አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የወድያነሽ


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


ፊት ለፊት የነበረውን ንጹሕ ግድግዳ በንዴት አፍጥጣ ተመለከተችው::
በዋለና ባደረ ብስጭት የደረቁ ከንፈሮችዋን በምላስዋ ጫፍ አወዛቻቸው:: ወደ ቀኝ መለስ አለችና «ወይኔ ልጂት! እኔን ያናደደኝ እኮ! » ብላ ዝም አለች፡፡ እኔና የውብነሽ ቀጥላ የምትናገረውን ለመስማት ጓጓን፡፡ እንደ ገና ደግሞ የግራ እጅ ጣቶችዋን ተራ በተራ ካንቋቋች በኋላ፣ ..ለምኔ ብዬ…. ሞልቷል ዕድሜ ለጉልበቴ እዚህ ቤት ብቻ ነው እንዴ ተሠርቶ የሚበላው! ማለቷና እኛን ማዋረዷ ነው» ብላ የታች ከንፈሯን የቀኝ ዳርቻ በላይና በታች ጥርሶችዋ
መካከል አስገብታ ነካከሰችው::

«አንችው በገዛ እጅሽ እኮ ነው ይህን ሁሉ ጣጣ የምታመጪው! » አለች የውብነሽ ያን በፍርሃት የሰለለ ድምዕዋን «እህህ» ብላ ለማስተካከል እየሞከረች፡፡

«እኩያዩ እኮ ብትሆን ኖሮ እንዲህ ባላንገበገበኝ! እንዴት አንድ ጥላ ብስ አውታታ ትዘንጥለኝ?» ብላ፣ ራሷ ላይ ሽብ ያደረገችውን ጥቅር ሻሽ አጠበቀችው፡፡ የሻሽ ጥብቅት ወደ ፊቷ የሚወርደውን ደም የገታው ይመስል የእናቴ ቀይዳማ ጉንጭ ጐርፍ የቦረቦረው መረሬ ዐፈር መሰለ፡፡

የውብነሽ ቀስ ብላ ከተነሣች በኋላ እናቴን ወደ ታች ያውጋር እያየች፣
«መቼም ቢሆን ሰውን ከዚያ በላይ መደብደብና ማንገላታት ደግ አይደለም፡
በምላሷ ልክ ገርፈሻታል፡፡ አሁን እንዲሀ ያስረቀረቀሽና ያስጨነቀሽ፡ ለምን
ተደፈርኩ ለምን መለሰችልኝ ብለሽ ነው” ብላ በፍርሃት የበረገገ ፊቷን በደረቅ
ፈገግታ አከሰመችው::

«ኧረ እንኳን የሄደችልኝ! ገላገለኝ፡፡ እንኳንም መኻል አናቷን ብዬ የሰው
ሰው ያልገደልኩ፡፡ ከቤቱ ነው ከምሰሶው! እኔ እንደሆነ ወይ ከዛሬ ወይ ከነገ
አንዷን ግልቱ አስመጣለሁ፡፡ እሷ ግን እግሯ እስኪነቃ ብትንከራተት፡ ሲሳዩ
የተትረፈረፈና እንደ ልብ ወጣ ገባ ተብሎ የሚጐረስበት፣ እንደ ባሻ ያየህ
ይራድና እንደ ተካበች ግፋ ወሰን ቤት ታገኛለች ማለት ዘበት ነው» ብላ
ከተካከዘች ሰኋላ ወደ መኝታ ቤት ገባች።

የውብነሽ፡ «ደበደበቻት፣ ደሟ እንደ ውሃ እስኪንቆረቆር ፈነከተቻት! እንግዲህ ከዚያ አልፋ ሥጋዋን ዘልዝላ አትሰቅለው» ብላ ራሷን በተራ ፀፀት እየነቀነቀች፣ ትልቁን የእንግዳ መቀበያ ክፍል በር ከፍታ ወጣች፡፡

ብቻዬን በመቅረቴ ንዴቱ ሁሉ የሚከመርብኝ ስለ መሰለኝ ተነሥቼ
ቆምኩ፡፡ «አልሠራም፣ አልታዘዝም ስትል ማሰናበት እንጂ ዱላን ምን አመጣው?
በማለት ቀደም ሲል በእናቴ ፊት ለመናገር የፈራሁትን ሐሳብ ለሪሴ ተነፈስኩና
ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ።

አባቴ አማካለችን ከተጉለት ሲያመጣት እኔ ገና የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ፡፡ ስምንት ዓመት ሙሉ እምብዛም ጠባይዋ ሳይለወጥ፣ ትልቅ ትንሹን እየታዘዘች፣ የተሰጣትን ሁሉ ትሠራ እንደ ነበር ትዝ አለኝ፡፡

እሷም እንደ እኔዉ አባትና እናት እኔም እኮ ጊዜ ጥሎኝ ነው እንጂ ጨዋና የትልቅ ሰው ዘር ነኝ ግን ምን ይሆናል! የታባቷ ይቺ ዐመዳም ዕድል እያለች ታጉተመትም ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜማ ታግላ ከማትጥለው ሐሳብና ከማትፈጽመው ምኞት ጋር ትንቅንቅ ትጀምርና በተሸናፊነት ስትሰክን ከዐይኖቿ
የሚጉርፈው የእልህ እንባ እፎይታ ይሰባት ነበር፡፡ በውስጧ የተዳፈነው ከንቱ
ኩራት ብዙ ጊዜ አሠቃይቷታል፡፡ ያንቺ ነገር እኮ የበቃኝ” ብላታለች እናቴ፣
"አንድ ቀን ቅራሪ የመሰለ ቡና አፍልተሽ ካጠጣሽኝ በኋላ ቤተኛዉ ሁሉ
መተኛቱንና ቤቱ እረጭ ማለቱን አይተሽ ግን አባቱ ይናገረኛል ብለሽ ቤቱን
ከፍተሽ ደጅ ማደርሽን ከሰማሁ ወዲህ ነው” ብላ እስኪያንገሸግሻት ተቆጣቻት።

ከኻያ ሦስት ዓመት የማይበልጣትና የቤታችን ሠራተኛ የነበረችው አማከለች ከሄደች ጥቂት ቀናት ቢያልፍም የእናቴ ንዴት ግን አልበረደም ነበር፡፡ለመጣው ሰው ሁሉ የአማከለችን ክፋትና መጥፎነት አንድ ባንድ ዘርዝራ ትናገርና ወሬዋን ስትደመድም «የሌላ የሌላውስ ግድ የለም፡ ዕድሌ ነው እንጂ እኔ ከማን አንሳለሁ ትበለኝ?” » እያለች የራሷን ክብር ከፍ በማድረግ ከምኗም !እንደማትደርስ ለማስረዳት ራሷን እንደ ገበሎ ስትነቀንቅ ሰነበተች፡፡

በአማከለች እግር ከከተማም ሆነ ከገጠር ሌላ የቤት ሠራተኛ ሳትተካ ድፍን ወር ዐለፈ። ምንም እንኳ ሁለቱ ቀሪ ሠራተኞች ወፍ ሳይንጫጫ እየተነሡ እስካ ውድቅት ቢሠሩም የሚሠራውን ሁሉ ለማጠናቀቅና ፋታ ለማግኘት ሳይችሉ ቀሩ፡፡ በዋል አደርም እናቴ ቀስ በቀስ ንዴቷን ተወችና ረሳቻት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ችምችም ብለው በቅለው እንደ ደጋን በጎበጡት ቅንድቦቹ ራስጌ ባለው
ገላጣ ግንባሩ ላይ ሦስት ጨምደድ ያሉ መስመሮች ተጋድመዋል፡፡ ከቅንድቦቹ
መገናኛ ላይና ከዐይኖቹ፣ ጣብቂያ መኻል እንደ ፍልፍል እንጨት ተቀርፆ የወጣ
የሚመስለው አፍንጫው ቀጥ እንዳለ ይወርድና የተድበለበለች ጫፍ ያልቃል፡፡
የአፍንጫው ቀዳዶች ከገበታቸው የተነሳ የባቄላ ጥቁር ግራ ይመስላሉ። ጠየም
ያለው ጠባብ ሰልካካ ፊቱ ቀጠን ብሎ ወርዶ በቅርፀ እንቀላል አገጭ ይጨርሳል።ከዚያች ጫፍ ላይ ሲያወራና ነገር ሲያሰላስል ቁልቁል የሚልጋትና የ“ሚያሻሽት አጠር ያለች ጢም አለችው::
ዘለግ ያለው ቁመቱ ሳይወፍርና ሳይቀጥን በመካከለኛ ሁኔታ የተገነባው አካሉ ቀልጣፋ አረማመድና እንቅስቀሴ ሰጥቶታል። ቀጠን ብላ እንደ መረዋ
የምትሰማው ድምፁ በቤተሰብ አካባቢ ሲቆጣ ታስደነግጣለች፡፡ ሲጫወት ግን
በተለይም ሲስቅ ለጆሮ ደስ ትላለች።

አባቴ 10 ዓመት ያህል በወረዳ ፍርድ ቤት በዳኝነት ሠርቷል። የአውራጃው ፍርድ ቤት ዳኛ ከሆነ አሁን አራት ዓመቱ፡ ነው:: ከቀበና ወንዝና ከአካባቢው በሰውና በእንስሳ ጉልበት ተግዞ በመጣ ድንጋይ ካምስት ክንድ በላይ በሆነ ግንብ ዙሪያውን የታጠረው ግቢያችን፣ ከውጪ ይልቅ ወደ ውስጥ ሲዘልቁ የስፋቱ መጠን ጎልቶ ይታያል፡፡ አባቴ ባሰበብ ባስባቡ በአካባቢው ከተነቀለ ድሆች ላይ የተገኘውን መሬት ከብጤዎቹ ጋር ተካፍሎ በመያዙ የግቢያችን ስፋት
የሦስትና የአራት ሰው የቦታ ድርሻ መጠን መሆኑ በጭፍን ያስታውቃል፡፡

«ሰፊ ግቢ ገመና ከታች ነው:: ሠርግ ኣለ፡ መከራ አለ፡ ድግስ አለ፡ለሰማይ ቤትስ ካሁኑ መሠረት ካልተጣላ ለኔ ቢጤው በስመ እግዚአብሔር ስም ካላለበሱና ካላጎረሱ መንግሥተ ሰማያት በጥባ አትገኝም። እንደ እኔ ያለ ሰው
ድንኳን መትከያ እና ዳስ መጣያ ቦታ ልመና አይሔድም፡፡ አታዩትም እንዴ
የነግራዝማችንና የነ ቀኛዝማችን ግቢ. ብሎ ሰፋ ሰፋ ያለትን ግቢዎች እየጠቀሰ
የራሱን ለማሳነስ ይፈልጋል፡፡

«የመኳንንትና የጨዋ ልጅ ሠፈር ነው ማለት አይገቡ ገብቼ በዚያን
ጊዜው ዐቅሜ ይህን መሳይ ቤት የሠራሁት ሰው እንዳላንስ ብዬ ነው» ይላል ለማስመሰል::

አዲስ አበባ ከቀበና ወንዝ ማዶ ከኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት በስተቀኝ
በኩል ትንሽ ራቅ ብሎ የሚገኘው ባለ አንድ ፎቅ መኖሪያ ቤታችን ከተሠራ
ከኻያ ጊዜ በላይ ደመራ ተተኩሷል::
በየዓመቱ ሐምሌና ነሐሴ እየተናደ በሚካብ ጥቋቁር የወንዝ ሽሙልሙል
ድንጋይ እና በከፊል በሸክላ ግንብ የተከበበው አጥር ግቢ ከውጪ ይልቅ ገብተው ሲመለከቱትና ሲጐበኙት ስሜትን ያምነሸንሻል፡፡

የአበቦቹና የአትክልቱ ውበት፣ የግራዋውና
የብሳናው፣ የጉራውና የአጫጭሮቹ ጥዶች ልምላሜ የሣሩን ውበትና የልዩ ልዩ ዕፅዋት ቅጠሎችን ርጋፊ ሲያዩት ደስ ይላል፡፡ ያቆጠቆጡት የባሕር ዛፍ ለጋ ቅርንጫፎች፣ በውስጡ የሚርመሰመሱት አዕዋፍ፣ ከእነዚህ ሁሉ ተውጣጥቶ የሚገኘው ድንቅ የተፈጥሮ መዐዛ፣ በሰፊው ዐፀድ ውስጥ የሚነፍሰው ቀዝቃዛ የአየር ሽውታ መልካም
የመንፈስ ጸጋ ነው::

አታክልትና ንጽሕና ለጤንነት ጥሩ
👍6
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

ልዩ ልዩ ጠባይና ፍላጐት ያላቸው ወንድና ሴት እንግዶች በየጊዜው ወደ ቤታችን ይመጣሉ፡፡ ከእነሱም መኻከል ወይዘሮ የውብዳር ተፈራ የሟቹ የሻምበል ባሻ አማረ ባለቤት ከባለቤታቸው ሞት ወዲህ ለትንሹም ለትልቁም ነገር እከሌ አጠቃኝ እከሌ ዛተብኝ፣ እገሊት ባሽሙር ሰደበችኝ እያሉ ቢያንስ ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ ያህል ይመጡ ነበር፡፡ ስላጋጠማቸው ጉዳይ ሁሉ ጨምረው ጨማምረው ቢያወሩም ከከንፈር መጠጣ በልፎ ሌላ ዕርዳታ የሚያደርግላቸው ግን አልነበረም፡፡ ሆኖም «እኔ እንኳ ባልኖር ትላለች እናቴ ከቅራሪው ከፍርፋሪው
አትከልክሏቸው፣ ማንን ብለው የመጡ ይመስላችኋል» እያለች ለሠራተኞች እደራ
ትነግር ነበር፡፡

ወይዘሮ የውብዳር ተቀምጠው እንኳን ረጂሙ ቁመታቸው የአጭር ሰው
ቁመት ሊያህል ምንም ያህል አይቀረውም፡፡ በቀዩ ፊታቸው ላይ የሚታየው ማዲያት አዲስ ሽማ ላይ የፈሰሰ የጥቀርሻ ንጣቢ ይመስላል። የውበታቸው ለዛ ከተገፈፈ ውሉ አድሯል፡፡ ቀጠን ቀጠን ብለው የረዘሙት የላይ ፊት ጥርሶቻቸው በጥቅምት ውርጭ የዛገ ካራ ይመስላሉ፡፡ መጠጥ በጣም ከመውደዳቸው የተነሣ የእኛ ቤት ሠራተኞች እንኳ «መጡ ደግሞ እኝህ የመጠንሰሻ እንስራ የሆኑ ሴትዮ፡ መጥኔ እቴ! ስንት አለ በየቤቱ» ይላሉ።

የአማከለችን መሔድ ከሰሙ ሰንብተዋል፡፡ «እንዴት ያለች ገረድ አመጣልዎታለሁ፡ ጥፍፍ ያለች፣ ሰው ቀና ብላ የማታይና ታማኝ፣ አቤት! ወዴት! ብላ የምታድር ችግረኛ፡ እኛ ሠፈር ከመጣች ገና ኣሁን አንድ ወሯ ዐለፈ። እስከ ዛሬም ያላመጣኋት ሁኔታዋን ሁሉ እስካጣራ ብዬ ነው» እያሉ ከሦስት አራት ጊዜ በላይ እየፎከሩ ሔደዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜማ በንግግራቸው ውስጣዊ ርግጠኛነት ስለሚሰማቸው ድምፃቸውን ወፈር አድርገው በመናገር፣ መጠጥ ባበላሸው ፊታቸው ላይ የቆረፈደ
ቆዳ የመሰለ ፈገግታ ያሳያሉ፡፡

አማከለች ከሔደች ድፍን ወር ዐለፈ። ቀኑ እሑድ ከቀኑ አራት ሰዓት ተኩል ነበር፡፡ ኣባቴ ከቤታችን ጓሮ በስተደቡብ በኩል ባለው የአትክልት ሥፍራ ውስጥ
አንዲት ታጣፊ የሽራ ወንበር ላይ በሁለት የኮክ ዛፎች መኻል ተቀምጦ ለብ ያለውን የረፋድ አየር እየመገመገ መጽሐፍ ያነብባል። ከነጭ ቡሉኮው ጋር
ሲታይ ከዕብነበረድ የተሠራና በአትክልት ሥፍራ ውስጥ የተተከለ የአረጋዊ ሰው
ነጭ ሐውልት ይመስላል። የአባቴ ረዘም ላለ ጊዜ እዚያ መቀመጥ በቤት ውስጥ
ለነበርነው እንደ ልብ የማውራት ነፃነት ስለ ሰጠን የሚረባ እና የማይረባውንም
ስናወራና ስናወካ አረፈድን፡፡ በመኻሉ ፍሬቢሱ ወሬ ስለ ሰለቸኝ ወደ መኝታ
ክፍሌ ገባሁ። በመስኮቱ በኩል የአጥር ግቢውን ሰሜናዊ አካባቢና ትልቁን
የግቢያችንን የአጥር በር ማየት ይቻላል፡፡ መስኮቱን ወለል አድርጌ ከከፈትኩ
በኋላ ነጩን ስስ መጋረጃ ወደ ግራና ቀኝ ሰበሰብኩት፡፡ የእንጨት ወንበሬን
መስኮቱ አጠገብ አስጠግቼ ደጅ ደጁን እያየሁ ተቀመጥኩ፡፡ ቅርቡንም፣ ሩቁንም
አሽቆልቁዬና፣ አሻግሬ ተመለከትኩ።
የአጥር ግቢያችን አንደኛው ክፋይ መዝጊያ በዝግታ ተከፈተ፡፡ ወይዘሮ
የውብዳር ባዘቶ የመሰለ ነጭ ሻሽ አሥረው፣ ዘወትር ከእጃቸው የማይለይዋትን ቆሸሽ ያለች ቀይ መሐረብ በግራ እጃቸው ይዘው፣ ርዝማኔዋ ላመል ታህል ከቁርጭምጭሚታቸው በላይ ከፍ ያለችውን የጭቃ ጫማ አድርገው፣ ቢጫ ጥለት ያለው ቀሚስና ኩታ ለብሰው ገቡ፡፡

ከኋላቸው አንዲት አቀርቅራ የምትራመድ ከወደ ቁመቷ ዘለግ ያለች ቀጭን ከሲታ ልጅ እግር በአሮጌ አዳፋ ነጠላ የተጠቀለለ ጓዝ በምብርቢጣዋ ይዛ
ገባች። ያቺ ግድ የለም እሜትዬ! ሰው ቀና ብላ የማታይ ባለሙያ አመጣልዎታለሁ» እያሉ በስሟ ጠላ ሲጠጡና ወደ ቤታቸውም ሲሔዱ ምናምን ሲያስቋጥሩባት የነበረችው ሠራተኛ ይህች መሆኗ ወዲያው ገባኝ፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ወይዘሮ የውብዳር ሲመጡ ደስ አይለኝም ነበር፡፡ ፀሐይ ሳትገር የመጡ ጀንበር የምዕራብን አድማስ ስትስምና እንዳንድ ቀንም ላይን ሲይዝ ዘንድሮ እንደሁ ያለው የሌለው አይሉም፡ ጨርቁ ነጣ ነጣ ካለ በል በለው ነው፣ ለጠላትና ለምቀኛ ደስ አይበለው» ብለው እስኪነሱ ድረስ አሰልቺ ሐሜታቸውና የማይረባ ወሬአቸው ማባሪያ የለውም፡፡ ወይዘሮ የውብዳር የትልቁን ቤት ደረጃ ትም ድም
እያደረጉት ወጥተው የእንግዳ መቀበያውን ክፍል በር ከፍተው ሲገቡ በሩ ተንሲያጠጠ። አብራ የመጣችው ሴት ግን ባዶ እግሯን ስለ ነበረች ኮቴ
አልተሰማም፡፡ እናቴ እንዲህ የአረማመዱ ድምፅ የማይሰማውን ሰው «ጥላ ቢስ
ከውካዋ» ትለዋለች፡፡ ከእናቴ ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ የወይዘሮ የውብዳር ድምፅ
ጎላ ብሉ ተሰማ። የመኝታ ክፍሉ በር በመዘጋቱ እየር ተሽክሞ የሚያመጣውን
ድምፃቸውን እንጂ የእነርሱን የአካል እንቅስቃሴ ማየት አልቻልኩም፡፡

«እንዴት ያለች ባለሙያ ጨዋ ልጅ መሰለቻችሁ» አሉ ወይዘሮ የውብዳር ውስጣዊ ፍላጎታቸውን ለማስረዳት ድምፃቸው በእያንዳንዱ ተለጣጣቂ
ቃል ሽቅብ እየናረ፡፡ «እንዳላችኋትና እንዳዘዛችኋት ሆና የምታድር ዘመድና ወገን የሌላት ናት» ብለው ዝም አሉ፡፡ እናቴ ቀጠን ባለች ድምፅ «ገና ዛሬ በነፍሴ ደረሱልኝ፡ እኔም እጇ ጥፍፍ ያለ ባለሙያ እወዳለሁ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ከጠይም ሰው ጋር ኮከብ ግብቡ ነው። ከሁሉም ከሁሉም የምጠላው የእጅ ዐመል ያለበትን ሰው ነው። ካለ ነገሬ ልክስክስ ሰው አልወድም ብላ ከዝምታቸው ተጋራች። ከወዲያም ከወዲህም ዝምታ ሆነ። ዐልፎ አልፎ ግን የመቀመጫው ሥር ሽቦ ዉሽጣ ጢሽ ሲል ይሰማ ነበር። የወይዘሮ የውብዳርን ወሬና ሐሜታ እየሰማሁ ከመበሳጨት ይልቅ ዞር ዞር ብዬ መመለስ የሚችል ስለ መሰለኝ ወደ እንግዳ መቀበያ ክፍል ዘለቅሁ፡፡ እናቴና ወይዘሮ የውብዳር ፊት ለፊት ተቀምጠው ነበር።
የውብነሽ በካባቢውም አልነበረች፡፡
እንደምትመስልና የት ቦታ እንደተቀመጠች ልብ ብዬ ሳላይ ውልቅ አልኩ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ተመልሼ ወደ ቤት ስገባ ዐሥራ አንድ ሰዓት ሆኖ ስለነበር ወይዘሮ የውብዳር ዛሬም እንደ ቀድሟቸው ያን ያህል ይቆያሉ ብዩ አልገመትኩም ነበር፡፡ ሆኖም እንደ ግምቴ አልሆነም፡፡ አንድ ጊዜ ሟቹ ባለቤታቸው በላያቸው ላይ ሌላ የጐረቤት ሴት የሚስት ያህል ወደው ስለነበር ወይዘሮ የውብዳር ጣውንታቸውን
እንዴት እንደ ደበደቧትና እንዳጠቋት በሞቀ ጉራና ዐልፎ ዐልፎ ሐሰት
ባድፌጠፈጠው ፈገግታ ወሬአቸውን ሲጠርቁ ደረስኩ። ደግነቱ መሔጃቸው
በመድረሱ በብርጭቆ ውስጥ የቀረቻቸውን ከግማሽ በላይ የምትሆን ጠላ ባንድ ትንፋሽ ሽመጠጡዋት፡፡

አፋቸውን በግራ እጅ መዳፋቸው ጠርገው በዚያች በቆሻሻ መሐረባቸው ደገሟት። ከዚያም እናቴን ትክ ብለው እያዩ «እሜትዩ እንግዲህስ ልሒድ ደኅና
እደሩ፡ እኔም ብቅ እያልኩ እጠይቃችኋለሁ። ፊት የሚሉ ነገር እንዳታሳዩዋት፡፡ ለገረድ ፊት ማሳየት መሣቅ ደግ አይደለም፡፡ ነባር ገረድ ደግሞ አጋላጭ ነው፡፡ከእነዚያ ከሾካኮችና መናጢዎች ጋር እየዋለች እንዳትማግጥና ቂጥ እንዳይገጥሙ ይቆጧት» አሉ፡፡ የሴትዮዋ እስከዚያ ጊዜ ድረስ መቆየት በጣም አናድዶኝ ስለ ነበር እነሱ ወዳሉበት ስገባ ማንንም ሰላም አላልኩም፡፡ ወይዘሮ የውብዳር
ያሻሻቸውን ሁኔታ በጃቸው ደባብሰው ካረጋገጡ በኋላ ትንሽ ራቅ ብላ መጽሐፍ
የምታገላብጠውን የውብነሽን አሻግረው እየተመለከቱ «አንቺ የኔ ልጅ! እስኪ
ሮጥ በይና ያቺን የዛሬይቱን ገረድ ጥሪልኝ» በማለት በትንሽ የመጠጥ ኃይል
በተገፋ ስሜት ጮክ ብለው ተናገሩ።

የውብነሽ መጽሐፏን እንደ ያዘች በዕቃ ቤት በኩል ወደ ማድ ቤት በሚያስኬደው መንገድ አዲሲቱን ሠራተኛ ለመጥራት ሄደች። የሴትዮዋ ቆመው ወሬ መቀጠል እናቴን
👍4
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሦስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

የጨቅላ ልጅ ቡጢ ያህል የፈጠጠው ቁርጭምጭሚቷ ተረከዝዋ በላይ የሚገኘው ወፍራም ወጣሪ ጅማቷ በኑሮ መጎዳትዋና መጎሳቆሏን በሚገባ ለማሳወቅ የቀረቡ አስረጂዎች ናቸው።
ከሳምንት በፊት እናቴና ወይዘሮ የውብዳር ሲነጋገሩ ካመጡልኝ አይቀር
ችግረኛዋንና ምንም ዘመድ የሌላትን የራባትንና እህል እህል ያሰኛትን ነው» ብላ
አደራ ያለቻቸው ትዝ አለኝና «ችግርንና እጦትን ረሃብንና እርዛትን ማስፈራርያ
እያደረገች ልትገዛት ፈልጋ ነው» በማለት መሪር ትዝብቴን ለራሴ አዋየሁት።
መላ ሰውነቴ በርኅራኄና በሃዘን ተነካ፡፡ ልቤ በትካዜ ሟሸሸች። በሥራ ብዛት
የተደቆስኩ ያህል ሕሊናዩ ዛለ፡፡

አዲሲቷ ሠራተኛ ያሳለፈችው ውራጅ ሕይወትና የዘቀጠ ኑሮ እስከ አጥንቷ ዘልቆ ታየኝ። ነገር ግን በእኔ ዕውቀትና በአጭር ጊዜ የምርምር ችሎታ
ገና በወጣትነቷ ለጨለመው ሕይወቷ አመርቂ ፍቺ አጣሁለት። ከዚያ ቀደም
ለማንም በዚያ ዐይነት አዘኔታና ልባዊ የስሜት ጭንቀት አንጎሌ ተብሰክስኮና
ተጠቦ አያውቅም፡፡

እናቴ የሠራተኛይቱን ሰውነትና ጠቅላላ ሁኔታ በመመልከት «ውይ! ምን በወጣኝ፡ ምን በደልኩዎት! ይቺማ በሽተኛ ናት፡. አልፈልግም» ሳትል በመቅረቷ በጣም ተገረምኩ፡፡

የውብነሽ አልጋዎቹን አንጥፋ ስትመለስ ልክ አራት ሰዓት ከሩብ ሆነ፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ የየውብነሽን መምጣት ስታይ ጠንቀቅ ብላ በንቃት ቆመች።
ከእናቴ በታች አዛዥ መሆንዋን ማወቋ ነበር። የውብነሽ ያን አጠር ብሉ ከርደድ
ያለ ጸጉሯን በግራ እጅዋ ይዛ እያሻሽች ከተመለከተችኝ በኋላ «ተነጥፎልሃል
መተኛት ትችላለህ» አለችኝ፡፡ እጅዋን ወደ ኋላ መልሳ ከግድግዳው ጋር ተለጥቃ
ወደ ቆመችው ሠራተኛ ዘወር ብላ «አንቺም ዕቃ ቤት ውስጥ ከዚያ ከትልቁ
በርሜል አጠገብ አንጥፈሽ ተኚ» ብላ ለማሳየት ወደ ዕቃ ቤት ገባች።
ሠራተኛይቱ ተከትላ ስትገባ ንፋስ እንደሚያወዛውዛት መቃ ወገቧ ልምጥ ልምጥ ሲል ቀዳዳው ቀሚሷ ከወዲያ ወዲህ ተወናወነ፡፡

ቁጥጥር ለማድረግ የታዘዝኩ ይመስል ተከትያቸው ገባሁ፡፡ የውብነሽ
ግድግዳው ላይ ወደ ተንጠለጠለው አጎዛ እያመለከተች «ነገና ከነገ ወዲያ ሌላ
ምንጣፍ ፈልገን እስከምንሰጥሽ ድረስ ለዛሬው ያን አጐዛ እዚህ ወለሉ ላይ ጣል
አድርጊና ተኚ። አይዞሽ አትፍሪ፡ ትለምጃለሽ» አለቻት፡፡

ሠራተኛይቱ አጐዛውን ከተንጠለጠለበት ምስማር ላይ ተንጠራርታ አወረደችው:: አጐዛው መኻል ላይ ቁልቁል የተሸረከተ የሕፃን ጭንቅላት የሚያሾልክ ትልቅ ቀዳዳ አለ። ቀዳዳውን እንዳየሁ አንድ ነገር ትዝ አለኝ።
የቤታችን ዘበኛ የነበረው ዘለቀ በግ ሲገፍ ሳት ብሎት ቆዳውን በሹል ቢላዋ ስለ
ሽረከተው አባቴ በዚያች የተነሣ ከሥራ እንዳባረረው ታወሰኝ። ከውስጣዊ
ፍርሃትና ጭንቀት የተነሣ ያ ከሲታ ፊቷ ከመጠን በላይ ጠውልጐ ይብስኑ
ሕይወት አልባ መሰለ።

«እስኪ ትንሽ አራግፈው እለች የውብነሽ በፊቷ ላይ ጥርጣሬ እየታየ፡፡
ገና ሁለት ጊዜ መታ መታ እንዳደረገችው ያንጠለጠለችው እዛ እምልጧት
ወደቀ። አጐዛው ላይ የነበረው አቧራ በመጠኑ ቦነነ ።ደንግጥ እነሣችው::
የውብነሽ አቧራውን እየተጸየፈች እስኪ እንደገና ቀስ ብለሽ መታ መታ
አድርጊው» አለቻት፡፡ ሠራተኛይቱም ከእኛ ለመራቅ ያህል ወደ ኋላ ፈግፈግ ብላ
በወዙ በኩል ሦስት አራት ጊዜ መታታችው። ልሙ ኣቧራ ወርዶ እግሯን
አለበሰው፡፡ ዕቃ ቤቱ በአቧራ ቡናኝ ተሞላ እህቴ አፍና አፍንጫዋን በቀኝ እጇ
አፈነች። ሠራተኛይቱ የአቧራው መቡነን እኛን የሚያስቆጣን ስለ መሰላት ብናኙን
እፍ እያለችና በእጅዋ እያራገበች ለማራቅ ሞከረች። አጐዛውን ከትልቁ በርሜል
ሥር ጣል ካደረገችው በኋላ ዱር አማከለች የምታነጥፈውን አሮጌ ብርድ ልብስ አጣጥፋ አስተካከለችው፡፡ ጎንበስ ቀና ባለች ቁጥር ጉልበቷ ይንቋቋል። የውብነሽ ወደ እኔ ጠጋ ብላ ለምን ታሳፍራታለህ? ሂድ እንጂ እነጣጥፋ ትተኛበት አለችኝ፡፡ «አንድ ጊዜ እንዳይ ብዩ ነው እንጂ እሺ እሄዳለሁ» ብዬ ዐይኔን ወደ ወለሉ መለስኩት፡፡ በአሮጌ ቀሚስ የተጠቀለሉ ጨርቆች መኝታው መኻል ላይ ጣለች፡፡ ወዲያው ነጠልጠል ስታደርገው ቀደም ብዩ ካየኋቸው ይበልጥ በጣም የቆሸሹና የተቀዳደዱ ቀሚሶችና ጨርቆች ወጡ፡፡ ከሁሉም ጐላ ብሎ የሚታየው ግን እንድ ጠርዝ ጠርዙ የተሸነታተረ ዐመድማ ስስ ብርድ ልብስ ነበር፡፡

ተንበርክካ ቀሚሶችዋን ካጣጠፈች በኋላ ለትራስ እንዲሆኑ አንድ ላይ ሽበለለቻቸው፡፡ የእኔ ልብ በሥቃይ ታፍና በሃዘን ስትቀዘቅዝና ጅማቴ ሲኮማተር
ተሰማኝ፡፡ ጉንበስ ቀና ባለች ቀጥር በስተኋላዋ ያለው የቀሚሷ ትልትልና ቀዳዳ ያንን ሸካራ ገላዋን በከፊል ያሳያል። እኅቴ እነዚያን የተበታተኑ ልብሶች
እየተመለከተች «ለመሆኑ ይኸ ልብስሽ ተባይ የለበትም?» ብላ ጠየቀቻት።

በእንግድነት ኃፍረት የተሸበበው አፍዋ ዝምታን ማመቅ እንጂ ቃላት ማውጣት
ስላልሆነላት ዝም አለች፡፡ እንግዳይቱ ሠራተኛ ግን አሮጌውን ልብስ አንዴ
ወረቀት ከሽመለለችው በኋላ የእግርዋን ትቢያ ሳታራግፍ መኝታዋ ላይ
ተቀመጠች። የተጠቀለለውን ብርድ ልብስ ሳብ አድርጋ ጉልበቷን ሽፈነችው።
ተጣጥፈው በስተኋላዋ ለትራስነት የተጠቀለሉት ልብሶችዋ ማቃጠያ ውስጥ
ተከማችተው የተቃጠሉ ወረቀቶች ይመስላሉ። ግንጭሏ የታጠፈውን ጉልበቷን እስኪነካ ድረስ ካቀረቀረች በኋላ ቀሚሷን አወለቀች፡፡ ከላይኛው ቀሚሷ የባሰበትና በጣም ያረጀ የውስጥ ልብስ ብቅ አለ።

ትከሻዋ ላይ ያለው ማንገቻ ረዝሞ
በመቋጠሩ እብቱ የቄብ እንቁላል ያህላል። በእድፍ የተሰላው ልብሷ ምን ዐይነት ቀለም እንደ ነበረው አይለይም። ቀሚሷን ስታወልቅ ያንን ዐመድ መስሎ
የተጐሳቆለ ጸጉሯን ሸፍኖት የነበረው ሻሽ ከቀሚሷ ጋር ሾልኮ ዱብ አለ፡፡ አጉሯ
ወደ ፊትና ወደ ኋላ ተመነጫጨረ።አንዱ ዘለላ ጥምል ቀለም መሳይ አንገቷ
ላይ ተጥመልምሉ ወረደ። ጸጉሯ ላይ ነውር ነገር የታየበት ይመስል በጣም
ደነገጠች። ወዲያው እየተርበተበተች በዚያው በሻሽ ሸንከፍ አደረገችው። ብዙ
የኑሮ ጉስቁልና ስለ ደረሰባት የአፍላ ወጣትነቷ ጠይም ውበት ወደ ሸካራ
ጥቁረት ተለውጧል፡፡ እህቴ ያን የመሰለ ፀጉር በማየቷ በአድናቆት ተመስጣ
በውስጣዊ የቅናት ጸገግታ ተመለከተቻት:: እኔ ግን በጣም ስላሳዘነችኝ በትካዜ እንባ ባቀረሩ ዐይኖቼ ሁኔታዋን አጤንኩት። አሮጌውን የብርድ ልብስ ሳብ አድርጋ እስከ አጐጠጐጤዎቿ ካደረሰችው በኋላ ተኮራምታ ስትተኛ ጭብጥ አከለች።

የውብነሽ «ወንድም ጋሼ አንተ ብትፈልግ ቆመህ እደር፡ እኔ ምን በወጣኝ ነው» ብላ ጥላኝ ሄደች። እኔ ግን ያቺን ከፊት ለፊቴ ከበርሜል ሥር ከላይ አዳፋ ደርባ ከታች የቆሽሽ ልብስ አንጥፋ የተኛችውን ሴት ትክ ብዬ እያየሁ ሦስት ደቂቃ ያህል ቆምኩ፡፡ ለጊዜው አጥጋቢ ትርጉምና ምክንያት ያላገኘለት የሐሳብ ሞገድ አእምሮዬ ውስጥ ተነሣ፡፡ ልወጣ አቅራቢያ እንደ ራባት የውሻ ቡችላ በቀጭኗ ተንፍሳ ገልበጥ አለች። ከዚያም ምንም እንኳ የብርድ ልብሱን ዐልፌ ማየት ባልችልም እንቅስቃሴዋን ተከታተልኩ። እጅዋ ወደ ጀርባዋ ከዞረ በኋላ ከገላዋ ላይ የሚገለፈፍ ነገር ያለ ይመስል ጥፍሮቿ ያን ሲሰሙት ብቻ በድምፁ የሚያስታውቅ ሸካራ ጀርባዋን ማከክ ጀመሩ፡፡ ወዲያው ሥቃይና የስቅቅታ ፍርሃት የረመጠጣት ቀጭን ሳል ኃይሏን ወለሉ እየዋጠው ሁለት ጊዜ ተሰምታ እየሰለለች ወደመች፡፡ ከዚያ በኋላ ገመምተኛ ፀጥታ በመተካቱ መብራቱን አጥፍቼ ወጣሁ፡፡

አንጐሌ ውስጥ በቂ ኀዘናዊ ትርዒት አጭቄ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡
የመጀመሪያው ቀን በዚህ ሁኔታ ተፈጽሞ ዘልዓለም ወደማይመለስበት የትዝታ
ክልል ገባ፡፡
👍4
#የወድያነሽ


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


...ከማንም ውርጋጥ ጋር ሆያ ሆዬ ሲባልልኝ ተውሏል! ቆይ! አረ ገና ምን አይተህ!» ብሎ አይቀጡ ቅጣት ከቀጣኝ ወዲህ ያቺኑ አልፎ አልፎ ወጣ ወጣ የማለት ድብቅ ነጻነቴን ቀስ በቀስ አጣኋት፡፡

ከአባቴ ፊት ለፊት ቆሜም ሆነ ተቀምጨ የታየኝን መናገርና እንደ ልብ
መዝናናት እንደ ቅብጠትና ብልግና ስለሚቆጠር ፍርሃት ያልሞሰሞሰው ለጋ
መንፈሴ ሥቃይ ፈጥሮብኛል...

አባቴ ተነሥ ግባ የተባለ ይመስል ድንገት ተነሥቶ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ። አባቴ በመሆኑ ባልጠላውም ተነሥቶ በመሔዱ ቀለለኝ፡፡

እንዲት አነስተኛ ጥፋት ባጠፋሁ ቁጥር በመመከርና በልዩ ዘዴ በመገሠጽ ፈንታ የምቆነጠጥና የምሠታ ስለሚመስለኝ ትንሽ የልጅነት ጥፋት ባጠፋሁ ቁጥር ፍርሃት ይንጠኝ ነበር፡፡

አንድን ነገር ለማሰብ ሳይሆን ያሰብኩትን ትክክለኛ ነገር ለመፈጸም ወኔ የሚከዳኝ በዚህ ስውር ጫና የተነሣ ነው::

መገረፍና መቆንጠጥ ከቀረልኝ ጥቂት ዓመታት ዐልፈዋል፡፡ ሆኖም ያ በልጅነቴ በፍርሃት የተበከለውና በቁጣ የበለዘው አንጎሌ ለብዙ ዓመታት ያህል ሊሽር አልቻለም፡፡

ምሳዩን በልቼ ስጨርስ ስምንት ሰዓት ከኻያ ደቂቃ ሆናል። እንግዴ መቀበያ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ትልቅ ራዲዮ ድምፁን ዝቅ አድርጌ ከፈትኩት። የአምባሰል ሙዚቃ ይዘፈን ነበር፡፡

አስካለ እንጀራውን ካነሣች በኋላ የእጅ ውሃ ይዛልኝ ተመለሰች።

«ውሃውን አስቀምጠሽ ሂጂ» ስላልኳት አስቀምጣ ሄደች። እጄን ሳልታጠብ ተነሳሁና የሙዚቃውን ሥልታዊ አነሳሥና አወዳደቅ እየተከተልኩ አንድ ቦታ ላይ ቆሜ ንፋስ እንደሚያወዛውዘው የመቃ ቀምበጥ ተወዛወዝኩ፡፡
የአዲሲቱ ሠራተኛ ከሲታና ጠውላጋ ፊት በጥቂቱ ፈገግ ሲል ታየኝ። እንደ
ኮቸሮ ደርቆ የተንቀፈረረው ከንፈሯ ላመል ታህል ተላቀቀ። አቀማመጣቸውና
ቅርፃቸው ቁመትና ስፋታቸው ከጠባቧ ፍንጭት ጋር ልብን የሚማርኩና ስሜትን
የሚያረኩ ጥርሶች ታዩ። በመጠኑ ወየብየብ ብለው ጐድፈዋል። ውበትን ጥቁር ደመና እንደ ጋረዳት ጨረቃ በፊት ለፊቴ አድፍጦ አየኋት፡፡ ደካማ ፈገግታዋ
ግን ወዲያው በንና ጠፋች።

የትዕዛዝ ሳይሆን የልመናን ሁኔታ በምትገልጽ ድምፅ «ለእጄ ውሃ
ብትስጪኝ?» ብዬ ጠየቅኋት። መወልወያውን መሬት ጣል አድርጋ መጣች፡፡
ማስታጠቢያውን አንስታ በቀጭኑ አንቆረቆረችልኝ:: ያን ከሩቅ ያየሁትን ጸጉሯን ከቅርበት እስተዋልኩት፡፡ አንዲት ነቀዝ መሳይ የራስ ቅማል በዞማው ጸጉሯ ላይ ስታዘግም ቆይታ፡ ወዲያው ፍልቅ መሸጐጫ አግኝታ ተሸጐጠች፡፡ ልቤ ግራር ፍም ላይ እንደ ወደቀች የጮማ ምታሪ በተመሰቃቀለ ስሜት ሟከከች፡፡ የአካላቷ ጠረን እጅግም ደስ ሳይለኝ አስታጥባኝ ሄደች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዋል እደር እንዳለች የተሰጣትን ሥራ ሁሉ በጥንቃቄ መሥራት በመቻ መላው ቤተሰብ ደስ ተሰኘ፡፡ ዋናው ምድብ ሥራዋ ግን የቤተሰቡን ልብሶች ማጠብና የምትችለውን መተኮስ ሲሆን አልጋ ማንጠፍና ቤት መወልወል ተጨማሪ ሥራዋ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ወደዳት። ትሕትናዋና ታዛዥነቷ ለተወዳጅነቷ
ዋና ምክንያት ነበሩ፡፡ ከመዋል ከማደር ከሲታው አካላቷ ሥጋ በመደረሱና
ደሟም መለስ በማለቱ በሦስት ወር ውስጥ መለል ብላ የምትታይና ማለፊያ
ፈገግታ ያላት አንገተ ሰባራ ወጣት ሆነች፡፡

ስለ ሠራተኛይቱ አሠራርና አስተያየት የነበረኝ ግምት ሁሉ ከቀን ወደ
ቀን ተለወጠ። ማንኛውንም ለእኔ የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ እሷው እየሠራችና እያዘጋጀች እንድታቀርብልኝ ሙሉ ፍቃዴና ፍላጐቴ ሆነ፡፡ የልብሶቼን መቆሸሽና ያለመቆሸሽ እሷው ራሷ እየተመለከተች የተቻላትን ያህል ማጠብ አንዱ የሥራዋ ክፍል ለመሆን በቃ፡፡ ከዕለት ወደ ዕለት ትሁት አቀራረቧና ሥራዋ ሁሉ አስደሰተኝ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እህቴ ኖረችም እልኖረችም ራቴንም ሆነ ምሳየን የምታቀብርልኝ እሷው በመሆኗ ጠባይዋንና ሁኔታዋን በየጊዜው ለማወቅና ለመረዳት ቻልኩ፡፡

በአማከለች የእኩል ነኝ ባይነት» ንግግር አንጀቷ አርሮ የነበረው እናቴ እንደ ልብ ታዛዥና አቤት እመት የምትል ሠራተኛ በማግኘቷ ካሰችኝ እያለች ስትጠራት ጥቂት ልደታዎች አለፉ፡፡

ሰው ሁሉ ስሟን ጠይቆ ለማወቅ የፈራ ይመስል በማናውቀው በዋናው
ስሟ ሳትጠራ ከስድስት ወራት በላይ ዐለፉ፡፡ ትልቁም ትንሹም «አንቺ ልጅ
ወይም «አንቺ እንግዳይቱ» እያለ ስለሚጠራት የቀድሞ ስሟን የረሳች ወይም ስም የለሽ አስመሰላት፡፡

እሑድ አራት ሰዓት ገደማ ነበር፡፡ ቀላል የራስ ምታት ወረር ስላደረገችኝ
ከመኝታዩ ላይ ሳልነሣ አረፈድኩ፡፡ ተነሥቼ የወጣሁ ስለ መሰላት አልጋ ለማነጣጠፍና ክፍሉን ለመጠራረግ በቀስታ እያንጎራጎረች ዘው አለች። ቀጥ ብዬ በጀርባዬ ተንጋልዩ ስለ ነበር አልጋው ላይ ሰው ያለ አልመሰላትም፡፡በእንጉርጉሮ
የምታስኬዳትን ዜማዋን ሳታቋርጥ የብርድ ልብሱን መኻል በእጅዋ ነካችው።
ለአፍታ ያህል ጸጥ ብዬ ሳዳምጥ ከቆየሁበት ብርድ ልብስ ውስጥ ከመቅጽበት ራሴን ብቅ ሳደርግ በድንጋጤ ፈዝዛ ቆመች፡፡ አቀርቅራ ጥቂት ዝም ካለች በኋላ
“እኔ እኮ ወደ ውጪ የወጡ ስለመስለኝ ነው የገባሁት ብላ መሬት መሬቱን
ማየት ቀጠለች።ድንጋጤዋ እንዲለቃትና ፍርሃቷ እንዲወገድላት በማሰብ
ለጊዜው በዚያች ሰዓት የማያስፈልገኝን «እስኪ ሂጂና ለፊቴ ውሃ አምጭልኝ
ብዩ አዘዝኳት። እንዳቀረቀረች ወጣች። የውስጥ ቁምጣዬን እንዳጠለቅሁ እና ነጭ እጀ ጉርድ የውስጥ ጥብቆ እንደለበስኩ ብርድ ልብሱን ወደ ግርጌ ሽብልዩ ደረብኩና አልጋዬ ጫፍ ላይ ዐረፍ አልኩ፡፡ ለብ ያለ ውሃ በንጹሀ
ማንቆርቆሪያ ይዛ ተመለሰች።

በግራ እጅዋ የያዘችው ቀለሙ የተላላጠ እሮጌ ነጭ ሳሀን ዐልፎ ዐልፎ የተላከከና የማይለቅ እድፍ ነበረበት፡፡ ጋቢውን ከላዩ ላይ ገፍፌ አልጋው ላይ አኖርኩት፡፡ ማንቆርቆሪያውን እንዳንጠለጠለችና ሳሀኑን እንደ ዘረጋች ፊቷን ወደ ጎን አዙራ ቆመች። ራቁቴን የቆምኩ ስለ መሰላትና አለማፈሬም ስላስደነቃት የተገላቢጦሽ እሷ ማፈሯ ነበር፡፡ በቤታችን ውስጥ ሰው ባለመኖሩ በሩን ዘጋሁት።
አሁንም ፊቷ ወደ ተዘጋው በር እንደ ዞረ፡ ከመጠን በላይ አቀርቅራና በሙሉ
ዓይኗ ሳታየኝ አስታጠበችኝ፡፡ ያንቆረቆረችልኝ ውሃ አወራረድ እስከ መጨረሻ ሳይለወጥ ተንቀረቆረች።አፌን ለመጉመጥመጥ እንደ ፈለገ ሰው ጣቶቼን ቀልብሽ መዳፌን ውሃ ለማቆር እስኪችል አጐደጐድኩት። ውሃ እንድታንቆረቁርልኝ እጄን ዘረጋሁ። በዝግታ አንቆርቁራ ሞላችልኝ። አቀርቅራ ስታይ በሳህኑ ውስጥ የሚገኙትን የሳሙና አረፋዎች የምትቆጥር ትመስል ነበር፡፡ ጸጉሯ በሻሽ ባለመሸፈኑ በእጄ ላይ ያቆርኩትን ውሃ በዝግታ ጸጉሯ ላይ እንጠባጠብኩት፡፡ምንም እንኳ ውሃ እንዳፈሰስኩባት ወዲያውኑ ቢሰማትም ቀና ብላ አላየችኝም፡፡ቆየት ብላ ግን ራሷን እየነቀነቀች «እችክእችክ እችክ» ብላ ዝም አለች። ነገር ግን ባፍንጫዎ በኩል የተሰማችው ለዛማ ቀጭን የሣቅ ድምፅ መሣቋን አሳወቀችባት።
ውሃው በግንባሯ በኩል አኳልሞ ቁልቁል ወረደና ወለሉ ላይ ተንጠባጠበ፡፡
የፈገገውን ጠይም ፊቷን ለመመልከት በጣም ካጎነበስኩ በኋላ እንገቴን ወደ ጎን
ቆልምሜና ፊቴን ጋደል አድርጌ አሻቅቤ በማየት የፈገግታዋን መጠን ለካሁ፡፡
«ስምሽ ማን ነው? እስኪ ንገሪኝ?» ብዩ የአካላቴን አኳኋን ሳልለውጥ ጠየቅኋት።
አሽቆልቁለው ጉንጩን የሚመለከቱት ዐይኖቿ በሰፊው ከተከፈቱ በኋላ የማለዳ
ፍንድ አበባ የሚመስሉ ከንፈሮቿ ተላቀቁ፡፡ ቀጠን ብላ ቃናዋ እጅግ በሚማርክ
ድምፅ የወዲያነሽ» ብላ ከንፈሮቿን ወደ ውስጥ ቀልብሳ መጠጠቻቸው። ቀና
ብዩ በትክክል ቆምኩ፡፡ ልቤ ባንዳች የድንጋጤ ኃይል የተናወፀች ይምስል
👍91
#የወድያነሽ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


....የአባቴ ተራ ድንጋጤና የእናቴ ያልታሰበ ተራ ድንፋታ ልቤን በደስታ አክናፍ አበረራት፡፡ የአባቴ ድብቅ ፍላጎት ሳያስበው በመጋለጡ የሁለቱ ፋይዳ ቢስ ጠብና ስሜት ለስሜት መሳለል በጣም ቢያስደስተኝ ምናልባት እናቴ በዚሁ በሰማችው ብቻ ቅናቷ እያደር ይጎለምስና የወዲያነሽን ታባርራት ይሆን? በማለት መጪውን ጊዜ በሥጋት ዐይን ተመለከትኩት የጨዋነቱ ክብር» የተገፈፈበት የመሰለው አባቴ ያ አይበገሬ መሳይ ወኔው ላመል ታህል በርግጎ ከቆየ በኋላ ለመከላከል ያህል «አማረባት አልኩ እንጂ ምን ሳደርግ አየሽኝ? እኔ ያየህ ይራድ ከማንም ብራሪና ውዳቂ ጋር የምልከሰከስ ነኝ እንዴ? ከጠረጠርሽኝ፣ ዛሬውኑ! አሁኑኑ መንጥቂያት!» ብሎ በንዴት ወደ መኝታ ቤት ገባ፡፡

የእናቴ ፊት በቁጣ ተከስክሶ ዐይኖቿ በሽሙጥ ሸኙት። ነገሩ ተባብሶና
እንደገና ሌላ ነገር ጭሮ ውጤቱ መጥፎ አይሁን እንጂ እሳትና ጭድ ያድርጋችሁ
ማለቴ አልቀረም፡፡

ከአባቴ ይበልጥ ያናደደኝና ውስጥ ውስጡን ያበሳጨኝ ግን የቤታችን
ዘበኛ ነበር። በእርሱ የተነሣ ልቤ በቅናት እሳት ተለብልባ ተሠቃይታለች።

በመልኩ፣ በሰውነት አገነባብና ለግላጋነት ከምኑም አልደርስ። ፈገግታውና የባቄላ አበባ የመሳሰሉ ጥርሶቹ ይማርካሉ። በሥራ ምክንያት በምድረ ግቢው ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲል ከየወዲያነሽ ጋር የተገናኙ እንደሆነ ተሣሥቀውና ተጠቃቅሰው ይተላለፋሉ፡፡ ከነዚያ ልበሳቸው ብዬ ከሰጠሁት ሸሚዞችና ሱሪዎች መካከል የለበሰ ለትማ ማለፊያ ሙሽራ ስለሚመስል ለባብሶ ባጠገቧ ሲያልፍ ዐይኖቼ በቅናት ደም ይለብሳሉ። አውልቅ ብዩ የምነጥቅበትና ሰበቡ የማይደረስበት ስውር ደባ በማጣቴ ሐሳቤ እንደ ጨው ሟምቶ ቀረ።

ለሥራው ደፋ ቀና ሲል ሰርቄ ሽንት ቤት ውስጥ ለመክተት ያሰብኩበት ጊዜም ነበር፡፡ አንድ ቀን ማታ እርሱና የወዲያነሽ ተከታትለው ወደ ማድቤት
ሲገቡ በማየቴ ጨለማ ለብሼ ከአንድ ትይዩ ቦታ ላይ ከሩቅ አደፈጥኩ፡፡ ከአንድ
ጐድጓዳ ሳህን ውስጥ ፍትፍት ቢጤ ሳይሆን አይቀርም ቶሉ ቶሉ እያወጡ ግራና ቀኝ ቆመው መብላት ጀመሩ። አንድ ሁለት ጊዜ ያህል ለራሷ ትጎርስና ለእርሱም ያንኑ ያህል ታጐርሰዋለች። የአፉን ውስጥ አላምጦ ሳይውጥ ሌላውን ከከንፈሩ ጫፍ ትደቅንለታለች፡፡ ፍትፍት መሆኑ በግምት የሚያስታውቀው ከጉርሻዋ በኋላ ጣቶቿን በማራገፏ ነበር። ከቅናትና ከጥላቻ ብዛት የተነሣ ቁርጠት የቀሠፈኝ ይመስል ሰውነቴ ብው ብሉ- አንጀቴ በንዴት ተቋጨ።

«ና ውጣ ብዬ እርሱን ከእርሷ ነጥዩ የማስወጣበት ምክንያት እንደ ሰማይ
ኮከብ ራቀኝ፡፡ ነገር ግን ወዲያው አንድ ቀላል ነገር ትዝ አለኝ። ቀስ ብዬ
እያሰላሁ እንድ አራት ያህል ደህና ደህና ድንጋይ ከለቀምኩ በኋላ ትልቁን
የአጥር በር በድንጋይ ጠመድኩት።

አራት ጊዜ ያህል እንደ መታሁ ጅብ እንዳየች ቡችላ ሳህኑን ለቆላት ተፈተለከ፡፡ እሷ የበሩን መቃን ተደግፋ ቆመች፡፡ የወዲያነሽንም በመጠኑ ለማስደንገጥ ያህል አንዲት ትንሽ ድንጋይ ወደ ማድ ቤቱ በር እነጣጥሬ ወረወርኩ፡፡ በቀጭን የድንጋጤ ድምፅ «ውይ» ብላ ወደ ውስጥ ሮጠች። የሁለቱም ትኩስ ድንጋጤ ሳይበርድ ልክ ከቤት እንደ ወጣ ሰው ተመስዩ ከተደበቅሁበት ቦታ መሰስ አልኩና «ማን ነው? የማን ነው ባለጌ በጨለማ በር የሚደበድብ?» ብዬ ጮህኩ፡፡ ማንም አልመለሰልኝም፡፡

ዘበኛው የወረወረውን ሰው ለማወቅ በሩን ከፍቶ ወጣ፡፡ ባልተረጋገጠ የቅናት መነሾ የፈጸምኩት የተንኮል ድርጊት ራሴን እያሳፈረኝ እፈን አፍኜ ሣቅሁ፡፡ ነገር ግን ወደ ውጪ በመሄድ ፈንታ ወደ ቤት ገባሁ፡፡ ሆኖም መቀመጥም መቆምም የሚነሳ አንዳች ውስጣዊ ግፊት መላ አካላቴን ናጠው፡፡ አልቻልኩትም::

ሩብ ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የወዲያነሽ ዕቃ ቤት ውስጥ
ስትንጐዳጉድ እገኘኋት። ጣቴን በቁጣ እየነቀነቅሁ «ከዚያ ከመድረሻ ቢስ ሴት
አውል ዘበኛ ጋር ያደረግሽውንና የምትሠሪውን ያላወቅሁ እንዳይመስልሽ!
የመጣው ይምጣ እንጂ የማደርገውን ዐውቃለሁ፡፡ እኔ ጌታነህ ትርክርክሽን ነው
የማወጣው» ብዬ አፍጥጨባት ተመለስኩ፡፡ ክፉኛ ክው ብላ ነበር።
በስውርና በግልጽ መቆጣጠሬን ቀጠልኩ፡፡ የወዲያነሽ ከእኔ ጋር ምንም
ዐይነት ፍቅራዊ ስሜትና ዝንባሌ እልነበራትም፡፡ ስለሆነም ስለ ግንኙነታችን
የምታደርገው አንዳችም ጥረት አልነበረም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው «ሊያታልለኝና የምመልስለትን ለማወቅ ፈልጎ ነው» ብላ እንደሆነ እያደር ተገለጸልኝ፡፡

«ከዘበኛው ጋር ስትዳሪና ስትላፊ አይቼሻለሁ» ብዩ ከገሠጽኳትና
ከተንደራራሁባት ወዲህ ግን ወይ በፍርሃት አለበለዚያም በውስጧ ተሰዉሮ በነበረ ለጋ ውዴታ ምክንያት እርሱን ችላ ብላ ወደ እኔ መለስ አለች፡፡ ሆኖም
በቀድሞው አንገተ ሰባራነቷ ላይ በፍርሃትና በበታችነት ስሜት በመጠመዷ
የዝቅተኝነት ጭንቀት አጠቃት።

አንድ ቀን ማታ ከእኔና ከእርሷ በስተቀር መላው ቤተስብ ከላይ እታች በተኛበት ወቅት ኮቴዬን ሳላሰማ ከመኝታ ቤቴ አስልቼ ወጣሁ፡፡

ዕቃ ቤት ውስጥ ወዳለው ወደ የወዲያነሽ መኝታ ክፍል ለመሄድ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ስደርስ ከበሩ አጠገብ ቆማ አየኋት። የተከፈተውን የዕቃ ቤት መዝጊያ ተደግፋ ቆማለች። አንዲት አራት ማዕዘን መስተዋት በግራ እጅ ይዛ በመስታወቱ ውስጥ ከምታየው ከሌላዋ ነፍስ አልባ «እርሷ» ጋር ፈገግ እያለች ትሥቃለች። ቀና ብላ በድንጋጤ ካየችኝ በኋላ በምን ይለኝ ኀፍረት በእጅዋ የያዘቻትን መስታወት ከቀኝ እጅ ብብቷ ውስጥ አጣብቃ ይዛ አቀርቅራ ቆመች። እግሬ ላይ መጫሚያ ባለመኖሩ በለስላሳው እግሬ ያደረግሁት እርምጃ በሥጋጃ ላይ የምትራመድ የድመት አካሔድ ሆኖ ነበር፡፡

እጠገቧ ደርሼ ቆም ስል ወደ ጎን ሽርተት አለች። ገፋፍቶ ያስወጣኝ ድፍረት እንደ ቅቤ ቀለጠ። ሰውነቴ በኃፍረት ተተብትቦ ግድግዳውን ተደግፌ ቆምኩ፡፡ አወጣጡ ግን ግድግዳ ተደግፌ ለመቀም አልነበረም፡፡

ትሰድበኝና አጉል ታዋርደኝ ይሆን» እያልኩ በፍራቻ ስሜት ውስጥ
ከቆየሁ በኋላ «እስካሁን ምን ታደርጊያለሽ የወዲያነሽ?» ብዬ ለማሽኮርመም ያህል ባቀጠንኳት ድምፅ ጠየቅኋት። እንዳቀረቀረች አሻግራ ወለል ወለሉን እየተመለከተች «ማድ ቤት ወርጀ ገላዩን ስታጠብ ቆየሁና ይኸ ጸጉሬ
እንዳያስጠላ ከመተኛቴ በፊት ልጎንጉነው ብዩ ነው» ብላ ዝምታዋን ተያያዘችው፡፡

ምናልባት ያ መዘዘኛ ዘበኛ ገብቶ አጫውቷት ይሆን? በማለት መላ
ሰውነቴ በቅናት ግው ብሉ ጋየ፡፡ «መታጠቡንስ ጥሩ አደረግሽ፡ ለመሆኑ ግን እያሸሽ ታጠብሽ?» ብዬ ጠየቅኋት።
“አስካለ፣ እስካለ ናት ፍትግ አድርጋ ያጠበችኝ» ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ በቅናት የተሥረቀረቀ ልቤን ለማፅናናት «እኔስ ያ ዘበኛ ነው ብዬ አልኳት፡፡ ፊቷ ጠወለገ፡፡ ከወደ ውስጥ የሚወጣውን ትካዜዋን ይገልፅ ይመስል የቀኝ እግሯን ሰበር አድርጋ «ውይ! ምነው ምን አልኩዎት፡ ከዚያች እርስዎ ከተቆጡኝ ቀን ወዲህ ቀና ብዬም አይቼው አላውቅ:: እኔስ ይቺው የድሃ እንጀራዬ ትበልጥብኛለች» ብላ ከፊቴ ላይ ሁኔታዬን ለመረዳት ሰረቅ አድርጋ አየችኝ። ነገሩን ለማቃለልና የእርሷም ያልተዘጋጀ እእምሮ ምን መልስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ስል የቀኝ እጅ ጣቶቿን ያዝ አደረግሁና እረ ለመሆኑ እኔ እንደምወድሽ ታውቂያለሽ ወይ?» ብዩ በሙሉ ድፍረት ጠየቅኋት። ሆኖም ዝምታዋን ጥሶ የሚወጣ የመልስ ቃል ሳላገኝ ቀረሁ። አገጯን ይዤ ወደ ላይ
ቀና አደረግኋት። ያቺን ለስላሳ የምታምር ድቡልቡል እገጯን ስነካ ሰውነቴ
ውስጥ ተናዳፊ ንዝረት ለቀቀብኝ። እንደ ዱር ሀረግ አንገቷ ላይ ተጠምጥሜ
ብስማት እፎይታ እንደማገኝ ታወቀኝ፡
👍5
#የወድያነሽ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


አንዳንድ ቀን አካባቢውን መልከትከት ብዩ ሰው ያለመኖሩን አረጋግጥና ሥጋዊ ስሜቷን ለመቀስቀስ የሚችለውን የአካላቷን ክፍል ከፍ ወይም ዝቅ ብዬ
መደባበስና መጎነታተል አዘወተርኩ፡፡ ከወደ ውስጥ እየጋፈረ የሚያጠልማት
የኃፍረቷ ጎርፍ አፏን አፍና የሣቋን ግፊት እንድታምቅ ያስገድዳታል። ፊቷን
ሽፍና መሽኮርመምና ሰብሰብ ብላ መቀመጥ የዘወትር ልማዷ ነበር፡፡ እንደ ዘበት ሽብ ያደረገችውን ሻሿን ድንገት ስቤ እይዝና ያንን ውብ ኑግ መሳይ ጸጉር
በታትኖ ማየት ወደ እርሷ ከሚስቡኝ ሁኔታዎች ሁሉ የበላይነትን ያዘ፡፡

እንድ ቀን እንደ ልማዴ የጊዜና የአካባቢውን ሁኔታ ተመልክቼ እጅዋን
እያልመዘሙዝኩ አፌን ለወሬ ሾል ሾል ሳደርግ “ዋ" እለችኝና ዐይኔን እያየች
እናትዎ ያዩዎትና አጉል ቅሊት ይቀልላሉ፡ የኔ እንደሁ ዕውቅ ነው፡ ያው ሂጂ
ውጪ ከቤቴ ብለው ማባረር ነው» ብላ የተሰደሩ ጥርሶቿን ፈልቅቃ አስጐበኘችኝ፡፡ ለወጉ ያህል ጥቂት ተላፋን፡፡ ልባችን ተቀራርቦ ስሜታችን ይበልጥ ተዋሐደ፡፡ በፍቅራዊ ስሜት ለሚከታተሏት ዐይኖቼ የምትሰጠው ምላሽ አርኪ በመሆኑ የፍቅራችን ጋቢ ዐርቡ እየሰፋ ሒደ፡፡

እሑድ ጠዋት ነበር። ወላጆቼ የውብነሽን አስከትለው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደዋል፡፡ እናቴ ስለ እኔ ወደ ቤተ ክርስቲያን ያለመሔድ ስትናገር
«የሱን ነገር ተዉኝ! የእናንተ ጸሎት ለሁላችንም ይበቃል” ይላል። አይጣል
እቴ! ይኸስ የጤናም አይደል» ትላለች፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የምታቀርበውን
ነቀፌታ ከጉዳይም አልቆጥረው:: ተኝቼ አረፈድኩ፡፡ ጋቢ ለብሼ የመኝታ ቤቴን
በር ስከፍት የወዲያነሽ አረንጓዴ የውስጥ ልብስ ብቻ ለብሳ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ውስጥ መወልወያ ጨርቅ ይዛ ቆማለች፡፡ ጸጉሯ በተንተን ብሉ በአንገቷ
ዙሪያ ተሽመልምሉ ይዘናከታል፡፡

የአካላቷ ሙላት የመጨረሻውን ደረጃ ይዟል። ያ ከዓመት በፊት በርኅራኄና በአኗኗሯ በዐዘኔታ ላይ ተመሥርቶ የነበረው ስሜቴ ፍጹም ተለውጦ
አሁን ወደ ልዩ ሥጋዊ ውዴታ አጋድሏል፡፡ ዛሬ በተለይ በልቤ ውስጥ የጉርምስና
ደም ተንሽከሽከ፡፡

በትዕዛዛዊ አቀራረብ ሳይሆን ልዩ የመቀራረብን ስሜት ለማብሠር
በምታስችል ለስላሳ ድምፅ "ነይ እስኪ የወዲያነሽ?» ብዬ ጠራኋትና አልጋው
ጫፍ ላይ ተቀመጥኩ። የመስታወት መወልወያዋን እንደ ያዘች በአለባበሷ አፍራ መዝጊያው አጠገብ ቆመች። ስልክክ ባለው ጠይም ፊቷ ላይ ወርዶ ከጉንጫ ላይ ሲደርስ የሚርመሰመሰው የወጣትነት ሙሉ ደም ግባቷ የምሆነውን አሳጣኝ፡፡

«ግቢ እንጂ ምን ያስፈራሻል?» ብዩ ለማግባባት ሞከርኩ። ዐፈር ከድቷት እንደ ዘመመች የድሃ ጎጆ አንገቷን ወደ ግራ ጎን ሰበር አድርጋ ቆመች።

እንደገና ነይ እንጂ ግቢ የወዲያነሽ» ብዩ አባበልኳት። ውስጥ ውስጡን የበላይዋና አዛዥ መሆኔ ስለ ተሰማት በፍርሃት እየተናጠች ገባች፡፡ በሩን ዘጋሁት። ደነገጠች። የፈገግታዋ ንጋት ቀስ በቀስ ጠለሰ። እንደሚንበረከክ ተማሪ ጉልበቷን ሰበር አድርጋ ወለሉ ላይ ተቀመጠች፡፡ እኔም ስለ ወለሉ ላይ ትቢያ ምንም ሳልጨነቅ ከፊት ለፊቷ ቁጭ አልኩ፡፡ በስሜት ተቁነጠነጥኩ፡፡ ቤቱና በቤት ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ «መጡብህ! ደረሱብህ! የሚሉኝ ስለ መሰለኝ ዐይኖቼ ቃበዙ፡፡ ድንገት ብድግ ብዬ «ተነሽ» አልኳት፡፡ አነጋገሬ ቁጣ ቅልቅል በመምሰሉ ወዲያው ተነሣች። ልፊያ ቢጤ ለመጀመር በማሰቤ ሽንጧ ላይ ነካኋት። ተሸማቀቀች። ታዲያ ምን ያደርጋል፡ ምን እንደምፈልግና እንደማደርግ መላ ቅጡ ጠፋኝ፡ መላ አካላቴ ብው ብሎ ጋለና ፍርሃቴን ገፈፈው፡፡ የለበስኩት ጋቢ ተንሸራትቶ እግሬ ሥር ወደቀና በእግራችን ረጋገጥነው። እጆቼን ባንገቷ ዙሪያ ጠምጥሜ በልዩ ደስታ እምነሽነሽ ስለ ነበር የወደቀውን ጋቢ ቁብም አላልኩት። ድንገት አፈትልካ ለመሄድ ሞከረች::
አልተሳካላትም፡፡ ፊቷን ወደ ተዘጋው በር አዙራ ተቀመጠች፡፡ ከበስተጀርባዋ ቆሜ
ጎንበስ አልኩና እጄን በትከሻዋ አኳያ ወደፊት ቁልቁል ሰደድኩት። እንደገና
ከፊት ለፊቷ ዞሬ ተንበረከከሁ፡፡

ሳትወድ በግድ በአገጯ ወደ ላይ ይዤ ፊቷን አየሁት። እንባዋ ይጎርፋል፡፡ በእጄ ስቢያት ተነሣሁ፡፡ «እኔ እኮ የቀልዴን ነው:: ደስ ይልሽ እንደሆን ብዩ ነው እንጂ ደስ የማይልሽ ከሆነማ ከዛሬ ጀምሮ ከደረስሽበትም አልደርስ እ! » ብዬ እጆቿን እንደ ያዝኩ ዝምታዬን ተጎናፀፍኩ። ለማስመሰል እንጂ ከልቤ አልነበረም፡፡ ተፋጠጥን፡፡ ዐይኖቼ ቦዙ። ዘንጉን በዳበሳ እንደሚፈልግ ዐይነ ሥውር እጆቿን ዘርግታ አንገቴ ላይ ተጠመጠመች፡፡ ደረቴ ላይ ተለጥፋ አገጬ ስር ከቀረቀረች፡፡ የፊቷ ትኩሳትና የደረቷ ሙቀት ሲገናኙ ኃይለኛ ነዛሪ
የርካታ ማዕበል አጥለቀለቀኝ፡፡ የተስተካከለ ንዝረት ግን አልነበረም፡፡ ደረቴ ላይ እንደ ተለከፈች በጉንጯ ላይ እያቋረጠ የሚወርደው እንባዋ ስሷን ልብሴን አረጠባት። አዲስ ሰመመናዊ ቆይታ ተጀመረ፡፡ ከከንዲት ሥር ላይ የበቀሉ መንታ መቃዎች መስልን። ፀጥ እና ቀጥ በማለታችን እካባቢውን ጸጥታ
ሰፈነበት።

ግድግዳው ላይ የተንጠለጠለው ገደ ቢስ ሰዓት ጥበባዊ ተግባሩን ለመፈጸም ደወለ፡፡ እኔና እርሷም በዚያቹ ቅፅበት ከሰመመናችን ባነንን፡፡ ከራሷ ቀና ብላ በእንባ የተከበቡ ዐይኖቿን እና ፊቷን አሳየችኝ::

የስሜቷ ዶፍ ተፍ እለ። በሰውነቴ ውስጥ ያለው ኃይል ተንጠፍጥፎ ያለቀ ይመስል እጆቼ ዛሉ፡፡ ቀስ በቀስ አየት ሳደርጋት ወለሉ ላይ የወደቀውን ጨርቅ ይዛ በዝግታ ወጥታ ሒደች:: ዐይኖቼ አብረዋት ተጓዙ፡፡ እኔም ወለሉ ላይ
ወድቆ ባቧራ የተልሞሰሞሰውን ጋቢ አራግፌ ወደ አልጋው ግርጌ ወረወርኩት።አልጋዩ ላይ ወጥቼ በጀርባዬ ተንጋለልኩ:: ተንጠራራሁ፡ አፋሸግሁ፥ እግሮቼን እያኮራመትኩ ዘረጋሁ። ጥልቅ ፍቅር በውስጤ ተፍለቀለቀች፡፡ የአልጋው ሽቦዎች እስኪያንሲያጢጡ ድረስ ተወራጨሁ፡፡ እንደገና ቀና ብዬ አልጋው መኻል ተቀመጥኩ፡፡በስተራስጌ በኩል በምስማር ላይ የተንጠለጠለውን ኮቴን ተንጠራርቼ አወረድኩና ከልብሲ ጋር የከረረ ጠብ ያለኝ ይመስል አሽቀንጥሪ ግድግዳው ላይ አላተምኩት፡፡ ከአልጋው ላይ እመር ብዩ ወርጄ የወዲያነሽ አጥባና ተኩሳ ያስቀመጠችልኝን ሱሪ ከሻንጣ አወጣሁ፡፡ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጬ እግሮቼን ባንድ ጊዜ ቁልቁል በሱሪው አቆልቋይ ሰደድኳቸውና ቀጥ ብዩ ቆምኩ፡፡ በዙሪያዩ ያለው ነገር ሁሉ አዲስና እንግዳ ነገር መስሎ ታየኝ፡፡ ሰማያዊ ሸሚዝ ለብሼና ግራጫ ኮት ደርቤ ጸጉሬን ሳላስጥርና ያደረ ፊቴን ውሃ ሳላስነካ መሰስ አልኩ፡፡ወዴት እንደምሒድ አልወሰንኩም፡፡

ደረጃውን ወርጀ ግቢው መኻል ደረስኩ፡፡ የወዲያነሽ የሚያምር ቢጫ ቀሚስ ለብሳና ዐመድማ ሻሽ አስራ ማድ ቤቱ በራፍ አጠገብ ቆማ አየኋት፡፡በግራ እጅዋ አንድ ንጹሕ ነጭ ጭልፋ ይዛ ነበር፡፡ በዚያ ሰምቼ በማልጠግበው ድምጿ «እጅዎን ላስታጥብዎት መምጣቴ ነበር፥ ቁርስ አዘጋጅቻለሁ ቆዩ አትሒዱ» አለችኝ፡፡ በአድራጐቴ ሁሉ እንዳልተቀየመችና ቅር እንዳላላት በማወቄ ልቤ በደስታ እንደ ፈረሰኛ ጎርፍ ሽቅብ ዘለለች። ላሳየችኝ ብሩህ ገጽ የተከማቸ ፈገግታ ላኩና «ተመልሼ እመጣለሁ አዘጋጅተሽ ጠብቂኝ» ብያት ወጣሁ። የትምዋልኩ እንጂ እንዳባባሌ አልተመለስኩም፡፡

ቤተሰቡ በሞላ ስለ ሁለታችን የስሜት ቁርኝት የሚያቀው አንዳችም ነገር
አልነበረም፡፡ የአባቴ የዕረፍት ሰዓታት ሃይማኖት ነክ መጻሕፍትን ለማንበብና
ያንኑ የሕግ መጽሐፉን በመነዝነዝ ላይ ስለተመደቡ ለሌላ ጉዳይ የሚውል ጊዜ
አልነበረውም፡፡ እናቴም የተማረ ሰው፣ ዐዋቂ ነው እያለች በጣም ስለምትመጣብኝዐበእርሷ እምነትና ልማድ ከ«ገረድ» ጋር ይህን መሰለን ግን
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

...በአቅራቢያችን ያለችው ኮክ ለጋ ቅርንጫፎች ደፋ ቀና እያሉ እርስ በእርሳቸው እየተሳሳሙ ይበተናሉ፡፡ ጉንጯ ላይ ሳም ሳደርጋት የፍቅር ደማቅ ችቦ ተሀኮሰ አፌን ወደጎን አንሸራትቼ የከንፈሮቼን ነዲድ ከከንፎሮቿ አርኪ ገለት ጋር በማጋጠም ምጣድና አክንባሉ ሆንን፡፡ በሕሊናችንም ውስጥ ያ የፍቅር ችቦ ፏ ብሎ ሲቀጣጠል ታየኝ።

የወጣትነት ጣዕም፣ የፍቅር ማራኪ ለዛ፣ አንድ የመሆን ፍላጎት በዝግታ ወደ ውስጣችን ሠረፀ፡፡ ሰማይ እንደ አክንባሎ በላያችን ላይ ተደፍታ ቁልቁል ታስተውለናለች። ምን ግዳችን! የሚንቦገቦጉት ክዋክብት በጨለማው ከርስ ውስጥ የሚገኘውን ነገር ሁሉ ብርሃናዊ ውበት ሊዘሩበት ይታገላሉ። እንደ ገና ለስለስ ብሎ ከሚነፍሰው ነፋስ በተገኘው የቅጠላ ቅጠሎች ውዝዋዜ ላይ የከዋክብት ኅብራዊ ቀዝቃዛ ብርሃን ሲያርፍበት በወርቃማ ቀለም የተለበጠ ዕፅኖታዊ ሥዕል ታየ

እኔ በእርሷ የሕይወት ሰበካ፣ እሷም በእኔ የሕይወት መስክ እየተኩነሰነስን ወደማይታይና ወደማይዳስስ የሰመመን ዓለም ተጓዝን። ጥቂት ደቂቃዎች ዕለፉ፡፡

«እኔ የምልሽ» ብዩ ጀመርኩና «እስኪ ይኸው አሁን ብቻችንን ነን እውነቱን ንገሪኝ ታፈቅሪኛለሽ?» ብዬ ጠየቅኋት። የምትመልስልኝን ለመስማት ጆሮዩን ቀሰርኩ፡፡ አንደበቷን ከባድ ኃፍረት እየተጫነው «የትልቅ ሰው ዘር
ናቸው:: ዞር ብለውም አያዩኝ፣ እኔም የሰው አገር ሰው ነኝ እያልኩ ነው እንጂ
ማፍቀሩንማ መጀመሪያውኑ...» ብላ በዚያ ስስ ጨለማ ውስጥ የፊቴን ሁኔታ
ማየት ትችል ይመስል ትኩር ብላ አየችኝ።

«እንዲሀ አድርገናል፣ እንዲህ ሠርተናል ብለሽ አትናገሪም? ከዚህ ቀደም
በተናገርኩሽና በተቆጣሁሽ ምክንያት አልተቀየምሽም?» ብዬ ሁለቱንም ትከሻዋን ያዝኩ፡፡

«የምን መቀየም? ኸረ እኔ ከየቴ! እንዲያውም ደስ ደስ ነበር የሚለኝ።
እኔ ምክንያታቸውን እንጃ፡ አንድ ሰሞን እናትዎ ፊት ሲነሡኝ ነገሩሩን ሁሉ
ውጩ ዝም ያልኩት እርስዎን በማየት ነበር» ብላ በትኩስ ደም ጢም ያሉ
ጣቶቿን ባንገቴ ዙሪያ ዘረጋቻቸው:: ደቂቃዎቹ ጭልፊት እንዳየች ጫጩት
በነበር ጢሻ ውስጥ ለመሰግሰግ ሸመጠጡ፡፡

«እሜቴና ጌቶች ከተኙ ቆይተዋል» ብሎ በሹሉክታ ገብቶ ምድር ቤት ውስጥ የተኛው ዘበኛ እንዳይሰማን ኮሽታ ሳናሰማ ወደ ውሃው ቧንቧ ተመለስንና ተላያየን፡፡
የውጪውን ደረጃ በቀስታ ከዘለቅሁ በኋላ መብራቱን አብርቼ ወደ ክፍሌ ገባሁ። ወዲያው ልብሴን አወላልቄ አልጋዬ ላይ ተሸመለልኩ፡፡ አምስት ደቂቃ
በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመኝታ ቤቴ በር በዝግታ ተከፈተ፡፡ እሷው መሆኗን
በአረማመዷ ለይቻት ነበር፡፡ ያመጣችውን ውሃ አልጋዩ ሥር ከትራስጌ በኩል
ስታስቀምጥ «ገጭ» የሚል አጭር ወፍራም ድምፅ ሁለት ጊዜ ሰማሁ። በውሃ የረጠቡ እጆቿን በቀሚሷ እያደራረቀች በሩን ቀስ ብላ ከወደ ውስጥ ዘጋችው፡፡ብርድ ልብሱን ከወደ ትከሻዩ በኩል ገልጣ እጅዋን ወደ ውስጥ አሾለከች።ደረቴን አንገቴን ግንባሬንና ጉንጩን ደባበሰችኝ፡፡ እጅዋ ከግንባሬ ላይ እንደተለጠፈ ከተዘጋው የመኝታ ቤቴ መዝጊያ ውጪ ትንሽ ራቅ ብሎ የሚከፈት
በር ሲንሲያጠጥ በመስማቴ ሰውነቴ በጥርጣሬ ተንዘፈዘፈ፡፡ ልቤ በድንጋጤ
የተሰነጣጠቀች መሰለኝ፡፡

የሰው ኮቴ ተሰማ፡፡ ቁልቁል ወደ አልጋው ሥር ለመስረግ ፈለግሁ። የማይሆን አይሆንምና አልቻልኩም፡፡ የኮቴው ድምፅ እየቀረበና እየጎላ መጣ ቀረበ መጣ ቀረበ በሁኔታው ቁጥጥር ሥር በመዋሌ ፈጣን ውሳኔ ለመስጠት አዳገተኝ፡፡ የወዲያነሽ እጅዋን በፍጥነት ከግንባሬ ላይ አነሳችው::ፊቴን ገለጥ አድርጌ ሳይ ከመዝጊያው በስተጀርባ ተለጥፋለች፡፡

በሩ ከወደ ውጪ ተንኳኩቶ መጨበጫው ተነቃነቀ እና ወደ ውስጥ ተገፋ። የወዲያነሽ ከበሩ ላይ ተለጥፋ አብራ እየተገፋች የኋሊት ሄደች፡፡
ረዢም የውስጥ ልብስና ወፍራም ጋቢ ደርባ ራሷን ከፈት ባለው መዝጊያ
በኩል ወደ ውስጥ በማስገባት «ተኝተሃል እንዴ? ምነው ድምዕህ ጠፋ? ደኅና
አይደለህም እንዴ?» ያለችኝ እናቴ ነበረች። ጉድ ፈላብኝ!!

ድንጋጤ ባፈናት ደቃቃ ድምፅ ምላሴ አፌ ውስጥ እየተርበተበተች
«ደኅህ ነኝ፡ ምንም አልሆንኩም። ገና በጊዜ እኮ ነው የተኛሁት። ሂጂ ግቢ ብርድ አይምታሽ» አልኳት የሞት ሞቴን።
የወዲያነሽን ካጋጠማት የጉድ ፍላት ሥቃይና የድንጋጤ ረግረግ ውስጥ
ባስቸኳይ ለማውጣት ስል እናቴ እዚያው እንደቆመች ተሸፋፈንኩ፡፡ ሰውነቴ
ተንቀጠቀጠ። እናቴ ፊት እንደነሡት ቀላዋጭ በሩን ዘግታው ተመለሰች።

የወዲያነሽ በድንጋጤ ድርቅ ብላ ብቻዋን እንደ ቀረች ያጥር ዕንጨት ቆማለች። እጆቿ ደረቷ ላይ ተለጥፈዋል፡፡ እናቴ የመኝታ ክፍሏን በር ስትዘጋና
ትልቅ እፎይታና ግልግል! የወዲያነሽ ከወጥመድ እንዳመለጠች እይጥ በሩን ከፍታ እግሬ አውጭኝ አለች። በላዩ ላይ የወረደው የድንጋጤ ዶፍና ውርጃብኝ ወዲያው ጎደለ። በምትኩም ትዝታ እና ሰመመን እንደገና ደግሞ ትኩስ የፍቅር ሐሳብ አእምሮዬ ውስጥ “ዳንኪራና ሆታ ጀመረ::የወዲያነሽ ፈገግታ ለዛና ግልፅነት ሲነካካኝ ታወቀኝ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
...አባቴ የታላቅ ወንድሙን ጭምትነትና ልበኛነት እያስታወሰ በሚያወራበት ጊዜ ሁሉ ትዝታው በሐሳብ ፈረስ አፈናጣው ወደ አለፉት ዓመታት የኋሊት ትሰግርና ትካዜ መቀመቅ ውስጥ አገርግራ ትጥለዋለች:: መጋቢት አቦን በያመቱ እንደሚዘከርና በታላቅ መንፈሳዊ እምነት
እንደሚያምናቸው ሲያብራራ ፊቱ በኅዘን ተኮፋትሮ ዐይኖቹ በቁጣ ይጎለጎላሉ።

«ወንድሜን የገደለው የገዛ አራሹ ነው። ያውም የዋንጫውን ልቅላቂ ጠጥቶ የገበታውን ፍርፋሪ በልቶ ያደገ፡፡ የወንድሜን ገዳይ ለማስያዝና ከሕግ ፊት
አቅርቤ ለማስቀጣት በተጉላላሁ ጊዜ የደረሰብኝን ከባድ ስቃይ እስከ ዕለተ
ሞቴም አልረሳው:: ታዲያ ስፈልግና ሳስፈልግ ኖሬ ወሎ ውስጥ ከደሴ የትናየት ተንታ ከምትባል ትንሽ ከተማ ውስጥ መኖሩ በጭምጭምታ ታወቀ። ስገሠግሥ ሄድኩ፡፡ እዚያች ከተማ የገባሁት መጋቢት አራት ነበር። በማግሥቱ አሮጌ ሽማዩን ተከናንቤ ስፈልግና ሳስፈልግ ዋልኩ፡፡ መሸታ ቤቶቹ በቁጥር ናቸው።የሰው ደም አይለቅ አይደል! አንዷ ኮማሪት ቤት ተወዝፎ አምቡላውን ሲግፍ አገኘሁት፡፡ ወዲያው በነጭ ለባሽ አስያዝኩና እያካለብኩ ደሴ አስመጣሁት፡፡ገድሎ ዱር መግባቱ ቀድሞውኑ ተመስክሮና ተረጋግጦ አልቆ ስለ ነበር የኋላ ኋላ በስቅላት ተቀጣ፡፡

ልክ ባመቱ ደግሞ የአቦ ዕለት የአጥቢያ ዳኛ ሆኜ ተሾምኩ፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ልክ የአቦ ዕለት ተካበች፣ ሙሉነህን ተገላገለች። ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ እንደ ተራዱኝ ነው:: ከዚያ ወዲህ እንደ አቅሜ ጠበል ጠዲቃቸውን አስታጉዬ አላውቅም። አሁንም ቢሆን ሁልጊዜ ከጐኔ እንደ ቆሙ ናቸው፡፡ በጠበላቸውና በቃል ኪዳናቸው ነው ነፍሴ ቆማ የምትሔደው፡፡ እንደ
ሐኪሞቹ በሩን መቀባጠርማ ይኸነዬ እጓሯቸው ነበርኩ፡፡ አሁንም በሆነ
ባልሆነውና በትልቅ በትንሹ በተበሳጨሁ ቁጥር የደም ብዛቴን የሚያስታግሣልኝ
እሳቸው ናቸው። በሳቸው ጠበል ተነክሬ ከእምነታቸው ስቀምስ ዐይኔ ሁሉ
ያበራል» በማለት ያስረዳል።

በያመቱ መጋቢት አምስት ቀን በቤታችን ውስጥ ቅልጥ ያለ ድግስ ይደገሳል፡፡ የሚጠመቀው ጠላ የሚጣለው ጠጅ የሚሠራው ወጥና የሚጋገረው
እንጀራ መጠንና ብዛቱ ምን ያህል እንደሆነ የሚያውቁት እናቴና በየዓመቱ
ለዚሁ ጉዳይ የሚመጡት ሠራተኛ ሴቶች ብቻ ናቸው።

በግቢው ውስጥ ባለው ሰፊ ገላጣ ቦታ ላይ ባንድ ጊዜ ከሁለት መቶ ሰዎች በላይ ለመያዝ የሚችል ድንኳን ይጣላል፡፡ አባቴን ፍርድ ቤቱ የሚያውቀውና ዝናውን የሰማ ዘመድ
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


...«አይዞሽ አትፍሪ! እዚህ እኔ አልጋ ላይ ወጥተሽ ተኚ፡ ስንገባ ማንም አላየ» ብዬ እየተርበተበትኩ በሩን ዘግቼባት ውልቅ አልኩ፡፡

በድንኳኑና በምድረ ግቢው ውስጥ ግማሽ ሰዓት ያህል ከተዘዋወርኩ በኋላ
አንዳች አካላዊ ኃይል እየገፈትረና እያፍነከነከ ወደ መኝታ ቤቴ ወሰደኝ፡፡ ሰውነቷ በሥራ ድካም በመቀጥቀጡ አንቀላፍታ ስለ ነበር ከደረቷ በላይ ገልጬ አየኋት:: ዘና ብላ በጀርባዋ በመተኛቷ እንቅስቃሴው የሰከነ ውበት ረቦባታል።

የአካላቴን ኃይለኛ ሰደድ ለመቀነስ የተከደኑ ዐይኖችዋን እና የተገጠሙ
ከንፈሮቿን ዳበስኳቸው:: በወዲያነሽ ልብ ውስጥ ልዩ የሆነ የመኖሪያ ዓለም
አሰስኩ።

አንድ ራሴን ለመቆጣጠርና ለመግታት ያልቻልኩበት የነዳድና የአካላዊ
ውጥረት ቅፅበት ደረሰ፡፡ በስተራስጌ በኩል አልጋው ጫፍ ላይ ዐረፍ ስል ነቃች።

ዐይኖቿ በፍቅር ቦግታ ልባዊ መስተንግዶ አደረጉልኝ፡፡ ወዲያው ፊቷን አዙሪ ሆድና ጉልበቷን አጣብቃ በፍርሃት እየተንቀረቀበች ተኛች፡፡ ከጎኗ ጋደም
አልኩ፡፡

ከገላዋ ላይ በወጣው ሙቀት ለብ ያለው የብርድ ልብስ ውስጥ ኣየር የሚያፍነከንክ ደስታ ሰጠኝ፡፡ ልብሷን በሙሉ አወላልቃ በመተኛቷ ገራገርነቷ ከፍላጎቴ ኃይል ጋር ትንቅንቅ ገጠመ፡፡

አንድ ኃይለኛ የሥጋዊ ፍላጎት ግፊት ናጠኝ። ራስን በመግታት ለፍላጐት በመንበርከክ መካከል የቀበጠ ፍልሚያ ተፈጠረ፡፡ የየወዲያነሽ ሕይወት
በእኔ ግድየለሽነት የሚሰናከል መሰለኝ፡፡

«ፍላጐቴን ፈጽሜ ስሜቴን ካረካሁ በኋላ የወዲ ያነሽን እስከ ዘለቄታው
ለመርዳትና በፍቅር ፀንቼ አብሬያት ለመኖር ያለኝ ቆራጥነትና የሕሊና ጥንካሬ
እስከ ምን ድረስ ነው?» እያልኩ በማውጣትና በማውረድ ከራሴ ጋር ትግል ጀምርኩ፡፡ ከራሴ ጋር የማደርገውን ክርክር ሳልደመድምና ኃላፊነቱን ለመሸከም ሳልወስን፡ የየወዲያነሽንም የሕይወትና የኑሮ ሁኔታ አንድ አቅጣጫ እስይዤ ሳልወስን ዕቅፌ አባበልኳት፡፡

ተመሳሳይ ፍላጎቶች ይዋሐዳሉ ሆነና ሰምና ወርቅ ሆንን፡ የልቧ ምት አየለ። የአተነፋፈሷ ፍጥነት በውስጧ ከፍተኛ የስሜት ሲቃ እንዳለ እወጣጡ
ይገልጻል። ለአጭር ጊዜ ትንፋሿን ዋጠች፡፡ ድንገት በመኻሉ የልቅሶ ድምፅ
ሰማሁ፡፡

«ወይኔ እናቴ! ምነው ያንቺን ቀን በሰጠኝ፡፡ ወይኔ ዕድሌ ወይ አለመታደሌ” ብላ ያመቀችውን ትኩስ አየር ለቀቀችው:: እንባዋ እንደ ጎርፍ ይወርድ ጀመር፡፡ በረጂሙ ከተነፈሰች በኋላ ወይኔ ዛሬ ፡ አዬ መከራዪ አዬዬ አበሳዬ!» ብላ በግንባሯ ተደፋች፡፡ ቀጣዮቹ ደቂቃዎች ምን ሊገጥማት እንደሚችል ወለል ብሎ ታይቷታል፡፡ ምንም እንኳ ለቅሶዋና የሚንስፈሰፈው ሰውነቷ ርኅራኄ ቢያሳድሩብኝም አካላዊ ፍላጎቴን ጎትተው የሕሊና ገደብ ሊገድቡብኝ አልቻሉም፡፡ የስሜቴ ልጓም ተበጠሰ፡፡ የልመናዋን መንደርደሪያ ቃላት ከመጤፍ አልቆጠርኳቸውም፡፡

“ይህ ሁሉ ልቅሶና ልመና ይከዳኛል ብለሽ ይሆን? ቃል እገባልሻለሁ አልከዳሽም፡፡ ምንም ቢባል ምንም ቢመጣ እስከመቼም ቢሆን አልከዳሽም፡ ይህ
ፍቅራችን ምስክሬ ነው » ብዬ ደንበኛ የልብ ማጥመጃ ቃል ገባሁ፡፡

ከዚያ በኋላ ቦርቧራ ልቧንና ንጹሕ ልቦናን በአንደበቴ ተጫንኳቸው:: ከግማሽ ሰዓት በኋላ የድንግልናዋን ኪላ ጣስኩት፡፡ እዩዩዋ አንጎሌ ውስጥ ሠረፀ።በመኻሉ የወዲያነሽ እኔ በምሰማው ሁኔታ ብቻ ኡኡ ልትል ስትል አፏን በአፌ ከደንኩት፡፡ ሕሊናዋን ስታ ዧ ብላ ተዘረረች፡፡ ተዝለፈለፈች፡፡ ልቤ በርህራሄና በሀዘኔታ ተንፈራፈረች፡፡

ከአልጋው ላይ ዘልዬ ወረድኩና የተቻለኝን ያህል ረዳኋት፡፡ የሌሊቱን ቀዝቃዛ አየር አርገበገብኩላት፡፡ ድካሟን አቃልዩ ብርታት ልሰጣት ባለመቻሌ በንዴት ተከንኩ። ያም ሆነ ይህ አንዴ ለተፈጸመ ነገር ሌላ አዲስ ፈጻሚ የለውምና እንደገና መብራቱን አጥፍቼ ከጐኗ ጋደም አልኩ። በደረቷ ተደፍታ ለጥ አለች፡፡

ከእንቅልፌ ስነቃ ከሌለቱ ዐሥር ሰዓት ነበር፡፡ በደማቁ የመብራት ብርሃን
በጥቃት የፈዘዘ ውበቷን አየሁት። መኝታችን ተበክሏል። የየወዲያሽ ማራኪ
ዐይኖች ትንገርበዋል፡፡ መብራቱን አጥፍቼ እንደገና ጋደም አልኩ፡፡ ሕልም መሰል
ቅዠቶች እየረከረኩኝ አለፉ፡፡ ዳግመኛ ስነቃ ዐሥራ አንድ ሰዓት ከሃያ ነበር፡፡
የጭንቀትና የፍርሃት ናዳዎች አንጎሌ ውስጥ እየጓኑና እየተውዘገዘጉ ሰላም
አሳጡኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩ፡፡ የመኝታ ክፍሌን መስኮት ከፍቼ አሻግሬ ማየት
ጀመርኩ፡፡

የማለዳዋ ፀሐይ ልትወጣ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቀርተዋል፡፡ ከሩቅ
የሚታየው ምሥጢራዊ አድማስ ያልያዘ ግሽርጥ መስሏA። ጎህ ቀደደ። ሰማዩ
በብርሃን አውታሮች ተሽነሸነ፡፡ ጋቢዬን ደርቤና የመስኮቱን ደፍ ተደግፋ የምድረ
ግቢውን የጨለማና የንጋት ውጋት የመጨረሻ ግፊትና የተተከለውን ድንኳን
በዐይነ ችላ አየሁት። ወገገ፡፡ የማለዳው ቀዝቃዛ አየር አካባቢውን በዝግታ ሲያስስ
የእኔም አንጐል በልዩ ልዩ ሐሳብ ተፈተሽ፡፡

የድግሱ አሳላፊዎችና አስተናባሪዎች እንዲሁም እንግዶች ከመነሣታቸው
በፊት የወዲያነሽ መውጣት ስላለባት አልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጥኩ፡፡

ግራ እጄን አሾልኬ ርኅራኄ ባጀበው ሁኔታ አንገትና ደረቷን ዳበስኩ:: እውነትም ጥሩ መላ ኖሮ ሳትደነግጥ ነቃች፡፡ ገለጥ ስትል ዐይን ለዐይን በመጋጨታችን ዐይኖቿ በኃፍረት ተሰበሩና ተሸፋፈነች፡፡

የተፈጸመው ሁሉ መታየትም ሆነ መሰማት ስለሌለበት በስጋት ተቅበጠበጥኩ፡፡ ከወላጆቼ በኩል እጅግ ከፍ ያለ የውርደትና የቅሌት ዶፍ
ቃላት እንደሚደርስብኝ ዐውቃለሁ፡፡ እሷም ባልታሰበ የመከራ ውርጂብኝ
እንዳትጐዳ በማሰብ «እስኪ እንደ ምንም ብለሽ ቀና በዪና ተነሽ» ብዩ ትሕትና
ባልተለየው አኳኋት ጠየቅኋት።

ፈገግ ብላ ቀና ስትል ልቤ በደስታ ተለጠጠች፡፡ የደቂቃዎቹ መደራረብና
መተካካት ሙሉ ንጋትን አስከተለ። የአፍንጫዋን ጫፍ በጣቴ እያነቃነቅሁ ከእኔ ጋር ተኝተሽ ማደርሽ እንዳይታወቅና እንዳይሰማ ሰው ሁሉ አንዳንድ እያለ
ከመነሣቱ በፊት ሹልክ ብለሽ ሒጂ» ብዩ ግዴታ የተቀላቀለበትን ንግግሬን
አሰማኋት። ምንም እንኳ ተኝታ ለማርፈድ እንደማትችል ብታውቅም ለጊዜው
ፊቷ በኃዘን ቅጭም አለ። ዐይኖቿ ቀዘዙ፡፡ የሐሳብ ጋሬጣ ጠቀጠቃት፡፡ ልብሷን
ለባብሳና ጸጉሯን እንደ ነገሩ ጎንጉና ከፊት ለፊቴ ቆመች፡፡ ሥቃይዋ አንጀቴን
አላወሰው:: እንደ ሰረቀ ሰው ተሸሽጋ እና ሹክክ ብላ ማንም ሳያይና ሳይሰማ
ወጥታ ሔደች፡፡ ያደረግሁት ድርጊት አስጸያፊና የግድ የለሽነት አሠቃቂ
ተግባር እንደሆነ ገባኝ፡፡ በፍቅር ስም የተፈፀመ ወንጀል፡፡ የእኔ ነገር ግመል ሠርቆ አጎንብሶ ሆነ፡፡ ሆኖም ግብ የለሽ ጸጸት ከተቃወሰ ሕሊና የሚፈልቅ የልቦና እድፍ በመሆኑ በብስጭት ታጥቦ አይጠራምና ድርጊቴ ክፉ አፉን እንደ ከፈተ ቀረ።

ራሴን ከሐሳብ ወጥመድ ነፃ ሳላወጣ፣ ከግራም ከቀኝም ከደጅም ከቤትም
የሰው ድምፅ ተስማ። አንድ ሰዓት ተኩል ላይ ከሰው ጋር ተደባለቅሁ፡፡ ወዲያ
ወዲህ አላልኩም፡፡ ከመኝታ ቤቴ ፊት ለፊት እንግዳ መቀበያው ክፍል ውስጥ
ጉብ አልኩ፡፡

በየወዲያነሽ ልብ ውስጥ አንጸባራቂ እምነት በማስቀመጤ ትነግርብኝ ይሆን? ጉዴን ፀሐይ ታሞቀው ይሆን? በማለት እምብዛም አልሠጋሁ። የውብነሽ
ያደረ ፊቷን ውሃ እንኳ ሳታስነካ ተፍተፍ ስትል መጥታ ያንን የእኔን እረንጓዴ
ፎጣ አንተ መኝታ ቤት ውስጥ አይቼው ነበር» ብላ ብሩን ከፍታ ዘው አለች።
ሰውነቴ የጥቅምት ውርጭ እንዳደረበት ብረት በድንጋጤ ቀዘቀዘ፡፡ ተነሥቼ ለመሸሽ ትንሽ ነበር የቀረኝ ዐይኔ በድንጋጤ ፈጥጦ አፌ ከመቅፅበት ኩበት ሆነ።ድንገት ከጭንቀቴ ምጥ ተገላገልኩ ፎጣውን አንጠልጥላ ተመለሰች፡፡ ልክ እንደ ሰከረ
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

...አንድ ሰዓት ገደማ ከፈጀው የኅብረተሰብ ኑሮ ክርክራችን በኋላ
ከየወዲያሽ ጋር በስውር ስለ ፈጸምነው ፍቅራዊ ግንኙነት ቦጨቅጨቅ አድርጌ
ገለጽኩለት። በአውራ ጣቱና በሌባ ጣቱ መካከል እያሽከረከረ ሲያፍተለትላት
የነበረችውን ወረቀት አሽቀንጥሮ ወረወራት። የሚናገረውን እጅግም ሳያሰላስል
“አንዳንድ ሰዎች መጥፎ ነገርን ለማቀድና ለመፈጸም ምንኛ ይቀናቸዋል?
ሕይወትን ከመገንባት ይልቅ መናድና መበታተን እንዴት ይከሠትላቸዋል? ሌሎችን እፍ ባለ ገደል ላይ መገፍተር ደስ ያሰኛቸዋል?» ብሎ ከፊት ለፊቱ ቆሞ የሚታይ ተናካሽ ሐሳብ የቆመ ይመስል አፈጠጠ፡፡ ቀላ ያለውን ዞማ ጸጉሩን በግራ እጁ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ማሻሸት ጀመረ፡፡ ምን እንደሚያስብ ባላውቅም ተበሳጨ፡፡ ሐሳቤንም ሆነ መላ አስተያዬቴን ሳይቀበለኝ ቀረ። አድራጎቴ ሁሉ በተራ እንስሳዊ ባሕሪ የተፈጸመ ስሕተት ብቻ ሳይሆን ወንጀል መሆኑንም አስረዳኝ::
ጭንቀት አጥለቀለቀኝ። ተገናናንታ ለመናገርና ለመፀጫወት ተዝናንታ
የቆየችው ምላሴ እሳት ውስጥ እንደ ገባች ጅማት ተኮማተረች።

«ልጓም አልባ ሥጋዊ ፍላጎትህን ለማርካትና ቅንጣት የሕይወት ደስታ
ለመቅመስ ስትል የሌላዉን የሕይወት መስኖ መድፈንና ዙሪያው ገደል
እንዲሆንበት ማድረግ መጥፎ ጭካኔ ነው። ሆምጣጣ ኑሮ እንዲጠብቀውና
እንዲሠቃይ ማቀድም ሰዎች ከሚፈጽሟቸው ነውረኛ ድርጊቶች መካከል አንዱ ክፍል ነው::

ሌላዉን ወደ ምድረ ፋይድ አሽቀንጥረህ አንተ ሽቅብ መመንጠቅ እንደማይገባህ ማወቅ ነበረብህ፡፡ ለአንተ በቂና ትክክለኛ የመሰለህ ምክንያት ሁሉ ለሌላዉ ስሕተትና ከንቱ ነገር ሊሆን ይችላል። እንዴት ሕይወትን በአንዲት ጠባብ የሕሊና መስታወት ብቻ ትመለከታታለህ? የሕሊናህ መስታወት ሰፊና
ንጽሕ መሆን አለበት» ብሎ ግንባሩን ማሻሸት ጀመረ፡፡ ማባሪያው እንዳልደረሰ
ገባኝ…. እውነትም ቀጠለ፡፡ «ይህን በመፈፀምና በርኩሰት የተጠቀለለ ጥቅም በማነፍነፍሀ ወደእንተ የኑሮ ደረጃ ልታደርሳት አትችልም፡፡ በሌሎች ላይ
የተተበተብክና የተንጠለጠልክ ግንደቢስ ሐረግ እንጂ ጠንካራና ሥር ሰድዳ
የበቀለች ችፍርግ ታህል እንኳ አይደለህም፡፡ በአንድ የሕይወት ጀልባ ላይ ለመንሳፈፍ የጋራ ውሳኔ ቢኖራችሁ ኖሮ እኔም በሐሳብሀ በተስማማሁ ነበር። ነገር ግን አንተና ብጤዎችህ ሁሉ ከሥሯ መነጋግላችሁ ለማድረቅና አበስብሳችሁ
ለመጣል ያሰፈሰፋችሁ ስግብግቦች እንጂ ለሰብአዊ እኩልነት መሥዋዕት ለመሆን እጃችሁን የምታነሡ እንዳልሆናችሁ ዕውቅ ነው:: የዚህ ዐይነቱን የግድ የለሽነት ድርጊትማ አንድ ተራ ኣራዊትስ ይፈፅመው የለም እንዴ? ገና ለገና ትተናኮለኝ ይሆናል ወይም ለምግብነት ትጠቅመኝ ይሆናል በማለት ሌላዋን የዋህ እንስሳ የሚያበክት አራዊትስ መች ጠፋና? ... ብሎ ክፍሉ ውስጥ ከተንቆራጠጠ በኋላ ፈንጠር ብሎ ሌላ መቀመጫ ላይ ተቀመጠ። ቀኝ እግሩ ግራ እግሩ ላይ ተደርባ
ወደ ፊትና ወደ ኋላ ስትወዛወዝ የሱሪውም ጫፍ አብራ ትርገፈገፋለች። ነገር እየቆፈረ ነው፡፡ በመስኮት በኩል ገብቶ እንደ ውሃ አዙሪት እየተሽከረከረ
ከሚወጣው አየር በስተቀር ሌላውን ድምፅ ተፈጥሮ የገዘተችው ይመስል ቤቱ
ረጭ አለ።

የጉልላት ቁጣና የክፍሉ ውስጥ ደንዳና ጸጥታ ስሜቴን አደነዘዘው:: ዐይኖቹ ጨፈን ገለጥ ጨፈን ገለጥ እያሉ ይርገበገባሉ፡፡ የዐይኑ እንቅስቃሴ
ዝምታን ጥሶ አካባቢውን ተንቀሳቃሽ ድምፆ ሊነዛበት አይችልምና ክፍሉ አውሬ
የማይላወስበት ውድቀት መመስሉን ቀጠለ፡፡ ብስጭቱ እየባሰበት በመሄዱ
በውስጡ ሲፈራገጥ የቆየው ንዴት ከንፈሩን እንደ ገጠመ «ህ እ» አሠኝቶ ዝም አሠኘው። ዝም ብዬ ማዳመጥ ፀጥ ብዪ በሐሳብ በትር መደብደብ ስለ መሰለኝ በውስጤ ያለውን ምክንያትና ሐሳብ ሁሉ ዘክዝኬ ለማቅረብ ተነሣሁ:: «አይ እንግዲህስ ሳይበቃህ አልቀረም» ብዬ በመጀመር «ምስጢሬን ያንዶለዶልኩልህና ሐሳቤን ያካፈልኩህ እውነተኛ ጓደኝነት ጠንካራ የሕሊና ግንኙነት ድልድይ በመሆኑ ነው:: ብሳሳትም ባልሳሳትም ባጠፋም ባላጠፋም የአንተ ሐቀኛ አቋም
የእኔ የሕይወት ምስክር ነው:: ያሰብኩትንና የወጠንኩትን የቸገረኝንና
ያጋጠመኝን ሁሉ ካላወየሁህማ የጓደኝነታችን ጥልቅ ትርጉምና መሠረቱ ምንድን ነው ሳልንገዳገድና ፊት
ለፊቴ ሳይጨግግ ልራመድና ልመለከትበት የሚያስችለኝን የአስተያየት መላ በማቅረብ ወደ ተደላደለ አካባቢ አዝልቀኝ እንጂ፣ መሳሳቴንማ እኔም ራሴ ቀደም ብዬ ተረድቸዋለሁ! » በማለት ጨረስኩ።ትኩር ብሎ አይቶኝ አቀረቀረና፣

«ብሳሳትም ባልሳሳትም ማለት አትችልም። አዎ ጓደኝነት የሁለት
ሰዎች መገናኛ የሕሊና ጋብቻ ናት” ብሏል አንድ የፈረንሳይ ምሁር ብሉ ጀመረና፣ ሙሉ ልቦናህ ጭምር እንጂ ሥጋዊ አካልህ ብቻውን ዘላቂና ድርጁ
አያደርገውም፡፡

ያውም ይኸ የአንተ አድራጎት የሌሎችን ሕይወትና ኑሮ የማጥቆሪያና የማሰናከያ ግልጽ ዝሙት እንጂ የጋብቻን ጠርዝ እንኳ የሚነካ ኢምንት የታማኝነት ድርጊት አይደለም፡፡

«በአንተና በእኔ ዐይነት ኑሮ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቁልቁል ወርዶ መኖር የሞት ያህል ያስፈራቸዋል። በሌሎች ትከሻ ላይ ቆመው ወደ ላይ መውጣት የሚጥማቸውን ያህል ወደ ታችኛው ኑሮና ዓለም መውረድ ግን እጅግ ስለሚመራቸው በኃይልና በግዴታ ካልተዘረጠጡ በቀር አይንበረከኩም፡፡
አይወርዱም፡፡»

“ምንም እንኳ የልብ ጓደኛዬ ብትሆን ለአካባቢህ ኅብረተሰብ መርዝ ሆነህ
የሌላውን ሕይወት ለማጨለም ስትጣጣር ላይም ሆነ ስሰማ ዝም አልልህም።አንድ ሰው 'ጓደኛዬ ነህ' ሲልህ ጠላቴ አይደለህም ማለቱ ነው:: ስለዚህም ከጠላት የሚለይበትን አብይ ቁም ነገር በሚገባ ማሳየት ይገባዋል» ብሎ ነገር ለማብላላት ተግ አለ፡፡ ውርጃብኙን ፈርቼ ዝም ኣልኩ። በቅሬታ ጉልበቱን መታ መታ አደረገና ያም ሆነ ይህ ጠላትህን ከማሞገስ ደካም ወዳጅህን ማሻሻልና ማረም ወደር የሌለው መልካም ተግባር ነው» ብሎ ከወንበሩ ላይ ተነሳ።

ቁጣውን በወንድማዊ ትህትናና ለዘብታ ለማቀዝቀዝና ለመግባባት በመፈለጌ ጥፋተኝነቴን በምታስረዳ ልም የጸጸት ፈገግታ ትክ ብዬ እያየሁ «መቼም በእኔ በኩል ያለው ነገር እንደ ከረመ እንቁላል በስብሷል። ከአንተ የምጠብቀው ደግሞ የቁጣ ቃላት ዶፍ ሳይሆን አራሚነት ያለው ተጨባጭ ድጋፍህን ነው» ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ ድጋፍ የምትጠይቀው አስነዋሪ ድርጊትህን የመደበቂያና ከማታመልጠው የሕሊና ፍርድ የማምለጫ ጥያቄ እንጂ እውነትን ለማፍረጥረጥ እና ለእርሷ እንደ ጸጉር የቀጠነችባትን የሕይወት ጐዳና
ለማስፋትና ለማደላደል አይደለም። እንደ ቀስተ ደመና አምረህ ለመጉበጥ እንጂ
መሰናክል እንዳላጋጠመው የብርሃን ጨረር ቀጥ ብለህ ለመጓዝ አይደለም» ብሎ ፊቱን አዙሮ ቆመ፡፡ «እኔ የምልህ እኮ፣ ዛሬ በምን ላይ ቆሜ ስለ ነገ በምን ሁኔታ መዘጋጀት እንደምችል ንገረኝ ነው:: በእኔ መዘዝ አስቸጋሪ ሕይውት
የሚያጋጥማትን ሰው በእጄ እየሳብኩ ወደ ትክክለኛ ዓለም የምትዘልቅበትን
መንገድና ዘዴ አሳየኝ ነው የምልህ» ብዬ በድፍረት መለስኩለት::

ድንገት ሳላስበው ፊቱን ወደ እኔ መለስ አደረገና የጊዜ ርዝመትም ሆነ እጥረት ያው ነው:: አንድን ተግባር ለማከናወን የሚፈጅብህን ጊዜ ማሳጠር ይቻላል፡፡ የአንዲት ደቂቃ የሕይወት ርዝማኔ ግን ምንጊዜም ቢሆን ያው ነው:: ትልቁ ግብግብ ያለው ካንተው ከራስህ ጋር ነው:: ሰው የለውጥ ምንጭ ነው፡ ነገ
ላይ ቆሜ፣ ዛሬ ላይ ተንበርክኬ ማለት የችግርህ ማቃለያ አይሆንም፡፡ ስንዘጋጅና
ዛሬ ነገ ስንል እፍኝ የማትሞላዋ ዕድሜያችን እንደ ማሰሻ ጨርቅ ነድዳ ነድዳ ታልቃለች ፡፡ የአንተ
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

...ሌላ የሕይወት ምዕራፍ ተከፈተ። የየወዲያነሽ የፈገግታ አበባ ቀስ በቀስ
ጠወለገ፡፡ አልደረቀም።

ድንገት በመኻሉ የየወዲያነሽ ቀንጣ ቀንጣ ማለት ሰካነ፡፡ እንቅስቃሴዋ ዝግ በዝግ ቀዘቀዘ፡፡ ዐቅም እያነሳት እንደ ጠራራ ቅጠል መጠወላለግ ጀመረች፡፡
ድምጿ ደቆ አካላቷ ዝሉ አረማመዷ ዳ አለ፡፡ ፊቷ ድምቡጭ ብላ ከመወፈሯም በላይ ግንባሯ አካባቢ ላመል ታህል ላብ አይታጣም። ፈገግታዋን ፍዘት ቢይዛትም የጠይምነቷ ውበት ተንደረበበ፡፡ ከወደ ዳሌዋ ኮራ አለች፡፡ ገላዋ ዳበረ ዐይኖቿ ንጸሕ የጠራራ ምንጭ ውሃ መስለው ጎደሉ፡፡ በአቋቋሟም ሆነ በአለባበሷ ግድ የለሽ ሆነች። እንዲህም ሆና ውበቷ ታይቶ አይጠገብም፡አብሶ ለእኔ፡፡
«ምን ነካት?» በማለት ውስጥ ውስጡን በሐሳብ ተብሰለሰልኩ። አንድ ቀን ወደ ሥራ ለመሔድ የሰበሰቡን ደረጃ መውረድ እንደ ጀመርኩ ከወደ ኋላዩ ከች አለችብኝ።

አንገቷን ሰበር አድርጋ ቁልቁል ደረጃ ደረጃውን እያየች ጊትዬ ብርቱካንና ሙዝ ገዝተህልኝ ለመምጣት ትችላለህ?» ብላ ጠየቀችኝ::

«አማረሽ እንዴ? ማታ ይዤልሽ እገባለሁ፡፡ በምሳ ሰዓት ግን አምጥቶ መስጠት ያስቸግራል» ብያት እሷ ወደ ቤት ስትመለስ እኔ ደረጃውን ወርጄ
ሂድኩ።

ማታ በወረቀት ከረጢት ጠቅልዬ ይዤላት ገባሁ፡፡ ከዚያች ቀን ጀምራ ልዩ ልዩ ነገሮች 'አማረኝ ግዛልኝ' አምጣልኝ ማለት ጀመረች። ባለርስቱ ሳያየው እሽት ሰርቆ እንደሚገባ ጭሰኛ እንደ ምንም ደብቄና አመሻሽቼ ይዤላት እገባለሁ፡፡ ከየውብነሽ ጋር የምታደርገው ወሬና አንዳንድ ተራ ድብቅ ልፊያም በጣም ቀነሰ። ተቀምጣም ሆነ ቆማ ብቻዋን ትተክዛለች። አንጎሏ ከባድ ሐሳብ
የተጠመደ መሰለ።

አንድ ቀን ማታ ከራት በኋላ ከመኝታ ቤቴ ወጥቼ እንግዳ መቀበያ ክፍል ስገባ ወደ መኝታ ክፍሏ በሚያስገባው በር አቅራቢያ እንጨት ወንበር ላይ ተቀምጣ አገኘኋት። አቀማመጧ ስሜቴን ነካው:: ኣጠገቧ ሄጄ ቆምኩ። እንባዋ በጉንጫ ላይ እንደ ካፊያ ጠፈጠፍ ይወርዳል፡፡ በተንተን : ያለው ጸጉሯ ባለመጎንጎኑ የተፈጥሮ ኅብሩ ሳይሆን ተጨማሪ ውበቱ ቀንሷል፡፡ ስታለቅስ በማየቴ እኔንም ተናነቀኝ፡፡ ትካዜዋ ልቤን ቦረቦረው:: ተነስታ ወደ ክፍሏ ስትገባ እኔም የክፍለሉን መብራት አጥፍቼ ተከትያት ገባሁ፡፡

ልብሶቿ ሁሉ ንጹሕ በመሆናቸው ደስ ይላሉ፡፡ እሷ አልጋዋ ጫፍ ላይ
ስትቀመጥ ፊት ለፊት ቆሜ እጅዋን ያዝኩና የወዲያ ምን ሆነሻል? ምን ነካሽ?
ደኅና አይደለሽም እንዴ?» አልኳት።
«ምንም አልሆንኩ» ብላ ባጭሩ
መለሰችልኝ።

“ታዲያ ለምን ታለቅሻለሽ?» ብዬ ጥያቄዬን ስደግም «እንዲያው በዕድሌ
ነው የማለቅሰው» ብላ የሚተናነቃትን እንባና የትካዜ ቁራሽ ለመዋጥ ሞከረች።

«ዕድልሽ ምን ሆነ? ምን መጥፎ ነገር ኢጋጠመሽ?» ብዪ አይኖቿን
ጠረግሁላት፡፡

«አይ ጌታነህ! ምን ብዬ ልንገርህ? አንተ ወንድ ነህ፡ ምን ቢሉህ ምን ታውቃለህ? እኔስ እንደዬ ከርታታ ነኝ፡፡ እንተ ደግሞ..» ብላ ሐሳቧን ሳትጨርስ ድምጿ በእንባና በልቅሶ ኃያል ተሸነፈ፡፡ መሪር ኀዘን ተሰማኝ፡፡ ብድግ ብላ አንገቴ ላይ ተጠመጠመች፡፡ እያንዳንዱ ስሜት የየራሱ ጊዜ አለው፡፡ ባየሁት ነገር ስሜቴ
በጨነቀ የከዚያ ቀደሙ የወንድነት ሥጋዊ ፍላጐቴ ሟሽሽ፡፡

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አስተኝቻት ወጣሁ። ምን እንደ ሆነችና ምን እንደ ነካት ለማወቅ ባለመቻሌ አእምሮዬ ምክንያት ፍለጋ ኳተነ። በማግሥቱ
ጧት ፊቴን ስታስታጥበኝ ትንሽ ፈገግታ አየሁባት፡፡ ፊቴን በፎጣ እየጠራረግሁ
አጠገቧ ቆም እንዳልኩ የትእዛዝ ሳይሆን የልመናን ሥልት በያዘች ዜማ «ጌታነህ፡
አትመረረኝና አሁንስ አበዛሽው አትበልና፣ ዛሬ የትም የትም አይቡ ገብተህ ዓሣ
ይዘህልኝ ና» አለችና ቀስ ብላ ከአጠገቤ ዘወር አለች።

ከአንድ ከታወቀ የሀገር ባሕል ምግብ ቤት በእንጀራ አስጠቅልዩ በንጹሕ ወፍራም ወረቀት ሸፍኜ በድብቅ ይዤላት ገባሁ፡፡ የዕቃ ቤቱን በር ዘግታ ዐፈር
አስጋጠችው፡፡

ከሁለት ሳምንት በኋላ አንድ ቀን ማታ ትልቁ ክፍል ውስጥ እንደ ተቀመጥኩ የወዲያነሽ ሰው የለም ብላ በመገመት የክፍሉን መብራት ለማጥፋት በውስጥ ልብሷ ብቻ መጣች፡፡ ያልታሰበ አጋጣሚ ነበር! የእናቱን ሞት እንዳረዱት ሰው ክው ብላ ደነገጠች። አይደበቄው ስውር ሸክሟ ተጋለጠ፡፡የደበቀችውን ችግርና የልቅሶዋን መነሾ በገሃድ አየሁት፣ ለየሁት። የወዲያነሽ አርግዛለች!!

በዚያች ደቂቃ ውስጥ የሥቃይዋ መነሾ ዋናዉ ጦስ እኔ እንደሆንኩ ስለ ታወቀኝ ራሴን በጸያፍ ወራዳ ደረጃ አየኋት፡፡ ሕይወቴንም እንደ ልክስክስና መርዘኛ አውሬ ቆጠርኳት። የጉልላት ቁጣና ተግሣጽ እንዲሁም አስተያየቶች ሁሉ
መንጋጋና ጥርስ አውጥተው ነቸፉኝ፡፡ ሕሊናዬ የማረፊያ ቦታ አጥታ በስቃይ
ገመድ ተንጠለጠለች። ስለ ችግሯ የማውጠነጥነው ሐሳብ ሁሉ እንደ ጥላ ነፍስ የለሽና የማይጨበጥ ሆነ፡፡ ማርገዝዋን ካወቅሁ አንድ ወር እንደ አንድ ሳምንት ዐለፈች።

የየወዲያነሽ ማሕፀን ተንቀሳቃሽ ሕይወት ሲያረግዝ የእኔ የአንጎል ማሕፀን ደግሞ ረቂቅ የጭንቀት ሐሳብ ፀነሰ። ያም ሆነ ይህ አንድ ቀን ቢስቱ ዓመት ይጸጸቱ” በመሆኑ የወዲያነሽ ይህን መሰሉን የተፈጥሮ ጉዳይ “ማታለልና መሸሽግ ስለማትችል እርግዝናዋን እናቴና እኅቴ በየተራ አወቁ፡፡ ከዚያም በኋላ
የእኔና የወዲያነሽ ነገር ከሆድ ያኖሩት ያድናል የተናገሩት ያስገድላል ሆነና
አባቴ እንዳይሰማና መሬት ቃጤ እንዳትሆን ተፈርቶ እርሱ ፊት እንዳትቀርብና ጉዳዩ እንዳይጋለጥ በእናቴና በእኅቴ በኩል ምስጤር ሆኖ ቆየ። የእናቴ የጥርጣሬ ዓይን በእኔ ላይ ተተከለ። ምን ይኸ ብቻ

«እኔ ልጂት እንኳንስ ይቺን ቀላሏን ሌላም ነገር ዐውቃለሁ፡፡ ከዘር ነው ካጥንት» ብላ ባሽሙር ነካካችኝ። ፊቴን ማየት አስጠላት። የነገሩን አዝማሚያ
ለመከታተልና ድንገት የሚሆነውን ለማወቅ ወፍራም ትዕግሥት ተከናነብኩ። ያም ሆነ ይህ በሕይወቴ ውስጥ የመጀመሪያዋ አስፈሪና አሳዛኝ ቀን መድረሷ አልቀረም፡፡

አንድ ቀን ማታ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ላይ የወዲያነሽ እንዳመጣላት የጠየቀችኝን እሽግ አሣ ይዤ ገባሁ፡፡ ለወትሮው ወደ ቤት ስገባ ማድ ቤት አካባቢ አለዚያም ትልቁ ክፍል ውስጥ አገኛት ወይም ኣሻግሬ አያት ነበር፡፡ ያን ዕለት ማታ ግን እንኳንስ አካሏ ድምጻም ጠፋ፡፡ መኝታ ቤት ውስጥ ከገባሁ በኋላ ካሁን አሁን ብቅ ትል ይሆናል በማለት ብዙ ጠበቅሁ፡፡ ምናልባት መግባቴን አላወቀች ይሆን በማለት በመስኮት በኩል ብቅ ብዬ በቀጭኗ አፏጨሁ፡፡ ፉጨቴን የአካባቢው አየር ከርስ ዋጣት፡፡ እንደገና ደግሞ ዘፈን መስል ፉጨት ሞከርኩ፡፡ እንደ ቀዳሚዋ ወደመች፡፡ ሰሚ በሌለበት አካባቢ ምንም መልስ አይኖርምና ሙከራይ ከንቱ ሆነ፡፡

ከወዴ ወላጆቼ መኝታ ክፍል ውስጥ ተራ እየጠበቀ የሚነሣ ሣቅ ይሰማል። ምናልባት እዚያ ትኖር ይሆን? እናቴ ሥራ አስይዛት ይሆን? የሚል ጥርጣሬ ገባኝ፡፡ የምሰማው ሣቅ ልቅሶ መስሎ ተሰማኝ። ቤቱ የኀዘን አዳራሽ መሰለኝ፡፡ መርዶ መጣብህ! ያውም አሳዛኝ መርዶ” እያሉ የሚነግሩኝም መሰለኝ፡፡

የማየውና ከፊት ለፊቴ የነበረው ነገር ሁሉ አስፈራኝ:: ሽሽ፣ አምልጥ? የሚል ቃል በሐሳቤ እየተመላለሰ አስጨነቀኝ፡፡ የተንጠለጠለው መብራት የብርሃን
ሳይሆን የሥቃይ ማሠራጫ መሳለኝ፡፡ የመጣው ይምጣ ብዬ መኝታ ክፍሏ ውስጥ ዘው ኣልኩ፡፡ የዕቃ ቤቱ ዕቃ ቤትነት አልተለወጠም፡፡ የየወዲያነሽ አልጋ መለመላውን ተዘርግቷል።
ልብሷና ሌላዉ ኮተቷ የለም፡፡ በቁሜ በደንኩ! ወደ ፊት ራመድ ብዬ ሽቅብም ቁልቁልም ተመለከትኩ። ቤቱ ኦና ሆነብኝ።
ግድግዳው ላይ
👍2
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

...«አዎ ይኸው ነው! ጨርሻለሁ! አንዲት ሕይወት አንጋድጃለሁ! ቅንና ገር ሕይወት ቀርድጄ ጥያለሁ» ብዪ አጠገቤ ያለውን ጠረጴዛ በቡጢ መታሁት፡፡

ጉልላትም «እኔም እኮ መጀመሪያውኑ ያውም ገና ከቡቃያነቱ ከፍ ሳይል
ነግሬህ ነበር» ብሎ ሲያነብ የቆየውን መፍሐፍ በሌባ ጣቱ አለበና «እንደ ጨው
ካሟሟሃት በኋላ ወደየትም ቦታ ትረጫታለህ፡ ወይም እንደ እንኮይ ከበላሃትና እንደ አጥንት ከጋጥሃት በኋላ እንትፍ ብለህ ትጥላታለህ ብዬህ ነበር፡፡ ክልልህና ክልሏ አንድ ካለመሆኑ የተነሣ እንዴ አጋጣሚ እንኳን ሆኖ ብትንጠለጠልባት እንደ ተልባ ሥፍር ትንሽራተታለህ፥ በአንተና በእርሷ መካከል: የኮርማና የአምቦሳ ያህል ልዩነት አለ» ብሎ ቁልቁል ወለል ወለሉን አየ። በየወጂያነሽ ላይ የደረሰውን ማንኛውንም ነገርና ሁኔታ ሁሉ ተርኬ ጨርሼለት ስለ ነበር አሁን ከእርሱ የምጠብቀው ምክሩን እንጂ በሰነበተው ሐሳቡ ውስጥ የነበረውን አፍራሽ ነቀፌታ አልነበረም፡፡

«ስማ» አለኝ የመጽሐፉን ገጾች እየገለባበጠና ዐይኑን በሐሳብ እያቦዘ፣
«ከእንግዲህ ምስጢርህ ሁሉ ያንተ እስረኛና ምርኮኛ መሆን አለበት፡፡ ከበተንከውና ከረጨኸው ግን አንተው የምስጢርህ ምርኮኛና ግዳይ ትሆናለህ፡፡ ምስጢርህን በውስጥህ ለማዳፈን የምትችል ከሆንክና እሷንም እንደማትከዳት ከራስህ ጋር
እውነተኛ ቃል ኪዳን ከገባ ዓላማህን ለመፈጸምና የትግልህን ምርት ለማፈስ
ነገሩ የካባድ ቀላል ይሆናል፡፡ አሁንም እንደገና ልንገርህ፤ ያለ ጥርጥር ድል
ማድረግ ትችላለህ !» ብሎ አንገቱን ወደ ኋላ ቀልሶ ጣራ ጣራውን ማየት ጀመረ።
ሳይታወቀው እግሩን ዘረጋ።

«ያጠፋሁትን የሕይወቷን ቀንዲል እንደገና ለመለኮስና በተደላደለ የኑሮ
መሠረት ላይ እንድትገኝ ለማድረግ ታጥቄ ተነሥቻለሁ! ዛሬ ባላገኛት ነገ፣ ነገ
ባይሳካልኝ ከነገ ወዲያ ከዚያም ከዚያም በኋላ ቢሆን አገኛት ይሆናል። ሆነም
ቀረም ያስጨበጥኳትን መራራ የኑሮ ጽዋ ከንብዬ ሌላ ጣፋጭ የሕይወት ጽዋ
እስጨብጣታላሁ! ሕይወቴም እፎይታና ልባዊ እርካታ ማግኘት የምትችለው
የተጉደፈደፈችበትን የጸጸት ዕድፍ አጥባ ስታጠራ ብቻ ነውና እስከ ዘለቄታው
እታገላለሁ:: ከጥንትን፣ ሥጋንና ደምን፣ ክብርንና ርካሽ አዋራጅ ቃላትንም
በቆራጥነት እቋቋማቸዋለሁ» ብዩ ተራ ለቀቅሁ።

ጣራ ጣራውን ሲመለከተ የቆዩትን ዐይኖቹን ወደ እኔ መለስ አደረገና
አንገቱን አስተካከሎ

«ሌላ ነገር ባደርግልሀና ብመክርህ ይሻለኛል፡፡ እኔም የሐሳብ እንጂ ሙሉ
የተግባር ሰው አይደለሁም፡፡ የወላጆችህን እምነትና አስተሳሰብ በቀላሉ መለወጥ እችላለሁ ብዬ አልናገርም፡፡ አስተሳሰብን መለወጥ እንደሚቻል ባውቅም አፈፃፀሙ ግን ብዙ ውጣ ወረድ አለበት፡፡ ለዘመናት የኖረን የሕዝብን እምነት መለወጥ ቀላል ጉዳይ አይደለም፡፡ አንተም ውስጥ እኮ ያ እምነት አለ፡፡ እኔም ዘንድ አለ:: ኋላ ቀር አመለካከትን ከሕሊና ላይ አጥቦ ለማፅዳት አያሌ ዓመታት ይፈጃል። በዚያ ላይ ርዝራዥ እስኪወገድ ብዙ ፈተና አለ። ይህ ጉዳይ ከተራው ዜጋ እስከ ከፍተኛው ባለሥልጣን ድረስ ይዘልቃል፡፡ ያም ሆነ ይህ አንተ ግን ከዛሬ ጀምረህ በዓለም ላይ ያለውን አንድ ተራ አድካሚ ሥራ ለማከናወን ሞክር፡፡«በመጠኑ እንኳ ከተሳካልህ ጥሩ ታጋይ ነህ ማለት ነው። አዎ ሌላ አይደለም፡ እስኪ በመጀመሪያ ራስህን ለማወቅና ለማሽነፍ ሞክር፡፡ ብልህ መሆን ማለት ስለ አንድ ስለ አጣኸው ወይም ስለማታገኘው ነገር ተጎልተህ መተከዝ አይደለም፡፡ ይልቅስ እሷ በአካልና በሕሊና የምትካስበትንና መልሰህም ማግኘት የምትችልበትን መንገድ መፈለግ ነው» ብሎ ጸጉሩን ማሻሸት ጀመረ።

ምንም እንኳ ሐሳቡ ረቅቆ የሚያመራምር ባይሆንም ለጊዜው ብቻዬን ሆኜ በአእምሮዬ ሰለቅሁት። በየበኩላችን ሐሳብ በማንሣትና በመጣል ላይ እንዳለን
እኅቱ ሻይ ይዛልን ከተፍ አለች፡፡

«ግን» አለ ያንን ሁለትና ሦስት ጊዜ ያህል እ-ፍ-እ-ፍ ብሎ ፉት ያለውን ሻይ ኣፉ ውስጥ አቀዝቅዞ ከዋጠው በኋላ፡፡

«ይኸው ለእኔ እንኳ ከምስጢርህ ውስጥ ጥቂቱን ነግረኸኛል፤ ቀሪውን ቀብረህ ለመጠበቅ የሚኖርህ ኃይል ግን አነስተኛ መሆን የለበትም። አደራህን! አንተ ልታምቀው ያልተቻለህን የገዛ ራስህን ምስጢር ሌላ ሰው ሊጠብቅልህ
አይችልምና ማንም የማይከፍተው የልብ ሳጥን ይኑርህ! ዓላማህን ለመፈጸምና
ከግብህ ለመድረስ ለራስህ ከራስህ የሚቀርብህና በፍጹም ተግባራዊ መሰልህ ሌላ ማንም እንደማይገኝ አትዘንጋ» ብሎ ወደ ሻዩ ዞረ።

ጓደኝነቱን በቃል ሳይሆን በተግባር ያከናወነልኝ ስለመሰለኝ ጉልላትን
ከቀድሞው በበለጠ ከራሴ ጋር አዋሐድኩት፡፡

ሐሳቡን ለአንድ አፍታ ቆም አድርጎ ደረጃ በደረጃ ፈገግ ካለ በኋላ ለዛ የሌለው ሣቅ ሣቀ። «ለመሆኑ አሁን ብታገኛት ምን ትላታልሀ? ” ምንስ ታደርግላታለህ?» ብሎ ደረቅ ፈገግታውን አሳየኝ፡፡

ድንገተኛ ጥያቄው ድንገተኛ መልስ እንድሰጥ ያስገደደኝ ይመስል
የንግግሬን አካሔድ ሳልመለከት የመጣው ይምጣ እንጂ ቤት ተከራይቼ
አብሬያት እኖራለሁ፡፡ ከዚያ ወዲያ ማንም ያሻውን ቢልና በእኔና በእርሷ የተነሣ
ቤተሰቦቼ እንኳ ብትንትናቸው ቢወጣ ግድ የለኝም» ብዬ መለስኩለት፡፡ አሁንም
ሐሳብ ሊሽከሽክ ሰምቶ ዝም አለ፡፡

ጉልላትን ከማደንቅበት አንደኛዉ ዋና ምክንያት የግል ሐሳቡን ስፋት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሰዎች ያገኘውን ዕውቀትና አነጋገር ሳይረሳ ለሌላ
የማስተላፍ ችሎታዉን ነው::

«መቼም በራስ መተማመንና ሕሊናን መግዛት የጀግንነት ምሰሶ ነው ብሏል አንድ ሊቅ» ብሎ ንግግሩን በመጀመር «የሚያዋጣትን ትክክለኛ መንገድ
ለማግኘት ስትል የምትፈራና የምትጨነቅ አእምሮ ፍጻሜዋ ያማረና የሠመረ
ይሆናል” ብሏል አንዱ ሌላ ሊቅ ደግሞ» በማለት የማዳምጥ መሆኔን ለመገንዘብ
ትኩር ብሎ አየኝ::

«እኔም ለፅኑ ጓደኝነታችንና ለፍቅራችን ዘላቂ ሕይወት ስል የችግሮችህ
ሁሉ ሙሉ ተካፋይ እሆናለሁ፡፡ በምታደርገው የውጣ ውረድ ትግልም ይሁን በሌላ ማናቸውም ነገር እኔ አንዱ ግማሽህ ነኝ፡፡ የብርሃናዊም ይሁን የጽልመታዊ ፍጻሜህ ማኅበርተኛ እሆናለሁ» ብሎ የማያወላውል ልበዊ ጓደኝነቱን አረጋገጠልኝ፡፡ የዕለቱ ምከራችንና ሐሳባችን ሰምና ወርቅ ሆኖ አለቀ።

የወዲያነሽ አድራሻና መገኛ ትላንትም ከትላንት ወዲያም እንደሆነው
ሁሉ፣ ወደፊት ግን የሕልም ሩጫ ሆኖ እንደማይቀር ሙሉ ተስፋ ነበረኝ።
የወዲያነሽን ፍለጋ ጉልላትም አብሮኝ ባዘነ፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል! የሁለታችንም
ልፋት የማይገኝ የቅዠት ወርቅ ሆኖ ቀረ።
እናቴን በጥላቻ ጥቁር ዐይኖች ተመለከትኳት። በቤተሰቤ መኻል እያለሁ
የከለልኩት የብቸኝነት ክልል ግን እኔኑ እንጂ ማንንም አልጎዳ፡፡ እኔ የእኔዉ
ረመጥ ነኝና የሕሊናዬ ረመጥ እኔኑ መልሶ ፈጀኝ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጥቅምት ኸያ አራት ቀን አንድ ያልተጠበቀና ያልታሰበ ምንም ዝግጅት
ያልተደረገለት ትልቅ የደስታ ቀን ሆኖ ዋለ፡ ቤታችን በእንግዶች እና በልዩ ልዩ
ስዎች ተጣበበ፡፡ ላለው ምን ይሳነው፡ ሆንና ለተገኘው ደስታ የተፋጠነ ድግስና
መጠነኛ ግብዣ ተደረገ፡፡ አባቴ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ እንዲሆን ተሾመ ትልቁ ክፍል ውስጥ መላወሻ ጠፍቶ ዋለ። አንዳንዶቹ ያልፈጸመውን እየጨመሩና እያሞጋገሱ የሆነና ያልሆነውን ዝና እየሰጡ አወሩ።
አንዳንዶቹ ደግሞ ግራ ቀኛቸውን መልከትከት ብለው ቤተኛ ሰው ያለመኖሩን ካረጋገጡ በኋላ ከሐሜታው
ወርወር አደጉ። አባቴ የመጣውን ሰው ሁሉ በደስታና በፈገግታ እየተቀበለ ሸኘ።
ሹመት ያዳብር ጌታዩ” እያለ የሚመላለሰውና እጅ የሚነሳው
👍4
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

....እሑድ ማለዳ ነበር፡፡ ሰማዩ በመፀው ደመና ተሸፍኗል። ብን ብን የምትለዋ ካፊያ ኻያና ሠላሳዎ በአንድ ላይ ተጠራቅማ አንድ ሙሉ ኩልልታ ሆና
ትንጠፈጠፋለች። ፀሐይ በወፍራም ጉምና ደመና በመሸፈኗ ጨረሯ ከደመናዉ ጣራ በላይ ውሏል። ዕለቱ ተስፋ የቆረጠ ሰው ፊት መስለ ፈገግታ እርቆቷል።

አንዳንድ ጊዜ እስከ ቤት ድረስ እየመጡ ከሚጠይቁኝ ተራ ጓደኞቼ መካክል ታምራት ደረሰ መጣ፡፡ ከመጠን በላይ ተለማማጭነትንና ጉብቂጥ ማለትን ስለሚያዘወትር በተለይ ከጉልላት ጋር በሐሳብና በአመለካከታቸው
አይጣጣሙም፡፡

እኔም ከተራ ጉዳይ በስተቀር ምስጢሬን አላካፍለውም፡፡ በቤት ውስጥ ከእኔና ወዲያ ወዲህ ከሚሉት ሠራተኞች በስተቀር ማንም አልነበረም፡፡ ቁም ነገር
የሌላቸው ልዩ ልዩ ወሬዎችን አወራን፡፡ ድንገት በወሬያችን መኻል ስለ ሰው
ልጅ ጠባይ ምርምር የወጠነ ይመስል “አይ የሰው ልጅ! » ብሎ ራሱን ነቀነቀ፡፡

በምርምር እንዳልበሰለ ፈላስፋ ብዙ ሐሳብ መቧጠጥ ልማዱ ነበር፡፡ ፊቱ
ላይ የነበረችው ፈገግታ ቀስ በቀስ ተዳቀቀች። ምክንያቱን ሳላጣራና ሳልሰማ
ብናገር ፈጥኜ መሳሳት ስለ መሰለኝ “ምነው?» እንኳ ሳልለው ቀረሁ፡፡

«መጀመሪያስ ፍላጐትና ስሜት አስገድዷቸው ፈጽመውታል እንበል! ከተወለደ በኋላ ግን እንደ ውሻ ቡችላ የትም አውጥተው መጣላቸው በጣም ያሠቅቃል፡፡የዘመናችን ሰዎች አረመኔና ከሃዲዎች ሆነዋል፡፡ በእንዲህ ዐይነቱ ሰዎች ላይ ፍርድ ስጥ ቢለኝ ምን ፍርድ እንደምሰጥ እኔ ዐውቅ ነበር፡፡ በጣም የገረመኝ ግን የእናትዮዋ ነው:: ለምና እንኳ ብታሳድገው ምን ነበረበት?» ብሎ ከንፈሩን በቁጭት ነካከሰው::

«ምን ሆነሃል? ምን ነካህ ዛሬ?» ብዬ ከመጠየቄ እንደ ገና ራሱን ነቅንቆ
«እስኪ እግዚኣብሐር ያሳይህ! ሰው ክቡር ነው; ሰው ከሁሉም ፍጥረታት በላይ
ነው። እግዚአብሐር እንኳ የፈጠረው በገዛ ራሱ የመልክ አምሳል ነው ይባላል፡፡
ዛሬ ምን ያየሁ መሰለህ! እንዷ እናት፣ ኧረ ይችስ እናትም ልትባል አይገባት፡
በተቦጫጨቀ እሮጌ ቀሚስ ጠቅልላ በእንድ በማይረባ ዝንጥልጥል ዝንቢል እንደ ቃሪያና ሽንኩርት ሽምልላ፣ ሰው ሳይነሣና ሳያያት ልጅዋን ያላንዳች ርኅራኄ
ለውርጭና ለፀሐይ ጥላው ሄዳ እየሁ» ብሉ ተሟግቶ እንደ ተረታ ሰው አቀረቀረ፡፡ የእኔን አንጎል ከፍተኛ ድንጋጤ የተጠናወተው፣ መብረቅ አጠገቡ
እንዳረፈበት ሰዉ ነው ያልኩት እሱ ገና ወሬውን እንዳጋመሰ ነበር፡፡ የሞቱ
ዘመዶቹን የመርዶ ስም ዝርዝር እየሰማ አሁን ደግሞ የሞተው ማን ይሆን እያለ
እንደሚጨነቅ ሰው ልቤ በሥጋት ተሸበረ፡፡

ውስጥ ውስጡን የጥርጣሬ ቃጠሎ አጋየኝ፡፡ አንጎሌ በፍርሃት ማዕበል
በመጠንጋቱ ራሴን መቆጣጠር የምችል አልመስል አለኝ፡፡ ወዲያው ተወልዶ
ወዲያው ያደገው ጥርጣሬዬ ጎለመሰ።

«ለመሆኑ ልጁ የተገኘው የት ነው?” ብዬ ጠየቅሁት። ከወንበሩ ላይ ተነሥቶ ሱሪውን ሽቅብ ወደ እንብርቱ ከፍ ከፍ ካደረገ በኋላ «ልጁ የተገኘውማ
ከእኛ ቤት አጠገብ ከግቢ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ዝቅ ብሉ ባለው መንደር
ውስጥ ከመንገድ ዳር ነው» ብሎ ተቀመጠ፡፡ «መቼ መሰለህ ዛሬ እኮ ነው
በማለት ንግግሩን ቀጠለ። ባሮጌ ብጭቅጫቂ ጨርቅ አቅፈው ልጅ እኮ ተጥሉ አገኘሁ እያሉ አንዲት ሴትዮ ለዐላፊ አግዳሚው ሲያሳዩ እኔም ጠጋ ብዬ አየሁ፡፡ያውም እኮ ይገርምሃል! ስንዝር የምትሞላ ብጫቂ ጨርቅ አላለበሰችውም፡፡ መክሳቱና መጎዳቱ ነው እንጂ እንዴት ያለ ደስ የሚል ልጅ መስለህ?» አለና ከክቧ ጠረጴዛ ላይ መጽሔት እንሥቶ ማገላበጥ ጀመረ። በጥርጣሬና በሐሳብ ተቃጥሉ እንኩቶ ሆነው ሰውነቴ ውስጥ እሳት የሚንቦለቦል መሰለኝ።

«በመጨረሻስ፣ ልጁን ወዴት አደረሱት?» ብዬ እኔም ተከራክሮ እንደ ተረታ ሰው ጸጥ አልኩ፡፡ መፅሔቱን እያገላበጠ «ከዚያ በኋላማ እዚያው አካባቢ
የነበሩ ልጆች ፖሊስ ጠርተው ካመጡ በኋላ ካገኙት ሴትዮ ጋር ይዘዋቸው
ካዛንቺስ ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሔዱ» ብለ በተራ ጸጸት እንደተለመዱ
ተራ ወሬ ነገረኝ፡፡

ጥርጣሬዬ ከመጠን በላይ እደገ፡፡ አፌን ደም ደም አለኝ። ወዲያው ደግሞ ከመጅ እንዳመለጠች ጥሬ ሌላ ሐሳብ ከጭንቅላቴ ውስጥ ተፈናጥራ ወጣች። እእምሮዬ ነገሩን አገላብጦ ለማየት ፋታና ትዕግሥት አጣ፡፡

የየወጂያነሽን ቀሚሶች አንድ ባንድ ዐውቃቸው ስለ ነበር «ለመሆኑ ሕፃኑ
የተጠቀለለበት ጨርቅ ምን እንደሚመስል ልብ ብለህ አይተኸዋል?» ብዬ እንደ ዘበት ጠየቅሁት፡፡ ከት ብሎ ከሳቀ በኋላ «አይ ያንተ ነገር! የልብሱ ዐይነት ምን ያደርግልሃል?» አለኝ፡፡

የምክንያቱ አመጣጥ እንዴት እንደ ቀናኝ እንጃ! «የአንዳንድ ስዎችን ጠባይ በልብሳቸው የቀለም ዐይነት ማወቅ ይቻላል ይባላል። ለዚህ ነው
የተጠቀለለበትን ጨርቅ የጠየቅሁህ» ብዩ ሐሳቤን ከሐሳቡ አራቅኋት። ዓይኑን
ከደን አድርጎ አስበና፡ ሐሳቡ ልጁ ወደ ተጣለበት አካባቢ ደርሶ ተመለሰ፡፡
በጨርቁ ላይ የደበዘዙ ሰፋፊና ሰማያዊ የአበባ ሥዕሎች አለበት። አንተ
የጨርቁን ትጠይቀኛለሀ፡ እኔ ስሜቴን በጣም የነካው ልጁ ነው» ብሎ አንደ
ቁምነገረኛ መለሰልኝ፡፡ አናቴን የተመታሁ ያህል እንዘፈዘፈኝ።

አፌ ውስጥ ከመንጋጋዬ ግራና ቀኝ የሚገኘውን ለስላሳዉን የውስጥ
ጉንጨን ነከስኩት። ከመጽሔቷ ላይ ቀና ብሎ እኔን እየተመለከተ የዘንቢሉ
ማንጠልጠያ ጆሮ በወፍራም ቀይ ሽቦ ተጠምጥሞ የተጠገነ ነው በማለት
ያልተጠየቀውን ጨምሮ አወጋኝ፡፡ ልቤ ክፉኛ ተርበተበተች፡፡ አንድ አዲስ
የጥርጣሬ ግምት አእምሮዩን ጠቅ አደረጋት፡፡ መንፈሴ ተበጠበጠ፡፡ አንዳንድ
አጋጣሚዎች ያልተጠበቀ መልካም ወይም መጥፎ ነገር ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ የአእምሮዬን ጓዳ አገላብጬ ፈተሽኩት፡፡ ማንጠልጠያው በቀይ የመዳብ ሽቦ የተጠገነ ዘንቢል ትውስ አለኝ፡፡ “ጠብቀኝ አልኩትና ወደ ዕቃ ቤት ገሰገስኩ።አንዷ ሠራተኛችን ዕቃ ስታንጉዳጉድ ደረስኩ። “ቀይ የሽቦ ማንጠልጠያ የነበረው ዘንቢል አልነበረንም እንዴ?» አልኳት በድፍረት:: ቀና ብላ አየችኝና «ያቺ እዚህ የነበረችው “ማን ነበር ስሟ ወንድሜ፣ ልብሷን ይዛበት ሄዳለች መሠለኝ» አለችኝ፡፡ «ከዚህ በላይ ምን ማረጋገጫ አለ» ብዬ ተመለስኩ፡፡ በነገሩ ላይ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ባልሆንም ያን ዘንቢል የተጠገነበትን የመዳብ ሽቦ በዘንቢሉ ላይ
የጠመጠምኩት እኔ ነበርኩ፡፡

ጉዳዩ ሲገጣጠም ታየኝና፡ ኡ ኡ ብዪ ወደ ማላመልጥበት የመከራ አዘቅት በሐሳብ እየዳህኩ ወረድኩ፡፡ የወዲያናሽንም መልካም ሕይወት እፍ ብዬ በማጥፋት አሳዛኝና አሠቃቂ የእናትነት ታሪክ እንዳሳቀፍኳት ግዙፍ ጥፋቴ ወለል
ብሎ ታየኝ::

እጅግ በጣም የጠቆረው የበደልና የግፍ፡ ሥራዬ ሰው ከመባል ደረጃ አሽቀንጥሮ እንደሚወረውረኝ ታወቀኝ፡፡ እንደገና ሰው ለመሰኘት ብዙ ትግልና ውጣ ውረድ ማለፍና ፈተናውን ሁሉ ድል ማድረግ እንደሚኖርብኝ ከራሴ ሕይወት ውስጥ ወዲያውኑ ለመረዳት ቻልኩ:: ታምራትም ለእርሱ አንደ ተራ ወሬ ለእኔ ግን ምናልባትም አንድ ትልቅ ስውር መርዶ የሆነውን ጉዳይ ከዘረገፈልኝ በኋላ እንደ
ልማዱ መጻሕፍት ተውሶ ሲሄድ፡ ያመጣውን ያልተረጋገጠ መርዶ ግን ይዞት አልተመለሰም::

“በርግጥ የወዲያነሽ ትሆን ይሆን? ወይስ ሌላ?” በማለት አያሌ የሥቃይንና የጭንቀት ደቂቃዎች አሳለፍኩ። ራሴን እንደ ሞኝና እንደ ወፈፌ ቆጥሬ ስብእናዬን ተጸየፍኩት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አባቴ የት እንደ ቀረ ባላውቅም እናቴና እኅቴ ከቤተክርስቲያን ተመለሱ እናቴ ያለፈውን ነገር ሁሉ ረስቶታል ወይም ንቆ ትቶታል ብላ ከእኔ ጋር እንደ ዱሮዋ
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


...ስሜቴ በመጠኑ በመለወጡ ደስታ መሰል ሁኔታ ተሰማኝ። ደስታዬ እርሷ በመታስሯ ሳይሆን እርሷ ትሆን በማለት ሲዋልል የሰነበተው ጥርጣሬዬ ወደ
አንድ መጠነኛ ውጤት በመቃረቡ ነበር፡፡ ወደ ውጪ ወጣ ብዬ ወደ ግራ ተጠመዘዝኩ። ጥቂት ርምጃዎች እንደ ተራመድኩ ፊቴን ወደ ሰሜን መለስኩ፡፡
እስር ቤቱ ከፖሊስ ጣቢያው በስተጀርባ ነው፡፡ አረማመዴ ፈጠን ያለ ስለነበር
ጠበንጃ ይዞ የቆመው ዘብ «ቁም ወዴት ትሄዳለህ?» አለኝ። ሥርዓት እንደጣስኩ
ገባኝ፡፡

ቃሉ ቃለ ሕግ በመሆኗ ቀጥ አልኩ፡፡ ቀጠን ሳለች አስደንጋጭ የቁጣ
ድምፅ «ማንን ነው የምትፈልገው?» አለኝ።

«አንዲት ሴት እስረኛ ለመጠየቅ ነው?» ብዬ ከቆምኩበት ሳልንቀሳቀስ
መለስኩለት። ለአካባቢው ፍፁም እንግዳ መሆኔ ገባው:: ውስጡ ትሁት እንደሆነ
ተሰማኝ፡፡ ፈገግ አለልኝ። ፈገግታው እለመቆጣቱን ስላስረዳኝ አራት እርምጃዎች ወደፊት ቀጠልኩ፡፡ እሷ መሆኗን ባላረጋግጥም የወዲያነሽን እስረኛ በማለቴ የልቤ ግርማ ሞገስ ተገፈፈ፡፡ በወታደሩና በእኔ መካከል ከስድስት ደኅና ደኅና ርምጃ
የማይበልጥ ርቀት ነበር፡፡

«ምን ይዘሃል? ባዶ እጅህን ነው እንዴ እስረኛ ጥሩልኝ የምትለው? እስረኛ እኮ በማንኛውም ሰዓት አይጠየቅም፡፡ የተወሰነ ጊዜ አለው» አለ አሁንም
በመጠነኛ ፈገግታ። አነጋገሩ የሰውየውን የፈቃደኝነት ስሜት ስላስረዳኝ ሁለት
እርምጃዎች ጨመርኩ፡፡

«ገና እርሷ መሆኗንም አላረጋገጥኩ፡ መጀመሪያ ላረጋግጥ ብዬ» ሳልጨርስ አይኖቼ ዕንባ አቀረሩ፡፡ ጊዜም አልሰጡኝ፡ ተንጠባጠቡ። እምብዛም ጥልቅ ኀዘን በማይታይበት ፊቴ ላይ ዕንባ ሲወርድ በማየቱ፣

«ምነው ምን ነካህ? ወንድ ልጅ ያውም አንተን የሚያህል ያለቅሳል እንዴ?» አለኝ፡፡

«ምንም አልሆንኩ፡ እንዲያው ብቻ...»
«ለመሆኑ ማን ትባላለች?»
«የወዲያነሽ ትባላለች?»።
«እረግ! ኧረ! ያቺን ዕብድ አይሏት ጤነኛ ነው እንዴ? እሷማ ያቻትልህ! ያቺው ተጨብጣ ተቀምጣልሃለች! በል ሂድ! ፈጠን በል! ታዲያ ሥርዓቱን ባለማወቅህና እደጅ በመሆኗ ነው እንጂ እቤት ውስጥ ብትሆን ኖሮ
አይፈቀድም ነበር። እዚህ ድረስም አይመጣም ሰዓቱም ገና ነው» ብሎ አደራ አዘል ፈቃድ ሰጠኝ። አጠገቧ ከመድረሴ በፊት ትንሽ ራቅ ብዬ ቆምኩ::
ሲሽመደመድ የሰነበተው ጥርጣሬዩ ቀና አለ፡፡

ቀሚሷ ተዘነጣጥሎ ተቀዷል፡፡ እግሯ በእሳት የተለበለበ የክትክታ ዕንጨት መስሎ ዐልፎ አልፎ ልብሷ ላይ ጭቃ ተለጥፏል። የተራቆተው ግራ ቀኝ ክንዷ ዐመድ የተነሰነሰበት መስሎ ጽጉሯ እዚህና እዚያ የተነቀለ የጓያ ማሳ
መስሏል። መናገርም መራመድም አቃተኝ፡፡ የወዲያነሽ ጉስቁልና ለሁለተኛ ጊዜ አናቴ ላይ ተከመረ፡፡

ጥርጣሬዬ ጥርጣሬ መሆኑ ቀረ። ለየለት። የወጺያነሽ ተገኘች! ያም ሆነ ይህ የፍቅር ዐይኖቼ አላምጠው ዋጧት እንጂ አልተጸየፏትም። አእምሮዬ ውስጥ
የፍቅር ደማቅ ነበልባል በራ እንጂ የጥላቻና የንቀት ጥቁር ማቅ አልተሸመነም።አንድ ቀጠን ያለ ድምፅ ከበስተጀርባዬ ቶሉ በል እንጂ ሰውዩ!» ሲለኝ ሰማሁ:: በሐሳብ ከማንቀላፋበት አጭር ሰመመን ባነንኩ፡፡ ወደፊት ራመድ ብዪ ከወዲያነሽ አጠገብ ቆምኩ፡፡ ጉልበቷ ላይ ተደፍታ ስለነበር ድንገት ስናገር እንዳትደነግጥ የቆምኩበትን ሸካራ ንጥፍ ድንጋይ በቀኝ እግሬ ረመረምኩት።የፈራሁት አልቀረም፣ በድንጋጤ ባንና ተነሣች። በጣም ከስታለች። ፊቷ ጢስ የጠገበ ቋንጣ መስሏል፡፡ ልብ ብሎ ባላየ ዓይን ቀና ብላ አየችኝ። ማን መሆኔን አላወቀችም፡፡

አገጯን በእግሮቿ መሃል አስገብታ እግር እግሬን እየተመከለተች
«ምነው? ምን አጠፋሁ? ወድጀ እኮ አይደለም! ምን አባቴ ላድርግ! የሚላስና
የሚቀመስ በማጣቴ በረሃብና በችግር ከሚሞት ለነፍሴ ያለ ወስዶ እንዲያሳድገው ብዬ መንገድ ዳር አስቀመጥኩት፡፡ ምነው ሞቴን ባቀረበው?» ብላ ንግግሯን እንደ
ጨረሰች ቀና ስትል የሻገተ እንቀልባ በመሰለው ጉንጫ ላይ ዕንባዋ ተዝረበረበ።

በቁጣ ስሜት ዐይኗን አፍጥጣ «ከዚህ ወዲያ ምን እሆናለሁ ግደሉኝ!
ስቀሉኝ! አንጠልጥለኝ?» አለችና ጉልበቷ ላይ ደፋ አለች።

ጐንበስ ብዬ የቀኝ እጅ ክንፏን ያዝኩና «እኔ ነኝ እኮ የወዲያነሽ፣ እኔ ጌታነህ እኮ ነኝ» አልኳት፡፡ ቀስ ብላ ቀና ካለች በኋላ አፏን በፍርሃትና በድንጋጤ ከፈተችው፡፡ በሰውነቷ ውስጥ ይገኛል ተብሎ በማይገመት እንቅስቃሴ ተነስታ
አንገቴ ላይ ተጠመጠመች፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ አይፈቀድም ያለኝ ፖሊስ
ምን ይል ይሆን በማለት ፈራሁ፡፡ መንማና ክንዶቿ ሥጋው ተፈቅፍቆ የወደቀ አጥንት እንጂ ሥጋ የለበሱ አይመስሉም፡፡ አንገቴ ላይ ተጠምጥማ እዬዬዋን ለቀቀችው፡፡ ተንሰቀሰቀች። የሟሸሹ ጉንጮችዋን ሳምኳቸው:: ደርቆና ተሰነጣጥቆ
ያረረ ደረቆት የሚመስለው ከንፈሯ ሻካራ ድንጋይ መስሏል። ያ ዝንፍልፍልና
የውበቷ ደረባ የነበረው ጸጉሯ ተሸላልቷል። አምክ እምክ የሚሽተው ጠረኗ የሥቃይዋን፡ ብዛት ያስረዳል፡፡ አይቼ ሳልጠግባትና አንዳች ነገር እንኳ ጠይቄ ሳልረዳ ፖሊሱ “በቃህ!» ብሎኝ ተመለስኩ:: እንባዋን እየረጨችና እያለቀሰች ተለያየን።

"እኔና የወዲያነሽ ተለያይተን የምንቆየው እስከ መቼ ይሆን ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። እጅ እግር ላልነበረው ለዚህ ድፍን ጥያቄ አሁን በአሁን መልስ አላገኘሁም፡፡ አዲስ የፈተናና የስራ ገፅ ተከፈተ። ወደ ቤቴ ከመመለሴና የወዲያነሽንም መታሰር ለጉልላት ከመንገሬ ቀደም ብዬ አንድ ነገር ለማከናወን ወሰንኩ። በኪሴ ውስጥ የነበረችኝን የገንዘብ ልክ ዐወቅሁ፡፡ ከዚያም አራዳ ልብስ ተራ ገባሁ፡፡ በግምት አንድ ጥሩ ቀሚስ እና የውስጥ ልብስ፡ በቀድሞ ቁጥሯ አንድ ተራ ጫማ፣ ዋጋው ቀነስ ያለ የብርድ ልብስ ወዲያ ወዲህ ተሯሩጬ ገዛሁ፡፡

ኀዘንና ደስታዬ በመስተካከሉ መፈንጠዣና መተከዣ የሚሆን ምክንያት አገኘሁ፡፡ የገዛሁትን ልብስ በፖሊስ አስመርምሬ ለየወዲያነሽ ሰጥቻት ተመለስኩ፡፡

ከዚያች ዕለት ጀምሮ በየሣልስቱና ባመቸኝ ቁጥር እየተመላለስኩ
መጠየቄን ቀጠልኩ። አብዳለች፣ ወፍፏታል የተባለው ሁሉ ጠንባራ ስሕተት
መሆኑን ከቀን ወደ ቀን ከሁኔታዎቿ አረጋገጥኩ፡፡

ከግራና ቀኝ የቆሰለ ሰው ሁለቱንም ቁስሎቹን ተራ በተራ እንደሚያይና እንደሚያክም ሰው፡ እኔም ልክ ከዐሥር ቀን በኋላ እንደገና ወደ ጋንዲ ሆስፒታል ሄድኩ፡፡ የተስፋ ቅራሪ ሳይሆን የርግጠኛነት ድፍድፍ ይዣለሁ፡፡
ልክ ሁለትና ሁለት ኣራት እንደሆነ ሁሉ ጋንዲ ሆስፒታል ውስጥ የተኛው ሕፃን
የየወዲያነሽ ልጅ መሆኑን ከዚህም ከዚያም እጅግ በሚገባ አረጋግጫለሁ፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የአጥንቴን ክፋይና የሥጋዬን ቁራጭ በአንዲት አነስተኛ ጠባብ ኣልጋ ላይ ደስ በሚያሰኝ ጥንቃቄና አኳኋን ተኝቶ አየሁት።

የወዲያነሽ መታሰር ልጁም ልጅዋ መሆኑን ማመኗ አብስለሰለኝ፡፡ ይህ
ሁሉ ከመሆኑ በፊት ባገኘኋት ኖሮ!!... እያልኩ በማሰብ፣ እከሌ እኮ እንዲህ
ቢደረግለት ኖሮ አይሞትም ነበር እያሉ ስለ ሞተ ሰው እንደሚጸጸቱ ሰዎች
በጸጸት ተቃጠልኩ፡፡ ዐመድ እንደገና ዕንጨት አይሆንምና ሐሳቤ በነነ፡፡ ያም ሆነ ይህ ሕይወት እጆቿን ዘርግታ ክቡር ስጦታ ሰጠችኝ! የእኔና የየወዲያነሽ ፍቅር
ጊዚያዊ መሪር ፍሬ አፈራ።

አስታማሚዋ አጠገቤ እንደ ቆመች ጎንበስ ብዬ ደጋግሜ ግንባሩን ሳምኩ፡፡ ከወዲያነሽ ማሕፀን የተገኘውን ክቡር ፍሬ እሷን በሳምኩበት ከንፈሬ
በመሳሜ ልቤ በደስታ ቦረቀች። በሕይወት መቃብር ውስጥ የሚፍለከለከው የወዲያነሽ ኑሮ ግን መንጠቆውን ይዞ አንጠለጠለኝ፡፡ በጸጥታ የሚያንቀላፋውን ሕፃን እየተመለከትኩ 'ጌታነህ! አንተ ጌታነህ! ዛሬ ደግሞ ሌላ
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

....«እኔ በበኩሌ ብዙ ጊዜ ነግሬሃለሁ። እናትህም ብትሆን ዘወትር እንደ ለመነችህ ነው:: የተማረ ሰው ጥቅምና ጉዳቱን ለይቶ ማወት ያቅተዋል ብዬ አላስብም፡፡ ርግጥ ነው፡ ዐዋቂም ቢሆን መካሪና ነጋሪ ያስፈልገዋል። ግን ሁልጊዜ የሚመከርና የሚነገር ጤነኛ ሰው አይደለም፡፡ በከንቱ ከምታማስነን ይልቅ ዐይንህን የጣልክባትና የወደድካት የጨዋ ልጅ ካለች ንገረኝ። አለበለዚያም እኔ
የምመርጥልህንና ደኅና ሰው ቤት ገብቼ የማመጣልህን ተቀበል፡፡ እኔማ ካነገርኩህ
ይኸው ሁለት ዓመት ዐለፈ፡፡ ምነው የወንድሞችህንና የእኀቶችህን ልብ ቢሰጥ ብሎ መልሴን ለመስማት ትክ ብሎ አየኝ፡፡

«አየህ አባዬ በማለት በተለመደች አጠሪሬ ንግግሬን ጀመርኩ።
“ማንኛውም ሰው የሚያገባው ራሱን ለማስደሰትና ኑሮውን ለመመሥረት እንጂ
ሌላውን ደስ ለማሰኘት አይደለም፡፡ አንተ የምትመርጥልኝን አልቀበልም ለማለት
ሳይሆን ላንተ የምትስማማህና ደስ የምትልህ ለእኔ ደስ አትለኝም ይሆናል።
"ማንኛውም ሰው እለማወት ወይ ድንቁርና ከተገቢዉ በላይ ብዙ እንዲያደንቅና በጠባብ አስተሳሰብ እንዲሠራ በስውርና በግልጽ ሊያስገድዱት ይችላሉ፡፡ እኔ በመጠኑም ቢሆን ከጠባብ አስተሳሰብ ተላቅቄአለሁ። በአጭሩ እንድታውቅልኝና እንድትገነዘብልኝ የምፈልገው ግን ለመግባባት የሚችል ሕሊና እንጂ ከቀን ወደ ቀን የሚለወጥ ሰብአዊ ውበት ብቻውን ጋብቻን ጽኑና ተፈላጊ መሠረት ሊሰጠው አይችልም» ብዬ ረዘም ባለው አነጋገሬ የምን ይለኝ ጅራፍ እየለመጠጠኝ
በመናገር አይኖቼን ወደ ወለሉ ተክዩ ዝም እልኩ፡፡

«ኤድያ! ኤድያ! ደርሶ መንዘባነን ደስ አይለኝ! የዘንድሮ ወጣቶች ሐሳብና መልስ በየቤቱ ይኸው ሆኗል፡፡ ቁም ነገር የሚሠራ ሰው ብዘ አያወራም፡፡ ጋብቻ የጎበዝና የደፋር ሙያ እንጂ ለሰነፍና ለፈሪ የሚታደግ የጠበል ፃዲቅ
ድርሻ አይደለም፡፡ አስተዋይ ልቦና ያለው እንዳቅሙ ይዘላል፡፡ ያለ መቸኮልህስ
ይሁን በጄ! የአቦ ዕለት ሲሉህ የመድኃኔ ዓለም ዕለት ማለት ግን በዛ፡፡ ዛሬን
እንደ ዛሬ ኑረህ ነገን እንደ ነገ መኖርና ነገን መስለህ መገኘት ቁርጥ ዓላማህና
ፍላጎትህ መሆን አለበት፡፡ ዝምታህ እምቢታ መሆኑን ዐውቃለሁ» ብሎ ከጉዳዩ ጋር የተያያዘውንና ያልተያያዘውን ሁሉ ተናግሮ ቆጣ አለ፡፡ ከጊዜያዊ ቁጣው
በኋላ ዝምታ እንዳይጀምር በማሰብ “ምናልባት በሰው ልጅ እኩልነት የምታምን ከሆነ ለምን የትልቅ ሰው ልጅ፡ አጥንተ ጥሩ፣ ባለክብር፣ ባለ ዝና እያልክ
ታማርጣለህ? » ብዬ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅንጣት ድፍረት የተቀላቀለባትን ጥያቄ
ሆዴ በፍርሃት እየተናጠ አቀረብኩኝ።

«አድሮ ጥጃ አለ ያገሬ ሰው ብዙ ጊዜ ነግሬሃለሁ፡ ለምን ነጋ ጠባ
ትጠይቀኛለህ? በማለት ንግግሩን ሲጀምር በቁጣ ትክ ብሎ
የማይሆነውንና የማይገባውን ሁሉ አትመኝ"ሐለሙ ሕልመ ወአልቦ ዘረከቡ"
ተብሏል፡፡ ማንም ሰው ቢሆን የኑሮ ደረጃውን መጠበቅና መመልከት አለበት።
እኔ እባትህ ከትልልቅና ካዋቂ ሰዎች ጋር የምውል ነኝ። አንተም እንደ እኔ
መሆን ይገባሃል።

ዝናና ክብር ቀላል ነገር አይምሰልህ፡፡ ከሜዳ ላይ አይታፈስም። የዘመኑ
ሰዎች ለጤና ያድርግላችሁ እንጂ “አለ "አብልሑ ልሳኖሙ ከመ አርዌ ምድር»
እንዳለው ሆናችኋል። የምታመጣት ልጅ ከጨዋ ቤተሰብ የተወለደች፣ ዘርና
ትውልዷ የታወቀና የጠራ መሆን አለበት። ወይራ ከወይራ ነው፡ ስንዴ ከጓያ
አይቀየጥም፡፡ «ከመልኮስኮስ መመንኮስ» ሲባል አልሰማህም እንዴ? «የማንንም ስድ አደግና ቅሬ ከየትም ለቅመህ ዝናና ክብሬን ብታጠፋት አደባባይ አውጥተሀ የገደልከኝ ያህል እቆጥረዋለሁ፡፡ የደሃ ቀርቀቦ ቢንከባለል ከደሃ ደጅ” ምኞትህ ሁሉ ልክስክስ አይሁን» ብሎ ቁጭቱን ለመግለጽ ያህል ራሱን ነቀነቀ።

ያቺ በስንትና ስንት ጊዜ ውስጥ የምታጋጥመኝ ጭቅጭቅ አይሏት
ውይይት አብዛኛውን ጊዜ ፍፃሜዋ አያምርም። የእኔና የእርሱ ሐሳብ በተቃራኒ አቅጣጫ ስለሚጓዝ ከመከራከርና ከመጨነቅ ይልቅ ሰምቼ መለየትን እመርጣለሁ።

«ማንንና እንዴት ለማግባት እንደምፈልግ ለመግለጽ እስከምችል ድረስ
የመዘጋጃ ጊዜ ቢሰጠኝና ከራሴ ጋር ብመክር ጥሩ ነው:: እኔ ግን ከአንዳንድ
ሁኔታዎች በስተቀር ማንኛውም ሰው በተፈጥሮ ዐይን ሲታይና ሲመዘን እኩል
ነው” በሚለው አምናለሁ» ብዬ እምነቴን ገለጽኩ፡፡ ለመነሣት ሲመቻች ጋብቻን
እንደ አንድ ትልቅ ጦርነት የምትፈራው መስለህ ታይተኸኛል። ጋብቻ ማለት
ሌላ ነገር አይምሰልህ፡ ከአንዲት ከምትወዳት ሴት ጋር ለመኖር የምታደርገው የኑሮ ውል ነው፡፡ ከሆነችህ አብረሃት መኖር፡ እንዲያ ሆነም ምን ውጣ ወረድ አለው፡ ደህና ዋይ ብሉ ማሰናበት ነው:: ከዛሬ ጀምሮ ግን አግባ አታግባ እያልኩ አልነታረክም፡፡ አስቦና የሚሻውን ወስኖ ለማደር ከቻለ አቅመ አዳም ከደረሰ ሰው ጋር ስለ ራሱ ጉዳይ መከራከር ከንቱ ድካም ነው::

«አንተማ በልብህ ግን እንደኔ ማለትህ አይቀርም፣ ንገሩኝ ባይ!»

“ከትንሽ ጅረት ውስጥ የምትንሳፈፍ ቅጠል ከትልቁ ኩሬ ውስጥ ስትገባ
ቁጫጭ አህላ ትታያለች፡፡ ዐወቅሁ ብለህ ሙተሃል፡፡ የሰው ልጅ ክፉ ጠላቱ ደግሞ
በውስጡ የታጎረው ሽካራ ሐሳቡ ነው:: ካንጀቴ ነው:: ራስን ለማረምና ለማሻሻልም እኮ ከሌሎች ሰዎች ስሕተት መማርና መረዳት ካስተዋይነታቸውም መልካም መልካሙን መቅሰም ማለፊያ ዘዴ ነው» ብሎ ፈንጠር ብላ በጸጥታ ነጠላ ወደምትቋጨው እናቴ አሻግሮ አየ። ምንም እንኳ ላቀረበው ሐሳብ ተነጻጻሪና የተሻለ መልስ ቢኖረኝም
እያደር የሚንር ቁጣውን በመፍራት ደጓን ዝምታ ቀጠልኩ።

የተጨማደደውን ግንባሩን እየጠራረገ ከተነሣ በኋላ ሐሳቤን በጠቅላላ
የሚቃወም መሆኑን ለማስረዳት ወለሉን በቀኝ እግሩ ጠፍ ጠፍ እደረገው፡፡
«የሚታየው እኮ እንዴትና የት ማደግህ ብቻ አይደለም፡ ከማን መወለድህም ጭምር እንጂ። መልካም አዝመራ የሚገኘው እንደ ገበሬውና እንደ
መሬቱ ብቻ ሳይሆን እንደ ዘሩም ነው» ብሎ በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቱ ሔደ::

ወደ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው ለስላሳ መቀመጫ ትንሽ በትንሽ በመሙላት ቅርጿ ተስተካከለ።

«እስኪ አሁን በኪዳነ ምሕረትና በእሑድ ምድር ባትጨቃጨቁ ምን ቸገረሀ ልጄ? ነጋ ጠባ ይነግርሃል፤ እርሱ አይደክመው፣ አንተ አይሰለችህ! መጥኔ እቴ! ወዴት አባቴ ልግባላችሁ ይሆን? በዚያ ላይ ደግሞ ስንተዜ ልንገርህ? ሲሆን
ሲሆን አንተና እኔ ምንና ምን? አንተ በትምርትህም ቢሆን አታጣውም፡ አሁን
በዚህ በአንተ ምልልስ የተነሣ ያ ሰበበኛ የደም ብዛቱ ቢነሣ አበሳው ለኛው ነው፡፡
እሞት አገር አድርሶ እንደሚመልሰው ታውቃለህ፡፡ ከሐኪሙ ቤት የሚያመጣውን አንድ ቁና ኪነን ታያለህ፡፡ እሱ በጦም በጸሉት እያለ ባይዘው ኖሮ ይኸነዩ ጥሪኝ አፈር ሆኖ ነበር። እሱ እንደሁ እሱ ነው: አንተ ግን ሲያመር ሲያመር ከፊቱ ገለል በልለት» በማለት ራቅ ብላ የተቀመጠችው እናቴ ምሬቷን ገለጸች፡፡

አሁንም እንደገና ከእናቴ ጋር የነገር ገበና ለመጫወት ባለመፈለጌ ሰምቼ
ዝም አልኩ። ዐልፎ በልፎ ከሚሰማው ከእናቴ የጉሮሮ ማስሊያ እህህታ በስተቀር
ቤቱ በዝምታ ታመቀ። በሐሳብ ዐውሎ ነፋስ ከወዲያ ወዲህ በመንገዋለል ላይ
እንዳለሁ ጉልላት ከቸች አለ።

እጆቹን ወደ ኋሳ አጥፍቶ እርስ እርሳቸው ካያያዘ በኋላ አንድ እግሩን ትንሽ ቀደም በማድረግ ጎንበስ ብሎ ለእናቴ ሰላምታ አቀረበ፡፡ እናቴ ስለ ጉልላት ስትናገር «እኔ ከሌላው ከሌላዉ ሁሉ የሚያስደስተኝ ትትናውን እጅ አነሳሡ ነው» ትላለች። ከጎኔ ተቀመጠ። ከእናቴ ጋር ልብ ለልብ ተገናኝቼ እንደማላወራ ስለሚያውቅ የጋሪ ወሬ ለመክፈት አልፈለገም፡፡
👍1
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

....በመካከላችን ባሉት አጥሮች መኻል የነበረው አንድ ረጂም ርምጃ የሚሆን ርቀት በእኔና በየወዲያነሽ መካከል የሚገኝ ጥልቅ የሥቃይ አዘቅት ሆነ።

ፊቴን ከእርሷ መለስ አድርጌ በዐይኖቼ ዙሪያ የሚንቀዋለለውን እንባ
በመሐረቤ አበስኩና “አይዞሽ ተስፋ አትቁረጪ! ሰው በሕይወቱ ከዚህ የባሰና
የከፋ መከራ ያጋጥመዋል። በተቻለሽ ዐቅም ሁሉንም ነገር ለመቋቋም ሞክሪ።
ላለፈው ነገር ሁሉ ያላግባብ ከተጸጸትሽ ግን እንደገና ደግሞ በራስሽ ብስጭት
ወህኒ ቤት ውስጥ ገባሽ ማለት ነው» ስላት ከበፊቱ የበለጠ ሆድ ባሳትና
ስቅስቅታዋ ትከሻዋን ሽቅብ እስኪያዘልለው ድረስ ልቅሶዋነ ቀጠለች፡፡

የወዲያነሽ በቀጠሮ ወህኒ ቤት ከገባች ጀምሮ ሕሊናዋ ቀዘቀዘ፡፡ ፊቷ የትካዜ ጭጋግ ለበሰ። እረማመዷ በኃዘን ጓግ ተቀየደ፡፡ ዐይኖቿ ሠረጉ፡፡ ነጣ ብሎ ወፈር ያለውን የመከለያ ፍርግርግ የእግር ዕንጨት በእጅዋ እያሸች እንገቷን
ሰበር አድርጋ ዕንባዋን ታንዶለዱለው ጀመር፡፡ በአፍንጫዋ የቀኝ ቀዳዳ በኩል ብቅ ያለችውን ራሰ ድቡልቡል ቀጭን ንፍጥ በግራ እጁዋ ቁርጥ አድርጋ
አሽቀነጠረቻት፡፡

ጎንበስ ብላ በውስጥ ልብሷ ዐይንና አፍንጫዋን እባብሳ ቀና አለች፡፡ዐይኖቿ ድልህ መሰሉ። ክንፈሮቿ መላቀቅ እየተሳናቸው «እኔ መቼም ዕድሌ
ነው፡ በጎደሎ ቀን ነው የተፈጠርኩት፡እግዚአብሔርም ከላደለኝ። አንተ ግን
ለእኔ ብለህ አትንገላታ፡፡ የልጄን ነገር አደራ አደራ በምድር አደራ በሰማይ!
የእኔ ሥራ እኔኑ ያንገበግበኛል፡፡ መቼም የሚሉኝን እስከሚሉኝ ታንቄ አልሞት።
ዐልፎ ዐልፎ ከጠየቅኸኝ ይበቃኛል። ያዩህና የሰሙብህ እንደሆነ ይጣሉሃል» ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ ትንፋሿ እጥር ቅትት አለ። ከነዚያ በቀላሉ እንባ
ከሚያፈልቁት ዐይኖቿ ያለማቋረጥ እንባ ወረደ። የተጠቂነቷ መግለጫ ነው::
የወሰድኩላትን ልዩ ልዩ ዕቃና ምግብ በሴቷ ወታደር አቀባይነት ከሰጠኋት በኋላ በዝምታ ቆምኩ፡፡ ዓይኖቿ ምስጋና አቀረቡ፡፡ «በይ እንግዲህ በደኅና ሰንብች ! እየመጣሁ እጠይቅሻለሁ፡፡ የሚፈቀደውንና የሚያስፈልግሽን ሁሉ
ጠይቂኝ፡ አመጣልሻለሁ፡፡ ስለ ልጁም በፍጹም አትሥጊ፡ አታስቢ፡ እኔ አለሁለት»
ብያት ትዝታዬን ጥዬላት መንገድ ገባሁ::

አላስችል ስላለኝ መለስ ብዬ ሳያት፡
እሷም ቆማ ትመለከተኝ ነበር። እግሮቼ ተግመድምደው መራመድ አቃተኝ
ዐይኖቼ በናፍቆት አዩዋት። የሰጠኋትን ኮተት አንሥታ በዝግታ ሔደች።

የውስጤን ብስጭትና ጥጥር ትካዜ ዘልቃ ለማወቅ የቻለች ይመስል

ቅስሟ ተሰብሮ በወጣትነቷ ስለጠወለገችው የየወዲያነሽ ሕይወት
እያሰላሰልኩ ሜክሲኮ አደባባይ ደረስኩ፡፡ ከዚያም እስከ አራዳ ጊዮርጊስ በታክሲ
ተጓዝኩ። ሰባት ሰዓት ሊሞላ ጥቂት ደቂቃዎች ቀርተው ነበር። በጠራው ሰማይ ላይ የምትንተገተገው ፀሐይ የዕለቱን ከፍተኛ የሰማይ ጣራ ነክታለች፡፡ ለምሳ ወደ ቤት ከመግባቴ በፊት ትንሽ ዘወርወር ማለት ስለፈለግሁ ወደ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሳሽቆለቁል የዕለቷን ከባድ የፀሐይ ሐሩር ለመከላከል ከራሱ በላይ የታጠፈ ጋዜጣ ዘርግቶ ከወደ ታች ሲያሻቅብ ከጉልላት ጋር ተገጣጠምን።

በየሳምንቱ እሑድ ወደ ወህኒ ቤት እንደምሔድ ስለሚያውቅ ገና ሰላምታ ሳይሰጠኝ «አልሔድኩም ብቻ እንዳትለኝ? ደርሰህ መጣህ እንዴ?» ብሎ
ጠየቀኝ፡፡

መልስ ሳልሰጠው ተጨባበጥን፡፡ «ደርሼ
መመለሴ ነው» ብዬ እርግጠኛነቴን ለማስረዳት ትኩር ብዬ አየሁት። ከግንባሩ በላይ ፀጉሩጥጋ ጥግ እንዲሁም ባፍንጫው አካባቢ የሚታየውን ያቸፈቸፈ ወዙን እየተመለከትኩ ዛሬም ተሠርታ አልወጣች እንዴ ያቺ መኪናህ?» ብዬ ፈገግሁ፡፡

የመኪናው ነገር ያስመረረው መሆኑን ፊቱን አቀጭሞ «እባክህ የሷን ነገር ተወኝ! ትላንት አንዱ ተጠግኖ እንደሁ ዛሬ ደግሞ ሌላው ይነክታል።
ችግር ነው ጌትነት” አሉ። ከናካቴው እኮ ውልቅልቋ ቢወጣ እኔም እፎይ እል
ነበር:: የዘወትር በሽተኛ እስቸገረ መድኃኒተኛ” ሆነብኝ ብሎ እንዳበቃ እኔም
ተመልሼ አሻቀብኩ፡፡

አሁንም የዚያቹ የመኪና ነገር ውስጥ ውስጡን ስለ ከነካነው «ከየትም
ከየትም ብዬ እለቃቃምና ባንድ ፊቱ አሳምሬ አሳድሳታለሁ፡፡ እንኩትኩቷ ወጥቶ እስክትወድቅ ድረስ ሌላ አልገዛም በደንብ አሳድሳታለሁ፡፡ አንተም እሑድ እሑድ ወደ የወዲያነሽ ትሔድባታለህ» ብሎ ድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ፡፡

ከተማ ገብቶ መንገድ እንደ ጠፋው ገጠሬ በዙሪያችን ያሉትን መንገዶች
ተራ በተራ ተመለከታቸው:: ወዲያው ባጠገባችን ሁለት ደም ግባታቸው
የሚማርክ ወጣት ሴቶች ዐለፉ። የጉልላትን ትከሻ በትከሻዬ ገጨት አድርጌ «ያቺ ልጅ፣ ያቺ በስተግራ በኩል ያለችው እታለማሁን አትመስልም?» አልኩት።

አታለማሁ ጉልላት በጣም የወደዳትና የእርሷ ፍቅር ምን ጊዜም ቢሆን
ከልቤ ውስጥ አይፋቅም» እያለ የሚያነሣት ፍቅረኛው ነበረች። ሆኖም
ፍቅራቸው በነበር መቃብር ውስጥ ተቀብሯል።

“የማን ናት እታለማሁ? እታለማሁን እኔ ብቻ ላሰላስላት፣ እኔ ብቻ በትዝታ ላመንዥካት። አታስታውሰኝ እያልኩ ብዙ ጊዜ ለምኜህ አልነበረም።”ብሎ ዐይን ዐይኔን በቅሬታ እያየ ቆም አለ፡፡

«በሕይወቴ የምጠላውና እንደ ውርደት የምቆጥረው ነገር ሌሎች ክብራቸውንና ዝናቸውን ለመጠበቅና ከፍ ለማድረግ ብለው አንድን እንደ ጥፋት የማይቆጠር ነገር በማጋነን ይቅርታ ጠይቅ ሲሉና ሲንጠራሩብኝ ብቻ ነው፡፡ለእነርሱ የሚመራቸውን ነገር ለምን ቅመስልኝ ይሉኛል? የእርሷ ነገር እንደዚያ
ነበር። ታውቀዋለህ፡፡ ስለዚህ ለወደፊቱ እታንሣት ...» ካለ በኋላ በቁጣ ወደ ፊት
ቸር እለ። ወደ ሀር ፍቅር የምታዘቀዝቀዋ መንገድ በቁልቁለታማነቷ እንዘፍ
እንዘፍ አደረገችው::

«ታዲያ ምን አጠፋሁ? ትመስላለች ማለት ነች ማለት አይደለም» ብዬ መለስኩለት፡፡ «ስማ ልንገርህ» ብሎ ከነማይዘልቅ ቁጣው ቆመ፡፡ “የምትጠላውንም
ሆነ የምትወደውን ሰው ስም “ማስታወስ ድርጊቱን ሁሉ እንድታስታውስ ያደርግሃል፡ከእርሷ በፊት ማንንም እንደ እርሷ እንዳላፈቀርኩ የማውቀው እኔው
ብቻ ነኝ፡፡ በምድር ላይም ሆነ በማላውቀው ጠፈር ውስጥ የሚገኙትን ጥሩና ውብ ነገሮች የምመኘው ለእኔ ሳይሆን ለእርሷ ነበር፡፡ ሕይወት በፈገግታ እንድትቀበላት የምጓጓው ለእርሷ ነበር ብዬ ስናገር ሰምተሃል። አሁንም ቢሆን የከበረ ፍቅሯን ሳላጎድፍ እና ሳላጠፋ በልቤ ውስጥ ይዤው እኖራለሁ፡፡ እሷ ግን የትም ትኑር የትም፣ ትዝ ባለችኝ ቁጥር ያን ያለፈ ጊዜ መለስ ብዪ የማይባት የትዝታ መነፅሬ ናት፡፡ ስሟን አእላፋት ጊዜ ብታነሳልኝና ስለ እርሷም ብትተርክልኝ የሕሊናዩ ከርስ አይጠግብም። ግን አታንሣብኝ በውስጤ አዳፍና የተወችው የፍቅር ረመጥ በትዝታዋ በተጫረ ቁጥር የሚያንገበግበኝ በቂዩ ነው» ብሎ
እባክህን በምትል አኳኋን እንገቱን ዘንበል አደረገ፡፡

ከዚያ በኋላ እኔም ስለ እርሷ አላነሣውም፡፡ ጉልላት አንድ ነገር ካፈቀረና
ካመነበት ትክክለኛ ነገርም መስሎ ከታየው እስከ መጨረሻው መጽናት እንጂ
መወላወል አይወድም።

የወዲያነሽ ጋር የጀመርኩትን ፍቅራዊ ግንኙነት እንድገፋበትና ትክክለኛ ፍጻሜውንም ለማየት ቆርጬ እንድነሣ ያለ ማቋረጥ አበረታታኝ። እስከ
ኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ድረስ በታክሲ ሔድን፡፡

ወደ ቤት ስንገባ እናቴና ወይዘሮ የውብዳር ፊት ለፊት ተቀምጠው
ወሬያቸውን ሲሰልቁ ደረስን፡፡ ወይዘሮ የውብዳር ብርጭቆአቸውን እንደ ጨበጡ
መለስ አሉና ኖር የእኔ ልጅ» ብለው ለወጉ ያህል ከመቀመጫቸው ቆነጥነጥ
አሉና ወሬያቸውን ቀጠሉ። በደፈናው ለሁለም እጅ ነሥተን ተቀመጥን፡፡

“የዚያችኛዋስ ምንም አይደል፡ እኔ ያናደደኝ የዚችኛዋ የዚች የከይሲ
👍3
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

....የማለዳዋ የጥር ወር ፀሐይ በመሬት ወለል አካባቢ ከየሚዳው! ከየተራራው፣ ከየዛፉ፣ ከየቤቱ፣ ከየጉራንጉሩ ቀዝቃዛ አየር ጋር ትንቅንቅ ገጥማለች። ተፈጥሮ ራሷን በራሷ የምታስተካክልበትና የምትለዋውጥበት ተፈራራቂ ኃይል ስላላት ቀዝቃዛው አየሩ ቀስ በቀስ ተረታ። ለውጥ የተፃራሪ ኃይሎች የግብግብ ውጤት ነው::

በእኔ ሕይወት ውስጥ ግን ጎልቶ የሚጠቀስ ለውጥ ባለመገኘቱ ሕሊናዩ
እየቀዘቀዘ ከመሔድ በቀር የብርታት ለውጥ አልታየብኝም፡፡ ከመኝታዬ ተነሥቼ
ልብሴን ስለባብስ ሰውነቴ ቀነቀነኝ፡፡ እውነተኛዎቹ የሐሳቤ ቅንቅኖች ግን አንጎሌ ውስጥ ይርመሰመሳሉ። የሥራ ቀን ነበር፡፡

መንገዱ የሚያልቅልኝ ስላልመስለኝ ቀደም ብዬ ተነሣሁ፡፡ ወደ ሕጋዊ ፍርድ ቤት ሳይሆን ወደ ግፈኞች የመከራ ሽንጎ የምገሠግሥ መሰለኝ፡፡ ከአራት ኪሎ እስከ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያለውን ርቀት በሁለት ታክሲ አጠቃለልኩት፡፡
ጠበቆች፣ ዳኞች፣ ጸሐፊዎች፣ ነገረ ፈጆችና ወኪሎች፣ ተሟጋቾችና አማላጆች፣ “ጫማ ጠራጊዎችና ሥራ ፈቶች፣ እንደየ ኑሮ ደረጃቸው ለብሰው ተራ በተራ ሁለትና ሦስት እየሆኑ በመምጣት የፍርድ ቤቱን አካባቢ የበጋ ወራት ገብያ
አስመሰሉት፡፡ አንዳንዶቹ ሰዎች የለበሱት ነጠላና ጋቢ በጣም ከመቆሸሹ የተነሣ
ዳግመኛ ታጥቦ የሚነጣ አይመስልም፡፡ ጥለቱ የተንዘለዘለ፣ ዐልፎ ዐልፎ አይጥ
የበላው ይመስል የተቀዳደደ፣ እንደ አረጀ ሻሽ አለቅጥ የሳሳ ልብስ፣ በተለያየ
የጨርቅ ዐይነት የተጣጣፈ ኮትና ሱሪ፣ ከታጠበ ብዙ ዓመታት ዐልፈውት እድፉ
እንደ ማሰሻ የተላከከበት ሱፍ ኮት፣ ከተወለወለ ወራት ያለፉትና የቆዳው ቀለም የተገጣጠባ ከወደ አፍንጫው በእንቅፋት አልቆ ቀዳዳው የደረቀ የዓሣ አፍ የመሰለ፡ ከወደ ተረከዙ ወይም ከወደ ጎኑ ባንድ ወገን ተበልቶ የተንጋደደ ጫማ፣
በፀሐይ ሐሩርና በውርጭ፣ በአቧራና በእንክርት ቀለሙ ጠፍቶ የነተበ ባርኔጣ፣
የለበሱ ያደረጉና የደፉ ሰዎች በተስፋ መቁረጥ ስሜት እዚህም እዚያም
ቆመዋል፡፡ ለአያሌ ወራትና ዓመታት የተንገላቱና የተጎሳቆሉ ባለጉዳዮች ናቸው::በረሃብና በጥማት በርዛትና በንዴት በመጎዳታቸው አብዛኛዎቹ ውርጭ ላይ ያደረ አንጋሬ ይመስላሉ፡፡ ሕይወታቸው በትካዜ በመሞላቱ የገጽታቸው ፈገግታ ደርቋል፡፡

ወዛቸው እንደ ቅቤ ቅል የሚቅለጠለጥ ፊታቸው በዶሮ ጮማ እንደተወለወለ የወይራ በትር የሚያበራ፣ ቦርጫቸው የመንፈቅ ርጉዝ መስሎ ሱሪያቸው መታጠቂያው ላይ የሪቅ አፍ የሚያህል፣ አለባበሳቸው ሁሉ በጣም ያማረና የተዋበ ደንደሳሞች፣ በየደቂቃው በሚረባና በማይረባው ሁሉ የሚሥቁ በጣም መሠሪ ሰዎች ከየቢጤዎቻቸው ጋር ሰብሰብ ከምችት ብለው አፍ ለአፍ
ገጥመው ያወራሉ። የያዙት የሰነዶች መያዣ ኮሮጆ እንደ ባለቤቶቹ የፀዳ ሲሆን
የልፋት እንክርት አልነካውም፡፡ የተሰበሰበውን ሰው በዝርዝር ሲያዩት እያንዳንዱ ብቻውን ቆሞ እጁን እያወራጨ ከራሱ ጋር ይሟገታል።

አብዛኛው ጨርቅ ለባሽ በሌላ ሰው ወረቀት እያስነበበ ይኽ ልክ ነው
የለም ይኽ ሐሰት ነው! ለዚህ በቂ ነቃሽ አለኝ! ያያት የቅድመ አያቴ ነው ይግባኝ እላለሁ፡ ከዳኛው ጋር ተዋውለው ነው። ወላዲተ አምላክን!” እያለ እሰጥ
አገባ ይላል። ሁሉም ከሕይወት ወዲያ ማዶ በውሸት ዓለም ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እንጂ በርግጠኛ ሕይወት በእውነተኛ ዓለም የሚኖሩ አልመሰሉኝም

የመጥፎ ነገር ጥቀርሻ በጥብጠው የጋቱኝ ይመስል አእምሮዩ ተጨነቀ፡፡
የማያቋርጠው የጊዜ ጎርፍ እየጋፈረ መጓዙን ቀጠለ። ደቂቃ የደቂቃ ርካብ ረግጣ እየተፈናጠጠች ላትመለስ ትጋልባለች።

ጎነ ረጂሙ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግዙፍ ሕንፃ ታላቅ የመከራ ተራራ መስሎ ፊት ለፊት ተገትሯል። የማደርገውን ጥንቃቄ አሟልቼ አካባቢዬን ገልመጥ እያልኩ እያየሁ መለስ ቀለስ አልኩ፡፡ ጭንቀቴና ጥበቴ እንደ ሐምሌ ጥቁር ደመና ከብዶ አንጎሌ ውስጥ አንዣሰሰ። በውስጤ የነበረው ሥጋት በድኃ ገበሬዎች አዋሳኝ እንዳለ የከበርቴ እርሻ መስፋቱን ቀጠለ። ረፈደ።

በወታደሮች ታጅበው በእግራቸውና በመኪና የመጡ አያሌ እስረኞች
በተለየ ቦታ ሰብሰብ አጀብ ብለው ቆሙ። ገር ገጭ ገጭ ገጭ፣ ሲጢጢጢጢጢ !
ካካካካካኪ! የሚል ድምፅ የምታሰማ ቮልስዋገን መጥታ አጠገቤ ቆመች፡፡ ጉልላት ነው። የየወዲያነሽ ቀነ ቀጠሮ በመሆኑ እኔና እርሱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት
ለመገናኘት ተነጋግረን ነበር። ድክምክም ባለ እንቅስቃሴ የመኪናይቱን ቋቋቲያም
“በር ከፍቶ ወጣና ጨበጠኝ፡፡

ለአራት ሰዓት ሩብ ጉዳይ እኮ ሆኗል እስካሁን አላመጧትም እንዴ?»
አለኝ፡፡ ከንፈሬ ተጣብቆና ምላሴ አልላወስ ብሎ ቢያስቸግረኝም የለም እስካሁን አላመጧትም» ብዬ ዝም አልኩ። ውካታ በበዛበት አካባቢ ጥቂት ዝም ብለን ቆምን። ትላንት ማምሻዬን ሦስት ባለሙያ ጠበቆች አነጋግሬ ነበር። ሁሉም የሰጡኝ መልስ በጣም ተቀራራቢ ነበር፡፡ ቢበዛ አምስት ዓመት” አሉኝ። እንተስ ምን ይመስልሃል?» ብሎ ዐይኔን ማየት ጀመረ።

«እኔ ምን ዐውቃለሁ፡፡ ማንም ቢሆን ከራሱ ላይ ይልቅ በሌላው ላይ
መፍረድ ይቀልለዋል። የፍርድ ሰጪዎቹን ማንነት ስታየው ግን አምስት ዓመት
የሚበዛ አይመስልም፡፡ ቢሆንም ለእኔና ለእርሷ እያንዳንዱ ደቂቃ የሕይወታችን
ማሻከሪያ ክፍለ ጊዜ መሆኗ ነው» ብዬ ዝም አልኩ፡፡

«መቼም ቢሆን» አለ ጉልላት ወደድክም ጠላህም ምን ጊዜም ቢሆን ሕግ አለ። በሕጉም የሚጠቀሙና ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ አሉ። አህያና ጅብ
ባንድ ላይ ሕግ አያረፉም፡፡ ለጨቋኝና ለተጨቋት በአንድ ጊዜ በእኩልነት
የሚያገለግል ሕግ የለም፣ አልነበረምም፡፡ ሕግ ስለተፃፈ ብቻ ሕጋዊ አሠራር አለ
ማለት አይቻልም። እኔና አንተ ባለንበት ሥርዓተ ማኅበር ውስጥ እጀግ በጣም
አያሌ ባለሥልጣኖችና አጫፋሪዎቻቸው በልዩ ልዩ የእሠራር ስልትና ሥልጣን
ፈጠር ከለላ ከሕግ በላይ የሆኑበትና የሚሆኑበት ሁኔታ እንዳለ መዘንጋት
የለበትም፡፡ ስለሆነም ሕግ በትክክለኛው መንገድ በሥራ ላይ እስካልዋለ ድረስ
የሌለ ያህል ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በስፋት የሚያነጋግግር ስለሆነ አሁን ከመጣንበት
ጉዳይ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት የለውም። ወደ መጣንበት ጉዳይ እንመለስ፡፡
ስለዚህ በሚሰጠው ፍርድ እንዳትገረም፡፡ የበዛ ወይም ያነሰ ሊሆን ይሆናል» ብሎ
ወደፊት ተራመደ፡፡ ርምጃዬን ከርምጃው ጋር አስተካክዩ ተከተልኩት።

ከእኛ ትንሽ ራቅ ብሎ አንድ ብረት ሽፍን ባለ ጥቁር ሰሌዳ አረንጓዴ መኪና ቆሟል፡፡ ጉልላት መኪናውን አሻግሮ እየተመለከተ «ለምንድን ነው አልመጣችም ያልከኝ? ያ እኮ ነው የወህኒ ቤቱ መኪና» ብሎ ጥሎኝ ሔደ፡፡
አልተከተልኩትም፡፡

መኪናው ውስጥ ከተቀመጠው ሰው ጋር ምን እንደተባባሉ ባይሰማም ጉልላት ትንሽ ራቅ ብሎ ተነጋገሩ። ወዲያው ወደ እኔ ዞር ብሉ ና ቶሉ በሚል አኳኋን ጠቀሰኝ እና ሄድኩ፡፡ እስረኞቹ ወደሚገኙበት አካባቢ እንደ ደረስን ዐይኔ
ያካባቢው የብርሃን መጠን ያነሣት ይመስል የውበት ሃያ መስኮቶቿ ተሸጎሩ።

አጠርጠር ያሉና በሰፊ የካኪ ጨርቅ ስልቻ ውስጥ የቆሙ የሚመስሉ
የወህኒ ቤት ሴት ወታደሮች እያንዳንዳቸው አጠር ያለ ዱላ ይዘው ቆመዋል። በአቅራቢያቸው አምስት ሴቶች ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል። የትካዜ እሳት ያነኮታቸው ይመስላሉ። ንዳድ እንደ ተነሣበት ሰው መላ ሰውነቴ ጋየ፡፡

የሕይወቴ ክፋይ የሆነችውና የማፈቅራት የወዲያነሽ አንገቷን ሰበር አድርጋና ጀርባዋን ለረፋዷ ፀሐይ ሰጥታ መሬት ትቆረቁራለች። ጉልላት ከሴቷ ወታደር ትንሽ ራቅ ብሎ በትሕትና እጅ ነሣ ራመድ ብዬ ከጎኑ ቆመኩ

በተከዘ ፊቱ ላይ ለማስደሰት የሚፍጨረጨር ፈገግታ እያሳየ «ከነዚህ
👍31
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


....«ስለ ልጅሽ አታስቢ አንቺንም በሚገባ እረዳሻለሁ። አየሽ አእምሮዩ ባንዲት ተስፋ ብቻ ትደሰታለች። ይኸውም ካንቺ ጋር እንደገና እንገናኛለን የሚለው ተስፋ ነው» ብያት ሳልወድ በግድ ዝም አልኩ።

ምላሴ ተቆልፋ እምቢ ባትለኝ ኖሮ በውስጤ የማግበሰበሰው ሐሳብስ ስፍር
ቁጥር አልነበረውም። በብስጭት ከመለብለብ ብዬ ጥያቸው ገለል አልኩ።
ጉልላትም ካሦስት ደቂቃ በኋላ ተለይቷት መጣ፡፡ የእሱን መኪና እንደ ተደገፈን
ብዙ ደቂቃዎች ዐለፉ። እንሒድ ተባብለን ወደ ፍርድ ቤቱ በር አካባቢ ተጠጋን፡፡

አንድ ወፈር ያለ ድምፅ «የወዲያአሉሽ አሸናፊ!» ብሎ ተጣራ፡፡ ለፈተና
እንዳልተዘጋጀ ሰነፍ ተማሪ ተርበተበትኩ፡፡ ሮጥ ሮጥ ብለን ሴቷን ወታደር
ደረስንባትና ስንተኛ ችሎት ነው የምትቀርበው?» ብለን ጠየቅናት።

«አንደኛ ወንጀል ችሎት» ብላ የወደያነሽን ለዕርድ እንደሚነዳ ሠንጋ ነዳቻት። በረዶ የመታኝ ያህል ተንዘፈዘፍኩ፡፡ ወደ ፍርድ ቤቱ ለመግባት ከባለጉዳዮችና ከአቸፍቻፊዎች ጋር ተደባልቄ ዘለቅሁ፡፡
የፍርድ ቤቱን ደፍ ራመድ እንዳልኩ፣ ልክ ከፊት ለፊቴ ድንገተኛ መብረቅ የወደቀ ይመስል አካላቴ በታላቅ ድንጋጤ ተተረተረ። ወዲያም ወዲህ ሳላይ ቀንዷን እንደ ተመታች ላም ወደ ኋላ ተመለስኩ፡፡ ተከታትለው የሚይዙኝ ይመስል ሽሽቴን ቀጠልኩ፡፡ የምገባበት ጨነቀኝ፣ ተቅበዘበዝኩ፡፡ መሬት ተሰንጥቃ
ብትውጠኝ ባልጠላሁ ነበር። መለስ ብዬ ብመለከት የጉልላትም ፊት ቡን ብሏል፡፡
ጭንቅላቴን ይዤ አፈሩ ላይ ተጎለትኩ፡፡ መላ ሰውነቴን አሳከከኝ። ዐይኔ ውስጥ
አሽዋ የገባበት ይመስል ቆረቆረኝ፡፡ ዙሪያው ጨለመብኝ። አተነፋፈሴ ፈጠነ፡፡
የእጮኛውን ሞት እንዳረዱነት ወጣት መላ አካላቴ በውስጣዊ የኃዘን ማረሻ
ታርሶ ተበረቃቀሰ፡፡

«የወዲያነሽ ስንት ዓመት ይፈረድባት ይሆን?» እያልኩ ከእግር እስከ ራሴ በፍርሃትና በሥጋት ማጥ ውስጥ ተዘፈቅሁ፡፡

የፍርድ ቤቱን ደፍ ገና ረገጥ ስናደርግ እኔንና ጉልላትን ያስበረገገን ግን
ከሦስቱ ዳኞች አንዱ ያውም የመኻል ዳኛው የእኔው አባት ባሻ ያየህይራድ
መሆኑ ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም እንደዚያ ያለ ድንጋጤ አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡
አቀርቅሮ የክስ ፋይል ይመለከት ስለነበር አላየኝም፡፡ እነዚያ በሕይወቴ ውስጥ
ዕድሜ እየሆኑ የተቆጠሩት አስደንጋጭ ደቂቃዎች እንደ ማንኛውም ደቂቃ
ዐለፉ፡፡ በዚያ ቅፅበት በእእምሮዬ ውስጥ የጎረፈውን የስጋት ሽብር በተግባር
ለቀመሰው እንጂ በወሬ ለሚሰማው ክብደት የለውም፡፡

አቃቤ ሕጉ በየወዲያነሽ ላይ የሚያቀርበውን ክስና አባቴ ከሁለቱ ዳኞች ጋር ሆኖ የሚሰጠውን የቅጣት ፍርድ ፊት ለፊት ለማየትና ለመስማት ባለመቻሌ ምን ጊዜም የማልበቀለው ጉዳት አጨቀየኝ።

የየወዲያነሽ ሰውነት በጣም በመኮስመኑና ስሟም በመጠኑ ተለውጦ
የወዲያ አሉሽ በመባሏ አባቴ ሊያውቃት አይችልም፡፡ አለባበሷና አንገተ
ሰባራነቷ እንደሚያዛልቅ ወለል ብሎ ታየኝ፡፡ ጭንቅላቴን ይዤ እንዳቀረቀርኩና
ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ ጉልላትም እንደ ማማ ተገትሮ እንደ ቆመ ግማሽ ሰዓት
ያህል ነጎደ። ወዴት እንደሚሔድ ባላውቅም የእግሩ ኮቴ ድምፅ ከወደ ኋላዬ እየራቀ ሄደ። አሁንም ጥቂት ደቂቃዎች ዐለፉ፡፡ እፎይታ ሳይሆን የመከራ ነዲድ በውስጤ ተግፈጠፈጠ።

የአባቴን ጠቅላላ የሕሊናና የአካል አቋም ከልጅነት እስከ ዕውቀት የማውቀውን ያህል እያሰላሰልኩ ከፊት ለፊቴ አቆምኩት፡፡ እርሱ በሚያነብበው
የሃይማኖት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ የሚነገርለት ሰው በላው ሰው ሰባ ስምንት
ሰዎች በልቷል እየተባለ ይነገራል። አባቴም በላዔ ሰብ እየተባለ የሚነገርለትን የክፉ ሰው አምሳል መስሎ ታየኝ።

እሱም እንደ ሰው በላው ሰው የሰው አካል አወራርዶና ግጦ የሰው ሥጋ ባይበላም ሰው በላ ነው:: የሰውን ሕይወት በማጥፋትና የሰውን ሕሊና በመግደል
መካከል ምንም ልዩነት የለም፡፡ ስለ እውነተኛ ርትእና ፍትሕ እየተናገረ
ከሓሰተኞች ጎን ቆሞ ፍርድ ያዛባል፡፡ ከሐቅ ጋር ለቆመ ድሃ ሳይሆን ከሐሰትና
ከክህደት ጋር ጡት ለተጣቡ ባለጊዜና ባለ ገንዘብ ይፈርዳል። ስለዚህም «ሰው
በላ» ነው፡፡

ስለ ድሀ መጨቆንና መበደል ሲያወራ ማንም የሚስተካከለው አይመስልም፡፡ የየአካላችን ደም ስለየሕሊናችን ቅንነትና መሠሪነት መስካሪ ቢሆን ኖሮ ከአባቴ ኣካል የሚንጠፈጠፍ ደም ምንኛ ባጋለጠው!

ከጥቅምና ከኑሮው ላይ ቅንጣት ታህል የሚነካ ሰው ከመጣ፡ አንዷ ሰው
በላው ሰው የሰው አካል ዘነጣጥሎ ባይበላም ነገር ሽርቦና ጉንጉኖ ዓመት ሳይተኩስ ጥርኝ ዐፈር ያደርገዋል።

«ጨርቅ ለባሽ፣ አጥንተርካሽ በማለት የሚጸየፋቸውን ሰዎች ስለ ስምና
ክብሩ ብሉ ያንገላታቸውን ድሆች ሳስታውስ አባቴ እንደዚያ እንደ ታሪኩ ሰው
በቀጥታ የሰው ሥጋ ሳይሆን የሰው ሕይወት በልቷል። ስለ ሰው ችግርና ሥቃይ ፍጹም ደንታ የለሹ አባቴ፣ ማንም ቢንገላታና በጊሳቆል የቁጫጭ ሞት ያህል አያሳዝነውም፡፡ በአባቴና በመሰሎቹ አካባቢ ግዙፍ በደል በድሉ፣ በእጅ አዙር ሰው አስገድሉ፣ ከድሆችና ከከልታሞች ዲቃላ ደቅሎ ምስጢርን መቅ መጨመር የመሠሪነት ሳይሆን «የትልቅ ሰውነት» መለዮ ነው:: ለዚህ ዐይነቱ ደባ የሹም ምልመላ ቢካሔድ አባቴ ያላንዳች ቀዳሚ በትራሹመቱን ይጨብጣል።

«እሳቸው የሞቱ ዕለት ስንቱ ዲቃላ ከየሥርቻ ስርኩቻው ይጎለጎል ይሆን?» በማለት ውስጥ ውስጡንና የሚያማው ብዙ ነው:: እንደ ሰው ሐሜትማ ከሆነ ከልዩ ልዩ ሴቶች ተወልደው በአባቴ የተካዱትን እኀት ወንድሞቼን በግምት ሳሰላስል፣ አባቴ ከሰው በላው ብሶ ታየኝ። በተለይም ጠለቅ ብሎ ሥር ከፍ ብሎ ግንድ የለሽ» እያለ ሌሎችን በማኮሰስ የራሱን የዘር ሐረግ ሲያሳምር ታየኝና አስተሳሰቡን ሁሉ ተፀየፍኩት፡፡

ጉልላት ተመልሶ ከፊት ለፊቴ ቆመ፡፡ በእጆቹ ጎትቶ አስነሣኝ፡፡ በፊቱ ላይ አደናጋሪ ፈገግታ እየታየ «የምሥራች ጌታነህ!» አለኝ፡፡

በዚያች አስጨናቂ ጊዜ ውስጥ አንዳችም የምሥራች ይገኛል ብዬ ስላልጠረጠርኩ ነገሩን ችላ አልኩት፡፡ ቀጠል አደረገና «ምነው ዝም አልክ? የወዲያነሽ እኮ ተፈረደባት። የምሥራች ያልኩህ ግን እጅዋ ከተያዘበት ቀን አንሥቶ አምስት ዓመት እንድትታሠር ስለተፈረደባት ነው:: 'የፈረዱብኝ የጌታነህ አባትና አብረዋቸው ያሉት ናቸው” አለችኝ፡፡ የቅጣቱን ውሳኔ ግን በንባብ ያሰሙት ያንተ አባት ናቸው አለች፡ በስሜ መለወጥና በመጎሳቆሌ
አላወቁኝም በማለቷ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ አለቀ። በፍርሃት የሚጠብቁት ሥቃይ
ካለፈ እፎይታ ነው» ብሎ ከሚተናነቀው ምስቅልቅል ሲቃ ጋር ዝምታውን ቀጠለ።

ከፍርዱ በኋላ የወዲያነሽ ወደ ነበረችበት አካባቢ አብረን ሄድን፡፡ ያ የዐይኗ ቋንቋ የሆነው እንባዋ ገነፈለ። ሴቷ ወታደር ትካዜያችንን አይታ አዘነች፡፡ እኔና ጉልላት እንደገና ጠጋ ብለን ለማነጋገር አዲስ ፈቃድ አልጠየቅንም፡፡

«አይዞሽ! ብዙ ጊዜ አይደለም፡፡ በወህኒ ቤት ውስጥም ሆነ እስራትሽን ጨርሰሽ ስትወጪ የእኔ ነሽ። እኔም ያንቺ እንጂ የማንም የሌላ እይደለሁም፡፡ የልብሽ አዳራሽ በዚህ እውነተኛ በሆነ የቃል ኪዳን ተስፋ ይሞላ። ይህን በላይሽ ላይ የጫንኩትን የመከራ ቀንበር አብሬሽ እሸከመዋለሁ፡፡ በመጨረሻም አብረን
እንሰባብረዋለን፡፡ ያጠቆርኩትን ሕይወትሽን በአዲስ የኑሮ ብርሃን እንዲደሞቅ እስከ መጨረሻው እታገላለሁ» ብዬ የልቤን ፅላት ሰጠኋት። አፏ ባይናገርም ልቧ ተቀብሉኛል፡፡ ያደረግሁት ንግግር ተፅፎ የተጠና እንጂ እዚያው ተቀናብሮ የተነገረ ስለማይመስል እኔኑ መልሶ ገረመኝ፡፡

መለስ ብዩ ለሴቷ ወታደር ምናምን ጨበጥ እደረኩላት፡፡ የማይፈቀድ
ነገር
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


....ከቤተሰቦቼ ጋር የነበረኝ ግንኙነት እምብዛም ሳያፈነግጥና ሳይቀርብ፣
ሳይጥምና ሳይሆመጥጥ ቀጠለ የወዲያነሽ አንድ ዓመት ከመንፈቋ እንደ አንድ የደስታ ቀን ፈጥኖ ዐለፈ፡፡ አንድ ቀን እሑድ ከሰዓት በኋላ ከአንድ ጓደኛዬ
የተዋስኩትን መቅረፀ ትርዒት (ካሜራ ወይም ፎቶ ማንሻ ይዤ ወደ ዕጓላ
ማውታ ሄድኩ

ከዚያ ቀደም ሲል ከወሰድኩለት ልብሶች መካከል ጥሩዋን ልብስ አልብሽ አነሣሁትና እንዴት እንደሚደርሳት ቀደም ብዪ ጨርሼ ስለነበር በሳምንቱ እሑድ
የልጇን ፎቶ ይዤ በጉልላት መኪና ወህኒ ቤት ሄድኩ። እንደ ተለመደው !
፣አስጠራኋት፡፡ የአጥሩን አግዳሚ ዕንጨት ተደግፋ ጥቂት አወራራን ድንገት !ሳታስበው ፎቶግራፉን ከኪሴ መዥረጥ አደረግሁና «በይ እስኪ በቃሽ እዪና ጥገቢው፡ ነጋ ጠባ፣ ልጄ! ልጄ ስትይ!...» ብዬ በወታደሪቱ ኣስተላላፊነት
አቀበልኳት፡፡ የወረቀቱን ግራ ቀኝ ጠርዝ በሁለት እጆቿ ይዛ ትኩር ብላ
ተመለከተችው:: ፊቷ ላይ ስታሸበሽብ የቆየችው ኮስማና ፈገግታ ደብዛዋ ጠፋ።

ወዲያው ብርሃኗ በጥቅጥቅ ጭጋግ እንደ ፈዘዘ ጨረቃ ፈዘዘች። እንባዋ
በዐይኖቿ ዙሪያ ግጥም አለ፡፡ አቀረቀረች። በሰንበሌጥ ላይ እየተንኳላላች እንደምትወርድ ጠፈጠፍ እንባዋ ጉንጯን ሳይነካ ከትንሿ ወረቀት ላይ ተንጠባጠበ።

ከሩኅሩኅ የእናትነቷ ባሕሪ የመነጨ የፍቅር ኩልልታ ስለነበር ለመጪው
ጊዜ የሚቀመጥ የትዝታ ጥሪት አስቀመጥኩ፡፡ ደግማ ደጋግማ ሥዕሉን ሳመች።እምብዛም ነገሬ ሳትለኝና እህ! ብላ ሳታዳምጠኝ ተሰናብቻት ተመለስኩ።

ከሌላ ስድስት ወር በኋላ የወዲ ያነሽ ሁለት ዓመት ሞላት።

እሑድ ከሰዓት በኋላ ነበር፡፡ የዕለቱን ጋዜጣ እያነበብኩ እንግዳ መቀበያ
ክፍል ውስጥ ተቀምጬ ሳለሁ የውብነሽ አጠገቤ ተቀመጠች። የያዘችውን
የአማርኛ ሰዋሰው መጽሐፍ እንደተገለጠ አጭሯ ክብ ጠረጴዛ ላይ ዘረጋችው።

ዐይኔ ተወርውራ የጊዜ ተውሳከ ግሥ የሚለውን ርዕስ አየች። ለነገርና
ለወሬ ማነሣሻ ይሆነኝ ዘንድ «ይልቅስ የአኳኋንና የሁኔታን ተውሳከ ግሥ
አታጠኚም» ብዬ መጽሐፉ ውስጥ የማነበው ያለኝ ይመስል አገላብጬ
አስቀመጥኩት። «እኔ የጊዜ ተውሳከ ግሥ አልዘለቅ ብሎኛል። አንተ ደግሞ
ሌላውን ትለኛልሀ» አለችና እጄ ላይ የነበረውን ጋዜጣ ወስዳ የመጀመሪያን ገጽ አርእስቶች በለሆሳስ አነበበች፡፡

«ሥራ አለብሽ እንዴ የውቢ? ከሌለብሽ አንድ ቦታ ደረስ ብለን እንምጣ» ብዬ ጸጉሬን አሻሸሁት፡፡ ጋዜጣውን አጣጥፋ አስቀመጠችው:: «እሺ እንሂድ፡፡ ይህን ማታም ቢሆን ልፈጽመው እችላለሁ» ብላ ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች።
«ምንም እንኳ ለጊዜው አሳዛኝ መስሎ እንደሚታይሽ ባውቅም የኋላ ኋላ
ግን ያስደስትሽ ይሆናል» ብዩ ኩራትን ለመግለጽ በሚያስችል ወፍራም ደርባባ
ድምፅ ተናገርኩ። ካንተ ጋር ከሆንኩ ምን ያሳዝነኛል? በመጨረሻ የሚያስደስተኝ
ነገር ሁሉ ደስ ይለኛል፡፡ እንሂድ ካልክ ልብሴን ልቀያይርና እንሂድ» ብላ ተነሣች፡፡ እንዲሁ ገባ እንዳለች ዘርፈጥ ብላ የተቀመጠችበት ቀሚሷ ከበስተኋላዋ
ልሙጥነቱ ጠፍቶ ወደ ልዩ ልዩ አቅጣጫ የተሰበጣጠረ ጭምድ መስመሮች
ሠርቷል። ልብሷን ለመቀያየር ወደ መኝታ ቤት ስትገባ እኔም ጸጉሬን ለማበጠር
ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡

የልብሴን መስተካከል በመስተዋት ከተመለከትኩ በኋላ ጸጉሬን በደረቁ
እበጥሬው ወጣሁ፡፡ ደረጃውን ወርጀ እንደ ጨረስኩ ደረሰችብኝ።

ምንም እንኳ ወዴት እንደምንሄድ ባታውቅም «የምንሔድበት ቦታ ብዙ
ሰዎች አለበት እንዴ?» ብላ ጠየቀችኝ፡፡ «ማንም የለም። የምንሄደው አንድ እሳዛኝ
ሰው ለማየት ነው» ብዬ አለባበስና አረማመዷን እያየሁ መንገድ ገባን፡፡ ደማም ወጣትነቷና እንስታዊ ውብ ቅርጺ ማራኪነት ሰጥቷታል፡፡ ፈገግ ስትል ፍልቅቅ የሚሉት ነጫጭ ውብ ጥርሶቿ ከደም ግባቷ ጋር የአተር አበባ አስመስለዋታል፡፡

እግረ መንገዳችንን ልዩ ልዩ የሚባሉ ነገሮች ገዛሁላት። ዐሥር ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በታክሲ ዕጓለ ማውታ ደረስን፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት
አስከትዩ በመሄዴ ያ ዘወትር ብቻዬን ስመላለስ የሚያየኝ ዘበኛ የውብነሽን
በማየቱ የመገረም ፈገግታ ታየበት።

አብዛኛውን ጊዜ ከቤቱ ታዛ አካባቢ ከብዙ ከልጆች ጋር ተቀምጦ ሲጫወት ከሩቁ የማውቀው በልብሱ ስለነበር ሜዳው መኻል ቆም እያልኩ የቢቶቹን የፊት ዙሪያ ተመለከትኩ፡፡ ብዙ ልጆች ጨዋታቸውንና ልፊያቸውን እየተዉ አዩን፡፡ ወደ መኝታ ክፍሉ ይዣት ገባሁ። እሱኑ ከሚያካክሉ ሁለት ልጆች ጋር ወለሉ ላይ ተቀምጦ እየተኮላተፈ ይጫወታል። ሁለቱ ልጆች መለስ ብለው ካዩን በኋላ ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡ የእኔ ልጅ ዐይኖች ግን እኔ ላይ
ተተከሉ፡፡ ጎንበስ ብዪ አነሣሁት፡፡

አባባና እማማ የሚባሉ ቃላት የማያውቀው፣ የወላጅ ፍቅር ያልቀመሰው
ልጄ እንደ ወፍ ዘራሽ የመስክ አበባ ያምራል። ለምን ወደ ዕጓለ ማውታ እንደ
መጣች ግራ የገባት የውብነሽ በመጠኑ ደንገጥ አለች፡፡ ወደ እርስዋ ዞሬ ትከሻዋን
ቸብ ካደረግሁዋት በኋላ እስኪ ይህን ልጅ ተመልከችው የውብነሽ ቆንጆ ልጅ
አይደለም እንዴ? ብዬ ጠየቅኋት። እ..ብላ ዝም አለች።

ሰውነቷ በጥርጣሬና በሐሳብ የተጠመደ መሰለ፡ ድንገት ከእንቅልፏ ነቅታ ባጋጣሚ ያየችው ይመስል ሁለት እጆቿን ዘርግታ «እውይ እማምዬ ማማሩ! ደስ ማለቱ?» ብላ ከእጁ ላይ ወስዳ ታቀፈችው፡፡

በፊቱ ላይ አንዳችም ሌላ ለውጥ ሳይታይና ፈገግታው ሳይቀንስ ዝርግፍ
ብሉ ወደ እርሷ በመሄዱ በጣም ደስ አለኝ፡፡ እንዲያውም እዚያች ጠባብ ደረቷ
ላይ ልጥቅ አለ፡፡ ነገር ግን ልጄን ለመጀመሪያ ጊዜ ያቺ የማፈቅራትና
የምንሰፈሰፍላት የወዲያዬ ሳትሆን እኅቴ አቅፋው በማየቴ በፋይዳ የለሽ ጥላቻ
ተናደድኩ፡፡ ጉንጮቹን ሳም ሳም ካደረገች በኋላ ፊቷን ወደ እኔ መለስ አድርጋ
<<የማን ልጅ ነው ?» ብላ በጓጓ ስሜት ጠየቀችኝ። የምናገረው እውነተኛና ርግጠኛ እንዲመስል ለመመለስ የማሰላሰያ ጊዜ አልወሰድኩም፡፡ «አንቺ የማታውቂው አንድ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ የዚህ ልጅ አባት ማለቴ ነው። ትዝ እይልሽም ይሆናል እንጂ እኛም ቤት አንድ ሁለት ቀን ያህል መጥቶ ነበር» ካልኩ በኋላ የነገሩን
ድምጥማጥ ይበልጥ ለማጥፋት «ነገር ግን ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት
በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሞቷል፡፡ ልጁ ግን ለጊዜው አሳዳጊ ዘመድ በማጣቱ
ይኸው እዚህ በምታይው ሁኔታ በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ልጅ አባት በጣም
ግሩም ሰው ስለ ነበር እሱን በማሰብና ለልጁ በማዘን ብቻ አልፎ አልፎ ብቅ
እያልኩ እጠይቀዋለሁ፡፡ ጉልላትም አንዳንድ ቀን እየመጣ ያየዋል» ብዬ ዋሸኋት፡፡ግንባሩን ሁለት ጊዜ ያህል ስማ ውብ ዐይኖቹን ባንጸባራቂ ሸጋ ዐይኖቿ ትኩር ብላ ተመለከተቻቸው::

«ምነው አንተም እንዲህ የሚያምርና የሚያስጐመዥ ልጅ በነበረህ» ብላ
እንደ ወይን እሽት የሚያስጐመዡትን ጉንጮቹን ሳመቻቸው:: ንግግሯ ለጊዜው
ረግቶና በርዶ የቆየውን የሕሊናዬን ባሕር በብስጭት ማዕበል አረሰው፡፡

“ምናልባት ሚስት ባገባ ማስቴን በርግዝናዋ ወራት ከቤት አታባርሯት
እንደሆነ ነዋ እንዲህ ያለ ልጅ ማግኘት የሚቻለው» ብዩ በሽሙጥ መለስኩላት።
ድንገተኛው የንግግሬ ይዘት ፊቷን አስቀጨመው:: ልጁን ከሰጠችኝ በኋላ
አንገቷን ስብራ አቀረቀረች። ከጥቂት ዝምታ በኋላ ከወለሉ ላይ ቃላት
እየለቃቀመች ትናገር ይመስል ወለሉን እያየች «ያ ያለፈው ሁሉ ሌላ ጉዳይ
ነው፡፡ የማይገናኙ ነገሮች አታገናኝ እኔን ምን አድርጊ ትለኛለህ? አንተ ከእኔ
የበለጠ ብልህ መሆንህን ዐውቃለሁ አባታችን ቢሰማ ኖሮ በአንተና በእርሱ
መካከል ትልቅ ጠብና ማለቂያ የሌለው
👍4
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል



...የካቲት ነበር፣ የመጀመሪያዉ እሑድ። ከዚያ ቀደም እንደማደርገው ልዩ ልዩ ነገሮች ይዤላት ወህኒ ቤት ሄድኩ። የወዲያነሽን ለማስጠራት ዐይኔ
እየዋተተ ጠሪ ስፈልግ ከስድስት ዓመታት በፊት በነበራት የፈገግታ ዐይነት ፊቷ
ፈክቶ ሣቅ ሣቅ እያለች «አንተ ጌታነህ! » ብላ ጠራችኝ፡፡ የአሁኑ ፈገግታዋ
ከቀድሞው የሚለየው ፊቷ ከሲታ ሆኖ በመገርጣቱ ብቻ ነው፡፡ ለምን ከአንጀቷ
ፈገግ እንዳለች የምከንያቱ መነሾ ጠፋኝ፡፡ ለወትሮው የወዲያነሽን የማገኛት
እያስጠራሁ ነበር፡፡ የዚያን ዕለት ግን ቀደም ብላ መጥታ ስትጠብቀኝ በመድረሴ ለውጡ ግራ ገባኝ፡፡

ምንም እንኳን ፈገግታዋና ሣቋ ደስ ቢያሰኘኝም ለጊዜው ደስታዬን አምቄ «ደኅና ነሽ ወይ? ደኅና ሰነበትሽ ወይ?» አልኳት። የደስታ ሲቃ እየተናነቃት አይታ የማትጠግበኝ ይመስል ዓይኖቿ ቃበዙ፡፡ አጥሩን ዘላ የምትወጣ መሰለች፡፡

አጥሩ ግን የሥቃይ ሕግ ግድግዳ እንጂ ተራ እንጨት አልነበረም፡፡አፏን ሁለትና ሦስት ጊዜ ከፍታ መልሳ ገጠመችው:: የወሰድኩላትን ጥቂት ዕቃና ምግብ በወታደሯ አማካይነት እንዲደርሳት አደረግሁ፡፡ በማስቀመጥ ፈንታ
ዐቅፋው ቆመች፡፡ የደነገጥን ይመስል
ዝም ተባባልን፡፡ የታቀፈችው ዕቃ
አምልጧት እግሯ ሥር ዱብ አለ፡፡ ተሰባሪ ነገር ስላልነበረበት አልደነገጥኩም፡፡
እዚያው እንዳለ ጎንበስ ብላ እግሮቿ መኻል አስገብታ እጣብቃ ይዛው ቆመች።
ባላት አካላዊ ሁኔታ ላይ ፈገግታዋ የመጨረሻውን ደረጃ ያዘ፡፡

«ጌታነህ» ብላ በዚያች ውብ የሴታ ሴት ድምጺ ከጠራችኝ በኋላ «ነገ ሮብ እኮ» ብላ ዝም እለች፡፡ ከበፊቱ በበለጠ ጥንቃቄ አቆብቁቤና አፍጥጬ
ተመለከትኳት። ዝግ ብላ ምራቋን ዋጠችና «ሮብ እኮሮብ እኮ ትለቀቂያለሽ'
ትፈቺያለሽ ተባልኩ» ብላ በዐይኖቿ ዙሪያ እንባ ከተረ፡፡ የሰማሁት ነገር እውነት
ስላልመሰለኝ ድንገተኛ የደስታ እና የድንጋጤ ሲቃ ያዘኝ፡፡ «ምን?! ምን
አልሽ?!» አልኩና ነፋስ እንዳስጎነበሳት ለጋ ቅርንጫፍ አንገቴን ወደፊት
አሰገግሁ።

«ሮብ ትለቀቂያለሽ ብለውኛል ነው የምልህ» ብላ ጥርሶቿን እንደ ፈለቀቀች ከነፈገግታዋ ዝም አለች፡፡ ዘልዬ በአንገቷ ዙሪያ እንዳልጠመጠምባትና ጮቤ እየዘለልሁ ደስታዬን እንዳልገልጽ በመካከላችን የተጋረጠው ዐፅሙ የገጠጠ አጥር የመከራ ገረገራ ሆኖ አገደኝ፡፡ የምይዝ የምጨብጠው ጠፋኝ። የደስታ ዕብደት አበድኩ፡፡ አዲስ የሕይወት ብርሃን ፏ አለ፡፡ የሰማይን ሰማያዊ ውብ ጣራ አንጋጥጬ ተመለከትኩ፡፡ በውብ የመስክ አበቦች መካከል እየተዘዋወረች ያሻትን አበባ እንደምትቀስም ንብ ሕሊናዬ ባስፈለጋት የደስታ ዐይነት መካከል
እያማረጠች ቦረቀች።

አምስቱ የሥቃይ ዓመታት እንደ አንድ ረዘም ያለ አስፈሪና አስደንጋጭ ሕልም አለፉ። የደስታ ዘለላዎች እየተሸመጠጡ የሚታደለ ተጨባጭ ነገሮች ቢሆኑ ኖሮ በዚያች ሰዓት ውስጥ ለአያሌ ሰዎች እተርፍ ነበር። በደስታ የሚንከባለሉትንና ብዙ ነገር ለማየት የጓጉትን ዐይኖቿን እየተመለከትኩ በይ እንግዲህ መሔዴ ነው፣ ለጉልላትም ልንገረው:: ሮብ ጧት ከሁለት ሰዓት ጀምሮ ካጥር ውጪ እጠብቅሻለሁ» አልኳት፡፡

«ሮብ ዕለት መጥተህ ወዴት ትወስደኛለህ? ከእንግዲህ ወዲያ ደግሞ
አንተን ላስቸግር ነው?» ብላ ተከዘች፡፡
የማያወላውል ዓላማና ግቤን ስለማውቅ በጊዜያዊ ትካዜዋ አልተበሳጨሁም፡፡
ለ ሮብ ዕለተ ጉዳይ የማውቅው እኔ ነኝ፡፡ ጉዳዩን ሁሉ ለእኔ ተይው:: አሁን ግን
ደኅና ዋይ! እንደ ልቤ ልፈንድቅበት!» ብያት ለመጀመሪያ ጊዜ በርግጠኛ ተስፋ
ተሰናብቻት መንገድ ገባሁ፡፡

ከዕለቱ የደስታ ማሕበል የተወለዱ አስደሳች ትርዒቶች በአንጎሌ ውስጥ
እያሸበሸቡ በመደዳ ከነፉ::

ወዲያ ወዲህ ሳልል በቀጥታ ወደ ጉልላት ቤት አመራሁ። የተሣፈርኩባት መኪና በጣም ያዘገመች ስለ መሰለኝ «ቶሎ ቶሎ በል ጃል» እያልኩ በተደጋጋሚ ወተወትኩ፡፡

ጉልላት «መቼ አነሱኝና · ይበቁኛል፣ ከብዙ ደረቅ ጥቂት ርጥብ ይበልጣል» የሚላቸውን የግቢውን አባቦችና አትክልቶች ዐልፌ ወደ ቤት ገባሁ።

እንግዳ መቀበያ ክፍላቸው ውስጥ ጉልላትና እናቱ ወይዘሮ አማከለች ጐን
ለጐን ተቀምጠው ሲያወሩ ደረስኩ፡፡ እንዴት ሰላምታ ሰጥቻቸው እንደ
ተቀመጥኩ አላስታውስም፡፡ ከእናትዬው ጋር ያደረግሁት «የእንደምን ሰነበቱ?
ሰላምታ በምን አኳኋን እንደ ተፈጸመች ሃች አምና የታየ ሕልምን ያህል እንኳ
አትታወሰኝም፡፡

«ጌታነህ» አሉ ከተቀመጡበት እየተነሡ «እስኪ አሁን ደግሞ ያንተ ተራ ይሁን ተጫወቱ » ብለው ወደ ውጪ ወጡ። እንዴት ብዬ እንደምጀምር ስለጰ ጠፋኝ ሁለት ጊዜ ሀይኔን ጨፈንኩ፡፡ አልከሠትልህ ስላለኝ ድንገት ተነሣሁ።

ጸጉሬን ካወዲያ ወዲህ አሽቼ መነጨርኩት፡፡ የፍርሃቴ ሸክም ከጭንቅላቴ ላይ ዘጭ ብሎ የወደቀልኝ ይመስል የምሥራች ጉልላት!» አልኩት።

አንጋጦ ዐይን ዐይኔን እያዬ «ምሥር ብላ! ምን አገኘህ?» ብሎ ለመስማት ተጣደፈ። በሕይወቴ ውስጥ ትልቁ ደስታ ሊጀመር፣ ነባሩ የትግላችን ምዕራፍ የፊታችን ሮብ ሲዘጋ ሌላው ደግሞ ወዲያው ይከፈታል!» ብዬ እንደገና አዲስ ብርታት በመጨመር የፊታችን ሮብ የወዲያነሽ ትፈታለች!» አልኩት ጮክ ብዩ።

«እስኪ ሙት በለኝ!» ብሎ አንገቴ ላይ ተጠመጠመ። ለብዙ ዓመታት
እንደ ተለያዩ ጓደኛሞች ተሳሳምን፡፡ ጉልላት በደስታ ባሕር ውስጥ ተዘፍቆ
ውስጣዊ ስሜቱን በይፋ ገለጠ፡፡ ትከሻዩን ያዝ እንዳደረገ ግራና ቀኝ ተቀመጥን።
ፈገግታ በፊቱ ላይ እስክስ አለች። «አየህ እኔና አንተ ባለፈው ቅዳሜ የተሳሳትነው አንድ ነገር ነበር። እጅዋ ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ የሚለውን የፍርድ ውሳኔ ዘንግተነዋል። የሰባት ወር ጊዜ ሲጠቃለል ሙሉ አምስት ዓመት
ይሆናል ማለት ነው» ካልኩ በኋላ ጣራ ግድግዳውን በጠቅላላ የቤቱን ዙሪያ
ተመለከትኩት፡፡ «እንግዲህ እኔ እንኳን ደስ ያለህ ነው ወይስ እንኳን ደስ ያለሽ
የምለው?» አለና በደስታ የፈዘዘ አእምሮዬን ለማንቃት ትከሻዬን ይዞ ነቀነቀኝ፡፡

«እኔን አይደለም እርሷን መሆን አለበት፡፡ የእኔማ ጉዳይ ገና ምኑ ተነካና! ገና ብዙ ፈተናና ተከታታይ ችግር ይጠብቀኛል። እሷንና ቤተሰቦቼን ለማገናኘት ወይም ዘላቂ መብትና የእኩልነት ሕልውናዋን ለማረጋገጥ ከመጪው ሮብ ጀምሮ አንድ ትልቅ ተጋድሎና ጦርነት እጀምራለሁ፡፡ የወዲያነሽ ሙሉ የሕሊና ነጻነት እስከምትጎናጸፍ ድረስ እታገላለሁ፡፡ በተመሳሳይ የሕሊና ባርነት ውስጥ የሚገኙ እልፍ አዕላፍ ሰዎች ስላሉ ብቻችንን አይደለንም፡፡ ያም ሆነ ይህ
ከወላጆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ግን ከሮብ ጀምሮ ከዋናው ግንድ ላይ ተሰብራ
በልጧ ብቻ የተንጠለጠለች ቅርንጫፍ እምሳያ መሆኑ ነው» ብዬ መለስኩለት፡፡
በንግግሬ ውስጥ ያለውን የሐሳብ ይዘት እያሰላሰለ ጥቂት ዝም ስላለ «ብዙ ጊዜ
ቢፈጅም አንድ ቀን ድል እንደማደርግ አውቃለሁ፡፡ ይህን አስፈሪ መሳይ ያረጀ
አፍራሽ የልማድ ድልድይ እንዴት ኣድርጌ እንደማልፈውና እንደምሻገረው ካሁኑ
ጭንቅ ጥብብ ብሎኛል። የምፈራውና የሚያርበተብተኝ ምን እንደሆነ አሣምረህ
ታውቀዋለህ፡፡ ፍርሃቴ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ግን የወዲያነሽን ለመከራ አሳልፈ መስጠቴ ነው» ብዪ እንደ ጨረስኩ ወደ ጉዳዩ ዝርዝር ክርክርና ፍሬ ነገር ገባን።

ያን ዕለት ከሰዓት በኋላ ወደ ዕጓለ ማውታ ሳልሄድ ቀረሁ። ከቤቱ ውስጥ ወበቅ ደጁ ይሻል ይሆናል በማለት ከቤት ከወጣን በኋላ ግራና ቀኝ ቆም እንዳልን
«እንግዲህ የወዲያነሽ ነገ ሮብ መፈታቷ ነው:: ከወህኒ ቤት እንደ ወጣች ከእኔ
ሌላ ምንም መግቢያና መጠጊያ የላትም፡፡ ስለዚህ ነገም ይሁን ከነገ ወዲያ ባፋጣኝ
👍2
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል


.....ሸዋዬ ከመኝታ ክፍሏ ውስጥ ሆና አንጀቷ በእልህና በቁጭት ሲቃጠልና በእምባ ብዛት ያበጡት ዐይኖቿን ስታሻሽ አረፈደች።

ባሏ ቶሎሳ ደግሞ የምሳ ሰዓት ሲደርስ ወደ ቤቱ ለመሄድ ከጀለና የሸዋዬን የጠዋቱን ሁኔታዋን ሲያስታውሰው ፍርሃት አደረበት። ልቡ በመሄድና በመቅረት መካከል ሲዋልል ከቆየ በኋላ “ግዴለም እዚያው ባልና ሚስትን በሚያስታርቀው አልጋ ላይ ብንገናኝ ይሻላል” በማለት ራሱን አሳመነና ሲመሽ ወደ ቤቱ መሄድን መረጠ፡፡

አምሽቶ ገብቶ ጌትነትንና ሸዋዬን ሊያስታርቃቸው፣የበደለን ይቅርታ እንዲጠይቅ የተበደለ ደግሞ ይቅር ለእግዚአብሄር እንዲል የማድረግ ዕቅዱን
ይዞ ምሳውን ከሆቴል ቤት ቀማመስና ስራው ላይ አመሸ፡፡ ሸዋዬ በወደ
ቀችበት አልጋ ላይ ቆይታ ከቀኑ ወደ ስድስት ሰዓት ተኩል ገደማ ብድግ
አለች። የተመሰቃቀሉ ልብሷንና የተበታተነ ፀጉሯን በወግ በወጉ ካደረገች
በኋላ ወደ ፊት አመራችና ግድግዳው ላይ የተንጠለጠለውን መስታወት አንስታ ፊቷን ጣደችበት። ዐይኖቿ ንብ የነደፋቸው መስለዋል። ብርቱካን የሚመስለው ቀይ ጉንጫ በቶሎሳ ጥፊ ምክንያት ደም መስሏል።አራት የጣት አሻራዎች ተጋድመውበታል። በአጠቃላይ ከለቅሶውና ከጥፊው ጋር ፊቷ ተጉረብርቦ ስታየው የሷ መሆኑን ተጠራጠረች።
ያንን አዲስ መልኳን ከመስታወቱ ውስጥ ትክ ብላ ስትመለከተው ሌላዋ
ሸዋዬን እንጂ ራሷን የምትመለከት አልመስልሽ አላት፡፡ ያቺ በመስታወቱ
ውስጥ የምታያት ሽዋዬ መልኳ የተበላሸበትን ምክንያት ወደ ኋላ መለስ
ብላ ስታስበው ደግሞ ለዚህ ሁሉ መንስኤው ራሷ የፈጠረችው ችግር
መሆኑን ከመስታወቱ ውስጥ ነጥሮ የሚመለስው የራሷ ምስል የሚመ
ሰክርባት ሌላ ስው ሆኖ ታያት፡፡ ምስሉ ውስጠ ገመናዋን ፈትሾ ሴሰኛነቷን ያሳበቀባት መሰላት፡ ጌትነትን ሆን ብላ በማሳሳት የፈፀመችውን እያንዳንዷን ድርጊት፣ እያንዳንዷ እንቅስቃሴ በመስታወቱ ውስጥ በምትመለከታት ሸዋዬ ውስጥ ቁልጭ ብሎ ታያት፡፡ በትናንትናው ምሽት ከጌትነት ጋር የፈፀመችው ድርጊት ሁሉ ወለል ብሎ የታያት አሁን ገና ያቺን ፊቷ የነፈረቀው ሸዋዬን ስትመለከታት ነበር፡፡ ቶሎሳ ለቅሶ ቤት አድሮ በጠዋቱ ቤቱ ሲገባ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች ተበዳይነቷን ለማስረዳት የለፈለፈችው፣ከፍላጎቷ ውጭ ጌትነት ለወሲብ የፈለጋት መሆኑን ለመግለጽ የሞከረችው ፣ የባሏ ታማኝ ሚስት መሆኗን ለማሳወቅ እንደ አለብላቢት የሚያቃጥል ምላሷን ያሾለችው፣ እነዚያ ሁሉ ባዶ ቃላቶቿ ደጋግመው በጭንቅላቷ ውስጥ አስተጋቡባት። ግን አልተቆጨችም፡፡ አልተፀፀተችም፡፡ ራሷንም አልወቀሰችም፡፡ራሷን ያልወቀሰችው ደግሞ በጌትነት የማይረባ ድርጊት ምክንያት ነው፡፡ እሷ ልትሰርቀው ስትመኝ፣ቀምሳ ልታጣጥመው ስትቋምጥ ባልጠበቀችውና ባልገመተችው ሁኔታ ራቁቷን ገፍትሮ መሬት ላይ ጥሎ አዋረዳት፡፡ በድንጋጤ አሽማቆ ሰድቦ አባረራት፡፡ አቤት ስድቡ! ቆጠቆጣት፡፡ ባለጌ! የአእምሮ ጠባሳ ነው፡፡ ከሱ አጥንት የሚሰብር ስድብስ የቶሎሳ ጥፊ ይሻላል አለች። የቶሎሳ ጥፊ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይጠፋል። የጌትነት ስድብ ግን ሁል ጊዜም እንዳንገ
በገባት ይኖራል።

“እስኪ መሰራረቅ ምን ነውር አለበት? የሚጣፍጠው ሰርቀው የበሉት
አይዴል? ቶሎሳስ ቢሆን ምኑ ነው? ደርሶ ታማኝነት... ወገኛ! እርጥብ ባላገር! ቆዳ !የሰው ቆዳ! እስኪ ምን ነበረበት በዚያ ባለቀለት ሰዓት በወሲብ እሳት ነደን፣ እንደ ቅቤ ቀልጠን፣ ወይ አርፎ አልተቀመጠ
ጭኖቼን ደባብሶ፣ ስሜቴን ቆስቁሶ፣ በመወስወሻው ወስውሶ፣ ከንፈሮቼን በከንፈሮቹ ዋግምት እየመጠጠ መቃጠል ስንጀምር ኣሽቀንጥሮ፣
ወርውሮ በረዶውን የለቀቀብኝ? ምቀኛ! መልኩ እንጂ ምኑም አየለን የማ
ይመስል ነሆለል! እኔው ነኝ ወራዳዋ ጥንት ሞቶ አፈር የለበሰውን ጀግና
በዚህ በቁርበት ባላገር ውስጥ አገኘዋለሁ ብዬ መመኘቴ!" ቅጥል አለች።

ከእንግዲህ በኋላ ሆድና ጀርባ ሆነዋል፡፡ አይጥና ድመት….ከአሁን በኋላ እትዬ አትበለኝ ሸዋዬ እያልክ ጥራኝ ትለው የነበረው ለምን እንደሆነ ታውቋል። ከአሁን በኋላ እንደዚያ እሱ ጋ ስትደርስ የምታሳያቸው ለየት ያሉ ባህሪያት ስስ የውስጥ ልብስ እየለበሱ በመኝታ ቤቱ ውስጥ ብቅ ጥልቅ ማለት፣ዳሌን እያውረገረጉ አንጀት ለመብላት መሞከር፣
ጡትን ደጅ እያሳደሩ ብርድ ማስመታት፣ አስር ጊዜ ጎንበስ ቀና እያሉ
ጭንን ለማስቃኘት የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ ምክንያታቸው ታውቋል።ቶሎሳን ለሁለት ነው እንዴ ያገባችሁኝ?! ስትል አንባርቃበታለች። ከእንግዲህ በኋላ ጌትነትን ለማግኘት የነበራት ተስፋ ሙጥጥ ብሎ አልቋል።

ከእንግዲህ በኋላ አብሮ የመኖሩ ጉዳይ የማይታሰብ ነው። ደግሞ ማን ያውቃል ከቶሎሳ ጋር ተያይዘው ነው ከቤት የወጡት። በዚህ አጋጣሚ የትናንትናው ድርጊቷን ያጋልጥ ይሆናል። ለትናንትናው ጥፋት መንስኤው እሷ መሆኗን አስቀድሞ ነግሮት አሳምኖት ከሆነ ደግሞ ጉድ ሊፈላ ነው። ጩኽቷ ሁሉ የውሸት፣ ለቅሶዋ ሁሉ የአዞ እንባ እንደነበረ ከተነቃባት ከቶሎሳ ጋር የመጨረሻቸው መሆኑ ታያት። ስለዚህ ያ በሷ ንፁህነት፣ በሷ ተበዳይነት የተጀመረው ድራማ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና በሷ አሸናፊነት በድል እንዲደመደም ከተፈለገ ጌትነት በፍጥነት ከዚያች ቤት እንዲባረር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ሃሳቧን ለማሳካት ደግሞ ባሏን እንደ ጠዋቱ እየጮኽች እያጓራችበት ሳይሆን ጣፋጭነቷን እየመገበችው፣ ፍቅሯን እያስኮመኮመችው፣ እያባበለችው ልቡን በመስለብ የትናንትናውን የጌትነት ድፍረት ፍርጥ አድርጋ ልትነግረው ተዘጋጀች...

ለአንድ ቀን ቶሎሳ ውጭ ቢያድር ያቺን ቀዳዳ ተጠቅሞ ለወሲብ ያባበላት
መሆኑን እሷ ግን ለትዳሯ ታማኝ በመሆን ያሳፈረችው መሆኑን ልትነግረውና በፍጥነት ከዚያች ቤት እንዲያባርረው ለማድረግ ዕቅዷን አጠናቅቀች። እንዳይመሽ የለም መሽ፡፡ የቶሎሳ መግቢያ ሰዓቱ ደረሰ። እሷ ተጨነቀች፣ ተጠበበች እንጂ ጌትነት ቀድሟት ነበር። “የት አባቱ ይሄዳል? መግቢያ ቀዳዳው ያቺው የቶሎሳ ጎጆ ነች ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም” ነበር ግምቷ። እሷ እንደገመተችው ሳይሆን ዳግም ላይመለስ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተሰናብቶ የሄደ መሆኑን ብታውቅ ኖሮ ቶሎሳን እንደዚያ ተሽቆጥቁጣ መሬት ሆና አትጠብቀውም ነበር። በጥፊ ሲያላጋት ሰማይ ምድሩ ነበር የተደበላለቀባት፡፡ እንደዚያ በጥፊ ሲደረግምባት ዘመዱን አግዞ ለዘመዱ አድልቶ የደበደባት መስሏት ስትበሳጭ ስትብከነከን ነበር የዋለችው። ጌትነት እንደወጣ የሚቀር መሆኑን አስቀድማ አውቃው ቢሆን ኖሮ አራስ ነብር እንደሆነች ትጠብቀው ነበር እንጂ እንደዚያ ላስላሳ ድመት ሆና አትለማመጠውም ነበር። ያንን የጌትነትን ውሳኔ አላወቀችምና ዱላውን ረስታ ብስጭቷን እርግፍ አድርጋ ትታ በፈገግታ
እጆቿን ዘርግታ በፍቅር ስለፍቅር ተቀበለችው።

“ለምንድነው ደግሞ ለምሳ ያልመጣኸው?” አንገቱን እቅፍ አድርጋ ከፊል ሳቅ ከፊል ንዴት ያለበት በሚመስል ሰው ሰራሽ የማስመሰል ችሎታዋ
ፊቷን ልውጥውጥ አድርጋ ጠየቀችው።

“ምን አባቴ ላድርግ ሸዋዬ? በጠዋቱ የቁርሴን ፋንታ አራስ ነብር ሆነሽ
በነገር አጣድፈሽ ከቤት ስታስወጪኝ የተረፈውን ደግሞ በምሳዬ ላይ ጨምረሽ እንዳታባርሪኝ ፈርቼ ነዋ!” አላት በመገረም የሚስቱን ዐይን ዐይኖቿን እያየ :
“ርቦሃል አይደል? ጠዋት ጦምህን እንደወጣህ ነህ አይደል? ! በል አረፍ በልና መክሰስህን ብላ”እጁን እየጎተተች ወደ ጓዳ አስገባችው። ዛሬ ለቶሎሳ አልጋው የመመገቢያ ጠረጴዛ ሆነለት።
“ተመስጌን አምላኬ ላንተ ምን ይሳንሃል? ጠዋት እንደዚያ አራስ ነብር ሆና ከቤት ያባረረችኝ ሴትዮ ማታ ላይ ደግሞ እንደ
👍3