አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹ምን ችግር አለው፡፡ አንድ ከተማዋን የሚያውቃት ጓደኛ ፈልጋ፡፡ አየህ ይሄንን የመሠለ አጓጊ ጨዋታ በአዲስ አበባ ግርግር ውስጥ መጫወት አልፈልግም፡፡በደብረዘይት ፀጥታና ውበት እየተደመምኩ ቢሆን እመርጣለሁ፡፡››

‹‹እሺ ይሁን ለጊዜው ከጓደኞቼ መሀከል ከተማዋን ማን እንደሚያውቃት ትዝ አይለኝም፡፡ ካልሆነ አንድ ሰው እቀጥራለሁ፡፡››

‹‹የግድ እኮ ወንድ ጓደኛህ መሆን የለበትም፤ሴትም ጓደኛህ ልትሆን ትችላለች...የመጨረሻ አንድ ማሳሰቢያ ሞባይል ስልኬን በመከታተል ጊዜ እዳታጠፋ...የተመዘገበው በእኔ ስም ሳይሆን እኔም በማላውቀው በሌላ ሰው ስም ነው፡፡አረብ አገር በሄደ ሰው ስም፡፡ለማንኛውም ቻው፡፡ ዝርዝር ህጎችን ቀኑን ስትወስን እንነጋገራለን፡፡ >> ሰልኩ ተዘጋ፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ ቤተሰቦች ዛሬም አንድ 10 ሰው እጠብቃለው👍  አሁንም እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #አድርጉ ያሰብነው ከሞላ ነገ እንገናኝ ይሆናል። 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍56😁7🔥3
ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አንድ ለጋ ወጣት ቁመቷ ሜትር ከሠባ የሚዘል የወገቧ ቅጥነትና የዳሌዋ ቅርፅ አፍ የሚያስከፍት ጠይም ወዟ የሚያብረቀርቅ ይህ ቀረሽ የማትባል ሠማያዊ ቀለም ያለው ከጉልበቷ ትንሽ ከፍ የሚል ጉርድ ቀሚስ ከሚማርክ ሮዝ ቀለም ካለው ከግማሸ ጡቷ እስከ እንብርቷ ከሚሸፍን አላባሽ ጋር ለብሳ በአጠገባቸው አለፈች፡፡ የሁለቱም ዓይን ተከተላት፡፡ በእጇ አንድ መፀሐፍ ይዛለች፡፡ ሁሴን ዞሮ ወደ መግቢያው ቃኘ፡፡ የተከተላት ሰው እንዳለ ለማረጋገጥ ነበር፡፡

ወደ ሁለተኛው ዝቅታ ሄዳ ፊቷን ወደ እነሱ አቅጠጫ አዙራ ተቀመጠች፡፡‹‹ዋው! ይህቺ ከሆነችማ .. እንኳን አንተ እኔም ሳላፈቅራት
አልቀርም፡፡››

‹‹እንኳን ልብ ድካም አልኖረብኝ፡፡›› ሁሴን ነበር፡፡ልጅቷ አስተናጋጅ ታዘዛት .. ወይን ቀረበላት .. እየተጎነጨች መፅሀፉን ማንበብ ጀመረች፡፡

‹‹መፅሀፉን አየኸው?›› ትንግርት ነበረች::

<<ምነው?>>

‹‹የሚሥጥር መፅሐፍ እኮ ነው!››

« አዎ አንቺ... !>>

‹‹በቃ እሷ ነች ማለት ነው>>

‹‹እስቲ አትቸኩይ ገና አስራ አንድ ሠዓት እንኳን አልሆነም...እስከ አስራሁለት ሠዓት ዕድሌን ተረጋግቼ መሞከር እችላለሁ፡፡››

‹‹ይህቺኛዋ ግን ያዘዘችውን ምግብ እንኳን መብላት አልቻለችም፤ አይኖቿ እኛው ላይ እንደተቅበዘበዙ ናቸው፡፡››

‹‹አሁን ባለው ሁኔታ ያለን ምርጫ ሁለት ናቸው ግን እስኪ እንጠብቅ ምን አልባት ሠዓቱ ከመገባደዱ በፊት ከሁለት አንዷ ተነስታ ትሄድ ያሆናል፤ያ ከሆነ ደግሞ ምርጫችን አንዷ ላይ ብቻ ያርፋል ማለት ነው፡፡››

አስራ ሁለት ከሃያ ሲል ምርጫው ከሁለት ወደ
አንድ ዝቅ ከማለት ይልቅ ወደ አራት ከፍ አለ፡፡
ሦስተኛው ዝቅታ ላይ ምግብ ፈፅሞ በአፏ
ገብቶ የማያውቅ ይመስል የአፍንጫዋ ትልቅነት ከፊቷ ስፋት ጋር የማይመጣጠን
የፀጉሯ እርዝመት ሾጣጣ መቀመጫዋን ሊነካ
ጥቂት የቀረው ቀይ ወጣት ልጅ ፊት ለፊቷ ሚሪንዳ አስቀምጣ አይኖቿን ሀይቁ ላይ ተክላ ተክዛለች፡፡

ሌላኛዋ ደንዳና ሠውነት ያላት መቀመጫዋን የለበሠችው ጥቁር ጅንስ ሱሪ ወጥሮ ሊተረትር የሚመስል ፈገግታዋ ከሩቅ
የሚጣራ ደረቷ ወደ ፊት ትንሽ ፈጠጥ ያለ ጡቶቿ ተራራ ላይ እንደታነፀ ቤተክርስቲያን ከሩቅ አይን የሚገቡ ፣ጎረድ ያለ አፍንጫ ያላት ወጣት ትታያለች፡፡ይህቺኛዋ አልተቀመጠችም ቀጥታ ወደ ሀይቁ ነው
የወረደችው፡፡ መድረኩ ላይ ያለውን የብረት ከለላ ተደግፋ ሀይቁን ትቃኛለች፣ተራራውን ታማትራለች፣ በሞባይሏ ትቀርፃለች፡፡ ዞራ ደግሞ ወደነ ሁሴን አማትራ ፈገግታዋን ትረጫለች፤መልሳ ደግሞ ፊቷን ወደ ሀይቁ ትመልሳለች፡፡

‹‹እሺ ጌታው ሠዓትህ እያለቀ ነው ወስና፡፡››

‹‹እንዴት ልወስን፤ አራት እኮ ሆነዋል!››

‹‹ነፍስህ ታውቃት የለ፤ከአራቱ እሷ የትኛዋ እንደሆነች ለያ..፡።››

‹‹ለተቀማጭ ሠማይ ቅርቡ ነው፡፡አሉ.. መች እንደዚህ ቀላል ሆነና››

‹‹አይ ምን አልባት የሥነ ልቦና ምሁር ስለሆንክ ብዬ ነዋ፡፡››

‹‹በናትሽ በአሽሙርሽ አትረብሸኝ፡፡››

‹‹ኦኬ ! ይቅርታ ትቼዋለሁ፤እራስህን አረጋጋና ስራህን ቀጥል፡፡››

‹‹ይሄውልሽ ይህቺን ወፍራሟን ቀልቤ አልወደዳትም ሠርዤያታለሁ››

‹‹ሦስት ቀረህ፡፡››

‹‹ያቺ ቆንጆዋ አንባቢ ምንም እንኳን የምታነበው የእሷን መጽሀፍ ቢሆንም ይሄ ያጋጣሚ ጉዳይ ይመስለኛል፤እሷ እንዲህ ግልፅ የሆነ መረጃ አትሠጠኝም፡፡ ስለዚህ ሠረዝኳት፡፡››

‹‹ጎበዝ ሁለቱ ቀሩ .. ያቺ ቀጫጫ ብቻ እንዳትሆን?፡፡››

‹‹እሱን አስር ደቂቃ ታገሺኝ፡፡ ወደ ታች ልወርድ ነው፡፡››

‹‹ይቅናህ .. እኔ አራተኛውን ቢራዬን አዛለሁ፡፡››

‹‹እንደፈለግሽ››በማለት ከመቀመጫው ተነሳና ወደ ታች በመሄድ ከብረት ወደተሠራው ወለል ወርዶ መደገፊያውን ተደግፎ ‹‹ሀይ›› አላት፡፡

ባለትላልቅ ጡቷ ከሱ ሦስት ሜትር ያህል እርቃ በሀይቁ ውስጥ የምትዋኘውን አንድ ፈረንጅ እያየች ትፈነድቃለች፡፡ ፊቱን ወደ ቀጭኗ ሴት አዞረ ሲጋራ እያጨሰች ነው፡፡ አካሏ እንጂ መንፈሷ እዚህ ያለ አይመስልም፡፡ አስተውሎ አያት ኧረ እንደውም እያለቀሰች ነው፡፡ይህቺ የምታፈቅረው ከድቷት ልቧ ተሠብሮ የስብራቱን ጥዝጣዜ እያንገበገባት ያለች ነች፡፡›› በማለት ጎኑ ወዳለችው ሀሳቡን ሰበሰበ፡፡ ቀስ ብሎ ወደ እሷ ቀረበ፡፡

‹‹እሷ ስትዋኝ አይተሽ ከምትፈነጥዢ ለምን እራስሽ ገብተሸ ደስታውን አታጣጥሚም?››

‹‹የእኔ ቆንጆ ለምክርህ አመሠግናለሁ፡፡ ነገር ግን ሠውነቴን እንኳን የምታጠበው እንዳልንፈራገጥ በሠንሠለት ታስሬ ነው፡፡››

‹‹እንዴ ይህን ያህል ውሃ ትፈሪያለሽ?››

‹‹ከመፍራት በላይ..፡፡››

<<ለመሆኑ የየት አገር ልጅ ነሽ?››

‹‹ምነው መልኬ... ፈገግታዬ ቆንጅዬ ኢትዮጲያዊ አልመስል አለህ?››

‹‹እንደዛ ማለቴ ሳይሆን .. ለምሳሌ የደብረ ዘይት፣ የአዲስ አበባ፣ የናዝሬት ... ወዘተ እንድትይኝ ፈልጌ ነው፡፡››

‹‹እነሱ ብጥስጣሽ የማንነት መገለጫዎች ናቸው፤ ሙሉው ማንነቴን ከፈለክ እንዳንተው ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡››

‹‹አንቺ አትቻይም፡፡››

‹‹መች ሞከርከኝና፡፡››

‹‹ይሄው ዳር ዳር እያልኩ አይደል?››

‹‹ዳር ዳር ባዬቹማ ብዙዎች ናቸው…ወደ መሀል ሚዘልቅ ደፋር ጠፋ እንጂ፡፡››

‹‹ይህቺማ እራሷ ነች፡፡›› ሲል ደመደመ፡፡ እንዲወስን ካገዙት አቢይ ምክንያቶች አንዱ በንግግሯ ያስተዋለው ብስለት፣ የድምፅዋ ለዛ እና ቶሎ መግባበት መቻላቸው ሲሆን ሁለተኛው አንገቷ ላይ ሀብል ማጥለቋ ነው፡፡ አበባውን ስትሰጠኝ እኔ ሀብል አጠልቅልሃለሁ ነበር ያለችው፡፡ እሱ ደግሞ ሀብልሽ አንገቴ ውስጥ እንደገባ እኔ ደግሞ ቀለበት እጣትሽ ላይ በክብር ሠካለሁ... ስምምነታቸው በምናብ ከለሰው…፡፡

‹‹ምነው ተከዝክ...ወደ መሀል መዝለቅ ፈራህ እንዴ?››

‹‹በፍፁም፤ ቆይ አንድ ጊዜ መጣሁ፡፡›› በማለት ወደ ላይ ወጣ ... ወደ ትንግርት

‹‹አበባውን ስጪኝ፡፡››

‹‹ወሠንክ፡፡›› አለችው፡፡ከቦርሳዋ እንቆቅልሽ የሚል ፁሁፍ የሚነበብበት ቁራጭ ወረቀት የተለጠፈበት ቀይ አበባ አውጥታ እየሠጠችው፡፡

‹‹አዋ እራሷ ነች፡፡›› እንዳመጣጡ እየተንደረደረ
ተመለሠ፡፡ በቀኝ እጁ አበባውን በግራ እጁ
ጃኬት ኪስ ውስጥ ያለውን ቀለበት በጉጉትና በጋለ ስሜት እያፍተለተለ፡፡ስሯ ሲደርስ በሚያምረው ፈገግታዋ ትላልቅ አይኖቿን
አፍጥጣ በአድናቆት ትመለከተው ጀመር፡፡

‹‹በመጀመሪያው ቀን ስለለየኋት በጣም ተደንቃብኛለች ማለት ነው፡፡›› ሲል በውስጡ እያሰበ ከአንገቱ ትንሽ ጎንበስ ብሎ አበባውን እንድትቀበለው ወደ እሷ በመዘርጋት ...‹‹እነሆ ወደ መሀል መግባት እፈልጋለሁ፡፡›› አላት፡፡ ተቀበለችውና ወደ አፍንጫዋ አስጠግታ በስሜት አሸተተችው፡፡

ወረቀቱን ገንጥላ አነበበችና <<እውነትም እንቆቅልሽ››


‹‹በመጨረሻም አገኘሁሽ አይደል?››

‹‹ሳታገኘኝ አትቀርም››

ቀለበቱን አወጣና መልሶ ከተተው፡፡ ቅድሚያ የእሷ ሀብል መቅደም አለበት፡፡ እጆቿን ወደ አንገቷ ወይም ወደ ቦርሳዋ እስካሁን አላከችም፡፡ በሁኔታው የተደመመች ትመስላለች፡፡ሊያስታውሳት ፈለገ፡፡ ‹‹ሀብሉ››

‹‹ምን ሆነ?››ፓፓዬ መስለው ባሞለሞሉ ሁለት ጡቶቿ ስንጥቅ መካከል ተኝቶ ወደ ተደበቀው ሀብል አፍጥጣ ተመለከተች፡፡ ቀስ ብላ እየመዘዘች አወጣችና ከላይ ደረቷ ላይ ለቀቀችው፤ክው ብሎ ደነገጠ፡፡ የልብ ቅርፅ አይደለም፤የመስቀል ቅርፅ ነው፡፡ የእሱም የመጀመሪያ ፊደል አይታይበትም፡፡

ይቀጥላል

ከተች ያለው #YouTube ቻናል ነው  #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ያስብነው ስላልሞላ ብዙ ቆየን ዛሬ ሐሳባችንን ሙሉትና በቅርብ እንገናኝ።
👍126😁16🔥43
‹‹አምስተኛዋ እኔ ነኝ፤አላየኸኝም እንዴ? እኔም እኮ ትናንት እዛ ነበርኩ››ፈገግ አለ፡፡

‹‹እኔ እንጃ፡፡ነበርሽ እንዴ? ምን አልባት በጣም ተጠግተሸኝ ተቀምጠሸ ከሆነ ‹ሎንግ ሳይት› በሽታ ስላለብኝ ቅርቤ ያለውን ነገር አጥርቼ ማየት ይቸግረኛል›› ሲል ተረቧን በተረብ መለሰ፡፡ ‹‹አስራ አምስት ደቂቃ ብቻ ነው የቀረህ››

‹‹እንደ እኔ ግን ሴትዮህ አሮጊቷ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ለደቂቃ እንኳን አይኗ ካንተ አይነቀልም፡፡አንተ ስትኮሳተር ፊቷን ታጠወልገዋለች፣ፈገግ ስትል ትገለፍጣለች፡፡ ምራቋን የዋጠች የሠከነች ሚስት እንደሚወጣት እርግጠኛ ነኝ፡፡››

‹‹እሷን እርሻት ባክሽ፡፡አታያትም ጥርሷ እራሱ እንዴት እንደሚገጥ፡፡››

‹‹ምን ሁኚ ምንም አፈቅርሻለሁ... አልተውሽም ብለሀታል፤እረሳኸው እንዴ?››

‹‹አረሳሁም፡፡ ግን እንዲህ አይነት ትሁን ማለቴ አይደለም፡፡ ቦርጯን እስቲ እይው? ከሠሎሞን እኮ አትተናነስም፡፡››

‹‹ያቺ ቀጫጫዋስ? ዛሬ ደግሞ ከትናንቱ በተቃራኒ ፈነዲሻ ሆናለች፡፡››

‹‹እሷ እንኳን ምንም አትል ግን ማደናገሪያ ትመስለኛለች፡፡ ስሜቴ እንደዛ ነው የሚነግረኝ፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ይህቺ አንባቢዋ ሳትሆን አትቀርም፡፡››

‹‹ትናንት እኮ እሷ ልትሆን አትችልም ብለኸኝ ነበር፡፡ እሷ ብትሆን የራሷን መፅሃፍ በማንበብ ግልፅ የሆነ ምልክት እንዴት ልታሳጥህ ትችላለች?»

‹‹ታዲያ ምን ላድርግ፤እሺ ንገሪኝ የትኛዋ ነች?>>

«ያቺ ቀዮስ?»

ፊቱን አዞረ፡፡ ሠርቃ ስታየው ተመለከታት‹‹አምጪ አበባውን ..…ታፍኜ አልፈነዳ››

ከቦርሳዋ አውጥታ ሠጠችው፡፡ እጁን ወደ ኪሱ ከተተና ቀለበቱ መኖሩን አረጋጠ፡፡ ከመቀመጫው ተነስቶ በተንቀረፈፈ እርምጃ ወደ ልጅቷ አመራ፡፡

‹‹ሠው አለው?›› ከፊት ለፊቷ ወዳለው ወንበር በጣቱ እያመለከተ፡፡

‹‹የለውም... ከዛ አባረረችህ እንዴ?››

ምንም ሳይመልስላት ተቀመጠ፡፡በዛው ቅፅበት በጨረፍታ ሲመለከት ጠይሟ ወጣት መጽሀፏን ዘግታ ከመቀመጫዋ ለቃ ወደ መውጫው ስታመራ ተመለከታት፡፡ በጥርጣሬ ታፍኖ በአይኑ ሸኛት፡፡ አሮጊቷም አምስት እርምጃ በማይሆን ርቀት ከኃላዋ አንገቷን ደፍታ ተከትላታለች፡፡ ግቢውን ለቀው ወጡ፡፡ አይኑን ሲመልስ ወርቃማ ፀጉሯን በቀጫጭን ጣቶቿ ወደኃላ እየላገች አፍጣ በመገረም ታየው ነበር፡፡

እንደመርበትበት አለና አይኖቹን ከአይኖቿ አሸሸ፡፡

‹‹የያዝከው አበባ ያምራል፤ የሚቀበልህ አጣህ እንዴ?>>

‹‹አበባውን የሚቀበለኝ ሳይሆን ክራይቴሪያውን የሚያሟላ ነው ያጣሁት፡፡››

‹‹ስላላፈቀርክ ነዋ፡፡››

<<እንዴት?>>

‹‹ክራይቴሪያ የሚኖረው እኮ ከፍቅር በፊት ነው፡፡ ካፈቀርክ ግን የክራይቴሪያ ዘረ ማንዘሮች ተጠራርገው እንጦሮጦስ ይገባሉ፡፡ ምክንያቱም ፍቅር ጉድለቶችን ሁሉ አይቶ የማለፍ ብቃት አለውና፡፡››

‹‹እንደመልክሽ ንግግርሽም ጣፋጭ ነው››

‹‹አመሠግናለሁ፡፡ ግን ያቺን የመሠለች ቆንጆ ብቻዋን አስቀምጠህ እዚህ የመጣኸው ልትጀነጅነኝ እንዳይሆን?››

‹‹ብጀነጅንሽ ምን አለበት?››

‹‹ምንም የለበትም፡፡ ክፋቱ ዛሬ መጀንጀን አላሠኘኝም፤ ለማንኛውም አበባውን ግን እቀበልሀለሁ ፤ልትሠጠኝ ከፈለክ ማለቴ ነው፡፡››

አበባ የያዘ እጁን ወደ እሷ ዘረጋ፡፡ተቀበለችው፡፡ ለደቂቃም በፅሞና ተመለከተችው፡፡ እላዩ ላይ የተለጠፈውን ቁራጭ ወረቀት አነበበች፡፡ ‹‹እንቆቅልሽ›› ጮክ ብላ አነበበችው፡፡ በዝግታ ከጎኗ ያስቀመጠችውን ቦርሳ አነሳችና ጭኗ ላይ አስቀምጣ መክፈት ጀመረች፡፡የሁሴንም ልብ አብሮ መከፈት ጀምሯል፡፡እጇን ቦርሳ ውስጥ ከታ ታተረማምሳለች፡፡

‹‹ቀስ ብለሽ ፈልጊው›› አላት ሳያስበው፡፡

ቀና ብላ አየችውና ፈገግ ብላ ወደ ፍለጋዋ ተመለሠች፡፡ እሱም እጁን ወደ ኪሱ ከቶ ቀለበቱን ባለበት ያፍተለትል ጀመር፡፡ዳግመኛ እጇ ከቦርሳዋ ሲወጣ ግን ይዛ የወጣችው የጓጓለትን ሀብል ሳይሆን ቢዝነስ ካርድ ነው፡፡ ፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችለትና፡፡ ከወንበሯ ተነሳች፡፡ ቦርሳዋን ትከሻዋ ላይ አድርጋ አበባውን በቀኝ እጇ እንደያዘች <<የኔ ማር ዛሬ ሙዴ ስላልሆነ ነው ፤ያው አድራሻዬ፤ ሌላ ቀን ብትደውልልኝ መገናኘት እንችላለን፡፡ እስከዛው አበባህን ውሃ እያጠጣሁ እንከባከባታለሁ›› በማለት ጎንበስ ብላ ጉንጩን ሳመችውና እየተውረገረገች ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ ሁሴን ባለበት ደነዘዘ፡፡ ምንም መናገር አልቻለም፡፡ ምራቁ መረረው፡፡ ትንግርት መጥታ ከጎኑ በመቀመጥ ብታናግረውም አልሠማትም፡፡ትከሻውን እያርገፈገፈች ለማናገር ሙከራዋን ቀጠለች፡፡

‹‹ስማ ነገሮች እኮ አላከተሙም፡፡ ሌላ አንድ እድል እኮ ይቀርሃል፡፡››

‹‹ተይኝ ባክሽ እንዲያውም አንቺ ነሽ›› አንቧረቀባት፡፡

‹‹ደግሞ እኔ ምን አደረግሁ?››

<<አሳሳትሽኛ፡፡ እኔ አሁን ይህቺን ዲቃላ መች አየኋት፡፡ አንቺ ነሽ የጠቆምሽኝ፡፡ ደግሞ አውቀሽ እንድሳሳት ፈልገሽ ነው፡፡››

‹‹እንዴት እንድትሳሳት እፈልጋለሁ?››

‹‹ከእሷ ጋር እንድንገናኝ እንደማትፈልጊ እኮ ከቅድሙ ንግግርሽ ተረድቼያለሁ፡፡ ደግነቱ አሁን ማን እንደሆነች አውቄያታለሁ ነገ ብቻ ይንጋ፡፡ ወደ ኃላ መመለስ አቃተኝ እንጂ ልክ እኔ ወደዚህ ስመጣ ነው እሷ ተበሳጭታ ስትወጣ ያየኋት፡፡››

‹‹እሷ ብቻ እኮ አይደለችም ተበሳጭታ የወጣችው እንዲያውም የእሷን ብስጭት አልተከታተልኩም፡፡ አሮጊቷ ግን አንገቷን ደፍታ ነበር እያዘነች የወጣችው፡፡››

‹‹በቃ ከአሁን በኋላ በራሴ መንገድ መሄድ ነው የምፈልገው ምክርም አልፈልግም፡፡ እንደውም ጥዋት እሸኝሻለሁ፡፡ የመጨረሻውን ፈተና ብቻዬን መጋፈጥ እፈልጋለሁ፡፡ አሁን ተነሽ ወደ ሆቴላችን እንሂድ..… በጣም መጠጣት አምሮኛል፡፡›› በማለት መቀመጫውን ለቆ ውጪ ወደቆመው መኪና አመራ፡፡ ከኋላው ተከተለችው፡፡ ቀጥታ ያመሩት አልጋ ወደያዙበት ቢሾፍቱ አፋፍ ሆቴል ነበር፡፡

ይቀጥላል

ቀጣዩ ክፍል ማታ #ሁለት #ሰዓት ይለቀቃል እስከዛው በብዛት ዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ
ጠብቁኝ ቤተሰቦች 😘
 
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍104🥰13🔥65
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹በጊዜ ነበር እኮ መምጣት የፈለኩት ለሆነች ጉዳይ ከአንድ መስሪያ ቤት ወደ ሌላው ስሯሯጥ መሸብኝ›› ሠሎሞን ነው፡፡

‹‹ምንም አይደል ዋናው መምጣትህ ነው›› ፎዚያ መለሠችለት ከፍሪጅ ያወጣችውን ቀዝቃዛ ቢራ ከፍታ ፊት ለፊቱ እያስቀመጠች፡፡

‹‹ወድጄ መሠለሽ ፤ ያ እብድ ሳታያት እንዳታድር ብሎ ስላስገደደኝ ነው የመጣሁት፡፡››

‹‹ሁሴን እያት ባይልህ አትመጣም ነበር ማለት ነው?›› አለችው ትንሽ እንደማኩረፍ ብላ፡፡

‹‹አይደለም፤ እንዲሁ ነገፀሩን አልኩ እንጂ መምጣቱንማ እኔም እፈልገው ነበር ምነው ቆመሽ ቀረሽ አንቺም ያዥና ቁጭ በያ ::

ፍሪጁን ከፍታ ሚሪንዳ አውጥታ ከፍታ ፊት ለፊቱ ቁጭ አለች፡፡

‹‹አይ ይሄማ አይሆንም.ቢራ ከሌለ ወጣ ብዬ ገዝቼ እመጣለሁ ካለበለዚያ ግን እኔን አልኮል እየጋትሽ አንቺ ለስላሳ እንዳትከፍቺ››

‹‹እንዴ! አረ እኔ አልጠጣም ።.››

‹‹ይቅርታ እንደዛ ፓጋን መስለሺኝ ነው፡፡

‹‹እዚህ ጋር ወራጅ አለ…እኔ ፊት እሱን መተቸት ክልክል ነው፡፡.››

‹‹ተቀብያለሁ...ለመሆኑ ዛሬ ደውሎልሻል?››

‹‹አልደወለልኝም ትናንት ነው የደወለልኝ ፣እንደውልለት እንዴ?››

‹‹አይ ተይው አሁን ከሀያ ደቂቃ በፊት አናግሬዋለሁ፡፡.››

‹‹እንዴት ነው ተሳካለት?›› በጉጉት ጠየቀችው፡፡

‹‹አልተሳካለትም፡፡ዛሬማ ሊያብድ ደርሷል፡፡እኔ በበኩሌ ምን እንደሚሻለው ግራ ግብት ብሎኛል፡፡.››

‹‹ምን አንተ ብቻ ኧረ እኔም የማደርገው ጠፍቶኝ እንዴት እንደተጨነቅኩ ብታይ! ወይኔ ወንድሜን ምን አይነት ምትሀተኛ ልጅ ገጠመው?

‹‹ያን ያህል ትወጂዋለሽ ማለት ነው?››

‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው የምትጠይቀኝ? እሱ እኮ ለእኔ ወንድሜም፣አባቴም፣ መላ ቤተሠቤ ማለት ነው፡፡መውደድ የሚለው ቃል ብቻ ይገልፀዋል፡፡.››>

ሠሎሞን በስሜት እየተንዘረዘረ ስታወራው በአንክሮ እየተመለከታት ውስጡ ቅናት ነገር ብልጭ አለበት‹‹እኔን ይሄን ያህል ከልብ የሚወደኝ ሠው ይኖር ይሆን? >> ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ ቢያስብ ቢያስብ ከልጆቹ በስተቀር ማንም ትዝ ሊለው አልቻለም፡፡ የቀረውን ቢራ
ጨለጠና እርሱ ተነስቶ ፍሪጁን ከፍቶ ድጋሚ ቢራ አውጥቶ ከፈተው፡፡

‹‹እኔ የሚገርመኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ?›› ፎዚያ ነች ንግግሯን የጀመረችው፡፡

‹‹ካልነገርሽኝ አላውቅም፡፡››

‹‹የትንግርት ነገር!››

‹‹የእሷ ነገር ስትይ?››

‹‹አብራው መንከራተቷ ነዋ፡፡ ምንም ቢሆን መቼስ አንሶላ መጋፈፋቸው አልቀረ፡፡ ያፈቀርኳትን ሴት አፋልጊኝ ሲላት እሺ ብላው አብራ መሄዷ፡፡

‹‹ምን ታድርግ! መቼስ የሚያፈቅሩት ሠው ሲያብድ ወይ በሠንሠለት አስሮ ህክምና መውሠድ አልያም ደግሞ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በሄደበት እየሄዱ ባደረበት እያደሩ ደህንነቱን መከታተል ነው.…እሷም እያረገች ያለችው እንደዚሁ ነው፡፡››

‹‹በፊት ለእሷ ያለኝ ስሜት የቀዘቀዘ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን እየወደድኳት መጣሁ፡፡››

‹‹በደንብ ውስጧን ብታውቂ ደግሞ ይበልጥ ታፈቅሪያታለሽ፡፡ ልዩ ሠው ነች፡፡ ምን እንዳደረገባት አላውቅም እንጂ እኔ እሱን ብሆን ዓይኔ ከእሷ ውጭ ሌላ ሠው አያይም ነበር፡፡ በስብዕናዋ፣በጥበብ አፍቃሪነቷ፣ በአስደሳች ገፅታዋ፣በምሁራዊ ምልከታዋ፣የሕይወትን ውስጠ ምሥጢር አብጠርጥራ በማወቋ በቃ በሁሉም ነገሯ ለእሱ የምትገባ ሴት ነበረች፡፡እንዴ! ትንግርት ማለት እኮ አንድ ሴት ሳትሆን አስር ሴት ነች፡፡››

‹‹ኤደንስ?››

‹‹የእሷ ትንሽ የተለየ ነው፡፡››

‹‹የተለየ ስትል?››

‹‹አየሽ ኤደን ስርዓቷም ሆነ አስተዳደጓ ለሁሴን የሚሆን አይደለም፡፡ ኤደን ማለት የተለመደች አይነት ሴት ነች፡፡ ቆንጆ ነች፣ ሃይማኖተኛ ነች፣ባህል አክባሪ ነች፣ አብዛኛው ህብረተሠብ በመኖር ላይ ያለውን ኑሮ መኖር የምትፈልግ ሴት ነች፡፡ ጋብቻ፣ ሠርግ፣ እቁብ፣ ዕድር፣ አራስ-ጥሪ፣ ክርስትና፣ ለቅሶ ... የመሳሠሉትን ማህበራዊ ሠንሠለቶችን ሳታዛንፍ መከወን የምትፈልግ ሴት ነች፡፡ ሁሴንን ተመልከተችው ከህብረተሠቡ ጋር ያለው ግንኙነት የላላ፣ ከባህሉ ጋር ያለው መስተጋብር የረገበ፣ እንዲሁም የግሌ ሃይማኖት አለኝ ብሎ የሚፈላሠፍ ግለሠብ ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ በሁለት ጽንፍ ያሉ ግለሠቦች እንዴት ይጣመራሉ? መጀመሪያ እንደውም ለምን አታገባትም ብዬ እጨቀጭቀው ነበር፤ አሁን በደንብ ቀርቤ ሳያትና ልዩነታቸውን ስገነዘብ የእሱ ውሳኔ ትክክል እንደነበር ነው የገባኝ፡፡ እሷ ባይሆን ለእንደኔ አይነቱ ተመራጭ ነች፡፡›› በፈገግታ ንግግሩን አጠናቀቀና ቢራውን አንስቶ ተጎነጨ፡፡

‹‹ለእንደኔ አይነቱ ስትል?››

‹‹አየሽ እኔም እንደ እሷ የተለመደ አይነት ኑሮ ነው የሚመቸኝ፡፡ ፍልስፍና ቅብጥርሴ ያን ያህል አይደለሁም፡፡ አብዛኛው እሷን የሚመቿት ነገሮች እኔንም ይመቹኛል፡፡ በዛ ላይ ቆንጆ ነች፡፡ ገንዘብ አባካኝ አይደለችም፣ እንደውም ጠንካራ ሠራተኛ ነች፣ ታማኝ ነች፣ እነዚህ ነገሮች ደግሞ እኔ በጣም እምፈልጋቸው ናቸው››

ከመጠጡ ጋር ወደ ውስጡ የዋጠውን ንግግሩን ስታላምጠው የሆነ ነገር ጫረባት፡፡ ‹‹ያፈቅራት ይሆን እንዴ?›› ስትል አሠበችና ማረጋገጥ ፈለገች፡፡

‹‹መጀመሪያ የሁሴን ፍቅረኛ ባትሆን ኖሮ እሷን ማግባት ትፈልግ ነበር?››

መልስ ሳይሠጣት ለደቂቃዎች በአትኩሮት ተመለከታትና መናገር ጀመረ<<አዋ እሺ ካለችኝ ለሁለተኛ ጊዜ ላገባ የምፈልገው እሷን ነው፡፡ ደግሞም እሺ የምትለኝ ይመስለኛል›

ደነገጠች፡፡ የሠከረም መሠላት ‹‹ስለ ኤደን እኮ ነው የምናወራው››

«አዎ ምነው?>

‹‹አገባታለሁ ስትል ምን ማለትህ ነው? የሁሴን ፍቅረኛ እኮ ነበረች፡፡››

‹‹ነበረች፤ አሁን ግን አይደለችም፡፡ ከተለያዩ አመት ሊደፍን ነው›

‹‹ቢሆንም የሁሴንን አምቧረቀችበት፡፡

ፈገግ አለና ‹‹ባክሽ አታካብጂ .. በመጀመሪያ ሀሳቡን ያቀረበው እርሱ ነው፡፡ ሁሴን ማን እንደሆነ አታውቂም መሠለኝ›

‹‹ይሄንን ነገር እኔ አላምንም ደግሞም ያው እሱ እብድ ነው ሊልህ ይችላል፡፡ እሷ ግን በፍፁም እሽ አትልህም፡፡››

‹‹በተወሠነ መልኩ ትክክል ነሽ፡፡ እስከ አሁን አገባሀለሁ ብላ ቃሏን አልሠጠችኝም፤ግን
የተወሠነ መንገድ ተጉዘናል፡፡››

‹‹ምን ዓይነት መንገድ?››

የሁለት ወር ጉዞ፡፡ እርግጥ የመጀመሪያ ቀን አብረን ስናድር አቅደን አይደለም፤ በተለይ እሷ በአዕምሮዋም አልነበረም፡፡

እኔ ግን ሁሴን ከፈለክ ቀጥል ካለኝ በኃላ የተወሠነ ፍላጎት በውስጤ ተጭሮ ነበር፤እናም የዛን ቀን እሷ በእሱ ተናዳ፣ እኔ በሚስቴ ተንገብግቤ ተገናኘን ጠጣን እስክንበሠብስ ሠከርን፣ አብረን አደርን፤ ማደር መቼም ምን ማለት እንደሆነ ይገባሻል፡፡

‹‹ቆይ ጥዋት በንፁህ አዕምሮዋ ስታስበው ምን አለች?››

‹‹ተቆጣች፣ አለቀሰች፣ ብዙ ተፀፀተች፣ ለአንድ ሳምንት አኮረፈችኝ ፣ ግን ቀስ በቀስ ለቀቀ እያለች መጣች ደጋግመን ማደር ጀመርን››

‹‹ታዲያ እዚህ ደረጃ ከደረሳችሁ መጋባቱም ቀላል ነው በለኛ!››

‹‹እሱ ላይ እንኳን ትንሽ ችግር አለ፣ ሁሴን አግብቶ ያየሁ ቀን በማግስቱም ቢሆን አገባለሁ ብላኛለች

‹‹የሚገርም ጉድ ነው፤ ታዲያ ይቅናው ብለህ

አትፀልይም?››

‹‹ኧረ ምን ፀሎት ብቻ አዲስ አበባ ለሚገኙት ታቦቶች በጠቅላላ ተስያለሁ››

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ ቤተሰቦች ዛሬም አንድ 10 ሰው እጠብቃለው👍  አሁንም እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #አድርጉ

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍129😁1614👎3
‹‹ከሚገባው በላይ አወራን፤ አሁን መተኛት ነው ያሠኘኝ፡፡ መጠጣት ከፈለክ ክፍልህ ግባና በራፍህን ዘግተህ አስነካው፤ ብቻ ልብህ እንዳትፈነዳ፤ ለማንኛውም ለሊት ከመሄዴ በፊት ሠላም ማደርህን ማረጋገጡን አልረሳም፡፡››

‹‹ቁርጤን ሳላውቅማ ሜዳ ላይ ብቻዬን ጥለሺኝ አትመለሺም፡፡›› በማለት አልፏት ሄዶ አልጋው ጎን ያለው ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ እሷም ምንም እንኳን ብቻዋን ሆና አልጋዋ ውስጥ ገብታ ስላወራችለት ነገር ዳግመኛ ማሰላሰል ብትፈልግም በግድ ግን ወደ ክፍሉ ልታባርረው አቅሙን አላገኘችም፡፡ አስተናጋጁ የታዘዘውን መጠጥ አምጥቶ በራፉን ዘግቶ ተመልሶ ሄደ፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍5917👎8😱8
‹‹የመሠናበቻ እንድትስመኝ እፈልጋለሁ፡፡››

ቀኝ እጁን በአንገቷ ዙሪያ ጠምጥሞ መላ እሷነቷን ቀስ ብሎ ወደ ደረቱ አስጠጋት፡፡ ዓይኖቿን ጨፍና በዝግታ ተሳበችለት፡፡ ከናፍሮቻቸው ተዋሃዱ፤ ኃይል በተቀላቀለበት አሳሳም ይመጣት ጀመር፡፡ እሷም እየቃተተች...
መጠመጠችው፤እርቧት ነበር፤የስድስት ወር እረሃብ፤ ደግሞም ለዝንተዓለም እንደማታገኘው ተሠምቷታል፡፡ ይበልጥ ሠውነቱ ላይ ተጣበቀችበት፡፡እሱም በፈረጠመ ጡንቻው ጨመቃት፤ከደረቱ ጋር አጣብቆ ጡቶቿን አፍረጠረጣቸው፡፡

ከሠላሳ ደቂቃ በኋላ ሲነቁ አልጋ ላይ ሳይሆን ወለሉ ላይ እርቃናቸውን ጎን ለጎን ተዘርረዋል፡፡ ምን ጊዜ የለበሠችውን ጉርድ መልሳ እንዳወለቀች ምን ሠዓት የእሱ ልብሶች እንደወላለቁ በእርግጠኝነት የሚያውቅ የለም፡፡

‹‹አመሠግናለሁ፡፡›› አለችው፤ ከተኛችበት ወለል ተነስታ ተመልሳ ወደ ሻወር ቤቱ እያመራች፡፡

‹‹እኔ ነኝ እንጂ ማመስገን ያለብኝ፤ምን ያህል አጥቼሽ እንደነበር ያወኩት አሁን መልሼ ሳገኝሽ ነው ::>>

ሻወር በራፍ ላይ ከደረሠች በኋላ ቆም አለችና ፊቷን ወደ እሱ አዙራ ‹‹ሳገኝሽ ሳይሆን ስሠናበትሽ በል፤ቃል ቃል ነው ይሄ የመጨረሻችን ነው›› በማለት ወደ ሻወሩ ገብታ ውሀውን ለቀቀችው፡፡ እሱም ከተጋደመበት በዝግታ ተነሳና ተከትሏት ሻወር ገባ፡፡ ሳሙናውን ከእጇ ተቀበለና አንገቷ እስከ እግር ጥፍሯ ድረስ ሠውነቷን በአረፋው አዳረሠው፤ እሷም ተቀበለችውና የእሱን ሠውነት በተመሳሳይ ሁለቴ በአረፋው ሸፈነችው፤ ውሀውን እስከ መጨረሻ ከፍተው ተራ በተራ እየተሻሹ መታጠብ ቀጠሉ፡፡ በመሀከል የእሱ እጆች ሁለት ጡቶቿ አካባቢ ሲደርሱ አንዳቸው ከአንዳቸው ወደ ኋላ ማፈግፈግ አልተቻላቸውም፡፡ያልታወቀው ኃይል ሁለቱንም አንድ ላይ አጣብቆ ጨምቆ ያዛቸው፤ ቀና ብላ በፍንጥርጣሪ ውሃዎች መሀከል አፈጠጠችበት፡፡ የተቃውሞም ሆነ የትብብር ስሜት አልታየባትም ፤ ወደ ራሱ ሳባትና አፉን አፏ ላይ ዳግመኛ ከደነ፡፡ የመጨረሻው መጨረሻ የሆነውን ጣፋጭና
አይረሴ ፍቅር ሠሩና ሠውነታቸውን ተለቃልቀው መታጠቢያ ቤቱን ለቀው ወጡ፡፡ ወለሉ ላይ የተዝረከረከ ሱሪውን አነሳና ከኪሱ ውስጥ ሞባይሉን አወጣ፤ ሠዓቱን ተመለከተ...10፡10 ይላል፡፡ ‹‹ኧረ ሠዓቱ ሄዷል›› በማለት በጥድፊያ ልብሶቹን ከተጣሉበት እየለቃቀመ መልበስ ጀመረ፡፡ ትንግርትም ቅድም ልትለብሰው የነበረውን ጉርድ ቀሚስ ወለሉ ላይ ስለተረጋገጠባት ሌላ ደማቅ ቀይ ሙሉ ቀሚስ ከሻንጣዋ አውጥታ መልበስ ጀመረች፡፡

<< ቶሎ በይ... በአስር ደቂቃ ውስጥ ሻንጣሽን

‹‹ለምን ከዛ ስንመለስ አናዘጋጅም?››

‹‹አይቻልም፤ወደዚህ መመለስ አልፈልግም፤ በዛው ነው የምንሄደው፡፡››

‹‹በቃ ያቺ ጠይም ወጣት ምስጢር እንደሆነች እርግጠኛ ሆነሀል ማለት ነው?በዛው ይዘሃት ወደ አዲስ አበባ ልትበር ቸኩለሃል..!!!››

‹‹አዋ! ለማንኛውም እስክትዘጋጂ የእኔን ሻንጣ መኪና ላይ ልጫን›› በማለት በራፉን ከፍቶ ወጣና ወደ ራሱ ክፍል ገባ፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍14030👏8
#ትንግርት


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


አስር ሠዓት ከሃያ ሲሆን ሻንጣቸውን ጭነው ሆቴሉን ተሠናብተው ወጡ፡፡ ቁልቁለታማውን ኮረኮንች መንገድ ጨርሰው ዋናው አስፓልት መንገድ ሊገቡ ሃምሳ ሜትር ገደማ ሲቀራቸው ወደ ገበሬዎች ሆቴል አጥር መኪናውን ጥግ አሲይዞ አቆመና ተንቀሳቃሽ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ መደወል ጀመረ፡፡

‹‹ሄሎ ፎዚ››

‹‹ደህና ነኝ››

<<እ .. ምን አልሺኝ?››

‹‹አግኝቻታለሁ...ዝርዝር ሁኔታውን ማታ ስመጣ አወራሻለሁ፡፡ አሁን የደወልኩት እንደምንም ብለሽ ለአስር ሠው የሚበቃ እራት ማዘጋጀት ትቺይ እንደሆነ ልጠይቅሽ ነው?››

‹‹ጎሽ... ብር የሚያንስሽ ከሆነ ከሰሎሞን ውሰጂ ፤ደውዬ እነግረዋለሁ››

‹‹ቻው... ሁለት ሠዓት አካባቢ እንደርሳለን፡፡››

በተቀመጠችበት ደንዝዛ በፍራቻና በሀዘኔታ የሚሠራውን ታስተውላለች፡፡ አዝማሚያው አላማራትም፡፡ እንዲህ የጓጓለትን ነገር ሲያጣ ተስፋ በመቁረጥ አንድ ነገር እንዳይሆን ፈራች፡፡ እሱ አንድ ነገር ከሆነ ደግሞ እሷ እራሷን ይቅር ማለት እንደማትችልና የከፋ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ ሲታሠባት ሠውነቷ ተንቀጠቀጠ፡፡ ሁሴን ሁለተኛ ስልኩን እያናገረ ነው …፡፡

‹‹አንተ ቦርጫም አመንክም አላመንክም ሁለት ሠዓት ላይ እቤቴ ይዣት ከች ነው፡፡››

‹‹ግዴለህም በእርግጠኝነት ማንነቷን ለይቼዋለሁ፤ ከአስር ደቂቃ በኋላ በእጄ ነች፡፡››

‹‹ኡፍ ... አሁን ክርክሩን ተውና ቤት ሄደህ ፎዚያን አግዛት፤ ባዶ ቤት ይዣት መምጣት አልፈልግም፤ እሺ ካለች ለኤደንም ንገራት ፤ሁለት ሠዓት ቤት እንድትገኝ፤ ቅር ካላለህ የውብዳርንም ደውዬ ብጠራት፡፡››

<< ... በቃ በቃ ትቼዋለሁ ..ቻው በቃ በሠዓቱ እንገናኝ፡፡››

ስልኩን አናግሮ ሲጨርስ መልሶ ኪሱ ከተተና መኪናውን አስነስቶ ወደ አስፓልቱ ገባና ወደ ግራ ታጥፎ አዲስ አበባ መውጫ ላይ ወደሚገኘው ፒራሚድ ሆቴል አመራ፡፡ምንም ሳይነጋገሩ ነበር ሆቴሉ ደርሠው ከመኪና በመውረድ የግቢውን ውስጥ ጠቅላላ ማየት የሚቻልበት ቦታ መርጠው የተቀመጡት፡፡ ትንግርት ደመነፍሷ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው፤ አዕምሮዋ ራሱ ማሠብ ያቆመ መስሎ ተሰማት፡፡

ሁሴን‹‹አየሻት አይደል?›› አላት በፈገግታ እንደተሞላ ፡፡

‹‹ማን..ን?›› አለችው ከደነዘዘችበት ባና፡፡

‹‹ማንን ነው ለማየት የመጣነው? ሚሥጥርን ነዋ፡፡ ከፊት ለፊትሽ አትታይሽም?››

በመከራ አንገቷን ካቀረቀረችበት አቅንታ አይኖቿን ወደ ጠቆማት አቅጣጫ ወረወረች፡፡ እውነትም ጠይሟ ወጣት በተመሳሳይ ሁኔታ ወይኗን እየተጎነጨች መጽሀፏን ታነባለች፡፡ ትንግርት እሷን በምታይበት ሠዓት እሷም አማትራ እነሱን ተመለከተችና እጇ ላይ ያሠረችውን ሠዓት በማየት ወደ ንባቧ ተመለሠች፡፡

‹‹ሠዓቷን እያየች ነው፤በማርፈድህ ቅር ሳይላት አይቀርም፡፡››

‹‹ዋናው አለመቅረቴ ነው ...>> አስተናጋጁ አቋረጣቸው... ሁለቱም ጭማቂ አዘዙና መጣላቸው፡፡

‹‹አበባውን ይዘሻል አይደል?››በዝምታ ቦርሳዋን ከፈተችና የመጨረሻው ዕድል መግለጫ የሆነችውን አበባ ሠጠችው፡፡ ‹‹ከበስተጀርባህ አሮጊቷ እንዳለች እንዳትዘነጋ፡፡›› አለችው፡፡

ቀስ ብሎ ወደ ጀርባው ሲገላመጥ እውነትም
ዛሬም ያን ቦርጯን ወደ ፊት አንገፍጥጣ አይኗን ጀርባው ላይ ተክላለች፡፡ሁሴን ፈጎ የዋለ ፊቱን በመጠኑ ቋጠረው ‹‹ይህቺ ክምርማ
እኔን አታጭበረብረኝም፡፡››

‹‹አጭበርባሪዋ የትኛዋ እንደሆነች በምን አወክ? ምን አልባት ይህቺ ጠይሞም ሚሥጥር ላትሆን ትችላለች፡፡ ምን አልባት ሁለቱም አጭበርባሪ ይሆናሉ፡፡››

‹‹እንግዲያው ሁለቱም አጭበርባሪዎች ከሆኑ ትክክለኛዋ ሚሥጥር አንቺ ነሽ ማለት ነው?››

ልትጠጣ ያለችው የጁስ ብርጭቆ ከእጇ ተንሸራቶ አመለጣት… እሱ በፍጥነት ባይቀልበው ኖሮ መሬት ወድቆ ተከስክሶ ነበር

‹‹ምን ነካሽ እያንቀላፋሽ ነው እንዴ? አየሽ ዛሬ ማዳመጥ የምፈልገው ስሜቴን ነው፤ስሜቴ ደግሞ ይህቺ ጠይም ወጣት ትክክለኛዋ የእኔዋ ሚሥጥር መሆኗን ነግሮኛል፡፡››

‹‹ታዲያ እርግጠኛ ከሆንክ ምን ትጠብቃለህ ተነስና አበባውን ስጣት፤ ሀብሉን አንገትህ ላይ ታጥልቅልህ፤ አንተም ቀለበቱን በጣቷ ላይ ሠካላት… እንደውም ጣቶቿ በጣም ያምራሉ››

‹‹ምን አስቸኮለሽ፤ ገና አንድ ሠዓት አለኝ፡፡ ልክ አስር ደቂቃ ሲቀረው ነው አበባውን የምሠጣት እስከዛ እኔ በጉጉት እንዳተሠቃየሁ እሷም ትንሽ ትሠቃይ፡፡››

‹‹እስከዛ ደንዝዘን ቁጭ እንበል?›› አለችው ትንግርት ተስፋው በተሟጠጠ ድምፅ፡፡

‹‹እኔ ለሠላሳ ደቂቃ ያህል የነገሮችን አጀማመርና አሁን ያሉበትን ሁኔታ ወደ ኃላ ተመልሼ ማሠብ እፈልጋለሁ፡፡ አስር ደቂቃ ሲቀረው አስታውሺኝ›› በማለት አይኖቹን ሠማይ ላይ ተክሎ እግሮቹን አንፈራጦ ሀሳብ ውስጥ ገባ፤ ከሚሥጥር እንዴት ፍቅር እንደያዘው፤ ከእሷ ጋር የተለዋወጣቸው የስልክ ምልልሶች፤ እሷን ለማግኘት
የተጋፈጣቸው ውጣ ውረዶች፤አንድ በአንድ
በቅደም ተከተል ማሠላሠል ጀመረ፡፡

በመሀከል ዓይኖቹን ወደ ጠይሟ አንባቢ ወጣት ይወረውራቸዋል መልሶ ወደ ሀሳብ ይገባል፡፡ሙሉ በሙሉ ከሀሳብ ተጎትቶ የወጣው ትንግርት ትከሻውን ስትነቀንቀው ነበር፡፡ ‹‹ሠዓቱ ደርሷል›› አለችው

በሚርገበገብ ድምፅ፡፡ሠዓቱን ተመለከተ፡፡

በእጁ የያዘውን ቀይ የፈነዳ አበባም አስተዋለ፤
እላዩ ላይ የተለጠፈውን እንቆቅልሽ የሚል ፅሁፍም ለመቶኛ ጊዜ ደግሞ ተመለከተ …፡፡

‹‹አጨበጨበና አስተናጋጁን ጠራ.... ያቺ የምታነበው ልጅ ትታይሀለች የእሷን እና ከጀርባዋ የተቀመጠችውን ወፍራም ሴትዬ ሂሳብ ስንት ነው፡፡ የእኛንም ጨምረህ ቢል አሠራ፡፡›› አስተናጋጁ ወደ ዋናው ሆቴል
እየተጣዳፈ ሄዶ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ቢል ይዞለት መጣ፡፡

መቶ ሠማንያ ስምንት ብር ከሃማሳ ሳንቲም ....ሁለት መቶ ብር አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ ወረወረና ወደ ትንግርት ዞሮ‹‹ቦርሳሽን ያዥና ተነሽ›› አላት፡፡

በድንጋጤ አንጋጣ አየችው፡፡

‹‹ተነሽ እኮ ነው የምልሽ፡፡›› ግራ እጇን ይዞ እየተጣደፈ ግቢው ውስጥ ወደ ቆመችው መኪናው ይዟት ገባ፡፡ መኪናውን ከግቢው አውጥቶ ፊቷን ወደ አዲስ አበባ በማዞር ወደ ዋናው አስፓልት ገብቶ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ በኋላ ማሳያ ስፖኪዬው ሲመለከት ጠይሟ ወጣት እና አሮጊቷ ጎን ለጎን ቆመው አይናቸውን እሱ መኪና ላይ ተክለው በመገረም ሲመለከቱት አያቸው፡፡

ትንግርትም በድንጋጤና በሠመመን ውስጥ ሆና ያለ ምንም እንቅስቃሴና ንግግር 

ደንዝዛለች፡፡ ዓኖቿ ፊት ለፊት ያለው አስፓልት ላይ ተተክለዋል፡፡ ጥያቄም ሆነ አስተያየት መሠንዘር አልቻለችም፡፡ መኪናዋን
በመጨረሻው ፍጥነት እያስፈተለከ ነው፡፡
ያበደም መሰላት፤ ‹‹ሁለታችንንም ወደ ግብዓተ መሬታችን ይዞን እየተጓዘ ነው እንዴ?››ስትል አሰበች…በጣም ፈራች፡፡...

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍107103🔥3👏3🤔2😁1
የመጋባትና የመደንዘዙ ተራ የሁሴን ሆነ፡፡ በዝግታ ከተቀመጠበት ተነሳ ...

‹‹ሚስጢር ማለት አንቺ ነሽ?››

‹‹አዎ፡፡ ሚስጢር ትንግርትም እኔው ነኝ፡፡››

‹‹ታዲያ ያቺ ጠይም ማን ነች? አሮጊቷስ?››

‹‹በተደጋጋሚ ቀን ያየሀቸው አምስቱም ሴት እኔ ያሠማራኋቸው ጓደኞቼ ናቸው››ጎትቶ ከተቀመጠችበት አስነሳትና ጭምቅ አድርጎ አቀፋት፤ ከንፈሯን... ጉንጯን....ግንባሯን…. እያፈራረቀ ሳማት፤ እሷም አፀፋውን መለሠችለት፡፡

ወደ ጆሮው ተጠግታ በሹክሹክታ‹‹ትናንት ጀምሬ ያልጨረስኩልህ ሦስተኛው የፍቅር ታሪኬ ይሄ ነው፡፡›› አለችው ፡፡

‹‹ሦስተኛው ብቻ ሳይሆን የመጨረሻም ይሆናል፡፡››ብሎ መለሠላት፡፡

እረጅም የእፎይታና የእርካታ ትንፋሽ እየተነፈሰች << አሜን ያድርግልኝ ፡፡›› አለች፡፡....

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏8335👍29🤩9🥰1😁1🎉1
ተፈናጣበታለች፡፡

ልዩ የእራት ግብዣው በሚያምር መስተንግዶ እየተካሄደ ነው፡፡ሁሉም እርስ በእርሱ እየተጫወቱ በመመገብ ላይ ናቸው፡፡

ወደ ማጠናቀቁ ሲደርሱ <<የዛሬ ዓመት ደግሞ ከልጃችሁ የክርስትና ድግስ ጋር አንድ ላይ ለማክበር ያብቃን››ሲል መረቀ ሰሎሞን፡፡

‹‹እንደዛ ከሆነማ ጊዜ የለህም በለኛ፤ዛሬ ማታውኑ ልጅ ሰርቼ ማደር አለብኝ፡፡››ሲል መለሰ ሁሴን፡፡

‹‹አይደረግም..!! አንተ በሌለህበት ብቻዬን አርግዤማ ብቻዬን አልወልድም፡፡ትምህርትህን አጠናቀህ ከመጣህ በኃላ ያኔ ትሰራለህ፡፡ እንደዛ ምትፈልግ ከሆነ እስከዛሬ ምን አዘገየህ…? እንደ ጀግኖቹ ፈጠን አትልም ነበር?››አለችው ትንግርት ጎን ለጎን ወደተቀመጡት ባልና ሚስቶች አሻግራ እያየች፡፡

ሰሎሞን ደረቱን ነፋ በማድረግ ንግግሩን ቀጠለ‹‹ወይ እህቴን… በፊቱኑም ምርጫሽን አበላሽተሸ እኮ ነው፡፡የሚያወራ ሁሉ የሚሰራ መስሎሽ፡፡››ቤቱ ሙሉ በተረቡ አስካካ::

‹‹ሰውዬ ይሄ እኮ የእኔ በዓል ነው፡፡ሙገሳ፣ አድናቆት እና ምርቃት እንጂ ስድብ
አይገባኝም...አይደል ኤዱ?››አለ ወደ ድሮ ፍቅረኛው ድጋፍ ፍለጋ ዓይኖቹን እያንከራተተ ፡፡

‹‹አዎ..ሚስትህ እና ባሌ ሊወቅሱህ ከፈለጉ ቀድመው ነበር፤እራሳቸውስ እስከአሁን የት ነበሩ?ደግሞ ችግሩ የማን እንደሆነ በምን ታወቀ?››በማለት የሚፈልገውን ድጋፍ በአጥጋቢ ሁኔታ ሰጠችው፤ቤቱ በድጋሚ በሳቅ ፈረሰ፡፡

ሶስት ሰዓት ላይ ሁሴን ከመቀመጫው ተነሳና መናገር ጀመረ፡፡

የተከበራችሁ ጓደኛቼ እና የእለቱ የክብር እንግዶች....ተወዳጇ እህቴ ይህቺን የደስታ ቀን ተባብራችሁ ስላደመቃችሁልን በእኔም በባለቤቴም ስም አመሰግናለሁ፡፡ ሁላችሁም እንደምታውቁት ዋናው የአንደኛ ዓመት የጋብቻ በአላችንን ማክበር ቢሆንም በተጓዳኝም የእኔ ሽኝት ነው፡፡

ትንግርት በጣም አፈቅርሻለሁ፡፡አንቺን ካገኘሁ እለት ጀምሮ በህይወቴ እርጋታ እና እርካታ እንደሞላ ልነግርሽ እወዳለሁ፡፡ ቤቴንም፤ኑሮዬንም ነው ያሞቅሽልኝ፡፡ለዚህም እንደው በቃል ብቻ አመሰግናለሁ ከምልሽ
ትንሽ ስሜቴን ቢገልፅልኝ ብዬ ስጦታ አዘጋጅቼልሻለሁ፡፡›› በማለት ከኪሱ በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ አነስተኛ ስጦታ እጇ ላይ አስቀመጠ፡፡

‹‹ይፈታ..ይፈታ››ሁሉም አጉረመረሙ ....ትንግርት ፈታችው ፤ የእጅ ብራስሌት ነበር... አጠለቀችው፡፡ቤቱ አጨበጨበ፤እሷም በደስታ ተጥለቀለቀች፤ አቅፋ ከንፈሩን በረጅሙ ሳመችው፡፡

‹‹እኔም ስጦታ አለኝ›› ብላ ወደፎዚያ በመዞር.<< ፎዚ...የቅድሙን ዕቃ ታመጪልኝ?›› አለቻት፡፡

ፎዚያ ወደ መኝታ ቤት ተንደረደረችና 35×1ዐሴ.ሜ ስፋት ያለው የታሸገ የስዕል ፍሬም ይዛ መጣችና ለትንግርት አቀበለቻት፡፡

‹‹ውዴ ...ይሄ በእጆቼ የሳልኩት ስዕል ነው፤ይሄንን ያደረግኩት በምትሄድበት አብሬህ መሄድ ስለምፈልግ ነው፡፡››አለችው፡፡

‹‹ተስገብግቦ ከእጇቿ ነጠቀና ከፈተው፡፡ የእራሷን ስዕል ስላ ነው ሰጠችው፡፡ በሚወደው የፀጉር አሰራር፣በሚወደው አለባበስ፣በሚወደው ጫማ በአጠቃላይ እሱ ሙሉ በሙሉ እሷ ላይ የሚወዳቸውን ነገሮች አድምቃና አጉልታ ነበር የሳለችው፡፡ስዕሉን ለአስር ደቂቃ በፍዘት ተመለከተው፡፡

ጥበቃው አሰልችቷቸው‹‹አሳየን..አሳየን››ሲሉት አቀበላቸውና እሱም በተራው ወደራሱ ጎትቶ ከንፈሯን መጠጠው፡፡ትንግርት ቁጭ አለች... እሱ ንግግሩን አራዘመ ‹‹የእኔ ፍቅር ለዚህ ድንቅ ስጦታሽ አመሰግናለሁ፡፡ እንዳልሺው ብቻዬን አልሄድም ማለት ነው፡፡ይሄ ባንቺ የተሳለ ያንቺው ምስል አብሮኝ እስካለ ድረስ አንቺም ከእኔ ጋር ነሽ ማለት ነው፡፡ ስትናፍቂኝ አቅፌው ተኛለሁ፡፡በተረፈ ያው ከሶስት ቀን በኃላ እበራለሁ፡፡ምን አልባት ሁኔታዎች ከፈቀዱ በጣም ስለምትናፍቁኝ በየስድስት ወሩ እየመጣሁ ላያችሁ እሞክራለሁ፡፡ እስከዛው ግን ባለቤቴንና እህቴን አደራ ተንከባከቡልኝ ፡፡

ትንግርት ያው እንግዲህ የጋዜጣውን ስራ በተመለከተ የእኔን ቦታ ተክተሸ በኃላፊነት ትመሪልኛለሽ፡፡ከእነዚህ ከምታውቂያቸውና ከምትወጂያቸው ጋዜጠኞች ጋር መስራት ብዙም እንደማይከብድሽ እተማመናለሁ፡፡ በተረፈ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ፡፡ እወዳችኋለሁ፡፡››ብሎ ንግግሩን አጠናቀቀ፡፡

ቀጥሎ ድንገት የፍኖተ-ጥበብ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ኤልያስ ከመቀመጫው ተነሳና ሁለት እጆቹን እያማታ አጨበጨባ፡፡የሁሉንም ትኩረት ለማግኘት ነው እንደዛ ያደረገው፡፡

‹‹ቀጥል እየሰማንህ ነው››አለው ሁሴን
ከኪሱ አንድ ወረቀት እና ማጣበቂያ ኡሁ አወጣና ወደ ግድግዳው ተንቀሳቀሰ፡፡ ከጋብቻው መልካም ምኞት መግለጫ ስር ለጠፈው፡፡

መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም ለሁሉም በደንብ ይነበባል

‹‹ብልጥ ዝንጀሮ በሞኝ ክምር(ድግስ)

‹‹ይሄ አባባል ግን በትክክል ነው የተፃፈው?››አንዱ ጋዜጠኛ ጠየቀ፡፡

‹‹ትክክል ሆነም አልሆነም ምን ለማለት ፈልገህ ነው ?››በመልዕክቱ ግራ የተጋባው ሁሴን ጠየቀ፡፡ለነገሩ ሁሌ በኤልያስ ነገረ ስራ ግራ እንደተጋባ ነው፡፡ነገሮቹ ሁሉ ድንገተኛና ከሚጠበቀው በተቃራኒ የሆኑ ናቸው፡፡

ላስረዳችሁ አይደል ፡፡እንግዲህ ይሄን ጉዳይ በህግና ደንቡ መሰረት ማድረግ ነበር ፍላጎቴ ፤ግን የሁሴን ድንገት ወደውጭ መሄድ ሀሳቤን ድንገት አስቀየረኝ ፡፡በዛ ላይ አሁን ካለው የኑሮ ግሽበት አንፃር እንዲህ አይነት ግብዣ ሲገኝ ለሁለት አላማ ብቻ ከመጠቀም ሶስተኛስ ምክንያት ፈጥረንለት ውጤት ተኮር ብናደርገው ለሀገራችን ብልፅግና ይጠቅማል ብዬ ነው፡፡››

‹‹ኧረ ማብራሪያውን ቁረጠውና ወደ ቁም ነገሩ ግባ››ትንግርት ነበረች ተናጋሪዋ፡፡

‹‹እኔ እና ፎዚያ ፍቅረኛሞች ነን....ልንጋባ ወስነናል፡፡››ድንገት አፈነዳው፡፡ቤቱ በአንዴ ዝም አለ...ፎዚያም ተቁለጨለጨች፡፡

‹‹ምነው ዝም አላችሁ?ፎዚ አረጋግጪላቸው እንጂ፡፡››በማለት የፍቅረኛውን እርዳታ ተማፀነ፡፡

‹‹አዎ..በጣ..ም ተፋቅረናል፡፡››አረጋገጠች ፡፡

‹‹እንኳን ደስ ያላችሁ..እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡›› ሁሉም ተራ በተራ እየተጠመጠመባቸው መልካም ምኞቱን ገለፀላቸው...ከሁሴን
በስተቀር፡፡እሱ እንደፈዘዘ ነው፤ፍፅም ያልጠበቀው እና ያልገመተው ነገር ነው፡፡

ሁሉ ነገር ከረገበ በኃላ ኤልያስ እንደቆመ >>> ሁሴን የሆነ ነገር በለና ?» አለው ዝምታው ግራ አጋብቶት፡፡ ...

‹‹ምን ልበላችሁ?››

‹‹እኔ እንጃ...ምነው ቅር ያለህ ነገር አለ?››

‹‹አዎ….ለመሆኑ የሀይማኖቱን ነገር አስባችሁበታል?››

በተራው ኤልያስ ዝም አለ፡፡ ግራ ገባው፡፡ፈፅሞ በዚህ ጉዳይ ላይ አስበውትም ሆነ ተነጋግረውበት አያውቁም፤ከኤልያስ በላይ ደግሞ ፎዚያ ደነገጠች፡፡

‹‹ምን ችግር አለው? አንተና ትንግርትስ ተጋብታችሁ አይደል?›› ሰሎሞን ነበር መሀከል ገብቶ አስታራቂ የመሰለውን ሀሳብ የሰነዘረው::
‹‹ሁለቱም ለየቅል ነው..እኔ እና ትንግርት ቀድሞውንም ለስም እንጂ ሀይማኖት ነበረን ማለት ይከብዳል፡፡እነሱ ግን ፎዚያ እንደምታውቃት ለሀይማኖቷ በጣም ቀናኢ ነች፤ኤልያስ ደግሞ የቄስ ልጅ ነው፤አባትዬው በዚሁ በአዲስአበባ ትልቅ ደብር የሚያስተዳድሩ ናቸው... ደግማችሁ በእርጋታ ብታስቡበት፡፡››በማለት ሀሳብን ዘጋ፡፡ኤልያስ በዝምታና በጨፈገገ ስሜት ወደ መቀመጫው ተመለሰ፡፡ፎዚያ በተቀመጠችበት ድንዝዝ አላት፡፡.....

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍10815👏3
ምን እንደምትመልስለት በማሰላሰል ላይ ሳለች ከጃኬት ኪሱ ውስጥ አንድ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተፃፈ የፍልስፍና መፅሀፍ አውጥቶ ከፈተና ማንበብ ቀጠለ‹‹ምን አይነት ጉረኛ ገጠመኝ?››አለች በልቧ ‹‹አሁን ደግሞ ሀብታም ብቻ ሳልሆን ምሁርም ነኝ ለማለት ነው አይደል..?ሁለት ገፅ ሳያነብ መጽሀፉን መልሶ ከድኖ መቀባጠሩን መጀመሩ አይቀርም፡፡›› ከራሷ ጋር ተወራረደች፡፡አዳሚ ቱሉ ሲደርሱ ከሀያ ገጾች በላይ አንብቧል ፡፡ ገረሜታዋ ጨመረ፤ ተደነቀችበት፤ተቁነጠነጠች፡፡ከዚህ በፊት ተሰምቷት የማያውቀውን የመረሳትና የመገፋት ስሜት ተሰማት፡፡እንዲያወራት... ስለማንነቱ እንዲነግራት ተመኘች፡፡እሱ ንባቡን ቀጥሏል፡፡አርሲ ነገሌ ሲደርሱም ዓኖቹን ከመጽሀፉ አልነቀልም ነበር፡፡

‹‹ይህቺ ከተማ ምንድነች?››አለችው፤የከተማዋን ማንነት ሳታውቅ ቀርታ ሳይሆነ እንዲያወራት ስለፈለገች ነበር ጥያቄውን የሰነዘረችው፡፡

ከንባቡ አይኑን ሳይነቅል‹‹ሲኦል ሳትሆን አትቀርም››አላት ፡፡

‹‹ወይኔ ምን አለበት አሁን አንድ ሺህ ብር ባገኝ፤ይሄው ሁለት መቶው ያበደርከኝ ነው ፤ይሄ ስምንት መቶ ብሩ ደግሞ ሻይ ጠጣበት ብዬ አፍንጫው ላይ ወረውርለትና እንዳበሸቀኝ አበሽቀው ነበር፡፡››ስትል በውስጧ ድምፅ አልባ ማጉረምረም አጉረመረመች፡፡ የሆነ ሀሳብ መጣላት፡፡ በቃ ቀልቡን ከገባበት መመሰጥ እንዴት መንጥቃ እንደምትዋጣው ተገለጸላት፡፡ እስካሁንም እንዴት እንዳላሰበችው ደነቃት፡፡

‹‹ባይ ዘዌይ ዲያስፖራ ነኝ ፡፡በቅርብ ነው ከአሜሪካ የመጣሁት፡፡››ከጎሬው የምታወጣበትን ወጥመዷን ወረወረች፡፡

ካቀረቀረበት ንባቡ ቀና ብሎ ፊት ለፊት አያት፡፡ ፈገገች ፡፡እንደገመተችው ኢትጵያውያን ከአሜሪካ ለመጣ ሰው ያላቸው ክብርና ጉጉት የሚገርም አይነት ነው፡፡አንድ ሰው ከገነት ነው የመጣሁት ከሚል ይልቅ ከአሜሪካ ነው የመጣሁት ቢል የበለጠ ቀልብ ይስባል፡፡ ከአሜሪካ ከመጣ ጓደኛዬ ጋር ስዝናና ቆየሁ ብሎ ማውራት እንኳን ትልቅ ዝናን ያስገኛል፡፡ ይሄንን ስነ ልቦና ስለምታውቅ ነው የልጁን ቀልብ ለመሳብ ለሳእታት ያልተሳካላትን በዚህ ዘዴ ለሞከር የወሰነችው፡፡

<< እና ምን ይጠበስ? ››አላትና ወደ ንባቡ ተመለሰ ፡፡በጣም ተደነቀች፡፡በእፍረት ኩምሽሽ ነው ያለችው፡፡ምን አይነት ሰው ነው ?:: እንኳን ኢትዬጵያ አሜሪካም እንዲህ አይነት ሰው አጋጥሟት አያውቅም..‹‹ይሄን ሰውዬማ በደንብ ማወቅ አለብኝ፡፡›› ለራሷ ቃል ገባች፡፡

ሻሸመኔን አለፉ..ሀዋሳ ገቡ..ጥቁር ውሀ አካባቢ ሲደርሱ መጽሀፉን ሊጨርስ አስር ገፅ ያህል ብቻ ቀርቶት ነበር፡፡

መነኻሪያ ከመድረሳቸው በፊት አንድ አሮጊት ‹‹ወራጅ›› አሉ፡፡ሚኒባሷ ሃምሳ ሜትር አካባቢ ከተጓዘች በኃላ ቆመች፤አሮጊቷ ሲወርዱ አብሻቂው ወጣትም ድንገት ተነሳ…‹‹እንዴ ልትወርድ ነው ?>>

‹‹አዎ... እዚህ አካባቢ ጉዳይ አለኝ >>አላት፡፡

‹‹እደውልልሀለው››

‹‹እሺ››ብሏት መውረድ ጀመረ…፡፡ተሳፋሪው ምን ይለኛል ብላ ሳትጨነቅ‹‹ግን ስምህ ማን ነበር?››ብላ ጠየቀችው ፡፡

‹‹ደስ ባለሽ ስም ጥሪኝ፤ችግር የለውም ››ብሏት መንገዱን ቀጠለ፡፡ሚኒባሷም ተንቀሳቀሰች፡፡መነኻሪያ ወረደችና ኮንትራት ባጃጅ ይዛ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቷ ወደሚገኝበት ስፍራ ሄደች ፡፡ሁሉም ችግሯ ወዲያው ተፈታላት፡፡ የሚስፈልጋትን ያህል ብር ከመስሪያ ቤቷ ተሰጣት፡፡ለጊዜው የምትጠቀምበት ስልክም ከነሲሙ ገዛች፡፡
ከዛም ወደ ተያዘላት መኝታ ክፍል ገብታ ሻወር ከወሳሰደችና ከተረጋጋገች በኃለ ለዛ ብሽቅ ልጅ ደውላለት ብሩን ልትሰጠውና ልታወራው ፈለገች፡፡ ቦርሳዋን አወጣችና ስልክ ቁጥሩን የጻፈበትን ወረቀት አወጣች እና ገልጣ አየችው፡፡ ደነገጠች..ሸውዷታል፡፡ቁጥር የለውም... ጹሁፍ ነው፡፡

<< ተመሳሳይ ችግር የገጠመው ሰው ስታገኚ ለእሱ አድርጊ...የዛኔ ለእኔ ብድርሽን እደከፈልሽ ይቆጠራል፡፡ >>

ይላል ወረቀቱ ላይ የተወላት ፅሁፍ፡፡‹‹ብሽቅ›› አለች፡፡

‹‹እንዴት በወቅቱ ገልጬ ሳላነበው ?›› በራሷ ላይ ተበሳጨች፡፡እርግጥ አጣጥፎ ነበር የሰጣት ፤ቢሆንም ገልጣ ማረጋገጥ ነበረባት፡፡ ለሊቱን ሙሉ በተኛችበት ጊዜያቶች እንኳን ልትረሳው አልቻለችም፡፡

ለሦስት ቀን የተካሄደው ሴሚናር ተጠናቀቀ፡፡

በሀዋሳ ቆይታዋ ላይ ሌላ ሦስት ቀን ጨምራ

ቅ/መስሪያ ቤቱ በመደበላት መኪና በመጠቀም የሀዋሳን ከተማ ጎዳናዎች

በመዞር ብታስስም ልጁ ግን ሊገኝ አልቻለም፡፡

ይበልጥ በፈለገችው ቁጥር ይበልጥ እየናፈቃት መጣ፡፡ ለአመታት አብሯት የኖረ
በጣም የቅርቧ ሰው ድንገት ተሰውሮ የጠፋባት ያህል ነው አዕምሮዋ እርብሽብሽ
ያለባት፡፡ምርጫ ስላልነበራት በቅሬታ እንደተሞላች ወደ አዲስአባዋ ተመለሰች፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች 5 እና ከዛ በላይ #ሰብስክራይብ ካገኘን ነገ ሁለት ክፍል ይለቀቃል። ቃላችንን አስጠብቁን👍

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍70👏86😁1
#ቅብጥብጡ_ውሻ

የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡

በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡

የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡

የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን አንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡

ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡

ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . .

ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡

ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!
   
🔘በዶ/ር እዮብ ማሞ🔘

         
ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን እንጂ ትላንት
5 ሰው ብለን ማንም #ሰብስክራይብ አላደረገም እስከ ማታ 5 ሰው #እጠብቃለሁ

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍745🥰4
ልጆቹን ከአባታቸው ጋር አገናኝቶ ለጊዜውም
ቢሆን እንዲሻላቸው ማድረግ፤በዘላቂነትም
መሆን ያለበትን ነገር ከአባትዬውም ሆነ
ከኤደን ጋር ተነጋግሮ ሁኔታዎችን ለማስተካከል
አቀደ፡፡..ቢያንስ የቅዳሜና የእሁድ የእረፍት ቀናቸውን አባታቸው ጋር ማሰለፍ እንዳለባቸውና ይሄንንም ማስተካከል የእሱ ኃላፊነት እንደሆነ ወሰነ፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
ሰብስክረይብ ያላደረጋችሁ በማድረግ ….ያደረጋችሁ ደግሞ ሌሎች እዲያደርጉ በማስተባበር ተባበሩኝ… አመሰግናለሁ፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍668😢4
#ትንግርት


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሀዋሳ

ሁሴን ወደ ሲዩዘርላንድ ከበረረ ሀያ ቀን አልፎታል፡፡ያለፉትን ሀያ ቀናት የእሱንም ቦታ ተክታ ለስራው ከላይ እታች በመሯሯጥ ብታሳልፍም ከናፍቆት ግን ማምለጥ አልቻለችም፡፡አዎ ሁሴን ባልተለመደ መልኩ በጣም ናፍቋታል፡፡እራሷን በሌላ ሰው ህልውና ላይ ይሄን ያህል መለጠፍ አትፈልግም ነበር፤ምንም ቋሚና ዘላቂ ነገር እንደሌለ ህይወት ደጋግማ አስተምራታለች፡፡የእኔ የምትለው ነገር ሁሉ አንድ ቀን በሰላምም ሆነ በአደጋ ብቻ በሆነ ምክንያት እንደሚለያትና ለዛም ዝግጁ ሆና መጠበቅ እንዳለባት የዘወትር መፈክሯና መመሪያዋ ነበር፡፡አሁን ግን መልሳ ደከመች፤እናም ባሏ ናፈቃት፡፡እለቱ ሰንበት ስለሆነ የቤቷ ሳሎን ሶፋ ላይ ጋደም ብላ ቴሌቪዢን እየተመለከተች ነው፡፡
አይድል ፕሮግራም..በሀዋሳ የሚካሄድ የማጣሪያ ውድድር እየተመለከተች ነው፡፡

በአብረሀም ወልዴ የሚመራው የዳኞች ቡድን
የዳኝነት ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ተወዳዳሪዎች በቅደም ተከተል ወደ መድረክ እየወጡ የተዘጋጁበትን ዘፈን በመዝፈን ተፈጥሮ
የቸረቻቸውን ድምጽና በጥረታቸው ያደበሩትን
ችሎታ በማዋሀድ ዳኞቹንም ሆነ ተመልካቾችን
በማሳመን ለአዲስአበባው ውድድር ለማለፍ ይጥራሉ፡፡ጥቂቶች ይሳካላቸዋል ፤ሌሎቹ ደግሞ አንገት ደፍተውና ፈዘው ከመድረኩ
ይሰናበታሉ፡፡ትንግርት ሁሌ ይህን ፕሮግራም ስታይ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የሚሰማት፡፡

ዘና የሚያደርገት እንዳለ ሁሉ የሚያሳዝኗትም
ተወዳዳሪዎች አሉ፡፡ከችሎታቸው በላይ
ጉጉታቸው የናረ፣ብዙ ተስፋ አድርገው መጥተው በዳኞቹ ቁርጥ ያለ ሞያዊ
አስተያየት ሽምቅቅ የሚሉ ወጣት ጨቅላዎች፤ ያሳዝኗታል፡፡ችሎታው እያላቸውም ፍራቻቸውን ብቻ ማሸነፍ ተስኗቸው ያላቸውን ነገር መግለጽ ባለመቻላቸው አጉል የሚሆኑም አሉ፤እነሱም ያሳዝኗታል፡፡

...አሁን ግን እያየች ያለቻው ድንቅና የሚያስደምም ችሎታ ነው፡፡አስር ሁለት አመት የማይበልጣቸው ሁለት ሴት ልጆች ናቸው የሚታዩት፡፡አንደኛዋ ጊታሯን ይዛ የተዘጋጀላት መቀመጫ ላይ ተቀመጠችና በጣቶቿ የጊታሩን ክሮች በመነካካት ፈታተሸች፤ሌለኛዋ ከፊት ለፊቷ በሜትሮች ርቀት ማይኩን ይዛ ::

አብረሀም ወልዴ መናገር ጀመረ....

‹‹እሺ እንኳን በሰላም መጣችሁ እያልኩ እራሳችሁን እንድታስተዋውቁ ዕድሉን ልስጣችሁ ፡፡››

‹‹ስሜ ሀሊማ ታዲዬስ ይባላል፡፡ የምጫወትላችሁ የተፈራ ካሳን ‹አባብዬ› የሚለውን ዘፈን ነው፡፡››

‹‹አሪፍ ነው፡፡ባለጊታሯስ ስምሽ ማነው ?››

‹‹ስሜ ሄለን ታዲዬስ ይባላል፤ጊታርና ፒያኖ ተጨዋች ነኝ።

<<እህት አማቾች ናችሁ ?››አረጋኸኝ መሀከል ገብቶ ጠየቀ፡፡

‹‹አዎ እህቴ ናት፡፡››

ይሄ ሁሉ ሲሆን ትንግርት ስትከታተል የነበረው በግማሽ ልቧ ነበር፡፡እህትማማቾች ነን ሲሉ ግን ትንሽ ግር አላት፡፡በእኩል ዕድሜ ላይ ናቸው፡፡የትኛዋ ታላቅ የትኛዋ ደግሞ ታናሽ ትሆን? ስትል እራሷን ጥያቄ ጠየቀች፡፡ ደግሞ ምናቸውም አይመሳሰልም <<የእናት ሆድ ዥንጉርጉር›› ይባል የለ ብላ ለራሷ መልስ ሰጠች፡፡

‹‹በሉ ቀጥሉ..መልካም ዕድል፡፡››ከዳኞቹ ፍቃድ አገኙ፡፡

ሄለን እነዛ ቀጫጭንና ለጋ ጣቶቾን የጊታሩ ክሮች ላይ ማርመስመስ ጀመረች ፡፡ የሙዚቃ መሳሪያውን ምት ተከትሎ የሀሊማ ተስረቅራቂና ማራኪ ድምጽ ይንቆረቆር ጀመር፡፡ በአዳራሹ የሞላው ተመልካች ብቻ ሳይሆን በየቤቱ በቲቪ ፕሮግራሙን የሚከታተለው ህዝብም ፀጥ የሚያሰኝ አደንዛዥ ድምጽ ነበር፡፡በዚህ ዕድሜ በእንዲህ አይነት ችሎታ? እንዴት ነው በዚህ ዕድሜ የሙዚቃ መሳሪያን ስልተ-ምት ጠብቆ ስይደናገሩና ሳይንሸራተቱ በዚህ ልክ መዝፈን የቻሉት?፡፡

ዳኞቹ ሳይቀር አፋቸውን ከፈቱ፡፡ደግሞ በሙዚቃው ሁለቱም ጉንጮች ላይ እንባ እየተንጠባጠበ ነው፡፡ሲጨርሱ የአዳራሹ ሰው ሁሉ አረንጎዴ ካርዱን እያወዛወዘ ከመቀመጨው ተነሳ፡፡ደኞቹም እያጨበጨቡ ቆሙ .. መድረክ ድረስ በመሄድ በየተራ አቅፈው ሳሟቸው፡፡

አስተያየት መስጠት ተጀመረ..የመጀመሪያው ዳኛ

‹‹በእውነት ሀዋሳ እናንተን የመሰሉ ባለድንቅ ችሎታ ሙዚቀኞችን ስላፈራች እድለኛ ነች፡፡

እኛም እዚህ መጥተን እናንተን ስላገኘን እድለኞች ነን፤በቃ ልዩ ናችሁ፡፡››

ሁለተኛው ዳኛ…..

‹‹ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ሙዚቃው ከህይወታችሁ ጋር የሚያይዘው ጉዳይ አለ? ሁለታችሁም ስታለቅሱ ነበር፡፡እኔንም አስለቅሳችሁኛል፡፡ምከንያት ነበራችሁ?››

ሀሊማ መናገር ጀመረች‹‹አዎ ሁለታቸንም አባታችንን በጣም እንወደዋለን፡፡እርግጥ ሁሉም ሰው አባቱን በጣም ይወዳል፡፡እመኑን የእኛ አባት ግን ልዩ ሰው ነው፡፡›› አዳራሹ በሳቅና በጭብጨባ ተናጋ፡፡

ሄለን ቀጠለች‹‹ታዲያ አንተ አባታችን ባትሆን ኖሮ እኛ ዛሬ እንዲህ አምሮብን ሙዚቃ እየተጫወትን እንዲህ አዳራሽ ሙሉ ህዝብ እያጨበጨበልን አንታይም ነበር.፡፡ምክንያም እድሉም ጊዜውም አይኖረንም ነበር፡፡አዎ አባት ባትሆነን ኖሮ ይሄኔ ሁለታችንም አሞራ ገደል
አካባቢ ከሚገኝ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ተበላሽቶ የተጣለ ምግብ ከቆሻሻው በመለየት በመመገብ ላይ ነበርን፡፡…እና ከእንደገና ስለፈጠርከን አመሰግናለሁ ...ታዲ እንወድሀለን፡፡››

ዳኞቹም ታዳሚዎቹም ከልጆቹ ችሎታ በላይ በንግግራቸው ድንግርግር እንዳሉ ፊታቸውን በመመልከት ማወቅ ይቻላል፡፡

‹‹እባክህ አቶ ታዲዬስ እዚህ አዳራሽ ውስጥ ካላህ ወደ መድረክ ወጥተህ አንድ ነገር በለን››ከዳኞቹ መካከል አንድ ተናገረ፡፡ በአዳራሹ ያላው ታዳሚ እርስ በርሱ ዞር ዞር በማለት መተያየት ጀመረ፡፡ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ መድረክ የሚወጣ ሰው ለመመልከት፡፡

‹‹ታዲ ና እንጂ››ሄለን ከመድረክ ተማፀነች፡፡

የሁለት ልጆች አባት ሳይሆን ተደባበዳቢ ቦዴ ጋርድ የሚመስል ጠይም ደንዳና ወጣት ወደ መድረኩ ወጣና ሁለቱንም ልጆቹን አቅፎ
ጉንጮቻቸውን ከሳመ በኃላ ማይኩን ተቀብሎ መናገር ጀመረ፡፡‹‹ታዴዬስ ማለት እኔ ነኝ፡፡ልጆቼ

ስለእኔ ያሉት ትንሽ ተጋኗል፡፡እውነታው በተቃራኒው ነው፡፡እነሱ ልጆቼ በመሆናቸው
በአሁኑ ወቅት በአለም በጣም እድለኛው ሰው
እኔ ነኝ፡፡ምን አልባት ችሎታቸውን አይታችሁ
ስታጨበጭቡላቸው ነበር፡፡ግን እመኑኝ መድረክ የመጀመሪያ ቀናቸው ስለሆነ የችሎታቸውን ግማሽም አላሳዮችሁም...እናም
ሁላችሁም እዚህ አዳራሹን የሞላችሁ ሁሉ ብትቀኑብኝ አይገርመኝም፡፡ምክንያቱም እኔ የእነዚህ ዕንቁ ልጆች አባት ነኝ፡፡አመሰግናለሁ፡፡>> ብሎ ወረደ፡፡ፕሮግራሙ ቢያልቅም ትንግርት
ስለልጆቹም ሆነ ስለአባትዬው ልትረሳ
አልቻለችም፡፡የሆነ ያልተለመደ ነገር ነው
የሆነባት፡፡<<አባታችን ባትሆን የቆሻሻ ገንዳ ላይ
ምግብ እንለቃቅም ነበር›› ሲሉ ምን ማለታቸው ነው?ግን የእውነት አባታቸው ነው ?

አልመሰላትም፡፡እንዴት አድርጎ ቢያሳድጋቸው
ነው በዚህ መጠን ሊወዱት የቻሉት?እውነትም
እሱ እንዳለው የሚቀናበት አባት ነው ? አለችና ቲቪውን አጥፍታ አየር ለመቀበል ቤቷን ለቃ ወደ ውጭ ወጣች፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች እያደረጋቹ አደለም በየቀኑ ለመልቀቅ እየሞከርኩ ነው እናንተም ማበረታታችሁን ቀጥሉ አመሰጎናለሁ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12213👏3🔥1
‹‹እንዴ ይሄው፤ አታውቂውም እንዴ?›› በማለት ባላዋቂነቷ ሳቀችባት፡፡ ስለ እዚህ ልጅ ይበልጥ ለማወቅ በጣረች ቁጥር እየራቀባት መጣ‹‹ስንት እህቶች አሉሽ?››

<<አራት>>

‹‹ወንድሞችስ››

«አንድ»

<<እናታችሁስ>>

<< እናት የለንም፤ የሁላችንም ሞተዋል፡፡››
በዚህ ጊዜ አሮጊቷ በትሪ ሙሉ እንጀራ ቆልለው
ልሙጥ ሽሮ በላዩ ላይ ፈሰስ አድርገው ይዘው
በመምጣት መሀከል ላይ አስቀመጡ፡፡ልጆቹ
መብላት ጀመሩ ፡፡ እሷም ልክ እንደነሱ ለራሷም እየጎረሰች እነሱንም እያጎረሰች ተመሳሰለቻቸው፡፡ ያሮጊቷ ሽሮ እንደሚታየው
አይደለም፤ልዩ ጣዕም አለው፡፡ ከአስር አመት
በፊት የሞቱትን አያቷን አስታወሳት፡፡ እሳቸው
ነበሩ እንዲ አይነት ሽሮ ያበሏት የነበሩት፤ ከዛ
በኃላ ግን በአጋጣሚ እንኳን እንደዚህ አይነት ምግብ አግኝታ አታውቅም፡፡ ሆቴል
ከምትበላው ምግብ ጋር ሲነፃፀር ልዩነቱ የትየለሌ ቢሆንም ለእሷ ግን መሰጣት፡፡
ከጨረሱ በኃላ የምግብ ሂሳቡን ልትከፍል ስትል ቀድሟት ከፈለ ፡፡ስለፈራችው ብዙ
አልተከራከረችውም ፡፡ ከምግብ ቤቱ ወጡ…፡፡

‹‹ጨለማው ያስፈራል ልጆቹን ላስገባና እሸኝሻለሁ፡፡››

‹‹እሺ ››ብላ ተከለተለችው፡፡እንደቅድሙ ግን ከአጥሩ ውጭ ቆማ ልትጠብቀው
አልፈለገችም ፡፡ከልጆቹ ጋር ተጋፍታ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ግቢው ሰፊ ነው፡፡ አምስት ሰርቪስ ቤቶችና አንድ በጣም ዘመናዊ የሆነ የተንጣለለ ቪላ ቤት አለ፡፡ ከሰርቪሶቹ ውስጥ አንዱን ተከራይቶ እንደሚኖር ገመተች፡፡ልጆቹ ግን ወደ ትልቁ ቤት እየተሯሯጡ ገቡ፡፡በረንዳ ላይ ሲደርሱ ቆመና << እንግዳዋን ሸኝቼያት መጣሁ እግራችሁን እየታጠባችሁ ጠብቁኝ›› ብሎ ፊቱን ሲያዞር እሷ ከህፃናቱ ጋር የቤቱን በራፍ አልፋ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ ቤቱ ከስምንት በላይ ክፍሎች ከሰፊ ሳሎን ጋር ከነ ሙሉ ቤት ዕቃው አለው፡፡ ረጅሙ ሶፋ ላይ አንድ የአስር አመት ልጅ ፎጣ ለብሳ ተኝታለች፡፡

‹‹ቅር ካላለህ ትንሽ ብቆይ? ››አለችው፡፡

‹‹በንዴት ፊቱን እንዳጠቆረ ምንም ሳይመልስላት አልፎት ወደ አንደኛው ክፍል ሄደና ከፍቶ ገብቶ ዘጋው፡፡መኝታ ቤቱ እንደሆነ ገመተች፡፡

እሷም በቀስታ እርምጃ ወደ ተኛችው ልጅ በመሄድ ከጎኗ ሶፋው ላይ ተቀመጠች፡፡

‹‹ስምሽ ማነው?››

«ሠላም»

‹‹ሠላም ማን?››ተመሳሳይ መልስ መለሰችላት፡፡

‹‹ምንሽን ነው የሚያምሽ?››

‹‹እግሬን፡፡››

‹‹እኔ ዶክተር ነኝ፤ልይልሽ?››

‹‹እሺ›› ብላ ፈቀደችላት፡፡ቀስ ብላ የለበሰችውን ብርድ ልብስ ገልጣ ስታይ ዝግንን አላት፡፡ የልጅቷ ቀኝ እግር ጥምዝዝ ብሎ እንዳልሆነ ሆኗል ፡፡ ጣቶቿ አቅጣጫቸውን ለውጠው በተቃራኒው ናቸው ፡፡ግን አዲስ ጉዳት አይደለም፡፡እንደተጠማዘዘ የዳነና የቆየ ነው፡፡

‹‹ምን ሆነሽ ነው ሰላም?››

‹‹ልጅ ሆኜ አባቴ ነው እንዲህ ያደረገኝ፡፡››

ደነገጠች

‹‹ታዲዬስ ነው እንዲህ ያደረገሽ?››

‹‹ኧረ አይደለም ..አይደለም>>
ልጅቷ ተንገፈገፈች፡፡

‹‹አይ አባቴ ስላልሺኝ እኮ ነው፡፡››

‹‹ታዲያ ያ ክፉውን የድሮውን አባቴን ማለቴ ነዋ፡፡ሊለምንብኝ ነው እንዲህ ያበለሻሸኝ፡፡አሁን ግን የለም ታስሯል..ታዲ ነው ያሳሰረው፡፡››

‹‹አሁን ታዲያ እንዴት አመመሽ..አልዳነልሽም ነበር?>>

‹‹አይ ድኖልኛል ...ግን ሰሞኑን ወለም ስላለኝ ነው ህመሙ የተነሳብኝ፡፡››

‹‹እኔ ዶክተር ስለሆንኩ ነገ መድሀኒት ይዤልሽ መጣና ትድኚያለሽ እሺ፡፡››
‹‹ታዲ እኮ ሀኪም ቤት ወስዶኝ ነበር.፡፡ መድሀኒትም ተሰጥቶኛል፡፡››

‹‹አይ ጥሩ ነው››ብላ ትኩረቷን ወደ ሌሎቹ ልጆች ስትመለስ ተለቅ ተለቅ ያሉት የትናንሾቹን እግር እያጠቡ ተመለከተች፡፡

‹‹አንቺ የታዲዬስ ምኑ ነሽ?›› ጠየቀቻት ሰላም፡፡

‹‹ጓደኛው፡፡››

<<ጓደኛ እኮ የለውም፤አንቺን ከየት አገኘሽ?››

‹‹ብቻውን ነው እንዴ የሚኖረው?››ሚስት የለውም ወይ ለሚለው የውስጥ ጥያቄዋ መልስ ለማግኘት የተሰነዘረ ጥያቄ ነው፡፡

‹‹አይ አይደለም፤ከእኛ ጋር ነው ሚኖረው፡፡ ብታይ በጣም ነው የሚወደን ፡፡እኛም ውድድ ነው ምናደርገው፡፡››

ወሬዋን ሳትጨርስላት ታዲዬስ ከተከተተበት ክፍል ወጣ፡፡ ወደ ቴሌቨዥኑ ሄደና የህፃናት የካርቶን ፊልም ከፈተ ‹‹ፊልም እያያችሁ ጠብቁኝ ሸኚቼያት ልምጣ፡፡›› ሲላቸው ሁሉም በአንድነት ‹‹እሺ ታዲዬ›› አሉት ፡፡ ከተቀመጠችበት ፍራሽ ተነሳችና ሠላምን ግንባሯን ስማት ሌሎቹን ጉንጫቸውን በመሳም ተሰናብታቸው ወጣች፡፡የውጭ በራፉን ከፍተው እንደወጡ‹‹ታድለህ›› አለችው ምን ብላ ከእሱ ጋር ወሬ እንደምትጀምር ግራ ገብቷት፡፡

‹‹ለምኑ?>>

‹‹ልጆችህ በጣም ይወዱሀል፡፡››

‹‹እኔም በጣም እወዳቸዋለሁ፡፡››

‹‹ግን እነዚህን ሁሉ ህፃናት ያለእናት ማሳደግ በጣም አይከብድም?››

‹‹አይከብድም፡፡ልጆቹ የተንደላቀቀ የቅምጥል ኑሮ የለመዱ አይደሉም፡፡ ይህቺን ህይወት ሀ ብለው ሲጀምሩ በጣም ከከፋ እና ከዘቀጠ የድህነት መንደር ውስጥ ነው ፡፡እኔ ከእዛ ትንሽ የተሻለ ነገር ነው የማደርግላቸው፡፡ከበረንዳ ማደር ወደ ቤት ውስጥ፤ ጆንያ ከመልበስ ብርድልብስ ወደ መልበስ፤ ትርፍራፊ እና የተጣለ ምግብ ከመመገብ ልሙጥ ሽሮም ቢሆን መብላት... ይሄው ነው ብዙ አይጠይቁኝም፤ይሄንን ማድረግ ደግሞ አይከብደኝም፡፡››

‹‹ግን እኮ ብቻህን ከምትቸገር ብዙ በህፃናት ላይ የሚሰሩ እርዳታ ድርጅቶች አሉ ፤ኮምንኬት ብታደርጋቸው ይረዱሀል፡፡››

‹‹እኔ እርዳታ አልፈልግም ፡፡እነሱ ከፈለጉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ህፃናት በየመንደሩ እና በየጎዳናው አሉ፡፡እነዚህ የእኔ ድርሻ ናቸው፡፡ ምን አልባት በምቾት እያኖርኳቸው መስሎ ያልተሰማሽ ከሆነ የተሳሳትሽ ይመስለኛል፡፡ እነዚህን ልጆች ግን ከምንም ነገር በላይ የሚርባቸው ፍቅር ነው፡፡ደግሞ እነዚህን ልጆች የማሳድጋቸው ደሀ ወይም ወላጅ አልባ
ስለሆኑ ከመሰለሽ ተሳስተሸል፡፡ሚጣ የኔ ልጅ ነች..ሌሎቹ አራቶቹ ደግሞ ወላጅ አልባ ብቻ ሳይሆኑ ጂኒዬሶችም ጭምር ናቸው..ለዛ ነው፡፡››

‹‹አልገባኝም፡፡››

‹‹ተይው በቀላሉ አይገባሽም፡፡››

እውነትም የዚህ ልጅ ነገር በቀላሉ አይገባም፡፡ ሊስትሮ እየሰሩ አምስት ልጆች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ ማሳደግ፤ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፡፡ወሬያቸውን እልባት ሳያበጁለት ዋናው አስፓልት ጋር ደርሱ፡፡

‹‹አሁን ታክሲ ወይም ባጃጅ ያዢና ወደ ሆቴልሽ ሂጂ፤እኔም ወደ ልጆቼ ልመለስ፡፡››

‹‹እሺ ስለ እራት ግብዣው አመሰግናለሁ፡፡ ልጆችህን ደግሞ በጣም ወድጄያቸዋለሁ፡፡ አንተም ጥሩ አባታቸው ብቻ ሳትሆን እናታቸውም ጭምር ነህ፡፡ደግሞ ቅድም የተናገርከው ልክ ነው ፤ ለሰው ልጅ ምግብ ብቻ ሳይሆን ፍቅርም መሰረታዊ ነገር ነው ፡፡›.ብላው ተሰናበተችው፡፡ እሱም ፊቱን አዙሮ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ታዲዬስን እንዳገኘችው ለአንድ ወር ሙሉ በአዕምሮዋ ሲጉላላ የከረመውን ዕንቆቅልሽ በቀላሉ የምትፈታ መስሏት ነበር የተደሰተችው፡፡አሁን ግን ሌላ ተጨማሪ እንቆቅልሽ ጨምራ በመብሰልሰል ወደ ክፍሏ ተመለሰች፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ #Share እያደረጋቹ ቤተሰቦች በቅንነት እባካቹ👍
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8811😁4👎1🥰1
#ወዳጄ_ሆይ!
🌟ሰውን የሚያስከብረው ጌጣጌጥ ነው ብለህ ጌጥ አታብዛ።የሰው ልጅ ክብሩ እውነተኛ ቃሉ እና ቅንነቱ መሆኑን ተረዳ ።

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟ተማረ ተመራመረ ብለህ ሰውን አታድንቀው ።ምንም ቢያውቅ ቢራቀቅ የሞቱን ቀን
አያውቅም ብለህ እዘንለት

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟የጋለ ምጣድ አትንካ ትቃጠላለህ።በስሜት ያበደን ሰው እይዛለሁ አትበል ታዝናለህ።

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟መንፈሳቸው እንደ ብረት ከቀዘቀዘባቸው ስዎች ጋር መኖር በጣም ከባድ ነው።አንተ እነርሱን
እስክታሞቅ እነርሱ አንተን ያበርዱሀልና ተጠንቀቅ ።

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟ፈረስ የፈለግበት ድረስ ያድርስህ እንጂ ፈረሱ የፈለገበት አትድረስ ። እንዲሁም ፍቅር
በሚመስል ነገር ስክረህ በከንቱዎች ምክር አትራመድ ።

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟መስማትና መስማማት ይለያያልና የስማህ ሁሉ የተስማማ መስሎህ አትዘናጋ ።
መስማማት ማድረግ ነውና የተስማማ ስውን በተግባር ታየዋለህ። ስዎች በጆሮ ሲስሙህ
ራሳቸውን ይነቀንቃሉ በልባቸው ሲያዳምጡህ ግን ከቀድሞ   ስህተታቸዉ ይርቃሉ ::ይለወጣሉ::
ተረድተውሀላ!!

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟ንግግርህ ፣አስተሳስብህን ፣ኑሮህን የምትመራበትን መመሪያህን ማሳያህ ነውና  ንግግርህን በማስተዋል አድርገው
አፍና በራፍ እኩል ይከፈታል።❤️

ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ ለ500 እኮ ትንሽ ነው የቀረው እባካቹ ቤተሰቦች
ሰብስክረይብ እያረጋቹ ያደረጋችሁ ደግሞ ሌሎች እዲያደርጉ #Share እያደረጋቹ አመሰግናለሁ፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍28👏186🥰1
ትናንት እራሱ ለእነሱ ይሄንን ስጦታ ስገዛ እግረ መንገዴን ለራሴም ሶስት ጥንድ ጫማዎች ገዝቼያለሁ.. እቤቴ ግን ቢያንስ ከመቶ በላይ ጫማዎች አሉኝ ፡፡በእነሱ ግን መርካት ባለመቻሌ እና ተጨማሪ ያስፈልገኛል ብዬ በማመኔ ነው የገዛሁት፤እንጂ ትርፍ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም፡፡አነዚህ አንድ ፍሬ ህፃናት ግን ከምንጠቀምበት በላይ አንሰበስብም ሲሉ እነሱን ተከራክሬ ለማሳመን ምን አይነት ሞራል ይኖረኛል?›› ብላ ንግግሯን ደመደመች፡፡

‹‹በቃ እኔ ላስታርቃችሁ ፤ አሁን እሷ ቅር እንዳይላት ያመጣችውን ስጦታ አመስግናችሁ ተቀበሏት፡፡ከዛ እሁድ ጓደኞቻችንን ልንጠይቃቸው ስንሔድ ለሚያስፈልጋቸው በእሷ ስም እንሰጣቸዋለን..ይሄ ያስማማናል?፡፡››

ሁሉም በፈገግታ ሀሳቡን ተቀበሉት፡፡የእሷን ጉንጭ በማመስገን እየሳሙ መልሰውላት የነበረውን ስጦታ ከያስቀመጡበት በመውሰድ ወደመቀመጫችው ተመለሱ፡፡

በዚህ ጊዜ ሳይንቲስቱ ሙሴ ከመሸገበት ክፍል ፈንደድ ፈንደድ እያለ መጥቶ ተቀላቀላቸው፡፡ታዲዬስ ወደራሱ ስቦ ግንባሩን ሳመው፡፡ዶክተር ሶፊያ የሙሴ ድርሻ የሆነውን ስጦታ ልትሰጠው ስትንቀሳቀስ‹‹ዶ/ር ተይው ….እሱን አስረድቶ ለማሳመን ለሊቱም አይበቃንም፡፡ይልቅ አሁን ሁላችንም ለእራት እንውጣ >> የሚል ሀሳብ አቀረበ፡፡›› ሁሉም በደስታ ተስማሙ፡፡

‹‹እስክትዘገጃጁ ታክሲ ጋር ልደውል?››

‹‹እኔ መኪና ይዤያለሁ›› አለችው ዶክተሯ፡፡

‹‹ውጭ የቆመችው መኪና ያንቺ ነች እንዴ?››

<<አዎ>>

ተያይዘው ወጡ፡፡መኪናው ውስጥ ገቡ፡፡ ውጪው በጣም ጨልሟል፡፡ ከተማዋ መብራት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል፡፡

‹‹መብራት ጠፍቷል እንዴ..?እናንተ ጋር ጄኔሬተር አለ ማለት ነው ? >> ስትል ጠየቀችው ዶክተር ሶፊያ እነሱ ቤት ለብቻው ተነጥሎ መብራት እየበራበት ሞሆኑ ገርሟት፡፡

‹‹እኛ እኮ ሀገሪቱን በመብራት አናስቸግርም ..እድሜ ለሙሴ እራሳችንን ችለናል፡፡››

<<እንዴት?>>

‹‹ሙሴ በራሱ ፈጠራ ከፀሀይ ሃይል የሚያመነጭ የራሳችንን በቂ ሀይል እንድናገኝ አድርጎናል..ነጻ ከወጣን አንድ አመት ሆነን፡፡ መብራት ኃይል የራሱን ቆጣሪ በብስጭት መሰለኝ ከቆረጠው ቆየ፡፡››

ወደ ግዙፉ ታዳጊ በአትኩሮት እየተመለከተች‹‹ይሄ ሙሴ ነው የሰራው ?>> ስትል ባለማመን ደግማ ጠየቀችው ፡፡

‹‹አዎ ይሄ የእኛ ሙሴ፡፡›› ፍርጥም ብሎ አረጋገጠላት

‹‹ለመሆኑ ስንት አመቱ ነው?››

‹‹አስር ወይም አስራ አንድ ይሆነዋል..ነገሮችን ለመስራት ግን ዋናው ዕድሜ አይመስለኝም ስጦታ እና ጥረት ካለ የእናት ጡት መጥባት ሳያቆሙ በፊትም ተዓምር መስራት ይቻላል፡፡››አለት፡፡

‹‹እሱስ እውነትህን ነው... በእንደ እናንተ አይነት የጉድ ቤት የማይቻል ነገር የለም !! እሺ አሁን ወዴት ልንዳ?›› አለችው፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የትልቅ ሆቴል ስም ነገራት፤ ወደዛው አሽከረከረች፡፡‹‹እዛ አካባቢ የሚገኝ ምግብ ቤት ለመጠቀም ፈልጎ ይሆናል፡፡›› ስትል ገመተች፡፡ደረሱ ፡፡መኪናውን ቦታ አሲይዛ አቆመች፡፡

ወርደው ግን ያመሩት እንደጠበቀችው ወደአነስተኛ ምግብ ቤት ሳይሆን ወደ ዋናው ባለኮከብ ሆቴል ነው፡፡ትናንት እራት ከበሉበት የአሮጊቷ ምግብ ቤት ጋር ሲነፃፀር የሲኦል እና የገነት አይነት ልዩነት አለው፡፡ተከትላቸው ወደሆቴሉ ገባች፡፡ሲገቡ አስተናጋጆቹ ሁሉ ተንጋግተው በመምጣት በሞቀ ሰላምታና በደመቀ ፈገግታ ተቀብለው ቦታ ሰጧቸው፡፡ እያንዳንዶቹን ህፃናት በየስማቸው እየጠሯቸው ያናግሯቸው ነበር፡፡ሶፊያ በጣም ነበር የተደመመችው፡፡የቤቱ ቋሚ ደንበኞች እንደሆኑ በእርግጠኝነት አመነች፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል እየተጫወቱና እየተዝናኑ ከቆዩ በኃላ መልሳ ቤት ድረስ ሸኘቻቸው፡፡ሲለያዩ‹‹ለእራት ግብዣው አመሰግናለሁ፡፡››አለችው፡፡

<<ችግር የለውም›› መለሰላት ታዲዬስ፡፡

‹‹አንድ ነገር ላስቸግርህ?››



<<ምን ልታዘዝ>>

‹‹ነገ ቁርስ ብጋብዝህ ደስ ይለኛል?››

<< ነገ?>>

‹‹አዎ ነገ ሁለት ሰዓት አካባቢ፡፡››

‹‹ይቻላል ስራ ቦታ ታገኚኛለሽ፡፡››አላትና ልጆቹን ይዞ ወደ ቤቱ ሲገባ እሷም መኪና• አስነስታ በተደመመ ስሜት ወደ ቤርጎዋ ተመለሰች፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ ለ500 እኮ ትንሽ ነው የቀረው እባካቹ ቤተሰቦች
ሰብስክረይብ እያረጋቹ ያደረጋችሁ ደግሞ ሌሎች እዲያደርጉ #Share እያደረጋቹ አመሰግናለሁ፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍67🥰42😁2👏1
በጊዜው ታዲዬስ እሷን ከሸኘ በኃላ እረፍት አላገኘም…፡፡በምን ዓይነት መንገድ ይህቺን ልጅ ከገባችበት ችግር እንድትወጣ ሊረዳት እንደሚችል በቀላሉ ሊገለጽለት አልቻለም፡፡ እንዲሁ በሀሳብ ሲባዝን አምሽቶ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነበር ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን የቻለው፡፡ሞባይል ስልኩን አነሳና ያሰበውን ወደተግባር ለመቀየር ያግዙኛል ወዳላቸው ሶስት ሰዎች ጋር  በተከታታይ የደወለው፡፡እቅዱን ለሁሉም በዝርዝር አስረዳና በእፎይታ እራሱን ለእንቅልፍ አሳልፎ ሰጠ፡፡

በማግስቱ ማለዳ 12 ሰዓት ነበር የአቶ ቂጤሳ ቤት በሶስት ሰዎች የተንኳኳው፡፡ድምፁን ሰምታ በድንጋጤ በመበርገግ በሩን ለመክፈት መኝታዋን ለቃ በራፍ ላይ ቀድማ የተገኘችው መርጊቱ ነች፡፡ ይሄ ያልተለመደ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ሰዓት ማን ነው?ማን ሞተ..…?‹‹ተልባ ቆይዋ እያለች..ጎመን ቀንጣሿ ምች መታት››የሚለው ሀገራዊ ብሄል በአዕምሮዋ ተሰነቀረ፡፡እሷን ማን ቀደማት?የትኛው ዘመድ ነው ከእሷ ጋር ፉክክር የገጠመው…?ማነው ቀድሟት የሞተው?ምን አለ አንድ ቀን ዘግየት ብሎ ቢጠብቋት ወይም ምን አለ አንድ ቀን ፈጠን ብትል? በሰከንዶች ሽርፍራፊ ይሄን ሁሉ እያሰላሰለች በራፉን ስትከፍት ሶስት ጎልማሳ ወንዶች በራፉን ሞልተው ቆመዋል፡፡

‹‹ምንድ ነው? ምን ተፈጠረ?››

‹‹ተረጋጊ ሰላም ነው፡፡››

‹‹በዚህን ሰዓት የምን ሰላም?››

‹‹ኧረ ሰላም ነው ፤ አባትሽን ማናገር ፈልገን ነው፤ቤተክርስቲያን ሳይሄዱ ልንደርስባቸው ስለፈለግን ነው በማለዳ የመጣነው፡፡

በድንጋጤ የሚንቀጠቀጠው ሰውነቷ ሳይረጋጋ ከበራፉ ገለል አለችና እንዲገቡ ፈቀደችላቸው፡፡

‹‹ግቡ ..ይቅርታ ቤቱ ግን እንደተዝረከረከ ነው፡፡››

‹‹አረ ግድ የለም፤ይልቅ አባትሽን ቀስቅሺልን፡፡››

‹‹እሺ ››ብላ ዞር ስትል አቶ ቂጤሳ ተነስተው ከመኝታ ቤታቸው በመውጣት ሳሎን ደርሰው ነበር::

መርጊቱ ትታቸው ወደ መኝታ ቤት ገባችና ጆሮዋን ግድግዳ ላይ ለጥፋ ማዳመጡን ቀጠለች፡፡

‹‹ሰዎች ምነው በሰላም ነው? አረ ቁጭ በሉ፡፡››

በተርታ ተገትራው የነበሩት ሶስት ሰዎች በአክብሮት እጅ እንደመንሳት አሉና ‹‹የመጣንበትን ጉዳይ ሳንናገር መቀመጥ አንችልም፡፡››

‹‹እኮ ቁጭ በሉና ትናገራላችሁ፡፡››

‹‹ኧረ ግድ የለም ቆመን ይሻላል፡፡››

‹‹እሺ ምን እግር ጣላችሁ?››

‹‹ልጃችሁን ለልጃችን እንድትሰጡን ልንጠይቅ ነው፡፡››

‹‹ልጃችሁን ለልጃችን?››አቶ ቂጤሳ ቃሉን መልሰው ደገሙት፡፡መኝታ ክፍል ሆና ስታዳምጥ የነበረችው መርጊቱ የምትሰማው ነገር የተዓምር ያህል አስደነገጣት፡፡ማን ነው
ላኪው? መቼስ እዚህ ቤት ከእኔ ሌላ ሌላ ሴት የለም፡፡የትኛው አፍቃሪዬ ነው እኔን ሳያማክር ለጋብቻ ሚስኪኑ አባቴ ጋር የላከው? በፍቅር የሚጎመዣትና ስትወጣ ስትገባ የሚለክፏትን አንድ ሶስት ወንዶች በምናቧ መጡላት፡፡ከእነሱ መካከል አንድ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነች፡፡ አሳቃትም፣ አሳዘናትም፡፡ሁለቱም ስሜት እኩል ነው የተሰማት፤አንድ ላይ ተዋህዶ አንድ ላይ ተጨፍልቆ፡፡መቼስ እርጉዝ መሆኗን እያወቀች ብትፈልግ እንኳን ይሄንን የጋብቻ ጥያቄ መቀበል አትችልም፤በሀጥያት ላይ ሌላ ሀጥያት አትጭምርም፡፡ጆሮዋን የመኝታ ቤቱ በራፍ ላይ እንደለጠፈች ሳሎን የሚካሄደውን ትዕይንት መከታተል ቀጠለች፡፡

‹‹ለመሆኑ ልጁ ማን ነው?››አባቷ ጠየቁ፡፡

‹‹እኮ ማ ነው? የእሱንና የቤተሰቦቹንም ማንነት ንገሩኝ?››

ያው እርሷ ባያውቁም ልጃችንና ልጆት ለረጅም ጊዜ ፍቅረኛሞች ነበሩ፤በጣም ይዋደዳሉ፤ያው አሁን መምጣታችን ነገሩን ሁሉ በእርሷ ፍቃድ እንዲሆን ስለፈለግን ነው፡፡››

‹‹ሰዎች ለምን የጠየቅኳችሁን አትመልሱም..? ልጁ ማን ነው?››ጋሽ ቂጤሳ ትግስት አጠራቸው፡፡

መርጊቱ ደግሞ ከሽማግሌ ተብዬዎቹ የምትሰማው ነገር ግራ አጋባት‹…እንዴ እንዲህ አይነት ውሸት አለ እንዴ?ማነው እንዴህ በድፍረት አይን ያወጣ ውሸት አሲዞ ሽማግሌዎችን የሚልክ?እሱ ተዋርዶ እነሱንም የሚያዋርድ?›› ተንደርድራ ወጥታ ለሽማግሌዎቹም ለአባቷም ምንም አይነት ፍቅረኛ እንደሌላትና ማንንም ማግባት እንደማትፈልግ ነግራቸው ነገሩን ለማሳጠርና ሁሉንም ከድካም ለመገላገል ወሰነችና ወደ ሳሎን ሳሎን ለመግባት መኝታ ቤቱን በራፍ ከፍታ አንድ እግሯን ስታነሳ ‹‹ጌታዬ ልጁ ታዲዬስ  ነው፡፡››የሚል ድምጽ ከሽማግሌዎቹ ሰማች... ባለችበት ደንዝዛ ቆመች፡፡

‹‹ታዲዬስ….ታዲዬስ የቱ?››

‹‹ታዲዬስ መሀንዲሱ ..እዚሁ እርሶ ቤት የሚኖረው፡፡››

አቶ ቂጤሳ ከመደንገጣቸው የተነሳ በተቀመጡበት እጆቻቸውን ጭንቅላታቸው ላይ ጫኑና አንገታቸውን ወደ መሬት ደፍተው ማሰላሰል ጀመሩ፡፡‹‹እንዴት እንዲህ ይሆናል?››አንድ ቀን እንኳን የረባ ጫወታ ሲጫወቱ፣ሲቀላለዱ ወይም ሲላፉ አጋጥሞቸው አያውቅም፡፡ሁለቱም እርስ በርስ ከመሳሳብ ይልቅ የመገፋፋት ባህሪ ነበር ዘወትር የሚያታይባቸው፡፡እንዴት ከእሷቸው በዚህን መጠን ግንኙነታቸውን መሰወር ቻሉ?

‹‹እሺ ያላችሁትን ሰምቼያለሁ፤ጉዳዩን ከልጅቷም ከዘመድ አዝማድም ጋር ልማከርበትና መልሱን ለሳምንት ልስጣችሁ፡፡››
በደመነፍስ እግሯን እየጎተተች በጓሮ በር ወጥታ ወደ ታዲዬስ ክፍል አመራች፤አንኳኳች፤ ከፈተላትና ወደ መኝታው ተመለሰ፡፡ ምንም ሳትናገር ወደውስጥ ገባችና በራፉን ዘጋችውና ወደ አልጋው በመውጣት ከውስጥ በመግባት ዝም ብላ ከጎኑ ተኛች፡፡ በአድናቆትና በዝምታ ተመለከታት፡፡ በጣም ደንግጣለች፤ በእንቅልፍ ልቧ እየተጓዘች የመጣች ትመስላለች፡፡ዝም ብሎ አይኖቾ እንባ ያመነጫሉ፡፡ከሃያ ደቂቃ የዝምታ ጊዜ በኃላ << ታፈቅረኝ ነበር እንዴ?››በማለት ያልጠበቀውን አደናጋሪ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

ግራ ተጋባ‹‹ምን አልሺኝ?››

‹‹ታፈቅረኝ ነበር ወይ ?ሳትዋሽ ንገረኝ፡፡››

‹‹በፍቅር እኮ ውሸትም ይሉኝታም አይገባም፤ፈጽሞ አፍቅሬሽ አላውቅም፡፡››

ሰውነቷ በደቂቃዎች እንደበረዶ ቀዘቀዘባት‹‹ታዲያ ለምን?አስበኸዋል ግን? ሰው ያፈቀረውን እንኳን ለማግባት ሞራል ባጣበት ጊዜ አንተ የማታፈቅራትን ለዛውም እርጉዝ የሆነችን ሴት ለማግባት መስዋዕትነትን ለመክፈል የፈለከው ?ነው ወይስ የውሸት ድራማ እየተጫወትክ ነው፡፡?››

‹‹የውሸት አይደለም፤ የእውነት ነው የማገባሽ..ማለቴ እንጋባለን፤አብረን እንኖራለን፡፡…ያለምንም ግንኙነት፤ልጅሽን ወልደሽ ሁኔታዎች ከተስተካከሉ በኃላ አልተስማማንም ብለን እንፋታና አንቺም የፈለግሽውን ማለት የሚያፈቅርሽንና የምታፈቅሪውን ታገቢያለሽ፤ እኔም እንደዛው፡፡››

‹‹እኮ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ገብተህ ይሄን ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ለምን ለመግባት ፈለክ?እኔ ምን አድርጌልህ አውቃለሁ? አንድ ቀን እንኳን ልብስህን ልጠብልህ ወይም ቤትህን ላፅዳልህ ብዬህ አላውቅ፡፡››
ስለተደረገልሽ ብቻ አይደለም የሆነ ነገር ማድረግ ያለብሽ፡፡ደግሞም ላንቺ ብዬ አይደለም፤ ለአባትሽ ስል ነው፡፡አንቺ እንዳልሽው በዚህ ዕድሜያቸው ጥለሻቸው ብትጠፊ እርግጠኛ ነኝ ለአንድ ወር በህይወት አይቆዩም፤በመጨረሻ ዕድሜያቸው ለእሳቸው ይሄ አይገባቸውም፡፡››


ይቀጥላል

ዛሬ በጠዋት ተከስተናል ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ እስከማታ የተወሰነ ሰው #Sebscribe ካደረገ በክፍል #31 እንገናኛለን #Shareም አይረሳ  አመሰግናለሁ፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12012😱5😢2
አየሽ እኔ ስራን የምሰራው ለብር አይደለም እያንዳንዱን የህይወት ዘርፍ ለማጣጣም እንዲያመቸኝ ነው፡፡ሳይት ኢንጂነር
ሆኜ ሰርቼያለሁ፤የሆቴል ማናጀር ሆኜያለሁ፤ተሸካሚ ሆኜ ሰርቼ አውቃለሁ፤ ዌይተርም ነበርኩ፤ አስተማሪም ሆኜ ሰርቼያለሁ..ብዙ ብዙ ነገር፡፡ይሄንን የማደርገው ከነዛ የስራ ዘርፎች የሚገኘውን የህይወት ልምድ ቀጥታ ለማግኘት ስል ነው፡፡››

‹‹የሚገርም ነው!!!የወደፊት እቅድህን ልትነግረኝ ትችላለህ?››

‹‹የወደፊት ዕቅዴ ህዝብና መንግስትን ማሳቀቅ ነው፡፡››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹አየሽ... ሰሞኑን የተዋወቅሻቸው አምስት ልጆቼን በየተሰጥኦዋቸው የመጨረሻው ስኬት ላይ እንዲደርሱ ማገዝ ነው ዋና የህይወት ግቤ፡፡…ያ ሲሆን ደግሞ እነዚህ ልጆች ከበረንዳ ኑሮ ከቆሻሻ ላይ ተነስተው የሀገሪቱ ምርጥ ሰው ሆነው ሲገኙ..መንግስትም ሆነ ማንም ገንዘብ አለኝ የሚል ግለሰብ ስንቱ ምጡቅ
አዕምሮ ያለው ትውልድ በየቆሻሻው ባክኖ እንደቀረ ማሰብና መቆጨት ይጀምራል፡፡ከዛም ከአንድ ሺ መካከል አንድ ሰው እንኳን የእኔን ልጆች ስኬት ተመልክቶ የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ቢነሳ ጎዳና ባክኖ የሚቀር አንድ ህፃን እንኳን አይገኝም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ በአጠቃላይ እኔ ይሄንን አድርጌያለሁ ... እናንተስ ?...ለማለት ነው..፡፡የተግባር ስብከት ለመስበክ፡፡››

ቀጣይ ምን እንደምትጠይቀው እያሰላሰለች ሳለ የእሱ ስልክ ድምፅ አሰማ፡፡

<ሄሎ ሰላም::>>

<<ሄሎ>>

<<ምን?>>

‹‹መጣሁ...በቃ ሄለን ሞባይሉን ስጫትና ከኋላ ትከተለው ..ደውዬላት ያሉበት ድረስ ሄዳለሁ፡፡›› ስልኩን ዘጋው፡

‹‹ምነው? ምን ሆንክ?››

‹‹ሙሴ ከግቢ ወጥቷል ...ሂሳብ ክፈይና እንሂድ፡፡››ከቦርሳዋ ብር አወጣችና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ በመነሳት ወደመኪናው አመራች ፡፡እሱም ተከትሏታል፡፡ የተፈጠረው ችግር አልገባትም፡፡

ከግቢው ወጥተው መንገድ እንደያዙ‹‹አልገባኝም..ሙሴ ከግቢ መውጣቱ ችግር አለው?››

‹‹አዎ..ሙሴ ትንሽ ክትትል የሚፈልግ ልጅ ነው፤ከግቢ የሚወጣው ብዙውን ጊዜ የሆነ ነገር ለመስራት አስቦ የሆነ ቁሳቁስ ሲያጣ ፍለጋ ነው፡፡››

‹‹ከየት ነው የሚፈልገው?››

‹‹ከየመንገዱ.፤ከየቆሻሻ መጣያው...የፈለገውን እሲኪያገኝ ድረስ ሲባዝን ነው የሚውለው..ካጣ ደግሞ ስለሚ።በሳጭ ያመዋል፡፡››

‹‹ምንድነው የሚያመው?››

‹‹የሚጥል በሽታ አለበት፡፡ሙሴ ተአምራዊ የሆነ የፈጠራ ብቃት አለው፡፡ ይሁን እንጂ በዛው ልክ ታማሚ፤ከሰው የማይግባባ፤የትምህርት ለመማር የሚያዳግተው የተለየ ልጅ ነው፡፡››

‹‹ቆይ ..አንድ የማይገባኝ ነገር እንዲህ የተለየ የፈጠራ ብቃት እያለው ትምህርት ለመማር እንዴት ይከብደዋል?››

‹‹በዚህ አለም የትምህርት ስርዓት ስትማሪ በካሪኩለሙ በተቀመጠው ልክ ካልተጓዝሽ ደደብ ነሽ፡፡››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ማለቴ ሰነፍም ከሆንሽ…በጣምም ከመጠን ያለፈ ጎበዝ ከሆንሽ በተመሳሳይ ‹ደደብ ነሽ >ነው የምትባይው...ምክንያቱም ሰነፍ ስትሆኚ የእውነት አንቺ አታውቂም ...በጣም ጎበዝ ስትሆኚ ደግሞ አንቺ ባወቅሺው መጠን
ካሪኩለሙም አስተማሪዎችሽም አያውቁም፡፡

የዛን ጊዜ ታዲያ መቼስ ማንም ቢሆን አስተማሪው አያውቅም ማለት ስለማይደፍር አንችኑ ደደብ ነሽ ይልሻል..ያሸማቅቅሻል፡፡

ሙሴን ያጋጠመው እንደዚህ አይነት ሁኔታ
ነው፡፡ለምሳሌ ሁለተኛ ክፍል ሆኖ አንድ ዶሮ ሲደመር ሶስት ዶሮ ስንት ይሆናል ? የሚል ጥያቄ ፈተና ላይ ቀረበለት፡፡ለዚህ ጥያቄ

አስተማሪው ከእሱ የሚጠብቀው መልስ አራት
ዶሮ የሚል ነበር፡፡እሱ ግን ‹መደመር አይቻልም> ብሎ መለሰ፡፡ ኤክስ አገኘ፡፡‹ አልተሳሳትኩም›ብሎ ክርክር አስነሳ << ..አንዱ ዶሮሴት..ሌላው ወንድ..አንዱ ጥቁር ሌላው ቀይ..አንዱ 5 ኪሎ ሚመዝን ሌላው 3 ኪሎ
ሚመዝን ሊሆን ይችላል፤ታዲያ እንዲህ በስም ካልሆነ በስተቀር በምንም የማይመሳሳሉ
የተለያዩ ነገሮች አንድ ላይ ጨፍልቆ አምስት ዶሮዎች ማለት ትልቅ ስህተት ነው ብሎ ሀሳቡን አብራራ፡፡ከእኔ በስተቀር ማንም ሀሳቡን
ሊረዳው የፈለገ ሰው አልነበረም፣አስተማሪዎቹ
ሳይቀሩ እንደጅል ነበር የቆጠሩት፡፡››

‹‹እውነትም እንክብካቤ የሚገባው ልጅ ነው››አለች ዶ/ር ሶፊያ በሙሴ ሁኔታ ውስጧ ተነክቶ፡፡ ታዲዬስም ሄለን ጋር ደወለ የሚገኙበትን ቦታ ነገረችው፤ ተቃርበዋል፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ  በጣም ቀንሳችኋል እስካሁን የተወሰነ ሰው ነው #Sebscribe ያደረገው ከዚ ፖስት በኋላ አንድ 20 ሰው እጠቦቃለው ሃሳባችን ከሞላ ጠዋት በክፍል 33 እንገናኛለን አመሰግናለው።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍10412🥰1😱1
ትንግርት ታዲዬስን ለመጨበጥ በአየር ላይ የዘረጋችው እጇን እንዳንከረፈፈች ፊቷን ሙሉ በሙሉ ወደ ዶ/ር አዞረች፡፡በህይወቷ መቼም ፊት ለፊት አገኛታለሁ ብላ ለሰከንድ እንኳን አስባ የማታውቀውን ሰው ፊት ለፊት ስታይ አፏን ከፈተች.. ለደቂቃዎች ሁለቱም ደንዝዘው በፀጥታ ተፋጠጡ፡፡ ሶስት ወንዶች ግራ ገባቸው፡፡

በመጋባት ጠየቀ::

‹‹እጅግ በጣም እንተዋወቃለን ››ብላ ስትናገር እና ጠረጴዛ ላይ ያለውን የለስላሳ ጠርሙስ አንስታ ዶክተሯ ጭንቅላት ላይ ስትከሰክሰው አንድ ነበር፡፡በሰከንዶች ቅፅበት በአከባቢው ከፍተኛ ግርግርና ድንጋጤ ተከሰተ፡፡.ዶ/ር ሶፊያ መላ ፊቷ በደም ተሸፍኖ እራሷን ስታ ተቀምጣበት ከነበረበት ወንበር ወደ ኃላዋ ተገነደሰች፡፡

<< ምን ነካሽ አብደሻል እንዴ…?››ኤልያስ
‹‹እንዴ ምነካሽ ?እኛን እንኳን አታከብሪም?››ጋዜጠኛው አመነጫጨቃት፡፡ ታዲዬስ ዶ/ር ሶፊያን በክንዶቹ አቅፎ ግራ በመጋባት ትንፋሿን ያዳምጣል፡፡

ከ5 ደቂቃ በኃላ ታዲዬስ እና ኤልያስ ዶ/ር ሶፊያን ለህክምና ወደ ሆስፒታል ይዘዋት ሲሄዱ በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶች በአፋጣኝ ደርሰው ወንጀለኛዋን ትንግርትን ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ አመሩ፡፡


ይቀጥላል


ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ
ነው በጣም አመሰግናለው
አሁንም #Sebscribe   ያለደረጋቹ እያደረጋቹ #ትንግርት እስከሚያልቅ 500 ##Sebscriber እጠብቃለሁ በቅድምያ ለሁላችሁሜ አመሰግናለሁ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍6915🤔6😱6
አይደለችም፡፡ከእሱ በፊት ቀርባቸው የነበሩት ሁለት ወንዶች እንዴት አይነት አስቸገሪ ሁኔታ ላይ ጥለዋት እንደነበረ ዛሬም ትዝ ሲላት ዝግንን ይላታል፡፡
አሁን የምትፈራው ይሄ ልጅ ይሄን ሁሉ  ነገር  ለምዶ  በቃህ  ከዛሬ  ወዲያ አንገናኝም ብትለው አሜን ብሎ ተሰናብቷት ይሄዳል? እዚህ ላይ ከባድ ጥርጣሬ አላት፡፡ይህንን ጥርጣሬዋን ለማጥራት የቅርብ የሆነ ጓደኛውን በጎን ቀጥራበት ለአንድ ወር ስታሰልለው ነበር፡፡ስለእሷ ምን እንደሚያስብ?እቅዱና ምኞቱን ምን እንደሆነ ?ለማወቅ፡፡በተቀዳ የድምፅ መረጃ ያገኘችው  መረጃ  ግን  ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የጣላት ነበር ፡፡ፈፅሞ እንዳሰበችው አይነት የዋህና ታዛዥ ብቻ የሆነ ሰው ሆኖ አላገኘችው፡፡እሷ  ላይ  የሞትና  የሽረት  የሆነ  ሰፊና  ጥልቅ  እቅድ እንዳለው ደርሳበታለች፡፡ ይሄን ካወቀች በኃላ ሳትበረግግና ስሜቷን ለእሱ በግልፅ ሳታሳውቀው እንዴት ከላዮ ላይ ጉዳት በማያስከትልባት ዘዴ ገለል እንደምታደርገው  እቅድ ማውጣት እዳለባት ገብቷት እየሰራችበት ነው፡፡
እሱ ግን እሷ ምንም እንደምታቅ ባያውቅም እንደተባለው ከእሷ በጣም የራቀ እና የተለየ እቅድ ነበረው፡፡ከእሷ ለዘላለምም ቢሆን የመለየት እቅድ በአእምሮዋ የለም፡፡በጣም እንደምታፈቅረው ነው የሚያስበው፡፡እሱም እለት ከእለት በጣም እያፈቀራት ሄዷል ፤ከዛም በላይ  ከእሷ  ጋር  ከተገናኘበት  ጊዜ  በኃላ  ኑሮውን ከሲኦል ወደገነት ቀይራለታለች፡፡በምንም አይነት ሁኔታ ይሄንን እድል ማባከን አይፈልግም፡፡ከውበቷም ከሀብቷም ፍቅር ይዞታል፡፡አሁን ወደቤቷ የሚሄደው ከእዚህ ጋር ለተያያዘ ጉዳይ ቀስ ብሎ በእርጋታ ሊያማክራት ነው፡፡ይሄንን ጉዳይ እስከመጨረሻው በፍቅርና በሰላም መስመር ለማስያዝ እስከመጨረሻው ጠብታ ይለፋል፡፡የሰላሙ መንገድ የማይሳካ ከሆነ ግን በየትኛውንም ሌላ አማራጭ በመጠቀም ሀሳቡን ለማሳካት ቆርጧል፡፡በሰላም ከሆነ ፍቅሯንም ሀብቷንም መቆጣጠር ይችላል፤ ያ ተመራጩና በጣም የሚፈልገው ነው፡ካልሆነ ግን

በየትኛውም መስዋዕትነት እሷን ዞር አድርጎ ሀብቷን ጠቅልሎ የመረከብ ፍላጎቱ ጣሪያ የነካ ነው፡፡


💫ይቀጥላል💫


አሁንም ዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ #Share እያደረጋቹ ቤተሰቦች በቅንነት እባካቹ👍

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍674