▶️ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ #ነብያት፣ #ካህናት፣ #ሐዋሪያት #ሁሉም ማለት ይቻላል ጸልየዋል። #ጸሎታቸውም በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር እንጂ እንኳን ወደ #ፍጡራን፣ ወደ #መላእክት የጸለየ አንድም #ሰው አናገኘም። #ድንግል #ማርያም እንኳን #በሉቃስ 1፤46-55 እንደተገለጸው <<ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፤ መንፈሴም በአምላኬ በመድሃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች.....>> በማለት እንዲሁም #በሐዋ 1፥25 #ከ120 #ሰዎች ጋር አብራ <<የሁሉንም ልብ የምታውቅ ጌታ ሆይ>> እያለች በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ነው የጸለየችው። #ኢየሱስ ክርስቶስም #በሥጋው ወራት #በርካታ ጊዜ ያለማቋረጥ ወደ #አባቱ <<አባት ሆይ...>> በማለት #ጸሎት አድርጓል [ዩሀ 17፥1]። #ክርስቶስ አገልግሎቱን #በጸሎት ጀምሮ [ማቴ 4፥1] በመስቀል ላይ #ነፍሱን ሲሰጥና #አገልግሎቱን ሲደመድም #በጸሎት ውስጥ ነበር። እርሱ እንዳደረገውም #እንዳስተማረን <<አባታችን ሆይ>> ብለን እንድንጸልይ እንጂ <<እመቤታችን ሆይ>> ብለንም ሆነ #ወደሌላ #እንድንጸልይ አላስተማረንም።
▶️ ክርስቶስ ስለ #ጸሎት ሁኔታ ከሰጠን #መመሪያዎች ውስጥ <<አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሀል>> [ማቴ 6፥6] ብሎ ነው ያዘዘን። #ሐዋሪያትም ቢሆኑ #ከክርስቶስ የተማሩትን #ትምህርት #አብነት (ምሳሌ) አድርገው <<የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ...">> [ #ሐዋ 1፥25]፣ <<ጌታ ሆይ አንተ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በእርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠረህ...>> [ #ሐዋ 4፥24] ፣<<ጌታ ኢየሱስ ሆይ...>> [ #ሐዋ 7፥59]..ወ.ዘ.ተ በማለት #ቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ብቻ ነው የጸለዩት። ስለሆነም እንደ እነርሱ #መጽሀፍቅዱስ <<በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ>> በሚለው መመሪያ መሰረት [ #ፊል 4፥6] ወደ #እግዚአብሔር #ቀጥታ እንድንጸልይ ያሳስበናል።
▶️ ጸሎት በራሱ #የቃሉ #ትርጉም #ከእግዚአብሄር ጋር #መነጋገር ማለት እግዚአብሔርን #ማክበር [ራዕ 4፤ 10-11] እግዚአብሔርን #ማመስገን [መዝ 106(107) ፤1-2] እግዚአብሔርን #መለመን [ያዕ 1፤5] እግዚአብሔር የሚናገረውን #ማዳመጥ [መዝ 84(85) ፤8] ማለት ነው። ለዛም ነው ዳዊትም በመዝሙሩ እንዲህ ያለው <<ሥጋ ለባሽ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል።>> ያለው [ #መዝ 65፥2]። በዚህም መሰረት በብሉይ ኪዳን #አዳም፣ #ኖህ፣ #አብርሃም፣ #ይስሐቅ፣ #ያዕቆብ፣ #ዮሴፍ፣ #ሙሴ፣ #ኢያሱ፣ #የሳሙኤል እናት #ሐና፣ #ሳሙኤል፣ #ጌድዮን፣ #ባርቅ፣ #ሳምሶን፣ #ዮፍታሔ፣ #ዳዊት፣ #ሰለሞን፣ #ኤልያስ፣ #ኤልሳዕ፣ #ኢዮስያስ፣ #ሕዝቅያስ፣ #ኢሳይያስ፣ #ኤርምያስ፣ #ኢዮብ፣ #ዕዝራ፣ #ነህምያ፣ #አስቴር፣ #ዳንኤል፣ #ሕዝቅኤል፣ #ዮናስ . . .ወዘተ በሐዲስ ኪዳንም 12ቱ #ደቀመዛሙርት፣ #ድንግል ማርያም፣ #ዘካርያስ፣ #ስምዖን፣ #ጳውሎስ፣ #ጴጥሮስ፣ በህብረት ደግሞ #ጳውሎስና #ሲላስ፣ #ሐዋርያት #በአንድነት፣ ራሱም #ኢየሱስ ክርስቶስ #በሥጋዌ ማንነቱ፣ እጅግ #ኃጢአተኞች ተብለው የሚቆጠሩት #በክርስቶስ ቀኝ የተሰቀለው #ወንበዴና ከሰፈር ውጭ ተጥለው የነበሩት #ለምጻሞች ሁሉ #ጸልየዋል። የጸለዩትም #ጸሎት #በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ሆኖ የከበረ #መልስ ማግኘታቸውም ሁሉ ለትምህርታችን #ተጽፏል። ስለዚህ ወደ #ማርያምም ሆነ ወደ ማንኛውም #ፍጡር መጸለይ #ኢ #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ዘመን አመጣሽ #ተግባር ነው። ደግሞም ዛሬ በአንዳንድ #ምእመናን እንደሚታየው ከላይ የጠቀስናቸው ሁሉ #ለመጸለይ #የልባቸውን #ጩኸት አቀረቡ እንጂ #ለጸሎት ብለው የተጠቀሙበት #የጸሎት #መጽሐፍ <<የሰኞ የማክሰኞ>> ወ.ዘ.ተ እያሉ የሚደግሙት #መጽሐፍ አልነበራቸውም። #በብሉይ ኪዳን ተጽፎ የነበረው #የመዝሙረ ዳዊት #መጽሐፍ #ኢየሱስ ክርስቶስና #ሐዋርያት ለትምህርቶቻቸው ይጠቅሱት ነበር እንጂ #ለጸሎቶቻቸው #ድጋፍ አድርገው አልተጠቀሙበትም። ስለዚህ #ጸሎት #ከልብ የሚመነጭ ስለሆነ በየቀኑ በብዙ #ገጾች የሚቆጠሩ የተለያዩ #ርዝመት ያላቸውን የተጻፉ #መጽሀፍትን #ማዘጋጀትና፣ #መደጋገም እንዲሁም #ህመም ሲሰማቸው #መጽሀፍቶቹን #መተሻሽት፣ #በራስጌ ላይ #ማንጠልጠል፣ #በአንገት ላይ #ማነገት አይደለም።
▶️ ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን #የፈሪሳውያን (የአህዛብ) #ጸሎት #ስነ - ሥርዓት <<አህዛብም በመናገራቸው #ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና #ስትጸልዩ እንደ እነርሱ #በከንቱ አትድገሙ ስለዚህ አትምሰሏቸው>> በማለት ተቃውሟል [ማቴ 6፤ 7-8]። ስለዚህ #ጸሎት ሰዎች በደረሱልን የ"ጸሎት" #ድርሰት #መጽሀፍ ወይም የሌሎችን #ጸሎት በመድገም #መጸለይ ሳይሆን እንደ ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ #እግዚአብሔር በመቅረብ የልባችንን #ጸሎት #በእውነትና #በመንፈስ #ከአክብሮት ጋር በማቅረብ ነው [ማቴ 26፤ 39-44 ፣ ዩሀ 17፤ 1-26]።
✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆