አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍቅር_ከፈላስፋ



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

#ክፍል_ሦስት

❤️ፌናን

...ፌናን እባላለው ብዬ ታሪኬን ልጀምር እንዴ..?በነገራችን ላይ ይሄ ስም በሰው አፋ ሲጠራ ድንግርግር ይለኛል…ብቻውን የራሱ የሆነ አካል አልባ ነፍስ ኖሮት የሚንቀሳቀስ ነው የሚመስለኝ…በአየር ላይ ሲንሳፈፍ ሁሉ የሚታየኝ ጊዜ አለው…ያ ተንሳፋፊ እራሱን የቻለ የራሱ ህይወት እና ህልውና ያለው ስም የሚሉት መንፈስ መጥቶ በሰውነቴ ሰርጎ ሲዋሀደኝ እና ከማንነቴ ጋ ተቀይጦ ነፍሱን ከነፍሴ ህልውናውን ከህልውናዬ ካዋሀደ ብኃላ አፌ ይላቀቃል…አቤት ብዬ እመልሳለው..እኔን ባይወክልም እኔ ውስጥ የሰረገውን መንፈስ ሊወክል ይችላል በሚል እምነት…ዘግይቼ አቤት እላለው…ጠሪዎቼ ይሄንን ስለማይረዱልኝ ብዙውን ጊዜ ትለጠጣለች ይሉኛል፡፡
እናቴ አምጣ ወለደችኝና ጣለችኝ… አባቴ አነሳና አሳደገኝ… ፡፡እናቴ ጣለቺኝ ስላችሁ ለሰራተኞች ነው…ምን አልባት ሶስት ወይም አራት ለሚሆኑ ሞግዚቶች፡፡እኔን አጫዋችና ተንከባካቢ አንድ ሴት ፤ምግቤን የምታበስል ሌላ ሴት፤ልብሶቼን የምታጥብ ሌላ፡ጤንነቴን የምትከታተልም ሌላ ነርስ….፡፡
ታዲያ እሷም ሆነች በዙሪያዬ ያለውን ጋጋታ የሚታዘብ ሌሎች ሰዎች ልጅን ማሳደግስ እንደዚህ ነው ይላሉ…..እሷም በዛ ኩራት ይሰማታል…፡፡
….እናቴ የጡቷን ጫፍ አንድ ቀን በስህተት አንኳን በአፌ ውስጥ አስገብታ አታውቅም…ስለሚያማት አልነበረም..እንደዘማናዬቹ ሴቶችም ጡቶቾ እንዳይረግቡባትም አልነበረም..ጊዜ ስለሌላት ነው፡፡ከወለደቺኝ ከሶስት ቀን ቡኃላ ቢሮዋ ነበረች….ምክንያቱም ቢዝነስ ነዋ..ደንበኞቾን ተቀናቃኞቾ ይነጥቁባታል ..ሰራተኞቾ በአሻጥር የሆነ ያህል ብር ያጭበረብሯታል….እና ብር ስላላት በሰራተኞች አስከብባኛ ከፊቴ ዞር አለች.
ነገር ግን አንድ እናትን አንድ ሺ ተንከባካቢ ሴት እንደማይተካት የሚያውቀው እንደእኔ የደረሰበት ብቻ ነው…
አባቴ…ዋው !!!!አባቴ ዕድሜውን ሙሉ አስተማሪ ሆኖ ኖሮ አሁንም በአስተማሪነት እያሰራ ያለ ሰው ነው፡፡በዛ ላያ ደራሲ ነው፡፡ምርጥ አሳቢም ነው፡፡እኔን ማፍቀር እና ማሰብ ቋሚ ስራው ነው፡፡ አባቴ ብስለት… እርጋታ…ቁጠብነት እና ረህራሄ መገለጫዎቹ ናቸው፡፡አባቴ ወደዚህ ምድር ከመጣውበት ቀን አንስቶ ለእኔ የሚሆን ጊዜ አጥቶ አያውቅም…ከማስተማር እና ከማንበብ የተረፈው ጊዜ የእኔው ነው፡፡
ከውልደቴ ጀምሮ የህፃንነት አልጋዬ አባቴ መኝታ ክፍል ውስጥ ከእሱ አልጋ ተጠግቶ ነበር ያለው…እናቴ ቀኑን ሙሉ በቢዝነስ ስብሰባዎች በድርድር እና ክርክር ደክሞት ሰለሚውል እናም ደግሞ ወደቤትም እኩለሊት አካባቢ ስለምትመጣ ወደክፍሎ ከገባች ቡኃላ መረበሽ አትፈልግም..በተለይ እንቅልፍ ከወሰዳት ቡኃላ የህጻን እሪታ እንዲረብሻት በፍጽም አይታሰብም…..አይኔን የምታየኝ ጥዋት ወደስራ ለመሄድ ለባብሳና ተኮኩላ ቁርስ አፈ ላይ ጣል አድርጋ ዝግጅቷን ካጠናቀቀች ቡኃላ እግረመንገዶን ለአንድ ወይም ለሁለት ደቂቃ ነው፡፡በዛ ላይ በዛን ሰዓት እኔ ብዝውን ጊዜ እንቅልፍ ላይ ልሆን እችላለው….
አባቴ በሚያስተማራቸው ሁለት ክፍለጊዜ መካከል የእንድ ክፍለጊዜ ክፍተት ካለው መኪናን አስነስቶ ወደቤት በመምጣት ጤና መሆኔን አይቶች አቅፎኝና ስሞኝ ተመልሶ ይሄዳል…ትንሽ ከፍ ስል የህፃን አልጋዬን ጥዬ የእሱን አልጋ መጋራት ጀመርኩ…በነገራችን ላይ የእናቴን ጡት አልጠባውም ስላችሁ ጡት ሳልጠባ ነው ያደኩት እያልኳችሁም አይደለም…ሶስት አመት እስኪሆነኝ ድረስ እንቅልፍ የሚወስደኝ የአባቴን ጡት ጫፍ አፌውስጥ ጨምሬ እየመጠጥኩ ከሆነ ብቻ እንደሆነ የቤቱ ሰው ሆነ ጎረቤት የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ የእኔ የአባቴን ጡት መጥባት ለሚመለከቱ ሰዎች አይገባቸውም… ቅብጠት ይመስላቸዋል ፤እወነቱን ግን እኔ ገላ ውስጥ የምትገኝ ነፍሴና አባቴ ብቻ ብቻ ነን ምናውቀው ….በልቡ ውስጥ የታጨቀው ለእኔ ያለው ፍቅር በደምስሩ በመሽሎክሎክ በጡቱ ጫፎች በመትነን ወደሁለንተናዬ ገብቶ ሲሰራጭ የሚሰማኝን እርካታ ቃላት ተሰብስበው ለማስረዳት ጉልበት አይኖራቸውም….የዛን ጊዜ እግዜብሄር ደረት ላይ የተለጠፍኩ ይመስለኛል…የዛን ጊዜ የእግዜር ቅዱስ እጅ እጣቶች ግንባሬ ላይ አርፈው ፀጉሬን የሚያርመሰምሱት ይመስለኛል…..
ሶስት አመት ካለፈኝ ቡኃላም ይሄንን ዓመሌን አላቆመክም…ደረቱ ላይ ተለጥፌ ጡቶችን እየመዘመዝኩ ተረት ያነብልኛል….የአባቴ ድምጹ ሙዚቃ ነው…የራሱ ምት የራሱ ዜማ እና የራሱ ውበት አለው…ደሞ ሚገርመኝ እግሮቼን ሰውነቱ ላይ ጭኜ ፤እጆቼን በአንገቱ ዙሪያ ጠምጥሜ፤ ደረቱ ላይ ተለጥፌ ለጆሮዬ ቅርብ ሆኖ የሚያነብልኘ የተረት መፃፍ ድምጽ ከፀሀይ ሽራፊ አካል ተሸርፎ… በጨረቃ አንደበት ውስጥ አልፎ… የሰማይ መስኮትን ልክ እንደማይክራፎን ተጠቅሞ ኩልል እያለ ከዛ እርቀት በመምጣት በጆሮዬ አድርጎ ሳይሆን ቀጥታ በልቤ ላይ በመንጠባጠብ በዝግታ እየቀለጠ ከማንነቴ ጋር የሚዋሀድ የፍቅር አዚም ነው የሚመስለኝ…
እንደነዚህ አይነት የጊዜ ሽራፌዋች ለእኔ የፀሎት ጊዜዎቼ እንደሆኑ ነበር የማስበው…የምመሰጥበት እና የምቀልጥበት….ማንነቴን የማጣበት እና የምጠፋበት….ለነገሩ አሁንም ድረስ የአባቴ ጉያ የእኔ የፀሎት ዋሻዬ ነው…::ደረቱ መስገጂያ መቅደሴ ፤ትንፋሹ ፀሎቴን ወደ ፈጣሪዬ የሚያደረስልኝ ከመቅደሱ የሚበተን የከርቤ ጭሴ ነው ….
አይዞችሁ አትሰልቹ የእኔ ታሪክ ሙሉ የአባቴ ታሪክ ነው…እኔ አባቴን ነኝ ፡፡በስጋ ብቻ አይደለም የወለደኝ በመንፈስም ጭምር ሙሉ የእሱ ልጅ ነኝ፡፡የሚያየውን አይቼ የሚያስበውን ማሰብ እችላለው…ከዛም በላይ አንድ ነን፡፡
====
አባቴ እና እናቴስ..የሁለቱ ግንኙነት በራሱ የተፈጥሮ ሚስጥር ነው፡፡እኔ በእድሜዬ ባልና ሚስት ሆነው አይቻቸው አላውቅም….ደግሞ አንደኛው ስለአንደኛው አደናቅፎት እንኳን ክፋት ፤ ስሞታ ወይም ቅሬታ ሲያሰማ ሰምቼ አላውቅም…ለምሳሌ ያው እንደነገርኳችሁ አባቴ አስተማሪ እንደመሆኑ መጠን የእሱ ወር ደሞዝ ለእናቴ አንድ የእራት ቀሚስ አይገዛላትም….እና ለነዳጅ እንዲሆንህ አንድ ሚሊዬን ብር ደብተርህ ላይ እስገብቼልሀለው ትለዋለች..ያው የእኔንም ሆነ የአባቴ መኪኖች የተገዙት በእናቴ ብር ነው…. ‹‹አመሰግናለው››ይላታል..ከሌላው ቀን ሳይፈግግ ሳይኮሳተርም….ከአምስት ወይም ከስድስት ወር ቡኃላ ‹‹ወይ በስራ ስሯራጥ እረሳውህ..ምን አለ ብታስታውሰኝ ትልና… ቼኳን አውጥታ አንድ‹‹አላምንህም ሚሊዬን ብር ጫር ጫር ታደርግና ታቀብለዋለች‹‹ግን የባለፈውን አልጨረስኩትም››ይላታል በዛው ተለመደ እርጋታው
አሳየኝ››
‹‹ሂጂ ደብተሬን ከምኝታ ቤት አምጪና አሰያት››ያዘኛል እኔን
ሄጄ ሳመጣው….ስምንት መቶ ሃምሳ ሺ ብር…..
‹‹ምን እየሰራህ ነው..?››ትንጨረጨራለች
‹‹ምን ሰራው..?››
‹‹እንዳለእኮ ነው ብሩ››
‹‹ምን ይሰራልኛል…ለቤት ወጪ አላወጣ….ደሞዝ አለኝ መፃፍ ብገዛ ና በሳምንት አንድ ቀን ከልጄ ጋ ወጣ ብለን ብንዝናና ነው…እሱንም ቢሆን እሷው ነች የምትከፍለው…እንደውም በትምህርት ቤት ትንሽ ገንዘብ የሚቸግራቸው አንድ አስር የሚሆኑ ተማሪዎቼን ትንሽ ትንሽ ብር ስለምሰጣቸው ነው….እንዴ እንደውም እኳ አንድ መፃፍም አሳትሜበታለው››ሊያሳምናት ይጥራል፡፡
‹‹አታበሳጨኝ ባክህ …የሆነ የሆነ ነገር አድርገህ ተጠቀምበት እንጂ….ሰው እንዴት ቢያንስ ከልጁ እኩል ብር መጠቀም ያቅተዋል…››…(ቁጣዋን ትቀጥላለች እግረመንገዶንም የእኔን አጥፊነት እየጠቆመች…)
‹‹እሺ አጠፋለው››
በኩርፌያ ወጥታ ወደተለመደ ስራዋ ትሄዳለች….
ሌላው ያው ብዙ ግዜ እናቴ በሽታ አያጣትም….እና ከሀኪም መድሀኒት ሲታዘዝላት….ስድስት ሰዓት
👍1
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_ሦስት


#በዮርዳኖስ

"አይዞሽ የኔ ውድ ማድረግ የምትፈልጊው ነገር አለ? ለምሳሌ መውጣት ወይም ሌላ ነገር...?"
እንዲያው ለአመል ይጠይቀኝ እንጂ ባለፉት ቀናት ብዙ ነገር አንዳላደርግ ሲከለክለኝና ሲደብቀኝ እንደነበር አስተውያለው ለምሳሌ ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንዲሁም ሞባይል ኢንተርኔት አንዳላይ አድርጎኛል።ከቤት መውጣቱንም ቢሆን አብሮኝ ካልሆነ አያስወጣኝም።ለኔ ተጠንቅቆ እንደሆነ ቢገባኝ ግን ማወቅ እና ማየትን እፈለጋለው ከቤት መውጣትንም እንደዛው።ግን አባቴ ስጋት ያለበት ይመስላል ደግሞም ይገባዋል ምክንያቱም ለሱ ብቸኛ ልጁ ነኝ ሊያውም ካለናት ያሳደገኝ።ያ ማለት ግን ከናቴ ጋር ተጣልተዋል አልያም ሞታለች ማለት አይደለም ሚስጥሩ ሌላ ነው።ለጊዜው ግን እኔና አባቴ ከአንድ ሰራተኛችን ጋር ነው የምንኖረው።ሰራተኛ ለማለት ግን ይከብዳል እህና አብሮ አደጌ ብላት ይሻላል። ብርቱካን ትባላለች የዋህ እና ንፁ ኢትየጵያዊ ምርጥ እናትና ጠሩ እህት ነች በቃ ከዚ ሌላ መግለጫ የለኝም።
አባቴ ላቀረበልኝ ጥያቄ መልስ"ከስራ ልትቀር...?"አልኩት በዘዴ "አንቺ ከፈለግሽ ካንቺ አይበልጥም"አለኝ
"አይ ብቻዬን ነው መውጣት የምፈለገው ካለሆነ ይቅር"አልኩ።አባቴ በረጅሙ ተንፍሶ"በርግጥ አሁን ይበልጥ ትሻያለሽ ደና ነሽ ግን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወደራስሽ እስክትመለሽና የቅርብ ጊዜ ትውስታሽ እስኪመለስ መጠበቅ አለብሽ ካልሆነ ግን ትንሽ ከደገኛ አይመስለሽም ሔዊ?" መልሶ በጥያቄ መለስልኝ።
"አይ አይመስለኝ እንድረጋጋና ነገሮችን አንዳስታውስ ከፈለክ ነፃ ብታደርገኝ የሚሻል ነው የሚመስለኝ"። እንደማቅማማት አለና "እሺ ወደ ሳሎን ነይና ቁርስ እንብላ"አለኝ እንደ እሽታ ቆጥሬ"አባዬ ስለተረዳኸኝ አመሰግናለው "አቅፌ ሳምኩት።ግን የአባቴን ጥንቃቄ አይታችሁልኛል ምን እንዳስታወስኩ እንኳን ጠይቆ ሊያስታውሰኝ አልፈለገም ምክንያቱም ማስታወስ እንደማልፈልግ ነግሬዋለዋ።
ለወትሮው አባቴ እስካለና እቅፍ ውስጥ ስሆን ፈርቼ አላውቅም በአባቴ መሉ እምነት ና መተማመን ነበረኝ።ልክ በአምላኬ እቅፍ ውስጥ ያለው ያህል ደህንነትና ሰላም ይሰመኝ ነበር።ግን በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የአባቴ እቅፍ ወደማያስጥለኝ ወደማያድነኝ አስፈሪ ገፅታ ወዳለውእና ማለቂያ የሌለው የሚመስል ስቃይ ውስጥ ራሴን ካገኘው ቡሗላ ግን ፍፁም ቀድሞ የነበረኝ ሰላምን ሊሰጠኝም ሆነ እምነት ሊኖረኝና ፍራቻን ሊያስወግድልኝ አልቻለም።

ሳሎን ስንደርስ ቀርስ ቀርቦ ግሩም ቃና ባለው ሻይ ሽታ ታውዶ ነበር።"ደና ደርሽ ሔዊ"አለች ቡርቴ በዝግታ ሔጄ ሳምኳትና"ሽታው በጣም አያስራበኝ ነው ባለሞያ እኮ ነሽ!"አልኳት።"አሱን በደንብ ስትበዪ ነው ማምንሽ በደንብ አትቢና ግን ወይልሽ!"አለች የውሽት ቁጣ እየተቆጣች።
"እሺ እናመስግን"አለ አባዬ ፊቱ ላይ አንዳች ስሜት እየተነበበ እንደተረበሸ ያስታውቃል።
በፊተት ከምወደውና ደንነት እንዲሰማኝ ከሚያደርገኝ ሌላው ነገር የአባቴ ፀሎት ነው ልጅ እያለው እንደሱ ለመፀለይ አለማመድና አንደ አባታችን ፀሎት አደጋግመው ነበር።የሚፀልይበትን እረጋታ እና ድምፅ አወደዋለው በአይምሮዬ ጥሩ ዜማ እንዳለው ተወዳጅ ሙዚቃ ተቀርጿል።"አሜን"ስል የእውነትም አባቴ በሚለው ነገር በአምላኬ ተሰሚነትን አንደማገኝ ወስጤ እረግጠኛ ሆንና አምኜ ነው።እና ይሄንን የአባቴን ፀሎት አድጌም አልጠጎበውም።ደስ ይለኛል ምግብ ላይም ይሁን በምንም አጋጣሚ ሲፀልይ ሰላም ወስጤን ይሞላዋል ከእግዚአብሄር ጋር የምገናኝ የማወራው እና እሚመልስለኝ ነው የሚመስለኝ።
ይሄንን ሁሉ የምላቹ አባቴ ለቁርስ እየፀለየ ነው እኔና ቡርቴ በአሜንታ እየተከተልነው አመስግነን ጨረስን።
ቁርስ በልተን እስክንጨርስና አባዬ ወደ ስራ እስኪካሄድ መጠበቅ በጣም ረዝሞብኝ ነው ቢሆንም ጠበኩ።አባዬ በቅራኔ እንደተሞላ ለመውጣት ሲወጋጅ ድንገት የት እንደምሄድ ጠየቀኝ የት ነው የምሄደው...?
"ገበያ..."አልኩት ዝም ብዬ
ገበያ....??" አለኝ በጥያቄ አይን አያየኝ
" አው አታስብ ቡርቴ የምትገዛው እቃ ስላለ ከሷ ጋር ነው የምሄደው" አልኩት አፌ ላይ አንደመጣልኝ።
"እሺ እንደዛ ከሆነ ገንዘብ ያስፈለግሻል"ከዋሌቱ የተወሰኑ መቶ ብሮችን እያወጣ "ምንያህል ያስፈለግሻል?
"አይ አትቸገር ብዙም አይደል"እንደዛ ከሆነ ካፌ ነገር ብትገቡ ወይም ደስ ያላችሁን ብታደርጉ ጥሩ ነው ብቻ ሚያዝናናቹን" ሰጠኝ።
"ይሄ ደሞ ላንቺ ነው"ለቡርቴ እያቀበላት ገና ከጓዳ እየወጣች ነበር"ለምን....?"አለች ከመጀመሪያው ስላልሰማች"ገበያ ልንሄድ አይደል...!"አልኳት ካፏ ነጥቄ።
"በሉ እሺ ልጆች መልካም ቀን ታዲያ እየተጠነቀቃቹ"ብሎ ስሞን ወጣ ከቡርቴ ጋር መወጣቴ እንዳስደሰተው አና ምን ያህል እንደቀለለው ሳይ ደስ አለኝ።አባቴ አንዲ ነው ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ፍቅር መስጠት እና ሰውን መውደድ አይሰስትም አያልቅበትምም።ብዙዎች ሀብታሙ ፓስተር ይሉታል።በርግጥ የራሱ ስራ ያለውና ደሞዝተኛ ነው።ከዛ ውጪ ትጉህ አገልጋይ እና ታታሪ ሰራተኛ ነው።ብዙ ጊዜ በአንድ ቤተ/ያን መገደብ ስለማይወድና ከሁሉም ጋር ህብረት ስለሚያደርግ በዚ ሰዎች ይተቹታል ሆኖም አባቴን ግድ ሰቶት አያውቅም ምክንያቱም ሲበዛ በአንድነት የሚያምንና ልዮነትና ክፍፍል የሚባል ነገር ስለማይወድ ነው።በቤተ/ያን ብቻ አይደለም አባቴ ሲበዛ በኢትዮጵያዊነት አንድነት የሚያምን ነው።ለማንም ሰው ስለብሔሩም ሆነ ስለዘሩ ሲናገር አትሰሙትም።የማይታመን ይሆናል ግን ለኔ እንኳን "እንትን ዘር ነኝ ስለዚ አንቺም እንደዚ ነሽ "ብሎኝ አያውቅም ለዛ እኔም ስለብሔሬም ሆነ ስለዘር ግድ ሰቶኝ አያውቅም።ከአባቴ የተማርኩት ምንም ትርጉምም ሆነ ጥቅም የሌለው ነገር መሆኑን ነው።ግን አባቴ ስለሁሉም ሰው ቢጠየቅ መልሱ "ኢትየጵያዊ ብቻ" የሚል ነው የሚሆነው።እኔም ስለነዚ ነገሮች ለማወቅ ጉቱም ፍላጎቱም አድሮብኝ አያውቅም ደሞም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያስብ የሚገባወና ሊይዘው የሚገባው አመለካከት ነው።ግን እንዴትና ለምን አንደሆነ ባይገባኝ በምማርበት ግቢ በአንድ ብሔር ተሰይሜ እና ተወክዬ ስቀጣ ነበር።ግን እነማን ነበሩ...? በምንስ ወከሉኝ...? መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ ነው።እነማንን መጠንቀቅ ይኑርብኝ እነማንን ማመን ይኑርብኝ እንኳ አላውቅም

በዚ ምክንያት ነው እስካሁን በፍርሀት እንድኖር የተገደድኩት።

አባቴ እንደወጣ ምን እንደማደርግ ቀድሜ እያቀድኩ ክፍሌ ገባውና ቀለል ያለ አለባበስ ለብሼ በፍጥነት ወደ ቡርቴ ሄድኩ
"ጨርሻለው!" አልኳት
ዞራ በአግራሞት ከላይ እስከ ታች አየችኝ።እኔም ግራ ገብቶኝ እንደገና አለባበሴን አየሁት ጅንስ ሱሪ፣ፓካወት እና ሸሚዝ ብዙ ጊዜ የማዘወትረውን እና ሚመቸኝን አለባበስ ነው የለበስኩት።
"ያጠፋሁት ነገር አለ? አለባበሴ ምን ሆነብሽ?"አልኳት
"አይ...ቶሎ..ጨረሽ ብዬ ነው"

"ልጅት ምን ሆነሻል ልብስ ስለብስ ጊዜ ፈጅቶብኝ አያወቅም ሁሌም እንዲ ነበርኩ"አልኳት ፊቷ ላይ የማየውን ስሜት ለመረዳት በጥንቃቄ እያየሗት።

"አይ ሔዊ ግን እኮ እንደዚ መልበስ ካቆምሽ ቆይተሻል"አለች።አሁን ገባኝ በራፍ ላይ እንደቆምኩ ለሴኮንዶች እያሰብኩ አፈጠጥኩባት እና ተጠግቻት
"ቢያንስ ለምን ያሀል ጊዜ..?"ጠየኳት።
"እንጃ 1...3 ዓመት እና ከዛ በላይ ይሆናል"
"እሺ ቡርቴ አንዳስታውስ እንድትረጂኝ እፈለጋለው አትረጂኝም...?"እጆቿን የዤ ጠየኳት።"
ሔዊዬ አንቺ አስታውሽና ደና ሁኝልኝ እንጂ ለምን ብዬ ነው ማልረዳሽ"
"ምንም ነገር ቢሆን የጠየኩሽን ታደርጊያለሽ?"
"ደስ ያለሽን" "ግን አባዬ ሳያውቅ ነው"
"ማለት..? ግን ለምን
👍51
#ሮዛ


#ክፍል_ሦስት (🔞)


#ሚስተር_ዊልያም_እና_ሚስስ_ ዊልያም


ተከታዩ ክስተት በሽርሙጥና ሕይወቴ እጅግ ለየት ያሉ ከምላቸው ገጠመኞቼ እንዱ ነው!

በአንድ ዝናባማ ጥዋት አልጋዬ ውስጥ እንዳለሁ ስልኬ አቃጨለ፡፡ የሞባይሌን ስክሪን ተመለከትኩት
Usman the pimp” ይላል፡፡ ሌሎች 4 ኡስማን የሚባሉ ደምበኞች ስላሉኝ ከነሱ ለመለየትእንደዚያ ብዬ
ነው ከሞባይሌ ማህደር የኡስማንን ስልክ save ያደረኩት፡፡ ሌሎቹን usman sudani usman Bahreni
፣usman exporter እና usman lecturer ብዬ መዝግቤያቸዋለሁ፡፡

ሄሎ ኡስማን እንዴት አደርክ?” “አልምዱሊላሂ ደህና ነኝ የት ነሽ!” “ቤቴ ተኝቻለሁ” “ኦ sorry! ከእንቅልፍሽ ስለቀሰቀስኩሽ ይቅርታ!” ( የኡስማን ትህትና ሁልጊዜም ይገርመኛል) ችግር
የለም! እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር ፤ውጪ ከባድ ዝናብ ስላለ ተነሽ ተነሽ አላለኝም” “ትንሽ ስራ ልሰጥሽ ነው፤ ካናዳውያን ባልና ሚስት ቦሌ አንድ የግል ገስት ሀውስ ውስጥ አርፈዋል፡፡
ብታገኚያቸው ምን ይመስልሻል?”

የልቤ ምት ጨመረ፣

“ማለት ባልየውን ብቻ አይደለም እንዴ ማግኘት ያለብኝ?”
“አይደለም ሮዚ ሁለቱንም ማግኘት አለብሽ! አዲስ አበባ ሲመጡ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፤ ባልና ሚስቱ ለደቂቃ
አይለያዩም፡፡ ከዚህ በፊት ኒና ነበር የምታስተናግዳቸው፡፡ ጥሩ ይከፍሉሻል ዛሬ አንቺ ብትጠቀሚ ብዬ
ነው፡፡ ሰሞኑን ተጎድተሻል፡፡”

ኡስማን ለወፎቹ ይጨነቃል፡፡ ደግ ነው፡፡ ኾኖም ባልና ሚስት በመሆናቸው የበለጠ ግራ ተጋባሁ፤ የልቤ ምት ጨመረ፤

“ይኸውልህ ኡስማን! ይቅርታ አድርግልኝና የሚስቱ ስራ ከባሏ ጋር ስናደርግ መሾፍ ብቻ ከሆነ ችግር
የለብኝም፡፡ ከዚያ ውጪ ግን አልችልም፡፡ “
“ሮዚ በደንብ ስሚኝ! ጥንዶቹ አዲስ አበባ ለሁለት ሳምንት ይቆያሉ፡፡ እንደነገሩኝ ከሆነ መደራረጉ
እንዳለ ሆኖ የመጡበት ዋና አላማ ግን ለዚያ አይደለም፡፡ የሚያነጋግሩሽ ጉዳይ አለ፡፡ እኔ ጋር የነበሩ ፎቶዎችሽን አይተዋቸው ወደዋቸዋል፡፡ቁመትሽ ሳይመቻቸው አይቀርም፡፡ ጉዳያቸውን ከተቀበልሽና ባሉት ከተስማማሽ ካናዳ ሞንትሪያል አብረሻቸው ትሄጂያለሽ”

የልቤ ምት ይባሱኑ ጨመረ፡፡ ሁለት ያልተፈቱ እንቆቅልሾች ከፊት ለፊቴ ተጋርጠዋል፡፡ በመጀመርያ የሚስትየው ወሲባዊ ዝንባሌዎ እንዴት ያለ ቢሆን ነው እኔን ማካተተ የፈቀደችው?ከወንድም ከሴትም ጋር ወሲብ የምትፈጽም Bisexual ልትሆን እንደምትችል ገመትኩ፡፡ ከዚህ በፊት «shemale) የሚባሉ ብራዚል የሚገኙ የወንድም የሴትም ዕቃ ያላቸው ሰዎችን በራኪ ሞባይል ላይ አይቼ ነገሩ ሊያስታውከኝ
ደርሶ ነበር፡፡ ሁለተኛውም እንቆቅልሽ ውስብስብ ይመስላል፡፡ ምን አይነት ዉለታ ብሰራላቸው ነው ፍቃደኝነቴን ከገለጽኩላቸው በሁለት ወራት ውስጥ ወደ አገራቸው ካናዳ የሚወስዱኝ?
የጠረጠርኩት የወሲብ ፊልም ሊያሰሩኝ ፈልገው ይሆናል ብዬ ነው፡፡ በፍጹም አላደርገውም።

“ኡስማንዬ ጉዳዩን አሁን ልትነግረኝ ትችላለህ?”

“ባውቀው እነግርሽ ነበር፤ ምንም የነገሩኝ ነገር የለም፡፡ በእርግጠኝነት የማውቀው ጥንዶቹ የናጠጡ
ሀብታሞች እንደሆኑ ብቻ ነው፡፡ ካስደሰትሽያቸው ለጋስነታቸው ወደር የለውም”

“ሁለቱንም ሳምንት በ«ገስት ሀውስ»ውስጥ አብሬያቸው ነው የምቆየው?” አንዳች ደስ የማይል ከባድ
ስሜት እየተጫጫነኝ ጠየቅኩት፤
“በፍጹም! ዛሬ «ቶፕ ሂል»ምሳ ይጋብዙናል፡፡ ከቤት ፒክ አደርግሻለሁ፡፡ ዛሬን አብረሻቸው ውለሽ ታድሪያለሽ፡፡ በተረፈ ሲደውሉልሽ ብቻ ነው ወዳረፉበት «ገስት ሃውስ>> የምትሔጂው፡፡ የሚከፍሉሽ ግን በ15 ቀን ሂሳብ ነው፡፡ ሚስትር ዊልያም እና ሚስስ ዊልያም ይባላሉ፡፡ በትዳር ከተጣመሩ 6 አመት
ሆኗቸዋል፡፡ "

“ሚስስ ዊልያም Bisexual ናት?” ብዬ ልጠይቀው አሰብኩና መጨቃጨቅ እንዳይመስልብኝ ከአፊ መለስኩት፡፡ ይህንን ብጠይቀው ኡስማን ገገማነቴ አናዶት እድሌን ለኒና አሳልፎ እንደሚሰጣት አሰብኩ
ያ ደግሞ የራሴን ብርሃን በገዛ እጄ እንደማጥፋት ነው፡፡ በምሽት በሰማይ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር
ከዋከብት ቢኖሩም አንደ ኮከብ “የጎረቤቴ ብርሀን ይበቃኛል” ብላ የራሷን ብርሃን አታጠፉም ''
በአጉል ውግአጥባቂነት ተሸብቤ ወርቃማውን እድል ለኒና አሳልፌ አልሰጥም፡፡ ካናዳ መሄድ እፈልጋለው
ኡስማን ከሁሉም ሴቶች አብልጦ ቢወደኝ ነው እድሉን እንድጠቀም አስቀድሞ እኔ ጋር የደወለው
ግብዣውን ውድቅ በማድረግ ኡስማንን ማሳዘን አልፈልግም፡፡

“አሪፍ ! ምሳ ሰአት ላይ ስልክህን እጠብቃለሁ፡፡ " በውስጤ በርካታ ጥያቄዎች እየተመላሰሉ ዘጋሁት፡፡

ኡስማን እኔን ከምኖርበት አፓርታማ ጥንዶቹን ደግሞ ከቦሌው ገሶት ሃውስ በመኪናው አሰባስቦን ሂልተን
ጋርደን ውስጥ ምሳ በላን ፡፡ ሂል ቶፕ ለመሄድ ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡ ጥንዶቹ ቀለል ያሉ ነበሩ ሙሉ
ሰአቱን በሂልተን ጋርደን እየተጨዋወትን አሳለፍን፡፡ ዛሬ የተገናኘን ሳይሆን ለበርካታ አመታት ያህል
የሚተዋወቁ ወዳጆች ነበር የምንመስለው፡፡

በእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዬ መደነቃቸውን አልደበቁኝም፡፡ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ሲመጡ ትልቁ ችግራቸው እንግሊዝኛን በቅጡ የሚናገሩ ሴቶችን ማግኘት እንደነበረም አጫወቱኝ፡፡ ሚስተር ዊልያም የጥርስ ሀኪም (Dentist) ነው፡፡ ሚስስ ስሚዝ የማህጻን ሀኪም ናት፡፡ ሁለቱም በካናዳ ጥሩ ዶላር ከሚያሳፍሱ ሞያዎች ውስጥ ይመደባሉ፡፡ በኔ ግምት የጥንዶቹ እድሜ ከአርባዎቹ መጨረሻ ወይም
ከሀምሳዎቹ መጀመሪያ አይዘልም፡፡

የዚያን እለት አዳር ለኔ አዲስ የወሲብ ተሞክሮ ነበር፡፡ ሚስቱ መላው ሰውነቴን እንደ ጣኦት ማምለክ ብቻ ነበር የቀራት፡፡ ሁለመናዬን ስታሽ፣ስትልስና ስትስም ነው ያደረችው፤ እንደ ፍርሃቴ አላገኘኋትም፤
ሴት ናት፡፡ ትርፍ ነገር የለባትም፡፡ በአርቴፊሻል የወንድ ብልት የምትወስበኝ መስሎኝ ነበር፡፡ ያ ስላልሆነ
ተደሰትኩ፡ የፈረንጅ የግልጽነት ባህል ገርሞኛል፡፡ “ሳላየው መወስለቱ ስለማይቀር እኔ ባለሁበት አብረን
ብንወሰልት ይሻላል" የሚል አይነት አቋም ያላት ትመስላለች ሚስቱ፡ በማግስቱ 500 የካናዳ ዶላሬን ተቀብዬ ቁርስ አብረን ከበላን በኋላ ከጥንዶቹ ጋ ተለያየሁ፡፡ ይሄን ከፍያ ወደ ኢትዮጵያ ብር ስተረጉመው ወደ 9000 ብር ገደማ ይጠጋል፡፡ እንዲህ ያለ ገንዘብ በጥቂት ሰአት ስራ በምን አገኛለሁ?እድሜ ለኡስማን! ሲመስለኝ ጥንዶቹ በጣም ተደስተውብኛል፡፡

ባሰኛቸውና ባስፈለጋቸው ጊዜ እየደወሉ በቀጣዮቹ ቀናትም ተመሳሳይ የሶስትዮሽ ደስታን አጣጣምን፡፡ በቆይታቸው በአጠቃላይ አምስት ሌሊቶችን እሳልፈናል፡፡ የሚፈልጉትን ዋና ጉዳይ በእሺታ እንድቀበላቸው ይመስላል በአምስተኛው ቀን 1000 የካናዳ ዶላር ሰጡኝ፡፡ ዉሀ ሆንኩኝ፡፡

«Roza, we know this is a lot of money for you, but not for us. If you agree on our proposal,
there will be much more money to flow to your purse, if you know what I mean"

ጠጠር ያለ ነገር ሊከተል እንደሆነ ገመትኩ፡፡

Sorry, what proposal are you talking about? Marriage Proposal or what?" ሁለቱም ተያይዘው ከሳቁ በኃላ…« actually it is more than that! አለችኝ ሚስትየው፡፡
ለካንስ 1000 ዶላሩ አንድ ሰአት ላልፈጀ ወሲብ ብቻ የተከፈለ አልነበረም፡፡ ጉድና ጅረት ከወደ በኋላ ነው

ይህ በእንዲህ እያለ የደነቀኝ ጥንዶቹ ለወሲብም ሲከፍሉ ዋጋ ይጋራሉ፡፡ አዋጥተው ነው
👍71👎1
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሦስት


#ራኪና_ለተብርሃን_ሲጠዛጠዙ

ራኪና ለተብርሃን ኮከባቸው አይገጥምም ኮከባቸው ብቻ ሳይሆን የሚያወጡት ወንድ አይመሳሰልም። ራኪ በለቲ ላይ ትናደዳለች። ለራሷ ክብር አትሰጥም፣ ከማንም`ቆለጣም ወንድ
እየተኛት ሴት ታሰድባለች” እያለች ትከሳታለች። ለተብርሃን (ለቲ) ደግሞ ሲበዛ የዋህ ናት። ሁሉም ወንድ እኔን ብሎ እስከመጣ ድረስ እኩል ነው ብላ የምታምን!

ለቲ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ራኪ በወንዶች ዘንድ ያላትን ተፈላጊነት አሳምራታውቀዋለች።ራኪ ሁል ጊዜ
ቢዝነስ መርጣ ነው የምትሰራው። ወንዶቹን እሷ ናት የምትመርጣቸው እንጂ እነሱ ስለመረጡ ብቻ አያገኟትም። በብር ሊደልሏት ከሞከሩ “ቢዝነሳቸውን ቀቅለው ይብዱት!” ትላለች፣ ካልጣሟት
አልጣሟትም ነው፤ በቃ።

አንድ ጊዜ ኃይለኛ ካድሬ ነኝ የሚል ጎረምሳ "ላዉጣሽ!” ብሎ ሲጠይቃት በጣም ተናደደችበት።ከዚያ ከቦርሳዋ ድፍን አስር ብር አውጥታ ጠርታ ሰጠችው። ግራ ገባው። … መጀመርያ እኔን ከመመኘትህ በፊት ይቺን ብሩ ላይ ያለችውን ሰፌድ የምትሰፋዋን ሴትዮ እያየህ ሴጋ ምታ" ብላ ሰው
ፊት አዋረደችው። ሁሉም ሰው ራኪ ያለቸውን ሰምቶ እየፈራ ሳቀ። ልጁ አበደ። ተንጎራደደ። ቤቱን ካላዘጋሁት ካድሬ አይደለሁም!” ብሎ ዛተ። መታወቂያውን አውጥቶ የቤቱን ባለቤት ሊያስፈራራ
ሞከረ። እርቃን ታስጨፍራላችሁ…የማናውቅ እንዳይመስላችሁ” ብሎ ሊከሰው ሞከረ። የሰማው
አልነበረም። እሱም እንዳልተፈራ ሲገባው ነው መሰለኝ ከዚያ በኋላ ዝር ብሎ አያውቅም። ወይም እኔ አይቼው አላውቅም።

ራኪ በጽዳት አትደራደርም። ከሷ አልፎ እኛንም ጸዳ ያሉ ቢዝነሶችን ታሰራናለች። የሆነ የሚያምር ልብስ ካየች ሺ ብር አውጥታ ገዝታ ትሰጠናለች፤ እንወዳታለን። የምር ጣጣ የላትም። ሁልጊዜም አዳዲስ የቢዝነስ መስክ የምትከፍትልን እሷ ናት። ዑስማን ዘ ፒምፕን እሷ ባትኖር ኖሮ የት እናገኘው
ነበር።

ሲነሳባት ግን እኛ ራሱ እንደማንመጥናት ከመናገር ወደኋላ አትልም።

«ስሚ! እንዳንቺ ኩሊ እንዳይመስለሽ ላዬ ላይ የሚጨፍርብኝ! የናትሽ አምስ» ትላታለች ለተብርሃንን።
ሁለቱ በነገር ሲተጋተጉ መስማት ያዝናናኝ ነበር። ለነገሩ እውነቷን ነው። ለቲ አይደለም ባለመኪና፣የላዳ ሾፌር እንኳ አውጥታ አታውቅም። ሰፊ እምሷን- ለሰፊው ህዝብ fair በሆነ ዋጋ እየቸረቸረች ትኖራለች፡፡በአንድ ሌሊት አነሰ ከተባለ ዘጠኝ- አስር “ሾርት” ትገባለች። ሲሳይ ራስታ በዚህ ጉዳይ
ሲቀልድባት «ለተብርሃን እኮ ከብዛት ነው የምታተርፈው» ይላል። ክፉ ልጅ።

ሲስ ራስታ» የሙሉ ጊዜ ስራው ሰውን መተረብ ነው። በትርፍ ጊዜው ነው ስዕል የሚስለው። ለቲን በሌላ ጊዜ ምን ቢላት ጥሩ ነው- ለተብርሃን! ለምን ግን አትክልት ተራ ቅርንጫፍ አትከፍቺም?»

ከሽንኩርትና ቲማቲም ጋር “ባብሿን እንድትቸርችረው በአሽሙር መናገሩ ነበር! ሲስ ነፍሴ ነፍሱ አይማርም።

ያኔ ትዝ ይለኛል በተናገረው ነገር ሁላችንም ከሳቅን በኋላ ደነገጥን። ለተብርሃን ይሰማታል በሚል ነበር
የደነገጥነው። ለቲ ቅስሟ የተሰራው ከቅል ነው። የዋህ ስለሆነች ቶሎ ይከፋታል ብለን አስበን ነበር

የደነገጥነው፡፡ እሷ እቴ የሲስ ንግግር ምንም አልመሰላትም፤ ወይም አልገባትም። " .እግዜር የሰጠኝ
ተመስገን ብዬ አድራለሁ፤ ለኔ ያለው የትም አይሄድም፣ አትክልት ተራ፣ ፍራሽ ተራ ምን ተራ አትበለኝ ሲሳይ እመቤቴ አለችልኝ ለኔ ያለውን ያለሁበት ድረስ ከቸች የምታደርግልኝ" አለች በሚተናነቃት አማርኛ።

ለተብርሃን ስታሳዝን፤ የሲስ ቀልድ እንኳን በትክክል የማይገባት የእግዜር ሴት-በግ።

ራኪ ደግሞ በተቃራኒው እድሏ ሆኖ ተራ ሰው አያወጣትም። ዕጣ ፈንታዋ የከበረ ድንጋይዋን በተከበሩ ሰዎች እያስቆፈረ ያኖራታል። ራሱን የሚጠብቅ ግልገል ባለስልጣን፣ በአጃቢ የሚያስጠራት ወፍራም ባለስልጣን፣ ጀማሪ ኢንቨስተር፣ አበባ የመሰለ የአበባ እርሻ ያለው ኢንቨስተር፣ እውቅ ኢንቨስተር፣
የኢንቨስተር ልጅ፣ ጥቁር መነጽር
የሚያጠልቅ ዲፕሎማት፣ አትሌት (አረብ አገር ብቻ ለሚሮጡ አትሌቶች ወይ ዋጋዋ እጥፍ ነው፤ ወይ አትወጣላቸውም)፣ ከርፋፋ አረብ፣ ብሸቅ አረብ፣ ሴታ ሴት
አረብ…፣ ነጭ ፈረንጅ፣ ጥቁር ፈረንጅ፣ ካሪቢያን፣ ብቻ እኔ ነኝ ያለ ሁሉ ዜጋ የራኪ ነው። ወይ በኡስማን ወይ በዝና ራኪ ጋ ይመጣሉ። እነሱን ነበር በየጊዜው የምታሾረው።

ምን ይሄ ብቻ! ከሷ ጋር ዉስኪ ስለጠጡ ብቻ የአዳር የሚከፍሏት ሚጢጢ ባለስልጣናት አሉ።ዲፕሎማት በመጣ ቁጥር ሂልተን ሸራተን ነው ዉሎና አዳሯ። ደግሞ ብትሞት ቆሸሽ ካለ ወንድ ጋር
አትወጣም። ጫማው ያልተወለወለ ወንድ ማየት ያንገሸግሻታል። አጭር፣ ወፍራም፣ ቦርጫም ወንድ በፍጹም አታወጣም። “ታፍኖ የሚሞት ወይ የሚፈነዳ ይመስኛል ትላለች። ይህ ኩራቷ በሁሉም ዘንድ
ይታወቅላታል። «ራኪ አይደለም እግሩ የሚሸት፣ካልሲው ነጭ ያልሆነ ደምበኛ ካጋጠማት ቢዝነሱን ትመልስለታለች እንጂ ጫፏን አይነካትም»ይባልላታል። ይሄ ዝናዋ ስለገነነ ወንዶች በጠራችላቸው ዋጋ ይሞቱላታል። ድሮም ወንዶች የተከለከሉት ነገር እንዳማራቸው ነው። ስንጠባረርባቸው ነው የኛ ዋጋ
የሚገባቸው።

ብቻ ራኪ ገጸ ባህሪ የምትመስል ሴት ናት። ሁሉ ነገሯ የሚጥም። እድል ዝም ብላ ትከተላታለች። አዱኛ ጭራዋን ትቆላላታለች። እሷ ምን ታድርግ! የራኪ እምስ እኮ ገና ሲፈጥረው የተባረከ ነው።በሰርጂን ዶክተር ባይከዳኝ ተመርቆ የተከፈ እምስ፣ ጣጣ የሌለው እምስ። ይኸው የዛሬ አምስት አመት ዶክተር
ባይከዳኝ ባርኮ የከፈተው፣ እስከዛሬ ሳይዘጋና ሳያዛጋ አንቀባሮ ያኖራታል።
"ሰርጀሪና" ሴክስ

ዶክተር ባይከዳኝ ሰርጅን ነው። ራሱን ከራኪ እምስ ጋር ስውር ሳይሰፋው አልቀረም። ሁለቱ በቀላሉ የሚፋቱ ሰዎች አልሆኑም። አሁንም ድረስ ይደዋወላሉ። ራኪም ከሱ ጋር በቀላሉ መለየት እንደማትችል ታውቀዋለች።

ዶክተር ባይከዳኝ
ላክምሽ እያለ አስገድዶ በዳኝ፤

ትላለች ገና ስልኩን ስታየው። “ሻርፕ” ነው ቀጠሮ ላይ። ቀን ቀን እንጂ በማታ አውጥቷት አያውቅም ነበር። ቅዳሜ ከሰዓት ነው ፍሪ የሚሆነው። ለአንድ ለሁለት ሰዓት ያህል ነው ታዲያ ፍሪ የሚሆነው። ካለችበት ፒክ አርጓት ወደያዘው ሆቴል እያከነፈ ይወስዳታል።በጂፑ። ሆቴል የሚይዘው ቀጥሎ ለሰርጀሪ ከሚሄድበት ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል ቅርብ የሆነውን መርጦ ነው። ብዙ ሆስፒታል ነው የሚሰራው። ሕይወቱ ሁልጊዜም ሩጫ የበዛበት ናት። ነጋ ጠባ ሰርጀሪ ነው። እኔ ግን እንዲህ
እየተጣደፈ ሰርጀሪ» የሚሰራ ከሆነ ስንት መቀስ የሰው ሆድ እቃ ውስጥ ረስቶ ሊሆን እንደሚችል እያሰላሰልኩ ይዘገንነኛል።

ራኪን አንድ ቀን ጥድፍድፍ አርጎ ይዟት ሲሄድ አይቼ ደወልኩላትና…«አንቺ ይሄ ዶክተርሽ ሳየው ቀልብ የለውም፤ እምስሽን እሱ የቀደደው መስሎት በተኛሽበት ግጥም አርጎ እንዳይሰፋልሽና ጎሮሮሽን እንዳይዘጋው» ብያት ስልኩን ዘጋሁት። ከአፍታ በኋላ መልሳ ደወለችልኝ፤ እስክስታ የሚያጅበውን ያን
ረዥም ሳቋን በረጅሙ ከለቀቀችው በኋላ ስትጨርስ “አንቺ አይጥ! ያልሽኝን ነገር ባይከዳኝን ነግሬው ምን እንዳለሽ በሰማሽ?”

“አንቺ! ለምን ነገርሽው? ስታስጠዪ! ምን አለ ግን?” አልኳት

“…የራኪ ቫጃይና… is too tight to forget any” ብሎሻል።”

በስልኩ ውስጥ ዶክተር ባይከዳኝ በራሱ ቀልድ እየተንከተከተ ሲስቅ ይሰማኝ ነበር

«ለሰርጂንና ለአትሌት እያንዳንዷ ማይክሮ ሰከንድ ትርጉም አላት» ይላል ዶክተር ባይከዳኝ እውነቱን ሳይሆን አይቀርም ህይወቱ ውስጥ አንዲት ሰከንድ አትባክንም። ራኪ ራሷ«እሱ ባክሽ እኔን ሲበዳ
ብቻ ነው የሚረጋጋው
👍9
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_ሦስት


#በሜሪ_ፈለቀ


.."የአባቴን ገዳይ ገድዬ ነው ከሃገር የተሰደድኩት።" አለኝ ዳግማዊ ምንም የሚያስደነግጥ ነገር እንዳልነገረኝ ሁሉ በመሀከላችን የትራስ ድንበር አበጅተን በምንተኛበት አልጋ ላይ እንደተገደመ።

"ገድዬ ማለት? "

"በገንዘብ ተጣልተው የገዛ ጓደኛው ነው በስለት ወግቶ የገደለው።"

"ከዛስ?"

"ሰውየው እንዴት እንደሆነ ባላወቅነው ሁኔታ በሶስተኛው ወር ተፈታ።"

"ከዚያ በኋላ ያለውን?" አልኩት አስደንጋጩን የወሬ ክፍል 'ገደልኩት' ያለኝን ለማረጋገ። ደምስሩ ተገታተረብኝ። ፊቱ ተቀያየረ። የአሁን ትንግርት የሚነግረኝ ይመስል ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ነው የሚያወራው። ሲያወራኝ ተመሳቀልኩ። ስሜቱን ለመረዳት እየሞከርኩ ስሜቴ ተሳከረ። ልክና ስህተት ውሉ ተጣረሰብኝ።

አባቱ ሲገደሉ በአይኑ አይቷቸዋል። በራፋቸው ላይ ነው የተገደሉት። ዳግማዊ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት በሚወስደው ጭር ያለ ቀጭን መንገድ እየገሰገሰ ሰፈር ሲደርስ ከወዳጃቸው ጋር እየተጓዙ አባቱን በርቀት አይቷቸዋል። እንዲያዩት ስላልፈለገ ወደ ኋላ ቀረት ብሎ ከአይናቸው ሰወር አለ። ቤታቸው መግብያ ጋር ሲደርስ የተቃቀፉ መስለው። ብዙም ሳይቆይ ግን አባትየው ወደቁ። ወዳጃቸው አካባቢያቸውን ቃኘት እያደረጉ ከሩጫ ባልተናነሰ ፍጥነት ከዳግማዊ በተቃራኒ አቅጣጫ መሄድ ጀመሩ። ዳግማዊ እየሮጠ አባተቱጋ ሲደርስ ጣር ላይ ነበሩ። ከደረታቸው የሚፈስ ደማቸውንና በእጃቸው ፍራፍሬና የተጠቀለለ ኬክ መያዛቸውን እኩል ቃኘው። የቅድስት አሰራ አምስት ዓመት ልደት በዓሏ ነበር። በጣር ስቃይ ውስጥ ሆነው እጁን ጨብጠው ቤተሰቡን እንዲንከባከብ ለመኑት። ዳግማዊ ገዳያቸውን ከመከተልና አባቱን ከማንሳት የቱ እንደሚቀድም ግራ ገብቶት ዋለለ። በደመ ነፍስ የእናቱን፣ የእህቱን፣ የኸንድሙን፣ የሚያስታውሰውን ሰው ስም ሁሉ በጩህት ተጣራ።

"እናቴ የኔን ጩህት ሰምታ ስትሮጥ ከቤታችን መግቢያ ደረጃ ላይ ወድቃ እግሯ ተሰብሮ ነው ስታነክስ ያየሻት" አለኝ እያንዘፈዘፈው።

ገዳይ የተፈቱት ገና የፍርድ ሂደቱ እንኳን ሳያልቅ ነበር። ይመለከተዋል ላሉት አካል አቤት አሉ። አቤቱታቸው መልስ ከማግኘቱ አስቀድሞ ገዳይ ሀገር መቀየረቻው ተሰማ። ዳግማዊ ተከተላቸው። የአባቱን አገዳደል ተመሳሳዩን አድርጎ ወደ ሱዳን ተሰደደ። ቤተሰቡም የሚኖርበትን የደብረ ማርቆስ ከተማ ጥሎ ናዝሬት ከተማ።

"አንዳንዴ ህይወት ፍትህ አታውቅም። ይሄኔ ፍትህን በራስ እጅ መስጠት! !" አለ ከቀድሞው ተረጋግቶ።

"ለዚህ ነው ቤተሰቦችህ እንደ መሲህ የሚያዩህ? " አልኩት ያልኩት ተገቢ መሆኑ ግራ እያጋባኝ።

አባቱ ከሞቱ በኋላ በአባትየው የእህል ንግድ ይተዳደር የነበረው ቤተሰብ ውጥንቅጡ ወጣ። ዳግማዊ ለአራት አመታት እዚህ ግባ የማይባል ኑሮ ሱዳን አገር አንገላታው። ይሄኔ ቢኒያም ትምህርቱን አቁሞ እህቱንና እናቱን ማስተዳደር ግድ ሆነበት።

"ባንተ ቦታ ሆኜ ስሜቱን አላውቅም። ግን በምንም ሂሳብ ጠፋት በጥፋት ተጣፍቶ መልሱ ልክ አይመጣም።" አልኩት።

"አንዳንድ ጥቃትና መቀማጥሽ በይቅርታና በተፃፈ ህግ እንደማይዳኝ የሚገባሽ ባሏን ለተቀማች እናቱና አባታቸውን ላጡ ታናናሾቹ ብቸኛ ተስፋቸው የሆነ ወንድ ልጅ ሆነሽ ስታይው ነው። አለኝ።

"ሳትገባኝ ቀርተህ አይደለም።" አልኩት ስሜቱን የጎዳሁት መስሎኝ እጄን አሻግሬ እጆቹን እየዳበስኩ።

"እንደማልገባሽ ይገባኛል።" ሲለኝ የሳሎኑ በር ተንኳኳ እና ለመክፈት ተነሳ። ለምን እንደተከተልኩት ሳላውቅ ተከትየው ሳሎን ሄድኩ። ቢኒያም ነው። ተስተካክሎ መቆም እስኪያቅተው ሰክሯል። እናትየው ከመኝታ ቤታቸው ብቅ አሉ። ከመጣን አራተኛ ቀናችን መሆኑ ነው። ከአታካች የአራት ቀን መሰንበት በኋላ ዛሬ ቢኒያም ስላመሸ ሳንተኛ እየጠበቅነው ነበር።

"ደህና አደራችሁ? ማለቴ አመሻችሁ? አለ ሶስታችንንም ተራ በተራ እያየ። ዳግማዊ ተናዷል። እናት ከዝነዋል። እኔ ካለመዋሸት በሁኔታው ሳቄ መጥቷል።

"ደሞ ተጣላችሁ? " አሉ እናቱ።

"አልተጣላንም። ተጣላችኝ" አለ ቢኒያም በቁሙ ሶፋው ላይ እየወደቀ።

"ማናት?" ጠየቀ ዳግማዊ።

"አለችልህ የሴት ጉድ!!። መለሱ እናት ፍቅረኛው መሆኗን እና ከእርሷ ጋር ሲጣላ እየጠጣ እንደሚያመሽ አከሉበት። ቀጥለውም "ቢቆጠር ከፍቅራቸው ፀባያቸው ይበልጣል። ልጅቷም ብቻዋን አይደለችም የሆነ ጋኔን ቢጤ ያግዛታል። ልጁን ጂል እኮ ነው ያደረገችው።" እየተናገሩ ወደ መኝታ ቤታቸው ተመለሱ።

"አሁን ግባና ተኛ ጠዋት እንነጋገራለን።" አለ ዳግማዊ በቁጣ ወደመኝታ ቤት ለመግባት እየተነሳ።

"ዲጉ ግን ፍሪጅ ውስጥ ነበር እንዴ የከረምሽው?" አለ ቢኒያም ስካርና ሳቅ እየተቀላቀለበት። ዳግማዊ ዘወር ብሎ አየው።

"ማለቴ አልተለወጥሽም።" ሲለው እኔ ሳቄን ለቀኩት። ዳግማዊ እኔንም እሱንም በአንድ ዙር ገላምጦን ገባ። አታምኑትም!! ሰክሮ ሲለፋደድ እንኳን የሚፈታተን መስህብ አለው። ባልተሰማ ለማለፍ የሚከብድ ፍም ስሜት።

"ትልቅ ልጅ እኮ ነው ልትቆጣው ባልሆነ" አልኩት ዳግማዊን እንደቅድማችን እንደተጋደምን። በነገራችሁ ላይ ምንም ተፈጥሮ አያውቅም። የእኔ ምክንያት ዳግማዊ የሚያማልለኝ አይነት ወንድ አይደለም። የእርሱን አላውቅም።

"ቤች 'ፕሊስ' ከቤተሰቤ ጋር እንዴት መግባባት እንዳለብኝ ለኔ ተይልኝ!!" አለኝ እንደተለመደው ጀርባውን አዙሮ እየተኛ።

"አብረን እየዋሸን ነው አላልከኝም? ቤተሰባዊነቱንም አብረን እየኖርነው ነው።"አልኩት። አልመለሰልኝም። ራሱን የቤተሰቡ እረኛ አድርጎ መቁጠሩ ከእድሜው የበዛ ጭምት አድርጎታል።

ከነጋ በኋላ እንቅልፍ እንዲወስደኝ ስገለባበጥ አርፍጄ ተነስቼ ጎዳ ስገባ እታባ ቁርስ እያበሰሉ አገኘኋቸው እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ያለው አጥርና ገደብ ይጨንቃል።የተመጠኑ እና የተለመዱ ጨዋታዎችን ከመጫወት ያለፈ ቅርርብ የላቸውም።እዚህ ቤት መከባበር እና መፈራራት ድንበራቸው ተቀላቅሏል።አብሬአቸው ስቀመጥ ልቤ ምጥ ይይዛታል።
የክፍል አለቃ እነዳስጠነቀቀዉ ተማሪ እጄን ማጣመር ሁሉ ይዳዳኛል ገደባቸውን አፍርሼ ላወራቸው ብሞክርም መልሳቸው አጭርና ለሌላ ጨዋታ የማይጋብዝ ይሆንብኛል ።እታባ ቁርስ ማብሰሉን እንዳግዛቸው ስላልፈቀዱልኝ አገጠባቸው ሆኜ የባጥ የቆጡን አወራለሁ።አንድ ወሬ እጀምራለሁ። ሳልጨርስ ሌላ እጀምራለሁ በዝምታ ከስንት አንዴ ዓይኔን እያዩ ከመስማት ያለፈ አይመልሱልኝም ሁሉም ሰው ሌላን ሰው ወደራሱ የሚጋብዝበት ርቀት ገደብ አለው።ጭራሹኑ ማንንም የማያስደፍረው የራሱ ክልልም ይኖረዋል።እኔ ደግሞ መሰረታዊ ችግሬ የሰዎችን ድንበር መጣስ ደስ ይለኛል። አንድን ሰው ስቀርበውና ቀስ በቀስ አጥሩን እያለፍኩ መዝለቅ የቻልኩ ሲመስለኝ ክብረ ወሰኑን እንዳሻሻለ አትሌት ሀሴት አደርጋለሁ።

"በይ ባልሽን ቁርስ ደርሷል በይው።" አሉኝ እታባ ከወሬዬም ለመገላገል ይመስላል። ለዲጉ መልእክቱን ካስተላለፍኩ በኋላ የማደርገው ሳይገባኝ ወደ ቢኒ ክፍል አመራሁ። ባንኳኳ መልስ የለም። ደግሜ አንኳኳሁ።

"አቤት?" አለ ቢኒ በጎርናና አንደበት። ለመግባት ፍቃድ ሳልጠይቅ ነው የዘለኩት። አልጋው ላይ እንደተጋደመ ሲጋራ እያጨሰ ነበር።እኔ መሆኔን ሲያውቅ ሲጋራውን ለማጥፋት ፈጠነ። እንደ መአት የሚፈራው ሚሴቱ ነኛ!

"አጭስ ችግር የለውም። ጭስ አታባክን ።" አልኩት።

"ልግባ ወይ አይባልም እንዴ? ራቁቴን ብሆንስ?" አለኝ ቀልድ በመሰለ ቅሬታ።

"ጠባሳ አለብህ እንዴ ታድያ? ራቁትክን የሆንክ እንደሆነስ?" መለስኩለት ከንፈሩን
ወደ ጎን ሸፈፍ አድርጎ ፈገግ አለ። ከንፈሩ የሚያቀ
👍4
#የወርቅ_በርጩማውን_ፍለጋ


#ክፍል_ሦስት(የመጨረሻ ክፍል)


#በእንዳለጌታ_ከበደ


...እናቷ ቀጠሉ፡፡ « . . . እንዴት እየኖርኩ እንደሆነ ብታይልኝ! የሰፈር ሰው ያሾፍብኛል ብጤዎቻችን ሊያሳብዱኝ ደርሰዋል . . .»

«አሁን ደግሞ ምን ሆናችሁ? ማለቂያ የለው የናንተ ጣጣ!»

ገንዘብ አይደለም የጎደለብን ልጄ! ከአፍሽ
ነጥቀሽ አይደል የምታጎርሽን? ዕድሜሽን ያርዝመው እንጂ ስራ ከጀመርሽ በኋላ ሰፈርተኛ የሚቀናብን ሆነናል
ተንቀባርረን ከሰው ጋር እንቀላቀላለን በፊት የአፈር ገንፎ ይመስላሉ እያሉ ይሳለቁብን የነበሩ ሁሉ አሁን
አፋቸውን ይዘዋል፡ ዕድሜ ላንቺ!»

ጆሮዬን ቀስሬ ማዳመጤን ቀጥያለሁ:: የእናትና የልጅ የሹክሹክታ ድምፅ፡፡

ከየጣሪያው ስር ስንት አይነት አቤቱታ አለ? ስንት አይነት የተከፋ ልብ? ስንት አይነት አፅናኝ ያጣ ልቅሶ? ልብን የሚያጨልም መልሶ መላልሶ፡፡

«አጥሩን ኣሳጠርኩት:: ቤቱን አሳደስኩት:: አሁን ደግሞ ታናሽሽ ሊያገባ ነው አግዢው አላችሁኝ።ስንቱን ቀዳዳ ልሽፍን? እኔስ እማ? እኔስ! ... ለእኔስ?! »

በእንባ ሳትታጠብ አልቀረችም፡፡ ድምፅዋ ነገረኝ፡፡

«ከወንድምሽ ጋር ተጣልተናል ... ተኮራርፈናል! ባንቺ ጉዳይም ተቀያይመናል»

__«በእኔ ጉዳይ? ለምን?!»

«እህትህን ለምን ታስቸግራታለህ? . . .
ለኛ በመጨነቅ ዕድሜዋን ልትገፋ ነወይ!
· . . ስለው
"እኔ ትዳር ልመሰርት ስል ነው ወይ እንደዚህ አይነት እንድታመነታና እንዳትረዳኝ የሚያደርጋት ሃሳብ
የምታመነጨው?' ብሎ ተቆጥቶ አኮረፈ .

ዘሪቱ «እሺ አሁን እኔ ምን እንዳደርግ ነው
የምትፈልጊው?» አለች።

«የሰርግህን መሉ ወጪ እሸፍንልሃለሁ ብለሽ ደብዳቤ ጻፈለት፡፡ ቁጥርና ፊደል ታውቂበት የለ? »

«እንዴ? የወንድሜን የሰርግ ወጪ ለመሸፈንኮ ቢያንስ ሁለት ሶስት ዓመት መስራት አለብኝ ያውም የደሞዝ ጭማሪ ካገኘሁ! .. .ከየት አመጣለሁ እማ? .
በእርግጥ ታሳዝኚኛለሽ ግን ... »

አሳዘነችኝ፡፡ ይህቺ ከተወለደች ሃያ አምስት ዓመት ያስቆጠረች የማትመስል ሴት ስንት መከራ ተሸክማለች?
ቆይ ደሞዟን ...

«ለሱ አታስቢ!» አሉ እናቷ

«ለምኑ?»

«ለወንድምሽ ሰርግ ወጪ»

«ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው የማላስበው? እናንተ ሃሳባችሁን ሁሉ እኔ ጫንቃ ላይ ጥላችሁ አይደል በሰላም
ዕንቅልፋችሁን የምትለጥጡት?! መስራት
የሚገባችሁን ያህል ለመስራት ሰንፋችሁ በኔ ገንዘብ የከርሞ እቅድ ትነድፋላችሁ! ...››

« ይኸውልሽ ዘሪቱ፣ ጅማ ያሉት የቀርከሃ ሶፋ የሚሠሩ ወንድሞቼ ተደራጂበት፣ ነግጂበት ብለው የላኩልኝ ሁለት መቶ ብር አለ፡፡ ለወንድምሽ ' ለአንዳንድ
ጉዳይ ማሟያ' ብለሽ ትልኪለታለሽ፡፡ ከማግባትህ በፊት ስራ መያዝ አለብህ' ብለሽ - ገንዘቡን 'ተሳፈርበት ወደኔ
ናበት' ትይዋለሽ፡፡ ከኪስሽ እንዳወጣሽው እንጂ እኔ እንደሰጠሁሽ ወፍ እንዳይሰማ!»

አንዳንዴ የምታመነጨው ሃሳብኮ
«አይ እማዬ . . .

«ምን ላድርግ? ብቻሽን ስትለፊ እያየሁ እጄን አጣጥፌ አልቀመጥ! ... የምሰጥሽን ብር ከላክሽለት
ከተማ ገብቶ መስራት ብዙ ገንዘብ የማያስገኝ ይመስለዋል»

የተስማሙ መሰለኝ።

እኔም እፎይ ብዬ ዘሪቱ እንደማትሄድብኝ እርግጠኛ ሆኜ በባለቤቴ ሞት ምክንያት ያገኘሁትን ብር ምን መስራት እንዳለብኝ እያውጠነጠንኩ፣ የለውጥ ቀን ቅርብ
እንደሆነ አስተውዬ . . . ወደ መኝታ ቤቴ ልሄድ ስል ስልኩ ጮኸ።

ደነገጥኩ፡፡

በዚህ ሰዓት የሚደወልልኝ ከአስቴር ነው::
አስቴር ምን ሆና ይሆን? ስፈራ ስቸር ስልኩን አነሳሁት። ልክ ነኝ።

ረጅም የሆነ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ፡
«እቴትዬ!» አለችኝ:: አቤት ድምዕዋ ውስጥ ያለው ፍቅር! በናፍቆት የተሞላ ዜማ! እንደዚህች ያለችዋን እህቴን በባዕድ አገር እንድትጎሳቆል መፍቀዱ ምን ሆኜ ነው?

«ወዬ!»

‹ደወለልኝ!! »

«ጓደኛሽ?››

«አዎ! ከደቡብ አፍሪካ! ... አሳዘነኝ:: ተላቀስን፡፡

እንዳያሳስበኝ ብለ አጽናናኝ:: የተባባልነወን እፅፍልሻለሁ ... እሺ እቴትዬ!»
«አይዟችሁ ይነጋል . . .»

«እንዴት ነው እቴት ቤተሰብ አቤቱታ ማሰማት አልጀመረም? . . ባለፈው የሰራሁበትን ብር ሁሉ ለጓደኛዬ ላክሁለት፡፡ ከወላጆቹ የወረሰውን ቤት አሳድሶ በኮንትራት ለሆቴል አከራይቶት እኮ ነው፤ በደቡብ አፍሪካ አድርጎ አሜሪካ ለመግባት ስንቁን የቋጠረው! .
ስንደራጅ ቤቱን እኛ እንስራበታለን!»
:
«ይሁን እስኪ እንግዲህ . . .»

«እቴትዬ! . . . ሁልጊዜ እጠይቅሻለሁ ብዬ እየረሳሁ!»

«ምን?››

«ሰራተኛሽ ዘሪቱ አጫውታሽ ያዝናናሽኝ ያ
የወርቅ በርጩማ ነገር የት ደረሰ? ለወንድሜ ተበረከተለት?»

ተሳሳቅን::

«ለምን ጠየቅሽኝ?»

«ወደሃገር ቤት ስገባ የራሴን የወርቅ በርጩማ ለመስራት ላቤን ማፍሰስ እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ በከንቱ
ምኞት የሚገኝ ሳይሆን ጠንክሮ የመስራት ውጤት ነው ያ የወርቅ በርጩማ!»

ያለችበት ሃገር ስራን አለመናቅን አስተምሯታል፡፡ ሰው ትልቅ የሚባለው ጊዜውን በተግባር መተርጎም የቻለ እንደሆነ መሆኑን ዕውቀትና ልምድ ቀስማለች።ይሄ ነው ብላ ልታሳየኝ የማትችለው ዲግሪ እንደተበረከተላትም ተረዳሁ:: ከመሪር ሕይወት የተገኘ
ዲግሪ!

«አሪፍ ሃሳብ ነው!» አልኳት!

ትንሽ ቆይታ «እቴትዬ! መርሮኛል! ትንሽ
ሰራርቼ እመጣለሁ ላብድ ጥቂት ነው የቀረኝ ..በየጊዜው የጓደኞቼ ቁጥር ሲቀንስ፣በሙቅ ውሃ ሲነፍሩ፣
ከፎቅ ሲወረወሩ አሟሟታቸው ሲከፋ እያየሁ እንዴት እንዴት ሆኜ ነው እዚህ በሰው አገር የምኖረው »
አለችኝ።

« ለምን አትመጪም? ነይ እዚህ! ዛሬ ነገ አትበይ! እኛም በስጋት አለቅንኮ! የግድ ቤተሰቦችሽ እንዲያልፍላቸው ያንቺ ህይወት ማለፍ አለበት?»

«አይ እቴትዬ! ...ዛሬ ነገ ሳትይ ነይ' አልሺኝ?
ምን ይዤ? መጥቼስ ምን ሰርቼ ልበላ?!»
«አንድ የመጣልኝን ሃሳብ ልንገርሽ?» አልኳት ለጥቂት ደቂቃ ሳሰላስል ቆይቼ።

«ምንድነው?»

«ላበድርሽ ነው! መለስተኛ ንግድ ሊያስጀምርሽ የሚችል ብር! .. ጓደኛሽ በውርስ ያገኘውን ቤት ወደ
ንግድ ተቋም የመለወጥ ዕቅድ አላችሁ አይደል? እረዳችኋለሁ!»

«ከየት አምጥተሽ?» እንደተገረመች ያስታውቃል::

«ለማንም እንዳትነግሪ! . . . ቤተሰብም ቢሆን እንዳያውቀው! ባለቤቴ ይሰራበት የነበረው ድርጅት ኢንሹራንስ ከፍሎኛል፡፡ ስለዚህ እሰጥሽና - ገንዘቡን
ትሰሪበትና - ዕቁብ ገብተሽ ትከፍይኛለሽ .. .»

«አይ እቴትዬ!» ከድምፅዋ ሃሳቤን እንደወደደችው ያስታውቃል፡፡

ስልኩን ከዘጋሁት በኋላ ነው፣ መፍትሄውን
የኮረጅኩት ከዘሪቱና ከእናቷ እንደሆነ የታወሰኝ!

በተገማሸረ መስክ ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውሃ
. . እፎይ ብላ የተረጋጋች የምትመስለዋ
ህይወታችን መንቀሳቀስ የምትጀምርበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን ተሰማኝ፡፡
የዛሬዋን ማታ ወደድኳት፡፡

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#አቀበት


#ክፍል_ሦስት (የመጨረሻ ክፍል)


#በገበየሁ_አየለ

..የሚሰማ ነገር የለም፡፡ ዓይኖቻቸውን እሽጉ በር ላይ እንደተከሉ እራስጌያቸው ያለውን መጥረቢያ በዳበሳ አነሱና ጠበቅ አድርገው ያዙት:: እንደገና ጥቂት
ካዳመጡ በኋላ፣ "መተኛቴን ነው የሚያዳምጠው" አሉና ጉሮሯቸውን በመሞረድ ያለማንቀላፋታቸውን
የሚያመለክት ድምጽ አሰሙ።ቀጥለው ደግሞ በያዙት መጥረቢያ ዛቢያ ወለላቸውን መታ መታ አደረጉት።

"አልተኙም እንዴ አካሌ!" አለ ተካ ከሳቅ ጋር በተቀላቀለ አነጋገር፡፡ የመጠጡ ኃይል ምላሱን ትንሽ ያዝ ያድርገው እንጂ. ወፍራም ድምፁ ስልቱን
አልሳተም::

"አይዞት አይፍሩ እኔ ጠብቅዎታለሁ" ብሎ እንደገና ሳቀ::

"ከግንድ ያጣብቅህ" ለማለት አሰቡና ተውት፡፡

"አገር ቤት ነው የከረምኩት" አለ በረጅሙ
ተንፍሶ። የነገሩ አቅጣጫ ድንገት
በመለወጠ ቢገርማቸውም፡ መልስ አልሰጡትም::

"እማዬ እንደምንዎት ደህና ከረሙ ወይ በዓይነ ስጋ ለመገናኘት ያብቃን ብላዎታለች::"

"ደህና ናቸው? " አሉ እካሌ ድምጻቸውን ከፍ እድርገው።

"ደህና ነኝ” ትላለች የገጠር በተለያ የሷ አካባቢ ሰው ደህና አይደለሁም ማለቱን አያውቅበትም። ቃሬዛ ላይ እስኪጫን ድረስ ደህና ነኝ ነው የሚል፡፡ የትውልድ
ቀዬዬ ሰዎች ደህንነትን የሚለኩት ቆመው ከመሄዳቸው አንፃር ነው።

"እህህም" አሉ አካሌ "በ-ጄ ቀጥል » በማለት አኳኋን፡፡የተካ ጉዳይ ከማስረሻ ጉዳይ ወደሌላ በመቀየሩና አነጋገሩም የወዳጅነት በመምሰሉ ፍርሃታቸው ረገብ አለ።

"ታናሽ እህቴ በምጥ ሞተች፡ ሰባተኛ ልጅዋን ስትገላገል፡፡ እኔ እዛው ሆኜ ነው የሞተችው:: አጎቴን ወባ ገላገለው:: እማዬ የአጎቴን ሞት ስታረዳኝ `አረፈ
አለችኝ፡፡ አረፈ ለአካባቢው አገላለጥ ትክክለኛ ቋንቋ ነው:: በችጋርና በበሽታ እየተገረፈ ለሚኖር ሕዝብ፡ ሞት እረፍት ነው: ግልግል:: አይደለም እንዴ አካሌ?"
አለ ድምጹን ከቀድሞው ጎላ አድርጎ።

“እህህም" ብለው ዝም አሉ:: የተካ ንግግር ቀስ በቀስ ወደ አንጀታቸው የሚገባ ቀዝቃዛ ስሜት አሳደረባቸው።

« ሰውን አረገፈው' ትላለች እማዬ ፡ ሞት
በአካባቢው ያለውን ብርታት ስትገልጥ፡፡ እገሌንና እገሌን ተስቦ ወሰዳቸው እገሌ በደም ተቅማጥ አረፈ፣ እገሌን ወራጅ ውሃ ወሰደው፣ ያን የመሰለ ጉብል ፣ 'እናቱ በሀዘን አብዳ መቃብር ቤት ነው እምታድር .. ከብቱ ሣር አጥቶ አለት እየጋጠ በየሜዳው ተፈነቸረ' "ትላለች።

"አቤት አቤት፣ ይሄ ከላይ የመጣ መዓት ነው" አሉ አካሌ ማቃሰት በሚመስል ድምጽ፡፡

"እማዬም እንዲሁ ነው የምትል:: የአገሩ ሰው በየቤተክርስቲያኑና መስጊዱ እየተሰበሰበ "እግዚኦ ከዚህ
መዓት ሰውረን" እያለ አምላኩን በመማጠን ላይ ነው::"ብሎ ካዛጋ በኋላ እንደመሳል አለና፣

"የእማዬ አገር ሰዎች አሟሟትን ያውቁበታል፡አንቀላፉ እንዴ አካሌ?» አለ።

"ኧረ ሰማሀለሁ አሉ ሀዘን በተጫነው ድምጽ፡”

በቁሙ ነው ሞትን የሚጀምረውም የሚጨርሰውም።

"እንዴት? "

'ከችጋር ጋር ስለሚኖር ረሀብ ገደለኝ አይልም፡፡ጠኔ ሲያንገላታው መገጣጠሚያ አንጓዎቹ ሲላሉ፡ በሌላ
በሽታ አመካኝቶ ጣጣቴ እየተተኮሰ፡ ሳንባው ከጀርባው ተጣብቆ መተንፈስ ሲያቅተው ፡ በዋግምት እየተነጠቀ. እንዲያ እንዲያ እያለ ይሞተዋል።

ይሰሙኛል?»

"አዎን እሰማሀለሁ"

"ሽዋዬ እንደሞተች እናቴ ዘንድ ሄድኩ፣ ሞትን እዚያ ሆኜ ልጠብቀው ብዬ:: ለካ ሞት ወደነገሰበት ሥፍራ ኖሯል የሄድኩት:: ፊት ለፊት የተገናኘሁት
እስኪመስለኝ ድረስ በሥራው አየሁት፡፡ በችጋርና በደዌ ፈረስ እየጋለበ ሕዝቡንና ከብቱን ፈጅቶታል፣ አገሩን ወና አድርጎታል፡፡"

"ሞትን ተሸክሜ እንደሄድኩባት ያልጠረጠረችው እናቴ ምን አለች መሰለዎት" ብሎ እንደማሰብ አለና፣
ለወራት ከተኛችበት መደብ ላይ ቀና ብላ፣ የፈዘዙ ዓይኖቿን እያንከራተተች፣ ማመን አቅቷት እንደ እንሰት በደረቁ እጆቿ እራሴንና ፊቴን እየደባበሰች፣ ቀባሪ
ያላሳጣኸኝ ፈጣሪ ተመስገን፡፡ በመሞቻዬ ዋዜማ የልጄን ዓይን አሳየኸኝ' አለች፡፡ ድምጽ አጣች እንጂ እልል ለማለትም ሞክራለች፡፡ በደረቁ ከንፈሮቿ ፊቴን፣ እራሴን የአንገቴ ሥር ሁሉ ሳመችኝ ከመኪና ተራ የገዛሁትን ደረቅ ዳቦ በውኃ እየነከርኩ ሳጎርሳት በስስት ቶሎ ቶሎ
በላችና፣ 'ተመስገን አምላኬ፣ እንደኔ ማንን አድለሃል በቃ አሁን ጠግቤአለሁ የሞት ስንቄን አግኝቻለሁ፣ቀባሪዪም መጥቷል፤
ቶሎ ውሰደኝ አለች::"

"እኔን እኔን እንዴት ተጎድተው ኖሯል? " አሉ አካሌ ከልብ በሆነ ሀዘኔታ፡፡

"ፀሎቷ አልተመለሰላትም፤ እስከዛሬ አለች::"ብሎ ትንሽ ዝም አለና ለጉድ የጎለተኝ' ትላለች እማዬ ስለራሷ በምትናገርበት ጊዜ፡፡ «የመከራ ምስክር አድርጎኛል ጎተራዬ ሙሉ፣ በረቴ በከብት ትንፋሽ የሞቀ፣ ቤቴ የርሃብተኞች መሸሻ እንዳልነበረ ሁሉ የችጋርና የሞት ምሳሌ ሆኛለሁ" ትላለች፡፡ «እየሰሙኝ ነው አካሌ?»

«አዎን፣ ሰማሃለሁ::»

"እንዲህ ሆኖ አገኘሁት፣ የእማዬንና የአካባቢዋን ሁኔታ:: እኔማ በድብቅ የምሞትበትን ሥፍራ መርጨ
ነበር ወደዚያ መሄዴ፡፡ ሀገሩ ግን የሚሸሹት እንጂ የሚሸሽበት አልሆነም፡፡ እኔ ውስጥ ካለው ሞት ይልቅ፣እዚያ ያለው ገዝፎ ታየኝ፡፡ የሞት መላእክት ትዕዛዝ ለመፈጸም በየተራራው አናት ላይ በተጠንቀቅ ቆመው ቁልቁል የሚመለከቱ እስኪመስል ድረስ ነው፣ አካባቢው
የሚያስጨንቀው:: ለዚህ ነው ሸሽቼ እንደሄድኩ የመጣሁት:: ሕይወት ካለ ተስፋም መኖሩ ተሰማኝ፡፡አንድ ቀንም ዕድሜ ነው አልኩ፡፡ ነገ የተሻለ ነገር ይዞ
አይመጣም ያለው ማነው? ብዬ አሰብኩ፡፡ የሞትን ሹክሹክታ ከማዳመጥ ይልቅ፣ ተስፋን ማዛጋት ጥሩ ሆኖ ታየኝ፡፡ ተስፋ ሲሞት ነው እውነተኛው ሞት::
አይደለም እንዴ አካሌ?››

"ነው እንጂ! እኔ እምልህ ተካ'

"እመት"

“እውን መንፈቁን በሙሉ እናትህ ዘንድ ነበርክ?"

"አዎን"

እንዴት ብትጨክን ነው ብቅ ብለህ እንኳን ሳታየን መክረምህ?

"ጨክኜ አይደለም አካሌ፣ እንደሞትኩ ቆጥራችሁ እንድትረሱኝ ፈልጌ ነበር፡፡ በተለይ ሚጣዬ እናቷን እንዳጣች ሁሉ እኔንም እንደሌለሁ ብትቆጥረኝ ይሻላል
ብዬ አሰብኩ፡፡ እናቷን ስታጣ ተሳቀቀች፣ እኔ ስለያት ደግሞ ለምን ትደንግጥ? በተለይ ይበልጥ ከተላመደችኝና
የአባትነቴ ትርጉሙ ከገባት በኋላ ስታጣኝ፣ ሀዘኗ መሪር ይሆናል በማለት ነበር

"ቀድሞ ሟቹን እግዜአብሄር ነው የሚያውቀው:: ደግሞም ቅድም እንዳልከው ደግ ደጉን ማሰብ ይሻላል"
አሉ አካሌ፡፡

"ደግ ደጉን በማሰቤ ነው መንገዴን የቀየርኩ"

"ይሻላል ደጉን ማሰብ፣ ደጉን ማድረግ. .

"ደጉን መኖር" አለ ተካ ፈጠን ብሎ ጥቂት ዝም አለና ደግሞ፣
"ታዲያ እርስዎ ስለኔ ለምን ደግ አያስቡም? " አለ

ዝም አሉት አካሌ፡፡

"አካሌ"

"ወይ"

"ስለኔ ደግ አያስቡም? "

"ስለራሱ ደግ ለማያሰብ ሰው እንደምን ደግ ይታሰብለታል?

እንዲህ ሲወያዩ እኩለ ሌሊት አለፈ:: አካሌ ሀሳባቸውን ወደ ክፍላቸው ሰብሰብ አድርገው ሲመለከቱ፣
ጨብጠውት የነበረ መጥረቢያ ከእጃቸው ተንሸራትቶ መሬት ወድቋል፡፡ ወደ ማስረሻ ተመለከቱ፣ ከእንቅልፉ ከነቃች የቆየች ትመስላለች፡፡ ዓይኖቿን በሰፊው ከፍታ
ታያቸዋለች:: አልጋው ላይ ወጡና ዘና ብለው በመተኛት አቀፏት::

"ስለ ራሴም ሆነ፣ ለእርስዎና ለማስረሻ መልካም ማሰቤን በተግባር አሳይዎታለሁ አካሌ" አለ ተካ ሲያሰላስል ቆይቶ:፡ ኣካሌ ዝም ብለው የማስረሻን ፊት አንሶላውን እስከደረቷ ዝቅ አደረገችው::

"አይግፉኝ አካሌ" አለ ተካ ድምጸን ለዘብ አድርጎ

ውይይታቸውን ማስረሻ እንድትሰማው ስላልፈለጉ ዝም አሉት

አይግፉኝ፣ ዕድል
👍3
#ቅበላ


#ክፍል_ሦስት


#ከአዶኒስ

...ውቃቢ እስኪርቀው የቁጣ መዓት ካወረደችበት በኋላ ዳግም
“እንዲህ ዓይነት ነገር” ሲያደርግ የሷና የሱ “መጨረሻ” እንደሚሆን አስጠንቅቃው ነበር ጭራውን ቆልፎ ወደ
ትምህርት ቤት የሄደው፡፡ ያም ሆኖ ማሙሸት ቢያንስ የአቅሚቲውን ያህል ለእናቱ ፍትህን ለመስጠት እንደሚያስችለው አጥብቆ ያመነበትን ይህን ነገር በቀላሉ ወደጎን ሊለው አልቻለም። ለእናቱ ማሳወቁን ብቻ
ይተውና ድርጊቱን ይቀጥላል፡፡ አጋጣሚው አመቺ መስሎ በታየው ጊዜ ሁሉ የእንግዶቹን ኪሶች መፈተሽና
እንደየሁኔታው አምስትም አሥርም እየመዘዘ በሚስጥር ማጠራቀም ይጀምራል፡፡

ማመሽት የእናቱን እንግዳዎች ኪስ ዘና ብሎ ለመፈተሽ የሚያስችለውን አስተማማኝ ስዓት ከልምድ አውቆታል፡፡ የዕለቱ እንግዳ የሆነው ሰው የመጣበትን
ጉዳይ ሊጨርስ አፍታዎች ሲቀሩትና አቅሉን ሙሉ በሙሉ ሊስት የሚያደርገውን ልጓም አልባ እንቅስቃሴና
የሚያወጣውን ያልተለመደ ዓይነት ድምጽ እንደሰማ ማሙሸት እጁን መሰስ አድርጎ በመላክ የሰውዬውን ኪሶች አንድ በአንድ ያብጠረጥርና የሚወስደውን ያህል ወስዶ የልብሶቹ አቀማመጥ ልክ እንደነበረው መሆነን ያረጋግጣል።

ታዲያ እናቱ በባሰባት በባሰባት ጊዜ ከአንድ የሃብታም ልጅ ከሆነና በየጊዜው
ከሚረዳው ጓደኛው አመጣሁ እያለ በዕለቱ ያስፈለጋትን ያህል ገንዘብ
ይሰጣታል።ለትምህርት ቤቱ የሚያስፈልገውን ወጪም ራሱ መሸፈን ከጀመረ ከራርሟል፡፡ የኋላ የኋላ ግን ፀዳል ሚስጥሩን ትደርስበታለች፡፡ ይሁን እንጂ ደጋግሞ ከጉድ ያወጣትንና አንድም እንግዳ ገንዘብ ጠፋኝ ብሎ አማርሮ የማያውቅበትን ይህን ረቂቅ የገንዘብ ምንጭ አጉል ነካክታ
ማድረቅ ርባናው አልታይ ይላታል፡፡ እንደውም ውሎ አድሮ ነገርየው እየጣማት ሲመጣ እንግዶቿ ልብሳቸውን
አውልቀው የሚያስቀምጡበትን ወንበር እንደዘበት ለማሙሽት በሚያመቸው ሁኔታ ወደ አልጋው ጠጋ ማድረግ ጀመረች ይህ ሁሉ ሲሆን እናትና ልጅ
ይህ ሁሉ ሲሆን እናትና ልጅ “ውሾን
ያነሳ ውሾ ይሁን” ዓይነት ስለጉዳዩ በይፋ ለመነጋገር ደፍረው አያውቁም:: ፀዳል ነገሩ እንደገባት ማሙሽት ያውቃል - እንደሚያውቅ እሷም ታውቃለች፡፡ ታዲያ
በሚቻላት ሁሉ ማሙሸት ራሱ አስቦ እስኪሰጣት ትጠብቃለች እንጂ አፍ አውጥታ አትጠይቀውም። አልፎ
አልፎ ሁሉ ነገር ጭልምልም ሲልባት ብቻ ምሬቷን ማጉተምተምና በትንሽ በትልቁ መነጫነጭ ትጀምራለች::
ይሄኔ የሁለታቸውን ብቸኛ ቋንቋ እያወራች እንዳለች የሚገባው ማሙሸት ወደ “ጓደኛው ይሄድና ገንዘብ ይዞላት ይመጣል።

ሰዓቱ ወደ እኩለ ሌሊቱ እየገፋ ሲሄድና የዕለቱ ተስፋዋ በእጅጉ እየተመናመነ ሳለ ነበር አንድ እንግዳ ድንገት ከጥቁሩ ሰማይ ዱብ እንዳለ መና ከበራፉ ገጭ ያለላት፡፡ እሷና ማመሽት ወጡ እንኳን ቢቀርባቸውቢያንስ ጥብስ ጠበስ አድርገው ጦማቸውን ለመያዝ በቂ ጊዜ እንዳላቸው ገመተችና በሆዷ ተመስገን አለች፡፡ሰውየው ከዚህ በፊት አንድ ሶስቴ ያስተናገደችው ሰው ነበረና ሞቅ ባለ ፈገግታ ተቀበለችው። በራፏ ላይ
እንደተቀመጠች አልፏት ወደ ውስጥ የዘለቀው ይህ እንግዳዋ ከአልጋዋ ጎን ካለው ብቸኛ ወንበር ላይ አረፍ አለ፡፡ ሞቅ ያለው ይመስላል:: ፀዳል ወዲያው ብድግ ብላ በሯን ቀረቀረችና ፀጉሯን በጣቶቿ እያፍተለተለች ዝግ ባለ አረማመድ ወደ እንግዳዋ በመቅረብ አልጋዋ ጫፍ ላይ ተቀመጠች::
"""
“ምነው ጠፋህ? አለችው ፈዘዝ ካለ ፈገግታ ጋር፡፡ ወደሷ ሲመጡ የመጀመሪያቸው ላልሆነ እንግዶች
ሁሉ እንደ ንግግር መክፈቻ የምትጠቀመው የተለመደ ጥያቄዋ ነው።
“እንዴት አልጠፋ ከዚህ ያልጠፋሁ ከየት
ልጥፋ?” አላት የጃኬቱን ቁልፍ እየፈታ እምብዛም የጨዋታ ቃና በሌለው አንደበት።
“እንዴ ምነው? - አጥፍቼም ከሆነ ካሺኝ
ይባላል እንጂ እንደው ዝም ብሎ ይጠፋል እንዴ?”አለች ለዛዋን በጥንቃቄ እየመከነች::
“እሱማ ትክሺኛለሽ - ወደሽ ነው የምትክሺኝ?”
አለ የጫማዎቹን ክሮች ተራ በተራ እየፈታና ባቀረቀረበት ከራሱ ጋር የሚያወሪ ዓይነት።

“ሃሃሃ! - ወድጄማ ነው።

ነ..... ው?” አላት ጫማዎቹን እያወለቀ፡፡
“አዎና..ሃሃሃ! - ሳይወዱ ካሳ አለ እንዴ?”
“ሴትዮ ለወሬ አይደለም የመጣሁት
ይልቅ ተዘጋጂ ብድግ ብሎ ሱሪውን ካወለቀና ካጣጠፈ በኋላ ወንበሩ ላይ አስቀመጠው:: ጃኬትና ሸሚዙንም እዚያው ላይ ከደረበ በኋላ ወንበሩን ብድግ በማድረግ ከአልጋው አርቆ ትይዩ ካለው ግድግዳ ጥግ አስቀመጠና ወደ
አልጋው ተመለሰ፡፡ ሰውዬው ጨዋታ ጨዋታ እንዳላለው የተረዳችው ፀዳል ያለ ምንም ተጨማሪ ቃላት ልብሶቿን አወላልቃ ጣለችና አልጋዋ ላይ ወጣች።

በአገልግሎት ብዛት የተዳከመው የፀዳል አልጋ የተለመደውን ዓይነት የማቃሰት ድምፅ ማሰማት ሲጀምር የማሙሸት ጆሮዎች ሙሉ በሙሉ በመንቃት ለክትትል ተዘጋጁ:: የእናቱን እንግዶች በድምፃቸው ብቻ የመለየት ችሎታው ከእለት ወደ እለት እየሰላ ለመጣው ለማሙሸት የሰውየው ድምፅ አዲስ አልሆነበትም:: ጥቂት እንዳሰላሰለ
በትክክል አስታወሰው:: ከጥቂት ሳምንታት በፊት እንዲህ እንደዛሬው አምሽቶ መጥቶ ነበር።ታዲያ ያን ዕለት
ከዚህ ሰው ኪስ ሃያ ብር ቀንጭቦ እንደነበር ማሙሸት ትዝ አለው።ዛሬም የዚያኑ ያህል ምናልባት ዕድል ከቀናችውም የተሻለ - እንደሚያገኝ ተስፋ አደረገ፡፡ ሙሉ ቀልቡን ከበላዩ እያቃሰተ ወዳለው አልጋ አድርጎ ማዳመጥና መጠባበቅ ጀመረ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያቺ ማሙሸት
የሚጠብቃት አመቺ ቅፅበት ደረሰችለት:: ወዲያውኑ በዝግታ እጁን መሰስ አድርጎ በማውጣት መደባበስ ጀመረ:: እንኳንስ የሰውዬው ልብሶች ወንበሩ ራሱ በቦታው
ያለመኖሩን ሲረዳ ግራ ተጋባ፡፡ የአልጋው ላይ ሁካታ ይብሱን እየደመቀ መጣ፡፡ ማሙሸት በዝግታ በደረቱ፡ እየተሳበ ወደ አልጋው ጠርዝ ተጠጋና ወለሉ ድረስ
የተንዠረገገውን የአልጋ ምንጣፍ፡ በጥቂቱ፡ ገለጥ አድርጎ ተመለከተ። የሰውዬው ልብሶች የተቀመጠበት ወንበር የአድማስ ያህል ርቆ ታየው:: እንደገና የኋሊት እየተሳበ ወደነበረበት ተመለሰና በደረቱ ለጥ እንዳለ የዕለት
ዕድሉን ክፉኛ ረገመ።ሰውዬውን እንደ አባቱ ገዳይ ጠላው:: አሁን ቀረ የሚባል ተስፋ ካለ ያቺው ሰውዬው ለእናቱ የሚወረውርላት አምስት ብር ናት:: ምኗን
ከምኗ አድርጋ ቅበላዋን እንደምትወጣው ስለ እናቱ እየተጨነቀላት ሳለ ከበላዩ ይካሄድ የነበረው ግርግር ጋብ አለ።

ቀድሟት ከአልጋ ወርዶ መለባበስ የጀመረው የፀዳል እንግዳ ጫማውን እያጠለቀ ነው:: እሷ ግን ገና ዱሮ ጥንቅቅ ብላ አልጋዋ ጫፍ ላይ ቁጢጥ
ብላለች:: እጆቿን ደረቷ ላይ እንዳጣመረች ነገረ ነገሩ ሁሉ ያላማራትን የዚህን ሰው እንቅስቃሴ አንድ በአንድ ትከታተላለች።

ጫማዎቹን አሥሮ እንዳበቃ ካቀረቀረበት ቀና አለና ከኋላ ኪሱ ቦርሳ አወጣ:: ግልፅ ከሆነ የምፀት ፈገግታ ጋር ቦርሳውን እየከፈተ ካየ በኋላ መልሶ ከዚያው ከኋላ ኪሱ ከተተውና ወደ ፀዳል ቀና አለ፡፡

“እ ...ሺ የኛ አራዳ - " አላት ወደፊት ዘመም ብሎና ክንዶቹን ጉልበቶቹ ላይ አንተርሶ ጣቶቹን እያፍተለተለ፡፡ “ዛሬ ሰራሁልሽ አይደል? - አየሽ እንዲህ
እንዲህ ነኝ እኔ የአራዳው ቆንጨራ!”

“ማለት? አለችው አይኖቹን አትኩራ እየመረመረች:: አልገባኝም::”

ኧረ.....? አልገባሽ.....ም? ታድያ ምን ችግር አለ ሲገባሽ ትነግሪኛለሻ!”

ምኑን?” ይብሱን ግራ የተጋባች ትመስላለች:: “ምኑን ነው ሲገባኝ የምነግርህ?”

“ስሚ - እንኳን እንዳንቺ ያለችው ደደብ ሸርሙጣ ሌላ አይበላኝም እኔ ቆንጨራው!”

“ምንድነው የምታወራው?”

“ምን እንደማወራማ እናትሽን ጠይቂያት! ለዚያውስ እናት ሲኖርሽ አይደል
👍3
#ማዕዶት


#ክፍል_ሦስት (የመጨረሻ ክፋል)


#በየዝና_ወርቁ

“እኔ ኮ ራሴን አላቀውም ሳሚ” አለችው በሚለማመጥ ቅላፄና በጨዋ ቋንቋ፡፡

ምንድን ነው የማታውቂው” ? አላት ግር
እንደመሰኘት ብሎ፡፡
«ኤች.አይ.ቪ ምርመራ ነዋ »አለችው::
«እኔም ወደውጭ አገር ስሄድ ተመርምሬ ነፃ መሆኔን ካወቅሁ ዓመት አልፎኛል፡፡ እንደገና ማድረግ ይኖርብኛል።

ይጠቀማል፡፡ ካልሆነ ግን እንደማዕዶት ዓይነት ያማረ
መልክና ቁመና ያላቸውና ረጋ ያሉ ሴቶችን ሲያገኝ

“ምንድ ነወ

“ታዲያ! አለችው - የምርመራ ነገር ሲነሳ ደፋር ለመምሰል ብትጣጣርም ፍርሃቷ ከውስጧ ማንሰራራት ጀምሯል።

«ታዲያማ ሰው የሚመረመረው፤ አስገዳጅ ሁኔታ ሲያጋጥመው ወይም ደግሞ ሲያገባ ወይም ልጅ ሊወልድ
ሲፈልግ ነው› አላት::
“ካልሆነስ?” አለችው - አንደበቷ እየጐለደፈባት፡፡
“መቼም እንዳንቺ የተማረ ሰው ኮንዶም አላቅም አይለኝም አላት በቀልድ ቃና እየሳቀ….ሳምሶን የሷን አቅጣጫ ተከትሎ ስለ ኮንዶም አወራ እንጂ በመሰረቱ ኮንዶም መጠቀም አይወድም::
አንዳንድ ጊዜ እንዲሁ አይቶ ወይም ሁኔታቸውን ታዝቦ የሚጠራጠራቸው ሴቶች ሊያጋጥሙት ብቻ ሳይወድ ይጠቀማል ካልሆነ ግን እንደ ማእዶት ያማረ መልክና ጠቁመናል ቁመና ያላቸውና ረጋ ያሉ ሴቶችን ሲያገኝ በነሱ በኩል ግፊቱን ካልመጣ እሱ አያስበውም። ስሜቱን
አርክቶ ማገናዘብ ሲጀምር ነው “ጭንቀት የሚሰማው፡፡በሌላ ጊዜ ግን መልሶ ያደርገዋል፡፡
ማዕዶት አነጋገሩን እስተዋለችና ጥሩ ግንዛቤ እንዳለው ገመተች፡፡ ለሷም ቢሆን ጥሩ ነገር እንደሆነ አሰበች፡፡ “ለጊዜው እሱ እንዳለው በኮንዶም እንቆያለን፡፡
ለመጋባት ስንወስን ደግሞ በቃ በመጀመሪያ ሳልነግረው ተደብቄ እመረምራለሁ። ፈጣሪ ረድቶኝ ነፃ ከሆንኩ
አብረን እንመረመራለን፡፡ ቫይረሱ ቢገኝብኝስ ... " ሐሳቧን መጨረስ አቃታት።ሰውነቷ ተንዘፈዘፈ....

መኪናቸው ውስጥ እንዳሉ ቦዩን ጠራውና
መኝታ ክፍል ተከራየ:: ወደዚያው ሲሄዱ
ብርጭቆዎቻቸውንና ጠርሙሱን ቦዩ ይዞ ተከተላቸው፡፡
እንደገቡ ሳምሶን ኮሞዲኖውን ከፈት አድርጎ ኮንዶም ሲያረጋግጥ አየችው:: ተረጋጋች።
ልብሶቻቸውን አውልቀው አልጋው ውስጥ ገቡ:: ትንሽ እንደተሳሳሙ ከኮሞዲኖው ውስጥ አንድ ፖኬት ኮንዶም
አወጣና ከውስጡ አንዱን ነጥሎ ጐረደው:: ቀሪውን ደግሞ ኮሞዲኖው ላይ አስቀመጠው:: ከዚያ ማሽጊያውን
ከፍቶ የውስጡን መዘዘና መብራቱን አጠፋው።

“መብራት አትወድም? አለችው።

“አዎ አላት - ድምጹም ድንገት ስልቱን አጣባት፡፡ስሜት ይዟቸው እልም አለ… በመጨረሻ አንሶላውን ከውስጥ ጎተተና አሸርጦ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄደ፡፡
ታጥቦ እንደተመለሰ መለኪያው ውስጥ የነበረው ማርቲኒ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠውና ሌላ ቀዳ:: የቀዳውን
ምንም ሳያናግራት ጨለጠው።

ግራ ተጋብታ አየችው:: ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ብሩህ ፈገግታ የነበረው ፊቱ ዳምኗል፡፡እንደገና ሲቀዳ
ፈራችውና ፤

“እንሂድ እየመሸ ነው አለች

አትጠውጪም? አላት- ስልቱን ባጣ ድምጽ፡፡

«በቃኝ» አለች - ለመልበስ እየተነሳች:: ለባበሱ ወጥተው ወደ ሳምሶን መኪና ሄዱ::
በቀጠሉት ሶስት ሳምንታት ሶስት ጊዜ ተገናኝተን ተመሳሳይ ሁኔታ አሳልፈዋል:: ማዕዶት ከድሮው ባህሪዋ በተለየ ሁኔታ ከሱ ጋር ስትሆን ሞቅ እስኪላት መጠጣት መጀመሯ ታውቋታል። ግን እያቀበጠ ስለሚያጠጣ ደስ ይላታል፡፡ እንደ ህፃን ስሜቱን መደበቅ የማይችል
መሆኑን እያስተዋለችም አብረውት ለመኖር የማይከብድ ዓይነት ሆኖባት ለማይቀረው የእንመርመር ጥያቄ
እንዲያበረታት ፈጣሪዋን እየተማፀነች ለጋብቻ ተመኝተዋለች

ድንገት ግን ያልጠበቀችው ነገር ተከሰተ፡፡ የወር አበባዋ በቀኑ ሳይመጣ ቀረ፡፡ ግራ ቢገባት መምጫ ቀኑን ኣዛብቶ የማያውቀውን የወር አበባዋን ሳምንት ሙሉ በተስፋ ጠበቀችው።መቅረቱን ስታረጋግጥ ብርክ ያዛት።

በስሜት ውስጥ ሆነን ሳናውቀውየተፈጠረ ስህተት ይኖር ይሆን?! ይኼ አደጋ ነው! ወይ በኔ ወይ
በሱ ላይ የመጣ እያለች አንጎራጎረች :: ልጁንም' ኮ ላይቀበለኝ ፣ ላያምነኝ ይችላል» ብላ አሰበችና ልትነግረው
ፈራች፡፡ እየቆየች ስታስበው ስታብላላው ግን ከመንገር ሌላ አማራጭ አጣችለት:: ሁለታችንም ሳናስበው የወደቅንበት አደጋ ላይ መወያየትና መፍትሄ መፈለግ
አለብን " አለች - ልትነግረው ወሰነችና ደውላ ለማታ ፕሮግራም አስያዘችው።

እንደሌለቹ ቀናት የመዝናናት ስሜት
አልነበራትም ራት መብላት አቅቷት መጠጣትም አስጠልቷት ስለነበር አሞኛል ብላ ዋሸችው:: ከዚያም
ብዙ ሳይቆዩ መብራቱን አጠፋው:: እሱ ስሜት ውስጥ ገብቷል፡፡ እሷግን ሀሳቧ ግራ በገባት ነገር እየተሰረቀ
አስቸግራት በስሜት ልትከተለው አልቻለችም፡፡ እና እሱን ለማስደሰት ብቻ እንደሚፈልገው እየሆነችለት ሳለ
መሀከል ላይ የተለየ ነገር ተሰማት:: ድንገት ጠረጠረችው።ድንጋጤ አስፈንጥራት ተነሳችና መብራቱን ቦግ አድርጋ አበራችው::ሳምሶን ኮንዶሙን በእጁ እንዳንጠለጠለው
ክው ብሎ ቀረ:: ማዕዶትም አንገቱን አንቃ ተንቀጠቀጠች። ከዚያ አንገቱን ለቃ ተስፋ በቆረጠ መንፈስ ፍራሹን እየደበደበችና፤
“አንተ አውሬ ነህ! ጭራቅ ነህ! ተኩሰህ እንደገደልከኝ ቁጣረው..... ምነው? ምን በደልኩህ?...” እያለች ትራሱ ላይ ተደፍታ ተንሰቀሰቀች፡፡ ሳምሶን ድንጋጤው መለስ
ሲልለት ፤

ምን እንዲህ ያደርግሻል? አንቺ ብቻ ነሽ ለህይወትሽ የምታስቢ? እኔ ከማንም ጋር የምጋደም መሰለሽ? ሰው መርጫ ነው" አለ በላይ ሆኖ እንደመቆጣት' እያደረገው
ከአፈርኩ አይመልሰኝ ዓይነት።

“የጅል ወግህን ተወውና ይኼንን ተንኮል የፈፀምክብኝ እውነት ተመርምረህ ቫይረሱ እንዳለብህ ሳታውቅ ከሆነ
ነገ እንመርመር " አለችው - እልህ እያንቀጠቀጣት፡፡

ሳምሶን ትኩር አድርጎ አያትና፤

“ይቻላል አለ - ትከሻዎቹን ከፍ አድርጎ ቁልቁል እየለቀቃቸው:: ዐይኖቹ ውስጥ ግን ፍርሃት በጉልህ ነግሶ ታየ።
እንደተኮራረፉ ልብሶቻቸውን ለብሰው ወጡ፡፡

በማግስቱ ለመመርመር ከተቃጠሩበት አሁን ውጤቷን እየጠበቀችበት ካለው ክሊኒክ ከሰዓቱ ቀድማ ደረሰች፡፡ ለዘመናት የራቀ የመሰላትን ያህል ጊዜ ጠብቃው ሲቀርባት በሞባይል ስልኳ ሞባይል ስልኩ ላይ ደወለችለት። ዘጋባት:: ሰዓቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ግማሽ ሰዓት አሳልፏል:: ትንሽ ቆየችና ሞክረች። መልሶ ዘጋባት፡፡ ብርክ እንደያዛት ተስፋ ቆርጣ በየመንገዱ እንባዋን ለመዋጥ እየታገለች በኮንትራት ታክሲ ወደቤቷ ሄደች መሥሪያ ቤቷ ደውላ መታመሟን ለአለቃዋ አሳውቀችና ተኛች፡፡ ከሰዓት በኋላ ለሳምሶን በሱቅ ስልክ ደወለችለት
አነሳውና እሷ መሆኗን ሲያውቅ ዘጋባት፡፡
ደጋግማ ሞከረች፡፡ ሊያናግራት ፈቃደኛ አልሆነም…

ማዕዶት የተፈጠረውን ነገር እንደክፉ ቅዥት ስትባንን ለቀናት አሰበችው::
ሳምሶንን ለማግኘት የምታደርገው ጥረትም ጥቅም የሌለው ሆነባት፡፡ ከዚህ ወዲያ ባገኘውስ ምን ያደርግልኛ
ል? ጠላቴን የልጄ አባት አድርጌ አልቀበለው አለችናእርግፍ አድርጋ ተወችው::
እያደር ግን ለራሷ ከመጨነቅ አልፋ በማህፀኗ ውስጥ ስላለው ልጅ ማሰብ ጀመረችና ትናንት ደሟን ለምርመራ ሰጠች….
ማዕዶት የሰመጠችበትን የትዝታ ባህር ዋኝታ ስትጨርስ ያው የተጠናወታት ቫይረሱ ቢገኝብኝስ የሚለው ጭንቀት በውስጧ እያንሰራራ ነበር ። እና
የኤች አይ ቪ ቫይረስ ሰውነቷን ቅርጥፍጥፍ አድርጎ ሲበላው ቤተሰቦቿ እንኳ ሊያስታምሟት ሲሳቀቁ ፣ከወዳጅ ዘመዶቿ መሀል ተነጥላ ብቻዋን ስትንጠራወዝ ታያት፡፡ በውስጧ የጭንቀት ትኩሳት ተሰራጨ፡፡
ጨምድዶ። ከያዛት ጭንቀት ለመውጣት እያባ ት : ንቀት እየተወራጨች ! 'ቢኖርብኝም ቫይረስ ላለባቸው
1👍1
#በኔ_የደረሰ


#ክፍል_ሦስት


#በጥላሁን

...እሄ መፈላሰፍ ነው እንዴ መፈላሰፍ እራሱ ምን ማለት ነው! ወጣም ወረደም ፍቅር የያዘው ሰው ሁለመናው ማፍቀሩን ስለሚናገር ምን ልናገር ብዬ ባልጨነቅስ!
የእረፍት ሰአት ተደወለና ተያይዘን ትንሽ እንደሄድን
"ለምን ነበር እረፍት ሰአት ልታናግሪኝ የፈለከው ሶልዬ?" ስትለኝ ደንግጬ አይን አይኗን ከማየት በስተቀር ሌላው እንኳን ቢቀር ወዬ ሊሊዬ የምትለውን ቃል ለመናገር ብሞክር ኔትወርኩ እንደጠፋ ስልክ ምላሴ ላይ እየተሽከረከረች አልወርድ አለችኝ።
የስልክ ኔትወርክስ ቦታ በመቀያየር ይፈለግ ይሆናል የኔን ኔትወርክ ምኑን ቀያይሬ ላምጣው!
ቸርነቱ ብዙ አንደበቱን ሰጥቶኝ
ፍቅሬን እንዳልገልጠው ፍቅርሽ ዲዳ አረገኝ እባክሽን ማሬ ያንደበቴን ትተሽ
ውስጤን ተረጅልኝ አይኔን ተመልክተሽ!!
ብለው ዘፍነው ይሆን እንዴ ዘፋኛቹ ?
አይመስለኝም •••
መጨነቄን በማስተዋል ስታይ የነበረችው ሊሊ
"ሶልዬ አትጨነቅ በቃ እንደምትወደኝ እንኳን እኔ ጓደኛቼም ያውቃሉ!
ታፈቅረኛለህ አደል?
እሱን ልትነግረኝ ፈልገህ ነው አደል እንዲህ ፈንጅ እንደረገጠ ሰው በቆምክበት ደርቀህ ምላስህም ሰውነትህም አልንቀሳቀስ ያለው ?ስትለኝ ጆሮዬን ማመን ተሳነኝ ።
ንግግሯ ምላሴ የታሰረበትን ገመድ በጣጠሰው መሰለኝ
" ሊሊዬ አዎ አፈቅርሻለሁ ግን እንደማፈቅርሽ በምን አውቅሽ ?
ጓደኛችሽ እንዴት አወቁ ? ስላት ሳቋን ለቀቅችው
"አንተስ እንዳፈቀርከኝ በምን አወክ? ብላ ግራ የገባው ጥያቄ በመጠየቅ ግራ አጋባችኝ ቢሆንም ምላሴ ተፈቷልና ለመመለስ አልቦዘንኩም•••
እኔማ እንዴት አላውቅም ሊሊዬ
ለሰከንድ ስላንቺና አንቺን ከማሰብ ተዘናግቼ አላውቅም ።
የሚዘፈነው የፍቅር ዘፈን በሙሉ ላንቺ የተዘፈነ ይመስለኛል ።
በፍቅሯ የሆንኩትን በሙሉ ለመዘርዘር ሲዳዳኝ •••
አንገቴ ላይ ድንገት ተጠምጥማ " እኔም እወድሀለሁኮ ሶልዬ!" ስትለኝ ከደረቴ በታች የሆነ ብቻ ለመግለፅም የሚከብድ እስከዛሬ ተሰምቶኝ የማያውቅ ስሜት ተሰማኝ።
ምን አልሽኝ ሊሊዬ አልኩ እንድትደግምልኝ ፈልጌ ዝም አለች። ደግሜ ለመስማት ፈልጌ በዝምታ ጠብኳት ። ደገመችው ።ደጋገመችው። አብረን ሆንን።
እኔ ከሊሊ ጋር በፍቅር ብን ማለቴ ጨርሶ ያልተዋጠለትና ያልተመቸው ሰው ቢኖር ጓደኛዬ ነው
እሄ ጓደኛዬ ኪሩቤል ይባላል ከወንድ ጓደኛቼ በጣም የምወደውና እንደወንድሜ የማየው ከልጅነት ጀምሮ ለብዙ አመታት ተለይቼው የማላውቅ ጓደኛዬ ነው
ታድያ እንደጓደኛ የማፈቅራት ልጅ እሺ ስላለችኝ እና አብራኝ ስለሆነች መደሰት ሲገባው ወረደብኝ ወረደብኝ አይገልፀውም በተግፃፅ እና በምፀት ደበደበኝ ብል ይቀለኛል
"አንተ ግን ምንድን ነው ወንድ አደለህ እንዴ ቆፍጠን በል እንጂ ምን ያዝረከርክሀል ኧረ በናትህ ለሴት ልጅ እሄን ያህል መሸነፍ መዋረድ ነው ለኔ ፍቅር ምናምን ትላለህ እንዴ ፍቅር አንተ ካልደረስክበት አይደርስብህም አንተ ፊት ካልሰጠከው ድርሽ አይልም ለሴት ልጅ የሚያለቅስ ጓደኛ ስላለኝ በጣም ነው ያፈርህምኩት ጓደኛቿ ሁሉ እኮ በፍቅሯ እግሯ ስር እንደጣለችህ ነው የሚያወሩት ኧረ እኔ ለሴት መቼም ቢሆን እንዳንተ ከምሆን ብሞት ይሻለኛል!"
አለኝ ይህን ፀባዩን እና አመለካከቱን በሌሎች ጓደኛቻችን ላይም ሲያንፀባርቀው ስላየሁ በውስጤ "ደርሶብህ እየው ያኔ ብናወራ ይሻላል ፍቅርን የሚያውቀው ያጣጣመው አልያም አልያም አናቱ ላይ ወጥቶ ያብከነከነው ብቻ ነው" እያልኩ ካጠገቡ ከመሄድ በቀር መልስ አልሰጠሁትም።
እንደው ሰው አማህ አትበሉኝና ጓደኛዬ ከምጣላበት የምወድለት ባህሪው በልጦብኝ ዘለቅን እንጂ የሚያናድድ ጢባር አለበት።
ደፋር ነኝ አደል ሰው አማህ አትበሉኝና ማለቴ ?
ቆይ እንዲህ በሀሜት አንስቼ እያፈረጥኩት
ሰው አማህ ካላላችሁኝ ምን ልትሉኝ ነው ?
ምን ላርግ ሲሉ ሰምቼ ነው።
ሲሉ ሰምቼ ያልኩትም ሲሉ ሰምተው ሲሉ ሰምቼ ነው።
አንዳንድ ሰዎች አንድን ሰው በሀሜት ስጋውን ቦጫጭቀው ባጥንቱ ሊያስቀሩት መንደርደር እንደጀመሩ መግቢያ አድርገው የሚጠቀሙት
"ሰው አማህ(አማሽ) አትበሉኝና!"
የሚለውን ፈንጅ አምካኝ ንግግር ነው ሰው ላይ የሀሜት ፈንጅ እየወረወሩ እነሱ ላይ የሚወረወረውን የትዝብት ፈንጅ የሚያመክኑት "ሰው አማህ /ሰው አማሽ አትበሉኝና" በሚለው ቅድመ ሀሜት ንግግራቸው ነው።
እናም ሁሌም እንደዚህ የሚሉ ሰዎች ሲያጋጥሟችሁ ሰው እያሙ ሰው አማህ ወይም ሰው አማሽ ካላላቹሀቸው ምን ምን እንደምትሏቸው ማሰብ ጀምሩ።
መልሱን ለናንተ ልተወውና ወደ ጉዳዬ ልመለስ
ሰው አማህ አትበሉኝና ጋደኛዬ ክሩቤል በተለይ በተለይ በፍቅር ዙርያ ያለው አመለካከትና በፍቅር መሀል ጣልቃ ለመግባት ያለው ድፍረት ያናድደኛል።
ፍቅርም አይዘኝም ፍቅር የምታስይዘኝም ሴት የለችም መፈክሩ ነው።
አንድ ቀን የኔዋ ሊሊ •••
"ጋደኛዬ ጓደኛህን ክሩቤልን ወዳዋለች ልጁ ግን እሚገባው ነገር አደለም እባክህን አናግረው እስቲ ሶልዬ!" ስትለኝ በጣም ደነገጥኩ ሄጄ ሳናግረው ምን እንደሚለኝ! እንዴት እንደሚላላጥብኝ! አንተን አረከኝ እንዴ ብሎ እንደሚዘልፈኝም አውቀዋለሁ ቢሆንም የማይቻል ወይም ጭራሽ የማይሞከር ካልሆነ በስተቀር ሊሊዬ ምንም አድርግልኝ ብትለኝ የትም ሂድልኝ ብትለኝ እምቢ ለማለት አቅም የለኝምና ኩሩቤልን አናግሬው ምላሹን እንደምነግራት ቃል ገብቼ ተለያየን።
ሄጄ ሳናግረው እንደፈራሁት ተላላጠብኝ ብዙ ነገር አውርቶ በመጨረሻ ጥየው ስሄድ ጮክ ብሎ "ቢጤሽን ፈልጊ በላት "አለኝ ።
ለሊዬ በቃ ልጁ አይሆናትም ይቅርባት ምላሹ ጥሩ አደለም አልኳት። ልጅታ ከሊሊ መልሱን ስትሰማ "ያፈቀረ ሲቆርጥም የመረረ!" እንዲሉ እርግፍ አድርጋ ተወችው ። ከተወሰነ ግዜ ቡሀላ ልጅቷ ከአንድ ልጅ ጋር ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ አዘውትራ መታየት ጀመረች።
ፍቅር ላይ ንጉስ ነኝ የሚለው ጓደኛዬ።
ፍቅሯ ተገልብጦ መቆሚያ መቀመጫ አሳጥቶታል ታግሎ ታግሎ ሲሸነፍ መሸነፉን ሊተነፍሰው ግድ ሆነበት ሲል የነበረውን ያውቀዋልና እንዴት እንደሚነግረኝ ግራ ገብቶት ሁለት ግዜ በጣም እፈልግሀለሁ እያለ ቀጥሮኝ ሳይነግረኝ ተለያየን ። የመጀመሪያው የትምህርት መንፈቀ አመት ተጠናቆ እረፍት ላይ ነበርን ለሶስተኛ ግዜ ቀጥሮኝ እቤታቸው ሄድኩኝ ክፍሉ ስገባ በሆዱ ተኝቶ ያስቴርን ሙዚቃ እያዳመጠ ነበር

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#ማምሻ


#ክፍል_ሦስት


#በአሌክስ_አብርሃም


ጀብድ ሠርቶ እንዳመለጠ የግፍ እስረኛ፣ በአድናቆትና እንኳን ተሳካላቸው ሰሚል ስሜት
የተሞላ ነበር፡፡

እማማ ዓምድነሽ፣ ልጃቸውን ማምሻን አይገቡ ገብተው አሳደጓት: ሰው ቤት ልብስ እያጠቡ፣ ጉሊት እየቸረቸሩ ትምህርቷን ሊያስተምሯት ጣሩ፡፡ ማምሻ ግን ትምህርቱም ብዙ አልሆነላትም፡፡ የሰፈሩ ማንጓጠጥ ትምህርት ቤትም ተከትሏት ነበር፡፡ እየወደቀች እየተነሳች እንደምንም ዘጠነኛ ክፍል ደርሳ አቆመች:: የሻይ ቤት አስተናጋጅነት ሥራ እንዲያፈላልግላት ደላላውን በሽርን ብትጠይቀው፣ ያንን ጫት የተለሰነበት ጥርሱን
እየገለፈጠ “ማምሻ! በዚህ ፊት አስተናጋጅነት!?…”አላት አሉ፡፡ ይህም አንድ ሰሞን
ተሳቀበት…በኋላ በወር ሰማንያ ብር እየተካፈላት የሰፈራችን ቦኖ ውሀ አስቀጅ ሆነች::
ውሀ አታፍስሱ ያለቻቸው የመንደሩ ሴቶች ያንኑ ቁሰሏን በሽሙጥ ስንጥር እየነካኩ፣
በመልከጥፉነቷ እያሸሞሩ ቁጡ አደረጓት፡፡
“ቆጥባ መልከ ጥፉነቷን ልታጥብብት ነው?
እያሉ:: በነጋ በጠባ ጸብ ሆነ፡፡

አንድ ቀን ማምሻ አንዷን አሽሙረኛ እንደ ነብር ዘልላ ተከመረችባት፡፡ ማን ያላቅቃት?
የዘመናት ብሶቷን እዚያች ዕጣው እወደቀባት ሴት ላይ አራገፈችው፡፡ በትርምሱ የውሀ
መቅጃ እንስራም አልተረፈ፣ ተከለከከለ፡፡ ከዚያቹም ሥራ ተባረረች፡፡ ደግሞ የማባረሪያ
ምክንያቱ ግነት! “ሕዝብ እንድታገልገል በተቀመጠችበት ቦታ፣ ሥልጣኗን ተገን
በማድረግ፣ ተጠቃሚውን ኅብረተሰብ በመደብደብና ንብረት በማውደም ቦንብ ጣይ
አውሮፕላን እያበረረች አንድ ከተማ ሕዝብ የደበደበች ዓይነት! ኅብረተሰቡን
በመደብደብ እና ንብረት በማውደም!”

ተራ ፌዝና ስላቃችን አንገት ያስደፋት ማምሻ፣ ሁሉንም እርግፍ አድርጋ ትታ፣ ባልቴት
እናቷ በየሰው ቤት ሠርተው በሚያመጧት ሳንቲም ኑሮዋን እየገፋች የወጣት ጡረተኛ ሆና እቤት ተቀመጠች፡፡ ይኼ መገፋት አጉብጧት እንዳቀረቀረች፤ እንጀራዋን እዚያው ባቀረቀረችበት አገኘችው፡፡ ልክ እንዲሰምጥ ወደ ባሕር የገፈተሩት ሰው የሚያስጎመዥ ዓሣ ይዞ የመውጣት ዓይነት ነበር ነገሩ፡፡ ማምሻ እንዳቀረቀረች ኪሮሽና ክር አነሳች፡፡እንዳቀረቀረች መርፌና ክር ታጥቃ በመራሩ ድህነት ላይ ዘመተች፡፡ በሰፊው የድህንትጥቁር ሸማ ላይ ውበትን ዘራችለት፡፡ ከዚያ የተገፋ ልብ፣ ያ ውበት እንዴት ወጣ?እላለሁ አንዳንዴ፡፡
ውበታቸው የመንደሩን ብቻ ሳይሆን፣ ከየትና የት ድረስ የሚመጡ የከተማውን ሴቶችን የሚያሻማ፣ ከምሶብ ዳንቴል እስከ ኤልጋ ልብስ፣ ከኩርሲ እስከሶፋ ልብስ፣ ከመጋረጃ እስከ ሐበሻ ቀሚስ ድረስ የጥልፍ ማጎተሟን አሳረፈች፡፡ ሰፈራችን በሙሉ በማምሻ የእጅ ሥራዎቿ ተጥለቀለቀ፡፡ የማምሻ ጥልፍ ያረፈባቸው መጋረጃወች በየመስኮቱ ተሰቅለው ሲታዩ፣ ማምሻ ገፊዎቿን በእጁ ጥበብ ድል ነስታ፣ ባንዲራዋን በድል
እድራጊነት በየቤቱ የሰቀለች ይመስል ነበር፡፡

በመቋጨት ይሁን በመጥለፍ፣ የማምሻ እጅ ያረፈበትን የባህል ቀሚስ ይሁን ነጠላ ለብሳ
ያልተውረገረገች፣ አንድ የመንደሩ ሴት ብትኖር፣ ማምሻ ራሷ ብቻ ነበረች። እንዲህ እያገባኝ ገብቼ የማምሻን የእጅ ሥራዎች ስመለከት፣ ከሌሎች ጥልፎች የተለዩ ይሆኑብኝ ነበር። ፍዝዝ ያለ ቀለም ባላቸው ክሮች፣ ደማቅ መደብ ላይ የምትጠልፋቸው አበቦች የራሷን ምስል የምትስል ሠዓሊ እስክትመስለኝ፣ አንዳች የሚያሳዝን ስሜት ውስጥ የሚያስገቡ ነበሩ:: በዚህም ሥራዋ እራሷን ባልቴት እናቷን በክር ጎትታ፣አንገታቸው
ከድህነት አዘቅት ብቅ እንዲል አደረገች፡፡ እናቷ በየሰው ቤት መንከራተት አቁመው እቤታቸው አረፉ፡፡ መንደርተኛውም ከማምሻ መልክ ይልቅ የእጅ ሥራዎቿ ዓይኖቹን ጋርደውት ከመዝለፍ ይልቅ ወደማድነቅ እና ማክበር የተሸጋገረ መሰለ፡፡ በእርግጥም ማምሻ መልከጥፉ ፊቷን በብርቱ እጆቿ ሽፍናው ነበር፡፡

ስም ውስጥ ሟርት አለ፡፡ ማምሻ እንደስሟ ማምሻ ሆነች: ሁሉም ነገር የተቀያየረው ድንገት ነበር፡፡ የእጅ ሥራዎቿን ሙሉ ለሙሉ ከገበያ ውጭ የሚያደርግ አጋጣሚ። ፈጣን እና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የጥልፍ መኪኖች በከተማው ውስጥ እንደ አሸን ፈሉ።
በአንድ ጀምበር ድፍን መንደር የሚያለብሱ፣ በደማቅ ከሮች ፎቶ የመሳሰሉ አበቦችን
የሚጠልፉ የ “ሲንጀር መኪኖች፡፡ የማምሻ ተስፋ ሟሸሽ! ጥበቧም ከምንም እስከ ሲንጀር መኪና ባለው ክፍተት መሀል ማምሻ መሸጋገሪያ ሆነ። በኑሮ አድማሷ ላይ ድንገት ብቅ ያለች ጀምበሯ፣ ሙቀትና ብርሃኗን በቅጡ ሳታጣጥማት ድርግም ብላ ጠፍታ፣ ዳግም የድህነትና የማንጓጠጥ ዝናብ ያዘለ ደመና በላይዋ ላይ ያንዣብብ
ጀመረ፡፡ ዳግም ወደ ማቀርቀር፣ ዳግም አንገት ወደ መድፋት ተመለሰች፡፡ ግና ምንም ያልተነኩ ቱባ ክሮችን ሰብስሳ ወስዳ ለባለሱቁ ከድሩ በርካሽ ሸጠችለት ተባለ፡፡ ያም የማምሻ የጥልፍ ሥራ ማብቂያ ሆኖ በጎረቤቱ ዘንድ ተወራ፡፡ በዚህም ተቀለደ፡፡ “ማምሻ ኪሮሽ ሰቀለችተባለ፡፡ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መጫወት ሲያቆሙ
ጫማ ስቀሉ” እንደሚባለው መሆኑ ነው፡፡ቀስ በቀስ እናቷ ወደ ሰው ቤት ሥራ ተመለሱ፣ ማምሻም እናቷን ለማገዝ እንጀራ መጋርና መሸጥ ጀመረች፡፡ ታዲያ በዚህ መሃል ትንሽ በጎነት ያሳየቻት ሴት ብትኖር፣ ሎዛ ነበረች፡፡ ከአባቷ ጣውላ ቤት የእንጀራ መጋገሪያ ሳጋቱራ በነፃ እንድትወስድ አስፈቅዳላት ነበር፡፡

ባልገባኝ ምክንያት የሎዛ ዓይኖች ሁልጊዜ ማምሻ ላይ ነበሩ፡፡ የሰፈሩ ሰው ርግፍ አድርጎ
በተዋቸው ሰዓት እንኳን የማምሻ እጅ ስራ የተጠለፈባቸው ልብሶችን ትለብስ የነበረች
ሴት ሎዛ ብቻ ነበረች፡፡ እንደውም ለእኔም ከማምሻ የገዛችውን አንድ የባህል ልብስ
ስጦታ ሰጥታኝ ነበር…ለብሸው ግን አላውቅም፡፡
።።።።።።።።።።።
ሎዛ ደውላ ሄይ አብርሽ… ከሥራ ስትወጣ እቤት እመጣለሁ፣ ጠብቀኝ አለችኝ፡፡
ከሥራ ስመለስ ቀድማኝ እኛ ቤት ደርሳ፣ የምትወደውን የጦስኝ ሻይ እየጠጣች ከእናቴ
ጋር ሲያወሩ ደረስኩ፡፡ እናቴ ፊት ብትስቅም ገና ሳያት እንዳኮረፈች ገብቶኝ ነበር፡፡
"ሙሽሪት” አልኩና በትከሻዬ ገፋ አድረጊያት ገባሁ፡፡ እናቴን ተሰናብታ ተያይዘን እንደወጣን፣ “ማምሻ ጋ አካሂደኝ አለችኝ፡፡

ለምን?

“ሚዜነቷ እንደቀረ ልነግራት!”

ቀረ እንዴ?” ዞር ብላ በብስጭት አይታኝ፣

“ደስ አለህ?” አለችኝ፡፡

“ለምን ደስ ይለኛል? …ግን አለ አይደል …”

በውስጤ ግን ደስ ብሎኝ ነበር፡፡ በትዝብት አይታኝ፣

በቃ ቀርቷል፡፡ አባባ ተዪው አለኝ፡፡ ማሚ አሳምናው መሆን አለበት፡፡ማንም ሰው ከጎኔ
አልቆመም፣ ደከመኝ” አለች፡፡ ስልችት ያላት ትመስል ነበር፡፡ ተያይዘን እነማምሻ ቤት
ስንደርስ፣ ማምሻ የዘመመችው የጭቃ ቤታቸው ጋር ተያይዛ ከላስቲክ እና ከቆርቆሮ
ተሠራች ማድ ቤት ውስጥ ከጭስ ጋር እየታገለች እንጀራ ስትጋግር አገኘናት፡፡
ከማድ ቤቷ አጎንብሳ ስትወጣና አይታን ፈገግ ስትል ዓይኔን ማሳረፊያ ሌላ ቦታ ፈለግሁ፡፡
የማይለመድ መልከ ጥፉነት ነው ያላት፡፡ መልከ ጥፉ ብቻ አይደለችም… የሆነ በቀለኛ አጋንንት
ፊቷን በአጉሊ መነጽር እያየ ትንሽ ሰው ሊስብ ይችላል ያለውን ነገር ሁሉ እየለቀመ ያፈራረሰው ነበር የሚመስለው፡፡ እኔ ነኝ ያለ ደራሲ ይቅርና ፎቶ አንሺ እራሱ የማምሻን መልከ ጥፉነት በበቂ ሁኔታ አሳይቶ መጨረስ የሚችል እስከማይመስለኝ፣ ፊታ እንደ አዲስ አስገረመኝ፡፡ ምን ይሳነዋል ልሥራው ካለ ይሠረዋል፤ ላበላሸው ካለ ያበላሸዋል እላለሁ ለራሴ::

ወደ ቤታቸው እየመራች አስገባችን፣ የቤቷ ውስጥ ካሰብኩት በላይ እጅግ ንጹሕና በሥርዓት የተዘጋጀ ነበር የማምሻ ዘመን ያለፈባቸው ጥልፎች እንደሙዚየም ከአልጋ እስከ ኩርሲ በሥርዓት ለብሰው ተቀምጠዋል
👍3
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


ለምን እንደሆነ ባይገባትም ሳታስበው! ሳትጠብቀው ከልቧ ወዳዋለች፣ ጭራው የማይያዝ፤ የማይጠመድ፧ከእጅ የማይገባ ጋማውን እያመስ የሚፈነጭ የዱር ፈረስ ነው የሆነባት።

ይህን እያወቀች የመጨረሻ ውሳኔዋ ላይ መድረሷ እብደት መሰላት፡፡ ገደል ግቢ' ብሎ ቢተዋትስ? “ኡፍ…” በረጅሙ ተነፈሰች፡፡

በወፍራሙ ቅቤ የቀባቸውን ዳቦ ያለርህራሄ ግምጥ አደረገችና
ከትኩሱ ወፍራም ቡና በረጅሙ ፉት አለችበት፡፡ ነፍሷ መለስ አለች፡፡

ከናትናኤል ጋር እንዴት እንደተገናኘች ስታስታውስ፤ ግንኙነታቸው ሲጀመር የነበራት ዓላማና የአሁኑን ስሜቷን ስታስብ ድንቅ ይላታል፡፡
ልታጠምደው ተዘጋጅታ ቀርባ እሷ ራሷ እንዴት ልትጠመድ እንደቻለች ጭራሽ አይገባትም ያደረገችውን ሁሉ የግል ጉዳይ ነው እያለች ራሷን ለማሳመን ብትታገልም ህሊናዋ ሊያርፍ አልቻለም
ቀድማ የዘረጋችውን መረብ ሳትሰበስብ ሌላ መረብ መጣሏ ለራሷም አስፈርቷታል።

ሶስና ባዘጋጀችው የልደት በአሏ ላይ ነበር ከናትናኤል ጋር የተዋወቁት አርፍዶ ነበር የመጣው:: ውስጥ እንደገባ በግራው
ያንጠለጠለ በስጦታ ወረጭት የተጠቀለለውን ለሶስና አቀብሎ ግራ
ጉንጫን ላይ ሳማትና ተያይዘው ወደ ውስጥ ዘለቁ፡፡ ዓይኗ የገባውና
ለይታ ያወቀችው ገና ከበር ነበር። መረቧን ጣለች፡፡ ቀጠን ብሎ ረዘም ያለ ነው ስልክክ ያለ ፊቱ ቅንድቦቹና ሽፋሽፍቶቹ
እንደጎርፍ በአገጩ ዙርያ ፏ ብሎ ግጥም ያለው ጥቁር ጺሙ በሩቅ ሳቧት።
.
“ሶስና እውነቷን ነው አሰበች እርብቃ ደስ የሚል ልጅ ላይ ነው የጣላት እግዜሩ አስጠሊታ ፍጡር ቢሆንም ኖሮ ገብሬልዬ!”

ሶስና ግራ እጁን ይዛ እየጎተተች ወደ እንግዳ መቀበያው ክፍል መሃል ወሰደችው፡፡ በክፍሉ ውስጥ የሚተራመሰው እንግዳ አይትያይም!
ሁሉም በቡድን በቡድን ጨዋታውን ያቀልጠዋል፡፡ ናትናኤል ብዙ የሚያውቀው ሰው ያለው አይመስልም፡፡ ቢሆንም የመደናገር ! ግራ የመጋባት መልክ አልታየበትም፡፡

ሶስና እጁን ይዛ እየጎተተች ኮጓደኞቿ ጋር ስታስተዋውቀው ዞሮ ዞሮ የመመጣው እሷውጋ መሆኑ ታስባትና ፈገግ አለች ርብቃ::

ኬክ ከተቆረሰ ሰኋላ ነበር የተዋወቁት፡፡

“ተዋወቃት:: ርብቃ ትባላለች፡፡ ጓደኛዬ ናት:: ርብቃ አብሬው ነው የምሠራው:: ናትናኤል ይባላል፡፡" አለች ሶስና አሁንም እጁን እየጎተተች አምጥታው፡፡

“ናትናኤል ግርማ፡፡” አላት እጁን ዘርግቶ፣ አስቂኝ ወሬ እንደሰማ ሁሉ ፈገግ ብሎ፡፡ በትክክል የተደረደሩ የሚያማምሩ ትናንሽ ነጫጭ ጥርሶች አሉት፡፡

“ርብቃ ዮሃንስ፡” እጇን ዘረጋችለት፡፡ ጠበት ኣድርጎ ጨበጣት፡፡

ሶስና ድንገት ወደ ጆሮዋ ጠጋ ተጠንቀቂ ታዲያ ዱርዬ ነው” አለችና “በሉ ተጫወቱ::” ብላቸው ከሰው መሃል ተደባልቃ ተሰወረች::

ዱርየው!” ይህ ነበር የምትፈልገው የማስጠንቀቂያ ቃል፡፡ ፈገግ አለች ርብቃ::

“ስምሽን ከዚህ በፊት የማውቀው መሰለኝ አላት ድንገት
“እ በሬድዮ ሰምተኸው ይሆናል ጋዜጠኛ ነኝ::” :
“አ! የአፍሪካ ምጣኔ ሀብት ላይ አላት እጇን ጠበቅ አድርጎ ጨብጦ፡፡

“አዎ፡፡” አለች ፈገግ ብላ ብሬድዮ የምታዘጋጀውን ፕሮግራም ስም
ያለስህተት በመጥራቱ ኮራ ብላ፡፡

“በጣም ነው የምጠላው እሱን ፕሮግራም::”

የሰማችውን ማመን አልቻለችም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ድፍረት ሲያጋጥማት የመጀመሪያ ጊዜዋ ነበር፡፡ መልስ አልጠበቀችም እጇን ከእጁ ውስጥ መንጭቃ ማውጣት ፈለገች፡፡ ነገር ግን ትክ ብለው የሚያይዋት ዓይኖቹ አልሰበር፤ አፋታ አልሰጥ አሏት፡፡

'ብሽቅ' አለች በል፡፡

“ትዝ ይለኛል… በአንድ ወቅት የብዙሁን ፓርቲ ስርዓትና የኢኮኖሚ እድገት በአፍሪካ በሜል ርዕስ አንድ ተከታታይ ዝግጅት አቅርበሽ ነበር…መላቅጡ የጠፋው ዝግጅት ነበር።” አላት ናትናኤል፡፡ ርብቃ ንዴቷን ልትቋቋመው አልቻለችም፡፡

“ካልወደድከው ለምን ትከታተለዋለህ ታዲያ?" አለች ደርዝ ባለው ድምፅ፡፡

“ድምፅሽን ስለምወደው ይሆናል...? አለና ድንገት ከት ብሎ ሳቀ፡፡ወዲያው ኮስተር አለና “ስራዬ አፍሪካ አጠቃላይ ሁኔታ ጋር የሚያገናኘኝ ነው። ስለዚህ ወደድኩትም አልወደድኩትም ፕሮግራምሽ እንዲያመልጠኝ አልፈልግም:: በተለይ እንግዶች ጋብዘሽ ቃለ ምልልስ በምታደርጊበት ወቅት፡፡” አለ ከጎናቸው ካሰ ጠረረጴዛ ላይ ከተደረደሩት በመጠጥ ከተሞሉት ብርጭቆዎች ሁለቱን አንስቶ አንዱን እያሳለፈላት፡፡ “የሚሰማኝን በግልፅ በመናገሬ እንዳልተቀየምሽኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡”

“እህእ...” ትከሻዋን ነቀነቀች፡፡ “ግድ የለኝም የፈለከውን ብትቀባጥር
ለማለት

የምታዘጋጂያቸው ፕሮግራሞች እንደተረዳሁት በአመዛኙ ለአፊሪካ ማንሰራራት ዋነኛ ተስፋ አድርገሽ የምትወስጂው በአፍሪካ አገሮች መሀል
ነው:: አገሮች በተናጠል ለሚያደርጉት ጥረት ቦታ የሰጠሽው አይመስለኝም።

ትክክል ነህ እውነቱ መራሪ ቢሆንም ልቀበለው ስለደፈርኩ ነው።አለች ርብቃ ለዘብ ብላ።

“ምንድን ነው እውነቱ?"

“የአፍሪካ አንድ ተስፋ የለሽ መሆናቸው ከገቡበት አዘቅት መቼም ቢሆን ሊወጡ አለመቻላቸው ተስፋ ያላት አንድ አፍሪካ ብቻ መሆኗ ነው እውነቱ::

“አልገባኝም!” አለ ናትናኤል ቅንድቦቹን አጠጋግቶ።

በአጭሩ በኔሬሬ አፍ እንደተባለው የአፍሪካ ነፃነት የሚገኘው በተዋሀደ እንቅስቃሴ ብቻ ነው::”

ጨርሽዋ!” አለ ናትናኤል ፈገግ ብሎ “ኔሪሪ ያለው ያንን ብቻ አይደለም'ኮ፡፡ ውህደቱ ሊጠናከር የሚችለው በኢኮኖሚያዊ መተባበር የግንኙነት መስመሮችን በማሻሻል በመጨረሻም በፖለቲካ ውህደት ነው መሰለኝ ያለው ኔሬሬ፡፡ ለዚህ ደግሞ እያንዳንዱ የአፍሪካ አገር በተናጠል የሚያደርገው ጥረት ዋጋ ሊሠጠው ይገባል፡፡
“የትኛው ይቅደም መሠለኝ ጥያቄው፡፡” አሀች ርብቃ በስሱ የገጠመቻቸውን ከንፈሮቿን አላቃ፡፡

“ከምኑና ከምኑ?" ጠየቃት ናትናኤል።
“ከኢኮኖሚው ትብብርና ከፖለቲካው ውህደት።”

ይህማ ግልፅ ነው:: የፖለቲካ ውህደት በኢኮኖሚና በሌሎችም ትብብሮች ላይ የሚገነባ : ነው፡፡ ስለዚህ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ይቀድማል።”

“እንደ መጽሐፍ ከሆነ ልክ ነህ መሰለኝ፡፡ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬና ትብብር ለፖለቲካ
ውህደት አንድ መሰረት መሆኑ አያጠራጥርም ጥያቄው ግን መፅሐፍ ላይ የተፃፈው ሳይሰራ ሲቀርስ? የፓለቲካ አቋም ልዩነት በራሱ ለኢኮኖሚው ጥንካሬና ለትብብሩም እንቅፋት ሆኖ ሲገኝስ መድሃኒቱ ምን ይሆናል :: የሚለው ነው፡፡ በአፍሪካ የሚታየው ችግር ይህ ይመስለኛል፡፡
አተኩራ ተመለከተችው፡፡ “መልስልኝ እንጂ፡፡” አለች ናትናኤል ያመነታ
ሲመስላት:: .
“ያገባኛል! ይባኛል እርግጥ የፖለቲካ አለመጣጣም…" ናትናኤል እያመነታ ጀመረ፡፡

“አንዱ የአፍሪካ አገር አለመጣጠማቸው
ለወጭ አራዊቶች ቅጥረኛ እየሆነ የጎረቤቶቹኝ ሰላም ሲያውክስ ኢኮኖሚ ሲያደቅስ አልፎ ተርፎ በገዛ አፍሪካውያን ወንድሞቹ ላይ ጦር ሲሰብቅ
መድሐኒቱ ምን ይሆናል?የተማሩ የተመራመሩ ቅምጥል የአፍሪካ ልጆች አፍሪካ ጥቁር አፈር ሲገለማቸውስ? ነጭ አፈር ፍለጋ ሲዘምቱስ? ጋሻ መከታ መኩሪያ መመኪያ መሪዎቻቸውን፣ በአፍሪካ ቦሀቃ የጠለቁትን ሊጥ በስዊዝ ባንክ ካልጋገርነው ሲሉስ? ፖለቲካ መድህኒት መሆኑ ቀርቶ የነአለብላቢት ጭልፊት፣ የነጎርሶ አይጠግቡ፤ የነውጦ አይጠረቁ ጋሻ ጃግሬ አጋፋሪ ሲሆንስ? መድሀኒቱ ምን ይሆናል? መጽሐፉ እንደሚለው ትብብር ይሁን እፈጠጠችበት።

ይገባኛልኮ ችግሮች መኖራቸውማ ያለ ነገር ነው ግን አለ ናትናኤል፡፡

“በማን ጀርባ ላይ እየተጨፈረ ያለ ነገር ነው? ወንድም ወንድሙን እያስማማ ፧ ከነጭ ወል እየተጋባ፤ ወንድም ወንድሙን እየቸበቸብ ከባዕድ ጡጥ
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

የጨቅላ ልጅ ቡጢ ያህል የፈጠጠው ቁርጭምጭሚቷ ተረከዝዋ በላይ የሚገኘው ወፍራም ወጣሪ ጅማቷ በኑሮ መጎዳትዋና መጎሳቆሏን በሚገባ ለማሳወቅ የቀረቡ አስረጂዎች ናቸው።
ከሳምንት በፊት እናቴና ወይዘሮ የውብዳር ሲነጋገሩ ካመጡልኝ አይቀር
ችግረኛዋንና ምንም ዘመድ የሌላትን የራባትንና እህል እህል ያሰኛትን ነው» ብላ
አደራ ያለቻቸው ትዝ አለኝና «ችግርንና እጦትን ረሃብንና እርዛትን ማስፈራርያ
እያደረገች ልትገዛት ፈልጋ ነው» በማለት መሪር ትዝብቴን ለራሴ አዋየሁት።
መላ ሰውነቴ በርኅራኄና በሃዘን ተነካ፡፡ ልቤ በትካዜ ሟሸሸች። በሥራ ብዛት
የተደቆስኩ ያህል ሕሊናዩ ዛለ፡፡

አዲሲቷ ሠራተኛ ያሳለፈችው ውራጅ ሕይወትና የዘቀጠ ኑሮ እስከ አጥንቷ ዘልቆ ታየኝ። ነገር ግን በእኔ ዕውቀትና በአጭር ጊዜ የምርምር ችሎታ
ገና በወጣትነቷ ለጨለመው ሕይወቷ አመርቂ ፍቺ አጣሁለት። ከዚያ ቀደም
ለማንም በዚያ ዐይነት አዘኔታና ልባዊ የስሜት ጭንቀት አንጎሌ ተብሰክስኮና
ተጠቦ አያውቅም፡፡

እናቴ የሠራተኛይቱን ሰውነትና ጠቅላላ ሁኔታ በመመልከት «ውይ! ምን በወጣኝ፡ ምን በደልኩዎት! ይቺማ በሽተኛ ናት፡. አልፈልግም» ሳትል በመቅረቷ በጣም ተገረምኩ፡፡

የውብነሽ አልጋዎቹን አንጥፋ ስትመለስ ልክ አራት ሰዓት ከሩብ ሆነ፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ የየውብነሽን መምጣት ስታይ ጠንቀቅ ብላ በንቃት ቆመች።
ከእናቴ በታች አዛዥ መሆንዋን ማወቋ ነበር። የውብነሽ ያን አጠር ብሉ ከርደድ
ያለ ጸጉሯን በግራ እጅዋ ይዛ እያሻሽች ከተመለከተችኝ በኋላ «ተነጥፎልሃል
መተኛት ትችላለህ» አለችኝ፡፡ እጅዋን ወደ ኋላ መልሳ ከግድግዳው ጋር ተለጥቃ
ወደ ቆመችው ሠራተኛ ዘወር ብላ «አንቺም ዕቃ ቤት ውስጥ ከዚያ ከትልቁ
በርሜል አጠገብ አንጥፈሽ ተኚ» ብላ ለማሳየት ወደ ዕቃ ቤት ገባች።
ሠራተኛይቱ ተከትላ ስትገባ ንፋስ እንደሚያወዛውዛት መቃ ወገቧ ልምጥ ልምጥ ሲል ቀዳዳው ቀሚሷ ከወዲያ ወዲህ ተወናወነ፡፡

ቁጥጥር ለማድረግ የታዘዝኩ ይመስል ተከትያቸው ገባሁ፡፡ የውብነሽ
ግድግዳው ላይ ወደ ተንጠለጠለው አጎዛ እያመለከተች «ነገና ከነገ ወዲያ ሌላ
ምንጣፍ ፈልገን እስከምንሰጥሽ ድረስ ለዛሬው ያን አጐዛ እዚህ ወለሉ ላይ ጣል
አድርጊና ተኚ። አይዞሽ አትፍሪ፡ ትለምጃለሽ» አለቻት፡፡

ሠራተኛይቱ አጐዛውን ከተንጠለጠለበት ምስማር ላይ ተንጠራርታ አወረደችው:: አጐዛው መኻል ላይ ቁልቁል የተሸረከተ የሕፃን ጭንቅላት የሚያሾልክ ትልቅ ቀዳዳ አለ። ቀዳዳውን እንዳየሁ አንድ ነገር ትዝ አለኝ።
የቤታችን ዘበኛ የነበረው ዘለቀ በግ ሲገፍ ሳት ብሎት ቆዳውን በሹል ቢላዋ ስለ
ሽረከተው አባቴ በዚያች የተነሣ ከሥራ እንዳባረረው ታወሰኝ። ከውስጣዊ
ፍርሃትና ጭንቀት የተነሣ ያ ከሲታ ፊቷ ከመጠን በላይ ጠውልጐ ይብስኑ
ሕይወት አልባ መሰለ።

«እስኪ ትንሽ አራግፈው እለች የውብነሽ በፊቷ ላይ ጥርጣሬ እየታየ፡፡
ገና ሁለት ጊዜ መታ መታ እንዳደረገችው ያንጠለጠለችው እዛ እምልጧት
ወደቀ። አጐዛው ላይ የነበረው አቧራ በመጠኑ ቦነነ ።ደንግጥ እነሣችው::
የውብነሽ አቧራውን እየተጸየፈች እስኪ እንደገና ቀስ ብለሽ መታ መታ
አድርጊው» አለቻት፡፡ ሠራተኛይቱም ከእኛ ለመራቅ ያህል ወደ ኋላ ፈግፈግ ብላ
በወዙ በኩል ሦስት አራት ጊዜ መታታችው። ልሙ ኣቧራ ወርዶ እግሯን
አለበሰው፡፡ ዕቃ ቤቱ በአቧራ ቡናኝ ተሞላ እህቴ አፍና አፍንጫዋን በቀኝ እጇ
አፈነች። ሠራተኛይቱ የአቧራው መቡነን እኛን የሚያስቆጣን ስለ መሰላት ብናኙን
እፍ እያለችና በእጅዋ እያራገበች ለማራቅ ሞከረች። አጐዛውን ከትልቁ በርሜል
ሥር ጣል ካደረገችው በኋላ ዱር አማከለች የምታነጥፈውን አሮጌ ብርድ ልብስ አጣጥፋ አስተካከለችው፡፡ ጎንበስ ቀና ባለች ቁጥር ጉልበቷ ይንቋቋል። የውብነሽ ወደ እኔ ጠጋ ብላ ለምን ታሳፍራታለህ? ሂድ እንጂ እነጣጥፋ ትተኛበት አለችኝ፡፡ «አንድ ጊዜ እንዳይ ብዩ ነው እንጂ እሺ እሄዳለሁ» ብዬ ዐይኔን ወደ ወለሉ መለስኩት፡፡ በአሮጌ ቀሚስ የተጠቀለሉ ጨርቆች መኝታው መኻል ላይ ጣለች፡፡ ወዲያው ነጠልጠል ስታደርገው ቀደም ብዩ ካየኋቸው ይበልጥ በጣም የቆሸሹና የተቀዳደዱ ቀሚሶችና ጨርቆች ወጡ፡፡ ከሁሉም ጐላ ብሎ የሚታየው ግን እንድ ጠርዝ ጠርዙ የተሸነታተረ ዐመድማ ስስ ብርድ ልብስ ነበር፡፡

ተንበርክካ ቀሚሶችዋን ካጣጠፈች በኋላ ለትራስ እንዲሆኑ አንድ ላይ ሽበለለቻቸው፡፡ የእኔ ልብ በሥቃይ ታፍና በሃዘን ስትቀዘቅዝና ጅማቴ ሲኮማተር
ተሰማኝ፡፡ ጉንበስ ቀና ባለች ቀጥር በስተኋላዋ ያለው የቀሚሷ ትልትልና ቀዳዳ ያንን ሸካራ ገላዋን በከፊል ያሳያል። እኅቴ እነዚያን የተበታተኑ ልብሶች
እየተመለከተች «ለመሆኑ ይኸ ልብስሽ ተባይ የለበትም?» ብላ ጠየቀቻት።

በእንግድነት ኃፍረት የተሸበበው አፍዋ ዝምታን ማመቅ እንጂ ቃላት ማውጣት
ስላልሆነላት ዝም አለች፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ ግን አሮጌውን ልብስ አንዴ
ወረቀት ከሽመለለችው በኋላ የእግርዋን ትቢያ ሳታራግፍ መኝታዋ ላይ
ተቀመጠች። የተጠቀለለውን ብርድ ልብስ ሳብ አድርጋ ጉልበቷን ሽፈነችው።
ተጣጥፈው በስተኋላዋ ለትራስነት የተጠቀለሉት ልብሶችዋ ማቃጠያ ውስጥ
ተከማችተው የተቃጠሉ ወረቀቶች ይመስላሉ። ግንጭሏ የታጠፈውን ጉልበቷን እስኪነካ ድረስ ካቀረቀረች በኋላ ቀሚሷን አወለቀች፡፡ ከላይኛው ቀሚሷ የባሰበትና በጣም ያረጀ የውስጥ ልብስ ብቅ አለ።

ትከሻዋ ላይ ያለው ማንገቻ ረዝሞ
በመቋጠሩ እብቱ የቄብ እንቁላል ያህላል። በእድፍ የተሰላው ልብሷ ምን ዐይነት ቀለም እንደ ነበረው አይለይም። ቀሚሷን ስታወልቅ ያንን ዐመድ መስሎ
የተጐሳቆለ ጸጉሯን ሸፍኖት የነበረው ሻሽ ከቀሚሷ ጋር ሾልኮ ዱብ አለ፡፡ አጉሯ
ወደ ፊትና ወደ ኋላ ተመነጫጨረ።አንዱ ዘለላ ጥምል ቀለም መሳይ አንገቷ
ላይ ተጥመልምሉ ወረደ። ጸጉሯ ላይ ነውር ነገር የታየበት ይመስል በጣም
ደነገጠች። ወዲያው እየተርበተበተች በዚያው በሻሽ ሸንከፍ አደረገችው። ብዙ
የኑሮ ጉስቁልና ስለ ደረሰባት የአፍላ ወጣትነቷ ጠይም ውበት ወደ ሸካራ
ጥቁረት ተለውጧል፡፡ እህቴ ያን የመሰለ ፀጉር በማየቷ በአድናቆት ተመስጣ
በውስጣዊ የቅናት ጸገግታ ተመለከተቻት:: እኔ ግን በጣም ስላሳዘነችኝ በትካዜ እንባ ባቀረሩ ዐይኖቼ ሁኔታዋን አጤንኩት። አሮጌውን የብርድ ልብስ ሳብ አድርጋ እስከ አጐጠጐጤዎቿ ካደረሰችው በኋላ ተኮራምታ ስትተኛ ጭብጥ አከለች።

የውብነሽ «ወንድም ጋሼ አንተ ብትፈልግ ቆመህ እደር፡ እኔ ምን በወጣኝ ነው» ብላ ጥላኝ ሄደች። እኔ ግን ያቺን ከፊት ለፊቴ ከበርሜል ሥር ከላይ አዳፋ ደርባ ከታች የቆሽሽ ልብስ አንጥፋ የተኛችውን ሴት ትክ ብዬ እያየሁ ሦስት ደቂቃ ያህል ቆምኩ፡፡ ለጊዜው አጥጋቢ ትርጉምና ምክንያት ያላገኘለት የሐሳብ ሞገድ አእምሮዬ ውስጥ ተነሣ፡፡ ልወጣ አቅራቢያ እንደ ራባት የውሻ ቡችላ በቀጭኗ ተንፍሳ ገልበጥ አለች። ከዚያም ምንም እንኳ የብርድ ልብሱን ዐልፌ ማየት ባልችልም እንቅስቃሴዋን ተከታተልኩ። እጅዋ ወደ ጀርባዋ ከዞረ በኋላ ከገላዋ ላይ የሚገለፈፍ ነገር ያለ ይመስል ጥፍሮቿ ያን ሲሰሙት ብቻ በድምፁ የሚያስታውቅ ሸካራ ጀርባዋን ማከክ ጀመሩ፡፡ ወዲያው ሥቃይና የስቅቅታ ፍርሃት የረመጠጣት ቀጭን ሳል ኃይሏን ወለሉ እየዋጠው ሁለት ጊዜ ተሰምታ እየሰለለች ወደመች፡፡ ከዚያ በኋላ ገመምተኛ ፀጥታ በመተካቱ መብራቱን አጥፍቼ ወጣሁ፡፡

አንጐሌ ውስጥ በቂ ኀዘናዊ ትርዒት አጭቄ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡
የመጀመሪያው ቀን በዚህ ሁኔታ ተፈጽሞ ዘልዓለም ወደማይመለስበት የትዝታ
ክልል ገባ፡፡
👍4
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


ጌትነት አዲስ አበባ አውቶቡስ ተራ ደረሰ። በመርካቶ ትርምስ፣ በህዝቡ ግርግር፣ በመኪናው ብዛት፣ በከተማዋ ውበት በእጅጉ ተደነቀ፡፡ አቶ ዓለሙ በነገሩት መሰረት ሴቼንቶ አስቆመና ጳውሎስ ሆስፒታል” ብሎ ተሳፈረ። "ከሆስፒታሉ ዋና መግቢያ በር ፊት ለፊት ያለውን ቀጭን የእግር መንገድ ተከትለህ ጥቂት ስትራመድ በባህር ዛፍ የተከበበ ትልቅ
የመኖሪያ ግቢ ታገኛለህ ከሱ አጠገብ ደግሞ አንድ ትንሽ በሸንበቆ የታጠ
ረች ግቢ ታገኛለህ፡፡ እሷ የቶሎሳ ግቢ ነች ምንም አያሳስትህም፡፡ ምናልባት ካላወቅከው ደግሞ በዚህ ስልክ ቁጥር ጎረቤት ደውለህ ቶሎሳን ታስጠራዋለህ” በማለት ስልክ ቁጥር ሰጥተውት ነበር፡፡

አቶ ዓለሙ ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ቅቤ ጭኜ ስለምሄድ አብረን እንሄዳለን ጠብቀኝ ብለውት ነበር፡፡ አስራ አምስት ቀን በጣም ረዝሞበት ሄጄ የዕድሌን ብሞክር ይሻላል ብሎ ቸኩሎ ነው ብቻውን የመጣው፡፡ ሴቼንቶው ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ አወረደው። እንደተነገረው ከሆስፒታሉ ዋና መግቢያ በር ፊት ለፊት ቀጭኗን የእግር መንገድ ወዲያውኑ አገኛት፡፡ ደስ አለው፡፡ ትንሽ ውስጥ ውስጡን እንደተራመደ ደግሞ የተ
ባለውን በባህር ዛፍ የተከበበ ሰፊ ግቢ በርቀት ተመለከተ። በደስታ ልቡ
ፈነጠዘች፡፡ እየተቃረበ ሲመጣ ደግሞ የሸንበቆ አጥሩን በቅርብ ርቀት
አየው፡፡

"ልክ ነው ያለጥርጥር የቶሎሳ ቤት እሱ መሆን አለበት! ሰው መጠየቅም
አያስፈልገኝ" አለና በቀጥታ ሄዶ በሩን አንኳኳ። አዲስ አበባንና ቤቱን ከዚህ በፊት የሚያውቅ እንጂ ከባሌ ገጠር ከተማ ወጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባን የረገጠ ሰው አይመስልም ነበር። ሸዋዬ ነበረች የወጣችው፡፡ የቶሎሳ ባለቤት...ባሏ ስለ ጌትነት አጫውቷታል። በሩን ከፍታአንገቷን ብቅ እንዳደረገች ባየችው ነገር ልቧ ስንጥቅ አለባት፡፡ ለቅፅበት ወዳለፈ የአስር ዓመት ትዝታዋ ውስጥ ሰተት ብላ ገባች። በአፍላ የጉርምስና ዘመኗ ያ በፍቅር ያበደችለት ውሽማዋ ሃምሳ አለቃ አየለ ራሱ
አፈሩን አራግፎ የመጣ ነበር የመሰላት። ዛሬ መሆኑን አላወቀችም እንጂ ሰሞኑን የቶሎሳ ዘመድ ከባሌ እንደሚመጣ ግን ታውቅ ነበር፡፡

"ጌትነት የምትባለው ነህ አይደል?" ፈገግ ብላ ተውረገረገችና ስሙን ጠርታ ጨበጠችው።ጌትነት ራሱን ከማስተዋወቁ በፊት ስሙን ስትጠራው ተገረመ።
"አዎን ጌትነት ነኝ፡፡ የጋሽ ቶሎሳ ዘመድ ነኝ፡፡ ከባሌ ነው የመጣሁት" ራሱን በሚገባ አስተዋወቀ፡፡ "ቶሎሳ ስላንተ ስላጫወተኝ ነው ቶሎ ያወቅኩህ፡፡ በል ግባ ወደ ቤት" እሷ ቀደም ብላ እሱን ከኋላዋ አስከተለችው።

ሸዋዬ መልኳ የቀይ ዳማ ሲሆን ደልደል ያለው ሰውነትዋ ከማራኪ ዳሌዋ እና ከቁመትዋ ጋር በምጥን የተሰራ የደስ ደስ ያላት ዐይነ ግቡ ሴት ናት። ቶሎሳን ከማግባቷ በፊት በሴተኛ አዳሪነት የምትተዳደር ወንዶች የሚሻሙባት ጉብል ነበረች፡፡ ባሏ ቶሎሳ ከባሌ ኮብልሉ አዲስ
አበባ ከገባ በኋላ የመጨረሻ እንጀራው የሆነውን የልብስ ስፌት ስራ በመጀመር ማለፊያ የእለት ገቢ እያገኘ ሲመጣ ከሸዋዬ ጋር የጀመሩትን ትውውቅ በትዳር ትስስር አጠናክረውት በሚያገኘው ገቢ በፍቅርና በደስታ መኖር ከጀመሩ ሁለት አመት ሆኗቸዋል፡፡ ቶሎሳ ጌትነት የሚመጣበትን ቀን በእርግጠኛነት ባያውቅም ሰሞኑን ሊመጣ እንደሚችል ግን ግምት ነበረው፡፡ ለምሳ ቤቱ ሲገባ ጌትነትን ጉብ ብሎ ሲያገኘው አላመነም፡፡ በደስታ ሄዶ ጉንጩን እያገላበጠ ሳመው ከዚያም የዘመድ አዝማዱን የጋራ ሽንተረሩን የአራዊት የእንስሳቱን ታሪክ ሳይቀር በሰፊው አንስተው ሲጨዋወቱ ቆዩ። ቶሎሳ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ቢሆንም ለጌትነት ሲል ተራራ የመውጣትን ያክል በሚከብደው የአማርኛ ቋንቋ ሊያዋራው ተገዶ ነበር፡፡ ከዚያም ስለ ሟቹ መኩሪያ አንስቶ ትንሽ ከተካከዙ በኋላ "ለመሆኑ ሽማጊሌ ሂንዴት ኖ?" በማለት ስለ አባቱ ጋዲሳ ጠየቀው።

"እንዴ! አባባ ጋዲሳ! በጣም ደህና ናቸው፡፡ ከሳቸው አንተ ሳታረጅ ትቀራለህ ጋሽ ቶሎሳ ?" ሲል ቀለደ ጌትነት።
“ኡነቲንኖ ጌቲነት ኢነሱኮ ቱኩስ ሆተት ቀማሚሳሉ። ሆተት ሀጢንት ጠንኪራል። ኤኛማ ሚን አላ? ሀንበሳ ሆተቲ ቢሎ ጠራ ሀረቄና በኢርድ ቢጥቢጥ በጠበጠች ኒቦቹ ፏፏቴ ሲም ሂንጂ ጢቂም ኤለም፡፡ ኒቦቹ ፏፏቴ
ሁሽቲ ኖ፡፡ ዚንቦቹ ፏፏቴ ማለት ኢሻላል፡፡ ማር ኤለም ኢርዲና ሱኳር ሰጠች ኡሃ ቢቻ! ሀንበሳ ሆተቲ ቢሎ ሞጋጊሶ ሀረቄ ሀንጀት ሊጣለች ኢንጂ ገልጊሎት ኤለም፡፡ ኡሳን በየቀኑ ቀማሚሶ ሀረጀ!” ጌትነት በቶሎሳ አነጋገር ይስቃል።

"ኦሮጊቷስ ሂንዴት ነች ባኪ?" አሁን ደግሞ ስለ እናቱ ነው ቶሎሳ ጠይቀው።
"እንዴ እማማ እቴነሽ?ያቺ የቁርጥማት በሽታቸው አልፎ አልፎ እየተነሳች ታስቸግራቸዋለች እንጂ በጣም ደህና ናቸው፡፡ መቼም በየበአላቱ የምትልክላቸውን አዲስ ልብስ እየለበሱ በየጎረቤቱ እየዞሩ እየመረቁህና
እያስመረቁህ በደስታ ሲፈነጥዙ ነው የሚከርሙት፡፡ ዕድሜውን ያርዝምልኝ ልጄ ደርሶ ጦረኝ እያሉ። በሬሳ ውስጥ ጥሩ ስም ነው ያላህ ጋሽ ቶሎሳ!” በዚህ ጊዜ አቶ ቶሎሳ ከጥርሶቹ ፈሽረክ አለ፡፡ ፊቱ እንደ ፀሀይ አበራ። ጥቃቅን ዐይኖቹ ሳቁ... ደስ አለው።

ቶው ባኪ! ደሲ ሲሎት መሪቃሌች ጌቲነት ?!"
“ጋሽ ቶሎሳ እነሱ እኮ ብዙ አይጠብቁም፡፡ ትንሿን ነገር እንደ ትልቅ ነው የሚቆጥሩት ዋና ደስታቸው ልጄ አስታወሰኝ በሚል ነው" ቶሎሳ መልኩ ወደ ጥቁረት ያደላል። ፊቱ መጣጣ ሲሆን ዐይኖቹ ጉድ
ጓዶቻቸው ውስጥ ገብተው የተደበቁና ግንባሩ የተሸበሸበ ያለ እድሜው
ያረጀ የሚመስል የሰላሳ ስድስት አመት ሰው ነው። ሰዎች ወሬ ሲያወሩለት" ቶሌ ኢኮ?" ማለት ይወዳል።“እሺ እባክህ?” እንደማለት። በዚህ ሁኔታ ሲጨዋወቱ ቆይተው ምሳቸውን ከበሉ በኋላ ሸዋዬ ያፈላችላቸውን ቡና መጠጣት ጀመሩ፡፡ቶሎሳ ወደ ስራው ተመልሶ መሄድ አልፈ
ለገም፡፡ ይልቁንም ከጌትነት ጋር ወጣ ብሎ መዝናናት ነው ያሰኘው። ቡናውን ጠጥተው ከጨረሱ በኋላ "ሸዋዬ ኮ!" አላት።ሁሌም ሊያቆላምጣት ሲፈልግ እንደሚለው ዐይን ዐይኖቿን በፍቅር እያየ፡፡ "የኔ ሸዋዬ" ማለቱ ነው፡፡ ቀና ብላ በነዚያ በሚያባብሉ ዐይኖቿ አየችው።

“ቲኒሽ ዞር..ዞር.ሀዲርጌ ሰፈሩን ሀሳዪቼ መጣሉ” ጌትነት እንዲሰማ በዚያው በተሰባበረ አማርኛ እያዋራትና ከወደኋላዋ መጥቶ በእነዚያ ጥቃቅን ዐይኖቹ መቀመጫዋን በፍቅር እያየ ነገራት።
“በሉ እንዳታመሹ” አለች ንቅሳታሚ ሽዋዬ፡፡ በዚያ አረግራጊ ዳሌዋ ትንሽ
ወዝወዝ እያለችና የቡና ጀበናውን ለማንሳት እያጎነበሰች።

"ሀናመሺም ቶሎ ኖ ሚኒመጣ ሽዉ.ኮ ጎንበስ ስትል አጭሩ ቀሚስ ወለል ካደረገው ውብ ጭኖቿ ላይ ዐይኖቹ በስስት ተተክለው እየተንከራተቱ፡፡ ጌትነት ዐይኖቹን ዘወር አደረገ፡፡ ተያይዘው ወጡ...
“ና ሂስቲ ኢዚ ቲኒሽ ኢረፍት ኢናዲርገው" ጠጅ ቤት ከመሄድ ይልቅ ለጌትነት ክብር ሲል የመረጠውን ግሮሰሪ በጣቱ ጠቆመውና ተያይዘው ገቡ፡፡
"ኢስቲ ባኪ ሁለት ቀዘቀዘ ቢራ አመጣ!" አለ ቶሎሳ ለአስተናጋጁ፡፡
"እኔ ቢራ አልጠጣም ጋሽ ቶሎሳ !" አለ ጌትነት፡
" ባኪ ጠጣ ቢራኮ ገቢሲ ኖ፡፡ ጠላ ማለቲ ኖ" ሊያግባባው ሞከረ።
“ጋሽ ቶሎሳ ሙት!አልጠጣም፡፡ ለኔ ለስላሳ ይምጣልኝ" አስተናጋጁን
ለስላሳ እንዲያመጣለት ጠየቀው። ከዚያም ለጌትነት ኮካ ለቶሎሳ ደግሞ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ተከፈተላቸው፡፡
“በጨቅጫቆ ሊቡን ደረቀ ኢስቲ ሆደ ቁም ነገሩ ጊባና ሲላንተ ጉዳይ ሚኒነጋገሮ" ጌትነት ይሄንን ርዕስ ጉዳይ በናፍቆት ሲጠባበቀው የነበረ በመሆኑ ደስ አለው። ሳያንገራግር ወደ ጉዳዩ በቀጥታ ገባ፡፡
“እንደምታውቀው አባባ ከሞተ በኋላ
👍31
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ


...“ኸንጉሥ እጅ እንዴት እናመልጣለን?...”
ኢሳያስ፣ የሰማት ይመስል ወደ ጉዳዩ መግባት ፈለገ። አንዴ
ዮልያናንና እንኰዬን ሌላ ጊዜ ደግሞ ግራዝማችን ዐይኑን ተክሎ
ተመለከተ። ፊቱን ወደ ዮልያና አዞረና ፈገግታ ለገሣቸው።

ዮልያና የሆነ ነገር ሊነግረኝ ነው ብለው ጠረጠሩ፤ ለመስማት ጓጉ።

“እመቤቴ... ዋናው የመጣንበት ጉዳይ...” ብሎ እንደገና ሁሉንም
ተመለከተ። ቀጠለና፣ “እመቤቴ... ዋናው የመጣንበት ጉዳይ... ጃንሆይ...በተለይም እኔን ልከውኝ ነው። እርሶ እንዳሳደጓት ስላወቁ የልዥ ልዥዎን እጅ ስለፈለጉ እኼን ለማብሰር ነው የመጣን። ቅድም ግቢው መግቢያ ላይ ልዣችሁ መሬት ላይ ጦር ሲተከል አይታ፣ ደንግጣ ነው መሰል፣ ኸተቀመጠችበት ተነሣች። ለበጎ እንደመጣን ንጉሥ እጅ ሲጠይቅ እንደሱ መሆኑን ሳታውቅ ቀርታ” አለ።

ወለተጊዮርጊስ አመዷ ቡን አለ፤ ሰማይ ምድሩ ዞረባት። ንጉሡ?
እንዴ ንጉሡ የኔን እጅ ሊጠይቁ? እንዴት ሁኖ አለች። እንግዶቹ የሷን
እጅ ሊጠይቁ እንደመጡ ደመነፍሷ ቢነግራትም ለንጉሥ ሚስትነት መሆኑ ግን ከግምት በላይ ሆነባት፤ ተደናገጠች፤ ተርበተበተች፤ ፊቷ የበሰለ ቲማቲም መሰለ፤ ጉንጮቿ ተቃጠሉ። ዐይኖቿን ጨፍና ራሷን
ነቀነቀች፤ ሊሆን አይችልም በሚል መልክ። አንዴ በኔና በጥላዬ
ማይመጣ የለም ማለት ነው? እንባ እንባ አላት። የምታስበው ጠፋት፣ ጭንቅላቷ ባዶ ሆኖ ተሰማት። ጣሪያው ላይ አፈጠጠች- ለዚህ አስደናቂ
ለሆነባት ጉዳይ መልስ ይሰጣት ይመስል። አያቷም በሰሙት ነገር ቢደናገጡም ስሜታቸውን ሰብሰብ አድርገው፣
“እኔ ላሳድጋት እንጂ የወለዱ እኮ እነሱ ናቸው” አሉ፣ መብረቅ
የመታቸው ያህል ድርቅ ብለው የተቀመጡትን ልጃቸውንና ግራዝማችን በአገጫቸው እያመለከቱ። “እነሱ ናቸው መጠየቅ ያለባቸው” አሉ፣
ራሳቸውን እየነቀነቁ።

ኢሳያስ፣ “ርግጥ ነው። የጃንሆይም ፍላጎት ያ ነው። ኻለነሱማ እንዴት ይሆናል? ለመቤቴም ለግራማችም ነው ጥያቄው የቀረበ። እመቤቴ..
ግራማች... ዛዲያ ምን ታስባላችሁ?” አለ። ንጉሥ ልጃችሁን ስጡኝ ሲል ለማንም ቢሆን ብስራት ነው የሚል ቃና ድምጹ ላይ አክሎበት።እመቤት እንኰዬንና ግራዝማች መንበርን በተራ ተመለከተ። የዮልያናን
ቅሬታ ያዘለ አነጋገር ማርገብ ችሎም እንደሆን ፊቱን መለስ አድርጎ አያቸው።

ዮልያና ግን ሐሳባቸው ሌላጋ ከንፏል። ከዓመታት በፊት አንድ
ሌሊት አይተውት የነበረውና ምንጊዜም ቢሆን ሲያስደንቃቸውና ላገኙት ሁሉ ሲያወሩት የነበረው ሕልማቸው ትዝ ብሏቸዋል።

ያን ሌሊት፣ እንደወትሯቸው ጸሎት አድርሰው ከተኙ በኋላ፣ ፀሐይ
ቤታቸው ሰተት ብላ ገብታ ተጎናጽፈዋት ተኝተው አዩ። ከእንቅልፋቸው ብንን ብለው ነቅተው ተቀመጡ። ባዩት ሕልም ተደነቁ። ጠሐይ ቤቴ የገባችው አለነገር ማዶል። ጠሐይ መሪ ነው፤ ብርሃን ነው ይላሉ፡፡
አገር ብርሃን ትሆናለች ማለት ነው። ግና እንዴት? አሉ፤ ለራሳቸው።

የሕልማቸውን ትርጉም ለማወቅ ተመራመሩ። መቸም አለምኸኛት
እንዲህ ያለ እልም አላሳየኝም፡፡ አንድ ነገር ቢኖር ነው። እስቲ ነገ
ጠዋት እኛ መነኩሴ ዘንድ ኸጀ ሚሉትን ሰማለሁ። አይ የነእንኰዬ
አባት በኖሩ። እሳቸው እኮ ኸኔ የተሻለ እልም መፍታት ይችላሉ እያሉ ሲገላበጡ አደሩ። እንቅልፍ ባይጠግቡም፣ ማለዳ ከመኝታቸው ተነሡ።ውዳሴ ማርያማቸውንና ዳዊታቸውን ደግመው መነኩሴውጋ ለመሄድ
ሲዘገጃጁ የደስ ደስ ስሜት አቅበጠበጣቸው። ቁርስ ላድርግ ሳይሉ አሽከር አስከትለው ወጡ።
መነኩሴው ወፍታ ጊዮርጊስ ግቢ ውስጥ ጥድ ስር ተቀምጠው
መቁጠሪያ ይዘው ይጸልያሉ። ዮልያና ወደቤተክርስቲያኑ ሄደው
ከተሳለሙ በኋላ፣ መነኩሴው ጸሎታቸውን እስኪጨርሱ ድረስ ፈንጠር ብለው ድንጋይ ላይ ተቀመጡ። መነኩሴው ጸሎታቸውን ሲጨርሱ፣
ለዮልያና እጅ ነሡ። ዮልያና ተነሥተው እጅ ነሥተው ሲቆሙ
እንዲቀመጡ መነኩሴው በምልክት ነገሯቸው።

ዮልያና ድጋሚ እጅ ነሥተው ጠጋ ብለው ተቀመጡ። ስለጤንነታቸው
ከጠያየቁ በኋላ፣ “ያው መቸም ኸርሶ ዘንድ ምመጣው አንድ ነገር
ሲገጥመኝ ነው። ዛሬ ስንኳ አንድ ዘመዴ እልም አይታ ሚፈታልኝ
ብትለኝ ነው የመጣሁት። ድቅድቅ ያለ ጨለማ ይመስለኛል አለች...
ጠሐይ ኸተኛሁበት ድረስ ገብታ ቤቴንና መላ ሰውነቴን አበራችው።
ኸያ በኋላ ጠሐይቱን ተጎናጽፌያት የተኛሁ ይመስለኛል ብላ ነገረችኝ።”

መነኩሴው በጥሞና ካዳመጡ በኋላ፣ “ብርሃን ሥልጣን ነው። እኼን እልም ያየች ሴት ንጉሥ ትወልዳለች” አሏቸው።
ዮልያና ደነገጡ። “እልሙን ያየችው ሴት ኸንግዲህ መውለድ
አትችልም። ዕድሜዋ አልፏል፤ የወር አበባም የላት” አሉ።

“ኸዘር ይፈጠማል። ኸልዥ ልዥም ይሆናል።”

ዮልያና በሐሳብ ከሄዱበት ተመለሱና እልሜ ገሀድ መሆኑ ነው። ድንቅ! የእዝጊሃር ፈቃድ ይፈጠም ብለው ልጃቸውን የጎንዮሽ ተመለከቱ። ወይዘሮ እንኰዬ ግን የቅድስት ወለተጴጥሮስን ንግርት
አስታውሰው እናታቸው እያይዋቸው መሆኑን ልብ አላሉም።

በአፄ ስሱንዮስ ዘመን የቆራጣ ገዳም እመምኔት የነበረችው ቅድስት ወለተጴጥሮስ መንገድ መሽቶባት ለአንድ ምሽት አያቶቻቸው ቤት ዐርፋለች። የቤቱ እመቤት ሌሊት ላይ ድንገት ምጥ ጸንቶባት ወደ በረት ተወስዳ፣ ሴቶች መቀነቻቸውን ወንዶች መታጠቂያቸውን ፈተው ሲጸልዩ፣ ወለተጴጥሮስም መቀነቷን ፈትታ ፊቷን ወደ ምስራቅዐመልሳ አጥብቃ ጸለየች። ሴቲቱም ወንድ ልጅ በደሕና ተገላገለች።
ወለተጴጥሮስ በማግስቱ መንገድ ከመጀመሯ በፊት፣ “ኸዝኸ እጣን ዘር መልካም ዝናው ሚነሣ ንጉሥ ይወለዳል። ንግሥቲቱም በሥራዋ ስሟ ሲወሳ ይኖራል። ኸዳር እዳርም አገሯን ታስከብራለች” ብላ ቋራን፣ “ምን ግዝየም አብቅይ፣ መልካም ፍሬ ይብቀልብሽ” ብላ ተሰናብታ ወጣች።

እረገኝ ንግሥቲቱ ወለቴ መሆኗ ነው። ንጉሡ ደሞ ኸሷ ሚወለደው ነው አሉ እንኰዬ።

ኢሳያስ “ምን ታስባላችሁ?” ለሚለው ጥያቄው መልስ ባለማግኘቱ ልጠይቅ አልጠይቅ እያለ ከራሱ ጋር እየተሟገተ ቆይቶ፣ “ዛዲያ ምን አሰባችሁ ግራማች?” አላቸው።
ግራዝማች መልስ መስጠት ፈልገው ምላሳቸው ተቆለፈ። “እ... እረ.. እንዳው...መቸም...” ድምፃቸው ተቆራረጠ፤ የጀመሩትን ለመጨረስ ቃል አጠራቸው።

ኢሳያስ ካቆመበት ቀጥሎ፣ “መቸም...” ብሎ ግራዝማችን አያቸው።
“መቸም ለልዥዎ ለንጉሥ ሚስትነት ኸመታጨት የበለጠ ዕድል ኸየት ይመጣል? የጐንደር ወይዛዝርት ሆኑ የጦቢያ የነገሥታት ዘሮች ሁሉ ያላገኙትን ዕድል እኮ ነው ያገኘች” አላቸው።
ዕድል? እንዴት ሁኖ ነው ዕድል ሚሆን? አለች ወለተጊዮርጊስ፣
እያየችው። ዞር ብላ አባቷን ተመለከተቻቸው። እሳቸው የጭንቀት ስሜት አጥብቆ የተሰማቸው ይመስላሉ። ግንባራቸው ላይ ቸፍ ያለው
ላብ ቁልቁል ሊወርድ ይጋበዛል። ሆዷ ውስጥ አንዳች ነገር ተላወሰ።
ግንባሯን ያራሰውን ላብ በእጅጌዋ ጫፍ አባበሰች።

ከበድ ያለ ፀጥታ ሰፈነ።

“ግራማች ዛዲያ ምን ያስባሉ?” አሉ፣ ከሁሉም ተለቅ ያሉት እንግዳ።

እንዳው ለነገሩ ጠየቁ እንጂ ግራዝማች ምርጫ እንደሌላቸው ያውቃሉ።ግራዝማች ግን በልባቸው ወይ አንተ የወፍታው አያልቅብህ፡፡ ያ ሁሉ ባላባት ዐይናማ ልዥህን እያለ ለራሱ ሆነ ለልዡ አማላጅ ሲልክ ሁነኝ ጋር አንድ ቀን እንታረቃለን፣ ልጄን ለልዥህ ብየ ሳበቃ እንዴት
👍12
#ሳቤላ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

« ለምን አልሔድም ? ሰዎች ሲጠይቁኝ አጋጣሚ መሰበሩን እንግራቸዋለሁ።

ሚስዝ ቬን ከት ብላ ሣቀችባትና
«ሰዎች ቢጠይቁኝ!» አለች በማፌዝ ድምፅ የሳቤላን አባባል በመድገም «እነሱማ የሎርድ ማውንት እስቨርን ልጅ የጌጥ
ችግረኛ ናት ብለው ከማሽሟጠጥ አልፈው ምን ሊሉ ኖረዋል ብላ አሾፈችባት።

ሳቤላ ሣቅ ብላ ራሷን ነቀነቀችና «አልማዞቹን ባለፈው የዳንስ ምሽት አይተዋቸዋል » አለቻት ።

« ይኽን በደል በኔ ላይ አድርሰሽው ቢሆን ኖሮ ፍራንሲዝ ሌቪሰን» አለችው ባልቴቷ «ለአንድ ወር ሙሉ ከቤቴ አላስደርስህም ነበር ። ምንድነው ነገሩ …...…… ኤማ? የምትሔዱ ከሆነ አሁን ሒዱ ። ዳንሱ የሚጀመረው በአራት ሰዓት ነው " በኔ ዘመን በአንድ ሰዓት ነበር የምንሔድ ፡ ዛሬ ደግሞ ሌሊቱን ወደ ቀን መለወጥ ልማድ ሆኗል ። »

« ሣልሳዊ ጆርጅ ራቱን የበግና ያትክልት ቅቅል በአንድ ሰዓት ይበላበት በነበረበት ጊዜ አለ ለአያቱ ከሚሲዝ ቬን የተሻለ አክብሮት ያልነበረው ካፒቴን ። ይኽን እየተናገሩ ደረጃዎቹን ደግፎ ሊያሳፍራት ስለፈለገ ወደ ሳቤላ ዞር አለ እንዳሰበው ይዞ ወርዶ ከሠረገላው ሲያሳፍራት ሚሲዝ ቬን ግን ብቻዋን ወርደች። በዚህ ጊዜ ይባሱን ብግን ብላ ተናደደች ።

« ደኅና እደር » አለችው ።
«ደኅና እደሩ አልላችሁም እኔም እናንተ እንደ ደረሳችሁ ተከትዬ እደርሳለሁ» አላት "

« አልመጣም ብለኸኝም አልነበር?የወንደላጤዎች ድግስ ያላችሁ መስሎኝ »

« ብዬ ነበር ግን ሐሳቤን ለወጥኩ " በይ ለአሁኑ ደኅና ሁኝ ወይዘሮ ሳቤላ "»

« እስኪ አሁን አንዲት ብጣሽ የተማሪ ሐብል አድርገሽ ያየሽ ሁሎ ምን ትመስይው ይሆን ? » አለች ሚሲዝ ቬን መነዝነዟን በመቀጠል "

« እሱስ ምንም አልነበረም ሚስዝ ቬን ? እኔን ያሳዘነኝ የመስቀሌ
መሰበር ነው ። እናቴ ልትሞት ስትል ነበር ይህን መስቀል የሰጠችኝ " ጉዳት ከማይዶርስበት ቦታ በደንብ አስቀምጬ አንዳች ችግር ሲደርስብኝ ወይም የሒሳብ እርዳታ የሚያስፈልገው ጉዳይ ሲገጥመኝ እሱን እያየሁ የእናቴን ምክር ለማስታወስ በመሞከር እንድከተላቸው ነግራኝ ነበር " አሁን ግን ተሰበረብኝ ነገሩ ደስ አላለኝም " ገዱ አላማረኝም " »

በሠረገላው ውስጥ እንዳሉ የመንገዱ የጋዝ መብራት ሳቤላ ፊት ላይ ቦግ ብሎ ሲበራ ፊቷ በዕንባ እንደ ታጠበ ሚስዝ ቬን አየቻት » «አሁንም እንደገና ማልቀስ ጀመርሽ ? እኔ ልንገርሽ ! በለቅሶ ደም የለበሱ ዐይኖችሽን እያየሁ አንቺን ይዤ ከዳርት ፎርድ መስፍን ዘንድ መቅረብ አልችልም " ስለዚህ ለቅሶን የማታቆሚ ከሆነ
ሠረገላው ወደ ቤት ይዞሽ እንዲመለስ አድርጌ እኔ ብቻዬን እሔዳለሁ »

ሳቤላ በረጂሙ ተነፈሰችና ዐይኖችዋን አብሳ ዕንባዋን አደረቀች » « ስባሪዎቹን ማስቀጠል እችላለሁ " ለኔ ግን እንግዲህ ተመልሶ እንደ ዱሮው ሊሆንልኝ አይችልም»

«ለመሆኑ ስባሪዎቹንስ ከምን አዶረግሻቸው ? » አለቻት ሚስዝ ቬን በቁጣ «ይዣቸዋለሁ እኒህውና ኪስ ስለሌለኝ ነው» አለቻትና ከምኗ ላይ እንዳኖረችው
በእጅዋ አሳየቻት "

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከግብዣው ቦታ ደረሱ ሳቤላም ንዴቷን ረሳችጡ ፀሐይ መስለው የበሩት ክፍሎች ልብን የሚሰውር የሕልም ዓለም መስለው ታዩአት
ምክንያቱም ልቧ ግና በአፍለኝነቱ ነበርና የመርካት ልምድ አልነበራትም የገባችበት ቦታና ሁኔታ ብርቅና ድንቅ ሆነባት ከዚያ በድምቀቱና በውበቱ ከሰወረው አዳራሽ እንደ ገባች ይቀርብላት የነበረው የአክብሮት ሰላምታ ስታይ እጅ ስትነሣ በጆሮዋ ይንቆረቆሩ የነበሩትን የውዳሴ ቃላት ስትሰማ የተሰበረውን
መስቀል እንዴት አድርጋ ታስታውሰው !

« ታዲያስ » አለ አንድ የኦክስፎርድ ተማሪ ለቫልስ ተጨዋቾች ቦታ ለቆ ወደ
ግድግዳው እየተጠጋ «እንደዚህ ወደ መሰሉ ቦታዎች መምጣት ያቆምክ መስሎኝ ነበር " »

« አዎን ትቸው ነበር » አለ ሁለተኛዉ «አሁን ግን በማፈላለግ ላይ ስለሆንኩ ሳልወድ ተመለስኩባቸው እኔ መቸም እንደ. ዳንስ አዳራሽ የሚሰለች ነገር ያለ አይመስለኝም " »

« ምንድነው የምታፈላልገው ? »

« ሚስት ነዋ ! አባቴ እስካልተሻሻልኩና እስካልታረምኩ ድረስ ዕዳ የሚባል ነገር እንደማይከፍልልኝ ለኔም አንዲት ሽልንግ እንኳን እንደማይጥልልኝ ምሎ ተገዝቶ ገንዘብ ከልክሎኛል " አሁን ለመስተካከል የመጀመሪያ ደረጃ ብሎ ያመነበት
ሚስት ማግባት ስለሆነ የምትመስለኝን መምረጥ ይዣለሁ እንዳልተወው ማንም ከሚያስበው በላይ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቄአለሁ ።

« ታዲያ አዲሲቱን ቆንጆ አታበም እንዴ ! »

« ማናት እሷ ? »

« ሳቤላ ሼን " »

« ለጥቆማህ በጣም አመሰግናለሁ» አለው «ግን ማንም ሰው ቢሆን ክብሩን የሚጠብቅ አማት እንዲኖረው ይፈልጋል " ሎርድ ዊልያምና እኔ ተመሳሳይ አመል ስለ አለን ከዜ ብዛት ልንጋጭ እንችላለን " »

« ሁሉ ነገር እኮ ተሟልቶ አይገኝም ልጂቱ በመልኳ መሰል የላትም ።
ያ ቀጣፊ ሌቪሰን ወደ አሷ ጠጋ ጠጋ ሲል አይቸዋለሁ እሱ ዶግሞ ሴቶችን በሚመለከት ረገድ የሚያቅተው ነገር ያለ አይመስለውም" »

« ታዲያ እኮ ብዙ ጊዜ እንዳሰበ ይሆንለታል " »

« እኔ አሱን ሰውዬ አጠላዋለሁ " ጫፉን ጥቅልል እያደረገ የያበጥረሙ ጸጉሩን የሚብለጨለት ጥርሶቹንና ነጫጭ እጆቹን እያየ ያለሱ ሰው ያለ አይመስለውም » ስለ ሰው ጉዳት ምንም ስሜት የለውም ለመሆኑ ያ ተዳፍኖ የቀረ
የሚስተር ቻርተሪዝ ጉዳይ ነገሩ እንዴት ሆነ ? »

« ማን ያውቀዋል ? ሌቪሰን ከነገሩ እንዶ ዐሣ ተሙለጭልጮ ወጣ " ሴቶቹም እሱ ከፈጸመው ጥፋት በሱ የደረሰበት በደል ይበልጣል ብለው ተከራከሩለት » ከሕዝቡም ሦስት አራተኛው አመናቸው " ይኸውልህ መጣ I የዊልያም ቬን ልጅም አብራው አለች " »

ሳቤላና ሌቬሰን እየቀረቡ መጡ " ስለ መስቀሉ በድንገት መሰበር እየደጋገመ ፀፀቱን ይገልጽላት ነበር " « እንግዲህ ተመልሶ እንደ ነበረው የሚሆን አይመስለኝም» አላት ቀስ ብሎ በጆሮዋ « መቼም uመኔን በሙሎ ልባL ኀን ስልጽ
ብኖር የምተካው አይመስለኝም "

መንፈስን እያነቃቃ የደስታ ስሜትን እየነካካ ከአእምሮ የሚገባው ረጋ ያለው ሥልተኛ አነጋገሩ ጆርን የሚያስደስት ልብን የሚያሳስት አደገኛ ነበር "
ሳቤላ ቀና ብላ ስትመለከተው ዐይኖቹ ከሷ ላይ ተተክለው ሲስለመለሙ አየቻቸው እንደዚያ ያለ ቋንቋ አጋጥሟት አያውቅም ነበርና እሶም ጉንጮቿ ተለዋወጡ
ዐይኖቿ ክድን አሉ ልትናገራቸው የነበሩት ቃላት ከከንፈሯ ደርሰው ጠፉባት "

« ሰውየው አጭበርባሪ ይመስላል» አለ መኮንኑ "

« ነውና " እኔ እንኳን ስለሱ አንድ ሁለት ነገሮች ዐውቃለሁ " አሁንም ይች ልጅ ቆንጆ ስለሆነች ለዝና ሲል ልቧን ያጠፋዋል " ከሷ ለሚቀበለው ስጦታ ግን ለመመለስና የሚያስበው ውለታ የለውም».....
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዌስት ሊን የፋብሪካ ወይም የአንድ ካቴድራል ከተማ ወይም የክልሉ አስተዳደር ዋና ከተማ አይደለችም" ነገር ግን ምንም እንኳን በጥንታዊ ልማዱና ባህሏ ወደ ኋላ ቀረት ያለች ብትሆንም ራሷን በተለይ ደህና ከተማ አድርጋ ትቆጥራለች ለፓርላማ ሁለት እንደራሴዎችን ትወክላለች
👍20👎1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሁለት ሳምንት አለፈው ካርለትና ከሎ የየራሳቸውን የጕዞ ዝግጅት ሲያደርጉ ሰነበቱ። ከሎ ሐመር ሲሄድ የሚያነባቸው ልብወለድና
ታሪክ ነክ የአማርኛ መጻሕፍት፣ መጽሔቶች፣ በእንግሊዝኛ የተጻፉ
ልብወለድና የሳይንስ መጻሕፍትን እየገዛ ከፊሉንም እየተዋሰ
አዘጋጀ"

በተለይም ካርለት ኮተቷ በዛ" በማስታወሻዋ በዝርዝር ከያዘችው
አስፈላጊ የምግብ ዓይነቶች የታሸገ የዓሣ፣ የአሳማ፣ የከብት ሥጋ የድንች የዱባ፣ ያጃ ሾርባI የፓፓያ፣ የብርቱካን፣ የአናናስ
ጭማቂ ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር የበዛበት ብስኩት ደረቅ ብስኩት የቆርቆሮ ቢራ ወዘተ ከመድኃኒ ዓይነትም ክሎሮኪን፣ ፓልዱሪን፣ ኒቫኩይን ለወባ መከላከያI ሌሎች፣ «አንቲባዮቲክስ» መድኃኒቶችንና የመጀመሪያ ሕክምና ኪት ኮዳክ ፊልሞችI ባትሪ
ድንጋዮችI ሶፍቶች ወዘተ. በአራት የፕላስቲh ሣጥኖች ደረደረች" ካኖንና ፔንታክስ ካሜራዋንና የተለያየ መጠን ያላቸውን ሌንሶች
በእጅ በሚንጠለጠለው ቦርሳዋ ካኪ ሱሪዎች፣ ካኔትራ፣ ውስጥ
ሱሪ ፎጣ፣ ጡት ማስያዣ፣ ስሊፒንግ ባግ፣ ግራጫ  መልክ ያለው ሹራብ በአየር የሚሞላና ሌላ ተጣጣፊ ፍራሽ፣ ሳሙና፣ ኦሞ፣
ከሁለት መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በሞዛርት የተቀነባበሩ የፒያኖ ሶናታና የፒያኖ ኮንቸቶ የቤቶቪን ሲንፎኒ ከሦስት ጊዜ በላይ
የወርቅ ዲስክ አሸናፊው ድምፃዊ የቢሊ ጆይል፤ ከሦስት መቶ ዓመት
በፊት የነበረውና የሲንፎኒ አባቱ የሃይደን እንዲሁም ሌሎቹን የባሮክ
ክላሲካል፣ ሮማንቲክና ዘመናዊ የሙዚቃ ካሴቶችን፣ ማስታወሻ፣
ብዕር መጻሕፍትና መጽሔቶች በአራት ማዕዘኑ የብረት ሣጥን
ውስጥ ከተተች" ለሽፍን ላንድ ክሩሰር ቶዮታ መኪናዋም በሁለቱም
ታንከር ነዳጅ ሞላች“ አምስት ጀሪካን ናፍጣም ለመጠባበቂያ ያዘች
ካርለት ለሦስት ወራት የሚያስፈልጋትን ቁሳቁስ ካሟላች በኋላ
ቀሪውን ዕቃዋንና ገንዘቧን ስቲቭ በሰጣት ክፍል ውስጥ
አስቀመጠች» ለአንዳንድ ወጪ ብላ የያዘችውን ሦስት ሺህ አምስት
መቶ የኢትዮጵያ ብርም በሹራቧ ውስጥ በሰፋችው ስውር ኪስ፣
አንገቷ ላይ በምታንጠለጥለው የጨርቅ ቦርሳና ብረት ሣጥኑ ውስጥ
አhፋፍላ ያዘች
ሰኞ ጠዋት ልክ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ላይ አራት ኪሎ ሞቢሉ
ጎን ካለው ሱቅ በር ላይ በቀጠሯቸው ተገናኙu ካርለት ልጥፍ የኋላ
ኪስ ያለው ካኪ ሱሪ፣ ተረከዙ ፕላስቲክ የሆነ ሽፍን ባለማሰሪያ
ማ፣ ቡና ዓይነት ቲ–ሸርት ለብሳ፣ አንገቷ ላይ አነስ ያለ ነጭ ፎጣ
ጣል አድርጋ፣ ከመኪናው በመውረድ የከሎን «ዩኤስኤ» የሚል
ወስፋት የነፋው የሕፃን ሆድ መስሎ የተወጠረ ቦርሳ የኋላ በሩን ከፍታ
በዕቃ ከሞላው መኪና ውስጥ በአንድ በኩል ባለው ክፍት ቦታ
አስገባችና ወደ መኪናው ውስጥ ገቡ" ካርለት የውኃ ኮዳዋን፣ ዳቦ
የያዘ ላስቲኳን አቀረበችና ከከሎና እሷ መካከል ካለው የካሴት ሣጥን
የሞዛርትን ፒያኖ ሶናታ ወደ መኪናው ቴፕ አስገብታ ማስታወሻዋን
በማውጣት የተነሡበትን ሰዓት መዘገበች" ከዚያም ፈገግ ብላ
«መሄድ እንችላለን?» አለችው።

«ኢ ህ» አላት ከሎ፣ ዝግጁ መሆኑን አንገቱን በማወዛወዝ እየገለጸ። ካርለት፣ ቀኝ እጇን ማርሹ ላይ በማስቀመጥ፣ በግራ እግሯ ፍሪሲዮኑን እረግጣ፣ የመኪናውን መስተዋት አየትየት በማድረግ
በአራት ኪሎው የድል ሐውልት ወደ ቀኝ ታጥፈው፣ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት አድርገው ቁልቁል ወደ መስቀል አደባባይ ወረዱ።
ከዚያም በደብረ ዘይት መንገድ ወደ ቃሊቲ፣ አቃቂ፣ዱከም ተጕዘው ደብረ ዘይት ከተማ ሲደርሱ ወደ ግራ ታጥፈው ሁለት ኪሎ ሜትር በመጓዝ ዠመኪናዋን ሆራ ሆቴል አቁመው ለቁርስ ወደ ውስጥ ገቡ" በስተጀርባ፣ ከሐይቁ ትይዩ የመርከብ ላይ መናፈሻ ከሚመስለው ስፍራ ሆነው የተለያዩና ቱር ቱር እያሉ በመዘመር
የሚበሩ አዕዋፍን እያዩ ቁርሳቸውን ተመግበው ወጡ" ካርለትና ከሎ
ሆራ በሞጆ ታጥፈው፣ ወደ ሻሸመኔ ጕዟቸውን ተያያዙ“ ካርለት፣በመንገዱ ግራና ቀኝ የግራር፣ የጥድ፣ የኮሶ፣ የዝግባ...ዛፎችንና
የተለያዩ ቀለም ያላቸውን እፅዋት እያየች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ከሚኙት ከሃያ በላይ አዕዋፋት ውስጥ የምታያቸውን በመልክና
በቅርፃቸው ለማወቅ በጆን ጂ ዊሊያምስና በኖርማን አርሎት የተጻፈውን የአዕዋፍ ምስል፣ ቀለም ባሕርይና የሚገኙበትን አካባቢ እያየች ተጓዙና ለምሳ በስምጥ ሸለቆ ካሉት ሐይቆችና የመናፈሻ ቦታዎች አንዱ ወደሆነው ወደ ላንጋኖ ከመንገዱ ወደ ግራ ታጥፈው ገቡ"

ላንጋኖ ሆቴል ምግብ ቤት ብዙ የውጪ ሀገር ዜጎች፣ አፍሪቃውያንና ኢትዮጵያውያን ክብ እየሠሩ በመጫወት ይመገባሉ። ከሆቴሉ ውጪ በቀላል ድንኳን ጥግ፣ በዋና ውስጥ ሱሪና ጡት ማስያዣ
ሆነው የፀሐይ ክሬም ሰውነታቸውን የሚቀቡና ሐይቁ ዳር ለዳር
የሚዋኙ ሴትና ወንዶች ይታያሉ" ጥቁርና ነጭ ሕፃናትም በመዋኛ
ፕላስቲክ ውኃውን በማንቦራጨቅ እየተንጫጩ ይጫወታሉ ከሎና ካርለት ከምግብ ቤቱ ትይዩ የፀሐይ ጃንጥላው ውስጥ
ተቀምጠው ቡናቸውን ሲጎነጩ ቆዩና ካርለት የሐይቁን ዳር ትርምስ
አሸጋግራ ስትቃኝ ቆይታ፣ «ሐይቅ ዳር ስሆን እረካለሁI አገሬ ውስጥ ከጓደኞቼና ቤተሰቦቼ ጋር ያለሁ ስለሚመስለኝ የደስታ ስሜት ይሰማኛል" በአውሮፓ፣ ብዙዎች መዝናኛዎች የሚገኙት ባሕር ዳርቻ ነው" ብቻ...» ካርለት ከሎ ሆራን በጎን ተመለከተችው“


«ኢ ህ» አላት እግሮቹን ወደፊት በመዘርጋት ሰውነቱን ለጥጦ" ካርለት የከሎ ሆራ ጠባይ ደንቋታል ግን አልከፋትም" በቀላሉ ከምትግባባቸው ሰዎች ይልቅ አስቸጋሪ ባሕርይ ያላቸውን ታከብራለች" ሁሉም ሰው ሊረዳው የሚችል ባሕርይ ያላቸው ሰዎች ለሷ አያረኳትም" እረቀቅ ያለ ባሕርይ ያላቸውን ግን አእምሮዋን
አስደንሳ መላ ፈጥራ፣ የተለያየ ስልት በመጠቀም እንደ ግል ሬዲዮና መከፈት መዝጋት እንደ መቻል
የምትረካበት ነገር የለም።
ለዚህም ካርለት «ዘመናችን የሚርጠው ልዩና ውስብስብ አስተሳሰብ ያላቸውን ነው" ምክንያቱም የነገው ፈጠራና ብሩህ
ሕልም ህላዊነት በመዳፋቸው መሃል ያለው ከእነዚህ ዓይነት ግራ
አጋቢ ባሕርይ ካላቸው ሰዎች ነው» ብላ ታምናለች።

ከሎ ቅንና ተባባሪ ሰው መሆኑን፣ ነገር ግን ይህን ባሕሪውን የሚገልጽ የቃላት ድርደራ ችሎታ የሚጎድለው መሆኑን ተገንዝባለች" ካርለት ከሎን የተለያዩ ነገሮችን እያወራች
እየጠየቀች የቱ እንደሚያስደስተው፣ የቱ አፍንጫውን እንደሚ
ያስነፋውና ጥንካሬውን ከደካማ ጎኑ ለመለየት ምርምሯን ስለ ቀጠለች
አንድ ወጥ በሆነው የሥውር ባሕርይው ዋሻ ለመግባት ትልቁ
የድንጋይ መዝጊያ ማንቀሳቀስ ጀምራለች።

«አዎ የከሎ ባሕርይ ራሱ መጠናት የሚገባው ነው" እሱን ለማጥናት ግን አስፈላጊውን ቁልፍ ማዘጋጀት አለብኝ» አለች
ካርለት፣ ከሻሸመኔ ከተማ ወጥታ የአርባ ምንጭን መንገድ ስትይዝ"
ከሻሸመኔ ትንሽ ራቅ ብለው የአስፋልቱ ጐዳና አልቆ ኮረኮንቹን መንገድ ሲጀምሩ ግን መኪናዋ እየተገጨች ስትንሰጠሰጥና ከፊት
ለፊቷ ያሉትን መኪናዎች ስታልፍና ከእሷ ተቃራኒ የሚያልፉት መኪናዎች የሚያነሡት አቧራ መኪናዋ ውስጥ እየገባ ማፈን
ሲጀምር፣ ካርለት መኪናዋን አቁማ፣ ጸጕሯን በመሸብለል፣ ቆብ
ደፋችበትና መኪናዋን በማንቀሳቀስ ከመሪው ጋር መታገል ጀመረች"
👍20🔥1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ፀጥታውን አዳመጠው፡ ይንጫጫል: ስልቱ ግን ጣፈጠው።እንደገና ጆሮውን አቁሞ ሰማ... “በዚህ ትርምስ በሞላበት ዓለም
ምናለ ፀጥታም በካሴት ታትሞ ቢሸጥ?“ ተፈላሰፈ።

ኤርቦሬ ማሕበረሰብ ውስጥ እያለ ህይወቱ ቀለል ያለ
ይመስላል። በእርግጥ ይበላል: ልብስ ግን አልነበረውም:

...ይህን ግዙልኝ መጫወቻ አምጡልኝ ኬክ ቤት
ውሰዱኝ..." ብሎ አላስቸገረም ወይንም አልተቸገረም:: እራሱን
ከጓደኞቹ ጋር በዚያ የእንቦቀቅላነት ዘመኑ አላወዳደረም: ሕይወት
ተመሳሳይ ነበረች። ራቁት ሆኖ አፈር ረጭቶ አቧራ አቡኖ ከበግና ፍየል ግልገሉች ጋር ሮጦ ነበር የኖረው።

“ተማር ህይወትህን ለውጥ ለወገንሀ ጠቃሚ ዜጋ ሁን..." ብለው ከባሕሩ አስወጡት: ያኔ እንደ ዓሣ ጨነቀው:: ግን መኖር ቻለ አዲስ ንድፈ ሃሳብን አወቀ።
አወቀ።ህልሙ ግን እውነት
አልሆነለትም ማወቅና መተግበር አራምባና ቆቦ ' መሆናቸውን ተረዳ። ተቀምጦ ታሪክ በሚያወራ ተማርሁ' ብሎ ብርጭቆ
ጨብጦ የካምፓስ ሕይወት" እያለ ከሚቦተልከው ራሱን አርቆ
ለሃገሩ ለአፍሪካ ለዓለም ለዚች ፕላኔት ቤዛ የመሆን ህልሙ አስኳሉ እንደወጣ እንቁላል ኮፈኑ ብቻ ቀረ። ኮፈኑ ይለብሳል ኮፈኑ
ያጌጣል ኮፈኑ ያዝናናል... ህሊናው ግን አፍሮ ተደብቋል።

የልመና እጆች ሲበራከቱ ማጣት ሲንሰራፋ ጥላቻና በቀል ለዚህ ማዳበሪያ እየሆነ አለመግባባትን ሲያበቅሉ እያዬ ሀዝቡን
እሚያስተምረው ስለ አተሞች በአይን ስለማይታዩት ሕዋሳት ነው::
የወገኑን ህይወት ለማይቀይረው ትምህርት ለዘመናት ባዘነ  ትምህርት ግን ማውራትን እንጂ ጥጃ መጠበቅን በጦር መሬት
ወግቶ በቆሉ መዝራትን አስረሳው። እውቀት ፈጠራ የነጮቹ ወሬ መናቆር የእኛ መሆኑን አምኖ እነሱ ሰርተው ላመጡት ግኝት ዜማ ይሰጡትና ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እያጨበጨበ እንዲዘምር ይነግሩታል።
እና! የወር ደመወዝ የሚያገኝበትን ሲዘምር ይውላል። ከዚያ ብርጭቆ
ውስጥ ተጠቅልሉ ያመሻል። ሲሞቀው እንደ ህፃን እየተወለጋገደ
ሲኮላተፍ ይተኛል።

ነገ ግን ያው ነች:: እሱም ነገን ለውጥ እንደሌላት ያውቃል፡ በትናንት የተዘራ በዛሬ የተኮተኮተ... የለም፡ እና ከነገ እንዴት ፍሬ
ይጠበቅ!

በእርግጥ በህፃንነት ዘመኑ ማንም ሳያስተምረው ያወቀው ማልቀስን ነው: ከዚያ መሰል ተፈጥሯዊ ክስተቶች ተጨማሪ ግን
ሁሉንም ነገር ለማወቅ ህሊናው ሲፈልግ እጆቹ ሲወራጩ እግሩ ሲኳትን... የእንቦቀቅላነት ዘመኑን ያሳለፈው በደስታ ነበር። ከሁለት በላይ በሆነ ባህል ውስጥ ተሰንቅሮ ይህን አትይ ያንን አትንካ እንደዚህ አትናገር ያ መጥፎ ነው ያስቀጣል ያሳስራል... እየተባለ በአዳዲስ ሃሣቦች ሲኮረኮም ሲገሰፅ ሲቆነጠጥ ኖረ:

ህሊናን የሚያዞር የህይወት ፈተና! የመፈቀርና የመጠላት እጣ የማግኘትና የማጣት የተንኮልና የጥላቻ... አንዱ እያጣደፈ
ሲያስቀምጠው ሌላው ሲያስኮፍሰው እንደ ፊኛ ሲነፋ ቱሽ ተደርጎ ሲጎድል ሕይወት ስትጥመው ስትመረው ያዝኩሽ ሲላት
ስትርቀው ራቅሽ ሲላት ቅርብ ነኝ እያለች ስትሸነግለው ኖረ።
ዛሬና ትናንት እንዲሁ በተስፋና ቅዠት አለፉ። ነገ ደግሞ አካሉ ያረጃል መንፈሱ ይደክማል ውበቱ ይረግፋል... ያኔ ይቆዝማል
ህይወት ግን ማዕበል አሳሯን እንደሚያሳያት ጀልባ እየዋዠቀች እንኳ የምትጥም ትሆንበታለች ህሊናው ሁሉም ያልፋል በሚል እምነት ቢታጨቅም የሚተማመንበት ያጣል መኖሩን ማሪጋገጥ
አይችልም ልቡ በፍቅር ቢጠማም ጥም መቁረጫውን አያገኝም።
መስታዋት የማያ ሰበቡ ይጠፋል... ከስዎች ጋር እንዳልናረ ሁሉ ያለፈ ህይወቱን ሲከልሰው ብቻውን ጡል ጡል እያለ መኖሩን ይረዳል። ይህን ሲያስብ ያሳላፈው ህይወት ጣምናው ይጠፋዋል።
ስለዚህ “መጥኔ... አይ ህይወት...” እያለ እየተትከነከነ ወደዚያ አቀበት
ይኳትናል  ወደ ሞት ሲረግጣት የኖረችው ምድር ስትውጠው እስትንፋሉ ሲቆም. ያኔ “...ይብላኝ ለቋሚ ( ሟችስ ጣጣውን ጨርሶ ወደ እውነተኛው ዓለም ሄዴ.. ተገላገለ” ይባላል። ይህም ግን
“ይባላል" ነው። ተዚያ ወዲያ ሕይወት የግል ሚስጥር ነች ለተጓዦች!

ሶራም ይህን ተራራ መውጣቱን ተያይዞታል: ጫፉ ዳመና  ውስጥ የገባው ተራራ ግን መንገድ አልባ እሾህ የበዛበት
የሚያንሸራትተው የበረከተ... አስፈሪ ነው:: ያለፉበትን ሲያዩት ያስፈራል
ገና የሚወጡት ደግሞ ከማስፈራራትም ያስጨንቃል: በዚያ ላይ የሚፈራረቀው ብርሐንና ጨለማ ቆፈንና ሙቀት. ያታከታል።

መፅናኛው ግን ብዙ ነው: ጠኔ ያስቸገረው አካለ ስንኩሉ የእለት ጉርሱ ያጣው በሽተኛው ያን ሲያዘይ የሙከራ ጥረቱ
ይጨምራል... ካሰበው ቦታ ስለመድረሱ ግን ማረጋገጫ ያለው የለም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ህሊናው አካሉን እየቧጨረ እየታገለ... እረፍት ሲነሳው
እንደቆየ የቤቱ በር ተንኳኳ።

“ይግቡ...” አለ በታከተ ድምፅ ቅላፄ። ደሞ ማን ይሆን እንደ መርዶ ነጋሪ በጠዋቱ የመጣብኝ' እያለ በር በሩን እያዬ በሩ በዝግታ ሲጢጥ…” ብሉ ሲከፈት ተረከዘ ሎሚ ከበሩ ግርጌ
ተመለከተ።

ማናት...?” አለ ግራ እየገባው ከዚያ ከተጋደመበት ቀና
ብሎ አይኑን እንደ አበያ በሬ አፍጥጦ ጆሮውን እንደ ጥንቸል ቀሰረ:

ግቢ... ማን ልበል?"  ያላሰበውን ዓረፍተ  ነገር ከራሱ አንደበት ሲወጣ ተስማው። እንግዳዋ ረጋ ብላ ወደ ውስጥ ዘለቀች።

“ይቅርታ!... ካለቀጠሮ በመምጣቴ...” አለችው የቤቱ ብርሃን ደብዘዝ ስላለባት አይኖችዋን ፈጠጥ አድርጋ፡

"ምንም አይደለም” ብሎ ፈገግ አለ፡ ማንነቷን ለማወቅ ህሊናውን ውለዳት ቢለውም ሊያገኛት ሊያውቃት አልቻለም።
ከመቀመጫው ተነሳና ወንበር ቀረብ አድርጎላት! “እዚህ ላይ አረፍ በያ! እያለ እሁንም ሊያስታውሳት ሞከረ: መልኳን ከዚህ በፊት
ያየው መሰለው። የት ነው የማውቃት?' ጠየቀ ራሱን።

"ካለቀጠሮ በመምጣቴ ይቅርታ" አለችውና አንገቷን ደፋች፡፡ “ለነገሩ  ቀጠሮ  አስፈላጊ ነበር ለማለትም ይከብደኛል" ቀና ብላ
አይታው አሁንም ሃሳቧን ገታችበት።
በሃሳቡ! ቀጠሮ የምን ቀጠሮ?' ብሎ እንዳሰበ በመላምት ህሊናውን አገለባበጠና ሃሳቡን ማጠቃለያ ላይ ለጊዜው ደረሰ: ልቡን ደስ አለው፡ ሴት ልጅ አፈቀርሁህ ብላው አታውቅም እሱ ግን ብዙ
ሌሊት ኮርኒሱን በአይኑ ሲቧጥጥ ቀን ላይ እንደ ክምር ፈጅ ገመሬ
ዝንጀሮ በአይኑ መሬት ሲያርስ ኖሯል፡

“ለጊዜው የኔም ቤት  የተከራየሁት ማለቴ ነው ከዚህ ብዙም አይቀርም። የማልኮራበትም ስራ አለኝ አለችና አሁንም በስርቆሽ ተመለከተችው።

ላቡ ግንባሩ ላይ ተንቸረፈፈ: ተቀጥቶ አፍህን ያዝ
እንደተባለ ህፃንም የፍርሃቱ ሳግ ላይ ላይ ሲያቃትተው

“ምን ነካኝ?” ብሎ
ተወራጨ። እግሮቹን እየቀያየረ አነባበራቸው፡ እጆቹን እንደ ሙሾ አውራጅ አወዛወዛቸው:

“ተናኘ... ተናኘ ወርቅ
እባላለሁ። ቶምም ይሉኛል
የሚቀርቡኝ:: ብዙ ጊዜ እንደ ቶማስ ሳላይ አላምንም ስለምል: ስለ ቶማስ ታውቃለህ መቼም? ቀና ብላ አየችው:

“አዎ! እየሱስ ሞትን ነስቶ ወደ ደቀመዝሙሮቹ መጥቶ
“እኔ ነኝ' ሲላቸው ካላየሁ አላምንም' ያለውን ነው" አላት። ፈገግ ብላ ትክክል መሆኑን አረጋገጠችለት “ሻይ ቡና” ምርጫ አቀረበላት:

“ኡፍ አንተም የሞቀ ውሃ ሰጥተህ የሚተናነቀኝን ቁልቁል ልታወርደው ትፈልጋለህ?" ነብር ሆነችበት አራስ ነብር::
👍26😁3
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሦስት

አስተናጋጅ ሆኜ ከተቀጠርኩ አንድ አመት  አለፈኝ።በሲቪዬ ላይ የስራ ልምድ በሚለው ርዕስ ስር የንብረት ክፍል ተቆጣጣሪ እና የሆቴል አስተናጋጅነት የአንድ አመት የስራ ልምድ የሚለውን አስገብቼ መፃፍ እችላለሁ፤አዎ ይሄ ቀላል ነገር አይደለም።እያንዳንዱን የሠው ትዕዛዝ በትሪ ይዤ አቀርብና በዛው ትሪ ባህሪያቸውን  ያስረክቡኛል። ትሁቱ... ቁጡ.. ጉረኛ... ጋግርታም... እርብትብት... ለጋስ...ንፉግና ተነጫናጭ...በየቀኑ ፀባዩ የሚገለባበጥ ሙልጭልጭ በቃ እኔ ትምህርት ሚኒስቴርን ብሆን ኖሮ ሳይኮሎጂ እና ሶሾሎጂ ለሚያጠኑ  ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ቢያንስ ለስድስት ወር እንደዚህ አይነት ቦታ አፓረንት እንዲወጡ አደርጋቸው ነበር..ሆቴል ማለት የሠው ባህሪ በብፌ መልክ የሚቀርብበት ቦታ እኮ   ነው።

አሁን ከምሽቱ አራት ሰዓት ሆኗል ፡፡ባሩ ውስጥ አንድ ተስተናጋጅ ብቻ ነው ያለው፡፡ ለዛውም ሴት ደንበኛ...፡፡ይሄንን ብላክ ሌብል  ትጋተዋለች ።አሁን አሷ ብትወጣልን ሌላ የቀረን ስራ ስለሌለን ወደየቤታችን እንሄድና አረፍ እንል  ነበር ስል አሰብኩ ስናስተናግድ ከነበረነው  ስምንት ሴትና አራት ወንድ አስተናጋጆች መካከል አምስቱ ሴት ቀድመው መውጫ ቆርጠው ሄደዋል?ምን? መውጫ ምንድነው ?አላችሁኝ... መውጫ ማለት አንድ ሴት አብሯት የሚያድር ሰው አግኝታ የስራ ሰዓቷ ከመጠናቀቁ በፊት መውጣትና ከደንበኛዋ ጋር መሄድ ከፈለገች እንደሰዓቱ እየታየ ከምታገኘው ላይ እንድትከፍል ይደረጋል...ያው ግብር በሉት ።
ብዙውን ጊዜ በኢትዬጵያ የቡና ቤት ሴቶች ግብር አይከፍሉም ይባላል..እኔም እንደዛ አምን ነበር፡፡ አሁን ግን እንዲህ ተጠግቼ ሳይ አመት እስከ አመት እንደውም እንደእነሱ የሚከፍል የለም? ያው ግብር ማለት ከደሀው  መቀነት  ተቀንሶ  ለኃያላኑ ጡንቻ ማፈርጠሚያ  በግዳጅም ይሁን በይሁንታ የሚሰጥ መባ ነው።ኃያሉ መንግስት ሊሆን ይችላል..ባለሀብት ሊሆን ይችላል...የሠፈር አስተዳዳሪ ባለጡንቻ ሊሆን ይችላል...፡፡  ሁሉም በሚስኪኑ ደሀ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ ከርሱን የሚሞላ  ብልጉ አውሬ ነው...ውይ በማሪያም አለቃዬን ነው ከሌላው ባለጉልበት ጨምሬ እንዲህ የጨፈጨፍኩት .አምላክ ሰምቶ ውለታ ቢስ ብሎ እንዳይቀየመኝ፡፡

አሁን ሆቴል ውስጥ የቀረነው ሁለት ወንድ  አስተናጋጆች እና አንድ ሴት አስተናጋጅ እና ደግሞ የእለቱን የተሰራ ሂሳብ ተረክቦ   እየደመረ ያለው ባሉካ ብቻ ነኝ...ሽኩክ ብዬ ወደእሱ ሄድኩና ፡፡
"ጋሼ እንዴት ነው?"

"ስለምኑ ነው የምትጠይቀኝ ጎረምሳው?"

‹‹ስድስት ሰዓት ሊሆን ነው...ተስተናጋጇን ልንዘጋ ነው ልበላት እንዴ?"

"አይ አይሆንም...ትልቅ ደንበኛችን ነች ..ቅር እንዲላት አልፈልግም.."

"አይ ለእሷም ቢሆን ይመሽባታል ብዬ እኮ ነው፡፡"

"የእኔ አሳቢ አይመሽባትም... ከተቀመጠችበት ተነስትታ አስር እርምጃ ከተራመደች የተከራየችበት ቤርጎ ትደርሳለች"

"ኦ ረስቼው… ለካ እዚህ ነው አልጋ የያዘችው"

"አዎ ባይሆን ልጇቹ ይግቡ ..ንገራቸው፡፡"

"እሺ ግን ጋሼ እሷ እስክትሄድ ብቻህን ልትሆን ነው?"

"አይ እኔ አይደለሁም ቀርቼ የማስተናግዳት ...አንተነህ.፡፡..በራሷ  ጊዜ በቅቷት ስትሄድ ቆላልፍና ሂድ...እኔ ሚስቴ ትጠብቀኛለች ...አንተ ከአይጥ ጋር ድብብቆሽ ለመጫወት ምን አስቸኮለህ?››

‹‹እንዴ ጋሼ ከጓደኞቼ ጋር የማወራው ነገር ተደብቆ ይሰማል እንዴ...?"ስል በውስጤ አልጎመጎምኩ፡፡ከሶስት ቀን በፊት ነበር ለሴቶቹ አንድ አይጥ አላስተኛ እንዳለቺኝና ልክ ስተኛ ጆሮዬን እየቀረጠፈች፤ ከንፈሬን እየነከሰች  አስቸገረችኝ ብዬ ያወራኋቸው...እነሱ ደግሞ አፍቅራህ ነው እያሉ ሲያሾፍብኝ ነበር..ይሄው አሁን ጋሼም ተቀላቀላቸው...
ጋሼ ሂሳቡን ሰርቶ ጨርሶ ለመሄድ ተነሳ፡፡

"ጋሼ ለመቆየቱ ግን ካሌብ አይሻልም?"

"ጓረምሳው ንብረቴን ለማን አምኜ ጥዬ እንደምሄድ የመወሰኑ መብት የእኔ መሰለኝ?...መልካም አዳር"ብሎኝ ጥሎኝ ወጣ...፡፡እኔም ሌሎቹ እንዲሄዱ ተናግሬ በዛ ውድቅት ለሊት ከአንድ እንስት ተስተናጋጅ ጋር ተፋጥጬ ተቀመጥኩ...፡፡
እኔም እንደሌሎች በዚህ ሰአት ክፍሌ ገብቼ አረፍ ባለማለቴ ከፍቶኛል ..ግን ደግሞ ጋሼ የተናገራት ነገር ልቤ ላይ አሪፍ  ደስታና ኩራትን አርከፋክፋብኛለች "ጓረምሳው ንብረቴን ለማን አምኜ ጥዬ እንደምሄድ የመወሰኑ መብት የእኔ መሰለኝ?ነበር ያለኝ አይደል?፡፡ "በእውነት መታመን ያስደስታል" ለዛውም አንድ አመት ባልበለጠው ጊዜ ውስጥ ይህን መሳይ ክብር ማግኘት ተስፋው ለፈረሰበት ሰውም ቢሆን  በህይወቱ ጥቂት መነቃቃትን ይፈጥራል፡፡

ጠረጴዛው ተንኳኳ ከነበርኩበት ባንኮኒ ውስጥ ፡ሮጬ ወጣሁና  ወደ ተጠራሁበት ቀርቤ፤ እጇቼን ወደኃላዬ አጣምሬ፤ ከጉልበቴ ሸብረክ ፤ ከአንገቴ ጎንበስ ብዬ"አቤት ምን ጎደለ ? ምን ላምጣ?"አልኩ፡፡

"እ ..ምንድነበር..?."በፈጣሪ ሰክራለች መሠለኝ ..?ለምን እንደጠራችኝ እንኳን  አታውቅም፡፡
"አዎ..ሙዚቃውን በጣም ቀንሰው እናም አንድ ብርጭቆ አምጣልኝ"
ወይ ፈጣሪዬ ሴትዬዋ ገና መጠጣት ልትጀምር ነው..ለዛውም በሁለት ብርጭቆ…. እንዳለችኝ የሙዚቃውን ድምፅ  ቀነስኩና ብርጭቆውን አጣጥቤ ይዤላት ሄጄ ጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጥኩላትና ልመለስ ስል "ተቀመጥ"አለችኝ...
ተቀመጥ በሚለው ቃሏ ውስጥ ምንም አይነት ትህትናም ሆነ ሀዘኔታ አይነበብም፡፡.

"ምን አልሺኝ እመቤቴ?"

"ቁጭ በል..ንግግሬ አይሰማም እንዴ?"

"ኸረ በደንብ ይሰማል"ብዬ ትዕዛዟን በማክበር ሽኩክ ብዬ ቁጭ አልኩ..ፊቷ የተቀመጠውን  የተጋመሰ ብላክ ሌብል ጠርሙስ አነሳችና አዲስ ያመጣሁት ብርጭቆ ውስጥ አንደቀደቀችው፤ስትጨርስ  ወደፊት ለፊቴ አሽከርክራ አሰጠጋችው።

"ኸረ ይሄ ነገር ለእኔ አይሆንም?"

"ባክህ አትንጠባረር ..ዝም ብለህ ጠጣ "ብላኝ እርፍ...
አሁን ይሄ ግብዠ ነው አስገድዷ ደፈራ፡፡ፈራኋት መሠለኝ አነስሁና አንዴ ጎንጨት አልኩለት...
.፡፡‹‹እራት መቼ ነበር የበላሁት?›› ስል እራሴን ጠየቅኩ፡፡ አዎ 12፡30 አካባቢ....‹‹ምንድ ነበር የበላሁት?›› ዳቦ በሙዝ ...፡፡.ሶስት ሙዝና ሁለት ዶቦ....፡፡‹‹አሁን ከስድስት ሰዓት በኃላ ምን እየጠጣሁ ነው›› ውስኪ፡፡...‹‹ይህቺ ጋባዤ አራት ሰዓት አካባቢ ምንድነበር ያዘዘችው..?››ለማስታወስ ሞከርኩ...አዎ ክትፎ ነበረ ያዘዘችው እናም ግማሹን በልታ ግማሹ እንደተመለሠ አይቼያለሁ....አሁን ኪችን ብገባ ግማሹን ትራፊ አገኝ ይሆን?

"እዚህ ሀገር ለስራ መጥተሽ ነው?"ጥያቄውን መጠየቅ ፈልጌ ሳይሆን ዝም ብሎ መቀመጥ ስለጨነቀኝ ነው የቀባጠርኩት። ቢዝነስ የሚሰሩ ሴት  አስተናጋጆች ግን  እንዴት ብለው ነው ከማያውቁት ሰው ፊት ለፊት ተቀምጠው ዘና ብለው የሚጠጡት...ከዛም አልፎ የሚስቁት፤ የሚጫወቱት?ለዛውም በየቀኑ…፡፡ጥያቄዬን ሰምታ ሲጋራዋን ለኮሰች ...እናም ጭሱን አትጎልጉላ እላዬ ላይ በተነችብኝ ፡፡...ልክ እንደቤተመቅደስ ማዕጠንት ዝም ብዬ በፀጋ ተቀበልኩና ወደውስጤ ማግኩት?

"ምሽቱ ደስ ይላል..."ሌላ የማይረባ አስተያየት ከአንደበቴ ድንገት ሾለከ፡፡

"ምሽቱ አንተን ነው የሚመስለው?"አለችኝ፡፡
👍522👎1👏1
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ሦስት

ካርለት መሳተፍ የማትችለውን የሽማግሎች ስብሰባ በርቀት
እየተመለከተች አልፎ አልፎም የካሜራ ችፕስ  በተደረገበት ባለዙም ካሜራዋ ፎቶ ስታነሳ ቆይታ ጎይቲን ፍለጋ ወደ መንደር
ተመለሰች

"ካርለት ነጋያ ... ነጋያ ... ያ ፈያው" አሉ ህፃናት የካርለትን ነጭ እጅ ለመያዝ እየተሽቀዳደሙ "ነጋያኒ  ጎይቲ ዳ! ደህና ነኝ
ጎይቲ አለች ብላ ጠየቀቻቸው በሐመርኛ

"እእ  ዳኒ" አለች አንዷ ህፃን ራሷን ዝቅ አድርጋ ሽቅብ
በመናጥ አለች ለማለት ካርለት  መዝጊያ ወደሌለው መግቢያ ጎንበስ ብላ በጠባቧ በር ወደ ውስጥ ስታይ ምርግ በሌለው የእንጨት መከታ መሐል ለመሐል በሚገባው ብርሃን ጎይቲ በርከክ ብላ እጆችደ
ከወፍጮው መጅ ላይ ሳይነሱ ራሷን ብቻ ወደ በሩ መልሳ አየቻትደ ካርለት የጎይቲን ማራኪ ፈገግታና የምትወደውን ጥርሷን ስታይ የደስታ ስሜት ውርር አድርጓት እሷም ሳቀች  ተሳሳቁ"

"አርዳ?" አለች ጎይቲ በአንገቷ እንደምትስባት ሁሉ አገጯን ወደ ታች እየሰበቀች ካርለት ፈገግ እንዳለች እሷን፥ ከኋላዋ
የተንጠለጠሉትን የቁርበት ልብሶች ግርግሙ ላይ የተንጠለጠሉትን
ዶላዎች (የወተት መያዣዎች) ግልጥጥ ያለውን የምድጃ ፍም:
በቀበቶው ጉጥ ላይ ቁልቁል የተንጠለጠለውን ክላሽንኮቭ ጠመንጃ
ልጆች አመዱን በውሃ በጥብጠው መግቢያው ጥግ ባለው የግድግዳ
ልጥፍ ላይ ያዩትን ለመሳል ያደረጉትን ጥረት ... በዐይኗ ስትቃኝ.

"አርዳ!" አለች ጎይቲ ደግማ አትገቢም! ለማለት ቃሉን ረገጥ አድርጋ።

"ፈያኔ" ብላ ካርለት እንደ ጅራት ከኋላዋ የተንጠለጠለውን
የፍዬል ቆዳዋን በግራ እጅዋ ወደ እግሮችዋ መሐል አስገብታ ቀኝ
እግሯን በማስቀደም በጠባቧ በር ሹልክ ብላ ገባች የሐመር ቤት
መዝጊያ የለውም  ቀንም ሆነ ማታ እንግዳ የአባት ሙት መንፈስ ከመጣ ሁሌም ሳይጠብቅ: ደጅ ሳይጠና ሰተት ብሎ መግባት አለበት ትንሽዋ በር ደፍዋ ከፍ ያለ በመሆኑ ለከብትም ሆነ ለአውሬ
ለመግባት አታመችም ቤት ለሐመሮች መቀመጫና መተኛ እንጂ መቆሚያ  አይደለም"  ሁሉም ነገር ትርጉም  ሊኖረው ይገባል
ስለሆነም ካለ ህፃናት በስተቀር በጣም አጭር ሰው እንኳ ጎንበስ ብሎ
ካልሆነ መቆም አይችልም ይህ የሆነው ደግሞ እንጨት ጠፍቶ ቦታ
ጠቦ ሳይሆን ለትርጉሙ ነው"

"ጎይቲ?"

"ዬ!"

ምነው ዛሬስ ስትፈጭ መዝፈን: ማንጎራጎሩን ተውሽው?" ብላ ጠይቃት ካርለት ፈገግ ብላ ጎይቲን ሳመቻት እንደ
ሐመር ሴቶች የልብ ሰላምታ ጎይቲ ካርለት ለጠየቀቻት መልስ  ሳትሰጥ አንገቷን ደፍታ እጅዋ ወፍጮው
መጅ ላይ እንዳለ በተመስጦ ስታስብ ቆይታ በቀኝ እጅዋ ማሽላውን ግራና ቀኝ ሰብስባ  ወደ ወፍጮው ጥርስ አስገብታ
ወገቧን ወደ ኋላና ወደ ፊት
እያረገረገች "ሸርደም: ሸርደም አድርጋ ፈጨችውና ብርኩማዋ ላይ ተቀመጠች
ከዚያ እኒያን ሐጫ በረዶ የመሳሰሉ ጥርሶችዋን
ገልጣ ለዓመል ያህል ፈርጠም አለችና

"ይእ!ካርለቴ ኧረ አሁን ሳንጎራጉር ነበር መቼ
እንጉርጉሮዬን እንደ አቆምኩት ግን እንጃ! አዝኜ እንኳን ቢሆን ሁልጊዜ መፍጨት ስጀምር እህሉ ከታች ሲደቅ እኔ ከላይ ትዝታዬን እየጨመርሁ እንጉርጉሮዬን አቀልጠው ነበር አሁን እኮ ኮቶ እግሯ
ወጣ ከማለቱ ነው አንች የመጣሽ ከኮቶ ጋር እየተከራከርን ሁላ እዘፍን ነበር  በኋላ ግን ኮቶ ለመሄድ ስትቁነጠነጥ እያወራች እንድትቆይ ብዙ
ክርክር ገጠምኋት
ታውቂያታለሽ ተከራክራ ተከራክራ ካልረታች እንደ ፍየል ልዋጋ ስትል ታስቀኛለች ስለዚህ ጥላኝ ከምትሄድ ብዬ ነገር ጀመርኋት

"ኮቶ ከተማ አትሄጅም?" ስላት

"ይእ! ኧረ ምን አልሁሽ እቴ እኔስ ያገሬ ጅብ ይብላኝ
አለችኝ ትንሽ ላስለፍልፋት ብዬ እኔ ግን መበላቴ ታልቀረ የጅብ ዘመድ አልመርጥም አልኋት አይምሰልሽ ጅሊት! ያገርሽ ጅብ ገሎ ነው የሚበላሽ  የሰው አገር ጅብ ግን እየበላ ነው የሚገልሽ ስትለኝ ይእ! አንች ምነው ታልጠፋ አውሬ ጅብን እንዲህ ዘመድ
አዋቂ አደረግሽው?
አልኳት‥ ይሄ እንኳ ምሳሌ ነው ስትለኝ ሞጥሟጤ  ምሳሌሽን ቀይሪያ!ታለበለዚያ ካለ
ጥንባቸው ሌላ
የማያውቁትን ጅቦች ካለስማቸው
ስም ሰጥተሽ ቅዱስ አድርገሽ ታውሬው ሁሉ አታቀያይሚያቸው" ብላት ወገቤን ደቅታኝ ሹልክ ብላ ሄደች ከዚያ ማንጎራጎር ጀምሬ ነበር ወዲያው ግን ድምፄ ለከት የለሽ ሆኖ ልቤ ግንድ የሚያመሽክ ምስጥ ይርመሰመስበት ጀመር

"ምን ሆነሽ ነው ጎይቲ የምን ጭንቀት ነው?"

"ወደው አይስቁ አለ ያገሬ ሰው ..." ብላ ጎይቲ ከትከት ብላ ስቃ።

"ይእ! ምነው እንዳንች ጅል ሆኜ እድሜ ልኬን ስጠይቅ
በኖርሁ" ስትላት ተያይዘው እንደገና ተሳሳቁ

"ካርለቴ! እውን ሴት ልጅ እግርና እጅዋ የሚያጥረው፥
ቀትረ ቀላል ሆና ድምጿ የሚሰለው ... ለምን እንደሆን አታውቂም?

"አላውቅም ጎይቲ ለምንድን ነው?"

"ይእ! እንግዲያ ዝናብ እንደበዛበት ማሽላ ታለ ፍሬ መለል ብለሽ ያደግሽ አገዳ ነሻ! ሙች አንችስ ተህፃን አትሻይም አንቺ እኮ! ተንግዲህ ወዲያ ትልቅ ሰው ነሽ! ጉያሽና ልብሽ ላይ የትዝታ ምሰሶ የተተከለ
ፈጭተሽ የምታበይ ጭሮሽ ውሃ ቀድተሽ ለጥም
መቁረጫ የምታጠጭ
የወንድ ልብ ሲጎመራ ጫካ መሃል ገብተሽ የምትካፈይ
ፍቅርሽን እንደ ህፃን ልጅሽ የምትግች ትልቅ ሴት እኮ ነሽ?" ትልቅ ሴት እኮ ነሽ?"

"ጎይቲ የባሰ ግራ ገባኝ?"

"ይእ! እንዲያ ይሻላል! ቁም ነገር አታውቂም ብዬ ተመንገር ሌላ እህ ላሳይሽ?"  ብላ ጎይቲ በአድናቆት ጨብጨብ ጨብጨብ አድርጋ በሣቅ ተፍለቀለቀች

ካርለት ከተቀመጠችበት
ፈገግ ብላ ተነስታ ጎይቲን ገፋ አድርጋት የወፍጮውን መጅ በግራ እጅዋ ይዛ ከሾርቃው በቀኝ
እጅዋ ማሽላውን አፍሳ ጨምራ

"እሽ እኔ እፈጫለሁ አንች ንገሪኝ?" አለቻት

"ይእ! እውነት ታላወቅሽውማ እነግርሻለሁ  እንጂ ብላ እግሯን ዘርግታ ቁርበቱ ላይ ቁጭ አለች ጎይቲ ወደ ቁምነገር
ስትመለስ የሚያስጨንቃትን
ለመናገር ስትዘጋጅ ውስጧን የሚጎማምደው ችግሯ የፈገግታ ፀዳሏን እየቸለሰ አከሰመው ደሟ
እንደቀትር ማዕበል ደረቱን ገልብጦ እየዘለለ በመፍረጥ አረፋ ደፈቀ
ታወከ
"ሐመር ላይ ሴት ልጅ የግል ችግር የለባትም እምትበላውን መሬቷ እምትጠጣውን ላሞች: ፍቅርን ደግሞ የሐመር ወንዶች እንደ ማሽላ ገንፎ እያድበለበሉ ያውጧታል ሴት ልጅ ወንዝ
ብትሄድ እንጨት ለቀማ ጫካ ብትገባ እህል ልታቀና ገበያ ብትወጣ ብቻዋን አትሆንም ሰው ከብቶች: ዛፎች አሉላት ሴት ብቻዋን ችግር የሚገጥማት የማትወልድ ስትሆን ነው መሐንነት ትታይሻለች ያች ፀሐይ " ዝቅ ብላ በግርግዳው ቀዳዳ ጮራዋን ፈንጥቃ የምትንቦገቦገውን የረፋድ ፀሐይ እያሳየቻት

"ይኸውልሽ መሐንነት ያችን በሙቀት የምትነድ እሳት ዘላለም እንደ ጨቅላ ህፃን ደረትሽ ላይ ታቅፈሽ መኖር: ታቅፈሽ መሞት ነው" ተዚያ እድሜ ልክሽን መቃጠል: መንደድ ነው"

"መሐንነቱ የመጣብሽ ሳታስቢው የሴት ብልትሽን ውሃ ነክቶት ይሆናል ሆን ብለሽ ባታደርጊውም ትዕዛዝ ነውና ቅጣቱ ቃጠሎው ወደ ገለብ ብትሮጭም አታመልጭውም ስትቃጠይ ደግሞ ሰው የሻጉራ እያዬ ይሸሽሻል ባይሆን ከቃጠሎሽ  ባይጠቅምሽም
ለእነሱም ባይጠቅማቸውም ለአባትሽ ለእናትሽ ለእህትሽ
ለዘመዶችሽ ታካፍያቸዋለሽ የተረገመ ቤተሰብ እያሰኘሽ" ብላ ዝም አለች ጎይቲ  እንደተላጠ ጣውላ ሰውነቷ ሟሾ

ግዙፍነት ለካ በአጥንትና ስጋ ብቻ አይደለምና  መጠንም በህሊና ይወሰናል ውበትና ቁመና ህሊና በሚፈጥረው መተማመን ተገዥ ነውና! እያለች ካርለት ጎይቲን እያየች ስታስብ
👍19👎1