አትሮኖስ
279K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
456 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት


#ክፍል_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ባኞ ቤቱ ውስጥ ጠብ ጠብ ከሚለው የውኃ ድምፅ በተጨማሪ ላይ ላይ የምትተነፍስ ሴት ድምፅ ይሰማል" የመታጠቢያ ገንዳው ውኃ እስከ ወገቡ የደረሰ ሲሆን ካርለት ውኃው ውስጥ ጋደም ብላ
ቀኝ እግሯን ገንዳው ከንፈር ላይ በማስቀመጥ ከግርጌዋ ያለውን የውኃ ማሞቂያ በተመስጦ ትመለከታለች" ከውኃ ገንዳው በስተቀኝ የእጅ መታጠቢያው ከፍ ብሎ ደግሞ በክፍሉ ሙቀት ሳቢያ የሚያዠው መስተዋት አለ የመታጠቢያ ክፍሉ ጠበብ ያለ ቢሆንም ንጹሕና ዘመናዊ ነው ከመግቢያው በር በስተግራ ካለው የቆሻሻ ልብስ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ካኔተራ፣ ሱሪና ጃኬት ተቀምጧል። ከሱ በላይ ሰፋና ረዘም ያለ በነጭና ሐምራዊ ቀለም የተዥጎረጎረ ፎጣ
ተንጠልጥሏል።

ካርለት የገንዳውን ውኃ ቀይራ ሰውነቷን በንጹሕ ውኃ ከተለቃለቀች በኋላ ከገንዳው ውስጥ ወጥታ በጥቁርና ነጭ ቀለም
የአጥር ሥዕል ከተሣለበት ጸጕራማ ምንጣፍ ላይ ቆመች" እርጥቡ ጸጕሯ ትከሻዋና ደረቷ ላይ ተለጥፏል" ከጸጕሯ ወደ ግንባሯ እየተንኳለለ የሚወርደው ውኃ በቅንድቧ ሥር እየሰረገ ተለቅና
ሰርጐድ ያለውን ዓይኗን ያራጥባል” በደረትና ትከሻዋ አካባቢ ቁጥር ቁጥር ያለ የውኃ እንክብል ከመታየቱም ባሻገር ከሴት ብልቷ ላይ ካለው ስስ ጸጕር ላይ ደግሞ በውርጭ ሰሞን ሳር ላይ የሚታየውን የመሰለ ትንንሽ የውኃ ነጠብጣብ ይታያል"

ካርለት ወደ መስተዋቱ ቀረብ እንዳለች ገፅታዋ ከሚያዠው መስተዋት ውስጥ ተከፋፍሎ ታያት። መስተዋቱን ተወት አድርጋ
በእጆቿ ጡቶቿን ጨበጥ ጨበጥ አደረገቻቸው" ቀኝ እጇ ቀኝ ጡቷ ላይ ሲቀር ግራ እጇ ግን ወደ ታች እየተንከላወሰ ጕዞ ጀመረ ወደ ሴት ብልቷ" እጇ የደረሰበትን በዓይኗ ተመለከተችው
ከሰፊው የመስተዋት መስኮትና ላዩ ላይ ከተንጠለጠለው ነጭና
ቡና ዓይነት መጋረጃ አልፎ አልፎ ዧ ብሎ የሚያልፍ የመኪና ድምፅ ይሰማል" ክፍሉ ውስጥ ካሉት ሁለት አልጋዎች መካከል አንድ
ኮመዲኖ አለ። ኮመዲኖው ላይ «ሶኒ» የሚል ምልክት ካለበት ሬዲዮ ካሴት ውስጥ ከዛሬ ሁለት መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በሞዛርት የተቀነባበረው ፒያኖ ሶናታ የሙዚቃ ስልት ድምፁን ሰለምለም
ሞቅ ሞቅ ሰለምለም...እያደረገ ይንቆረቆራል ከመስኮቱ ጠርዝ አካባቢ ሁለት ሶፋና አንድ ጠረጴዛ ያለ ሲሆን ጠረጴዛው ላይ ከግማሽ
በላይ የተጠጣለት የማር አረቄ ይታያል"

ስቲቭ ማርቲን የአደረው «የዞረ ድምር» ዓይኖቹን ከርቸም ያለ እንቅልፍ አጋድሞታል በአዲስ አበባው ሒልተን ሆቴል
በተዘጋጀው የቡፌ ግብዣ ላይ ሦስት ወንበር እንዲያዝላቸው በማዘዝ ሁለቱ የፍቅር ጓደኛሞች ከከሎ ሆራ ጋር በመሆን ምሽቱን ከምግብ ጕዝጓዙ በኋላ መጎንጨቱንና በአፍሪቃውያን ሙዚቃ መውረግረጉን
እስከ እኩለ ሌሊት ሲያስኬዱት ቆይተው ነው ሁለቱ ፍቅረኛሞችና
ከሎ ሆራ «መሥመርህን ለይ» የተባባሉት"

ካርለት እና ስቲቭ የሥራ ቦታቸው በጣም የተራራቀና
የትራንስፖርትም ችግር ያለበት በመሆኑ ተመልሶ ለመገናኘት ቢያንስ የሦስት ወር ጊዜ ያስፈልጋቸዋል" በፍቅር አባዜ ለተያዙት ለእነዚህ ወጣቶች ደግሞ ጊዜው የትየለሌ ነው ሩቅ። ስለ መለያየታቸው እንጂ ስለ መገናኘታቸው የማይተማመኑት ፍቅረኛሞች በወሲብና በፍቅር ጨዋታ ሰዓታቸውን በሚገባ ለመጠቀም በአንድ ወጥ ስሜት ጥረዋል" ድብቅነት በሌለው ንጹሕ የፍቅር ጨዋታ ልባቸውን
ስልትና ቃናው በሚጣፍጥ ቅላፄ እያስጨፈሩ ራሳቸውን በመሆን በፍቅር ባሕር ከመዋኘት አልፈው ዘቅጠውበት አድረዋል።

ካርለት እንደምንም በድኗን ከስቲቭ እቅፍ መንጭቃ ተነሥታ ወደ ባኞ ክፍሉ በመሄድ ገላዋን ተጣጥባ ስትጨርስና በፎጣ ገላዋን
ስታደራርቅ ከስቲቭ ረዘም ላለ ጊዜ የመለየቷን፣ የፍቅርና ወሲብ ጥመኛ የመሆኗን ትርዒት በእዝነ ልቦናዋ ስትቃኝ ፍርሃትና ጭንቀት መንፈሷን ሰንገው ያዙት ተፈጥሯዊ ስሜቷ መኪና አይቶ እንደማያውቅ ፈረስ አእምሮዋን ጥሎ በረገገባት"
አንገቷን ዘንበል በማድረግ መጀመሪያ ጡቶቿን ከዚያም
እምብርቷንና ሰርጓዳ ወገቧን፣ ለስላሳ ጭኖቿን ስትመለከት ስሜቷን
በአእምሮዋ ለመቆጣጠር ተሳናት" ካርለት ስሜቷን ልትጫነው ስላልፈለገች በግዴለሽነት የመታጠቢያ ከፍሉን በር በርግዳ ስትወጣ ስቲቭ ቀኝ እግሩን አጠፍ አድርጎ ጭኖቹን በመበርገድ ተንጋሎ ተኝቷል።

ካርለት ስቲቭን ስታየው የሆነ ስሜት በመላ አካሏ ቅጽበታዊ መተረማመስ ፈጠረና ፍቅር አመንጭ ሕዋሳቶቿ ተከፋፍተው ወደ ፊት ገፈተሯት አእምሮዋም በስቲቭ አካል ላይ ቀስቱን ደገነ የልግጠም፣ ይውጋኝ ፍልሚያ። «ግንኮ የስቲቭ ስሜት እንደኔ ላይሆን ይችላል? ስሜቴን መቆጣጠር መቻል አለብኝ" ሊደከመውም እኮ ይችላል!» ብላ አሰበች" ታስብ እንጂ መንቀሳቀሷን አላቆመችም የሚገፋፋት ስሜት ወደፊት አዳፋት ተጠጋችው» ካርለት ያሰቡትን ለማድረግ መወሰን የሚሳንበት ወቅት መሆኑ ገብቷታል"

«ስቲቭ» አለች የእጅ ጣቶቿን ወደ ቡናማው ጸጕሩ እየሰገሰገች።
ቦንብ ቢፈነዳ እንኳን የሚነቃ የማይስለው ፍቅረኛዋ የእሷን ውብ ድምፅ ሰምቶ ዓይኖቹን ሲገልጥ የሚወደው ምስል እርቃነ ሥጋውን ከአጠገቡ ቆሞ ሲያይ፣ «ኦ...» ብሎ ዓይኖቹን ገለጠ።

«ፍቅር የሚጣፍጠው ሲልሱት ሳይሆን ሲግጡት፣ ኩርሽምሽም አድርገው ሲውጡት፣ ከአካል ጋር ሲዋሐድ፣ የተፈጥሮ ቦታውን
ሲይዝ፣ ደባቂና ተደባቂ ሲሆን እንጂ በቃላት ድርደራ አይደለም»ብላ የምታምነው ካርለት ለስቲቭ፣ «ና» የሚል ምልክት በእጇ አሳየችው ያ እጇ ሁሌም ከሚያስደስተው አካሏና ውስጣዊ እሷነቷ
እንደሚያደርሰው ያውቃልና ተከተለው።

በጣም ደክሞታል፤ ከካርለት እጆችና የፈገግታ ኃይል ግን ራሱን ሊለይ አልተቻለውም። ስለዚህ ወደ ተጠራበት አቅጣጫ ተጓዘ ጒዞው ራቀበት ከተጠራበት አካል ቶሎ ደርሶ ለመደሰት በጣም ጓጕቷል ካርለት ባኞ ቤት ውስጥ እንደገቡ ገፍትራ ለብ ካለው ውኃ
ውስጥ ከተተችው ሣቀ ሣቀች ሁለመናቸው ተሣሣቀ
ጭኖቿን ተመርኵዞ አንጋጦ ሲያይ የገነትን በር ያየ መሰለው ታዲያ የዚያን ውብ ስፍራ በር ከፍቶ የማይገባ ማን አለ? በየጅማቱ ሥር ተበታትኖ የነበረው ኃይል ዘቅዝቆ ወደ ብልቱ ሲንዶለዶል
ተሰማው" ያ የተበታተነ ኃይል እንኳን የተፈቀደለትን፣ ሌላ ጠንካራ በር እንኳ ጥሶ የሚያስገባ ኃይል እንዳለው አመነ።

«እወድሃለሁI ፍቅርህን አልጠግብምI ስግብግብ ነኝ እንድትለቀኝ አልፈልግም...» የሚል ድምፅ የሰማ መሰለው
የቃላት ምልልስ ወቅቱ አለመሆኑን በመረዳቱ ግን እግሮቿን እየዳሰሰ
ተነሣ ሁለቱ አካሎች ተዋሐዱ ፍጡር ካለ ክንፍ ወደሚንሳፈፍበት ወደ ሰማየ ሰማያት ተነጥቆ የገነትን ውበት ወደሚጎበኝበት ማራኪ መዓዛ ውብና እንከን የለሽ ተፈጥሮ ወደሚታይበት፣
እውነተኛ የፍቅርና የደስታ ዜማ ወደሚዜምበት ዓለም ተያይዘው ነጐዱI በሩ ተከፍቶ ተዘጋ።

።።።።።።።።።።።
ካርለት አልፈርድ በኦhስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በሶስዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ካገኘች በኋላ በዩኒቨርሲቲው የአንትሮፖሎጂ
ዲፓርትመንት አባል በመሆን በወቅቱ ታዋቂ በነበሩት አንትሮ ፖሎጂስቶች የተዘጋጁትን ጽሑፎችና ዲስኩሮች ተከታትላለች።

ከአሥራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን በተለይም ሳይንስና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ እመርታን ካሳየበት ከዛሬ መቶ ሃምሳ ዓመት ወዲህ እየተዋጡ
የመጡት ቅርሶች፣ የተናቁት ባህሎችና ለከፍተኛ ውጤት ሊያበቁ የሚችሉት የአርኪዮሎጂና የሌሎችም ጥናቶች የምሁራኑን አእምሮ ይበልጥ በመሳባቸው እንደ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ አሜሪካና ጃፓን የመሳሰሉት ምሁራን ትኵረት እንደ ሰጡት እንግሊዛውያንም ምሁራንም በመስኩ እጅግ ተስበው ነበር"
👍46
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከኢትዮጵያ ጥናትና ምርምርና ከሌሎች ተቋማት ለጥናቷ
አስፈላጊ የሆኑትን ውጤቶች ካነበበችና ከግለሰቦች ጋር ሐሳብ
ለሐሳብ ከተለዋወጠች በኋላ እግረ መንገዷን ሊረዳት የሚችል የክልሉ ተወላጅ አድራሻ፣ የጥናትና የጕዞ ፈቃድ አውጥታ ወደ
ጥናት ቦታዋ ከመጓዟ በፊት ምሽቱን በአዲስ አበባው ሒልተን እንግሊዝ ኤምባሲ ከሚሠራውና ለተወሰኑ ወራት በአዲስ አበባው
ቆይታዋ ጠረኑን ከለመደችው ጓደኛዋ ጋር እቅፉ ውስጥ ስትንቀሳቀስ
አድራ እንደገና ገላዋን ታጠበችና ልብሷን ለባብሳ ወጣች"

በአስተሳሰቧ፣ በግልጽነቷና በውበቷ የነሆለለው ስቲቭ
አለባበሷን፣ ከሰዓታት በፊት ፍቅር አመንጪ የነበረው አካሏ ተለውጦ ለሥራ መዘጋጀቷን ሲያይ እሱ ፍቅር ከፈጠረው የደስታ
ዓለም ከነበረበት ፈጽሞ ሳይንቀሳቀስ እሷ ግን ገስግሳ ወደ ገሐዱ
ዓለም በመመለሷ በፍጥነቷ ተደንቆ በተመስጦ ሲመለከታት ቆየና፣

«የኔ ቆንጆ አሁንም ታምሪያለሽ» አላት።

«ማማሬን እርሳው» አለችው።

«ለምን?»
«ከጥቂት ሰዓታት በፊት እኔም እረስቸዋለሁና።»

«የኔ ቆንጆ፣ ታዲያ ምን እንድልሽ ትፈልጊያለሽ?»

«የጉጉትን ዘዴ፣ የንስርን ማስተዋል፣ የአንበሳን ልብ፣ የኢዮብን ትዕግሥት፣ የአባትሽን ተስፋ አይቆርጤነትና አእምሮ ይስጥሽ በለኝ» ብላ፣ ጉንጩን ሳም አደረገችው"

ስቲቭ አስተያየቱን ጠለቅ አድርጎ ሲያስተውላት ቆየና፣ «አሁን አንችን የመሰለ ውብ ከእነዚያ ዘላኖች...» ሊናገር የፈለገውን ሳታስጨርሰው አፉን በአመልካች ጣቷ ከደነችው።
«ማፍቀር ያለብህ እኔን ብቻ ሳይሆን ፍላጎቴንም እንዲሆን እፈልጋለሁ" ትልቁ ውበት ደግሞ ሥራ መሆኑን አትዘንጋ» አለችውና ሌላ ቃል ሳይለዋወጡ ለቁርስ ክፍሉን ቆልፈው ወጡ"
  ።።።።።።።።።።።።።
ፈርጠም ያለ፣ የቀይ ሽንኩርት ቅርፅ መሳይ አፍንጫ ያለው! ዳጐስ ብሎ ቀላ ያለውን ከንፈሩን ሲገልጥ ነጫጭ ፍልጥ ጥርሶቹ የሚያማምሩና ከሸበላው ቁመናው ጋር የተስተካከለ አቋም ያለው
ከሎ ሆራ ለየት ያለ ባሕርይ ይታይበታል።

ቁጥብነቱን፣ ጅንንነቱን፣ ጥርጣሬውንና ብቸኝነት መውደዱን ያዩ ጓደኞቹ፣ «ነብሮ» ይሉታል የዩኒቨርሲቲ ጓደኞቹ" ቀልድ፣
ቧልት ከጀመሩለት እንደ ቆሰለ ጎሽ በንዴት ጦፎ ይፎገራል" ከሰው ጋር ደጋግሞ እንደ መጣላቱ ግን ኃይሉን ተማምኖ ተማቶ
አያውቅም" ሁለቴ ሦስቴ ቃጥቶ ቃጥቶ ማንም በማይገባው ቋንቋ
አኩተምትሞ ዘወር ይላል" ታዲያ ብዙዎቹ አዳልጧቸው ቀልድ ብጤ ጀማምረው በዚያ ፈርጣማ ጡንቻው በሰነዘረ ቁጥር ጠረመሰን
እያሉ አንዴ ከተሳቀቁ፣ «እርም» ብለው ይሸሹታል" ስለዚህ ምን እንደሚያበሽቀው ያለፈው ሕይወቱ ምን እንደሚመስል፣
ብቸኝነቱ ከመቼ ወዲህ እንደ ጀመረው ከፍቶ ማየት የሚችል ሰው አልተገኘም ግለቱ ስላላስቀረበ"

የተማሪን ቆብ አውላቂ መምህራን በለመዱት ቧልት «ጢብ ጢብ» ሊጫወቱበት ይዳዳቸውና እንደ ከለመዳሪ የሚነፋውን
ከንፈሩንና እሳት ተፊ ትናንሽ ዓይኖቹን ሲያዩ በተለይም
በአንቀሳቀሰው ቁጥር እንደ አሎሎ የሚንከባለለውን ጡንቻውን ሲመለከቱ! «በቸር አውለኝ» ብለው አቅጣጫቸውን ሲቀይሩ
ዓመታት ተቈጠሩ“

ከሎ ሆራ የአራተኛ ዓመት የሶሲዮሎጂ ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ በተቃረበበት ወቅት በቀጭን ወገቧ ጂንስ ሱሪዋን በቀላል «ቲሸርት» አስተካክላ ለብሳ፣ የተጐነጐነ ረዥም ጸጕሯን ወገቧ ላይ እያላጋች፣ ቶሎ ቶሎ በመራመድ ጫማዋን ቀጭ ቋ ቀጭ ቋ እያደረገች የምትገሰግሰው ወጣት ከዩኒቨርሲቲው ፖስታ ቤት ወረድ ብሎ ከሚገኘው ኮሪደር ጫፍ ላይ ቁጭ ብሎ እግሩን እያወዛወዘ!
ጠጠር ወደሚወረውረው ጥቁር ወጣት ተጠግታ፣ «ይቅርታ ከሎ ሆራ ነህ አይደለም?» ብላ ጠየቀችው፣ በእንግሊዝኛ"

«አዎ ነኝ» አለ ከሎ፣ ከተቀመጠበት ሳይንቀሳቀስ"

«ካርለት አልፈርድ እባላለሁ" እንግሊዛዊት አንትሮፖሎጂስት
ነኝ" ስለ ሐመር ሴቶች ጥናት ለማድረግ ዓላማ አለኝ" አንተም የሐመር ተወላጅ መሆንህን ከዲፓርትመንትህ ኃላፊ ጠይቄ አረጋግጫለሁ» አለችና ንግግሯን በመግታት ትኵር ብላ ተመለከተችው
ከሎ ሆራ፣ የመርበትበት ስሜት አሳየና ከተቀመጠበት ፈጥኖ ተነሣ
ላብ ከወደግንባሩና ቅንድቡ አካባቢ ችፍፍ ችፍፍ ሲል ከንፈሩ አመድ የነሰነሱበት መሰለ።

«ሶ ለምን ፈለግሽኝ?» አላት በተቆራረጠ ድምፅ
«እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ» አለችው፣ በዓይኗ እየመረመረችው
«እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ?» ብሎ አባባሏን ደገመና ለትንሽ ጊዜ የመመሰጥ ሁኔታ አሳይቶ፣

«አዝናለሁ፣ ልረዳሽ አልችልም» አላት"

ካርለት፣ የከሎ ሰውነት ሲለዋወጥና ከብስጭቱ ጋር ሲታገል ያስተዋለች መሰላት ስለዚህ ወጣቱ ከሷ ያለበለዚያም ራሱ ከራሱ
ጋር ያልተግባቡት ወይንም ለእሷ ግልጽ ያልሆነላት ሌላ ምክንያት እንዳለው በመረዳቷ ተጨማሪ ጥያቄ ሳታነሣ፣ «አመሰግናለሁ“ ነገ
ግን ጊዜ ወስደህ ካሰብክበት በኋላ ሐሳብህን ከቀየርክ አይ.ኢ.ኤስ
ልታገኘኝ ትችላለህ ካለዚያም ስልክ ቁጥሬን ልሰጥህ እችላለሁ» ብላ፣ ፍጹም ልብ በሚነካ ፈገግታ የአድራሻዋን ካርድ ሰጥታው
«ደህና ሁን» እያለች፣ እጇን አውለብልባለት ሄደች"

ከሎ ሆራ ወደ መቀመጫው ሲመለስ፣ የሚሰበቀውን ወገቧንና ጀርባዋ ላይ ከብለል  ከብለል የሚለውን ጉንጉን ጸጕሯን ሲመለከት
ሐሳቡ ሸፈተበት" ከዓይኑ እስክትሰወር ድረስ በመደመም ሲመለከታት ቆየና ከጥቂት ደቂቃ በፊት የነበረበትን ድንገተኛ ሁኔታ ለማስታወስ ሞከረ» «ሐመር ጥናት ውብ እንግሊዛዊት የሐሳብ
ፍጥጫ፣ የተዳፈነ እሳት ጭረት.እሳት ጫሪ አንትሮፖሎጂስት...ወጣትና ውብ...ዳሚት» አለ፣ እጆቹን ከተቀመጠበት ደረጃ
ጋር እያላተመ።
  ።።።።።።።።።።።።።
ልቡ የአዶከበሬ አታሞ ይመስል እየተነረተ፣ ሰውነቱ ፀሐይ እንዳቆረናው የበረሃ ባልጩት ድንጋይ እያተኮሰ፣ እንቅልፍ ሲመኝ ግን ሲነቃ፣ ዕረፍትን ሲሻ፣ ሲንጠራወዝ፣ ሲገለባበጥ፣ በሐሳብ
ሲድህና ፎቀቅ ፎቀቅ ሲል አድሮ ዋለ"

ብዙ አወጣ አወረደI ያለፈ የልጅነት መጥፎ ትዝታውንም አስታወሰ" አሁን ሊያደርግ የማይፈልገውን እንዲያደርግ ግብዣው
ቀርቦለታል" ሌላው ቀን አልፏል። ለዛሬ ሥሩ ትናንት ነው" ትናንት ደግሞ እሱ የመከራ ጽዋውን የጨለጠበት ወቅት ነው" ዳግመኛ ሬት ሊያወርድ የሚችል ጉሮሮ የለውም” ስለዚህ በትናንት ቂም ያረገዘው አእምሮው አጓርቶና ድብልቅልቁ ወጥቶ እንዲሟሟና እንዲተን
ይፈልጋል" ችግሩ እንዳሰበው ለማድረግ አቅሙ አለ ወይ ነው።

የልጅነት ጊዜው መጥፎ ትዝታ ጥርሱን አግጥጦ፣ ጥፍሩን በማሾል፣ የታባክ ይለዋል“ ይኸኔ እንደ ልጅነቱ ልጅ ይሆንና በጭንቀት እየተንቦራቸ ይርበተበታል" ሊጮህ ይፈልግና ድምፁ
አልወጣልህ ይለዋል" ትናንት ከገደል ውስጥ ወጥቷልI ዛሬ ግን ወደ
ገደል ተገፍቶ ለመግባትና ለመሞት ዝግጁ አይደለም" መሞትም አይሻም ለምን?

እንግዲህ ችግሩ ያለው በትናንትናና በዛሬ መካከል ነው" ልጅ ከነበረው ከሎና አሁን በአካልና በአእምሮ ካደገው ከሎ መካከል
አንዱ ሽሽቱን ማቆምI አለበለዚያም፣ «በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ» እንዲሉ፣ በፍርሃት ላይ የጅብን ፍርሃት እያከለ ወደ ኋላ ሳያይ የሕይወትን ሩጫ መሸምጠጥ አለበት።

ትንሹ ከሎ ማምለጥ፣ መሸሽ ይፈልጋል ከሐመር። ትልቁ ከሎ ደግሞ ልቡ ከሁለት ቦታ ተንጠልጥሎበታል" ከሎ ውሳኔው ሲከብደው ካርለት ከተወችለት ካርድ ላይ በብዕር የተጻፈውን ስልክ
ቁጥር ተመልክቶ ስልክ ደወለ" «ሔሎ ከሎ» አለችው እንደ ሕፃን
ተቁነጥንጣ።

«...ደህና ነኝ» አላት"
«ምነው ልትገልጽልኝ የምትፈልገው ጉዳይ አለ?» አለችው።

«ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ» አለ ከሎ።
👍29
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሁለት ሳምንት አለፈው ካርለትና ከሎ የየራሳቸውን የጕዞ ዝግጅት ሲያደርጉ ሰነበቱ። ከሎ ሐመር ሲሄድ የሚያነባቸው ልብወለድና
ታሪክ ነክ የአማርኛ መጻሕፍት፣ መጽሔቶች፣ በእንግሊዝኛ የተጻፉ
ልብወለድና የሳይንስ መጻሕፍትን እየገዛ ከፊሉንም እየተዋሰ
አዘጋጀ"

በተለይም ካርለት ኮተቷ በዛ" በማስታወሻዋ በዝርዝር ከያዘችው
አስፈላጊ የምግብ ዓይነቶች የታሸገ የዓሣ፣ የአሳማ፣ የከብት ሥጋ የድንች የዱባ፣ ያጃ ሾርባI የፓፓያ፣ የብርቱካን፣ የአናናስ
ጭማቂ ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር የበዛበት ብስኩት ደረቅ ብስኩት የቆርቆሮ ቢራ ወዘተ ከመድኃኒ ዓይነትም ክሎሮኪን፣ ፓልዱሪን፣ ኒቫኩይን ለወባ መከላከያI ሌሎች፣ «አንቲባዮቲክስ» መድኃኒቶችንና የመጀመሪያ ሕክምና ኪት ኮዳክ ፊልሞችI ባትሪ
ድንጋዮችI ሶፍቶች ወዘተ. በአራት የፕላስቲh ሣጥኖች ደረደረች" ካኖንና ፔንታክስ ካሜራዋንና የተለያየ መጠን ያላቸውን ሌንሶች
በእጅ በሚንጠለጠለው ቦርሳዋ ካኪ ሱሪዎች፣ ካኔትራ፣ ውስጥ
ሱሪ ፎጣ፣ ጡት ማስያዣ፣ ስሊፒንግ ባግ፣ ግራጫ  መልክ ያለው ሹራብ በአየር የሚሞላና ሌላ ተጣጣፊ ፍራሽ፣ ሳሙና፣ ኦሞ፣
ከሁለት መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በሞዛርት የተቀነባበሩ የፒያኖ ሶናታና የፒያኖ ኮንቸቶ የቤቶቪን ሲንፎኒ ከሦስት ጊዜ በላይ
የወርቅ ዲስክ አሸናፊው ድምፃዊ የቢሊ ጆይል፤ ከሦስት መቶ ዓመት
በፊት የነበረውና የሲንፎኒ አባቱ የሃይደን እንዲሁም ሌሎቹን የባሮክ
ክላሲካል፣ ሮማንቲክና ዘመናዊ የሙዚቃ ካሴቶችን፣ ማስታወሻ፣
ብዕር መጻሕፍትና መጽሔቶች በአራት ማዕዘኑ የብረት ሣጥን
ውስጥ ከተተች" ለሽፍን ላንድ ክሩሰር ቶዮታ መኪናዋም በሁለቱም
ታንከር ነዳጅ ሞላች“ አምስት ጀሪካን ናፍጣም ለመጠባበቂያ ያዘች
ካርለት ለሦስት ወራት የሚያስፈልጋትን ቁሳቁስ ካሟላች በኋላ
ቀሪውን ዕቃዋንና ገንዘቧን ስቲቭ በሰጣት ክፍል ውስጥ
አስቀመጠች» ለአንዳንድ ወጪ ብላ የያዘችውን ሦስት ሺህ አምስት
መቶ የኢትዮጵያ ብርም በሹራቧ ውስጥ በሰፋችው ስውር ኪስ፣
አንገቷ ላይ በምታንጠለጥለው የጨርቅ ቦርሳና ብረት ሣጥኑ ውስጥ
አhፋፍላ ያዘች
ሰኞ ጠዋት ልክ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ላይ አራት ኪሎ ሞቢሉ
ጎን ካለው ሱቅ በር ላይ በቀጠሯቸው ተገናኙu ካርለት ልጥፍ የኋላ
ኪስ ያለው ካኪ ሱሪ፣ ተረከዙ ፕላስቲክ የሆነ ሽፍን ባለማሰሪያ
ማ፣ ቡና ዓይነት ቲ–ሸርት ለብሳ፣ አንገቷ ላይ አነስ ያለ ነጭ ፎጣ
ጣል አድርጋ፣ ከመኪናው በመውረድ የከሎን «ዩኤስኤ» የሚል
ወስፋት የነፋው የሕፃን ሆድ መስሎ የተወጠረ ቦርሳ የኋላ በሩን ከፍታ
በዕቃ ከሞላው መኪና ውስጥ በአንድ በኩል ባለው ክፍት ቦታ
አስገባችና ወደ መኪናው ውስጥ ገቡ" ካርለት የውኃ ኮዳዋን፣ ዳቦ
የያዘ ላስቲኳን አቀረበችና ከከሎና እሷ መካከል ካለው የካሴት ሣጥን
የሞዛርትን ፒያኖ ሶናታ ወደ መኪናው ቴፕ አስገብታ ማስታወሻዋን
በማውጣት የተነሡበትን ሰዓት መዘገበች" ከዚያም ፈገግ ብላ
«መሄድ እንችላለን?» አለችው።

«ኢ ህ» አላት ከሎ፣ ዝግጁ መሆኑን አንገቱን በማወዛወዝ እየገለጸ። ካርለት፣ ቀኝ እጇን ማርሹ ላይ በማስቀመጥ፣ በግራ እግሯ ፍሪሲዮኑን እረግጣ፣ የመኪናውን መስተዋት አየትየት በማድረግ
በአራት ኪሎው የድል ሐውልት ወደ ቀኝ ታጥፈው፣ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት አድርገው ቁልቁል ወደ መስቀል አደባባይ ወረዱ።
ከዚያም በደብረ ዘይት መንገድ ወደ ቃሊቲ፣ አቃቂ፣ዱከም ተጕዘው ደብረ ዘይት ከተማ ሲደርሱ ወደ ግራ ታጥፈው ሁለት ኪሎ ሜትር በመጓዝ ዠመኪናዋን ሆራ ሆቴል አቁመው ለቁርስ ወደ ውስጥ ገቡ" በስተጀርባ፣ ከሐይቁ ትይዩ የመርከብ ላይ መናፈሻ ከሚመስለው ስፍራ ሆነው የተለያዩና ቱር ቱር እያሉ በመዘመር
የሚበሩ አዕዋፍን እያዩ ቁርሳቸውን ተመግበው ወጡ" ካርለትና ከሎ
ሆራ በሞጆ ታጥፈው፣ ወደ ሻሸመኔ ጕዟቸውን ተያያዙ“ ካርለት፣በመንገዱ ግራና ቀኝ የግራር፣ የጥድ፣ የኮሶ፣ የዝግባ...ዛፎችንና
የተለያዩ ቀለም ያላቸውን እፅዋት እያየች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ከሚኙት ከሃያ በላይ አዕዋፋት ውስጥ የምታያቸውን በመልክና
በቅርፃቸው ለማወቅ በጆን ጂ ዊሊያምስና በኖርማን አርሎት የተጻፈውን የአዕዋፍ ምስል፣ ቀለም ባሕርይና የሚገኙበትን አካባቢ እያየች ተጓዙና ለምሳ በስምጥ ሸለቆ ካሉት ሐይቆችና የመናፈሻ ቦታዎች አንዱ ወደሆነው ወደ ላንጋኖ ከመንገዱ ወደ ግራ ታጥፈው ገቡ"

ላንጋኖ ሆቴል ምግብ ቤት ብዙ የውጪ ሀገር ዜጎች፣ አፍሪቃውያንና ኢትዮጵያውያን ክብ እየሠሩ በመጫወት ይመገባሉ። ከሆቴሉ ውጪ በቀላል ድንኳን ጥግ፣ በዋና ውስጥ ሱሪና ጡት ማስያዣ
ሆነው የፀሐይ ክሬም ሰውነታቸውን የሚቀቡና ሐይቁ ዳር ለዳር
የሚዋኙ ሴትና ወንዶች ይታያሉ" ጥቁርና ነጭ ሕፃናትም በመዋኛ
ፕላስቲክ ውኃውን በማንቦራጨቅ እየተንጫጩ ይጫወታሉ ከሎና ካርለት ከምግብ ቤቱ ትይዩ የፀሐይ ጃንጥላው ውስጥ
ተቀምጠው ቡናቸውን ሲጎነጩ ቆዩና ካርለት የሐይቁን ዳር ትርምስ
አሸጋግራ ስትቃኝ ቆይታ፣ «ሐይቅ ዳር ስሆን እረካለሁI አገሬ ውስጥ ከጓደኞቼና ቤተሰቦቼ ጋር ያለሁ ስለሚመስለኝ የደስታ ስሜት ይሰማኛል" በአውሮፓ፣ ብዙዎች መዝናኛዎች የሚገኙት ባሕር ዳርቻ ነው" ብቻ...» ካርለት ከሎ ሆራን በጎን ተመለከተችው“


«ኢ ህ» አላት እግሮቹን ወደፊት በመዘርጋት ሰውነቱን ለጥጦ" ካርለት የከሎ ሆራ ጠባይ ደንቋታል ግን አልከፋትም" በቀላሉ ከምትግባባቸው ሰዎች ይልቅ አስቸጋሪ ባሕርይ ያላቸውን ታከብራለች" ሁሉም ሰው ሊረዳው የሚችል ባሕርይ ያላቸው ሰዎች ለሷ አያረኳትም" እረቀቅ ያለ ባሕርይ ያላቸውን ግን አእምሮዋን
አስደንሳ መላ ፈጥራ፣ የተለያየ ስልት በመጠቀም እንደ ግል ሬዲዮና መከፈት መዝጋት እንደ መቻል
የምትረካበት ነገር የለም።
ለዚህም ካርለት «ዘመናችን የሚርጠው ልዩና ውስብስብ አስተሳሰብ ያላቸውን ነው" ምክንያቱም የነገው ፈጠራና ብሩህ
ሕልም ህላዊነት በመዳፋቸው መሃል ያለው ከእነዚህ ዓይነት ግራ
አጋቢ ባሕርይ ካላቸው ሰዎች ነው» ብላ ታምናለች።

ከሎ ቅንና ተባባሪ ሰው መሆኑን፣ ነገር ግን ይህን ባሕሪውን የሚገልጽ የቃላት ድርደራ ችሎታ የሚጎድለው መሆኑን ተገንዝባለች" ካርለት ከሎን የተለያዩ ነገሮችን እያወራች
እየጠየቀች የቱ እንደሚያስደስተው፣ የቱ አፍንጫውን እንደሚ
ያስነፋውና ጥንካሬውን ከደካማ ጎኑ ለመለየት ምርምሯን ስለ ቀጠለች
አንድ ወጥ በሆነው የሥውር ባሕርይው ዋሻ ለመግባት ትልቁ
የድንጋይ መዝጊያ ማንቀሳቀስ ጀምራለች።

«አዎ የከሎ ባሕርይ ራሱ መጠናት የሚገባው ነው" እሱን ለማጥናት ግን አስፈላጊውን ቁልፍ ማዘጋጀት አለብኝ» አለች
ካርለት፣ ከሻሸመኔ ከተማ ወጥታ የአርባ ምንጭን መንገድ ስትይዝ"
ከሻሸመኔ ትንሽ ራቅ ብለው የአስፋልቱ ጐዳና አልቆ ኮረኮንቹን መንገድ ሲጀምሩ ግን መኪናዋ እየተገጨች ስትንሰጠሰጥና ከፊት
ለፊቷ ያሉትን መኪናዎች ስታልፍና ከእሷ ተቃራኒ የሚያልፉት መኪናዎች የሚያነሡት አቧራ መኪናዋ ውስጥ እየገባ ማፈን
ሲጀምር፣ ካርለት መኪናዋን አቁማ፣ ጸጕሯን በመሸብለል፣ ቆብ
ደፋችበትና መኪናዋን በማንቀሳቀስ ከመሪው ጋር መታገል ጀመረች"
👍20🔥1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከሎ ከተቀመጠበት ስፍራ ላይ ጕልበቱን ሰብሰብ አድርጎ በመታቀፍ ከንፈሩን እያኘከ የሚተነፍገውን የወይጦ በረሃ የእፅዋት
ሽታ ይምጋል ከየጉድባው ወጥተው ድብልቅልቅ በሚያደርግ ድምፅ የሚያገሱት አንበሶች፣ በቀጭንና ወፍራም ድምፅ ጨለማን ተገን አድርገው ድምፃቸውን በነፃነት የሚያስተጋቡትን የአራዊት
ትርምስ እያዳመጡ ሁለቱም በሐሳብ ተውጠው ቆዩ"

ከዋክብት ሰማዩ ላይ ሆጨጭ ብለው ብርሃናቸውን ብልጭ
ድርግም ሲያደርጉ፣ ገና የተወለደች ጨረቃ ካለአቅሟ ግዙፉን
ጨለማ ከዝሆን ጋር እንደሚታገል ዝንብ በብርሃን ድል ለማድረግ
ከተራራው አናት ወደ መሃል ሰማይ ስትገሰግስ፣ በበረት የታጎሩት ከብቶች እያመነዠኩ ሲያቃስቱ፣ ካርለትም ሆዷ እየተሸበረ፣
በምትፈጥረው ወኔ ግን እራሷን እየደለለች እንደ ከብቶች ላይ ላይ
እየተነፈሰች ታቃስታለች።

የወይጦ በርሃ በተለይም በቀትር ላይ ሙቀቱ እንደ ደመራ እሳት ይጋረፋል" የአራዊቱና የእፅዋቱ አካል ሳይቀር በሙቀቱ ስለሚቀረና አካባቢው ለየት ባለ ሽታ ይታፈናል" በዚህ ወቅት እንግዳ ሰው እንደ
ውሻ እያለከለከ የሚስበው አየር ፍለጋ አፍንጫውን እንደ አንቴና አቁሞ ያንጋጥጣል። ሆኖም ግን የፀሀይ ማኅበረሰብ፣ ሰጎን፣ አንበሳ፣ የሜዳ ፍየል፣ ጉርኑክና የመሳሰሉት እንስሳት በደስታ ተዝናንተው
ይኖሩበታል።

የወይጦ በረሃ ግለት እየቀነሰ ሲመጣ የፀማይ ማኅበረሰብ አባላት
ከማሳ፣ ከወንዝ፣ ከከብት ጥበቃ፣ ከአደን፣ ከማር ቆረጣ፣ከመንገድ...
ወደየመንደሩ ሲከት፣ ከተለመደው ውጭ ነጭ መኪና፣ ጸጕሯ ረዘም ያለ ነጭ ሴት፣ ልብስ የለበሰ ጠይም ከተሜ መንደራቸው
ውስጥ ድንኳን ከትመው አገኛቸው" በዚያን ወቅት፣ ድፍን የፀማይ ኗሪ ስልክና ሌላ መገናኛ ባይኖርም የሰማው ላልሰማው መልእክቱን በቃል እያስተላለፈ፣ ቤት ለቤት የሚውሉ ሽማግሌና ባልቴቶች ሳይቀሩ «ነጭ በቆሎ» የመሰለችውንና ብልጭልጭ ቅራቅንቦ
የተቀረቀበባትን መኪና፣ ለማየት ጎረፉ።

በካርለት ጸጕርና እጅ ላይ ብዙ የፀማይ «ተመራማሪ» እጆች አረፉበት እንደ አንበሳ ጐፈሬ የለሰለሰ ጸጕር፣ እንደ እብነ በረድ የነጣና የለሰለሰ ገላ፣ የትንባሆ አጢያሽ የመሰለ ጥርስ ሲመለከቱ፣
«ይህች ሰው ምንድ ናት?» ብለው ሲደነቁ ቆዩ። ከመካከል አንዱ፣
«ፈረንጅ ናት» አለ፣ ነቃ ያለው።

«ፈረንጅ...ኡ» አሉ፣ በአድናቆት አፋቸውን እየያዙ“

«አሃ ፈረንጅማ ከሆነች ያች በፍየልና ማር ከነጋዴ
የምንለውጣት የሽጉጥ ጥይት የመሰለችው የፈረንጅ መድኃኒት ትኖራለች» ተባባሉ እርስ በእርሳቸው ከሎ ሆራ ፀማይኛ አይችልም
አንዳንድ ፀማዮች ግን ሐመርኛ ስለሚችሉ መድኃኒቷን እንድትሰጠን
ጠይቅልን አሉት፥ ለምልክት አንድ የ«ቴትራሳይhሊን» እንክብል እያሳዩት" ፀማዮች ካርለትና ከሎ ቋንቋቸውን ባለመቻላቸው በተለይ
ሴቶችና ጎረምሶች ግራ ገብቷቸዋል፣ «ሆሆይ ለካ እናንተዬ ፀማይኛም የማይችል ሰው አለ!» ብለው ተሳልቀዋል።

በዚህ መልክ ራቁታቸውን የሆኑ ሕፃናት፣ ጎረምሳና አዋቂ ወንዶች ግልድም ያገለደሙ፣ ከወገባቸው በታች የለበሱት ቆዳ
መሬት ለመሬት የሚጎተት ትንሽ እንጨት ያለበት ሴቶች ካርለትን እንደ ጉድ ተመለከቷት እሷም እነሱን በተመስጦ እየተመለከተች
የሁለት ወገን ጉዶች ካለ ቋንቋ በጥቅሻ ሲነጋገሩ፣ አንዱ ሌላውን ለመግባባት ሲጣጣር ቆይተው የምሽቱ የአራዊት ትርምስና ጨለማ
ሳያሸብራቸው በየአቅጣጫው በመሄድ ቀስ በቀስ ተበታተኑባት"።

ካርለት፣ hአዲስ አበባው ሒልተን ሆቴል ወደ አርባ ምንጩ በቀለ ሞላ ሆቴል፣ ከአርባ ምንጩ ሆቴል ወደ ድንኳን አዳር እየወረደች
የምትበላውም መጠኑና ዓይነቱ በጣም እየቀነሰ
ቢመጣም፣ በጣም የተቸገረችበት ጉዳይ ሌላ ነበር። እስከ አሁን
እንዳስተዋለችው ፀማይ መንደር ውስጥም ሆነ መንገድ ላይ ሽንት ቤት አላየችም። ለመጸዳዳት ወደ ጫካ ሲገቡ ተመልhታለች" እሷ ደግሞ ጫካ ሄዳ መጸዳዳቱን ሕሊናዋ ሊቀበለው አልቻለም" በጕዞዋ ባሳለፈችው ቆይታ በሶፍት እየተጸዳዳች በማቃጠል፣ እየተጠቀመች
ነው። ሐመር ስትሄድ ግን በዚሁ መልክ መቀጠል የሚቻላት አይሆንም" ሽንት ቤት አስቆፍራ እንዳትጠቀም ለአካባቢው እንግዳ ሁኔታ በመፍጠሯ መልካም ግንኙነት ላይኖራት ነው“ ስለዚህ ሊታይ
በማይችልና መጠነኛ ጥልቀት ባለው ጉድጓድ መጠቀሙን እያሰበችበት ነው።

በእርግጥ እንኳን ካደጉበት ባህል ውጭ ላተወሰነ ጊዜ
ከተከታተሉት ባህልን ለየት ወዳለ ሲገባ የመጨነቅ ስሜት መፈጠሩ
የነበረ ነውና ካርለትም የኢንግላንድ ዘመናዊነት፣ የለንደን ከተማ፣
ማንችስተር የሚገኙት አያቶቿ፣ የወንድና ሴት ጓደኞቿ፣ መዝናኛዎች፣ የጭፈራ ቦታዎች ቀርተው ራቁታቸውን ከሚሄዱ ጥቋቁር ሰዎች፣ ከከብቶች በረት፣ ከፍየልና በጎች ጋጥ አካባቢ መሆንዋ
ሕልም እንጂ እውን ሊመስላት አልቻለም።

ካርለት ወደ ኢትዮጵያ ለጥናት ከመምጣቷ በፊት የአገር ቤቱን ሕይወት ለመለማመድ ወደ ስፓኝ በመሄድ «የስፓኝ በር» ተብላ በምትታወቀው የሁልቫ ከተማ የበጋ መዝናኛዋን በማድረግና ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በብርቱካንና የሱፍ ማሳ አቅራቢያ ተቀምጣ ፀሐይ ላይ ብዙ መቆየት፣ ብርድና፣ ብቸኝነትን ለመለማመድ ሞካክራ ነበር።ያን ጊዜ የወደፊት የጥናት ቦታዋ በአሥር እጅ ከዚያ ሊለይ
እንደሚችል ብትገምትም አሁን ግን ዘጠና ዘጠኝ እጅ ያላሰበችውና
ያልገመተችው ዓይነት ሆነባት"

ካርለት እንዲህ በሐሳብ ጉና ስትንጨዋለል፣ እያንቋረረ
የሚከፈተውን የከሎን ጕሮሮ ስትሰማ ከሰመመኗ ተመለሰች።ከዚያም ዓይኗንና ሕሊናዋን ወደ እሱ መለሰች።፣

እስከ አሁን ከከሎ ጋር ባደረገችው ቆይታ ካላናገሩት የማይናገረው ጥቁሩ ወጣት በራሱ ፍላጎትና አነሳሽነት፣ ሊያወጋት መዘጋጀቱ ሳያስደንቃት አልቀረም።
«ሚንጊ ነኝ» አለ ከሎ ድንገት።

«ምን?» አለች ካርለት፥ የጠቀሰው ቃል አልገባሽ ብሏት

«ሚንጊ ማለት በሐመር ቋንቋ ገፊ ማለት ነው» አሁንም የባሰ ተደነጋገረችI ስለዚህ፣ እንዲግባቡ ለማድረግ ገለጻውን ሰፋ አድርጎ ጀመረ።

«ሕፃን ልጅ በሽማግሌዎች ፈቃድ ይወለዳል።»

«ካለ ሽማግሌ ፈቃድ መውለድ አይቻልም? ለመውለድ የሽማግሌዎችን ፈቃድ እንዴት ይጠየቃል? ሽማግሌ የተባሉት ልዩ
ችሎታ ያላቸው ሰዎች ናቸው?» ካርለት ልጅ ለመውለድ ሲያስፈልግ የሐኪም፣ ካስፈለገም የሥነአእምሮ ጠቢብ ምክር
ሊጠየቅ እንደሚችል ታውቃለች" ይህም ቢሆን ችግር ያለባቸውና
በማኅበራዊ ጠንቅ ውስጥ እንዳይዘፈቁ የሰጉ ሰዎች የሚፈጽሙት እንጂ ለማንኛውም ዜጋ የተደነገገ ሕግ አይደለም" ሆኖም፣ ሽማግሌ የተባሉት ለየት ያለ ችሎታ ያላቸው ይሆናሉ ብላ ገመተች።

«አንችን ለማስረዳት ለኔ ከባድ ነው" በኋላ ቀስ በቀስ
ልታውቂው ትችያለሽ ሽማግሌ የተባሉት ግን በዕድሜና በልምድ
ተደማጭነት ያላቸው ሲሆኑ ማንም የሐመር ማኅበረሰብ ሴት ባሏ ጥሎሽ ጥሎ እሱ ዘንድ ካመጣት በኋላ አንድ ቅል አሸዋና አንድ ቅል
ወተት ይዛ ወደ ክልሉ ሽማግሎች ዘንድ ትሄድና ትመረቃለች"ከዚያም ወተቷን ትሰጥና አሸዋውን የያዘውን ቅል ቤቷ አምጥታ
ግርግም ላይ ታንጠለጥለዋለች" ከዚያ፣ ከባሏ ጋር የግብረሥጋ
ግንኙነት አድርጋ ፅንስ ከፀነሰች፣ ወደ ሽማግሎች ሄዳ መፀነሷን ታስታውቃለች። አንዴ መፀነሷን ሽማግሎች ከሰሙ፣ ባሏና እሷ
ፅንሱ አድጎ ከተወለደ በኋላ ጥርስ ማብቀል እስኪጀምር ድረስ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አይፈጽሙም።»
👍30
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


...ካለ ሽማግሌ ፈቃድ የተወለደ ግን እንደ እርኩስ ስለሚቈጠር የማደግ ዕድል አያገኝም" የማስወረድ ዘዴውም ልምድ ያላቸው ሰዎች በማኅፀን ውስጥ ያለውን ፅንስ  ጭንቅላት ከውጭ በኩል በመዳሰስ ሲያገኙ ጭንቅላቱን በሁለት አውራ ጣታቸው ውስጥ ደጋግመው በመጭመቅ..» ሲል ካርለት ፊቷ በስሎ የተበላሸ ቲማቲም መሰለ፣ ከንፈሮቿ ተንገረበቡ፣ መላ አካሏ ራደ"

ከሎ ግን ንግግሩን ቀጠለ፣ «...እድታስወርድ ይደረጋልI ከተወለደም ሕፃኑ ጫካ ይጣላል። ስለዚህ አንድ የሐመር ሴት በሽማግሎች ፈቃድ ማርገዟ ከታወቀ በኋላ ከባሏ ጋር ግንኙነት ሳታደርግ ፅንሱ አድጎ መውለጃዋ ሲደርስና ምጥ ቢይዛት በአካባቢዋ የሚኖሩ
ሴቶች ይሰበሰቡና እጅና እግሯን ጥፍር አድርገው ይዘው፣ አፍዋን ያፍኗታል" ይህም ልጁ የእናቱን ማኅፀን ለቆ ተፈትልኮ
እንዲወጣ ይረዳል» ሲል ካርለት ፍርሃት መላ አካሏን አንገጫገጨው። እሷም እንደታፈነች ሁሉ ልቧ ዘለለባት።

«ውልጃ ባፈና? በምጥ ላይ ሌላ ምጥ? » ከሎ ግን ጨዋታውን ቀጠለ።

«እንግዲህ እንደ ነገሩ ታርሳ ራቁቱን ለተወለደው ሕፃን መታቀፊያ፣ ፎጣ፣ ሙቀት፣ ጂኒ ጃንካ ሳያስፈልገው የቡና ውኃ በማጠጣት
አቀባበል ይደረግለታል። ልጁ ቁሩንና ሙቀቱን ተቋቁሞ አደግ እያለ
ሲመጣ ግን እናቱ ከማማጡ በላይ ትጨነቃለች አባትም ውስጥ
ለውስጥ ይሳቀቃል።

የሚጮኸው ጅብ ሆድ ዕቃዋን፣ የከሎ ወሬ ደግሞ ሕሊናዋ አተረማመሰባት። ትሰማዋለችI የምትሰማው ግን ለማወቅ ሳይሆን
በቃ ከአቅሜ በላይ የሆነ ‹አስፈሪ ነው ብላ መናገር ተስኗት ነው ደንታ ቢሱ ከሎ ግን ጨዋታውን ቀጠለ"

«በሐመር ማኅበረሰብ ላም፣ በሬ፣ በግ...ጥርስ የሚያበቅሉት በታችኛው ድዳቸው ስለሆነ ‹ቅዱስ› ሲባሉ አህያ፣ ፈረስ፣ ጅብ...
ጥርስ የሚያበቅሉት በላይኛው ድዳቸው በመሆኑ እርኩስ ይባላሉ"
የሰው ልጅም የመጀመሪያውን (የወተት ጥርስ ማብቀል የሚገባው
እንደ ቅዱሳን እንስሳት በታችኛው ድዱ መሆን ሲኖርበት፣ እንደ እርኩሳን እንስሳት በላይኛው ድዱ ካበቀለ ከእርኩሳን እንስሳት እንደ አንዱ ስለሚቆጠር ለማኅበረሰቡ አይበጅም ቢያድግም አባቱ
የሚጋፋ፣ የሚገድል፣ የሚበጠብጥ ስለሚሆን ገፊ ወይንም በአካባቢው አጠራር «ሚንጊ» ተብሉ ይጣላል።
«ጥርስ እንደማብቀሉ ሁሉ መውለቁ ላይም በቅድሚያ መውለቅ የሚገባው በታችኛው ድድ የበቀለው ጥርስ መሆን ሲገባው፣
በላይኛው ድዱ የበቀለው ጥርስ ቀድሞ ከወለቀ ሚንጊ ነው ተብሎ
አሁንም ይጣላል ከዚህ በተጨማሪም፣ ሕፃኑ የታችኛው ጥርሱ ከመውለቁ በፊት በአጋጣሚ እንኳ ወድቆ ወይንም በሌላ መንገድ
የላይኛው ጥርሱ ቢወልቅ ሚንጊ ተብሎ ከማኅበረሰቡ እንዲወገድ ይደረጋል» ከሎ ሆራ «ኢ ህ አለና፣

«እና እኔም እንደነገርኩሽ ሚንጊ ነኝ» አላት"

«ታዲያ አንተ ‹ሚንጊ ነህ› ተብለህ ተጥለህ ነበር?» ካርለት፣ ካለማብራሪያ መልሱን በአሉታ ወይንም በአወንታ እንዲመልስላት
በሕሊናዋ እየተማጸነች ጠየቀችው"

«አዎ!» ብሎ፣ ጭንቅላቱንና ትከሻው ላይ በጦር የተወጋውንና በድንጋይ የተፈነከተውን አሳያት" ከዚያ ቀና ብሎ ጨለማውንና
ከዋክብቱን ተመለከተና እንዴት አድርገው እንደ ጣሉት ጨዋታውን
ሲቀጥል ካርለት በሕሊናዋ «ከሎ ለእኔም የሚያዝን አንጀት ይኑርህ እንጂ» በማለት፣ እየተብሰከሰከች የማይቀርላትን ጨዋታ ለመስማት ጉንጯን በጣቶቿ ደግፋ፣ ዓይኖቿን በማፍጠጥ ዓይን ዓይኑን
ተመለከተችው"

«እኔ የተወለድኩት ሐመሮች ተሰባሰቡበት ከሚባለው የቡስካ ተራራ ስር ላላ ከተባለው መንደር ነው" እናቴ በንቲ ኃይሎ ትባላለች" አባቴ ደግሞ ሆራ ሸላ ይባላል። እናቴ ለአባቴ አምስተኛ ሚስት ስትሆን፣ አምስት ልጆችም ወልዳለታለች" እናቴ፣ በልጅነቴ ሁል ጊዜ በምትለብሰው ቆዳ ሸፈን አድርጋ ከሰውነቷ ጋር ትለጥፈኝና ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ቆይታ፣ «ጨዋንዛ» በሚባል ሸካራ ቅጠል
ጥርሴን ትሞርድልኝ ነበር" በወቅቱ ባይገባኝም ኋላ ኋላ ግን የተጣልሁበትን ምክንያት ስሰማ የጥርስ አበቃቀሌ በትክክለኛው መንገድ ማለትም መጀመሪያ በታችኛው ድዴ፣ ቀጥሎ በላይኛው ድዴ ነበር አሉ የበቀለው" ይሁን እንጂ፣ አንድ ጊዜ ጥጃ
ለመመለስ ስሮጥ ወድቄ የላይኛው ጥርሴ አንዱ ወለቀ፣ አንደኛው
ተሸረፈ። እንዳበቃቀሉ ሁሉ፣ በቅድሚያ የታችኛው ድዴ ላይ የበቀለው ጥርስ መውለቅ ሲገባው፣ የላይኛው ጥርሴ ቀድሞ
በመውለቁ፣ ለአደጋ ተጋለጥሁ" እናቴ፣ በሸካራው የጨዋንዛ ቅጠል
ጥርሴን ስትሞርድልኝ የነበረው ለካ የታችኛው ድዴ ጥርስ ቀድሞ የወለቀ ለማስመሰል ኖሯል"

«ይሁን እንጂ፣ ጥረቷ ከንቱ ነበር" ወድቄ ሳለቅስና ጥርሴ ወልቆ ያዩኝ ሰዎች ለሽማግሎች መንገራቸው አይቀሬ ነበር" እናም አንድ
ቀን አባቴ ባልነበረበት ወቅት፣ ሚንጊ የተባሉ ልጆችን የሚጥሉ
ሽማግሎች ወደ እኛ ጎጆ መጡ" እናቴ፣ ከርቀት እንዳየቻቸው ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ሰውነቴን እንቦሳዋን እንደምትልስ ላም እየሳመችና እየላሰች አለቀሰች።

«ከእናቴ ጋር በተለያየ አጋጣሚ እንለያይ ነበር ከብቶች በድርቅ ጊዜ እርቀው ሲሄዱ፣ ወደ ማሳ፣ ለገበያ ወዘተ.ስትሄድ ሁለትና ሦስት ቀናት፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ከዚያም በላይ እንለያያለን ታዲያ ስንለያይ እናቴ ታለቅሳለች እኔ ግን የእሷ ሁኔታ ቢረብሸኝም
ተሎ ወደ ጨዋታዬ እመለስ ነበር። የዛን ቀን ሽማግሎች፣ «ጥርሱ
አስወልቀን እናምጣው» ብለው፣ በጠንካራው እጃቸው ትንሿን እጄን በጨመቁ ቁጥር ግን እንባዬ ሳያቋርጥ ይንዠቀዠቅ ነበር"
«እናቴ ሽማግሎች ጥርሱን አስወልቀን እናምጣው ብለው ሲጠይቋት ካለምንም ተቃውሞ ገፋ አድርጋ አሳልፋ ብትሰጠኝም! ትከሻዋን በሁለት እጆቿ አቅፋ፣ ድምፅዋን አጥፍታ፣ አምርራ
ስታለቅስ ለአደገኛ ሁኔታ እንደተጋለጥኩ ገመትሁ" ሆኖም ግን ምን እንደሚደርስብኝና ለምንስ እንደምቀጣ አላወቅሁም ነበር"

«ሁለቱ ሰዎች ከመንደራችን እያራቁ ሲወስዱኝ እናቴ እጇ
እያርገበገበች ስታለቅስ ትታየኝ ነበር። እንዲያውም እስከ አሁን ድረስ እንኳ ሰው እንደ እሷ ስፍስፍ ብሎ ሲያለቅስ አይቼ
አላውቅም"

«ከመንደራችን ብዙ ርቀን ወደ ጫካው ውስጥ እስክንገባ ሽማግሎች ምንም ሳያወሩኝ ሄድንና የሆነ ገደል አጠገብ ስንደርስ ከፊለፊታቸው ወደነሱ ሳልዞር እንድቆም ነገሩኝ" እኔ ግን፣ ያሉኝን
ለመፈጸም ስላልተቻለኝ ዘወር ስል፣ አንደኛው ሽማግሌ ጦሩን ወደ
ትከሻዬ ሲሰድ ተመለከትኩኝ" ከዚያ በኋላ ሰውነቴን ሲወጋኝና
ለመጮህ ስሞክር፣ ገፍትረው ወደ ገደሉ ከተቱኝ ገደሉ ውስጥ የነበረው ድንጋይ ደግሞ እራሴን ተረተረኝ፤ ደም ፊቴን አለበሰው የሞት ሞቴን ግን የእናቴን፣ የወንድሜን፣ የአባቴን...ስም እየጠራሁ
ጮሁኩ" የደረሰልኝ ግን አልነበረም።

«ስለዚህ፣ ጉድጓድ ውስጥ እንደሆንኩ ስጓጉር ውዬ አድሬ፣ ጠዋት ላይ ድምፄ ተዘጋ። ረፈድፈድ ሲል የሰው ድምፅ ሰማሁ"
የሰማሁት ድምፅ ግን የሰው ቢሆንም ቋንቋው የማውቀው ሐመርኛ
አልነበረም" ለመጣራት ብሞክርም ድምፄ እምቢ አለኝ።

«የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ፣ አንዷ በልቅሶ የተዘጋውን ድምፄን ሰምታ ኖሮ፣ አብረዋት ከሐመር ቆቄ ከተማ የመጡትን ሴቶች ጠርታ በድንጋጤ ተያይዘው ሄዱ መሰለኝ ድምፃቸው ጠፋብኝ" ብዙ ቆይቼ
ግን፣ እንደገና የወንዶችና ሴቶች ድምፅ ተሰማኝ ከወላጆቼ ጋር ሳለሁ፣ እነዚያን መሳይ ሰዎች ወደ መንደራችን ሲመጡ፣ በፍርሃት ፈርጥጬ እሮጥ ነበር" ሆኖም ግን፣ የማልፈራቸው የኔ ወገኖች
ስለጨከኑብኝ መሰለኝ፣ አለባበሳቸውንና ቋንቋቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ከጉድጓድ ውስጥ አውጥተው የሚበላ ሲሰጡኝና ሲያሳክ
ሙኝ፣ አንድም ተቃውሞ አላሰማሁም"
👍23
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ዲመካና ቱርሚ ሁለቱም የሐመር አውራጃ የገጠር ከተሞች ናቸው" ለቆላማው የሐመር ክፍል ቱርሚ፣ ለደጋማው ደግሞ ዲመካ
አማካዮች ሲሆኑ፣ ሁለቱም ደረቅና ቁጥቋጦ የበዛበት መሬት ያላቸው ናቸው። ቱርሚ መንገድ ዳር ያለ ከተማ ሲሆን፣ ከዲመካ ይልቅ ሁለት ትናንሽ ምግብ ቤቶች፣ ወደ አምስት የሚደርሱ ሻይና ቂጣ
መሸጫ ቤቶች፣ ሁለት በመጠን ከፍ ያሉና ትናንሽ ሳሙና፣ ባትሪ ድንጋይ፣ ክብሪት...የሚሸጥባቸው መንገድ ላይ የሚዘረጉ ሱቆች አሉ። በተለይም በገበያ ቀን ከተማዋ ደመቅዐመቅ ብላ ትታያለች
ገበያ ውስጥ ለመጠጥ ቦርዴና የአበሻ አረቄ፣ ግልድም የሚሆን ከጥጥ
ተሠርቶ ከኮንሶ በነጋዴዎች የሚመጣ ሳዳጎራ፣ ጨሌና አንባር፣በቆሎና ማሽላ ዓይነተኛ ሸቀጦች ናቸው" ቱርሚ፣ በከብት እርባታና
በቁፋሮ ምርት ለሚተዳደረው የሐመር ሕዝብ ድል ያለች ከተማ፣
ታምሮና ተውቦ የሚታዩባት፣ ጐረምሳና ሴቱ አብሮ መሸታ ገብቶ የሚደባበስባት፣ የተጣላ የሚታረቅባት፣ ሽማግሎች ተሰባስበው
የሚመክሩባት፣ ብርቅዬ ከተማ ናት ለሐመሮች።

ዲመካ ግን፣ ከዋናው መንገድ ወጣ ብላ፣ ሰቀላ ቤቶች በአራት ማዕዘን ተሰትረው የሚታዩባት ከተማ ናት። በየሰቀላ ቤቶች ፊት ለፊትና በስተኋላ የግራር፣ የብርብራ.ዛፍ ያለ ሲሆን ከከተማው ግርጌ፣ ከወንዙ ጥግ በሚስዮናውያኑ የተተከለ በፀሐይ ብርሃን በሚንቀሳቀስ መስኖ የለማ የፍራፍሬ፣ የበቆሎና ሌሎችም ወቅታዊ
አዝርእቶች የሚታይ ሲሆን፣ ከጎን በኩልም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሕንፃና ጋራዡ፣ ዲመካን አንድ ዓይና ከመሆን አድኗታል"የገበያ ቀን፣ በየሰቀላ ቤቱ ጠጅ የሚሸጥ ሲሆን፣ ምግብ ቤት ግን ከናካቴው የለም" ደግነቱ፣ እንግዳ ብርቅ በመሆኑ ጋባዡ ብዙ ስለሆነ
እግር የጣለው ሰው ሕቅ ብሎ ሲያዝን አይሰማም" በተረፈ ገበያ ውስጥ ያለው ሸቀጥ ከቱርሚ ጋር ተመሳሳይ ነው ሁለቱንም ከተሞች ቡስካ ስር ካሉት ላላና ሻንቆ እስከ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዳ
መንደር ድረስ የሚያገናኛቸው የማኅበረሰብ ሕይወት የሆነው የከስኪ ወንዝ ነው ከብቱ፣ ፍየሉ፣ በጉ፣ ሰው፣ አዕዋፍ...ሁሉም ጥሙን
ይቈርጥበታል።

ካርለትና ከሎ ሆራ ከዲመካ ወጣ ብላ ከምትገኘው የሻንዛ መንደር መኖር ከጀመሩ ሁለት ወራት አለፋቸው የክልሉ ኗሪዎ
ከሎ ሆራን እንዳዩ፣ «የሆራ ሻላ ልጅ» እያሉ፣ ሰላምታና ስጦታ አጐረፉለት ቆዳ ለባሽ እናቱና እኅቶቹም ደረታቸውን በመድቃት
የደስታ እንባ እያነቡ አስተናገዱት።

ካርለት፣ በቆይታዋ የተለያዩ ልምዶችን አገኘች። ከዘመናዊ ሕይወቷ እንደ ባንዲራ ወርዳለችI ይህን አጋጣሚዋን ግን በግላዊ
ትርጕሟ እንደ መጥፎ ከመውሰድ ይልቅ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰዷ የሚሰማት ስሜት የደስታ ስሜት ነው። ይህ ደግ
ማኅበረሰቡን ለመቅረብና ለመርዳት እንድትጣጣር አድርጓታል ስለዚህ፣ ካርለት የከሎ ሆራን እናትና እኅቶች፣ የአካባቢው ሴቶችና ወንዶች ለመቅረብ የቋንቋ ትምህርቷን በማጠናከር ልትግባባ ሞክራለች ቢሆንም ግን፣ በወደፊቱ ጥናቷ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት
እየሆነባት የመጣው በሴቶች ላይ ያለው ባህላዊ ተፅዕኖ እንደ ጋለ ብረት ምጣድ አላስጠጋሽ አላት"¸

በማኅበረሰቡ፣ ሴት ሣቂታ ወንድ ኰስታራ ነው" ሴት በልጃገረድነቷ የአባቷ፣ ባል ካአገባች ደግሞ የባሏ ጥገኛ ናት" ስለዚህ
በልባዊ ኵራት የተሞሉት የሐመር ወንዶች ካርለት ሴት ሆና እንዴት ባሏን ወይንም አባቷን ጥላ ወደ እነሱ እንደ መጣች በጣም
አስገርሟቸዋል" ሽማግሎች እንዲያውም፣ «ይእ! እሷ ምን ታድርግ? አባቷ ወይም ባሏ፣ ብቻዋን መልቀቃቸው ከቶ ምን ያሉ ነፈዞች ቢሆኑ ነው» ብለው አውግዘዋል"
ስለሆነም፣ ካርለት የጥናት ኮተቷን ይዛ ለጥያቄ ቀረብ ባለቻቸው ቍጥር የደስታ ገጽ ስለማታይባቸው ለተወሰነ ቀን ግራ ተጋብታ
ነበር" አንድ ቀን ግን ወንዶች ሊያደርጉት ባሰቡት ስብሰባ ለመካፈል ሄደች። ገላጣ ስፍራ ላይ ካለ ትልቅ ግራር ጥላ ሥር፣ የሻንቆ መንደር
ሽማግሌ፣ አባወራ፣ ጐረምሶች ተሰብስበዋል" ከወገብ በላይ ራቁት
ሆነው፣ ቆዳቸው የተሸበሸበ፣ ጸጕራቸው ገለል ብሎ ሽበት ጣል
ጣል ያደረገበት አዛውንት በሁለት ወገን ጦር የተሰካበት ብትር ይዘው፣ መሬቱን ወጋ ነቀል እያደረጉ ወዲያ ወዲህ እየተንቀሳቀሱ
ንግግር ሲያደርጉ ሁሉም ጸጥ ብሎ በተመስጦ ሲያዳምጥI ካርለት
ስብሰባውን ለመካፈል ጓጕታ ቀስ እያለች ተጠግታ ልትቀመጥ ስትል
ሁሉም ዘወር ብለው አይዋትና በስብሰባው መካፈል እንደማትችል
ነገሯት"

ካርለት፣ ወንዶችን ለመቅረብ አለመቻሏ ብቻ ሳይሆን፣ ሴቶችም
ምሥጢራቸውን ሊገልጹላት ባለመቻላቸው ግራ ተጋብታ ቅር ተሰኘች" በተለይ ደግሞ፣ ለመሳተፍ ጓጕታለት በነበረው የወንዶች
ስብሰባ ልትካፈል ባለመቻሏ ጥልቅ ኀዘን ከመስማት አልፎ ለወደፊቱ አደርገዋለሁ ብላ የደከመችለት ጥናት ሊሳካ አይችልም ብላ ሠጋች"
ስለዚህ፣ ዓይኗ ቁንዶ በርበሬ መስሎ እስኪቀላ ድረስ እያለቀሰች፣ «ከሎ! ለምን ወንዶች ጥያቄዎቼን ለመመለስ ፈቃደኛ
አይሆኑም? ለምንስ በስብሰባቸው እንዳልካፈል ይከለክሉኛል? በዚህ
ዓይነት ጥናቴንስ እንዴት ማድረግ እችላለሁ? » ብላ ጠየቀችው።

«በሐመር ማኅበረሰብ ሴት ወንድን ለመርዳትና ለማገልገል የተፈጠረች ጸጋ ናት። ለወንዶች ትንባሆ ታዘጋጃለች ልጃገረድ
ከሆነችም ታርሳለች፤ የከብቶችን በረት ታጸዳለች ሕፃናትን ትንከባከባለች ምግብ ታበስላለች.እንጂ ከወንድ ጎን ተቀምጣ ስለ
ማኅበረሰቡ ችግር በመነጋገርና በመምከር መፍትሔ መፈለግና ጦርነት
መግጠም አትችልም።

«ካርለት፣ አንቺ ወንድ ብትሆኚ ኖሮ ምንም ችግር ላያጋጥምሽ ይችል ነበር" ሆኖም ግን አንቺ ሴት ነሽ። ለሐመር ሴቶች የወጣው
ደንብ ማንኛዋንም ሴት ያጠቃልላል፣ ብለው ስለሚያምኑ በስብሰባቸው እንድትካፈይ አለመፍቀድ ብቻ ሳይሆን፣ የምትጠይ
ቂያቸውንም ሙሉ በሙሉ ለመመለስ ፈቃደኛ አይሆኑም" እኔም
ይህ ችግርሽ እጀ ሰባራ ሊያደርግሽ እንደሚችል እየተሰማኝ መጥቷል" ምናልባትም ችግሩ ግልጽ ከሆነልሽ የግልሽን መፍትሔ
ውሰጂ» አላት"

ካርለት ፈጽሞ ያልጠበቀችውን መልስ በማግኘቷ በባህላዊ
ልዩነቱ በጣም ተሸማቀቀች በአሁኑ የጥናት አያያዟ በእርግጥ ለመቀጠል አለመቻሏ ቁልጭ ብሎ ታያት በአእምሮዋ አውጥታ
አውርዳ የወሰነችው ውሳኔ፣ እስከ አሁን ያደረገችው ጥረትና ጒዞ ጥሩ የድንጋይ ምት እንዳረፈበት መስተዋት ከሽ ብሎ ሊሰበር
የተቃረበ መስሎ ታያት። ያ ችሎታዋንና ጥንካሬዋን የሚያስመሰክረው፣ ማንነቷን የሚያረጋግጠው፣ ብቃቷን ማያዋ መስተዋት
እንዲሰበር ግን ጭራሽ አትፈቅድም። በዚህም ተባለ በዚያ የጀመረችውን ከግቡ ለማድረስ ሕሊናዋ እሷን ወደፊት መግፋት
አለበት" ሰዎች ከጎሪላና ከእፉኝት፣ ከአንበሳና ከተኩላ ጋር በሐሩርና
በረዶ መኖር መቻላቸውን አስመስክረዋል" እሷም ዓላማዋን ከግቡ
ለማድረስ ተጣጣፊና ጠንካራ ለመሆን ከራሷ ጋር ተማማላች" ግን ምን መላ ትምታ? ለተወሰነ ቀን ካለ ዕረፍት በዚህ ጉዳይ ላይ ስታስብ ከቆየች በኋላ ምንም እንኳ የችግር ኮተቱን ዓይኗን ጨፍና አላይም
ብትልም፣ የሚያጋጥማት ሥቃይ ከባድ መሆኑን አውቃ ቀበቶዋን አጠበቀች

ከዚያም፣ ያሰበችውን መላ ለመጀመር ያስችላት ዘንድ ባል አለማግባቷን የሚገልጽ ወሬ ለአገኘችው ሁሉ አወራች" ወሬው ተዛምቶ በየመንደሩ መዳረሱን ስታረጋግጥ ደግሞ ጐረምሶች፣ ወጣት
ባለትዳር ወንዶች፣ ያላገቡና ባለ እጮኛ ልጃገረዶች ምሽትን ተገን አድርገው ወደሚቦርቁበት የምሽት ጭፈራ «ኢቫንጋዲ» ለመካፈል ነኢማ ከምትባለው የከሎ ሆራ እኀት ጋር ስትሄድ ምንም ተቃውሞ ሳይደርስባት ቀረ።
👍271
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሦስት ወራት አለፈ" ካርለት በሐመር ቆይታዋ ብዙ ልምድ አካበተች ያልጠበቀችውንም እርካታ አገኘች ካርለት ከሎን ወደ ዲመካ፣ ቱርሚና ጂንካ ከተማ ሲሄዱ እግረ መንገዷን መኪና ማሽከርከር ስላስለመደችው መረዳዳት
ጀምረዋል" ካርለት በሐመር ኑሮዋ ዕቃዋን፣ ገንዘቧን ለማስቀመጥ የምትተማመነው በመኪናዋ ውስጥ ነው፤ በተለይም ሙዚቃ ለማዳመጥ መኪናዋ ከፍተኛ ጥቅም ትሰጣታለች" በነዳጅ በኩል እስከዚያ ወቅት ድረስ ችግር አላጋጠማትም፤ ካስፈለጋት ግን ጂንካ ከተማ ናፍታ ማግኘት እንደምትችል ተረድታለች።

የሐመር ሰማይ ጥርት ያለና አልፎ አልፎ ብን ያለ የጥጥ ባዘቶ መሳይ ዳመና ይታይበታል” የዝናቡ ወቅት፣ እምብዛም የሚያስተማምን ባይሆንም፣ ድንገት እያጓራ የሚያጋሽብ ጥልመት ዳመና ከታየ «አህያ» የማይችለው ዝናብ፣ መዓቱን ያወርደዋል" በዚህ
ወቅት የዕጽዋት ቅጠሎች እንደ በረዶ ብን ብን እያሉ ሲወድቁ ከብቶች ጅራታቸውን ሸጒጠው፣ ጆሮአቸውን ይጥላሉ።

በዚህ ወቅት፣ የከሰኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ዛፍ ቅጠሉን እያተራመሰ፣ ባሕርይውን ይቀይርና በመደንፋት፣ እየተነሣ ይፈርጣል"
በዚያን ጊዜ ከሰኬ ወንዝና የሐመር ማኅበረሰብ፣ ከብቱ፣ ፍየሉ፣ ይኰራረፋሉ «አትድረስብኝ» አንመጣብህም ይባባላሉ"
አንድ ጊዜ፣ ካርለትና ከሎ መዝነቡን ሳያውቁ ከጂንካ ወደ ሻንቆ ሲሄዱ፣ ከሰኬ ወንዝን በመኪና ገብተው ሊሻገሩ ሲሉ መኪናዋ
በአሸዋው ተያዘች እነሱም ከመኪናቸው ወርደው በዶማና አካፋ
ለማውጣት ሲሞክሩ «ፉ..ፉ..ፉ.» የሚል ድምፅ ሰሙ። ቀና ሲሉ ደረቱን ገልብጦ፣ የሚጣደፍ ደራሽ ውኃ ተመለከቱ። ካርለትና ከሎ ብርክ ይዟቸው እንደ ሕፃን ልጅ ተንቦራቹ። ውኃው ግን ገሰገሰ ካርለትና ከሎ ዳር ላይ ሊደርሱ ሲሉ ውኃው ሲያጠናግራቸው
ተንገዳገዱ፤ ሳያስቡት እጅ ለእጅ መያያዛቸው ግን በጃቸውና ለትንሽ
አመለጡ። ደራሽ ውኃው መጀመሪያ መኪናዋን እያነቃነቀ ፈተሻት፣
ቀጥሎ በጎኗ፣ ከዚያም በጭንቅላቷ አቆማት።
«አምላኬ!» አለች፣ ካርለት መኪና የሚያገለባብጠው ውኃ እነሱን ቢያገኝ እንዴት ብትንትናቸውን እንደሚያወጣቸው እያሰበች።

ዛፉ «ቋ..ቀሽ.."ቀሽቀሽ...» ይላል፤ ግንድና ቅጠሉ ብቅ–ጥልቅ ይጫወታሉ፤ ውኃው፣ ሣር ቅጠሉን ያግበሰብሳል" መኪናዋ ጎማዋ ሲታይ ቆይታ በጎኗ ተጋደመች። ደራሽ የውኃ ሙላቱ ግን ለማንም
በሚያስገርም ሁኔታ እየቀነሰ፣ እየቀነሰ መጣና ጸጥ አለ። ካርለትና
ከሎ መኪናዋን ማውጣት ባለመቻላቸው፣ በየቦታው የተገነደሰውንም
ግንድ ለብቻቸው ማነቃነቅ የማይሞከር በመሆኑ፣ የሻንቆን መንደር
ኗሪ በእግር ሄደው ጠርተው፣ በስንት ችግር መኪናዋን ሊያወጡ
ቻሉ" ስለዚህ፣ ሐመር ላይ ዝናብ ሲዘንብ ከስኬ ሰው፣ ከብት፣ መኪና ሳይቀር ስለሚወስድና ስለሚያሰምጥ ምሱን አያጣም፤ ከብቱን፣ አራዊቱን፣ ሰውን...ድንገት ጠልፎ በመዋጥ የቆየ ልምድ አለው። ካርለትና ከሎ በቆይታቸው የተለያዩ ዕጽዋትንና ጥቅማቸውንም ተረድተዋል። ወንዴና ሴቴ ቃጫ ለገመድና ቤት ሥራ፣
ጠዬ ለዱላ፣ ሌልሜ ለቤት ሥራ፣ ፌጦ ለመፋቂያ፣፣ ኩንኩሮ ለተለያየ ጥቅም፣ ፊላና ሰንበሌጥ ለቤት ሥራ እንደሚውሉ ተረድተዋል።
በተረፈ ጨው ሊንባ፣ እንኮይ፣ ዘምባባ፣ አጋም፣ ጨዋንዛ፣ ግራር
ወዘተ የሐመርንና የአጐራባቾችን መሬቶች አስውበው ሲመለከቱ፣
ከመንፈስ እርካታው በተጨማሪ አንዳንዶቹን መጠቀም ችለዋል።
ካርለትና ከሎ ሻንቆ፣ ላላ፣ ወሮ፣ ዴንባይቴ፣ ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዴ...መንደሮች ሲዘዋወሩ ከማኅበረሰቡ
አባላት ጋር ከሚገናኙበት አንዱ ሸፈሮ ቡና (የቡና ገለባ) የሚፈላበት
ወቅት ነው። የሐመር ቡና የሚፈላው በጀበና ሳይሆን በትልቅ እንስራ ነው ቡናው የሚጠጣው ንጋት ላይ ጀምሮ እስከ ረፋዱ ድረስ
ሲሆን፣ ያደረሰው ሁሉ መጠጣት ይችላል። አንድ ጊዜ ታዲያ፣ ካርለትና ከሎ ሻንቆ መንደር ለመጀመሪያ
ጊዜ ቡና ሊጠጡ ሄደው፣ ኦይጊ የተባለችው የመንደሩ ኗሪ ቤቷ ለመጡት እንግዶች በሾርቃ ከትልቅ ቅል ላይ በተከፈለ መጠጫ
ለሁሉም እንግዳ ስታድል፣ ለሁለቱም ሰጠቻቸው" ካርለት አንዱን
ሾርቃ እንደምንም ጨርሳ ‹ተገላገልኩ› ብላ፣ ሾርቃውን ለአይጊ አቀበለቻት በሐመር ባህል ሾርቃውን ቡናውን ለምትቀዳው ካቀበሉ
ድገሚኝ እንደማለት በመሆኑ፣ ኦይጊ ቡናውን በሾርቃ ሞልታ ለካርለት ሰጠቻት፤ «አምላኬ!» አለች ካርለት የመጀመሪያው ቋቅ
ሊላት ደርሶ፣ ሁለተኛውን ስታስታቅፋት።

ካርለት፣ ቡናውን መጠጣት ከበዳት። ቁጭ አድርጋ ትታ
እንዳትሄድ፣ ባህሉን መናቅ እንዳይሆንባት ሠግታ ስትጨነቅ ቡናውን
በያዘው ሾርቃ ላይ ዝንቦች እየገቡ ተንሳፈፉ። ካርለት፣ «ጥሩ አጋጣሚ» ብላ፣ እየሣቀች፣ «ዝንብ ገባበት» በላቸው አለችው ከሎን!
«ድፊው» ይሉኛል ብላ። እነሱ ግን፣ «ጠጭው ምንም አይልሽም፣
ይሄ የወተት እንጂ፣ የቆሻሻ ዝንብ አይደለም» አሏት። ካርለት፣ ሌላ አማራጭ ስላልነበራት የሚንሳፈፉትን ዝንቦች «እፍ» እያለች
ቡናውን ጠጥታ ጨረሰች።

ካርለት በሐመር ኑሮዋ በጣም የከበዳት ችግሯ ግን የሐመሮች የጊዜ ዕውቀት አለመኖር ነው። ካለፕሮግራሟ በተለይ በገበያ ቀን ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ቀይአፈርና ጂንካ በመኪናዋ እንድትወስዳቸው
ይጠይቋትና መኪናዋ ውስጥ ዱቄት፣ ፍየል፣ በግ፣አረቄ፣ ማርና ቅቤ
ሰለሚጭኑ ሁሌ ትሳቀቃለች" አንዳንዴም አፍ አውጥታ! «አልሄድም» ትላለች።

ካርለት ምግብ፣ ደብዳቤ፣ መጽሔት፣ ከቤተሰብ ጋር የስልክ ግንኙነት ለማድረግ አዲሳባ ስትሄድም በጕዞው ከሎ ሆራ መኪና
ማሽከርከር ቢረዳትም ወንዝ እየሞላ፣ ጭቃ ሲይዛቸው ትማረራለች።

ካርለትና ከሎ ወደ አዲሳባ ሲሄዱ አልፎ አልፎ የሚላኩት መልእክት የተወሰነ ሲሆን አቡጀዲ፣ የላስቲክ ጫማ፣ ሸፈሮ ቡና
ሽጉጥ መሳይ መድኃኒት «ቴትራሳይክሊን ወይም ክሎሮፌኒኮል”ዋነኞቹ ናቸው"

ካርለት ሐመር ሦስት ወር ቆይታ አዲሳባ እንደሄደች፣ ከስቲቭ ጋር ተገናኙ። ስለ ሐመር ሕይወቷ፣ ስላየቻቸው ነገሮች፣ ስላጋጠማት ችግርና ስለ ወሰደችው የመፍትሔ እርምጃ አጫወተችው
ስቲቭ ከነገረችው ሌላ፣ ካርለት አንገቷና እጇ ላይ ያለውን ነገር ከማየቱም ባሻገር፣ ሳታቋርጥ ስታክ ተመለከታት» ከዚያም፣ «የኔ
ፍቅር፣ ይህን ያህል ለምን ራስሽን ለችግር ታጋልጫለሽ?» አላት
ስቲቭ"

«ችግር ስትል ምን ማለትህ ነው?»

«ይህ ደረሰብኝ እያልሽ ያወራሽኝ ሁሉኮ ጋሪ ላይ የተጫነ ጭነት ሳይሆን፣ አንች የተሸከምሽው ችግር ነው?» አላት"

«ስቲቭ፣ አንድ ሰው የምኖረው ትርጕም ያለው ሥራ ለመሥራት ነው ካለ፣ ሕይወቱም ትርጕም ያለው ይሆናል" ሌላው ደግሞ
(ምኖረው ለመሞት ነው› ካለ በውስጡ እውነትነት አለው” ሕይወቱ ግን፣ ትርጕም አልባ ይሆንበታል"

«ማንኛውም አጋጣሚ በየግላችን አእምሮ አመዛዝነን፣ መክረን፣
እናወጣ እናወርደዋለን፣ ቀጥሎ ጥሩ ወይም መጥፎ ትርጕም እንሰጥና ተግባሩ ላይ ያን አጋጣሚ እንጠላዋለን ወይም እንወደዋለን።

«አንዱ መኖርን ጥሩ ሥራ ለመሥራት እንደሆነ ተረድቶ ሲጥርI ሌላው ደግሞ መኖሩ ለመሞት መሆኑን አውቆ ተስፋው ይኰሰምናል"
👍25🥰2
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ስምንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

..ደልቲ ገልዲ በራሱ የሚተማመን ጀግና በመሆኑ በዚህ ዓለም ላይ
ከእሱ በላይ ሰው ያለ አይመስለውም" ስለሆነም፥ የሚፈልገውን አጣለሁ የሚል ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለውም" በስሙ ሲዘፈንና ሲዘመር ጥርሱን እየፋቀ በርኳታው (መቀመጫው) ላይ ቁጭ ብሎ ወይንም ጋደም ብሎ መዝናናት ነው;

ጀግንነት ከሀብት ጋር ገና ዕድሜው ሳይገፋ፥ «ቤት ለእንቦሳ» ሲል «እንቦሳ እሠር» ብሎ፥ ተቀብሎታል" በእርግጥ እያንዳንዱ
የሐመር ጓዳ ላጠቃላይ ማኅበረሰቡ ግልጽ ነው። ተካፍሎ መመገብ፥
ተሰባስቦ መጨፈር፥ ተከባብሮ መኖር፥ ጠላትን በጋራ ማጥቃትና
መደናነቅ የማኅበረሰቡ ወግና ልማድ ነው። ደልቲ ገልዲም የዚህ ባህላዊ ኑሮ ተሳታፊና ተገዥ በመሆኑ ኃይሉን ተማምኖ ሌላውን የሐመር አባል ማጥቃትም ሆነ ንብረት መቀማት ክብሩን ለውርደት፥ ሀብቱን
ለጥፋት ስለሚያበቃ ከልጅነቱ ጀምሮ ክብርንና መብትን በጥንቃቄ
መያዙንና ተከባብሮና ተመካክሮ መኖርን ሊዘነጋ አልቻለም።

ደልቲ ገልዲ፥ በዚያን ሰሞን ወደ መንደራቸው የመጣችውን እንግዳ የተመለከታት በኲራት ነበር" የለበሰችውን ጨርቅና
የምትሸተው ቃና ከአካባቢው ልጃገረዶች ጠረን የተለየ በመሆኑ ራቅ
ብሎ ነው ያስተዋላት።

«እንደ ሐመር ሴቶች ቆዳ የማትለብሰውና ጭኖቿን የማታሳየው ምናልባት የሚያሳፍር ነገር ቢኖርባት ይሆናል» ብሎ፥ከመገመቱም
በላይ የሴትነት ጠረኗን የዋጠው ሽታ አስጠልቶት ነበር በተደጋጋሚ
ቀናት እንዳያትም በሚኰርፍ ነገር መተጣጠቧ ብልግናዋን ከማረጋገጡም በላይ መጥፎ ጠረኗን ለማጥፋት መሆኑን አምኖበታል"

የሐመር ልጃገረዶች በውኃ አይታጠቡም። «ብልታቸውን ውኃ ከነካው መካን ይሆናሉ» ስለሚባል፣ በጣም ነውር ነው" ይህችኛዋ እንግዳ ግን አልፎ አልፎ ብቻ ሳይሆን ዘወትር ስትተጣጠብ ያያታል" «መካንነቷ መቼም የማይቀር ነው" ግን ሴት ሆና ስትተጣጠብ
የማታፍር ምኒቱ ባለጌ ናት?» እያለ ኮንኗታል። ሌላውም እንደሱ
በድርጊቷ ጠልቷታል"

ሆኖም እሱ የጀግኖች ጀግና ነው፤ እንዲህ ዓይነቷን ባለጌ ልክ የማግባቱ ኃላፊነት ከሱ ትከሻ ላይ የወደቀ ነው" ስለዚህ፣ እንግዳይቱን በግርፋትም ቢሆን ሥነ ሥርዓትን ሊያስተምራት ይችላል"
ይህን ለማድረግ ደግሞ፣ እሷን ማግባት አለበት" ካለበለዚያ ዝንቧንም እሽ ማለት ላይችል ነው ደግሞኮ የሱ ሚስቶች በመልካቸው ጥቋቁሮች ናቸውI ስለዚህ ነጭ ሚስት ያስፈልገዋል" ሀብቱ
እንደሆነ የትየለሌ ነውI ሦስት በረት ከብት፣ በየጋጡ ብዛት ያለው ፍየል፣ በየጫካው ለቍጥር የሚታክት ቀፎ አለው" በዚያ ላይ የቀጭኔ፣ የጎሽ፣ የአንበሳና የሰው ገዳይ ነው።

ስለዚህ፣ ይህችን ባለጌ ለማረቅ እንዲችል እሷን የራሱ የሚያደርግበት በቂ ሀብት አለው። እና፣ የሚጠየቀውን ጥሎሽ ከፍሎ የሱ ንብረት ካደረጋት በኋላ ቢቀጣት ጠያቂ የለበትም። ለዚህ ሁሉ
ግን፣ ሚስቱ እንድትሆን ማድረግ እንዳለበት አመነ። አብሯት የመጣው ከሎ ሆራ እንደሆነ ምኗም እንዳልሆነ አረጋግጧል"

አንድ ቀን ካርለትና ከሎ ሆራ ሲጨዋወቱ ደልቲ ገልዲ
«ነጋያ» ብሎ አጠገባቸው ለመቀመጥ ይዞት በሚዞረው በርኮታ ላይ
መሣሪያውን ጭኖቹ መሃል አድርጎ ተቀመጠ" ከዚያም፣ «ባል  አለሽ?» ብሎ በቋንቋው ጠየቃት" ይሉኝታና ፍርሃት የሐመርን
ተወላጅ ሲያልፍም አይነካካውም" ደግሞስ ሰው ሰው ነው" ያውም
እሱ ጀግናው። ከሎ ሆራ ያለውን ለካርለት ተረጐመላት።

«የለኝም» አለችው" ካርለት በቀኝ እጇ ግንባሯ  ላይ
የተበታተነውን ጸጕር ወደ ኋላዋ እየመለሰች።

«አባትሽ ስንት ከብት አለው?» አላት፣ ደልቲ።

«ከብት የለውም፣ ፕሮፌሰር ነበር" ስለዚህ ደመወዙ…»
ፕሮፌሰር፣ ደመወዝ ያለችው ሊገባው አይችልም። ከባለጌ የሚጠበቅ
ተራ የተራ ነገር ይሆናልና ስለሱ ማሰብ አያስፈልግም።

«ቀፎና ፍየልስ?» ጠየቀ ደልቲ።

«የለውም» አለች" አባቷ ደሃ ቢሆን ነው ማለት ነው ወደዚህ የላካት ብሎ አዘነላት" በሐመር ማኅበረሰብ ሀብት ማለት ከብት፣ ፍየል፣ ቀፎ ነው። ከዚህ ውጭ ደመወዝ፣ ቪላ፣ መኪና ብሎ ሐተታ፣
የሚገባው የለም። ደልቲ ገልዲ በክልሉ የሀብት ሁሉ ባለቤት አባወራው እንደሆነ
አሳምሮ ያውቃል" ስለዚህ፣ እንግዳዋን ስለ እናቷ
አያስፈልግም" ደግሞ ሴትን፣ «ሀብት አላት ወይ?» ብሎ መጠየቅ ነውር ነው። የእንግዳዋን አባት ሁኔታ እንደሆነ ጠይቆ፣ ድህነቱን
ተረድቷል

ደልቲ ገልዲ በእሱና በእንግዳዋ አባት ሀብት መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል ሰፍቶ ታየው" ለምግብ ማቅረቢያ፣ ለመኝታ የምትጠቀምበት፣ በተለይም ማታ ማታ «ፋ» የምታደርገው መብራትና ብልጭልጭ ቅራቅንቦዋ፣ ከሱ ንብረት አንፃር ሲታይ
ጠጠርና ተራራን ማወዳደር ቢሆንም፣ አባቷ ሀብቱን ለምን ለእሷ እንደተወላት ግራ ገብቶታል። የሱ ወገን የሆኑት የሐመር ሴቶች የግሌ የሚሉት ሀብታቸው የሚለብሱት ቆዳ፣ ጨሌና አንባራቸውን ብቻ
እንደሆነ ጥርት አድርጎ ያውቃል።

ያም ሆነ ይህ ግን፣ እንግዳዋን አግብቶ በግርፋት መግራት እንዲችል ሊያገባት መፈለጉን ለሽማግሎች ማማከር አለበት ሽማግሎች የሚሉት ባይታወቅም ብልግናዋን ገልጾ ሊገራት እንደሚፈልግ
ሲነግራቸው እነሱም ይህን ስለሚረዱ ተቃውሞ እንደማይኖራቸው
ተማምኗል" አንድ ግን ግራ የገባው ጉዳይ አለ" ጋብቻውን ሽማግሎች ቢቀበሉት «ልጅቱን ለማግባት፣ አባቷ የት ተገኝቶ በሽማግሎች
ይጠየቃል? ጥሎሹንስ እንዴት ወስዶ ከችግሩ ይላቀቃል?» ብሎ
አሰበ።

ይህ ከሆነ በኋላ ግን፣ ብዙም ሳይቆይ ደልቲ ገልዲና ካርለት በምሽት ጭፈራ ተገናኙ ካርለት ያ አስደናቂ ጥያቄ ሲጠይቃት
የነበረው ወላንሳ እየዘለለና እያሸበሸበ ሲደንስና ሲሥቅ፣ ደጋግማ
ስታየው ሁሉን ነገር በተለይም ስለሱ የሚባለውን ሁሉ አስታወሰች። ስለዚህ፣ ዛሬ ይህን ስሙ በሐመር ሰማይ ላይ የሚንሳፈፍ ሰው ማንነት ማወቅ አለባት"

ያም ሆኖ ግን ካርለት ስሜቷ ለሁለት ተከፈለባት" በአገሯ ምን ዓይነት ውበትና ጠባይ ያላቸው ወንዶች በሴቶች እንደሚፈቀሩ፣ ከሞላ ጎደል ታውቃለች። እሷም ብትሆን በአፍላው የወጣትነት ጊዜዋ የነበራት የስሜት ቅብጥብጥነትና በምታፈቅረው ወንድ ላይ

ታጠምደው የነበረውን መረብ አስታወሰች" ሆኖም ይህ ሰው እዚ
ከምታውቃቸው ሰዎች በብዙ መልኩ ይለያል ለነገሩ የደልቲ ውበት
ጭጋግ ለብሶ ይታያልI ያውም ይኖራል ብላ ያልገመተችው ውበ
የሐመር ልጃገረዶችን ሕሊና ያማልላል ተብሎ የሚደነቀውን ልበ ሙሉ ወንድ ጭጋጉን በታትና ሥነ ውበቱን በትክhል መቁጠር አለባት" የለንደኑ፣ የቦኑ፣ የማንቸስተሩ..ወጥመዷ ያለውን የመያዝ ችሎታም መፈተን ይኖርባታል"

እንደ ባልጩት ድንጋይ የለሰለሰውን ገላውንና በጨረቃ የሚያንፀባርቁት ጥርሶቹን ባሰበች ቍጥር ጥርት ጎላ እያሉ ታይዋት
ስለዚህ፣ ማራኪውና የመጨረሻ ዓይነት የጭፈራ ምት መጀመሪያው ጊዜ መቃረቡን ስታውቅ፣ ሐሳቧን ተግባራዊ ለማድረግ ለሩጫ
እንደሚዘጋጅ ሯጭ አደፈጠች።

ያን የወቅቱን ወላንሳና ቀብራራ ሐመር ጠብቃ ለዳንስ ስትጋብዘውና እያኮበኮበ፣ አየሩን በመቅዘፍ ቀርቦ ጥቁሩ ጭኑ ከነጩ ጭኗ ሲተሻሽ፣ ሸካራና ጠንካራ እጆቹ ትከሻዋን ሲይዙ፣ ስሜቱ
በስሜቷ ውስጥ ሲሟሟ፣ ያለችበትን ቦታና ሰዎችን በመዘንጋት የሚያቃጥል፣ የሚነዝርና በሰመመን የሚያሰጥም ስሜት እንደ
ተሰማት፣ ከራሷ ቍጥጥር ውጭ ሆነች" ስለዚህ፣ ሁሉን ነገር ዘንግታ
ተንጠራርታ አንገቱን በማቀፍ ከንፈሯን ከከንፈሩ ጋር ለማላተም
ተጣጣረች ደልቲ ግን፣ በጠንካራ እጆቹ እጇን ያዝ አድርጎ፣ የዳንሱን ቦታ ጥሎ፣ ወደ ጫካ ይዟት ገባ፤ ጥቁሩና ነጭ አባይ ጫካ መሃል ተገናኙ።
👍24👎1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የሐመር ዕጽዋት ለምልመው፣ ንቦች ከአበባ ወደ አበባ እየተዘዋወሩና እየዘመሩ ሲቀስሙ፣ ከብቶች ጨሌ ሳራቸውን እያመነዠኩ ሲያገሱ፣ እንቦሶች ቃጭላቸውን እያቅጨለጨሉ ሲቦርቁ፣
ልጃገረዶችም ማሳውን እያረሱ ሲያዜሙ፣ ልጆች እራቁታቸውን ሆነው በቀስት ጫካ ለጫካ ተሪ ለመግደል ሲሯሯጡ በሚውሉበት፣
ጎረምሶች ሹልሹላ፣ ሹርባ...ጸጕራቸውን እየተሠሩ «አኖ» በተባለው አፈር ሰውነታቸውን በማዥጐርጐር ለማታው ጭፈራና ድሪያ ሲዘጋጁ፣ የብልታቸውን ጸጕር እየተላጩ በመኸር ጊዜ የሚዘፍኑትን ዘፈን ሲያዜሙ በሚውሉበትና ሐመር የክቱን የተፈጥሮ ሕይወት
ለብሳ ኗሪዎቿን በምታስፈነጥዝበት ወቅት ድንገተኛ ሁኔታ ታየ።

ካርለት አልፈርድ ሰቀላ ቤት አሠርታ መኖር ከጀመረች ዘጠኝ ወር አለፋት። ከሷ በስተግራ ከሃያ ሜትር ላይ የከሎ ክብ ጎጆ አለ።
በግቢያቸው የዱር አበባ፣ ቦዬ፣ ጉደሬ በቅሏል። ከነሱ ግቢ ራቅ ብሎ አለፍ አለፍ በማለት የሐመሮች መኖሪያ ይታያል። ካርለት ቤቷ ሆና
ፀሐይ ስትወጣ ከፊት ለፊት፣ ስትገባ ደግሞ ከበስተኋላ ሆና ልታያት
ትችላለች"

በእርግጥ በፖስት ካርድ ፀሐይ ስትወጣና ስትገባ አስደናቂ ፎቶዎችን ተመልክታለች። ሕይወት ያላት የሐመሯ ፀሐይ ግን ምሽት ላይ በተለያዩ ቀለማት ተውባ እንደ ዕንቁ እያንፀባረቀች አካባቢውን
ቀይ፣ ቢጫ ሐምራዊ ድብልቅልቅ ቀለማትን ስትለዋውጥ ስታያት
ግን በሕይወቷ ካየችው ውብ ነገር ይልቅ፣ በሐሳቧ የቀረፀችው የገነት
ውበት ይታያታል።

ታዲያ፣ በጣም ተመስጣ የአካባቢውን ውበት ስትመለከት ውበትን በትክክል ለማስቀመጥ፣ መጨመር የምትፈልገውንም
ጨምራ ለመርካት፣ ከአንትሮፖሎጂስትነቷ ይልቅ ባለቅኔ ወይንም
ሠዓሊ መሆን ያምራታል
ካርለት ያጣችው ነገር የለም አይባል" የዋና ቦታ አላገኘችም ኑሮዋ ዘመናዊ አይደለም" ያም ሆኖ ግን በሚያውዳት የተፈጥሮ
መዓዛ፣በስሜት በምትውረገረገው የምሽት ጭፈራ፣ ባየችውና
በቀረበችው ቍጥር ጥልቅ እሳቤን የሚጠይቃት የተፈጥሮ ምሥጢር፣ በንጹሕ ሕሊና የምታነባቸው መጻሕፍት የደስታ ሚዛኗን
ይጠብቁላታል።

አሸጋግራ የምታየው የሐመር ሰንሰለታማ ተራራ፣ መሸት ሲል ከየዋሉበት ብቅ ብቅ የሚሉት ሰዎችና እንስሳት፣ ስታንቀላፋ
የዋለችው መንደር፣ ሞቅ ሞቅ ደመቅ ስትል፣ ሁሉም ከፀሐይ ውበት ጋር ውሕደት፣ ቅንብር ሲፈጥሩ ስሜቷ ይረካል» እንዲያውም ከዚህ
ለየት ላለ ያልተበረዘ ተፈጥሮ ያላት ፍቅር «ምነው እናቴ፣ ወንድሜ፣ እኅቴና ስቲቭ ይህን ባዩ» ብላ፣ ቅን ሐሳብ እንድታልም
ያደርጋታል"

አንድ ቀን ግን፣ የተለመደ ትርዒቷን ስትመለከት፣ በግምት የአሥራ አምስት ዓመት ልጃገረድ፣ ከጥቁር ፍየል ለፍቶ የተሠራውን
ቆዳ ዙሪያዋን በነሐስና ጨሊ አስጊጣ ለብሳ፣ አንገቷ ላይ በደረደረችው ጨሌ ራሷን አሰማምራ፣ ዳሌዋንና ቀጥ ብለው ግጥም ያሉ ማራኪ የእግር ቅርፅዋን ስታይ ካርለት አፏን በአድናቆት ከፈተች
«በእርግጥ በጣም ቆንጆና ለየት ያለች ነች መቼም አይቻት እንደማላውቅ እርግጠኛ ነኝ» እያለች በባለ ሌንሱ ካሜራዋ ደጋግማ
ከርቀት አነሣቻት" ልጃገረዷ ካለምንም ሥጋት ወደ ካርለት ሰቀላ ቀርባ ሰላም ብላ ካርለትን ቆም ብላ ካየቻት በኋላ ጸጕሯን በጣቶቿ እሷም በተራዋ እየነካካች አድናቆቷን በሣቋ ገልጣ ልትሄድ ስትል
ካርለት «ወይ አምላኪ፣ አምላኬ! ኧረ ጥርሶቿስ እንዴት ያምራሉ!» አለችና እንድትቀመጥ ጋበዘቻት" ልጃገረዷ ግን፣ ካርለትን የቤት ውስጥ ሁኔታ አንገቷን አስገብታ ቃኝታ በድጋሜ
ፈገግ ብላ፣ «ደህና ሁኝልኝ» ብላ ሄደች"

ከሎ ሆራ የሐመሯን ውብ ቀደም አድርጎ ይመለከታት ነበርና ውበቷ ደንቆታል" በተለይ ወደ እሱ ቤት አቅጣጫ ስትመጣ ልቡ
መዝለል፣ ሐሳቡ መተረማመሱን ጨመረ። ከሎ ሆራ እስh ዛሬ
ታይቶበት የማያውቅ መርበትበትና ድንጋጤ ታየበት"

ልጃገረዷ፣ «ደህና ዋልህ» ብላው፣ ከተከፈተው የጎጆ ቤት መስኮት ላይ ተንጠልጥላ ስታይ እግሮቿ፣ ጭኗ፣ ዳሌዋና የሚሳበው
| ወገቧ ከሎን በሲቃ አፈኑት። ልጃገረዷ፣ የሚተኛበትን መኝታና
ዕቃዎቹን ተመልhታ ስትወጣ የሱም ልብ አብሮ ተከተላት እሷ እንደምታውቀው በማንኛውም የሐመር ቤት የሚገኝ ለመተኛ ቁርበት፣ ለመመገቢያና ለመጠጫ ሾርቃ (ከቅል የተሠራ)
እንስራ (ለሸፈሮ ቡና ማፍያ) ነው" ከነጯ ቤትና እንደ ሐመሮች መልክ ያለውና ጨርቅ ለባሹ ቤት ግን አይታው የማታውቀው ዕቃ
አለ" በኮተቱ ብዛት ትገረም እንጂ አልተደነቀችም“ እንዲያውም ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑት ቁርበት፣ ሾርቃ፣ እንስራ ቤታቸው
ውስጥ ባለመኖሩ ተደንቃለች።

ከሎ ቤቱ በር ፊት ለፊት ሆኖ ጠበቃት በሐመር ባህል ደንብ ልጃገረድ ከቡር ናት ካለፍላጎቷና ሳያግባባ መታገል የውርደት
ውርደትና ነውር ነው" ልጃገረድ እንደሚሰበር ዕቃ የሚጠነቀቁላት፣ እንደ ሕፃን ልጅ ፍላጎቷን የሚያከብሩላት መሆን ይገባል"ልጃገረድ የምትፈልገውን ወንድ ቀጠሮ ትሰጠዋለች" ያውም
ከተመቻት ነው" ካለበለዚያ፣ ካለ እሷ ትብብር አፈቀርኩ፣ ወደድኩ፣ በዚህ ወጥቶ በዚያ ወርዶ፣ ምን ሲባል ያን አይተሽ፣ እያሉ መሟዘዝ በባህሉ አይታወቅም
በሐመር ማኅበረሰብ ልጃገረድ ቀሳሚ ንብ፣ ወንዶች አበባ ናቸው" ባል ካገባች በኋላ ግን ሴት የባል ዕቃና ንብረት ናት።

ስለዚህ ልጃገረዷ ካለፍላጎቷ የሚደርስባት ችግር እንደሌለ
ስለምታውቅ ከሎን አልፈራችውም ከሎ ሆራ ግን ድንገት «እጅ ወደ ላይ» እንደተባለ ሰው ደንዝዟል" ካርለት የሁለቱን ሁኔታ
ከርቀት በጕጕት ትመለከታለች" ልጃገረዷ ሰላምታ አቅርባለት
መንገዷን ሰትቀጥል፣ ከሎ በባህሉ ኰራ ብሎ መታየት ሲገባው ተርበተበተ"

ሰንበት ብሎ ሲያስበው ራሱን ቢታዘብም በሕይወቱ በጣም አደገኛ ወጥመድ ላይ የወደቀበት ጊዜ ያ መሆኑን ራሱ ለራሱ አመነ"
ልጃገረዷ ግን ዳግመኛ ወደ መንደሩ አልተመለሰችም።

ሆኖም ከሎ፣ «ከየትኛው መንደር ይሆን የመጣችው? እጮኛ አላት ይሆን?» እያለ፣ በሐሳቡ መዋለሉ አልቀረም።

«...የሐመር ወንዶች ቢያፈቅሩም ፍቅራቸውን በግልጽ ማሳየት
ነውር ነው። ቢሆንም ልጃገረድን መዳራት ነውርነት የለውም» ብሎ፣
ከሎ የነገራትን ካረለት አስታወሰች"

ከሎ ሲቆዝምና ሐሳብ ሲያበዛ፣ ካርለት በፍቅር ሰመመን መዋጡን በመረዳቷ፥ «ከሎ ያችን ልጃገረድ እውን አፍቅሮ ይሆን? ፍቅሩንስ በምን መልክ ይገልጽ ይሆን? ባህላዊውን ወይስ ዘመን
አመጣሹን ይሆን የሚጠቀመው? ኧረ ኅብረተሰቡስ ምን ይሰማው
ይሆን?» በማለት፣ ካርለት በጥንቃቄና በተመስጦ ማሰቧን ቀጠለች።

«ምን ዓይነት ድንቅ ነገር ነው!» ሁሉም ነገር ምሥጢር ሆኖባት
ተገረመች። ስሜት ረቂቅ ነው፤ አይጨበጥም። ስሜት በአካባቢ ላይ
ተፅዕኖ ቢኖረውም፣ አካባቢም በስሜት ላይ ጫናው ከባድ ነው"
ማፍቀርና መፈቀር ተፈጥሯዊ ነውና ማንም ከዚህ ስበት ሊያመልጥ
አይችልም" ችግሩ ከፍቅር ቀጥሉ ግንኙነቱ በምን መልክ መሆን ይኖርበታል ነው። እኒህ ሁለት ሥረ ግንዳቸው አንድ የሆኑ፣ አካባቢያቸው ግን ለውጥ ያለው ሰዎች እውነት እንዳሰቡት ቢፋቀሩስ?»

አዲሱን ምርምሯን በተለያዩ መንገዶች ተጠቅማ ማወቅ
ይኖርባታል" «ከሎ ከልጃገረዷ ጋር ፍቅር ቢይዘው ልብስ በመልበሱ
ትንቀው ትችል ይሆን? አውሬ ወይንም የጎሳው ጠላት የሆነውን ሰው አልገደለም ከብት የለውም ስለዚህ ዘመናዊዋም ሆነች ቆዳ ለባሿ ሴት ክብርና ዝናን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈላጊ ስለሆነች
ላትቀርበው ትችላለች"»

«ከሎም ቢሆን ልጃገረዷን ለማግባት ኡክሊ ሆኖ በየዘመዶቹ መዞር፣ ከብት መዝለልና ለኮይታ (ጥሎሽ) የሚሰጠው ከብት፣
ፍየል፣ በግና ማር ማግኘት አለበት"
👍30😁3
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከሻንቆና ከላላ የተሰባሰቡት ሽማግሎች በደልቲ ገልዲና በካርለት ጋብቻ ላይ ሸንጎ ከመቀመጣቸው በፊት በኅብረተሰቡ አጋጣሚ ላይ
ትንበያ መስጠት ይችላሉ የተባሉት፣ «ጫማ ጣዮች» ደጋግመው ጫማ በመጣል ጋብቻው ስለ መሥመሩ አስተያየታቸውን ሰጡ"

ከጫማ ጣዮቹ ቀጥሎ ደግሞ ፍየል ታርዶ «ለአንጀት አይታዎች» ቀርቦ ጋብቻውን በተመለከተ እነሱም አስተያየት እንዲሰጡ ተጠየቁ። እነሱም ተጋቢዎቹ ልጅ ስለ መውለድ አለመውለዳቸው
ሊታያቸው ባለመቻሉ ሦስት ፍየል ከታረደ በኋላ፣ «ጋብቻው ቀና ነው» በሚል ብቻ አድበስብሰው ተውት"

በእርግጥ፣ ይህ ጉዳይ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ያወያየ ሲሆን፣ በተለይም በሽማግሎቹ ዘንድ ጋብቻውን በመጠራጠር በቀጠሮ በተለያየ ጊዜያት ለመወያየት አስቻላቸው"
ካርለት አንጀት አይታዎች በሰጡት አስተያየት መደናገጧና መደነቋ አልቀረም" በሐመር ማኅበረሰብ መካን ሴት ፈላጊ እንደ ሌላት ታውቃለች" አንድ ሴት ለአባቷ ጥሎሽ ተከፍሎ ባሏ ዘንድ ከሄደች በኋላ ልጅ ሳትወልድ ብትቀር ባሏ እሷን መልሶ ታናሿን፣
ካለበለዚያም ቅርብ ዘመዷን ያገባል" ያም ሆኖ ካልተሳካለት፣ ልጅ
መውለድ ካልቻለች ላባቷ የከፈለውን ጥሎሽ ያስመልሳል ሴቷም፣
«መካን የሆነችው በውኃ ብልቷን ታጥባ ይሆናል» ተብላ ትጠረጠራለች» መካን ሴት የተገኘችበት ቤተሰብም እንደ መጥፎ
ቤተሰብ ስለሚቈጠር ጋብቻ የሚፈልገው ሁሉ ይሸሻል" ይህ ደግሞ አባት በልጆቹ ጥሎሽ ያገኘው የነበረውን ከብት፣ ፍየል፣ በግ፣ ማር
ያስቀርበታል" ከዚያም ተጨማሪ፣ ምናልባት አባትየው ሦስት ሴት
ልጆች ቢኖሩት የመጀመሪያ ልጁን ጥሎሽ ተቀብሎ ቢድርና መካን ብትሆን ሁለተኛዋን፣ ሁለተኛዋም መካን ከሆነች ሦስተኛዋን! |
ሦስተኛዋ መካን ከሆነች የዘመድ ልጅ...በመስጠት ሞክሮ ካልተቻለ ግን የተቀበለውን ጥሎሽ ይመልሳል"

«ስለዚህ አንደኛ ነገር እኔ በውኃ ስተጣጠብ ስለሚያዩ መካን ትሆናለች የሚል ግምት መጀመሪያውንም ነበራቸው" ሁለተኛ ደግሞ
አንጀት አይታዎችና ጫማ ጣይዎች ልጅ ልወልድ አለመቻሌን ለማኅበረሰቡ አስታውቀዋል። ሌላው ግን የኔው የራሴ ጉዳይ ነው
ለጥንቃቄ እንዳላረግዝ የሕክምና መከላከያ አለኝ" ስለዚህ ልወልድ
አለመቻሌን አውቀዋለሁ" እነሱም ባለመውለዴ እጅግ በጣም አምነዋል" ግንኮ እንዴት? የፍየል አንጀት ከኔ ጋር ምን አገናኘው ካርለት፣ ራሷ ለራሷ ሐሳቧን አካፍላ ራሷን ጠየቀች።

ካርለት በእውነቱ ከሆነ ጥሎሽ ከደልቲ ገልዲ ማግኘት አትሻም
ጥሎሽ አያስፈልግም ብትል ግን የሱ የግል ንብረትነቷ ማረጋገጫ አጣ ማለት ነው" ጋብቻው ከዚህ ሁሉ ቢቀርስ እንዳይባል ደግሞ እሷ ባህላዊ ግድቡን ጥሳ ጥናቷን ለማካሄድ፣ ደልቲ ደግሞ ባለጌዋን እንግዳ የራሱ አድርጎ በግርፋት ሥነ ሥርዓትንሊያስትምራት
ቈርጧል።

በግልና በተናጠል የላላና ሻንቆ ኗሪ ሲመክርና ለሽማግሎቹ
የመሰለውን አስተያየት ሲሰጥ ሰንብቶ በመጨረሻ ሽማግሎቹ በጥልቅ ከተመካከሩ በኋላ

«እንግዳዋ ምንም እንኳ በመልክና በቋንቋዋ ከእኛ ብትለይም የቦርጆ (የአምላካችን) ፍጡር ናት። እኛን ብላ፣ እኛን መርጣ መጣች እንጂ ማሌ፣ በና፣ ዳሳነች፣ ሙርሲ...ምድር ልትሄድ ይቻላት ነበር።
በእውነት ከሆነ ብልግናዋ የበዛ ነው" ይህ ደግሞ የሷ ስሕተት ሳይሆን፣ ያባቷ ስሕተት ነው» ብለው ጋብቻውን ለመቀበል ወሰኑ።

በመቀጠልም፣ «ይህች እንግዳ አባቷ በቅርብ ባለመኖሩ ደልቲ ገልዲ የሚከፍለውን ጥሎሽ የሚቀበል አባትና ጥሎሹን የሚወስን ሰው የላትም" ስለዚህ እሷ የፈለገችውን ሰው በአባትነት ትምረጥ።
ከእንግዲህ በኋሳ የምትለብሰው፣ ጠረኗ እንደ ሐመር ልጃገረዶች

እንዲሆንና እስከ አሁን የፈጸመችውን ስሕተት እሷም ራሷ ስለምታውቅ ለወደፊት የፍየል ቆዳ ለፍቶና ተሰፍቶ እንድትለብስ፣በጨሌና አንባር በማጌጥም ጸጕሯን አጠር አድርጋ አስቈርጣ ሹርባ እንድትሠራና በእግሯ እንድትሄድ» ብለው ተስማሙ"

«ባባቷ በባንኪ ሞሮ ደንብ መሠረትም ጥሩ ሴት ለመባል አባት ብላ ለምትመርጠው ወንድ ልጅ ወይም በዘመዱ ወንድ ልጅ የከብትጨዝላይ ወቅት በባራዛ አርጩሜ ዱላ ቻይ መሆኗን ለማስመስከር
ላትሸማቀቅ ፀንጋዞች (ባዕዳን) በሚባሉት ጐረምሶች እንድትገረፍና
ጀርባዋ ላይ የሚቀረው የግርፋት ምልክት ለሽማግሎችና ለአካባቢው ሰው እንዲታይ በግልጽ እንድትተወውና እንድታጌጥበት»
ተባብለው ተማመኑ።

ከሎ ሆራ የሽማግሎችን ሁኔታና አጠቃላይ ውሳኔያቸውን ለካርለት ሲነግራት ጥርሷ እስኪፋጭ ድረስ ተንቀጠቀጠች" መናገር †ሳናት" በእውነቱ ለተመለከታት የማንኛውንም ሰው አንጀት የምትበላ ሲሆን፣ በሌላ በኩልም ጋብቻ ለመፈጸም ማሰብ የግብዝነት ተግባር ነው ሊያሰኝ የሚችል ነበር።

ካርለት ከከሎ ተለይታ ሰቀላዋ ውስጥ ገብታ ምን እያደረገችና ወደፊትስ ምን ሊያጋጥማት እንደሚችል ስታስብ፣ እንባዋ
እየተንፎለፎለ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ከዚህ ቀደም የኖረችበት ዓለም
እውነት አሁን ባለችበት መሬት ላይ ሳይሆን ከሌላ ፈለክ (ፕላኔት) የመጣች እንግዳ ፍጡር የሆነች መሰላት" ሽማግሎቹ ካቀረቡላት ቅድመ ሁኔታና ባህላዊ የውጣ ውረድ  ይልቅ በትንሿ የመርፌ
ቀዳዳ ሾልኮ ማለፍ እንደሚሻል ገመተች"

እሷ የምታውቀው ሕይወትና አሁን ያለችበት ዓለም የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል ተብሎ በርቀት ልዩነት ብቻ የሚለካ
ሳይሆን፣ ፈጽሞ ሊተያይ የማይችል ሆድና ጀርባ ሆነባት"

ግርፊያ.ቆዳ መልበስ…በባዶ እግር መሄድ ...አለመታጠብ ልት
ረዳው፣ልታምነው፣
ልትሰማማው የማትፈልገው ጉዳይ ነው።ስለሆነም ይህን ፈጽሚ ማለት፣ በሷ ላይ ትልቅ ችግር መፍጠር ብቻ ሳይሆን ይቅር የማይባል ግፍ እንደ መፈጸም ያክል ነው" አባባሉን እንኳን በተግባር በቃል ልትሰማው ከበዳት።

ታላቁ የሴቶች እንቅስቃሴ ለመላው አውሮፓ ሴቶች ያጎናጸፈው መብት ብናኙ እንኳን ወደማይገኝበት መጥታ መገኘቷ፣ ከመላ ሴቶች ጎን ተነጥላ ወደ ዘንዶ አፍ የመወርወር ያህል ሆኖ ተሰማት ስለዚህ ለምን ወደዚህ ጣጣ ራሷን እንደዶለች ማሰላሰል
ጀመረች ካርለት ፍዝዝ፣ ትክዝ እያለች ቀስ በቀስ አንገቷን ወደ ሰማይ በማስገግ ወደ አውሮፓ በሐሳብ ተጓዘች።

እናቷ ሚስስ አልፈርድ፣ ታናሽ እኅቷ ሴሻ አጠገቧ ቢኖሩላት ኖሮ ጭንቀቷን ገልጻላቸው ተያይዘው ያለቅሱ ነበር። ግን ምንስ ብላ ልትገልጽላቸው ነው?
«እኔ እራሴ እንኳ ሁኔታዎች ከቍጥጥሬ ውጭ ሆነውብኝ መላ ብዬ የፈጠርኩት እንጂ እነሱማ መጀመሪያውንስ እንዴት ሊረዱኝ ይችላሉ? እናቴና እኅቴ እንዳፈቅር ገፋፍተውኛል" ለታናሽ እኅቴም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ምን ዓይነት የደስታ ስሜት እንደሚፈጥር
የነገርኳት እኔ ነኝ” ጋብቻ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ከባድ ነገር መሆኑን እንደሆነ የእንግሊዝ አገር ወጣት በየትምህርት ቤቱ፣ በቲያትርና ሲኒማው የሚያውቀው የአደባባይ ምሥጢር ነው።

«የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፍቅር ዋነኛው ቅመም ቢሆንም በራሱ ግን ፍቅር አይሆንም" ያልተፈለፈለ፣ እዶሮ እቅፍ ውስጥ ያለ እን
ቍላል እንደ ማለት ነው እንቍላሉ ነፍስ ሆኖ ከመፈጠሩ በፊት እን
ስቷ ዶሮና አውራው መገናኘት አለባቸው" የሰዎች ግንኙነት ደግሞ
ከዚህ በላይ ነው" በሐሳብ መጣጣምና መግባባት ያስፈልጋቸዋል"።
👍17
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ

ከሎ ሆራ ልቡን የሰረቀችውን የሐመር ውብ ለማግኘት ብዙ መድከሙ
አልቀረም።ካርለትም ብትሆን የሐሳቡን መናወጥ
ስላጤነችና ለጥናቷም እገዛ ይኖረዋል ከሚል እምነት በመነሣት ያችን ውብ ኮረዳ ማፈላለጉ ላይ አልሰነፈችም ሻንቆና ላላ መንደር
አለመኖሯን ግን ሁለቱም በየፊናቸው አረጋግጠዋል።

እንደ ተለመደው ከሎ ሆራና ካረለት በየመንደሩ በመዞር
ለማጠናከር ሲንቀሳቀሱ፣ ከዲመካ ከተማ ወደ አምስት ኪሎ ሜትር
እራቅ ብላ ከምትገኘው ኮረብታማ መንደር ወሮ ሄዱ"ከዚያ እንደ ደረሱ ወንዶች ወደ ወንዝ፣ ሴቶችም እርሻና ማሳ ጥበቃ ሄደው ስለነበር፣ መንደሯ ውስጥ ያገኙት የሚያላዝኑ ውሾችንና አሮጊቶች
ብቻ ነበር። መሸትሸት ሲል ግን ከብትና ኗሪው ከየውሎው ወደ
መንደሯ መጠረቃቀም ጀመረ።

ይህ ትዕይንት ለካርለት እንግዳ አልነበረምና ከመንደሯ ወጣ ብለው የአካባቢውን ውበት ሲቃኙ፣ ከሎ ደንገጥ ብሎ ዓይኑን ወደ አንድ አቀጣጫ ደገነ" አንዲት ልጃገረድ ስታርስበት የዋለችበትን ሞፈርና ቀንበር ከበሬዎች ጫንቃ ስታላቅቅ፣ ከበስተኋላ ተመለከቱ"።
እግርቿ ግጥም፣ ዳሌዎ ኮራ ከወገቧ ሰርጎድ ያለችውን ኮረዳ ሁለቱም ከበስተኋላዋ በማየት ብቻ ማንነቷን አወቁ" ልጅቷ በሬዎቹን
ፈትታ ዘወር ስትል፣ ሁለቱም ዓይናቸው እሷ ላይ ነው" ኮረዳዋ አንዳችም የመደነጋገር ሁኔታ ሳታሳይ ፈገግ ብላ በዚያ ኰራ ባለው አረማመዷ ወደነሱ ሄደች"።

ከሎ ምራቁን ቶሎ ቶሎ ከማንጐራጐጭ በስተቀር የሚመለከተው ልጅቷን ነው" ካርለት ደግሞ በተመስጦ የምትከታተለው እሱን ነው"

በልጅነቷ ወንድና ሴት ተቃቅፈው አልጋ ላይ ሲተኙ የሚያደርጉትን ለማወቅና ብዙ ጊዜ ለማየት ትጓጓ ነበር" ነፍስ ካወቀች
ጊዜ ጀምሮ የምትተኛው በግል መኝታ ቤቷ ሲሆን፣ አንድ ቀን ታዲያ የናቷ ጓደኛና ባሏ በእንግድነት እቤታቸው ይመጣሉ" እንዳጋጣሚ ሆኖ ለእንግዳ የተዘጋጀው የመኝታ ከፍል ተይዞ ስለነበር እንግዶች
ካርለት መኝታ ክፍል እንዲያድሩ ተደረጉ፣ እሷ ከወላጆቿ መኝታ ቤት ካለው ትንሽ ክፍል እንድትተኛ ይደረጋል" ካርለት ግን
እንቅልፍ ከመተኛት ይልቅ አንድ ለብዙ ጊዜ ለማወቅ ትጓጓ የነበረውን ሁኔታ ለመፈጸም አሰበች" እናም፣ የቆየ የልጅነት ፍላጎቷን ለማሟላት እንግዶች እሷ ከምትተኛበት ክፍል ገብተው ከመተኛታቸው በፊት አልጋው ሥር ገብታ ተደበቀች" ባልና ሚስቱ
በመጠጥ ኃይል ሞቅ ብሏቸው ነበርና እየተሣሣቁ ተደጋግፈው ገብተው አልጋ ላይ እንደ ወጡ ተያያዙ"

ካርለት የአልጋ ላይ ጨዋታቸውን ሁሉ ልቅም አድርጋ ሰማች"ከዚያ በኋላ ሰዎቹ ሲተኙ፣ ወላጅ እናቷ ካርለት ከተኛችበት ከፍል
ልታያት ስትገባ ድንግጥ አለች ቀስ አድርጋ እጇን ልጇ አልጋ ላይ ስትጭን ጨርቅ ብቻ ሆነባት በድንጋጤ ጮኸች። አባት፣ እንግዶች
ሳይቀሩ እየተሯሯጡ ሲመጡ የለችም ቤቱ ቢታሰስ፣ ብትፈለግ
በቀላሉ ልትገኝ አልቻለችም" በጨረሻ ግን አልጋ ስር እንደ ውሻ ተጠቅልላ ተገኘች" እና ዛሬም እንደ የዛኔው እንዲታወቅባት
ስላልፈለገች የኮረዳዋንና የከሎን ሁኔታ በጥንቃቄ መከታተል ቀጠለች።

ከሎና ካርለት ከልጅቱ ጋር ፊትና ኋላ ወደ መንደሩ እንደ ደረሱ፣ከልጅቷ መኖሪያ ቤት ትይዩ ድንኳን ለመትከል እንደ ፈለገች ለከሎ
ሆራ ሆነ ብላ አማከረችው «ኢህ» ብሎ ፈቃደኛነቱን ገለጸላት ለነገሩማ እንሂድ ብትለውስ መቼ በጄ ይል ነበር።

ከሎ፣ ስለ ብዙ ነገር እንዳላወጣ እንዳላወረደ አሁን የሚፈልገውና የሚያየው ውብ ልጅ ነው  የሐመሯን ኮረዳ" አጠገቧ
ካለው ድንኳን ውስጥ ሆኖ እሩቅ ያለች ይመስል አለማት" ከሎ ሴት
አያውቅም ለማለት አይቻልም" በተለይ በገንዘብ የሚገኘውን የስሜት እርካታ በሚገባ ያውቀዋል" የሴት ጓደኛም ለመያዝ ብዙ
ሞካሮ ነበር" ግን፣ ከሙሉ ስሜቱ እንዲህ እንደ አሁኑ ነፍሱ ምንጥቅ እስክትል ወዶ አያውቅም"

ልጃገረዷ ደግሞ በሕይወቷ እንደ ወንድ ጓደኛ ግንኙነት
የጠገበችው የለም። ከሚጠይቋት ወንዶች ውስጥ ከመረጠቻቸው ጋር
ብቻ ተዝናንታለችI ዕድሜ ለሐመር ደንና ጫካ።

እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ልጃገረዷ ወላጆቿን በሥራ በመርዳት ስታገለግል ቆይታ ለምሽት ጭፈራው መሰናዳት ጀመረች"የጐረምሶችን ጩኸት እንደ ሰማች ከጓደኞቿ ጋር ለመደነስ ስትሄድ፣እነ ከሎ ተመለከቷት" አባቷ እንዳያገኛት ተጠንቅቃ አለፈች።

ልጃገረድ በኢቫንጋዲ (የምሽት ጭፈራ) መካፈሏን ባህሉ የሚፈቅድ ቢሆንም ወደ ጭፈራ ቦታ ስትሄድ ግን አባትየው ሳያይ
ሲሆን፣ ከጐረምሳ ጋር ስትዳራ ካገኘም አባት ተኵሶ ጐረምሳውን
እስከመግደል ድረስ መብት አለው" ይህ መብት እንጂ ያደርጋል ማለት ግን አይደለም። ስለዚህ፣ ለደንቡ ያህል ጭፈራውም ሆነ
ድሪያው አባት በማያየው መንግድ እንዲሆን ልጃገረዶች የራሳቸውን
ጥናቃቄ ይወስዳሉ"
በአጋጣሚ ግን እሷ ባህሉ ያደገችበት ሆነና ብትጠነቀቅም፣ አባቷ
ግን ከሌሎች የሐመር ወንዶች ለየት ያለ ነው።
በኢቫንጋዲ ጭፈራ ልጃገረዷ ኮከብ ደናሽ ስትሆን፣ የክልሉ ጎረምሶች
በፍቅር ሲያጫውቷትና ወደ ጫካ ሄድ መለስ ስትል ከሎን ግን ለዳንስ ሳትጋብዘው ቀረች። ወደ እኩለ ሌሊት አካባቢ ሲሆን የወንዶች ድምፅ ተሰማ። በመንገድ ላይ የሚያልፉ
ገበያተኞች እግረ መንገዳቸውን ለጭፈራ ሲመጡ የተለመደ ነበርና
ጨዋታው ቀጠለ። ካርለት አሁንም ክትትሏን እንደ ቀጠለች ነው" ጭፈራው ደመቀ፣ ውዝዋዚው ጦፈ፣ ከዚያ የመጨረሻው የዳንስ
ስልት ጊዜ እነ ካርለት የሚከታተሏት ኮረዳ ከአንድ መልከ መልካም ሸበላ ጋር መርፌና ክር ሆኑ ካርለት ያ ሰው ማን እንደሆነ ለመገመት ጊዜ አልፈጀባትም። መጀመሪያ እዳልነበረ እርግጠኛ ነች። ከገበያ ከተመለሱ መንገደኞች ጋር እንደ መጣ አወቀች" ደልቲና ኮረዳዋ
ወደ ጫካው ሲሠወሩ፣ ከሎና ካርለት ተፋጠጡ።

ውቢቷ ልጃገረድ ጎይቲ አንተነህ ትባላለች። በሐመርኛ ጎይቲ ማለት መንገድ ሲሆን፣ የስሟ ትርጓሜ ከመንገደኛ የተወለደች ለማለት ነው" ካርለትና ከሎ የሐመርኛ ቋንቋ አቀላጥፎ የሚናገ
ረውንና በአኗኗሩም ሆነ በአለባበሱ ሐመር የሆነው የጎይቲ ወላጅ አባት ጠዋት ከከብቶች በረት ሲመለስ፣ እንግዶች ከቤቱ ፊት ለፊት
ድንኳን ተክለው አየ አንተነህ (ጋልታምቤ) እንግዶቹን አንዳየ በጨዋ መልክ ሰላምታ ከሰጠ በኋላ፣ ጨዋታ ቢጤ ጀማመሩ።
የመጡበትን ጉዳይና ማንነታቸውን ከገለጸለት በኋላ፣ «ሸፈሮ ቡና
እንጠጣ» ብሎ፣ ወደ ቤቱ ይዟቸው ገባ።

ቡናውን ያፈላችውና የምትቀዳው ውቧ ልጃገረድ ጎይቲ አንተነህ ከአባቷ ፊት በጣም ጨዋና ረጋ ያለች ናት ካርለትና ከሎ በጣም
ጠባብ ወደ ሆነው የጎጆው በር በየተራ ገብተው ከተነጠፈው ቁርበት
ላይ እንደ ተቀመጡ፣ ጎይቲ በሾርቃ ሞልታ ሸፈሮ ቡናውን ለካርለት
አቀበለቻት ቀጥላ ለከሎ ስትሰጠው በአጋጣሚ እሷን እሷን እያየ ነበር እሷ ደግሞ ሾርቃውን የያዘ መስሏት ስትለቅለት ከመሬት
ወርዶ ተሰበረ። ሁለቱም በጣም ደነገጡ" ካርለት ድንገተኛ ሣቅ አፈናት፤ የልጃገረዷ አባትና ሌሎች ሁለቱ ሐመሮች ግን ጸጥ ብለው ሁኔታውን አረጋጉ።

ቡናው የውኃ ጥምን ስለሚከላከል ማንኛውም ሐመር በየመንደሩ
ቡና በእንስራ ተጥዶ፣ ሁለትና ከሁለት በላይ ሾርቃ ሳይጠጣ ከመንደሩ የሚርቅ የለም" አንተነህ ይመር ጎይቲ (ሴት ልጁ) ቡናውን
አጠጥታ ስትጨርስ፣ «ረሃብ፣ ችግር ከሐመር ምድር ይራቅ ከብቶች ይጥገቡ፤ ንቦች አበባ ይቅሰሙ፤ ሰማዩ ውኃ ያውረድ ፍቅር ሰላም ለሐመር ሕዝብ ቦርጆ ያውርድ አንቺም ተባረኪ የተባረh ባልና ትዳር ይስጥሽ፤ ሁላችሁም ተባረኩ» ብሎ ሸፈሮ ቡናውን ወደ አራቱም አቅጣጫና ወደ ጎይቲ፣ «ፕስስ...» አለና አማተበ።
👍171
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከሎ ሆራ ጨርቆሉ ማዝ ሆኖ ደም፣ ወተት፣ ሥጋና ማር እየተቀለበ፣ ከሰልና ቅቤ ተቀላቅሎ ፊቱንና የተላጨውን ራሱን
ተቀብቶ፣ ከሚዜው ጋር ውሎው ጫካ ነው። ከሎ የወገኖቹን ባህላዊ
የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ለመጀመር ምክንያቱ አንድ ነበር ፍቅር። ሥነ ሥርዓቱን እያሟላ ሲመጣ ግን፣ አዲስ ስሜት አእምሮው ማፍለቅ ጀመረ።

ወገኖቹ የሆኑት ሐመሮች በአንድ ወቅት ከማኅበረሰባቸው
አግልለውት ነበር" ያውም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ፣ እንዲሞት ተደርጎ ተጥሏል። ከሚወዳቸው ወላጆቹና እኅት ወንድሞቹ፣ ከሚያፈቅረው የፍየልና ጥጃ ጥበቃው፣ ከቦረቀበትና ከተጫወተበት ማራኪ
የሐመር ምድር ተጎትቶ ተወስዶ፣ በጦር ተወግቶ፣ ወደ ገደልም ተገፍቶ፣ የሞትን ጽዋ ጕድጓድ ውስጥ እንዲቀምስ ተደርጎ ነበር።

የሕፃንና የወጣትነት አእምሮው ይህን የደረሰበትን መራራ ጽዋ
ጠንጥኖ በገዛ አእምሮው የዛን ጊዜውን መሪ ተዋናይ ሲያስታውሰው አፉን ደም ደም ይለዋልI ልሳኑ ይዘጋበታል ሕይወቱ የላሸቀ፣ የተበላሸ እንቍላል ሆኖ ባለመጥቀሙ ተሽቀንጥሮ የተወረወረ
ይመስለዋል።

የዛኔው የቍስል ስሜት ምልክት ጥሎ ካለፈ ዓመታት ቢቈጠሩም
ሁሌም አጋጣሚውን ባስታወሰ ቍጥር ሥቃዩ ይጀምረዋል" ሞት
ጒሮሮው ላይ ቆሞ ስለታም ሰይፉን ጕሮሮው ውስጥ ሊቀረቅርበት ሲመጣ ይታየውና ይባባል፤ መሸሻ፣ መደበቂያ፣ ማምለጫ መንገድ ያጣል። ከራስ ሕሊና የሚፈጠር አስፈሪ ነገር በምን አንቀጽ
ይከሰሳል! ምን ዓይነት ጠንካራ በር ያግደዋል?

«እኮ ለምን? ምን ባደረኳቸው በእንቦቀቅላነቴ ወቅት ልሸከመው
የማልችለውን ሞትና ፍርሃት አሸከሙኝ ምን ባደረኳቸው ከእናት  ጉያ ነጥለው፣ አብሬአቸው ከምዘላቸው ጓደኞቼ ለይተው ለመከራ
ዳረጉኝ?» ባለፈው ሕይወቱ ከሎ ሆራ ራሱን በራሱ እየጠየቀ መልስ ያጣበት ጉዳይ ነው" ለብዙ ዓመታት የዕለት ተዕለት ትዕይንት ሆኖ የሚቀርበውን የቆየ ትዝታ ባስታወሰ ቍጥር የመጨረሻውን ረድፍ
ይዘው የሚደረደሩት ጥያቄዎች ከላይ የተዘረዘሩት ሲሆኑ መልሳቸው ግን ሰው ወይንም መዝገበ ቃላት ሳይመልሰው እስከ ዛሬ አብረውት ዘልቀዋል"

ከሎ ሆራ በሕይወቱ ሙሉ ያምንበት የነበረው አሁን ግን እንደ አጉም እየበነነ አልጨበጥልህ ይለው ጀምሯል" ወደ ወገኖቹ ብቻ
ሳይሆን ወደ ሐመር ምድር ለመመለስ አልሞም አያውቅም። የኖረው
እነሱን ሲረግምና ሲሸሽ ነው። አሥራ ሁለተኛ ክፍል እንደ ጨረሰ በአገር አቀፍ የመሠረተ ትምህርት ዘመቻውም ወቅት፣ ከዘመቻው መቅረት ወይንም መለወጥ አልቻልህ ብሎት እንጂ እግሩንም
ለማንሣት አያስብም ነበር" የዛኔም ቢሆን ደግሞ፣ «ጌታዋን የተማመነች በግ...» እንዲሉ፣ መንግሥትን ተማምኖ እንጂ እንኳን የከፍተኛ ትምህርት ዕድሉ ሌላው ሁሉ ነገር ቢቀር ወደ ሐመር
ተመልሶ ለመምጣት አያስብም። በቆይታውም አይጥና ድመት ሆነው
ቆዩ እንጂ አልተቀራረቡም።

አሁን ግን ከሎ ሆራ አይጡም ድመቱም እሱ እንደሆነ በመቁጠር ወደ ቤቱና ወደ ባለቤቶቹ መመለስ ይከጃጅለዋል"

ከሎ ሆራ በእርግጥ አሁን ያለው ሐመር ነው" ሐመሮች በተለይም ዘመዶቹ ባዩት ቍጥር ይሳሱለታል" ወላጅ እናቱ ልክ እንደ ልጅነቱ እጆቹን እያፍተለተሉ እንባቸውን ያፈሱለታል ያላቸውንና
ቤት ያፈራውን ጎጆው ድረስ ተሸከመው ያመጡለታል፤ ከብት ለመዝለል በየዘመዶቹ ቤት ሲዞር እንደ ብርቅ ስመው አስተናግደውታል ከብት በሚዘለልበትም ወቅት ዘመዶቹ ዝግጅቱን በማሟላትና በለምለም ቅጠል መልካም ዕድልን በመመኘት አብረውት
ተጨንቀዋል ልጃገረድ ዘመዶቹም የዝምናድ ምልክት የሆነውን
ግርፋት በወኔና በፍላጎት ተገርፈውለታል።
ከሎ ሆራ ይህን ሁሉ ካመዛዘነ በኋላ ለዘመናት በአእምሮው ተቀብረው
የኖሩትን ጥያቄዎች ከመቃብራቸው እያወጣ መጣል ጀምሯል እናቱ እንደ ብርቅዬ ልጃቸው፣ ወንድምና እኅቶቹ እንደ
ተወዳጅ ወንድማቸው አድርገው ይቈጥሩታል“ ታዲያ ማንን ይጥላ?
ለሥቃዩ ሁሉ ተጠያቂው ማን ሊሆን? ለምንስ እንዲሞት አድርገው
ጣሉት?

ከሎ ሆራ አእምሮው ለጥያቄዎቹ መልስ አገኘ" ለመጣል ያበቃው ባህል ነው። እሱን ለመጉዳት፣ ከእናቱ ጉያ ለመነጠል የደፈሩት የአገር ሽማግሎች አንኳን ለሱ ከሜዳ ተነሥተው hፉ አላሰቡም”

የሐመር ሕዝብ ባህሉን አክባሪ፣ ካለ ዘመናዊ ሕግና ደምብ በባህላዊ ደምቦችና ሥርዓቶች የሚመራ፣ ተፋቅሮና ተዛዝኖ የሚኖር
ማኅበረሰብ ነው። ማንንም የማያገል፣ ባህሉን ከመከተል ዝንፍ
የማይል ሕዝብ መሆኑን አረጋግጧል። «ታዲያ ወገኖቼ በእኔ ላይ
ብቻ ልዩ ቅጣት አልፈጸሙብኝማ። ባህላዊው ደንብ መሟላት
ነበረበትና ተገደልኩ፤ ከሙትነት ተነሥቼ ስመጣ ግን ተቀበሉኝ" አሁን የተቀበሉኝ ስለ ተማርሁ፣ ከእነሱ የተለየ ሕይወት ስላየሁ አይደለም ባህሉ ስለሚፈቅድ ብቻ ነው ታዲያ ባህል ባመጣው ጦስ ወገኖቼን መጥላት አለብኝ?» ጨርቆሌ ማዝ ተብሎ ጫካ ለጫካ
የሚዞረው ከሎ ሆራ ዕድሜ ልኩን አእምሮውን ሰንገው ይዘው ያስጨንቁት የነበሩትን ጥያቄዎች መመለስ ጀመረ።
።።።።።።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ሰው ራሱን ማስተማር የሚችል ታላቅ ፍጡር ነው" በተለይም ታታሪ ሰዎች ከአምላክ የተሰጠውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ
እየተጣጣሩ ናቸው። እየተሳካላቸውም ነው

በምርምር እንደ እብድ ያልለፈለፈ ፈላስፋ፣ ቀንና ሌሊት በምርምርና በሙከራ እልሁን ያልጨረሰ ሳይንቲስት፣ እንደ
ሚፈጥራቸው ገጸባሕርያት ስቅስቅ ብሎ ያላዘነ አሊያም በደስታ ያልተፍነከነከ ደራሲ፣ የሚሥለውን ሥዕል የተዋጣ ለማድረግ
ረቂቁን የተፈጥሮ ምሥጢር ለማወቅ በመጣጣር ያልዳከረ ሠዓሊ
l ሊኖር አይችልም" ካለም ከነሆድ አምላኩ ወገን የሆነ አስመሳይ መሆኑ ነው"

ካርለት የሐመር ሴቶችን ሕይወትና ማኅበራዊ ተሳትፎ የምታጠና
ወጣት አንትሮፖሎጂስት ናት ያለችበት ዘመን ሳይንስና ተክኖሎጂ የመጠቀበት፣ የሰው ልጆች በአዲስ ግኝቶች የሚንበሸበሹበት ወቅት ነው„

«እንደ ዱሮው ዘመን ይህን  ይህን ማድረግ ያስቸግራል የሚል አዳማጭም ሆነ ተመልካች አያገኝም" መሆን አለበት ብዬ ብዙ
ሞከርኩኝ ፈተናና ሥቃይም ገጠመኝ፤ በመጨረሻ ግን ተሳካልኝ ሲባል አድናቆታዊው ጭብጨባ መቅለጡን አውቃለሁ። የሰው ልጅ በውኃ ውስጥ በባቡር መጓዝ በቻለበት፣ ሕዋ ላይ ከተማ በከተመበት፣አይጥና ድመት አብረው እንዲጫወቱ በተደረገበት ወቅት እኔስ
ሰውነቴ ቢቈስል፣ የአእምሮ ጭንቀት ቢደርስብኝ፣ ብገረፍ፣ ባል ባገባ ምኑ አዲስ ነገር ነው። ከዚህስ የቀለለ የዓላማ መሥዋዕትነት ምን
ሊኖር ይችላል?» ካርለት መኝታዋ ላይ ተጋድማ የምታስበው ነበር
ካርለት ለአንድ ወር ያክል በከብት ዝላይ ወቅት የተገረፈችው ቁስል አሠቃያት ጫማ የለመደውን እግሯንም እንቅፋቱና እሾሁ
እየተተካካ አንሰፈሰፋት" እየቆየ ሲመጣ ግን ይህ ሁሉ ሥቃይ እየታገሠ፣ ቍስሉም እየደረቀ፣ እግሯም እየደነደነ መጣ ካርለት በቃን በማይሉት ማስታወሻዎቿ የየዕለት ገጠመኞቿን
እያሰፈረች፣ በካሜራዋ እይታዋን እያጠናከረች፣ በድንኳኗ አካባቢ
አገገመች ካርለት አልፈርድ ልብሶቿን በሻንጣዋ ቆልፋ፣ ቆዳዋን በመልበስ፣ በባዶ እግሯ በጨሌና አንባር አጊጣ ስትወጣ ብዙ አዲስ
👍22
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ከሎ ሆራ በጨርቆሌ ማዝነት በደንብ እየተቀለበ ከቆየ በኋላ ሚዜው ሰውነቱ እንደ ተመለሰ አረጋገጠ። ስለዚህ ከሎ ሆራና ሚዜው
ከተሪ (ዲክ ዲክ) ቆዳ የተተለተለ ቀበቶ መሳይና ኩርኩፋ ይዘው
በደንቡ መሠረት ጎይቲ አንተነህን በድብቅ ማሳደድ ጀመሩ።

ጎይቲ አንተነህ ከሎን አልወደደችውም እሷ ልቧ የጠፋባት ለዚያ ጀግና ለደልቲ ገልዲ ነው" መሬቱን በልበሙሉነት እየረገጠ
ሲንጐማለል፣ የሷንም ልብ እንደ ጠረማመሰው ሁሉ በፍቅር ታቃስታለች።

በኢቫንጋዲ ጭፈራ ወቅት አንዳንዴ መንደራቸው ብቅ ካለ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑትን ሌሎቹን የዳንስ ምቶች ከሌሎች ጋር
ብትጨፍርም ጭንን በጭን የማግባቱ ጊዜ ቀድማ የምትጋብዘው እሱን ነው። ጭኑን በጭኗ ውስጥ ሲያስገባ የአእምሮዋን እንቅስቃሴ ያዛባና በቍጥጥሩ ስር ያደርጋታል" ከወገቧ ልጥጥ ብላ ወንድ ብልቱ ላይ ትለጠፍበታለች" በዚያ ወቅት ስሜት እንደ ቅቤ ይቀልጥና እሱም እሽት፣ እሷም አሽት፣ እሱም እሽት...ሲደራረጉ ይቆዩና
ሁለቱም ሲሸነፉ፣ ውጥረት ሲበዛባቸው ተያይዘው ወደ ጫካ፣ ወደ ልዩው የተፈጥሮ መኝታ ክፍል ጐራ ይላሉ“

ጫካው ውስጥ ወፎች፣ አራዊት፣ እባቦችና ሰዎችም ጭምር ፍቅራቸውን በነፃነት ይለዋወጣሉ ጫካ ውስጥ ትርዒት አቅራቢ እንጂ
ተመልካች አይኖርም። «ሁሉም ለየራሱ…» ብቻ መባባል ነው።

ጎይቲ አንተነህ ታዲያ ያ አራዊትን፣ ሰውን የገደለ ጀግና የፍቅርም ጀግና ሆኖ አግኝታዋለች" ጠምዘዝ አድርጎ በጠንካራ እጆቹ ወደ እሱ እያስጠጋ ትንፋሿ እስኪቋረጥ የሚስማትና እንደ ሕፃን ልጅ አቅፎ የሚያጫውታት ሁሉ ትዝታን ያልፈጠረባት እፎይታን ያልሰጣት ጊዜ የለም።

ከሎ ሆራ፣ ጎይቲ አንተነህን ባየ ቍጥር ከፍቅሩ ፅናት አንፃር ሰውነቱ እየተልፈሰፈሰ ቢርበተበትም ተፈቃሪዋ ግን ኵሩ ሆና ኵሩ ወንድ፣ ጅንን ጀግና፣ ስሙ የገነነ ወንድ ፈላጊ ነበረችና እሱ ለእሷ
ሲል ልብሱን አውልቆ ራቁቱን ቢሄድም፣ ሊያደርገው ያላሰበውን
እንዲያደርግ ፍቅሯ ቢያስገድደውም፣ እሷ ግን ለሱ ቁብ የማይሰማት
ሆነችበት"

የጎይቲ አንተነህ ልብ ያለው ደልቲ ገልዲ ላይ ሲሆን፣ የከሎ ሆራ ልብ የማለለው ደግሞ፣ ለጎይቲ አንተነህ ነው። ቢሆንም ከሎ
ሆራ እሷን የማግኘት ተስፋው አልጨለመበትም" እሱም ሆነ ሽያው
(ሚዜው) ከቀናቸው ጎይቲ አንተነህን ብቻዋን ሰከም ሰከም ስትል ሊያገኟት ይችላሉ።

አንድ ቀን በሬ ጠምዳ ስታርስ፣ አጥማጆቿ በርቀት ቍጥቋጦው ውስጥ ተደብቀው ሲከተሏት ዋሉ። መቼም እንደዚያን ቀን በከፊል የተመቻቸ ቀን ከዚህ በፊት አላጋጠማቸውም" በሬዎችን በጅራፍ ሸንቆጥ በማድረግ፣ ከወገቧ ወደ ጎንና ጎን ለጠጥ፣ ዳሌዎቿን ወጣ  ገባ....እያደረገች ስለ ሐመር ጀግኖች፣ ስለ ከስኬ ወንዝ፣ ስለ በልጉ ታንጐራጕራለች። አጠገቧ የአጎቷ ልጅ ብቻ ነው ያለው፤ እሱ ዘወር ካለላቸው ፈጥነው ሊይዟትና የልባቸውን ሊያደርሱ ይችላሉ " እሱ እያለ ግን ምንም መሥራት አይችሉም ጎይቲ የተዘጋጀላትን ወጥመድ በጭራሽ አላወቀችም ዝም ብላ እርሻዋን ታርሳለች። አፍቃሪዋም፣ ከዘምባባው ዙሪያ ካለው ሰንበሌጥ ውስጥ ሆኖ በገዛ ምራቁ ይታነቃል።

አጥጆቿ፣ የኦጎቷን ልጅ ቦርጆ (አምላክ) ከዚያ አካባቢ ዘወር እንዲያደርገው ይመኛሉ" የአጎቷ ልጅ ደግሞ፣ ጎይቲ አንተነህ ልጃገረድ በመሆኗ ብቻዋን ትቷት ቢሄድ ሊደርስባት የሚችለውን
አጋጣሚ አሰበ" ኋላ እሱና ሌሎች ጐረምሳ ዘመዶቿ መጠበቅ ተስኗቸው ጀግንነት፣ ሀብት ከሌለው አንዱ ቢተናኮላት የሌሎች
ልጃገረዶች ማሽሟጠጥና በጓደኞቹ «ፈሪ» ተብሎ መናቁ፣ እሱንና ዘመዶቹን ስለሚያናድዳቸው ብቻዋን ትቷት ለመሄድ አልፈለገም።
ስለዚህ አዳኞች ታዳኟን በቍጥጥር ሥር እንዳያውሉ የአጎቷ ልጅ
«ጕሮሮ አጥንት» ሆኖባቸው ሳይሳካላቸው ቀረ።

በሌላ ቀናትም ውኃ ለመቅዳት ስትሄድ፣ ገበያ ስትመላለስ ትክለ
ቁመናዋን፣ ፈገግታዋን፣ የሚነጥረውን መቀመጫዋን ቀምሶ
ያልጠገበውና እያየ በመሳሳት ላይ ያለው የመንደሯ ጐረምሳ፣ እንደ
ሴት ውሻ ከቦ ስለሚከታተላት በድብቅ ለሚከታተሏት እንቅፋት
ሆኖባቸው ሰነበተ።

ከሎ ሆራ ከሚዜው ጋር ጫካ ለጫካ ሲዞርና ጎይቲ አንተነህን  ሲከታተል ጕሮሮው ሲጮህበት ቢውልም፣ እየቆየ ግን መሰላቸት ጀመረ። ፊት ለፊት ሄዶ የደንቡን ለመፈጸም ያስብና ባህሉን ባለማክካበሩ የሚደርስበትን ውግዘትና ቅጣት እያሰበ፣ ሐሳቡን ከሕሊናው አውጥቶ ያሽቀነጥራል"

አንድ ቀን ግን፣ ጎይቲ አንተነህ ደንገዝገዝ ባለ ምሽት፣ ከቤቷ ወጥታ መንገዱን ስትነካው እነከሎ ተከተሏት" ከመንደሯ ዘወር
እንዳለች የመሮጥ ያህል እየተራመደች ወደፊት ገሰገሰች" ከሎ ሆራ፣
«የት እየሄደች ይሆን? ብቻዋን ካለፍርሃት እንዴት ትሄዳለች» በማለት ግራ ገባው ከወሮ ራቅ ብለው ካሉት መንደሮች ለመድረስ
ከመቻሏ በፊት ግን እነሱ ያቀዱትን ከመፈጸም የሚያግዳቸው የለም።

«አቤት ለስንት ጊዜ እንዳለፋን በግላጭ አገኘናት» ተባብለው
ከሎና ሚዜው ተቃቅፈው ደስታቸውን ተገላለጹና ፍጥነት ጨምረው
ለመያዝ ወደ ፊት ሽምጥ ሮጡ" እሷ ዘንድ ከመድረሳቸው በፊት ግን
ሁለቱም ሩጫቸውን ገትተው ቆሙ ከግራር ጥላው ሥር መሣሪያ የያዘና በርኮታው ላየ የተቀመጠ ሰው ያዩ መሰላቸው» አበሸቃቸው፣ ገረማቸውም፣ «ማን ይሆን?» ጠየቀ ከሎ፣ «እንጃ!» አለ ሚዜው። ስለዚህ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ቃጫው ተክል ገባ ብለው አደፈጡ። ጎይቲ አንተነህ ወደዚያ
ሰው እየቀረበች ስትሄድ እየተደነባበረች የሰካራም ጕዞ ጀመረች ሰውየው መጀመሪያ አላያትም ነበር። ዱካዋን ሲሰማ ግን
ከተቀመጠበት ፈንጠር ብሎ ተነሥቶ መሣሪያውን ሲደግን፣ ወደሱ
የምትገሰግሰው ጎይቲ አንተነህ ናት። መሣሪያውን አቃንቶ፣ እጁን ከፍቶ ጠበቃት፤ ያው እንደ ልማዱ እንደ ቀንድ የቆመው ጡቷን
ከሰውነቱ ስታሻሽለት፣ እሱም የኰራውን ዳሌዋን በሁለት እጁ ወደ
እሱ ይበልጥ እየሳበ፣ ትንፋሿ እስኪቈረጥ ድረስ ሳማት። እሷም ሆነ እሱ በተፈጠረው ሙቀት እንደ ቅቤ ቀለጡ።

ከሎ ሆራ፣ ይህን ትርዒት ራሱ እንደሚሠራ ሁሉ፣ እሱም ባለበት ደነዘዘ። ሰውነቱ ሁሉ ባለበት ሲወጣጠር ታወቀው። በእሱ ላይ የተለጠፈችበትና አቅፎ የሚስማት መሰለው። ዋና ተዋናይዎቹ ግን ወደ ዋናው እርካታ ጕዟቸው ለመሄድ አንዱ በሌላው ውስጥ ዘልቆ ሲገባ ከሎ ከሰመመኑ ነቃ። የሚወዳት ጎይቲ አንተነህ ከሱ ጋር
ሳይሆን ያለችው ከሌላ ሰው ጋር ነው። እሱ ያቀፈውና የሳመው ለካ ግንዱን ነው" እሱ ግንድ አቅፎ ሲስም፣ እሷ ሰው አቅፋ
ትቃበጣለች፣ «ዳሚት» አለ ከሎ፣ ሊቈጣጠረው በማይችለው ስሜት ተወጥሮ።

ከሎ ሆራ ሰውዬውን በደንብ ቢያስተውለውም ሊለየው
አልቻለም። ሚዜው ግን ነገረው፣ «አያ ደልቲ ገልዲ ነው» አለው።

"አዎ እሱ ነው ካለሱ እሷን እንዲህ የሚያደነባብራትና
ትንፋሿን የሚያሳጣት ወንድ የለም» በማለት፣ በእልህ ወደ ተዋጠ ሰሜት ውስጥ ገባ" ሚዜው ግን፣ ከርቀት የሚታየው ቅብጠት አፉን
አስከፍቶታል።

ፍቅረኛሞች የፍቅር ጥማቸውን ለማርካት እየደጋገሙ ሲጫወቱ ቆዩና ተለያዩ" ጎይቲ አንተነህ ወደ መንደሯ ስትመለስ ከኋላ የቀረባት ሰው እንዳለ ሁሉ ልቧ ተንጠልጥሎ አልፈጠነችም። መንደሯ
👍22🥰2
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ደልቲ ገልዲ በካርለት ባህል አፍራሽነት ቆሽቱ አርሮ የነበረውን ያህል አሁን ግን አእምሮው መዝናናት ጀምሯል" መቼም እሱ
የያዘው ነገር መስተካከሉ የማይቀር በመሆኑ እንግዳዋ እሱን መቅረብ
ከጀመረችና ግንኙነት ካደረጉ በኋላ ብልጭልጭ ቅራቅንቦዋን አወላልቃ ጥላ ቆዳ መልበሷ፣ በባዶ እግሯ ካለ ጫማ መሄዷ፣ እንደ
ሐመር ልጃገረዶች ጸጕሯን አሳጥራ በጨሌና አምባር ማጌጥ መጀመሯ፣ እሱን ፍርሃት እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት እንደማይኖራት ስለ ተገነዘበ ደስታ እየተሰማው፣ «ኧረ ገና ይቀራታል» ብሎ
ፎክሮባታል።

ካርለት የከሎ ሆራ ከብት ዘለላ ወቅት ከልጃገረዶች መሃል ሆና አንጋዞች ሲገርፏት ግርፊያውን ፈርታ ስትንቀጠቀጥ የነበረውንና
ከተገረፈችም በኋሳ የጮኸችውን ደልቲ ገልዲ ሰምቶ ሐፍረት
ተሰምቶቷል፣ «ባለጌ! ልጃገረድ እንዴት ለግርፋት ትንቀጠቀጣለች? ...ቆይ ብቻ ልክ ሳላገባት ከቀረሁማ እኔ አይደለሁም! እያለ ተማሮባታል"

ደልቲ ገልዲ የእንግዳዋ ልጃገረድ አቀራረብ ልቡን የሚያራራ ሆኖ ቢያገኘውም፣ የሐመር ልጃገረዶች የሚያሟሉትን ባህላዊ ደንብ
ባለማሟላቷ ግን ቅር መሰኘቱ አለቀረም" ደልቲ መቼም አንዴ ከአፉ
አውጥቶ ሊያገባት በመወሰኑ እንጂ ልቡ ያለው ከሌላ ልጃገረድ ጋር
ነው። ያችን ልጃገረድ ሊያገባትና የግሉ ሊያደርጋት ቢችል ኖሮ
መቼም በሕይወቱ ቀረኝ የሚለው ነገር ባልነበረም ነበር። ግን ልጃገረዷን ሊያገባት አይችልም" አንድ ቤተሰብ ናቸው፤ የልጅቷ
እናት የካርላ ጎሳ አባል ናት። እሱም ከዚሁ ቤተሰብ ነው። የካርላ ጎሳ የጉለትን ጎሳ ሊያገባ ይችላል" የካርላ ጎሳ የካርላን ጎሳ፣ የጉለት ጎሳ የጉለትን ጎሳ ግን ሊያገባ አይችልም" ሊጋቡ የሚችሉት ፀንጋዞች
(ባዕዳን) ብቻ ናቸው" ይህም ሆኖ ግን ደልቲ ሊያገባት ባይችልም
ሊወሽማት ይችላልI ችሏልም" ጉድ የሚፈላው ግን ባል አግብታ የሄደች እንደሆነ ነው።

ባል እንዳታገባ ደግሞ ሊያግዳት አይችልም" ይህን ላድረግ ካለ አባትየው አይቀበለውም" አባቷ ከልጁ ባል ጥሎሽ ማግኘት አለበት" ጥሎሹን ካገኘ ደግሞ የሷ ጉዳይ «ጉም መዝገን» መሆኑ ነው።
በእርግጥ ደልቲ ሌላ ባል መጥቶ ከሚወስዳት እጥፍ የሆነ ጥሎሽ ከፍሎ ሊወስዳት ይችል ነበር። ችግሩ ግን ይህ አልነበረም፤ የሱ ችግር እሷና እሱ የአንድ ጎሳ አባል በመሆናቸው ጋብቻ ሊፈጽሙ አለመቻላቸው ነው። ከሎ ሆራ ግን የጉለት ጎሳ በመሆኑና ጎይቲ
አንተነህ የካርላ ጎሳ በመሆኗ ሁለቱ ፀንጋዞች (ባዕዳን) ስለሆኑ መጋባት
ይችላሉ።

ጎይቲ አንተነህም እንደ ደልቲ ገልዲ በውኗ መቃዠቷ አልቀረም። ብዙ ወንዶች ታውቃለች፤ እንደሱ ግን ልቧን የሰረቀባት
ወንድ የለም" መጀመሪያም ቢሆን ከእሱ ጋር አካል ለአካል ከመነካካታቸው በፊት የወሮን መንደር ኗሪ እንደ አውሎ ነፋስ
በነፈሰው ወሬ የደልቲ ገልዲ ጀግንነት እየተወራ፣ ዘፈኑና ሙገሳው ሲቀልጥ፣ በዝናው በእጅጉ መጐምዠቷ አልቀረም
ከልጅነቷ ጀምሮ ከአባቷ እየሰማች ያደገችው የጀግንነት ታሪክ፣
ጀግንነት ውሎ፣ የጀግንነት ሞት ነው" ስለዚህ፣ ጀግና ትወዳለች፣ ገዳይ ታከብራለች" በየወንዙና በየእንጨት ለቀማው፣ ማንነቱን ገና ያላወቀችውን ጀግና ስም በሐመር ጫካና ተራራ ድምፅዋ እያስተጋባ
ዘፍናለታለች" ከልጃገረዶች ጋርም ገና ሳያዩት እየተሣሣቁ፣ «የኔ
ነው የኔ ነው» ተባብለው ተነታርከውበታል"

ጎይቲ አንተነህ ይህን ሰው የምትወደውና የምታደንቀው ከልቧ
ነበር። የሌሎችን ልጃገረዶች እውነተኛ ስሜት ግን አታውቅም። ያ ሰው ግን እንዲያ በቀላሉ ሊከሰትላትና ልታየው አልቻለችም"

አንድ ቀን ከሌሎች ልጃገረዶች ጋር ገበያ ውላ ስትመስ ግን ከወንዶች መሃል ሳዳጉራውን (ሽርጡን) ለብሶ፣ በላዩ ላይ ዝናር የታጠቀ፣ በአንገቱ ልጃገረዶች የሸለሙትን ጨሌ ለማስታወሻ አጥልቆ፣ ክናዱ ላይ አንባር፣ ጣቱ ላይ ደግሞ የመዳብ ቀለበት ያጠለቀ፣ ጸጕሩን በባህሉ መሠረት ተሠርቶ የሰጎን ላባ የሻጠ ሸበላ ላይ ልጃገረዶች ሲጠቋቆሙ፣ «ይእ! ምንድን ነው? ማነው?» ብላ
ጠየቀች  ጎይቲ። ልጃገረዶች «ይእ! አታውቂውም ማለት ነው? »
ተሣሣቁባት አፈረችና፣ «በቃ አላወቅሁትም ንገሩኝ» አለቻቸው
“ደለቲ ገልዲን ነው የማታውቂው? ይልቅስ አታሹፊብን» አሏት።

ያን ሁሌ የምታልመውን ሰው፣ እንዲህ እንደ ዘበት አይታው ልታልፍ፣ «እሱ ነው ለካ፣ አፈር በሆንኩት!» አለች ጎይቲ፣ ለምን
እንደዚያ እንዳለች ግን አልገባትም። «አሁን ይሄ እውነት ሰው ነው?
አቤት ውበት! አቤት ቁመና!» በማለት አፏን ከፍታ ማየቷን ቀጠለች" ጓደኞቿ እርስ በርስ እየተጨዋወቱ፣ እሷም አብራ ያለች መስሏቸው የተለመደ የወሬ ፍትፍታቸውን መጐራረስ ቀጠሉ።

«እከሌን ታውቂዋለሽ? »
«ይእ! እንዴት ነው ታውቂዋለሽ?»
«ግንኙነት አላችሁ? »
«አዎና!»
«አንችስ? »
«እኔም አዎን አውቀዋለሁ።» ይሣሣቃሉ። ደግሞ እንደገና
ሌላውን ይጠያየቃሉ። መቼም በሐመር ልጃገረዶች አንድ ላንድ ብቻ መወሰን ጥላቻንም ሊፈጥር ይችላል። የኔይቱ ቆንጆ ባትሆን ነው፣የኔው ቆንጆ ባይሆን ነው፣ ሌላው (ሌላይቱ) ያልፈለገው (ያልፈለገችው) ስለሚባባሉ መራራቅ በመሃላቸው ሊፈጠር ይችላል" በሐመር
ማኅበረሰብ ፍቅር ነፃ ጨረታ ነው" የጨረታው ዕጣ ግን በሴቷ ፍላጎት
ይወሰናል" ስለዚህ አንዲት ልጃገረድ ለብዙ ወንዶች፣ ብዙ ልጃገረዶች በአጠቃላይ ለመንደሩ ጐረምሶች ይሆኑና መቃበጥ ነው።

ጎይቲ አንተነህ ከልጃገረዶች ተለይታ ደልቲ ገልዲን እንደ
ተአምር ስትመለከት፣ ጓደኞቿን ረሳቻቸው ደልቲ ገልዲ ይህ ሁሉ ሲሆን አላያትም ነበር፤ በኋላ ግን ድንገት ዓይኑን ወርወር ሲያደርግ ዓይኗን ቀድሞ ተመለከተው አያት፤ አየችው፤ እንደገና አያት፣
እሷም አየችው። ብዙ ከቆዩ በኋላ ለሰላምታ አንገቱን አወዛወዘሳት"እሷም አጸፋውን መለሰች።

በሐመር ባህል ሰላምታ ከዕረፍት በኋላ ነው። ወዳጅም ሆነ ዘመድ
ድንገት ሲገናኝ ሮጦ አይተቃቀፍም፤ ሰላምታ አይለዋወጥም"
የሚደረገው ራቅ ራቅ ብሎ መቀጥ ወይንም መቆም ነው።ከሩቅ አካባቢ የመጣ ከሆነ እንዲያውም ካለምንም የቃል ልውውጥ ቁርቀት ይነጠፍለትና ለመቀመጫም፣ ለትራስም የሚገለገልበትን በርኮታ
ተንተርሶ ይተኛና ዕረፍት ይወስዳል። በሐመር ማኅበረሰብ መንቀዥቀዥ፣ መዘባረቅ የለም። ሁሉም የሚፈጸመው በሥርዓት ነው።

ስለዚህ እንግዳው፣ «እንደምን ናችሁ?» ይላል።
«ደህና ነን፤ እናንተስ እንደምን ናችሁ?» ይላል አባወራው ወይንም የቤተሰቡ አባል።

«ደህና ነን። ከብቶችስ ደህና ናቸው? » እንግዳው ደግሞ
ይጠይቃል።

«ደህና ናቸው። የእናንተስ?»
«ደህና ናቸው።»

«የአባካቢያችሁ ሰላምስ እንዴት ነው?»

«ደህና ነው" እናንተስ ዘንድ?»እየተባባሉ ጨዋታቸውን በሥርዓትና በእርጋታ ይቀጥላሉ እንጂ አፍ እንዳመጣ መዘላበድና
«ሲበሉ እንደላኩት» ያንንም ይህንንም ያዝ ለቀቅ ማድረግ የለም።ከዚያ በኋላ የሚበላ ይቀርብና ሚስት ለብቻዋ ወይንም ከልጆች ጋር፣ባለቤቷና እንግዳውም ለየብቻቸው ቤት ያፈራውን ይቀማምሳሉ።
👍243
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ካርለት ቆዳ ለባሽ፣ በባዶ እግሯ ተጓዥ፣ እንጨት ለቃሚ ብትሆንም ከዓለም ሕዝብ በመንፈስ አልራቀችም" ሕይወትን እስአ ሥሯ ድረስ ጠልቀው በማየት የኳተኑና የሰው ልጅን ውድቀትና ድል፣ ሽንፈትና ግብ፣ የሕይወትን ለስሳሳና ሻካራ፣አቀበት
ቁልቁለት ጐዳና እየለዩ ሳያሳርሩ ወይም በረዶ ሳያደርጉ የቀሩት
የታታሪ ሰዎች የሕሊና ጭማቂ የሆነውን መጽሐፍ ታነባለች" አዲሳባ
ከከሉ ጋር ስድስት ጊዜ ደርሳ ስትመለስ ይዛቸው የምትመጣቸው
መጽሔቶችም በዓለም ላይ በመከናወን ላይ ያለውን የፖለቲካ የኢኮኖሚ ለውጥ እንድትገነዘብ አስተዋጽኦ ከማድረጉ ሌላ ከተለያዩ
ጣቢያዎች የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ትከታተላለች።

ካርለት በሐመር ለጥናት ለመቆየት ያሰበችው ጊዜ ስላነሳት እንዲራዘምላት ጠይቃ የተፈቀደላት ሲሆን፣ ለዓለም የሴቶች ድርጅት
ያቀረበችው የፕሮጀክት በጀትም ተቀባይነት በማግኘቱ በጀት
ተጨምሮላታል" ይህም ከሎና ጎይቲን የእንግሊዝን አገር አንዲጎበኙ ስቲቭ የተቻለውን ሁሉ እንዲጥርላት ለመንገር አደፋፈራት ካርለት በሐመር ኑሮዋ መጽሐፍ ከማንበቡ ሌላ ሙዚቃ ማዳመጥ
የምትወድ ሲሆን ከሦስት መቶ ዓመት በፊት የኖረውን የሐይደ ሲንፎኒ፣ የጀርመናዊው የባህን የባሮክ ሙዚቃ የሞዛርትንና የቤቶ ፒያኖ ሶናታና ኮንችት ከጥንቱ ሙዚቃ የምታዳምጥ ሲሆን፣ የተለያዩ ባለ ስርቅርቅ ድምፃውያን የአገረሰብ፣ ሮክና ሮል ሙዚቃ ከማዳመ
ጧም ሌላ በዘመናዊ መንገድ በኮምፒውተር፣ በሒሳባዊ ቀመርና
በአጋጣሚ የተቀነባበሩ «አጥንት በሽ» ሙዚቃ ሰው ሠራሽ እጅ ካልገባበት የተፈጥሮ አካባቢ ሆና ስታዳምጥ እሷም እውነተኛ
ስሜት ይሰማትና እንባዋ በእርጋታ እየተንኳለለ ሲወርድ ትንሽ ወንዝ
ዳር እንዳለች ሁሉ ኮለልታው ይሰማታል። ከስሜቷ ታዳምጣለች
ትመሰጣለች ትረካለች፤ ታነባለች ወደ ታች ጠልቃ ወደ ላይ መጥቃ ትጓዛለች" ትክክኛ ስሜት ንጹሕ አየር ይፈልጋል የተፈጥሮ መዓዛና ውበትን ይሻል" የሐመር ተፈጥሮ ደግሞ ለዚህ የተፈጠረ ነው አዕዋፍ በነፃነት የሚያዜሙበት፣ ዕጽዋት ጎንበስ ቀና
የሚሉበት፣ ንጹሕ አየር እንደ ጊሽጣ የሚገመጥበት ነው የሐመር ምድር!

በዓለማችን ስንቱ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አሮጊቶች,በጦርነት
የእሳት ላንቃ ተጠበሱ፤ dንትና ስንት ሰው በተፈጥሮ አደጋ አለቀ ስንቱስ በረሃብ ላንቃ ተቀጠፈ አቤት ይህች ዓለም ስንት ዋይታ
ተሰማባት? ስንቱ እንባውን አፈሰሰባት? እነዚያ ሁሉ እንባዎች እስከ አሁን ብዙ ውቅያኖስና ባሕር ፈጥረዋል፤ ወደፊትም ለቁጥር የሚታክት ውቅያኖስ መፍጠራቸው አይቀሬ ነው የዘመናችን
ውጣውረድና ጠባሳ ከቶ በምን ይለካ ይሆን?

ካርለት ዋይታው፣ ለቅሶው፣ የዝናቡ ነጠብጣብ ሳይቀር ሕሊናዋን እየሰረሰሩ የሚገቡ እስኪመስላት ተመስጣ ታነባለች የሙዚቃ
ቃናዎችን ትረዳለች። አዎ ማየትማ ሁሉም ያያል መስማትማ ሁሉም ይሰማል። ሁሉም አምስት የስሜት ሕዋሳት አለው።
ብዙዎቻችን ግን አምስቱን ሕዋሶቻችንን የምንጠቀመው ለየቅል
ተናጠል ነው ጥቂቶች ብቻ አንድ አድርገው ያዩትን ይዳስሱታል ያሸቱታል፤ ይቀምሱታል፤ ይስሙታል።
ካርለትና ከሎ ሆራ የታደሉት ይህን ጸጋ ነው" የሚፈልጉትን ነገር በመላ ሕዋስ መፈተሽ፣ በሥራ መበርታት፣ ለዓላማ ስኬት
መሞት፣ ያሰቡትን ከፍጻሜ ማድረስ መቻልን ከልምድ ተማሩ።

ስለዚህ ሲጀምሩት ራሳቸውን የወቀራቸው ጭንቀት በአእምሮ ፈውስ
ተተካ። ዛሬ ዛሬ ከነበሩበት ይልቅ እየፈሩ የገቡበት ሕይወት ጥልቅና እውነተኛ ነው። ካርለት የደልቲ ገልዲ ሚስት ሆና ለመገረፍ፣
በእንብርክኳ ትንባሆ ለማቀበል፣ ሸፈሮ ቡና ለማፍላት፣ የከብት አዛባ
ለመዛቅ ቸኩላለች። ካርለት አሁን የእውነተኛ አንትሮፖሎጂስትነት
ስሜት እየተሰማት፣ ራሷን በራሷ የማትደልል፣ ከሕሊና ወቀሳ የራቀችና ከአምላክ የተሰጠውን ጸጋ የተላበሰች ናት። ሁሉን ለማወቅ፣
ከባዱን ለመሞከር መቻሏን ፈትናለች ከእንግዲህ በዚህ ውድድሯ አሸንፋ ለመውጣት ከቻለች፣ «ለመሆኑ በማሸነፍሽ ለምን ደስ አለሽ?» ተብላ ብትጠየቅ መልሷ፣ «ምክንያቱም ውድድሩ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው» ብላ መመለሷ አይቀርም" ማሸነፍ የሚያረካው ደግሞ
የውድድሩ ውጣ ውረድ ሲበዛና ተወዳዳሪዎችም ጠንክረው ሲገኙ ነው።

«በሕይወት ውድድር ላይ ያለ ሰው ውድድሩ ከራሱ ጋር እንጂ በምድራችን ያሉትን ቢሊዮን ሕዝቦች በማሰብ መሆን የለበትም"
ይህን ካሰበ ግን በጭንቀት ብቻ ተደናቅፎ ይወድቃል» በማለት ካርለት ከሎን ደጋግማ መክራዋለች።

ደልቲ ገልዲ ካርለትን ለማግባት ኮይታው በሽማግሎች እንዲወሰን አስደረገ። ጥሎሹ ብዙም ከባድ አልነበረም፤ ቢያንስ
አራትና አምስት ዓመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ከፍሎ ሊጨርስና
እንግዳዋን የራሱ አድርጎ ያኔ በሚያውቀው ባህላዊ ደንብ ደህና አድርጎ ይገራታል።

ካርለት አሸዋማና ገላጣ ስፍራ ላይ፣ ዙሪያውን የፌጦ፣ የኩንኩሮ፣ የጠዬ የዝግባና ዋንዛ ዛፍና የሻንቆ መንደር ባለበት
የኢቫንጋዲ ጭፈራ ቦታ ከደልቲ ገልዲ ጋር ሲጨፍሩ በተለይም ወደ ጫካ ሲገቡ የምታወልቀው የውስጥ ሱሪ፣ ወደ ላይ ከፍ አድርጋ
የምትገልበው ልብስ፣ አሁን የላትም። የውስጥ ሱሪዋም ሆነ ልብሷ ቆዳዋ ነው፤ በውኃ መታጠቧን አቍማለች፤ ጸጕሯን በቅቤ የተለወሰ አፈር ትቀባለች። ይህን በማድረጓ የደረሰባት የጤና ችግር የለም"
በእርግጥ መጀመሪያ አካባቢ ቆዳዋ ለብ ለብ የተደረገ ለጋ ስጋ ጥብስ፣ ቀጥሎ ተዘልዝሎ የደረቀ ቋንጣ መስሉ ጠቁሮ ታይቷል።በተረፈ የቈሰለው ሁሉ ድኖላት፣ ወዟ እንደ ሐመር ልጃገረዶች ነው፤
ሕሊናዋም ደስተኛ ነው።

ደልቲ ገልዲ ግን አሁንም ብዙ የምታስተካክለው እንዳለ ያምናል" ያ ደግሞ የሚሆነው እሱ እሷን አጠቃሉ የራሱ ካደረገ
በኋላ ነው። ስለሆነም ጥሎሹን በቶሎ ለመጀመር ወስኗል።

በመካከሉ ግን፣ ከሎና ካርለት ከተመካከሩ በኋላ ከሎ ሆራ ደልቲ ገልዲ ዘንድ ሄደ። ደልቲ ገልዲ፥ ከሎ ሆራ የሱ ፍቅረኛ የሆነችውን
ጎይቲ አንተነህን ለማግባት የተሪ ቆዳ አጋድሞ፣ ኩርኩፋ
አጉርሷታል። ስታስደንሰው፣ ስታዝናናው የነበረችውን ፍቅረኛውን ሊነጥቀው ነው። ደልቲ ገልዲ እሷን ሊያጣ በመቃረቡ ልቡ እየዘለለ
ፈርጦበታል። ከከሎ ሆራ ጋር ግን ነገር የለውም። ከሎ ሆራ ሐመር ነው። በሐመርነቱም ብቻ ሳይሆን ባህላዊ ሥርዓቱንና ደንቡን
አሟልቶ እጮኛውን ለመምረጥ ዞሮ ጎይቲን መርጧል። ይህ መብት
የመላው ሐመር ማኅበረሰብ መብት ነው፣ «ፍቅረኛዬን ቀማኸኝ
እገላለሁ፤ እታነቃለሁ» እያሉ ማላዘን ንክ ያሰኛል" ጀርባን
ግርፋት፣ የበረት ከብትን ለጥፋት ይዳርጋል። በማኅበረሰቡ ትልቁ
ኃይል ያለው በዚያው በማኅበረሰቡ እጅ ነው። መሣሪያና ጕልበት
ያለው ጀግና የሚባለውም የማኅበረሰቡን ባህልና ደንብ ሲያከብር ነው። ካለበለዚያ ግን በኃይል የሚያምን ልብ እንደ ጌሾ በማኅበረሰቡ እጅ ይወቀጣል። «ከባሕር የወጣ ዓሣ» ይሆናል። ስለዚህ፣ ከሎ ደልቲ ገልዲ ዘንድ ሲሄድ በፍቅር ተቀበለውና ሲጨዋወቱ ቆዩ።በዚህ መልክ ትንሽ እንደ ቆዩ ከሎ ሆራ ወደ መጣበት ርዕሰ ጉዳይ
ተመለሰና፣ «...እንግዳዋ ለብዙ ጊዜ እዚህ አትቆይም። ከተወሰነ
ጊዜ ቆይታ በኋላ ትመለሳለች። ስለዚህ አንተን በቅርቡ ልታገባህና
ልታገለግልህ ትፈልጋለች» አለው፣ ከሎ።

«ይእ! ጥሎሹን ገና ሳልጀምር፤ እንዴት ሆኖ ይሆናል? መቆየት አለባት እንጂ። ደግሞስ የኔ ሚስት መሆን ከፈለገች የት ነው
የምትሄደው? እኔስ ይህን እፈቅድላታለሁ? የትም አትሄድም። እዚሁ ሥራ ትሠራለች» አለ ደልቲ።
👍18👎1👏1😁1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ጎይቲ አንተነህ ከሎ ሆራ አጎት ቤት እንደ መጣች ፈጽሞ መንፈሷ ሊረጋጋላት ባለመቻሉ ካርለት የምታደርገውን አጣች" ጎይቲ ጽጕሯን ስትላጭ ካርለት ብቸኝነት እንዳይሰማት አብራት ተላጨች በከሰልና በቅቤ የተለወሰውንም ቅባት መላ ሰውነቷን ስትቀባ ካርለትም አብራት ተቀባች"

ጎይቲ አንተነህና ካርለት አልፈርድ ቆጥ ላይ ከተደበቁ በኋላ ካርለት ጎይቲን ለማጽናናትና ለማደፋፈር ብትጣጣርም አልሳካልሽ አላት ጎይቲ እንዲያውም ፊቷን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዞረችባት
ካርለት ሁኔታው አስደንጋጭ መሆኑን ብታውቅም ሦስት ወር  እስኪሞላቸው ድረስ ቆጡ ላይ መቆየት ነበረባቸውና እስከዚያ ድረስ
በመካከላቸው እርቀ ሰላም እንደሚወርድ ተመኘች"

ቀኑንና ምሽቱን ቆጥ ላይ ከቆዩ በኋላ ለአንድ አፍታ ወረድ ብለው ከሎ ከመምጣቱ በፊት ለመናፈስ ወጡ" ጎይቲ አነተነህ ቆጥ ላይ መውጣቱ አልዋጥልሽ ብሏታል።

«አሁን እሱ የወንድ ልብ አግኝቶ እኔን ሊመታኝ? በየትኛው ወኔውና ጀግንነቱ፤ ወይ ሲያየኝ እሱ ራሱ ባልተርበተበተ አይደል?
ወይኔ ጎይቲ የወንድ ልጅ ዱላም ይናፍቃል ለካ?» አለች ለካርለት ይሁን ለማን እንደተናገረች ሳይታወቅ።

ወደ ጎጇቸው ሲመለሱ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከከሎ ሆራ ጋር ፊት ለፊት ተገናኙ" ከሎ ሆራ ሁለቱንም ሲያይ ደንገጥ ብሎ ቆመ!
ካርለት በዓይኗ ጠቅሳ እንዲመታት ልትነግረው ፈልጋ ነበር። ለእሱ
«ና ምታት» ብላ በዓይን ለማመልከት እንዴት እንደምታደርግ ስከታስብ ግን እሱ ከቆመበት ደረሱ። ከሎ ሆራ መንገዱን ለቆ
አሳለፋቸው። ካለፉ በኋላ ግን ተሰማው፤ በባህሉ መሠረት እንዳያት ደህና አድርጎ መግረፍ ነበረበት። ያን ሲያስብ የብሽቀት ስሜት ታየበት፤ ጎይቲ አንተነህን ይወዳታል፣ ባህሉንም ያከብራል
ቅሬታና ቂም የሚይዝ ከሆነ አካል በማይጎድልበት መንገድ መምታቱ
የሚያመጣው ችግር የለም።

«ወደፊት ግን ይህን ጥፋት መድገም የለብኝም" በመምታቴ ጎይቲ አንተነህን የሚሰማት ነገር የለም። እንዲያውም እሷን ባለመደብደቤ ቅሬታ ሊያድርባት ይችል ይሆናል» እያለ፣ ራሱን ወቅሷል"
ካርለትም በበኩሏ ትንሽ በሽቋታል። ከሎ ሆራ ጎይቲ አንተነህን ፊት ለፊት ባገኛት ጊዜ ሁሉ እንዲገርፋት ተመካክረዋል። ጎይቲ
አንተነህ ደግሞ የከሎን የፍቅር ፍርሃት ባለመረዳት ሲርበተበት ስታየው ባሕርይው ያስጠላታል። ከሎ ወንድ ወንድ አልሸትሽ
ብሏታል። «ከሎ ትክክል አልሠራም። እሱ ጎይቲን ልክ ከተማ እንዳየው
ብዙ ሕይወቱን እንዳሳለፈበት በጠባይ ሊያግባባት፣ ሊያቀርባት
ፍቅሩን ሊገልጽላት ይፈልጋል" ጎይቲ ግን ወንድ ልጅ በቅድሚያ የምትፈልገው ኰስታራነት ነው ኵሩ ወንድ፣ ሸንቆጥ የሚያደርግ ወንድ፣ እሷን በፍቅር ገርቶ፣ በፍቅር አብሯት መጋለብ ይችላል
ሴት ልጅ ዱላ ሲያርፍባት የሴትነት ፍላጎቷ ከአሸለበበት ይቃል»
አምጭ አምጭ የሚላት፣ ፍቅር የሚናፍቃት፣ ድሪያ የሚታወሳት ያኔ ነው፤ ከሎ ደግሞ ይህን አልተረዳውም። እንግዳ ነገር ሆኖበታል ሕጉን እያወቀ በተግባር ግን አያከብርም። ይህ ደግሞ ስሕተቱ ነው ካርለት በእንግሊዝኛ ለጎይቲ ነገረቻት። ጎይቲ አንተነህ ግን ያለችው  በጭራሽ አልገባትም እንግሊዝኛ ደግሞ የት አውቃ

ጎይቲ አንተነህ አጠገቧ ያለችው ቀውስ ብቻዋን ስትለፈልፍ ብትደነቅም፣ እሷም ተመሳሳዩን ፈጸመች።

«ይኸዋ ይህ ቦቅቧቃ! እንኳንስ ሲያየኝ እንደ ወንዶቹ ሊገርፈ
ይቅርና መንገድ ለቆ አሳለፈኝ" ባል እኔ ነኛ! እሱ ሚስት ነው እንዴት ሆኜ ከዚህ ሴት ጋር እኖራለሁ? ምነው ያን ቀን ደልቲ
ገልዲን ብዬ ባልሄድሁ ኖሮ፤ እሱን ብዬ በመሄዴ ቀናው እንጂ የታባቱ ያገኘኝ ነበር ይህ ሴት" ሴት ልጅ የባሏ ዱላ ሕይወቷ ፍቅሯ ነው" ታዲያ ይህ ሰው እኔንኮ ሕይወቴን እያጠፋ ነው" እሽ
የኔስ ነገር ይቅር ነገር ግን የሚወለዱት የሁለት ሴት ልጆች መባላቸው አይደል? ወይኔ ያልታደሉት" ወይኔ ወይኔ» እያለች፣ እንባዋ
ታወርደው ጀመር"
ካርለት ትንሿን ቴፕ ከፍታ የምትለውን እየቀዳች በማስታወሻ ደግሞ የሚሰማትን ትከትባለች» ካርለት በአንዳንድ ሁኔታ ላይ እሷም ራሷ እየተስማማች መጣች» በአገሯም፣ አንዳንድ እውቅ ሴቶች ስለ ወንድ ፍቅረኛቸውና ከእሱ ስለሚጠብቁት ባሕርይ ሲያወሱ ነካ አድርገው የሚያልፉት ነገር አለ፣ «ከፍቅረኛዩ ጋር ስንላፋ
ስንታገል፣ የፍቅር ዱላ ገላዬ ላይ ሲያርፍ ልቤ እስኪጠፋ ድረስ ራሴን እሰጠውና የሱን ደግሞ ለመውሰድ ሙሉ ፍላጎት አሳያለሁ ከዚያ በኋላ የምንሠራው የፍቅር ጨዋታ ሁሉ እንደ አይስhሬም እየጣፈጠኝ፣ መላ አካሌ ከጸጕር እስከ እግር ጥፍሬ በርካታ
ሲንበሸበሽ ይሰማኛል" እንደዚህ አድርገው ከኔ ጋር የተጫወቱ ወዶች የፍቅር ዙፋኑን ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም» ብለው
የተለያዩ ሴቶች አስተያየት ሲሰጡ ሰምታለች።

እሷም ቢሆን አንዳንድ ልምዶችን አሳልፋለች" አንድ ጊዜ፣ ስሜ ጃክ ነው ብሎ የተዋወቃት አሜሪካዊ፣ ማንችስተር ውስጥ
ለጉዳይ መጥቶ አንድ የምሽት ዳንስ ላይ ይተዋወቃሉ“ ካርለት
በእርግጥ ወደ ዳንሱ ቦታ የሄደችው ከወንድ ጓደኛዋ ከዴቪድ ጋር ነው ታዲያ አሜሪካዊው አንድ ሁለት ጊዜ በትእዛዝ መልክ ዳንስ
ጋበዛትና ሰውነቷን በጠንካራ እጆቹ ጠበቅ አድርጎ እያሸ፣
አሳመማት። ቀደም ብላ ባሳለፈችው ሕይወቷ ወንዶች እንደዚያ ሰው
አድርገዋት አያውቁም" ሰውነቷን የሚደባብሱት ቀስና ላላ አድርገው
ነው። ሰውዬው ግን መሞረዱ አንሶ በረጅም እጁ መቀመጫዋን ደህና አድርጎ ቸብ ቸብ አደረገላት «ተው» ማለት እየፈለገች፣ ቃሉ ግን
ከጕሮሮዋ አልወጣልሽ አላት" በእርግጥ፣ ዴቪድም ከሌላ ሴት ጋር እየደነሰ ስለነበር እነሱን ልብ አላላቸውም።

አሜሪካዊው ፍጹም በማታውቀው መንገድ ሰውነቷን እየመታ፣ እየሞረደ፣ ልቧን ስልቱን አስቀየረው ከንፈሯን እንኳን
ሲስማት የንከሻ ያህል ሆኖባት እግሯን አንሥታ ለመጮህ ትንሽ ቀርቷት ነበር ግን አልጮኸችም" ዳንሱ አብቅቶ ሲለያዩ ካለልብ ወደ ቦታዋ ተመለሰች እንደ ምንም ታግሣ ሁለት ጨዋታዎችን
አሳልፋ ልቧን ወደ ቦታው ለመመለስ ወደ አሜሪካዊው ሰው ሄደች።
ቆንጅት እንደምትመጪ አውቅ ነበር...» ብሎ አሜሪካዊው ተመጻድቆባታል" ግን ፊቷን አዙራ አልተመለሰችም፤ ተመልሳ ካቴና እጆቹ መሃል ወደቀች ሞራርዶ፤ ቸባችቦ፤ ብድግ አድርጎ ተሸክሟት ወደ አንድ ክፍል ሲገባ፣ እግሮቿ አልተፈራገጡም"
እጆቿ አልተወራጩም፤ አፏም አልቀባጠረም።

ካርለት ይህንን አሜሪካዊ እስከ አሁን ድረስ በዚያች ለሰዓታት ብቻ በዘለቀች የፍቅር ጨዋታ የማትረሳው ትዝታ አስታቅፏት ነግዷላ" ያንን ሰው ለብዙ ጊዜ የተካው ወንድ አልነበረም። ኖራ ኖራ ግን ሐመር ላይ ተመሳሳዩን አገኘች" የሷም ብቻ ሳይሆን የጎይቲም የሆነው ሰው በእርግጥ ለየት ያለ በመሆኑ ሳይወዱ በግድ ሌላ ወንድ ቢያስንቃቸው አይፈረድባቸውም"
ካርለት ቆጥ ላይ እንዳሉ እንዲህ በሐሳብ ተዘፍቃ ቆየችና እናቷ ትዝአሏት" ስለዚህ፣ ደብዳቤ ለመጻፍ ብዕርና ወረቀቷን
አስተካከለችና መጻፍ ጀመረች።

ውድ እናቴ፣

ምን ጊዜም እንደማፈቅርሽ፤ እንደማልምሽ የምትዘነጊ
👍23🤔1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ከሎ ሆራ ጥሩ ጥሩ የባራዝ አርጩሜ ይዞ እሱና ጎይቲ በሚዞሩበት መንደር ሲጓዙ በየምክንያቱ ጎይቲ አንተነህን በአርጩሜ
ይገርፋታል” ለሽንት ስትቆም ለምን ቆምሽ፣ እንቅፋት ሲመታት ለምን መታሽ፣ ደክሟት ቁጭ ስትል ለምን ቁጭ አልሽ እያለ
በየምክንያቱ እንዲገርፍ ባህሉ ያስገድዳል" ሴት ልጅ በኋላ ከቁጥጥር ውጭ ሆና እንዳታስቸግር፣ ባሏ እየገረፈ በማሽቆጥቆጥ ቅን ታዛዥ ሽር ያለች አገልጋይ እንድትሆን ያደርጋል"

ካርለት አልፈርድ ማስታወሻ፣ ካሜራ፣ ድንኳኗን በጨርቅ
ከረጢት ይዛ፣ የፍየል ቆዳዋን በመልበስ አብራቸው እየተጓዘች ከሎ
ጎይቲ የሚያደርጉትን ትቃኛለች የከሎ ዘመዶች ለከሎ የሚያደርጉለትን ስጦታም ትመለከታለች"

ከሎ ሆራ እናቱ ዘንድ ስጦታ ለመቀበል ላላ መንደር ሲሄድ፣ ካርለት እጅግ በጣም አዘነች" ከሎም በጣም ተሰማው። እናትዬዋ
እንዳዩት አቅፈው፣ አንገቱን ሲያሻሹ ቆዩና ካርለትና ሚስቱን ሰላም ብለው ትክዝ ብለው ቁጭ አሉ" ለልጃቸው ምን እንደሚያደርጉለት ጨነቃቸው። ለሱ ስጦታ ያዘጋጁለት መካከለኛ መጠን ያለው ሁለት
ቅል ቅቤና አንድ ቅል ማር ብቻ ነው ከሎ የእናቱን ሁኔታ አይቶ ኃዘን ተሰምቶት ዘወር ሲል፣ ካርለት ተጠጋቻቸው"

«ለምን ያለቅሳሉ?» አለች ትንሽ ዐረፍ ካለች በኋላ።

«ይእ! ልጄ የሚያስፈልገውን ያህል ስጦታ አላገኘማ።»

«እርስዎ ለልጅዎ የሚሰጡት ከብት፣ ፍየል... የለዎትም?»

«የለኝም»

«ለምን?»

«ይእ! እኔ ከብት፣ ፍየል... ኖሮኝም አያውቅም ወደፊትም አይኖረኝም" በልጃገረድነቴ ከብቶች፣ ፍየሎች፣ በጎች የአባቴ
ነበሩ" ባል ሳገባ ደግሞ፣ የባሌ ነበሩ። አሁን ባሌ ሞቷል፤ የከሎ አባት ቢኖር ለልጄ ብዙ ሀብት ይሰጠው ነበር።»

«የባልዎትን ሀብት አልወረሱም?

ይእ! ሚስት እንዴት የባሏን ሀብት ትወርሳለች? ባሏ ሲሞት ለወንድሙ በውርስ ትተላለፍና ወንድሙ ሌላውን ሀብት እንደ ወረሰ
እሷንም ይወርሳል። እኔም፣ ለባሌ ታናሽ ወንድም እያገለገልኩ እኖራለሁ"» አሁንም ባልቴቷ ፍዝዝ እንዳሉ ናቸው"

«ባልዎ የሞቱ ጊዜ መቼም እንዳሁኑ የበለተቱ አይመስለኝም፤ከታናሽ ወንድምየው ጋር ይቃበጡ ነበር?»

«ይ..እ ይሄማ ይጠየቃል፤ ባሌ እያለም ቢሆን ከታናሽ
ወንድምየው ጋር እንጨዋወታለን። እንዲያውም ከሎን የወለድኩት ከሆራ ሼላ ታናሽ ወንድም ነው።» ባልቴቷ ፈርጠም አሉ፣ የሞጨሞጨውን አይናቸውን ወደ ካርለት እየመለሱ።

«ምን? ማለቴ የከሎ ወላጅ አባት ሆራ ሼላ አይደለም ነው የሚሉኝ? የሚጠራው እኮ ከሎ ሆራ ተብሎ ነው።» ካርለት መልሱን ለመስማት ጓጓች።

«ይ..እ! በኛ ባህል አንድ ሴት ከባሏ ታናሽ ወንድም ልጅ ብትወልድ የልጇ አባት የሚሆነው ባሏ ነው። ባሏ እንኳ ሞቶ ከሌላ ወንድ ብትወልድ የልጇ አባት ስም በሟቹ ባሏ ስም ነው
ሚሆነው;»

«እና የከሎ እውነተኛ ወላጅ አባት በሕይወት አለ?»

«አዎን አለ።»

«አሁን እርስዎን የሚጦርዎ ማነው? »

«እሱና ልጆቼ።» ካርለት ይህ ለሷ እስከ አሁን ያልሰማችው አዲስ ነገር ነው" ከሎ ሆራም ስለ ወላጅ አባቱ የሚያውቅ አልመሰላትም" ምክንያቱም የግል ታሪኩን ሲነግራት አባቴ ሞቷል ብሎ ነበር።
ካርለት ወደ ከሎ ሄዳ ጉዳዩን ስትነግረው በጣም ተገረመ። ይህን ምሥጢር እሱ ቀደም ብሎ አያውቅም። ወደፊትም ለማወቅ የሚችል
አልመሰለውም።

«ካርለት አሁን የምትነግሪኝ ሁሉ ለኔ አዲስ ነገር ነውኮ፤
በጥረትሽ ወላጅ አባቴን እንዳውቅና እንዳገኝ እያደረግሽኝ እኮ ነው»
አላት ከሎ።

ካርለት፣ «ምንም አይደለም፣ ይልቁንስ አባትክን ማግኘ;
ይኖርብናል» አለችው።
።።።።።።፡፡።።።።።።።።።።።።
ጂሚ ሼላ ብዙ አላረጀም።  ሰውነቱ ስላለው ጠንካራ ቢሆንም ዕድሜውን ከ60 በላይ ነው። ካርለትና ከሎ ሆራ እሱ ዘንድ ሲመጡ ከጎጆው ፊት ለፊት በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ ፀሐይ እየሞቀ አገኙት። ካርለት ጂሚን ስታየው ደንገጥ ብላ ከሎን ዞራ አየችው ከሎ ሆራና ጂሚ ሼላ በጣም ይመሳሰላሉ። ካርለት ጂሚን እንዳየች
ከሎ ሆራ አርጅቶ ከፊት ለፊት የተቀመጠ መስሏት ነበር"

ጂሚ ሼላ ከሎ ሆራን ለመጠየቅ ሻንቆ መንደር ሄዶ ሳለ ካርለትን
አይቷታል። ስለዚህ እንዳያቸው አወቃቸው" እነሱም ሄደው አጠገቡ
ቁጭ አሉና በሐመር ባህል መሠረት ዕረፍት ከወሰዱ በኋላ፣

«እንዴት ነዎት?» አሉት።

«ደህና ነኝ" እናንተስ እንዴት ናችሁ?» አለ ጂሚ ሼላ።

«ከሎ ለእርስዎ ምንዎ ነው?»

«የወንድሜ ልጅ ነው"» ጂሚ ካርለትን በተመስጦ
ተመለከታት።

«መልኩ ግን ቁርጥ እርስዎን ነው የሚመስለው?»

«ሆራ ሼላና እኔም እንመሳሰል ነበር እኮ።»

«ከሎ የእርስዎ ልጅ እንደሆነ ሰምቻለሁ" እንዴት ነው?»

ካርለት ዋናው ነጥብ ላይ ዘላ ጥቡልቅ አለች።

«እንዴት ተደርጎ?» ጂሚ ሼላ መልሶ ጠየቃት"

«እርስዎ ከከሎ እናት ጋር... ያረጉ አልነበረም? »

«ያማ ባህል ነው።»

«እና እንዴት ከሎ የማን ልጅ እንደሆነ ያጡታል?»

«ይሕ! በሐመር ባህል ልጅ ከወንድም ተወለደም፣ ከውሽማ በአባትነት የሚታወቀው ባል ነው። እኔም ከከሎ እናት ጋር ወንድሜ እያለም ሆነ፣ ከዚያን ወዲህ ግንኙነት ቢኖረኝም ከሎ ከማንኛችን
እንደ ተወለደ የምታውቀው እናቱ ብቻ ናት"»

ካርለት ነገሩ ገባት። «በሐመር ማኅበረሰብ የልጇን ትክክለኛ ወላጅ አባት የምታውቀው እናት ብቻ ናት ለካ!» ብላ፣ ተደንቃ
ቆየችና፣ «ለምን ስምዎ ጂሚ ተባለ?» አለችው፣ ጂሚ ሼላን።

«አንድ ጂሚ የሚባል ፈረንጅ እዚህ መጥቶ፣ ከአባቴ ጋር ተዋውቆ ነበር። እንዳጋጣሚ እናቴ እሱ ከዚህ ሳይሄድ እኔን ወለደችኝ በሐመር ባህል እንግዳ መጥቶ በአጋጣሚ ልጅ ቢወለድ ስሙ
በዚያው ሰው ስም ነው የሚጠራው።»

ካርለት ነገሩ ወዲያው ገባት" ምክንያቱም በዚህ መልክ በሷ ስም የሚጠሩ ሁለት ሕፃናት ታውቃለች
«የከሎ ሆራ እናት፣ የከሎን ትክክለኛ አባት ጠይቄያቸው እርስዎ እንደሆኑ ነገሩኝ» ስትለው፣ ጂሚ ምንም መልስ ሳይሰጣት ከሎ
ሆራን ዓይን ዓይኑን ሲያይ ቆየና እጁን ጎተት አድርጎ ያዘው" ከሎ የወላጅ አባቱ ጣቶች እጁን ሲነኩት፣ ደስታ አይሉት ኃዘን ቅጡ የጠፋ ስሜት በመላ አካሉ ተስለከለከበት" ትንሽ ቆይተው አባትና
ልጅ ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው ተቃቀፉ። የወላጅና ልጅ ፍቅር
በመካከላቸው ታየ ካርለትም የደስታ እንባ አነባች የሐመር ፀሐይ
ግን ወደ መሠወሪያዋ ወደቀች"
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ከሎ ሆራ በፈቃድ ከዩኒቨርሲቲው በተገለለ በሁለተኛ ዓመቱ
ትምህርቱን ለማጠናቀቅ አዲስ አበባ ሄደ። ከሎ አዲሳባ ዩኒቨርሲቲ
ገብቶ ትምህርቱን ከጀመረ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለስቲቭ ደወለለት። ቀጠሮ ተሰጣጡና እሑድ ዕለት ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ከሎ
ከስቲቭ ቀድሞ በቀጠሮው ቦታ ተገኘ። ስቲቭ ልክ በሰዓቱ ሲገባ፣ከሎ ገና ከበሩ ወደ ቀኝ ሲታጠፍ ተመለከተው። ስቲቭ፣ የሆነ ፖስታ ይዞ የመሮጥ ያህል ሲራመድ፣ ከሆቴሉ ማዕዘን ላይ ካለው ሶፋ ላይ ነጫጭ ጥርሶቹን የሚያብለጨልጨውን ከሎን ተመለከተው። ስቲቭ
በማስብበት ወቅት ላገኝህ በመቻሌ በጣም ተደስቻለሁ» አለ ስቲቭ፣
የፈገግታውን መጠን እየጨመረ።
👍34🥰2
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ስሞንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ካርለት የሁለት ዓመት ከሦስት ወር የሥራ ፈቃዷን ልትጨርስ የቀራት አንድ ሳምንት ብቻ ነው ከዚህ በፊት ከአንድም ሁለት ጊዜ፡
የጥናት ፈቃዷን አራዝማለች" ዘመናዊው ሕይወቷን በመዘንጋት ለሐመሩ ንጹሕ ሕይወት ረክታለች" ዛሬ የሐመር ሕዝብ ለሷ የለንደን
ሕዝብ ነው።
ከእንግዲህ ወዲያ ካርለት ኢትዮጵያዊት ነች" ለንደን
የሥጋ ዘመዶቿ፣ ሐመር ደግሞ የመንፈስ ወዳጆቿ የሚገኙበት ነው" በዚህ ቀን ካርለት ከከሎ ጋር ስለ ማኅበረሰቡ የወደፊት ዕጣ
ተነጋግረው ነበርu ካርለት፣ «ሐመሮች በእርግጥ የሚያውቁት ራሳቸውን ነው ከነሱ ውጭ ያለው ዓለም ምን እንደሚመስል
አያውቁም። ይሁን እንጂ ከዓለማችን ውጭ በራሳቸው ደሴት
ተጠልለው ዝንተ ዓለም መኖር አይችሉም" ተወደደም ተጠላ
በክልላቸው ሳይንስ የፈጠራቸው ተሽከርካሪዎችና በራሪዎች
ያልፋሉ። ስለ እነሱ ሌላው ሲያውቅ፣ እነሱም ስለ ሌላው ለማወቅ መቻል አለባቸው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ድልድይ የሐመር ወጣቶች ሲሆኑ፣ የዘመኑን ትምህርት መቅሰም መቻል አለባቸው» ብላ ነገራዋለች" ከሎም ሐሳቧ የሱም እምነት እንደሆነ አረጋግጦላታል"

ካርለት፣ ሐመርን ለመልቀቅ የተወሰኑ ቀናት ሲቀራት ሆዷ
ተሸበረ ተጨነቀች" የገርሲ፣ ፌጦ፣ ኩንኩሮ፣ ጨዋንዛ፣ ግራር ዘንባባ፣ አጋም፣ ጠዬ፣ አንቃ፣ ሌሊሚ፣ ጨውሊምባ፣ ሾላ፣ ዋንዛ፣
እንኮይ...ደኑ የአሰሌ፣ የካራ ሰንሰለታማ ተራራ፣ የላላ፣ የሻንቆ፣የወሮ…መንደር፤ የሐመር ልጃገረድ፣ ጐረምሳ፣ አዛውንት፣
ሽማግሌ፣ ባልቴት ቀብራራው ደልቲ ገልዲ በአእምሮዋ እንደ
ፔንዱለም ባለማቋረጥ እየተመላለሱ (ጨክነሽ ጥለሽን ልትሄጂ እያሉ፣ ልቧን አንጠለጠሉባት።
ካርለት ቀሪውን ጊዜዋን ከብቱን፣ ሰውን፣ ጫካውን ፎቶ ስታነሣ ሰነበተች። ልቧ ግን እንደ ታረደ ዶሮ እየተነሣ ፈረጠባት ስትመጣ
ዳር ዳር ቆመው የተመለከቷት ሐመሮች የጕዞዋን ዜና ሲሰሙ
ሕሊናቸው ኩምሽሽ ብሎ ዓይናቸው በእንባ ሲሞላ ተመለከተች ስትቀርባቸው ሊወጓት ቀንዳቸውን ያዞሩባት የነበሩት ከብቶች
ጠረኗን እየፈለጉ ተጠግተው እጆቿን ላሷት።

ካርለት በሕይወቷ እንዲህ ልብ ሰራቂ የሆነ የሰውና የተፈጥሮ ፍቅር አጋጥሟት አያውቅም። ስለዚህ፣ ልቧ ደረቷን ሲረግጥ፣
ሕሊናዋ አነባ! ዓይኖቿም አለቀሱ።

ካርለት ሐመርን ልትለቅ አንድ ቀን ሲቀራት የኢቫንጋዲ ጭፈራውን ለመካፈል አሸዋማ፣ ገላጣና ዙሪያውን በለመለሙ የሐመር እፅዋት ተከቦ ፍቅር እየተቦካ ወደሚጋገርበት፣ ንብ አበባ
ወደምትቀስምበት፣ አዕዋፍና ሰዎች ጥዑም ዜማቸውን ወደሚያዜሙበት፣ የእፅዋት፣ የአራዊት፣ የአዕዋፍ፣ የሰው ዳንኪራ
ወደሚረገጥበት ስፍራ ተጓዘች።

ካርለት በኢቫንጋዲ ጭፈራ ወቅት ሁሌም እንደምታደርገው
ጀግናውን በዓይኖቿ አማተረች" ጀግናው እየዘለሉ አየሩን ከሚቀዝፉት ጐረምሶች መካከል የለም ካርለት፣ «አምላኬ!» ብላ፣
እንደ መኪና ጎማ ተነፈሰች" በጭንቀት ዓይኖቿ ሲቅበዘበዙ ግን ደልቲ ገልዲ ካለወትሮው ተክዞ፣ ራቅ ብሎ ቆሞ አየችው" ጀግናውን ተክዞ አይታው አታውቅም። ቀጭኔ፣ አንበሳ...የገደሉት አነጣጣሪ
ዓይኖቹ ቦዘው ስታይ ሰውነቷ ተዝለፈለፈባት። ጭንቀት ያዘለው ዶፍ
ዝናብ ሊያለብሳት መጣሁ ወረድሁ እያለ አጕረመረመባት። ካርለት
በደመ ነፍስ ወደ እሱ እየተንቀሳቀሰች፣ «ምን ሆኖ ይሆን?» ብላ ራሷን ጠይቃ ፊት ለፊቱ ሄዳ ቆመች።

«ካርለት» አላትና ዝም ብሎ ዓይን ዓይኗን ተመለከተ

«ምን ሆንክ ደልቲ?» ብላ ጠየቀችው።

ዝም ብሎ ዓይኖቹን ከሷ ላይ አንሥቶ ወደ ጨረቃዋ ወረወራቸው" ካርለት ዘለሽ እቀፊው እቀፊው አሰኛት።
ካርለት» አለ ደልቲ ዓይኖቹን ሳያወርድ።
«አቤት» አለችው:
ደልቲ ገልዲ ግን ዝም አለ ተመልሶ።

እንደ ባልጩት ድንጋይ እያብለጨለጨ የተከፋፈለው የጭኑና
አጁ ጡንቻ፣ ሣንቃው ደረቱ፣ የሚንቦገቦጉት ትናንሽ ዓይኖቹ በጨረቀዋ ብርሃን ካርለት ስታይ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋት
መላ አካሏ እሳት ላይ የወደቀ ቋንጣ ይመስል ኩምትርትሩ ወጣ"

«ወይ አምላኬ፣ ምናለ የልቡን በነገረኝ፤ ምናልባት
መለያየታችን አስጨንቆት ይሆን? መቼም ማለት የፈለገው ነገር አለ
ከአንደበቱ እንዳያወጣው ግን እየተናነቀው ነው» ብላ አሰበች"

ይህን ስታስብ፣ «ካርለት መሄድሽ ነው?» የሚል ከደልቲ ጕሮሮ አፈትልኮ ወጣ"

«አዎ መሄዴ ነው» አለች ካርለት፣ «ምን ሊለኝ ይሆን አምላኬ» ብላ ዓይን ዓይኑን እየተመለከተችው» ደልቲ ግን አሁንም ጸጥ አላት።

«ትወደኝ ነበር?» ብላ የሞኝ ጥያቄ ጠየቀችው ደልቲ ግን ትክ ብሎ አይቷት፣ «አይ» አላት፣ በምፀት" ካርለት መልሱ ከልቡ እንዳልሆነ በሚገባ ተረዳች" ካርለት ያኔስ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆነች ጀግናው እንደገና ጣላት። ስለዚህ፣ እጇን ሰዳ እጁን ያዘችውና ወደ
ሰንበሌጡ ይዛው ገባች“ ከዚያ ጭፈራው በዓይነት በዓይነት ቀጠለ ዳንኪራው ተመታ። አሁንም እንደ ባለፈው ተመልካች በሌለበት የተፈጥሮ አዳራሽ ትርዒታቸውን ለራሳቸው አሳዩ። ዳንኪራው ግን
እንዳለፈው ተስፋ ሰጪ ሳይሆን ለየት ያለ፣ የሰቀቀን፣ የኃዘን፣
የህምታ ውዝዋዜ ሆነ።

በነጋታው ፀሐይ ከወደቀችበት ተነሥታ ወደ መሃል ሰማይ ስትገሰግስ ካርለት ዕቃዎቿን በስቴሽን ዋገን መኪናዋ ላይ ከከሎ ጋር አስተካክለው ጭነው እንደ ጨረሱ ሐመሮች ከየመንደሩ ተሰባስበው

ሴቶቹ ደረታቸውን እየደቁ ሲያለቅሱ፣ ወንዶቹ በርኮታቸው ተቀምጠው ተከዙ። ካርለት ዓይኗ በእንባ ሊጠፋ ተቃረበ" የሁለት
ዓለም ዘመዳሞች ሲለያዩ አምርረው አዘኑ"

ካርለት፣ ከሎ ሆራና ጎይቲ በሽማግሎች ተመርቀው፣ ጀርባቸው በከብት እበት ከተቀባ በኋላ ሦስቱም መኪና ውስጥ ገብተው መኪናዋ ተንቀሳቅሳ አቧራው ሲነሣ የሐመር ጭንቅላቶች ወደ መሬት
አቀረቀሩ" ካርለት ትንሽ ከተጓዘች በኋላ ኢቫንጋዲ የጨፈረችበትንና
የቦረቀችበትን የሐመር ጫካ ለመሰናበት መኪናዋን አቁማ ስትወርድ፣ ከሎና ጎይቲም አብረው ወረዱና እንባቸውን አወረዱ..
ወፎች ግን እየዘመሩ፣ ቱር እያሉ እየበረሩ፣ እየተዳሩ ምግባቸውን መፈለጋቸውን አላቆሙም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በዋናው የመኸር ወቅት የሐመር የተፈጥሮ ውበትና ልምላሜ የክቱን አውጥቶታል" እፅዋት ለምልመው አብበዋል የከስኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ሆኖ ይፈሳል። የቡስካ ተራራ አሁንም ከቦታው ሳይንቀሳቀስ የሐመሮች የታሪክ ሐውልት ሆኖ ፈገግታውን በልምላሜ ያሳያል"

ከአሰሌ ሰንሰለታማ ተራራዎች እስከ ኬንያ ጠረፍ፣ ከኤርቦ እስከ አሪ ማኅበረሰብ የሐመሮች ዘፈንና ዳንኪራ አሁንም ከጫፍ እስከ ጫፍ ያስተጋባል። የሐመር ተፈጥሮ ለሰዎች ብቻ ሳይሆን ከድንቢጥ ወፍ እስከ ጥንብ አንሳ ጆፌ አሞራ፣ ከትል እስከ ተሳቢው
ዘንዶ ከከብት እስከ ሚዳቋና ድኩላ ይፈነጭበታል"

ሁሉም የተፈጥሮ ድምፁን ባሰማ፣ እንቅስቃሴ ባደረገ ቁጥር ውብ የሙዚቃ ቅማሬ ከጋራ ጋራ፣ ከቋጥኝ ቋጥኝ ይስተጋባል" የሐመር ምድር ለሚመጡትም ለሚሄዱትም ሁሌም ያው ነው" መለምለም፣ ማበብ፣ መጠውለግ፣መድረቅ..ተልሶ ደግሞ መለምለም።

ደልቲ ገልዲን መኪናዋ የሚወዳቸውን ጭና በአራት እግሯ ከቡስካ በስተጀርባ ተሠውራበታለች መዝናኛዎቹ፣ መደሰቻዎቹን
ሌባዋ ይዛ በአቧራ ደመና ገብታ ጠፍታበታለች" ደልቲ አሁን ሁለት እግር ያለው ከሌላ ፍጡር ያልተለየ መሆኑን ሳይረዳ አልቀረም
የጎሽን ጀርባ በአንድ ምት ብቻ አከርካሪውን አድቅቆ
የሚያንበረክከው አንበሳ መጨረሻ የዝንብ መዝናኛ መሆኑ የማይቀር እውነት መሆኑን ደልቲ የግድ ሊመለከተው፣ ሊደርስበት ነው"
👍283
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ልክ በስድስተኛ ወሩ እንግሊዝ አገር ውስጥ በሚገኘው የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ሁለት ቆዳ ለባሽ ሴቶች፣ አንድ
ሳዳጎራ ያገለደመ ወጣት፣ ተቃቅፈው በመግባት ቦታቸውን ይዘዋል"
አፉን ከፍቶ የነበረው አዳራሽ ቀስ በቀስ ሞልቶ ተጨናነቀ" የዕለቱ
አንትሮፖሎጂካዊ ጥናት አቅራቢ የአፍሪካ ውስጥ ምርምሯን ይዛ ወደ መድረክ ወጣች።

«…ክቡራትና ክቡራን፣ በተመራማሪነቴ የሠለጠነው ዓለም
ከረሳው ተፈጥሮና ሕዝብ መካከል ተገኝቼ፣ ለዘመናት የዳበረ ባህልና ጥበብ ያለውን ክልል ለማየትና ሕይወቱንም ለመኖር ችዬ እኔ ያገኘሁትን ዕውቀት ለቀሪው ዓለም ሕዝብ ለመግለጽ በመብቃቴ
ደስታዩ ወደር የለውም።

«የሐመር ተፈጥሮ፣ ሰው ሠራሽ ብክለት ያልተጠናወተው ንጹሕ
ተፈጥሮ ነው። በዓለማችን ፍጹም ደስታ ያለው ሕዝብ አለ የሚል እምነት የለኝም" ደስተኛ ሕዝብ አለ ከተባለ ግን ከሐመር ሕዝብ
የበለጠ ደስተኛ፣ ግልጽ፣ በመካከሉ ጠንካራ መፈቃቀር ያለው ያለ
አይመስለኝም።

«በዘመናችን እንደ ብርቅ የሚታየው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሐመሮች ለብዙ ዘመናት የሕልውናቸው የማዕዘን ድንጋይ አድርገውት ኖረዋል" ከዚህ በተጨማሪም፣ የሐመሮች የዳበረ የከብት አረባብ ዘዴ፣ የአመጋገብ ሥርዓት፣ ብሒሎችና ትውፊቶች ወዘተ.ዝብርቅርቁ የወጣውን የዘመነውን ዓለም ዓይነ ልቦና የሚስብ
እንደሆነ አምናለሁ።
«...ለማጠቃለል
ያህል፣ እኔ የምናገረው የማውቀውን ብቻ
ሳይሆን የሚሰማኝንም ጭምር ነው" በእርግጥ ሐመር ላይ ሊሻሻሉ፣
ሊያድጉና እገዛ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ቁም ነገሮች እንዳሉ
አምናለሁ" ሆኖም ግን ከሠለጠነው ዓለም የአካባቢ ብክለት ችግር፣
የበሽታ መስፋፋት፣ ተፈጥሮአዊ ካልሆነ የአኗኗር ሥርዓት ችግር አንፃር የሐመር ተፈጥሮ ማራኪ ነው" ሕዝቡም ንጹሕ ሕሊና፣የዳበረ የአኗኗር ልምድ፣ ተፈጥሮአዊ ፍቅርና በራሱ የሚተማመን
ሕዝብ መሆኑን ሳረጋግጥ በዓለማችን እውነቱን በመመስከር ከታወቁት ምስክሮች ራሴን እንደ አንዱ እቈጥረዋለሁ።

«..ቀሪው ዓለም አፍሪቃውያንን መርዳት ብቻ ሳይሆን፣አሁንም ከአፍሪቃውያን ብዙ የሚማረው እንዳለ ማወቂያው ጊዜ
አሁን ነው» የሚለው፣ በጽሑፍና በተንቀሳቃሽ ሥዕል የተደገፈው
ጥናቷ ተመልካቿን ከመቀመጫው ናጠው።
ተመራማሪዋ በባዶ እግሯ፣ ቆዳዋን እንደ ለበሰች ጥናቷን ስታቀርብ ቆይታ ስታጠቃልል ያችን ችግርና ሰቆቃ ተቋቁማ፣ የሁለቱን ዓለም ልዩነትና አለመግባባት አስወግዳ፣ እውነተኛ ሰብአዊ ፍቅርንና ሕይወትን ያሳየች ተመራማሪ የአድናቆት ጭብጨባና ጩኸት ለደቂቃዎች በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ
በማይታወቅ መልክ ቀረበላት። ካርለት አልፈርድ ተባባሪዋንና ጓደኞቿን ይዛ ወደ መድረክ ስትወጣ ጭብጨባው ይበልጥ ጋለ"
ከሎና ጎይቲም ሕሊናቸው በደስታ ረካ።

ሦስቱም ጓደኛሞች በሐመር ደን መካከል እንዳደረጉት ሁሉ፣በማንቸስተሩ የጉባኤ አዳራሽም ተቃቅፈው አነቡ እየሣቁ አለቀሱ።
በአውሮፓ ሕይወት ከሎ ብዙውን ጊዜውን በትምህርት አሳለፈ
ጎይቲ ግን ከካርለት ቤተሰቦች ጋር ተቀመጠች" ጎይቲ በዓይን ማየት
ቀርቶ በወሬ እንኳን በአሳለፈችው ሕይወት ያልሰማችው ጉድ ውስጥ
ስትገባ በእውኗ መቃዠት አበዛች።

ከካርለትና ከከሎ ጋር መጀመሪያ ከሐመር ሲነሡ የመኪናው ጕዞ ደስ ብሏት ነበር" ከካርለት ጋር በመኪና መካ፣ ቱርሚ፣ ጂንካም
ሄዳ ስለነበር እንደ ልማዷ መኪናዋ ስትጓዝ የሐመር ሰዎችና እፅዋት ወደ ኋላ ሲሮጡ እሷ በሣቅ ፍርስ ብላለች" አንዴ ወደፊት፣ አንዴ ወደኋላ ስታይ እንደ ቆየች ግን የሆነ ነገር ሆዷን አሸበራት" ወዲያው
ለካርለትና ለከሎ፣ «ይእ! አያችሁልኝ የኔን ነገር አገሩን ሁሉ ስሰናበት አያ ደልቲን ግን ሳልሰናበተው ስመጣ? ምናለ እናንተዬ
ብትመልሱኝ? አሁን ባል በማግባቴ አንጀቱ የተኰማተረው አንሶት
መሄዴን ሲሰማ ሆዱ መንቦጫቦጩ ቀረ! ጀግና ሰው ልቡ ቶሎ
ይቀየማል» አለች።

«ጎይቲ አሁንማ ብዙ ርቀን መጥተናል" ቀደም ብለሽ አስበሽው ቢሆን ኖሮ ብንመለስም አይከብድም ነበር" አሁን ግን ብዙ ርቀናል" አንቺስ አያ ደልቲ የሚገኘው ከስኬ ወንዝ አሸዋ ላይ ተጋድሞ
መሆኑን እያወቅሽ ለምን ሄደሽ ሳትሰናበችው ቀረሽ?» አላት ከሎ
«ይእ! እናንተ ልቤን አጠፋችሁታ" እንዲህ አሁን ሆዴን ሊያጥወለውለኝ እዚች መኪናይቱ ላይ መውጣቱም አጓጓኝና
እረሳሁት እንጂ ምነው እናንተዬ ኧረ ኃዘኑ ቅስሙን ይሰብረዋል"ጀግና ሰው ዕድሜው አጭር ነውI መርቀኝ፣ ላገርሽ ያብቃሽ በለኝ ሳልለው ወጥቼ ስመለስ ባጣው ጸጸቱ ዕድሜ ልኬን ይወጣልኛል?» አለች"

«ጎይቲ አያ ደልቲን አሁንም ታልሚዋለሽ ማለት ነው። ድሮ የተቃበጣችሁት አይበቃም?» አላት ከሎ ፈርጠም ብሎ"

«ይእ! ኧረ እይልኝ የአያ ደልቲ ጨዋታ እንደ ከተማ ልብስ የሚወልቅና
የሚታጠብ መሰለህ! ሆድ ዕቃ ውስጥ ነው የሚቀመጥ ያ ደልቲ አንፈራጦ ብቻውን ይዞት የነበረውን ስፍራ አንተ ገብተህ እሱን ወደ ጥግ ወሰድከው እንጂ ከሆድ
አልጣልከው" እኔና እሱ የአንድ ጎሳ ልጅ መሆናችንና አንተ ባዕድ ሆንህ እኔና አንተን አገናኘን እንጂ የዚያ ጀግና ሎሌ ሆኜ ብኖር
ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር» ብላ በሣቅ ስትፍለቀለቅ፣ ካርለትና ከሎአብረው አጀቧት።

ካርለት ጎይቲ በሐመርኛ ቋንቋ የተናገረችውን ካዳመጠች በኋላ፣
«ምነው ሰው ሁሉ እንዳንቺ ግልጽ በሆነ፣ እውነተኛ ስሜቱን ባልደበቀ እዚህ ወርቅ መሳይ ብልጭልጭ ዓለም እውነተኛው ወርቅ
ሕይወት ሐመር ላይ አለ ቢሉት ማን ጆሮውን ይሰጣል" መተማመን
ቀርቶ መጠራጠር ዘውድ በጫነበት በዚህ የውሸት ዓለም እስከ መቼ መኖር ይቻላል?» ብላ፣ ስታስብ ካይኖቿ ስር መጀመሪያ ጉም መሰለ ነገር፣ በኋላ ተከታትሎ እየተስረገረገ የሚንኳለል ትኵስ እንባ
ዓይኗን ሲሞላ፣ መኪናዋን አቁማ መሪው ላይ ተደፍታ መንሰቅሰ ጀመረች።

ጎይቲ መጀመሪያ ካርለት እየሣቀች መስሏት ነበር" የቀላው? ፊቷንና የራሰውን ዓይኗን ስታይ ግን ልቧ በኃዘን ተሰብሮ ቆየችና፣
“ይእ! ምነው አይደክማት እሷ ብቸዋን ደፋ ቀና እያለች እኛ ዝም አልናት። በይ አንቺስ ከምታለቅሺ ዕርዱኝ አትይም? እንደ እርፍ
ወዲያ ወዲህ የምታማስይውን እንደሁ አያቅተኝም። መዘወሩንም
ቢሆን አላጣውም» አለቻት

«ጎይቲዬ አመሰግናለሁ" መንዳቱ ለአንቺ እንኳ ይhብድሻል ባይሆን መኪናውን ከሎ ያሽከርክር፣ ወደፊት ግን አንቺም
ታሽከረከሪያለሽ» ብላ ቦታዋን ለቀቀችለት"

ጎይቲ አንተነህ ደስ ያላት ጕ" እያንገሸገሻት ሄደ" አንገቷ
ደፍታ የማታውቀው ጎይቲ ሆዷን አቅፋ፣ አንገቷን አዘነበለች
ጎይቲ በአውሮፕላኑ ጕዞም ሆነ በአውሮፓው ሕይወት ቋንቋውን ገጽታውን የማታውቀው ትያትር ተመልካች ሆና ሁሉም ነገር
ታከታት። ኵሩው አረማመዷ ስብር ስብር አለ ጥርሶቿ በከንፈሮቿ በጥብቅ ተጋረዱ" የሐመሯን ሸጋ ህምታ ሰፈነባት" ፀሐይ ከእሷ በጣም ርቃ ሙቀቷ ሳይሰማትና ብርሃኗ ሳያስደስታት ወጥታ ገባች
ጨረቃን ከናካቴው ከሰማይ ላይ አጣቻት" ሲያዩት የሚያብለጨልጨውና የሚያምረው ሰው ሠራሽ ውበት፣ እየቆዩ በሄዱ ቁጥር
እያፈናት መጣ" መለምለም፣ ጠውልጎ መድረቅ፣ ተልሶ
መለምለም የማያውቀው የተፈጥሮ ቅመም የጎደለው የቴክኖሎጂው
ዓለም ለውጥ አልባ በመሆኑ እጅ እጅ አላቸው። ንጹሕ አየር፣ ተለዋዋጩ የተፈጥሮ ውበትና የሚያውደው መዓዛ፣ የአዕዋፍ ዝማሬና
የአውሬዎች ጩኸትና ግሳት፣ የጨረቃ ወቅት ዳንስና ጣፋጩ የጫካ
ውስጥ ፍቅር በእዝነ ሕሊናቸው ውል እያለ አስቈዘማቸው"
👍29😁1