ ሴት ከሆነች ደግሞ እመዋ ስም አዉጥታላታለች: ማን ብላ? ቱናት። ቱናትን በዳሰሳ ተሰናበትኋት፡ ፀእንዲያዉ ነዉ የተሰናበትኂት እንጂ፣ መቼስ እኔ ሞቼ
ቱናት አትተርፍ፡ አብረን ወደ ሞት ተጓዦች ነን

“ዉብርስት?” የሚል ቃል ድንገት አጠገቤ ሰማሁ ገዳዬ አይደል? እንደ ምንም የአንድ ዓይኔን ሽፋሽፍት ፈልቅቄ ስገልጥ፣ ገዳዬ ቆሞበት በነበረ ሥፍራ ቢራራ ቆሞበታል እንደገና ጨፈንሁና ብገልጥም፣ ከቢራራ በቀር ማንም በፊቴ የለም፡፡

“የት ገባ?”

“ማ ?”

“ባለ ዲጂኖዉ?”

ፍርስ ብሎ የንቀት ሳቁን ለቀቀብኝ፡ “ለካ ስ እንዲህ ፈሪ ነሽና” እያለ
እንደ መሽኮርመም እያደረገዉም ጭምር አሁንም አሁንም አሽካካብኝ::እዉነትም ገና ድንጋጤዬ አለቀቀኝም: ድንገት እርም እርም የሚል የብዙ
ሰዉ ሆታ ሰማሁና፣ ዞር ስል ሰዎች ወደ ቤተልሔሙ እና ወደ ግምጃ
ቤቱ ይሯሯጣሉ፡ አንዳንዱ አፈር፣ አንዳንዱ ዉሃ፣ አንዳንዱ ደግሞ
ቅጠል እየያዘ ይራወጣል ያ ይባስ ያ ይቅደም ያን ተወዉ. እዚህ
ጋ አምጣዉ የሚል የተለያየ ሰዉ ድምፅ ተሰማኝ፡

እሳቱ! አሁን ገና ወደ ልቡናዬ ተመለስሁ፡

“እሳቱ! ወይኔ ወይኔ! ቤተልሔሙን ፈጀዉ” ስል ጮኹኩ፣ በሚርገበገብ ድምፅ ብሞትስ ቆይ!? ደግሞ እኮ ለሰማዕትነት ዝግጁ ነኝ እያልሁ ስመጻደቅ ነበር እንደ ደህና ሰዉ በቤተ ክርስቲያን ከመጡብኝ እንኳንስ
ሌላ፣ ሞትንም አልፈራ ባይ ነበርሁ ሐሰት ይኼዋ ልኬን አወቅሁት መስዋእትነቱም ይቅርና፣ ከራሴ ቀድሜ የማተርፈዉ ምንም ነገር
አለመኖሩን ነዉ ያየሁት ቢሆንም ግን ቀደም ብዬ የደወልሁት ደወል
የጠራቸዉ ምዕመናን እንደ ደራሽ ጎርፈዉ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እሳቱን በአጭር አስቀረተዉታል። ቢራራም አጠገቤ ቆሞ በእኔ የሚስቀዉ፣ የእሳቱን መጥፋት ካረጋገጠ በኋላ እንደሆነ ገባኝ፡
ሰአሊ ለነ!

“ቆይ ግን ገዳዬ የት ተሰለበ? አሁን እኮ እንዲህ ብሎ ቆሞ ነበር''
አልሁት ቢራራን፣ እጄን ጦር እንደሚወረዉር አዳኝ አድርጌ እያሳየሁት እሺ እሳቱስ ከምኔዉ ጠፋ? ይኼ ሁሉ ሲሆን እንዴት እንደሆነ የማስታዉሰዉ ምንም ነገር የለኝም:: የሚደንቀዉ ደግሞ አሁንም ገና ድንጋጤዉ ጨርሶ አልለቀቀኝም: ቆመች ቆመች እንደሚባልላት ጨቅላ
የሚያደርገዉን የጉልበቴን መንቀጥቀጥ ማንም እንዳያይብኝ ተሳቀቅሁ፡ቢራራ ከፊቴ እስከሚሄድልኝ ድረስ በዝምታ ብጠባበቀዉም አልሄድልሽ
አለኝ፡ ባለሁበት ቁጢጥ አልሁና ወደ ልቡናዬ ለመመለስ፣ መድኃኒቴ የሆነችዋን ጸሎቴን በለሆሳስ አደረስሁ: ከቅድሙ አንጻር ልቤም የሚመታበት ፍጥነቱ በረድ ቢልም፣ ጨርሶ ግን ልክ ሊሆንልኝ አልቻለም

"እና ፈርቼ ነዉ?” አልሁት ቢራራን፣ ፈቀቅ ብሎ ወዳለዉ የእንጨት
መቀመጫ እየጎተትሁት።

“እንክት!” አለኝ፣ በእርግጠኝነት

“በእርግጥ ፈተና ባይኖር ሁሉ ተማሪ፣ ጠያቂ ባይኖር ሁሉ አስተማሪ መባሉን አዉቃለሁ: ግን እንደዚያ ነበርሁ ወይ እኔ? ተሞክሬ ባላዉቅ ነዉ
እዉነት? በጅቦች መካከል፣ በጨለማ አካፋይ ሞትን ተፋጥጬዉ አላዉቅም? ሌላዉ ሌላዉ ቢቀር፣ ሲራክን ከተቀላቀልሁ እንኳ ን
ይኼዉ ኹለተኛ ዓመቴን ጨልጫለሁ: እስከ አሁንም ድረስ ሐሞቴን የሚፈትኑ ስትና ስጓት ተልእኮዎች በየዕለቱ ከማዕከሉ እቀበላለሁ:: እንዲያዉ ምን ብረሳ ብረሳ በታላቁ ቤተ መንግሥት የገጠመኝን እረሳዋለሁ? እዉነት አተስ ያን ጀብዱ ሳትሰማ ቀርተህ ነዉ?” አልሁት፣ ቤተ መንግሥቱን መጥቀሴ ክፋት እንደ ሌላዉ በማስተዋል እኔ አሁን ጀብዱ ስለምለዉ ነገሬ ላይሰማ ቢችልም፣ ማዕከላችን ሲራክ ፯ በቤተ መንግሥት ምስጢር እንዳለዉ ያወቅነዉ ግን አብረን ነበር

“ሳትሰማ ቀርተህ ነዉ እዉነት ቢራራ?” አልሁት፣ ባለማመን። ይኼ ታሪክ ከተፈጸመ በኋላ፣ እንደኔ ላሉ የሲራክ ፯ መረጃ ሰብሳቢዎች በነበረዉ ወቅታዊ ስልጠና ጭምር ለምሳሌነት ተጠቅሶ እንደ ነበር
በማስታወስ፡
“በታላቁ ቤተ መ ግሥት?”
“ታዲያስ!”
“እንደምታዉቀዉ፣መአከላችን ሲራክ ዋና ዋና በሚባል
የመንግሥት…ብዬ ጀመርሁለት። እዉነትም አልሰማም ኖሯል
እየተቁነጠነጠ አዳመጠኝ።
እንደምታዉቀዉ፣ ማዕከላች ሲራክ ዋና ዋና በሚባሉ የመንግሥት እና ዓለም አቀፍ ዋና በሚባሉ የመንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ዉስጥም እጅግ ቁልፍ ሥራ ያላቸዉን ዳሳሾች (Sensors) እና ካሜራዎች በሥዉር አስቀምጧል: አንዳንዶቹ ድምፅ፣ አንዳንዶቹ ምስል፣ አንዳዶቹ ደግሞ እንቅስቃሴ በድብቅ እየዳሰሱ እና እየቀዱ ወደ ማዕከላችን የመረጃ ቋት
በቀጥታ የሚልኩ ናቸዉ:: ስለሆነም እነዚህ መሣሪያዎች በተሸሸጉበት አካባቢ ሁሉ የተፈሳችም ሆነ የተተነፈሰች ነገር ሲራክን አምልጣ ?
አታዉቅም: ምንም እንኳን መተዳደሪያ ሥነ ሥርዓቱ ስለማይፈቅድልኝ በየትኛዉ ቦታ ስንት ዳሳሽ መሣሪያ እንደ ተተከለ የማዉቅበት ደረጃ ላይ ባልሆንም፣ ከዐሥር ሺ ያላነሱ ዘመናዊ ዳሳሾች በተለያዩ ቦታዎች
እንደሚኖሩ እገምታለሁ: ለግምቴ ደግሞ በቂ ምክንያት አለኝ” አልሁት፣ የማዳመጥ ጉጉቱን ቀና ብዬ እያስተዋልሁበት ቋምጧል።

“ሰኞ ይሁን ማክሰኞ ቀኑን ዘነጋሁት እንጂ…”

ሰኞ ይሁን ማክሰኞ ቀኑን ዘነጋሁት እንጂ፣ የዛሬ ሰባት ወር ገደማ
ለአንድ ተልእኮ እንድዘጋጅ በራሱ በቀድሞዉ የሲራክ ፯ ኃላፊ ታዘዝሁ። “ ስለ ምንነቱ በዝርዝር ከመንገሩ በፊት፣ ስለ አደገኛነቱ አጥብቆ ሊያስረዳኝ ከሞከረ፡ እኔም ተልእኮዉ ምን ይሁን የት ይሁን ገና ሳላዉቀዉ፤ ምንም
ሥጋት እንዳይገባዉ በልበ ሙሉነት ገለጽሁለት።

“የለም የለም፣ የገባሽ አልመሰለኝም” አለኝ እንደገና፣ ጉዳዩን ማቃለሌ ገርሞት ባላስተዋልኋቸዉ ነገሮችም ሳይታዘበኝ የቀረ አይመስለኝም።
እንዲሁ ላይ ላዩን ፍርጥም አለብኝ፡ እዉነትም ከእሱ ጋር ቃል እየተመላለስሁ መሆኑን ራሱ ያስተዋልሁት ዘግይቼ ነበር
“ለወትሮዉ ማንኛዉንም ተልእኮ የምቀበለዉም ሆነ ተልዕኮዬን በተመለከተ የምነጋገረዉ ከቅርብ ኃላፊዬ ጋር ብቻ ነዉ። ሲጀመር የቀድሞዉን ዋና “ ኃላፊ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅርበት ያየሁት ራሱ፣ በዚሁ ዕለት ባልቻ
#ገረገራ


#ክፍል_አስር


#በታደለ_አያሌው


ዉሃ ሆንሁ፣ የመጨረሻዉን ድንጋጤ ደነገጥሁ።

ከነበርሁበት የምድር በታቹ የሲራክ ፯ ማዕከል ወጥቼ በቅርበት ወደሚገኘዉ የድንግል ማርያም ገዳም ለጸሎት ገባሁ አንድ ያለኝ አቅም ጸሎት ነዉና፣ አሳፍሮኝ የማያዉቀዉን አምላክ በእናትህ እርዳኝ አልሁት ተንበርክኬ ከተንበረከክሁበት ተነስቼ በምሥራቅ በኩል ባለዉ የቅጽሩ
በር ልወጣ እየተራመድሁ ልክ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ ላይ ስደርስ፣ ደስ የሚያሰኝ የሕጻናት መዝሙር በጆሮዬ ጥልቅ አለ በክፍቱ መስኮት አስግጌ ወደ ዉስጥ ስመለከት፣ ሰልፍና ልብሳቸዉን ያሳመሩ ሕጻናት “ሀገሪትነ” የሚለዉን ነባር ዝማሬ በኅብረት ያጠናሉ። ለአጭር
አፍታ ከዝማሬያቸዉ ቀምሼ መንገዴን ልቀጥል እግሬን ሳነሳ አንድ በየት
በኩል እንደ መጣ ያላየሁት፤ 'ቤ መ' የሚል ኮድ ያለዉ ታርጋ የለጠፈ
መኪና ከሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ በር ጥሩንባዉን ነፋና ሲጢጥ ብሎ ቆመ። የታርጋዉ ኮድ ትኩረቴን ስለ ሳበዉ፣ በአዳራሹ እና በግቢዉ አጥር መካከል ወዳለዉ ሰዋራ ሥፍራ ተሰዉሬ የሚሆነዉን ሁሉ በሥርቆሽ መከታተሌን ጀመርሁ: አፍታም ሳትቆይ፣ ሕጻናቱን
እያስጠናች የነበረችዋ ወጣት ወደ በሩ ብቅ ብላ አየችዉና ልጆቹን
እንዲወጡ ጠራቻቸዉ። ሕጻናቱም በደስታ እየፈነደቁ ተሯሩጠዉ ወጥተዉ የመኪናዉ በር እስከሚከፈትላቸዉ ድረስ ተቁነጠነጡ።

“ኧረ ክፈቱልን” ይላል አንደኛዉ ሕጻን፣ አላዳርስ ብሎት በሩን ራሱ
ለመክፈት እየታገለ

“ስሚ ለማን እንደምዘምር አዉቀሻል ግን? ለመንግሥት እኮ ነዉ” ትላለች ሌላኘዋ ጓደኛዋን ለማስቀናት በሚመስል አኳኋን አንገቷን እየወዘወዘች።
“ለመግሥት? ኧረ አይባልም!” ብላ አረመቻት ያቺኛዋ፣ በሳቅ ቡፍ
እያለችባት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስም ጠርታ፣ መንግሥት ያለችዋን ልጅ አላገጠችባት።

አሁን ነዉ እንግዲህ መፍጠን አልሁት ለራሴ፡ ዕድሎች ከስንት አንድ
ከላይ ይወርዱልናል፣ አብዛኞቻችን ግን ራሳችን ነን የፈጠርናቸዉ› ሲባል
ሰምቼ ነበር በማዕከላችን በሲራክ ፯ ከስንት አንድ ከሚወርዱት ዕድሎች
አንደኛዉ ይኼዉ የዓይኔ ብረቱ ሥር ወርዶልኛል።

እንዴት ብጠቀመዉ ይሻላል?

ሁሉም ሕጻናት ከወጡ በኋላ መዝሙሩን ያስጠናችዋ ወጣት መብራቱን
አጠፋፍታ ነጠላዋንም በቅጡ እያጣፋች መጣች፡ ይኼ ሁሉ ሲሆን ሾፌሩ
አልወረደም አለመዉረዱ ሲገርመኝ፤ በሩንም ራሷ እንድትከፍትላቸዉ
ጠበቃት እሷ ደርሳ ስትከፍትላቸዉ ልጆቹ እሽቅድምድም ፈጥረዉ አይገቡ የለም እርስ በእርስ እየተጣጣሉ ገቡ፡ አሁን መኪናዉ ፊቱን አዙሮ ይሄዳል ብዬ ስጠባበቅ፣ ምን እንደ ረሳች እንጃላት፣ አስጠኛቸዉ ወረደችና ተመልሳ ወደ አዳራሹ ሮጣ ገባች። ይኸኔ ጥግ ለጥግ
ተሹለኩልኬ የአዳራሹን የኋላ በር በኃይል አንኳኳሁባት። ያለ ምንም ፋታ ደጋግሜ ሳንጓጓባት ብልጭ ብሎባት በእልህ ከፈተችልኝ።

“እ! ምንድነዉ?” አለች፣ በሩን በጥድፊያ ስትከፍተዉ እኔ በድንግዝግዙ
ዉስጥ ብቁለጨለጭባት የተመለሰችዉ ከበሮዉን ረስታዉ ኖሯል ለካ፣
በቀኝ ትከሻዋ አንግታዋለች ለኹለት ሰዓታት ሰመመን ዉስጥ የሚከተዉን ቅባት የረጨሁባቸዉ መዳፎቼን እያፋተግሁ ትንሽ የመዘናጊያ ፋታ ከሰጠኋት በኋላ ዘልዬ አፏን አፈንሁት፡ በቅጽበት መዝለፍለፍ ስትጀመርልኝ፤ ከበሮዉን በአንድ እጄ፣ እሷን ደግሞ
በሌላኛዉ እጄ ለመደገፍ ሞከርሁ፡ ሽርተት ብላ መሬት ያዘችልኝ፡ ዝቅ ብዬ እጄን በመሬቱ አሽቼ ቅባቱን ካረከስሁት በኋላ፣ ነጠላዋን ልክ እሷ ተከናንባዉ እንደነበር አድርጌ አጣፋሁትና ከበሮዉን አንስቼ አነገትሁት ክራሬንም በግራ እጄ አንጠለጠልሁትና መብራቱን አጠፋፋሁ፡፡
መኪናዉም ፊቱን አዙሮ ለመሄድ ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቀኝ፡ ከሾፌሩ ይልቅ ሕጻናቱ እንዳይለዩኝ የባሰ ስለ ሰጋሁ፣ ከበሮዉን ከኋላ ጭኜ፣ ጋቢና ገባሁ ብቻ የፈራሁትን ያህል ሳልቸገር፣ ወደ ታላቁ ቤተ መንግሥት ገባሁ የመኪና ማቆሚያዉ ላይ ስንደርስ፣ ሌላ ሰዉ ተቀብሎን ወደ
ግብዣዉ አዳራሽ ወሰደን በዚያ ስንደርስ ደግሞ አንዲት ባህላዊ ቀሚስ
የለበስች ሴት ተቀብላ ከመድረኩ ጀርባ ካሉት ክፍሎች ወደ አንደኛዉ
አስገባችን ክፍሉን ሳየዉ ጠበብ ያለ ቢመስለኝም፣ ስንገባበት ግን ጠብ
እንኳን አላልንበትም ሌላ ብዙ ሰዉ ቢጨመር ሁሉ አይጠብም፡ በዚያም
ላይ የመድረኩን ትዕይንት በቀጥታ የሚያስተላልፍልን ዘመናዊ
ቴሌቪዥን ግድግዳዉ ላይ ተሰቅሎበታል

አሁን ነዉ ጉዱ ከሕጻናቱ ጋር በደማቅ ብርሃን ልፋጠጥ ነዉ፡ መቼም ጥያቄ
መጠየቃቸዉ አይቀር፣ ወይ ደግሞ እንድናገር የሚያደርጉበት አንድ ነገር
አያጡም: ያስጠናቻቸዉ ወጣት እንዳልሆንሁ ሲያዉቁ ምን ያደርጉ
ይሆን? በተቻለኝ መጠን አንገቴን አቀርቅሬ ወዲያ ወዲህ እያልሁ ራሴን ባተሌ አደረግሁባቸዉ። ዓይናቸዉ ዉስጥ ላለመግባት ብዙ ተፍተለተልሁ መቆያ ክፍል የሰጠችን ደርባባ ሴት ተመልሳ መጣችና የመርሐ ግብሩ ቅደም ተከተል የሰፈረበት ወረቀት ሰጠችኝ፡ አስከትላም፣
የኛ ተራ እስከሚደርስ ድረስ የመጨረሻ ልምምድ ማድረግ ከፈለግን፣
ያለንበት ክፍል ድምፅ ወደ ዉጪ ስለማያስወጣ እዚሁ መለማመድ
እንደምንችል አሳወቀችኝ፡ ስለዚያ ገና ሳላመሰግናት፣ መቆያ ምግብ
እንድናዝዝ ጎንበስ ብላ ጠየቀችን፡ እንዲህ ያለችዋ ሽቁጥቁጥ ሴት ለሕጻናቱ ከተመደበች፣ ለዋናዎቹ እንግዶችማ እንዴት ያለ ሰዉ ሊመደብ እንደሚችል ገመትሁ። መቼም ትሕትናዋ ወደር አይገኝለትም: ምንም እንኳን ሕጻናቱ ምርጫቸዉን እየለዋወጡ ረዥም ሰዓት ቢወስዱባትም፣ከበሬታዋ ግን አልቀነስም፡ እኔም እንዲሁ ወዳፌ የመጣልኝን የባቄላ
ሾርባ አዘዝሁ።

የሕጻናቱን መዝሙር ተከትሎ መንዙማ የሚያቀርቡ ሙስሊም ሕጻናትም መኖራቸዉን ያወቅሁት ወረቀቱ ላይ የሰፈረዉን ዝርዝር መርሐ ግብር ከተመለከትሁ በኋላ ነበር ሰዓቴን ስመለhት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ይላል። በዕቅዱ መሠረት መዝሙር ለሚቀርብበት ተራ፣ ሃያ ደቂቃዎች ይቀራሉ ማለት ነዉ: ከፊቴ የተሰቀለዉ ቴሌቪዥን፣
የአዳራሹን ትዕይንት ቀጥታ እያመጣ ስለሚያሳየኝ፣ የተጠቀሱት መርሐ
ግብራት ያለ ምንም መጓተት በየተራቸዉ እየቀረቡ መሆኑን አዉቄያለሁ:

ሲንሾካሾኩ ሰምቼ በቀስታ ዞር ብል ሁሉም ሕጻናት አፍጥጠዉብኛል ዝምታየ ሽሽቴ፣ አድራጎቴ ሁሉ ገርሟቸዉ! ወዲያ ስልም ወዲህም ስል በዓይናቸዉ ይከታተሉኛል። የመጣዉ ይምጣ ብዬ ክንብንቤን ገለጥ
አደረግሁና፤ ማንነቴን በከፊል ነገርኋቸዉ።

“እንዴ?” ተባባሉ

“አላልኋችሁም? እግዚሐርያ አይደለችም” አለ አንደኛዉ ሕጻን፣ዉርርዱን በማሸነፍ።

“እሷስ?”

“እግዚሐርያስ?”

"በጥያቄ አካለቡኝ"

“እግዚሐርያ እኮ ድገት አሟት ተተኪልኝ ብላኝ ነዉ” አልኋቸዉ፣ መዝሙሩን ያስጠናቻቸዉ ልጅ እግዚሐርያ መባሏን ከራሳቸዉ አፍ ስላወቅሁ ስሟን መጥራቴ ለአመኔታ እንደሚያግዘኝ በማሰብ

“ኧረ ቅድም ደህና አልነበረች? ከምኔዉ አመማት?” አለ፣ ከመካከላቸዉ
ቅድም ጀምሮ ቀደም ቀደም የሚለዉ ልጅ።

“ግድየለምቆይ፤ በኋላ በስልክ አገናኛችኋለሁ: አሁን መዝሙሩን
ለመጨረሻ ጊዜ እንለማመደዉ? የማቅረቢያ ሰዓታችን እየደረሰ ነዉ። በሉ
ተነሱ። ተነሷ” አልሁ በመለማመጥም በማጣደፍም ጭምር፣ ከዚህ በላይ
እንዳይከራከሩኝ በልቤ እየጸልይሁ፡ ክራሬን እየቃኘሁ “በሉ እሺ፤
መዝሙሩን ለመዘመር፣ በአብ በወልድ በመፈስ ቅዱስ ስም…”አልኋቸዉ፣ ፋታ ላለመስጠት እዉነትም አላሳፈሩኝም፤ ብድግ ብድግ አሉልኝ፡ ከመካከላቸዉ ትንሽ ከፍ የምትለዋ ልጅ ከበሮዉን አነሳች፡ እኔም መዝሙሩን በቅጡ የምችለዉ ስለሆነ፣ እምብዛም
ሳልደነቃቀፍባቸዉ ጥሩ አድርገን አብረን ወጣነዉ
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በታደለ_አያሌው

...ረቂቋን የጆሮ ማዳመጫ አዉቆብኝ ኖሯል፤ መንጭቆ አወጣብኝ፡፡
ማደመጫዉን የያዘበትን እጁን ሳይ ተገለጠልኝ ባልቻ በአንድ ወቅት
ከፍተኛ የመንግሥት ደኅንነት ሹሞችን አጠቃላይ መገለጫቸዉን ለጥቂት
የሲራክ፯ አባላት በገለጸልን ጊዜ፣ ስለዚህ ሰዉ ልዩ ምልክት የነገረን አስታዉሼ ይኼን ሰዉ ገመትሁት አወቅሁት የቀለበት ጣቱ ከስሯ ጀምራ የለችም: በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ሰው
እጅ መግባቴን፣ አሁን አወቅሁ ሰዉዬዉ የሀገር ዉስጥ ደንነት ዋና መምሪያ ሹም መሆኑን አሁን ገና፣ ነገሮች ሁሉ ከተጨመላለቀ በኋላ ተረዳሁ። አጠመድሁ ስል እንደ ተጠመድሁ ያወቅሁት፣ አሁን ገና ሁለት እጆቹ ካነቁኝ፣ ድፍርስ ዓይኑ ካፈጠጠብኝ፣ ድርብርብ ጥርሱ ካገጠጠብኝ በኋላ ነበር። መጠርጠር አልነበረብኝም? ነበረብኝ።

«ላም ሆይ ላም ሆይ ሞኟ ላም ሆይ
ሣሩን አየሽና ገደሉን ሳታይ
እልም ካለው ገደል ወደቅሽብን ወይ

እያልሁ፣ መስኮት ቀርቶ ስንጥቅ እንኳን በሌለዉ አመዳም ግድግዳ ላይ
አፍጥጬ በራሴ አላገጥሁበት።

“ጥሩ” አለ የተገለበጠችዋን ወንበር አቃንቶ ራሱ እየተቀመጠባት
“እንተዋወቃ… ማን ብዬ ልጥራሽ?”

ባፍንጫዬ አናፍቼ ብቻ ጭጭ አልሁበት።

“ኦ..ይቅርታ፤ መጀመሪያ ራሴን ማስተዋወቅ ይገባኛል ለካ። ኮሎኔል…"
ብሎ ስለራሱ ሊነግረኝ ሲጀምር ጆሮዬን ያዝሁበት ስሙን እንዲጠራብኝ
አልፈለግሁም አዉቄዋለኋ!

“ማ..ነ..ሽ?” አለኝ በዝግታ፣ በዚያች ኦና ቤት ዉስጥ ብቻ ለብቻ ሲከበኝ
ቆይቶ በዓይኔ እንኳን እንዳልላወስ ከግድግዳዉ ጋር እያጣበቀኝ
ወዲያዉኑ ጆሮዉን ወደ ከንፈሮቼ አምጥቶ ለረዥም አፍታ መልሴን መጠባበቅ ቢጀምርም፣ ትንፋሼን ሳይቀር ዋጥሁበት እንኳንስ ለኮሎኔ ይቅርና፣ ለገዛ እናቴ እንኳን እንዲህ ነዉ ብዬ የማፍረጠርጠዉ ማንነት የለኝ እኔ፡ ዉብርስት እባላለሁ የሲራክ አባል ነኝ የምል መስሎታል? አያዉቀኝማ! አ ያ ዉ ቀ ን ም! ሲራክ.፯ን ጨርሶ አያዉቀንም ማለት ነዉ። የሆነዉ ሁሉ ሆኖም፣ ኮሎኔሉ ከዚህ በላይ
ትዕግሥት የሚኖረዉ አይመስለኝም: ቀጣዩን ጥያቄዉንም እንደዚሁ
ተለሳልሶ እንደማይጠይቀኝ ቁልጭ ብሎ ታይቶኛል።

ስለዚህ አእምሮዬን ማሠራት አለብኝ፡

እኔ ስለማደርገዉ ሳወጣ ሳወርድ፤ እሱ ቀድሞኝ ጆሮዉን ከከንፈሮቼ አንስቶ ከንፈሮቹን ወደ ጆሮዬ አመጣብኝ፡ ይህም ሳያንስ የጥምቀትን ዉርጭ የሚያስመሰግን ቀዝቃዛ ትንፋሹን ለቀቀብኝ ፡ ከዚያ ምላሱን እና
የላይኛዉን ትናጋዉን በማጋጨት መሰለኝ፣ ሦስት ሰቅጣጭ ድምፆች
አከታትሎ አጮኸብኝ በምላስም ማጨብጨብ ይቻላል እንዴ?

“ጣ! ጣ! ጣ!”

ጣዉላ እና ጣዉላ ቢጋጭ ራሱ እንደዚህ መጮሁን እኔ እንጃ በቅጽበት አንድ ጎረምሳ እንደ ሳምሶናይት ያለ ትልቅ ቦርሳ ተሸክሞ ከተፍ አለለት የመጨረሻ ዕድል ሰጥቼሻለሁ፣ የምትነግሪኝ አለ? ማነሽ ለማለት በሚመስል ሁኔታ በጥልቀት ሲያስተዉለኝ ቆይቶ ወደ በሩ አመራ።
በሩን ከፍቶ እንደ መዉጣት ካለ በኋላ፦

“ቶሎ!” የሚል ትእዛዝ ሰጠዉ

“እሺ፤ እንደ ተለመደዉ” ሲል መለሰለት፣ ባለ ሳምሶናይቱ አናዛዥ። እኔና አናዛዡ ብቻ ቀረን፡ በሩን ቀጭ አድርጎ ቆለፈና መክፈቻዉን በኪሱ ወሽቆ ሳምሶናይቱን እዚያች ደረቅ ወንበር ላይ አስቀመጠ። እስኪከፍተዉ ድረስ እሱም ዓይኑን ከዓይኔ፣ እኔም ዓይኔን ከእጁ ላይ አልነቀልንም አንደኛዉን ኪስ ከፍቶ ዘረገፈዉ፡ ሰአሊ ለነ! ያላመጣዉ ምንም የስለት መሣሪያ የለም፡ ትንሿ የብረት መጋዝ ሳትቀር መጥታለች፡ ከሳምሶናይቱ
ሌላኛዉ ኪስም እንዲሁ መርፌዎች እና መርዝ የተሞሉ አራት ብልቃጦች ዘረገፈ፡ ይኼ ሁሉ ለኔ እንዳይሆን ብቻ! ነዉ?

“ቶሎ ምረጭ፣ የቱ ላስቀድምልሽ?”

“እ?” አልሁት፣ ድምፄን ቢከዳኝ በቅንድብ ምልክት፡
“‹ለሞኝ ጉድኋድ አያሳዩትም፣ ቤት ነው ብሎ ራሱ ይገባበታል› ተብሎ ሲተረት ብሰማም፤ የቆንጆም ሞኝ እንዳለዉ ግን አቺን አሁን ገና አየሁ ገና በገዛ'ጅሽ ሰተት ብለሽ እንጦሮጦስ ትወርጃለሽ? ጅል!”

ደም የጠማዉ ነፍሱን በጥርሱ በኩል አሳየኝ፡፡ በኹለቱም ጎኗ ስለት ያላትን ቢለዋ እና ፒንሳ እያጋጨ ወደኔ መጣ፡ ሥራዉ የሰዎችን አካል እያፈረሰ የሚያናዝዝ ሰዉ መሆኑ ያስታዉቃል ለእንደ'ሱ ዓይነት ሰዎች ደግሞ ጥፍር መንቀል፣ የዉሃ ጥም እንደ መቁረጥ ያለ እርካታ ያመጣላቸዋል እንጂ እንዲች ብሎ አይስቀጥጣቸዉም፡ ለምደዉታል:
ርኅራኄ የሚባለዉን ነገር ከዉስጣቸዉ ጨልጠዉ ደፍተዉታል እንዲያዉም ብዙ ጊዜ የሚመረመረዉ ሰዉ ለሐቅም ሆነ ራሱን ለማትረፍ ሲል፣ ገና ሳይነኩት ቶሎ የተናዘዘ እንደሆነ በኃይል ይናደዳሉ ይባላል።

“ጅል ነሽ እንዴ ? ”

እንደ ቅድሙ ባፍንጫዬ አናፍቼ ብቻ ጸጥ አልሁት።

ቁልቁል እያየኝ ከአጠገቤ ቆሞ ነበር። ወደ ኋላ የሚመለስ መስሎ፣ ከመሬቱ ጋር ደባለቀኝ፡ ምኔን በምኑ እንደ መታኝ እንኳን አላየሁትም። ብቻ ብዥ ጭልም ብሎብኝ ቆየሁ።

ነፍሴ ስትመለስ ብልቃጧን ሲያነሳ አየሁት በብልቃጧ ላይ የሰፈረዉን
ስም አሻግሬ ሳነበዉ ሪማሾ-ሚር (Himacio-mir) የሚባለዉ የሰመመን
መርዝ መሆኑን አወቅሁ። ከሚያስቃዠዉ ሰመመን በፊት ጡንቻ የሚያኮማትር እና ሽቅብ ሽቅብ የሚያስብል ንጥረ ነገሮችም አብረዉ እንደ ተቀበመሙበት አዉቃለሁ እሱን የተወጋ ሰዉ ታዲያ እንባ እንደ ዝናብ
እስኪወርደዉ ድረስ ያምጣል እንጂ ወጥቶለት የሚገላገለዉ ነገር
አይኖረዉም፡ ለማስመለስ ጫፍ ይደርስና ይመለሳል። ስለሆነም ጭንቁ አያድርስ ነዉ በጠባብ ጫማ ከመዋልም፣ ሽንት አቋርጦ ከመቋጠርም፣ ሚስማር ላይ ከመቀመጥም ሁሉ ይብሳል

መርፌዉን ተክሎ ሲሪንጁ እስኪሞላ ድረስ ብልቃጧን ምጥጥ አደረጋት።
ሲሪንጁ ጢቅ አለለት: ይኸኔ ጡንቻዎቼን ማነቃቃት ጀመርሁ። ከቀደመኝ አበቃልኝ፡ ልክ እጁን አንከርፍፎ ሲመጣ፣ የፈራሁ መስዬ አንድ ዓይኔን በእጆቼ ጨፈንሁ: ወደ ማጅራቴ መርፌዉን ሲሰድ እጁን
ለቀም አድርጌ ያዝሁትና፣ ፋታ ሳልሰጠዉ ጠምዝዤ ደረቱ ላይ ስካሁለት ዓይኔን እንኳን እስከማርገበግብ አልዘገየም፣ ትዉኪያ ሲያጣድፈዉ ልክ የገማ ጣት እንደ ጎረሰ ሰዉ፣ እንባዉ ዱብ እስኪል ድረስ ሽቅብ ቢለዉም ምንም አይወጣዉ። “ህእእእ!” ይላል በየቅጽበቱ፣ ስቃይ ብቻ! በዚያ ላይ የሠራ አካላቱ እየዛለበት መጣና፣ እንደ አሮጌ ጨርቅ እጥፍጥፍ ብሏል ጊዜ ኖሮኝ ባዘንሁለትማ ደስታዬ ነበረ ግን ለሐዘኔታ የሚሆነዉን ጊዜ የት ልዉለድለት? ይልቅ አሁኑኑ ማምለጥ አለብኝ፡፡ ባይሆን
እያመለጥሁ አዝንለታሁ
ያዉም ከቻልሁ ከኪሱ ባወጣሁት ቁልፍ በሩን ቀስ አድርጌ ከፍቼ አንገቴን ሳሰግግ
በአካባቢዉ ማንም የለም:: ቢሆንም ግን እርግጠኛ መሆን አልቻልሁም:
ያለሁት ዋነኛዉ ቤተ መንግሥት ዉስጥ ነዉ፡ ቤተ መንግሥትን ያህል ግቢ፣ በሚታዩና በሚዳሰሱ ወታደሮች ብቻ ይጠበቃል ማለት ጅልነት
ነዉ። በየሥርቻዉ ካሜራ፣ በየቦታዉ ረቂቅ ዳሳሾች መኖራቸዉ አያጠራጥርም።

“ህእእእ. አህክ እትፍ! ህእእእ አህክ እትፍ!” ይላል አሁንም፣አንጀቱ ከጉሮሮዉ ጫፍ እስኪደርስበት እየሳበዉ፡ ደም ከሚያስንቅ እንባ በቀር ሌላ ምንም ጠብ አይለዉም: መጨከን አለብኝ እንጂ፣ ሁኔታዉ አንጀት ይበላል ያሳዝናል። የሐፍረተ ሥጋዉን መሸፈኛ ብቻ ትቼለት
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በታደለ_አያሌው


....“ራስህ ነህ፤ አዎ: ግን እንዴት?” አልሁት መኪናዉን የቤተመንግሥት ታርጋ እንዳየሁበት አስታዉሼ። ለነገሩ ባልቻ የማያልፍበት ምን የመርፌ ቀዳዳ አለና ነዉ? ልክ ወደ መዉጫዉ በር ስንቃረብ፣
መኪናዉን ድንገት ሲጢጥ አድርጎ አቆመዉ።

"አይሆንም በዚህ መልኩ መዉጣት አንችልም። ይኸኔእኮ በሩ ተከርችሞ ወታደሮችም በጥፍሮቻቸዉ ቆመዉ እየጠበቁሽ ይሆናል: ኮሎኔሉ ሳይቀር መሬቱን እየጠለዘ በመንቆራጠጥ ላይ ነዉ የሚሆነዉ።ምክንያቱም ከግብጽ ትሆኚ ከኤርትራ፣ አሸባሪ ትሆኚ ተገዳዳሪ፤ ምንነትሽን እንኳ ን በቅጡ ያላወቁሽ አንቺ ከእጃቸዉ ስላመለጥሽባቸዉ እታሰስሽ ነዉ የምትሆኝዉ: ስለዚህ በየትኛዉም በር መዉጣት አንችልም ደኅነት እና ወታደር ሁሉ ተነስንሶ እያፈላለገሽ ከሆነ ደግሞ አስቢዉ፣ግቢም ደግሞ መቆየት አንችልም: አጣብቂኝ ዉስጥ ነን”
አለኝ፣ እንደ መረታት ብሎ።

“እንዲህ ብናደርግስ?” አልሁት፣ ሰዓቱን እንዲመለከት እየጠቆምሁት።
“በመርሐ ግብሩ መሠረት፣ በአዳራሽ የነበሩት እንግዶች መዉጫቸዉ ነዉ: በእርግጥ አልፏል: የፈለገ በየሰበቡ አንዛዝተዉ ቢያቆዩአቸዉ
እንኳን፣ መዉጣታቸዉ ግን አይቀርም: መቼሰ እዚሁ አያሳድሯቸዉ።ይወጣሉ። እነሱ እስከሚወጡ ድረስ ጠብቀን በየመኪናቸዉ ተከታትለዉ
ሲወጡ እኛም ተደባልቀን መዉጣት እንችላለ”

“ፍተሻዉ ቀላል ይሆናል ብለሽ ነዉ?” አለ የመኪናዉን መብራቶች
አጠፋፍቶ በዝግታ ወደ ተነሳንበት ቦታ ወደ ኋላ እያሽከረከረ ወደ ሰፊዉ የመኪና ማቆሚያ ተመልሰን ልክ ከመቆማችን፣ የጋቢናዉ በር ተንኳኳ።
ስአሊ ለነ! መኪና ማቆሚያዉ ጠባቂ እንዳለዉ እንዴት አልገመትንም?እንኳንስ የቤተ መንግሥቱ ተራ የመንገድ ዳር መኪኖችስ ጠባቂ አላቸዉ
አይደል እንዴ? ቀሽሞች ነን! የኔስ እሺ፣ ባልቻ እንዴት ልብ አላለዉም
ይኼን?

ጋቢናዉ በድጋሚ ተንኳኳ

“አቤት?” አለ ባልቻ እኔን ወንበር ሥር እንድደበቅ በዳበሳ ምልክት
ከሰጠኝ በኋላ፣ መስታዎቱን ዝቅ አድርጎ፡

“ችግር አለ?” አለ ጠባቂዉ፣ በትሕትና

“እህህ” ብሎ የማስመሰል ሳቅ አስቀደመ፣ ባልቻ። “እህህ… ያዉ
ታዉቀዉ የለ የኛን ሥራ? አለቆቼ አድ ቦታ ላኩኝና እየወጣሁ ሳለ ደግሞ እንደገና እንድተወዉ ደዉለዉልኝ ነዉ እንጂ ችግር የለም: የማደርሳቸዉ እንግዶች ሳይኖሩ አይቀርም”

“አይደል? ተደዉሎልህ?” አለ ሰዉዬዉ ልብ በሚወጋ ስላቅ።
ወዲያዉኑ በአቅራቢያ የሚያልፉ ኹለት ወታደሮችን አፏጨላቸዉ።
እየበረሩ እንደ መጡ ኮቴያቸዉ ነግሮኛል።

“ይቅርታ ጌቶቼ፣ የሚያጠራጥር ነገር ካለ አሳዉቅ ተብዬ ነበር። መቼም ሰዉ ያለ ምክንያት መብራት አጥፍቶ ወደ ኋላ አይነዳም: ምናልባት
የምትፈልጉት ዓይነት ሰዉ እንደሆነ ብዬ ነዉ” አላቸዉ፣ ወደ ባልቻ እየጠቆመ። መሣሪያቸዉን አነጣጥረዉ ከመኪናዉ በቀስታ እንዲወርድ አዘዙት።

“እንዳትሳሳቱ፣ እኔ ተራ ሹፌር ነኝ: ከዚህ ሁሉ ለምን ጉቦዳን
አትጠይቁትም?”

ምን አስቦ እንደሆነ ባይገባኝም፣ አመላለሱ ግን ሆነ ብሎ ጥርጣሬያቸዉን የሚያጎላ ነዉ ምክንያቱም ገና አንድ ጥያቄ እንኳን ሳይጠይቁት፣
በዉስብስብ ጥያቄዎች እንዳስመረሩት ሁሉ መቀለማመዱ ከባልቻ የሚጠበቅ አይደለም: እንዲያዉም እሱ ራሱ “ጅል ለስለላ ሄዶ ምግብ
ቢያቀርቡለት ስለላ ላይ ነኝ ብሎአረፈዉ” ብሎ በተልካሻ የመረጃ አነፍናፊዎች ሲስቅ ሰምቼዋለሁ። የእሱ የተቻኮለ መልስ ግን ከጅሉ በላይ
ቢብስ እንጂ አይተናነስም

“ጉቦዳን ጠይቁት”

“ማነዉ ደግሞ ጉቦዳ?”

“ጉቦዳ የመኪና ስምሪት ኃላፊዉ ነዋ: አታዉቁትም? ጉቦዳ ?”

“ና ቅደም እስኪ ለማንኛዉም” ብለዉ ወሰዱት እርስ በእርስ ትንሽ
ከተመካከሩ በኋላ።

እኔን ማንም ሳያየኝ መኪና ዉስጥ ቀረሁ አሁን ሐሳቡ የገባኝ መሰለኝ፡ ኹለታችንም ከምንያዝ፣ እኔን አትርፎ ራሱን ማጋለጡ ነዉ። ባልቻ አይደል ሰዉዬዉ? መhራዬን መዉሰድ ያዉቅበት የለ? መንገድ አብረን እየሄድን ድንገት ጋሬጣ ሲያደናቅፈኝ ‹እኔን ባዩ ሰዉ! ለማለቱማ ማንም ሰዉ ይለኝ ይሆናል፣ ከልቡ መሆኑን ግን ከእሱ በቀር የማምነዉ ማን
አለኝ? ከእናቴ ቀጥሎ ከሰዉ ማንም እንደሱ የለም ባልቻ ብቻ!

ባልቻን በወሰዱበት መንገድ አፍጥጬ እንባ እያፈሰስሁ ለደቂቃዎች በድንዛዜ ቆየሁ ከዚያ እንደ ምንም እንባዬን ጠራርጌ ዓይነ ልቡናዬን እንዲያበራልኝ አጭር ጸሎት ማድረስ ስጀምር፣ በርከት ያለ ድምፅ ሰማሁ። እንግዶች መዉጣት ጀምረዋል። አሁን የዕቅድ ለዉጥ አድርጌም
ቢሆን ከዚህ ግቢ ቶሎ ማምለጥ አለብኝ፡ እንዴት? መቼም እንግዶቹ
ሲወጡ በር ላይ ጠበቅ ያለ ፍተሻ መኖሩ የማይቀር ነዉ። ያን ጊዜ
ትኩረቱ ሁሉ ወደ በሩ ይሆናል ማለት ነዉ፡ እንደዚያ ከሆነ ደግሞ እኔ በአጥር መዝለል እችላለሁ፡ በእርግጥ እንኳንስ በአጥሩ መዝለል ይቅርና፣ አጥሩ አጠገብ መድረሱ በራሱ ዋዛ እንደማይሆንልኝ አልጠፋኝም: ነገር ግን ከጥበቃ ማማዎች ወደሚቀርበኝ ቃኚ ወታደር መስዬ እያዘናጋሁ እቀርበዉና ያቺን የሰመመን መርዝ ጠቅ አደርግበታለሁ። ይወድቅልኝ
የለ? ያን ጊዜ ከራሱ ማማ እመር ብዬ ወደ ዉጪ እዘላለሁ፡ ምናልባት በግራና በቀኝ በኩል ባሉ ማማዎች ያሉ ወታደሮች ቢተኩሱብኝ ነዉ ቢሆንም ግን የመጨረሻዉ ቀላል ማምለጫ ይኼ ብቻ ነዉ ሌላ አልታየኝም:

ያቀድሁት ሁሉ ሰምሮልኝ ዘልዬ ወደ ዉጪ ከመዉደቄ እንደ ጠበቅሁት የተኩስ እሩምታ ይዘንብብኝ ጀመር። እየተንከባለልሁ ወደ ዋናዉ ጎዳና
ስወርድ፣ ማንነቱ የማይታይ ሰዉ አንዲት ሚኒባስ ታክሲ እያበረረ
አጠገቤ አድርሶ በሯን ከፈተልኝ፡ የሲራክ፯ አባላትን የምታግባባዋን
የመኪና ጥሩምባ ቀድሞ ስለነፋልኝ፣ ለእኔ የመጣ መሆኑን አወቅሁና ሳላቅማማ ተወርዉሬ ገባሁባት ነዳጁን ረግጦ ከግቢ ገብርኤል በታች ወዳለዉ የመንደር መንገድ ወሰደኝ።

አመለጥሁ።

ከቤተ መንግሥቱ መራቃችንን ሲያዉቅ፣ ሹፌሩ የመኪናዉን የዉስጥ መብራት አብርቶ በድል አድራጊነት አየኝ፡ አየሁት።
“አ-ባ-ቴ?!” ብዬ በጩኸት አቀለጥሁት ባልቻ ነዉ። በምን ተአምር እንዳመለጠ ልጠይቀዉ ወይስ ዝም ብዬ ከአንበሳ ጉሮሮም ቢሆን የሚያተርፈንን አምላክ ላመስግን? ቸገረኝ እኮ፡ ሰአሊ ለነ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

“ባልቻ ነዋ ሰዉዬዉ! እንዴት አያመልጥ?” ሲል አቋረጠኝ፣ ቢራራ እኔም ልክ አሁን የሆነ ያህል ነበር በስሜት ያጫወትሁት።

በዚህ እና ከዚህ በባሱ መዐት ሞቶች መካከል አልፌ የማዉቀዋ እኔ፣ ዛሬ ግን ፈራሁ። እዉነትስ ፈተና ባይኖር ሁሉ ተማሪ፣ ጠያቂ ባይኖር ሁሉ አስተማሪ የሚለዉ አባባል ይመለከተኛል? በጭራሽ! በጅቦች መካከል፣ በጨለማ አካፋይ ሞትን ተፋጥጬዉ አልፏል።

“እንግዲያዉ ለምን ፈራሁ አሁን? አንተ እስክትሳለቅብኝ ድረስ ለምን
ተንቀጠቀጥሁ?”

“ይኼን ስትነግሪኝ ምን እንደመጣብኝ ታዉቂያለሽ?ስለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጴጥሮስ ያነበብሁት አንድ ምዕራፍ” አለ፣ በሞባይሉ መጽሐፍ ቅዱስ እየከፈተ። የሚፈልገዉን ምዕራፍ ሲያገኘዉ፤ “ከዚህ ጀምረሽ
አንብቢዉማ” ብሎ ሞባይሉን አቀበለኝ። ታሪኩ ጌታችን ኹለት ዓሣ እና አምስት እንጀራ አበርክቶ ሕጻናቱንና ሴቶቹን ሳይጨምር አምስት ሺ ወንዶችን ያጠገበ ዕለት፤ ሌሊቱን የሆነ ነዉ።
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በታደለ_አያሌው


....“አንድ ጊዜ ከባልቻ ጋር እዚህ መጥታችሁ ነበር አይደል?” አለችኝ እንደ ዋዛ፣ ወደ ታላቁ ቤተ መንግሥት በቅንድቧ እየጠቆመችኝ፡

“አዎ” አልኋት፣ እኔም እንደ ዋዛ፡ “እ?” አልኋት ወዲያዉ፣ ዉሃ ሆኜ ምን ምን? ያለችዉን ነገር እኮ ገና አሁን ነዉ ልብ ያደረግሁበት::
ከማን ጋር ምንድነዉ ያለችኝ? ባልቻ? እርፍ! እንዴት እንዴት ነዉ ነገሩ? በድንጋጤ ተዝለፍልፌ አለመዉደቄ፣ ለራሴ ደነቀኝ፡ መሬቱን ይዤ አረፍ ማለትም አሰብሁ፡ ቢሆንም ግን ቸኩሎ መደናገጥን የሲራክ ፯ ማንነቴ
ስለማይፈቅድልኝ ማስጨረስ አለብኝ፡ ጥርሴን ነክሼ እንደ ምንም ተበራታሁ።

“በዚህ በኩል” አለችኝ፣ ወደ ታዕካ ነገሥት ቤተ መዘክር እያስገባችኝ
ወደ ቤተ መዘክሩ ስመጣ የመጀመሪያዬ ስላልሆነ ብርቅ አልሆነብኝም እንጂ፣ እንደዚህ ማንኛዉንም ሰዉ መንፈሳዊ የሚያደርግ ወደረኛ ቦታ
አለ ቢሉኝ አላምንም ሲጀመር በከተማ ዉስጥ ካሉ ገዳማት እንደዚህ የጸጥታ እና የአርምሞ ገዳም አላዉቅም። በበርሐ ካሉትም የሚስተካከል
ትክክለኛ የገዳም ይዞታ ያለዉ ግቢ ነዉ፡ ዕድሜ በጠገቡ እና ራሳቸዉ ታሪክ በሠሩ ጽዶች የተሞላ ስለሆነ፣ እዚህ ግቢ የገባ ሰዉ ዉጣ ዉጣ አይለዉም እንኳንስ ለአማኝ እና ለተማጻኝ ይቅርና፣ ለማንኛዉም ሰዉ
መረጋጋትን የሚሰጥ ገራሚ ሥፍራ ነዉ።

ቤተ መዘክሩ ዐሥር ብር የከፈለ ማንኛዉም ታሪክ ወዳጅ የሚጎበኘዉ ሕዝባዊ ቤት ቢሆንም፣ የሚገኘዉ ግን በዋናዉ የገዳሙ ሕንጻ ምድር ቤት ነዉ፡ ስለዚህ ወደ ቤተ መዘክሩ ለመግባት የግድ ጫማ አዉል
በቅኔ ማኅሌቱ በኩል ማለፍ ይጠይቃል። በዋናነት የዳግማዊ ምኒልክ፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ የእቴጌ ዘዉዲቱ፣ የአቡነ ማቴዎስ
ግብጻዊ የልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ ዐጽሞች በየራሳቸዉ ወርቃማ ሳጥን ዉስጥ ተከብረዉ የተቀመጡበት ሲሆን፣ ዓይነተ ብዙ የካህናት እና የነገሥታት ቅርሳ ቅርሶችም አሉበት ከነዚህም መካከል ሮማዊዉ ሊቀ ጳጳስ ለአፄ ምኒልክ የላኩላቸዉ የሚካኤል አንጀሎን ትክክለኛ የእጅ ሥዕል ጨምሮ ብዙ የሚነገርላቸዉ ከሩስያ ከግሪክ ከጣልያን እና ከተለያዩ ሀገራት መንግሥታትን የተበረከቱ ቅርሶች
ሞልተዉ ተትረፍርፈዉበታል። እንዲሁም ንግሥተ ነገሥታት ዘዉዲቱ ለጸሎት ይጠቀሙበት የነበረ ወንበር፣ የእጅ ጽሑፋቸዉ ያለበት ዉዳሴ ማርያም እና ሌሎች የብራና መጻሕፍት እና ለእሳቸዉ የተሰጡ ታሪዊ ስጦታዎች ጭምር አሉበት። ለአድዋ ዘመቻ ሲታወጅ የተጎሰመዉ ነጋሪት፣ አድዋ
ድረስ የዘመተችዋ ድል አድራጊዋ የጃንሆይ መቀመጫ ወንበር ሁሉ
የሚገኙት በሌላ አይደለም፡ እዚሁ ታዕካ ነገሥት ቤተ መዘክር ዉስጥ
ነዉ።

ያም ሆኖ ግን ቤተ መዘክሩን የሚጎበኘዉ ሰዉ በታሪኩ ልክ ብዙ ነዉ ማለት አይቻልም እስከዚህም ነዉ ያን ያህል ንጉሥ ንጉሥም፣ ካህን ካህንም የሚሸት እና ቢናገሩለት የማያልቅ የቅርስ ክምችት እንዳልሞላበት
ሁሉ፣ ጎብኚ ግን ከስንት አንድ ነዉ ብቅ የሚልበት። ያዉም የዉጪ
ሀገር ሰዉ፡ ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ ከነጭራሹ ማንንም አላየሁበትም። አስጎብኚዎቹም እንኳን በአካባቢዉ የሉም

“እና፣ ወደ ቤተ መንግሥቱ ያመጣችሁን ጉዳይ እንደሚሆን እንደሚሆን ከዉናችሁት ልትወጡ ስትሉ ተይዛችሁ ነበር አሉ?” አለችኝ እመዋ፣ በዚያ የዉድ ዉድ እቃዎች ክምር መካከል ለብቻችን ስንዋኝ።

ዝም ብዬ ባዳምጣት ይሻለኛል ምን ልል እችላለሁ? ጭጭ እርጭ ብዬ አዳመጥኋት። ጭራሽ ተዪዛችሁ ነዉ ያለችዉ? በስመ አብ!

“ከዚያ ባልቻ አቺን ደብቆ ራሱን አጋለጠ። አንቺ ይኸኔ የእሱ መጨረሻ እያሳሰበሽ እንደ ምንም ከቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ስታመልጪ ቀድሞሽ ውጪ አገኘሽዉ በምን ተአምር ከእነሱ እጅ እንዳመለጠ ግን እስከ
አሁንም ድረስ ባሰብሽዉ ቁጥር ይገርምሻል አይደለም? በእርግጥም ግን እኮ ይገርማል። የመንግሥት ደኅነቶች ለመያዝ ዘገምተኞች ናቸዉ እንጂ ከያዙ እኮ አይለቁም ይባላል”

እመዋን አላዉቃትም ለካ በእርግጥ ግን ይቺ ሰዉ እመዋ ራሷ ናት ከንግግሩ አነጋገሯ ከአነጋገሯ ሁኔታዋ! እሷ ማለት ለኔ የስልሳ አራት ዓመት አሮጊት፣ ከጾምና ከምሕላ ሌላ የምታዉቀዉ የሌላት ምስኪን
ሃይማኖተኛ ናት፡ እንዲያዉ አዳሯ በገዛ ቤቷ ከመሆኑ በቀር፣ ሙሉ
ሕይወቷ ከመናኝ አይተናነስም፡ በቤተ መንግሥት ዙሪያዉን ባሉ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት፣ ለትንሽ ለትልቁ የምትታዘዝ ገዳማዊት ብቻ ናት። በጭራሽ እናቴን አላዉቃትም በቃ።

“በዚህ በኩል” አለችኝ፣ ከሩስያዉ የመጨረሻ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ኒኮላስ ለኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ የተላh መሆኑን የሚያመላክት ጽሑፍ በግርጌ ወደ ሰፈረበት ጽዋዕ እየወሰደችኝ
ከዚህ ቀደም ቤተ መዘክሩን በጎበኘሁ ጊዜ አስጎብኚዉ ስለ ጽዋዉ ያብራራልኝን አልረሳሁትም ከጽዋዉም አልፎ ጽዋዉን ስለላከዉ የሩስያ ንጉሥ ጭምር ገልጾልኛል። ለሃያ ሦስት ዓመታት ገደማ በሩስያ መንገሡን፣ የሩስያ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ድረስ በቅዱስነቱ እንደምታወሳዉ፣ ዝነኛዉ የሀገሩ አብዮት ዘመኑን እንደ ቀጨበት
ያብራራልኝን ከነፊቱ ገጽ አስታዉሰዋለሁ። ስለ ንጉሡ ያልነገረኝ አልነበረም።
ይኼ ሩስያዊ ንጉሥ ለሐበሻዉ ንጉሥ የላከዉ ጽዋዕ አጠገብ ስትደርስ፣እመዋ ፈገግ ብላ አየችኝ። ደግሞ ምን ልትለኝ ይሆን?

“ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም”

ስትል በፊቴ አንጎራጎረች፣ የሩስያዉ ንጉሥ ለአፄ ምኒልክ የላከዉ ጽዋዕ አጠገብ ቆማ ፊቷ የፈገግታ ብርሃን እንደ ፈነጠቀበት

“ዳዊት እደግማለሁ ቆሜ ገረገራ
እመቤቴ ማር ያም ኢትዮጵያን አደራ
ነይ ነይ እምዬ ማርያም”

ከመሬት ተነስታ እንዳልዘመረችዉ ይገባኛል። ምንም እንኳን መዝሙሩ ነባር እና ሕዝባዊ መዝሙር ቢሆንም፣ የእሷን ምክንያት ግን አግኝቼዋለሁ በሲራክ ፯ ማዕከል ዉስጥ ሥራዎቻችንን ጨርሰን ትንሽ
ፋታ ያገኘን እንደሆነ፣ አባላቱ ሁሉ ከበዉ የሚያዘምሩኝ እኔም እንደ
ጸሎት የምቆጥረዉ መዝሙር ነዉ። ከዚህ በላይ፣ ራሷ አፍ አዉጥታ የሲራክ ፯ አባል ነኝ እስከምትለኝ ልጠብቅ ካላልሁ በቀር፣ እናቴ ግን እንደማስባት ዓይነት ሰዉ ብቻ አለመሆኗን በተግባር ጭምር
አሳይታኛለች፡

“ተከተዪኝ” አለችኝ ጽዋዉን ትኩር ብላ ስታይ ቆይታ፣ ዘወር ብሎ
ወዳለዉ ሥዕል ደግሞ እየተራመደች። ልክ ከፊት ለፊቱ ስትቆም፣ ነፋስ የነካዉ ያህል ሥዕሉ መወዛወዝ አመጣ፡ ዓይኔን ተክዬ የሚሆነዉን ሁሉ
ተጠባበቅሁ: አፍታ ያህል ሲወዛወዝ ከቆየ በኋላ፣ የድምፅ ፍጥነትን በሚስተካከል ፍጥነት ተገልብጦ የፊቱ ወደ ጀርባ፣ የጀርባዉ ወደ ፊት ተለወጠ። ሥዕሉ ግን አሁንም ያዉ የቅድሙ ዓይነት ነዉ።

የሆነዉ ሆኖ ሥዕሉ ሥዕል ብቻ፣ እመዋም እመዋ ብቻ እንዳልሆነች
ገብቶኛል።

“አሁን ባልቻ እንዴት እንዳመለጠ ሳይገባሽ አልቀረም” አለችኝ
በፈገግታ።

ወደ ቤተ መንግሥቱ ግቢ የሚዘልቅ የዋሻ መንገድ አለ ማለት ነዉ?አፌን ከፍቼ፣ ዓይኔን በልጥጬ እንዳፈጠጥሁባት ቀረሁ እየቆየ የባሰ እየደነቀኝ፣ ሁሉም ነገር ቅዠት እየመሰለኝ መጣ፡ ጭንቅላቴ በጥያቄ
መዐት ተጠቃ። ሚሊዮን ጥያቄ በዉስጤ እየተዥጎደጎደ፣ አንደኛዉ ከሌላኛዉ ተሽቀዳደመብኝ፡ የሲራክ ፯ አባል ነሽ? እሺ አባል ከሆንሽ ምን
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_አራት


#በታደለ_አያሌው


....“ሃያ ስምጉት ሳምንት: ደህና። መቼም ዉሃ እስከሚበቃ ጠጥተሻል አይደለም?” አለችኝ፣ ኮስተር ብላ በአንዴ ከጓደኛነት ወደ ሐኪምምነት እየተሻገረች።.


"አዎ፤ ሽንቴን ለመቋጠር ስቁነጠነጥ አታዪኝም?”

“ደምሽንስ እየተከታተልሽዉ ነዉ፤ ጥሩ ነዉ?”

“እዉነቱን ለመናገ Check አድርጌዉ አላዉቅም ወሰድ መለስ ሲያደርገኝ ሰንብቼ ወደ ቀልቤ የተመለስሁት ገና ዛሬ ነዉ
አልገርምሽም? ቅድም ስንገባ ራሱ ምድር ቤት መለካት እችል ነበር።

ደርሼ ልምጣ እንዴ አሁንም?”

“አይ አይ፤ ኧረ እዚሁ እናየዋለ”
እጅጌዬን ሰበሰብሁና ጠረጴዛዉ ጠርዝ ላይ አስደግፌ ዘረጋሁላት። የደም
ግፊት መለኪያዉን አምጥታ አሰረችልኝ፡

“oK. Nice, right? 128/74 ይላል። ጥሩ ነዉ ያለሽዉ። ሌላ የተለየ
ያጋጠመሽ ነገር የለም አይደል?”

ለመናገር ዳድቼ፣ እንደ መሳቀቅ ብዬ ቀረሁባት።

“ምንድነዉ እሱ፤ አለ እንዴ? "

“አልፎ እልፎ፣ ቀለል ያለ ደም ይፈሰኛል” በዚያ ላይ ቀደም ብሎ ይሰማኝ
የነበረዉ የፅንሱ እቅስቃሴ፣ አሁን እየተሰማኝ አይደለም”

"ምን'? ታዲያ መምጣት አልነበረብሽም? የተለየ ነገር ከገጠመሽ እንድትመጪ ተስማምተን አልነበረ?”

ልክ መሆኗን ስላወቅሁ፣ ምላሽ የሚሆን አላገኘሁላትም። ዝም ብዬ
አቀርቅሬ መሬት መሬቱን አየሁ፡

“እሺ መቼ ነዉ የጀመረሽ?”

“ምኑ?”

“ደም መፍሰሱ”

“እ፤ ደም መፍሰሱ እኳን ትናንት ነዉ የጀመረኝ ገና የእሷ እንቅስቃሴ ግን
ከተሰማኝ ሰንብቷል: አንድ ሳምት አያልፍም ብለሽ ነዉ?”

አስከትላ ማንኛዉም ለእርግዝና ክትትል የመጣ ታካሚ የሚጠየቀዉን ሁሉ ጠየቀችኝ: መቼስ ከሐኪም እና ከንስሐ አባት የሚደበቅ የለም ይባል የለ? ስለ ምግብ፣ ስሜት፣ የአካል እንቅስቃሴ፣ መንፈሳዊ ብርታት እና ስለመሳሰሉት ሁኔታዎቼ ሁሉ እንደ አጠያየቋ በግልጽነት እዉነት ዉነቱን ብቻ መለስሁላት የሁሉም መልስ ግን ያዉ ነዉ በአጭሩ፣
የትኛዎቹም ላይ ግድ የለሽ እንደ ነበርሁ አመንሁላት፡ አሁን እንደ ጓደኛም እንደ ሐኪምም ብትቆጣኝ እንደሚያምርባት ስለማዉቅ ራሴን ለዚያ አመቻችቻለሁ

“ዉብዬ፣ እኔ አንቺን እንዲህ አድርጊ ወይ አታድርጊ አልልሽም" ራስሽ
ታዉቂዋለሽ” ብላ ወደ በሩ እንደ መራመድ ካለች በኋላ፣ በሩን በኃይል ቦርቀቅ አድርጋ ከፍታ አፈጠጠችብኝ

ተከትያት ልነሳ በእጄ እሸቴ ጭን ላይ ስመረኮዝ፣ ስልኩን ሰረቅ አድርጎ አሳየኝ አሁኑኑ የሚል መልእክት ከባልቻ ተልኮለት ኖሮ፣ ምን ይሻላል የሚል ፊቱን አስነበበኝ። ቃል ሳናወጣ አዉርተን፣ አሁኑኑ ወደ ሲራክ ፯ መሄድ እንዳለበት ተማከርን ተግባባን፡

ብድግ አለ

“ወዴት ነዉ እሸቴ? እዚህ እኮ ልትጠብቀን ትችላለህ” አለችዉ፣ በቢሮ መቆየቱ አሳቅቶት የተነሳ መስሏት።

“አይ አይ፤ መሄድ አለብኝ: አጉል አድርጌ የተዉኩት ሥራ ነበረብኝ
አሁኑኑ መሄድ አለብኝ”

“እንዴ! ዉቤን ለብቻዋ ጥለሃት?”

“ምን ታደርጊዋለሽ፤ የእኀጀራ ጉዳይ…”
“ይኼን ያህል? የት ነዉ ግን የምትሠራዉ?”

“እ” ተንተባተበ፡፡ እንዲያዉም እንዲያ ነሽ አሉ ተረተኞች? እንኳን እሱ
እኔም ከእሷ ያልጠበቅሁት ጥያቄ ስለነበር፣ ክዉ ብያለሁ።

“የየየየየየ መንግሥት መሥሪያ ቤት ነዉ የምሠራዉ” አለ ለፊቷ መመለሻ፣ ወዳፉ እንደ መጣለት፡ ጎበዝ አልሁት በምልክት

“ተዉ እንጂ፣ የት?”

“..እ..…ንንንን..ግድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባክ”

“አሪፍ! ባንከሮችማ መናፈሻችሁ ሳይቀር የብር ጫካ ነዉ አላሉም?''

“ሳቅንላት፡ ተሳሳቅን፡ አጋጣሚዋን በመጠቀም፣ እሸቴ በሳቅ እያታለለ
ሹልክ ብሎ ወጣ፡ በቅጡ እንኳን አልተሰናበታትም

"አንቺስ ዉቤ?

“እ..ኔ ምን?” አልኋት፣ የእሸቴን መንተባተብ እኔም እየደገምሁት
የት እንደምትሠሪ መቼ ነገርሽኝ''
“አይ እኔ እንኳ ን ለጊዜዉ ሥራ የለኝም። ምናልባት አንቺ በሆስፒታላችሁ
ታስቀጥሪኝ እደሆነ እንጂ፣ የቤት እመቤት ነኝ”

"አግኝተነሽ ነዉ? በይ ነይ ተነሺ ይልቅ አልትራሳዉድ ክፍል ደርሰን እንምጣ” አለችኝ፣ እንድነሳ በግማሽ ዓይኗ እየደገፈችኝ።

"ውቤ! ሰዓቱን ግን ልብ ብለሽዋል? ባለሙያዉ አልትራሳዉንድ ክፍሉን
ጠርቅሞት ይኼድልሽና በብላሽ መመለስሽ ነዉ: አጅሬዉ ጠዋት ሲገባ
ማርፈዱን እንጂ፣ ከመዉጫ ሰዓቱ እንኳን ደቂቃ ማሳለፉንም አያዉቅበት። ቶሎ በይ፣ እንድረስበት”

እኔ ሆኜባት ነዉ እንጂ፣ አብራ የመዉጣት የመዉረድ ግዴታዋ ሆኖ አይደለም ለየክፍሉ የየራሱ ባለሙያ ስላለዉ፣ ሂጅ ዉጤቱን አሰርተሽ አምጪ ማለት ትችላለች እኔ ግን እኔ ሆንሁባት
እንዳለችዉም፣ ስንደርስ ባለሙያዉ ሊወጣ በር በሩን እያየ ነበር ልክ
ሲያየን ብልጭ አለበት፡ በተለይ እሷን ከፍ ዝቅ አድርጎ ጮኸባት፡ ባለፈዉ በእኔ ጉዳይ ተዋክባ እሷ እሱን በዚሁ ድምፀት ስታናግረዉ ሰማኋት ያን ያህል አልደነገጥሁም፡ ብድሩን ነዉ የመለሰባት፡

“ምን ነካሽ ዶክተር? መዉጫ ሰዓቴን ጠብቀሽ መምጣት ምን የሚሉት
ነገር ፍለጋ ነዉ? ''

“ግድየለም፣ ያን ያህል ጊዜ አልፈጅብህም” አለችዉ፣ ልክ ትርፍ ዉለታ እንደምትጠይቀዉ ሁሉ በመለማመጥ

""ቤቴ የት ሀገር እንደሆነ እያወቅሽ?”

“ነገርኩህ እኮ፤ከመዉጫ ሰዓትህ አንዲት ደቂቃ አላሳልፍብህም ካሳለፍሁብህ ደግሞ ታቋርጠኛለህ። ቶሎ በል ይልቅ አብራዉ አጠፋፍተኸዋል መሰል ደግሞ”

እኔም ጊዜ ለመቆጠብ፣ እስከምታዘዝ ድረስ ሳልጠብቅ ቀልጠፍ ብዬ
አልጋዉ ላይ ለምርመራ ተመቻችቼ የእንግላል ሆንሁላቸዉ
እየተነጫነጨም ቢሆን የፈጀዉን ጊዜ ፈጅቶ፣ ሁሉንም ነገር ዝግጁ አደረገዉ
ከዶክተር ሸዊት የወደድሁላት ጥሩ ጸባይ፣ ያለ ሙያዋ ጥልቅ አትልም ዛሬም ሆነ ባለፈዉ እንዳስተዋልኋት ከሆነ፣ ጣልቃ መግባት ቢያስፈልጋት እንኳን፣ ቢያንስ ቢያንስ ፈቃድ ትጠይቃለች፡ ዛሬም
እንዲህ ባለቀ ሰዓት ዉስጥ ሆና፣ ባለሙያዉን ጠበቀችዉ፡ ለነገሩ
ሙያዉም ያንን አይፈቅድም፡፡ በተለይ አልትራሳዉንድ በባሕሪዉ፣ ለማዳ እጅ ይፈልጋል ዉጤቱን ትክክልም ስሕተትም የሚያመጣዉ ከመሣሪያዉ ዘመናዊነት ይልቅ የባለሙያዉ (የራዲዮሎጂስቱ) ልምድ ያለው እጅ መሆኑ ነው ይባላል።

“እያየሽዉ ነዉ ዶክተ?” አለ ራዲዮሎጂስቱ፣ መከሰቻዉ ላይ ዓይኑን
ሰክቶ ልክ ያልሆነ ነገር እንዳየ አዉቂያለሁ

“እ፤ እስኪ እስኪ” አለች እሷም፣ ትንፋሿ እየተቆራረጠ፡ ባለሙያዉን
ገፈተረችዉና ራሷ ገባችበት፡ “NO! አይደረግም!” ብላ ጮኸች።
ወዲያዉ ደግሞ በፊቴ መደንገጧ ይበልጥ አስደነገጣት፡ ጀርባዋን ሰጥታኝ
ያልደነገጠች ለመምሰል ብትሞክርም፣ እንደገና ከድንጋጤዋ ለመመለስ
ብትሞክርም፣ የትኛዉም አልሆነላትም

“በቃ፣ ጨርሻለሁ። መዘጋጋት ትችላለህ” አለችዉ ግራ ቀኝ ስትንቆራራጠጥ ቆይታ፣ ከአልጋዉ ላይ ደግፋ እያስነሳችኝ፡፡
“ኧረ ችግር የለም፣ የማግዝሽ ነገር ካለ እንዲያዉም ያን ያህል የሚ ያስቸኩል ጉዳይ የለኝም” አላት፣ እንደዚያ እሳት ለብሶ የነበረዉ ሰዉዬ በአንድ ጊዜ ዉሃ እየሆነ በሐዘኔታ አየኝ፡

“ዉብዬ” አለችኝ፣ የተከሰተዉን እንድመለከተዉ በአገጯ እየጠቆመችኝ
ግብኔን ወደ ጠቆመችኝ መከሰቻ አዞርሁላት። “ያዉ፣ ባለፈዉ እንደ ጠበቅነዉ፤ እንደፈራነዉ ሳይሆን አልቀረም በእርግጥ ያን ጊዜ ምልክቶቹን ባየን ጊዜ፣መልሶ ይቀንሳል የሚል ጭላንጭ ተስፋ ነበረኝ በበኩሌ።ሆኖም ፅንሱን እንደምታይዉ
ባልተመጣጠነ የጭንቅላት የፈሳሽ መጠን የተነሳ፣ ጭንቅላቱ ከመጠን በላይ አድጓል። ይኼ እንዳለ ሆኖ፣ መጀመሪያም ምልክቱን ያየነዉ የጀርባዋ አጥት ክፍተት ደግሞ እየሰፋ መጥቷል”
ትንሽ ተያየን፡፡ ከእሷም በሆዴ ካለችዋም ጋር አጭር ቆይታ አደረግሁ
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በታደለ_አያሌው


...እንደ ክራሞቴ ቢሆን፣ ይኼን ስሰማ ጸጥ ብዬ መሞት ነበረብኝ፡ ያን ያህል ግን ከብዶ አልታየኝም፡ ብሎ ብሎ ድንጋጤ ሁሉ ከዉስጤ
ተሟጥጦ አለቀ መሰለኝ፣ የሐኪሜን ያህል ቀርቶ እንዲች ብዬ አልደነገጥሁም ጭራሽ እሷን ለማበረታታት ሁሉ ምንም አልቀረኝም

“ዉብዬ፣ መገናኛ አካባቢ ዶክተር ሙደያን ሻምሩን የሚባል አንድ ስመ ጥሩ ሐኪም አለ: he is a senior neurosurgeon. ለሰባት ዓመታት ያህል በሙያዉ ላይ ቆይቶበታል። እሱ ዘንድ እልክሻለሁ። ያዉ እዚህም
ሌሎች ታካሚዎች ስለቀጠርሁ ነዉ እንጂ፣ አብሬሽ መሄድ ነበረብኝ: ቢሆንም ግን በዶክተር ሙደያን ፊት ያን ያህል እንግድነት አይሰማሽም፣ እንደኔ ልትቆጥሪዉ ትችያለሽ”

ከሁኔታዋ አንጻር የተለየ ቀረቤታ እንዳላቸዉ ከመጠራጠር ባለፈ፣ እስከ ምን ድረስ እንደሆነ ግን አልጠየቅኋትም
“ያም ሆኖ ግን ታዲያ፣ ከዚያ የምናገኘዉን ምክርም ሆነ ዉጤት እንደ ተጨማሪ ግብአት እንጠቀምበታለን እንጂ፣ዉሳኔዉን የምንወስነዉ እኛዉ ነን። እኔ፣ አንቺ እና እሸቴ ብቻ” አለችኝ፣ እኔ ሥጋት እንዳይገባኝ ራሷ ሰግታ

ከተባለዉ ዶክተር ዉጤቱን እንዳገኘሁ ወደ እሷ እንድመለስ ለነገ ተቀጣጥረን ተለያየን፡

ከሆስፒታሉ ስወጣ፣ መጨላለም ጀምሯል፡በምሳ ሰዓት እመዋን ካገኘኋት ጀምሮ የነበረኝ በጎ ስሜት እስከ አሁንም ድረስ ባለመቀዝቀዙ እየተደነቅሁ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ በፈገግታ ተሞልቼ ለባልቻ ደወልሁለት። ከደወልሁለት፣ በተለይም በዚህ ስሜት
ሆኜ ካናገርሁት ሰንበት ብያለሁ።

“አባትዮዉ”

“ልጅዮዋ”

“ማግኘት ይቻላል?”

“ክራርሽን ይዘሽ ከመጣሽ?”

“በደስታ ነዋ ያዉም!”

“እንደሱ በይኛ! በይ ነይ: እንግዲህ አንቺ ከቢሮዬ እስከምትደርሽ ድረስ
ዓይኔን ከበሩ እንደማላነሳዉ ልባርጊ። ነዪልኝ ቶሎ” ከእሱ ይልቅ እኔ ራሴ እያንጎራጎርሁ ክራሬን መግረፍ፣ የዉሃ ጥም ያህል ቢያሰኘኝም፣ የእመዋን ነገር አንስቼለት በሚያወራልኝ ተጨማሪ ምስጢር ለመደመም ካለኝ ጉጉት አንጻር ግን ምኑም ላይ አይደርስም፡ ምን እና ምን! የእሷን ነገር ባሰብሁት ቁጥር አግራሞት ከደሜ ጋር በሠራ አካላቴ
ይዘዋወርብኛል ቅድም እንኳን ከሐኪሜ ጋር እንዲያ ሆነን ሁሉ፣
በየመሀሉ ትዉስ እያለኝ እንዲሁ ሲያደርገኝ ነበር

ወይ ጉድ!

ከእሱ አፍ እስከምሰማዉ እንደ ቸኮልሁ፣ በፊቴ ያገኘሁትን ታክሲ
ተኮናትሬ አቋራጭ አቋራጭ ቅያሶችን ለሾፌሩ እየጠቆምሁት ወደ ዋናዉ የማኅበሩ ሕንጻ አንከብክቦ አደረሰኝ፡፡ ወደ ሕንጻዉ ከገባሁ በኋላ፣ ጻድቃን መንግሥተ ሰማያትን ለመዉረስ ከሚያልፉበት መከራ ትንሽ መለስ ያለ ፍዳ የሚያቀምሰዉን ጠባቡን የሲራክ፯ መግቢያ እንደ ወትሮዬ በጥንቃቄ
አለፍሁበት፡

“አባትዮዉ” አልሁ ለራሴ፣ ወደ ባልቻ ቢሮ መሬቱን በኃይል እየረገጥሁ ብደርስም ቢሮዉ ዉስጥ አጥቼዉ ስቅቅ እያልሁ። ልመለስ ስል፣ ከኋላዬ
መጥቶ አቀፈኝ፡

“አባትዮዉ፣ ቀጥረኸኝ የት ገብተህ ነዉ?”

“መንገድ ላይ እኮ ባጠገቤ ነዉ ያለፍሽዉ: ብጠራሽ ብጠራሽ ልትሰሚ„ ነዉ አንቺ?”

“ባክህ ነፍሴንም አላዉቀዉ: ይልቅ ከየት ልጀምርልህ?”

“ምኑን?”

“የእመዋን ነገር ነዋ”

“ቆይ: ቆዪኝ እሺ እመለሳለሁ: እዚሁ እኔ ቢሮ ጠብቂኝ: ከእሸቴ ጋ
አንዲት ጊዜ የማትሰጥ ሥራ ላይ ነበርን። እሷን ከዉነን ቶሎ
እንመጣለን: እምጷ!” ብሎኝ በአንድ ትንፋሽ፣ hፊቴ አጣሁት
በጉጉቴ ነበልባል ላይ እንትፍ ብሎበት እንደሄደ ግን ይወቀዉ!
ከቢሮዉ ገብቼ ብዙ ጠበቅሁት ለብቻዬ እየተቁለጨለጭሁ፣ ደቂቃዎች በሄዱ ቁጥር ይኼኛዉ ጉጉቴ እየቀነሰ፣ ወንድሜ በሐሳቤ እየሞላ መጣ:ወንድሜ ጃሪም: እንደ ዋንጫ ጠላ እህትነትሽ በቅቶኛል እያለ የሚግደረደርብኝ ወንድሜ፡ በሚያዉቀንም በማያዉቀንም ሰዉ ዘንድ
እህቱ አይደለችም ተብዬ የታማሁበት፣ ጃሪም

የዛሬ ኹለት ወር ገደማ፣ ዐመጸኞችን እየመራ የቅዱስ ዑራኤልን ካቴዴራል ለማቃጠል ሲመጣ፣ በዓይኔ በብረቱ ያየሁትን የማይታመን ነገርስ ለማን ነገርሁት? ያን ጊዜ የጃሪምን ምስሎች ለሲራክ ፯ ብልክም፣
የኔ ወንድም ስለመሆኑ ግን እስካሁንም የታወቀ አይመስለኝም: እኛ በዋናነት ከምንላፋቸዉ አካላት መካከል የኔ ወንድም ጃሪም እንዳለበት
ከእኛ ማን ያዉቃል? ባልቻ? እመዋ? ኧረ አይመስለኝም:

ይብላኝላት ለእመዋ፤ ከገዛ ልጇ ጋር ለምትዋጋዉ!

ታዉቅ ይሆን ግን ይኼን ጉዷን? ጃሪም ራሱስ ሲራክ ፯ን ያዉቀዋል? የእመዋን እና የኔን ምስጢርስ? የሲራክ ፯ አባል መሆናችንንስ?

ማለቂያ የሌላቸዉን ጥያቄዎቼን ተከትሎ፣ ደዉይ ደዉይ የሚል ስሜትዐተጠናወተኝ፡ ከመሬት ተነስቶ ወይ ደግሞ ሐሜተኞችን ሰምቶ፣ የእናቴ ልጅ አይደለሽም, ብሎ የገዛ ሰማዩን ሳይቀር ከነቀነቀዉ በኋላ እኮ ፊት
ፊት ተገጣጥመን አናውቅም: እንኳንስ እንደ እህትና ወንድም
ልንደዋወል ቀርቶ፣ በመንገድ ላይ እንኳን ላለመተያየት ያልበላነዉ ፍዳ የለም

ለምሳሌ ባለፈዉ ወደ ልደታ ቤተ ክርስቲያን እየሄድሁ ነበር ከርቀት
በመንገዴ ላይ እሱ ሲመጣ አየሁት: መንገዷ ደግሞ ቀጭን በመንደር መካከል መሿለኪያ ስለሆነች፣ ግንባር ለግንባር መገጣጠማችን የማይቀር
ነበር። ካየሁት በኋላ፣ ልክ አንድ ርምጃ በተራመድሁ ቁጥር ልቤ
መዉደቅ መነሳት ጀመረች: በዚያች ቅጽበት ስንቱን እንዳሰብሁት!ከልጅነታችን ጀምሮ ያሳለፍነዉ ጊዜ ሁሉ አንድ በአንድ እንደ ነፋስ ሽዉ እያለ አለፈብኝ፡ ከከተማ ከተማ፣ ከገዳም ገዳም፣ ከቤት ቤት፣ ከጨዋታ ጨዋታ እየተፍነከነክን የተሽከረhርነዉ ሁሉ መጣብኝ፡፡ ይኼንን
ለሚያህል ትልቅ ቤተሰብ የአንድ ሰዉ ያዉም የአንድ ካህን ደሞዝ
በቂያችን ሆና፣ ከእኛ አልፈን ወላጆቻችንን ጭምር የኑሮዉ ጫና እንዳይሰማቸዉ ማድረግ ችለን ነበር፡ ከሌሎች እህቶቼና ወንድሞቼ ጋር ክብ እየተቃቀፍን ጨለማዉን ቀን፣ ቀኑን ደግሞ ምርጥ ቀን አድርገን ያሳለፍነዉ ሳይቀር ትዝ አለኝ፡፡ ቀና ብዬ አየሁት እየተደራረስን ነዉ፡
እሱም እርምጃዎች ወደኔ ሲመጣ፣ እኔም ያን ያህል በተጠጋሁት ቁጥር፤
አሁን ግን ምን እንባባል ይሆን? የሚል ጭንቅ ዉስጥ ወደቅሁ።
መቼም ከአንዴም ኹለት ሦስት ጊዜ አፍ አዉጥቶ እህቴ አይደለሽም ብሎኛል። ካቴዴራል ሊያቃጥል ሲል ዓይኔ በብረቱ አይቶታል፣ ተፈራርተን ወር ሆኖናል፡ ታዲያ አሁን እንዲህ ብቻ ለብቻ ስንገናኝ፣ ምን ሊዉጠን ነዉ? ቆይ ምን ከመባባልስ ነዉ የምንጀምረዉ? በበኩሌ ለሰላምታ ራሴን እያረጋጋሁ ሳለ፣ እሱ አየኝ፡፡ ለካንስ እስከ አሁን አላየኝም ኖሯል፡ ልክ ሲያየኝ በምን ቅጽበት እንደ ተሸበለለ! ጥቅልል ብሎ ዞሮ ወደ መጣበት ፈረጠጠ፡ ልክ እንደዚህ ሁሉ ስንትና ስንት ጊዜ
ተመላልጠናል፡ በዚህ ሁኔታ መሆናችንን ሆዴ እያወቀዉም፣ ደዉይ ደዉይ የሚለዉ
ስሜት ለምን አሁን እንደ ተጠናወተኝ አልገባኝም: ብቻ ጸንቶብኛል ለነገሩማ ምንስ ቢሆን ወንድሜ አይደል? ያዉም ከፍ ዝቁን አብሮኝ ያየ የእናቴ ልጅ!

ደወልሁለት

አያነሳም

ደግሜ ብሞክርም፣ አያነሳም: ከተደጋጋሚ ሙከራ በኋላ በስልክ
የማግኘቱ ጉዳይ እንዳልሆነልኝ ሳዉቅ፣ ሌላ አማራጭ አጣበርሁ በአካል መፈለግ አማራጭ ሆኖ መጣልኝ፡፡ ነገር ግን፣ በዚህ ባሕር በሆነ ከተማ አንድ እሱን በእግር በፈረስ ፈልጎ ማግኘቱ፣ ባሕር ዉስጥ የወደቀችን ጠጠር ፈልጎ እንደ ማግኘት የማይሞከር ነገር ነዉ፡ ስለዚህ ከሲራክ ቢያንስ አንድ የሚረዳኝ ሰዉ ያስፈልገኛል፡
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በታደለ_አያሌው


...“ጥሩ” አሁኑኑ ወደ ፊንፊኔ የባህል ሆቴል መሄድ ትችያለሽ: በዚያ ያሉ
የእኛ ሰዎች ሽፋን እንዲሰጡሽ ተነግሮልሻል። ከመግቢያዉ በር ገባ ብሎ (ቀለወ) ብሎ ሰላምታ የሚያቀርብልሽ አስተናጋጅ ተከተዪዉ: አደራሽን ቸኩለሽ ነገር እንዳታበላሺ። ጃሪም አንቺ እዚያ ካየሽ መደንበሩ ነዉ። በፍጹም ሊያይሽ አይገባም”

“ገብቶኛል”

በይ እንግዲህ ልጅ ወልደሽ እስከምንስማት ድረስ፣ ይኼኛዉ
የመጨረሻ ተልእኮሽ ይሆናል”

“እሺ”

“መልካም ዕድል”

“ለማኅበራች!” ብዬ ስልኩን ዘጋሁት፣ ሁልጊዜም ተልእኮ ስንቀበል እንደ አመቺነቱ እንደምናደርገዉ ሁሉ ማተቤን እየጨበጥሁ፡

ባልቻ እንዳለኝ ልክ ከባህል ሆቴሉ የዉጪ በር ገባ እንዳልሁ፣ አንድ
ወጣት አስተናጋጅ መጥቶ ንግሥት እንደሚያገለግል ሰዉ ተሽቆጥቁጦዐበፊቴ እጅ ነሳ ቀጥሎ ምንም ፋታ ሳይሰጠኝ፣ “የባህሎች ሁሉ መታያ
ወደ ሆነዉ ሆቴላችን እንኳንም በደህና መጡልን ቀለዘ እባላለሁ፤
ምሽትዎ እንደ ፈቃድዎ ለማድረግ እጅግ ጓጉቻለሁ” አለኝ፣ ነፍስ
በሚያረካ ፈገግታ እና ትሕትና

“እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፣ አመሰግናለሁ ወንድሜ” ስል ፈገግታዉን ተጋራሁት።

“ይከተሉኝ እባክዎ”

“በደስታ” ብዬ ተከተልሁት እንግዳ መቀበያዉ ያለበትን በግራ በኩል
ትቶ ወደ ጀርባ በር መራኝ ትኩረት ላለመሳብ የሚያደርገዉን ጥንቃቄ
ሳይ አደነቅሁት
“በዚች በኩል ይምጡ እባክዎ። የመጡት የባህል ቤት ነዉ: በባህላችን ደግሞ ንግሥት እና ነፍሰ ጡር የፈቃዳቸዉ ልናሟላላቸዉ ግዳችን ነዉ።
እኔ በበኩሌ፣ እርስዎ የሚፈልጉትን ማንኛዉም ነገር ሁሉ ለማሟላት
የማልሰንፍ መሆኔን ይወቁልኝ እመቤቴ”

“እዉቃለሁ: ግን እኮ፣ ለቤታችሁ ያን ያህል እንግዳ አይደለሁም

“አይደል?”

“አዎ አልፎ አልፎ ብቅ እላለሁ”

“ልክ ነዉ፤ አንድ ጊዜ ቤታችንን ያዩ ሁሉ አዘዉትረዉ እንደሚመለሱ እናዉቃለ። ስለ ደበኝነትዎ ሞልቶልን ሽልማት ባናዘጋጅልዎ፣ ቢያንስ
ደህና መስተግዶ ግን ይገባዎታል እንኳስ ንጉሥ ይሁን ንግሥት
በሆድዎ ይዘዉ!”

ለብ ያለ ሳቅ ሳቅሁለት በጀርባ በር ከወጣን በኋላ፣ ትንሽ እንደ ሄድን
በተለየ ክፍያ የተለየ መስተንግዶ የሚሰጥበት ልዩ (VIP) ቤት ይዞኝ ገባ:: የገጠሩን ድባብ ለመፍጠር ይመስላል፣ ክፍሉ ጭልጭል የሚሉ ኹለት ፋኖሶች በግራና በቀኝ በኩል ባለዉ ግድግዳ ላይ ተለኩሰዉበታል፡ ያም ሆኖ ግን በቤቱ ያሉትን ሰዎች ቀርቶ፣ ራሳቸዉን ፋኖሶቹን ለማየት የጅብ
ዓይን ሳይቀር ይፈትናሉ በቤቱ አማካይ የሆነ ቦታ ላይ በተሠራዉ
መድረክ፣ ኹለት ወጣቶች ከዘፋኟ እና ከሙዚቀኞች ጋር እየተናበቡ
ቅልቅል ባህላዊ ጭፈራ እያቀረቡ ናቸዉ፡ እነሱ ብቻ እንደ ልብ ይታያሉ ከእነሱ በቀር ጥላ የሚመስል ነገር ነዉ የሚታየኝ፡፡ በዚያ ላይ የመድረኩ አሸሸ ገዳሜ ድምፅ ስለዋጠዉ፣ ጥላ የሚመስሉት የቤቱ ተስተናጋጆች
የሚያወሩትን አንዱንም መስማት አልቻልሁም

መጀመሪያ እንዲያዉም ትርኢት ለመመልከት ወደ ብሔራዊ ቴአትር አርፍጄ የገባሁ ነበር የመሰለኝ፡ ቴአትር ከተጀመረ በኋላ የመድረኩ መብራት ብቻ ስለሚቀር፣ ቴአትር ቤት አርፍጄ ስገባ መቀመጫ ለማግኘት የማየዉን ፍዳ አስታወሰኝ፡፡

ከበር ጀምሮ ያመጣኝ አስተናጋጅ፣ ወደ ወንበር ባይመራኝ ኖሮ ስደናበር የሆነ ተስተናጋጅ ላይ መከመሬ አይቀርም ነበር፡ ደግነቱ እሱ የቤቱን ዐመል በዳበሳ ያዉቀዋል፡ በመሆኑም እጄን ይዞ እየጎተተ ወሰደኝና ክብ ሠርተዉ ለተቀመጡ ጥላዎች ጀርባዬን እንድሰጥ አድርጎ አስቀመጠኝ።
ጨለማዉን እየለመድሁት ስመጣ ከአጠገቤ ክብ ሠርተዉ ተቀምጠዉ የሚነጋገሩት ሰዎች ጥላ እንደ መድመቅ እያለልኝ መጣ፡፡ በመጠኑም ቢሆን ወገግ አለልኝ፡፡ ጆሮዬን አቁሜ እየተቀባበሉ የሚናገሩትን ማዳመጥ ስጀምር፣ አንደኛዉ በድንገት የጃሪምን ስም ጠርቶ የሠራ አካላቴን አቀለጠብኝ

“ጃሪም ካነሳቸዉ ነጥቦች ላይ” ብሎ ጀመረ፡ ጀርባዬን እንደ ሰጠሁ
በተወዛዋዦቹ ላይ ጥዬ፣ ቁጭ
ብዬ፣ የመድረኩን ትዕይንት እንደሚከታተል ሰዉ ዓይኖቼን
ከተወዛዋዦች ላይ ጥዬ ተናጋሪዎችን ማዳመጡን ተያያዝሁት ጃሪም አነሳቸዉ የተባሉት ነጥቦች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ለመስማት ቸኮልሁ

ጀሪም ካነሳቸዉ ነጥች ላይ ምንም የሚወድቅ ነገ አላገኘሁም: ነገ ዛሬ ሳንል፣ ነገሮችን ማዕከላዊ እና መስመራዊ ማድረግ አለብን ያለበዚያ እንዲህ እያቦጫረቅን ከማደፍረስ ያለፈ የትም ማድረስ አንችልም። አዛዥ ያስፈልገናል። መስመር መያዝ አለብን። ለምንወስዳቸዉ እርምጃዎች ሁሉ ግብ የሚሰጠን አካል ያስፈልገናል ኪሳራዎቻች ዜሮ ማድረስ ባንችልም፣ መቀነስ ግን አያቅተንም ለዚያ ደግሞ ለሁሉም
መግቢያዎቻችን መዉጫ የሚያበጅልን አካል ያስፈልገናል። ሕመም እና ሕልማችንን የሚጋሩን ብዙ እንደሆኑ ባዉቅም፣ ተበታትነን ስለምታገል ጉዟችንን አርዝሞብናል: ስለዚህ በአንድ እዝ ሥር የሚያደርገን አካል
ያስፈልገናል። ያለበዚያ መድረሻችን አንድ ሆኖ ሳለ፣ ባለመተዋወቅ እና የጋራ መሪ በማጣት ብቻ ራሳችን የራሳችን እንቅፋት እየሆንን መቀጠላችን ነዉ: አንድ አካል ያስፈልገናል። ያን አካል ደግሞ አሁኑኑ መሠየም አለብን በበኩሌ ሙሉ ሆነን እስከምንመርጥ ድረስ፣ ጃሪም
ጊዚያዊ አዛዥ ቢሆነን…

“ቆይ ቆይ!” አለች ሌላኛዋ፣ የቀደማትን ተናጋሪ ከአፉ ቀምታ
“ቆይ እንጂ! መጀመሪያ ሐሳቡን እንስማማበት እና ምርጫዉን
እንደርስበታለን” አለ ሌላኛዉም፣ ተቀብሏት “በእርግጥ እንደተባለዉ
ነዉ። እስከ አሁን ግብ አልነበረንም ማለት ሳይሆን፣ የነጠረ ለማድረግ እና
እርስ በእርስ ለመናበብ ግን የተደራጀን መሆን እንዳለብን እኔም አምንበታለሁ”

“ከዚያ በፊት” ሲል ተቀበለ ሌላኛዉ፣ ምን እንደሆነ ያላየሁትን መጠጥ ገርገጭ አድርጎ ተጎንጭቶለት: ጉሮሮዉ ፏፏቴነት አለዉ እንዴ ብያለሁ በልቤ፣ የተጎነጨዉን ሲዉጥ ያወጣዉ ድምፅ አስገርሞኝ፡ “ከዚያ በፊት
ስለ እህቱ አንድ ነገር ማለት የለብንም ወይ?”

እህቱ? ስለ ማን እህት? ስለ ጃሪም እህት፣ ስለ እኔ እንዳይሆን ብቻ!

“እ..ህ..ቴ አይደለችም!” አለ ጃሪም፣ እጅግ በተቆጣ እርጋታ፡ እፍን ባለ ንዴት… “ዉብርስት የሚባል እህት አላውቅም ብያችኋለሁ: እኔ እህት የለኝም! ማንም ሰዉ እህትህ እንዲለኝ አልፈልግም ከዚህ በኋላ::
ማንም!”

“ከልብህ መሆኑን አሳየና”

“ምን አድርጌ ነዉ የማሳይህ በል? አትመና ከፈለግህ! ምን ይላል ይኼ?” አለ ንዴቱ እየተገለጠበት፡ እንዲያዉም ለድብድብ የሚነሱ ነበር
የመሰለኝ፡ “ና ሆዴ ዉስጥ ግባ: ግባና በልቤ ዉስጥ እሷን እህት፣ እናቷ ደግሞ እናቴ ሆና ካገኘኻት ፈልጋታ! ና በላ!”

ከእሱ በኋላ ደፍሮ የተናገረ የለም፡

ረዥም ዝምታ ሆነ፡

“ቀን ነዉ የምጠብቅላት: አንተ እንድታምን ስል ግን የማደርገዉ ነገር የሚኖር እንዳይመስልህ! አንድ የሚያጠራጥር ነገር ስላየሁባት እሱን እያጣራሁ ነዉ: የሆነ ቡድን ከጀርባዋ ያለ ይመስለኛል: ወጣ ወረደ
ከዚህ በኋላ የእናት የአባቴ ቤት ላይ እንዳሻቸዉ እንዲሆኑ
አልፈቅድላቸዉም: አፈር ነዉ የማገባት! አለብሳታለሁ!”

የሆንሁትን አላዉቀዉም፡ ብቻ ግን፣ ጭዉ የሚል ድምፅ ይሰመኛል።
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በታደለ_አያሌው



“ምንድነዉ እመ?”

እየቆየ ፍርሐት እየለቀቀብኝ፣ ላብ እያጠመቀኝ መጣ፡ ቢያንስ ቢያንስ እንዴት ድምፅዋን እንኳን አልሰማሁትም? ለምን አላለቀሰችም? “ኧረ ልጄስ? ልጄ አታመጡልኝም?” አልሁኝ ከአሁን አሁን ቱናትን አምጥተዉ ያስታቅፉኛል ብዬ ብጠብቅ ዝም ስላሉኝ፡ አጭር ጊዜ በፈጀ
ቀዶ ሕክምና ቢሆንም የወለድሁት፣ የእናት ወጉ ደርሶኝ ገና ጡቴን ለልጄ አላጠባኋትም ጡት ማጥባት ቀርቶ ለዓይኔ እንኳን አላሳዩኝም፡

“አይ፣ ለትንሽ ጊዜማ ማሞቂያ ክፍል አትቆይም ብለሽ ነዉ? እንግዲህ ዶክተርሽ ያለችን እንደዚያ ነዉ” አለች እመዋ፣ ከእሸቴና ባልቻ ጋር የያዘችዉን ሞቅ ያለ ጨዋታ አቋርጣ ትኩረት እየሰጠችኝ፡

“እኮ ባይሆን አሳዩኛ። ላያት እፈልጋለሁ”

“ቆይ ትንሽ ተብለሽ እኮ ነዉ: አንቺም ትንሽ አረፍ በይ እስኪ ፊት”

“እመዋ፤ ወይ ወደ ልጄ ዉሰጅኝ ወይ ደሞ ልጄን አምጭልኝ” አልሁኝ፣ ከአልጋዬ ላይ ለመነሳት እየተገለገልሁ አቅም አጣሁ እንጂ ማንም አይመልሰኝም ነበር ለምንም ነገር እንዲህ ሆኜ አላዉቅም ለካ እንዲህ ነዉ የሚያደርገዉ? አሁን በአሁን እናት ሆኜ እርፍ! የእናት ሆድ ኖሮኝ
ቁጭ! ጭራሹን ያላየኋት ልጄ በዓይን በዓይኔ ዞረች᎓᎓ ናፈቀችኝ፡ ራበችኝ፡ ደግሞ ልቤ እንዴት ነዉ የሚደልቀዉ? ልጄን እንጂ የፍርድ ቤት ዳኛ አይደል የምተያየዉ፡

የናፍቆቱስ እሺ ይገባኛል፤ ፍርሃቱን ግን ምን አመጣዉ?
የልቤ መንቀጥቀጥ ቆዳዬ ላይ እስከሚታወቅ ድረስ በጣም ፈርቻለሁ ጭንቅላቷን ማየት ነዉ ፤ያስፈራኝ: ትልቅነቱ ምን አህሎ ይሆን? ራሷስ ምን ታህል ይሆን? ኹለት ኪሎ እንኳን መሙላቷን እንጃ አተነፋፈሷ ልክ ነዉ? በቅድመ ወሊድ እንደ ተፈራዉ፣ የጀርባዋ ነርቭ ክፍተት ፈጥሮ ይሆን? ቢያንስ እግሮቿን ማንቀሳቀስ ትችልም እንደሆነ
እኮ ገና የነገረኝ የለም: ዓይኖቿም በትክክል ማየታቸዉን አላወቅሁም
ወይስ እግዚአብሔር ተአምር ሠራ? ባልቻ እና እመዋ እንደ ተማመበት ድንቅ ሥራዉን አሳይቷቸዉ ይሆን? በተአምሩ የሰዉ መልክ፣ የሰዉ ጤና፣ የሰዉ ትንፋሽ ሰጥቷትስ ቢሆን! እሱንስ ቢሆን ማን ነገረኝ?
እግዚአብሔር እኮ ሥራዉ የሚታወቀዉ አንድም በጨቅላዎች ነዉ ይባላል፡፡ ከማሕጸን እንደ ወጡ ገና የጡትን ቦታ እና ጥቅም አጥተዉት
አያዉቁም: ልጄንስ ጡት አያምራት ይሆን? ካላየኋትማ መሞቴ ነዉ፡

እንደገና ፈራኋት ፡ እንደገና ናፈቅኋት።

“አንቺ ግን አየሻት ወይ እመ?” አልኋት፣ እጆቼን ከጡቶቼ ላይ ሳላነሳ።

“ማንን፣ ቱናትን?”

“አሃ፤ ስምም አዉጥታችሁላታላ?” አለ ባልቻ፣ ከእመዋ አፍ ተቃምቶ።

“ቱናት ብያታለሁ በበኩሌ” አለች፣ እመዋ:

“እመዋ” ስል ጠራኋት ቆጣ ብዬ፣ የባልቻ አጠያየቅ ወሬ ለመለወጥ
መሆኑ ስለ ገባኝ፡

“ዉብዬዋ” አለችኝ፣ የእናት እጇን ጭምር እየሰጠችኝ ይኼዋ እንዴት
እንደምታቆለማምጠኝ! ቁልምጫዋንስ ማቆላመጥ ታዉቅበት የለ? እሷ እናትነቷን እንዲህ ባጠጣችኝ ቁጥር፣ የእኔም ጉጉት ሰማይ ይደርሳል
እሷ ለእኔ እንደምትሆነዉ፣ እኔም ለልጄ ለመሆን ቋምጫለሁ

“እመዋ”

“እመት ዓለሜዋ”

“ስሞትልሽ! ስሞትልሽ ልጄን አምጭልኝ'

“ኧረ ቀስ! ምነዉ ልጄ? ወዲያዉስ የሐኪምሽ ወዳጅነት ላንቺ መስሎኝ! እንዲህ ሆነሽ ትወስድሽ ሆይ ወይ ደግሞ ቱናትን እንዲያ እዳለች ታመጣልሽ እንደሆነ፤ ሐኪምሽን ራስሽ የማትጠይቂያት”

"እኮ ጥሪልኛ እመዋ ዶክተሯን ጥሪልኝ እሺ”

እንደማልለቃቸዉ ሲያዉቁ ዶክተሯን ማስፈለግ ጀመሩ፡ ነገር ግን ሌላ ተረኛ ነፍሰ ጡር ለማዋለድ፣ ወደ ማዋለጃ ክፍል ቅርብ ጊዜ እንደ ገባች ከነርሶቹ መስማታቸዉን ነገሩኝ፡
አላመንኋቸዉም በይበልጥ
እየፈራሁላት፣ በይበልጥ እየተጠራጠርኋቸዉ መጣሁ ቅጽበት በቆየሁ ቁጥር ክፉ ክፉዉን ለሚያሳስበኝ መንፈስ መረታት ያዝሁ፡ ጭራሽ በሕይወት ባትኖር ይሆናል እንጂ፣ ቢያንስ እንዴት ድምፁዋን እንኳን
አያሰሙኝም?

“አአአ..አንድ ሐሳብ መመመመ..መጣልኝ” ሲል ሰማሁት እሸቴን፣ እስከ
አሁን ዓይኖቹን ከማንከራተት በቀር ትንፍሽ ሳይል ቆይቶ፡ “ዉዉዉ..
ዉቤ? ”

“እየሰማሁህ ነዉ”

ሐሳቡን አንድ ብሎ ሊነግረኝ ሲጀምር ገና፣ ልታዋልድ ኦፕራሲዮን ክፍል ገብታለች የተባለችዋ ዶክተር የክፍሉን በር ከፍታ ገባች፡

“ኦንኳን ማርያም ማረችሽ” አለችኝ፡

“ማርያም ታኑርሽ” አለች እመዋ ቀድማኝ ወዲያዉም ከጎኔ ቁጭ
ካለችበት የአልጋዉ ጫፍ ብድግ ብላ፡ ዶክተር ሸዊት ያ ብዙም
የማይለያትን ፈገግታዋን
ሳትቀንስ ሁሉንም እያቀፈች ሰላምታ ከተለዋወጠች በኋላ፣ እኔንም ጎንብስ ብላ ሳመችኝ፡፡ ግንባሬን አንገቴን እና እጆቼን እየደባበሰችኝ ሳለ፣ ለምን ልጄን እንደማያመጡልኝ ልጠይቃት ስል ቀልቧን ወደ እመዋ አደረገችብኝ፡፡

“እመዋ? እንኳን ደስ አለዎ”

“በአምላክሽ!”

“መቼስ ረስተዉኝ አይሆንም፤ ረሱኝ እንዴ ? "

“ተይ እንጂ! ምን ብረሳ ብረሳ፣ አንቺን እረሳ ብለሽኝ ነዉ? ምነው
አንድዜ እንኳ ከዉብዬ ጋ ለክረምቱ ይሁን ለገናዉ ዕረፍት
መጥታችሁ አብረንም አልሰነበትን?”

“አልረሱኝማ”

“ አንቺን? እንዲያዉ ያቺን ጨዋታሽ የምረሳልሽ መስሎሻል?”

“የቷን?” አለች፣ ለመፍካት ችኩል የሆኑ ጥርሶቿን እየገለጠች

“ምነዉ እንኳን አንድዜ፣ የሩስያ ምንቴስ ነዉ ያልሽኝ ሰዉ በዉብርስቴ ደም ግባት የሆነዉን ሁሉ አጫዉተሽኝ?”

“ስለ እሱ ጉድ ነግሬሽ ነበር ወይ እመዋ?”

“እህሳ”

“ለእኛም ንገሪን እንጂ ዶክተር” አለ ባልቻ፣ ያለ ወትሮዉ ለወሬ ሰፍ ብሎ፡ የእሸቴም ጆሮ ከምኔዉ ቀጥ እንዳለ! የእሸቴ እና የባልቻስ ይሁን እሺ፣ እመዋ እንኳን እንደ አዲስ ለመስማት በዓይኖቿ ደጅ ስትጠናት ሳይ እኔም የልጄ ናፍቆት በረድ አለልኝ፡፡

“ጉዷ ያልቅ መስሏችኋል?” ብላ ጀመረች፡ “ይቺ ጉደኛ! የተመረቅን
ሰሞን ነዉ ነገሩ። ቀድሞዉንም ቢሆን በዉጤት እንደ ምንም እቀራረባት እንደሆነ እንጂ ደርሼባት አላውቅም:: በተለይ የመመረቂያ ጥናቷን ያዩላት ሰዎች ሁሉ እዴት ይደነቁባት እንደነበር አትጠይቁኝ። እና እንደ አጋጣሚ፣ በዚያ ሰሞን የሩስያ አምባሳደር ከሀገራቸዉ የመጡ በጎ ፈቃደኛ
ሀኪሞችን እየመሩ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መጥተዋል። ጠሪዉ ደግሞ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ነዉ: የዚያን ዕለት ታዲያ፣ የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዜዳንት ራሱ ስልክ ደዉሎላት ኹለት ሁነኛ ሰዎች እንድትመርጥ እና በጎ ፈቃደኛ ሩስያዊ ሀኪሞችን እንድታግዝ ያዝዟታል”

“ማንን?”

“ይቺን ነዋ፤ ዉብርስትን''

“እሺ”

"እሷ ደግሞ እኔን እና አንድ ሌላ ሐኪም ስትጠይቀን፣ እናግዛለን ብለን ሳይሆን እንጠቀማለን ብለን ወደ ተባሉት በጎ አድራጊዎች በጠዋት †ነስተን ተከተልናት።
በዚያች አንድ ቀን ታዲያ፣ ሩስያዉያኑ ያልደረሱበት የጎንደር ዙሪያ ጤና ጣቢያ የለም። እኛም አብረናቸዉ እየዞርን እነሱ ለጤና ጣቢያዎቹ ያመጡልን መድኃኒት ስናድል እና ለጥቂት አበሻ ሕመምተኞች ደግሞ መጠነኛ ሕክምና ሲሰጡ ስናይ ዋልን
ማታዉኑ፣ ዩኒቨርስቲዉ እንግዶቹን እራት ካልጋበዝሁ አለ። አምባሳደሩ ግን አመሻሹ ላይ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ቢሆንም ዕቅዳቸዉ፣ ከስንት መለመን በኋላ የበረራ ሰዓታቸዉ እንዲዘገይ ተስማምተዉ በግብዣዉ ላይ
ተገኙ። እኛም እንደ እንግዶች በክብር ተጠርተን፣ መጥሪያዉ ላይ በተጠቀሰዉ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ተገኝተናል። የከተማዉ ከንቲባ፣ የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዜዳንት፣ምክትሎቻቸዉ እና ዘመዶቻቸዉ ጭምር
መጥተዉ ሳይሆን አይቀርም፣ ያን የሚያህል አዳራሽ ጢም ብሏል።
የጎንደር መታወቂያ የሚባሉ አዝማሪዎችም መድረኩን ሞልተዉታል።ብርቆዎች፣ ጨዋታዎች፣ ሳቆች ድብልቅልቅ አድር ገዉታል”
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በታደለ_አያሌው


...."“እስኪ…” አለች ዶክተር ከብዙ ዝምታ በኋላ፣ ወደ በሩ እያመለከተቻቸዉ። “እስኪ አድ አፍታ ላስቸግራችሁ፣ ዉጪ ጠብቁ ያለ ምንም ጥያቄ ሁሉም ምሰስ እያሉ ሲወጡ፣ በክፍሉ እኔና እሷ ብቻ ቀረንበት.

“ልጄን…” ስል ተቀበልኋት፣ ባልቻን የሸኙ ዓይኖቿ ወደኔ ሲመለሱልኝ፡
“ልጄ አታሳዪኝም?”

“ናፈቀችሽ አይደል?”

“ኧረ አልቻልሁም ሽዊት”

“ይገባኛል። አዉቃለሁ”

“ታዲያ አምጭልኛ”

“እያወቅሽዉ? እንደሱማ አይሆንም”

“እንዴት ናት ግን? እንደ ፈራነዉ ሆነ ወይስ እግዜር ተአምሩን አሳየሽ?” አልኋት፣ ፈራ ተባ እያልሁ።

“ኹለቱም”

የምትለዉን እንድትል ጠበቅኋት፡
“እንደ ፈራሁትም ነዉ፤ እግዚአብሔርም ተአምሩን አሳይቶኛል። ኹለቱንም”

አሁንም ጭጭ ብዬ አዳመጥኋት፡ ጠበቅኋት እያየኋት የግንባሯ ሰማይ ዳመነ፡ የዳመኑ ዓይኖቿም እንባ አዘሉ፡ ምንም ሳይቆይ ያዘለዘለ እንባዋ ቡልቅ እያለ ሲወርድ እኔም አልቻልሁም: የኔም ጉንጮች ቀዝቃዛ እንባ አለፈባቸዉ: ከመሬት ተነስቶ ብርድ አንሰፈሰፈኝ

“ቁርጤን ልስማዉ?” አልኋት፣ መጥፎ ነገር ብትነግረኝ ፍጥርቅ ብዬ ለመሞት እየተሰናዳሁ: ከመሞት በቀር ምን ምርጫ አለኝ? ምንም:: እሞታለሁ

“ግልጹል ንገርሽ: ወደ ኦፕራሲዮን ክፍሉ ስገባ፣ አንቺን ለማትረፍ
እንጂ ልጅሽ በሕይወት ትመጣለች ብዬ አልጠበቅሁም ነበር። በሆድ
ሳለች የልብ ምቷ ስናዳምጠዉ በጣም አስፈሪ ነበር። አንቺም ትናትና እንዳልሽኝ በሆድሽ ዉስጥ እየተንቀሳቀሰች አልነበረም: በዚያ ላይ ከመደበኛዉ የመወለጃ ጊዜ እጅግ ቀድማ ስለመጣች፣ ላንቺ ፈርቼልሽ ነበር: በግልጽ ልንግርሽ አይደል ዉብዬ? የልጅሽ በሕይወት መትረፍ፣ ያንቺም በጤና መገላገል የእግዚአብሔርን ሥራ በዓይኔ በብረቱ ያየሁበት
ተአምር ነዉ”
“እንግዲያዉ ምድነዉ የሚያስለቀሰሽ?”
ለመናገር ዳዳችና ተወችዉ፡፡

በጥያቄ የተጥለቀለቀ ፊቴን ስታይ ቆይታ፣ የነርሶቹን መጥሪያ ደወል ተጫነችዉ፡ ደወሉን ሳትለቀዉ ገና፣ ከቅድም ጀምራ በተለየ ሁኔታ ጠብ እርግፍ ስትልልኝ የነበረችዋ ነርስ ያለንበትን ክፍል ከፈት አድርጋ ገባች
“አቤት ዶክተር''
“እስኪ ባክሽ አንድ ነገር ላስቸግርሽ”
“ምን ልታዘዝ ዶክተር?''
“እስኪ ባክሽ ዉብርስት ወደ lCሀ ክፍል እንዉሰድና አንዳፍታ ልጇን
በዓይኗ እናሳያት”
“ኧረ?” አለች፣ ድንግጥ እያለች:
“አይዞሽ፤ አብሬሽ አለሁ: ኃላፊነቱን ራሴ እወስዳለሁ” ስትል
አደፋፈረቻት፣ ነፍሴን የያዘልኝ ግሉኮስ የተንጠለጠለበትን ዘንግ ራሷ ከፍ አድርጋ እያነሳችና መንገድ እየጀመረች:

ነርሷም ትንሽ እንደ ማቅማማት ስትል ከቆየች በኋላ መታዘዟን
አስበልጣ የተንጋለልኩበትን አልጋ
ማሽከርከር ጀመረች መኪና ማቆም ከሚያያስችለዉ የሕንጻዉ ሰፊ አሳንሰር ከነአልጋዬ ከጫኑኝ በኋላ ኹለት ፎቆች ወደ ላይ ወሰዱኝ፡ ከአሳንሠሩ ወርደን ትንሽ እንደ ሄድን፣ ጥልቀት ያለው እንክብካቤ ወደሚደረግበት (ICU) ክፍል ደረስን፡ እጅግ ሰፋ
ወዳለዉ አዳራሽ ከመግባቴ፣ የተለያየ ስምና መጠን ያላቸዉ ማሽኖች ተደርድረዉ አየሁ፡ በአብዛኛዎቹ ማሽኖች፣ በተለይም ያለ ዕድሜያቸው የተወለዱ ሕጻናት ተኝተዉባቸዋል፡ ያዉም በሆድ፣ አፍና አፍንጫቸ
ላይ በልዩ ልዩ ማስተላለፊያዎች ተተብትበዉ፡ በነዚህ ትብታቦች
አማካኝነት በዋናነት ምግብ እና አየር የሚያገኙ ሲሆን፣ ማሽኖች
የየራሳቸዉ ማሞቂያም ሆነ ማቀዝቀዣ የተሟላላቸዉ መሆናቸዉን በስማቸዉ አዉቃቸዋለሁ መሀል ለመሀል እየወሰዱኝ ሳለ፣ በግራም
በቀኝም በኩል ዓይኔ ዉስጥ የገቡትን ሕጻናት ሥራዬ ብዬ ተመለከትሁ ሁሉም እንደየአቅማቸዉ እግርና እጃቸዉን ያወራጫሉ።

ቱናትን ላያት ነዉ፡

ብዙ የተገመተላትን፣ የልጄን ዓይን በዓይኔ ላየዉ ነዉ፡፡ ልጄ ቱናት
ያለችበት ክፍል ዉስጥ መሆኔን ሳዉቅ፣ ይኼ ነዉ ብዬ መግለጽ
የማልችለዉ ሽብር ወረረኝ፡፡ ፍርሃቴም ናፍቆቴም ተደራርበዉ ልቤን ጫፍ ላይ አደረሱብኝ፡፡ ልትወጣ ምንም አልቀራትም፡፡

ፍርሃቴ ጫፉ ላይ ደርሷል፡

“ይቅርታ” አለች ዶክተር፣ ወደ ነርሷ ዘወር ብላ፡ ሲመስለኝ ቱናት
ያለችበት አጠገብ ደርሰናል በዓይኔ ባጣብራት ግን ላገኛት አልቻልሁም ጭንቅላቷ ከፍ ያለ ልጅ ፍለጋ ዓይኔን ባንከራትትም አላገኘኋትም፡ የዶክተሯ ጥቅሻ ገብቷት ነርሷ የያዘችዉን የአልጋዬን ብረት ለቀቀችና
ተመልሳ ወጣች:: ኹለት የክፍሉ ባለሙያዎች በክፍሉ ያሉ ቢሆንም፣በማሽኖች አጠገብ ግን አይደለም የቆሙት ዝም ብለዉ ብቻ እንደ ንቁ ወታደር፣ ወዲያ ወዲህ ይንጎራደዳሉ።

እኔም እሷም ወደ'ዚህ ክፍል ለመግባት፣ ቢያንስ የእነሱ ፈቃድ
እንደሚያስፈልግ እኔም ገምቻለሁ
በመሆኑም በየስማቸዉ ጠርታ ሰላም እያለቻቸዉ ወደ እነሱ ቀረበች: ምን እንደ ተባባሉ ባይሰማኝም፣ ብቻ የሆነ ነገር ብላ አሳምናቸዉ መጣች: በአንድ እጇ ግሉኮስ የተንጠለጠበትን የብረት ዘንግ፣ በሌላ እጇ ደግሞ አልጋዬን በትራስጌ በኩል እየገፋች ዉስጥ ለዉስጥ ተሂዶ ወደሚገኝ ሌላ ክፍል አደረሰችኝ፡: ጠጋ ብላ
ካነጋገረቻቸዉ ባለሙያዎች አንደኛዉ ቀደም ብሎ በመዳፉ አሻራ በሩን ከፈተልንና ገባን፡፡ እሱን በደረቅ ፈገግታም ጭምር እጅ ነስታ ከሸኘችዉ በኋላ፣ እስከ አሁን በጭራሽ አይቼባት የማላውቀዉን ፊቷን አሳየችኝ፡፡

ከተለዩትም የተለየ እክብካቤ ስለሚያስፈልጋት፣ ልጅሽ ያለችዉ
በዚህኛዉ ለይቶ ማቆያ ክፍል ነዉ: ልጅሽን የማየት መብት ቢኖርሽም፣ መንገዱ ግን አሁን የመጣንበት አይደለም: እንግዲህ ያለ ግርግር መምጣት የፈለግሁበት ምክንያት አንቺም የምታጭዉ አይመስለኝም”
ለጥያቄ አፌን እያሞጠሞጥሁ ሳለ፣ ቀልጠፍ ብላ ከአጠገባችን ያለዉን ማሽን ቁልፎች መነካካት ጀመረች ማሽኑ እጅግ ግዙፍ ሲሆን፣ ከላይ የተገለበጠ ሙኸዶ የሚመስል ክዳን አለዉ፡ ልክ መነካካት ስትጀምር፣
ቀድሞ ወደ ላይ ተስቦ የተከረፈደዉ ይኼዉ ክዳን ነዉ፡ በእርግጥ ክዳኑ ብርሃን አስተላላፊ ስለሆነ፣ ለቆመ ሰዉ እንደ ተከደነም ቢሆን ወደ ዉስጥ
ከማየት አይከለክልም፡ እኔ ግን እንደ ተንጋለልሁ ስለሆነ ተከፍቶልኝ እንኳን ልጄን ማየት አልቻልሁም እስከመጨረሻዉ ድረስ አልጋዬን ከወገብ በላይ አቃንታልኝ፣ ራሷ የመሸከም ያህል ደግፋ ቀና አደረገችኝ
እና ወደ ዉስጥ እንድመለከት አመቻቸልኝ፡

በሙሉ ዓይን ባይሆንም፣ አንገቴን ቀና አድርጋ አሳየችኝ አየኋት
ቱናትን አገኘኋት።እንደ ተፈራዉ ናት።

“ስንት ኪሎ ሆነች?” አልኋት፣ የጭንቅላቷን ግዝፈት እያስተዋልሁ፡አትሆንም እንጂ ኹለት ኪሎ እንኳን ብትሞላ ከግማሽ በላዩን የሚመዝነዉ ጭንቅላቷ እንደሚሆን ያስታዉቃል፡ ዓይኖቿ ወደ ዉስጥ
መቀበራቸዉ ሳያንስ ከተመለከቱም የሚመለከቱት ቁልቁል ብቻ ነዉ፡ እንቅስቃሴ የሚባል የላትም፡ የተኛ ሰዉ እንኳን ሲተነፍስ ሆዱ ላይ ብቅ ጥልቅ ይታይበታል፡ ልጄ ግን ጸጥ ብላለች፡ እኔን ልጄ!

“መቼስ እግዚአብሔር ምን ይሉታል?” አልሁ፣ ተአምሩን ለእኔም ያልገለጠልኝን አምላክ በመቀየም እና በማመስገን መካከል ሆኜ:

“ኧረ እንጃ። ከፊት ለፊትሽ ግን እንዲህ ነዉ የማይሉት ፈተና እንዳለ ልዋሽሽ አልፈልግም: ትእዛዝ ተቀባይ ነርቮች ብዙዎቹ በትክክል አይሠሩም: ስፓይናቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ ከጠበቅናቸዉም በላይ ሆነዉ
#ገረገራ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በታደለ_አያሌው

...“እኮ ልትገድሏት?” አልኋት፣ በምን ተአምር ከአልጋዬ እንደ ተነሳሁ ሳይታወቀኝ፡ በቂጤ ቁጭ ብያለሁ

“ሽዊት? ለካ እስከዚህ ድረስ ጨካኝ ሆነሻል?”

“መቼም እኔን ታዉቂኛለሽ:: እኔ በሙያም በእምነትም ዓይን ስለማየዉ፣ እንደማልስማማበት ታዉቂያለሽ: ግን በእሱ እምነት ይኼ መግደል ሳይሆን ማዳን ነዉ”

“ቆይ ቆይ! ለምንድነዉ ይኼን ለኔ የምትነግሪኝ አሁን?”

“እኔ እንጃ: ምናልባት እንዲህ ያለ እምነት ያለዉ ሐኪም መኖሩንም
ማወቅ ከፈለግሽ ብዬ እደሆነ”

“አወቅሁ: ከዚያስ?”

“እመኚኝ ዉቤ፣ እኔም አልተስማማሁበትም…”

“በቃሽ!”

ንዴት አቅሌን አሳተኝ፡፡

ክፉና ደጉን የተጋራኋት የቀድሞ ጓደኛዬ አስጠላችኝ፡ ብዙ የተፈተንሁባትን ልጄን መግደል እንደ ማዳን የሚቆጥር ወዳጅ እንዳላት ከነገረችኝ በኋላ፣ ፈጽሞ ዓይኗን አያሳየኝ አልሁ: ዉዬ አድሬ ሳብሰለስለዉ እንዲያዉም፣ ሐሳቡ የወዳጇ ብቻ ሳይሆን የእሷም ጭምር መሆኑን ስለጠረጠርሁ ለሆስፒታሉ አስተዳደር ሳይቀር ከሰስኋት። እሷ የነገረችኝ ለብቻዬ ቢሆንም፣ እኔ ግን ያላዳረስሁባት ሰዉ የለም፡፡

ጨርሼ፣ እንደ ቀዉስ ሆኜ ሰነበትሁ።

ቱናትን ከተገላገልሁ ዛሬ ኹለት ወር ስለ ሞላኝ ቱናትን ይዤ
ከሆስፒታል የምወጣበት ቀን መሆኑን ሰምቻለሁ ዛሬ፣ በጥልቀት
እንክብካቤ ይደረግላት ከነበረችበት ክፍል ወጥታ በእቅፌ ትገባለች ጡቶቼን አጉርሻት በእናት ስስት እያየኋት፣ እስከማጠባት ጓጉቻለሁ።በዚ ላያ ላይ የሆስፒታል ቆይታዬም ጉሮሮዬ ላይ ደርሷል፡ ከዚህ በላይ
እንደ እስረኛ በአንዲት ጠባብ ክፍል ተከልክዬ ለመሰንበት ቀርቶ
ለአንዲትም አዳር የሚበቃ ትዕግሥት የለኝም፡ ሙጥጥ ብሎ አልቋል።

“በሉ ልጄን አምጡልኛ፣ ልዉጣበት” አልኋት ነርሷን፣ መጥሪያዉን ደዉዬ እንደ መጣችልኝ፡

“ሂሳብ ክፍል ያለዉን ነገር ጨረስሽ? ከጨረስሽ መዉጣት ትችያለሽ''

ልክ ይኼን ብላኝ ስትጨርስና ባልቻ በሩን ከፍቶ ሲገባ አንድ ሆነ፡
ከሆስፒታሉ ያለብን ቀሪ ሂሳብ ቀድሞም ተነግሮን ስለነበር፣ ገንዘቡን ይዞልኝ መምጣቱ ነዉ፡ የሚከፈለዉን ከፍለን፣ የሚፈረመዉንም ሁሉ
ፈርመን ስናበቃ፣ ቱናት ኹለት ወር ሙሉ ጥልቅ እንክብካቤ ስታገኝበት ከነበረዉ ልዩ ክፍል በነጭ ፎጣ ተጠቅልላ መጣችልን፡፡ ያመጣችልንን
ነርስ ደህና አድርገን አመሰገንናት፡ ልጄን ተቀብዬ ላቅፋት እጄን ስዘረጋ ሁሉ፣ ቅር ብሏታል ነርሶች ግን ታድለዉ! ልበ ጥሩዋ ነርስ፣ ቱናትን የሰዉ ሰዉ ሳትል እንዴት እንደምትሳሳላት ሳይ እንደገና አመሰግንኋትአስከትላም ልናደርግላት የሚገባዉን ጥንቃቄ
አስረዳችን: ቱናት ራሷን ችላ ካካ ማድረግ ስለማትችል ትንሿን ጣታችንን እየተጠቀምን እንዴት ማጸዳዳት እንዳለብን አደራ አለችን በተጨማሪም ሌሎች ማስታወሻዎች በሥዕላዊ መንገድ የተገለጹበትን መጽሔት
ሰጠችንና፣ አስታቀፈችኝ፡፡
ልጄ ቱናትን ለመጀመሪያ አቀፍኋት፡

ከወለድኋት ከኹለት ረዣዥም ወራት በኋላ፣ ከቱናት ጋር ትንፋሽ
ለትንፋሽ ተገናኘን፡ ወደ ታች ተቀብሮ ግራና ቀኝ እንደ ነገሩ ከሚቃብዘዉ ዓይኗ እና ሲር ሲር ከሚለዉ የጭንቅ ትንፋሿ በቀር እንዲህ ነዉ የሚባል
እንቅስቃሴ የላትም፡ እግሯ አይላወስም፡ ጡቴን ዳብሳ ታገኘዋለች ብጠብቅም፣ አፏ ላይ አድርሼላት እንኳን ጎርሶ መጥባቱ አልሆንልሽ አላት፡ ዝም ብዬ ጭምጭም እያደረግሁ ሳምኋት
ትንፋሿን አሸተትሁት ደስ ይላል
“ወደ እመዋ ቤት አይደል?” አለኝ ባልቻ፣ መኪናዉ ዉስጥ እንደ ገባን የወንበሩን ቀበቶ በትካሻዉ ላይ እያዋለ፡፡ ቁልፉን ወደ ቀኝ ጠምዝዞ ሞተሩን አስነሳና፣ በፊተኛዉ መስታዎት ወደ ኋላ እያየኝ መልሴን
ተጠባበቀ

“አይ እኔ እንኳን ቤቴ ነበር መሄድ የፈለግሁት” አልሁት፣ ሲራክ ፯ ወደ ተከራየልኝ ምስጢራዊዋ የግሌ ቤት ለመሄድ በመምረጥ፡ “ለእመዋም ተጨማሪ ጫና ከምሆንባት፣ ፈተናዬ ራሴ ብወጣዉ ነበር የሚሻለኝ።
እሷን ለማሳመን የሚሆነዉን ምክንያት ግን ከየት ልዉለደዉ?”

“አለማፈርሽ!” አለ፣ ባልቻ “ሆ!”

“የአራስ ወጉ እዳይቀርብኝ ብለህ ነዉ?”

“ኧረ ተዪ አቺ! እናቷን አስቀምጣ ለብቻዬ ካልታረስሁ ያለችዋ
የመጀመሪያዋ እናት ልትሆኚነዉ እንዴ? ሆ! በይ ተይ፤ ዕድልሽንማ
አትቀልጅበት!''

“በል እሺ እንሂድ”

“ወደ እመዋ ቤት?”

“ይሁን”

ወደ እመዋ ቤት ሄድን፡፡ ልክ ከግቢዋ በር ስንደርስ በሕልሜም በዉኔም ያለልጠበቅሁት እልልታ መንደሩን አቀለጠዉ፡ መነሻዉን ለማወቅ ዞር ዞር ስል ያደገደጉ ቆንጆዎች እና ጎበዞች እርጥብ ጨፌ እየጎዘጎዙ ተቀበሉን፡፡ በአቀባበሉ እየተደነቅሁ ወደ ዉስጥ ብቅ ስል፣ የእመዋ ግቢ
ጭራሽ የጥምቀት አደባባይ መስሏል: ከግቢዉ ጫፍ እስከ ጫፍ የሚደርስ ዳስ ተጥሎበት፣ የንፋስ ማለፊያ እስኪጠፋ ድረስ በሰዉ ጢቅ ብሏል፡ ያልመጣ የአዲስ አበባ ሰዉ መኖሩን ሁሉ እንጃ፡፡ የእመዋ ጎረቤቶች፣ በቀጥታ እኔን የሚተዋወዉቁኝ፣ በባልቻ በኩል የሚያዉቁኝ፣
የእሸቴ ዘመዶች፣ በእህቶቼ በኩል የሚያዉቁኝ ሁሉም እዚህ አሉ፡
የንስሐ አባቴን ጨምሮ፣ በዛ ያሉ ካህናት ሁሉ ተገኝተዋል። ከሁሉም
ከሁሉም በላይ የገረመኝ ግን የተጣላኋት አዋላጅ ሐኪሜን፣ ሸዊትን እዚህ ማግኘቴ ነዉ፡ ተጣልቻት ንግግርም ከልክያት እንዳልነበር፣ ሚያሸንፍ ፈገግታዋ እንደዚህ ስታየኝ ግን አልቻልሁም: እኔም ፈገግ አልሁላት ወደ ዉስጥ በዘለቅሁ ቁጥር፣ ልክ ለንግሥ የወጣ ታቦት በአጠገባቸዉ የሚያልፍ ይመስል፣ጎንበስ ቀና እያሉ እልልታዉን አደበላለቁት “እንኳን ማርያም ማረችሽ” የሚል ምርቃት እንደ ጉድ ተዥጎደጎደ፡ እንደ ታቦትም፣ እንደ ሙሽራም፣ እንደ አራስም ነዉ የተከበርሁ፡ እመዋ በተለይ፣ አይቼባት የማላዉቀዉ ዓይነት ደስታ
ፈልቆባታል ልክ እንደ ልጅ አድርጓታል፡

ቱናትን ስታቅፋትማ ደስታ የሚያደርጋትን ነዉ ያሳጣት፡ ያዉም እኮ እንደ ተሸፋፈነች አቀፈቻት እንጂ ገና ገልጣ እንኳን አላየቻትም እንቅልፍ ወስዷት ስለነበር፣ ፀሐይም ላይ ላለመግለጥ ብላ እንደ
ተሸፋፈነች ከልቧ አጠገብ ደረቷ ላይ ልጥፍ አደረገቻት እና እኔን ወደ ዋናዉ ቤት ጎተተችኝ፡፡

ደስታ በደስታ ሆናለች ፍልቅልቅ ብላለች

“እመዋ”

“አቤት የኔ ልጅ”

“ምንድነዉ ጉዱ?”

“የምን ጉድ? ደስታ ነዉ ጂ! ሰርግሽም አይደል?''

“እ?” አልኋት፣ ከተናገረችዉ ያልስማሁት ቃል ያለ ይመስል
“ዓለሜን አሳየሽኝ ልጄ: ድሮዉንም ቢሆን ከአባትሽ ጋ እንጨቃጨቅ
የነበረዉ በአንቺ የሕይወት መንገድ የተነሳ አልነበር? እኔ ወትሮዉንም ዓለምሽን ማየት ነበር ምኞቴ: ይኼዉ ደራርበሽ አሳየሽኝ። ክብር አለበስሽኝ። ደግ አደረግሽ የኔ ልጅ! እልልልልል!”
ደስታዋ መረጋጋቷን ነጥቋታል: እያቻኮለች ወደ ዋናዉ ቤት አስከትላኝ ገብታ፣ ቱናትን ልታስተኛልኝ ክፍት ካሉት መኝታ ክፍሎች ያደረሳትን
መረጠች: እንዳደረሳት የመረጠችዉ ክፍል ግን የጃሪም መሆኑ የኔን ያህል ቀርቶ ምንም ያሰጋት አልመሰለኝም: በእርግጥ ይኼኛዉ ክፍል ለሳሎኑ ቅርብ በመሆኑ ቱናትን አስተኝቻት ብወጣ እንኳን ቶሎ ቶሎ እየመጣሁና እየሄድሁ በደህና መተኛቷን ለማየት ያመቸኛል: ችግሩ ግን
የጃሪም ክፍል ነዉ፡ ይኼን ጭንቄን ያላወቀችልኝ እመዋ፣ ዝም ብላ ቱናትን በጥንቃቄ አስተኛችልኝ፡ ከዚያ ቀዝቀዝ የምትልበት ትንሽ አፍታ
ከታገሰቻት በኋላ፣ ገለጥ አድርጋ አየቻት፡ እንደገና ሳመቻትና በንጹሕ
አዲስ ጋቢ ጥቅልል አድርጋ መልሳ አስተኛቻት፡፡ ቅሬታዬን እንኳን ለመግለጽ ፋታ ሳትሰጠኝ፣ ወዲያዉኑ እጄን ይዛ እንግዶች ወደ ሞሉት ዳስ ጎተተችኝ፡፡

“አንዴ? ልጄን ትቼ!?”

“ተኝታ የለ፤ ምንም አትሆንም”

“ብቻዋን?”
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ


#በታደለ_አያሌው


ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያለሁበት ክፍል ተንኳኳ።

“ጎሽ! ደረስሽልኝ ሸዊት?” አልሁ፣ እንባ ሲጠምቁ የቆዩ ዓይኖቼን በቱናት ጋቢ እያደራረቅሁ። ቱናት ደክሟት ይሁን እንጃ፣ ብቻ እየሰለለ መጥቶ የነበረዉ ለቅሶዋን ጨርሳ ትታዋለች: እንዲያዉም ያንን ሲር የሚል ትንፋሿን እንደገና መስማት ጀምሬያለሁ፡ ቢሆንም ግን
አላመንኋትም እነዚያ ቁልቁል ሰርገዉ እንደ ነገሩ ግራ ቀኝ የሚባክኑት
ዓይኖቿን ድንገት የምትከደንብኝ መሰለኝ፡፡ ይቺኑ ትንፋሿንም የማጣት መሰለኝ፡ ፍርሃት ፍርሃት ብሎኛል።

እሷን እሷን እያየሁ የጎድን ሄጄ፣ የበሩን ቁልፍ ጠምዝዤ ከፈትሁት

“አገኘሽ? አመጣሽልኝ?” አልሁ ቀና ብዬ እንኳን ሳላይ፣ መልሼ ጣቶቼን የቱናት ልብ ላይ እያስቀመጥሁ የልብ ምቷ አንጻራዊ መሻሻል እንዳለዉ ሳዉቅ፣ ተመስገን› ብዬ ሙሉ ቀልቤን ወደ ሸዊት ሳዞር
አጣኋት: እሷን በጠብቅሁበት ቦታ፣ ጃሪም ድፍርስ ዓይኑን ልጄ ላይ ተክሎ ቆሞበታል ለካ ለእሱ ነዉ በሩን የከፈትሁለት?

“የልጅሽ አባት…” አለኝ፣ ዓይኖቹን ከቱናት ላይ ሳይነቅል።

ደንግጫለሁ። ደረቅ ሊሾ ላይ እንደ ወደቀ ሸክላ ነዉ ድቅቅ ያልሁት።

እዚህ መሆኔን እንዴት አወቀ? ምን ቀረዉና መጣ ደግሞ? ምን ሊያደርገኝ? ልጄን ሊገድልብኝ? እንዲያዉም ፍርሃት ላይ ነበርሁ፣ ጨረሰኝ: በዓይኑ እና በቱናት መካከል ቆሜ አንዴ እሱን፣ አንዴ ደግሞ
ቱናትን በማየት ተወጠርሁ ከአሁን አሁን እጁን አነሳባት እያልሁ፣
ለመከላከል እንደ ምንም ጡንቻዎቼን አነቃቅቻለሁ።
“የልጅሽ አባት ግን ማነዉ? ማነዉ ያ ደብተራ ሰዉዬ፣ ባልቻ ነዉ ማን
የምትዪዉ ?»
መልስ አልሰጠሁትም አሁን እዉነት ባልቻ ጠፍቶት ነዉ "ያ" ብሎ የማያዉቀዉ የሚመስለዉ? ካላወቀም ሲራክ ፯ን እና ባልቻ የሲራክ፯ ዋና ኃላፊ መሆኑን አይወቅ እንጂ፣ ቢያንስ በአነጋጋሪ ድርሰቶቹ የተነሳ ባልቻን የማያዉቅ ሐበሻ የለም አለማድነቅ ሌላ፣ አለማወቅ ግን ሌላ ዉሸት፡

“ከእሱ ነዉ የወለድሻት ኣ? ብቻ ከማንም ዉለጃት፤ እሱ አይመለከተም ነበር ! ግ ን እሱ ሰዉዬ፣ ያለሁበት ድረስ ትናትና መጥቶ ሲመክረኝ ሲመክተኝ.” አለ፣ በማላገጥ በዙሪያዬ እየተንጎራደደብኝ፡ “ባይገርምሽ በንግግሩ ከመነካቴ የተነሳ፣ እራቴን እንኳ ን ሳልጠጣ ነዉ ያደርሁት
ብታይ። በጣም ነዉ የተሰማኝ"
ልጄን ለመከለል በእሱ እንቅስቃሴ ትይዩ እየተንቀሳቀስሁ፣ ስላቁን
አዳመጥሁለት “እናትሽ እናቴ አይደለችም, አልሁ እንጂ እናቴ አትወደኝም ያልሁት ይመስል፣ ‹እናትህ ትወድሃለች እያለ ሊሰብከኝ አማረዉ። ሱራሎ፣
እናትህ፣ አባትህ፣ ወደዚህ፣ ወደዚያ እያለ ሲዘበዝብብኝ አመሸ''
አለኝ፣ ስላቁን ለዘብ አድርጎ፡
“ትዝ አይልህም ግን?''
“ምኑ?”
“የሱራሎዉ ጊዜ ጎርፍ: ያ ጊዜ ረሳኸዉ? እመዋን ለማትረፍ ዘለህ የገባኸዉን? ሁላችንም የተሟሟትነዉ ? ''
ጀርባዉን ሰጥቶኝ ቆመ፡

“ረሳኸዉ?”

“አለማፈርሽ!” አለ የደም ሥሮቹ እየተገታተሩ። “አፍሽን ሞልተሽ
ሱራሎ ስትይ አለማፈርሽ! ቆይ ቀድሞ ነገር በምን ሆነና እናትሽ እናቴ አለመሆኗ ፣አንቺም እህቴ አለመሆሽ የተገለጠዉ? መቴ መሰለሽ? !! እ'
ከዚያ በኋላ እኮ ነዉ”

ዓይኖቼን በልጥጬ፣ አፍ አፉን አየሁ
“እንደዚያ ነፍሴን ለአደጋ ሰጥቼ ከዉሀ ሙላት ያተረፍኋት እናትሽ በቡናዉ እና በየእድሩ የምታወድሰዉ አንቺን ብቻ ሆነ። (ዉዷ ልጄ የምትለዉ፣ (መመኪያ የምትለዉ፣ (አተረፈችኝ የምትለዉ አንቺን ብቻ ነዉ። እኔስ? ሌሎቹስ? ጭራሽ በቦታዉ እንኳን የነበርን አታስመስይዉ
ነበር እኮ: አሁን ምን ተገኝቶ ነዉ ታዲያ፣ ሱራሎ ሱራሎ አልሽኝ በይ? እ!?”

“ኧረ እኔ የተለየ አፍ ኖሮኝ አያዉቅም: ሱራሎ አስቤ አንተ ረስቹ
አላዉቅም: የሱራሎን ነገር ለሰዉ ስነግርም፣ በዚያ ጊዜ ወንድሞቼ እና
እህቶቼ የፈጸማችሁትን ሁሉ በጭራሽ ረስቼዉ አላዉቅም”

“ተዪ እንጂi” አለኝ፣ ቢያሳየኝ ቢያሳየኝ የማያልቅበትን የሽሙጥ ሳቁን
መልሶ እያመጣብኝ፡፡ “እሱን ተዪዉና፣ ባልቻ ተብዮሽ፣ ምን ብሎ እንደ
ጠየቀኝ ነገረሽ? ‹ቤተሰብህን ለምን ማፍረስ ፈለግU? ብሎኝ አረፈዋ!
እንዴት ነርቬን እንደ ነካኝi” አለኝ፣ ወዲያ ወዲህ መንጎራደዱን ትቶ ፍጭጭ ያለ ሳቅ እየሳቀብኝ፡ “ግን እኮ እዴት እኔ ማፍረስ እችላለሁ? ነዉ ወይስ መጀመሪያዉኑም፣ ቤተሰባችን የዉሸት ቤተሰብ ነበር?”

“የዉሸት?” አልሁት፣ አላስችል ቢለኝ በቆየሁ ቁጥር ለእሱ የነበረ ፍርሃት ለቀቅ እያደረገኝ መጥቷል። ልጄ ግን በረኀብ እንዳትሞትብኝ አሁንም እፈራላታለሁ

“እህስ!”

“እንዴት ነዉ የዉሸት?''

“ሌላዉ ይቅር እሺ። ግን… ኹለት ልጆች፣ መንታ ሳይሆኑ ግን ደግሞ ከአንድ እናት ተወልደዉ ዕድሜያቸዉ እኩል መሆኑ አይደንቅም ነዉ የምትዪኝ? ''

“እንዴት?” እንዴት አልሁኝ፣ እዉነትም አሁን አሁን ስናድግ እየተዉነዉ መጣን እንጂ፣ የእኔና የእሱ ልደት ይከበርልን የነበረዉ በአንድ ቀን መሆኑ ትዝ ብሎኝ፡፡

“ኅዳር 14 አይደል?”

“ልደታችን?”

“እ”

“አዎ” አልሁት፣ ምን እየጠቀለለብኝ እንደሆነ እንኳን ሳይገባኝ።

“እና ኹለታችንም ኅዳር 14 ተወልደን ነዉ የምትዪኝ?''

“ሌላ ምን ይሆናል?”

“መንታ ነን እንዴ ? ''

“አይ፣ እንደዚያ እንኳን አይመስለኝም”
“እሺ በተለያየ ዓመት ግን በአንድ ዓይነት ቀን ተወልደን ነዉ?”

“እንደሱም አይመስለኝም” አልሁት፣ በዕድሜ እንደማንበላለጥ
አስታዉሼ፡ የኹለታችንም ዕድሜ እኩል ከሆነ በተለያየ ዓመት ልንወለድ
አንችልም።

“አየሽ ጅልነታችሁን? ስትሸዉዱ እንኳን ብልሃቱን እታዉቁበትም: ኅዳር
14፣ አባትሽ አባቴን በመተት ገድሎ ርስቱን የቀማበት ቀን ነዉ። እንደዚህ
ነዉ የተሳለቃችሁብኝ! የእኔ የሐዘን ቀን ለእናንተ በዓል ነዉ! በእናቴ ቤት
ነዉ እናትሽ እንኳን እናት የመሰለችዉ!”

“ኧረ በማርያም! በማርያም ተዉ። እንዴት እዴት ነዉ የምታወራዉ?”

“ገብቶሻል። ግጥም አድርጎ ገብቶሻል”

“አንዴ” ሳቄን መያዝ አልቻልሁም: ለቀቅሁት። “ቆይ ምኑ ነዉ
የሚገባኝ? ''

እሱ ግን ብልጭ አለበት፡ እንደ ምንም ለመረጋጋት ወደ ግድግዳዉ ዞሮ
ከቆየ በኋላ፣ በዚያ ድፍርስ ዓይኑ መልሶ ጥብስቅ አድርጎ ያዘኝ፡፡ ያዉም
በኃይል እስከሚያመኝ ድረስ!
“ሲራክ ማነዉ?” አለኝ፣ ከዓይኑ ማምለጫ እየፈለግሁ ሳለ፡ እርፍ! ጭራሽ ሲራክ ፯ን ያዉቀዋል? መንግሥት እንኳን እስካሁን ያልደረሰበትን ሲራክ ፯ን ጃሪም ያዉቀወዋል? የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት
አገልግሎት እኮ ማኅበራችንን በፖለቲካ ከመጠርጠር ባለፈ፣ እስከዚህ
አያዉቀዉም: ተአምር ነዉ!

“ሲራክ ምንድነዉ?” አለኝ፣ የባሰ ፍጥጥ ብሎ

“እ?”

“አቺና እናትሽ እዚያ ምን ትሠራላችሁ?”
ትንሽ ተንተባተብሁ፡ ሙልጭ አድርጌ መካድ ቢኖርብኝም፣ አልቻልሁም: አመነታሁ። ነገር ግን መላወሻ የሚባል አልሰጠኝም።

ስለዚህ የታየኝ አማራጭ እዉነቱን ማፍረጥረጥ ብቻ ነዉ፡ በእርግጥ
በሲራክ ፯ ሥነ ምግባር መሠረት፣ ቁጥር አንድ የሚባለዉ ወንጀል፣
አሁን እኔ ቀጥዬ የማደርገዉ ድርጊት ነዉ፡፡ እንደ ሕጋችንማ፣ ከቅርብ ኃላፊዬ ግልጽ ይሁንታ ካልተሰጠኝ በቀር፣ ማንም ቢያስፈራራኝም ሆነ
ቢያዉጣጣኝ፣ እንኳንስ በማኅበራችን ሥር ስላለዉ ሲራክ፯ ህልዉና ይቅርና፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱሱ መጽሐፈ ሲራክ ቢሆንም ማዉራት አልችልም፡ ይኼ በማንኛዉም አባል የሚጠበቅ ሕግ ነዉ

አሁን ግን ይኼን ሕግ በመተላለፌ የጃሪምን ልብ የማለሰልሰዉ
ስለመሰለኝ፣ ልሽረዉ ነዉ፡
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በታደለ_አያሌው


...ብችል ሀገር፣ ካልቻልሁ ግን ከተማ መለወጥ እንዳለብኝ ወስኜ ልጄን ጠቅልያለሁ ዓይኔን ጨፍኜ ስለ መጥፊያ አማራጮቼ ሳስብ ቆየሁና፣ ልጄን አቅፌ ቀና ስል በሰዉ ተከብቢያለሁ፡ እየቆየ ትንፋሽ እስከሚያጥረኝ ድረስ በዳስ የነበረዉ እድምተኛ ሁሉ እየመጣ ተኮደኮደ፡ ሁሉም
የቅድሙን የጃሪምን ሁኔታ ተመልክቷልና፣ አንድ አንድ እያለ መጥቶ መኝታ ክፍሉን እጭቅ ብሎበታል፡ የጃሪም መኝታ ክፍል ከሳሎኑ ጋር አንድ ግድግዳ የሚጋራ እና በሩም ሰፋ ያለ በመሆኑም ፣ ከዉስጥ የተረፈዉ
ሰዉ በዋናዉ ሳሎን ሆኖ ትከሻ ለትከሻ እየተጋፋ በበራፉ በኩል ቱናትን በዓይኑ ይወጋል። ያሽሟጥጣል፡ ከሩቅም ከቅርብም፣ ሹክሹክታ
ይሰማኛል፡

“እንዲህ ናት እዴ ለካ?” አለች አንደኛዋ በለሆሳስ፣ ግን ደግሞ
እንዲሰማኝ አድርጋ
“ጭንቅላቷ ደግሞ ምንድነዉ የሚ ያህለዉ?” ስትል ተቀበለቻት ሌላኛዋ፣ ገንፎ ያላመጠችበት ጥርሷን ለሳቅ እያገጠጠችዉ፡፡
“ገዳም ቅብጥርሴ ይላሉ እንዴ ቄሱ ደግሞ? ሆ! ሲጀመር ልክስክስነቷ መስሎኝ እዲንህ ያለ ልጅ ያስታቀፋት! መኝታዋን እንኳን በወጉ ለማድረግ ያላስቻላትን፣ እንዴት ብላ ነዉ ለገዳም ማዕረግ ትበቃለች ብለዉ የጠበቋት?”

“ጉድ እኮ ነዉ! ኧረ የሕጻኗን ዓይን ተመለከቺልኝ: እንዴት ነዉ ደግሞ
የምታቃስተዉ በናትሽ? አይ ይቺ ልጅማ አትተርፍም። ምናለች በዪኝ
ኋላ፤ የሳምንት ዕድሜ እንኳን አይኖራትም”

“የልጇ አባት ግን የትኛዉ ነዉ፤ ያ ከጎኗ ተቀምጦ የነበረዉ ጅላጅል ነዉ እዳትዪኝ ብቻ

ነዉ እንጂ እሸቴ ይባላል አሉ: ከሴተኛ አዳሪ ጭን አይጠፋም ሲሉ ሰምቻለሁ”

“ሂጅ ሂጅ ሂጅ… በስመ አብ!”

“ይቺን የመሰለች ልጅ ወስዶ እዚያ ምን እንደጣላት ላምን አልችልም
መቼም”

“አንቺ ደግሞ፣ሙሉ አድርጎ የፈጠረዉ ሰዉ አለ ብለሽ ነዉ? እንጂ እሷንም አታያትም? እኔ ነኝ የምትል ቆንጆ ደፍራ በዉብርስት አጠገብ ታልፋለች? ቆንጆ የሚለዉ ቃል እኮ አይበቃትም: ታዲያ ምን ዋጋ አለዉ? በአልጋ ሲለምኗት አፈር ሆና አረፈቺዋ! የቆንጆ ልክስክስ እሷን አየን”

“እግዚአብሔር ሲጣላ ደግሞ እንዴት እንደሚቀጣ አየሽልኝ አይደል?”

“አመንሽ? ባለፈዉ ለጃሪም እህቱ አይደለችም ስልሽ፣ እንዲያ
ስትሟገችኝ አልነበር? ይኼዉ ዛሬ ከራሱ አፍ ሰምተሽ እንኳን ለአፍ
እላፊሽ እፈሪ ተዋርደሻል''

“ኧረ እሱስ ደገቆኛል: እህቱ አይደለችም ማለት ነዉ በቃ?”
“እሷ ብቻ ናት ወንድሜ ስትለዉ የምትሰማዉ እንጂ፣ የእሷ እህትነት ከእሱ አፍ ተሰምቶ አይታወቅም ነዉ የሚባለዉ። እንዲያዉም ይኼ ግቢ
ከነቤቱ የእናት የአባቱ ነዉ አሉ እኮ: ከእነእናቷ አስወጣታለሁ እያለ ሲዝት የሰሙት ሰዎች ናቸዉ የነገሩኝ በእናትም በአባትም አይገናኙም አሉ

አሮጊቷ ራሱ በገዛ ርስቱ ላይ ተደላድላ ለመኖር ስትል እናት መሰለች እንጂ፣ የእናትነት ምልክቱ የላትም”

“ አንዴ... በየከተማዉ በየገጠሩ ሲንከራተቱ ኖረዉ ቅርብ ጊዜ
አደለም እንዴ ወደዚህ የመጡት?''

“እኮ! ድንገት ዱብ ብለዉ ነዉ አሉ አሁን ባለቤት የመሰሉት''

“እኔ አሁንም ላምን አልቻልሁም:: ጭራሽ አሮጊቷ የጃሪም እናት
አይደለችም ማለት ነዉ?''

“እየነገርሁሽ!”

“ይገርማል”

“የእሱ ይገርምሻል እንዴ አንቺ? ዝማምን ታዉቂያት የለ?''
“ዝማም ዝማም… ዝማም የዚችን እህት ማለትሽ ነዉ ወይስ ሌላ?”
“ወይ እህት እቴ: እኔማ ገና ትናንት አይደል እንዴ የምሰማዉ ?

“ምኑን? ”

“እህቷ አይደለችም''

“እርፍ! እሷም?”

“አይደለችም”

አንድ አንድ ብሎ እየገባ ቤቱን ጥቅጥቅ ብሎበት የነበረዉ እንግዳ ሁሉ፣ የቻለዉን ያህል ልጄን ተጠቋቁሞባት ሲበቃዉ፣ ቀስ በቀስ ስለ ወጣ በቤቱ
የቀረዉ ሰዉ ቀነሰ፡ ቀለል ማለቱን ተጠቅሜ ሐሜተኛ ሴቶቹን ዞሬ
በዓይኔ አጣበርኋቸዉ፡ ትኩር ብዬ ስመለከታቸዉ ልክ በድምፃቸዉ
እንደ ጠረጠርሁት እነዚያዉ ተናግሮ አናጋሪዎች ናቸዉ፡ ከአራት ወር በፊት፣ በታዕካ ነገሥት ገዳም ከእመዋ ጋር ቆይቼ ስወጣ መንገዴ ላይ ቆመዉ እህቱ ናት እህቱ አይደለችም እያሉ የተወራረዱብኝ ሴቶች ናቸዉ ምንም አላልኋቸዉም በዚያም ላይ፣ ልቤ ቆሟል ወዴት እንደምሄድ ባላዉቀዉም፣ ልጄን ይዤ ብን ብዬ ከመጥፋት ዉጪ ምንም ምርጫ አይታየኝም ጨክኛለሁ እንግዳዉ ከዳሱ እየተንጠባጠበ ወጥቶ ወጥቶ፣ ጥቂት ሰዎች ቀርተዉበታል፡ የመስኮቱን መጋረጃ በስሱ ገለጥ አድርጌ አሳልፌ ስቆጥር
እመዋ፣ ባልቻ፣ እሸቴ እና ጥቂት የቅርብ ዘመዶቻችን ብቻ ቅስማቸዉ ድቅቅ ብሎ ይታዩኛል፡ እርስ በእርስም አያወሩም: የደስታ ጫፍ እንቀምስበታለን ያሉት ቀን በብላሽ ቀርቶባቸዉ ከፍቷቸዋል፡ እኔ እርግጥ ወደምጠፋበት ለመጥፋት ከአሁን የተመቸ ጊዜ አላገኝም፡ ነገር ግን ጨቅላ ልጅ ይዤ በእግሬ ልሂድ ብል የት እደርሳለሁ? ያዉም ጨቅላዋ ቱናት ሆና፡ በዚያ ላይ፣ መጀመሪያ ወደ ምስጢራዊዋ ቤት ሄጄ
አንድ አንድ ነገሮችን መያዝ ይኖርብኛል ደግነቱ ዕድሜ ለሲራክ ፯ የብዙ ሀገራት ፓስፖርት በተለያየ ማንነት ወጥቶልኛል፡ ከሀገር መዉጣቴ ካልቀረ፣ ቢያንስ ፓስፖርቶቼን መያዝ አለብኝ ያለ ገንዘብም
የሚሆን ነገር የለም ዞሮ ዞሮ ወዲያ ወዲህ ማለቴ ላይቀር ነዉ።
እንደዚያ ከሆነ ደግሞ መኪናዬ የግድ ታስፈልገኛለች: አሁን የት
እንዳለች ግን አላዉቅም: ምክንያቱም ከነዳኋት ቆይቻለሁ፡ ሆስፒታል ከገባሁ ጀምሮ ታናሽ እህቴ እንድትጠቀምበት ፈቅጄላት እሷ ይዛት ስለሰነበተች፣ ምናልባትም ዳሱ ሲሠራ ቦታ እንዳታጣብብ ብላ፣ በጎረቤት
ግቢ ወይም የሆነ መንገድ ዳር አቁማት ይሆናል፡ በእርግጥ፣ የኔ ብቻ ሳይሆን የማንም መኪና በግቢዉ የለም።

የራሴን መኪና ማግኘቱ ቀላል አለመሆኑን እንዳወቅሁ፣ አልፎ አልፎ መኪና በማልይዘበት አጋጣሚ አገልግሎት የሚያደርግልኝን የታክሲ ደንበኛዬን ደዉዬ ጠራሁት። ወዲያዉኑ፣ ጥላዬን ጠብቄ በጀርባ በኩል
ወዳለችዋ ጠባብ የግቢያችን በር ሰተት አልሁ ሽሽት መሸነፍ መሆኑን ባዉቅም፣ ለልጄ ስል የትም ብሄድ አይገደኝም: ቢቻል ቢቻል ላሳክማት፣ ከሰዉ አፍ ላተርፋት ይገባል፡ ከዚህ በኋላ ማንም እንዲያይብኝ
አልፈልግም ማንም በልጄ ጤና እንዲሳለቅ አልፈቅድለትም።

እንዲያዉስ ገዳምሽ ናት ብለዉኝ የለ የንስሐ አባቴ? ታዲያ ወደ ገዳሜ መግባት አለብኛ! ልበል እንግዲህ ልጄ ዉስጥ ገብቼ ልመንኩስ፡፡
የሚጠበቅብኝን የአመክሮ ጊዜ እንደሆነ በሆስፒታል ቆይታዬ ተወጥቼዋለሁ

ምናልባት ቱናት፣ ከዝቋላ ወይ ከደብረ ሊባኖስ ገዳም የምትለየዉ የራሷ ትክለኛ ስለ ሌላት ብቻ ነዉ፡ ወፍጮም ሆነ እህል የሚገብርላት የለም
እንጂ፣ እሷም ሆነ ዝቋላ የእግዚአብሔር መኖሪያዎች እንደሆኑ ግን አልጠራጠርም ስለዚህ በከተማ የገደምኋትን ገዳም የሚቸግራት ነገር
እንዳይኖር ከፈለግሁ በከተማ ማገልገሉን እገደድበታለሁ
ከከተማም ደህና ሕክምና የምታገኝበት፣ ደህና ከተማ መምረጥ አለብኝ፡

አንዴ ከመነኮሱ በኋላ ደግሞ ዞሮ ማየት እንደ ሌለ አዉቃለሁ፡ አምሮቴ፣ ትዳሬ፣ ሥራዬ፣ ወዳጆቼ፣ ዘመዶቼ የሚሉትን ሁሉ መተዉ ቀዳሚዉ የገዳማዉያን ሕግ መሆኑን አዉቃለሁ ዞሮ አለማየት ፈታኝ ቢሆንም፣ የቀረዉ ይቀራል እንጂ ይኼኛዉን ሕግ ግን አልሽረዉም፡፡ በፍጹም!
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በታደለ_አያሌው


...መቼም ባልቻን በግልፍተኛነት የሚያማዉ አይገኝም የጃሪምን ግልምጫ ከምንም ሳይቆጥር ፈገግ ብሎ አሳለፈዉና፣ ወደኔ መጥቶ አቀፈኝ፡ እሱን
እዚህ መሆኔን እንዴት አወቀ አይሉትም፡ እኔም በችኮላ ተንከረፈፍሁ እንጂ የትም ብሄድ ከሲራክ ፯ ማምለጥ እንደማልችል ማስተዋል ነበረብኝ፡ እንኳንስ እንደዚህ ተንዘላዝዬለት ይቅርና! የንዝህላልነቱ ንዝህላልነት ደግሞ በገዛ ስልኬ ለሸዊት ስልክ መደወሌ፡ በዚህ ስሕተቴ
እንኳንስ የሲራክ ፯ቱ ባልቻ፣ የተናቀ የመንደር ደመኛ እንኳን ሊያገኘኝ ይችላል።

ባልቻ ከመግባቱ አፍታ ሳይቆዩ እሸቴ እና ሸዊት ተከታትለዉ ገቡ።

“አንቺ?” ስል ተቀበልኋት፣ ከእሸቴ ኋላ መጥታ ለሰላምታ ስታቅፈኝ፡
“እንዲያዉ እስካሁን እያለቀሰችም ቢሆን ገና አሁን ነው የምትደርሽልኝ ማለት ነዉ?” አልኋት፣ ለቂሜ መወጫ ጠበቅ አድርጌ እያቀፍኋት።
የአሁኑ መተቃቀፋችን ትርጉሙ የትየለሌ ነዉ: አንድም በሆስፒታል
ቆይታዬ ዓይንሽን ለአፈር ብያት የነበረዉን ኩርፊያ ጨርሼ ረሳሁላት፣አንድም ለቱናት አምጭልኝ ያልኋትን ወተት ያዉም የሚሆናትን መጠጫ ጡጦ ጭምር ስላመጣችልኝ አመሰገንኋት፣ አንድም ነባሩ
ሰላምታችን እንደዚህ ነዉ፡ እንደገና እቅፍ አድርጌ ጨመቅኋት።

"እ?"

“ኧረ እኔስ ወዲያዉ ነበር የደረስሁት”

“አዎ” አለ ባልቻ፣ ክንዱን ትከሻዋ ላይ እየጫነ፡ “ወተቱን ብቻ ይዛ
ስትመጣ አግኝቻት፣ እኔ ነኝ ጡጦም ጨምራችሁ አምጡ ብዬ ከእሸቴ ጋ መልሼ የላክኋቸዉ። መቼም ምን ዶክተር ብትሆን፣ በዕድሜ ታናሼ ስለሆነች፣ በዚህ ቅር የምትሰኝብኝ አይመስለኝም”

“ኧረ በጭራሽ!” አለች፣ ወተቱን እና የጡጦ እቃዉን እያቀበለችኝ:
“ኧረ ስሚኝማ ዉቤ” አለች፣ የመደነቅ ፊቷን እየገለጠችልኝ፡፡
“ምን”
“ወንድምሽን እኮ ሊፍቱ ጋ አግኝቼዉ አሁን''

“ማንን?” አልኋት ለወጉ፣ ማንን ማለቷ እንደሆነ ባላጣዉም፡፡

“ጀሪምን ነዋ”

“እሺ”

“ምን እሺ ትይኛለሽ? ሰላምታ ከልክሎኝ ሄደ እኮ”

“ኧረ?” አልኋት፣ ከእሽጉ ዉሃ ከፍቼ ወደ ጡጦዋ እየቀነስሁ ዉሃዉ መቼ እንደ ተቀመጠልኝ ግን አላወቅሁም: ከአጠገቡ ሶፍት፣ ፎጣ እና ሌሎች አልባሌ ነገሮችም መኖራቸዉን ሳይ ማረፊያ ክፍሉን ከመያዜ
በፊትም ተቀምጠዉ እንደነበር ገባኝ፡፡

“አይገርምሽም? መቼስ ረስቶሽ ነዉ አትዪኝም ጃሪም እኔን ሊረሳ? ጉድ እኮ ነዉ! ያኔ እንዲያ …” ብላ፣ ተገርማ ቀረች፡፡ እየቆየ እንደገና በኃይል ከነከናት፡ ምክንያቷን አላጣሁትም፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሳለን ለአንድ ዕረፍት እኛ ቤት በነበርንበት ጊዜ፣ ጃሪም ዓይን አብዝቶባት ነበር
እንዲያዉም ደጋግሞ ወድጃታለሁ እንዳለኝ አስታዉሳለሁ ስሜቱን በግልጽ ለእሷ እንደ ነገራት ግን አላውቅም፡ ከአሁኑ ሁኔታዋ
እንዳስተዋልሁት ከሆነ፣ መንገር ብቻም ሳይሆን እሞትልሻለሁ› ጭምር ሳይላት እንዳልቀረ ገመትሁ ያ ሁሉ ቀርቶ አሁን ግን እንደማያዉቃት ከሆነባት፣ ባይገርማት ነበር የሚገርመኝ፡ ያዉ፣ የእኔ ጓደኛ አይደለች?
በእሱ ቤት እኮ አሁን፣ የእኔ የሆነ እና እኔ የነካሁት ሁሉ ርኩስ
ሆኖበታል።

“አጀብ ነዉ አለ ጅብ? የሆነዉስ ይሁንና በምን ዝም አሰኘሻት?” አለች፣ ቱናትን ገለጥ እያደረገቻት፡ ከጀርባዋ አጥንት ላይ ላለዉ ቁስል ጥንቃቄ አድርጋላት፣ አቀፈቻት እና ልትቀመጥ ብትፈልግ መቀመጫ አጣች: ገና
ይኸኔ ነዉ የሆቴል ማረፊያ ክፍል ዉስጥ መሆኔ ራሱ ትዝ ያላት:
የጃሪምን ፊት መንሳት ማመን አቅቷት ዋናዉን ጥያቄዋን እንደ ረሳችዉ ልብ አደረገች፡፡

“ቆይ ቆይ፣ አንቺ ግን እዚህ ምን ትሠሪያለሽ? ከእመዋ ቤት ያዉም ያን ድግስ ጥለሽ? ያዉም ይቺን ጨቅላ ይዘሽ? ምን ልትሆኚ እዚህ መጣሽ በይ?”

ይኸዋ! እንደ ፈራሁት የማርያም መንገድ እንኳን ሳታስቀርልኝ ጥያቄዋን አመጣችዉ ያልሰማሁ መስዬ ዝም ልላት ፈልጌ ነበር፡ ነገር ግን እሷን ሽሽት ዓይኔን የጣልሁበት ባልቻም ከእሷ በላይ አፈጠጠብኝ፡፡ ለራሱ ጉዳይ
ቢሆን፣ ሽንቱ እንኳን የፈለገ ወጥሮ ቢይዘዉ የሲራክ ፯ ጉዳይ ፋታ
እንደማይሰጠዉ እያወቅሁ፣ ለእኔ ሲል ነዉ አትረፍርፎ የሚሰጠኝ። እኔ ግን እንደ ደመኛ ተደብቄዉ እዚህ ሲያገኘኝ ማዘን ይበቃዉ ይሆን? እንኳን ማኩረፍ ሌላም ቢያደርግ እዉነት አለዉ፡ ግን እሱ ነዉና ሰዉዬዉ፣ መተዉ ያዉቅበታል፡ ያም ቢሆን ግን ጥያቄዋን ተጋርቷታል።
እንድመልስላት ከእሷ እኩል እየተቁለጨለጨብኝ ሳለ እሸቴ በሩን ከፍቶ ገባ፡፡ መቼ እንደ ወጣ ግን አላየሁትም ነበር፡፡ ለካንስ እመዋ ደዉላለት፣ እሷን ለማነጋገር ወጥቶ ኖሯል።

“እመዋ ናት የደወለችልኝ። (ልምጣ ወይ እያለች ነዉ፣ ትምጣ እንዴ?" አለ፣ ሳይታወቀዉ በሸዊትና
በባልቻ ከተፋጠጥሁበት ጥያቄ
ሲያስመልጠኝ፡ ባልቻ ቅር እንዳለዉም ቢሆን ቸለል አለልኝ፡ ሸዊትም እንዲሁ ቱናትን እንዳቀፈቻት ከአልጋዉ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ወተቱን ለማጥባት ሞከረች::

“እናንተ?” አለች፣ ወተቱን ልታጠጣት ሞክራ ሞክራ እንዳልሆነላት ስታዉቅ ተስፋ እየቆረጠች። “ቱናት የተለየ ልምምድ ሳያስፈልጋት
አይቀርም: ከተወለደች አንስቶ ኹለቱን ወር ሙሉ የከረመችዉ ግሉኮስ ተተክሎላት ስለነበር፣ ከጡትም ሆነ ከጡጦ ምግብ ስትሞክር ይኼ የመጀመሪያዋ ነዉ። ስለዚህ፣ እንደኔ እንደኔ አሁኑኑ ወደ ሆስፒታል ተመልሳ መግባት ያለባት ይመስለኛል” አለች፣ እኔ ደግሞ እንድሞክራት
እያቀበለችን፡ “ለጊዜዉ ጉሉኮሱም ቢሆን ማግኘት አለባት” አታዩትም
አተነፋፈሷንስ? የባሰ ሲር ሲር እያለ እኮ ነዉ። ለመሆኑ የቀጣይ
ሕክምናዋን ጉዳይ አማክራ ችሁበታል ወይ?”

“ማንን፣ ይኼዉ አንቺ አለሽል አይደል? አንቺዉ ምከሪን እጂ” አለ ባልቻ፣ እኔም እንደዚሁ ልላት ስል ቀድሞኝ፡፡

ይኼ ሙያዬ አይደለም: ስለዚህ እኔ በቅጡ ከምፈተፍት፣ ጉዳዩን ይሁነኝ ብለዉ የተማሩት
ባለሙያዎች ስላሉ ወደ እነሱ መሄድ ይኖርብናል”

«የት ናቸዉ እነሱ ታዲያ?”

“ምን እሱማ ባላውቃቸውስ በአብዛኛዉ ሆስፒታሎች አይጠፉም ነበር:: ግን የመሣሪያዎች ዉስንነት አለ: ለጊዜዉ ሕክምናዉ በኹለት
ሆስፒታሎች ብቻ እንደሚገኝ ነዉ የማዉቀዉ”

“በስመ አብ!” አለ ባልቻ፡ “ወረፋዉ አያድርስ ነዉ በይኛ''

“በጣም!”

ከመንግሥት ሆስፒታሎች መካከል ይኼን ሕመም ጉዳዬ ብሎ በብቸኝነት ሕክምና ወደሚሰጠዉ ዘዉዲቱ ሆስፒታል ሄድን፡፡ አቤት ወረፋዉ! ያሉት
አልጋዎች ዉስን ናቸዉ፤ ተመዝግቦ ተራዉን የሚጠባበቀዉ ግን የትየለሌ! እንዲያዉም የኋላ ኋላ እንደ ሰማነዉ ከሆነስ፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ብቻ ከሃያ ሺ የሚበልጡ ሕጻናት የቱናት ዓይነት እክል ያጋጥማቸዋል አሉ፡ ቁጥሩን አሰብሁት ስንት የሚወራላቸዉ
ወረርሽኞችም እኮ ከዚህ የከፉ አይደሉም

የቱናንት ሁኔታ አጣዳፊ መሆኑን ልናስረዳ ብንልም፣ የሚሰማን
አላገኘንም: አብዛኛዉ እዚህ የመጣዉ ሰዉ ሁሉ ቱናት ካለችበት የሚተናነስ አለመሆኑን አምነን ተቀበልን፡፡ ሆኖም ሕክምናዉን በተመለከተ እስከሚወሰንልን ድረስ፣ ባይሆን በረኀብ እንዳትሞትብን በሚል ግሉኮስ ተፈቅዶልን አንድ ጥግ ላይ ተተከለላት:: በረንዳ ላይ:
መኝታ ክፍልማ የሚታሰብም አይደለም፡

“በቃ እናንተ ሂዱ እጂ” አልኋቸዉ፣ ለግማሽ ሰዓት ያህል እንደዚሁ
እንደ ቆየን፡፡ እሳቱ የማይበርድ ችግር እየተጠባበቃቸዉ ሳለ፣ የሦስቱም እዚህ መቀመጥ ከቱናት ሕክምና ባልተናነሰ አሳስቦኛል ሸዊትም ፋታ የለሽ ሐኪም ናት፣ ባልቻም ባልቻ ነዉ፣ እሸቴም ያዉ ነዉ፡፡ “ሂዱ አረ! ሂዱ” አልሁኝ፣ እንደማግባባትም እንደማጣደፍም እያደረግሁ::
“መጨረሻዉን ሳንሰማ?” አለ ባልቻ፣ ስልክ ስልኩን ሲያይ እንዳልነበር ሁሉ፡
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_ሦስት


#በታደለ_አያሌው


...በእኩል ሰሞን ኹለት ተቃራኒ የሚመስሉ ጥቅሶች ሰማሁ አንደኛዉ:-

“ተስፋ የሚባል ተሟጦ ተሟጦ፣ ጭልጥ ብሎ አልቋል:
እንጥፍጣፊዉ እንኳን በማንም እጅ ላይ የለም፡ አሁን ማንም
ላይ መንጠልጠል አንችልም:: የራሳችንን ተስፋ ግን ራሳችን
እንዳንፈጥር የሚከለክለን የለም!” ሲለኝ

ሌላኛዉ ደግሞ፡-
“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን
ያድሳሉ፧ እንደ ንሥር በክንፍ ይወጣሉ፡ ይሮጣሉ፣አይታክቱም: ይኼዳሉ፣ አይደክሙም” ይላል

ኹለቱም ስለ ተስፋ ናቸዉ፡፡ ለኹለቱም ምንጭ ተጠቅሶልኛል ኹለቱንም የነገሩኝ ሰዎች ለእኔ ከማሰብ እንደ ነገሩኝ አዉቃለሁ የመጀመሪያዉን በቅጡ የማዉቃቸዉ ዘመናዊ የሥነ ልቡና ባለሙያ፣ ኹለተኛዉን ደግሞ
በቅጡ የሚያዉቁኝ የንስሐ አባቴ ናቸዉ የነገሩኝ፡ የመጀመሪያዉ
እምነቱንም ሥራዉንም ያንቺ ጉዳይ ነዉ ሲሉኝ፤ ኹለተኛዉ ደግሞ ማመኑ ያንቺ፣ ሥራዉ ግን የእግዚአብሔር ነዉ ብለዉኛል፡

ሕይወት ደግሞ የምርጫ ወንበር ናት አሉ᎓ ታዲያ እኔ የቱን ልምረጥ?
የቱን ነዉ መምረጥ ያለብኝ?

እህቶቼ እና ወንድሞቼ እንደ ዋዛ ጀምረዉ፣ አንድ በአንድ ሸርተት እያሉ ጥለዉኝ ጥለዉኝ፣ አሁን አፉን ሞልቶ እህቴ ነሽ የሚለኝ ጠፍቷል።

እንዲያዉ ምናልባት ቆርጠዉ ያልቆረጡ ቢኖሩም እንኳን፣ ጨክነዉ እህታችን አይደለሽም አይሉኝ እንደሆነ እንጂ፣ እንደ ወትሮዉ ግን በእርግጠኝነት ‹እህታችን ነሽ አይሉኝም: እኔን ከመጥላታቸዉ የተነሳ
እህ ብላ የወለደቻቸዉን እመዋን ሳይቀር የዉብርስት እናት› እስከ ማለት ደርሰዋል የጃሪምስ እንዲያዉም አይወራም:

ይኼ ሁሉ ለሆነብኝ ለእኔ፣ ልጄ ባትኖርልኝ ኖሮ፣ ይኸኔ ሟች ነበርሁ። አፈር ገብቼ ነበር።

በስንት ዉጣ ዉረድ ቢሆንም፣ ልጄ ቱናት የመጀመሪያ ሕክምናዋን አግኝታልኛለች:: ጭንቅላቷ ላይ የሚመነጨዉ የዉሃ ክምችት እና ጥቅም
ላይ የሚዉለዉ ዉሃ
እንዲመጣጠን የሚያደርግ ቀዶ ሕክምና ተደርጎላታል በእርግጥ ሕክምናዉ እንኳንስ የእኔን የእናቷን አንጀት፣ ደመኛዬ ነሽ የሚለኝን ጃሪምን ሳይቀር አንሰፍስፋዋለች አሉ ያቺን ከደም የቀዘቀዘች እርጥብ ገላዋን ተቀዳ፣ ጀርባዋ ላይ ለነበረዉ የአጥንት ክፍተት
ጉዳቷ ሕክምና ተደርጎላታል፡ ይኼም አይብቃሽ ብሏት፣ ከላይ
ከጭንቅላቷ እና ዝቅ ብሎ ደግሞ ሆዷ ላይ ቀዳደዉ ነበር ማስተንፈሻ ቱቦዉን (shunt) የቀበሩላት።

አቤት መቻሏ!

እንደ'ኔ ፍራቻ ሳይሆን እንደ እሷ ብርቱነት፣ በትንሽ በትልቁ ሞተችብኝ እያልሁ ሥርበተበት ቱናት ናትና ልጅቷ፣ ሁሉንም ቻለችዉ፡ ችላ አሳለፈችዉ፡ እንደ ቱናት ቻይ አለ ወይ በምድር? እኔ አላዉቅም።

“አልሄድሽም እንዴ እመዋ?” አልሁ፣ ከልጄ ጋር ብቻ ዘግቼ
የተቀመጥሁበትን ክፍል በር ድንገት ያንኳኳችብኝ እመዋ መስላኝ ሌላ ሰዉ መሆኑን ያወቅሁት ድምፁን ስሰማ ነዉ፡፡

“ሰላም አደርሽ ዉብርስት?''

“እግዚአብሔር ይመስገን ማነዉ?” አልሁ፣ በሩን ለመክፈት
እያቅማማሁ አቅማምቼ አቅማምቼ ስከፍተዉ፣ አንድ ወጣት ከደጅ ቆሞ አገኘሁት ቁመናዉ ልጅ እግር ቢሆንም፣ አንተ ብሎ ማቅለሉ
አልመጣልኝም የእመዋን ቤት በረሃ፣ ልጄ ቱናትን ደግሞ ገዳም አድርጌ እሷ ዉስጥ ከመነንሁ ወዲህ፣ የመነኮሳቱ ባህል እና ሥርዓት እያደረብኝ መጥቷል፡ ማልዬለታለሁ አነጋገሬን፣ አመጋገቤን፣ ጸሎቴን፣ አጠቃላይ
ሥነ ሥርዓቴን እና ለዓለም ያለኝን ርቀት እንደ መነኮሳት ለማድረግ
ልምምድ ላይ ነኝ የማነባቸዉ መጻሕፍት ሁሉ የምንኩስናን ሕይወት የሚያወሱ እንዲሆኑ እመርጣለሁ፡ ከዚህ ሌላ፣ ማንኛዉም ወደ ዓለም የሚስብ ነገር ላይ ድርሽ ማለቱን ትቼዋለሁ፡ ፈታኙን የቱናትን የሕክምና
ጣጣ ጨርሼ እመዋ ቤት ባለኝ ክፍል ዉስጥ ጠቅልዬ ከገባሁ
ወዲህ የከተማዉን ግርግር አይቼዉ አላዉቅም፡ እንኳንስ በአካል በወሬም እንኳን፣ ስለ ከንቱዉ ዓለም የመስማት ፍላጎቴ ሞቷል፡ አላስችል ብሎኝ
ካስቀረኋት አንድ ክራሬ በቀር የቀድሞ ልብሶቼን፣ የቀድሞ ጌጣጌቶቼን የቀድሞ ሥራዬን ሁሉ እንዳለ እርግፍ አድርጌዋለሁ

“ምን ልርዳዎ የኔ ወንድም?” አልሁት፣ በደህና ትሕትና᎓

“ጋሽ ባልቻ ሊያናግሩሽ ይፈልጋሉ” አለኝ፣ ሞባይሉን ሊያቀብለኝ እጁን
ወደ'ኔ እየዘረጋ

“ባልቻ?”

“አዎ፤ መስመር ላይ ናቸዉ: እንኪ አናግሪያቸዉ” አለ፣ እንደገና የበለጠ ቀረብ ብሎኝ፡፡

“ሄ..ሎ” አልሁ፣ እያቅማማሁ ሞባይሉን ተቀብዬ ወደ ጆሮዬ አድርጌዉ፡

“ማንም አልቀደመኝም አይደል?” አለኝ ባልቻ፣ አብሮኝ ያደረ ይመስል ጨርሶ ሰላም እንኳን ሳይለኝ፡

“ምኑን?”

“እህ! ረስቼዋለሁ እንዳትዪኝ ብቻ”

“ምኑን?”

“አንቺ! ቀኑን ረስተሽዋል?”

“እህእ፣ የቱን ቀን?”

“የዛሬ ዓመት እኮ ነዉ ቱናት የተወለደችዉ። ልደቷ መሆኑ ረስተሽዉ ነዉ?”

ወይ መርሳት! እንኳንስ የተወለደችበትን ይቅርና፣ መቼ ሕክምና እንደ ገባች፣ መቼ እንደ ወጣች፣ ለመጀመሪያ ጊዜ መቼ ፈገግ እንዳለችልኝ፣ የትኛዉን ልብሷን መቼ እንዳስገዛሁላት ጭምር ከነዕለቱ እና ከነሰዓቱ
ልረሳዉ አልችልም: ያም ቢሆን ግን የልደት ቀኗ ላይ ትንሽ ተወዛግቤ ነበር፡ ያለ ቀኗ ከሆዴ የተወለደችበትን ዕለት ነዉ ልደቷ ብዬ የማከብርላት ወይስ ከዚያ በኋላ ለኹለት ወራት ያህል ቆይታ ከማቆያ ክፍል ወጥታ እቅፌ ዉስጥ የገባችበትን ዕለት የሚለዉ ግራ አጋብቶኝ
ነበር ባልቻ የሚለዉን ከወሰድሁ ግን፣ እዉነትም የቱናት ልደት ዛሬ
ዛሬ ከሆዴ ከወጣች አንድ ሙሉ ዓመት የደፈነችበት ዕለት ነዉ።

“ረስተሽዋል አይደል?”

“ኧረ በጭራሽ!”

“እኮ ይዘሻት ነያ”

“የት?”

“አጠገብሽ ያለዉ ልጅ መኪና ይዟል: እሸቴ ነበር ሊመጣልሽ የነበረዉ: ግን አንድ ድንገተኛ ተልእኮ ተሰጠዉ እና መምጣት አልቻለም አንቺ እስከምትደርሺ ግን እሱም ሥራዉን ይጨርሳል። ስለዚህ ቱናት ቆንጆ አድርገሽ አልብሻትና ይዘሻት ቶሎ ነይ”

“እህእ፤ መቀለድህ ነዉ እንዴ? ከመቼ ወዲህ ነዉ እንኳንስ ገዳሜ
ቱናትን ይዤ ይቅርና ለራሴስ ብሆን ከዚህ ወጥቼ የማዉቀዉ?”

“ይልቅ እንዳትቆዩ” ብሎ፣ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ጠረቀመዉ፡ እንደ
ወትሮዉ ቢሆን እንኳንስ እያወራሁለት ሊዘጋብኝ ይቅርና፣ ቻዉ ተባብለን እንኳን ለመዝጋት እጁ እሺ አይለዉም: የአሁኑ ግን በእሱ የማላዉቀዉ እንግዳ ዐመል ሆነብኝ፡ ተዋክቦ ነዉ እንዳልል፣ ምንም የቸኮለ አይመስልም: መቼም ጊዜ ባይኖረዉ ኖሮ የቱናትን ልደት ካላከበርን
አይለኝም።

ከተቀየመም ይቀየመኝ እንጂ ቱናትን የትም ወስጄ አላንገላታትም ብዬ
ወሰንሁና ሞባይሉን ለሰጠኝ ልጅ ልመልስለት ዞር ስል አጣሁት ባልቻን
አናግሬ ስጨርስ እንደምከተለዉ እርግጠኛ በመሆን ከግቢ ዉጪ ወደ
መኪናዉ ተመልሷል፡ እየጠበቀኝ ስዘገይበት ጊዜ፣ ያቺን የሲራክ ፯ ኮድ
የሆነችዋን የመኪና ጥሩንባ አሰማኝ፡ ቢያንስ ሞባይሉን መመለስ
ስላለብኝ፣ ልጄ ለቅጽበት ብታጣኝ የማጣት መስሎኝ እንደ ፈራሁላት
ወደ መኪናዉ ሮጥሁ።

“ይቅርታ ወንድሜ፣ ባልቻ ዝም ብሎ ነዉ እዚህ ድረስ ያደከመዎ” አልሁት፣ በመነኩሴ የትሕትና ልምምዴ፡

ቱናት ገዳምሽ ናት ብለዉኝ የለ የንስሐ አባቴ? ታዲያ ገዳምን ወዳለበት
ሄደዉ ይሳለሙታል እንጂ፣ ራሱ ገዳም ተነቅሎ ካልመጣልኝ ይባላል እንዴ? በጭራሽ! ያዉም የገዳምን ክብር ከሚያዉቀዉ ከባልቻ ይኼ
ይጠበቃል? አዝናለሁ፣ ያለ ተፈጥሮዋ ወደ ጩኸት አዉጥቼ ገዳም አላስረብሻትም: አልሄድም፡ በእሷ የሚያድረዉን አምላክ ማመስገን የፈለገ ቢኖር እየመጣ ይሳለማት እንጂ፣ ገዳሜን ለመንቀል በጭራሽ አላደርገዉም

አልሞክረውም
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በታደለ_አያሌው

“እንደምን አረፈድሽ የኔ እህት?” አለችኝ አንዲት ደርባባ ሴት፣ እንጀ አጋጣሚ በመንገዱ እያለፈች ሳለ እንደ ዋዛ መለስ ብላ እጅ ነስታኝ።

“እግ..እግዚአብሔር ይመስገ” አልሁኝ፣ እንደ መደናገር ብዬ፡ መልኳ እንግዳ አልሆነብኝም:

“ምነዉ በደህናሽ ነዉ፤ ልጅ ይዘሽ በመንገድ ዳር?”

“ደህና ነኝ” አለሁኝ፣ የሴትዮዋን መልክ አስታዋሽ ልቤ ላይ ብቅ ብሎ
ጥልቅ እያለብኝ፡፡ የት እንደማዉቃት ልጠይቅ አልጠይቅ ብዬ ከራሴ ጋር
ትንሽ ተከራከርሁ፡

“ቱናትስ እንዴት ናት?”

ይኸዋ! እሷ ጭራሽ ከእኔም አልፋ ከማንም ሸሽጌ የማኖራትን ገዳሜን
ሳይቀር ታዉቃለች፡ ኧረ ይቺ ሰዉ ማናት?

“አጠፋሽኝ መሰል”

“አይ ማጥፋት ሳይሆ” አልሁ፣ እሷ በዚህ መጠን አዉቃኝ እኔ አላወቅሁሽም ማለቱ ቢያሳፍረኝ፡

“ምነዉ እንኳን” አለችኝ፣ ጭንቀቴ ገብቷት ልትገላግለኝ፡ “ምነዉ
እንኳን ዘዉዲቱ ሆስፒታል ተዋዉቀን ?”

"አዎ!” አልሁ፣ ነፍሴን እያሳረፍኋት። “እዚያ ነዉ አይደል
የምንተዋወቀዉ ?»

መጣችልኝ፡ የቱናትን ሕክምና ለመጀመር ወደ ዘዉዲቱ ሆስፒታል የገባን ዕለት ማታዉን የተዋወቅናት ሴት ናት ከዳር ሀገር መጥታ፣ እዚያ ዘግናኝ ወለል ላይ ወረፋ ጥበቃ ወር ሙሉ ሕመምተኛ ልጇን ይዛ
መቀመጧን ነግራን እንደ ነበር ሁሉ አስታወስሁ፡ አስታወስኋት
የቀድሞዉ ባሌ መተት አስመትቶብኝ፣ ልጄ እንዲህ ሆኖብኝ ቀረ› ብላ ለእመዋ የነገረቻት ሴትዮ ናት።

እዴት ሆነልዎ ... ማነዉ ... እንዴት ሆነለሽ ልጅሽ?” አልኋት አንቱ
ማለት እና አንቺ በማለት መካከል እየዋለልሁ: አሁን አሁን
ምቸገርባቸዉ ነገሮች አንደኛዉ ይኼ ነዉ፡ በምለማመደዉ የምንኩስና ሕይወት ማንኛዉንም ሰዉ አንቱ ብዬ ማክበር እፈልጋለሁ ግን ደግሞ ቀደም ብዬ አንተ ወይ አንቺ እያልሁ የማዉቃቸዉ ሰዎች ግራ
እንዳይጋቡብኝም እሰጋለሁ።

“መቼም ወረፋዉ ደርሶሽ ይሆናል። ዳነልሽ፤ እንዴት ሆነ ልጅሽ?”
“ወረፋዉስ ደርሶኝ ነበር” አለች፣ በቅጽበት አንገቷን እየሰበረች ክፉ ነገር እንዳትነግረኝ እግዚአብሔርን በልቤ ለመንሁት፡ ልጇ እንደዳነላት ብቻ ነዉ መስማት የምፈልገዉ፡
“አልሆነም” አለችኝ፡፡

“እ?”

“አልዳነልኝም ወረፋዉ ደርሶት እንደ ነገ ተቀጥሮልኝ፣ እንደ ዛሬ
ማታዉን እቅፌ ላይ አረፈብኝ” አለችኝ፣ እንባዋን በሺህ መንታ
እያወረደች፡ የእኔም እንባ መቆሚያ አጣ፡ የልጁ ሁኔታ አሁንም ዓይኔ ላይ አለ፡ ምንም እንኳን ልጇን ገጥሞት የነበረዉ ከቱናት ቀለል ባለ ሁኔታ፣ ያልተመጣጠነ የጭንቅላት የዉሃ መጠን (hydrocephalus) ብቻ
ቢሆንም፣ ሁኔታዉ ግን አንጀት ይበላ ነበር፡፡ እሷም ይድንልኛል ብላ ያን ሁሉ መከራ አይታ በመቀርቷ አንጀቴን በላችዉ፡
“አልቅሼ ያልሞትሁትም አንዲት
ማጽናናት የሚያዉቁበት እናት
አባብለዉኝ ነዉ። አሁን እኮ እንዲያዉም እሳቸዉ ጸበል ጸዲቅ
ካልቀመስሽ ብለዉኝ ነዉ የልጄን ሬሳ ይዤ የወጣሁበትን ከተማ
ከመንፈቅ በኋላ ዳግመኛ የተመለስሁበት ያ ጊዜ እሳቸዉ ባይራዱኝ ኖሮ እኮ የልጄን ሬሳ እንኳን ጭኜ ወደ ሀገሬ መዉሰድ ባልቻልሁ ነበር።ዉለታቸዉ አለብኝ። በምን እከፍላቸዉ ይሆን ብለሽ?”

“እግዚአብሔር ዉለታ አዋቂ ነዉ። ግድየለም፣ እሱ በነፍስ ይክስልሻል”አልኋት፣ የተባሉት ሴትዮ ደግነት እያስቀናኝ፡

“ልመልስስ ብል በምን አቅሜ እቴ! እንዲያዉ የማትቸኩይ ከሆነ
እንዲያዉ ባስቸግርሽ፤ አብረን ሄደን ብናመሰግናቸዉ”

“አይ” አልሁ፣ እሺም እምቢ ማለትም እየከበደኝ፡

“እዚያች ዘንድ፣ ያዉና እኮ ቤታቸዉ: ያ በሰፊ ቆርቆሮ የታጠረዉው ግቢ ነዉ ቤታቸዉ መሆኑን ሰዎች የጠቆሙኝ። ነይ እንሂድ እስኪ እባክሽ”።

የእኔ አስፈላጊነት ባይገባኝም፣ እምቢ ማለት ግን አልቻልሁም፡ እሺ ብዬ ባለ ተሽከርካሪዉን የቱናትን አልጋ እያሽከረከርሁ ተከተልኋት። እሷም ጮራዋ የቱናት ዓይኖች ላይ መፈንጠቋን አይታ አላስቻላትም የራሷን ነጠላ ቀልጠፍ ብላ አውልቃ፣ ራስጌዋ ላይ አጠላችላት።

በነበርንበት የመንገዱ ጠርዝ ትንሽ ተራምደን መንገዱን አቋረጥነዉ።
ከዚያ በማቋረጫዉ ፊት ለፊት ባለዉ ቅያስ ትንሽ እንደ ሄድን በቆርቆሮዉ አጥር የታጠረዉን ግቢ በር አገኘነዉ: ቅድም ቆመንበት ከነበረዉ መንገድ
ዳር ሆኖ የታየዉ አጥር እዚህ ድረስ መስፋቱን አይቼ፣ ‹ምን ዓይነት ሴትዮ ቢሆኑ ነዉ? መቼም ሀብታም መሆን አለባቸዉ ልላት ወደ እሷ ስዞር ፊቷን በሳቅ ሞልታ ጠበቀችኝ፡

“ዝግጁ?” አለችኝ፣ በደስታ እየተፍለቀለቀች

“እኮ ሴትዮዋን ለማመስገን?” አልኋት፣ ድንገት ስለ ተሞላችዉ
የደስታዋ ምንጭ ምክንያት እየፈለግሁለት።

“እ" እንደዚያ ነዉ አዎ ግን ምንም ቢገጥምሽ እንዳትደነግጪ። ዝግጁ ነሽ አይደል ለዚያ?”

“ይቅርታ…”

“ይቅርታ አድርጊልኝ ዉብርስት: ትንሽ ዋሽቼሻለሁ: ዉለታ የዋሉልኝ
ሴትዮ የአንቺ እናት፣ እመዋ ናቸዉ። ይኼ በር ሲከፈትም የምናገኘዉ እመዋን እና የእሳቸዉ ዓይነት ዉለታ ዋዮችን ነዉ በእርግጥ ሌላ ያልጠበቅሽዉ ሰዉም ልታይ ትችያለሽ። ምንም ቢሆን ግን እንዳትደነግጪ” አለችኝ፣ እንደ ማቀፍ ጭምር እያደረገችኝ።

ተለዋዋጭ ሁኔታዋን ሳይ ትክክል አልመሰለችኝም፡ እንደዚያም ሆኖ ግን የሚጎዳ ነገር ዉስጥ እንደማትከተኝ በነፍሴ አምኛታለሁ ለምን እንደሆነ እንጃ ከቅድሙ ሹፌር ይልቅ እሷን በሙሉ ልቤ ነበረ ያመንኋት የልጄን ተሽከርካሪ አልጋ የሚገፉ እጆቼን ጠበቅ አድርጌ ይዤ፣ የሚሆነዉን ሁሉ
ለማየት ዓይኔን በሩ ላይ ተከልሁ። እኔን ያቀፈችበትም ሆነ በሩን
ለመክፈት የሚገፋዉ እጇ ይንቀጠቀጣል፡ ቀስ አድርጋ ከርፈድ አደረገችልኝ፡ አንድ የጠመጠሙ ቄስ ቀድመዉ ዓይኔ ዉስጥ ገቡ።

አሁንም ቀስ አድርጋ መግፋቷን ጨመር ስታደርግልኝ፣ ወዲያ ወዲህ የሚሉ የሰንበት ተማሪዎችን መለዮ የለበሱ ወጣቶች አየሁ ክፍተቱን
ሰፋ ባደረገችዉ ቁጥር፣ ዓይኔ ዉስጥ የሚገባዉም ሰዉ እየጨመረ እየጨመረ መጥቶ ጨርሳ ሙሉ በሙሉ ወለል አድርጋ ስትከፍተዉ፤አንድ ትልቅ ጉባዔ የሚሞላ ብዙ ሰዉ በግቢዉ ተጥለቅልቋል፡ በተለይም በአንደኛዉ ማዕዘን በኩል በድንኳን ዉስጥ ሰብሰብ ብሎ ወደ እኛ የሚመለከተዉን ሕዝብ ተመለከትሁት ነገሩ፣ ትክክለኛ ጉባዔ ነዉ።

“እንዴት እንዴት ነዉ ነገሩ?” አልኋት ወደ ሰዎቹ እንድንሄድ
የመጎተት ያህል ስትመራኝ። “ጭራሽ እመዋም አለችበት? ባልቻም፣ እሸቴም? ኧረ ምንድነዉ ጉዱ?” አልሁኝ፣ በቀረብን ቁጥር እንደ አዲስ እያላበኝ፡ ዓይኔን ከጫፍ እስከ ጫፍ አንከራተትሁት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ጨምሮ፣ ሦስት ጳጳሳት ከጉባያተኛዉ የፊተኛዉ ረድፍ ላይ
ይታዩኛል፡ የጤና ሚኒስትሯን ጨምሮ አንዳንድ የማዉቃቸዉ
የመንግሥት ባለስልጣናትም መኖራቸዉን አስተዋልሁ: በርከት ያሉ ካህናት፣ የማኅበራችን ዋና ሊቀመንበር፣ ባልቻ፣ እሽቴ፣ እመዋ
ሌሎች የማኅበራችንም ሆነ የሲራክ ፯ አባላት ሁሉ አሉበት።

“እንኳን በደህና መጣችሁ” ሲሉ ተቀበሉን፣ ሁሉም: ያልቆመ
የማያጨበጭብ አለ ይሆን?

“ክቡራንና ክቡራት እንግዶቻችን፣ የጉባዔያችን መነሻ ምክንያቶቻችንም ተሟልተዉ ተገኝተዉልናል እንደ ቆማችሁ ማርያም ትቁምላችሁ እባካችሁ በየመቀመጫችሁ አረፍ አረፍ በሉልን” አለ የመርሐ ግብር
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በታደለ_አያሌው

...የጃሪም አወጣጥ በኃይል እየቆረቆረኝ ቢሆንም፣ ደስታዬ ግን ጢም እንዳለ ነዉ።

የመሠረት ድንጋዩ በጳጳሳቱ እና ሌሎች ታላላቅ ስዎች ተቀምጦ ከአበቃና የጉባዔዉ አጋፋሪ ‹ሂዱ በሰላም› ካለን ከብዙ ደቂቃዎች በኋላም ቢሆን፣ ችዬ መነሳት አልቻልሁም ነበር፡ ልጄ ቱናት የተኛችበትን አልጋ ወደ
ተቀመጠዉ የመሠረት ድንጋይ አስጠግቼ፣ በደስታ እንባዬን ሳወርድ ብዙ ቆየሁ፡ ሁኔታዬን ሁሉ እመዋ በሩቁ ስትመለከት ኖሯል መሰለኝ፣ ከእንግዳዉ ጋር መዉጣቷን ትታ ወደ'ኔ መጣች፡

“ደስ እለሽ ዉብዬዋ?” አለችኝ፣ ወደ እቅፏ እየሳበችኝ፡፡

“በጣም!” አልኋት፣ እንባዬን በቀሚሷ እያበስሁ

“እሰይ! እንኳ ንም ደስ አለሽ ልጄ”

“እንደ ዛሬዉም ደስ ብሎኝ አያዉቅ”

“እኔም” አለችኝ፣ ወደ አንገቷ ሥር ጠበቅ አድርጋ እየሳበችኝ ቀና ብዬ
ሳያት፣ እዉነትም ተጫጭኗት የነበረዉን እርጅና ሳይቀር ድል ነስታዉ ታየችኝ: ግንባሯ ላይ በተደረደሩ መስመሮች ሁሉ ደስታ ሲፈስ አየሁ በጣም ደስ ብሏታል። ይኼ ደስታዋ የኔንም ደስታ የትና የት አደረሰዉ።

“የቱናት እናት” አለ ባልቻ፣ እንግዳዉ ቀለል እስከሚልለት ድረስ ሲሸኝ ቆይቶ ወደ እኛ እየመጣ፡ የእሱም ፊት ከእኛ በሚስተካከል ደስታ ተጥለቅልቋል ቱናትን ከነአልጋዋ አቅፎ አነሳትና የመሠረት ድንጋዩ አናት ላይ ጉብ አደረጋት: “ይኼን ወደ መሰለ ሥፍራ ስጠራት እንዲያ
እንዳልተግደረደረች፣ ደስታ እንዴት እንደሚያደርጋት አየሽልኝ አይደል
ይቺን እናትሽ?” አላት፣ ቱናትን በስስት እየተመለከታት

የመሠረት ድንጋዩ ላይ ከነአልጋዋ ያደረግናትን ቱናትን ለረዥም ጊዜ
ከብበን ከቆየንና፣ ለዚሁ ደስታችንም ወሰን ልናበጅለት ከሞከርን በኋላ እኔና ባልቻ ቱናት የተኛችበትን አልጋ ከግራ እና ከቀኝ ይዘን ወደ ባልቻ
መኪና ተሳፈርን

“በሉ እንግዲህ” አለችን እመዋ፣ ከሀገር ርቀን የምንጓዝ ይመስል አቅፋ እየተሰናበተችን፡

“አብረሽን አትሄጅም ወይ እመዋ? ዉቤ እኮ ወደ ሲራክ እየተመለሰች
ያለችዉ ከዓመት በኋላ ነዉ። መቼም በዚህ አንድ ዓመት ዉስጥ
በማዕከላችን የተለዋወጠዉ ነገር ሁሉ እያየች እንደ ጀማሪ ጎብኚ
ይኼ ደግሞ ምንድነዉ እያለች በጥያቄ ማስቸገሯ አይቀርም: ብቻዬን እችላታለሁ ብለሽ ነዉ?” አለ ዓይኖቹን በእኔ፣ በእመዋ እና በቱናት ላይ እያንከባለለ፡፡

“ወደ ሲራክ ነዉ እንዴ የምንሄደዉ?”

“አዎ ምነዉ?” አሉኝ እኩል፣ ድንግጥ ብለዉ፡ ደግሞ ልትለመንብን ነዉ› ብለዉ ነዉ መሰለኝ፣ በቅጽበት አመዳቸዉ ቡንን አለ

“እሺ”

“እኮ! እንዳንቺም በሕጋችን የቀለደበት ሰዉ የለም: እንዲያዉ የቱናት እናት መሆንሽ አተረፈሽ እጂ፣ አንቺስ ደህና አድር ገዉ ቢቀጡሽ ሁሉ የምታጸድቂ ወንጀለኛ ነሽ” አለኝ፣ እንደ መሳቅም በእፎይታ እንደ
መተንፈስም ብሎ፡

“ታዲያ እኔ እምቢ ብዬ ነወይ? ልብ ካላችሁ መቅጣት ነበራ” አልሁት፣ የቱናትን ልብስ እያስተካከልሁ

“ይቀርልሽ መስሎሻል!”

“ቆይ ምን አጥፍቼ ነዉ ግን?”
ያልሰማኝ መስሎ ፊቱን አዞረብኝና፣ እመዋን እንደገና ተሰናበታት፡ እኔም እንደ'ሱ የመኪናዉን መስታዎት ዝቅ አድርጌ ልሰናበታት ስል፣ ሆነ ብሎ
መኪናዉን አንቀሳቀሰብኝ፡፡

“ አየሽልኝ አይደል ምቀኝነቱን እመዋ?” አልኋት፣ ልክ እንደ በባቡር ተጓዥ እጄን እያዉለበለብሁላት፡

እሷን ተለይተን መንገድ ከጀመርን በኋላ፣ ቅድም ያልሰማ መስሎ
ያለፈብኝን ጥያቄዬን እንደገና አነሳሁበት

“እ፣ በል ገረኛ”

“ምኑን?”

“ብቀጣበት የምትጸድቁበትን ጥፋቴን ነዋ”

ፍርጥም ብሎ ጥርሶቹን ገለጠልኝ፡

“እዉነት ጥፋትሽ ጠፍቶሽ ነዉ አንቺ? ሌላዉ ቢቀር፣ አንዲት የሲራክ አባል ብትወልድም እንኳን ፈቃዷ ምን ያህል እንደሆነ አጥተሽዉ ነዉ?”

“ወይ ጉድ… እኔስ አሁንም ወደ ሲራክ እየሄድሁ መሆኑ ደንቆኛል”

ቱናትን ከወለድሁ፣ በተለይም ኋላ በሕክምናዎቿ ጊዜ ያለፈችበትን አበሳ ካየሁ በኋላ፣ ወደ ሲራክ ፯ እመለሳለሁ አላልሁም ነበር፡ እንኳንስ እስከዚህ ድረስ፣ ገዳሜን ከገደምሁበት የእመዋ ቤት አንድም ርምጃ ንቅንቅ የምል አይመስለኝም ነበር፡ ዛሬ ግን ባልቻ ገና ‹እንሂድ› ሲለኝ፣
‹እሺ› ብዬ ከመከተል በቀር ምንም ያሳሰብኝ ነገር የለም፡

በዚህ ሁኔታ ከዋናዉ የማኅበራችን ሕንጻ ደርሰን፣ ጥብቁን እና ረዥሙን የሲራክ ፯ መንገድም አልፈን ከመጨረሻዉ በራፍ አጠገብ ስንደርስ ድንገት ቆመ፡፡ ጭራሽ እንደ መቅለስለስ ብሎ አየኝ፡፡ ይኼ አስተያየቱ
ነበር ቀድሞዉንም እኔን እና እሱን በሌላ ያስጠረጥረን የነበረዉ፡፡ ግራ ገብቶኝ አየሁት፡ በሩ ደግሞ ሲጠም፣ እኛ መሆናችንን አዉቆ በራሱ ጊዜ እንደ ቀድሞዉ ይከፈትልናል ብዬ ብጠባበቀዉም፣ ክርችም እንዳለ ቀረ፡

ምነዉ” አልሁት፣ ዓይን ቢያበዛብኝ፡ “ኧረ አባትዮ፣ እንዴት እንዴት እየሆንህ እንደሆነ ታዉቆሃል ግ?”

“እንዴት እንዴት ሆንሁ?”

“ለራስህ አይታወቀህም?''
መቅለስለሱን ተከትሎ፣ በዚያዉ ሐሳብ ገባዉና፣ ቁዝም ብሎ ቆየብኝ፡

“ምንድነዉ ጉዱ፣ የማትነግረኝ?”
“እንዳትቆጪኝ ፈራሁ እንጂ”

“እንዳትቆጪኝ?”ፈራሁ

“ለእሷ የምትሆኚዉን ሳይ፣ ትንሽ ፈራሁ”

“ማናት ደሞ እሷ?”

ልጅሽ፣ ቱናት” አለኝ፣ የቱናትን አልጋ የያዘ እጄን እያስለቀቀብኝ፡ እሱዐበአንደኛዉ ጎን፣ እኔ ደግሞ በሌላኛዉ ጎን ሆነን ነበር በየእጃችን የያዝናት አሁን ግን የመፈልቀቅ ያህል እጄን አስለቅቆ ለብቻዉ ወደ እቅፉ ወሰዳት አድራጎቱ ሊገባኝ ባይችልም፣ ባልቻ ነዉና ሰዉየዉ ልጄን አትንካብኝ ብዬ ልከላከለዉ አልቻልሁም፡ ትንፋሼን ዉጬ
መጨረሻዉን ጠበቅሁት፡፡ በእርግጥ፣ ደግሞ ሌላ የምሥራች
የተዘጋጀልኝም መስሎኝ ራሴን ለደስታ እያመቻቸሁ ነበር የለመደች ጦጣ አሉ!

“በቃ ዉቤ፤ በቃ ቱናትን ወስጄብሻለሁ” አለ፣ ስለ ራሱ ንግግር ራሱ ሐፍረት እየተሰማዉ፡፡

"እ" አልሁት፣ በግንባሬ፡ ብቻ ያንን የመሰለ ደስታ እንዳይከስምብኝ፡
ዓይኔን በልጥጬ በግርታ አየሁት፡

“አዎ”

“ኧረ አባትዮዉ ተዉ አታስቀኝ” ብዬ፣ እንደ ምንም ጥርሴን ለመግለጥ ሞከርሁ: ሳቄን የሚጋራኝ መስሎኝ ሳቅ ብርቃቸዉ የሆኑት ጥርሶቹ እስኪገለጡ ብጠብቅም፣ እሱ ግን ክርችም እንዳለ ነዉ አሁንም:

“እየቀለድህብኝማ አይደለም: ነዉ እንዴ?”

“በፍጹም! ከእሽቴ ጋርም ተመካክረበታል: ለማኅበራች
ሊቀመንበርም አወያይቼዋለሁ:: ያዉ እመዋንም ቢሆን ጫፍ ጫፏ
አጫዉቻታለሁ: ሁላችንም ጋ ያለዉ ሐሳብ ተመሳሳይ ነዉ''

“ቆይ ቆይ”

“ተዪ ዉቤ: በቃሽ: እዲያዉም ግልጹን ንገረኝ ካልሽኝ፣ ቱናት በዚህ መልኩ የምትጠቅሚያት አይመስለኝም” አለ፣ ቆምጨጭ ብሎ፡ ጭጭ ብዬ ከማዳመጥ በቀር የምሆነዉን እንጃልኝ፡፡

“ስለዚህ ቱናት እየወሰድሁብሽ ነዉ። ከእንግዲህ ቱናትን ለብቻሽ ቤት ዘግተሽባት የብቻሽ ማድረግሽ ይቀርና፣ የሁላችንም ልጅ አድር ገንእናሳድጋታለን። አንቺም ቱናት የምታገኛት እንደ ማናችም አልፎ አልፎ እና ከሥራ ዉጪ ይሆናል ማለት ነዉ። በማኅበራችን የሕጻናት መዋያ ዉስጥ እናስገባት እና እንደ ማንኛዉም ልጅ ጨዋታ እና ግበረ ሕጻናት እየፈጸመች ታድጋለች”

“እንደ ማንኛዉም ልጅ?”
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በታደለ_አያሌው


“እንዴት? ተለዉጫለሁ ማለት ነዉ በቃ?” እያልሁ፣ ከራሴ ጋር
ስተዛዘብ ቆየሁ።

እንዲያዉ ራሴንም ጭምር ስዋሸዉ የናፈቀኝ የለም አልሁ እንጂ፣ እንዴት ነዉ የማይኖረዉ? የጎዳናዉን ሰዉ ሁሉ የልቤ ሰዉ ማድረግ ይሆንልኝ የነበርሁት እኔ ዉብርስት፣የእናቴን ልጆች ከልቤ ችዬ ላስወጣ? አይሆንም፡ የናፈቀኝ የለም ያለ አፌን ይዤ እንኳንስ በባልቻ ፊት፣ በራሴ ኅሊናም ሚዛን ላይ ለመቆም ተሸማቀቅሁ።

አፈርሁ።

“ወዴት ነዉ ታዲያ?” አለኝ ባልቻ፣ ቱናት ያለችበትን አልጋ እየሳብሁ
ወደ መዉጫዉ ስራመድ አይቶኝ፡

“ወደ በረሃ”

“ወዴት?”

“ገዳሜን ወደ ገደምሁበት ወደ በረሃዬ። ወደ እመዋ ቤት!”

“ቅድም ምን ተባብለ'? ተይ እንጂ በማርያም: ይልቅ ቱናትን ይዘሽ
የማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት እየጎበኛችሁት፣ ቅድም ያልሁሽን
አታስቢበትም?”

“እኔ የፈለገዉን ያህል ባስበዉ፣ የሚሆን የሚሆን መስሎ አልታኝም”

“ግድ የለሽም፣ እስከማታ ጊዜ አለሽ: ደጋግመሽ አስቢበት”

“እስኪ ይሁን። እሺ። መኪናህን አታዉሰኝም ታዲያ? ለማሰቡም ቢሆን እኮ የከረምሁባት በረሃዬ ትሻለኛለች: ወደ እመዋ ቤት መሄድ አለብኝ ትክ ብሎ ሲያየኝ ቆየና አንገቱን በይሁንታ ነቅንቆ፣ ቀድሞኝ ወደ በሩ አመራ፡ ዝም ብዬ ኖሯል እንጂ ቀደም ቀደም ያልሁት፣ ቀድሞ የነበሩኝ
የትለፍ ፈቃዶች ሁሉ መልሰዉ ካልታደሱልኝ በቀር ያለ'ሱ ወደ ሲራክ ፯ መግባትም ሆነ ከማዕከሉ መውጣት
አልችልም:: ስለሆነም
ጠመዝማዛዉን እና ባለ ብዙ በሩን ሲራክ ፯ አሳልፎኝ መኪናዉ
እስከቆመበት ድረስ ቱናትን ከነአልጋዋ አቅፎ አደረሰልኝ፡፡
“በይ እንግዲህ። ማታ፣ ልክ አንድ ሰዓት ሲሆን እደዉልልሻለሁ” አለኝ፣ የጠየቅሁትን የመኪናዉን ቁልፍና ያልጠየቅሁትን አንድ የእጅ ስልክ ጭምር አዉጥቶ እያቀበለኝ፡፡ እሺም፣ እምቢም፣ ቻዉም ሳልለዉ፣ ቱናትን ጭኜ የመኪናዉን ሞተር አስነሳሁ፡ እንደ ድሮዉ በችኮላ ሳይሆን፣ የመኪና መሪ ከነካሁ ቢያንስ መንፈቅ እንዳለፈኝ እና ከአጠገቤ
የጫንኋትም ሰዉ ገዳሜ ቱናት መሆኗን በማሰብ ወደ እመዋ ቤት
የሚወስደኝን ጎዳና በዝግታ አሽከረከርሁበት እንደ ደረስሁ፣ የግቢዉን በር ራሴዉ ለመክፈት ቀልጠፍ ብዬ ወረድሁ።
ስሞክረዉ ግን አልከፈትልሽ አለኝ፡፡ ለወትሮዉ ማናችንም የቤተሰቡ አባላት አድርሶን በመጣን ጊዜ እንዳንቸገር በሚል፣ ግቢያችን ተቆልፎብን
አያዉቅም: እንዲሁ በዉስጥ በኩል ይሸነጎርና፣ መሸንጎሪያዋን
የምንስብባት ደግሞ እኛ ብቻ የምናዉቃት አልባሌ ገመድ አለችልን፡አሁን ግን ይቺ ገመድ በሩን ልትከፍትልኝ አልቻለችም፡፡ እንዲያዉም እጄ ላይ ስለቀለለችብኝ፣ ሳብ ሳደርጋት ጭራሽ ምዝዝ ብላ ወጣች ገመዷ
ተበጥሳለች::

ቆይ፣ ገመዳችንን የበጠሰብን ማነዉ? ምንድነዉ?

“ኤጭ!” አልሁኝ፣ ንድድ ብሎኝ፡ በዚያ ላይ ልጄ ቱናት ምግብ
ከቀመሰች ቆይታለች፡፡ እንዲያዉም ለመንገድ ብዬ ይዤላት የነበረዉ
ምግብ ስለ ቀዘቀዘባት፣ እዚህ ደርሼ ትኩስ ምግብ እስከማጎርሳት ነበር
ችኮላዬ::
“ቆይ፤ ገመዳችንን ማነዉ የበጠሰብን?” አልሁኝ፣ እጄ ላይ ያለዉን የገመድ ቁራጭ ጨብጬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ቢገባኝ፡

“እኔ” አለኝ፣ ከዉስጥ በኩል።

“አሃ፣አላችሁ እንዴ? በሉ ክፈቱልኝ' አልሁኝ በደፈናዉ፣ ማን
እንዳናገረኝ ስላላወቅሁት

“ምን ልትሆኚ?” አለኝ አሁን በድምፁ ለየሁት፡ ጃሪም ነዉ፡

“ክፈትልኝ”

“እንዳታስቢዉ!”

“ኧረ ባክህ አትቀልድብኝ። ለራሴ ልጄን ርቦብኛል። በል ክፈተዉ ይልቅ”

“አይ እግዲህ! በቋንቋሽ መሰለኝ ያናገርሁሽ!''

“ምን መሆንህ ነዉ፣ ክፈትልኝ እኮ ነዉ የምልህ”

“ሴትዮ! ምናለበት ባትፈታተኚኝ? ነገርሁሽ፤ ከዛሬ በኋላ እዚህ ግቢ ላይሽ አልፈልግም”

“እኔ ተናግሪያለሁ ጃሪም! ክፈተዉ ልጄን ርቧታል። አላበዛኸዉም እንዴ ?
ብለህ ብለህ ደግሞ ወደ እናቴ ቤት እንዳልገባ ልትከለክለኝም ያምርሃል ጭራሽ?” እልህ እየመጣ ጉሮሮዬን ተናነቀኝ፡፡

“ዉነት የእናትሽ ቤት እንግዲያዉስ እርምሽን አዉጪ። ሰማይ ዝቅ
ቢል ይቺን ግቢ ደግመሽ አትረግጫትም: በጭራሽ! ለአንቺም ሆነ ለእናትሽ፣ በቂ ጊዜ ሰጥቻችሁ ነበር: የማያልቅ መስሏችሁ ስትቀልዱበት
ያለቀባችሁ እንደሆነ፣ እኔ ጃሪም ምን እዳዬ? ከዚህ በቀር ምን
ላድርጋችሁ? የራሳችሁ ችግር ነዉ፣ ሥራችሁ ያዉጣችሁ: ከደጄ ግን ፈቀቅ! ያቺ ቆዳ እናትሽ መቼም ልብ የላትም፣ ያልኋትን ረስታ ድርሽ እንዳትልብኝ ብቻ!"
ይኼን ሁሉ ስንባባል፣ ጎረቤት እና አላፊ አግዳሚዉ ሁሉ በግላጭ
እየሰማና እያየኝ ነዉ አንዳንዱ ለእኔ አዛኝ መስሎ ጠጋ ይልና፣ ‹እንዲህ በይዉ› ብሎ ይመክረኛል የተረፈዉ ደግሞ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደ'ሱ ልክ ልኳን ንገራት ጃሪምን
ይመክረዋል አንዳንዱ እንዳትከፍትላት፣ ደግ አደረግህ!» ይለዋል እሱን፣ ሌላዉ ደግሞ ምን አለማመነሽ? ፈሪ ነሽ እንዴ? መኪና ይዘሽ የለ? ዝም ብለሽ ደርምሰሽዉ የማትገቢ! ይለኛል እኔን፡ አልደነቀኝም ምክራቸዉን ሰምቼ የእናቴን
አጥር ብደረምሰዉ እና ቢፈርስ፣ እኛ እንጂ እነሱ አይጎዱም፡

መካሪ እና ግርግሩ መብዛቱን ሳይ፣ ለመሸሽ መረጥሁ: ምስስ ብዬ ወደ መኪናዉ ገባሁና፣ ቆይቼ ብመለስ
አልፎለት እንደሚጠብቀኝ
በመተማመን፣ እሱን ትቼ እመዋን ፍለጋ ወደ ኋላ መንዳት ጀመርሁ።

እሺ ጎረቤት እና አልፎ ሂያጅስ የእኛን ነገር ያባብስብን ግድየለም፣ የቀሩት
እህትና ወንድሞቼን ድምፅ አለመስማቴ ግን ደነቀኝ፡፡ መቼም በግቢዉ
ዉስጥ ያለዉ ጃሪም ብቻዉን አይመስለኝም: ያም ብቻ ሳይሆን፣ እኔን
ከብቦ እኔንም ግፊ፣ እሱንም ግፋ ይል ከነበረዉ ሰዉ መሀል አንደኛዋ
እህቴ ጭጭ ብላ፣ ልክ እንደሌላዉ ሰዉ ስትታዘበን አይቻታለሁ የሆነዉ ሆኖ በቅቶኛል፡ እየተንገሸገሽሁ ከመንደራችን ራቅ እንዳልሁ፣ መኪናዉን ዳር አስይዤ
አቆምሁትና፣ አብሮ በሚዞረዉ አልጋዋ ላይ ከኋላዬ ያስተኛኋትን ልጄን
ዳበስኋት፡ ቱናትን፡ ትራፊ ምግብ አላበላትም ብዬ የመብያ ሰዓቷን
በጣም አሳልፌባታለሁ፡ አሁን ግን አማራጭ ስለ ሌለኝ፣ ቅድም
ቀማምሳለት የተረፈዉን ቀዝቃዛ ፍትፍትም ቢሆን ማብላት አለብኝ በተጨማሪም እንደ ልማዴ ዓይኔን ጨፍኜ እየተንሰፈሰፍሁ፣ ትንሿን ጣቴን በፊንጢጣዋ በኩል ሰድጄ ካካ ማስባል አለብኝ፡ ይኼንንም በየሦስት
ሰዓቱ ማድረግ ሲጠበቅብኝ፣ ዛሬ ግን አሳልፌባታለሁ በዚያም ላይ
ከጠዋት ጀምሬ ወዲያ ወዲህ ስላልኋት ነዉ መሰለኝ፣ እነዚያ ቁልቁል
የሰረጉ ዓይኖቿ ይበልጡኑ ቡዝዝ ብለዉ ታዩኝ፡

ቱናትን እንደ ነገሩ አቀማመስኋትና፣ ሌላ ሌላዋንም እንደሚሆን እንደሚሆን አድርጌላት ስጨርስ፣ ወደ ነበረችበት መልሼ አስተኛኋት። ከዚያ፣ እመዋን ፍለጋ ወደ ታዕካ ነገሥት ገዳም ማሽከርhር ጀመርሁ።
ምን እየተደረገ እንደሆነ እመዋን መጠየቅ አለብኝ፡፡ መቼም እሷ መልስ
አታጣልንም አሁኑኑ አግኝቻት እስከዛሬ እየናቅሁ ያለፍሁትን ጥያቄ
ሁሉ መጠየቅ አለብኝ፡ ምን እስኪፈጠር ነዉ ከዚህ በላይ? አይበቃም? ኧረ በቃ በቃኝ...

“እመዋን አይተዋታል አባ?” አልኋቸዉ ቄሰ ገበዙን፣ በሥዕል ቤት ኪዳነምሕረ እና ታዕካ ነገሥት በዓታ መካከል ባለዉ ሰፊ አደባባይ አግኝቻቸዉ፡

“እግዚአብሔር ይመስገን: ደህና ዉለዋል?” አሉኝ፣ መንገዳቸዉን ገታ አድርገዉ አቤት ትሕትና! እኔን እኮ ነዉ አንቱ ያሉኝ፡ መቼም ትሕትና ከገዳም ሌላ መኖሪያም የላት! ያልኋቸዉን ባይሰሙኝም፣ ሰላምታ እንዳቀረብሁላቸዉ ገምተዋል።

“እመዋን አይተዋት ይሆን?” ስል አቻኮልኋቸዉ አሁንም፣ ሰላምታቸዉ ጊዜ የሚወስድብኝ ስለመለሰኝ፡፡
#ገረገራ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በታደለ_አያሌው

...ለአንዳፍታም ቢሆን እንኳን ቱናትን መለየት ያሸብራል፡ መቼስ እንዲህ የሚያደርገኝ ልጅነቷ ወይም መላመዳችን ወይ ደግሞ ገዳሜ ስለሆነች ብቻ አይመስለኝም፡ ታዲያ ምንድነዉ?
ብቻ ክብድ ብሎኛል፡

ደረስሁ።

ከጨዋታ ይልቅ ለዝምታ የሚያመቸዉን በትላልቅ ሀገር በቀል ዛፎች የተሞላዉን ግቢ፣ በተለያየ ዕድሜ የሚገኙት ሕጻናት ይቦርቁበታል። አንዳንዶች ክብ ሠርተዉ፣ አንዳንዶች በመስመር ሆነዉ፣ ሌሎች ዝብርቅርቅ ብለዉ የልባቸዉን ይጫወቱበታል፡ አለፍ ብሎ ባለዉ ሜዳ ላይ ሰፊ ምንጣፍ ተነጥፎላቸዉ ጨቅላዎች ይንከባለላሉ ከእነሱ በወራት
ዕድሜ ከፍ ያሉት ደግሞ ራሳቸዉን ችለዉ ለመቆም ይዉተረተራሉ
የሕጻናቱ ተንከባካቢዎች እንደየምድባቸዉ የሚቆሙት ቆመዉ፣ ያቀፉት ደግሞ ተቀምጠዉ በየትዕይንቱ ይደሰታሉ።

መሥራትስ እንደ እነሱ ነዉ› አልሁኝ፣ በቅናት።

ሆኖም ሥጋቴ ሊያልፍልኝ አልቻለም: እንዲሁ ከመኪናዬ ወረድሁና ቱናትን ከአልጋዋ አንስቼ አቀፍኋትና፣ የግቢዉ አማካይ የሚሆን ሥፍራ ላይ ቆምሁ፡፡ በየትኛዉ ቢሮ የትኛዉን ሰዉ ማናገር እንዳለብኝ በዓይኖቼ
ወዲያ ወዲህ ስል አንዲት በልተት ያሉ ሴትዮ ቀረቡኝ፡

“እንኳን በደህና መጣችሁ” አሉ፣ ልብ በሚሞላ ፈገግታ እኔንም
ቱናትንም አይተዉ ይበልጥ እየቀረቡን፡፡

“እንኳን ደህና አገኘኋችሁ” አልሁ፣ አንገቴን ወደ ጉልበታቸዉ
በመስበር ለትሕትናቸዉ ጭምር አክብሮት እየሰጠሁት፡
እዉነትም እነ እመዋ ነገሮችን ጨራርሰዉልኝ ኖሮ፣ ማነሽ የሚለኝ ሰዉ ቀርቶ ቅጽ እንድሞላ እንኳን የጠየቀኝ ሰዉ የለም፡ ቀድሜ ያገኘኋቸዉ ሴትዮ ለቱናት የተመደበላትን ማደሪያ ክፍል፣ ክፍሉን የሚጋሯትን
ሕጻናት፣ ያለማስታጎል እንዲከታተላት የተመደበላትን ነርስ፣ የምግቦቿን ዝርዝር መርሐ ግብር፣ልብሶቿን እና ሌሎች ነገሮችን በዚያዉ በማይለዋወጥ ትሕትናቸዉ ከገለጹልኝ በኋላ፣ ሥጋት ወይም አስታያየት
ይኖረኝ እንደሆነ ጠየቁኝ፡፡

“እንግዲያዉ መዋእለ ሕጻናት ብቻ አይደለማ ይኼማ?” አልኋቸዉ:
“ትክክል። ያዉ እንደምታዉቂዉ” አሉ፣ ደጋገሜ አንቺ እንዲሉኝ
የለመንኋቸዉን እንደ ምንም ተስማምተዉልኝ፡ “ያዉ እንደምታዉቂዉ አብዛኛዉ የማኅበራች አገልጋዮች ሌት ከቀ ሥራ ላይ ናቸዉ። በዚህም
የተነሳ ለልጆቻቸዉ በቂ እክብካቤ ለማድረግ ይቸገራሉ። ይኼ የሕጻናት መዋያ ከተከፈተ ወዲህ ግን እንደየአገልግሎት ጸባያቸዉ፣ ሙሉ ኃላፊነቱን ለእኛ ለመተዉ የተፈቀደላቸዉ አገልጋዮች አሉ: ሥራቸዉ ፋታ የሚሰጣቸዉ ያሉ እንደሆነ ግን ኃላፊነት የም ወስድላቸዉ ወይ ቀኑን ወይ ማታዉን ብቻ ይሆናል ማለት ነዉ” አሉኝ፣ ቱናትን ባዘጋጁላት
አልጋዋ ላይ እያሳረፏት፡
“ታዲያ” አልሁኝ፣ ከሁሉም ቅድሚያ ለቱናት የሚበላ እንዲሰጡልኝ ለመጠየቅ እንደገና እየዳዳሁ የአንገት ሰላምታ በርቀት ሰጥተዉኝ ከነበሩት ሴቶች አንደኛዋ፣ የልቤን አዉቃልኝ ይሁን የቱናትን ቡዝዝ ማለት አይታ እንደሆነ እንጃ፣ ትኩስ የሥጋ ፍትፍት አመጣችላት። ደቀቅ
ያለዉን የሥጋ አመታሮ በቀይ እንጀራ ፈትፍታ አምጥታ ስታጎርሳት እኔ ምራቄን ብዉጥም፣ቱናት ግን እምቢ አለች: ለማጫወት ብትሞክራት ሁሉ ለማልቀስ ተነፋነፈች።

“ግድ የለም” አሉ፣ ባልቴቷ። “ግድየለም፤ እንግድነት ተሰምቷት ነዉ። ትንሽ ትፋሽ ትዉሰድና እኔ አጫዉቼ አበላታለሁ”

“አይ አልሁኝ፣ ሥጋቴን መደበቅ እያቃተኝ፡

“ግድ የለሽም”

“እንዲያዉ ዛሬ እምብዛም ሳትበላ ነዉ የዋለችዉ”

“ሐሳብ አይግባሽ፤ አጫዉቼ አበላታለሁ”

“እንግዲህ ምን እላለሁ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ከማለት በቀር አልኋቸዉ ኹለቱንም፣ ስለ በጎ አድራጎታቸዉ፡
"ተዪ ተዪ: እኛ ነን ማመስገን ያለብን: እንኳንም እግዚአብሔር ልዩ አድርጎ የሰጠሽ ልጅሽ እንድናገለግላት ዕድሉን ሰጠሸን”

“አይ… እንዲያዉ ወድጄ እንኳን አይደለም ያመጣኋት: ልጄ ከብዳኝ ወይ ደግሞ ከእሷ የሚበልጥብኝ ሥራ ኖሮብኝም አይደለም”

“ይገባኛል”

“የሆነዉ ሆኖ እንግዲህ ከኹለት ወይ ከሦስት ሰዓት በላይ
አላስቸግራችሁም”

“ማስቸገር? የለም የለም: ለእሷ ከምናደርግላት ይልቅ፣ እሷ ለእኛ
የምታደርግልን ይበልጥብናል። ከባሪዎቹ እኛዉ ነን''

“ይሁን” ብዬ፣ ወጣሁ።

ለቅሶዋን ከኋላዬ እየሰማሁ፣ እንደ ምንም ጨክኜ ወጣሁ ወደ ጦር ሜዳ እየኼድሁ እንደሆነ ነዉ የሚሰማኝ፡ ከወንድሞቼ እና
ከእህቶቼ፣ በተለይም ከጃሪም ጋር ፊት ለፊት እስከምገጥም ቸኩያለሁ።እሱም ቢሆን ሌላ ምንም ምርጫ አልተዉልኝም፡፡

‹ምን ይሉት ፍርጃ ነዉ ግን? ኧረ እንደ ዋዛ የት ነዉ የደረስነዉ
በማርያም? እያልሁ እንዲችዉ እንደ ተብሰለሰልሁ፣ በአዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ ዋናዉ ግቢ በኩል ባለዉ ቁልቁለት ወረድሁ።

ለነገሩ ለምን በእነሱ ብቻ እፈርዳለሁ? ጥፋቱ የራሴም ጭምር አይደል?እነሱ ሆኑብኝና ተለማመጥኋቸዉ፡ የእኔ በሕይወት መኖር በእነሱ ፈቃድ እስኪመስል ድረስ ግፊያቸዉን ሁሉ ቻልሁላቸዉ᎓ የጃሪም ወንድምነት
ቢቀርብኝ እሞት ይመስል፣ ያለ ጥፋቴ ጭምር ማረኝ ማረኝ አልሁት።

ቆይ፤ እዉነት ግን አልሞትም? ያለ ጃሪም ወንድምነት፣ ያለ እህቶቼ
እህትነት ምንድን ነኝ እኔ?

ወደ ማኅበራችን ሕንጻ የሚያደርሰኝን መንገድ እንደ ተያያዝሁት፣ የዛፍ እና የንብ ሽርክና በልቡናዬ ክችች አለብኝ፡፡
ሠራተኛዋ ንብ ለማኅበረ ንቧ የሚሆነዉን ምግብ ለመቅሰም አበባ ወዳለው ዛፍ ታርፋለች:: ከአበባዉ ላይ የምታገኘዉን ዕጩ ማር ከቀሰመች በኋላ ተጨማሪ ፍለጋ ወደ ሌላ ባለ አበባ ዛፍ ትሄዳለች: ነገር ግን ከዛፋ
በምትነሳበት ጊዜ፣ የአበባዉ ወንዴ ዘር በጸጉራም አካሏ ላይ ተሳፍሮ ይከተላታል። ወደ ቀጣዩ የአበባ ዛፍ በምታርፍ ጊዜም፣ ያ ከዚያኛዉ ዛፍ ያመጣችዉ ወንዴ ዘር፣ እዚህኛዉ ዘንድ ካለዉ የአበባዉ ሴቴ ዘር ጋር ይገናኛል፡ በዚህም ምክንያት፣ ንቧ ምግቧን ፍለጋ ከዛፍ ዛፍ ባረፈች
ቁጥር፣ የአበባ ዛፎች እንዲራቡ ታደርጋለች ማለት ነዉ ንብ ያለ አበባ ማለት እንግዲህ ያለ ምግብ፤ አበባም ያለ ንብ ማለት ደግሞ ያለ መራባት ስለሆነ ተከላክለዉ አያዉቁም:: እርስ በእርስ ቢከላከሉ፣ አንዳቸዉም መኖር እንደማይችሉ ኹለቱም ጠንቅቀዉ ያዉቁታል።

ስለዚህ ንብ እና አበባ አይለማመኑም:: አለመለማመን ብቻም ሳይሆን፣ ነፍሳቸዉ እስኪገባ ድረስ ይዋደዳሉ
እንደ እዉነቱ፣ እኔና ጃሪምም ሆንን ከሌሎች እህትና ወንድሞቻችንም
ጋር ግን፣ አበባና ንብ ብቻ አይደለንም፡፡ ወይ ንብ እና ንብ፣ ወይ አበባና አበባ ነን፡ ያዉም ወይ የአንድ እናት ንብ እናት አበቦች ነን፡፡ እንዲያዉ እሱም አጉል ሆኖ ቢፈርስ ግን፣ ቢያንስ ንቦች፣ ወይ ደግሞ የአንድ እንደ አበባና ንብ እንኳን መሆን እንዴት ያቅተናል?

የእኔም እጅ አለበት፡፡

አዎ፣ አለበት!

እኔ ያለ እነሱ መኖር እንደማልችል ብቻ እንጂ፣ እነሱም ያለ እኔ መኖር
እንደማይችሉ ነግሪያቸዉ አላዉቅም አበባ የንብን ጥቅም ባያዉቅ ኖሮ አያከብረዉም: የማያከብረዉን ደግሞ የሚወድ የለም፡ መናቅን እንጂ፣በእጄ ነሽ፣ ብለቅሽ ያልቅልሻል፣ ተሸከምሁሽ፣ በደልሽኝ ማለትን እንጂ
እንደ'ኔ ማለትን ያስተዋል፡፡ እህትነቴ እንዲተናነቃቸዉ፣ እነ ጃሪም እዚህ እንዲደርሱ የእኔም ሚና አለበት፡፡

“የት ናት?” አልሁት ባልቻን፣ ከራሴ ጋር እንዲህ እየተዋቀስሁ ወደ
ሲራክ ፯ ማዕከል ደርሼ ቢሮዉ ዉስጥ ያገኘሁት ከኹለት ሰዎች ጋር እየተነጋገረ ቢሆንም፣ ምንም ሳይመስለኝ፡