አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ማዕዶት


#ክፍል_አንድ


#በየዝና_ወርቁ

“ወይኔ !... ዘንድሮ እንዴት ጉድ ሆንኩ!? አለች ማዕዶት ለራሷ ብቻ በሚሰማ ድምፅ - ራሷን በቁጭት እየነቀነቀችና ገና ሁለት ወር እንኳ ያልሞላው ፅንስ በእጇ ይታወቃት ይመስል ከእምብርቷ በታች ያለ
ሰውነቷን እየዳሰሰች :: ሰሞኑን ሁሉ እንዲህ እየተቆጨችና እየተበሳጨች ነበር የሰነበተችው:ፈ።

ዛሬም የሰነበተባት ጭንቀት እያናወዛት
የምርመራ ውጤቷን ለመስማት በክሊኒኩ የእንግዶች ማረፊያ አግዳሚ ወንበሮች በአንዱ ላይ ተቀምጣለች።ወረፋ አስከባሪዋ ተረኛ ለመጥራት ብቅ ስትል ትደነግጣለች፡፡ ሌላ ሰው ጠርታ ስትመለስ ደግሞ ትጨነቃለች፡፡ ሁለቱ ቀያይ ጉንጮቿ ፍም መስለዋል፡፡
ለወትሮው እንደህፃናት ዐይኖች ጥርት ብለው የሚጉሎት ዐይኖቿ ደፍርሰው ቀጫጭን የደም ስሮች ቅርንጫፎቻቸውን ዘርግተውበታል፡፡ ሳምንቱን ሙሉ
ማበጠሪያ ያልገባበት ፀጉሯ በተከናነበችው ጥቁር ሻርፕ
ቢሸፈንም በግንባሯ ዳርዳር ክርችፍ ብሉ ይታያል፡፡ጭንቀት ያጋለው ሰውነቷ ላብ ማመንጨት ሲጀምር ራሷን ያሳክካት ጀመር፡፡
እንደ እሷ የምርመራ ውጤታቸውን የሚጠብቁ ሰዎች በወረፋ ቁጥራቸው እየተጠሩ ውጤት ወደሚሰማበት ክፍል እየገቡ ይወጣሉ፡፡ ማዕዶትውጤታቸወን ለመገመት ፊታቸወን አተካራ
ታስተወላለች፡፡ አንዳንዶቹ የግንባራቸወን ላብይጠርጋሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ መልዕክት አድርሱ የተባሉ
ይመስል እየተጣደፉ ከግቢ ይወጣሉ፡፡

አንዳንዶቹ ምንም ስሜት አይነበብባቸውም።እንዲህ ፊታቸውን እያነበበች ሁኔታቸውን እያስተዋለች ውጤታቸውን ለመገመት ስትሞክር ትቆይና ሳትወድ ወደ ምትሸሸው ወደ ራሷ ትመለሳለች፡፡ በሃሳቧ የተሰራ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭ የሚል ወረቀት ፊቷ ላይ
ሲደቀን ይዘገንናታል፡፡ እንደመባነን ዐይነት ራሷን በኃይል ትነቀንቃለች:: በሰራ አካላቷ የጭንቀት እሳት ይቀጣጠላል።

“ወይኔ ምን አሳበደኝ? ደግሞ ትክክለኛ ስሜንና አድራሻዬን እንዴት እሰጣለሁ? ምን አደነዘዘኝ? ትላለች።

ደም ከመስጠቷ በፊት የምክር አገልግሎት የሰጠቻት ነርስ የምርመራ ውጤትሽ በምስጢር የሚያዝ
ነው:: መዝገብ ላይ የምናሰፍረው ለስታትስቲክስ እንዲሆን በኮድ ቁጥር ነው:: ካንቺ ፈቃድ ውጭ ለማንም አይነገርም

ብላታለች፡፡ መጀመሪያ አምናት ነበር፡፡ ደም ከሰጠች በኋላ ግን የማይታመን ነገር ሆነባት፡፡ በዚያም ላይ ምንም እንኳ ለመመርመር የፈለገችበትን ትክክለኛ
ምክንያት ባትነግራትም ከነርሷ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ አውርተዋል፡፡ ከአሁን በኋላ የትም ቦታ ብታገኛት እንደምታውቃት አሰበች፡፡ እና ነርሷ በከተማው ሙሉ
ተባዝታ ታየቻት፡፡ ታክሲ ውስጥ ፣ ገበያ መሀል ፣መዝናኛ ቦታዎች... ምናልባትም እኮ የሚያውቃት ሰው ዘመድም ጓደኛም ጉረቤትም ልትሆን ትችላለች! እንዲህ
ባሰበችው ቁጥር - በአደባባይ መሀል እርቃኗን የቆመች እየመሰላት ሄደ፡፡ እና “እንዲያውም ምስጢር ባይባል
ኖሮ ስራዬ ተብሎ ይወራ ይችል ነበር!» አለች:: እጆቿ በጭንቀት ይንቀጠቀጣሉ፡፡

ወረፋ አስከባሪዋ ግን ብቅ ትልና በተረጋጋ
መንፈስ በቁጥራቸው እየጠራች ትመለሳለች:: ማዕዶት ከከአሁን አሁን ተጠራሁ እያለች በ ጭንቀት
ታስተውላታለች፡፡ የወረፋ ቁጥራቸው ደግሞ ቅደምተከተልና የጠበቀ አይደለም፡፡ እና የሷን ቁጥር እያለፈች
ሌላ ስትጠራ ትባትታለች፡፡

“በቃ ነኝ ፣ ነኝ...” ትላለች፡፡ “
ፖዘቲቭ የሆንነውን ነው ወደኋላ ያቆዩን፡፡ ረዥም ምክር ሊሰጡን፣ እንዳንሸበር
በቂ ጊዜ ሰጥተው ሊያረጋጉን ፣ ለሌሎች እንዳናስተላልፍ ሊያስተምሩን! ... አቤት ፈጣሪዬ! ... ምን አሳበደኝ?
... ምነው እንደሸሸሁት ሳልመረመር ብቀር?...»
ማዕዶት መጀመሪያ ፍቅረኛዋ ከአያልነህ ጋር በጥል የተለያዩ ወዲህ ለበርካታ

ዓመታት በጥርጣሬና


በ ጥ ንተት እየታመሰች ከወንዶች ርቃ ኖራለች።ተመርምራ ሁኔታዋን ለማወቅ እየፈራችም ብዙ የትዳር አጋጣሚዎቿን ሽሽታ አሳልፋቸዋለች:፡ እምነታችንን
በፈጣሪ አድርገን ሳንመረመር እንጋባ የሚሏትን ወንዶች ትጠራጠራቸዋለች | ትፈራቸውና እርግፍ አድርጋ ትተዋቸዋለች፡፡ “ተመርምረን ነው መጋባት ያለብን የሚለ ሲያጋጥሟት ደግሞ ራሷን ትጠራጠርና መመርመሩን ትፈራና ትጨነቃለች፡፡ ድንገት ቫይረሱ
በደሟውስጥ ቢገኝስ? ከዚያ ወዲያ ህይወትም ዓለምሌላት ሆኖ ይታሰባታል:: እና አያልነህን ትረግምና ሳታገባም ሳትወልድም እንዲሁ መኖርን ትመርጣለች፡፡

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እንዲሁ ሳታገባ ሳትወልድ ህይወቷ የማለፉ ነገር ያስጨንቃታል፡፡ እናት የመሆን
ፍላጐት ፣ ባለትዳር የመሆን ምኞት ተጠናውቶ ይወተወታታል።ታዲያ ውትወታው እረፍት ሲነሳት ፣ ቀስፎ ሲያስጨንቃት ፣ ዕድሜዋን ታሰላና
«ገና ብዙ ጊዜ አለኝ:: እስከዚያ መድኃኒቱ ይገኝ ይሆናል» ትልና ራሷን ትደልላለች::

በርካታ ወዳጅ ዘመዶቿ ቀጠን ረዘም ያለውንና በአለባበስ አዋቂነቷ ታግዞ የሚዋበውን ተክለ ሰውነቷን፣አጠር ካለው አፍንጫዋ በላይ እንደከዋክብት የሚያበሩትን ዐይኖቿን ፣ ከፊቷ ጋር በሚስማማ ቅርፅ እየተቆረጠች
በካውያ አለስልሳ በምታበጥረው ፀጉሯ የሚፈካውን የደም ገምቦ ገፅታዋን እያስተዋሉ ሳታገባ ጊዜዋ መንጎዱ
ይከነክናቸዋል።
በአንዳንድ አጋጣሚዎች ተደፋፍረው
እንድታገባ ሲመክሯት ግን ምክንያት እየደረደረች ስትከራከር ሃያዎቹን ጨርሳ ወደ ሰላሳዎቹ ተሻግራለች::

ወዳጅ ዘመዶቿን እንዲህ ግራ ይግባቸው እንጂ እሷማ ከአስር ዓመት በፊት በወጣትነት እድሜዋ አግብታ
ጉልበቷ ሳይደክም በሞቀ ፍቅርና ትዳር ልጆቿን የማሳደግ ዕቅድ ነበራት:: ከንግድ ስራ ኮሌጅ በቢሮ ማኔጅመንት በዲኘሎማ ተመርቃ አሁን ከምትሰራበት መስሪያ ቤት እንደተቀጠረች ሰሞን የሠራተኞች ጉዳይ
ኤክስፐርት ከነበረው ከአያልነህ ጋር ተግባቡ:: በፍቅር ተስማምተው ለመጋባት ወሰኑ:: ያንጊዜ የሃያ ሶስት ዓመት ወጣት ነበረች:: እሱም ወደ ሃያዎቹ መገባደጃ
ደርሷል፡፡

በዚያን ዘመን ከኤች.አይ.ቪ ራስን ለመጠበቅ የሚታሰበው ተጋብቶ አንድ ላንድ ተወስኖ በመኖር እንጂ ከጋብቻ በፊት ተመርምሮ ራስን ማወቅ ትኩረት
የሚሰጠው ጉዳይ አልነበረም:: በዚያም ላይ በአብዛኛው ሰው እምነት ኤች.አይ.ቪ የጠጪ ወንዶችና የሴተኛ አዳሪዎች መቅሰፍት ነበር፡፡

የአያልነህ ተግባቢና ቀበጥባጣ ባህሪ ከማዕዶት ጭምትነት ጋር ሲዋሀድ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንኳን
ለነሱ ላያቸውም ወደድኳቸው የሚያሰኝ ህብር ፈጥሮ ነበር፡፡
ተጋብተው ጎጆ ለመውጣት ከሁለቱም ደሞ እየቀነሱ ሲያጠራቅሙ፣ ስለሰርጋቸው ድግስ ፣ ስለዚቤት ዕቃ... እያሰሉ ሲብተከተኩ ሁለት ዓመት አሳለፉ

በመሀከሉ አያልነህ በእድገት የሠራተኛ ማስተዳደሪያ ክፍል ኃላፊ ሆኖ ወደ ናዝሬት ተዛወረ:: ማዕዶት ያገኘው የሁለት መቶ ብር ጭማሪ ቀርቶበት ባይለያዩ ነበር
የፈለገችው:: ለአያልነህ ግን የሞኝ ሀሳብ ሆነበት፤

“እድገት እንዴት እምቢ ይባላል፡፡ እንኳን
ይኼንን ያህል የደሞዝ ልዩነት እያለው አላት::
“ፍቅራችን በመካከላችን እስካለ ድረስ እንኳን ዘጠና ዘጠኝ ኪሎ ሜትር አንድ ሺም ቢሆን ችግር የለውም
ብሎ አግባባት::

የመጀመሪያዎቹን ስድስት ወራት በየሳምንቱ መጨረሻ ያለማቋረጥ እየተገናኙ ጥሩ ጊዜ አሳለፉ፡፡
አያልነህ ሲያስበው ግን ከደመወዛቸው ከወጪ ቀሪ ሆኖ የሚጠራቀመው ገንዘብ እንዲያወም እድገት ሳያገኝ ከነበረው ያንስበት ጀመር:: በዚህ ከቀጠሉ ትዳር
የመመስረታቸው ነገር የህልም እንጀራ ሆኖ ታየው። እና በአስራአምስት ቀን አንድ ጊዜ ቢገናኙ እንደሚሻል በጨዋታ መሀል አነሳባት:: ጠረጠረችውና ተቆጣች።
እንዲያውም ለነገር የማይመች ሆኖባት ነው እንጂ በሱ ተግባቢ ባህርይ ተለያይተዉ መኖራቸወ የበለጠ
እያሳሰባት
👍3
#ማዕዶት


#ክፍል_ሁለት


#በየዝና_ወርቁ

ያመሸበትን ብስጭት ቻል አድርጎ ነገር ሊያበረድ አሰበና ሊያቅፋት እጁን ዘረጋ፣

በዚህ ሁኔታህ በዚ መጥፎ ጊዜ እንዴት ላምንህ እችላለሁ አለች ፤እንዳያቅፉት እጁን እየገፋች።ያመረረች ስላልመሰለው

እንደጠረጠርሺኝ ከሆንኩማ ለአንቺም ከተረፈሽ ቆይቷል ማለት ነው አለ እየሳቀ ከዚያ ሊያቅፋት እንደገና እጁን ዘረጋ ማዕዶት የባሰ እየተናደደች

'አጉል ቀልድ' አለችና ተስፈንጥራ ተነስታ የአልጋውን ልብስና አንዱን ትራስ አንጠልጥላ ሄዳ ሶፈው ላይ ተኛች።የምሯን አልመሰለውም ነበር። የምትመለስ ስለመሰለው ሲጠብቃት እንደቆየ እንቅልፍ ወሰደው ወፍ ሲንጫጫ ተነስታ በበራሪ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች።

አያልነህ የወደፊቱ ህይወታቸው እንዴት እንደሚቀጥል በጣም አሳሰበው።በዚህ ዓይነት ቢጋቡ ህይወቱ ሰላም እንደሚያጣ ታየው። እና በጋብቻ ከመተሳሰራቸው በፊት ግኑኝነታቸው ቢቋረጥ እንደሚሻል ወሰነ።መአዶት ግን ለመታረቅ ፍቃደኛ አለመሆኗ እርግጠኛ ባትሆንም አያልነህ ሳይደውልላት የሚቀር አልመሰላትምነ ነበር። አለመደወሉ የጠረጠረችው ሁሉ አረጋገጠላት
ምነው ከሱ እንደተለየሁ ወዲያውኑ ጨክኜ በተመረመርኩ፡፡ ቁርጤን አውቄ ህይወቴን አስተካክል ነበር አለች- እንደመባነን እያደረጋት:: ሳታስበው ሃያው
ደቂቃ ነጉዷል:: በእንግዳ ማረፊያው አግዳሚ ወንበሮች ላይ ተኮልኩለው ከነበሩት ብዙ ሰው ሄዷል። እንደገና
ሰዓቱ ሳይታወቃት እንዳያልፍ ሐሳቧን ወረፋ ወደሚጠብቋት ሰዎች መልሳ ፊታቸውን ማጥናት ጀመረች።ብዙዎቹ በአስማት የተያዙ ይመስል ድንዝዝ
ብለው ለየብቻቸው ተቀምጠዋል።

የውጤት መቀበያው ክፍል ተከፈተና ወጣት ወንድና ሴት ፊታቸው በደሰታ በርቶ ወጡ። ደረጃውን እንደወረዱ ሁለቱም ድንገት ተቃቀፉና በደስታ ስሜት
ከንፈር ለከንፈር ተሳሳሙ። እንደገና ተላቀው ዐይን ለዓይን ተያዩና ተቃቀፉ። ከተቀመጡት ሰዎች ከፊሎቹ ነቃ እንደማለት ብለው ደስታቸውን ተጋሩ። አንዳንዶቹም የባሰ ተሳቀቁ። ማዕዶትም ለመጋባት የተመረመሩ መሆናቸውን ገመተችና ራሷን እየወቀሰች ጭብጥ ብላ
ተቀምጣ አስተዋለቻቸው።

ተከትሎ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ እንዳለባት ይሰማት ጀመር።

በዚሁ የተነሳ ባለፈው አመት ከወንዶች እንደምትርቅ አስተውሎ ከቀረባት ሰው ጋር ፍቅር ጀምራ ነበር፡፡ ባህርያቸውን ተጠናንተው ለትዳር እስኪወስኑ
አልፎ አልፎ የገቡበትን ስሜትም ኮንዶምን ተከልለው አሳልፈዋል፡፡ በኋላ ግን ለጋብቻ መተሳሰባቸውን ተከትሉ
በዚህ የተነሳ ባለፈው ዓመት ከወንዶች
ያነሳባትን የእንመርመር ውትወታ መቋቋም ስላቃታት ራቀችው፡፡ እሱም ተመርምሮ በመጋባት አጥብቆ ያምን
ስለነበር ብዙ ጊዜ ሊያሳምናት ሊያደፋፍራት ጣረ።በመጨረሻ እየሸሸችው መሆኗን ሲረዳ ግን የሷን ያህል የተማረ፤ ዘመናዊ ሰው ተመርምሮ ራሱን ለማወቅ የማይደፍርበት ምክንያት ሊገባው አልቻለም።ሰለዚህ ቀደም ብላ ተመርምራ ብታውቅ ነው ብሎ ጠረጠረና
ፈራት። ከዚያም ተዋት።

ብቸኝነት እንደገና ! ዓመት አለፈ...

ማዕዶት ሳይታወቃት ለረዥም ጊዜ ጭብጥ ብላ ተቀምጣ ስለቆየች ሳይሆን አይቀርም ሆዷ ላይ ህመም ተሰማትና ቀና አለች።ከዚያ የተሰማትን ህመም
ለማስታገስ ወደኋላዋ ጋለል ብላ ሆዷን እየዳሰሰች ፍዝዝ ብላ እንደቆየች ሃሳብ ነጥቆ ለማርገዟ ምክንያት ወደሆናትና ማስታወስ ወደማትፈልገው ከሳምሶን ጋር
ወዳሳለፈችው ጊዜ ጭልጥ አርጎ ወሰዳት ...
ከሳምሶን ጋር የተዋወቁት ከሶስት ወራት በፊት ለስብሰባ በአውሮኘላን ወደ ድሬዳዋ ስትሄድ ነበር፡፡ የለበሰው
ሰማያዊ ጅንስ ጃኬትና ሱሪ ሰውነቱ ላይ ልክክ ብሎ ወንዳወንድ ቁመናውን አጉልቶ አውጥቶታል።ቀላል ጓዝ የያዘ የመንገድ ሻንጣውን በትከሻው ላይ አንጠልጥሉ
አነስ ያለ የእንግሊዘኛ መፅሐፍ በእጁ ይዟል፡፡ ንጥረ ንጥር የሚለው አረማመዱ ነጭ እስኒከር ጫማው ውስጥ ስኘሪንግ የተቀበረ አስመስሎታል።ያለ ጉዳይ በሰፊው የመንገደኞች መቆያ ወለል ላይ እየተንሸራሽረ ዐይኖቿን ከሳበው በኋላ በዐይኖቹ ያጫውታት ጀመር፡፡ በመጀመሪያ ላይ “ዐይናውጣ በሚል ተሳዳቢ አስተያየት ገላምጣዋለች::
ዐይኖቿንም ልትነፍገው ሞክራ ነበር፡፡ በኋላ ግን ከዓመት በላይ የወንድ ገላ ነፍጋው የቆየችው ሰውነቷ የመልካም
ቁመናውን ጥሪ የሚቋቋም አልሆነም:: እና የመነሻ ሰዓታቸው ደርሶ ወደ አውሮኘላኑ ሲጓዙ እንደተከተላት
እያወቀች አልራቀችውም:: ተከታትለው ስለገቡ አንድ ላይ ለመቀመጥ አልተቸገሩም:: ገና እንደተቀመጠ
የደህንነት ቀበቶውን እያጠበቀ፣

“ጥሩ ቀን ይመስላል፣ አየሩ ብሩህ ነው” አላት፡ በአዎንታ አረጋገጠችለት:: ከዚያ መፅሃፉን ገለጠና ወደኋላው ለጠጥ ብሎ ማንበብ ጀመረ።
ፀጥ ብሎ ማንበቡን ሲቀጥል ማዕዶት ባልጠበቀችው ድርጊቱ ግራ ተጋብታ የግራ እጁን የቀለበት ጣት መልካት
አደረገች፡፡ ለጌጥ የተደረገ የወርቅ ቀለበት ነው፡፡ የጋብቻ አለመሆኑን አረጋገጠችና ዘና ብላ ተቀመጠች፡፡ በብልጠት
የበለጠችው መሰላት እንጂ እሱም ጣቶቿ ላይ የጋብቻ ቀለበት አለመኖሩን ገና እንግዶች ማረፊያ ወስጥ እያሉ
ነው ያረጋገጠው።

ለአስር ደቂቃ ያህል ከኣሁን አሁን እንደገና
ያናግረኛል ብላ ጠበቀችው መፅሀፉ ላይ አተኩሮ ጭራሽ መኖራንም የረሳ መሰለ፡፡ ተናደደችና ራሷን ከወንበሯ የኋላ መደገፊያ ላይ ጣል አድርጋ ፊቷን በትንሹ ወደሱ አቅጣጫ መለስ አደረገች:: ከዚያ እንቅልፍ እንደያዘው ሰው ዐይኖቿን ጨፈነቻቸው:: ሳምሶን ሁኔታዋ ገባውና
ዘወር ብሎ እያያት፤

ደበርኩሽ አይደል?” አለ፡ ልክ ረዘም ያለ ጊዜ ትውውቅ እንዳላቸው ሁሉ ፈገግ ብሎ:: ጥርሶቹ በንፅህና የተያዙ ናቸው:: ጠቆር ካለው የፊቱ ቆዳና ደፍጠጥ
ብሉ ቀዳዳዎቹ ሰፋ ካሉት አፍንጫው ስር እጅብ ካለው ጢሙ ጋር ህብር ፈጥረዋል:: አነስ ያሉት ዐይኖቹ ንቁ
ናቸው።

ግድየለም አንብብ » አለችው፣ እንቅልፍ
እንደያዘው ሰው ድክምክም ብላ፡፡

“ጥሩ የመንገድ ጓደኛ አይደለህም እያልሽኝ ነው አይደል? አላት መፅሐፍ ባልያዘበት ግራ እጁ ትከሻዋን
መታ አድርጎ እየሳቀ:: ነቃ ብላ እንደ መሳቅ እያለች አየችውና የየሰው ተሰጥኦ ገረማት።የሚያግባባ የሚያላምድ ፊትና ሁኔታ አለው::

"ኖ! ኖ! አንብብ እኔ እተኛለሁ አለችው።
"በአጭር የአውረፕላን ጉዞ ውስጥ ይኄ እንዳልኩት እንዳልኩት ደባሪ እያልሽኝ ነው! »

እንዲህ በክርክር ቢጤ ወሬ ጀመሩና በዚያ ቀጠሉ፡፡ ወደ ድሬዳዋ ለምን እንደምትሄድ ጠየቃት ከፍተኛ ኤክስፐርት መሆኗንና ለስብሰባ እንደምትሄደ
ነግራው የሱን ጠየቀችው:: በመንግስት መስሪያ ቤት ደህና ቦታ ላይ ይሰራ እንደነበርና አሁን ግን የግል ስራ
ለመጀመር ድሬዳዋ ሁኔታዎችን ለማጥናት እየሄደ መሆነን ነገራት፡፡

አውሮኘላኑ ያሬዳዋ አውሮኘላን ማረፊያ ደርሶ ሲለያዩ ፤ አዲስ አበባ ሲመለስ ሊጠያየቁ፡ ተስማምተው በየሞባይል ስልክ ቁጥሮቻቸውን ተለዋወጡ፡፡ በማግስቱ ስብሰባውን ተካፍላ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች፡፡

ከዚያ በኋላ ማዕዶት ሳምሶን ይደወላል ብላ ስትጠብቅ ሰነበተች።ሳምንት አለፈው፤ አልደወለም፡አስረኛው ቀን ቆጠረች ድምጹን አላሰማትም፡፡
ልትደውልለት ፈለገች:: ጥሩ አልመሰላትም፡፡ ተወችው፡፡በዚህ ሂደት ግን ብዙ አሰበችው:: ባሰበችው ቁጥር ደግሞ አእምሮዋ ውስጥ እየጎላ እየጎላ ቦታ እየያዘ ሄደ::በሶስተኛው ሳምንት ላይ ሳምሶን ደወለ። ጉዳዩ አላልቅ ብሎት ሁለት ጊዜ ድሬዳዋ ደርሶ መመለሱን
ነገራት እያይዞም ራት እስረው እንዲበለ ጋበዛት፡፡

ከስራ በአስራ አንድ ሰዓት ተኩል ስትወጣ መኪና ይዞ በር ላይ ጠበቃት የበዙ ጊዜ ትውውቅ ያላቸው ያህል እየተሳሳቁ ተሳሳሙ፡፡ ደህንነታቸውን በመጠያየቅ
👍3
#ማዕዶት


#ክፍል_ሦስት (የመጨረሻ ክፋል)


#በየዝና_ወርቁ

“እኔ ኮ ራሴን አላቀውም ሳሚ” አለችው በሚለማመጥ ቅላፄና በጨዋ ቋንቋ፡፡

ምንድን ነው የማታውቂው” ? አላት ግር
እንደመሰኘት ብሎ፡፡
«ኤች.አይ.ቪ ምርመራ ነዋ »አለችው::
«እኔም ወደውጭ አገር ስሄድ ተመርምሬ ነፃ መሆኔን ካወቅሁ ዓመት አልፎኛል፡፡ እንደገና ማድረግ ይኖርብኛል።

ይጠቀማል፡፡ ካልሆነ ግን እንደማዕዶት ዓይነት ያማረ
መልክና ቁመና ያላቸውና ረጋ ያሉ ሴቶችን ሲያገኝ

“ምንድ ነወ

“ታዲያ! አለችው - የምርመራ ነገር ሲነሳ ደፋር ለመምሰል ብትጣጣርም ፍርሃቷ ከውስጧ ማንሰራራት ጀምሯል።

«ታዲያማ ሰው የሚመረመረው፤ አስገዳጅ ሁኔታ ሲያጋጥመው ወይም ደግሞ ሲያገባ ወይም ልጅ ሊወልድ
ሲፈልግ ነው› አላት::
“ካልሆነስ?” አለችው - አንደበቷ እየጐለደፈባት፡፡
“መቼም እንዳንቺ የተማረ ሰው ኮንዶም አላቅም አይለኝም አላት በቀልድ ቃና እየሳቀ….ሳምሶን የሷን አቅጣጫ ተከትሎ ስለ ኮንዶም አወራ እንጂ በመሰረቱ ኮንዶም መጠቀም አይወድም::
አንዳንድ ጊዜ እንዲሁ አይቶ ወይም ሁኔታቸውን ታዝቦ የሚጠራጠራቸው ሴቶች ሊያጋጥሙት ብቻ ሳይወድ ይጠቀማል ካልሆነ ግን እንደ ማእዶት ያማረ መልክና ጠቁመናል ቁመና ያላቸውና ረጋ ያሉ ሴቶችን ሲያገኝ በነሱ በኩል ግፊቱን ካልመጣ እሱ አያስበውም። ስሜቱን
አርክቶ ማገናዘብ ሲጀምር ነው “ጭንቀት የሚሰማው፡፡በሌላ ጊዜ ግን መልሶ ያደርገዋል፡፡
ማዕዶት አነጋገሩን እስተዋለችና ጥሩ ግንዛቤ እንዳለው ገመተች፡፡ ለሷም ቢሆን ጥሩ ነገር እንደሆነ አሰበች፡፡ “ለጊዜው እሱ እንዳለው በኮንዶም እንቆያለን፡፡
ለመጋባት ስንወስን ደግሞ በቃ በመጀመሪያ ሳልነግረው ተደብቄ እመረምራለሁ። ፈጣሪ ረድቶኝ ነፃ ከሆንኩ
አብረን እንመረመራለን፡፡ ቫይረሱ ቢገኝብኝስ ... " ሐሳቧን መጨረስ አቃታት።ሰውነቷ ተንዘፈዘፈ....

መኪናቸው ውስጥ እንዳሉ ቦዩን ጠራውና
መኝታ ክፍል ተከራየ:: ወደዚያው ሲሄዱ
ብርጭቆዎቻቸውንና ጠርሙሱን ቦዩ ይዞ ተከተላቸው፡፡
እንደገቡ ሳምሶን ኮሞዲኖውን ከፈት አድርጎ ኮንዶም ሲያረጋግጥ አየችው:: ተረጋጋች።
ልብሶቻቸውን አውልቀው አልጋው ውስጥ ገቡ:: ትንሽ እንደተሳሳሙ ከኮሞዲኖው ውስጥ አንድ ፖኬት ኮንዶም
አወጣና ከውስጡ አንዱን ነጥሎ ጐረደው:: ቀሪውን ደግሞ ኮሞዲኖው ላይ አስቀመጠው:: ከዚያ ማሽጊያውን
ከፍቶ የውስጡን መዘዘና መብራቱን አጠፋው።

“መብራት አትወድም? አለችው።

“አዎ አላት - ድምጹም ድንገት ስልቱን አጣባት፡፡ስሜት ይዟቸው እልም አለ… በመጨረሻ አንሶላውን ከውስጥ ጎተተና አሸርጦ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄደ፡፡
ታጥቦ እንደተመለሰ መለኪያው ውስጥ የነበረው ማርቲኒ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠውና ሌላ ቀዳ:: የቀዳውን
ምንም ሳያናግራት ጨለጠው።

ግራ ተጋብታ አየችው:: ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ብሩህ ፈገግታ የነበረው ፊቱ ዳምኗል፡፡እንደገና ሲቀዳ
ፈራችውና ፤

“እንሂድ እየመሸ ነው አለች

አትጠውጪም? አላት- ስልቱን ባጣ ድምጽ፡፡

«በቃኝ» አለች - ለመልበስ እየተነሳች:: ለባበሱ ወጥተው ወደ ሳምሶን መኪና ሄዱ::
በቀጠሉት ሶስት ሳምንታት ሶስት ጊዜ ተገናኝተን ተመሳሳይ ሁኔታ አሳልፈዋል:: ማዕዶት ከድሮው ባህሪዋ በተለየ ሁኔታ ከሱ ጋር ስትሆን ሞቅ እስኪላት መጠጣት መጀመሯ ታውቋታል። ግን እያቀበጠ ስለሚያጠጣ ደስ ይላታል፡፡ እንደ ህፃን ስሜቱን መደበቅ የማይችል
መሆኑን እያስተዋለችም አብረውት ለመኖር የማይከብድ ዓይነት ሆኖባት ለማይቀረው የእንመርመር ጥያቄ
እንዲያበረታት ፈጣሪዋን እየተማፀነች ለጋብቻ ተመኝተዋለች

ድንገት ግን ያልጠበቀችው ነገር ተከሰተ፡፡ የወር አበባዋ በቀኑ ሳይመጣ ቀረ፡፡ ግራ ቢገባት መምጫ ቀኑን ኣዛብቶ የማያውቀውን የወር አበባዋን ሳምንት ሙሉ በተስፋ ጠበቀችው።መቅረቱን ስታረጋግጥ ብርክ ያዛት።

በስሜት ውስጥ ሆነን ሳናውቀውየተፈጠረ ስህተት ይኖር ይሆን?! ይኼ አደጋ ነው! ወይ በኔ ወይ
በሱ ላይ የመጣ እያለች አንጎራጎረች :: ልጁንም' ኮ ላይቀበለኝ ፣ ላያምነኝ ይችላል» ብላ አሰበችና ልትነግረው
ፈራች፡፡ እየቆየች ስታስበው ስታብላላው ግን ከመንገር ሌላ አማራጭ አጣችለት:: ሁለታችንም ሳናስበው የወደቅንበት አደጋ ላይ መወያየትና መፍትሄ መፈለግ
አለብን " አለች - ልትነግረው ወሰነችና ደውላ ለማታ ፕሮግራም አስያዘችው።

እንደሌለቹ ቀናት የመዝናናት ስሜት
አልነበራትም ራት መብላት አቅቷት መጠጣትም አስጠልቷት ስለነበር አሞኛል ብላ ዋሸችው:: ከዚያም
ብዙ ሳይቆዩ መብራቱን አጠፋው:: እሱ ስሜት ውስጥ ገብቷል፡፡ እሷግን ሀሳቧ ግራ በገባት ነገር እየተሰረቀ
አስቸግራት በስሜት ልትከተለው አልቻለችም፡፡ እና እሱን ለማስደሰት ብቻ እንደሚፈልገው እየሆነችለት ሳለ
መሀከል ላይ የተለየ ነገር ተሰማት:: ድንገት ጠረጠረችው።ድንጋጤ አስፈንጥራት ተነሳችና መብራቱን ቦግ አድርጋ አበራችው::ሳምሶን ኮንዶሙን በእጁ እንዳንጠለጠለው
ክው ብሎ ቀረ:: ማዕዶትም አንገቱን አንቃ ተንቀጠቀጠች። ከዚያ አንገቱን ለቃ ተስፋ በቆረጠ መንፈስ ፍራሹን እየደበደበችና፤
“አንተ አውሬ ነህ! ጭራቅ ነህ! ተኩሰህ እንደገደልከኝ ቁጣረው..... ምነው? ምን በደልኩህ?...” እያለች ትራሱ ላይ ተደፍታ ተንሰቀሰቀች፡፡ ሳምሶን ድንጋጤው መለስ
ሲልለት ፤

ምን እንዲህ ያደርግሻል? አንቺ ብቻ ነሽ ለህይወትሽ የምታስቢ? እኔ ከማንም ጋር የምጋደም መሰለሽ? ሰው መርጫ ነው" አለ በላይ ሆኖ እንደመቆጣት' እያደረገው
ከአፈርኩ አይመልሰኝ ዓይነት።

“የጅል ወግህን ተወውና ይኼንን ተንኮል የፈፀምክብኝ እውነት ተመርምረህ ቫይረሱ እንዳለብህ ሳታውቅ ከሆነ
ነገ እንመርመር " አለችው - እልህ እያንቀጠቀጣት፡፡

ሳምሶን ትኩር አድርጎ አያትና፤

“ይቻላል አለ - ትከሻዎቹን ከፍ አድርጎ ቁልቁል እየለቀቃቸው:: ዐይኖቹ ውስጥ ግን ፍርሃት በጉልህ ነግሶ ታየ።
እንደተኮራረፉ ልብሶቻቸውን ለብሰው ወጡ፡፡

በማግስቱ ለመመርመር ከተቃጠሩበት አሁን ውጤቷን እየጠበቀችበት ካለው ክሊኒክ ከሰዓቱ ቀድማ ደረሰች፡፡ ለዘመናት የራቀ የመሰላትን ያህል ጊዜ ጠብቃው ሲቀርባት በሞባይል ስልኳ ሞባይል ስልኩ ላይ ደወለችለት። ዘጋባት:: ሰዓቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ሆኗል፡፡ ግማሽ ሰዓት አሳልፏል:: ትንሽ ቆየችና ሞክረች። መልሶ ዘጋባት፡፡ ብርክ እንደያዛት ተስፋ ቆርጣ በየመንገዱ እንባዋን ለመዋጥ እየታገለች በኮንትራት ታክሲ ወደቤቷ ሄደች መሥሪያ ቤቷ ደውላ መታመሟን ለአለቃዋ አሳውቀችና ተኛች፡፡ ከሰዓት በኋላ ለሳምሶን በሱቅ ስልክ ደወለችለት
አነሳውና እሷ መሆኗን ሲያውቅ ዘጋባት፡፡
ደጋግማ ሞከረች፡፡ ሊያናግራት ፈቃደኛ አልሆነም…

ማዕዶት የተፈጠረውን ነገር እንደክፉ ቅዥት ስትባንን ለቀናት አሰበችው::
ሳምሶንን ለማግኘት የምታደርገው ጥረትም ጥቅም የሌለው ሆነባት፡፡ ከዚህ ወዲያ ባገኘውስ ምን ያደርግልኛ
ል? ጠላቴን የልጄ አባት አድርጌ አልቀበለው አለችናእርግፍ አድርጋ ተወችው::
እያደር ግን ለራሷ ከመጨነቅ አልፋ በማህፀኗ ውስጥ ስላለው ልጅ ማሰብ ጀመረችና ትናንት ደሟን ለምርመራ ሰጠች….
ማዕዶት የሰመጠችበትን የትዝታ ባህር ዋኝታ ስትጨርስ ያው የተጠናወታት ቫይረሱ ቢገኝብኝስ የሚለው ጭንቀት በውስጧ እያንሰራራ ነበር ። እና
የኤች አይ ቪ ቫይረስ ሰውነቷን ቅርጥፍጥፍ አድርጎ ሲበላው ቤተሰቦቿ እንኳ ሊያስታምሟት ሲሳቀቁ ፣ከወዳጅ ዘመዶቿ መሀል ተነጥላ ብቻዋን ስትንጠራወዝ ታያት፡፡ በውስጧ የጭንቀት ትኩሳት ተሰራጨ፡፡
ጨምድዶ። ከያዛት ጭንቀት ለመውጣት እያባ ት : ንቀት እየተወራጨች ! 'ቢኖርብኝም ቫይረስ ላለባቸው
1👍1