አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
486 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ማምሻ


#ክፍል_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም


አብሮ አደጌ ሎዛ እና ዳግም(ዳግማዊ ነው ሙሉ ስሙ ሊጋቡ ሽር ጉድ ሲባል፤ ለሁቱም የቅርብ ጓደኛ ስለነበርኩ አብሬ ላይ ታች ማለት ጀመርኩ። ከዳግም ጋር ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ ጓደኞች ነን። በመሃል አቋርጦ ቤተሰቦቹ ጋር አውሮፓ ሄደ እንጂ ዩኒቨርስቲ የገባነውም አብረን ነበር። ታዲያ ስንት ዓመት ሙሉ እዚህ አጠገቤ ሆኖ ያልነገረኝን፣ አውሮፓን በረገጠ በወሩ በጻፈው ደብዳቤ “ከሎዛ ጋር 'ርሌሽን ሽፕ
ጀምረናል!" አለኝ እስቲ ምን አሰደበቃቸው!? እሱስ እሽ የሷ መደበቅ ምን ይባላል?ጭራሽ በኋላ ስሰማ፣ የፍቅር ግንኙነት ከጀመሩ ሁለት ዓመት አልፏቸው ነበር፡፡ ዳግም ስንትና ስንት ቀን አበሳጭቶኝ “ይኼ ከርፋፋ ብጉራም” ብዩ ለሎዛ አምቼዋለሁ፡፡ የአውሮፓ ኑሮ እንዲህ የተወለወለ መስተዋት ሳያስመስለው በፊት፣ ያኔ እንደ ጧት ጤዛ ያበጡ ብጉሮች የወረሩት አሰቃቂ ፊት ነበረው፡፡ የሆነ ሆኖ ከዓመታት በኋላ ሊጋቡ፡
ይኼው ለዳግም ሚዜ እሆን ዘንድ ጠየቁኝ፡፡ እንቢ አይባል ነገር።

ሰርግም ይሁን ሌላ “ማኅበራዊ ጉዳይ" በሚል የዳቦ ስም የተጠቀለለ ግርግር ባልወድም፡
የዚያን ሰሞን ግን ከነሎዛ ቤት አልጠፋ አልኩኝ ሰበቡ “የሎዛን ቤተሰብ እንደቅርብ ሰውነቴ ሥራ ማገዝ አለብኝ የሚል ቢሆንም እውነቱን ለመናገር ግን ምንም የሚታገዝ ሥራ አልነበረም፡፡ ልክ ከሥራዬ እንደወጣሁ ወደነሎዛ ቤት መሮጤ ምስጢሩ ወዲህ ነው፡፡ ሰርጉ ሁለት ሳምንት ሲቀረው፡ በየቀኑ ማታ ማታ በርከት ያልን የቅርብና የሩቅ ጓደኞች ተሰብስበን ያሳለፍነውን እያነሳን መሳሳቅ ከሩቅና ከቅርብ ከተሰበሰቡ የሎዛ እና
የእህቶቿ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሴት ጓደኞች ጋር ሲሳሳቁና ሲያወሩ ማምሸት፣ ደስ የሚል ስሜት ነበረው፡፡ እነሎዛ እነዚህን ሁሉ ሴቶች ምን ቀን እንዳወቋቸው እንጃ፡ለነገሩ እንኳንም አወቋቸው፡፡ ደግሞ ተመራርጠው የተወዳጁ ይመስል ሁሉም
ቆንጆዎች፣ በውድና በቆንጆ ልብሶች የተሽቀረቀሩ ፣ የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች መዓዛ አየሩን ሞልቶ የሚናኝ፡ ሁሉም ጨዋታ አዋቂዎች፡ እግዜር ድግስ እንዲያደምቁ የፈጠራቸው የሚመሳስሉ ውብ እና ወጣት ሴቶች እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ቆነጃጅት
ከብዙ ሳቅና መሽኮርመም ጋር እዚያ ቤት ያመሻሉ ቢባል፣ እንኳን የእኔ ቢጤው ወጣት፣
እንደ ዶሮ በጊዜ አልጋው ላይ የሰፈረ ሽማግሌም ቢሆን እስቲ ምርኩዜን አቀብሉኝ ብሎ ወደነ ሎዛ ቤት ማዝገሙ አይቀርም፡፡

አንድ ቀን ታዲያ እንደልማዴ ከሥራ ስመለስ፣ ቶሎ ልብስ ቀይሬ ወደነሎዛ ቤት ተጣደፍኩ:: እቤት ስደርስ ሎዛ ፊቷ በርበሬ መስሎ፣ ስስ ነጭ መጋረጃ የመስቀያ ብረት ላይ ትሰገሰጋለች፡፡ ሁሉንም ሰላም ካልኩ በኋላ “ሙሽሪት?” ብዬ ለመቀለድ ሞከርኩ፡፡

ሁልጊዜ ስታኮርፍ እንደምትሆነው ዓይኔን ሳታይ እ” ብላ ጉንጨን ጉንጨን በጉንጫ
ነካ አድርጋ ወደ መጋረጃዋ ተመለሰች የምቀመጥበት ስፈልግ “ና እዚህ ጋ አብርሽ
አለችኝ ፍኖት፤ በተቀመጠችበት ረዥም ሶፋ ላይ ጠጋ ብላ ቦታ እያመቻቸችልኝ፡፡ የሎዛ እህት ነች፡፡ እሷም ፊቷ ልክ አይደለም፡፡ አብሮ ከማደግ ባገኘሁት ልምድ፣ የቤተሰቡን ፊት እንደ መጽሐፍ በማንበብ ተክኛለሁ፡፡ ይኼን ፊት አውቀዋለሁ፡፡ከሎዛ ጋር ሲጣሉ ዓይኗ ሁልጊዜ በቁጣ ይጉረጠረጣል፡፡ አንድም ቀን ተስማምተው አያውቁም:: እናታቸው ሁልጊዜ “እናንተ ልጆች ምን እንደ ጣውንት ያናጫችኋል?” ይላሉ:: በውስጤ ነገር አለ እያልኩ ሂጄ አጠገቧ ተቀመጥኩ፡፡ ፍኖት ከወደታች ስፋ ስለምትል ቦታው ጠበበኝ፡፡

ከተቀመጥኩ በኋላ ጉልበቷን ቸብ አድርጊያት ሰላም ነው?» አልኳት፡፡

“ምን ሰላም አለ! ይች ክሬዚ እያለች” አለችኝ፡፡ እንዲህ ናት ፍኖት ነገር ከያዘች ቶሎ ማፍረጥ ነው፡፡

“ምን አደረገች ደግሞ? ሙሽራኮ ቀልብ የለውም”

አንተ ምናለብህ! ስሰላም ሥራህ ውለህ ትመጣለህ… ቤቱ ሲታመስ ነው የዋለው:: ማሚ
በብስጭት እራሷን አሟት ተኝታለች”

“ምንድነው? ባል ይቀየርልኝ አለች እንዴ? እሷኮ አታደርግም አይባልም” በቀልዱ ከመሳቅ ይልቅ በእልህ ወደ ሎዛ እያየች “ባክህ አትቀልድ! ይኼ ነገር ሲሪየስ' ነው አለችኝ ከረር ባለ ድምፅ።

እኮ ምንድነው? ችግር አለ?”

እሷ ካለች ሁልጊዜም ችግር አይጠፋም፡፡ እስከዛሬ ማን እንደሆነች አልናገርም ብላ
የደበቀቻት ሚዜ ታውቀች እለችኝ፡፡

ከወራት በፊት ተናግራ፣ የአንዷን ማንነት ግን “ሰርጉ ካልደረስ አልናገርም ብላ ሰለነበር፣

አረ ባክሽ!…ማን ሆነች?” በጣም ነበር ለማወቅ የጓጓሁት ሎዛ ሁሉንም ሚዜዎቿን ሰው ሁሉ በድብብቆሹ ግራ ተጋብቶ ነበር። እስቲ አሁን ሚዜ ምን ይደበቃል?እየተባለ፡፡ ነገሩ ይበልጥ ያጓጓኝ ደግሞ፣ እኔንም በቀጥታ ስለሚመለከተኝ ነበር፡፡

ስድስት የወንድ ሚዜዎች ተመርጠን፣ አምስት የሴት ሚዜዎች ብቻ በመታወቃቸው፣
ከእኔ ውጭ አምስቱም ሚዜዎች ከሴቶቹ ጋር ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ የኔዋ እየተጠበቀች
ነበር፡፡ ሚስትም እንዲህ በጉጉት አይጠበቅ” እስኪባል፡፡ መቸም በሰርግ ላይ ከባልና
ሚስት ቀጥሎ የሚዜዎች ጥምረት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር ነው፡፡ አንዳንዴም ሚዜዎች እጩ ሙሽራ የሚሆነበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ ማን ያውቃል? አምስቱ የወንድ ሚዜዎች፣ እነዚያን ሽንጣቸው እንደ ነብር ሸንጥ የሚመዘዝ፣ ጸጉራቸው ወገባቸው ላይ የሚዘናፈል፣ እንደ ወንዝ ዳር ቄጤማ ነፋስ የሚያወዛውዛቸው
የሚመሳስሉ ሴቶችን አቅፈው ዳንስ ሲለማመዱ፣ ሁለት ሁለት እየሆኑ ከወዲያ ወዲህ ሲሉ፧ ሚዜ ሳይሆኑ አብረው የሚዳሩ አምስት ሙሽሮች ይመስሉ ነበር፡፡

ቤተሰቡም ሆነ ሚዜዎቹ ባያምኑኝም፣ ሎዛ ለእኔም የተደበቀችዋን ሚዜ ማንነት
አልነገረችኝም ነበር፡፡ እውነቴን ነበር አልነገረችኝም። ሁሉንም ነገር የምትነግረኝ ንስሐ
አባቷ እደረጉኝ እንዴ? ከገዛ ጓደኛዬ ጋር ሁለት ዓመት፣ ያውም አፍንጫዬ ሥር በፍቅር
ዓለሟን ስትቀጭ ራሱ መች ነገረችኝ? ሁሉም ያሰቡት እኔና ሎዛ ሚስጢረኞች ስለሆንን፡
የእኔዋን ልዕልት መጨረሻ ላይ የምታመጣት አድርገው ነበር፡፡ ከትንሽ አድሎ ጋር ቆንጆዋን ካለሽሚያ ልታሳቅፈኝ፡፡ ለነገሩ ጉራ ሳይሆን፣ ከወንዶቹ ሚዜዎች፣ በመልክም ይሁን በአቋም፣ እኔ እንደማምር በአለፍ ገደም ነግረውኝ፣ ኩራት ቢጤና የተሻለችው ሚዜ ትገባኛለች የሚል ትንሽ ትዕቢት ልቤ ውስጥ ነበር፡፡

ፍኖት ታዲያ የሚዜዋን ማንነት ስጠይቃት፣ ከግርምትና ከብስጭት "ሆሆ ጋር የተቀላቀለ ሳቅ ስቃ፣ አንገቷን እየሰበቀች፣

“የማታውቅ ለመምሰል ነው?” አለችኝ

እግዚአብሔርን ፍኖት! ለምንድነው የማታምኚኝን ታውቂያት የለ እንዴ ሎዛን? ችክ ካለች አለች ነው፡፡ ምንም አልነገረችኝም

እንግዲያስ ጉድህን ስማ! ማምሻ የምትባለውን ሴትዮ ሚዜ አደርጋለሁ እያለች ነው አለችኝና እጅ በደረት አድርጋ ፍጥጥ ብላ አየችኝ፡፡

ማምሻ? ማምሻ? ይቺማምሻ?” አልኩ በጣቴ ወደነማምሻ ቤት አቅጣጫ እየጠቆምኩ :

“አወና አለችኝና ትክ ብላ እየችኝ፡፡ ዓይን ለዓይን ተፋጠን ለሰኮንዶች እንደቆየን፡

“ካላመንክ ራሷን ጠይቃት!"አለች፣ በአገጯ ወደ ሎዛ እየጠቆመች፡፡ ሳቅሁኝ መጀመሪያ ቀልድ ነበር የመሰለኝ፡፡ ፍኖት ኮስተር ስትል ግን፣ ነገሩ የምር መሆኑ ገባኝና፣ እንደገና መሳቅ ጀመርኩ፡፡

“ሳቅ፡ አንተ ምናለብህ? አልደገስክ ሰው አልጠራህ! ውርደቱ የኛ” ብላኝ ተነስታ
እየተቆናጠረች ወደ ውስጥ ገባች፡፡ ፊቴ ላይ ለይቶለት ያልፈነዳ ሳቅ እያንዣበበ
ባለማመን ወደ ሎዛ ስመለከት፣ ዓይን ለዓይን ተገጣጠምን፡፡ ኮስተር ብላ በከንፈር
እንቅስቃሴ ብቻ “ዋት?” አለችኝ፡፡ መስማቴን አውቃለች:: ሳላስበው ንጥሻ የሚመስል
ሳቅ ከውስጤ ወጣ:: ትከሻዬ
👍1
#ማምሻ


#ክፍል_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም


ተነስቼ ወደ ውስጥ ስገባ፤ሎዛ ከምኔው እንደደረሰች እንጃ እየተቆናጠረች ኮሪደሩ ላይ
ገፍታኝ አለፈችና፣ እናቷ ያሉበትን ክፍል በርግዳ ቀድማኝ ገባች::

አንችን ማን ጠራሽ? እንዲያው አታውሩ እትተንፍሱ ነው እንዴ? አሉ እናቷ ግልፍ ብለው።

ለመጣው ለሄደው ሁሉ ስሞታ፤ ቆይ እናንተ ምናችሁ ተነካ ፡ አምባረቀች፡፡

"ምናችን እንደተነካ እኛ ነን የምናውቀው፡፡ አሁን አትቅለብለቢብኝ ላውራበት አሉ፤ በቁጣ: ግራ ገብቶኝ ቁልጭ ቁልጭ ስል፣

አብርሽ! ይኼው ሞልቶ ለሚንጋጋ ጓደኛ…እኔን ካላዋረድኩ…የአገር መሳቂያ መሳለቂያ
ካላደረኩ፣ ሙቼ እገኛለሁ እያለች ነው፡፡ እንግዲህ አንተም አብረህ ተዋረጅ መሳቂያ ሁኚ ካልክ ደህና! ካልሆነ ይችን እብድ እንደጓደኝነትህ ምከር ዝከር ነገ ቤተሰብ የላትም ወይ መካሪ ጓደኛ የላትም ወይ? ነው የሚባለው"

ኦ ማይ ጋድ! …ማሚ፣ ማምሻ ሚዜ ስለሆነች ምንድነው የምትዋረዱት? ምንድነው አገር የሚስቀው! ኧረ እግዚኣብሔራችሁን ፍሩ፤ ሰውስ ሲሰማችሁ ምን ይላል? እንደ እናንተው ሰው ናትኮ! ሰውሰው!” ብላ ጮኸች፡፡ ስትቆጣ ከንፈሯም እጇም ይንቀጠቀጣል…እልኸኛ ናት፡፡ ከልጅነታችን አንስቶ ያለችው ካልሆነ፡ አገር ነው
የሚታመሰው፡፡

ወዲያ አትፈላሰፊብኝ…ሰው ሲታጣ ይመለመላል ጎሰጣ አሉ…ታዲያ ሰው የሆነች እንደሆነስ? እግዜር ሲፈጥረን መቼም ቦታ ቦታ አዘጋጅቶ ነው፡፡ እኔ መልኳን አልሠራሁ ምንድነው ሰው ለማስኮነን ሩጫ!? ሚዜ ለዓይን የሚያምር፡ ቀልጠፍ ያለ፣ እኩያሽ ሲሆን፤ ለተመልካችም፣ ለደጋሽም፣ ለፎቶም፣ ለቪዲዮም ደስ ያሰኛል ፎቶውም ታይቶ
አይጠገብም፡፡ እኔ ማምሻ ለሚዜነት አትሆንም አልኩ እንጂ፣ ሰው አይደለችም ወጣኝ…ምናለ ክፉ ባታስብዪኝ፣ ከጎረቤት ባታነካኪኝ ከፈለግሽ ከሰርጉ በኋላ በአንቀልባ አዝለሻት ዙሪ” ፍኖት ከኋላዬ በሩን ተደግፋ እንደ ቆመች ቡፍ ብላ ሳቀች፡፡ሎዛ ፊቷ ተቀያየረ፡፡ ወደ እህቷ ዙራ ፓ 'ዲያና' ብላ፣ አሽሟጠጠቻትና እናቷን
ቆፍጠን ባለ ንግግር፣ “ከሰርጉ በኋላ ሚዜ አያስፈልገኝም፡፡ ማምሻ አንደኛ ሚዜዬ
ትሆናለች! አለቻቸው፡፡

ዋ..ት..?” አለት ፍኖት፡፡

አይ! ተይው፣ ተይው እናቴ እኔ ጤነኛ መስለሽኝ ነው… ጭራሽ አንደኛ ሚዜነት እንግዲህ እኔ ሙቼ ከሆነ እናያለን!” አሉ እናቷ ጉልበታቸው ላይ ያስቀመጡትን ትራስ አንስተው፣ በቁጣ ወደጎናቸው እየወረወሩ፡፡

“ቆይ ይኼ ሁሉ ማካበድ ምንድነው?…ሰርግ አይደል እንዴ? የሆነ ሌላ ተአምር
እስመሰላችሁትኮ?”

“ሰርግኮ የአንድ ቀን የባርቲ ቤት ጭፈራ አይደልም፡፡ ታሪክ ነው፡፡ ታሪክ በፎቶ በቪዲዮ
እያንዳንዱ ነገር ተመዝግቦ ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ይገባሻል!?…ተይው፣ ጥፋቱ የአባትሽ ነው፡፡ ሰው ሁሉ ዩኒበርስቲ ገብቶ ሐኪም፣ መሐንዲስ ሲሆን፣ አንቺ እብደት ልማር ስትይ፣ ይለይልሽ ብሎ ፈቀደ፣ ይኼው …ልብስ መጣል ነው የቀረሽ! (ሰው ሁሉ የሚሉት የሎዛንን ታላላቆች ነው) ..እንግዲህ አሻፈረኝ፣ ከኔ በላይ ሰው ካልሽ፣ …እዛው አባትሽ እንደሚያደርግ ያድርግ” ሎዛ ፍልስፍና ነው ያጠናችው፡፡ ያኔም ፍልስፍና ልማር ስትል፣ እንዲሁ ቤቱ ታምሶ ነበር፡፡ የሎዛ አባት “የወደደችውን ትማር” ብለው ፈቀዱ፡፡ ተመርቃ ካለሥራ ሁለት ዓመት በመቀመጧ፣ በተለይ እናቷ “ብዬ ነበር እያሉ ባላቸውን ይወቅሳሉ፡፡ ደግነቱ
አባትዬው ለወቀሳም ለምስጋናም ግድ ያላቸው ሰው አልነበሩም፡፡ ሎዛ የአባቷ ነገር ሞቷ ነው፡፡ ከሕፃንነቷ ጀምሮ ከአባቷ ሥር አትጠፋም፡፡ ሰፈራችን ውስጥ ወዳለው ግሮሰሪ ሳይቀር ተከትላቸው እየሄደች፣ ባለጌ ወንበር ላይ እግሯን አንጠልጥላ፣ እሳቸው ከጓደኞቻቸው ጋር ዘና ሲሉ፣ እሷ ለስላሳዋን ይዛ ቁጭ ትል ነበር፡፡

የሎዛ ኣባት የተለዩ ሰው ናቸው:: በከተማው የታወቀ ጣውላ ቤት አላቸው። ሲበዛ
ዝምተኛና የሥራ ሰው ነበሩ፡፡ ሚስታቸውን ጨምሮ፣ ወንዶቺም ሴቶቹም ልጆቻቸው
ለከተማው የታወቁ ዘናጮች ቢሆኑም፣ ሰውዬው ከሰኞ እስከ ሰኞ ቱታቸውን ለብሰውና፡
አፉቸው ላይ ከቀንድ የተሠራች ጥቁር ፒፓቸውን ሰከተው ሥራ ላይ ናቸው፡፡ ሁለት ወንድ ልጆቻቸው ሐኪሞች ናቸው፡፡ አንዷ ሴት ልጃቸው፣ ለከፍተኛ ትምህርት ውጭ አገር ነው ያለችው። አርክቴክት ናት፡፡ የሎዛ ታላቅ ፍኖትም በምሕንድስና ነው
የተመረቀችው፡፡ ከቤቱ ልጆች ተለይታ ፍልስፍና ያጠናቸው ሎዛ ነበረች፡፡ ያውም በከፍተኛ ውጤት ዩኒቨርስቲ ገብታ ሥራዬ ብላ መርጣ፡፡ ሎዛ ከልጅነቷም መሬት ከፍ ሰማይ ዝቅ ቢል፣ ካመነችበት ነገር ወደ ኋላ የማትል ልጅ ናት፡፡ እንደዚያም ሆኖ ታዲያ፣ የጓደኞቿ ብዛት ለጉድ ነበር፡፡ እኔ ጋር በአሥር ጉዳዮች ላይ ብናወራ፣ በዘጠኝ ተኩሱ እንስማማም፤ ግን እንዴት እንደሆነ አይገባኝ ሩጨ እሷ ጋር ነኝ ፣እሷም ከአጠገቤ
አትጠፋም፡፡ አሁን ከምታገባው ከዳግም ጋር ራሱ፣ አስር ጉዳዮች ቢያወሩ፣ በአስሩም
እይስማሙም፤ ግን ይኼው ሊጋቡ ነው፡፡ የሎዛ ነገር እንዲህ ነው፡፡ ጭቅጭቋ እንደ ፍቅር
ቃል ሱስ የሚሆን፡፡ በምድር ላይ የሎዛንን ሐሳብ የሚያስቀይር አንድ ሰው ብቻ ነው አባቷ! ይኼው ማምሻ የምትባለውን የሰፈራችንን ልጅ ሚዜ አደርጋለሁ በማለቷ የተነሳው ጭቅጭቅ፣ ለሰርጓ ከየአገሩ በመጡ እህትና ወንድሞቿ፣ በምንቀርባትም ጓደኞቿ እልባት ባለመገኘቱ ጕዳዩ ለውሳኔ ወደ እባቷ ተላከ፡፡ አባት ምንም ይበሉ፣
በውሳኔያቸው ላይ ይግባኝ የለም፡፡

።።።።።።።።።።።።።።
ማምሻ” ብለው ስም ያወጡላት አባቷ ጋሽ ቢሆነኝ ናቸው። “ማምሻ ቢሆነኝ” (የአባትና
ልጅ ስም እንዲህም ገጥሞ አያውቅ፤ ይላሉ የሰሙ ሁሉ) እሳቸው እንኳን ለክፋት
አልነበረም፤ ወንድ ልጅ ክፉኛ ይፈልጉ በነበረበት ሰሞን፣ የመጀመሪያ ልጃቸው ሴት ሆነች ያውም እናቷን ወይዘሮ ዓምድነሸን የምታስከነዳ መልከ ጥፉ! ጎረቤቱ ቁርጥ እናቷን” እያለ በሰላሙ ጊዜ ለመናገር የማይደፍረውን የወይዘሮ ዓምድነሸን መልክ ጥፉነት፣ በአራስ ጥየቃ ሰበብ ተነፈሰው ቆንጆ ልጅ!ገና ምን አይታችሁ? ከፍ ስትል
መልኳዋ ይወጣል” አሉ አንዳንዶች፡፡ የአራስ ጥየቃ ውጉ ነው ብለው: ማምሻ ከፍ ስትል
ግን ጭራሽ ድንቡሸ የልጅነት ሥጋ ደብቆት የነበረ መልከጥፉነቷ ቁልጭ ብሎ ወጣና፣
ድንገት ሲመለከቷት እንደ ልጅ ስመው ሳይሆን፣ እንደተከሰተ ጋኔል አማትበው የሚያልፉት ልጅ ሆና አረፈች፡፡ እንዲያው ለወላጆቿ ይሉኝታ ሲል ማምሻን ለመሳም የሚገደድ ጎረቤት ዓይኑን መጨፈን ግድ ይሆንበት ነበር። የሆነ ሆኖ ወንድ ልጅ እስኪወለድ መቆያ ትሆናለች ሲሉ፣ አባት “ማምሻ አሏት፡
ይኼን የማምሻ ገድል በመሀላችን እየኖረች፣ ግን በሆነ ሩቅ ዘመን እንደኖረች ጕድ፡ እንደተረት የነገሩን ታላላቆቻችን ነበሩ፤ ያውም በብዙ ሳቅና ፌዝ አጅበው

ይኼ ፌዝና ሳቅ ያጀበው ታሪክ እንዲህ እያሉ ሲያሙሽ፣ ለምን አላችኋት ብዬ ተጣላሁ
በሚል መጠቅለያ፤ ተቆርቋሪ ነን ሲሉ በሚዳዳቸው ነገር አድራሾች፣ ለማምሻ ለራሷ
ይደርሳታል: በዚህ ዓይነት ፌዝ ነበር እኩል ከእኩዮቿ ጋር የመቆም መብቷን በየቀኑ ሰነጣጥረን፣ አንዲት ግፋችን ከብዷት ገና በልጅነቷ የጎበጠች ወጣት የፈጠርነው፡፡
ፌዛችን አንገት ማስደፋቱ፣ ለደፊዋ እንድናዝን ሳይሆን፣ በፌዛትችን ጥንካሬ እንድንደመም
እድርጎን፣ ስየቀኑ አዲስ ቀልድና ስላቅ መፈብረክና የግፍ ምርታችንን በጎበጠ ጀርባዋ ላይ ጭነን መሳቅ ቀጠልን:: እናቶችም ለማጉበጡ አልሰነፉ፤ሕፃናት ልጆቻቸው ሲረብሹ
ለማስፈራራት ምን ይሉ ነበር?… “ማምሻን እንዳልጠራት!” ልጆቹ ወደኋላ ተገላምጠው
በፍርሃት ይርዳሉ: መንደሩ ከእናት ጡት በላይ የማምሻን ማስፈራሪያነት እየተጋተ ባደገ
ሕፃን የተሞላ
👍3
#ማምሻ


#ክፍል_ሦስት


#በአሌክስ_አብርሃም


ጀብድ ሠርቶ እንዳመለጠ የግፍ እስረኛ፣ በአድናቆትና እንኳን ተሳካላቸው ሰሚል ስሜት
የተሞላ ነበር፡፡

እማማ ዓምድነሽ፣ ልጃቸውን ማምሻን አይገቡ ገብተው አሳደጓት: ሰው ቤት ልብስ እያጠቡ፣ ጉሊት እየቸረቸሩ ትምህርቷን ሊያስተምሯት ጣሩ፡፡ ማምሻ ግን ትምህርቱም ብዙ አልሆነላትም፡፡ የሰፈሩ ማንጓጠጥ ትምህርት ቤትም ተከትሏት ነበር፡፡ እየወደቀች እየተነሳች እንደምንም ዘጠነኛ ክፍል ደርሳ አቆመች:: የሻይ ቤት አስተናጋጅነት ሥራ እንዲያፈላልግላት ደላላውን በሽርን ብትጠይቀው፣ ያንን ጫት የተለሰነበት ጥርሱን
እየገለፈጠ “ማምሻ! በዚህ ፊት አስተናጋጅነት!?…”አላት አሉ፡፡ ይህም አንድ ሰሞን
ተሳቀበት…በኋላ በወር ሰማንያ ብር እየተካፈላት የሰፈራችን ቦኖ ውሀ አስቀጅ ሆነች::
ውሀ አታፍስሱ ያለቻቸው የመንደሩ ሴቶች ያንኑ ቁሰሏን በሽሙጥ ስንጥር እየነካኩ፣
በመልከጥፉነቷ እያሸሞሩ ቁጡ አደረጓት፡፡
“ቆጥባ መልከ ጥፉነቷን ልታጥብብት ነው?
እያሉ:: በነጋ በጠባ ጸብ ሆነ፡፡

አንድ ቀን ማምሻ አንዷን አሽሙረኛ እንደ ነብር ዘልላ ተከመረችባት፡፡ ማን ያላቅቃት?
የዘመናት ብሶቷን እዚያች ዕጣው እወደቀባት ሴት ላይ አራገፈችው፡፡ በትርምሱ የውሀ
መቅጃ እንስራም አልተረፈ፣ ተከለከከለ፡፡ ከዚያቹም ሥራ ተባረረች፡፡ ደግሞ የማባረሪያ
ምክንያቱ ግነት! “ሕዝብ እንድታገልገል በተቀመጠችበት ቦታ፣ ሥልጣኗን ተገን
በማድረግ፣ ተጠቃሚውን ኅብረተሰብ በመደብደብና ንብረት በማውደም ቦንብ ጣይ
አውሮፕላን እያበረረች አንድ ከተማ ሕዝብ የደበደበች ዓይነት! ኅብረተሰቡን
በመደብደብ እና ንብረት በማውደም!”

ተራ ፌዝና ስላቃችን አንገት ያስደፋት ማምሻ፣ ሁሉንም እርግፍ አድርጋ ትታ፣ ባልቴት
እናቷ በየሰው ቤት ሠርተው በሚያመጧት ሳንቲም ኑሮዋን እየገፋች የወጣት ጡረተኛ ሆና እቤት ተቀመጠች፡፡ ይኼ መገፋት አጉብጧት እንዳቀረቀረች፤ እንጀራዋን እዚያው ባቀረቀረችበት አገኘችው፡፡ ልክ እንዲሰምጥ ወደ ባሕር የገፈተሩት ሰው የሚያስጎመዥ ዓሣ ይዞ የመውጣት ዓይነት ነበር ነገሩ፡፡ ማምሻ እንዳቀረቀረች ኪሮሽና ክር አነሳች፡፡እንዳቀረቀረች መርፌና ክር ታጥቃ በመራሩ ድህነት ላይ ዘመተች፡፡ በሰፊው የድህንትጥቁር ሸማ ላይ ውበትን ዘራችለት፡፡ ከዚያ የተገፋ ልብ፣ ያ ውበት እንዴት ወጣ?እላለሁ አንዳንዴ፡፡
ውበታቸው የመንደሩን ብቻ ሳይሆን፣ ከየትና የት ድረስ የሚመጡ የከተማውን ሴቶችን የሚያሻማ፣ ከምሶብ ዳንቴል እስከ ኤልጋ ልብስ፣ ከኩርሲ እስከሶፋ ልብስ፣ ከመጋረጃ እስከ ሐበሻ ቀሚስ ድረስ የጥልፍ ማጎተሟን አሳረፈች፡፡ ሰፈራችን በሙሉ በማምሻ የእጅ ሥራዎቿ ተጥለቀለቀ፡፡ የማምሻ ጥልፍ ያረፈባቸው መጋረጃወች በየመስኮቱ ተሰቅለው ሲታዩ፣ ማምሻ ገፊዎቿን በእጁ ጥበብ ድል ነስታ፣ ባንዲራዋን በድል
እድራጊነት በየቤቱ የሰቀለች ይመስል ነበር፡፡

በመቋጨት ይሁን በመጥለፍ፣ የማምሻ እጅ ያረፈበትን የባህል ቀሚስ ይሁን ነጠላ ለብሳ
ያልተውረገረገች፣ አንድ የመንደሩ ሴት ብትኖር፣ ማምሻ ራሷ ብቻ ነበረች። እንዲህ እያገባኝ ገብቼ የማምሻን የእጅ ሥራዎች ስመለከት፣ ከሌሎች ጥልፎች የተለዩ ይሆኑብኝ ነበር። ፍዝዝ ያለ ቀለም ባላቸው ክሮች፣ ደማቅ መደብ ላይ የምትጠልፋቸው አበቦች የራሷን ምስል የምትስል ሠዓሊ እስክትመስለኝ፣ አንዳች የሚያሳዝን ስሜት ውስጥ የሚያስገቡ ነበሩ:: በዚህም ሥራዋ እራሷን ባልቴት እናቷን በክር ጎትታ፣አንገታቸው
ከድህነት አዘቅት ብቅ እንዲል አደረገች፡፡ እናቷ በየሰው ቤት መንከራተት አቁመው እቤታቸው አረፉ፡፡ መንደርተኛውም ከማምሻ መልክ ይልቅ የእጅ ሥራዎቿ ዓይኖቹን ጋርደውት ከመዝለፍ ይልቅ ወደማድነቅ እና ማክበር የተሸጋገረ መሰለ፡፡ በእርግጥም ማምሻ መልከጥፉ ፊቷን በብርቱ እጆቿ ሽፍናው ነበር፡፡

ስም ውስጥ ሟርት አለ፡፡ ማምሻ እንደስሟ ማምሻ ሆነች: ሁሉም ነገር የተቀያየረው ድንገት ነበር፡፡ የእጅ ሥራዎቿን ሙሉ ለሙሉ ከገበያ ውጭ የሚያደርግ አጋጣሚ። ፈጣን እና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የጥልፍ መኪኖች በከተማው ውስጥ እንደ አሸን ፈሉ።
በአንድ ጀምበር ድፍን መንደር የሚያለብሱ፣ በደማቅ ከሮች ፎቶ የመሳሰሉ አበቦችን
የሚጠልፉ የ “ሲንጀር መኪኖች፡፡ የማምሻ ተስፋ ሟሸሽ! ጥበቧም ከምንም እስከ ሲንጀር መኪና ባለው ክፍተት መሀል ማምሻ መሸጋገሪያ ሆነ። በኑሮ አድማሷ ላይ ድንገት ብቅ ያለች ጀምበሯ፣ ሙቀትና ብርሃኗን በቅጡ ሳታጣጥማት ድርግም ብላ ጠፍታ፣ ዳግም የድህነትና የማንጓጠጥ ዝናብ ያዘለ ደመና በላይዋ ላይ ያንዣብብ
ጀመረ፡፡ ዳግም ወደ ማቀርቀር፣ ዳግም አንገት ወደ መድፋት ተመለሰች፡፡ ግና ምንም ያልተነኩ ቱባ ክሮችን ሰብስሳ ወስዳ ለባለሱቁ ከድሩ በርካሽ ሸጠችለት ተባለ፡፡ ያም የማምሻ የጥልፍ ሥራ ማብቂያ ሆኖ በጎረቤቱ ዘንድ ተወራ፡፡ በዚህም ተቀለደ፡፡ “ማምሻ ኪሮሽ ሰቀለችተባለ፡፡ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መጫወት ሲያቆሙ
ጫማ ስቀሉ” እንደሚባለው መሆኑ ነው፡፡ቀስ በቀስ እናቷ ወደ ሰው ቤት ሥራ ተመለሱ፣ ማምሻም እናቷን ለማገዝ እንጀራ መጋርና መሸጥ ጀመረች፡፡ ታዲያ በዚህ መሃል ትንሽ በጎነት ያሳየቻት ሴት ብትኖር፣ ሎዛ ነበረች፡፡ ከአባቷ ጣውላ ቤት የእንጀራ መጋገሪያ ሳጋቱራ በነፃ እንድትወስድ አስፈቅዳላት ነበር፡፡

ባልገባኝ ምክንያት የሎዛ ዓይኖች ሁልጊዜ ማምሻ ላይ ነበሩ፡፡ የሰፈሩ ሰው ርግፍ አድርጎ
በተዋቸው ሰዓት እንኳን የማምሻ እጅ ስራ የተጠለፈባቸው ልብሶችን ትለብስ የነበረች
ሴት ሎዛ ብቻ ነበረች፡፡ እንደውም ለእኔም ከማምሻ የገዛችውን አንድ የባህል ልብስ
ስጦታ ሰጥታኝ ነበር…ለብሸው ግን አላውቅም፡፡
።።።።።።።።።።።
ሎዛ ደውላ ሄይ አብርሽ… ከሥራ ስትወጣ እቤት እመጣለሁ፣ ጠብቀኝ አለችኝ፡፡
ከሥራ ስመለስ ቀድማኝ እኛ ቤት ደርሳ፣ የምትወደውን የጦስኝ ሻይ እየጠጣች ከእናቴ
ጋር ሲያወሩ ደረስኩ፡፡ እናቴ ፊት ብትስቅም ገና ሳያት እንዳኮረፈች ገብቶኝ ነበር፡፡
"ሙሽሪት” አልኩና በትከሻዬ ገፋ አድረጊያት ገባሁ፡፡ እናቴን ተሰናብታ ተያይዘን እንደወጣን፣ “ማምሻ ጋ አካሂደኝ አለችኝ፡፡

ለምን?

“ሚዜነቷ እንደቀረ ልነግራት!”

ቀረ እንዴ?” ዞር ብላ በብስጭት አይታኝ፣

“ደስ አለህ?” አለችኝ፡፡

“ለምን ደስ ይለኛል? …ግን አለ አይደል …”

በውስጤ ግን ደስ ብሎኝ ነበር፡፡ በትዝብት አይታኝ፣

በቃ ቀርቷል፡፡ አባባ ተዪው አለኝ፡፡ ማሚ አሳምናው መሆን አለበት፡፡ማንም ሰው ከጎኔ
አልቆመም፣ ደከመኝ” አለች፡፡ ስልችት ያላት ትመስል ነበር፡፡ ተያይዘን እነማምሻ ቤት
ስንደርስ፣ ማምሻ የዘመመችው የጭቃ ቤታቸው ጋር ተያይዛ ከላስቲክ እና ከቆርቆሮ
ተሠራች ማድ ቤት ውስጥ ከጭስ ጋር እየታገለች እንጀራ ስትጋግር አገኘናት፡፡
ከማድ ቤቷ አጎንብሳ ስትወጣና አይታን ፈገግ ስትል ዓይኔን ማሳረፊያ ሌላ ቦታ ፈለግሁ፡፡
የማይለመድ መልከ ጥፉነት ነው ያላት፡፡ መልከ ጥፉ ብቻ አይደለችም… የሆነ በቀለኛ አጋንንት
ፊቷን በአጉሊ መነጽር እያየ ትንሽ ሰው ሊስብ ይችላል ያለውን ነገር ሁሉ እየለቀመ ያፈራረሰው ነበር የሚመስለው፡፡ እኔ ነኝ ያለ ደራሲ ይቅርና ፎቶ አንሺ እራሱ የማምሻን መልከ ጥፉነት በበቂ ሁኔታ አሳይቶ መጨረስ የሚችል እስከማይመስለኝ፣ ፊታ እንደ አዲስ አስገረመኝ፡፡ ምን ይሳነዋል ልሥራው ካለ ይሠረዋል፤ ላበላሸው ካለ ያበላሸዋል እላለሁ ለራሴ::

ወደ ቤታቸው እየመራች አስገባችን፣ የቤቷ ውስጥ ካሰብኩት በላይ እጅግ ንጹሕና በሥርዓት የተዘጋጀ ነበር የማምሻ ዘመን ያለፈባቸው ጥልፎች እንደሙዚየም ከአልጋ እስከ ኩርሲ በሥርዓት ለብሰው ተቀምጠዋል
👍3
#ማምሻ


#ክፍል_አራት


#በአሌክስ_አብርሃም


....አገሩ የበጎች ነው፤ ግን የበጎች ታሪክ ቦታ የለውም! በጎች ራሳቸው የሚተርኩት
የአንበሶችን የጀግንነት ጀብዱ ነው፡፡ ምናልባት ታሪኩ የበጎችን ስም ካነሳ፣ በጎች በአንበሶች እንዴት እንደተበሉ ከመተረክ አያልፍም፡፡ የበግ ቆዳ የለበሱ አንበሶች፣ ጠላታቸው የለበሰው ቆዳቸው ነው፤ ስለዚህ ይህን ቆዳ እንዲገፉትና ታሪካቸው እንዲጻፍ ትንሽ መርዳት አለብን፡፡ ብዙ አይደለም…ትንሽ! ለምሳሌ የራሳቸውን ቆዳ የሚገፉበት ቢላ ማቀበል፤ ሕመሙን ችለው የራሳቸውን ቆዳ መግፈፍና የራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡ ሌሎች ቆዳቸውን እንግፈፍላችሁ ሲሏቸው አይገባም፡፡ ማንም የማንንም ሕመም አያውቅም፡፡ቆዳ ለመግፈፍ በሰነዘሩት ቢላ፣ ሥጋቸውን ቦጭቀው የዕድሜ ልክ ጠባሳና ሕመም ሊተውብቻው ይችላሉ

እንግዲህ ልትፈላሰሚብኝ ነው ሎዛ” አልኩ እየሳቅሁ…ከእናቷ ኮርጄ ነው አባባሉን፡፡
ከተጋቡ በኋላ ባሏ ዳግም ወደ አውሮፓ ተመልሶ ነበር፡፡ አልፎ አልፎ ታዲያ ያው እንደሰፊታችን እየተገናኘን ሻይ ቡና እንላለን፡፡ ዛሬም እፈልግሃለሁ ብላ፣ ተገናኝተን ገና
ከመቀመጣችን፣ የአንበሳእና የበግ ተረኳን አዘነበችብኝ፡፡ ታዲያ ልቀልድ እንጂ በቁም
ነገር እያዳመጥኳት ነበር፡፡ ሎዛ ውስጧ የሆነ ነገር አስቦ እየተቁነጠነጠች እንደነበር
ታዝቤያለሁ ያሰበችው ምንም ይሁን ምን ካላደረገችው እንደማታርፍ አውቃለሁ።
እናም እየሰማኋት ነው፡፡

“ትላንት ማምሻ ደውላልኝ ነበር” አለች፡፡

ሎዛ! በቃ "ሶሪ" ብያለሁ፣ አጥፍቻለሁ፥ በሰዓቱ ከጎንሽ አልቆምኩም… እንደገና ስለዚያ ሚዜነት እንዳታነሽብኝ በፈጠረሽ በቃ!” አልኩ ምርር ብሎኝ ማምሻ ሚዜ እንዳትሆን ተባብረሃል እያለች በስልክም በአካልም ስትነተርከኝ ነው የከረመችው።

“ዝም ብለህ ስማኝ፣ እሱ ውስጥህ ስለሚጮህብህ ነው ራስህ ቀድመህ የምታነሳው፡፡አሁን የምለውን ስማኝ፣ ሌሊቱን ሳስብ ነበር፡፡ ስደሰት ነበር…የማወራህ ስለ ማምሻ አይደለም፡፡ ስለ እኔ፣ ስለ አንተ፣ ስለ እናትህ፣ ስለ ምናልባትም ነገ ስለምትወልዳት ሴት
ልጅ…ስለ ማኅበረሰቡ ነው፡፡ ስማኝ አብርሽ፣ ቢያንስ መስማት እንዴት ነው ያቃተህ?…ስማኝ' ተነጫነጨች!

ኦ ኬ እየሰማሁ ነው፣ አትጨቅጭቂኝ፣ አውሪኝ፣ እኔን ካልወቀስሽ ማውራት አትችይም

እየሰማህ አይደለም! ገና “ማምሻ ስል፣ የምናገረውን ቀድመህ ገምተህ፣ የራስህን ግምት
ነው እየሰማህ ያለኸው ይኼ ወሬ ቶሎ አልቆ ሌላ ርዕስ እንድንጀምር ነው የምትፈልገው፡፡ ሌላ ርእስ የለም …ስማኝ …”
"
"እንደዛ አላሰብኩም!"

አስበሀል! …” ተፋጠጥን እና ሳቅሁኝ፡ በቃ እንደዚህ ናት:: እና ደግሞ ልክ ስለነበረች ሳቄ
እፍረት የተቀላቀለበት ነበር፡፡

ተመስጣ ወሬዋን ቀጠለች፡፡ ማምሻ ወደ ጣውላ ቤታቸው በየቀኑ እየሄደች፣ ሳጋቱራ ሰብስባና ጣውላ ቤቱን አጽድታላቸው ትመለሳለች፡፡ የምትሄደው ሳጋቱራ በነፃ ለመውሰድ” ቢሆንም፣ በገንዘብ ሲመነዘር የሳጋቱራውን አምሰትናስድስት እጥፍ የሚሆን የፅዳት ስራ ሰርታላቸው ነበር የምትመለሰው፡፡ ይኼን ለረዥም ጊዜ ነው ያደረገችው::የዚያን ሰሞን ግን ሳጋቱራ ስትጠርግ አንድ ነገር ተፈጠረ፡፡ አንድ ሠራተኛ የዛፍ ግንድ
መሰንጠቂያ ማሽኑ ላይ ለማስቀመጥ ይታገላል፡፡ ግንዱ ከባድ ስለነበር አልቻለም፡፡ማሽኑን አስደግፎ የሚያግዘው ሰው ለመጥራት ወደ ውጭ ወጣ፡፡ ማምሻ እዚያው ቁማለች፣ ግን አግዥኝ አላላትም፣ ምክንያቱም ሴት ናት! ልጁ የሚያግዘው ሰው ይዞ
ሲመለስ ግን፣ ያ ከባድ ግንድ በትካከል መሰንጠቂያው ላይ ተቀምጦ አገኘው፡፡ ዙሪያውን
ተመለከተ፡፡ ሰው የለም ማምሻ ፈገግ ብላ “ላግዝህ ብዬ ነው” አለችው፡፡ አንዲት ሴት
ለወንድ ያቃተ ግንድን ገፍታ ማሽን ላይ ማስቀመጧ የሚዋጥላቸው አልሆነም፡፡ ቢሆንም
በነገሩ ተሳስቀውና ቀልደው አለፉት፡፡ ማምሻ ግን ሐሰቧ በዚያ አልቆመም፡፡ ሎዛን ቃል በቃል እንዲህ አለቻት፡፡

አስቀያሚ ነኝ፡ ግን ጤነኛ ነኝ! እጆቼ ቆንጆና ለስላሳ አይደሉም፤ ግን ጠንካራ ናቸው
ጸጉሬ ቁጭራ ነው፤ ጸጉሬ የበቀለበት ጭንቅላቴ ግን ያስባል… ይማራል፤ ይረዳል! እዚህ
አልጋና ቁምሣጥን፣ ሶፋና በር የሚሠሩት ወንዶች፣ ከእጅ፣ ከአእምሮና ከጥንካሬ ውጭ
ከእኔ የተለየ ምንድን ነው ያላቸው?.ምናልባት ልምድ፡ እሱንም ቢሆን እዚሁ ስለቆዩ ነው፡፡ ስለዚህ እኔ ለምን ሳጋቱራ እጠርጋለሁ? እነሱ ለምን ይኼን ሁሉ ነገር በጥሩ ክፍያ
ያመርታሉ?ለምን…?”

ሎዛ ትክ ብላ አየችኝና ንገረኝ እስቲ፥ ወንዶቹ ምንድነው የተለየ ነገር ያላቸው”ትከሻዬን ወደላይ ሰብቄ “ምንም” አልኳት።

“ምንም! ብላ ደገመችውና፣ ማምሻ አባባን እንዳስፈቅድላትና እንደ ኣንድ ሠራተኛ
እንዲያሰለጥናት እና እንዲያሠራት ነገረችኝ፡፡ ለረዥም ጊዜ ሠራተኞቹ የሚሠሩትን
ስትመለከት እና መስራት እንደምትችል ስታስብ እንደነበር፣ ትንሽ ካለማመዷት እሷም
መሥራት እንደምትችል ነገረችኝ፡፡ ውስጤ እንዴት እንደተደሰተ አትጠይቀኝ፡፡ ለአንዲት ሴት በተለይ “ቆንጆ ሴት” ነን ብለን ለምናስብ ሴቶች፣ አቅማችንን እንዳንጠቀም እስር ቤት የሚሆንብን የራሳችን ቁንጅና ነው፡፡ የራሳችን ቆዳ የራሳችን እስር ቤት ነው!

በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሴትነት እና ቁንጅና የሚባል የእስር ፍርግርጋችንን እያስዋብን ተሟሙቀን የወንዶችን ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሆነናል ሁሉም እስር ሰንሰለቱ ፈጦ አይታይም እንደውም አንዳንዱ እስራት ለታሳሪው ለራሱ ጭምር አይታይም፡፡ ማኅበረሰቡ አንዲትን ሴት የብረት መዝጊያ የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ፤ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም! ስለዚህ የእነሱን የምኞት ስር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት፣ አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሮዋንም ሳይሆን እግሯን እንድትከፍት ከሕፃንነቷ ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል”
እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መራመድ ነው፤ ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ
እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ በሥነጽሑፉ፣ በፊልሙ አእምሮዋ ውስጥ ስታጭቅባት ኑራለች፡፡ ለዚያም ነው ከፊታቸው የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ረግጠውና ዋጋ ከፍለው ወዳሰቡበት ከሚራመዱ ሴቶች ይልቅ፤ ከየትም ባገኟት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው፣ እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሊያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት እግራቸው ከለሰለሰ በኋላ፣ አዝሎ
የሚያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ፡፡

እጅ የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መሥራት ነው ብዙ የፋሽን እና ዘመናዊውን የውበት ሚዛን የሚደፉ 'ዘመናዊ ሴቶች እጃቸው ከሚበላሽ ስማቸውም ሕይዎታቸውም ቢበላሽ እና እጃቸው እንደለሰለሰ ቢኖር ይመርጣሉ፡፡ ልስላሴ ሳይሆን በንጽሕናና ራስን ችሎ መቆም እንጨባበጥ ከተባለ ማንናት ደፍራ እጇን የምትዘረጋ?! ለብዙኃኑ ወንዶች ጠንካራ የሴት እጅ አገርን ያቆመ ሳይሆን፣ ሴትነትን የገፋ መስሎ ነው የሚታያቸው ለዚያ ነው በሥራ ስለደደረ የሴት መዳፍ፣ ዘፋኙም መዝፈን፣ገጣሚውም መግጠም
የማይወደው፡፡ድንጋይ ፈልፍሎና እምነበረድ ጠርቦ ውብ የእጅ ጣት ያላት ሴት ሐውልት
የሚያቆመውን ቀራጺ እጅ ግን ተመልከተው፣ በሥራ የጎለዴፈ ሆኖ ታገኘዋለህ ከግማሽ
በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሴት በሆነበት አገር፣ ሴቶች እጃቸውን አስውበው መደርደሪያ
ላይ እንዲያስቀም ጡት በማድረግ፣ ለውጥ ጠብ አይልም፤ እንዲሩ ማደፋፈር እጅ ወደተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማ እንዲመለስ መሰበክ አለበት!

ማምሻ ቆንጆ አይደለችም ዕጣ ፋንታዋ ዓይንና ጥርሷ ላይ ሳይሆን፣ እጆቿ ላይ እንዳለ
ግን ተገልጦላታል ወንድ በእግሮቿ መሃል ካላለፈ የሚያልፍላት
👍1
#ማምሻ


#ክፍል_አምስት(የመጨረሻ ክፍል)


#በአሌክስ_አብርሃም


ሎዛ ከዓመት በኋላ ባሏ ጋ ጠቅልላ አውሮፓ ገባች፡፡ ያው እዚህ እንደነበረው ቶሎ ቶሎ
ባንገናኝም አልፎ አልፎ ትደውልና ተጨቃጭቀን፣ ተሰዳድበን፣ አኩርፋ ጆሮዬ ላይ ዘግታብኝ፤ ከሆነ ጊዜ በኋላ መልሳ ደውላ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ እናወራለን፡፡ በመሃል ሰፈራችን ከላይ እስከታች ፈራርሶ ጎረቤቱ ሁሉ ተበታተነ፡፡ ሰፈራችን ሲፈርስ አብሮ ያልፈረሰ ነገራችን አልነበረም፡፡ ስንድህ፣ ዳዴ ስንለማመድ የትንንሽ መዳፎቻችን አሻራ
የታተመበት ደጅ ከታሪክ ገጽ ተሰረዘ፣ የተላለፍንባቸው መንገዶች ዳናችንን እንደያዙ
ጠፉ፣ የቆምንባቸው ጥጎች ላይመለሱ ከሰሙ፣ ከየት መጣችሁ? ቢሉን ዙረን የምነጠቁመው ነገር እስከናጣ ሰፈራችን… ትንሽ አገራችን ፈረሰች!! ማንም ሰው የመጀመሪያ አገሩ ሰፈሩ ነው፡፡ አገራችን ፈረሰች!! ከሎዛም ጋር እንዲሁ መደዋወላችን እየተቀዛቀዘ ሂዶ ሙሉ ለሙሉ ተጠፋፋን!! ጭራሽ እኔ የስልክ ቁጥሬን ከቀየርኩ በኋላ ፊት የሚያውቁኝ የሰፈር ልጆች ጋር ሁሉ ተጠፋፋሁ፡፡ ዓመታት ነጎዱ፡፡ ትላንታችን
ወደ ኋላ ሮጠ፡፡ አዲስ ሕይዎት አዳዲስ ጓደኞች ረብርበን ባለፉ ቀናቶች ላይ ከፍ ብለን ቆመን፡፡ በቆምንበት ከፍታ ትላንታችንን ረስተን ነገን ልናይ ተንጠራራን፡፡
።።።።።።።።።።።
ከሰባት ወይም ስምንት ዓመት በኋላ ይመስለኛል፣ የጓደኛችን እናት አርፈው፣ የአስከሬን ሣጥን ልንገዛ ሁለት ሁነን ወደ ፒያሳ ሄድን፡፡ ከተደረደሩት ሱቆች ከአንዱ ወደ ሌላው እያልን ዋጋ ስናወዳድር ቆይተን፣ ወደ እንዱ መሸጫ ጎራ አልን፤ ገና ከመግባታችን ሁለት ወጣት ልጆች አጣደፉን፡፡ እየተቀባባሉ ስለ አስክሬን ሣጥኑ ጥንካሬ፣ ስፋት፣ ምቾት ሳይቀር እየነገሩ አግለበለቡን፡፡ ዋጋ ቀንሱ አትቀንሱ ስንከራከር፣ ድንገት ከውስጥ
ቀንሱላቸው የሚል የሴት ድምፅ ሰምተን ዞር አልን፡፡ጠቆር ያለ አጭር ጋውን የለበሰች
ሴት፣ እጅና እጁን ጋውኑ ኪስ ከትታ ከኋላችን ከነበረ ከፍል ብቅ አለች፡፡ በግርምት ፈጥጨ ቀረሁ፡፡ ይሄን ፊት ማን ይረሳል …ማምሻ ነበረች፡፡

ማምሻ” አልኳት ፈገግ ብዬ፣

እንዴ! አብርሽ ባልሆንክ…ትልቅ ሰው! ትልቅ ሰው…” ጮኸች መጀመሪያ ለማጣራት
ብላም እንደሆን እንጃ፣ ግርምቷን ቆም አድርጋ፣
“ምነው? ማን ሙቶባችሁ ነው?” አለችኝ፡፡

“የጓደኛችን እናት ናቸው

የባጥ የቆጡን እያወራን፣ እንትና ደህና ነው? እነ አትናስ? እየተባባልን የአስከሬን ሣጥኑን ራሷ መረጠችልን፡፡ ልጆቹ ሳጥኑን እስኪያዘጋጁልንና እስኪጭኑት ድረስ፣ ወደ ውስጥ አስገብታን በግራና በቀኝ የአስክሬን ሣጥን በተከመረበት ሰፋ ያለ ቢሮዋ ውስጥ፡ ሻይ ጋበዘችን፡፡ በጣም ጎበዝ ጣውላ ሠራተኛ ከመሆን አልፋ፣ የራሷን ትንሽ ጣውላ ቤት ከፍታ ነበር፡፡ እዚህ ሥራ ላይ “ምን እግር ጣለሽ” አልኳት የከበቡንን የአስከሬን
ሣጥኖች እያየሁ፣

ሳቀችና እማማ ስታርፍ ራሴ ነኝ የአስክሬን ሣጥኗን የሠራሁላት….. አልጋ፣ ሶፋ፣ ቁም
ሳጥን እንሠራለን፡፡ ለምን እንደሆን እንጂ ከዚያ በኋላ የአስክሬን ሣጥን ስሠራ ደስ ነው
የሚለኝ፡፡ ወደድኩት! ሳጥኖቹን ስሠራ ሰላም ይሰጠኛል፡፡ ጨርቆቹ ላይ ያሉትን ጥልፎች የምሰራው ራሴ ነኝ፤ ሰዎች ሲሞቱ ከነሣጥናቸው ወደ እግዚአብሔር የሚያርጉ ይመስለኛል …" እግዚአብሔር ሣጥኖቹ ብቻ ሳይሆን በጥልፎቹም የሚደመም ይመስለኛል ብላ ሳቀችና “ይኼውልህ ይችን ሱቅ ተከራይቼ በዚሁ ሥራ ቀጠልኩ፡፡
ማምረቻትን ከኋላ በኩል ነው፡፡ ወይ አብርሽ ትልቅ ሰው ሆንክ ብላ በመደመም እጇን እፏ ላይ ስትጭን የጋብቻ ቀለበት ማድረጓን አየሁ፡፡ ግን ምንም አላልኩ፡፡

እማማ መቼ አረፉ” አልኳት፣

ትንሽ ዝም ብላ ቆየችና “አራት ዓመት ሆናት” አለችኝ፡፡

ሶሪ…" ዝም ተባብለን ቆየን! እንዲሁ ዝምታውን ለማስወገድ

የሰፈር ሰዎችን አግኝተሻቸው ታውቂያለሽ?» አልኳት፣

እዎ ተራ በተራ እየሞቱ ነው፣ ከዚሁ ነው ሣጥን የሚወስዱት፣ ደንበኛ ሁነናል…”አለችና
የአሽሙር የሚመስል ፈገግታ ፈገግ ብላ ከጠረጴዛዋ መሳቢያ ውስጥ ካርድ አውጥታ
ሰጠችኝ፡፡ “ማምሻ የጣውላ ሥራ አልጋ፣ ሶፋ፣ በሮች እንሠራለን እንዲሁም የተለያዩ
የአስከሬን ሣጥኖችን እናቀርባለን ይላል።

ሳጥኑ ተጭኖልን ስንወጣ፣ ማምሻ ፈገግ ብላ ጨበጠችኝና “ሎዛ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ መጥታ በእግር በፈረስ ብታስፈልግህ አጣችህ..ፖስታ ስጭው ብላ እኔ ጋር
አስቀምጣልህ ነበር፤ እቤት ነው ያለው፡፡ ያለህበትን ንገረኝና የሆነ ቀን አቀብልሃለሁ
ወይም መጥተህ ውሰድ አለችኝ፡፡ የእጇ ጥንካሬ እጄን የቆረጠመኝ እስኪመስለኝ አጥብቃ ጨበጠችኝ

ሰንመለስ፣ አብሮኝ የነበረው ጓደኛዬ “ማናት?” አለኝ፡፡

ማምሻ ትባላለች የሰፈራችን አንደኛ አስቀያሚ ልጅ ነበረች…” ብዬ ከመጀመሬ፣

“አሁንም'ኮ በጣም አስቀያሚ ናት! ጭራሽ ይኼን መልክ በአስክሬን ሣጥን ተከቦ ማየት፣ አስበኸዋል!?” አለኝና በራሱ ቀለድ ከትከት ብሎ ሳቀ፡፡ እውነቱን ለመናገር የማምሻን መልክ ነገሬ ብዬ አላስተዋልኩትም ነበር፡፡

ከሳምንት በኋላ ለማምሻ ደወልኩላትና ሎዛ የተወችልኝን ፖስታ ልትሰጠኝ አንድ ካፌ
ተገናኘን፡፡ ቡና ጋብዣት እያወራን በወሬ ወሬ “አላገባህም?” ከሚል ጥያቄ ተነስቶ ነገሩ
ወደ እሷው ዞረና ማግባቷን ነገረችኝ ፤ ልጅ መውለዷንም ጭምር ፡፡ “እንኳን ደስ ያለሽ?
ከማለት ባለፈ ምንም ነገር ለመጠየቅ ፈራሁ፡፡ “ማንን አገባሽ” አልል ነገር “ማነው አንችን ያግባ!” ይመስልብኛል ብዬ …..ዝምታ ዓይኔን እዛና እዚህ ሳንከራትት ራሷ እግዚእብሔር ጥሩ ሰው ሰጠኝ …የሎዛ አባት ቤት ሶፋ የሚሰራ፣ ዳንኤል የሚባል ልጅ ታስታውሳለህ ? አለችኝ አላስታወስኩትም፡፡ የሎዛ መልክ ራሱ ደብዝዞብኛል፡፡

እሱ ጋር ተጋባን :-እጄን ይዞ ነው ጣውላ ስራ ያስተማረኝ፡፡እንጋባ ሲለኝ እየቀለደ ነበር
የመሰለኝ

ለምን?” አልኳት፡፡ የራሌ እንዳላወቀ መምሰል እያስጠላኝ::

ሳቀች እያወከው አብርሽ እኔን በዚህ መልኬ፣ እንኳን ማግባት አብሮኝ የሚቆም ወንድ አልነበረም ሃሃሃሃሃ ብላ ሳቀች፡፡

“ይሄን ያህልማ አታካብጅው አልኩ፣ ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ በሆነ ማጽናናት፡፡

ፈገግ ብላ ስንተዋወቅ” በሚል አስተያየት አየችኝ “እንደተሳቀስክሁ ነው የኖርኩት…ከሰው
እንደራቅሁ፡፡ ስወልድ እንኳን አስብ የነበረው እንደ እናት ስለ ልጄ ደህንነትም ሆነ ስለ ምጡ ስቃይ አልነበረም፡፡ ከምጡ በላይ ሐሳብ የሆነብኝ የልጄ መልክ ምን ይመስል ይሆን? የሚል ጭንቀት ነበር፡፡ አምጥተው ሲያሳቅፉኝ፣ገና ሳትታጠብ በፊት…ፍከት ባለ ቆዳዋ ከእኔ ዕጣ ማምለጧን ስመለከት በደስታ አለቀስኩ፡፡ ማንም ኤልገባውም! እናት መሆን ብቻውን ያስለቀሰኝ መስሏቸው ነበር፡፡

ዘጠኝ ወር ያረገዝኩት ጭንቀት እንደ መንታ በማሕጸኔ ከልጄ ጋር እያደገ ነበር፡፡
ተገላገልኩት፡፡ ልጄ ምኗም እኔን ባለመምሰሉ ፈጣሪን አመሰገንኩ፡፡ ሁልጊዜ የሚገርመኝ
ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ባለቤቴ አንቺን የምትመስል ልጅ ነው የምፈልገው ያለኝን
ነገር! እኔን ለማጽናናት ብሎ ይናገረውም አልያም ከልቡ ይሁን እንጃ! ብቻ ይሄ ንግግር ውስጤ ቀረ፡፡ ሰዎች “ቁርጥ አባቷን ሲሉ ነፍሴ ሐሤት ታደርጋለች አባቷ እኔን ከጥላቻ… ልጃችንንም እኔን ከመምሰል ሳያውቀው አድኖናል፡፡ በሄድኩበት ሁሉ ሎዛየንና ባለቤቴን ስማቸውን አንስቸ አልጠግብም፡፡ ነፍሴ ታከብራቸዋለች አሁንም ግን እንደገና ልጅ መውለድ እፈራለሁ፤ እኔን ብትመስልስ እያልኩ፡፡ አሁንም እሰጋለሁ… አንድ ቀን ባሌ እኔንም ልጄንም ጥሎን ቢሄድስ እያልኩ፡፡ እንጃ ከዚህ በሽታ እንዴት እንደምፈወስ!

የሎዛን ፖስታ ስከፍተው
👍5