አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_አንድ


#በዮርዳኖስ

ያለሁበትን ቦታ በውል ባላውቀውም ግን ኢትየጵያ ወስጥ እንዳለሁ እርግጠኛ ነኝ።ሆኖም ስፍራወን እስካሁን በትክክል አላወኩትም።አከባቢው በአስፈሪ ጨለማ ተከቧል የጫካ ድባብ አለው ግን ጫካ አይደለም።ከደቂቃዎች በፊት ስለነበረው ነገር ብዙ ማስታውሰው የለም ራሴን ስቼ ነበር እናም አሁን ያለሁበትንም እንጃ።የነብሳት ድምፅ ከየምሽጋቸው ሲያስተጋባ ይሰማኛል።ውስጤ በፍራቻ ሲርድ ድንጋጤ በያንዳንዷ የደም ስሬ ሲሰራጭ ይታወቀኛል ሰውነቴ የኔ አልመስልሽ እስኪለኝ ድረስ በድን ሆኗል።በርግጥ ብቻዬን አይደለሁም በግምት ወደ አስር እንሆናለን ማናቸውንም ባላወቃቸውም ግን ከኔው እድሜ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ወንድና ጥቂት ሴቶች ወጣቶች ዙሪያዬን ልክ እንደኔው ግራ ሲጋቡና ሲያለቅሱ ይታያሉ።የት እንዳለን የምናውቀው ነገር የለም ሁሉም ግራ ተጋብቷል።እኔም እዚ እንዴት እንደተገኘው የማውቀው ነገር የለም እጆቼ ወደ ኋላ ተጠፍረው እንደታሰሩ ከህመሙ ተረድቻለው።ሌሎች አብረውኝ ያሉ ልጆችም እንደዛው አንዳንድ አፋቸውን የታሰሩ ሴቶችም ይታዩኛል ሆኖም ይጮሀሉ።ነብስ ተጨንቃ አይን ባያለቅስ አንደበት እንዴት ዝም ሊል ያስችል? ሌላው እንደኔ በድንጋጤ ደርቆ ግራ መጋባቱ ብቻ ከፊቱ ይነበባል የቀረው ያለቅሳል።ሁሉንም ከቃኘው ቡኋላ አንጋጥጬ ወደላይ ተመለከትኩ ከከበቡን ዛፎች ባሻገር ጥቁር ሰማይ ብቻውን ካላንዳች ኳክብትና ጨረቃ ጨልሞ ይታያል።ከአምላክ ጋር ፊትለፊት እማወራ ይመስል "የት ነኝ አንትስ ወዴት ነህ?" በውስጤ አነበነብኩ።ከንፋሱ ጋር አብሮ ከሚመጣው ሽውታ ጋር አንዳች ድምፅ የሰማው መሰለኝ ጆሮዬን ሰጠው አበረውኝ ካሉ ልጆች ለቅሶና ድምፆች ማለፍ አልቻለም።አይኖቼን ጨፍኜ የነበርኩበትን ለማስታወስ ሞከርኩ ።ምንም። አይምሮዬ ባዶ የሆነ መሰለኝ።መልሼ ወደ አከባቢው ትኩረቴን አደረኩ በድጋሚ ድምፅ ሰማሁ።ልክ ነበርኩ ድንገት ካለንበት ራቅ ካለ ስፍራ የባትሪ ና የእሳት ብርሀን ጭላንጭል ወደኛ ሲቀርብ አስከትሎም በዛ ያሉ ሰዎች ድምፅ በግልፅ ለሁሉም ተሰማ።ብርሀኑ ሲቀርብ ያለንበት ጫካ የመሰለው ቦታ በግልፅ ታየን ዙሪያውን በቀንጭብ የታጠረና በዛፎች የተሞለ ሰፊ ግቢ ነው።ሰዎቹ ሲቃረቡ ጫጫታ ተጀመረ ሁሉም ተደናገጠ ፈራን ግማሹ ያለቅሳል ሌላው ለእረዳታ የድረሱልን ጩኸቱን ይጮሀል የቀረው አለቀልን ሲል ሌላው እባካቹ ብሎ ይማፀናል።እኔ ብቻ ሳለሆን አልቀርም የደነዘዝኩት።ድንገት ኬት መጣ ያላልኩት እጅ ፀጉሬን ጨምድዶ ወደ ላይ ሲጎትት የደመ ነብሴን ተንደርድሬ ተነሳው ሌሎቹንም ልጆች እንደዛው ሰዎቹ ገና በአንደኛው የቅንጭብ መግቢያ እየገቡ ነበር ስለዚ ሲጠብቁን የነበሩ ሌሎች ሰዎች እዚው ባቅራቢያችን ነበሩ ማለት ነው።አየገፈታተሩ ና ሲከፋም በምት ጭምር እየተመራን እዛው አከባቢ ወዳለ የከብት ጋጣ ወደሚመስል ቤት አስገቡን።እርስ በእርሳቸው ቢያወሩም ግን ቋንቋቸው ሊገባኝ አልቻለም እነማን ይሁን? ምን ይሁኑ? ለምን ይያዙን? የሚያውቅ እንደሌለ ግልፅ ነው አብረወኝ ያሉ ልጆች እነማን ይሁኑ የማውቀው ነገር የለም።እዚ ስንደርስ ጠመንጃ የያዙ ሰዎች ቀደመው እየጠበቁን ነበር።እናም ለእያንዳንዳቸው ተሰጣቸው ጫጫታው ባሰ።አንዱ ሰውዬ ለየት ብሎ ከመካከላቸው
ወቶ ባላወቅነው ቋንቋ አየጮኸ ፊት ለፊታችን ቆሞ አፈ ሙዙን ወደኛ አስተካከለ።አሁን ነገሩ የገባኝ መሰለኝ በእርግጥ ምን ብሔር ይሁኑ እኛም ኬትኛው ብሔር ተወክለን እንደመጣን ባይገባኝም ግን ከዚ ቤት ማናችንም በሕይወት እንደማንወጣ ከፊታቸው ገፅታና ቁጣ ተረዳው።እኔ ብቻም ሳለሆን ሁሉም ወጣቶች ፊት ላይ ይሄ ተስፋ መቁረጥ ተነበበ።ሰውየው ቁልቁል እየተመለከተን ይለፈልፋል ሁሉም በአስፈሪ ፀጥታ ሚሆነውን ይጠብቃል። ያላዘዝኩት እንባዬ ቁልቁል በጉንጮቼ ላይ ሲወርድ ታወቀኝ ድንጋጤ በድን አካሌን ያፈረካከሰው መሰለኝ።ስቅስቀታ ያጀበው ፀጥታ ና የሚያነቡ አይኖች ሁሉም ሞቱን ሊገናኝ ሕይወትን እየተሰናበተ ይመስላል ።ሁሉንም ካየው ቡኋላ እሱ ጋር ስደርስ አንገቱን እየወዘወዘ በፈዘዘ አይን እያየኝ ነበር ከመጀመሪያው ጀምሮ እንደኔ ረጅም ዝምታ ውስጥ የነበረ ወጣት የማውቀው መሰለኝ ።አው አውቀዋለው አንድ ግቢ ነው የምንማረው አስተወስኩት "አልቆለናል ብሩክቲ"አለኝ በደከመ ድምፅ እንባው አየወረደ።የመጀመሪያው ጥይት በሱ ላይ ሲያርፍ ቤቱን እንደገና ጩኸት ሞላው። ያኔ ደንግጬ ነቃሁ።
:
:
💫 ይቀጥላል💫

ለአስተያየታችሁ እንደሁም ማስተካከል ያለባትን ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት
👍3
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_ሁለት


#በዮርዳኖስ

ከሌሊቱ 10:52 አይኖቼን ስገልጥ ከክፍሌ ጨለማ ጋር ተፋጠጥኩ በዳበሳ መብራቴን አብርቼ በፍጥነት አከባቢዬን ቃኘው።አስማት ወይንም ተዓምር ሊመስል ይችላል ግን አሁን እቤቴ ነኝ።ትንፋሼ ይቆራረጣል።ከፍተኛ ሙቀት ስለተሰማኝ ከብርድልብሴ ወጣው ላብ ጥምቅ አድርጉኛል። ልቤ ክፉኛ ይመታል በፍጥነት ተነስቼ ወደ በሩ አመራው።ነብሴ ስለ ተጨነቀች እንጂ የትም ልሔድ አልነበረም።ተመልሼ አልጋዬ ጫፍ ተቀመጥኩ ቀን ማስበውንና ምፈራው ትውስታ ነው ሌሊት በህልሜ ሳይ እና ስቃዥ የማድረው።

ለሊቱ በሀይለኛ ፀጥታ ተውጧል ምንም ድምፅ የለም።ወደ መስኮቴ በቀስታ ሄጄ ከፈትኩት ሊነጋ ማቅላላት ጀምሯል ካልተሳሳትኩ ከደቂቃዎች ቡሗላ የመስጊድ አዛን መሰማት ይጀምራል።ፍፁም እርጋታ አና ፀጥታ የተሞላው ሌሊት ደስ በሚል እና ሰላምን በሚያስተጋባ ቀዝቃዛ ንፍስ ታጅቧል ። ይሄንን በነፈሰበት አብረውት እኩል በነፃነት ከሚደንሱት ዛፎች ውጪ የሚያስተውለውም ሆነ የሚያጣጥመው ግን ያለ አይመስልም። እንዳለመታደል ሆኖ ግን እኔም እንኳን እንዲ እያስተዋልኩት ልደሰትበትም ሆነ ላጣጣመው አልቻልኩም። ምክንያቱም ደግሞ ከእርጋታውና ፀጥታው ይልቅ ውስጤ ያለው ጩኸት እና ጫጫታ ይበልጡኑ ስለሚሰማኝ እና ስለሚበረታ ነው።ተመልሼ ወደ አልጋዬ አመራው ግን እንቅልፌን ፈራሁት።ቀሪዎቹን ሰዓታት ማሳለፊያ ነገር መፈለግ ሰይኖርብኝ አይቀርም።

ከሌሊቱ11:20 እንቅልፍ የሚባል ባይኔ ዝር አላለም።ሴከንዶች ደቂቃን ደቂቃዎች ሰዓታትን እየተኩ ይሄዳል። ለኔ ግን የቆመ ነው የሚመስለው ።
በማያቋርጥ ቅዠት የተሞላ ቀን እና ለሊቶችን ማሳለፍ ከጀመርኩ ሰነባበትኩ።ሰው ያላወቀውን ህመም ከታመምኩ ቆየ፣ሊነግሩት በማይቻል ሰው በማይረዳውእና ሊገለፅ በማይቻል ጥለቅ ፍርሀት ውስጥ መዋልና ማደር ከጀመርኩ ሳምንታት አልፈው ወር አስቆጠረዋል።ራሴን ማውራት ወስጤን ማድመጥ እፈራለው ሆኖም ግን ውስጤን ዝም ማሰኘት አልችልም ያለማቋረጥ ይጮሀል።ንዴት፤ቁጭትና ፀፀት፤ቂም፤ተስፋ መቁረጥ ይሁን እልህ በትኛውም ቃል በትክክል ልገልፀው ያልቻልኩት ስሜት ውስጤን አጨልሞታል።

ምናልባት አንዳንዴ ያለሁበትን እረሳለው ስለነበረውም እንደዛው አይምሮዬን ስቼ እቆይና ስመለስ ደግሞ ላመልጠው ካልቻልኩት መጥፎ ትውስታ ውስጥ ራሴን አገኘዋለው።እንደገና ያንንም ልረሳው እና ባዶ ልሆንም እችላለው።ብቻ በዚ ሁኔታ ቀናትን አሳልፍያለው ወደ ራሴ ለመመለስ የሚወስድብኝ ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ ባላውቅም ግን ይሄ ስቃዬ እንዲያበቃና ከዚ ቅዠት መውጣት እፈልጋለው።
ስሜን እንዳላስተዋውቃቹ ልረሳው ስለምችልና በውል ስለማላስታውሰው ይቆያቹ።ግን....ብሩክቲ ነኝ ይሆን እንዴ....? እንጃ።

ከሌሊተለ 11:40 የምፈልገውን አላውቀም ግን የሆነ ነግር ፈልግያለው ያጣሁትን ባላውቅም ግን አንዳች ያጣሁት ነገሮ አለ ግን አይምሮዬ ጥያቄውን ብቻ እንጂ መልሱን አይነግረኝም።
ለደቂቄዎች በወረቀት ላይ ለመፃፍ ሞኩርኩ ግን ምን ልፅፍ አልቻልኩም ከባዶ ነጭ ወረቀቴ ጋር ተፋጠጥኩ ግን የምፅፈው ነገር የለኝም ወይም የምፅፈውን አላውቅም።የነበርኩበት የት ነው አንዴትስ መጣው ማን አመጣኝ ኬትስ ነው የመጣሁት ሌሎቹስ ታድያ...??? መልስ የሚሰጠኝ የለም ግን አይምሮዬ የሚያሰማኝ ያንን ስቃይ የተሞላበትን ቅዠቴን የው።ለምንድነው በደንብ ማስታወስ ማልችለው?እንጃ ቢያምም ግን የግድ ማስታወስ እፈልጋለው ደሞም አለብኝ።
ለሊቱ ነግቶም ከክፍሌ ንቅንቅ አላልኩም አሁንም ከባዶ ወረቀቴ ጋር እይደተፋጠጥኩ ነው ምክንያቱም መመለስ አለብኝ። ስሚ....ስሚ...."ሔዋን ሔዋን "የክፍሌ በር ተንኳኳ።አው ስሜ በትክክል ሔዋን ነው ሔዋን በድሉ እናም የሚጠራኝ አባቴ ነው እቤቴ ነኝ የምማረው እና የነበርኩት ግን university ነው የ3ኛ ዓመት ህክምና ተማሪ።ግን የት? እንጃ።
"ሔዋን" አባቴ ነው "አቤት አባ ግባ"አልኩት።"ሰላም አደርሽ ልጄ" አለኝ።ጥያቄውን እንዲሁ በዘልማድ መመለስ ስላልፈለኩ ትንሽ አሰብ አድርጌ አንገቴን ነቅንቄ "አይ ሲያቃዠኝ ነው ያደረኩት"
"ያስታወሽው ነገር አለ እንዴ?"ፀጉሬን አየዳበሰ ጠየቀኝ አሁንም አሰብ አረኩና "ማስታወስ የማልፈልገው ነዋ...."አልኩት እንባ ሊተናነቀኝ እያለ.....



💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየታቹ እንዲሁም ማስተካከል ያለባትን ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት
👍2
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_ሦስት


#በዮርዳኖስ

"አይዞሽ የኔ ውድ ማድረግ የምትፈልጊው ነገር አለ? ለምሳሌ መውጣት ወይም ሌላ ነገር...?"
እንዲያው ለአመል ይጠይቀኝ እንጂ ባለፉት ቀናት ብዙ ነገር አንዳላደርግ ሲከለክለኝና ሲደብቀኝ እንደነበር አስተውያለው ለምሳሌ ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንዲሁም ሞባይል ኢንተርኔት አንዳላይ አድርጎኛል።ከቤት መውጣቱንም ቢሆን አብሮኝ ካልሆነ አያስወጣኝም።ለኔ ተጠንቅቆ እንደሆነ ቢገባኝ ግን ማወቅ እና ማየትን እፈለጋለው ከቤት መውጣትንም እንደዛው።ግን አባቴ ስጋት ያለበት ይመስላል ደግሞም ይገባዋል ምክንያቱም ለሱ ብቸኛ ልጁ ነኝ ሊያውም ካለናት ያሳደገኝ።ያ ማለት ግን ከናቴ ጋር ተጣልተዋል አልያም ሞታለች ማለት አይደለም ሚስጥሩ ሌላ ነው።ለጊዜው ግን እኔና አባቴ ከአንድ ሰራተኛችን ጋር ነው የምንኖረው።ሰራተኛ ለማለት ግን ይከብዳል እህና አብሮ አደጌ ብላት ይሻላል። ብርቱካን ትባላለች የዋህ እና ንፁ ኢትየጵያዊ ምርጥ እናትና ጠሩ እህት ነች በቃ ከዚ ሌላ መግለጫ የለኝም።
አባቴ ላቀረበልኝ ጥያቄ መልስ"ከስራ ልትቀር...?"አልኩት በዘዴ "አንቺ ከፈለግሽ ካንቺ አይበልጥም"አለኝ
"አይ ብቻዬን ነው መውጣት የምፈለገው ካለሆነ ይቅር"አልኩ።አባቴ በረጅሙ ተንፍሶ"በርግጥ አሁን ይበልጥ ትሻያለሽ ደና ነሽ ግን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወደራስሽ እስክትመለሽና የቅርብ ጊዜ ትውስታሽ እስኪመለስ መጠበቅ አለብሽ ካልሆነ ግን ትንሽ ከደገኛ አይመስለሽም ሔዊ?" መልሶ በጥያቄ መለስልኝ።
"አይ አይመስለኝ እንድረጋጋና ነገሮችን አንዳስታውስ ከፈለክ ነፃ ብታደርገኝ የሚሻል ነው የሚመስለኝ"። እንደማቅማማት አለና "እሺ ወደ ሳሎን ነይና ቁርስ እንብላ"አለኝ እንደ እሽታ ቆጥሬ"አባዬ ስለተረዳኸኝ አመሰግናለው "አቅፌ ሳምኩት።ግን የአባቴን ጥንቃቄ አይታችሁልኛል ምን እንዳስታወስኩ እንኳን ጠይቆ ሊያስታውሰኝ አልፈለገም ምክንያቱም ማስታወስ እንደማልፈልግ ነግሬዋለዋ።
ለወትሮው አባቴ እስካለና እቅፍ ውስጥ ስሆን ፈርቼ አላውቅም በአባቴ መሉ እምነት ና መተማመን ነበረኝ።ልክ በአምላኬ እቅፍ ውስጥ ያለው ያህል ደህንነትና ሰላም ይሰመኝ ነበር።ግን በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የአባቴ እቅፍ ወደማያስጥለኝ ወደማያድነኝ አስፈሪ ገፅታ ወዳለውእና ማለቂያ የሌለው የሚመስል ስቃይ ውስጥ ራሴን ካገኘው ቡሗላ ግን ፍፁም ቀድሞ የነበረኝ ሰላምን ሊሰጠኝም ሆነ እምነት ሊኖረኝና ፍራቻን ሊያስወግድልኝ አልቻለም።

ሳሎን ስንደርስ ቀርስ ቀርቦ ግሩም ቃና ባለው ሻይ ሽታ ታውዶ ነበር።"ደና ደርሽ ሔዊ"አለች ቡርቴ በዝግታ ሔጄ ሳምኳትና"ሽታው በጣም አያስራበኝ ነው ባለሞያ እኮ ነሽ!"አልኳት።"አሱን በደንብ ስትበዪ ነው ማምንሽ በደንብ አትቢና ግን ወይልሽ!"አለች የውሽት ቁጣ እየተቆጣች።
"እሺ እናመስግን"አለ አባዬ ፊቱ ላይ አንዳች ስሜት እየተነበበ እንደተረበሸ ያስታውቃል።
በፊተት ከምወደውና ደንነት እንዲሰማኝ ከሚያደርገኝ ሌላው ነገር የአባቴ ፀሎት ነው ልጅ እያለው እንደሱ ለመፀለይ አለማመድና አንደ አባታችን ፀሎት አደጋግመው ነበር።የሚፀልይበትን እረጋታ እና ድምፅ አወደዋለው በአይምሮዬ ጥሩ ዜማ እንዳለው ተወዳጅ ሙዚቃ ተቀርጿል።"አሜን"ስል የእውነትም አባቴ በሚለው ነገር በአምላኬ ተሰሚነትን አንደማገኝ ወስጤ እረግጠኛ ሆንና አምኜ ነው።እና ይሄንን የአባቴን ፀሎት አድጌም አልጠጎበውም።ደስ ይለኛል ምግብ ላይም ይሁን በምንም አጋጣሚ ሲፀልይ ሰላም ወስጤን ይሞላዋል ከእግዚአብሄር ጋር የምገናኝ የማወራው እና እሚመልስለኝ ነው የሚመስለኝ።
ይሄንን ሁሉ የምላቹ አባቴ ለቁርስ እየፀለየ ነው እኔና ቡርቴ በአሜንታ እየተከተልነው አመስግነን ጨረስን።
ቁርስ በልተን እስክንጨርስና አባዬ ወደ ስራ እስኪካሄድ መጠበቅ በጣም ረዝሞብኝ ነው ቢሆንም ጠበኩ።አባዬ በቅራኔ እንደተሞላ ለመውጣት ሲወጋጅ ድንገት የት እንደምሄድ ጠየቀኝ የት ነው የምሄደው...?
"ገበያ..."አልኩት ዝም ብዬ
ገበያ....??" አለኝ በጥያቄ አይን አያየኝ
" አው አታስብ ቡርቴ የምትገዛው እቃ ስላለ ከሷ ጋር ነው የምሄደው" አልኩት አፌ ላይ አንደመጣልኝ።
"እሺ እንደዛ ከሆነ ገንዘብ ያስፈለግሻል"ከዋሌቱ የተወሰኑ መቶ ብሮችን እያወጣ "ምንያህል ያስፈለግሻል?
"አይ አትቸገር ብዙም አይደል"እንደዛ ከሆነ ካፌ ነገር ብትገቡ ወይም ደስ ያላችሁን ብታደርጉ ጥሩ ነው ብቻ ሚያዝናናቹን" ሰጠኝ።
"ይሄ ደሞ ላንቺ ነው"ለቡርቴ እያቀበላት ገና ከጓዳ እየወጣች ነበር"ለምን....?"አለች ከመጀመሪያው ስላልሰማች"ገበያ ልንሄድ አይደል...!"አልኳት ካፏ ነጥቄ።
"በሉ እሺ ልጆች መልካም ቀን ታዲያ እየተጠነቀቃቹ"ብሎ ስሞን ወጣ ከቡርቴ ጋር መወጣቴ እንዳስደሰተው አና ምን ያህል እንደቀለለው ሳይ ደስ አለኝ።አባቴ አንዲ ነው ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ፍቅር መስጠት እና ሰውን መውደድ አይሰስትም አያልቅበትምም።ብዙዎች ሀብታሙ ፓስተር ይሉታል።በርግጥ የራሱ ስራ ያለውና ደሞዝተኛ ነው።ከዛ ውጪ ትጉህ አገልጋይ እና ታታሪ ሰራተኛ ነው።ብዙ ጊዜ በአንድ ቤተ/ያን መገደብ ስለማይወድና ከሁሉም ጋር ህብረት ስለሚያደርግ በዚ ሰዎች ይተቹታል ሆኖም አባቴን ግድ ሰቶት አያውቅም ምክንያቱም ሲበዛ በአንድነት የሚያምንና ልዮነትና ክፍፍል የሚባል ነገር ስለማይወድ ነው።በቤተ/ያን ብቻ አይደለም አባቴ ሲበዛ በኢትዮጵያዊነት አንድነት የሚያምን ነው።ለማንም ሰው ስለብሔሩም ሆነ ስለዘሩ ሲናገር አትሰሙትም።የማይታመን ይሆናል ግን ለኔ እንኳን "እንትን ዘር ነኝ ስለዚ አንቺም እንደዚ ነሽ "ብሎኝ አያውቅም ለዛ እኔም ስለብሔሬም ሆነ ስለዘር ግድ ሰቶኝ አያውቅም።ከአባቴ የተማርኩት ምንም ትርጉምም ሆነ ጥቅም የሌለው ነገር መሆኑን ነው።ግን አባቴ ስለሁሉም ሰው ቢጠየቅ መልሱ "ኢትየጵያዊ ብቻ" የሚል ነው የሚሆነው።እኔም ስለነዚ ነገሮች ለማወቅ ጉቱም ፍላጎቱም አድሮብኝ አያውቅም ደሞም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያስብ የሚገባወና ሊይዘው የሚገባው አመለካከት ነው።ግን እንዴትና ለምን አንደሆነ ባይገባኝ በምማርበት ግቢ በአንድ ብሔር ተሰይሜ እና ተወክዬ ስቀጣ ነበር።ግን እነማን ነበሩ...? በምንስ ወከሉኝ...? መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ ነው።እነማንን መጠንቀቅ ይኑርብኝ እነማንን ማመን ይኑርብኝ እንኳ አላውቅም

በዚ ምክንያት ነው እስካሁን በፍርሀት እንድኖር የተገደድኩት።

አባቴ እንደወጣ ምን እንደማደርግ ቀድሜ እያቀድኩ ክፍሌ ገባውና ቀለል ያለ አለባበስ ለብሼ በፍጥነት ወደ ቡርቴ ሄድኩ
"ጨርሻለው!" አልኳት
ዞራ በአግራሞት ከላይ እስከ ታች አየችኝ።እኔም ግራ ገብቶኝ እንደገና አለባበሴን አየሁት ጅንስ ሱሪ፣ፓካወት እና ሸሚዝ ብዙ ጊዜ የማዘወትረውን እና ሚመቸኝን አለባበስ ነው የለበስኩት።
"ያጠፋሁት ነገር አለ? አለባበሴ ምን ሆነብሽ?"አልኳት
"አይ...ቶሎ..ጨረሽ ብዬ ነው"

"ልጅት ምን ሆነሻል ልብስ ስለብስ ጊዜ ፈጅቶብኝ አያወቅም ሁሌም እንዲ ነበርኩ"አልኳት ፊቷ ላይ የማየውን ስሜት ለመረዳት በጥንቃቄ እያየሗት።

"አይ ሔዊ ግን እኮ እንደዚ መልበስ ካቆምሽ ቆይተሻል"አለች።አሁን ገባኝ በራፍ ላይ እንደቆምኩ ለሴኮንዶች እያሰብኩ አፈጠጥኩባት እና ተጠግቻት
"ቢያንስ ለምን ያሀል ጊዜ..?"ጠየኳት።
"እንጃ 1...3 ዓመት እና ከዛ በላይ ይሆናል"
"እሺ ቡርቴ አንዳስታውስ እንድትረጂኝ እፈለጋለው አትረጂኝም...?"እጆቿን የዤ ጠየኳት።"
ሔዊዬ አንቺ አስታውሽና ደና ሁኝልኝ እንጂ ለምን ብዬ ነው ማልረዳሽ"
"ምንም ነገር ቢሆን የጠየኩሽን ታደርጊያለሽ?"
"ደስ ያለሽን" "ግን አባዬ ሳያውቅ ነው"
"ማለት..? ግን ለምን
👍51
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_አራት


#በዮርዳኖስ

"እና መጀመሪያ ምንድነው ምንገዛው?" አለችኝ።ገበያ ደርሰን ነበር ገበያው ያን ያህል አልደራም ቢሆንም በቂ ሱቆች ተከፍተዋል።"አንቺ የፈለግሽውን" አልኳት
"እንደዛ ከሆነ ነይ በዚ እንቁላል እና ወተት አንግዛ"
በአትክልት ተራው አልፈን ወደ እህል ተራ በሚወስደው መንገድ ስንደርስ በአንደኛው መታጠፊያ ይዛኝ ገባች።ወደ ትልቁ የገበያ አዳራሽ ማዕክል እና የቤት እቃዎች በመሸጫዎች መሀል አቋርጠን እዛው ወዳለው ወደ ወተት ተራው ገባን።"ደንበኛዬ አልመጣችም በዛ ላይ ሀይላንድ ያስፈልገኛል መጣው እዚሁ ጠብቂኝ"ብላኝ ሔደች ትኩረቴ እሷ ጋር ስላልነበረ ግድ አልሰጠኝም ነበር።ግራና ቀኙን መቃኘት ጀመርኩ አንዳንድ እቃው ባለሱቆች ገና ከፍተው እቃ በማውጣጣት ላይ ሲሆኑ አብዛኛው ጨርሶ ቁጭ ብሏል።የማውቀውን ሰው ፍለጋ ይመስል ሁሉንም እያስተዋልኩ አያለው።
"ኧረ እማ እንሒድ በቃ ለኔኮ ጫማ አልገዛንም..."
"አይ የልጅ ነገር በቃ ከራስህ ውጪ አታስብም አይደል መጀመሪያ የምንበላውን ልገዛ እስኪ" እናትና ልጅ ትኩረቴን ስለሳቡኝ እሰማቸው ጀመር።
"ገና እኮ ጠዋት ነው ማሙሽ ሱቁም በደንብ ይከፈት እናትህን አታስቸግራት እንጂ" ሌላኛዋ ሴት እንቁላል ለእናትየው እያቀበለቻት የእንቁላል ነጋዴ ነች።
"እሺ እዛጋ ያንን"ህፃኑ ለናቱ እየጠቆማት እድሜው በግምት ወደ ሰባትና ስምንት የሚጠጋ ይመስላል።
"ምን የቱ ጋር?" አለች እናቱ።እኔም ጥቆማውን ተከትዬ አይኔን ጣልኩ
"ምንድ ነው እሱ አትናገርም እንዴ?" እናትየው የታያት አይመስልም እኔ ግን በትክክል አይቼዋለው የልጁ እሳቤ ቀድም የነገረኝ ይመስል ተረድቼዋለው።በቀስታ ወዳየሁት ነገር መራመድ ጀመርኩ።

"ያውና ሰው የሚታረድበት ነገር እኮ ነው!!"
"ምን.... ?በስመአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ!!"
እናትየው እንቁላሉን ስትለቅ ይሰማኛል።እግሬ አየተንቀጠቀጠ ቀረብኩ በቁጥር በዛ ያሉ ስለታቸወና አዲስነታቸው ከሩቅ የሚያብለጨልጭ ባንጋዎች ናቸው ሰውነቴን አየሰቀጠጠኝ አጠገቡ ቆሜ ወደታች አየውት።

"ደሞ ኬት አመጣኸው ይሄንን? ሁለተኛ አንደዚ እንዳትል እሺ አባቴ ሁለተኛ!! ና ከዚ እንሒድ"የናትየው ድንጋጤ ከድምጿ ቃና ይታወቀኛል።የሷ ብቻ አይደለም እኔም ፍርሀቴ ሲጀምረኝ እና ወደነዛ ቀናት በትውስታ የተመለስኩ ሲመስለኝ ይተወቀኛል። ህፃኑ ያለው በአይምሮዬ ተስሎ ታየኝ።

ይሄ ነው እንግዲ የማንነት የትውልድ ኪሳራ፣ ይሄ ነው እንግዲ አዲሱ ለትውልድ የምናስተላልፈው ታሪክ እና ገድላችን ፣ይሄ ነው እንግዲ ሰውነት ከእንስሳነትም ከእቃነትም ተራ አልፎ የረከሰበትና የቀለለበት ዘመንና ትውልድ ፤ይሄ ነው የማንነት ክስረት። ይሄንን የማንነት ውደቀታችን ነው በታናናሾቻችንና በልጆቻችን አይምሮ እየሞላንና እየቀረፅን ያለነው።
"ጉድ እኮ ነው አንቺ ይሄ ህፃን እንኳ እንዲ ይናገር....አጃኢብ!!!

"ሰማሽ አይደል ለነገሩ ምን ያድርግ በሱም አይፈረድም።እነሱስ ቢሆኑ ሰው እንደዚ በተጨካከነበትና በሚጨራረስበት ወቅት እንደዚ በሰፊው ይሄን መነገዳቸው ምን ማለታቸው ነው? እንዲያው ሲያዮት እንኳ አንዴት ይዘገንናል!"።

"ሔዊ ምነው" ደንዝዤ ከቆምኩበት የቡርቴ ጥሪ ከኋላዬ ተሰማኝ።"እንዴ እያለቀሽ ነው እንዴ ሔዋን ምነው የኔ ወድ?"
የተናነቀኝን እንባ እያየች።ግን የድንጋጤ እና የፍረሀት ወይም
የሀዘን እንባ አልነበረም ቁጭትና እልህ እና ንዴት እንጂ።
"የኔ ጥፋት ነው ይዤሽ መውጣትም ሆነ ብቻሽን መተው አልነበረብኝም"እንባዬን አየጠረገች።
"ቡርቴ..?"አልኳት"ሁለቱን ሳምንት ታግቼ ነበር አይደል? ለነገሩ እሱ በጣም ግልፅ ነው ደሞም ይሄንን አባቴም ሆነ አንቺም በደንብ ታውቃላቹ!!

"ምን...? ለምንድነው እንደዚ የምትይው ነይ ከዚ አንሂድ መዳኒትሽን መውሰድ አለብሽ..."እጄን ይዛ ጎተተችኝ።

"አይ አይሆንም ለቀቂኝ!"እጄን አስለቀኳት
"አቁሚ በጭራሽ አልሄድም አሁን ባልሺኝ መሰረት የምጠይቅሽን እሺ በማለት ታደረጊያለሽ!"ጥያቄ ሳይሆን ትዕዛዝ ነበር።

#ሕዳር 20/12 ቀን የታገቱ ተማሪዎች እስካሁን ድምፃቸው አልተሰማም።
ይላል ሙሉ ዜናውን ለማግኘት ፔጁን ተቀላቀልኩ።
January 24
#ከ 35 ሺህ በላይ ተማሪዎች ቤታቸው ናቸው።በአንዳንድ የሀገሪቱ ዮኒቨርስቲዎች ውስጥ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት መደበኛ ት/ታቸውን አቋርጠው የተመለሱ ተማሪዎች ወደ ትም/ት ገበታቸው አልተመለሱም።

#የኢትዮጵያ የሳይንስና የከፍተኛ ት/ት ሚኒስተር በ22ቱ ዮኒቨርስቲዎች ባካሄደው ምርመራ እና ቅኝት በግማሽ መንፈቅ ዓመት ብቻ የ12 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።
=> ታህሳስ 27
ሌሎች የታገቱ ተማሪዎች እንዳሉና ቁጥራቸውም 4 እንደሚደርስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳዶር በጋዜጣዊ መግለጫ የገለፁበት ቀን

#በሕዳር 20/12 ስለታገቱ ተማሪዎች የጠቅላይ ሚንስተሩ ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬተርያት በሰጡት መግለጫ፦አጠቃላይ 27 ተማሪዎች ታግተው እንደነበረና 21ዱ መለቀቃቸው 6ቱ ደግሞ ታግተው እንዳሉ ገልፀዋል።የሚልና ሌሎች ተመሳሳይ የወጡ ዜናዎችን በብዛት ካየሁ ቡሗላ
አሁን ሁሉም በግልፅ የገባኝ መሰለኝ።

የሰጠሗትን ትዕዛዝ ላለመቀበል ጋሼ ቢጠየቁኝስ ምን እላቸዋለው?"ነበር ያለችኝ እኔም
ቃል በገባሁላት መሰረት አባቴ ሳይመለስ ቀድሜ ቤት ለመገኘት ከሷ እንደተለየው ጊዜ ሳላባክን ወደ ኢንተርኔት ቤት ነበር ያመራሁት።እና የምፈልገውን ካየው ቡሗላ ቶሎ እሷ ጋር መሄድ ስለነበረብኝ ባጃጅ አስቁሜ ገባው ውስጤ ብዙ ሀሳብ ይመላለሳል ግን የትኛውን በትክክል መስማት እንዳለብኝ እንጃ። እስካሁን ምንም ባለማወቄ እና በዝምታዬ የተሞኘውም መሰለኝ
ሀገሪቱ ላይ የሚካሄደውና የሰው ሁኔታ ግን ግርምትን የሚያጭር ነው። ምንም እንዳልተፈጠረ መኖራችን አስገርሞኛል። ለምሳሌ ያለሁበት ባጃጅ ሹፌር ዕድሜው ከኔው ጋር ተመሳሳይ ነው። እርግጠኛ ነኝ በነዛ ወጣቶች ላይ የተፈጠረውን/ይቅርታ በኛ ላይ ልበል እንጂ ስለተፈጠረውና ስለተፈፀመው ድርጊት በሚገባ ሰምቷል።እና ናላ በሚያዞር ምንነቱ በማይገባ ዘፈን ባጃጁን መጓጓዣ ሳይሆን ክለብ አስመስሎ እስከቂጡ ከፍቶ ባጃጇን እንደ አየር ያከንፋታል። ተማሪዎች ከየት/ት ቤታቸው ተለቀው በተለያየ ዮኒፎርማቸው ሲተራመሱ ይታያሉ። ይሄን ሁሉ ጊዜ ቤት መጥቼ ቁጭ ስልም ሆነ ስወጣ ማንም ሰው ስለነዛ ልጆች ሲያወራ ና ሲያነሳ አጋጥሞኝ አለማወቁም የማይታመን ነው
ሚድያዎቻችንም ቢሆኑ
ከምንም በላይ ያስገረመኝ ግን የራሴው አባት ነው።ምንም ያሀል ልጁን የሚወድ አባት ሊሆን ይችላል ግን ደሞ ይሄ ትልቅ ራስ ወዳድነት ይመስለኛል።ስለኔ ብቻ ሳይሆን የሌሎቹም ነብስና መጨረሻ ሊያሳስበው ይገባ ነበር።
ለማንኛውም ግን ማወቄንም ሆነ ማስታወሴን በድብቅ ለመያዝ እና ለመቀጠል ወስኛለው ምክንያቱም ማንኛውም ወላጅ ቢሆን ለጁ እንዲያደርግ እማይፈልገውን ነገር ለማድረግ ስለወሰንኩ ነው።በርግጥ አንደማንኛውም ሰባዊ ሰው ሲታይ ልክ የሆነና ተገቢ ድርጊት ሊሆን ይችላል።እንደ ወላጅ ግን አይደለም!
" ደርሳሻል እናት"አለኝ ወጣቱ ባለባጃጅ ድምፁን ከፍ አድርጓ፤ እስኪ ምናለበት ከመጮህ ዘፈኑን ቢቀንሰው ያለኝን ብር ከፍዬ በፍጥነት ወደቤት ገባው።አባቴ ገና አልመምጣቱ ካረጋገጥኩ ቡሗላ ወደ ቡርቴ ሮጥኩ
"ውይ ተመስገን ለትንሽ ነው የደረሽው"አለችኝ
"ቡርቴ..?"
"እ...?"
"ብሌንስ...??"ውስጤ ሲመላለስ የነበረውን ጥያቄ ጠየኳት።


💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየታችሁ እንዲሁም ማስተካከል ያለባት ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት
1👍1
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_አምስት


#በዮርዳኖስ

ቤቱን የሞላውን ሁካታ ጩኸት ለማስቆም ሁለተኛው ጥይት ተተኮሰ ተኩሱን ተከትሎም ሁሉም ዝም አለ ቤቱን እንደገና ፀጥታ ወረሰው።
ፊትለ ፊታችን ከተጋደመው እሬሳ ትኩስ ደም እየተምዘገዘገ ወደስራችን ቁልቁል ይወርዳል።ግን ሁላችንም በፍራቻና በድንጋጤ ትንፋሻችን እንኳ እንዳይሰማ ሆኖ ዝም አልን ማንም አያለቅስም
መጮህ አይታሰብም ምክንያቱም በተነፈሰው ሁለት ቃል ምክንያት ወደ ሞት የተሸኘውን ሁሉም ስላየ ስቅስቅታ የለም የሚቆራረጡ ትንፋሾች እንጂ ተጨንቆ በተለይም ሰሚም ሆነ ደራሽ እንደሌለ አውቆ ተስፋ እንደመቁረጥ ፈርቶ መሽሽና ማምለጥ እንዳለመቻል ሞትን እያሰቡና ፊት ለፊት እየተጋፈጡት ማልቀስ እየፈለጉ አንዳለማልቀስ መጮህ እየፈለጉ አንዳለመጮህ ምንም ማለትና መደረግ እንዳለመቻል እሚያም ነገር የለም።

የሚከተለውን በማሰብ ማንም ደሙን ለመሸሽ ንቅንቅ አላለም።
ለመዳን መፀለይ ይኑርብኝ ንሰሀ መግባት አላወኩም ግን ሁለመናዬ ይንቀጠቀጣል ልብ ምቴ ለሁሉ እሚሰማ እስኪመስለኝ ድረስ በፍጥነት ይመታል ትንሽ ቆይቶ ግን መቆሙ እማይቀር ይመስላል እየሆነ ያለው እና የማየውን በህለሜ ይሁን በውን እንጃ ግን በህሌሜ ከሆነ ለምን አልባነንኩም ስል አሰብኩ በውኔ ከሆነ ደግሞስ እንዴት ተቋቋምኩት?

አጋቾቻችን አና ገዳያችን እርስ በእርሳቸው መነጋገርና መጯጯህ ጀመሩ።እኛ ብቻ ሳንሆን እነሱም መጠነኛ ድንጋጤ የደነገጡ ይመስላል።እኛን ትተው እርስ በእርስ ጭቅጭቅ ጀመሩ "ለምን?" የሚል ጥያቄና ቁጣም እያቀረቡበት ይመስላል። እሱም ሳይፈራ "እንኳን!"የሚል በሚመስል ልበሙሉነትና ቁጣ በጩኸት ይመልስላቸዋል።ከዚ በላይ ግን የሚሉትን ለመረዳት አልቻልኩም።

ድንገት ያለንባት በረት መሳይ ትንሽዬ ቤት በር ከፍተኛ ድምፅ አሰምቶ ተከፈተ።
እንደገና ጩኸት።
እኛን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ያስደነገጠ ክስተት ሆነ።
"አንዳትንቀሳቀስ...! እንዳትንቀሳቀስ ብያለው እንዳትበላሽ ዋ...!!"አለ ከውጭ የሚመጣ ድምፅ። ጠመንጃውን አስቀድሞ በቀስታ ወደ ውስጥ ዘልቆ ብቅ እንዳለ "ልጆች እዚ ምን እየተካሄደ ነው.."አሉ በዕድሜ ጠና ያሉት ሽማግሌ ሁሉንም በጥንቃቄ እያዮ።የመጀመሪያው አማረኛ ተናጋሪ ናቸው አይናቸው ውስጥም ክፋት ወይምን ጭካኔ አይታይም እንደውም ገፅታቸው ርህራሄ ይነበብበታል።ከሰማይ የመጣ አዳኝ መለዓክ ይሆን እንዴ..?አልያም አምላክ አዝኖ እኛን ለማስመለጥ የላከልን ታዳጊያችን ሰው ይሆኑ?! ብቻ ግን ውስጤ እንደገና በተስፋና ዳንኩ በምትል ትንሽ የደስታ መንፈስ ሲወራጭ ተሰማኝ።እኔን ብቻ ሳይሆን ሁሉም እንደዛ ያሰበ ይመስለኛል።

ግን ድንገት ከመካከላቸው አንድ ተነስቶ "እንዴ....ጋሽ ሽመልስ...! እርሶ ኖት እንዴ...?"አለ ለሰላምታ እቀፉን እያዘጋጀ።አማረኛው ጥርት ያለ ነው ግን እስካሁን አንዲትም የአማረኛ ቃል አልተነፈሰም ነበር።
"እህ...ሙሴ ጎረምሳው አንተም አለህ እንዴ...?ታድያ ምን አያደረጋችሁ ነው?"የፊት ገፅታቸውን ወደ ቁጣ ቀይረው ጠየቁት።
"ኧረ ሰላም ነው ምንም አይደል አጎቴ..."አለ

እንዳሰብነው ሳይሆን ቀረና ሔዶ ተጠመጠመበት ተቃቀፉ ያብቻ አይደለም ሌላ በእድሜ ተለቅ የሚለውና ዋናው አዛዥ የሚመስለውም ተነስቶ በክብር ሰላም አላቸው ና ማውራት ጀመሩ።ሁሉም የሚያውቋቸው ና የተከበሩ የአከባቢው ነዋሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሁኔታቸው መገመት ይቻላል። ግን ተወላጄ እንዳልሆኑ ግለፅ ነው።ባዩት ነገር እንደደነገጡና እንዳዘኑም የፊት ገፅታና አስተያየታቸው ያሳብቃል።በርግጥም ሊያድኑን ፈልገዋል ሆኖም ምንም ያህል ደግ ቢሆኑም አና ሀዘኔታ ቢኖራቸውም ግን እነሱን መቃወም ሆነ እንዲለቁን ማድረግ እንዳልቻሉ ግልፅ ሆኖልን ነበር። አይናቸው ላየ ሀዘኔታ ይነበባል ጥለው ለመሄድ አልፈለጉም። እሳቸውም የማይችሉት ነገር እንደሆነ ተረድተዋል ቢሆንም እርዳታን እሚማፀኑና የሚያለቅሱ አይኖች በተስፋ እሳቸው ከማየትና ከመጠበቅ አልቦዘኑም።

"አይ እንደዛ ከሆነማ እሺ እኔ ደሞ ምን ተፈጠረ ብዬ እኮ ነው።እንዲያ ከሆነማ..."ለአፍ ይበሉ እንጂ ከልባቸው አይደለም የሚናገሩት።
"አይ እርሶን አያሳስቦት ቀላል ነገር ነው ያው እንዳለኮት ነው አንጎዳቸውም ታውቁ የለ..."ይላል ከመጀመሪያው ተነስቶ ያቀፋቸው ሰው።
ፊታቸው ቅራኔን እንደተሞላ ደጋግመው አየተዟዛሩ ካዮን በበሗላ ለአራጆቻችን ጥለውን ወጡ።ግን ውስጤ ተስፋ አልቆረጠም ከሁኔታቸው አንዳየሁት ሰዎችን ይዘው ተመልሰው መተውም ቢሆን ከማዳን ወደ ሗላ እንደማይሉ እርግጠኛ ሆኜባቸው ነበር።

"ምንም ችግር አይፈጠርም..?"አለ አንደኛው ሰው
"የዚው አከባቢ ሰው ናቸው አሳልፈው አይሰጡንም"አለ አጎቴ ሲል የነበረው።
"አይ አይመስለኝም"አለ አዛዡ በአይን ምልክት አንዲከተሉት ትዕዛዝ እየሰጠ።
ወዲያው ሁለት ሰዎች በፍጥነት ተከታትለው ወጡ።
እንደገና ቋንቋቸውን ቀይረው መጨቃጨቅ ጀመሩ መጀመሪያውም ያልተስማሙት አጋቾች እንደገና በነዚ ሰው ምክንያት አለመግባባት የተፈጠረባቸው ይመስላል።ቋንቋውን በፍፁም ሰምቼው አላውቅም ምናልባት ብዙ እማይነገር የአንዱ ብሔር ቋንቋ ሊሆን ይችላል አልያም ደግሞ እዚው ለመግባቢያ የፈጠሩት ሌላ የኮድ ቋንቋ ሊሆን ይችላል።ሁለተኛውን የመሆን እድሉ ግን ሰፊ ይመስለኛል።

እኛ ታዳጊ መልክተኛችኝ አባት ምን ሆነው ይሆን...? አምልጠው ያድኑን ይሆን ወይስ እነሱም ተይዘው እዚው እኛው ጋር ይቀላቀሉ....? በሚል ሀሳብ ውስጥ እንደተዋጥኩ ቀጥሎ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመርኩ።

በግምት 3 ደቂቃ ያህል ይሆናል ምንም የለም እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም የሚሆነውን በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቀ ይመስለኛል።ምክንያቱም ከነኚያ ሰው ጋር ተስፋችንን አብረን ልከናል የመሞትና የመዳን ዕድላችን በሳቸው የሚወሰን ሆኗል በሳቸው ምክንያት ተስፋ አልያም ሞት ይቀጥላል በቃ።
ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ። ቢያመልጡ እንጂ ቢያዙ መቼም ይሄ ሁሉ ደቂቃ አይቆዮም ብዬ ደመደምኩ። ምናልባት እስከ ነገ ቢፈጅባቸው ነው ከዛም መተው ያድኑናል ብዬ ሙሉ ለሙሉ ተስፋ አደረኩ ደስም ያለኝ መሰለኝ።አሁን እግዚአብሔርን የምለምነው እስከ ጠዋት በህይወት እንዲያቆየን ብቻ ነው ግን እስኪነጋ ማን ይሙት ማን ይትረፍ የምናውቀው ነገር የለም ምናልባት ሁላችንም በአንድ ሽጉት ቀላሀ ብቻ ልናልቅ እንችል ይሆናል አልያም ሁላችንንም አንተርፋለን።ወይም ምን ይታወቃል እዚሁ በጭድ በተሞላው ቤት ውስጥ እንዳለን ቤንዚን አርከፍክፈው ያነዱን ይሆናል
ብቻ ቀጥሎ የሚሆነውን ማንም መገመትም ሆነ ማወቅ አይችልም።
በቃ የሚመጣውን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለም።
ግን አሁን ትንሽም ቢሆን ተስፋ አለን።

ከአስራዎቹ ደቂቃ ቡሓላ የሄዱት ሰዎች ኮቴና ድምፅ ተሰማን።ባዶዋቸውን እንደተመለሱም እርግጠኛ ሆንኩ።
ግን ሳይሆን ቀረና ያ ተስፋዬን አብሬ የላኩበት ሰው ተስፋዬን ጥሎብኝ አብሯቸው መቶ ነበር

"እህሳ ፈልገኸኝ ነበር? ከመንድ ሲያስመልሱኝ ጊዜኮ ችግር የተፈጠረ መስለኝ"አሉ ድንጋጤያቸውን ለመደበቅ እየጣሩ እንዳሉ በሚያሳብቅ ንግግር።
"አይ ችግር የለም እንደው አግረመንገዶን ከመጡ አይቀር ለምን አንድ ነገር አላሳይዎትምና አላማክሮትም ብዬ እኮ ነው"አለ ዋናቸው ሰው እጁን ትክሻቸው ላይ አስደግፎ ይዟቸው እየወጣ በድጋሜ በዛ ርህራሄ በሞላበት አይናቸው ቃኘት አድርገውን ነበር የወጡት ነገሩ ግራ አጋባኝ ቢሆንም ከኛ ጋር አለመቀላቀላቸውን ወይም መንገድ ላይ አለመገደላቸውን ተስፋ አድርጌ መጠበቅ እንደጀገመርኩ በዛው ቅስፈት ከወደውጪ ተኩስ ተሰማ ልቤ ከልባቸው እኩል አብሮ ምቱን ያቆመ መሰለኝ
👍1
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_ስድስት


#በዮርዳኖስ

ቀሪውን ሰዓት መተኛት እማይታሰብ ስለሆነ እንዲሁ ክፍሌ ውስጥ ስንጎራደድ አነጋው።
ከአባቴ ቀድማ የምትነሳው ቡርቴ ስለሆነች እሷ እስክትነቃ ነው የምጠብቀው።
አባቴ ትናንት ስላደረግነው ነገርም ሆነ ስለሄድኩበት እና ስላደረኩት ነገር አንዳያውቅ ስለተነጋገርን እኔም ሆንኩ ቡርቴም አልነገርነውም።

ከወደ ውጭ ድምፅ ስለሰማው በሬን በቀስታ ከፍቼ ወጣው።እንዳሰብኩትም ቡርቴ ተነስታ ኩሽና ውስጥ ነበረች።
"ምነው በጠዋት?"አለች። እንዳየችኝ ምጣድ ልታሰማ እንደሆነ ያስታውቃል።

"ዝም ብዬ ነው አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ስለፈለኩ ነው"አልኳት

"አንቺ ልጅ ብቻ እንደትናንትናው ልታረጊኝ አንዳይሆን...!"

"አይ እሱን እንዳልተፈጠረ አርገሽ እርሺው የትናንትና ውሎዬን አልረሳሁትም የነገርሽኝንም እንደዛው ግን ሌላ ጥያቄ ነው"

"እውነት በይ ከምርሽን ነው እየተሻለሽ ነው ማለት ነው የኔ ቆንጆ ጠይቂኝ ምንድነው...?"አለች ሰፍ ብላ

"እ....ብ..ሌ..ንስ...?"ሌሊቱ እስኪነጋ ያስቸኮለኝን ጥያቄ ነገርኳት።ፊቷ በቅስፈት ልውጥውጥ ሲል አስተዋልኩ።

"አሁን የትናንት ውሎዬን አስታውሳለው ብለሽ ነበር እኮ በቃ እስከዚ ነው ምታስታውሺው?"
ማለት? አልኩኝ በውስጤ
ቀጥላ "ትናንት እኮ ነግሬሽ ነበር?"አለች
"እና ምን?"ጠየኳት
በረጅሙ ተንፍሳ"ሔዊ ብሌን እዚ የለችም ያው ት/ት እንደሔደች ነው ግኝ እባክሽ መልሰሽ ይሄን ጥያቄ እንዳጠይቂኝ"አለች።ልክ ያልሆነነገር እንዳለ አነጋገሯና ገፅታዋ ሳይደብቁ ይነግሩኛል በተፈጥሮዋ ምንም መደበቅ አትችልም።ቢሆንም በአሁን ሰዓት ማፋጠጡ ሞኝነት መስሎ ስለታየኝ ብዙ አልተከራከርኳትም ምክንያቱም በቀላሉ ማወቅ የምፈልገውን ሁሉ እንድትነግረኝ ለማድረግ ሌላ ዘዴ መጠቀም አለብኝ ካልሆነ ግን ለአባቴ ተናግራ ልታስቆመኝም ትችላለች ምክንያቱም ከአባቴ ትዕዛዝ እንደደረሳት ግልፅ ነው።እንዳለችው ዶክተሩ ባለው ምክንያት ይሆን ወይም በሌላ ባላወኩት አንድ ምክንያት ብቻ ከብዙ ነገር እንድከለከል ተደርጓል።ስለዚ አባቴ ሳያውቅ እሷ እንድትረዳኝ በጥንቃቄ መያዝ እንዳለብኝ ገባኝ።

ግን ስለ ብሌን ውስጤን ሰላም አይሰማውም ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኘንበትን ወይም ያወራነውን ባላስታውስም ግን ውስጤ ያውከኛል።ምናልባት ከነሙሉ ማንነቷም አላስታውሳትም ይሆናል።ግን አይምሮዬን ሞልታዋለች።አለ አይደል አንዳንዴ እንዴትና ምን እንደጎደለን ሳናውቅ ጎዶሎነት ወይም የማጣት ስሜት ወይም ባላወቅነው ምክንያት ውስጣችን ሲከፋ እና ሲያዝን የሚሰማን አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ።በትክክል ባይገባኝም ግን ካላንዳች ምክንያት ውስጤ ይሄንን አያሰማኝም።
የምትማርበትን ብቻ ልጠይቃት አሰብኩ ቢሆንም ትንሽ ማረሳሳት ስለነበረብኝ ቁርስ በልተን አባቴ ስራ እስክሄድ ጠበኩ።

"ቡርቴ እባክሽ አንዴ ብቻ አንድ ነገር ልጠይቅሽ ደግሜ አልጠይቅሽም..."አልኳት በልምምጥ እያየኋት

"እሺ...ምንድነው? "አለች በረጅሙ ተንፍሳ
"የምትማርበትን ንገሪኝ እና ስልክ...."አላስጨረሰችኝም
"ውይይ ሔዊ ...ለማንኛውም ነይ ተከተይኝ "ተነስታ ከሳሎኑ እየወጣች።እኔም ተከትያት ወጣው "ይመስለኛል አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ አንቺን ይረዳሻል ብዬ በማሰብ እንጂ ጋሼ ቢያውቅ የሚፈቅድ አይመስለኝም ግን ደም መጥፎ ነገር አይመስለኝም"አለች ወደ አንዱ ክፍል ይዛኝ እየገባች።ምን ልታደርግ እንደሆነ ለማወቅ ጓጓው።
"ምን መሰለሽ አሁን እንደተረዳሁት ነገሮችን በጥልቀት ለማስታወስ ነው የቸገረሽ እንጂ ምንም አልረሳሽም ስለዚ ለምን የቀድሞ ማስታወሻ እና ደብተሮችሽ አታይም በጣም መፃፍ ትወጂ ስለነበር ብዙ ነገሮችን በተለይም ለየት ያለ ነገር ስታይ በትኩረት ስለዛ ነገር ትፅፊና በጥልቀት ስለዛ ነገር ለማወቅ ትጥሪና ትጠይቂ ነበር አው ትዝ ይለኛል የኔና የናቴን ታሪክም ትጠይቂኝና ትፅፊ ነበር ምን ላይ አድርሰሽ እንደተውሺው ባላውቅም ስለዚ እርግጠኛ ነኝ ስለብዙ ነገሮች ፅፈሻል።"አለች አንድ ተለቅ ያለ በደብተርና መፅሀፍ የተሞላ ካርቶን እያቃበለችኝ።
ያለችን እስታወስኩ ልክ ነች ብዙ ጊዜ በነገሮቸ እሳባለው በነዛ ነገሮችም መደነቅ በጣም እወዳለው እና የሳበኝን ነገር እስከመጨረሻው ማወቅና መመራመር ተፈጥሮዬ ነው ደሞም ፀሀፊ ነኝ አው ሕይወት እንደገባችኝ መጠን እና ባስተማረችኝ ልክ ማስታወሻ የምፅፍላት ፀሀፊ።

"እሺ ቡርቴ በጣም አመሰግናለው ምርጥ እኮ ነሽ!"ካርቶኒውን ከጇ የመመንተፍ ያህል ተቀበልኳት ክበደቱ እንደጠበኩት ሳይሆን በጣም ከባድ ነበር።

"በጣም ጥሩ ነው ያደረግሽው ይሔ በጣም ይረዳኛል ቢሆንም ግን አባዬ ማወቅ የለበትም ነይ ከዚ ቶሎ እንውጣ!"ይዣት ወጣው።

እርግጠኛ ነኝ አባቴ ይሔንን አይፈልግም ባይሆን ኖሮ ደብተርና መፀሀፍቶቼ ከክፍሌ ውጭ እንዲቀመጡ አይሆንም ነበር።ምክንያቱም አደገኛ ነው።በፍፁም ነገሮችን እስከመጨረሻው ጥግ ካልደረስኩባቸው እንደማልተው እና እንደማላርፍ ውዱ አባቴ አሳምሮ ያውቃል እና አደገኛ የሚያደርገውም ይሔ ነው።ስለ ብሌን መጠየቄን ከጀመርኩ ስላለችበትና ስለሁኔታዋ መጠየቄን ቀጥዬ ያለችበት ድረስ መፈለጌን እሰከመጨረሻው መታገሌን እንደማላቆም ያውቃል ካለዚያ አይምሮዬ አያርፍም የፈለኩትን ነገር ከማድረግ ደግሞ ምንም ማንም እንዲያስቆመኝ እማልፈቅድ ጠማማ እና ደረቅ ነኝ ስለዚ አባቴ ሊያደርግ የሚችለው በተቻለው አቅም ስለ እገታዬም ሆነ ላጋራ ስለምችለው ስለመጥፎ ነገሮች እንዳላውቅ መጣር ነው።ካልሆነና ጫፍ ከያዝኩ ግን በጭራሽ አላቆምም ለዚም ይሆናል እንዳላስታውስ የተደረኩበት ምክንያት ምናልባት በቀጥታ አባቴ እንዳላስታውስ አድርጎ ወይም ፈልጎ ላይሆን ይችላል ግን የሌላ ሰው እጅ ሊኖርበት ይችላል ምክንያቱም በዚን ሰዓት ማንንም አላምንም ጠላቴ ማን ይሁን ወዳጄ ማን ይሁን የማወቀው ነገር የለም ግን መጠርጥሩ አይከፋም ከዚ ቡኃላ ጥንቁቅ መሆን ያለብኝ ይመስለኛል ።ቢሆንም አባቴ ካወቀ ግን ለማስቆም መሞከሩ የማይቀር ስለሆነ በሚስጥር ለመያዝ እና ለመቀጠል እገደዳለው።

ክፍሌ ገብቼ በሩን ከወደ ወስጥ በላዬ ላይ ቆለፍኩት።ቁልፍ መሆኑን ካረጋገጥኩ ቡኃላ መኝታዬ ላይ ከዘረጋኃቸው ማስታወሻና መፅሐፍቶች ምፈልገው ለማግኘት አገላብጠው ገባው።

"ትህትና... 1987"
የሚል ፅሁፍ አገኘሁ ስሙን በትክክል አውቀዋለው።ቀጥዬ ገለፅ ገለፅ አደረኩና ማየት ጀመርኩ።

"በቅስፈት ከሰውነት ወደ አውሬነት የተቀየረ መሰለኝ ከሌሎቹ ቀናት በተለየ ተናዶና በጭካኔ ነበር የመታኝ እና አጠገቤ ባገኘሁት ዘነዘና ያገኘሁት ቦታ ዝም ብዬ መታሁት እና እግሬ ስር ተዘረረ።እንደመደንገጥ አልኩ ምኑን እንደመታሁት በውል ስላላወኩ የገደልኩትም መሰለኝ።ብቻ ግን በድንጋጤ ውስጥ እንዳለሁ በደመነፍሴ ሮጬ ከቤት ወጣው አላመንኩትም የሚከተለኝ ነው የመሰለኝ የምችለውን ያህል ሮጥኩ ኋላ የመታኝ ቦታ ሕመሙ ብሶ ሲሰማኝ ላፍታ ጨለማ ውስጥ ቆም ብዬ አሰብኩ።ይሄም ሁሉ ለብሌን ለናቴ ና ለወንድሜ ለቤተሰቤ ስል ያደረኩት ነበር።እነሱ ጥሩ ትዳር እንዳለኝ እንዲያሰቡ ስለፈለኩ አልነግራቸውም ነበር እና በድነገት ተጣላው ብዬ እነሱ ጋር መሔድ እንደሌለብኝ ስላሰብኩ መግቢያዬን አስብ ጀመር።"
ይላል የብሌን እህት እንደሆነች ስላወኩ ለጊዜው ደብተር ዘጋሁ እና ቀጣዮን ተመሳሳይ ደበተር አነስቼ ከፈትኩት።

"የሕይወት ምሳሌየፍቅር የአንድነት እና የተስፋ ማሳያ፦ብ...ሌ...ን" ይላል።
ቀጣዮን በሚስጥር ስለፃፍኩት እርሳርስ ማግኘት ነበረብኝ እና እሱን አውጥቼ ሌሎቹን በአንድ ላይ ሰብስቤ ወደካርቶኑ ከመልሰኳቸው
👍3