አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህያብ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በኤርሚ

ነሀሴ መጨረሻ ላይ ውጤት መጣ ተባለና አየን ጥሩ ውጤት ነው ያመጣሁት ግን ሩቅ ሀገር ነው የመደቡኝ ጎንደር ዩንቨርስቲ በምፈልገው ዲፓርትመንት(ህክምና)

እናቴን እና ልጄን ትቼ እንዴት ችዬ ይህን ያክል እርቃለሁ.. ትምህርቴን መተው እናቴን እንደመቅበር ነው። ሁላችንም ቢከብደንም ግዴታ ሄጄ መማር አለብኝ።
.....
ስራ ቦታዋ ሄጄ ለእናቴ ስነግራት እልልታዋን አቀለጠችው። ደንበኞቿ ምን እንደተፈጠረ ሲጠይቁኝ ነገርኳቸው እንኳን ደስ ያለሽ እያሉ እናቴን አቀፏት..... ከሁኔታቸው እኔ ሳልሆን እናቴ ውጤት የመጣላት ነበር የሚመስለው....
......
ቤት ውስጥ ጎረቤቶቻችንና አንዳንድ የእናቴ ወዳጆች በተገኙበት መጠነኛ የሽኝት ዝግጅት ተደረገልኝ። ልለያት እንደሆነ ያላወቀችው ልጄም ከኔ እኩል ፍንድቅድቅ ብላለች። እንግዶች በልተው ማዕዱ ከፍ ካለ በኋላ እናቴ ወደ መሀል ወጣችና
"አንዴ ፀጥታ...." ብላ ጨብጨብ ስታደርግ ሁሉም ሰው ባንዴ ዝምምም አለ።

"በህይወቴ እንደዛሬ የተደሰትኩበት ቀን የለም ... ልጄ ዩንቨርስቲ ገባችልኝ። ይሄ ከምንም በላይ ትልቁ ህልሜ ነው። እዛ ሄዳ በስኬት እንደምትመለስ እተማመንባታለሁ። ትልቅ ነገርም ባይሆን ይሄን ስጦታ በእናንተ ፊት እሰጣታለሁ" ወደኔ መጥታ ጉንጬን አገላብጣ ከሳመችኝ በኋላ የተጠቀለለውን ስጦታ ሰጠችኝና"ክፈቺው..." አለችኝ። የተጠቀለለበትን ወረቀት ስከፍተው ሞባይል ከነ ቻርጀሩ ብቅ አለ። አላመንኩም እናቴ ለኔ የእጅ ስልክ ገዛችልኝ... በዚያን ጊዜ አብዛኛው ሰው ባለ ሞባይል እየሆነ ቢሆንም እኔ ይኖረኛል ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"አመሰግናለሁ እናቴ.... ደግሞ ቃል እገባልሻለሁ... አኮራሻለሁ"

"እተማመንብሻለሁ የኔ ጀግና.... ሳትሳቀቂ በናፈቅሺን ሰዓት መደወል ብቻ ነው...."ወደ ደረቷ ወስዳ ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ። ይሄን እቅፍ እኮ ስወደው..............
ቃል ባትናገር እንኳን በእቅፏ ብቻ ብዙ መልዕክት የምታስተላልፍልኝ ይመስለኛል።
"በርቺ....
ባንቺ እተማመናለሁ....
እኔ አለሁልሽ...
እወድሻለሁ......." ብቻ ስታቅፈኝ ከዚህም በላይ ብዙ የምትለኝ ይመስለኛል።
..............

የምወዳት ልጄን እና እናቴን ተሰናብቼ ወደ አፄ ፋሲል ሀገር ጥንታዊቷ ጎንደር ተጓዝኩ ።
..........

ምዝገባ እና ሌሎች ፕሮሰሶች አልቀው ትምህርት የምንጀምርበት ቀን ደረሰ...... የመጀመሪያ ቀን እንደመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ቀድሞ ክፍል ተገኝቷል ከነኛ መሀል አንዷ እኔ ነኝ።
.....
ከደቂቃዎች በኋላ
"ይሄ ሸበላ ብቻ እንዳይሆን የሚያስተምረን" ከኋላዬ ያለችው ልጅ ወደ ጆሮዬ ተጠግታ አንሾካሾከችልኝ። ከንግግሯ እኩል ቀና ብዬ ወደ ፊት ለፊቴ አየሁ..... " ዋው ውበት ..... ዋው ቁመና.... ዋው ደረት...." ብዙ ዋው የሚያስብሉ ነገሮችን ያሟላ ሸበላ ሰው.....
......
"እሺ ዛሬ ብዙም የምንማረው ነገር አይኖረንም እርስ በርሳችን እንተዋወቅና ኮርስ አውትላይን እሰጣችኋለሁ...... እምም ከፊት ልጀምር ስምሽን አስተዋውቂን እስኪ...." ምኑ ነው ምን አለ እስከምረጋጋ እንኳን ሌላ ሰው ቢጠይቅ

"ህያብ በዛብህ እባላለሁ የመጣሁት ከአዲስ አበባ" ጣቱን ከኔ ቀጥሎ ወዳለችው ልጅ ጠቆመ

"መቅደስ ገዛህኝ..... ከሀዋሳ
ተፈሪ ይልማ...... ከደሴ
አብሳላት አበበ.... ከአዳማ
የትናዬት ዘመረ..... ከአዲስ አበባ......" ሁሉም ስማቸውን እና የመጡበትን ከተማ ተናገሩ ሁላችንንም ከሰማ በኋላ

" የኔ ስም ደግሞ ዮናታን ይባላል የ...." ከዚህ በኋላ ያለውን አልሰማሁትም .... ዮናታን.... ዮኒ ስሙ ደስ ይላል መልኩም ደስ ይላል። ሳላውቀው ስለሱ ብዙ አሰብኩ.... እጄ ላይ ያረፈ ወረቀት ከሀሳቤ አነቃኝ

"ያልኩትን ሰምተሽኛል ህያብ" ድንብርብሬ ወቶ አይን አይኑን አየው ጀመር እሱም ትንሽ ካየኝ በኋላ

" ተወካይ እስክትመርጡ ድረስ አንቺ ተወካይ ሆነሽ እነኝህን ወረቀቶች ለሁሉም አዳርሺ...." መልሴን ሳይጠብቅ ክፍሉን ለቆ ወጣ። እንዴ ቆይ ደግሞ ስሜን እንዴት ባንዴ ያዘው..... ይገርማል
........
" እና እኔንም አፈዘዘኝ እያልሽኝ ነው" አለችኝ ከፊት ለፊቴ መጥታ

"ይቅርታ እህቴ ምን......"

."ቅድም አልሰማሽኝም የትናየት.... የትናዬት ነው ስሜ"

"እሺ የትናዬት የምትይው አልገባኝም"

"ቀስ ብሎ ይገባሻል ለማንኛውም የራሴን ልውሰድ." አንዱን ወረቀት አንስታ እየተቆናጠረች ከክፍሉ ወጣች።

"ወይ አምላኬ ስንት አይነት ሰው አለ" ብዬ ስዞር ሁሉም አፍጠው የሚያዩኝ እኔን ነው።

ህይወት ልክ በምኞታችን ውስጥ እንዳሰብናት ቀላልና ጣፋጭ አይደለችም። ልንመራት ያወጣነውን እቅድ አስጥላ በራሷ ምህዋር ላይ ታሽከረክረናለች። እምቢ ብለን ብናስቸግራት እንኳን ወይ ከራሳችን እቅድ ወይም ሽክርክሪቱ ከሚያመጣው ነገር ሳንቋደስ ሜዳ ላይ እንቀራለን።

ዩንቨርስቲ መግባትን ሳስብ የሚታየኝ ጠንክሮ መማርና መማር ብቻ ነበር። ግቢ ውስጥ ሆኜ ከትምህርቴ የበለጠ ቦታ እሰጠዋለሁ ብዬ የማስበው ምንም ነገር አልነበረም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የሆነ ሰው መጥቶ ይህን ጥያቄ ቢጠይቀኝ በመጠየቁ ልናደድበት እችል ነበር። ዛሬ ግን ያን እምነቴን የትላንት እቅዴን ሊያከሽፍ የሚችል ፍቅር ያዘኝ። ያውም ውድድር የበዛበት ፍቅር.....
አብሬው ልሁን ብዬ ባስብ እንኳን ከሱ እኔን አለማፍቀር ውጪ ከደርዘን በላይ ሴቶች ጋር መጋፈጥ ይኖርብኛል..... ያውም እኔ የማውቃቸው ብቻ።

ያለኝ አማራጭ አንድ ብቻ ነው ቢከብደኝም ስሜቴን አምቄ መያዝ እና በሰላም ትምህርቴን መቀጠል። ምንም ሳይተነፍሱ ሁሉንም በልብ መያዝ ከምንም በላይ ህመም ነው.... በተለይ ደግሞ ፍቅር ሲሆን...

ብዙ ጊዜ ይሄን አስባለሁ ለእናቴ ይሄ አይገባትም አይደል? ... ስኬቴን ለምትናፍቅ እናቴ ስል ከመጋፈጥ ይልቅ መሸሽን መርጫለሁ። የምሸሽበት ምክንያት ዋናው ቁም ነገሩ እኮ ማፍቀሬ አይደለም ፍቅር በየትኛውም ጊዜ እና ሁኔታ ውስጥ ሊከሰት የሚችል ስሜት ነው። ችግሩ ለዚህ ፍቅር ስል ብፋለም ለትምህርት የሚሆን ነፃ አይምሮ ላገኝ እችላለው ወይ? የበለጠው ችግር ደግሞ ያፈቀርኩት ሰው ሁሉንም ቀማሽ መሆኑ ነው።
፧፧፧፧፧፧
ከዛን ቀን ጀምሮ ማለትም ከመጀመሪያ የትምህርት ቀናችን ጀምሮ በዮኒ ፍቅር ተለክፊያለሁ። ፍቅር እንደያዘኝ እንኳን እያወኩ ላለማመን ከራሴ ጋር ለወራት ተከራክሪያለሁ። የትናዬት በየቀኑ እኔን ማስበርገግ ስራዬ ብላ ከያዘች ቆይታለች። በተለይ ዮናታን አስተምሮን ሲወጣ ወይ ከጎኔ ናት ወይም ከፊት ለፊቴ.... እልፍ ጊዜ እኮ አብረው አይቻቸዋለሁ... ብዙ ጊዜ ቢሮው ስትገባ ያዩዋት ነግረውኛል...... እኔ ደግሞ በተቃራኒው ከሱ ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ሁላ ላፈርስ የምሞክር ሰው ነኝ። ለምን ይሄን ያክል የቤት ስራ እንደሆንኩባት አላውቅም። አሁን ግን መሮኛል ፀብ ላለመፍጠር እያልኩ እንደፈሪ መታየት መሮኛል።

ዛሬም እንደለመደችው ከጥሩ ትወና ጋር የአሽሙር ንግግሯን ተናግራኝ ከክፍሉ ወጣች። ብሽቅ ብዬ ወረቀቶቼን ሰብስቤ ተከትያት እየወጣሁ እያለ አንድ ሰው ከኋላዬ ያዘኝ። ዞር ስል ቢኒ ነው ከተማሪዎች ሁሉ የተለየው ዝምተኛ ልጅ።

"አቤት ቢኒ" አልኩት ኮስተር ብዬ... ግንባሬን አይቶ እጁን ከክንዴ ላይ አነሳ እና

"ይቅርታ ህያብ.... ጣልቃ ልገባ ፈልጌ አይደለም ግን እኔ የታየኝን አንድ ነገር ልበልሽ..."

"ምን"
👍4910👏3🥰1🤔1
#ህያብ
:
:
#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በኤርሚ


አንዳንዶች ለወደዱት ብቻ ጥሩ ይሆናሉ.... አንዳንዶች ደግሞ እንዲሁ በተፈጥሯቸው ጥሩነትን ይታደሉታል። ቢኒ እንደዛ ነው መልካምነትን የታደለ ጥሩ ልብ ያለው ልጅ ነው። ድሀ ወይም ሀብታም፣ ክርስቲያን  ሙስሊም ወይም ሌላ እምነት፣ ቆንጆ ወይም መልከ ጥፉ፣ ቢኒ ጋር መስፈርት አይደሉም። ለሁሉም እኩል ፍቅርና እንክብካቤ ሲሰጥ ታዩታላችሁ..... ግቢ ውስጥም ሆነ ከተማ ውስጥ ያሉ የበጎ አድራጎት ስራዎች አያመልጡትም.....

"ቢኒዬ ግን እርግጠኛ ነህ እዚህ ብሆን አረብሽህም.." እረጅም ሰዓት ተጨቃጭቀን እስከፈለኩ ድረስ ቤቱ እንድኖር ከነገረኝ በኋላ ሀሳቡን ቢቀይር ብዬ ጠየኩት

አጠገቤ መጣና ቁጭ አለ.... እጆቹን ልኮ ሁለት እጆቼን ያዘና አይን አይኔን እያዬ "ህዩ አንቺ ጓደኛዬ ነሽ... ጓደኝነት ውስጥ ደግሞ እኔ የሚባል ነገር የለም በተለይ እኔ ካንቺ እኔን ላስቀድም አልችልም ምክንያቱም......" ከንፈሮቹ ተንቀጠቀጡ።

"ምክንያቱም ምን ቢኒዬ" እጄን ለቆ ተነሳና ጀርባውን ሰቶኝ ከመስኮት ዳር ቆመ።

"ህያብ ጊዜ የነገሮች ጌታ ነው ብዬ አምናለሁ... እናም ሁሉም በጊዜው ሲሆን ደስ ይላል። አሁን ከኔ ምክንያት በላይ ያንቺ ሁኔታዎች ናቸው መስተካከል ያለባቸው...." ክትክት ብዬ ሳቅሁ... የእብደት ሳቅ
ከሳቄ በኋላ

" እስኪ ንገረኝ ምኑን ነው የምታስተካክለው.... እናቴን ልጄን ወይስ ከሀዲው ባሌን ማንን መልሰህ ልታመጣልኝ የምትችል ይመስልሀል..." ድጋሚ አመመኝ... መቋቋም አቃተኝ... በሁለት እጄ ጭንቅላቴን ጥፍንግ አድርጌ ያዝኩት። የሆነ ሽክርክሪት ውስጥ እንዳለሁ ይሰማኛል ዥውውውውውውውው.... ሳቅ ከዛ ደግሞ ዝምምምምታ.... ከዛ ደግሞ ሌላ ሳቅ.... ይሄኛው አለም የተሻለ ይመስለኛል።

የሆነ ሰው አፌ ውስጥ የሆነ ነገር ለማስገባት ታገለኝ አልከለከልኩትም ዋጥኩት ከዛ ሁሉም ነገር ፀጥ አለ።

ምን ሰዓት እንደተኛሁ ባላውቅም ራሴን ጋቢ ለብሼ ሶፋ ላይ ተኝቼ አገኘሁት። ቀና ብዬ ተስተካክዬ ቁጭ ስል ቢኒን ከእግሬ ስር ቁጭ ብሎ መፅሀፍ ቅዱስ ሲያነብ አየሁት።

"ይቅርታ ቢኒ ረበሽኩህ መሰለኝ.." መፅሀፍ ቅዱሱን ዘግቶ ከሳመ በኋላ የኔንም ግንባር ነካ አደረገበትና ተነስቶ አስቀምጦ ተመለሰ።

"ሁለተኛ እንደዚህ እንዳትይኝ ማስቸገር ገለመሌ የሚባል ታሪክ የለም ያራቅሺኝ ነው የሚመስለኝ..."

"እሺ በቃ አይለመደኝም..... ይልቅ እስኪ ንገረኝ የውጪ ቆይታህ እንዴት ነበር የተመለስከውስ መች ነው"

"ቆይታዬን በደፈናው ጥሩ ነበር ልበልሽ መሰለኝ። የተመለስኩት ሁለት ወር አካባቢ ሆነኝ ግን ቀጥታ ቤተሰብ ጋር ክፍለ ሀገር ነው የሄድኩት ከተመለስኩ ገና ሳምንትም አልሞላኝ"

"እና ለምን ልትፈልገኝ ወደ ቤት አልመጣህም..." ክፍት ነው ያለኝ ምንም እንኳን የሱን ስም ሲሰማ ባሌ ቢናደድም ቢኒ ላጣው የማልፈልገው ጓደኛዬ ነው እና እንዴት...

"ወዳንቺ ጋር እየመጣሁ እያለ እኮ ነው መኪና ውስጥ የገባሽብኝ"

"ኦ እሺ እንደዛ ከሆነ"

"አልተዋጠልሽም አይደል ህያቤ ብዙ ጊዜ እንዳልደወልኩልሽ አውቃ..." አቋረጥኩት

"ምን ብዙ ጊዜ ትላለህ ከሄድክ ጀምሮ ሁለቴ ብቻ እኮ ነው የደወልከው.... እናም አልዋሽህም ተቀይሜሀለሁ"

"ምክንያቴን ስታውቂ እንደምትረጂኝ ስለማውቅ ችግር የለውም.... የሆነ ነገር መብላት አለብን ምን ትፈልጊያለሽ..." አለኝ ወደ ኪቺን እየገባ

"ፍላጎትሽን አትናገሪም ካለዛ ዱባ ወጥ ነው የምሰራው ሀ ሀ ሀ" ሽርጡን አገልድሞ ብቅ አለ

" ዱባ ስራና ሶስት ቀን ውጪ አሳድሬ ነው የማበላህ.... አንተ ደግሞ ሼፍ መስለህ የለም እንዴ"

"ነይ አሁን ተነሺ ቢያንስ ዱባውን እንኳን በመክተፍ አግዢኝ" ከስሙ ጭምር እንደምጠላው ስለሚያውቅ እኮ ነው ...ዱባን....

"ሀ ሀ ሀ አንተ እብድ ትቀልድብኛለህ አ" ከረጅም ጊዜ በኋላ ሳቅሁ
......

፨፨፨ ፨፨፨፨ ፨፨፨፨
ጎንደር ዩንቨርስቲ ሁለተኛ አመት

"ቢኒ ዮናታንን እወደዋለሁ ከዚህ በላይ መቋቋም አልችልም እናም እነግረዋለሁ"

"ህያብ ዮናታንን ታውቂዋለሽ.... እሺ አለሽ እንበል ከዛ እነኝህን ሁሉ ሴቶች ትቶ ካንቺ ጋር ብቻ የሚሆን ይመስልሻል"

"አላውቅም ግን እድሌን ልሞክር.."

"ተይ ህያብ ይቅርብሽ"

"አይሆንም ቢኒ እድሌን እሞክራለሁ" ይሄን ሁሉ የምንጨቃጨቀው ዮናታን የሚያመሽበት ጭፈራ ቤት በር ላይ ሆነን ነው። ወደ ውስጥ ገባሁ... አይኔን ዞር ዞር እያደረኩ ፈለኩት ጥግ ሶፋ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር የተሰፋ ያክል ተጣብቋል.... በደንብ ቀረብኳቸው... አንገቱ ስር ስማው ቀና ስትል አይን ለአይን ተገጣጠምን... የትናዬት....

ደንዝዤ አንደቆምኩ የሆነ ሰው እጅ ትከሻዬ ላይ አረፈ "የኔ ቆንጆ በዛኛው በኩል ቦታ አግኝቻለሁ.... እንሂድ አይደል"  ውጪ ቆይ አላልኩትም ነበር.... ቢሆንም ግን ወሳኝ ሰዓት ላይ ነው የደረሰው።

"አየሽ አይደል በራስሽ ላይ ምን እያመጣሽ እንደሆነ"

ሲጀመር እሱን ብቻውን አገኘዋለሁ ብዬ ማሰቤ ነው የኔ ጥፋት እርር ድብን ብሽቅቅቅቅ ብያለሁ እኮ

"አረጋጊው እንጂ ውዷ ጉበትሽን መትፋት አማረሽ እንዴ"

"ተወኝ ባክህ ልጠጣበ" ከነ ጠርሙሱ አንስቼ ለመጠጣት ስሞክር ከእጄ ቀማኝና

"ነይ በቃ እንሂድ ግቢ ይዘጋል" አለኝ

"የትም አልሄድም ተወኝ"

"ይሄንን ነው መፍራት... ኧረ ህያብ በፈጠረሽ..." ጠርሙሱን ተቀብዬው እየተንገዳገድኩ እነሱ ወዳሉበት ቦታ ሄድኩ....

"ህያብ አንቺ ህያብ" የእናቴ ድምፅ መሰለኝ.... እየጠራችኝ ነው።

"አቤት እማ መጣሁ" ብዬ ከተኛሁበት ለመነሳት ስሞክር ሀይለኛ ራስ ምታት አናቴን ይዞ እየፈለጠኝ ነው። ጭንቅላቴን በሁለት እጄ ጥፍንግ አድርጌ ይዤው ከቆየሁ በኋላ አይኔን በደንብ ከፍቼ ሳይ ያለሁት እናቴ ቤት አይደለም....

ከፊት ለፊቴ ቢኒ ተቀምጦ የማደርገውን ነገር ያያል።

"ኡፍፍፍፍ የት ነው ያለሁት ምን ተፈጥሮ ነው.... ቆይ እማዬ የጠራችኝ አልመሰለኝም.."

"ባክሽ እኔ ነኝ የጠራሁሽ ክፍል ልቀቁ እየተባልን ነው ተነሺ..." ቢኒ እንደዚህ አውርቶኝ አያውቅም....

"ምንድነው ቢኒ ችግር አለ እየተነጫነጭክ እኮ ነው ምነው ማታ አስቀየምኩህ እንዴ.... ማታ....ቆይ ቆይ እንዴት ወደዚህ ልመጣ ቻልኩ? ማነው ያመጣኝ? ማለት ምን ተፈጥሮ ነው?..." የጥያቄ መአት አከታተልኩበት

"በመጀመሪያ ተነሽና ታጠቢ ከዛ ወደ ግቢ እንመለስና ዶርም ገብተሽ እረፍት አድርጊ ከዛ ተገናኝተን ጥያቄዎችሽን እመልስልሻለሁ እስከዛው ትዝ የሚልሽ ነገር ካለ ራስሽ ጥያቄሽን መመለስ ትችያለሽ" እንዴ ምንድነው ጉዱ ቢኒ እንደዚ ከረር ብሎ አይቼው አላውቅም ጭራሽ የማላውቀው ሰው ነው የሆነብኝ። ተጨማሪ ጥያቄ ሳልጠይቅ ጭንቅላቴን ደግፌ እየተጎተትኩ መታጠቢያ ቤት ገባሁ።
ሰውነቴ ስብርብር ያለ ያክል እየተሰማኝ ታጥቤ ጨረስኩ

፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨

"አንተ ቢኒ ግን አልተኛህም እንዴ አይንህ እኮ በርበሬ ነው የሚመስለው" ወደ ግቢ እየሄድን ጠየኩት
👍448😁1
#ህያብ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በኤርሚ

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

"እኔ ምንም እየገባኝ አይደለም ቢኒ ምንድነው እያወራህ ያለኸው"

"ተረጋጊ እነግርሻለሁ.... ዮናታን የያዝነው ክፍል ድረስ መጥቶ እንድናወራ ጠየቀኝ.... እሺ ብየው ተያይዘን ወደ ሆቴሉ ባር አመራን እናም ቁጭ ብለን ያልጠበኩትን ነገር ነገረኝ"

"ቀጥል ምን አለህ"

#ምሽት_8_ሰዓት_ላይ

የሆነውን ሁሉ እኔ ነኝ የምተርክላችሁ.... ቢኒያም

ከዮናታን ጋር ወደ ባሩ ከወረድን በኋላ መጠጥ አዘዘ እና
"የውልህ ቢኒያም ተረጋግተህ እንድትሰማኝና ከቻልክ እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ..."

"ለማንኛውም የምትለኝን ልስማህ" እስከዚህ ድረስ እንኳን አብሬው የመጣሁት ድጋሚ ካስተማረን F እንዳያስታቅፈኝ በሚል ፍራቻ ነው

"ሁሉም ሰው የሚያውቀው እኔ ሴት አተራማሽ እንደሆንኩ ነው። በእርግጥ እውነታም አለው ጥቂት ከማይባሉ ሴቶች ጋር ግንኙነት ነበረኝ ግን ነበር ነው ከ2 አመት በፊት በመጀመሪያ እይታ አንዲት ልጅ ልቤ ውስጥ ገባች። እናም ልክ ለሌሎቹ እንደሚሰማኝ ተራ ስሜት ነው ብዬ የነበረው ህይወቴን ለመቀጠል ሞከርኩ ግን እንደድሮው መሆን አቃተኝ። ለተወሰነ ጊዜ ስወዛገብ ከረምኩና ፍቅሬን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝና እሷን የኔ እንዴት እንደማደርግ ማሰብ ጀመርኩ።

ልጅቷ ኮስታራ እና የማያስቀርብ ፊት ነው ያላት ያለኝ አማራጭ አብራ ከምትማራቸው ሴቶች ስለሷ ሊነግረኝ የሚችል ሰው ፈልጌ መቅረብ ነበር እናም የትናዬትን ቀረብኳት...."

"ሰውዬ ስለምን እያወራህ ነው" እዚህ ጋ መምህር መሆኑን ረሳሁ

"ቢኒያም ለኔ ሁሉም ነገር የተገለፀልኝ ዛሬ ነው.... እና ከቻልክ ተረጋግተህ ስማኝ"

"ከየትናዬት ጋር ከተቀራረብን በኋላ በተደጋጋሚ ቢሮዬ እየጠራኋት ስለ ህያብ እንድትነግረኝ አደርጋት ነበር።"

"ምን እያልክ ነው እና ህያብን አንተም ታፈቅራታለህ" ማመን ከበደኝ

"አዎ ያውም በመጀመሪያ እይታ ነው ያንበረከከችኝ ለማንም ሴት እንደዚህ ሆኜ አላውቅም። የኔ ብትሆን ብዬ በምናቤ ስስላት የነበረችን ልጅ ነው በአካል ያገኘኋት"

"እሺ ከዛስ ምን ተፈጠረ"

" የትናዬት እንኳን ጠርቻት ሳልጠራትም እየመጣች ብዙ ነገር እንዳውቅ አደረገችኝ። የምትነግረኝ ነገሮች ግን ህያብን እንድቀርብ ሳይሆን እንድፈራ እና እንድሸሽ የሚያደርግ ነበር።"

"ምን ብላህ ነው"

"በመጀመሪያ ከሷ ጋር ኢለመንተሪ ጀምሮ አብረው እንደተማሩ እና እንደምትታየው ሳይሆን ውስጥ ውስጡን ወንድ አተራማሽ እንደሆነች ነገረችኝ። አላምንም ስላት በማስረጃ አረጋገጠችልኝ።"

"መቼ ነበር ያረጋገጠችልህ ማለቴ የት"

"ከአመት በፊት ካንተ ጓደኛ ጋር ቤርጎ ሲገቡ በአይኔ በብረቱ አየሁ እናም የምትለኝ እውነት እንደሆነ አረጋገጥኩ"

"የውልህ ዮናታን ያየኸው እውነት ነው ግን እንደምታስበው አይደለም። ጓደኛችን በሀይሉን ፍቅረኛው ከድታው ሌላ ሰው ጋር ሆነች እናም እሷን ማስቀናት እንደሚፈልግ ነገረን.... እኔም ለህያብ ነገርኳትና እምቢ ብትልም በግድ አሳመንኳት ከዛ ፍቅረኛው የምታይበትን ሁኔታ አመቻችተን አብረው ወደ ክፍል ሲገቡ እንድታያቸው አደረግን። ግን አንተ እዛ እንደነበርክ ማንም አላወቀም እንዴትስ ልትገኝ ቻልክ"

"የትናዬት ናት አላምንም ስላት 'ከቢኒያም ጋር ፍቅር ፍቅር እየተጫወተች የገዛ ጓደኛው ጋር ትማግጥበታለች' አለችኝ ማረጋገጥ ከፈለክ ብላ ወደዛ ቦታ ወሰደችኝ እና በአይኔ እንዳይ አደረገችን በሰዓቱ ራሴን መቆጣተር አቅቶኝ ነበር እናም እሱን ልደበድብ እሷን ልሰድብ ስራመድ የትናዬት አስቆመችኝ.... ከዛ በኋላ የምትለኝን ሁሉ አምናት ነበር እስከ ትላንትና ድረስ..... አሁን ግን ሁሉንም ከራሷ ከህያብ ነው ማረጋገጥ የምፈልገው"
ነገሩ ካሰብኩት ውጪ ሆነብኝ የትናዬት ተንኮለኛ ብትሆንም ይህን ያክል ርቃ ትሄዳለች ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"እሺ ሌላስ ምን ነገረችህ"

"አንተ ፍቅረኛዋ እንደሆንክ እና አዲስ አበባ ከሌላ የወለደቻት ልጅ እንዳለቻት"

"ምንድነው የምታወራው እኔ ከህያብ ጋር አብሬ ስለምታይ ፍቅረኛዋ ነው ብትል እሺ ግን ልጅ ከየት ፈጥራ ነው የነገረችህ...." ኪሱን በርብሮ የሆነ ፎቶ አወጣና እጄ ላይ አስቀመጠልኝ። ህያብ ልጅ አቅፋ.....

"ግን እኮ እህቷም ልትሆን ትችላለች" ካልኩ በኋላ ለእናቴም ለአባቴም አንድ ነኝ ብላ የነገረችኝ ትዝ አለኝ።

"አይደለችም ልጇ ነች ይሄን አረጋግጫለሁ ግን አንተ የምታውቅ ነበር የመሰለኝ"

"ኧረ በፍፁም ግራ እያጋባህኝ ነው" ፎቶውን ተቀብሎኝ ወደ ኪሱ ከተተና

"ቢሆንም ይሄ ጉዳዬ አይደለም.... ለሷ ያለኝን ፍቅር ያለፈ ታሪኳ ሊቀይረው አይችልም የሚያሳስበኝ የአሁኑ ነው..." ግንባሩን አሸት አሸት እያደረገ ትንሽ ከቆየ በኋላ

"ቢኒያም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እናም ሳትዋሽ መልስልኝ" አለኝ

"እሺ ጠይቀኝ"

"ከህያብ ጋር ፍቅረኛሞች ናችሁ?"

"አይደለንም" ፈገግ ሲል አየሁት

"እሺ ታፈቅራታለህ" ከንግግሩ እኩል ደነገጥኩ

"አይ አላፈቅራትም" መሬት ተንበርክኮ መሳም ነው የቀረው ደግሞ ደጋግሞ ፈጣሪን አመሰገነ... ሁኔታውን ሳይ የነገረኝ ሁሉ እውነት እንደሆነ ገባኝ።

"እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ"

"ጠይቀኝ" አለኝ በፈገግታ ተሞልቶ

"የትናዬት ፍቅረኛህ ካልሆነች ወይም የሆነ ግንኙነት ከሌላችሁ እንደዛ ተጠባብቃችሁ አንገትህን ስትስምህ...." ሳያስጨርሰኝ

"እሱ ለኔም የሚገርም አጋጣሚ ነበር። ህያብ እኛ ወደተቀመጥንበት ስትመጣ እኩል አየናት እናም የትናዬት ሳላስበው ጥምጥም ብላብኝ ሳመችኝ። ደንግጬ ስለነበር ላስቆማት አልቻልኩም ምን እያረግሽ ነው ብያት ዞር ስትልልኝ ህያብ ቆማ እያየችን ነው ወዲያው አንተ መተህ ወሰድካት"

"እንጂ ምንም አይነት ግንኙነት የላችሁም"

"ቢኖረን ለምን እዋሽሀለሁ"

ወደ ያዝነው ክፍል ከተመለስኩ በኋላ ረጅም ሰዓት ወስጄ ለማሰብ ሞከርኩ ከሁሉም አንድ ነገር ደጋግሞ አቃጨለብኝ.... "ህያብን ታፈቅራታለህ"

አዎ አፈቅራታለሁ አልኩ ጮክ ብዬ ልክ እንዳንተ መጀመሪያ ያየኋት ቀን ነው ልቤን የሰረቀችው ግን ምን ያደርጋል እሷ የምታፈቅረው አንተን.... ወዲያው በንግግሬ ደንግጬ ዝምም አልኩ ደግነቱ ከራሴ ውጪ የተናገርኩትን ማንም ሊሰማ አይችልም። ፍጥጥ እንዳልኩ ነጋ ግን ከራሴ ጋር ልስማማ አልቻልኩም እውነት ህያብ የሌላ ሰው ስትሆን ማዬት እችል ይሆን???
።።።
እኔ ነኝ ህያብ!
ፍንድቅድቅ ብያለሁ ከዚህ የበለጠ ምን ሊያስደስተኝ ይችላል በማፈቅረው ሰው መፈቅርን የመሰለ ምን ነገር አለ። ከነገረኝ ነገሮች ሁሉ ዮናታን ያፈቅርሻል የሚለው ሙሉ እኔን ተቆጣጥሮኛል።

"ህያብ ደስታሽን ላበላሽ ፈልጌ ሳይሆን እባክሽ ጥያቄዬን መልሽልኝ" ጮክ ብሎ ተናገረ

"ምን አልከኝ ቢኒ" በራሴ አለም ስዋዥቅ ምን እንዳለኝም አልሰማሁትም ነበር።

"ልጅ አለሽ" ከመደንገጤ የተነሳ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ።

"ህያብ እንደጓደኛሽ የምታይኝ ከሆነ እውነቱን ንገሪኝ ልጅ አለሽ" ከተቀመጠበት ተነስቶ እጄን ያዘና አንድቀመጥ አደረገኝ ከዛ በተማፅኖ አይን አይኔን ያይ ጀመር "እባክሽ ህያብ ላስጨንቅሽ ፈልጌ አይደለም... ግን ዮናታን ፎቶ ሲያሳየኝ ተጠራጠርኩ" የባሰ ድንጋጤ

"ምን? ዮናታንም ያውቃል"

"አዎ እሱ ነው የነገረኝ ስነግርሽ እኮ አልሰማሽኝም መሰለኝ"
👍488🥰2👏1
#ህያብ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በኤርሚ


"ህያብ ያለፈ ታሪክሽ ምንም ይሁን ምን አንቺን ከማፍቀር ሊያቆመኝ አይችልም። የኔ ቆንጆ የፍቅር ጓደኛዬ ትሆኛለሽ?"

"ዮኒ.." ተርበተበትኩ... ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ፈገግ ብሎ እያዬን ነው። ፈገግታው ውስጥ ሁሉም ነገር ሰላም ነው የሚል መልዕክት ያነበብኩ መሰለኝ••• አበባውን ተቀበልኩ

ከዮኒ ጋር ህልም የሚመስሉ ሁለት ሳምንታትን አሳለፍን። ሁሉም ነገር በጣም ደስ የሚል ነበር እያንዳንዷን ቀን ደስ በሚል ሁኔታ አሳለፍናት።

ጎንደርን ለቆ ወደ አዲስ አበባ የሚሄድበት ቀን ደረሰ እኔና ቢን ቀድመን ለመሰናበት አገኘነው።
ካፌ ተገናኝተን ሞቅ ያለ ወሬ እያወራን በመሀል ቢኒ
"ይህን ሁሉ ጊዜ አስለፍተሀት አንድ ወርም ሳይቆይ ልትሄድ ነው?" አለው።

"በልፋት እንኳን ከኔ የበለጠ የለፋች አይመስለኝም ሀሀሀሀ ስቀልድ ነው። ይሄን የመሰለ ፍቅር ትቼ መሄዴ ሳያስከፋኝ ቀርቶ መሰለህ በእርግጥ መጀመሪያ ወድጄና ፈቅጄ እንደውም በጣም ፈልጌው ነበር ዝውውር የጠየኩት" ያልሰማሁት አዲስ ነገር ሆነብኝ

"አንተ ጠይቀህ ነው እንዴ የተዘዋወርከው" ግርም ብሎኝ ጠየኩት

"አዎ ለዚህ ዝውውር እስከ ጥግ ለፍቻለሁ አሁን ግን አልፈልገውም ነበር ግን ምንም ማድረግ አልችልም" እዝን ብሎ አንገቱን ደፋ

"ለምን ነበር ዝውውሩን የጠየከው" ቢኒ ጣልቃ ገባ

"በሷ ምክንያት ነዋ" እጄን በእጁ እያጠላለፈ "ያን ሁሉ ነገር ሰማሁ ምንም ብሰማ እንኳን ላንቺ ያለኝ ፍቅር ሊቀንስ አልቻለም ጭራሽ የማላውቀው ስበት ወዳንቺ ይገፋኛል። መቋቋም አቃተኝ ስራዬ ላይ ሳይቀር ተፅዕኖ ፈጠረብኝ እናም መሸሽን መረጥኩ እና ዝውውር ጠየኩ"

"የዚህ አመት ትምህርት ሲያልቅ እመጣ አይደል ከእናቴ ውጪ የሚቀበለኝ ሰው አለ ማለት ነው" መሄዱ ሀዘን እንዳይለቅብኝ መልካም መልካም ነገሮችን ለማውራትና ለማሰብ ሞከርኩ

"እስከዛው አደራ የምለው ላንተ ነው ቢኒያም.... ናፍቆት ናፍቆት እያለች ትምህርት ላይ እንዳትዘናጋ ደግሞ በስልክም እናወራለን" ቢኒ በአንገት ንቅናቄ እሽታውን ገለፀ።

ፍቅሬን ሞቅ ባለ ስንብት ወደ አዲስ አበባ ሸኘነው።

እኔ ልሁን እሱ ይሁን ማን እንደተቀየረ ባይገባኝም ከቢኒ ጋር እንደድሯችን ልንሆን አልቻልንም ሳገኘው ሳወራው  የሆነ ክፍተት እንዳለ ይሰማኛል። መጥፎ ስሜቶች አብረውኝ እንዲቆዩ አልፋግም እሱን ለማውራት ወሰንኩ

"ቢን ግን የተፈጠረ ችግር አለ ማለቴ ምንም እንደድሮው ልንሆን አልቻልንም እኮ ያጠፋሁት ጥፋት አለ እንዴ"

"ኖ ህያብ ምንም አላጠፋሽም እኔ ነኝ በራሴ ችግር ምክንያት ነው አንቺም ለይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ አላወኩም.... "

"እና ችግሩን ንገራታ መፍትሄው እኮ በሷ እጅ ነው" የቢኒ ጓደኛ ሀብታሙ ከየት መጣ ሳይባል አጠገባችን ተገኝቷል

"እየውልሽ ህያብ ቢኒ ባንቺ ምክንያት ሀገ..." ንግግሩን ሳይጨርስ የቢኒ እጅ አፉ ላይ አረፈ እና እንቅ አድርጎ ያዘው ትንሽ ከታገሉ በኋላ ለቀቀው

"ባለፈው እንደነገርኩህ ነው ወይ ንገራት ካለዛ እኔ እነግራታለሁ"

" ቢኒ ምንድነው ማወቅ ያለብኝ ነገር አለ" ቢኒ ግራ ገብቶት አንዴ እሱን አንዴ እኔን ያያል።

"አቦ ዝም ብለህ እኮ ነው የምታካብደው" ሀብታሙ በንዴት እየተወናጨፈ ትቶን ሄደ

"ቢን ንገረኝ ምንድነው ከኔ የምትደብቀው ነገር አለ እንዴ"

"አይ ህያብ ለመደበቅ አይደለም እነግርሻለሁ ምን መሰለሽ ግን.... እ...እ....እ ማለቴ እኔ ካንቺ..... ማለቴ ....አንቺን.... "

እኔ ቢኒያም ነኝ ልተርክላቹ

ከመጀመሪያ ጀምሮ ምን እንደተፈጠረ ልንገራችሁ። ህያብን አፈቅራታለሁ አጠገቤ እያለች የማንም ሳትሆን በየቀኑ አብሪያት ስሆን ስንተቃቀፍ ስናወራ አብረን ስንበላና ስንጠጣ ጭንቅላቴ የሚያስበው ጓደኛዬ እንደሆነች ቢሆንም ይህ ልቤ ግን ሁሉን ነገር ፍቅር ብሎ ይወስደው ነበር። ሁሉም ነገር የገባኝ ህያብን በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ሳያት ነው። መቋቋም አቃተኝ

ከዮኒ ጋር ካወራን በኋላ እሷ ያለምንም ጥርጥር የሱ እንደምትሆን አመንኩ በዛው ልክ ደግሞ ህያብን ላጣት እንደሆነ እና መቼም የኔ እንደማትሆን ተረዳሁ....  አለ አይደል በቃ ሳስብ የኖርኩት የዮኒ ብልግና የሆነ ቀን አንገሽግሿት እሱን መፈለጓን ለማቆም የምትወስን..... ከዛ የኔ የምትሆንበት ሰፊ እድል.....
በነዛ ሁሉ ጊዜያቶች ለራሴ ስነግረው የነበረው ህያብ መቼም ቢሆን ከዛ ባለጌ ዮኒ ጋር ልትሆን እንደማትችል እና የኔ እና የኔ ብቻ እንደምትሆን ነበር። ሁኔታዎች ግን ባላሰብኩት መንገድ ድብልቅልቃቸው ወጣ ህያብን በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ላያት ሆነ።

ለዶርም ጓደኞቼ ህያብም ሆነ ማንም ቢጠይቃቸው ቤተሰብ ጋ እንደሄድኩ እንዲነግሩ አስጠንቅቄ ከሀብታሙ ጋር አዲስ አበባ አክስቱ ቤት ሄድን። ሀብታሙ ከስር ከመሰረቱ ለሷ ያለኝን ፍቅር ያውቃል እንድቀርባትም ያደፋፈረኝ እሱ ነበር ለዛም ነው ብቻዬን ልሂድ ስለው አይሆንም ብሎኝ አክስቱ ጋር በነፃነት መሆን እንደምንችል አሳምኖኝ አብሮኝ የመጣው

ለቀናት ጠጣሁ ሰከርኩ በእብደት አለም ውስጥ ዋዠኩ። መርጋጋት የሚባለው ነገር ከኔ በእጥፍ እራቀ። ሁኔታዬ ያሳሰበው ሀብትሽ ከቀናት በኋላ መጠጥ ከሚባል ቦታ እንዳልደርስ በግድ ከለከለኝ

ወደምጠጣበት ቦታ ለመሄድ ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ጫማዬን እያሰርኩ ፊት ለፊቴ መጥቶ ቆመና "ምን እየሆንክ ነው በዚህ ሁኔታህ ህያብን የምታገኛት ይመስልሀል። ቢኒያም እንደዚህ እየሆነ መሆኑን የምታውቅ መሰለህ.... እሷማ የምታውቀው ቢኒ እንደታላቅ ወንድም የምታየው ጓደኛዋ እንደሆነ ነው። ንገረኝ እስኪ በማን ላይ ነው የተናደድከው ህያብ ላይ ነው?"

"አይደለም" አልኩት አንገቴን እንደደፋሁ

"በፍቅር ነው?"

"አይደለም እሷን በማፍቀሬማ ደስተኛ ነኝ"

"በራስህ ነው?"

"አዎ ምክንያቱም እስከዛሬ ያመንኩበት ሁሉ ገደል ገባ"

"ይህ እንዳይሆን ማድረግ የምትችለው ነገር ነበር?"

"አላውቅም ምን ላደርግ እችላለሁ መጀመሪያ ነግሪያት ቢሆን የምትወደው ጓደኛዋ ለመሆን አልችልም ነበር። መሀል ላይ ደግሞ ያመንኩት የሱ ነገር ስልችቷት እኔን እንደምታይ ነበር። አሁን ደግሞ ረፍዷል እና በራሴ የትኛውን ነገር አላደረክም ብዬ ልናደድበት?"

"ጥያቄዬን በጥያቄ ሳይሆን በቀጥታ መልስልኝ በራስህ ነው የተናደድከው?"

"አይደለም" አልኩት

"በዮኒ ነው?"

"አይደለም"?

" እና በማን ነው"?

"አላውቅም" አልኩት እውነት ግን በማን ነው የተናደድኩት

"እሺ ለምንድነው እንደዚ እየሆንክ ያለኸው"

"ትቀልዳለህ እንዴ ህያብ የኔ ስለማትሆን ነዋ! በናትህ አሁን መጠጣት ነው የምፈልገው" አልኩት ወሬውን ጨርሶ ዞር እንዲልልኝ በማሰብ

"እንደዚህ መሆንህ ህያብን ያንተ እንድትሆን ያደርጋታል?"

"አያደርጋትም" ከፊት ለፊቴ ዞር አለና ከኮመዲኖ ላይ ቁልፍ እነሳ ከዛ ቀጥታ ወደበሩ አመራ እና ቁልፉን እያሳየኝ

"ስለዚህ በማን እንደተናደድክ አታውቅም ግን ምስኪኑን ጨጓራህን በመጠጥ እያነደድከው ነው ቢያንስ ለጨጓራህ በጠዋት እየተነሳሁ እስከማታ በመጠጥ የማነድህ በዚህ ሰው ተናድጄ ነው ብለህ አንድ ምክንያት ንገረው። ህያብ ደግሞ ከእጅህ ወጥታለች ስለዚህ ሁኔታዎችን አምነህ ተቀበል ወይም ያንተ የምትሆን ከሆነ ያንን ጊዜ ጠብቅ.... ወደራስህ ተመልሰህ ጠብቀኝ ምግብ ይዤ እመጣለሁ" በሩን ቆልፎብኝ ሄደ

ያለሁበት አንድ ክፍል ቤት ሌላ መውጫ የለውም ከተቀመጥኩበት ተነሳሁና አልጋ ላይ ወጥቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ።
👍9611👏4🔥2🤩1
#ህያብ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በኤርሚ

"የትም አለሁ ልጅሽ የማውቃትን አንዲት ልጅ አስታወሰችኝ። ብቻ ተይው የማይገናኝ ነገር ነው" አለኝና ትክዝ አለ

"ምንድነው እሱ"

"አይ ምንም" ሸኝቸው ከተመለስኩ በኋላ ለደቂቃዎች ሁኔታውን አሰብኩትና ለምን እንቁን ሲያያት እንደዚህ ፈዘዘ ለሚለው ጥያቄ መልስ ያገኘሁ መሰለኝ ስለሷ ምንም ስላልነገርኩትና ቢጠይቀኝም እንደማልነግረው ስለሚያውቅ ነው።

ከዚህ በኋላ ያሉት ጥቂት አመታቶች ተመሳሳይ ነበሩ። ለእረፍት መምጣት፣ ከዮኒ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ጊቢ መሄድ፣ ከቢኒ እና ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር የነበረንን ግንኙነት መቀጠል፣ መማር፣ ማንበብ፣ የተለያዩ ሆስፒታሎች አፓረንት መውጣት.... ባጠቃላይ ብዙም አዲስ ነገር የሌለበት ተመሳሳይ ጡዘት ነበር።

የመጨረሻ አመት ላይ ውጥረቱ ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ነበር። ዩንቨርስቲያችን ከፍተኛ ውጤት ያመጡ አስር ልጆችን ስኮላርሽፕ እንደሚሰጥ ያወቅንበት ጊዜ ነበር። ጥቂት ቢ እና ኤ ማይነስ ውጤቶች ቢኖሩኝም እድሉን አገኛለሁ ብዬ እየተፍጨረጨርኩ ነበር። ቢኒ እና ሀብትሽ እንኳን በእርግጠኝነት ከአስሮቹ መሀል ይሆናሉ። ሀብታሙ እስካሁን ያለው ውጤቱ ኤ እና ኤ ፕላስ እንደሆነ ነው የምናውቀው። ቢኒ ደግሞ ሁለት ቢ ሌላው ኤ በአጠቃላይ የግቢያችን ሰቃዮች የእስኮላሩም ባለ እድሎች ይሆናሉ ብዬ ከምጠብቃቸው መሀል ናቸው።

ውጥረቱ እንዳለ ቀጥሎ ፋይናል ፈተና ተፈተንን እና እፎይ አልን። ምርቃታችን አንድ ሳምንት ሲቀረው ሂዊ እና ቤዛ ወጣ ብለን ፈታ እንበል ብለው ሲጨቀጭቁኝ እሺ አልኳቸው። ሌላ ፕሮግራም ያለብን ይመስል ከግራ ቀኝ እየተቀባበሉ አስዋቡኝ።

"ለቢኒ ልደውልለት እንዴ ከተመቸው አብሮን ቢሆን ደስ ይለኛል" ስላቸው እርስ በርሳቸው ተያዩና ቤዛ

"ትችያለሽ" አለችኝ። እሺ ብዬ ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት ሁለቴ እንደጠራ አነሳውና

"ሀሎ ዶክተር ህያብ እንደምን አሉ" አለኝ ድምፁን እንደ ሽማግሌ እያደረገ ሳቅሁና በምላሹ

"አለን እግዚአብሔር ይመስገን እርሶስ እንዴት ኖት ዶክተር ቢኒያም" አልኩት።

"አለን ክብሩ ይስፋ ይገርሞታል አሁን ከባድ ቀዶ ጥገና አለብኝ እና ወደዛ ልገባ" አቋረጥኩትና

"እንደዛ ከሆነማ አብረን ቀደን እንጠግነዋለን ሀ ሀ ሀ ሀ የት ነህ ከነ ቤዚ ጋር ልንወጣ ነው ከቻልክ ተቀላቀለን" አልኩት።

"ደስ ይለኛል እንደውም ብቻዬን ደብሮኝ ነበር"

"ሀብትሽስ" አልኩት

"ሀብትሽማ አክስቱ ከአዲስ አበባ መጥታ ረስቶኛል ያው አትፍረጅበት የመዓረግ ተመራቂ ነገር "በል አሁን ወሬውን ተውና ውጣ እኛ ወተናል" ስልኩን ዘጋሁና ቦርሳዬን አንስቼ ከዶርም ወጣን።

በኮንትራት ራቅ ወዳለ ቦታ ሄድንና አንድ ውስጡም ውጪውም ውብ ወደሆነ ሆቴል ገባን።

"እናንተ ፈታ እንበል ብላችሁ ሆቴል ኧረ ፌር አይደለም" አለ ቢኒ ወደነሂዊ እያየ እኔም ሀሳቡን ተጋርቼው በጥያቄ መልክ አይን አይናቸውን እያየሁ እያለ ሂዊ

"ህያብ ሰርፕራይዝ አለሽ" አለችና ሳታስፈቅደኝ አይኔን በጨርቅ አሰረችው። እጄን ይዛኝ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ወደ ፎቅ ደረጃ ወጣንና በድጋሚ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ቆምን

"አይንሽን መግለጥ አይቻልም" አለችኝ ቤዚ

"እኔንም ግራ እያጋባችሁኝ ነው ምንድነው ነገሩ" ቢኒ ተናገረ። የበር መከፈት ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ተዘጋ።

"ሰፕራይዝ" ብለው ባንዴ ጮሁና አይኔ ላይ ያለውን ጨርቅ ሲያነሱት እኔ ደግሞ በተራዬ ጮህሁ። አንዴ ወደግራ አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ደግሞ ፊት ለፊቴ ወደተንበረከከው ዮኒ እያየሁ ነው። ከመደንገጤ የተነሳ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል። ቤዚን ሳያት ጭንቅላቷን በአዎንታ ነቀነቀችልኝ ሂዊም እንደዛው ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ድንዝዝ ብሎ ቆሟል።

"ታገቢኛለሽ የኔ ቆኝጆ" ብሎ ለሁለተኛ ጊዜ ደገመልኝ

"አዎ የኔ ፍቅር አዎ አገባሀለሁ" የደስታ እንባ ከአይኔ ኮለል ብሎ ወረደ። ግራ እጄን ዘረጋሁለትና የቀለበት ጣቴ ላይ የሚያምር ቀለበት አድርጎልኝ ሳም ካረገው በኋላ ጥምጥም ብሎ አቀፈኝ.... እኔም ልጥፍ አልኩበት...

ወዲያው በሩ ጓ ብሎ ሲዘጋ ሰማሁ ከእቅፉ ወጥቼ ዞር ስል ቢኒ የለም። ምን ሆኖ ነው ግራ ተጋባሁ...
የቢኒን ነገር በይደር ያዝኩትና ወደ ደስታችን ተመለስኩ። እነ ሂዊ ትንሽ አብረውን ከቆዩ በኋላ ቻው ብለውን ሄዱ እነሱን አስወጥቼ በሩን ዘግቼ ስዞር ዮኒ አጠገቤ መጥቶ ቆሟል። ጊዜ እንኳን ሳይሰጠኝ ከንፈሬ ላይ ተጣበቀ።

ሁሉም ነገር በስሜት ጡዘት ውስጥ እየሆነ ነበር ማንም መመሪያ ሳይሰጥ እያንዳንዱን ምዕራፍ ገለጥነው ከምዕራፎቹ መሀል አንደኛው ላይ ግን ነገር ተበላሸ። ከምትወደው ዮናታን ጋር በስሜት አለም የምትቃትተው ህያብ ጠፋችና የአስራ ሶስት አመቷ ህያብ ተከሰተች።

"እባክህን ተወኝ.... ሳግ... እንባ... እባክህን አትንካኝ.... ብዙ ትንቅንቅ..... ለእናቴ መድኋኒት ልገዛ ነው.....እናቴን አሟታል..... እባክህን ተወኝ ልሂድ....." ከላዬ ላይ ምንጭቅ ብሎ ተነሳና እየወዘወዘኝ ህያብ ህያብ ብሎ መጣራት ጀመረ ድምፁ ከሩቅ ቢሰማኝም ካለሁበት የህልም አለም ግን መንቃት አልቻልኩም

"እባክህ ተወኝ" ግራ ሲገባው መሰለኝ በተኛሁበት ውሃ አምጥቶ ፊቴ ላይ አርከፈከፈብኝ የውሃው ቅዝቃዜ ካለሁበት መጥፎ አለም መንጭቆ አወጣኝና ተነስቼ ቁጭ አልኩ። የሆነው ሁሉ ስለገባኝ አይኑን ማየት ፈራሁ እንገቴን ባቀረቀርኩበት ከጀርባዬ መጣና ጥምጥም ብሎ አቀፈኝና

"የኔ ፍቅር" አለኝ ሀዘኔታ በተሞላበት ቅላፄ

"ወዬ ውዴ ይቅርታ እሺ በጣም አዝናለሁ እንደዚ የምሆን አልመሰለኝም ነበር" ምላሴ ተሳሰረ ጫፉን እንኳን ስለማያውቀው እንዲያውቅም ስለማልፈልገው ታሪክ ምን ብዬ አስረዳዋለሁ።

"ተደፍረሽ ነበር አይደል" አለኝ። ረጅም ደቂቃ መልስ ሳልመልስለት ዝምም አልኩት

"ይገባኛል ህያብ ማውራት የማትፈልጊው ርዕስና ቁስልሽ እንደሆነ ግን እኔ ባልሽ ልሆን ነው ህመምሽም መካፈል ሀዘንሽን መጋራት እፈልጋለሁ። ሚስቴ ብቻዋን ስትሰቃይ ማየት የበለጠ ነው የሚያሳምመኝ" ንግግሩ አንጄቴን በላው ግን ምን ብዬ ልንገረው ምክንያቱም እኔም እናቴም የነገርነው አዲስ አበባ ተወልጄ እንዳደኩ ነው። ለእናቴ ደግሞ ቃል ገብቼላታለሁ
ማንም ቢጠይቀኝ የአዲስ አበባ ልጅ እንደሆንኩ እንድናገር ነግራኛለች። ምክንያቷ የትውልድ መንደሬን ስም በተናገርኩ ቀጥር ያንን መጥፎ አጋጣሚ በየጊዜ እንዳላስበው ብላ ነው። ይህም የሆነው ሰለዛ ሀገር ከሷ ጋር እንኳን ባወራንበት አጋጣሚ ከሷ ዞር ብዬ ሳለቅስና ሁኔታዎቼ ሲቀያየሩ ስላየች ነበር። እሷም ስለዛ ላታወራ እኔም ማንም ቢጠይቀኝ የተወለድኩት አዲስ አበባ እንደሆነ ልናገር ቃል ያስገባችኝ።

ከጊዜ በኋላ ሁኔታውን ለመድኩትና እውነትም አዲስ አበባ የተወለድኩ እስከሚመስለኝ የምናገረው ውሸት እውነት ሆነልኝ።

"አዎ ልክ ነህ ተደፍሪያለሁ ግን እንዴት? የት? ምናምን ብለህ አትጠይቀኝ ምክንያቱም ድጋሚ በዝርዝር ካሰብኩት እታመምብሀለሁ። ብቻ እመነኝ ከዚህ ሁኔታ ውስጥ እወጣለሁ እንደዚ የምሆን ስላልመሰለኝ ነው እኮ ችላ ብዬው የነበረው"

"ይገባኛል አትጨነቂ የስነ ልቦና አማካሪ ትፈልጊያለሽ"

"አዎ ግን አንተ አትቸገር በራሴ አደርገዋለሁ የማውቃቸው ጎበዝ ሳይካትሪስቶች አሉ" ደረቱ ላይ ልጥፍ ብዬ እቅፍ አድርጎኝ ተኛን ወዲያው ወደ እንቅልፍ አለም ተሸጋገርኩ
👍726🤔1
#ህያብ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በኤርሚ

የሆነ እንደመልዓክ የቆጠራችሁት ሰው ከሆነ ጊዜ በኋላ ውስጡ ያለውን የሚያስፋራ አውሬ አውጥቶት ሊበላችሁ እየገሰገሰ ሲመጣ ምን ይሰማችኋል። ትሸሻላችሁ ወይስ ቆማችሁ ትበላላችሁ። እኔ ግን ብዙ ነገሬ እስከሚያልቅ ቆሜ ነበር የተበላሁት

የልቤ ንጉስ  ብዬ የፍቅር ማማ ላይ የሰቀልኩት ሰው ልክ የዛን ቀን ትክክለኛ ማንነቱን አየሁት። ማንኛውም ሰው ሲናደድ ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል የሱ ግን ከዛ የተለየ ነበር። ነገሮችን ለመስማትም ለመረዳትም ፈቃደኛ አልነበረም ያነበበው ደብዳቤ ሳይቀር ቢኒ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅሩን እንደገለፀልኝ እየነገረው እሱ ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ ፍቅረኛሞች ነበራችሁ ብሎ ደመደመ።

"ጯ ጯ" ይህ በማፈቅረው ሰው የተመታሁት የጥፊ ድምፅ ነው። የቦክስን ድምፅ ደግሞ በቃል መግለፅ ይከብዳል እንጂ እኔን እንደመታኝ ቢኒ ዘሎ ተነስቶ ያቀመሰውን ቦክስ ከዛም አንዴ ቢኒ አንዲ ዮኒ ገላጋይ እስኪመጣ የተደባደቡትን በቃል እገልፅላችሁ ነበር።

ከድብድቡ በኋላ ሁለቱንም ሰው ይዟቸው

"አንተ ውሻ አላፈቅራትም ብለህ ያጣበስከኝ ፍቅረኛህን ነበር አይደል?(ደም ያዘለ ምራቅ ከአፉ እየተፋ) አትረባም ወንድ አይደለህም እሺ... ቀሚስ ልበስ"

ቢኒ ደግሞ ሌላ ትዕይንት ነው ከድብድቡ በኋላ እሱንም ሰዎች ቢይዙትም ለመወራጨትም ሆነ ለመሳደብ አልሞከረም የንዴት ትንፋሽ እየተነፈሰ ዝምም ብሎ ዳር ላይ ቆሜ አንዴ እሱን አንዴ ዮኒን እያፈራረቅሁ የማየውን እኔን ያየኛል

"እባካችሁ ልቀቁኝ ምንም አይፈጠርም እሷን ግን ሊጎዳት ይችላል። ሚስቱ ናት ግን እባካችሁ እንዳይጎዳት አድርጉ" አወራሩ ያሳዝን ነበር። ለቀቁትና ወደኔ መጣ

"ይሄ ውሻ ሚስቴ አጠገብ እንዳይደርስ እንዳትነካት አትጠጋት"
ብዙም ሳይቀርበኝ ቆመ

"ከሳምንት በኋላ እበራለሁ እስከዛ ግን ችግር ካለ ደውይልኝ እዛ ስሄድ ደግሞ እኔ እደውልልሻለሁ" አለኝና መልሴን ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ ከመናፈሻው ወጣ

።።።። ።።።።። ።።።። ።።   ።።። 
ሳሎን ሶፋ ላይ ኩርምት ብዬ ተቀምጫለሁ። ዮኒ ደግሞ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ ያለማቋረጥ እየተመላለሰ ይለፈልፋል

"ንገሪኝ እስኪ ስንት ጊዜ ሆናችሁ?" መልሴን ሳይጠብቅ ደግሞ

"የትናዬት ልክ ነበረች አይደል" ለመናገር አፌን እንደከፈትኩ

"ዝምምም በይ ምንም አትናገሪ ባትነግሪኝም አውቄዋለሁ። ግን ከመች ጀምሮ ነው ፍቅረኛ የሆናችሁት አንደኛ አመት እያለሽ"

"ኧረ እኔ ከቢኒ ጋር"
" ዝምም በይ አትንገሪኝ መገመት አይከብደኝም" ለመናገር መሞከሬን አቆምኩና ንዴቱ ሲበርድለት እነግረዋለሁ ብዬ አሰብኩ ግን በፍፁም ያሰብኩት አልሆነም። በውስጡ ያመነበትን የመከዳት፣ የመቀደምና የመሸወድ ስሜት ከውስጡ እንዳስወግድለት እድል ሊሰጠኝ አልቻለም። በራሱ ጭንቃላት ታሪክ ፈጠረና በፈጠረው ታሪክ ደግሞ አመነበት። ህያብ ከቢኒያም ጋር የአንደኛ አመት ተማሪ እያሉ ነው ፍቅር የጀመረችው። እኔ ላይ ተመካክረው ነው የተጫወቱብኝ ይህን እና ሌሎች ነገሮችን በጭንቅላቱ ውስጥ ሞላቸው የሚያውቀውን እውነት ሳይቀር ካደ። ከዛ በኋላማ ያሳለፍኩትን እንዴት ልገልፀው እችላለሁ በአጠቃላይ ህይወቴ ሲኦል ሆነ።

ተመስገን ይህን ሰሞን በፍቅር የተሞላ ጊዜ አሳለፍን ብዬ አመስግኜ ሳልጨርስ ሌላ ታሪክ ይፈጠራል። በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ግን ለሱ ያለኝ ፍቅር እንደድሮው ነበር። ትቼው እንኳን ለመሄድ አቅም አልነበረኝም። በእርግጥ ትቼው ብሄድ ከሱ የተሻለ ደሞዝ ያለኝ ራሴንም ሆነ ልጄን እና እናቴን ቀጥ አድርጌ ማስተዳደር የምችል ሰው ነበርኩ። ግን አፈቅረዋለሁ አንድ ቀን እውነቱን ለመረዳት እንደሚሞክርም አምናለሁ። እምነቴ ከምንም በላይ ለሱ ያለኝ ፍቅር በደልን ችዬ እንድኖር አደረገኝ

ይህ ከተፈጠረ ከአመት በኋላ እናቴ በፀና ታማ ሆስፒታል ገባች። እኔ የምሰራበት ሆስፒታል ነበር።  እንደማትተርፍ እያወቅሁ ብዙ ጣርኩ ግን ልመልሳት አልቻልኩም።

እናቴ ጥላኝ ሄደች እንደሚሰበር እንቁላል የምትጠነቀቅልኝ እናቴ እንደ አይኗ ብሌን የምትጠብቀኝ እናቴ ለኔ እንደኖረች ተምሬ ደርሸላት ትንሽ እንዳሳረፍኳት ገና ውለታዋን ሳልመልስ በደንብ እፎይይይ ብላ መኖር ሳትጀምር ሞት ነጠቀኝ። አመመኝ.... እጅግ በጣም አመመኝ። ከኔ የበለጠ እንቁን ማፅናናት ከባድ ነበር። እማዬ ሁሉ ነገሯ ነበረች።

ለአንድ ቀን መዓድ የተጋራሀውን ሰው እንኳን በሞት ማጣት ከባድ ነው። እማ ከዛም በላይ አለሜ ነበረች፤ የራሴን ውብ አለም ፈጥራ ከፍራቻዬ የሸሸገችኝ፣ ጓደኛዬ፣ ስታመም ሀኪሜ፣ ስጨነቅ አማካሪዬ፣ ተቆጪ መካሪዬ፣ ዘጠኝ ወር በሆዷ ተሸክማ ሶስት አመት ጡቷን አጥብታ ያሳደገችኝ እናቴ ለሰው አንድ ለኔ ግን ብዙዬ ነበረች።
ይገርማል አይደል ነው ከመባል ነበር ወደመባል የምንሸጋገርባት የሽርፍራፊ ሰከንዶች ሞት....

አስፈላጊ ያልናቸውን እቃዎች ሰብስበን ወደኔ ቤት ካመጣን በኋላ ቤቱን አፅድተን ለአከራይዋ ቁልፉን አስረከብን።

አከራይዋን ቻው ብለናቸው ልንወጣ ስንል እንቁ
"ማሚ እዚሁ ነው መኖር የምፈልገው እማዬን ትቼ የትም አልሄድም" እየተንሰቀሰቀች የተቆለፈው በር ስር ሄዳ ቁጭ አለች። አጠገቧ ሄጄ ቁጭ አልኩና አቀፍኳት.... ለረጅም ደቂቃ አብረን ተላቀስን።

አከራይዋ ወ/ሮ ትርንጎ ከቤት ሲወጡ ተቃቅፈን ስንላቀስ አዩንና  ወደኛ መጡ

" ምነው ልጆቼ ተነጋግረን አውርተን... ተው እንጂ እኔንም ሆድ አታስብሱኝ እናታችሁንም አትረብሿት ነብሷ በሰላም ትረፍ። በእናንተ እንደዚህ መሆን ደስተኛ የምትሆን ይመስላችኋል በሉ ልጆቼ ኑ ተነሱ" እጇችንን ይዘው ካነሱን በኋላ እንባችንን ጠራረጉልንና መክረውንና አፅናንተውን በር ድረስ ሸኙን።

"በቃ ቻው እማማ ትርንጎ እየመጣን እንጠይቆታለን ብዬ ቃል አልገባልዎትም ግን ቤተ ክርስቲያንም ቢሆን መገናኘታችን አይቀርም። የምሰራበትንም ሆስፒታል ያውቁታል አይደል ለጤናዎትም ብቅ ማለት ይችላሉ። ቤትም ይምጡ አይጥፉ። በሉ ቻው... ከዚህ በላይ አይቸገሩ" ተሳስመን መኪና ውስጥ ገባንና ወደ ቤት ሄድን።

እንቁ ሙሉ ለሙሉ እኛ ቤት መኖር ከጀመረች በኋላ የዮኒ ፀባይ ተስተካክሏል። ቶሎ ወደ ቤት ይገባል ትምህርት ቤት ያደርሳታል እልፎ አልፎ አብረው ይዝናናሉ። እኔ ብዙውን ጊዜ በስራ ስለማሳልፍ ባልቀላቀላቸውም የልጄ የአባትነት ክፍተት ሲሞላ በማየቴ ደስተኛ ነበርኩ። ሁልጊዜ አባቴ ማነው የሚለው ጥያቄዋ ሊያሳብደኝ ነበር የሚደርሰው.... ለጊዜውም ቢሆን ጥያቄዋን ትታ ዮኒን እንደ አባት ስታየው ማየቴ እፎይታን ሰጥቶኛል።

ትልቅ ልጅ እየሆነች ነው። አንዳንዴ እማዬ እየሳቀች "መልኳ እኮ አንቺን አስደግፈው የሳሏት ነው የምትመስለው። አንቺም ልጅ ሆነሽ እንደሷ እኮ ነው መልክሽ ካላመንሽ  ያንን አልበም አምጪና ፎቶሽን እና እሷን አስተያይ" ትለኝ ነበር።

ልጅ ሆና ብቻ ሳይሆን እያደገች ስትመጣም የኔኑ መልክ ያዘች።

ከዮኒጋ አልፎ አልፎ ጭቅጭቅ እንደ ቅመም ጣል ጣል ያለበት ራት በልተን እንገባለን። ቢሆንም ግን ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር ተመስገን ያስብላል። ትንሽም ቢሆን ቤቴ ትዳሬ ማለት ጀምሯል ያ ለኔ ትልቅ ነገር ነበር።

ቢኒ ከሄደ ጀምሮ ሶስቴ ነው የደወለልኝ። አንደኛው ከእናቴ ሞት በኋላ እግዜር ያፅናሽ ለማለት ነበር። ከዛ በፊት ሁለቴ ደውሎ ቢያውቅም ያን ያክል ግን አላወራንም ነበር ሌላው ቢቀር ስለመጫረሻው ቀናችን ደፍሮ የጠየቀ እንኳን አልነበረም።
ቻው ከማለቱ በፊት
" ግን ደስተኛ ነሽ" ይለኛል።
👍6414😱3👎1
#ህያብ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በኤርሚ


"ባልሽን አሳርፊው ልንማር እንጂ ልንሸረሙጥ አልመጣንም ቴሌግራም ላይ ሙሉ መረጃውን ታገኛለሽ" ይላል። እየተጠራጠርኩ ቴሌግራም ከፈትኩ ፊት ለፊት የመጣልኝን መልዕክት ስከፍተው
ፎቶ እና አጭር ቪድዮ.....  ዮኒ ከሌላ ሴት ጋር....

እየሰሙ አለማመን ያለም የሚጠበቅም ነው። እያዩ አለማመን ግን ምን ይባላል። በአካል መጥተው ዮኒ ከእከሊት ጋር ማገጠብሽ ቢሉኝ አይደለም እሱን ልጠራጠር ከነገረኝ ሰው ጋር ልጣላ እችላለሁ። አሁን ግን እውነታ ነው ቁጭ ያለልኝ... ከምወደው ባሌ ጋር እርቃን ገላዋን አብራው የምታብድ ሴት እያየሁ ነው። የአንዷ አልበቃ ብሎ ከሌላ ሴት ጋር ደግሞ ከንፈሯ ላይ ተጣብቆ ያለ ፎቶ እያየሁ ነው... ግን አንድ ነገር ብቻ ነው የምለው። "የኔ ዮኒ አያደርገውም" አድርጎታል እኮ ...ግን ይህንን ማመን ያልፈለገ ውስጥ አለኝ... እናም እውነታውን እያየ ግግም ብሎ አላምን አለኝ። አንደኛው ውስጤ ደግሞ ፍቅርን ሳይቀር ወደጎን ብሎ በቀልን ፈለገ። ቢችል አሁን ያለበት ሄዶ ስጋውን ቢዘለዝለው ተመኘ። የማያምነው ውስጤ ገኖ ወጣና
"ዮኒ አያደርገውም" በጩኸት ቤቱን አደበላለኩት። ሰራተኛዬ እልፍነሽ መኝታ ቤቴን ከፈት አደረገችና

"ሰላም ነው ህያብ" አለችኝ

"ሰላም ነው እልፌ ወደ ስራሽ ተመለሽ" በሩን ዘግታ ተመለሰች። ረጅም ደቂቃ ዝምምም ብዬ ስልኬ ላይ አፈጠጥኩ

ሀሳቡ አደከመኝ ያየሁት እውነት አራደኝ በዛ ላይ ሰሞኑን የተለየ ኬዝ ስለነበረ ያለ እንቅልፍ ሆስፒታል ነበርኩ። ስልኬን ዘግቼ ያስቀመጥኩት መሰለኝ... ከዛ ወደ አልጋዬ ተራመድኩ.... አንድ.... ሁለት..... ጭልም አለብኝ።

"እናት ኧረ ንቂ የኔ ፍቅር" ይሄን ጥሪ ከሰማሁት ስንት አመት ሆነኝ.... ሁለት.... ሶስት... ብቻ በዛ መሀል... አሁንስ ለምንድነው እየሰማሁት ያለሁት... ሁሉም ነገር ከረፈደ... ካለፈበት በኋላ ለምን?... አይኔን ሳልገልጥ እንቅስቃሴውን እየተከታተልኩ ነው።

"ንገሪኝ እስኪ እናት ማነው ጥፋተኛ እኔ ወይስ አንቺ? በእርግጥ የኔ ጥፋት ሚዛን ይደፋል... ምክንያቱም ካየሽው ውጭ እንኳን ብዙ ጥፋቶችን ሰርቻለሁ ግን ባንቺ ጥፋት ላይ ተመርኩዤ ነው። ታውቂያለሽ ከቢኒ ጋር ድሮም እጠረጥርሽ ነበር እና ጥርጣሬዬን የሚያረጋግጥልኝ ነገር ሳገኝ እውነት አይደለም ብዬ ማመን አቃተኝ። ልታስረጅኝ ስትሞክሪ ውሸቷን ነው ብዬ አልሰማም አልኩሽ እናም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ ማገጥኩብሽ... ግን እናት ያሁኑ በደሌ በዛ..... (ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ እና ትንሽ ዝም ካለ በኋላ ቀጠለ) ከስንት ጊዜ በኋላ በአንዲት ልጅ ምክንያት ራሴን አዳመጥኩት። አብረሽኝ ካልተኛሽ ውጤትሽን አበላሸዋለሁ ብዬ አስፈራራኋት.... ብዙ ለመነችኝ... ልመናው አልሰራ ሲላት ግን ያንቺን አድራሻ ፈልጋ ሆስፒታል መጣችና አየችሽ። ስለትዳራችን ሳይቀር ብዙ መረጃ ሰበሰበች ከረፈደ ቢሆንም  ንግግሯ ከእንቅልፌ አነቃችኝ... ትልቁን በደሌን የሰራሁ እለት ከእንቅልፌ ነቃሁ

'ሚስትህ ነፍሷን ሳትሰስት ትሰጥሀለች... አንተ ማመን ባልፈለከው ውሸት ውስጥ ተደብቀህ በሀጢያት ተጨማልቀሀል... ለሷ አትገባትም ምክንያቱም ንፁህ ናት... ግን እግዜር ይቅር የማይለው የለም አምላክህንም ሚስትህንም ይቅርታ ጠይቀህ ወደራስህ ተመለስ። ለውጤቴ ስል አብሬህ ላድር አልፈልግም በተለይ ያቺ ሚስኪ ላይ ይሄን ላደርግ አልችልም። ከፈለግህ ኤፍ አድርገው ህሊናዬን አላቆሽሽም'  ብላኝ ስላንቺ እንዴት እንዳወቀች ሁሉንም ነገር አብራራችልን እና ለአመታት ከተኛሁበት እንቅልፍ ዛሬ ቀስቅሳኝ ሄደች። ያሰብኩት ለሀያ ደቂቃ ብቻ ነው። ወደራሴ ተመለስኩ... እውነታውን ማየት ቻልኩ... በንግግሮቼም ሆነ በተግባር ብዙ እንደገፋሁሽ አወቅሁ... በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን እንዴት እንደምትጠነቀቂልኝ... ምን ያክል እንደምትወጂኝ ተረዳሁ። ወደዚህ ለመምጣት እየተጣደፍኩ ስወጣ ቢሮ በር ላይ ከዚህ በፊት በውጤት አስፈራርቻት አብሪያት የተኛሁትን ልጅ አገኘኋት እናም ቪዲዮና ምስል ላንቺ እንደላከችልሽ ነገረችኝ። ምንም ሳልል ወደዚሁ መጣሁ ወድቀሽ አገኘሁሽ።
ህያቤቴ እየሰማሽኝ እንደሆነ አውቃለሁ። ይቅር በይኝ አልልሽም በተለይ በአንድ ጉዳይ ያንቺ ይቅርታ አይገባኝም... ብቻ አይንሽን ግለጪና የፈለግሺውን ቅጪኝ" አይኔን ገለጥኩ ከወገቤ ቀና አልኩና ትራስ ተደግፌ ቁጭ አልኩ። ለረጅም ደቂቃ በዝምታ አፈጠጥኩበት

"ደስ ያለሽን አድርጊኝ የፈለግሺውን ቅጪኝ " አንደበቴ ሊናገር ቢፈልግ እንኳን ውስጤ ዝምምምም ብሏል የሚያስፈራ ዝምታ

"ደግሞ አሁን እሰማሻለሁ ከቢኒ ጋር ያደረጋችሁትን ንገሪኝ እኔ እንደተናዘዝኩ ተናዘዢልኝ.... ይቅር ተባብለን  አብረን ባንቀጥልም ጥያቄዎቼን እንድትመልሽልኝ እፈልጋለሁ... የምናሴ አባት ማነው። ህያብ አንቺም እኮ ድብቅ ነሽ ከኔ የደበቅሺው ብዙ ሚስጥር አለሽ" ዝምምምም

"እንቁን አሟት ነበር ልያት" ከመኝታ ቤታችን ወጥቼ ወደሷ ስሄድ

"እወቂ ለዚህ ሁሉ ነገር ያንቺም እጅ አለበት....ወይኔ አምላኬ ምንድነው ያደረኩት" ሰማሁት ግን ባልሰማ ወደ ልጄ ክፍል ሄድኩ

በሩን ከፈት አድርጌ ሳያት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝታለች ወደ ውስጥ ገባሁና ቀስ አድርጌ ዘጋሁት። የአልጋዋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብዬ የትኛችውን እንቁዬን አየኋት ግንባሯ ላይ ቸፈፍ ያለ ላብ አለ። ፎጣ አንስቼ ስጠርግላት እጄን ለቀም አድርጋ ወረወረችውና

"እባክህ አትንካኝ እባክህ" ከእንቅልፏ ደንግጣ ነቃች

"ምንድነው ልጄ ማንን ነው አትንካኝ የምትይው"

"አይይ እእ....እ

"የምን እእ ነው ምንድነው ንገሪኝ" ለአመታት ስቃዥ የነበረው ትዝ አለኝ... አይ አይሆንም

"በህልሜ የሚያስፈራ ሰው ገደል ውስጥ ሊከተኝ ሲል አየሁ" ኡፍፍፍፍ.... እኔ ደግሞ ስንቱን አሰብኩት

"አሁን እንዴት ነው ቁርጠቱ ተሻለሽ" ዮኒ በሩን ከፍቶ ገባ

"ምን ሆነሽ ነው ምናሴ ብዙ አመመሽ እንዴ ጠዋት እኮ ረፍዶብኝ ሳላይሽ ሄድኩ" የቅድሙን የተፀፀተ ፊት ሳይሆን ፍም እሳት የሚተፋ አይኑን አየሁት... እንቁ ፊቷን አዙራ ተኛች

"ምንድነው አንቺ ባለጌ ለአባትሽ መልስ ስጪው እንጂ" ፊቷን እንዳዞረች

"ደና ነኝ ተሽሎኛል" አለችው። ተነሳሁና ትቻቸው ወጣሁ። ሳሎን ሶፋ ላይ ቁጭ ብዬ ቲቪው ላይ አፈጠጥኩ..... ሀሳቤ ግን ሩቅ ሄዶ ነበር። መች ነው ይሄን ክፍተት የፈጠርኩት... ለራሴ ደግሜ ልነግረው አልፈልግም የምለውን ያን የመደፈር ታሪኬን ከመደበቅ... አዎ ከዛ ነው የጀመርኩት... ከዛ  የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ አልኩት... ከዛ... ከዛ... ከቢኒ ጋር እንኳን ምንም ግንኙነት የለንም... እሱም እንዳስረዳው እድሉን አልሰጠኝም።

ቢዘገይም ነገሮችን አጥርቼ መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ እና ታሪኬን ከአንድ ጀምሬ እነግረዋለሁ ብዬ ወሰንኩ... ግን አሁን አይደለም።

ህያብን ምን ይጨንቃታል ብትሉ ሰውን ተጣልቶ ማኩረፍ እላችኋለሁ። በህይወቴ እንደመኮራረፍ የምጠላው ነገር የለም አኩርፌ ማደርም አልችልም... በቃ ከሰው ጋ ተጋጨሁ አይደል ወይ እዛው ጋ ችግሩን እነግረዋለሁ ወይም ዝም ብዬ አልፈዋለሁ... ብቻ ያስከፋኝም ላስከፋውም ድጋሚ ሳገኘው ያንን ሰው አዋራዋለሁ። ከዮኒጋ በአንድ ጣራ ስር... አንድ አልጋ ላይ እየተኛን በየቀኑ እያየሁት ለማኩረፍ ሞከርኩ ግን አልተሳካልኝም በደሉን ባልረሳውም ሳላስበው አዋራሁት።
👍606
#ህያብ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በኤርሚ



#ከጊዜያት_በኋላ

"ንገሪኝ እስኪ ህያብ ሀኪም እንዲያይሽ ባትፈልጊም ህመምሽን ለኔ ንገሪኝ ዝምምም ብዬ እሰማሻለሁ። ስለ ልጅሽ ስለ ዮኒ ስለተፈጠረው ሁሉንም ንገሪኝ" ሶስት ወራትን በዝምታ ስለዚህ ነገር ሳያነሳብኝ ሳላወራው በየጊዜው የአእምሮ ህመሜ እየተነሳ ከኔው እኩል ሲሰቃይ አሳልፈናል። ትዕግስቱ እንክብካቤው ፍቅሩ ድሮ ከማውቀው የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ግን ምን ዋጋ አለው ፍቅር አንዳንዴ ፍትሀዊ አይደለም ቢሆንማ ኖሮ የማፈቅረው ዮኒን ሳይሆን ቢኒን ነበር። ወደ መኝታ ቤት ሄድኩ... ተከተለኝ... በሩን ከፍቼ ገባሁና ቤቴ ሄደን ካመጣናቸው እቃዎች መሀል አነስተኛውን ሻንጣዬን አወረድኩት... ከፈትኩት... ውስጡ ያለው ሁሉም የልጄ ማስታወሻ ነው። ለአዲስ አመት የሳለችልኝን አበባ አገኘሁት... እሱን አቅፌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ

"የኔ ልጅ... የኔ እንቁ... ናፈቅሽኝ እኮ" ቢኒ አጠገቤ ብርክክ ብሎ ትከሻዬን ያዘኝ ከዛም ወደራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ። ህመሜ ሳይነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን አረጋጋሁና ከእቅፉ ወጥቼ ከመፅሀፍ መሀል አጣጥፌ ያስቀመጥኩትን ደብዳቤ አወጣሁት... ከባዱን መርዶ ያረዳኝን... መራራውን እውነታ የጋተኝን ደብዳቤ አወጣሁና ለቢኒ ሰጠሁት። ግራ በተጋባ ፊት ካየኝ በኋላ ከፈተው... ደጋግሜ ከማንበቤ የተነሳ እያንዳንዱን ቃል እንደ ውዳሴ ማርያም የሸመደድኩትን ደብዳቤ እሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያነበው ከፈተው... እንዲህ ነው የሚለው...

"ማሚ ከበደል ሁሉ የቱ እንደሚከፋ ታውቂያለሽ... አባቴ የምትይው ሰው በስሜት ጦዞ ጭንሽን ሊከፍት ሲታገል ማየቱ...... ማም እውነቱ ይገልሻል አውቃለሁ ...ግን እንደዛ ጠንካራ ስነ ልቦና እንዲኖራት አድርገሽ ያሳደግሻት ልጅሽ ለምን ራሷን አጠፋች? የሚለው ጥያቄም ይገልሻል። ማም እውነቱን እወቂው..... መጀመሪያ የውሸት ቆይቶ ደግሞ የእውነት አባት የሆነኝ ዮኒ የውሸት አባቴ እያለ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ደፍሮኛል። ታስታውሻለሽ ያኔ ፔሬድ አሞኝ ነው ብዬሽ የተኛሁ ጊዜ... ለመጀመሪያ ጊዜ የደፈረኝ ቀን ነበር። አንቺ ውስጥ እያለሽ ሊጠይቀኝ ሲመጣ ፊቴን አዙሬበት ነበር አይደል? ከዛ አንቺ ወጣሽ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ 'በሶስተኛው ቀን መድገም አለብን ካላዛ ተደፍነሽ ትቀሪያለሽ' አለኝ። እናም በሶስተኛው ቀን መኝታ ቤቴ ድረስ መጣ... መከላከል ደከመኝ እና በዝምታ አየሁት ሳይራራልኝ እላዬ ላይ ጨፍሮ ሄደ... ያንኑ ድርጊቱን የአባትነት እውነታው እስከሚታወቅ ድረስ ደጋገመው። በተለይ ፊልድ መውጣትሽ ለሱ ምቹ ሁኔታ ለኔ ደግሞ ስቃይን ፈጠረ

ካንቺ ፊት ላይ የየሁትን ደስታ እኔ ጋር ፈልጌ አጣሁት። ማም እንዴት ልደሰት... አባቴን አገኘሁ ብዬ እንዴት ደስ ይበለኝ...? አባትነቱን እኮ ጭኔ መሀል ቆፍሮ ቀብሮታል። እናም አባቴ አይደለም ሊሆንም አይችልም ብዬ በዝምታ ተሸብቤ ቁጭ ብዬ እያለ ሌላ ክስተት ተፈጠረ። በየጊዜው እየመጣ ይቅርታ ብሎኝ 'አደራ ለናትሽ እንዳትነግሪያት' ከሚለኝ ከህሊናቢሱ አባቴ የስምንት ሳምንት ነብሰ ጡር እንደሆንኩ ሆስፒታል አረጋገጥኩ። ያኔ በራሴ ላይ ወሰንኩ... ታሪክ ራሱን አይደግምም... ማም አንቺ አባት እንደሌለኝ እያሰብሽ ወልደሽ እሳደግሺኝ... የኔ ልጅ አባት ግን አባቴ ነው... እናም በራሴ ላይ እና ባልወለድኩት የአባቴ ልጅ ላይ የሞት ፍርድ ወሰንኩ።

ማሚዬ ለኔ ስትይ ጠንክረሽ ኑሪ እወድሻለሁ።
እድለቢሷ ልጅሽ"

ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ ቢቆይም እንባ ከአይኖቹ እየወረደ ፍዝዝ ብሎ ተቀምጧል።

"ይህን ደብዳቤ ሳገኘው ቢኒ ጊዜው ረፍዷል... የልጄ ገዳይ አጠገቤ አልነበረም... ትቶኝ ሄዶ ነበር... ፈለኩት በየሆስፒታሉ በየሆቴሉ ግን አጣሁት... ባገኘው በአደባባይ ስጋውም ዘልዝዬ ለአሞራ እሰጠው ነበር"። እያለቀሰ መጥቶ አቀፈኝ ረጅም ሰአት ተቃቅፈን ተላቀስን...።

"እባክሽ አንድ ነገር እሺ በይኝ የስነልቦና ሀኪም ይይሽ እባክሽ ለኔ ስትይ" ለብዙ ጊዜ ደጋግሞ ቢጨቀጭቀኝም እምቢ ነበር መልሴ

"እሺ ደስ ያለህ ሀኪም ጋ ውሰደኝ"

።።።።። ።።።።። ።።።። ።።።።። ።።።

የስነ ልቦና ህክምናዬን ከጀመርኩ አንድ ሳምንት ቢያልፈኝም ለዶክተሬ ምንም የነገርኩት ነገር አልነበረም። የሆነ ቀን ግን ልክ ከዚህ በፊት ያለውን ታሪክ እንደሚያውቀው ሁሉ

"ዮኒን ብቻ ጥፋተኛ አድርጌ እንዳልፈርድ የሚያደርገኝ እንደዚህ ያሳመመኝ ብዙ ፀፀት ውስጤ አለ። ብዙ ቢሆን ኖሮ.... ብዙ.... ብዙ....

•ከመጀመሪያው ታሪኬን ነግሬው ቢሆን ኖሮ

•ስራ ስራ ማለቴን ትቼ ለልጄ ጊዜ ሰጥቻት ቢሆን ኖሮ

•እንደዛ ሆና እያየኋት ትንሽ እንኳን ለምን አልተጠራጠርኩም... አሁን እኔ ዶክተር እባላለሁ...

ከሁሉም በላይ ፀፀቱ በልቶ ጨረሰኝ... መገጣጠሚያ አጥንቴ እስከሚታይ ከሳሁ... ጠቆርኩ... ታመምኩ... አበድኩ ...ግን ትርጉም አልነበረውም... እኝህ ሁሉ የኔን እንቁ አይመልሱልኝም ባዶ... አንተስ የኔን እንቁ ትመልስልኛለህ? አየህ እዚህ መጥቼ መፋጠጣችንም ትርጉም የለውም ባዶ..." አልኩት። ዝምምም ብሎ ካየኝ በኋላ ከወንበሩ ተነስቶ መጥቶ ፊት ለፊቴ ሶፋ ላይ ተቀመጠ

ከስድስት ወራት ያላሰለሰ የህክምና ክትትል በኋላ ወደራሴ ተመለስኩ ወደ ስራየም ጭምር። ከቢኒ ጋር ደስ የሚል የፍቅር ግንኙነት ጀመርኩ... ህይወት ድጋሚ ቀጠለች። ያለፈው ባይረሳም ህመሙ ቀንሷል... የልቤ በልቤ ተቀብሮ መሳቅ ቻልኩ።

ከቢኒ ጋ ልንጋባ ነው ማለትም ከሁለት ወር በኋላ እንጋባለን። ለፊርማው እንጂ የምንኖረው አንድ ቤት የምንተኛው አንድ አልጋ ላይ ከተጋባን ቆይተናል ለማለት ነው። ልንጋባ መሆኑን ያወቀው ሀብታሙ ካለበት ሀገረ አሜሪካ የሚያምር ቬሎና ሱፍ ልኮልናል። ለቢኒ ሚዜ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ።

የሆነኛው ሌሊት ላይ ተኝቼ ልጄን በህልሜ አየኋት... ብቻዋን አይደለም ዮኒ ሲደፍራት "ድረሽልኝ" እያለች ስትጮህ... ጮኬ ከእንቅልፌ ነቃሁ... አጠገቤ የተኛው ቢኒ ጩኸቴ አስደንግጦት

"ምንድነው ፍቅር አይዞሽ ቅዠት ነው" አለና እቅፉ ውስት ከተተኝ... እኔ ግን የበቀል ጥሜ ድጋሚ አንሰራራ... እፈልገዋለሁ እናም እገለዋለሁ... እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።

ለቀናት በሀሳብ ተብሰከሰኩ እናም ወሰንኩ ይህን ነገር ከስሩ መንግዬ መጣል ይኖርብኛል። ተቆርጦ ባቆጠቆጠ ቁጥር ህመሙ እየባሰ ነው የሚሄደው ስለዚህ እ ገ ለ ዋ ለ ው

#አሁን

ትቼው ልሄድ ነው። በቃ ልሄድ ነው የመጨረሻ ውሳኔዬን ወስኛለሁ የምሄደው እንደ ሌላው ጊዜ ጥላቻንና ክህደትን ሽሽት አይደለም... ፍቅርን እንጂ።
እናም በሀሳብ እየዋዠኩ ደብዳቤ ልፅፍለት ወሰንኩ ቢያንስ ምክንያቴን ማሳወቅ አለብኝ አይደል... ደግሞ ጠፋች ብሎ ሀገር ምድሩን ነው የሚያምሰው...

መፃፍ ጀመርኩ

"አንዳንዴ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ይሆንብኛል። ፍቅርህ፣ ስስትህ፣ እንክብካቤህ፣ አንተን ትተህ ለኔ ደስታ መድከምህ፣ ከቃላት ጋጋታ ይልቅ በተግባር የምታሳየኝ መውደድህ በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህን መቋቋም ያቅተኛል።
👍7414🔥2😁1