#አቀበት
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በገበየሁ_አየለ
አካሌ ቀድሞ ከነበሩበት ፈረንሳይ ለጋስዮን፣ አሁን ወዳሉበት ቶሎሣ ሰፈር ከተዛወሩ አንድ ዓመት ቢሆናቸውም፣ ከአካባቢውም ሆነ ከቅርብ ጎረቤቶቻቸው
ጋር መላመዱ አልሆነላቸውም፡፡ ዓይናፋርና ሽቁጥቁጥ ናቸው፣ ቶሎ ሰው የማይቀርቡ፡፡ የቀድሞ መኖሪያቸውን
የቀየሩት፣ ቀዳሚና ተከታይ ያልነበራት ልጃቸው ሸዋዬ ስትሞትባቸው ነው። ባላቸው በአፍላ ዕድሜ በድንገተኛ
ህመም ስለሞቱባቸው እናትም አባትም ሆነው ነበር ሸዋዬን ያሳደጓት በኋላም የዳሯት፡፡
ሸዋዬና መምህሩ ባሏ ተካ ትዳራቸውን ለማደላደል ሌተ ቀን ይጥሩ ጀመር፡፡ በተጋቡ በዓመቱ ሴት ልጅ ወለዱ። በሸዋዬ መውለድ እጅግ የተደሰቱት፣ ከባልና ሚስቱ ይልቅ አካሌ ናቸው:: ሕጻኗን ከእቅፋቸው አላወጣት አሉ: በኋላም ውሎና አዳራቸው በአብዛኛው
እዚያው ሆነ፡፡ የዚህ ምክንያቱ፡፡ በፊት በፊት የህጻኗ ፍቅር ቢሆንም፣ በኋላ ግን የሸዋዩ ሕመም ነበር።ከዛሬ ነገ ይሻላታል ቢባል፣ ከሆስፒታል ሆስፒታል ቢያንከራትቷት፣ የሚፈውሳት መድኃኒት ታጣ፡፡ የኋላ ኋላ ሀኪሞቹ በሽታዋ የማይድን መሆኑን ገልጠው"ሸዋዬ ሕጻኗን ጡት እንዳታጠባት" በማለት አስጠነቀቁ።
በዚህ ሁኔታ የሸዋዬ በሽታ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ ሄደና በዓመት ከመንፈቋ ሞተች፡፡ እሷ ባሞተች በሳልስቱ ባሏ ተካ የሚሄድበትን ሳይናገር ተሰወረ::በሽዋዬ ሞት ቅስማቸው የተሰበረው አካሌ ክፉኛ
ደነገጠ:: በከባዱ ሀዘናቸው ላይ እናትና አባት የሌላትን ሕጻን የማሳደጉ ኃላፊነት ተጨመረ፡፡ዙሪያው ገደል ሆነባቸው:: "ይሁን፣ ተመስገን፣ ሸዋዬ ምትኳን ትታልኝ
ነው የሞተችው:: ህጻኗ በዕድሏ ታድጋለች" እንዳይሉ፣
"ሸዋዬን የገደላት ክፉ ደዌ ወደ ልጅዋም ይተላለፋል" ማለትን ስለሰሙ ተስፋቸው ይበልጥ ጨለመ።
ያኔ ነው የአሁኗ ቡና አጣጭ ጎደኛቸው ወይዘሮ ብርቄ ህፃኗን እናስመርምራት
እንደሚባለው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል እኮ ያሏቸው:: እንዳሉት አደረጉ፣
ህጻኗ ከደዌው ነጻ ነች ተባለ፡፡ ይህ ለአካሌ ታላቅ የምስራች ነበር፡፡ "ተመስገን አምላኬ የዓይን ማረፊያ አልነሳኸኝም፣ የሀዘኔን ማስረሻ ሰጥተኸኛል" አሉ፡፡
ህጻኗንም ማስረሻ ብለው ጠሯት፡፡
የአካሌ ጓደኛ ወይዘሮ ብርቄ ትንሽ ዘግየት ብለው ደግሞ ሌላ ምክር አመጡ፡፡ "ሸዋዬ እሞተችበት ሆስፒታል እንሂድና የሞቷን ምክንያት የሚገልጥ ወረቀት ስጡን እንበላቸው:: የሞተችበት በሽታ እርዳታ የሚያስገኝ ሆኗል።ወረቀቱ ከተገኘ ህጻኗን ይዘው ወደ እርዳታ ለጋሾቹ በመቅረብ 'ወላጆቿን አጥታለች::ደካማ አሮጊት ነኝ፣ እልሰው እቀምሰው የሌለኝ ይበሉ፡፡በደንብ ይረዱዎታል :: ማንም አይደለም እንዴ የሚረዳው? ዛሬ በአዲሱ በሽታ ዘመድ የሚሞትበት ድሀ እርዳታ ይገኛል! ነባሮቹ በሽታዎቻችን እንዲህ ከእርዳታ ጋር ቢመጡ ኖሮ ደግ ነበር፣ 'የቸገረው ዱቄት ከንፋስ ይዛመዳል ማለትኮ ውነትነት አለው' አሉ
ዓይኖቻቸውን እያሻሹ::
አካሌ በብርቄ ምክርና አይዞሽ ባይነት እየተበረታቱ በየቢሮው ብዙ ከተንከራተቱ በኋላ ተሳካላቸውና በኤድስ
ህመም ወላጆቿን ያጣች ህጻን አሳዳጊ በመባል ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች እርዳታ ያገኙ ጀመር፡፡የማስረሻን አባት፣ የተካን መሰወር አስመልከተው ሰዎች ብዙ መላምት አወሩ፣ "ሚስቱን የገደላት በሽታ
እሱንም የያዘው መሆኑን ስላወቀ እራሱን ገድሏል፣ገዳም ገብቶ ነው፣ እማይታወቅበት ስፍራ ሄዶ ኑሮውን
እዚያው መስርቷል. .አሉ፡፡
እንዲህ ያለ ብዙ ነገር ከተወራበትና ከተረሳ ከ 6 ወር በኋላ ተካ አንድ ቀን ብቅ አለ።
የቅርብ ጎረቤቶቹ በመገረምም፣ በሀዘኔታም፣ "እንኳን ደህና መጣህ" እያሉ ሲቀባበሉት፣ አካሌ ግን "ዓይኑን
አላየውም" አሉ ክፉኛ ተቀይመውት፡፡ ከዚያም ይልቅ ከተረሳና እንደሞተ ከተቆጠረ በኋላ መምጣቱ ለመልካም
አለመሆኑ ተሰማቸው:: "ያሰበው ደባ ቢኖር ነው" ብለው
ክፉኛ ሰጉ፡፡ በመሆኑም አማላጆች ቢለምኗቸው፣ ቢማጠኗቸው "ከኔ ጋር አይኖራትም!" አሉ።
በአማላጅነት አልሆንልህ ያለው ተካ፣ አካሌን የቀበሌ ሹሞች ዘንድ ከሰሳቸው:: ሹሞቹ የሁለቱንም ክርክር ካዳመጡ በኋላ፣ "ጠፍቶ ቢከርምም፣ የቤቱ
ተከራይ እሱ ነው፣ አብሮኝ አይኖርም፣ አጠገቤ አይድረስ ካሉ የቤቱ መሀል በር ታሽጎ ሁለት ላይ ይከፈልና
በተለያየ በርና አቅጣጫ እየተገለገላችሁ ለየብቻ መኖር አለባችሁ" በማለት ወሰኑ፡፡
በዚሁ መሠረት በግድግዳ የተለያዩ ደባሎች ሆነው አንድ ሳምንት ያህል እንደቆዩ፣ ተካ እንደገና አካሌን
ከሰሰና ሹሞቹ ዘንድ አቀረባቸው::
አንድ ቀን አመሻሹ ላይ አካሌ እንደ ሁልጊዜያቸው ቡና አፈሉና ብርቄን ጠሯቸው።ሥጋትና ፍርሃታቸውን ሊያወያዩዋቸው አስበዋል፡፡
"ይሄን ሰውዬ ፈራሁት" አሉ አካሌ የቀዱትን አቦል ቡና ለብርቄ እየሰጧቸው፡፡
የቀይ ዳማ ፊታቸው እንደለበሱት የሀዘን ልብስ ጠቁሯል።
"ተካን ማለትዎ ነው?" አሉ ብርቄ ትንንሽ
ዓይኖቻቸውን አፍጠው።
«አዎን» በረጅሙ ተነፈሱ አካሌ፡፡
ከእንግዲህ የሚያገናኛችሁ በር ታሽጓል» አሉ ሽበታቸውን በእንዝርታቸው ጫፍ እያከኩ።
"ያ ከምን ያግደዋል ብርቄ ? ይህችን ልጅ
ለመውሰድ ሲል እሽጉን በር ሰብሮ በመግባት ቢገድለኝስ? ምኑ ይታመናል? የት ከርሞ እንደመጣ፣ ወዴትስ እንደሚሄድ ማን ያውቃል?"
"ዛሬ ከተካ ጋር አካባቢው ሹሞች ዘንድ
የቀረባችሁት ለምን ነበር?" አሉ ብርቄ
"ከሶኝ ነዋ ልጄን ትስጠኝ ብሎ::"
"ማስረሻን?"
አካሌ በአዎንታ እራሳቸውን ነቀነቁና በማቃሰት ተነፈሱ፡፡
"ማስረሻ ልውሰዳት ማለቱ እንዴት ሊያሳድጋት ነው? ምን ሊያበላት? ለራሱ ይቀምሰው ይልሰው የለው:: አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል' አሉ፡፡"
"ምን አውቄለት፡፡" አሉ አካሌ ማስረሻ ወደተኛችበት ቦታ አልጋ አንጋጠው እየተመለከቱ፡፡
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

👍4
#አቀበት
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#በገበየሁ_አየለ
"ምን አሉት ታዲያ ሹሞቹ?"
"ትሰጭዋለሽ ወይ ብለው ጠየቁኝ፡፡
አላደርገውም ብዬ ክፉኛ ስከራከራቸው ጊዜ ፍርድ ቤት ሂድና ክሰሳት፣ ይህን የመሰለውን ጉዳይ መበየን የኛ ስልጣን አይደለም" አለት።
"እሰይ፡ ይሂድና ይክሰስዎት፣ ያኔ ደግሞ አንድዬ ያውቅሉሃል::"
"ኧረ እሱ እስከዚያውም የሚታገስ አይመስል ክፉኛ ነው የፎከረብኝ::"
ብርቄ ፡ "ልጅቱን አላሳይ ስላሉት ነው ልውሰዳት ማለቱ።ምናለበት ብቅ እያለ እንዲያያት ቢፈቅዱለት?"ለማለት አሰቡና ተውት።አካሌ በግልጽ አይናገሩት
እንጂ ተካ ከማስረሻ ጋር እንዳይቀራረብ አጥብቀው የሚከላከሉት ከሷ ይለየኛል ብለው ብቻ ሳይሆን እሱ ከወሰዳት በሷ ምክንያት የማገኘው እርዳታ ይቀርብኛል
በሚል ሥጋት ጭምር መሆኑን ተረድተዋል፡፡
ሁለቱም የየራሳቸውን አሳብ ሲያሰላስሉ ሳለ ብርቄ ጉሮሯቸውን ሞረዱና "የሰፈሩ ሰዎች ናቸው ተካን ክፉ የሚመክሩት፡፡ መከራ ሰውን ዓመለኛ ያደርገዋል እንጂ
ተካ ደግ ሰው ነበር" አሉ።
"መክረውት ይሆናል ብዬ እኔም እጠራጠራለሁ::ቢያደርጉትም አያፈረድባቸውም፡ አብሯቸው የኖረ እሱ፡
እኔን የት ያውቁኛል፡፡" አለ አካሌ ማስረሻን ከአልጋ ላይ አንስተው እያቀፏት::
መከራም ያልፋል::" አሉ የማስረሻን ፀጉር እያሻሹ::
"ሰው ቢመክርና ቢመቀኝ ምን ሊያመጣ የማታ እንጀራ ያልነፈገዎ ፈጣሪ ያውቅሉሀል::" አሉ ብርቄ
ትንሽ አሰብ አደረጉና ደግሞ እኔም አለሁ
በደከሙ ዓይኖቼ እየተጨናበስኩና እየፈተልኩ ልቃቂት ሽጨ አዳሪዋ፣ ፈጣሪ ቢያድለኝና ሁለቱ ልጆቼ በሕይወት
ቢኖሩልኝ ኑሮ ያሳርፉኝ ነበር::"
“ሁለት ብቻ ነበር የወለዱት? "
"አዎን ሁለት ብቻ ነበሩ፡: ደረሱልኝ ሊያሳርፉኝ ነው እያልኩ ዓይን ዓይናቸውን በጉጉት ስመለከት ሳለሁ ድንገት ብድግ ብለው ለናት አገራችን ካልሞትን አሉ፡፡
ተው ልጆቼ እኔን ለማን ጥላችሁ ነው የምትሞቱ፡ከመኖራችሁ እንጂ ከሞታችሁ ምን እጠቀማለሁ የምትገዳደሉትኮ ያንድ እናት ልጆች ናችሁ::' ብላቸው
አልሰማሽ አሉ:: ፀባቸውን ከቤት ጀመሩት:: ከመገዳደል ሌላ የፀብ ማብረጃ መንገድ አልታይ አላቸው:: አንደኛው የመንግሥት ሆነ ሌላው ከመንግሥት ጋር ከሚጣላው
ወገን ነበረ፡፡ እየተዛዛቱና እየተጣደፉ ወደሞታቸው ሮጡ:: እንዳሉትም ተገዳደሉና እኔን የወላድ መካን
አደረጉኝ:: ማን የት እንደወደቀ እንኳን የሚነግረኝ አላገኘሁም::" ብለው እንባቸውን በነጠላቸው ጫፍ እየጠራረጉ "ፎቶግራፋቸውን አቅፌ ቀረሁ” አሉ፡፡ አካሌም እንባ ያጤዙ አይኖቻቸውን ጠራረጉና፣" አይዘኑ፣ እስከዛሬ ያኖረዎ እግዚአብሄር ያውቅልዎታል፡ ሀዘንም ይረሳል፡መከራም ያልፋል::" አሉ የማስረሻን ፀጉር እያሻሹ::
በዚህ ሁኔታ ሲወያዩ ካመሹ በኋላ ብርቄ ወደ ቤታቸው ለመሄድ በላስቲክ ከረጢት የያዙትን ጥጥ እንዝርት ያስተካክሉ ጀመር፡፡
"እንግዲህ ያድምጡኝ ተካ ዛሬ ክፉኛ ነው
የዛተብኝ:: ከተተናኮለኝ መጮሄ አይቀርም::" አሉ ኣካሌ ጓደኛቸውን ለመሸኘት ብድግ እያሉ፡፡ "አይዝዎት፣
እንኳን ከዛቻ ከተወረወረም የሚያድን አምላክ ይጠብቅዎታል" አሉ ብርቄ ዓይኖቻቸውን ወደጣራው
አቅንተው።
አካሌ ብርቄን ከሸኙአቸው በኋላ ማስረሻን በነጠላቸው ጥብቅ አድርገው አዘሏትና የምሽት ተግባራቸውን ለማጠናቀቅ ጉድ ጉድ ይሉ ጀመር፡፡ ተካ
ከመጣ ወዲህ ሲንቀሳቀሱም ሆነ ሲቀመጡ ማስረሻ እንዳትለያቸው ወስነዋል፣ አካሏ ከአካላቸው ትንፋሽዋ
ከትንፋሻቸው እንዳይርቅ::በራቸውን ከወትሮው ይልቅ ጠበቅብቅ አድርገው
ዘጉት:: ተካ ያመጣብኛል ብለው የፈሩት ችግር ከደቂቃ ደቀቃ ከሰዓት ወደ ሰዓት ያሳስባቸው ጀመር፡፡
"የሚያደርገውን ያድርግ እንግዲህ ምነው ኣካለወርቅ የሚሆነው ከመሆኑ በፊት በፍርሃት አልሞትም::" አሉ
ለራሳቸው::
እንዲህ እራሳቸውን ለማጎበዝ ይሞክሩ እንጂ ምሽቱ፡እየገፋ በሄደ ቁጥር ብርታታቸው መናዱ ኣልቀረም።
ማስረሻን አልጋቸው ላይ እስተኙዋትና፣ ቆም ብለው ወደ ተካ ክፍል ያስገባ የነበረውን እሽግ በር በጥርጣሬ
ተመለከቱት፣ የተካ ኣቋራጭ ማጥቂያ በዚያ እንደሚሆን እርግጠኛ ናቸው።
አሮጌ መጥረብያቸውን ከስርቻ ፈልገው ያዙና በእድሜ የላላ የእጅ ጡንቻቸውን ፈርጠም አድርገው ለጥቂት ጊዜ ወደ እሽጉ በር ካፈጠጠ በኋላ። እራስጌያቸው አስቀመጡት::
እንዲህ በማድረግ ላይ ሳሉ ነው ድንገት ተካ ክፍል ውስጥ የእርምጃና የእንቅስቃሴ ድምጽ የሰሙት::ወዲያውኑ የልባቸው አመታት ስለፈጠነባቸው
ደረታቸውን በሁለት እጆቻቸው ያዙና "እንዴ!" አሉ በሹክሽኩታ:: ተካ ከወትሮው ቀደም ብሎ መምጣቱ
ይበልጥ አስደነገጣቸው በፀጥታ አዳመጠ:: እያገሣ ያንጎራጉር ጀመር፡፡ ሞቅ ብሎት ሲመጣ የሚያደርገው
ልምድ ነው:: አካሌ ከአስፈሪ አውሬ ጋር የተፋጠጡ ይመስል እቆሙበት ተተክለው ቀሩ፡፡
"ዝግጅቱን በጊዜ ለመጀመር ነው ቀደም ብሎ የመጣው" አሉ በአሳባቸው:: የተካ እንጉርጉሮ ብዙም አልቆየ ሰው የሌለበት እስኪመስል ድረስ ክፍሉን ፀጥታ ዋጠው
አካሌ ለአስር ደቂቃ ያህል በዝምታ ካዳመጡ በኋላ፡ ቀስ ብለው አልጋቸው ጠርዝ ላይ ቁጭ አሉ።
እንደገና ለአምስት ደቂቃ ያህል አዳመጡ ከማስረሻ የእንቅልፍ ልብ አተነፋፈስና ከራሳቸው ልብ ምት ሌላ የሚሰማ ነገር የለም አይኖቻቸውን እሽጉ በር ላይ እንደተከሉ እራስጊያቸው ያለውን መጥረቢያ በዳበሳ አነሱና ጠበቅ አድርገው ያዙት:: እንደገና ጥቂት
ካዳመጡ በኋላ፣ "መተኛቴን ነው የሚያዳምጠው"አሉና ጉሮሯቸውን በመሞረድ ያለማንቀላፋታቸውን
የሚያመለክት ድምጽ አሰሙ:: ቀጥለው ደግሞ በያዙት መጥረቢያ ዛቢያ ወለላቸውን መታ መታ አደረጉት።.....

🔥1
#አቀበት
፡
፡
#ክፍል_ሦስት (የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
#በገበየሁ_አየለ
..የሚሰማ ነገር የለም፡፡ ዓይኖቻቸውን እሽጉ በር ላይ እንደተከሉ እራስጌያቸው ያለውን መጥረቢያ በዳበሳ አነሱና ጠበቅ አድርገው ያዙት:: እንደገና ጥቂት
ካዳመጡ በኋላ፣ "መተኛቴን ነው የሚያዳምጠው" አሉና ጉሮሯቸውን በመሞረድ ያለማንቀላፋታቸውን
የሚያመለክት ድምጽ አሰሙ።ቀጥለው ደግሞ በያዙት መጥረቢያ ዛቢያ ወለላቸውን መታ መታ አደረጉት።
"አልተኙም እንዴ አካሌ!" አለ ተካ ከሳቅ ጋር በተቀላቀለ አነጋገር፡፡ የመጠጡ ኃይል ምላሱን ትንሽ ያዝ ያድርገው እንጂ. ወፍራም ድምፁ ስልቱን
አልሳተም::
"አይዞት አይፍሩ እኔ ጠብቅዎታለሁ" ብሎ እንደገና ሳቀ::
"ከግንድ ያጣብቅህ" ለማለት አሰቡና ተውት፡፡
"አገር ቤት ነው የከረምኩት" አለ በረጅሙ
ተንፍሶ። የነገሩ አቅጣጫ ድንገት
በመለወጠ ቢገርማቸውም፡ መልስ አልሰጡትም::
"እማዬ እንደምንዎት ደህና ከረሙ ወይ በዓይነ ስጋ ለመገናኘት ያብቃን ብላዎታለች::"
"ደህና ናቸው? " አሉ እካሌ ድምጻቸውን ከፍ እድርገው።
"ደህና ነኝ” ትላለች የገጠር በተለያ የሷ አካባቢ ሰው ደህና አይደለሁም ማለቱን አያውቅበትም። ቃሬዛ ላይ እስኪጫን ድረስ ደህና ነኝ ነው የሚል፡፡ የትውልድ
ቀዬዬ ሰዎች ደህንነትን የሚለኩት ቆመው ከመሄዳቸው አንፃር ነው።
"እህህም" አሉ አካሌ "በ-ጄ ቀጥል » በማለት አኳኋን፡፡የተካ ጉዳይ ከማስረሻ ጉዳይ ወደሌላ በመቀየሩና አነጋገሩም የወዳጅነት በመምሰሉ ፍርሃታቸው ረገብ አለ።
"ታናሽ እህቴ በምጥ ሞተች፡ ሰባተኛ ልጅዋን ስትገላገል፡፡ እኔ እዛው ሆኜ ነው የሞተችው:: አጎቴን ወባ ገላገለው:: እማዬ የአጎቴን ሞት ስታረዳኝ `አረፈ
አለችኝ፡፡ አረፈ ለአካባቢው አገላለጥ ትክክለኛ ቋንቋ ነው:: በችጋርና በበሽታ እየተገረፈ ለሚኖር ሕዝብ፡ ሞት እረፍት ነው: ግልግል:: አይደለም እንዴ አካሌ?"
አለ ድምጹን ከቀድሞው ጎላ አድርጎ።
“እህህም" ብለው ዝም አሉ:: የተካ ንግግር ቀስ በቀስ ወደ አንጀታቸው የሚገባ ቀዝቃዛ ስሜት አሳደረባቸው።
« ሰውን አረገፈው' ትላለች እማዬ ፡ ሞት
በአካባቢው ያለውን ብርታት ስትገልጥ፡፡ እገሌንና እገሌን ተስቦ ወሰዳቸው እገሌ በደም ተቅማጥ አረፈ፣ እገሌን ወራጅ ውሃ ወሰደው፣ ያን የመሰለ ጉብል ፣ 'እናቱ በሀዘን አብዳ መቃብር ቤት ነው እምታድር .. ከብቱ ሣር አጥቶ አለት እየጋጠ በየሜዳው ተፈነቸረ' "ትላለች።
"አቤት አቤት፣ ይሄ ከላይ የመጣ መዓት ነው" አሉ አካሌ ማቃሰት በሚመስል ድምጽ፡፡
"እማዬም እንዲሁ ነው የምትል:: የአገሩ ሰው በየቤተክርስቲያኑና መስጊዱ እየተሰበሰበ "እግዚኦ ከዚህ
መዓት ሰውረን" እያለ አምላኩን በመማጠን ላይ ነው::"ብሎ ካዛጋ በኋላ እንደመሳል አለና፣
"የእማዬ አገር ሰዎች አሟሟትን ያውቁበታል፡አንቀላፉ እንዴ አካሌ?» አለ።
"ኧረ ሰማሀለሁ አሉ ሀዘን በተጫነው ድምጽ፡”
በቁሙ ነው ሞትን የሚጀምረውም የሚጨርሰውም።
"እንዴት? "
'ከችጋር ጋር ስለሚኖር ረሀብ ገደለኝ አይልም፡፡ጠኔ ሲያንገላታው መገጣጠሚያ አንጓዎቹ ሲላሉ፡ በሌላ
በሽታ አመካኝቶ ጣጣቴ እየተተኮሰ፡ ሳንባው ከጀርባው ተጣብቆ መተንፈስ ሲያቅተው ፡ በዋግምት እየተነጠቀ. እንዲያ እንዲያ እያለ ይሞተዋል።
ይሰሙኛል?»
"አዎን እሰማሀለሁ"
"ሽዋዬ እንደሞተች እናቴ ዘንድ ሄድኩ፣ ሞትን እዚያ ሆኜ ልጠብቀው ብዬ:: ለካ ሞት ወደነገሰበት ሥፍራ ኖሯል የሄድኩት:: ፊት ለፊት የተገናኘሁት
እስኪመስለኝ ድረስ በሥራው አየሁት፡፡ በችጋርና በደዌ ፈረስ እየጋለበ ሕዝቡንና ከብቱን ፈጅቶታል፣ አገሩን ወና አድርጎታል፡፡"
"ሞትን ተሸክሜ እንደሄድኩባት ያልጠረጠረችው እናቴ ምን አለች መሰለዎት" ብሎ እንደማሰብ አለና፣
ለወራት ከተኛችበት መደብ ላይ ቀና ብላ፣ የፈዘዙ ዓይኖቿን እያንከራተተች፣ ማመን አቅቷት እንደ እንሰት በደረቁ እጆቿ እራሴንና ፊቴን እየደባበሰች፣ ቀባሪ
ያላሳጣኸኝ ፈጣሪ ተመስገን፡፡ በመሞቻዬ ዋዜማ የልጄን ዓይን አሳየኸኝ' አለች፡፡ ድምጽ አጣች እንጂ እልል ለማለትም ሞክራለች፡፡ በደረቁ ከንፈሮቿ ፊቴን፣ እራሴን የአንገቴ ሥር ሁሉ ሳመችኝ ከመኪና ተራ የገዛሁትን ደረቅ ዳቦ በውኃ እየነከርኩ ሳጎርሳት በስስት ቶሎ ቶሎ
በላችና፣ 'ተመስገን አምላኬ፣ እንደኔ ማንን አድለሃል በቃ አሁን ጠግቤአለሁ የሞት ስንቄን አግኝቻለሁ፣ቀባሪዪም መጥቷል፤
ቶሎ ውሰደኝ አለች::"
"እኔን እኔን እንዴት ተጎድተው ኖሯል? " አሉ አካሌ ከልብ በሆነ ሀዘኔታ፡፡
"ፀሎቷ አልተመለሰላትም፤ እስከዛሬ አለች::"ብሎ ትንሽ ዝም አለና ለጉድ የጎለተኝ' ትላለች እማዬ ስለራሷ በምትናገርበት ጊዜ፡፡ «የመከራ ምስክር አድርጎኛል ጎተራዬ ሙሉ፣ በረቴ በከብት ትንፋሽ የሞቀ፣ ቤቴ የርሃብተኞች መሸሻ እንዳልነበረ ሁሉ የችጋርና የሞት ምሳሌ ሆኛለሁ" ትላለች፡፡ «እየሰሙኝ ነው አካሌ?»
«አዎን፣ ሰማሃለሁ::»
"እንዲህ ሆኖ አገኘሁት፣ የእማዬንና የአካባቢዋን ሁኔታ:: እኔማ በድብቅ የምሞትበትን ሥፍራ መርጨ
ነበር ወደዚያ መሄዴ፡፡ ሀገሩ ግን የሚሸሹት እንጂ የሚሸሽበት አልሆነም፡፡ እኔ ውስጥ ካለው ሞት ይልቅ፣እዚያ ያለው ገዝፎ ታየኝ፡፡ የሞት መላእክት ትዕዛዝ ለመፈጸም በየተራራው አናት ላይ በተጠንቀቅ ቆመው ቁልቁል የሚመለከቱ እስኪመስል ድረስ ነው፣ አካባቢው
የሚያስጨንቀው:: ለዚህ ነው ሸሽቼ እንደሄድኩ የመጣሁት:: ሕይወት ካለ ተስፋም መኖሩ ተሰማኝ፡፡አንድ ቀንም ዕድሜ ነው አልኩ፡፡ ነገ የተሻለ ነገር ይዞ
አይመጣም ያለው ማነው? ብዬ አሰብኩ፡፡ የሞትን ሹክሹክታ ከማዳመጥ ይልቅ፣ ተስፋን ማዛጋት ጥሩ ሆኖ ታየኝ፡፡ ተስፋ ሲሞት ነው እውነተኛው ሞት::
አይደለም እንዴ አካሌ?››
"ነው እንጂ! እኔ እምልህ ተካ'
"እመት"
“እውን መንፈቁን በሙሉ እናትህ ዘንድ ነበርክ?"
"አዎን"
እንዴት ብትጨክን ነው ብቅ ብለህ እንኳን ሳታየን መክረምህ?
"ጨክኜ አይደለም አካሌ፣ እንደሞትኩ ቆጥራችሁ እንድትረሱኝ ፈልጌ ነበር፡፡ በተለይ ሚጣዬ እናቷን እንዳጣች ሁሉ እኔንም እንደሌለሁ ብትቆጥረኝ ይሻላል
ብዬ አሰብኩ፡፡ እናቷን ስታጣ ተሳቀቀች፣ እኔ ስለያት ደግሞ ለምን ትደንግጥ? በተለይ ይበልጥ ከተላመደችኝና
የአባትነቴ ትርጉሙ ከገባት በኋላ ስታጣኝ፣ ሀዘኗ መሪር ይሆናል በማለት ነበር
"ቀድሞ ሟቹን እግዜአብሄር ነው የሚያውቀው:: ደግሞም ቅድም እንዳልከው ደግ ደጉን ማሰብ ይሻላል"
አሉ አካሌ፡፡
"ደግ ደጉን በማሰቤ ነው መንገዴን የቀየርኩ"
"ይሻላል ደጉን ማሰብ፣ ደጉን ማድረግ. .
"ደጉን መኖር" አለ ተካ ፈጠን ብሎ ጥቂት ዝም አለና ደግሞ፣
"ታዲያ እርስዎ ስለኔ ለምን ደግ አያስቡም? " አለ
ዝም አሉት አካሌ፡፡
"አካሌ"
"ወይ"
"ስለኔ ደግ አያስቡም? "
"ስለራሱ ደግ ለማያሰብ ሰው እንደምን ደግ ይታሰብለታል?
እንዲህ ሲወያዩ እኩለ ሌሊት አለፈ:: አካሌ ሀሳባቸውን ወደ ክፍላቸው ሰብሰብ አድርገው ሲመለከቱ፣
ጨብጠውት የነበረ መጥረቢያ ከእጃቸው ተንሸራትቶ መሬት ወድቋል፡፡ ወደ ማስረሻ ተመለከቱ፣ ከእንቅልፉ ከነቃች የቆየች ትመስላለች፡፡ ዓይኖቿን በሰፊው ከፍታ
ታያቸዋለች:: አልጋው ላይ ወጡና ዘና ብለው በመተኛት አቀፏት::
"ስለ ራሴም ሆነ፣ ለእርስዎና ለማስረሻ መልካም ማሰቤን በተግባር አሳይዎታለሁ አካሌ" አለ ተካ ሲያሰላስል ቆይቶ:፡ ኣካሌ ዝም ብለው የማስረሻን ፊት አንሶላውን እስከደረቷ ዝቅ አደረገችው::
"አይግፉኝ አካሌ" አለ ተካ ድምጸን ለዘብ አድርጎ
ውይይታቸውን ማስረሻ እንድትሰማው ስላልፈለጉ ዝም አሉት
አይግፉኝ፣ ዕድል

👍3