#በኔ_የደረሰ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በጥላሁን
የኔም የጓደኛዬም ፍቅረኞች ሁለቱም ሀብታም የሚለው ምን አይነት ሀብታም? የሚለን ጥያቄ የማያብራራ ጥቅል መጠሪያ ከማይገልፃቸው ከበቃቸው ሀብታም ቤተሰቦች የተወለዱ ናቸው።
የኔና የጋደኛዬ ቤተሰቦች ለመኖር የማይቸገሩ መካከለኛ የኑሮ ደረጃ በመባል የሚጠራውን አይነት ኑሮ የሚኖሩ ናቸው ። የኔ ፍቅር ሊሊ ስትባል የጋደኛዬ ፍቅረኛ ኪሪያ ትባላለች ትርጉሙስ ካላችሁ እኔን ሳይሆን እራሷን ጠይቋት ።
ገና በአዳማ ዩኒቨርስቲ የአንደኛ አመት የአካውንቲንግ ተማሪ ነኝ ፍቅር የጀመርኩት አስረኛ ክፍል ሆኜ ነው ታድያ ለፍቅር ምን አጣደፈህ አትበሉኝ የደረሰበት እንኳን እንደማይለኝ አውቃለሁ ያልደረሰባችሁ ካላችሁ
" አርፎ ትምህርቱን አይማርም ለፍቅሩ ይደርስበታል!" ምናምን እያለችሁ ብትሞልጩኝም እችለዋለሁ።
መጀመሪያ በጥፊ ተመቶ ቀጥሎ በኮብል የተፈነከተ ሰው የመጀመሪያውን ጥፊ ወድያው ረሳው ቢሉት ባይረሳው ገረመውን ይገርመው ነበር አለ ገረመው
የራሴ አባባል ነች ስለዚህ አሁን በተቆለለብኝ ዱብዳ የተነሳ ጭንቅላቴ ስድብም ብጨቃም ዝልዘላም አይሰማውም አቅማችሁ የቻለውን ያህል ተሳደቡ አጋጣሚውን ተጠቀሙበት።
እናላችሁ ••• ከዚቹ ከኔ ፍቅር ከሊሊ ጋር ፍቅር የጀመርነው ከሁለት አመት በፊት አስረኛ ክፍል እያለሁ ነው ። አንድ ክፍል ነበርን ቀድሜ የወደድኳት እኔ ነበርኩ እንደወደድኳት ግን ነግሪያት አላውቅም እንኳን ለሷ ልነግራት እኔ እራሴ የያዘኝ ፍቅር መሆኑን መች ቶሎ ገባኝና ብቻ እኔ የማውቀው
ስተኛ ትዝ እንደምትለኝ ።
ስበላ እንደማስታውሳት።
ሴት ልጅ ከሩቁ ባየሁ ቁጥር እሷ እንደምትመስለኝ።
ሳትጠራኝ የጠራችኝ እየመሰለኝ ብንን እንደምል።
ጥዋት ገብቼ ለመማር ሳይሆን እሷን ለማየት ከክፍሉ ተማሪ በሙሉ ቀድሜ እንደምገኝ።
ሌሎች ወንዶች ሲያናግራት የሆነ የሚያቃጥል ነገር እንደሚሰማኝ በለው በለው ንከሰው ቦጭቀው እንደሚለኝ።
አጠገቤ ስትቀመጥ ላብ እንደሚያሰምጠኝ ።
ስታወራኝ ምላሴ ወደውስጥ ገብቶ እማወራው ነገር እንደሚጠፋብኝ ።
ቅዳሜና እሁድ የሚባል ነገር እንደሚያስጠላኝ ።
ሰኞ እንደምፅአት ቀን እንደምትርቅብኝ ብቻ ነበር።
ለእንደኔ አይነቱ ጭምት እንኳን ፍቅር ሊጀምር የፍቅር ፊልም እንዲያይ አባቱ የማይፈቅድለት
ከደብተሩና ከቤተሰቦቹ ውጪ ከሌላው አለም ጋር ሳይተዋወቅ ያደገ ልጅ ከላይ የታዩበት ምልክቶች የፍቅር ምልክት መሆናቸውን መለየት ከባድ ነበር አይ ፍቅር ዶክተር አልባ ህመም ።
እናማ በአንድ አጋጣሚ የቤተሰብ ፕሮግራም ላይ ለአንድ የአክስቴ ልጅ የፍቅር ህመም ምልክቶቼን አውራሁለት
በቃ ሳያት ደስ ይለኛል ተለይቻት ፊቷ ከፊቴ ላይ አይጠፋም ለምን እንደሆነ እኔ እንጃ ከሌላ ወንድ ጋር ስታወራ እናደዳለሁ ስለው
ረጅም ሳቅ ሳቀብኝ በትግስት ጠበኩት የትግስቴን ፍሬ ነገረኝ ። "ፍቅር ይዞሀል ሶልዬ " አለኝ። ብትችል ትምህርትህን እስክትጨርስ እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ ባትገባ ይሻል ነበር
አሁን ግን ከነገርከኝ አንፃር ላትመለስ ተዘፍቀህበታል እና ንገራት" የሚለውን አስከትሎ ተለየኝ ። ንገራት! ንገራት! ንገራት! የሚለው ቃሉ ጭንቃላቴ ላይ ሲያቃጭልብኝ አምሽቶ አነጋ ። እነግራታለሁ ወሰንኩ ሰኞ ለሊት አስራ አንድ ሰአት ተነስቼ ገላዬን ታጠብኩ ። ጥዋት ሶስት ፔሬድ ሙሉ የተማርኩትም የፃፍኩትም ትዝ አይለኝም ።
ምን እንደምላት ስፅፍ ስለማመድ ቆየሁ•••
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

❤1
#በኔ_የደረሰ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#በጥላሁን
ንገራት ንገራት ንገራት የሚለው ቃሉ ጭንቃላቴ ላይ ሲያቃጭልብኝ አምሽቶ. አነጋ ። እነግራታለሁ ወሰንኩ ሰኛ ለሊት አስራ አንድ ሰአት ተነስቼ ገላዬን ታጠብኩ
ጥዋት ሶስት ፔሬድ ሙሉ የተማርኩትም የፃፍኩትም ትዝ አይለኝም ።
ምን እንደምላት ስፅፍ ስለማመድ ቆየሁ•••
ምን ብዬ እንደምጀምር ምን ብዬ እንደምቀጥል እና ምን ብዬ እንደምደመድም የትኛው ሀሳብ መቅደም የትኛው መከተል እንዳለበት መግቢያ ማጠናከሪያ መደምደሚያ ብዬ ከፋፍዬ ላስቀምጥ ብሞክርም ውስጤ ያለውን የፍቅር ንዳድ በደንብ ሊገልፁላት የሚችሉ ቃላቶች ማግኘት ፈተና ሆነብኝ።
መግቢያ:- ሊሊዬ ለብቻሽ ላናግርሽ የፈለኩት አንድ ጉዳይ ነበረኝ ለዛ ነው ለብቻሽን ላናግርሽ የፈለኩት....
ወይ ጣጣ እሄ ደሞ የፍቅር ጥያቄ ሳይሆን ብድር የሚጠይቅ ሰው የሚጠቀምበት የመግቢያ ንግግር ይመስላ አቦ አልኩና እላዩ ላይ ትልቅ የኤክስ ምልክት አጋድሜ ግድግዳውን ተደግፌ ከክፍሉ ሴት ተማሪዎች በሙሉ እንኳን የትምህርትቤቱን ይንፎርም የተቀዳደደ ጆንያ ለብሳ ብትመጣ ውበቷ የማይጎድልብኝን የለበሰችው የሳቀችው የተናገረችው ሁሉ ልዩ እና ውብ መስሎ የሚታየኝን እኔ ከተቀመጥኩበት በስተግራ እክፍሉ መሀል ላይ ከሁለት ሴት ጓደኛቿ መሀል ላይ ያለችውን ሊሊዬን ከጀርባ እያየሁ የምላትን ማሰብ ጀመርኩ።
የመጣልኝን ሁለተኛውን ሀሳብ መፃፍ ጀመርኩ•••
ፅሁፉ እየመራኝ ይሁን እኔ እየመራሁት ባይገባኝም ፊደሎቹ እየተፈላለጉ መመሳሰል ጀመሩ ። ሳላስበው እንደመግጠምም አደረገኝ•••
ምን መሰለሽ ? እሄውልሽ ሊሊዬ
እኔ ባንቺ ፍቅር ሁሉን ነገር ጥዬ
ሳይሽ ደስ ይለኛል
ካጠገብሽ ስርቅ ጭንቀት ይወረኛል
ሲለው ፍርሀት ፍርሀት ብርድ ብርድ ይለኛል
በቤተሰብ መሀል እቤቴ ቁጭ ብዬ
ብቻዬን የሆንኩኝ ያህል ይሰማኛል
ሳቅሽ ይርበኛል
አንቺ ሳትኖሪ ድምፅሽ ይጠራኛል
በውድቅት ለሊት ሰው ሁሉ ተኝቶ
እኔ አስብሻለሁ
አንቺ ሳትመጪ ኮቴሽ ይሰማኛል
የቱንስ ልንገርሽ የቱኛውን ትቼ
በፍቅርሽ ሳስቼ እራሴን ረስቼ
ምግብ መብላት ትቼ
መኖር እንደጀመርኩ እኔን ላንቺ ትቼ
ስትስቂ ካየሁ ባንቺ ደስታ ስስቅ
የከፋሽ ሲመስለኝ ሲልብኝ ድብልቅልቅ
በጣም የሚገርመው ይህ ሁሉ በኔ ላይ ሲሆን የነበረው በፍቅርሽ መያዜን ከቶም ሳልረዳው ጭራሽ ሳይገባኝ ነው
እናም የኔ ፍቅር
ፍቃድሽ ከሆነ ወድሻለሁና
ያንቺ ልሁንና ላንቺው ፍቅር ልኑር።
አሁን ይሄን ባነብላት ከዚህ በፊት ሁለት ስንኝ ያላት ግጥም ስፅፍ አይታኝ አታውቅ ላንቺ የውስጤን ይገልፅልኛል ብዬ የፃፍኩት ግጥም ነው ብላት ያንን ደስ የሚል ሳቋን ስቃ። አይ ሶልዬ በዳዲ ሞት ሙድ መያዝህን ተውና ግጥሙን ወድጄዋለሁ ይልቅ ኬትኛው መፅሀፍ ላይ ነው ያገኘከው ብትለኝ ምን ይውጠኛል ከዛ ቡሀላ ቁምነገር ነው ብላትም አላግጣብኝ ነው እምትሄደው ይቅርብኝ።
ባይሆን እሄን ግጥም ምናልባት ከሊሊ በላይ ማፍቀሬን ባልነግረውም የሚረዳኝ እና ውስጤን የሚያውቀው የፍቅር አምላክ አሳክቶልኝ እሺ ብላኝ አብራኝ ከሆነች ቡሀላ ባነብላት ይሻላል ።
ይሄም ተሰረዘ ። ግጥሙን የፃፍኩባትን ወረቀት በጥንቃቄ አጣጥፌ ኪሴ ውስጥ ከተትኩና ሌላ ባዶ ወረቀት ፊቴ አስቀመጥኩ።
ይልቅ እንድታምነኝ ንግግሬን በሀይለ ቃል አጅቤ ማዥጎድጎድ እንዳለብኝ ውስጤ ሹክ አለኝ።
በቃ በፍቅርሽ ጨርቄን ጥዬ ማበዴ ነው አልቻልኩም እኔስ አፍቅሬሽ ልበድ ላንቺ ማበዴ አይበዛብሽም ግን ደግሞ የኔ ማበድ ለቤቴሰቦቼ ከባድ ነው የማይቋቋሙት ትልቅ ሀዘን ውስጥ እንደሚገቡ አውቃለሁ ያንን ሳስበው ደሞ እንደዛ የሚንሰፈሰፉልኝ ቤተሰቦቼ በኔ ምክንያት ተጎድተው ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ ። እውነቴን ነው ሊሊዬ እኔ አብጄ ሁሌ እያዩኝ የስቃይ ሂወት ከሚገፉ ዛሬውኑ ብሞት ይሻለኛል።
እሄን የፍቅር ጥያቄ ሳይሆን ከፊሉ ዛቻ ከፊሉ ኑዛዜ የመሰለ ፅሁፍ ወረቀት ላይ አስፍሬ የራሴ ሀሳብ ሳይሆን ሰው ፅፎ የሰጠኝ ይመስል መልሼ ሳነበው ተናደድኩ። ወረቀቱን በጫጭቄ ጣልኩት።
ሁለተኛው የትምህርት ክፍለ ግዜ ተጠናቆ ሶስተኛው ተጋመሰ።ሲደወል እረፍት ነው። ሊሊን አዋራታለሁ። እስካሁን ግን ምን እንደምላት አልወሰንኩም ።
ደቂቃዎቹ እያለቁ በሄዱ ቁጥር ንዴቴ እየጨመረ መጣ። የእረፍት ሰአት ሲደወል ።መፃፉን አቃረጥኩና ብእሩን ዴክሱ ላይ አስቀምጬ እጄን አጣጥፌ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ•••
ቆይ ግን ፍቅር እኔን የያዘኝ አለማምዶ ነው እንዴ? ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነና እንዴት እንደሚያደርግ እንደማላውቅ እያወቀ አደል እንዴ ዘሎ የተከመረብኝ ታድያ ምን እንደምል እንዴት እንደማስረዳት እንዴት እንደማሳምናት እያሰብኩ ምን አጨናነቀኝ።
ልክ ሳገኛት ለስንት ወራት ውስጤ ተቀምጦ የነበረው ፍቅር እራሱን ይግለጥላት።
ሰው ምን ብዬ ባስረዳት ታምነኛለች እያለ መጨነቅ ያለበት ፍቅሩ የውሸት ከሆነ ብቻ ነው። እኔ እሷን ማፍቀሬ ግን እውነት ነው። እውነት ደሞ እራሱን የሚገልጥበት መንገድ አያጣም። የቃላት ቀመር የንግግር ልምምድ አያስፈልገውም። ምክንያቱም ምን ልበል ብዬ አላስብም የምለው ነገር በሙሉ የሆንኩትን ነው።
የሆነውን ነገር መናገር ቢያቅተኝ እንኳን እሷ ፊት ቆሜ የልቤን ህመም መግለጥ አለመቻሌ በራሱ ፍቅር ነው አልኩና።
ያሰብኩትን ደግሜ ሳስበው ይገርማል ፍቅር ፈላስፋም፣ ዘፋኝም፣ ገጣሚም፣ እብድም፣ ፀሀፊም፣ አልቃሽ ደስተኛም ተካዥም፣ ብቸኛም ያረጋል ሲባል አይገባኝም ነበር ዛሬ ግን ያሰብኩት ምን ማለት እንደሆነ ለራሴም ግራ እስኪገባኝ ፈላስፋ አድርጎኝ አረፈው።
ግን ይሄ መፈላሰፍ ነው እንዴ መፈላሰፍ እራሱ ምን ማለት ነው! ወጣም ወረደም ፍቅር የያዘው ሰው ሁለመናው ማፍቀሩን ስለሚናገር ምን ልናገር ብዬ ባልጨነቅስ!
የእረፍት ሰአት ተደወለና ተያይዘን ትምሽ እንደሄድን
"ለምን ነበር እረፍት ሰአት ልታናግሪኝ የፈለከው ሶልዬ?" ስትለኝ ደንግጬ አይን አይኗን ከማየት በስተቀር ሌላው እንኳን ቢቀር ወዬ ሊሊዬ የምትለውን ቃል ለመናገር ብሞክር
ኔትወርኩ እንደጠፋ ስልክ ምላሴ ላይ እየተሽከረከረች አልወርድ አለችኝ።
የስልክ ኔትወርክስ ቦታ በመቀያየር ይፈለግ ይሆናል የኔን ኔትወርክ ምኑን ቀያይሬ ላምጣው!
ቸርነቱ ብዙ አንደበቱን ሰጥቶኝ
ፍቅሬን እንዳልገልጠው ፍቅርሽ ዲዳ አረገኝ
እባክሽን ማሬ ያንደበቴን ትተሽ
ውስጤን ተረጅልኝ አይኔን ተመልክተሽ!!
ብለው ዘፍነው ይሆን እንዴ ዘፋኛቹ ?
አይመስለኝም •••
💫የቀጥላል💫

👍1🔥1
#በኔ_የደረሰ•
፡
፡
#ክፍል_ሦስት
፡
፡
#በጥላሁን
...እሄ መፈላሰፍ ነው እንዴ መፈላሰፍ እራሱ ምን ማለት ነው! ወጣም ወረደም ፍቅር የያዘው ሰው ሁለመናው ማፍቀሩን ስለሚናገር ምን ልናገር ብዬ ባልጨነቅስ!
የእረፍት ሰአት ተደወለና ተያይዘን ትንሽ እንደሄድን
"ለምን ነበር እረፍት ሰአት ልታናግሪኝ የፈለከው ሶልዬ?" ስትለኝ ደንግጬ አይን አይኗን ከማየት በስተቀር ሌላው እንኳን ቢቀር ወዬ ሊሊዬ የምትለውን ቃል ለመናገር ብሞክር ኔትወርኩ እንደጠፋ ስልክ ምላሴ ላይ እየተሽከረከረች አልወርድ አለችኝ።
የስልክ ኔትወርክስ ቦታ በመቀያየር ይፈለግ ይሆናል የኔን ኔትወርክ ምኑን ቀያይሬ ላምጣው!
ቸርነቱ ብዙ አንደበቱን ሰጥቶኝ
ፍቅሬን እንዳልገልጠው ፍቅርሽ ዲዳ አረገኝ እባክሽን ማሬ ያንደበቴን ትተሽ
ውስጤን ተረጅልኝ አይኔን ተመልክተሽ!!
ብለው ዘፍነው ይሆን እንዴ ዘፋኛቹ ?
አይመስለኝም •••
መጨነቄን በማስተዋል ስታይ የነበረችው ሊሊ
"ሶልዬ አትጨነቅ በቃ እንደምትወደኝ እንኳን እኔ ጓደኛቼም ያውቃሉ!
ታፈቅረኛለህ አደል?
እሱን ልትነግረኝ ፈልገህ ነው አደል እንዲህ ፈንጅ እንደረገጠ ሰው በቆምክበት ደርቀህ ምላስህም ሰውነትህም አልንቀሳቀስ ያለው ?ስትለኝ ጆሮዬን ማመን ተሳነኝ ።
ንግግሯ ምላሴ የታሰረበትን ገመድ በጣጠሰው መሰለኝ
" ሊሊዬ አዎ አፈቅርሻለሁ ግን እንደማፈቅርሽ በምን አውቅሽ ?
ጓደኛችሽ እንዴት አወቁ ? ስላት ሳቋን ለቀቅችው
"አንተስ እንዳፈቀርከኝ በምን አወክ? ብላ ግራ የገባው ጥያቄ በመጠየቅ ግራ አጋባችኝ ቢሆንም ምላሴ ተፈቷልና ለመመለስ አልቦዘንኩም•••
እኔማ እንዴት አላውቅም ሊሊዬ
ለሰከንድ ስላንቺና አንቺን ከማሰብ ተዘናግቼ አላውቅም ።
የሚዘፈነው የፍቅር ዘፈን በሙሉ ላንቺ የተዘፈነ ይመስለኛል ።
በፍቅሯ የሆንኩትን በሙሉ ለመዘርዘር ሲዳዳኝ •••
አንገቴ ላይ ድንገት ተጠምጥማ " እኔም እወድሀለሁኮ ሶልዬ!" ስትለኝ ከደረቴ በታች የሆነ ብቻ ለመግለፅም የሚከብድ እስከዛሬ ተሰምቶኝ የማያውቅ ስሜት ተሰማኝ።
ምን አልሽኝ ሊሊዬ አልኩ እንድትደግምልኝ ፈልጌ ዝም አለች። ደግሜ ለመስማት ፈልጌ በዝምታ ጠብኳት ። ደገመችው ።ደጋገመችው። አብረን ሆንን።
እኔ ከሊሊ ጋር በፍቅር ብን ማለቴ ጨርሶ ያልተዋጠለትና ያልተመቸው ሰው ቢኖር ጓደኛዬ ነው
እሄ ጓደኛዬ ኪሩቤል ይባላል ከወንድ ጓደኛቼ በጣም የምወደውና እንደወንድሜ የማየው ከልጅነት ጀምሮ ለብዙ አመታት ተለይቼው የማላውቅ ጓደኛዬ ነው
ታድያ እንደጓደኛ የማፈቅራት ልጅ እሺ ስላለችኝ እና አብራኝ ስለሆነች መደሰት ሲገባው ወረደብኝ ወረደብኝ አይገልፀውም በተግፃፅ እና በምፀት ደበደበኝ ብል ይቀለኛል
"አንተ ግን ምንድን ነው ወንድ አደለህ እንዴ ቆፍጠን በል እንጂ ምን ያዝረከርክሀል ኧረ በናትህ ለሴት ልጅ እሄን ያህል መሸነፍ መዋረድ ነው ለኔ ፍቅር ምናምን ትላለህ እንዴ ፍቅር አንተ ካልደረስክበት አይደርስብህም አንተ ፊት ካልሰጠከው ድርሽ አይልም ለሴት ልጅ የሚያለቅስ ጓደኛ ስላለኝ በጣም ነው ያፈርህምኩት ጓደኛቿ ሁሉ እኮ በፍቅሯ እግሯ ስር እንደጣለችህ ነው የሚያወሩት ኧረ እኔ ለሴት መቼም ቢሆን እንዳንተ ከምሆን ብሞት ይሻለኛል!"
አለኝ ይህን ፀባዩን እና አመለካከቱን በሌሎች ጓደኛቻችን ላይም ሲያንፀባርቀው ስላየሁ በውስጤ "ደርሶብህ እየው ያኔ ብናወራ ይሻላል ፍቅርን የሚያውቀው ያጣጣመው አልያም አልያም አናቱ ላይ ወጥቶ ያብከነከነው ብቻ ነው" እያልኩ ካጠገቡ ከመሄድ በቀር መልስ አልሰጠሁትም።
እንደው ሰው አማህ አትበሉኝና ጓደኛዬ ከምጣላበት የምወድለት ባህሪው በልጦብኝ ዘለቅን እንጂ የሚያናድድ ጢባር አለበት።
ደፋር ነኝ አደል ሰው አማህ አትበሉኝና ማለቴ ?
ቆይ እንዲህ በሀሜት አንስቼ እያፈረጥኩት
ሰው አማህ ካላላችሁኝ ምን ልትሉኝ ነው ?
ምን ላርግ ሲሉ ሰምቼ ነው።
ሲሉ ሰምቼ ያልኩትም ሲሉ ሰምተው ሲሉ ሰምቼ ነው።
አንዳንድ ሰዎች አንድን ሰው በሀሜት ስጋውን ቦጫጭቀው ባጥንቱ ሊያስቀሩት መንደርደር እንደጀመሩ መግቢያ አድርገው የሚጠቀሙት
"ሰው አማህ(አማሽ) አትበሉኝና!"
የሚለውን ፈንጅ አምካኝ ንግግር ነው ሰው ላይ የሀሜት ፈንጅ እየወረወሩ እነሱ ላይ የሚወረወረውን የትዝብት ፈንጅ የሚያመክኑት "ሰው አማህ /ሰው አማሽ አትበሉኝና" በሚለው ቅድመ ሀሜት ንግግራቸው ነው።
እናም ሁሌም እንደዚህ የሚሉ ሰዎች ሲያጋጥሟችሁ ሰው እያሙ ሰው አማህ ወይም ሰው አማሽ ካላላቹሀቸው ምን ምን እንደምትሏቸው ማሰብ ጀምሩ።
መልሱን ለናንተ ልተወውና ወደ ጉዳዬ ልመለስ
ሰው አማህ አትበሉኝና ጋደኛዬ ክሩቤል በተለይ በተለይ በፍቅር ዙርያ ያለው አመለካከትና በፍቅር መሀል ጣልቃ ለመግባት ያለው ድፍረት ያናድደኛል።
ፍቅርም አይዘኝም ፍቅር የምታስይዘኝም ሴት የለችም መፈክሩ ነው።
አንድ ቀን የኔዋ ሊሊ •••
"ጋደኛዬ ጓደኛህን ክሩቤልን ወዳዋለች ልጁ ግን እሚገባው ነገር አደለም እባክህን አናግረው እስቲ ሶልዬ!" ስትለኝ በጣም ደነገጥኩ ሄጄ ሳናግረው ምን እንደሚለኝ! እንዴት እንደሚላላጥብኝ! አንተን አረከኝ እንዴ ብሎ እንደሚዘልፈኝም አውቀዋለሁ ቢሆንም የማይቻል ወይም ጭራሽ የማይሞከር ካልሆነ በስተቀር ሊሊዬ ምንም አድርግልኝ ብትለኝ የትም ሂድልኝ ብትለኝ እምቢ ለማለት አቅም የለኝምና ኩሩቤልን አናግሬው ምላሹን እንደምነግራት ቃል ገብቼ ተለያየን።
ሄጄ ሳናግረው እንደፈራሁት ተላላጠብኝ ብዙ ነገር አውርቶ በመጨረሻ ጥየው ስሄድ ጮክ ብሎ "ቢጤሽን ፈልጊ በላት "አለኝ ።
ለሊዬ በቃ ልጁ አይሆናትም ይቅርባት ምላሹ ጥሩ አደለም አልኳት። ልጅታ ከሊሊ መልሱን ስትሰማ "ያፈቀረ ሲቆርጥም የመረረ!" እንዲሉ እርግፍ አድርጋ ተወችው ። ከተወሰነ ግዜ ቡሀላ ልጅቷ ከአንድ ልጅ ጋር ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ አዘውትራ መታየት ጀመረች።
ፍቅር ላይ ንጉስ ነኝ የሚለው ጓደኛዬ።
ፍቅሯ ተገልብጦ መቆሚያ መቀመጫ አሳጥቶታል ታግሎ ታግሎ ሲሸነፍ መሸነፉን ሊተነፍሰው ግድ ሆነበት ሲል የነበረውን ያውቀዋልና እንዴት እንደሚነግረኝ ግራ ገብቶት ሁለት ግዜ በጣም እፈልግሀለሁ እያለ ቀጥሮኝ ሳይነግረኝ ተለያየን ። የመጀመሪያው የትምህርት መንፈቀ አመት ተጠናቆ እረፍት ላይ ነበርን ለሶስተኛ ግዜ ቀጥሮኝ እቤታቸው ሄድኩኝ ክፍሉ ስገባ በሆዱ ተኝቶ ያስቴርን ሙዚቃ እያዳመጠ ነበር

👍2
#በኔ_የደረሰ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በጥላሁን
...ፍቅር ላይ ንጉስ ነኝ የሚለው ጓደኛዬ።
ፍቅሯ ተገልብጦ መቆሚያ መቀመጫ አሳጥቶታል ታግሎ ታግሎ ሲሸነፍ መሸነፉን ሊተነፍሰው ግድ ሆነበት
ሲል የነበረውን ያውቀዋልና እንዴት እንደሚነግረኝ ግራ ገብቶት ሁለት ግዜ በጣም እፈልግሀለሁ እያለ ቀጥሮኝ ሳይነግረኝ ተለያየን ። የመጀመሪያው የትምህርት መንፈቀ አመት ተጠናቆ እረፍት ላይ ነበርን ለሶስተኛ ግዜ ቀጥሮኝ እቤታቸው ሄድኩኝ ክፍሉ ስገባ በሆዱ ተኝቶ ያስቴርን ሙዚቃ እያዳመጠ ነው •••
ስገባ ቀና አለ ። ሁኔታውን ሳየው እንኳን እሱ እኔም ሲለኝ የነበረውን ነገር ሁሉ ረሳሁት። አንጀቴን በላኝ ትናንት እንደዛ ስትል እንዳልነበር ዛሬ እያልኩ በፍቅር በወደቀው ዛፍ ላይ መጥረቢያ ማብዛቱን በጭራሽ አልፈለኩም።
እንኳን እንደዛ ልለው የሆነውን ከሁኔታው ተረድቼ ሳለሁ ምን ሆነሀል? ብዬ ላስጨንቀው አልፈለኩም።
እራሴ ወደጉዳዩ ቀጥታ ብገባ ሁለቴ ቀጥሮኝ ለመናገር የከበደውን ነገር እንደማቀልለት አሰብኩና •••
ትናንት ያጣጣልካትን ልጁ መልሰህ ስላፈቀርካት አይሰማህ ጋደኛዬ ይህ ፍቅር ጉልበቱን የሚያሳይበት አንዱ ባህሪው ነውና "ትናንት እሷ አፍቅራኝ ቢጤሽን ፈልጊ ያልኳትን ልጅ እንዴት እንዲህ በፍቅሯ ልንበረከክ ቻልኩ " እያልክ ከራስህ ጋር አትጣላ የደካማነት ስሜትም እንዳይሰማህ።
ማፍቀር መታደል እንጂ መሸነፍ ወይም መዋረድ አይደለም።ስለፍቅር ሊያውም ጥቂቱ የሚያውቀው ያፈቀረ ብቻ ነው ። ትናንት ስለማታውቀው ፍቅር ምንም ብትል አይገርምም።
አሁን ማፍቀር ዝቅ ማለት መሸነፍ መዝረክረክ ሳይሆን መታደል መሆኑን የተረዳህ ይመስለኛል? ይህን ተናግሬ ቀና መልሱን ስጠብቅ ጭንቄቱን በማወዛወዝ አዎንታውን ከገለፀልኝ ቡሀላ
"እና ያኔ ባልኩህ ነገር አልተቀየምከኝም ማለት ነው ጓደኛዬ? ከተቀየምከኝ ግን ይቅርታ!" አለኝ። አነጋገሩ እና አስተያየቱ በጣም ያሳዝን ነበር።
በጭራሽ አልተቀየምኩህም ጓደኛዬ በጣም የምወድህ ጓደኛዬ እኮ ነህ ከልጅነታችን ጀምሮ ብዙ ነገር አብረን ያሳለፍን ወንድማማቾች ነን ።
እኔ እናት እና አባቴ እህት እንጂ ወንድም አልሰጡኝም አንተ ነህ ከፈጣሪ የተሰጠከኝ ወንድሜም ጋደኛዬም ።
ጋደኛማቾች ነን ማለት ግን አንድ አይነት አስተሳሰብና አመለካከት አለን ማለት አይደለም የአመለካከት ወይም የሀሳብ ልዩነት ደግሞ አያቀያይምም። በርግጥ ጣልቃ ገብተህ ስትገስፀኝ እናደድብህ ይሆናል ቢሆንም በፍቅር ዙርያ የነበረን የአመለካከት ልዩነት ጓደኝነታችንን የማሻከር አቅም የለውም። ስለው ተነስቶ አቀፈኝ። ተቃቀፍን።
"እሺ ምንድን ነው የማናደርገው ሶልዬ እኔ የማብድ የማብድ እየመሰለኝ ነው ከልጁ ጋር ፍቅር የጀመሩ ይመስልሀል?" ሲለኝ•••
አይመስለኝም ለሁሉም ነገር መጀመሪያ የኔዋ ሊሊን ያለውን ነገር በግልፅ እንድትነግረኝ እጠይቃታለሁ ከዛ የሷን መልስ ከሰማሁ ቡሀላ ያለህበትን ሁኔታ መንገር ይኑርብኝ አይኑርብኝ ወስናለሁ።
ጋደኛዬ አንድ ነገር ግን ልነግርህ እፈልጋለሁ ልጅቷን በጣም እንዳፈቀርካት ተረድቻለሁ ከተሳካ እሰየው ባይሳካም ግን ሂወት እንደምትቀጥልና ያንተ ብትሆን ኖሮ እንደሚሳካ ያልተሳካው ፈጣሪ እሷን ላንተ ስላላላት መሆኑን አምነህ ለመቀበል ተዠጋጅ።
ካልሆነ ግን ከዚህኛው ጉዳት ያኛው ይከብዳል ። የሰው እንደሆነች እና እንደማታገኛት እያወክ ማፍቀርን የመሰለ ከባድ ህመም የለም።
ህመሙ ባይቀርልህም እንዳይጠናብህና እራስህን እንዳትጥል ቅድም እንዳልኩህ ሌላ ሂወት እንዳለና ያንተ የሆነችውን ለማግኘት ያንተ ያልሆነችውን ረስተህ እራስህን ሳትጥል መጠበቅ እንዳለብህ ማመን አለብህ ያለበለዝያ ያንተ ያልሆነችውን በማይሳካው የፍቅር አለም ውስጥ ስታሳድድ ያንተ የሆነውን ሁሉ ታጣለህ።
በቅድሚያ ከራስህ ትጣላለህ ። በመቀጠል በዙርያህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ያስጠሉህና ከነሱም ትጣላለህ ።
ከዛ በየመንገዱ ከድንጋዩም ከግድግዳውም ከአየሩም ከንፋሱም መጣላት ብቻህን ማውራት ትጀምራለህ ። በመጨረሻ አብደህ ከፈጠርህ ጋም ትጣላና የሰይጣን ትሆናለህ።
ስለዚህ በማፍቀርህ ልክ ባይሳካ ለመርሳትም ተዘጋጅ።
እሺ ሶልዬ በጣም አመሰግናለሁ ግን ልጁን የምታፈቅረው ይመስልሀል?"
እኔ በምን አውቃለሁ ጓደኛዬ እኔም እንዳንተው አብረው አየኋቸው እንጂ ሌላ ምንም የማውቀው ነገር የለም ።
ስንቱ ተቃቅፎ እየሄደ በሆዱ በሚሰዳደብባት አለም አብረው ስለተቀመጡና አብረው ስለሄዱ ብቻ ይፋቀራሉ ብሎ መደምደም መጃጃል ነው
"እሺ አሁን ሊሊን መቼ ልታናግራት ወሰንክ ሶልዬ!"
"ነገ እንገናኛለን ነገ አናግራታለሁ "
"ኧረ ሶልዬ እስከነገ ለምን አሁን ብትደውልላት አይሻልም ቢያንስ ከልጁ ጋር ያላትን ጉኑኝነት ሰምቼ ቁርጤን እንዳውቅ!" ከስልክ ይልቅ ሳገኛት ባወራት እንደሚሻል ውስጤ ቢያምን በዚህ ስሜት ውስጥ ሆኖ አልደውልም ብለው ምን ያህል እንደሚከፋው በማሰብ ስልኬን አውጥቼ ደወልኩ።
ሊሊዬ ስልኬን አንስታው የራሳችንን ወሬ ከጨረስን ቡሀላ በጎደኛዋና ሰሞኑን አብራት በሚታየው ልጅ መካከል ያለው ግኑኝነት ምን እንደሆነ ስጠይቃት ገብቷት ነው መሰለኝ ረጅም ሳቅ ሳቀች።
ሳቋን ስትጨርስ ለምን እንደሳቀች ስጠይቃት
"ለምን እንደሳኩ እንድነግርህ አንተ በቅድሚያ ለምን እንደጠየከኝ ንገረኝ?" አለችኝ አሁንም ሙሉ በሙሉ ከሳቋ ሳታባራ።
ምን እንደምላት ጨነቀኝ ፍንጭ ካልሰጠኋት ልትነግረኝ እንደማትችል ስረዳ ከጓደኛዬ ክፍል እየወጣው
" ማንነቱን ሳልነግራት አንድ ጓደኛዬ በፍቅሯ እየትንገላታ መሆኑን ልነግራት ገና በቃ አንድ ጋደኛዬ አፍቅሯት•••
ስል በድጋሚ ሳቋ አቃረጠኝ ከሳቋ ከጠል አድርጋ
"ዋው ቀመራችን ሰርቷል ማለት ነዋ "
አለች የምን ቀመር ሊሊዬ?
ቀመሩ ወንዶች ስትባሉ የጣላችሁትን እንኳን ሲያነስባችሁ እንደምትወዱ አውቀን የቀመርነው ነዋ!"
"ልጁ ዘመዷ ነው አብራ መታየት የጀመረችው ሆን ብለን ተማክረን ነበር ጓደኛህ ወጥመዳችን ውስጥ ዘሎ መግባቱ እንደማይቀር ገምቼ ነበር ስትለኝ ደነገጥኩም ደስ አለኝም።
ስልኩን ዘግቼ የጓደኛዬን ክፍል በር በርግጄ ገባሁ

❤1👍1
#በኔ_የደረሰ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#በጥላሁን
"ዋው ቀመራችን ሰርቷል ማለት ነዋ "
አለች የምን ቀመር ሊሊዬ?ቀመሩ ወንዶች ስትባሉ የጣላችሁትን እንኳን ሲያነስባችሁ እንደምትወዱ አውቀን የቀመርነው ነዋ!"

ስልኩን ዘግቼ የጓደኛዬን ክፍል በር በርግጄ ገባሁ •••
ገብቼ ሊሊዬ ያለችን ስነግረው ያ እንደሀምሌ ወር የፍቅር ደመና የጠቆረው ስሜቱ ፈጎ እንደመስከረም ፀሀይ አብራ።
ወድያው በድጋሚ ሊሊዬ ጋር ደውዬ በነገው ቀጦሮአችን ላይ ኬርያንም ይዛት እንድትመጣ ነገርኳት።
በንጋታው ተገናኝተን ሁሉም ነገር በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቀቀ። ሁለቱም አብረው ሆኑ።
አራታችንም የይንቨርስቲ መግቢያ ፈተና እስክንፈተን እና እስክንበታተን ድረስ ሁለት አመታትን አስደሳች የፍቅር ግዜ በዛው ትምህርት ቤታችን ውስጥ አሳለፍን ።
የማትሪክ ውጤት እኔ ሊሊዬ እና ስናመጣ ኬርያ አልተሳካላትም
እኔ አዳማ ዩንቨርስቲ ስመደብ ሊሊዬ ድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ ደረሳት ቢሆንም አባቷ ከአጠገቡ ርቃ እንድትሄድ ስላልፈለገ ውጪ ሀገር ልኮ እንደሚያስተምራት ቃል ገብቶ አስቀራት። ጋደኛዬ ጅማ ዩንቨርስቲ ደረሰው ። በተመደበልን ግዜ እኔ ወደ አዳማ እሱ ወደ ጅማ ተጓዝን ።
ፍቅራችን ካለበት ሞቅታ ሳይቀዘቅዝ ጭራሽ መነፋፈቅ እያጋለው ቀጠለ።
ዩንቨርስቲ ገብተን ስድስት ወር ሳንማር አለምን ባስጨነቀው ባዲሱ ወረርሽኝ በኮሮና ምክንያት ሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ዩንቨርስቲዎች ተዘግተው ወደየቤታችን እንድንሄድ ተደረገ።
ሊሊዬ ያደገችበት ቤተሰብ እና እኔ ያደኩበት ቤተሰብ ለየቅል ነው ።
በዚህ ምክንያት ፍቅር ሀ ብለን ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ የማይዋጥላት ነገር አባቴን አብዝቼ መፍራቴ ነው። ባትረዳኝ አልፈርድባትም። አሁን ከዩንቨርስቲ እቤት ተቀመጡ ተብለን ከመጣን በሳምንቱ ደውላ
"እኔ ዝም ብሎ በስልክ ብቻ አንተን እያገኙ መኖር ከበደኝ ሶልዬ ሳምንት ሆነን እኮ እዚሁ አንድ ከተማ ውስጥ ሆነን ሳምንት ሙሉ አለመገናኘት ምን ማለት እንደሆነ አስበከዋል ቆይ አልናፍቅህም ግን ?
" ኧረ ሊሊዬ በርግጠኝነት የኔን ያህል አትናፍቂም ግን ምን ላድርግ ያባዬን ባህሪ ታውቂው የለ እንኳን ወረርሽኝ ገባ ከቤት አትውጡ ብሎ መንግስት አውጆለት ድሮም ቢሆን መች ያለ ምክንያት መዞር ይፈቀድልኛል?
"ሶልዬ እኔ ጋር መምጣት በቂ ምክንያት ነው ከዚህ በላይ ምን ምክንያት አለ ደሞ ልዙር ፍቀድልኝ በላቸው መች አልኩህ እንገናኝ ልትለኝ ካልሆነ እንዳትደውልልኝ አኩርፌሀለሁ በቃ በቃ የምሬን ነው! "
ሊሊዬ እንዲህ ነች ተናግራ ነው እምታኮርፈው።
እውነቷን ነው ናዝሬት ትምህርት ላይ በነበርኩበት ባለፉት ወራት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ እንገናኝ ነበር ።
የምሯን እንደሆነ እንደተናደደችብኝ አውቃለሁ ግን ምን ላድርግ ።
አባዬ እንደሆነ ድሮም ድሮ ነው እሄ ወረርሽኝ ሀገራችን ገባ ከተባለበት ግዜ ጀምሮ መንግስት ብቻ ሳይሆን አባዬም ቤቱን ወደ ቤተሰብ ለይቶ ማቆያ የቀየረው እስኪመስለን ድረስ እኔም እህቴም እናቴም እንኳን ወደ ውጪ ልንወጣ የውጪ በር ሲንኳኳ እንኳን እንድንከፍት አይፈቀድልንም።
አባዬ ከቁጥጥሩም ባልተናነሰ ለኛ ለልጆቹ ያለው ፍቅር እስከጥግ ነበርና ቁጥጥሩ በፍቅሩ ስለሚጣፋ በጭራሽ ላስቀይመው አልፈልግም በኔ አዝኖ ከማየው ሞቴን እምመርጥ ይመስለኛል ።
መቆጣት ሲኖርብት የሚቆጣ ፍቅር መመገብ ሲኖርበት ፍቅሩን ሳይሰስት ለልጆቹ የሚመግብ አባት ነው አባቴ በቁጣው በቁጥጥሩ ውስጤ ሲነድ በፍቅሩ ዝናብ እያጠበ ያበርደኛል።
የተመጣጠነ ምግብ ብቻ ሳይሆን የተመጣጠነ ባህሪ መግቦ ነው ያሳደገን።
ምንም ብለው ስለማይፈቅድልኝ ሊሊዬን ሳልፈልግ ዝም አልኳት ። ስልክም አልደወልኩም ሶስት ቀን ሳንደዋወል ስንቆይ ጨነቀኝ ቢሆንም ቻልኩት።
አምስት ቀን ሞላን።
በአምስተኛው ቀን ልክ ከቀኑ በስምንት ሰአት አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ በፊት ተገናኝተን ደብረዘይት ሀዋሳ እየሄድን በምንዝናናበት ወቅት የተነሳናቸውን ፎቶዎች በተመስጦ እየተመለከትኩ ከፎቶው ጋር ሳወራ ድንገት የጮኸው ስልኬ አስደንግጦ ከሄድኩበት የትዝታ አለም ጎትቶ አወጣኝ።
ሊሊዬ ነበረች የደወለችው ።
የኔ ፍቅር በኔ እንደማይስችልሽ እኮ አውቃለሁ ግን ደናነሽልኝ ስላት •••
" አንተ ግን አስችሎህ ዘጋከኝ አደል ?" አልች ድምጿ ውስጥ መከፋታ ያስተጋባል ።
ምን ላድርግ ሊሊዬ አባዬን ከማስቀይመው ብዬ እኮ ነው
ልክ ነህ አባትህን ከምታስቀይመው እኔን ብታስቀይመኝ ይሻላል ተረዳሁህ
ይቅርታም አረኩልህ ግን ከነገወድያ ልደቴ ነው ልደቴ እንዴት እንደሚከበርልኝ ታውቃለህ የፈለገውን ያህል ቢከበርልኝ አንተ ከሌለህ ግን ምኑም ደስ እንደማይለኝም ታውቃለህ ታድያ ልደቴንም ልትቀር ነው ?
ስትለኝ መሀል አናቴን በዘነዘና የተረከኩት እስኪመስለኝ በቆሙኩበት ስንጥቅ አልኩ። አዋ ልደቷ እንዴት እንደሚከበርላት በደንብ አውቃለሁ ። ለሷ ልደት የሚወጣው ወጪ ሶስት መለስተኛ የድሀ ሰርግ ይሸፍናል ብል አልተጋነነም ።። ቀን የተጀመረ ሲበላ ሲጠጣ ተመሽቶ ማታ ለዚሁ ልደት በተዘገጀው ሌላ ክፍል ውስጥ በድጄው ልብ የሚሰውሩ ሙዚቃዎች ለጉድ ሲቀውጥ ሲጨፈር ይታደራል ።
ትልቁን የህይወት ፈተና እየተፈተንኩ መሰለኝ። ሊሊዬን ልደትሽ ላይ አልገኝም ብላት በተገኘሁበት ላትደርስ ምላ እንደምትለየኝ አልጠራጠርም።
አባዬ ደግሞ በዚህ ግዜ እንኳን ውሎ እና አዳር ልሂድ ልለው ከቤታችን ፊት ለፊት ካለው ሱቅ የሞባይል ካርድ ገዝቼ ልምጣ ስለው ቁጭ በል እኔ አመጣላሀለሁ ብሎ ያረጀች ቮልስ ዋገን መኪናውን እያስጮኸ ሄዶ ያመጣልኛል እንጂ ገዝተህ ና ብሎ እንደማይፈቅድልኝ አውቃለሁ።
ኮሮና ብሎ የተረገመ በሽታ መጥቶ ገና አንድ ወር ሳይሆነው ሂወቴን ፈተና አደረጋት ።
ሊሊዬ በዚህ ሰአት ልክ አምና እንዳከበርሽው ያ ሁሉ ሰው ተጠርቶ ሊከበር ነው ማለቴ ለሊት ጭፈራ ምናምን እኮ በዚህ ግዜ ስል ገና ካፌ ቀብል አድርጋ•••
"ቲቭው ላይ ሰልችቶን ያጠፋነውን በአስቸኳይ በአስገዳጅ የሚሉት አዋጅ የተከለከሉትን ምናምን አንተም ልደግምልኝ ነው ሶል
ደሞ ብዙ ሰው የሚመጣ አይመስለኝም የማታው የጭፈራ ብሮግራም ግን የማይቀር ነው!"
ቲቪውን ከምታጠፉት በሽታውን ባጠፋችሁት ይሻል ነበር እያልኩ ስልጎሞጎም
"ምን አልከኝ ?"አለችኝ ።
አይ ምንም !
"እሺ ትመጣለህ አትመጣም?
መምጣት መጣለሁ ግን ቀን አልመጣም ተረጅኝ ሊሊዬ እኛ ቤት እራት በግዜ ሁለት ሰአት አከባቢ ሁላችንም አብረን ስለምንበላ የግድ እራት ላይ መገኘት አለብኝ ከዛ ክፍሌ ውስጥ ገብቼ የተኛሁ በማስመሰል የበሩን ቁልፍ ሰርቄም ቢሆን ውጥቼ ለመምጣት እሞክራለሁ። አልኳት ደርሶ ሊሂድ አልሂድ ባላውቅም እንደዛ ከማለት ውጪ አማራጭ አልነበተኝም።
"እሺ ይሁን የኔ ፍቅር ፍቅር እኮ ነህ ዋናው መምጣትህ ነው ግን እሞክራለሁ ሳይሆን እመጣለሁ ነው የሚባለው ኪኪኪኪ ደሞ ልትወጣ ቢያንስ ሀያ ደቂቃ ሲቀርህ ደውልልኝ ዳጊን እልከውና ይዞህ ይመጣል እሺ?"
እሺ አልኳት። ዳጊ ሹፌራቸው ነው። ተስነባበትን።ሁለቱን ቀናት እማዬ•••
"ልጄ ትናንት እና ዛሬ በአካል እዚህ ከኛው ጋር ቁጭ ብለህ በሀሳብ ብን ብለህ ስትጠፋ እያስተዋልኩ ነው ምንድን ነው እሱ ምን ሆነሀል?"
ብላ እስክትጠይቀኝ ድረስ በጭንቀት አሳለፍኳቸው የሊሊ ቤተሰቦች ስራቸው በሙሉ ከውጪ ሀገር ጉዞ ጋር የተያያዘ ነው ወንድማ ዱባይና ሳውዲ እየሄደ እቃ ያመጣል አጎቷ አባቷ ከንግድ ስራቸው ጋር በተያያዘ ውጪ

👍1
#በኔ_የደረሰ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በጥላሁን
በድንጋጤ ከደረጃው ላይ ቁልቁል ልፈጠፈጥ ምን ቀረኝ በደንብ አየሁት አጎቷ ነው ጉሉኮስ ተደርጎለታል
እንዴ ምን ሆኖ ነው ያ አጎታችሁ ነው አደል ስላት እህቷን
"አዎ ባክህ በቅርቡ ነው ከውጪ የመጣው መጥቶ ትንሽ እንደቆየ ታመመ!"
ታድያ ሀኪም ቤት አልወሰዳችሁትም ?
"ምን ለውጥ አለው ባክህ እዛም ቢሄድ ዶክተር ነው እሚያየው !
እዚህ ድረስ እየመጣ የሚያየው የቤተሰብ ዶክተር አለ!"
እያለችኝ ያጎታቸውን ሳል ሰማሁት ድንብርብሬ እንደወጣ በድን ሆኜ እነ ሊሊ ወዳሉበት ክፍል ስገባ ቤቱ ከጥግ እስከ ጥግ ጢም ብሏል።
ፊትህን አዙረህ እሩጥ እሩጥ እለኝ•••
ገና ብቅ ስል ያየችኝ ሊሊ እየተርገበገበች መጥታ ተጠመጠመችብኝ ብዙ ሰው አይመጣም ብላኝ አልነበር እንዴ እያልኩ በሀሳብ ቢዥታ ውስጥ ሆኜ እኔም አቀፍኳት የሷስ ይሁን ከታዳሚው ተገንጥለው አብረዋት የነበሩ አራት ጓደኛቿ በየተራ "ሰላም ነህ?" ቅብርጥሶ እያሉ በጉንጮቻቸው ጉንጬን ደበደቡት "አትሳሳሙ" የሚለው ማስታወቂያ ትዝ አለኝ ወደ ቤት ከመጣሁና ባባዬ ቁጥጥር ስር ከዋልኩ ወድሂ የመጀሚሪያውን የአትሳሳሙ ህግ ለመጀመሪያ ግዜ ጣስኩ።
በተለይ መጨረሻ ላይ የሳመችኝ የምግብ ብዛት እና አይነቱ እየዘጋት እህል በልታ የማታውቅ የምትመስለው ቅጭጭ ያለች ቀጫጫ ልጅ የፀጉር አሰራራ ነው መሰለኝ እሱን እንድትመስለኝ ያደረገኝ ብቻ የጉንጫ አጥንት ጉንጬን ሲወጋው እራሱ ኮረና ዛሬ አታመልጠኝም አገኘሁህ ያለኝ ነው የመሰለኝ።
ኪሴ ውስጥ ያለችውን በትንሽ ብልቃጥ የያዝኳትን ሳኒታይዘር አውጥቼ እጄን ሳይሆን ፊቴን ልታጠብበት ፈለኩ። ለካ ለእጅ እንጂ ለፊት አይሆንም። ቢሆን ኖሮስ ቤት በኩል ልታጠብ
እንኳን ለመታጠቢያ ለመተንፈሻም ግዜ ሳይሰጡኝ
ሊሊ እና ጓደኞቿ መሀላቸው አስገብተው እያዋከቡ እቤት ውስጥ ወዳሉት ታዳሚዎች መሀል ወሰዱኝ።
እነዛ እቤታቸው ግርግዳ ላይ አንዲት በረሮ ቢያዩ እርርርይ እያሉ ቤቱን ጥለው የሚጠፉ የሀብታም ልጆች ኮሮናን አይፈሩትም ብቻ ሳይሆን ትዝም አይላቸውም ማለት ነው ብዬ እራሴን ጠየኩ ሌላ ማንን እጠይቃለሁ ብጠይቅስ ማን ይመልስልኛል?።
ሁሉንም ሳያቸው ሀገራችንን ጨምሮ በአለም ዙርያ ስለዚህ በሽታ በሚድያ የሚለፈፈውን የሚስበው የኛ ቴሌቭዥን እና ዲሽ ብቻ ነው እንዴ አልኩ።የሚያዳምጠውም የሚያየውም አባዬ ብቻ መስሎ ተሰማኝ።
ጭራሽ ሊሊዬን ሞቀኝ ወደ በሩ አከባቢ ብንሆንስ ብዬ ስጠይቃት የሰመችው ያቺ ኮሮና ስጋ ለብሶ መስላ የታየችኝ ቀጭኗ ልጅ ያጋመሰችውን ቢራ ወደ አፌ እያስጠጋች •••
"እንካ ጎንጨት በልበትና ሞቅ ይበልህ ሞቅ ሲልህ የቤቱ ሙቀት አይታወቅህም ክክክክክክ" አለች። ተከትለዋት ሁሉም ሳቁ ። እኔ እንኳን የምስቅበት የማገጥበትም ጥርስ አልነበረኝም።
አመሰግናለሁ ግን አልጠጣም ብዬ ቢራዋን ከነጇ ከአፌ አከበቢ ገፋ አደረኩት።
ጓደኛዬንና ፍቅረኛውን ከሩቅ አየኋቸው እራሳቸውን አያውቁም በራሳቸው አለም ርቀው ሄደዋል ሊሊዮዬን ጠጋ አልኩና በድጋሚ •••
ስገባ አጎትሽን አየሁት ልበል? አሞታል እንዴ ሊሊዬ? ለምን አልነገርሽኝም እንዳስተዋወቅሽኝ ረስተሽው ነው። መጥቼ እጠይቀው ነበርኮ ።
ዘንድሮ በሽትኛ መጠየቅ ቀርቷል እኮ አልሰማህም እንዴ ኧረ በክህ በልደቷ ቀን ጓደኛዬን ስለበሽታ ስለጥየቃ ምናምን ማውራቱን ተውና ዘና በል " አለችኝ። አሁንም ያችው ልጅ። ወይ ጣጣ ልጅቷ ሊሊ በፊርማዋ አረጋግጣ ውክልና የሰጠቻት ነው እምትመስለው ገና ሊሊን ማናገር ስጀምር ወሬዬን ሳልጨርስ እሷ መልስ እየሰጠች አላስወራ አለችኝ።
ከዛ ቡሀላ አንዳች የሚገላግል ነገር ከዛች ልጅ ካልገላገለኝ በቀር ላለማውራት ወሰንኩ።
ሊሊዬ ከዛም ከዛም እየጠሯት ውክብክብ ስላለች ፍቴን ማየትና መረዳት እንኳን አልቻለችም ነበር።ሁለተኛውን ህግ ጥሻለሁ ርቀቴን ሳልጠብቅ በብዙ የሊሊ ልደት ተጋባዦች መሀል ሆኜ ድንገት ወጥመድ ውስጥ ገብታ መውጫ እንዳጣች ጦጣ ግራ ተጋብቼ ግራ እና ቀኝ ስቁለጨለጭ ቆየሁና በሚጠጡ ፣በሚደንሱ፣ በሚሳሳሙ፣ በሚተሸሹ ሰዎች መሀል ሆኖ በተጨነቀ ፊት መቆየት ከባድ ሆነብኝ።
ይለይለት ብዬ ይሁን ይለይልኝ ብቻ ከቢራውም ከውስኪውም ከወይኑም ቀላቅዬ ስጠጣ ፍርሀት እና ደስታ የተቀላቀለበት ስካር ሰከርኩ።
መጠጡ በላይ በላይ ሲመጣ ፍርሀቱ ጠፍቶ ጊዛዊው ጀግንነት መጣ ድፍረቴ ጨቅ አለ።
ባንድ ግዜ እንደማያ ተለዋውጬላችሁ ቁጭ አልኩ።ኧረ የምናባቱ ኮሮና ሺ አመት አይኖር ሙዚቃውን ከፍ አድርገው ዲጄው ምንድን ነው ለቅሶ ቤት አስመሰለው እኮ ሊሊዬ ዲጄውን ከሰልስት ላይ ነው እንዴ አስነስታችሁ ያመጣችሁት ኬኬኬኬኬኬኬኬ"
እሷም ተከትላኝ
" ኪኪኪኪኪኪኪኪ እሄንን ሶል ነው ስፈልገው የነበረው!" ሊሊም ጓደኞቻም ሳቁ።
ቤቱ አልበቃ አለኝ ከላይ የለበስኩትን ጃኬት አውልቄ ጣልኩት።
ተቀላቀልኩ ፣ ጨፈርኩ ፣ዘለልኩ፣ እየተቀባበልኩ ጠጣሁ፣ ከሊሊዬ ጋር በየደቂቃው መሳሳም፣ መደነስ እስኪደክመን ከጓደኛቿም ጋር ተራ በተራ ጨፈርን አበድን ፣ ከነፍን በረርን ፣
እነሱ የረሱትን ሁሉ ረሳሁ። እነሱ የናቁትን ሁሉ ናቅሁ! እነሱ የሆንኩትን ሁሉ ሆንኩ።
ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ሲሆን አባዬ ትዝ ብሎኝ ወደቤቴ ካልሸኘሽኝ ብዬ ቤቱን ባንድ እግሩ አቆምኩት በወሰደኝ መኪና ተመልሼ ልክ ግቢያችን በር ላይ ስደርስ ስካሬ ብን ብሎ ጠፋ።
ሹክክ ብዬ እንደወጣሁት ሹክክ ብዬ በመግባት ተጠቀለልኩ።
አይነጋ የለ ነጋ ። ጥዋት 2:30 አከባቢ እማዬ የክፍሌን በር አንኳክታ ሰለሞኔ ተነስ ቁርስ ቀርቧል እየጠበቅንህ ነው ስትለኝ ።መብረቅ ክፍሌ ላይ የወረደባት ይመስል ክው አልኩላችሁ።
ለካ እሄም አለ አሁን እኔ ለሊት እዛ ሁሉ ጉድ ውስጥ አሸሸ ገዳሜ ስል አድሬ እንዴት ነው ከሽማግሌው አባቴና ከአረጊቷ እናቴ ጋር መአድ ባንድ ላይ ቀርቤ እምበላው ?

👏1
#በኔ_የደረሰ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት (የመጨረሻው ክፍል)

ለካ እሄም አለ አሁን እኔ ለሊት እዛ ሁሉ ጉድ ውስጥ አሸሸ ገዳሜ ስል አድሬ እንዴት ነው ከሽማግሌው አባቴና ከአረጊቷ እናቴ ጋር መአድ ባንድ ላይ ቀርቤ እምበላው ••••
እምለው እማረገው ሁሉ ጨነቀኝ ቀና ብዬ እዛው አልጋዬ ላይ ቁጭ አልኩና ሁለቱን እጄቼን ወደ ፊት ዘርግቼ እያየኋቸው •••
ማታ እንዳልተለከፍኩ በምን እርግጠኛ ነኝ እራሴን ጠየኩት?
በምንም ደሞ ጉሮሮህ አከባቢ ህመም እየተሰማህ ነው ይዞህ ይሆን እንዴ ? አለኝ ውስጤ
ጉሮሮዬ እንኳን ማታ ብዙ አይነት መጠጥ እየቀላቀልኩ ስለጠጣሁ ሊሆን ይችላል ያመመኝ ።
ላይሆንም ይችላል በሽታውም አንዱ ምልክቱ እንደዛ ነው?
እስቲ አስበው በዚህ እጅህ ስንቱን ነገር ነክተሀል፣ ከስንቱ ጋር ተጎራርሰህ በልተሀል ፣ከስንቱ ጋር እየተቀባበልክ ጠጥተሀል ፣ ስንቱ የተቀባበለውን ቢራ መክፈቻ ተጠቅመሀል
ውስጤ ሌላ ሰው ተቀምጦ የሚያስፈራራኝ መሰለኝ በሁለት ሀሳብ ተከፍዬ ከራሴ ጋር ስከራከር እራሴን አመመኝ።
አንድ ሰው የማንፈልገውን ወይም የሚረብሸንን ወሬ ቢያወራብን ዝም እንዲል አልያም ወሬ እንዲቀይር እንነግረዋለን ካልሆነ ካጠገቡ ተነስተን እንሄዳለን ከሚድያ ላይ የሚወራውን መስማት ካልፈለግን ተነስተን እንጠረቅመዋለን።
ከደጅ የሚመጣን ጩኸት መስማት ካልፈለግን ጆሮአችንን እንይዛለን
ከውስጣችን የሚመጣውን ጩከት መስማት ባንፈልግ ምናችንን እንይዘዋለን ወዴትስ እንሸሻለን?
እማዬ ድጋሚ የክፍሌን በር አንኳኩታ "ኧረ አባትህ እየጠበቀህ ነው ሰለሞኔ ቁርስ ቀርቧል እኮ!" አለችኝ።
ወጥቼ ሻወር ቤት ገባሁና ከሰዉነቴ ክፍሎች ሁሉ እጄን ደጋግሜ ታጠብኩት።
"ውስጥህንስ በምን ታጥበዋለህ ይዞህ ከሆነ በትንፋሽም እኮ ይተላለፋል አለኝ ከበሽታው በላይ ውጋት የሆነብኝ የውጤ ሀሳብ ነው።
እናባዬ ወዳሉበት ሳሎን ገባሁ ። ግን ሳልጠገቸው ፈንጠር ብዬ ብቻዬን ተቀመጥኩ።
"ዛሬ ምን ሆኗል ልጄ ና እንጂ ቁርስ እንብላ አንተን አይደለም እንዴ የምንጠብቀው" አለ አባዬ።
አይ አይሆንም አባ ካሁን ቡሀላ እሄ ክፉ በሽታ ከሀገራችን ተጠራርጎ እስኪወጣ ምግብም ቢሆን አብረን ለመብላት ስንል መቀራረብ የለብንም ። ለብቻዬ ብታቀርብልኝ ይሻላል አይሻልም አባ? ስል•••
እማ ጣልቃ ገብታ " አበስኩ ገበርኩ የደጁን ይሁን ስል ልጆቼንም ከጉያዬ ሊያርቅብኝ ነው እሄ በሽታ ከመች ወዲህ ነው ልጄ መአድ ተነጣጥለን በልተን የምናውቀው መአድ በአንድ ላይ ቀርቦ መብላት ፍቅርን ያደረጃል ልጄ።
ደሞ በኛ መሀል ኬት ይመጣል ከቤት ወጥተን አናውቅ የምንፈልገውን እቃ እንኳን የባታችሁ ወንድም ነው ገዝቶ የሚያመጣልን እቃ ገዝቶ መጥቶ እንኳን በር ላይ አስቀምጠህ ሂድ እንጂ ግባ ብሎት አያውቅ አባታችሁ።
ዛሬ ድንገት ተነስተህ ለብቻዬ አቅርቡልኝ ማለቱን ምን አመጣው ጥሩ ህልም አላየህም ልጄ እስቲ ንገረኝ?" ብላ ዝም ብዬ ሳያት እኔን ትታ ወደአባዬ ፍቷን መለሰችና
"፣እሄው ልጆቼን የፀሀይ ብርሀን እስኪናፍቃቸው ድረስ አላላውስ ብለህ ተጭነህ ስታስጨንቃቸው በጭንቀት ብዛት የልጄን አይምሮ እንዲቃወስ አድርገከው አረፍክ " ብላ ስታፈጥበት
ደና ነኝ እማዬ ምንም የሆንኩት ነገር የለም አባንም እንደዛ ማለት የለብሽም አባ ልክ ነው ። በቃ ተራራቁ ተብሏል እንራራቅ ነው ያልኩት ቀለል አርጋችሁ እዩትና እሺ በሉኝ እናንተ አንድ ላይ ብሉ ለኔ ለብቻዬ ስጪኝ። ስል እህቴ ከነበረችበት ተነስታ •••
"ባክህ የሌለ ነገር እያወራህ አታጨናንቃቸው ተነስና እንብላ!" እያለች እጄን ይዛ ልትጎትተኝ ነው መሰለኝ ወደኔ ስትጠጋ
ከተቀመጥኩበት ተፈናጥሬ በመነሳት እንዳትጠጊኝ እህቴ ነግሬሻለሁ እንዳትጠጊኝ በቃ ስል አባም ግራ ተጋብቶ ተነስቶ ሲቆም
ተጠግቶ ሳይዘኝ ቤቱን ጥየላቸው ብን ብዬ ልጠፋ አሰብኩና እናቴ ልጄ አበደ ብላ እራሷን ከማጥፋት እንደማትመለስ ሳስበው ፈራሁ።
አንተም እንዳትጠጋኝ አባ በቃ ተረዱኝ አትጠጉኝ አልኩ አትጠጉኝ እያልኩ ወደ ክፍሌ በመግባት ከውስጥ ዘጋሁት።
በስንት ውዝግብ አሳምኛቸው ምግብ መስኮት ላይ እየተደረገልኝ በልቼ አጥቤ እየመለስኩ ስምንት ቀን ሆነኝ ። በዘጠነኛው ቀን ጥዋት ጋደኛዬ ደውሎ
የነ ሊሊ ቤተሰቦች በሽተኛ እቤት ውስጥ መኖሩ ተጠቁሞባቸው ቤተሰቡን በሙሉ አፋፍሰው ካስገባቸው ቡሀላ በምርመራ ሌሎቹ የቤተሰብ አባላት ላይም ስለተገኘ ያን ቀን የሊሊ ልደት ላይ የተገኙት በሙሉ እየታደኑ ወደማቆያ እየተወሰዱ ነው አሉ እኛ ጋም መምጣታቸው አይቀርም አልቆልናል ሶል!"
ሲለኝ እኔ እዛው በተኛሁበት አለቀልኝ ። የተኛሁበት በላብ ሲዘፈቅ ትዝ ይለኛል ካልጋዬ ላይ መነሳት አቃተኝ ካንድ ቀን ቡሀላ ብንን ስል መስኮት ላይ ያስቀመጡትን ምግብ ወስጄ አለመብላቴ ያስጨነቃቸው ቤተሰቦቼ እህቴን በመስኮት አዘልለው በማስገባትና ከውስጥ እንድትከፍት በማረግ አልጋዬ ላይ ዙሪያዬን ከበውኝ እስክነቃ በጭንቀት ሲጠባበቁ ተመለከትኩ ። በሂወቴ እንደዛች ቅፅበት መሪር ሀዘን እና የነብሰ ገዳይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ። እርርይ አልኩ።
በንጋታው ሁላችንንም ወደ ማቆያ ወሰዱን ከቀናት ቡሀላ የምርመራ ውጤቱ ሁላችንም እንዳለብን አመለከተ።
ውጤቱን ስሰማ በተለይ ቤተሰቦቼን በመሉ ማስያዜን ስሰማ ድጋሚ እራሴን ሳትኩ ከሳምንታት ቡሀላ ወደራሴ ስመለስ እና ስነቃ እቤታችን ውስጥ ነኝ።
ሶስታችን አገገምን አባዬ ግን ከመሀላችን
ጎድሏል ።
በነበረበት ስኳር እና ሌላ ተጓዳኝ ህመም ምክንያት በሽታውን መቋቋም አቅቶት በሀገራችን በዚህ በሽታ ከሞቱት ሰዎች መሀል አንዱ ሆነ ።
ይህ ሁሉ በኔ ነው በኔ የደረሰ በማንም አይድረስ!!
💫ተፈፀመ💫
እስቲ ሁላችሁም ይቺን ፅሁፍ በዚች ደቂቃ እያነበባችሁ ያላችሁ #ኮረና የመጣ ጊዜ #ጥንቃቂያችሁ እንዴት ነበር❓❓#አሁንስ❓❓ መልሱን ለራሳችሁ
ግን አሁንም በሽታው ምንም የተቀየረ ነገር የለም መድሃኒት አልተገኘለትም አሁንም የኛ ብቻ ሳይሆን የአለም ስጋት ነው። በየቤታችን እስኪገባ አንጠብቅ እናም ይሄ ታሪክ አንድ ሰው ያስተምራልና #Share እያደረጋቹ።
🛑አሁንም ግን🛑
#እርቀታችንን_እንጠብቅ
#ማክስ_በአግባቡ_እናድርግ
#እጃችንን_በአግባቡ_እንታጠብ
#ከቻልን_ቤት_እንቆይ #ውዶቼ