አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቅበላ


#ክፍል_አንድ


#ከአዶኒስ

በደብዛዛ ቀይ ብርሃን በተሞላችው ባለ አንድ ክፍል ቤቷ ውስጥ ወደ በሩ ጠጋ ብላ ተቀምጣ ውጭ ውጭውን ታያለች፡፡ ቅዝዝ ያሉ ዐይኖቿን ጨለማው ላይ የሰካች ቢሆንም ምንም ነገር የምታይ አትመስልም።ቀያይ ጭኖቿ ለሚተላለፈዉ መንገደኛ በቅጡ እንዲታዩላት ባለስንጥቅ ቀሚሷን ሆነ ብላ ገለጥለጥ
አድርጋዋለች።አልፎ አልፎ በውል የማይሰሙ ቃላት እያጉተመተመች ከንፈሯን ትመጥጣለች:: ድንገት
ስትታይ ጠና ያለች ሴት ብትመስልም ልብ ብሉይ ላስተዋላት ከሰላሳ አምስት እስከ አርባ ባሉት የዕድሜ አንጓዎች መሃል እንደምትገኝ መገመት አያዳግትም፡፡
ፀዳል ትባላለች።

ከፀዳል በር በስተግራም በስተቀኝም በርካታ ተመሳሳይ በሮች በመደዳው ይታያሉ:: እያንዳንዱ ቤት ምን ያህል ጠባብ እንደሆነ ከበሮቹ መቀራረብ መገመት ይቻላል፡፡ በየቤቱ የተለያዩ ቀለማት ያላቸው አምፖሎች በርተዋል፡፡ ከአንዳንዱ ቤት የሚወጣው ደመና መሰል የጊርጊራ ጢስ መጀመሪያ የቤቱን የመብራት ቀለም እንደያዘ በራፉ ላይ ቡልቅ ይልና ወዲያው ደግሞ ጭለማው ውስጥ ክስም ይላል።

አለፍ አለፍ ብለው ጥቂት የተዘጉ በሮች ይታያሉ፡፡እነኚህ ታዲያ ከውጪ የተቆለፉ ሳይሆኑ ምሽቱ የቀናቸው ባለቤቶቻቸው ለጊዜው ከውስጥ የቀረቀሯቸው
ናቸው:: ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይከፈቱና የተቀሩትን በሮች ይመስላሉ፡: ባለቤቶቻቸውም ልክ ምንም ያልተፈጠረ ዓይነት ምሽቱ ላይ እንደገና ያፈጡበታል፡፡

እዚህ ቦታ እያንዳንዱ ምሽት ለእያንዳንዷ ሴት አዲስ ነው። ትናንት እንዲህ ነበረና ዛሬ እንዲህ ይሆናል ብሎ መገመት አይቻልም:: ዛሬ ሶስት አራት ደንበኞች
ያስተናገደች ሴት ነገ አንድም ላይቀናት ይችላል።ገበያ የሸሻቸው ዕለት ሴቶቹ የማይጠረጥሩት ነገር የለም።ቢሆንም ባይሆንም በሚል የተለያዩ ሙከራዎችን
ያደርጋሉ:: አለባበስ ይቀይራሉ - ልዩ ልዩ ነገሮች በውሃ እየበጠበጠ ደጃፋቸውን ይረጫሉ የጊርጊራቸውን ጭሳጭስ እየቀያየሩ ይሞክራሉ የተረጩትን ሽቶ
በገደቢስነት ይጠረጥሩና ሌላ ሽቶ ይረጫሉ - የፀጉር አሰራራቸውን ይቀይራሉ - ብቻ የዕለቱ “ቋጠሮ” ይፈታ
ዘንድ የመሰላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡

ዛሬ ከሁለት ወር በኋላ የሚፈታው አቢይ ፆም የሚያዝበት የቅበላ ምሽት ነው:: እናም ፀዳል ወዲህም ወዲያም ብላ ቢያንስ ግማሽ ኪሎ ሥጋ - ይህም አልሆን ካለ የሁለት የሶስት ብር ቅንጥብጣቢ መግዛት መቻል አለበት።
ባጣ ባጣ አንድ ደንበኛ አላጣም በሚል
ተስፋ ወዲያውም በግራና ቀኝ ያሉ ባላንጣዎቿ “አጣች ብለው ደስ እንዳይላቸው” በማለት - ሽንኩርቷን
ስትከታትፍና ስታቁላላ ነው ያመሸችው::

__የፓርላማው ሰዓት የአራት ሰዓቱን ደወል አሰማ::ፀዳል እንደመገረምም እንደመቁ ነጥነጥም አለች::
በባለላስቲክ ጨርቅ ወደላይ ሰብሰባ አስይዛው የነበረውን ፀጉራን የመመንጨቅ ዓይነት ፈታችና ወደ ታች
እየነሰነሰች ማስተካከል ጀመረች።

በስተቀኝ ካለችው የሥራ ባላንጣዋ ቤት እየመጣ ፀዳልን ሲረብሻት የቆየው ቅቤ የጠገበ የረጋ ወጥ ሽታ ጭራሹን እየገነነ መጣ፡፡ ፀዳል መጥፎ ጠረን እንደሽተታት
ሁሉ በአውራ ጣቷና በሌባ ጣቷ አፍንጫዋን ጨመቅ ጨመቅ አደረገችና ከአንገቷ ብቻ ወደ ውስጥ ዘወር ብላ
ግድግዳው ጥግ ካለችው የኬሮሲን ምድጃዋ ላይ አንድ አገር ሽንኩርት ከትፋ የጣደችበትን አነስተኛ የብረት ድስት
አየችው፡፡ ለአፍታ ያህል ወደ ውስጧ ፈገግ ብላ በራሷ ስትመፀት ቆየችና ድንገት በመርፌ ጠቅ ያደረጓት ይመስል
ነጠቅ ብላ በመነሳት ወደ ምድጃው አመራች:: ድስቱን አውርዳ ኬሮሲኑን አጠፋችና እጆቿን ደረቷ ላይ አጣምራ
ከወዲያ ወዲህ መንቆራጠጥ ጀመረች፡፡

“እንግዲህ ወይ እዛች ሜንጦ ጋ ደርስህ ትመጣ እንደሆን እንጂ አለች ለጣራ ግድግዳው የምታወራ ዓይነት።“አንዳንድ ቀን እኮ አያምጣው ነው::” ስትል አጉተመተመችና እንደገና ቦታዋን ይዛ ተቀመጠች።

በመንገዱ የሚያልፈውና የሚያገድመው ሰው ቁጥር እየሳሳ መጥቷል።ብዙም ሳይቆይ መሉ በመሉ ጥምብዝ ማለታቸው በግልፅ የሚታይባቸው አንድ አዛውንተ መላ ቅጡ በጠፋ አረማመድ እየተውተረተሩ በማለፍ ላይ ሳሉ ከፀዳል በራፍ ሲደርሱ ቆም አሉና
ነፋስ እንዳየለበት ለጋ ተክል እየተወዛወዘ ትክ ብለው ያዩዋት ጀመር፡፡ ፀዳል ስንጥቁን ቀሚሷን ከወትሮው በተለየ ግልጥልጥ አድርጋ ጭኖቿን እያሳየቻቸውና ይበልጥ ይስቧቸው ይሆናል ብላ የገመተቻቸውን
ተጨማሪ “እንቁልልጮች እያፈራረቀችባቸው ወጥመዷን ማጠባበቅ ጀመረች:: እጆቻቸውን ሱሪ
ኪሳቸው ውስጥ እንደከተቱ አዛውቱ- ለአፍታ ያህል ዐይኖቻቸውን በፀዳል የተጋለጠ ጭኖች ላይ ሲያንከባልሉ
ከቆዩ በኋላ ግንባራቸውን ቋጠር ፈታ ከንፈራቸውን ሸፈፍ ሸፈፍ አደረጉና ትከሻቸውን ሰብቀው እየተወላከፉ
መንገዳቸውን ቀጠሉ:: ዐዳል ሁለመናዋን መልሳ በመጠኑ ሽከፍከፍ አደረገችና በመገረም ዓይነት እንደገና ከንፈሯን መጠጠች።

“አንተን አይደለም እንዴ ምለው? - እዛች መናጢ ጋ ደርሰህ ና ማለት አማርኛ አይደለም?” አለች ዐይኖቿን ከመንገዱ ላይ ሳትነቅል ወዲያው ከአልጋዋ ስር በደረቱ እየተሳበ አንድ እድሜው ከአስራ አምስት የማይበልጥ ልጅ ብቅ አሐ።

ምን ልበላት” ሲል ጠየቃት ከጀርባዋ ቆሞ ራሱን እያከከና እንደመንጠራራት እያለ።

ስትላት ካለሽ አስር ብር ካልሆነልሽ ደግሞ አምስትም ቢሆን ላኪልኝ ነገ ጠዋት ለቡና ስመጣ ይዤልሽ እመጣለሁ አደራ አደራ ጦም መያዣ አጥቼ ነውና የዛሬን ብቻ ቅበሪኝ ብላሻለች በላት አለችው፣ ዘወር ብላ እንኳን ሳታየው ዐይኖቿን መንገዱ ላይ እንዳቀዘዘች፡፡ “ደግሞ እንደ ዔሊ ስትጎተት ዓመት
ቆይተህ ና አሉ!
ማሙሽት ሙት አምስት ደቂቃ አሳልፍና እንተያያለን

ማሙሸት ልጇ ነው :: ገና ወጣት ሳለች በትዳር ከተቆራኘችውና ብዙም አብሯት ለመኖር ካልታደለው የሕግ ባለቤቷ ያፈራችው:: ማሙሸት ሁለተኛ ዓመቱን
እንኳን በቅጡ ሳያገባድድና አዲሱ ትዳርም ገና ሞቅ ሞቅ ሳይል ነበር የማመሸት አባት ወደ አፈርነቱ
የተመለሰው:: ሕይወተ ገና በጠዋቱ፡ በረቂቅ ጥፊዋ ያስደነገጠቻት ፀዳል ባለቤቷ ትቶላት ባለፈው አነስተኛ
ጥሪት ጥቂት ጊዜ ስትንገታገት ቆየች:: ቀሪ ሀብቴ የምትለውና መማያዋም መገዘቻዋም የሆነው ማሙሸትም
ትምህርት ጀምሮ አንድ ሁለት ክፍል ቆጠረ:: የአባቱ በሕይወት ያለመኖር ልጇ ላይ ሊፈጥርበት የሚችለውን
ክፍተት ለማጥበብ ፀዳል የአቅሟን ሁሉ ጣረች።በሕይወት እስካለች ድረስም ማሙሸት ቢያንስ መሰረታዊ
የሚባሉት ነገሮች ሲያጥሩት ላለማየት ለራሷ ቃል ገባች፡፡

ይሁን እንጂ ነገሮች እንደግምቷ አልሄዱም። ዕለት ተዕለት ማጣፊያው እያጠራት መጣ፡፡ ይሄኔ ነበር
እንደመጨረሻ አማራጭ ሴትኛ ለማደር የቆረጠችው።ታዲያ ይህም ቢሆን እንደአጀማመሩ አልቀጠለም።
ከዓመት ዓመት ዝቅ እያለ የሚሄድ የሕይወት ቁልቁለት ሆነ። ፀዳ ፀዳ ባሉ ሆቴሎችና መዝናኛዎች የተጀመረው
የእንጀራ ገመዷ እየሰለሰለ በመምጣት እዚህ አሁን ካለበት ደረጃ ደረሰ። ያም ሆኖ የልጇ የማሙሸት ትምህርት
አንድም ጊዜ ተስተጓጉሉበት አያውቅም። ማሙሸት የሚያስፈልጉትን ነገሮች ያሟላች ከመሰላት ደግሞ ሌላ
የሚያሳስባት ነገር የለም። በተለይ አሁን አሁን ለዐዳል ሕይወት” ማለት ማሙሸት” ማለት ሆኗል።

በዚህ እንጀራ ከተሰማሩ የፀዳል ጎረቤቶች የተወሰነቱ እንደሷው ሁሉ ባለልጆች ናቸው:: ታዲያ በሥራው ፀባይ ምክንያት ልጆቻቸውን እንደሚፈልጉት
አድርገው ማሳደግ አይቻላቸውም:: ደንበኞቻቸውን የሚያስተናግዱት በአብዛኛው ከአመሻሹ እስከ እኩለ
ሌሊት ባለው ጊዜ ውስጥ በመሆኑ ይሄንን ጊዜ ልጆቹ ከየቤታቸው ውጪ ለማሳለፍ ይገደዳሉ። አንዱ ሎተሪ
ሲያዞር ያመሻል - ሌላው
👍1
#ቅበላ


#ክፍል_ሁለት


#ከአዶኒስ

እንደው በፈጠረሽ ልጅሽ አይደል እንዴ? "እንዴት ያን ሁሉ ጉድሽን እንዲሰማ ታደርጊያለሽ?"

ስትል ለመጀመሪያ ጊዜ ትጠይቃታለች የፀዳል ድርጊት
በእጅጉ ከዘገነናቸው መሰል ጎረቤቶቿ አንዷ፡፡ የተቀሩትም በየራሳቸው ጊዜ ይህንኑ ይጠይቋታል:: “እንደናንተ ልጆች ዱርዬ . ሌባ - መጨረሻው ከርቸሌ የሚሆን ወንጀለኛ ከሚሆንብኝ ጉዴን ቢሰማብኝ ይሻለኛል::” ትላቸዋለች
ደግሞስ ምኑ ላይ ነው ጉድነቱ?
የእናንተዎቹም እኮ አልጋችሁ ሥር ሆነው አልሰሙም አላዩም ማለት አያውቁም ማለት አይደለም::”

እንጀራችን አይደል እንዴ? ይህ አባባሏ ለፀዳል በቂ ምክንያት ያቀረበች መስሉ ይታያት እንጂ ለጎረቤቶቿ ጨርሶ
አይዋጥላቸውም:: በተለይ እሷ በሌለችበት ጉዳዩን ካነሱት እየተቀባበለ ሲያብጠለጥሏት ነዉ የሚመሸዉ
የሚነጋው:: ደግሞኮ ዱርዬ ከሚሆንብኝ ትላለች . ሞልቃቃ! ሆሆ......ይ! - የገዛ ልጄ ገበናዬን ከሚያይብኝ እንኳን ዱርዬ ለምን ሰው የሚበላ ጭራቅ አይሆንብኝም!”
አልጋ ሥር ተኝቶ የእናቱን ጉድ
ሲሰማ ማምሽት ልጅን ጨዋ የሚያደርግ ከሆነ እንግዲህ እናያለና - የኛ ዘበናይ - ከጎኗ ስታገኘው ልክ ትገባ የለ!” ትላለች ሌላዋ:: ሌላ ርዕስ እስኪገኝ “ዘበናይ”ቱን መላጥ መፈልፈሉ ይቀጥላል፡፡

ፀዳል ከወደመንገዱ የማመሸት ኮቴ እየቀረበ ሲመጣ ተሰማት፡፡ እንኳንስ ብቻውን ሆኖ በሚተላለፍ ግርግር መሃልም የማሙሸትን ኮቴ መለየት ተስኗት
አያውቅም:: ሌላው ቀርቶ የላከችውን ነገር አግኝቶ ሲመጣና አጥቶ ሲመጣ እንኳን በአረማመዱ ታውቃለች::

“የለኝም አለችህ አይደል ይቺ የተረገመች ሜንጦ?” አለችው ገና ከመግባቱና የመልዕክቱን ቃላት በሆዱ እያረቀ ሳለ፡፡

“እምም እንዳለችሽ - " በማለት ጀመረ ፀጉሩን አከክ አከክ እያደረገ፡፡ “የኔ ቆንጆ የኔ ቆንጆ - ምናምኒት የለኝም - እንደውም እኔ ራሴ ትንሽ ካለሽ ብዬ አንቺጋ
ልመጣ ስል ነው የላክሺብኝ - እንግዲህ - ባይሆን ....

“ዝጋ!” እንደብራቅ ጮኻ አቋረጠችው:: “ወሬ ይዘህልኝ ና ብዬ ነው የላኩህ? አልሰጠችኝም ማለት አትችልም በአጭር አማርኛ? ዱሮስ ከዚች መናጢ
እጅ ገንዘብ ይወጣል ብዬ ሊያውም በዛሬው ቀን ! -ተወው እኔው ነኝ ጥፋተኛዋ::”

“ምን አስጨነቀሽ ግን ፀዲ?
አላት በአንድ እጁ ፀጉሯን በሌላኛው እጁ የገዛ ሆዱን እያሻሽ፡፡ “ሥጋ
ቢቀርስ? - ምንድነው ይሄን ያህል? ”::
“ እሱማ ቀርቷል ! - ወደህ ነው የሚቀረው? አለችው ውጪ ውጪውን እያየች፡፡

እኔ ምልህ -አንተ ስትደርስ ምን ምን
እያደረገች ነበር?

.....ምንም::”

“እንዴት “ምንም ? "

“በቃ - ቡና ተፈልቷል - ቄጤማ ምናምን ተጎዝጉዟል ፈንዲሻ ምናምን ... በቃ::”

“ሌላስ ?”

“ሌላ ቴፑ ተከፍቷል ... ሰንደል ይሁን እጣን ነገር ይጨሳል....በቃ::”

“ማሙሽት!” አለችው አሁንም ዐይኖቿን ከመንገዱ ላይ ሳትነቅል፡፡ “አርቲ ቡርቲውን ትተህ የጠየኩህን
መልስልኝ - እሷ ምን እያደረገች ነበር?”

“እሷ? . ምንም::”

“ንገረኝ ! ” አምባረቀችበት።

“እንትን - እንትን እያደረገች - ”

“ምን እያደረገች?”

"እም እንትን"

“ንገረኝ አንተ! ” አፉ አልላቀቅ ወዳለው ልጇ ዞራ አጉረጠረጠችበት።

“እ - እየ - እየከተፈች::”

“ምን እየከተፈች?

“እም....እ - እንትን::”
..
“ዋ ብቻ ዛሬ! ሰይጣኔን ባታመጣው ይሻልሃል! . "አለችው ብድግ ብላ ልታንቀው እየቃጣት:: “ምን
ድነው - እየከ - ተፈች የነ - በረው?”

“' ሥ. .” ጋ ።

መች አጣሁት! - ይቺ ከርሳም!” ፊቷን ወደ
መንገዱ መልሳ አንገቷን በትዝብት ወዘወዘችና ዐይኖቿን ድቅድቁ ላይ ተከለች:: በል አንተ ደግሞ እነዚህ
አትገተርብኝ::” ማለቷ ማሙሸት እንደሰለጠነ ውሻ ሸክክክ ብሎ አልጋዋ ስር ገባ።

“እኔ ምልህ አለች ለአፍታዎች ያህል
ስታሰላስል ከቆየች በኋላ:: ያ ጓደኛህስ? - ትንሽ እንኳን ሊያገኝልህ አይችልም? ከፊት ለፊቷ: ካለው ጭለማ እንጂ ከልጇ ጋር የምታወራ አትመስልም::
“እሱ ቢችልማ እስካሁን አስችሎኝ ዝም እልሽ ነበር? አላት ማሙሸት አልጋው ሥር እየተመቻቸ፡፡ይህ እናትና ልጅ የተግባቡበት ቋንቋ የሁለታቸው ብቻ
ሚስጥር ነው:: ያ ጓደኛህስ? " ስትለው ምን ማለቷ እንደሆነ ማሙሸት ገብቶታል
እሷም እንደሚገባው ታውቃለች:: ግን ፡ ማሙሸት ምንም ዓይነት ጓደኛ እንደሌለው እንኳንስ እናቱ እያንዳንዱ መንደርተኛ ያውቃል።

ከሰባት ዓመታት በፊት ማሙሸት ከእናቱ ጋር ወደዚህ ቦታ እንደመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ በእናቱ አልጋ ሥር ያሳለፈው ምሽት ቀሪ ዕድሜውን ሙሉ ሊረሳው የማይችለውና የስምንት ዓመት ጮርቃ
አዕምሮው ውሉ እንደጠፋ ጉልጉል ልቃቂት ዳግም ወደ ቀድሞ ሁኔታው
ላይመለስ የተዛባበት ነበር::

ያን ምሽት የመጀመሪያው የፀዳል እንግዳ እንደገባ ቀደም ብሎ አልጋው ጋር ቦታውን ይዞ የነበረው ማሙሸት እናቱ በሰጠችው መመሪያ መሰረት ትንፋሹን
ሳይቀር እየተቆጣጠረ ፀጥ ረጭ ብሎ መጠባበቅ እንደጀመረ ነበር ድንገት አንድ ጥያቄ ዉል ያለበት::
በእርግጥ ፀዳል በዚህ በአዲሱ ሥራዋ ለሁለታቸውም የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች የምታሟላበት ገንዘብ ልታገኝ
እንደምትችል አስቀድማ ነግራዋለች:: ይሁን እንጂ አሁንም ግልፅ ያልሆነለት ነገር አለ፡፡ ይህ የመጣው ሰውዬ በእርግጥ ከፀዳል የሚፈልገው ምንድነው? ምንስ ብታደርግለት ነው ገንዘብ ሊሰጣት የሚችለው? ለምንስ
ይሆን ወደሷ የሚመጡት እንግዶች ሁሉ ወንዶች እነደሚሆኑ የነገረችው?

ሕፃን ማሙሸት እነኚህን ጥያቄዎች እየፈተለና እያጠነጠነ ሳለ በሚሰማቸው ድምፅች ፀዳልም እንግዳውም ልብሶቻቸውን እያወላለቁ እንደሆነ ይረዳል።

አእምሮው ውስጥ እየተብላሉ ባሉት ጥያቄዎች ላይ ሌላ ጥያቄ ! ልብስ ማውለቅን ደግሞ ምን አመጣው?
ማሙሸት እስከሚያውቀው ድረስ ልብስ የሚወለቀው ገላ ለመታጠብ ወይ ደግሞ ለመተኛት ነው:: እና ውሃም ሆነ ዕቃ ስታዘጋጅ አላያትም:: ስለዚህ ገላቸውን
ሊታጠቡ ሊሆን አይችልም። አብረው ሊተኙ ነው ማለት ነው? ከሆነስ ሰውዬው
ከፀዳል ጋር ለመተኛት ሲል ብቻ ገንዘብ ይከፍላታል?

ከጥቂት አፍታዎች በኋላ የአልጋው ትዕይንት ይጀመርና ከበላዩ በሚሰማሁ ድምፅ ማሙሸት ጭራሹን ግራ ይጋባል። የትግል ዓይነት ድምፅ ይሰማዋል፡፡ሰውዬው ቁና ቁና ይተነፍሳል:: ፀዳል አልፎ አልፎ የማቃሰት ዓይነት ሕእ” ማለቷ በቀር ድምጿ ሰውየው ፀዳልን ምን እያደረጋት እንደሆነ ለመገመት ማሙሸት
የቱንም ያህል ጨቅላይቱ ናላወን ቢያዞራት ቢያሽከረክራት ይህ ነው የሚባል ስዕል አልመጣልህ ይለዋል፡፡ በደፈናው ግን በአንድ ነገር ላይ እርግጠኛ
ይሆናል ይህ ሰውየው ፀዳልን እያደረጋት ያለው ነገር ምንም ይሁን ምን በጭራሽ ፀዳል የምትፈልገው ነገር አይደለም:: ማሙሸት አንድ ከዚህ በፊት የማያውቀው
ዓይነት የፍርሃት ስሜት ይጫነዋል፡፡

ማሙሸት ከእናቱ ጋር የገባበትንና ገና ከጅምሩ ውንጅብጅብ የሆነበትን ይህን አዲስ ሕይወት ቀስ በቀስ ለመላመድ የወሰደበት ጊዜ ቀላል አልነበረም። ከዚህም በላይ በየምሽቱ፡ ለዚህ ምን እንደሆነ ሊገባው ላልቻለ እንቆቅልሽ ጉዳይ ከእናቱ ዘንድ የሚመጡት የተለያዩ
ወንዶች እናቱ ላይ የሚያደርሱባት የስጋም ሆነ የመንፈስ ጫና ጉዳያቸውን ጨርሰው ሲወጡ ከሚጥሉላት አራትና አምስት ብር ጋር ጨርሶ ተጣጥሞለት
ኢያውቅም።እናም - ለእነዚህ በድምፃቸው እንጂ በአካል ለማያውቃቸው የእናቱ እንግዶች ያለው አመለካከት በጥላቻና በበቀል ስሜት የተለወሰ ሆነ።

ከወራት በፊት አንድ አመሻሽቶ የመጣ የእናቱ እንግዳ ሱሪውን
👍2
#ቅበላ


#ክፍል_ሦስት


#ከአዶኒስ

...ውቃቢ እስኪርቀው የቁጣ መዓት ካወረደችበት በኋላ ዳግም
“እንዲህ ዓይነት ነገር” ሲያደርግ የሷና የሱ “መጨረሻ” እንደሚሆን አስጠንቅቃው ነበር ጭራውን ቆልፎ ወደ
ትምህርት ቤት የሄደው፡፡ ያም ሆኖ ማሙሸት ቢያንስ የአቅሚቲውን ያህል ለእናቱ ፍትህን ለመስጠት እንደሚያስችለው አጥብቆ ያመነበትን ይህን ነገር በቀላሉ ወደጎን ሊለው አልቻለም። ለእናቱ ማሳወቁን ብቻ
ይተውና ድርጊቱን ይቀጥላል፡፡ አጋጣሚው አመቺ መስሎ በታየው ጊዜ ሁሉ የእንግዶቹን ኪሶች መፈተሽና
እንደየሁኔታው አምስትም አሥርም እየመዘዘ በሚስጥር ማጠራቀም ይጀምራል፡፡

ማመሽት የእናቱን እንግዳዎች ኪስ ዘና ብሎ ለመፈተሽ የሚያስችለውን አስተማማኝ ስዓት ከልምድ አውቆታል፡፡ የዕለቱ እንግዳ የሆነው ሰው የመጣበትን
ጉዳይ ሊጨርስ አፍታዎች ሲቀሩትና አቅሉን ሙሉ በሙሉ ሊስት የሚያደርገውን ልጓም አልባ እንቅስቃሴና
የሚያወጣውን ያልተለመደ ዓይነት ድምጽ እንደሰማ ማሙሸት እጁን መሰስ አድርጎ በመላክ የሰውዬውን ኪሶች አንድ በአንድ ያብጠረጥርና የሚወስደውን ያህል ወስዶ የልብሶቹ አቀማመጥ ልክ እንደነበረው መሆነን ያረጋግጣል።

ታዲያ እናቱ በባሰባት በባሰባት ጊዜ ከአንድ የሃብታም ልጅ ከሆነና በየጊዜው
ከሚረዳው ጓደኛው አመጣሁ እያለ በዕለቱ ያስፈለጋትን ያህል ገንዘብ
ይሰጣታል።ለትምህርት ቤቱ የሚያስፈልገውን ወጪም ራሱ መሸፈን ከጀመረ ከራርሟል፡፡ የኋላ የኋላ ግን ፀዳል ሚስጥሩን ትደርስበታለች፡፡ ይሁን እንጂ ደጋግሞ ከጉድ ያወጣትንና አንድም እንግዳ ገንዘብ ጠፋኝ ብሎ አማርሮ የማያውቅበትን ይህን ረቂቅ የገንዘብ ምንጭ አጉል ነካክታ
ማድረቅ ርባናው አልታይ ይላታል፡፡ እንደውም ውሎ አድሮ ነገርየው እየጣማት ሲመጣ እንግዶቿ ልብሳቸውን
አውልቀው የሚያስቀምጡበትን ወንበር እንደዘበት ለማሙሽት በሚያመቸው ሁኔታ ወደ አልጋው ጠጋ ማድረግ ጀመረች ይህ ሁሉ ሲሆን እናትና ልጅ
ይህ ሁሉ ሲሆን እናትና ልጅ “ውሾን
ያነሳ ውሾ ይሁን” ዓይነት ስለጉዳዩ በይፋ ለመነጋገር ደፍረው አያውቁም:: ፀዳል ነገሩ እንደገባት ማሙሽት ያውቃል - እንደሚያውቅ እሷም ታውቃለች፡፡ ታዲያ
በሚቻላት ሁሉ ማሙሸት ራሱ አስቦ እስኪሰጣት ትጠብቃለች እንጂ አፍ አውጥታ አትጠይቀውም። አልፎ
አልፎ ሁሉ ነገር ጭልምልም ሲልባት ብቻ ምሬቷን ማጉተምተምና በትንሽ በትልቁ መነጫነጭ ትጀምራለች::
ይሄኔ የሁለታቸውን ብቸኛ ቋንቋ እያወራች እንዳለች የሚገባው ማሙሸት ወደ “ጓደኛው ይሄድና ገንዘብ ይዞላት ይመጣል።

ሰዓቱ ወደ እኩለ ሌሊቱ እየገፋ ሲሄድና የዕለቱ ተስፋዋ በእጅጉ እየተመናመነ ሳለ ነበር አንድ እንግዳ ድንገት ከጥቁሩ ሰማይ ዱብ እንዳለ መና ከበራፉ ገጭ ያለላት፡፡ እሷና ማመሽት ወጡ እንኳን ቢቀርባቸውቢያንስ ጥብስ ጠበስ አድርገው ጦማቸውን ለመያዝ በቂ ጊዜ እንዳላቸው ገመተችና በሆዷ ተመስገን አለች፡፡ሰውየው ከዚህ በፊት አንድ ሶስቴ ያስተናገደችው ሰው ነበረና ሞቅ ባለ ፈገግታ ተቀበለችው። በራፏ ላይ
እንደተቀመጠች አልፏት ወደ ውስጥ የዘለቀው ይህ እንግዳዋ ከአልጋዋ ጎን ካለው ብቸኛ ወንበር ላይ አረፍ አለ፡፡ ሞቅ ያለው ይመስላል:: ፀዳል ወዲያው ብድግ ብላ በሯን ቀረቀረችና ፀጉሯን በጣቶቿ እያፍተለተለች ዝግ ባለ አረማመድ ወደ እንግዳዋ በመቅረብ አልጋዋ ጫፍ ላይ ተቀመጠች::
"""
“ምነው ጠፋህ? አለችው ፈዘዝ ካለ ፈገግታ ጋር፡፡ ወደሷ ሲመጡ የመጀመሪያቸው ላልሆነ እንግዶች
ሁሉ እንደ ንግግር መክፈቻ የምትጠቀመው የተለመደ ጥያቄዋ ነው።
“እንዴት አልጠፋ ከዚህ ያልጠፋሁ ከየት
ልጥፋ?” አላት የጃኬቱን ቁልፍ እየፈታ እምብዛም የጨዋታ ቃና በሌለው አንደበት።
“እንዴ ምነው? - አጥፍቼም ከሆነ ካሺኝ
ይባላል እንጂ እንደው ዝም ብሎ ይጠፋል እንዴ?”አለች ለዛዋን በጥንቃቄ እየመከነች::
“እሱማ ትክሺኛለሽ - ወደሽ ነው የምትክሺኝ?”
አለ የጫማዎቹን ክሮች ተራ በተራ እየፈታና ባቀረቀረበት ከራሱ ጋር የሚያወሪ ዓይነት።

“ሃሃሃ! - ወድጄማ ነው።

ነ..... ው?” አላት ጫማዎቹን እያወለቀ፡፡
“አዎና..ሃሃሃ! - ሳይወዱ ካሳ አለ እንዴ?”
“ሴትዮ ለወሬ አይደለም የመጣሁት
ይልቅ ተዘጋጂ ብድግ ብሎ ሱሪውን ካወለቀና ካጣጠፈ በኋላ ወንበሩ ላይ አስቀመጠው:: ጃኬትና ሸሚዙንም እዚያው ላይ ከደረበ በኋላ ወንበሩን ብድግ በማድረግ ከአልጋው አርቆ ትይዩ ካለው ግድግዳ ጥግ አስቀመጠና ወደ
አልጋው ተመለሰ፡፡ ሰውዬው ጨዋታ ጨዋታ እንዳላለው የተረዳችው ፀዳል ያለ ምንም ተጨማሪ ቃላት ልብሶቿን አወላልቃ ጣለችና አልጋዋ ላይ ወጣች።

በአገልግሎት ብዛት የተዳከመው የፀዳል አልጋ የተለመደውን ዓይነት የማቃሰት ድምፅ ማሰማት ሲጀምር የማሙሸት ጆሮዎች ሙሉ በሙሉ በመንቃት ለክትትል ተዘጋጁ:: የእናቱን እንግዶች በድምፃቸው ብቻ የመለየት ችሎታው ከእለት ወደ እለት እየሰላ ለመጣው ለማሙሸት የሰውየው ድምፅ አዲስ አልሆነበትም:: ጥቂት እንዳሰላሰለ
በትክክል አስታወሰው:: ከጥቂት ሳምንታት በፊት እንዲህ እንደዛሬው አምሽቶ መጥቶ ነበር።ታዲያ ያን ዕለት
ከዚህ ሰው ኪስ ሃያ ብር ቀንጭቦ እንደነበር ማሙሸት ትዝ አለው።ዛሬም የዚያኑ ያህል ምናልባት ዕድል ከቀናችውም የተሻለ - እንደሚያገኝ ተስፋ አደረገ፡፡ ሙሉ ቀልቡን ከበላዩ እያቃሰተ ወዳለው አልጋ አድርጎ ማዳመጥና መጠባበቅ ጀመረ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያቺ ማሙሸት
የሚጠብቃት አመቺ ቅፅበት ደረሰችለት:: ወዲያውኑ በዝግታ እጁን መሰስ አድርጎ በማውጣት መደባበስ ጀመረ:: እንኳንስ የሰውዬው ልብሶች ወንበሩ ራሱ በቦታው
ያለመኖሩን ሲረዳ ግራ ተጋባ፡፡ የአልጋው ላይ ሁካታ ይብሱን እየደመቀ መጣ፡፡ ማሙሸት በዝግታ በደረቱ፡ እየተሳበ ወደ አልጋው ጠርዝ ተጠጋና ወለሉ ድረስ
የተንዠረገገውን የአልጋ ምንጣፍ፡ በጥቂቱ፡ ገለጥ አድርጎ ተመለከተ። የሰውዬው ልብሶች የተቀመጠበት ወንበር የአድማስ ያህል ርቆ ታየው:: እንደገና የኋሊት እየተሳበ ወደነበረበት ተመለሰና በደረቱ ለጥ እንዳለ የዕለት
ዕድሉን ክፉኛ ረገመ።ሰውዬውን እንደ አባቱ ገዳይ ጠላው:: አሁን ቀረ የሚባል ተስፋ ካለ ያቺው ሰውዬው ለእናቱ የሚወረውርላት አምስት ብር ናት:: ምኗን
ከምኗ አድርጋ ቅበላዋን እንደምትወጣው ስለ እናቱ እየተጨነቀላት ሳለ ከበላዩ ይካሄድ የነበረው ግርግር ጋብ አለ።

ቀድሟት ከአልጋ ወርዶ መለባበስ የጀመረው የፀዳል እንግዳ ጫማውን እያጠለቀ ነው:: እሷ ግን ገና ዱሮ ጥንቅቅ ብላ አልጋዋ ጫፍ ላይ ቁጢጥ
ብላለች:: እጆቿን ደረቷ ላይ እንዳጣመረች ነገረ ነገሩ ሁሉ ያላማራትን የዚህን ሰው እንቅስቃሴ አንድ በአንድ ትከታተላለች።

ጫማዎቹን አሥሮ እንዳበቃ ካቀረቀረበት ቀና አለና ከኋላ ኪሱ ቦርሳ አወጣ:: ግልፅ ከሆነ የምፀት ፈገግታ ጋር ቦርሳውን እየከፈተ ካየ በኋላ መልሶ ከዚያው ከኋላ ኪሱ ከተተውና ወደ ፀዳል ቀና አለ፡፡

“እ ...ሺ የኛ አራዳ - " አላት ወደፊት ዘመም ብሎና ክንዶቹን ጉልበቶቹ ላይ አንተርሶ ጣቶቹን እያፍተለተለ፡፡ “ዛሬ ሰራሁልሽ አይደል? - አየሽ እንዲህ
እንዲህ ነኝ እኔ የአራዳው ቆንጨራ!”

“ማለት? አለችው አይኖቹን አትኩራ እየመረመረች:: አልገባኝም::”

ኧረ.....? አልገባሽ.....ም? ታድያ ምን ችግር አለ ሲገባሽ ትነግሪኛለሻ!”

ምኑን?” ይብሱን ግራ የተጋባች ትመስላለች:: “ምኑን ነው ሲገባኝ የምነግርህ?”

“ስሚ - እንኳን እንዳንቺ ያለችው ደደብ ሸርሙጣ ሌላ አይበላኝም እኔ ቆንጨራው!”

“ምንድነው የምታወራው?”

“ምን እንደማወራማ እናትሽን ጠይቂያት! ለዚያውስ እናት ሲኖርሽ አይደል
👍3
#ቅበላ


#ክፍል_አራት


#ከአዶኒስ

"እኔ ትርፍ ቃል አልወጣኝም ሂሳቤን ስጠኝ ማለት ትርፍ ቃል ነው እንዴ?"

“የምናባሽ ሂሳብ? ገና የሶስት አለብሽ!” አላት ጥርሱን እየነከሰና እያጉረጠረጣባት።

“ገባሽ የኛ አራዳ? የዛሬው ሲቀነስ ገና የሶስት ቀን ይቀርብሻል!"

“ የሶስት ቀን?? - የምን ሶስት ቀን ነው እሱ? . ምንድነው የምታወራው?”

“ባክሽ ሂጂና የምታጃጅይውን አጃጅይ! - የመቼዋ ነሽ በናትሽ?”

“ ኦ ....! የባሰበት መጣ አሉ - እሺ ለማንኛውም ሂሣቤን ስጠኝ::”

“እንዴታ! በጣም ነው እንጂ የምሰጥሽ - በ ...ጣም!”

“ሰውዬ - ምን አለ ነገር ባታመጣ?”

“ኧረ ....? ማስፈራራትሽ ነው?”

“እኔ አላስፈሪራሁህም - ሂሣቤን ስጠኝ፡፡”

“አንቺም ሃያ ብሬን ቁ .....ጭ! - ከዛ በኋላ ሂሣብሽን መጠየቅ ትችያለሽ።"

“ ሃያ ብሬን? ” ግንባሯን አጨመታተረች:: “የምን ሃያ ብር

“ኧረ? አላወቅሺውማ ?”

“የምን ሃያ ብር ሰጥተኸኛል?”

“ ምናባሽ እሰጥሻለሁ - በሆነ ተዓምር ከኪሴ ሞጨለፍሺኝ እንጂ ! ”

· “ከኪሴ?”

አዎ! እንዴትአባሽ አርገሽ እንደሆን ባለፈው ከቦርሳዬ ነጥለሽ ላፍ ያረግሺኝን
ሃያ ብር ቁጭ አርጊያት!”

“እኮ እኔ ካንተ ቦርሳ?”

“አይ የለ ሰይጣን ወሰደው በይኛ! እዚህ መታጠፊያው ላይ ያለችው ሱቅ ዘርዝሬ
ከአንዴም ሁለቴ ቆጥሬ -ቦርሳዬ ውስጥ አስተካክዬ ከትቼ - በቀጥታ ወዳንቺ የገባሁ ሰውዬ - ከዚህ ወጥቼም ወዲህ ወዲያ ሳልል በቀጥታ ወደ ቤት የገባው ሰውዬ ከቦርሳዬ ሃያ ብር ሲጎድል
የት ገባ እንድል ትፈልጊያለሽ? ሟሟ በይኛ ! - እ ? -ተነነ በይኛ!”

“ሰውዬው አብደህ ከሆነ አማኑኤል መሄድ ትችላለህ አሁን ግን ሂሳቤን።"

“ዛሬ ግን ሰራሁልሽ! ልብሴን ከአጠገብሽ ራቅ አድርጌ አስቀመጥኩ! - እንዴት አባሽ ትደርሺበት? አየሽ እንዲ ነኝ እኔ!"

“አሁን ሂሣቤን ትሰጠኛለህ አትሰጠኝም?"

“አልሰጥሽም! - ምናባሽ እንደምታመጪ አያለሁ::

“እኔ ምንም አመጣለሁ አላልኩም - ሂሣቤን ስጠኝ።

“ኧረ ....? ሰጠሁሽ እንዴ? - ገና አሥራ አምስት ብር ይቀርብሻል እኮ ነው ምልሽ! ገና ሶስቴ እመጣልሻለሁ ደስ ባለኝ ቀንና ሰዓት! ”

“ሰውዬ በጉልበትህ አምላክ - ሂሣቤን`

“ ገንዘብ የሌለኝ መስለሽ እንዳይሆን ቦርሳውን እያሳያት “ይኸውልሽ ተመልከች በርሳዬ ውስጥ ያለውን
ብር ግን ሰባራ ሳንቲም አልሰጥሽም! - ሞሽላቃ ሌባ!”
ፀዳል ከላይ እስከ ታች እንደ ማንቀጥቀጥ አደረጋት:: ሥሮቿ መገታተር ጀመሩ:: አገጯ ጥግ ያሉ የመንጋጋ አጥንቶች የትርታ ዓይነት ሁለት ሶስቴ ገባ
ወጣ አሉ፡፡ አተነፋፈሷ ፍጥነት ጨመረ::

ዠሂሣቤን - ስጠኝ::” አለችው ጥርሶቿን ግጥም አድርጋ እንደነከሰች ከንፈሮቿን ብቻ በማንቀሳቀስ::

“ሂጂና የምታስፈራሪውን አስፈራሪ እሺ? - እንኳን አንዲት ኪስ አውላቂ ሌባ ሌላም አያስፈራራኝ! ለመውጣት ዓይነት ብድግ አለ::

“ሂ - ሣ - ቤን! - በንጥቀት ተነስታ በሁለት እጆቿ ጃክቱን ጨመደደችው::

“ሴትዮ ልቀቂኝ! - ሂሣብ ያለብሽ አንቺ ነሽ ማለት አማርኛ አይደለም?” እጆቿን መንጭቆ ጃኬቱን ካስለቀቀ በኋላ ባለ በሌለ ኃይሉ አሽቀንጥሮ አልጋዋ ላይ
ጣላት። “ካሁን ወዲያ ብትጠንጊኝ በእጄ ስበብ እንደምትሆኚ እወቂ!

ፀዳል ከወደቀችበት በግማሽ ቀና አለችና እሳት የምትተነፍስ ዓይነት እያለከለከች እዚያው በዚያው ደም በለበሱ ዐይኖቿ ሰውዬውን አምርራ አየችው:: ወዲያው
ተስፈንጥራ ተነሳችና አስር ጣቶቿን እንዳንጨፈረረች ዘልላ ፊቱ ላይ ተከመረችበት ባልጠበቀው እርምጃዋ
የተደናገጠው ሰው የሸሚዙ ቁልፎች ተበጣጥሰው እስኪወድቁና ፊቱና ደረቱ በቡጥጫዋ እስኪዥጎርጎር ድረስ ታግሎ እንደምንም ከተላቀቃት በኋላ በሰነዘረው
ቡጢ መንጋጭላዋን ሲላት እንደገና እዚያው አልጋዋ ላይ በጀርባዋ ፍንችር ኣለች:: ለመነሳት እየተንገታገተች
ሳለ ሰውዬው ተንደርድሮ ሰውየው ጉብ ይልባትና በሁለት እጆቹ

አንገቷን አንቆ ወደዚያው ደፈቃት:: ፀዳል እጆቹን በእጆቿ ግጥም አድርጋ ይዛ ለማስለቀቅ እየታገለች እግሮቿን አወራጨች፡፡ ለመጮህ ስትሞክር ከታነቀው ጉሮሮዋ ድምፅ አልወጣ አላት:: ጣዕራ ጨመረ።

ማሙሸት ጭንቀት ገባው:: እናቱ በእንግዳዋ ስትበሻቀጥ ስትሰደብም ሆነ ስትደበደብ የመጀመሪያዋ አይደለም:: የተለያዩ ደንበኞቿ በተለያዩ ጊዜያት ይህን
ያደርጋሉ:: ታዲያ እናቱ ምንም ዓይነት ፀብ ውስጥ ብትገባ ራሷ እንደምትወጣውና እሱ በምንም ዓይነት
ከቦታው ንቅንቅ እንዳይል ጥንቱኑ ስላስጠነቀቀችው ለጥ ብሎ ከማዳመጥና ሕመሟን ከመታመም ሌላ ጣልቃ ለመግባት ሞክሮ አያውቅም:: በኋላ በኋላማ ከነገሩ ተደጋጋሚነት የተነሣ እየለመደው ሲመጣ ከበላዩ በሚያዳምጠው ግርግር መሃል ሌሎች ሌሎች ዕለታዊ ፍሬከርሲኪዎችን ማሰላሰል እስከመቻል ደርሷል::
የዛሬው ግን ለየት ያለ ሆነበት:: እናም ክፉኛ ተፈታተነው:: በደረቱ እንደተኛ አንደኛውን ጆሮውን ወደአልጋው ቀስሮ
ማዳመጥና መቁነጥነጥ ጀመረ።

ማሙሽት እየሰማው ካለው ግርግር ብቻ ሰውዬው ፀዳልን በጣም እየጎዳት መሆኑን አልተሳነውም፡፡ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት ትንሿ ደመነፍሱ ክፉኛ ጨቀጨቀችው:: ይሁን እንጂ የእናቱን ሕግ መጣሰም የዚያኑ ያህል ስለከበደው እንደምንም ጥርሱን ነከሰ፡፡
የሰውዩው ሁለት እጆች አሁንም በፀዳል ቀጭን አንገት ዙርያ እንደተቆላለፈ ነው።
የሰውየውን እጆች ጭምድድ አድርገው እንደያዙ ጥፍሮቿ ቆዳውን ዘልቀው ገብተዋል።እግሮቿን እያወናጨፈች
የሰውየውን እጆች ከአንገቷ ለማላቀቅና ድምዕ ለማውጣት ጣረች:: ውጪ ድረስ ሊሰማላት የሚችል ድምፅ ማውጣት ግን አሁንም አልሆነላትም ሰውዬው ያምጣል ያለከልካል ከስሩ የሞት የሽረቷን የምትወራጨው ሴት የግምቱን ያህል ቀላል ሆና ያገኛት አይመስልም....

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ነገ እንጨርሰዋለን መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#ቅበላ


#ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል)


#ከአዶኒስ

ውድ ተከታታዮቼ እንዴት ናችሁ ካቅም በላይ በሆነ ችግር በቃሌ አልተገኘሁም የጀመርኩትን መጨረስ አልቻልኩም ለዚህም ይቅርታዬ ባያላችሁበት ይድረስልኝ🙏

....የሰውዬው ሁለት እጆች አሁንም በፀዳል ቀጭን አንገት ዙሪያ እንደተቆላለፉ ነው:: የሷም
የሰውየውን እጆች ጭምድድ አድርገው እንደያዙ ጥፍሮቿ ቆዳውን ዘልቀው ገብተዋል:: እግሮቿን እያወናጨፈች
የሰወዬወን እጆች ከአንገቷ ለማላቀቅና ድምፅ ለማውጣት ጣረች።ውጪ ድረስ ሊሰማላት የሚችል ድምፅ ማውጣት ግን አሁንም አልሆነላትም።ሰውዬው
ያምጣል ያለከልካል ።ከሥሩ የሞት የሽረቷንየምትወራጨውን ሴት የግምቱን ያህል ቀላል ሆና ያገኛት አይመስልም:: ድንገት ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባሰበና
ጫናውን ጨመረ:: ፀዳል እየታረደ እንዳለ ዶሮ እግሮቿን አወነጨፈቻቸው:: አናቷን ግራ ቀኝ እያወራልጨች ከአልጋው ጋር ታላጋው ጀመር፡፡

ማሙሸት መቋቋም ተሳነው። በሰራ አካላቱ ያሉ ጅማቶች መወጣጠር ጀመሩ:: የልብ ትርታው አየለ::
የእናቱ ሕግ ከዚህ በላይ አስሮ ሊያቆየው አልቻለም፡፡ኮሽ እንዳይልበት እየተጠነቀቀ በደረቱ፡ ዳግም ወደ አልጋው ጠርዝ በመሳብ የተንዠረገገውን የአልጋ ምንጣፍ ገለጥ አደረገና ዐይኖቹን በጠባቧ ክፍል ከወዲያ ወዲህ አማተረ፡፡
ቅድም ፀዳል ሽንኩርት የከተፈችበት ቢላ እዚያው መክተፊያው ላይ እንደተወችው ነበር፡: ማሙሸት አንዲት ቅፅበት አላጠፋም፡፡ በደረቱ እየተሳበ ከአልጋው ሥር ወጣ፡፡ ቢላውን ለቀም አድርጎ አነሳና እጀታውን በእጆቹ መሃል እያመቻቸ እናቱ ላይ እንደ ጥንብ አንሳ እያጆፈጆፈባት ወዳለው ሰው ተንደረደረ፡፡ እንደደረሰም
በሁለት እጆቹ አጥብቆ የያዘውን ቢላ ከአናቱ በላይ አንስቶከቁልቁል በሰውዬው ማጅራት መሃል ሰካው።

ከየት መጣ ሳይለዉ ማጅራቱ ወስጥ
በተሰነቀረበት ቀዝቃዛ ባዕድ ነገር ለጊዜው ግራ የተጋባው ሰው እዚያው ባቀረቀረበት ዐይኖቹ ፈጠጡ፡፡ ቀስ በቀስም በፀዳል አንገት ዙሪያ ያቆላለፋቸው ጣቶቹ እየላሉ መጡ::
ማሙሸት ወደ በሩ አፈገፈገና ቁና ቁና እየተነፈስ ሁኔታውን መከታተል ጀመረ:: ሰውዬው በዝግታ ከፀዳል ላይ ቀና አለ፡፡ ከማጅራቱ የሚፈሰው ደም ቁልቁል
በጀርባው መውረድ ጀምራል፡፡ ዝግ ባለ እንቅስቃሴ እጆቹን ወደ ማጅራቱ ላከና እጀታው ሲቀር ስለቱ ሙሉ በሙሉ
የገባበትን ቢላ ደባበሰው:: ፀዳል የግንባሯ ሥራሥሮች እንደተገታተሩ በአንድ እጇ ማንቁርቷን እያሻሸችና በሀይል እያሳለች በሌላኛወ እጇ አልጋውን ተደግፋ ከተንጋለለችበት በከፊል ቀና አለች:: ሰውዬው ቢላውን ለመንቀል ይታገላል:: ማሙሸት በሩ ላይ በጀርባው
እንደተለጠፈ አንዴ ሰውዬውን አንዴ እናቱን እያየ ያለከልካል፡፡ የታችኛው ከንፈሩ ይንቀጠቀጣል። ፀዳል
ሳሏ ጋብ እንዳለላት ቆባቸው የተንጠለጠለ ዐይኖቿን እንደምንም ገልጣ ከፊት ለፊቷ ጣረ-ፍዳውን እያየ ያለውን ሰውና በሩጋ ቆሞ የሚብረከረከውን ልጇን በነጎድጓድ
ብልጭታ ፍጥነት እያፈራረቀች ተመለከተቻቸው፡፡

“በል ቶሉ ውጣ ቶሎ ውጣ አላችው ሁለመናውን ጆሮ አድርጎ አፍ አፏን እያየ ለሚጠብቃት ልጇ፡፡ “ቶሎ ውጣና ከዚህ ሰፈር ጥፋ! ማንም ቢጠይቅህ
ትሰማኛለህ?ምንም የሰማኸው ማንም ቢጠይቅህ - ምንም ያየኸው -ምንም የምታውቀው ነገር የለም!
ጨርሶ እዚህ አካባቢ አልነበርክም ማለት ነው! - እሺ?”

ማሙሸት ራሱን በመነቅነቅ እሺታውን ገለፀላት:: “እኮ በል ውጣ! - ውጣ!` አካለበችው - ከትንፋሿ ጋር ቁርጥ
ቁርጥ በሚሉ ቃላት:: ማሙሸት በሚርበተበቱ እጆቹ በሩን ከፈተና ፈትለክ ብሎ በመውጣት ከድቅድቁ ጭለማ
እቅፍ ገባ፡፡

ሰውዬው ድንገት አጓራ።በግራ እጁ ከማጅራቱ በላይ ያለውን አናቱን ደግፎ ይዞ በቀኝ እጁ ቢላውን ለመንቀል እየታገለ የሞት ሞቱን ማሙሸት በከፈተውበርግጥ ወጣ፡፡ መራመድ የተሳነው ዓይነት እዚያው ደጃፉ
ላይ ቆም አለና ማጓራቱን ቀጠለ፡፡

ወዲያው ጩኸቱን በሰሙ ተላላፊዎችና
ከየጉራንጉሩ እየተሯሯጡ በመጡ የመንደሩ ሰዎች የፀዳል ደጃፍ ተጥለቀለቀ:: ወደሚያጓራው ሰው
ለመቅረብ የሞከረ አንድም ሰው የለም። በጥቂት ክንዶች ርቀት ከብበው ጣዕር ላይ ያለውን ሰው በተሻለ ለማየት
ይጋፋሉ፡፡

የሰውዬው ድምፅ እየደከመ መጣ፡፡ ቢላውን ለመንቀል ያደርግ የነበረውን ጥረት ትቶታል:: ደሙ ቁልቁል በሰውነቱ ሙሉ ወርዶ ከመንገዱ የድንጋይ
ንጣፍ ላይ ተንጠባጠበ፡፡ ተጨፍነው የቆዩ አይኖቹን እንደምንም በግማሽ ገለጠና ወደፊት እንደመንቀሳቀስ
ሲል ከፊትለፊቱ የነበሩት ተመልካቾች በሽሽት እየተጋፉ ወደግራና ወደ ቀኝ ተበተኑ። አንድ ሁለቴ እንደተራመደ
በሙሉ ቁመቱ እንደ ደመራ ግንድስ ብሎ ወደቀ፡፡ ሰዎቹ እንደገና የወደቀውን ሰው በቅርበት ለማየት መጋፋት
ግርግሩ ደመቀ፡፡ ተጨማሪ ሰዎች ወደ ሥፍራው መጉረፍ ጀመሩ፡፡ የወደቀው ሰው ምንም እንቅስቃሴ .አይታይበትም:: አሁንም ወደ ሰውዬው በቅጡ ለመቅረብ
የደፈረ የለም:: እያንዳንዱ ሰው በየቆመበት የየራሱን አስተያየት ይወረውራል፡፡

“ሳይሞት አይቀርም! - የታል የሚተነፍሰው? ምናለ በሉኝ ሞቷል!”

“መሞትስ አልሞተም! - ይልቅ ቢላው ይነቀልለት!"

“አአ - ቢላው ከተነቀለማ አለቀለት! - ደሙ ፈስሶ ያልቅ የለ እንዴ? - ይልቅስ እንዲሁ እንዳለ ሆስፒታል ማድረስ ነው!”

“በጭራሽ! . አባዲና ሳይመጣ አንድ ሰው
እንዳይነካው! - ኋላ ጣጣ ውስጥ እንዳትገቡ!”

“አዎ - አሻራ ሳይነሳማ መንካት አይገባም

“ይልቅ ፖሊስ ይጠራ!”

“ፖሊስ ምን ይረዳዋል? - አምቡላንስ ነው
መጥራት

ከወዲህም ከወዲያም አስተያየቶች ተዥጎደጎዱ፡፡

በዚህ መሃል ፀዳል በአንድ እጇ ወገቧን እንደያዘች በሌላኛው እጄ ያንኑ ጉርርዋን እያሻሸች በዝግታ ወደ በሯ ብቅ አለች፡፡ ወዲያውኑ የሁላቸውም ትኩረት ሃውልት መስላ በሯ ላይ ወደተገተረችው ሴት ዞረ
ምንም ዓይነት የመደናገጥ ምልክት አይታይባትም፡፡ይልቁንም - ተጋጣሚውን በዝረራ እንዳሸነፈ ሻምፒወን ሰውየውን ቁልቁል እያየች የሚሆነውን የምትጠባበቅ መሰለች፡፡ ከተመልካቾቹ መሃል ወደእሷም ለመቅረብ የደፈረ የለም:: በቅርብ የሚያውቋት ሴት ጎረቤቶቿ ብቻ ከግራም ከቀኝም በጥያቄ አጣደፏት፡፡ ዐይኖቿን ለአፍታ እንኳን ከወደቀው ሰው ላይ ያልነቀለችው ፀዳል የሰዎቹን ጥያቄዎች መመለስ ይቅርና ቀድሞ ነገር የምትሰማቸው
አትመስልም::

ብዙም ሳይቆይ ጥቂት ፖሊሶች እየተጣደፉ ከቦታው ደረሱ። የከበበው ሰው ገለል ገለል አለላቸውና ሰውየውን በቅርበት እያጤኑት ሳለ በሯ ላይ ቆማ
የነበረችው ፀዳል እንደገና ወደ ውስጥ ገባች፡፡ ሰውዬውን አልብሶት የቆየው ጥላዋም እንደ ጥቁር ቬሉ ከኋላዋ
እየተጎተተ ተከትሏት ገባ። ይሄኔ መንገዱ ላይ የተንጋለለው ሰው ከላዩ ጣል ተደርጎበት የነበረ ስስ ከፈን የተነሳለት ዓይነት እንደገና በግልፅ መታየት ጀመረ፡፡

የፀዳልን ወደ ውስጥ መዝለቅ ልብ ያሉት ፖሊሶች እርስበርስ ተጠቋቆሙ። ወዲያው ከመሃከላቸው ሁለቱ ወደ በሯ እንደማምራት ሲቃጣቸው ፀዳል ነጠላ ቢጤ ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ እንደገና ብቅ አለች::

ሁለቱ ፖሊሶች ከተቀሩቱ ጋር በፖሊስኛ
ከተንሾካሾኩ በኋላ ወደ ፀዳል አቅጣጫ መንቀሳቀስ እንደጀመሩ እሷው ራሷ በሯን መለስ አደረገችና ወደ እነሱ በማምራት በመሃላቸው አልፋ ከፊት ከፊታቸው
እየመራች የዋናውን መንገድ አቅጣጫ ያዘች።

ሰዉ ወደየመጣበት ተበታተነ።ማሙሸት ብቻ ታጅባ እየተወሰደች ያለችውን እናቱን በርቀት ሲከተላት ቆየ።
በስፋት የተንጣለለው ግራጫ የአስፓልት ጎዳና ፀጥ ረጭ ብሏል:: ቀስ በቀስ በማሙሸትና በእነፀዳል መሃል
ያለው ርቀት እየሰፋ እየሰፋ ሄደ::
👍1