ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ጸሎት #የልባችንን #መሻት ወደ #እግዚአብሔር የምናቀርብበት እንደ መሆኑ መጠን ማንኛውም #የጸሎት #መጻሕፍት ትክክለኛ ቃላት ያላቸው ቢሆኑም እንኳ #የልባችንን ያክል ሊገልጡልን በፍጹም አይችሉም። በሰው ልብ ብዙ #ሃሳብ አለ {ምሳ 19፥21}። ይህን ሃሳብ #ለእግዚአብሔር #በጸሎት መንገድነት መግለጥ ያለብን #በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት {ሮሜ 8፤ 26-27} #በኢየሱስ #ክርስቶስ ስም ብቻ ነው {ዩሐ 16፥24}።

▶️ ለምሳሌ በተለምዶ <<ፀሎተ እግዚእትነ ማርያም>> ተብሎ የሚታወቀውን #የማርያምን #ጸሎት ከሉቃስ 1፤ 46-55 ብናየው #ማርያም #እግዚአብሔር ለራሷ ታላቅ ነገር ስላደረገላት የግል #የምስጋና ጸሎት አቀረበች እንጂ የእኛን #የግል #ጸሎት እያቀረበችልን አልነበረም። በሌሎችም መጽሐፍ #ውዳሴ ማርያም፣ #መልክዓ ማርያም፣ #አንቀጸ ብርሃን፣ #ይዌድስዋ መላእክት፣ #አርጋኖን#መልክዓ ኪዳነ ምህረት፣ #መልክዓ ኤዶም፣ #መጽሐፈ ባርቶስ፣ #ሰኔ ጎልጎታ ወ.ዘ.ተ የሚያወሩት ስለእኛ #የግል ሁኔታ አይደሉም። ምናልባትም እኛ #ስለስራ#ስለቤተሰቦቻችን#ስለንግድ #ትርፋችን#ስለትምህርታችን. . . ወ.ዘ.ተ ከሆነ #የልባችን #መሻት እነዚህን #መጻሕፍት አርባ ጊዜ ብናገላብጣቸው በአንዳቸውም ውስጥ #በበቂና በተሟላ ሁኔታ #ልባችንን አይገልጡልንም። እንዲያውም የቆዩ #ስነ - ቃሎችና #አባባሎች ናቸው። ስለዚህ #በእውነትና #በመንፈስ ሆነን <<የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል>> ያለውን ጌታ ሰምተን #የልባችንን #ጩኸት #በኢየሱስ ስም እናቅርብ {ዩሐ 15፥7፣ ቆላ 3፥17}።

▶️ እንግዲህ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶችና ቃሎቹ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተስማምተው አድራሻቸው ወደ #ማርያም የሆኑ #መጽሐፍት ሁሉ #ለክርስትና ሕይወት ተገቢነት የሌላቸው #የአሕዛብ ልማዶች ናቸው። #በየጫካው#በየዋሻው#በየገደላ ገደሉ ተተርጉመው ተገኙ እየተባሉ #ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የጻፏቸውንም ብጥስጣሽ የድሮ #አጋንንታዊ #መጻሕፍትን መከተል ከንቱ #ድካም ከመሆኑ ውጪ #ኃጢአትም ጭምር ነው። እንግዲህ #ውዳሴ {ራዕ 7፥12፣ ራዕ 4፥11} #ምስጋና {መዝ 150፤ 1-6} #ስግደት {ዘጸ 20፤ 3-5፣ ማቴ 4፥10} #መዝሙር {ኤፌ 5፥19} እንደተጻፈው #ለእግዚአብሔር ብቻና ወደ #እግዚአብሔር ብቻ #በመንፈስ ሊሆን ይገባል። አሜን!!

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆