▶️ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን #ደቀመዛሙርቶቹ ተሰብስበው #ስለጸሎት እንዲያስተምራቸው በጠየቁት ጊዜ እንግዲህ እናንተ እንዲህ #ጸልዩ፦ <<በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ፥ #ስምህ #ይቀደስ፤ #መንግሥትህ #ትምጣ፤ ፈቃድህ #በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ #በምድር ትሁን፤ የዕለት #እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን #ይቅር እንደምንል በደላችንን #ይቅር በለን፤ ከክፉም #አድነን እንጂ ወደ #ፈተና አታግባን፤ #መንግሥት ያንተ ናትና #ኃይልም #ክብርም #ለዘለዓለሙ፤ አሜን።>> በሉ በማለት አስተምሯል። [ማቴ 6፤ 9-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]።
▶️ ከዚህ ጌታ #ኢየሱስ ከሰጠው #የጸሎት #መመሪያ ላይ በመቀጠል #አድራሻው ወደ #ማርያም የሆነ፦ <<እመቤታችን ቅድስት #ድንግል #ማርያም ሆይ በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ....>> ምናምን የሚለው #ጸሎት ቢኖሮ ኖሮ ወይም መኖር ቢኖርበት ኖሮ ደቀመዛሙርቱ #ጸሎት #አስተምረን ባሉት ጊዜ ባገኘው ምርጥ #አጋጣሚ ወደ #ማርያም #መጸለይ #ትክክል ወይም #ተገቢ መሆኑን ባሳየ ነበር። #ዝንጋኤ የሌለበት በማስተዋልም #ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ <<መንግስት ያንተ ነውና ኃይልና ክብርም ለዘላለሙ አሜን>> ብሎ #የመዝጊያ #ቃል አስቀምጦ ባልደመደመውም ነበር።
▶️ መምህራችንና #ሊቃችን አንድ እርሱም #ክርስቶስ የሆነው #ጌታ [ማቴ 23፤ 8-11] ያላስተማረውን #ትምህርት ከእርሱ ይልቅ #ሊቅ ለመሆን #በመሞከርና #በመጨመር ሌላ ድርሰት ማምጣት #ከንቱ #ድካምና #ፍሬ #ቢስ ከመሆኑም በላይ የሚያመጣው #ፋይዳ (ጥቅም) አይኖርምና <<እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን #በቃሉ አንዳች #አትጨምር።>> [ምሳ 30፥6]።
▶️ በመሰረቱ <<አባታችን ሆይ>> በሚለው #የማህበር #ጸሎት ላይ <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን ብቻ ሳይሆን <<ሊቃውንቶች>> የጨማመሩት #ሠላም #ለኪን፣ #ውዳሴ #ማርያምን፣ #አንቀጸ #ብርሃንን፣ #ይወድስዋ #መላዕክትን፣ #መልክዓ #ማርያምን....ወ.ዘ.ተ ደራርበውበታል።
▶️ የካቶሊክ #ቤተክርስቲያንና ሌሎች #እህትማማች ተብለው የሚጠሩት #አብያተ #ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ካለው የ<<እመቤታችን.... ሆይ>> ጸሎት #የቃላትና #የይዘት #ልዩነት አለው። የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትለው፦ <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል ነሽ የአሸናፊ የልዑል እግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ይገባሻል እንዲሁም ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታውን ለምኝልን ኃጢታትችንን ያስተሰርይልን ዘንድ አሜን[1]።>> የሚል ሲሆን #የካቶሊክና፣ #የእህትማማች #አብያተ ክርስቲያናት (የግሪክ፣ የህንድ፣ የአርመን የግብጽ. . .ኦርቶዶክስ) ደግሞ <<ድንግል ወላዲት ሆይ! ማርያም ሆይ፣ ጸጋ የሞላሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው፤ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የነፍሳችንን አዳኝ ተሸክመሻልና ደስ ይበልሽ[2]>> #ብቻ ነው የሚለው። ይህ ግን #መጽሀፍ ቅዱስ የማይቀበለውና #መጽሀፍ ቅዱሳዊ #ማስረጃ የሌለው ከንቱ #ፈጠራ ነው።
✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ ጌታቸው አየነው (መምህር)፤ "የዘውትር ጸሎት በአማርኛ"፥ ገጽ 5 ፥አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።
[2] 📚፤ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጽ/ጠ/ጽ/ቤት ሐዋርያዊ ስራ መምሪያ ፤ "ሕያው እግዚአብሔር" ፤አማርኛ ትርጉም ገጽ 316፤ በገላውዲዎስ ተቋም በአባ ጳውሎስ ጻድዋ ካርዲናል ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እንዲታተም የተፈቀደ፤ ማስተር ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።

▶️ በቅዱስ ገብርኤል #ሰላምታ #ሰላም እልሻለሁ የሚለውን #ቃል ራሱ ብናየው #የተሳሳተ #አባባልና #ያልተለመደ #ንግግር ነው። በሌላ አገላለጽ #ዩሐንስ #ለጋይዮስ #ሰላም ለአንተ ይሁን ባለው #ሰላምታ [3ኛ ዩሀ 1፥15] #ጋይዮስ ሆይ #በዩሐንስ ሰላምታ #ሰላም እልሃለው እንደማለት ነው። ነገሩን #ግልጽ ለማድረግ አቶ #አበበ አቶ #ከበደ ቤት ገብቶ <<አቶ #ከበደ በአቶ #አበበ #ሰላምታ #ሰላም #እልሀለው>> ብሎ #ሰላምታ እንደመስጠት ያክል ነው። ይህም በማንኛውም #ህብረተሰብና #ክፍለዘመን ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው #ከጤናማው #የሰላምታ ሥነ-ሥርዓት የወጣ #አባባል ነው።
▶️ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #መልዕክት አድርስ ተብሎ ወደ #ድንግል ማርያም በመምጣት ያደረገውን #ሰላምታ ተንተርሶ #አጼ #ዘረዓ #ያዕቆብ <<ይወድስዋ መላእክት - {መላዕክት ማርያምን ያመሰግኗታል}>> የሚል #ድርሰት ሲያዘጋጅ #የቦረናው #አባ #ጊዮርጊስ #ዘጋስጫ ደግሞ <<ተፈሥሒ ኦ ሙኃዘፍስሐ፤ የተድላና የደስታ መፍሰሻ ሆይ ደስ ይበልሽ መላእክት ብለዋታል[1]>> ብሏል። ነገር ግን ወደ #ማርያም ተልከው የመጡት #መላእክት ሳይሆኑ አንድ #መለአክ ነው። እርሱም ቅዱስ #ገብርኤል ሲሆን ንግግሩም #ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደተላከ ማሳወቅና #ክርስቶስን ያለ #ወንድ #ዘር #በድንግልና እንደምትወልድ የሚገልጽ እንጂ የተለየ #ምስጋና ለመስጠትና #የተድላና #የደስታ #መፍሰሻ እንደነበረች ያሳሰበበት #ክፍል አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን #መልአኩ እርሱ ከመምጣቱ በፊት #ማርያምን #የሚያመሰግንበትም የተለየ #የሰራችው አንዳች ነገር የለም። ያም ሆኖ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት #መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም በነበራቸው የአጭር ጊዜ የመረዳዳት #ውይይትን እንደመደበኛ #የግል #ጸሎታቸው አድርገው #መጽሀፍ አዘጋጅተው የሚደግሙ አሉ። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው መልአኩ #ገብርኤልም ሆነ #ድንግል #ማርያም #ውይይት አደረጉ እንጂ #አንዱ #ለአንዱ ያቀረቡት #ጸሎት የለም። ንግግራቸውም #የዘውትር #ጸሎት እንዲሆንላቸው ያሳሰቡት ነገርም የለም።
▶️ ጌታ #ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ #ሰማይ ሲያርግ #ድንግል #ማርያም ባለችበት #በማርቆስ #እናት ቤት ሐዋሪያት #በአንድነት #በጸሎት ሲተጉ አጠገባቸው ያለችውን #ማርያምን <<በገብርኤል #ሰላምታ ሰላም እንልሻለን #በነፍስሽም #በስጋሽም ድንግል ነሽ ከተወደደው #ልጅሽ #ይቅርታ #ለምኚልን #ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ>> አሏሏትም፤ #የጸሎት #ማዕከላቸውም አልነበረችም። እርሷም እነርሱም በአንድነት << #የሁሉንም #ልብ የምታውቅ #ጌታ ሆይ>> እያሉ #ጌታን እያከበሩ ወደ #ጌታ ሲጸልዩ ነበር። በድንገት #መንፈስ ቅዱስም ለእሷም ለእነሱም #እኩል ያለልዩነት ወረደባቸው። [ሐዋ 1፤ 12-14፣ ሐዋ 2፤ 1-4]።
በተለይ ደግሞ << #ይቅርታን #ለምኚልን>> የሚለው #ቃል ጠቅላላውን #የክርስቶስን #ይቅርታ #ለሰው ልጆች እንዴት እንደተሰጠ አለማወቅና #የክርስቶስን #የደኅንነት #መስዋዕት #ከንቱ የሚያደርግ ነው። በመሆኑም ይህን #ጸሎት ማቅረብ #የጸሎትን #ትርጉም አለማወቅ ብቻ ሳይሆን በግልጽ #የክርስቶስ #ተቃዋሚ መሆን ነው።
✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ "መጽሐፈ ሰዓታት" ገጽ 29።

<<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን የተቀነባበረ <የጸሎት> ክፍል #በኢየሱስ ክርስቶስ #አስተምህሮ #ወቅት ብቻ ሳይሆን ከእሱ ቡሀላም ለብዙ #ዘመናት አልነበረም። ምናልባትም ሌሎች እንደሚሉት #ማርያም ገና #ክርስቶስን ሳትወልድ የነበረ #የገብርኤል #ሰላምታ ነው ተብሎ እንዳይወሰድ እንኳን #መልአኩ መጥቶ ያደረገው #ውይይት እንጂ #ጸሎት አይደለም። #ክርስቶስም #ለደቀመዛሙርቱ #ጸሎት ባስተማረበት #ወቅት #የገብርኤልንም #ሰላምታ ጨምሩበት በማለት ባስተላለፈ ነበር፤ ያንን ደግሞ አላደረገውም [ማቴ 6፤ 1-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]። << #በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ....>> የሚለው #የጸሎት #አስተምህሮቱን #ድንግል ማርያምን በትክክል በሚያውቋት #በደቀመዛሙርቱ ፊት ምናልባትም #በአስተምሮው #ወቅት ብዙ ጊዜ በምትገኝዋም #በድንግል #ማርያምም በራሷ ፊትም ተናግሯል።
▶️ ስለሆነም የተቀነባበረው <<የማርያም የጸሎት>> ምዕራፍ #በክርስቶስ #ወቅት ያልነበረ ከዚያም ቡኋላ #ሐዋሪያቱ #በአገልግሎታቸውና #በጸሎታቸውም ወቅት የማያውቁትና #የጥንት #ቤተ ክርስቲያን #አባቶችም በልዩ ልዩ ምክንያት #ጉባኤ ሲያደርጉ ለምሳሌ፦ #በኒቂያ ጉባኤ #በ325 ዓ.ም 318 የሃይማኖት አባቶች በእነ #እስክንድሮስ አፈጉባዔነት በንጉስ #ቆስጠንጢኖስ ዘመን ተሰብስበው #አርዮስን <<ወልድ #ፍጡር ነው>> ያለበትን #የክህደት ትምህርት #ሲያወግዙና #የሃይማኖት መግለጫ ሲያወጡ #ኢየሱስን ከመውለዷ ውጭ #ስለማርያም ፈጽሞ #መሠረታዊ #ትምህርት እንኳ በወቅቱ እንዳልነበረ መረዳት ይችላል። እንዲሁም #በቁስጥንጥንያ #በ375 ዓ.ም 150 #የሃይማኖት #አባቶች #በጢሞቴዎስ ዘአልቦጥሪት በንጉሥ ዘየዓቢ #ቴዎደስዩስ ወቅት #መቅደንዩስ << #መንፈስ ቅዱስ #ሕጹጽ ወይም #ሀይል ብቻ>> ብሎ በተነሳ ጊዜ ተሰብስበው #አውግዘው ትምህርቱንና እርሱን ሲለዩ #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #የአስተምህሮ #መግለጫ ሲያወጡ ያኔም ቢሆን #ኢየሱስን #ከመውለዷ ውጪ #ስለማርያም ያስተላለፉት ምንም #አዲስ #ትምህርት የለም። #በኤፌሶን ሀገርም #በ435 ዓ.ም 200 #የሃይማኖት #አባቶች #በቄርሎስ አፈጉባዔነት በቴዎደስዩስ ዘይንእስ ንጉሥነት ጊዜ ንስጥሮስ << #ክርስቶስ #ሁለት #አካል #ሁለት #ባህሪይ ነው>> ብሎ ሲነሳ #እርሱንም #ትምህርቱንም #አውግዘው #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #አስተምህሮ በመግለጫ መልክ ሲያስቀምጡ ድንግል #ማርያም #ክርስቶስን እንደወለደች ብቻ እንጂ << #እመቤታችን>> ብለውም ሆነ << #ለምኝልን>> የሚል አስተምህሮ አያውቁም። #ጤናማ #አስተምህሮ አይደለምና።
▶️ ዛሬ ሁሉም #አብያተክርስቲያናት የሚቀበሉት #ሙሉ #የሃይማኖት #መግለጫቸው፦
<<ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን የተፈጠረ ሳይሆን የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምን ምንም የሆነ የለም በሰማይም ያለ በምድርም ያለ ስለእኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፈጽሞ ሰው ሆኖ በጴንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ ሞተ ተቀበረም በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና ሙታንንም ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም ጌታ ማህየዊ በሚሆን ከአብ በሰረጸ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋሪያት በሰበሰባት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሰረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።>> የሚል ነው።
ይህንንም መግለጫ #በ1530 ዓ.ም #ሉተራውያን << #የአውግስበርግ #መግለጫ>> በሚል አጸደቁ። እንዲሁም #በ1546 ዓ.ም #ካቶሊክ በድጋሜ << #የትሬንት #መግለጫ>> በማለት አጸደቀችው። #በ1571 ዓ.ም ደግሞ #የአንግሊካን #ቸርች መግለጫውን ተቀብላ አጸደቀችው። #በ1646 ዓ.ም #ፕሪስቢቴሪያን << #የዌስት #ሚኒስቴር #መግለጫ>> በሚል አጸደቀችው[1]።
▶️ ኦርቶዶክስ #ቤተክርስቲያን መግለጫውን በድጋሜ << #ጸሎተ #ሃይማኖት>> በማለት #በ1426-1460 ዓ.ም በኢትዮጵያ የነገሰው #አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ ሙሉውን ተቀበሉና ሌላ #በመጨመር << #ለማርያምና #ለእፀ መስቀሉ (ለመስቀሉ እንጨት) #ስግደት ይገባቸዋል>> በማለት እንዲሁም <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን <<ከአባታችን ሆይ>> #ቀጥሎ እንዲባል ብሎ #አዋጅ አወጣ። ከዚህም የተነሳ በርካታ #ካህናት << #አባቶቻችን ካስቀመጡት #ከሃይማኖት #መግለጫው ውጪ ተጨማሪውን #አንቀበልም>> በማለታቸው #በሰይፍ እንደቆራረጣቸውና እንዳሳደዳቸው #ገድለ #እስጢፋኖስ፣ #ገድለ #አበው ወአኀው፣ #ገድለ #አባ አበከረዙል፣ #ገድለ #አባ ዕዝራ፣ #ገድለ #ደቂቀ እስጢፋኖስን ማንበብ #በቂ ነው።
▶️ ነገር ግን #በዘር #ቅብብሎሽ አማካኝነት የነበረው #የንግስና #ሥርአት ለዚህ <<አዳራሻውን ወደ ሳተው ጸሎት>> ሰፊ እድል አግኝቶ #ሰይፍ ያስፈራቸውና በክርስትናው #ትምህርት ብዙም #መሰረታዊ #እውቀት ያልነበራቸው #ህዝብና #ካህናት #የጸሎት #ምዕራፋቸው አድርገው ለቀጣዩ #ትውልድ በማስተላለፋቸው ይሀው አሁን የምናየውን #ከእግዚአብሄር #ቃል ውጪ የሆነ #ትውልድ ፈጥረውልናል። ዛሬ ዛሬ #በየጸሎቱ #መዛግብት ውስጥ እየተጨመረ ተጽፎ #ምዕመናን ሁሉ #በቀን ቢያንስ #አንድ ጊዜ እንዲደግመው በመደረጉ እንግዳው <<ጸሎት>> #የተለመደ ሆኖ ቀረ። እንዲያውም በዚህ #ዘመን አስቀድመን እንዳልነው <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል #ጥቅሶችን ያለቦታቸው እንደ #ስጋ #ዘንጥለውና #በጣጥሰው #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል የሚታገሉ ተነስተዋል። እኛ ግን <<የእግዚአብሔርን ቃል #ቀላቅለው #እንደሚሸቃቅጡት እንደ #ብዙዎቹ አይደለንምና፤ #በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ #ተላክን #በእግዚአብሔር ፊት #በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።>> [2ቆሮ 2፥17]
✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን፤ አውግስበርግ ሃይማኖታዊ መግለጫ፤ በአማርኛ የተተረጎመ፤ አ.አ፥ 1993 ዓ.ም።

▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ነብያት፣ #ካህናት፣ #ሐዋሪያት #ሁሉም ማለት ይቻላል ጸልየዋል። #ጸሎታቸውም በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር እንጂ እንኳን ወደ #ፍጡራን፣ ወደ #መላእክት የጸለየ አንድም #ሰው አናገኘም። #ድንግል #ማርያም እንኳን #በሉቃስ 1፤46-55 እንደተገለጸው <<ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፤ መንፈሴም በአምላኬ በመድሃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች.....>> በማለት እንዲሁም #በሐዋ 1፥25 #ከ120 #ሰዎች ጋር አብራ <<የሁሉንም ልብ የምታውቅ ጌታ ሆይ>> እያለች በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ነው የጸለየችው። #ኢየሱስ ክርስቶስም #በሥጋው ወራት #በርካታ ጊዜ ያለማቋረጥ ወደ #አባቱ <<አባት ሆይ...>> በማለት #ጸሎት አድርጓል [ዩሀ 17፥1]። #ክርስቶስ አገልግሎቱን #በጸሎት ጀምሮ [ማቴ 4፥1] በመስቀል ላይ #ነፍሱን ሲሰጥና #አገልግሎቱን ሲደመድም #በጸሎት ውስጥ ነበር። እርሱ እንዳደረገውም #እንዳስተማረን <<አባታችን ሆይ>> ብለን እንድንጸልይ እንጂ <<እመቤታችን ሆይ>> ብለንም ሆነ #ወደሌላ #እንድንጸልይ አላስተማረንም።
▶️ ክርስቶስ ስለ #ጸሎት ሁኔታ ከሰጠን #መመሪያዎች ውስጥ <<አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሀል>> [ማቴ 6፥6] ብሎ ነው ያዘዘን። #ሐዋሪያትም ቢሆኑ #ከክርስቶስ የተማሩትን #ትምህርት #አብነት (ምሳሌ) አድርገው <<የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ...">> [ #ሐዋ 1፥25]፣ <<ጌታ ሆይ አንተ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በእርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠረህ...>> [ #ሐዋ 4፥24] ፣<<ጌታ ኢየሱስ ሆይ...>> [ #ሐዋ 7፥59]..ወ.ዘ.ተ በማለት #ቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ብቻ ነው የጸለዩት። ስለሆነም እንደ እነርሱ #መጽሀፍቅዱስ <<በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ>> በሚለው መመሪያ መሰረት [ #ፊል 4፥6] ወደ #እግዚአብሔር #ቀጥታ እንድንጸልይ ያሳስበናል።
▶️ ጸሎት በራሱ #የቃሉ #ትርጉም #ከእግዚአብሄር ጋር #መነጋገር ማለት እግዚአብሔርን #ማክበር [ራዕ 4፤ 10-11] እግዚአብሔርን #ማመስገን [መዝ 106(107) ፤1-2] እግዚአብሔርን #መለመን [ያዕ 1፤5] እግዚአብሔር የሚናገረውን #ማዳመጥ [መዝ 84(85) ፤8] ማለት ነው። ለዛም ነው ዳዊትም በመዝሙሩ እንዲህ ያለው <<ሥጋ ለባሽ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል።>> ያለው [ #መዝ 65፥2]። በዚህም መሰረት በብሉይ ኪዳን #አዳም፣ #ኖህ፣ #አብርሃም፣ #ይስሐቅ፣ #ያዕቆብ፣ #ዮሴፍ፣ #ሙሴ፣ #ኢያሱ፣ #የሳሙኤል እናት #ሐና፣ #ሳሙኤል፣ #ጌድዮን፣ #ባርቅ፣ #ሳምሶን፣ #ዮፍታሔ፣ #ዳዊት፣ #ሰለሞን፣ #ኤልያስ፣ #ኤልሳዕ፣ #ኢዮስያስ፣ #ሕዝቅያስ፣ #ኢሳይያስ፣ #ኤርምያስ፣ #ኢዮብ፣ #ዕዝራ፣ #ነህምያ፣ #አስቴር፣ #ዳንኤል፣ #ሕዝቅኤል፣ #ዮናስ . . .ወዘተ በሐዲስ ኪዳንም 12ቱ #ደቀመዛሙርት፣ #ድንግል ማርያም፣ #ዘካርያስ፣ #ስምዖን፣ #ጳውሎስ፣ #ጴጥሮስ፣ በህብረት ደግሞ #ጳውሎስና #ሲላስ፣ #ሐዋርያት #በአንድነት፣ ራሱም #ኢየሱስ ክርስቶስ #በሥጋዌ ማንነቱ፣ እጅግ #ኃጢአተኞች ተብለው የሚቆጠሩት #በክርስቶስ ቀኝ የተሰቀለው #ወንበዴና ከሰፈር ውጭ ተጥለው የነበሩት #ለምጻሞች ሁሉ #ጸልየዋል። የጸለዩትም #ጸሎት #በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ሆኖ የከበረ #መልስ ማግኘታቸውም ሁሉ ለትምህርታችን #ተጽፏል። ስለዚህ ወደ #ማርያምም ሆነ ወደ ማንኛውም #ፍጡር መጸለይ #ኢ #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ዘመን አመጣሽ #ተግባር ነው። ደግሞም ዛሬ በአንዳንድ #ምእመናን እንደሚታየው ከላይ የጠቀስናቸው ሁሉ #ለመጸለይ #የልባቸውን #ጩኸት አቀረቡ እንጂ #ለጸሎት ብለው የተጠቀሙበት #የጸሎት #መጽሐፍ <<የሰኞ የማክሰኞ>> ወ.ዘ.ተ እያሉ የሚደግሙት #መጽሐፍ አልነበራቸውም። #በብሉይ ኪዳን ተጽፎ የነበረው #የመዝሙረ ዳዊት #መጽሐፍ #ኢየሱስ ክርስቶስና #ሐዋርያት ለትምህርቶቻቸው ይጠቅሱት ነበር እንጂ #ለጸሎቶቻቸው #ድጋፍ አድርገው አልተጠቀሙበትም። ስለዚህ #ጸሎት #ከልብ የሚመነጭ ስለሆነ በየቀኑ በብዙ #ገጾች የሚቆጠሩ የተለያዩ #ርዝመት ያላቸውን የተጻፉ #መጽሀፍትን #ማዘጋጀትና፣ #መደጋገም እንዲሁም #ህመም ሲሰማቸው #መጽሀፍቶቹን #መተሻሽት፣ #በራስጌ ላይ #ማንጠልጠል፣ #በአንገት ላይ #ማነገት አይደለም።
▶️ ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን #የፈሪሳውያን (የአህዛብ) #ጸሎት #ስነ - ሥርዓት <<አህዛብም በመናገራቸው #ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና #ስትጸልዩ እንደ እነርሱ #በከንቱ አትድገሙ ስለዚህ አትምሰሏቸው>> በማለት ተቃውሟል [ማቴ 6፤ 7-8]። ስለዚህ #ጸሎት ሰዎች በደረሱልን የ"ጸሎት" #ድርሰት #መጽሀፍ ወይም የሌሎችን #ጸሎት በመድገም #መጸለይ ሳይሆን እንደ ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ #እግዚአብሔር በመቅረብ የልባችንን #ጸሎት #በእውነትና #በመንፈስ #ከአክብሮት ጋር በማቅረብ ነው [ማቴ 26፤ 39-44 ፣ ዩሀ 17፤ 1-26]።

▶️ ይህ <<ሰኔ ጎለጎታ>> የተባለው #የጸሎት መጽሐፍ #ማርያም #በጎለጎታ #በኢየሱስ መቃብር ስፍራ ገብታ #ስትጸልይ ኢየሱስ #ክርስቶስ ከላይ የተገለጸውን #የተስፋ ቃል እንደ #ቃልኪዳን አድርጎ እንደሰጣት የሚናገር በመሆኑ በተለይ #እናቶቻችን ሲታመሙ ይህንን መጽሐፍ #በየኮሮጃቸውና ሲተኙ #በራስጌና #በግርጌያቸው #በመንተራስ ደግሞም ሲነቁ #አንገቶቻቸው ላይ በማሰር በል ሲላቸውም ባላቸው #እህል #ጎተራዎቻቸውች እንደ #መድኃኒት እጽ በመያዝና #በመድገም ተታለው በቀላሉ #ሆስፒታል ሄዶ ታክሞ #መዳን ሲችሉ #ከገሃዱ እውነት ወጥተው #ያለቁትን ማን ይቁጠራቸው?
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
@gedlatnadersanat
(8.7▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
@gedlatnadersanat
(8.7▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ ጸሎት #የልባችንን #መሻት ወደ #እግዚአብሔር የምናቀርብበት እንደ መሆኑ መጠን ማንኛውም #የጸሎት #መጻሕፍት ትክክለኛ ቃላት ያላቸው ቢሆኑም እንኳ #የልባችንን ያክል ሊገልጡልን በፍጹም አይችሉም። በሰው ልብ ብዙ #ሃሳብ አለ {ምሳ 19፥21}። ይህን ሃሳብ #ለእግዚአብሔር #በጸሎት መንገድነት መግለጥ ያለብን #በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት {ሮሜ 8፤ 26-27} #በኢየሱስ #ክርስቶስ ስም ብቻ ነው {ዩሐ 16፥24}።
▶️ ለምሳሌ በተለምዶ <<ፀሎተ እግዚእትነ ማርያም>> ተብሎ የሚታወቀውን #የማርያምን #ጸሎት ከሉቃስ 1፤ 46-55 ብናየው #ማርያም #እግዚአብሔር ለራሷ ታላቅ ነገር ስላደረገላት የግል #የምስጋና ጸሎት አቀረበች እንጂ የእኛን #የግል #ጸሎት እያቀረበችልን አልነበረም። በሌሎችም መጽሐፍ #ውዳሴ ማርያም፣ #መልክዓ ማርያም፣ #አንቀጸ ብርሃን፣ #ይዌድስዋ መላእክት፣ #አርጋኖን፣ #መልክዓ ኪዳነ ምህረት፣ #መልክዓ ኤዶም፣ #መጽሐፈ ባርቶስ፣ #ሰኔ ጎልጎታ ወ.ዘ.ተ የሚያወሩት ስለእኛ #የግል ሁኔታ አይደሉም። ምናልባትም እኛ #ስለስራ፣ #ስለቤተሰቦቻችን፣ #ስለንግድ #ትርፋችን፣ #ስለትምህርታችን. . . ወ.ዘ.ተ ከሆነ #የልባችን #መሻት እነዚህን #መጻሕፍት አርባ ጊዜ ብናገላብጣቸው በአንዳቸውም ውስጥ #በበቂና በተሟላ ሁኔታ #ልባችንን አይገልጡልንም። እንዲያውም የቆዩ #ስነ - ቃሎችና #አባባሎች ናቸው። ስለዚህ #በእውነትና #በመንፈስ ሆነን <<የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል>> ያለውን ጌታ ሰምተን #የልባችንን #ጩኸት #በኢየሱስ ስም እናቅርብ {ዩሐ 15፥7፣ ቆላ 3፥17}።
▶️ እንግዲህ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶችና ቃሎቹ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተስማምተው አድራሻቸው ወደ #ማርያም የሆኑ #መጽሐፍት ሁሉ #ለክርስትና ሕይወት ተገቢነት የሌላቸው #የአሕዛብ ልማዶች ናቸው። #በየጫካው፣ #በየዋሻው፣ #በየገደላ ገደሉ ተተርጉመው ተገኙ እየተባሉ #ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የጻፏቸውንም ብጥስጣሽ የድሮ #አጋንንታዊ #መጻሕፍትን መከተል ከንቱ #ድካም ከመሆኑ ውጪ #ኃጢአትም ጭምር ነው። እንግዲህ #ውዳሴ {ራዕ 7፥12፣ ራዕ 4፥11} #ምስጋና {መዝ 150፤ 1-6} #ስግደት {ዘጸ 20፤ 3-5፣ ማቴ 4፥10} #መዝሙር {ኤፌ 5፥19} እንደተጻፈው #ለእግዚአብሔር ብቻና ወደ #እግዚአብሔር ብቻ #በመንፈስ ሊሆን ይገባል። አሜን!!